inputs
stringlengths
86
2.15k
targets
stringlengths
1
2.05k
language
stringclasses
1 value
split
stringclasses
3 values
template
stringclasses
9 values
dataset
stringclasses
1 value
config
stringclasses
1 value
length
int64
46
653
አጥኚዎቹ በወባ በሽታ የተጠቃ ሰው ልብስ ለውሾቹ በማስሸተት ለረጅም ወራት አሰልጥነዋቸዋል። በተለይ በአፍሪካና በእስያ በየዓመቱ የብዙ ሰዎችን ህይወት የሚቀጥፈው የወባ በሽታን ለመከላከልና ለማጥፋት በሚደገረው አለምዓቀፍ ርብርብ ይሄኛው ግኝት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል። ምንም እንኳን የምርምር ውጤቱ ገና በሙከራ የሚባል ደረጃ ላይ የሚገኝ ቢሆንም፤ የወባ በሽታን ለመርመር እንደ አዲስ መንገድ ሊያገለግል ይችላል። • የወባ በሽታ ያለ ደም ምርመራ ሊታወቅ ነው • ሐረር በፈረቃ ውሃ ማግኘት ጀምራለች ጥናቶች እንሚያሳዩት በወባ በሽታ ስንጠቃ የሰውነታችን ጠረን የሚቀየር ሲሆን፤ የወባ ትንኞች ደግሞ በዚህ ጠረን ስለሚማረኩ የተጠቂውን ሰው ደም ቀድመው በመምጠጥ በሽታውን ያስተላልፋሉ። አሁን ደግሞ ውሾች ይህንን ጠረን በማሽተት በሽታውን መከላከል ይችላሉ። የተመራማሪዎቹ ቡድን በጋምቢያው 'አፐር ሪቨር' ክልል የሚገኙ ህጻናት የለበሷቸውን ካልሲዎች አሰባስበው ወደ እንግሊዝ በመላክ ነው ጥናቱ የተጀመረው። ከተላኩት 175 ካልሲዎች ደግሞ 30 የሚሆኑት በወባ በሽታ የተጠቁ ህጻናት የለበሷቸው ነበሩ። ምንም እንኳን ውሾቹ አብዛኛውን በበሽታው የተጠቁ ህጻናትን ካልሲዎች ቢለዩም፤ ከአስር ህጻናት አንዱ በሽታው ሳይኖርበት እንደ ተጠቂ ቆጥረውታል። ይሄ ደግሞ ውሾቹን እስከመጨረሻው ከማሰልጠን ጋር የተያያዘ ነው። የተመራማሪ ቡድኑ መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ስቲቭ ሊንዲሴይ በጥናቱ ውጤታማነት እጅግ መደሰታቸውንና ለጊዜው ውሾቹ የምርመራ አገልግሎት ላይ እንደማይውሉ ገልጸዋል። • በኦነግ እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በምዕራብ ኦሮሚያ ግጭት እንደነበር ተነገረ ውሻዎቹ በሽታውን ሙሉ በሙሉ መለየት የሚችሉበት ደረጃ ለማድረስ የማሰልጠን ስራው እንደሚ... Continue the article for another 4000 characters max:
ቀጥልና፤ ሌሎች በሽታዎችንም መለየት እንዲችሉ ለማድረግ እንደሚሰሩ ፕሮፌሰር ስቲቭ ጨምረዋል። በሙከራ ደረጃም በአየር መንገዶችና ሌሎች ሰዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች ውሻዎቹን በማሰማራት ውጤታማኑትን ለመፈተሽም ታስቧል።
amh_Ethi
train
xp3longcontinue
GEM/xlsum
amharic
221
Given the below title and summary of an article, generate a short article or the beginning of a long article to go along with them. Title: ኮሮናቫይረስ፡ በዓለማችን ከ30 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል\nSummary: በጆንስ ሆፕኪንስ አሐዝ መሠረት በዓለም በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ30 ሚሊዮን አልፏል። 940,000 ሰዎች ሞተዋል።\nArticle (Max 500 characters):
ከየትኛውም የዓለማችን አገራት በበለጠ በሕንድ ቫይረሱ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው በወረርሽኙ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው አሜሪካ፣ ሕንድና ብራዚል ናቸው። አውሮፓ ውስጥ ደግሞ ቫይረሱ እያገረሸ ነው። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ቫይረሱ በሁለተኛ ዙር የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ተጨማሪ የጥንቃቄ እርምጃዎች ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል። እስራኤል ለሁለተኛ ጊዜ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ መጣሏ ይታወሳል። አፍሪካ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። እየተካሄደ ያለው ምርመራ ቢጨምር ከዚህም በላይ በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ የሚል መላ ምት አለ። ክፉኛ የተጎዱ አገራት በቫይረሱ ክፉኛ የተጎዳችው አሜሪካ ናት። 6.6 ሚሊዮን ሰው በበሽታው ሲያዝ 197,000 ሰዎች ሞተዋል። አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከሐምሌ አንጻር እየቀነሰ ነው። በሕንድ በቫይረሱ
amh_Ethi
train
xp3longgenarticle
GEM/xlsum
amharic
148
በኮሮናቫይረስ ላይ የሚደረግ ምርምርን ሰልለዋል የተባሉ ሁለት ቻይናውያን ክስ ተመስርቶባቸዋል። ክሱ የተመሰረተው አሜሪካ ቻይናን በበይነ መረብ ስለላ አምርራ መተቸቷን ተከትሎ ነው። ባለፈው ሳምንት አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ካናዳ፤ ሩስያ የኮቪድ-19 ምርምር ለመስረቅ ሞክራለች ብለው ነበር። አሜሪካ የከሰሰቻቸው ቻይናውያን የቀድሞ የኤሌክትሪክ ምህንድስና ተማሪዎቹ ሊ ዢያዩ እና ዶንግ ጂአዚ ናቸው። የንግድ ሚስጥር በመስረቅና ለበይነ መረብ የገንዘብ ምዝበራ በመመሳጠር ተወንጅለዋል። አሜሪካ የከሰሰቻቸው ቻይናውያን የቀድሞ የኤሌክትሪክ ምህንድስና ተማሪዎቹ ሊ ዢያዩ እና ዶንግ ጂአዚ ናቸው። ክሱ ምንድን ነው? ዐቃቤ ሕግ እንደሚለው ከሆነ ሁለቱ ቻይናውያን መጋቢት ላይ የማስቹሴትስ የባዮቴክኖሎጂ ተቋምን ሰልለዋል። በተቋሙ ለኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘት ጥናት እየተደረገ ይገኛል። ሜሪላንድ የሚገኝ ድርጅት ኮሮናቫይረስ ላይ ምርምር እያደረገ መሆኑን አስታውቆ በሳምንቱ ቻይናውያኑ የድርጅቱን በይነ መረብ ሰርስረው እንደገቡም ተገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ አብዛኛውን ጊዜ በግላቸው በበይነ መረብ መረጃ ቢሰርቁም፤ አልፎ አልፎ የቻይና ሰላዮች ድጋፍ ያደርጉላቸዋል ተብሏል። ድጋፍ አድርገዋል ከተባሉት መካከል የቻይና የብሔራዊ ደህንነት ኃላፊ ይገኙበታል። ከጎርጎሮሳውያኑ 2009 ወዲህ በመቶ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የንግድ ሚስጥር እና አዕምሯዊ ንብረት መስረቃቸውን ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል። ቻይና የሚኖሩት እነዚህ ግለሰቦች፤ ስለ ኮሮናቫይረስ ክትባት፣ ህክምና እና ምርመራ መረጃ ለማግኘት የባዮቴክ ተቋማትን የመረጃ መረብ ደህንነት ጥሰዋል። ከአሜሪካ በተጨማሪ አውስትራሊያ፣ ቤልጄም፣ ጀርመን፣ ጃፓን፣ ሊቱኒያ፣ ኔዘርላንድስ፣ ስፔን፣ ስዊድን እና ዩናይትድ ኪንግደም ኢላማ ... Continue the article for another 4000 characters max:
ተድገዋል። ቻይናውያኑ የዩኬን ሰው ሰራሽ ክህሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) ተቋም፣ የስፔንን የመከላከያ ተቋም እና አውስትራሊያን የፀሐይ ብርሃን ሀይል ተቋም ሰረስረው መግባታቸው በክሱ ተመልከቷል። ቻይና ለምን ስለላውን ትደግፋቸዋለች ተባለ? ዐቃቤ ሕግ እንደሚናገረው፤ ግለሰቦቹ ለግል ጥቅማቸው የሚሠሩበት ጊዜ አለ። ከዚህ በፊት አንድ ድርጅት ሚስጥሩን እንዳያጋልጡበት ገንዘብ እንዲከፍላቸው መጠየቃቸው እንደ ምሳሌ ተጠቅሷል። ከግል ጥቅም ባሻገር ግን ለቻይና መንግሥትም ያገለግሉ ነበር ተብሏል። ወታደራዊ መረጃ ሰርቀው ለቻይና መንግሥት መስጠታቸው በክሱ ተገልጿል። በተጨማሪም የሆንግ ኮንግ የዴሞክራሲ አቀንቃኝ እንዲሁም የቀድሞ የቲያናመን አደባባይ ተቃዋሚን የይለፍ ቃል ለቻይና መንግሥት አሳልፈው ሰጥተዋል ተብሏል። ተባባሪ ዐቃቤ ሕግ ጆን ደምረስ “ቻይና ለበይነ መረብ ወንጀለኞች ከለላ በመስጠት አሳፋሪ የሆኑትን የሩስያ፣ የኢራን እና የሰሜን ኮርያን ጎራ ተቀላቅላለች። ግለሰቦቹ በድካም ያገኘነውን አዕምሯዊ ንብረት ለቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ያስተላልፋሉ” ብልዋል። የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ ሁዋ ቹንያንግ፤ ቻይና አሜሪካ ላይ የበይነ መረብ ጥቃት ከፍታለች የሚለውን ክስ አጣጥለዋል። ኮቪድ-19ን የተመለከቱ ምርምሮችን ለመስረቅ ተሞክሯል የሚለውን ውንጀላም “የማይመስል” ሲሉ አስተባብለዋል። በያዝነው ወር መባቻ የአሜሪካ የምርመራ ተቋም ኤፍቢአይ ዳይሬክተር ክሪስቶፈር ዋሪ፤ ቻይናን “የዓለም ብቸኛዋ ፈርጣማ አገር ለመሆን የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም” ማለታቸው ይታወሳል። ድርጅቱ አሁን ላይ በየአስር ሰዓቱ ከቻይና ጋር የተያያዙ የደህንት ሥራዎች እንደሚያከናውን ተናግረዋል። በተቋሙ ሥር ካሉት ወደ 5,000 የሚጠጉ የደህንነት ጥበቃ የምላሽ ስለላዎች (ካውንተርኢንተለጀንስ) መካከል ግማሹ ቻይና ላይ ያነጣጠሩ መሆናቸውንም አክለዋል።
amh_Ethi
train
xp3longcontinue
GEM/xlsum
amharic
381
Content: የቻይናው ዜና ምንጭ ዢኑዋ ደግሞ ግልፅ ባለ ቋንቋ "ዶናልድ ትራምፕ እንኳን ተወገዱ!" የሚል መልዕክት በትዊተር ገፁ አስፍሯል። ብሄራዊው ግሎባል ታይምስ ጋዜጣም እንዲሁ የሁለቱን አገራት ግንኙነት በተመለከተ ባወጣው ዘለግ ባለ ፅሁፍ "ቻይና ከትራምፕ የስልጣን ዘመን የተማረችው ነገር ቢኖር ሁለቱ አገራት ግንኙነትን በተመለከተ ምንም መጠበቅ እንደሌለባት ነው። የቻይናና አሜሪካን ግንኙነት በተመለከተ እውነታውን የማያንፀባርቅ ተስፋ የለንም፤ ምንም አንጠብቅም" በሚል አስፍሯል። በተለይም በትራምፕ አስተዳደር ተሰናባቹ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ ላይ ባለስልጣናቱ ስድብ ቀረሽ የሰላ ትችት ሰንዝረዋል። የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሚያደርገው የተለመደው መግለጫም ቃለ አቀባይዋ ሁዋ ቹንይንግ "በማይክ ፖምፔዮ በኩል ሲነዛ የነበረው መርዛማ ውሸት በሙሉ ይጠራል። ልኩ እሱም ተጠርጎ እንደወጣው ውሸቱም በታሪክ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ ይጣላል" ብለዋል። ነገር ግን ቃለ አቀባይዋ ማይክ ፖምፔዮን ይናፍቋቸዋል ወይ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሻቸው "በደንብ! በርካታ መዝናኛ የሚሆኑ ነገሮችን እኮ ያመጣልን ነው። በየቀኑ ድራማ እየተከታተልን ነበር" በማለት ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ አወዛጋቢ ጉዳዮችን በመፃፍ የሚታወቁትን ትራምፕ ግሎባል ታይምስ "ውደዱትም፣ ጥሉትም። ማህበራዊ ሚዲያው ያለ ዶናልድ ትራምፕ ተመሳሳይ አይሆንም። ለብዙዎች አሳዛኝ ነው ብሏል" ጋዜጣው መረጃዎችን ዋቢ አድርጎ እንደፃፈው " በዊቡ ማህበራዊ ሚዲያ ዶናልድ ትራምፕ በመፈለግ የቁንጮነት ቦታን ይዘዋል። በ2020ም በከፍተኛ ሁኔታ ስማቸው በመነሳትና በዊቡ አንደኛ ስፍራን በመያዝ 589 ጊዜ 'ትሬንድ' አድርገዋል። ይኼም የወረርሽኙን ዜና፣ ታዋቂ ሰዎችንና እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን በመብለጥ ነው" በማለትም አስፍሯል። \nThe previous content can be summarized as follows:
የቻይና ባለስልጣናት አስተያየት የሚንፀባረቅባቸው የመንግሥት ሚዲያዎች በተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና ደጋፊዎቻቸው ከስልጣን መወገድ የተሰማቸውን ስሜት ለአለም ከመንገር ወደኋላ አላሉም።
amh_Ethi
train
prevcontent
GEM/xlsum
amharic
223
Doc to summarize: የሐረር ከተማ የመሬት መንቀጥቀጡ ያጋጠመው በሃረማያ፣ በድሬዳዋና ሐረር ከተሞች እንዲሁም በአቅራቢያቸው በሚገኙ አካባቢዎች እንደሆነ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ አነስተኛ መጠን እንዳለውና በርዕደ መሬት መለኪያ ሦስት እንደተመዘገበ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦሎጂ፣ አስትሮኖሚና የህዋ ምርምር ዳይሬክተር እንዲሁም የርዕደ መሬት ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ርዕደ መሬቱ ባጋጠመባቸው አካባቢዎች የነበሩ ሰዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ለጥቂት ሰከንዶች የቆየው ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ ሐሙስ ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ38 ደቂቃ ላይ እንደተከሰተ ገልጸዋል። የመሬት መንቀጥቀጡ ባጋጠመበት ጊዜ በሃረማያ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የነበረ አንድ ተማሪ ርዕደ መሬቱ በተከሰተበት ጊዜ ተማሪዎች ከነበሩባቸው ህንጻዎች ተሯሩጠው መውጣታቸውን ለቢቢሲ ተናግሯል። ጨምሮም በመሬት መንቀጥቀጡም ሆነ ተማሪዎች ከህንጻዎች ለመውጣት በሚሯሯጡበት ጊዜ "ከድንጋጤ በስተቀር የደረሰ አደጋ ወይም ጉዳት የለም" ብሏል። "እንቅጥቃጤው በተከሰተባቸው ጥቂት ሰከንዶች ውስጥ ህጻው ወደ ግራና ቀኝ የሚወዛወዝ ወይም የሚነቃነቅ ይመስል ነበር። እንዲሁም ከባድ ድምፅ ይሰማ ነበር" ሲል ተናግሯል። ርዕደ መሬቱ ከተከሰተባቸው ከተሞች አንዷ በሆነችው ሐረር ነዋሪ የሆነው አብዱራህማን በበኩሉ "ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ ሲፈጠር ቤታችን ላይ አንዳች ነገር የወረደ ያህል ነበር የተሰማኝ፤ ነገር ግን ወደ ውጪ በመውጣት ስመለከት ግን ምንም ነገር አልነበረም" ብሏል። የርዕደ መሬት ተመራማሪው ፕሮፌሰር አታላይ አየለ እንደሚሉት "ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ በዋናነት የተከሰተው ኤጀርሳ ጎሮ በምትባለው ቦታ ሲሆን ስፍራው ለሃረማያና ለድሬዳዋ የሚቀርብ ነው።" ሐሙስ ምሽት ያጋጠመው ቀላል የመሬት መንቀጥቀጥ የፈጠረው ንዝረት እስከ ሐረር ከተማ እንደተሰማ ማረጋገጣቸውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲው ፕሮፌሰር አታላይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጨምረውም ርዕደ መሬቱ በሬክተር ስኬል 3 ደረጃ ላይ የተመዘገበ ሲሆን መጠኑም አነስተኛ ከሚባሉት የሚመደብ በመሆኑ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት እንደሌለ አመልክተዋል። ኢትዮጵያን ለሁለት በሚከፍለው የስምጥ ሸለቆ ውስጥ በሚገኙ በርካታ ቦታዎች ላይና ከፍታማ ስፍራዎች ላይ እንዲህ አይነቱ ርዕደ መሬት መከሰቱ የሚጠበቅ እንደሆነ ፕሮፌሰር አታላይ ተናግረዋል። ርዕደ መሬቱ የተከሰተበት "ይህ ቦታ በስምጥ ሸለቆ ጫፍ ላይ የሚገኝ ስለሆነ የሚጠበቅ ነው። ከዚህ በፊትም በአካባቢው ተመሳሳይ ነገር ተከስቶ ያውቃል" ብለዋል። እንዲህ አይነቱ የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ የሚያጋጥመው ግን አፋር ውስጥ በሚገኘው ሰመራ አካባቢ 'አይሻ ብሎክ' በሚባለው ቦታ መሆኑን ጠቁመዋል። የመሬት መንቀጥቀጦች መጠንና የሚከሰቱባቸው ጊዜያት በትክክል ቀድሞ ስለማይታወቅ በተለይ በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ባሉ ቦታዎች የሚገነቡ ህንጻዎች አደጋውን በሚቋቋሙበት ሁኔታ በጥንቃቄ መሠራት እንዳለባቸው ፕሮፌሰር አታላይ ይመከራሉ። \nSummary in the same language as the doc:
በኢትዮጵያ ምሥራቃዊ ክፍል ውስጥ በሚገኙ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ትናንት ሐሙስ ምሽት ርዕደ መሬት መከሰቱን ባለሙያና ነዋሪዎች ገለጹ።
amh_Ethi
train
docsummary
GEM/xlsum
amharic
340
Title: ከባህር ዳር - አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ዛሬም አልተከፈተም\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ይሄው መንገድ ትናንት ይከፈታል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ዛሬም አለመከፈቱን ተሳፋሪዎችና የደጀን ወረዳ አስተዳዳርና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ካሳሁን አስፋው ለቢቢሲ ገልፀዋል። ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ከጎንደር የተሳፈረችው ትዕግስት ደሴ ትናንት ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት አካባቢው ላይ ሲደርሱ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተሽከርካሪዎች ተደርድረው እንደተመለከተችና መንገድ መዘጋቱን እንደሰማች ትገልጻለች። ተሳፋሪዎቹ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች እንደሆኑ የምትናገረው ትዕግስት፤ ወደ ደጀን ከተማ ተመልሰው ለማደር እንደተገደዱ ትናገራለች። ደጀን ከተማ ተመላሽ ተሳፋሪዎችን በሙሉ የሚያስተናግዱ ሆቴሎች ባለመኖራቸው አብዛኛው ሰው በቤተክርስቲያንና ሌሎች ቦታዎች ደጅ ላይ ተጠልለው በከተማው ሕዝብ ምግብና አንዳንድ እርዳታዎች ተደርጎላቸው እንዳደሩ ተመልክታለች። ዛሬ ጠዋት መንገዱ ይከፈት ይሆናል በሚል ተስፋ ደጀን ያደሩት ተሳፋሪዎቹ፤ መንገዱ ዛሬም ባለመከፈቱ ሕፃናት፣ ሴቶች እና አረጋዊያን ለእንግልት እየተዳረጉ ነው ብላለች። • ነገ በአዲስ አበባ የሚደረግ ሠልፍም ሆነ ስብሰባ የለም-የአዲስ አበባ ፖሊስ • "ምን ተይዞ ምርጫ?" እና "ምንም ይሁን ምን ምርጫው ይካሄድ" ተቃዋሚዎች ዛሬ እንደውም ይባስ ብሎ ከአዲስ አበባ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎችም መንገዱ በመዘጋቱ ወደ መጡበት ለመመለስም የትራንስፖርት አገልግሎት አለመኖሩን አክላለች። ትናንት ከአዲስ አበባ የሚመጡ ተሽከርካሪዎች ማለፍ የሚችሉ ቢሆንም ይከፈታል በሚል ተስፋ ግን ከመመለስ ይልቅ መጠባበቁን እንደመረጡ በመናገር። "የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምዝገባ በጥቅምት አንድና ሁለት ነው፤ እኔ የተሳፈርኩበት አውቶብስ ውስጥ አብዛኞቹ ተሳፋሪዎች ለምዝገባ ለመድረስ የተሳፈሩ ተማሪዎች ናቸው" ትላለች። ትናንት በነበረው ሁኔታ የሕዝብ ማመላለሻዎች ብቻ ሳይሆኑ ማንኛውም ዓይነት መኪና ማለፍ እንዳማይችልም እንደታዘበችም ነግራናለች። የደጀን ወረዳ አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ የሆኑት አቶ ካሳ አስፋውም በአሁኑ ሰዓት ኦሮሚያ ክልል ያለው መንገድ ስላልተከፈተ ደጀን ከተማ ላይ በርካታ መኪኖችና መንገደኞች በከተማዋ እንዳሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል። መንገዱ የተዘጋው ኦሮሚያ ክልል የአባይ በረሃ አፋፍን ወጣ እንዳሉ ወረ ጃርሶ ወረዳ ላይ መሆኑን መስማታቸውን የሚናገሩት አቶ ካሳ ስለምክንያቱ የምናውቀው የለም ብለዋል። ከትናንት ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ በደጀን ከተማ ያለፉ የሕዝብ ማመላለሻ መኪኖች መመለሳቸውን የሚናገሩት ኃላፊው ትናንት ቀኑን ሙሉ ከኦሮሚያ ፖሊስ ባልደረቦች ጋር ሲደዋወሉ እንደነበር እና እናጣራለን እንዳሏቸውም ያስታውሳሉ። ትናንት ከቀኑ አስር ሰዓት ላይ መንገዱ ተከፈተ ተብሎ እንደነበር በመግለፅም መኪኖች መንቀሳቀስ ቢጀምሩም ምሽት አንድ ሰዓት ላይ ማለፍ ባለመቻላቸው በድጋሚ መመለሳቸውን ይገልፃሉ። መኪኖቹን የፀጥታ ኃይሎች ፈትሸው ቢያሳልፉም ወጣቶች እንደመለሷቸው ከመንገደኞቹ መስማታቸውን ይናገራሉ። በአንድ ቀን ሰባ፣ ሰማኒያ መኪና፣ በምሽት ደግሞ ከእጥፍ በላይ ከደጀን ወደ አዲስ አበባ መስመር የሚንቀሳቀሱ መኪኖች መኖራቸውን በመናገር ከተማዋ ላይ አሁን ከፍተኛ የመኪና ቁጥር መኖሩን ገልፀውልናል። በትናንትናው ዕለት በከተማዋ ከ200 በላይ መኪኖች ማደራቸውን ተናግረው፤ ተማሪዎች፣ አርሶ አደሮች፣ አዛውንቶች፣ ነፍሰጡሮች እንዳሉ፤ ተማሪዎቹም የመመዝገቢያ ቀን እንዳያልፍባቸው ስጋት እንደገባቸው ያስረዳሉ። ከትናንት ጀምሮ የሕዝብ ማመላለሻ መኪኖች ማለፍ እንደማይችሉ ሌሎች ግን ማለፍ እንዳልተከለከሉ አክለዋል- አቶ ካሳ። ዛሬ ማለዳ ግን ከኦሮሚያ ፖሊስ ምላሽ እንዳላገኙ ተናግረዋል። በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን የጸጥታ ኃላፊ አቶ ለማ ሆርዶፋ በበኩላቸው...
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
401
የእስራኤል ጦር ታንኮችን ጭምር ወደ ጋዛ ድንበር አስጠግቷል የእስራኤል መከላከያ ኃይል እንደሚለው ጥቃቱ አሁንም ድረስ እየተካሄደ ሲሆን ወታደሮች በአየርና በእግረኞች በመታገዝ ጥቃቱን እየፈጸሙ ነው። ነገር ግን ወታደሮች ወደ ጋዛ አለመግባታቸው ተለግልጿል። በጋዛ ሮኬቶች፣ ተዋጊ ጀቶችና ሄሊኮፕተሮች ጥቅም ላይ ሲውሉ እንደነበር የቢቢሲ ዘጋቢ ተመልክቷል። እስራኤል እና ፍልስጤማውያን ሰኞ ዕለት ወደለየለት ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ እስካሁን ከ100 በላይ ሰዎች ጋዛ ውስጥ የተገደሉ ሲሆን እስራኤል ውስጥ ደግሞ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። በሌላ በኩል እስራኤል ውስጥ የሚገኙ አይሁዶችና አረቦችም ግጭት ውስጥ ገብተዋል። የእስራኤል ባለስልጣናት ነገሮች በዚህ መልኩ ከቀጠሉ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንዳያመራ ስጋታቸውን ገልጸዋል። የመከላከያ ሚኒስትሩ ቤኒ ጋንትዝ በበኩላቸው በአገሪቱ የተቀሰቀሰውን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር እየተሰማራ እንደሆነና እስካሁንም ከ400 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ደግሞ መከላከያ ኃይሉ በጋዛ ታጣቂዎች ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ አስፈላጊ እስከሆነበት ጊዜ ድረስ እንዲቀጥል በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። በመግለጫውም ጋዛን የሚመራው ኢስላማዊው ቡድን ሃማስ ላደረሰው ጉዳት ከባድ ዋጋ ይከፍላል ብለዋል። የእስራኤል ጦር ጋዛ ድንበር አቅራቢያ ሐሙስ ዕለት የሃማስ ቃል አቀባይ የሆኑት ግለሰብ በበኩላቸው ቡድኑ የምድር ጥቃት ለመፈጸም የሚወስን ከሆነ የእስራኤልን ወታደሮች መራር ትምህርት እንሰጣቸዋለን ሲሉ ተደምጠዋል። የእስራኤል መንግሥት በእስራኤላዊያን እና አረቦች መካከል ከፍተኛ አመፅ መነሳቱን ተከትሎ በሎድ ከተማ የአስቸኳይ ... Continue the article for another 4000 characters max:
ግዜ አዋጅ ማወጁ ይታወሳል። በሎድ ከተማ በተነሳው አመፅ መኪኖች ጋይተዋል እንዲሁም 12 ሰዎች ተጎድተዋል። የከተማው ከንቲባም ስማቸው ከእርስ በእርስ ጦርነት ጋር ተያይዞ እየተነሳ ይገኛል። ማክሰኞ ምሽት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ በሎድ ከተማ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መታወጁን ይፋ አድርገዋል። የእስራኤል የድንበር ጠባቂ ፖሊሶችም ከዌስት ባንክ እንዲመጡ ተደርጓል። በቴል አቪቭ አቅራቢያ ባለችው የሎድ ከተማ የሚኖሩ እስራኤላዊያን አረቦች የጀመሩት የተቃውሞ ሰልፍ ወደ ረብሻ ተቀይሮ ፖሊስ ላይ ድንጋይ በመወርወሩ ፖሊስ ከፍተኛ ድምፅ በሚያሰሙ ፍንዳታዎች ምላሽ ሰጥቷል። የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በሎድ ከተማ በርካታ የንግድ ሱቆች እና ምኩራቦች በእሳት ተያይዘዋል። ሮይተርስ እንደዘገበው አንድ አረብ እየነዳ በነበረበት ወቅት አይሁዶች መኪናውን በድንጋይ አጥቅተዋል። የፍልስጤም ተዋጊዎች በበኩላቸው እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ባካሄደችው የአየር ጥቃት አንድ ህንፃ ሙሉ ለሙሉ መውደሙን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሚሳኤሎችን ወደ ቴል አቪቭ ተኩሰናል ብለዋል። የዚህ ሳምንቱ ግጭቱ ከአውሮፓውያኑ 2014 በኋላ ከባዱ የተባለ ሲሆን በርካታ ንጹሀን ዜጎችና መሰረተ ልማቶች ከፍተኛ ጉዳት እያስተናገዱ ይገኛሉ። የእስራኤል መከላከያ እስከ 7 ሺ የሚደርሱ ተጠባባቂ ወታደሮችን የጠራ ሲሆን ወደ ጋዛ ድንበር ደግሞ ወታደሮችን እና ታንኮችን ማስጠጋት ጀምሯል። ግጭቱ አምስተኛ ቀኑን መያዙን ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሁለቱም አካላት ግጭቱን ለማበረድ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
amh_Ethi
train
xp3longcontinue
GEM/xlsum
amharic
371
Given the below title and summary of an article, generate a short article or the beginning of a long article to go along with them. Title: የዓለም አክስዮን ገበያ በኮረናቫይረስ እየተቃወሰ መሆኑ ተገለፀ\nSummary: በዓለም አቀፍ ደረጃ የአክስዮን ገበያ ከአውሮፓውያኑ የ2008 የዓለም የገንዘብ ቀውስ ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ መቃወሱ ተነገረ።\nArticle (Max 500 characters):
በእስያ የተቀሰቀሰው ኮረናቫይረስ አውሮፓ መድረሱን ተከትሎ የእስያ ገበያዎች በአክስዮን ገበያ መናጋት ክፉኛ ችግር ውስጥ ገብተዋል። የዋልስትሪት ዶጆንስ ሰንጠረዥ ትናንት በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ዝቅተኛ ነጥብ ተመዝግቦበታል። ተመሳሳይ የአክስዮን ገበያ ማሽቆልቆል በጃፓን፣ አውስትራሊያ፣ ኮሪያና ቻይና የአክስዮን ገበያዎች የተመዘገበ ሲሆን ይህም ባለሃብቶችን ክፉኛ እንደጎዳ ተገልጿል። በተለይም የኮረናቫይረስ በጣልያን መቀስቀስ ከተገመተው በላይ ቫይረሱ የዓለም ኢኮኖሚ ላይ ተፅእኖ ሊያሳሰድር ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። የቻይናው እውቅ የኢኮኖሚ ባለሙያ ኢሪስ ፓንግ "ገበያዎቹ በጣም ተስፋ ነበራቸው፤ አሁን ግን በጣም ተስፋቢስ ሊሆኑ ይችላሉ" ሲሉ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። • "ኮሮናቫይረስ በአሜሪካ የሥራ ዕድልን ሊያሳድግ ይችላል" • ኮሮናቫይረስ፡ የወቅቱ አሳሳቢ
amh_Ethi
train
xp3longgenarticle
GEM/xlsum
amharic
141
በመጠለያዎቹ ውስጥ በርካታ ነብሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች ይገኛሉ በመጋቢት ወር የድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በአንድ መጠለያ ስፍራ ብቻ በሚገኙ ሕፃናት ላይ ያየውን የምግብ እጥረት "ድንገተኛ ከሚባለው ወለል በላይ ያለፈ" ነው ብሎታል። አክሎም ቡድኑ በምግብ እጥረት እጅጉን የተጎዱ ነብሰ ጡር እናቶችንም መመልከቱን አትቷል። • ጌዲዮ በዐቢይ ጉብኝት ማግስት • በጉጂ እና ጌዲዮ ግጭት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ "የመጠለያ ጣቢያዎቹ እጅጉን የተጨናነቁ መሆናቸውን በአስከፊ የኑሮ ሁኔታ ላይ መገኘት እንዲሁም ተፈናቃዮቹ ወረርሽኝ ሊከሰት በሚችልበት ሁኔታ ውስጥ መኖራቸውን ተመልክተናል። ተፈናቃዮቹ በተደጋጋሚ ቀያቸውን እንዲለቁ መሆኑ ጤናቸው አስጊ በሆነበት ሁኔታ እንዲኖሩ አድርጓቸዋል።" ብለዋል በስፍራው ያሉት የድንበር የለሽ ሐኪሞች ማህበር የመስክ ባለሙያና አስተባባሪ ማርከስ ቦይኒንግ። ድንበር የለሽ የሐኪሞች ከአካባቢው አስተዳደር ጋር የተፈናቃዮቹን የሚያገኙትን ምግብ ለማሻሻል እየሰራ ይገኛል። የመፈናቀሉ መንስዔ ምንድን ነው? ለአሁኑ ሰብአዊ ቀውስ ምክንያት የሆነው መፈናቀል የጀመረው፤ ባለፈው ዓመት በጉጂ እና በጌዲዮ ተወላጆች መካከል ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ነው። ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ላይ፤ በሁለቱም ማህበረሰቦች መካከል በተነሳ ግጭት ሰዎች መሞታቸው፣ ቤቶች መቃጠላቸው እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቀዬያቸውን ጥለው መሰደዳቸው ተዘግቦ ነበር። • በጉጂ እና ጌዲዮ ግጭት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ ይህን ተከትሎም ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዱ። ብዙ የጌዲዮ ተወላጆችም ከምዕራብ ጉጂ ዞን ተፈናቅለው ጌዲዮ ዞን ወደሚገኙ አካባቢዎች ገብተው መጠለል ጀመሩ። ከጉጂዎች በኩልም የተፈናቀሉ እንዳሉም ይነገራል። \n\nGive me a good title for the article above.
የጌዲዮ ተፈናቃዮች የከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል
amh_Ethi
train
goodtitle
GEM/xlsum
amharic
210
Given the below title and summary of an article, generate a short article or the beginning of a long article to go along with them. Title: እነ አፕል ጉግልና ማይክሮሶፍት በ14 የኮንጎ ቤተሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው\nSummary: አፕል፣ ጎግል፣ ቴስላ፣ ማይክሮሶፍት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሕጻናት የማዕድን አውጪዎች መሞታቸውን ተከትሎ በተከፈተው ክስ ላይ ስማቸው ተጠቅሷል።\nArticle (Max 500 characters):
ክሱ የተከፈተው 14 ኮንጓዊ ቤተሰቦችን በመወከል በዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች በኩል ነው። ክሱ እንደሚያሳየው ድርጅቶቹ ለምርታቸው የሚጠቀሙበት ኮባልት ከህጻናት ጉልበት ብዝበዛ ጋር እንደሚያያዝ ያውቃሉ ሲል ያትታል። ዲሞክራቲክ ኮንጎ ዓለማችን ከሚያስፈልጋት የኮባልት ምርት 60 በመቶውን ታመርታለች። • ከኮርኔል በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ረድኤት አበበ ማዕድኑ የኤሌትሪክ መኪናዎችን፣ ላፕቶፖችንና ስማርት ስልኮችን ለማንቀሳቀስ የሚያገለግለውን ሊቲየም አየን ባትሪ ለማምረት ይውላል። ይኹን እንጂ ምርቱ ከሕገ ወጥ የማዕድን ማውጣት ጋር እንዲሁም ከሰብዓዊ መብት ጥሰትና ከሙስና ጋር ስሙ ተደጋግሞ ይነሳል። በአሜሪካ የተከፈተው ክስ እንደሚያስረዳው እነዚህ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎቹ የሚጠቀሙት የኮባልት ማዕድን ከሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ
amh_Ethi
train
xp3longgenarticle
GEM/xlsum
amharic
146
Title: ሁለት ሜትር ከሃያ አምስት ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ሴኔጋላዊ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ከዓለም ረዥሙ የቀድሞው የእግር ኳስ ተጫዋች ሮማኒያዊው ጆርጅ ሙሬሳን በ6.3 ሴንቲ ሜትር የሚያጥረው የ23 አመቱ ታኮ፤ የታዋቂው የቦስተን ሴልቲክስ ከቋሚዎቹ አስራ አምስት ተጫዋቾች አንዱ ለመሆንም ጥረት ላይ ነው። • የደቡብ አፍሪካ ባሕር ጠላቂዎች በኬንያ አስክሬን ፍለጋ ላይ ሊሰማሩ ነው • የካቶሊክ ቄሶች ማግባት ይፈቀድላቸው ይሆን? • በአሜሪካዊቷ ፖሊስ የፍርድ ሂደት ምስክርነት የሰጠው የዐይን እማኝ ተገደለ ሴልቲክስ ታኮ ፎልን የመረጠበት ምክንያትም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቡ እንደሆነም ተገልጿል። በሴኔጋሏ መዲና ዳካር የተወለደው ታኮ፤ ወደ አሜሪካ የሄደው በ16 ዓመቱ ሲሆን፤ በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሴንትራል ፍሎሪዳ ቅርጫት ኳስ ይጫወት ነበር። ታኮ ለቢቢሲ እንደተናገረው፤ ዩኒቨርስቲው ውስጥ ብዙዎች ሙያውን እንዲያሳድግ ድጋፍ አድርገውለታል። ታዳጊ ሳለ ብዙም ስለ ቅርጫት ኳስ እንደማያውቅ ይናገራል። ጊዜውን ያሳልፍ የነበረው ካርቱን ፊልሞች በማየት ነበር። የአያቱ ቅርጫት ኳስ መውደድ ስፖርቱ ላይ ፍቅር እንዲያሳድር አድርጎታል። ወደ አሜሪካ ከሄደ በኋላ ሙሉ ትኩረቱን ወደ ቅርጫት ኳስ አድርጓል። ጉዞው ግን አልጋ በአልጋ አልነበረም። "ቅርጫት ኳስ መጫወት አልችልም ነበር። ብዙ ነገር መማር ይጠበቅብኝ ነበር። እድለኛ ሆኜ ብዙ ሰዎች ራሴን እንዳሻሽል ረድተውኛል" ይላል። ሂውስተን አንድ ዓመት ከቆየ በኋላ ወደ ቴኒሲ፣ ጂዎርጂያ እና ፍሎሪዳ አቅንቷል። በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሴንትራል ፍሎሪዳ ሁለት ዓመት ቆይቷል። "አንድ ሴኔጋላዊ ታዳጊ ነበርኩ። ቅርጫት ኳስ መጫወት የጀመርኩትም ከስድስት ዓመት በፊት ነበር። ኤንቢኤ ውስጥ ለመጫወት ብዙ ለፍቻለሁ። በጣም እድለኛ እንደሆንኩ ይሰማኛል። ቅርጫት ኳስ ሕይወቴ ነው። አንድ ቀን እንኳን ሳልጫወት ባልፍ አዝናለሁ" ሲል ይናገራል።
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
224
Doc to summarize: እርሳቸው እንደሚሉት በማረሚያ ቤቱ በመጠጥ ውሃ ሽሚያ ምክንያት በሁለት ታራሚዎች መካከል ግጭት ይነሳል። በወቅቱ የነበሩት ስድስት ተረኛ ጠባቂዎች ግጭቱን ለማብረድ በመካከላቸው ይገባሉ። ይሁን እንጂ ታራሚዎቹ ፖሊሶቹን በመደብደብ በዋናው በር በኩል አምልጠዋል ብለዋል። • የምክር ቤቱ ስብሰባ ኢህአዴግን ወዴት ይመራው ይሆን? አቶ ኡዶል ለጊዜው የደረሳቸው መረጃ ይሄ ይሁን እንጂ ድርጊቱ ለመጥፋት ቅድመ ዝግጅት የተደረገበት ሳይሆን እንደማይቀር መንግሥት ጥርጣሬ አለው ብለዋል። "የውሃ እጥረት በሌለበት አካባቢ የመጠጥ ውሃ የግጭት መነሻ መሆኑ በራሱ ተቀባይነት" የለውም ሲሉ ያክላሉ። 316 ታራሚዎች በሚገኙበት በዚህ ማረሚያ ቤት 14 ተረኛ ጠባቂዎች የሚመደቡ ሲሆን ትናንት ግን ስድስት የጥበቃ ፖሊስ አባላት ብቻ እንደነበሩ ታውቋል። ቀሪዎቹ ስምንት ተረኛ ጠባቂዎች እስረኞች ወደ ፍርድ ቤቶች ለማድረስ ሄደው እንደነበር መስማታቸውን ኃላፊው ነግረውናል። • ትውስታ- የዛሬ 20 ዓመት ኢትዮጵያ ሞባይል ስልክን ስትተዋወቅ አቶ ኡዶል በስፍራው ሄደው ያነጋገሯቸው ፖሊሶችም "በሁለቱ ታራሚዎች መካከል ያለውን ግጭት ለመፍታት በመካከል ስንገባ በድንጋይ ደብድበውን ጥለውን ወጡ" ሲሉ ገልፀውላቸዋል። እስረኞቹ በግድያና በተለያዩ ወንጀሎች የተፈረደባቸው ሲሆኑ የፖለቲከኛ እስረኞች አለመሆናቸው ተናግረዋል። • "ኢትዮጵያ የከሸፈች ሀገር እየሆነች ነው" ሻለቃ ዳዊት ከእስር ቤቱ አምልጠው የወጡት ታራሚዎች እስካሁን ያልተያዙ ሲሆን ምርመራና ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል ኃላፊው። በአካባቢው የሙቀት ወቅት በመሆኑ እስረኞች ከክፍላቸው ወጥተው በግቢው ውስጥ ባሉ ቦታዎች እየተዘዋወሩ መቆየት የተለመደ ነው። \nSummary in the same language as the doc:
ትናንት ከረፋዱ 4፡30 አካባቢ 89 ታራሚዎች ከጋምቤላ ማረሚያ ቤት ማምለጣቸውን የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪ ኃላፊ አቶ ኡዶል ለጉዋ ለቢቢሲ ገለፁ።
amh_Ethi
train
docsummary
GEM/xlsum
amharic
213
Title: ቻይና የገቡት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ጂንፒንግን አድንቀዋል\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ሆኖም ፕሬዝደንት "ዢ ሰሜን ኮሪያ የኒውክሊዬር መሣሪያዋን ከጥቅም ውጭ እንድታደርግ የበለጠ ጠንክሮ ሊሠራ ይገባል" ሲሉም አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። "ቤጂንግ በንግድ ጉዳይ ከአሜሪካ የተሻለች ሆና መገኘቷ ቻይና ተጠያቂ አያደርግም" ሲሉ መናገረቸው ግን ብዙዎችን ያስደነገጠ ነበር። የሰሜን ኮሪያ ዋነኛ የምጣኔ ሃብት አጋር እንደሆነች በሚነገርላት ቻይና የሚገኙት ትራምፕ ዋነኛ ትኩረታቸውን የኪም ጁንግ ኡን ኒውክሊዬር መሣሪያ ማምከን ላይ አድረገዋል። ትራምፕና ዢ የ250 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ስምምነት የተፈራረሙ እንደሆነም አሳውቀዋል፤ ነገር ግን ምን ያህሉ አዲስ ምን ያህሉ ደግሞ የቆየ ስምምነት እንደሆነ የታወቀ ነገር የለም። ከቻይና በፊት በደቡብ ኮሪያ ጉብኝት ያደረጉት ትራምፕ ሰሜን ኮሪያ ወደ ስምምነት እንድትመጣ ጠይቀው ፒዮንግያንግ አሜሪካንና ሌላውን ዓለም ልትነካ ባትሞክር እንደሚሻላት አስጠንቅቀዋል። • ዶናልድ ትራምፕ ለሰሜን ኮሪያ፡ "እንዳትሞክሩን" አልፎም ቻይና ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንድታቋርጥና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰሜን ኮሪያ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ተግባራዊ እንድታደርግም ጠይቀዋል። ትዊተር የተሰኘው ማሕበራዊ ድር-ገጽ በተከለከለባት ሃገረ ቻይና ከደረሱ በኋላ ትራምፕ ቢያንስ አራት ጊዜ በትዊተር ገፃቸው ላይ ሃሳባቸውን ያሰፈሩ ሲሆን ስለጉዳዩ የተጠየቁት የዋይት ሃውስ ባለሥልጣን "የፈለጉትን ነገር መፃፍ ይችላሉ" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ትራምፕ ዕለተ ሐሙስ በቻይና ቤተ-መንግሥት የእራት ግብዣ ካደረጉ በኋላ ወደ ቪየትናም እንደሚሄዱም ይጠበቃል።
amh_Ethi
train
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
187
Doc to summarize: ሜክሲኳዊቷ ነርስ የፋይዘር ባዮንቴክ ክትባትን ለመወጋት የመጀመርያዋ የላቲን አሜሪካ ዜጋ ሆናለች። ይህ ዘመቻ የተጀመረው ትናንት ሐሙስ ሲሆን ሜክሲኮ 3ሺህ ብልቃጥ ክትባት ወደ አገሯ እንደገባ ነው ዘመቻውን የጀመረችው። ሜክሲኮ ተህዋሲው በርካታ ዜጎችን ከገደለባቸው የዓለም አገራት ተርታ ትመደባለች። በዓለም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በተህዋሲው ያለቀባቸው አገራት በቅደም ተከተል አሜሪካ፣ ብራዚል ሕንድና ሜክሲኮ ናቸው። ሜክሲኮን ተከትሎ ቺሌ እና ኮስታሪካ የጀርመን/አሜሪካ ሰራሹን ፋይዘር ባዮንቴክ ክትባትን ለዜጎቻቸው መስጠት ጀምረዋል። አርጀንቲናም በተመሳሳይ ከቀናት በኋላ ክትባት መስጠት ልትጀምር እንደሆነ ይፋ አድርጋለች። ሆኖም አርጀንቲና የመረጠችው የክትባት ዓይነት ራሺያ ሰራሹን ሰፑንትኒክቪ ሲሆን 300ሺህ ብልቃጥ ቦነስ አይረስ መድረሱ ተሰምቷል። ከደቡብ አሜሪካ አገሮች ከፍተኛ ሕዝብ በተህዋሲው የሞተባት ብራዚል ግን እስከ አዲሱ የፈረንጆች ዓመት የካቲትድረስ ክትባቱን መስጠት እንደማትጀምር ተዘግቧል። አወዛጋቢው ፕሬዝዳንቷ ቦልሴናሮ ክትባቱን እንደማይወስዱ ተናግረዋል። ምክንያቱም እኔ በቫይረሱ ተይዤ ስለነበረ የመከላከል አቅም አዳብሪያለሁ ብለዋል። ረቡዕ ሜክሲኮ የደረሱበት 3ሺህ ብልቃጥ ክትባቶች የተመረቱት ቤልጂየም ውስጥ ነው። የመጀመርያዋ ተከታቢ ነርስ ክትባቱን ስትወስድ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሎፔዝ ኦፕራዶር በተገኙበት ለሕዝብ በቀጥታ ተላልፏል። የሜክሲኮ መንግሥት በቀጣይ ሁሉንም የጤና ባለሙያዎች ቅድሚያ ሰጥቶ ክትባቱን ለማዳረስ እንደሚሞክር ቃል ገብቷል። ሜክሲኮ 1 ሚሊዮን 300ሺህ ዜጎቿ በተህዋሲው ተይዘው 120ሺህ የሚሆኑት ሞተውባታል። ቺሊ 600ሺህ ሰዎች ተይዘውባት 16ሺ የሚሆኑት ሞተውባታል። አርጀንቲና 1 ሚሊዮን 600ሺ ሰዎች ተይዘው 42ሺ የሚሆኑት ሞተዋል። የቺሌው ፕሬዝዳንት ሰባስቲያን ፓኔራ የክትባቱ መጀመር የአዲስ ተስፋ ዘመን መምጣትን ያመላክታል ሲሉ ለሕዝባቸው ንግግር አድርገዋል። \nSummary in the same language as the doc:
በላቲን አሜሪካ አገሮች የኮቪድ-19 ክትባትን ለመጀመርያ ጊዜ በዘመቻ መስጠት ተጀምሯል። በተለይ ሜክሲኮ በዚህ ረገድ ቀዳሚ ሆናለች።
amh_Ethi
train
docsummary
GEM/xlsum
amharic
226
Title: አረጋውያንን በነጻ የሚያሳፍረው ባለታክሲ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
አቅመ ደካሞችን በመንገድ ላይ እያዩ ማለፍ ይከብደኛል የሚለው ማርቆስ በተለይ ነፍሰጡሮችን ዝም ብሎ ለማለፍ ልቡ ስለማያስችለው ገንዘብ ሳይጠይቅ በነፃ ወደሚፈልጉበት ቦታ ይወስዳቸዋል። ይህ ተግባሩ በብዙ ሰዎች ዘንድ እውቅና ያሰጠው ማርቆስ በአካባቢው ባይኖር ብዙ ሰዎች በስልክ ደውለው ይጠሩታል። እሱም የተለመደ መተባበሩን ያከናውናል። ''ሥራ ላይ ካልሆንኩኝ በፍጥነት ሄጄ እተባበራቸዋለሁ። '' ይላል • አምስት ነጥቦች ስለቀጣዩ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ • በሰው ክፋይ ሕይወት መዝራት - የኩላሊት ንቅለ ተከላ ''ታክሲው ባዶ ሆኖ መሄድም ቢሆም አልወድም። '' እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን የመተባበር ሥራ ላይ ስታተኩር ዋናው ሥራህ ጋር አይጋጭብህም ወይ? ስንል ለማርቆስ ጥያቄ አቅርበንለት ነበር። ''ሲጀመር እኔ ምንም አላስበውም፤ ከሥራዬም ጋር እስካሁን የተጋጨብኝ ነገር የለም። እንደውም መጀመሪያ ያንን ሥራ አስቀድሜ ከጀመርኩ ቀኔ ደስ የሚል ሆኖ ነው የሚውለው'' በማለት ይመልሳል። በጠዋት ከቤት ሲወጣ ለትራንስፖርት አገልግሎት የተሰለፉ ዕድሜያቸው የገፋ ሰዎችን ሲመለከት ሁለትም ይሁን ሦስት ፌርማታ ድረስ የሚፈልጉበት ቦታ ያደርሳቸዋል። አንዳንዴ አምስትም ስድስትም ሊወስድ እንደሚችል ይናገራል። አንዳንድ ጊዜም ደንበኛ ጭኖ እየሄደ እንኳን አቅመ ደካሞችን ሲመለከት አስፈቅዶ ሰዎቹን እንደሚጭናቸው ይናገራል። ደንበኞችህ፣ ጓደኞችህና ሌሎች በአቅራቢያህ ያሉ ሰዎች ምን ይሉሃል? ለሚለው ጥያቄ መልስ ሲሰጥ፣ ''ደንበኞች በጣም ደስ ይላቸዋል። አንዳንዶቹ እኔ በምሄድበት መንገድ ከሆነ ምንም ችግር የለውም ይላሉ። ሌሎቹ ደግሞ የሚሄዱበት መንገድ ካልሆነ ደስተኞች አይሆኑም'' ብሏል። ''ሁሉም ሰው አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ሊኖረው አይችልም። ጓደኞቼ ደግሞ ''በርታ፣ ጠንክር እኛ ያላሰብነውን ነገር ነው እያደረግክ ነው ያለኸው ይሉኛል።'' የላዳ ታክሲ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ሁለት ዓመት የሆነው ማርቆስ፤ በሹፌርነት ተቀጥሮ በሚሠራበት ወቅትም ይህንኑ ተግባር ያከናውን እንደነበር ይናገራል። ''ታክሲው ባዶ ሆኖ መሄድም ቢሆም አልወድም። '' ''ወደ ተለያዩ ቦታዎች ስላክ ብዙ ጊዜ ብቻዬን ስለሆነ የምሄደው በመንገዴ ያገኘኋቸውን ሁሉ እየጫንኩ አልፍ ነበር። ተቀጣሪ እንደመሆኔ የመኪናው ባለቤቶች ደስተኞች አይሆኑም። እኔ ግን ዝም ብዬ የተቸገሩ ሰዎችን ሳገኝ እተባበር ነበር።'' '' እንደውም የራሴ መኪና ቢኖረኝ እኮ እንደልቤ እሠራ ነበር እያልኩ እመኝ ነበር፤ አሁን ይኸው የተመኘሁትን ነገር እያደረግኩ ነው።'' ማርቆስ ይህንን በጎ ተግባር ሲፈጽም ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ እንዳልሆነ ይናገራል። • ለ10 ዓመታት እጆቹን ያልታጠበው የቴሌቪዥን አቅራቢ • ሜድ ኢን ቻይና- የሀገር ባህል አልባሳቶቻችን አንዳንድ ሰዎች ተቸግረናል እዚህ ቦታ ቶሎ ድረስልን ብለው ደውለውለት እሱ በቦታው ደርሶ ሲደውልላቸው አውቀን ነው፤ እውነተኛ መሆንህን ለማረጋገጥ ፈልገን ነው የሚል ምላሽ እንደሚሰጡት ይናገራል። ''ረጅም መንገድ ተጉዤና ያንን ሁሉ ጊዜዬን አባክኜ እንዲሁም ነዳጄን ጨርሼ በቦታው ስደርስ 'ታማኝነትህን ለማረጋገጥ ነው' የሚሉ ሰዎች ናቸው ትንሽ ያስቸገሩኝ።'' ከዚህ በተረፈ ግን እስካሁን ምንም ችግር እንዳላጋጠመው የሚናገረው ማርቆስ ወደፊትም ቢሆን ይህንን በጎ ተግባሩን እንደሚቀጥልበት ጽኑ እምነቱ ነው።
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
378
በዚህም መሠረት ትምህርት ቤቶች ከመከፈታቸው በፊት በጸረ ተህዋስ መድኃኒት እንዲጸዱ ማድረግና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል፣ የእጅ ማጽጃ ማሟላት እንዲሁም አካላዊ ርቀትን ማስጠበቅ የሚያስችላቸውን ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም እንደየ ትምህርት ቤቶቹ ነባራዊ ሁኔታ ትምህርት በፈረቃ እና አንድ ቀን በመዝለል በተራ የማስተማር ሥራቸውን ማከናወን ይችላሉም ተብሏል። የተማሪዎችን ቁጥር በተመለከተም ሚኒስቴሩ ባስቀመጠው መስፈርት መሰረት በአንድ ክፍል ውስጥ ከ20 እስከ 25 ተማሪዎችን ማስተማር እንደሚቻል ፈቅዷል። በተጨማሪም በአገሪቱ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በሦስት ዙር ትምህርት እንዲጀምሩ ሊደረግ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ቤቶችን ዳግም መክፈት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት እየተደረገ ባለው ውይይት ላይ ይህ ምክረ ሃሳብ መቅረቡን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጠቁሟል። ውይይቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀን ጨምሮ፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችና ሌሎች ሚኒስትሮችም የተገኙ ሲሆን፤ የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁንም በሦስት ዙር የሚከናወነውን ትምህርት የማስጀመር ሂደትን በተመለከተ ምክረ ሐሳባቸውን አቅርበዋል። በዚህም መስረት በገጠር ወረዳና ቀበሌ ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች መጀመሪያ በተባለው ዙር ጥቅምት 9/2013 ዓ.ም፣ በሁሉም ዞንና የክልል ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በ2ኛው ዙር ጥቅምት 16/2013 እንዲጀምሩ ሃሳብ ቀርቧል። ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞን የሚገኙት ደግሞ ትምህርት ሚኒስቴር በሦስተኛ ዙር ብሎ ባስቀመጠው ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም ይጀም... Continue the article for another 4000 characters max:
ሩ የሚል ምክረ ሐሳብ ማቅረቡ ተገልጿል። የብሔራዊ ፈተና የሚወስዱት የ8ኛና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሁሉም ለፈተና እንዲቀመጡና የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናም ህዳር 22 እና 23/2013 ዓ.ም እንዲወስዱ ታቅዷል። ፈተና ላይ መቀመጥ የሚችሉት ተማሪዎች የ7ኛ ክፍልን ተምረው ያጠናቀቁና የ8ኛ ክፍል አንደኛ መንፈቀ ዓመት ትምህርትንም የተከታተሉ ሊሆኑ እንደሚገባም ሚኒስቴሩ ጠቁሟል። በተመሳሳይ መልኩ ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መቀመጥ የሚችሉትም የ11ኛ ክፍልን አጠናቀው ያለፉና የ12ኛ ክፍል የመጀመሪያ መንፈቀ ዓመት ትምህርት የተከታተሉ ሊሆኑ ይገባል ብሏል። የ12ኛ ክፍልም መልቀቂያ ፈተና ወቅትም ከህዳር 28 አስከ ታህሳስ 1/2013 ዓ.ም እንደሚሆንም በምክረ ሐሳቡ መጠቀሱን ሚኒስቴሩ አመልክተወል። የትምህርት አሰጣጡን ሂደት በተመለከተ ለመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚወጣው መመዘኛ በግል ትምህርት ቤቶች ተፈፃሚ እንደሚሆን ያሰፈረ ሲሆን በምክረ ሐሳቡ ላይ የሚደረገው ውይይት እንደቀጠለ መሆኑም ተገልጿል። ባለፈው ዓመት የኮሮናቫይረስ በኢትዮጵያ መገኘቱ ከተረጋገጠ በኋላ ትምህርት በቶች በመጀመሪያ ለሁለት ሳምንታት እንዲዘጉ ተደርጎ የነበረ ሲሆን፤ በተከታይነት የበሽታውን መስፋፋት ለመግታት በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሰረት አስካሁን ተዘግተው መቆየታቸው ይታወሳል።
amh_Ethi
train
xp3longcontinue
GEM/xlsum
amharic
333
Content: ነገር ግን አበረታች መድሃኒት አለመውሰዳቸውን ማረጋገጥ የሚችሉ የሩሲያ ሯጮች የሩሲያን ሳይሆን ነፃ ሰንቅ ዓላማ አንግበው መሳተፍ እንደሚችሉ ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ አስታውቋል። ይህ እገዳ እንደ አውሮፓውያኑ በ2014 በሩሲያ ሶቺ ተዘጋጅቶ በነበረው ውድድር ላይ በመንግሥት እውቅናና ድጋፍ ስፖርተኞች አበረታች መድሃኒት ወስደዋል በሚል ምርመራ መደረጉን ተከትሎ ነው። "ከዚህ ጥፋት በኋላ ጉልህ መስመር ማስመር ያስፈልጋል" ብሏል ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውሳኔ በመላዋ ሩሲያ ተወግዟል። አንዳንድ ፖለቲከኞች ደግሞ ኦሊምፒክ ውድድሩ ላይ ጨርሶ አለመሳተፍ ያስፈልጋል በማለት ውትወታ ላይ ናቸው። ሌሎች ደግሞ ንፁህ ለሆኑ ሯጮች የመሳተፍ እድል መሰጠቱን በአዎንታዊነቱ ተመልክተውታል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባህና ቦርዱ ውሳኔውን ማክሰኞ እለት በሎዛን ሲያስተላልፉ መጀመሪያ ላለፉት 17 ወራት በቀድሞ የስዊዘርላንዱ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ሽሚድ መሪነት የተደረገው የምርመራ ግኝትና ምክረ ሃሳብን በሙሉ ካነበቡ በኋላ ነው። ውሳኔውም በግልፅ ያስቀመጠው የሩሲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መታገዱን፤ ነገር ግን ንፁህ ሯጮች "ሯጭ ከሩሲያ ኦሊምፒክ" ተብለው እንዲሳተፉ እንደሚጋበዙ ነው። ምንም እንኳ ሩሲያ በተደጋጋሚ ብታስተባብልም የሺሚድ ሪፖርት ግን ሩሲያ የፀረ አበረታች መድሃኒት ህጉን በመተላለፍ ከአራት ዓመት በፊት ሯጮች አበረታች መድሃኒት እንዲወስዱ መንግሥት ነገሮችን ማመቻቸቱን ይጠቁማል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባህ "የሩሲያ ድርጊት የኦሊምፒክ ውድድሮችና የስፖርትን ክብር የሚነካ ነው። ስለዚህም ውሳኔው ለወደፊቱ አበረታች መድሃኒት ላይ ጠንካራ አቋም ለመያዝ የሚያስችል፤ ለደረሰው ጥፋትም የማያዳግም መስመር የሚያሰምር መሆን አለበት"ብለዋል። በደቡብ ኮሪያዋ ፒዮንግቻንግ የሚካሄደው ኦሊምፒክ ውድድር እንደ አውሮፓውያኑ የካቲት ዘጠኝ የሚጀምር ሲሆን የስፖርቱ ማማ የሆነችው አገር ሩሲያ በሌለችበት የሚካሔድ ይሆናል። የሩሲያ አሎምፒክ ኮሚቴ ለምን ታገደ? ምርመራውና ሁሉም ነገር የጀመረው እንደ አውሮፓውያኑ በ2014 የሶቺ ውድድር ወቅት የሩሲያ ፀረ አበረታች መድሃኒት ቤተሙከራ ዳይሬክተር የነበረው ዶክተር ግሪጎሪ ሮድቼንኮቭ ነገሩን የይፋ ማውጣቱን ተከትሎ ነው። ዶክተሩ በአገሪቱ የተቀናጀ ለስፖርተኞች አበረታች መድሃኒት የመስጠት አሰራር እንዳለ እሱም አበረታች መድሃኒቶችን ማዘጋጀቱን፤ በምርመራ እንዳይደረስበትም የሽንት ናሙናዎችን ያቀያይር እንደነበር ተናግሯል። ዓለም አቀፉ ፀረ አበረታች መድሀኒት ኤጀንሲ (ዋዳ) ደግሞ የካናዳ የህግ ፕሮፌሰር እና የስፖርት ጠበቃው ዶክተር ሪቻርድ ማክላረን ጉዳዩን እንዲመለከቱት አድርጓል። የማክላረን ሪፖርት እንደ አውሮፓውያኑ ከ2012 እስከ 2015 በተለያየ ስፖርት ውስጥ የነበሩ አንድ ሺህ ሯጮች አበረታች መድሃኒት እንዲጠቀሙ ከማድረግ እቅዱ ተጠቃሚ ሆነዋል። ከሩሲያ ስፖርት ቤተሙከራ የወጣ ነው ተብሎ ዋዳ የደረሰው መረጃ ከማክላረን ድምዳሜ ጋር የሚጣጣም ነው። በውጤቱም በርካታ ሯጮች በቀደመ መረጃ ሁሉ እንዲታገዱ ተደርጓል። ሜዳሊያዎችም ተነጥቀዋል። ባለፈው ሳምንት ደግሞ በስዊዘርላንዳዊው ጠበቃ ዴኒስ ኦስዋልድ የሚመራው የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሌላ ኮሚሽን ደግሞ ከዶክተር ሮድቼንኮቭ ለተገኘው መረጃ ምሉዕ ትንታኔ ሰጥቷል። \nThe previous content can be summarized as follows:
ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአበረታች መድሃኒት ጋር በተያያዘ ሩሲያ በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት በፒዮንግቻንግ በሚደረገው ኦሊምፒክ ውድድር ላይ እንዳትሳተፍ እገዳ ጣለባት።
amh_Ethi
test
prevcontent
GEM/xlsum
amharic
381
Title: "ደስ ብሎኛል፤ የ98 ዓመቷ እናቴ ከኮሮናቫይረስ ድናለች"\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
የወ/ሮ ዳፌን ሻህ ከልጃቸው ዌስሊ ሻህ ጋር አሮጊቷ እናቴ ወደ ሆስፒታል በተወሰደች ጊዜ፣ በተለይም በኮሮናቫይረስ መያዟን ስሰማ አልዋሻችሁም ለመጥፎ ዜና ራሴን እያዘጋጀሁ ነበር። አምቡላንሱ መጥቶ ሲወስዳት እውነት ለመናገር በድጋሚ አያታለሁ ሁሉ አላልኩም ነበር። ሐኪሞቹም ቢሆኑ 99 ዓመት ሊደፍን ወራት የቀሩት ሰው ቫይረሱን ድል ሲመታ አይተው የሚያውቁ አይመስለኝም። እናቴ ዳፌን መጀመርያ ወደ ናይንዌልስ ሆስፒታል ነበር የተወሰደችው። እዚያም አንድ ሳምንት ለሚሆን ጊዜ የሆስፒታል አልጋ ይዛ ቆይታለች። ከትናንት ወዲያ ሰኞ ለታ ነው ከሆስፒታሉ የወጣችው። በዚያ ሆስፒታል ምን ተአምር ተፈጥሮ እንደዳነች ለኔም ትንግርት ነው። የትንፋሽ መርጃ ቬንትሌተር እንኳ አላስፈለጋትም ነው ያሉኝ ሐኪሞቹ። ከሆስፒታሉ ስትወጣ ግን አተነፋፈሷ ትክክል ነበር ማለት አልችልም። የስኮትላንድ የብሔራዊ ጤና አገልግሎት መኮንኖች ሁልጊዜም ምስጉን ናቸው። አሁን ግን የማይታመኑ ነው የሆኑብኝ። እናቴን ላለፉት 20 ዓመታት ተንከባክቢያታለሁ። ያም ማለት አባቴ ከሞተ ጀምሮ እንደማለት ነው፡፡ ለዚህን ሁሉ ጊዜ ጤናዋ እክል አልነበረበትም አልልም። ሆኖም የከፋ ነገር ገጥሟት አያውቅም። በቅርቡ ግን ደረቅ ሳል ስትስልና ትኩሳቷ ሲጨምር ይሄ ነገር ምነድነው ብዬ ሐኪሞች ዘንድ ደወልኩኝ። የጠረጠርኩት አንዳች የባክቴሪያ ኢንፌክሽን አግኝቷት ይሆናል ብዬ ነው፤ በቃ አንቲባዮቲክ ሰጥተዋት ትድናለች ስል አሰብኩ። ሆኖም አንቲባዮቲክ ወስዳ ሳይሻላት ሲቀር ይሄ ነገር ምንድነው ብዬ ወደ ሆስፒታል ወሰድኳት። ከደረቅ ሳሉ በተጨማሪ የምግብ ፍላጎቷ እልም ብሎ ጠፍቶ ነበር። በዚያ ላይ ድካም ይሰማታል። እናቴ በመጪው ሐምሌ ወር ላይ 99 ዓመቷን ትደፍናለች። እንደምንም 100 ዓመት ሞልቷት ከግርማዊነታቸው ንግሥት ኤልዛቤጥ 2ኛ የቴሌግራም የደስታ መግለጫ እንዲላክላት ከልቤ እመኛለሁ። ኮቪድ ሕይወቷን ቢያሳጣት ኖሮ ሐዘኔ ቅጥ ያጣ ይሆን ነበር፤ ምክንያቱም እርሷ ጠንካራ ሴት እንደሆነች አውቃለሁ፡፡ ጤንነቷም ለክፉ የሚሰጥም አልነበረም፡፡ በዚህ ሁኔታ ብትሞት ትልቅ ሐዘን ላይ ነበር የምወድቀው። እርሷ አልጋ በያዘችበት ሆስፒታል አንድም ሰው እንዲጠይቃት አይፈቀድም ነበር። መጀመርያ አካባቢ እናቴ ምን እየሆነ እንዳለ የገባትም አይመስለኝም። "ልጄ ምነው ቸል አለኝ፤ እንዴት ታምሜ አይጠይቀኝም" ስትል ተገርማ ነበር። በናይንዌልስ ሆስፒታል ነርሶቹ እንደነገሩኝ "እናትህ ደጋግማ ልጄ የታለ? ልጄን ጥሩልኝ!" ትል ነበር። የጤና ረዳቶቹ ነገሩን ሊያስረዷት ቢሞክሩም ልትሰማቸው የፈቀደች አይመስለኝም። በቀን ቢያንስ አራት ጊዜ ወደ ሆስፒታሉ እደውላለሁ። በእውነት የጤና ባለሞያዎቹን እንዴት ማመስገን እንዳለብኝ አላውቅም። አሁን ይህንን የእናቴን ታሪክ ለሚያነቡ ታማሚዎችም ሆኑ አስታማሚዎች የምለው ነገር አለኝ። "ኮሮና ቫይረስ ክፉ ደዌ ነው፤ ይህ ምንም ጥያቄ የለውም፤ ነገር ግን የ98 ዓመት አሮጊቷ እናቴ ድል ነስታዋለች፤ የምን ተስፋ መቁረጥ ነው ታዲያ!"
amh_Ethi
validation
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
347
የአሜሪካ መንግሥት የ 'ዋካንዳ' ግዛትን ዝርዝሩ ውስጥ በስህተት ያስገባው በግብርና ክፍል የሠራተኞች ፈተና ወቅት ነበር። የክፍሉ የዋጋ ቁጥጥር ዝርዝር ሲወጣ፤ 'ዋካንዳ' ን ከዳክዬ፣ ከአህያ እና ከላሞች ተርታ ወጥቶ ነበር። 'ዋካንዳ' በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ የሚኖር በጣም ኃይለኛ የሆነ ጥቁር ግስላ የሚኖርበት ልብ ወለዳዊ አገር ነው። • አምሳለ ዋካንዳ በጢስ አባይ ይገነባ ይሆን? • ዶናልድ ትራምፕ በመከሰስ ሶስተኛ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆኑ • በሺዎች የሚቆጠሩ የጀርመን ተማሪዎች የኢሜላቸውን ይለፍ ቃል ለማግኘት ወረፋ ይዘዋል የአሜሪካ መገናኛ ብዙሀን ስለጉዳዩ ሲጠይቁ፤ ልብ ወለዳዊ አገሩ ከዝርዝሩ ተሰርዟል። "አሜሪካ የንግድ ጦርነት ጀምራለች" የሚሉ ሽሙጦችም ተሰምተዋል። 'ዋካንዳ' ለመጀመርያ ጊዜ የወጣው፤ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1966 'ፋንታስቲክ ፎር' የተሰኘ ፊልም ላይ ነበር። አምና ኦስካር ሽልማት ያሸነፈው 'ብላክ ፓንተር' ፊልም ላይ ሲነሳ ደግሞ ሁለተኛው ነው። 'ዋካንዳ' በስህተት ዝርዝር ውስጥ እንደገባ ያወቀው ፍራንሲስ ቴስንግ የተባለ ኒውዮርክ የሚኖር የሶፍትዌር መሃንዲሰ ነበር። ላመለከተው ስልጠና መርሃ ግብር የእቃዎች ዋጋ ዝርዝር በሚመለከትበት ግዜ ነበር 'ዋካንዳ' ን ዝርዝሩ ውስጥ ያየው። ፍራንሲስ 'ዋካንዳ' ን ዝርዝሩ ውስጥ ሲያገኘው "በጣም እንደተደናገረ" ነበር ለሮይተርስ የተናገረው። "አገሩን ፊልሙ ላይ እንደማውቀው ረስቼው ከሌላ ነገር ጋ ተምታቶብኝ ነበር" ብሏል። 'ዋካንዳ' ከዝርዝሩ ውስጥ ከተሰረዘ በኋላ የአሜሪካ ግብርና ክፍል ቃል አቀባይ ለዋሽንግተን ፖስት እንዳሉት፤ 'ዋካንዳ' ሠራተኞችን ለመፈተን ሲባል ዝርዝር ውስጥ የገባ እንጂ በይፋ የተካተተ እንዳልሆነ ተናግረዋል። "ስለ ዋካንዳ የወጣው መረጃ ለ... Continue the article for another 4000 characters max:
መፈተን ከወጣ በኋላ መሰረዝ ነበረበት፤ አሁን ተሰርዟል" ብለዋል። ልብ ወለዳዊ ስሞች በስህተት በገሀዱ ዓለም ሲመጡ ይህ ለመጀመርያ ግዜ አይደለም። በ2017 የፖላንድ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ዊቶልድ ዋዚስዝክዎስኪ ለሪፖርተሮች 'ቤሊዝ' እና ሳን 'ኤስኮበር' የተባሉ የሌሉ ስሞችን ተጠቅመው ተናግረው ነበር።
amh_Ethi
validation
xp3longcontinue
GEM/xlsum
amharic
239
Given the below title and summary of an article, generate a short article or the beginning of a long article to go along with them. Title: ኮሮናቫይረስ ፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመንገደኞቹ የኮቪድ-19 ኢንሹራንስ ሽፋን ጀመረ\nSummary: በአፍሪካ ትልቁና ፈር ቀዳጅ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመንገደኞቹ የኮቪድ-19 ኢንሹራንስ ከመስከረም 21/2013 ዓ.ም መጀመሩን አስታውቋል።\nArticle (Max 500 characters):
የኢንሹራንስ ሽፋኑ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚጓዙ ዓለም አቀፍ መንገደኞች በሙሉ ሲሆን፤ መንገደኞችን መመለስ፣ ለይቶ ማቆያና ሌሎችም የህክምና ወጪዎችን እንደሚሸፍን አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። 'ሼባ ኮምፎርት' የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ኢንሹራንስ መንገደኞች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፍረው በጉዟቸው ወቅት በኮቪድ-19 ቢያዙ የህክምና ወጪያቸው እስከ አንድ መቶ ሺህ ዩሮ ድረስ ይሸፈንላቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ለለይቶ ማቆያም በየቀኑ 150 ዩሮ፣ ለአስራ ቀናትም ያህል እንደሚሸፈንላቸው ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። አየር መንገዱ የመንገደኞቹን ጤናና ደኅንነት ለመጠበቅና ያለምንም ሃሳብ በሰላም እንዲጓዙ ለማድረግም ይህንን የኢንሹራንስ ሽፋን መጀመሩን አስታውቋል። ዓለም አቀፉ የኢንሹራንስ ሽፋኑንም በተመለከተ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
amh_Ethi
train
xp3longgenarticle
GEM/xlsum
amharic
147
Title: ያለመከሰስ መብት ለማን? እስከምን ድረስ?\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
የፍትህ ወርቃማ ሚዛን የዚህ «ልዩ ከለላ» ተጠቃሚዎች ከሆኑት መካከል የህዝብ እንደራሴዎች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት እና የዳኝነት አካላት ይገኙበታል። የመብቱ የጀርባ አመክንዮ ግለሰቦቹን እና አካላቱን በመክሰስ ወይንም ለፍርድ በማቅረብ ከሚገኘው ጠቀሜታ ይልቅ ካለ ክስ እና ተጠያቂነት በማለፍ የሚሳካው ማህበረሰባዊ ግብ የላቀ ነው ከሚል ዕምነት ጋር ይያዛል። ሆኖም ይሄ የከለላ መብት ተነስቶ ግለሰቡ ወይንም አካሉ ላይ ክስ የሚከፈትባቸው አግባቦች ፈፅሞ የሉም ማለት አይደለም። • አብዲ ሞሃመድ ያለመከሰስ መብታቸው ተገፈፈ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲዊ ሪፐብሊክ ህገ- መንግስት እና የክልል ህገ-መንግስታት ይሄንን መብት ከሰጣቸው ወገኖች መካከል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የክልል ምክር ቤት አባላት ተጠቃሽ ናቸው። ለአብነት የህዝብ ተወካዮችን በሚመለከተው የአፌዲሪ ህገመንግስት አንቀፅ 55 (6) ላይ የአለመከሰስ መብትን እና መብቱ የሚነሳበትን አግባብ እንደሚከተለው ደንግጓል። «ማንኛውም የምክር ቤቱ አባል ከባድ ወንጀል ሲፈፅም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለ ምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም፣ በወንጀልም አይከሰስም።» ይሄን መሰረት አድርጎ ያለመከሰስ መብታቸውን ከተነጠቁት የቀድሞ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መካከል የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ እና የቀድሞው የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ ዓለማየሁ ጉጆ ይጠቀሳሉ። • «ወይዘሮ ጎሜዝ፤ እርስዎ አያገባዎትም! አርፈው ይቀመጡ በልልኝ» ከሰሞኑ ደግሞ የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚደንት አብዲ ሙሃመድ ኡመር እና ስድስት የክልሉ ምክር ቤት አባላት በሶማሌ ክልል ምክር ቤት ውሳኔ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል። እንደ ኢፌዴሪ ህገ-መንግስት ሁሉ በሶማሌ ክልላዊ መንግስት ህገ -መንግስት አንቀፅ 48 (6) ላይ የክልሉ ምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት የሚነጠቅበት አግባብ መቀመጡን ልብ ይሏል። • የፖለቲካ አለመረጋጋት ለኢንስትመንት ደንቃራ ሆኖ ነበር
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
241
Title: 'የምፅዓት ቀን' እምነት ተከታዮቹ ጥንዶች በልጆቻቸው ግድያ ክስ ተመሰረተባቸው\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
የ7 ዓመቱ ጆሽዋና የ17 ዓመቷ ታይሊ ሪያን አስክሬን የተገኘው በአንደኛው ተከሳሽ ዴቤል መኖርያ ቤት ሲሆን ተከሳሽ ደራሲ እንደነበር ታውቋል። ከዚህም ባለፈ ጥንዶቹ 'የምፅአት ቀን' የተሰኘ እምነት ተከታይ መሆናቸውና ባል ቻድ ዴቤል እምንቱን በተመለከተ የተለያዩ ድርሰቶች ማዘጋጀቱ ጉዳዩ የመገናኛ ብዙሃንን ቀልብ ስቦ ነበር። ጥንዶቹ የሚከተሉት ይህ እምነት ለዓለም ፍፃሜ መዘጋጀትን በእጅጉ የሚያበረታታ በመሆኑ ምንአልባት ከህፃናቱ ሞት ጋር ግንኙነት ይኖረዋል በሚል ነው ትኩረትን ያገኘው። በተጨማሪም ዴቤል አዲሱን ትዳር ከመሰረተ ከሳምንት በኋላ የቀድሞ ባለቤቱ መሞቷን ተከትሎ በሌላ የግድያ ወንጀልም ተከሷል። ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን ማስረጃን በመሰወር ነበር የተከሰሱት። ታዲያ ይህ የፍርድ ሂደት ባልተጠበቀ ሁኔታ ተቀይሮ ባለፈው ማክሰኞ ጥንዶቹን በግድያ ወንጀል ተከሰዋል። ጥንዶቹ ከግድያው ክስ ባሻገር በሌብነትና በኢንሹራንስ ማጭበርበር ክስ እንደሚጠብቃቸውም ተገልጿል። የፍሪሞንት ካውንቲ አቃቤ ሕግ ሊንዚ ብሌክ 'የምፅአት ቀን' እምነት ተከታዬቹ ጥንዶች ሆን ብለው 3 ንፁሀንን ገድለዋል ለማለት የሚያስችል በቂ ምክንያት አለን ሲሉ ተደምጠዋል።
amh_Ethi
train
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
154
Title: መምህራን የበለጠ ክብር የሚያገኙት የት ሀገር ነው?\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
በተገላቢጦሽ በብራዚል፣ እስራኤልና ጣሊያን መምህራን ከተማሪዎቻቸው ክብርን ለማግኘት እንኳ ቢናፍቁ ምኞታቸውን ውሃ ይበላዋል እንጂ አያገኟትም። እንግሊዝ ከአሜሪካ ከፈረንሳይና ከጀርመን ተሽላ በደረጃ ከተቀመጡት 35 ሀገራት ዝርዝር ውስጥ መካተት ችላለች። • ጡረተኛው የፍቅር አጋር ለማግኘት በማሰብ እድሜውን ለማስቀነስ ፍርድ ቤት ሄደ • ትራምፕ ጠቅላይ አቃቢ ሕጉን አባረሩ ተማሪዎች ለመምህራኖቻቸው ያላቸው ክብርን በተመለከተ ከተጠየቁ 35 ሺህ ሰዎች መካከል በርካቶች ከሁሉም አናት ላይ ቁጭ ያደረጓት ቻይና ናት። በአውሮጳና በደቡብ አሜሪካ "በአጠቃላይ ተማሪዎች መምህራኖቻቸውን አያከብሩም የሚል አመለካከት አለ" ይሁን እንጂ ተማሪዎች ለመምህራኖቻቸው ያላቸው ክብር እንደ ደቡብ ኮሪያና ሲንጋፖር ባሉ የኤዢያ ሀገራት ጠንካራ ነው። በእነዚህ ሀገራት የሚገኙ ተማሪዎችም ዓለም አቀፍ ፈተናዎች ላይ ሲቀመጡ ተፎካካሪዎቻቸውን ሲዘርሩ ነው የሚስተዋለው። ጥናቱን ያካሄዱት ባለሙያዎችም እንዳሉት ለመምህርነት ክብር ባለበት ስፍራ ብቃቱ እና ተሰጥኦው ያላቸውን መምህራን በማምጣት የተማሪዎቹን ተወዳዳሪነት ከፍ ማድረግ እንደሚያስችል ያሳያል ብለዋል። የመምህርነት ሙያን ተወዳጅ መሆኑን ለማሳየት ከተጠየቁት ጉዳዮች መካከል ወላጆች ለልጆቻቸው መምህርነትን እንደሙያ እንዲቀበሉት ይነግሯቸዋል ወይ የሚለው ነው። በቻይና፣ ሕንድና ጋና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወላጆች ልጆቻቸው መምህር እንዲሆኑ ይነግሯቸዋል። ወላጆች ለመምህራን ያላቸው አመለካከትም በጥናቱ ተካትቷል። በጥናቱ ከተካተቱ ሀገራት መካከል በርካታ ወላጆች የመምህራን የስራ ሰዓትን ዝቅ አድርገው ይመለከታሉ። ይህ መምህራን ረጅም ሰዓት በሚሰሩበት ኒው ዚላንድም ሆነ ዝቅተኛ ሰዓት በሚሰሩበት ፓናማና ግብፅ ተመሳሳይ ነው። በትምህርት ስርዓታቸው የላቁ በተባሉት ካናዳና ፊንላድ የሚገኙ መምህራን ትንሽ ሰዓት ቢሰሩም ወላጆች ግን ረጅም ሰዓት እንደሚሰሩ ያስባሉ። መምህራን የሚከበሩባቸው ሃገራት በደረጃ 1. ቻይና 2. ማሊዢያ 3. ታይዋን 4. ሩሲያ 5. ኢንዶኔዢያ 6. ደቡብ ኮሪያ 7. ቱርክ 8. ህንድ 9. ኒውዚላንድ 10. ሲንጋፖር
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
243
Given the below title and summary of an article, generate a short article or the beginning of a long article to go along with them. Title: በዚህ ዓመት በጣና ላይ የሚታየውን አረም ለማጥፋት እየተሰራ ነው\nSummary: በ2013 ዓ.ም በጣና ሐይቅ ላይ በዓይን የሚታየውን አረም ለማጥፋት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ።\nArticle (Max 500 characters):
ትኩረቱን እምቦጭ እና ሌሎች መጤ አረሞች ላይ ያደረገው የጣና ሃይቅና ሌሎች ውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አያሌው ወንዴ (ዶ/ር) እንዳስታወቁት በዘንድሮው ዓመት በዓይን ሊታይ የሚችለውን አረም ለማስወገድ ይሰራል ብለዋል። በዚህም በዕቅዱ መሠረት ሙሉ በሙሉ በዓይን የሚታይ አረም እንዳይኖር የሚደረግ ቢሆንም በቀጣዩ ዓመት የእምቦጩ ዘር በተለያየ ምክንያት ሐይቁ ላይ በመቅረት 10 በመቶ አረም በድጋሚ ሊኖር ይችላል ብለዋል። በጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም በአንድ ወር ዘመቻ ለማጥፋት ከጥቅምት 09 እስከ ህዳር 09/2013 ዓ.ም የሚቆይ የአንድ ወር ዘመቻ መጀመሩ ይታወቃል። የዘመቻው ዋና ዓላማ 90 በመቶ እምቦጭን ከጣና ሐይቅ ለማረም እና ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮችን በማቀናጀት በጋራ ችግሩን በመፍታት ተምሳሌት ለማድረግ መሆኑን ጠ
amh_Ethi
train
xp3longgenarticle
GEM/xlsum
amharic
153
Content: በጋና ዩኒቨርሲቲ መምህራን የሆኑት ፕሮፌሰር ራንስፎርድ እና ዶክተር ፖል ክዋሜ ቡታኮር 'ሴክስ ፎር ግሬድ' የተሰኘው የምርመራ ዘገባ ላይ እንደተማሪ ሆነው በቀረቡት ሪፖርተሮች ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ ሲፈፅሙ ተቀርፀዋል። ራንስፎርድ ግያምፖ ለስድስት ወራት ከስራ የታገዱ ሲሆን ፖል ቡታኮር ደግሞ ለአራት ወራት ከስራቸው ተገልለው እንዲቆዩ ዩኒቨርሲቲው ወስኗል። • በጋና በቢቢሲ ዘጋቢ ፊልም ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ ሲፈፅሙ የታዩ መምህራን ከሥራቸው ታገዱ • የናይጄሪያ ዩኒቨርስቲ በቢቢሲ ዘገባ ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ ሲፈፅም የታየውን መምህሩን አገደ አጣሪ ኮሚቴው ማስረጃዎቹን ከማጋለጡ በፊት ድርጊታቸውን እንዲያምኑ ለፕሮፌሰር ግያምቦ እና ዶክተር ቡታኮር የጋና ዩኒቨርሲቲ ጥሪ አቅርቦ ነበር። ይሁን እንጂ ሁለቱም የዩኒቨርሲቲው መምህራን "ድርጊቱን አልፈፀምንም" ሲሉ ውንጀላውን በመቃወም ክደውታል። በተመሳሳይ በዚሁ የቢቢሲ የምርመራ ዘገባ ላይ በድብቅ የተቀረፁት በናይጄሪያ የሚሰሩ መምህራንም ከሥራቸው መታገዳቸው ይታወቃል። በናይጄሪያ ሌጎስ ዩኒቨርሲቲ ፣ ዶክተር ቦኒ ፌስ ኢግቤኔጉ እና ዶክተር ሳሙዔል ኦላዲፖ የተባሉት ሁለት መምህራንን ከሥራቸው ያገደ ሲሆን ይህንኑ የሚመረምር ኮሚቴ አቋቁሟል። በምዕራብ አፍሪካ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የተሰራው የቢቢሲ የምርመራ ዘገባ መምህራኖች የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ወሲብን እንደመደራደሪያነት እንደሚያቀርቡ ያሳያል። ማሳሰቢያ : ይህ ታሪክ ግልጽ ወሲባዊ ቃላት አሉበት በዘጋቢ ፊልሙ ውስጥ ዶክተር ፖል ቡታኮር ተማሪ መስላ የመጣችውን ሴት ሪፖርተር በድብቅ ጾታዊ ግንኙነት እንዲመሰርቱ ጥያቄ ሲያቀርብ ይታያል። ቀጥሎም ይህንን ካደረገች የትምህርት ሕይወቷ የተሳካ እንደሚሆን ይገልጻል። ፕሮፌሰር ራንስፎርድ ግያምፖ ደግሞ ለሪፖርተሯ የአግቢኝ ጥያቄ ሲያቀርቡ ይታያል። አስከትለው ደግሞ ከየትኛው ትምህርት ቤት እንደመጣች ጠይቀዋት ስትመልስላቸው ከዛ ትምህርት ቤት የሚመጡ ሴት ተማሪዎች 'የወንድ ብልት' እንደሚያስደስታቸው መስማታቸውን ይገልጻሉ። በምዕራብ አፍሪካ አገራት ያሉ የዩንቨርስቲ መምህራን በተማሪዎቻቸው ላይ የሚፈጽሙት ወሲባዊ ትንኮሳ በቢቢሲ ምርመራ ተጋለጠ። ዘጋቢ ፊልሙ ከተላለፈ በኋላ በጋና እና ናይጄሪያ ከፍተኛ ቁጣና ተቃውሞ ተቀስቅሶ የነበረ ሲሆን የጋና ዩኒቨርሲቲ መምህራኑ ምርመራው እስኪጠናቀቅ ያለምንም ክፍያ ከስራቸው ታግደው እንዲቆዩ ተደርገው ነበር። ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ለእይታ የበቃውን የቢቢሲ የምርመራ ዘገባ ተከትሎ የጋና ዩኒቨርሲቲ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ምርመራውን ከጀመረ ወራት የተቆጠሩ ሲሆን ከትናንት በስቲያ (ሰኞ) ባስተላለፈው ውሳኔ ሁለቱም መምህራን የዩኒቨርሲቲውን ህግና ደንቦች ጥሰዋል ብሏል። ቅጣታቸውን ከጨረሱ በኋላም ስለዩኒቨርሲቲው የጾታዊ ትንኮሳ ሕጎች ስልጠና እንዲወስዱ የሚደረግ ሲሆን ጸባያቸው ታይቶ ደግሞ ወደ ማስተማር ስራቸው ሊመለሱ እንደሚችሉ ኮሚቴው ገልጿል። ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታትም ቁጥጥር ይደረግባቸዋል ብሏል ኮሚቴው። • ወሲባዊ ትንኮሳ ያደረሰባት አለቃዋን በማጋለጧ የታሠረችው ሴት • ወሲባዊ ትንኮሳን ሪፖርት በማድረጓ ተቃጥላ የተገደለችው በዩኒቨርሲቲ መምህራኑ ላይ የተላለፈው ውሳኔ በዋና ከተማዋ አክራ የተቀላቀለ ስሜትን እንደፈጠረ በቦታው የሚገኘው የቢቢሲ ሪፖርተር ቶማስ ናዲ ገልጿል። አንዳንዶች ውሳኔው እጅግ የሚያሳዝንና እንደውም ሌሎችንም የሚያበረታታ እንደሆነ ገልጸዋል። '' እስከዛሬ ሲደረግ የነበረውን ምርመራ ቀልድ የሚያስመስለው ውሳኔ ነው የተላለፈው። ስድስትና አራት ወራት ብቻ ያለደመወዝ ከስራ ማገድ ማለት እኮ ዓመታዊ እረፍት ወሰደው እንዲዝናኑ እንደማድረግ ነው። ይሄ ችግር...\nThe previous content can be summarized as follows:
ወሲባዊ ትንኮሳ ሲፈፅሙ በቢቢሲ ጋዜጠኞች በድብቅ የተቀረፁት ሁለት ጋናውያን መምህራን የለምንም ደሞዝ ከሥራቸው እንዲታገዱ እንደተወሰነባቸው ተገለጸ።
amh_Ethi
train
prevcontent
GEM/xlsum
amharic
402
Title: በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ንቦች የአውሮፕላን በረራ አስተጓጉለዋል\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ጉዳዩ ግራ ያጋባው የአየር መንገድ የንብ ማነብ ባለሙያዎችን በመጥራት እርዳታቸውን ጠይቋል። ባለሙያዎቹም በቦታው በመድረስ ቁጥራቸው እስከ 20 ሺ ይደርሳል የተባሉትን ንቦች ከሶስት የአውሮፕላን ሞተሮች ውስጥ በሰላም አስወጥተዋቸዋል። • ጉባኤው ብአዴንን የት ያደርሰዋል? • «አዲስ አበባ የሁሉም ናት» አርበኞች ግንቦት 7 አጋጣሚው አስገራሚና ያልተለመደ ነው ያሉት ከባለሙያዎቹ አንዱ አክለውም ምናልባት ንቦቹ ራቅ ወዳለ ቦታ እየተጓዙ ደክሟቸው የአውሮፕላኑን ሞተር እንደ ማረፊያ ተጠቅመውት ሊሆን ይችላል ብለዋል። ነገሩን አስገራሚ የሚያደርገው ንቦች ለማረፊያነት የሚመርጧቸው ቦታዎች ብዙ ጊዜ አበባዎች በብዛት የሚገኙበትና ጥሩ መአዛ ያላቸው ናቸው። በአውሮፕላን ነዳጅ ሽታና ሌሎች መጥፎ ጠረኖች የተሞላውን ሞተር መምረጣቸው ደግሞ ለባለሙያዎቹ ግርምታን ፈጥሮባቸዋል። ንቦቹ የበረራ ፈቃዳቸውን እየጠበቁ የነበሩ ሶስት አውሮፕላኖች ሞተሮች ውስጥ ገብተው ሙሉ በሙሉ በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ 25 ደቂቃ እንደፈጀባቸው የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ ሰርጂዮ ዶሳንቶስ ገልጸዋል። የንብ ማነብ ባለሙያው ሜልቪን ዳውሰን ከዚህ በፊት ብዙ የንብ መንጋዎችን ከተለያዩ ቦታዎች እንዳስወጣና ይሄኛው አጋጣሚ ግን የመጀመሪያው እንደሆነ ለጋዜጠኞች ተናግሯል። በአሁኑ ሰአት ንቦቹ በተመሳሳይ የስራ ዘርፍ ተሰማርቶ ከሚገኘው የወንድሙ የእርሻ ማሳ ውስጥ እንደሚገኙም አክሏል።
amh_Ethi
validation
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
169
Title: ራስዎን ካላስፈላጊ የስልክ ጥሪ እንዴት ይታደጋሉ?\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
የማይስፈልግ የስልክ ጥሪ ሊደርስዎት ይችላል 'ሄሎ' በሚል ሰው ፈንታ የህክምና ኢንሹራንስ ይፈልጉ እንደሆነ የሮቦት ድምጽ ቢጠይቅዎስ? ከጣፋጭ እንቅልፍዎ የተነሱት ያለምንም ምክንያት በመሆኑ ይበሳጫሉ። ተመሳሳይ ሁነት ከአንዴም ሁለት ሦስቴ ሊገጥም ይችላል። ነገሩ ወዲህ ነው። በስልክ የሚሰማው ድምጽ የማሽን ሲሆን 'ሮቦኮልስ' በመባል ይታወቃል። በስልክ የሚተላለፈው ድምጽ ከጥሪው በፊት የተቀዳ የማሽን አልያም የሮቦት ድምጽ ነው። የስልክ ጥሪውን በህጋዊ መንገድ የሚጠቀሙበት ቢኖሩም ባልተገባ ሁኔታ ለንግድ የሚያውሉትም አልታጡም። ለአብነት አሜሪካና ካናዳን ብንወስድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ይጠቀሙበታል። አየር መንገዶችም ማስታወቂያ ለመንገር ይገለገሉበታል። ባለፈው ሚያዝያ አሜሪካ ውስጥ 3,400 ሚሊየን የሮቦኮል ጥሪዎች ለ 324 ሚሊዮን ሰዎች መድረሳቸውን የካሊፎርኒያው ዩሜል ድርጅት አሳውቋል። በዋነኛነት ጥሪውን የሚያደርጉት የህክምና እና የመኪና ኢንሹራንስ ድርጅቶች እንዲሁም የቤት ደላላዎችና ሥራ አፈላላጊዎች ናቸው። እነዚህ ድርጅቶች ለሰዎች የሚደውሉት በዘፈቀደ ነው። ለአንድ ግለሰብ በቀን ወይም በሳምንት ውስጥ በርካታ ጊዜ ሊደውሉ ይችላሉ። አንዳንድ ድርጅቶች በደቂቃ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠር ጥሪ ማድረግ ይችላሉ። ሮቦኮል እንደሀሰተኛ ኢሜል ነው ፌደራል ትሬድ ኮሚሽን የተሰኘው ድርጅት እንደሚያመለክተው የስልክ ጥሪው ሲደረግ የደዋዩ ቁጥር ሊደበቅ ወይም የተሳሳተ ቁጥር ሊወጣ ይችላል። ትክክለኛ የስልክ ቁጥር በመጠቀምም ጥሪው የሚተላለፍበት አጋጣሚ አለ። ባለፈው ዓመት በአንድ ወር ውስጥ 375 ሺህ ሰዎች ስለስልክ ጥሪዎቹ ቅሬታ አቅርበዋል። ድርጅቱ እንደሚለው የስልክ ጥሪዎቹ ሲደረጉ ደዋዮቹ ያሉበትን ቦታ መደበቅ የሚችሉበት ቴክኖሎጂ ስለሚጠቀሙ ከየት እንደተደወለ ለማወቅ አስቸጋሪ ነው። እነዚህ ጥሪዎች ሲደርሱዎ ምን ማድረግ እንዳለብዎት ያውቃሉ? መሰል ጥሪ ሲደርስዎት መጀመሪያ ማድረግ ያለብዎት ስልኩን በፍጥነት መዝጋት ነው። በስልክዎ ላይ ቁጥር እንዲያስገቡ ቢጠየቁም አያስገቡ። ቁጥር አስገቡ ማለት ራስዎን ለተጨማሪ ስልክ ጥሪዎች አጋለጡ ማለት ነው። አስከትለው የስልክዎን ሲም ለገዙበት ድርጅት ስለሁኔታው ያሳውቁ። ደዋዩን ወደ ስልክዎ እንዳይደውል ማድረግ ይችላሉ። ቲሎውስ ወይም ሁኮልስ የተባሉ ድረ ገጾች መሰል ጥሪዎችን ለማመልከት የተዘጋጁ ስለሆኑ መጠቀም ይችላሉ። የቴክኖሎጂ መረጃዎች የሚሰራጩበት ዘ ቨርጅ የተባለው የዩቲዩብ ገጽ አርታኢ የሆነው ክሪስ ዌልች "በየቀኑ ስድስት የተሳሳቱ ጥሪዎች ይደርሱኛል" ይላል። ከጥሪዎቹ መሀከል ትርጉም አልባ የሆኑ ማስፈራሪያዎች ይገኙበታል። "ግብር ካልከፈሉ ይታሰራሉ" የሚል መልዕክትን እንደምሳሌ የሚጠቅሰው ክሪስ "መልዕክቶቹ በጣም ይረብሻሉ" ይላል። ክሪስ እንደመፍትሄ የሚያስቀመወጠው ስልክ ቁጥሩን መዝግቦ ሲደውል እንዳይታይ ማገድ (ብሎክ ማድረግ) ነው። ሮቦኮል የሚያደርገውን ስልክ ቁጥር ማመልከትም ይቻላል። የማይፈልጉት ጥሪ ከሆነ ስልኩን ይዝጉት ጥሪ ለማገድ የሚያስችል መተግበሪያ ያላቸው የስልክ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች አሉ። አግልግሎቱን ለማግኘት ጥያቄ ማቅረብም ይቻላል። ሮቦኮል የሚያስቸግራቸው ሰዎች የተለያዩ መተግበሪያዎችን መጫንም ይችላሉ። ዩሜል፣ ሮቦኪለር፣ ትሩኮለር ወይም ሂያ የተባሉ መተግበሪያዎችን ክሪስ ይጠቅሳል። ክሪስ እንደሚናገረው ስልክ ሲገዛ ሮቦኮል ማገድ የሚችል መተግበሪያ አላቸው። ለአብነት ያህል የሳምሰንግ ጋላክሲ ኤስ እና ኖት ስልኮች የሮቦኮል ማስጠንቀቂያ ይሰጣሉ። የስልክ ቀፎ ላይ ከተመዘገቡ ቁጥሮች ውጪ ሲደውሉ ተጠቃሚው እንዳያይ የሚያስችሉ መንገዶች አሉ። 'ዱ ኖት ዲስተርብ'...
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
394
Title: ቁንጅና ተስፋዬ፡ ፋሽንን ከሕንፃ ንድፍ ጋር ያዛመደችው ዲዛይነር\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ቁንጅና ተስፋዬ "በዩኒቨርሲቲ የነበረኝ ቆይታ በማልፈልገው የትምህርት ዘርፍ ቢሆንም እንዲህ ፍላጎት በሌለኝ ነገር ላይ ጉልበቴንና ጊዜዬን ማፍሰስ መቻሌ የምወደውን ነገር ብሠራ ደግሞ ከዚህ በላይ ውጤታማ መሆን እንደምችል በእራሴ ላይ እምነት የፈጠረብኝ ቆይታ ነበር" ትላለች። ቁንጅና በ2006 ዓ.ም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ስትቀላቀል ፋሽን ዲዛይን ትምህርትን የመከታተል ፍላጎቷን ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ማሳካት ስላልቻለች የሥዕል ዝንባሌዋን ለመጠቀም ሥነ-ሕንፃ 'አርኪቴክቸር' ወይም የምህንድስና አስተዳደር 'ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት' ለማጥናት ወሰነች። በዚህም "የፋሽን ዲዛይን ለመሥራት ጊዜ ስለሚሰጠኝ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንትን መረጥኩኝ" ትላለች። • ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን አርቲስቶች ለመዋብ ምን ያህል ይከፍላሉ? "አስተማሪዎቻችን አርክቴክቶች ስለነበሩ የሕንፃ ዲዛይን እንዴት እንደሚሠራ ለማወቅ ዕድሉን ሰጠኝ" የምትለው ቁንጅና ትምህርቱ የመጀመሪያ ምርጫዋ ባይሆንም ትምህርቱ ባካተታቸው የሕንፃ ንድፍ ትምህርቶች የፈጠራና የዲዛይን ችሎታዋን በተለያየ መልኩ ማዳበር እንድትችል ዕድል እንደሰጣት ትናገራለች። በ2010 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስትመረቅ በተመሳሳይ ዓመት ደግሞ የአፍሪካን ሞዛይክ ፋሽን ዲዛይን ውድድር በፈጠራና ተስፋ የተጣለባት ዲዛይነር በመሆን አርቲ-ቴክቸር (አርትንና አርኪቴክቸርን ያቀላቀለ ስያሜ) በተባለ ስብስቧ አሸንፋለች። አርቲ-ቴክቸር (አርትንና አርኪቴክቸርን ያቀላቀለ ስያሜ) ቁንጅና "2010 ዓ.ም ሁለቱን የተለያዩ ዓለሞቼን ያጣመርኩበት ዓመት ነው" ስትል "አፍሪካ ሞዛይክ ያሸነፍኩበት ዲዛይን 'አርቲ-ቴክቸር' ብዬ የሰየምኩትም በውስጡ ሥነ -ሕንፃን ከሥዕል ጥበብ ጋር አዛምጄ ስለሠራሁት ነው" ትላለች። • አክሱምና ላሊበላ ለስራዎቹ መስፈርት የሆኑት ዲዛይነር ልብሶቿ ከሕንፃ ዲዛይን የተዋሱትን መልክ ስትገልፅ ቀጥተኛ መስመሮች፣ ማዕዘናዊ ቅርፆችንና የሕንፃ ንድፍ ላይ የሚካተቱ የተለያዩ ምልክቶችን ትጠቅሳለች። "የአፍሪካ ሞዛይክን ሳሸንፍና ከዩኒቨርሲቲ ስመረቅ ሁለቱንም በአንድ ላይ አጣምሬ መጠቀም እንደምችል የተረዳሁበት፤ እናም ምንም እንኳን አንዱን መርጬ የተማርኩት ባይሆንም በመንገዱ ለተሰጥዖዬ የእራሱን አስተዋፅዖ አድርጎልኝ የሁለት ስኬቶችን ደስታ ማክበር የቻልኩበት ጊዜ ነበር" ትላለች። ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ የሚያጠኑት ዘርፍ በፍላጎታቸው ቢሆን ብዙዎች ስኬታማ ሊሆኑ ይችላሉ ብላ የምታመነው ቁንጅና "እኔ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንትን ስማር እኔን የሚስቡኝ የዲዛይን ክፍሎች ካልሆኑ በስተቀር ብዙዎቹን ክፍል ውስጥ ቁጭ ብዬ ሌላ ነገር ስስል ነው ያሳለፍኩት" ትላለች። ልብስ ዲዛይን የማድረግ ተሰጥዖዋን በጊዜ ማሳየት የጀመረችው ቁንጅና አጀማመርዋን ስታስታውስ፤ በማህበራዊ ሚዲያም ላይ የሠራቻቸውን ልብሶች ታቀርብ ነበር። "አንዴ ውጪ ያለች አክስቴ የሠራሁትን በፌስቡክ አይታ ወዲያውኑ የመስፊያ ማሽን ላከችልኝ፤ ከዚያም በእራሴ ቤት ውስጥ መለማመድ ጀመርኩ" ትላለች። የመጀመሪያ ዲዛይኖቿ 12ኛ ክፍል የአካባቢ ጥበቃ ቀን በተመለከተ ከወዳደቁ ነገሮች የሠራችውና የዩኒቨርሲቲ አንደኛ ዓመት ተማሪ በነበረችበት ወቅት የተሳተፈችበት በሴቶች ቀን ላይ ያተኮረ የፋሽን ሾው እንደሆኑ ቁንጅና ታስታውሳለች። አራተኛ ዓመት ተማሪ ሆና ለልምምድ ስትወጣ ጎን ለጎን የፋሽን ዲዛይን ትምህርትን መከታተል የጀመረችው ቁንጅና ሁለት የተለያዩ ትምህርቶችን እየተማሩ ለማስኬድ መሞከር በጣም ከባድ እንደሆነ ትናገራለች። • የኬንያ ዳኞችን አለባበስ የቀየረች ኢትዮጵያዊት ሁለቱንም ትምህርቶቼን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማጠናቀቅ "የዩኒቨርስቲ ትምህርት ቦታዬ ጦር ኃይሎች...
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
383
Content: የሪፐብሊካን ቃለ አቀባይ እንደተናገሩት ሚዲያ እንዳይሳተፍ የተወሰነው ከኮሮናቫይረስ መመሪያዎች ጋር በተያያዘ መሆኑንም አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል። በሰሜን ካሮላይና የሪፐብሊካን ልዑካን ተሰባስበውም እጩ ፕሬዚዳንቱን ዶናልድ ትራምፕን በይፋ እንደገና ይመርጣሉ። 336 የሚሆኑ ልዑካን በሰሜን ካሮላይና ግዛት፣ ቻርሎቴ ከተማ በዚህ ወር ይሰባሰባሉ። እነዚህ ልዑካን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ቁጥሩ በመገደቡ መገኘት ያልቻሉትን በሺዎች የሚቆጠሩ አባላትን ወክለው ይገኛሉ። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፓርቲያቸው ብቸኛ እጩ ተወዳዳሪ ሲሆኑ፤ እንደገና በይፋ መመረጣቸውም የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻቸውንም እንዲሁ በይፋ መጀመሩን የሚያበስር ነው ተብሏል። "ፓርቲያችን በፌደራል እንዲሁም በተለያዩ ግዛቶች የወጡ የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን በመከተልም ነው ስብሰባውን የሚሳተፉ ሰዎች ቁጥርን የወሰንነው" በማለት ቃለ አቀባይዋ ተናግረዋል። ይህ ውሳኔ ከዚህ በፊት ይደረጉ የነበሩ ስብሰባዎቸን አካሄድ የቀየረ ነው ተብሏል። ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነቱ ስብሰባ የበርካታ ሚዲያዎችን ቀልብ የሚስብና ለህዝቡም መልዕክቶች ይፋ የሚሆኑበት ነበር። የሰሜን ካሮላይና አስተዳዳሪ በሚገኙት ሰዎች ብዛትና አካላዊ ርቀት ጋር ተያይዞ ስብሰባውን ወደ ሌላ ቦታ እንዲያደርጉት መጠየቀቻውን ተከትሎ ግንቦት ወር ላይ ወደ ጃክሰን፣ ፎሎሪዳ እንደሚደረግ ትራምፕ ተናግረው ነበር። ነገር ግን ወደ በኋላ ፍሎሪዳ ሊደረግ የነበረውን ስብሰባ በመሰረዝ ወደቀደመው እቅድ በመመለስ ሰሜን ካሮላይና እንዲካሄድ ተወስኗል።ግዛቲቷ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ያለምክንያት እያቀጣጠሉ ነው በማለት ወንጅለዋል። \nThe previous content can be summarized as follows:
የአሜሪካ የሪፐብሊካን ፓርቲ በዚህ ወር እጩ ፕሬዚዳንቱን በይፋ ለመምረጥ እቅድ ይዟል። ይህ ምርጫም ሚዲያዎች እንዳይሳተፉበትና በዝግም እንደሚካሄድ ተገልጿል።
amh_Ethi
train
prevcontent
GEM/xlsum
amharic
193
Title: የሜላንያ ትራምፕ ሃውልት በትውልድ አገሯ ስሎቫንያ ተቃጠለ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
የሃውልቱ ቀራፂ ብራድ ዶውኒይ እንዳለው ሃውልቱን ያቃጠሉት ሰዎች አሜሪካ የነፃነት ቀኔ ነው ብላ የምታከብረውን ክብረ በዓልም ለመቃወም ነው ብሏል። በበርሊን መቀመጫውን ያደረገው ይህ አርቲስት የሃውልቱን ቀሪ አካልም በነገታው ሙሉ በሙሉ እንዲወገድ አድርጓል። ሃውልቱንም ያቃጠሉ ግለሰቦችንም ፖሊስ እየፈለገና ምርመራ መክፈቱንም ሮይተርስ ዘግቧል። በሃውልቱ መቃጠል ዙሪያ ዋይት ሃውስ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። ሃውልቱ በትውልድ ቦታዋ በስሎቫንያ ማዕከል ሰቭኒካ ይገኝ የነበረ ሲሆን ከዛፍ ግንድም ተቀርፆ ነበር የተሰራው። ሃውልቱ የአሜሪካ ቀዳማዊት እመቤት ሰማያዊ ኮት ለብሳ እጆቿን ወደላይ (ወደ ሰማይ) ዘርግታም የሚያሳይ ነው። በባለፈው አመትም ሲተከል ውዝግቦችን አስከትሎ ነበር። ቀራፂው ለሮይተርስ እንደተናገረው ሃውልቱን ያቃጠሉት ሰዎች "ለምን እና እነማን እንደሆኑ ማወቅ እፈልጋለሁ" ብሏል። ሃውልቱ በአሜሪካ ውስጥ ያለውን ፖለቲካዊ ሁኔታ በተለይም ስደተኞች ጋር የተያያዘ ፖሊሲን አስመልክቶ ውይይት ይከፍታል የሚል ሃሳብ እንደነበረውም ተናግሯል። የዩጎዝላቪያ አካል በነበረችው ስሎቫንያ የተወለደችው ሜላንያ ወደ አሜሪካ የተሰደደችውም ከሁለት አስርት አመታት ነበር። ቀዳማዊት እመቤቷ የፋሽን ሞዴል ነበረች። ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት መሆናቸውንም ተከትሎ የቀዳማዊት እመቤቷ ትውልድ ቦታ የበርካታ ቱሪስቶች መናኸሪያም ሆና ነበር። በባለፈው አመትም በስሎቫኒያ መዲና ልጁብልጃና የዶናልድ ትራምፕም ከእንጨት የተሰራ ሃውልትም ቆሞ ነበር። እንደ ሜላንያ የትራምፕ ሃውልትም በርካታ ውዝግቦችን የያስነሳ ሲሆን፤ ስምንት ሜትር እርዝማኔ ያለው ይህ ሃውልትም በእሳት የወደመው ከወራት በፊት ነው።
amh_Ethi
train
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
196
Content: ምናልባትም ባለ ረዥም ተረከዝ ጫማ አለመጫማት የተሻለ ይሆን? በአሁኑ ሰዓት ሴቶች ባለ ረዥም ተረከዝ ጫማዎችን ለመዘነጫነት ቢጫሟቸውም በቀድሞው መጠሪያዋ ፐርሺያ በአሁኗ ኢራን ባለረዥም ታኮ ጫማ ይጫሙ የነበሩት ወንዶች እንጂ ሴቶች አልነበሩም። የኢራን ፈረሰኛ ወንድ ወታደሮች በጦርነት ወቅት የጫማቸው ታኮ ሚዛናቸውን እንዲጠብቁ ይረዳቸው ነበር። ከእነዚህ ምርጫዎች መካከል የሚፈልጉትን ዕቃ ይምረጡና እንዴት የጭቆና መሣሪያ እንደሆነ ይመልከቱ። መዋቢያ ቁሳቁስ "ወንዶች ፊታቸውን ሳያስውቡ ቢወጡ ምንም ነገር አይባሉም" ምቾች የሌለው ፋሽን "ሰዎች ለምን እንደሚያደርጓቸው አይገባኝም። ያማሉ፣ አይመቹም ደግሞም ቋሚ የሰውነት በሽታ ያስከትላሉ" ቤት ውስጥ የተዘጋጀ ምግብ "ሴት ልጅ ማብሰያ ክፍል ውስጥ ብቻ ነው መሆን ያለባት የሚለው ሃሳብ ሰልችቶኛል" - ኤማ የቤት ውስጥ ሥራዎች "እኩልነት ከቤት ስለሚጀምር ወንዶች ተነስታችሁ ቤት አፅዱ።" ጡት መያዣ "መዋብ ግዴታዬ አይደለም። ያለእሱ ቆንጆም አዋቂም ነኝ̃።" - ሊዛ ዝነኛ ሰዎችን የማድነቅ ባህል "ሁሉም የቁንጅና ሞዴሎች ሰውነት አንድ ዓይነት ነው፤ ደግሞም ደስተኛ አይመስሉም። ይሰለቻል።"- ዌንዲ ጋብቻ "እንደኔ እንደኔ የቃልኪዳን ቀለበቶች በሴት መብት ተሟጋቾች ዘንድ የስድብ ያህል ናቸው። ምክንያቱም ቀለበት ያደረገች ሴት የሌላ ሰው ንብረት መሆኗን ስለሚያመለክት።" ማቲልድ ማህበራዊ ድረ ገፆች "ለታዳጊ ወጣቶች አዕምሮ ሰላም በጣም አደገኛ ነው። በተለይ ለሴቶች። ምክንያቱም ከእውነታ የራቁና አደገኛ በሆኑ አመለካከቶች ተከበዋል።" - ሮሻን በፆታ የተለዩ መጫወቻዎች "በፆታ የተከፋፈሉ መጫወቻዎች በሙሉ ወንዶችንም ሴቶችንም ልጆች የተወሰኑላቸውን ነገሮችን ብቻ እንዲወዱ ያደርጋሉ።" - አና ተጨማሪ ዕቃ የጭቆና መሣሪያዎች ምንድን ናቸው? 'የፀረ-ነፃነት ቆሻሻ መጣያ' የተሰኘውን አመላከከት ምን እነዳስጀመረው ለማየት የራስዎን መሣሪያ ያጋሩን። 2016 ላይ የአንድ ተቋም እንግዳ ተቀባይ ባለ ረዥም ተረከዝ ጫማ እንድትጫማ በአሰሪዎቿ ብትታዘዝም ፍቃደኛ ሳትሆን ሥራዋን በገዛ ፍቃዷ ለቃለች። ከዚያም የእንግሊዝ መንግሥት ሰራተኞች ባለ ረዥም ተረከዝ ጫማ መጫማት ግዴታ እንዳይሆን ህጉ እንዲቀየር ጠይቃ ነበረ። የእንግሊዝ መንግሥት ግን ህጉን ባይቀይረውም በስራ ቦታዎች ላይ የሰራተኞችን የአለባበስ ስርዓት በተመለከተ ማስተካከያዎችን አደርጋለሁ ብሎ ነበር። \nThe previous content can be summarized as follows:
በርካታ ጥናቶች ባለ ረዥም ተረከዝ ጫማዎችን መጫማት የሰውነት ጡንቻ እና አጥንት ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ይጠቁማሉ። ጫማዎቹ ምቾት ስለሚነሱ ተጨማሪ የጫማ ሶል እና ሌሎች ምርቶችን ለመግዛት ያስገድዳሉ።
amh_Ethi
train
prevcontent
GEM/xlsum
amharic
294
Title: አደጋ የተጋረጠበት የትግራይ በለስ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
በለስ ትሉ በክልሉ ያለውን የበለስ ምርት ሲያጠፋ ገበሬው መዓት ወረደብን ነው ያለው። ገበሬው ''የበለስ መዥገር'' ብሎ የሚጠራውን ይህ ትል እስካሁን መፍትሔ አልተገኘለትም። መንግሥትም መድሃኒት ፍለጋ ከመባዘን ውጪ አንዳች ያገኘው ነገር የለም። • የመጭው ዘመን አምስቱ ምርጥ ምግቦች ትሉ ወደ አገር ቤት እንዲገባ የተደረገው ህዝቡን ይጠቅማል ተብሎ ነበር። በመጀመርያ አካባቢ ጥቅሙ በተግባር ታይቷል፤ ገበሬዎች ትሉን በኪሎ እስከ 40 ብር መሸጥ ጀምረውም ነበር። ኮችኔል (የትል) ወደ ትግራይ የገባው በአንድ ቺሊያዊ ኢኮኖሚስት ከ10 ዓመት በፊት ነበር። 60 በመቶ የፔሩ እና የሜክሲኮ ገበሬዎች ትሉን በመሸጥ በሚያገኙት ገቢ እንደሚተዳደሩ ይነገራል። አንድ ኪሎ ኮችኔል እስከ 40 ዶላር ስለሚያወጣ ''ወርቅ የሆነ ትል ነው'' ይሉታል። • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? በትሉ ውስጥ የሚገኘው ቀይ ቀለም ''ካርኒክ አሲድ'' የሚባል ንጥረ ነገር የያዘ ነው። ይህ ንጥረ ነገር ወይንና ቪኖን የመሳሰሉ መጠጦች ቀይ ለማድረግ ይጠቅማል። በተጨማሪ ማርጋሪን እና ማርማላት፣ ኬክና በርገር፣ ሊፒስቲክና የጥፍር ቀለም እንዲሁም ሌሎች ነገሮችን ለመስራት ያገለግላል። ሆኖም ከቁጥጥር ውጪ በመሆኑ ላለፉት በርካታ ዓመታት በለስ ላይ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል። ትሉ በባህሪው በቀላሉ በንፋስ የሚበተን እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በዚህ ምክንያትም በፍጥነት ሊዛመት ችሏል። ደቡባዊ ዞንን አዳርሶ እንደርታ የገባ ሲሆን አሁን ደግሞ በዓጋመ ጋንታ አፈሹም በመከሰቱ ትልቅ ጭንቀት ፈጥሯል። በኮችኔል የተጠቃ በለስ ምርመሩ የት ደረሰ? በ2008 ዓ.ም ትሉ ደቡባዊ ዞንና እንደርታን አልፎ ወደ ሌሎች የትግራይ አካባቢዎች እንዳይዛመት በክልተ አውላዕሎ እና ደጉዓ ተንቤን የማገጃ አካባቢ ተብሎ ተከልሎ ነበር። ይህን ተግባራዊ ለማድረግም የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና የክልሉ የእርሻ እና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊነት ወስደው ነበር። ነገር ግን ትሉ ወደ ወረዳዎቹ ከመግባት ያገደው ነገር የለም። የአዲግራት የበለስ ምርምር ተቋም ሐላፊ አቶ የማነ ካሕሳይ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ''ትሉ እንከላከለዋለን ካልንበት አካባቢ አልፎ ቢገባም ከቁጥጥር ውጪ ግን አይደለም። እንዳመጣጡ ቢሆን ኤርትራ ይደርስ ነበር'' ይላሉ። • ለአደጋ የተጋለጡ ሦስት የትግራይ ቅርሶች ''በለስ በአንድ ዓመት ውስጥ መጥፋት ይችል ነበር። ነገር ግን ከህብረተሰቡ ጋር ባደረግነው ጥረት ብዙ አደጋ አድርሷል ማለት አንችልም። ስለዚህ ከቁጥጥር ውጪ አይደለም ብለን ነው የገመገምነው'' በማለት አስረግጠው ይናገራሉ። ምርምሩ ሲጀመር ትሉን የሚያጠፋ መድሃኒት ተገኝቷል ተብሎ ነበር። እስካሁን ግን ጥቅም ላይ የዋለ የለም። እስካሁን ተቋሙ ትሉን ለመከላከል ያበረከተውን አስተዋጽኦን በተመለተ፤ የሚረጭ መድሃኒት እንደመፍተሄ እንዳልተወሰደ እና የተሻለው ከብራዚል በተገኘ ተሞክሮ ትሉን መቋቋም የሚችል ዝርያ መትከል ላይ እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል። በተለይ መቀለ ዩኒቨርሲቲም በመኾኒ ትሉን የሚቋቋም ዝርያ የመትከል ሙከራ እያደረገ እንደሆነ ኃላፊው ይናገራሉ። ከዚህ ውጪ ትሉን ለማጥፋት የሚያስችል መድሃኒት ተገኝቷል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ጥቅም እንዳልሰጠ የሚገልጹት ኃላፊው፤ ዩኒቨርሲቲው ከሚመለከታቸው አካላትና የውጭ በጎ አድራጊዎች ጋር እየሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል። የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ በለስ ምርምር ተቋም ሀላፊ አቶ የማነ የገበሬው ድርሻ ምንድን ነው? 'እግዚኣብሔር ያመጣውን መዓት እራሱ ይመልሰወቅ'' የሚሉ ገበሬዎች አሉ። አብዛኞቹ ደግሞ መንግሥት እራሱ እንዳመጣው እራሱ መፍትሄ ያምጣ የሚል አመለካከት አላቸው። ዩኒቨርሲቲው ለአርሶ አደሮቹ...
amh_Ethi
validation
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
418
Doc to summarize: ሲዲሲ ትናንት በድረ-ገጹ ላይ ባወጣው ጽሑፍ ላይ ክትባቱ ለበሽታው የበለጠ ተጋለጭ ለሆኑ ሰዎች እስከ ጥቅምት አጋማሽ ሊሰራጭ እንደሚችል ጠቁሟል። “ሲዲሲ ግዛቶች ቀድመው እንዲዘጋጁ በማሰብ ዝግጁ ሊሆን የሚችል የክትባት መጠን እና ጊዜን ለግዛቶች አሳውቋል። ከጥቅምት አጋማሽ እስከ ሕዳር መጨረሻ ድረስ መጠናቸው አነስተኛ ቢሆንም የክትባት ስርጭት ሊኖር ይችላል” ሲሉ የሲዲሲ ቃል አቀባይ ለሬውተርስ ተናግረዋል። ኒው ዮርክ ታይመስ ደግሞ ቀደም ሲል ሲዲሲ ከሁሉም 50 የአሜሪካ ግዛቶች እና አምስት ግዙፍ ከተሞች ከስርጭት ጋር ተያይዞ ያሉ የእቅድ መረጃዎችን ጠይቋል። በኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ ላይ ሲዲሲ ጥቅምት አጋማሽ ላይ በቁጥር አነስተኛ የሆኑ አንድ ወይም ሁለት የኮቪድ-19 ክትባቶች ለስርጭት ዝግጁ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁሟል። ለበሽታው የበለጠ ተጋላጭ ናቸው ለተባሉ እንደ የጤና ባለሙያዎች፣ ለደህንነት ሰራተኞች እና እድሜያቸው የገፉ ሰዎችን የሚንከባከቡ ነርሶች እና ባልደረቦች ክትባቱ ያለ ክፍያ ይሰጣቸዋል ይላል የሲዲሲው ዶክመንት። የተላላፊ በሽታዎች ባለሙያው ዶ/ር አንቶኒዮ ፋውቺ ለኤምኤስኤንቢሲ ቴሌቪዥን ትናንት ሲናገሩ፤ ለኮቪድ-19 ክትባት ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥርን ከግምት በማስገባት እስከ ሕዳር ወር ድረስ የትኛው የኮቪድ-19 ክትባት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ እንደሚሆን መለየት ይቻላል ብለዋል። ሞደርና፣ አስትራዜኔካ እና ፐፊዘር የተሰኙ መድሃኒት አምራቾች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ የሆነ የኮቪድ-19 ክትባት ለማዘጋጀት ጥረት ላይ ይገኛሉ። \nSummary in the same language as the doc:
የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) የአሜሪካ ግዛቶች የጤና ኃላፊዎች የኮሮናቫይረስ ክትባት የበለጠ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ቀድሞ የሚታደልበት አማራጭ ላይ ቀድመው እንዲዘጋጁ ማሳሰቡ ተነገረ።
amh_Ethi
train
docsummary
GEM/xlsum
amharic
210
Content: አሜሪካ ሀገር በሚገኝ ሴርኪኡዝ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን የተማሩት አቶ ቡልቻ ለአስር አመት ካገለገሉ በኋላ ተመልሰውም ወደ ውጭ ኃገር ሄዱ። አሜሪካ በነበሩበትም ወቅት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ይሰሩ የነበሩ ሲሆን ኢትዮጵያም መጥተው ቀዳሚ የግል ባንኮች አንዱ ከሆኑት አዋሽ ባንክን አቋቁመዋል። የባንኩም ዋና አላማ ለኦሮሞ አርሶ አደር ብድር ለማመቻቸት እንደሆነ አቶ ቡልቻ ይናገራሉ። •ከተማ ይፍሩ፡ ያልተነገረላቸው የአፍሪካ አንድነት ባለራዕይ ኢህአዴግ ስልጣን ከተቆናጠጠ በኋላ የፓርላማ አባል የነበሩት አቶ ቡልቻ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል። የፓርላም አባል ነበሩ። ስለ ፖርላማው ምን ሀሳብ አለዎት? የኢትዮጵያን ፓርላማን ለማየት እንጅ የእዉነት ነው ብየ አይደለም የገባሁት። ምክንያቱም እንደሌሎች ሃገራት ህዝቦች በቁጥራቸዉ መጠን አልነበረም የሚወከሉት።ለምሳሌ እኔ ከወለጋ ነበር የተመረጥሁት። እዉነት ቢሆን ኖሮ እኔ ከተመረጥኩበት ወረዳ ሶስት ሰዎች ይወከሉ ነበር።ማን የት እንደሚመረጥ ደግሞ ኢህአዴግ ይወስን ነበር። ስለዚህ ለመረጠኝ ህዝብ ድምጽ መሆን ከንቱ ምኞት ሆኖ ቀረ። •ጤፏን ለማስመለስ እየተውተረተረች ያለችው ኢትዮጵያ ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያን ችግር ማዉራት ብፈልግም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ግን ስለመጣሁበት ቀበሌና እንድናገር ስለተገደድኩ በወከልኩት አካባቢ ታጥሬ ነበር። እንደ አንድ የኢትዮጵያ ዜግነቴ ስለመላዉ ኢትዮጵያ እንጅ ስለቦጅድርማጅ እና ላሎ አሰብ ብቻ ማዉራት አለብኝ እንዴ? ለምሳሌ ያህል ኢትዮጵያ ሶማሊያ ላይ ለምን ጦርንነት ታዉጃለች ብየ ስጠይቅ ምን አገባህ የሚል መልስ ተሰጥቶኛል። ለዚህም ነዉ የኢትዮጵያ ፓርላማ እንደሌሎች አይደለም የምለው። እንደሚታወቀው ፓርላማዉ የነሱ ብቻ ነበር። ከኢህአዴግ ሀሳብ ውጭ የሚናገሩ ካሉ በጠላትነት ይታዩ ነበር። ።በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው? በጊዜዉ ፓርላማዉ እንጅ የዴሞክራሲ ፅንሰ ሃሳብ አልነበረም። ፍላጎታቸው በፓርላማው ውስጥ የነሱን ሃሳብ የሚያንፀባርቅና ተመሳሳይ ንግግሮችን የሚያደርግ ሰው ነው የሚፈለገው። ለኔ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ይፈልጋል የሚለውን ነው ቅድሚያ የምሰጠው። ለምሳሌም ያህል ስለ ሀገሪቷ የምጣኔ ሃብት፣ የዉጭ ጉዳይና ግብር ስለመሳሰሉ ጉዳዮች ጥያቄ አነሳ ነበር። በተለይም ትምህርት ቤቶች ሊስፋፉ እንደሚገቡ አፅንኦት ሰጥቼ እናገር ነበር። በኋላም ላይ ትምህርት ቤቶችን አስፋፍተዋል ለዚህም ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነዉ። ባጠቃላይ ግን ስናየው ያ መንግስት ሀገር የሚያሳድግ ሳይሆን የሚያቀጭጭ ነበር። ለዉጡን እንዴት ያዩታል? ይሄ ለዉጥ በዚህ አጭር ጊዜ ይመጣል ብየ አላሰብኩም ነበር። ምክንያቱም በተደጋጋሚ የኢህአዴግ መንግሥት የሚመጡትን 25 አመታት አስተዳድራለሁ ይል ስለነበር። አምላክ በዚች አጭር ጊዜ ይሄን ብርሃን ያሳየናል ብየ አላሰብኩም። ወደዚህ ሀገር ከተመለስኩ በኋላ ብዙ አዲስ ነገሮችን አይቻለሁ። ለምሳሌ አሁን ቃለመጠይቁን በራሴ ቋንቋ ነዉ እየሰጠሁህ ያለሂሁት።ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት እድል አግኝተን አናዉቅም ነበር። ከ20 አመት በፊት ለቢቢሲ ሁለት ደብዳቤ ጽፌ ነበር። የኦሮሞ ህዝብ ብዙ ቁጥር ስላለዉ በራሳችን ቋንቋ ሚዲያ እንዲከፍትልን ነበር።አሁን ይሄዉ ቢቢሲ በራሳችን ቋንቋ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።ለለዚህም ቢቢሲን አመሰግናለሁ። ኢትዮጵያዊነትን እና ኦሮሞነትን እንዴት ያዩታል? ከኦሮሞ ዉጭ ኢትዮጵያ የለችም። ይሄ ብቻም አይደለም። አማራም ጉራጌም እና ሌሎች ብሄሮችም ለኢትዮጵያ ያስፈልጓታል።እኔ ኦሮሞነትን ከፍ አድርጌ ኢትዮጵያዊነትን የማሳንስ አይደለሁም። ኦሮሞን በስፋትና በብዛት ካየን የኢትዮጵያ የበኩር ልጅ...\nThe previous content can be summarized as follows:
ፖለቲከኛው ቡልቻ ደመቅሳ በመንግሥት ስራ መሳተፍ የጀመሩት በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ሲሆን በወቅቱም የገንዘብ ሚኒስቴር ም/ሚኒስትር በመሆን ለአስር አመት ያህልም አገልግለዋል።
amh_Ethi
validation
prevcontent
GEM/xlsum
amharic
417
Title: የላውሮ ግምት፡ አርሴናል ከቶተንሃም እንዲሁም ሊቨርፑል ከኤቨርተን\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
አርሴናል ከቶተንሃም ኤምሬትስ ላይ አርሴናል ቶተንሃምን ሲያስተናግድ አንፊልድ ላይ ደግሞ ሊቨርፑል እና ኤቨርተን ይጫወታሉ። ቼልሲ በበኩሉ በሜዳው ፉልሃምን ያስተናግዳል። የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን እነዚህን ጨምሮ የሌሎቹንም ጨዋታዎች ግምት አስቀምጧል። የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት ቀጣዩ የፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ማን ይሆን? አወዛጋቢው የእግር ኳስ ዳኞች ማስመሪያ የላውሮ ግምቶች አርብ ካርዲፍ ከዎልቭስ ዎልቭሶች ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ማግኘት የቻሉት አንድ ነጥብ ብቻ ነው። ከእነዚህ ጨዋታዎች በአንዳንዶቹ ጥሩ መንቀሳቀስ ችለዋል። ካርዲፎች በበኩላቸው በኤቨርተን 1 ለ 0 ተሸንፈዋል። ኤቨርተኖች ጨዋታውን ማሸነፍ የሚገባቸው ቢሆንም ካርዲፎች ጥሩ ተንቀሳቅሰዋል። ይህን ደግሞ ከዎልቭስ ጋርም ይደግሙታል። የላውሮ ግምት: 1-1 ቅዳሜ ክሪስታል ፓላስ ሁለቱም ቡድኖች ከወራጅ ቀጠና ትንሽ ከፍ ያሉ ሲሆን ጎል የማስቆጠር ችግርም አለባቸው። ፓላሶች ባለፈው ሳምንት ወደ ኦልድትራፎርድ በማቅናት አንድ ነጥብ ማግኘታቸው ጥሩ ሲሆን በዚህ ሳምንት ነጥብ መጣል አይኖርባቸውም። የላውሮ ግምት: 1-0 ሃደርስፊልድ ከብራይተን ዎልቭስን ካሸነፉት ሃደርስፊልዶች ጋር የሚደረገው ጨዋታ ለብራይተኖች ከባድ ነው። ሃደርስፊልዶች ካለፉት ደካማ ውጤቶች በኋላ ጥሩ ውጤት ከማስመዝገባቸውም በተጨማሪ ጥሩ እየተንቀሳቀሱ ነው። የላውሮ ግምት: 1-0 ሌስተር ከዋትፎርድ ሌስተሮች በሜዳቸው ካሸነፉ ወራት ተቆጠሩ። ዋትፎርዶች ባለፈው ሳምንት በሊቨርፑል በሦስት ጎል መሸነፍ አልነበረባቸውም። የላውሮ ግምት: 2-0 ማንቸስተር ሲቲ ከበርንማውዝ በርንማውዞች ከሦስት ሽንፈት በኋላ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታም የተለየ ውጤት አይጠብቁም። ስለድል ማሰብ ያለባቸው ከዚህ ሳምንት በኋላ ነው። ምክንያቱም ብዙ ቡድኖች ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ሲጫወቱ የሚያስቡት በዚህ መልኩ ነው። የላውሮ ግምት: 3-0 ኒውካስል ከዌስት ሃም ኒውካስሉ አሰልጣኝ ራፋኤል ቤኒቴዝ ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ሲጀምሩ ለብዙ ጨዋታዎች ነው። ባለፉት አራት ጨዋታዎችም አልተሸነፉም። ዌስት ሃሞች ደግሞ ከስድስት ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ነው ያሸነፉት። አቋማቸው የሚዋዥቅ ቡድን ቢሆንም ወደ ወራጅ ቀጠና ይገባሉ ብዬ አላምንም። የላውሮ ግምት: 2-0 ሳውዝሃምፕተን ከማንቸስተር ዩናይተድ ሳውዝሃምፕተኖች ውጤታማ መሆን እየቻሉ አይደለም። ማንቸስተር ዩናይትዶችም ቢሆኑ ጥሩ ባይሆኑም በዚህ ጨዋታ ግን የበላይ ይሆናሉ። ከክሪስታል ፓላስ እና ያንግ ቦይስ ጋር እንዳየነው ዩናይትዶች በአጥቂ መስመር ችግር አለባቸው። ሆኖም ይህን ጨዋታ እንደሚያሸንፉ እገምታለሁ። የላውሮ ግምት: 0-2 እሑድ ቼልሲ ከፉልሃም አዲሱ የፉልሃም አሰልጣኝ በመጀመሪያ ጨዋታቸው ድል ቢያስመዘግቡም ይኼኛው ግን ከባድ ይሆንባቸዋል። እንደገመትኩትም ቼልሲዎች ባለፈው ሳምንት ወደ ቶተንሃም በማቅናት የመጀመሪያ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል። ሆኖም ተከታታይ ሽንፈት ወይም ውጤት ማጣት ይገጥማቸዋል ብዬ አላስብም። የላውሮ ግምት: 2-0 አርሴናል ከቶተንሃም ቶተንሃሞች ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሊጉም ሆነ በአውሮፓ ደረጃ ከባድ ጨዋታዎች ቢገጥሟቸውም ሁሉንም አሸንፈዋል። ከዚህ በተጨማሪ የተጫዋቾች ከጉዳት መመለስና ማገገም ይህን ጨዋታ ያሸንፋሉ እንድል አድርጎኛል። አርሴናሎች ባለፉት ጨዋታዎች አላሳመኑኝም። ሆኖም ባለፉት 18 ጨዋታዎች ሳይሸነፉ ለመጓዝ ችለዋል። የላውሮ ግምት: 1-2 ሊቨርፑል ከኤቨርተን ኤቨርተኖች በአሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ ስር ጠንካራ በመሆን ላይ የሚገኙ ሲሆን መጀመሪያ የመርሲ...
amh_Ethi
test
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
390
Content: መግለጫው በዋነኛነት ያተኮረው ከሰሞኑ የታሠሩበት አባላቱን ኤልያስ ገብሩና ስንታየሁ ቸኮል ላይ ሲሆን፤ ከአንድ ዓመት በፊት እስረኞች ተፈተው የነበረው ሁኔታ ወደ ኋላ እንደተቀለበሰም እስክንድር ተናግሯል። • "ከጄ/ል አሳምነው ጋ በምንም ጉዳይ ያወራሁበት አጋጣሚ የለም" እስክንድር ነጋ • "ታከለ ኡማ አዲስ አበባን መምራት የለባቸውም" እስክንድር ነጋ "እስር ቤቶቻችን የህሊና እስረኞች አልባ የነበሩ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን የህሊና እስረኞች ያሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፤ እነዚህም እስረኞች ኢ- ሰብአዊ በሆነ ሁኔታ ነው የተያዙት፤ ይህንንም መግለጫ ስንጠራ ያሉበትን ሁኔታ ለማሳወቅ እንዲሁም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ለመጠየቅ ነው" ብሏል። መግለጫው ተጀምሮ ለምን ያህል ደቂቃ ተሰጥቶ እንደነበር በትክክል እንደማያውቅ ለቢቢሲ ገልጾ፤ መግለጫው ተነቦ ጋዜጠኞች ሁለት ጥያቄ ጠይቀው መልስ መስጠት ሲጀምሩ እንደተቋረጠ ተናግሯል። መግለጫው ለመቋረጥ የበቃው "ጥያቄ አለን" በሚሉ ሰዎች በተነሳ ረብሻ ሲሆን፤ በባላደራው ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ላይ የተገኙ በቁጥር 10 የሚሆኑ ወጣቶች ደምፃቸውን ከፍ አድርገው ''ባንዲራችን ይህ ነው'' በማለት ባለ ኮከቡን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርገው ሲያሳዩ ነበር። ''አገር መገንባት ነው የምንፈልገው አንጂ ማፍረስ አይደለም''፣ ''አይሳካልህም''፣ ''ምክር ቤቱ ኦሮሞን ያገለለ ነው''፣ ''ታከለ [የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ] መጤ አይደለም''፣ ''አዲስ አበባ የሁሉም ናት'' የሚሉ መፈክሮችን ደጋግመው ሲያሰሙ ነበር። የነበረውን ሁኔታ አረጋግቶ መቀጠል አይቻልም ነበር ወይ? በሚል ከቢቢሲ ለቀረበለት ጥያቄ "ማረጋጋት አይቻልም" የሚል ምላሽ የሰጠው እስክንድር፤ የታቀደበት እንደነበርና የተደራጀም እንደነበር ገልጿል። "ሰንደቅ አላማዎቹ በደንብ ተዘጋጅተው፣ ጥቃት የሚያደርሱበት ስውር መሣሪያዎች ይዘው፤ የሚናገሩት ነገር በስሜት ሳይሆን በደንብ የተጠና እንደነበር የሚያመላክቱ ነገሮች አግኝተናል" ብሏል። ነገሮችን ለማረጋጋትና ሁኔታው ወደ ሌላ ከማምራቱም በፊት ቶሎ ከአዳራሹ እንደወጣም ይናገራል። • “የመከላከያው በአደባባይ ሚዲዎችን እከሳለሁ ማለት አስፈሪ ነው” ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይ • ለባለስልጣናቱ ግድያ አዴፓ ራሱን ተጠያቂ እንዲያደርግ ህወሐት ጠየቀ "የምናዝነው ከመልዕክቱ ይልቅ የተፈጠረው ነገር በመጉላቱ ነው፤ የተነሳንበትን ዋነኛ አላማ ውጦብናል፤ በዚህም በጣም እናዝናለን" ብሏል። መግለጫውን ከመስጠታቸው ከአንድ ቀን በፊት "የተለመዱ" የሚላቸው ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎች እንደነበሩ የሚናገረው እስክንድር በስልክ፣ በቪዲዮም ማስፈራሪያ እንደደረሰው ገልጿል። ጥዋት ላይም ቢሮ ሊገባ በነበረበት ወቅት 'ሲቪል የለበሰ' አንድ ፖሊስ ቢሮ ላይ ጠብቆ እንዳይገባ ከልክሎት እንደገፈተረው ለቢቢሲ ተናግሯል። ከዚህም በተጨማሪ ጋዜጠኞች እንዳይገቡ እንደተከለከሉና የምክር ቤቱ አባል ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉና ሌላ አንድ አባል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው እንደነበር ግን ብዙም ሳይቆይ እንደተለቀቁ ገልጿል። በተደጋጋሚ የባልደራስ ምክር ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ሲዘጋጅ የተሰረዘበትን እስክንድር የፖለቲካ ምህዳሩ ስለመጥበቡ አንድ "ቁንፅል ማሳያ" ነው ይላል። ከዚህ በላይ ግን ሰሞኑን አገሪቱ ውስጥ ከተከሰቱ ችግሮች ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በፀረ-ሽብር ሕግ መጠየቃቸው "ግዙፋ ማሳያ" እንደሆነም ይናገራል። "አገራችን ወደ ኋላ እየተጓዘች ስለ መሆኗ፤ የተገባው ዲሞክራሲ፣ ይመጣል ተብሎ የተገባው ቃል ለመታጠፉ ምንም ማስረጃ የለም፤ ያ ትልቅ ማስረጃ ነው" ብሏል። አክሎም "በአጠቃላይ አገራችን ጥሩ አቅጣጫ ላይ አይደለም። ነገር ግን...\nThe previous content can be summarized as follows:
በጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ የሚመራው የባላደራ ምክር ቤት ዛሬ ሐምሌ 3፣ 2011 ዓ. ም በምክር ቤቱ ቢሮ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ተቋርጧል።
amh_Ethi
train
prevcontent
GEM/xlsum
amharic
414
ኮሮናቫይረስ ፡ ዱባይ ውስጥ ሥራ አጥተው የተቸገሩ ወገኖቿን የምትመግበው ኬንያዊት\nየኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት ዋንጌቺ ዋሩይሬ ለዱባይ ታክሲ ሹፌር ነበረች። ዋሩይሬ "የተወሰነ ወራት በዝቅተኛ ክፍያ ከሰራሁ በኋላ በዋናው አየር መንገድ የሚገኘው አንደኛው ተርሚናል በወረርሽኙ ምክንያት በመዘጋቱ የተነሳ በጥቅምት ወር ላይ ሥራ ፈታሁ" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። የሶስት ልጆች እናት የሆነችው ዋሩይሬ፣ በርካቶች በወረርሽኙ ምክንያት ስራ አጥተው መቸገራቸው ስትመለከት፣ ቢያንስ የሚበሉትን በነጻ በመስጠት ጭንቀታቸውን ለማቃለል ማሰቧን ገልጻለች። የዋሩይሬ ባለቤት ሥራ አለመፍታቱን ገልጻ እርሱ በሚገዛላት አስቤዛ፣ ሥራ ፈትተው ቤታቸው ለተቀመጡ የአገሯ ልጆች ምግብ በማዘጋጀት በፌስ ቡክ ገጿ ላይ በማጋራት አቅራቢያዋ የሚኖሩ መጥተው እንዲወስዱ መጠየቅ ጀመረች። ዋረያሬ በሳምንት ሁለቴ ከ 20 እስከ 25 ሰው እንደምትመግብ ትገልጻለች። ከዚህ ቀደም በመንግሥት ብርቱ አሽከርካሪነቷ ታይቶ 'ምርጥ የዱባይ ታክሲ አሽከርካሪ' ተብላ ተሸልማ ነበር። \n\ntl;dr:
ኬንያዊቷ በዩናይትድ አረብ ኤምሬተስ በኮሮናቫይረስ ምከንያት ሥራ ፈትተው ለተቀመጡ ኬንያውያን ምግብ እየሰራች በነጻ እንደምትመግብ ተሰምቷል።
amh_Ethi
train
tldr
GEM/xlsum
amharic
130
Given the below title and summary of an article, generate a short article or the beginning of a long article to go along with them. Title: «ከእወደድ ባይ ፖለቲከኞች ተጠንቀቁ» ባራክ ኦባማ\nSummary: ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ ከፍ ባለ መድረክ ላይ አሰሙት የተባለው ንግግር ብዙዎችን አስደንቋል። ንግግራቸው አሁን አሜሪካ ውስጥ ሥልጣን ይዞ ያለውን መንግሥት በሾርኔ ወጋ ለማድረግ የተጠቀሙበት ነው እየተባለ ይገኛል።\nArticle (Max 500 characters):
15 ሺህ ያህል ሰው በታደመበትና የደቡብ አፍሪቃውን የነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላን ለመዘከር በተዘጋጀው መድረክ ላይ ንግግር ያሰሙት ኦባማ የማሕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መነጋገሪያም ሆነው ነበር። እስቲ ኦባማ ካሰሙት ንግግር መካከል አምስት አበይት ነጥቦች መርጠን ወደእናንተ እናድርስ። ማንዴላን ውትድርና ያሰለጠኑት ኢትዮጵያዊ ፩. እውነት የተቀደሰች ናት «በእውነታ ልታምኑ ይገባል» አሉ ኦባማ፤ «እውነታውን መሠረት ያላደረገ ነገር ለትብብር አይገፋፋምና።» «እኔ ይሄ አትሮነስ ነው ስል፤ 'አይ አቶ ኦባማ ተሳስተዋል እንዴት ዝሆኑን አትሮነስ ይሉታል' ካላችሁኝ ነገር ተበላሸ ማለት ነው።» በተመሳሳይ ርዕስ ላይ የቆዩት ኦባማ በአየር ንብረት ለውጥ የማይስማሙ ሰዎች ጋር መስማማት ሊከብዳቸው እንደሚችል ጠቁመዋል። ተቀማጩ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፓሪሱ የአየር ን
amh_Ethi
test
xp3longgenarticle
GEM/xlsum
amharic
160
Title: የውጭ ሀገራት ዜጎች በደቡብ አፍሪካዋ ሶዌቶ ጥቃትን እየሸሹ ነው\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ከሱቁ ፊት ለፊት ጥቃት የደረሰበት ሶማሊያዊ የሀገሪቱ ፖሊስ እስከ አሁን ድረስ 27 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን ጥቃቶቹንም አውግዟል። በ«ዋትስአፕ» የመገናኛ አውታር የአካባቢው ሰዎች ሶማሊያዊ ተከራዮችን ከቤታቸው እንዲያስወጡ ካልሆነ ግን ጥቃቱ ለእነሱም እንደሚተርፍ ቀን ገደብ የተቀመጠለት የዛቻ መልዕክት እንደተሰራጨም ተነግሯል። የአከባቢው ነዋሪዎች የውጪ ሃገር ዜጎች የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ምርቶች ይሸጣሉ ሲሉ ይወቅሷቸዋል። በሶዌቶ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ሶማሊያዊያን ፣ዚምባብዌያዊያን እና ፓኪስታንያዊያን ሱቆችን ከፍተው ይሰራሉ። ጥቃቱን ተከትሎ በንግድ እንቅስቃሴ ላይ የነበሩት እኒህ ወገኖች ጓዛቸውን እየሸከፉ ከስፍራው እየለቀቁ እንደሆነ ተሰምቷል።
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
96
Doc to summarize: የዓለማችን ከፍተኛው የህዝብ ቁጥር የምትይዘው ቻይና ኢንተርኔት በእጅጉ ቁጥጥር ከሚደረግባቸው ሀገራት የመጀመሪያውን ረድፍ ትይዛለች። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት ደግሞ በቅርቡ ኢንተርኔት ለሁለት ይከፈላል፤ በቻይና የሚመራውና በአሜሪካ የሚመራው ተብሎ። • ሁሉንም በደህንነት ካሜራ የምትመለከተው ቻይና • ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት? ይህንን ሀሳብ ባለፈው ዓመት ወደፊት ያመጡት የጉግል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኤሪክ ሽሚት ናቸው። የቻይና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች መንግሥት እንዲያዩት የሚፈቅድላቸውን መረጃዎች ብቻ ነው መመልከት የሚችሉት፤ ለምሳሌም እንደ ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ድሮፕቦክስ ወይንም ፒንትረስት ያሉ የማህበራዊ ሚዲያዎችና መገልገያዎችን መጠቀምም አይችሉም። በታይናንሜን አደባባይ ስለተፈጸመው ጭፍጨፋም ሆነ ማንኛውም ስለ ፕሬዚዳንታቸው ሺ ዢን ፒንግ የተሰጡ ትችቶችን በኢንተርኔት ላይ ፈልገው መመልከት አይችሉም። ምንም እንኳን ቻይና በዓለማችን ትልቁን የህዝብ ቁጥር ብትይዝም ትልልቅ የሚባሉ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ መስራት ባለመቻላቸውና መረጃ እንደ ልብ መቀያየር ባለመቻሉ ምክንያት ቻይናን ለቅቀው መሄድ እየመረጡ ነው። ሌላው ቀርቶ ወደ ቻይና ገበያዎች መግባት የሚፈልጉ ድርጅቶች ኢንተርኔት የተገደበ በመሆኑና ደንበኞቻቸውን እንደልብ ማግኘት ስለማይችሉ ወደ ሌሎች ሃገራት መሄድን ይመርጣሉ። ግዙፉ አፕል እንኳን እ.አ.አ. በ2017 ለቻይና ገበያ ከሚያቀርባቸው ስልኮች ላይ 'የኒውዮርክ ታይምስ' እና 'ስካይፕ' መተግበሪያዎችን እንዲያጠፋ ቀጭን ትእዛዝ ተሰትቶት ነበር። የአሜሪካው ስልክ አምራች ኩባንያም ሳያቅማማ ትእዛዙን ፈጽሟል። 'ሊንክድኢን' የተሰኘው የማህበራዊ ሚዲያ መገልገያ በመላው ዓለም የሚገኙ ስራ ፈላጊዎችንና እና ቀጣሪዎችን በአንድ መድረክ ለማገናኘት ተብሎ የተሰራ ቢሆንም ቻይናውያን ተጠቃሚዎች ከቻይና ውጪ ካሉ ሰዎች ጋር መገናኘት አይችሉም። በተጨማሪም ማንኛውም ፖለቲካዊ መልእክት ያለውን ገጽ ቻይናውያን እንዳያገኙት ይደረጋል። • ቻይና እሥር ቤት ያሉ ሙስሊም ዜጓቿን እያሰቃየች ነው በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ብሪቲሽ ኮሎምቢያ የቻይና ዘመናዊ ባህሎች ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ሬንሬን ያንግ እንደሚሉት የቻይና መንግስት ይህን ሁሉ ቁጥጥር የሚያደርገው ዜጎች ስለ ኮሙኒስት ፓርቲው እና ስለሃገራቸው ያላቸውን አመለካካት ለመቆጣጠር እንደሆነ ይናገራሉ። የቻይና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ጉግል እና ዋትስአፕን መጠቀም ባይችሉም ባይዱ እና ዊቻት የተባሉ አማራጮች ቀርበውላቸዋል። \nSummary in the same language as the doc:
ቻይናውያን የተቀረው ዓለም እንደ ልቡ ኢንተርኔትን በርብሮ የሚያገኛቸውን መረጃዎች ማግኘት አይችሉም። ለምሳሌ አንድ ቻይናዊ በጉግል መፈለጊያ ላይ ገብቶ ቻይና ብሎ ቢጽፍ የሚያገኘው መረጃ የተቀረው ዓለም ከሚያገኘው በእጅጉ የተለየ ነው።
amh_Ethi
train
docsummary
GEM/xlsum
amharic
296
አውስትራሊያ ዜጎች በዉሃን አየር ማረፊያ ከቻይናዋ ዉሃን ግዛት የተነሱት የአውስትራሊያ ዜጎች የስደተኞች ማቆያ ቦታ ተደርጋ ወደምትታወቀው ክርሲማስ ደሴት እየተጓጓዙ ነው። ደሴቷ ከአውስትራሊያ በ2700 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም ደሴቷ ጥገኝነት የጠየቁ ስደተኞች ለማቆያ ስፍራነት አገልግሎት ስትሰጥ ነበር። በአሁኑ ወቅት 4 የሴሪላንካ ዜግነት ያላቸው የቤተሰብ አባላት ብቻ ናቸው በደሴቷ ላይ እየኖሩ የሚገኙት። ኮሮናቫይረስ፡ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች በቻይና ከቻይና እየተጓጓዙ ያሉት አውስትራሊያውያን ለሁለት ሳምንት በደሴቷ ላይ ይቆያሉ። 89 ታዳጊዎችን ጨምሮ ዛሬ ጠዋት 243 ዜጎች እና የአውስትራሊያ ቋሚ ነዋሪዎች ወደ ደሴቷ ለመጓዝ አውሮፕላን መሳፈራቸውን የአውስትራሊያ መንግሥት አስታውቋል። ከ600 በላይ የአውስትራሊያ ዜጎች ቫይረሱ በተከሰተበት ሁቤይ ግዛት ውስጥ ይኖራሉ። የተቀሩ ዜጎችን ለማጓጓዝ ተጨማሪ በረራዎች እንደሚዘጋጁ መንግሥት አስታውቋል። የህክምና መስጫ ስፋራዎች ቀደም ብለው በክሪስማስ ደሴት ላይ ተዘጋጅተዋል። ኮሮናቫይረስ በመላዋ ቻይና መዛመቱ ተነገረ፤ የሟቾችም ቁጥር እየጨመረ ነው ኮሮናቫይረስ፡ የወቅቱ አሳሳቢው የዓለማችን የጤና ስጋት የአውስትራሊያ መንግሥት ስደተኞች ለማቆያ በሚጠቀምበት ደሴት ላይ ዜጎቹን ለይቶ ለማቆየት መወሰኑ ከበርካቶች ትችት ተሰንዝሮበታል። ከዚህ በተጨማሪ መንግሥት በደሴቱ ላይ ያዘጋጀው የህክምና መስጫ ስፍራዎች ደረጃ ዝቅ ያለ ነው የሚሉም በርካቶች ናቸው። መንግሥት ግን 24 ዶክተሮችን እና ነርሶችን ማስማራቱን እና ከዚህ ቀደም እያንዳንዱ ከቻይና የሚጓጓዝ ዜጋ ወይም ቋሚ ነዋሪ እንዲከፍል ተጠይቆ የነበረው 1ሺህ የአውስትራሊያ ዶላር እንዲቀር ተወስኗል ብሏል። 24 ዶክተሮችን እና ነርሶችን ወደ ደሴቷ መሰማራታቸውን መንግሥት አስታውቋል። በአውስትራሊያ 12 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መኖራቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል ሶስቱ ከቫይረሱ ድነው ከሆስፒታል ወጥተዋል። እስካሁን በጠቅላላው 360 ሰዎች በላይ በቫይረሱ የሞቱ ሲሆን፤ ከ17ሺህ በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መኖራቸው ተረጋግጧል። አሜሪካ፣ ፈረንሳይ እና ጃፓን ዜጎቻቸውን ከቻይና ካስወጡ አገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው። \n\nGive me a good title for the article above.
አውስትራሊያ ከቻይና ተመላሾችን ራቅ ወዳለች ደሴት ማጓጓዝ ጀመረች
amh_Ethi
train
goodtitle
GEM/xlsum
amharic
255
በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1949 ማኦ ዜዱንግ ወይም ሊቀመንበር ማኦ የኮሚዩኒስት ጥምር ኃይሎች ደም አፋሳሹን የርስ በርስ ጦርነት ማሸነፋቸውን ተከትሎ ፒአርሲ መመስረቱን አወጁ። ዘመናዊት ቻይና በሚያስገርም ፍጥነት እያደገች ቢሆንም በብዙዎች ዘንድ ነፃነትን በመግታትም የሰላ ትችት ይቀርብባታል። •የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ትውስታዎች በኢትዮጵያውያን ዓይን •የጤፍ ቢራ አሜሪካ ውስጥ ገበያ ላይ ዋለ ፕሬዚዳንት ዢ ሺንፒንግ በቲናንማን አደባባይ የተደረገውን ከፍተኛ ወታደራዊ ትዕይንትን ተከትሎ እንደተናገሩት የትኛውም ኃይል ቻይናን እንደማያነቃንቃት ነው። "የትኛውም ኃይል ቢሆን ቻይናንም ሆነ ህዝቦቿን ወደፊት ከመሄድ አያግዳቸውም" በማለት ለተሰበሰበው ህዝብ ተናግረዋል። ማኦ የቻይና ህዝቦች ሪፐብሊክን መመስረት ባወጁበት ተመሳሳይ ቦታ ከመቆም በተጨማሪ ማኦ በጊዜው ለብሰውት የነበረውን ተመሳሳይ ልብስም ለብሰው ታይተዋል። ፕሬዚንዳት ዢ አብዮታዊውንና መስራቹን አባትም ራዕይም ሆነ ትዝታ ከማጋራትም አልተቆጠቡም። ነገር ግን በዛሬው ዕለት የሚደረገውን አከባባበር በሆንግ ኮንግ የሚደረገው ተቃውሞ እንዳያጠለሸው ተሰግጧል። •ቻይና የዶናልድ ትራምፕን ስልክ ጠልፋው ይሆን? በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ቤጂንግ በሆንግኮንግ ማህበረሰብና ፖለቲካ ላይ የምታደርገውን ቅጥ አልባ ቁጥጥር በመቃወም ተቃውሟቸውን ማሰማት ከጀመሩ ዋል አደር ያሉ ሲሆን፤ በዛሬውም ዕለት ተቃውሟቸውን ይቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል። የመከላከያ ሚኒስትር እንዳሳወቀው 15ሺ ወታደሮች፣ 580 ወታደራዊ ቁሶች እንዲሁም 160 የጦር አውሮፕላኖች በዚህ ወታደራዊ ትዕይንት ተሳታፊ ሆነዋል። የሃገሪቷ አዲስ ወታደራዊ የቴክኖሎጂ ግኝቶች በትእይንቱ ላይ የቀረቡ ሲሆን፤ ታንኮች፣ ሄሊኮፕተሮች፣ ዲኤፍ 41 የሚል መጠሪያ የተሰጠው የባሊስቲክ ሚሳይልም ይገኙበታል። ከወታደራዊ ትዕይንቱ በተጨማሪ ከተለያየ የማህበረሰቡ ክፍል የተውጣጡ ከመቶ ሺ በላይ ግለሰቦች የሚሳተፉበት ደመቅ ያለ ዝግጅትም የተደረገ ሲሆን፤ በዚህም አርሶ አደሮች፣መምህራን፣ ዶክተሮችና ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል። ዝግጀቱ ለመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ ለተጋበዙ ግለሰቦችና ለውጭ ኃገር ዲፕሎማቶች ክፍት ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ግለሰቦች በያሉበት ሆነው የሚከታተሉት ይሆናል። የፀጥታው ቁጥጥር በማዕከላዊ ቤጂንግ ለሳምንታት ያህል በጣም የጠበቀ ሲሆን በተለይም በትዕይንቱ አካባቢ ድሮን (ሰው አልባ አውሮፕላንን)ጨምሮ ለውድድር የሚሆኑ እርግቦችም ተከልክሏል። • ከተማ ይፍሩ፡ ያልተነገረላቸው የአፍሪካ አንድነት ባለራዕይ ሚዲያን ሳንሱር በማድረግ በምትተቸው ቻይና ወታደራዊ ትዕይንቱን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ ቁጥጥር የጠበቀ ሲሆን የተለያዩ ፕሮግራሞችን የሚያስታላልፉ ሚዲያዎች የፕሮግራሞች ዝርዝር የተሰጣቸው ሲሆን በኦንላይንም ላይ የኮሚዩኒስት ፖርቲንም ሆነ መሪዎቹን መተቸት ክልክል ነው። \n\nGive me a good title for the article above.
ቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ የተመሰረተበትን 70ኛ አመት እያከበረች ነው
amh_Ethi
train
goodtitle
GEM/xlsum
amharic
300
Title: የደመራ በዓል አከባበር፡ የመስቀል ደመራ በዓል ሙሉ ኃይማኖታዊ እሴቱና ስርዓቱ ሳይጓደል ይከበራል- ቤተክርስቲያኒቱ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
የቤተክርስቲያኒቱ የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ዐብይ ኮሚቴ አባል የሆኑት መጋቤ ሰላም ሰለሞን ቶልቻ፤ በአዲስ አበባ በርካታ ምዕመናን ተገኝተው የሚያከብሩበት የመስቀል አደባባይ በግንባታ ላይ መሆኑ የበዓሉን ሐይማኖታዊ እሴቱና ሥርዓቱ እንደማያጓድለው ጠቅሰዋል። በዓሉን ለማክበር የሚታደሙ ምዕመናን ቁጥር በተወሰነ መልኩ መቀነሳቸውን የገለፁት መጋቤ ሰላም ሰለሞን፤ አካባቢው ግንባታ ላይ መሆኑ እና የግንባታ ቁሳቁስ በስፍራው ላይ መኖር እንዲሁም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለዚህ ምክንያት መሆናቸውን አንስተዋል። መስከረም 16 በመስቀል አደባባይ በመገኘት በዓሉን የሚታደሙና የሚያከብሩ ሰዎች ቁጥር ከ5000 እንደማይበልጥ የተናገሩት መጋቢ ሰላም ሰለሞን፤ የመግቢያ ባጆች ከ3000 እስከ 5000 እንደሚታተሙ ተናግረዋል። ቤተክርስትያኒቱ ከፀጥታ አካል ጋር በመተባበር በበዓሉ ላይ ለሚታደሙ የክብር እንግዶች እንዲሁም ምዕመናን፣ መዘምራንና ቀሳውስት ባጆችን እንደምታዘጋጅ አረጋግጠዋል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌልና የሐዋሪያዊ ተልዕኮ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት መጋቢ ሰላም ሰለሞን ለቢቢሲ አንደገለፁት፤ የ2013 የመስቀል በዓልን ለማክበር ያሉት ተግዳሮቶች ሦስት ናቸው። አንዱና ቀዳሚው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ነው ያሉ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት በዓሉን ምዕመናኑ በነቂስ ወጥተው አካላዊ ርቀታቸውን ጠብቀው ማክበር እንደማይችሉ ተናግረዋል። ሁለተኛው የፀጥታ ጉዳይ ነው ያሉት ኃላፊው፤ የመንግስት የፀጥታ አካል በዓሉ ያለ ችግር እንዲከበር ከቤተክርስቲያኒቱ የበዓል አከባበር ኮሚቴ ጋር በጥምረት እንደሚሰራ ገልፀዋል። ሦስተኛው የመስቀል አደባባይ በግንባታ ሂደት ላይ መሆኑን በማስታወስ፤ የበዓሉ ታዳሚያን ቁጥር ይቀንሳል እንጂ ሐይማኖታዊ ሥርዓቱ ሳይጓደል ይከበራል ሲሉ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በበዓሉ ላይ የሚቀርቡ ያሬዳዊ ዝማሬዎች፣ በሊቃውንቱ መካከል የተዘጋጁ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን መዝሙሮችና የሙሉ ትርዒቱ ዝግጅት መጠናቀቃቸውንና እንደሚቀርቡም አመልክተዋል። የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ቅዱስ ፓርቲያሪኩን ጨምሮ ይገኛሉ ያሉት መጋቢ ሰላም ሰለሞን፤ ከዚህ በተጨማሪም ጠቅላላ ሊቃውንትና ካህናቱ እንደሚገኙ ገልፀዋል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በሚመለከት ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሚሰጠው ምክር ተግባራዊ እንደሚደረግ የሚናገሩት ኃላፊው፤ አካላዊ ርቀት መጠበቅ እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ በበዓሉ አከባበር ወቅት የሚተገበሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ከዚህ በፊት የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች፣ ከምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤና ከፀጥታ አካል ጋር በመሆን በመስቀል አደባባይ ጉብኝት ማድረጋቸውን የገለፁት ኃላፊው፤ በዚህም ምልከታ እንግዶች በየት በኩል እንደሚስተናገዱ፣ መዘምራን በየት በኩል ዝማሬ እንደሚያቀርቡ እንዲሁም ደመራ እንዴት እንደሚደመር ጥናት መደረጉን ገለፀዋል። በርካታ ቱሪስቶችና የውጭ አገራት ዜጎች ይታደሙበት የነበረው የመስቀል ደመራ በዓል በኮሮናቫይረስ ምክንያት የቱሪስቶች እንቅስቃሴ በዓለም ዙሪያ በመስተጓጎሉ በዚህ ዓመት እንደከዚህ ቀደሙ ብዙ ጎብኚዎች ላይገኑ ይችላሉ። የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ በርካታ ሕዝብ ታድሞባቸው ከሚከናወኑ ሐይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች መካከል አንዱ ሲሆን፤ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርትና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት እንደተመዘገበም ይታወቃል።
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
355
አህጉሪቱ ውስጥ የመጀመሪያ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ይፋ የተደረገው ግብፅ ውስጥ ነው። ይህ ዜና ከተሰማ በኋላም ቢሆን ወረርሽኙ አፍሪካ ላይ ብርቱ ክርኑን ወዲያው አላሰረፈም ነበር። አውሮፓውያን እንደቅጠል ሲረግፉ፤ አሜሪካውያን ለሞት ሲሰለፉ፤ አፍሪካ ግን ሃገር ሰላም ብላ ነበር። ይህ ለምን ሆነ ብለው የተንገበገቡ ሰዎች ጥናት እናካሂድም ብለው ነበር። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአህጉሪቱ ሃገራት በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው። በቀን አንድና ሁለት ሰው የመዘገበችው ኢትዮጵያ እንኳ ትላንት [ነሐሴ 8/2012] በ24 ሰዓታት ብቻ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ይፋ አድርጋለች። ደቡብ አፍሪካ በበኩሏ ከአህጉር አልፋ በዓለም ደረጃ መወዳደር ይዛለች። በአሁናዊ አሃዝ መሠረት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮሮናቨይረስ የተያዙባት ደቡብ አፍሪካ በዓለም አምስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ከደቡብ አፍሪካ በተጨማሪ ግብፅ፣ ናይጄሪያ፣ ጋና እና አልጄሪያ፤ በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ ከተያዙ ሰዎች 75 በመቶ ገደማ የሚሆነውን ድርሻ ይይዛሉ። ምንም እንኳ ቁጥሩ ከጊዜ ጊዜ ቢጨምርም የዓለም ጤና ድርጅት ወረርሽኙ አፍሪካ ላይ መች እንደሚበረታ መገመት አልቻልኩም እያለ ነው። ድርጅቱ የአፍሪካ ሃገራት የኮሮናቫይረስ ምርመራቸውን በገጠራማ ሥፍራዎችም እንዲያከናወኑ በፅኑ ያሳስባል። በተለይ ደግሞ ድንበር አካባቢ ያሉ ከተማዎች የቫይረሱን ሥርጭት መጠን የሚያሳዩ ናቸው ይላል ድርጅቱ። አውሮፓና አሜሪካ በወረርሽኙ ሲደናገጡ የእንቅስቃሴ ገደብ ጥለው የነበሩ የአፍሪካ ሃገራት አሁን ወረርሽኙ ፊቱን ወደ አህጉሪቱ ቢያዞርም እንቅስቃሴዎችን ማላላት ጀምረዋል። ከ54ቱ የአህጉሪቱ ሃገራት 25ቱ ድንበራቸውን ዘግተዋል። 23 ደግሞ ወደ ሃገር ለሚገቡ... Continue the article for another 4000 characters max:
ና ለሚወጡ ሰዎች የግዴታ የኮሮናቫይረስ ምርመራ እንዲያከናውኑና የምርመራ ውጤት እንዲያመጡ ያዛሉ። የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠር ማዕከል [ሲዲሲ] በላይቤሪያ፣ ሲዬራ ሊዮን፣ ዛምቢያ፣ ዚምባብዌ፣ ካሜሩንና ናይጄሪያ ውስጥ የበሽታ መከላከል [አንቲቦዲ] ምርመራ ላከናውን ነው ብሏል። ማዕከሉ ይህን ማድረግ ያስፈለገው በሽታው በምን ያክል ፍጥነት እየተጓዘ እንዳለ ለመረዳት ነው። የአንቲቦዲ ምርመራ ማለት ሰዎች ከዚህ በፊት በኮሮናቫይረስ ይሆን ወይ የሚለውን የሚለይ ነው።
amh_Ethi
train
xp3longcontinue
GEM/xlsum
amharic
258
Title: ሙጋቤ የማይሳተፉበት የመጀመሪያው የዚምባብዌ ምርጫ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ኤመርሰን ምናንጋዋ በዚምባብዌን የነጻነት ትግል ሚና ተጫውተዋል አሁን ግን ዚምባብዌ ሮበርት ሙጋቤ የማይሳተፉበት ምርጫ ታካሂዳለች። ምርጫው ካሳተፋቸው መካከል አሁን ሀገሪቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ዛኑ ፒኤፍ ፓርቲን የሚወክሉት ኤመርሰን ምናንጋግዋና ተቃዋሚው ኔልሰን ቻሚሳ ይገኙበታል። ለኤመርሰን ምናንጋግዋ የተሰጠው ድጋፍ ከተቀናቃኛቸው የሙቭመንት ፎር ዴሞክራቲክ ቼንጅ መሪ ኔልሰን ቻሚሳ የተወሰነ ብልጫ አሳይቷል ተብሏል። • ደቡብ ሱዳን ለመኪና መግዣ 16 ሚሊየን ዶላር አወጣች • ዚምባብዌ ለሙጋቤ ብሔራዊ ቀን ሰየመች • ሙጋቤ ቅንጡ ኑሯቸውን ይቀጥላሉ ተባለ የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ሮበርት ሙጋቤ በበኩላቸው እሳቸውን ለሚተካ ፕሬዘዳንት ድምጻቸውን እንደማይሰጡ ተናግረዋል። በሀገሪቷ ታሪክ በምርጫ ሲሳተፉ የመጀመያቸው የሆኑ ወጣቶች ድምጽ እንደሚሰጡ ይጠበቃል። ለምርጫ ከተመዘገቡት አብዛኞቹ ከ35 ዓመት በታች ናቸው። በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋሞች ምርጫውን ለመታዘብ ወደ ዚምባብዌ ያቀኑ ሲሆን ተቃዋሚዎች ምርጫው ሊጭበረበር እንደሚችል ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል። ኔልሰን ቻሚሳ ከተመረጡ በሀገሪቱ ታሪክ ወጣቱ መሪ ይሆናሉ ምርጫው ዚምባብዌን ምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ ውስጥ የከተታት የዓመታት የጭቆና አገዛዝን ተከትሎ የመጣ ነው። የቀደመው አገዛዝ በሀገሪቱ የትምህርት፣ የጤና እንዲሁም የኢንቨስትመንት ዘርፍም እክል ሆኗል። የሀገሪቱ የሥራ አጥነት መጠን 90 በመቶ መድረሱም የአገዛዙ ውጤት ነው ተብሏል። "አዞው" (በእንግሊዘኛው ዘ ክሮኮዳይል) በሚል ቅጽል ስም የሚጠሩት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ምጣኔ ሀብታዊ ለውጥ ያመጡ ይሆናል ተብሎ ይታመናል። ሥራ አጥነትን እንደሚያስወግዱም ቃል ገብተዋል። የሮበርት ሙጋቤ ደጋፊዎች እንደሆኑ የሚነገርላቸው ቡድኖች በተደጋጋሚ የግድያ ሙከራ አድርገውባቸዋል። ተፎካካሪዎቹ ኤመርሰን ምናንጋግዋ እና ኔልሰን ቻሚሳ ኔልሰን ቻሚሳ የህዝብ እንደራሴ የሆኑት በ25 ዓመታቸው ነበር። አሁን 40 ዓመታቸው ሲሆን፣ የ75 ዓመቱ ተቀናቃኛቸው ኤመርሰን ምናንጋግዋን አሸንፈው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ከሆኑ በዚምባብዌ ታሪክ ወጣቱ መሪ ይሆናሉ። ከተመረጡ ሀገሪቷ በምጣኔ ሀብት እድገት ቀን እንደሚወጣላት ቃል ቢገቡም እቅዳቸው የተለጠጠ ነው የሚል ትችት ተሰንዝሮባቸዋል። ከተመረጡ ዚምባብዌ ኦሎምፒክ እንድታስተናግድ ከማስቻል ባሻገር ሀገራቸውን የፈጣን ባቡር ባለቤት እንደሚያደርጓትም ተናግረዋል። ሮበርት ሙጋቤ ከሁለቱ ተፎካካሪዎች ኔልሰን ቻሚሳን ይደግፋሉ።
amh_Ethi
validation
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
272
Title: መስቀል በቤተ-ጉራጌ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
የጉራጌ ብሄር ተወላጆች ለመስቀል ወደትውልድ ቀያቸው ያመራሉ ከመስከረም 12 በፊት የጉራጌ ብሄር ተወላጆች፤ ከመላው የሀገሪቱ ክፍል ወደ ትውልድ ስፍራቸው ይተማሉ፡፡ የዕድሜ ባለጸጋው አቶ ፍቃዱ ካሶሬ እንደሚያምኑት፤ ከወጣቶች በሰው እስከሚደገፉ አዛውንቶች ድረስ የመስቀል ሰሞን ሀገር ቤት የመግባታቸው ነገር አያጠያቅም፡፡ በዚያ ሰሞን በጉራጌዎች የንግድ ተሳትፎ ፈክታ የከረመችው አዲስ አበባ ጭርታ ይመታታል፡፡ • የአዲስ አበባ የመስቀል ሽር ጉድ በፎቶ • ካለሁበት 30፡ መስቀል እና አረፋን ሳስታውስ ውስጤ ይረበሻል ‹‹አሁን በዚህ ሰሞን መርካቶ ብትሄድ፣ የተወረረ ቦታ መስሎ ታገኘዋለህ›› ይላሉ እሳቸው ሁኔታውን ሲስሉት፡፡ ልጃቸው መሳይ ፈቃዱን ጨምሮ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የብሄረሰቡ ተወላጆች ወደ ቀያቸው አቅንተዋል፡፡ ምክንያቱም መስቀል በጉራጌ ሃይማኖታዊ በዓል፣ የመተጫጫ ወቅት፣ የእርቅ እና የአንድነት አውድ ስለሆነ በመሳይ አገላለጽ ‹‹መች በደረሰ የሚያስብል ወቅት›› ነውና፡፡ ከወሬት ያህናእስከ አዳብና አቶ ፈቃዱ ካሶሬ እንዳወጉን፤ መስከረም 13 ወሬት ያህና በተሰኘው የበዓል መክፈቻ መሰናዶ ሰሞነ መስቀል ይጀመራል፡፡ ወሬት ያህና ጉጉት እና ናፍቆት የፈጠረውን እንቅልፍ አልባ ቀን የሚዘክር ቃል ነው፡፡ መስከረም 14 የእርድ ዋዜማ ሲሆን የልጆች የደመራ ፣ የሴቶች የአይቤ እና ጎመን ቀን ይባላል፡፡ ቤቶች የሚሰነዳዱበት የእንፋሎት ቆጮ የሚቀርብበት ቀንም ነው፡፡ መስከረም 15 ዋናው የጉራጌ የመስቀል በዓል (ወኀምያ ) ነው፡፡ በዚህ ዕለት እርድ ይፈጸማል፡፡ መስከረም 16 ምግይር ወይም ደመራ የሚባለው ቀን ነው (የአባቶች ደመራም ይባላል)፡፡ በየቤቱ፤ ጠዋት የህጻናት ማታ ደግሞ የአባቶች ደመራ ይለኮሳል፡፡ በዚህ ዕለት ከብቶች ከቤት አይወጡም፡፡ በዋናው በዓል እርድ ይፈጸማል መስከረም 17 ንቅባር ወይንም ትልቁ በዓል ነው፡፡ ዘመድ አዝማድ ሻኛ አስመርቆ በጋራ የሚቋደስበት፣ ጎረቤት በአንድ ሆኖ ሲስቅ ሲያወካ የሚውልበት የማህበረሰብ መሰብሰቢያ ቀን ነው፡፡ ከመስከረም 18 እስከ 23 የጀውጀው የሚባለው ስርዓት ይቀጥላል፡፡ የጀውጀው የመተያያ ቀን ሲሆን ባለትዳሮች ስጦታ እና መመረቂያ ይዘው የወላጆቻቸውን ቤት በማቅናት የሚጠይቁበት ነው፡፡ የመዝጊው በዓል አዳብና ይባላል፡፡ አዳብና ጎረምሶች እና ልጃገረዶች የጭፈራ ችሎታቸውን የሚያሳዩበት፤ የወደፊት የትዳር ተጣማሪያቸውን የሚያዩበት፣ የሚያጩበት በዓል ነው፡፡ ጭፈራው ለተወሰኑ ቀናትን ሊቀጥል ይችላል፡፡ • ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን • ታሪካዊዋን ሐረርና ጀጎልን በምስል የአቶ ፈቃዱ ካሶሪ ልጅ፤ ባህሉ በሚፈቅደው መንገድ ካጨና ካገባ ዘንድሮ አንድ ዓመት እንደደፈነ ይናገራል፡፡ እንግዲህ መስቀል በሚመጣ ጊዜ ‹‹ለእኔ ድርብ በዓል ነው›› ብሎናል፡፡ የዓመት ሰው ይበለን ወደ ሁለት ሚሊየን የሚገመቱ የብሄረሰቡ አባላት እንደሚሳተፉበት የሚነገረው በዓል የሚያካትታቸው ክንውኖች ካለ ምርቃት እና መልካም ምኞቶች አይደመደሙም፡፡ የዕድሜ ባለጸጎች ‹‹የሀገራችንን ዳር ዳር ለጠላት እሳት፤ ለህዝቦቿ መሃሏን ገነት ያድርግልን›› ከሚለው ምርቃት ጀምሮ፤ ሰው፣ ከብቱ፣ ጋራ እና ሸንተረሩ ሰላም እና ልምላሜ፣ በረከት እና ጸጋ እንዳይለየው ይመረቃል፡፡ ታዳሚውም የአባቶችን ምርቃት እየተከተለ ‹‹አሜን!›› ይላል፡፡ የዓመት ሰው ይበለን- አሜን!
amh_Ethi
validation
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
373
Doc to summarize: ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት በተደረገው ሰልፍ ላይ፣ የአዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ርምጃዎች የሚደግፉ እና ስለ ኢትዮጵያ አንድነት የሚሰብኩ መፈክሮች ተሰምተዋል፡፡ ለዓመታት የኢትዮጵያን መንግሥት በሚቃወሙ መድረኮች እና ሰልፎች ላይ በመገኘት ንግግሮችን በማድረግ የሚታወቀው አርቲስት ታማኝ በየነ ጨምሮ ታዋቂ የፖለቲካ እና የኪነጥበብ ሰዎች በሰልፉ ላይ መገኘታቸውም ታውቋል፡፡ በሰልፉ ላይ ቅዳሜ ሰኔ 16 በአዲስ አበባ በነበረው የድጋፍ ሰልፍ ላይ በደረሰው የቦንብ ፍንዳታ ለሞቱ እንዲሁም በዓመታት ውስጥ ‹ለፍትህ እና እኩልነት ሲታገሉ› ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የህሊና ጸሎት ተደርጓል፡፡ ሽመልስ ወልደ ገብረ-ሰንበት የተባሉ የሰልፉ ተሳታፊ ‹‹ሰልፉከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያዊያን ከተቃውሞ ወጥተው ለምስጋና እና ደስታ የተሰባሰቡበት ነበር ›› በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል፡ \nSummary in the same language as the doc:
ነዋሪነታቸውን በአሜሪካን ሀገር ያደረጉ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ትናንት ሰኔ 20/2010 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ለመደገፍ ያለመ ሰላማዊ ሰልፍ አከናውነዋል፡፡
amh_Ethi
train
docsummary
GEM/xlsum
amharic
129
የግድቡ ግንባታ በሚካሄድበት ወረዳ ውስጥ በበሽታ የተያዘ ሰው መገኘት በግንባታው ላይ ምን አይነት ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል? ሠራተኞቹስ በምን አይነት ስሜት ውስጥ ይገኛሉ የሚሉ ጥያቄዎችን አጭሮ ነበር። ከ7000 በላይ ሰራተኞች ያሉት የአፍሪካ ግዙፉ የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግንባታ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ሊያስከትልበት የሚችለውን ጫና ለመቋቋም ምን እየተደረገ ነው ስንል የፕሮጀክቱን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮን አነጋግረናል። • ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የኢትዮጵያን ሃሳብ አልቀበልም አለች "ፕሮጀክቱ ምንም እንኳ ከጉባ ወረዳ ቢገኝም፤ በቫይረሱ መያዙ በምርመራ የተረጋገጠው ግለሰብ የሚኖርበት ቦታ እና ፕሮጀክቱ ያለበት ስፍራ ይራራቃሉ" ይላሉ። የጉባ ወረዳ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ወረዳዎች ሰፊው መሆኑን ያስታወሱት ኢንጅነር ክፍሌ፤ "በቫይረሱ የተያዘው ሰው የተገኘበት ፓዊ በሚባል በቫይረሱ ተጠርጥረው ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች መካከል ነው። በዛ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ደግሞ ከሱዳን የሚመጡ ሰዎች ተለይተው የሚቆዩበት ቦታ ነው። ከፕሮጀክታችን ጋር አይገናኘም" ብለዋል። ከኮሮናቫይረስ ስርጭት በኋላ በግንባታ ሂደቱ ላይ ምን ተቀየረ? የኮሮናቫይረስን ወረርሽኝ ተከትሎ አሰሪዎች ሰራተኞቻቸው ርቀታቸውን ጠብቀው በጥንቃቄ እንዲሰሩ አልያም ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ ትዕዛዝ ሲያስተላልፉ ታይተዋል። በርቀት ሆኖ ሥራን ማከናወን ከማይቻልባቸው መካከል አንዱ የግንባታ ሥራ ነው የሚሉት ኢንጅነር ክፍሌ፤ "ጥንቃቄን በማጠናከር ከመስራት ውጪ ሠራተኞችን መቀነስ ወይም ከርቀት ሆነው እንዲሰሩ ማድረግ አልቻልንም" ይላሉ። "ሠራተኞች በሥራ ቦታ ላይ ርቀታቸውን እና ንጽህናቸውን ይጠበቃሉ። የፊት እና አፍ መሸፈኛ ጭንብል እያደረጉ ነው" ብለዋል። "እንደ ከዚህ ቀደሙ የፕሮጀክት ግንባታ ጉብኝት እንዲቆም ተደርጓል። እንዳጋጣሚ ወደ ፕሮጀክቱ የሚገባ ካለ ለ14 ቀን ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገባ ተደርጎ እና ከክትትል በኋላ ነው ከሠራተኞች ጋር የሚቀላቀለው" ይላሉ የፕሮጅክቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ። • ስለአዲሱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ጥቂት እንንገርዎ ኢንጀነር ክፍሌ እንደሚሉት ሌላው ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉት የግንባታ ግብዓቶችን ጭነው የሚመጡ መኪኖች ናቸው። እንደ ኢንጂነሩ ገለጻ ከሆነ ተሽከርካሪዎቾ ወደ ግንባታው ከመቃረባቸው በፊት በጸረ-ተዋሲያን እንዲጸዱ ይደረጋሉ። ሠራተኞቹም ቢሆኑ ከአሽርከርካሪዎቹ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳይኖራቸው ይደረጋል። ለቻይኖች አዲስ ዓመት በዓል የፕሮጀክቱ ሠራተኞች የነበሩ ቻይናውያን ወደ አገራቸው ተጉዘው እንደነበረ ያስታወሱት ኢንጅነር ክፍሌ፤ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ በአዲስ አበባ ለ14 ቀናት በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ መቆየታቸውን እና ወደ ፕሮጀክቱ ሥፍራ በልዩ አውሮፕላን እንደተመለሱ፤ በግድቡ ግንባታም ክትትል ከተደረገላቸው በኋላ ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጉን ተናግረዋል። ከቻይናውያን በተጨማሪ በህዳሴ ግድብ ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉ የጣሊያን፣ ጃፓን እና ጀርመን ዜጎች እንዳሉ ይታወቃል። ኢንጅነር ክፍሌ የቫይረሱን መከሰት ተከትሎ የፕሮጀክቱ ሠራተኞች ሆነው ወደ ትውልድ አገራቸው የተመለሱ የውጪ አገር ዜጎች እንደሌሉ ተናግረዋል። ኮሮናቫይረስ በፕሮጀክቱ ውስጥ ቢከሰት ዝግጅቱ ምን ይመሥላል? መንግሥት ለዚህ ፕሮጅከት ከፍተኛ ትኩርት ሰጥቷል ያሉት ኢንጅነር ክፍሌ፤ "በጥበቃ ረገድም ተጨማሪ የጸጥታ ኃይል ተመድቦ የደህንነት ስራውን በቅርበት እያከናወኑ ይገኛሉ። የጤና ሚንስቴር እና አሶሳ የሚገኘው ማዕከል ለፕሮጀክቱ ሠራተኞች ልዩ ትኩረት ሰጥተዋል" ብለዋል። በሽታው እንዳይከሰት የቅድመ ጥንቃቄ... \n\nGive me a good title for the article above.
ኮሮናቫይረስ፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት
amh_Ethi
train
goodtitle
GEM/xlsum
amharic
404
በሁለቱ አገራት ጦርነት ምን ይመስል ይሆን? ይህንንም ተከትሎ ፒዮንግ ያንግ የአሜሪካን ቦምብ ጦር አውሮፕላኖችን የመምታት መብት እንዳላትም ጨምረው ተናግረዋል። ዮንግ የጦር አውሮፕላኖቹ የሰሜን ኮሪያ ክልል ውስጥ መገኘት አይጠበቅባቸውም ብለዋል። ለዚህ ንግግር ዋይት ሀውስ የሰጠው ምላሽ "አስቂኝ" የሚል ነው። ፔንታጎንም ቀጠል በማድረግ ፒዮንግ ያንግ ጠብ አጫሪነቱን ማቆም አለባት በማለት አስጠንቅቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ይህ "ጠብ አጫሪ ንግግር" ጦርነትን ሊጋብዝ ወደሚችል አለመግባባጠት ይቀየራል ብለዋል። የሰሜን ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሱን ያቀረቡት ትራምፕ 'የሰሜን ኮሪያ አመራር በዚህ ጉራው ከቀጠለ ለረጅም ጊዜ እንደማይቆዩ' በትዊተር ገፃቸው ላይ ካሰፈሩ በኋላ ነው። "ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማስታወስ ያለበት መጀመሪያ አሜሪካ ናት በአገራችን ላይ ጦርነት ያወጀችው።" በማለት ሪ ዮንግ ሆ የተናገሩት ኒውዮርክ ውስጥ በመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ተሳትፈው ሲወጡ ከሪፖርተሮች ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው። "ከአሜሪካ እየተቃጣብን ላለው ሥጋት የራሳችንን እርምጃ እንወስዳለን። ይሄም ማለት የአሜሪካ ቦምብ ጣይ የጦር አውሮፕላኖችን በአየር ቀጠናዎቻችን ላይ ባይሆኑም የማጥቃት መብት አለን" በማለትም ጨምረው ተናግረዋል። የትራምፕ የትዊተር ፅሁፍ የመጣው ሪ ዮንግ በመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአሜሪካ ፕሬዚዳንትን አስመልክቶ "አእምሮው የቀወሰ፣ በስልጣን የሰከረ፣ ራስን በማጥፋት ዘመቻ ላይ ያለ" በሚል ኃይለቃል የተሞላበት ንግግር ከሰጡ በኋላ ነው። የፔንታገን ቃልአቀባይ ኮሎኔል ሮበርት በበኩላቸው "ሰሜን ኮሪያ ይህ ጠብ አጫሪነት ፀባይ ካላቆመች ፕሬዝዳንታችን ሰሜን ኮሪያን አስመልክቶ ምን አይነት እርምጃ መወሰድ እን... Continue the article for another 4000 characters max:
ዳለበት የተሻለ አማራጭ እንሰጣለን።" በማለት ተናግረዋል።
amh_Ethi
validation
xp3longcontinue
GEM/xlsum
amharic
205
Title: በረከት ስምኦን ስለራሱ ይናገራል\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
በረከት ስምኦን በኋላ ላይ ግን የተፃፈው ነገር እሱን ብቻ ሳይሆን ሁለት እህቶቹንም አካተተ። ያኔም በርካቶች ይፈሩት፣ ይደነግጡ ጀመር፤ በዚህ ወቅት ስጋት ገባው። ከኤርትራዊያን የተወለደው በረከት ስምኦን ያደገው አዲስ አበባ ፖፖላሬ አካባቢ ሲሆን በልጅነቱ ክረምትን ያሳልፍ የነበረው ከቤተሰቦቹ ጋር በመሆን ኤርትራ ውስጥ ነበር። • «ወይዘሮ ጎሜዝ፤ እርስዎ አያገባዎትም! አርፈው ይቀመጡ በልልኝ» ኑሮውን በፈረንሳይ ካደረገ 40 ዓመታትን ያስቆጠረው በረከት ስምኦን በስሙ ምክንያት ብዙ ችግሮች ገጥሞታል። ከኢትዮጵያ ከመውጣቱ በፊት ስለነበረው ሕይወት ብዙ ያጫወተን በረከት ለዘመቻ (ዕድገት በሕብረት) ወደ ወለጋ ተልኮ ከነበረበት ጥሎ ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሰና ኢህአፓን በአዲስ አበባ ውስጥ ወረቀት በመበተን መቀላቀሉን ያስታውሳል። በረከት በወቅቱ የኢህአፓን የፕሮፓጋንዳ ጽሑፎች ቤት ለቤት ይበትን ነበር። ከዚያም አልፎ በየመንግሥት መሥሪያ ቤቶች 'መንግሥትን ክደዋል' ተብሎ ስም ዝርዝራቸው የተያዘ ግለሰቦችን ሰነድ ሰርቆ ያጠፋ እንደነበርም ያስታውሳል። አንዳንዴ የጦር መሣሪያዎችን እንዲደብቅ ወይም እንዲያቀብል ይጠየቅና ይከውን እንደነበርም አልሸሸገም። በረከት እንደሚያስታውሰው በዙሪያው ከነበሩት ሰዎች መካከል የጠፉ፣ ሀገር ጥለው የወጡ፣ የታሰሩና የተገደሉ አሉ። • በደብረማርቆስ 'ባለስልጣኑ አርፈውበታል' የተባለው ሆቴል ጥቃት ደረሰበት በረከት ከዕድገት በሕብረት ዘመቻ በመመለሱ አቋርጦት የነበረውን ትምህርቱን የመቀጠል ብርቱ ፍላጎት ነበረው። በዚህ ወቅት ነው ስሙ 'ኮብልሏል' ከሚል ዝርዝር ውስጥ መካተቱን ያወቀው። ይኼኔ ይላል በረከት "ወረቀት የመስረቅ ልምድ ስለነበረኝ አራት ኪሎ ከሚገኝ መሥሪያ ቤት ገብቼ ስሜ የነበረበትን ደብዳቤ፤ አጣጥፌ በኪሴ ደብቄ ወጣሁ።" ይህን በማድረጉ ከመንግሥት ትኩረት ለጊዜውም ቢሆን መሰወር ስለቻለ ወደ ሊሴ ገብረማሪያም ተመልሶ ትምህርቱን አጠናቀቀ። ከሊሴ ገብረማሪያም ከተመረቀ በኋላም ነፃ የትምህርት ዕድል አግኝቶ ወደ ፈረንሳይ ማቅናቱን ይናገራል። "ወረቀቱን ከሠረቅኩበት መሥሪያ ቤት ሄጄ ከሃገር ለመውጣት እንድችል የሚያሰፈልገኝን ወረቀት እንዲፈርሙልኝ ጠየኳቸው... እነሱም ፈረሙልኝና ወጣሁ።" የበረከት ስምኦን መታወቂያ በረከት ስምኦን ማን ነው? በረከት ስምኦንን፤ የቀድሞውን የመንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትርና በአሁኑ ወቅት በባህር ዳር በማረሚያ ቤት የሚገኙት ሞክሼው ጋር ይተዋወቁ እንደሆን ስንጠይቀው "ማን እንደሆነ አላውቅም። አግኝቼውም አላውቅም። እኔ ግን በረከት ስምኦን እባላለሁ" ሲል መልሶልናል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ማስታወቂያ ሚኒስትር የነበረው በረከት ስምኦን ስሙን የወረሰው ከእኔ እንደሆነ የሚገልጽ ጽሑፍ ወጥቶ እንደነበር ሰምቻለሁ የሚለው በረከት፣ በዚህም የተነሳ ሰዎች ከእሱ ጋር እንደሚያመሳስሉት ይናገራል። "መጀመሪያ ምንም አልሰማሁም ነበር። በረከት ስምኦን ትክክለኛ ስሙም ይመስለኝ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት እህቶቼ አሥመራ እያሉ 'ወንድማችሁ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየሠራ ነው' ብለዋቸው ትኩረቴ ተሳበ። ምን እንደሆነ ለማየት ብቻ አሥመራ ሄድኩኝ። ሲያዩኝ ሌላ ሰው እንደሆንኩኝ ሲገነዘቡ ምንም አላሉኝም።" • "...ባለሐብቶችን ለቅመህ እሰር ብሎኝ ነበር" አቶ መላኩ ፈንታ ከዚያ ቀጥሎ ግን በበይነ መረብ ብዙ ነገሮች ማንበብ እንደጀመረ ይናገራል። ከስም መመሳሰል ውጪ እርሱን ከበረከት ስምኦን ጋር ማገናኘታቸው ግራ እንደሚያጋባው ገልጾ "ታሪኩ ከእኔ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም" ይላል። "ጸሐፊው እንዴት አድርጎ እኔ ላይ እንዳተኮረ ሊገባኝ አልቻለም" የሚለው አቶ በረከት "በተለይ...
amh_Ethi
train
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
398
Given the below title and summary of an article, generate a short article or the beginning of a long article to go along with them. Title: የኢትዮጵያ አየር መንገድ 'የቻይና በረራዬን መቀጠሌ ትክክል ነበር' አለ\nSummary: በአፍሪካ ትልቁ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የኮሮናቫይረስ ቻይና ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ጊዜ ድርጅታቸው ወደዚያ ሲያደርግ የነበረውን በረራ አለማቋረጡ ትክክል እንደነበር ተናገሩ።\nArticle (Max 500 characters):
ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተወልደ ገብረማሪያም ለቢቢሲ እንደተናገሩት በንግድ ግንኙነት ምክንያት ከቻይና ጋር ጥብቅ ቁርኝት ላላቸው የአፍሪካ አገራት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወሳኝ አገልግሎትን ሰጥቷል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው አየር መንገዳቸው በቀጥታ በረራና በኮቪድ-19 ስርጭት መካከል ግንኙነት አለው ብሎ እንደማያምንም ተናግረዋል። ጨምረውም በጣም ጠበቅ ያለ የጉዞ ቁጥጥርና እገዳዎችን ባወጡ አገራት ውስጥ ሳይቀር ወረርሽኙ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን አመልክተዋል። ነገር ግን በረራዎችን በማገድ በኩል በምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታዎችና በሕዝብ ጤና መካከል ሚዛን መጠበቅ ከግምት ውስጥ መግባት እንዳለበት ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻይና ውስጥ በሽታው ተስፋፋፍቶ በነበረበት ወቅት ቤይጂንግና ሻግሃይን ወደመሳሰሉ ከተሞች በረራ ያደርጉ ከነበሩ የተወሰኑ አየር መንገዶች መካከል አንዱ ነበ
amh_Ethi
train
xp3longgenarticle
GEM/xlsum
amharic
158
Content: ፕሬዝደንቱ፤ በቅርቡ ሁለት ተቃውሞ ሰልፍ ላይ የነበሩት ሰልፈኞችን ገድሏል ተብሎ የተጠረጠረ ታዳጊና ሌሎች ከፀረ-ዘረኝነት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ጋር የተጋጩ ሰዎች ራሳቸውን ነው የተከላከሉት ሲሉ ተደምጠዋል። ፕሬዝደንቱ የመጭው ምርጫ ተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን የግራ ዘመም ተሟቾችን ድርጊት አልወቀሱም ሲል ተችተዋቸዋል። ጆ ባይደን ከምርጫው በፊት በመራጮች ዘንድ የተሻለ ተቀባይነት ያላቸው ዕጩ ሆነው እየመሩ ይገኛሉ። ሰኞ ዕለት በቤተ መንግሥታቸው [ዋይት ሐውስ] መግለጫ የሰጡት ፕሬዝደንት ትራምፕ በዴሞክራት አገረ ገዥዎችና ከንቲባዎች በሚመሩ አካባቢዎች ለተፈጠረው ግርግር ተቃናቃኛቸው ባይደንና ፓርቲያቸውን ተጠያቂ አድርገዋል። ሲኤንኤን የተሰኘው ጣቢያ ጋዜጠኛ 'የእርሶ ደጋፊዎች ከተቃዋሚዎች ጋር ተጋጭተው ጉዳት አድርሰዋል፤ ይህንን ይነቅፋሉ ወይ?' ሲል ለፕሬዝደንቱ ጥያቄ ሰንዝሮላቸው ነበር። በተለይ ፖርትላንድ ግዛት ውስጥ ኦሬጎን ከተማ በሁለቱ ፅንፍ ደጋፊዎች መካከል ከፍተኛ ግጭት ተፈጥሮ ነበር። በታዳጊው ተገድለዋል ከተባሉ ሁለት ሰዎች በተጨማሪ የቀኝ ዘመም ርዕዮተ ዓለም ደጋፊ የሆነ ሰው መገደሉ ተነግሯል። ለተሰነዘረላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ፕሬዝደንቱ "እርግጥ ነው በርካታ ሰዎች ሰልፍ ወጥተዋል፤ ነገር ግን ሰላማዊ ሰልፍ ነበር" ብለዋል። በዊስኮንሰን ግዛት ኬኖሻ ከተማ አንድ የ17 ዓመት ተጠርጣሪ በመሣሪያ ሁለት ተቃዋሚ ሰልፈኞችት ገድሏል መባሉንስ ይነቅፋሉ ወይ ለትራምፕ የቀረበላቸው ሌላኛው ጥያቄ ነው። የ17 ዓመቱ ካይል ሪትንሃውስ ሶስት ሰዎችን በጥይት መቷል፤ ሁለቱ ሞተዋል ተብሎ ተጠርጥሯል። ታዳጊው ይህን ደርጊት የፈፀመው በከተማዋ ጃኮብ ብሌክ የተሰኘ ጥቁር አሜሪካዊ በፖሊስ ሰባት ጊዜ በጥይት መመታቱን ተከትሎ በተቀሰቀሰ ሰልፍ ላይ ነው። ፕሬዝደንቱ ታዳጊውን በተመለከተ ለቀረበላቸው "እሱን እያጣራን ነው" ነው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። "በጣም የሚገርመው እናንተ ያያችሁትን ምስል ነው እኔም ያየሁት። እሱ [ታዳጊው] ከሰልፈኞቹ ለማምለጥ እየሞከረ ነበር፤ ሲመስለኝ እንደዚያ ነው። ከዚያ ሲወድቅ ከበው ጥቃት አደረሰቡት።" "ጉዳዩ ምርመራ ላይ ነው" ሲሉ ፕሬዝደንቱ ስለታዳጊው ተጠርጣሪ ያላቸውን አስተያየት ቋጭተዋል። የዴሞክራት ፓርቲ ሰዎች በፕሬዝደንቱ አስተያየት የተሰማቸውን ግርታ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋለውና በአዋቂዎች ወንጀል የተጠረጠረው ታዳጊ እስካሁን ፍርድ ቤት አልቀረበም። ፕሬዝደንት ከጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ግድያ በኋላ ለተቃውሞ ሰልፍ አደባባይ የወጡ አሜሪካውያንን ዘራፈዎች፣ አመፀኞች፣ አጥፊዎች እንዲሁም ወንበዴዎች ሲሉ ነው የሚጠሯቸው። ተቃናቃኛቸው ጆ ባይደን በቅርቡ በሰልፈኞች መካከል የተፈጠረውን ግጭት አውግዘው ፕሬዝደንት ትራምፕ ሃገሪቱን ሰላም አልባ አድርገዋታል ሲሉ ወቅሰዋል። የዚህኛው ዙር ተቃውሞ የተቀሰቀሰባት የዊስኮንሰን ግዛት ለሁለቱ ፓርቲዎች ወሳኝ ይዞታ ናት። \nThe previous content can be summarized as follows:
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ሞት ያስከተለ ግጭት ውስጥ የተሳተፉ ደጋፊዎቻቸውን ተከላክለዋል።
amh_Ethi
test
prevcontent
GEM/xlsum
amharic
327
Given the below title and summary of an article, generate a short article or the beginning of a long article to go along with them. Title: ኮሮናቫይረስን ለማከም ስለተፈቀደው መድኃኒት ሬምዴሲቬር ምን ይታወቃል?\nSummary: የአሜሪካ ምግብና መድኃኒት አስተዳደር ተቋም ለኢቦላ በሽታ የሚውለውን ሬምዴሲቬር የተባለውን መድኃኒት ለአስቸኳይ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ህክምና እንዲውል ፈቀደ።\nArticle (Max 500 characters):
የኮሮናቫይረስ ህሙማንን ለማከም እንዲውል የተፈቀደው ሬምዴሲቬር በዚህም መሰረት ይህ ጸረ ቫይረስ የሆነው መድኃኒት በኮሮናቫይረስ በጽኑ ታመው ሆስፒታል የሚገኙ ሰዎችን ለማከም ይውላል። የአሜሪካ ምግብና መድኃኒት አስተዳደር ኮሚሽነር የሆኑት ስቴፈን ሃን "ይህ የኮሮናቫይረስን ለማከም ዕውቅና የተሰጠው የመጀመሪያው መድኃኒት ነው" ብለዋል። በቅርቡ ሬምዴሲቬርን በመጠቀም በተደረገ ሙከራ በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ታመው ሆስፒታል የገቡ ሰዎች የሚያገግሙበትን ጊዜ ማፋጠን እንዳስቻለ ተረጋግጧል። ነገር ግን ይህ በተቋሙ መድኃኒቱን ለመጠቀም የተሰጠው የአስቸኳይ ጊዜ ፈቃድ ሙሉ ፈቃድ አለመሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ መደበኛ ዕውቅና ለማግኘት ከፍ ያለ ምዘናን ይጠይቃል። ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህ ኢቦላን ለማከም የተሰራው መድኃኒት ኮሮናቫይረስን እንደሚፈውስ ተአምረኛ መፍትሄ መወሰድ የለበትም።
amh_Ethi
train
xp3longgenarticle
GEM/xlsum
amharic
142
Title: አሜሪካ ፡ የትራምፕ ሥልጣን ሊያበቃ በተቃረበበት ጊዜ ሁለተኛው የሞት ቅጣት ተግባራዊ ሆነ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
በዚህም በአገሪቱ ውስጥ ከሌላው ጊዜ በተለየ ባለፉት ሁለት ቀናት የሞት ቅጣት የተግባራዊ የሆነበት ሁለተኛው ሰው ሆኗል። ከአልፈርድ በፊት ባለፈው ሐሙስ ብራንደን በርናንድ በሞት ተቀጥቷል። የዶናልድ ትራምፕ የሥልጣን ዘመን ጥር 20 ከመገባደዱ በፊት ሦስት ተጨማሪ ሰዎች የሞት ቅጣት እንደሚፈጸምባቸው ተገልጿል። የሞት ቅጣት ላለፉት 17 ዓመታት ተቋርጦ ነበር። በዚህ ዓመት መባቻ ላይ ግን ቅጣቱ በድጋሚ እንዲጀመር ትራምፕ አዘዋል። የሞት ቅጣት በተወሰነባቸው ሰዎች ላይ በአጠቃላይ ከተተገበረ፤ ከሌሎቹ በተለየ ትራምፕ ፕሬዘዳንት ብዙ ሰው በሞት የቀጡ መሪ ይሆናሉ። ላለፉት 130 ዓመታት የአሜሪካ ፕሬዘዳንቶች ሥልጣን ሊለቁ ሲሉ የሞት ቅጣትን ይገታሉ። ቀጣዩ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ጥር 20 በዓለ ሲመታቸው ይከናወናል። ባይደን የዳልዌር ሴናተሩ ሳሉ ጀምሮም ለአስርት ዓመታት የሞት ቅጣትን እንደሚቃወሙ ሲገልጹ ነበር። ሥልጣን ከያዙ የሞት ቅጣትን እንደሚያስወግዱም አስታውቀዋል። ፍርድ ቤት እንዳለው የሞት ቅጣት የተፈጸመበት አልፈርድ የሁለት ዓመት ሴት ልጁ ላይ ወሲባዊ ጥቃት እንዳደረሰ ተነሯል። የጭነት መኪና አሽከርካሪ ሳለ በቴክሳስ በኩል ሲያልፍ ልጁን እንደገደላትም ፍርድ ቤቱ ገልጿል። ዐቃቤ ሕግ እንዳለው፤ መኪናውን እያቆመ ሳለ ልጁ መኪናው ውስጥ ፈሳሽ ሲደፋባት ከመኪናው መስታወትና ከውስጠኛው ክፍል ጠርዝ ጋር አጋጭቶ ነበር የገደላት። የአልፈርድ ጠበቆች እንዳሉት፤ አልፈርድ የአእምሮ ውስንነት (ኢንተለክችዋል ዲስኤቢሊቲ) ስላለበት በሞት ሊቀጣ አይገባም ነበር። ሌሎች የሞት ቅጣት የተላለፈባቸው ታራሚዎች ሊሳ ሞንተግመሪ፡ እአአ 2004 ላይ ሚዙሪ ውስጥ ነፍሰ ጡር ሴትን አንቃ ልጇን ከማህጸኗ ወስዳ አፍናለች። ጥር 12 የሞት ቅጣት ይፈጸምባታል ተብሏል። ጠበቃዋ እንደሚሉት ሊሳ ልጅ ሳለች በደረሰባት ድብደባ ምክንያት ከፍተኛ የአእምሮ ህመም አለባት። ከ1953 ወዲህ በሞት የተቀጣት የመጀመሪያዋ ሴት ትሆናለች። ኮሪ ጆንሰን፡ ሪችመንድ፣ ቨርጂንያ ውስጥ ከነበረ አደንዛዥ እጽ ዝውውር ጋር በተያያዘ በሰባት ሰዎች ግድያ ነው የተከሰሰው። ልጅ ሳለ በደረሰበት አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጥቃት ሳቢያ የአእምሮ ውስንነት እንዳለበት ጠበቆቹ ተናግረዋል። ደስቲን ጆን ሂግስ፡ እአአ 1996 ላይ ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ሦስት ወጣት ሴቶችን አፍኖ በመግደል ነው የተከሰሰው። ግለሰቡ ሴቶቹ እንዲገደሉ ዊሊስ ሀይንስ የተባለ ግብረ አበሩን አዟል እንጂ ግድያውን አልፈጸመም። ጥር 15 የሞት ቅጣት ይፈጸምበታል ተብሏል።
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
304
Doc to summarize: ፖሊሶች በዩኒቨርስቲዎች ቅጥር ጊቢ ገብተው ተማሪዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ የተኮሱ ሲሆን፤ በባቡር ጣቢያዎች ተሳፋሪዎችን እየፈተሹ በመሆኑም መጨናነነቅ ተፈጥሯል። ባለፈው ሰኞ ከፍተኛ ተቃውሞ መካሄዱ ይታወሳል። • ''ፕሬዝደንት ትራምፕ እባክዎ ሆንግ ኮንግን ይታደጉ'' ሰልፈኞች • ተቃውሞ በቻይና፡ መንግሥት 'የውጭ ኃይሎችን' እየወቀሰ ነው • የሆንግ ኮንግ 'የተቃውሞ' ኬክ ከውድድር ታገደ አንድ የመብት ተሟጋች በፖሊስ የተተኮሰበት ሲሆን፤ ሌላ ተሟጋች ደግሞ በእሳት ተቃጥሏል። ሁለቱም በአሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። ዛሬ በርካታ ትምህርት ቤቶች የደህንት ስጋት በመኖሩ እንደሚዘጉ ለተማሪዎቻቸው ቤተሰቦች በአጭር የጽሁፍ መልዕከት አስታውቀዋል። የሆንግ ኮንጓ ካሪ ላም በበኩላቸው አለመረጋጋት ቢኖርም ትምህርት ቤቶች እንደማይዘጉ ገልጸዋል። ሰኞ ተማሪዎችና ፖሊሶች መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የባቡር አገልግሎት ተስተጓጉሎ፣ መንገዶች ተዘግተውም ነበር። በ 'ቻይኒዝ ዩኒቨርስቲ' ተቃዋሚዎች ፖሊሶች ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ ፖሊሶች ደግሞ በምላሹ የፕላስቲክ ጥይት ሲተኩሱ ነበር። ይህን ተከትሎም በርካታ ዩኒቨርስቲዎች ትምህርት አቋርጠዋል። ሰኞ ከ260 በላይ ሰዎች የታሰሩ ሲሆን፤ ተቃውሞው ከጀመረበት ጊዜ እስካሁን በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች ቁጥር 3,000 ደርሷል። ካሪ ላም ተቃዋሚዎች "የሕዝብ ጠላት" ናቸው ሲሉ፤ አሜሪካ ደግሞ ሆንግ ኮንግ የገባችበት ውጥንቅጥ አሳስቦኛል ብላለች። የሆንግ ኮንግ እስረኞች ለቻይና ተላልፈው ይሰጡ የሚል ረቂቅ አዋጅን በመቃወም የተጀመረው ተቃውሞ፤ ረቂቁ ውድቅ ቢደረግም እንደቀጠለ ነው። የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች ዴሞክራሲ ይስፈን፣ ፖሊሶች ለተግባራቸው ተጠያቂ ይደረጉ ሲሉ ድምጻቸውን ማሰማቱን ቀጥለዋል። \nSummary in the same language as the doc:
በሆንግ ኮንግ ትምህርት ቤቶች በደህንነት ስጋት ተዘግተዋል።
amh_Ethi
train
docsummary
GEM/xlsum
amharic
202
Given the below title and summary of an article, generate a short article or the beginning of a long article to go along with them. Title: ዶናልድ ትራምፕ በስሎቬኒያ የባለቤታቸው መኖሪያ ቤት ሐውልት ቆመላቸው\nSummary: አነጋጋሪው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስሎቬኒያ በሚገኘው የባለቤታቸው መኖሪያ ቤት ከእንጨት የተሰራ ሐውልት ቆመላቸው።\nArticle (Max 500 characters):
የዶናልድ ትራምፕ ከእንጨት የተሰራ ሐውልት ከባለቤታቸው ሜላኒያ ሐውልት በስተግራ 8 ሜትር የሚረዝመው ሐውልት የቆመው በግለሰብ ይዞታ ላይ ሲሆን ጭንቅላታቸውና አገጫቸው አራት መዓዘን ቅርፅ ይዞ የተሰራ ነው። ዶናልድ እጃቸውን በድል ምልክት ወደላይ ዘርግተው ይታያል። ሰማያዊ ሙሉ ልብስ በቀይ ክራቫት ለብሰውም የኒዮርኩን የነፃነት ሐውልት ያስታውሳሉ። • አሜሪካ ሩሲያዊቷን በሰላይነት ከሰሰች • አሜሪካ፡ የመድኃኒት ዋጋ ሰማይ የደረሰባት ሃገር ታዲያ በርካቶች በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት አልተቆጠቡም። የሐውልቱ ቀራፂ ለኤ ኤፍ ፒ የዜና ወኪል እንዳለው የሕዝቡን ስሜት ለማንፀባረቅ መስራት እንደፈለገ ተናግሯል። ሐውልቱ የተሰራውም የባለቤታቸው ሜላኒያ ትራምፕ ሐውልት በትውልድ ቦታዋ ስቭኒካ ከቆመ በኋላ ነው። ሐውልቷ ከእንጨት ተፈልፍሎ የተሰራ ሲሆን ሰማያዊው ኮት ለብሳ እ
amh_Ethi
train
xp3longgenarticle
GEM/xlsum
amharic
148
ከጥቃቱ ከተረፉት ሰዎች፣ ከሟች ቤተሰቦች እና ከነጆ ወረዳ አስዳዳሪ ቢቢሲ እንደተረዳው ዓርብ ዕለት የሸኔ አባላት ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች በ10 የመንግሥት ሠራተኞች ላይ በተፈጸመ ጥቃት አራቱ ሲገደሉ ሦስቱ የመቁሰል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ሦስት ሰዎች ደግሞ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከጥቃቱ ተርፈዋል። ግንቦት 21/2012 ዓ.ም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር ለማከፋፈል ከተለያዩ ቢሮዎች የተወጣጣ ኮሚቴ አሞማ ዴገሮ ወደ ሚባል ቀበሌ ተጉዞ እንደነበነር የነጆ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ተሊላ ተፈራ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "የመንግሥት ሠራተኞቹ ከሄዱበት ስፍራ በሰላም ሥራቸውን ጨርሰው እየተመለሱ ዋጋሪ ቡና ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሲደርሱ ጸረ ሰላም በሆኑት የሸኔ ታጣቂዎች ተኩስ ተከፍቶበናቸዋል" ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል። ለመስክ ሥራ ተሰማርተው የነበሩት ሰዎች በአጠቃላይ 10 እንደነበሩ የሚያስታውሱት አቶ ተሊላ በጥቃቱ ከመካከላቸው አራቱ ተገድለዋል። "አንደኛው ሟች አብዲ አበራ የሚባል ሹፌር ሲሆን ሁለተኛው የእንስሳት ሐኪም የነበረው ዳዊት ተርፋሳ ሲሆን፤ ባሕሩ አየለ እና እስራኤል መርዳሳ የሚባሉት ሟቾች ደግሞ የወረዳው ሚሊሻ አባላት ናቸው" ብለዋል። በታጣቂዎቹ በተሰነዘረባቸው ጥቃት ከተገደሉት ሰዎች በተጨማሪ ሦስቱ በጥቃቱ የቆሰሉት ሲሆን፤ ከጥቃቱ ጉዳት ሳይደርስባቸው ያመለጡት ደግሞ ሦስት ናቸው። የተፈጠረው ምን ነበር? በመንግሥት ሠራተኞቹ ላይ ጥቃቱ የተሰነዘረው ዓርብ ከሰዓት በኋላ ላይ ነበር። የአስሩ የመንግሥት ሠራተኞች መንግሥታዊ ባልሆነ ድርጅት ድጋፍ የተገኘውን የምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ በጸጥታ ችግር ምክንያት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ለማከፋፈል ወደ አሞማ ዴገሮ ይጓዛሉ። እ... Continue the article for another 4000 characters max:
ነዚህ የመንግሥት ሠራተኞች ከወረዳው የአደጋ ዝግጁነት እና ቁጥጥር ጽህፈት ቤት፣ ከእንስሳት ጤና፣ ከሚሊሻ የተወጣጡ ነበሩ። ለመስክ ሥራ የተሰማሩት ሠራተኞቹ የሄዱበትን ሥራ ፈጽመው ወደ ነጆ ከተማ እየተመለሱ ሳለ ከሰዓት በኋላ 9 ሰዓት ከ35 ገደማ ዋጋሪ ቡና ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የሸኔ አባላት ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸዋል። "በቅድሚያ የመኪናውን ጎማ በጥይት መቱ" ያሉት አቶ ተሊላ፤ መኪናው ሲቆም በመኪናው ውስጥ በነበሩት ሠራተኞች ላይ ተኩስ መከፈቱን ይናገራሉ። "ከዓይን እማኞች መገንዘብ እንደቻልነው ጥቃቱን የሰነዘሩት ታጣቂዎች በቁጥር ስምንት ይሆናሉ" ብለዋል። "መኪናው በጥይት ተመትቶ እንደቆመ ሮጠው ማምለጥ የቻሉት ህይወታቸውን ማትረፍ ችለዋል። በመኪናው ውስጥ ከነበሩት መካከልም በጥይት ተመተው 'ሞተዋል' ብለው ያለፏቸውም አሉ" ይላሉ አቶ ተሊላ። በጥቃቱ የተገደሉት አራቱ ሰዎች ህይወታው ያለፈው ወዲያ ጥቃቱ ከተፈጸመበት ስፍራ መሆኑን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ተሊላ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ፈጽመው በመኪናው ውስጥ ያሉትን ሰዎች ከገደሉና ካቆሰሉ በኋላ የመንግሥት ሠራተኞቹ ይዘዋቸው የነበሩትን 4 የጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ ሌሎች ንብረቶችን ዘረፍው መሄዳቸውን ገልጸዋል። ከጥቃቱ በኋላ በአካባቢው ተሰማርቶ የሚገኘው የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የአሮሚያ ልዩ ኃይል የጥቃቱን ፈጻሚዎች ለማግኘት አሰሳ እያካሄደ መሆኑን እና እስካሁን ግን ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር የዋለ እንደሌላ አስረድተዋል። ሥራ በጀመረ በሦስተኛ ሳምንቱ የተገደለው ሹፌር በታጣቂዎቹ ከተገደሉት መካከል አንዱ የሆነውና መኪናውን ሲያሽከረክር የነበረው አብዲ አበራ ነው። የአብዲ ታላቅ ወንድም ቴዲ አበራ "ወንድሜን ድንጋይ ተሸክሜ ነው ያሳደኩት፤ ሥራ ከጀመረ እንኳ ገና ሦስተኛ ሳምንቱ ነው" ይላል። "ያለ አባት ነው ያደገው። ከተቀጠረ እንኳን ገና ሦስት ሳምንት አልሆነውም። የአንድ ወር ደሞዝ እንኳን አልበላም። የአንድ ዓመት ከሁለት ወር ወንድ ልጅ አለው። ይሄው ልጁም ልክ እንደሱ ያለ አባት ሊያድግ ነው" ሲል በመሪር ሐዘን ውስጥ ሆኖ ስለወንድሙ ለቢቢሲ ተናግሯል። ቴዲ "አስክሬኑን አመጥተው ነው የሰጡን። ማን ገደለው? ለምን ተገደለ? ብለን የምንጠይቀው እንኳን የለም። ሰው ቀና ብሎ የማያይ፤ ሰዎች የሚወዱት ገና የ21 ዓመት ልጅ ነበረ" ሲል ታናሽ ወንድሙን ያስታውሳል። ስለወንድሙ ሲናገር እምባ የሚቀድመው ቴዲ፤ ታናሽ ወንድሙ አብዲ ከሦስት ሳምንት በፊት ይህን የሹፍርና ሥራ በወረዳው ተቀጥሮ መስራት ከመጀመሩ በፊት በነጆ ከተማ የሰው ባጃጅ እየነዳ ይተዳደር እንደነበረ ገልጿል። በሐዘን ክፍኛ የተጎዳው ቴዲ በመረረ ስሜት የወንድሙን ሞት "ተስፋዬ ነበር። ተስፋዬን ቀበርኩ። በእኛ ላይ የደረሰው በጠላት ቤት እንኳን አይግባ" ሲል የደረሰበት መከራ ሌሎች ላይ እንዳይደርስ ተመኝቷል። የመንግሥት ሠራተኞች ስጋት ? የነጆ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ተሊላ ተፈራ እንደሚሉት፤ በተለይም የመንግሥት ሠራተኞችን ዒላማ ያደረገ መሰል ጥቃት በአካባቢው ሲፈጸም ይህ የመጀመሪያው አይደለም። "አንድ ግልጽ መሆን ያለበት ነገር እነዚህ ቡድኖች የልማት ሥራዎች ሲሰሩ አይደሰቱም። ከዚህ ቀደም የመንግሥት ሠራተኞችን ኢላማ ሲያደርጉ ነበር" ይላሉ። ከዚህ በፊት የወረዳ፤ የቀበሌ አስተዳዳሪ ተገድሏል፣ ሚሊሻ ተገድሏል፣ ማዕድን አውጪ ባለሙያዎች መገደላቸውን የሚናገሩት አቶ ተሊላ "አሁን ጥቃት የተፈጸመባቸው ሠራተኞች በመንግሥት መኪና መንቀሳቀሳቸውንና ሚሊሻ ከእነሱ መሆኑ ሲያውቁ ነው ጥቃት የሰነዘሩባቸው" ይላሉ። ይህ በአካባቢው የሚፈጸመው ተደጋጋሚ ጥቃት በመንግሥት...
amh_Ethi
train
xp3longcontinue
GEM/xlsum
amharic
601
Doc to summarize: ቆዳቸውን ለማንጣት ቅባቶችን የተጠቀሙት ካሪሽማ፣ አኑሻና ሳብሪና በጥንታዊት ቻይና ሴቶች እግር ትንሽ መሆን አንድ የውበት መገለጫ በመሆኑ እግራቸው እንዲታጠፍና እንዲሰበርም ይገደዱ ነበር። በዓመታት ውስጥ ማኅበረሰቡ በቻይና እንደሚደረገው እጅና እግር ተጠፍሮ እግር ባይሰበርም ባለንበት ዓለም ማስታወቂያዎች፣ ፊልሞች፣ ሙዚቃዎች በተለያ መንገድ ተፅእኖን ያሳርፋሉ። የጎን አጥንትን ከማስወጣት ጀምሮ፣ ከንፈር፣ ጡትና የተለያየ የአካል ክፍልን ለማስተካከል ቀዶ ጥገና የሚያደርጉ በርካቶች ናቸው። የቁንጅና እሳቤ ኢ-ፍትሃዊ ከሆነው አባታዊ ሥርዓት ጋር ብቻ ሳይሆን ከዘረኝነትም ጋር በፅኑ የተቆራኘ እንደሆነ ተችዎች አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። ከዚህም ውስጥ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የሚፈስበት ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሆነው የቆዳ ማንጫ ምርቶች ይገኙበታል። ነጭ የቆዳ ቀለም የበላይ ነው በሚል እሳቤም በርካቶች ቆዳቸውን ለማንጣት ፊታቸውን ለጉዳት የሚያጋልጥ ቅባቶችን ይጠቀማሉ። በማንኛውም መንገድ ፊትን ለማንጣትም የሚታገሉ በርካቶች ናቸው። "በየቀኑ ገላዬን ስታጠብ የመጀመሪያ ሥራዬ ጥቁረቴ እንዲለቅ በሚል ቆዳዬን መፈግፈግ ነበር" ትላለች ካሪሽማ ሌክራዝ። ማኅበረሰቡ ቆንጆ ነሽ የሚለውን እንዲያጎናጽፋትም ብዙ መስዋዕትነት ከፍላለች። ቆዳዋን ከመፈግፈግ ጀምሮ ቆዳ ሊያነጡ የሚችሉ ቅባቶችንም መጠቀም የጀመረችው ገና በ13 ዓመቷ ነው። "ነጭ የቆዳ ቀለም ቢኖረኝ ቆንጆ እንደምሆን ይሰማኝ ነበር" ትላለች። "ብዙዎች ልቅም ያልኩ ቆንጆ እንደሆንኩ ይነግሩኛል። ነገር ግን በአሳፋሪ ሁኔታ ቆዳዬ ጥቁር ነው" ትላለች የ27 ዓመቷ ካሪሽማ ከቢቢሲ ሬድዮ ዋን ኒውስ ቢት ጋር ባደረገችው ቆይታ። ካሪሽማ የቆዳ ቀለሟ እንዲነጣ ቅባት ያስጀመሯትም ቤተሰቦቿ ናቸው። የመጥቆሯ ነገር በቤተሰቦቿ ዘንድም ተቀባይነት ስላልነበረው እንድትነጣ ወይም ፈካ ብላ እንድትታይ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም። "በባህላችን ዘንድ ስር የሰደደ ጉዳይ ነው። አንድ ሰው ቆንጆ የሚባለው ነጭ የቀለም ቆዳ ሲኖረው ነው" ትላለች። ካሪሽማ ባህሌ የምትለው ነጭ የቆዳ ቀለም ከፍ ያለ ቦታ የሚሰጠውን የደቡብ እስያን እይታ ነው። ከቆዳ ቀለም ማንጣት ጋር ተያይዞ ስሙ የሚጠራው 'ፌር ኤንድ ላቭሊ' አምራቹ ዩኒሊቨር ነው። በነጭ ፖሊስ በግፍ የተገደለውን የጆርጅ ፍሎይድን ሞት ተከትሎ በተፈጠረው ተቃውሞና የዘር ውይይት ግዙፉ የውበት እቃዎች አምራች ዩኒሊቨር ስምና የማስታወቂያ ሃሳቡን እንዲቀይር ተገዷል። ኩባንያው "ነጣና ፈካ" ያለ ቆዳ የሚለውን አባባል በእስያና በአፍሪካ ገበያዎች ላይጠቀም ቃል ገብቷል። ጋብቻ ፈላጊ ጥንዶችን የሚያገናኘው ሻዲ የተባለው በእስያ ተቀማጭነቱን ያደረገ ድረገፅም እንዲሁ "የቆዳ ማፍኪያ" የሚለውን አገላለጹን አስወግዷል። "ፀሐይ ላይ ብዙ አትቀመጪ" እንደ ካሪሽማ ሳብሪና ማንኩም ስለ ጥቁረቷ አሉታዊ ነገሮችን ከቤተሰቦቿ አንደበት በተደጋጋሚ ስትሰማ ነው ያደገችው። "ህፃን ሆኜ የበለጠ እንዳትጠቁሪ ፀሐይ ላይ አትቀመጪ እባል ነበር" የምትለው የ23 ዓመቷ ሳብሪና፤ አገላለጹ በተለይም በፑንጃቢ ቋንቋ ሲሆን ደግሞ የበለጠ ጨለምተኛ ትርጉም እንዳለውና "መንፈስንም ስብርብር" የሚያደርግ እንደሆነ ገልፃለች። ሳብሪና ቆዳዋን ፈካ የሚያደርግ ቅባትንም እንድትጠቀም ያደረጓት ገና የአስር ዓመት ታዳጊ እያለች ሲሆን ለስምንት ሰዓታት ያህል ያለማቋረጥ ተጠቅማዋለች። የቤተሰብ አባላት ብቻ ሳይሆኑ ማኅበረሰቡ በአጠቃላይ ስለቆዳ ቀለም ያለው አመለካከት ከፍተኛ ተፅእኖ እንደሚፈጥርም ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ላላቸው ህንዳውያን ፈታኝ መሆኑንም ይናገራሉ። ለአኑሻ ትምህርት ቤት እያለች አቻዎቿ በቆዳ ቀለሟ ላይ ይሰጡት...\nSummary in the same language as the doc:
ሴቶች ቆንጆ ብቻ እንዲሆኑ ብቻ በሚጠበቅባት ዓለም ውብ ሆኖ ለመገኘት የማይከፈል መስዋዕትነት የለም። ውበት ወይም ቁንጅና ምንድን ነው? ማኅበረሰቡ የፈጠረው አይደለም ወይ የሚለውን መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳብን ስናጤነው ውበት የሞትና ሽረት ጉዳይ ለምን ሆነ? የሚለው ጥያቄ ግራ ያጋባል።
amh_Ethi
train
docsummary
GEM/xlsum
amharic
435
ቼዳር ደሴት ላይ ነዋሪ የነበሩት እኒህ ላሞች የተረፉት ውቅያኖስ ላይ ሲዋኙ ከከረሙ በኋላ ሳይሆን አልቀረም ተብሏል። ሳይሞቱ አልቀረም ተብለው የተገመቱት ላሞች አንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ካለ ፓርክ ውስጥ ሳር ሲግጡ ተገኝተዋል። ሦስቱ ላሞች 8 ኪሎ ሜትር ያህል የውቅያኖስ አካል በዋና ሳያካልሉ አልቀረም የሚሉት የፓርኩ ሰዎች ላሞቹን ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው ለመመለስ ዕቅድ እየነደፉ ነው። አንድ የፓርኩ ሠራተኛ ነው ከላሞቹ አንዷ ፓርኩ ውስጥ ስትንጎማለል ባለፈው ወር ያያት። ላሚቱ ከተገኘች ቀናት በኋላ ደግሞ ወዳጆቿ ሣር ሲከረክሙ ተገኝተዋል። የፓርኩ ባለሙያ የሆኑት ሆርቫርት ላሞቹ ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስ ጥልቅ ሥፍራ አለመጋባታቸው ዕድለኛ ናቸው ይላሉ። ባለፈው መስከረም ሃሪኬን ዶሪያን ጎርፍ የቀላቀለ ከፍተኛ ዝናብ ሲጥል በጎርፍ የተወሰዱ በርካታ ፈረሦች ነበሩ ተብሏል። የፓርኩ ባለሙያ ላሞቹ በ8 ኪሎ ሜትር ዋናቸው ስንቱን እንዳሳለፉ በመገመት «መቼም ብዙ የሚካፍሉን ታሪክ ይኖራል» ሲሉ ቀልድ ጣል አድርገዋል። ሃሪኬን ዶሪያን መስከረም ላይ ወጀቡን ሰሜን ካሊፎርኒያ ላይ ሲያሳርፍ ንብረት እና እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። ይህ ወጀብ ወደ ባሃማስ ደሴት አቅንቶ የሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጥፋት እንዳደረሰ አይዘነጋም። \n\nGive me a good title for the article above.
ጎርፍ በቀላቀለ ወጀብ ተወስደው የነበሩት ላሞች ውቅያኖስ ዳር በሕይወት ተገኙ
amh_Ethi
train
goodtitle
GEM/xlsum
amharic
170
Doc to summarize: ባለፈው ዓመት በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች መካከል የተከሰተውን ግጭት መፍታት ያስችል ዘንድ ወደ ጅግጅጋ እንዳቀኑ የተነገረላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በቆይታቸው ከክልሉ ፐሬዚዳንት እና ከማሕበረሰቡ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል። እንደ አዲስ መሪነታቸው በክክልሎቹ መካከል ለተፈጠሩ ግጭቶች መፍትሄ ያመጡ ይሆን ሲል የሕብረተሰቡ አባላት ጥያቄ እንዳቀረቡላቸው ቢቢሲ ሶማልኛ ዘግቧል "እንደ ኢትዮጵያዊነታችን ሕገ-መንግሥቱ ላይ የተቀመጡ መብቶቻችን እንዲከበሩልን ዘንድም አንጠይቃለን፤ እስከ ጠቅላይ ሚኒስትር ሹመት ድረስ" በማለት የሕብረተሰቡ አባላት ጥያቄ እንዳነሱም ተዘግቧል። አልፎም ነዋሪዎቹ ገዢውን ፓርቲ ኢህአዴግን የሚመሰርቱ አራቱ ፓርቲዎች ያላቸው የውሳኔ ሰጭነት ኃይል ለሶማሊ ክልልም ይገባል ሲሉም ተደምጠዋል። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ በበኩላቸው በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደቀያቸው ለማስመለስ ቃል ገብተዋል። "ለሰላምና ለአብሮነት በሚደረጉ ማንኛውም ዓይነት ሥራዎች ውስጥ በቀደምትነት እንደምሳተፍ ፊት ለፊታችሁ ቃል እገባለሁ። ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የሶማሌ ወንድሞቻችን በሰላም ወደ ቀያቸው እንዲመለሱም የሚቻለንን ሁሉ እናደርጋለን።" በማለት አቶ ለማ መገርሳ ገልፀዋል። ከኦሮሚያና ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎችን አናግሮ የዘገበው ቢቢሲ ሶማልኛ ከሁለቱም ወገን ወደቀያቸው ለመመለስ የሚፈልጉ ዜጎች መኖራቸውን ጠቅሶ ተመሳሳይ ግጭቶች ዳግም እንዳይከሰቱ የሚሰጉ ሰዎች መመለሰ አንሻም እያሉም መሆኑን ጨምሮ ገልጿል። በጅግጅጋ ከተማ 01 ቀበሌ ነዋሪ የነበረው ኬረዲን ከድር በአሁኑ ወቅት በአማራሴ ተፋናቃዮች ጣቢያ ተጠልሎ ይገኛል። በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የጅግጅጋ ጉብኝት የተሰማውን ደስታ የሚገልፀው ኬረዲን "ሰላም ለአንድ ሃገር መሠረት ነው" ይላል። ሆኖም ግን "ያለው ነገር እስኪፈታ ድረስ ለመመለስ ስጋት አለኝ፤ ምክንያቱም በግጭቱ ጊዜ የነበረውን ሁኔታ ሳስብ በጣም አስፈሪ ነው።" በማለት ያለውን ስጋት ገልጿል። ከዚህ በፊት እንደሚታወሰው የሁለቱ ክልሎች በለሥልጣናት ግጭቱን ለመፍታት ቃል ገብተው ነበር። የአሁኑን ውይይት ግን ለየት እንደሚያደርገው የፖለቲካ ተንታኙ ገረሱ ቱፋ ይገልፃል። "በትክክልም ግጭቱ ተፈቷል በተባለ በሰዓታት ልዩነት ዳግም ሲያገረሽ አስተውለናል። ይህ ተፈጥሯዊ ግጭት አይደለም፤ ማለትም በግጦሽ ወይም በመሰል ምክንያቶች የተከሰተ ግጭት አይደለም። ይህ የተቀናበረ ግጭት ነው ብዬ ነው የማምነው። ስለዚህ እንዲፈታ የማይፈልግ ኃይል መኖሩ እሙን ነው" ሲል ገረሱ ያስረዳል። "ምናልባትም ይህን ጉብኝት ልዩ የሚያደርገው የኦሮሚያ አስተዳደሪ የነበረ ሰው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሆኖ መሄዱ ነው። ሙሉ ሥልጣን አለው ወይ? ሌላ ጥያቄ ሆኖ ሳለ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚያመጡትን ለውጥ ማየት ግን አጓጊ ነው" በማለት ገረሱ ይገልፃል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በቀጣይ ወደ አምቦ እንዲሁም መቀሌ በመጓዝ ከነዋሪዎችና እና አስተዳዳሮዎች ጋር ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ እንደያዙ እየተዘገበ ይገኛል። \nSummary in the same language as the doc:
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በመጀመሪያው ይፋዊ የሥራ ጉዟቸው ምክትላቸው ደመቀ መኮንን እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ለማ መገርሳን በማስከተል ወደ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና ጅግጅጋ አቅንተው ነበር።
amh_Ethi
train
docsummary
GEM/xlsum
amharic
361
Title: ተመድ፡ “የከፋ የአየር ንብረት ለውጥ ከመከሰቱ በፊት ማስጠንቀቂያ ያስፈልጋል”\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ድርጅቱ ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው፤ የከፋ የአየር ሁኔታ ከመከሰቱ በፊት ማስጠንቀቂያ የሚሰጥበት መንገድ እንዲኖር አገራት ገንዘብ ፈሰስ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ባለፉት 50 ዓመታት በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የተፈጥሮ አደጋዎች እየተበራከቱ ነው። ዓለም ላይ ከሦስት ሰዎች አንዱ/አንዷ የአየር ሁኔታ ማስጠንቀቂያ እንደማይደርሳቸው ጥናት ያሳያል። በቀጣይ አሥር ዓመታት በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት እርዳታ የሚሹ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ይጨምራል ተብሎ ይገመታል። በጥናቱ ከ16 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ከዓለም አቀፉ የአየር ሁኔታ ትንበያ ተቋም የተወጣጡ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። ባለፉት 50 ዓመታት ከአየር ሁኔታ፣ ከአየር ንብረት ለውጥ እና ከውሃ አካል ጋር የተያያዙ 11 ሺህ አደጋዎች ተከስተው፤ ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ሞተዋል። ምጣኔ ሀብትም የ3.5 ትሪሊዮን ዶላር ኪሳራ ገጥሞታል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2018፤ 108 ሚሊዮን ሰዎች ተፈጥሯዊ አደጋ ከፈጠረባቸው ጫና ለመላቀቅ የዓለም አቀፍ ድርጅቶችን ድጋፍ ጠይቀዋል። የተመድን ሪፖርት የጻፉት ባለሙያዎች፤ በ2030 እርዳታ የሚሹ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ አድጎ፤ ምጣኔ ሀብት ላይ የሚያሳድረው ጫና በዓመት 20 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ያስረዳሉ። “የከፋ የአየር ሁኔታ ከመምጣቱ በፊት ማስጠንቀቂያ ያስፈልጋል” ተመድ እንደሚለው፤ የከፋ የአየር ሁኔታ ከመከሰቱ በፊት በተገቢው መንገድ ማስጠንቀቂያ መሰጠት አለበት። ይህም የአየር ሁኔታ ምን እንደሚመስል ከመተንበይ ባለፈ፤ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ያካተተም መሆን ይገባዋል። ማስጠንቀቂያዎች በታዳጊ አገራት እንዲሁም በደሴቶች የበለጠ አስፈላጊ ናቸው። እነዚህ አገራት ባለፉት አምስት አሠርታት ከአየር ሁኔታና የአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ አጥተዋል። ከተፈጥሮ አደጋ ጋር በተያያዘ ከተከሰቱ ህልፈቶች 70% የተከሰቱት በድሃ አገራት ነው። የዓለም አቀፉ የአየር ሁኔታ ትንበያ ተቋም እንደሚለው፤ አፍሪካ ውስጥ ካሉ የአየር ሁኔታ ትንበያ ተቋሞች ደረጃቸውን የጠበቁት 26% ብቻ ናቸው። ኮሮናቫይረስ የአየር ሁኔታ ማስጠንቀቂያ ላይ ጫና ማሳደሩን የድርጅቱ ሪፖርት ይጠቁማል። ሆኖም ግን የአየር ንብረት ለውጥ ተፈጥሯዊ አደጋ እያስከተለባቸው ያሉ ድሃ አገራት መረሳት እንደሌለባቸውም ተገልጿል። የዓለም አቀፉ የአየር ሁኔታ ትንበያ ተቋም ዋና ጸሐፊ ፕ/ር ፔትሪ ታላስ “ዝግጁ ሆኖ በተገቢው ጊዜ፣ በተገቢው ቦታ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል። የሰዎችን ሕይወትና ቤት ንበረታቸውን ለመታደግ ያስችላል” ሲሉ ገልጸዋል። አያይዘውም፤ “ኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ የጤና ሥርዓትና ምጣኔ ሀብትንም አቃውሷል። ከዚህ ለማገገም ዓመታት ይወስዳል። የአየር ንብረት ለውጥ ለዘመናት በሰው ልጆች፣ በሥነ ምህዳር፣ በምጣኔ ሀብት ላይ ዘላቂ ተጽዕኖ እንዳለው መረሳት የለበትም” ብለዋል። በተመድ የአደጋ ቅነሳ ክፍል ልዩ ተወካይ ማሚ ሚዙቶሪ እንዳሉት፤ ኮቪድ-19 ያመጣው የአደጋ ጊዜ ርብርብ ዓለምን ከአየር ንብረት ለውጥ ለመታደግም መተግበር አለበት። ምን ይደረግ? በተመድ ሪፖርት መሠረት ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ስድስት ነጥቦች ቀጣዮቹ ናቸው፦
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
355
Given the below title and summary of an article, generate a short article or the beginning of a long article to go along with them. Title: ካለሁበት 22፡ የተወለድኩባት፣ የቤተሰብ ፍቅርና ህይወት ያሞቃት ቤቴ ትናፍቀኛለች\nSummary: ስሜ ነፃነት ተስፋሚካኤል ይባላል። የተወለድኩት ኢትዮጵያ ነው፣ ያደግሁት ግን ኤርትራ ነው።\nArticle (Max 500 characters):
የፊልም ደራሲ፣ ተዋናይ፣ ጋዜጠኛና የሁለት ልጆች እናት ነኝ። ከኤርትራ ወደ ሆላንድ ሐውዘን ወደሚባል ቦታ የመጣሁት እ.አ.አ. በ2005 ነበር። ወደ ሆላንድ የመጣሁት ልቤን ፍለጋ ነበር። ባለቤቴ ስደተኛ ነበረ፣ ኑሮውንም በሆላነድ ነበር ያደረገው። 'በቤተሰብ በማሰባሰቢያ' ፕሮግራም ምክንያት እኔም ከእርሱ ጋር አንድ ላይ ለመሆን ወደ ሆላንድ አቀናሁ። ከጊዜ በኋላ ቋንቋም ተማርኩኝ ሁለት ልጆችም አፈራን። እዚህ መመገብ ከምወዳቸው ነገሮች ነገሮች መካከል የድንች ጥብስ በማዮኔዝ መብላት ነው። ምክንያቱም ርካሽም ነው ደግሞም ይጣፍጣል። ነገር ግን አሁኑ እንደሚያወፍር ስላወቅኩኝ ለመቀነስ እየሞከርኩኝ ነው። ድንች ጥብስ በማዬኔዝ የሃገሪቱ ታዋቂ ምግብ ነው ኔዘርላንድን ከኤርትራ ጋር ሳነፃጽር የሚያስደንቀኝ ኤርትራን አንድ ሦስተኛ እያከለች 17 ሚሊዮን ሕዝብ መያዟ ነው።
amh_Ethi
test
xp3longgenarticle
GEM/xlsum
amharic
145
Doc to summarize: ፓርቲው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፈው ደብዳቤ ላይ የአቶ ልደቱ ጉዳይ በፍርድ ቤት እየታየ እንደሆነ በመጥቀስ "አቶ ልደቱ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከወንጀል ጋር የተገናኘ ድርጊት ፈጽመው ሳይሆን በፖለቲካ ታስረዋል ብሎ ፓርቲያቸው እንደሚያምን" መግለፁን አቶ አዳነ ታደሰ የኢዴፓ ፕሬዝዳንት ለቢቢሲ ገልጸዋል። ፓርቲው በደብዳቤው ላይ አቶ ልደቱ በአሁኑ ሰዓት የታሰሩበት ሁኔታ ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ እንደሚያደርጋቸው መንግሥት ተመልክቶ በጉዳዩ ላይ ጣልቃ በመግባት እርምጃ መውሰድ እንዳለበት መጠየቁን በተለይ ለቢቢሲ ገልጿል። አቶ አዳነ አክለውም ይህ እየተወሰደ ያለው እርምጃ አጠቃላይ ሰላማዊ ትግሉ ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ በመግለጽ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቅሬታቸውን ማቅረባቸውን ተናግረዋል። በተያያዘ ዜና አቶ ልደቱ ዛሬ ሰኞ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አዳነ ታደሰ አረጋግጠዋል። ከዚህ በፊት ፍርድ ቤቱ የሰባት ቀን ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ችሎት የቀረቡትም ፖሊስ የደረሰበትን እንዲያስረዳ እንደነበር ተናግረዋል። ፖሊስ ተጨማሪ ነገር ይዞ ሊቀርብ አለመቻሉን የሚናገሩት አቶ አዳነ "የሽግግር መንግሥት ሠነድ እጃቸው ላይ ተገኝቷል፤ በዚህ ሰነድ ሰበብም ብጥብጥና ሁከት ተነስቷል የሚል የፖሊስ ማስረጃ ችሎቱ ተመልክቶ ውድቅ አድርጎ፣ ከስልካቸው ላይ የተወሰዱ የድምጽና የመልዕክቶች ከቴሌ አስገልብጠናል እርሱን አደራጅተን፣ አስተርጉመን ለማቅረብ እንዲመቸን የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ይፈቀድልን ሲል ፖሊስ ጠይቋል" ሲሉ ተናግረዋል። አቶ ልደቱም ያሉበትን የጤና ሁኔታን በመጥቀስ የዋስትና ጥያቄ ቢያቀርቡም ችሎቱ በድጋሚ የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ ማድረጉን የተናገሩት አቶ አዳነ፤ አቶ ልደቱ ዛሬ ችሎት ፊት በቀረቡበት ወቅት ከዚህ ቀደም አምስት ጊዜ መታሰራቸውን በመጥቀስ፣ አምስት ጊዜም በነጻ መሰናበታቸውን፤ አሁንም በነጻ እንደሚወጡ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል ብለዋል። ጨምረውም አሁን እየታየ ያለው የፍትህ ሂደት ጥርጣሬ ላይ እንደጣላቸው በማስረዳት "ችሎቱ ለፖሊስ ብቻ እድል እየሰጠ እርሳቸውን ግን እያጉላላቸው እንደሆነ" ጠቅሰው ቅሬታቸውን እንዳቀረቡ አቶ አዳነ ተናግረዋል። ችሎቱም ፍርድ ቤቱ ከማንኛውም የፖለቲካ ተጽዕኖ ነፃ እንደሆነ በመግለጽ፤ ነገር ግን ከቴሌ መጣ የተባለው ድምጽና የመልዕክት ማስረጃ መተርጎምና መቅረብ ስላለበት ለመጨረሻ ጊዜ በሚል የሰባት ቀን ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል። አቶ ልደቱ አያሌው ለቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ መርማሪ ፖሊስ ለምርመራ ተጨማሪ ሰባት ቀናት እንደተፈቀደለት አቶ አዳነ ገልፀው ቀጣይ ቀጠሮ ለነሐሴ 25 ተሰጥቷል ብለዋል። አቶ ልደቱ አያሌው የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በቢሾፍቱ ከተማ አመጽና ተቃውሞ እንዲነሳ ሲቀሰቅሱና ሲያስተባብሩ ነበር በሚል ከአዲስ አበባ በፌደራል ፖሊስ ተይዘው ለኦሮሚያ ፖሊስ ተላልፈው ከተሰጡ በኋላ ጉዳያቸው በቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል። \nSummary in the same language as the doc:
የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑትና በኦሮሚያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ቢሾፍቱ ማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙትን አቶ አቶ ልደቱ በሚመለከት ቅዳሜ ዕለት ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ደብዳቤ መጻፉን ፓርቲያቸው አስታወቀ።
amh_Ethi
train
docsummary
GEM/xlsum
amharic
377
Title: ጃዋር መሐመድ፡ የእነ አቶ ጃዋር ጠበቆች ማስፈራሪያና ጫና እየደረሰብን ነው አሉ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ይህንን የተናገሩት ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ከተከሰተው ሁከት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉትን የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ አባላት እንዲሁም ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች እየተከታተሉ የሚገኙት 13 አባላት ያሉት የሕግ ባለሙያዎች ቡድን ተወካይ የሆኑት አቶ ምስጋን ሙለታ ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት ከጠበቆቹ መካከል በተወሰኑት ላይ በተለያዩ አጋጣሚዎች እየገጠማቸው ያለው ጫናና ማስፈራሪያና እየበረታ መምጣቱን ምሳሌዎች በመጥቀስ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጠበቆቹ ቡድን ተወካይ በእራሳቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ እየደረሰ ነው ያሉትን ችግር በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ ቢቢሲ ያነጋርናቸው የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጽህፈት ቤት ምክትል ጠቃላይ ዐቃቤ ሕግ የሆኑት አቶ ፍቃዱ ፀጋ፤ ጠበቆቹ እየደረሰብን ነው ያሉትን ተጽዕኖ አስመልክቶ ጽህፈት ቤታቸው የደረሰው መረጃው እንደሌለ ገልፀዋል። "የተባለውን ነገር በተመለከተ መረጃ የለኝም። እነርሱ የሕግ ባለሙያዎች ናቸው፤ የሕግ ባለሙያ ስለሆኑ እንዲህ አይነት ችግር ሲገጥማቸው ለየትኛው አካላት ማሳወቅ እንዳለባቸው ያውቃሉ። እስከ አሁን በዚህ ረገድ አንድም የደረሰን ቅሬታ የለም" ብለዋል። አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ በሌሎቹ ተከሳሾች ጉዳይ ላይ በቡድን በመሆን ፍርድ ቤት በመቅረብ ጉዳያቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት እነዚህ ጠበቆች፤ "በሙያችን ለደንበኞቻችን ቆመን በመከራከራችን ምክንያት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚደርስብን ማስፈራሪያ እና ችግር እየበረታ መጥቷል" ሲሉ ተወካያቸው አቶ ምስጋን ተናግረዋል። አቶ ምስጋን ሙለታ እንደአብነትም በእራሳቸው ላይ ደረሰ ያሉትን አጋጣሚ ሲያስረዱ "አንድ ቀን በቡራዩ ከተማ ፍርድ ቤት ለአንድ ተከሳሽ ተከራክሬ ስወጣ በፖሊስ ተጠራሁ። ከዚያም ወደ ቢሮ እንደገባሁ ያስጠራኝ ሰው ዘለፋና ተገቢ ያልሆኑ ቃላትን በመጠቀም ስልኬን ተቀብለው መፈተሽ ጀመሩ። ሸኔ ነህ ብለውም አስረው አጉላልተውኛል" ይላሉ። ከዚህ በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ የአራዳ ፖሊስ ጣቢያ የተገኙት ሌላ የጠበቆቹ ቡድን አባል የሆኑት አንድ የሕግ ባለሙያ ላይ በጦር መሳሪያ ማስፈራራት እንደተፈጸመባቸው ጠቅሰዋል። እንዲሁም ባልታወቁ ሰዎች ከጠበቆቹ መካከል መኪና ተሰብሮ የተለያዩ ሰነዶች እንደተወሰደባቸው በማንሳት ጫናው የተለያየ መሆኑን አቶ ምስጋናው ጨምረው ገልፀዋል። በዚህም ሳቢያ "ጠበቆች በሚደርስባቸው የመታሰር፣ ዘለፋ፣ ማንጓጠጥ እና ማስፈራራት የተነሳ የመኖሪያ አካባቢያቸውን ለቅቀው እስከመሄድ የደረሱም አሉ። ስለዚህ የሚታይ ተጽዕኖና የሥነ ልቦና ጫና እየደረሰብን ይገኛል" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል። ምክትል ጠቃላይ ዐቃቤ ሕጉ አቶ ፍቃዱ ፀጋ በበኩላቸው "እስካሁን ጠበቆች ፍርድ ቤት ቀርበው በነጻነት ለደንበኞቻቸው ሲከራከሩ እያየን ነው" በማለት "ነገር ግን እንዲህ አይነት ቅሬታ ካላቸው ደግሞ እዚያው ፍርድ ቤት ላይ እየገጠመን ነው የሚሉትን ጉዳይ በማንሳት እንዲስተካከልላቸው መጠየቅ ይችላሉ" ሲሉ ለቢቢሲ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። አቶ ፍቃዱ እንደሚሉት የተጠቀሱት አይነት ችግሮች አጋጥመው ከሆነ "በጠበቆች ላይ የሚፈፀም ተጽዕኖ በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት የለውም" ብለዋል። "ግለሰብ ይህንን ድርጊት ሊፈጽም ይችላል። በቢሮ ደረጃ እንዲህ አይነት ነገር ይፈፀማል ብዬ አላስብም። ተደርጎ ከሆነ ደግሞ ትልቅ ወንጀል ነው" ሲሉም አክለዋል። ጨምረውም ጠበቆቹ በሙያቸው በሕግ ፊት ለተከሳሾች መብት ተከራካሪ መሆናቸው አመልክተው፤ ይሁን እንጂ "በቀረበው ቅሬታ እውነትነት ላይ ጥርጣሬ አለኝ" ሲሉ ተናግረዋል። ነገር ግን የትኛውም ጠበቃ ደረሰብኝ ለሚለው የትኛውም አይነት ተጽዕኖ ተጨባጭ መረጃ ካለው ወደ...
amh_Ethi
train
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
414
Content: ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የሰኔ 15ቱን ሁኔታን አቅልሎ ማየት ልክ አይደለም ያሉ ሲሆን መንግሥታቸው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን በፍጥነት መቆጣጣር ባይችል ኖሮ አስከፊ ነገር ይዞ የሚመጣ አደገኛ ክስተት ነበር ብለዋል። ጀኔራል ሰዓራ መኮንንን ገድሏል ተብሎ የተጠረጠረው ግለሰብ ስለሚገኝበት ሁኔታ ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ተጠርጣሪው በህይወት እንደሚገኝ እና አንገቱ ላይ ለደረሰበት ጉዳት የህክም እርዳታ እያገኘ ሲሆን በጉዳቱ ምክንያት መናገር ባለመቻሉ ከእርሱ ይገኝ የነበረ መረጃ ማግኘት አለማቻሉን አስረድተዋል። ይሁን አንጂ ጀኔራሉን በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ በስልክ ሲገናኛቸው የነበሩ ሰዎች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መደረጉን እና ከእነርሱም ብዙ መረጃዎች መሰብሰባቸውን ገልጽዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ተጨማሪ ጀኔራሎችን ለመግደል እንቅስቃሴ ሲደረግ እንደነበር መረጃ አለንም ብለዋል። መንግሥት የሰኔ 15ቱን ክስተት መሰረት አድርጎ የግለሰቦች እና የመገናና ብዙሃንን ድምጽ ለማፈን ሙከራ አድርጓል የሚል ቅሬታ ይቀርብበታል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሲመልሱ ፤ ይህ እውነት አይደለም መንግሥት የሰዎችን ደምጽ የማፈን ፍላጎት የለውም እንደውም ከዚህ ቀደም በመንግሥት ተዘግተው የነበሩ መገናኛ ብዙሃን እንዲከፈቱ ተደርጓል ብለዋል። የኢንተርኔት አገልግሎትን በተመለከተ፡ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል፤ የጸጥታ ችግር በተከሰተ ቁጥር ለምን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ይደረጋል? የሚል ይገኝበታል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፤ እራሳችንን ከበለጸጉት ሃገራት ጋር ማወዳደር የለብንም፤ በበለጸጉ ሃገራት ሰዎች ኢንተርኔትን በመጠቀም ብሔርን ከብሔር የሚያጋጭ ምልዕክት አያስተላልፉም፣ በበለጸጉት ሃገራት ሰዎች ኢንተርኔትን ለበጎ ነው የሚጠቀሙት ያሉ ሲሆን፤ የሰዎችን ህይወት እና ንብረት ከጥቃት ለማትረፍ አስፈላጊ ሆኖ እስከተገኘ ድረስ ለሳምንት ሳይሆን እስከ ወዲያኛው ኢንተርኔት ሊዘጋ ይችላል ብለዋል። የሰብዓዊ መብት አያያዝን በተመለከተ፡ የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ መንግሥት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሰብዓዊ መብት አያያዝን በተመለከተ ቅሬታዎች እየተነሱበት እንደሆነ በመጠቀስ መንግሥታቸው በዚህ ረገድ የነበረው አቋሙ ስለመቀየሩ ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ አሁንም ጭለማ ቤት የታሰረ የለም፣ ሰው አይገረፍም፣ ጥፍር አይነቀልም ያሉ ሲሆን በሰብዓዊ መብት አያያዝ ያለን አቋም አልተቀየረም፤ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲስፋፋ ነው ፍላጎታችን ብለዋል። የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግነኙነትን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መልካም ግነኙነት ከኤርትራ ጋር መመስረቷን በማስታወስ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የኤርትራ ህዝብ እና መንግሥት ከኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግሥት ጋር አብሮ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተናግራዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ሁለቱ ሃገራት ግኑኝነታቸውን አድሰው ወደስራ ሲገቡ ግን በርካታ የባህል እና የኢኮኖሚ መዛባቶች መስተዋላቸውን አልሸሸጉም። ይህ የሁለቱን ሃገራት ግነኙነትም ስርዓት ለማስያዝ እየተሰራ መሆኑን እና ይህም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ጠቁመዋል። የሲዳማ ዞን የክልል እንሁን ጥያቄን በተመለከተ፡ የትኛውም ህዝብ ፖለቲካዊ መብቱን የመጠየቅ እና የማስከበር መብት አለው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ፤ የክልልነት ጥያቄው ከፖለቲካ መብት በተጨማሪ የሃብት ክፍፍል እና ህጋዊ ሂደቶች ያስፈልጉታል በማለት፤ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ህዝበ ውሳኔው እንደሚከናወን ተናግረዋል። የአዴፓ እና የህወሃት የቃላት ጦርነትን በተመለከተ፤ ከሰሞኑን በህወሃትና በአዴፓ መካከል የተፈጠረው የቃላት ጦርነት በፖለቲካ...\nThe previous content can be summarized as follows:
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ዛሬ ከሰዓት በሰጡት መግለጫ የሰኔ 15ቱ ግድያ እና 'መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ'፣ ቀጣዩን ምርጫ እና የሰብዓዊ ምበት አያያዝን በሚመለከት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
amh_Ethi
train
prevcontent
GEM/xlsum
amharic
408
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪምና የሩስያው ፑቲን ተገናኙ\nሁለቱ መሪዎች በሩስያ ምስራቃዊት ከተማ ቭላዲቮስቶክ አቅራቢያ በሚገኝ ረስኪ የተባለ ቦታ ነበር የተገናኙት። ኪም እና ፑቲን የኮርያ ሰርጥን ከኒውክሌር ነጻ ስለማድርግ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። • የሰሜን ኮርያ የኒዩክሌር ሚሳየል ሙከራ ደቡብ ኮርያንም ልምምድ እንድታካሂድ አስገድዷል በተጨማሪም ኪም ጆንግ ኡን ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ያደረጉት ውይይት መክሸፉን ተከትሎ፤ ኪም ከሩስያው ፕሬዘዳንት ድጋፍ ሊጠይቁ ይችላሉ። ኪም ትላንት ሩስያ ሲገቡ የሀገሪቱ ባለስላጣኖች ሞቅ ያለ አቀባባል አድርገውላቸዋል። በወታደራዊ ባንድ ሙዚቃ ዘና እንዲሉ ከተደረገ በኋላ ዘወትር ከመኪናቸው ጎን ለጎን በሚሮጡ ጠባቂዎቻቸው ታጅበው ተወስደዋል። "ጉብኝቴ ውጤታማ እና ጠቃሚም ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" ሲሉ ኪም ለሩስያ የቴሌቭዥን ጣቢያ ተናግረዋል። • ኪም ጆንግ ኡን የጦርነት ልመና ጥሪ በማድረግ ተወቀሱ የሰሜን ኮርያና የሩስያን የሁለትዮሽ ግንኙነትን ከማጠናከር ባለፈ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ስለ ኮርያ ሰርጥ ጉዳይ ለመወያየት እቅድ እንደያዙም ኪም ተናግረዋል። የሩስያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ የኮርያ ሰርጥ የኒውክሌር ጉዳይን በተመለከተ አሁን ላይ ውጤታማ ሊሆን የሚችል ዓለም አቀፍ ጥረት እምብዛም አለመኖሩን ተናግረዋል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2003 ተጀምሮ የቆመው የሰሜን ኮርያ፣ ደቡብ ኮርያ፣ ቻይና፣ ጃፓን፣ ሩስያና አሜሪካ ውይይትን ቃል አቀባዩ ጠቅሰዋል። ሰሜን ኮርያና ሩስያ ምን ይፈልጋሉ? ተንታኞች እንደሚሉት፤ የኪም እና ዶናልድ ትራምፕ ውይይት ፍሬ ስላላፈራ ሰሜን ኮርያ እንደ ሩስያ ያሉ ወዳጆች ከጎኗ ማሰለፍ ግድ ይላታል። ሰሜን ኮርያ በምጣኔ ሀብት ረገድም ብቸኛ አጋሯ አሜሪካ አንዳልሆነች ማሳየት ትፈልጋለች። • ሰሜን ኮርያ የአሜሪካውያንን አጽም መለሰች ሩስያ በበኩሏ በኮርያ ሰርጥ ጉዳይ ቀንደኛ ተዋናይ መሆን ትፈልጋለች። ፑቲን ከኪም ጋር ለመገናኘት በጉጉት ሲጠብቁ ነበርም ተብሏል። እንደ አሜሪካና ቻይና ሁሉ ሩስያም የሰሜን ኮርያ ኒውክሌር ክምችት እንቅልፍ ይነሳታል። \n\ntl;dr:
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኝተዋል።
amh_Ethi
validation
tldr
GEM/xlsum
amharic
251
Given the below title and summary of an article, generate a short article or the beginning of a long article to go along with them. Title: መንግሥት የአውሮፓ ሕብረት መግለጫ መሬት ላይ ያለውን እውነታ ያላገናዘበ ነው አለ\nSummary: የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር የአውሮፓ ሕብረት በትግራይ ክልል ከሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ጋር በተገናኘ ያወጣው መግለጫ በትግራይ ያለውን ተጨባጭ እውነታን ያላገናዘበ ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በክልሉ እያቀረበ ያለውን የሰብዓዊ ድጋፍ ከግንዛቤ ያላስገባ ነው ብሏል።\nArticle (Max 500 characters):
የአውሮፓ ሕብረት ትናንት ባወጣው መግለጫ በትግራይ እየተፈጠረ ያለው የሰብዓዊ ቀውስ እጅጉን አሳስቦኛል ብሏል። ሕብረቱ በመግለጫው የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢያዎች ክልከላ እንዳይደረግባቸውና መንግሥት ለስደተኞችና ሲቪሎች ጥበቃ እንዲሰጥ ጠይቋል። የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር በበኩሉ "መንግሥት በአካባቢው የሕግ ማስከበር ስራን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሕብረቱ የሚያወጣው መረጃ ሚዛናዊነቱን ያልጠበቀ እና ተገቢነት የሌለው ነው" ብሏል። የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱ በበርካታ የትግራይ ክልል ተደራሽ እንዲሆን መንግሥት እየሰራ ነው፤ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች እንዲጎበኝ ተደርጓል ብሏል። የተባበሩት መንግሥታት በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ 4.5 ሚሊየን ሕዝብ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልገዋል ማለቱ ይታወሳል። ከቀናት በፊ
amh_Ethi
validation
xp3longgenarticle
GEM/xlsum
amharic
161
ከግብይትዎ በኋላ "እስኪ ስልክህን/ሽን ንገረኝ/ንገሪኝ" ብለው በተንቀሳቃሽ ስልክዎ አማካኝነት ክፍያ ሊፈጸሙ ይችላሉ። በአጭሩ ስልከዎ አንድ የባንክ መስኮት የሚሰጠውን አገልገሎት ማቅረብ ይችላል። እንዴት? ይህ በእጅ ስልክ ገንዘብ የማንቀሳቀስ አስራር በበርካታ አገራት የተለመደ ሆኗል። ጎረቤት ኬንያ ከ14 ዓመታት በፊት የጀመረችው 'ኤምፔሳ' የተሰኘውን የሞባይል ገንዘብ ስርዓት አሁን ላይ 72 በመቶ የሚሆነው የአገሪቱ ነዋሪ እየተጠቀመው ይገኛል ይላል ቮክስ ከተባል ድህረ ገጽ የተገኘ መረጃ። በሰባት አገራት የሚሰራው ኤምፔሳ 42 ሚሊዮን ንቁ ደንበኞችና 400 ሺህ ወኪሎች አሉት። 50 በመቶ የሚሆነው የኬንያ ዓመታዊ ጥቅል ምርት [GDP] በዚሁ ስርዓት በኩል ይንቀሳቀሳል። በኡጋንዳ ከጠቅላላ ህዝቡ የባንክ አካውንት ያለው 11 በመቶ ሲሆን ኤምፔሳን የሚጠቀመው ሰው ግን 42 በመቶ ተሸጋግሯል። እናም እነዚህ አገራት ከግብይት በኋላ ቁጥርህ/ሽን ንገረኝ ማለት የተለመደ ነው። ከትናንት በስትያ [ማክሰኞ ግንቦት 3 - 2013] ይፋ የሆነው ቴሌብር መሰል አገልግሎትን በኢትዮጵያ የማቅረብ አላማ ይዟል። የኢትዮጵያ ሞባይል ገንዘብ አገልግሎት - ቴሌብር ከቢቢሲ ጋር ቆይታ የነበራቸው የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ኩባንያቸው ያሉትን መሰረተ ልማቶች ለድምጽ፣ ለጽሁፍ መልዕክትና ለኢንተርኔት አገልግሎት ብቻ ሲያውለው መቆየቱን አውስተዋል። ታድያ ቴሌብር የተሰኘው አዲሱ አገልግሎት መሰረተ ልማቱን ገንዘብ ለመቀበል፣ ለመላክ፣ የግብይትና የአገልግሎት ክፍያን ለመፈጸምም እንዲውልና "ክፍያን ለማሳልጥ" እንዲያግዝም ያስችላል ሲሉ ያስረዳሉ። በተጨማሪም የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ከውጪ ሀገራት ገንዘብ መቀበል ይችላሉ ብለዋል ዋና ስራ አስ... Continue the article for another 4000 characters max:
ፈጻሚዋ። በኢትዮጵያ የፋይናንስ አገልግሎቶች በባንክና መሰል ተቋማት ብቻ እየተሰጠ የቆየ መሆኑን የሚገልጹት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ኢትዮ ቴሌኮም ደግሞ ከቴሌኮም አገልግሎት በተጨማሪ የፋይናንስ ስርዓት ላይ መሳተፍ የሚችልበት የህግ ማዕቀፍ አልነበረም ብለዋል። "አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስችል የቴክኖሎጂ ስርአቱን ቢዘረጋም ከባድ ያደረገው ግን ኢትዮቴለኮም ይህንን አገልግሎት መስጠት እንዲችል የሚያደርገው የህግ ማዕቀፍ ለማሻሻል የሄድንበት ርቀት ግን ረጅምም አስቸጋሪም እንዲሁም ፈተናም የነበረበትም ነው ሲሉ" ተናግረዋል። ሁለት ዓመት ከፈጀ "ውጣ ውረድ" በኋላ ግን ይህንን አገልግሎት መስጠት እንዲችል ኩባንያው የተቋቋመበት ደንብ ማሻሻያ ከተደረገበትና ከብሄራዊ ባንክ ፍቃድ ካገኘ በኋላ አገልግሎቱ በ10 ቀናት ውስጥ ይፋ መሆኑን ገልጸዋል። መሰል ስርዓቶችን ለመዘርጋት ከ ሁለት እስከ ሶስት ዓመታት ሊፈጅ እንደሚችል ያነሱት ፍሬህይወት 'ሆኖም ፍቃድ እንደምናገኝ ተስፍ በማደረግ በአምስት ወራት ዝግጁ አድርገናል' ብለዋል። ከባንኮች ወደ ቴሌብር የገንዘብ ዝውውር ለመፍጠር ለሁሉም ባንኮች ግብዣ ልከናል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ባንኮቹን ለማስተናገድ የሚያስችል ስርዓት መዘርጋቱን ተናግረዋል። ንግድ ባንክ በሁለት ሳምንት ውስጥ 'ሲስተሙን ከኛ ጋር እንደሚያቀናጅ አሳውቆናል'ም ብለዋል። ይህ ማለት ቀድሞ ያሉ የሞባይል ባንክ ስርዓቶች የአንድ ባንክ ደንበኛ መሆንን ይጠይቃሉ። በአንፃሩ ቴሌብር የየትኛውም ባንክ ደንበኛ መሆን ሳይሆን ሲምካርድን ብቻ ይጠይቃል። አገልግሎቱን እንዴት ማግኘት ይቻላል? ኢትዮ ቴሌኮም አሁን ላይ 53 ሚሊዮን ደንበኞች ያሉት ሲሆን ከዚህ ውስጥ ደግሞ 25 ሚሊዮኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ናቸው። 23 ሚሊዮን ደንበኞች ደግሞ ስማርት ስልክ አላቸው። እናም እንደዋና ስራ አስፈጻሚዋ ገለጻ 23 ሚሊዮኑ ደንበኞች ለዚህ አገልግሎት የተዘጋጀውን መተግበሪያ በማውረድ መጠቀም ይችላሉ። ሌላኛው አማራጭ ደግሞ ኮከብና [*]መሰላልን [#] በመጫን በሚቀርቡ አገልግሎቶች ወይም USSD እና በአጭር የጽሁፍ መልዕክት መሆኑን አስረድተዋል። የስልክ ቁጥርዎ ልክ እንደ ባንክ አካውንት ቁጥር ያገለግላል። በእጅዎ ያለውን ጥሬ ገንዘብ ለኢትዮ ቴሌኮም ወኪል ይሰጣሉ ወኪሉ ደግሞ በእጅዎ ያለውን የገንዘብ መጠን ወደ እጅ ስልክዎ ይልከዋል። ወይም በተቃራኒው ከእጅ ስልክዎ ገንዘብ ወደ ወኪሉ ልከው ወኪሉ ደግሞ የላኩትን መጠን በጥሬ ገንዘብ ይሰጥዎታል። ሞባይል በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በስፍት መገኘቱ ከፋይናንስ ተቋም በበለጠ የገንዘብ ዝውውርን ለማስፋፋት ያግዛል የሚሉት ስራ አስፈጻሚዋ "በርካታ አገራት በቀላሉ ዜጎች ለግንኙነትና መረጃ ለመለዋወጥ የሚጠቀሙበትን ተንቀሳቃሽ ስልኮችን በመጠቀም ገንዘብ መላክና መቀበል እንዲሁም ክፍያ እንዲፈጽሙ በማድረግ የፋይናንስ ተደራሽነትን ከፍ ማድረግ ችለዋል" ብለዋል። በኢትዮጵያ 35 በመቶ የሚሆነው ዜጋ የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆኑን የጠቀሱት ስራ አስፈጻሚዋ "የቀረው ሰፊው በሚሊዮን የሚቆጠር ማህበረሰብ ሊሳተፍ ያልቻለ ነው ማለት ነው። .....ስለዚህ በሞባይል ቴክኖሎጂ ታግዘን ሰፊውን ማህበረሰብ በፋይናንስ አግልግሎት ተደራሽ ብናደርገው ጤነኛ የሆነ የፋይናንስ ፍሰትና ዘለቄታዊነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ ያግዛል" ሲሉ ይገልጻሉ። እናም የቴሌ ብር ዋነኛው ዓለማ ባንክን የመሰሉ የፋይናንስ ተቋም ያላገኘውን ሰፊውን የኅብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ማድረግ ነው። አገልግሎቱን ለማግኘት ተጠቃሚዎች በራሳቸው መተግበሪያውን በማውረድ ወይም #127* በመደወል አልያም 127 የጽሁፍ መልዕክት በመላክ መመዝገብ እንደሚችሉም...
amh_Ethi
train
xp3longcontinue
GEM/xlsum
amharic
575
Title: ከጄሰን ድሩሎ ጀርባ ያሉት ኢትዯጵያውያን ተወዛዋዦች\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
የኢትዮጵያዊነት ቡድን አባላት "ሌትስ ሸት አፕ ኤንድ ዳንስ" የሙዚቃው መጠሪያ ነው። "እስኪ ሌላ ሌላውን ትተን፣ ዝም ብለን እንደንስ" እንደማለት ነው። • በአማርኛ የሚያንጎራጉረው ፈረንሳያዊ የሙዚቃው ቪድዮ ላይ በዳንስ ብቃቱ የገነነው ጄሰን ድሩሎ ሲወዛወዝ ይታያል። ጃፓናዊያኑ ኤንሲቲ 127ቶችም ይውረገረጋሉ። የበርካታ ኢትዮጵያዊያንን ቀልብ የሳቡት ግን በቪድዮው ላይ ያሉት ኢትዮጵያዊያን ተወዛዋዦች ናቸው። የሙዚቃ ቪድዮው ሲጀምር የፑል መጫወቻ ጠረጴዛ ላይ የሚደንስ ኢትዮጵያዊ ህጻን ይታያል። ከዚያም በስኬት ቦርድ የሚንቀሳቀሱ ወጣቶች። ጄሰን ድሩሎ በሙዚቃው እኩሌታ ላይ "ኢትዮጵያውያን ሴቶች እስኪ ትከሻችሁን አሳዩኝ?" በሚል መልክ ኢትዮጵያዊያን እንዲወዛወዙ የሚጠይቅ ስንኝ አለው። • ተፈራ ነጋሽ፡ "በነገራችን ላይ ሙዚቃ አልተውኩም" ኢትዮጵያውያኑ ተወዛዋዦችም እስክስታውን ይወርዱታል። ለንደን፣ ሎስ አንጀለስ፣ ጃማይካ፣ እስያ. . . ሙዚቃው የተለያዩ የዓለም ክፍሎችን ውዝዋዜ ያሳያል። "ኢትዮጵያዊነት" "ኢትዮጵያዊነት" በወጣት ተወዛዋዦች የተመሰረተ የባህላዊ ውዝዋዜ ቡድን ነው። የቡድኑ አባላት ባህላዊ ውዝዋዜን ከዘመነኛ ዳንስ ጋር በማዋሀድ ይታወቃሉ። በርካታ የሙዚቃ ቪድዮዎች ላይ የሚወዛወዙት ወጣቶች፣ በጄሰን ድሩሎ የሙዚቃ ቪድዮ ላይም ተሳትፈዋል። ከዘጠኝ ዓመት በፊት "ኢትዮጵያዊነት"ን የመሰረቱት ስድስት ወጣቶች ዛሬ ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ቪድዮ ላይ ችሎታቸውን ማሳየት ችለዋል። • የሙዚቃ ሕክምና በኢትዮጵያ • የፕሮፌሰሩ ዳንስ ሕንዶችን አስደንቋል ተወዛዋዦቹ 'ባላገሩ አይዶል' የተሰኘውን ውድድር በውዝዋዜ ዘርፍ ማሸነፋቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያዊነቶች በጄሰን ድሩሎ የሙዚቃ ቪድዮ ላይ የተሳተፉት የቪድዮው አዘጋጆችን ጥሪ ተከትለው እንደሆነ ከቡድኑ አባላት አንዱ የሆነው ፍቅረማርያም በቀለ ይናገራል። ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች የተውጣጡ ዳንሰኞች ሥራቸውን የሚያሳይ ቪድዮ ለአዘጋጆቹ ካሳዩ በኋላ "ኢትዮጵያዊነት" ተመርጧል። "ልምምድ የምናደርግበት ቦታ መጥተው ቪድዮ ሲቀርጹን በጣም ወደውን ነበር። ይህን ቪድዮ ዓለም ነው የሚያየው። ድሮ የምንሰራው ቪድዮ ግን ሀገር ውስጥ የተገደበ ነበር። እኛ ከምንም በላይ የምንፈልገው ኢትዮጵያዊ ባህላችን ዓለም ላይ ከፍ እንዲል ነው።" ተወዛዋዦቹ ከዚህ ቀደም ከሠሩባቸው የሙዚቃ ቪድዮዎች የቤቲ ጂ፣ የፍቅረአዲስ ነቃጥበብና የዮሴፍ ገብሬን መጥቀስ ይቻላል። • ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን • ዳንስን በሁለተኛ ዲግሪ ኢትዮጵያዊነቶች በውዝዋዜ መላው ሀገሪቱን እንደሚወክሉ ለማሳየት የቡድናቸውን መጠሪያ መምረጣቸውን ፍቅረማሪያም ይናገራል። ፍቅረማሪያም የሙዚቃ ቪድዮው ኢትዮጵያን እንዲሁም ባህሏን እንደሚያስተዋውቅ ያስረዳል። "ውዝዋዜ ቋንቋ ነው" የሚለው ፍቅረማሪያም ተወዛዋዦችን እንደ ባህል አምባሳደር ያያቸዋል። እንደ ጄሰን ድሩሎ ባሉ እውቅ ሙዚቀኞች ቪድዮ ክሊፕ ላይ መታየት የተወዛዋዦቹን እውቅና እንደሚያሳድገው ያምናል። የሙዚቃ ቪድዮው አዘጋጆች የቡድኑን ስድስት አባላትና ኬንያዊያን ተወዛዋዦችን ይዘው ወደ ሐረር ካቀኑ በኋላ ነበር ቪድዮው የተቀረጸው። ቪድዮውን ቀርጾ ለማጠናቀቅ አራት ቀን ወስዶባቸዋል። ቪድዮው ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙም ያልታወቁ ባህሎችን ቀንጭቦም ቢሆን እንደሚያሳይ ተወዛዋዡ ያስረዳል። • ሙዚቃ ሳይሰሙ መወዛዋዝ ይችላሉ? ኢትዮጵያ ውስጥ ውዝዋዜ ከማጀቢያነት ባለፈ ራሱን እንደቻለ ጥበብ እንደማይታይ የሚናገረው ፍቅረማሪያም፤ ተወዛዋዦቹ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ መታየታቸው የተዛባውን አመለካካት በመጠኑም ቢሆን እንደሚቀርፈው ተስፋ ያደርጋል።
amh_Ethi
validation
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
382
Doc to summarize: ሪም ኮግሊን እና ኢሳም አብዱልራሂም ለመገባት ሲወስኑ በቆዳ ቀለማቸውን ልዩነት ምክንያት ትችት ገጥሟቸዋል [ማሳሰቢያ፡ ይህ ፅሑፍ አንዳንድ ፀያፍ ቃላት የይዟል] ከጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ግድያ በኋላ ዘረኝነትን የሚቃወሙ ሰልፎች ዩናይትድ ስቴትስንና የተቀረውን ዓለም በናጡበት በአሁኑ ወቅት አገሬ ሱዳን ሌላ ዓለም ውስጥ ናት። የጥቁሮች ሕይወት ዋጋ አላት ወይም #BlackLivesMatter የተሰኘው የማኅበራዊ ድር-አምባ የንቅናቄ ጥሪ በሱዳን እምብዛም ቦታ አልነበረውም። በምትኩ ሰዎች ታዋቂው ሱዳናዊ እግር ኳሰኛ ኢሳም አብዱልራሂም ቀላ ያለች አረብ የሜክ-አፕ ባለሙያ የሆነችው ሪም ኮግሊን ሊያገባ መሆኑን ተከትሎ እየዘለፉት ይገኛሉ። "የምርሽን ነው? ንግሥት ባሪያዋን ስታገባ. . . ይህ ሃራም [ሃጥያት] ነው።" ይላል አንድ ግለሰብ ፌስቡክ ላይ የፃፈው አስተያየት። መሰል አስተያየቶች በርካታ ናቸው። ነገር ግን አብዛኛዎቹ ዜጎች ራሳቸውን አረብ እንጂ አፍሪካዊ አይደለንም ብለው በሚያስቡባት ሱዳን ይህ ብዙም አስደናቂ አይደለም። ሱዳን ሁሌም ነጣ ያለ የቆዳ ቀለም ባላቸውና አረብኛ በሚናገሩ ኃያላን ነው ስትገዛ የቆየችው። በደቡባዊና ምዕራባዊ ግዛት የሚገኙ ጥቁር ሱዳናዊያን ደግሞ መገለለና አድልዎ ሲደርስባቸው ከርሟል። ጋዜጦች ጭምር ጥቁሮችን ለመግለፅ 'ባሪያ' እንዲሁም ሌሎች አስፀያፊ ቃላት ሲጠቀሙ ይስተዋላል። ከጥቂት ቀናት በፊት አንድ እስላማዊ አምደኛ፤ የቀድሞው ፕሬዝደንት ኦማር አል-ባሽር ደጋፊ እንደሆነ በሚታመነው በዕለታዊው አል-ኢንታባሃ ጋዜጣ ላይ 'ጋነርስ' የተሰኘ የታዳጊ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን አሠልጣኝን ባሪያ ሲል ገልጿታል። አነስ ያሉ ጸረ ዘረኝነት ተቃውሞዎች ተካሂደው ነበር በመዲናዋ ካርቱም ያሉ ሁሉም መገናኛ ብዙሃን ማለት ይቻላል የስርቆት ወንጀል ላይ የተሰማሩ ሰዎችን የአረብ ዘር ስለሌባቸው 'ኒግሮ' ሲሉ ይጠሯቸዋል። አብዱልራሂም እየደረሰበት ስላለው ጥቃት እንዲነግረኝ ስጠይቀው "የበለጠ ጥቃት እንዳይደርስብኝ በመፍራቴ ማኅበራዊ ገፆቼ ላይ ምንም ዓይነት ነገር መለጠፍ አስፈርቶኛል" ሲል ነግሮኛል። ነገር ግን የ29 ዓመቱና የ24 ዓመቷ ባልና ሚስት የጫጉላ ሽርሽራቸውን በፌሰቡክ ቀጥታ ሲያስተላልፉ ነበር። 'ፍቅር ውስጥ ነው ያለነው፤ የቆዳ ቀለማችን እዚህ ቦታ የለውም' ሲሉም ተደምጠዋል። በሌላ አጋጣሚ ደግሞ ለሴቶች መብት የሚከራከር ቡድን ኃላፊ የሆነች ሴት አንድ ወጣት ጥቁር ከነጭ አውሮፓዊት ሚስቱ ጋር ሆኖ የተነሳው ፎቶ ላይ 'ምናልባት ሚስት በዝንጀሮና በሰው መካከል ያለውን ፍጥረት እያፈላለገች ይሆናል' ስትል ፅፋለች። ከዚህ በኋላ ግን የደረሰባትን ወቀሳ ተከትሎ ኢህሳን ፋጊሪ ከኃላፊነቷ ራሷን ለማግለል ብትወስንም ድርጅቱ ግን አስባ ያደረግችው አይደለም በሚል አልቀበለውም ብሏል። ዘረኝነት ሱዳን ውስጥ በረቀቀ መንገድ ነው የሚቀርበው። አገሪቱ ነፃነቷን ካገኘች ጀምሮ ከፍተኛ ሥልጣን ላይ የሚገኙ ሰዎች ጠቅላላ ከሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የመጡ ናቸው - ከአረብ እና ከኑቢያ ጎሳዎች። ሁሉም የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ማለት ይቻላል ከእነዚህ ጎሳዎች የመጡ ናቸው። ካርቱም ውስጥ ወደ አንድ ባንክ ወይም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ብትገቡ በጣም ጥቁር ሰዎች ነው የምትመለከቱት። የሱዳን ባለሥልጣናት ያላቸው ሃብት ተዘርዝሮ ሊቀመጥ ይቅርና የሱዳን ሕዝብ በጎሳ ሲከፋፈል የሚኖረው ድርሻ በውል አልተቀመጠም። ነገር ግን ለጥቁሮች መብት የሚከራከርና መቀመጫውን ዳርፉር ያደረገ አንድ ቡድን ካርቱም ውስጥ 60 በመቶ የሚሆኑት ጥቁሮች ናቸው ይላል። ቀደም ባለው ዘመን ሱዳን ዋነኛ የባሪያ ንግድ ማዕከል ነበረች ሱዳን ውስጥ ያለው ዘረኝነት...\nSummary in the same language as the doc:
ጋዜጠኛ ዘይነብ ሞሐመድ ሳሊህ በአገሯ ጥቁሮች ስለሚደርስባቸው መድልዎ ይህን ፅፋለች።
amh_Ethi
train
docsummary
GEM/xlsum
amharic
420
Content: መስፍን ለቤተሰቡ አምስተኛ ልጅ ነው። ቤተሰቡ እርሱን ጨምሮ ስምንት ልጆች አሏቸው። ሁለቱ ከአንድ እናት ቀሪዎቹ ደግሞ ከሌላ እናት የተወለዱ ናቸው። ቤተሰቡ የሚተዳደረው በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ ወታደር የነበሩት አባታቸው በሚያመጡት ገቢ ነበር። አቶ ሽመላሽ በደቡብ ካምፕ ውስጥ በነበሩ ጊዜ በተማሩት የልብስ ስፌት ሙያ ነበር የተሰማሩት። ልባሽ ጨርቆችን በመሸጥም ቤታቸውን ይደጉሙ ነበር። በዚህ መሃል ግን ታመሙ። ያኔ መስፍን የ4ኛ ክፍል ተማሪ ነበር። አቶ ሽመላሽ ህመማቸው ከአዕምሮ ጋር የተያያዘ ስለነበር ሥራቸውን መቀጠል አልቻሉም። እርሳቸውን ለማዳን ለስድስት ወራት ያህል መላው ቤተሰብ ተረባረበ። በሕክምና፣ በሃይማኖት፣ በባህልም ተሞከረ፤ አልሆነም። ቤተሰቡ ችግር ላይ ወደቀ። ሁሉም በየፊናቸው የዘመመ ጎጇቸውን ለማቃናት መታተር ጀመሩ። ከባለቤታቸው ጋር ተፋትተው ገጠር ይኖሩ የነበሩት የእነ መስፍን እናት ሳይቀሩ ልጆቻቸውን ለማስተማር በቤት ሰራተኝነት ተቀጠሩ። ሌሎቹ በሚያውቁት የእጅ ሙያ ተሰማሩ። ታላቅ ወንድሙ ቡታጋዝና ፌርሜሎ [የከሰል ማንደጃ] እየጠጋገነ መሸጥ ጀመረ። አሳዳጊ እናታቸውም አባታቸው የተዉትን የልባሽ ጨርቅ ሥራ ጀመሩ። ግን ከሙያው ጋር እምብዛም ቅርበት አልነበራቸውምና አላዋጣቸውም፤ ከሰሩ። በዚህ ጊዜ ታላቅ ወንድሞቹ ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደዱ። የመጀመሪያው ልጅ ልባሽ ጨርቆችን መነገድ ጀመረ። ሌላኛው ደግሞ ብረታ ብረት ቤት ገባ። መስፍንም እንደ ቤተሰብ አባላቱ ሥራ አላማረጠም። የአራተኛ ክፍል ተማሪ ሳለ ባልጠና ጉልበቱ የብረታ ብረት ሥራ ጀመረ። በዚህ ሁኔታ ወንድሙ ትምህርቱን መቀጠል ባይችልም መስፍን ግን ግማሽ ቀን ጋራዥ እየሰራ፤ ግማሽ ቀኑን ለትምህርቱ ሰጠ። በእርግጥ እርሱም ቢሆን የሚማረው የማቋረጥ ያህል ነበር። አንድ ወር ቢማር አንድ ወር አይሄድም። ይህን ገጽ ይዞ ሕይወት ቀጠለ። ወንድሙ ማታ ማታ ሰርቶ የማይጨርሳቸውን አሮጌ የከሰል ማንደጃዎች እና ቡታጋዝ ፤ መስፍን በጠዋት ተነስቶ አጠናቅቆ፤ ሸጦ ገንዘቡን ለወንድሙ ሰጥቶ በዚያው ትምህርት ቤት ይሄዳል። መስፍን በአካባቢው ሰው ቀልጣፋና ጎበዝ እንደሆነ ይታወቃል። በርካቶች ስለእርሱ ወደፊት እምነት ነበራቸው። መስፍን "ጋሽ መሃመድ" እያለ የሚጠራቸው ግለሰብ እጅግ ያበረቱት እንደነበር ያስታውሳል። "በጋ ላይ የሰራሁትን ወስጄ ስሸጥላቸው ይቆጡኝ ነበር፤ 'መስራት ያለብህ ክረምት ነው' እያሉ ትንሽም ቢሆን ገንዘብ ሸጎጥ ያደርጉልኝ ነበር" ይላል። "አንተ ዶክተር ነው የምትሆነው" ይሉት ነበር። ምንም እንኳን አብረውት ከሚሰሩት ጓደኞቹ በትምህርት አብረውት የገፉ ባይኖሩም፤ እርሱን ግን በአቅማቸው ይደግፉት ነበር። ወላጅ እናቱም ሰው ቤት ተቀጥረው በሚያገኙት ገንዘብ ደብተርና የትምህርት ቤት የደንብ ልብስ አያሳጡትም። "እናቴ እንደ ህጻን ልጅ "ነይ!" እየተባለች ስትላላክ ማየት ያመኝ ነበር" መስፍን ተወልዶ ያደገው በደሴ ከተማ እምብርት አራዳ በተባለ አካባቢ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በመንበረ ፀሐይ፤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በንጉስ ሚካኤል እንዲሁም የመሰናዶ ትምህርቱን ሆጤ ትምህርት ቤት ተከታትሏል። ተምሮ የቤተሰብ ችግሩን መፍታት ምኞቱ ነበር። በሕይወቱ የገጠመውን ፈተና መለወጥ ይፈልግ ነበር። አባቱ ባጋጠማቸው የአዕምሮ ጤና ችግር ምክንያት፤ ሰዎች "አባቱ እብድ ነው" የሚሉትን ንግግር መቀየር ይፈልግ ነበር። እናቱንም ለመጠየቅ ሲሄድ ፤ የወለዱት እናቱ እንደ ልጅ "ነይ!" እየተባሉ ሲላላኩ ማየትም ህመም ነበር ለእርሱ። ይህን ለመለወጥ ያለው ብቸኛው አማራጭ ደግሞ ትምህርት ብቻ ነበር። የሩቅ ህልሙን ለማሳካት ወገቡን አጠበቀ።...\nThe previous content can be summarized as follows:
በሕይወት ዳገት የማይፈተን የለም። ይህን ፈተና ተቋቁመው በፅናት የሚወጡት ግን ጥቂቶች ናቸው። ዶ/ር መስፍን ሽመላሽ ከእነዚህ ብርቱዎች አንዱ ነው።
amh_Ethi
train
prevcontent
GEM/xlsum
amharic
425
Given the below title and summary of an article, generate a short article or the beginning of a long article to go along with them. Title: ካለሁበት 13፡ ''ለእኔ ስኬት ማለት ገንዘብ ማግኘት ብቻ አይደለም''\nSummary: አብዱሰላም አባጀበል እባላለሁ በአሜሪካ በኒው ዮርክ ከተማ የ'ኦሲስ ጅማ ጁስ ባር' ባለቤት ነኝ።\nArticle (Max 500 characters):
አብዱልሰላም ሕይወትን ለማሸነፍ በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፏል ተወልጄ ያደኩት በጅማ ከተማ አካባቢ ልዩ ስሙ ሸቤ በሚባል ቦታ ነው። ዕድሜዬ ለትምህርት ሲደርስ ሸቤ ትምህርት ቤት በመግባት እስከ 7ኛ ክፍል ድረስ ተምሬያለሁ። ከዚያም ሌላ ቦታ እስከ 8ኛ ክፍል ለመማር ዕድሉን ባገኝም በአባቴ ሞት ምክንያት ትምህርቴን ለማቋረጥ ተገደድኩ። ያደኩት በሰፊ ቤተሰብ ውስጥ ሲሆን ከእናቴና አባቴ የተወለዱ 14 እህትና ወንድሞች ሲኖሩኝ ወደ 30 የሚጠጉ ደግሞ የጉዲፈቻ እህቶችና ወንድሞች አሉኝ። አባቴ ሰዎችን ሰብስቦ ማብላትና ማጠጣት ይወዱ ነበር። ነገር ግን ሲሞቱ ያሁሉ እየጠፋ መምጣት ጀመረ። ከ8ኛ ክፍል ወደ ክሊኒክ ባለቤትነት ትምህርቴን በማቋረጥ ቤተሰቦቼን ለመርዳት ስል ሥራ መፈለግ ጀመርኩኝ። በመጀመሪያም ሳዶ ወደምትባል አካባቢ በመሄድ ከአባቴ ባገኘሁት የሕክምና ሞያ ክሊኒክ
amh_Ethi
train
xp3longgenarticle
GEM/xlsum
amharic
153
Doc to summarize: ትግራይ ስታዲየም በ2009 ዓ.ም በርካታ ቁጥር ያለው የስቴዲየም ብጥብጥ በተለይም በላይኛው ፕሪሚየር ሊግ ቢዘገብም ከብጥብጦቹ ጀርባ እግር ኳስን የሚሻገሩ ገፊ ምክንያቶች እምብዛም እንዳልነበሩ ይጠቀሳል። በያዝነው ዓመት በልዩ ልዩ ምክንያቶች የሚለኮሱ ግጭቶች እና ረብሻዎች ቁጥር አይሏል። ከተጀመረ ጥቂት ሳምንታትን ብቻ ባስቆጠረው የ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ከረብሻዎች ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተለያዩ ክለቦች ላይ የጣለው ቅጣት ግማሽ ሚሊዮን ብር እንደደረሰ ጉዳዩን የሚከታተሉ ባለሞያዎች ያስረዳሉ። መጠናቸው ይለያይ እንጅ ባለፉት ሁለት ወራት ሃዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ አዲግራት፣ ጅማ እና በቅርቡ ደግሞ ወልዲያ ከተሞች ውስጥ ግጭቶች እና ረብሻዎችን አስተናግደዋል። ባለፈው እሁድ በወልዲያ ስፖርት ክለብ እና በመቀሌ ከተማ መካከል ሊደረግ የነበረው የእግር ኳስ ጨዋታ ከመጀመሩ ከሰዓታት በፊት በሁለቱ ቡድኖች ደጋፊዎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ህይወት የጠፋ ሲሆን ንብረት ላይ ዘረፋና ወድመት ተከስቷል። በዕለቱ ማገባደጃ ላይ በመቀሌ ከተማ መንገዶች ላይም ክስተቱን ለመቃወም በርካታ ሰዎች ወጥተው ነበር። ጨዋታው ካለመካሄዱ በተጨማሪ የግጭቱ አሻራ እስከቀጣይ ቀናት ቀጥሏል። የትግራይ ክልል የእግር ኳስ ፈዴሬሽንም ክስተቱን በማውገዝ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈደሬሽን ጉዳዩን ኣጣርቶ በአጥፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ በደብዳቤ ጠይቋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ የወልዲያው ክስተት ከእግር ኳስ የሚሻገር ገፅታ እንዳለው ይገልፃሉ። በሴካፋ ውድድር ከሚሳተፈው የወንድ አዋቂዎች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ጋር ናይሮቢ የሚገኙት አቶ ጁነዲን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ግጭቱ ከስፖርት ሜዳ ውጭ መቀስቀሱን አስታውሰው "ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ይዘት ያለው ነገር ነው። ሜዳ ውስጥ ቢሆን ከኳስ ድጋፍ ጋር ይያያዝ ነበር፤ ሌላ ትኩሳት ያለበት ነው የሚመስለኝ፤ እግር ኳስ ብቻውን አይመስለኝም" ሲሉ ተናግረዋል። ከማኅበረሰባዊነት እስከ ብሔረተኛነት በስፖርቱ ዓለም የተመልካቾች ነውጠኛነት ምክንያቶች ብዙ ናቸው ሲል የሚያስረዳው የስፖርት ተንታኙ መንሱር አብዱልቀኒ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ ወይንም ምጣኔ ኃብታዊ ብሶቶች ስቴዲየም ላይ ሊያጠሉ እንደሚችሉ ይናገራል። በኢትዮጵያ እግር ኳስን የታከከ ብጥብጥ ሲከሰት "የመጀመሪያው ባይሆንም እየተባባሰ ግን ሄዷል። የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን ስናጤን ደግሞ ከእግር ኳስ ባሻገር ሌሎች የጀርባ ምክንያቶች እንዳሉ ግልፅ ነው"ይላል። እግር ኳስ ማኅበረሰባዊ መሰረት ከሌለው በስተቀር የጠነከረ የእኔነት ስሜት ሊፈጥር አይቻለውም የሚለው መንሱር፤ ይሁንና ክለቦች ከማኅበረሰባዊ መሰረታቸው በዘለለ ብሔር ተኮር መልክን እየተላበሱ የመምጣታቸውን አዝማሚያ "አደገኛ ነው" ይለዋል። "ከአንዳንድ በጥባጭነት እጅግ ወደተደራጀ ነውጠኛነት ሊሄድ ይችላል። ቀስ በቀስ ወደመቧደን እየተሄደ ነው። ራሳችንን መከላከል እና ማዘጋጀት አለብን በሚል ደጋፊዎች ራሳቸውን ማደራጀት ከጀመሩ የሚያሰጋ ዓይነት እውነታ ሊፈጠር ይችላል።" ላለፉት ሁለት ዓመታት መቀሌ ከተማ የእግር ኳስ ክለብን የደገፈውና ባለፈው እሁድ ማለዳ የወልዲያ አመሻሹን ደግሞ የመቀሌ ኹከቶችን የታዘበው ገብረመድህን ኃይለስላሴ በዚህ አስተያየት ይስማማል። "የእኔነቱ መንፈስ ከርሮ ከኳስ ወዳጅነት ወደብሔርተኝነት ነው እየሄደ ያለው፤ ከዚህ ቀደም ብጥብጡ ተጀምሮ የሚያልቀው ስቴዲየም ነው፤ ከዚያ አያልፍም። አሁን አሁን እየታየ ያለው ግን የባሰ ነው" ሲል ለቢቢሲ አስተያየቱን ሰጥቷል። የፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ክለብን የሚደግፈውና የድጋፍ እንቅስቃሴዎችን...\nSummary in the same language as the doc:
የኢትዮጵያ እግር ኳስ በደጋፊዎች መካከል ለሚቀስቀስ ግጭት እና እርሱን ተከትሎ ለሚፈጠር ኹከት ባይተዋር ባይሆንም የቅርብ ጊዜ ክስተቶች ግን ከስፖርትም በዘለለ የአገሪቱን ፖለቲካዊ ነባራዊ መልክ የሚያንፀባርቁ መሆናቸውን ማስተዋል ይቻላል።
amh_Ethi
train
docsummary
GEM/xlsum
amharic
428
Title: በሴኔጋል የጡት እና የማህጸን ጫፍ ካንሰር ህክምና ነጻ ሊደረግ ነው\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
''በውሳኔው በጣም ተደስተናል፤ ምክንያቱም እነዚህ ሁለት የካንሰር አይነቶ ሴቶችን በብዛት እያጠቁ ያሉ ናቸው'' ብለዋል የሴኔጋል ካንሰር መከላከያ ሊግ ፕሬዝደንት የሆኑት ዶክተር ፋትማ ጉዌኖን። • የማላዊ ሴተኛ አዳሪዎች ህይወታችን ተቀይሯል እያሉ ነው • በወር አበባ ምክንያት መምህሯ ያንጓጠጣት ተማሪ ራሷን አጠፋች ከዚህ በተጨማሪ በሌሎች የካንሰር አይነቶች የሚጠቁ ደግሞ ለህክምና ከሚያወጡት ወጪ 60 በመቶ የሚሆነው በመንግሥት እንደሚሸፈን ተገልጿል። እርምጃው ለብዙዎች ምሳሌ መሆን የሚችል እንደሆነና ምናልባትም በሃገሪቱ ያለውን የሞት መጠን ለመቀነስና ድህነትን ለመዋጋት ቁልፍ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አንድ የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ባለሙያው ዶክተር ባራንጎ ፕሬቦ እንደሚሉት እንደ ሩዋንዳ፣ ናሚቢያ እና ሲሸልስ ያሉ የአፍሪካ ሃገራት ከሴኔጋል ቀድመው ይህንን እርምጃ የወሰዱ ቢሆንም አሁንም ለሌሎች ሃገራት ምሳሌ መሆን ትችላለች። ነጻ የጡትና የማህጸን ካንሰር ህክምናው ፕሮግራሙን ለማስጀመር የሴኔጋል መንግስት 1.6 ቢሊየን ዶላር መድቢያለሁ ብሏል። እ.አ.አ. በ2015 ደግሞ የማንኛውም ካንሰር ህክምና 30 በመቶ ወጪ መንግሥት ለመሸፈን ተስማምቶ ነበር። • በ2050 የወባ በሽታ ከዓለማችን ሊጠፋ ይችላል ተባለ • "የሴቶች የንፅህና መጠበቂያን ከቀረጥ ነፃ እናደርጋለን" ዶ/ር አሚር አማን ነገር ግን ካንሰርን በተገቢውና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማከም ብዙ የአፍሪካ ሃገራት ሲቸገሩ ይስተዋላል። የጡት ካንሰርን ለመመርመር የሚረዳው 'ማሞግራም' የተባለው መሳሪያ በሴኔጋል የሚገኙ ሴቶች በቀላሉ ማግኘት የሚችሉበት ሁኔታ መፈጠር እንዳለበት ዶክተር ፋትማ ጉዌኖን ይናገራሉ።
amh_Ethi
train
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
204
ኢሜልዳ ኮርቴዝ የተሰኘችው የ20 ዓመት ወጣት ሴት ብዙ ወሲባዊ በደል በሚያደርስባት እንጀራ አባቷ ተደፍራ ነው ያረገዘችው። መፀዳጃ ቤት ውስጥ ሴት ልጅ ከመገላገሏ በፊት ውርጃ ለማካሄድ ሞክራለች ሲሉ ነው ዶክተሮች ኢሜልዳን የከሰሷት። ሴት ልጇ በመልካም ደህንነት ብትገኝም ኢሜልዳ በፖሊስ ተይዛ ፍርዷን እየተከታተለች ለ18 ወራት ያክል እሥር ቤት ከረመች። • "በምንም ዓይነት መልኩ ሕዝቡን የሚጎዳ ከሆነ ተቀባይነት የለውም" አቃቤ ሕግ ሴቲቱ ስለእርግዝናዋ ለማንም አለመናገሯ፤ ሕክምና አለመከታተሏ እና ውርጃ ለመፈፀም መሞከሯ እስከ 20 ዓመት እሥር የሚያደርስ ጥፋት ነው ሲል ተከራክሯል። ሰኞ ዕለት ችሎት የዋለው የሃገሪቱ ፍርድ ቤት ግን ኢሜልዳ በእንጀሯ አባቷ በተደጋጋሚ በመደፈሯ ምክንያት ነፍሰ-ጡር መሆኗን ሳታውቅ ነው የወለደችው በሚል ነፃ እንድትሆን በይኗል። ጠበቃዎቿ ቀለል ያለ ቅጣት መቀጣት ካለባትም ልጇን ችላ በማለቷ ለአንድ ዓመት ልትቀጣ ይገባል እንጂ 20 ዓመት አይገባትም በማለት ተከራክረው ነበር። ፍርድ ቤቱ ግን ምንም ዓይነት ወንጀል ባለመፈፀሟ ነፃ ናት ሲል ለሃገሪቱ ህዝብ ጆሮ አዲስ እና አስደሳች የሆነ ብይን አሰምቷል። • የቀይ ሽብር ተከሳሹ ሄግ ፍርድ ቤት ቀረበ ኢሜልዳ ነፃ መሆኗን የሰሙ ወዳጅ ዘመዶቿ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ሰዎች መፈክር በመያዝ ፍርድ ቤቱን አጥለቅልቀውት ታይተዋል። አቃቤ ሕግ የ70 ዓመቱ አባቷ በቁጥጥር ሥር ውሎ ፍርዱን እየተከታተለ እንደሆነ አሳውቋል። ኤል-ሳልቫዶር ዓለማችን ላይ ጠንካራ ፀረ-ውርጃ ሕግ ካላቸው ጥቂት ሃገራት አንዷ ነች፤ ምንም ዓይነት የውርጃ ድርጊት ለእሥር ይዳርጋል። ውርጃ ለመፈፀም የሞከሩ ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ ድርጊቱን እያወቁ የደበቁ የሕክምና ባለሙያዎችም ከበ... Continue the article for another 4000 characters max:
ድ ያለ እሥር ሊጠብቃቸው ይችላል። • የፓኪስታን ፍርድ ቤት ሞት የተፈረደባትን ክርስቲያን ነፃ ለቀቀ
amh_Ethi
train
xp3longcontinue
GEM/xlsum
amharic
227
Title: ሁለት ጊዜ በጥይት ተመታ በህይወት የተረፈችው አራስ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
በወላዶች ክፍል ላይ በተሰነዘረው በዚህ ጥቃት እናቶች፣ ጨቅላ ህጻናት እና ነርሶችን ጨምሮ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 24 የደረሰ ሲሆን በርካቶች መቁሰላቸውን የአገሪቱ ጤና ሚንስትር ተናግረዋው ነበር። ከዚህ ጥቃት ቀጥሎ በነበረው ቀንም፤ አንድ የቀብር ሥነ ሥርዓትን ታድመው በነበሩ ሰዎች ላይ አንድ አጥፍቶ ጠፊ እራሱን በቦምብ አጋይቶ ለሌሎች 34 ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል። በፖሊስ አዛዡ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ለተፈጸመው ጥቃት አይኤስ ኃላፊነቱን እውስዳለሁ ብሏል። እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ አካል ባልተገኘለት የሆስፒታሉ ጥቃት ከሞቱት በርካታ ሰዎች ባሻገር በርካቶች ሲቆስሉ አንዲት አራስ በሁለት ጥይት ተመትታ ተርፋለች። እናቶችን ኢላማ ባደረገው በዚህ የካቡል ሆስፒታል ጥቃት 16 ወላዶች ተገድለዋል። ከሟቾቹ መካከል የጨቅላዋ አሚና እናት ትገኝበታለች። ጨቅላዋ አሚና ግን ሁለት ጊዜ በጥይት ብትመታም በህይወት መትረፍ ችላለች። የአሚና አባት የነበረውን ሁኔታ ሲያስታውሱ፤ ታጣቂዎች ሆስፒታሉ ላይ ጥቃት መሰንዘር ሲጀምሩ አሚና ገና መወለዷ ነበር። ታጣቂዎቹ ወደ ሆስፒታሉ ዘልቀው በመግባት እናቶችን ዒላማ አድርገው ሲገድሉ፤ አሚናም ሁለት ጊዜ እግሯ ላይ በጥይት ተመታለች። ዶክተሮች የአሚናን በህይወት መትረፍ "ታዓምራዊ ነገር ነው'' ሲሉ ይገልጹታል። "የተኩስ ድምጽ እየተሰማ እያለ ባለቤቴ 'አጥፍቶ ጠፊ ነው?' ስትል ጠየቀችኝ። እንዳትጨነቅ በማሰብ 'አጥፍቶ ጠፊ አይደለም' አልኳትንና እንድትደበቅ ነገሪያት አንዱን ታጣቂ ተከትዬ ወጣሁ። "ስመለስ አሚናን እንደታቀፈች ተገድላ አገኘኋት" በማለት የጨቅላዋ አባት ራፊኡላ ይናገራል። ባለቤቱ ልቧ ላይ እና አግሯን በጥይት እንደተመታች የሚናገረው ራፊኡላ፤ አዲስ የተወለደችውን ሴት ልጁን ለማዳን በፍጥነት ህክምና እንድታገኝ ለማድረግ መጣሩን ይናገራል። "ባለቤቴን እየቀበርኩ እያለሁ ዶክተሮች ደውለው 'የአሚና እግር መቆረጥ አለበት' አሉኝ እኔም 'እባካችሁ እግሯን አትቁረጡ። እናት የሌላት ጨቅላ ናት። የወደፊት ህይቷን አታክብዱባት' አልኳቸው" ይላል። የተቻላቸውን ለማድረግ ቃል የገቡለት ሃኪሞች ያካሄዱት የቀዶ ህክምና ተሳክቶ የአሚና እግር ሳይቆረጥ ቀርቷል። በተደረገላት ሁለት ተከታታይ የቀዶ ህክምና አሁን ላይ ሃኪሞች አሚና ከፍ ስትል መራመድ እንደምትችል ተስፋ አድርገዋል።
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
268
ኮሮናቫይረስን፡ በአዲሱ የሞባይል ቴክኖሎጂ ላይ የተነዛው ሐሰተኛ ወሬ ጉዳትን አስከተለ\nበማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች በስፋት ሲዘዋወሩ በነበሩ ቪዲዮዎች ላይ እንደታየው ብሪታኒያ ውስጥ በሚገኙት በርሚንግሐምና መርሲሳይድ ከተሞች ውስጥ የሞባይል ግንኙነት ማማዎች በእሳት ሲጋዩ ታይተዋል። ይህንን ተከትሎ የሴራ ንድፈ ሐሳብን በመመርኮዝ ዘመናዊው የአምስተኛው ትውልድ [5ጂ] ቴክኖሎጂ ለኮሮናቫይረስ መሰራጨት ምክንያት ሆኗል የሚለው ክስ በሳይንስ ባለሙያዎች ሐሰት ተብሎ ተወግዟል። አዲሱ ቴክኖሎጂ በሽታውን እያስተላላፈ ነው የሚሉ መላምቶችን የያዙ መልዕክቶች ዕውቅና ባገኙና በመቶ ሺህዎች ተከታይ ባሏቸው የፌስቡክ፣ የዩቲዩብና የኢንስታግራም አካውቶች በኩል ሳይቀር በስፋት ሲሰራጩ ነበር። ነገር ግን ሳይንቲስቶች ይህ በኮቪድ-19 እና በ5ጂ አገልግሎት መካከል አለ የተባለው ግንኙነት "ፍጹም የማይረባ" ከመሆኑ በተጨማሪ ከሥነ ፍጥረት እሳቤ አኳያም ሊሆን የማይችል ነው ሲሉ አጣጥለውታል። የሴራ ንድፈ ሐሳብን የሬዲዮ ሞገዶችን በመጠቀም ለሞባይል ስልክ አገልግሎት የሚውለውን የ5ጂ ቴክኖሎጂ በስፋት እየተሰራጨ ላለው የኮሮናቫይረስ ተጠያቂ በማድረግ ይህንን ሐሰተኛ መረጃ በስፋት እያሰራጩ ያሉት ሰዎች የሴራ ንድፈ ሐሳብን መሰረት አድርገው ነው። ይህ ወሬ መሰራጨት የጀመረው በጥር ወር መጨረሻ አካባቢ የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ታማሚ አሜሪካ ውስጥ በተገኘበት ሰሞን ሲሆን፤ ክስተቱ ከ5ጂ ጋር ግንኙነት እንዳለው በፌስቡክ በኩል ነበር ሲወራ የነበረው። የሚሰራጨውም ወሬ ሁለት ገጽታ የነበረው ሲሆን አንደኛው 5ጂ የተፈጥሮ በሽታን የመከላከያ አቅምን በመቀነስ ሰዎችን ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ ያደርጋል የሚሉ ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ ቫይረሱ በቀጥታ በ5ጂ ቴክኖሎጂ በኩል ይተላለፋል ሲሉ ያልተረጋገጡ መልዕክቶችን በስፋት አሰራጭተዋል። በሬዲንግ ዩኒቨርስቲ የሥነ ህይወት ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክትር ሳይመን ክላርክ ግን እነዚህን ሁለት ሐሳቦች "ሙሉ ለሙሉ የማይረቡ" ሲሉ አጣጥለዋቸዋል። "5ጂ የሰዎችን በሽታን የመከላከል አቅም ይቀንሳል የሚለው ሐሳብም ለንግግር የሚበቃ አይደለም" ይላሉ ዶክተር ክላርክ። "የተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅማችን በተለያዩ ምክንያቶች ዝቅ ሊል ይችላል፤ አንድቀን ሲደክመን ሌላ ጊዜ ደግሞ ጥሩ ምግብ ሳናገኝ ስንቀር መዋዠቁ አይቀርም። ይህም ትልቅ ነው የሚባል ባይሆንም በቫይረሱ ለመያዝ ተጋላጭ ሊያደርግን ይችላል። "በእርግጥ የራዲዮ ሞገዶች ጠንካራ በሚሆኑበት ጊዜ የሰውነታችን በሽታን የመከላከል ሥርዓት በአግባቡ ሥራውን ሊያከናውን አይችልም። ነገር ግን የ5ጂ የራዲዮ ሞገድ በጣም ዝቅተኛ ስለሆነ በሽታን የመከላከል ሥርዓታችንን ሊያስተጓጉል የሚችልበት አቅም የለውም። በዚህም ዙሪያ በርካታ ጥናቶች ተሰርተዋል።" የቫይረሱ ተፈጥሮና ባህሪይ በብሪስቶል ዩኒቨርስቲ የህጻናት ህክምና ፕሪፌሰር የሆኑት አዳም ፊን እንደሚሉት ደግሞ የ5ጂ ቴክኖሎጂ ቫይረሱን ያስተላልፋል የሚባለው ነገር ፈጽሞ የማይሆን ነገር እንደሆነ ተናግረዋል። "ኮሮናቫይረስ ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው የሚተላለፍ መሆኑ ይታወቃል። ቫይረስና ለሞባይል እንዲሁም ለኢንትርኔት ግንኙነት የሚያገለግለው ኤሌክትሮማግኔቲክ ሞገድ በአሰራራቸው የተለያዩ ነገሮች ናቸው" ብለዋል። ከ5ጂ ቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ የሚወራው ነገር ትክክል እንዳልሆነ እንደማሳያነት ከተጠቀሱት ምሳሌዎች መካከል፤ በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የኮሮናቫይረስ በስፋት የተሰራጨባቸው ከተሞች ገና የ5ጂ አገልግሎትን ያላገኙ ናቸው። በተጨማሪም በበሽታው ክፉኛ ከተጠቁት አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢራን ቴክኖሎጂውን ሥራ ላይ ለማዋል ገና ጥረት እያደረገች ነው። የ5ጂ ቴክኖሎጂን በተመለከተ የኮሮናቫይረስ ከመምጣቱ ቀደም ብሎ...\n\ntl;dr:
የሞባይል ስልክ አገልግሎትን ፈጣንና ዘመናዊ ያደርገዋል ተብሎ የታመነበት የአምስተኛው ትውልድ [5ጂ] ቴክኖሎጂ የኮሮናቫይረስን እያሰራጨ ነው በሚል በተናፈሰው ወሬ ምክንያት በንብረት ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው።
amh_Ethi
train
tldr
GEM/xlsum
amharic
406
Title: በቫይረሱ ምክንያት በቤት እስር የቆየው የቀድሞ የትራምፕ ጠበቃ እስር ቤት ተመለሰ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር በተያያዘ ህጋዊ ያልሆነ ክፍያ ፈፅሟል በሚል የሶስት አመት እስር ተፈርዶበት ያለው ማይክል ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ስጋት በግንቦት ወር ተለቆ በቤቱ እንዲወሰን ትዕዛዝ ተላልፎለት ነበር። ባለስልጣናቱ እንዳሉት ጠበቃው የቤት እስሩን ሁኔታዎች በመጣሱ ወደ እስር ቤት እንዲመለስ ተደርጓል ብለዋል። የማይክል ኮኸን ጠበቃ ጄፍሪ ሌቪን በበኩሉ ደንበኛው ለተለያዩ ሚዲያዎች ቃለ መጠይቅ መስጠትም ሆነ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መፃፍ ተከልክሎ ነበር ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ ከሰሞኑም ከባለቤቱና ከባልና ሚስት ጓደኞቹ ጋር ማንሃተን በሚገኝ ሬስቶራንት ውስጥ እራት ሲበላ መታየቱ ጋር ተያይዞም ነው በቤት መወሰኑን መመሪያ ተላልፎ ወደ እስር ቤት እንዲመለስ የተወሰነው። ማይክል የነበረበት እስር ቤት በርካታ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎም ነበር በቤቱ እንዲቀመጥ የተወሰነው በትናንትናው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርቦም ውሳኔው እንዲቀለበስና በቤቱ ውስጥ የመወሰን ሁኔታ እንዲከበርለትም ለማድረግ እንደሞከረም ተዘግቧል። ከፈደራል እስር ቤቶች ቢሮ የወጣው መግለጫው እንደሚያትተው "በቤት ውስጥ እንዲወሰን ትዕዛዝ ቢተላለፍለትም ይህንን ስለጣሰ ወደ እስር ቤት እንዲመለስ አድርገናል" ይላል። የማይክል ጠበቃ በበኩሉ ውጭ ወጥቶ ሬስቶራንት ምግብ የመብላቱን ሁኔታ ምንም መመሪያ የሚጥስ አይደለም ብሎ የተከላከለ ሲሆን ለሚዲያዎች አትናገር ብሎ መከልከሉም የደንበኛውን መብት የሚጥስ ነው ብሏል። የአምሳ ሶስት አመቱ ማይክል ከሶስት አመታት በፊት በነበረው ሩሲያ በአሜሪካ ምርጫ ላይ ጣልቃ መግባት አለመግባቷን በሚመረምረው አካል ባደረገው ማጣራት የትራምፕ የምርጫ ዘመቻ እንዳይበላሽ በሚል ከፕሬዚዳንቱ ጋር ወሲባዊ ግንኙነት አላቸው የሚባሉ ሁለት ሴቶችን ዝም ለማስባል ክፍያ መፈፀሙ ተገልጿል። እንዲሁም ከፕሬዚዳንቱ ጋር ግንኙነት የሌላቸው የግብርና የባንክ ማጭበርበር ተግባራትን ፈፅሟል በሚልም ነው ለእስር የተዳረገው።
amh_Ethi
test
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
233
Doc to summarize: "ሳሊ፣ ሳሊ፣ ሳሊ፤ ሰላማዊት" - ድምፃቸው በተራራው መካከል ይሰማል። የገደል ማሚቶው ድምፅም ሳሊ፣ ሰላማዊት እያለ በከፍተኛ ድምፅ ያስተጋባዋል። ተራራውም ስሟን መልሶ የሚጣራ ይመስላል። እነዚህ ሴቶች ማን ናቸው? ስሟን የሚጠሯትስ ሳሊ ወይም ሰላማዊትስ? በእድሜ ጠና ያሉት እነዚህ ሴቶች ክብረ፣ መንቢ፣ ብሩክታዊትና ፅዮን ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓን) የትጥቅ ትግል ተቀላቅላ ከአርባ አመት በፊት የጠፋችው እህታቸውን ሳሊ (ሰላማዊት ዳዊትን) ስም ነው የሚጠሩት። ከአስርታት በፊት አቆላምጠው እንደሚጠሯት ሳሊ፣ ሳሊ፤ ሰላማዊት ይላሉ። ትግራይ ውስጥ የምትገኘው የአሲምባ ተራራ የወጣቶቹ የፅናትና ቆራጥነት ተምሳሌት፣ የአኬልዳማ መሬት፤ የህልም መነሻና መቀበሪያ፤ ታጋዮችን ውጣ ያስቀረች። "ቢወቀጥ አጥንቴ ቢንቆረቆር ደሜ፤ ለአዲስ ሥርዓት ልምላሜ፤ ፍጹም ነው እምነቴ፤ ትግሉ ነው ሕይወቴ" ብሎ ያ ትውልድ የዘመረባት ቦታ ናት። የአሲምባዋ ታጋይ ሳሊ የሕዝብን ትግል ትግሌ ብላ፣ ለሕዝብ የማንነት ጥያቄ ምላሽ፣ በጭቆና ለሚማቅቀው የነፃነትን ወጋገን ለማሳየት፣ በእራፊ ጨርቅ እጦት፣ በድህነት አለንጋ ለሚገረፈው፣ ጉርሱን ላጣው የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በቤታቸው በወጡበት ካልተመለሱት መካከል አንዷ ናት። በዚህች ተራራማ ስፍራ መሸገው የነበሩ የዚያ ትውልድ የኢሕአፓ አባላትም በመንፈስ እየሰሙ ይሆናል - የእህትማማቾቹን ጥሪ። ከአራት አስርት ዓመታት በኋላ በአሲምባ ተራራ ስር ያለችው የገጠር መንደር፣ በድንጋይ የተሰሩ ህድሞ ቤቶች፣ ጋቢያቸውን ደረብ አድርገው የሚመለከቱ አዛውንት፣ ነጠላቸውን የደረቡ እናቶች፣ በአቧራማው ሜዳ ላይ ኳስ የሚጫወቱ ህፃናትም የሳሊንና የሌሎቹን መስዋዕትነት ያወሱት ይሆን? ለነፃነት ቆርጣ በረሃ የገባችው ሳሊ (ሰላማዊት) ፈገግታ የማይለያትና 'ቀይዋ' በሚል መለዮ ነበር የአካባቢው ነዋሪዎች የሚያውቋት። ልክ እንደ ኢሕአፓ ጓዶቿ ፖለቲካዊ ትምህርት ከመስጠትም ባለፈ ለሴቶች ድጋፍ በማድረግ የታመሙትን በማከም 'ነርሷ' የሚል የቅፅል ስምም አትርፋ ነበር። ለቤተሰቦቿስ? ሳሊ ፈገግታ የማይለያት፣ ሳቂታ፣ ለመቅረብ ቀለል ያለች፣ በጣም ጎበዝ፣ ውይይት የምትወድ፣ ፓርቲ የምታዘወትር፤ ፀጉሯንና ጥፍሯን ተሰርታም ዝንጥ ብላ መውጣትም ትወድ ነበረች። ይህ ግን ትግሉን ከመቀላቀሏ በፊት ነበር። ትግሉን ከተቀላቀለች በኋላስ? የፀረ-ኢምፔሪያሊዝም አቋሟ፣ የማኅበራዊ ፍትህ ጥያቄዋ፣ ደርግን እጥላለሁ ብላ ወደ ትጥቅ ትግል መግባቷ በቤተሰቡ ውስጥ የሚወራም አይደለም፤ ተዳፍኖ የቀረና የማይነሳ ጉዳይ ነው። የሳሊ ደብዛ መጥፋት ለቤተሰቧ ጠልቆ የሚሰማ ህመም ያለው የማይድን ቁስል ነው። የእህታቸውን ትዝታ ተመልሶ መፈለግ የማይሽር የዘመን ጠባሳ መመልከትና በርካቶች መስማት የማይፈልጉትን በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የጨለማ ጊዜንም መመልከት ነው። ስለዚህ ትግሉም አይነሳም፤ ሳሊም አትወሳም። ለቤተሰቡ ህመም የሆነው የሳሊ የትግል ታሪክም መቀበር ለወንድሟ ልጅ ታማራ ማርያም ዳዊት፤ ሳሊ የምትባል አክስት እንደነበረቻት ይቅርና እስከነ መፈጠሯ እንዳታውቅ ምክንያት የሆናት። በ30ዎቹም እድሜ ላይ ሆና ነው ሳሊ (ሰላማዊት) የምትባል አክስት እንዳለቻት፣ የኢህአፓ ታጋይ እንደነበረች የተረዳችው። የአክስቷን ታሪክ፣ ማንነት ፍለጋ በዝምታ የተሸበበውን የቤተሰቡን ምስጢራዊ መጋረጃንም 'ፋይንዲንግ ሳሊ' [ሳሊን ፍለጋ] በሚለው ፊልሟ ታሳያለች። ካናዳ ተወልዳ ያደገችው ታማራ ስለ አፄ ኃይለ ሥላሴ ከስልጣን መገርሰስ፣ የተማሪዎች እንቅስቃሴ፣ የቀይ ሽብር ጭፍጨፋዎች ብትሰማም ከእሷ ቤተሰብ ጋር ግንኙነት አለውም ብላ አልጠረጠችም። ነገር ግን ይህ...\nSummary in the same language as the doc:
አራት ሴቶች መስዋዕትነት በተከፈለባት በአሲምባ ኮረብታ ላይ ጮክ ብለው ይጣራሉ።
amh_Ethi
train
docsummary
GEM/xlsum
amharic
405
Title: በሶማሊያ አልሽባብ ምግብ ቤት ላይ ባደረሰው ጥቃት ስድስት ሰዎች ተገደሉ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
በሌላም በኩል በዋና መዲናዋ ሞቃዲሾ ወደብ አቅራቢያ በአጥፍቶ ጠፊ በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት ቢያንስ ሰባት ሰዎች ቆስለዋል። እስላማዊ ታጣቂ ቡድኑ አልሽባብ ከሁለቱም ጥቃቶች ጀርባ እንዳለ ተናግሯል። ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎቹ በባይዶአ ምግብ ቤቱ ውስጥ ስብሰባ እያካሄዱ የነበሩ ግብር ሰብሳቢዎችና ወታደሮችን ኢላማ አድርገው እንደነበር ተናግረዋል። በጥቃቱ ሁለት ወታደሮች መገደላቸውን ታጣቂ ቡድኑ ቢያስታውቅም ባለሥልጣናት ግን ሁሉም ተጎጂዎች ሰላማዊ ናቸው ብሏል። የሞቃዲሾ ባለሥልጣናት ቦምብ የተጠመደበት መኪና በፍተሻ ጣቢያው ላይ አልቆም ሲል ተኩስ ከፍተው እንደነበር ለቢቢሲ ገልፀዋል። አጥፍቶ ጠፊው መኪናውን እያሽከረከረ ከወደቡ ፊት ለፊት ያለውን ፖሊስ ጣቢያ ለመምታት ቢሞክርም የፀጥታ አካላት እንደተኮሱበትና ከዚያም ተሽከርካሪው እንደፈነዳ አክለዋል። በዚህም ሁለት ፖሊሶችና በአካባቢው ሲተላለፉ የነበሩ አምስት ሰላማዊ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። አንድ የወደቡ ሰራተኛ “በወደቡ ውስጥ የእንጨትና የብረት ቁርጥራጮች በሁላችንም ላይ ወደቁብን፤ ከዚያም ተኩስ ሰማን” ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ለሮይተርስ ተናግረዋል። በአሜሪካ የሚደገፈው የሶማሊያ መንግሥት ላለፉት አስር ዓመታት አገሪቷን ለመቆጣጠር ከአልሽባብ ጋር እየተፋለመ ይገኛል።
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
156
Title: ከ43 ዓመት በኋላ የተገናኙት ኢትዮጵያዊ እናትና ስዊድናዊ ልጅ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ሀሊማ ሀሰን እና ማንስ ክላውዘን ከ43 ዓመት በኋላ ሲገናኙ ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ፣ ስድስት ኪሎ አካባቢ ማንስ የልጅነት ልጄ ነው። በእኔና በአባቱ መካከል ችግር ነበር። ሥራ ፈቶ የሚረዱት አባቱ ነበሩ። ቤተሰቦቼ የልጆቼን አባት ስላልወደዱት ተጣልተን ነበር። ሲቸግረኝም ወደ ቤተሰቦቼ ለመመለስ አፍሬ ብቻዬን ተጋፈጥኩ። ማንስን አርግዤ የእለት ጉርስና አንገት ማስገቢያ አጣሁ። ሀሰንን አዝዬ ማንስን በሆዴ ይዤ በጣም የምቀርባቸው ጓደኞቼ ቤት አድር ጀመር። ዛሬ አንዷ ጋር፤ ትንሽ ቀን ሌላዋ ጋር አሳልፍ ነበር። ከነችግሩ እርግዝናዬ እየገፋ መጣ. . . ሁለት ወር፣ አምስት ወር. . . ስምንት ወር. . . እንደቸገረኝ መውለጃዬ ደረሰ። ምጤ የመጣው እንኳን ለሰው ለእንስሳም የማይመች ቦታ ነበር። ሰው ከማጣቴ የተነሳ ሆስፒታል የሚወስደኝ አልነበረም። ጠዋት 12 ሰዓት ምጥ የጀመረኝ እስከ ምሽት 12 ሰዓት ብቻዬን አምጬ ቤት ውስጥ ወለድኩ። • የፍስሀ ተገኝ የቤተሰብ ፍለጋ ጉዞ ስወልድ እትብት የሚያትብ ሰው እንኳን ጠፋ። ልጄን በልብሴ ታቅፌ ደሜ ላይ ቁጭ አልኩ። የገዛ ደሜን በእጄ አፈስኩ። ምን ልብላ? ምን ልጠጣ? ለእግዚአብሔር ያሉ ሰዎች ቡና አፍልተው ባዶ ቡና ቁርስ ሰጡኝ። የነበርኩበት ቦታ ከራስጌዬ እሳት ይነድ ነበር። ለመኖር አይመችም። የልጆቼን አባት እህት 'እባክሽ ከዚህ ቦታ አንሽኝ፤ ወይ ውጪ ልውደቅና ዘመድም ይስማኝ' ብዬ ሳለቅስባት ቀበና አካባቢ ያለ ቤታቸው ውስጥ አንድ ክፍል ይሰጣት ብላ አዘዘች። ወቅቱ ዝናብ ነበር። የሦስት ቀን አራስ ሆኜ በታክሲ ወደቤታቸው ወሰዱኝ። የልጆቼ አባት፣ አባቱ ብር ሲሰጡት ወይ ያመጣዋል ወይ ይጠጣበታል። አንዳንዴ እንደ እብድ ሆኖ ይመጣል። ሦስት ዓመት ከእሱ ጋር ስቀመጥ የነበረኝ የሦስት ወር ፍቅር ብቻ እንጂ ስለ ሕይወት የማውቀው ነገር የለም። እህቱ ቤት እያለሁ ሲሰጡኝ መብላት ካጣሁኝም መተው. . . አቤት የልጆቼ ስቃይ. . . እንደ ውሻ ደረቅ ጡቴን ጎትቼ ልጄን አጠባ ነበር። የልጆቼ አባት ከእህቶቹ ጋር አልተስማማም፤ ከእኔጋም ተለያየን። ከዚያ አንድ የወታደር ጊቢ ውስጥ ተከራየሁ። አንድ ቀን ልጆቼን በጣም ሲያምብኝ የካቲት 12 ሆስፒታል ወሰድኳቸው። በሰው በሰው የማውቀው ጆንሰን የሚባል ዶክተርን አገኘሁ። ልጆቼን ሳሳክም 'መንታ ናቸው?' አለኝ። በተቀራራቢ ጊዜ ስለተወለዱ ነው እንጂ መንታ አይደሉም አልኩት። በዚያው እንዲህ ሆኜ፣ እንዲህ ሆኜ እያልኩ ችግሬን ነገርኩት። 'ልጆችሽ በምንም አይነት አያድጉም፤ ከሚሞቱብሽ ጥሩ ቦታ [በማደጎ] ይሂዱ' ብሎ አምስት ኪሎ ማርኪ የምትባል ስዊድናዊት ጋር እንድሄድ መከረኝ። ቢሮዋ ሄድኩ። ባለቤቷ ኢትዮጵያዊ ነበር። ተቀበለችኝና ለህጻናቱ የታሸገ ጡጦ፣ ወተትና ለታክሲ ብላ 20 ብር ሰጠችኝ። በዚያ ጊዜ 20 ብር ትልቅ ነው። 'ልጆቹ የጤና ምርመራ ያስፈልጋቸዋል' ስላለችኝ ለሁለቱም ምርመራውን ጀመርኩ። ትልቁ ልጄ ቶሎ በእግሩ አልሄደም ነበር። ራጅ ላይ 'ልቡ ትልቅ ሆኗል፤ ሌላ ሆስፒታል ይታይ' ተባለ። ሌላ ሆስፒታል ሲታይ ደግሞ ጤናማ ነው አሉ። የማንስ ምርመራ ግን ፈጠኖ አለቀለት። ማንስ 'ጡትሽን እንዲተው የህጻናት ማቆያ ይግባ' ተባለ። ከዚያ ፍርድ ቤት ለመቅረብ ቀጠሮ ተሰጠኝ። አንድ የማርኪ ተወካይ 'ሁለቱም እኮ አይሄዱም' አለኝ። ተናድጄ 'ሁለቱም እኮ እቃ አይደሉም! ስለቸገረኝ ነው እንጂ ሁለቱም እንዲሄዱ ፍቃደኛ አይደለሁም' አልኩ። ፍርድ ቤት ወሰደኝና 'ለ18 ዓመት' ብለው አስፈረሙኝ። በወቅቱ አባቴ በጣም ታመው ሆስፒታል ነበሩ። ትንሽ ቆይተው አረፉ። ልጄ 'ጡት እንዲተው' ሰባ ደረጃ አካባቢ ያለ ማቆያ ያስገባሁት አባቴ ከማረፋቸው ከአንድ ሳምንት በፊት ነበር። የአባቴን ለቅሶ...
amh_Ethi
train
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
455
Title: በእዳ ተይዞ የነበረው ብቸኛው የዚምባብዌ አውሮፕላን በረራ ጀመረ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ኤይር ዚምባብዌ በአንድ አውሮፕላን ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ብቸኛ መዳረሻውም ጆሃንስበርግ ከተማ ነው ይህ ብቸኛ አውሮፕላን ወደ ደቡብ አፍሪካ፣ ጆሃንስበርግ በረራ ካደረገ በኋላ ነበር ለደቡብ አፍሪካ መንግሥት መክፈል የነበረበትን እዳ እስኪከፈል ተይዞ የቆየው። የዚምባብዌ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ኤይር ዚምባብዌ፤ በጆሃንስበርግ አየር ማረፊያ የአገልግሎት ክፍያዎች ውዝፍ እዳ አለበት ተብሏል። አየር መንገዱ ያለበት የዕዳ መጠን እና አውሮፕላኑን ነጻ ለማውጣት ምን ያክል ክፍያ እንደፈጸም አልተገለጸም። • የዝሆን ግልገሎች ለዓለም ንግድ እንዳይቀርቡ ታገደ • የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ አረፉ • ዚምባብዌ እንዴት ሰነበተች? ባለቤትነቱ የዚምባብዌ መንግሥት የሆነው ኤይር ዚምባብዌ፤ በአንድ አውሮፕላን ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ብቸኛ መዳረሻውም ጆሃንስበርግ ከተማ ነው። "በረራችንን ዛሬ ጀምረናል። አውሮፕላኑ ዛሬ ጠዋት ወደ ጆህንስበርግ በረራ አድርጓል" ሲሉ የኤይር ዚምባብዌ ኮርፖሬት አግልግሎቶች ኃላፊ የሆኑት ታፋደዘዋ ማንዶዜ ለሄርልድ ኒውስ ተናግረዋል። "በረራ ለማድረግ የሚያስፈልገንን ፍቃድ አግኝተናል። የሚጠበቅብንን ክፍያዎችም ፈጽመናል" ብለዋል። ኤይር ዚምባብዌ እአአ 2017 ላይ በተከማቸበት ከፍተኛ ውዝፍ እዳ ከግማሽ በላይ ሠራተኞቹን ለማሰናበት ተገዶ ነበር። ይህም ብቻ ሳይሆን ኤይር ዚምባብዌ በደህንነት ስጋት ምክንያት በአውሮፓ አገራት አየር ክልል የመብረር ፍቃድ የለውም።
amh_Ethi
train
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
178
ቤትሆቨን በሙዚቃው መጠበቡ ብቻ ሳይሆን ብዙዎችን የሚያስደንቀው ከ28 ዓመቱ በኋላ የመስማት ችገር አጋጥሞት 44 ዓመቱም ላይ ሙሉ በሙሉ መስማት አይችልም ነበር። መስማት ሳይችል እንዴት ሙዚቃን አቀናበረ? የሚለው ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኗል። ብዙዎችም በህይወት የሚያጋጥም ተቃርኖ ይሉታል። በካናዳ ውስጥ ታዋቂ የምግብ አብሳይ (ሼፍ) የሆነችው ጆሽና ማሃራጅም ይሄው ተቃርኖ ሊባል የሚችል ጉዳይ ገጥሟታል። ለአምስት ዓመታትም ያህል የማሸተትም ሆነ የመቅመስ ስሜቷን እንዳጣችም ከወራት በፊት ይፋ አድርጋለች። •"ሞትን ተሻገርኳት" ከኮሮናቫይረስ ያገገመች ሴት •በኮሮናቫይረስ ከተቀጠፉ ኢትዮጵያውያን መካከል ጥቂቶቹ ያጣችውንም የስሜት ህዋሷን ለመመለስ እንዲሁ እየደከመች ነው። በመጀመሪያ ያጣችው የማሽተት ስሜቷን ሲሆን እንዲሁ በአንድ ሌሊት አይደለም። ቀስ በቀስ ነበር። በመጀመሪያው ላይ ምግብ ማሳረር ጀመረች፤ የኮክ ኬክ እየጋገረች፣ ቀምበር ማለት ቢኖርበትም ማሽተት ባለመቻሏ አሮ ወጣ። "አንዳንዴ ያረረውን ቆርሶ ማቅረብ ይቻል ይሆናል። በዚህ ወቅት ግን ሙሉ በሙሉ በማረሩ ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ተጣለ" ትላለች። በሌላ አጋጣሚም እንዲሁ ከጓደኞቿ ጋር ታዋቂ የሥጋ ጥብስ የሚሸጥበት ሬስቶራንት እያለፉ፤ ጓደኞቿ በሥጋው ጥብስ መዓዛ ሲደመሙ እሷ ግን ምንም ማሽተት አልቻለችም። "መጀመሪያ አልገባኝም ነበር ችግሩ፤ በኋላም ሁኔታዎችን ስከታተል፤ አፍንጫዬ ማሽተት አይችልም የሚለው ተገለፀልኝ" ትላለች። "እውነቱን ለመናገር በወቅቱ መንፈሴ በሙሉ ነው የተረበሸው። ማሽተት ሳልችል እንዴት ሼፍ እሆናለሁ የሚለውም ያስጨንቀኝ ጀመር። ሥራዬን ላቁመው የሚለውም ሃሳብ ይመላለስብኝ ነበር" ትላለች። ሆኖም የሆዷን በሆዷ ለማድረግ ወሰነች "ምስጢርሽን ትደብቂያለሽ፤ ማን... Continue the article for another 4000 characters max:
ም ቢሆን መስማት የለበትም" በማለትም ከእራሷ ጋር ንግግር አድርጋ ወሰነች። ቶሮንቶ ተወልዳ ያደገችው ጆሽና፤ የሥርዓተ ምግብ መብት አቀንቃኝ፣ ደራሲ ስትሆን በዓለም ላይ ካሉ ታዋቂ የሕዝብ ተቋማት፣ ዩኒቨርስቲዎችና ሆስፒታሎች ምግብ በምን መንገድ ማብሰል እንዳለባቸውና ለአቀራረቡም የተለየ እሳቤ በማምጣት ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ችላለች ይሏታል። በአሁኑ ወቅት ግን 'አኖሶሚያ' በሚባል በሸታ ተጠቅታለች፤ በሸታው ሙሉ በሙሉ የማሽተት የስሜት ህዋስን የሚያጠፋ ነው። በዓመታት ውስጥ ምግብ መድረስ አለመድረሱን በሽታ መለየት ትችል የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ ወደ ሰዓት መሙላትና የቅመም መጠናቸው ከፍተኛ ወደሚባሉ ምግቦችም ተሸጋገረች። ጠንካራና ሸታ ያላቸውን ቅመሞች መጨመር፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ዝንጅብል እንዲሁም በቅመም ያበደውን የህንዱን ከሪ ማብሰል ጀመረች። የማሽተትና የመቅመስ ስሜት ጠንካራ ግንኙነት መኖሩን ተከትሎ የመቅመስ ስሜቷንም ያጣችው ወዲያው ነው። አኖሶሚያ የሚባለው ህመም በተለያዩ ምክንያቶች ይመጣል፤ በቀላሉ በቫይረስ ከመጠቃት ጀምሮ እስከ ከፍተኛው የአዕምሮ ጉዳት አኖሶሚያን ያስከትላል። በቅርቡም ተመራማሪዎች የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ውስጥ ብለው ከጠቀሷቸው ውስጥ የመቅመስና የማሽተት ስሜትን ማጣት ይገኙበታል። ጆሽና ማሃራጅም ለዓመታት ያህል በሳይነስ አለርጂ ትሰቃይ ነበር፤ በተደጋጋሚም ከአንገቷ በላይ ባለው የመተንፈሻ አካሏ ችግርም መፍትሄ ልታገኝለት አልቻለችም ነበር። አፍንጫዋም ስለሚታፈን መተንፈስም ከባድ ነበር። "ያልሞከርኩት አይነት ህክምና የለም። የቻይና የአገር በቀል መድኃኒት፣ ምግብ መቀየር፣ አኩፓንክቸር እንዲሁም በተደጋጋሚ በአፍንጫ የሚወሰድ መድኃኒት ወስጃለሁ" ትላለች። በባለፈው ዓመትም ይህንኑ ለማስተካከል ቀዶ ጥገና አድርጋ በወራት ውስጥም የማሽተት ስሜቷ ትንሽ ተመለሰ። የህንዷን ባንጋሎር ግዛት እየጎበኘች ባለችበት ወቅት ድንገት የማንጎ ሽታ ሸተታት፤ ራሷን ተጠራጠረች። ሆቴሏም ስትመለስ በእንግዳ መቀበያው አካባቢ የአበባ ሽታ ሸተታት። ሆኖም በሚያሳዝን ሁኔታ ማሽተትም ሆነ መቅመስ የቻለችው ለሁለት ሳምንታት ብቻ ነበር። በተለይም ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ ክሮሺያ በሄደችበት ወቅት ሁኔታው በጣም ከብዷት ነበር። ቤተሰቧ ጋር የተለያዩ ሬስቶራንቶች ሄደው የምግቡን ጣዕም ሲያመሰግኑ፣ በምግብ ሽታ ሲደመሙ ለእሷ ግን ሁሉ ነገር ባዶ ነበር። ያልናፈቀችው አይነት ሽታ የለም። ነጭ ሸንኩርት፣ ዝንጅብል ቁሌት፣ የአራስ ልጅ ሽታ... "ጓደኛዬ ከወራት በፊት ስትወልድ ፊቴን አስጠግቼ ጨቅላውን ለማሽተት ሞከርኩ። ምንም ነገር አልሸተተኝም። በጣም ነው ልቤ የተሰበረው፤ ሐዘኔ ጥልቅ ነው" ትላለች። ይባስ ብሎ ማሸተት ከተለያዩ የሰው ልጅ ስሜቶች ጋር ግንኙነት እንዳለው አንድ ጓደኛዋ ነግሯት ጠለቅ ብላም የተለያዩ ምርምሮችን ማንበብ ጀመረች። የማሽተት ስሜት ማጣት ለድብርት፣ ጭንቀት እንደሚያጋልጥም መረጃዎችን አገኘች። ይህንኑም ተከትሎ ስለህመሟ ለሌሎች ሰዎችም መናገር እንዳለባትና መፍትሔም መፈለግ እንዳለባት ተረዳች። በኢንስታግራም ገጿም ላይ ስለ ችግሯ ፃፈች። በመቀጠልም እንደ አዲስ የማሽተት ስልጠናንም መውሰድ ጀመረች፤ አዕምሮዋንና አፍንጫዋን የሚያገናኘውንም መስመር ለመጠገንም ህክምና እንደገና ጀመረች። በለንደን ተቀማጭነቱን ያደረገና የሽታና የመቅመስ ስሜታቸውን ላጡ እንደገና የሚመልሱበትን፤ እንዲሁም ግንዛቤ በማዳበር ላይ የሚሰራ 'አብሰንት' የሚባል ድርጅትም አገኘች። በዓለም ላይ 5 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ የማሽተት ስሜት በማጣት እንደሚሰቃይ መረጃዎች ይጠቁማሉ። "የተለያየ ምግብ መብላትና መጠጥ መጠጣት ለሚወዱ፤ ማብሰልን ለሚናፍቁ ሰዎች...
amh_Ethi
train
xp3longcontinue
GEM/xlsum
amharic
573
Title: ፈረንሳይ፡ ቻርሊ ሄብዶ መፅሄት አወዛጋቢውን የነብዩ መሐመድ ካርቱንን እንደገና አተመ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
የሽብር ጥቃቱን በዋነኝነት ያቀነባበሩት ሁለት ፅንፈኛ አክራሪዎችና እነሱንም በመርዳት አስራ አራት ግለሰቦች የፍርድ ሂደት በነገው እለት የሚጀመር ይሆናል። የመፅሄቷ ጋዜጠኞች ስብሰባ ላይ እያሉ በተሰነዘረው ጥቃት ታዋቂ ካርቱኒስቶችን ጨምሮ አስራ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። በዚያኑ ቀንም እንዲሁ በፓሪስ በደረሰ ሌላ ጥቃት አምስት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ይህንንም ተከትሎ ፀረ- ጂሃድ ተቃውሞዎች ፈረንሳይን አጥለቅልቀዋት ነበር። መፅሄቱ በፊት ገፁ ላይ በአሁኑ ወቅት ይዞት የወጣው የነብዩ መሃመድን የሚወክል አስራ ሁለት ካርቱኖችን ናቸው። እነዚህ ካርቱኖች በቻርሊ ሄብዶ መፅሄት ላይ ከመውጣታቸው በፊት አንድ የዴንማርክ ጋዜጣ ነበር መጀመሪያ ይዞት የወጣው። በአንደኛው ካርቱንም ላይ ነብዩ መሃመድ በተርባን ጥምጥም ፈንታ ቦምብ ጭንቅላታቸው ላይ ይታያል። በፈረንሳይኛም "ይሄ ሁሉ የደረሰው ለዚህ ነበር" የሚልም መልዕከትን አስፍሯል። መፅሄቱ በርዕሰ አንቀፁም ላይ እንዳሰፈረው ከአምስት አመት በፊት የደረሰውን ጥቃት ተከትሎም የነብዩ መሐመድን ተመሳሳይ ካርቱን እንዲያትሙ ከፍተኛ ጥያቄ እንደቀረበላቸው ነው። "ተመሳሳይ ካርቱኖች እንድናትም ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖርም ፈቃደኛ አልነበርም። ህጉ ቢፈቅድልንም ምክንያት አልነበረንም። በአሁኑ ሰዓት ግን ጥቃቱን ያደረሱት ግለሰቦች የፍርድ ሂደት በሚጀመርበት ሳምንት መሆኑ እንደገና ማተሙ ትርጉም አለው" በማለት አስፍሯል። በፍርድ ሂደቱ ምን ይጠበቃል? የቻርሊ ሄብዶ የፓሪስ ቅርንጫፎቹን ጨምሮ፣ በአይሁዶች ባለቤትነት የሚገኝ መደብር ጥቃት ደርሶባቸዋል። አንድ ፖሊስ እንዲሁ የሽብር ጥቃቱ ኢላማ ሆኗል። ሶስቱ ተጠርጣሪዎች በሌሉበት ጉዳያቸው የሚታይ ሲሆን ወደ ሶሪያና ኢራቅ ሳይሄዱም አልቀሩም ተብሏል። በፍርድ ሂደቱ ላይ ከጥቃቱ የተረፉትን ጨምሮ፣ ወዳጅ ዘመድ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ 200 የሚጠጉ ምስክሮች እንደሚሰሙበትም የፈረንሳዩ አርኤፍአይ ዘግቧል። ፍርዱ መጋቢት ላይ ይጀመራል ተብሎ ዕቅድ ተይዞለት የነበረ ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተራዝሟል። ሂደቱም እስከ ህዳር ድረስ ይቆያል ተብሏል። ቧልት ቀመስ የሆነው ቻርሊ ሄብዶ በቀኝ አክራሪዎች ላይ በመዘባበት በርካታ ስራዎችን የሚያቀርብ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በካቶሊክ፣ ይሁዲና እስልምና እምነቶችም ላይ ፌዝና ቀልድ ማቅረቡ አወዛጋቢ አድርጎታል። ሆኖም ነብዩ መሃመድን በካርቱን ማሳየታቸው በተደጋጋሚ የሽብር ጥቃት ኢላማ አድርጓቸዋል። መፅሄቱም ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ነው በሚል ካርቱኑን ደግፎ አዘጋጁ ስቴፈን ቻርቦኒየር (ቻርብ) ተከራክሯል " ሙስሊሞች በስዕላችን ስላልሳቁ ምንም አልላቸውም። እኔ የምኖረው በቁርዓን ህግ ስር ሳይሆን በፈረንሳይ ህግ ነው" በማለት በ2012 መናገሩንም አሶሺየትድ ፕሬስ አስነብቦ ነበር። በ2015 ጥቃት በኋላም በርካቶች " እኔ ቻርሊ ነኝ" በሚልም ለመፅሄቱ ያላቸውን ድጋፍ አሳይተዋል። በአወዛጋቢነቱና በቆስቋሽነቱ በአለም የገነነው መፅሄቱም የሌሎችን እምነት እንዲያከብርም ከፍተኛ ትችት እንደደረሰበትም የጋዜጣው ስራ አስኪያጅ ጄራርድ ቢያር ለቢቢሲ ጥቃቱ ከደረሰ ከአመት በኋላ ተናግረው ነበር።
amh_Ethi
train
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
349
አንድ የ83 ዓመት ሰው አፈናውን እንደፈጸመ የተጠረጠረ ሲሆን፤ ሴትየዋ ገና የ13 ዓመት ታዳጊ እያለች ነበር በግዳጅ ወደ ዋሻው ያመጣት። ሴትየዋ እንደገለጸችው በልጅነት እድሜዋ በመንፈስ የተሞላ እንደሆነ አሳምኗት ቆይቶ ነበር። ለብዙ ዓመታትም በምሽት ወደ ቤቱ እየወሰደ ጾታዊ ጥቃት ይፈጽምባት እንደነበርም ተናግራለች። በአካባቢው የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ሰውዬው ሃይማኖታዊ ፈውስ የሚሰጥና የባህላዊ ህክምና ባለሙያ መሆኑን እየዘገቡ ነው። •ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ •የተነጠቀ ልጅነት •"ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" እ.አ.አ በ2003 ጥቃቱ የተፈጸመባት ሴት የ13 ዓመት ታዳጊ እያለች ለህክምና ተብሎ ወደ ተጠርጣሪው ቤት በቤተሰቦቿ መወሰዷንና በዛው መቅረቷን ፖሊስ ገልጿል። ሰውዬው በጾታዊ ጥቃትና የህጻናት መብት ጥሰት ክስ ቀርቦበታል። ለህክምና ወደ ሰውዬው ቤት በሄደችበት ያልተመለሰችውን ልጃቸው የት እንደሄደች ሲጠይቁት የተሻለ ስራ ፍለጋ ወደ ሃገሪቱ መዲና ጃካርታ መሄዷን እንደገለጸላቸው ታውቋል። ቤተሰቦቿና ሌሎች ዘመዶች ታዳጊዋን ለመፈለግ ጥረት ቢያደርጉም ሊሳካላቸው ስላልቻለ ለፖሊስ ጠፍታብናለች ብለው አስታውቀው ነበር። ፖሊስ እንደገለጸው ከሆነ ባለፈው እሁድ ሴትየዋን በአንዲት ትንሽ ዋሻ ውስጥ ተገኝታለች። በዋሻው ውስጥም አንዳንድ የቤት ውስጥ መገልገያዎችን ማግኘቱንም ጨምሮ ገልጿል። ታዳጊዋ ለማምለጥ ብትሞክር እሱ የሚቆጣጠረው መንፈስ ጉዳት እንደሚያደርስባትና ቤተሰቦቿንም እንደሚከታተላቸው ስለነገራት በፍርሃት ለማምለጥም ሆነ ቤተሰቦቿን ለማግኘት አለመሞከሯን ተናግራለች። ተጠርጣሪው ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ እስከ 15 ዓመት ድረስ የእስር ቅጣት ሊጠብቀው እንደሚችል ተገልጿል። \n\nGive me a good title for the article above.
አስራ አምስት ዓመታት በዋሻ ውስጥ የታገተችው ኢንዶኔዥያዊት ታዳጊ ነፃ ወጣች
amh_Ethi
train
goodtitle
GEM/xlsum
amharic
204
በፋሽን ኢንዱስትሪ ላይ የተሰማራው የ44 ዓመቱ ዩሳኩ ወደ ጨረቃ የሚጓዝ የመጀመሪያው ሲቪል ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ጉዞው የዛሬ ሁለት ዓመት በግሪጎሪ አቆጣጠር 2023 ላይ የሚከናውን ሲሆን ከ1972 በኋላ ወደ ጨረቃ የሚደረግ የመጀመሪያው ጉዞ ሊሆን ይችላል። በመረጃ መረብ አማካይነት ፍላጎቱን ይፋ ያደረገው ጎልማሳው ቱጃር ይህንን 'ልዩ ጉዞ' አብራኝ የምትጓዝ ልዩ እንስት ከወዴት አለች? እያለ ነው። ከ27 ዓመቷ ተዋናይት ፍቅረኛው ጋር በቅርቡ የተለያየው ዩሳኩ በድረ-ገፁ ላይ ባለ መረጃ መስበስበያ ላይ ሴቶች መስፈርታቸውን እንዲያስቀምጡ አቤት ብሏል። «ብቸኝነትና ባዶነት ሊጠናወቱኝ እየሻቱ ስለሆነ መፍትሄው አንዲት ሴትን ማፍቀር ነው» ሲል በድረ-ገፁ አሥፍሯል። «የሕይወት አጋር እፈልጋለሁ፤ ከወደፈቷ አጋሬ ጋር ከውጭው ምህዋር ሆኜ የዓለም ሰላምን እሰብካለሁ» ሲል አክሏል። ሶስት ወራት የሚቆይ የዩሳኩ ውሃ አጣጭ ፍለጋ ሂደት ብዙ መስፈርቶችን አዝሎ በድረ-ገፁ ላይ ሰፍሯል። በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ያልሆነች፣ ዕድሜዋ ከ20 በላይ፣ ቅን አስተሳሰብ ያላትና ወደ ሕዋ ለመብረር ዝግጁ የሆነች የዩሳኩ መስፈርቶች ናቸው። የማመልካቻው ቀን መዝጊያ ጥር 8/2012 ሲሆን አሸናፊዋ ሴት በመጋቢት ወር መጨረሻ ይፋ ትሆናለች። አንድ ባንድ ውስጥ በከበሮ መቺነት ያገለግል የነበረው ዩሳኩ ወጣ ባሉ ድርጊቶቹ ይታወቃል። በዚህ ወር መጀመሪያ እንኳ በትዊተር ገፁ ላይ የሚሰፍሩ መልዕክቶቹን ለሌሎች ያጋሩ 100 ሰዎችን መርጬ 925 ሺህ ዶላር አከፋፍላለሁ ማለቱ አነጋጋሪ ነበር። ዞዞ የተባለ የልብ ዲዛይን ባለቤት የሆነው ዩሳኩ የተጣራ ትርፉ 3 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ይገመታል። \n\nGive me a good title for the article above.
ጃፓናዊው ቢሊዬነር ወደ ጨረቃ አብራው የምትጓዝ 'ውሃ አጣጭ' እየፈለገ ነው
amh_Ethi
train
goodtitle
GEM/xlsum
amharic
210
Title: የበረራ አስተናጋጆች ከአደጋው በኋላ በነበራቸው በረራ ምን ተሰማቸው?\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
አደጋው በመላው ዓለም ድንጋጤን የፈጠረና ያሳዘነ ነበር። ታዲያ በረራ የዘወትር ሥራቸው ለሆነው የበረራ አስተናጋጆች ከአደጋው በኋላ በነበራቸው በረራ ምን ተሰምቷቸው ነበር? ስሟ እንዲጠቀስ ያልፈለገች የበረራ አስተናጋጅ ስለአደጋው የሰማችው ቤት ውስጥ ከቤተሰብ ጋር ተሰብስበው እየተጫወቱ እንደነበር ታስታውሳለች። ከዚያም ድንገት ስልኳ አቃጨለ "ተርፈሻል?" ለማለት ከጓደኛዋ የተደወለ ስልክ ነበር። የሰማችውም ያኔ ነው። " በፍፁም ላምን አልቻልኩም ነበር " ትላለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የሀዘን መግለጫ ሲያወጡ የሚወራው ሁሉ እርግጠኛ መሆኑን እንዳረጋገጠች ትናገራለች። • "እናቱ ስታየኝ 'ልጄ ያሬድ ይመጣል' እያለች ታለቅስ ነበር"- በናይሮቢ የካፒቴኑ ጸጉር አስተካካይ ከዚያም በየተራ ሰው መደወል ጀመረ... ያኔ " እኔም ልሆን እችል ነበር ... ብዙ ጊዜ በማክስ አውሮፕላን እበራለሁ፤ በ20 ሰዓት ልዩነት ስለምንመደብም ልመደብ እችል ነበር" ስትል በሃዘኔታ አጋጣሚውን ታስታውሰዋለች። "አደጋው ሁላችንንም ያስለቀሰ ነበር፤ እሞታለሁ ብለንም ስለማንወጣ በጣም ነበር ያዘንኩት፤ ለተሰጠን ሥራ 'እንደ ወታደር' እሽ ብለን ነው የምንሄደው" ስትል ታክላለች። ያው የሥራ ጉዳይ ነውና ይህች የበረራ አስተናጋጅ አደጋው በተፈጠረ ዕለት ማታ ወደ ታይላንድ፣ ባንኮክ በረራ ነበራት። ይሁን እንጂ ቤተሰቦቿ እንዳትሄድ አጥብቀው ተማፅነዋት እንደነበር ታስታውሳለች። "እናቴም፣ አያቴም፣ ሁሉም ዛሬ ከቤት አትወጭም! እንደዚህ ሆኖ ይወጣል? ሰው ሞቱን ነው ወይ የሚፈልገው?" ሲሉ ከልክለዋት ነበር። • 'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ? በጊዜው እርሷም ፍርሃትና ጭንቀት ገብቷት እንደነበር አልደበቀችም "ከበረራ በፊት ውይይት ስናደርግ ሕይወታቸው ያለፉት አስተናጋጆች ትዝ ይሉን ነበር፤ ድባቡ ያስጠላ ነበር፤ ከባድ ነበር ...እንቅልፍ ሁሉ ነስቶኝ ነበር" ትላለች። "አደጋው ያጋጠመው አውሮፕላኑ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ስለነበር፤ እኛም ልክ አውሮፕላኑ ገና ሲነሳ ሁሉም እያለቀሰ ነበር፤ አገልግሎት መስጠት ተስኖን ነበር" ስትል ታስታውሰዋለች። "ከበፊት ጀምሮ ከቤት ስወጣ ለእግዚያብሔር አደራ ሰጥቼ ነበር የምወጣው፤ አሁንም ይህንኑ ማድረግ የዘወትር ተግባሬ ነው" ትላለች። ይህች የህግ ምሩቅ የሆነችው አስተናጋጅ ቤተሰቦች በአደጋው ምክንያት በስጋት መኖራቸው አልቀረም "አባቴ በተመረቅኩበት ትምህርት እንድሰራ ማስታወቂያዎችን እያየ 'ሞክሪ!... እስከመቼ ተሳቀን እንኖራለን' " ሲሉ ይወተውቷት ነበር። እርሷ ግን ሥራዋን አብዝታ ስለምትወደው የእነርሱን ውትዎታ ከቁብም አልቆጠረችው። ሌላኛዋ ያነጋገርናት የበረራ አስተናጋጅ ለምለም ያደሳም የተለየ ሃሳብ የላትም። የአደጋው ዕለት በርካታ የስልክ ጥሪዎችን አስተናግዳለች። አንዳንዶቹ ሊያጋጥም የሚችል ነገር ነው እያሉ ሲያበረታቷት ቤተሰብ ግን "ሥራውን ተይው" እስከማለት ደርሰው ነበር። ይሁን እንጂ በማንኛውም ሥራ ላይ ሊያጋጥም የሚችል በመሆኑና ለሥራው ፍቅር ስላላት ለንግግራቸው ጆሮዋን አልሰጠችም። • "በመጨረሻ ላይ ሳትስመኝ መሄዷ ይቆጨኛል" እናት ከአደጋው ማግስት በረራ የነበራት ወደ ደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ነበር። ቤተሰቦቿ ሲሸኟትም የውስጧን በውስጧ አድርጋ "አይዟችሁ ምንም አልሆንም፤ አታስቡ" የሚል መፅናኛ ቃል እንደሰጠቻቸው ታስታውሳለች። "መጀመሪያ ስገባ በጣም ፈርቼ ነበር፤ እንዲህ ዓይነት አደጋ ይፈጠራል ብለን አስበን ስለማናውቅ በጣም ተጨንቄ ነበር" የምትለው ለምለም ከዚያ በኋላ ጥንቃቄ ላይ ትኩረት እንድትሰጥ ምክንያት እንደሆናት ትናገራለች። "ብዙ ዓይነት አደጋዎች ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ምን...
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
402
ይህ የታወቀው በቅርቡ በታተመው የሳይንቲስቱ የገዛ የጉዞ ማስታወሻዎች ላይ ነው። ይህ አቻ ያልተገኘለት ሳይንቲስት በዚህ ደረጃ ዘረኛና መጤ-ጠል (xenophobic) እንደነበር የሚያሳብቁ በርከት ያሉ አንቀጾች በማስታወሻው ላይ ሰፍረው መገኘታቸው ዓለምን ማነጋገር ይዟል። እንደ ጎርጎሮሲያዊያን አቆጣጠር ከጥቅምት 1922 እስከ መጋቢት 1923 የተጻፉት የግል ማስታወሻዎቹ ኤንስታይን በኢስያ እና በመካከለኛው ምሥራቅ ቆይታው ያስተዋላቸውን ነገሮች የከተበበት ነበር። ጥቅልና ጅምላ ኮናኝ የሆኑት እነዚህ ማስታወሻዎቹ እሱ በተጓዘባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ሕዝቦችን ዘረኛ በሆነ መንገድ ይመለከታቸው እንደነበር አሳብቀዋል። ለምሳሌ ቻይናዎችን "የማይደክማቸው ሠራተኞች፣ ቆሻሾችና ደነዝ ሕዝቦች" ሲል በማስታወሻው ገልጧቸዋል። አንስታይን በመጨረሻ ሕይወቱ አሜሪካ ውስጥ ለሰብአዊ መብት ተሟጋች እንደነበር ሲታሰብ ከእነዚህ አስተያየቶቹ ጋር እሱን ለማስታረቅ ከባድ ሆኗል። እንዴትስ በዚህ ደረጃ ዘረኛ ሊሆን ቻለ የሚለው ጥያቄ የብዙዎች ሆኗል። ዘረኝነትን አንስታይን "የነጮች በሽታ" ሲል ነበር የሚጠራው። የኤንስታይን ማስታወሻዎች ራሳቸውን ችለው በመድበል መልክ በእንግሊዝኛ ሲታተሙ ለመጀመርያ ጊዜ ነው። ኤንስታይን በዚያ ዘመን ከስፔን ተነስቶ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ከዚያም በሲሪላንካ ወደ ቻይናና ጃፓን ተጉዞ ነበር። በግል ማስታወሻው ስለ ግብጾች እና የሲሪላንካ ሕዝቦችም በተመሳሳይ ሁኔታ መልካም ያልሆኑና ከርሱ የማይጠበቁ አስተያየቶችን መስጠቱን ከመጽሐፉ መደራት ይቻላል። በሌላ አንቀጽ ስለ ቻይና ሕጻናት ያልተገባ አስተያየት ሲሰጥ "ድንዙዝና ምንም የልጅነት ፈንጠዚያ እንኳ ያልፈጠረባቸው፣ እንዲሁም ፈዛዞች" ብሏቸዋል። ይህም ሳያንሰው ቻይኖች "እንደ በግ በጅምላ የሚነዱ፣ ሰው ሰው የማይሸቱ ሮቦቶች" ብሏቸዋል። "ሴቱን ከወንዱ እንኳ ለመለየት የሚያስቸገር ሕዝብ" ሲልም ተሳልቋል። እጅግ ሲከበር የኖረው ይህ ጎምቱ ሳይንቲስት በናዚዎች ላይ ከሚደርሰው ጭቆና በመሸሽ ወደ አሜሪካ ምድር የገባው በ1933 ነበር። በወቅቱ በጥቁሮችና በነጮች መሐል የነበረውን መከፋፈል ሲመለከት እጅግ መደንገጡ ይነገራል። ጥቁሮችና ነጮች የተለያየ ትምህርት ቤትና የተለያየ ሲኒማ ቤት እንደሚሄዱ ባየ ጊዜም ሐዘን ተሰምቶት ነበር። ይህን ያልተገባና ኋላቀር ዘረኝነት ለመቃወምም በወቅቱ የነበረውን ከጥቁርና ከነጭ የተወለዱ ዜጎች ያቋቋሙት የብሔራዊ ባለቀለም ዜጎች ማኅበርን ተቀላቅሎ ነበር። እንዲያውም በንግግሮቹ ውስጥ አሜሪካ በጥቁሮች ላይ የምታደርሰውን መገለል ጀርመን በነበረበት ወቅት በአይሁዶች ላይ ከሚደርሰው ጭቆና ተመሳሳይ ነው ሲል ይናገር ነበር። ስለ አንጻራዊ ለውጥ Relativity theory አብዝቶ የተጨነቀውና ለዓለም አዲስ እሳቤን ያበረከተው ይህ ጉምቱ ሳይንቲስት አንጻራዊ ዘረኝነቱን በሂደት አራግፎት ይሆን? \n\nGive me a good title for the article above.
አንስታይን ቻይኖችን "ቆሻሾች" ሲል ተሳድቧል
amh_Ethi
train
goodtitle
GEM/xlsum
amharic
306
Content: የአጋጣሚ ነገር ሆኖ የመጻሕፍት ጉልቶች እጅብ ብለው ነው የሚገኙት። ከአቶ ተስፋዬ በቀር። አቶ ተስፋዬ ጋንዲ ሆስፒታል አካባቢ አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን አጥር ጥግ በፅድ ተከርክሞ በተሠራ መጽሐፍ መሸጫ ውስጥ ተቀምጠው ለደንበኞቻቸው መጻሕፍትን ሲያከራዩና ሲሸጡ ለዘመናት ኖረዋል። ክረምትና ንባብ “ከወጡት ስራዎቼ ይልቅ ገና የሚወጡት ናቸው ትልቅ ቦታ ያላቸው” አለማየሁ ገላጋይ በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ-መንግሥት ሥራ ሲጀምሩ ጋዜጣ በመሸጥ ነበር። በወቅቱ የነበሩትን እነ ታይም፣ አዲስ ዘመን፣ ኒውስ ዊክ፣ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ ሪደርስ ዳይጀስት፣ አፍሪካ ጆርናል፣ ሄራልድ ትሪቢዩን፣ የኤርትራ ድምፅ፣ የድሮዋን ቁም ነገር መጽሔት፣ ጎህን እያዞሩ ይሸጡ ነበር። በንጉሱ ስርዓት መውደቂያ አካባቢ ከመፅሔቶቹ ይልቅ የማኦ ሴቱንግ መፃህፍቶች እየበዙ እንደመጡ ይናገራሉ። እነዚህን መጻሕፍት ከአከፋፋዮች አንዱን በ10 ሳንቲም ዋጋ ተረክበው ሲቀና መቶ ሳይሆን ሀምሳውን በአንድ ቀን ሸጠው ያድራሉ። በወቅቱም ለነዚህ መፃህፍት ከፍተኛ ፍላጎት እንደነበር ያስታውሳሉ። በዚህም የተነሳ አንዳንድ የሀገር ውስጥ አሳታሚዎች የማኦ ጥቅስን የያዙ፣ የፖለቲካ የኢኮኖሚ ሥራዎችን፣ አራቱ ድርሰቶች፣ የቦልሼቪክ ፓርቲ፣ የሴቶች ጥያቄ፣ የቬትናም አብዮት የሚሉ የወቅቱን እንቅስቃሴ የሚያንፀባርቁ መጽሐፎች ብቅ ብቅ ማለት እንደጀመሩ ይናገራሉ። እነዚህ መጻሕፍት ሲመጡ በከተማው ፈላጊያቸው ብዙ እንደነበር ከትዝታ ከረጢታቸው ፈትተው አጫውተውናል። አቶ ተስፋዬ እና ባልደረቦቻቸው እነዚህን መጻሕፍት እያመጡ ይቸበችቡት ያዙ። ከዚህ በኋላ ደግሞ በሀገር ውስጥ የነበሩ መፃህፍት የቀድሞ ታላላቅ የሀገራችን ሰዎች የተማሩባቸው፣ ታሪክን የሚነግሩ፣ ከየትምህርት ቤቱ እና ከየድርጅቱ እየወጡ መጣል ጀመሩ። "እነዚህ መጽሐፎች የሚጣሉና የሚወድቁ አልነበሩም" ይላሉ አቶ ተስፋዬ። "ፍቅር እስከ መቃብር"ን በአይፎን 7? በወቅቱ የነበረው መንግሥት ግን መጻሕፍቱ እንዲጣሉ አልያም ተሰብስበው እንዲቃጠሉ ያደርግ እንደነበር አቶ ተስፋየ ያስታውሳሉ። የየትምህርት ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራን ግን እነ አቶ ተስፋዬን እየጠሯቸው ሳይቃጠል ከተጣለበት እንዲወስዱ ያደርጉ ነበር። ስለዚህም እነዚህን መጻሕፍት በትንሽ ዋጋ እየገዙ መሸጥ ጀመሩ። ያኔ እነዚህን መጻሕፍት እያዞሩ መሸጥ መዘዝ ነበረው። መጻሕፍቱ ውስጥ የጃንሆይ ምስል ከተገኘበት ያለምንም ጥያቄ አምስት ወራትን ያሳስር ነበር። ስለዚህ የጃንሆይን ምሥሎች እየፈለጉ መገንጠልና ማስወገድ የግድ ነበር። "በመጻሕፍት የተነሳ ታስሬ አውቃለሁ" የታሰሩበትንም ምክንያት ሲያስረዱም በደርግ ሥርዓት ውስጥ "የሹራብ ነጋዴውም፣ የካልሲ ነጋዴውም አፈሳ ተብሎ ልቅምቅም ተደርጎ ታፈሰ" በማለት ይጀምራሉ። "መጽሐፍት ነጋዴውም ሕገ ወጥ ነው ብለው ያዙን። ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እስከ መጽሐፎቻችን ታሰርን።" አቶ ተስፋዩ እና ሌሎች መፃሕፍት ሻጮች ለ15 ቀን ያህል በእስር ሳሉ ደራሲ ማሞ ውድነህ ለግል ጉዳያቸው ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ይመጣሉ። በሩ ላይ መጽሐፍ ተደርድሮም ያያሉ። ቀዩን ረዥሙን ደራሲ ማሞ ውድነህን ፖሊሱ አላወቃቸውም ነበር። ጋሽ ማሞ 4 ሰዓት ላይ በእጃቸው ላይ የሆነች ወረቀት ይዘው ነው ወደ ስድስተኛ የገቡት። ቀና ብለው ሲያዩ መጽሐፍ ተደርድሯል። አቶ ማሞ ለካ መጀመርያ መጽሐፉን ሲያዩ ለእስረኞች እንዲያነቡት የመጣላቸው ነው የመሰላቸው። "ዛሬስ ለእስረኞቻችሁ መጽሐፍ ቤት ከፈታችሁ እንዴ?" በማለት እንዳደነቁ አቶ ተስፋዬ ይናገራሉ። የጥበቃ ጓዱ ከመጻሕፍት ነጋዴዎች ጋር አብረው የታሰሩ መጻሕፍት እንደሆኑ አስረዳቸው። ማሞ ውድነህ ሐዘን ገባቸው። በተለይም...\nThe previous content can be summarized as follows:
በአሁኑ ወቅት መጽሐፍ የሚፈልግ ቢያሻው ወደ ብሔራዊ ቲያትር ካልሆነም ፒያሳ ጊዮርጊስ ማቅናት የተለመደ ነው። የጠፉ መጻሕፍትን የሚፈልግ ደግሞ ሜክሲኮ ሊወርድ ወይም መርካቶ ሊወጣ ይችላል።
amh_Ethi
train
prevcontent
GEM/xlsum
amharic
418
ኮሮናቫይረስ፡ የሚሞቱ ህሙማንን የመጨረሻ ኑዛዜያቸውን የምትቀበለው ነርስ\nምንም እንኳን ቬንትሌተር በህይወት እንዲቆዩ ቢያግዝም፣ በጠና በታመሙት ዘንድ የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት ቢያመጣም ህይወትን መቀጠል አያስችለውም። እናም የመጨረሻዋ ደቂቃ ስትቃረብ፣ በማሽንም መተንፈስ ሲያዳግት፣ ማሽኑ ሊነቀል ግድ ይላል። ወደ ሞት እየሄዱ ላሉ ህሙማን ምን አይነት ስሜት ይኖረው ይሆን? ማሽኑን ለሚነቅሉት የጤና ባለሙያዎችስ? •"ሞትን ተሻገርኳት" ከኮሮናቫይረስ ያገገመች ሴት •በሴቶች የሚመሩ አገራት ወረርሽኙን በተሳካ ሁኔታ እንዴት ተቆጣጠሩት? በለንደን ሮያል ፍሪ ሆስፒታል በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ለምትሰራው ዋና ነርስ ጁዋኒታ ኒትላ በአብዛኛው መተንፈሻ ማሽኖችን መንቀል የሥራዋ አንድ አካል ነው። በብሔራዊ የጤና አገልግሎት በፅኑ ህሙማን ልዩ ነርስ በመሆንም ለአስራ ስድስት ዓመታት ያህል አገልግላለች። ነገር ግን ጊዜው ሥራውንም ሆነ የሚሰማትን ስሜት አላቀለለውም። "ልብ የሚሰብር ነው፣ ህመሙም ጠልቆ ይሰማኛል" የምትለው የ42 ዓመቷ ጁዋኒታ "አንዳንድ ጊዜም ለእነዚህ ሰዎች ሞት ተጠያቂ ነኝ ብዬ አስባለሁ" ትላለች። ኮሮናቫይረስ ሳንባን ከጥቅም ውጭ በሚያደርግበት ጊዜ ቬንትለተሮች የሰውነትን የመተንፈስ ሥርዓት በመቆጣጠጠር እንዲተነፍሱ ይረዳሉ። ህሙማኑም በሽታውን እንዲታገሉና እንዲያገግሙም ያግዛቸዋል። አንዳንድ ጊዜ ግን ይህ ሁሉ በቂ የማይሆንበት ሰዓት አለ። ህሙማኑም ሳይሻላቸው ሲቀር፣ ከቀን ወደ ቀን ሁኔታቸው ሲብስ የጤና ባለሙያዎችም ምን እንደሚወስኑ ከፍተኛ ፈተና ውስጥ ይገባሉ። የሞትና የህይወት ጉዳይም ስለሆነ ማሽኖችን ለመንቀል የህሙማኑን የተለያዩ መረጃዎች ከግምት ውስጥ ያስገባሉ። የህሙማኑ እድሜ፣ ተደራራቢ ህመም ካለባቸው፣ ቫይረሱን መቋቋምና ማገገም መቻል አለመቻላቸውን በተመለከተ ያሉ መረጃዎች ያጤናሉ። ከሁለት ሳምንታት በፊት የጠዋት ፈረቃዋን ልትጀምር ባለችበት ወቅት በሃምሳዎቹ እድሜ ላይ ለምትገኝ የኮሮናቫይረስ ህመምተኛ ነርስ ህክምና ማቆም እንዳለባት ተነገራት። ካለው የኮሮናቫይረስ ስጋትም ጋር ተያይዞ የነርሷ ልጅ ሆስፒታል ባለመገኘቷ ጁዋኒታ ማድረግ የቻለችው ደውላ ህክምናውን ሊያቆሙ እንደሆነና እንደምትሞትም ነገረቻት። "እናቷ ህመም ላይ እንዳልሆነችና፣ ፊቷም ላይ ሰላም ይነበብባታል ብዬ አረጋገጥኩላት" የምትለው ጁዋኒታ "እናቷ ከእምነቷ ጋር ተያያይዞ እንዲፈፀም የምትፈልጋቸው ጉዳዮችም ካሉ ጠየቅኳት" ትላለች። ህመምተኛዋ የተኛችበት ክፍል ስምንት አልጋዎች ያሉት ሲሆን፤ ሁሉም ራሳቸውን የማያውቁና በጠና የታመሙ ሰዎች ናቸው። "ህመምተኛዋ ያለችበትን መጋረጃ ዘጋሁ፣ የመጥሪያ ደወሎቹንም አጠፋሁ" ትላለች። የጤና ባለሙያዎቹም በዝምታ ተዋጡ፤ ክፍሉም ፀጥ፣ ረጭ አለ። "ወደ ህመምተኛዋ ጆሮም ስልኩን አስጠጋሁና ልጇን እንድትናገር ጠየቅኳት።" ከዚያም በልጇና በቤተሰቦቿ ጥያቄ መሰረት የመረጡትን ሙዚቃ እያጫወትን የመተንፈሻ ማሽኑን ከህመምተኛዋ ላይ አላቀቅነው። "በመቆጣጠሪያው ላይ ብርሃን ብልጭ፣ ብልጭ ይላል፤ ከዚያም የልብ ምቷ ዜሮ፣ በሰሌዳው ላይም ቀጥ ያለ መስመር ሆነ።" "ከዚያም አጠገቧ ሆንኩና እጆቿን ጨብጬ እስክትሞት ጠበቅኳት" ትላለች ሃዘን በተሞላ ድምፅ። ህመምተኛዋም ከአምስት ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ህይወቷ አለፈ፤ ጁዋኒታ ከህመምተኛዋ ጋር የተገናኙ ቱቦዎችን ነቃቀለች። ይህ ሁሉ ሲከናወን የህመምተኛዋ ልጅ በስልክ እያወራች ነበር፤ ከዚያም ሁሉ ነገር እንደተፈፀመ አረዳኋት። "ከአንድ የሥራ ባልደረባዬም ጋር በመተባበር ገላዋን አጠብናት። በጨርቅ ጠቀለልናትና ለአስከሬን በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ አድርጌ ከመዝጋቴ በፊት ግንባሯ ላይ የመስቀል ምልክት አደረግኩ" ትላለች። •በቺካጎ የኢትዮጵያውያን...\n\ntl;dr:
በኮቪድ-19 በጠና ለታመሙ ህሙማን የኦክስጅን መተንፈሻ ማሽን (ቬንትሌተር) ድጋፍ በህይወት እንዲቆዩ ለማድረግ ይረዳል።
amh_Ethi
validation
tldr
GEM/xlsum
amharic
393
Title: ትግራይ ፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት የእዳጋ ሐሙስ ከተማን መያዙን መንግሥት ገለጸ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ከመንግሥት በኩል ስለ ወቅታዊ ሁኔታ መረጃን የሚያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ ዛሬ ኅዳር 13/2013 ዓ.ም እንዳለው እዳጋ ሐሙስ ከአዲግራት ወደ መቀለ በሚወስደው መስመር ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። ቅዳሜ ዕለት በትግራይ ክልል ሁለተኛ ከተማ የሆነችው የአዲግራት ከተማ በኢትዮጵያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ሙሉ ለሙሉ መዋሏ ተገልጾ ነበር። እዳጋ ሐሙስ ከክልሉ ዋና ከተማ መቀለ 116 ኪሎ ሜትሮች ያህል ርቃ ከምትገኘውና የምሥራቃዊ ትግራይ ዞን ማዕከል ከሆነቸው አዲግራት ከተማ ቀጥላ ትገኛለች። አርብ ዕለት የኢትዮጵያ ሠራዊት ትግራይ ውስጥ ከሚገኙት ቁልፍ ከተሞች መካከል የሆኑትን የአክሱምና የአድዋ ከተሞችን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጠሮ የአዲግራት ዙሪያ መያዙን ገልጾ ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት በፌስቡክ ገጹ "በአዲግራት ከተማ ላይ የከባድ መሳሪያ ድብደባ መፈጸሙንና በዚህም ሠላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል" ያለ ሲሆን ከተማዋ በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ስለመዋሏ ያለው ነገር የለም። ይህንን ዜና በተመለከተ እስካሁን ከገለልተኛ ወገን የተገኘ ማረጋገጫ የለም። አዲግራት፣ አክሱምና አድዋ በትግራይ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ትላልቅ ከተሞች መካከል የሚጠቀሱ ሲሆን በተለይ አክሱምና አድዋ በታሪካዊና በሐይማኖታዊ ቦታነት ቀዳሚ ናቸው። በዚህም ምክንያት በከተሞቹ ያሉትን ታሪካዊና ሐይማኖታዊ ስፍራዎችን ለመጎብኘት በርካታ ቱሪስቶች ከውጪና ከአገር ውስጥ የሚጎበኟቸው ናቸው። የአዲግራት ከተማ የምሥራቃዊ ዞን ማዕከል ከመሆኗ በተጨማሪ የመድኃኒት ፋብሪካን ጨምሮ የተለያዩ ፋብሪካዎች ያሉባት ከተማ ናት። ሦስተኛ ሳምንቱን በያዘው በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊትና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ባለው ወታደራዊ ግጭት ከቀናት በፊት በተለያዩ የትግራይ ክፍሎች የሚገኙትን ሽረ፣ ጨርጨርና አላማጣ የተባሉ ቦታዎችን መንግሥት መቆጣጠሩን ማሳወቁ ይታወሳል። መንግሥት በመግለጫው ላይ በምዕራብ ግንባር የሚገኘው ሠራዊቱ ሰለህለሃ ላይ ከህወሓት ኃይል ከባድ መከላከል ገጥሞት እንደነበር ገልጾ ይህንን "መከላከል በመስበር አክሱምን መቆጣጠሩን" አመልክቷል። ጨምሮም ሠራዊቱ ከአክሱም በኋላ ወደ አድዋ ባደረገው ዘመቻ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ መከላከል ቢገጥመውም አድዋን ለመቆጣጠር መቻሉን ገልጿል። አርብ አመሻሽ ላይ በትግራይ ክልል እተካሄደ ያለውን ወታደራዊ ግጭት በተመለከተ መግለጫ የሰጡት ሁለት የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ግን በቁጥጥር ስር ስለዋሉት ከተሞች ያሉት ነገር የለም። አቶ ጌታቸው ረዳ በእንግሊዝኛ፣ አቶ ገብረ ረብረጻድቅ በአማርኛ በሰጡት መግለጫ ላይ በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ከባድ ውጊያ መካሄዱንና ጉዳት እንደደረሰ ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ በትግራይ ለሚገኙ የልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት በሠላም እጃቸውን እንዲሰጡ የተቀመጠው ቀነ ገደብ ማብቃቱን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት ላይ "በቀጣይ ቀናት የመጨረሻው ሕግን የማስከበር ተግባር ይከናወናል" ብለው ነበር። ትግራይ ውስጥ በሚገኘው የሠሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈጸሙ ከተገለጸ በኋላ የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭት ሦስተኛ ሳምንቱ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ሠራዊቱ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ቦታዎችን በመቆጣጠር ወደ ክልሉ ዋና ከተማ መቀለ እያመራ መሆኑም ተገልጿል። በፌደራል መንግሥቱና የትግራይን ክልል በሚያስተዳድረው ህወሓት መካከል ለወራት የቆየው አለመግባባት ተካሮ ወደ ግጭት ካመራ በኋላ በክልሉ ውስጥ ያሉ የግንኙነት መንገዶች በመቋረጣቸው ዝርዝር መረጃ በቀጥታ ከቦታው ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል።
amh_Ethi
test
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
409
ባይደን 243 የኤሌክቶራል ኮሌጆች ድምጽ ሲኖራቸው ትራምፕ ደግሞ 214 አላቸው። ኋይት ሃውስ ለመግባት 270 ማግኘት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቀሪዎቹ ወሳን ግዛቶች አሪዞና፣ ጆርጂያ፣ ኔቫዳ፣ ፔንሲልቬንያ፣ ሰሜን ካሮላይና እና ዊስኮንሲን ናቸው ፡፡ ወደ ድል የሚወስዱ የተለያዩ መንገዶች አሉ ፡፡ 270ን ቁጥር ለመድረስ ትራምፕ በዊስኮንሲን በአስር ድምፅ ተሸንፈው በጆርጂያ (16 ድምጽ)፣ በሰሜን ካሮላይና (15)፣ በፔንሲልቬንያ (20)፣ በአሪዞና (11) ወይም በኔቫዳ (6) ማሸነፍ አለባቸው ፡፡ ባይደን በበኩላቸው ያለ ፔንሲልቬንያ (ውጤት በቅርቡ የማይጠበቅበት ነው) ሊያሸንፉ ይችላሉ። ሆኖም አሪዞና፣ ጆርጂያ እና ኔቫዳን ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል ፡፡ አንዳንድ የዜና አውታሮች በዊስኮንሲን እና አሪዞና ባይደን አሸናፊ እንደሆኑ ቢገልጹም ቢቢሲ ግን ውጤቱን ለመግለጽ ገና መሆኑን በወኪሎቹ በኩል ለማረጋገጥ ችሏል፡፡ ባይደን ከዊስኮንሲን ጋር አሪዞና እና ኔቫዳ ላይ ብቻ በማሸነፍ ፕሬዝዳንት ይሆናሉ፡፡ ቆጠራው እንደቀጠለ ሲሆን ባለሥልጣናቱ ውጤት በቀጣይ ሰዓታት ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡ ሁሉም ድምፆች እስኪቆጠሩ ድረስ ሌሊቱን በሙሉ ቆጠራቸውን እንደሚቀጥሉ የጆርጂያ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡ በግዛቱ የትራምፕ መሪነት ወደ 24,000 ድምፆች ቀስ እያለ እየቀነሰ ነው ሲል ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል። በኔቫዳ የድምጽ ልዩዩቱ ጠባብ ሲሆን ባይደን ከ8000 ባነሰ ድምፅ ይመራሉ፡፡ ቀጣይ ውጤቶች ሐሙስ ከሰዓት በኋላ እንደሚለጠፉ ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል፡፡ በፔንሲልቬንያ በሰፊ ልዩነት ሲመሩ የነበሩት ትራምፕ አሁን ልዩነታቸው ጠቧል። 90 በመቶ ድምጾች ተቆጥረው ትራምፕ በ164 ሺህ 414 ድምፅ ይመራሉ፡፡ ባይደን በአሪዞና በ80,000 ያህል ድምጽ እየመሩ ሲሆን ተጨማሪ ውጤቶች ሐሙስ ይጠበቃሉ። በሰሜን ካሮላይና አብዛኛው ድምጽ የተቆጠረ ሲሆን ትራምፕ 77 ሺህ በሚጠጋ ጠባብ ድምጽ በመምራት ላይ ይገኛሉ። ጆ ባይደን ከ 20 ሺህ በላይ ድምጽ እየመሩ ነው በሚባልበት ዊስኮንሲን አጋራችን ሮይተርስ አሸናፊነቱን ያልሰጣቸው ሲሆን ሌሎች የዜና አውታሮች ግን ባይደን በግዛቱ እንዳሸነፉ እየዘገቡ ነው። \n\nGive me a good title for the article above.
የአሜሪካ ምርጫ፡ በወሳኝ ግዛቶች ምን እየተከናወነ ነው?
amh_Ethi
test
goodtitle
GEM/xlsum
amharic
250
የአስተምህሮቱ ዋና ዋና ይዘቶች እንደወንድ ወጥተው የሚሰሩ ሴቶች መጨረሻቸው አያምርም፣ ሴቶች የማህበረሰቡ መጨረሻ መሆን እንጂ ከፍ ለማለት መሞከር እንደሌለባቸው፤ እንዲሁም ሴቶች የአባቶቻቸውን፣ የባሎቻቸውንና የወንድ ልጆቻቸውን ትዕዛዝ መቀበል እንዳለባቸው የሚገልፁ ናቸው። በተጨማሪም ሴቶች ባሎቻቸው ሲደበድቧቸው ወይም ሲጮሁባቸው መመለስ እንደሌለባቸውና አንዲት ሴት ከሦስት ከሚበልጡ ወንዶች ጋር ወሲብ ከፈፀመች ልትታመምና ልትሞት ትችላለች ብለውም ይመክራሉ። ይህ ማዕከል ስለሚያስተምረው ጉዳይ ዜናው ይፋ በወጣበት ጊዜ የአገሪቱ መላ ህዝብን እጅጉን አስቆጥቷል። መንግሥትም ማዕከሉን በመዝጋት አፋጣኝ እርምጃ ወስዷል። ህዝቡ በመገናኛ ብዙሃንና በማህበራዊ ድረ ገፆች ያደገረው ግፊት የቻይና ትምህርት ሚኒስቴር "የማዕከሉ አስተምህሮ ማህበራዊ እሴቶቻችንን የሚፃረር ነው" በማለት እርምጃ እንዲወስድ አስገድዶታል። የ17 ዓመቷ ጂንግ አንድ ጊዜ ትምህርት ቤቱ ገብታ ነበር። በተወሰደው እርመጃ ደስተኛ መሆኗን ለቢቢሲ ገልፃለች። የ13 ዓመት ታዳጊ ሳለች ረባሽ ነች ብላ በማመን እናቷ ባህላዊ ትምህርቱ አደብ እንድትገዛ ያደርጋታል በማለት ወደ ትምህርተ ቤቱ ትልካታለች። የጂንግ እናት ወደ መሰል የባህል ትምህርት ልጆቻቸውን እንደሚልኩ ቤተሰቦች በገጠር ያደገችና ብዙም ያልተማረች ነች። "የትምህርቱ አካል ነው ተብሎ፤ ካለጓንት በእጄ ሽንት ቤት አፀዳ ነበር" በማለት ያሳለፈችውን ስቃይ ታስታውሳለች። በቆይታዋም ይህን ሴቶች ሊያደርጉት እንደሚገባና የተፈጠሩትም ወንዶችን ለማገልገል እንደሆነ ተምራለች። ጂንግ እስካሁንም ለምን ጓንት እንዳልተሰጣትና እንደዚያ እንድትሰቃይ እንደተፈለገ አይገባትም። ሌላው የማስተማሪያ ዘይቤ ሴቶቹ ጥፋት የሚሉትን እንዲናዘዙ ማድረግ ነው። ጂነግ እ... Continue the article for another 4000 characters max:
ንደምትለው የትምህርት ቤቱ ሥርዓተ-ትምህርት በጥንት አስተምህሮቶች እንዲሁም የቤት ውስጥ ሥራ ላይ ያተኮረ መሆኑን ትናገራለች። አስተምህሮቱ ማንኛዋም ጤነኛ ሴት የምትቋቋመው አይደለም። "እኔም ሰባት ቀን መቆየት ሲኖርብኝ አራተኛው ቀን ምሽት ላይ የትምህርት ቤቱን የብረት አጥር ዘልዬ ወጣሁ"ትላለች። ጂንግ እንደምትለው እንደ ቤጂንግና ሻንጋይ ባሉ ከተማዎች የሚኖሩ የተማሩ ሴቶች የዚህን ትምህርት ቤት ዜና ሲሰሙ እጅግ ሊደነግጡ ይችላሉ። ነገር ግን እነዚህ ዘመን ያለፈባቸው የትምህርት ቤቱ አስተምህሮቶች በገጠር አካባቢዎች በተለይም በቻይና ትንንሸ ከተሞች እንዳሉ ናቸው። ለብዙ ሺህ ዓመታት በነበረው የቻይና ፊውዳል ሥርዓት እንዲህ ዓይነቱ የሴቶች ባህሪ በጣም አስፈላጊ የሚባል ነበር። ይህ ማለት ደግሞ የአባትን ትእዛዝ ማክበር፣ ክብረ ንፅህናን መጠበቅና ከዕውቀት ነፃ ሴት መሆን ከሴቶች የሚጠበቅ ነበር። እነዚህ ነገሮችን ሴቶች በቤትና በትምህርት ቤት እንዲማሩት ይደረግ የነበረ ሲሆን ይህ ደግሞ ሴቶችን ለመጨቆንና ለመርገጥ አስችሏል። ማኦ "ሴቶች የሰማይን ግማሽ የያዙ ናቸው" በማለት ነገሮችን እስኪለውጡ ድረስ ሴቶች በጭቆና ስር ነበር የሚኖሩት። ከዚያ በኋላ ግን ሴቶች በማህባራዊ ህይወት ደረጃቸው እየተሻሻለ መጥቷል። ቢሆንም ግን በባህላዊ ትምህርት ስም ሴትን የሚጨቁኑ የፊውዳል ሥርዓት እሴቶች ተመልሰው ሊመጡ ነው የሚል ስጋት እየተፈጠረ ነው። ገንዘብ መሰብሰብ የፉሸን ዓይነቱ ትምህርት ቤት አላማ ፖለቲካ ሳይሆን ገንዘብ ነው። ትምህርት ቤቱ ለማስተማር ፍቃድ የሌለው ቢሆንም እያስከፈለ ያስተምራል። መስራቾቹ በተለያዩ የቻይና ከተሞች ትምህርት ቤትና ማዕከሎችን በመክፈት ሲነቀሳቀሱ ቆይተዋል። የመገናኛ ብዙሃን ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ትምህርት ቤቱ ሲዘጋ 10ሺህ ተማሪዎች ነበሩት። ትምህርት ቤቱን ያቋቋመው ኢንተርፕራይዝ የተቋቋመው ግን በተማሪዎች ልገሳ ነው። ኢንተርፕራይዙ ጎን ለጎን የሚያካሂደው ሌላ ንግድም አለው። ትምህርት ቤቱ አስቸጋሪ ልጆች ያላቸውን ቤተሰቦች ኢላማ ያደርጋል። ኩባንያዎችንም ጥሩ የሥራ ግንኙነት እንዲፈጠር እናደርጋለን በማለት ይቀርባል። እንደ አውሮፓውያኑ 2014 ላይ ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ያደርግ የነበረ ሌላ ማዕከል ተዘግቷል። እንደእነዚህ ያሉ ተቋማት ባህላዊ ትምህርትን በማስፋፋት ስም ትርፍ እየሰበሰቡ በመሆኑ እርምጃ እየተወሰደባቸው ነው። ቢሆንም ግን አሁንም እየተንቀሳቀሱ ያሉት በርካታ ናቸው። የፉሸን ዋናው ማዕከል ቢዘጋም አሁንም በሌሎች ከተሞች ያሉ ቅርንጫፎቹ እየሰሩ ነው። የዚህ ዓይነት ትምህርት ቤቶች ለምን ገበያ ኖራቸው? ብዙዎቹ ተማሪዎች ያልተማሩ የገጠር ሴቶች፣ በትዳራቸው ደስተኛ ያልሆኑና በባሎቻቸው የሚጨቆኑ ናቸው። ስለዚህም ወደ ትምህርት ቤቱ ሄደው እንደእነሱ ያሉ ሴቶችን ማግኘት ያስደስታቸዋል። አጋር ያገኙም ይመስላቸዋል። መገናኘታቸውንና ሀሳብ መለዋወጣቸውን በመውደድ ሴቶቹ በመጨረሻ የትምህርት ቤቱ በጎ ፍቃድ አገልጋይ ይሆናሉ። አንድ የገጠር ሴቶች ላይ የሚያተኩር ጋዜጣ አዘጋጅ የሆነችው ዚ ሉሃ፤ የዚህ ዓይነቱን ችግር ሴቶችን እንዲማሩ፣ ማህበራዊ ድጋፍ እንዲኖራቸውና የህግ ከለላ እንዲያገኙ በማድረግ ለመፍታት ትክክለኛው መንገድ እንደሆነ ትናገራለች። ይህ ካልሆነ ግን የገጠር ሴቶች ላይ እየደረሰ ያለው ፆታዊ ጥቃት እና የመሬት ባለቤት መሆን ያለመቻል ችግር መቼም እንደማይፈታ ትጠቁማለች። ነገር ግን "ታሪክ በአንዴ አይለወጥም። እነዚህ ሴቶች ዝቅ እንዲሉ ለሚያስተምሩ ማዕከሎች ትልቅ ቦታ መስጠት አያስፈልግም። ይልቁንም ቀልደው የሚያልፏቸው ዓይነት ናቸው። የቻይና ህዝብ የሴቶችን እኩልነት እየተቀበለ መጥቷል'' ትላለች።
amh_Ethi
test
xp3longcontinue
GEM/xlsum
amharic
577
Content: ፕሬዝዳንቷ በፈረንጆቹ የካቲት 1 ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ከቀረቡባቸው ውንጀላዎች በሙሉ ይህኛው ጠንካራ ነው ተብሏል። ጦር ኃይሉ ለውንጀላው ማስረጃ አላቀረበም። ብርጋዴር ጄነራል ዛው ሚን ቱን፣ ዊን ሚንት እና ሌሎች ሚኒስተሮችን በሙስና ወንጅለዋል። የሳን ሱ ቺ ፓርቲ ናሽናል ሊግ ፎር ዲሞክራሲ ባለፈው ዓመት የተደረገውን አገራዊ ምርጫ በአብላጫ ድምጽ ማሸነፉ ይታወሳል። የሚያንማር ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ግን ምርጫው የተጭበረበረ ነው ሲሉ አስታውቋል። ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች የጦር ኃይሉን የተጭበረበረ ምርጫ ነው የሚል ክስ የሞገቱ ሲሆን ምንም የታየ ስህተት የለም ብለዋል። ሳን ሱ ቺ ላለፉት አምስት ሳምንታት በወታደራዊ ኃይሉ ቁጥጥር ስር ቢሆኑም ያሉበት ስፍራ ግን እስካሁን ድረስ አይታወቅም። ወታደራዊ ባለሥልጣናት በሳን ሱ ቺ ላይ "ፍርሃትና ሥጋት በመቀስቃስ"፣ በሕገወጥ መንገድ የሬዲዮ መሳሪያዎችን በመያዝ እና የኮቪድ-19 እገዳዎችን በመጣስ ክሶች መስርተውባቸዋል። እስካሁን ድረስ ከቀረቡባቸው ክሶች መካከል ሐሙስ ዕለት የተሰማው ሕገወጥ ገንዘብ መቀበል ትልቁ ነው። ሳን ሱ ቺ ተቀብለውታል የተባለው ወርቅ በገንዘብ ሲሰላ 450 ሺህ ፓውንድ ይሆናል ተብሏል። ሚያንማር ሳን ሱ ቺ በቁጥጥር ስር ውለው ወታደሩ ሥልጣንን ከተቆጣጠረ ጀምሮ በጎዳና ላይ ነውጦች እየታመሰች ትገኛለች። ሐሙስ ዕለት ብቻ ሰባት ተቃዋሚ ሰልፈኞች መገደላቸውን ተከትሎ የሟቾች ቁጥር 60 ደርሷል። የዓይን ምስክሮች እንደሚሉት የተወሰኑ ተቃዋሚ ሰልፈኞች የሞቱት ግንባራቸውን በጥይት ተመተው ነው ። የተባበሩት መንግሥታት፣ አሜሪካ እና ሌሎች አገራት የተቃዋሚ ሰልፈኞቹን ግድያ ያወገዙ ሲሆን ባለስልጣናቱም ከኃይል እርምጃ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። የአገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ግን የቀረበበትን ውንጀላ በሙሉ አጣጥሎ ጥፋቱ በሙሉ የሱ ቺ ነው ብሏል። \nThe previous content can be summarized as follows:
የሚያንማር ጦር ኃይል አመራሮች ከሥልጣን የተወገዱት ፕሬዝዳንት ሳን ሱ ቺ በሕገወጥ መንገድ 600 ሺህ ዶላር ተቀብለዋል ሲሉ ወነጀሉ።
amh_Ethi
train
prevcontent
GEM/xlsum
amharic
235
Title: የመጀመሪያው ጥቁር የኦክስፎርድ ተማሪ ክሪስትያን ኮል\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ነገር ግን ክሪስትያን ኮል ማነው? ጥቁር ሆኖ ዩኒቨርሲቲ መቀላቀል 'አስደናቂ' በሚባልበት ወቅት ይህንን እንዴት ማድረግ ቻለ? የክላሲክ ሙዚቃ ስልትን ሊያጠና ወደ ኦክስፎርድ ብቅ ያለው ጥቁሩ ኮል ቅጥር ግቢውን ሲረግጥ የወሬ ርዕስ መሆኑ አልቀረም። ጊዜው በአውሮፓውያኑ 1873 ነበር። የ21 ዓመቱ ኮል ከሴራሊዮን ዋተርሉ ከተማ በመምጣት በወቅቱ አቅም ያላቸው እንግሊዛውያን የሚማሩበትን ትምህርት ቤት ተቀላቀለ። ይህም ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪየውን የሴቶች ትምህርት ቤት ከማቋቋሙ ስድስት ዓመታት ቀደም ብሎ ነው። "ከተማዋ አስፈሪ ነገር ሆና ሳትጠብቀው አትቀርም" ይላሉ የዩኒቨርሲቲው የማሕደር ባለሙያ ዶ/ር ሮቢን ዳርዋል ስሚዝ። "በዚያን ጊዜ ለነበሩ ተማሪዎች ኮል፤ በሕይወታቸው ያዩት የመጀመሪያው ጥቁር ሠው ሳይሆን አይቀርም" ይላሉ ዶ/ር ሮቢን። 'የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር ተማሪዎች ያልተነገረ ታሪክ' የሚል መጽሓፍ ያሳተሙት ታሪክ አጥኚዋ ፓሜላ ሮበርትስ እንደሚያምኑት፤ ለኮል ከሴራሊዮን ወደ ብሪታኒያ የእንግሊዝኛ አነጋገር ዘይቤውን መቀየር በራሱ ፈታኝ ነገር ነበር። እርግጥ ኮል ሴራሊዮን እያለ ምን ዓይነት ሕይወት ይመራ እንደነበር ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም። ቢሆንም ትምህርት የመቀበል ልዩ ችሎታው ከሌሎች ነጥሮ እንዲወጣ ምክንያት እንደሆነው ፓሜላ ይናገራሉ። ኮል ሴራሊዮን ውስጥ የእንግሊዝ ቤተክርስትያን ቄስ የነበሩ ሠው የማደጎ ልጅ ነበር። በሴራሊዮን ዋና ከተማ ፍሪታውን ባለ ታዋቂ ትምህርት ቤትም ተማሪ ነበር። በኦክስፎርድ ቆይታውም የመክፈል አቅም የሌላቸው ተማሪዎች በሚረዱበት ሥርዓት ውስጥ ነበር የተማረው። ከአጎቱ የሚላክለትን መጠነኛ ገንዘብን በትርፍ ጊዜ የሙዚቃ ትምህርት በማስተማር ከሚያገኘው ጋር አድርጎ ራሱን ይደጉምም ነበር። እንዲህ ራሱን ለመደጎም ላይ ታች ቢልም በኦክስፎርድ ሕይወቱ ሰኬትን ከማጣጣም አላገደውም ነበር ሲሉ ዶ/ር ሮቢን ይተርካሉ። በዩኒቨርሲቲው የመከራከሪያ መድረክ ላይ ንግግር ያደርግ የነበረው ሲሆን፤ በኦክስፎርድ የተማሪዎች ሕብረትም የነቃ ተሳትፎ አድርጓል። ታዋቂነትንም አትርፎ እንደነበረም ይወሳል። በስተመጨረሻም ዩኒቨርሲቲው የክብር ድግሪ በሚሰጥበት ሥነ-ሥርዓት ላይ የክርስቲያን ኮል ስም ሲጠራ የነበረውን ጩኸት እና ጭብጨባ ዩኒቨርሲቲው በታሪክነት አስቀምጦታል። "ሥነ-ሥርዓቱን ለመታዘብ የመጡ ሠዎች ማነው ይህ እንዲህ የሚጨበጭብለት ሲሉ 'ክሪስትያን ኮል ነው። ከሴራሊዮን ነው የመጣው' ብለው ሲናገሩ ይታሰበኛል" ሲሉ ዶ/ር ሮቢን ያወሳሉ።
amh_Ethi
train
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
282
Given the below title and summary of an article, generate a short article or the beginning of a long article to go along with them. Title: ኮሮናቫይረስ፡ የሕንዱ ድርጅት በኮቪድ-19 ለሞቱ ሠራተኞቹ ቤተሰቦች ካሳ ሊከፍል ነው\nSummary: በሕንድ አንድ የብረት ማምረቻ ድርጅት በኮቪድ-19 ሳቢያ ለሞቱ ሠራተኞቹ ቤተሰቦች ካሳ እንደሚከፍል አስታወቀ።\nArticle (Max 500 characters):
ይህን ያለው በሕንድ ከትላልቅ የብረት ፋብሪካዎች አንዱ የሆነው ታታ ስቲል ነው። ድርጅቱ የሞቱ ሠራተኞቹ የጡረታ እድሜ [60 ዓመት] እስከሚደርስ ደመወዝ፣ የቤትና የሕክምና ጥቅማ ጥቅም እከፍላለሁ ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ለግንባር ቀደም ሠራተኞቹ ልጆች እስከሚመረቁ ድረስ የትምህርት ክፍያ እንደሚከፍል ቃል ገብቷል። ሕንድ ወረርሽኙ ከተከሰተ አንስቶ 300 ሺህ ሰዎችን በቫይረሱ አጥታለች። ባለሙያዎች ግን ቁጥሩ ከዚህም ሊበልጥ እንደሚችል ይናገራሉ። ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ታታ ስቲል በዚህ አስፈሪ ወረርሽኝ ወቅት በተቀጠፉ ውድ ሠራተኞቹ ማዘኑን ገልጾ ከቤተሰቦቻው ጎን እንደሚቆም ገልጿል። በእርግጥ ታታ ስቲል ይህን ያለ የመጀመሪያው ድርጅት አይደለም። ባለፈው ሳምንት የሆስፒታል ግሩፕ ኦዮ ሩምስ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ የሞቱ ሠራተኞቹን ቤተሰቦች በተለያየ መንገድ እንደሚረዳ ገ
amh_Ethi
train
xp3longgenarticle
GEM/xlsum
amharic
148
Title: አስጊነቱ እየጨመረ ያለው ካንሰር\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ላለፉት አስራ አራት ዓመታት በልጃቸው ስም ባቋቋሙት "ማቴዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ"ለታማሚዎች እንክብክካቤ ማቀረብ እንዲሁም ስለበሽታው ግንዛቤ መፍጠርን የህይወታቸው ግብ ከማድረጋቸውም ባለፈ ተቋሙን ማስተዳደር አሁን የሙሉ ጊዜ ሥራቸው ነው። ማቴዎስ ያልተጠበቀና በእርጅና የመጣ ልጅ ቢሆንም አዲስ በረከትን ይዞላቸው እንደመጣ የሚናገሩት አቶ ወንዱ " የማቴዎስ መወለድ ህይወታችንን በጣም ነው የቀየረው" ይላሉ። በሁለት ዓመቱ ህመም ሲሰማው ወደ ህክምና ይዘውት በሄዱበት ወቅት ነው የደም ካንሰር እንዳለበት የተነገራቸው። ህክምናውም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተጀመረ። አቶ ወንዱ እንደሚናገሩት መድሃኒቶቹ ኃገር ውስጥም ስለሌሉ ከውጭ ነበር የሚያስመጡት። ከሁለት ከሶስት ወር በኋላ ታክሞ ይድናል የሚል ተስፋን ቢሰንቁም እያገረሸበት መጣ እናም ከህክምና ማዕከሉም የተሰጣቸውም ምላሽ " ህክምናው እዚህ ሀገር የለም ውጭ አገር ይዛችሁት ሂዱ የሚል ነው" በማለት አቶ ወንዱ ይናገራሉ። በኬሞ ቴራፒው ምክንያት ማቴዎስ ስለተዳከመ አውሮፕላን ላይ መውጣት እንዳልቻለ አቶ ወንዱ ይናገራሉ። "ማቲ የተሻለ ህክምና ማግኘት እየቻለ ህክምናው ኢትዮጵያ ባለመኖሩ ብቻ አይናችን እያየ ከዚህ አለም በሞት ተለየ" ይላሉ። ህክምናው በጣም ውስብስብና አስቸጋሪ እንደነበር የሚናገሩት አቶ ወንዱ በአፉም ደም ይተፋና ተስፋ አስቆራጭም እንደነበር ነው። "ከዚህም የተነሳ ራሴን ለማጥፋት ያሰብኩበት ጊዜ ነበር" ይላሉ። ከአስራ ዓመታት በኋላ የሀገሪቱን የካንሰር የጤና ሽፋን በሚመለከቱበት ጊዜ ለውጥ እንዳለ የሚመለከቱት አቶ ወንድ በመንግሥት ደረጃ የተቋቋመው የአገር አቀፍ የካንሰር መቆጣጠሪያ እቅድ ከሁለት አመት በፊት መውጣቱ እንዲሁም ጎንደር፣ መቀሌና ጅማ ትልልቅ የካንሰር የግንባታ ማእከል እየተሰራ መሆኑ ነው። አሁንም ክፍተቶች እንዳሉ የሚናገሩት አቶ ወንዱ ከነዚህም ውስጥ መድሃኒቶች በበቂ አለመገኘት፣የባለሙያዎች ከፍተኛ እጥረትን ይጠቅሳሉ። በተለይም ከህፃናት የካንሰር ህክምና ጋር ተያይዞ ሶስት የህክምና ባለሙያዎች ብቻ እንዳሉ ይናገራሉ። አሁን በሚሰሩት ስራ ከፍተኛ እርካታ የሚሰማቸው አቶ ወንዱ "ሰው በረዳን ቁጥር ልጃችንን እንደረዳን ወይም ወደ ልጃችን እንደቀረብን ነው የምናስበው" ይላሉ። ካንሰር በኢትዮጵያ በኢትዮጵያካንሰር በርካቶችን በዋናነት ለህልፈት ከሚያበቁ ተላላፊ ያልሆኑ አራት በሽታዎች አንዱ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ይገልፃል። በኢትዮጵያ ምዝገባ ባለመኖሩ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ የሚያዳግት መሆኑን የሚናገሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የካንሰር ህክምና ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ማቴዎስ አሰፋ ናቸው። በአዲስ አበባ ውስጥ ባለ የካንሰር ምዝገባ ወደ 8500 አዳዲስ የካንሰር ህሙማን የሚመጡ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 2/3ኛው ሴቶች መሆናቸውን ዶ/ር ማቴዎስ ይናገራሉ። ከዚህም የተነሳ የዓለም ጤና ድርጅት በየዓመቱ 60ሺ አዳዲስ የካንሰር ህመምተኞች እንደሚኖሩ መጠቆሙን ዶ/ር ማቴዎስ ጨምረው ያስረዳሉ። በሴቶች ላይ 30% የሚሆነው የጡት ካንሰር አንደኛ ደረጃን ሲይዝ፣ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ከዚያ ቀጥሎ ደግሞ የአንጀት ካንሰር እንደሆነ ዶ/ር ማቴዎስ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በወንዶች ላይ ደግሞ በአንደኛ ደረጃ የትልቁ አንጀት ካንሰር፣ በሁለተኛ ደረጃ የፕሮስቴት ካንሰር እና ከተለያዪ እጢዎች የሚነሱ የካንሰር አይነቶችን ይጠቀሳሉ። ዶክተር ማቴዎስ ለካንሰር ከሚያጋልጡ ጉዳዮች መካከል ብለው የሚጠቅሷቸው የእድሜ መጨመር፣ ጤናማ ያልሆነ የአኗኗር ሁኔታ ይህም ብዙ ቅባት ያለው ምግብና ስጋን መመገብ፣ ትምባሆ ማጨስ፣ መጠን ያለው አልኮል...
amh_Ethi
train
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
405
Given the below title and summary of an article, generate a short article or the beginning of a long article to go along with them. Title: ቤተ ክርስቲያኒቱ 'አጭር ቀሚስ ለብሳችሁ ባትመጡ ደስ ይለኛል' አለች\nSummary: በኬንያ ናይሮቢ የምትገኝ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ሴቶች አጫጭር ቀሚሶችን እየለበሳችሁ እየመጣችሁ ተቸግሪያለሁ ብላለች።\nArticle (Max 500 characters):
በኬንያ በስፋት የሚሰራጨው የኬንያ ዴይሊ ኔሽን እንደዘገበው ከሆነ ቤተ ክርስቲያኒቱ 'ሴት ምዕመናን እባካችሁ አለባበሳችሁን ፈሪሀ እግዚአብሔር ያደረበት ብታደርጉ' ስትል ተማጽናለች ብሏል። ቅዱስ ጴጥሮስ ክላቨር ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ናት ይህን መልእክት ያስተላለፈችው። በተለይ መልእክቱ የተለላፈበት መንገድ ለብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል። • "በጎጃም ማርያም ቤተክርስቲያን ለመስጊድ 3ሺ ብር ረድታለች' ተባልኩኝ" ሐጂ ዑመር ኢድሪስ • ኤርትራ፡ ''እናቶች ከህጻናት ልጆቻቸው ጋር ታስረዋል'' ቤተ ክርስቲያኒቱ ይህንን መልእክት ለምእመናኑ ያስተላለፈችው የቤተ ክርስቲያኒቱ መግቢያ በር ላይ የሰሌዳ ማስታወቂያ በመስቀል ጭምር ነው። በዚህ ማስታወቂያ ላይ ሴት ምእመናን ሊለብሷቸው አይገባም ያለቻቸውን 10 ዓይነት አለባበሶችን በፎቶ ጭምር በማስደገፍ ዘርዝራለች። ከነዚህ መሀል አጭሬ
amh_Ethi
train
xp3longgenarticle
GEM/xlsum
amharic
142
Title: ኮሮናቫይረስ፡ አሜሪካ የቫይረሱ መነሻ እንደገና ይጠና ማለቷን ቻይና አወገዘች\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ቻይና፤ ቫይረሱ ከቤተ ሙከራ ነው የወጣው የሚለውን መላ ምት አትቀበልም የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በቫይረሱ መነሻ ላይ የደኅንነት ተቋም ሪፖርት ውጤትን ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ አሜሪካንን 'በፖለቲካ ሴራ እና በሌላ ማሳበብ' ከሷል። ሚኒስቴሩ የኮቪድ-19 እና በቻይናዋ ዉሃን ከተማ ያለው የቫይረስ ምርምር ቤተ ሙከራ ምንም ግንኙነት የላቸውም ብሏል። ኮቪድ-19 ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው እአአ በ2019 መጨረሻ በዉሃን ከተማ ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ168 ሚሊየን በላይ ሰዎች ባቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 3.5 ሚሊየን ገደማ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። የቻይና ባለሥልጣናት መጀመሪያ አካባቢ የኮቪድ-19 በሽታን በዉሃን ከሚገኘው የባሕር ምግቦች መሸጫ ገበያ ቦታ ጋር አያይዘውት ነበር። ይህም ተመራማሪዎች ቫይረሱ ከእንስሳት ወደ ሰው እንደሚተላለፍ ጽንሰ ሃሳብ እንዲይዙ መርቷቸዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ቫይረሱ ከቤተ ሙከራው አፈትልኮ ነው የወጣው ከሚለው ጋር ምንም እንደማይገናኝ አስታውቋል። ድርጅቱ ይህንን ያለው በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የወረርሽኙን መነሻ ለመመርመር ወደ ዉሃን ከተማ ያደረገውን ጉብኝተ ተከትሎ ነው። የጉዞው አካል የነበሩት የዓለም ጤና ድርጅት የቫይረስ ተመራማሪ ማሪዎን ኩፕማንስ የአሜሪካ ባለሥልጣናት መረጃ ካላቸው ሊያጋሩ ይገባል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይሁን እንጅ በቅርቡ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ቫይረሱ ከቻይና ቤተ ሙከራ ምን አልባትም በድንገተኛ ክስተት ሊወጣ እንደሚችል አመላክተዋል። አሁን ውዝግቡ ለምን ተፈጠረ? ረቡዕ ዕለት ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ "ተህዋሱ ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ እንስሳት ጋር ባላቸው ንክኪ መጣ? ወይስ ከቤተ ሙከራ አፈትልኮ የወጣ ቫይረስ ነው?" የሚለውን ጨምሮ ስለቫይረሱ ሪፖርት እንዲቀርብላቸው ጠይቀው ነበር። ፕሬዚደንቱ እንዳሉት የደኅንነት አባላቱ ቫይረሱ ከቤተ ሙከራ ያፈተለከ ነው በሚለው እና ከእንስሳት ወደ ሰው የተላለፈ ነው በሚሉት ሁለት መላ ምቶች ተከፋፍለዋል። የትኛው ሊሆን እንደሚችል ግን በግልጽ የሚያሳይ በቂ መረጃ እንዳላገኙ ፕሬዝደንቱ አምነዋል። በመሆኑም አሁን ላይ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ተቋማት አቅማቸውን በእጥፍ ጨምረው መረጃዎችን እንዲሰበስቡና እንዲተነትኑ ጆ ባይደን ትዕዛዝ ሰጥተዋል። ሐሙስ ዕለት ፕሬዚደንት ባይደን የማያውቁት ነገር ከሌለ በስተቀር ያላቸውን ሪፖርት ይፋ እንደሚያደርጉ ማቀዳቸውን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ የቫይረሱ መነሻ ላይ የተሻለ ግንዛቤ ለመያዝ አሜሪካና ሌሎች አገራት የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚደግፉ ድምጻቸውን አስምተዋል። ይሁን እንጅ ረቡዕ ዕለት የተሰጠው መግለጫ የቻይና ባለሥልጣናትን አስቆጥቷል። ቻይና፤ ቫይረሱ ከቤተ ሙከራ ነው የወጣው የሚለውን መላ ምት አትቀበልም። የአገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን "ይህ የሚያሳየው አሜሪካ ስለ እውነት ግድ እንደሌላትና ስለቫይረሱ መነሻ ለሚደረግ ሳይንሳዊ ጥናት ፍላጎት እንደሌላት ነው" ብለዋል። "ዓላማቸው ወረርሽኙን ማግለልን ለመፍጠር፣ ለፖለቲካ ሴራ እና አንዱ በአንዱ ላይ ጣት እንዲቀስር መጠቀም ነው። ለሳይንስ ፣ ለሰዎች ሕይወት እና ወረርሽኙን ለመዋጋት ለተቀናጀ ጥረት ውጤታማነት ክብር አልሰጡም" ብለዋል። የአሜሪካ የደኅንነት ተቋማት የተሳሳተን መረጃ በማሰራጨት "ጥቁር ታሪክ " ነው ያላቸው ሲሉም ቃል አቀባዩ አክለዋል። በአሜሪካ የቻይና ኤምባሲ ባወጣው መግለጫም የባይደንን ትዕዛዝ በቀጥታ ባይጠቅስም "የስም...
amh_Ethi
validation
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
413
Given the below title and summary of an article, generate a short article or the beginning of a long article to go along with them. Title: የቺቦክ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ የቦኮ ሃራም እገታ የጽሑፍ ቅጂዎች\nSummary: ሞተር ሊሰርቁ መጥተው የነበሩት የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች የፈለጉትን ሲያጡ የነበሩትን ወደ 200 ገደማ ልጃገረዶች አገተው ወደ ሳምቢሳ ይዘዋቸው ለሜሄድ ወሰኑ... ከዚያስ? \nArticle (Max 500 characters):
አንዳንዶቹ ሴቶች በታጣቂዎቹ መኪኖች ላይ ተጭነው ብዙዎቹ ደግሞ ሽጉጥ ተደቅኖባቸው ብዙ ኪሎሜትሮችን ከተራመዱ በኃላ የጭነት መኪኖች መጥተው አፈሷቸው። ማስታወሻ ደብተሮቹን ማን ጻፋቸው? የእገታውን ማስታወሻ የመጀመሪያ ክፍል ለማግኘት ይህን ይጫኑ። ወደ ቦኮ ሃራም መደበቂያ ደን እያመሩ ሳለ አንዳንድ ተማሪዎች ከጭነት መኪኖቹ እየዘለሉ መውረድ ጀመሩ ግን አንደኛዋ ልጅ ለአንደኛው አጋች ነገረችው። ድንገት ብቻዋን ትቀራለች ብላ ፈርታ ወይም ሥልጣንን ለማክበር ወይም ደግሞ በስቃይ ብቸኛ ላለመሆን ሊሆን ይችላል። "መኪናው ውስጥ የነበረችው አንደኛዋ ልጅ 'ሹፌር አንዳንድ ሴቶች ለማምለጥ እየዘለሉ ነው' አለችው። ሹፌሩም በሩን ከፈተና በእጅ መብራት ቢፈልጋቸውም ማንንም ማየት አልቻለም። ስለዚህ አንድ ቦታ ሳይንቀሳቀሱ መቀመጥ እንዳለባቸው ተናገሩ። ካሁን ወዲህ እሷም ሆነች ማንም ሲዘል
amh_Ethi
validation
xp3longgenarticle
GEM/xlsum
amharic
158