query_id
stringlengths
32
32
passage_id
stringlengths
32
32
query
stringlengths
2
300
passage
stringlengths
78
8.98k
category
stringclasses
7 values
link
stringlengths
28
740
⌀
negative_passages
listlengths
5
5
2377f2f27ff1b9c0ebc3ff81ed590acc
51da772166285795b33f37e5c94534e9
የ3ሺ ሜትር መሰናክል የመጪው ዘመን ተስፋ
ያለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በእርግጥም አንድ እውነት በዓለም አትሌቲክስ ልቆ ያንጸባረቀበት ወቅት ነበር። በሦስት ሺ ሜትር መሰናክል ውድድር ለዓመታት ወደ አንድ ወገን ያደላው የበላይነትም ባልታሰበ አቅጣጫ የተጓዘበት ሆኖ ይታወሳል። በበርካታ ዓመታት የአትሌቲክስ ታሪክ ውስጥ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቶች ዓለምን ያስደመሙትና በውጤት ያሸበረቁት በመምና ጎዳና ላይ የረጅም ርቀት ሩጫ ነበር። ለኢትዮጵያ ቀንደኛ ተፎካካሪ ከሆኑት ሃገራት መካከል ቀዳሚዋ ኬንያ በተለይም በ3ሺ ሜትር መሰናክል ሩጫ እስካለፈው ዓመት ድረስ በዓለም ውጤታማና ከሌሎች ተፎካካሪዎቿ ፍፁም የበላይ ነበረች። እአአ በ2019 ግን በዚህ ርቀት ኢትዮጵያም ተስፋ ያላት ሃገር መሆኗን በተለያዩ ውድድሮች ማረጋገጥ እንደተቻለ የዓለም አትሌቲክስ ሰሞኑን በድረ ገጹ ያሰፈረው ሰፊ ሐተታ ይጠቁማል። ለኢትዮጵያ በታላቅ የውድድር መድረክ በርቀቱ የመጀመሪያው ድል የተመዘገበው በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ሲሆን፤ በኳታር ዶሃ በተካሄደው ውድድር ለሜቻ ግርማ በጥቂት ማይክሮ ሰከንዶች ተቀድሞ የብር ሜዳሊያ በማጥለቅ ታሪክ ማስመዝገብ ችሏል። በወቅቱ አትሌቱ 8:01.36 የሆነ ሰዓት ሲያስመዘግብ በኬንያዊው ኮንሴሉስ ኪፕሩቶ የተቀደመበት አጋጣሚ እጅግ የሚያስቆጭ ሆኖ ይታወሳል። በርቀቱ ለኢትዮጵያ ተስፋ ሰጪ የሆነው ሌላኛው ድል ደግሞ በውድድር ዓመቱ ዳይመንድ ሊግ ላይ ነበር የተመዘገበው። ወጣቱ አትሌት ጌትነት ዋለ በርቀቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የዳይመንድ ሊግ አጠቃላይ አሸናፊ ከሆኑ አስር የተለያዩ ርቀት ተወዳዳሪ አትሌቶች መካከል አንዱ ሊሆን ችሏል። እነዚህ በዓለም ታላላቅ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያን በአዲስ ርቀት ተስፋ እንድታደርግ ያስቻሉ አትሌቶች የሚሰለጥኑት በአንድ አሰልጣኝ ስር ነው። ይህ አሰልጣኛቸውም ብሄራዊ ቡድንን የሚወክሉ በርካታ አትሌቶችን በማፍራት ላይ የሚገኘው ተሾመ ከበደ ነው። በተለይ ጌትነት በ3ሺ ሜትር መሰናክል በዓመቱ ያሳየው ብቃት እጅግ አበረታች በመሆኑ ድረገጹ ትኩረት የሰጠው ሲሆን፤ ቀጣዩ የርቀቱ ኮከብ እንደሚሆንም ነው ተስፋውን የገለጸው። አትሌት ጌትነተ ዋለ በደቡብ ምሥራቅ የሃገሪቷ አካባቢ በምትገኘው ሰቀላ የተባለ ስፍራ ስምንት ልጆች ካሏቸው ቤተሰብ መካከል የተገኘ ፍሬ ነው። ዛሬ አትሌት ለመሆኑ ምክንያቱ ደግሞ በየዕለቱ በጠዋት እየተነሳ ከቤቱ በአራት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ትምህርት ቤቱ የሚያደርገው ሩጫ ነበር። ይህ ልምድም ትምህርት ቤት ውስጥ ለሚካሄዱ የሩጫ ውድድሮች ሲያሳጨው፤ በ13 ዓመቱ በ1 ሺ 500 እና 3 ሺ ሜትር አሸናፊ መሆንም ችሎ ነበር። ይህ ሁኔታ ለቀጣይ የአትሌቲክስ ህይወቱ መንገድ የጠረገለትን አጋጣሚ የፈጠረም ነበር። ይህም ጌትነት በትምህርት ቤቱ ተገኝቶ ብቃቱን ለተመለከተው የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ አሰልጣኝ እይታ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። ጌትነት ከዚያ በኋላ የሆነውን ሲያስታውስም ‹‹አሰልጣኙ በእኔ ላይ ፍላጎት ስላሳደረ ቤተሰቦቼን አስፈቅጄና የትምህርት ማስረጃዎቼን ይዤ ወደ አዲስ አበባ አብሬው እንድሄድ ጠየቀኝ›› ይላል። ያ አሰልጣኝ ዛሬም ድረስ በስኬቱ ከጎኑ ያለው ተሾመ ሲሆን፤ ለዓመታት በነበራቸው የአብሮነት ቆይታ አትሌቱ በመሰናክል የተሻለ ብቃት እንዳለው መረዳት በመቻሉ ወደዚያው እንዲገባ አድርጓል። እአአ 2016 በተካሄደው ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ቻምፒዮና ደግሞ የአሰልጣኙ ጥረትና የጌትነት ችሎታ በእርግጥም ለስፖርት ቤተሰቡ በግልጽ ሊታይ የቻለበት ነው። ይህ ተስፈኛ አትሌት በፖላንድ ባይዳጎዝ ከተማ በተካሄደ ዓለም አቀፍ ውድድር ተሳትፎ የነሐስ ሜዳሊያ ቢያገኝም፤ በወቅቱ ብቃቱ ያን ያህል ትኩረት ያገኘ አልነበረም። ይሁን እንጂ ሁለተኛ ከወጣው አትሌት በ16 ሰከንዶች የዘገየውና 8፡22.83 የሆነ ሰዓቱ የግሉ ፈጣን ሰዓት ነበር። በወቅቱ የነበረው ብቃት በአትሌቲክስ ቤተሰቡ ዘንድ እምብዛም ትኩረት ባያገኝም በሪዮ ኦሊምፒክ ግን ለብሄራዊ ቡድን ለመመረጥ ዕድሉን አስገኝቶለታል። ወጣቱ አትሌት በታላቁ መድረክ ሃገሩን በመወከሉ ደስ ቢሰኝም በበዛ የጭንቀት ስሜት በመዋጡ እንዳሰበው ሜዳሊያ ማግኘት ሳይችል ቀረ። በባይዳጎዝ በተካሄደው የወጣቶች ቻምፒዮና ብቃቱን ለተረዳው ማናጀሩ ግን ይህ ምንም ማለት አልነበረም። ማናጀሩ ሁሴን ማቄ ‹‹ጌትነት ትልቅ ልብ ያለው አትሌት ነው። በውድድሩ ላይ ሁለት ጊዜ ወድቆ ከሜዳሊያ ሰንጠረዡ ሳይወጣ ለብር ሜዳሊያ በተጠጋ ውጤት ማጠናቀቅ መቻሉ አስደናቂ ነው›› ሲል ይገልጸዋል። ጌትነት በቀጣዩ ዓመትም ውጤታማነቱ እንደቀጠለ ነበር። በሃገር አቀፉ ቻምፒዮና አሸናፊ ከሆነም በኋላ በሄንግሎ በተካሄደው ከ20 ዓመት በታች ውድድር በብሄራዊ ቡድኑ ተካተተ። ውድድሩንም 8፡12.28 በሆነ ሰዓት የክብረወሰን ባለቤት በመሆን አጠናቀቀ። ይኸውም በዚያው ዓመት (እአአ 2017) በተካሄደው የለንደን አትሌቲክስ ቻምፒዮና ሃገሩን እንዲወክል አደረገው፤ በ17 ዓመቱም ልምድ ካላቸው አትሌቶች ጋር ተፎካክሮ ዘጠነኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀ። እአአ በ2018 የውድድር ዓመት በፊንላንድ የወጣቶች ቻምፒዮና ተሳታፊ ቢሆንም፤ ባልተጠበቀ መልኩ በሌላኛው የሃገሩ ልጅ ተቀድሞ የነሐስ ሜዳሊያ ነበር ያጠለቀው። ይህ ተደጋጋሚ የውድድር ልምድም እአአ 2019 የውድድር ዓመት በሚገባ እንዲዘጋጅና ያለውን ብቃት በተገቢ መንገድ እንዲያሳይ አደረገው። የስልጠና ጫናውን በመጨመርም በሳምንት ከ100-120 ኪሎ ሜትር በመሸፈን ልምምዱን ይሠራም ነበር። ከቡድን አጋሩ ለሜቻ ግርማ ጋር ጠንካራ ልምምድ በመሥራታቸውም ሁለቱም የግል ውጤታቸውን ማየትና ለሃገራቸውም ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል። ጌትነት ከዓለም አትሌቲክስ ድረገጽ ጋር በነበረው ቆይታም ‹‹ከለሜቻ ጋር በአካዳሚው አብረን የምንኖር ጓደኛሞች ነን። በልምምድ ጊዜ ጠንክረን የምንሠራ በመሆናችን የሥራችንን ፍሬ ልናገኝ ችለናል›› ይላል። የዳይመንድ ሊግ ውድድሮቹን ሲያስታውስም ‹‹ራባት በጭራሽ የሚዘነጋ አይደለም፤ ምክንያቱም ከዚያ ቀደም የምሠራቸውን ስህተቶች ያረምኩበት ውድድር ነው። በቅድሚያ ሩጫውን ለመቆጣጠር ቻልኩ ከዚያም በመጨረሻው ዙር የመጨረሻውን ውሃ በጥንቃቄ በመዝለል ቀዳሚ ሆኜ በአሸናፊነት አጠናቀቅኩ›› ሲል ውጤታማውን ውድድር መለስ ብሎ ያስታውሳል። በውድድሩ ያስመዘገበው ሰዓትም የኢትዮጵያ የርቀቱ ክብረወሰንና በዳይመንድ ሊጉ ሦስተኛው ፈጣን ሰዓት ነበር። አሸናፊ ከሆነም በኋላ ‹‹አሸናፊነቴ ለኢትዮጵያ ትልቅ ድል ነው፤ ምክንያቱም ከዚህ ቀደም በዳይመንድ ሊግ የ3ሺ መሰናክል ውድድር አሸናፊ የሆነ አትሌት አልነበረም። በመሆኑም በራስ መተማመን ሰጥቶኛል፤ ወደፊት ደግሞ ከስምንት ደቂቃ በታች መሮጥ እንደምችል ፍንጭ ያገኘሁበት ነው›› በማለት ስሜቱን ያጋራል። በዓለም ቻምፒዮናው ተሳታፊ የነበረው ጌትነት የአሸናፊነት ቅድመ ግምት ካገኙት አትሌቶች መካከል ቢሆንም፤ ያጠናቀቀው በሜዳሊያ ሰንጠረዡ የቅርብ ርቀት ላይ አራተኛ ሆኖ ነበር። በዓመቱ በተካሄደው የቤት ውስጥ የዙር ቻምፒዮና ተሳትፎውም ከሦስቱ ውድድሮች በሁለቱ አሸናፊ መሆን ችሏል። በብራሰልስ በነበረው የዳይመንድ ሊጉ ማጠናቀቂያ ውድድር ያሳየው ብቃትና አጨራረስ ለዚህ የውድድር ዓመት ይደገም ይሆን በሚል የስፖርቱ ቤተሰብ እንዲጠብቀው ያደረገም ነበር። የእርሱም እቅድ በዚህ ዓመት ሊካሄድ በታሰበው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በርቀቱ ታሪክ መሥራት ነበር። ሆኖም በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮሮና (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ ምክንያት እንደ ውድድሩ ሁሉ ብቃቱም በቀጠሮ ለሚቀጥለው ዓመት ሊራዘም ችሏል። ሆኖም በቤቱ ውስጥ ሆኖ በሳምንት ሦስት ቀናት ልምምድ ማድረጉን አላቋረጠም። ‹‹በብቃቴ ለመቆየት ማድረግ ያለብኝን እያደረኩ ነው። በቅርቡ ወደ ውድድር እንመለሳለን የሚል ተስፋም አለኝ›› ሲል ተስፈኛው አትሌት ይናገራል። በዚህ ወቅትም ኑሮውን ካደረገባት አዲስ አበባ ወደ ተወለደበት አካባቢ በማቅናት ቤተሰቡን በመርዳት ላይ ይገኛል። ውድድሩ በተመለሰ ጊዜም በ3ሺ ሜትር መሰናክል ኢትዮጵያዊያን ለሌሎች ተፎካካሪ አገራት አትሌቶች ፈተና እንደሚሆኑ እምነቱ ነው። ‹‹በመሰናክል ጠንክረን በመሥራት መልካም ውጤት ማስመዝገብ በመቻላችን ደስተኞች ነን›› የሚለው ጌትነት ይህም የበላይነቱን ለረጅም ጊዜ ይዘውት ለቆዩት ኬንያዊያን ማስጠንቀቂያ መሆኑን ድረ ገጹ በሰፊ ሐተታው መደምደሚያ አስምሮበታል። አዲስ ዘመን ሰኔ 15/2012ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=34859
[ { "passage": "ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአትሌቲክሱ ዓለም በተለይም በመካከለኛና ረጅም ርቀቶች ትኩረት እያገኘ የመጣው ወጣት አትሌት ሰለሞን ባረጋ የስኬት ማማ ላይ ለመቆም ብዙ ጊዜ አልወሰደ በትም። ከዕድሜው ከፍ ብሎ ከታላላቆቹ ጋር በመፎካከርም በተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ለማመን የሚከብዱ ድሎችን አጣጥሟል። ይህም በረጅም ርቀት በተለይም በአምስት ሺ ሜትር ኢትዮጵያ ከነ ቀነኒሳ በቀለ ወዲህ ማግኘት ያልቻለችውን ሁነኛ ተተኪ አትሌት በቅርቡ ልታገኝ እንደምትችል ፍንጭ የሰጠ መሆኑን የስፖርቱ ባለሙያዎች ሲናገሩ ይደመጣል።በዳይመንድ ሊግ ተሳትፎው ገና በሁለተኛ ዓመቱ የአምስት ሺ ሜትር አጠቃላይ አሸናፊ መሆን የቻለው ሰለሞን ዕድሜው አስራ ሰባት ዓመት ቢሆንም በልምድ የሚበልጡትን አትሌቶች የሚያስንቅ የሩጫ ተሰጥኦ እንዳለው በተለያዩ አጋጣሚዎች ማሳየት ችሏል። 2018 የውድድር ዓመትም ስኬታማ የሆነበት ነው ማለት ይቻላል። ይህም እ.ኤ.አ ከ2011 ወዲህ አንድም ኢትዮጵያዊ አትሌት በዓለም የዓመቱ ኮከብ አትሌቶች ምርጫ ከአስሮቹ እጩዎች ውስጥ እንኳን ባልተካተቱበት ሁኔታ ሰለሞን በወጣቶች ዘርፍ ከመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች መካከል አንዱ እንዲሆን አስችሎታል። ሽልማቱን የማሸነፍ ሰፊ ዕድል እንደሚኖረውም ይጠበቃል።የደቡብ ፖሊሱ ክለብ አትሌት የሆነው ሰለሞን ባረጋ እያስመዘገበ ላለው ስኬት ከሁለት ወራት በፊት ክለቡ የኢንስፔክተርነት ማዕረግ የሰጠው ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት እያሳየ ያለው አስደናቂ ብቃት ወደ ፊት ተስፋ እንዲጣልበት አድርጓል። በ2018 የውድድር ዓመት የአምስት ሺ ሜትር አጠቃላይ የዳይመንድ ሊግ አሸናፊ ሲሆን በርቀቱ ከሃያ ዓመት በታች የዓለም ክብረወሰንን 12፡43፡02 በሆነ ሰዓት ከመጨበጡ ባሻገር እ.ኤ.አ 2005 ላይ ቀነኒሳ በቀለ በርቀቱ ካስመዘገበው ሰዓት ወዲህ ፈጣን ሰዓት መሆኑ ይታወሳል። ሰለሞን በዓለም ከሃያ ዓመት በታች ቻምፒዮናና በአፍሪካ አትሌቲክስ ቻምፒዮናም በርቀቱ አራተኛ ደረጃን ይዞ በመፈፀም በውድድር ዓመቱ በርካታ ስኬቶችን አግኝቷል። ይህንንም በተመለከተ ከዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ድረ ገፅ ጋር ሰሞኑን ቃለ መጠይቅ አድርጓል።የ2018 የውድድር ዓመት ልምምዱን ሲጀምር ከውድድሮች ይልቅ ልምምዱ ላይ ትኩረት አድርጎ በተለየ መንገድ ለመሥራት ከአሰልጣኞቹ ጋር እንደተስማማ የሚናገረው ሰለሞን በውድድር ዓመቱ የተለየ ብቃት ለማሳየቱ ምክኒያቱ ይህ መሆኑን ይናገራል።ሰለሞን በውድድር ዓመቱ በቤት ውስጥና ከቤት ውጭ ውድድሮች አስደናቂ ብቃት ቢያሳይም በብራሰልስ ዳይመንድ ሊግ ፈጣን የተባለውን 12፡43፡02 ሰዓት ለመሮጥ እንዳላሰበ ያብራራል። ይሁን እንጂ ይህን ጣፋጭ ድል የግሉ ካደረገ በኋላ ሰዓቱን ሲመለከተው ለማመን ተቸግሮ እንደነበር አልሸሸገም። «የዳይመንድ ሊግ አጠቃላይ አሸናፊ መሆን ለእኔ አስገራሚ ስኬት ነው፤ ይህን ሰዓት ማስመዝገብ ደግሞ ፈፅሞ ሊታመን የማይችል ነበር» ያለው ወጣቱ አትሌት ይህ የሩጫ ዘመኑ ሁሉ ትልቅ ስኬት እንደሆነ ይናገራል።ቀደም ሲል በአምስት ሺ ሜትር ከነበረው የራሱ ምርጥ ሰዓት 12፡55 በታች መሮጥ የሁል ጊዜም ፍላጎቱ እንደሆነ የሚናገረው ሰለሞን 12፡43 በሆነ ሰዓት ርቀቱን ማጠናቀቅ መቻሉ ሁሉንም ነገር እንደቀየረው ያስረዳል። ይህም ከአስራ አምስት ዓመታት በላይ በቀነኒሳ በቀለ ተይዞ የቆየውን የአምስት ሺ ሜትር የዓለም ክብረወሰን አንድ ቀን በእጁ ለማስገባት ጠንክሮ እንዲሠራ እንዳነሳሳው ያብራራል።ከ18 እና ከ2o ዓመት በታች የዓለም ወጣቶች ቻምፒዮና አሸናፊ መሆን የቻለው ሰለሞን ባለፈው የለንደን የዓለም ቻምፒዮና በቀጥታ ወደ ትልቅ ደረጃ ተሸጋግሮ የኢትዮጵያውያንን የአምስት ሺ ሜትር ስብስብ ምን ያህል አስፈሪ እንዳደረገው ይታወሳል፡፡በሁለት ኦሊምፒኮችና በሦስት የዓለም ቻምፒዮናዎች ኢትዮጵያ በሞ ፋራ የተነጠቀችውን የአምስት ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ለንደን ላይ በሙክታር ኢድሪስ አማካኝነት ስታስመልስ የሰለሞን ሚና ቁልፍ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በበርሚንግሃሙ የዓለም ቻምፒዮና ዮሚፍ ወርቅ ባጠለቀበት ውድድር ሰለሞን የብር ሜዳሊያ ባለቤት በመሆን ያሳየው ድንቅ አቋም በቀጣይ ዓለም አቀፍ መድረኮች ከመካከለኛ እስከ ረጅም ርቀቶች ኢትዮጵያውያን የበላይነታቸው ከወዲሁ ጎህ እየቀደደ እንደሚገኝ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው። ", "passage_id": "bd110c2c1109e57dd88bc098cb65051a" }, { "passage": "ቦጋለ አበበበኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋት ለበርካታ ወራት ተቋርጠው የቆዩ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች ካለፈው ሐምሌ መጨረሻ ጀምሮ በሂደት ወደ መደበኛ መርሃግብራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ውድድሮች በተመለሱበት ጥቂት ወራትም በተለይም የረጅም ርቀት የዓለም ክብረወሰኖች ለማመን በሚቸግር መልኩ ሲሰበሩ እየተስተዋለ ይገኛል፡፡ ይህም የስፖርቱን አፍቃሪዎች ከማነጋገሩ ባሻገር ተንታኞች ጭምር ግራ እንዲጋቡ ያደረገ ክስተት ሆኗል፡፡ በተለይም የዓለም ግማሽ ማራቶን ክብረወሰን ከወረርሽኙ በፊትም ቢሆን ከሌሎች ርቀቶች በተለየ በሁለቱም ፆታ በተደጋጋሚ ሲሰበር መስተዋሉ አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡ የዓለም ግማሽ ማራቶን ክብረወሰን በዓለም አትሌቲክስ እኤአ ከ2004 አንስቶ እውቅና እየተሰጠው ከመጣ ወዲህ በወንዶች አምስትና በሴቶች ስድስት የዓለም ክብረወሰኖች ተመዝግበዋል፡፡ ከዚህ ዓመት በፊት በርቀቱ የተመዘገቡ ሰዓቶች በዓለም አትሌቲክስ ‹‹የዓለም ፈጣን ሰዓት›› በሚል ይታወቅ ነበር፡፡ የወንዶች ግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረወሰን ባለፈው እሁድ በቫሌንሲያ የተመዘገበ ሲሆን ኬንያዊው አትሌት ኪቢዎት ኬንዲ 57፡32 በሆነ ሰዓት የክብረወሰኑ ባለቤት ሆኗል::የሴቶቹ ደግሞ ባለፈው የካቲት በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የራስ አል ኪማህ ግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አባብል የሻነህ በ1፡04፡31 በሆነ ሰዓት ያስመዘገበችው ነው፡፡ ይህም በጥቅምት 2017 ኬንያዊቷ ጆይስሊን ጂፕኮስጌ በቫሌንሲያ ግማሽ ማራቶን ካስመዘገበችው የቀድሞው የዓለም ክብረወሰን በሃያ ሰከንድ የተሻለ ነበር፡፡ በመስከረም 2019 ሌላኛዋ  ኬንያዊት\nብሪጊድ ኮስጌ በኒውካስትል ታላቁ\nሩጫ 64፡28 በሆነ ሰዓት\nከቀድሞው ክብረወሰን በሃያ ሦስት\nሰከንድ የተሻለ ፈጣን ሰዓት\nብታስመዘግብም የዓለም አትሌቲክስ ለክብረወሰኑ\nእውቅና አልሰጠውም። እኤአ ከ2011 ጀምሮ\nየዓለም አትሌቲክስ የሴቶች ግማሽ\nማራቶን ክብረወሰኖችን በሴትና በወንድ አሯሯጭ\nየተመዘገቡ ብሎ በሁለት ከፍሏቸዋል።  በሴት\nአሯሯጮች የተመዘገበው የርቀቱ ክብረወሰንም በኬንያዊቷ\nአትሌት ፔርስ ጂፕቺርቺር 1፡05፡16 በሆነ ሰዓት\nከወር በፊት በፖላንድ ጊዲኒያ\nየዓለም ግማሽ ማራቶን ቻምፒዮና\nየተመዘገበ ነው። ባለፈው ሐምሌ መጨረሻ ለአስራ ስድስት ዓመታት ያልተደፈረው የቀነኒሳ በቀለ የአምስት ሺ ሜትር ክብረወሰን በዩጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቺፕቴጌ ሞናኮ ላይ ከተሰበረ ወዲህ የዓለም ክብረወሰኖች በተለይም በረጅም ርቀት ውድድሮች እንደልብ የሚሰበሩ ሆነዋል። ከዩጋዳዊው ያልተጠበቀ ክብረወሰን በኋላ አንድ ወር ባልሞላ ልዩነት ትውልደ ሶማሊያዊው የእንግሊዝ አትሌት ሞ ፋራህ እኤአ 2007 ላይ በጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ተይዞ የቆየው ‹የአንድ ሰዓት ውድድር› የዓለም ክብረወሰን ብራሰልስ ዳይመንድ ሊግ ላይ ከ21፡330 ወደ 21፡285 ተሻሽሏል። በተመሳሳይ ርቀት እንዲሁም በተመሳሳይ ቀንና ውድድር በኢትዮጵያዊቷ አትሌት ድሬ ቱኔ 18፡930 ተይዞ የቆየው የዓለም ክብረወሰን በትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድስ አትሌት ሲፈን ሃሰን 18፡517 በሆነ ሰዓት ተሻሽሏል። የሁለቱ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የአንድ ሰዓት ውድድር የዓለም ክብረወሰኖች በተሰበሩ በአንድ ወር ልዩነት ዩጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቺፕቴጌ ለአስራ አምስት ዓመታት ያልተደፈረውን የቀነኒሳ በቀለ የአስር ሺ ሜትር ክብረወሰን በ6፡53 ሰከንድ መስበር ችሏል። በተመሳሳይ ቀን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ በሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌትና የረጅም ርቀት ንግስት ጥሩነሽ ዲባባ ለአስራ ሁለት ዓመታት ተይዞ ሳይሰበር የቆየውን የአምስት ሺ ሜትር ክብረወሰን 14፡06 በሆነ ሰዓት ሰብራዋለች። ኬንያውያን አትሌቶችም ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ ባንሰራራው የአትሌቲክስ ውድድር የክብረወሰን ተቋዳሽ ናቸው። ለዚህም በዓለም ግማሽ ማራቶን በአርባ ሁለት ቀናት ልዩነት ሁለት የዓለም ክብረወሰኖችን የጨበጠችው ኬንያዊቷ ፔስር ጂፕቺርቺር ትክክለኛ ማሳይ ናት። መስከረም ላይ በፓራጓይ ግማሽ ማራቶን የሴቶችን ብቻ የርቀቱን የዓለም ክብረወሰን በ1፡05፡24 ሰዓት ያሻሻለችው ኬንያዊት አትሌት ከአርባ ሁለት ቀናት በኋላ በፖላንድ ጊዲኒያ የዓለም ግማሽ ማራቶን ቻምፒዮና የራሷን ክብረወሰን በአስራ ስምንት ሰከንድ ማሻሻል ችላለች። እነዚህ ሁሉ ክብረወሰኖች ሲሰባበሩና አትሌቶች በተለየ መልኩ አስደናቂ ብቃት ሲያሳዩ አብዛኛው የስፖርት ቤተሰብ ሁለት ነገሮችን ጠርጥሯል። ይህም በወረርሽኙ ምክንያት አትሌቶች ለረጅም ጊዜ ከውድድር በመራቃቸው ሰፊ የዝግጅት ጊዜ በማግኘት ወደ ውድድር ሲመለሱ ምርጥ ብቃት ሊኖራቸው እንደቻለና በነዚያ የረፍት ጊዜያት በጉዳት ላይ የነበሩ አትሌቶች በበቂ ሁኔታ ማገገም በመቻላቸው እንደሆነ ይታሰባል። ስፖርቱን በጥልቀት የሚመለከቱ በርካታ ተንታኞች ግን ከዚህም የበለጡ ገፊ ምክንያቶች ከክብረወሰኖቹ መሰባበር ጀርባ እንዳሉ ያምናሉ። የልምምድ ስነልቦናና ሂደት በወረርሽኙ ምክንያት እየተለወጠ መምጣቱ ለክብረወሰኖቹ መሻሻል አንድ ምክንያት ተደርጎ ይወሰዳል። ይህም የወረርሽኙ ስጋት ቀደም ብሎ አትሌቶች በርከት ብለው በአንድ አሰልጣኝና በአንድ ካምፕ ውስጥ ሆነው የሚያደርጉትን የተለመደ ዝግጅት ወደ ጎን ትተው በተናጠል በሚመቻቸው ስፍራና በቤታቸው ሆነው እንዲዘጋጁ እድል መስጠቱ ነው። ይህ አጋጣሚ አትሌቶች አንዱ አንዱን ሳይጠብቅ በራሳቸው መርሃግብር መሰረት ወጥ በሆነ መልኩ እስከ አቅማቸው ጥግ ድረስ እንዲዘጋጁ ያስቻላቸው ሲሆን በስነልቦናውም ረገድ ጠንካራ እንዲሆኑ አድርጓል። ለዚህም ከወረርሽኙ በኋላ ክብረወሰኖችን ያሻሻሉ አትሌቶች ቀደም ሲል ይከተሉት የነበረው የልምምድ መልክ በወረርሽኙ ሳቢያ መቀየሩ ለክብረወሰኖች መሻሻል ቁልፍ ሚና እንዳለው የሚያስቀምጡ ባለሙያዎች በርካታ ናቸው። በሌላ መልኩ አትሌቶች በወረርሽኝ ምክንያት ውድድሮች ቢቆሙም የሆነ ጊዜ ላይ እንደሚቀጥሉ አውቀው ዝግጅታቸውን ሳያቋርጡ ተግተው መስራታቸው የክብረወሰን ባለቤት እንዳደረጋቸው ይታመናል። አትሌቶች ወረርሽኙ የጤና ስጋት ቢሆንም መጥፎን አጋጣሚ ወደ ጥሩ ለውጠው ተጠቅመዋል። አቋማቸው እንዳይወርድ በመጠንቀቅ መዘጋጀታቸው ኋላ ላይ ለስኬት አብቅቷቸዋል። በተለይም እቤት የመቀመጥ አስገዳጅ ሁኔታው ቀደም ሲል የነበረባቸውን የተጣበበ የልምምድና የውድድር ጫና በማስቀረቱ በበቂ ሁኔታ እንዲዘጋጁ በር ስለከፈተላቸው በደህናው ጊዜ ማሳካት ያልቻሉትን ክብረወሰን እንዲያሳኩ አድርጓቸዋል። ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ መልካም አጋጣሚዎች እንዳሉ ሆነው የስፖርት ቴክኖሎጂ እየዘመነ መምጣት ለተመዘገቡት ክብረወሰኖች የአንበሳውን ድርሻ እንደሚይዝም ዓለም አቀፍ የስፖርቱ ምሁራን የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ባለፉት ጥቂት ወራት ሲመዘገቡ ያየናቸው በርካታ ክብረወሰኖች አትሌቶች የሚያስመዘግቧቸው ሰዓቶች ላይ ሰፊ ልዩነት በሚፈጥሩ ዘመናዊ የመሮጫ ጫማ እንዲሁም አሯሯጮች በተለይም በመም ውድድሮች ከሰው ይልቅ ቴክኖሎጂ ሆኖ አትሌቶችን እስከ መጨረሻ ድረስ በሚፈለገው ደረጃ በማገዝ የተመዘገቡ ናቸው። ግዙፉ የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያ ናይኪ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሚያቀርባቸው የመሮጫ ጫማዎች ቀደም ሲል የዓለም ክብረወሰን ሲመዘገብባቸው ከቆዩ የመሮጫ ጫማዎች አንፃር በአትሌቶች ፍጥነት ላይ የጎላ ተፅዕኖ እንዳላቸው አትሌቶችም ይሁን የስፖርት ቤተሰቡ ይስማማሉ። ከዚህ በላይ የጥሩነሽ ዲባባ የአምስት ሺ ሜትር ክብረወሰን በሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ለተሰንበት ግደይ እና የቀነኒሳ በቀለ የአምስትና አስር ሺ ሜትር ክብረወሰኖች በዩጋዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቺፕቴጌ ሲሰበሩ አትሌቶቹን በአሯሯጭነት ያገዛቸው በመሮጫው መም ዙሪያ የተገጠመው መብራት(Wave-lights) እንደነበር ይታወቃል። ይህ ቴክኖሎጂ አትሌቶቹ በምን ያህል ፍጥነት እያንዳንዱን ዙር ሮጠው ክብረወሰን እንደሚጨብጡ አስልቶ በማሯሯጥ እስከ መጨረሻ ድረስ ደግፏቸዋል። አሯሯጭ በአትሌቲክሱ ዓለም ክብረወሰኖችን ለማስመዝገብ ወሳኙ ነገር እንደሆነ ይታወቃል። አንዳንድ ጊዜ ሴት አትሌቶች በወንድ አሯሯጮች ታግዘውም አሯሯጮች በሚፈለገው ፍጥነት መጓዝ ካልቻሉ ክብረወሰን የማይሰበርበት አጋጣሚ ጥቂት እንዳልሆነ ይታወቃል። አሯሯጩ ቴክኖሎጂ ሆኖ እስከ መጨረሻ ድረስ ወጥ በሆነ ስሌት አትሌቶችን ሲያግዝ ግን የተለየ እንደሚሆን የቅርቦቹ ክብረወሰኖች ምስክር ናቸው።አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 5/2013 ", "passage_id": "bd9d938962843a2319cf059722b904bd" }, { "passage": "ኢትዮጵያ በታወቀችበት የአትሌቲክስ ዘርፍ ስመጥር የሆኑ አትሌቶችን መጥቀስ ቢያስፈልግ ሁለቱ ቀዳሚ ናቸው፤ ኃይሌ ገብረሥላሴ እና ቀነኒሳ በቀለ። እነዚህ ሁለት የአትሌቲክስ ዕንቁዎች በ5ሺ እና 10ሺ ሜትሮች ተጽእኖ ከማሳደራቸውም ባለፈ በርካታ ክብረወሰኖችን የግላቸው ለማድረግ ችለዋል። አሁን ግን ሁለቱ ከዋክብት በመም ላይ አይታዩም ይልቁንም ቦታቸውን ለተተኪዎች አቀብለዋል። በአንጋፋዎቹ እግር\nከተተኩት ወጣት አትሌቶች መካከል አንዱ ደግሞ የሁለቱን አትሌቶች ስም አጣምሮ የያዘው አትሌት ጥላሁን ኃይሌ በቀለ ነው። ይህ ተስፈኛ የ20 ዓመት\nወጣት ከጅምሩ እያሳየ ያለው ብቃትም በበርካታ የአትሌቲክስ ቤተሰብ ዓይን እንዲገባ ምክንያት ሆኖታል። ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበርም በድረ-ገጹ ላይ ስለ ወጣቱ አትሌት ሰፊ ሽፋን ያለውን ዘገባ አስነብቧል። አትሌቱ ከድረ\nገጹ ጋር በነበረው ቆይታም በቅድሚያ የሁለቱን አትሌቶች መጠሪያ ስላጣመረው ስሙ ነበር ማብራሪያ የሰጠው። «ሩጫ ከመጀመሬ አስቀድሜ ነው ስሜ የሁለቱን አትሌቶች ስም እንደሚጋራ አስብ የነበረው። በቴሌቪዥን ስማቸው ሲጠራ ስመለከት አንድ ቀን እንደእነርሱ እሆናለሁ እል ነበር። ምክንያቴ በስማቸው ሲሆን፤ የእኔ ተምሳሌት ግን ታሪኩን እያደመጥኩ ያደኩት አትሌት አበበ ቢቂላ ነው። በሩጫ ሕይወቴ ጥንካሬን እንድገነባም አድርጎኛል»። በደቡብ ክልል\nጉራጌ አካባቢ የተወለደው ጥላሁን ከአራት ወንድሞቹ እና አንዲት እህቱ ጋር በገጠራማ ስፍራ ነው ያደገው። ስለ አስተዳደጉ ሲገልጽም «ቤተሰቦቼ አርሶ አደሮች ቢሆኑም፤ እንዳግዛቸው አይፈቅዱልኝም ነበር ምክንያታቸው ደግሞ ትምህርቴ ላይ ትኩረት እንዳደርግ ነው» ይላል። ወደ አትሌቲክስ ስፖርት ከመግባቱ አስቀድሞም በቴኳንዶ ስፖርት ተሳትፏል፤ ነገር ግን አሰልጣኙ ወደ ሌላ አካባቢ መዘዋወሩን ተከትሎ ከስፖርቱ መራቅ የግድ ሆነበት። ከትምህርት ዓለም ከመለያየቱ ቀድሞም የሰውነት ማጎልመሻ መምህሩ የአትሌቲክስ ስፖርት ዝንባሌ እንዲሁም አካላዊ መብቃት ያላቸውን ተማሪዎች ሲለዩ ጥላሁን ከእነዚያ መካከል ሊሆን ቻለ። ይህ አጋጣሚም ጥላሁንን በድጋሚ ወደ ስፖርት ሲመልሰው በስሙ ምክንያት እንደእነርሱ ለመሆን በሚመኛቸው አትሌቶች መንገድ የመጓዝን ዕድል ፈጠረለት። በትምህርት ቤት ውድድር ተሳትፎውም በ800ሜትር\nአራተኛ በ1ሺ500ሜትር\nደግሞ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀ። ይህም የአትሌቲክስ ሕይወቱን ወደፊት እንዳመላከተው ይጠቁማል። እአአ ከ2015 ጀምሮም የአትሌቲክስ ሥልጠናን ተቀላቀለ፤ ከሁለት ዓመታት በኋላም በኢትዮጵያ ሻምፒዮና ተሳትፎው 13:44.9 የሆነ\nየግሉን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ ሁለተኛ ሆኖ ውድድሩን ደመደመ። ጥላሁን ወቅቱን ሲያስታውስም «በሻምፒዮናው ይህንን ሰዓት ማስመዝገቤ ለእኔ ጥሩ ሆኖልኛል። ተጨማሪ ጉልበት እንዲሁም ከዚህም በላይ መስራት እንደምችልም አሳይቶኛል። ውጤቴም ቢሆን ለተሻለ ነገር እንድጓጓ ነው ያደረገኝ» ይላል። ውጤቱም ብቃቱን ከማስመስከሩ ባሻገር ከወቅቱ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሁሴን ሸቦ ጋር ለመስራት በር ከፈተለት። በብሔራዊ ቡድኑ ሲካተትም በ5ሺ\nሜትር ከእርሱ ጋር የሚሰለጥኑት ወጣት አትሌቶች የዓለም ሻምፒዮናው ሙክታር እድሪስ፣ የዳይመንድ ሊግ አሸናፊው ሰለሞን ባረጋ እንዲሁም ሐጎስ ገብረሕይወት ነበሩ። ይህ ጥምረትም ከፍተኛ ፉክክር ያለበትና ተመጣጣኝ ብቃት ያላቸው አትሌቶች መሆኑ እንዳገዘው ያምናል። እአአ በ2017 የውድድር ዓመትም በዓለም አቀፍ ውድድር ተሳትፎው ራሱን ሊመዝን ቻለ። በበርሊን በተካሄደው የ10ኪሎ\nሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተሳትፎውም ሦስተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ ርቀቱን 27:53 በሆነ ሰዓት ነው የሸፈነው። በቀጣዩ ዓመትም በዚሁ ውድድር ላይ የተሳተፈው አትሌቱ ብቃቱን በማሳደግ ኬንያዊውን በዓለም ሀገር አቋራጭ የብር ሜዳሊያ ባለቤት ጃኮብ ኪፕሊሞን ተከትሎ በሁለተኛነት እንዲጨርስ አድርጎታል። በመም ላይ ሩጫም የአትሌቱ ብቃት በኦስትሮቫ ይበልጥ ሊንጸባረቅ ችሏል፤ በዚህ ውድድር ላይ የተሳተፈው በ3ሺ\nሜትር ሲሆን፤ ያስመዘገበው ሰዓትም 7:38.55 ነበር። በሌላ የ5ሺ\nሜትር ውድድር ደግሞ የግሉን የሕይወት ዘመን ፈጣን ሰዓት (13:04.63) ሊያስመዘግብ ችሏል። ይህ ዓመት (2018) ወጣቱን አትሌት በበርካታ ውድድሮች የመሳተፍ ዕድል ያስገኘለት ሲሆን፤ በቴምፕሬ በተዘጋጀው የዓለም ከ20ዓመት\nበታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮናም ተካፋይ አድርጎታል። ጥላሁን በሻምፒዮናው ላይ የአሸናፊነት ግምት ቢያገኝም በኬንያዊው አትሌት ተበልጧል፤ ለዚህም ምክንያቱ በቦታው የነበረው ከፍተኛ ሙቀት መሆኑን አስረድቷል። በማብራሪያውም «ባላሸንፍም ጥሩ ብቃት አሳይቻለሁ፤ ጥሩ ልምድም አግኝቼበታለሁ» ሲል አመልክቷል። የተያዘውን የውድድር ዓመት (በአውሮፓውያኑ) የጀመረውም የኢትዮጵያን የ5ሺ\nሜትር ክብረወሰን የግሉ በማድረግ ነው። በሻንጋይ በተካሄደ ውድድር ላይም ዮሚፍ ቀጄልቻን በመከተል አምስተኛ ደረጃን አስመዝግቧል። ውጤቱን አስመልክቶም «አቅሙ እና ችሎታው እንዳለኝ አውቃለሁ፤ ስለዚህም ጠንክሬ መስራት ይገባኛል» ሲል ገልጿል። ከቆይታ በኋላም በሮም በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ፤ ከልምምድ አጋሩና ሌላኛው ወጣት አትሌት ሰለሞን ባረጋ ጋር የአንገት ለአንገት ትንቅንቅ በማድረግ ሊያሸንፈው ችሏል። የርቀቱን የመጨረሻ መስመር የረገጠበት ሰዓትም 12:52.98 ሆኖ ተመዝግቦለታል። «ውድድሩን እስካጠናቅቅ ድረስ አሸንፋለሁ የሚል ግምት አልነበረኝም፤ ነገር ግን ጉልበቴን በማሰባሰብ ወደፊት ገፍቼ መሄድ ቻልኩ። በማሸነፌም እጅግ ደስተኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ሰለሞን ጠንካራ እና ብቃት ያለው ወጣት ነው»። በዚህ ውድድር ላይ አትሌቶቹ በርቀቱ ማጠናቀቂያ ላይ ካደረጉት የአሸናፊነት ትንቅንቅ ባሻገር ጥላሁን አሸናፊነቱን ካረጋገጠ በኋላ ደስታውን የገለጸበት መንገድም ሌላኛው ትኩረት ሳቢ ትዕይንት ነበር። አንድ እጁን ወደ ትከሻው አጥፎ በሌላኛው እጁ የተንቀሳቃሽ ምስል ካሜራ ስላስመሰለበት ሁኔታ ሲጠየቅም፤ «ይህ ያልተለመደውና ከአሸናፊነት በኋላ ያሳየሁት ምልክት ደስታዬን ለመግለጽና ደጋፊዎቼን ለማዝናናት ያደረኩት ነው» ሲል አብራርቷል። በሄንግሎ የኦሊምፒክ\nስታዲየም በተደረገው የሚኒማ\nማሟያ ያስመዘገበው ሰዓትም\nለቀጣዩና በጉጉት ለሚጠበቀው\nታላቅ ውድድር ተሳታፊነት\nያረጋገጠበት ሆኗል። ይህንን\nሲገልጽም «ተስፋዬ በዓለም\nአትሌቲክስ ሻምፒዮና 5ሺ ሜትር\nጥሩ ሰዓት በማስመዝገብ\nማሸነፍ ነው። ለወደፊትም\nበሩጫ ራሴን ብቻ ሳይሆን\nኅብረተሰቡን እና ሀገሬን\nየመለወጥ ተስፋ አለኝ።\nይህ መነሻ እንጂ\nመጨረሻ አይደለም፤ የታላቁ\nስኬት ቅንጣት እንጂ»\nሲልም ህልሙን ገልጿል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 29/2011", "passage_id": "5b3fb6a4f98104778861a7ab8de743d4" }, { "passage": "አዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ያላትን ስምና ዝና እንዲሁም ውጤት ለማስቀጠል ሲባል በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የተለያዩ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ውድድሮችን ለማድረግ ቅድመ ማጣሪያ ውድድሮችን ማድረግ የተለመደ ተግባር ሆኖ ቆይቷል፡፡ በየዓመቱ ከሚደረጉ ቅድመ ማጣሪያ ውድድሮች አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ይጠቀሳል፡፡ በኦሮሚያ ክልል አሰላ ከተማ ላይ ተተኪ አትሌቶችን ለማግኘት ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች አትሌቶች ክለቦቻቸውን በመወከል ያላቸውን አቅም ማሳየት ከጀመሩ ሰባተኛ ዓመታቸውን ይዘዋል፡፡ ዘንድሮ ለ7ኛ ጊዜ የሚካሄደው ሻምፒዮናው በትናንትናው እለት በአሰላ አረንጓዴው ስታዲየም በይፋ ተጀምሯል።የውድድሩ ውጤታማ አትሌቶች የውድድሩ ዓላማ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲካሄዱ የወጣቶች ውድድር አገራቸውን ወክለው የሚካፈሉ እንደሆነ የተጠቀሰ ሲሆን ፤ቀጣይ ለአገሪቱ አትሌቲክስ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እንደሆነም ጭምር መሆኑን ተነግሯል። የሻምፒዮናው አላማ ይሄንን መልክ የያዘ ቢሆንም ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ከውድድሩ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማግኘት ያለመ ቢሆንም ፤የዕድሜ ተገቢነት ችግር አሁንም ሊፈታ ያልቻለ ጉዳይ እንደሆነ የተለያዩ ባለሙያዎች እየተናገሩ ይገኛሉ።ፌዴሬሽኑም ይህን መቆጣጠር አስቸጋሪ እንደሆነበትና ክልሎችና ክለቦች ሲጠየቁ ክለብ ሲገባ ዕድሜውን እንዲቀንስ ተደርጎ የተመዘገበበትን ሀሰተኛ የሆነ ማስረጃ እንደሚያቀርቡ በተደጋጋሚ ሲነገር ነበር። በዚህ ምክንያት ዕድሜያቸውን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ መሆኑ ይነሳል። ከዚህ በመነሳትም የዘንድሮው የሰባተኛው ከ20 ዓመት በታች የታዳጊዎች ሻምፒዮና ከዚህ ችግር የጸዳ በሆነ መልኩ ተጀምሮ የሚጠናቀቅ ስለመሆኑ ጥያቄን አስነስቷል። ሻምፒዮናው ከትናንት ማለዳ ጀምሮ መካሄድ ጀምሯል።በእለቱ ከተካሄዱ ውድድሮች የስሉስ ዝላይ ሴቶች ከኦሮሚያ ክልል እንደቴ ሮቤ 11.67 ሜትር በመወርወር አንደኛ ስትሆን ፣ ኡጁሉ ኦዶላ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 11.64 በመወርወር ሁለተኛ ፣ ኩለኒ ድሪባ ከኦሮሚያ ክልል 14.54 በመወርወር ሶስተኛ ሆነዋል። ዲስከስ ውርወራ ወንዶች የሲዳማ ቡና ለማ ከተማ 47.44 በመወርወር አንደኛ ሲሆን፣ የመከላከያው ጌታቸው ተመስገን እና የአማራ ክልሉ አየነው ኮሴ 47.23 እና 42.80 በመወርወር ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። በሴቶች ዲስከስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ መሪያምመዊት ፀሀዬ 38 .73 ሜትር በመወርወር አንደኛ ሆናለች። ማርታ በቀለ ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ 34.99 ሜትር በመወርወር ሁለተኛ ፣ ትንጓደድ ተሰማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከንግድ ባንክ 32.89 በመወርወር ሶስተኛ ሆናለች። የወንዶች 10 ሺ ሜትር ሌላው በትናንትናው እለት የተካሄደ ውድደር ሲሆን ጸጋዬ ኪዳኑ 29፡34፡27 ሰዓት በመግባት ከመስፍን ኢንጂነሪንግ አሸናፊ ሲሆን እርሱን ተከትሎ ሚልኬሳ መንገሻ ከሰበታ ከነማ ክለብ 29 ፡35፡65 ሁለተኛ እንዲሁም ወርቅነህ ታደሰ ከኦሮሚያ ክልል 29፡39፡98 ሰዓት አስመዝግቧል።በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም የሚካሄደው ሻምፒዮናው ለቀጣይ አራት ቀናት በድምቀት የሚቀጥል መሆኑን ታውቋል። ከጥር 15 እስከ 19 ቀን 2011 ዓ.ም በሚካሄደው ውድድሩ 9 ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም 34 የተለያዩ_ ክለቦችና ተቋማት ተካፋይ ሆነዋል።አዲስ ዘመን ጥር 16/2011ዳንኤል ዘነበ", "passage_id": "c90b10f6d6ef9e95a9b4a3ed0f3565c4" }, { "passage": "የጉዳት መጠናቸው ቢለያይም በስፖርቱ ዓለም ባለሙያዎቹ የሚፈፅሟቸው ስህተቶች በአብዛኛው የሁለት ምክንያቶች ውጤት መሆናቸው ይታመናል። አንዳንዶቹ በውጫዊ ተፅዕኖ ማለትም በደጋፊና በሌሎችም ጫናዎች ሲከሰቱ፤ አብዛኞቹ ደግሞ በስፖርተኞቹ ትኩረት ማጣት ሲከሰቱ ይስተዋላል። የስፖርት ሳይንስ ባለሙያዎች እንደ ሚገልፁት፤ በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር መጠናቀቁ እስካልተረጋገጠ ድረስ አሸናፊ ነኝ ብሎ ደስታውን ማጣጣም ስህተት ነው። ለአብነት እግር ኳስን ስንመለከት በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች የሚፈጠረው አይታወቅምና የጨዋ ታውን መጠናቀቅ የሚያበስረው የዳኛ ፊሽካ እስካልተሰማ «አሸንፌአለሁ» ማለት ሞኝነት ነው። በሰፊ የግብ ልዩነት መምራትም ብቻውን ዋስትና አይሰጥም። ይልቅስ ጨዋታው ሊጠናቀቅ የቀሩ ደቂቃዎችን ታሳቢ ማድረግ የግድ ይላል። በአትሌቲክሱም ቢሆን አንድ አትሌት የመጨረሻዋን መስመር ማለፉን እስካላረጋገጠ ድረስ ማሸነፉን ማረጋገጥ አዳጋች ነው። አንድ አትሌትም አሸናፊ ለመሆን ብቃቱን ከመጠቀም በተጓዳኝ ሌሎች ተግባራትን መከወን ግድ ይለዋል። በተለይ መነሻን እንጂ መድረሻውን ማወቅ ካልቻለ እጅግ ከባድ ዋጋ መክፈሉ አይቀርም። ይህን ጠንቅቆ መረዳት ይኖርበታል። ፊት ያለ ሁሉ መሪ ሳይሆን ተደራቢ ሊሆን ይችላልና የትኛው አትሌት ቀዳሚ ሆኖ እየመራ እንደሚገኝና ጠንቅቆ ማወቅም ግድ ይለዋል። ከሁሉም በላይ ውድድሩ ሊጠናቀቅ የቀሩትን ዙሮች ጠንቅቆ ማወቅ የግድ ይላል። ምክንያቱም በርካታ አትሌቶች የመግቢያ መስመሩን ማለፋቸው እንደ አሸናፊነት በመውሰድ በደስታ ሲፈነጥዙ ከኋላ በነበሩ አትሌቶች ተቀድመው ወርቃማ ዕድላቸውን አሳልፈው ሰጥተዋልና ነው። ከሰሞኑ በኢትዮጵያዊው አትሌት ሃጎስ ገብረሕይወት ላይ የሆነውም ይህ ነው። አትሌቱ ከሳምንት በፊት በተካሄደ የ5 ሺህ\nሜትር ውድድር ብዙ ዙሮችን ሲመራ ቢቆይም በኋላ ለማመን በሚከብድ መልኩ «ዙሩ አልቋል» በሚል በድል አድራጊነት ውድድሩን ሲያቋርጥ ታይቷል። መነሻን እንጂ መድረሻውን ማወቅ ያልቻለው አትሌት ሐጎስ፤ በስዊዘርላንድ በተካሄደው የዳይ መንድ ሊግ ውድድር 4 ሺህ 600 ሜትሮችን እንደሮጠ የመጨረሻ መስመር የደረሰ ሲመስለው በድል አድራጊነት እጁን እያነሳ አሸናፊነቱን ሲገልፅ ሚሊዮኖች ተመልክተውታል። የ25 ዓመቱ\nአትሌት በጊዜያዊ ዝንፈትና ድክመት የፈፀመው ስህተትም የውድድሩን የአሸናፊነት አቅጣጫ ቀይሮቷል። ሐጎስ ዙሩን ሳይጨርስ ያሸነፈ መስሎት ውድድሩን ያቋረጠበትን ምክንያት ሲያስረዳም፤ «የዙሩ የመጨረሻ መግለጫ ደወል ሲደወል አልሰማሁም፤ ውድድሩን እየመራሁ በነበረበት ወቅት ከፊት ለፊቴ አንድ ካሜራማን ነበር፤ በዚያ ምክንያትም ውድድርን በመሪነት ጨርሻለሁ ብዬ አሰብኩና ቆምኩ፤ ተወዛግቤ ነበር፤ ሌሎች ተወዳዳሪዎች አልፈውኝ ሲሮጡ ሳይ እንደገና መሮጥ ጀመርኩ፤ ውድድሩን እንዴት እንደጨረስኩ ባላውቅም ክስተቱ መጥፎ አጋጣሚ ነበር» ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። በአትሌቲክሱ ዓለም መሰል ስህተቶችን በመስራት አሸናፊነቱን አሳልፈው የሰጠው አትሌት ሐጎስ ብቻ ግን አይደለም። ብዙም ባይሆን የኢትዮጵያዊውን ዓይነት የሚያስቆጩ ስህተቶች የሰሩ አትሌቶች አሉ። ከእነዚህ መካከል ደግሞ እስራኤላዊቷ አትሌት ሎናህ ሳልፒተር ከሁሉ ቀድማ ትታወሳለች። አትሌቷ ባሳለፍነው ዓመት በአውሮፓ አትሌቲክስ ሻምፒዮን ሺፕ ውድድር ላይ የመግቢያ መስመሩን ሁለተኛ ሆኗ ማለፏን እንደ አሸናፊነት በመውሰድ በደስታ ስትፈነጥዝ ከኋላዋ የነበሩ አትሌቶች ቀድመዋት በመሄድ ውጤቷን ነጥቅዋታል። አትሌቷ በወቅቱ የውድድሩ የመጨረሻ ዙር መሆኑን የሚጠቁመው የደውል ድምፅ ከማስተዋልና ማዳመጥ ይልቅ ደስታዋን ለማጣጣም በመቸኮሏ አራት መቶ ሜትር እየቀራት ሩጫዋን አቋርጣለች፡፡ ምንም እንኳን ካቋረጠችበት ብትቀጥለም በአንዳች ቅፅበት የሰራችው ስህተት ግን ወርቃማ ዕድሏን አሳልፋ እንድትሰጥና አራተኛ ሆና እንድታጠናቅቅ አስገድዷታል። መስል ሁነቶች በአትሌቲክሱ ላይ ብቻም ሳይሆን በሞተር ሳይክል ውድድር ላይም ሲከሰት ታይቷል። እኤአ በ2012 በተካሄደው በጣሊያን ሞተር\nሳይክል ሻምፒዮን ሺፕ ሪካርዶ ሩሶ አንድ ዙር እየቀረው ለደስታ ጊዜውን ሲመድብ ተቀናቃኞቹ ቀድመውት አሸናፊነቱን በገዛ እጁ አሳልፎ ሰጥቷል። አንደኛ የነበረው ሞተረኛም አስራ አራተኛ ሆኖ ውድድሩን አጠናቋል። ምንም እንኳን እነዚህ ስፖርተኞች በአንዳች ቅፅበት በጥቃቅን ስህተት የፈፀሙት ተግባር ውድ ሽልማቶችና ክብሮችን ቢያሳጣቸውም፤ «የማይሳሳተው የሞተ ነው» እንደሚባለው፤ ተግባራቸው የሚያስተቻቸው አይሆንም። በስፖርቱ ዓለምም ስህተቶቹ ነገም መከሰታቸው አይቀሬ ነው። የስህተቶቹ የጉዳት መጠን ቢለያይም እንኳ፣ ዋናው ቁም ነገር እንዳይደገሙ ማስተካከል፣ነገ እንዳይለመዱም ማቅናትና ማፅናት ነው።አዲስ ዘመን  ሐምሌ 9/2011", "passage_id": "118f9d0732266d99ba67fea07cfcf4a0" } ]
f1d9fde6c996fc3d25d55403f4ea035c
dca33b176ecc5ddc4df0206a6d83ede4
« የጥቁር ሕይወት ዋጋ አለው»!
የምን ጊዜም የቦክስ ስፖርት ንጉሱ መሐመድ አሊ የዓለም የቦክስ ቻምፒዮንና ታላቅ የቡጢ ተፋላሚ ብቻ አልነበረም። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፤ የጥቁር ህዝቦች ሰንደቅ፤ በመላው ዓለም በስፖርትና በታላቅ ስብዕና ተምሳሌትም ጭምር ነው። ብዙዎች ቦክስ ስፖርት ሳይሆን የጥጋበኞች ድብድብ አድርገው ከመሳል አስተሳሰብ አውጥቶ የቦክስን ስፖርት ጥበባዊ ገፅታ በማላበስ ተወዳጅና አሁን ላይ በዓለማችን በአንድ ጊዜ በርካታ ሚሊየን ዶላሮች የሚያሳቅፍ ግንባር ቀደም ስፖርት እንዲሆን ተፅዕኖውን አሳርፏል። ሙዚቀኛም ሆኖ ለሂፕሆፕና ራፕ የሙዚቃ ስልቶች ጉልህ ሚና ተጫውቷል። በቦክስ ስፖርት ታሪክ የምንግዜም ምርጥ ቦክሰኛ የተባለውም በተለያዩ የቡጢ ፍልሚያዎች ዘመን የማይሽራቸው ገድሎችን በማስመዝገብ ነው። መሐመድ አሊ የቦክስ ጓንቱን ሰቅሎ ስፖርቱን በቃኝ ብሎ ከተሰናበተ ከሦስት ዓመታት በኋላ እኤአ በ1984 ከስፖርቱ ልምድ ጋር በተያያዘ ፓርኪንሰንስ በተባለ በሽታ ተይዞ ነበር።ለሰላሳ ሁለት ዓመታት ከዚህ ህመሙ ጋር ሲታገል ቆይቶ ከአምስት ዓመት በፊት በሰባ አራት ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።ባለፉት ሳምንታት በአሜሪካ ሚኒያፖሊስ ከተማ ነጭ ፖሊስ ያልታጠቀ ጥቁር አሜሪካዊ አንገትን በጉልበቱ እረግጦ ለሞት ማብቃቱን ተከትሎ የዓለም ሕዝብ ትኩረት ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወደ ሟቹ ጆዮርጅ ፍሎይድ ጉዳይ ዞሯል።ይህ ዘግናኝ ክስተት ከዓመታት በፊት በተመሳሳይ ቁጣን የቀሰቀሰውና በነጭ የፖሊስ አባላት ጭካኔ የሞተውን ኤሪክ ጋርነርን ያስታወሰ ሆኗል። ኤሪክ በወቅቱ በፖሊስ አንገቱ ተቆልፎ ‹‹እባካችሁ መተንፈስ አልቻኩም›› እያለ ነበር የሞተው። የጂዮርጅ ፍሎይድ አሰቃቂ ግድያ ዛሬም ድረስ በሞተባት አገሩ አሜሪካና ሌሎች የዓለማችን ክፍሎች ትልቅ ቁጣን ቀስቅሶ ይገኛል።በታላላቅ ከተሞችም‹‹ የጥቁር ሕይወት ዋጋ አለው›› የሚሉ መፈክሮች በተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎች ተፅዕኖ ፈጥረዋል።አዲስ ዘመን ስፖርትም በሳምንታዊ የስፖርት ማሕደር አምዱ ‹‹የጥቁር ሕይወት ዋጋ አለው›› ብሎ ለጥቁሮች እኩልነት ስለታገለው የቦክሱ ዓለም የምንጊዜም ኮከብ መሐመድ አሊ ሕይወት ላይ ትኩረቱን ለማድረግ ወደደ።መሐመድ አሊ ወደ ቦክስ ሕይወት የመጣበት አጋጣሚ አስገራሚ ነው። የአስራ ሁለት ዓመት ልጅ በነበረበት ወቅት ብስክሌቱ ተሰርቆበት በሊውስቪል ኬንታኪ ለሚገኝ ጆ ማርቲን ለተባለ ፖሊስ አመለከተ።«የሰረቀኝን ባገኘው ልክ አገባው ነበር» ብሎም ምሬቱን ይገልፃል።የቦክስ አሰልጣኝ የነበረው ፖሊስ ትንሹን መሐመድ ራሱን እንዴት ከጥቃት መከላከል መማር እንዳለበት መከረው።የተወሰኑ ስልጠናዎችን ሲወስድ ቆይቶም ብስክሌቱ ከተሰረቀች ከስድስት ሳምንታት በኋላ በሰፈሩ በአንድ አማተር የቦክስ ግጥሚያ ላይ ተሳተፈና በነጥብ አሸናፊ መሆን ቻለ።ይህች አጋጣሚም በዓለም በገነነበት ስፖርት የመሰረት ድንጋይ ነች። መሐመድ የትውልድ ስሙ ካሴስ ክሌይ ቢሆንም በ19ኛው ክፍለ ዘመን ባሮችን ነፃ ለማውጣት በታገሉ ታላቅ ሰው መታሰቢያነት የወጣለት ስም ነበር።ለመጀመርያ ጊዜ የዓለም ከባድ ሚዛን ቻምፒዮን ከሆነ በኋላ በማግስቱ ስሙን ለመቀየር ወሰነ።የነፃነት ታጋዩን ማልኮለም ኤክስ ከጎኑ አድርጎ በሰጠው መግለጫ «ዘ ኔሽን ኦፍ ኢስላም» የተባለውን ተቋም መቀላቀሉን በማሳወቅ የባርያ ስም ይለው የነበረውን ካሴስ ክሌይ በመቀየር በቀድሞ ስሙ ላለመጠራት ወሰነ። በወቅቱ «ኔሽን ኦፍ ኢስላምን» ይመራ የነበረው ኤልጅያህ መሃመድ እኤአ በ1964 ላይ መሐመድ አሊ የሚለውን ስም ካወጣለት በኋላ እሱን በማፅደቅ እስከ ህይወት ዘመኑ መጨረሻ ተጠራበት። ለሃያ አንድ ዓመታት በፕሮፌሽናል ቦክሰኛነት በርካታ የቡጢ ፍልሚያዎችን ከአሜሪካ እስከ አፍሪካ እንዲሁም ሌሎች ዓለማት ላይ የተፋለመው መሐመድ አሊ ለሦስት ጊዜ የዓለም ከባድ ሚዛን ቻምፒዮን ሆኗል።ለመጀመርያ ጊዜ የዓለም የከባድ ሚዛን ቻምፒዮን ለመሆን የበቃውም የሃያ ሁለት ዓመት ወጣት እያለ ነው። ዓለም አቀፍ ደረጃ ባላቸው ፕሮፌሽናል የቦክስ ግጥሚያዎች ላይ ስልሳ አንድ ጊዜ ተሳትፎ ሃምሳ ስድስቱን ማሸነፍም ችሏል። ከነዚህ ድሎቹም ሰላሳ ሰባት ያህሉን ተጋጣሚዎቹን በበቃኝ በመዘረር ነው። አስገራሚው ነገር በሰላሳ አንድ ተከታታይ የቦክስ ግጥሚያዎች ሳይሸንፍ ለመጀመርያ ጊዜ የተሸነፈው የክፍለ ዘመኑ ምርጥ ፍልሚያ በተባለው ግጥሚያ በጆ ፍሬዘር ነበር።በፕሮፌሽናል የቦክሰኛነት ዘመኑም ሽንፈትን የቀመሰው አምስት ጊዜ ብቻ ነው። የመጨረሻው ፍልሚያም እኤአ በ1981 ከትሬቨር ቤሪቢክ ጋር በማድረግ ስፖርቱን በቃኝ ብሏል። አሜሪካ በቬትናም በ1970ዎቹ መጀመርያ ያደረገችውን ጦርነት በመቃወሙ ለሦስት ዓመታት ከፕሮፌሽናል ቦክስ ውድድሮች ታግዶ የቆየው መሐመድ አሊ እገዳው በተጣለበት ወቅት ከአስር የማያንሱ የዓለም ከባድ ሚዛን ቻምፒዮናዎች ባያመልጡት አሁን ካሉት የበለጠ በርካታ ክብሮችን መጎናፀፍ ይችል ነበር። በዚህም ከሰማንያ ሚሊየን ዶላር በላይ ሀብት ማፍራት ችሏል። ለዚህም ሀብቱ ምንጭ ስፖርቱን ከተሰናበተ ወዲህ ግንባር ቀደም ተዋናዮቹ ስሙንና ምስሉን የሚጠቀሙ ከአርባ በላይ ኩባንያዎች ናቸው። ታሪካዊው ኢትዮጵያዊ አትሌት አበበ ቢቂላ በ1960 የሮም ኦሊምፒክ በባዶ እግሩ ሮጦ ለጥቁር ህዝቦች የመጀመሪያውን የማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ ሲያስመዘግብ መሐመድ አሊም በቦክስ የወርቅ ሜዳሊያ አጥልቆ ነበር። ሁለቱ ታሪካዊ የጥቁር ህዝቦች ከዋክብት ፊርማቸውን ተለዋውጠውም ነበር። ይሁንና መሐመድ አሊ ይህን የወርቅ ሜዳልያውን ለአገሩ ከማበርከት ይልቅ በሊውስ ቪል ግዛት በሚገኘው የኦሃዮ ወንዝ ጨምሮታል። ሜዳልያውን ለአሜሪካና ለትውልድ ከተማው ሊውስ ቪል ቢቀዳጅም ለጥቁሮች በርገር የመግዛት መብት ባለመኖሩ ተቃውሞውን ለመግለፅ ነበር ይህን ርምጃ የወሰደው። በ1996 አገሩ አሜሪካ ባስተናገደችው የአትላንታ ኦሊምፒክ ችቦውን እንዲለኩስ ከመደረጉ ባሻገር ወንዝ የጨመረው የወርቅ ሜዳልያ ምትክ ሌላ ሜዳሊያ በአንገቱ ተጠልቆለታል። በ1980 በላስቬጋስ በተካሄደ የቡጢ ፍልሚያ በቴክኒካል የበቃኝ ውጤት ቢሸነፍም መሐመድ ትልቁን ክፍያ ስምንት ሚሊየን ዶላር ያፈሰው በዚያ ውድድር ነው።« ራምብል ኢን ዘ ጃንግል» በተባለውና እስካሁንም ከስፖርት ቤተሰቡ አዕምሮ በማይጠፋው በአፍሪካ ምድር በተካሄደው ፍልሚያ መሐመድ አሊ ምን ጊዜም ይታወሳል። እኤአ በ1974 መሐመድ አሊ በሰላሳ ሁለት ዓመቱ ሽንፈትን አይቶ ከማያውቀው ከሃያ አምስት ዓመቱ ጆርጅ ፎርማን ጋር በኮንጎ ኪንሻሳ የቡጢ ፍልሚያ ገጥሞ ነበር። በወቅቱ የኮንጎ ፕሬዝዳንት የነበሩት ሞቡቱ ሴሴኮ ለሁለቱ ቦክሰኞች በኪንሻሳ ከተማ እንዲጫወቱ በነፍስ ወከፍ አምስት ሚሊዮን ዶላር ከፍሏቸው ነበር።መሐመድ አሊ በውድድሩ ስምንተኛ ዙር ላይ በዝረራ ቢሸነፍም ከወጣት ተፋላሚው ጋር ያደረገው እልህ አስጨራሽ የቡጢ ፍልሚያ እስካሁንም ከህሊና የሚጠፋ አይደለም። በ1970 የዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ መታሰቢያ ሽልማት የተቀበለው መሐመድ አሊ፤ የዓለም አቀፋዊ ወዳጅነት ተምሳሌት ሆኖም ያውቃል። የተባበሩት መንግስታት የሰላም መልዕክተኛ ሆኖም ከ1998 እስከ 2008 በታዳጊ አገራት በመዘዋወር አገልግሏል። በህይወቱ ዙርያ በሚያተኩሩ ጥናታዊና የሙሉ ጊዜ ፊልሞች የሰራ ሲሆን በተለይ ለመጀመርያ ጊዜ በተዘጋጀውና ዘ ግሬተስት በተባለ ፊልም ላይ ተውኗል።የህይወት ታሪኩ ላይ በማተኮር ከተሰሩ ፊልሞች የኦስካር ሽልማት በጥናታዊ ፊልም ዘርፍ ያገኘው «ዌን ዊ ዌር ኪንግስ»ና ዝነኛው የሆሊውድ ተዋናይ ዊል ስሚዝ በመሪ ተዋናይነት የተጫወተው «አሊ» የተባሉት ይጠቀሳሉ።ታላቁን የደቡብ አፍሪካ ነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ከእስር እንደተፈቱ በአካል ተገኝቶ ደስታውን ለመግለፅ መሐመድን የቀደመው የለም። በአካል ካገኛቸው ታላላቅ መሪዎች የእንግሊዟ ንግስት ኤልሳቤት፤ የሮማው ሊቃነ ጳጳስ ፖፕ ጆን ፖል፤ የኩባው መሪ ፊደል ካስትሮ እንዲሁም የኢራቁ ሳዳም ሁሴን ይገኙበታል።አይም ዘ ግሬተስትና ስታንድ ባይ ሚ ከዘፈን ስራዎቹ መካከል የሚጠቀሱት ናቸው።በንግግር ችሎታው፤ በልዩ የግጥም ስንኞቹም ተወዳጅነት ያተረፈ መሐመድ አሊ ነው።«በማይሞት እምነትና ፍቅር ዓለም የተሻለ ዓለም መፍጠር እንደሚቻል አሳይቶናል።ሁሌም ቻምፒዮን ነው»።በማለት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን ጨምሮ በርካታ የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪና ታላላቅ ሰዎች በቀብር ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው መሐመድን ወደማይመለስበት ሸኝተውታል። እሱ ቢያልፍም ጥቁሮች ዛሬም ድረስ ‹‹የጥቁር ሕይወት ዋጋ አለው›› ብሎ ከዘመናት በፊት ትግሉን የጀመረውን ጀግና ያስቡታል።አዲስ ዘመን ሰኔ 14/2012 ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=34797
[ { "passage": "እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!በክርስቲያኖች ዘንድ መስቀል የድልና የፈተና ምልክት ነው። አባቶቻችን ያለ ፈተና ክብር አይገኝም ይላሉ። መስቀሉም በአንድ በኩል እስከ ሞት የሚደርስ መሥዋዕትነትንና ፈተናን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ማንም ሊያስቀረው የማይችለውን ድል አድራጊነትን ያስታውሰናል። ሀገር ልቃ እንድትወጣ በሁለቱም ውስጥ ታልፋለች። በፈተናና በድል ውስጥ። ፈተናው ብቻ ቢሆን ተስፋ በቆረጥን ነበር። ግን ድል እንዳለ ስለምናምን መከራውን ተቋቁመን እናልፈዋለን። ድል ብቻ ቢሆንም ተዘናግተን በተቀመጥን ነበር። የምትፈለፈል ቢራቢሮ ከዕንቁላሉ ለመውጣት የምታደርገው ትግል፤ ለጥንካሬዋ አስፈላጊ እንደሆነው ሁሉ፤ በፈተና ውስጥ በጽናትና በትግል ማለፋችንም መሠረተ ጽኑ ያደርገናል።አንዳንዶች ስለፈተናው ብቻ ያወራሉ። ስለዚህም ተጨንቀው ሕዝብን ያስጨንቃሉ። ሰው ፈተናን ብቻ ካሰበ የዓለም መጨረሻ የደረሰ ይመስለዋል። ነገሮችን ሁሉ ያለቀላቸውና ያበቃላቸው አድርጎ ያያቸዋል። ንግሥት እሌኒ መስቀሉን ለማውጣት ስትነሣ ብዙዎቹ ስለመቀበሩ ብቻ ነበር የሚነግሯት። የት እንደተቀበረ እንደማይታወቅ፤ ከተቀበረ ብዙ ዘመናትን ያስቆጠረ፤ ለማውጣት አስቸጋሪ የሆነ፤ ሁኔታው ሁሉ ተስፋ እንደሚያስቆርጥ ነበር የሚነግሯት። እርሷ ግን እንደተቀበረ ብቻ ሳይሆን እንደሚወጣም ታምን ነበር። እንደጠፋ ብቻ ሳይሆን ሊገኝ እንደሚችልም ታምን ነበር። እነርሱ ስለ ፈተና ሲናገሩ፤ እርሷ ግን ከፈተናው ወዲያ ስላለው ድል ጭምር ነበር የምታወራው። ልዩነታቸው እዚህ ላይ ነበረ።‹ፈተና› ደካማና ተሸናፊዎችን ሲሰብራቸው በተቃራኒው ለአሸናፊዎች የትምህርት ዕድል ነው። አሸናፊዎች ከፈተናው ትምህርት ወስደው ይለወጡበታል፤ እንደ ብረት ጠንክረው፣ እንደ ካስማ ጸንተው ይወጡበታል። ፈተና ለሚሸነፉ ሰዎች ተስፋ መቁረጫ ጥቁር ጭንብል ነው። በፈተናው ይማረራሉ እንጂ ከፈተናው አይማሩም፤ ድቅድቁን ጨለማ እንጂ ደማቁን ብርሃን ሊያዩ አይችሉም፤ የፈተናው መንገድ እንጂ የፈተናው ፍጻሜ በጭራሽ ዐይታያቸውም።በክርስቲያኖች ዘንድ መስቀል ‹ኃይልና ቤዛ› ተደርጎም ይታሰባል። የእምነታቸው ምልክትም ነው። መጽናናትና መዳንን ያገኙበት ውድ ስጦታቸው ነው። ይሄን የሚያውቁ የዚያን ዘመን ጨቋኞች መስቀሉን ሲቀብሩት ዓላማ ነበራቸው። ክርስቲያኖቹ ትእምርት እንዳይኖራቸውና በተሸናፊ ሥነ ልቡና ውስጥ እንዲኖሩ ይፈልጋሉ። ልክ እንደ መስቀሉ ጭንቅላታቸውን እንዲቀብሩ፣ ዝቅ አድርገው እንዲያስቡና ዝቅ ያለ መንፈስ እንዲላበሱ የማድረግ ጽኑ ፍላጎት ነበራቸው። ነገር ግን ይሄ በመስቀሉ የሚያምኑትን አላሸነፋቸውም። ከዓመታት በኋላ ውድ ስጦታቸውን፣ ያንን የተቀበረ መስቀል በብዙ ጥረትና ትጋት ቆፍረው አውጥተውታል።የብልጽግና ጉዟችን ለእኛ ለኢትዮጵያውያን እጅግ ወሳኝና ውድ ስጦታችን ነው። ለዘመናት በድህነትና ኋላቀርነት፣ በርሃብና በቸነፈር፣ በልዩ ልዩ ችግሮች ትከሻዋ የጎበጠው ሀገራችን ከሸክሟ የሚያሳርፏት፤ ብሩህ ነገዋን እንድታይ ቀና የሚያደርጓት፤ ክብርና ዝናዋን ከሚመጥን የብልጽግና ደረጃ ላይ የሚያደርሷት ልጆችዋን ትሻለች። በጥቃቅን ፈተናዎች ሳይሸነፉ፣ በእንቅፋትና በጋሬጣው ተጠልፈው ሳይወድቁ፣ ከመከራው ወዲያ የሚታየውን የሚጨበጥ ተስፋ ይዘው ወደፊት እንዲገሠግሡ ሀገራችን ትፈልጋለች።ያኔ መስቀሉ ተቀብሮ ሳለ በመስቀሉ ፊት ሦስት ዓይነት ሰዎች ነበሩ። የመጀመሪያዎቹ መስቀሉን የማይፈልጉትና ከመሬት በታች የቀበሩት ሲሆኑ ዓላማቸው የመስቀሉን ደብዛ ማጥፋት ነበር። በሁለተኛው ረድፍ ያሉት ተስፋ ቆርጠው ሌላውን ተስፋ ለማስቆረጥ ታጥቀው የተነሡት ናቸው። በየአጋጣሚው መስቀሉን ቆፍሮ ስለማውጣት ሲነሣ የሚያከላክሉና አብዝተው ስለመከራው የሚናገሩ ነበሩ። ተአምር ተፈጥሮ እስካልወጣ ድረስ የመስቀሉ ነገር እንዳከተመለትም ያምናሉ። በተቃራኒው ሦስተኛ ላይ ያሉት መስቀሉ እንዲወጣ ጽኑ ፍላጎት ነበራቸው፤ ከሁሉም በላይ ‹መስቀሉ ይገኛል› የሚል ጽኑ እምነት የነበራቸው ብርቱዎች ናቸው።እነዚያ ብርቱ ክርስቲያኖች የተቀበረውን መስቀል ለማየት የበቁት ተራራውን ንደው፤ ክምሩን ቆሻሻ ደረማምሰው፤ አፈሩን ምሰውና ብናኝ አቧራውን በአፍና በአፍንጫቸው ጠጥተው ነበር። ላብ ሳያስወጣ፣ ጉልበት ሳያብረከርክ፣ አቧራ ሳያለብስና ምንም ሳያስለፋ የሚሳካ መልካም ነገር የለም። የሀገራችን ዴሞክራሲ የሚሳካው፣ ነጻነትና እኩልነት እውን የሚሆነው ተገቢውን የዴሞክራሲ ግንባታ ሂደት ተከትለን ስንሠራ እንጂ እንደ ተአምር ከሰማይ የሚወርድልን ነገር አይደለም። ፖለቲካችን የሚስተካከለው፣ ኢኮኖሚያችን የሚያድገው፣ ብልጽግናችን እውን የሚሆነው ዳር ቆመን በመመልከት ወይም እንደ ታዛቢ አፋዊ አስተያየት በመሰንዘር ሳይሆን ባለቤት ሆነን ስንሠራው፣ የበኩላችንን ማበርከት ስንችልና የውጣ ውረዱ አካል ስንሆን ብቻ ነው።እኛ ኢትዮጵያውያን መከራችንን ከሚያብሱና ፈተናችንን ብቻ ከሚነግሩን መሠናክሎች ማምለጥ አለብን። እነሱ ዘላለም ፈተናችን ላይ ብቻ እንድንጣድ የሚፈልጉ ናቸው። ዘወትር በልቅሶና በትካዜ እንድንኖር ከማድረግ ውጭ ለቁስላችን መድኃኒት፣ ለተራበ ሆዳችን ምግብ፣ ለታረዘ ገላችን አልባስ አያቀርቡልንም። በጊዜያዊ ችግሮቻችን እንድንጠመድ ከማድረግ በዘለለ ሥር ለሰደዱ ችግሮቻችን ዘላቂ መፍትሔ አያቀብሉንም። ከማላዘን ፖለቲካ ምን ጠብ የሚል ነገር እናገኛለን ብንል መልሱ ኪሳራ እንጂ ትርፍ፤ መከራ እንጂ ዕረፍት አይሆንም።ኢትዮጵያ እስካሁን ተፈትናለች፤ አሁንም እየተፈተነች ነው፤ መጠኑ ቢለያይም ወደፊትም ፈተና ማጋጠሙ አይቀርም። ዋናው ቁም ነገር ከፈተና በኋላ እንደ ወርቅ ነጥሮ መውጣት መኖሩን አለመርሳት ነው። እሳት ለወርቅ ማቃጠያው ብቻ ሳይሆን ማንጠሪያውም ጭምር ነው። ይበልጥ በእሳት ሲመታ፤ ይበልጥ ንጹሕ ይሆናል። ይለወጣል። ፈተናዎቻችን ነጥረን እንድንወጣ እንጂ ቀልጠን እንድንቀር አያደርጉንም።ሀገራችን ወደፊት እንዳትራመድ አስረው የያዟት ትብታቦች የቱንም ያህል ቢበዙ ተበጣጥሰው ማለቃቸው አይቀርም። ግድግዳ ሆነው መንገድ የዘጉባት ቋጥኞች የቱንም ያህል ቢገዝፉ ተንደው ይወድቃሉ። ሕብዛችን ብሩህ ቀን እንዳያይ የሚያደርጉት የጽልመት መጋረጃዎች በብርሃን ሰይፍ ይቀደዳሉ። ገፍተው መስቀለኛ መንገድ ላይ ያቆሟት ሲያልፉ፣ ሀገራችን ተስፋ ባላቸው ኅሊናዎች፤ በተባበሩ እጆች፤ በቆረጡ ልቦች፤ በልዩነት ውስጥ አንድነትና ፍቅር እንዳለ በሚያምኑ ልጆችዋ ብርታት ከችግሮቿ በላይ ከፍ ትላለች፤ ብልጽግናዋም ያለጥርጥር እውን ይሆናል።መስቀሉ ከተቀበረበት ቀን ይልቅ የወጣበት እለት እንደሚከበር ሁሉ ኢትዮጵያም የድል ታሪኳን እያከበረች መሄዷን ትቀጥላለች። ከእንግዲህ ሥልጣኔና ብልጽግናዋን አፈር ለሚያለብሱ አካላት ቦታ የላትም። ለጊዜው መኖራቸው እያወቀች፣ መንገዷን እንደሚቆፍሩ እያየች፣ ‹አንድ ቀን ወደ ቀልባቸው ሊመለሱ ይችላሉ› በሚል ተስፋ ዐይታ እንዳላየ ታልፋቸው ይሆናል። ነገር ግን በየትኛውም ዕንቅፋት ከመንገዷ አትገታም፡፡ አቧራውን ጠርጋ፣ አፈሩንም ንዳ ታሪክ መቀጠል እንደምትችል፣ ጉድጓድ ሲምሱላት የነበሩም ራሳቸው ሲገቡበት ታያለች። የኢትዮጵያ ድል የፈተናዎቿን ብቻ ሳይሆን የፈታኞቿንም ታሪክ እንደሚዘጋ ምንም ጥርጥር የለውም።", "passage_id": "51d8189d94bd752528e776cccf260acc" }, { "passage": "አሜሪካ ሕግን በመጠቀም ጥቁር ዜጎቿ ላይ ግፍ ትፈፅማለች?\\nዓለምም ጆርጅ ፍሎይድ ህይወቱ እንድትተርፍ ሲማፀን፣ የሞቱ እናቱን እንዲደርሱለት ሲጣራ፣ የመጨረሻ እስትንፋሱን እንዲሁም ህይወት አልባ ሰውነቱን ተመልክቷል።\n\nበሚኒያፖሊስ እንደ እንስሳ የተገደለው ጆርጅ ፍሎይድ አሟሟት አሜሪካን ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም የሚገኙ ጥቁሮችን እንዲሁም የመብት ታጋዮችን ቁጣና ተቃውሞ አቀጣጥሏል።\n\nየጆርጅ ፍሎይድ ሞት በአገሪቷ ውስጥ ያለውን ለመቶዎች ዓመታት የቆየውን መዋቅራዊ ጭቆና፣ ታሪካዊ ኢ-ፍትሐዊነት፣ የፖሊስ ጭካኔና ሌሎችም መሰረታዊ ችግሮች ፍንትው አድርጎ አሳይቷል።\n\nብዙዎችም ጥቁር አሜሪካውያን በባርነት ንግድ በግዞት ከመጡ ጀምሮ እየደረሰባቸው ያለውን ግፍም፣ ለነፃነት የተደረጉ ትግሎችን እንዲሁም እንዴት አሜሪካ ጥቁር ዜጎቿ ላይ አሁንም ቢሆን እንዴት አይነት ግፍ እንደሚፈፀምባቸው እየተናገሩ ነው፤ እየፃፉም ነው።\n\nሚሊዮን ጥቁር አሜሪካውያን በማረሚያ ቤቶች በሚማቅቁባት፤ አገሪቱ ያወጣቻቸው ሕግና ሥርዓቶች መዋቅራዊ ጭቆና ያደርሳሉ ወይ? \n\nእስቲ አገሪቱ ፍትህን በማስፈንና ወንጀልን በመቆጣጠር ዘርፍ ረገድ በጥቁር አሜሪካውያን ላይ የሚፈፀሙ መድሎዎችን እንመልከት\n\nከታዳጊዎች ጀምሮ በተለያዩ እድሜ የሚገኙ ላይ ጥቁር አሜሪካውያን በፖሊስ ጥይት ቆስለዋል እንዲሁም ተገድለዋል። \n\nበአስራዎቹ የሚገኙ ጥቁር ታዳጊዎችም በፖሊስ በተገደሉባቸው ወቅቶችም ፖሊሶች \"ለህይወታችን ፈርተን ነው፤ ሽጉጥ ሊያወጡ መስሎን ነው\" የሚሉ ምላሾች ሲሰጡም ተሰምተዋል።\n\nይህንንም መሰረት በማድረግ የአሜሪካ ፖሊሶች ተጠርጣሪ ናቸው ብለው ጥይት የተኮሱባቸውን ሰዎች በምናጤንበት ወቅት ጥቁር አሜሪካውያን በፖሊሶች በጥይት መመታት ወይም የመገደላቸው እድል ከፍተኛ ነው።\n\nከጥቁር አሜሪካውያን በመቀጠልም ከነጭ ሕዝቦች በበለጠም ቀደምት ሕዝቦች፣ እንዲሁም ላቲን አሜሪካውያንም በፖሊሶች ይተኮስባቸዋል እንዲሁም ይገደላሉ። \n\nበአሜሪካ ከዓመት በፊት የነበረውን የሕዝብ ቁጥር ብናይ ጥቁር አሜሪካውያን አስራ አራት በመቶ ቢሸፍኑም፤ ፖሊስ ክፉኛ ካቆሰላቸው ወይም ከገደላቸው አንድ ሺህ ሰዎች ውስጥ 23 በመቶውን ይሸፍናሉ። \n\nይህም ቁጥር ከጎርጎሳውያኑ 2017 ዓመት ጀምሮ በተመሳሳይ መልኩ እየሄደ ሲሆን፤ በተቃራኒው በፖሊሶች በሽጉጥ የሚተኮስባቸው ወይም የሚገደሉ ነጮች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን መረጃዎች ያመላክታሉ።\n\nበአሜሪካ ውስጥ የአደንዛዥ ዕፅን መጠቀም በነጮችና በጥቁር አሜሪካውያን ተመሳሳይ ሁኔታ ቢኖረውም፤ ጥቁር አሜሪካውያን አደንዛዥ ዕፅ ይዘው ከተገኙ ዘብጥያ ይወርዳሉ።\n\nለምሳሌ በጎርጎሳውያኑ 2018 የተደረጉ እስሮችን እንደ ማጣቀሻ ብናይ፤ በጥቁር አሜሪካውያን ዘንድ ያለው እስር 750 ከመቶ ሺህ ሲሆን ለነጭ አሜሪካውያን ደግሞ 350 ከመቶ ሺህ ነው። \n\nነገር ግን ብሔራዊ የአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም ላይ ከጎርጎሳውያኑ 2018 በፊት በተደጋጋሚ የወጡ ቁጥሮችን ብናይ በነጭ አሜሪካውያንና በጥቁር አሜሪካውያን ዘንድ የዕፅ አጠቃቀም ልማድ ተመሳሳይ ነው።\n\nሆም የአሜሪካ የሲቪል መብቶች ህብረት ባደረገው ጥናት ጥቁር አሜሪካውያን ድንገት ዕፀ ፋርስ ይዘው ቢገኙ ያለምንም ምህረት በቁጥጥር ስር እንደሚውሉ ይፋ ያደረገ ሲሆን ይህም ከነጮች ጋር ሲወደዳር 3.7 እጥፍ እንደሆነም መረጃው አመላክቷል። \n\nበሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን በጥቃቅን ወንጀሎች እስር ላይ እንደሚገኙ የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ። \n\nበተለያየ ጊዜያትም አሜሪካ ጥቁርና ላቲን ሕዝቦቿን ወደ እስር ቤት በመወርወር ለነፃ የጉልበት ሥራ ዳርጋቸዋለች እንዲሁም የተለያዩ ኩባንያዎችም የእስር ቤት ጉልበትን በመጠቀም ላይ እንደሚገኙ የሚኣመለክቱ በርካታ ፅሁፎች ወጥተዋል። \n\nበእስር ላይ የሚገኙ ጥቁር አሜሪካውያን ከነጮች ጋር...", "passage_id": "c7c7bb18a4828ee9bef5e5d8b31a21f2" }, { "passage": "ሚሊዮኖችን የጨፈጨፉ፣ የባርያ ፈንጋዮችና የዘረኞች ሃውልቶች መገርሰስ\\nንጉስ ሊዮፖልድ ሁለተኛ አስር ሚሊዮን የሚሆኑ ኮንጎዎችን ጨፍጭፏል።\n\nምንም እንኳን እነዚህ ሰዎች ለምዕራባውያኑ ትልቅ ቢሆኑም በአፍሪካውያንም ሆነ በደቡቡ ዓለም ጭፍጨፋ፣ ዝርፊያና መደፈርን ሌሎች አሳፋሪ ታሪኮችን የፈፀሙ ናቸው። \n\nየቤልጅየሙ ንጉሥ ሊዮፖልድ ኮንጎ ላይ አስር ሚሊዮኖችን ጨፍጭፏል፣ እጅ ቆርጧል፣ ሰቅሏል። አሳሹ ክርስቶፎር ኮሎምበስም እንዲሁ ቀደምት አሜሪካውያንን ጨፍጭፏል፤ ከምድረገ ፅም እንዲጠፉ ብዙ ጥሯል። ሌሎችም ስመ ጥር የሆኑ ምዕራባውያን በርካታ ናቸው።\n\nአውሮፓና አሜሪካ በባርያ ደም እንዲሁም በቅኝ ግዛት በተዘረፈ ንብረት ከመገንባታቸው አንፃር፤ የሚኩራሩበት \"ስልጣኔም\" ሆነ በጀግንንት የሚያሞካሿቸው ሰዎች ጭቆናን በተጸየፉ የዓለም ሕዝቦች \"ዝርፊያና ጭፍጨፋ ስልጣኔ አይደለም\" በሚል ተጋልጠዋል።\n\nበአፍሪካ ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋም ሆነ ጭቆና ከታሪክ መዛግብት ለመፋቅና አዲስ ትርክት ለመፍጠር ቢሞከርም አልተቻለም። ባርያዎችን በማጋዝ የሚታወቁ፣ በቅኝ ግዛት ወቅት ጭፍጨፋን የፈጸሙ ምዕራባውያን ሃውልቶች በአሁኑ ወቅት እየተገረሰሱና እየወደሙ ይገኛሉ። \n\nከሰሞኑ ከተገረሰሱትና ጉዳት ከደረሰባቸው ሃውልቶችና ከሃውልቶቹ ጀርባ ያሉትን ሰዎች ታሪክ እንቃኝ፦ \n\nበአስራ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን የባርያ ነጋዴ የነበረው እንግሊዛዊው ኤድዋርድ ኮልስተን ከ80 ሺህ በላይ አፍሪካውያንን ወደ አሜሪካ አግዟል። ከሰሞኑም ከፍተኛ ግፍ የፈፀመውን የኤድዋርድን ሃውልት ተቃዋሚዎች ከትውልድ ቦታው ብሪስቶል በመገርሰስ ውሃ ውስጥ ከተውታል።\n\nእንግሊዝም ሆነ የትውልድ ከተማው ብሪስቶል በባርያ ንግድ ሃብትን አከማችታለች፤ በአፍሪካውያን ጫንቃ፣ ላብና ደም በልጽገዋል። \n\nባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የሃውልቱ መገርሰስን ተከትሎ የእንግሊዝ መንግሥት ድርጊቱን ቢያወግዝም ተቃዋሚዎች ግን የለውጥ ምልክት ነው ብለዋል።\n\n\"የሃውልቶች መቆም የሚያመላክተው ታላላቅ ሥራዎችን ላበረከቱ ነው። ኤድዋርድ ግን የባርያ አጋዥና ነፍሰ ገዳይ ነበር፤ ለእሱ ምልክት መቆሙ አይገባውም በማለት\" የታሪክ አዋቂው ዴቪድ ኦሉሶጋ ለቢቢሲ ተናግረዋል። \n\nሄንሪ ዱንዳስ \n\nባርነት እንዳይቆም የታገለው የሄንሪ ዱንዳ ሃውልት\n\nበስኮትላንድ መዲና ኤደንበራ ባርነት እንዲወገድ ጥያቄ ቢቀርብም በእምቢተኝነቱ ፀንቶ ያዘገየው ፖለቲከኛ ሄንሪ ዱንዳስ ሃውልት ቆሞለታል።\n\nከሰሞኑም ሃውልቱን በቀለም በመርጨት ጆርጅ ፍሎይድና ብላክ ላይቭስ ማተርስ የሚሉ ቃላቶችም ተፅፈውበታል።\n\nበቅዱስ አንድሪው አደባባይ የሚገኘው ሃውልት 46 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን በጎርጎሳውያኑ 1823 ነው የቆመው።\n\nበ18ኛው እና በ19ኛው ክፍለ ዘመን ተፅእኖ ፈጣሪ የነበረው ፖለቲከኛ \"ያልተቀባው ንጉሥ\" የሚል ስያሜም እንዲሰጠው አድርጎታል።\n\nየባርያ ንግድን የሚያስቆም ረቂቅ ሕግ በጎርጎሳውያኑ 1792 ቢቀርብም ፖለቲከኛው ለአስራ አምስት ዓመታት አዘግይቶታል ተብሏል።\n\nበሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ሃውልቱ እንዲገረሰስ ፊርማ አሰባስበዋል።\n\nምንም እንኳን ተቃውሞዎች ቢበረክትም ሃውልቱ ላይ ከተማዋ ከባርያ ንግድ ጋር የነበራትን ግንኙነት የሚያንፀባርቅ መግለጫ እንደሚጨመርና፤ ሃውልቱ እንደሚቆይ ገልፀዋል።\n\n\"በዓለም ታሪክ ውስጥ ኤደንብራ የነበራትን አስተዋፅኦ መንገር አለብን። የምንኮራበትን ታሪክ ብቻ ሳይሆን እንዲህ ሁላችንንም የሚያሳፍሩ ታሪኮችም ይፋ ሊወጡ ይገባቸዋል\" በማለት የከተማዋ ኃላፊ አዳም ማክቬሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል።\n\nንጉሥ ሊዮፖልድ ሁለተኛ \n\nንጉስ ሊዮፖልድ ሁለተኛ አስር ሚሊዮን የሚሆኑ ኮንጎዎችን ጨፍጭፏል።\n\nቤልጅየምን ለረዥም ዘመናት የገዛው የንጉሥ ሊዮፖልድ ሁለተኛ ሃውልት እንዲገረሰስ ጥያቄዎች እየቀረቡ ነው።\n\nበተለያዩ ድረ ገፆች ላይ የይገርሰስ...", "passage_id": "4b7c1d2b5606ff49b5c9c70b04bbe31d" }, { "passage": "ባሕር ዳር፡ የካቲት 24/2012 ዓ.ም (አብመድ) ምሰሶዋ አጥንት፣ ማስዋቢያ ደም፣ መሠረቷ አለት የሆነ ጠላት ችሎ የማይገፋት፣ ወርውሮ የማያጠፋት ምሥጢር የሆነች ምድር ናት፡፡ ዳሯ እሳት ነው፡፡ መካከሏ ግን ሠላም የነበረ፣ ያለ፣ የሚኖር ድንቅ ምድር ናት፤ ኢትዮጵያ፡፡ የገፋት ራሱ ወድቋል፤ የተኮሰባት ሞቷል፡፡ ያሴረባት በራሱ ገመድ ታንቆ አልፏል፡፡ እልፍ ነጋሥታት ወልዳች፤ እልፍ ልጇቿን ለመሠዋዕት አቅርባለች፡፡ ለመሠዋዕት ያቀረበቻቸው ልጆቿ ደምና አጥንት የማትናወጥ ምድር ገነባ፡፡ አርበኞቿ ነፍጥ አንግተው ይተኩሳሉ፤ ጠላትንም ከድንበር ይመልሳሉ፡፡ ብፁዕ የሆኑ ልጆቿ ደግሞ ራሳቸውን ጎድተው ሳይሰለቹ ለፈጣሪያቸው ጸሎት ያደርሳሉ፡፡ እንደኢትዮጵያ የተሰጠውን ያከበረና የተከበረም የለም፡፡አሁን የምትኖርባት ኢትዮጵያ የምትባለው ቢጫ ወርቅ በዘመን ሽክርክሪት ብቻ የመጣች አይደለችም፤ የመሠዋዕትነት ሀገርም ናት፡፡ ያቀረበችው መሠዋዕት ያሳለፈችው አያሌ የመከራ ዘመን ነው ከፍ እንደትል ያደረጋት፡፡ ትናንት ዓድዋ ላይ የወደቁት አውሬ ሲያድኑ አይደለም፤ አገር ሲያስከብሩና ሲከብሩ እንጂ፤ ዓድዋ ላይ የተተኮሰው የአርበኞች ጥይት ፊት ለፊታቸው የቆመውን የጣልያንን ወታደር ብቻ አልነበረም የሚመታው፡፡ ዓድዋ የደረሰውን በአካል ይገድላል፤ ሮምና በሌሎቹ የጣልያን ምድር የሚገኙትን ጣልያናውያን ደግሞ ወኔና ተስፋ በጭንቀት ገድሏል፡፡በዓድዋ ጥይት ነጭ ሰው ሲጠቁር ጥቁር ሰው ቀልቷል፡፡ ጥቁሩ የቀላው በኢትዮጵያውያን አርበኞች ደም መከራውን አጥቦ ነው፡፡ ነጩ ወራሪ ደግሞ ከዚያ ዘመን ጀመሮ እንገቱን እንደደፋ ነው፤ ጥቁር ግን ቀና ብሎ ሄዷል፡፡  አያቶች የጦርነቱን ዘመን አሳልፍውታል፡፡ ዓድዋ ላይ በተኮሱት ጥይት በወረወሩት ጦር አልፈው የዛሬውን ትውልድ ዕድል ያዩ ነበር፡፡ የዚህ ትውልድ ተራ የጦርነቱን ዘመን አሳልፈው ጠላት ያልረገጣት አገር የሰጡትን አያቶች እያመሠገኑ በሠላሙ ዘመን በአንድነት መኖር ነው፡፡ ዓድዋ ላይ የተተኮሰው ጥይት በአንድነትና ለአንድነት፤ ለጋራ ክብርና ልዕልና ነበርና፡፡", "passage_id": "0b0ea3c6e4f43f83651ff4b9a46490dc" }, { "passage": "ቃለመጠይቅ ከዶክተር እዝቅዔል ጋቢሳ ጋር“ባርነት የሰው ልጅ ከሰራቸው ማህበራዊ ተቋማት ውስጥ ሆነ ብሎ የሰውን ልጅ ከሰውነት አውጥቶ ወደ ንብረትነት ዝቅ አድርጎ ለመጨቆን የተመሰረተ ማህበራዊ ተቋም ነው። አብዛኛውን ጊዜ በደሉ ነው የሚታወቀው። ይሁን እንጂ ላለንበት ዓለም መሰረት የጣለ ነው። ባንድ በኩል በሶስትዮሹ የባሪያ ንግድ የተከማቸ ትርፍ ነው የካፒታሊዝም ስርዓትን የሀብት ክምችት የፈጠረው” ", "passage_id": "202c771bab6b65f5ad529ed4e083bd4a" } ]
dbf5f0842cdc5cdc6cd055a3c7aa39c8
25f633bff5f11cb8c93cf9c80464b628
“የትግራይ ሕዝብ የገጠመውን ፈተና ከፌደራል መንግሥት ጎን በመቆም ሊሻገረው ይገባል” ዶክተር ሙሉ ነጋ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ
ጽጌረዳ ጫንያለው አዲስ አበባ፡- የትግራይ ህዝብ የገጠመውን ፈተና ከፌደራል መንግሥት ጎን በመቆም ሊሻገረው እንደሚገባ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ጥሪ አቀረቡ ::የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ በዓሉን አስመልክተው በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ በክልሉ የሕግ ማስከበር ከተጀመረ ጀምሮ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ ናቸው:: በተለይም ሰላምና መረጋጋትን ከማምጣት አንፃር ጥሩ እንቅስቃሴ አለ፡፡በዓሉን ለማክበር መሰረታዊው ነገር ሰላም ነው:: በዚህ ጉዳይ ላይ ውጤታማ ሥራዎች በመሥራት ላይ ናቸው ያሉት ዶክተር ሙሉ፣ በዓሉን ተመርኩዞ ዋና አስፈላጊ የሆኑት አስቸኳይ ዕርዳታ የሚፈልጉ አካላትን ማገዝ ነው:: ይህም በከፍተኛ ሁኔታ እየተከናወነ ነው ብለዋል :: ብዙ የትግራይ አካባቢዎችም ከመብራትና ስልክ ጀምሮ ችግር የገጠማቸው በመሆናቸው ይህንንም ለማስተካከል ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን አመልክተው፣ በክልሉ ባንኮች እንዲከፈቱ መደረጉም የዚህ ትኩረት አካል እንደሆነ ጠቁመዋል:: መብራትና ስልክ እንዲሁም ውሃ ያላገኙ አካባቢዎች በዓሉን በጭለማ እንዳያሳልፉ እየተሠራ መሆኑን የሚጠቁሙት ዶክተር ሙሉ፤ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ በመሰረተ ልማት ችግር ምክንያት በተለይም በመንገድ ችግር የዕለት ደራሽ ዕርዳታውን ለማድረስ ችግር ገጥሟል:: ችግሩን በተቻለው ሁሉ በመፍታት ህዝቡ በዓልን በተረጋጋ መንፈስ እንዲያከብር እየተሞከረ ነው ብለዋል:: የገና በዓል ለትግራይ ህዝብ ቀላል አይደለም የሚሉት ዶክተር ሙሉ፤ በችግር ወቅት ውስጥ በመሆናቸው የቀደመ የመረዳዳት ባህላቸውን ተጠቅመው ተደጋግፎ፣ ሰላሙን ጠብቆና ተቃቅፎ ነገ ብሩህ ነውና ችግራቸውን ሊያልፉት እንደሚገባ አመልክተዋል። ሕዝቡ ተረጋግቶ በዓሉን እንዲያከብር ከማድረግ አንፃር በክልሉ የፀጥታ ሃይሉን የማደራጀት ሥራ መጀመሩን የገለፁት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽንም መመደቡን አስረድተዋል:: በተመሳሳይ በመንግሥት መሥሪያ ቤት ደረጃ የተሳለጠ አገልግሎት ሕዝቡ እንዲያገኝ ለማድረግም የመንግሥት መዋቅሩ ታችኛው ድረስ እንዲሠራ የማድረግ ሥራው ተጀምሯል:: የክልሉ ካቢኔም ሥራውን እየሠራ ይገኛል:: ከሰባት ዞኖች ውስጥም ስድስቱ የዞን አመራሮች ተመድበው እየሠሩ ናቸው:: ሥራውም በሚቀጥለው ሳምንት እንዲጠናቀቅ ተደርጎ በመሥራት ላይ ነው ብለዋል:: የትግራይ ህዝብ የገጠመውን ፈተና እርስ በእርስ ተጋግዞና ከፌደራል መንግሥት ጎን ቆሞ እንዲያልፍ ጥሪ ያቀረቡት ዶክተር ሙሉ፣ መጪው ጊዜ ለትግራይ ህዝብ የሰላም፣ የፍቅር፣ የብልጽግና እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 30/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=39072
[ { "passage": "\nየትግራይ ክልል በእስካሁኑ እንቅስቃሴ ሕገ-መንግስቱን አደጋ ላይ መጣሉን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አስታወቁ፡፡ አፈ ጉባዔ አደም ፋራህ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቆይታ ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕገ-መንግስታዊ ሂደቱን በጠበቀ መልኩ ምርጫውን እንዲራዘም ቢወስንም “ለሕገ መንግስቱ ተገዥ ያልሆኑና ሰላም የማይፈልጉ ቡድኖች ሕዝቡን የማወናበድ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ” ብለዋል፡፡ ምርጫ ማስፈጸም የምርጫ ቦርድ ስራ ሆኖ የትግራይ ክልል ግን ኢ- ሕገ-መንግስታዊ በሆነ መልኩ ምርጫ ቦርድ በማቋቋም፣ አግላይ በሆነ መንገድ ምርጫ በማካሄዱ በክልሉ አስተዳደር ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል በቂ ሕገ-መንግስታዊ መሰረት መኖሩን አስታውቀዋል፡፡\nእንደ አቶ አደም የክልሉን ሕግ አውጪና ሕግ አስፈጻሚዎችን ማገድ እና ለፌዴራል መንግስት ተጠሪ የሆነ ጊዜያዊ መንግስት ማቋቋምና የፌዴራል የፀጥታ አካላት በማሰማራት ሕገ-መንግስቱን አደጋ ላይ የጣለውን ድርጊት መቆጣጠር ሊወሰዱ ከሚችሉ እርምጃዎች መካከል ናቸው፡፡\nስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች መደበኛ ስራቸውን እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል።\nበኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ-መንግሥት ትርጉም በማሰጠት 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ እንዲራዘም ወስኖ ምርጫው እስኪካሔድ የፌዴራል እና የክልል ምክር ቤቶች ስራቸውን እንዲቀጥሉ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እና ከምርጫ ጋር በተያያዘ የሚተረጎም የሕገ-መንግሥት አንቀጽ አለመኖሩን በመጥቀስ የምርጫውን መራዘም የተቃወመው የትግራይ ክልል መንግሥት በክልል ደረጃ የምርጫ ኮሚሽን አቋቁሞ በክልሉ ምርጫውን አካሒዶ አዲስ መንግሥት መስርቷል፡፡\nበትግራይ ምርጫው ከመካሔዱ በፊት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ክልሉ ምርጫውን ከማድረግ እንዲቆጠብ አሳስቦ ፌዴሬሽኑ ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ ያለው ምርጫው ቢካሔድ እንኳን በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 9 (1) መሰረት እንዳልተካሔደ ይቆጠራል በሚል ለምርጫው እውቅና እንደማይሰጥ አስታውቋል፡፡\nጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኮሮና ቫይረስ ስጋት አለመሆኑ ከታወቀ በኋላ ምርጫው እንዲካሔድ በሚወሰንበት ጊዜ የትግራይ ክልል መንግሥት ምርጫውን አልቀበልም የሚል ከሆነ ችግር እንደሚፈጠር መግለጻቸው ይታወሳል፡፡\nበቅርቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከጤና ሚኒስቴር የቀረበለትን ምክረ-ሀሳብ ተቀብሎ ለምርጫው ዝግጅት እንዲደረግ ዉሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡ ይህን ተከትሎ ምርጫው በትግራይ ክልልም ጭምር እንደሚካሔድ የም/ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ የገለጹ ሲሆን ትግራይን የሚመራው ህወሓት ደግሞ የክልል ም/ቤት ምርጫ ከዚህ በኋላ የሚካሔደው ከ5 ዓመት በኋላ ነው ከማለቱም ባለፈ በባለስልጣናቱ አማካኝነት ለፌዴራሉ መንግስት ከመስከረም 25 በኋላ እውቅና እንደማይሰጥ ገልጿል፡፡\nበአሁኑ ወቅት የፌዴራሉ መንግስት እና የትግራይ ክልል መንግስት ዉጥረት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን የሕገ-መንግሥቱን ጥሰት ጨምሮ በኢትዮጵያ ለሚከሰቱ የተለያዩ የጸጥታ ችግሮች አንዳቸው ሌላኛቸውን ተጠያቂ በማድረግ ይወነጃጀላሉ፡፡", "passage_id": "a742ec24ec32cacaf3eeb7402b04f35a" }, { "passage": "የትግራይ ክልል ምክር ቤት ክልላዊ ምርጫው ይህ ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት እንዲካሄድ መወሰኑ አስታውቋል፡፡ይሁን እንጂ ምርጫው መቼ እንደሚካሄድና በማን እንደሚከናወን የጠቀሰው ነገር አለመኖሩ ተገልጿል።የትግራይ ክልል ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ታረቀ ለቢቢሲ እንደገለፁት ምርጫው ከጵጉሜ በፊት እንዲካሄድ መወሰኑን አረጋግጠዋል።የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዘንድሮ ነሐሴ መጨረሻ ላይ ለማካሄድ ታቅዶ የነበረውን አገራዊ ምርጫ ማከናወን አልችልም ማለቱ የሚታወስ ሲሆን በዚህም ምክንያት የሕገ መንግሥት አጣሪ የመንግሥትን የሥራ ዘመን ባማራዘም ምርጫው የሚራዘምበትን አማራጮች ካቀረበ በኋላ፤ የሕገ-መንግሥት ትርጓሜ የሚለው አማራጭ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁ ይታወሳል።ጉዳዩን የመረመረው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ደግሞ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ሆኖ እስከቀጠለ ድስረ ሁሉም የፌደራልና የክልል ምክር ቤቶች በሥራ ላይ እንዲቆዩ እና ምርጫው የበሽታው ስጋት መወገዱ ከተረጋገጠ በኋላ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ባለው ጊዜ እንዲካሄድ ሲል ከቀናት በፊት ወስኗል።የትግራይ ክልልን የሚያስተዳድረው ህወሓት ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ምርጫው መካሄድ አለበት ሲል አቋሙን ሲያንጸባርቅ የነበረ ሲሆን የፌደራል መንግሥቱ የሥራ ዘመኑን በማራዘም ምርጫ ለማካሄድ ያቀረበውን አማራጭ በመቃውም፤ በክልል ደረጃ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት አደርጋለሁ ማለቱም ይታወሳል።ይህንንም ተከትሎ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱኳን ሚደቅሳ “ክልላዊ ምርጫውን ለማካሄድ አስበው ከሆነ ትክክለኛ አካሄድ አይሆንም። ሕገ-መንግሥታዊም አይሆንም” በማለት፤ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 102 የተቋቋመውና እርሳቸው የሚመሩት ምርጫ ቦርድ በፌደራል፣ በክልል እና በቀበሌ ደረጃ የሚካሄዱ ምርጫዎችን የማስፈጸም ብቸኛ ስልጣን የተሰጠው መሆኑን አስታውቀው ነበር ሲል ከቢቢሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡", "passage_id": "33a447ef636e7335a1d290232c86bd9e" }, { "passage": "የትግራይ ክልል ም/ር/መስተዳድር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካዔል የህወኃት 45ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበርን አስመልክተው ትናንት የካቲት 12 ቀን 2012 ዓ.ም በጽህፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫን ሰጥተዋል፡፡\nበዓሉ የተለየ ትርጉም ባለው መልኩ በስኬት መከበሩን ደብረጽዮን በመግለጫቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡ ህወኃት ለግማሽ ምዕት ዓመት የተቃረበ እድሜን አስቆጥሮ የምስረታ በዓሉን ማክበሩ ብቅ ብለው በቶሎ እንደሚጠፉ ፖለቲካ ፓርቲዎች አለመሆኑን እና ተቋማዊ ቅርጽ መያዙን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡\nይህ የካበተ ያሉት ልምድ ለጦርነት የሚጋብዙ ጸብ አጫሪ ድርጊቶች በፌዴራል መንግስቱ ሲፈጸሙ እንኳን በትዕግስት ለማስቆምና ህግና ስርዓት እንዲከበር ጠይቆ ለማለፍ እንዳስቻላቸውም ነው የገለጹት፡፡ ለዚህም ወደ መቀሌ መጥቶ ነበር ያሉትን የታጠቀ የፌዴራል ኃይል በማሳያነት አንስተዋል፡፡\nይህ ወደ ውጊያ ለመግባት በቂ ምክንያት ቢሆንም ከክልሉ እውቅና ውጭ የገባውን ታጣቂው ኃይል ከኤርፖርት እንዳይወጣ በመክበብ ተልዕኮው እንዳይሳካ አድርገናልም ነው ያሉት፡፡ አሁንም ሊጣሱ የማይገባቸው ቀይ መስመሮች አሉ ብለዋል፡፡\nምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ዘለግ ያሉ ሰዓታትን በወሰደው ጋዜጣዊ መግለጫቸው የተለያዩ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ አጀንዳዎች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡\nህጋዊነት የለውም ባሉት የኢህአዴግ ውህደት በህዝብ ያልተመረጠ ፓርቲ ስልጣን መያዙን ገልጸዋል፡፡ እስከ ምርጫ ድረስም ስልጣኑ የኢህአዴግ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡\n”ችግሩ መዋሃዱና ፓርቲ መመስረቱ ሳይሆን የስልጣን ወራሽ ነኝ ማለቱ ነው፤ ይህም በአቋራጭ ስልጣን መያዝ ነው ክልሎች ተቀጽላ ሆነው በብልጽግና መቀጠል አይችሉም“ ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ተቋም የሚገነባበት አንዱ መንገድ ነው ባሉት ምርጫ ይህ ችግር ይፈታል የሚል እምነት እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡\nሆኖም በፌዴራል የተወከሉ የህወኃት አባላት ከምርጫው በፊት ከኃላፊነት ሊነሱ እንደማይገባና በጉዳዩ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተወያይተው የተመደቡ ሰዎች እንዳሉና ጥያቄው ይመለሳል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ነገር ግን ገና እንደሆነ ተናግረዋል፡፡\n“የውሳኔ ነው” ባሉት በዚህ ዓመት ሊካሄድ የታሰበው ምርጫ ከነጉድለቱም ቢሆን እንዲካሄድ እንደሚፈልጉ፤ የማይካሄድ ከሆነ ግን ለውሳኔ የሚያበቋቸው አማራጮች በእጃቸው ላይ እንደሆኑ የውሳኔያቸውን ምንነትም በጊዜው እንደሚያሳዩ አስታውቀዋል፡፡\nበምርጫው የተሻለ ሀገር አቀፍ እንቅስቃሴን ለማድረግ የሃሳባቸው ደጋፊ የሆኑ የፌዴራሊስት ኃይሎችን እንደሚያሰባስቡና አሁንም ጥምረቱን የሚቀላቀሉ አዳዲስ ኃይሎች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡\nዶ/ር ደብረጽዮን በህዳሴው ግድብ ጉዳይ እጅግ አዝኛለሁ ብለዋል፡፡ ግድቡን በራስ አቅም በመገንባት የኃይል ፍላጎትን ለማሟላት እግረ መንገድንም የኃይል ምህንድስና ኢንዱስትሪዎችን ለማቋቋም ተይዞ የነበረው ሀገራዊ ውጥን መጨናገፉንም ነው የገለጹት፡፡\nሊስተካከሉ የሚችሉ አስተዳደራዊ ስህተቶች በግንባታ ሂደቱ እንደነበሩ ግን አልሸሸጉም፡፡\nሆኖም በአመራር ክፍተት ምክንያት ተጽዕኖ መምጣቱንና መሄድ የማይገባው የራስ ጉዳይ ወደ ዋሽንግተን መሄዱ ለበለጠ ጫና ማጋለጡንም ጠቁመዋል፡፡\nየትግራይንና የኤርትራን ህዝብ ወደ ቀደመ ሰላማዊ ግንኙነቱ ለመመለስ ከአሁን ቀደም የተጀመሩ የግንኙነት ስራዎችን የማስቀጠል ፍላጎት አለን ያሉ ሲሆን የሚደረጉ ግንኙነቶች ግልጽ ሊሆኑና ተቋማዊ መልክ ሊኖራቸው እንዲሁም በሚደረጉ ስምምነቶች ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡\n”ባድመ እንዲሰጠን ፌዴራል መንግስቱ ቢወስንም ወያኔ እንዳይሳካ እያደረገ ነው“ በሚል ከሰሞኑ በመሪዎች ተሰጠ የተባለውን ንግግር ኮንነዋል፡፡ “የባድመ ጉዳይ የሃገር እንጂ የትግራይ አይደለም ፤ የማይመለከተው መሪ በእኛ ሃገር ጉዳይ አያገባውም፤አደገኛ ጣልቃ ገብነት እየተደረገ ነው” ሲሉም ተችተዋል፡፡\nጠቅላይ ሚኒስትሩ በባሌ አደረጉት የተባለውን ንግግር በማስተርጎም ማድመጣቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ”የተናበበ ሴራና የውጭ ጣልቃ ገብነት አለ“ የምንለው ለዚህ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡\nመንግስት ይህን ማስቆም እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡\nኤርትራውያን ስደተኞች እንዳይመጡ መከልከሉና እና ካምፑ ይፍረስ መባሉም ተገቢ እንዳይደለ ተናግረዋል፡፡ ይህ መፍትሄ አይሆንም ያሉም ሲሆን፣ ስደተኞችን ካምፑ ባይቀበል እኛ እንቀበላለን ብለዋል፡፡\n", "passage_id": "9c37a8a79f61f9a87ca05b717055bfed" }, { "passage": "በትግራይ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ አስፈፃሚ አካላትና በፌደራሉ መንግሥት መካከል ያለው የተበላሸ ግንኙነት ህግን መሠረት ባደረገ አሠራር ብቻ እንደሚፈታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል።የሃገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር “የተሟላ ዝግጅት አለ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተወካዮች ምክር ቤት አባላት ዛሬ ባደረጉት ንግግር። ሃገሪቱ ባለፈው ዓመት “6.1 ከመቶ አጠቃላይ የምጣኔ ኃብት ዕድገት አስመዝግባለች” ብለዋል።\n", "passage_id": "9439886aa5975a16ce665fe16720fff9" }, { "passage": "\"የፌደራል መንግሥት ከውጭ ኃይሎች ተመሳጥሮ የትግራይ ሰላም ለማወክ እየሰራ ነው\" ሲሉ የህወሓት ሊቀምንበርና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ።ዶ/ር ደብረፅዮን ይህንን ያሉት የህወሓት ምስረታ 45ኛ ዓመት የካቲት 11 በዛሬው ዕለት በመቀሌ ከተማ በተከበረበት ግዜ ነው።በንግግራቸው \"በአሁኑ ግዜ በዕኩልነት የተመሰረተ አንድነት በመከተል መጓዝ ይስፈልጋል ካልሆነ የትግራይ ህዝብ በትግሉ ያመጣው መብቱ እጁ ላይ ነው ያለው\" ብለዋል።በዚህ ጉድይ ምላሽ የጠየቅነው የብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያ መንግሥት ለምስራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋት የሚሰራ እንጂ ለትግራይ ሰላም መደፍረስ ይሰራል የተባለው መሰረተ ቢስ ነው ብልዋል።\n", "passage_id": "de6527a49dc08b40131a671b9f11b718" } ]
0c70d98fe7a98997cda682e549d5392a
ca1d6c666bf66670c8f808c4b0031a68
“የኢትዮ -ሱዳን የድንበር ግጭት የአገሪቱን ልማትና ሰላም የማይፈልጉ ኃይሎች ሴራ ነው” ዶክተር ደመቀ አጭሶበአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የፖሊቲካል ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህር
ዋቅሹም ፍቃዱ አዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያና ሱዳን ለዘመናት አብረው በሰላም የኖሩና ሰፊ ድንበር የሚጋሩ ጎረቤት አገራት ቢሆኑም በቅርብ ጊዜ በድንበር አካባቢ የተፈጠረው ግጭት ከድንበር በዘለለ የኢትዮጵያን ልማትና ሰላም የማይፈልጉ ሃይሎች አገሪቱን የማተራመስ ሴራ መሆኑ ተገለፀ:: በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የፖሊቲካል ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር ደመቀ አጭሶ የድንበር ግጭቱን አስመልክቶ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ የኢትዮጵያና ሱዳን ሰፊ ድንበር የሚጋሩ፣ ለዘመናት በሰላም አብረው የኖሩ ሕዝቦች ናቸው።በአገራችን እየተካሄደ ያለውን የሕግ ማስከበር ሂደት ተከትሎ ሱዳን በድንበር አካባቢ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት መክፈቷ ያልተለመደ ክስተት መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ደመቀ፤ ከግጭቱ በስተጀርባ የአገራችንን ሰላም የማይፈልጉ ግብጾችና የኛው አኩራፊ ሃይሎች መኖራቸው ቅንጣት አያጠራጥርም ብለዋል:: ኢትዮጵያ ከግብጽ ይልቅ የሱዳን ታሪካዊ ወዳጅና አጋር መሆኗን ያመለከቱት ዶክተሩ፤ እ.ኤ.አ በ1973 እስከ 1983 በኮሎኔል ኒሜሪ ዘመን በታሪክ ተረጋግታ የማታውቀው ሀገር ሱዳን ለአስር ዓመታት ያህል በንጉሥ ኃይለ ሥላሴ እገዛ ሰላም ሰፍኖባት እንደነበር አስታውቀዋል:: በወቅቱ አንፃራዊ ሰላም የሰፈነው ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ኮርድ አማካይነት ለደቡብ ሱዳኖች እውቅና ሰጥታ ወደ ፌዴራል መንግሥት እንዲካተቱ በማገዟ እንደሆነም አመልክተዋል::እ.ኤ.አ በ1989 በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን በያዙት በኮሎኔል ኦማር አልበሽር ዘመንም በደቡብ ሱዳንና በሱዳን መካከል በተፈጠረው ግጭት፣ በተለይ በዳርፉር ግጭት አስከፊ ሰብዓዊ ቀውስ እንዳይፈጠር የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ድርሻ ጉልህ መሆኑንም ጠቁመዋል::ሱዳን በዓባይ ወንዝ፣ በድንበር፣ በህዝቦች አሰፋፈር ወይም ትስስርና በሌሎች ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ጋር የተሳሰረች በመሆኑዋ፤ አገሪቱን በጥንቃቄ መያዝ እንደሚያስፈልግ ገልፀው፤ የህዳሴው ግድብ ድርድር ፍትሐዊ እንዲሆን ሱዳን ለኢትዮጵያ ያደረገችው ድጋፍ ቀላል ባይሆን ግብጾች ፍላጎታቸውን ለማሳካት ሱዳንን አጥብቀው እንደሚፈልጉ መዘንጋት የለብንም ብለዋል:: በእጅ አዙር ኢትዮጵያን ለመጉዳት ፈልጋ ነው እንጂ፤ ግብጽ በታሪክ የሱዳን አጋዥና ወዳጅ ሆና እንደማታውቅ ይልቁን ከቅኝ ገዥዋ ከእንግሊዝ ጋር በመሆን ደቡብና ሰሜን ሱዳንን በሃይል መግዛቷን ዶክተሩ አስታውቀዋል። እ.ኤ.አ በ1929 እና በ1959 የዓባይ ውሃን አጠቃቀም አስመልክቶ በግብጽና በሱዳን መካከል የተደረገው ስምምነት እንኳ የሱዳንን ብሔራዊ ጥቅም በእጅጉ የሚጋፋ መሆኑን በማስታወስ፤ ግብጽ በታሪክ ሱዳንን ከመጉዳት ወደኋላ ያለችበት ዘመን እንዳልነበር አስታውቀዋል::እንደ ምሁሩ ገለፃ፣ ሱዳን በብዙ ምክንያቶች በርካታ ጥንቃቄ የምትፈልግ ጎረቤት አገር ናት:: አንደኛ ሱዳን በታሪኳ ዘመናዊ /ህዝባዊ/ መንግሥት አቋቁማ ስለማታውቅ በዘመናዊ መንገድ የመደራደር አቅሟ አስተኛ ነው:: በሌላ በኩል ደግሞ ሁኔታን በማየት አቋሟን የምትቀያይር አገር ናት:: በኢትዮጵያ በኩል ነገሮች ጥሩ ሲሆኑ ወደ ኢትዮጵያ ፣ ሲከፋት ደግሞ ከግብጽ ጋር የመወገን አዝማሚያ አላት:: ሌላው ችግሯ ደግሞ አሁን አገሪቱን እያስተዳደሩ ያሉ ሃይሎች በተለይ ወታደራዊ ሃይሉ የውስጥ ችግሩን በማዳፈን ሥልጣን ላይ ለመቆየት ከግብጽ ድጋፍ ለማግኘት ከኢትዮጵያ ጋር የሚጋጨውን የግብጽ አጀንዳ ለማራመድ ይገደዳል ያሉት ዶክተር ደመቀ፤ ለዚህ ማሳያ ደግሞ የሱዳን ሚሊሻዎች በድንበር አካባቢ እየፈጠሩ ያሉት ችግር በቂ ነው ብለዋል::ኢትዮጵያ በታሪክ የሌላውን ድንበር ጥሳ ባታውቅም፣ የግብጽም ሆነ የሌሎች አኩራፊ ሃይሎች ድብቅ ዓላማ ለማክሸፍ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የአገራችን ሉዓላዊነትን ባስከበረ መልኩ የሱዳንንም ጥቅም ባልጎዳ ሁኔታ ታሪካዊ ሁኔታዎችን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ድንበር የማካለል ሥራ ከወዲሁ መጀመር እንዳለባት ጠቁመዋል። ሰላም ማውረድ በአንድ አገር ፈቃደኝነት ብቻ የሚረጋገጥ ስላልሆነ በሌላኛው ወገን ከዲፕሎማሲ አልፎ በጉልበት ተገፍቶ በአገር ሉዓላዊነት ላይ የሚመጣው ማንኛውንም ጥቃት ለማስተናገድ ታሪካችንም ስለማይፈቅድ መመከት የመጨረሻ አማራጭ እንደሚሆን ገልፀዋል:: አሁን የተፈጠረው ችግር በጥንቃቄ ካልተያዘ በብዙ ነገሮች የተሳሰሩ የምሥራቅ አፍሪካ አገራትንም ቀውስ ውስጥ ሊከት እንደሚችልም ምሁሩ አሳስበዋል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 30/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=39077
[ { "passage": "የሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዶክ ከሱዳን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ሀገራቸው ከጎረቤት ኢትዮጵያ ጋር ጸብ የመፍጠር ዓላማ የላትም ሲሉ ተናግረዋል፡፡\nጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄን ያሉት በሱዳን በነበረው የለውጥ እንቅስቃሴ ወቅት የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ሀሰን አልበሽርን ከስልጣን ካወረደ በኋላ ለተቃውሞ አደባባይ የነበሩ ሰልፈኞች ወደ ቤታቸው እንዲገቡ በማስጠንቀቅ በወሰደው እርምጃ በርካታ ሰዎች የተገደሉበትን አንደኛ ዓመት መታሰቢያ በማስመልከት ከብሔራዊ ቴሌቪዥኑ ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው፡፡\nከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ የተለየ የድንበር ችግር ጉዳይ የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ቀደም ሲልም በተለያዩ ጊዜያት የነበረ ነው ብለዋል፡፡ ሱዳን ከተለያዩ ጎረቤት ሀገራት ጋር የድንበር ችግሮች ሲያጋጥሟት እንደነበርም አውስተዋል፡፡\n“ከኢትዮጵያ ጋር ያለን ግንኙነት በባህል ፣ በታሪክ እና በመልክአ ምድር እና በመልካም ጉርብትና የተሳሰረ ነው” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ እናም “በመካከላችን የሚፈጠሩ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችሉ ስልቶች አሉን” ብለዋል፡፡ በመሆኑም ከሰሞኑ የተፈጠረው ክስተትም በዚህ መንገድ እንደሚፈታ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዶክ ገልጸዋል፡፡\nበትናንትናው እለት ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ቆይታ ያደረጉት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን “ከሱዳን ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ ሲናፈሱ የሰነበቱት ጉዳዮች የግድቡን አጀንዳ ወደ ድንበር አጀንዳነት ለማምጣት በማሰብ የተደረጉ” እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ባለፈ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተለየ ለግጭት የሚዳርግ ምክንያት እንደሌለ እና የቆየ ወዳጅነት ያላቸው ሁለቱ ሀገራትበድንበር አካባቢ አልፎ አልፎ የሚፈጠሩ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ የሚፈጡበት የቆየ ስልት መኖሩን አውስተዋል፡፡\nሆኖም የሃገራቱን የጋራ ጥቅም በሚያስተሳስር መልኩ ግጭቱ እንዲፈታ የሃገራቱ ህዝብና መንግስታት ፍላጎት በመሆኑ ለዚህ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡\nሱዳንና ኢትዮጵያ አመታትን የዘለቀ ጠንካራ ዘርፈ ብዙ ግንኙነት አላቸው ያሉት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊው ግጭት እንዲቀሰቀስ በማሰብ የተዛቡ መረጃዎችን በስፋት ለህዝቡ በሚያደርሱ የሶስተኛ ወገን ሚዲያዎች የሰሞኑ ሁኔታ ተጋንኖ እየተራገበ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡\n", "passage_id": "55cf23577829060e03e05602a6e67413" }, { "passage": "ዘላለም ግዛው አዲስ አበባ፦ ሱዳን የድንበር ውዝግቡን አስመልክቶ እየሄደችበት ያለው የተሳሳተ መንገድ በአባይና በሌላም ምክንያት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ከሚፈልጉ አገራት ጋር ሊያያዝ እንደሚችል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ተገኝ ገብረእግዚአብሄር አስታወቁ ፕሮፌሰር ተገኝ በወቅታዊው የኢትዮ-ሱዳን የድንበር አለመግባባት ዙሪያ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት ፣ ሱዳን የድንበር ውዝግቡን አስመልክቶ እየሄደችበት ያለው መንገድ በአባይና በሌላም ምክንያት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚፈልጉ አገራት ጋር የሚያያዝ ሊሆን ይችላል። አሁን ሀገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ እንደ ጥሩ አጋጣሚ የወሰዱት ይመስላል። አንዳንድ አገራት ኢትዮጵያ ከተበታተነች የህዳሴ ግድቡ ሊቆም ይችላል የሚል እምነት እንዳላቸው የጠቆሙት ፕሮፌሰሩ፣ አላማቸውን ለማሳካትም ሀገሪቱ አለመረጋጋት ውስጥ የምትሆንበትን ጊዜ እንደሚመርጡ ገልጸዋል። አሁን ሀገሪቱ ያለችበትን ሁኔታም እንደ ጥሩ አጋጣሚ ወስደው እየተንቀሳቀሱ ስለመሆናቸው ድርጊታቸው በግልጽ ያሳያል ብለዋል። አሁን በኢትዮጵያ ሰሜኑ አካባቢ ያለውን የጸጥታ አለመረጋጋት እንደምቹ ሁኔታና ጊዜ የተመለከቱት ይመስለኛል ያሉት ፕሮፌሰር ተገኝ፣ የድንበር ችግሩ ለረጅም ጊዜ በእዚህ ደረጃ ሳይነሳ ቀርቶ አሁን በተለየ መልኩ መነሳቱና ችግሩን ባልተገባ መልኩ ለመፍታት መሞከሩ ይህንኑ እውነታ በተጨባጭ የሚያሳይ እንደሆነ አመልክተዋል። የህዳሴ ግድቡ ላይ ሱዳን ብዙ ጊዜ የሚያወላውል አቋም እንዳሳየች ያስታወሱት ፕሮፌሰሩ ፤ አሁንም በግድቡ ላይ ያላትን አቋም በግልጽ ለይቶ ማወቅ እንደሚያስቸግር አመልክተዋል። ግብጾች ግን ግድቡ እንዳይሰራ፣ ግንባታው እንዲቆም፣ የግድቡ ግንባታ እንዲሰናከልና ግድቡ ውሃ እንዳይሞላ ብዙ ጥረት ማድረጋቸውንና ይሄንኑም በግልጽም መናገራቸውን አስታውሰዋል።", "passage_id": "58da1d72705ad054e3bd7bd972203c73" }, { "passage": "ከአንድ መቶ ዓመታት በላይ ያለምንም መፍትሄ የዘለቀው ኢትዮጵያ ሱዳን ድምበር ይገባኛል ጥያቄ በተለያዩ ጊዜያት ለሚከሰቱ ደም አፋሳሽ ግጭቶች ምክንያት መሆኑን አንድ የወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር ገለጹ፡፡መንግሥት በይገባኛል ጥያቄው አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ የታሪክና የሰነድ ማስረጃዎች፤የምሁራን ግብአቶችንም መጠቀም ይገባዋል ነው ያሉት።በወሎ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁር የሆኑት ዶ/ር አለማየሁ እርቅ ይሁን የሦስተኛ ድግሪያቸውን የማሟያ ጽሁፍ\"የጠረፍ ጉዳይና የድምበር ይገባኛል በኢትዮጵያና ሱዳን መካከል\" በሚል ርዕስ ነው የሰሩት፡፡በቅርቡ በሁለቱ አገራት የተስተዋለውን የድምበር ግጭት አስመልክቶ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ አስተያየታቸውን ጠይቋቸዋል፡፡\n", "passage_id": "3908373b6267777898fe7f9cbffd9186" }, { "passage": "ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ሁለት አገሮችን ያወዛገበ ድንበር፤ ከፍ ያለ የእርሻ ልማትና ተያያዥ ኢንቨስትመንቶች የሚደምቁበት አካባቢ ነው።ለመሆኑ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር መልክ ምን ይመስላል?ለመሆኑ ከዚህ ድንበር ጋር በተያያዘ ያለው ታሪክ ምንድነው?የአልፋሽቃ ማዕዘን በሁለቱም አገሮች የሚገኙ የአካባቢው ነዋሪ ድንበርተኞች የይገባናል ጥያቄን ያነሱበታል፡፡ ይህ ለረዥም ዘመን የዘለቀ ጉዳይ ነው።ባለፈው ሳምንት በርካታ የሱዳን ወታደሮች ከኢትዮጵያ በኩል በተሰነዘረ የሚሊሻ ጥቃት መገደላቸው ተዘግቧል።ካርቱም ክስተቱን \"የደፈጣ ጥቃት\" ስትል ጠርታዋለች፤ ድርጊቱ የተፈጸመው በሚሊሻዎች እንደሆነ ተጠቅሷል።በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በኩል ክስተቱ ያልተስተባበለ ሲሆን \"ድንበር ጥሰው በገቡ ኃይሎች ላይ የተወሰደ ራስን የመከላከል አስፈላጊ እርምጃ ነው\" ብለውታል።እንዲህ ዓይነት የድንበርተኞች ግጭት በተደጋጋሚ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ላይ ይከሰታል። ግጭቱ ቦታው የእኛ ነው በሚሉ ኢትዮጵያዊያን አራሽ ገበሬዎች እና \"የለም አካባቢው የእኛ ነው\" በሚሉ የሱዳን ጎረቤቶቻቸው መካከል የሚከሰት ነው።ይህ ክስተት የተሰማው ደግሞ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትግራይ ክልል የተካሄደው ሕግን የማስከበር ወታደራዊ እርምጃ መጠናቀቁን በገለጹ ማግስት መሆኑ ነገሩን ላልተረጋገጡ ፖለቲካዊ ትርጓሜና መላምቶች አጋልጦታል።የፌዴራል መንግሥት ወታደሮች መቀለን መቆጣጠራቸው እንዲሁም ጦርነቱን ተከትሎ 50ሺህ ዜጎች ወደ ሱዳን መሰደዳቸው የቅርብ ሳምንት ትኩስ ክስተት ነው።የድንበር ግጭቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትዊተር ሰሌዳቸው፤ \"እንዲህ ዓይነቱ ክስተት በሁለቱ አገሮች ያለውን ጥብቅ ቁርኝት አይበጥሰውም፤ እኛ ሁልጊዜም ችግሮቻችንን በውይይት ነው የምንፈታው\" ብለዋል።ሁለቱ አገሮች ዛሬ ማክሰኞ ይህን ለዘመናት ያልተፈታውን የድንበር ችግር በተመለከተ ንግግር ይጀምራሉ ተብሏል። ይህንንም የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጽሕፈት ቤት እሑድ ዕለት ነው ቀደም ብሎ ያስታወቀው።ኢትዮጵያና ሱዳን የሚጋሩት ድንበር ርዝመት 750 ኪሎ ሜትር ያካልላል። ነገር ግን ይህ ድንበር አብዛኛው ርቀት ግልጽ በሆነ መንገድ መሬት ላይ አልተመላከተም።ይህን ለማሳካት ተደጋጋሚ ንግግሮች ተጀምረው በተደጋጋሚ ተቋርጠዋል።አሁን ኢትዮጵያና ሱዳን ያሉበት አካባቢ ታሪካዊ ሁኔታዎች ከብሉ ናይል እና አትባራ ወንዞች ጋር በአንድም በሌላም መልኩ የተጋመዱ ናቸው።እነዚህ ወንዞች ሁለቱ ሕዝቦች በንግድና በሌሎች መልኮች እንዲገናኙ ለዘመናት ምክንያት ሆነው የቆዩ ናቸው። ነገር ግን ንግድ ብቻ ሳይሆን ለተከታታይ ግጭቶችም መነሻ ናቸው፡፡ በተለይም ድንበር ላይ ለሚነሱ ግጭቶች።በ19ኛው ክፍለ ዘመን የቅኝ ገዢዎች ያበጇቸው ድንበሮች ሱዳንን፣ ግብጽንና ሌሎች የሰሜን ምሥራቅ አፍሪካ አገራትን የአሁን ቅርጽና መልክ ፈጥረውላቸዋል።ዶ/ር ወንድወሰን ተሾመ የተባሉ ተመራማሪ፤ \"የአፍሪካ ቅኝ ግዛት ዘመን ድንበሮች በተለይም የሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ\" በተሰኘና በእንግሊዝኛ በተጻፈ ጥናታቸው እንደገለጹት የሁለቱ አገሮች ድንበር የአሁን ጊዜ ወሰን እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1902 እና በ1907 የተደረጉ የአንግሎ-ኢትዮጵያ የካርታ ላይ ምልከታ ስምምነቶችን መሠረት ያደረጉ ናቸው።በቅኝ ግዛት ወቅት በሱዳንና በኢትዮጵያ መሬት ላይ ለተመላከቱ ድንበሮች ኃላፊነቱ ተሰጥቶት የነበረው ሁነኛ ሰው የአይሪሽ ተጓዥና አሳሽ የነበረው ቻርለስ ግዊይን ነበር።የሱዳን ገዳሪፍና ብሉ ናይል ግዛቶች ከአማራ ክልል ጋር ይዋሰናሉ። በ1908 ነበር በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ድንበር የተሰመረው።መልካሙ ዜና በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያና በሱዳን መንግሥታት መካከል ይበል የሚያሰኝ ግንኙነት ነው ያለው፡፡ ይህም ማለት ሁኔታዎች ከመካረራቸው በፊት በንግግር የመፍታት ሰፊ ዕድል ይሰጣል።የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር በ2001 ዓ.ም አዲስ አበባን ሁለት ጊዜ ጎብኝተዋል።የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም በቀጣዩ ዓመት፤ ማለትም በ2002 (እ.አ.አ) ካርቱምን ጎብኝተዋል። ይህም በሁለቱ አገሮች መካከል የነበረው ግንኙነት መልካም እንደነበረ አንድ ማሳያ ነበር፡፡ ይህ ግንኙነት አሁንም መልኩን አልቀየረም።ቀረብ ባለው ዘመንም ቢሆን በሚያዚያ 2012 የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ በሱዳን ጉብኝት አድርገው ነበር።ባለፈው ግንቦት ወር ደግሞ የሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ኦማር በሽር ማኒስ ወደ አዲስ አበባ ልኡክ ይዘው ሄደው ነበር። በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ ቡድን ለንግግር ተቀምጦ ነበር።ይህ ውይይት በግንቦት 10/2012 ሲጠናቀቅ የድንበር ንግግሩ የወሰን ማካለሉን ጉዳይ ወደተሻለ ደረጃ ሊያደርስ፣ የአካባቢው ሕዝቦችን ዘላቂ ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችል ደረጃ መድረሱን አቶ ደመቀ ጠቅሰው ነበር።አርሶ አደሮች ያለስጋት ወደ ግብርናቸው እንዲመለሱ፣ ተገቢነት የሌላቸው እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ ሁለቱ አገሮች መስማማታቸውም ያን ጊዜ ተገልጾ ነበር።ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በይገባኛል የምትወዛገብብት አካባቢ ረዥም የግዛት ድንበር ነው ያላት። ሁለቱም አገሮች ለም ነው የሚባለውን ፋሽቃ አካባቢን እጅጉኑ ይፈልጉታል።ይህ በሁለቱ አገሮች ዓይን ውስጥ ያለው አካባቢ የአልፋሽቃ ማዕዘን ወይም የአልፋሽቃ ጥግ ተብሎ ይጠራል።በዚህ ድንበር ሁለቱም አቅጣጫ የሚገኙ ገበሬዎች ባሻገራቸው ያሉ ለም መሬቶች ላይ ያማትራሉ። አልፋሽቃ ማዕዘን በደቡብ ምሥራቅ ሱዳን ምሥራቃዊ ገዳሪፍ የሚገኝ ለም መሬት ነው።አልፋሽቃ መሬት 250 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍንና 600 ሺህ ኤክር ለም መሬትን የሚሸፍን ነው። ለለምነቱ ምክንያት የሆኑት እንደ አትባራ፣ ሰቲት እና ባስላም ወንዞችም በቅርብ ይገኛሉ።የሱዳን ባለሥልጣናት አልፋሽቃ የሱዳን ግዛት ነው ይላሉ። አሁን በኢትዮጵያን እጅ ለምን ሆነ ሲባሉ፣ \"የሱዳን መንግሥት ከአገሪቱ ጋር ባለው የትብብርና የመግባባት ስምምነት መንፈስ ነው የኢትዮጵያ ገበሬዎች ቦታውን አሁን እያለሙት ያሉት\" ይላሉ።ሁለቱ መንግሥታት ከዚህ ቀደም ይህንን አወዛጋቢ ድንበር በድጋሚ ለማስመር፣ የጋራ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር እና የአካባቢው ሕዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር።ቀደም ካለው አስተዳደር ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት በአገሬው ሕዝብ ሉአላዊ መሬቱን ቆርሶ እየሰጠ ነው በሚል ተደጋጋሚ ወቀሳ ሲቀርብበት ነው የቆየው።እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2014 የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የወቅቱ ሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸውን ድንበሩ መሬት ላይ የሚመላከትበትን የመጨረሻ ቀን እንዲያሳውቁ መመርያ አስተላልፈውላቸው ነበር።ሆኖም አወዛጋቢውን ድንበር መሬት ላይ የማመላከቱ ሥራ እስከዛሬም አልተሳካም፡፡ይህ ዛሬ የሚጀመረው ንግግርስ ለውዝግቡ የመጨረሻ እልባት ይሰጣል ወይ? የሚለው በጊዜ ሂደት የሚታይ ነው የሚሆነው።", "passage_id": "933ee8d5cd2418f6675c4c1fe129745f" }, { "passage": " በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል የድንበር ማካለል ሥራ እንደሌለ የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ ለቪኦኤ ገለፁ፡፡“ከአሉባልታና ከወሬ ያለፈ ነገር የለም” ብለዋል አስተዳዳሪው፡፡አንዳንድ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ደግሞ በውጭ መገናኝ ብዙኃንና በማኅበራዊ መገናኛዎች ድንበር የማካለል እንቅስቅስሴ እንዳለ ይናገራሉ።ከድንበር አከባቢ ተፈናቅለዋል ወይም ተሰድደዋል የሚሏቸውንም በዋቢነት ያቀርባሉ።መለስካቸው አምሀ በአካባቢው ተገኝቶ ነዋሪዎችንና ባለሥልጣናትን አነጋግሯል፡፡የዘገባውን የመጀመሪያ ክፍል ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡", "passage_id": "3a5f7aa45d14f7fda2de78b90753174c" } ]
0fed57323c23fc1885acc7a3da084f0e
b174af5f494c5f9f4397da73fecb56bb
የተፃፈበትን የብር ኖት አትቀበሉ በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ መሠረተ ቢስ መሆሙ ተገለፀ
 በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ ፦ የተፃፈበትን የብር ኖት አትቀበሉ በሚል እየተሰረጨ ያለው መረጃ መሠረተ ቢስ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።ባንኩ ለዝግጅት ክፍሉ በላከው መግለጫ እንደሚታወቀው፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የብር ኖት አሳትሞ ሥራ ላይ አውሏል። ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም በመላ አገሪቱ የብር ኖት ቅያሪ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡የብር ኖት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚታተም የሕዝብ ሀብት መሆኑን በመግለጫው የጠቆመው ባንኩ፣ የብር ኖቱ በጥንቃቄ ተይዞ ሕብረተሰቡ ለረጅም ጊዜ ሊገለገልበት እንደሚገባ አመልክቷል። ከዚህ አንፃር ሆን ተብሎ ወይም በቸልተኝነት በብር ኖት ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት እንዲሁም ብዛት ያለው ገንዘብ ሕግን ባልተከተለ መልኩ ያለአግባብ እንዳይከማች ለማድረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር CMD/01/2020 ማውጣቱ አስታውሷል፡፡በመሆኑም፣ የብር ኖቱ ረጅም ጊዜ እንዲያገለግል በማስብ) በብር ኖቱ ላይ መፃፍ፣ መቅደድና በቀለም ማበላሸት፣ የትኛውንም ዓይነት ጉዳት ማድረስና ምልክቶቹን ያለፈቃድ ማባዛት የተከለከለና በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን አስታውቋል።ለማስታወቂያሥራ ከተፈለገ ለማባዛት የባንኩን ፈቃድ ማግኘት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁሞ፣በጣም የተጎዱ የብር ኖቶች ሲያጋጥሙ ከዝውውር ስለሚወጡበት ሁኔታ ዝርዝር መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጿል።ባንኩ መመሪያውን ወደ አማርኛ በማስተርጎምና በማብራራት ስለብር ኖት አጠቃቀም በየጊዜውለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ የሚሠራ መሆኑን አመልክቶ፣ “የተፃፈበትን የብር ኖት አትቀበሉ” እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ መሠረተ ቢስ መሆኑን አስታውቋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 30/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=39076
[ { "passage": "የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነባሩን በአዲሱ ብር ለመተካት እየተካሄደ ባለው እንቅስቃሴ፣ ከ90.4 ቢሊዮን ብር በላይ አዲሱን ብር ማሠራጨቱንና በአገሪቱ ከሚገኝ አንድ ቅርንጫፍ ውጪ ለ6,561 ቅርንጫፎች መድረሱን አስታውቋል፡፡ ከብር ለውጡ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በትናንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ብሔራዊ ባንክ ከ74.9 ቢሊዮን ብር በላይ አሮጌውን ብር ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሰብስበዋል፡፡ የባንኩ ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ደስታ እንደገለጹት፣ በአሁኑ የብር ለውጥ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ጠቁመው፣ ከአንድ ቅርንጫፍ ውጪ በሁሉም የባንክ ቅርንጫፎች አዲሱ የብር ኖት መሠራጨቱን አመልክተዋል፡፡ በአንዱ ቅርንጫፍ አዲሱን የብር ኖት ማድረስ ያልተቻለውም ከፀጥታ ችግር ጋር ስለመሆኑም ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡ በትናንቱ የብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ፣ ከአዲሱ የብር ኖት ለውጥ ጋር በተያያዘ አዲስ የተከፈቱ የባንክ አካውንቶች ቁጥርን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ከተሰጠው መረጃ የተለየ አኃዝ የሌለ መሆኑን ነው፡፡ ቀደም ብሎ በዋና ገዥው በተሰጠ መግለጫ በብር ለውጥን ምክንያት ከ580 ሺሕ በላይ አዳዲስ የባንክ ሒሳቦች መከፈታቸው የተገለጸ ቢሆንም፣ ትናንት መግለጫ የሰጡት ምክትል ገዥው የተከፈቱት አዳዲስ የባንክ ሒሳቦች 273 ሺሕ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የአካውንቶቹ ቁጥር ከፍና ዝቅ ሊል ይችላል በሚል የጠቀሱት አቶ ሰለሞን፣ በእነዚህ 273 ሺሕ አዳዲስ የባንክ አካውንቶች እስካሁን ከ13.5 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡ በኢኮኖሚ ውስጥ ይዘዋወራል ተብሎ ከሚገመተው 140 ቢሊዮን ብር አንፃር አሁን የተሠራጨው አዲሱ የብር ኖት የ90 ቢሊዮን ብር አካባቢ በመሆኑ የገንዘብ ለውጡ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን የሚያመለክት መሆኑ ተገልጿል፡፡ አሮጌውን የመቶ ብር፣ ከአዲሱ ደግሞ መቶና ሁለት መቶ ብር ኖትን ፎርጅድ ለመሥራት ተሞክሯል፡፡ ነገር ግን ይኼ አዲሱ የብር ኖት በጣም ረቀቅ ያለ የደኅንነት መጠበቂያዎች የተሠራ በመሆኑ፣ ጥረት ሆኖ ይቀራል እንጂ ሊሳካ የማይችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ፎርጂድ የብር ኖት ፈፅሞ ከትክክለኛው የብር ኖት የሚለይ፣ እንዲሁም በቀላሉ ማንም ሊለየው የማይችል በመሆኑ አስመስሎ ለመሥራት የማያመች በመሆኑ ኅብረተሰቡ መጠንቀቁ ተገቢ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ይሁንና በእነዚህ በተጠቀሱ አካባቢዎች አስመስለው የሚሠሩ (ሐሰተኛ) ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ይደረስባቸዋል የሚል እምነትን እንዳላቸውም አቶ ሰለሞን አስረድተዋል፡፡ እስከዚያው ድረስ ግን ኅብረተሰቡ በጣም ጥንቃቄ አድርጎ መከታተል አለበት፡፡ አዲሱን ብርና ሐሰተኛውን ብር በቀላሉ መለየት እንደሚቻልም ተናግረዋል፡፡ ‹‹ከዚህም ሌላ ሐሰተኛውን የብር ኖት ዝውውር በመጠኑም ቢሆን ለመቅረፍ፣ ኮማንድ ፖስቱ በየቦታው እየከታተለ ነው፤›› ያሉት አቶ ሰለሞነ፣ ሌሎች አካላትም ተመሳሳይ መረጃ በመስጠት እየሠሩ ነው፡፡ አዲሱን የብር ኖት ፎርጂድ ለመሥራት አስቸጋሪ ስለመሆኑ የጠቀሱት ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የከረንሲ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ አበበ ሰንበቱ በበኩላቸው፣ በእያንዳንዱ አዲስ የብር ኖት ከአሥር በላይ የደኅንነት መጠበቂያዎች ያሉና ይህንን በቀላሉ ለመሥራት ስለማይችሉ፣ ሊሠራ ይችል የሚል እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡ ሆኖም ኅብረተሰቡ እነዚህን ሐሰተኛ ገንዘቦች በቀላሉ ሊለያቸው ስለሚችል ጥንቃቄ ያደርግ ዘንድ አመልክተዋል፡፡ ሐሰተኛ የገንዘብ ሥርጭት አሳሳቢነት ያለመሆኑን የገለጹት ኃላፊዎቹ፣ ቀደም ባለው ጊዜ እንድ ወይም ሁለት ቅጠሎች፣ ሐሰተኛ ገንዘብ የሚሠሩ ቢኖሩም የፀጥታ ኃይሎች ተከታትለው ሊይዟቸው እንደሚችሉ እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሕገወጥ ወደፊትም ሊኖር ስለሚችል ይህንን ተገንዝቦ ሕዝቡ ለመከላከል እንዳለበትም አስረድተዋል፡፡ በውጭ አለ ከሚባለው የብር ኖት ጋር ተያይዞም በተለይ ጂቡቲ አለ የሚባለውን ብር በተመለከተ ኮማንድ ፖስቱ፣ ጂቡቲ በመሄድ የሠራው ሥራ ስለመኖሩ የጠቀሱት አቶ ሰለሞን፣ ምን ያህል ገንዘብ ሊኖር እንደሚችልና ከፖለቲካ አኳያም ምን መደረግ እንዳለበት እየታየ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህም ሆኖ ግን በየቦርደሩ ላይ ቁጥጥር የሚደረግና ገንዘብ እንዳይገባ ቁጥጥር እንደሚደረግ አክለዋል፡፡ በመሆኑ ይህ ገንዘብ የመጨረሻ ዕጣው መምከን ስለመሆኑ ከማብራሪያው ለመረዳት ተችሏል፡፡ ስለዚህ በውጭ የሚገኝ ገንዘብ ሕጋዊ እስካልሆነ ድረስ ይመክናል፡፡ በውጪ የሚገኝ ገንዘብ አዲሱን ገንዘብ እንዲያነቡና ሥራ የጀመሩ የኤትኤም ማሽኖች ቁጥር 5,308 ደርሰዋል፡፡ በቅርቡ 131 የሚሆኑ ማሽኖችም ሥራ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡  ", "passage_id": "1ae923542e2ff229d20fde3dcdca653d" }, { "passage": "አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 1 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)አዲሱ የብር ኖት መሰራጨት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከ46 ቢሊየን ብር በላይ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የግል ባንክ ቅርንጫፎች መሰራጨቱ ተገልጿል።የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብሔራዊ ባንክን በመወከል አዲሱን የብር ኖት ለግል ባንኮች ጭምር በማሰራጨት ላይ መሆኑን የባንኩ ፕሬዜዳንት አቶ አቤ ሳኖ ገልጸዋል።በዚህም አዲሱን የብር ኖት ማሰራጨት ከተጀመረ ጀምሮ እስካሁን ባለው ጊዜ ከ46 ቢሊየን ብር በላይ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የግል ባንክ ቅርንጫፎች መሰራጨቱን ጠቁመው÷ከዚህ ውስጥ 28 ቢሊየን ብር ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች መሰራጨቱን ገልፀዋል።ከዚሁ ጋር በተያያዘ 22 ቢሊየን አሮጌው የብር ኖት ወደ ማዕክል ገቢ መደረጉንም አቶ አቤ ጨምረው ገልፀዋል።አምስት ሺህ ብር እና ከዛ በላይ ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብር ለመለወጥ የሚመጡ ደንበኞች የብሔራዊ ባንክ መመሪያ በሚያዘው መሠረት በቁጥር ስልሳ ሦስት ሺህ ደንበኞች አዲስ የባንክ አካውንት መክፈታቸውን ገልጸዋል።በዚህም ከ 6 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ መቆጠቡንም አቶ አቤ አስረድተዋል።አዲሱን የብር ኖት በብር መክፈያ ኤቲኤም ማሽኖች ለመክፈል አዲሱን ብር እንዲለምዱ ከማድረግ አኳያም በርካታ ሥራዎች መሠራቱንም ተናግረዋል።በአሁኑ ጊዜም የኢትዮጰያ ንግድ ባንክ 3 ሺህ 700 ኤቲኤም ማሽኖች በሙሉ ማለት በሚያስችል ደረጃ አዲሱን የብር ኖት እንዲከፍሉ የማድረግ ሥራ መሰራቱንም የባንኩ ፕሬዘዳንት ገልፀዋል።ከመቶ ሺህ ብር በላይ ለሚቀይሩ ደንበኞች በቀሩት 5 ቀናት ውስጥ ሰንበትን ጨምሮ በመስራት ላይ ወዳሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች በመምጣት በቀነ ገደቡ እንዲጠቀሙ አቶ አቤ ማሳሰባቸውን ከንግድ ባንክ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።#FBCየዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።", "passage_id": "1a46aa9b39c8f56ea6455700a4ea2d38" }, { "passage": "የአሮጌው ብር ኖት ቅያሬ ታህሳስ 6 /2013 እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የስታወቀ ሲሆን  ከያዝነው ወር ህዳር 22 ጀምሮ ደግሞ በአሮጌው የብር ኖት ግብይት መፈጸም የማይቻል መሆኑም ተጠቁሟል።ከመስከረም 6/2013 አሮጌ የብር ኖቶች በአዲስ የብር ኖቶች እየተቀየሩ መሆኑ ይታወቃል።የብር ኖት ቅያሬው በሶስት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መወሰኑም ይታወሳል።ከዚህ ቀን በኋላ በባንኮች አሮጌ የብር ኖት እንደማይኖርም ገልጿል።በዚሁ መሰረት የተፈቀደው የብር መቀየሪያ የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ 25 ቀናት ብቻ እንደቀሩት ይፋ መደረጉን አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል።", "passage_id": "879d7bcef7f09fc85db17117575f8767" }, { "passage": "በመንግስት እና በግል ባንኮች የብር ቅያሪ ከተጀመረ ወዲህ ባለፉት 26 ቀናት ውስጥ 920 ሺ ገደማ አዳዲስ አካውንቶች መከፈታቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡\nዶ/ር ይናገር ከኢቲቪ ጋር በቀጥታ ስርጭት ባደረጉት ቆይታ አዲስ በተከፈቱት አካውንቶች 31 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡ የመቀየሪያ ጊዜው እስከሚጠናቀቅ በርካታ ባንክ የማይጠቀሙ ሰዎች አካውንት እንደሚከፍቱ እና ከባንክ ዉጭ የሚገኝ ገንዘብ ወደባንክ እንደሚመጣም ዶ/ር ይናገር  አብራርተዋል፡፡\n90 ቢሊዮን አዲሱ የብር ኖት ለባንኮች መሰራጨቱንም ነው የገለጹት፡፡ከ100ሺህ-1.5 ሚሊዮን ብር ለመቀየር ከተሰጠው የ 1 ወር ጊዜ ውስጥ የቀረው 4 ቀን ብቻ መሆኑን በማስታወስ የተጠቀሰውን ያህል ገንዘብ በእጁ ላይ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብም ይሁን ድርጅት በነዚህ ጥቂት ቀናት ገንዘቡን ሊቀይር እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡\nየብር ቅያሪው በመላው ሀገሪቱ በአብዛኛው “በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል” ያሉት ዶ/ር ይናገር በአንድ አንድ ቦታዎች “ሀሰተኛ የብር ኖቶች ገበያ ላይ እየታዩ ነው” ሲሉም ተናግረዋል፡፡\nሀሰተኛ የብር ኖቶች በገበያው ላይ መሰራጨት ኢኮኖሚውን ስለሚጎዳ የጸጥታ አካላት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ እና ህብረተሰቡም ይህን ለመከላከል የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡\nዶ/ር ይናገር እንደተናገሩት ከውጭ ሀገራት የኢትዮጵያ ብር አለን በኤምባሲ በኩል እንቀይር የሚል በርካታ ጥያቄ እየቀረበ ነው፡፡\nይሁን እንጂ ወደ ውጭ የሚወጣ ሰው ይዞ እንዲወጣ “ከሚፈቀደው የብር መጠን በላይ በ ውጭ ሀገር የኢትዮጵያ ብር ምንም አይሰራም ፤ ይህንን አንቀይርም” ነው ያሉት ዶ/ር ይናገር፡፡ በተለየ ሁኔታ ሊታዩ የሚችሉ ሊኖሩ እንደሚችሉ ግን የብራዊ ባንክ ገዢው አንስተዋል፡፡\nከባንክ ብር በፈለጉት መጠን ማውጣትን የሚከለክል ህግ ያስፈለገው በዚህ የሚሰራ ወንጀልንም ለመከላከል እንደሆነ በመጥቀስ በቀን በግለሰብ ደረጃ 50 ሺ ብር በተቋም ደግሞ 75 ሺ ብር ብቻ እንዲወጣ የተወሰነውም በጥሬ የሚወጣውን የብር መጠን ለመገደብ እንደሆነ ነው የገለጹት፡፡\nከዚህ በፊት ከነበረው መጠን የአሁኑ የቀነሰው በተለያዩ ባንኮች አካውንት በከፈቱ ግለሰቦች “አዲሱም ገንዘብ በብዛት እየወጣ ስለሆነ ነው” ብለዋል፡፡\nገንዘብ ላይ ምንም አይነት ጽሁፍ መጻፍ እና የተለያየ ምልክት ማድረግ በህግ የተከለከለ እንደሆነ እና ለዚህም መመሪያ መዘጋጀቱንም ነው ዶ/ር ይናገር የተናገሩት፡፡\n", "passage_id": "717c0b0ad26ece78057286b4609a9f4c" }, { "passage": "አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከነገው ዕለት ጀምሮ ከ100 ሺህ ብር በላይ አዲሱን የገንዘብ ኖት በአሮጌው ገንዘብ ኖት መቀየር እንደማይቻል ተገለፀ፡፡መስከረም 4 ቀን 2013 ዓ.ም የጀመረውን የገንዘብ ቅያሬ ሂደትን አስመልክቶ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ እና የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታ መግለጫ ሰጥተዋል።በመግለጫው ላይም ባለፈው አንድ ወር የነበረው የገንዘብ ቅያሬ ሂደት ውጤታማ እንደነበረ ነው የተናገሩት።የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በመላ ሀገሪቱ ወደ ሚገኙ የመንግስት እና የግል ባንክ ቅርንጫፎች 96 ቢሊየን ብር አዲሱ የገንዘብ ኖት መሰራጨቱን አስታውቀዋል። በዚህም ከ920 ሺህ በላይ አዳዲስ የባንክ አካውንቶች እንደተከፈቱ የገለፁት ገዢው ከባንክ ውጭ ሲዘዋወር የነበረ 31 ቢሊየን ብር ወደ ባንክ ሊገባ መቻሉን ተናግረዋል።ይህም የባንክ አካውንት ተጠቃሚዎችን ቁጥር ከማሳደጉ ባሻገር ያለአግባብ ሲዘዋወር የነበረውን ህገ ጥ ገንዘብ ወደ ህጋዊ ስርዓት እንደመለሰውም አንስተዋል።ዶክተር ይናገር ከ100 ሺህ እስከ 1 ነጥብ 5 ሚለየን ብር ያለው የገንዘብ ቅያሬ የጊዜ ገደብ ዛሬ ማብቃቱን ተከትሎ ከዚህ በኋላ የመቀየር ሂደቱ ከ100 ሺህ ብር በታች መሆኑን ገልፀዋል።የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በበኩላቸው የአንድ ወር የገንዘብ ለውጥ ሂደቱ ስኬታማ እንደነበረ ያነሱ ሲሆን ከህጋዊ መንገድ ውጭ ሲዘዋወር የነበረ በርካታ ገንዝብ ወደ ህጋዊ ስርዓቱ መግባቱን ተከትሎ የሀገሪቱ መደበኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጤናማ በሆነ መልኩ እየሄደ እንደሆነም ጠቁመዋል።ለዚህም ከህዝቡ በተጨማሪ የንግዱ ማህበረሰብ አሮጌውን ገንዘብ በአዲሱ የገንዘብ ኖት ለመቀየር በየቀኑ በማስገባት ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከቱንም ነው የተናገሩት።ከዚህ በኋላም መረጃ ላልደረሳቸውን የአርብቶ አደር እና አርሶ አደር የህብረተሰብ ክፍል አዲሱ የገንዘብ ኖት ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራም አውስተዋል።የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር ቀነዓ ያደታ እንዳሉት የብር ኖቱን ወደ ተገቢው ቦታ ለማጓጓዝ እና ህገ ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር የመከላከያ ሠራዊቱን ጨምሮ ሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ውጤታማ ተልዕኮ ፈፅመዋል፡፡በቀጣይም የብር ደህንነትን ለመጠበቅ እና ቅይይሩ የተሳካ እንዲሆን ከመከላከያ ሠራዊት እና ከሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ብዙ ይጠበቃልም ነው ያሉት፡፡ሆኖም በሂደቱ ሁለት መጠነኛ ችግሮች መስተዋላቸውን ያነሱት ሚኒስትሩ ከሀሰተኛ የገንዘብ ኖት (ፎርጂድ) ጋር በተያያዘዘ በአማራ ክልል፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአዲስ አበባ እና በደቡብ አንዳንድ ምልክቶች ተስተውለው የነበሩ ሲሆን የፀጥታ ግብረ ሀይሉ በጥምረት ባከናወነው ስራ ድርጊቱን መቆጣጠር መቻሉን አስረድተዋል።በተለይም በአማራ ክልል ማሽን ተክለው ሀሰተኛ የብር ኖት ሲያትሙ የነበሩ አካላት ከእነማሽናቸው በመያዙ በኩል የአማራ ክልል የፀጥታ ሀይል ከሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመሆን ለሰራው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።በፀጋዬ ንጉስ", "passage_id": "f69d6c147f56fbedc94447810e7f57c8" } ]
a8abb541b4baaab971eace42bb00ac77
a295232d2472edff94d8c4f1ef5dc51f
በመተከል ዞን የማንቡክ ከተማ ነዋሪዎች የፀጥታ ኃይል አባላት ሰንጋዎችን አበረከቱ
 መተከል (ኢዜአ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የማንቡክ ከተማ ነዋሪዎች በዞኑ ሕግ በማስከበር ሥራ ላይ ለሚገኘው የፀጥታ ሃይል አባላት ለገና በዓል 210 ሺህ ብር ወጪ የተደረገባቸው ስድስት የእርድ ሠንጋዎችን አበረከቱ።በፌዴራል መንግሥት የተቋቋመው ግብረ ሃይል በመተከል ዞን ፀረ ሰላም ሃይሎችን በማደንና በአካባቢው ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለመፍጠር እየሠራ ይገኛል።ግብረ ሃይሉ ከዞን እስከ ቀበሌ ባለው መዋቅር በተንኮልና ሴራ ውስጥ የገቡ አመራሮችን የማጥራት፣ ህዝባዊ አንድነትን የማጠናከርና ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን የመፍታት ሥራዎችን አጠናክሮ ቀጥሏል። በአካባቢው በዜጎች ላይ ጥቃት በመፈፀም በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ሽፍቶችን በማደን ለሕግ የማቅረብ ሥራም በማከናወን ላይ ነው።ግብረ ሃይሉ ባከናወነው ተግባር በርካታ አካባቢዎች ወደ ቀደመ ሰላማቸው እየተመለሱ ሲሆን ህዝባዊ የውይይት መድረኮችም በመካሄድ ላይ ናቸው።በዚህም ደስተኞች ነን ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡ በዞኑ ዳንጉር ወረዳ የማንቡክ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።ነዋሪዎቹ ለፀጥታ ሃይሉ ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት የበዓል መዋያውን ማበርከታቸውን ገልፀዋል።ግብረ ሃይሉ በአካባቢው ስላመጣው አንፃራዊ ሰላም ደስተኞች መሆናቸውን የገለፁት ነዋሪዎቹ፤ ድጋፋቸው እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።በዳንጉር ወረዳ ህዝቡ ባደረገው ውይይት ህዝብን ከህዝብ የማጋጨትና ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንዲፈፀም ያደረጉ አካላት ተለይተው እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቀዋል።የአካባቢው ማህበረሰብ ማንኛውንም በዓል በጋራ የማክበርና የአብሮነት ልምድ እንዳለው የገለፁት የአካባቢቅው ሽማግሌዎች “የገና በዓልን በለመድነው አብሮነት እያከበርን ነው” ብለዋል።ማህበረሰቡ የለገሰውን ስጦታ የተረከቡት ሻለቃ ፍቃዱ ጃፍራ ለተደረገው ድጋፍ ሁሉ በሠራዊቱ ስም አመስግነዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 30/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=39087
[ { "passage": "ሰኞ ማታ 2 ሰዓት ገደማ በጉባ ወረዳ አቡጃር ቀበሌ ላይ ታጣቂዎች በተፈጸመው ጥቃት 14 ሰዎች መገደላቸውን እነሱም \"የአማራ ተወላጆች ሲሆኑ ብዙዎቹም ከሰከላ አካባቢ የሄዱ ናቸው\" ሲሉ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ ለቢቢሲ ተናግረዋል። \n\nህይወታቸው ካለፈው ሰዎች በተጨማሪ ስድስት ሰዎች መቁሰላቸውን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። \n\n\"የታጠቀ የሽፍታ ቡድን ነው ጥቃቱን ያደረሰው። . . . በተቃደ መንገድ ነው የተገደሉት\" በማለት ጥቃቱ የታሰበበትና \"የብሔር ግጭት ለማስነሳት\" ታስቦ የተፈጸመ እንደሆነም ተናግረዋል። \n\nከጥቃቱ ፈጻሚዎች መካከል አንዳንዶቹ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር ጭምር ተኩስ መግጠማቸውን የጠቆሙት አቶ ግዛቸው፤ ገዳዮቹ ሳይያዙ ጫካ መግባተቻውን አስታውቀዋል። \n\n\"አካባቢው ጫካ የበዛበት አካባቢ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለመያዝ ትንሽ የሚያስቸግር ሁኔታ አለ\" በማለት ጥቃት ፈጻሚዎቹን ለመያዝ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። \n\nከጥቃቱ በኋላ የመከላከያ ሠራዊት ወደ አካባቢው መሰማራቱን አቶ ግዛቸው ጠቁመው፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥትም አስፈላጊውን ሥራ እያከናወነ በመሆኑ አሁን ላይ ስፍራው ከሞላ ጎደል ሠላም እየሆነ ነው ብለዋል። \n\nየአማራ እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ የክልላዊ መንግሥታት ከአሁን ቀደም የነበሩ መፈናቀሎችን በውይይት እና በመመካከከር \"የአማራ ከልል ዋጋ ጭምር እየከፈለ የተፈናቀሉትን መልሰን እያቋቋምን ሠላም እና መረጋጋት በአካባቢው ነበር\" ብለዋል። \n\nየአማራ መገናኛ ብዙህን ድርጅት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የጉባ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አሕመድ ኩምሳሪን ጠቅሶ እንደዘገበው ጥቃት የፈጸሙት የታጠቁ ሽፍቶች ናቸው።\n\nበጥቃቱም የ14 ሰዎች ሕይወት ማለፉንም አረጋግጠዋል፤ የቆሰሉት ከስድስት በላይ ሰዎችም ወደ ፓዌ ሆስፒታል ለሕክምና እንደተወሰዱም ዋና አስተዳዳሪው አረጋግጠዋል።\n\nሽፍቶቹን ለመያዝም የክልሉ ፀረ ሽምቅ ኃይል ክትትል እያደረገ መሆኑን አስተዳዳሪው ጨምረው አስረድረተዋል። ሽፍቶቹ ከዚህ ቀደምም መኖሪያቸውን ጫካ ውስጥ በማድረግ ሚሊሻ እና የአካባቢ ሽማግሌዎችን ሲያፍኑ፣ ሲያንገላቱ እና መሣሪያም ሲነጥቁ የነበሩና በፀጥታ ኃይሎች የሚፈለጉ መሆናቸውን አቶ አሕመድ አስታውቀዋል፡፡\n\nስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የአካባቢው ነዋሪ እንደተናገሩት \"ወደ 100 የሚጠጉ እና ከሁለት ቀበሌ የተወጣጡ ናቸው\" ጥቃቱን የፈጸሙት ይላሉ። \n\nግለሰቡ እንደሚሉት ከክልል የመጡ ኃላፊዎች ወደ ቦታው ቢያቀኑም ጥቃት አድራሾቹ ከቦታ ቦታ ስለሚንቀሳቀሱ ማግኘት አልተቻለም ብለዋል። \n\nበጥቃቱ ከሞቱት ሰዎች መካከል በትላንትናው እለት ብር ተዋጥቶ የ11ዱ አስከሬን ወደ ሰከላ መሸኘቱንም ግለሰቡ ለቢቢሲ ተናግረው፤ የመቁሰል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ደግሞ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን እንደሰሙ ገልፈዋል። \n\nከጉባ ከተማ 54 ኪሎ ሜትር አካባቢ ርቆ በሚገኝ ቦታ ደረሰ በተባለው ጥቃት ምክንያት ከ50 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ተፈናቅለው ወደ ከተማው መግባታቸውም ተሰምቷል። \n\nግለሰቡ ጨምረውም ጫካ ውስጥ አድረው በእግር የሚጓዙ ሰዎች መኖራቸውን ጠቅሰው በዚህም የተፈናቃዮች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ብለዋል። \n\nሕዝቡ ለተፈናቃዮች ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ የክልሉ መንግስትም 30 ኩንታል ስንዴ መስጠቱን ነግረውናል። \n\n\"ጥቃት አድራሾቹ ከነገ ዛሬ ይመጣሉ እየተባለ ሰዉ ስጋት አለበት እንጂ እስካሁን ሠላም ነው\" ያሉት ነዋሪው በጉባ ከተማ የተወሰኑ የመከላከያ ሠራዊት አባላት መግባታቸውንም ጠቁመዋል። \n\nበአካባቢው ከአንድ ዓመት በፊት የዘጠኝ ሰዎች ህይወት በበተመሳሳይ ጥቃት ካለፈ በኋላ፤ የአሁኑ ጥቃት... ", "passage_id": "76013cd2391b0118df9e5446a126766e" }, { "passage": "“በመተከል በዜጎች ላይ ለተፈፀመው ጭፍጨፋ የጉሙዝና የሌሎች ብሄረሰቦች የሥራ ኃላፊዎች እጅ አለበት” የድባጤ ወረዳ ነዋሪዎችባሕር ዳር፡ ጥር 01/2013 ዓ.ም (አብመድ) በመተከል ዞን በዜጎች ላይ ለተፈፀመው ጭፍጨፋና የንብረት ውድመት የጉሙዝና የሌሎች ብሄረሰቦች የሥራ ኃላፊዎች እጅ እንዳለበት የድባጤ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ።በፌዴራል መንግስት ተቋቁሞ የመተከል ዞን የጸጥታና ሕግ ማስከበር ሥራ የተረከበው ኮማንድ ፖስት በዞኑ የተለያዩ ቀበሌዎች መሽጎ በነበረው ሽፍታ ላይ እርምጃውን አጠናክሮ ቀጥሏል።ኮማንድ ፖስቱ ከመኖሪያ አካባቢዎቻቸው የተፈናቀሉ ወገኖችንም ተመልሶ ማቋቋምና ዘላቂ ሰላም ማግኘት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከኅብረተሰቡ ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል።የኮማንድ ፖስቱን የጸጥታና ሕግ ማስከበር ሥራ የሚመሩት ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ጌታሁን አብዲሳ ከድባጤ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።የውይይቱ ተሳታፊዎች እንዳሉት፤ በወረዳው ብሎም በዞኑ ለተፈጸመው ዘርን መሰረተ ያደረገ ጥቃትና ውድመት ከጉሙዝም ሆነ ከሌሎች ማኅበረሰቦች የተወከሉ የሥራ ኃላፊዎች ተጠያቂ ናቸው። በዚህ ወንጀል ተሳታፊ የሆኑ ሁሉ በሕግ እንዲጠየቁ ነዋሪዎቹ ጥያቄ አቅርበዋል።የዚህ ሁሉ እልቂትና ጭፍጨፋ መሪና አቀናባሪ የትህነግ ቡድን ያቋቋመው የጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) ነው የሚሉት ተሳታፊዎቹ፤ ከጉሙዝ ወጣቶችን በማታለል ለጥፋት እየመለመለ መሆኑንም ገልጸዋል።የጉህዴንን ውሳኔ አንቀበልም ያሉ የጉሙዝ ማኅበረሰብ አባላትም እንግልት ከማድረስ አልፎ ግድያ እንዲፈፀምባቸው እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚኖር ማንኛውም ማኅበረሰብ በሰላምና በነፃነት የመኖር መብት አለው ብለዋል።የኮማንድ ፖስቱን የጸጥታና ሕግ ማስከበር ሥራውን የሚመሩት ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ በዞኑ አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ኮማንድ ፖስቱ በሽፍታዎች ላይ ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገልጸዋል።እርምጃ መውሰድ ብቸኛ አማራጭ ባለመሆኑ የጉሙዝ አባቶች በተሳሳተ መረጃ ወይም በፍርሃት ጫካ የገቡ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።በርካታ ታጣቂዎችም በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እየሰጡ መሆኑንም አመልክተዋል።", "passage_id": "d570c95688fa2aefdb071eff4a11278c" }, { "passage": "አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የጁንታውን የሕወሓት የጥፋት ተልዕኮ ይዘው በንጹኃን ዜጎች ላይ ጥቃት ሲያደርሱ በነበሩ 23 የጸረ-ሠላም ኃይሎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የዞኑ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል፡፡", "passage_id": "b1fdc3d147d502433a7b7b63530cfe0c" }, { "passage": "ከአራት ቀን በፊት ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ጉባ ወረዳ በአንዳንድ ቀበሌዎች የተፈፀመው ጥቃት በቁጥጥር ሥር መዋሉን የጉባ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቡድን መሪ አስታውቋል።የቡድን መሪው ዛሬ ለቪኦኤ እንደተናገሩት በወረዳው ዛሬ ወደ ነበረበት ሠላማዊ እንቅስቃሴ ተመልሷል ብለዋል።የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅ/ ቤት በበኩሉ በጉባ ወረዳበተከሰተው ጥቃት ህይወታቸውን ያጡ 14ዜጎች ቤተዘመዶቻቸው በሚገኙበትአካባቢ ስርዓተ ቀብራቸው በክብር መፈፀሙን ገልፀዋል።።\n", "passage_id": "7d7164a12750c061a8f47456cc06681c" }, { "passage": "አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መከላከያ ሠራዊትና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የጸጥታ አካላት በድባጤ ወረዳ የተለያዩ አካባቢዎች ጥቃት ለማድረስ በገባው ጸረ-ሠላም ኃይል ላይ በወሰዱት እርምጃ በርካታ የጸረ ሠላም ኃይሎች መደምሰሳቸው ተገለጸ።", "passage_id": "ae69da89ae766e2fe954350e26d88aca" } ]
91604f5e4f61a53b72c94ac4fb111208
28261b71f98d88d96d6d45cfc834543c
በአፍሪካ የጋራ የነፃ ገበያ መመስረት የኢንቨስትመንት ፍሰትን እንደሚያሳድግ ተገለፀ
ራስወርቅ ሙሉጌታአዲስ አበባ፦ በአፍሪካ የጋራ የነፃ ገበያ መመስረት የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማሳደግና ግሽበትን ለመቀነስ ብሎም የእውቀት ሽግግር እንዲስፋፋ ለማድረግ እንደሚረዳ ተገለፀ። የአፍሪካ የጋራ የነፃ ገበያ ትስስር በጥንቃቄ ከተመራ እያንዳንዱን የአፍሪካ ሀገር ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ተጠቆመ። በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ዶክተር ደመላሽ ሀብቴ በጋራ የነፃ ገበያ ዙሪያ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በአፍሪካ አገራት መካከል የተቀናጀ የኢኮኖሚ ግንኙነት ባለመኖሩ አህጉሪቱ ከሰማንያ በመቶ በላይ የንግድ እንቅስቃሴዎች እያደረገች ያለችው ከአውሮፓ፣አሜሪካና እስያ አገራት ላይ ጥገኛ በመሆን ነው። በዚህም የተነሳ አህጉሪቱ ደካማ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ፣ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት የሚከሰትባትና ዝቅተኛ የእውቀት ሽግግር የሚስተዋልባት ሆና ቆይታለች። ከዚህ ቀደምም የአፍሪካ አገራት እርስ በእርስ ያላቸውን የንግድ ትስስር ለማሳደግ የተሠሩ ጅምሮች ቢኖሩም ውጤታማ ባለመሆናቸው እስከ አሁን እርስ በእርስ ያላቸው ግንኙነት ከሃያ በመቶ የዘለለ አልነበረም ያሉት ዶክተር ደመላሽ፤ በተመሳሳይ ደረጃ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ግብአቶችንም ሆነ እንደ ነዳጅ ያሉ ያለቀላቸውን ምርቶች አፍሪካ አገራት ውስጥ በስፋት እየተመረቱ ቢሆንም ሌሎች ተጠቃሚ ጎረቤት አገራት የሚያስገቡት ካደጉት አገራት ነው ብለዋል። በአህጉሪቱ የተጠናከረ የንግድ ልውውጡና የዳበረ የነፃ ገበያ ተፈጥሮ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴው የተቀላጠፈ እንዲሆንና በሚጠበቀው ደረጃ እንዲያድግ የአፍሪካ አገራት የንግድ ልውውጥ በጋራ ነፃ ገበያ ሊጠናከርና ሊስፋፋ ይገባዋል ብለዋል። በተጨማሪም የአፍሪካ የጋራ የነፃ ገበያ መመስረትና ወደተግባር መግባት አፍሪካ እንደ አህጉር ከሌላው ዓለም ጋር ለሚኖራት የንግድና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶች በር የሚከፍት እንደሚሆንም አመልክተዋል። ነፃ ገበያው በአሁኑ ወቅት በስፋት የሚታየውን ወደመካከለኛው ምሥራቅና ሌሎች አገራት የሚደረገውን የሰው ኃይል ፍልሰት ወደአፍሪካ እንዲሆን ያግዛል ያሉት ዶክተር ደመላሽ፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የእውቀት ሽግግሩም በየደረጃው የተቀላጠፈ እንዲሆን ይረዳል፤ በአገራት መካከል የሚኖረውም የዲፕሎማሲ ግንኙነት የተጠናከረ እንዲሆን ያግዛል ብለዋል። የአፍሪካ አገራት የጋራ የነፃ ገበያ ከመሰረቱ ከፈለጉ በዶላር ወይንም በራሳቸው በሀገራቱ የመገበያያ ገንዘብ እንዲሁም እቃ በእቃ የመገበያየት ዕድሉ ስለሚኖራቸው የውጭ ምንዛሬ እጥረትን እንደሚቀንስ ጠቁመው፤ ይህም ሆኖ የመንግሥት ታክስ ሊቀንስ ይችላል እንዲሁም በአገራቱ መካከል የተመጣጠነ ዕድገት ባለመኖሩ የሚፈጠር ጫና ሊኖር እንደሚችል አመልክተዋል።የአፍሪካ የጋራ የነፃ ገበያ ትስስር በጥንቃቄ እየተቆጣጠሩ መሥራት፣ ትልልቅ ተቋማትን መገንባትና ጥራት ያላቸውን ምርቶች በማምረት ለጠንካራ ውድድር መዘጋጀት ከተቻለ እያንዳንዱ የአፍሪካ አገር ተጠቃሚ ይሆናል ሲሉም ዶክተር ደመላሽ ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 30/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=39078
[ { "passage": "የአፍሪካ ሀገራት ነጻ የንግድ ቀጠናን ተግባራዊ ለማድረግ ተስማሙ። ስምምነቱ የሀገራቱን ምጣኔ ሀብት በእጅጉ የሚያሳድግና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለዉን የንግድ ልዉዉጥ በእጥፍ ሊያሳድግ የሚችል ስለመሆኑም ተነግሯል።ስምምነቱን 54 የአፍሪካ ሀገራት ሲፈርሙ ኤርትራ ብቸኛዋ እምቢታዋን የገለፀች ሀገር ሆናለች፡፡የአፍሪካ ሀገራት ከአራት አመታት ብርቱ ክርክርና ዉይይት በኋላ ባለፈዉ መጋቢት ወር ላይ በስምምነት የተቋጨዉ የአፍሪካ ሀገራት ነፃ የንግድ ቀጠናን የመመስረት እቅድ ትላንት በናሚቢያዋ መዲና ኒያሚ በተካሄደዉ 35ኛዉ አስቸኳይ የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ በ54ቱ ሀገራት መሪዎች ፊርማ መደምደሚያዉን አግኝቷል።በዘንድሮዉ የመሪዎቹ ጉባኤ ወሳኝና የአህጉሪቱን ምጣኔ ሀብታዊ ትስስር ያጠናክራሉ የተባሉ ዉሳኔዎች ተላልፈዋል።ነፃ የንግድ ቀጠናዉ 1.3 ቢሊየን የሚሆኑትን የአህጉሪቱ ዜጎች የሚያስተሳስርና 3.4 ትሪሊየን ዶላር የሚገመት ምጣኔ ሀብታዊ ቀጠና የሚፈጥር እንደሚሆን ታምኖበታል። በርግጥ አዲሱ ስምምነት የአህጉሪቱን ቀጣይ የልማት ትንሳኤ የሚያበስር እንደሚሆንም ይጠበቃል።መሪዎቹ በትላንትናዉ ዉሳኔያቸዉ ምዕራብ አፍሪካዊቷ ጋና የንግድ ቀጠናዉ መቀመጫ እንድትሆን ዉሳኔ አስተላልፈዋል።የአለም የንግድ ተቋም ከ25 አመታት በፊት በፈረንጆቹ 1994 ከተመሰረተ ወዲህ በግዙፍነቱ ሁለተኛ ነዉ የተባለለት አዲሱ የአፍሪካ ሀገራት ነፃ የንግድ ቀጠና፣ በአህጉሪቱ ሀገራት መካከል የንግድ ትስስርን የሚያጠናክር፣ የአቅርቦት ሰንሰለቶችን የሚያሰፋና የአህጉሪቱን ምጣኔ ሀብት በእጅጉ የሚያሳድግ እንደሚሆን ታምኖበታል።በስምምነቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርና የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱልፈታህ አልሲሲ አፍሪካዊያን እርስ በእርስ በመደጋገፍ አህጉሪቱን ለማልማት ከስምምነት በመድረሳችን የአለም አይኖች ሁሉ ወደ አፍሪካ እንዲዞሩ ሆኗል ብለዋል።የስምምነቱ መፈረም በአህጉረ አፍሪካ ምጣኔ ሀብታዊ እድገት ለማስመዝገብና የህዝቦቿን የዘመናት የልማት ህልም ለማሳካት ብሎም ኑሯቸዉንም በዘላቂነት ለመቀየር ፅኑ መሰረትን የሚጥል ስለመሆኑም አልሲሲ አንስተዋል።የአፍሪካ ሀገራት እርስ በእርሳቸዉ የሚያደርጉት አህጉር አቀፍ የንግድ ትስስር ከሌሎች አህጉራት ጋር ስነፃፀር እጅጉን ዝቅተኛ እንደሆነ ይነገራል። ለአብነት በፈረንጆቹ 2017 የእስያ ሀገራት 59 በመቶ የአዉሮፓ ሀገራትም ቢሆኑ 69 በመቶ ያክሉን የንግድ ልዉዉጥ ያደረጉት እርስ በእርሳቸዉ ነዉ።በአፍሪካ ሀገራት በአንፃሩ በአህጉሪቱ የነበረዉ የእርስ በእርስ የንግድ ልዉዉጥ ከአህጉሪቱ አመታዊ የዉጭ ንግድ 17 በመቶ ያክሉን ብቻ የሚሸፍን ነበር። ይህ መሆኑ ደግሞ ሌሎች የንግድ ቀጠናዎች ባለፉት አስርት አመታት በጋራ በመስራታቸዉ ያስመዘገቡትን ምጣኔ ሀብታዊ ስኬት አፍሪካዊያን ሀገራት እንዳይጋሩት አድርጓቸዉ ቆይቷል።በእርግጥ አፍሪካዊያን ተመሳሳይ የንግድ ትስስሮችን ላለመፍጠራቸዉ እንቅፋቶች እንደነበሩ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ያነሳሉ። በተለይም እንደ መንገድ የመሳሰሉ የመሰረት ልማት ዝርጋታዎች አናሳ መሆን፣ አሳሪና ነፃ ያልሆኑ የድንበር ላይ አሰራሮች፣ ስር የሰደደ ሙስናና በተለያዩ የአህጉሪቱ አከባቢዎች የሚስተዋሉ አለመረጋጋቶችና የሰላም እጦት ዋነኞች ምክኒያቶች ናቸዉ።54 የስምምነቱ ፈራሚ ሀገራት በአብዛኞቹ ምርቶቻቸዉ ላይ የቀረጥ ቅነሳ ለማድረግ ወስነዋል። ይህ ደግሞ እንደ አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ግምት የአሁኑ ነፃ ንግድ ቀጠና መመስረት የአህጉሪቱን ንግድ ከ15 እስከ 25 በመቶ እንዲያድግ ያስችላል። ከዛም በዘለለ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች፣ በተለይም እንደ ሙስናና ዉስብስብ አሰራሮች የሚወገዱ ከሆነ የአህጉሪቱ ንግድ ከተባለዉም በላይ በእጥፍ ኢያድግ ይችላል ተብሎ ይገመታል።በእርግጥ በተለያዩ የአፍሪካ ክፍሎች ተመሳሳይ አላማን ያነገቡ እንደነ ECOWAS፣ EAC፣ SADC እና COMESA የመሳሰሉ ቀጠናዊ ተቋማት የነበሩ ቢሆንም ከምስራቅ አፍሪካዉ EAC ዉጭ ቀሪዎቹ ተቋማት ይህ ነዉ የሚባል የስኬት ታሪክ የላቸዉም። በተለይም በሀገራት መካከል ያለዉ የሀሳብ መለያየት ለዚህ ዋነኛዉ ምክኒያት ነዉ።የአሁኑን ስምምነት ስኬት ይነፍጉታል ከተባሉት ጉዳዮችም የሀገራት የሀሳብ መለያየት አንዱ ነዉ። በተለይም እንደነ ናይጄሪያ ለመሳሰሉት ባለ ግዙፍ ምጣኔ ሀብትና ኢኮሚያቸዉ በነዳጅ ላይ ለተመሰረተ ሀገራት የአሁኑ ስምምነት እምብዛም የጎላ ጥቅም የለዉም። ይህም ለናይጄሪያና መሰሎቿ የስጋት ምንጭ ሆኗል።እንደነ ደቡብ አፍሪካ የመሳሰሉት ሀገራት በአንፃሩ ከስምምነቱ የተሻለ ተጠቃሚዎች እንድሚሆኑ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ገምተዋል።እናም በሀገራት መካከል ያለዉን የተጠቃሚነት ልዩነት መቅረፍና ልዩነቱን ማጥበብ የአዲሱ ስምምነት ፈታኝ ስራ ይሆናል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።", "passage_id": "f6034cd09dc604156c499661f6ebc996" }, { "passage": "በአፍሪካ ነጻ የጋራ ንግድ ቀጠና ላይ ያተኮረ የፋይናንስ፣  የዕቅድና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሮች ጉባኤ በቀጣዩ ወር በአዲስ አበባ ይካሄዳል።“የአፍሪካ የጋራ የንግድ ቀጠና ለስራ ፈጠራና ለኢኮኖሚ ብዝሃነት ያሉ የፋይናንስ አማራጮች\" በሚል መሪ ሐሳብ ከግንቦት 3 እስከ 7 ቀን 2010 ዓ.ም በአፍሪካ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚካሄድ ይሆናል።ጉባኤው ዘንድሮ ሲካሄድ ለ51ኛ ጊዜ ሲሆን የትኩረት አቅጣጫው የአፍሪካ ነጻ የጋራ ንግድ ቀጠናና ተጓዳኝ ጉዳዮች ይሆናሉ።መጋቢት 12 ቀን 2010  በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው 10ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች አስቸኳይ ስብሰባ የአፍሪካ ህብረት አባል አገሮች የአፍሪካ ነጻ የጋራ ንግድ ቀጠና ስምምነት መፈረማቸው ይታወሳል።የሚኒስትሮቹ ስብስባ ግንቦት ስድስትና ሰባት ቀን 2010  የሚካሄድ ሲሆን  በመሪ ሀሳቡ ላይ ተመስርቶበከፍተኛ ደረጃ የፖሊሲ ውይይት እንደሚደረግና በአፍሪካ አህጉር በኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ላይ እንደሚመክሩ ተገልጿል።የአፍሪካን አገሮች የንግድና የኢኮኖሚ ትስስር ይበልጥ በማሳደግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው በሚያሳድጉበት ሁኔታም ይወያያሉ ተብሏል።የሚኒስትሮቹ  ጉባኤ ከመካሄዱ በፊት ከግንቦት 3 እስከ 5 2010  የአፍሪካ አገሮች የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ስብሰባ እንደሚካሄድና ባለሙያዎቹ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎችን በማቅረብ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።በተጨማሪም ግንቦት 5 ቀን 2010 ከጉባኤው ጎን ለጎን በአፍሪካ ኢኮኖሚ ዙሪያ ያተኮሩ ዝግጅቶች እንደሚኖሩ ተጠቁሟል።በጉባኤው ማጠናቀቂያ 52ኛውን ጉባኤ የሚያስተናግድ አገር ይመረጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን በድረ ገጹ አስፍሯል።በየዓመቱ የሚካሄደው ይህ የፋይናንስ፣ ዕቅድና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሮች ጉባኤ ባለፈው ዓመት በሴኔጋል ርዕሰ መዲና ዳካር ሲካሄድ በአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገትና በስራ አጥነት ቅነሳ ላይ ትኩረት አድርጎ መወያየቱ ይታወሳል። (ኢዜአ)", "passage_id": "b79b70b02896a3b7375b76c1ac5bb10e" }, { "passage": "አዲስ አበባ፡- አዲስ የተሻሻለው የኢንቨስትመንት ህግ ተጨማሪ የኢንቨስትመንት ዘርፎችን የሚፈቅድ በመሆኑ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ዘርፉን ይበልጥ ተወዳዳሪ ያደርገዋል ተባለ። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ መኮንን ኃይሉ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ በሃገሪቱ እየተካሄደ ባለው የኢኮኖሚ ሪፎርም የሃገር ውስጥ እና የውጭ ባለሃብቶች በአዳዲስ ተጨማሪ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ማለትም በቴሌኮም፣ በኃይል አቅርቦት፣ በሎጀስቲክስ፣ በስኳር ኢንዱስትሪና በሌሎች መሰል ዘርፎች በስፋት እንዲሳተፉ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።ይህ አዲስ የተሻሻለው የኢንቨስትመንት ህግ ለሀገሪቱ ኢንቨስትመንት የጎላ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ከዚህ በፊት ለግሉ ባለሃብት የማይፈቀዱ ዘርፎችን ክፍት ማድረግ የቻለ በመሆኑ የግሉን ዘርፍ ሚና ይበልጥ የሚያጎለብት ከመሆኑም በላይ ኢንቨስትመንቱ ለዜጎች ሰፊ የስራ ዕድል ይፈጥራል። ይህም በአገሪቷ የሚታየውን የስራ አጥነት ቁጥር በመቀነስ የጎላ አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚችል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ስትጠቀምበት የነበረው የኢንቨስትመንት ህግ ከሰባት ዓመት በላይ የቆየ በመሆኑና ይህ የተሻሻለው ህግ ደግሞ በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ያለውን ተጨባጭና ወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ ያገናዘበ መሆኑን የገለፁት አቶ መኮንን፤ አገሪቷ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ከመሳብ አንጻር ይበልጥ ተወዳዳሪ እንደሚያደርጋት እና የኢንቨስትመንት ፍሰቱንም በከፍተኛ መጠን መጨመር እንደሚያስችላት ተናግረዋል።ኢትዮጵያ በአገልግሎት ዘርፍ፤ በተለይም በቴሌኮም አገልግሎት ዘርፍ የውጭ ባለሀብት መሳተፍ እንዲችል ክፍት ማድረጓን ተከትሎ፤ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ የውጭ ካምፓኒዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እያሳዩ ይገኛሉ። በዚህም መንግስት ሁለት አዳዲስ የውጭ ካምፓኒዎችን በቴሌኮም ዘርፍ መወዳደር እንዲችሉ ፈቅዷል። በማለት በቀጣይ ስድስት ወራት ውድድሩን የሚያሸንፉ ሁለት ካምፓኒዎች ወደ ስራ እንደሚገቡ የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ ኢትዮጵያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ከምስራቅ አፍሪካ ግንባር ቀደም መሆኗን አስታውሰዋል።አዲስ ዘመን የካቲት 16/2012ፍሬህይወት አወቀ", "passage_id": "863b896ffed2092e6d1450e2c1dbe743" }, { "passage": "አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 3ኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂዷል።በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው ፎረሙ “በህዝቦች፣ በፕላኔት እና በብልፅግና ላይ መዋዕለ ንዋይን” በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው ።የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ቬራ ሶንግዌ ፎረሙን በንግግር የከፈቱ ሲሆን፥ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተው ልምዳችውን አካፈለዋል።የዚምባቡዌው ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ በፎረሙ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት፥ ወደ ፊት ለመራመድ የኢነርጂ ዘፍር በጣም ወሳኝ ነው።ዚምባቡዌ ላይ የተጣለው ማዕቀብ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ሀብቶች ላይ ብቻ ጥገኛ እንድትሆን እንዳስገደዳትም ነው ፕሬዚዳንቱ ያነሱት።በዛሬው እለት መካሄድ የተጀመረው መድረክ ላይ የአየር ንብረት ለውጥ በሚያስከትሉት ፈተናዎች፣ ቀጣይነት ያለው የኢነርጂ አቅርቦት፣ በጤና አጠባበቅ፣ በታዳሽ ሀይል፣ በመድሃኒት እና የህክምና ቁሳቁስ ማምረቻዎች፣ በአስተዳደር እና ቀጣይነት ያለው ልማት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን የሚያደርግ ነው።", "passage_id": "303becc586fa85dda4cd71a7699d7f18" }, { "passage": "በአዲስ አበባ  የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ፎረም እየተካሄደ ነው፡፡ፎረሙን በንግግር የከፈቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም እንዳሉት ኢትዮጵያ በዘረጋችው ሁሉን አቀፍ የልማት ፖሊሲ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ጥረት ስታደርግ ቆይታለች።አገሪቱ ባለፉት 12 ዓመታት ባለሁለት አኃዝ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገብ የቻለች መሆኗንና ኢኮኖሚዋንም በሶስት ዕጥፍ ማሳደግ መቻሏን ነው የተናገሩት።በዚህም የድህነት መጠን በፈረንጆች ዓመት 2000 ከነበረበት 44 በመቶ ወደ 23 በመቶ ማውረዷን፣ የዜጎቿን የኑሮ ሁኔታንም በእጅጉ ማሻሻሏንና አብዛኛውን የሚሊኒየም የልማት ግቦች በማሳካት ከፍተኛ እመርታ ማሳየቷንም ተናግረዋል።ኢትዮጵያ በ2025 መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ለመሰለፍ ራዕይ እንዳላት የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ራዕይ እንደሚሳካም ባለፉት አምስት ዓመታት በተገበረችው የመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የተገኘው ውጤት አመላካች ነው ብለዋል።ከቀጣዩ በጀት ዓመት ጀምሮ በሚተገበረው ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ኢኮኖሚውን ወደ ኢንዱስትሪ መር ለማሸጋገር ግብ ተጥሏል።በዕቅዱ ኢንዱስትሪውና የግሉ ዘርፍ ዋነኛ የዕድገቱ አንቀሳቃሽ ሞተሮች እንዲሆኑ ግብ መጣሉንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያብራሩት።ዕቅዱ ግቡን እንዲመታም መንግስት የኢንዱስትሪውንና የግል ባለሃብቱን ተግዳሮቶች በመለየት ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሰራ ነው ብለዋል።በቀጣይም አገሪቱ ለውጭም ሆነ ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች መዋዕለነዋይ ማፍሰሻ ምቹ መሆኗን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ኃይለማርያም ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ትኩረት በመስጠት የኢንዱስትሪ ዞኖችን የማልማቱ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።ከዚህ ባለፈም የብድር አቀርቦትን ማመቻቸት፣ የግብር ስርዓቱን ማዘመን፣ የኢንቨስትመንት መነሻ ሁኔታዎችን ማሻሻልና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን አስተማማኝ ማድረግ ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸውንም ነው የተናገሩት።ባለፉት 10 ዓመታት የቻይናና አፍሪካ የንግድና ኢንቨስትመን ግንኙነት በእጅጉ ማደጉን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ወደ አፍሪካ የሚገባው የቻይና ቀጥታ ኢንቨስትመንት በዓለም ላይ ካለው አጠቃላይ ኢንቨስትመንት የ5 በመቶ ድርሻ መያዙንም ተናግረዋል።በአሁን ወቅትም ከ2 ሺህ 200 በላይ የቻይና ኩባንያዎች በአፍሪካ የኢንቨስትመንት መስክ ተሰማርተው ይገኛሉ።ይህም ለአህጉሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፤ በርካታ የሥራ ዕድል እንዲፈጠርም አስችሏል ብለዋል።በ2012 በኢትዮጵያ ሥራ የጀመረውና በዓመት ሁለት ሚሊዮን ጥንድ ጫማዎችን የማምረት አቅም ያለው ሁጂያን የጫማ ፋብሪካ ለ3 ሺህ 500 ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረና ሥራ በጀመረበት ዓመት ትርፋማ መሆኑን በማሳያነት አንስተዋል።እንደ ጆርጅ ሹ ያሉ ሌሎች መሰል ኩባንያዎችም የራሳቸውን የኢንዱስትሪ መንደር በመክፈት የአገሪቱን ኢንዱስትሪ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግና ራሳቸውም ተጠቃሚ ለመሆን እየተንቀሳቀሱ መሆኑንም ነው የተናገሩት።ለሁለት ቀናት የሚቆየው ይህ ፎረም በኢትዮጵያ መንግስት፣ በቻይና የልማት ባንክ፣ በመንግስታቱ ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት፣ በዓለም ባንክ እና በቻይና አፍሪካ ልማት ፈንድ ትብብር የተዘጋጀ ነው።“በአፍሪካ መዋዕለ ነዋይን ማፍሰስ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ፎረም በአህጉሪቱ የኢንዱስትራላይዜሽን እና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የወደፊት አቅጣጫዎች፣ በኢንዱስትሪ መንደሮች፣ በግል ዘርፍ ተሳትፎ፣ በመሰረተ ልማትና በንግድ አሰራር ሂደቶች ላይ እየመከረ ነው።(ኢዜአ)", "passage_id": "320d1d7fa2b62244359ffedec229b7db" } ]
27e86dfabaacaa7aa8b8c446e7f7b972
9287ae4f121adfc202dd9ca1ee55926b
የአዲስ ዘመን ስፖርት ትዝታዎች
በ1933 ዓ.ም ተቋቁሞ በየእለቱ ለአንባቢያን የሚደርሰው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ባለፉት ሰባ አምስት ዓመታት በስፖርቱ ዙሪያ የተለያዩ የአገር ውስጥ ውድድሮችንና ታላላቅ ዓለም አቀፍ የስፖርት መድረኮችን በመከታተል ታሪካዊ ዘገባዎችን አስነ ብቧል። ከታላቁ የስፖርት መድረክ ኦሊምፒክ አንስቶ እስከ ዓለም ዋንጫና የአፍሪካ ዋንጫ እንዲሁም የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናዎች ድረስ በርካታ አይረሴ ዘገባዎችን ለአንባቢዎቹ እንካችሁ ብሏል። አዲስ ዘመን አሁን ሰባ ዘጠነኛ ዓመቱን እያከበረ በሚገኝበት በእዚህ ወቅት ካለፉት ሰባት አስርት ዓመታት በላይ በተለይም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች ኦሊምፒክንና የአፍሪካ ዋንጫን በመሳሰሉት መድረኮች በደመቀችባቸው ዘመናት ለንባብ ያበቃቸው ታላላቅ ዘገባዎች የስፖርቱ ማህደር አንድ አካል ናቸው። ከነዚህ ታሪካዊ ዘገባዎች መካከልም በተወዳጁ የአፍሪካ ዋንጫ በተለይም ኢትዮጵያ ባነሳችው ዋንጫ ወቅት የነበረውን ታሪካዊ ዘገባ እየቀነጨብን መለስ ብለን እንመለከታለን።አዲስ ዘመንና የአፍሪካ ዋንጫ ትዝታዎቹኢትዮጵያ የአፍሪካ እግር ኳስ የመሰረት ድንጋይ ያኖረች አገር እንደመሆኗ መጠን የመድረኩን ጣፋጭ ድል ለአንድ ጊዜም ቢሆን መጎንጨት ችላለች። ኢትዮጵያ በወርቃማ የእግር ኳስ ዘመኗ የአፍሪካ ዋንጫን ከአምስት አስርት ዓመታት በፊት ማንሳት ስትችል አዲስ ዘመን ጋዜጣ ኢትዮጵያ አዘጋጅ አገር እንደመሆኗ መጠን ከመስተንግዶው ጀምሮ እስከ ዋንጫው ፍፃሜ ዘገባዎችን ለአንባብያን ሲያደርስ የነበረ ግንባር ቀደም የህትመት ውጤት ነበር። ጥር 6 ቀን 1954 የአፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጇ ኢትዮጵያ የመክፈቻ ጨዋታውን ከቱኒዚያ ጋር ያደረገችውን ጨዋታ እውቁ የስፖርት ጋዜጠኛ ሰለሞን ተሰማ ጥር 9 ቀን 1954 ለአንባቢያን በበቃው አዲስ ዘመን ጋዜጣ የስፖርት አምድ ላይ ያቀረበው ዘገባ የሚከተለውን ይመስል ነበር። « የሦስተኛው ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ የፉትቦል ውድድር ጥር 6 ቀን 1954 ዓም ከቀትር በኋላ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ስታድዮም ላይ በኢትዮጵያና ቱኒዚያ ብሔራዊ ቡድን መካከል ተጀምሮ የኢትዮጵያ ቡድን 4ለ2 ማሸነፉን ከጨዋታው ስፍራ በመገኘትና በራዲዮን በመስማት ሴት ወንዱ፤ ልጆችና ሽማግሌዎች ተባብለው ሳይከፋፈሉ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከልብ የተደሰተ በመሆኑ ሰሞኑን በመስሪያ፤ በመኖሪያ፤ በሆቴልና በቡና ቤቶች፤ በገበያና ንግድ ሱቆች፤ በሴይቼንቶና በአውቶብስ ውስጥ እንዲሁም በልዩ ልዩ አደባባዮች የሚወራው ወሬ አንዳችም ጣልቃ ሳይገባበት የኢትዮጵያን ቡድን አድናቆት የተመልካችን ሁኔታና ይኽንኑ የመሳሰሉ ወሬዎች ብቻ ናቸው»። ሰለሞን የጨዋታውን መክፈቻ በእዚህ መልኩ ካካተተ ከቀናት በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በተመሳሳይ ውጤት ግብፅን በፍፃሜ ጨዋታ በመርታት እስካሁን የምንጠቅሰውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ትልቅ ስኬት ማስቀረት ችሏል። በወቅቱም አዲስ ዘመን ማክሰኞ ጥር 15 ቀን 1954 ዓም ባወጣው እትሙ የፊት ገፅ ላይ « ቀልጣፋው የኢትዮጵያ ምርጥ ቡድን የግብፅን ቡድን 4ለ2 አሸነፈ» በሚል ርእስ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለቡድኑ አምበል ሉቺያኖ የአፍሪካ ዋንጫውን ሲያበረክቱ የሚያሳይ ፎቶ ግራፍ ይዞ ወጥቷል። የዘገባው መግቢያም የሚከተለውን ይመስላል« ለ3ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሚደረገው የእግር ኳስ ውድድር ጥር 13 ቀን 1954 ዓም ባለፈው እሁድ ቁጥሩ ከ5o ሺህ የማያንስ ህዝብ በተሰበሰበበት በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ስታድዮም ተደርጎ ፤ የኢትዮጵያ ምርጥ ቡድን የግብፅን ብሔራዊ ቡድን 4ለ2 አሸንፎ የአፍሪካን ዋንጫ ወስዷል። በሁለቱ አፍሪካዊ ቡድኖች መካከል የሚደረገውን ውድድር ለማየት በስታድየሙ ውጭና ግቢ አሰፍስፎ ይጠብቅ የነበረው ተመልካች ታሪካዊ አቀባበል የሚመሳሰል ነበር። ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት ግርማዊ ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መንግሥት ወራሽ ልዑል መርዕድ አዝማች አስፋ ወሰንን፤ ልዑል ራስ እምሩንና ሌሎችንም የክብር ተከታዮቻቸውን አስከትለው በፖሊስ ሰራዊት ሞተር ብስክሌተኞች ታጅበው ከስታድየም ደረሱ»።በኢትዮጵያ እግር ኳስ ከፍተኛ ንቅናቄን በፈጠረው የ2o13 የደቡብ አፍሪካ ዋንጫም አዲስ ዘመን ከዘመኑ ጋር ተጉዞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሰላሳ አንድ ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ሲመለስ በርካታ ጨዋታዎችን ተከታትሎ ዘገባዎችን ለአንባቢ አቅርቧል። በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው እየተመራ ቤኒንን ከእዚያም ሱዳንን በመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታ በደርሶ መልስ ውጤት ዋልያዎቹ ድል አድርገው ወደ አፍሪካ ዋንጫ ሲመለሱ ጥቅምት 3ቀን 2oo5 ዓም ይዞት በወጣው እትሙ በፊት ገፁና በስፖርት ባለቀለም ገፁ የአሰልጣኞች፤ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ስሜትን የሚገልፁና በቃለ መጠይቅ የዳበሩ በርካታ ዘገባዎችን ማቅረብ ችሏል።አዲስ ዘመን ሰኔ 1/2012  ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=34012
[ { "passage": "በኢትዮጵያ\nአንጋፋ ከሆኑ የስፖርት መድረኮች ቀዳሚ እንደሆነ የሚነገርለት የሠራተኛ ስፖርት ነው:: ይህ የስፖርት መድረክ በሠራተኛው መካከል በሚካሄዱ ውድድሮች አገራቸውን በዓለም አቀፍ መድረኮች ወክለው ማስጠራት የቻሉ ስመ ጥርና የስፖርቱ ባለውለታ የሆኑ ስፖርተኞችን ማበርከቱም በውስጡ ያለፉ አንጋፋ ሰዎች ይመሰክሩለታል:: ይሁን እንጂ ይህ የስፖርት መድረክ እንደቀድሞ ዝናውን ይዞ መዝለቅ አልቻለም:: ለአገር\nእንደዋለውና እንዳበረከተው አስተዋፅኦም ሲነገርለት አይስተዋልም:: ይህ የስፖርት መድረክ ቀድሞ የነበረውን ዝና የሚመሰክር በወቅቱ የነበረ ሰው በቀላሉ ማግኘትም ከባድ ነው:: የሠራተኛው ስፖርት ወርቃማ ዘመን ላይ ከነበሩት አንጋፋ ግለሰቦች አንዱ አቶ ብርሃኑ አበራ ናቸው:: አቶ ብርሃኑ በኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) የስፖርት ክፍል ኃላፊ ሆነው ለበርካታ ዓመታት አገልግለዋል:: በ1990 ዓ.ም ከኃላፊነታቸው ከለቁቁ በኋላ የሠራተኛው ስፖርት በሚካሄድባቸው ስፍራዎች አይጠፉም:: የፊታችን ረቡዕ ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን ሲከበር ጅማ ከተማ ላይ በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች አብሮ ይከበራል:: ይህንንም አስመልክቶ የሠራተኛው ስፖርት ድሮና ዘንድሮ ምን አይነት ገፅታ እንዳለው አቶ ብርሃኑ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደሚከተለው ያወጋሉ::የሠራተኛው\nስፖርት አጀማመር የስፖርት እንቅስቃሴ በሠራተኛው መካከል ሲጀመር አብረው የጀመሩት አቶ ብርሃኑ አንጋፋው የስፖርት መድረክ ኢሠማኮ ከመመስረቱ በፊት የኢትዮጵያ ሠራተኞች የስፖርት ማህበር በሚል ይንቀሳቀስ እንደነበር ያስታውሳሉ:: እዚያ ውስጥም የተወሰነ ሠራተኛ በራሱ ተሰባስቦ በስፖርቱ ይንቀሳቀስ እንደነበር:: ኢሠማኮ በዘጠኙ ኢንዱስትሪዎች ተከፋፍሎ ሲመሰረት አቶ ብርሃኑ በፋብሪካ ኢንዱስትሪ ማህበር ውስጥ ነበሩ:: መጀመሪያ የተደራጀውም ይህ እንደነበር ይናገራሉ:: ዘጠኙ ኢንዱስትሪ ማህበራት ከተቋቋሙ በኋላ የስፖርት ማህበር ስለማቋቋም ሲነሳም ለአመራርነት ኮሚቴ ሰዎች ተወክለው ነበር:: ታዲያ\nያኔ እንደ አጋጣሚ አቶ ብርሃኑ የመመረጥ እድሉ ገጠማቸው:: የሠራተኛው ስፖርት በዓል ተብሎ 1970 ዓ.ም ላይ ተከብሮ እንደነበር የሚናገሩት አንጋፋው የሠራተኛ ስፖርት መሪ፣ የላብአደሩ የስፖርት እንቅስቃሴ ከዚያ ጊዜ አንስቶ እየተጠናከረ መምጣቱን ያወሳሉ:: ‹‹1975 ዓ.ም ላይ የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ሲቋቋም (የታወቁ የስፖርት ድርጅቶች ነበር ያኔ የሚባለው) አንዱ የሠራተኛው የስፖርት ማህበር ነበር ይላሉ›› በወቅቱም እሱን ጨምሮ ሃምሳ አንድ ክለቦች ተቋቋሙ፣ አሁን የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ሥራ አስኪያጅ የሆነው ሰለሞን በቀለ ነበር አዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን የነበረው:: አሁን ላይ በአገራችን ትልልቅ ስም ያላቸው እነ ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ያሉ ክለቦችም በዚያን ወቅት ተወዳድረው እንደወጡ ያስታውሳሉ:: ከነዚህም\nበተጨማሪ ወደ አስራ አምስት ክለቦች በወቅቱ የወጡት ከሠራተኛው ነበር:: ይህም ከዚያ በፊት ፈርሶ ለነበረው የአገሪቱ ስፖርት የሠራተኛው ስፖርት መቋቋም ዳግም የአገሪቱን ስፖርት እንዲያንሰራራ ማድረጉንም ይመሰክራሉ::የዚያን ጊዜ ከነበሩ ክለቦች የፈረሱ ቢኖሩም አሁንም ድረስ በአገር አቀፍ ደረጃ ትልቅ ስም ያላቸው ሆነው እንደዘለቁም በማስታወስ የሠራተኛው ስፖርት የነበረውን አስተዋፅኦ ያብራራሉ::የሠራተኛው\nስፖርት ድሮና ዘንድሮ የሠራተኛው ስፖርት በወርቃማ ዘመኑ በበርካታ የስፖርት አይነቶች ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ የወከሉ ባለውለታዎችን ማፍራት ችሏል:: በተለይም በሦስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ቻምፒዮን ስትሆን የሠራተኛው ስፖርት ትልቅ አቅም ነበረው:: አቶ ብርሃኑ ያን ዘመን ሲያስታውሱ ‹‹ሁሉም ነገር እንደጊዜው ነው›› ይላሉ:: ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የነበረው አመራር በስፖርቱ ላይ የሚያረካ ባለመሆኑ የሠራተኛውን ስፖርት ስምና ዝና ይዞ መቀጠል እንዳልቻለም ያብራራሉ:: ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህም ቢሆን የተወሰነ መነቃቃት ቢኖርም ሠራተኛው በስፖርቱ ላይ አልነበረም የሚል እምነት አላቸው:: እንዲያውም አሁን ያሉት አመራሮች እነ ፍሰሃፂዮን ቢያድግልኝ (የኢሠማኮ ስፖርት ኮሚቴ ሰብሳቢ) የተወሰነ እያነቃነቁት መጡ እንጂ ስፖርቱ አልነበረም ማለት እንደሚቻል ይናገራሉ:: አቶ ብርሃኑ በእርሳቸው ዘመን የነበረውን ሰፊ የሠራተኛ ስፖርት እንቅስቃሴ መለስ ብለው ሲያወጉም ‹‹በእኛ ዘመን ስፖርት ለጤንነት፣ ለሰላምና ለምርታማነት በሚል ከዳር እስከ ዳር ይንቀሳቀስ ነበር›› ይላሉ:: ይህ ነገር አሁንም አስፈላጊ መሆኑንም ይጠቁማሉ:: ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ አሉ ከሚባሉት አሰልጣኞች መካከል እነ አስራት ኃይሌ፣ ነብሱን ይማርና እነ ስዩም አባተ በእግር ኳስ ላይ ስልጠና እንዲወስዱና ውጭ ድረስ እንዲማሩ ያደረገው ይሄው ቤት መሆኑን የሚናገሩት አቶ ብርሃኑ እነዚህ የቀድሞ ተጫዋቾችና የአሁን አሰልጣኞች እንዳሁኑ ዘመን የገንዘብ ፍቅር እንዳልነበራቸው ይመሰክራሉ:: እነ ትግል ፌሬ፣ ርምጃችንና ሌሎችትላልቅ ክለቦች የወቅቱ የስፖርቱ ወርቃማ ዘመን መገለጫዎች ነበሩ:: እነዚህ ክለቦች ሲመሰረቱ በዚህ መምሪያ ስር እንደነበሩ የሚናገሩት አቶ ብርሃኑ፤ ኋላ ላይ ወደ ኢንዱስትሪያቸው ይመለሱ ተብለው ከተመለሱ በኋላም በጥንካሬያቸው መቀጠላቸውን ያስታውሳሉ:: ‹‹አሁን ላይ እኔ የሚመስለኝ አመራሩ ለሠራተኛው የሰጠው ግምትና አመለካከት ዝቅተኛ ነው:: የሠራተኛው ስፖርት አሁን ላይ እንዲቀዘቅዝ ያደረገውም ይህ ነው፣ ይሄ ቤት ቢጠነክር ከዲሲፕሊን ጋር በተያያዘም ይሁን ከሥራ አጥነት ጋር በተያያዘ ወጣቱ በስፖርቱ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ትልቅ ነበረ›› በማለት የአሁኑን ዘመን የሠራተኛ ስፖርት ይገልፁታል:: የሠራተኛው ስፖርት ቀደም ሲል እንደነበረውአስመራ፣ ሐረር፣ ድሬዳዋ፣ ባህርዳር፣ ጎንደርና ሌሎች አካባቢዎች እንቅስቃሴው ቢጠናከር ወጣቱ ወደ ስፖርቱ እንደሚገባ ጠንካራ እምነት አላቸው:: ወጣቱ ሥራውን እየሠራ ስፖርቱ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ይሆንለታል ብለው ያምናሉ:: በቀድሞው ዘመን እንዳሁኑ ምቾት እንዳልነበረ የሚያስታውሱት አቶ ብርሃኑ ‹‹ወጣቱ የሠራተኛ ክፍል ለስፖርቱና ለማለያው የነበረው ፍቅር ቀላል አልነበረም›› ይላሉ:: ይህም ለብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ሲመረጥ ከጦሩና ከሠራዊቱ ሁለት ወይም ሦስት ተጫዋች ካልሆነ በስተቀር አብዛኛው ከሠራተኛው ቡድን እንዲገኝ ማድረጉን ያስታውሳሉ::የሠራተኛው\nስፖርትና ዓለም አቀፉ የሠራተኛ ቀን አቶ ብርሃኑ ሜይ ዴይን አስመልክቶ በቀድሞው ዘመን ሁሉም ቡድኖች አስቀድመው በየኢንዱስትሪያቸው ጨዋታዎችን እንደሚያደርጉ አይዘነጉትም:: በእርግጥ እንዲህ በዓል ጠብቆ ሳይሆን በየቀኑ ውድድሮች እንደነበሩም ይናገራሉ:: ዘጠኙም ኢንዱስትሪዎች የራሳቸውን ውድድር ካደረጉ በኋላ አሸናፊዎቹ ተለይተው ሜይ ዴይ ላይ ለዋንጫ ጨዋታ ይቀርባሉ:: ከዚህ ውድድር በላይ ግን ብዙ ጊዜ ሜይ ዴይ ይከበር የነበረው ወንጂ ስቴድየም ላይ እንደመሆኑ ድምቀቱ የተለየና የማይረሳ መሆኑን ያስታውሳሉ:: ከስፖርተኛው ጋር አብሮ የሚመጣው ሠራተኛ ቁጥርም የበዓሉ ሌላ ድምቀት እንደነበር አይረሱትም:: ክረምት\nላይም ሠራተኛው ውድድር ያዘጋጅ እንደነበር የሚናገሩት አቶ ብርሃኑ፣ በተለይም ድሬዳዋ በሚዘጋጁት ውድድሮች ከአሥመራ ድረስ እየመጡ የተለያዩ ቡድኖች እንደሚሳተፉ ያስታውሳሉ:: እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው የኢትዮጵያ ዋንጫ የሚባል ነበር:: ከዚያ ውድድር ሁለትና ሦስት ሳምንት ቀደም ብለው የተለያዩ ቡድኖች ወደ ሠራተኛው ውድድር ለመምጣት የማያደርጉት ጥረት አልነበረም፣ ከጎንደር፣ ከጅማ ድረስ ይመጣሉ:: ይህም አዳዲስ ተጫዋቾችን እያዩ ክለቦች ራሳቸውን የሚያጠናክሩበት አጋጣሚ ይፈጥርላቸው እንደነበር አንጋፋው ሰው ይናገራሉ::የሠራተኛው\nስፖርና ስፖርታዊ ጨዋነት የሠራተኛው ስፖርት ከቀድሞ ዝናው ይዞት የቀጠለው ነገር ቢኖር ስፖርታዊ ጨዋነት ነው:: አሁን የሚመሰገንበት ስፖርታዊ ጨዋነትም መሰረቱ ያኔ የወርቃማው ዘመን እንደሆነ አቶ ብርሃኑ እንዲህ በማለት ያስታውሱታል ‹‹በሠራተኛው ስፖርት ወርቃማ ዘመን ሥራና ስፖርት እንጂ ፖለቲካና ሌሎች ነገሮች ውስጥ ጊዜ አይባክንም ነበር። አሁንም\nየሠራተኛው ስፖርት በስፖርታዊ ጨዋነት አይታማም›› አቶ ብርሃኑ ከሠራተኛው ስፖርት ወጣ ብለው በአገራችን እግር ኳስ ስለሚስተዋለው የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ካካበቱት ልምድ በመነሳት ሃሳባቸውን ይሰነዝራሉ:: በአንድ ወቅት ለአምስት ዓመት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስኪያጅ ሆነው በሠሩበት ጊዜ የነበረውን ሁኔታ ሲያስታውሱ እንዲህ ይላሉ ‹‹ ያኔ እንዳሁኑ ጠብ ሳይሆን ትልቅ ፍቅር ነበር፣ ሜዳ ላይ ማንም ተጫወተ ማንም የኔ ነው ብሎ የሚደግፈው ስፖርቱ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ ነው፣ ያኔ አይደለም ተጫዋች ስፖርት የሚወዱ ትላልቅ ባለስልጣናት ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ አንድም ነገር ቢያደርጉ ስቴድየም እንዳይገቡ ይቀጡ ነበር››::ይህን\nሀሳብ ለማጠናከርም በአንድ ወቅት የገጠማቸውን ያወሳሉ::‹ ጄነራል አበራ አያኔ የሚባሉ ኳስ አፍቃሪ ነበሩ፣ እኚህ ጄነራል አንድ ቀን ስቴድየም ውስጥ ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ የሆነ ነገር ተናገሩ፣ በዚህም ስቴድየም እንዳይገቡ ታገዱ:: አሁን ይሄ ይደረጋል? እኚህ ጄነራል ቅጣቱን ተቀብለው ስፖርቱን ከመውደዳቸው የተነሳ ካታንጋና ሚስማር ተራ ተደብቀው በመግባት ጨዋታ ይመለከቱ ነበር። ይህን\nየሚያደርጉት ከስፖርቱ ፍቅር የተነሳ እንጂ ለሌላ ነገር አይደለም በሚል እገዳውን በኋላ ላይ አነሳንላቸው» የአገራችን የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር አንዱም የስፖርት ጋዜጠኞች እውነት አለመናገራቸው ሲሆን አመራር ላይ ያሉትም ሰዎች ችግር አለባቸው የሚል እምነት አላቸው:: «አንዱ ክለብ ወደ አንዱ ሄዶ መጫወት መፍራት የለበትም» የሚሉት አቶ ብርሃኑ፤ ክለቦች በሜዳቸው እንዳይጫወቱ ማድረግ ነገሩን ማባባስ ነው ይላሉ:: ‹‹በእኛ ጊዜ የስፖርት ምክር ቤት ነበር፣ እንዲህ አይነት ችግር ሲኖር ክለቦች ተሰብስበው ይመክሩ ነበር። አሁን\nእንደዚያ አይነት ነገር ያለ አይመስለኝም። እውነተኛ የስፖርት እንቅስቃሴም አይታየኝም። የውሳኔ ችግር አለ። ተገቢና ተመጣጣኝ ቅጣት ቢኖር ይሄ ሁሉ አይፈጠርም›› በማትም ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ:: ወገንተኝነታችን ለስፖርቱ እንጂ ለሌላ ነገር መሆን የለበትም። የስፖርቱን ሕግ ማወቅ በስፖርቱ ሕግ መቅጣት ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባም ምክረ ሃሳባቸውን ይለግሳሉ::የሠራተኛው\nስፖርት ዕጣ ፋንታ ኢትዮጵያ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር በምታደርገው ሽግግር ውስጥ በርካታ ኢንዱስትሪዎች የመቋቋም ዕድል አላቸው ተብሎ ይታመናል:: በዚህ አጋጣሚም ወጣቶች በብዛት የሥራ ዕድል እንዲያገኙ ሊያደርጋቸው ይችላል:: ያም ማለት አብዛኛው የሠራተኛ ክፍል ወጣት ሲሆን ከስፖርቱ ጋር ለማቆራኘት መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል:: ይሄን አጣጥሞ መሄድ ትልቁ የቤት ሥራ ነው:: አቶ ብርሃኑ ከያኔው ይልቅ አሁን ኢንዱስትሪዎች ተበራክተዋል ሰፊ እንቅስቃሴም እንዳለ የታዘቡትን ይናገራሉ:: በዚህ ውስጥ ሠራተኛና አሰሪውን አንድ ማድረግና መያዝ የሚቻለውም በስፖርቱ አማካኝነት መሆን እንደሚገባው ያብራራሉ::‹‹ይህን ስናደርግ ስራውም ጥሩ ይሠራል፣ አሰሪውም ከሠራተኛው ጋር በስፖርቱ ምክንያት ይቀራረባል። ቤተሰባዊ ስሜት መፍጠር ይቻላል›› ይላሉ። በዚህ አጋጣሚ ወደ ስፖርት ማህበሩ ያልገባ ድርጅት ካለ ቆም ብሎ ማሰብ እንዳለበት አፅኖት ሰጥተው ይናገራሉ:: ሠራተኛውን በስፖርት ማደራጀት ለጤንነት፣ ለአንድነትና ለስነ ምግባር ቁልፍ ፋይዳ አለው ‹‹ሠራተኛው ዝም ብሏል፣ ይህ ዝምታ ደግሞ ጥሩ አይደለም፣ አንዳንዴ ሠራተኛው በስፖርት ሲደራጅ ቅር የሚለው ይኖራል። የሚያስፈልገው ግን ሠራተኛውን በስፖርቱ በቀላሉ ማደራጀት ›› መፍትሄ መሆኑን ያስቀምጣሉ:: የሠራተኛው ስፖርት አሁንም ጠንካራ ስራ ከታከለበት እንደቀድሞው በእግር ኳስ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ስፖርቶች ለብሔራዊ ቡድን ሊመረጡ የሚችሉ ሠራተኞችን የማፍራት ዕድል አለው:: ኢሰማኮ\nየጀመረውን የማነቃቃት ሥራ አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል:: አሁን በአብዛኛው የሠራተኛው ክፍል ወጣት ነው፤ የበለጠ መቅረብና ማጠናከር ያስፈልጋል፤ ይቺ አገር በሌላት የውጭ ምንዛሬ ተጠባባቂ ወንበር የሚያሞቅ ተጫዋች ከውጭ ክለቦቻችን ማምጣት የለባቸውም የሚል አቋም አላቸው። ክለቦች ታዳጊዎችን ማየት ቢከብዳቸው ከሠራተኛው ስፖርት ዞር ብለው መመልከት እንዲችሉ ማድረግ እንደሚገባ በመግለፅም ሃሳባቸውን ይቋጫሉ::አዲስ ዘመን ሚያዝያ 19/2011ቦጋለ\nአበበ", "passage_id": "fa2bc115d10fe05d6f7aae71721650d0" }, { "passage": "ይርገዱ ጫኔ ኢራቅ በነበረችበት ጊዜ ለዓመታት በቱርኮች ባለቤትነት በሚመራው የስፖርት ማወራረጃ ተቋም ውስጥ በመጀመሪያ በጽዳትነት ቀጥሎ ደግሞ በገንዘብ ያዥነት አገልግላለች። ይህም የስፖርት ውርርድ ሥራ ምን እንደሚመስል ጥልቅ ግንዛቤና እውቀት እንዲኖራት አስችሏታል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆና ለጥቂት ዓመታት ከሠራች በኋላ እውቀትዋን ወደ አገሯ ይዛ በመምጣት ለራስዋና ለሌሎች ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ወሰነች።ኢትዮጵያ ከተመለሰች በኋላ ሥራዋን ለመጀመር ስትነሳ የገጠማት የመጀመሪያው ፈተና ሥራው በአገራችን ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ ሥራውን ለማስጀመር የሚረዳ ሕጋዊ ማዕቀፍ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አለማዘጋጀቱ ነበር። ነገር ግን ይህ ተስፋ አላስቆረጣትም ይልቅስ ብሔራዊ ሎተሪን በማሳመንና የስፖርታዊ ውርርዶች የሚመሩበት አዲስ ሕግ እንዲወጣ በማድረግ በአንድ ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ከሦስት ዓመት በፊት አክሱም ቤቲንግን በዘርፉ ፈር ቀዳጅ ሆኖ ተመሰረተ። “የሥራ ዘርፉን ጀማሪዎች በመሆናችን በርካታ ተግዳሮቶች ገጥመውናል። በተለይ ሥራው ለአገራችን እንግዳ በመሆኑ ከሕግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ድርጅታችንን ለማቋቋምና ህልማችንን ዕውን ለማድረግ ጊዜ ወስዶብናል” በማለት ይርገዱ ስለመጀመሪያውና ፈታኙ እንቅፋት ትናገራለች።አክሱም ቤቲንግ አሁን ሥራውን ከጀመረበት ጊዜ ጋር ሲነጻጸር ካፒታሉ በአምስት እጥፍ ያደገ ሲሆን 25 ቋሚና 150 ጊዜያዊ ሠራተኞች አሉት። ይርገዱ ድርጅትዋን ከመሰረተችበት ጊዜ ጋር ሲነጻጸር አሁን ስፖርት ቤቲንግ በመታወቅ ላይ ያለና ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኘ የመጣ የመዝናኛ ዘርፍ እየሆነ ይገኛል። ለዚህም ማሳያው ዐሥር የንግድ ፈቃድ የወሰዱ ድርጅቶች መኖራቸውና አምስት ኩባንያዎች ደግሞ ዝግጅት ላይ መሆናቸው ነው።በስፖርት ቤቲንግ የሥራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩት ድርጅቶች አጠቃላይ ካፒታል ሀያ ሚሊዮን እንደሆነ የሚገመት ሲሆን ለብዙ ሰዎች የሥራ ዕድል እየፈጠሩና ለደንበኞቻቸው የገቢ ምንጭ እየሆኑ ይገኛሉ። ለዚህም ይመስላል ገና በጠዋቱ የስፖርት ውርርድ የሚከናወንባቸው ቤቶች ሲከፈቱ ዳንኤል ፍቅሬን መሰል ወጣቶች ለመወራረድና ስፖርታዊ ውድድሮችን ለማየት ቤቱን የሚሞሉት። በሥራ ቀናት በአማካይ 450 ሰዎች ከአክሱም ቤቲንግ የመወራረጃ ትኬቶችን ለመግዛት የሚመጡ ሲሆን ቅዳሜና እሁድ ይህ ቁጥር ወደ አንድ ሺሕ ከፍ ይላል።አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኝ አንድ የግል ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የአንደኛ ዓመት የአካውንቲን ተማሪ የሆነው ዳንኤል የዐሥራ ዘጠኝ ዓመት ወጣት ነው። ዳንኤል ከልጅነቱ ጀምሮ የእግር ኳስ አድናቂ የነበረ ቢሆንም ስለሕጋዊ የስፖርት ውርርድ ከጓደኞቹ የሰማው በቅርቡ ነው። ምንም እንኳን የመጀመሪያ ውርርዱን ቢሸነፍም ከአምስት ወር በፊት ግን በ25 ብር በገዛው ትኬት ከጋላክሲ ቤቲንግ አምስት ሺሕ ብር ማሸነፍ ችሎ ነበር። ዳንኤል “መጀመሪያ ላይ ለመዝናናት ነበር ትኬት የምገዛው አሁን ግን ከመዝናናት አልፎ እንደ አንድ የገቢ ምንጭ ነው የምቆጥረው” ይላል። እንደ ግርማ አለሙ (ሥሙ የተቀየረ) ያሉ ወጣቶች ደግሞ አሸናፊውን ቀድመው መገመትን እንደመዝናኛ ነው የሚቆጥሩት። ግርማ ከአንድ ዓመት በፊት ጀምሮ የጋላክሲ ቤቲንግ ደንበኛ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ ከጋላክሲ በተጨማሪ የአቢሲኒያ ቤቲንግ ድኅረ ገጽ መጠቀም ጀምሯል። “ሱሰኛ አይደለሁም። ነገር ግን ቅዳሜና እሁድ የእግር ኳስ አድናቂ ከሆኑት ጓደኞቼ ጋር ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ ስል አሲዤ እጫወታለሁ። በዐሥር ብር የገዛዋት ትኬት እምብዛም የማያጓጓን ጨዋታ አጓጊ ታደርገዋለች” በማለት ከአንድ ወር በፊት ሦስት ሺሕ ከጋላክሲ እንዲሁም ከሰባት ወር በፊት ደግሞ አንድ ሺሕ ብር ከአቢሲኒያ አወራራጆች ማሸነፉን የሚናገረው ግርማ ለምን የስፖርት ውርርድ ትኬቶችን እንደሚገዛ ያስረዳል። አብዛኞቹ የእነዚህ አወራራጅ ደንበኞች ከዳንኤልና ከግርማ ጋር የሚመሳሰል አስተያየት ነው የሚሰጡት።በወፍ በረር በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉ ስፖርት ባሮችን ያየን እንደሆነ ስፖርታዊ ውርርዶች ምን ያህል የከተማ ሕይወት አንዱ አካል እየሆነ እንደመጣ መገንዘብ ይቻላል። ምንም እንኳን ከተጫዋቾች አንጸር ነገሩን ካየነው ማንም መወራረድ የፈለገ ሰው በአቅራቢያው አገልግሎቱን ወደሚሰጡት ቦታዎች ሔዶ ከ30 እስከ 300 ሺሕ ብር በማስያዝ መሳተፍ የሚችል ቢሆንም ከስፖርት ቤቲንግ አገልግሎት ሰጪዎች አንጻር ካየነው ግን ነገሩ ቀላል አይደለም። ተቋማቱ የእያንዳንዱን ስፖርት ጨዋታ ተወዳዳሪ የማሸነፍ ዕድል ቀድሞ በመገመት ከፍተኛ የማሸነፍ ዕድል ላለው ቡድን ትንሽ ክፍያ መመደብን ጨምሮ አገልግሎታቸው ውስጥ ያካተቱትን ከሰማንያ በላይ አማራጮችን በጥንቃቄ ማዘጋጀት ይጠይቃል። ይህንን በአግባቡ የተረዳ ተወዳዳሪም በዛ ያለ ብር የማግኘት ዕድሉ እየሰፋ ይሔዳል። ለምሳሌ አክሱም ቤቲንግ የድርጅታቸው ከፍተኛ ክፍያ የሆነውን 300 ሺሕ ብር ለሦስት ደንበኞቹ ከፍሏል። የአክሱም ቤቲንግ የገንዘብና አስተዳደር ኀላፊ የሆነው ናዚም እንደገለጸው ከሆነ ድርጅታቸው በወር በአማካይ በጠቅላላው እስከ 7 ሚሊዮን ብር ለደንበኞቻቸው የሚከፍሉ ሲሆን ወርሃዊ ገቢያቸው ደግሞ 300 ሺሕ ይደርሳል።ከአክሱም ቤቲንግ በኋላ ወደ ኢንደስትሪው የገቡት እንደ ጋላክሲ ቤቲንግ ያሉ የስፖርት አወዳዳሪ ተቋማትም ተመሳሳይ ልምድ አላቸው። በቅርቡ ጋላክሲ ቤቲንግ የ300 ሺ ብር ዋጋ ያላቸውን በርካታ ትኬት ለገዛ አንድ ደንበኛቸው ሁሉንም ማሸነፍ በመቻሉ 3 ሚሊዮን ብር ከፍሎታል። “ሥራው በባሕሪው የሚዋዥቅ በመሆኑ ቀድሞ ትርፍና ኪሳራን መተንበይ አስቸጋሪ ነው። የዚህ ወር ገቢ የሚቀጥለው ወር ወጪ ሊሆን ይችላል” የምትለው የጋላክሲ ቤቲንግ ባለቤት የሆነችው ሳሮን ሰለሞን ናት።ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንዶች ስፖርት ቤቲንግ ሱስ የመሆን ዕድል አለው የሚል ሥጋት አላቸው። ዳንኤል ለዚህ ሥጋት ጥሩ ማሳያ ነው። ለትምህርት ቤት ክፍያ የሚሆነኝን ክፍያ ትኬት ገዝቼበት ነበር። በወቅቱ ጓደኞቼ ባያበድሩኝ ኖሮ ትምህርቴን ለማቋረጥ እገደድ ነበር ብሏል። ናዚም ምንም እንኳን ጨዋታው ሱስ የመሆን አቅም ቢኖረውም ከ18 ዓመት በላይ ያሉ እና ማገናዘብ የሚችሉ ሰዎች በፈቃዳቸው የሚጫወቱት ጨዋታ በመሆኑ አስጊ አይደለም በማለት ይከራከራል። በሌላ በኩል ደግሞ የአቢሲኒያ ቤቲንግ ባለቤት ስፖርት ቤቲን ወጣቶችን እንደ መጠጥ፣ ሲጋራና ሺሻ ካሉ አጓጉል ሱሶች ይጠብቃል ባይ ነው። እንዲሁም ሰዎች እየተዝናኑ ተጨማሪ ገቢ የሚያገኙበት መንገድ ነው ይላል። የስፖርት ጋዜጠኛ የሆነው ግርማቸው ከበደ በበኩሉ ድሮም ስፖርታዊ ውርርዶች በልማድ በየሰፈሩ የሚከናወን ተግባር መሆኑን ገልጾ እንዳሁኑ ሕጋዊ በሆነ መንገድ መጀመሩ መልካም መሆኑን ያምናል፤ ነገር ግን ይህ ዘርፍ በጠንካራ ሕጎች ቁጥጥር ሊደረግበት እንደሚገባ አሳስቧል። “ጠንካራ ሕግ ከሌለ ግን ያኔ ነው ችግር የሚፈጠረው” በማለትም አክሏል።ቅጽ 1 ቁጥር 33 ሰኔ 15 2011", "passage_id": "510cb012e3e91186adf94728dea3ba1e" }, { "passage": "የቦክስ ስፖርት ከጥንታዊያኑ ስፖርቶች መካከል አንዱ ነው። መሰረቱ በጥንታዊቷ ግሪክ ሲሆን፤ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ688 ይዘወተር እንደነበር ይነገራል፡፡ በ16ኛውና 18ኛው ክፍለ ዘመን በታላቋ ብሪታንያ ማደጉን ታሪክ ያስረዳል። ዘመናዊው ቦክስ በታላቋ ብሪታንያና በአሜሪካ በ19ኛው\nክፍለ ዘመን ተጀምሮም በነዚህ አገራት ይበልጥ መጎልበቱ ይገለፃል። ቦክስ በኢትዮጵያ መቼ እንደገባ የጽሁፍ ማስረጃዎች ባይኖሩም በሁለተኛው የጣልያን ወረራ ወቅት ከ1928 ዓ.ም እስከ 1933ዓ.ም\nበነበሩት ጊዜያት እንደሆነ ይገመታል።ቦክስ\nበኦሊምፒክ የሚዘወተር የስፖርት ዓይነት ነው። ኢትዮጵያም ከአትሌቲክሱ በመቀጠል በኦሊምፒክ ተሳትፋበታለች። በሌላ በኩልም የኢትዮጵያ ቦክሰኞች ለውድድር በየሄዱበት ሀገር በመጥፋት ይታወቃሉ። እስካሁንም ባለው የኦሊምፒክ ተሳትፎ ከተሳታፊነት ባለፈ እምብዛም የሚነገርለት ውጤት አልተመዘገበም። በቦትስዋና በተደረገው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በአራት ቦክሰኞች የተሳተፈች ሲሆን ከእነዚም መሀል ለመጀመሪያ ጊዜ አንዲት ሴት ተሳታፊ መሆን የቻለችበት አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር፡፡ በዚህም ውድድር ሶስት ሜዳሊያዎች ተገኝተዋል። ኢትዮጵያ 38 የሚሆኑ የአፍሪካ አገራት በተካፈሉበት ውድድር አምስተኛ ደረጃን የያዘችበት አጋጣሚም በወቅቱ በጉልህ ይጠቀሳል፡፡በታላቁ ኦሊምፒክ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በ18ኛው የጃፓን ቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ ኢትዮጵያ በአራት ቦክሰኞች የተወከለች ሲሆን እነሱም አርዓያ ገብረግዚ ከኦሜድላ፣ አበበ መኮንን ከመቻል፣ በቀለ አለሙ ከቅዱስ ጊዮርጊስና ታደሰ ገብረጊዮርጊስ ከኦሜድላ ናቸው። ሁለተኛው ተሳትፎ በሜክሲኮዋ ሜክሲኮ ሲቲ የ20ኛው ኦሊምፒክ ሲሆን ታደሰ አላምረው ክብደት በመቀነስ ምክንያት አልተሳካለትም። በካናዳ ሞንትሪያል ኦሊምፒክም ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት አልተሳተፉም፡፡ በሚቀጥለው ኦሊምፒክ ቡድኑ ወደ ሶሻሊስቷ አገር ኩባ ለልምምድ ተልኮ አባላቱ በዛው ወደ ካናዳ የኮበለሉበት አጋጣሚ ተፈጥሯል፡፡ እነዚህ ቦክሰኞች በኢትዮጵያ ቦክስ ታሪክ የመጀመሪያዎቹ ጠፊዎች ሲሆኑ ከእነሱ ቀጥለውም በርካቶች በወጡበት መቅረትን ባህላቸው አድርገውታል፡፡ በቦክስ ከሰለጠኑና ሀገራቸውን በመወከል ውጤት\nያመጣሉ ተብለው የሚሳተፉ ጥቂት የማይባሉ ቦክሰኞች ወደ ውጪ ሀገራት የሚሄዱ ቢሆንም ተመላሾቹ ግን እጅግ ጥቂት እንደሆኑና አልፎ አልፎ የሄዱት ሙሉ የቡድኑ አባላት ሳይመለሱ እንደሚቀሩ መረጃዎች አሉ፡፡ በሄዱባቸው ውድድሮች የኮበለሉ ቦክሰኞች አብዛኛዎቹ በተለያዩ ስራዎች ላይ ቢሰማሩም ጥቂቶች ደግሞ በካናዳ፣ በኳታር፣ በአውስትራሊያና በተለያዩ ሀገራት ታዋቂ ተጫዋቾችና አለም አቀፍ አሰልጣኞች ለመሆን ችለዋል።በ1978ዓ.ም ወደ ኩባ ለልምምድ ሄደው ከጠፉት ካሱ ወልዴ፣ ሲፉ መኮንንና ሳህሉ በቀለ ከተባሉት ቦክሰኞች ጀምሮ እስከ 2004 ሲድኒ ኦሊምፒክ ድረስ ወደተለያዩ አገራት 28 የሚደርሱ ቦክሰኞች ኮብልለዋል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ሊኮበልሉ በሞከሩበት አገር ፖሊስ እየተያዙ እንዲመለሱ ተደርገዋል። ለመኮብለል ሞክረው ካልተሳካላቸውና ተመልሰው ወደ አገራቸው ከገቡ ቦክሰኞች መካከል አንዱ የባህር ሀይል ተጫዋች የነበሩት አቶ አበባው ከበደ ናቸው። በአሁኑ ሰዓት በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩትና የብሔራዊ ቦክስ ዳኛ የሆኑት አቶ አበባው የኩብለላ ሙከራ ያደረጉት ለውድድር በሄዱበት ሞሪሽየስ ሲሆን ወደ ደቡብ አፍሪካ በማቅናት የአሜሪካን ኤምባሲን ጥገኝነት ቢጠይቁም ሳይሳካላቸው ቀርቶ በአገሪቱ ፖሊስ ተይዘው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል።አቶ አበባው በአንድ ወቅት እንደተናገሩት፤ ለውድድር ከሄዱት ስምንት የቡድን አባላት መካከል ሰባቱ የመጥፋት ሙከራውን ያደረጉ ሲሆን እሳቸውና አንዱ የቡድኑ አባል ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡ የተቀሩት የቡድኑ አባላትም ተበታትነዋል በየሀገሩ ከተበታተኑት ቦክሰኞች መካከል በተለይ አንዱ በአሁኑ ወቅት ጥሩ ደረጃ ላይ እንዳለም ተናግረው ነበር፡፡ ለቦክሰኛው መጥፋት እንደ ምክንያት የተሻለ ገቢና ኑሮ ለማግኘት መሆኑን በርካቶች ይስማሙበታል፡፡ጸጋስላሴ አረጋዊ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ውስጥ ተጫዋች የነበሩ ሲሆን በዚሁ ክለብ የቦክስ ዋና ቡድን መሪ በመሆን አገልግለዋል። አቶ ጸጋስላሴ በተሳተፉባቸው ውድድሮች ሁሉ ውድድሮችን ተሳትፈው ከመመለስ በቀር ስለመጥፋት አስበው ከማያውቁት መካከል ናቸው፡፡ ቦክሰኞች አሁንም ድረስ ከአገር ከወጡ የማይመለሱባቸው አጋጣሚዎች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ ለአብነትም ባለፈው ዓመት በአፍሪካ ቻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ ያስመዘገበች ሴት ቦክሰኛ ወደ አገር ቤት አልተመለሰችም፡፡ የቦክስ ስፖርት በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ተወዳጅና በቀላሉ የሰው ትኩረት የሚያገኝ በመሆኑ በዘመናችን በአንድ ውድድር ብቻ እስከ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚያሳፍስ የስፖርት ዘርፍ ነው፡፡ ያም ሆኖ በአገራችን ቦክሰኞች ‹‹ፅድቁ ቀርቶ በቅጡ ቢኮንነኝ›› እንደሚባለው በስፖርቱ እንኳን ሊተዳደሩ ቀርቶ የእለት ጉርሳቸውን የሚሞላ አይነት አልሆነም፡፡ ቦክሰኞቻችን በፕሮፌሽናል ደረጃ ትልቅ ገንዘብ የሚያሳቅፍ ውድድር ማድረግ ባይችሉ እንኳን በአገር ውስጥ ውድድሮች ኑሮን የሚያሸንፉበት አጋጣሚ መመቻቸት አለመቻሉ ይገርማል፡፡ አልፎ አልፎ አንዳንድ ውድድሮች በአገራችን ሲካሄዱ የምንመለከትበት ጊዜ ቢኖርም በአጭሩ ሲቀጭ ይስተዋላል፡፡ በአገራችን እነዚህ ውድድሮች እየቀነሱ የመጡት ቦክሰኞች ጠፍተው ነው ወይስ ውድድሩ ጠፍቶ ነው?፡፡የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን የፅሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጳውሎስ ማዳ የጠፋው ቦክሰኛው ሳይሆን የመቧቀሻ ቦታው መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ‹‹ዋናው ችግራችን የስፖርቱ ማዘውተሪያ ነው፣ ስፖርቱ ማደግ የሚችለው ማዘውተሪያ ስፍራ ሲኖር ነው፣ ሪንግና ሪንጉ የሚቀመጥበት ቦታ የስፖርቱ ማነቆ ነው፣ በተለይም የመወዳደሪያ ቦታ ጅምናዚየም አለመኖሩ ችግር ነው፣ አዲስ አበባ ውድድር እያደረግን አይደለም›› ይላሉ፡፡ ፌዴሬሽኑ ቀደም ሲል ትንሿ አዲስ አበባ ሁለገብ ስቴድየም ውድድሮችን ያደርግ እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡ ፌዴሬሽኖቹ በዓመት አንድና ሁለት ጊዜ የኢትዮጵያ ቻምፒዮና በሚል የተወሰኑ ውድድሮችን ያካሄዱ እንደነበር ገልፀው፤ በአሁኑ ወቅት ግን ትንሿ ስቴድየም በእጅ ኳስ፣ ቅርጫት ኳስና ቮሊቦል ውድድሮች መጨናነቋን ነው የጠቆሙት፡፡ ፌዴሬሽኖቹ አሁን በነቃ ሁኔታ ክለቦችን በማደራጀት ውድድሮችን ስለሚያካሂዱ ቦታ ማግኘት እንደማይቻል ያስረዳሉ፡፡ ‹‹እኛ አንድ ጊዜ ለውድድር ሪንግ ካስቀመጥን ለማንሳት ስድስትና ሰባት ቀን ይፈጃል፣ ስለዚህ ከነሱ ጋርም በመግባባት ለመስራትም የማይቻል ነው›› በማለት አቶ ጳውሎስ ያመለክታሉ፡፡ አራት ኪሎ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል የሚገኘው ጅምናዚየም የቦክስ ውድድሮችን ለማድረግ ሌላ አማራጭ ቢሆንም ጅምናዚየሙ በስፖርት ለሁሉምና የተለያዩ የቴኳንዶ ውድድሮች የተጨናነቀ በመሆኑ የሚቻል አለመሆኑንም ይጠቁማሉ፡፡ አንድ ሌላ አማራጭ የወጣቶች አካዳሚ ጅምናዚየም ሲሆን እሱም የተለያዩ ስልጠናዎችን የሚያስተናግድ በመሆኑ የቦክስ ውድድሮችን ለማድረግ አመቺ እንዳልሆነ አቶ ጳውሎስ ያብራራሉ፡፡ በአለምም ሆነ በአፍሪካ ደረጃ በቂ ስፖርተኞች እንዳሉን የሚናገሩት አቶ ጳውሎስ፣ «ችግራችን ማዘውተሪያ ስፍራ እንጂ የአቅምና ችሎታ አይደለም ሲሉ ይገልፃሉ፡፡ በአሰልጣኝነትና ቡድን በመምራት በአፍሪካም በዓለምም ደረጃ የተለያዩ ውድድሮች ላይ የተካፈሉበትን ልምድ በማንሳት የኢትዮጵያ ቦክሰኞች ጥሩ ተፎካካሪ ብቻ ሳይሆኑ ውጤታቸውም መልካም የሚባል እንደሆነ ይመሰክራሉ፡፡ በመሆኑም በፕሮፌሽናል ደረጃ ለማጫወት ምንም ችግር አለመኖሩን፣ ትንሿ ስቴድየም ቦታ ተገኝቶ እንኳን ውድድር ለማድረግ ቢታሰብ በከፍተኛ ወጪ የተገዛው ሪንግ በፀሃይና በዝናብ እንደሚበላሽ ይዘረዝራሉ፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት ለተለያዩ ባለሃብቶችና ግለሰቦች ጥሪ መደረጉን የሚናገሩት አቶ ጳውሎስ፤ ሆቴል መገንባት ብቻ ሳይሆን አንድም ለራስ አንድም ለአገር ለማድረግ ጥሩ ጅምናዚየም ሰርቶ በኪራይም ይሁን በሌላ አማራጭ መጠቀም ቢቻል የተሻለ መሆኑን ይመክራሉ፡፡ ‹‹ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተገናኝተን አውርተናል፣ ያለው ትንሽ ተስፋ በአዲስ አበባ በሚገነባው ብሔራዊ ስቴድየም ዙሪያ ላይ መንግስት ከእግር ኳሱና አትሌቲክሱ ባሻገር የጅምናዚየም ግንባታም በእቅድ ውስጥ አለ፣ ይሄ ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም እንጠብቃለን›› ይላሉ፡፡ እስከዚያው ድረስ የቦክስ ስፖርት በተስፋና እንቅፋቶች መካከል ሆኖም በአንዳንድ ሆቴሎች ትብብር ውድድሮችና ልምምዶችን ለማሰራት ፌዴሬሽኑ ጥረት እንደሚያደርግ ነው የጠቆሙት፡፡ከኢቢኤስ፣ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንዲሁም ከወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ጋር በመሆን በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ሰሚ ፕሮፌሽናል ውድድር ሲዘጋጅ እንደነበረ ያስታወሱት አቶ ጳውሎስ፤ ይህም መልካም ጅምር የነበረ ቢሆንም ውድድሮችን ማስቀጠል እንዳልተቻለ ይናገራሉ። ውድድሮችን ማስቀጠል ያልተቻለበት ምክንያትም ብዙ በጀት በማስፈለጉ መሆኑንም አመልክተዋል። አሁን ግን በጀቱ ተመቻችቶና ጊዜ ተወስዶ ዳግም የሰሚ ፕሮፌሽናል ውድድሮችን የማካሄድ ሃሳብ እንዳለ ያስረዳሉ፡፡ ‹‹ዋናው ስፖርቱን ማሳደግ ብቻ ሳይሆን ስፖርተኛውንም ተጠቃሚ ማድረግ ነው፣ ስፖርቱ አለ እንላለን ስፖርተኛው ግን ተጠቃሚ አይደለም›› ይላሉ፡፡ ከውድድሮች ባሻገር ቦክሰኞችን ተጠቃሚ ማድረግም ትልቁ ችግር መሆኑን ያነሳሉ፡፡እንደ አቶ ጳውሎስ ማብራሪያ፤ ስፖርቱ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ ወጣ ገባ እያለም ቢሆን የተወሰነ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡ አምና ሞሮኮ ላይ በተደረገ ውድድር በአንድ ሴትና በአንድ ወንድ ሁለት ወርቅ፥ ሁለት ብርና አንድ ነሐስ ተገኝቷል፡፡ አልጄርስ ላይ በተደረገው የወጣቶች ኦሊምፒክ አንድ ወርቅ፥ ሁለት ብርና ሁለት ነሐስ ተመዝግቧል። ይህም ቀላል የሚባል ሳይሆን በስፖርቱ ለአገር አንድ ነገር ማሳየት መቻል ነው፡፡ ያም ሆኖ ስፖርተኞቹ ምን ያህል ተጠቃሚ ናቸው? ቢባል ምላሹ ደስ የማይል መሆኑን አቶ ጳውሎስ ይናገራሉ፡፡ ‹‹ ስፖርተኛ ተጠቃሚ ካልሆነ ስፖርቱ ሊነሳ አይችልም›› ብለው፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በእግር ኳሱ ስፖርተኞች ምን ያህል ተጠቃሚ እንደሆኑ የሚመለከቱ ወላጆች ከድሮው በተቃራኒ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ሳይሆን ወደ ኳስ ሜዳ እንዲሄዱላቸው ለአሰልጣኞች ገንዘብ በመክፈል ጭምር ፍላጎት እያሳዩ መሆናቸውን በምሳሌነት ያነሳሉ፡፡ ይህን ምሳሌ ያነሱት ዝም ብለው እንዳልሆነም ይጠቅሳሉ፡፡ በቦክስ ስፖርት ተጠቃሚ መሆን ካልተቻለ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ስፖርቱ አይልኩም ከሚል ስጋት መሆኑንም ነው የሚያስረዱት፡፡ ይህም ለስፖርቱ ሌላ ፈተና መሆኑን አቶ ጳውሎስ ይገልፃሉ፡፡ ‹‹በስፖርቱ ላይ ተጠቃሚነትን እያዩ ብዙዎች ይመጣሉ፣ ቦክስም ላይ አገርን ማስጠራት ብቻ በቂ አይደለም፣ አገራቸውን አስጠርተው ሜዳ ላይ የቀሩ ብዙዎች አሉ፣ አገርን ከማስጠራት ጎን ለጎን ተጠቃሚ እንዲሆኑና ታዳጊዎች ወደ ስፖርቱ እንዲመጡ አልሰራንም፣ እየጀመርን እናቋርጣለን›› በማለትም ያብራራሉ፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ችግሮች እያሉም በተለያዩ ቦታዎች የአማተር ውድድሮችን በማካሄድ በሦስት ዙር የብሔራዊ ቡድን ቦክሰኞችን መምረጥ እንደተቻለ ይናገራሉ። እነዚህን ልጆችም ከስፖርት ኮሚሽንና ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር በመሆን ሆቴል ገብተው እንዲሰለጥኑ እየተደረገ መሆኑን ይጠቁማሉ። ለ12ኛው\nመላ አፍሪካ ጨዋታ ሞሮኮ ላይ አገራቸውን የሚወክሉ መሆኑንም ያመለክታሉ፡፡ በመቀጠልም ለኦሊምፒክ የሚዘጋጁ መሆኑን ጠቅሰው፤ የውድድር ልምድ፣ የስልጠናና ዝግጅት ማነስ ካልሆነ በቀር በተለያዩ ውድድሮች ውጤታችን ዝቅ ሊል የሚችልበት ሌላ የተፈጥሮ ምክንያት እንደሌለ ነው ያስረዱት፡፡እንደ አቶ ጳውሎስ ማብራሪያ፤ የአገሪቱ የቦክስ ስፖርት ዘርፍ መልካም የሚባሉ አበረታች ውጤት የተጉበትና ወደፊትም ከተሰራበት ተስፋ ሰጪ የሚባል በመሆኑ በዘርፉ ያሉትን ተግዳሮቶቹ ከወዲሁ ከመቅረፍ አኳያ የሚመለከተው አካል የበኩሉን ሊወጣ ይገባል፡፡ አዲስ ዘመን ቅዳሜ  ግንቦት  17/2011ቦጋለ አበበ", "passage_id": "1d08efc6b009aa60f8aa860254065f0c" }, { "passage": "ጥንታዊያኑ ግሪኮች አማልክትን ለማስታወስ ስፖርታዊ ክብረ በዓላትን ያዘጋጁ ነበር።\nበዘጠነኛው ምዕተ ዓመት አካባቢም የሶስቱ ግዛት መሪዎች ጊዜያዊ የተኩስ አቁም አድርገው ነበር። «የተቀደሰ ስምምነት» የሚል ርዕስ\nየተሰጠው ስምምነቱ ስፖርታዊው ክብረ በዓል «ኦሊምፒክ» እስኪጠናቀቅ የነበሩትን ቀናት የሚሸፍን ነበር። ታሪክ ይህንን ሲጠቅስ ሰነዶች ደግሞ የኦሊምፒክ ግብ ለሰላም ግንባታ እንዲሁም\nለወጣቱ ትውልድ ከልዩነት የጸዳ ሰላማዊ ዓለምን ለማሳየት መሆኑን ይጠቁማሉ። ይህ የስፖርት አስኳል ሃሳብ ሲሆን፤ ስፖርታዊ ውድድሮች\nደግሞ መከባበር፣ መረዳዳት፣ አብሮነት፣ ወዳጅነት እና እኩልነት የሚዘመርባቸው መድረኮች ናቸው። ወደ 19ኛው ክፍለ ዘመን መለስ ብንልም በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት (እአአ\nበ1914) የገና ወቅት የእንግሊዝና ጀርመን ጦሮች ትጥቅ ፈተው እንደነበር የጽሁፍ ማስረጃዎችን ማንሳት ይቻላል። ለአንድ ቀን በተካሄደው\nተኩስ አቁም ሁለቱ ተዋጊዎች ሰላማዊውን ጦርነት በመምረጣቸው ዕለቱን በኳስ ጨዋታ ሊያሳልፉም ችለዋል።የሚሊኒየሙን ግብ ለማሳካት ከተቀመጡት መንገዶች መካከልም አንዱ፤ ሰላምን በስፖርት\nለማሳደግ የሚለው ተጠቃሽ ነው። ዩኔስኮም ስፖርትን ተጠቅሞ ዓላማውን ለማሳካት አቅዶ በመስራት ላይ ነው የሚገኘው።     በስፖርት ምክንያት የበረዱ ግጭቶች፤ ከስፖርታዊ ውድድሮች የተነሱ ወዳጅነቶችንም\nዓለም በታሪክ ማህደሯ አስፍራለች። ከጥንታዊው ኦሊምፒክ እስከ አለፈው ዓመቱ የክረምቱ ኦሊምፒክ ድረስም ስፖርት የሰላም ወዳጅና\nመሰረት መሆኑን በተግባር አሳይቷል።  በኢትዮጵያስ፤ ስፖርት «ለሰላምና ወዳጅነት» እየዋለ ነው ወይስ ሚናው ተዘንግቷል?\nይህንን ጥያቄ ይደግፍ ዘንድ አንዳንድ ነጥቦችን እናንሳ። ባለፉት ዓመታት ሃገሪቷ ውስጥ በነበረው ሁኔታ ትልልቅ ውድድሮች ሳይካሄዱ\nቀርተዋል። በስፖርት ማህበራት ይዘጋጁ የነበሩ ሻምፒዮናዎችም ገባ ወጣ ይሉ ነበር። ሁኔታዎችን ተቋቁመው በተካሄዱ ውድድሮች ላይም\nተሳታፊዎቹ እንደሚጠበቀው ሙሉ አልነበሩም።       እንደ ብሄራዊ የኦሊምፒክ ውድድር የሚታየው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች፤ ለ6ኛ\nጊዜ በ2010ዓም መካሄድ ቢኖርበትም እስካሁን አልተካሄደም። በተያዘው ዓመትም ስለመካሄዱ እርግጠኛ መሆን እስካሁን አልተቻለም።\nሌላኛው ዓመታዊና በጉጉት ተጠባቂ ከሆኑት ውድድሮች መካከል የሚጠቀሰው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውድድር፤ ከ2007 በኃላ ተቋርጧል።\nየትምህርት ቤቶች እና የባህል ስፖርቶች  ውድድርም በመሃል ተቋርጠው\nነበር።  የስፖርት ሚና አንድነትና ወዳጅነትን ማሳየት ከሆነ ግጭቶች በመነሳታቸውና አለመረጋጋት\nበመኖሩ ምክንያት ውድድሮች ሊቋረጥ አይገባም። እንዲያውም የግጭትና የአለመግባባትን እሳት እንደ ማጥፊያ መሳሪያ መጠቀም ይቻላል።  አንድ የሚታወቅ እውነት አለ፤ ይህም ብሄራዊ ቡድኖች  በትልልቅ ውድድሮች ላይ የተሳታፊነት ዕድል ሲያገኙ የህዝቡ አትኩሮት በሙሉ\nወደዚያው ይሆናል። አትሌቶች ሮጠው ሲያሸንፉ አሊያም በየትኛውም ስፖርት አሸናፊነት ሲኖር ደግሞ የሃገር ፍቅር ስሜቱ ከምን ጊዜውም\nበላይ የላቀ ይሆናል። በመሆኑም አለመግባባቶችን ለማለዘብ ስፖርትን ይበልጥ ማጉላትና ማድመቅ ጠቃሚ ይሆናል። ፊሊፒንስና ኮሎምቢያ ህጻናትን በፕሮ ጀክቶች በመያዝና በማበረታታት ሰላምን ለማሳደግ\nፕሮጀክት ቀርጸው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ሃገራት ናቸው። ዓላማውም ህጻናት በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወቅት ማሸነፍና መሸነፍን፣ የቡድን\nስሜት እንዲሁም መሪነትን አዳብረው፤ በወደፊት ህይወታቸው ነገሮችን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የሚረዳቸው ይሆናል። ይህም መጪውን\nትውልድ ቅድሚያ ለሰላም እንዲሰጥ የሚያደርግ ነው። ሃገራት በዓለም ላይ ስማቸው ከሚነሳባቸው በርካታ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ስፖርት\nነው። አንድ ቡድን ድል አስመዝግቦ ዋንጫ ሲያነሳ አሊያም አንድ ተወዳዳሪ አሸንፎ ሜዳሊያ ሲያጠልቅ ደስታው የግሉ ብቻ አይሆንም።\nውጤቱ የስፖርተኞች የጥረት ውጤት ቢሆንም የሚወክለው ግን ሃገርን እስከሆነ ድረስ የጋራ ያደርገዋል። እንዲህም ሲሆን፤ በከፍተኛ ደረጃ የብሄራዊ ስሜትንና የአብሮነት አስተሳሰብን\nያነሳሳል። ህዝቡ ስፖርትን የሚወድ እንደመሆኑም በውድድሮች አለመ ግባባቱን ገታ አድርጎ ትኩረቱን ወደዚያው ለማድረግ ያስችላል።\nየተለያዩ መልዕክቶችን በማሰራጨትም ህዝቡ ዘንድ በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ ይቻላል። ይህ የስፖርት ባህሪም ዓለም አቀፋዊ እንደመሆኑ በኢትዮጵያም ኮሽ ባለ ቁጥር ውድድሮች ተቋረጡ ከማለት ይልቅ እንደ መሳሪያ\nመጠቀሙ የተሻለ እንደሚሆን የሚመለከታቸው ሁሉ ሊያስቡበት ይገባል።አዲስ ዘመን የካቲት 18/2011", "passage_id": "95c1de2f14a4c44fae469a58769e25d4" }, { "passage": "ያለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በእርግጥም አንድ እውነት በዓለም አትሌቲክስ ልቆ ያንጸባረቀበት ወቅት ነበር። በሦስት ሺ ሜትር መሰናክል ውድድር ለዓመታት ወደ አንድ ወገን ያደላው የበላይነትም ባልታሰበ አቅጣጫ የተጓዘበት ሆኖ ይታወሳል። በበርካታ ዓመታት የአትሌቲክስ ታሪክ ውስጥ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቶች ዓለምን ያስደመሙትና በውጤት ያሸበረቁት በመምና ጎዳና ላይ የረጅም ርቀት ሩጫ ነበር። ለኢትዮጵያ ቀንደኛ ተፎካካሪ ከሆኑት ሃገራት መካከል ቀዳሚዋ ኬንያ በተለይም በ3ሺ ሜትር መሰናክል ሩጫ እስካለፈው ዓመት ድረስ በዓለም ውጤታማና ከሌሎች ተፎካካሪዎቿ ፍፁም የበላይ ነበረች። እአአ በ2019 ግን በዚህ ርቀት ኢትዮጵያም ተስፋ ያላት ሃገር መሆኗን በተለያዩ ውድድሮች ማረጋገጥ እንደተቻለ የዓለም አትሌቲክስ ሰሞኑን በድረ ገጹ ያሰፈረው ሰፊ ሐተታ ይጠቁማል። \nለኢትዮጵያ በታላቅ የውድድር መድረክ በርቀቱ የመጀመሪያው ድል የተመዘገበው በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ሲሆን፤ በኳታር ዶሃ በተካሄደው ውድድር ለሜቻ ግርማ በጥቂት ማይክሮ ሰከንዶች ተቀድሞ የብር ሜዳሊያ በማጥለቅ ታሪክ ማስመዝገብ ችሏል። በወቅቱ አትሌቱ 8:01.36 የሆነ ሰዓት ሲያስመዘግብ በኬንያዊው ኮንሴሉስ ኪፕሩቶ የተቀደመበት አጋጣሚ እጅግ የሚያስቆጭ ሆኖ ይታወሳል። በርቀቱ ለኢትዮጵያ ተስፋ ሰጪ የሆነው ሌላኛው ድል ደግሞ በውድድር ዓመቱ ዳይመንድ ሊግ ላይ ነበር የተመዘገበው። ወጣቱ አትሌት ጌትነት ዋለ በርቀቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የዳይመንድ ሊግ አጠቃላይ አሸናፊ ከሆኑ አስር የተለያዩ ርቀት ተወዳዳሪ አትሌቶች መካከል አንዱ ሊሆን ችሏል። \nእነዚህ በዓለም ታላላቅ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያን በአዲስ ርቀት ተስፋ እንድታደርግ ያስቻሉ አትሌቶች የሚሰለጥኑት በአንድ አሰልጣኝ ስር ነው። ይህ አሰልጣኛቸውም ብሄራዊ ቡድንን የሚወክሉ በርካታ አትሌቶችን በማፍራት ላይ የሚገኘው ተሾመ ከበደ ነው። በተለይ ጌትነት በ3ሺ ሜትር መሰናክል በዓመቱ ያሳየው ብቃት እጅግ አበረታች በመሆኑ ድረገጹ ትኩረት የሰጠው ሲሆን፤ ቀጣዩ የርቀቱ ኮከብ እንደሚሆንም ነው ተስፋውን የገለጸው። \nአትሌት ጌትነተ ዋለ በደቡብ ምሥራቅ የሃገሪቷ አካባቢ በምትገኘው ሰቀላ የተባለ ስፍራ ስምንት ልጆች ካሏቸው ቤተሰብ መካከል የተገኘ ፍሬ ነው። ዛሬ አትሌት ለመሆኑ ምክንያቱ ደግሞ በየዕለቱ በጠዋት እየተነሳ ከቤቱ በአራት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ትምህርት ቤቱ የሚያደርገው ሩጫ ነበር። ይህ ልምድም ትምህርት ቤት ውስጥ ለሚካሄዱ የሩጫ ውድድሮች ሲያሳጨው፤ በ13 ዓመቱ በ1 ሺ 500 እና 3 ሺ ሜትር አሸናፊ መሆንም ችሎ ነበር። ይህ ሁኔታ ለቀጣይ የአትሌቲክስ ህይወቱ መንገድ የጠረገለትን አጋጣሚ የፈጠረም ነበር። ይህም ጌትነት በትምህርት ቤቱ ተገኝቶ ብቃቱን ለተመለከተው የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ አሰልጣኝ እይታ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። \nጌትነት ከዚያ በኋላ የሆነውን ሲያስታውስም ‹‹አሰልጣኙ በእኔ ላይ ፍላጎት ስላሳደረ ቤተሰቦቼን አስፈቅጄና የትምህርት ማስረጃዎቼን ይዤ ወደ አዲስ አበባ አብሬው እንድሄድ ጠየቀኝ›› ይላል። ያ አሰልጣኝ ዛሬም ድረስ በስኬቱ ከጎኑ ያለው ተሾመ ሲሆን፤ ለዓመታት በነበራቸው የአብሮነት ቆይታ አትሌቱ በመሰናክል የተሻለ ብቃት እንዳለው መረዳት በመቻሉ ወደዚያው እንዲገባ አድርጓል። እአአ 2016 በተካሄደው ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ቻምፒዮና ደግሞ የአሰልጣኙ ጥረትና የጌትነት\n ችሎታ በእርግጥም ለስፖርት ቤተሰቡ በግልጽ ሊታይ የቻለበት ነው። \nይህ ተስፈኛ አትሌት በፖላንድ ባይዳጎዝ ከተማ በተካሄደ ዓለም አቀፍ ውድድር ተሳትፎ የነሐስ ሜዳሊያ ቢያገኝም፤ በወቅቱ ብቃቱ ያን ያህል ትኩረት ያገኘ አልነበረም። ይሁን እንጂ ሁለተኛ ከወጣው አትሌት በ16 ሰከንዶች የዘገየውና 8፡22.83 የሆነ ሰዓቱ የግሉ ፈጣን ሰዓት ነበር። በወቅቱ የነበረው ብቃት በአትሌቲክስ ቤተሰቡ ዘንድ እምብዛም ትኩረት ባያገኝም በሪዮ ኦሊምፒክ ግን ለብሄራዊ ቡድን ለመመረጥ ዕድሉን አስገኝቶለታል። ወጣቱ አትሌት በታላቁ መድረክ ሃገሩን በመወከሉ ደስ ቢሰኝም በበዛ የጭንቀት ስሜት በመዋጡ እንዳሰበው ሜዳሊያ ማግኘት ሳይችል ቀረ።\nበባይዳጎዝ በተካሄደው የወጣቶች ቻምፒዮና ብቃቱን ለተረዳው ማናጀሩ ግን ይህ ምንም ማለት አልነበረም። ማናጀሩ ሁሴን ማቄ ‹‹ጌትነት ትልቅ ልብ ያለው አትሌት ነው። በውድድሩ ላይ ሁለት ጊዜ ወድቆ ከሜዳሊያ ሰንጠረዡ ሳይወጣ ለብር ሜዳሊያ በተጠጋ ውጤት ማጠናቀቅ መቻሉ አስደናቂ ነው›› ሲል ይገልጸዋል። \nጌትነት በቀጣዩ ዓመትም ውጤታማነቱ እንደቀጠለ ነበር። በሃገር አቀፉ ቻምፒዮና አሸናፊ ከሆነም በኋላ በሄንግሎ በተካሄደው ከ20 ዓመት በታች ውድድር በብሄራዊ ቡድኑ ተካተተ። ውድድሩንም 8፡12.28 በሆነ ሰዓት የክብረወሰን ባለቤት በመሆን አጠናቀቀ። ይኸውም በዚያው ዓመት (እአአ 2017) በተካሄደው የለንደን አትሌቲክስ ቻምፒዮና ሃገሩን እንዲወክል አደረገው፤ በ17 ዓመቱም ልምድ ካላቸው አትሌቶች ጋር ተፎካክሮ ዘጠነኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀ።\n እአአ በ2018 የውድድር ዓመት በፊንላንድ የወጣቶች ቻምፒዮና ተሳታፊ ቢሆንም፤ ባልተጠበቀ መልኩ በሌላኛው የሃገሩ ልጅ ተቀድሞ የነሐስ ሜዳሊያ ነበር ያጠለቀው። ይህ ተደጋጋሚ የውድድር ልምድም እአአ 2019 የውድድር ዓመት በሚገባ እንዲዘጋጅና ያለውን ብቃት በተገቢ መንገድ እንዲያሳይ አደረገው። የስልጠና ጫናውን በመጨመርም በሳምንት ከ100-120 ኪሎ ሜትር በመሸፈን ልምምዱን ይሠራም ነበር። ከቡድን አጋሩ ለሜቻ ግርማ ጋር ጠንካራ ልምምድ በመሥራታቸውም ሁለቱም የግል ውጤታቸውን ማየትና ለሃገራቸውም ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል። \nጌትነት ከዓለም አትሌቲክስ ድረገጽ ጋር በነበረው ቆይታም ‹‹ከለሜቻ ጋር በአካዳሚው አብረን የምንኖር ጓደኛሞች ነን። በልምምድ ጊዜ ጠንክረን የምንሠራ በመሆናችን የሥራችንን ፍሬ ልናገኝ ችለናል›› ይላል። የዳይመንድ ሊግ ውድድሮቹን ሲያስታውስም ‹‹ራባት በጭራሽ የሚዘነጋ አይደለም፤ ምክንያቱም ከዚያ ቀደም የምሠራቸውን ስህተቶች ያረምኩበት ውድድር ነው። በቅድሚያ ሩጫውን ለመቆጣጠር ቻልኩ ከዚያም በመጨረሻው ዙር የመጨረሻውን ውሃ በጥንቃቄ በመዝለል ቀዳሚ ሆኜ በአሸናፊነት አጠናቀቅኩ›› ሲል ውጤታማውን ውድድር መለስ ብሎ ያስታውሳል። በውድድሩ ያስመዘገበው ሰዓትም የኢትዮጵያ የርቀቱ ክብረወሰንና በዳይመንድ ሊጉ ሦስተኛው ፈጣን ሰዓት ነበር።\nአሸናፊ ከሆነም በኋላ ‹‹አሸናፊነቴ ለኢትዮጵያ ትልቅ ድል ነው፤ ምክንያቱም ከዚህ ቀደም በዳይመንድ ሊግ የ3ሺ መሰናክል ውድድር አሸናፊ የሆነ አትሌት አልነበረም። በመሆኑም በራስ መተማመን ሰጥቶኛል፤ ወደፊት ደግሞ ከስምንት ደቂቃ በታች መሮጥ እንደምችል ፍንጭ ያገኘሁበት ነው›› በማለት\n ስሜቱን ያጋራል። በዓለም ቻምፒዮናው ተሳታፊ የነበረው ጌትነት የአሸናፊነት ቅድመ ግምት ካገኙት አትሌቶች መካከል ቢሆንም፤ ያጠናቀቀው በሜዳሊያ ሰንጠረዡ የቅርብ ርቀት ላይ አራተኛ ሆኖ ነበር። በዓመቱ በተካሄደው የቤት ውስጥ የዙር ቻምፒዮና ተሳትፎውም ከሦስቱ ውድድሮች በሁለቱ አሸናፊ መሆን ችሏል። \nበብራሰልስ በነበረው የዳይመንድ ሊጉ ማጠናቀቂያ ውድድር ያሳየው ብቃትና አጨራረስ ለዚህ የውድድር ዓመት ይደገም ይሆን በሚል የስፖርቱ ቤተሰብ እንዲጠብቀው ያደረገም ነበር። የእርሱም እቅድ በዚህ ዓመት ሊካሄድ በታሰበው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በርቀቱ ታሪክ መሥራት ነበር። ሆኖም በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮሮና (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ ምክንያት እንደ ውድድሩ ሁሉ ብቃቱም በቀጠሮ ለሚቀጥለው ዓመት ሊራዘም ችሏል። ሆኖም በቤቱ ውስጥ ሆኖ በሳምንት ሦስት ቀናት ልምምድ ማድረጉን አላቋረጠም። \n‹‹በብቃቴ ለመቆየት ማድረግ ያለብኝን እያደረኩ ነው። በቅርቡ ወደ ውድድር እንመለሳለን የሚል ተስፋም አለኝ›› ሲል ተስፈኛው አትሌት ይናገራል። በዚህ ወቅትም ኑሮውን ካደረገባት አዲስ አበባ ወደ ተወለደበት አካባቢ በማቅናት ቤተሰቡን በመርዳት ላይ ይገኛል። ውድድሩ በተመለሰ ጊዜም በ3ሺ ሜትር መሰናክል ኢትዮጵያዊያን ለሌሎች ተፎካካሪ አገራት አትሌቶች ፈተና እንደሚሆኑ እምነቱ ነው። ‹‹በመሰናክል ጠንክረን በመሥራት መልካም ውጤት ማስመዝገብ በመቻላችን ደስተኞች ነን›› የሚለው ጌትነት ይህም የበላይነቱን ለረጅም ጊዜ ይዘውት ለቆዩት ኬንያዊያን ማስጠንቀቂያ መሆኑን ድረ ገጹ በሰፊ ሐተታው መደምደሚያ አስምሮበታል።\nአዲስ ዘመን ሰኔ 15/2012ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "51da772166285795b33f37e5c94534e9" } ]
0114fb911a7af1a57e6b73c23662097d
5d5812235e0b9d3c3c9c7f940ab12618
‹‹በአስቸጋሪ ጊዜ ውስጥም ቢሆን የግል ባለሀብቱ ከስፖርቱ ጎን ሊቆም ይገባል›› -አቶ ነብዩ ሳሙኤል ፈረንጅ
በዛሬው የስፖርት ገፅ አምዳችን ከአንድ እንግዳ ጋር ጭውውት ለማድረግ ወደን አንድ ርዕሰ ሃሳብ መዘናል። የጋበዝናቸው የስፖርቱ ባለውለታ በፈተና ውስጥም ሆኖ የስፖርቱን ዘርፍ በተለይ የግል ባለሃብቱ ሊደግፈው እንደሚገባ የራሳቸውን የህይወት ተሞክሮ በማንሳት አጫውተውናል። እኛም የስፖርቱን ወዳጅ ስኬታማ እንቅስቃሴና የወቅታዊ ጉዳይ ምክረ ሃሳብ በዚህ መንገድ አስቀምጠነዋል። አቶ ነብዩ ሳሙኤል ፈረንጅ በአሜሪካን አገር ኑሯቸውን ያደረጉ ቢሆኑም ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን ግን አልቀየሩም። በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ የኮምፒውተር ሳይንስ ትምህርት አጥንተው ዲግሪያቸውን ይዘዋል። ለዓመታት የተለያዩ የግል ስራዎች ሲሰሩም ቆይተዋል። ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ሲሆኑ አሁን በአገራቸው ላይ በኮንስትራክሽን እና በሌሎች ዘርፎች ላይ ተሰማርተው እየሰሩ ይገኛሉ። በተለይ ደግሞ የጎልፍና የብስክሌት ስፖርቶችን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ላይ ሰፊ አበርክቶ እንዳላቸው የስፖርቱ ባለሙያዎች ሲናገሩ ይደመጣል። «ትምህርት ቤት በነበርኩበት ጊዜ የመንግስቱ ወርቁ፣ ሉቺያኖ ቫሳሎ፣ የበረኛው ጌታቸው ዱላ አድናቂ ነበርኩ» በማለት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ በነበሩበት ዘመን በአገር ውስጥ ትልቅ ስፍራ የነበራቸው እግር ኳስ ተጫዋቾች ይሳቡ እንደነበር ጊዜውን መለስ ብለው እያስታወሱ አጫውተውናል። ስፖርት ወዳድነታቸው ዘርፉን እንዲደግፉ ገፊ ምክንያት ሆኗቸዋል። በተለይ የብስክሌት፣ የጎልፍና ጠረጴዛ ቴኒስ ስፖርት ላይ ባላቸው ጠንካራ ተሳትፎ ይታወቃሉ። አሁንም ድረስ በአዲስ አበባ ደረጃ የሁለቱም የበላይ ጠባቂ ናቸው። የብስክሌት ስፖርት አቶ ነብዩ በርካታ ፈተናዎች የተጋረጠበትን የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ከአመራሮች ጋር በመተባበር እየደገፉት ይገኛሉ። ከስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች አካባቢ የማይጠፉት ሰው እንዴት ወደ ብስክሌቱ ዘርፍ ሊመጡ ቻሉ? ምን አይነት ተግባራትስ እስካሁን ድረስ አከናውነዋል። አቶ ገረመው ደንቦባ በኢትዮጵያ የሳይክል ስፖርት ጅማሮ ትልቅ ስፍራ አላቸው። እኚህን አንጋፋ ሰው ማመስገን ክብር ለሚገባው ተገቢውን ክብር ከመስጠት ባለፈ ስፖርቱ እንዲነቃቃ ትልቅ እድል የሚከፍት በመሆኑ፤ ከአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን እንዲሁም ከብስክሌት ፌዴሬሽኑ ጋር በመተባበር የሃሳቡ ጠንሳኝና ቀዳሚ ስፖንሰር በመሆን 623 ኪሎ ሜትር የሸፈነ የመጀመሪያው «ጉዞ ወደ አባይ የሳይክል ቱር» በማዘጋጀት እኚህ አንጋፋ ሰው በክብር እንግድነት እንዲገኙ እና ለወጣት ስፖርተኞቹ ብርታት እንዲሆኑ ማድረግ ችለዋል። ከአንድ ዓመት በፊትም የኢትዮ-ኤርትራን የሰላም ስምምነት ምክንያት በማድረግ ከአዲስ አበባ አስመራ አገር አቋራጭ የብስክሌት ስፖርት ቱር ከኮካ ኮላ ኢስት አፍሪካን ቦትሊንግ ጋር በመተባበር እንዲካሄድ የአንበሳውን ድርሻ ወስደዋል። በዚህ ከሺህ በላይ ኪሎ ሜትሮች የሸፈነ ውድድር ላይ 150 የሚጠጉ ወጣት ብስክሌተኞች፣ጋዜጠኞችና የሚመለከታቸው የስፖርት አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። በጊዜው ከሌሎች ስፖርቶች ቀዳሚ በመሆን በብስክሌትና የጠረጴዛ ቴኒስ ሰላም የማብሰር ፈር ቀዳጅ ብስራት ሲሰማ እኚሁ የዘርፉ ወዳጅ ባለሀብት ዋናው መንገድ ቀያሽ ነበሩ። የጎልፍ ስፖርት አዲስ ምዕራፍ በአዲስ አበባ ጎልፍ ክለብ ጨዋታ በማድረግ የሚታወቁት አቶ ነብዩ ስፖርቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ተስፋፍቶ ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኝ ትልቁን ድርሻ በመውሰድ ከፊት መስመር ተሰላፊ ናቸው። ከእንግሊዝ ኤምባሲ ጎልፍ ኮርስ፣ ከኮሚሽነር ዘሪሁን ቢያድግልኝ ፣ በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ ጎልፍ ፕሬዚዳንት ከሆነው ከአቶ አበባው ቢሆነኝና ሌሎች የኮሚቴ አባላቶች ጋር በመሆን የመጀመሪያውን የጎልፍ ማህበር እንዲቋቋም አድርገዋል። የጎልፍ ስፖርትም ልክ እንደሌሎቹ ፌዴሬሽኖች ሁሉ በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እንዲያገኝ በቻሉት አቅም ደግፈዋል። አሁንም እየደገፉ ይገኛሉ። «በወቅቱ ብዙ ኢትዮጵያዊ ጎልፈኞች አልነበሩም። ከ60 በመቶ በላይ አባላቱ የውጪ ዜጎች ነበሩ» በማለት ለስፖርቱ መሰረተ ለመጣል ብዙ ስራዎች መስራታቸውን ያስታውሳሉ። በራሳቸው ድርጅትና የገንዘብ ወጪም የመጀመሪያውን ስፖንሰር ማድረግ ችለዋል። በግል ከመደገፍ ባሻገርም ስፖንሰሮች በማምጣት ጉልህ ድጋፍ አድርገዋል። በወቅቱ የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ዘሪሁን ቢያድግልኝም ከእርሳቸው ጋር በመሆን ለምስረታው እና ህጋዊ ፍቃድ ማውጣቱ ላይ ትልቅ ስራ መስራታቸውን ይናገራሉ። ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በርካታ ስፖርቶች ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ በመንግስትና በፌዴሬሽኖች አማካኝነት እገዳ ተጥሎባቸዋል። በዚህ ምክንያት አዲስ እንቅስቃሴ እየተስተዋለ አይደለም። የአዲስ አበባ እና የኢትዮጵያ የጎልፍ ማህበራት የዚህ ክልከላ አካል ናቸው። ሆኖም ስፖርት ማህበራዊ ሃላፊነት መወጣትንም ስለሚጨምር በወረርሽኙ አማካኝነት ቀጥተኛ ተጋላጭ ለሆኑ ድጋፍ የሚፈልጉ ወገኖች እርዳታ የማስተባበር ስራዎችን ከመስራት አልቦዘኑም። የዚህ ስፖርት ቀጥተኛ ተሳታፊ የሆኑ አባላት እርዳታ በማሰባሰብ ለመንግስት ገቢ አድርገዋል። በተጨማሪ በጎልፍ ክለቡ ለሚገኙ ሰራተኞች ወረርሽኙ የፈጠረባቸውን ጫና ለመቀነስ በሚል (በአቶ ነብዩ ሳሙኤልን አስተባባሪነት) የፋሲጋ ሰሞን ከመቶ ሺ ብር በላይ በመሰብሰብ አጋርነታቸውን አሳይተዋል። የአጭር ጊዜ ግብን ለማሳካት የስፖርቱ ወዳጅና ደጋፊ የሆኑት አቶ ነብዩ ዓለም አቀፍ ልምድን በማጣቀስ ወቅቱን ባገናዘበ መንገድ ጥንቃቄ ሳይለይ የጎልፍ ስፖርት መቀጠል እንዳለበት ይናገራሉ። ይሄ የእለት ጉርሳቸውን ለመደጎም የሚጥሩ ደጋፊ ሰራተኞችን ኑሮ ለመደጎም እንደሚያስችል ይጠቅሳሉ። መንግስት ባወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መመሪያ መሰረት ጎልፍ መጫወት ማቆማቸውን ይጠቅሳሉ። ሆኖም የጎልፍ ክለብ ማኔጅመንት በቅርቡ ከሱዳን ለመጡ ዜጎች ማቆያ እፈልገዋለሁ በማለት ማንም በግቢው ውስጥ እንዳይገባ መከልከሉን ይናገራሉ። በዚህ ምክንያት 168 ሰራተኞችና በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች የሚዝናኑበት ስፍራ ስራውን እንዳቆመ ይገልፃሉ። ሰራተኞቹም ከአገልግሎት ክፍያ (ሰርቪስ ቻርጅ) የሚያገኙት ገቢ በመቋረጡ ችግር ውስጥ መሆናቸውን ያነሳሉ። ለማቆያ በጎልፍ ክለቡ ግቢ ውስጥ የሚገኙት ዜጎች ከ3 የማይበልጡ በመሆናቸው አጠቃላይ ግቢውም በጣም ሰፊ ከመሆኑ አኳያ ማቻቻል ቢቻልና ስፖርታዊ እንቅስቃሴውም ሆነ ሬስቶራንቱ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መመሪያ መሰረት በጥንቃቄ ቢቀጥል መልካም መሆኑን ያነሳሉ። ‹‹የጎልፍ አባላቱና ሌሎች ዜጎች በተንጣለለው ግቢ ውስጥ ተራርቆ በባለሙያ በኬሚካል እየተፀዳ የሩጫና እርምጃ ስፖርት ከዚህ ቀደም ይደረግ ነበር›› የሚሉት አቶ ነብዩ፤ አሁን ሙሉ ለሙሉ እንዲቆም መደረጉን ይገልፃሉ። ኢትዮጵያ ደረጃውን የጠበቀ ባለ 18 ጉድጓድ የጎልፍ ማዘውተሪያ ስፍራ እንዳላት አንስተውም፤ ይህ ቦታ በርካታ ሚሊዮን ዶላር ወጥቶበት የተሰራ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ በዚህ መልካም አጋጣሚ መጠቀም እንዳለባትም ያምናሉ፡፡ ‹‹ጎልፍ ኮርሱ የተሰራው በንጉሱ ጊዜ ነበር። ሆኖም በደርግ ጊዜ የቡርዧ ጨዋታ ነው በሚል ተከልክሎ ስፍራው የራሺያ ወታደራዊ ካምፕ ሆኖ ቆይቷል›› የሚሉት አቶ ነብዩ፤ ስርአቱ ሲቀየር በኢህአዴግ ጊዜ ከነበረው ስታንዳርድ ይበልጥ ተሻሽሎ በ18 ጉድጓድ ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ተሰርቶ እስካሁን ድረስ አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነም ያነሳሉ። የጎልፍ ክለቡ በባህልና ስፖርት ቱሪዝም ሚኒስቴር ስር ሆኖ አገልግሎት መስጠት ቢጀምር የውጪ ምንዛሬን ለማግኘትና ቱሪዝምን ለማሳደግ ጠቀሜታ አለው የሚል ምክረ ሃሳብም ያነሳሉ። 34 የጎልፍ ማዘውተሪያ ያላት ጎረቤት አገር ኬኒያ እንዲሁም ታይላንድ ጎልፍን ከቱሪዝም ጋር በማያያዛቸው ተጠቃሚ መሆናቸውንም በምሳሌነት ይጠቅሳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በተለይ በቤተ መንግስት ‹‹አንቲክ›› የሆኑ የአገር ሃብቶችን በማልማት ለምሳሌ ያህል በቤተ መንግስት ‹‹የአንድነት ፓርክን››፣ ‹‹የእንጦጦ ፓርክ››፣ ‹‹የሸገር ወንዞችን የማስዋብ ፕሮጀችክ›› እና ሌሎች አካባቢዎች ላይ ግንባታ አከናውነው ለአገር ጥቅም እንደቀየሩት በምሳሌነት መውሰድ እንደሚቻልም ይጠቁማሉ። ጎልፍንም በዚህ መንገድ ተመልክቶ ያለውን ሃብት መጠበቅና ይበልጥ ማልማት ያስፈልጋል የሚል ሃሳብም ያነሳሉ። በአሁኑ ሰአት የቱሪዝም ዘርፉን ሊያነቃቁ የሚችሉ መሪዎች ስላሉ ይበልጥ የሚደግፍ እንደሆነም ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዘንድሮ ክረምት ከ5 ቢሊዮን በላይ ችግኝ እንዲተከል ጥረት እንደሚያደርጉት ሁሉ ይህንን የአገር ሃብት የሆነውን ‹‹ለምለማማ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ›› በተገቢው ሚኒስትር መስሪያ ቤት ስር እንዲተዳደር በማድረግ ለያዝነው የብልፅግና ጉዞ አጋዥ እንዲሆን እንዲያመቻቹት ይጠይቃሉ። ‹‹የአዲስ አበባን ጎልፍ ክለብ የመከላከያ ፋውንዴሽን ቢያስተዳድረውም ልንኮራበት የሚገባ በእጃችን ያለ ሀብት ነው›› የሚሉት የስፖርቱ ወዳጅ በቱሪዝም ረገድ የሚያስገኘው ጥቅም ይበልጥ በባለሙያዎች ተጠንቶ አሁን ካለው የተሻለ እንዲሆን መሰራት ይኖርበታል ይላሉ። የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆኑት ወጣቱ (በርሳቸው አባባል ኢነርጃይቲኩ) ኢንጅነር ታከለ ኡማ የጎልፍ ስፖርት ቢስፋፋ የሚያስገኘውን የቱሪዝም መነቃቃት በሳይንሳዊ መንገድ ቢያስጠኑትና እንዲስፋፋ አመራር እንዲሰጡ ጥያቄያቸውን ያቀርባሉ። በጥቅሉ የሁሉም ዜጎች አላማ ኢትዮጵያ ከድህነት ተላቅቃ ወደ ብልፅግና ለመውሰድ ስለሆነ ጉዳዩን ሊታሰብበት ይገባል ይላሉ። አቶ ነብዩ ሃሳባቸውን ሲያጠቃልሉ በአገራችን የሚገኙ ባለሃብቶች የተለያዩ ስፖርቶችን በመደገፍ፣ ስፖንሰር በማድረግና ግዜያቸውን በመስጠት ቢሳተፉ፤ ወጣት የሆነውን ትውልድ አምራች ዜጋ እንዲሆን አስተዋፅዖ ማበርከት ይቻላል ይላሉ። ለምሳሌ ያህል የአዲስ አበባ ጎልፍ ክለብ ባቋቋመው ኮሚቴ ምክንያት ባለፉት 13 ዓመታት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኤሜሬትስ አየር መንገድ፣ኬኒያ ኤርዌይስ፤ ሚድሮክና ቢጂአይ እንዲሁም ከኤምባሲዎች ዙምባቢዌ፣ስፔን፣ ቼክ ሪፐብሊክና ከአሜሪካ ኤምባሲዎች በርካታ ሚሊዮን ገንዘብ በማሰባሰብ ስፖርቱን ለመደገፍ እንደተቻለ ያነሳሉ። በመሆኑም በተመሳሳይ ባለሃብቶች ያላቸውን አቅምና ሃብት ለዚህ በጎ ዓላማ ይጠቀሙበት ሲሉ ምክረ ሃሳባቸውን በመናገር ይቋጫሉ። አዲስ ዘመን ሰኔ 3/2012ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=34121
[ { "passage": " አዲስ አበባ፡- የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ አንዱ መፍትሄ ቢሆንም በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለው ቸልተኝነት ዋጋ እንዳያስከፍል ስጋት ማሳደሩ ተገለጸ፡፡\nየአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል መንግሥትና መገናኛ ብዙኃን እየለፉ ቢሆንም፤ በከተማዋ አሁንም ማህበራዊ ርቀትን የማይጠብቁና በቸልተኝነት የሚያልፉ ሰዎች መኖራቸው ይታያል፤ ይህም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ይቻል ዘንድ የሚደረገውን ርብርብ ወደ ኋላ የሚጎትትና ስጋት የሚፈጥር ነው፡፡\nየመዲናዋ ነዋሪ አቶ መርከቡ አህመድ እንደተናገሩት፤ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ጨምሮ ባለሙያዎች የቫይረሱን ስርጭትና የመከላከያ መንገዶች በተመለከተ በየጊዜው ግንዛቤ ቢሰጡም፤ ህዝቡ ‹‹በቫይረሱ ምን ያህል ሰው ተያዘ›› የሚለውን ከማዳመጥ ውጭ በተለይ ማኅበራዊ ርቀትን ከመጠበቅ አኳያ ለውጥ ማምጣት አልተቻለም፡፡ ህይወት ከተቀጠፈ በኋላ መጸጸት ስለማይቻል ህዝቡ የመንግሥትን መመሪያ በማክበር\n ለሌላው ህይወት መጨነቅ ይኖርበታል፡፡\nሌላኛው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ አቶ ሂርጳ ዳዲ በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ ቫይረሱ ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ የተለያዩ አካላት በትኩረት መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ሲያስተላልፉ እንደቆዩና አሁንም ሙሉ ጊዜያቸውን ግንዛቤ በመስጠት ላይ እያሳለፉ መሆኑን ጠቁመው፤ በህብረተሰቡ ዘንድ በቂ የሆነ ግብረ መልስ አለመኖሩን ገልጸዋል፡፡ ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ መመሪያዎችን ንቆ በመተው ይልቁንም የተለመደውን ማህበራዊ ቅርርብ በማጉላት የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ሰዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ ኃላፊነትን የዘነጋ እንቅስቃሴ በዚሁ ከቀጠለ ዋጋ እንደሚያስከፍልም አሳስበዋል፡፡ \nበአዲስ አበባ ያለው ማህበራዊ ህይወት ‹‹ማህበራዊ ርቀትን›› ለመተግበር አዳጋች መሆኑን የሚናገሩት ወይዘሮ ምሥራቅ አንዳርጌ፤ የበሽታው ተጽእኖ ከዚህ የከበደ በመሆኑ ህዝቡ ቫይረሱን ለመከላከል ሲባል የግድ የጤና ሚኒስቴር መመሪያዎችን መተግበር እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡ ስጋቱ የሁሉም ህብረተሰብ እንደሆነው ኃላፊነት መውሰዱም የሁሉም መሆን እንዳለበት አመላክተዋል፡፡\n የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፤ በመዲናዋ አንዳንድ ሱቆችና የንግድ ሥፍራዎች ላይ በርካታ ዜጎች ተጠጋግተው እየተገበያዩ መሆኑን በመጠቆም፤ ይህ አካላዊ ርቀትን ያልጠበቀ እንቅስቃሴ መዘናጋትን የሚፈጥርና የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት አደጋች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ \nሚኒስትሯ አክለውም፤ በተለይም በሰዎች መካከል ያለውን ርቀት ስለ መጠበቅ አስፈላጊነትና የእጅ ንፅህናን ያለመዘናጋት የመጠበቅን ጠቃሚነት አስገንዝበዋል። መንግሥት ይህንን ለማስተግበር የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ሥራ ላይ ማዋሉን በማውሳት፤ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሂደቶች በቀጣይ ይከናወናሉ ብለዋል፡፡ በመንግሥት በኩል የሚተላለፉ መመሪያዎችን የማስተግበሩ ሂደትም በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡\nየሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬና ሌሎች ሚኒስትሮች ትላንት በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የኮሮና ቫይረስን ህብረተሰቡ እንዴት መከላከል እንደሚገባው ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ አከናውነዋል።\n አዲስ ዘመን መጋቢት 23/2012\nአዲሱ ገረመው", "passage_id": "9ca8f46d710f3a45ba589ae4cc0c0cf5" }, { "passage": "አትሌቲክስ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ስፖርታዊ የውድድር መድረኮች በውጤታማነት ስሟን ለዓለም ያስተዋወቀችበትና ገናናነትን ያተረፈችበት መሆኑን ብዙዎችን የሚያስማማ ሀቅ ነው።ኢትዮጵያና አትሌቲክስ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች እንደመሆናቸውም ብርቅዬ አትሌቶቿ በዓለማችን ትልቁ የስፖርት መድረክ በኦሊምፒክና በሌሎችም ሻምፒዮናዎች ወርቅ ተለይቷቸው አያውቅም።\nከአትሌቲክስ ልዩ ልዩ ውድድሮች መካከል ደግሞ የረጅምና መካከለኛ ርቀት ሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ተጠቃሽ ውጤት ያስመዘገቡባቸው የውድድር ፈርጆች ናቸው።በተለይም በረጅም ርቀት በዓለም ትኩረት ያገኘችበትና ኩራትን የተጎናጸፈችበት ስለመሆኑ የአትሌቶቻችን ድሎች ማሳያዎች ናቸው ።አትሌቶቻችን በዓለም አቀፍ ውድድሮች ከአንድ እስከ ሦስት ተከታትለው በመግባት ዓለምን ያስደመሙባቸው ወቅቶች በርካታ ናቸው።በዚህ ረገድ በሲድኒ ኦሊምፒክ የታየው ወርቃማ ታሪክ «አረንጓዴው ጎርፍ»ን (green flood ) ማስታወስ በቂ ምስክር ይሆናል።\nምንም እንኳን በዚህ ምልክ በተለይም ቀደም ባሉት ዓመታት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ የረጅምና መካከለኛ ርቀት ሩጫ ውድድሮች ፈርጥ መሆን ቢችሉም አሁን ግን ይህ የቀደመ ውጤታማነታቸው አብሯቸው አለመሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች ይታያሉ።\nለዚህ የውጤት መራቅም በተለይ በአህጉርም ሆኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዓመታትን ጠብቀው እስካልሆነ በአምስትና አስር ሺ ሜትር የሚካሄዱ ውድድሮች በእጅጉ መቀንስ፣ በምክንያትነት ይጠቀሳል። ይሁንና በአሁኑ ወቅት የጎዳና ውድድሮች መበራከታቸውን ተከትሎ በርካታ አትሌቶች ለአምስትና አስር ሺ ሜትር ውድድር የሚረዳ ልምምድ ከመስራት ይልቅ ለጎዳና ውድድሮች ትኩረት በመስጠት ወደዚያው መፍለሳቸው ዋነኛው ችግር ሆኖ ይጠቀሳል።አዲስ ዘመን ጋዜጣም በመም ውድድሮች በተለይ የአምስትና አስር ሺ ሜትር የኢትዮጵያን የቀድሞ ስምና ክብር በማስመለሱ ሂደት በአሁኑ ወቅት ዋነኛ ተግዳሮት የሆነውን የአትሌቶች ለጎዳና ውድድር ትኩረት መስጠት እና ወደ ጎዳና ውድድሮች መፍለስን እንዴት በመከላከል ውጤታማ መሆን ይቻላል ሲል የዘርፉ ባለሙያዎች አነጋግሯል።ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አትሌቲክስ ክለብ ዋና አሰልጣኝ ንጉሴ ተፈራ፤ቀደም ባሉት ዓመታት በዓለም አቀፍ ደረጃ በአምስት እና አስር ሺ ሜትር ውድድሮች የዓለም ትኩረት ማረፊያ የነበረችው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በርቀቱ ያላት ስምና ክብር በቀድሞው ልክ አለመሆኑን ይስማሙበታል።\nየዚህም ዋነኛ ምክንያት በሙሉ ለማለት በሚያስደፍር መልኩ አገሪቱ በርቀቱ የነበራትን ክብር ነገ ከነገ ወዲያ አስጥብቀው ይቀጥላሉ የተባሉ አትሌቶች ጭምር ወደ ጎዳና ውድድሮች ፈልሰዋል የሚሉት አሰልጣኙ፤አሁን ከአልማዝ አያና ውጪ በርካታ አትሌቶች በጎዳና በተለይ በማራቶን ውድድር መጠመዳቸውን ይጠቅሳሉ።ይህም ሁሉም ግላዊ ፍላጎቱን ወደ ማርካት ማድላቱና ገንዘብ ላይ በማተኮሩ የተፈጠረ መሆኑን የሚገልፁት አሰልጣኙ፤ ሁሉም ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ማናጀሮች ትኩረት የሚሰጡት፣ አሰልጣኞችም የሚያሰለጥኑት አትሌቶችን ለጎዳና ውድድር ለማብቃት መሆኑን ይገልፃሉ።\nበተለይ ማናጀሮችና አሰልጣኞች አንድን አትሌት ነገ ስለሚካሄድ የጎዳና ውድድር እንጂ በቀጣይ ወራት ስለሚካሄድ ትላቅ አህጉር አቀፍ ሻምፒዮና ላዘጋጀው የሚል ሀሳብ የላቸውም» የሚሉት አሰልጣኙ፤አትሌቶቹ ወደ ጎዳና ውድድር እንዲያዘነብሉ በማድረጉ በኩል አብዛኛው ችግር ያለው አሰልጣኞቹ ዘንድ መሆኑን ያሰምሩበታል።‹‹የገንዘብ ጉዳይ ከሆነ ገንዘቡ በትራክ ውድድሮች ላይም አለ ›› የሚሉት አሰልጣኙ፤ በአግባቡ ከተሰራበት የትራክ ውድድርም ገንዘብ እንዳለውና ለዚህም ቀነኒሳ በቀለ፤ደራርቱ ቱሉ እነ ስለሺ ስህን የመሳሰሉ አትሌቶች በትራክ ውድድር ትልቅ ገንዘብ ሲያገኙ እንደነበር በማሳያነት በመጥቀስ ያብራራሉ።\nየአገሪቱን የቀደመ የረጅም ርቀት እውቅና እና ክብር መልሶ ለማስቀጠል የመም ውድድር አትሌቶችን በልዩነት መያዝ ይገባል የሚሉት ዋና አሰልጣኝ ንጉሴ፣ ለዚህም ራሱን የቻለ ህግ መውጣት እንዳለበት ነው የሚጠቁሙት፡፡ይህ እስካልሆነ ድረስ ነገም ከዚህ የከፋ አደጋ ውስጥ እንደምንወድቅ አልጠራጠርም»ይላሉ።እንደ ዋና አሰልጣኙ ገለፃ፤ በአሁኑ ወቅት ዓለም አቀፍ ውድድር በተቃረበ ቁጥር የጎዳና ተወዳዳሪ አትሌቶችን ወደ መም ለማምጣት ሲሞከር ይስተዋላል።ይሁንና በዚህ ዓይነት አካሄድ ውጤታማ ለመሆን መዳከር አግባብ አይደለም። እንደ የውድድሩ ባህሪም የሚገኘው ውጤትም ለየቅል የሆነውም ለዚሁ ነው።አንድ ሻምፒዮና ሲደርስ አትሌቶች ቢያንስ ከሦስት ወራት ቀድመው ማንኛውንም የጎዳና ውድድር ከማድረግ እንዲቆጠቡ ማድረግ እስካልተቻለ ድረስ አትሌቶች ከመም ውድድሮች ይልቅ ጉዳናን ምርጫቸው ከማድረግ እንደማይ ቆጠቡ ተናግረው፣ይህ አካሄድ የመም ውድድር አትሌቶችን እስከማሳጣት እንደሚደርስም ነው የሚያስገነዝቡት።ዋና አሰልጣኙ ይህን ችግር ለመፍታት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም አቅጣጫ ማስቀመጥ እንደሚኖርበት፣ለዚህም አዲስ አሰራር መተግበር የግድ እንደሚለው ይጠቁማሉ፡፡ ለአብነት ጎዳና ላይ የነበሩ አትሌቶች ከተወሰነ ወር በፊት ወደ ትራክ እንዳይመጡ፤የመም ተወዳዳሪ አትሌቶችም ከጎዳና ውድድር እንዳይመረጡ የሚገድብ ህግ መተግበር እንዳለበት ያስገንዝባሉ።አሰልጣኝ ሙልዬ እያዩም ኢትዮጵያ በተለይ በረጅም ርቀት የመም ውድድሮች የነበራት ዝና መደብዘዙን ይስማሙበታል።የዚህም ዋነኛ ምክንያት የጎዳና ውድድሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት እየተሰጣቸው መምጣቱ መሆኑን ያሰምሩበታል።\nእንደ አሰልጣኝ ሙልዬ ገለፃ፤በአሁኑ ወቅት ከ27 ሺ 800 በላይ የጎዳና ውድድሮች በየዓመቱ ይካሄዳሉ። እነዚህ ውድድሮችም ከጊዜ ወደ ጊዜ አዝናኝነታቸው ተመራጭ እየሆነ በመምጣቱም አዘጋጅ አገራት የአትሌቶቹን ቀልብ በእጅጉ መቆጣጠር ከመቻላቸውም በተጨማሪ ፣በተለይ በቱሪዝም ዘርፉ ለገቢ ምንጭነት እየተጠቀሙት ይገኛሉ።ይህ እንደመሆኑ ኢትዮጵያን በርቀቱ የመወከል አቅም ያላቸው ወጣት አትሌቶች ጭምር ወደ ጎዳና እየፈለሱ መሆናቸውን የሚያረጋግጡት አሰልጣኝ ሙልዬ፤ይህ ማለት ግን የውድድሮቹ መብዛት አትሌቶቹን ወደ ጎዳና ስቧቸዋል አሊያም ማናጀሮቻቸው በሚያሳድሩባቸው ጫና ወደ ጎዳና ውድድር ሄደዋል ለማለት እንደማያስደፍር ያስቀምጣሉ።አትሌቶች ከትራክ ውድድር ይልቅ ለጎዳና ውድድሮች ቅድሚያ እንዲሰጡ በአሰልጣኝና ማናጀሮቻቸው በኩል ጫና ይደርስባቸዋል የሚለውን አስተያየት አሰልጣኙ አይስማሙበትም፡፡ይህ ማለት ለግል ጥቅማቸው ሲሉ አትሌቶችን ለጉዳት በሚዳርግ መልኩ ለረጅም ጊዜያት ከሳምንት እስከ ሳምንት በአስፋልት ውድድር ሙሉ ስልጠና የሚሰጡ አንዳንድ ማናጀሮች የሉም ማለት እንዳልሆነም ይጠቁማሉ።\nአትሌቶች ወደ ጎዳና ውድድሮች የሚፈልሱት በማናጀሮቻቸው ገፋፊነት ብቻም ሳይሆን በአብዛኛው በግል ውሳኔ ቀደም ሲል የነበሩ አትሌቶችን በመመልከት ነው የሚሉት አሰልጣኙ፤አትሌቶችም በውድድር በመካፈላቸው ብሎም ካሸነፉ የሚያገኙት ጥቅም ከፍተኛ በመሆኑም የጎዳና ውድድሮችን እንዲመርጡ እያስገደዳቸው መሆኑን ያስገነዝባሉ።አሰልጣኙ በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ትላልቅ መድረኮች የአምስት እና አስር ሺ ሜትር ሩጫ የምስራቅ አፍሪካውያን መድመቂያ ነው፤ ኢትዮጵያውያንም የዚህ ድምቀት ፈጣሪዎች ናቸው፡፡ ይሁንና ይህ ትዕይንት አሁን ደብዝዟል ከማለት የቀደመውን ስምና ዝናችንን እንዴት መመላስ እንችላለን የሚለውን መመለስ ይገባል ሲሉ ያመለክታሉ።\nለዚህም በቀዳሚነት የመም ውድድር አትሌቶችን እንዴት በብቃት ማፍራት እንዲሁም ወደ ጎዳና የፈለሱትን በምን መልኩ ፊታቸውን እንዲያዞሩ ማድረግ ይቻላል የሚለውን የሚመለስ ተግባር መፈፀም እንደሚገባ ይጠቁማሉ።«ይህን ለማድረግ በቀዳሚነት በትራክ ውድድር የሚሳተፉ አትሌቶች የሚያገኙትን ጥቅም ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል›› የሚሉት አሰልጣኙ፤አትሌቶች ወደ ጎዳና የመውጣታቸው ምክንያት ህይወታቸውን ለመደጎም መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ይህን ችግር ለመፍታትም በመም ውድድር ለሚካፈሉት ከፍ ያለ ሽልማት ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ በመጠቆም፣ይህ ሲሆንም ተተኪ አትሌቶች ማግኘት እንደሚቻል ያመለክታሉ።ከዚህም ባሻገር በዚህ ዘርፍ ፍላጎት ያላቸውን ልጆች ማፍራት እንደሚገባ በመጠቆም፣ ለዚህም የተመረጡት ልጆች ቀጣይነት ባለው መልኩ ህይወታቸውን መምራት የሚያስችላቸው ራሱን የቻለ ፕሮጀክት መቅረጽ እንደሚያስፈልግም ይገልጻሉ።\nእንደ አሰልጣኙ ገለፃ፤ትራክ ላይ የሰራ አትሌት ውድድር ለማግኘት አንድና ሁለት ዓመት መጠበቅ ግድ ይለዋል።ከዚህ ባንፃሩ የጎዳና ውድድሮችን ቶሎ ቶሎ ማግኘት ይችላል።ይህ በሆነበት የጎዳና ውድድር መምረጡ አይቅሬ ነው።በመሆኑም መሰል ችግሮችን ለመፍታት የውድድር ተደራሽነት መስፋት ያስፈልጋል፡፡ በመም ውድድሮች በተለይ በአምስትና አስር ሺ ሜትር የኢትዮጵያን የበላይነት የውጤት ክብር ለማስቀጠል ውድድሮችን በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ በማዘጋጀት ተደራሽነቱን ማስፋት ያስፈልጋል። ምንም እንኳን የጎዳና ላይ ሩጫዎች ተበራክተው የትራክ ውድድር ቢያንስ ሁለቱን ለማስታረቅ አትሌቶቹ ራሳቸውን ሳይጎዱ የሚካፈሉባቸው የልምምድ ዓይነቶችን ማዘጋጀትም የተሻለ ውጤት ማምጣት ይቻላል።\n«የጎዳና ላይ ውድድር የግል ህይወትን ማሻሻያ እንጂ ለክብር እና ለአገር ተብሎ የሚሮጥበት አይደለም» የሚሉት አሰልጣኝ ማሙዬ፤ከሁሉም በላይ አትሌቶች ለአገርና ለክብር ያላቸውን ስሜት በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር በድጋሚ እንዲያ ረጋግጡ ግንዛቤ የማስረፅ ተግባር ማከናወን እንደሚገባም ይገልጻሉ።የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዚዳንትና ተወካይ አትሌት ስለሺ ስህን፤ በአሁኑ ወቅት የአስርና አምስት ሺ ሜትር የመም ውድድሮች ከቀደመው ጊዜ አንፃር ሲታይ በእጅጉ መቀነሳቸውን ጠቅሶ፣ ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል ለማለት እንደማያስደፍር አሁንም ትልልቅ ውድድሮች እንዳሉ ያብራራል።የግል ጥቅም አትሌቶቹ ወደ ጎዳና ለመውጣታቸው ምክንያት እንደማይሆን የሚናገረው አትሌት ስለሺ፣ በመም ውድድሮች ላይ ውጤታማ መሆን ከማራቶን ባልተናነሰ በስፖንሰር፤በዳይመንድ ሊግ የመመረጥ እና ሌሎችም ረብጣ ሽልማቶች የሚያስገኝበት ሁኔታ እንዳለም ያስረዳል።ለዚህም አሁንም በመም ውድድር አልማዝና እና ገንዘቤ እንዲሁም ሰለሞን ባረጋ እየሮጡ መሆናቸውን በአብነት ይጠቅሳል።\n‹‹እርግጥ ነው ማራቶን ጥቅም ሊኖረው ይችላል።ይሁንና ማራቶን በመጪዎቹ የአትሌቲክስ ዕድሜዎች የሚደረስበት ውድድር ነው›› የሚለው አትሌት ሰለሺ፤ ከጎዳና ውድድሮች በተለይም አንድ ጊዜ ማራቶን ላይ ገብቶ ሁለትና ሦስት ዓመታት ከቆዩ በኋላ ጨርሶኑ መጥፋት ጉዳት እንጂ ጥቅም እንደሌለውም ነው ያብራራው።በአሥርና አምስት ሺ ላይ የሚቆይ አትሌት ወደ ማራቶን ሲሄድ ውጤታማ መሆን እንደሚ ችልና በተለይ ወጣት አትሌቶች በልጅነት ዕድሜያቸው ወደ ማራቶን ከሚገቡ በመም ውድድሮች ላይ ብዙ ዓመታት መስራት ቢችሉ ውጤታማ ስለመሆናቸው ጥርጥር ሊገባቸው እንደማይገባም ይጠቁማል።\nእንደ አትሌት ስለሺ ገለፃ፤ይህን ችግር ለመፍታት በቀዳሚነት አትሌቶች ቸኩለው ወደ ጉዳና መውጣታቸው ስህተት እንደሆነና በቀጣይ የሩጫ ህይወታቸው ውጤታማነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳርፍ ጠንቅቀው እንዲረዱት ግንዛቤ ማስጨበጥ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ዓይነት ውድድር ውስጥ ለማለፍ እንደማይጠቅም በውድድሩ ቢያልፉም ውጤታማ እንደማይሆኑ ማስረዳት ይገባል፡፡ በመም ውድድሮች በስለው ወደ ጎዳና ውድድሮች ቢሄዱ የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆኑ ማስገነዘብ የግድ ይላል።ከሁሉም በላይ የአገር ፍቅር ስሜት የሚባለው እንዲሰርፅባቸው ማድረግ ይገባል።አንድ አትሌት ወደ ጎዳና የሚወጣው በአሰልጣኝ አሊያም ማናጀሩ ከፍተኛ ጫና እያሳደረበት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ መሆኑን የሚመሰክረው አትሌት ስለሺ፤እነዚህ ገንዘብ ተኮር የሆኑ አሰልጣኝና ማናጀሮችን መቆጣጠር እንደሚያስፈልግ ይናገራል፡፡ይህን ችግር መፍታትም የፌዴሬሽኑ ኃላፊነት መሆኑን ይናገራል።\nየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ ዱቤ ጅሎ፤በዓለም አቀፍ ደረጃ የመም በተለይ የአሥርና አምስት ሺ ሜትር ውድድሮች እየቀነሱ መምጣታቸውን ጠቅሶ፣ ፌዴሬሽኑም ራስ ምታት እንደሆነበት ይገልጻል፡፡ በተጠቀሱት ውድድሮች ሚኒማ ለማሟላት አትሌቶች ወደተለያዩ አገራት በመላክ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እየከፈለ መሆኑንም ይገልፃሉ።ከመልክዓ ምድር ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ዓለም አቀፉ ፌዴሬሽን የሚያስቀም ጠውን ሚኒማ ማሟላት አይቻልም፤ይህ እንደመሆኑ ፌዴሬሽኑ አትሌቶችን በመምረጥ ወደ ተለያዩ አገራት በመውሰድ እያወዳደረ መሆኑንም ያስረዳሉ።\nየረጅም ርቀት ውድድሮች እያበቃላቸው፤ የጎዳና ላይ ውድድሮች እየተበራከቱ መምጣታቸውና ሽልማታቸውም እየገዘፈ በመሆኑ አሰልጣኞች፤ ማናጀሮች እንዲሁም አትሌቶች ወደ ጉዳና እየፈለሱ መሆናቸውን ፌዴሬሽኑንም እንደሚያሳስበው ያስረዳሉ።ይህ ችግር እያደር በመባባሱም ፌዴሬሽኑ በተለይ አጭር ርቀት ላይ እንዴት እንስራ የሚለውን አቅጣጫ እስከመከተል እንዳደረሰው የሚገልፁት አቶ ዱቤ፤ፌዴሬሽኑም ክልሎችና ክለቦችን በመደገፍ የትራክ አትሌት የማይጠፋበት ሁኔታ እንዲፈጠር የበኩሉን እያደረገ መሆኑንም ነው ያስረዱት።አሁን የመም ውድድሮችን የሚሳተፉ አትሌቶችን ለመለየትና ለማብቃት እንቅፋት ከሆኑት መካከል አንደኛው የመወዳደሪያ ቦታ እጥረት መሆኑንም የሚያስረዱት አቶ ዱቤ፤በቀጣይ የመም ውድድር ራጮችን ፍፅሞ ከማጣት ቀድሞ መሰል የመወዳደሪያ ቦታ እጥረቶች መስተካከል እንደሚገባ ይናገራሉ፡፡ለዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የየበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ያቀርባሉ።\nየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ስፖንሰር አድራጊ ተቋማትን ፈልጎ እንዲሁም የአገር ውስጥ ውድድሮችን በማዘጋጀት ተወዳዳሪ አሸናፊዎች የተሻለ ጥቅማ ጥቅም የሚያገኙበትን አሰራር መዘርጋት እንዲሁም ለትራክ ተወዳዳሪዎች የሚሰጠውን ሽልማት ከፍ ለማድረግ መስራት እንደሚገባ ይጠቁማሉ።ታምራት ተስፋዬ", "passage_id": "29de9c359db0ea3019780eda698c1526" }, { "passage": "ባሕር ዳር፡ መስከረም 20/2012 ዓ/ም (አብመድ) በ17ኛው የዶሃ ዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ላይ የተካፈሉ የኢትዮጵያ የማራቶን አትሌቶች በሙሉ ለጤንነትና ለአስተዳደራዊ አሠራር ሲባል ከ3 ወር በፊት ምንም ዓይነት ውድድር ማድረግ እንደሌለባቸው በዶሃ የተገኘው የፌዴሬሽኑ አመራር ወሰነ።አመራሩ ይህንን ውሳኔ የሚመለከታቸው ሁሉ እንዲያከብሩም በጥብቅ አሳስቧል።ውሳኔውን መተላለፍ ከበድ ያለ እርምጃ እንደሚያስከትልም አስጠንቅቋል።በዶሃ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ሁሉም ኢትዮጵያን የወከሉ ሴት አትሌቶች ውድድሩን በሙቀት ምክንያት ማቋረጣቸው መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡ምንጭ፡- የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን", "passage_id": "a296eb2ff4d6ca603c7caf909e46b141" }, { "passage": "የብሔራዊ ሎቶሪ አስተዳደር በጉዳዩ ላይ የተለየ አቋም መያዙ ተጠቆመአዲስ አበባ፡- የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) በሚል በአገሪቱ የሚስተዋለው ቁማር እንዲቆም ከስምምነት መደረሱን የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ሲገልፅ፤ የብሔራዊ ሎቶሪ አስተዳደር ግን በጉዳዩ ላይ የተለየ አቋም መያዙ ተጠቁሟል፡፡በሚኒስቴሩ የወጣቶች ስብዕና ልማት ዳይሬክተር አቶ ዓለሙ ሠይድ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ የስፖርት ውርርድ በሚል የሚካሄደው የቁማር ጨዋታ አዲስ ዘመን ጋዜጣ አጀንዳ ካደረገው ጀምሮ ለሁለት ወራት በተሠራው ተከታታይ ሥራ የቁማር ጨዋታው እንዲቆም ተወስኗል፡፡ እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ፤ 26 አባላትን ያቀፈ የፌዴራል የአሉታዊ መጤ ልማዶችና አደንዛዥ ዕፅ ግብረ ኃይልና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ የሆኑበት መድረክ በማዘጋጀት የስፖርት ውርርድ ቁማር በዜጎች ሥነ ልቦናዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና አጠቃላይ ችግሮች ላይ የሚያደርሰው ችግር ተፈትሿል፡፡ ዳይሬክተሩ ‹‹በወቅቱ በተደረገው መድረክ የብሔራዊ ሎቶሪ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያመጣንለት አዲስ የመዝናኛ ቴክኖሎጂ ነው›› ማለቱን አስታውሰው፤ ግብረ ኃይሉና በመድረኩ የተገኙ የተለያዩ የሕብረተሰብ ተወካዮች ድርጊቱ ቁማር እንደሆነ ለአገር ፀር መሆኑን አምነው እንዲቆም መግባባት ላይ ቢደርሱም፤ አስተዳደሩ ግን ለሕዝቡ መዝናኛ ቴክኖሎጂ ነው በሚል በአቋሙ መፅናቱን ገልፀዋል፡፡ ከዕድሜ ጋር ተያይዞ ያለውን ገደብ የሕግ ማሻሻያ እንደሚደረግና ውርርዱ ግን ሊቀጥል እንደሚገባ አቋሙን እንዳራመደ የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ የስፖርት ውርርድ ቁማር እንጂ ቴክኖሎጂ አለመሆኑን ጠቅሰው፤ ‹‹ሕዝቡ እንደማይጠቅመው እየተናገረ ብሔራዊ ሎቶሪ አስተዳደር ይህን መሰል አቋም መያዙ ለሕዝብ የተቋቋመ ድርጅት ቢሆንም እንኳ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ግን የሕዝብ ውግንናው አጠራጣሪ ነው፡፡ ችግሩን ለማቃለልም ዝግጁ አይደለም›› ብለዋል፡፡የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚሻው\nበርካታ ቴክኖሎጂ መኖሩን\nየጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ በአሁኑ\nወቅት የአገሪቱ ዜጎች\nመንግሥትን የሚጠይቁት የዳቦ፣\nየዘይት፣ የወጣቱን ዕውቀትና\nክህሎት የሚያዳብሩና ሥነ\nምግባራቸውን ሊገነባ የሚችል\nእንዲሁም መሰል ኑሯቸውን\nየሚያሻሽሉበትን ቴክኖሎጂ ሲሆን፤\nውርርዱ ግን ጭርሱን\nየዜጎችን ዳቦ መግዣ\nየሚቀማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ዳይሬክተሩ ዜጎች ወር ጠብቀው የሚያገኙትን ደመወዛቸውን የሚቀማ በሚሊየኖች ኪሣራ ጥቂቶች የሚከብሩበት፣ ዜጎች ከፈጣሪነት ይልቅ ሳይሠሩ መክበርን የሚያስተምረውን ይህን የቁማር ተግባር ምንም እንኳ አስተዳደሩ መዝናኛ ነው ቢልም ቁማር ግን መዝናኛ ሊሆን እንደማይችል፤ ይልቁንም ከቤተሰብ አልፎ ለአገር ፀጥታም ሥጋት መሆኑን አመላክተዋል፡፡እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ፤ በተከናወኑ ጥናቶች ጉዳዩ በጣም አሳሳቢና በተለይ ወጣቶችን፣ ሴቶችንና ሕፃናትን የሚጎዳ መሆኑ ተደርሶበታል፡፡ በተመሳሳይ ለአገሪቱ የዕድገት ደረጃ የሚመጥን ያልሆነው ይህ ቁማር ባህልን፣ እሴትን እንዲሁም ሃይማኖትንም የሚፃረር ነው፡፡ በዚህም የሃይማኖት አባቶች ያወገዙት፣ ተጠቂ የሆኑ ሚስቶች እንዲሁም ወጣቶች ሱሰኛ እንደሆኑና መንግሥት እንዲያስቆምላቸው እየጠየቁ አስከፊነቱን እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ዳይሬክተሩ የሚያስከትለውን ጉዳት ባለመረዳት የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የችግሩ ሰለባ ሲሆኑ እንደሚስተዋሉ በመጠቆም፤ ከዚህ ቀደም ሲደረግ እንደነበረው ከፌዴራል ጀምሮ እስከ ታች ወረዳ ድረስ የሚገኙ መዋቅሮችን በመጠቀም ሕብረተሰቡን ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ በጥናት የተደገፈ መረጃ እየተደራጀ መሆኑን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ ፈቃድ ሰጪ ሆኖ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ቀርቦ ጉዳዩ እንዲታይና ሕጉ ማሻሻያ እንዲደረግበት እንደሚቀርብ፤ ማሻሻያ የሚደረገው ግን ሚኒስቴሩና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ሙሉ በሙሉ እንደማያስፈልግ ባሳዩት ዕምነት መሠረት የሕዝቡን ጥቅም ማዕከል ያደረገ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡በጥር ወር ውስጥ ለስፖርት ውርርድ በሚል ይሰጥ የነበረው ፈቃድ የቆመ ሲሆን፤ አይጠቅምም ተብሎ ከተወሰነ በሥራ ላይ የሚገኙት አቋማሪ ድርጅቶች የውላቸው ጊዜ እስኪጠናቀቅ ብቻ ሊቆዩ እንደሚችሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ ዳይሬክተሩ እንደገለፁት በአሁኑ ወቅት ጉዳዩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ደርሷል፡፡ በዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ ችግሩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰና በተለይ ወጣቶችና ሕፃናቶችን የሚጎዳ ድርጊት እንደሆነም ምክር ቤቱ አምኗል፡፡ ስለሆነም ሂደቱ ተጠብቆ የሚመለከታቸው አካላት ደረጃ በደረጃ ለችግሩ ትኩረት እንዲሰጡት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ሣይንሳዊና ሌሎች አገራትም እንደ መነሻ ሊወስዱት የሚችሉት አገር አቀፍ ጥናት ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው፤ በሁለት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በችግሩ ተጠቂ የሆኑ አካላት የተካተቱበት ጥናታዊ ዘጋቢ ፊልም (ዶክመንተሪ) እየተሠራ ነው፡፡በክልል የሚገኙ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥተው ፈቃድ አሰጣጡን እንዲመረምሩ፣ ያልጀመሩት ደግሞ ከክልል ፕሬዚዳንቶች ጀምሮ የሚመለከታቸው የቢሮ ኃላፊዎች ፈቃድ አሰጣጡን እንዲያጤኑና ፍቃድ እንዳይሰጥ መግባባት ላይ መደረሱን ያመለከቱት ዳይሬክተሩ፤ እርምጃ መውሰድ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት በመጀመሩ ይዋል ይደር እንጂ ችግሩ እልባት እንደሚያገኝ ጠቁመዋል፡፡አዲስ ዘመን የካቲት 4/2012 ፍዮሪ ተወልደ ", "passage_id": "643270570a0b25a7a5a516ad2cd654cf" }, { "passage": "ከኮሮናቫይረስ ስጋት ጋር በተያያዘ የስፖርት ውድድሮችን ጨምሮ የንግድ ዘርፉ ላይ ተጽዕኖን እያሳደረ መሆኑን የዓለማችን ታዋቂ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ለቢቢሲ ተናገረ።በ10 ሺህ ሜትር ውድድር የሁለት ጊዜ የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነው ኢትዮጵያዊው ኮከብ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ወረርሽኙ በሩጫው ዘርፍና በንግድ ሥራው ላይ እያስከተለ ያለውን ጫና በተመለከተ እንደተናገረው ውድድሮች እየተሰረዙ የንግድ ሥራዎችም እየተስተጓጎሉ ነው ብሏል።በተለያዩ ቦታዎች ሊካሄዱ የነበሩ የሩጫ ውድድሮች ወረርሽኙ በፈጠረው ስጋት ሳቢያ ሲሰረዙ በተወዳዳሪዎች ላይ ከባድ ተጽእኖን እንደሚያሳድር ኃይሌ ገልጿል። \"እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አዳዲስና ተስፋ ያላቸው፣ እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ በውድድሮች ላይ ለመሳተፍ ሲዘጋጁ የነበሩትን ሯጮችን ብታናግሩ ውድድሮች በመሰረዛቸው የገጠማቸውን የልብ ስብራት መረዳት ትችላላችሁ።\"ኃይሌ ገብረሥላሴ እንደሚለው ቻይና ውስጥ ብቻ በየዓመቱ ከ350 በላይ የማራቶን ውድድሮች ይካሄዳሉ። ከኮረናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ ሁሉም በቻይና የሚደረጉ የማራቶን ውድድሮች ተሰርዘዋል። በአውሮፓም ውስጥ እንዲሁ በፈረንሳይ የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮንሺፕ ለሌላ ጊዜ መተላለፉን የጠቀሰው ኃይሌ፣ የፓሪስና የሮም ማራቶን መሰረዝን በመጥቀስ \"በርካታ ውድድሮች በበሽታው መስፋፋት ምክንያት ብቻ ተሰርዘዋል፤ አልያም ወደሌላ ጊዜ ተሸጋግረዋል\" ብሏል።\"አስቡት ለረጅም ጊዜ ልምምድና ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተው በድንገት ቻይና ውስጥ ውድድር አይደረግም፣ አውሮፓና አሜሪካ ውስጥ ውድድር አይኖርም ሲባል በጣም ከባድ ነገር ነው\" ሲል ኃይሌ ተናግሯል።\"እንደ ቀደምት ሯጭነቴ ወደኋላ መለስ ብዬ ሳስብ፤ ረጅም ጊዜ የፈጀ ዝግጅት ካደረግኩ በኋላ ውድድሩ ቢሰረዝ በጣም ልብን የሚሰብር ነገር ነው።\" የበሽታው መዛመት ስፖርትን ብቻ ሳይሆን ንግድንም እየጎዳው መሆኑን በተለያዩ የንግድ ዘርፎች የተሰማራው ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ተናግሯል። ጨምሮም ኪሳራው እያጋጠመ ያለው በቻይናና በአውሮፓ ውስጥ ብቻ ሳይሆን \"እዚህ ኢትዮጵያ የእኔን ኪስም እየነካው ነው\" ብሏል። \"የንግድ ሥራዬን በተመለከተም ከቻይና ያዘዝኳቸው ኮንቴይነሮች እዚያው ቆመዋል። አዳማ ውስጥ ሆቴል ለመክፈት እየተዘጋጀሁ ነበር ነገር ግን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ቻይና ውስጥ ሥራ ስለሌለ ሥራዬ ተስተጓጉሏል\" የሚለው ኃይሌ በሥራ ላይ ባሉት ሆቴሎቹ ውስጥም የእንግዶች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን አመልክቷል።የኮሮናቫይረስ ስጋት ከአትሌቲክስ ስፖርት በተጨማሪ በአውሮፓ የሚካሄዱ የእግር ኳስ ውድድሮችን እንዲሰረዙ ወይም በዝግ ስታዲየሞቹ እንዲደረጉ አስገድዷል። በሽታው ከቻይና ባሻገር በርካታ አገራትን እያዳረሰ ሲሆን እስካሁን ድረስ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ4366 በላይ የደረሰ ሲሆን በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ደግሞ ከ122 ሺህ በላይ ሆኗል። ", "passage_id": "7ce26276ef0b19a35d536040b686feee" } ]
c07771743f2adb00b19e7505a849f34b
846b2f87050a5a93510236ec8a3a9149
ለእግር ኳስ አሰልጣኞች ስልጠና ሊሰጥ ነው
በኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ እና በአሰልጣኝ አምሳሉ ፋንታሁን አማካኝነት በሀገራችን ላሉ የእግር ኳስ አሰልጣኞች ስልጠና ሊሰጥ መሆኑ ተነገረ።የአሰልጣኞች ስልጠናው በካፍ ኢንስትራክተር እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ በሆነው አብርሃም መብራቱ የተዘጋጀ ሲሆን በዋናነትም በኢንስትራክተሩ ይሰጣል ተብሏል። በተጨማሪም በርካታ ኢትዮጵያውያን አሰልጣኞች ወደ አሜሪካና ስፔን ተጉዘው ስልጠና እንዲወስዱ ከዚህ ቀደም ሲያመቻቹ የነበሩት በአሜሪካ የሳክሬም የእግር ኳስ አካዳሚ ሴቶች ዳይሬክተር እና አሰልጣኝ አምሳሉ ፋንታሁን አማካኝነት ከአስር ቀናት በኋላ ይሰጣል። ስልጠናው በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ለሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች በዋናነት የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም በሴቶች እግር ኳስ ላይ ለተሰማሩ አንድ አንድ አሰልጣኞች የሚካተቱበት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።የአሰልጣኝ ስልጠናው በዋናነት የሚያጠነጥነው አሰልጣኞች አሁን ካለው ሁኔታ በመነሳት ራሳቸውን ማሻሻል በሚኖርባቸው ሁኔታዎች፣ በሀገራችን እግር ኳሳዊ ሃሳቦች፣ በአሰልጣኝነት ብቃት ላይ ይሆናል። ስልጠናው በኮቪድ -19 ምክንያት ስፖርታዊ ውድድሮች በመበተኑ በቤታቸው እያሳለፉ የሚገኙ አሰልጣኞች ከሙያው እንዳይርቁና፤ ውድድር ሲጀመር ከዜሮ እንዳይነሱ በማድረግ መነቃቃት የሚፈጥር መሆኑን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል ። የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አቋማቸውን እየፈተሹ ይገኛሉ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ የሆኑ በርካታ ክለቦች የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን እያደረጉ ይገኛሉ።በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ፕሪሚየር ሊጉ ከቀናት በኋላ ወደ መደበኛ ውድድር ሊመለስ መሆኑን ተከትሎ ክለቦቹ ቀደም ብለው የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎች እያደረጉ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።አለም ዓቀፍ ስጋት በሆነው የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ፕሪሚየር ሊጉ ዳግም ለመመለስ እኤአ ሰኔ 10 ቀን 2020 ቀጠሮ ተይዟል።ክለቦች ወደ መደበኛ ጨዋታቸው ሊመለሱ ቀናት የቀሩት በመሆኑ ወደ ነጥብ ጨዋታ ከመግባታቸው በፊት አቋም መፈተሻዎችን እያደረጉ ይገኛሉ።በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተመልካች እንዳለው የሚነገርለት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰኔ 10 ይጀመራል።ፕሪሚየር ሊጉ ከተቋረጠ ከወራት በኋላ ወደ ውድድር መመለሱ በክለቦችና ተጫዋቾች ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ለመቀነስ ከዛ በፊት በርካታ የሊጉ ክለቦች እርስ በእርስ አልያም ከሌሎች ክለቦች ጋር የአቋም መፈተሻ ግጥሚያዎችን በማድረግ ላይ እንደሆኑ ታውቋል። በፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ከሆኑ ክለቦች አንዱ የሆነው ማንችስተር ዩናይትድ በኦልድ ትራፎድ ሃሪ ማጉዌር በአምበልነት የመራው ቡድን በሜዳው በብሩኖ ፈርናንዴስ የሚመራውን ቡድን ገጥሟል። በአቋም መፈተሻ ጨዋታው የሃሪ ማጓየር ቡድን የብሩኖ ፈርናንዴዝን ስብስብ 2 ለ 0 መርታት ችሏል። ከወራት በኋላ ማርከስ ራሽፎርድ እና ፖል ፖግባ ደግሞ ወደ ሜዳ ተመልሰዋል።የማይክል አርቴታ መድፈኞቹ ግን ከእርስ በእርስ ግጥሚያ ይልቅ የቻምፒየን ሺፕ ክለብን በሜዳቸው ማስተናገድን መርጠዋል። ከቻርልተን ጋር የወዳጅነት ግጥሚያ ያደረጉት አርሰናሎች 6-ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።ከዚህ በተጨማሪም ቼልሲ፣ ሊቨርፑል፣ ዌስት ሃም አስቶን ቪላ እና ኒው ካስል ዩናይትድም ከ10 ቀናት በኋላ ለሚጀመረው ሊግ እራሳቸውን ዝግጁ ለማድረግ እርስ በእስር ግጥሚያ የሚያደርጉ ክለቦች መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። አዲስ ዘመን ሰኔ 2/2012
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=34005
[ { "passage": "በኳታር እና ቤልጂየም እግርኳስ ፌዴሬሽን የጋራ ትብብር የተዘጋጀው የኦንላይን ስልጠና ዛሬ ከሰዓት ለ2ኛ ጊዜ ሲሰጥ የሀገራችንም አሰልጣኞች በስልጠናው ላይ ተካፍለዋል።በቤልጂየም የእግርኳስ እድገት ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየተሰጠ ያለው ይህ የኦንላይን ስልጠና ሀሙስ ምሽት እንደተጀመረ ይታወቃል። ሀሙስ በነበረው ቆይታም በግብ ጠባቂዎች ላይ ያተኮተ ትምህርት በቤልጂየም የወጣት ቡድን አሰልጣኝ ፓትሪክ ክሪመርስ አማካኝነት ተሰጥቷል። በዚህ ስልጠና ላይም የኢትዮጵያ ወንዶች እና ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የግብ ጠባቂ አሰልጣኞች እንዲሁም የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪምየር ሊግ ክለቦች የግብ ጠባቂ አሰልጣኞች እንደተሳተፉ ታውቋል።ስልጠናውን ያዘጋጁት አካላት በማስፈቀድ እየተሳተፉ የሚገኙት የሃገራችን አሰልጣኞች ዛሬ ከሰዓትም በ2ኛ ክፍል የስልጠና መርሃ ግብር ትምህርት ወስደዋል። በዛሬው የኦንላይን የትምህርት መርሃ ግብር ላይ ደግሞ ስለቤልጂየም ብሄራዊ ቡድን የስኬታማነት ጉዞ ላይ ያተኮረ ትምህርት ተሰጥቷል። በተለይ ቤልጂየም ወደ ታላቅነት ለመምጣት የተከተለቻቸውን መርሆች እና የስልጠና መንገዶች በተብራራ መንገድ ጋይ ቤከር እንደሰጡ ስልጠናውን የወሰዱት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል።ይህንን ስልጠና የወሰዱ አብዛኞቹ የሃገራችን አሰልጣኞች ጥሩ ትምህርቶችን እንደቀሰሙ ተናግረዋል። በተለይ የሀሙሱን የግብ ጠባቂዎች ስልጠና የተከታተሉ የተለያዩ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የግብ ጠባቂ አሰልጣኞች ተመሳሳይ ስልጠናዎች በቀጣይነት እንዲመቻች መጠየቃቸውን ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ አያይዘው ገልፀዋል።በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በአሰልጣኝ አምሳሉ ፋንታሁን እና ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ አስተባባሪነት እግር ኳስ እና ቴክኖሎጂ በሚል ርዕስ ለሃገራችን አሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።", "passage_id": "2d299b7b4a18bcedae0b87b5115c59e6" }, { "passage": "የዳሽን ቢራ አጋር የሆነው የእንግሊዙ ክለብ አርሰናል የታዳጊ ተጫዋቾች ሁለት አሰልጣኞችን በመላክ ለ32 ሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል አድርጓል።የአርሰናል እግርኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሃላፊ የሆነው ሳይመን ማክማነስ እና ካርለን ኤድጋር ስልጠናው የሰጡ እንግሊዛዊያን ናቸው፡፡ በሁለት ቀናት ስልጠና ሰልጣኞች የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ትምህርቶችን እንዲቀስሙ መደረጉን የዳሽን ቢራ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዴቭሊን ሄንስወርዝ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልፀዋል፡፡ የተግባር ትምህርቱ ሲኤምሲ አከባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የልምምድ ሜዳ ተደርጓል፡፡ ዳሽን እንደዚህ ዓይነት ያሉ ስልጠናዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የዳሽን ቢራ የገበያ ዋና ሃላፊ ሪታ ፀሃይ ተናግራለች፡፡ስልጠናው ከሰጡት አሰልጣኞች መካከል አንዱ የሆነው ካርለን ኤድጋር ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጠው አስተያየት የታዳጊዎች ስልጠና አራት መሰረታዊ ነገሮችን መያዙን ተናግሯል፡፡ “የአፍሪካ አሰልጣኞችን ተመልክተን ጥሩ አቅም እንዳለ ተመልክተናል በእድገት ደረጃ፡፡ እዚህ ላይ የምንመለከተው አንድ ታዳጊ ተጫዋች በታክቲክ፣ ቴክኒክ፣ በተክለ ሰውነት፣ በአዕምሮ እና ማህበራዊ በሆኑ ነገሮች ላይ ማሳደግ ነው፡፡ በታዳጊ ስልጠና ላይ የተሰማሩ ሰዎችን የምናበረታታው እኒህን ነገሮች እንዲሰሩ ነው፡፡ ይህ የታዳጊ አሰለጣጠን ዘዴ በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኙ የእግርኳስ ትምህርት ቤቶች የሚሰጥ በመሆኑ ተመሳሳይ ነው፡፡”አሰልጣኝ ኤድጋር ሲቀጥል የአፍሪካ እና አውሮፓ እግርኳስ መለያየቱ የታወቀ ቢሆንም በታዳጊ ስልጠና ላይ ተመሳሳይ እንደሆነ አስረድቷል፡፡ “ይህ ስልጠና ለእግርኳስ ነው የተዘጋጀው፡፡ የሁሉም እግርኳስ የየራሱ የሆነ ባህል በውስጡ ይኖረዋል፡፡ ይህ ተፈጥሯዊ ነው፡፡ መሰረታዊ በሚባሉ ጉዳዮች ላይ  እና በታዳጊ እግርኳስ ላይ ግን ቅድም የጠቀስኳቸው አራት ነገሮች ተመሳስለው ይታያሉ፡፡”በስልጠናው ላይ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ቡድኖች፣ ከእግርኳስ ፌድሬሽን፣ ከክልል ስፖርት ኮሚሽኖች እና ከግል የታዳጊዎች እግርኳስ ፕሮጀክት የተወጣጡ አሰልጣኞች ተሳትፈዋል፡፡ በስልጠናው ማጠናቀቂ ላይ በበሻሌ ሆቴል የስልጠናው ተሳታፊዎች የምስክር ወረቀት ከዋና ስራ አስፈፃሚው ሄንስወርዝ እጅ ተቀብለዋል፡፡", "passage_id": "5f80de425d563b5b270c8007a24d911f" }, { "passage": "የስፔኖቹ ሶክስና የእግርኳስ ማዕከል እና ኢ ፎር ኢ የኢንቨስትመን አማካሪ ድርጅት ከኢትዮጵያው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ያስገነባውን የይድነቃቸው ተሰማ የእግርኳስ አካዳሚን ለማስተዳደር የአምስት አመት ውል ሐሙስ መፈፀማቸው ይታወሳል፡፡ የሶክስና ምክትል ፕሬዝደንት ዴቪድ ሎፔዝ እና የኢ ፎር ኢ ማኔጂንግ ፓርትነር ሁሊዮ ፓዞ ስለውል እና ተያያዥ ጉዳች ላይ ለጋዜጠኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ስለውሉ አጠቃላይ ሁኔታዴቪድ ሎፔዝ፡ የተፈራረምነው የአምስት ዓመት ውል ሲሆን ከህዳር 1 (በፈረንጆቹ) ጀምሮ ነው ተፈፃሚ የሚሆነው፡፡ አምስት አሰልጣኞች ለአካዳሚው ስልጠና ወደ አዲስ አበባ የምናስመጣ ይሆናል፡፡ በመጀመሪያ በሁለት የእድሜ እርከኖች ከፍለን 50 ታዳጊዎችን የምናሰለጥን ይሆናል፡፡ ከአምስቱ አሰልጣኞች ሁለቱ የቡድኖቹን ስልጠና ሃላፊነት የሚወስዱ ሲሆኑ አንድ የአካል ብቃት አሰልጣኝ እንዲሁም አንድ መልማይ ይኖረናል፡፡ አምስተኛው አሰልጣኝ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ነው የሚሆነው፡፡በመጀመሪያ ደረጃ የምናደርገው እምቅ ችሎታ ያላቸውን ተጫዋቾች የመመልመል ስራ ነው፡፡ በአጠቃላይ የቅዱስ ጊዮርጊስ የወጣቶች አካዳሚ አወቃቀር ከስፔን ፕሮፌሽናል አንደኛ ዲዚቪዮን ክለቦች ጋር ተመሳሳይ ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያዊያን አሰልጣኞች በምክትል አሰልጣኝነት በአካዳሚው የሚያገለግሉም ይሆናል፡፡ሊሰራ ስለታቀደው የጨዋታ ስልት እና አሰለጣጠንሁሉም ወደ አዲስ ስፍራ ስትጓዝ ማድረግ ያለብህ በቦታው ስላለው ነባራዊ ሁኔታ ማጥናት ነው፡፡ ስፔናዊያን ስለሆንን ሁሉንም ነገር እንቀይራለን ማለት አይደለም፡፡ እዚህ ያለውን ነገር መመልከት እና ማጥናት ይገባናል፡፡ ስለተጫዋቾች ባህሪ ካወቅን በኃላ የትኛው ስልት እና አሰለጣጠን ዘዴ አዋጪ እንደሆነ የምንወስን ይሆናል፡፡ሁሊዮ ፓዞ፡ እውነት ለመናገር ስምንጠቀመው የአሰለጣጠን ዘዴ፣ እንዴት አንድን ታዳጊ ብቁ እንደምናሳድግ ገና በጥናት ላይ ነን፡፡ ነገርግን ይህ ሲጠናቀቅ ታዳጊዎቹ በጥሩ ስልጠና ብቁ የሚሆኑበትን ነገር ይመቻቻል፡፡ ይህ ደግሞ የሶክስና ስኬት ዋናው ሚስጥር ነው፡፡ ሶክስና በስፔን ያለውን የእግርኳስ ስርዓት መለወጥ የቻለ እና ለውጡም ስኬታማ መሆኑ የታየ ነው፡፡ በተለያዩ ሃገራትም ጥሩ ልምዶች አሉት፡፡ በቻይና እና ካዛኪስታን ጥሩ ልምዶችን ማካበት ችሏል አሁን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል፡፡ በአፍሪካ ውስጥ ሶክስና ሲሰራ ይህ ለመጀመሪያ ግዜ ነው እናም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የችሎታ ደረጃ በጥሩ እና ሳይንሳዊ ስልጠና መልካም ውጤት እንድናመጣ ያስችለናል፡፡ እዚህ አሰልጣኞችን ማምጣት ብቻ ሳይሆን የእግርኳስ ልማት ትምህርትንም ሃገሪቱ እንደሚጠቅም አድርጎ ማቅረብ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ እግርኳስ በግንባር ቀደምትነት መጠቀስ ያለባት ሃገር ነች ነገር ግን አሁን ባለው ደረጃ ፕሬዝደንት አብነትም እንዳስረዱን ኢትዮጵያ በታዳጊዎች ስልጠና ላይ ያልተሳካ ስርዓትን የገነባች ሃገር መሆኗን ነው፡፡ስለእድሜ እርከንአሁን ላይ መቶ በመቶ ውስኔ ላይ አልተደረሰም፡፡ ነገር ግን በመጀመሪያ በእድሜ ያነሱ ተጫዋቾች አይኖሩንም፡፡ ምንአልባት ከ15 ዓመት ጀምሮ ነው ስልጠናው የሚሰጠው፡፡ ሃሳባችን ተጨማሪ አሰልጣኞች አመጥቶ ከ15 ዓመት በታች ያሉ ታዳጊዎችንም ማሰልጠን ነው የቀጣይ አመት እቅዳችን፡፡ እድሜ እየጨመሩ በመጡ ቁጥር ታዳጊዎችን ማሰልጠን በዛው ልክ እየከበደ ነው የሚመጣው፡፡ከአምስት አመት በኃላ ስለሚኖረው የክለቡ እና ተቋማቱ ግንኙነትከአምስት ዓመት በኃላ ከፕሬዝደንት ጋር አብነት ለተጨማሪ አመታት ውል እንደምንፈራረም ተስፋ አለኝ፡፡ እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ እግርኳስ ቀጣይ ህልውና በኢትዮጵያዊያን አሰልጣኞች እጅ ነው የሚኖረው፡፡ በተፈጥሮ ይህ ነው ሊሆን የሚገባው፡፡ ከአምስት ዓመት በኃላ ልንረዳ የምንችለው ጉዳይ ካለ እዚሁ ለመስራት እንፈልጋለን፡፡ ምን አልባት ትብብራችን እንዳሁኑ ሳይሆን የተለየ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን አሁን ላይ እኛ ትኩረታችን በአምስት አመቱ ላይ ነው፡፡ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት የመስፋፋት እቅድከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ጋር ለመስራት እቅድ ይዘን እየተንቀሳቀስ ነው ያለነው፡፡ ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካ፡፡ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ደቡብ አፍሪካ አቅንተን በትብብር ለመስራት ውይይቶችን የምናደርግ ይሆናል፡፡ እዘህ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ካደረግነው የትብብር ስምምነት የሚለይ ሲሆን ትብብራችን ከደቡብ አፍሪካ መንግስት ጋር ነው የሚሆነው ቢሆንም ቅዱስ ጊዮርጊስ እኛ ወደ አፍሪካ ስራችንን ለመጀመሪያ ግዜ ያስፋፋንበት ክለብ ስለሆነ በልባችን የተለየ ቦታ አለው፡፡", "passage_id": "2faa0e007c609e759887e2d08507d8ee" }, { "passage": "ለሦስት ተከታታይ ቀናት ኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከጀርመኑ ባየር ሙኒክ ጋር በመተባበር ለፕሪምየር ሊግ አሰልጣኞች ያዘጋጀው ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል።የፌዴሬሽኑ ቴክኒክ ኮሚቴ ባዘጋጀውና 20 የሚሆኑ የሴት እና የወንድ የፕሪምየር ሊግ አሰልጣኞች በተካፈሉበት በዚህ ሥልጠና ለሦስት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ስታዲየም በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር ሲሰጥ ቆይቶ ዛሬ ተጠናቋል። ይህ ስልጠና በቀጣይ ጊዜያትም እንደሚቀጥል ሰምተናል።ስልጠናውን ከተካፈሉት መካከል የስልጠናውን ጠቀሜታ አስመልክቶ የሁለት አሰልጣኞችን ሀሳብ አካተናል።“እግርኳሰ በአንድ ቀን የስልጠና ፕሮግራም የሚስተካከል ሳይሆን በእቅድ መሰራት እንዳለብን ጥሩ ጠቀሜታ ያገኘንበት ሥልጠና ነው” ፀጋዬ ኪ/ማርያም(ሀዲያ ሆሳዕና)\n“እንደሚታወቀው ባየር ሙኒክ የ120 ዓመት ታሪክ ያለው አንጋፋ፣ ትልቅ እና ከፍተኛ ልምድ ያለው ክለብ ነው። እግርኳሱንም ወደ ሳይንስ በመቀየር ስኬታማ እየሆኑ መጥተዋል። ዓላማቸው ኢትዮጵያ ውስጥ አካዳሚ መክፈት እንደሆነ ይታወቃል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የአሰለጣጠን እቅድ አወጣጥ ለምሳሌ በውድድር ጊዜ የዕለት፣ የሳምንት፣ የወር አወጣጥ እና በእረፍት ወቅት አንድ ፕሮፌሽናል ክለብ ሊከተው የሚገባው የእቅድ አወጣጥ ጥሩ ትምህርት ሰጥተውናል። በሦስት ቀን ሁሉ ነገር ይጠናቀቃል ማለት ባይቻልም አንድ ቡድን የያዘውን የአጨዋወት ፍልስፍና ከተጋጣሚ ቡድን ጋር ሲጫወት ፍልስፍናውን ሳይለቅ እንዴት መቅረብ እንዳለበት። ከታች ጀምሮ በምን መልኩ መስራት እንደሚገባን በተጨማሪም ከተግባር በላይ በፕላን ላይ ብዙ ማተኮር እንደሚገባን ጥሩ ልምድ ያገኘንበት። እግርኳሰ በአንድ ቀን የስልጠና ፕሮግራም የሚስተካከል ሳይሆን በፕላን መሰራት እንዳለብን ጥሩ ጠቀሜታ ያገኘንበት ሥልጠና ነው”።“በጨዋታ ወቅት በከፍተኛ ውጥረት እና በዝቅተኛ ውጥረት ወቅት እንዴት መጫወት እንዳለብን ተምረናል” ፍሬው ኃ/ገብርኤል (የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ)\n” በሥልጠናው ሦስት ነገር አግኝቼበታለው፤ በመጀመርያ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና ጠቀሜታው ትናንት የተማርከውን ነገር አሁንም ደግመህ የምታስታውስበት፣ አዳዲስ ነገሮች የምትማርበት ትምህርት ነው። በሁለተኛ ደረጃ የባየር ሙኒክ ክለብ ይዞልን የመጣው አዲስ ነገር ኳስን ተቆጣጥሮ መጫወት (ጎል ለማስቆጠር ክፍት ሜዳ ፍለጋ) ብዙ አይነት ቢሆንም ለታክቲክ ዲሲፕሊን እንዴት ተገዢ መሆን እንዳለብህ። የእኛ ሀገር ተጫዋቾች ጎል ለማስቆጠር ቦታ አጠቃቀም (ተቀባይ እና አቀባይ) ላይ የአቅም ውስንነት ያለ በመሆኑ ሦስተኛ ወገኖች እንዴት እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለባቸው፣ በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ በጨዋታ ወቅት በከፍተኛው ጥረት እና በዝቅተኛ ውጥረት ወቅት እንዴት መጫወት እንዳለብን ተምረናል። ከዚህ በተጨማሪ ስልጠናውን የተከታተልን አሰልጣኞች የሀሳብ ልውውጥ ያደረግንበት ጥሩ ስልጠና ነበር። ”በተያያዘ ዜና ባየር ሙኒክ በዓመቱ የሚያዘጋጀውና የተለያዩ ሀገራት የሚሳተፉበት የታዳጊዎች ውድድር ላይ ኢትዮጵያ እንደምትሳተፍ ተገልጿል። ከ16 ዓመት በታች ዕድሜ ላይ በሚገኙ ታዳጊዎች መካከል በሚደረገው በዚህ ውድድር ላይ ለሚካፈለው ቡድን የሚሆኑ ተጫዋቾችን ለመምረጥ የሚከናወኑ ጨዋታዎች የካቲት 19 እና 20 በአዲስ አበበ ስታዲየም የሚደረጉ ይሆናል።", "passage_id": "26a636e58e821031b8f160aed61387b2" }, { "passage": " የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ከኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ እና ከኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቲኒስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ከጥቅምት 9 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀን የሚቆይ የጠረጴዛ ቴኒስ የደረጃ አንድ የአሠልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። ይህ ስልጠና በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጥ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የኮሚኒኬሽን ክፍል ያደረሰን መረጃ ያመለክታል። በስልጠናው ላይ ከዘጠኝ ክልሎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 40 አሠልጣኞች እየተሳተፉ የሚገኙ ሲሆን፤ ቱኒዚያዊው የዓለም አቀፉ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን የአፍሪካ ልማት ማናጀር ሚስተር ራምዚ ማብሩክ ስልጠናውን እየሰጡ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ተክለወይኒ አሰፋ ስልጠናውን በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን ‹‹ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ስራዎች መካከል ለዘርፉ ተዋንያን ሁለገብ እና ወቅታዊ የሆነ የአቅም ግንባታ ስራ መስራት አንዱና ቁልፍ ተግባሩ ነው›› ብለዋል። ስለሆነም ኮሚቴው የሚመራበትን ስትራቴጂክ እቅድ ማዕከል አድርጎ ለሚመለከታቸው የአገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት ባለሙያዎች ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊና ሳይንሳዊ የስፖርት ስልጠናዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በማመቻቸት እየሰጠ እንደሚገኝ አብራርተዋል። የእንደዚህ አይነት ስልጠናዎች ፋይዳም አገራችን በምትሳተፍባቸው አገር አቀፍ፣ አህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ትልቅ አቅም በመፍጠር ወደ ውጤታማነት ጎዳና ለመጓዝ መደላድል እንደሚፈጥር አቶ ተክለወይኒ አብራር ተዋል። አቶ ተክለወይኒ አክለውም፣ ሰልጣኞች ለሰባት ቀናት ስልጠናውን ከሚሰጡት አሰልጣኝ አቅም አሟጦ በመጠቀም በዘርፉ ያለውን እውቀትና ክህሎት በማጎልበት ለአገራችን ስፖርት ዕድገት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳ ንት አቶ ተስፋዬ ብዛኒ በበኩላቸው፣ ሰልጣኞች ስልጠናውን በጥሞና በመከታተልና አቅምን በማሳደግ የጠረጴዛ ቴኒስ ስፖርትን በአገር አቀፍ ደረጃ በማስፋፋት፣ በአህጉርና ዓለም አቀፍ ደረጃ አገር የሚያስጠሩ ስፖርተኞችን ለማፍራት በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 13/2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "688d2b07043f695eb4efe5e94b4f18d7" } ]
c2d4d82ca3f59d97647be48f7b9523f9
8e2a666e20fe37bfd69acf094aab1b0d
የጥፋት ስትራቴጂስቱና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሃት ነጋ በቁጥጥር ስር ዋለ
ራስወርቅ ሙሉጌታአዲስ አበባ፦ የጥፋት ስትራቴጂስቱና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሃት ነጋን ጨምሮ ሌሎች የጥፋት ቡድኑ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ። የመከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ትናንት እንዳስታወቁት፣ በአገራችን ላለፉት 27 ዓመታት የማተራመስ ስትራቴጂ የነደፈ ያስተባበረና ያደራጀ በመጨረሻም ጦርነት እንዲቀሰቀስ በማድረግ በሀገራችን ሰራዊት ላይ እጅግ ዘግናኝ ጦርነት በመክፈት ሰራዊቱን ያስጨፈጨፈው የጁንታው ቁንጮ፣ ስብሃት ነጋ በቁጥጥር ስር ውሏል።ለሰው ልጅ እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ሰርጥ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን የገለጹት ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ፣ የጥፋት ቡድኑ አባላት በሰርጡ ውስጥ ተሸክመው በማስገባት ደብቀውት እንደነበርም አመልክተዋል። ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ አካላት በጋራ ባደረጉት ፍተሻና አሰሳ፣ ከተደበቀበት በማውጣት በቁጥጥር ስር እንዳዋሉትም ጠቁመዋል። ከመከላከያ የከዱ ሌሎች ከሃዲ የጁንታው አባላት ከስብሃት ነጋ ጋር አብረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጠቆሙት ኃላፊው፣ አባላቱ ከመከላከያ በመክዳት የጁንታውን ታጣቂ ኃይል በማዋጋትና በማሰልጠን እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈፀም ሲሰሩ እንደነበር አስታውቀዋል። የጁንታውን አመራር ዙሪያ ጥበቃ ሲያስተባብሩ ቆይተው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ገልፀዋል። ጁንታውን ለመያዝ በተካሄደው ኦፕሬሽን የጁንታውን አመራሮች ለመከላከል በአካባቢው ጥበቃ ላይ የነበረ ታጣቂ ኃይል መደምሰሱን አስታውቀዋል።እንደ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ መግለጫ፤1. የጁንታው ቁንጮ አመራርና የጥፋት ስትራቴጂስት፣ ስብሃት ነጋ 2. ሌተናል ኮሎኔል ፀአዱ ሪች- የስብሃት ነጋ ባለቤትና ቀደም ሲል በጦር ኃይሎች ሆስፒተል ሃኪም የነበረች፣ በኋላም በጡረታ የተገለለች 3. ኮሎኔል ክንፈ ታደሰ- ከመከላከያ የከዳ 4. ኮሎኔል የማነ ካህሳይ- ከመከላከያ የከዳ 5. አስገደ ገ/ ክርስቶስ -ከመሃል ሀገር ተጉዞ ቡድኑን የተቀላቀለና ለጊዜው ኃላፊነቱ ያልታወቀ 6. አምደማርያም ተሰማ ተወልደ፣ የክልሉ የቅሬታ ሰሚ ፅ/ቤት ኃላፊ የነበረ፤7. ኮማንደር በርሄ ግርማ፣ የክልሉ ልዩ ኃይል ሎጀስቲክ ኃላፊ የነበረ በቁጥጥር ስር ውለዋል።ከተደመሰሱትና ከተያዙት በተጨማሪ የሜጀር ጀነራል ሃየሎም አርአያ ባለቤት የነበረችና ኑሮዋን በአሜሪካ አድርጋ የቆየች በኋላም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ወደ ጁንታው ተቀላቅላ የነበረች፣ ወይዘሮ አልጋነሽ መለስ ጁንታውን በመያዝ ኦፕሬሽን ሂደት ውስጥ ለማምለጥ ስትሞክር ገደል ገብታ ሕይወቷ ማለፉን ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ገልፀዋል።በተመሳሳይ ዜና አራት የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች ከነአጃቢዎቻቸው መደምሰሳቸን፤ ዘጠኝ የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የመከላከያ ኃይል ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ከትናንት በስቲያ ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡በዚህም መሰረት፣1. የጁንታው ቃል አቀባይ ሴኩቱሬ ጌታቸው፣ የሰሜን ዕዝን በ45 ደቂቃ ውስጥ መብረቃዊ ጥቃት በመፈጸም ከጥቅም ውጪ አድርገነዋል ሲል በትግራይ ቴሌቪዥን የተናገረ ፤2. ዘርአይ አስገዶም የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሥራ አስኪያጅና የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበረ፤3. አበበ አስገዶም የድምጸ ወያኔ ኃላፊ የነበረ፤4. ዳንኤል አሰፋ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ የነበረ ከሹፌሮቻቸውና ከጥበቃዎቻቸው ጋር በጀግናው የመከላከያ ሰራዊት፣ በፌዴራል የጸጥታ ተቋማትና በትግራይ ሕዝብና በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በተደረገ የተቀናጀ ዘመቻ መደምሰሳቸውን ብርጋዴል ጀኔራል ተስፋዬ አስታውቀዋል።ከተደመሰሱት በተጨማሪም 9 የጁንታው ቁልፍ አባላት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን እነሱም፣1. ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ የቀድሞ የክልሉ አፈጉባኤ የነበረች፣2. ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ የቀድሞ የትግራይ ክልል ከተማ ልማት ቢሮኃላፊና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ የነበረ፣3. አቶ ተክለወይኒ አሰፋ የማረት ሥራ አስፈጻሚ የነበረ፣4. አቶ ገብረመድህን ተወልደ የክልሉ ንግድ ቢሮ ኃላፊ የነበረ፣5. አቶ ወልደጊዮርጊስ ደስታ የክልሉ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ የነበረ፣6. አምባሳደር አባዲ ዘሙ በሱዳን የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር የነበረና የጁንታውን ፖለቲካ ክንፍ የተቀላቀለ፣7. አቶ ቴዎድሮስ ሃጎስ የመለስ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንትና የኢፈርት ቦርድ ኃላፊ የነበረ፣8. ወይዘሮ ምህረት ተክላይ የክልሉ ምክር ቤት ሕግ አማካሪ የነበረች እንዲሁም9. አቶ ብርሃነ አደም መሃመድ የክልሉ የንብረትና ግዢ ሥራ ሂደት ኃላፊ የነበረ ነው። የህወሓት ጁንታ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር የዋሉት በጫካና ዋሻ ለዋሻ ሲንቀሳቀሱ በተደረገ ጠንካራ አሰሳ መሆኑን የገለጹት ብርጋዴር ጀኔራሉ፣ የአገር መከላከያ ሰራዊት እነዚህ የጁንታው ቁልፍ የጥፋት ቡድን አባላት እንዲደመሰሱና በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ያላሰለሰ ድጋፍ ላደረገው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ምስጋናውን አቅርቧል። ሰራዊቱ ወንጀለኞቹን አድኖ ለመያዝ ቃል በገባው መሰረት ግዳጁን እየተወጣ መሆኑን አመልክተው፣ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት የጀመረውን ቀሪ የጁንታውን ርዝራዦችን አድኖ ለመያዝና በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። ሕዝቡ እያደረገ ያለውን ድጋፍና ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=39156
[ { "passage": "አቶ ያሬድ ዘሪሁን\n\nአቶ ያሬድ ዘሪሁን ትናንት ሌሊት 5 ሰዓት ላይ በዱከም ከተማ ኮኬት ተብሎ በሚጠራው ሆቴል ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተዘግቦ ነበር።\n\nተጠርጣሪው አቶ ያሬድ በዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበዋል።\n\nሰሞኑን በሙስናና በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ከ60 የሚበልጡ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።\n\nየኢትዮጵያ ብሄራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት ምክትል ሃላፊ የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ብርሃኑ ፀጋዬ በትዊተር ገፃቸው ላይ አረጋግጠዋል።\n\nኢቢሲ እንደዘገበው አቶ ያሬድ ዘሪሁን በቁጥጥር ስር የዋሉት ትናንት ህዳር 5 ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ ወደ ኬንያ ለመሸሽ ሲሞክሩ በፌደራል ፖሊስና በኦሮሚያ ፖሊስ ክትትል ዱከም ከተማ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡\n\nበወቅቱም 22ሺህ ብር ፣ ሁለት መታወቂያ እና መንጃ ፈቃድ ይዘው መገኘታቸውን ዘገባው ጨምሮ ገልጿል። \n\nአቶ ያሬድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ተሾመው የነበረ ቢሆንም በአጭር ጊዜ ማለትም ከአንድ ወር በኋላ በጤና እክል ምክንያት በአቶ ዘይኑ ጀማል መተካታቸው የሚታወስ ነው።\n\nአቶ ያሬድ ወደ ፌደራል ፖሊስ ከመሄዳቸው በፊት ለረጅም ጊዜ በደህንነት ተቋሙ በምክትል ሃላፊነት ያገለገሉ ሲሆን የቀድሞ የተቋሙ ዋና ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋም ቀኝ እጅ እንደነበሩ ይነገራል።\n\n• ሜጀር ጄኔራል ክንፈ፡ ‘‘ደሞዜ አነስተኛ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ጠበቃ እንዲያቆምልኝ እጠይቃለሁ’’ \n\nተጠርጣሪውን አቶ ያሬድ ለማስመለጥ ሞክረዋል የተባሉት የነፍስ አባታቸውና ሾፌራቸው ትናንት በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበው ነበር።\n\nየፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ማክሰኞ ሕዳር 3 ቀን 2011 ዓ. ከስልሳ በላይ በሚሆኑ ተጠርጣሪዎች ላይ ከሰብዓዊ መብት ጥሰትና ከሙስና ጋር በተያያዘ የተሰሩ ወንጀሎችን በተመለከተ ያደረገውን ምርመራ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።\n\n ", "passage_id": "7b37dace164ecc381b3aa0274d00b74a" }, { "passage": "አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት ከህወሃት የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው በጋምቤላ ክልል ብሄር ብሄረሰቦችን ለማጋጨት አሲረው ሲንቀሳቀሱ ነበር በሚል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ።ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ፥ ጸጋዬ መብርሃቱ (ካህሳይ)፣ ገብረማሪያም አናንያ፣ ዋስትና ተሾመ (ጃል ሴና)፣ አብርሃም መሃሪ፣ ኮሎኔል ተስፋዬ (ባሌስትራ) እና ሌሎች 19 የህወሃትና የኦነግ ሸኔ የጥፋት ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።በክልሉ ብሄር ብሄረሰቦችን በማጋጨት አካባቢውን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ አሲረውት የነበረው ሴራ ከሽፎ ግለሰቦቹም በቁጥጥር ስር ውለዋልም ነው ያለው።በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ተፈጽሞ የነበረ ተመሳሳይ ጥፋት በዚያው በክልሉ ውስጥ በአሶሳና ካማሼ ዞኖች ብሔር ብሄረሰቦችን በማጋጨት አካበቢውን የትርምስ ቀጠና በማድረግ እልቂት ለመፈጸም የህወሃት የጥፋት ቡድን አባል ከሆነው አባይ ጸሃዬ ተልዕኮ ወስደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ዮሃንስ ግርማይና ርዕሶም ግርማይ የተባሉ ግለሰቦች ከሌሎች 20 ግብረ አበሮቻቸው ጋር በቁጥር ስር መዋላቸውንም ገልጿል።በጋምቤላና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች እነዚህን የጥፋት ሃይሎች በቁጥጥር ስር ለማዋልና ሴራቸውን ለማክሸፍ በተካሄደ ዘመቻም የብሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም የየክልሎቹ የጸጥታ አካላት በቅንጅት መሳተፋቸው ተገልጿል።በሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ ጥፋት ለመፈጸም ተልዕኮ ወስደው ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የጥፋት ሃይሎች ላይ ጥብቅ ክትትል እየተደረገ ነው ብሏል።አጠቃላይ የጥፋት ሴራውን በማክሸፍ ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተም በተከታታይ መረጃዎችን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል።", "passage_id": "ef33ff5fff7f1007f5ee316dc1ae3520" }, { "passage": "የስኳር ኮርፖሬሽን የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኪሮስ ደስታ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር ውለዋል። ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በኮርፖሬሽኑ የቤቶችና የመስኖ ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ መሆናቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።አቶ ኪሮስ ደስታ ከሃላፊነታቸው ከተነሱም ገና ዓመት ያልሞላቸው መሆኑም ተመልክቷል።በተያያዘ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣንን ለረጅም ዓመታት በዋና ዳይሬክተርነት የመሩት አቶ ዛይድ ወልደገብርኤል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።በተመሳሳይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያለመከሰስ መብታቸውን ያነሳው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዓለማየሁ ጉጆ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር ውለዋል።በዚህም መንግስት በሙስና ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ ነጋዴዎች እና ደላሎች ቁጥር የዛሬዎቹን ጨምሮ 51 ደርሷል-(ኤፍ.ቢ.ሲ)። ", "passage_id": "0086865a08df39358ad6513c333695d1" }, { "passage": "በሰራዊቱ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ያደረጉ ከመከላከያ የከዱ የጁንታው አመራሮች እርምጃ ተወሰደባቸው አገርን ለመበታተን አቅደው በመከላከያ ሠራዊት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ያደረጉ አሸባሪዎችና ዋነኛ የጁንታው አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ።ከአገር መከላከያ ሠራዊቱን በማስከዳት ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩና በጦርነቱ ከሠራዊቱ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ መኮንኖች፣ መስመራዊ መኮንኖችና የግል ጥበቃዎቻቸው ላይ እርምጃ መወሰዱንም የመከላከያ ሠራዊት ሃይል ስምሪት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዴል ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ገልጸዋል።ብርጋዴል ጄኔራሉ ጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ጥምር ሃይል የፍተሻ ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉንም ተገልጿል።ብርጋዴል ጄኔራል ተስፋዬ እንደገለፁት የቀድምው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሰባት የጁንታው ሲቪል አመራሮች እንዲሁም ከመከላከያ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ አመራሮችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።በዚሁ መሰረት እርምጃ የተወሰደባቸው፡-1ኛ- ሜጀር ጄኔራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል፡- ቀደም ሲል የመከላከያ ሎጂስቲክ ሃላፊ የነበረና አሁን የጁንታው ሎጂስቲክ ሃላፊ የነበረ2ኛ- ብርጋዴል ጄኔራል ገብረኪዳን ገብረማርያም፡- የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ሃላፊ የነበረና በጡረታ ከተሰናበተ በኋላ ጁንታውን የተቀላቀለ3ኛ- አስር ከፍተኛ መኮንኖች4ኛ – ሁለት መስመራዊ መኮንኖች5ኛ- አንድ የክልሉ ረዳት ኮሚሽነር የነበረና ከፖሊስ ከድቶ ወደ ጁንታው የተቀላቀለ ናቸው።በተጨማሪም የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩ የጁንታው አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብርጋዴል ጄኔራሉ ገልፀዋል።እነዚህም፦1ኛ- አቶ አባይ ወልዱ፡- የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበረ2ኛ- ዶክተር አብርሃም ተከስተ- የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበረ3ኛ- ዶክተር ረዳኢ በርሄ፡- የክልሉ ኦዲተር ሃላፊ የነበረ4ኛ ዶክተር ሙሉጌታ ይርጋ፡- የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊ የነበረ5ኛ- አቶ ዕቁባይ በርሄ- የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሃላፊ የነበረ6ኛ- አቶ ጌታቸው ተፈሪ፡- የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትና የሠላምና ደህንነት ሃላፊ የነበረ7ኛ- ወይዘሮ ኪሮስ ሃጎስ፡- የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የነበረች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።በተጨማሪም ሁለት ከመከላከያ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን እነሱም ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር አምባዬና ኮሎኔል ትርፏ አሰፋ መሆናቸውን ብርጋዴል ጄኔራሉ  ለኢዜአ ገልፀዋል።", "passage_id": "3e3c70acb5168972829c66485315a226" }, { "passage": "ትግራይ፡ አቶ ስብሐት ነጋና ሌሎችም በመከላከያ ሠራዊት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ\\nስብሐት ነጋ (ፎቶ ከፋይል)\n\nየህወሓት መስራች ከሆኑት ሰባት ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ስብሐት ነጋ ተደብቀውበት ነበር በተባለው ቦታ ላይ ሠራዊቱ ባካሄደው ዘመቻ ከሌሎች ተፈላጊ ሰዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የመከላከያ ሠራዊት የስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዲየር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ገልጸዋል።\n\nኃላፊው ጨምረው እንደገለጹት አቶ ስብሐት ነጋ ለመንቀሳቀስ እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ስፍራ ውስጥ ተደብቀው ቆይተው በሠራዊቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አመልክተዋል። \n\nየመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸው የሚፈለጉትን ከፍተኛ የህወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮችን ለመያዝ የመከላከያ ሠራዊቱና የፌዴራል የፀጥታ አካላት በጋራ ባደረጉት ፍተሻና አሰሳ አቶ ስብሐትና ሌሎች ተፈላጊዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉና ሌሎች ደግሞ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ብርጋዲየር ጀነራል ተስፋዬ ገልጸዋል።\n\nበዚህም ከአቶ ስብሐት በተጨማሪ የቀድሞ የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት አባላት የነበሩና የከዱ ሌሎች የህወሓት ወታደራዊ መኮንኖችም በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል። \n\nበቁጥጥር ስር የዋሉት ወታደራዊ መኮንኖች የቡድኑን ኃይል በማሰልጠንና በማዋጋት ሚና የነበራቸው መሆኑን ጠቁመው፤ በመጨረሻም የአመራር ጥበቃ ሲያስተባብሩ ቆይተው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከፍተኛ ኃላፊው ገልጸዋል።\n\nበቁጥጥር ስር መዋላቸው ከተገለጹት ከአቶ ስብሐት ነጋ በተጨማሪ ባለቤታቸው ሌተናል ኮሎኔል ፀአዱ ሪች፣ ኮሎኔል ክንፈ ታደሰ፣ ኮሎኔል የማነ ካህሳይ የተባሉ የቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የነበሩ ናቸው ተብሏል። \n\nከተጠቀሱት በተጨማሪ ሎችም ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ከዚህ ባሻገር ደግሞ በዙሪያቸው የነበረ ታጣቂ ኃይል ላይ እርምጃ እንደተወሰደበት ብርጋዲየር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ገልፀዋል።\n\nሐሙስ ዕለት መከላከያ ሠራዊቱ በሕግ ከሚፈለጉ ከፍተኛ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል አራቱ መገደላቸውንና ዘጠኙ ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ማሳወቁ ይታወሳል። \n\nከእነዚህም የህወሓት አመራሮች መካከል የአቶ ስብሐት ነጋ እህት የሆኑትና የቀድሞ የትግራይ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ ይገኙበታል። \n\nበእርምጃው ከተገደሉት መካከል አቶ ሴኩቱሬ ጌታቸው፣ የህወሓት ቀደምት ታጋይና የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘርዓይ አስገዶም፣ የህወሓት የመገናኛ ብዙሃን ተቋም የሆነው ድምጺ ወያኔ ኃላፊ አቶ አበበ ገብረመድኅን፣ የትግራይ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳንኤል አሰፋ ከተገደሉት ከፍተኛ አመራሮች መካከል እንደሆኑ ተገልጿል።\n\nከተገደሉት አራት ሰዎች ባሻገር ሌሎች ዘጠኝ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጀነራሉ ተናግረዋል።\n\nቀደም ሲል የተያዙ \n\nባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይም በተመሳሳይ የጸጥታ ኃይሉ ባደረገው አሰሳ የተገደሉና በቁጥጥር ስር የዋሉ የህወሓት ወታደራዊ መኮንኖችና ሲቪል አመራሮች የስም ዝርዝር ይፋ መደረጉ ይታወሳል።\n\nእስካሁን ድረስ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤልም ሆኑ ሌሎች ከፍተኛ ሹማምንቶች ያሉበት ሁኔታ በዚህ መግለጫ ላይ አልተጠቀሰም።\n\nከጥቂት ሳምንት በፊት የመከላከያ ሠራዊቱ ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች ያሉበትን ለጠቆመ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት ማዘጋጀቱን መግለጹ ይታወሳል።\n\nበዚህ መግለጫ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ዓርብ ታኅሳስ 23 ቀን 2013 ዓ. ም. በሰጠው መግለጫ፤ የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ ሙሉ ገብረእግዚአብሔርና በርካታ ወታደራዊ መኮንኖች መማረካቸውን እንዲሁም በርካቶች መደምሰሳቸውን አስታወቆ ነበር።\n\nመንግሥት በቁጥጥር ስር ውለዋል...", "passage_id": "1666f0f4d9bb5ebd2b5b1a1ed3fd32ad" } ]
2022e41b2194c76f05b4f9bdf8f5c33b
12db259907fb260bf60b4983c23a53fe
የላቁ ስፖርተኞችና ብቃት ያላቸው የስፖርት ባለሙያዎችን ለማፍራት
በስፖርት ማሰልጠን፣ መምራትና ማስተባበር ተሳታፊ የሆኑ ባለሙያዎች ለስፖርት እድገትና ውጤታማነት ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚጫወቱ እሙን ነው። በዚህ ምክንያትም ሀገር አቀፉ የስፖርት ሪፎርም ፍኖተ ካርታ እንደ ግብ ከያዛቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል አንዱ ባለሙያዎችን በብዛትና በጥራት ማፍራት ነው። የማዕከላዊው ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በ2004 ዓ.ም ባወጣው መረጃ መሠረት በወቅቱ 2ሺ376 ዳኞችና 2ሺ476 አሰልጣኞች እንደነበሩ ያመላክታል። ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት ደግሞ በተለያዩ የስፖርት ሙያ ዘርፎች 30ሺ560 ባለሙያዎችን በአጭር፤ 2ሺ388 ባለሙያዎችን ደግሞ በረጅም ጊዜ ሥልጠና ለማፍራት መቻሉ በፍኖተ ካርታው ሰፍሯል። ይሁን እንጂ ሥልጠናውን ለተገቢው ባለሙያ ከማድረስ አኳያ፣ በብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ደረጃቸውን የጠበቁ የሥልጠና ማኑዋሎች አለመኖር፣ የሥልጠናው ግብ አለመታወቅና ተያያዥ አለመሆኑ፣ የንድፈ ሃሳብና የተግባር ሥልጠናው አለመመጣጠን፣ በምዘና እና ፈቃድ አሰጣጥ ላይ ችግሮች መኖር፣ ቅንጅታዊ አሠራር ባለመኖሩ የሥልጠና አሰጣጥ ባለድርሻ አካላት አለመናበብ፣ ተመሳሳይ እና በማይሰሩበት ሙያ ሥልጠና መውሰድ እንዲሁም መሰል ችግሮች መኖራቸውንም ሰነዱ ያመላክታል። ይህንን ችግር ለመቅረፍም ፍኖተ ካርታው ወጥ የሆነ የባለሙያዎች የእድገት መሰላል፣ የሥልጠና ካሪኩለም እንዲሁም የሥልጠና ማኑዋል በብሔራዊ የስፖርት ማህበራት ማዘጋጀት እንደሚገባም በመፍትሄነት ያስቀምጣል። በዚሁ መሠረትም የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የላቁ ስፖርተኞችንና ብቃት ያላቸውን የስፖርት ባለሙያዎችን ለማፍራት፤ ብሔራዊ የሥልጠና ሞዴል እና አገር አቀፍ የስፖርት ባለሙያዎች የእድገት መሰላል እየተዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል። ባለሙያዎች በአጭርና መካከለኛ ጊዜ ሥልጠና እንዲሁም በረጅም ጊዜ ትምህርት ብቃታቸው እየተሻሻለ አቅማቸው እየተገነባ ሊሄድ ይገባል። በመሆኑም የሀገር አቀፍ የስፖርት ሪፎርም ጥናቱ ውጤት የሆነውንና የለውጥ ሃሳቦችን ለማስተግበር የሚያስችሉ ሰነዶች ዝግጅት መጀመሩን በኮሚሽኑ የትምህርት እና ሥልጠና ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ሳሙኤል ማስገንዘባቸውንም ኮሚሽኑ በድረ ገጹ አስነብቧል። የስፖርት ባለሙያዎች ልማት እና ጥራት አንዱ የሀገሪቷ ስፖርት ልማት ማዕዘን ነው። የስፖርቱን ችግር ይፈታል የተባለው የስፖርት ሪፎርም ፍኖተ ካርታው ለይቶ ካስቀመጣቸው ዘጠኝ ዋና ዋና ምሰሶዎች አንዱም የስፖርት ባለሙያዎች ልማት እና ጥራት ነው። ለአንድ ሀገር ስፖርት እድገት የባለሙያዎች ብቃት፣ ጥራት እና አቅርቦት እጅግ ወሳኝ መሆኑን የሪፎርም ፕሮግራሙ ያመላክታል። በመሆኑም ባለሙያዎች በአጭር እና መካከለኛ ጊዜ ሥልጠና እንዲሁም በረጅም ጊዜ ትምህርት ብቃታቸው እየተሻሻለ አቅማቸው እየተገነባ ሊሄድ እንደሚገባ የጥናት መርሃ ግብሩ ይጠቁማል። በሰነድ ዝግጅቱ ላይም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ከስፖርት ፌዴሬሽኖች፣ ከሥልጠና ማዕከላት፣ ከብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞች እና ሌሎችም በዘርፉ ከፍተኛ ልምድና እውቀት ያላቸው ምሁራን ተሳታፊ እንደሚሆኑም ታውቋል። አጠቃላይ ዝግጅቱን በተመለከተም በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን አልዩ የሥራ መመሪያ ተሰጥቶ ወደ ሥራ መገባቱም ተጠቁሟል።አዲስ ዘመን ሰኔ 4/2012 ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=34184
[ { "passage": "የስፖርት ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው በእጅጉ እየጨመረ እንደመጣ ይታወቃል። የዓለም አገራት የስፖርት ሴክተሩን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ በመረዳት ብቻ የሚቆሙ እንዳልሆኑ በዘርፉ ያስመዘገቡት ውጤት ማሳያ ነው። በዓለማችን በበርካታ አገራት ከሌሎች ሴክተሮች ባልተናነሰ መልኩ ለስፖርት ልማቱ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይን በማፍሰስ ስማቸውን በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ብሎ እንዲጠራ ከማድረግ አልፈው ብዙ ማትረፍ ችለዋል፡፡ ለስፖርት ሴክተሩ ትልቅ ትኩረት መስጠት በማህበራዊ ፋይዳው አምራችና ጤናማ ዜጋን በማፍራት\nረገድ ያለውን ውጤት ከመረዳት ይመነጫል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ ትላልቅ ውድድሮች በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ከሚገኘው ድል ጀርባ\nለአገር ፖለቲካዊ ትርፍ ማጣጣም ማስቻሉንም መታዘብ ይቻላል፡፡ ስፖርተኞች ከውድድር ድል በኋላ የሚያገኙት ረብጣ የሽልማት ገንዘብና\nየአገር ኢኮኖሚን በማንቀሳቀስ የሚገኘው ትርፍም ቀላል አይደለም፡፡ የስፖርቱን ዘርፈ ብዙ ፋይዳን በጥልቅ በመረዳት የስኬት ማማ\nላይ የወጡ እንደ ጀርመን ያሉ አገራትን ማንሳት ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለስፖርት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ረገድ ጀርመን\nበግንባር ቀደምነት ተጠቃሽ ናት። ይህች አገር ስፖርቱ በጠንካራ የፋይናንስ መሠረት ላይ ማቆም መቻሏ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መሠረቱን\nሳይለቅ መጓዝ የቻለ አደረጃጀት መፍጠሯ ለስኬቷ ምክንያት ተደርጎ ይነሳል፡፡ የጀርመን መንግሥት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ከሚያፈስባቸው\nዘርፎች ዋነኛው ስፖርት ሊሆን የቻለውም ለዚህ ነው፡፡ ስፖርት በጀርመን ኢኮኖሚ ውስጥ 2 ነጥብ 2 በመቶ ድርሻ ይይዛል። ስፖርቱን በፋይናንስ\nአቅም እንዲጎለብት ከማድረግ በተጓዳኝ፤ ጠንካራ አደረጃጀት የተዘረጋለት ነው። በጀርመን የስፖርት ዘርፍ ይህን መልክ መላበሱ ከዘርፉ\nየሚገኘው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳ እንዲጎላ ማድረጉ ይነሳል። በኢትዮጵያ ለስፖርቱ ዘርፍ የተሰጠውን ትኩረትና ውጤት\nከሌሎች አገራት አንጻር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ በቀደሙት ጥቂት ዓመታት ለስፖርቱ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች፣ ከመንግሥትና ከሌሎች\nባለድርሻ አካላት በኩል ኢትዮጵያ ለስፖርቱ ዘርፍ ተገቢ ትኩረት መስጠቷ ይነገራል፡፡ ለስፖርት ዘርፍ በተገቢው ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶት\nእየተሰራ አለመሆኑንና የዘርፉ እድገት በቁልቁለት ጉዞ ውስጥ መሆኑም በሌላ ወገን ይነሳል። የስፖርት ሴክተሩ ውጤት አልባ መሆኑ\nግን ሁለቱንም ወገኖች እንደሚያስማማ ለመታዘብ ይቻላል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በመንግሥት ደረጃ ይኸው እውነታ ታምኖበት እየተሰራ\nስለመሆኑ በተደጋጋሚ እየተነገረ ይገኛል። በኢፌዴሪ ስፖርት\nኮሚሽን የዕቅድ በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንድሪስ አብዱ፤ በአገሪቱ ባለፉት ሁለት የዕድገትና\nትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመናት ዘርፉ ለአገሪቱ ማበርከት ካለበት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጠቀሜታዎች አንፃር በሚፈለገው\nደረጃ ላይ አለመገኘቱና ውጤቱም በመላ አገሪቱ ተደራሽነት ላይ ክፍተቶች መኖራቸው እንደታመነበት ይናገራሉ:: ለዚህም የስፖርት ሴክተሩን\nመሠረታዊ ችግር በተረዳ መልኩ የ10 ዓመት የስፖርት ሴክተር ስትራቴጂክ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እንዲሆን በኮሚሽኑ በኩል እንቅስቃሴ\nከተጀመረ መሰንበቱን ያስረዳሉ፡፡ ስፖርቱን ወደፊት\nለማራመድ እንቅፋት ከሆኑ መሠረታዊ ምክንያቶች መካከል በዋነኛነት ከአደረ ጃጀት፣ ከፋይናንስ፣ ከሰው ኃይል ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች\nመሆናቸውን የጠቆሙት የኮሚሽኑ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር አቶ እንየው አሊ፤ የ10 ዓመቱ ስትራቴጂክ እቅድ የተጠቀሱትን\nክፍተቶች በጥናት እንዲመልስ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ያስቀምጣሉ፡፡ ስትራቴጂክ ዕቅዱ አገራዊ የስፖርት ሪፎርምን መነሻ በማድረግ\nበስፋት የተዘጋጀ መሆኑንም ይገልፃሉ። በመሆኑም በአገሪቷ ቀጣይ የስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ለውጥና ውጤት ማምጣት እንደሚያስችል\nታምኖበታል፡፡ የስፖርት ሴክተሩ ሪፎርም ፕሮግራም ዘርፍን መለወጥ የሚችሉ ብዙ ያመላከታቸው ነጥቦች እንዳሉም ያስረዳሉ። በዚህም\nከአደረጃጀት ፣ ከፋይናንስ፣ ከሰው ኃይልና ሌሎችም ጉዳዮች አንፃር ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት እንደሚቻል ተስፋ የተጣለበት መሆኑን\nይጠቅሳሉ፡፡ በሪፎርሙ ላይ የሴክተሩ ችግሮች የተለዩ ሲሆን በተመሳሳይ መፍትሄዎች መመላከታቸውንም ያክላሉ። ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ\nተግባራዊ የሚደረገውና ከስፖርት ሪፎርሙ የሚቀዳው የ10 ዓመቱ ስትራቴጂክ እቅድ ዘርፍን የተሻለ እንደሚያደርገውም ያላቸውን እምነት\nይገልፃሉ፡፡ አቶ እንድሪስ በበኩላቸው፤\nበቀጣይ ዓመት ተግባራዊ የሚደረገው ስትራቴጂክ ዕቅድ ትኩረት ያደረጋቸው አንኳር ጉዳዮች መኖራቸውን በመጥቀስ በሴክተሩ በቀጣይ\n10 ዓመታት በትኩረት የሚሰራባቸው ተብለው የቀረቡት ቁልፍ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች እንዳሉ ይናገራሉ:: በመጀመሪያ መንግሥታዊ የስፖርት\nአደረጃጀቶችን የመፈፀም እና የማስፈፀም አቅም በማጎልበት፤ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎችን እና የአሠራር ሥርዓቶችን ተግባር ላይ ማዋል\n፤ ሕዝባዊ የስፖርት አደረጃጀቶችን በዓለም አቀፍ እና በአገር አቀፍ መስፈርቶች መሠረት ማደራጀት የስትራቴጂክ እቅዱ ትኩረት መሆናቸውን\nያስቀምጣሉ:: በሁለተኛ ደረጃ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የማሰልጠኛ ማዕከላት ተደራሽነት፣ ሕጋዊነት እና ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን\nመሠረት በማድረግ በጥራት የሚገነቡበትን ስልት ሥራ ላይ ማዋል ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ያስረዳሉ። በአህጉር እና ዓለም አቀፍ የውድድር\nመድረኮች በተፈጥሮ ብቃታቸውን መሠረት በማድረግ አገራችንን የሚወክሉ እና ውጤታማ የሆኑ ተተኪ ስፖርተኞችን በሳይንሳዊ ስልጠናዎች\nማፍራት ትኩረት ተደርጎ የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑንም ያብራራሉ፡፡ ስፖርት ለማህበራዊ ልማትና ለአገር ብልፅግና ፣ ለሕዝቦች መቀራረብ\n፣ ለገፅታ ግንባታ እና ለቱሪዝም ዕድገት መሣሪያ ሆኖ እንዲያገለግል ትኩረት ሰጥቶ መስራትም የስትራቴጂክ እቅዱ ቁልፍ ጉዳዮች ናቸው።\nበስትራቴጂክ ዕቅዱ የተጠቀሱትን አንኳር ጉዳዮች መሠረት አድርጎ የተዘጋጀው ግብ ወደ ተግባር መቀየር ከተቻለም የስፖርት ሴክተሩ\nውጤታማ መሆን እንደሚችል እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡የባህልና ቱሪዝም\nሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ፤ በአገር አቀፍ የስፖርት ፖሊሲ ባለፉት ሁለት አስር ዓመታት የተመዘገቡ በርካታ አበረታች\nውጤቶች ቢኖሩም የአገራችን የስፖርት ዕድገት ከዕድሜው አኳያ ሲመዘን በሚፈለገው ደረጃ ባለማደጉ ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ ያመላክታሉ።\nበአሁኑ ወቅት መንግሥት ስፖርቱን እንደ አንድ የልማትና ብልፅግና መሣሪያ አድርጎ በመውሰድ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየሰራ እንደሚገኝ\nየሚናገሩት አቶ ሃብታሙ ፤ የስፖርት ዘርፍ በታሪኩ በዚህ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶት እንደማያውቅ ያብራራሉ:: የብሔራዊ የስፖርት ምክር\nቤት በኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ሰብሳቢነትና የበላይ ጠባቂነት መመራቱ መንግሥት ለስፖርቱ ሴክተር የሰጠውን\nትኩረት እንደሚያሳይም ያስቀምጣሉ፡፡ በመሆኑም የስፖርት ዘርፍን ከትናንት በተሻለ መልኩ ዛሬ ትኩረት በማግኘቱ ዕድሉን በአግባቡ\nበመጠቀም ጠንክሮ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡አዲስ ዘመን አርብ ጥር 22/2012ዳንኤል ዘነበ\n", "passage_id": "03113203decaadfcc71b27a06362f673" }, { "passage": "ዘመናዊው\nዓለም ስፖርትን ከአካል እንቅስቃሴ፣ ውድድር እና መዝናኛነቱ ባለፈ፤ ከትምህርት፣ ከጥናትና ምርምር፣ ከማህበራዊ ህይወት፣ ከኢኮኖሚ፣ ከቴክኖሎጂ፣… ጋር ያያይዘዋል። በተለይ ልምምድና ስልጠናን ዘመናዊ በማድረግ ተፎካካሪና ውጤታማ ለመሆን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እየተለመደ ነው። እነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶችም ስፖርተኛው ስላለበት ወቅታዊ አቋም ለማሳወቅ፣ በልምምድና በውድድር ወቅት ያሳየውን ብቃት ለማነጻጸር፣ መስፈርት ለማስቀመጥ፣ ጉዳትን ለመቀነስ እንዲሁም የአሰልጣኞችን ስራ ለማቅለል ዓይነተኛ ሚና ይጫወታሉ። በተወዳጁ የእግር ኳስ ስፖርት በዚህ ወቅት በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ከሚገኙት መሳሪያዎች መካከል አንዱ የተጫዋቾችን አቅም የሚለካው «ጂፒኤስ» ነው። ይህ\nመሳሪያ በእጅ ሊያዝ የሚችል አነስተኛ መጠን ያለው ሲሆን፤ ለመያዣ በተዘጋጀለት መልበሻ ተጫዋቾች ለብሰውት ልምምዳቸውን ያደርጋሉ። አሰልጣኙም ከመሳሪያው ጋር በሚገናኝ ኮምፒውተር አማካኝነት ተጫዋቹ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ እየለካ ግብረመልስ ይሰጣል። ኢትዮጵያ ውጤታማ ባልሆነችበት በዚህ ስፖርት በባለሙያዎች እንደ ድክመት ከሚነሱት መካከል አንዱ የተጫዋቾች የአካል ብቃት ደረጃ ማነስ ነው። በአንድ ወቅት ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረጉት የስፖርት ሳይንስ ባለሙያ ዶክተር ኤሊያስ አቢሻክራ፤ ለስልጠና መሰረታዊ ነገር የአካል ብቃት ሆኖ ሳለ በኢትዮጵያ ያለው ግን ከዚህ በተቃራኒ እንደሆነ በማንሳት ሃሳቡን ያጠናክራሉ። እርሳቸው በዘመናዊ መሳሪያ ታግዘው በአምስት ክለቦች ባደረጉት ልኬት ችግር መኖሩን ተገንዝበዋል። ከ17ዓመት በታች ቡድን የተመለከቱትም፤ ጥቂት የሚሆኑት በዓለም አቀፍ ደረጃ በእድሜያቸው የሚጠበቀውን ፍጥነት የሚያሟሉ መሆኑን ነው። ግማሾቹ የተሻለ ሰዓት ሲኖራቸው በተቀሩት ደግሞ ቢሰራባቸው ፈጣን መሆን ይችላሉ። በአውሮፓ አካዳሚ ባለው ተሞክሮም፤ አንድ የ14ዓመት ታዳጊ፤ በሰዓት 17ኪሎ ሜትሮችን ይሸፍናል። በኢትዮጵያ አዋቂ የሚባሉት ተጫዋቾች ግን በሰዓት 13 ኪሎ ሜትር ብቻ ይሮጣሉ። ይህ ደግሞ ተጫዋቾችን ለ70ደቂቃ ብቻ ነው ለመጫወት የሚያስችላቸው። ከዚህ\nበመነሳትም አውሮፓውያኑ እድሜያቸው እየጨመረ ሲሄድ ቅልጥፍናቸው ሲጨምር፤ በአንጻሩ ኢትዮጵያውያን እየተዳከሙ እንደሚሄዱ ነው መረጃው የሚያሳው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምህር የሆኑት ዶክተር ዘሩ በቀለ በመሳሪያው የተጫዋቾችን ብቃት በመለካት ላይ የሚገኙ ባለሙያ ናቸው። የኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች የአካል ብቃት በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛል የሚለውን በተደራጀ መልኩ ማግኘት እንደማይቻል ይገልጻሉ። ሊኖር የሚችለው ምናልባትም በዚህ ዙሪያ ጥናት ባደረጉ ግለሰቦች እጅ አሊያም አሰልጣኞች ጋር ነው። ከዚህ\nባሻገር ከ17 ዓመት በታች እንደ ስታንዳርድ የተቀመጠውን ብቻ ነው ማግኘት የሚቻለው። ከዚህ ባለፈ የተቀመጠ ልኬት ባይኖርም ለወደፊት ብሄራዊ ቡድኖች ደረጃ ይቀመጥላቸው ይሆናል የሚል ሃሳብ አላቸው። ይህንን ችግር ለመፍታት በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ የ«ጂፒኤስ» ቴክኖሎጂን መጠቀም ይመከራል። በሌላው ዓለም ይህንን መሰል መሳሪያ በፕሮፌሽናሎች ብቻም ሳይሆን በተራ ስፖርተኞችም ደረጃ እየተጠቀሙት እንደሚገኙ ዶክተር ዘሩ ይጠቁማሉ። በብዛት ገበያ ላይ የሚገኘው መሳሪያው የተጫዋቾችን ውሳጣዊና ውጫዊ የልምምድ ጫና እስከመለካትም የሚደርስ ነው። መሳሪያው የተጫዋቾችን ሁኔታ በመመዝገብና በመተንተን ግብዓት የሚሰጥ በመሆኑ በአሰልጣኝ ላይ የሚኖረውን ጫና የሚቀንስ ነው። የአሰልጣኙ ስራ የሚሆነውም የተጫዋቾችን ብቃት መጨመር ነው። አሁን ባለው ሁኔታ አሰልጣኞች የ11ተጫዋቾችን ሁኔታ በትክክል መገምገም አይችሉም፤ መሳሪያው ግን እያንዳንዱ ተጫዋች በእያንዳንዱ ደቂቃ የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ ነው። ተጫዋቾች ከውድድር ውድድር ያላቸውን አቅምም ያነጻጽራል።በአሰልጣኞችና\nተጫዋቾች መካከል የሚነሳውን ጭቅጭቅ የሚያስወግድ ሲሆን፤ ተጫዋቾች ከልምምድ ብዛት ወደ ጉዳት እንዳይገቡ ይታደጋል። ቡድኖች በመሳሪያው ልኬት መሰረት የራሳቸውን ምርጥ ማውጣት አሊያም ከፕሮፌሽናል ተጫዋቾች አኳያ ማነጻጸር ይቻላል። ከዚህ ባሻገር ከውድድር አስቀድሞ አሊያም ውድድሮች በመጠናቀቅ ላይ እያሉ ተደጋጋሚ ልኬቶችን መውሰድ መስፈርቶችን ለማስቀመጥ እንደሚችልም ዶክተር ዘሩ ያስረዳሉ። ለዚህም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን 50 የመለኪያ መሳሪያዎችን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መለገሱ የሚታወቅ ነው። 60ግራም የሚመዝነው ይህ መሳሪያ፤ «ካታፑልት ጂፒኤስ» ይሰኛል። እጅግ ዘመናዊ በመሆኑም የሰውነት ብቁነትን ሲለካ፣ ለታክቲካዊ ትንተናዎች የሚረዱ ግብዓቶችንም ይሰጣል። አንድ ተጫዋች የሚሸፍነው ርቀት፣ ያስመዘገበውን ፍጥነት፣ ጉልበት እና መሰል መረጃዎችን በማጠናቀርም፤ በአንድ ሰከንድ ውስጥ 1ሺ የሚጠጉ መረጃዎችን የመመዝገብ አቅም አለው። ከመሳሪያው የሚሰበሰበው ይህ መረጃም በቀጣይ የሚኖሩ የልምምድ መርሃ ግብሮችን ለመቅረጽ እንዲሁም የተጫዋቾችን ጤንነት በመጠበቅ ከጉዳት ለመከላከል እንደሚውልም ፌዴሬሽኑ ተስፋ አድርጓል። መሳሪያው ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሊምፒክ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ልምምድ ላይ መተግበሩ የሚታወስ ነው። በእርግጥ መረጃውን ለመስጠት ተደጋጋሚ ልኬቶችን ማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም፤ በትግበራው ምን ታይቷል የሚለውን ግን መጥቀስ ይቻላል። ቡድኑ ወደ ውድድር ከመግባቱ አስቀድሞ በተደረጉት የተወሰኑ ልኬቶች፤ ተጫዋቾቹ በአንድ ደቂቃ ምን ያህል ርቀት መሸፈን ይችላሉ የሚለው መታየቱን ዶክተርዘሩ ይጠቅሳሉ። በዚህም መሰረት ለማረጋገጥ የተቻለው አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች ከአማካይ በላይ የሚሸፈኑ መሆኑን ነው። በጨዋታ ወቅት ለማየት እንደተቻለው ከሆነም ተጫዋቾቹ በሜዳ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ እንዳላቸው ነው። ጥቂት\nነገር የሚቀራቸው ተጫዋቾችም ተለይተውበታል፤ ከዚህ ባሻገር ግን ተጫዋቾቹ በወቅታዊ አቋማቸው ከተቀመጡት መስፈርቶች አብዛኛውን የሚያሟሉ ነበሩ። የቡድኑ ዋና አሰልጣኝም ይህንን ልኬት እንደ ግብዓት በመጠቀም አሰላለፏ ላይ ተግባራዊ ማድረጓንም ዶክተር ዘሩ ያስታውሳሉ። ከብሄራዊ ቡድኖች ባሻገር ክለቦችም መሳሪያው ቢኖራቸው ደግሞ ተጫዋቾቻቸውን ለብሄራዊ ቡድን ለማስመረጥ የሚጠቀሙበት ይሆናል። የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝም ተጫዋቹ በጨዋታዎች ላይ የሚያሳየውን አቋም በመሳሪያው አማካኝነት በመገምገም ግብረመልስ ሊሰጥና ከክለቡ ጋርም ሊወያይ ይችላል። ይህም\nየብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞች በየጨዋታው ተገኝተው ተጫዋቾችን ለመምረጥ የሚያደርጉትን ጥረት በመቀነስ፤ መረጃዎች ላይ ተመስርተው ስራቸውን ለማከናወን የሚጠቅማቸው ይሆናል። ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን በመለየት ከአጨዋወቱ ጋር የሚሄደውን ተጫዋች እያዘጋጁ መሄድም ያስችላል። በርካታ ጥቅሞች ያሉት ይህ መሳሪያ በቀጣይ በምን መልኩ ተግባር ላይ ይውላል ለሚለውም፤ በዚህ ጉዳይ ከብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞች ጋር ውይይት እንደሚደረግ ዶክተር ዘሩ ይጠቁማሉ። ክለቦችም\nራሳቸውን ችለው በዚህ መሳሪያ ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ስልጠና የመስጠት እቅድ አለ። ክለቦች መሳሪያውን ለመግዛት ብዙም የሚቸግራቸው አይሆንም፤ ስለዚህም በአጭር ጊዜ ስልጠና ወደ ተግባር የሚገቡበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይቻላል። ክለቦች ይህንን ነገር መጠቀም ከቻሉም እንደ ሃገር ስታንዳርዶችን ለማውጣት የሚረዳ ይሆናል። የትኞቹ ጠንካራ የትኞቹ ደግሞ ደካማ ተጫዋቾች ናቸው የሚለውንም በዚህ መለየት እንደሚያስችልም ነው ተስፋ የተጣለበት።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 21/2011ብርሃን\nፈይሳ", "passage_id": "b5d3d6a248cf37bd1a6a0c1a8be631bd" }, { "passage": "በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የፈለቁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለበርካታ ዓመታት በታላላቅ የዓለማችን የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ ለኢትዮጵያ የላቁ ውጤቶችን እያስመዘገቡ ቆይተዋል፡፡ በረጅም ርቀት 10ሺ እና\n5ሺ ሜትር፤ እንዲሁም በመካከለኛ ርቀት የአትሌቲክስ ውድድሮች ዓለምን ተቆጣጥረዋል፡፡ በማራቶንና በጎዳና ላይ ሩጫዎች በሚያስመዘግቧቸው ውጤቶችም የገነኑ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ የሰንደቅ ዓላማዋ ምልክትና መታወቂያዋ የሆነው የአትሌቲክስ ስፖርት ከእጅ\nሳያመልጥ፤ እንዲሁም በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በፍፁም የበላይነት በሜዳሊያ እያሸበረቅን ውጤት ባስመዘገብንባቸው የአት ሌቲክስ ውድድሮችን ጠብቆ ለማስጓዝም ሆነ ተጨማሪ ድሎችን ለማስመዝገብ አዳዲስ የአሠራር ስልቶችን መከተል እንደሚገባ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ በዓለም አቀፍ\nደረጃ ስሟ በገነነው የሯጮች ምድር ኢትዮጵያ በተንጣለሉ መስኮች እና ጋራዎች ልምምድ እና ስልጠና ማካሄድ የተለመዱ ትእይንቶች ቢሆኑም፤ የትኛው አካባቢ ለየትኛው የስፖርት ዓይነት ልምምድ ይሆናል የሚል ሳይንሳዊ እሳቤን ተከትሎ በመስራት ረገድ ከፍተት መኖሩንና፤ ለአትሌቲክሱ ስፖርት የተሰጥኦ አካባቢዎችን ለይቶ አትሌቶችን ማፍለቅ ትኩረት የሚሻው ጉዳይ ስለመሆኑ የሚናገሩት የዘርፉ ምሁራን ይህን መሰል ሳይንሳዊ ጥናትና ዘመናዊ የልምምድ መዋቅር በአግባቡ ተዘርግቶ ሊሰራበት እንደሚገባም ያሳስባሉ፡፡ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር አረፋይኔ መስፍን እንደሚሉት፤ የተሰጥኦ ስፍራ የሚባለው በዋናነት በኢትዮጵያ የተለመደውን የረጅም ርቀት ሩጫ መነሻ ያደረገ ነው፡፡ ሳይንሱም የሚደግፈው ይህንኑ ነው፡፡ ረጅም ርቀትን በሚመለከት ከዚህ ቀደም የተጀመሩ ሥራዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ደብረ ብርሃንና አሰላ በቆጂ አካባቢዎች ለረጅም ርቀት ተስማሚ ስፍራዎች ናቸው ተብለው ይታሰባሉ፡ ፡ በደቡባዊ የትግራይ ክፍል ማይጨውና ራያ አካባቢ ለረጅም ርቀት ሩጫ ተስማሚ ከሚባሉት ስፍራች መካከል ናቸው፡፡ በአማራ ክልል ጎጃም ጢስ አባይ አካባቢም ተከላ የሚባለው ስፍራ እንዲሁ አመቺ ቦታ ነው፡፡ ደቡብ ጎንደር ወረታን ተከትሎ ባሉት ደጋማ አካባቢዎች እስካሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ከተሰጥኦ ስፍራዎች ውስጥ ተመድበው እየተሰራባቸውና የተሻለ የአትሌቲክስ ስፖርተኞች እየፈለቁባቸው ይገኛል፡፡ በዋናነት አሁን ያሉት የረጅም ርቀት ቦታዎች ለመካከለኛ ርቀት ሩጫዎችም ያገለግላሉ፡፡ ‹‹ለአጭር ርቀትና የሜዳ ተግባራት የስፖርት ዓይነቶች በአብዛኛው በአገሪቱ ያሉ ቆላማ አካባቢዎች ተመራጮች ናቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ መስክ ያን ያህል በዓለም መድረክ አንታወቅበትም፡፡ ለዚህ የስፖርት ዓይነት የተሰጥኦ ቦታዎችን ለይቶ መስራት ከተቻለ ግን ውጤት ይገኝበታል፡፡ በእርግጥ ጅማሬዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ቆቦ አካባቢ ይህንን በተከተለ መንገድ የተጀመሩ ሥራዎች አሉ፡፡ በምሥራቅ የአገሪቱ አካባቢዎች ሱማሌና አፋር አካባቢ ተስማሚ ቦታዎች አሉ፡፡ የሜዳ ተግባራት በተለይ ውርወራ በደቡብ ኦሞ አካባቢ ያሉት ስፍራዎች ልምምድ ቢደረግባቸው ምቹ መሆናቸው ይመከራል፡፡ በጋምቤላና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ አካባቢዎችም በፕሮጀክትም ሆነ በክለብ ደረጃ ያሉ አትሌቶች ኢትዮጵያን በመወከል ትልቅ ውጤት እያመጡ በመሆናቸው ስፍራው ትኩረት እንዲደረግበት ያነሳሳል›› ሲሉ ረዳት ፕሮፌሰር አረፋይኔ የትኛው ሥፍራ ለየትኛው የስፖርት ዓይነት መለማመጃ እንደሆነ ያብራራሉ፡፡ የተሰጥኦ ስፍራ የሚባሉ ቦታዎችን ለመለየት የረጅም ርቀት ከፍታን መሠረት ያደረጉ የአየር ጣባዮች፣ ለአጭር ርቀትና ለሜዳ ተግባር ስፖርቶች በባህሪያቸው ኃይልን ስለሚፈልጉ፤ የጡንቻና ሌሎች አካላት ውህደትን በመጠቀም ስለሚሰራ፤ ለአተነፋፈስ ሥርዓቱ ምቹ የሆኑ የአየር ጠባያትን በመለየት አካባቢዎችን ማወቅ እንደሚቻል ነው ረዳት ፕሮፌሰር አረፋይኔ የሚናገሩት፡፡ እንደ እርሳቸው ማብራሪያ፤ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የተሰጥኦ አካባቢዎችን በመለየት ልምምድ የማድረግ ሁኔታው በከፊል ያለ ቢሆንም ከውጤት አኳያ ሲመዘን ግን በዚህ ሂደት የመጓዝ ልምዱ ተጨማሪ ሥራዎችን የሚጠይቅ ሆኗል፡፡ ለዚህም ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የተጀማመሩ ነገሮች ቢኖሩም ሙሉ ለሙሉ አጥጋቢ ናቸው ለማለት ግን አያስደፍርም፡፡ ለስፖርቱ የተለዩ የተሰጥኦ ስፍራችን መጠቀም ማለት 50 በመቶውን የስፖርቱን ሥራ እንደማቃለል ነው የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ በተፈጥሮ ላይ ተመስርቶ መስራቱ በዋናነት የበለጠ ውጤታማ እንደሚያደርግ፤ በመሆኑም የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላትን የተሰጥኦ ስፍራዎች ባሉባቸው አካባቢዎች በመገንባት የላቀ ሥራ መስራት እንደሚያስፈልግ ይመክራሉ፡፡ በተለይ ለአጭር ርቀት ተስማሚ የሆኑ ቆላማ አካባቢዎችን ለይቶ ማዕከላትን ማስፋፋት ከተቻለ በዚህ ዘርፍ ውጤታማ መሆን እንደሚቻልም ይጠቁማሉ፡፡ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምህር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር አማረ ጥጋቡ በበኩላቸው፤ ስፖርትን በሚመለከት የተሰጥኦ ሥፍራ የሚባለው ለስፖርቱ በቂ አቅም መስጠት የሚችል አካባቢ ነው ይላሉ፡፡ አክለውም በኢትዮጵያ በተለምዶ ደጋማው አካባቢ ብቻ የተሰጥኦ ስፍራ የሚመስላቸው መኖራውንና ነገር ግን ምቹ የአትሌቲክስ ቦታዎች ደጋማ አካባቢዎች ብቻ አለመሆናቸውን፤ ስፍራዎቹም የሚወሰኑት በስፖርቱ ዓይነት መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ረዳት ፕሮፌሰር አማረ እንደሚሉት፤ በኢትዮጵያ ያሉ አትሌቶች በረጅምም ይሁን በአጭር ርቀት ላይ የሚሳተፉት አንዱን አካባቢ ብቻ መርጠው ነው፡፡ ይህም በተደጋጋሚ ስለሚተገበር አካባቢው ላይ ያለውና ስፖርቱን የሚያዘወትረው የማህበረሰብ ክፍል አዕምሮ ውስጥ በመያዙ፤ ሙያተኛውም ቢሆን ለአትሌት የተመረጡት እነዚህ ስፍራዎች ብቻ ናቸው ብሎ በመፈረጁ አማራጭ የተሰጥኦ ስፍራዎችን ለይቶ መተግበር አልተቻለም፡፡ ጥናትንና ሳይንስን መሠረት ባደረጉ በተለይም ከአየር ንብረቱ ጋር ተያይዞ የትኛው ስፖርት በየትኛው አካባቢ መሰራት እንዳለበት ግንዛቤ መያዝ ሲገባ ከዚህ አንጻር ብዙ ያልተሰሩ ጉዳዮች መኖራቸው ተስተውሏል፡፡ ‹‹በተለይ በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢ ያሉ አትሌቶች ልምምዳቸውን በዘልማድ ስለሚያደርጉ እነዚህን አትሌቶች ምሳሌ በማድረግ ገና ከጀማሪነታቸው ተለምዷዊ የሆነውን የስልጠና ሥፍራ ለመምረጥ ይገደዳሉ፡፡ ታዋቂ አትሌቶችን ምሳሌ የማድረጉ አዝማሚያ ከቦታ መረጣ ብቻ ሳይሆን የሩጫውንም ርዝመት መነሻ ያደረገ ነው፡፡ ለምሳሌ በአንድ ቦታ በብዛት የረጅም ርቀት አትሌቶች ካሉ አዳዲሶቹም መሮጥ የሚፈልጉት ረጅም ርቀቱን ነው፡፡ ይህ እንደ ባህል የቀድሞ አትሌቶችን እግር ተከትሎ የመጣ ነው›› ይላሉ ረዳት ፕሮፌሰር አማረ ጥጋቡ፡፡ ረዳት ፕሮፈሰር አማረ፤ የአጭር ርቀት ሩጫዎች የበለጠ ሳይንሳዊ እውቀትን ስለሚጠይቁና እንደ አገርም ለዚህ የሚያበቃ አቅም ባለመኖሩ ባልተጠኑና ለዚህ የሩጫ ዘርፍ ተብለው ባልተመረጡ ስፍራዎች ላይ የመሮጥ ችግርም በተደጋጋሚ እንደሚስተዋል፤ አብዛኛውንም ልምምዱን የሚያደርጉት በራሳቸው ጥረት እንደ ሆነና ሙያዊ እገዛ ላይ ክፍተቶች እንዳሉም ጠቅ ሰዋል፡፡ ‹‹በኢትዮጵያ ያሉ አትሌቶች እንደየስፖርቱ ተፈጥሯዊ ሁኔታ በተመረጡ የተሰጥኦ ስፍራዎች ላይ ልምምድ ቢሰሩ አሁን በተለመደው የ5ሺ እና የ10ሺ ርቀቶች ላይ ብቻ ተንጠልጥለው አይቀሩም ነበር፡፡ በሁሉም የስፖርት ዓይነቶች ተጠቃሚ መሆን ይቻል ነበር፡፡ ለምሳሌ በኦሊምፒክ ውድድር በብዙ የስፖርት ዓይነት ባለመሳተፍ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንገኛለን፡፡ በመሆኑም በአገሪቱ የሚገኙትን ተፈጥሯዊ ሁኔታን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የስፖርት ዓይነት ተሳትፎን ማብዛት ያስፈልጋል፡፡ በእያንዳንዱ የስፖርት ዓይነት በርካታ ቁጥር ያላቸው ስፖርተኞችን ማፍለቅ ከተቻለ አገሪቷ ስሟ ከሚወሳው የአምስትና አስር ሺ ሩጫ በተጨማሪ በአጭር ርቀትና የሜዳ ተግባራት የውድድር ዓይነቶች የመሳተፍ እድሏ ከፍ ይላል፡፡ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ እያንዳንዱን ስፖርት ለይቶ ስልጠና መስጠትና በርካታ ፕሮጀክቶችን ማስፋፋትን ያካትታል›› ሲሉም ረዳት ፕሮፌሰሩ አማረ ምክረ ሀሳባቸውን ያስቀምጣሉ፡፡አዲስ ዘመን ግንቦት 2/2011", "passage_id": "f7834939b4ef273e7b0677ed22773dba" }, { "passage": "ስፖርት የማይካተትበት ዘርፍ የለም፤ ቴክኖሎጂም እንዲሁ።ሁለቱም ዘርፎች በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ጋር በመቆራኘት ህይወትን በማቅለል ለዘመናዊው ዓለም የጎላ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ።ከዚህ ባለፈ አንዱ ለሌላኛው ቁልፍ ጉዳይ መከወኑም አልቀረም።በልምድ ይካሄድ የነበረው ስፖርት በሳይንስና ቴክኖሎጂ በመደገፉ፤ ዘመናዊውን ስፖርት ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ለይቶ ማሰብ በዚህ ወቅት አዳጋች ሆኗል።በቴክኖሎጂ የታገዙ ፈጠራዎች መበራከትም የስፖርተኞችን ብቃት በማሳደግ እንዲሁም የስልጠና ሂደቱን በማቃለልም ዘርፉን ትርፋማ ማድረግ ችሏል።የዘመኑ ስትንፋስ የሆነው ቴክኖሎጂ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ስፖርትን ተቀላቅሎ በቁጥር የማይተመኑ ለውጦችን አስገኝቷል።በስፖርት ትጥቅና የስልጠና ቁሳቁስ፣ ውድድሮችን በቀጥታ ለደጋፊዎች በማስመልከት፣ በውድድር ሜዳዎች ተገኝቶ ለመመልከት ትኬት የመቁረጫ አማራጭ፣ የስፖርት ሜዳዎች ሁለገብና ዘመናዊ እንዲሆኑ፣ ከውድድር አጨራረስ እንዲሁም ዳኝነት፣ የስፖርተኞችን መረጃና ውጤትን በመመዝገብ፣ ከዚህ ቀደም የነበረን ውድድርና ብቃት ለመገምገም፣ ስለ ስፖርቱ የሚወጡ አዳዲስ መረጃዎችን ለመከታተል፣ ስፖርተኞችን ከደጋፊዎቻቸው በማገናኘት፣ ንጹህ ስፖርትን ለማካሄድና በስፖርት የሚፈጸሙ የረቀቁ ወንጀሎችን ለማጣራት (ከአበረታች ቅመሞች ጋር በተያያዘ)፣ ከጉዳት ለማገገም (ስፖርት ህክምና)፣ በትልልቅ ጨዋታዎችና ውድድሮች ከአየር ሁኔታ ጋር በተያያዘ ችግር እንዳይገጥም እንዲሁም ዘርፈ ብዙ ግኝቶችንም አበርክቷል። በዋናነት እነዚህ ተጠቀሱ እንጂ ቴክኖሎጂ በእያንዳንዱ ስፖርት ለእያንዳንዱ ሂደት እየተወጣ ያለው አስተዋጽኦ ይዘርዘር ቢባል አዳጋች ነው የሚሆነው።ለአብነት ያህል ግን ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በጉልህ ከታዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል በሁለት ተወዳጅ ስፖርቶች የታዩትና የስፖርት ቤተሰቡን ቀልብ የሳቡትን ማንሳት ይቻላል።በአትሌቲክስ ስፖርት በመሮጫ ጫማ ላይ የነበረው የቴክኖሎጂ እገዛ የሰው ልጅ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች በመሮጥ አዲስ ታሪክ እንዲያስመዘግብ አድርጓል።በቪዲዮ የታገዘ ዳኝነት በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መተግበሩም እስካሁን በእግር ኳሱ ነጥረው ያልወጡ ጉዳዮች እንዲስተዋሉ ያደረጉ ሆነዋል። የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ዓለምን በእጅጉ እያስጨነቀ ባለበት በዚህ ወቅት ደግሞ ቴክኖሎጂ ለስፖርቱ እጅጉን አስፈላጊ መሆኑ በተግባር እየታየ ይገኛል።በተለይ ከስፖርታዊ ውድድሮች መሰረዝና ‹‹ከቤት አትውጡ›› ትዕዛዝ ጋር በተያያዘ ስፖርተኞች እንዲሁም ስፖርት ወዳዶች ቴክኖሎጂን እንደ አማራጭ ይዘውታል።የስፖርት መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ድረ ገጾችም የውድድሮች አለመኖርን ተከትሎ ከዚህ ቀደም የተካሄዱ ውድድሮችን በድጋሚ በማስታወስ ላይ ይገኛሉ።ስፖርተኞች በበኩላቸው በግላቸው የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች በተለያዩ ድረ-ገጾች ለሌላው ህዝብ በማጋራት ላይ ናቸው።አሰልጣኞችም ስፖርተኞች በቤታቸው ሲቆዩ እንዳይዘናጉ በተለያዩ ቴክኖሎጂ አፈራሽ መንገዶች ስልጠናቸውን ቀጥለዋል።የውድድር አዘጋጅ አካላት ደግሞ በአካል ስፖርተኞችን ማፎካከር ባይችሉም በስልኮች ላይ በሚጫን መተግበሪያ ውድድሮችን እያካሄዱ ይገኛሉ።የ ‹‹በቤት ቆዩ›› ቻሌንጆችም በዓለም ላይ እየተበራከቱ መሆኑ በግልጽ የሚታይ ነው። ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያም እየተለመደ ያለ ሲሆን፤ ስፖርተኞች፣ ባለሙያዎች፣ የስፖርት ማህበራት እንዲሁም ስፖርቱን የሚመሩ አካላት የብዙሃን መገናኛዎችንና ድረገጾችን በመጠቀም ህዝቡን ተደራሽ እያደረጉ ናቸው።አሰልጣኞችም በማህበራዊ ድረ-ገጾች ከሰልጣኞቻቸው ጋር ግንኙነት ያደርጋሉ። የስፖርትና የስልጠና ባለሙያዎችም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዴት እንደሚከወን ህብረተሰቡን ግንዛቤ እያስጨበጡና እያነቁም ይገኛሉ።የኢትዮጵያን ስም ከገነኑ አትሌቶች እኩል የሚያስነሳው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ አማካኝነት የሩጫ ውድድር እያካሄደ ይገኛል።‹‹ቨርቹዋል ሬይስ›› የሚሰኘው ይህ የውድድር ዓይነት እየተለመደ ያለና በርካቶች ተሳታፊ እየሆኑበትም ይገኛሉ፡፡በወቅታዊው ሁኔታ ስፖርት ለጊዜውም ቢሆን ከአካላዊ እንቅስቃሴ ጋር መለያየቱን ተከትሎም ከስፖርት ቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ የሚሰሩ ድርጅቶች ገበያቸው እየደራ መሆኑም ተስተውሏል።ፎርብስ በዚህ ጉዳይ ላይ የሰራው ዘገባ፤ ስፖርተኞች በቤት ውስጥ ከመቆየታቸው ጋር በተያያዘ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መከወኛ መሳሪያዎች ፍላጎትና ግዢ ጭማሪ አሳይቷል።በእንግሊዝ የሚገኝ አንድ የስፖርት ቁሳቁስ አምራች ከድረ-ገጹ ጋር በነበረው ቆይታ፤ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ባልታየ መልኩ የፈረንጆቹ\n2020 ከገባ በኋላ ጥያቄው መበርታቱን ጠቁሟል።በተለይ የኦሊምፒክ ተሳታፊ አትሌቶች፣ ቡድኖች እና ታዋቂ አትሌቶች ደግሞ ቀዳሚ ፈላጊዎች መሆናቸው ታውቋል። ዘ ኢኮኖሚክስ ደግሞ የዓለም ስፖርት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በወራት ውስጥ ከአካላዊ እንቅስቃሴ ወደ ዲጂታል (በቴክኖሎጂ የታገዘ) መቀየሩን አመላክቷል።ይህ ‹‹ኢ-ስፖርት›› የተሰኘው ውድድር በኮምፒዩተር የሚካሄድ ሲሆን፤ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ የሚያሸልም ነው።በዚህም ምክንያት የተሳታፊዎቹ ቁጥር በእጥፍ እያደገ መሆኑ ተረጋግጧል።ቁጥራዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነም፤ እአአ በ2019 የተሳታፊዎች ቁጥር 443 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፤ ይህም ከ2018 ጋር ሲነጻጸር በ12 ከመቶ ጭማሪ ያሳየ ነው።በዚህ ዓመት ደግሞ በዚህ ጨዋታ ተሳታፊ ከሆኑ ሰዎች አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱም ታውቋል።አዲስ ዘመን ግንቦት 17/2012 ብርሃን ፈይሳ አጫጭር ዜናአትሌቷ\nእርዳታ አድርጋለች ኢትዮጵያን በኦሊምፒክ፣\nበዓለም ቻምፒዮና፣ በዳይመንድ\nሊግ እንዲሁም በሌሎች\nውድድሮች በ5 እና\n10 ሺ ሜትሮች የሜዳሊያ\nባለቤት ያደረገችው አትሌት\nአልማዝ አያና እርዳታ\nአድርጋለች።አትሌቷ ከባለቤትዋ ጋር\nበመሆን ከአሁን በፊት\nየጀመረችውንና ከ30 በላይ\nየሚሆኑ አቅመ ደካማ\nአዛውንቶችን ለሁለተኛ ጊዜ\nየለገሰች ሲሆን፤ ከ50\nለማያንሱ ገቢያቸው አነስተኛ\nለሆነና ወደፊት ሀገራቸውን\nሊያስጠሩ ለሚጥሩ አትሌቶችም\nእርዳታውን ማበርከቷን የኢትዮጵያ\nአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በድረ\nገጹ አስነብቧል።ተረጂዎች እያንዳንዳቸው\nእንዳንድ ካርቶን ፓስታ፣\n5 ሊትር ዘይት እና\n50 ኪሎ ዱቄት አግኝተዋል።ከዚህ\nባሻገር የኮሮና ወረርሽኝን\n(ኮቪድ 19) ለመዋጋት\nበሚደረገው ጥረት የሚውል\n150 ሺህ ብር ለድጋፍ\nአስተባባሪው አምባሳደር ምስጋኑ\nአረጋ አስረክበዋል።አትሌቷ በጥቅሉ\n267ሺ ብር እርዳታ\nነው ያደረገችው።ሁለተኛ ዙር የምገባ መርሃ ግብር ተጀመረ የኢፌዴሪ\nስፖርት ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ\nአትሌቲክስና እግር ኳስ\nፌዴሬሽኖች እንዲሁም ቢጂአይ\nጋር በመሆን ለአንድ\nወር የሚቆይ የምገባ\nመርሃ ግብር ማካሄዳቸው\nየሚታወስ ነው።አሁን ደግሞ\nለአንድ ወር የሚቆይና\nበአዲስ አበባ ስቴድዮም\nዙሪያ የሚገኙ ችግረኞችን\nየሚያቅፍ ሁለተኛ ዙር\nየምገባ መርሃ ግብር\nበይፋ ተጀምሯል።ምገባውን የኢፌዴሪ\nስፖርት ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ\nአትሌቲክስና እግር ኳስ\nፌዴሬሽኖች፣ ከኢትዮጵያ ጸረ\nአበረታች ቅመሞች ጽህፈት\nቤት፣ ከወጋገን ባንክ፣\nከቢጂአይ ኢትዮጵያ እና\nከአቶ አብነት ገብረመስቀል\nጋር በመተባበጀር የሚካሄድ\nመሆኑም ታውቋል። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በቀጣዩ ወር ይመለሳል\nበኮሮና\nቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት\nየተቋረጡ የሊግ ውድድሮች\nእየተመለሱ መሆኑ ይታወቃል።ከእነዚህ\nመካከል አንዱ የሆነው\nተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪምየር\nሊግም በቀጣዩ ወር\nየሚቀጥል መሆኑን ቢቢሲ\nአስነብቧል።ባሳለፍነው ሳምንት መጀመሪያ\nልምምድ የጀመሩት ክለቦቹ\nከ17 ቀናት በኋላ\nውድድር የሚጀምሩ መሆኑን\nየፕሪምየር ሊጉ ዋና\nስራ አስፈጻሚ ሪቻርድ\nማስተር አረጋግጠዋል።በሊጉ ከሚሳተፉ\n20 ክለቦች ውስጥ ባሉ\nተጫዋቾች በተደረገው የኮቪድ\n19 ምርመራ በሶስት ክለቦች\nውስጥ የሚገኙ ስድስት\nተጫዋቾች ላይ መገኘቱም\nየሚታወስ ነው።አዲስ ዘመን ግንቦት 17/2012", "passage_id": "4a980366ef66ea523c47939ecb1a465e" }, { "passage": "አትሌቲክስ መለያዋ በሆነው ኢትዮጵያ ከስመጥር አትሌቶች ጀርባ ብዙም ያልተባለላቸው ነገር ግን ዘመን ተሻጋሪ ታሪክ የሰሩና እየሰሩ የሚገኙ በርካታ አሰልጣኞች አሉ። በዚህ ወቅትም በማራቶን ስፖርት ዓለም ያከበራቸውን ታላላቅ ስኬቶችን የተጎናፀፉ አትሌቶችን በማሰልጠን ላይ ከሚገኙት መካከል በቀዳሚነት ስማቸው የሚነሳው የኤሊት ስፖርት ማናጅመንት ተወካይና አሰልጣኝ ሃጂ አዲሎ ናቸው። ሃጂ አዲሎ ከአሰልጣኝነታቸው አስቀድሞ በአትሌትነት ሀገራቸውን አገልግለዋል። በጉዳት ምክንያት መሮጥ ማቆማቸውን ተከትሎም እአአ ከ2002 ጀምሮ ወደ ማሰልጠን እንቅስቃሴ ውስጥ የገቡ ሲሆን ዛሬ ላይ በዓለም በተለይም በማራቶን ገናና ስም ካተረፉ ሳተና አትሌቶች ስኬት ጀርባ እጃቸው አለበት። እአአ ከ2005 ጀምሮም ጠቅልለው አሁን ወደ ተሰማሩበት የአትሌቲክስ አሰልጣኝነት ሙያ የገቡ ሲሆን፤ በርካታ በመሮጥ ላይ ያሉና ሩጫን ያቆሙ አትሌቶች የስኬት ምስጢር ናቸው። አሰልጣኝ ሃጂ ከአዲስ ዘመን ቅዳሜ ጋር ስለ አሰልጣኝነታቸው ስኬታና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ ያደረጉት ቃለምልልስ እንደሚከተለው ቀርቧል።አዲስ ዘመን፡- በአሁኑ ወቅት\nበዓለም ላይ ስኬታማ የሆኑ አትሌቶችን ከሚያሰለጥኑት መካከል አንዱ መሆንዎ ይታወቃል። የዚህ ስኬት ምስጢሩ ምን ይሆን?አሰልጣኝ ሃጂ፡- የተለየ ነገር የለውም፤ ምስጢሩ ሥራ ነው። እኔና አብረውኝ የሚሰሩት ሁለት አሰልጣኞች በስፖርት ሕይወት ያሳለፍን ነን። በስፖርቱ ራሳችንም ተፈትነን ያለፍንበት በመሆኑ የአሰለጣጠን ሁኔታችንን የትኛው ይጎዳል የትኛውስ ጠቃሚ ነው የሚለውን በመለየት በተሻሻለ ሁኔታ ወቅቱን ያማከለ ስልጠና እየሰጠናቸው ስለሆነ ነው በርካታ ውጤታማ አትሌቶችን ማፍራት የቻልነው። አዲስ ዘመን፡- ከበርካቶቹ\nስኬታማ አትሌቶች መካከል ጥቂቶቹን ቢጠቅሱልን?አሰልጣኝ ሃጂ፡- ስልጠናውን በጀመርኩበት ወቅት የነበሩ፤ እንደነ ታደሰ ቶላ፣ ድሬ ቱኔ፣ ጠይባ ኢርኪሶ፣ አማኔ ጎበና፣ ድሪባ መርጊያን ማስታወስ ይቻላል። በዚህ ወቅት በርቀቱ ተጠቃሽ ከሆኑት መካከል ደግሞ ፈይሳ ሌሊሳ፣ ሌሊሳ ዴሲሳ፣ ሮዛ ደረጀ፣ ሩቲ አጋ፣ ሹራ ቂጣታ፣ ማሬ ዲባባን ማንሳት ይቻላል። በእኛ ማናጅመንት ስር ከሚገኙ የመም ተወዳዳሪዎች መካከልም ሰምበሬ ተፈሪና ሰለሞን ባረጋን የመሳሰሉ አትሌቶች ይገኙበታል።አዲስ ዘመን፡- ወደ ራስዎ\nልመልስዎና የአትሌትነት ሕይወት ይከብዳል ወይስ የአሰልጣኝነት? አሰልጣኝ ሃጂ፡- ድካም ያለው ቢሆንም አትሌትነት ቀላል ነው። አሰልጣኝነት ግን ከባድ ነው፤ ምክንያቱም አትሌት አድርግ የተባለውን ሲያደርግ አሰልጣኝ ግን ሁሉን የመቆጣጠር ኃላፊነት አለበት። ሰው ላይ የሚሰራ እንደመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልግ ሥራ ነው፤ ካልሆነ ግን የሰውን ልጅ አደጋ ላይ የሚጥልም ነው። አትሌቶች መሸከም የሚችሉትን ጫና እንደየአቅማቸው ወቅቱን ጠብቀንና አእምሯችንን አስጨንቀን የምናመጣው ስለሆነ ከበድ ይላል።አዲስ ዘመን፡- እርስዎ በተሻለ\nስኬታማ የሆኑበት በየትኛው ነው ብለው ያስባሉ፤ በአትሌትነት ወይስ በአሰልጣኝነት? አሰልጣኝ ሃጂ፡- በአትሌትነቱ የመጨረሻ ብቃቴን ሳልመለከት ነው ያቆምኩት፤ ውጤት ወደማግኘት ደረጃ ስደርስ በጉዳት ምክንያት ከሩጫ ወጣሁ። ከዚያ በላይ መቀጠል ባልችልም ግን በወቅቱ መልካም ሁኔታ ላይ ነበርኩ። ውጤታማ የሆንኩት ግን በአሰልጣኝነቱ ነው።አዲስ ዘመን፡- ብዙዎች አሁን\nበአትሌቲ ክሱ ያለውን ሁኔታ ከቀደመው ጋር ሲያነጻ ጽሩ አትሌቶች እንደ ድሮው ለረጅም ጊዜ በውድድር ከመቆየት ይልቅ ጥቂት እንደታዩ\nይጠፋሉ ይላሉ። የዚህ ምክንያት ምን ይመስልዎታል? አሰልጣኝ ሃጂ፡- በፊት አዳዲስ አትሌቶች ሲመጡ ገደብ ነበረባቸው፤ ለረጅም ጊዜ በመም ላይ የሚቆዩ ከመሆኑ ጋር በተያያዘም ስምና ዝናቸውን እንደያዙ ለረጅም ጊዜ ይቆዩ ነበር። በወቅቱ በርካታ ውድድሮች በመኖራቸው ምክንያትም ለረጅም ጊዜ በመም ላይ ይቆዩ ነበር። በዚህ ወቅት ደግሞ አትሌቶች ከመም በቶሎ ወደ ማራቶን ይገባሉ። በእርግጥ ብዙ ውጤታማዎች አሉ በእኛ ሀገር ግን በተለይ የሚታወቁት በኦሊምፒክና ዓለም ቻምፒዮና ውጤታማ የሆኑ ናቸው። በርካቶች በማናጀር ስር ሆነው ውድድሮችን ቢያደርጉም ታዋቂ መሆን አልቻሉም። በመሆኑም እኔ ቶሎ ታይተው ይጠፋሉ በሚለው አልስማማም። ምክንያቱም እኔ ከጀመርኩበት ጊዜ ጀምሮ ዕድሜ ገድቧቸው ካልሆነ ውጤታቸውን እንደያዙ ነውያሉት። እንደ አሰልጣኝ ስመለከተው ምናልባትም በጉዳት ካልሆነ በቀር ውጤታማዎቹ እንዳሉ አሉ። አዲስ ዘመን፡- በአንድ ወቅት\nስምዎ ከቻይና ብሔራዊ ቡድን ጋር ይያያዝ ነበረና ይህ ከምን ደረሰ?አሰልጣኝ ሃጂ፡- ከቻይና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቀረበልኝ ጥያቄ በቀጥታ ወደዚያው ሄጄ እንዳሰለጥን ነው። እኔ ደግሞ እዚህ በርካታ አትሌቶችን በመያዜ እና የማንቀሳቅሰው ድርጅት በመኖሩ እንደማይሆን ገለጽኩላቸው። ነገር ግን እዚህ ቢሰሩ የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆኑ በነገርኳቸው መሠረት ተስማምተው አትሌቶቻቸው ወደዚህ መጥተው ሰልጥነዋል። በዚህም ውጤታማ ሆነው እስካሁን ያላዩትን ስኬት አስመዝግበዋል፤ በቅርቡም በድጋሚ የሚመጡ ይሆናል። አዲስ ዘመን፡- በማራቶን\nሁለተኛው ፈጣን አትሌት ከሆነው ቀነኒሳ በቀለ ጋርስ አብረው ሰርተዋል?አሰልጣኝ ሃጂ፡- አዎ፤ የሀገር ባለውለታ ከሆነው ታላቁ አትሌት ጋር በቅርቡ አብረን መስራት ጀምረናል። ቀነኒሳ ከመም ከወረደ በኋላ ከጤንነቱ ጋር በተያያዘ የማይመጥነውን ውጤት ሲያስመዘግብ ነው የቆየው። አትሌቱ ብቃት እያለው እንዲህ መሆኑ ሁሌም ጥያቄ ስለሚያጭርብኝ አናገርኩት። ህመሙንም ሆላንድ ድረስ በመሄድ ከታከመ በኋላ ከእኛ ቡድን ጋር ተቀላቅሎ መስራት ጀመረ። ደስተኛ ሆኖ በመስራቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ ለውጥ እያሳየ፤ ከሁለት ወራት ስልጠና በኋላ ወደ በርሊን በመሄድ ትልቅ ውጤት አስመዝግቧል። በአጭር ጊዜ ስልጠናም ከዓለም ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት ማስመዝገቡ ብቃቱን ያስመሰክራል። ለቀጣይ ውድድሮችም አብረን በመስራት ላይ እንገኛለን።አዲስ ዘመን፡- ከሰሞኑ አንድ\nየውጭ ዜጋ አሰልጣኝ ቀነኒሳ ማራቶንን ከ2ሰዓት በታች መግባት እንደሚችል ሲገልጹ ነበር። እርስዎስ በዚህ ያምናሉ?አሰልጣኝ ሃጂ፡- ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ የሮጠው በርካታ ርብርቦሽ ተደርጎለት ነው። የቀነኒሳ ብቃት ግን ምንም ሳይደረግለት ከሁለት ሰዓት በታች ይሮጣል የሚል ሙሉ እምነት አለኝ። ቀነኒሳ በየትኛው ውድድር እንደሆነ ባላውቅም ከሁለት ሰዓት በታች የሚሮጥበት ብቃት አለው።አዲስ ዘመን፡- የቶኪዮ ኦሊምፒክ\nእየተቃረበ ይገኛል፣ እንደሚታወቀው ቶኪዮ ከኢትዮጵያ ማራቶን ታሪክ ጋር ጥብቅ ቁርኝት አላት፤ በዚህ ኦሊምፒክ የፈርቀዳጁን አትሌት\nአበበ ቢቂላን ታሪክ ለመድገም ምን ቢደረግ ጥሩ ነው ይላሉ? አሰልጣኝ ሃጂ፡- ሁላችንም ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመሆን ትኩረት ሰጥተን ከወዲሁ የምንሰራ ከሆነ ብቃት ያላቸው ልጆች አሉ። በዓለም ቻምፒዮና እና ኦሊምፒክ የኢትዮጵያን ውጤት የሚያጨናግፈው የአየር ሁኔታው ነው። እንደሚታወቀው ውድድሩ የሚካሄድበት ሀገር ሞቃት የእኛ ደግሞ ዝናባማ ነው (ከሲድኒ ኦሊምፒክ በቀር)። አሁንም ከዚህ ሞቃታማ አየር ጋር ለመስማማት ከወዲሁ አትሌቶችን ማዘጋጀት ከተቻለ እኔ በአትሌቶቹ ብቃት አልጠራጠርም። ዋናው ነገር መስራት ነውና ተናበን ከሰራን የአበበ ቢቂላ ታሪክ ይደገማል የሚል እምነት አለኝ። አዲስ ዘመን፡- እርስዎ የማራቶን\nአሰልጣኝ እንደመሆንዎ በተለየ የሚጠብቁት አትሌት ይኖር ይሆን?አሰልጣኝ ሃጂ፡- በርግጥ አሉ፤ ነገር ግን የአትሌቶቹ ብቃት ተቀራራቢ በመሆኑ በተለየ ለመግለጽ ይከብደኛል። አዲስ ዘመን፡- ከቅርብ ጊዜ\nወዲህ በምዕራባውያኑ ዘንድ እኛ የምንታወቅ ባቸውን ርቀቶች ከውድድር በማውጣት ራሳቸውን ተጠቃሚ የማድረግ እንቅስቃሴ ዎች ይስተዋላልና\nበዚህ ላይ ምን ይላሉ።አሰልጣኝ ሃጂ፡- ይሄ በጣም ሊታሰበበት የሚገባ ጉዳይ ነው። አፍሪካውያንን ለማራቅ እየተደረገ ያለ ነገር ይመስለኛል፤ እኔ አትሌት በነበርኩበት ጊዜ በርካታ የ10ሺ ሜትር ውድድሮች ነበሩ። አሁን ግን አንድም የለም፤ ለዚህም ነው ለኦሊምፒክና ዓለም ቻምፒዮና ፌዴሬሽኑ ማጣሪያ የሚያዘጋጀው። ይህም በተለይ ለምሥራቅ አፍሪካ አስቸጋሪ ነው፤ ምክንያቱም በርካታ አትሌቶች እየመጡ ባሉበት ወቅት ነው ውድድሮች የጠፉት። እንደሚመስለኝ በተለያዩ ሀገራት በሚዘጋጁ ውድድሮች የሽልማት ገንዘብ በሙሉ ወደ አፍሪካ ስለሚመጣ ነው። እነርሱ ደግሞ ወደ አጭር ርቀቱ ነው የሚያዘነብሉት፤ በ5ሺ እና 10ሺ ሜትር እንደ እኛ ውጤታማ ቢሆኑ ውድድሮቹ እንደማይጠፉም እርግጠኛ ነኝ። ስለዚህም አፍሪካውያን በቻልነው መጠን ውድድሮችን ማዘጋጀት ተገቢ ነው። በሀገራችንም እንደነ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያሉ ውድድሮችን ማስፋፋት አስፈላጊ ይሆናል። ከተቻለም የሌሎች ሀገራት ዜጎችም ከእኛ ጋር መፎካከር እንዲችሉ ማድረግ ያስፈልጋል። ፌዴሬሽኑም ከሌሎች ፌዴሬሽኖች ጋር መነጋገርና በዓለም አትሌቲክስ ላይ ጫና መፍጠር አስፈጊ ነው። በዚህ ከቀጠለ ግን በቅርቡ ከጨዋታ እንደምንወጣና ይሄ ስጋት ወደ ማራቶንም እንደሚመጣ እገምታለሁ። አዲስ ዘመን፡- በመጨረሻም\nበኢትዮጵያ አትሌቲክስ መስተካከል ይኖርበታል የሚሉት ሃሳብ ካለ መልዕክትዎን ቢያስተላልፉ።አሰልጣኝ ሃጂ፡- ከዚህ በፊት ገናና አትሌቶችን ስናወጣ የነበረው ከትምህርት ቤት ነው። ብቃት እያላቸው በተለይም በገጠር ያሉ ተማሪዎች ዕድሉን ባለማግኘት የሚቀሩበት ሁኔታ ስላለ የትምህርት ቤቶች ውድድር ላይ ትኩረት ቢደረግ እላለሁ። አዲስ ዘመን፡- አሰልጣኝ ሃጂ አዲሎ ስለሰጡን ጊዜና ስለነበረን\nቆይታ አመሰግናለሁ።አዲስ ዘመን ኅዳር 13/2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "ab762468e79f548380c2ebf8d7e90987" } ]
e0bb3e3c5c355cdca8c12f4459144b2a
47f9450967032091dad5b0edc43ff344
ያልተዘጋው የፓሪሱ ዶሴ
 እ.ኤ.አ ሰኔ 7 ቀን 1933 በሴኔጋል ዳካር ከተማ አንድ ህጻን ተወለደ። በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ስር በነበረችው ሴኔጋል መወለዱ ለቤተሰቦቹ ቅር ቢያሰኝም፤ ከህጻኑ አይኖች ያነበቡት ተስፋ መጽናናትን የሰጣቸው ነበር። የህይወት ውጣ ውረዱም ደስታን ከሀዘን እያፈራረቀ ቀጠለ። በሴኔጋል ምድር የበቀለው ህፃን የህይወት ውጣ ውረድን በመጋፈጥ፤ በአንካራ የልጅነት ጊዜውን አሳልፏል። በጊዜ ቅብብሎሽ ልጅነቱ ወደ ወጣትነት ሽግግር አደረገ። ከልጅነት ጀምሮ የሚፍለቀለቀው የስፖርት ፍቅር በዘመን ሳይሻር አብሮ ያደገ ነበር። በአንካራ ህይወት ቀላል አልነበረምና በፈታኙ የህይወት መንገድ ነገን የተሻለ ለማድረግ መጓዝ አማራጭ እንደሌለው በማመን ጉዞው ቀጠለ። ከልጅነት ጀምሮ ለስፖርት የነበረው ፍቅር ግን ወጥ በሆነ መስመር የተጓዘ ነበር። በስፖርት ፍቅር መሰረት የተገነባው የህይወት ኡደት የስኬት ቁልፍንም በስፖርቱ አማካኝነት እስከ መጨበጥ የደረሰ ታሪክ ባለቤት ናቸው የቀድሞ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበር ፕሬዚዳንት ላሚን ዲያክ።ላሚን ዲያክ ስፖርትን እንደ መሰላል በመጠቀም ስኬትን መጨበጥ ከቻሉ ጥቂት አፍሪካዊያን ውስጥ ይመደባሉ። የ86 ዓመት አዛውንቱ ላሚን ዲያክ በህይወት ፈተና ውስጥ ሳይሰናከሉ ያደረጉት ጉዞ ለዚህ ደረጃ መዳረሻ እንደሆናቸው «በሥራ ዘመኔ ከፍተኛ የፖለቲካ ፈተናዎች ገጥመውኝ ነበር።ዓላማ ስለነበረኝ ሁሉም አልፏል፣ ስለ አፍሪካ አንድነት በማውራት ጊዜውን ሁሉ ተጠቅመናል»ሲሉ ይደመጣሉ። ሴኔጋላዊው ዲያክ ወደ ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ አመራርነት በመምጣት ሀገራቸውን ከማስጠራታቸው ቀደም ብሎ በዝላይ ውድድር ሀገራቸውን ሲያስጠሩ ነበር። በወጣትነት ዘመናቸው በዝላይ ውድድር ሃገራቸውን በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች በመወከል ተሳትፈዋል። ከብዙዎቹ በጥቂቱ እኤአ 1950 በፍረንሳይ በተካሄደው የአትሌቲክስ ቻምፒዮን በመሳተፍ ባለድል ሆነዋል። ዲያክ በተደጋጋሚ የቻምፒዮናነት ክብር ባለቤት መሆን የድልን ጣዕም ለሀገራቸው በማቅመስ ትልቅ ታሪክ መስራታቸው ይነገራል።ሴኔጋላዊያን እርሳቸው ካስመዘገቧቸው ድሎች መካከል በተለይ በዝላይ ውድድር ከ1957 እስከ 1960 የምዕራብ አፍሪካን ክብረወሰን መያዝ የቻሉበት አጋጣሚ ትልቅ ስፍራ ይሰጡታል።የአፍሪካን እግር ኳስ በማነቃቃት ግንባር ቀደም የሆነችው ሴኔጋል ያበቀለቻቸው ላሚን ዲያክ በአትሌቲክሱ የተወዳዳሪነት ጊዜያቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ስፖርቱ አመራርነት ነበር ያዘነበሉት።በዚህም የተሳትፎ ደረጃቸውን በፍጥነት ማሳደግ ችለዋል። እኤአ 1999 እስከ 2013 የአለም ዓቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል በመሆን አገልግለዋል።በኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል በመሆን ሲያደርጉ የነበረው ተሳትፎ ወደ ሌላ ምዕራፍ ያሸጋገራቸው ነበር።እኤአ 1995 የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበር ፕሬዚዳንት እንዲሸጋገሩ መሰላል ሆኗቸዋል። የላሚን ዲያክ ወደ መሪነት መምጣት በሴናጋል ብቻም ሳይሆን በአፍሪካዊያን ዘንድ ትልቅ ደስታን የፈጠረ ነበር።የዓለምን አትሌቲክስ በአፍሪካዊያን መመራቱ አዲስ ታሪክ ከመሆኑ ባሻገር፤ ለአፍሪካዊያን የይቻላል መንፈስን ያወረሰ ተብሏል።የዲያክ የዓለምን አትሌቲክስ የመምራት ሂደት ለ16 ዓመታት ነበር የተጓዘው።እኤአ በ2015 ላሚን ዲያክ ስልጣናቸውን ለተመራጩ ለሴባስቲያን ሎርድ ኮ አስረክበዋል።ሴኔጋላዊው ላሚን ዲያክ በስልጣን ዘመናቸው በአትሌቲክሱ ዓለም የተበላሹ የአመራር ክፍተቶችን እንዳሉ በስፋት የሚነሳ ቢሆንም ከሞላ ጎደል ጥሩ ሥራዎችንም ማከናወናቸውን አብሮ ይነሳል።በተለይ ለአፍሪካ አትሌቲክስ የነበረቸው አበርክቶ የሚጠቀስና እስከ ሽልማት የተሻገረ ነበር።በአህጉሪቱ የአትሌቲክስ ስፖርት ላይ የሚያጠነጥነው «አፍሪካ አትሌቲክስ ፋውንዴሽን »ለላሚን ዲያክን እውቅና በመስጠት ረገድ ግንባር ቀደም ነበር። የዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበር ፕሬዚዳንት በመሆን ላሚን ዲያክ ባገለገሉባቸው ዓመታት የአፍሪካ አትሌቲክስ ህዳሴ መሆን ጉልህ ድርሻ ነበራቸው። ለዚህም እውቅናና ሽልማት ይገባቸዋል ሲል አመስግኗቸዋል።የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን በተመሳሳይ እውቅናውን አልነፈጋቸውም።እኤአ መጋቢት 4 ቀን 2015 የኮንፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚዎች 26ኛውን ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ በተካሄደበት ወቅት ለዲያክ ምስጋናና እውቅና ቸሯቸዋል። በወቅት ኮንፌዴሬሽኑ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፤ የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን በጋራ የእውቅና እና የስንብት ዝግጅት በማድረግ ለአበረከቷቸው አመስግነዋቸዋል።ዲያክ በፈተና የተሞላውን ጉዞ በድል መወጣት ቢችሉም፤ የህይወት ፈተና አላበቃም ነበር። የአለም አትሌቲክስ መሪነት ዘመናቸው ጨርሰው ስልጣናቸውን ካስረከቡ ማግስት ወደ ሌላ ፈተና ተሻገሩ። የአለም ዓቀፍን አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበርን ለ16 ዓመታት የመሩት ላሚንዲያክ መንበረ ስልጣናቸውን ባስረከቡ ማግስት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በ86 ዓመታቸው ፍርድ ቤት ነበር የቆሙት። ዲያክ በፈረንሳይ ፓሪስ የቁም እስረኛ ሲሆኑ፤ እኤአ ጥቅምት 4 ቀን 2015 ጀምሮ በፓሪስ ፍርድ ቤት ዲያክ የሩስያ አትሌቶች አበረታች መድሃኒት መውሰዳቸውን ለመደበቅ ረብጣ ሽልንግ ተቀብለዋል፤ የምርጫ ድምፅን በገንዘብ ገዝተዋል፤በሕገ-ወጥ ገንዘብ ዝውውር ጋር ተያይዞ ነበር ክስ የተመሰረተባቸው። በተጠቀሱት ወንጀሎች ዲያክን ጨምሮ አራት ግለሰቦች ተከሳሽ ሲሆኑ፤ የዲያክ ልጅ ፓፓ ማሳታ ዲያክ አንዱ ነው። ፓፓ ማሳታ ሴኔጋል ሆኖ የክስ ሂደቱን እየተከታተለ ይገኛል። ሴኔጋል ልጅዬውን አሳልፋ ለፈረንሳይ እንድትሰጥ ጥያቄ ቢቀርብም ሴኔጋል አሻፈረኝ ብላለች።በዚህ መሰረት ፓፓ ማሳታ አባቱንና እሱን ነፃ ያወጣል ያለውን ማስረጃ ለፍርድ ቤቱ በማስገባት ሙግቱን እያደረገ ቢሆንም፤ የክሱ ሂደት አላግባብ መጓተቱን ተከትሎ ወላጅ አባቱ ላሚን ዲያክ ለእንግልት መዳረጋቸውን እየተናገር ይገኛል።የክስ ሂደቱ ከተጀመረ አምስት ዓመት ቢያስቆጥርም መቋጫ እንዳላገኘ ገልጿል።በዲያክም ሆነ እርሱ በቀረበበት ክስ ላይ በቂ የሆነ ማስረጃ የሌለ በመሆኑና ካለወንጀላቸው ክስ የተመሰረተ ነው ሲል ቅሬታውን ያሰማል። በጠበቆቻቸው በኩል ይሄው በተደጋጋሚ እየተነሳ ሲሆን ወደ አገራቸው ሴኔጋል ተመልሰው የክስ ሂደቱን እንዲከታተሉ ጥያቄ እያቀረቡ ይገኛሉ።በፈረንሳይ ፍርድ ቤት ግን ውድቅ ተደርጓል። የፈረንሳይ ፍርድ ቤት ከአምስት ዓመት በፊት የተጀመረው የዲያክ የክስ ሂደቱ መፍትሄ ለማበጀት በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ማግስት እንዲታይ ቀጠሮ ይዞ ነበር። ፍርድ ቤቱ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ሰኔ ወር እንዲዛወር አድርጎታል። በፈረንሳይ በቁም እስር ላይ የሚገኙት የ87 ዓመቱ ላሚን ዲያክ በቀጠሮ መሰረት ባሳለፍነው ሰኞ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተሰምቷል።የፓሪሱ ፍርድ ቤትም በቀድሞዋ የአለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ላሚኔ ዲያክ ላይ ከሩሲያ ጋር በመመሳጠር ከዶፒንግ ጋር ተያይዞ በፈጸሙት ወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ የተመሰረተባቸውን የክስ ሂደትን ተከታትሏል።ፍርድ ቤቱ በዲያክ ላይም ዶፒንግን በሶስት ሚሊዮን ዩሮ በመለወጥ ሲል ክስ የመሰረተባቸው መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል። የ 87 ዓመቱ ላሚን ዲያክ ፊታቸውን ጭምብል በመሸፈን ፍርድ ቤት ተገኝተው የክስ ሂደታቸውን ተከታትለዋል።የፓሪሱ ፍርድ ቤትም ለቀጣዮቹ ስድስት ቀናት ችሎት ተሰይሞ የክስ ሂደቱን እንደሚሰማ ማስታወቁን አትቷል።የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ንግግር፤ «ሴኔጋላዊው ዲያክ በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉ ዓመታት ቢቆጠሩም ወንጀሉ ጥልቅ ምርመራ የሚፈልግ ከመሆኑ ጋር እንደሚያያዝ አስታወቋል።ዓመታትን በፈጀው ምርመራም የተዘበራረቀና ውስብስብ የሙስና ወንጀል መፈጸሙን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ተገኝተዋል። በተያዙት ሰነዶችም ከአውሮፓ እስከ እስያ እና አፍሪካ የተዘረጋ ጠንካራ የሆነ የወንጀል ሰንሰለት መኖሩን የሚያረጋግጡ ናቸውን»ሲሉ ማስረዳታቸውን ዘገባው አካቷል። የፓሪስ ፍርድ ቤት በዲያክ ላይ የሰበሰበውን ማስረጃዎች መሰረት በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ በስድስት ቀናት ችሎት እነዚህን ማስረጃዎችን በማቅረብ ወደ ውሳኔ እንደሚኬድ ፍርድ ቤቱ ማስታወቁን ጽፏል።በፈረንሳይ ፍርድ ቤት ክስ የተመሰረተባቸው ላሚን ዲያክ በተጠረጠሩበት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ እስከ 10 ዓመት የሚዘልቅ እስር ሊፈረድባቸው ይችላሉ ተብሏል። አዛውንቱ ዲያክ ቀሪ የእድሜ ዘመናቸውን ወሕኒ ሊያሳልፉ እንደሚችሉ ተነግሯል። ነገር ግን ከተከፈተ አምስት ዓመታት የሆነው የፓሪሱ ዶሴ የሚዘጋበት እለት አጓጊ እንደሆነ ቀጥሏል።አዲስ ዘመን ሰኔ 5/2012 ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=34246
[ { "passage": " ብዙዎች ጥቂቶችን ተከትለው ሃገራቸውን ለማስጠራት ታትረዋል። ሰንደቅ ዓላማ አስታቅፎ በምርቃት የሸኛቸውን ህዝብ አሳፍረው አያውቁም። ከጉዳት መልስ፣ ከወሊድ በኃላ እንዲሁም በጤና መታወክ ተበግረው ከውድድር ማፈግፈግንም አልሞከሩም። የቀንና ሌሊት መፈራረቅ የማያሳስበው የሩጫ ወዳጅም በድጋፉ አብሯቸው ዘመናትን ተሻግሯል። ጥረታቸው ሰምሮ የሃገራቸው ሰንደቅ ኣላማ በድል ከፍ ሲል በደስታ አንብተዋል። ህዝባቸውን በጀግንነት ስለሚያኮሩም በአበባ ጉንጉን ይቀበላቸዋል። ከሽልማትና ስፖንሰር የሚያገኙትን ገንዘብ ሃገራቸው ላይ ፈሰስ በማድረግም ለበርካቶች የስራ ዕድል ፈጥረዋል። እነርሱም ተምሳሌት ያደረጉ ታዳጊዎችም እንደምንጭ ከስር ከስር እየፈለቁ ረጅም ዓመታትን አስቆጥረዋል። ለምስራቅ አፍሪካ ሃገራት በተለይም ለኢትዮጵያ እና ኬንያ የ10ሺህ እና 5ሺህ ሜትር ሩጫ ታላቅ ትርጉም ያለው ነው። ያሉበት የመልካምድር አቀማመጥና የአየር ሁኔታ ለስኬታማነታቸው እንዳገዛቸው በባለሙያዎች ይነሳል። በግልጽ እንደሚታየው ባለፉት ዓመታት በርቀቶቹ በተካሄዱ ውድድሮች የበላይነቱን የያዙት የሁለቱ ሃገራት አትሌቶች እየተፈራረቁ ነው። በዚህም ምክንያት በአካባቢው እንደ ባህል ስፖርት እንዲታይ ምክንያት ሆኗል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን በእነዚህ ርቀቶች የሚካሄዱ ውድድሮች በዓለም ላይ እየተመናመኑ ነው የሚገኙት። የ10ሺህ\nሜትር ሩጫ በብቸኝነት የሚታየው በዓለም ሻምፒዮና እና ኦሊምፒክ ላይ ብቻ ነው። በዳይመንድ ሊግ ይካሄድ የነበረው የ5ሺህ ሜትር ሩጫም ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ እንደማይካሄድ ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር አስታውቋል። ይህም ሃገራቱን ያስቆጣ ሲሆን፤ ቅሬታዎቻቸውን በማንሳት ውሳኔውን ለማስቀልበስ የተለያዩ እርምጃዎችን በመወሰድ ላይ ይገኛሉ። ከሳምንት በፊት በዴንማርክ የተካሄደው የዓለም ሃገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ ጉዳዩን የተቃወሙት ኢትዮጵያ እና ኬንያ በተናጥል የዓለም አቀፉን ማህበር ፕሬዚዳንት ሰባስቲያን ኮን አናግረዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉም ከፕሬዚዳንቱ ጋር ቆይታ አድርጋለች። በውይይቱ ላይ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል አንዱም የ5ሺህ ሜትር ውድድር ጉዳይ አንዱ ነበር። በኦሊምፒክ 10ሺህ ሜትር የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት አትሌት በመሆን አፍሪካን ያስጠራችው ደራርቱ፤ «እኔን እና ሌሎች አትሌቶችን ያሳወቀን 5ሺህ እና 10ሺህ ሜትር ሩጫዎች ናቸው። ኢትዮጵያም የታወቀችበትና የተከበረችበት ይኸው ርቀት ነው። በመሆኑም እንዲህ መሆን የለበትም፤ እኛንም እንደ ህዝብ እና እንደ ምስራቅ አፍሪካ ያስከፋ በመሆኑ በድጋሚ ሊታይ ይገባል» ትላለች። ከማህበሩ ፕሬዚዳንት ጋር በነበራቸው ንግግር ላይም፤ አትሌቶች ወደ ሩጫ ሲገቡ ከ3ሺህ ሜትር በታች ባለው አጭር ርቀት ነው። ከዚያ በኃላ ነው ወደ ማራቶን የሚሄደው። አሁን ግን በቀጥታ ወደ ረጅም ርቀት ለመግባት ይገደዳሉ። ስለዚህም ውሳኔው በድጋሚ ሊታይ ይገባል የሚል ሃሳብ ማንሳቷን ትገልጻለች። በቅርቡ አቢጃን ላይ በሚኖረው ስብሰባ ጉዳዩ የሚነሳ በመሆኑም፤ የሚሆነውን በጋራ እንደምታይም ጠቁማለች። ከዚህ ባሻገር የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን የቦርድ አባል እንዲሁም የምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆኗ፤ የተለያዩ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደምትገኝ ታስረዳለች። «ከኬንያው የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ጋር በቅንጅት ምን መሰራትና እንዴት መሰራት እንዳለበት በመነጋገር ላይ እንገኛለን። የአፍሪካ ተወካይ እንደመሆናቸው ጉዳዩ ሲወሰን ለምን ዝምታን እንደመረጡ ጥያቄ እናቀርባለን። እነርሱን መተካት ካለብንም ሌሎች ጠንካራና መሞገት የሚችሉ ሰዎችን ከኢትዮጵያም ቢሆን መተካት እንዳለብን እዚያ የምንነጋገር ይሆናል»ም ብላለች። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴም፤ ዓለም አቀፉ ማህበር ከዚህ ቀደም በዳይመንድ ሊግ ይካሄድ የነበረውን የ10ሺህ\nሜትር ሩጫ ማስቀረቱን አስታውሶ፤ እ.አ.አ ከ2020 ጀምሮ\nየኢትዮጵያ አና የአፍሪካ ባህላዊ ሩጫ የሆነውንና በርካታ አትሌቶችም ለራሳቸውና ለሃገራቸው አኩሪ ድል ያስመዘገቡበትን የ5ሺህ ሜትር ሩጫ ከውድድሩ እንደሚቀንስ ማስታወቁን እንደማይደግፍ በመግለጫው ማስታወቁ ይታወሳል። ይህንን በተመለከተም ኮሚቴ በማቋቋም ውሳኔ የማስቀልበስ ስራውን ጀምሯል። በርቀቱ  ታዋቂና ዝነኛ የሆኑ አንጋፋ አትሌቶች በተካተቱበት ኮሚቴ ውስጥም የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት ገብረእግዚአብሄር ገብረማርያም አንዱ ነው። ፌዴሬሽኑ እና ኦሊምፒክ ኮሚቴው ከዓለም አቀፎቹ ማህበራት ጋር የሚያደርጉት ግንኙነት እንዳለ ሆኖ የዚህ ኮሚቴ ስራ ድጋፍ መስጠት መሆኑን ይጠቁማል። የኮሚቴው ተግባር ሃሳብ መስጠት ሲሆን፤ ሃገር አቀፎቹ ማህበራትም በዓለም አቀፍ ደረጃ ሃሳቡን የሚያንጸባርቁ ይሆናል። ገብረእግዚአብሄር ሲያብራራም «5ሺህ ሜትርን ከዳይመንድ ሊግ ማስወጣት ስፖርቱን በጣም የሚጎዳና ለመረሳትም የሚያበቃ ነው። በርቀቶቹ ለዓለም ሻምፒዮና እና ለኦሊምፒክ ብቻ መዘጋጀቱም አስቸጋሪ ይሆናል። ይህንን ተያያዥነት ያለው ስፖርት ማስቀጠል ካስፈለገም 5ሺህ ሜትር መመለስ አለበት የሚለው የፌዴሬሽኑ አቋም ነው። ይህንንም በደብዳቤ ለማህበሩ አሳውቀናል፤ እስካሁን የተባለ ነገር ባይኖርም ወደፊት ግን ምላሽ ይሰጣሉ በሚል ይጠበቃል» ብሏል። የውሳኔ ዜናው እንደተሰማ ከኢትዮጵያም ቀድማ ተቃውሞዋን ይፋ ያደረገችው ጎረቤት ሃገር ኬንያ ነበረች። ነገር ግን በዴንማርክ በተካሄደው የዓለም ሃገር አቋራጭ ሻምፒዮና በኋላ ሃገሪቷ የአቋም ለውጥ ማድረጓን የሚያሳይ ዜና ተሰምቷል። የሀገሪቷ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ከዓለም አቀፉ ማህበር ፕሬዚዳንት ጋር ቆይታ ካደረጉ በኋላ ውሳኔው የተደረሰበት ምክንያት እንዳሳመናቸው ገልጸዋል። ይህ የኬንያዊያን የአቋም መወላወል ኢትዮጵያ የምታቀርበው ተቃውሞ ላይ ተጽእኖ ያሳድር ይሆን የሚለው የብዙዎች ስጋት ነው። አንጋፋው አትሌት ገብረእግዚአብሄር ግን «ተቃውሞው አንድ እና ሁለት መሆኑ ሳይሆን የሚያሸንፈው እውነታው ነው» የሚል\nእምነት አለው። «ወጣቶች\nከአጭር ርቀት በአንዴ ዘለው ማራቶንን መቀላቀል የለባቸውም። በመሆኑም እኛ ደጋፊ ኖረም አልኖረም እውነታውን ይዘን ነው የምንቃወመው። በእነርሱ በኩል የተቃውሞ መቀዛቀዝ ቢኖርም ትክክለኛውን ሃሳብ ይዞ መጓዙ ይሻላል» በማለትም የተቃውሞውን ቀጣይነት ያረጋግጣል።አዲስ ዘመን መጋቢት 30 /2011 ", "passage_id": "3250a503d75327e78d92b138d9603d50" }, { "passage": "ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ያወጣውን አዲስ ህግ ተከትሎ፤ ደቡብ አፍሪካዊቷ የመካከለኛ ርቀት አትሌት ካስተር ሰመኒያ ማህበሩ ላይ ክስ መመስረቷ የሚታወስ ነው። ጉዳዩ በመላው ዓለም መነጋገሪያ ከሆነ የሰነባበተ ሲሆን፤ ዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት የሚያስተላልፈው ውሳኔ በጉጉት እየተጠበቀ ነው። ይህ በእንዲህ አንዳለም የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ካውንስል «ጉዳዩ ሰብዓዊ መብትን የሚጥስ ነው» ማለቱን ቢቢሲ በዘገባው አስነብቧል። ካውንስሉ ሁኔታውን ሲገልጽ «አላስፈላጊ፣ የሚያዋርድ እና ጎጂ» ያለ ሲሆን፤ ማህበሩ በበኩሉ «የተሳሳተ መግለጫ» ብሎታል። ከካውንስሉ ባሻገር በርካታ አካላት በጉዳዩ ላይ አስተያየት እየሰጡ ሲሆን፤ አብዛኛው የአትሌቷን ቅሬታ የሚደግፍ መሆኑም ታይቷል። ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር፤ በተፈጥሯቸው «ቴስቴስትሮን» የተባለው የቅመም መጠን ከፍተኛ የሆነባቸውን ሴቶች የተመለከተና ከተያዘው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ህግ አውጥቷል። ይህም የቅመሙ መጠን ማህበሩ ካስቀመጠው ልኬት ጨምሮ ሲገኝ፤ ከወንዶች ጋር እንዲወዳደሩ፣ የመድሃኒት መጠኑን እንዲቀንሱ አሊያም የሚካፈሉበትን ውድድር ወደ ረጅም ርቀት(10ሺ ሜትር)\nእንዲቀይሩ የሚያደርግ አማራጭም ነው ያስቀመጠው። ይህም በተለይ የደቡብ አፍሪካዊቷን አትሌት ካስተር ሰመኒያን ስሜት በመንካቱ ክስ እስከመመስረት አድርሷታል። የ800 ሜትር\nየሁለት ጊዜ የኦሊምፒክ ሻምፒዮናዋ አትሌት ተክለ ሰውነት እንዲሁም በውድድሮች ላይ የምታሳየው ልዩነት ከዚህ ቀደም ማህበሩን ጥርጣሬ ውስጥ መክተቱ የሚታወስ ነው። በዚህም በህክምና ጾታዋ እንዲለይ እስከማድረግም ተደርሷል። ከዓመታት በኋላም ይህ ደንብ መውጣቱ አትሌቷን ሊያስቆጣ ችሏል። አሁን ላይ የአትሌቷ የቴስቴስትሮን መጠን ምን ያህል እንደሆነ ባይታወቅም፤ እርሷ ግን ማህበሩን ከመታገል ወደኋላ አላለችም። ሌሎች አካላትም ሃሳቧን የሚደግፍ አቋማቸውን በማሳየት ላይ ይገኛሉ። በዩኔስኮ የሰብዓዊ መብት ካውንስልም በቅርቡ ስብሰባውን ባደረገበት ወቅት ይህንኑ እንደ አንድ ጉዳይ በመያዝ መግለጫ አውጥቷል። በዚህም ስፖርቱን ለሚመሩት አካላት «ጫና የሚፈጥሩ ህግና ፖሊሲዎችን በማውጣት ሴት አትሌቶችን መግፋት አላስፈላጊ፣ የሚያዋርድ እና ጎጂ ነው። ሲል ከዚህ እንዲታቀቡ» ጠቁሟል። በእንግሊዝ የሚገኝ አንድ የህክምና መጽሄትም ውሳኔውን የተቃወመ ጽሑፍ አስነብቧል። መጽሄቱ ጉዳዩን አስመልክቶ «ሳይንሳዊ ያልሆነ» በሚል ሲፈርጅ፤ ስለ ቴስቴስትሮን መረጃ ሳይኖር የተደረሰበት ውሳኔ እንደሆነም አትቷል። «የህክምና ሙያ በተፈጥሮ የሚገኘው ቅመም መጠን ብቻውን ለሰውነት ጉልበት ይሆናል አይልም» ይላልም ጽሑፉ። 16 በመቶ የሚሆኑት ወንዶች አነስተኛ ቴስቴስትሮን በሰውነታቸው ሲኖር፤ 14 ከመቶ የሚሆኑት ሴቶች በአንጻሩ ቅመሙ በከፍተኛ መጠን ሰውነታቸው ውስጥ ይኖራል። ይህም ቅመሙን አንዱ ጠቋሚ ያደርገው ይሆናል እንጂ ሚናውን የሚጫወቱት ግን በርካታ ሁኔታዎች እንደሆኑ ጠቁሟል። ጽሑፉ አክሎም «ተጨማሪ ሳይንሳዊ መረጃ የሚያስፈልግ ከሆነም በጤና ላይ ምርምር የሚያደርጉ ሙያተኞችን ማማከር ይገባል። የዚህን ውሳኔ ትክክለኛነት ማጣራትም ታሪካዊ ግዴታ ነው። ማህበሩም ቢሆን ከፍተኛ መጠን ባለው ቴስቴስትሮን እና ብቃት መካከል ያለውን ልዩነት በቅድሚያ ማወቅ ይገባዋል» ሲልም መክሯል። ከተለመደው በላይ መጠን ያለው ቅመም በሰውነት ውስጥ መኖር፣ የአጥንት መስፋት እና የጡንቻ ጥንካሬ ብቻውን የዓለም ስኬታማ አትሌት ሊያሰኝ እንደማይችል የሚያስገነዝበው ደግሞ መቀመጫውን በካናዳ ያደረገ በስነ-ጾታ እና ጤና ላይ ጥናትና ምርምር የሚያደርግ ተቋም ነው። የተቋሙ ዳይሬክተር ካራ ታኔንባም ኤኤፍፒ በሰጡት አስተያየት «ጥሩ አትሌት ለመሆን የሚያስፈልገው ከ10 ሺ ሰዓት በላይ ልምምድ መሥራት፣ ትኩረት፣ ስነ-ምግባር፣ የሰዓት አጠቃቀም፣ አሰለጣጠን እንዲሁም ስትራቴጂ ነው» በለዋል። አክለውም «የቴስቴስትሮን መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ ሴት አትሌቶችን ከመካከለኛ ርቀት የምናስወጣ ከሆነ ግን ከተለመደው በላይ ቁመት ያላቸውን ወንድ የቅርጫት ኳስ ተጫዋቾችን ከስፖርቱ ማራቅ ይገባል ማለት ነው። አንድ ነገር ብቻ በመያዝ በሴቶችና ወንዶች መካከል ልዩነት መፍጠር ሳይንሳዊ አካሄድ አይደለም» ሲሉም ገልጸዋል። የ28 ዓመቷ አትሌት ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽኑ እንዲሁም ከህክምና ባለሙያዎች ላገኘችው ድጋፍም ምስጋናዋን አቅርባለች። «የደቡብ አፍሪካ አትሌቲክስ ማህበርን ጨምሮ የተለያዩ አካላት የሴቶችን መብት በሚጋፋው ደንብ ላይ ላሳዩት ተቃውሞ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ለዓለም አቀፎቹ ተቋማትም በተመሳሳይ» ብላለች። የቀድሞው የመካከለኛ ርቀት አትሌት የአሁኑ የማህበሩ ፕሬዚዳንት እንግሊዛዊው ሎርድ ኮ እየተነሳ ላለው ተቃውሞ ምላሽ ሰጥተዋል። ዘ ቴሌግራፍ ላይ ቀርበው በሰጡት ምላሽ ላይም «ይህንን ደንብ ለማውጣት አስፈላጊ የሆነው፤ በዚህ ሁኔታ ሌሎች ሴቶች አሸናፊ አሊያም የክብረ ወሰን ባለቤት መሆን ስለማይችሉ ነው» ብለዋል። ይህንን ተከትሎም ሰመኒያ ደንቡ የሴቶችን ስፖርት የማያግዝ፤ የፕሬዚዳንቱ ንግግር ደግሞ የቆየውን ቁስል የሚነካ እንደሆነ ነው የጠቀሰችው። የአትሌቷ ጠበቃዎች በበኩላቸው፤ ደንቡ ጾታቸውን ቀይረው የሚሮጡ አትሌቶችን የማበረታታት አዝማሚያ ላይ እንዳለ ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ካስተር ሰመኒያ ከመወለድ ያገኘችውን ተፈጥሮ መቀየር ስለማትፈልግ ህክምና ለማድረግ እንደማትሻ ነው ያስረዱት። «የፕሬዚዳንቱ ሃሳብ ስህተት ነው፤ ሰመኒያ በሩጫው ስኬታማ የመሆን ፍላጎት ላላቸው ሌሎች ሴቶች አርዓያ የምትሆን አትሌት ናት። የእርሷ ህልም ያለ ምንም ፍረጃ እና ጫና መሮጥ ነው፤ ሌላው ዓለምም እርሷን እንዳለች እንዲቀበላት ትፈልጋለች» ማለታቸውን ያስነበበው ደግሞ ኒውስ 24 ነው። ጉዳዩን የያዘው የዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋዮች ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም ጉዳዩ አስቸጋሪ በመሆኑ ጥቂት ጊዜ እንደሚወስድበት አስታውቆ ነበር። ይሁን እንጂ በድጋሚ ምላሽ ሳይሰጥበት እስከ መጪው ወር መጨረሻ ያዘገየው መሆኑን አስታውቋል። ለመራዘሙ ምክንያት የሆነውም በሁለቱም አካላት ያልተሟሉ ነገሮች በመኖራቸው ነው።አዲስ ዘመን መጋቢት 23/2011 በ", "passage_id": "4c4a8af6488598a78e69bd76676f0a58" }, { "passage": "የዓለም\nአቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር እ. ኤ. አ. ከ2020 ጀምሮ አምስት ሺ ሜትር ሩጫ ውድድር ከዲያመንድ ሊግ ፉክክሮች እንዲወጣ ውሳኔ ላይ መድረሱን አስታውቋል፡፡ በዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ከፍተኛው ርቀትም ሦስት ሺ ሜትር ብቻ እንደሚሆንና በአጠቃላይ በወንድና በሴት 12 የውድድር ዓይነቶች ብቻ እንደሚኖሩ ከትናንት በስቲያ ኳታር ዶሃ ላይ ውሳኔ ተላልፏል፡፡ ይህንን ተከትሎም በርቀቱ የዓለምን የበላይነት የያዙት አፍሪካውያን ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ፡፡ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ፕሬዚዳንትና የቀድሞ የአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር የኦሊምፒክ አሸናፊ እንግሊዛዊው ሴባስቲያን ኮ ወደ ስልጣን ሲመጡ የረጅም ርቀት የቀድሞ ዝናና ስም ለመመለስ እንደሚሠሩ ቃል ቢገቡም አሁን ቃላቸውን አጥፈዋል፡፡ ምሥራቅ አፍሪካውያን በተለይም ኢትዮጵያና ኬንያውያን የገነኑበት የረጅም ርቀት ውድድር (አምስትና አስር ሺ ሜትር) ባለፉት ዓመታት እየተዳከመ መሄዱ ይታወሳል፡፡ በተለይም አስር ሺ ሜትር የመም ወይንም ትራክ ውድድሮች በዓመት ውስጥ አንድ ጊዜ እንኳን የማይካሄዱበት አጋጣሚ እየተፈጠረ ይገኛል፡፡ ይህም በርካታ ምሥራቅ አፍሪካውያን አትሌቶች ፊታቸውን ወደ ጎዳናና ማራቶን ውድድሮች እንዲያዞሩ ያስገድዳቸዋል፡፡ ይህ በሆነበት ሁኔታ አምስት ሺ ሜትር ከዳይመንድ ሊግ እንዲሰረዝ መደረጉ ረጅም ርቀት ውድድሮችን እንደመቅበር ይቆጠራል፡፡ በመሆኑ አፍሪካውያንን ቅር ማሰኘቱ አልቀረም፡፡ ጀግናው አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ይህን ውሳኔ ተከትሎ ተቃውሞውን ያሰማ ሲሆን ለሮይተርስ በሰጠው ቃለመጠይቅ የአይ. ኤኤ.ኤፍ ውሳኔ ኢትዮጵያና ኬንያ በእጅጉ ተጎጂ እንደሚሆኑ አብራርተዋል፡፡ ይህ ውሳኔ በርቀቱ የነገሡትንና ባህላቸው ያደረጉትን ምሥራቅ አፍሪካውያንን በአትሌቲክስ ለማዳከም የተደረገ ፍትሐዊ ያልሆነ ውሳኔም ነው ብሎዋል፡፡ የኬንያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትጃክሰን ቱዌ ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረጉት ቆይታ ውሳኔው የአፍሪካ አትሌቲክስን ተጎጂ እንደሚያደርገው በመግለጽ ተቃውመ ዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ለአይ.ኤኤ.ኤፍ ውሳኔውን በመቃወም በፌዴሬሽናቸው በኩል ጠንካራ ደብዳቤ እንደሚልኩ በመግለፅም ከሌሎች አፍሪካ አገራት ጋር በመሆን ውሳኔው እንዲ ቀለበስ እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡ አትሌቲክስን ፈታኝ ስፖርት ከሚያደርጉት ውድድሮች አንዱና ዋነኛው ረጅም ርቀት፣ ማራቶንና የአገር አቋራጭ ሩጫ ነው። እነዚህ ውድድሮች አትሌቲክስን ፈታኝ ብቻም ሳይሆኑ ተወዳጅና ቀልብ ሳቢ ካደረጉት ምክኒያቶች ዋነኞቹ ናቸው፡፡ በእነዚህ ውድድሮች የምሥራቅ አፍሪካውያን የበላይነት እየገዘፈበት ከመጣ ጀምሮ ግን ተወዳጀነቱ እየቀነሰ የሚሰጠውም ትኩረት እያነሰ መጥቷል። ይህም ከአውራው የስፖርት መድረክ ኦሊምፒክና የዓለም ቻምፒዮና እንዲወጡ ከምዕራባውያን በኩል ግፊት እንዲደረግ አድርጉዋል፡፡ በተለይም የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና በየሁለት ዓመቱ ራሱን ችሎ የሚካሄድ ቢሆንም በዋናው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናም ይሁን ከኦሊምፒክ ውጪ ተደርገዋል፡፡ በዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር አገር አቁዋራጭ ውድድርን ወደ ኦሊምፒክ ለመመለስ እንቅስቃሴ ጀምሬያለሁ በሚልበት በዚህ ወቅት አምስት ሺ ሜትርን ከዳይመንድ ሊግ ውጪ ማድረጉ አስገራሚ ነው፡፡ የአገር አቋራጭ ሩጫ በዋናው ኦሊምፒክ መድረክ እኤአ ከ1912 እስከ 1924 በወንዶች መካከል ብቻ ተካሂዶ ነው የተቋረጠው። ከዚህ በኋላ ግን የኦሊምፒክ መርሐግብር መሆኑ ቀርቶ የአትሌቲክስ ጉዳይ ብቻ ሆኖ ቀርቷል። ለዚህ ብዙ ምክኒያቶች በተለያዩ ጊዜዎች የሚቀርቡ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ በተካሄደው የፓሪስ ኦሊምፒክ ላይ በርካታ አትሌቶች ውድድሩ ከብዷቸው ሲፍረከረኩና ራሳቸውን ሲስቱ ጭምር ነበር። ይሁን እንጂ አገር አቋራጭ ሩጫ በተካሄዱባቸው ሦስት ኦሊምፒኮች የፊንላንድ አትሌቶች የበላይነት እንደነበር በታሪክ ተጽፎ ይገኛል። ከዚህ በኋላ የተፈጠረው የአትሌቲክስ ትውልድ በተለይም በረጅምና መካከለኛ ርቀቶች የአፍሪካውያን የበላይነት እየጎላየመጣበት እንደመሆኑ በአገር አቋራጭ የዓለም ቻምፒዮናዎችም ይሁን በግል አፍሪካውያን የበላይነቱን ተቆጣጥረውታል። ይህም አገር አቋራጭ ሩጫ ወደ ኦሊምፒክ እንዲመለስ የሚደረገውን ሂደት እንዳዘገየው የሚያምኑ በርካቶች ናቸው። አፍሪካውያን ይህ ውድድር ወደ ኦሊምፒክ እንዲመለስ ብዙ ጊዜ ታግለዋል። ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ፤ የመም ውድድሮችና የአገር አቋራጭ ውድድሮች ንጉሡ አትሌት ቀነኒሳ በቀለና የኬንያው ታሪካዊ አትሌት ፖል ቴርጋት አገር አቋራጭ ውድድር ወደ ኦሊምፒክ እንዲመለስ ትግል ካደረጉት መካከል ይጠቀሳሉ። በተለይም እነዚህ ሦስት ድንቅ የምሥራቅ አፍሪካ የምን ጊዜም ኮከብ አትሌቶች እኤአ 2008 ላይ ለወቅቱ የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ጃኩዌስ ሮግ በአንድ ላይ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ይታወሳል። ይህን ሃሳብ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበርና በርካታ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የደገፉት ቢሆንም ተግባራዊ ሳይሆን ዘመናትን ተሻግሯል። ለዚህ ደግሞ ምዕራባውያኖች ተፎካካሪ መሆን ስለተሳናቸው ብቻ መሆኑን ልብ ማለት ይገባል፡ ፡ አስር ሺ ሜትርን እያዳከሙ የመጡት ራሳቸው ምዕራባውያን ናቸው፡፡ በአምስት ሺ ሜትርም ተፎካካሪ መሆን ባለመቻላቸው ጠንካራ አትሌቶችን ከማፍራት ይልቅ ውድድሩን እንዲዳከም ማድረግ ምርጫቸው ሆኗል፡፡ ረጅም ርቀት ውድድሮች የበለጠ አፍሪካውያንን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በመሆኑ የአፍሪካ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (ሲ ኤኤ)፤ የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴ(አኖካ)፤ የአፍሪካ ተጽዕኖ ፈጣሪ መገናኛ ብዙሃንና ጋዜጠኞች ግፊት ማድረግ አለባቸው ተብሎ በኦሊምፒክ መድረክ አሜሪካና ምዕራባውያን በርካታ ሜዳሊያ በመሰብሰብ የበላይነት ይዘው የሚያጠናቅቁት በአንድ ስፖርት ዓይነት ብቻ ከአስር በላይ ሜዳሊያ መሰብሰብ የሚያስችላቸው ዕድል ስላላቸው ነው። ለዚህም በውሃ ዋና ውድድር አንድ አትሌት ብቻ ከአስር በላይ የወርቅ ሜዳሊያ የሚያፍስበት አጋጣሚ እንዳለ ማስቀመጥ ይቻላል። ምዕራባውያኑ እንዲህ ዓይነቱ አጋጣሚ በኦሊምፒክ እንዲስፋፋና የበላይነታቸውን ይዘው እንዲዘልቁ ያገኙትን ዕድል ይጠቀማሉ። አሁንም በቀጣዩ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ እንኳን የነሱ ፍላጎት ያለባቸው ወይንም ሜዳሊያ ያስገኝልናል ብለው ያሰቡትን ማንኛውንም እንቅስቃሴ የኦሊምፒክ ስፖርት እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡ ለዚህም በቀጣዩ ኦሊምፒክ ብሬክ ዳንስ ሳይቀር እንዲካተት አድርገዋል፡፡ አፍሪካውያንም ከምዕራባውያን ጋር በኦሊምፒክ ተፎካካሪ ሆነው ለመገኘት እንደ አገር አቋራጭ ሩጫ ዓይነት ውድድሮችን ከመጠቀም ባለፈ ረጅም ርቀቶች ላይ ያንዣ በበውን አደጋ ለማስቀረት በጋራ መጋፈጥ ግድ ይላል፡፡ ከአሁኑ ካልታገሉ ግን እንደ አገር አቋራጭ ውድድር ሁሉ አስርና አምስት ሺ ሜትር ውድድሮች በቅርቡ ከየትኛውም ውድድር ላለመሰረዛቸው ማስተማመኛ አይ ኖርም፡፡አዲስ\nዘመን መጋቢት 5/2011በቦጋለ\nአበበ", "passage_id": "0a22757201500271f1758c596fc216a9" }, { "passage": "ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሎራ የሚል ስያሜ የተሰጠው ሃሪኬን ወይም ከባድ ዝናብ የተቀላቀለበት የአውሎ ነፍስ ማዕበል፣ ዛሬ ማለዳ ላይ በደቡብ ምስራቋ ክፍለ-ሀገር ሊዊዝያና ላይ ካረፈ በኋላ፣ በመጠኑ እንደተዳከመ ተገልጿል። ክፍለ-ግዛቱ ላይ ሲያርፍ፣ አደገኛ የሆነው አራተኛ ደረጃ የተሰጠው፣ የአውሎ ነፋስ ማዕበል ነበር። ከፍተኛው ቁጥር አምስት ነው።የሀገሪቱ ብሄራዊ የሃሪኬን ማዕከል በገለጸው መሰረት፣ በአሁኑ ወቅት ሃሪኬን ሎራ፣ በሰዓት 195 ኪሎ ሜትር እየነፈሰ ሲሆን፣ ወደ ሦስተኛ ደረጃ ወርዷል።", "passage_id": "27af0dc65581b5a31f05368dd6a50adc" }, { "passage": "ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ስፖርት ስሟ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ሀገራት ተርታ ትመደባለች፡፡ በተለይም ማራቶንን ጨምሮ በረጃጅም ርቀት የአትሌቲክስ ዘርፎች የስፖርቱ ቁንጮ ሆና ቆይታለች፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስም ይህንኑ ክብሯን አስጥብቃለች፡፡ ሆኖም ዛሬ የረጅም ርቀት የአትሌቲክስ ክብሯ በጎረቤት ሀገር ኬንያ ከተነጠቀ ቆየትየት ብሏል፡፡ኦዲቲ ሴንትራል የተሰኘው ድረገፅ ከሰሞኑ ያወጣው ዘገባ ደግሞ ከአትሌቲክስ ውድድሮች ሁሉ ቁንጮ የሆነው የማራቶን ሩጫ ከከተማ ጎዳናዎች ውጪ እንደዚህም ይካሄዳል ይላል፡፡ኦይማያኮን የተሰኘችው በሩሲያ የምትገኝ መንደር አማካይ የሙቀት መጠኗ ከዜሮ በታች ከ50 ዲግሪ ሴሊሺየስ ፈቀቅ የማይልና እጅግ ቀዝቃዛ ከሆኑ የዓለማችን ቦታዎች ውስጥ አንዷ ናት፡፡ በዚህ የተነሳም ሰዎች ለፊታቸው መከላከያ ሳያደርጉ ቢንቀሳቀሱ በሰከንዶች ውስጥ ፊታቸው በቅዝቃዜው ምክንያት ይሰነጣጠቃል፤ በቴርሞ ሜትር ውስጥ የሚገኘው ሜርኩሪ ሳይቀር ይቀዘቅዛል፡፡መንደሯ ለኑሮ ምቹ ናት ተብሎ ቢታሰብም ቀዝቃዛ የአየር ጠባይዋ ግን ስፖርታዊ ወድድርን ለማካሄድ አደገኛ እንደሆነ ይነገርላታል፡፡ ሆኖም በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መግቢያ ቅዝቃዜዋን ለመጋፈጥ በቆረጡ 16 አትሌቶች አማካኝነት በታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የቀዝቃዛ ማራቶን ውድድር አካሂዳለች፡፡ጥር 5 በተካሄደው በዚሁ ውድድር ዕድሜያቸው ከ21 እስከ 71 ዓመት ውስጥ የሚገኙና በደንብ የሰለጠኑ ደፋር ሯጮች ቅልጥም በሚሰብረው የ42 ኪሎሜትር የማራቶን ሩጫ ውድድር ለ 5፣10፣20፣30 እና 42 ኪሎ ሜትር ተፎካክረዋል፡፡ውድድሩ ሲጀመር የቦታው የሙቀት መጠን ከዜሮ በታች 52 ዲግሪ ሴሊሺየስ በመሆኑ ለሯጮቹ እጅግ ፈታኝ የነበረ ሲሆን የመጨረሻው ተወዳዳሪ 39 ኪሎሜትር ላይ ሲደርስ የሙቀት መጠኑ 4 ዲግሪ ሴሊሺየስ ብቻ ነበር የቀነሰው፡፡‹‹ቀዝቃዛውን የማራቶን ወድድር ለመታደም ከአውስትራሊያ፣ ታይዋን ፣ጃፓንና ህንድ የመጡ ቱሪስቶች በውድድሩ እጅግ ተደንቀዋል›› ሲል ሳርጂላን ኒዮስትሮይቫ የተሰኘው የውድድሩ ተሳታፊ ገልጿል፡፡‹‹እጅግ ቀዝቃዛ የማራቶን ወድድር ስናዘጋጅ ይህ የመጀመሪያችን ነው፤ በቀጣዩ ዓመት ሌላ ውድድር በዚሁ ቦታ እናዘጋጃለን፡፡ ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ አትሌቶችንም እንቀበላቸዋለን›› ሲልም ተደምጧል፡፡የማራቶን ውድድሩን ከዜሮ በታች 45 ዲግሪ ሴልሺየስ በሆነ የሙቀት መጠን በማካሄድ ውድድሩ ተቀባይነት እንዲኖረውና አትሌቶች በቅዝቃዜ መሮጥ እንዲለምዱ ማድረግ እንፈልጋለን›› ሲልም ሌላኛው የውድድሩ ተሳታፊ ይጎር ብራሞቭ ጨምሮ ጠቁሟል፡፡በዚህ ቀዝቃዛ የማራቶን ሩጫ ረጅሙ ኪሎሜትር የተሸፈነው ኢሊያን ፔስቴሬቭ በተሰኘው የኢሚሳ መንድር ኃላፊ ሲሆን፣ እሱም 39 ኪሎሜትር ሮጧል፡፡ የውድድሩ ወጣት ተሳታፊ ደግሞ የሃያ አንድ ዓመቱ ኢኖኬነቲ ኦሌሶቭ ሲሆን 10 ኪሎ ሜትሩን በ 1 ሰዓት ከ8 ደቂቃ ሲያጠናቅቅ በዕድሜ ትልቁ የውድድሩ ተሳታፊ የ71 ዓመቱ ይጎር ፔርማያኮቭ 15 ኪሎሜትሩን ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት ተኩል እንደፈጀበት ዘገባው ገልጿል፡፡አዲስ ዘመን ጥር 7/2011አስናቀ ፀጋዬ", "passage_id": "30dccbb3a796d654780bc2fa22c3fb67" } ]
29e4a62e56bc0a30b52455f25f77cb6d
7c47f9a75ff3e98196a243494a6afca1
የቢሮ ሕንፃው ያሰጋቸው ሄልሜት አጥልቀው የሚኖሩ ህንዶች
መንግሥት ከህዝብ ከሚሰበስበው ግብር የዜጎችን መሠረታዊ ፍላጎት ማሟላቱ ግድ ነው፡፡ ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብለው የመንግሥት የዕለት ተዕለት ሥራ እየሠሩ ደግሞ በአለቆቻቸው ችላ ከተባሉ የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር አለ ማለት ነው፡፡ ወይም አመራሩ ምንዝሩን (የበታቹን ሠራተኛ) በማማረር አልያም አለቃው በመደናበር ግዴታውን ያለመወጣቱ ማሳያ ነው፡፡ ሕንፃቸው እያሰጋቸው መሆኑን ለመንግሥትና ለመገናኛ ብዙኃን ተደጋጋሚ አቤቱታ ሲያቀርቡ የነበሩ ህንዳውያን ተሰላችተው ‹‹ለቢሮ ሥራቸው ሄልሜት አጥልቀው መሥራት ጀመሩ፡፡›› ይለናል የኦዲቲ ሴንተራል ዘገባ፡፡ በግሌ የአለቆችን ቸልተኝነት ብንቅም የህንዳውያን ምንዝሮች ሥራን ግን አደንቃለሁ፡፡ እኛ ብንሆን ኖሮ ሕንፃ ለመደርመስና ሕይወት ለማፍሰስ እንሮጥ ነበር፡፡ ህንዳውያኑ ሀገራቸውን ስለሚወዱ መንግሥት ቢሮክራሲ በማብዛት ችላ ቢላቸውም ለሀገራቸው ለመሥራት ግን አልቦዘኑም፤ ሀገራቸውንም ችላ አላሉም፡፡ በህንድ ኡተር ፓራዳሽ ግዛት ባንዳ ከተማ የሚገኙ እነዚህ የመንግሥት ሠራተኞች የሞተር ሳይክል ሄልሜት (የራስ ቅልን ከአደጋ መከላከያ) አጥልቀው የቢሮ ሥራ እየሠሩ በቅርቡ በማኅበራዊ ድረ ገፅ የብዙዎችን ትኩረት ስበው ነበር፡፡ ምናልባት የሕንፃው ጣራ በላያቸው ላይ ሊራገፍ ቢችል ተብሎ መሆኑን የኦዲቲ ሴንተራል ዘገባ አስረድቷል፡፡ በከተማው የኤሌክትሪክ ክፍል ቅጥር ሠራተኞች ትልልቅ የሞተር ሳይክል ሄልሜት ለጭንቅላታቸው አጥልቀው ቢሯቸው ሲሠሩ የሚያሳዩ ፎቶዎችን ማኅበራዊ ትስስር ገፆችና የህንድ ዜና አገልግሎት ተጋርተውታል፡፡ አብዛኛዎቹ ምንጮች የመንግሥት ተቀጣሪዎቹ የሞተር ሳይክሎች ደጋፊ ወይም አቃፊ አይደሉም። ቀስ በቀስ እየተፈረካከሰ ያለው ጣራ ግን እንዳይጎዳቸው ጭንቅላታቸውን ለመከላከል ሊሆን ይችላል፡፡ ከዓመታት በፊት ለሪፖርተሮች የጽህፈት ቤቱ ሕንፃ እንደሚያሰጋቸው ቢናገሩም ማንም መፍትሔ የሚሰጥ አልተገኘም፡፡ እናም የራስ ቅላቸውን ከአደጋ ሊከላከል የሚችለውን ሄልሜት አጥልቀው ወደ ቢሮ እየገቡ ለመሥራት ወስነው ተገበሩት፡፡ ‹‹ይህን መሰል ሁኔታ ያጋጠመን እኔ ከተቀላቀልኩ ከሁለት ዓመት በፊት ነው፡፡ ለባለሥልጣኖች ጽፈን ነበር ግን ጆሮ ዳባ ልበስ አሉን፡፡›› ሲሉ ከተቀጣሪዎች መካከል ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰብ ለህንድ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል፡፡ የዛሬይቱ ህንድ የተባለ ጋዜጣ እንደዘገበው፤ የጽህፈት ቤቱ ሠራተኞች አንዲት ስንስዝር ያጋነኑት ነገር የለም፡፡ በቤቱ መካከል ጣራው እንዳይፈረካከስ የሚረዳ ምሰሶ ወይም አምድ ቢኖረውም ጣራዎቹ በቀዳዳዎች የተሞሉ ናቸው፡፡ የሚገርመው በህንድ ቢሮዎች የሞተር ሳይክል ሄልሜት አጥልቀው የሚገቡ ሠራተኞች በዜና ሲዘገብ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ እኤአ ከ2017 ወዲህ በተሰነጣጠቀ የመንግሥት ሕንፃ ውስጥ ስለሚሠሩ ሠራተኞች ቢሀር በሚባል አካባቢ በተመሳሳይ መልኩ የቢሮ ሥራቸውን ለመሥራት በስጋት ሄልሜት ለማጥለቅ እንደተገደዱ ተዘግቦ እንደነበር የኦዲቲ ሴንተራል ዘገባ ያመለክታል፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 05 ቀን 2012 ዓ.ም ኃይለማርያም ወንድሙ
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=22780
[ { "passage": " ከሦስት ወራት በፊት መጋቢት 20 ቀን 2011 ዓ.ም በታተመው አዲስ ዘመን ጋዜጣ «ዓመታትን የዘለቀው የላስቲክ ቤት ነዋሪዎች እሮሮ» በሚል ርዕስ በሰንጋ ተራ 9 ዓመታትን በላስቲክ ቤት ውስጥ ያሳለፉ ሰዎችን ሕይወት የተመለከተ ዘገባ አቅርቦ ነበር። በወቅቱ አዲስ ዘመን ያናገራቸው የልደታ ክፍለ ከተማ አመራሮችም ችግሩን ለመፍታት እንደሚጥሩ ተናግረው ነበር። ክፍለ ከተማው ቃሉን ጠብቆ በላስቲክ ቤት ነዋሪ ከሆኑት መካከል ለ30 ዎቹ 10/90 ኮንዶሚንየም ቤት ሰጥቷል። ከአንድ ወር በፊትም ለ35 የላስቲክ ቤት ነዋሪዎች የቀበሌ ቤቶችን ለመስጠት የዕጣ አወጣጥ ሥነሥርዓት ሲደረግ አዲስ ዘመን በቦታው ተገኝቶ ሁኔታውን ተከታትሏል። አዲስ ዘመን በዚህ ሳያበቃ የቀበሌ ቤቶቹ በዕጣ የተሰጧቸው የላስቲክ ቤት ነዋሪዎች ያሉበት ድረስ በመሄድ እንዴት ዓይነት ቤቶች እንደተሰጧቸው ተመልክቷል። በዕጣ ቤት ተሰጣቸው የተባሉት ሰዎች ቤቶቹን ለማየት ቦታው ድረስ ሲሄዱ ፈጽሞ ያልጠበቁት ነገር እንደገጠማቸው ለአዲስ ዘመን ገልጸዋል።በሰንጋ ተራ\nመልሶ ማልማት ቦታ ዘጠኝ ዓመታትን ላስቲክ ቤት ውስጥ የኖሩት የሁለት ልጆች እናት ወይዘሮ ጥሩነሽ ፍቃዱ ቤት ተብሎ የተሰጣቸው ጣሪያና ግድግዳ የሌለው ዘጠኝ ዓመት ፈርሶ የተቀመጠ ባዶ መሬት መሆኑን ይገልጻሉ። እርሱንም ከግራና ቀኝ ካሉት ነዋሪዎች አንደኛው ቦታውን አልፈው ሰርተውበታል የሚሉት ወይዘሮዋ የቀረው ሁለት ሜትር በሁለት ሜትር እንኳን የሚሆን ቦታ አይደለም ብለዋል። የተሰጣቸውን ባዶ\nመሬት እያሳዩ «ይህንን ባዶ መሬት ቤት ነው ብለህ አትኖርበትም። እንኳን የሰው ልጅ ውሻ እንኳን አይተኛበትም። ላስቲክ እንኳን ወጥሬ ልጆቼን ሰብስቤ እገባበታለሁ የምልበት ቦታ አይደለም።» ሲሉ ይገልጹታል። ለክፍለ ከተማው ቅሬታ ሳቀርብ የክፍለ ከተማው ቤቶች አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ሲሳይ «ለእናንተ ጣሪያና ግድግዳ ያለው ቤት እንዴት ይሰጣችኋል? የላስቲክ ቤት ነዋሪዎች የድሃ ድሃ ተብላችሁ ነው ይህንም ታግለን የሰጠናችሁ በጣም ትቀልዳላችሁ። የምትወስጂ ከሆነ ውሰጂ፤ ብትፈልጊ አትውሰጂ፤ አልፈልግም ብለሽ ፈርመሽ ውጪልኝ» ብለውኛል የሚሉት ወይዘሮ ጥሩነሽ ፍቃዱ እኔ ቤት የመገንባት አቅሙ ቢኖረኝ ኖሮ ሜዳ ላይ ከስምንት ዓመት በላይ እተኛለሁን? ሲሉ ይጠይቃሉ።ዘጠኝ ዓመታትን በላስቲክ ቤት መጠለያ ውስጥ መኖራችንን በሚገባ በመግለጽ ለሚመለከተው አካል ለማድረስ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ለሰራው ዘገባ እጅግ በጣም አድርጌ አመሰግናለሁ በማለት ሀሳባቸውን መግለጽ የጀመሩት አቶ ጌታቸው ከበደ፣ 20 እና 30 ሺ ብር አውጥተን ቤት መገንባት የምንችልበት አቅም ቢኖረን ኖሮ ዘጠኝ ዓመት ሙሉ ችግሮች ተጋፍጠን ሜዳ ላይ የምንኖርበት ምክንያት አይኖርም ነበር ብለዋል። ቤቶቹ የፈራረሱና የሚጠገኑ መሆናቸውን አስቀድመው ነግረውናል፤ የሚሉት አቶ ጌታቸው ዕጣ ወጥቶ ሄደን ስናይ ያገኘነው ባዶ መሬት ነው። ሊያውም ሁለት በሁለት ሜትር ወይም ሁለት በሦስት የሆነ አልጋ እንኳን የማያዘረጋ ነው። በዚያ ላይ ከሽንት ቤት ጋር የተያያዘ ወይም ሽንት ቤት አቋርጦት የሚሄድና የሚፈልቅበት ስፍራ ሆኖ ነው ያገኘነው፤ እኛ በዚህ ደረጃ አልጠበቅንም ነበር ብለዋል።አቶ ጌታቸው «የቤት ዕጣ የወጣልን ከአንድ ወር በፊት ቢሆንም አሁንም ጎርፉን ችለን ለዓመታት በኖርንበት ላስቲክ ቤት ውስጥ እየኖርን ነው። ከሰላሳ አምስቱ ሰዎች አራትና አምስት ሰዎች ናቸው ቤት የደረሳቸው። የአብዛኞቹን አይቻለሁኝ ወንዝ ዳር፣ ሜዳና ሽንት ቤት የሚፈስበት ኦና መሬት ነው የተሰጣቸው። አሁን ደግሞ የላስቲክ ቤታችሁን አፍርሳችሁ የሰጠናችሁ ባዶ ቦታ ላይ ላስቲክ ወጥራችሁ ኑሩ ነው እየተባልን ያለነው» ሲሉ እየተደረገ ያለው ነገር እጅግ ግራ እንዳጋባቸውና እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።በመኪና አደጋ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ከደረሰባቸው ባለቤታቸው ጋር ለዓመታት ላስቲክ ቤት ውስጥ የኖሩት አቶ ተስፋዬ በቀለም ውሃ የሚያልፍበት ምንም ነገር የሌለው ባዶ መሬት ተሰጥቷቸዋል። ከተሰጠን ቦታ አሁን እየኖርን ያለንበት ላስቲክ ቤት ይሻላል የሚሉት አቶ በቀለ፣ የተሰጡን የቤት ቁጥር የሚጠቀስላቸው ነገር ግን ቤት የሌላቸው ባዶ መሬቶች ናቸው። እኛ ቤት የመስራት አቅም የለንም ብለዋል።የልደታ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ እንድሪስ በዕጣ አወጣጥ ሥነሥርዓቱ ወቅት ስለቤቶቹ ሁኔታ ሲናገሩ «ክፍለ ከተማው ላይ ያለውን ሙሉ አቅም አሟጠን ጥገና ሊደረግላቸው የሚገባ ሰላሳ አምስት የፈራረሱ ቤቶችን ሰጥተናቸዋል። ነዋሪዎቹን ፣ ወረዳውንና ሌሎች የልማት አካላቶችን አስተባብሮ አስፈላጊ የሆነውን ድጋፍ በማድረግ ጥገና ተደርጎላቸው ሊኖርባቸው የሚችሉ እንዲሆኑ ታስቦ የተደረገ ነው።» ብለው ነበር።ለልደታ ክፍለ ከተማ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ለአቶ ብሩክ ከድር «የቤት ቁጥር ያለው ነገር ግን ባዶ መሬት በቀበሌ ቤት ስም መሰጠት ነበረበትን?» በሚል አዲስ ዘመን ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ «በእኛ ክፍለ ከተማ 19 ሺህ ገደማ የቀበሌ ቤቶች አሉ። እነዚህ ቤቶች ረጅም ዓመታት በመቆየታቸው ግማሾቹ ፈርሰዋል፤ ቀሪዎቹ ደግሞ ለኑሮ አመቺ ባልሆነ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ናቸው። የሰጠናቸው ቤቶች ይዞታቸው ቢፈርስም የቤት ቁጥር አላቸው፤ ሙሉ ለሙሉ ያልፈረሱም አሉ። እነዚህን ቤቶች እንደ አማራጭ ስንሰጣቸው እንደግፋችኋለን ብለን ነው። ለምሳሌ በክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ ሥራን በማስተባበር በጥገና ጭምር እገዛ እናደርጋለን ብለናል። ቤቶቹ በተለያየ ምክንያት የፈረሱ ቢሆኑም የቀበሌ ቤት መሆናቸውን የሚያሳይ የቤት ቁጥር አላቸው» ብለዋል። «የምንቀበለው እውነታ ሰዎቹ መደገፍ አለባቸው። እኛ እንደ ክፍለ ከተማ በወጣቶች በጎ ፍቃድ እንቅስቃሴ ብዙ ቤቶች አስጠግነናል። ሙሉ ለሙሉ አቅም ለሌላቸውም የጉልበትና የቁሳቁስ ድጋፍ እናደርጋለን። ያለው የድህነት ደረጃ ጥልቅ ስለሆነ ፍላጎቱም ከፍተኛ ነው። ያን ተከትሎም ችግር አልፈታችሁልንም የሚለው ቅሬታ ሰፊ ነው። በ2011 ዓ.ም ብቻ ከ155 ቤቶች በላይ ጠግነናል፤ በያዝነው ክረምትም መቶ ቤቶችን የመጠገን ዕቅድ ይዘናል። ያቀረቡት ቅሬታ ተገቢ ነው። ጉዳያቸውን በልዩ ሁኔታ አይተን ምላሽ ለመስጠት ጥረት እናደርጋለን ብለዋል»።አዲስ ዘመን ሐምሌ 10/2011 ", "passage_id": "136a390aed784d3ace329fd7f8375f56" }, { "passage": "እናት ህፃን ልጇን አዝላ ከገበያ እየተመለሰች ነው፡፡ በዘንቢሏም እቤት ለሚጠብቋት ልጆቿ የሚሆን ሙዝ፣ ሸንኮራ አገዳና መሰል ቁሶች ይዛለች፡፡ የእናታቸውን ከገበያ መመለስ የተመለከቱ ህፃናት ልጆቿና ውሻቸው እናቲቱን ለመቀበል ወደ እሷ ሲሮጡ የሚያሳየው ሥዕል ዓይንን ጨምድዶ የሚይዝ ቅርፅ ነው፡፡ የግርማችን ፒ ኤል ሲ ሥራ አስኪያጅና የአክሲዮኑ አባል አቶ አንዷለም ግርማ “ከሁሉ በላይ ይኼ ምሥል ልቤን ይገዛዋል፡፡ ይህ ነገር የእኔም፣ የአንቺም የሁሉም ሰው እውነተኛ የህይወት ነፀብራቅ ነው” ይላሉ፡፡ ገበያ ሄዳ ሸንኮራና ሙዝ ለልጇ ይዛ ያልመጣች እናት አለች ብለው እንደማያምኑም አጫውተውኛል፡፡ ሌሎች ሥዕሎችም በብዛት ይታያሉ፡፡ በህንፃው ስር ባለው ሰፊ በር ወደ ውስጥ ሲዘልቁ ነው የቤቱን ተዓምራት መመልከት የሚጀምሩት፡፡ ገና ሲገቡ መሬት ላይ ባለው ሰፊ ባር መሀል ላይ ትልቋና ባለ ግርማ ሞገሷ ንስር፣ ክንፏን ዘርግታ ምንቃሯን ከፈት አድርጋ ይመለከታሉ፡፡እሱን አይተው ሳይጠግቡ ንስሯ በተቀረፀችበት ፏፏቴ ዙሪያ የተደረደሩት የዝሆን ምስል ያላቸው ወንበሮች እንደገና ያስገርምዎታል፣ እዛው ላይ ቆመው ዞር ዞር እያሉ ግድግዳውን መቃኘት ሲጀምሩ ደግሞ “ለመሆኑ ይኼ ቤት ሆቴል ነው ወይስ ሙዚየም” ብለው እንደሚጠይቁ ጥርጥር የለኝም፡፡ በግድግዳው ላይ ተቀርፀው በልዩ የቀለም ህብር ካማሩ ሥዕሎች ውስጥ ፍቅር፣ ጭፈራ፣ የአባ ገዳ ሥርዓት፣ የእርቅ ሥርዓት፣ የፈረስ ግልቢያ፣ የክሊዮፓትራ ምስል፣ የገጠሩ ሕዝብ አኗናር…በስዕልና በቅርጽ ያልተዳሠሠ ነገር የለም፡፡ ይህን ትንግርት የሚመለከቱት በአዳማ ከተማ መብራት ኃይል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቀበሌ 06 ሞቅ ደመቅ ካሉት የምሽት ጭፈራ ቤቶች በአንዱ ነው፡፡ ታዲያ ለሥራም ይሁን ለመዝናናት ወደ ከተማዋ ጐራ ያለ ማንኛውም ሰው፣ አካባቢውን ሳይጐበኝ ይመለሳል ለማለት ይቸግራል፡፡ አንዳንዶች አካባቢውን “የአዳማው ቺቺኒያ” ይሉታል፡፡በዚሁ አካባቢ ግን አንድ ትልቅ ኤግል ተፈጥሯል፡፡ ኤግሉ ከዚህም በፊት የነበረና ገበያ የነበረው ሆቴል ሲሆን ወደ ትልቅ ኤግልነት ለመቀየር አራት አመት ፈጅቷል፡፡ ተጠናቆ ስራ ከጀመረም ገና ሦስት ወሩ ነው፡፡ የቤተሠቡ ጊዜና ጉልበት ሳይታሠብ 55 ሚሊዮን ብር የጨረሠው አዲሱ ኤግል፣ 40 የመኝታ ክፍሎችን የያዘ ባለ ሰባት ፎቅ ህንፃ ነው፡፡ ኤግል ሆቴል በአምስት ወንድማማቾች፣ በእህትና በእናታቸው በወ/ሮ አበበች ወ/ሥላሴ የተመሠረተ አክሲዮን ነው፡፡ የቤተሰቡ መነሻ አርሲ ውስጥ በአርባ ጉጉ አውራጃ ጮሌ በተባለች መንደር ውስጥ ሲሆን አባታቸው አቶ ግርማ ኃይሉና ባለቤታቸው ወ/ሮ አበበች ወ/ሥላሴ የቢዝነስ መሠረታቸው ሆቴል እንደሆነ የአክሲዮኑ ሥራ አስኪያጅ አቶ አንዷለም ግርማ ይናገራሉ፡፡ልጆቻቸውን በፍቅርና በስራ ገርተው ያሣደጉ ጠንካራ ወላጆች እንደነበሩ የሚናገሩት አቶ አንዷለም፤ ታላላቆቻቸውም ሆነ ታናናሾቻቸው ከልጅነት ጀምሮ ደረጃ በደረጃ ሥራን ከቤተሠብ ጋር እየለመዱ እየተዋደዱና እየተከባበሩ ማደጋቸውን ይገልፃሉ፡፡ “ለምሣሌ እኔን ብትወስጂ አርሲ በነበረን ሆቴልና ሥጋ ቤት ውስጥ ለሰው ስጋ በማድረስ፣ ከዚያ ለቆራጭ በማቀበል ብሎም ሥጋ ቆራጭ በመሆን ደረጃ በደረጃ ሠርቻለሁ” በማለት የስራ ተሞክሯቸውን አጫውተውኛል፡፡ “የቤተሰቡ ትልቁ የትምህርት ደረጃ 12ኛ ክፍልን ማጠናቀቅ ነው፣ ከዚያ በላይ የተማረ የለም” ያሉት አቶ አንዷለም ፤ ከሰባት ዓመት ዕድሜያቸው ጀምሮ አዳማ ውስጥ እንዳደጉ ይናገራሉ፡፡ ትልቁ ኤግል ከመሠራቱ በፊት ከኪራይ ቤቶች የተከራዩት ትንሽ ሆቴል እንደነበር ገልፀው፤ ትንሹም ሆቴል በጣም ደማቅና የከተማዋን ሁኔታ ያገናዘበ እንደነበር ያብራራሉ፡፡ “ሆቴሏ በጣም ብዙ ገበያና ጥቅም የምታስገኝ ነበረች” የሚሉት የፒኤልሲው ስራ አስኪያጅ፤ በቤተሠቡ ውስጥ ያለው ትልቅ ነገርን መስራት እንደሚቻል የማመን ብቃት አሁን ትልቁን ኤግልና በውስጡ የዓይን ማረፊያ የሆነውን የባህል የፍቅር፣ በአጠቃላይ የጥበብ ሥራ መፍጠሩን ገልፀው፤ ወረቀት ላይ ያሠፈሩት ቅርፅና ሥዕል በቤተሰባችን አዕምሮ ውስጥ ተቀርፆ ያለቀውን ነው” ይላሉ አቶ አንዷለም፡፡የተዋበ ሆቴል ለመሥራት የነበራቸውን ፍላጎት ሲናገሩ “ሰው በመጠጥና በምግብ ሰውነቱን ከመሙላት ባለፈ አዕምሮውም ምግብና እረፍት እንደሚያስፈልገው በማመን ነው የሠራነው” የሚሉት ሥራ አስኪያጁ፤ ይኼ ሲሠራ ግን ቀጥታ ዒላማው ገንዘብ ያመጣል የሚል ሳይሆን ሰዎች የበለጠ ምቾት እንዲሰማቸው ማድረግ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ወደ ሆቴሉ ቅኝት ስንመለስ ፏፏቴው ሲለቀቅ የተለያዩ ትዕይንቶች ይታያሉ፡፡ ለምሳሌ ኤግሏ የተቀረፀችው ወፎች ውሃ ሲነካቸው ለማራገፍ ክንፋቸውን በሚዘረጉበት ዓይነት ነው፡፡ ከሁሉም ያስገረመኝ ቅርፅ ደግሞ እነሆ፡- አንዲት እንቁራሪትና አንድ ህፃን ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀምጠዋል፡፡ ፏፏቴው ሲለቀቅ እንቁራሪቷ ህፃኑ ላይ ትተፋለች፤ ህፃኑ ደንግጦ ሲያያት የሚያሳይ ቅርፅ ነው፡፡ ነገሩ ለህፃናት መዝናኛነት ታስቦ ቢሠራም ትልልቆችንም የሚያፈዝ ነው፡፡ ሁለቱን ፎቅ ወጥተው ቴራሱ ላይ ሲደርሱ እንደ ፔንዱለም ወዲህ ወዲያ የሚወዛወዝ ወንበር ያገኛሉ፡፡ ይህ ወንበር መኻል ላይ ጠረጴዛ ያለውና ፊት ለፊት ለሚቀመጡ ሰዎች በተለይም ህፃናት እየተወዛወዙ እንዲዝናኑ የታሰበ ቢሆንም በወንበሩ እየተወዛወዙ ሲዝናኑ ያየናቸው ግን አዋቂዎች ናቸው፡፡ አጠቃላይ የሆቴሉ አሠራር የአምፊ ቴአትር (ጣሪያ የሌለው) አይነት ነው ፤ለምሣሌ ቴራስ ላይ ቁጭ ብለው አቆልቁለው፣ አሊያም አግድመው በየፎቆቹ ላይ ያሉትን ትዕይንቶች በግልፅ ለመመልከት ምቹ ነው፡፡ በሆቴሉ የተለያዩ ግድግዳዎች ላይ በፈረንሳይኛ፣ በጀርመንኛና በቻይንኛ ቋንቋ ኤግል ሆቴል የሚሉ ፅሁፎች ተፅፈዋል፡፡አቶ አንዷለም ስለዚሁ ሲያስረዱ፤ ትንሿ ኤግል እያለችም ሆነ አሁን ትልቁም ከተሠራ በኋላ የሦስቱም አገር ዜጐች የሆቴሉ ተጠቃሚዎች በመሆናቸው የእነሱን ቀልብ ለመሳብ የተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ሆቴሉ የተሠራው የከተማዋን ነዋሪ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው ያሉት አቶ አንዷለም፤ ከከተማው ነዋሪ በተጨማሪ ከሌላ ቦታም የሚመጣ ሰውና የውጭ አገር ቱሪስቶችም የሚስተናገዱበት እንደሆነ ያብራራሉ፡፡ “ቤቱ ደረጃውን የጠበቀ ነው፤ ነገር ግን ቢራ 17 ብር ይሸጣል፣ ድራፍት 13 ብር ነው ይሄ ቫትን ጨምሮ ነው” የሚሉት ስራ አስኪያጁ፤ ምግብም ቢሆን በ40 እና በ50 ብር መካከል መሆኑን ይናገራሉ፡፡ አልጋዎቹ ሶስት ደረጃ ያላቸውና ደረጃቸውን የጠበቁ ሲሆኑ ከ280 ብር እስከ 480 ብር ዋጋ ተተምኖላቸዋል፡፡ ይኼም አቅምን ግምት ውስጥ አስገብቶ የተተመነ እንደሆነ አቶ አንዷለም አጫውተውናል፡፡ ሆቴሉ በአሁኑ ሰዓት ለ235 ቋሚ ሠራተኞች የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በሆቴሉ የሰው ኃይል አስተዳደር ሆነው በኃላፊነት እየሠሩ የሚገኙት አቶ አቡ፤ የብዙ ሙያ ባለቤት ናቸው፡፡ከመምህርነት ሙያ ጀምሮ በርካታ ሥራዎችን ሰርተዋል፡፡ በሆቴሉ የቅርፃቅርፆች ሥራ ላይ በስፋት የተሳተፉ ሲሆን በውስጣቸው የነበረውን የአርት ሙያ እዚህ ሆቴል ቅርፃቅርፆች ላይ እውን በማድረጋቸው ደስተኛ ናቸው፡፡ “በኤግል ሆቴል ግንባታ ውስጥ አንድም አርት ያልሆነ ነገር የለም” በማለት አስተያየታቸውን የጀመሩት አቶ አቡ፤ ኤግሏን ለመስራት በተለይ ማንቁርቷ በርካታ ጊዜ ፈርሶ እንደተሠራ ይገልፃሉ። ኤግል በአለም ላይ በርካታ ታሪኮች እንዳሏት የሚናገሩት አቶ አቡ፤ የጥንካሬ፣ የውበት፣ የጠንካራ እይታ እና የመሰል ጥራት መገለጫዎች መሆኗን ጠቁመው በአጠቃላይ ከሆቴሉ እቅድ ጀምሮ በአርቱም ላይ በመሳተፋቸው ጭምር ደስተኛ እንደሆኑም ይናገራሉ፡፡ አርቱ ከግንባታው ጐን ለጐን በተጓዳኝ የተሠራ በመሆኑ ቅርፃቅርፆቹም አራት ዓመት እንደፈጁ ነው የሚናገሩት፡፡ አቶ አቡ መምህር በነበሩበት ጊዜ አርት ስኩል ውስጥ የመማር እድል የገጠማቸው ቢሆንም እንደ አባታቸው ኢንጂነር የመሆን ፍላጐት ስለነበራቸው ትምህርታቸውን ማቋረጣቸውን ገልፀው፤ ሆኖም የአርት ፍቅራቸው እየጠነከረ ሲመጣ ከግርማችን ፒ ኤል ሲ ባለ ድርሻዎች አንዱ ሆነው ህልማቸውን እውን ለማድረግ በመብቃታቸው ደስተኛ ናቸው።የግርማችን ፒኤልሲ ባለ አክሲዮኖች የቢዝነስ መሠረት ምንም እንኳ ሆቴል ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት በትራንስፖርት ዘርፍ፣ በህንፃ መስታወት ገጠማና መሰል ቢዝነሶች መሠማራታቸውን አቶ አንዱአለም ይናገራሉ፡፡ አሁን ኤግል ሆቴል ካለበት ሥፍራ አጠገብ የማስፋፊያ ቦታ እየጠየቁ ነው፡፡ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የመዋኛ ሥፍራ፣ የህፃናት መጫወቻና አረጋውያን ለብቻቸው በትንሽ ክፍያ የሚዝናኑበት የራሣቸው የሆነ ደረጃውን የጠበቀ መዝናኛ የማሠራት ሀሣብ እንዳላቸው የግርማችን ፒ ኤል ሲ ባለድርሻዎች ይናገራሉ፡፡ “ስለ አረጋዊያኑ መዝናኛ ማሰባችንን ለእናታችን ስናጫውታት ‘ይህ ትልቁ ሐሣብ ነው’ በማለት ደስታዋን ገልፃልናለች” የሚሉት አቶ አንዷለም ፤ የጊዜ ጉዳይ እንጂ እንደሚሳካ ጥርጥር እንደሌላቸው ይናገራሉ፡፡ በአዳማ ከተማ ትልቅ የእንግዳ ማረፊያ በመገንባትም ላይ ይገኛል፡፡ አቶ አንዷለም እንዳጫወቱን፤ እንግዳ ማረፊያው አስራ ስምንት ክፍሎች የሚኖሩት ሲሆን አንዱ ክፍል መኝታ፣ ሳሎን፣ መታጠቢያና ማብሰያ ክፍሎችን ያጠቃልላል፡፡ እንግዳው የሚፈልገውን ነገር አብስሎ ለመመገብ እንዲችል የታሠበ ሲሆን እቃ ለመግዛት ሩቅ ሄዶ እንዳይቸገር በግቢው ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ሱፐር ማርኬት ይኖረዋል፡፡የሚያበስልለት የሚፈልግ ከሆነም በገስት ሀውሱ ውስጥ ዝግጁ የሆኑ ሠራተኞች ይኖራሉ ተብሏል፡፡ ኤግል ሆቴል ፊት ለፊት አስፓልቱን ተሻግሮ “ናሽናል” የተሠኘ ታዋቂ ጭፈራ ቤት አለ፡፡ ጭፈራ ቤቱ በግርማችን ፒኤልሲ ባለቤትነት የሚመራ ነው፡፡ ይህ ጭፈራ ቤት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ሊገነባ ዲዛይኑ አልቆ በጀት እንደተመደበለት የሚናገሩት አቶ አንዷለም፤ እጅግ ዘመናዊና የከተማዋን ደረጃ በጠበቀ መልኩ ሊሠራ ዝግጅቱ ተጠናቋል ብለዋል፡፡ የኤግል መኝታ ክፍሎች ውስጥ በሁለት አቅጣጫ ሲቆሙ ማለትም በምስራቅና በምዕራብ የከተማዋን የተለያዩ ገጽታዎች መቃኘት ይችላሉ። ለምሣሌ የመኝታ ክፍሎቹ ውስጥ ቆመው ወደ ምዕራብ ሲመለከቱ ከሆቴሉ ከምድር ቤቱ ባር ጀምሮ አጠቃላይ የሆቴሉን እንቅስቃሴ መቃኘት ይችላሉ፡፡አሻግረው ሲመለከቱ ትልቁን ገልማ አባገዳ፣ የንፋስ ኃይል ማመንጫውን ተሽከርካሪና በርካታ የከተማዋን ክፍል ይመለከታሉ፡፡ ይህን ሆቴል በሚያስፋፉበት ጊዜ የገጠማቸው ችግር ምን እንደሆነ ጠይቀናቸው ሲመልሱ “አሁን ደስተኛ ብንሆንም በፊት ግን ፈተና የሆነብን ለማስፋፊያው ሲባል 11 አባወራዎች መነሣት ነበር” ይላሉ አቶ አንዷለም፡፡ ምንም እንኳ ይኖሩበት የነበረው ቤት በጣም ጠባብ ቢሆንም ከለመዱበት ቦታ ማስነሣቱ ፈታኝ እንደነበር አስታውሠው፤ ከከተማው መስተዳድር ጋር በመነጋገር ቦታ ተመርጦ ለእያንዳንዱ አባወራ 80ሺህ ብር በማውጣት አምስት አምስት ክፍል ቤት አሠርተው ማስረከባቸውን ገልፀዋል፡፡", "passage_id": "130a5f95ae657461d3b65c1626fb0bf9" }, { "passage": "ታይላንድ ላይ በአንድ ትልቅ ዋሻ ውስጥ በደረሰው የውሃ መጥለቅልቅ ምክንያት መውጫ አጥተዋል የተባሉትን አሥራ ሁለት በአሥሮች ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ የእግር ኳስ ተጫዋቾችንና አሰልጣኛቸዋን የመፈለጉ ጥረት ለአራተኛ ቀን ቀጥሏል።ልጆቹና አሰልጣኛቸው ከልምምድ ቦታ ሳይመልለሱ ከቀሩ በኋላ ነበር ባለፈው ቅዳሜ መጥፋታቸው የተገለፀው። ዋሻው ውስጥ ፍለጋ የተጀመረው ቢስኪሌቶቻቸውና የኳስ ጨዋታ ጫማዎቻቸው በዋሻው በር አከባቢ ከተገኙ በኋላ ነው።", "passage_id": "fc7d1d7b58265686bf8b3ccc02f13c7f" }, { "passage": "ከክርስቶስ ልደት በፊት በግብፅ ሥልጣኔ ዘመን መኖሪያን በጨርቃ ጨርቅ እና በእንስሳት ቆዳዎች በማሸብረቅ የጀመረው ሕንፃን የማስዋብ ጥበብ ከዘመን ጋር እየዘመነ አሁን ላይ ከደረሰበት የእድገት ደረጃ ላይ ደርሷል። ሕንፃን የማስዋብ ጥበብ በሁሉም ቦታ ለአንድ ዓይነት አላማ ይዋል እንጂ ከቦታ ቦታ የማኅበረሰቡን የአኗኗር ዘይቤ መሠረት አድርጎ የማስዋቡ ሒደት እንደየአካባቢው ይለያያል። ሕንፃን የማስዋብ ጥበብ የሰዎችን ስሜት ማጥናት፣ ሰዎች ከአካባቢው ጋር ያላቸውን መስተጋብር የማየት፣ የሥራ ቦታዎችም ከሆኑ የሚሠሩትን ሥራ በውበት በመግለፅ መኖሪያንም ሆነ ሕንፃን ወይም የሥራ ቦታን ማስዋብ ነው። ይህም በሰዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ጥሩ ስሜትን የሚፈጥርና ምቹ የሥራ ከባቢን ለመፍጠር ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳለው የዘርፉ ምሁራን ይገልፃሉ።ውልደቱን ከወደ ፈርኦኖች ምድር ያደረገው የሕንፃን ውስጣዊ ክፍል የማስዋብ ጥበብ ታዲያ በአገራችን ኢትዮጵያም ቀላል የሚይባል ዕድሜ እንዳላስቆጠረ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ። ከእድሜ ጠገብ የእምነት ተቋማት ሕንፃዎች ውስጣዊ እና ውጫዊ አካል ለመረዳት እንደሚቻለው የቀደምት ኢትዮጵያዊያን ሕንፃን የማስዋብ ጥበብ አሻራዎችን መመልከት ይቻላል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በትምህርት የታገዘ እና በዘመናዊ መንገድ ሕንፃዎችንና የሥራ ቦታዎችን የማስዋብ ሒደት እድገትን እያሳየና የሰዎችንም ቀልብ እየሳበ ይገኛል። ይህንም ተከትሎ አሁን ላይ ቁጥራቸው ላቅ ያሉ በዘመናዊ መንገድ ሕንፃን የሚያስውቡ ድርጅቶች ወደ ገበያ እየገቡ እንዳሉ በዚህ ዘመን ላይ ያሉትን ሕንፃዎችና የሥራ ቦታዎች መመልከት በቂ ማስረጃ ነው። በዘርፉ ግንባር ቀደም ከሆኑትና አመርቂ ሥራን እያስመዘገቡ ካሉ ድርጅቶች መካከል “ቤት ለእምቦሳ” በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው። በፈረንጆች 2011 በወጣት የዘርፉ ባለሙያዎች የተቋቋመው ይህ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መኖሪያን፣ ሕንፃዎችን፣ የሥራ ቦታዎችን ውስጣዊ ክፍል እንዴት ማስዋብ እንደሚቻል የቴሌቪዥን መርሐ ግብር በመጀመር ሙያዊ ምክርን ለተመልካች ያደረሰ ድርጅት ነው።የቤት ለእምቦሳ የሥነ ህንፃ ባለሙያ የሆኑት ፍቅር አበበ እንደሚሉት የሕንፃ ውስጥ ማሰዋብ በብዛት አገራቸን ውስጥ አልተለመደም። ለዚህ እንደ ዋና ምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ ይህ የሕንፃ ውሰጥ ማስዋቢያ ትምህርት አገራቸን ውስጥ አለመሰጠቱ እንዲሁም ሁሉም የሕንፃ ውስጥ ማሰዋብ ሥራን በአብዛኛው የሚሠራው ከሌሎች አገሮች ጋር ልምድ ልውውጥ በማድረግ የሚሠራ ሲሆን ብዙ ጊዜ የሚጠቀሙትም ሆቴሎች፣ ሆስፒታሎች እንዲሁም ካፌ እና ሬስቶራንቶች ናቸው። እነዚም ከሌሎች ለየት በማለት ተመራጭ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያግዛል። ሆኖም በእኛ ድርጅት ዋናው አላማችን ደንበኞቻችን እንዲወዱት የማድረግ ሥራ እስከሆነ ድረስ ሁሉንም ሰው ባማከለ ዋጋ እንሠራለን ይህ ማለት ደግሞ ሁሉም አሠራሮች የተለያየ ዋጋ ቢኖራቸውም ደንበኞቻችን በፈለጉት መንገድ ሠረተን እናስረክባለን በማለት የሥነ ሕንፃ ባለሙያው ስለ ሕንፃ ውስጥ ማስዋብ ያላቸውን አስተያየት ገልፀዋል።የቤት ለምቦሳ ሕንፃ ማስዋቢያ ድርጅት ደንበኛ የሆነው የዋው በርገር ሥራ አስከያጅ አብዩ መኮነን እንደሚሉት “ለእኛ የካፌያችንን ዲዛይን በተለየ ሁኔታ የሰራልን ቤት ለምቦሳ ነው። ይሁንና ይህን ለማረግ ያነሳሳን ዋነኛው ምክንያታችን ደንበኞቻችን እኛ ጋር ሊጠቀሙ በሚመጡበት ጊዜ ለዓይንናቸው አመቺ እና ማራኪ እንዲሆን በማሰብ ነው” ብለዋል። ሆኖም የሥራ ቦታችንን በዚህ መንገድ የተሸለ በማደረጋችን ተመራጭ እና ተወዳጅ ስላደረገን በዋው በርገር ሥር ከሚገኙ ስምንት ቅርንጫፍዎች ውስጥ አራቱን ዲዛይን ያረጉልን እነሱ ናቸው ሲሉ አብዩ ተናግረዋል።በኢትዮጵያ ውስጥ እያደገ የመጣውን የሕንፃ ውስጥ ማስዋብ ሥራን ተከትሎ ዛሬ የካቲት 16/ 2011 ኢንደስትሪዉን የሚቀላቀለውን ማኪ የሕንፃ ውስጥ ማስዋብና የሥነ ጥበብ ማዕከልን እናገኛለን።የማኪ የሕንፃ ውሰጥ ማስዋብና አርት ጋለሪ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ማራኪ ተጠምቀ ስለ አዲሱ ድርጅታቸው ሲያብራሩም የሕንፃ ውስጥ ማስዋብ ሞያችን ሆኖ ሳለ በተጨማሪ በውስጣችን ያለው የአርት ፍቅር ምክንያት በዋነኝነት ይህን ድርጅት ለመክፈት ካነሳሳን ነገሮች አንዱ ሲሆን በአገራችን በሚገነቡ ሕንፃዎች ውስጥ የተለያዩ ችግሮችን በማስተዋል በግልፅ ከሚታዩት ክፍተቶች ውስጥ ስታንዳርድ ባለመጠበቅ የሚፈርሱ የውስጥ ግንባታዎች ባለቤቱን ለኪሳራ ከማጋለጡም አልፎ በአገሪቷም ላይ ከፍተኛ ውድቀት እየስከተለ መምጣቱ፣ የክፍሎችን አከፋፈል ለተገቢው ነገር የሚመች አድርጎ በበቂ ሁኔታ አለመጠቀም እና የብርሃንና የአየር አለመመጣጠን በብዙ ሕንፃዎች ላይ የሚታይ ችግር ሲሆን የመብራት የወለልና የኮርኒስ እንዲሁም የዕቃና ከለር አመራረጥን ታሳቢ አድርገን እነዚን ችግሮች በጥቂቱም ቢሆን ለመፍታት በማሰብ ነው ድረጅታችንን ያቋቋምው ሲሉ ሥራ አስኪያጅዋ ገልፀዋል።የሕንፃ ውስጥ ማሰዋብ ሲሠራ የውስጥን ገጽታ ከአካባቢውና ከአገሪቱ የአየር ሁኔታ ጋር በማዋሀድ የአካባቢውን አትሞስፌርን መጠበቅ ዋነኛው የሥራ ድርሻ ከመሆኑ ባሻገር በሕንፃ ውስጥ ለጤና ተስማሚ የሚሆኑ አትክልቶችን በማዘጋጀትና በማቅረብ የሕንፃ ውስጥ የአየር ዝውውር ተስማሚ እንዲሆን ከማድረግ አልፎ ጥሩና ምቹ ስፍራ ለማግኘት የሚረዳን ይሆናል። እንዲሁም ከሕንፃ ውስጥ የጀመርነውን ጥሩና ምቹ ስፍራ ከግቢ ውስጥና በአካባቢውም ጤናማና ተስማሚ ቦታ እንዲሆን ትልቅ አስተዋፆ እንደሚፈጥር በማመናችን የሕንፃ ውስጥ ውጪን በአትክልት ሥራ የተዋበ ለማደረግ እየተዘጋጀን ነው ሲሉ ሥራ አስኪያጅዋ ጨምረው ይናገራሉ።የድርጅታቸን ዋና ዓላማ በአገራችን ውስጥ የሚታዩ ችግሮችን ፈቺ ተቋም ከመሆን አልፎ በሌሎች አገራት ውስጥ እውቅና የሚያገኝ ድርጅት መፍጠር እና የአገራችንን የጥበብ ውጤት በተለየ ሁኔታ ለማሳደግ ቀደምት የአባባል ዘዴዎችንና ጥበቦችን ወደ ጥበቡ መድረክ ተመልሰው እንዲገቡ እንዲሁም ሰዓሊው በከፍተኛ ደረጃ የጥበቡ ተጠቃሚና ታዋቂ እንዲሆን በማድረግ በተለያዩ የሀገር ውስጥ እና ሀገር ውጪ መድረኮች ላይ በመሳተፍ ሀገራችንን በከፍተኛ ሁኔታ ማስተዋወቅ ሲሆን ከሌሎቹ የሚለየው የኛ ድርጅት የተለያዩ የስራ ዘርፎችን በአንድላይ በመስራት የሰዎችን ልፋት በመቀነስ ፍላጎትን የሚያሟላ ሲሆን በምንሰራው ሥራ ላይ የተማረ የሰው ኃይል መኖሩ እንዲሁም ተጠቃሚው የሚፈልገውን ነገር መረጦ የመግዛት እና የማማከር አገልግሎት እንዲኖራቸው ዕድል መስጠታች ነው ብለዋል።የቤት ውስጥ ማስዋብ ሥራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት ግለሰቦች በግላቸው የሥራ ቦታቸውን ምቹ ለማድረግ በሚስማማ መልኩ እየስዋቡ እንደሆነ እንመለከታል። የብሉ ሙን ሥራ ፈጠራ ድርጅት መሥራች ኢሌኒ ገብረመድህን በቅረቡ አዲስ ለጀመሩት ብሉ ሰፔስ የሥራ ማዕከል በግላቸው የማስዋቡን ሥራ እንደሰሩት ይናገራሉ። ይህም በአሁኑ ሰዓት የማስዋብ ጥበብ በሰዎች ዘንድ ምን ያህል ተቀባይነትን እያገኘ እንደመጣ መረዳት ይቻላል።ቅጽ 1 ቁጥር 15 የካቲት 16 ቀን 2011", "passage_id": "11c77d8f1598a6cf9ff7b8c84dab8368" }, { "passage": "ከትናንት በስቲያው ቅዳሜ የዱከም ጤና ጣቢያ ግጥር ግቢ በታካሚዎች ተጨናንቋል፡፡ በሕክምና ክፍሎቹ በረንዳ ላይ የተሰለፉ ታካሚዎች ስማቸው እየተጠራ ወደ ሕክምና ክፍሉ ውስጥ ዘልቀው ይገባሉ፡፡ የጥርስ፣ የወገብና፣ የነርቭ ህመም ያለባቸው ታካሚዎች በነፃ ሕክምና እያገኙ ሲወጡ ተመልክተናል፡፡ ባለቤትነቱ የደቡብ ኮሪያ የሆነውና በዱከም የሚገኘው ኢኮስ (EKOS) የብረታብረት ፋብሪካ አስተባባሪነትና ድጋፍ ከደቡብ ኮሪያና ከኮሪያ ሆስፒታል በመጡ 22 የሕክምና ባለሙያዎች ቡድን በዱከም ጤና ጣቢያ ለኅብረተሰቡ ነፃ የሕክምና አገልግሎት በመሰጠት ላይ ነው፡፡የዱከም ነዋሪ\nየሆኑት\nአቶ\nሲሳይ\nኢሮ\nበኮሪያ\nየሕክምና\nቡድን\nነፃ\nሕክምና\nይሰጣል\nተብሎ\nበማስታወቂያ\nሲነገር\nሰምተው\nየጥርስ\nህመማቸውን\nለመታከም\nእንደመጡ\nገልጸውልናል፡፡\nበገንዘብ\nችግር\nምክንያት\nህመማቸውን\nችለው\nለወራቶች\nእንደቆዩ\nአስታውሰው\n‘በኮሪያ\nየሕክምና\nባለሙያዎች\nነፃ\nሕክምና\nይሰጣል’\nሲባል\nጊዜ\nሳያጠፉ\nወዲያው\nየተቦረቦረ\nጥርሳቸውን\nለማስወለቅ\nወደ\nጤና\nጣቢያው\nእንደመጡ\nነግረውናል፡፡የሕክምና ባለሙያዎቹ አገልግሎት አሰጣጥና ትህትና በጣም እንደማረካቸውና ጥርሳቸውን በቀላሉና ስቃይ በሌለበት ሁኔታ እንዳወለቁላቸው ገልጸዋል፡፡ «በጣም የሚገርመው» አሉ አቶ ሲሳይ «ከሦስት ዓመት በፊት አንድ ሺ ብር ከፍዬ ጥርሴን አስወልቄያለሁ፡፡ በጣም ህመም ነበረው፡፡ ህመሙና የክፍያው መብዛት ብቻ ሳይሆን የጊዜ ቀጠሮውና እንግልቱም ቀላል አይደለም፡፡ በአንጻሩ የኮሪያዎቹ የሕክምና ባለሙያዎች የተጎዳውን ጥርስ ሲያወልቁ ህመም የለውም፤ ደምም አይፈስም፤ በጥቅሉ ዘመናዊ ሕክምና በነፃ ነው ያገኘሁት» ሲሉ ደስታቸውን አጋርተውናል፡፡«ተፈልጎ የማይገኝ\nዕድል\nነው\nያገኘሁት»\nየሚሉት\nአቶ\nሲሳይ\nጥርስ\nለማስነቀል\nበትንሹ\nሦስትሺህና ከዚያ በላይ ብር ያወጡ እንደነበር አመልክተው በኢኮስ አማካኝነት በነፃ ሕክምና መሰጠቱ ፋብሪካው የኅብረተሰቡን ችግር ለመጋራት ያለውን እንቅስቃሴ አጎልቶ ያሳያል ብለዋል፡፡ ሌላዋ ሕክምናውን አግኝተው ከጤና ጣቢያው ግቢ ሲወጡ ያገኘናቸው ወይዘሮ ፀሐይ ማህመድ ወገባቸውና እጃቸውን ለማንቀሳቀስ ሲቸገሩ እንደነበር አውስተው ሕክምናውን ከአገኙ ወዲህ ግን ማንቀሳቀስ መቻላቸውን፤ ሕክምናው ከዚህ በፊት አይተዋቸው በማያውቋቸው ዘመናዊ መሣሪያዎች መደግፉና በአጭር ጊዜም ውጤት ማየታቸውን ነግረውናል፡፡ በነፃ የተሰጣቸው የፊዚዮ ቴራፒ አገልግሎት ከገንዘብና ከእንግልት አኳያ ሲታይ በጣም የሚያስደስት እንደሆነ መስክረዋል፡፡«ከሕክምናው በላይ የሚያስደስተው የሕክምና ባለሙያዎቹ ትህትና ነው» የሚለው ወጣት ከሊል ፊጤንሳ «የወገብ ሕክምና በዘመናዊ ሕክምና መሣሪያዎች በመታገዝ አገልግሎቱን አግኝቻ ለሁ፡፡ በጤና ጣቢያው የማይሰጡ የሕክምና ዓይነቶች ከአቅራቢያችን በሚገኘው ኢኮስ ብረታ ብረት ፋብሪካ አማካኝነት በነፃ በጤና ጣቢያው አገልግሎቱ ለገጠሩና አቅም ለሌለው ኅብረተሰብ ክፍል መሰጠቱ ከምንም በላይ ያስደስታል፡፡ ቀዬህ ድረስ መጥተው አገልግሎቱን ስታገኝ እርካታ ነው የሚሰማህ» ሲልም አስተያየቱን ሰጥቷል። ከሊል ልክ እንደ ኢኮስ ሁሉም ተቋማት ለኅብረተሰቡ በተለያዩ መስኮች ድጋፍ ቢያደርጉ ድርጅቶቹንና ማህበረሰቡን በማቀራረብ በኩል ለተሻለ ዕድገት እንዲሰሩ የትስስር ገመድ ይሆናቸዋል የሚል አቋም አለው፡፡የነርቭ፣ ፊዚዮቴራፒ እና የጥርስ ሕክም ከጤና ጣቢያው አቅም በላይ በመሆናቸው እንደማይሰጡ የሚገልፁት የዱከም ጤና ጣቢያ ዳሬክተር አቶ ታምራት ማሞ በኢኮስ ድጋፍና አስተባባሪነት እነዚህ ሕክምናዎች ለኅብረተሰቡ በአቅራቢያው መሰጠታቸው ኢኮስንም ሆነ ባለሙያዎቹን ሊያስመሰግናቸው የሚገባ ተግባር ነው መሆኑን ተናግረዋል፡፡እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ የፊዚዮቴራፒና የነርቭና የጥርስ ሕክምናዎች በቀላሉ የሚገኙ አይደሉም፡፡ ዋጋቸውም ውድ ነው፡፡ ለምሳሌ በአሁኑ ጊዜ አንድ ጥርስ ለመትከል 20ሺ ብር ወጪን ይጠይቃል፡፡ ከዚህ አኳያ እነዚህ ሕክምናዎች ለኅብረተሰቡ በነፃ መሰጠታቸው ትልቅ እገዛ ነው፡፡ የቡድኑም እዚህ መምጣትና ይህን ዓይነቱን ዘመናዊ አገልግሎት መስጠቱ የጤና ጣቢያው የሕክምና ባለሙያዎች የልምድና የእውቀት ልውውጥ እንዲያደርጉ ያግዛቸዋል፡፡በኢኮስ ብረታ ብረት ፋብሪካ የማስታወቂያና የትምህርት ክፍል ኃላፊ ሚስተር ሊሂንግ እንደገለጹት ፋብሪካው ከኮሪያ ሆስፒታል ጋር በመተባበርና ከውጭ የሕክምና ባለሙያዎችን በማስመጣት ፋብሪካው የሚገኝበት የዱከም ነዋሪ የነፃ ሕክምና ተጠቃሚ እንዲሆን አድርጓል፡፡ ይህም ፋብሪካው ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ስለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ፋብሪካው ድጋፍ የሚሰጠው ነፃ ሕክምና የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ቢሆንም ቀጣይነት እንደሚኖረው የገለፁት ኃላፊው ለአራት ቀናት የሚሰጠው የነርቭ፣ የፊዚዮ ቴራፒ፣ የስኳር፣ የጥርስ ነቀላና ተከላ የነፃ ሕክምና አገልግሎቶች ከአንድ ሺ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል፡፡ሚስተር ሊሂንግ የነፃ ሕክምና አገልግሎቱ በጅማ፣ ድሬዳዋና ሐረር ለመስጠትም ዕቅድ መኖሩን ጠቁመው፣ ፋብሪካው ዱከም አካባቢ የኤሌክትሪክ ኃይል የማያገኙ 38 አርሶ አደሮች የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ለማድረግ ተቋማቸው ዕቅድ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም ለአካባቢው ኅብረተሰብ የውሃ አቅርቦትን ለማሟላትና የቴኳንዶ ስልጠናም ለመስጠት ዕቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ኢትዮጵያና ኮሪያ በደም የተሳሰረ ግንኙነት እንዳላቸው የገለጹት ኃላፊው ፋብሪካው ከኢትዮጵያና ኮሪያ ረጅም ግንኙነት መገለጫዎች አንዱ እንደሆነ፤ ወደፊትም ከአካባቢው ኅብረተሰብ ጋር በመሆን በማህበራዊ አገልግሎቶች ዘርፍ ላይ አተኮሮ የሚሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡አዲስ ዘመን ነሃሴ 27/2011ጌትነት ምህረቴ", "passage_id": "05abe7710dd5b13561e64dbfcb552b22" } ]
1fe4eb5e2f5e758740b904093af971a8
bf4bab508ff73e38ba6dad5d61b0e48d
ዲግሪን በዘጠኝ ዓመት
 በሀገራችን ባለው አሠራር ሕፃናት ቅድመ መደበኛ ትምህርት መከታተል የሚጀምሩት በአራት ዓመታቸው እንደሆነ ይታወቃል፤መደበኛ ትምህርት እንዲጀመሩ የሚጠበቀው ደግሞ በሰባት ዓመታቸው ነው፡፡ ይህ በከተሞች እየተሠራበት ሲሆን፣ በገጠር እና በአንዳንድ ከተሞች ግን የቅድመ መደበኛ ትምህርት ጉዳይ በቄስ ትምህርት ቤት እና ቁርአን ትምሀርት ቤቶች የሚሸፈን እንደ መሆኑ የአጸደ ሕፃናት ትምህርት አለ የሚባል አይደለም፡፡ አንዳንድ ሕፃናት ግን ከሰባት ዓመታቸው በፊት ትምህርት እንዲጀምሩ ሲደረግ ይስተዋላል፡፡ ትምሀርት የጀመሩት በአምስት ዓመታቸው መሆኑን የሚገልጹ ያጋጥማሉ፡፡ እነዚህ ተማሪዎች 12ኛ ክፍልን መቼ ጨርሰው መቼ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን እንደሚይዙ መገመት አይከብድም፡፡ በአምስት ዓመታቸው አንደኛ ክፍል ቢገቡና ብርቱ ሆነው አስራ ሁለተኛ ክፍልን በሰዓቱ ቢያጠናቅቁ ከ21 ዓመታቸው በፊት የመጀመሪያ ዲግሪ ለመያዝ አይችሉም፡፡ በ7 ዓመታቸው የሚገቡት ደግሞ መቼ ሊጨርሱ እንደሚችሉ እናስብ፡፡ በእኛ ሀገር አንዳንዶች ትምህርት ቤት ሊገቡ በሚችሉበት ዕድሜ የመጀመሪያ ዲግሪ የያዙ ታዳጊዎች ያጋጥማሉ፡፡ ኤንዲቲ የተሰኘው ድረ ገጽ በቅርቡ ይዞት የወጣ ዘገባ እንዳመለከተው የአምስተርዳም ነዋሪው የዘጠኝ ዓመት ሕፃን የመጀመሪያ ዲግሪውን በቅርቡ እንደሚይዝ ይጠበቃል። በዚህም በዓለም የመጀመሪያ ዲግሪ ያየዘ በሕፃንነቱ መያዝ የቻለ ብቸኛው ሕፃንም ለመባል በቅቷል።፡ በኤይንሆቭን ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ለውረንት ሲሞንስ የተባለው ይህ ሕፃን የመጀመሪያ ዲግሪውን የሚይዘው በኤሌክትሪካል ምህንድስና ነው፡፡ ሕፃኑ የመጀመሪያ ዲግሪውን በሚቀጥለው ወር እንዳጠናቀቀም ፣ከሦስት ወራት በኋላ ሦስተኛ ዲግሪውን ለመያዝ ትምህርት እንደሚጀምርም ተናግሯል፡፡ እናቱ ሊዲያ የልጁ አያቶችና መምህራን ልዩ ተሰጥኦ እንዳለው ሁሌም ይናገሩ እንደነበር ስትገልጽ፣ አባቱ አሌክስንደር ሲሞንስ በበኩሉ ልጁ በእርግጥም መረጃ በመያዝ በኩል ማንም አይደርስበትም ሲል ገልጿል፡፡ ሎውረንት ገና ምኑ ተይዞ ይላል፡፡ ለዘ ቴሌግራፍ በሰጠው አስተያየትም ወደ ካሊፎርኒያ በመሄድ ትምህርቱን ለመቀጠል ይፈልጋል፤አባቱ ግን እንግሊዝ ሄዶ ቢማርለት እንደሚመርጥ አስታውቋል፡፡ የ37 ዓመቱ የጥርስ ሀኪም የሆነው አባቱ ‹‹ኦክስፎርድና ካምብሪጅ በአንግሊዝ ዋና ዋናዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ከእነዚህ ዩኑቨርሲቲዎች በአንዱ ገብቶ ቢማር ምርጫው መሆኑን አስታውቋል፡፡ ላውረንት ሲሞንስ ለሲኤንኤን በሰጠው አስተያየት በቀጣይም ማጥናት የሚፈልገው ኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ መሆኑን ጠቅሶ፣ በተወሰነ ደረጃ የህክምና ትምህርት መማርም ይፈልጋል፡፡ ቤተሰቦቹ በሕፃንነቱና በእውቀቱ መካከል የሆነ ሚዛናዊ ነገር እንደሚፈልጉ ሎረንት ገልጾ፣ እሱ ደግሞ ለትምህርቱ ከሚሰጠው ትኩረት በተጓዳኝ የተለየዩ ጨዋታዎችን መጫወት፣ ከጓደኞቹ ጋር መሆን እንደሚወድ ይናገራል፡፡ በኢንስታግራም በኩል ከ11 ሺህ በላይ ተከታዮች አንዳሉት ተናግሮ፣ በዚህም አማካይነት የህይወትን የተለያዩ ጎኖች እንደሚመለከት ያብራራል፡፡ እስከ አሁን ባለው መረጃ መሰረት በዓለም በልጅነቱ የመጀመሪያ ዲግሪ በመያዝ የሚታወቀው ሚካኤል ኬርኒይ የተባለ ታዳጊ ሲሆን ፣ዲግሪውን የያዘውም በአስር ዓመቱ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 9/ 2012 ዓ.ም ዘካርያስ
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=22776
[ { "passage": "አዲስ አበባ:- ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሁለተኛና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ መጀመራቸው ተጠቆመ፡፡ የመጨረሻ ዓመት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ደግሞ ከየትምህርት ተቋሞቻቸው የሚላኩላቸውን የትምህርት ሰነዶች እያነበቡ እንደሚቆዩ ተገልጿል፡፡ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ኤባ ሚጀና በኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ በሽታ ምክንያት በዚህ ወቅት ይካሄድ ስለነበረው የከፍተኛ ተማሪዎች የምረቃ መርሃ ግብር ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት፣ በኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ በሽታ ምክንያት የሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ትምህርቱን እንዲከታተሉና ከአማካሪዎቻቸው ጋርም የሚገናኙበት ምቹ ሁኔታ በመኖሩ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ባይኖርም አንዳንድ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ እንደ ጀመሩ አመልክተው፣ በዚህም ጅማና ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ይጠቀሳሉ ብለዋል፡፡ ትምህርታቸውን ያልጨረሱ ተማሪዎችም እንደሚኖሩ ጠቁመዋል፡፡ ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ለመጨረስ የቻሉት በተመቻቸው የቴክኖሎጂ የማስተማሪያ ዘዴ በአግባቡ መጠቀም በመቻላቸው፣ እንዲሁም በተማሪውና በአማካሪዎቻቸው ጥንካሬ እንደሆነ የጠቆሙት ዶክተር ኤባ፣ የትምህርት ተቋማቱም በየጊዜው አስፈላጊውን ክትትልና ግምገማ በማድረግ ውጤታማ መሆኑ መቻላቸውን አመልክተዋል፡፡የመጨረሻ ዓመት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን በተመለከተም ዶክተር ኤባ እንዳብራሩት፣ በወረርሽኙ ምክንያት ባለመማራቸው፣ አንዳንዶችም የመጀመሪያ መንፈቅ (ሴሚስተር) ፈተና ለመውሰድ ዝግጅት ላይ እያሉ ወረርሽኙ በመከሰቱ ምክንያት ባለመፈተናቸው በዚህ ክረምት ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁ ተማሪዎች አይኖሩም፡፡እነርሱን በተመለከተ መደረግ ስላበት ነገር በየሳምንቱ ከየትምህርት ተቋማቱ የትምህርት አመራሮች ጋር ግምገማ እየተደረገ እንደሚገኝ አመልክተው፣ ወረርሽኙ ቢገታ ወይም ቢቆም መደረግ ስላለበት ሁኔታ ከወዲሁ ዝርዝር ዕቅድ ያዘጋጁ የትምህርት ተቋማት መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡ ዝርዝር ዕቅዱ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ምን ላይ እንዳቆሙ እና ካቆሙበት በመቀጠል ደግሞ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ በመሸፈን ትምህርታቸውን ማጠናቀቅ እንደሚችሉ የሚያሳይ እንደሆነም አስረድተዋል፡አሁን ትልቁ ሥራ ወረርሽኙን መከላከልና የሰው ህይወት መታደግ ላይ ትኩረት መደረጉን ዶክተር ኤባ ጠቁመው፣ በወረርሽኙ ምክንያት ትምህርት እንዲቋረጥ ሲደረግ፣ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸው በቤታቸው የሚያነቡት የትምህርት ሰነዶች እንዲሰጣቸው የሚል አቅጣጫ ተሰጥቶ እንደነበር አመልክተዋል። በሚኒስቴሩም በተለያየ የቴክኖሎጂ ዘዴ ተማሪዎችን ተደራሽ ለማድረግ ጥረት መደረጉን አመልክተው፣ ጥረቱ ተማሪዎች ጊዜያቸውን እንዲጠቀሙ እንጂ ወደ ሚቀጥለው የትምህርት ምዕራፍ እንዲያልፉ የሚረዳቸው እንዳልሆነ ገልፀዋል፡፡ አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታም ተማሪዎች በየትምህርት ተቋማቶቻቸው የሚላኩላቸውን ሰነዶች በማንበብ እንደሚቆዩ አስታውቀዋል፡፡አዲስ  ዘመን ግንቦት 20/2012 ለምለም መንግሥቱ ", "passage_id": "ca02c13409d8b60f1e9a55c21f072e43" }, { "passage": " በግል ኮሌጆች ምስረታ ቀዳሚና ፈርቀዳጅ የሆነው ሂልኮ ኮሌጅ ዛሬ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) አዳራሽ 350 ያህል ተማሪዎችን በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያስመርቃል፡፡ ትኩረቱን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (ኮምፒዩተር ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ) ላይ በማድረግ በ1990 ዓ.ም የተመሰረተው ሂልኮ ኮሌጅ ባለፉት 18 ዓመታት ከ3000 በላይ ተማሪዎች አሰልጥኖ ማስመረቁን የኮሌጁ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ናስር ዲኖ ገልፀዋል፡፡ በሁለት ማስተርስ ዲግሪ ማሰልጠን የጀመሪት ከ7 ዓመት በፊት ሲሆን የመጀመሪያዎቹን ሰልጣኞች ከሁለት ዓት በፊት በ2013 አስመርቀዋል፡፡ በዛሬው ዕለት በሁለተኛ (ማስተርስ) ዲግሪ የሚመረቁት 250 ተማሪዎች ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ 160 በኮምፒዩተር ሳይንስ፣ የተቀሩት በሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ፣ በኮምፒዩተር ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ደግሞ 100 ተማሪዎች እንደሚመረቁ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡ ለአገራችን ዕድገትና ልማት የበኩላችንን አስተዋፅኦ ለማበርከት መንግሥት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በቀየሰው የትምህርት ስትራቴጂ መሠራት እየተጓዝን ነው ያሉት ዶ/ር ናስር፣ መንግሥት በበከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሴቶች ተሳትፎ 30 ከመቶ እንዲሆን በወሰነው መሰረት እኛ ዛሬ ከምናስመርቃቸው ውስጥ 25 ከመቶ ሴቶች ናቸው፡፡ ሲመረቁ ቁጥራቸው ይህን ካከለ ሲመዘገቡ ምን ያህል ከፍተኛ እንደነበር መገመት አያቅትም፡፡ አሁን ካለው የሳይንስና ኢንጂነሪንግ ተፈላጊነት አንፃር ጥሩ እየሰራን ነው፡፡ እኛ ለየት የሚያደርገን ነገር አለን፡፡ ተማሪዎቻችንን ተመርቃችኋል ብለን ጋዋን አልብሰንና ዲግሪ ሰጥተን አንሸኝም፡፡ ምረቃውን ሥራ ነው የምናደርገው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ እያንዳንዱ የማስተርስ ዲግሪ ተማሪ ሪሰርች ፕሮጀክት ወይም ሪሰርች ቴሲስ ምርምር ሳይሰራ አይመረቅም፡፡ የምርምር ስሜት ካልፈጠርንበት አዳማጭነት ብቻውን ለውጥ አያመጣም፡፡ ማሰብ፣ መመራመር፣ ማዳመጥ፣ ወደ ሥራ መተርጎም በሙሉ አስፈላጊ ሂደቶች ናቸው፡፡ ተማሪዎቹ የሰሯቸው ምርምሮች በኢሲኤ አዳራሽ ለኤግዚቢሽን ቀርበዋል፡፡ የምንጋብዛቸው እንግዶች ወላጀች ብቻ ሳይሆኑ ወደፊት ተማሪዎቹን ሊቀጥሩ የሚችሉ የድርጅትና፣ የኢንዱስትሪ ባለቤቶችና ኃላፊዎች የልጆቹን ችሎታ እንዲያዩ እናደርጋለን፡፡ ዘንድሮ ተማሪዎቻችን የሰሯቸው ብዙ ምርምሮች እውቅና አግኝተው በአገር ውስጥ በዓለም አቀፍ ጆርናሎች (መጽሔቶች) ታትመዋል … በማለት አስረድተዋል፡፡ የመጀመሪያም ሆነ የሁለተኛ ዲግሪ ምርምር ውጤቶች ተመዝነው ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ሰርቲፊኬት እንደሚሸለሙ ዶ/ር ናስር ዲኖ ገልጸዋል፡፡ ", "passage_id": "bb51dd6b24c9bb3c895c0f7c6bb3b26e" }, { "passage": "መምህር ፒተር ታፒቺ የ2019 የዓለም የምርጥ አስተማሪነት ውድድርን ነው ያሸነፉት። ጥቂት መጻሕፍት ባሉበትና በተማሪዎች በተጨናነቁ ክፍሎች እያስተማሩ ተማሪዎቻቸው ለመርዳት ያሳዩት ትጋት ብልጫን አስገኝቶላቸዋል።\n\n እኚህ መምህር ልዩ የሚያደርጋቸው ታዲያ የደመወዛቸውን 80 እጅ ለተቸገሩ በተለይም ወላጅ አልባ ለሆኑ ተማሪዎቻቸው የደንብ ልብስና መጽሐፍ መግዣ መስጠታቸው ነው።\n\n• ሴት ተመራቂዎች ለምን ሥራ አያገኙም?\n\nመምህሩ ፕዋኒ መንደር፣ ናኩሩ አውራጃ በሚገኘው ከሪኮ ሚክስድ ዴይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነበር የሚያስተምሩት።\n\n ተማሪዎቻቸውንም «የወደፊቱ ተስፋ በሳይንስ ነው፤ ጊዜው የአፍሪካ ነው» በሚል ያበረታቱ ነበር።\n\nየሽልማት ሥነ ሥርዓቱ የተካሄደው በዱባይ ሲሆን ለዚህ ሽልማት ከ179 አገራት አስር ሺ የሚሆኑ መምህራን እጩ ነበሩ።\n\nየመምህሩን ያልተጠበቀ ድል ተከትሎ የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ኡሁሩ ኬንያታ የእንኳን ደስ ያለዎት መልእክትን አስተላልፈዋል።\n\n• 'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ?\n\n• በእርግጥ የአብራሪዎቹ ስልጠና ከአደጋው ጋር ይያያዛል? \n\n ", "passage_id": "60162b3a9ae9302a3c06dd653d71f7c4" }, { "passage": "ሙከረም አሊ ኑር ይባላል። በኮምፒውተር ሳይንስ እና ኢንጂነሪንግ እንዲሁም በኤሌክትሮኒክስ እና ኮሙኒኬሽን ኢንጂነሪንግ ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተመርቋል።የመጀመሪያው ቢ...\"ላይብረሪ ብዙም አልጠቀምም\"\"አባቴ ነጋዴ እንድሆን ይፈልግ ነበር\"3.93 በማምጣት የግቢውን ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቦ ዋንጫ ተሸልሟል።ሙከሪም በአንድ ጊዜ በሁለት ዲግሪ ነው የተመረቀው። በዩኒቨርስቲው አንድ ተማሪ የተሻለ ውጤት ካለው ሁለት ዲግሪዎችን በተመሳሳይ ጊዜ መማር ይችላል።3.5 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች ሁለተኛ የትምህርት ክፍል በመምረጥ መማር ይችላሉ። ሁለት ዲግሪ ሲወሰድ ትምህርቶቹ ተመሳሳይ እንዲሆኑ ይጠበቃል። ይህ ማለት ደግሞ የሚወሰደው ትምህርት ብዛት ስለሚቀንስ በአምስት ዓመት ውስጥ መጨረስ ይቻላል ማለት ነው።ከሙከሪም ጋር በሁለት ዲግሪ የተመረቁት 33 ተማሪዎች ናቸው።በኮምፒውተር ሳይንስ እና ኢንጂነሪንግ 170 የትምህርት ሰዓት (ክሬዲት አወር)፣ በኤሌክትሮኒክስ እና ኮሙኒኬሽን ኢንጂነሪንግ 23 የትምህርት ሰዓት (ክሬዲት አወር) ወስዶ ትምህርቶቹን በአምስት ዓመት ውስጥ እንዳጠናቀቀ ይናገራል።ሙከሪም አብዛኛውን ትምህር 'ኤ' አግኝቶ ነው የተመረቀው።\"አንድ ሁለት ቢ ይኖራል። ሌላው ኤ እና ኤ ማይነስ ናቸው\" ይላል።ኤ ማግኘት የለመደው ተመራቂው ቢ ሲያገኝ እንደሚያዝን ይናገራል። ለመጀመሪያ ጊዜ ቢ ያገኘበትን ጊዜም እንዲህ ያስታውሳል. . .\"የመጀመሪያውን ቢ ያገኘሁት የመጀመሪያ ዓመት፣ ሁለተኛው መንፈቀ ዓመት ላይ ነበር። ከዚያ ትምህርት ውጭ የሁሉንም ውጤት አይቼ ነበር። ሁሉም ኤ እና ኤ ቻርጅ ነበሩ። እና የቀረችዋ አንድ ኮርስ ኤ ብትመጣ ኖሮ 4 ነበር የማመጣው። እሷን በጣም ጠብቄ ነበር። በእርግጥ ጫናዎች ስለበዙብኝ እንዳልሰራሁ ገብቶኝ ከኤ በታችም ጠብቄ ነበር።ቢ ሳመጣ በጣም ነው ውስጤ የተነካው። ያዘንኩበት ጊዜ ነው። ወደፊት እንደዚያ አይነት ነገሮች እንዳይደገሙ የተሻለ ለመሥራት ነበር ያቀድኩት።\"ሁሌም ወደ ፈተና ከመግባቱ በፊት በጎ ነገር እንደሚያስብ ይናገራል። \"ብዙ ጊዜ ነገሮችን የማቅለል ባህሉና ልምዱ አለኝ\" የሚለው ሙከረም፤ ቀለል አድጎ የማንበብና ፈተናውን እንደሚሠራ እርግጠኛ የመሆን ልማድ እንዳዳበረ ያስረዳል።የሚያነበውና የሚያውቀው ሐሳብ ላይ ያተኩራል። ፈተና ከመጀመሩ በፊት ውጤቱ ጥሩ እንደሚሆን እርግጠኛ ሆኖ ይገባል።\"ሳልገባም፣ ስገባም፣ ከወጣሁም በኋላ የተሻለ ውጤት እንደሚመጣ እጠብቃለሁ\" የሚለው ተመራቂው ፈተና ላይ ሳለ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ የተሻለ ውጤትን ይጠብቃል።ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቡ የዋንጫ፣ ሜዳሊያ እና ላፕቶፕ ሽልማቶች አግኝቷል። ከሁሉም በላይ ግን ከሰዎች ያገኘው ከበሬታ ያስደስተዋል።\"የሰውን ምላሽ ሳይ ትልቅ ውጤት እንዳስመዘገብኩ ነው እየተሰማኝ\"ያለው ሙከሪም፣ \"ከሰዎች የምታገኘው ሞራል በጣም ደስ የሚል ነገር ነው\" ሲል ያክላል። \"ዩኒቨርሲቲው የማስተርስ ሙሉ ስኮላርስፕም ሰጥቶናል።\"ከተመረቀ በኋላ ዋንጫውን ይዞ ኮምፒውተሩን ለመውሰድ ወደ ቤተ ሙከራ አምርቶ እንደነበር ያስታውሳል።ታዲያ ቤተሰቦቹ ሲደውሉት \"ላብ ነኝ\" ብሎ ሲመልስላቸው ለጥናት የሄደ መስሏቸው \"በምርቃቱ ቀን ያጠናል\" ብለው አስበው እንደነበርም አውግቶናል።ሙከሪም ብዙም ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ማጥናት አያዘወትርም። እንዲያውም ትኩረቱ የቡድን የቤት ሥራዎች ላይ ነው።\"ዶርም ከጓደኞቼ ጋር እየተረዳዳሁ። ሁላችንም የየራሳችን አቅም አለን። እኔ ያለኝን አቅም ለሌሎች አሳያለሁ፤ አስረዳለሁ። እነሱም ደግሞ ከእኔ የተሻለ አቅም ስላላቸው ባላቸው አቅም እኔን ያስረዱኛል። ይህ የግሩፕ ጥናት ከአንደኛ ዓመት ጀምሮ እስከምንመረቅበት ድረስ ስናደርግ የነበረው ነው።\"ከክፍል ከወጡ በኋላ ከማጥናት ይልቅ ክፍል ውስጥ የማተኮር ልማድ ያለው ሙከሪም፤ \"ክፍል ውስጥ ያልተረዳሁትን ነገሮች እዚያው ነው ጨርሼ የምሄደው\" ይላል።እሱና ጓደኞቹ ከእነርሱ በታች ያሉ ተማሪዎችን ያስተምራሉ። ይህም የበለጠ እንዲያነብ አግዞታል።ከዩኒቨርስቲው ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ተከትሎ እንቅጠርህ ያሉት ድርጅቶች እንደነበሩና እሱ ግን በትምህርቱ የመግፋት ሐሳብ እንዳለው ይናገራል።በዩኒቨርሲቲው የፌስቡክ ገጽ ላይ ውጤቱን አይተው ያደነቁት፣ ያበረታቱት እንዳሉም ያስታውሳል።ቀጣይ እቅዱ በአገር ውስጥና በውጪም ትምህርቱን ገፍቶበት በሙያው ማኅበረሰቡን ማገልገል ነው።\"ኢትዮጵያውያኖች እንደ ማኅበረሰብ ብዙ ችግር አሉብን። እነዚያን ነገሮች ባለኝ እውቀት መፍታት እና ማኅበረሰቡን የመጥቀም ትልቅ ፍላጎት አለኝ። ግን እሱን ለማድረግ እራሴ ጠንካራ እውቀት ሊኖረኝ ይገባል በሚል አሁን ትምህርቱ ላይ ነው ያተኮርኩት። ከዚያ በኋላ ግን እነዛን ተጠቅሜ የመሥራት ሃሳቡ አለኝ።\"ማኅበረሰቡን የሚጠቅሙ ሶፍትዌሮች መሥራት ህልሙ ነው።በኮምፒውተር ሳይንስ እና ኢንጂነሪንግ፣ በሰው ሠራሽ ክህሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ)፣ በማሽን ለርኒንግ እና ዳታ ሴንስ ዘርፎች ብዙ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ያምናል።በአይሲቲ ዘርፍ ላለፉት አምስት ዓመታት በውድድር ሲሳተፍ እንደነበረና ይህንን በአዳማ ዩኒቨርስቲ እንደጀመረው ይናገራል።ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች የማስፋፋት እቅድም አለው።የሙከሪም አባት ባለ ሱቅ ናቸው። እስከ 12ኛ ክፍል ሲማር ከትምህርት ሰዓት ውጪ ሱቅ ውስጥ ይሠራ ነበር። አባቱ ንግድ ላይ እንዲያተኩር ይፈልጉ እንደነበርም ይናገራል።\"ያደግኩት ንግድ ላይ ነው። አባቴ ሱቅ ውስጥ እንድሠራ ይፈልግ ነበር። እስከ ስምንተኛና ዘጠነኛ ክፍል ድረስ ያሉትን ውጤቶች ሲያይ ግን ወደ ትምህርት ብታደላ የሚል ነገር አመጣ\" ሲል ያስታውሳል።ቤተሰቡ የዩኒቨርስቲ ውጤቱን ሲያዩ ያሉትንም እንዲህ ያስታውሳል. . . \"ደስታቸውን መግለጽ ነው ያቃታቸው። ያኔ ያሰብነው ነገር [ንግዱ] ትክክል እንዳልነበረ ነው ያሰቡት። አሁን ደስተኛ ናቸው። ቤተሰቦቼ የነበረውን ብዙ ጫና ተቋቁሜ በማለፌ ደስተኛ ናቸው።\" \"ቤተሰብን የመርዳት እና የእነርሱን ሃቅ የመጠበቅ ግዴታ ይኖርብኛል። ከሥራዬና ከትምህርቴ ጋር የማይጋጭብኝ ከሆነ ለማገዝ ፍቃደኛ ነኝ\" የሚለው ተመራቂው፤ ከዚህ በኋላ ምናልባትም ከትምህርት ለእረፍት ወደቤት ሲሄድ እንደ ድሮው ቤተሰቦቹን በሱቅ ሥራው ያግዝ ይሆናል።በእርግጥ ከቤተሰቡ በተጨማሪ ሌሎችንም የሚያግዝ ሰው ነው።ዩኒቨርስቲ ከገባበት ጊዜ አንስቶ ለአምስት ዓመታት ተማሪዎችን አስተምሯል።\"ያለኝን እውቀትና ልምድ ለሌሎች የማስተላለፍ ግዴታ አለብኝ ብዬ ስለማስብ ሁሌም አስተምር ነበር። በዚያ የተነሳ ከብዙ ሰዎች ጋር ግንኙነት ፈጥሬያለሁ። በተማሪዎች ዘንድ ትልቅ ተወዳጅነት ነው ያለኝ። ሁሉም ሰው እውቀቱን ለሌሎች ማካፈል አለበት ብዬ ነው የማስበው\" ሲልም ምክሩን ያካፍላል።አብዛኛው ተመራቂ በቀላሉ ሥራ እንደማያገኝ ከግምት በማስገባትም፤ ተመራቂዎች መቀጠርን ብቻ ግብ ከማድረግ የራሳቸውን ሥራ መፍጠር አለባቸው ይላል።\"ግዴታ ቅጥር መጠበቅ የለብንም። ባለኝ እውቀት ምን መሥራት እችላለሁ? ማኅበረሰቡ ላይ ምን ችግር አለ? ምን እድልስ አለ? የሚለውን በደንብ ካየን ያንን መፍታትና ወደ ሥራ መቀየር እንችላለን።\"", "passage_id": "3e04cb60f6416f7021aad0f8e824919f" }, { "passage": "የዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ በተፈጥሮ ሳይንስ ለወንዶች 176፣ ለሴቶች 166 እንዲሆን ተወስኗል፡፡ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ለወንዶች 174፣ ለሴቶች 164 እንዲሆን ተወስኗል፡፡ለታዳጊ ክልሎች የመግቢያ ነጥቡ በተፈጥሮ ሳይንስ ለወንዶች 166፣ ለሴቶች 156፤ በማህበራዊ ሳይንስ ለወንዶች 164፣ ለሴቶች 154 እንዲሆን ተወስኗል፡፡ለአካል ጉዳተኞች ደግሞ መስማት ለተሳናቸው በተፈጥሮና በማህበራዊ ሳይንስ ለወንዶች 120፣ ለሴቶች 115፣ ለአይነ ስውራን በማህበራዊ ሳይንስ ለወንዶች 110፣ ለሴቶች 105 እንዲሆን መወሰኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ", "passage_id": "23df6ce8f253287e6bb77fa4e0209a6c" } ]
87ecf514311349c41b6afcf02971c1fa
5ae2e2375b53d779e4a234768d414b18
ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ በጁባላንድ ኮሪደር በጋራ መስራት በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያዩ
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ በሚዋሰኑበት ድንበር በጁባላንድ ኮሪደር በጋራ መስራት በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያዩ፡፡ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ እንደ ሚያ መለክተው ፣ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ በሚዋሰኑበት ድንበር በጁባላንድ ኮሪደር በጋራ መስራት በሚቻልበት አግባብ ላይ ውይይት ተካሂዷል ፡፡በውይይቱ በቀጣናው ስላለው ወቅታዊ የጠላት እንቅስቃሴ የመከሩ ሲሆን በቀጣናው በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡በውይይቱ ላይ የሴክተር ሁለት አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ጄማ፣ የሴክተር ስድስት ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ማኩርጋ ፓናርድ፣ የ5ኛ ሞተራይዝድ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አሰፋ መኮንን፣ የጁባላንድ ክልል ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና የፌደራል ኤስ ኤን ኤ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የጁባላንድ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡የጁባ ላንድ ምክትል ፕሬዚዳንት ማህሙድ ሰይድ ሶማሊያ ፣ ኢትዮጵያና ኬንያ ወንድማማች ህዝቦች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡የአዋሳኝ ድንበር ቦታዎች ላይ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር የጋራ ጠላት የሆነውን አልሸባብን በጋራ መዋጋት ይገባልም ብለዋል፡፡በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል (አሚሶም) የሴክተር ስድስት ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ማኩርጋ ፓናርድ፥ የኢትዮጵያና ኬንያ ሰላም አስከባሪ ሃይል በጋራ በአካባቢው ሰላም ለማስፈን እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡የክልሉ የፀጥታ ሃይል፣ ከፍተኛ የስራ አመራሮችና ህብረተሰቡም ከጎናቸው እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡የ5ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አሰፋ መኮንን በበኩላቸው፤ የቀጣናውን የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ለማጠናከር አልሸባብን በመዋጋት እንዲሁም የኬላ ፍተሻዎችን በማጠናከር የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡አዲስ መን ታህሳስ 28/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=38959
[ { "passage": "ኢትዮጵያ የጂቡቲ ወደብን  በጋራ የማልማት እድል እንዲሰጣት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ጠየቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮቸ ዙሪያ መክረዋል። ሁለቱ መሪዎች ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የጋራ የሚኒስትሮች ውይይትም ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እንደገለጹት፤ የአገሮቹ ኢኮኖሚያዊ ትብብር  ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ ላይ ድርሻ ተሰጥቷት እንድታለማ ጠይቀዋል። በተመሳሳይ የጂቡቲ መንግስት በቴሌኮምና ሌሎች ልማቶች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ቢሰሩ ትስስሩን የበለጠ እንደሚያጠናክር አስታውቀዋል። ከዚህም ሌላ በህዝቦች መካከል ለዘመናት የዘለቀውን ማህበራዊ ትስስር ማጎልበትና አብሮ የመልማቱ ስራ ብዙ  ርቀት ሊኬድብት እንደሚገባም አውሰተዋል። የመሰረተ ልማት ትስስሩንና የንግድ ልውውጡን ለማጠናከር ከፍተኛ ጥረት እንደሚደረግም ጠቁመዋል። በቆይታቸውም የሁለቱን አገሮችን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በእርሳቸው በኩል ያለውን ቁርጠኝነት ይፋ አድርገዋል። የጂቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ የተሻለ ግንኙነት  በመመስረት \"ህዝቡ ተጠቃሚ እንዲሆን አብረን እንሰራለን\" ብለዋል። የመሰረተ ልማት ትስስር ለመፍጠርና የተቀላጠፈ የወደብ አገልግሎት ለመስጠትም ጥረት እንደሚደረግ ገልጸዋል። ቀጣናዊ ሰላምና መረጋገት እንዲሰፍን በትኩረት የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑን ጠቁመው፤ በውይይታቸው በትኩረት እንደተነጋገሩበት መሪዎቹ አስታውቀዋል ። (ኢዜአ) ", "passage_id": "d548ee62c776a2f44829c82faed4b9e8" }, { "passage": "ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር  ዐቢይ  አህመድ  የሶማሊላንድ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲንና ልዑካቸውን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ሁለቱ ወገኖች በሀገራቱ መካከል ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ ስለማጠናከር፣ በሶማሊላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ደኅንነት ስለማስጠበቅና በሰላምና ደኅንነት ዙሪያ ተባብሮ ስለመሥራት ተወያይተው ስምምነቶች ላይ ደርሰዋል። ፕሬዝዳንት ሙሴ በበኩላቸው ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ለቀጣናው ውሕደት የወሰዷቸውን ርምጃዎች በማንሣት አስተዳደራቸው ከሶማሊያ መንግሥት ጋር በይብልጥ ተቀራርቦ አብረው እንዲሠሩ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ያቀረቡትን ጥሪ እንደሚቀበሉ ገልጰዋል። በተጨማሪም ወደፊት በጋራና በተናጠል ቀጣይ ውይይቶችን ለማካሄድ ተስማምተዋል። ሲያጠቀልሉም ሁለቱ ወገኖች ስለ ወደብ አጠቃቀምና ሌሎችም የኢኮኖሚ ትሥሥር ላይ ተወያይተዋል።ምንጭ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት", "passage_id": "407ecfe1387e58a54199b7e379a79f3f" }, { "passage": "በኢትዮጵያና ኬንያ መካከል የሚደረገው “ስፔሻል ስታተስ” የተሰኘው ልዩ የንግድና ምጣኔ ሃብት ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ በኢትዮጵያ በኩል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡የኬንያ መንግስት ከፍተኛ ድጋፍ እንዳለው የተገለጸ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ባለሃብቶችም በዚሁ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ተጠቃሚ የመሆን ዕድላቸው ሰፊ መሆኑ ተብራርቷል፡፡በኢፌዴሪ ንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር የወጪ ንግድ ጥናትና ማስተዋወቅ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሃይማኖት ጥበቡ ለዋልታ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት፤ በኢትዮጵያ በኩል ተጠናቆ ለኬንያ መንግስት የቀረበው “ስፔሻል ስታተስ” የተሰኘው ልዩ የንግድና ምጣኔ ሃብት ስምምነት ረቂቅ ለሁለቱ ሃገራት የኢኮኖሚያ ትስስር መሰረት የሚጥል ይሆናል፡፡ስምምነቱ በተለየ ትኩረቱም በድንበር አካባቢ ያለውን የኮንትሮባንድ ንግድን ህጋዊ መሰረት በማስያዝ ዜጎችን እውነተኛ የህዝብ ለህዝብ የንግድ ግንኙነት ተጠቃሚ ለማድረግ የወጠነ ነው ተብሎለታል፡፡በርካታ የኢትዮጵያ እና ኬንያ ባለሃብቶች እንዲሁም የንግድ ሰዎች የተሳተፉበት በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የቢዝነስ ፎረም ላይ የተሳተፉ የሁለቱ ሃገራት ተወካዮችም አሁን ላይ እየተጠናከረ የመጣው የሃገራቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን እንዳነሳሳቸው ነው የተናገሩት፡፡እየተጠናከረ ባለው የሃገራቱ ዲፕሎማሲ ኢኩይቲ ባንክ እና ፋሚሊ ባንክ የተባሉ ሁለት የኬንያ ባንኮች በአዲስ አበባ ቅርንጫ ለመክፈት መሰናዳታቸው ነው የተገለጸው፡፡በተለይም ኢኩይቲ ባንክ በተያዘው ሃምሌ ወር መጨረሻ በአዲስ አበባ የሚከፍተውን ቅርንጫፉን እውን በማድረግ የሁለቱን ሃገራት የንግድ ግንኙነት እንደሚያሳልጥ ታምኖበታል፡፡በኬንያ በኩልም የቆዳ ውጤቶች፣ አበባ እና በኢትዮጵያ ለሚመረቱ በርካታ የግብርና ምርቶች መዳረሻ የሚሆን የገበያ እድል መኖሩ ተገልጿል፡፡በአፍሪካ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ የፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ ስኬት ያላቸው ኢትዮጵያ እና ኬንያ በዚህ በኩል ያላቸውን የዓመታት የቀጠናዊ ትብብር ስኬታቸውን ወደ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለማምጣት ብሎም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር አዲስ ምዕራፍ ከፍተው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡በቅርቡ በኬንያ መዲና ናይሮቢ የሁለቱ ሃገራት የ55 ዓመታት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ክብረ በዓልን በማስመልከት በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት ተዘጋጅቶ በነበረው የቢዝነስ ግንኙነት የውይይት መድረክ ኬንያውያን ባለሃብቶች ለንግድና ኢንቨስትመንት ኢትዮጵያን ዋነኛ ትኩረታቸው አድርገው እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡አዲስ አበባ እና ናይሮቢ በጆሞ ኬንያታና ቀዳማዊ አጼ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገራቸው ይነገራል፡፡ ", "passage_id": "e4b12a712cfb8c656af952d91383ec23" }, { "passage": "የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የሚመራ ልዑካን ቡድን ከጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኡመር ጌሊ ጋር ተወያዩ፡፡በትላንትናው ዕለት በጅቡቲ ባደረጉት ውይይት ፕሬዝዳንት ኡመር ጊሌ የሁለቱ ህዝቦች ዘመን የማይሽረው ወዳጅነት የበለጠ እየተጠናከረ መሆኑን ገልጸዋል።ኢንጂነር አይሻ ከዶክተር አብይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለፕሬዝዳንቱ ያቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው የሁለቱ አገራት ግንኙነት የህዝቦቻቸውን ጥቅምና ፍላጎት መሰረት በማድረግ ወደ ላቀ ደረጃ መሸጋገሩን ገልጸው ሁለቱ ወገኖች የተስማሙባቸው የልማት ውጥኖች ተግባራዊ እንዲሆኑ በጋራ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኡመር ጌሊ በበኩላቸው የሁለቱ አገራት ግንኙነት ለአፍሪካ ቀንድና ለአህጉሪቱ ተምሳሌት መሆኑን ለልዑካን ቡድኑ አስረድተው ይኸው ወንድማዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል መንግስታቸው እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።የልኡካን ቡድኑ ከሁለትዮሽ ግንኙነቱ መጠናከር ጎን ለጎን በአካባቢያዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ከፕሬዝዳንቱ ጋር ውይይት ማድረጋቸውም ተገልጿል፡፡ (ምንጭ፡-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት)", "passage_id": "3234962cb18ab247281c80f0d35f7d07" }, { "passage": "ኦሮሞ አባገዳዎች በሶማሌላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተዋል፡፡በውይይቱም የኢትዮጵያና ከሶማሌላንድ ህዝቦች  የሚያስተሳስሯቸውን በርካታ ነገሮችን ለጋራ ተጠቃሚነት ለማዋል  በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ  ተወያይተዋል ።በውይይቱ ላይ የተገኙት የኦሮሞ አባገዳዎች አንድነት ሰብሳቢ አባገዳ በየነ ሰንበቶ እንደገለፁት በተለያዩ የስራ መስኮች ለተሰማሩ ኢትዮጵያዊያንና የሶማሌላንድ ዜጎች ሰላምና አንድነትን ማረጋገጥ ቁልፍ ተግባራት በመሆናቸው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ብለዋል ።በውይይቱ የተገኙት ኢትዮጵያውያንም የሁለቱ አገሮች በትብብር መሥራት የህገወጥ ንግድና የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የሚያደርጉትን  ጥረት  እንደሚያግዝ ገልጸዋል።በተመሳሳይ ሁኔታ የኦሮሞ አባገዳዎች ከሶማሌላንድ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ከሆኑ የአገር ሽማግሌዎችና ሱልጣኖች ጋር ውይይት አካሂደዋል።የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ በከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎችም መቀጠል ይገባዋል ሲሉ በውይይቱ ላይ አንስተዋል።በቀጣይም የሶማሊላንድ የህዝብ ልዑካን  ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝና ተመሳሳይ ጉብኝት በማከናወን ግንኙነቱን ማጠናከር እንደሚገባ የአገር ሽማግሌዎቹ ጠቁመዋል።በሶማሌላንድ ዋና ከተማ ሐርጌሣ የኢትዮጵያ ኮሌጆች፣ የሕክምና ተቋማት እና ሬስቶራንቶች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።በሶማሌላንድ ከ16 ሺህ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩም መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡", "passage_id": "cb665d28feaa2da7fd9b0b0805885ba1" } ]
b3c36df09f2093c7ea034e2dd1f58513
5185dadf64d68adb195255824800fbd0
የማህበረሰባችን ሞራል የት ደረሰ?
በልጅነቴ ያስተዋልኩትን ሐቅ ልንገራችሁ። ነገሩ እንዲህ ነው። ሰዎች ተሰባስበው፣ እንዲቀናቸው ተመርቀው አደን ይሸኛሉ፡፡ኑሯቸውን በዱርና በገደል ያደርጋሉ፡፡በዚህ ሁኔታ ለወራት በመቆየት በለስ የቀናው አንበሳ በመግደል ጀግና ይሰኛል፡፡በለስ ያልቀናው በርሃብ ሲናውዝ ከርሞ ይመለሳል። ገዳዩም ጀግንነቱን በገበያ ያስመርቃል፤ ያውጃል፡፡የገደለውን የአንበሳ ቆዳ በትከሻው ላይ ይደርባል፤ ፀጉሩንም ቅቤ ይቀባል፡፡ከዚያም ሌሎች ጥቂት የሥጋ ዘመዶቹን አስከትሎ በገበያው መሐል እየተንጎማለለ ስለመፈጠሩ እንኳን በውል የማያውቁት በርካታ ሰዎችን በመንጋ ያስጨፍራል፤ ሲዘፍኑለት ይውላሉ፡፡እርሱም እንደሙሽራ ሲሳምና ሲሸለም የሞራል ግለቱ ጣራ ይነካል፡፡እግር የጣለው ሁሉ እያጨበጨበ አብሮ ይተማል፡፡የእንስሳት መብት ተሟጋች በማያውቃት አገራችን በቀደሙት ጊዜያት የአንበሳ ነፍስ ማጥፋት በመንጋ ያስከብርና በመንጋ ያዘፍን ነበር፡፡አሁን ላይ ይባስ ብሎ የሰው ልጅ ሕይወትን በመንጋ ማጥፋት እና በመንጋ አስክሬን መጎተት በመንጋ ያስከብር ይዟል፡፡በመንጋም ሲያስጨፍር አስተውለናል፡፡ እርግጥ ነው በዚህ የመንጋ እንቅስቃሴ ውስጥ የሀብት ጥሪት የመቋጠር ዕድል ያጋጠማቸው እንዳሉም ሹክሹክታ ይሰማል፡፡በመንጋው በአባልነት ተቀላቅለው የዘመቱ በቀን እስከ 500 ብር ሲቋደሱ፤ በመንጋው ዘመቻ በርካታ ሰው በመውረር ‹‹አራስ ነብር›› ሆነው ለዋሉ ደግሞ እንደዘመቻ አውዱ በበቃኝ ሳንቲም እንዲዘግኑ ይደረጋል መባሉን ከመከራ ቀማሿ ድሬ ሹክ ብለውናል፡፡አጃኢብ ያሰኛል፤ ጆሮ አይሰማው የለ፡፡ይሄ ገንዘብ የሚበቅልበትን ዛፍ አምላክ ይወቀው፡፡ተሠርቶ ያልተገኘ በጂኒ የሚመጣ ገንዘብ ሕዝቡን በመንጋ የጂኒ አመል እንዲኖረው አደረገ፡፡ለመልካም ተግባር ሲሆን የመሰባሰቡና የመደመሩ ጉዳይ ዳገት ይሆንብናል፡፡የእኛ ትውልድ እንዲህ ነው፡፡ቅን መሪዎችን ሳይሆን ቅንቅኖችን የሚሻ፡፡ከአብዮች ሳይሆን ከአባዮች የሚወዳጅ፣ ከሚወዱት ሳይሆን ከሚንቁት ጉልበት ሥር የሚወሸቅ፤ ተራማጅ አስተሳሰብን ያልፀነሰ ጮርቃ ሆኗል፡፡ ቢቆነጠጥና አደብ ቢይዝ አይሻልም ትላላችሁ? ‹‹አገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል›› ነበር ብሂሉ፡፡ታዲያ አገሬ ተባይ ማፍራቷ አርጅታ ይሆን እንዴ? እንጃ አይመስለኝም፡፡ትውልዳችንን ልንፈትሽና ልንመረምር ይገባል፡፡ወቅቱን ጠንቅቆ የሚረዳ ብልጥ ትውልድ ያስፈልግ ይመስለኛል፡፡ዋሽቶ ማስታረቅ እንጂ ዋሽቶ ማጋደል በክብር ሲያስጠራ ከታሪካችን አልሰማንም፤ አልተማርንም፤ ለማንም አይበጅም፡፡ዘመኑን የተነጠቀና ቀልቡ የተገፈፈ ባካኝ በአንዳንዶች አጠራር ‹‹የተረገመ›› ትውልድ እንዲበቅል ቆላ ከደጋ እየባከኑ ደም ሲያራጩ መዋልን ሥራዬ ብለው የተያያዙት በርክተዋል፡፡አዎ አገሪቱ እንዲህ አይነት አዳዲስ የሥራ መስኮች የሚፈጥሩ ሰዎች እንዳሻቸው የሚኖሩባት አገር ሆናለች፡፡የተራ ዜጋውም ጉዳይ ‹‹በሬ ካራጁ ….›› አይነት ሆኗል ወዳጄ፡፡‹‹ከደሙ ንፁህ ነን›› ባይ አፈቀላጤዎችም ወንድም ወንድሙን መግደልና ሲያሸብሩ መዋል እንደ ሥራ ስለመቆጠሩ እየነገሩን ነው፡፡እንደው ማን ይሙት በእኔ ልጅ ደም የእሱን ልጅ እንጀራ የሚያበስል የዋህ ኢትዮጵያዊ ስለመፈጠሩ እንደመስማት የሚያንገሸግሽ ሕመም ምን አለ?፡፡ በእምነት ቅንብብ አጥር ውስጥ በቅሎ እዚህ የደረሰ ኢትዮጵያዊ ‹‹ያልዘራውን የሚያጭድ›› አለመኖሩን መረዳት አያዳግተውም፡፡ የሰው ልጅ በሥራው ልክ ተመዝኖ የሚከፈለው በአንድ ወቅት በዓለም ላይ የበቀለ አረም ተደርጎ ሊታይ ይገባል፡፡ራሱን ዘላለማዊ በማስመሰል የአልማዝ፣ የወርቅና የብር ደረጃዎች እየሰጡ እያንዳንዱን ነገር ‹‹ለእኔ›› እያሉ መስገብገብ የኢትዮጵያውያን ስብዕናም አይደለም፡፡የሰው ልጅ ሕይወት መጥፋት የሚያስጨፍረው አካል መታየት ሲጀምር መላ ሊበጅለት ይገባል፤ ሕመም መለከፉን መረዳት ያስፈልጋል። ነገ ራሱ ተራ ጠባቂ ሟችነቱን ረስቶታል ማለት ነው፡፡‹‹ሆሆይ›› ለካ ነገረ ሥራው ከተቀየረ ዋል አደር ብሏል። የምኑ እንዳትሉኝ፤ ከመኖሪያ ቀያችሁ እስከ ፌስቡክ ሰፈራችሁ የምታዩትንና የምትሰሙትን ወሬና ድርጊት አብጠርጥራችሁ ፈትሹ፡፡‹‹ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር…›› ነው ነገሩ፡፡ከእነ እንትና ሰፈር ዕሳት እየጫሩ በእነ እንትና ሰፈር በ‹‹ቪ ኤይት›› ቄንጠኛ መኪና መንፈላሰስ ዋ! ካላስባለ፣ ነገ ጨዋ ልጅ ከሰፈርህ ቀርቶ ከአብራክህ ሊወጣ አይችልም፡፡የሰውነት ሚዛናችን እያነሰ የእንስሳነት አመላችን እየጎለመሰ ይሄድ ይዟል፡፡ እኔ ለአቅመ ማስተዋል ከደረስኩበት ጊዜ አንስቶ ያስተዋልኩት የሰው ልጅ ሞራል የማጣት ልክ እንደዚህ ጊዜ ሲዘቅጥ አስተውዬ አላውቅም፡፡ምን አልባት የእኔ የማስተዋል ልክ ከሆነ አላውቅም፡፡ኧረ እንደውም ባደግንበት ወግና ባህልማ የሰው ልጅ በሕይወት ሲኖር ከሚያገኘው ክብር የላቀ አስክሬኑ ይከበር ነበር፡፡አብሮን ባደገው የመበቃቀል ክፉ ልማዳችንም ውስጥ ቢሆን እንጥፍጣፊ መከባበር ነበረበት፡፡እንኳንስ ሰውን ያህል ነገር ቀርቶ የእንስሳትም ቢሆን አስክሬን የተመለከተ ሰው ያዝናል፤ ባስ ሲልም በዓይኑ በብረቱ የሰው አስክሬን ወድቆ በድንገት የተመለከተ ሰው ራሱን ለከፍተኛ ፀፀት ይዳርጋል፡፡ምን የሠራሁት ሐጢያት (ክፉ ሥራ ) ቢኖር ይሆን ፈጣሪ ይሄን ያሳየኝ፤ በሚል ነፍሱን እሱ ያጠፋ ያህል ፈጣሪውን በፀፀት ይለምናል፡፡ነፍሱ በፈጣሪው ፊት ትጠየቅ እስከሚመስለው ድረስ ይፀፀታል፡፡‹‹ማረኝ›› ይላል፡፡አሁን አሁን የሚስተዋለው ድርጊት ግን ለየቅል ሆኗል፡፡እመኑኝ ታሪክ ዋሽቷል ወይም ትውልዱ ላሽቋል የሚያሰኝ ደረጃ ላይ እንገኛለን፡፡በመንጋ ተነስቶ በመዝመት የሰው ልጅ ሕይወትን ማጥፋት በየትኛውም እምነት የተወገዘ ብቻ ሳይሆን አውሬነት ተደርጎ የሚቆጠር ተግባር ነው፡፡እንዲህ አይነት የአውሬነት ተግባር የመፈፀም ድፍረት እንዲሁ በአጭር ጊዜ የሚለመድ ባህሪ አይምሰላችሁ፡፡ይህ ትውልድ ጤንነቱ ሊፈተሽ የሚገባ ይመስለኛል፡፡በማንኛውም መመዘኛ ሊያሳምን የሚችል አመክንዮ የሚቀርብበት ጉዳይ አይደለም፡፡አዲስ ዘመን ኅዳር 11/2012 ሙሐመድ ሁሴን
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=22886
[ { "passage": "እዚህ ከእምነት ከፍ ባለ መልኩ የሚታይ ሰው የሚባል ፍጡር አለ፡፡ እዚህ በአብሮነት የተጋመደ የእርስ በርስ ፍቅር ያሰረው አንድነት አለ፡፡ እዚህ የእምነት ልዩነት ያልገደበው በጎ ተግባር ለሰብዓዊነት የተሰጠ ከፍ ያለ ቦታ አለ፡፡ ይህ ኢትዮጵያ ነው፡፡ እምነት እዚህ ቦታ ላይ በሰብዓዊነት ይደምቃል፤ በእርስ በርስ ፍቅር ከፍ ይላል፡፡ ምክንያቱም ይህች ምድር እምነቶች በፍቅር አንድ ላይ ሆነው በመተጋገዝ በየራሳቸው የሚያመልኩባት ኢትዮጵያ ነች፡፡ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ የ“ቦሌ ሩዋንዳ የጃዓፋር መስጂድ” ምዕመናን እምነት ሳይገድባቸው በጎ ሰብዓዊ ተግባር ፈፀሙ፡፡ ሌላኛውን የኢትዮጵያዊያንን የአብሮነት ተምሳሌት አንፀባረቁ፡፡ እማሆይ ምናሉ ገብረ ማሪያም አቅማቸው የደከመ፤ ጧሪ የሌላቸው የመኖሪያ ቤት እጦት ከችግር ጋር ያጎሳቆላቸው የ79 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋ ናቸው፡፡ ከዓመታት በፊት መጠጊያ አጥተው ከአንዱ ቤት ወደሌላው ሲንከራተቱ የተመለከቱ እዚያው ቦሌ ሚካኤል አካባቢ የሚገኙ አንዲት ሙስሊም ሴት ለማረፊያ የሚሆናቸው አንዲት ክፍል ቤት ይሰጧቸዋል፡፡ ከጊዜ በኋላ ቤቱ በእድሜ ምክንያት ተበሳስቶ ጣሪያው ተገነጣጥሎ ዛሬ ላይ ይደርሳል፡፡ እማሆይ እዚያው ዘመን በቀየረው፤ ጊዜ ባሳሳው ቤት ውስጥ ዝናብና ፀሀይ ሲፈራረቅባቸው ለዓመታት ኖሩ፡፡ይህንን የተመለከቱ በአካባቢው ላይ ባለ የቦሌ ሩዋንዳ ጃፋር መስጂድ ምዕመናን የእማሆይን ችግር አይተው ማለፍ አልቻሉም። እድሜ ያደከማቸውን፤ ችግር የበረታባቸውን እናት ትተው መሄድን አልፈቀዱም፡፡ ወደ ቤተ እምነቱ ተመልሰው ተመካክረው ገንዘብ አዋጥተው የእማሆይን ቤት በአዲስ መልክ ለማነፅ ተነጋገሩ፡፡ ይሄንን በጎ አላማቸውን ወደ ተግባር ለውጠው በአዲሱ ዓመት ለእማሆይ አሮጌውንና ለፀሀይና ለቁር ሲዳርጋቸው የነበረውን ቤት በአዲስ ለውጠው አስረከቡ፡፡ እማሆይ በአዲስ ዓመት ኑሮን በደስታና በአዲስ መልክ፤ ጀመሩ፡፡ ለዚያውም ለኑሮ የሚሆናቸውን የቤት እቃ በማሟላት፡፡በተደረገላቸው በጎ ምግባር የተደሰቱት እማሆይ ምናሉ ገብረ ማሪያም “ለዓመታት ችግር ውስጥ ነበርኩ አሁን ወገኖቼ በሰሩልኝ ቤት እንደሰው መኖር ጀምሬያለሁ” በማለት ወገናዊ ድጋፉ እረፍት እንደሰጣቸው ይናገራሉ፡፡ በእምነት ብንለያይም ኢትዮጵያዊነት ባሰረው ፍቅር አንድ መሆናቸው የሚያስደስት መሆኑን የተደረገላቸውን ሰናይ ተግባር ከወገናዊ ፍቅር ጋር ያስተሳስሩታል፡፡“ሰብዓዊነት ከምንም ይልቃል” የሚሉት አቶ ሰይድ ሙሀመድ የጃፋር መስጂድ አስተዳዳሪና የእማሆይ ቤት ሲሰራ አስተባባሪ ናቸው፡፡ በእምነት ልዩነት ብቻ የተቸገረን ሰው አይቶ ማለፍ በእምነቱ የማይፈቀድ መሆኑን የተናገሩት አቶ ሰይድ ሰው መሆናቸው እንጂ የእምነታቸው ጉዳይ በጎ ተግባር ከማድረግ ወደ ኋላ እንዲሉ እንዳላደረጋቸው ይገልፃሉ፡፡ የእምነት አባቶች ሰብዓዊነት የሁሉም አማኞች ዋንኛ ተግባር እንዲሆን ሊመክሩ እንደሚገባም ያስረዳሉ፡፡ በጎ ተግባር ለማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር ማድረግ እንደሚገባና ሀይማኖት፤ ዘርና ሌላ የሚለይ ጉዳይ መሰረት ሳያደርጉ ለሁሉም ሰው እኩል ማድረስ ተገቢ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ እንደ ሀገር የጋራ የሆኑ እሴቶቻችንን በማጎልበት የእርስ በእርስ ትስስራችንን ማጠንከር እንደሚገባም ያሳስባሉ፡፡ አቶ አህመድ ሙሀመድ ይባላሉ የበጎ ተግባሩ ተሳታፊ ናቸው፡፡ “እምነት ሳይለይ በጎ ተግባር ለሁሉም ማድረስ ይገባል! የእምነት ዋንኛ ተልዕኮውም ሰውን መርዳት ነው።” በማለት የሰናይ ምግባሩ መነሻ ቅን ልብ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ በማህበረሰባችን ዘንድ ሊለመድ የሚገባና አምላካዊ ትዕዛዝ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ወደፊትም መሰል ተግባራት መቀጠል እንዳለባቸው የገለፁት አቶ አህመድ፤ በቤተ እምነታቸው መሰል በጎ ተግባራትን የማድረግ ሥራ አጠናክረው ለመቀጠል እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡አዲስ ዘመን መስከረም 9/2012ተገኝ ብሩ ", "passage_id": "c023a9573dc28c1e58a9157266c89cec" }, { "passage": "ክፍለዮሐንስ አንበርብርወይዘሮ ሽታዬ ወትዬ፣ ጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ ጎቲቲ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው። ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት በመንግስት እና ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በተሰኘው ግብረሰናይ ድርጅት ድጋፍና አያሌ ጥረት የሠላም አየር መተንፈስ ቢችሉም፤ በ2010 ዓ.ም የጉጂ ኦሮሞዎች እና ጌድኦዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት በሕይወታቸው የማይረሳ ክፉ ጠባሳ ጥሎባቸው ያለፈ ወቅት መሆኑን ያስታውሳሉ።ወይዘሮ ሽታዬ፣ ‹‹በወቅቱ መንታ ወልጄ ነበር። ምንጩ ምንድነው የሚለውን እስከዛሬ በቅጡ በማናውቀው ግጭት አካባቢው የጦር አውድማ ሆነ። ግራ እና ቀኝ እሳት ነው፤ የማያቋርጥ ጥይት ሩምታ ነበር። አዝመራው ወደመ፣ እንስሳት ተዘረፉ። የተገኘውን ቤት ንብረት ማውደምና ማቃጠል ሆነ። ነገሩ የውጭ ወራሪ ጠላት የመጣ እንጂ ወንድማማች በሆኑ ሕዝቦች መካከል የተከሰተ ጊዜያዊ ግጭት አይመስልም ነበር። ከሰፈር ውስጥ ወንድና ሴቱ ሁሉ እግሬ አውጪኝ ብሎ ወደ ጫካ ተሰደደ። እኔም ሁለት ልጆቼን ታቅፌ በእግሩ ድክ ድክ የሚለውን ሌላኛውን ልጄን አስከትዬ ነብሴን ለማትረፍ ወደ ጫካ ብን ብዬ ሄድኩ። መሳሪያ በየአቅጣጫው ያለማቋረጥ ይተኮስ ነበር። በዚህ ጊዜ በእግሩ ይራመድ የነበረው ሕፃን ልጄ ወደየትኛው ሥፍራ እንደተሰወረ ማወቅ አልቻልኩም፤›› ይላሉ በወቅቱ ያሳለፉትን ከባድ ፈተና ሲያስታውሱ።በ2010 ዓ.ም በተፈጠረው ግጭት የመከራው ሰለባ ከሆኑት መካከል በአሁኑ ወቅት የ12ተኛ ክፍል ተማሪ የሆነው አቡሽ በቀለ ሌላኛው ባለታሪክ ነው። በወቅቱ የተከሰተው ችግር ሲያስታውስ እንባውን መቆጣጠር አልተቻለውም። “እንኳንስ ሰው ሣር ምድሩ ተጨንቆ ነበር። የዓለም ገበያን ትኩረት ይስብ የነበረው የቡና ምድር፤ የደም ምድር ሆኖ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች መሳለቂያ መሆናችን ያሳዝናል። ያኔ! አካባቢው ተወረረ። ቤት፣ ሳር ቅጠሉ ነደደ። የተገኘውን ሁሉ መግደልና መዝረፍ ሆነ። አቅመ ዳካማ ሴቶችና አባቶች ሳይቀሩ ፍዳቸውን አዩ። ሮጦ ማምለጥ ያልቻለ ሰው የጥይት ራት ሆነ። ይህ የሆነው ደግሞ በደስታም በመከራም ተለያይቶ በማያውቅ የአንድ አካባቢ ማህበረሰብ ሲሆን፤ የሆነው ሁኔታ ግን ያሳዝናል፤” ሲል በትካዜ የሆነውን ይናገራል።‹‹ግጭቱ ቢያልፍም የዘመናት ህልማችንን ይዞት ሄዷል። ከ30 ዓመት በፊት አባታችን የሰራው ቤትና በቤቱ ውስጥ የነበረው ንብረት በሙሉ ወድሟል። ያፈራው ጥሪት ወደ ዶጋ አመድ ተቀይሯል። ለነገ ብለን ያሰብነው ለዛሬውም ትውልድ ሳይሆን መጥፎ ታሪክ ልናወራ ተገደናል። አሁን ያለነው በፈጠሪ መልካም ምህረትና ግብረ ሰናይ ድርጅት እገዛ ነው›› የሚለው ተማሪ አቡሽ፤ በአሁኑ ወቅት ግን ትምህርቱን ቢቀጥልም አንድ ዓመት በችግሩ ምክንያት በሠላምና ስንቅ እጦት ትምህርት ማቋረጡን ተናግሯል።የገደብ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሲሣይ ታደሰ በበኩላቸው እንደሚሉት፤ ወቅቱን ለማስታወስና የሆነውን ለመናገር “የጨከነ ልብ” ያስፈልጋል። ያ ችግር እንዳይፈጠር ግን ቀደም ብሎ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማቃለል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይቶች ሲደረጉ ነበር። በአካባቢ ችግሮች ቢኖሩ እንኳን በአባገዳዎችና የሃይማኖት አባቶች ተግሳፅ አፈንግጦ ለንብረት ውድመትና ለሕይወት መጥፋት የሚዳርግ ክስተት አልነበረም። በ2010 ዓ.ም የተፈጠረው ግን በአካባቢ ነዋሪዎች ዘንድ በእጅጉ የከፋ ጠባሳ ጥሎ ያለፈ ነበር።ሆኖም ችግሩ ከተከሰተ ጀምሮ አጎራባች ወረዳዎች፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት፣ ኦሮሚያ ክልል መንግስት፣ የፌደራል መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት ርብርብ በማድረግ ነገሮች ወደ መደበኛ ሁኔታዎች እንዲመለሱ ጥረት ተደርጓል። በአሁኑ ወቅትም ነዋሪው በመንግስትና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ትብብር ወደ ቀድሞ ቀያቸው ተመልሰው ኑሯቸውን በተለመደው ሁኔታ እያስኬዱ ለዘላቂ ሠላም ውይይት እየተደረገ ነው። በወረዳው 45ሺ ተፈናቃዮች እና በ13 ቀበሌዎች የሚገኙ 4ሺ200 ቤቶች ተቃጥለው እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሲሳይ፤ በተደረገው ድጋፍ የወረዳው ነዋሪዎች ወደ ሰላማዊ መንገድ ከመመለሳቸውም በተጨማሪ፣ በአደጋው 855 ቤቶችና ቤተ እምነቶች በዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ግብረ ሰናይ ደርጅት ድጋፍ ተመልሶ መገንባታቸውን ተናግረዋል። በችግሩ ለተጎዱ ቤተሰቦችም የምግብና አልባሳት ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ፣ ዶሮዎችና በጎች መሰጠታቸውንም ገልጸዋል። ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በአርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ አስተባባሪነት በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2013 ሳዑዲ አረቢያ 163ሺ ኢትዮጵያውያንን አገሬ ለቃችሁ ውጡልኝ ብላ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ስታደርስና ኢትዮጵያውያን ሲንገላቱ የተመለከቱ ኢትዮጵያውያን ተቆርቋሪነት የተመሰረተ የበጎ አድራጎት ደርጅት ሲሆን፤ በኢትዮጵያ አራቱም አቅጣጫዎች ችግሮች ሲከሰቱ በርካታ እገዛዎችን ሲያደርግ መቆየቱን የሚናገሩት ደግሞ ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት የቦርድ አባል ፕሮፌሰር አቻለምየለህ ደበላ ናቸው።ፕሮፌሰር አቻምየለህ እንደሚሉት፤ ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ከምስረታው ጀምሮ በውጭ እና በአገር ውስጥ ያሉ ኢትዮጰያውያን እክል በገጠማቸው ጊዜ ከአጠገባቸው አልተለየም። ለአብነትም ከቡራዩ፣ ሻሸመኔ፣ ወልቃይትና ጉራፈርዳ በግጭት ሳቢያ ለተፈናቀሉ ዜጎች በሚሊዮኖች የሚቆጠር ድጋፍ አድርጓል። የኮረና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ብሎም ከዓመታት በፊት የቆሼ የቆሻሻ ክምር ተንዶ በዜጎች ላይ ላደረሰው ጉዳትም ድጋፍ አድርጓል።በጌዴኦ በተፈጠረው ግጭት ለተፈናቀሉ ዜጎች በወርልድ ቪዥን አማካኝነት የምግብና የአልባሳት ቁሳቁስ ሲያደርግ ቆይቷል። ከዚህ በተጨማሪም 37 ሚሊዮን 700ሺ ብር በማውጣት በእሳት የወደሙ ቤቶችንን የመገንባትና ነዋሪዎችን ወደቀያቸው የመመለስ ሥራ ማከናወኑንና በቀጣይም ለኢትዮጵያውያን ክብርና ሥም የሚመጥን በጎ ተግባር እንደሚያከናውን እና በመላው ዓለም ድጋፍ የማሰባሰብና አገር የመታደግ ሥራውን እንደሚያጠናክሩ ፕሮፌሰር አቻምየለህ አረጋግጠዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 15/2013 ", "passage_id": "880a9eb18efac4ceb4de8b9c38372c82" }, { "passage": "ንድ ወጣት ሶስት ጉልቻ ሊያቆም አስቦ ከህይወቱ ረጅሙን ዘመን በምርጫ ያሳልፋል። የሚያማልለውን መልክ ሲያስስ የባህሪ ነገር ያሳስበዋል፤ መልኳም ባህሪዋም የተስተካከለውን ሲያገኝ ደግሞ የሙያዋ ነገር አልሳካ ይለዋል። እነዚህን ሁሉ አሟልታለች ብሎ ያገኘ ግዜ ደግሞ ቤተሰቦቿ እሱ እንደሚፈልገው የተመረጡ ፣ የከበሩና የተከበሩ አይሆኑም። እንዲህ ግራ በመጋባት በሰፊ የምኞት ጀልባ የሚቀዝፈው ውቅያኖስ አልገፋ ሲለው የቤተሰቡ የንሰሀ አባት ወደ ሆኑት አንድ መነኩሴ ጥያቄውን፣ የጨነቀውን ሊያካፍልና መንፈሳዊ ከሆኑት ግራ ቀኙን አይተው ምክር ይለግሱኛል ብሎ ወደተማመነባቸው አባት ያመራል። የተለመደውን ሰላምታ ሰጥቶ ቡራኬ ያቸውን ከተቀበለ በኋላ ከጎናቸው አረፍ ብሎ አይን አይናቸውን ተመለከተ። አባ ? “አቤት ልጄ ምን እግር ጣለህ”? ጥያቄያቸው አስቀደሙ ከአፉ የሚወጣውን ለመስማት አንገታቸውን ጎንበስ አድርገው እየጠበቁ። እሱም ምን ብሎ እንደሚጀምር ግራ ገብቶት ትንሽ መሰላሉን ቀጠለ። ወጣቱ ቀጠለ”ሚስት ላገባ ፈልጌ ነበር ?” አባት ፈጠን ብለው” እንዴ ይሄማ ጥሩ ነው፤ የፈጣሪን ትእዛዝ መፈፀም እኮ ነው።” ወጣቱ “አይ አባ ግን ሊሳካልኝ አልቻ ለም። አባ” “ለምን ?” ወጣቱ”እኔ የምፈልጋት አይነት ሴት ማግኘት አልቻልኩም።” አባ”አንተ ምን አይነት ሴት ነው የምትፈልገው?” ወጣቱ ”ቆንጆ ፣ደግ ፣ የተማረች፣ ስነምግባር ያላት\n፣ሀብት ያላት…” ቀጠለ ከልቡ ያለውን ፍላጎት ሁሉ ዘረዘረላቸው። አባ ከአጎነበሱበት ቀና ብለው ”አይ ልጄ እንዲህ አይነት ሴት ብትኖር ኖሮ እኛም ባልመነኮስን ነበር”። አሉ።\nይሄውልህ ሰው ሁሉ በተፈጥሮ በሁሉ ነገር ሙሉ አይደለም። በአንዱ ስታመሰግነው በአንዱ ይጎልብሃል፤ በዛ ላይ ሰዎች እኛ እንደምንፈልገው እንዲሆኑ በተመኘን ቁጥር የበለጠ ጎዶሎ ሆነው ይታዩናል። ስለዚህ አንተ በሁሉም ነገር ወደመረጥካት ለመቅረብ ራስህን አስተካክል እንጂ የተስተካከለ ለማምጣት አትሞክር። ፍፁማዊ ሰው ፍፁማዊ ህይወት የለምና ይሄን አትመኝ። አንተም በሌሎች ሰዎች ብዙ ጉድለቶች አሉብህ። ሆኖም ከሰው ጋር ለመኖር የጎደለው እየሞሉ እየተቻቻሉና እየተደጋገፉ ነው ብለው ምክር ለገሱና ሸኙት። ይህን የቆየ ትርክት ያቀርብኩላችሁ አታውቁትም ብዬ ሳይሆን ለሀሳቤ መንደርደሪያ ቢሆ ነኝ ብዬ ነው እንጂ የኔ ነገር ወዲህ ነው። ከቀናት በፊት ነው የመሬት ካርታ ጉዳይ ለማስፈፀም በአዲስ አበባ ከሚገኝ ክፍለ ከተሞች በጠዋት የተገኘሁት። በክፍለ ከተማው መሬት አስተዳደር ቢሮ የተገኘሁት ለአምስተኛ ግዜ ቢሆንም የነበረው አካሄድ ያለጥርጥር ደጋግሜ እንደምመላለስ የሚያሳብቅ ነበር። እናም ምሬትም ተስፋ መቁረጥም መበሳጨ ትም የታከለበትን ውይይት አብረውኝ ካሉት ተገልጋዮች ጋር ጀመርን። ሁላችንም በሚሰጠው አገልግሎት ደስተኞች አልነበርንም። የየራሳችንን ችግር ውጣ ውረድ እያነሳን አሰራሩ እንዴት መስተካከል እንዳለበትም የግል አስተያየታችንን ሰነዘርን። ትንሽ ቆይተው የተቀላቀሉን አንድ አዛውንት ግን ችግሩ ዛሬ ባሰበት እንጂ እዚህ ሀገር ሁሌም መጉላላት እንዳለ ማብራራት ጀመሩ። በንጉሱ ዘመን ከየትምና የእከሌ ልጅ ነው ካልተባለ የሚሰማህ የለም። ለእነሱ የሆነ እንደሁ የባላምባራስ ልጅ ነው፤ የነጋድራስ ልጅነው አንዳንዴም የእከሌ ዘመድ ነው ካልተባለ ጉዳይህን የሚሰማ የለም። እጅ መንሻም አቅርበህ እንኳ የምትገፋበት ግዜ ነበር። ደርጉም ያው ነው የጄነራል እከሌ፤ የኮሎኔል እከሌ እየተባለ ማእረግ ስልጣን ካልተጠራ ከመስከረም እስከ መስከረም ብትመላለስ ዞር ብሎ የሚያይህ የለም። አቤት ለማለት እንኳ የሚፈራበት ግዜ ነበር። ይቆጡሃል፤ ትገለመጣለህ ፤ትሰደባለህ። አሁንም ያው ነው ለስሙ ዲሞክራሲ መብት ምናምን ይባላል እንጂ ለደሀው የተረፈው ስብሰባና ወሬ ብቻ ነው። ድሮ ተቆጥተው፣ ገላምጠው፣ አገጫብረው አመት ሁለት አመት ያመላልሱ ነበር። አሁን ደግሞ ፈገግ ብለው እየሳቁ አመት ሁለት አመት ያመላልሱናል። ደግሞ እኮ እንደአህያ መልክ ሁሉም መስሪያ ቤት ያሉት ሰራተኞች በክፋት አንድ ናቸው። ሀኪም ቤት ሂድ፤ ውሃ ፍሳሽ ሂድ…. ምን አለፋህ ህዝብን በደሉ፣ አንገላቱ፣… ተብለው የተቀመጡ ነው የሚመስሉት። አዛውንቱ ቀጠሉ፤ እስካሁን ያለችውን ኢትዮጵያን ያለበሷት ማቅ አልበቃ ብሏቸው ወደ ፊቷም ጀመሩ። እናንተ ልጆች ናችሁ ብቻ ፈጣሪ እድሜ ሰጥቶ ያሳያችሁ እንጂ የዛሬ አርባ አመትም እዚች ሀገር ምንም የሚቀየር ነገር የለም። አያያዙ ሁሉ ያስታውቃል። አንዱ ወጣት ጣልቃ ገብቶ ከሞቀ ወሬያቸው አናጠፋቸው እርስዎ ምንድ ነው የሚሰሩት ? አሁንማ ምን እሰራለሁ ጡረታ ከወጣሁ አስር አመት ሊሞላኝ ነው። ድሮማ ምን ያልሰራሁበት ቦታ አለ አለ መዘጋጃ ቤት ብትል፤ መብራት ሀይል ብትል፤ ውሃና ፍሳሽ ብትል ምን አለፋህ በቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ዘመን ከንግድ ስራ ኮሌጅ በዲፕሎማ ከተመረቅኩበት ግዜ አንስቶ ጡረታ እስክወጣ ድረስ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ስር ያልነካሁት ቦታ ያላየሁት ጉድ የለም እያሉ በጣፋጭ አንደበታቸው ትረካውን ምሬቱን እያቀ ላቀሉ ያቀርቡልን ጀመር። እኛም ለማድ መጡ ጆሮ ሰጥተናል። ማንም ያጥፋ ማን ተወቃሹ ትውልድ እኛ አይደለን? ወጣቱ በስጨት ብሎ አዛውንቱን አስከፍቶ ውይይቱን ለመበተን ያበቃውን ንግግር ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ። ከተረት ውጪ ያለ ድካም ማርና ወተት የምታቀርብ ሀገር የለችም። እኔ እርሶዎን ብሆን ዲፕሎማዬን እንደያዝኩ ሀገሪቱን እለቅ ነበር። አሁንም ግን እንደማትቀየር እርግጠኛ ከሆኑ የሚሄዱበት ሌላ ሀገር ፈልገው ቢሄዱ ጥሩ ይመስለኛል። ተስፋ መቁረጥ አንድ ነገር ነው ሰውን ተስፋ ማስቆረጥ ግን ለማንም አይበጅ። ስለዚህ እያንዳንዳችን እየሰራን ብንጠይቅ ለኛም ለሀገርም ለህዝብ ይበጃል አለ። ሁላችንም በዚህ ሀሳብ ተስማማን። በያለንበት በየደረስንበት ያለፈን ታሪክ ከመተረክ አሁን በተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት መስራት፤ ወጣቱን ተስፋ ከማስቆረጥ ወጣቱን በተስፋ መሰነቅ፤ ስነልቦናውን ማነሳሳት፣ ሰርቶ ማሰራት… ያኔ የጎደለው ይሞላል። የሰነፈው ይንቀሳቀሳል፤ ሙሰኛው ያፍራል፤ ለዚህ ግን ሰጪም ተቀባይም እጁን መሰብሰብ አለበት ባይ ነኝ።አዲስ ዘመን ሰኔ 23/2011 ", "passage_id": "92495d7076d8d72f84f3365280b6e405" }, { "passage": " በር ላይ ካናቴራ የለበሱ ወጣቶች ተራርቀው በመቆም እንግዶችን በክብር እጅ ይነሳሉ፡፡ ወደ ግቢው ሲዘልቁ በሞቀ ሰላምታና ፈገግታ ይቀርብልዎታል፡፡ መምጣትዎ ለምን እንደሆነ ስለሚታወቅ ታላቅ ሰብዓዊ ክብር ይቸርዎታል፡፡ መጋቢት 4 ቀን 2012 የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ይፋ መደረግ ተከትሎ መንግስትና ህዝብ ወረርሽኙ እንዳይዛመት ዘርፈ ብዙ ጥረቶች በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ወረርሽኑ ከመቆጣጠር ጎን ለጎን በሽታው በፈጠረው ስጋት ለኢኮኖሚያዊ ችግር የተጋለጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ለመደገፍ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ይገኛሉ ፡፡ ከነዚህ የበጎ ፈቃድና እርዳታ ማሰባሰብ እንቅስቃሴዎች አንዱ ሰብአዊ ጥምረት የሀገር ፍቅር የበጎ ፍቃደኞች ማህበር እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ተጠቃሽ ነው ፡፡ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ውስጥ ማህበሩ በኮሮና ምክንያት ለተለያዩ ችግሮች ለተጋለጡ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ ከማህበረሰቡ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል፡፡ የማህበሩ አስተባባሪና መስራች የሆነው አርቲስት ያሬድ ሹመቴ ሀገር እና ህዝብ ችግር ላይ በሚወድቁበት ወቅት መተባበር የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ያስረዳል፡፡ ማህበሩ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶችን በማስተባበር ከለጋሾች የተለያዩ የምግብ ፣ የዓልባሳትና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኝ ይናገራል፡፡ በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖች ለችግር እንዳይጋለጡና በወረርሽኙ ምክንያት የሚደርስባቸው ጉዳት ለመቀነስ በገንዘብና በዓይነት የተለያዩ ድጋፎችን እያሰባሰቡ ፤ እስካሁን የተሰበሰበው እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ለማድረስ በዝግጅት ላይ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ እስካሁንም በማህበሩ ስም በተከፈተ የሂሳብ ቁጥር ከ800ሺ በላይ ብር መሰብሰቡን ፤ በዓይነት ደግሞ 220 ማዳበሪያ ሞኮሮኒ፣ 70 ኩንታል የስንዴ ዱቄት፣ 500 ካርቶን ፓስታ፣ 600 የተለያየ ሊትር መጠን ያለው ዘይት፣ 152 ካርቶን ሳሙና እና 350 ፈሳሽ ሳሙና (የተለያዩ የሊትር መጠን ያላቸው) እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶችን ከለጋሾች መገኘቱን ያብራራል ፡፡ ማህበረሰቡ ሊከሰቱ ይችላሉ ተብለው የተገመቱ ችግሮችን ለመከላከል እያደረገ ያለውን ትብብርና መደጋገፍ አጠናክሮ ሊቀጥልበት ይገባል ያለው አርቲስት ያሬድ ፣ የገጠመንን አለምቀፍ ወረርሽኝ እንደ ሀገር ሊቋቋም ተባብሮ መቆም የሚያስፈልግበት ወቅት እንደሆነም ያስረዳል፡፡ በማህበሩ ስም የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በመስጠት ላይ እያለ ያገኘነው ወጣት ዮናስ ምትኩ በበኩሉ ፣ ማህበረሰቡ በሚችለው ሁሉ በመደጋገፍ ይህንን ጊዜ ማለፍ የሚጠበቅበት መሆኑን ይገልፃል:: ኮሮናን ለመከላከልና የሚያፈጥረው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ ለመቋቋም ማህበረሰቡና መንግስት እያረጉ ያሉት እንቅስቃሴ የሚያበረታታ ነው ያለው በጎ ፍቃደኛው ወጣት፣ በህብረት ችግሩን ለመፍታት መንቀሳቀስ ዋነኛ መፍትሄ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 28/2012 ተገኝ ብሩ", "passage_id": "5920ec7a65a31984c0f43f87043f723e" }, { "passage": "ጥቂት\nየማንባል ሰዎች አሁን አሁን ከዕለት ሩጫችን የምትተርፍ ጊዜ ብትኖር የቅርብ ዘመዶቻችንን አሊያም ወዳጆቻችንን ለመጠየቅ ማዋል ትተናል፤ የእኛን ጊዜ ከሚፈልጉ ቤተሰቦቻችንም ሆነ ጎረቤቶቻችን ጎን ከመገኘት ይልቅ በተለያዩ ድረ ገፆች በተለይ በተለይ ደግሞ በማህበራዊ ትስስር ገፅ ላይ ማፍጠጥን እንመርጣለን፡፡ ስራችንን ወደጎን በመተውም በየአምስትና አስር\nደቂቃ ውስጥ ተንቀሳቃሽ ስልካችንን አሊያም ደግሞ ኮምፒውተሮቻችንን መነካካት ከተጠናወተን ቆይቷል፡፡ የቱ መቅደም አለበት የሚለው ውሉ ጠፍቶናል፡፡ ለራሳችን ስለራሳችን ጊዜ\nበመስጠት በጥሞና የምናሳልፋት ፍርፋሪ ጊዜ ብንፈተሸ አይገኝብንም፡፡ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ስለተለጠፈው እያንዳንዱ ነገር ስንመራመር፣ በሚሰጡ አስተያየቶች ሆዳችን እስኪቆስል ድረስ ስንስቅ፤ አለፍ ሲልም በመልዕክቶቹ ዙሪያ በተቃርኖ ወይም በድጋፍ የመሰለንን አስተያየት ስናሰፍር አቻ የማይገኝልን ትጉህ ሰራተኞች እንመስላለን፡፡ በማንባቡ፣ በመፃፉና በመሳቁ አንዳንዴም በምናነበው አሊያም በምናየው ተንቀሳቃሽ ምስልም (እውነትም ሐሰትም ሊሆን\nመቻሉ እንደተጠበቀ ሆኖ) ለማልቀስ ስለሚዳዳን የሚታይብን የፊት ገፅታ ምንም ይምሰል ምን አጠገባችን ያለው ማንም ይሁን ማን ግድ አይሰጠንም፡፡ በጣም ስስ ሆነናል፡፡ ይህን\nጉዳይ ለማንሳት ምክንያት የሆነኝ ነገር ወዲህ ነው፡፡ አንድ ጎረቤታችን አባወራ ባለቤቱ ስራዋ አንድ ሳምንት ቀን ሲሆን፣ አንድ ሳምንት ደግሞ ሌሊት በመሆኑ የምትሰራው በፈረቃ ነው፡፡ የማታ የማታ ስትሆን አንድ ዓመት ያልሞላውን ህፃን ልጇን ያው ለአባት ትታ ትሄዳለች፡፡ ይሁንና ስጋት ስለሚያድርባት እስከሚተኙ ድረስ በየ20 እና 30 ደቂቃ ልዩነት መደወሏም የተለመደ ነው፡፡ አባወራው ግን\nህፃኑን ከመከታተል ይልቅ አይኖቹንም ሆነ እጆቹን ከተንቀሳቃሽ ስልኩ ላይ ለአፍታም ቢሆን አያነሳም፡፡ ይህም ‹‹እውነት ይህ ህጻን የእርሱ ነውን›› ብሎ ለመጠየቅ ያስገድዳል፡፡ እንዲያው ልጁ አጠገብ ሆኖ ስልኩን መነካካቱና በማህበራዊ ድረ ገፁ ላይ በተለጠፉ መልዕክቶች ምላሽ ለመስጠት አለመቦዘኑ አይደለም ዋናው ጭንቅ፣ አንድ የሆነ መረጃ (የውሸት ይሁን የእውነት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ) ሲያነብ ካለበት ቤት ወጥቶ ፊት ለፊት ካለው ቤት የሚገኘውን ሌላውን አባወራ በመጥራት ‹‹እንትና የፃፈው አልገረመህም?! እኔማ ጥሩ አድርጌ መልሼለታለሁ…፡፡›› ሲል ብጤውን በመጥራት የባጡ የቆጡን ሲቀበጣጥር ህፃኑን እስከማስለቀስ ይደርሳል፡፡ ይህ እንግዲህ የተለመደ ተግባሩ ከመሆኑም በላይ መድኃኒት ያልተገኘለት ሱስ ሆኖበታል፡፡ እንደተለመደው አንድ ምሽት ላይ የልጇን ወተት ራሷ አፍልታ ትሄድ የነበረች እናት በስራ ከመዋከቧ የተነሳ እንዲያፈላለትና አቀዝቅዞ እንዲሰጠው ከአደራ ጭምር አስጠንቅቃው ወደስራዋ እብስ ትላለች፡ ፡ አባወራው ከስራ\nእንደተመለሰ ሱሱን ጋብ ሊያደርግ የፈረደበት ማህበራዊ ትስስር ገፅ ላይ መጣድ እንጂ ወተቱን መጣዱን ጭርሱኑ አላሰበውም፡፡ ህፃኑ ምርር ብሎ ሲያለቅስ ከተጣደበት ማህበራዊ ትስስር ገፅ ሁለንተናውን ያነሳና ወደ ህፃኑ ማፍጠጥ፤ ከዛም መደንገጥ ይሆንበታል፡ ፡ ፈጥኖም ህፃኑን ለማባበል ከእቅፉ ያስገባዋል፡፡ በሐሳቡ ህፃኑ\nዝም ካለለት በኋላ ወተቱን ለመጣድ ነበር፡፡ ቤት ውስጥ ወዲህ ወዲያ እያለ ህጻኑን ሲያባብል ደቂቃዎች ተቆጠሩ፤ በውስጡም ስላነበባቸውና ስለሰጠው አስተያየት ማሰላሰል ያዘ፤ አፍታም ሳይቆይ ደግሞ ህፃኑን በእቅፉ እንደያዘ ወደ ውጭ ወጣ አለ፡፡ ያንኑ ሰው ይጠራውና ‹‹እኔ የምልህ? ምን ብሎ አፉን እንዳስያዘው አየህ አይደል?! እሱ እኮ ማለት ድሮም ቢሆን አንበሳ ነው፤ እንትናስ ዛሬ ምንም አላለ ይሆን?…›› እያለ ሌላ የወሬ ምዕራፍ በሰፊው ሊጀምር ሲል በአባቱ እቅፍ ውስጥ በብዙ ውዝወዛ ለመረጋጋት የሞከረው ህፃን ርቦት ስለነበር በድጋሜ ምርር ብሎ ሲያለቅስ ወተቱን አለመጣዱ ትውስ ብሎት ዘሎ ወደቤት ይገባል፡፡ በዚህ መሃል በለቅሶ ብዛት የተዳከመው እንቦቀቅላ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ስለወሰደው ወተቱን ይጥዳል፡፡ ሱስ መቼም ቢሆን እስካልተቆረጠ ድረስ ሱስ ነውና ወተቱ እስኪፈላ በማለት ያንኑ የፈረደበትን ስልኩን መነካካት ይጀምራል፤ በሚያየውና በሚያነበው ጉዳይ መመሰጡን ይቀጥላል፡ ፡ ከነጎደበት ዓለም\nየተመለሰው የህፃኑ ወተት አንዲት ጠብታ እንኳ ሳይቀር ሙሉ ለሙሉ ምድጃው ላይ ገንፍሎ ካበቃ በኋላ ነበር፡፡ ወጥቶ ወተት አይፈልግ ነገር ምሽቱም ነጉዷል፤ ህፃኑም ምርር ብሎ ሲያለቅስ ቆይቶ የተኛው ባዶ ሆዱን ነው፡፡ ግራ ተጋባ፤ ባለቤቱ ዘንድ አይደውል ነገር ይብሱኑ እሷን ማናደድና እንድትጨነቅ ከማድረግ ዉጭ አንዳች ፋይዳ የለውም፡፡ የፈራው አልቀረም፤ ህፃኑ ነቃ፤ ለቅሶው እንደ አመሻሹ አይነት አልነበረም፡፡ ሆድ የሚያባባ አይነት እንጂ፡፡ አባትም የፀፀት እንባ ተናነቀው፡፡ የህፃኑን አይን የአዋቂ አይን እስኪመስለው ድረስ ሸሸው፡፡ አይኖቹን ከአይኖቹ አራቀው፡፡ ይህን ድክም እያለ የመጣውን የህፃን ድምፅ የሰሙ ጎረቤት ውድቅት ቢሆንም ‹‹አሞበት ይሆናል፤ እናቲቱም የለች…›› ሲሉ ወደእርሱ ይመጡና ህፃኑን ይቀበሉታል፡፡ መራቡንና ወተቱ ገንፍሎ ማለቁን ሲረዱም በማቀዝቀዣ ውስጥ የነበራቸውን ወተት አስታውሰው ‹‹ቆይ…›› ሲሉ ሮጠው ወደቤታቸው በመግባት እና ወተቱን በማምጣት የጋዝ ምድጃው ላይ እንዲያው ለስሙ ያህል ብቻ ሞቅ አድርገው ለህፃኑ በመስጠታቸው ለጊዜው ህፃኑ እፎይታን አግኝቶ ያሰማ የነበረውም የሲቃ ድምፅ ጠፍቶ ጡጦውን ብቻ በስስት ይምግ ጀመረ፡፡ ምናለ የህፃኑ ወተት እስኪፈላ ለአፍታ ያህል እንኳ ቢታገስ ማለታችሁ አይቀርም፡ ፡ ስንቶቻችን ነን\nበማህበራዊ ትስስር ገፅ ላይ ተጥደን በምንሰጠው አስተያየትና በምንለጥፈው መልዕክት የብዙዎችን ህይወት ያበላሸነው፤ ምናለ ቢቀርስ፡፡ ስንቶቻችን ነን ከተንቀሳቃሽ ስልካችን ጋር ተጣብቀን መትረፍ የሚችለውን ሰው በሰዓቱ ተገኝተን ካለማከማችን የተነሳ ለህይወቱ ማለፍ ምክንያት የሆነው፡፡ ስንቶቻችን ነን ባለጉዳይ ፊት ለፊታችን ቆሞ ሲማፀነን እያየንና እየሰማን በማህበራዊ ድረ ገፅ በመጣዳችን ብቻ ምላሽ ሳንሰጠው ወደቤቱ በምሬት እንዲመለስ ያደረግነው፡፡ ምናለ በልኩ\nብንሆን፡፡ በማያገባንስ ነገር\nገብተን ያልሆነ አስተያየት\nበመሰንዘር አንዱን ከሌላው\nያፋጀነው ስንቶቻችን እንሆን፤\nምናለ አስተያየትስ ሳንሰጥ\nማለፍ ብንችል፡፡ አገርም\nከነውጥ፣ የቅርብ የምንላቸውም\nሰዎች ከስጋት እንዲሁም\nከፅሁፉ እንደተረዳነው ደግሞ\nህፃናት ከረሃብ መትረፍ\nይችላሉና ብናስብበትስ፡፡አዲስ ዘመን ሚያዝያ 29/2011", "passage_id": "169982b48fde2a288c81907954f25211" } ]
2003e5ce6624d9898ab41b0f32c9ada7
9147b8e23c7a66fc6999222e020bd253
መገናኛ ብዙሃን የአገር ሰላምንና አብሮነትን በማጎልበት ረገድ የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ እንዳልሆነ ተገለጸ
 አዲስ አበባ (ኢዜአ)፦ መገናኛ ብዙሃን የአገር ሰላምና የህዝቦችን አብሮነትን በማጎልበት ረገድ የሚጠበቅባቸውን ሚና እየተወጡ እንዳልሆነ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔና የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ትናንት በጋራ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሃፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ እንዳስታወቁት፤ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መገናኛ ብዙሃን እውነተኛ መረጃን ከማሰራጨት ይልቅ የህዝቦችን አብሮነት የሚሸረሽሩ ዘገባዎችን እያቀረቡ ነው። መገናኛ ብዙሃን የሚያሰራጯቸው መረጃዎች በዜጎች ደህንነት ላይ የሚፈጥሩትን አደጋ ሊገነዘቡ እንደሚገባም ያመለከቱት ቀሲስ ታጋይ፤ ‘እኛና እነሱ’ በሚል አስተሳሰብ የሚሰራጩ የተሳሳቱ ዘገባዎች በርካታ ንጹሃን ላይ ጉዳት እንዲደርስ ምክንያት መሆኑን አስታውቀዋል።የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር ሙላቱ አለማየሁ በበኩላቸው፤ በተለይ የፖለቲካ ሰዎችና አክቲቪስቶች በሚዲያ ቀርበው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የጥላቻ ንግግሮችን ሲያስተላልፉ እንደሚስተዋል ተናግረዋል።“አብዛኞቹ የጥላቻ ንግግሮችም በዜና መልክ ለህዝቡ የሚቀርቡ ናቸው” ብለዋል።በርካታ የመገናኛ ብዙሃን ለሰላም ግንባታ ያላቸው ሚና በአግባቡ ከመወጣት ይልቅ ግጭቶች ላይ ትኩረት አድርገው እየሰሩ መሆኑንም አስታውቀዋል።በቅርቡ 15 ያህል መገናኛ ብዙሃን ላይ በተደረገ ጥናት 28 በመቶ የሚሆኑት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።18 በመቶው የሚሆነው ሽፋናቸው ደግሞ በግጭቶችና ከዚያ ጋር ተያይዞ በሚከሰቱ ሰብዓዊ ቀውሶች ላይ ትኩረት ያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።ጥናቱ መገናኛ ብዙሃን ለሰላም መስፈን ያበረከቱት አስተዋጽኦ ዝቅተኛ መሆኑን ያመላከተ እንደሆነም አስታውቀዋል።“የመገናኛ ብዙሃን አሰራር በሚፈለገው ልክ አለመዘመን ተልዕኳቸውን በአግባቡ እንዳይወጡ አድርጓል” ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አንዷለም ናቸው።የሚዲያ ስነ-ምግባር ከየትኛውም ሃይማኖት አስተምህሮ ጋር የሚጣጣም በመሆኑ በተለይ የህብረተሰቡን መልካም እሴቶች አጉልቶ በማውጣት ረገድ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸውም ገልጸዋል።የመገናኛ ብዙሃኑም ህግና ስርዓትን አክብረው ለአገሪቷ ሰላምና መረጋጋት የድርሻቸውን እንዲወጡ የአቅም ግንባታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ተናግረዋል።የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ጠባቂ አባቶችም መገናኛ ብዙሃን ለአገሪቷ ሰላምና ለህዝቦች አንድነት የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።አዲስ መን ታህሳስ 28/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=38960
[ { "passage": "አዲስ አበባ፡- በግጭቶች ወቅት መገናኛ ብዙሃን በሁለት አካላት መካከል ያሉ ልዩነትን በማለዘብ ሰላምን ፣አንድነትንና አብሮነትን የሚያሳይ የአዘጋገብ ስልትን መከተል እንዳለባቸውም ተጠቆመ ።በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር ሙላቱ ዓለማየሁ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት ፤መገናኛ ብዙሃን በግጭቶች ወቅት በሁለት አካላት መካከል ያሉ ልዩነትን በማለዘብ ሰላምን ፣አንድነትንና አብሮነትን የሚያሳይ የአዘጋገብ ስልትን መከተል አለባቸው።“ መገናኛ ብዙሃን\nበቀውስ ጊዜም ሆነ\nከቀውስ ጊዜ ውጭ\nበተቻለ አቅም ዘገባዎቻቸውን\nሚዛናዊ ማድረግ አለባቸው።\nየሁሉንም ማህበረሰብ ሃሳብ\nማንፀባረቅም ይጠበቅባቸዋል። በተለይም\nበግጭት ወቅት እንደ\nኢትዮጵያ ባሉ የተለያዩ\nየብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች፣\nየተለያዩ ሃይማኖቶች፣ የተለያየ\nየአናኗር ዘይቤና ባህል በሚስተናገድበት አገር ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል”ብለዋል። “መገናኛ ብዙሃን የተፈጠረውን ችግር የሚያጎላ ሳይሆን ሊያጠብ በሚችል መልኩ መዘገብ ይጠበቅባቸዋል። በተለይም በቀውስ ወቅት በርካታ የሚጎዱ ሰዎች ይኖራሉ። የእነዚህን ተጎጂ ድምፆች በማካተት ምን አይነት አመለካከት እንዳላቸው ማሳየትም ከመገናኛ ብዙሃን ይጠበቃል” የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ በዚህም ተጎጂዎች አስፈላጊውን ኢኮኖሚያዊና ስነልቦናዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ ተገቢ እንደሆነ አመልክተዋል። ግጭት በሚበዛበት ወቅት\nየመፍትሔ ሃሳብ አመንጪ\nመንግስትን ብቻ አድርጎ\nማየት ተገቢ አይደለም\nያሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤\nመገናኛ ብዙሃን የታላላቅ\nሰዎችን ፣ የሃይማኖት\nእና የባህል አባቶችን\nሃሳብ በማካተት ቀውሶችን\nየማርገብ ሃላፊነት እንዳለባቸው\nአብራርተዋል። ብዙ ጊዜ\nገጭቶች ሲነሱ የብሄር\nቅርጽ ሊይዙ ስለሚችሉ\nመገናኛ ብዙሃን በዘገባዎቻቸው መጠቀም ያለባቸውን ቃላቶች በጣም በጥንቃቄ መጠቀም እንዳለባቸውም ጠቁመዋል። በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሚዲያ ጥናት ትምህርት ክፍል መምህር ደሳለኝ ዓይናለም በበኩላቸው ፣ መገናኛ ብዙሃን በበጎም ሆነ በተቃራኒ መንገድ ከፍተኛ ሚና መጫወት ይችላሉ። በበጎ ከተሰለፉ ማህበረሰቡ ወደ አንድ ሃሳብ እንዲመጣና መግባባት እንዲፈጠር፣ መተሳሰብና መቻቻል እንዲኖረው በማድረግ የአብሮነት ዕሴቶችን ማስቀጠል ይችላሉ። በተቃራኒው ከቆሙ ደግሞ አፍራሽ ተግባራትን ያባብሳሉ፡፡በዚህ ረገድ ድምፀ\nወያኔ፣ ኦ ኤም\nኤን/OMN/፣ አስራት\nቴሌቪዥን እስከተዘጋበት ጊዜ\nድረስ አፍራሽ የሆኑ\nተግባራትን በመከተል በሰፊው\nቅስቀሳ ሲያደርጉ እንደነበር\nአስታውሰዋል። መሰል ችግሮች\nበሌሎች አገራትም ሲያጋጥም\nይታያል ያሉት መምህር\nደሳለኝ፤ መገናኛ ብዙሃን\nህብረተሰቡን ወደ አንድ\nየሚያመጡ ይዘቶች ላይ\nአተኩረው እንዲሰሩ ለማድረግ\nማሳሰ ቢያዎችን መስጠት፤\nአቅማቸውን መገንባት ቀዳሚው ተግባር መሆን እንዳለበት አመልክተዋል። ይህ ካልሆነ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድ ተገቢ ነው ብለዋል። የሀገሪቷ ተጨባጭ ሁኔታ መገናኛ ብዙሃን የሚያስተላልፉትን መልዕክት ገምግሞ ትክክለኛና ትክክል ያልሆነውን ለመለየት እንደ ሀገር ያለው አቅም ዝቅተኛ መሆኑን የገለፁት መምህር ደሳለኝ፤ ይህም የከፋ ጉዳት እንደሚያስከትል አስታውቀዋል። ሚዲያው በትክክል ገንቢ በሆነ መንገድ እንዲሰማራ ጣልቃ መግባት አስፈላጊ መሆኑን በተለያዩ መፅሐፍት በሚገባ የተብራራ መሆኑን ተናግረዋል። የመገናኛ ብዙሃንም ሆኑ ማንኛው ተቋም የመጨረሻ ግቡ ሊሆን የሚችለው የተሻላ ህዝብና ሀገር መፍጠር ነው ያሉት መምህር ደሳለኝ፤ መንግስትም የተሻለ ህዝብና የተሻለ ሀገር መፍጠር ካለው ኃላፊነት አንፃር ቀውስ ሲፈጠር ቀውሱን የሚያባብሱ አካላትን ከአፍራሽ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማድረግ የመጀመሪያ ግዴታው መሆኑን አመልክተዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 9/2012 ፍሬህይወት አወቀ", "passage_id": "2dcd90a37151c7dc73fee625ce3b7f3f" }, { "passage": "ኢትዮጵያ ቀጣይ የምታካሂደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫው ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ መገናኛ ብዙሃን ለመራጩ ማህበረሰብ ሙያዊ ስነ-ምግባርን ያማከለ መረጃ ማድረስ እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ፡፡እንደ አራተኛ መንግስት የሚቆጠረው መገናኛ ብዙሃን ስልጣን በህዝብ ምርጫ የሚወሰንበት ፍትሃዊ ምርጫ ለማካሄድ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ እንደሆነ የዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ንጉሴ መሸሻ ተናግረዋል፡፡ዶ/ር ንጉሴ አክለውም መገናኛ ብዙሃን ማህበረሰቡ ሃገሪቱን በብቃት እንዲሁም ዜጋውን በትጋት የሚያገለግለውን መንግስት ለመወከል ስለሚመርጠው የፖለቲካ ፓርቲ በቂ እውቀት እንዲኖረው ማድረግ ተቀዳሚ ስራው ሲሆን ሙያዊ ስነ-ምግባሩን ባማከለ መልኩ የምርጫ ሂደቱን መዘገብ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎች የመራጩን ህዝብ ይሁንታ ለማግኘት የሚጓዙበት ጎዳና የግጥሚያ ዘይቤ፣ የፍልሚያ ትዕይንት የሚፈጥር እንዲሁም በማህበረሰቡ መካከል አለመግባባትን የሚያነግስ መሆን እንደሌለበት የተናገሩት ዶ/ር ንጉሴ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትም የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሃሳብና መልዕክት በሚገባ በመመልከት ለህብረተሰብ ጆሮ መጠንቀቅ ይገባል ብለዋል፡፡የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትም የምርጫ መረጃዎችን ከማቅረብ በዘለለ ነፃና ገለልተኛ የሆነ ምርጫ ለማካሄድ ቁልፍ የሆነውን ፍትሃዊነት ተግባራዊ በማድረግ ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች ያሳተፈ የውይይትና የክርክር መድረክ መፍጠር እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ምርጫ ለአንድ ሃገር ዴሞክራሲያዊ ጎዳና ምሰሶ በመሆኑ ማህበረሰቡን ያሳተፈ ፍትሃዊ እንዲሁም ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ መረጃን የማድረስ የመገናኛ ብዙሃን ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ምክትል ስራ አስፈፃሚ ሰጠኝ እንግዳው ገልጸዋል፡፡የመገናኛ ብዙሃን ተቀዳሚ ትኩረት መሆን የሚገባው የቅድመ ምርጫ ተግባራት ላይ መሆኑን ገልፀው፣ ማህበረሰብ አሳታፊ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሃሳብ የቃኘ ለሀገር እድገትና ብልፅግና የሚበጅ መሪ መምረጥ ያስችል ዘንድ በር ከፋች የሆነ መረጃን ማድረስ ይገባዋል ሲሉ ምክትል ስራ አስፈፃሚው ለዋልታ ተናግረዋል፡፡አያይዘውም የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙሃን በሚፈጠርላቸው የውይይት መድረክ አንድነት አፍራሽ፣ ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ሃሳቦችን ማንፀባረቅ እንደሌለባቸው እንዲሁም መገናኛ ብዙሃን ይህን የሚያቃና ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል፡፡(በሄብሮን ዋልታው)", "passage_id": "e6304f4cbbb292669b41e91736cc9688" }, { "passage": " – በአገሪቱ ያሉ የመገናኛ ብዙሃን የራሳቸውንና ሕብረተሰበቡን ሃሳብ በነጻ የመግለጽ ሕገመንግስታዊ መብታቸው ባግባቡ ሊጠቀሙበት እብንደሚገባ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽሕፈትቤት አስታወቀ ።የሚድያ ህግ ያስፈለገው በአገሪቱ የሚሰሩ የሚዲያ ተቋማት ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ  ለሕብረተሰቡ እንዲያቀርቡና የተለያዩ የዜጎች አስተያየቶች በነጻነት እንዲያስተናገዱ ለማስቻል ከመሆኑም ባሻገር የዴሞክራሲ ስርዓቱን ለማጠናከር  ያላቸውን የጎላ ድርሻ በመገንዘብ መሆኑን ገልጸዋል።ሚኒስትሩ አቶ ሬድዋን ሰሞኑን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ሀሳብን በነጻ መግለጽና ህግን መተላለፍ  ተደበላልቀው ሊታዩ አይገባም ብለዋል።በአንድ አገር ሕግንና ስርዓትን የማስከበር ተግባር የመንግስት ቀዳሚ ስራ በመሆኑ ህግን የማያስከብር መንግስት አገር መምራት እንደማይችል ጠቁመው  ማንኛውም ጸሐፊም ሆነ ጋዜጠኛ በሚፈጽመው ሕግን የመተላለፍ ጥፋት  ተጠያቂ መሆኑ የግድ  መሆኑን ተናግረዋል።አንዳንድ ሰዎች ህግን በመጣስ መታሰርና  ስማቸውን ማስጠራት እንደ ጀግንነት እየቆጠሩት መምጣታቸው የጠቆሙት ሚኒስትሩ በአገሪቱ ሀሳብን በነጻነት በመግለጽ ሽፋን ተቋማትን የማሽመድመድ፣ ስርዓት አልበኝነትን ማስፈን እንደማይቻል ተናግረዋል።የአምድ አዘጋጆች ለሕብረተሰቡ መረጃ ለመስጠት የታዘቡትን፣ ያዩትንና የስሜታቸውን  በነጻነት በጋዜጦች ከመጻፍ ባለፈና ባልተለመደ ሁኔታ ለጸረ ሰላምና ጸረ ህዝብ ዓላማቸው ማስፈጸሚያ ገንዘብ ከፍለው የሚጽፉ እንዳሉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።መንግስት ህግን የማስከበር ተግባሩን በሚወጣበት ጊዜ ተያያዥነት ከሌለው ጉዳይ ጋር በማገናኘት የማደናገር ስራ እንደሚሰራ የገለጹት ሚኒስትሩ ህግን በጣሱ የግል ሚድያዎች እየተወሰደ ያለውን  ህጋዊ እርምጃ ከምርጫው ለማያያዘ  መሞከሩን ጠቁመዋል።የምርጫ ጉዳይ የህዝብ ጉዳይ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ የገጠሩም ሆነ የከተማው ህዝብ አሉቧልታ የማንበብ ጊዜና ፍላጎት እንደሌለውና የሚያነበውም ቢሆን በሐሰተኛ ወሬ ሳይይፈታ ኑሮውን ለመቀየር ደፋ ቀና በማለት ላይ መሆኑን አቶ ሬድዋን አስገንዝበዋል ።ሚኒስትሩ አያይዘውም በሰከነ መንገድ በተጨባጭ መረጃ ላይ በመመስረት ፣ በመተንተንና የፓርቲዎችን ጥንካሬና ድክመት በመተቸት ህዝቡ የሚጠቅመውን ለመምረጥ ማበረታታት የሁሉም ሚድያዎች ሃላፊነት ነው ብለዋዋል።አምኒስቲ ኢንተርናሽናልና ሁማን ራይትስ ዎችና  መንግስት ልማትን ለማፋጠን፣  ድንቁርናንና ድህነትን ለማጥፋት እያደረገ ያለውን ሁለንተናዊ ጥረት ለማደናቀፍ ህዝብ ተፈናቀለ፣ ሰብአዊ መብት ተጣሰ እያሉ  የሚያሰሙት እሮሮ መሰረተቢስና ጸረ ልማት መሆኑን አስታውቀዋል።ህዝብ ሳይሻሻል በጋርዮሽ ኑሮ እንዲኖር፣ በሰቆቃ ውስጥ ሆኖ የሰብአዊ መብት ተቋማት መዝናኛና የበሬ ወለደ ወሬ የህልውናቸው ማዳመቂያ እንዲሆን በመፈለግ የሚያደርጉት መፍጨርጨር ጊዜ ያለፈበት መሆኑንም አስረድተዋል ።የሰብአዊ መብት ተቋማት ተግባር  ለሰው ልጆች መጨነቅ ሳይሆን በሰው ልጆች ሰቆቃ መነገድ ነው ያሉት አቶ ሬድዋን ሁሴን በህዝብ ሰቆቃ ስም የተመሰረተው ህይወታቸው እየተናጋ መሆኑንም ጠቁመዋል። ", "passage_id": "662a344f95be3226b8b3f03a41d27dda" }, { "passage": "በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን የሰላም ባህል በማሳደግና ዘላቂ ሰላምን በአገሪቱ ለማስፈን የሰላም ሚዲያ ኔትወርክ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ፡፡የሰላም ሚኒስቴር መገናኛ ብዙሃን ለሀገር ሰላም በሚሰሩበት ሁኔታ ላይ ከኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች የዘርፍ ማህበር ጋር የጋራ መግባቢያ ሰነድ ዛሬ ተፈራርመዋል፡፡የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አልማዝ መኮንን በዚህን ወቅት ስለ ሰላም ለመገናኛ ብዙሃን የግንዛቤ ስልጠናዎችን ከመስጠት ጀምሮ የሚዲያ ተቋማት ትክክለኛና ኃላፊነት የተሞላበት መረጃዎችን ለህዝቡ እንዲያደርሱ ሚኒስቴሩ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ነው ብለዋል፡፡የስምምነቱ ዋነኛ ዓላማም መገናኛ ብዙሃን በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሚስተዋለውን የሰላም እጦት እንዲገታ አሻራቸውን እንዲያኖሩ ለማስቻል ነው ተብሏል፡፡በመግባቢያ ሰነዱ የፊርማ ስነሥርዓት መንግስት የሰላም መደፍረስ መንስኤዎችን በመገናኛ ብዙሃን እንዲያጋልጥ የበኩሉን ድጋፍ ማድረግ እንዳለበትም ተገልጿል፡፡ ", "passage_id": "21f5570aa85bc53fcf6d1d960888decb" }, { "passage": "አዲስ አበባ፡- የመገናኛ ብዙሃኑ ትክክለኛ መረጃዎችን ለህዝብ በማድረስ ስራ ላይ እንዲጠመዱ በኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ጥሪ አቀረቡ። የመንግስት ረዳት ተጠሪ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ መገናኛ ብዙሃኑ በምክር ቤቱም ይሁን ከአስፈፃሚ አካላት የሚተላለፉ መረጃዎችን በትክክል ከምንጫቸው በማጥራትና ፈልፍሎ በማውጣት ለህዝብ የማድረስ ስራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። እንደ አምባሳደር መስፍን ገለጻ፤ መገናኛ ብዙሃኑ በህዝቡ ውስጥ ያሉ ችግሮችን ያለማጋነንና ያለማሳነስ እንዲሁም ቦታው ድረስ በመሄድ በትክክለኛ መረጃዎች የታገዘ ስራ መስራት አለባቸው። ይህን በማድረጋቸው በአንድ በኩል መንግስት ስራውን በአግባቡ እንዲወጣ ከማገዙም በተጨማሪ በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት ኃላፊነቱን በማይወጣበት ጊዜ ህዝብ የመረጠው ምክር ቤት ተፅዕኖ እንዲፈጥር ያስችላል። ረዳት ተጠሪው፣ ‹‹የማህበራዊ ሚዲያው አገራችን ባጋጠማት ችግር ውስጥ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፣ አገሪቱ አንድነቷ እንዲጠናከር በሚያደርጉ መረጃዎች ላይ ማተኮር አለበት። በየቀኑ ህዝቡን የሚያጋጩ የተሳሳቱ መረጃዎች መተላለፍ የለባቸውም። የዜናዎቹና የመረጃዎቹ ምንጭ በአግባቡ መጣራት ይኖርባቸዋል›› ሲሉ ጠቅሰው፤ለሁሉም የመገናኛ ብዙሃንና የማህበራዊ ሚዲያ ላይ ላሉ አካላት መረጃ በጥራትና በወቅቱ እንዲሁም በትክክለኛ መንገድ ማስተላለፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል። ‹‹መገናኛ ብዙሃን ሰላማችንን ዘላቂ የሚያደርግ፣ የዴሞክራሲ ስርዓትን የሚያጎለብት፣ የአገሪቱን አንድነት የሚያጠናክርና በህዝቦች መካከል ያለውን የቆየ የባህል፣ የቋንቋና የታሪክ ትስስርና አንድነትን ይበልጥ ከፍ የሚያደርግ ስራ ላይ መጠመድ አለባቸው›› ያሉት አምባሳደር መስፍን፣ ልዩነትን ከሚሰብኩና ከሚያባብሱ ግለሰቦችና የፖለቲካ አቋም ካላቸው ጋር የሚደረግ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለአገር አይበጅም ሲሉ ገልጸዋል። ስለዚህ ሚዲያው በዚህ ላይ ትክክለኛ ስራ ቢሰራ ምክር ቤቱ ለሚያደርገው የለውጥ እንቅስቃሴው ሚናው የጎላ እንደሆነም አመልክተዋል። አዲስ ዘመን መጋቢት 10/2011በ ", "passage_id": "50203d486a1ede20b6bbedd70d6159d1" } ]
a0029c313cf0f4f90ba350bd387de7a8
ff0227b399f04d5e01002f2f502a6739
ኮሚሽኑ ለመተከል ተፈናቃዮች ዘላቂ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ
አሶሳ፡- በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የመተከል ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም የሚደገውን ጥረት በዘላቂነት እንደ ሚደግፍ አስታወቀ፡፡ በኮሚሽኑ የአሶሳ ንዑስ ቢሮ ኃላፊ ሚስ ጆላንዳ ቫን ለኢዜአ እንዳስታወቁት ፣ ኮሚሽኑ የመተከል ተፈናቃዮችን ለመደገፍ ከክልሉ መንግስት ጋር በቅንጅት እየሠራ ነው፡፡በክልሉ የተለያዩ የተባበሩት መንግስታት ረጂ ድርጅቶች እንዳሉ የጠቀሱት ኃላፊዋ፤ ድጋፉን ለማጠናከር ቅንጅታዊ አሰራር ፈጥረን እየተንቀሳቀስን ነው ብለዋል፡፡ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ ለዞኑ ተፈናቃዮች ምግብ ነክ ያልሆኑ የቁሳቁስ ድጋፎች ሲደረጉ መቆየታቸውን አመልክተዋል፡፡የመተከል ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም መንግስት የሚያደርገውን ጥረት ኮሚሽኑ በቀጣይም በዘላቂነት እንደሚደግፍ አስታው ቀዋል፡፡ ከኮሚሽኑ ጋር በመቀናጀት ለመተከል ተፈና ቃዮች ድጋፍ እያደረጉ ከሚገኙ ተቋማት መካከል አክሽን ፎረ ዘ ኒዲ የተባለ ረጂ ድርጅት የአሶሳ ቅርንጫፍ አንዱ ነው፡፡ የቅርንጫፉ ኃላፊ አቶ መላኩ ገዛኸኝ እንዳሉት፤ ድርጅቱ ሰሞኑን ለመተከል ተፈናቃዮች ባደረገው የመጀመሪያ ዙር እገዛ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በድጋፍ አቅርቧል፡፡ከቁሳቁሶች መካከል የምግብ ማብሰያ እና መመገቢያ ቁሳቁሶች፣ አልባሳት፣ ፍራሽ፣ የአልጋ አጎበር እና ሌሎችም ለክልሉ አደጋ ስጋት እና ስራ አመራር ኮሚሽን ማስረከቡን ጠቅሰው፤ ድጋፉ ቀጣይነት እንደሚኖረው አስታውቀዋል፡፡የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋት እና ስራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ታረቀኝ ተሲሳ በበኩላቸው ፣በክልሉ የመተከል ተፈናቃዮችን መልሶ ማቋቋም መንግስት ብቻውን የሚወጣው ባለመሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የማሳተፍ ስራ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ድርጅቶቹ ለቀረበላቸው ጥያቄ ተግባራዊ ምላሽ እየሰጡ ነው ብለዋል፡፡ድጋፉን እያደረጉ ከሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መካከል የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እና አብረው የሚሰሩት ድርጅቶች ዋነኞቹ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ድጋፉን በክላስተር በመለየት ለማሰባሰብ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ ድጋፉን ወደ መተከል በቀጥታ ማድረስ የማይችሉ ድርጅቶች በአሶሳ እና አካባቢው እንዲያስረክቡ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ እስካሁን በርካታ ምግብ እና ቁሳቁሶች በድጋፍ መሰብሰባቸውን ጠቁመዋል፡፡በቅርቡ የተሰባሰበው ድጋፍ ወደ መተከል ቡለን እና ድባጤ ለማድረስ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ቀደም ሲልም ለመተከል ተፈናቃዮች ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉ በወቅቱ ተገልጿል።አዲስ መን ታህሳስ 28/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=38973
[ { "passage": "በምዕራብ ጉጂና ጌዴዖ ዞኖች ግጭት ቀዬውን ጥሎ እንዲበተን የተገደደው ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ዛሬም ደራሽ ዕርዳታ ይሻል።ለግጭቶቹ ዘላቂ መፍትሔና ተፈናቃዩን ሕዝብ መልሶ ለማቋቋም የአካባቢውና የፌድራል መንግስት ሊወስዱ ከሚገቡ እርምጃዎች ባሻገር ዜጎች በሕይወት አድኑም ሆነ በሃገር ደረጃ ብጥብጥን በሚያርቁና ሰላም በሚያመጡ ጥረቶች ዜጎች ያላቸውን ሁነኛ ድርሻ የሚያመላክት ምግባር ነው።የዋሽንተን ዲሲው “ዓለምቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት” የተሰኘው የጋራ ግብረ-ኃይል መሰንበቻውን ለጌድዎ ተፈናቃዮች እርዳታ አሰባስቧል።ከግብረ ኃይሉ ሊቀ መንበር ከአርቲስት ታማኝ በየነ ጋር የተካሄደውን ቃለ ምልልስ ሁለተኛ ክፍል ከዚህ ያድምጡ።\n ", "passage_id": "4c77a1f755c3cae62671cdb649d8a67d" }, { "passage": "የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ድጋፍና ድንገተኛ አደጋዎች አስተባባሪ ጽ/ቤት፤ በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው ለነበሩና ወደ ቀዬአቸው ለተመለሱ ኢትዮጵያውያን አለማቀፉ ሕብረተሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ፡፡ ከሰሞኑ በኢትዮጵያ የግጭት ተፈናቃዮች የሚገኙባቸውን ቦታዎች የጎበኙት የጽ/ቤቱ ሃላፊ ማርክ ሎውስክ፤ “ወደቀያቸው የተመለሱ ተፈናቃዮችን ማቋቋም የኢትዮጵያ መንግሥት ብቻውን የሚወጣው ጉዳይ አይደለም፣ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ከመፈጠሩ በፊት አለማቀፉ ሕብረተሰብ የተጠናከረ ድጋፍ ማድረግ አለበት” ብለዋል፡፡ የጽ/ቤቱ ኃላፊ እንደገለፁት፤ ወደ ቀያቸው የተመለሱ ተፈናቃዮች በክረምቱ ወራት የግብርና ሥራ ባለማከናወናቸው ቀጣዩን አመት ሙሉ እርዳታ ጠባቂ ሆነው ይቆያሉ፡፡ 3 ሚሊዮን ከሚጠጉት ተፈናቃዮች በተጨማሪም አገሪቱ 8.5 ሚሊዮን ዜጎቿ በቀጣዩ ዓመት ሙሉ የምግብ፣ መጠለያ፣ ሕክምና፣ አልባሳት እርዳታ ፈላጊ ናቸው ብሏል - ጽ/ቤቱ፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ውስብስብ ቀውሶችን እየተጋፈጠች ትገኛለች›› ያሉት የጽ/ቤቱ ኃላፊ፤ ከእነዚህም መካከል ድርቅ፣ ጎርፍ፣ የበሽታ መስፋፋትና የብሄር ግጭቶችን በመጥቀስ  የኢትዮጵያ መንግሥት እየተጋፈጣቸው ያሉትን እነዚህን ተግዳሮቶች አለማቀፉ ማህበረሰብ ተረድቶ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡  ", "passage_id": "5c76e3dabe919cccae8678a2819025f9" }, { "passage": "አሜሪካ በትግራይ ክልል በተካሄደው የህግ የማስከበር ተግባር ለተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል ከ18 ሚሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ ማድረጓን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ አስታውቀዋል፡፡ድጋፉ በዩኤስጂ አጋሮች የተገኘ ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ ሰብአዊ ድርጅቶችን በማገዝ ከኢትዮጵያ ተፈናቅለው በሱዳን የሚገኙ ከ52 ሺህ በላይ ስደተኞችን ፍላጎት ለሟሟላት እና በጅቡቲ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የሚገኙ ተፈናቃይ ዜጎችን ለማገዝ ነው ተብሏል፡፡ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል፣ በጎርፍ የሚጠቁ ማህበረሰቦችን ለመርዳት እና ከኤርትራ ተፈናቅለው በኢትዮጵያ የሚገኙ ዜጎችን ለማቋቋም የታሰበ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ድጋፉ መጠለያዎችን፣ አስፈላጊ የጤና እንክብካቤን፣ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታን፣ ትምህርትን፣ የአካባቢ ጽዳትና ንፅህና አገልግሎቶችን ለስደተኞች እና ለተፈናቀሉ ዜጎች ለማቅረብ እንደሚውል ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡", "passage_id": "1f2e87710ba412b3f9f8a80426b9d67f" }, { "passage": "አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2013(ኤፍ.ቢ.ሲ) የአለም ዓቀፍ በጎ አድራጎት ተቋማት በህግ ማስከበሩ ሂደት ለተፈናቀሉ ወገኖች በጎንደር፣ ደባርቅ እና ዳባት በመገኘት በሰላም ሚኒስቴር ከሚመራው ቡድን ጋር በመቀናጀት የተጎዱትን መልሶ ማቋቋም ላይ እንደሚገኙ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የፋና ድረ ገጽ ይጎብኙ፤ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን ይወዳጁንዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!", "passage_id": "b0bf1914023f598c262621d88f30c31d" }, { "passage": "በኢትዮጵያ ከቀያቸው ተፈናቅለው ከሚገኙ ዜጎች ውስጥ 900 ሺህ የሚጠጉትን ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ማድረጉን መንግስት አስታውቋል፡፡ከግጭት እና መፈናቀል ጋር በተያያዘ እስከ አሁን 1 ሺህ 300 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ዛሬ በሰጠው መግለጫ ያስታወቀው፡፡በኢትጵዮጵያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ከማንነትና የወሰን አስተዳዳር ጋር በተያያዘ ከቀያቸው ተፈናቅለው ይገኛሉ፡፡እነዚህ ዜጎችን አንድም ጊዜያዊ ሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ በማድረግ በሌላ በኩል ደግሞ በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ለማድረግ ህዝብና መንግስት ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡በዚሁ ጉዳይ ላይ መግለጫ የሰጠው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በኢትዮጵያ ከነባር የመከባበርና የባሀል እሴቶች ባፈነገጡ መልኩ ዜጎች ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ መደረጉን አንስቷል፡፡እነዚህን ዜጎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያገኙ ብሎም ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ መደረጉን ነው የገለፀው፡፡መጭው የክረምት ወቅት እንደመሆኑ ተፈናቃዮች ለህመም እንዳይዳረጉ መንግስት 5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በመመደብ ዓለም አቀፍ የመድሃኒት ግዥ እየፈፀመ መሆኑን ያነሱት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊው አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለግጭትና መፈናቀል ምክንያት የሆኑ እና በዚህ ሂደትም በቀጥታ ተሳትፎ ያላቸውን አካላት ተለይተው በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እንደተከናወነም ገልፀዋል፡፡ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥላቻ፣ ተፈናቃዮችን የገንዘብ ምንጭ አድርጎ መነገድ እንዲሁም መደበኛና ማህበራዊ ሚዲያዎች ጥንቃቄ የጎደለው ዘገባን ማሰራጨታቻው ለግጭትና መፈናቀል ከተለዩ ችግሮች ውስጥ እንደሚጠቀሱ አቶ ንጉሱ ገልፀዋል፡፡የሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክት የገበታ መርሃ ግብር በተመለከተ በአዲስ አበባ ላይ ፕሮጀክቱ ተጀምሮ በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞችም እንደሚቀጥል ማሳያ ነው ያሉት አቶ ንጉሱ ለፕሮጀክቱ የተለያዩ ዓለምአቀፍ ድርጅቶችና ሀገራት ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡የሸገር ገበታ መርሃ ግርብር በመጪው ግንቦት አስራ አንድ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሚካሄድ ሲሆን ፕሮጄክቱን ለማጠናቀቅ ሶስት ዓመታትን እንደሚፈጅ ታውቋል፡፡ ", "passage_id": "0313d464862199d032b177baf4dd6e16" } ]
a068bd97ab6741a96eabc91cc3b6aa37
548896a85a6f3a40c83b6d19a8d83b8f
ከባድ ፈተናን ተሻግሮ የሚወለድ ስኬት
ማንኛውም ሰው በሕይወት ዘመኑ ፈተና ይገጥመዋል፡፡ ፈተናው ከባድም ቀላልም ሊሆን ይችላል፡፡ ቁምነገሩ ፈተናውን አልፎ ወደሚታሰብ ስኬት መድረስና ለዚህም ተስፋ ሳይቆርጡ የሚቻለውን ብቻ ሳይሆን የማይቻለውን ነገር ለመሞከር ጥረት ማድረግ ነው፡፡ የስፖርቱ ዓለም ሰዎች ወደ ታላቅ ስኬት ከመሸጋገራቸው በፊት የተለያዩ ከባድ ፈተናዎችን የመጋፈጥ አጋጣሚዎች በሕይወት ዘመናቸው ሲከሰቱ ማየት የተለመደ ነው፡፡ የስፖርቱ ዓለም በርካታ ከዋክብቶች ከሞላ ጎደል በዚህ ዓይነት የሕይወት ውጣ ውረድ ማለፋቸውን የስኬታቸው ጫፍ ላይ ሆነው ሌሎችን ለማስተማርና ለማነሳሳት ብሎም በሕይወት ዘመናቸው የቱንም ያህል ከባድ ፈተና ቢገጥማቸው ውስጣቸውን በተስፋ ለመሙላት ሲናገሩት ይደመጣል፡፡ ዓለማችን በጤና ቀውስ ውስጥ ባለችበት በዚህም ወቅት የተለያዩ የስፖርቱ ዓለም ወጣትና ተስፈኛ ትውልዶች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ችግሮች ሊደቀኑባቸው እንደሚችሉ እርግጥ ነው፡፡ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ አገራት ውስጥ ነገን በትልቅ ተስፋ የሚጠባበቁ ወጣት ስፖርተኞች የአገራችንም ይሁን የዓለም ስፖርት መድረኮች ሽባ በሆኑበት በዚህ ወቅት በምጣኔ ሀብትና በሌሎች ፈተናዎች ሊወጠሩ እንደሚችሉ ግልፅ ነው፡፡ ይህን ፈተና በፅናት ለማለፍ የሥነልቦና ጥንካሬና ተስፋ አለመቁረጥ በባለሙያዎችም ይመከራል፡፡ ከዚህም በዘለለ አሁን ላይ በስኬት ማማ ላይ የተቀመጡ ከዋክብቶች ካለፉባቸው የሕይወት ውጣ ውረዶች በመማር ራሳቸውን በተስፋ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለዚህም የሼን ደፊ ፈተናና የኋላ ስኬት ታሪክ አንዱ ምሳሌ ሊሆን ይችላል፡፡ እ.አ.አ በ2010 ሰኔ ወር ሼን ደፊ መልዕክት ደረሰው። ለአየርላንድ ብሔራዊ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ መጠራቱን የሚያበስር መልዕክት ነበር። ገና በአስራ ስምንት ዓመቱ ለብሔራዊ ቡድን መጠራቱ ታላቅ ተስፈኛነቱን ያረጋገጠለት ስለነበር ደስታው ወደር አልነበረውም። ደፊ ዘለግ ያለ፣ ደንደን ያለ የፈርጣማ ሰውነት ባለቤት ነው። ሃያ ዓመት ሳይሞላው ዘጠና ኪሎ ግራም ይመዝናል። ቁመቱ ደግሞ 1ነጥብ 93 ሜትር ይረዝማል። እ.አ.አ በ2010 በኤቨርተን ጥቂት ጨዋታዎች ላይ እንደተሰለፈ ጆቫኒ ትራፓቶኒ ለአየርላንድ ብሔራዊ ቡድን የጠሩት ለመሐል ተከላካይነት ስፍራ ያስፈልጋል የሚሉት ተክለ ሰውነት ስላለውም ጭምር ነበር።አየርላንድ ከፓራጓይ ላለባት ግጥሚያ ቡድኑ ዝግጅት ጀመረ። በልምምድ ማዕከሉ የልምምድ ጨዋታ ሲያደርግ ደፊ በተከላካይነት ሚናው ተጫወተ። በጨዋታው እንቅስቃሴ መሐል ከክንፍ በኩል ኳስ ተሻማ። ደፊና የተከላካይ መስመር አጋሮቹ የሚያጠቃው ቡድን ተሻጋሪዋን ኳስ እንዳያገኛት ለማገድ ተረባርበው ታገሉ። ደፊም ተሻማ። ግን ግጭት ደርሶበት ወደቀ። አጋጣሚው ወትሮ ከሚያጋጥም የ«ጎል ላስቆጥር፣ አታስቆጥርም» ፍልሚያ የተለየ አልነበረም። ጉዳቱም ከተለመደ ጉዳት ይለያል ብሎ መገመት አይቻልም። ግን ግዙፉ ጎረምሳ ከወደቀበት መነሳት አቃተው። የተቧጨረ፣ የደማ፣ የተሰበረ የውጪያዊ ሰውነት ክፍል አይታይበትም። ሆኖም ደፊ ጣር ያዘው። ተሰቃየ። የሲቃ ድምፁን አሰማ። የአየርላንድ ቡድን የሕክምና ቡድን አባላት ህመም የሚሰማው የትኛው የሰውነቱ ክፍሉ ላይ እንደሆነ ሲጠይቁት በጎድን አጥንቱ ስር ያሳያቸዋል። ስቃዩን አይተው የገጠመው ጉዳት ቀላል እንዳልሆነ በመረዳታቸው በአስቸኳይ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ወሰዱት።በደብሊን በሚገኘው ማተር ሆስፒታል ሲደርስ አስቸኳይ ቀዶ ጥገና ታዘዘለት። ግብ ክልል ውስጥ የነበረው ፍትጊያና ግጭት ውጪያዊ ሳይሆን ውስጣዊ አካሉ ላይ ከባድ ጉዳት አድርሶበታል። በቢላዋ የሸረከቱት ይመስል ጉበቱ ተቀደደ። 3ነጥብ6 ሊትር ደም በመፍሰሱ ሆዱ ተነፋ። ከሰውነቱ የደም መጠን ሁለት ሦስተኛ የሚሆነው ሆድ ዕቃውን ሞላው። እሱንም ለማስቀረት የቀዶ ጥገና ርብርቡ ቀጠለ። በዚያች ክፉ ማክሰኞ አደጋው ደርሶበት ሆስፒታል ከገባ በኋላ እስከ ሐሙስ ድረስ ራሱን ስቶ ቆየ። ከዚያም እስከ እሁድ ድረስ በከፍተኛ የሕክምና ክትትል መስጫ ክፍል ውስጥ ከረመ። በሆስፒታል ኮሪደር ላይ በጭንቅ ወዲያ ወዲህ የሚሉት ወላጆቹ ከከፍተኛ የሕክምና ባለሙያዎቹ ቁርጡ ተነገራቸው። «ልጃችሁ የመትረፍ ዕድሉ ጠባብ ነው» ተባሉ። የልጃቸውን የሞት ዜና መጠባበቅ ጀመሩ።የደፊ ጉበት ደም ስሮች በመተርተራቸው ደሙ ውስጡ ተንዠቅዥቋል። ብዙ ደም ከመደበኛ ሥራው ውጪ ሆኗል። የተጫዋቹን ሕይወት ለመታደግ ብዙ ደም ወደ ሰውነቱ መጨመር አስፈለገ። ልቡና አእምሮው ደም ማጣት የለባቸውምና። በእግር ኳስ ሜዳ ላይ እንዲህ ዓይነት ጉዳት የተለመደ አይደለም። ጉዳቱ በከባድ የመኪና አደጋ ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል እንደሆነ ዶክተሮቹ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ ሕክምናው ስኬታማ ነበር። አቅሉን ከሳተበት ሲመለስ ምን ዓይነት አደጋ እንደደረሰበት ተነገረው። እርሱም «በቃ አበቃልኝ» በማለት ተስፋ ቆረጠ። ሐኪሞቹ ግን ጥረታቸውን ቀጠሉ። ደፊ ከጉዳቱ ሙሉ ለሙሉ ለማገገም ስድስት ሳምንታት አስፈለጉት። ለማገገም ብዙ ለፍቶ ከስድስት ወራት በኋላ ልምምድ ጀመረ። ዘጠና ኪሎ ግራም ይመዝን የነበረው ተከላካይ አስራ ስምንት ኪሎ ግራም ቀንሶ ወደ ሰባ ሁለት ኪሎ ግራም ወረደ። አቅሙን ሁሉ ለመመለስ ሁለት ዓመት ገደማ ፈጀበት። ደፊ ከዚህ ሁሉ ፈታኝ ውጣ ውረድ በኋላ ወደ ጨዋታ ሲመለስ ግን ኤቨርተን ቀድሞ የሚያውቀውን ብቃቱን ማግኘት አልቻለም። ስለዚህ እ.አ.አ ከ2011 እስከ 2016 ድረስ በበርንሊ፣ ስካንትሮፕ ዩናይትድና ዩኦቪል ታውን በውሰት ተዘዋውሮ ለመጫወት ተገደደ። ከ2014 – 2016 ደግሞ በብላክበርን ሮቨርስ ቆየ። ከአሰቃቂው ጉዳት ስድስት ዓመታት በኋላ በሁለተኛው ዲቪዚዮን የሚወዳደረው ብራይተን ኤንድ ሆቭ አልቢዮን አስፈረመው። ያኔ የመከራውና የጭለማው ዘመን አልፎ የንጋቱ ወጋገን ደምቆ ታየው። «ሳቢሳዎቹ» ወደ ፕሪሚየር ሊግ ሲያድጉ ደፊ ከቁልፍ ተጫዋቾቻቸው አንዱ ለመሆን በቃ። እ.አ.አ በሰኔ 2017 የአየርላንድ ብሔራዊ ቡድን ይህን ከሞት የተረፈ ተጫዋች በድጋሚ ጥሪ አደረገለት፡፡ እንደ አጋጣሚም ሆኖ ይሁን የዕጣ ፈንታ ጉዳይ ደፊ ለብሔራዊ ቡድን ጥሪ ሲደረግለት ዳግም ጣጣ አላጣውም፡፡ ከሊድሱ ተጫዋች ዩናይ ኦካኒ ጋር ከትውልድ ከተማው ዴሪ ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ካምፕ በመጓዝ ላይ ሳሉ የመኪና አደጋ ደረሰባቸው። ሆኖም አደጋው ጉዳት ሳያደርስባቸው አለፈ። የመኪና አደጋ ሳይሆን እግር ኳስ ጨዋታ የመኪና አደጋ ያህል የጎዳው ሼን ደፊ ዛሬ ላይ ዕድሜው ሃያ ስምንት ደርሷል። የመከራው ጊዜ አልፎለት በየሳምንቱ መጨረሻ ለፕሪሚየር ሊጉ ብራይተን ተሰልፎ ለመጫወትም በቅቷል፡፡ ፅናቱም በተሻለው ደረጃ ላይ አስቀምጦታል። ከዚያ ሁሉ መከራና የጭንቅ ጊዜ አልፎም ከአጥቂዎች ጋር በግብ ክልል ውስጥ ሲታገል ታይቷል፣ ሲከላከልም ሆነ ሲያጠቃ የ2010ሩ አሰቃቂ የሕይወት አጋጣሚው አይታወሰውም። ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=33455
[ { "passage": "ዕድሜ ሲመሽ አካላዊ ብርታትን ስለማሳጣቱ አስረጂ አያሻም። እንደወትሮው ሰውነትን ማቀላጠፍ፣ ያለ ድካም ስራን ማከናወን እንዲሁም እንደ ወጣትነት የፈለጉትን ለማድረግ መነሳትም የማይጠበቅ ነው። የጡንቻዎች መሟሸሽ፣ የመገጣጠሚያዎች አለመታዘዝ፣ ብርድ ብርድ ማለት እንዲሁም በትንሽ በትልቁ በህመም መቀሰፍም በእርጅና ጊዜ የሚመጣ ለውጥ ነው። በሴቶች ላይ ደግሞ እድሜን ተከትሎ ተፈጥሮአዊው ጸጋ ልጅ ወልዶ መሳምም የማይታሰብ ይሆናል። «ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም» አይደል የሚባለው የሚያስደንቅ እና ግርምትን የሚያጭር ነገር ሲገጥም። በትንሿ ወር ጷጉሜ «አጀብ» የሚያሰኝ ነገር ኦዲቲ ሴንትራል አስነብቧልና ነው እንዲህ ማለታችን። አንዳንዴም ተፈጥሮ ከጸጋዋ እንዲሁም ከህግጋቷ እንደምታፈነግጥ ማሳያ እንዲሆንም ማሳያ ነው። «የ74 ዓመቷ ባልቴት የመጀመሪያ ልጃቸውን ከሰሞኑ በመገላገል በዓለም ትልቋ እናት ተሰኝተዋል» የሚለው ዜና (ጉድ ሳይሰማ… አትሉም)። ነገሩ እንዲህ ነው በህንድ አንታር ፕራዴሽ ከተባለ ስፍራ ነዋሪ የሆኑት ማንጋያማ የተሰኙ ሴት፤ ኔላፓርታሂፑዲ ከተባለ አካባቢ ከተገኙት ወጣት አርሶ አደር ጋር እአአ በ1962 በትዳር ይጣመራሉ። የአንድ ጎልማሳ እድሜ ባስቆጠረው የትዳር ዘመናቸውም እንደ ወጉ ወልደው መታቀፍ ቢፈልጉም አልተሳካላቸውም። በልጅ አምሮትም ለዓመታት ያልሄዱበት ሃኪም ቤት ያልረገጡት የሃይማኖት ስፍራም አልነበረም። ትዳራቸው በልጅ ላለመባረኩም የአካባቢው ሰው አንዳች ሃጢያት አሊያም መርገምት ቢኖርባቸው ነው ሲል መጠቋቆሚያ አድርጓቸው ቆይቷል። ሌሎች እንዲያ ይበሉ እንጂ ባላቸው ግን ማንጋያማን በማጽናናት እና በማጠንከር ዓመታትን አብረው ዘልቀዋል። ተስፋ ለመቁረጥ ሩቅ የሆኑት ጥንዶቹ ከ25ዓመታት በፊት በህክምና እርዳታ ልጅ ለማግኘት ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም ነበር። ያለፈው ዓመት ታዲያ አንዲት የ55 ዓመት ጎረቤታቸው ህክምናውን አግኝታ ማርገዟን ተከትሎ ጥንዶቹ በእርጅናቸው ሳያቅማሙ ወደ ህክምና ይሄዳሉ። ባለሙያዎችም በማንጋያማ እድሜ ህክምናውን እስካሁን ያልደፈሩት ቢሆንም አስፈላጊውን ምርመራ ሁሉ እንዲያደርጉ ያዛሉ። የምርመራው ውጤትም ባልቴቷ ጤነኛ ስለመሆናቸው የሚመሰክር ቢሆንም፤ በእርግዝና ወቅት የሚኖረውን ድካም እንዲሁም አእምሯቸው ዝግጁ ስለመሆኑ መጠየቃቸው አልቀረም። ይህ ከሆነ በኋላም ህክምናው ቀጠለ። ላለፉት ዘጠኝ ወራትም አስር ዶክተሮች የወይዘሮ ማንጋያማን ጤንነት እንዲሁም እርግዝናው በትክክለኛ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ይቆጣጠሩ ነበረም ብሏል ዘገባው። በመጨረሻም ተስፋቸው ፍሬ አፍርቶ ጤነኛ እና መንትያ ሴቶችን መገላገል ችለዋል። ይህም ባልቴቷን በ74 ዓመታቸው ወልደው የሳሙ የዓለማችን አዛውንቷ እናት አድርጓቸዋል። ከዚህ ቀደም የክብረወሰን ባለቤት የነበሩት ሴት ዳልጂንደር ካኡር እአአ 2016 በዚሁ ህክምና ወንድ ልጅ በ70 ዓመታቸው በመገላገላቸው ነበር። ማንጋያማ ስለሆነላቸው ነገር ሲገልጹም «በጣም ደስተኛ ነኝ፤ አምላክ ለጸሎታችን ምላሽ ሰጥቶናል። አሁን የራሳችን ልጆች ስላሉን በዓለም ላይ ደስተኞቹ ጥንዶች ነን» ብለዋል። «በፈጣሪ ክብር እና በዶክተሮቹ ጥረት የሁለት ሴት ልጆች አባት ሆኛለው፤ በዚህም ኩራት ይሰማኛል። አምላክ ከ54 ዓመታት በኋላ ለልመናችን ምላሽ ሰጥቶናልና ደስተኛ ነኝ» ያሉት ደግሞ የ80 ዓመቱ ባለቤታቸው ናቸው። ዶክተሮች በበኩላቸው ህክምናውን አስተማማኝ የሚያደርገው የእናትየዋ አካላዊ ጤንነት መሆኑን ነው የሚገልጹት። ዜናው በህንድ ከተሰማ በኋላም በስኬትነት የተጠቀሰላቸው ቢሆንም፤ በዚህ ዕድሜ ህክምናውን እንዲያገኙ እንዴት ሊፈቀድ ቻለ የሚለውም አጠያያቂ ጉዳይ ሆኗል። ሌሎች በበኩላቸው በዚህ ዕድሜ ያሉ እናቶች ለምን ያህል ጊዜ ልጆቻቸውን ሊንከባከቡ ይችሉ ይሆን ሲሉም ጥያቄ ያነሳሉ። ዜናውን የሰማነው እኛስ የሆነውን «የማታ ስጦታ» ብንለው አይገልጸው ይሆን? አዲስ ዘመን\nጳጉሜ 4/2011 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "ed1a176673bc0ba5b67489e08b4c24ab" }, { "passage": "የሰው የሕይወት ገጠመኞች እጅግ ብዙ ናቸው:: ከጥንት እስከ ዛሬ:: በየዘመኑ አስገራሚ አሳዛኝ ታሪኮች ይከሰታሉ:: ዳርቻ የላቸውም:: እንደገናም ሰው ይወለዳል:: ያድጋል፤ይኖራል፤ ይሞታል::በደስታም ኖሮ ይሁን በሀዘን ያልፋል:: ዘመን ያደመቃቸው ዘመን ያከሰማቸው:: በእጅጉ ውስጥን ይመስጣሉ:: ብዙ ቦታዎች ተዘዋውሮ የሰራ የብዙ ሙያዎች ባለቤት የነበረ ጎልማሳ የሕይወቱ መስመር እንደተዛባ ይረዳና በስፋት የሚታወቅበትን ቦታ ለቆ ይጠፋል:: በእጁ\nላይ ለነገ ብሎ ያስቀመጣት ምንም አልነበረውም:: የስራው ባህርይ ሀገር አቋራጭና ተንከራታች ቆላና ደጋ ሰሜንና ደቡብ ምስራቅና\nምዕራብ የሚያዞር እንዲያም ሲል ከሞት ጋር ተጋፍጦ ከቀናው ተርፎ የሚመለስበት ስለነበር ለእሱ ስለነገ ማሰብ ብሎ ነገር አልነበረም::\nነገ ሌላ ቀን ነው:: መሽቶ ሲነጋ ጨለማው ገፎ ወለል ሲል ይታሰብበታል ባይ ነበር:: ዘርፈ\nብዙ ሙያው የትም ቢሄድ ጾም እንደማያሳድረው ጠንቅቆ ያውቃል:: በእድሜ ዘመኑ ያካበተው እውቀት ትምህርትና ልምድ የትም ሆነ የት\nየሚመነዘር ጥሬ ገንዘብ ነበር:: በባሕርይው ተወዳጅ ሰው አክባሪ አብሮነትን የሚወድ ጨዋታ አዋቂ:: ሀረር ሸንኮር የሚባል አካባቢ\nተወልዶ አድጎ በንጉሱ ዘመን መጨረሻ ሠራዊቱ ቤት በልጅነቱ ገብቶ ልዩ ሙያዎችን ቀስሟል:: ድፍን ኢትዮጵያን አካሏል:: በሙያው\nአንድ ሰው ሊያገኘው ወይንም ሊሆነው የማይችለውን መሆን የቻለም ነበር:: የተማራቸው ሰፊ ሙያዎች ድንቅ ድንቅ የሚሰኙ:: ፈሪሀ\nእግዚአብሄር ሲበዛ የነገሰበት በሰራው ብቻ መኖር የሚፈልግ ያለውን በትኖና አካፍሎ መኖር የሚወድ ሰው ታውቅ እንደሁ ጎልማሳው እንደሱ\nነበር:: በእጁ ትንሽም ሳንቲም ብትሆን ያለው ‹‹ራበን ታረዝን›› ለሚሉ ሁሉ በትኖ ወደደሳሳው ጎጆው የሚመለስ ብቻውን የሚኖር\nሰው:: ድሮ ድሮ ጎረምሳ እያለ አንድ ወንድና ሴት ልጅ ሀረር ላይ እንደነበሩት የሚናገሩ አሉ:: በሶማሌ ጦርነት ተለያይተው ልጆቹን\nሳይገናኝ ሳያውቃቸው እስከመጨረሻው ኖረ:: ይሄኔ እኮ መንገድም ተላልፈው ይሆናል:: ወይ በጉርብትና ኖረው አሊያም አብረው ሰርተው\nሊሆን ይችላል:: ካልተዋወቁ አልተዋወቁም :: ጎልማሳው\nበአንድ አጋጣሚ የትላንቱን ሕይወቱን እርግፍ አድርጎ ጥሎ የከተማ ልጅነቱን በልቡ ሸሽጎ መዲናዋን አዲስ አበባን ዳግም አልመለስብሽም\nብሎ በመኪና ሳይሆን በእግሩ እየተጓዘ ለቋት ወጣ:: በእግር መጓዙን የኖረበት ነው:: ሱሉልታን ጫንጮን አልፎ ገሰገሰ:: እግሩ\nበመራው ሄደ እንጂ ወደዚያ ስፍራ ጓደኛ ዘመድ የሚያውቀው ሰው አልነበረውም:: እንዲያ እያለ ደብረ ጽጌ ደረሰ:: የጽጌዎች ደብር::\nእሱም ሀገሩን ሀገሩም እሱን አያውቀውም:: ትንሽ ደካማ ቤት ፈልጎ\nተከራይቶ አነስተኛ ምግብ ቤቶችን ፈልጎ እየተመገበ ያገኘውን እየሰራ ዳግም እንደገና መኖር ጀመረ:: ባህሪው በውስጡ የተካነው ሙያና\nእውቀት በአጭር ጊዜ ብዙ ወዳጅ ጓደኛ ተከታይ አፈራለት:: እውቀት ለዘለአለም ይኑር:: ጎልማሳው እኔ ነኝ ያለ መካኒክ ሾፌር፤ የቅርጻ ቅርስ ባለሙያ፤\nየንድፍ ሰራተኛ፤ ቤት ቀያሽ መሀንዲስ፤ መሆኑን በአጭር ጊዜ የከተማው ነዋሪ ተረዳ:: አከበረው:: ወደደውም:: ይህም ሁኖ ሌሎች\nድንቅ ሙያዎች ነበሩት:: በፍጹም አይናገርም:: ያገኘውን ስራ ሰራ:: ያገኘውን ገንዘብ እዛው ከወጣቶች ጋር ይካፈላል:: ቤት ኪራዩን\nይከፍላል:: ማታ ሲሆን የከተማው ወጣት ያጅበዋል:: አብሮት ያመሻል:: መጨረሻ ወደተከራያት ጎጆ አድርሰውት ይመለሳሉ:: እንዲህ\nነበር የሚኖረው:: ጠዋት ማልደው ይቀሰቅሱትና ወደቀጣይ ስራቸው ይሄዳሉ:: ስለትላንት\nህይወቱ እንዲህ ነበርኩ እንዲያ ነኝ የሚል ወሬ ከአፉ አይወጣም:: ስንትና ስንቱን ሕይወት አሳልፎታል መሰለህ:: በል ሲለው ደብረሊባኖስ\nገዳም ሄዶ ይከርማል:: ደብረ ጽጌን እትብቱ የተቀበረባት ያህል ወደዳት:: ከልቡም አፈቀራት:: የሕዝቡ አብሮነት ፍቅር መተሳሰብ\nመከባባር አብሮ እንብላ እንጠጣ ባይነት በደስታና በሀዘን አለመለያየት ባሕሉን ወዳድነት ምርኮኛ አደረገው:: ሁሉን እርግፍ አድርጎ ጥሎ ከአዲስ አበባ የተሰደደበት ዋነኛ ምክንያት\nውስጡ በሀዘን በመሰበሩ ምክንያት መሆኑን አንዳንዴ ብቻ ይናገራል:: እንዴትና ለምን የሚለውን አያነሳም:: በቀድሞው የስራ ሕይወቱ\nበሙያው በችሎታው በድንቅ ክህሎቱ በጥቂቶች ሳይሆን በብዙ ሺሕ ሰዎች ይታወቅ ይከበርም የነበረ ነው:: በድንገት የመሰወሩና የት\nእንደገባ ያለመታወቁ ጉዳይ ብዙዎችን ሲያስጨንቅ ኖሯል:: ድፍን አዲስ አበባ፤ ሀረር፤ ደብረዘይት፤ ሻሸመኔ፤ ሀዋሳ፤ ወሎ፤ ጅጅጋ\nአፋር ድረስ ሌሎችም ቦታዎች ያዩት የት እንደሆነ የሰሙ ካሉ በሚል ሲታሰስ የነበረ ቢሆንም ምንም ፍንጭ ሳይገኝ ኖሯል:: አንድ ቀን ደብረጽጌ ከተማዋ ውስጥ በምትገኝ ትንሽ ጎሚስታና ጋራዥ\nሶስት ከአባይ ማዶ አቅጣጫ እየተምዘገዘጉ የሚበሩ ላንድክሩዘሮች የተለያዩ ሰዎችን እንደጫኑ መጥተው ጎማ ለማስሞላት ይቆማሉ:: ጎልማሳው\nበዙሪያው አምስት የሚሆኑ የከተማዋ ወጣቶች ከበውት የተበላሸች መኪና ፈታቶ ለመግጠም እየሰራ ነው:: ከላንድክሩዘሮቹ የወረዱት ሰዎች\nበዝግታ እየተሰራች ወዳለችው መኪና ተጠጉና ጎማ ለመቀየርና የመንተፋተፍ ችግር ያለበትን መኪና ባለሙያ ካለ እንዲያይልን ነው ሲሉ\nጉዳዩ ቀልቡን የሳበው ጎልማሳ በድንገት ቀና ብሎ ‹‹አቤት ምን ነበር›› ሲል ከሶስቱም ሰዎች ጋር አይን ለአይን ተገጣጠሙ:: ጠንቅቀው ያውቁታል:: ውድ ሙያ አሰልጥኗቸዋል:: አስተምሯቸዋል::\nኩሩ ቆፍጣና ስነስርአት አክባሪና አስከባሪ የብዙ እውቀት ጌታ የሆነ አለቃቸው ነበር:: ጊዜ ገፍቶትና ከፍቶት ከመሰወሩ በፊት::\nረዥም አመታት እንደጠፋ ተፈልጎ ተፈልጎ ፍንጭ አለመገኘቱን ጭምር ያውቃሉ:: እናም ሰዎቹ እራሳቸውን ይዘው ጮሁ:: አምስቱ ወጣቶች\nደንግጠው ምን ተፈጠረ በሚል መንፈስ ባሉበት ቆመው ቀጣዩን ክስተት መከታተል መረጡ:: ሻምበል፤ ሻምበል፤ ሻምበል ብለው ተጠመ ጠሙበት:: አቅፈው እየሳሙትም\nአልበቃቸው አለ:: መልሶ መላልሶ እያቀፈ ሳማቸው:: አይኖቹ በማያቋርጥ እምባ ታጠቡ:: ብዙ ፈተናና ውጣ ውረዶችን አብረው አሳልፈዋል::\nእዛው እንደቆሙ መኪናዎቻቸውን ሰራርቶ ጨረሰ:: ጎማዎቹን አስሞላ:: ገንዘብ አውጥተው ቢሰጡትም እምቢኝ አለ:: ባዶ ኪሱን ለይሉኝታ\nብሎ የሚግደረደር ሰው ታውቃለህ አይደል? ይሄ ድርጅት የአንተ ነው ሲሉ ጠየቁት:: አይደለም ሰውየው አያውቀኝም:: ለሙከራ ብሎ\nነው የገባሁት ሁለት ቀኔ ነው አላቸው:: ወጣቶቹ አሁንም ይሰማሉ አጠገቡ አሉ:: አይ ግዜ አይ አለመተዋወቅ\nእስቲ ጥሩት ባለቤቱን አሉ:: ተጠርቶ መጣ:: እሞክራለሁ ስላለ እንጂ ሰውየውን አላውቀውም አላቸው:: ከት ብለው ሳቁ:: አንተ\nልክ ነህ:: አታውቃቸውም:: እኛ ደግሞ በሚገባ እናውቃቸዋለን:: ለዛሬ ደረጃ አስተምረው አሰልጥነው ያበቁን ሰው ናቸው አሉ::\nጎልማሳው ትንፍሽ አላለም:: በግድ በግድ የተጠቀለሉ መቶዎች በኪሱ ሸጉጠው ነገ እንመጣለን የትም እንዳትሄድ ብለው መኪናቸውን አስነስተው\nተፈተለኩ:: ሶስቱም ከፍተኛ ሹማምንት ነበሩ:: የዛኑ እለት ወጣቶቹ የሰሙትንና\nያዩትን ሁሉ ለትንሽዋ ከተማ ነዋሪ የጥሩምባ ያህል አዳረሱ:: ሰውየው ለሀገር ብዙ ያገለገሉ የተከበሩ ሻምበል ናቸው:: ከእንግዲህ\nእያንዳንድሽ በማዕረጋቸው ነው መጥራት ያለባችሁ ተብሎ አዋጅ ተነገረ:: ባለላንድ ክሩዘሮቹ አዲስ አበባ እንደገቡ አስራ ስድስት\nአመት ጠፍቶ ተሰውሮ የኖረው ተወዳጁ ሰው ደብረጽጌ ላይ መገኘቱን ለብዙዎች አበሰሩ:: በራሪ ነብሮቹ ከያሉበት እየሄዱ አገኙት:: እንውሰድህ ቢሉትም ከእንግዲህ\nየእኔ ወገን የክፉና የችግሬ ቀን ደራሽ የሀዘኔ ማስረሻ ሰው አክባሪውና ወዳጁ የደብረጽጌ ሕዝብ ስለሆነ ብሞትም የሚቀብሩኝ እነሱ\nናቸው የትም አልሄድም አለ:: አንድ ቀን የተከራያት ትንሽ ቤት ውስጥ ሊያዩት ሄዱ:: የሬሳ ሳጥን ገዝቶ ሸፍኖ አስቀምጦታል::\nይሄ እንጨት ምንድነው ብሎ አንዱ ጣል ያረገበትን ጨርቅ አወረደው:: ምነው አሉት:: ምንድነው ምነው ማለት ሕዝብ ማስቸገር የለብኝም::\nብሞት በዚሁ እንዲቀብሩኝ ነው የሚል መልስ ሰጠ:: አንደኛው ጓደኛው ተሸክሞ አውጥቶ ሰባበረው:: የሚገርመው ብዙም ሳይቆይ አለፈ::\nበስልክ ሁሉም ከያለበት ተጠራርቶ መኪናውን እየስጓራ ወደ ደብረጽጌ ተፈተለከ:: ድንኳን ጥሎ የተቀመጠው ጎረቤቱና ሕዝቡ ነው::\nሚስት ድስት አልነበረውም:: ቀብሩ ካበቃ በኋላ ራሱን ዝቅ አድርጎና ደብቆ 16 አመታት በኖረበት\nብዙም የኋላ ታሪኩንና ማንነቱን በቅጡ ለማያውቁት የአካባቢው ነዋሪዎች የጎልማሳው የሕይወት ታሪክ ተነበበ:: በንጉሱ ዘመን የነበረው\nስፔሻል ፎርስ አባልና ልዩ ኮማንዶ፤ መኮንን ከሆነ በኋላ የኢትዮጵያ አየር ወለድ አባልና የኮማንዶ አሰልጣኝ፤ የዘመቻ መኮንን፤\nየንድፍና የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያ፤ ሾፌር መካኒክ፤ ከሶማሊያ ጦርነት እስከ ኤርትራ ብዙ በረሀዎች ያሳለፈ ብቸኝነትን መርጦ ኖሮ ያለፈ\nሰው መሆኑ ተነገረ:: ዳግም እሪታ ጩሀት አንጀት የሚያላውስ ለቅሶ በቀብሩ ዙሪያ ባለው ጫካ ደጋግሞ አስተጋባ:: ሞልቶት ዘለቀ::\nሞልቶም ፈሰሰ:: አዲስ ዘመን ነሀሴ 16/2011ወንድወሰን መኮንን\n", "passage_id": "e587b2385a919ef55cb10df77be40efc" }, { "passage": " በታላቅ አገር ታናሽ ሆኖ እንደማደር፤ በዕምቅ ወረቶች ተከብቦ ወደ ባዕድ አገራት እንደማማተር፤ በበርካታ የተፈጥሮ ጸጋዎች ታጅቦ ከድህነት ጋር እንደማበር፤ የወጣት ትኩስ ኃይል በቀዘቀዘ አስተሳሰብ ውስጥ እንደመዳከር፤ እልፍ እሴቶችን ታጥቆ ከክብር ውሃ ልክ ቁልቁል እንደመንደርደር፤ በአራቱም ማዕዘናት እምቅ ሀብት ተሸክሞ የኑሮ ሸክም ሳይቃለል ዘመንን እንደመሻገር ከቶውንም አገርንና ትውልድን አንገት የሚያስደፋ ምድራዊ ሀቅ ሊኖር አይችልም።“በድህነት የቆረበ” አገር እንደማይኖር ሁሉ ሠርቶ መለወጥ የሚያስችል አሸናፊ ሃሳቦችን ነፍስ ዘርቶ መንቀሳቀስ የድል ጅማሬ በመሆኑ፤ አክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ ለቱሪዝም ሴክተር የሚውሉ ተሽከርካሪዎችን በአገር ውስጥ በመገጣጠም በዘርፉ አዎንታዊ ሚና ለማበርከት ደፋ ቀና እያለ ነው። በዚህ አዲስ የሥራ ፈጠራ እሳቤ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና ከካምፓኒው አገር የማህበራት ጥምረት ጋር አብሮ በመሆን ወደ ሥራ ገብቷል። ዋነኛ ዓላማው ሥራ መፍጠርና በሂደቱም የቱሪዝሙን መስክ ላቅ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ ነው የሚሉት፤ የኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰሎሞን ሙሉጌታ፤ ህዝብ ለሚናፍቀው ሠላምና እድገት ብርቱ ክንድ በመሆን ያለውን እውቀት፣ ጉልበትና ጥበብ በማስተባበር የአገርና ትውልድን አንገት ቀና ከሚያደርጉ የልማት ስምሪቶች፤ ቱሪዝም በመንግሥትም ትልቅ ትኩረትና ክብደት ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል መገኘቱ አበርክቶውን ተስፋ ብቻ ሳይሆን፤ ትርጉም አዘል ወደ ሆነው የሥራ ፈጠራ ዕድል ውስጥ ሊያካትተው እንደሚችል ይናገራሉ። እርሳቸው እንደሚሉት፤ በርካታ ዕድገት የፈጠነላቸው አገራት ልምድ እንደሚያሳየው የግሉ ዘርፍ ተሳትፎና የመንግሥት ድጋፍ ተሰናኝተው በመሄዳቸው የሚኖረው ለውጥ ወሳኝ ነው። በተመሳሳይ በዚህ አገራዊ የለውጥ ጉዞ የግሉ ዘርፍና መንግሥት ኃይላቸውን አጥብቀው ፈጣን ዕድገት ለማምጣት የተጀመረውን አንቂና ጋባዥ ድባብ ካምፓኒውን ወደ ተሟላ የተግባር ስበት ውስጥ እንዲገባ ትልቅ አቅም ፈጥሮለታል። የሄሎ ታክሲ ባለቤት\nየሆኑት አቶ ዳንኤል\nዮሐንስ እንደሚናገሩት፤ የሄሎ\nታክሲ ከዚህ ቀደም\n40 ታክሲዎችን አስመርቆ በይፋ\nሥራ ያስጀመረ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የቱሪስት ታክሲ ወደ አገልግሎት በማስገባት ሥራውን ጀምሯል። ሄሎ ታክሲ ከዚህ ቀደም በታክሲ አገልግሎት ተሰማርተው መኪኖቻቸው አሮጌ በመሆናቸው ከአገልግሎት ውጪ ለሆኑባቸው አሮጌውን መኪና ተቀብሎ በአዲስ በመተካት የታክሲ ባለቤቶችን እየታደገ ያለ ድርጅት ነው። የተሰበሰቡ አሮጌ ታክሲዎችም ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመንጃ ፍቃድና ተግባራዊ የመኪና ጥገና መማሪያ እንዲሆኑ፤ ከዚያም ሲያልፍ የዋጋ ተመን ወጥቶላቸው ወደ ማቅለጫ ገብተውና ለውጭ ገበያ ተሽጠው ገቢ እንዲያስገኙ ሥራ እየተሠራ ነው።አቶ ዳንኤል አክለውም፤ ሄሎ ታክሲ የተቋቋመው የአየር ብክለትን በመከላከልና የከተማ ውበትን በመጨመር ለተገልጋዩ ማኅበረሰብ አርኪ አገልግሎት ለመስጠትና ማኅበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት ነው ብለዋል። በታክሲ አገልግሎቱ ከ250 በላይ የሰማያዊ የታክሲ ባለቤቶች አሮጌ ታክሲያቸው እንደ ቅደመ ክፍያ ተወስዶ አዲስ መኪና ለመስጠት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ኃላፊነቱን መውሰዱንም ገልጸዋል። በቱሪስት ታክሲ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ባለ ዕድል ከሆኑት መካከል አቶ ጸጋዬ አለባቸው ተጠቃሽ ናቸው። ለ40 ዓመታት ሲያሽከረክሯት የነበረችውን ታክሲ ዛሬ ላይ በመቀየርና በአዲስ ተሽከርካሪ መተካታቸው ደስታን አጎናጽፏቸዋል። አሁን ላይ መዘመንን በማሰብ የህዝብ አገልጋይነትን ስሜት ከፍ ባለ ደረጃ እንደጨመረላቸውም ይገልጻሉ። በዚህ ረገድ መንግሥት እያደረገ ያለውን አበርክቶም አመስግነዋል። ዕድሉን የመስጠት የማገዝና ባለ ሀብቶችን የመደገፍ ሃሳቡ ቀጣይነት ያለው መሆን እንዳለበት አመላክተዋል። ባገኙት አዲስ ታክሲ ህዝብን ከማገልገል አልፈው የተሻለ ገቢ ኖሯቸው ኑሯቸውን ለመምራት እንደሚያስችላቸውም እምነታቸውን ገልጸዋል። አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና እንደመሆኗ ጭምር የዘመነ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚያስፈልጋትና ለበርካታ ጊዜ ያገለገሉ የትራንስፖርት ተሽከርካሪዎችን ዛሬም እየተጠቀሙበት መሆኑ መንግሥትና የከተማ አስተዳደር በልዩ ትኩረት እንደሚመለከተው ተናግረዋል። አሮጌ መኪናቸውን ቀይረው በአዲስ የቱሪስት ታክሲ ሥራ ለመጀመር ዕድሉን ያገኙት ወይዘሮ ሠላማዊት ኤፍሬም በበኩላቸው፤ ከዚህ ቀደም ባሳለፉት የሥራ ዘመናት ደስተኛ ባይሆኑም አንድ ቀን መልካም ዕድል እንደሚገጥማቸው ሁሉንም በትዕግስት ሲጠብቁ እንደነበር ይናገራሉ። ጊዜው ደርሶ ዛሬ ላይ የዚህ ዕድል ባለቤት ስለሆኑም ቀጣይ ተስፋቸው መለምለሙንና ባገኙት ዕድልም ለሚያስተዳድሯቸው ቤተሰቦቻቸው አዲስ የህይወት ምዕራፍ እንደከፈተላቸው ጠቅሰዋል። የተፈጠረው የሥራ ዕድል መንፈሰ ጠንካራ እንደሚያደርግ የሚናገሩት ወይዘሮ ሠላማዊት፤ በአገር ላይ ሠርቶ የማደግን ትልም እንዳሳካላቸውና የተሰጣቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ደግሞ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩና ለዘርፉ የራሳቸውን አሻራ እንደሚያሳርፉ በሙሉ ልብ ያምናሉ። የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው በበኩላቸው፤ መንግሥት የታክሲ ሞተሮች ከቀረጥ ነፃ ሆነው ወደ አገር ቤት እንዲገቡ የወሰነው ግብር መሰብሰብ አቅቶት ሳይሆን፤ አሮጌ መኪኖች በአዲስ ተተክተው የአየር ብክለት እንዲቀንስ፣ ሀገር ውስጥ ሲገጣጠሙም ተጨማሪ የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ፣ ዜጎች በሀገራቸው ሠርተው እንዲከብሩ፣ የታክሲው ባለቤቶችም ስርቆትን የሚፀየፍ ጥሩ አገልጋይ እንዲሆኑ ለማስቻል ነው ይላሉ።የሥራው ባለቤት የሆኑና መልካም ዕድል የተፈጠረላቸው ሰዎችም ታክሲዎችን በአዲስ እንደቀየሩ ሁሉ አስተሳሰባቸውንና ሕይወታቸውን በመቀየር ለቱሪስቶችም ቀድሞ መረጃ በመስጠትና ኢትዮጵያን በማስተዋወቅ የአገሪቷን ገጽታ እንዲገነቡ ሚኒስትሯ ያሳስባሉ። ለዚህም በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ህጋዊ አሠራርን መከተል የሚያስችል የክህሎትና የአገልግሎት አሰጣጥ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለታክሲ ሹፌሮች እንደሚሰጥ ገልጸዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 25 ቀን 2012 ዓ.ምበ አዲሱ ገረመው", "passage_id": "47d480731149af8c128e75693273dec6" }, { "passage": " ከእለታት አንድ ቀን ብር ቸግሮኝ የማዘርን ቦርሳ ፈልጌ አጣሁኝ ተናደድኩኝና ሀሳቤን ለውጬ እቃ ልሸጥ ወሰንኩ ከጓዳ አውጥቼ የሚሸጠውን እቃ ሳወጣጣ ሳለሁ ድንገት ድስት ስር አስር ብር አገኘሁ በደስታ ብዛት እጆቼን እየሳምኩ ከቤቴ ስወጣ ደጓ ማዘርዬ አየችኝ አፍጥጣ ‹‹መስከረም ሲጠባ አደይ ሲፈነዳ እንኳን ሰው ዘመዱን ይጠይቃል ባዳ›› የምትለውን ስንኝ እየደጋገምን ወደ ትምህርት ቤት ማልደን የምንሄድበት ሁኔታ አሁንም ድረስ በአይነ ህሊናዬ ይታየኛል። መስከረም ወር የሁሉም ነገር የመጀመሪያ ነች በተለይ ለተማሪዎች ከነበሩበት ክፍል አንድ ጨምረው ስለሚመጡ ደስታና ፍርሃት ይቀላቀልባቸዋል። ምክንያቱም አዲስ ክፍል ሲገባ ሊከብድ ይችላል፣ አስተማሪዎቹ ሀይለኛ ሊሆኑ ይችላሉ እንዲሁም ሌሎች ምክንያቶች ናቸው። እኔ የትምህርት መክፈትን ተከትሎ ከማይረሱኝ ሁነቶች መካከል በተለይ የደብተር መሰረቅና መነጠቅ ከፍተኛውን ድርሻ መያዙ ነው። እርግጥ ነው፤ ትምህርት ቤት ውስጥ እያንዳንዱ ቀን የራሱ የሆነ ታሪክ አለው። እኛም በትምህርት ቤት ያሳለፍናቸውን አንዳንድ አይረሴ ሁነቶችን እያስታወስን እናውጋ። አይ የኔ ነገር ከላይ ያስቀመጥኩት ግጥም እንዴትና በምን ምክንያት እንደተፃፈ አላጫወትኳችሁም። መቼም ሌባ ነበርክ ብላችሁ አትፈርዱብኝም አይደል! ያው የዛሬ ጭውውታችን በትምህርት መክፈቻ ቀን ላይ ስላሉት ገጠመኝም አደል! መልካም! አሁን ልቀጥል። ከላይ ያሰፈርኳት ያላለቀች ግጥም ካንተ ጋር ምን አገናኘው ካላችሁ በትምህርት መክፈቻ ቀን የተከሰተች አስደንጋጭ ሁነት ናት። እህ ብላችሁ አድምጡኝ! ሰባተኛ ክፍል በገባሁበት ዓመት ኃይሌ ገብረ ስላሴ ሲድኒ ኦሎምፒክን አሸንፎ ስሙ የገነነበት ወቅት በመሆኑ እሱን ለማስታወስ ምስሉ ደብተር ላይ እንዲወጣ ተደርጎ ነበር። አባቴም አገር ወዳድና ጀግና የሚያደንቅ በመሆኑ ስድስት የካቲት ደብተርና ሁለት የኃይሌ ምስል ያለበት ደብተር ገዛልኝ። የየካቲት ደብተሮቹን በጋዜጣና በላስቲክ ስሸፍን የኃይሌ ምስል ያለበትን ደብተሮች ግን በላስቲክ ብቻ ሸፍኜ አዘጋጀሁ። የትምህርት መጀመሪያ ቀን ላይ እንደምታውቁት የደንብ ልብስ አይለበስም፤ ቦርሳም አይያዝም። እኔም ወደ ትምህርት ቤት እንደፈለኩ የሚያደርገኝን ልብሶች አድርጌ፣ ሸበጥ ጫማዬን ተጫምቼ እና ሁለት የኃይሌ ምስል ያለባቸውን ደብተሮች ይዤ ሄድኩኝ። የምማርበት ክፍል እንደደረስኩም ተሸቀዳድሜ ቦታ ያስኩኝ። እንደምታውቁት መንግስት ትምህርት ቤት አንድ ክፍል ውስጥ ለ80 ሆኖ መማር የግድ ነበር። በዚህም በመጀመሪያ የትምህርት ቀን ክፍል ውስጥ የቦታ ነገር በጣም ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ተረዱልኝ። ቀድሞ መጥቶ ቦታ ያልያዘ ተማሪ የተሰባበረ ወንበር ላይ ተቀምጦ ዓመቱን ማሳለፍ ግድ ይለዋል። ይሄ እሽቅድድም ተለምዶ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ሲገባም ቀድሞ ዶርም በመግባት ጥሩ መተኛ ፍራሽ መረጣ ውስጥ እንደሚገባ አትርሱልኝ። እኔ ሲፈጥረኝም አንድ ቦታ ተረጋግቶ መቀመጥ አይሆንልኝምና የያዝኩት ቦታ ላይ ደብተሬን ማስቀመጫው ስር ከትቼ ከጓደኞቼ ጋር ልጫወት ወጣሁ። የመጀመሪያ ቀን እንደመሆኑ መምህራን ክፍል አልገቡም። ከልጆች ጋር ሳር ለሳር ስሯሯጥና ጭቃ ስወራወር ልቤ ጥፍት እስኪል ኳስ ስራገጥ ሰዓቱ ደርሶ ኖሮ ደብተሬን ላመጣ ክፍል ገባሁ። ግን ያየሁትን ማመን ነበር ያቃተኝ፤ ምክንያቱም የሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ምስል ያለበትና በላስቲክ ተጠንቅቄ የሸፈንኩት፣ ከቤት ስወጣም ሁለት ሶስቴ በጥንቃቄ እንድይዘው የተነገረኝ ደብተር ከቦታው የለም። በጣም ተደናገጥኩ! አባቴ ማታ ከስራ ሲመጣ ‹‹ዛሬ ምን ተማራችሁ ደብተርህን አምጣ›› ብሎ ይጠይቀኛል። አማራጭ ስላልነበረኝ ምንም እንዳልተፈጠረ ወደቤቴ ሄድኩ። እቤት እንደደረስኩ ለታላቅ ወንድሜ እየተቅለሰለስኩ ደብተሬ መጥፋቱን ነገርኩት። ጉዳዩን ቀለል አድርጎ ‹‹ታድያ አንተም ትሰርቃለሃ›› ብሎ አበረታታኝ። የማታውን የአባቴን ጥያቄ በመላ አልፌ ጠዋት እንዴት አድርጌ ደብተር እንደምሰርቅ ሳሰላስል አደርኩ። ጠዋት ወደ ትምህርት ቤት ስሄድም ባዶ እጄን ነበር። ወደ ቅጥር ግቢው እንደገባሁም ጓደኞቼን ሰብስቤ በቀጥታ ያመራነው ደብተር ልናገኝበት ወደምንችለው አራተኛና አምስተኛ ክፍል መደዳ ነበር። በእለቱም አስር ያህል ደብተሮች የሰበሰብን ቢሆንም እኔ የተሰረኩትን አይነት የሃይሌ ምስል ያለበት ደብተር ግን ማግኘት አልተቻለም። ደብተሩን ለመግዛት ደግሞ ገንዘብ ያስፈልጋል ነገር ግን ቤተሰብ እንዳሁኑ የኪስ ገንዘብ አይሰጥም ነበር። ያለኝ የመጨረሻ አማራጭ ከቤት በሆነ መንገድ ገንዘብ መውሰድ ብቻ ሆነ፤ እናም ለደብተሮቹ የሚሆን አስር ብር ልሰርቅ ስል እጅ ከፍንጅ ተያዝኩ፤ የተገረፍኩትን ግን አትጠይቁኝ። የግርፊያ ያበቃኝን ሁኔታ ለማስታወስም ከላይ የተቀመጠውን ግጥም ጻፍኩ። ሌላኛው በትምህርት መክፈቻ ወቅት ያጋጠመኝ ትንሽ ለየት ይላል። ወቅቱ የሚሊኒየም ዓመት የተበሰረበት ጊዜ በመሆኑ ትምህርት ቤት የገባነው በጉጉት ነበር። በመጀመሪዋ የትምህርት ቀን ከጓደኞቼ ጋር ውይይት ተብላ በምትጠራው ታክሲ ተሳፍረን መጓዝ ይዘናል። ትይዩ በመቀመጣችን ከጓደኞቼ ጋር በክረምት ስላሳለፍነው እረፍት ሞቅ ያለ ጨዋታ ውስጥ ለመግባት ጊዜ አልፈጀንም። የወሬውን አቅጣጫም አንዲት ሰፈራችን የምትገኝ ልጅ ላይ አደረግን። ከጓደኞቼ ጋር ስለ ልጅትዋ ክርክር ውስጥ ገባን፤ በወሬያችን መደማመጥ ባለመኖሩም የሌሎች ተሳፋሪዎችን ቀልብ ለመሳብ ቻልን። ከተሳፈሩት ሰዎች መካከል በትምህርት ቤታችን የሂሳብ መምህር ከጥግ መቀመጡን አላስተዋልንም ነበር። እርሱ ግን በአንክሮ እኛንም ወሬያችንንም ሲከታል ቆይቶ መውረጃችን ሲደርስ ቀድሞን ከአካባቢው ተሰወረ። ‹‹አይመጣምን ትተሸ ይመጣልን ፍሪ›› የሚለው አባባል በተግባር ያየሁት ያኔ ነው። የመጀመሪያ ቀን እንደመሆኑ መምህራችን በየክፍላችን እየገቡ እየተዋወቁን ስለ ባህሪያቸውና ውጤት አያያዛቸው ሰፊ ማብራሪያ እየሰጡ ይወጣሉ። ካልተሳሳትኩ ሶስተኛው ክፍለ ጊዜ ላይ ይመስለኛል አብሮን የመጣው መምህር ወደ ክፍላችን ገባ፤ ክፍል ውስጥ ሲንጎራደድ ቆይቶም እኔ አጠገብ ሲደርስ ትኩር ብሎ አይቶኝ ሲያበቃ ሰሌዳው ፊት ለፊት እንድቆም አዘዘኝ። ያዘዘኝን ካደረኩ በኋላም ታክሲ ውስጥ ሳወራት የነበረውን እያንዳንዱን ጉዳይ በአስተማሪው ጠያቂነት እንድናገር ተገደድኩ። ዝብዘባዬን እንደጨረስኩም አስተማሪው ምክር ይሁን ስድብ ባልገባኝ ቃላት ያለሁበትን ቦታ እስክስት ተቆጣኝ ፤ አልበቃ ብሎትም የመጀመሪያውን የእሱን ፈተና ጥሩ ውጤት ካላመጣሁ የመጀመሪያውን ሴሚስተር ውጤት አልተሟላም (incomplete) እንደሚለኝ ቁጣ በተቀላቀለበት ሁኔታ ነገረኝ። በመጀመሪያው የትምህርት ቀኔ በእንዲህ አስደንጋጭ ሁኔታ የጀመርኩበትን ሁኔታ እስካሁንም በደንብ አስታውሰዋለሁ። ይህን ያህል ካወጋኋችሁ እናንተም የትምህርት መክፈቻ ዕለት ገጠመኞቻችሁን እያሰታወሳችሁ በትዝታ ኮምኩሙ… እኔ ለዛሬ አበቃሁ።አዲስ ዘመን  መስከረም 26/2012 መርድ ክፍሉ", "passage_id": "db47bdeebba2f33976b9208f1a71fea7" }, { "passage": "ብዙዎች ከዛሬ 20 አመታት በፊት በሆነውና እንደዋዛ ሊዘነጉት ባልቻሉት አሳዛኝ ዕለት ዙሪያ በትዝታ ሲመላለሱ ውለዋል። ይህ ጊዜ ለአገሪቱ ብቻ ሳይሆን ድንገቴውን የአደጋ ዜና ለሰማው የዓለም ክፍል ሁሉ እጅግ አሳዛኝ ቀን ነበር። ህዳር 14 ቀን\n1989 ዓም።\nበክፉ\nአሳቢዎቹ\nጠላፊዎች\nውጥን\nበኮሞሮስ\nደሴት\nዳርቻ\nየወደቀውና\nንብረትነቱ\nየኢትዮጵያ\nአየር\nመንገድ\nበሆነው\nየበረራ\nቁጥር\nኢቲ\n961 ቦይንግ\n767 የመንገደኞች\nአይሮፕላን\nላይ\nበደረሰው\nአደጋ\nየበረራ\nሰራተኞችን\nጨምሮ\nየበርካታ\nሀገራት\nዜጎች\nህይወት\nስለማለፉ\nተሰማ\n።\nበወቅቱ በኢትዮጵያዊው\nፓይለት\nካፒቴን\nልዑል\nጥረትና\nበተአምር\nከተረፉት\nጥቂት\nተሳፋሪዎች\nባሻገር\nየአደጋው\nክብደት\nለብዙሀኑ\nአይረሴ\nሆኖ\nአልፏል።\nይህን\nክፉ\nአጋጣሚ\nበየአመቱ\nከመዘከር\nባሻገር\nበኢትዮጵያ\nየበረራ\nታሪክ\nጥቁር\nአሻራቸውን\nጥለው\nካለፉት\nአደጋዎች\nመካከል\nአንደኛው\nሆኖ\nተመዝግቧል።\nየበርካቶች ህይወት\nበኮሞሮሱ\nየአይሮፕላን\nአደጋ\nያለፈበትን\nየቀን\nክፉ\nሲያስቡ\nየዋሉ\nበርካታ\nኢትዮጵያውያን\nወደ\nማምሻው\nየሰሙት\nሌላ\nየትራፊክ\nአደጋ\nዜና\nደግሞ\nከክፉ\nቀን\nትውስታቸው\nፈጥነው\nእንዳይወጡ\nምክንያት\nሆነ።\nህዳር 14 ቀን\n2012 ዓም።\nበአገሪቱ\nየተለያዩ\nሥፍራዎች\nበተመሳሳይ\nጊዜና\nሰዓት\nየደረሱ\nየመኪና\nአደጋዎች\nየ49\nሰዎችን\nህይወት\nቀጥፈው\nበርካቶችን\nለከፋ\nየአካል\nጉዳት\nማጋለጣቸው\nተነገረ።\nዕለቱም\nየክፉ\nቀናት\nግጥጥሞሽ\nሆነና\nበየቀኑ\nየትራፊክ\nአደጋዎችን\nወሬ\nእየሰማ\nለሚያድረው\nሁሉ\nእጅግ\nየከፋ\nዜና\nሆኖ\nሊያመሽ\nግድ\nአለ።\nነፍሰጡሯ\nወይዘሮ\nዘጠኝ\nወራትን\nእየቆጠረች\nየመውለጃ\nጊዜዋን\nስታሰላ\nከርማለች።\nያሳለፈችው\nየእርግዝና\nጊዜ\nፈታኝ\nቢሆንም\nከቀናት\nበኋላ\nወልዳ\nየምትስመውን\nፍሬዋን\nእያሰበች\nጭንቀቷን\nሁሉ\nትረሳለች።\nለአራስነት\nቆይታዋ\nቤት\nጓዳዋን\nአሟልታ\n‹‹ለእንኳን\nማርያም\nማረችሽ››ወግ መቃረቧን ስታስብ ደግሞ የድካም ጎኗን አሳርፋ እፎይታዋን አሻግራ ትናፍቃለች። ይሄኔ ወደ አዲሱ ዓለም ለመምጣት ‹‹ልቀቁኝ››የሚለው ጽንስ ከውስጧ ሲፈራገጥ ይሰማታል። ይህ እውነትም የእናትና ልጁን ቁርኝት አጥብቆ ዓይን ለዓይን የሚተያዩበትን ዕለት እያስጠጋ ቀናት ማፋጠኑን ቀጥሏል። እነሆ! ህዳር 14 ቀን 2012 ዓም የቁርጡ ቀን የቀረበ ይመስላል።ዘጠኝ ወራትን በእርግዝና የቆየችው ወይዘሮ የናፈቀቸውን ልጇን ታቅፍ ታጠባው ዘንድ ጊዜው ደርሷልና ህመም ቢጤ ይሰማት ይዟል። ምልክቱ የምጥ እንደሆነ የገመቱ ቤተሰቦች የልጃቸውን በሰላም መገላገል ናፍቀው ምጡ ሳይፋፋም ወደ ጤና ተቋም ሊያደርሷት ተሰባስበዋል። ባጃጅ ቀርቦ ወላዷ ወደውስጥ እንደገባችም ከጎኗ ሆነው በጭንቀቷ ሊገኙ የወደዱ ቤተሰቦቿ አጅበዋት ጉዞ ጀምረዋል። መንገዱ ወደ ጤና\nጣቢያ ሲያመራ ሁሉም\nከቆይታ በኋላ ስለሚቀበሉት\nአዲስ እንግዳ እያሰቡ\nነበር። ይህ ሕልም\nግን ከዳር አልደረሰም።\nበድንገት ትንሽዋ ባጃጅ ባጋጠማት ከባድ የመኪና ግጭት ከመንገድ ተስፈንጥራ ወደቀች። ወዲያውም ነፍሰጡሯን ጨምሮ የስድስት ቤተሰብ አባላት ህይወት ተቀጠፈ። ይህ ብቻ አይደለም። በዚሁ ቀን ጉዞውን ወደ አምቦ ከተማ ያደረገው የሕዝብ ማመላለሻ ሀይሩፍ ሚኒባስ ከአንድ ቱርቦ ከባድ መኪና ጋር ተጋጭቶ በውስጡ የነበሩ 17 ተሳፋሪዎች ህይወት ወዲያውኑ ተቀጥፏል። በሚኒባሱ ውስጥ ከነበሩት መካከል ሰባት ያህሉ የአምቦ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ናቸው። አብዛኞቹም ለመመረቅ ጥቂት ጊዜያት የቀራቸው፣ ስለነገ መልካም ተስፋን የሰነቁና ሀገራቸውም በጥብቅ የምትሻቸው ዜጎች ነበሩ። አደጋው በደረሰበት ቀን መሰማት የጀመሩ የትራፊክ አደጋ ዜናዎች በዚህ ብቻ አልተቋጩም። በአገሪቱ የተለያዩ ስፍራዎች በመኪና መገጨት፣ መገልበጥና መጋጨት በደረሱ ክስተቶች 49 ሰዎች ስለመሞታቸው ተመዝግቧል።ከተጠቀሰው ዕለት በፊትም ሆነ በኋላ ለጆሮ የሚከብዱ አደጋዎችን እየሰማን ስለነገ በስጋት ማደራችንን ቀጥለናል። አሁን ላይ የትራፊክ አደጋ ጉዳይ እጅግ ከባድና አሳሳቢ እየሆነብን ይገኛል። በአደጋው የበርካቶች ህይወት ጠፍቶ ብዙሀኑን ለከፋ የአካል ጉዳት ዳርጓል። ጠዋት ወጥተን ማታን በሰላም ለመመለስ ተስፋ በሆነበት አጋጣሚም ልጆች ያለ አሳደጊ ቀርተዋል። ጥቂት የማይባሉ ቤተሰቦች ጎጆ ተዘግቶ አረጋውያን ያለጧሪና ሰብሳቢ በሀዘን እንዲኖሩ ተፈርዶባቸዋል። በሚሊዮን የሚቆጠር ንብረት ወድሞም በርካቶች ያለፉበትን ጥሪት አጥተዋል።ዛሬም በየቀኑ የምናይና የምንሰማቸው አደጋዎች አልተቋረጡም ። ማመን ከምንችለው በላይ ቁጥራቸው እያሻቀበ በየሰከንዱ ከስጋት ጋር እንድንራመድ ምክንያት ሆነውናል። ብዙዎች የአገሪቱ ስም በክፉ ለሚያስጠራው የትራፊክ አደጋ መበራከት ከአሽከርካሪውና ከተገልጋዩ ጋር በማያያዝ የራሳቸውን ምክንያትና ሰበብ ያስቀምጣሉ። ከ33 አመታት በላይ በሹፍርና ሙያ የቆዩት የባስ ካፒቴን ታምራት ወልደ ጊዮርጊስ ግን ‹‹ሁሉም ለስነምግባር ደንቦች ተገዢ ቢሆን ለአደጋ የተጋለጠ አይሆንም ነበር›› በሚል ያምናሉ። በቀድሞ ሰራዊት የፈንጂ አምካኝ ባለሙያ እንደነበሩ የሚጠቅሱት አቶ ታምራት ይህ ጥንቃቄ የተሞላበት ልምድም ዕድሜያቸውን ለገፉበት የሹፍርና ሙያ መሰረት ሆኖ አብሯቸው መዝለቁን ያመለክታሉ። ስራ ጀምረው እጃቸው ከመሪ ጋር ሲገናኙም ከመንገዳቸው በቀር ስለምንም አያስቡም። «የፈንጂ ማምከን ስራ ስህተቱ ሞት ብቻ ነው። ማሽከርከርም ቢሆን ስህተት ከተገኘበት ውጤቱ በሞት ይደመደማል» ይላሉ። ዛሬ አንጋፋው ሾፌር ተቀጥረው በሚሰሩበት የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በጠንቃቃ አሽከርካሪነታቸው በየአመቱ አመስግኖ ከሚያከብራቸው ሰራተኞች መካከል አንዱ ሆነዋል። አቶ ታምራት ለአምስት ተከታታይ አመታት ያለምንም አደጋ በመጓዛቸው የወርቅ ሜዳሊያና የዋንጫ ተሸላሚ ናቸው። የባስ ካፒቴን ሰለሞን ዋሴም ለሶስት ተከታታይ አመታት አደጋን ተከላክሎ በማሽከርከር የገንዘብና የብር ሜዳሊያ ከተሸለሙ ሾፌሮች መካከል አንደኛው ነው። ሰለሞን ጎንደር በነበረበት ጊዜ ለአመታት የህጻናት ማመላለሻ ሾፌር በመሆን አገልግሏል። በወቅቱ ለህጻናቱ የሚያደርገው ጥንቃቄና ትኩረትም አመታትን ለተሻገረበት ሙያ መነሻ እንደሆነው አይሸሽግም። ሰለሞን ብዙዎች ለሚያደርሱትና ለሚደርስባቸው የትራፊክ አደጋ መንስኤው ያለመረጋጋት ችግር መሆኑን እንደምክንያት ያስቀምጣል። ‹‹የአንድ ወገን ጥንቃቄ ብቻውን ውጤት አያመጣም›› የሚለው ባስ ካፒቴኑ ‹‹አንዱ ለሌላው ሰበብ ሳይሆን መንገድን ከስጋት በራቀ ጉዞ ማጠናቀቅ ለሁሉም ይበጃል›› ሲል መልዕክቱን ያደርሳል።አዲስ ዘመን ጥር 2/2012መልካምስራ አፈወርቅ", "passage_id": "ebfe96e0db4a51d77a99126309cee4c3" } ]
d526c6154a1d67de1f5d856fe78ced57
d1e1d8fb996069b2ab657ee61c2de97b
የውድድሮች መመለስ ስጋትና ጥቅሙ ሚዛን ላይ ሲቀመጥ
በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ስጋት ምክንያት ተቋርጠው የቆዩ እንቅስቃሴዎች አሁን ወደ ነበሩበት እየተመለሱ ነው። የአውሮፓ ሊጎችም የውድድር ዓመቱን ካቆመበት በመቀጠል ሂደት ላይ ናቸው። የጀርመን ቡንደስ ሊጋ ከሁሉም ቀድሞ ወደ ውድድር የተመለሰ ሲሆን፤ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ፣ የስፔን ላሊጋ እና የጣሊያን ሴሪ ኤም ከተያዘው የፈረንጆቹ ወር ጥቂት ቀናት በኋላ ካቆሙበት ለመቀጠል ክለቦች ልምምድ ጀምረዋል። የዓለም አትሌቲክስም የዳይመንድ ሊግ ውድድሮችን ለማስጀመር ቀን መቁረጡ ታውቋል። በዚህ ወቅት ሃገራት ከቫይረሱ ቀውስ መጠነኛ ማገገም እንጂ ጥናትና ምርምሩ ያልተጠናቀቀውን ወረርሽኝ ጨርሰው ተቆጣጥረውታል ለማለት አዳጋች እንደሆነባቸው ግልጽ ነው። ዓለም በዚህ ጭንቀት ውስጥ ባለችበት ወቅት ስፖርት ወደነበረበት መመለሱ በጤና ነው? የሚሉ አስተያየቶች ከተለያዩ አቅጣጫዎች እንዲነሱ አድርጓል። እርግጥ ነው ክለቦች እንደ ቀድሞው የተጫዋ ቾቻቸውን ሙሉ ደመወዝ መክፈል በማይችሉበት ደረጃ ተቸግረዋል። አትሌቶችም በውድድሮች መሰረዝና መራዘም ምክንያት ገቢ ማግኘት አልቻሉም። በአጠቃላይ በስፖርቱ ዘርፍ የሚሰሩ አካላት በቢሊዮን ለሚቆጠር የገንዘብ ኪሳራ ተዳርገዋል። አሁን ካሉበት በጥቂቱም ቢሆን ለማገገም ደግሞ ውድድሮችን ማካሄድ ይኖርባቸው ይሆናል። ለተመልካች ዝግ የሆኑ ስታዲየሞችና የስፖርት ሜዳዎችም አማራጭ በመሆናቸው ላይ ሁሉም የሊግ አመራሮች ተስማምተዋል። እንዲያም ሆኖ ግን የጤና ባለሙያዎች ዓለም ራስ ምታት ከሆነባት ወረርሽኝ ሳታገግም ወደ ውድድሮች በመመለሳቸው ስጋታቸው ማየሉን አልሸሸጉም። በመድሃኒቶች ላይ የማማከር ስራ የሚሰሩት ዶክተር ማሶድ ኤጋ ‹‹ይህ ወቅት አሁንም መገለል የሚያስፈልግበት እንጂ ውድድሮች የሚጀመሩበት ነው ለማለት ያስቸግራል›› ሲሉ ቲአቲ ወርልድ ለተባለ ድረ ገፅ ስጋታቸውን ገልጸዋል። አሁን በጨዋታ ላይ የሚገኘው ቡንደስ ሊጋ ከመንግስት ፈቃድ ያገኘው እያንዳንዱ ክለብ ንጽህናውን በሚገባ እንዲጠብቅ በማሳሰብ ጭምር ነው። ከዚህ ቀደም በእግር ኳስ ማህበሩ ሁለት ዲቪዚዮን ውስጥ የሚጫወቱ 1ሺ724 ተጫዋቾች ላይ በተደረገው ምርመራ 10 የቫይረሱ ተጠቂዎች መገኘታቸውን ዘገባው አስታውሷል። በመሆኑም ንጽህናን ከመጠበቅ ባሻገር እያንዳንዱ ተጫዋች በየዕለቱ መመርመር እንዳለበት ዶክተር ማሶስ ያሳስባሉ። ይህ ካልሆነ ግን ቫይረሱ ድምጹን አጥፍቶ ከአንዱ ተጫዋች ወደሌላው ከዚያም ወደ ክለቦች በመዛመት ለመቆጣጠር አደገኛ ሊሆን እንደሚችልም ይጠቁማሉ። አሁንም ከተመልካች ውጪ ጨዋታን ማካሄድ አቻ የሌለው አማራጭ መሆኑ በስፖርት ቤተሰቦች ዘንድ ታምኗል። የጤና ባለሙያዎች በአንጻሩ ተመልካቾች ባይኖሩም በስታዲየም አካባቢ ከ100 የሚልቁ ሰዎች መገኘታቸው ከስጋት እንደማያድን ነው የሚያስገነዝቡት። ሊጎች እንዲሁም ክለቦች በበኩላቸው ከገቡበት የኢኮኖሚ ጫና ለመውጣት ባላቸው ብርቱ ፍላጎት ምክንያት የባለሙያዎችን ምክር ችላ እንዳሉ ቀጥለዋል። ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ቀሪዎቹን 92 ጨዋታዎች በማካሄድ የውድድር ዓመቱን ካላጠናቀቀ የ1ነጥብ25 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ የሚያጋጥመው ይሆናል። በመሆኑም በተመረጡ ስታዲየሞች ከደጋፊ ውጪ ጨዋታዎቹን ለማካሄድ ቀናት ብቻ ቀርተዋል፤ ክለቦችም የልምምድ ሜዳዎቻቸውን ከፍተዋል። የጤና ባለሙያዎች በበኩላቸው ጨዋታዎቹን የግድ መቀጠል ቢገባ እንኳን ክለቦች ተጫዋቾቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ላይ ሞት ሊከተል እንደሚችል፣ የሚገጥማቸውን ኪሳራ እንዲሁም ካሳን ታሳቢ ማድረግ እንዳለባቸው ያሳስባሉ። ሌላው የባለሙያዎች ስጋት የወረርሽኙ ፈጣን ስርጭት ሲሆን፤ በላብ እንዲሁም በግብ ጠባቂዎች ጓንት አማካኝነት የመዛመት እድሉ ሰፊ መሆኑንም ነው ያመላከቱት። ለዚህ ስጋት ምክንያት የሆነው ደግሞ ባለሙያዎቹ ለሚሰጡት ምክር የየክለቡ የጤና ባለሙያዎች ትኩረት እየሰጡ አለመሆናቸውን ነው። ከዚህ ባሻገር ተጫዋቾች በሚገባ በየዕለቱ ምርመራ እያደረጉ እንኳን፤ ደጋፊዎቻቸው ደግሞ ጨዋታን በቴሌቪዥን ለመከታተል አካላዊ ርቀታቸውን ሳይጠብቁ ይሰባሰቡ ይሆናል የሚል መሆኑን ዶክተር ማሶድ ያሰምሩበታል። የቡድን ስፖርቶች በባህሪያቸው ለአካላዊ ርቀት የማይመቹ በመሆናቸው እንደየስፖርት ዓይነቱ ውድድሮች ቢቀጥሉ የሚል ምክረ ሃሳብ የሚያቀርቡት ደግሞ በአሜሪካ የኮቪድ 19 ግብረ ኃይል አማካሪ እንዲሁም የብሄራዊ የኢንፌክሽን በሽታዎች ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር አንቶኒ ፉሲ ናቸው። መታሰብ ያለበት ወረርሽኙ እንዴት በቀላሉ ከአፍንጫ ወደ እጅ ከዚያም ወደ ልብስ በመጨረሻም ወደ ሌላ ሰው እንደሚተላለፍ ነው። በመሆኑም ቀጣዩ የስጋት አቅጣጫ ጨዋታዎችና ግጥሚያዎች እንዳይሆኑ መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው። የዓለምን እግር ኳስ የሚመራው ፊፋ የሕክምና ኮሚቴ ሊቀመንበርና የፊፋ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶክተር ሚካኤል ባሮን ሆግ በበኩላቸው ‹‹ዓለም ለእግር ኳስ ውድድሮች ዝግጁ አይደለችም›› ይላሉ። ቤልጂየማዊው ዶክተር ዘ ሰን ከተባለው ድረ ገጽ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ዓለም ለጤና እና ለመድሃኒት ቅድሚያ መስጠት ያለበት ወቅት ላይ መሆኗን ይገልጻሉ። አደጋውን ሲያመለክቱም ‹‹በዚህ ድራማዊ በሆነ ክስተት ውስጥ ኃላፊነት መውሰድ ከባድ ነው። ተጫዋቾች በትክክል ሁለት ሜትሮችን ተራርቀው አይጫወቱም፤ የፊት ጭምብል ማድረግም አይችሉም። በሜዳ እና በመልበሻ ቤትም አብረው ናቸው። በዝግ ስታዲየም ይጫወቱ ቢባልም በሆነ አጋጣሚ ቡድናቸውን ለመደገፍ የገቡ ደጋፊዎች ይገኛሉ። ምርመራውን በየወቅቱ ማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም፤ አንድ ሰው በቫይረሱ ተያዘ ማለት ግን ቡድኑን በሙሉ ወደ ለይቶ ማቆያ ማስገባት የግድ ይሆናል። ስለዚህ እግር ኳሱ መታገስ እና የጤና ባለሙያዎችን ምክር መስማት አለበት›› በማለት ያስረዳሉ። አዲስ ዘመን ግንቦት 24/2012ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=33507
[ { "passage": "\n \n‹‹ ከሁለቱ ምድቦች ጠንካራ ቡድኖች የሚገኙበት ምድብ ይህ ነው። በአንደኛው ዙር ከማያቸው ቡድኖች ፣ ከሚመዘገቡት ውጤቶች እና ከወቅታዊ አቋም አንፃር ከፍተኛና እልህ አስጨራሽ ፉክክር ነበር፡፡ በሁለተኛው ዙርም ከዚህ በበለጠ ፉክክር ይጠበቃል። የውድድር ቀላል ባይኖርም በተለይ በዞናችን ከሚገኙት ስድስት ቡድኖች ጋር ያለው የደርቢነት ስሜት ከፍተኛ በመሆኑ የሚጠብቀን ጨዋታ ጠንካራ ይሆናል፡፡ ››\n \nቅድም እንዳልኩት በአንደኛው ዙር ላይ የነበረው ጠንከራ ፉክክር አሁንም እንደሚያጋጥመን እንጠብቃለን፡፡ ባለን የተጨዋቾች ጥራት ፣ በስታፉ ጥንካሬ እና በከተማ መስተዳድሩ ጥረት ጠንካራ ቡድን ሰርተናል፡፡ እንደዛም ቢሆን አጥቂና አማካይ ላይ ያሉብንን ክፍተቶች በጥልቀት ገምግመን ለክለቡ ይመጥናሉ ፣ በፍጥነት ከቡድኑ ጋር ተዋህደው ይጠቅሙናል ያልናቸውን ተጨዋቾች (ከሆሳህና ሀፍቶም ገ/እግዚአብሄር ፣ ከመድን ያሬድ ፣ ከድሬደዋ ከተማ በድሩ) አካተናል፡፡ በሜዳችንም ከሜዳችን ውጭም ጥሩ ውጤት ለማምጣት ጠንካራ ዝግጅት አድርገናል። የህዝቡ ስሜትና ድጋፍ አስደናቂ ነው፡፡ ጨዋታ ባለን ቁጥር ሕዝቡ ከቤቱ ነቅሎ ወጥቶ ነው የሚደግፈን፡፡ የልምምድ ሜዳ ሳይቀር እየመጡ ነው የሚያበረታቱን፡፡ ስለዚህ እነሱንም ለማስደሰት ጠንክረን እንሰራለን››\n \n‹‹ቡድኖች በእንደዚህ አይነት መንገድ እየተጠጉ ሲመጡ ለውድድሩ ከፍተኛ ትኩረት እንድትሰጥ ያደርግሀል፡፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ በደረጃ ሰንጠረዡ ከአንድ እስከ አምስት ከሚገኙት ጋር የምንጫወተው በሜዳችን የምናገኛቸው በመሆኑ እነርሱን ለማምለጥ እንሰራለን። ከፍተኛ ትኩረት አድርገን የሕዝቡን ፍላጎት እናሳካለን ። ››\n \n‹‹ በምስራቅ አፍሪካ የተለያዩ ሀገሮችን ስታድየሞች ተመልክቻለው፡፡ እንዲህ አይነት ስቴዲዮም አላየሁም ። ሁሉነገሩ የለሟላለት ሜዳ ነው። በዚህ ውብ ስቴዲዮም የምንጫወትበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡ በቅርብ ቀን ይመረቃል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ››\n \n‹‹ የ1ኛው ዙር ፉክክር በጣም ጠንካራ ነበር፡፡ ከአንድ እስከ አምስት ያሉት ቡድኖች ነጥባቸው ተቀራራቢ ነው፡፡ የክለቦቹም አቅም ተመጣጣኝ በመሆኑ ፍክክሩ ጥሩ ነበር። ሁለተኛው ዙርም ጠንካራ ፉክክር እንደሚጠብቀን ጥርጥር የለውም››\n \n‹‹ በተወሰኑ ክፍተቶቻችን ላይ ተጫዋቾች ለመጨመር ሞክረናል፡፡ አምና ጅማ አባቡና የነበረው ተከላካዩ ምንያህልን እንዲሁም ገዛኸኝን ከአማራ ውሃ ስራ አምጥተናል፡፡ ራሳችንን አጠናክረን ጥሩ ስራ እንሰራለን ብለን እናስባለን፡፡››\n \n‹‹ይህን ምድብ ልዩ የሚያደርገው የነጥብ መቀራረቡ ነው፡፡ ከፊት ያሉትን ብቻ ሳይሆን ከኋላ ያሉትንም በንቃት የምንጠብቅበት ውድድር ነው፡፡ እያንዳንዱ ጨዋታ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው በመሆኑ በትኩረት ውድድር የምናደርግበት ይሆናል››\n \n‹‹ ውድድሩ በጣም ከባድ ነው፡፡ በተለይ እኛ ያለንበት ምድብ ፕሪሚየር ሊጉን የሚያውቁ 5 ክለቦች ያሉበት መሆኑ ፣ የፋይናስ አቅማቸው የተደራጀ ቡድኖች ያሉበት መሆኑ፣ በፕሪሚየር ሊጉ ተጫውተው ያለፉ ልምድ ያላቸው ተጨዋቾች የሚገኙበት ቡድኖች ያሉበት መሆኑ ፉክክሩ ከሁለተኛው ምድብ ይልቅ የኛ ምድብ ከባድ ነው ። ከፕሪሚየር ሊጉ ያልተናነሰ ፉክክር ያለበት ምድብ ነው። ››\n \n‹‹ በ1ኛው ዙር የነበሩብንን ጠንካራና ደካማ ጉን አይተናል፡፡ ያሉብን ክፍተቶች ለመድፈንና በየቦታው ያሉብንን ችግሮች ለማስተካከል ተጨዋቾችን አስፈርመናል፡፡ ጠንካራ ቡድን ሆነን እንቀርባለን››በሁለተኛው ዙር ከመሪዎቹም ሆነ ከተከታዮቻችን የሚመጣውን ለመቋቋም ተዘጋጅተናል ። በእኛ በኩል በአንደኛው ዙር ከሜዳ ውጭ ጥሩ ነበርን፡፡ በሜዳችን ላይ ማግኝት የሚገባን ውጤት ለማግኝት ጠንክረን እንሰራለን፡፡ ህዝቡም እኛን እየደገፈ በመሆኑ ከፍተኛ መነቃቃት ውስጥ ነን፡፡ ስለሆነም ጥሩ ውጤት እናመጣለን። ››———–\n", "passage_id": "ff4d0999ffc3dfbb255a78bc6373cb89" }, { "passage": "ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ሜዳዎች ላይ ስርዓት አልበኝነት እየተንሰራፋ መምጣቱን ተከትሎ የ2012 ውድድር ዓመት ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ትልቅ ስጋት አንዣቦበት እንደነበር ይታወሳል፡፡ እርግጥ ነው ባለፉት ዓመታት የታዩት የስቴድየም ሁከቶች አዝማሚያቸው አዲሱን የውድድር ዓመት ስጋት እንዲሰፍንበት ቢያደርግ አይገርምም፡፡ ይሁን እንጂ አስፈሪው ስጋት የበለጠ ጥፋት ሳያስከትል አልፎ አዲሱም የውድድር ዓመት በመልካም መንገድ ላይ ጉዞውን ቀጥሎ ፕሪሚየር ሊጉ ስምንተኛ ሳምንቱ ላይ ይገኛል፡፡ የስፖርታዊ ጨዋነት ጉዳይ ግን አልፏል ብለን የምንተወው ወይም ስጋት ሲፈጥርብን ብቻ የምናነሳው ጉዳይ አይደለም፡፡ ይልቁንም ካለፈው የምንማርበት ዘወትር የሌሎችን ተሞክሮና ታሪኮች አንስተን ነገን የተሻለ ለማድረግ የምንታትርበት መሆን ይገባዋል፡፡ በዛሬው የስፖርት ማህደር አምዳችንም አንድ ሰው ለኩሶት የብዙዎችን ሕይወት የቀጠፈ ዓለማችን የማይረሳ የስቴድየም ግጭት መለስ ብለን በማስታወስ ከታሪኩ የምንማርበት እንዲሆን ወደድን፡፡ የዚህ ዘግናኝ የስቴድየም ግጭት ታሪክ ከዚህ ይጀምራል፡፡እኤአ ሰኔ 29 ቀን 1985፣ በሄይሰል ስታዲየም፣ ቤልጅየም የአውሮፓ የክለቦች ውድድር ፍፃሜ ነበር። የሊቨርፑልና ጁቬንቱስ ጨዋታ ሊጀመር ደቂቃዎች ቀርተዋል። በ1920ዎቹ በተገነባው ያረጀ ስታዲየም 58ሺህ ተመልካች ተጠቅጥቋል። የጁቬንቱስ ደጋፊዎች ከስታዲየሙ ‹‹Z›› ክፍል የላይኞቹ ደረጃዎች ወደ ታችኞቹ፣ አንዳቸው ሌላቸው ላይ ተነባብረው እየተገፋፉ ጎረፉ። የብረት ዘንግ የያዙ የሊቨርፑል ደጋፊዎች ያባርሯቸዋል። ተቀጣጣይ ነገሮች ይወረወሩባቸዋል። ሁከት ነገሠ። የራስን ነፍስ ለማዳን ሲባል በሌሎች ላይ መረማመድ ግድ ሆነ። መራወጡ፣ መደራረቡ፣ መተፋፈጉ ቀጠለ። ማዕበሉ ሄዶ፣ ሄዶ በስታዲየሙ ግድግዳዎች ተገደበ። የሰው ልጅ በማይቆጣጠረው ኃይል ተገፍቶ ከሸክላና ጡብ ከተሰራ አጥር ጋር ተጣበቀ። ግድግዳዎቹም ግፊቱን መቋቋም አቅቷቸው ፈረሱ። የስፖርት ቤተሰቡ ከአርማታ ስብርባሪ ጋር ተደባልቆ ተጨፈላለቀ። የ20 ዓመቱ ሲሞኔ ስተርን ወደ ጨዋታው የመጣው በአባቱ ጉትጎታ ነበር። የገዛው ቲኬት ጣዕረ ሞት በተንሰፈሰፈበት የስታዲየሙ ደቡባዊ ክፍል ‹‹Z›› ያስገባል። አንድ መግቢያ ብቻ ስለነበር በራፉ ላይ ትርምስ ተፈጥሯል። በቅጡ አልተፈተሸም፣ ደጋፊዎች ያለቲኬት በሩን ሲያልፉ፣ የቢራ ጠርሙስ የያዙም ሲገቡ ማየቱን ያስታውሳል። ወንበር የሌላቸው ደረጃዎች መቀመጫ ከሆኑበት ከዚህ የስታዲየሙ ክፍል የሊቨርፑል ደጋፊዎች ከተሰጣቸው ሌላው ክፍል ጋር ይጎራበታል። የሚለያቸው በኋላ የተደረመሰው የሽቦ አጥር ብቻ ነው። የመጀመሪያው ቁስ በአንድ ደጋፊ ገና እንደተወረወረ አባቱ ‹‹ከስታዲየም እንውጣ›› ብለው ሲሞኔን አጣደፉት። ጨዋታውን ሳይመለከት መውጣትን ባለመፈለጉ አባቱን ለመከተል አመነታ። በመዘግየታቸው ሁለቱም በሺዎች ተገፍተው ከግድግዳ ጋር ተጣበቁ። ነፍስ ግቢ፣ ነፍስ ውጪ ሆነባቸው። ሲሞኔ የሞት ሞቱን ግድግዳ ቧጦ፣ ሽቦ ተንጠላጥሎ በስታዲየሙ መፀዳጃ ቤት ጣሪያ ላይ ወጣ። ከዚያም አባቱን ከመታፈግና መረጋገጥ ለማዳን ከላይ ሆኖ ወደ ታች እጃቸውን ይዞ መጎተቱን ቀጠለ።‹‹አብሮን እንደነበረ የማናውቀው አንዳች ጉልበት በዚያች ሰዓት መጣልን። አባቴን ጎትቼ ወደ ጣሪያው አወጣሁት›› ይላል ሲሞኔ። ከመታፈጉ ሲወጡ ግን አባት እጃቸው ይደማ ነበር። የሞት ሞታቸውን ራሳቸውን አድነው በስታዲየሙ አጠገብ ወዳለ የቀይ መስቀል እርዳታ ማዕከል ሲሄዱ ተረጋግጠውና ተጨፈላልቀው የሞቱ ደጋፊዎችን አስከሬን መሃል ራሳቸውን አገኙ፡፡ ስርዓት አልበኝነት ባስከተለው ጣጣ 32 ጣልያናዊያን፣ አራት ቤልጅየማዊያን፣ ሁለት ፈረንሳዊያን እና አንድ ብሪታኒያዊ ህይታቸውን አጡ። የልጅ ልጆች ያሏቸው ኦቴሎ ሎረንቲን የ‹‹Z›› ታዳሚ ነበሩ። ከልጃቸው ሮቤርቶ እና ከሁለት የልጅ ልጆቻቸው አንድሪያ እና ግራኒ ጋር በዚሁ ቦታ የፍፃሜውን ጨዋታ ለመመልከት ወደ ሄይሰል መጥተዋል። ከእነርሱ ጋር የህክምና ባለሙያው ሮቤርቶ ሎረንቲን ነበር። በመገፋፋቱና በመረጋገጡ ሰዎች በመጎዳታቸው ሮቤርቶ የሙያውን ለማበርከት ጉዳተኞችን ሊታደግ ወደኋላ ቀረ ። ‹‹እንግሊዛዊያኑ የማይወረውሩብን ነገር የለም። ሮቤርቶ!… ሮቤርቶ!… ና ውጣ!… እንሂድ! ብዬ ተጣራሁ። ብረት፣ የአርማታ ፍንካችና ድንጋይ ወደኛ ይዘንባል። ህፃናትና ሴቶች አብረውን አሉ። እየተገፋን፣ እየተገፋን ከግድግዳው ጥግ ደረስን። ከዚያ ራሴን በቅፅበት በመጫወቻ ሜዳው ላይ አገኘሁት›› በማለት ኦቴሎ ክፉውን ቀን ያስታውሳሉ።‹‹ወደ ደረጃዎቹ እያየሁ ሮቤርቶን መጣራቴን ቀጠልኩ። በፍለጋዬ መሃል የእህቴ ልጅ አንድሪያ ጭንቅላቱን በሁለት እጁ ይዞ ከድንጋጤ ጋር ቆሞ አየሁት። የጠራሁት ሮቤርቶ በስታዲየሙ መቀመጫ ደረጃ ላይ ተንጋሏል። ጆሮዬን ከደረቱ ላይ አጣብቄ አዳመጥኩ። የሚሰማኝ የራሴው የልብ ትርታ ብቻ ነበር። ህይወቱ አልፏል። ይህን ሳደርግ የቴሌቪዥን ካሜራ ባለሙያ ይቀርፀኛል። በኋላም የሞተውን ልጄን ስፈልግ የሚያሳየውን ፊልም በቴሌቪዥን አየሁት።›› ይላሉ፡፡ሮቤርቶ ሌሎችን ለመርዳት ሲል ህይወቱን አጥቷል። የደጋፊዎች አስከሬን ተሰብስቦ በጊዜያዊ ማዕከል ተከማቸ። አባት ኦቴሎ ሌሊቱን የልጃቸውን አስከሬን ለመረከብ ወደ ሆስፒታል ሄዱ። ‹‹በሆስፒታል ከሶስት ሰዓታት በላይ አስጠበቁን። ሌሊት 9:00 ሰዓት ላይ የልጄን አስከሬን አየሁት። የአንገቱ ሃብልና የጋብቻው ቀለበት ተወስደዋል። ‹ማንነቱን ለመለየት ብለን ነው ያወለቅናቸው› የሚል ምክንያት ሰጡኝ። ነገር ግን በልጄ ጌጣጌጥ ላይ ስሙ አልተፃፈባቸውም ነበር። ሰርቀዋቸው ነው›› ይላሉ።የሞት ትራፊዎቹ ደጋፊዎች ስለሄይሰል ማውራት አይፈልጉም። ለብዙ ጁቬዎች የሄይሰል ስም ነውር ነው። ከአደጋው በኋላ አንድ ደጋፊ የመናገር አቅም አጥቶ ደንዝዞ ቃል ለመተንፈስ ወራት አስፈልገውታል። ሌላው ደጋፊ ደግሞ ከጓደኛው ጋር ወደ ስታዲየሙ መጥቶ በአደጋው ያጣውን ባልንጀራውን አስከሬን ከሙታኑ መሐል አገኘው። በሃዘን ወደ መኪናው ቢመለስም የመኪናው ቁልፍ እርሱ ዘንድ እንዳልሆነ አስታወሰ። በአስከሬኑ ኪስ ውስጥ ነበር። በወቅቱ የ14 ዓመት ታዳጊ የነበረ ደጋፊ የአባቱን መሞት ሳያውቅ በሰዎች ላይ በእግሩ ተረማምዶ ራሱን ማዳኑን ዛሬ በፀፀት ያስታውሳል። “ቢሆንም በባዶ እግሬ ነበርኩ። ጫማዬ በግርግሩ ከእግሬ ላይ ወልቆ ጠፍቶብኝ ነበር” እያለ ያዝናል። ከዚህ ሁሉ ትራጀዲ በኋላ ጨዋታው እንዲደረግ መወሰኑ አወዛጋቢ ነበር። በዚያ ርጉም ቀን ጨዋታው ቢቀጥልም ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የሊቨርፑሉ ማርክ ላውረንሰን የትከሻ ውልቃት ጉዳት ደርሶበት ተቀይሮ ወጣ። ጉዳቱ ከበድ ያለ ስለሆነ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ተወሰደ።“አምቡላንስ ውስጥ ተኝተህ ተጓዝ ተባልኩ። እኔ የፈለግኩት ደግሞ ተቀምጬ መሄድ ነበር። በድጋሚ እንድተኛ ታዘዝኩ። አሻፈረኝ አልኩኝ። እንደገና ኮስተር ባለ ትዕዛዝ እንድተኛ ተነገረኝ”\nይላል። ትዕዛዙ የጠነከረበት፣ አንድ የሊቨርፑል ተጫዋች በአምቡላንስ ውስጥ መኖሩ እንዳይታወቅ ተብሎ ነበር። የመጣው ከእነ ማሊያው ነው። በላዩ ላይ የደረበበት የቱታ ጃኬትም ቀይ ነው። ማሊያውም ስለሚታይ ማንነቱን ለመለየት ቀላል ነበር። ሆስፒታል ሲደርስ በጓሮ በር አስገቡት። በሆስፒታሉ የሞቱትና ክፉኛ የቆሰሉት ደጋፊዎች ወገኖች ይገኛሉ። ሁሉም በሊቨርፑል ላይ አምርሯልና ላውረንሰን ተደብቆ መግባቱ ተገቢ ነበር። የወለቀ ትከሻውን በቦታው የመለሰው ቀዶ ጥገና ከተጠናቀቀ በኋላ ተጨዋቹን እዚያው አልጋ ላይ ተውት። አቅሉን መልሶ አግኝቶ ቀና ቢል አውቶማቲክ ጠብመንጃ የታጠቀ ወታደር በግርጌው ተቀምጦ አየ። ወታደሩም እጁን ዘርግቶ ፈጥኖ እንዲተኛ ምልክት ሰጠው። ላውረንሰንም ፈጥኖ ወደ አልጋው ተመለሰ።በነጋታው ጠዋት በባለቤቱና ከረዳት አሰልጣኞች በአንዱ ታጅቦ በድብቅ ከሆስፒታሉ ወጣ። የቤልጅየም ባለስልጣናትም አፋጥነው የሊቨርፑልን ተጨዋቾች ወደ ኤርፖርት ወስደዋቸው ወደ ሃገራቸው በረሩ። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርጋሪት ታቸር ግፊት የእንግሊዝ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክለቦቹ ከአውሮፓ ውድድሮች እንዲገለሉ አደረገ። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ደግሞ የሊቨርፑል ደጋፊዎችን ጥፋት ተመልክቶ የእንግሊዝን ክለቦች ለአምስት ዓመት ከማንኛውም ውድድር አገደ። ቅጣቱ ሄይሰል የተወውን የህሊና ጠባሳ ሊሽረው አልቻለም። በአንድ ደጋፊ የተጫረ ረብሻ ለብዙ ቤተሰቦች ጥልቅ ሐዘን ምክንያት ሆነ። ‹‹አዎን›› ይላል የወቅቱ የሊቨርፑል አምበል ፊል ኒል። ‹‹አዎን! በዚያ ቀን ምክንያት ከህይወት አስፈሪ ቅዠት ጋር ተጋፈጥኩ። ከጉዳቱ ለማገገምም ዘመናት አስፈለጉኝ።››አዲስ ዘመን ጥር 3/2012 ቦጋለ አበበ", "passage_id": "a96f3084f819dc453f4d6cfcc8d681e9" }, { "passage": "በተደጋጋሚ እንደሚነገረው እግር ኳስ የንክኪ ስፖርት ነው። ተጫዋቾች እርስ በእርሳቸው ከሚያደርጉት ንክኪ በተጨማሪ ከመሬት፣ ከኳስ እና በግብ ጠባቂዎች ምሳሌ ደግሞ ከግቡ ቋሚ ጋር ሊጋጩ የሚችሉበት ዕድል ከፍ ያለ ነው። ማንኛውም ፊት ላይ የሚደርስ ጉዳት ከፍተኛ ችግር የማስከተል ዕድሉ ላቅ ያለ ስለሆነ በጥንቃቄ ሊመረመር እና ሊታከም ይገባል።በአብዛኛው ጊዜ የጭንቅላት ግጭት እና ክርን ከጭንቅላት ጋር የሚኖረው መላተም የፊት ጉዳት መንስኤ ሲሆኑ ይታያል።  ለሚደረገው ህክምና ጉዳቱ የተከሰተበት መንገድን እና የግጭቱን ፍጥነት (velocity) ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው ።የፊት ጉዳቶችን ሜዳ ላይ ማወቅ እና መመርመር ከባድ ስለሆነ የተሟላ የራዲዮሎጂ ስፔሻሊቲ ወዳለበት ሆስፒታል መላክ አስፈላጊ ነው። ይህን ጉዳት የሚያክመው ባለሙያ ተያይዘው ሊመጡ የሚችሉ ጉዳቶችን በማወቅ እና በመጠርጠር ስራውን ማከናወን ይኖርበታል።ማንኛውም የፊት ጉዳት ሲታከም መጀመሪያ የሚሰራው ስራ ‘ABC of life’ የሚባሉትን የህይወት አድን እርምጃዎች መተግበር ነው። Airway (የአየር ዝውውር) – Breathing (አተነፋፈስ) – Circulation (የደም ዝውውር) ላይ ያሉ ለከፍተኛ ጉዳት ሊዳርጉ የሚችሉ እክሎች መኖራቸው ከተጣራ በኋላ የተጫዋቹ ንቃተ ህሊና የሚታይ ይሆናል። አብዛኛውን ጊዜ ፊት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች ለህይወት አስጊ የሚባሉ አይደሉም። ይህ ጉዳት ሁለቱን የቆዳ ክፍሎች (Dermis and Epidermis) የሚያጠቃ ነው። የሚያጋጥመውም ጠንኳራ ከሆነ ነገር ጋር ፊት ሲፋተግ እና ቆዳ ሲላጥ ነው። የመጀመሪያ የማከሙ ስርአት ትኩረት የሚያደርገው ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር በመከላከሉ ላይ ነው። ቁስሉ እንዲድን ይህንም ተከትሎ ዘለቄታ ያለው ጠባሳ ቆዳ ላይ እንዳይፈጠር መከላከል አስፈላጊ ነው። ከግጭት በኋላ የሚኖር ከላይ የሚፈጠር (blunt trauma) አደጋ ነው ። ተጫዋቹ ሊያሳያቸው የሚችል ዋና ምልክቶች ህመም እና ደም መቋጠር ካለ ደግሞ ወደ ሰማያዊነት የሚለወጥ የቆዳ ቀለም ነው። ይህን ለማከም ጉዳት የደረሰበት ቦታ ላይ በረዶ መያዝ (ice packs) አስፈላጊ ነው። እየታረፈ ለ24-48 ሰዐት ያህል በረዶ መደረግ ይኖርበታል። ይህ በጡንቻዎች እና በተለያዩ የሰውነት አካላት (spaces) ላይ የሚኖር ደም መቋጠር ነው። ሰማያዊ ወይንም ጠቆር ያለ እብጠትን ጉዳቱ የደረሰበት ቦታ ላይ ማስተዋል ይቻላል።ደም መቋጠር የተስተዋለው በአፍንጫ ወይንም ጆሮ ጫፍ ላይ ከሆነ ተጫዋቹ ጨዋታውን እንዲቀጥል የሚፈቀድለት ቢሆንም ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በድጋሚ የሚታይ ይሆናል።ይህ ጉዳት ክፍት የሆነና ቆዳን የሚያጋልጥ ነው ። ከላይ (Superficial) አልያም ጥልቅ (Deep) የሆኑ የቆዳ መሰንጠቅ ጉዳቶች አሉ። ፊት ላይ ከሚኖሩ ብዙ የሚባሉ የደም ስሮች ምክንያት መድማት የተለመደ ምልክት ነው። ሰለዚህ ደሙን ለማቆም በቀጥታ ቁስሉን ተጭኖ መያዝ አስፈላጊ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ፊት ላይ የሚኖረው የቆዳ መሰንጠቅ ለማስተካከል መስፋት ሊያስፈልግ ይችላል ። ከላይ ከተዘረዘሩት በእግር ኳስ ጨዋታ ወቅት ፊት ላይ ከሚደርሱ ጉዳቶች ተዘውትሮ የሚታየው የአፍንጫ መድማት ነው።አፍንጫ በሚደማበት ወቅት ተጭኖ በመዝጋት እና ለተወሰነ ደቂቃ ይዞ በመቆየት መቆጣጠር ይቻላል። መድማቱ እንደቆመም ተጫዋቹ ወደ ጨዋታ ሜዳ እንዲመለስ የሚፈቀድለት ይሆናል ማለት ነው። መድማቱ የሚቀጥል ከሆነ በፋሻ ለማቆም ጥረት መደረግ ይኖርበታል። በቀጣይ ፅሁፋችን በፊት ላይ የሚደርሱ የአጥንት ስብራቶችን ይዘን የምንቀርብ ይሆናል። ለዚህ ፅሁፍ Football Emergency Medicine Manual 2nd edition 2015 የተባለውን መጽሐፍ በዋና ግብዓትነት ተጠቅመናል።", "passage_id": "0bca0098805ce46a0ffa032068a8a840" }, { "passage": "ዓለምን በአንድነት እያስጨነቀ የሚገኘው ወቅታዊ ጉዳይ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) ወረርሽኝ መሆኑ ይታወቃል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ያስቻለ ፈውስ በዓለም ሳይንቲስቶች፣ የህክምና ጠቢባንም ይሁን በሃያላን አገራት አቅም ማምጣት አልተቻለም። ይህም የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ ከመለወጥ አንስቶ በተለያዩ ዘርፎች ላይ በርካታ አሉታዊ ተፅዕኖው እንዲያርፍ አድርጓል። የስፖርቱ ዓለም በቫይረሱ ስጋት ሳቢያ ብዙ ተጽዕኖ እያስተናገደ ከመሆኑ ባሻገር፤ ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጉን መረጃዎች ያመላክታሉ። በወረርሽኙ ሳቢያ ትልልቅ የስፖርት ውድድሮች በመራዘማቸው፣ በመሰረዛቸው እና በመስተጓጐላቸው ኢንዱስትሪውን ከፍተኛ ገቢ እንደሚያሳጣው የተለያዩ ትንበያዎች አመልክተዋል። \nየስፖርት ኢንዱስትሪውን በስፖንሰ ርሺፕ የሚደግፉ ትልልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የበጀት ቀውስ ውስጥ መግባታቸው፣ ከትኬት ሽያጭ ከማርኬቲንግና ከተለያዩ ንግዶች የሚገኙ ገቢዎች መቆማቸው ሁሉንም ስፖርት ጎድቷቸዋል፡፡ በተለይ የእግር ኳስ ስፖርት ከፍተኛ ድርሻ የሚይዝ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል። በዚህ ዓመት የእግር ኳሱ ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል ተብሎ ሲጠበቅ ከተላላፊው ቫይረስ ጋር በተያያዘ ገቢው በእጅጉ እያሽቆለቆለ ይገኛል። የስፖርት እንቅስቃሴን ጨምሮ ሌሎች መደበኛ እንቅስቃሴዎችን በቅርብ ጊዜ ማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ ተስፋ ሰጪ ምልክቶች እየታዩ አለመሆኑ፤ በኢንደስትሪው ላይ የሚደርሰው ቀውስ እንዲያሻቅብ እንደሚያደርገው ተነግሯል። \nየቫይረሱ ስርጭት በዓለም ዙሪያ እያሻቀበ በመሆኑ ታላላቅ ስፖርታዊ ውድድሮች በቅርቡ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው የሚመለሱበት ሁኔታ ጠባብ መሆኑ እየተነገረ ባለበት ወቅት ቢቢሲ ከቀናት በፊት ይዞት የወጣው መረጃ ተስፋ ሰጪ ሆኗል። ቢቢሲ ፤ የዓለማችን ታላላቅ የእግር ኳስ ሊጎች በዝግ ስታድየምም ቢሆን\n የውድድር ዓመቱን ቀሪ መርሃግብሮች ለማጠናቀቅ በቅርቡ ወደ ውድድር ሊመለሱ መሆኑን ጽፏል። ከዚህ ውስጥ ደግሞ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ግንባር ቀደም ሊሆን እንደሚችል አስነብቧል። የውድድር ዓመቱን ቀሪ መርሃግብሮች ለማጠናቀቅ ማሳባቸውን ጠቅሶ፤ በተለይ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሊጉን ለማጠናቀቅ ቆርጠው ተነስተዋል ሲል አስነብቧል። \nየዓለም ጤና ድርጅት የሕክምና ባለሙያዎች ግን ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በትልቅ ደረጃ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው እንዳይመለሱ ምክራቸውን መለገሳቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡ የዓለማችን ታላላቅ የእግር ኳስ ሊጎች በዝግ ስታድየምም ቢሆን የውድድር ዓመቱን ቀሪ መርሃግብሮች ለማጠናቀቅ የተለያዩ ሀገራት ሊጎች እንደ አማራጭ እየቀረበ ይገኛል። በዝግ ስታዲየም ውድድሮችን አማራጭን ወደ ተግባር ለመቀየር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ቆርጠው መነሳታቸውን አስነብቧል። \nየ2020 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት መጋቢት ወር መግቢያ ላይ ነበር የተቋረጠው። ሊጉ የውድድር ዘመኑ ሊጠናቀቅ 92 ጨዋታዎች ይቀሩታል። የቫይረሱ ስርጭት በዓለም ዙሪያ እያሻቀበ መሄዱን ተከትሎም የውድድር ዘመኑን በመደበኛው መልኩ ለማካሄድ ለመመለስ የሚያስችል ተስፋ የለም። የ2020 ውድድር ዘመን 92 ጨዋታዎችን እንዴት እናጠናቅ በሚለው ዙሪያ የሊጉ ክለቦች የቪድዮ ስብሰባ አድርገዋል። \nበስብሰባው ላይ እንደ ሕክምና ባለሙያዎች ያሉ ያገባቸዋል የተባሉ ሰዎችም ተገኝተው ነበር። ክለቦች ሊጉ በቀላሉ ወደ ውድድር እንደማይመለስ መግባባት ላይ ደርሰዋል። የውድድር ዓመቱን ለማጠናቀቅ የተቀሩትን ውድድሮች በዝግ ስታዲየም ለማድረግ ከስምምነት መድረሳቸውን ቢቢሲ አስነብቧል። በቪዲዮ ስብሰባ ወቅት «የሊጉ ክለቦች ይህን ለማድረግ ደግሞ ቢያንስ 10 ገለልተኛ ሜዳዎች ያስፈልጋሉ ። ገለልተኛ\n ሜዳዎችን መጠቀም ያስፈለገው ደጋፊዎች ከሜዳ ውጪም ቢሆን እንዳይሰበሰቡ በማሰብ ነው። አልፎም የሚመረጡት ሜዳዎች ከፖሊስና የስፖርት ሜዳዎችን ደህንነት ከሚመረምር አካል ይሁንታ ያገኙ መሆን አለባቸው» መባሉን በዘገባው አስፍሯል። በተጨማሪም ተጫዋቾች በሳምንት ሁለት ጊዜ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ይደርግላቸዋል። በየቀኑ ደግሞ የበሽታው ምልክት ታየባቸው አልታየባቸው የሚለው ይለካል። አልፎም ሜዳዎች በየጊዜው ንፅህናቸው ይጣራል ተብሏል። ተጫዋቾች ከጨዋታ ውጪ ባሉት ጊዜያት ሁሉ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ አለባቸው። በውድድር ስፍራዎች ውስጥም ምግብ መብላትም ሆነ ገላን መታጠብ እንዳይችሉ የሚደረግ መሆኑን አመልክቷል። \nየእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሊጉን ለማ ጠናቀቅ በገለልተኛ ሜዳ ውድድሮችን ለማድረግ ከስምምነት መድረስ ቢችሉም ከሀገሪቱ መንግስት በኩል የሚኖረውን ተቀባይነት ምን ሊሆን ይችላል ? የሚለው ምላሽ የሚያሻ መሆኑን ዘገባው አንስቷል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን መጋቢት ወር መግቢያ ላይ ነበር በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እንዲቆም የተደረገው። የፕሪሚየር ሊጉ አስተዳዳሪ አካል መንግሥት ይሁንታ ሲሰጥ ብቻ ወደ ሜዳ የሚመለስ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። \nየውድድር አመቱ የቀሩትን 92 ጨዋታዎች ለመጫወት ከስምምነት ቢደርሱም የሀገሪቱ መንግስት ውሳኔ ምን ሊሆን እንደሚችል የተባለ ነገር አለመኖሩን ዘገባው ጠቅሷል። የዚህ ዓመት ወድድር ይቋረጥ የሚል ሐሳብ ከየትኛውም ክለብ አልመጣም ነበር። በመሆኑም በሁሉም የሊጉ ክለቦች በኩል የተወሰነው ውሳኔ ከመንግስት ድጋፍ የሚያገኝ ከሆነ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መቋጫው በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ሊሆን እንደሚችል ግምቱን አስፍሯል። የእንግሊዝ መንግሥት እንቅስቃሴዎች ቀስ በቀስ ወደነበሩበት እንዲመለሱ ካደረገ በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በዝግ ሜዳ ወደ ውድድር እንደሚመለስ ይጠበቃል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 27/2012ዳንኤል ዘነበ", "passage_id": "35430572a053b74df06f2fa400489660" }, { "passage": "እግር ኳስ በመዝናኛነቱ እንዲቀጥል ሰላማዊ የውድድር መድረክ መፈጠሩ የግድ ነው። ስኬታማ ሊግ ለመመልከት ደግም ጊዜና ገንዘቡን ወጪ አድርጎ፣ ፀሐይና ብርድ ሳይበግረው፣ተስፋ አስቆራጩን ሰልፍ ተቋቁሞ ስታድየም የሚገኘው የስፖርት ቤተሰብ የአደጋገፍ ስርዓትና ስፖርታዊ ጨዋነት ወሳኝነት አለው።ወጥ የውድድር መርሃ ግብር እጦት፤የዳኝነት ውሳኔ አሰጣጥ ችግር እንዲሁም ደጋፊዎች፤ የተጫዋቾችና የአሰልጣኞች ስፖርታዊ ጨዋነት ምግባር ችግር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መገለጫ መሆን ከጀመሩ ዋል አደር ብለዋል።\nየወንድማማችነትና የመግባባት ምሳሌ የሆነው ንፁህ እግር ኳስ ተብክሏል። የስታድየም ድምቀትና ለእግር ኳሱ ውበት ዋና ተዋናይ የሆኑ ደጋፊዎች የአደጋገፍ ስርአት ተለውጧል።ከስታድየሞቻችን የሚሰሙት ህብረ ዝማሬዎች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየደበዘዙ በአንፃሩ አፀያፊ ስድቦችና ፀብ አነሳሽ ድርጊቶች ጎልተው ተሰምተዋል፤ታይተዋል።በእግር ኳስ ሁነት ማሸነፍና መሸነፍ ያለና ወደፊትም የሚኖር መሆኑ ተረስቷል።\nይህን ተከትሎ በሚነሱ ግርግሮች ስጋትም ስታድየሞቻችን ለህፃናት፣በእድሜ ለገፉ ሰዎች፣ሴቶችና ለአካል ጉዳተኞች ምቾት የሚነሱ ሆነዋል።አዳዲስ ተመልካችን ለመመልከት እስኪያቅትም የካምቦሎጆው መንደር ለእንግዶቹ በሩን የዘጋ መስሏል።ይሁንና በተለይ ባለፈው ዓመት የፕሪሚየር ሊጉ መገለጫዎች እስኪመስሉ የተስተዋሉና የአገሪቱን እግር ኳስን መቀመቅ የሚከቱ እክሎች በዘንድሮው የሊግ ውድድር እንዳይስተዋሉ ሊጉም ካለፉት ጊዜያት በተሻለ በስፖርታዊ ጨዋናት የታጀበ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ብዙ ደክሟል።\nየኢትዮጵያ እግር ኳስ የፌዴሬሽኑ አዲስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጂራ በየክልሉ እየዞሩ ስፖርታዊ ጨዋነትን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ከከተማ አስተዳደሮች ጋር ተወያይተዋል።ክለባትና የደጋፊ ማህበራትም በየፊናቸው የየበኩላቸውን ተወጥተዋል።ክለቦች ተጨዋቾቻቸውን በስነ ምግባርና በእውቀት በማነጽ ረገድ የቤት ስራቸውን እንዲወጡ ተደርጓል። ከሳምንት በፊት በአዳማ ከተማ በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ የስፖርት ቤተሰቡን ያሳተፈ ውይይትም ተካሂዶ ነበር ።ይሁንና በስድስተኛው ስምንት የሊጉ መርሃ ግብር ፌዴሬሽኑም ሆነ የስፖርት ቤተሰቡ ጥረት ከንቱ ሆኖ የተለያዩ መድረኮች የተካሄዱ ስብሰባዎችም ፍሬ አልባ ሆነው ታይታል።በእለቱ በቅድሱ ጊዮርጊስና በሃዋሳ ከተማ መካከል ሊካሄድ በነበረው ጨዋታ ቀደም ሲል ለስፖርታዊ ጨዋነት ምክንያት ሆነው የሚቀርቡ ፤የዳኛ ውሳኔ አሰጣጥ ጉድለት፤ አሊያም ዳኞችን ውሳኔ አምኖ አለመቀበል፤ክብር የሚነኩ ዘለፋዎች፣የተጫዋቾችና አሰልጣኞች ለፀብ የሚያነሳሱ ድርጊቶች አልተስተዋሉም።ይልቅስ የስፖርታዊ ጨዋናት ጉድለቱ ጨዋታው ከመጀመሩ ቀድሞ የተከሰተ እንደመሆኑ ሌላ የግጭት መነሾ ተስትውላል። ከጨዋታው መጀመር 25 ደቂቃ ቀድሞ በደጋፊዎች መካከል የተካሄደው አምባጓሮም በርካታ የስፖርት ቤተሰቡን አባላት ለጉዳት ዳርጓል።ክስስቱም ጨዋታውን ለመታዳም ወደ ሜዳ የገቡ ደጋፊዎች ስሜት ክፉኛ አሳዝኗል፣አንገት አስደፍቷል።\nአስር ሰዓት ላይ መጀመር የነበረበት ጨዋታ እስከ ምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ድረስ ቢጠበቅም የኋላ ኋላ በተለይ ሃዋሳ ከተማዋዎች ጨዋታውን ለማካሄድ ባለመፈለጋቸው ሳይካሄድ ቀርቷል።ከብጥብጡ በኋላ ለክስተቱ ዋነኛ ምክንያት ሆኖ የቀረበው፤ በእለቱ ለእንግዳ ደጋፊዎች የተዘጋጀው የመቀመጫ ስፈራ አናሳ ሆኖ መቅረቡ ነው የተባለ ሲሆን፤ይህ ግን ብቻውን ለክስተቱ አሳማኝና በቂ ምክንያት ነበር ብሎ ለመናገር አያስደፍርም። ምክንያቱም የቦታ ጥያቄ ከሆነም በውይይት መፍታት ሲቻል ድንጋይ የሚያወራውር አንዳችም ምክንያት ይኖራል ተበሎ አይታሰብም።\nምንም እንኳን በእለቱ የግጭቱ ቀስቃሽ የሆኑ ደጋፊዎችን በውል መለየት ቢያስችግርና ቅድሚያ ጥፋተኛ የነበረው ማነው የሚለውን አጣርቶ ውሳኔ የሚያሳልፈው የሊግ ኮሚቴው በእለቱ በስታዲየሙ አንድ አቅጣጫ የተስተዋለው ግጭትና በሜዳው ክልል የነበረው ድብድብ በእጅጉ የሚያሳፍ፤ የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግም ስርዓቱን የሚያስጠብቅለት እንደሌለ የሚመሰክር ሆኖ ታይቷል።ከሁሉም በላይ በእንግዳ ክለብ ደጋፊዎች በአግባቡ መለየትና ከአደጋ መከላከል የማያስችል አጥር መኖሩም ጉዳቱን ከባድ አድርጎታል።በተለይ የድንጋይ ውርውራውን ተከትሎ ሸሽተው ወደ ሜዳው ክልል በገቡ የሃዋሳ ደጋፊዎችና በቅዱስ ጊዮርጊስ ስትዋርትቶች መካከል የተፈጠረው ግብ ግብ እጅጉን የሚያሳዝን ሆኖ ታይታል።ይሁንና ስታዲየሙን ከአፍ እስከ ገደፉ የሞሉት የፈረሰኞቹ ደጋፊዎች ከምንም በላይ ለስፖርታዊ ጨዋነት በመገዛት ወደ ፀብ አለመመራትና ሜዳ ወደነበሩት የሃዋሳ ደጋፊዎች አለመግባታቸውም በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አሰጥቷቸዋል።\nየስታድየሙን ፀጥታ ለማስከበር የሚመደቡ የፖሊስ ኃይሎች ቀደም ሲል ከነበረው ታሪክ ጋር ሲነፃፃር ችግሮችን በውይይት ከመፍታት ይልቅ ዱላን አማራጭ አድርገው አለመታየታቸው በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አሰጥቷቸዋል።\nበአጠቃላይ አንድ እርምጃ ፈቀቅ ማለት በተሳነው እግር ኳሳችን መሰል ክስተቶች መመልከት የሚቆመው እንዲሁም ሊጉን ስነስርዓት የማስጠበቅ ኃላፊነት ያለባቸው የስፖርት ቤተሰቦች ይህኑ ተግባራቸውን በአግባቡ የሚወጡት መቼ እንደሆን ለመረዳት አዳጋች ሆኗል።ከሁሉም በላይ በቅዱስ ጊዮርጊስና በሃዋሳ ከተማ መካከል ሊካሄድ ከነበረው ጨዋታ ቀድሞ የተከሰተው የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ግን ሊጉ ዘንድሮም ስርዓቱን የሚያስከብርለት ማጣቱን አሳይቷል።የሊጉን ስነስርዓት ለማስጠበቅ ከስፖርት ቤተሰቡም በላይ ከባድ ኃላፊነት ያለበት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተለይም ጠንካራ ህግጋትን በማስተላለፍ ረገድ ከባድ የቤት ስራ እንዳለበት አመላክቷል።\nይህን መሰሉ የስታድየም ብጥብጥና ሁከት በጊዜ መፍትሄ ካልተበጀለት፤ ነገሮች ፈራቸውን ሳይለቁ አስቀድሞ ነገሮችን ማስተካከልና መስመር ማስያዝ ካልተቻለ ከዚህም በከፋ ሁኔታ ወደ መቀመቅ መውረዳችን ሳይታለም የተፈታ ይሆናል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 9/2011ታምራት ተስፋዬ", "passage_id": "a584f5aadc30450c16fe4134c39a5306" } ]
c9877fb05e3b1eacb4b3fa18da1f9983
2a7cf8fc16f8ee5a8efc81cc955ff885
ለአፍሪካ እግር ኳስ ፈተና ድጎማ ዘላቂ መፍትሄ ያመጣ ይሆን?
በመላው ዓለም ከ210 ሀገራት በላይ የተዛመተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የዓለምን የስፖርት እንቅስቃሴ በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ከቶታል። በወረርሽኙ ሳቢያ ትልልቅ የስፖርት ውድድሮች በመራዘማቸው፣ በመሰረዛቸው እና በመስተጓጐላቸው ኢንዱስትሪውን ከፍተኛ ገቢ እንደሚያሳጣው የተለያዩ ትንበያዎች አመልክተዋል። የስፖርት ኢንዱስትሪውን በስፖንሰርሺፕ የሚደግፉ ትልልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የበጀት ቀውስ ውስጥ መግባታቸው፣ ከትኬት ሽያጭ ከማርኬቲንግና ከተለያዩ ንግዶች የሚገኙ ገቢዎች መቆማቸው ሁሉንም ስፖርት ጎድቷቸዋል፡፡ በተለይ የእግር ኳስ ስፖርት ከፍተኛ ድርሻ የሚይዝ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል። በዚህ ዓመት የእግር ኳሱ ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል ተብሎ ሲጠበቅ ከተላላፊው ቫይረስ ጋር በተያያዘ ገቢው በእጅጉ እያሽቆለቆለ ይገኛል። የአብዛኛዎቹ የእግር ኳስ ክለቦች ዋነኛ ገቢያቸውን የሚያገኙት ከሶስት ምንጮች ሲሆን፤ ይኸውም ከመገናኛ ብዙሃን የስርጭት መብት፣ ከስፖንሰርና ማስታወቂያዎች እንዲሁም በጨዋታ ወቅት ከስታዲየም የትኬት ሽያጭ እንደሆነ የወርልድ ኢኮኖሚ ፎረም መረጃዎች ያመላክታሉ።10 በሚደርሱ ሊጎች ያለው ቁጥራዊ መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነም ክለቦቹ ከሚዲያ መብት ብቻ ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያገኛሉ። ይህም ከአጠቃላይ ገቢያቸው 60 ከመቶ ይሸፍናል። በወረርሽኙ ምክንያት የውድድሮች መቋረጥን ተከትሎ ክለቦች ከእነዚህ ምንጮች የሚያስገቡት ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን ያመላክታል። ዴይሊሜይል በዚሁ ዙሪያ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን እንደማሳያ በመጥቀስ ያወጣው ይሄንኑ ያጠናክራል። የዓለማችን እጅግ ተወዳጅ ከሆኑ ሊጎች በግንባር ቀደምነት የሚጠቀሰው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በወረርሽኙ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳቱን በዘገባው ጠቅሷል። ፕሪምየር ሊጉ ባለፈው ዓመት አዲስ በገባው (ለሶስት ዓመታት) ኮንትራት 12 ቢሊዮን ዶላር ከሚዲያ መብት ብቻ ለመሰብሰብ አቅዶ ነበር። እግር ኳሱ አሁን ካለው ቁመና አኳያ እቅዱን ማሳካት የሚቻል አይሆንም ሲል ዘገባው አትቷል። ውድድሩ ሁለት ወራትን እንኳን ሳያስቆጥር ክለቦቹ ከ60 እስከ 150 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ማስተናገዳቸውን እያስታወቁ ይገኛሉ። በመሆኑም ከቴሌቪዥን መብት ከሚገኝ ገቢ ብቻ እያንዳንዱ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ክለብ 750 ሚሊዮን ፓውንድ ያጣል። ስለዚህ ፕሪሚየር ሊጉ በዚህ ምስቅል ቅል ውስጥ ሆኖ ለማግኘት ያቀደውን ገቢ ማሳካት እንደማይችል በመግለጽ ፤ የኮቪድ -19 ወረርሽኝ የእግር ኳሱን ኢንዱስትሪ ለከፍተኛ የፋይናንስ ቀውስ የዳረገው መሆኑን በዘገባው አትቷል። የእግር ኳስ ጨዋታዎችና መሰል እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ መደረጉን ተከትሎ እንደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁሉ በሁሉም ሀገራት የሊግ ውድድሮች ላይ መጠኑ ይለያይ እንጂ በፋይናንስ ቀውሱ የተጎበኙ መሆናቸው መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ። በተለይ በአህጉር አፍሪካ የሚገኙት ክለቦችና ብሄራዊ ፌዴሬሽኖችን በከፍተኛ ደረጃ እንዳቃወሳቸው ተነግሯል። የአፍሪካ ሀገራት ወረርሽኙን ለመከላከል የእንቅስቃሴ እግዳ መጣላቸውን ተከትሎ ኢኮኖሚያዊ መቃወስ ውስጥ አስገብቷቸዋል። የኢኮኖሚው መቃወስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የክለቦች ቀጣይ ህልውና አስጊ ደረጃ የሚያደርስ ይሆናል። በዓለም አቀፍ ደረጃ አንቱ የተባሉ የእግር ኳስ ተንታኞች «የኮቪድ -19 ወረርሽኝ የዓለም እግር ኳስን በተለይ የአፍሪካ እግር ኳስን ከባድ ፈተና ይገጥመዋል» የሚሉ መላምቶችን እያስቀመጡ ይገኛሉ። የአህጉሪቱ እግር ኳስ በተለያዩ ችግሮች ተተብትቦ «የእድገት ውስንነት በሽታ» ሰለባ መሆኑን ያነሳሉ። የዓለም ፈተና የሆነው ኮቪድ-19 የወለዳቸው ችግሮች ተደምረውበታል። ይህም «በእንቅርት ላይ ጆሮ… » ያደርግበታል ። መጪው ጊዜ በተለይ ለአህጉር አፍሪካ እግር ኳስ ህልውና እጅጉን ፈታኝ እንደሚሆን መላምቶች እየተሰጡ ይገኛሉ። ለዓለም እግር ኳስ እድገትና ድምቀት እርሾ የሆነችውን አፍሪካ የእግር ኳኳ ህልውና ከገባበት አጣብቂኝ እንዲወጣ ድጎማ ማድረግ እንደሚገባ ምክረ ሃሳቦች ቀርበዋል። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የቀረቡትን ምክረ ሃሳቦች መሰረት ያደረገ ተግባር ሊፈጽም መሆኑ በሳምንቱ መጨረሻ ይፋ አድርጓል። ካፍ ዓለምን በአንድ የጭንቀት ቀረጢት ውስጥ የከተተው የኮቪድ -19 ወረርሽኝ በእግር ኳሱ ላይ ያሳደረውን ጫና ከፍትኛ መሆኑን በመረዳት የበኩሉን ድጋፍ ለማድረግ ውጥን መያዙን አስታውቋል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገሮች ዓመታዊ የእግር ኳስ መርሐ ግብሮቻቸውን በዓለም አቀፉ ኮቪድ 19 ወረርሽን ምክንያት በሰረዙበት በዚህ ወቅት፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ለአባል አገሮቹ የገንዘብ ድጎማ ሊያደርግ መሆኑ ታወቀ፡፡ ኮንፌዴሬሽኑ ለእያንዳንዱ አገር 200 ሺሕ ዶላር ሊሰጥ ማቀዱ ነው ያስታወቀው ፡፡የ54 አገሮች ብሔራዊ ፌዴሬሽኖችን የሚያስተዳድረው ካፍ፣ በየዓመቱ በመደበኛነት ከሚያከናውናቸው ውድድሮች መካከል የአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግና የአፍሪካ ክለቦች ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ ይሁንና ሁሉም በወረርሽኙ ምክንያት ውድድሮቹ እንዲሰረዙ አድርጓል፣ የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን በሚመለከት አሁን ላይ ምንም ያለው ነገር የለም፡፡ የዘንድሮን የውድድር ዕጣ ፈንታ በሚመለከት ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ስለመደረጉ ወይም ስለመሰረዙ ውሳኔ ላይ ባይደርሱም፣ 16 አገሮች መደበኛ ውድድሮቻቸውን መሰረዛቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያ የዓመቱን ውድድር ከመሰረዟም በላይ በሚቀጥለው ዓመት በአፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግና የክለቦች ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውክልና እንደማይኖራት ለጊዜውም ቢሆን ይፋ አድርጋለች፡፡ የተቀሩት 15 አገሮች ደግሞ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ውድድሩ እስከተቋረጠበት ድረስ በደረጃ ሰንጠረዡ በተቀመጠላቸው ውጤት መሠረት የሚያሳትፏቸውን ክለቦች በማሳወቅ ውድድሮቻቸውን መሰረዛቸው ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡ እነዚህም ቡርኪና ፋሶ፣ ጋምቢያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሞሪሸስ፣ አንጎላ፣ ኬቨርዴ፣ ጊኒ፣ ቶጎ፣ ዴሞክራቲክ ኮንጎ፣ ኬንያ፣ ካሜሮን፣ ሩዋንዳ፣ ኒጀር፣ ኮንጎ ብራዛቪልና ላይቤሪያ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ አህጉራዊው ተቋም እንደ አውሮፓና መሰል አህጉሮች በእሱ ሥር የሚያስተዳድረውን እግር ኳስ ወደ ገንዘብ በመለወጡ ረገድ ክፍተኛ ክፍተት ያለበት መሆኑ ተጠቅሷል ፡፡ ይሁንና ካፍ በየዓመቱ ለአባል አገሮቹ የሚሰጠውን የገንዘብ ድጎማ ሳያቋርጥ ለመስጠት ማረጋገጫ መስጠቱን የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የካፍን ድረ ገጽ ዋቢ በማድረግ ዘግበዋል፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ለአባል ሀገራቱ የ200 ሺህ ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርገው ሁሉ፤ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) የ150 ሺህ ዶላር ድጋፍ አደርጋለው ማለቱን ይታወሳል። ከዓለም እግር ኳስ ራስ የሆነው ተቋም ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑ፤ ከሰሞኑ ደግሞ የአህጉሪቱ እግር ኳስ የበላይ ጠባቂ ካፍ ለአባል ሀገራቱ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል። የአፍሪካ እግር ኳስ በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት መጪው ጊዜ ፈታኝ እንደመሆኑ፤ ፈተናውን በድጎማ ይታለፍ ይሆን? አዲስ ዘመን ግንቦት 25/2012ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=33579
[ { "passage": "ገንዘቡ ያስፈልጋታል የተባለው ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት መሆኑ ተገልጿል።\n\n የተቋሙ ዳሬክተር ክርስታሊና ጆርጂቫ እንዳሉት ዓለም አፍሪካ ከገባችበት ቀውስ እንድታገግም ለመደገፍ ዓለም ብዙ መስራት አለበት ብለዋል።\n\nበአፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ እንዲሁም የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከሌሎች አህጉራት ያነሰ ነው፤ ነገር ግን የዓለም ባንክ በወረርሽኙ ሳቢያ ተጨማሪ 43 ሚሊዮን የሚሆኑ አፍሪካዊያን ለከፋ ድህነት የመጋለጥ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ብሏል።\n\nበወረርሽኙ ሳቢያ የሥራ እድሎች በመታጠፋቸው እና የቤተሰብ ገቢ በ12 በመቶ በመቀነሱ የደረሰው የኢኮኖሚ ተፅእኖ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአፍሪካ እየታየ የነበረውን ጠንካራ እድገት እየቀለበሰው መሆኑን የገንዘብ ተቋሙ ዳሬክተር በበይነ መረብ በነበራቸው የተቋሙ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።\n\nችግሩንም ለማቃለል በርካታ አፍሪካ አገራት መንግሥታት ከልማት እቅዳቸው 2.5 በመቶ ያስወጣቸውን ፖሊሲዎች አስተዋውቀዋል። \n\nአይኤም ኤፍ የአፍሪካ አገራት ከደረሰባቸው ተፅዕኖ እንዲያገግሙ 26 ቢሊዮን ዶላር የለገሰ ቢሆንም፤ የግል አበዳሪዎች እና በሌሎች አገራት ድጋፍ ቢኖርም፤ አሁንም ግን ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እጥረት አለ ብለዋል።\n\n\"አንዳንድ አገራት ከብድር አግልግሎትና ተጨማሪ የማህበራዊና ጤና ወጪዎች መካከል እንዲመርጡ የሚያስገድዳቸውን የዕዳ ጫናዎች እየተጋፈጡ ነው\" ብለዋል ኃላፊዋ።\n\nይህንን ችግር ለመፍታትም ተበዳሪዎች ብድራቸውን የሚከፍሉበት ጊዜ እንዲራዘም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ ለብድር የሚሆን ተጨማሪ ገንዘብ ማቅረብ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።\n\nበአፍሪካ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ ወደ 37 ሺህ የሚጠጉት ሕይወታቸውን አልፏል።\n\n ", "passage_id": "e508925e606195c8062e80e58091075b" }, { "passage": "ብርሃን ፈይሳ በኢትዮጵያ ስፖርት፤ ማህበራትና ክለቦች ከመንግስት እገዛ አለመላቀቃቸውና ሃብት በማመንጨት ተግባር ላይ ተሳታፊ አለመሆናቸው እንደ ድክመት ይነሳል።የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአጭር ጊዜ ውስጥ ፕሪሚየር ሊጉ በአክሲዮን ማህበር እንዲተዳደር በማድረግና ከጥገኝነት እንዲላቀቅ የማድረጉ ጅማሬም መልካም የሚባል ነው።ስፖርቱን በበላይነት በሚመራው ብሄራዊ የስፖርት ምክር ቤትም የፌዴሬሽኑ ተግባር ለሌሎች ስፖርት ማህበራትም አርአያነት ያለው መሆኑ በሪፖርት ቀርቧል።ይሁን እንጂ ስፖርቱ በገቢ ረገድ ችግር እየደረሰበት መሆኑ ነው ፌዴሬሽኑ የጠቆመው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ\nፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ\nጂራ በመድረኩ ላይ\n፤ እግር ኳሱ\nበስፖንሰር ምክንያት እየደረሰበት\nያለውን ችግርና ችግሩ\nየተፈጠረበትን ምክንያት መንግስት\nማጤን ይኖርበታል ሲሉ\nገልጸዋል።ይኸውም በህዝብ ተወካዮች\nምክር ቤት የወጣውን\nየአልኮል መጠጦች ማስታወቂያ\nበህዝብ መገናኛ ብዙሃን\nእንዳይተላለፍና በስታዲየሞች \n ውስጥ እንዳይሰቀል የሚከለክለው አዋጅን በቀጥታ እግር ኳሱን የጎዳ መሆኑን ይጠቁማሉ።በእርግጥ መንግስት ዜጎቹን የመጠበቅ ኃላፊነት ይኑርበት እንጂ መታየት ያለባቸው ጉዳዮች ሳይመዘኑ ታልፈዋል የሚሉት አቶ ኢሳያስ፣ ‹‹ጉዳት አድርሶብናልና ቢፈተሽ›› ሲሉ ጥያቄያቸውን ለብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤቱ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ፌዴሬሽኑ ባለፈው ዓመት ከዋሊያ ቢራ ጋር 56 ሚሊየን ብር የስፖንሰር ስምምነት አድርጎ ነበር፤ ነገር ግን ይህ አዋጅ በወጣ ማግስት ስምምነቱ ተቋርጧል።በዓለም ላይ በሃብቱ ቀዳሚ የሆነው የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ በሃይንከን ቢራ ስፖንሰር እንደሚደረግ ያነሱት ፕሬዚዳንቱ፤ ሌሎች ሊጎችም በመጠጥ አምራች ተቋማት ስፖንሰር የሚደረጉበት አሰራር በዓለም ላይ የተለመደ መሆኑን ጠቁመዋል።ፌዴሬሽኑ በዚህ ረገድ ያለውን ሃሳብ በጽሁፍ ለመንግስት ማቅረቡንና አዋጁ በፌዴሬሽኑ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ በድጋሚ እንዲፈተሽ ካልሆነም መንግስት ብሄራዊ ቡድኖችን እንዲደግፍ ጠይቀዋል። እንደ ፕሬዚዳንቱ ማብራሪያ፤\nችግር ሲያጋጥም እርዳታ\nከማድረግ ባለፈ በኢፌዴሪ\nስፖርት ኮሚሽን ስር\nካሉ የስፖርት ማህበራት\nመካከል ምንም ዓይነት\nድጋፍ ከማይደረግላቸው መካከል\nአንዱ የኢትዮጵያ እግር\nኳስ ፌዴሬሽን ነው።ፌዴሬሽኑ\nበስሩ ያሉትን ሰባት\nብሄራዊ ቡድኖችን (በሁለቱም\nጾታ በተለያየ የዕድሜ ክልል እና ዋናውን ቡድን ጨምሮ) በራሱ ነው የሚያስተዳድራቸው።ካሜሩን ለምታዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን(ዋሊያዎቹ) ከማዳጋስካር፣ ኒጀር እና ኮት ዲቭዋር ጋር ተደልድሏል።በመሆኑም ቡድኑ የጉዞ፣ የሆቴልና ሌሎች በርካታ ወጪዎችን ማድረጉ የግድ ነው።በተመሳሳይ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከዚምቧቡዌ እና ከጋና ጋር ባላት ድልድል ሌሎች ወጪዎችን ማድረግም ይጠይቃል።ሌሎቹ ብሄራዊ ቡድኖችም ለሚኖሯቸው አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ተጨማሪ ወጪዎች ይጠበቃሉ።መንግስት ይህንን በባለቤትነት ወስዶ ብሄራዊ ቡድኖችን ሊያግዝ ይገባዋል። ብሄራዊ ቡድን ሃገር የምትወከልበት መሆኑ መንግስት ሊደግፈው ይገባሉ ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚካፈለው የአትሌቲክስ ቡድን በመንግስት እገዛ እየተደረገለት መሆኑን በማሳያነት ይጠቅሳሉ።ይህ የስፖርት ማህበራት ድክመት ደግሞ ብሄራዊ ቡድኑንም ደካማ አድርጎታል፤ በመሆኑም መንግስት ድጋፍ ሊያደርግለት ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል። አብዛኛዎቹ የእግር ኳስ ክለቦች የሚተዳደሩት በመንግስት እንደመሆኑ፤ ፌዴሬሽኑ ደግሞ ይህ መንግስት የሚመድበው ከፍተኛ ገንዘብ በዚህ መቀጠል የለበትም የሚል ሃሳብ እንደሌለው ገልጸዋል።ክለቦችን ወደ ግል ተቋም ለመመለስ በማቀድ ለሶስት ዓመታት ፕሮጀክት በመያዝ እየተንቀሳቀሱ ሲሆን፤ የመጀመሪያዎቹን ስድስት ወራት ከአንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ጋር በመሆን በትምህርት ቀጣዮቹን ጊዜያት ደግሞ 30 ከመቶ የሚሆኑትን ክለቦች 30 በመቶ መንግስት 40 በመቶ ህብረተሰቡ እንዲይዛቸው የግል ባለሃብት ተሳትፎ በማከል ሙሉ ለሙሉ ከመንግስት ለማላቀቅ ታቅዷል።በመሆኑም ምክር ቤቱ አንድ አቅጣጫ መስጠት እንደሚገባው አሳስበዋል፤ ይህ ካልሆነ ግን መንግስት ድጋፉን ቢያቋርጥ አስቸጋሪ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ጠቁመዋል። ክልሎችም በስራቸው የሚያስተዳድሯቸው ክለቦች እንደመኖራቸው ለዚህ ስራ ተባባሪና በሚወጣው ደንብም ለመመራት እገዛ እንዲያደርጉም ፕሬዚዳንቱ ጠይቀዋል። በመድረኩ ላይ ሃሳባቸውን ያንጸባረቁት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ፤ ባለፉት ዓመታት በሁለቱም ጾታዎች በዋናው ብሄራዊ ቡድንም ሆነ በእድሜ በተቀመጡት ቡድኖች የተደረጉት እንቅስቃሴዎች ደካማና አንገት የሚያስደፉ እንደሆኑ መታየታቸውን ይጠቁማሉ።ብሄራዊ ቡድኖች ሲያሸንፉ በተለያዩ የሃገሪቷ ከተሞች ላይ በህዝቡ ዘንድ የሚፈጠረው ተነሳሽነት ታይቷል። ሰብሳቢው አንድ ያልታተመ ጥናትን ዋቢ በማድረግ በ2011/12 ዓ.ም በስፖርቱ ወደ 2ነጥብ2 ቢሊየን ብር ወጥቷል፤ ነገር ግን ውጤት አልመጣም ይላሉ።በመሆኑም እግር ኳስ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት በዚህ መንገድ ይቀጥላል ወይስ ክለቦች ወደ ግል እንዲዘዋወሩና በገንዘብ ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ ታቅዷል የሚለው መመልከት አስፈላጊ መሆኑንም ነው ሰብሳቢው ያመላከቱት። በእቅዱ ላይ ክለቦች ከመንግስት ተረጂነት ሊወጡ ይገባል በሚለው ላይ ፖሊሲ አውጥቶ ወደ ግል ይዞታነት የሚዘዋወሩበትን ስትራቴጂ መንደፍ አስፈላጊ ሲሆን፤ ተግባራዊነቱም ሊመዘን ይገባል። በዚህ ወቅት ከመንግስት ጥቂት መቋቋሚያ ቢያገኙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ራሳቸውን የሚችሉና ከፍተኛ ደጋፊ ያላቸው ክለቦች መኖራቸውንም ሰብሳቢው ይጠቁማሉ።በመሆኑም ይህ ሊታሰብበትና በብሄራዊ የስፖርት ምክር ቤቱ አቅጣጫ ሊሰጠው የሚገባ ነው ይላሉ። የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር፤ በ1990 ዓ.ም የወጣው የስፖርት ፖሊሲ ከስፖርት ማህበራትና ክለቦች አደረጃጀት ጋር በተያያዘ ቀስ በቀስ ከመንግስት ድጎማ መውጣት እንዳለባቸው የሚያመላክት መሆኑን ይጠቅሳሉ።ይህንን ተከትሎ የተከናወኑ ስራዎች ቢኖሩም አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከጥቂቶቹ በቀር የተቀሩት በመንግስት የሚተዳደሩ ናቸው። ዓለም አቀፍ ደረጃቸው ሲፈተሽም፤ ከስያሜ፣ ከመዝሙር፣ ከአርማ፣… ጋር የተያያዙ ጉዳዮች መስተካከል ይገባቸዋል። ብሄራዊ ምክር ቤቱም ከዚህ ቀደም አቅጣጫ ቢያስቀምጥም ብዙም አልተሄደበትም።ክለቦቹም ከመንግስት ድጎማ በመውጣት ራሳቸውን እንዲችሉ ስልቶችን መቀየስ ይገባቸዋል።ለአብነት ያህልም የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎቹን ወደ አክሲዮን የቀየረበት መንገድ ገቢውን ከማሳደግ ጎን ለጎን የታዳጊ ቡድኖችን የያዘበት ጅማሮ የሚበረታታ ነው፡፡ ፌዴሬሽኖች በገቢ ራሳቸውን እንዲችሉ ከማድረግ ባሻገር መንግስት በስሩ ያሉትን ከ30 በላይ ማህበራት ድጋፍ የማድረግ አቅሙ ውስን ነው።በመሆኑም ክለቦችና ስፖርት ማህበራት በራሳቸው ከሚያደርጉት ባሻገር ኮሚሽኑም ጥናት ላይ ተመስርቶ በቀጣይ የሚሄድበት መሆኑን ጠቁመዋል።  ", "passage_id": "36f13b967202258e302af2bc40e2da9c" }, { "passage": "የአፍሪካ ዋንጫየአፍሪካ ዋንጫ በየሁለት ዓመቱ በ24 ሃገራት መካከል ይካሄዳል፡፡ ይህ ውሳኔ በአፍሪካ ካሉት ጥራት ያላቸው ብሔራዊ ቡድኖች እጥረት አንጻር የውድድሩን ጥራት የሚገድል እንደሆነ ብዙዎች ይከራከሩበታል፡፡ በቀላሉ ከማጣርያ የማለፍን እድል የሚፈጥር በመሆኑም አጓጊ የማጣርያ ጨዋታዎችን ዋጋ ቢስ እንደሚያደርጋቸው እርግጥ ነው፡፡በሌላ ጎኑ ደግሞ የተሳታፊ ቁጥሩ መጨመር ለውድድሩ ባይተዋር ሆነው የቆዩ ፣ ከአመታት አንድ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ የሚሳተፉ ቡድኖችን ተስፋ ያለመለመ ውሳኔ ሆኗል፡፡ ለአብነትም የምድብ ማጣርያን አልፋ ወደ አፍሪካ ዋንጫ አምርታ የማታውቀው ኢትዮጵያ በውሳኔው ተጠቃሚ ሊሆኑ ከሚችሉ ሀገራት አንዷ ናት፡፡ በጥቂት አጋጣሚዎች የምድብ ማጣርያዋን በሁለተኝነት ማጠናቀቅ የቻለችው ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ በሚደረጉ የአፍሪካ ዋንጫዎች ላይ በመደበኝነት ለመካፈል ከዚህ ቀደም ከነበረው ያነሰ ፈተና የሚገጥማት ቢሆንም የብሔራዊ ቡድን የጥንካሬ ደረጃዋን ማሻሻል ይጠበቅባታል፡፡በ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ማርጣያ በምድብ 6 የተደለደለችው ኢትዮጵያ በጋና 5-0 ተሸንፋ የምድቡ ግርጌ ላይ የምትገኝ ሲሆን ቢያንስ በሁለተኝነት ከሚያልፉ ሀገራት መካከል ሆና አፍሪካ ዋንጫውን ለመቀላቀል ከሴራሊዮን እና ኬንያ ነጥቦች መሰብሰብ ይጠበቅባታል፡፡ከላይ ቻርቱ እንደሚያመለክተው ኢትዮጵያ ለመካፈል ከበቃችባቸው ውድድሮች መካከል በአዘጋጅነቷ (3) ፣ ያለፈው ውድድር ቻምፒዮን በመሆኗ (1) ማጣርያ ባለመኖሩ (2) በአጠቃላይ 6 ጊዜ ካለ ማጣርያ ነው ያለፈችው፡፡ በ1966 በኬንያ ብትሸነፍም ኬንያ ከውድድሩ ራሷን በማግለሏ ወደ ውድድሩ አምርታለች፡፡ በ1970 (ሱዳን) ፣ በ1983 (ሊቢያ) እና በ2013 (ደቡብ አፍሪካ) በተስተናገዱት ጨዋታዎች ደግሞ በጥሎ ማለፍ መልክ ቢበዛ ሁለት የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ብቻ አድርጋ ወደ አፍሪካ ዋንጫ አልፋለች፡፡ ከ1992 የአፍሪካ ዋንጫ ጀምሮ ተግባራዊ በተደረገው የምድብ ማጣርያ ኢትዮጵያ በ10 አጋጣሚዎች የምድብ ማጣርያ ብትቀላቀልም በአንዳቸውም ወደ አፍሪካ ዋንጫው መግባት አለመቻሏን ስንመለከት የተሳታፊዎች ቁጥርን ወደ 24 የማሳደጉ ውሳኔ ለኢትዮጵያ መልካም ነገር ይዞ ሊመጣ ይችላል፡፡በዘንድሮው የውድድር ዘመን ከ8 ወደ 16 ክለቦች በተቀየረው የአፍሪካ የክለቦች የምድብ ውድድር አሰራር ቅዱስ ጊዮርጊስ በኢትዮጵያ ክለቦች ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ምድብ ድልድሉ እንዲገባ እንደረዳው ሁሉ የአፍሪካ እግርኳስ ላይ በጥንካሬያቸው ከሚጠቀሱ ሀገራት ጋር የሚደለደሉ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራት በሁለተኝነት ወደ አፍሪካ ዋንጫው የመሻገር እድላቸው ይሰፋል፡፡ከተስፋ ባሻገር…በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በተለይም በፌዴሬሽኑ አመራር እና በብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ላይ የተቀመጡ አሰልጣኞች ካለ ብዙ ጥረት የሚገኙ ድሎችን እንደትልቅ ስኬት የመቁጠር ባህል ይታያል፡፡ የሴካፋ ውድድሮችን ማሸነፍ ፣ የቻን ውድድር ላይ መካፈል እና አንድ ወይም በሁለት የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ብቻ ለአፍሪካ ዋንጫው መካፈል እንደ ግዙፍ ስኬት ተጋንኖ በሚወራባት ሀገር በቀጣይ አፍሪካ ዋንጫዎች ላይ በቀላል ፈተና መካፈል መቻል እንደ እድገት መለኪያ በመቁጠር ወደተሳሳተ መንገድ እንዳይመራን ያሰጋል፡፡ለዚህ እንደ ማሳያ የሚሆነን በ2013 የአፍሪካ ዋንጫ ሁለት የደርሶ መልስ ተጋጣሚዎችን ብቻ አልፈን ወደ አፍሪካ ዋንጫው መግባታችን የእግርኳሳችን እድገት ነጸብራቅ ሆኖ መታየቱና ራሳችንን ከታላላቅ የአፍሪካ እግርኳስ ሀገራት ተርታ ያሰለፍን ያህል ተሰምቶን ነበር፡፡ ነገር ግን እግርኳሳችን ከደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ የወረደበት ቁልቁለት ሁላችንም የተመለከትነው ነው፡፡የተዘበራረቀ ካሌንደር ለማስተካከል በር የሚከፍተው የውድድር ወቅቶች ለውጥየአፍሪካ ዋንጫው የሚካሄድበት ወቅት ከጥር ወር ወደ ሰኔ/ሐምሌ የተዛወረ ሲሆን የክለቦች ውድድር (ቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ) መጀመርያ ወቅት ከጥር (ጃንወሪ) ወደ ኦገስት (ነሀሴ) ተሸጋግሯል፡፡ይህ ለውጥ ከአውሮፓውያን የውድድር ዘመን ፎርማት ጋር ተመሳሳይ በሆነ አካሄድ ለምትጠቀመው ኢትዮጵያ መልካም ነገሮችን ይዞ ሊመጣ የሚችል ነው፡፡ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ ሀገራት ቁጥር ወደ 24 መለጠጡን ተከትሎ ከሌላው ጊዜ በተሻለ የማለፍ እድል የሚሰጣት ኢትዮጵያ ወደ ውድድሩ የምታልፍ ከሆነ በአዲሱ አሰራር የአፍሪካ ዋንጫ ጁን (ሰኔ) ላይ የሊግ ውድድሯን ካጠናቀቀች በኋላ ለማካሄድ ያግዛታል፡፡በ2013 የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ኢትዮጵያ መሳተፏን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዙር ሳይጠናቀቅ ተጫዋቾች ወደ አፍሪካ ዋንጫው በመጓዛቸው ውድድሩ ምንያህል ተዘበራርቆ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ የጥሎ ማለፉ ውድድር እንኳን የተጠናቀቀው በቀጣዩ አመት እንደነበር ይታወሳል፡፡ይህ የአፍሪካ ዋንጫ ለውጥ ሊጉን ወጥ በሆነ የውድደር ወቅቶች ለማስኬድ እንዲያስገድደን በር ይከፍታል፡፡ ምክንያቱም የአፍሪካ ዋንጫው ወደ ሰኔ ወር በመዛወሩ ሊጋችንን ቢያንስ ግንቦት ወር ላይ እንዲጠናቀቅ የሚያደርግ አሰራር እንድንከተል ያደርገናል፡፡የአፍሪካ የክለቦች ውድድሮች ከኢትዮጵያ ጋር በሚመሳሰል የውድድር ወቅት እንዲካሄድ መወሰኑ የሀገራችንን እግርኳስ ጊዜ አጠቃቀም እንዲስተካከል የሚያስገድድ በመሆኑ በመልካም ጎኑ የሚነሳ ነው፡፡ከላይ በሰንጠረዡ እንደሚታየው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመናት የሚጀመርባቸው እና የሚጠናቀቅባቸው ወቅቶች ወጥ ያልሆኑ ናቸው፡፡ የአፍሪካ የክለብ ውድድሮች በኦገስት (ነሐሴ አጋማሽ) የሚጀምሩ በመሆኑ በውድድሩ የሚካፈሉ የኢትዮጵያ ክለቦች የግድ በነሀሴ ወር ወደ ውድድር መግባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዲስ የውድድር ዘመን መጀመርያ ወቅትም ከአፍሪካ ውድድር ጋር የተቀራረበ እና አብሮ የሚሄድ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ እንደ ከዚህ ቀደሙ በጥቅምት እና ህዳር ወራት የሚጀመር ከሆነ ግን የውድድሩ መጠናቀቂያ ወቅት ወደ ክረምት እየገፋ ስለሚሄድ በቀጣዩ አመት የአፍሪካ ውድድር ላይ ለሚካፈሉ ክለቦች በቂ እረፍት የማይሰጥ ይሆናል፡፡የአፍሪካ የክለቦች ውድድር ኦገስት (ነሀሴ አጋማሽ) ሲጀመር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአዲስ አመት መግቢያ ቀናት ላይ የሚጀመር ከሆነ ቢበዛ በሜይ (ግንቦት) ወር መጀመርያ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ ሰኔ ፣ ሐምሌ እና ነሐሴ ወራትን በእረፍት እና በቅድመ ውድድር ዘመን አሳልፈው ወደ ውድድር እንዲገቡ ያግዛቸዋል፡፡ ይህም በአፍሪካ ውድድር አስገዳጅነት ወደ ትክክለኛው መንገድ እንዲጓዙ በር የሚከፍት መልካም አጋጣሚ ይሆናል፡፡የወጣቶች እግርኳስ ውድድር ማጣርያዎችካፍ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት የአፍሪካ ከ17፣ 20 እና 23 ዓመት በታች ውድድሮች የሚደረጉ ማጣሪያዎች ልክ እንደቻን በዞን ተከፋፍሎ ይካሄዳል፡፡ ይህም እንደዋናው የአፍሪካ ዋንጫ ሁሉ በማጣርያ ወደ ውድድሩ ማለፍ ዳገት ለሆነባት ኢትዮጵያ መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ነው፡፡በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ እንደ ባህል የተለመደው ነገር ስለ ወጣቶች ትኩረት የሚሰጠው የወጣቶች ውድድሮች በሚኖሩበት ወቅት መሆኑ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በማጣርያው የወጣቶች እግርኳስ ላይ በተደጋጋሚ የበላይነታቸውን ባስመሰከሩ የምዕራብ አፍሪካ ቡድኖች ተሸንፋ በጊዜ የምትሰናበት በመሆኑ ወጣት ተጫዋቾቻችን በውድድሩ ላይ የመታየት ተስፋቸው የመነመነ ሆኖ ቆይቷል፡፡ በአዲሱ አሰራር በዞኗ ማጣርያዋን የምታደርገው ኢትዮጵያ የተሻለ የማለፍ እድል የምታገኝ በመሆኑ ለወጣት/ታዳጊ ቡድኖቻችን በተደጋጋሚ በአፍሪካ ውድድሮች ላይ ልምድ የማካበት አጋጣሚን ይፈጥራል፡፡በሰንጠረዡ ላይ እንደሚታየው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ወጣት ውድድሮች ላይ የመካፈል ልምድ የላትም፡፡ ከ17 አመት ውድድር ላይ ከተካፈለች 14 አመታት ሲቆጠሩ ከ20 አመት በታች ውድድር ላይ ለመጨረሻ ጊዜ የታየችው በ2001 (እኤአ) ራሷ ባስተናገደችበች ውድድር ላይ ነው፡፡ በመሆኑም አዲሱ የማጣርያ ስርአት ለኢትዮጵያ ነገሮችን ቀላል ሊያደርግላትና ለአፍሪካ ውድድሮች ልትበቃ ትችላለች፡፡ምናልባትም ማጣርያዎች በዞን የተከፈሉ መሆናቸው ለደካማው የምስራቅ አፍሪካ ዞን የሚሰጠው ኮታ ጥቂት ከሆነ ጠንካራ ፉክክር የሚጠብቃት ይሆናል፡፡", "passage_id": "cb7b6c32691b1aaf3f70243385d8719f" }, { "passage": "ካፍ በአመራር ደረጃ ለውጥ ካደረገ ወዲህ ለውጦች እንደሚኖሩ ይታመን ነበር፡፡ በተለይ አዲስ አበባ ላይ በተካሄደው የመጋቢቱ የካፍ ጠቅላላ ጉባኤ ኮንፌድሬሽኑን ለ29 ዓመታት የመሩትን ካሜሮናዊውን ኢሳ ሃያቱ እና ደጋፊ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላቶቻቸውን አሰናብቶ የ57 ዓመቱ ማዳጋስካራዊውን አህመድ አህመድን ተክቷል፡፡ ታዲያ የፊፋው ፕሬዝደንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ታማኝ ወዳጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አህመድ ከወዲሁ የሃያቱ አስተዳደር ሲመራባቸው የነበሩ አካሄዶቹን ወደ መሬት ለመቅበር መዘጋጀታቸው አጠራጣሪ አይደለም፡፡ ኢንፋቲኖም በአፍሪካ እግርኳስ ላይ ያላቸውን ተፅዕኖ አሁንም በማስቀጠል ላይ ይገኛሉ፡፡በካፍ የፕሬዝደንታዊ ምርጫ ላይ ኢንፋንቲኖ በዚህ ጉዳይ ፈፅሞ ባይስማሙም እጃቸው ረጅም መሆኑን አሳይተዋል፡፡ በተለይ ሃያቱ በኢንፋቲኖ ጣልቃ ገብነት መጋቢት ላይ በነበረው የካፍ ጠቅላላ ጉባኤ ምሬታቸውን አህመድ፣ የፊፋ ዋና ፃሃፊ ፋቱማ ሳሞራ እና ኢንፋንቲኖ ላይ ሲገልፁ ተስተውሏል፡፡ የ70 ዓመቱ ካሜሩናዊ የቀድሞ አትሌት በምርጫው ከተሸነፉም በኃላ ለሰላምታ እጃቸው የዘረጉት ፋቱማ ሳሞራን ከቁብ ሳይቆጥሯቸው ማለፋቸው ተከትሎ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆነው ቆይተዋል፡፡በስምፓዚየሙ የነተሱት አብዛኞቹ ሃሳቦች ወደ ትግበራ እንዲገቡ የተደረጉት ውሳኔዎች የአውሮፓውያን ጥቅም፣ ፍላጎት እና ተፅዕኖ ከማስጠበቅ አንፃር የተደረጉ ናቸው የሚሉ ወገኖች በርካታ ናቸው፡፡ለውጡ አዎንታዊ ብቻ ሳይሆን አሉታዊም መሆኑንም መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ለአብነት ያህል የተወሰኑትን ውሳኔዎች ደግመን ብንመረምር ‘ገቢን ከማሳደግ’ የሚለው ቃል ተደጋግሞ ይመጣል፡፡ ይህ የሚያመለክተው ካፍ የፋይናንስ አቅሙን ከማጠንከር አንፃር የወሰዳቸው እርምጃዎች እንደሆኑ ያመለክታል፡፡ የተወሰኑ ውሳኔዎች (በተለይ ስር ነቀል ለውጥ የተደረገባቸው) ያላቸውን አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅእኖ ከፋፍለን እንመልከት፡፡የአፍሪካ ዋንጫ የተሳታፊ ሃገራትን ቁጥር ከ16 ወደ 24 ማሳደግእንደአውሮፓዊያኑ የዘመን ቀመር በ1957 የአፍሪካ ዋንጫ ሲጀመር ሶስት ተሳታፊ (ግብፅ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን) ነበሩት፡፡ ከ1996 ወዲህ የታሳፊ ሃገራት ቁጥር ወደ 16 አድጓል፡፡ በ1996 ናይጄሪያ ራሷን ከውድድሩን በማግለሏ በ15 ሃገራት መካከል ሲካሄድ በ1998 ቡርኪናፋሶ ውድድሩን ስታስተናግድ 16 ሃገራት ለመጀመሪያ ግዜ ተካፍለዋል፡፡አዎንታዊ ጎን56 አባል ፌድሬሽኖች ባሉበት አህጉር 16 ቡድኖች በአፍሪካ ዋንጫው ይሳተፋሉ፡፡ ይህም በመቶኛ ሲቀመጥ 29% ነው፡፡ አሁን ላይ የቁጥር ጭመራውን ተከትሎ 43% ይደርሳል፡፡ የቁጥሩ መጨመር እውን መሆኑን ተከትሎ እምብዛም የመሳተፍ እድል ያላገኙ ሃገራትን እድል ያሰፋል፡፡ እንደኢትዮጵያ ያሉ በማጣሪያ ውድድሮች በደካማ ጉዞ ለሚዳክሩ ሃገራት የተሳታፊ ሃገራት ቁጥር መጨመር ጥሩ ዜና ይመስላል፡፡ የተሳታፊ ቁጥር ከተጨመረ በዛው የሚደረጉ ጨዋታዎቹ ብዛትም ይጨምራል፡፡ ይህ ደግሞ ከቴሌቪዥን መብት የሚገኘው ገቢ እንዲጨምር ያስችለዋል፡፡ ስለዚህም የተሳታፊ ሃገራት ቁጥር መጨመር አንድም ያላየናቸው የአፍሪካ ሃገራት በውድድሩ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ሲያስችል ከስፖንሰር እና ቴሌቪዥን መብቶችን የሚገኘውን ገቢ በእጅጉ ይጨምራል፡፡በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፈው የማያውቁ ሃገራት የመሳተፍ እድልን ማግኘቻቸው መልካም የሆነ ጎን አለው፡፡ በተለይ እንደኢትዮጵያ ያሉ ሃገራት ተጫዋቾቻቸው በትልቅ ደረጃ እንዲታዩ በር ከፋች ነው፡፡ በ2013 የአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈው ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች በውጭ ሃገር ሊጎች የመጫወት እድል ማግኘት የቻሉት እንደአፍሪካ ዋንጫ ባሉ ውድድሮች መሳተፍ በመቻላቸው ነው፡፡ይህ ብቻ ሳይሆን አሁን ባለው ተጨባጭ እውነታ አብዛኞቹ ከ2010 የአለም ዋንጫ አዘጋጅ ከነበረችው ደቡብ አፍሪካ እና ሰሜን አፍሪካ ሃገራት ውጪ ያሉ የአፍሪካ ሃገራት የ24 ሃገራት የአፍሪካ ዋንጫ የማስተናገድ አቅሙ ያላቸው አይመስልም፡፡ ቢሆንም በጣምራ የሚያዘጋጁ ሃገራትን በርከት ብለው እንዲኖሩ ያስችላል፡፡ ይህም ጥሩ ጎን አለው፡፡ ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ ሚሊኒየም ጋና እና ናይጄሪያ እንዲሁም በ2012 ኤኳቶሪያል ጊኒ እና ጋቦን በጣምራ ካስተናገዱት የአፍሪካ ዋንጫ ውጪ በጣምራ የሚያዘጋጁ ሃገራት እምብዛም አይታይም፡፡ ይህም በሃገራት መካከል ያለው ግንኙነት ከማዳበሩ ባሻገር አዘጋጅ ሃገራት ለመሰረት ልማት የሚሰጡት ትኩረት ይዳብራል፡፡ ጥራት ያላቸው ስታዲየሞች የመገንባታቸው እድል ይበዛል፡፡አሉታዊ ጎን24 ሃገራት በአፍሪካ ዋንጫ መካፈል የሚጀምሩ ከሆነ አሁን ባለው የአፍሪካ ሃገራት የኢኮኖሚ አቅም የማይሆን ይመስላል፡፡ ከ16 ሃገራት ይልቅ 24 ሃገራት መሳታፈቸውን ተከትሎ የስታዲየም፣ የመለማመጃ ቦታዎች እና የሆቴል አቅርቦት አሁን ባለው አህጉሪቱ አቅም ማስተናገድ የሚችሉ ሃገራት ቁጥር በጣም ውስን ናቸወ፡፡ ውድድሩን ለማስተናገደም ከፍተኛ መዋለ ንዋይ ማፍሰስ ግድ ይላል፡፡ አሁን ባለው የአህጉሪቱ አቅም ይህ የማይቻል ነው፡፡\nየጨዋታዎች ጥራት ላይም ትልቅ ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ተሳታፊ ሃገራት ሲጨመሩ በማጣሪያው እምብዛም ሳይፈተኑ የሚያለፉ ሃገራት ቁጥርም ይጨምራል፡፡ ስለዚህም በአፍሪካ ዋንጫ ላይ በሰፊ ግብ ልዩነት የሚሸነፉ ቡድኖችም ቁጥር ይጨምራል፡፡ ጥራት ያላቸው ቡድኖች 16 ሃገር በሚሳተፉበት የአፍሪካ ዋንጫ ላይ መገኘታቸው ባህል ሆኗል፡፡ አሁን የመጣው የቁጥር መጨመር ይህንን ባህል እንዳያፋልስ ያሰጋል፡፡ የማጣሪያ ጉዞውንም ጣዕም እንዳያጣ ከሚያሰጉ ጉዳዮች መካከል ነው፡፡የኬንያው ሲቲዝን ቲቪ ዘገቢ የሆነው ጄኮብ ኢሲያ በራባት የነበረውን ሲምፖዚየም በስፍራው ተገኝቶ ተከታትሏል፡፡ ጄኮብ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጠው አስተያየት የቁጥር መጨመሩ ውድድሩ ያለውን ጣዕም እንዳያጣ ይሰጋል፡፡ “በ24 ሃገራት መካከል የሚደረገው ውድድር ጣዕም አይኖረውም፡፡ የፉክክር መጠኑንም በዛው ልክ እየወረደ ነው የሚመጣው፡፡ አሁን ላይ ባለው ሁኔታ ይህ መሆኑ ለእኔ ጥሩ አይመስለኝም፡፡” ይላል፡፡የአፍሪካ ዋንጫ ከ2019 ጀምሮ ወደ ሰኔ/ሐምሌ ወር መዛወርየአፍሪካ ዋንጫ በጥር/የካቲት ወር ለረጅም ግዜያት መካሄዱን ተከትሎ የኢሳ ሃያቱ አስተዳደር ከአውሮፓ ክለቦች ጋር የጥቅም ግጭት ውስጥ አስገብቷቸዋል፡፡ በፊፋ ህግ መሰረት ደግሞ ክለቦች ተጫዋቾቻቸውን በብሄራዊ ቡድን ጨዋታዎች ወቅት የመልቀቅ ግዴታ አለባቸው፡፡ የጥር ወር የአብዛኞቹ የአውሮፓ ሊጎች የአንደኛ ዙር ጨዋታቸውን የሚያጠናቀቁበት እና በሊጉ ወሳኝ ወቅት የሚደርሱበት ግዜ ነው፡፡ ይህንን ተከትሎም በአፍሪካ ዋንጫ የሚካፈሉ ተጫዋቾቻቸውን ላለመልቀቅ ሲያመነቱ ይስተዋላል፡፡አዎንታዊ ጎንውድድሩን ከጥር/የካቲት ወደ ሰኔ/ሐምሌ መወሰዱ አፍሪካን ከሚጠቅምባቸው አንዱ አሁንም የገቢ ምንጭ ማደግ ነው፡፡ በሰኔ/ሐምሌ ወራት ላይ በአፍሪካ ተወዳጅነትን ያተረፉ የአውሮፓ ሊጎች ተጠናቀው እረፍት ላይ እንዲሁም የቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት የሚጀምሩበት ወቅት መሆኑ ቢያንስ የአፍሪካ ዋንጫ የሚመለከተውን የተመልካች ቁጥር ይጨምረዋል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ይህም ከገቢ አንፃር ካፍ ከተለያዩ ስፖንሰሮች እና የቴሌቪዥን መብት የሚያገኘውን ረብጣ ገንዘብ በይበልጥ ያሳድግለታል፡፡በአውሮፓ የእግርኳስ ህይወታቸውን ለሚመሩ አፍሪካዊያን ተጫዋቾች እና ክለቦቻቸው ይህ መልካም ነው፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ የሚጫወቱ ተጫዋቾች በብዛት ወደ ክለቦቻቸው ሲመለሱ በተለይ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ የነበሩት በቀላሉ ወደ ቋሚነት ለመመለስ እና ወጥ የሆነ አቋም ለማሳየት ይሳናቸዋል፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ ወቅትም ክለቦቻቸው በምትካቸው ሌሎች ተጫዋቾችን በብዛት ማስፈረማቸው ሌላው የአፍሪካዊያን ተጫዋቾች ጭንቀት ነው፡፡ የወቅት ለውጡ ግን ክለቦችንም ተጫዋቾችንም ከዚህ ጭንቀት ይገላግላል፡፡ብዙ አፍሪካዊያን የሚያደንቋቸው የአፍሪካ ከዋክብት ተጫዋቾችን እንዲመለከቱ ይረዳል፡፡ ውሳኔው በካፍ እና በአውሮፓ ክለቦች መካከል ያለውን ቅራኔ ስለሚፈታ በተለያዩ ሃገራት የሚጫወቱ ከዋክብቶችን በአፍሪካ ዋንጫ ለመመልከት ያስችለናል፡፡እንደኢትዮጵያ ባሉ በዘመናዊ ፕሮግራም በማይመሩ ሃገራት የአፍሪካ ዋንጫው የወቅት ለውጥ ማድረጉን ተከትሎ የውስጥ ሊግ ውድድሮቻቸውን (ዋናውን ሊግ እና ጥሎ ማለፉን) በፍጥነት እንዲያጠናቀቁ ያስገድዳል፡፡ ይህ በጎ ነው፡፡ ለምሳሌ የዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተጠናቀቀው ሰኔ አጋማሽ ላይ ሲሆን አሁን ላይ የአፍሪካ ዋንጫው በሰኔ እንዲሁም የአፍሪካ ክለቦች ውድድር በነሃሴ እንዲጀመሩ መደረጉ ፌድሬሽኑ የፕሬግራም አወጣጡን እና አጠቃላይ ሊጉን የሚመራበትን መንገድ እንዲያጤን በእጅጉ ጫና ላይ ይከተዋል፡፡ጄኮብ በዚህ ውሳኔ ላይ ያለውን ምልከታ እንዲ ይገልፀዋል፡፡ “በካፍ እና አውሮፓ ሊጎች መካከል ያለው ቅራኔ ማብቃት ነበረበት፡፡ ከዋክብት የሆኑ አፍሪካዊያንን በአፍሪካ ዋንጫው መመልከት እንፈልጋለን፡፡ ተጫዋቾች በሃገራቸው ጥሪ እና ቀጣሪ ክለቦቻቸው መካከል ሆነው የሚደርስባቸው ጫናን ማስቀረቱ በጎ ነው፡፡”አሉታዊ ጎንሰኔ/ሐምሌ በአብዛኞቹ የአፍሪካ ሃገራት የዝናብ ወቅት ነው፡፡ ጥራት ያላቸው ሜዳዎች በስፋት በማይገኙባት አፍሪካ በዝናባማ አየር ሁኔታ ጨዋታዎችን ማካሄድ እጅግ ከባድ መሆኑን ለመረዳት የሳይንስ አዋቂ መሆን አይጠይቅም፡፡ የኢሳ ሃያቱ አስተዳደር ውድድሩን ወደ ክረምቱ ወቅት ከማምጣት የተቆጠበው ዋነኛ ምክንያቱ ይህ ነው፡፡ እዚህ ላይ የአህመድ አህመድ አስተዳደር ይህንን እውነታ ከግምት ውስጥ ያላስገባ ውሳኔ መስጠቱ አስገራሚ ያደርገዋል፡፡የ24 ሃገራት የአፍሪካ ዋንጫን የማስተናገዱ ሙሉ አቅም አሁን ባለው ደረጃ አላቸው በሚባሉት የሰሜን አፍሪካ ሃገራት ደግሞ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በክረምቱ ወቅት ይመዘገባል፡፡ ለምሳሌ በአልጄሪያ በሰኔ ወር የሙቀት መጠኑ ከ37-40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ይደርሳል፡፡ በከፍተኛ ሙቀት ጨዋታዎችን ማካሄድ አሁንም አስቸጋሪ ነው፡፡ አውሮፓዊያን በለውጥ ሰበብ ለረጅም ግዜ ሲመኙት የነበረውን ጥቅማቸውን በአዲሱ አስተዳደር አሳክተዋል፡፡ ይህም ካፍ ከሶስተኛ ወገን ጫና እና ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ከመላቀቅ ይልቅ ይበልጥ እጁን እየሰጠ መሆኑን አመላካች ነው፡፡የቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌድሬሽን ዋንጫ የወቅት ለውጥ\nየካፍ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ከነሃሴ-ግንቦት እንዲካሄድ መወሰኑ ከጉዳት ይልቅ ጥቅሙ ያመዝናል፡፡ የአብዛኞቹ ሃገራት የሊግ ውድድሮች የሚካሄዱት በዚሁ ወቅት መሆኑ ደግሞ ይበልጥ ጥቅሙን ያጎላዋል፡፡ ከመጋቢት-ህዳር ይካሄድ በነበረው የክለቦች ውድድር የበላይነቱን የሚይዙት ክለቦች በፋይናንስ፣ አደረጃጀት እና በቡድን ስብስብ ጥራታቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሱ ናቸው፡፡ ለዚህም ማሳያ አንዲሆነን በቅርብ አመታት ውድድሮቹን ያሸነፉ ክለቦችን መመልከት በቂ ነው፡፡ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የ2016 የቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ በሆነበት ወቅት ያለሟቋረጥ የሊግ፣ የጥሎ ማለፍ እና የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎችን በተጣበበ ግዜ ማካሄድ ነበረበት፡፡ ሰንዳውንስ ካለው አቅም አንፃር ይህንን ቢቋቋምም ለአብዛኞቹ አፍሪካ ክለቦች ግን ይህ ፈፅሞ የማይታሰብ ነው፡፡ እንደካፍ መረጃ ከሆነ ከ70% በላይ አፍሪካ ሊጎች የሚካሄዱት ከነሃሴ-ግንቦት ባለው ግዜ ነው፡፡ ስለዚህም ይህ የግዜ ለውጥ ምክንያታዊ እና ትክክለኛ ነው፡፡ የተዝረከረከ እግርኳስ አሰራር ባለባት ኢትዮጵያም ይህ ለውጥ መደረጉ ቢያንስ ፌድሬሽኑ እና ክለቦች ላይ የውስጥ ሊግ ውድድሩን የሚመሩበትን እና የሚያስኬዱበትን ኃላቀር አሰራር እንዲያሻሽሉ ጫና ሊያደርግባቸው ይችላል፡፡ ለምሳሌ በ2005 መጨረሻ መካሄድ የነበረበት የቅዱስ ጊዮርጊስ እና መከላከያ የኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታ በ2006 ነበር የፍፃሜ ጨዋታው የተካሄደው፡፡ አሁን ላይ የካፍ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ተሳታፊን የሚለየው ኢትዮጵያ ዋንጫ እንደቀድሞ እየተንጓተተ እንዳይካሄድ ይህ ለውጥ ፌድሬሽኑን ጫና ውስጥ ይከታል፡፡ ይህ ጠቀሜታው ፌድሬሽኑ አሁን ላይ ከመቸውም በላይ እራሱን እንዲፈትሽ ያስገድደዋል፡፡የእድሜ ማጭበርበርበታዳጊዎች ውድድር ላይ የአፍሪካ ሃገራት በእድሜ ማጭበርበር ይበልጥ ይታወቃሉ፡፡ በእግርኳሱ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ስፖርቶች በተለይም አትሌቲክስ ላይ ይህ በሰፊው ይስተዋላል፡፡ ይህን የእግርኳስ እድገት ገቺ ተግባር ለማስቆም ካፍ ዘመናዊ አካሄዶችን እንደሚከተል ውሳኔ አስፍሯል፡፡ ውሳኔው እውነትም ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ አባል ሃገራት ለወጣቶች እግርኳስ ላይ እንሰራለን ከሚሉ ጆሮ አደንቋሪ ባዶ አስተያየቶች ታቅበው ወደ ትክክለኛው መንገድ እንዲያመሩ ያችላል ተብሎ ይታሰባል፡፡ የታዳጊዎች ውድድር ዋና አላማ ዋንጫ ማሸነፍ ሳይሆን ተተኪዎችን ማፍራት ነው፡፡ በአፍሪካ ውስጥ ግን የታዳጊዎች ውድድር ላይ ውጤት ፍላጋ ላይ ብቻ በማተኮር ፌድሬሽኖች እና ክለቦች በአህጉሪቱን እምቅ ችሎታ ያላቸውን ታዳጊዎች እንዳይፈሩ እንቅፋት ሆነዋል፡፡ ስለዚህም ፌድሬሽኖች እና ካፍ በእድሜ ማጭበርበር ላይ ያለቸው አመለካከት መቀየር ከቻለ የተወሰነው ውሳኔ አህጉሪቱን እግርኳስ ተስፋ እንዲያንሰራራ ያስችላል፡፡ የአመለካከት ለውጥ ማምጣት ካልቻለ ግን አሁንም አህጉሪቱ ጥሩ ብቃት ያላቸውን ታዳጊዎች እንዳይፈሩ ይሆናል፡፡", "passage_id": "590d93ad07e7944046d6bd28224a863e" }, { "passage": "የእግር ኳስ ስፖርትን በዓለም ተወዳጅ እንዲሆኑ ያስቻሉ ምክንያቶች በርካቶች ናቸው። በአንጻሩ በተወዳጅነቱ ላይ ጥቁር ነጥብ የሚጥሉትም ጥቂት የሚባሉ አይደሉም። ከእነዚህ መካከል አንዱ ዘረኝነት ሲሆን፤ በተለይ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸውን ተጫዋቾች ለይቶ አንገት ማስደፋት በዓለም አቀፎቹ ማህበራት ጭምር መፈታት ያልቻለ ጉዳይ ነው። በስታዲየሞች ውስጥ በድምጽ፣ በምስል እንዲሁም በስድብም ጭምር ተጫዋቾች ላይ ጫና ለመፍጠር የሚደረግ እንቅስቃሴም ነው። ይህ ተግባር በተለይ በሌሎች ሊጎች በስፋት ይስተዋላል ቢባልም፤ በተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግም መከሰቱ አልቀረም። በቅርቡ ስታምፎርድ ብሪጅ በቼልሲ እና ማንቸስተር ሲቲ መካከል በተካሄደው ጨዋታ የሲቲው ተጫዋች ራሂም ስተርሊንግ መሰል ጥቃት ማስተናገዱም የሚታወስ ነው። ተጫዋቹ ከፕሪምየር ሊጉ ባሻገርም በአውሮፓ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ላይም ክስተቱ ተስተናግዷል። ሌሎች እርሱን መሰል ተጫዋቾችም በተመሳሳይ በዘረኝነት ተግባራት ተጠቅተዋል። ይህንን ተከትሎም አሰልጣኞች አስተያየት የሰጡ ሲሆን፤ በተጫዋቾቻቸው ላይ መሰል ችግሮች ሲስተናገዱ ተጫዋቾቻቸውን ከጨ ዋታ ውጪ እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል። ከእነዚህም መካከል የቼልሲው አሰልጣኝ ሞሪዚዮ ሳሪ፣ የሊቨርፑሉ የርገን ክሎፕ፣ እና የቶትንሃሙ ሞሪሲዮ ፖቸቲኖ ይጠቀሳሉ። የዌስት ሃሙ አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሪኒም ማህበሩ በዚህ ጉዳይ ላይ ጠንካራ ቅጣት መጣል እንዳለበት ነበር የጠየቁት። አሰልጣኞች ይህንን ይበሉ እንጂ ስተርሊንግ ከሁለት ቀናት በፊት በሰጠው አስተያየት፤ ተጫዋቾች ችግሩ ሲደርስባቸው ጨዋታውን ማቋረጥ እንደሌለባቸው መግለጹን ቢቢሲ በድረገጹ አስነብቧል። ተጫዋቹ ችግሩ በለንደን ሳይሆን ወደ ሊቨርፑል ከተማ የሚስተዋል መሆኑንም አልሸሸገም። ነገሩን ሲያስረዳም «አንተ ሜዳውን ጥለህ ከወጣህ፤ እነርሱ ያሸንፋሉ። የሚፈልጉት አንተን መጉዳት በመሆኑ፤ በጨዋታ ማሸነ ፍህና ግብ ማስቆጠርህ ይጎዳቸዋል። ጥቁር እንደሆንኩ ሲነግሩኝ ኩራት ይሰማኛል፤ ምክንያቱም በአካሌ ልበሙሉ ነኝ» ብሏል። የችግሩን ክብደት ከግምት ያስገባው የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በበኩሉ በጨዋታ ወቅት እንዲህ ያሉ ጉዳዮች ሲስተዋሉ ዳኞች ጨዋታውን እስከማቋረጥ የሚደርስ እርምጃ መውሰድ እንደሚችሉ አስገንዝቧል። የማህበሩ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሴፍሪ «ተግባሩ በተፈጸመበት ቅጽበት ጨዋታውን ማቆም አሊያም ማቋረጥ ተገቢ ነው። እርግጠኛ ነኝ ይህ ሲሆን በስታዲየሙ ከሚገኙት ሰዎች 90በመቶ የሚሆኑት ተግባሩን በፈጸሙት ላይ እርምጃ ይወስዳሉ። ይህ 2019 እንጂ ከ100 ዓመታት በፊት\nያለ ወቅት አይደለም» ማለታቸውን ቢቢሲ አስነብቧል። ከወራት በፊት በተካሄደ አንድ ዳሰሳዊ ጥናት ላይ በየሃገራቱ ይህ ተግባር በምን ደረጃ ላይ ደርሷል የሚለውን መተንተኑ ይታወሳል። በቅርቡም በርካቶች በቆዳ ቀለማቸውና በኋላ ታሪካቸው ምክንያት ሜዳ ላይ ሲዘለፉ ታይተዋል። ይህንን ተከትሎም የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ወደ እርምጃ መግባቱን አስታውቋል። ፕሬዚዳንቱ በዚህ ዙሪያ በሰጡት አስተያየት ላይም «ከዳኞች ጋር በድጋሚ ተነጋግረናል። ከውሳኔ ለመድረስ እንዳይፈሩ እና በመወሰናቸውም ልበ ሙሉነት እንዲሰማቸው ነግረናል። ይህ በተለይ በምስራቅ አውሮፓ ጎልቶ የሚታይ ችግር ነው፤ ከኢኮኖሚ ጋር በተያያዘ በርካቶች ወደዚያ እንደሚያቀኑ ይታወቃል። ነገር ግን ይህ ችግር ስርዓት ከጎደላቸው ሰዎች የሚመነጭ እንጂ እንደ ህዝብ ያለ አይደለም» ብለዋል። አክለውም ማህበሩ\nጠንካራ እርምጃዎችን ወደ መውሰድ\nእንደሚገባ ያሳወቁ ሲሆን፤\nየገንዘብ ቅጣትን ጨምሮ\nክለቦችን እስከ ማገድ\nእንዲሁም ከተመልካች ውጪ ጨዋታዎችን\nእስከማካሄድም የሚደርስ ይሆናል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 3/2011በ", "passage_id": "bf070c807bb80841da28b262bdf1fd23" } ]
c78f34b4103116c4dadb1411c51ff206
7e5e36b2bb400322dbc8ac93c3165d71
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለብሄራዊ ፌዴሬሽኖች ቃል የገባውን ገንዘብ ዛሬ ያስረክባል
የዓለም ህዝብን በአንድ የጭንቀት ቋጥ ውስጥ ባስገባው የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት በስፖርቱ ዘርፍ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ማሳደሩ ይነገራል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በሀገሪቱ የኮሮና ወረርሽኝ በስፖርቱ ላይ እያሳደረ ያለውን ጫና የሚዳስስ ውይይት ከሀገር አቀፍ ፌዴሬሽኖች ጋር አድርጎ ነበር። የሁሉም ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ውቅር የሆነው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከሀገር አቀፍ ፌዴሬሽኖች ጋር ካደረገው ውይይት መነሻነት እንዲሁም ፌዴሬሽኖቹም በሰጡት ጥናት መሰረት አንድ ውሳኔ አስተላልፏል። «ብሔራዊ ፌዴሬሽኖችን የገንዘብ ድጋፍ ይደረግላቸው ። ከዚህ በተጓዳኝ የገንዘብ አቅም የሌላቸው ስፖርቶችና ስፖርተኞች ወቅታዊ ብቃታቸው እንዳይወርድ ዕገዛ ይደረግላቸው» ሲል ነበር። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ትናንት በመደበኛ የፌስቡክ ገጹ ፤« የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገባውን የገንዘብ ድጎማ ማክሰኞ ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚያስረክብ አስታወቋል። በኢትዮጵያ የተለያዩ ስፖርቶችን ለማሳደግና ለማስፋፋት የተቋቋሙ ከ26 በላይ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ዓለም አቀፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ ከማናቸውም ዓይነት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተቆጥበዋል፡፡ በኅብረተሰቡ ዘንድ በስፋት የሚዘወተሩት ስፖርቶች ከሚመሩ ፌዴሬሽኖች በቀር ብዙዎቹ በወረርሽኙ ምክንያት ከቢሮ ይልቅ ቤት ውስጥ መዋል ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡ ኦሎምፒክ ኮሚቴው የብሄራዊ ፌዴሬሽኖችን ምክረ ሐሳብን መነሻ በማድረግ ቃል የተገባውን ገንዘብ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነሩ እና ምክትል ኮሚሽነሩ በተገኙበት ርክክቡ የሚደረግ ይሆናል ብሏል። ኦሎምፒክ ኮሚቴው ሥነ ሥርዓቱን መገናኛ ብዙሃን በስፍራው ተገኝተው መረጃውን በመከታተል ለህዝብ ተደራሽ ያደርጉለት ዘንድ ጥሪውን በመደበኛ ማህበራዊ ፌስቡክ ገጹ አስፍሯል። ሕጋዊ ሰውነት አግኝተው በአገሪቱ በመንቀሳቀስ ላይ ከሚገኙ ብሔራዊ ፈዴሬሽኖች የኢትዮጵያ አትሌቲክስና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ካልሆኑ ሌሎቹ በአጠቃላይ ከመንግሥት ቋት በሚለቀቅላቸው አነስተኛ በጀት የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ መንግሥት ከሚመደብላቸው በጀት ይልቅ ከስፖርት ኮሚሽንና ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተሻለ የገንዘብ ድጎማ እንደሚደረግላቸው የሚናገሩት ብሔራዊ ፌዴሬሽኖቹ፣ ስፖርት በቂ ፋይናንስ ታክሎበት ካልሆነ በስተቀር ብሔራዊ በሚለው ስያሜ ብቻ ትርጉም ያለው እንቅስቃሴና ውጤት ማስመዝገብ እንደማይችል ጭምር ያምናሉ፡፡ የፌዴሬሽኖቹ አመራሮችም የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለወትሮ በዓመት አንድ ጊዜ እንደ አስፈላጊነቱ ይሰጥ የነበረው የሙያ ማሻሻያ ኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ በወረርሽኙ ምክንያት ስለመቋረጡ ጭምር ይናገራሉ፡፡ አዲስ ዘመን ግንቦት 25/2012ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=33574
[ { "passage": "በኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን አስተባባሪነት የሀገር አቀፍ ስፖርት ማኅበራት እና የአትሌቶች ማህበር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚውል የ3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከቱ ።በዓለማችን ብሎም በሀገራችን በፍጥነት እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከል መንግስት የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተማቋቋሞ የተለያዩ ድጋፎችን በማሰባሰብ ላይ ይገኛል ፡፡መንግስት ያቀረበውን የድጋፍ ማሰባሰብ ጥሪ በመቀበል የኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን ሀገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት እና የአትሌቶች ማህበርን በማስተባበር ያሰባሰበውን 3 ሚሊዮን ብር ለብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ስታዲየም በመገኘት አስረክቧል ፡፡\nበርክክብ ስነ ስርዓቱ በመገኘት ድጋፉን ያስረከቡት የኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እንዳሉት “የኮሮና ቫይረስ ዓለማችንን በከፍተኛ ሁኔታ እያስጨነቀ እና ለዜጎች ህልፈተ ህይወት ምክንያት የሆነ ወረርሽኝ መሆኑን ጠቁመው ፤ ወረርሽኙ በዓለም እና በሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ ባሻገር በስፖርቱ ረገድም በውድድሮች እና ስልጠናዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የፈጠረ እና ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ያስቆመ ተግባር ነው ብለዋል ።በመሆኑም የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል እና የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ በሚደረገው ርብርብ የስፖርት ቤተሰቡ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል ፡፡ በዛሬው ዕለትም የሀገር አቀፍ ስፖርት ማህበራት እና የአትሌቶች ማህበር ከአላቸው ውስን በጀት እና ሀብት ላይ በመቀነስ ቫይረሱን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት አጋርነታቸውን አሳይተዋል ሲሉ ከምስጋና ጋር ገልፀዋል ፡፡ ወረርሽኙ እስኪጠፋ ድረስ በግልም ይሁን በቡድን የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል ፡፡ኮሚሽነሩ አያይዘውም እያንዳንዱ ዜጋ ቫይረሱን ለመከላከል መንግስት እና የጤና ባለሙያዎች የሚሰጡትን መመሪያዎች ሳይሰለች መተግበር እንደሚገባ እና ቫይረሱን ለመከላከል ከቤት ውጭ የሚደረገውን እንቅስቃሴ በመገደብ እቤት ውስጥ መቀመጥ እንደሚገባ ገልፀዋል ፡፡ ከቤት ውስጥ ስንቀመጥም ከጭንቀት እና ከድብርት ለመውጣት ቀለል ያሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል ፡፡የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተ/ፕሬዝዳንት አትሌት ኮሮኔል ደራርቱ ቱሉ በበኩሏ ሆቴል ያለው ሆቴሉን ፤ መኪና ያለው መኪናውን ገንዘብ ያለው ገንዘቡን በመለገስ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ድጋፉን እያሳየ ነው በዚህም ኢትዮጵያዊ በመሆነ ኮርቻለሁ ብላለች ፡፡ በመሆኑም እኛ ኢትዮጵያዊያን ተባብረን እና አንድ ሆነን የቫረሱን ስርጭት ልንከላከል ይገባል ፤ አሁን ከምንም ጊዜ በላይ ከህዝባችን ጎን የምንቆምበት ነው ፤ ሁላችንም በአለን አቅም ልንረባረብ ይገባል ስትል መልዕክቷን አስተላልፋለች ፡፡ ስፖርተኞች ፣ አሠልጣኞችና ማናጀሮች ሳንዘናጋ በአለንበት እራሳችንን እየጠበቅን ፤ ምን እና እንዴት ልስራ የሚለውን እያቀድን ልምምድ ልናደርግ ይገባል ብላለች ፡፡የተሰበሰበውን ድጋፍ የተረከቡት የብሔራዊ የኮሮና ቫይረስ ድጋፍ አሰባሳቢ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር ምስጋናው አረጋ በበኩላቸው ፤ ስፖርት ከማዝናናት ባለፈ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው ፤ ሀገራችን አሁን ያለችበት ሁኔታ እና ወረርሽኙን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ትልቅ አቅም እና ብሔራዊ አንድነትን ፤ መተባበርን የሚጠይቅ ሲሆን፤ በእንደዚህ ዓይነት ሀገራዊ ጥሪ ቅድሚያ ተሰላፊ የሆነው የስፖርት ቤተሰብ ይህንን ተረድቶ ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ ስለሆነ በብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡ መሰል ድጋፎችም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አምባሳደሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ፡፡", "passage_id": "1a2571812b53a5c5b1639e2de27f45a3" }, { "passage": "ብርሃን ፈይሳ በኢትዮጵያ ስፖርት፤ ማህበራትና ክለቦች ከመንግስት እገዛ አለመላቀቃቸውና ሃብት በማመንጨት ተግባር ላይ ተሳታፊ አለመሆናቸው እንደ ድክመት ይነሳል።የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአጭር ጊዜ ውስጥ ፕሪሚየር ሊጉ በአክሲዮን ማህበር እንዲተዳደር በማድረግና ከጥገኝነት እንዲላቀቅ የማድረጉ ጅማሬም መልካም የሚባል ነው።ስፖርቱን በበላይነት በሚመራው ብሄራዊ የስፖርት ምክር ቤትም የፌዴሬሽኑ ተግባር ለሌሎች ስፖርት ማህበራትም አርአያነት ያለው መሆኑ በሪፖርት ቀርቧል።ይሁን እንጂ ስፖርቱ በገቢ ረገድ ችግር እየደረሰበት መሆኑ ነው ፌዴሬሽኑ የጠቆመው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ\nፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ\nጂራ በመድረኩ ላይ\n፤ እግር ኳሱ\nበስፖንሰር ምክንያት እየደረሰበት\nያለውን ችግርና ችግሩ\nየተፈጠረበትን ምክንያት መንግስት\nማጤን ይኖርበታል ሲሉ\nገልጸዋል።ይኸውም በህዝብ ተወካዮች\nምክር ቤት የወጣውን\nየአልኮል መጠጦች ማስታወቂያ\nበህዝብ መገናኛ ብዙሃን\nእንዳይተላለፍና በስታዲየሞች \n ውስጥ እንዳይሰቀል የሚከለክለው አዋጅን በቀጥታ እግር ኳሱን የጎዳ መሆኑን ይጠቁማሉ።በእርግጥ መንግስት ዜጎቹን የመጠበቅ ኃላፊነት ይኑርበት እንጂ መታየት ያለባቸው ጉዳዮች ሳይመዘኑ ታልፈዋል የሚሉት አቶ ኢሳያስ፣ ‹‹ጉዳት አድርሶብናልና ቢፈተሽ›› ሲሉ ጥያቄያቸውን ለብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤቱ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ፌዴሬሽኑ ባለፈው ዓመት ከዋሊያ ቢራ ጋር 56 ሚሊየን ብር የስፖንሰር ስምምነት አድርጎ ነበር፤ ነገር ግን ይህ አዋጅ በወጣ ማግስት ስምምነቱ ተቋርጧል።በዓለም ላይ በሃብቱ ቀዳሚ የሆነው የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ በሃይንከን ቢራ ስፖንሰር እንደሚደረግ ያነሱት ፕሬዚዳንቱ፤ ሌሎች ሊጎችም በመጠጥ አምራች ተቋማት ስፖንሰር የሚደረጉበት አሰራር በዓለም ላይ የተለመደ መሆኑን ጠቁመዋል።ፌዴሬሽኑ በዚህ ረገድ ያለውን ሃሳብ በጽሁፍ ለመንግስት ማቅረቡንና አዋጁ በፌዴሬሽኑ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ በድጋሚ እንዲፈተሽ ካልሆነም መንግስት ብሄራዊ ቡድኖችን እንዲደግፍ ጠይቀዋል። እንደ ፕሬዚዳንቱ ማብራሪያ፤\nችግር ሲያጋጥም እርዳታ\nከማድረግ ባለፈ በኢፌዴሪ\nስፖርት ኮሚሽን ስር\nካሉ የስፖርት ማህበራት\nመካከል ምንም ዓይነት\nድጋፍ ከማይደረግላቸው መካከል\nአንዱ የኢትዮጵያ እግር\nኳስ ፌዴሬሽን ነው።ፌዴሬሽኑ\nበስሩ ያሉትን ሰባት\nብሄራዊ ቡድኖችን (በሁለቱም\nጾታ በተለያየ የዕድሜ ክልል እና ዋናውን ቡድን ጨምሮ) በራሱ ነው የሚያስተዳድራቸው።ካሜሩን ለምታዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን(ዋሊያዎቹ) ከማዳጋስካር፣ ኒጀር እና ኮት ዲቭዋር ጋር ተደልድሏል።በመሆኑም ቡድኑ የጉዞ፣ የሆቴልና ሌሎች በርካታ ወጪዎችን ማድረጉ የግድ ነው።በተመሳሳይ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከዚምቧቡዌ እና ከጋና ጋር ባላት ድልድል ሌሎች ወጪዎችን ማድረግም ይጠይቃል።ሌሎቹ ብሄራዊ ቡድኖችም ለሚኖሯቸው አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ተጨማሪ ወጪዎች ይጠበቃሉ።መንግስት ይህንን በባለቤትነት ወስዶ ብሄራዊ ቡድኖችን ሊያግዝ ይገባዋል። ብሄራዊ ቡድን ሃገር የምትወከልበት መሆኑ መንግስት ሊደግፈው ይገባሉ ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚካፈለው የአትሌቲክስ ቡድን በመንግስት እገዛ እየተደረገለት መሆኑን በማሳያነት ይጠቅሳሉ።ይህ የስፖርት ማህበራት ድክመት ደግሞ ብሄራዊ ቡድኑንም ደካማ አድርጎታል፤ በመሆኑም መንግስት ድጋፍ ሊያደርግለት ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል። አብዛኛዎቹ የእግር ኳስ ክለቦች የሚተዳደሩት በመንግስት እንደመሆኑ፤ ፌዴሬሽኑ ደግሞ ይህ መንግስት የሚመድበው ከፍተኛ ገንዘብ በዚህ መቀጠል የለበትም የሚል ሃሳብ እንደሌለው ገልጸዋል።ክለቦችን ወደ ግል ተቋም ለመመለስ በማቀድ ለሶስት ዓመታት ፕሮጀክት በመያዝ እየተንቀሳቀሱ ሲሆን፤ የመጀመሪያዎቹን ስድስት ወራት ከአንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ጋር በመሆን በትምህርት ቀጣዮቹን ጊዜያት ደግሞ 30 ከመቶ የሚሆኑትን ክለቦች 30 በመቶ መንግስት 40 በመቶ ህብረተሰቡ እንዲይዛቸው የግል ባለሃብት ተሳትፎ በማከል ሙሉ ለሙሉ ከመንግስት ለማላቀቅ ታቅዷል።በመሆኑም ምክር ቤቱ አንድ አቅጣጫ መስጠት እንደሚገባው አሳስበዋል፤ ይህ ካልሆነ ግን መንግስት ድጋፉን ቢያቋርጥ አስቸጋሪ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ጠቁመዋል። ክልሎችም በስራቸው የሚያስተዳድሯቸው ክለቦች እንደመኖራቸው ለዚህ ስራ ተባባሪና በሚወጣው ደንብም ለመመራት እገዛ እንዲያደርጉም ፕሬዚዳንቱ ጠይቀዋል። በመድረኩ ላይ ሃሳባቸውን ያንጸባረቁት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ፤ ባለፉት ዓመታት በሁለቱም ጾታዎች በዋናው ብሄራዊ ቡድንም ሆነ በእድሜ በተቀመጡት ቡድኖች የተደረጉት እንቅስቃሴዎች ደካማና አንገት የሚያስደፉ እንደሆኑ መታየታቸውን ይጠቁማሉ።ብሄራዊ ቡድኖች ሲያሸንፉ በተለያዩ የሃገሪቷ ከተሞች ላይ በህዝቡ ዘንድ የሚፈጠረው ተነሳሽነት ታይቷል። ሰብሳቢው አንድ ያልታተመ ጥናትን ዋቢ በማድረግ በ2011/12 ዓ.ም በስፖርቱ ወደ 2ነጥብ2 ቢሊየን ብር ወጥቷል፤ ነገር ግን ውጤት አልመጣም ይላሉ።በመሆኑም እግር ኳስ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት በዚህ መንገድ ይቀጥላል ወይስ ክለቦች ወደ ግል እንዲዘዋወሩና በገንዘብ ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ ታቅዷል የሚለው መመልከት አስፈላጊ መሆኑንም ነው ሰብሳቢው ያመላከቱት። በእቅዱ ላይ ክለቦች ከመንግስት ተረጂነት ሊወጡ ይገባል በሚለው ላይ ፖሊሲ አውጥቶ ወደ ግል ይዞታነት የሚዘዋወሩበትን ስትራቴጂ መንደፍ አስፈላጊ ሲሆን፤ ተግባራዊነቱም ሊመዘን ይገባል። በዚህ ወቅት ከመንግስት ጥቂት መቋቋሚያ ቢያገኙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ራሳቸውን የሚችሉና ከፍተኛ ደጋፊ ያላቸው ክለቦች መኖራቸውንም ሰብሳቢው ይጠቁማሉ።በመሆኑም ይህ ሊታሰብበትና በብሄራዊ የስፖርት ምክር ቤቱ አቅጣጫ ሊሰጠው የሚገባ ነው ይላሉ። የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር፤ በ1990 ዓ.ም የወጣው የስፖርት ፖሊሲ ከስፖርት ማህበራትና ክለቦች አደረጃጀት ጋር በተያያዘ ቀስ በቀስ ከመንግስት ድጎማ መውጣት እንዳለባቸው የሚያመላክት መሆኑን ይጠቅሳሉ።ይህንን ተከትሎ የተከናወኑ ስራዎች ቢኖሩም አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከጥቂቶቹ በቀር የተቀሩት በመንግስት የሚተዳደሩ ናቸው። ዓለም አቀፍ ደረጃቸው ሲፈተሽም፤ ከስያሜ፣ ከመዝሙር፣ ከአርማ፣… ጋር የተያያዙ ጉዳዮች መስተካከል ይገባቸዋል። ብሄራዊ ምክር ቤቱም ከዚህ ቀደም አቅጣጫ ቢያስቀምጥም ብዙም አልተሄደበትም።ክለቦቹም ከመንግስት ድጎማ በመውጣት ራሳቸውን እንዲችሉ ስልቶችን መቀየስ ይገባቸዋል።ለአብነት ያህልም የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎቹን ወደ አክሲዮን የቀየረበት መንገድ ገቢውን ከማሳደግ ጎን ለጎን የታዳጊ ቡድኖችን የያዘበት ጅማሮ የሚበረታታ ነው፡፡ ፌዴሬሽኖች በገቢ ራሳቸውን እንዲችሉ ከማድረግ ባሻገር መንግስት በስሩ ያሉትን ከ30 በላይ ማህበራት ድጋፍ የማድረግ አቅሙ ውስን ነው።በመሆኑም ክለቦችና ስፖርት ማህበራት በራሳቸው ከሚያደርጉት ባሻገር ኮሚሽኑም ጥናት ላይ ተመስርቶ በቀጣይ የሚሄድበት መሆኑን ጠቁመዋል።  ", "passage_id": "36f13b967202258e302af2bc40e2da9c" }, { "passage": " በመላው ዓለም የኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ-19) ለመዋጋት የሚደረገው ርብርብ እንደቀጠለ ነው። በኢትዮጵያም የስፖርት ቤተሰቡ ተሳትፎ ገና ከጅምሩ አበረታች የሆነ መንገድ ያሳየ ሲሆን፤ እውቅ ስፖርተኞችና የስፖርት ማህበራት ድጋፋቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦችና ተጫዋቾች በገንዘብና በዓይነት ድጋፋቸውን በመስጠት ላይ ካሉት መካከል በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ። የሃዲያ ሆሳዕና እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞችና የጽህፈት ቤት ሰራተኞች የደመወዛቸውን 50 በመቶ መስጠታቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል። በዚህም 443 ሺ 366 ብር ስርጭቱን ለመቆጣጠር ለሚቋቋመው ግብረ ኃይል አበርክቷል። የጅማ አባጅፋር እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች እና አጠቃላይ የክለቡ ሠራተኞች 130 ሺ ብር ድጋፍን አድርገዋል። የድሬዳዋ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾችና አባላት በበኩላቸው ሙሉ ደመወዛቸውን ለዚሁ ዓላማ እንዲውል ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ታውቋል። የሲዳማ ቡናው አጥቂ አዲስ ግደይ፣ የመከላከያው አጥቂ ሀብታሙ ወልዴ፣ የጅማ አባጅፋሩ አማካይ ንጋቱ ገብረስላሴ፣ የሃላባ ከተማው ልመንህ ታደሰ እና የጅማ አባጅፋር ተከላካይ መላኩ ወልዴ በጋራ ለትውልድ ከተማቸው አጋሮ በጥሬ ዕቃ ድጋፋቸውን አድርገዋል። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች 80 ሺ ብር የሚገመት የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ማስረከባቸውን ለማወቅ ተችሏል። ከዚህ በተጨማሪም ቆሼ ተብሎ ወደ ሚጠራው ስፍራ በመጓዝ ለ541 አቅመ ደካሞች ርዳታ ሰጥተዋል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ኮሚሽኑን ጨምሮ በስሩ የሚገኙ የስፖርት ማህበራት ድጋፋቸውን አጠናክረው ከቀጠሉት መካከል ይገኛሉ። በከተማው የውሹ ፌዴሬሽን 45 ሺ 800 ብር በከተማ ደረጃ ለተቋቋመው ኮሚቴ የሚውል ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ስፖርት ኮሚሽነር አበርክቷል። ከዚህም ውስጥ በስራ አስፈፃሚው ውሳኔ ፌዴሬሽኑ 20 ሺ ብር፣ 15 ሺ 800 ብር እና የምግብ ግብዓቶች ከክለብ አሰልጣኞች እንዲሁም የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ማስተር ፍሬህይወት ሽታዬ በግላቸው 10 ሺ ብር አበርክተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽንም በስሩ ያሉ ማዕከላትን እስከ ታችኛው የወረዳ መዋቅር ድረስ ለቅድመ መከላከልና መቆጣጠር ለሚያስፈልጉ ተግባራት ሁሉ እንዲውሉ መወሰኑ ይታወቃል። ከዚህ መካከል አንዱ የሆነው የጃን ሜዳ ስፖርት ማዕከል በጊዜያዊነት ወደ አትክልት ተራነት ተዘዋውሮ ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል።አዲስ ዘመን መጋቢት 27/2012ዳንኤል ዘነበ", "passage_id": "c7359f79daf14553b513a2b8d155ceab" }, { "passage": "ይህ ዓመት እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ቢሆን፤ በስፖርቱ ዓለም በተለይ በዚህ ወቅት በርካታ ውድድሮች፣ ጉባኤዎችና ሥልጠናዎች ሊካሄዱ ይችሉ ነበር። ነገር ግን ሳይታሰብ ተከስቶ ዓለምን ባዳረሰው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) ወረርሽኝ ምክንያት ውድድሮች ብቻም ሳይሆኑ በርካታ ጉዳዮች በታቀደላቸው ሁኔታ እንዳይካሄዱ ማድረጉ ግልጽ ነው። ታዲያ የስፖርት ማህበራትና ሌሎች ተቋማት እቅዶቻቸው በዚህ መልኩ አቅጣጫቸውን ሲስቱ ምን ዓይነት አማራጮችን ተጠቀሙ? ከዓመት እስከ ዓመት በሩጫ ላይ ከሆኑና በሥራ ከሚወጠሩ ፌዴሬሽኖች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው። የፌዴሬሽኑ የሥልጠና ጥናትና ምርምር ዳይሬክተሩ አቶ ሳሙኤል ብርሃኑ የሚናገሩት አላቸው። የኢትዮጵያ\nአትሌቲክስ ቻምፒዮናን ጨምሮ የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን፣ የወጣቶች ቻምፒዮና እንዲሁም ሌሎች ውድድሮች ፌዴሬሽኑ በዚህ ዓመት ያላካሄዳቸው የውድድር ዘርፍ እቅዶች ናቸው። በሥልጠና ጥናትና ምርምር ዘርፍ ደግሞ የዚህ ዓመት ዋነኛ እቅድ የነበረው ባለሙያዎችን ማብቃትና መመዘን መሆኑን ዳይሬክተሩ ይገልጻሉ። ዳኞችና አሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ሥልጠናዎችን አግኝተው ደረጃቸውን እንዲያሳድጉ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ባለበት ወቅት ግን የዓለም ትኩሳት የሆነው ጉዳይ በመከሰቱ እንደታሰበው ማስኬድ አልተቻለም ይላሉ። በተለይ ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ወር ድረስ የሥራ ክፍሉ በዚህ ለማሳለፍ ያስቀመጠው እቅድ ወደ መሬት ሳይወርድ ቀርቷል። በዓመቱ\nኦሊምፒክና ሌሎች ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ መሳተፍና ብሔራዊ ቡድንን የማዘጋጀት እቅድም ተመሳሳይ ዕጣፈንታ ገጥሞታል። ለብሔራዊ ቡድን የተጠሩ አትሌቶችም ተበትነው ወደየ ቤታቸው ሄደዋል። ይህ ሁሉ ሲሆን ፌዴሬሽኑ ግን ሥራውን ከማቋረጥ ይልቅ ሌሎች አማራጮችን መጠቀምን መርጧል። ዋናው የአትሌቶች ጤንነትና በብቃት መቆየት በመሆኑም የተሻለ ያለውን ተግባር ሲከውን እንደቆየ ዳይሬክተሩ ያስረዳሉ። ፌዴሬሽኑ\nከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ስፖርታዊ ክዋኔዎችን ማካሄድ አዳጋች መሆኑን በመገንዘቡ ቀደም ብሎ ወደ ዝግጅት መግባቱን ይጠቁማሉ። አትሌቶች ሥልጠና ማቋረጣቸውን ተከትሎ ከስፖርቱ እንዳይርቁ እንዲሁም አሰልጣኞችም ከአትሌቶቻቸው በጋራ ያላቸው ግንኙነት እንዳይቋረጥ ምን ማድረግ ይገባል? የሚለውን በማሰብም ነው በቴሌቪዥን ስርጭት በትምህርትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ፕሮግራሞች እንዲተላለፉ የተደረገው። በዚህም የስፖርቱ ባለሙያዎችን በማካተት በሦስት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለስድስት ሳምንታት ለአትሌቶች ጠቃሚ የሆኑ መርሃ ግብሮች ሲተላለፉ ቆይቷል። የመርሃ ግብሩ ይዘትም ሥነ-ልቦና፣ ሥነ-ምግብ፣ ሕክምና፣ ማህበራዊ ግንኙነት፣ የተምሳሌት አትሌቶች መልዕክት፣ የአሰልጣኞች ምክረ ሃሳብ እንዲሁም አትሌቶች በአጠቃላይ ምን ማድረግ ይገባቸዋል የሚለውን ያጠቃለለ ነበር። ከቴሌቪዥን ስርጭቱ ባሻገር በፌዴሬሽኑ ይፋዊ ማህበራዊ ገጽ (ፌስ ቡክ) እንዲሁም በድረገጹ አማካኝነትም አትሌቶችን ተደራሽ ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህ\nሂደትም ፌዴሬሽኑ ማድረግ የሚገባውን መልካም ተግባር ማከናወኑን ለመታዘብ ተችሏል። አትሌቶችና ሌሎች ባለሙያዎችም ለዚህ የሚሰጡት ግብረ መልስ ጥሩ ሥራ መሰራቱን የሚያሳይ ነው። አትሌቶች ቤታቸው በሚሆኑበት ወቅት ምን መስራት እንዳለባቸው ግራ ተጋብተው ነበር የሚሉት ዳይሬክተሩ፣ አሰልጣኞች በሚሰጧቸው አቅጣጫ ተጠቃሚ ሆነዋል። በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙና እነዚህን አማራጮች የማያገኙ አትሌቶችን ደግሞ አሰልጣኞች በስልክና በሌሎች መንገዶች በተመሳሳይ እየረዷቸው ይገኛሉ። አሁን ካለው ሁኔታ አንጻር ጥናት መስራትና አትሌቶችን ማግኘት ባይቻልም በተለያዩ መንገዶች ምስጋናቸውን ያደርሳሉ። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምክር የሚጠይቁ አትሌቶች ቁጥር መበራከትም ይህንኑ የሚያመላክት ነው። አሰልጣኞች በበኩላቸው ወትሮ ከነበረው ሁኔታ በተሻለ መልኩ ከፌዴሬሽኑ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያጠናከሩ ሲሆን፤ ግብረመልስ በመስጠትም አጋርነታቸውን እያሳዩ ነው። ከዚህ\nበኋላም ፌዴሬሽኑ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት ጎን ለጎን መርሃ ግብሩን በአዲስ መልክ የሚያስቀጥልም ይሆናል። የሀገርን ስም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያስጠራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በሚደረገው ርብርብ ቅድሚያ ተሰላፊ መሆኑን በተግባር በማሳየት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። ከዚህ ቀደም በግሉ፣ ከሌሎች ተቋማት ጋር እንዲሁም በአትሌቶቹ አማካኝነት በገንዘብ እንዲሁም በቁሳቁስ የድርሻውን በማድረግ ላይ ይገኛል። አመራሩና ሌሎች ታዋቂ አትሌቶችም ለሕዝቡ መልዕክት በማስተላለፍ ላይ ናቸው። አሁንም ከዚህ በላቀ መልኩ ለመስራት የሚያስችል ተነሳሽነት አለ። እንደሚታወቀው\nበዚህ ወቅት ውድድሮችና ሌሎች የሥልጠና መርሃ ግብሮች ተቋርጠዋል። በዚህ ምክንያት ፌዴሬሽኑ ቀድሞ የያዛቸውን እቅዶች በመቀየር የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮች ላይ ለማተኮር ማቀዱን ዳይሬክተሩ ይጠቁማሉ። በዚህም ከፌዴሬሽኑ ስፖንሰር ማልታ ጊነስ ጋር በመሆን በቴሌቪዥን የሚተላለፉ መርሃ ግብሮችን በመስራት ላይ ነው። በአንድ ወር ውስጥ ለ16 ቀናት ያህል የሚተላለፈው መርሃ ግብሩ እንደ ቀድሞ በምክረ ሃሳብ ላይ ሳይሆን በተግባር ላይ የተመሰረተ እንደሚሆንም ታውቋል። በአትሌቶች ዘንድ ተምሳሌት የሆኑና ዝነኛ አትሌቶች እንዲሁም ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ሲሆን፤ ተከታታይነት ያላቸው እንቅስቃሴዎች በምን መልኩ እንደሚሰሩ የሚያሳይም ይሆናል። እንቅስቃሴው ከአትሌቶች ጋር ብቻ ሳይሆን ሌላውን ኅብረተሰብም የሚጠቅምም ነው የሚሆነው። ለዚህ የሚሆነው ዝግጅት በመጠናቀቁ በቅርቡ አየር ላይ የሚውልም ይሆናል። በዚህ\nወቅት አብዛኛው ኅብረተሰብ ትኩረቱ የመገናኛ ብዙኃን ላይ በመሆኑ፤ ትብብራቸውን እንዳያቋርጡ ይጠይቃሉ። ከቴሌቪዥን ባሻገር በርካቶችን ተደራሽ የሚያደርጉ የመገናኛ ብዙኃን አብሮነታቸውን እንዲያሳ ዩም ጠይቀዋል።አዲስ\nዘመን ግንቦት 19/2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "66e0e14f27a08cecb713d5ae9e964fe9" }, { "passage": "ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ፈደረሽን ፊፋ(FIFA) የጉቦ ገንዘብ ነው ተብሎ በዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣኖች የተያዘበትን ገንዘብ ለማስመለስ በሚያድርገው ጥረት የከፍተኛው አመራር አባላት የዓለም ዋንጫ ድምጾችን የሸጡበት ጊዜ እንደነበር አምኖ እንደተቀበለ ተዘግቧል።ፊፋ(FIFA) ለዩናይትድ ስቴትስ ጠበቆች መስሪያ ቤት ባቀረበው ሰነድ ባለፉት አመታት የማጭበርበር ተግባር ተስፋፍቶ እንደነበር ሲያስረዳ የሙሰኛ ግለ-ሰቦች ሰለባ ሆኛለሁ ይላል።ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ፈደረሽን የታገደበትን ገንዘብ ለማስመለስ በሚያደርገው ጥረጥ ለባለስልጣኖቹ የተከፈለው የጉዞ እለታዊ አብልን፣ የጉዞ ዋጋንና ለመስለ ወጪዎች የሰጠው ገንዘብ ሊመለስልኝ ይገባል ይላል። ያጣው ገንዘብ $28.2 ሚልዮን ዶላር እንደሚሆን ጠቁሟል። ", "passage_id": "d62c363a45460e505ceb0b546b7d1119" } ]
7e2a71c9429381ff7be3117ead173eb4
550c564b74472fc797ee8b1b9d39b489
የዘረኝነት ተቃውሞ በስፖርቱ ዓለም ከዋክብት
ዘመናዊው ኦሊምፒክ በተመሰረተበት ወቅት ከጸደቁ ድንጋጌዎች መካከል በግምባር ቀደምትነት የሰፈረው ሃሳብ ‹‹ስፖርት ለሰው ልጆች ሰላምና ሁለንተናዊ ስብዕና መዳበር እንዲውል ማድረግ›› ይላል፡፡ ይህንንም ከምስረታው (እ.አ.አ 1896) ጀምሮ በውድድር ሜዳዎች ሳይወሰን መልካም ያልሆኑ አሠራሮችን በመቃወምና የህብረተሰቡ ትግል አጋር በመሆን ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባሳተመው መጽሔት ላይ ሰፍሯል፡፡ ለአብነት ያህልም እ.አ.አ 1964 ኮሚቴው አፓርታይድን በመቃወሙ ደቡብ አፍሪካን ከቶኪዮ ኦሊምፒክ ተሳትፎ ማገዱን ማስታወስ ይቻላል:: ከዚህም ባለፈ የራሱን ቡድን በማቋቋምም ደቡብ አፍሪካዊያኑ በአፓርታይድ ምክንያት ከሚደርስባቸው ጭቆና እስኪላቀቁ ድረስ መታገሉም ተጠቃሽ ነው፡፡ የስፖርት ውድድሮች ሁሉ ራስ የሆነው ኦሊምፒክ ተሳትፎ ዓላማና ግብ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም በተለያዩ ጊዜያት በዓለም ላይ የታዩ ኢ ሰብዓዊ የሆኑ ክስተቶችን በመቃወም፤ የስፖርት መነሻና መድረሻው ሰብዓዊነት መሆኑን አስመስክሯል፡፡ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ሁነቶች ጎን በመቆም ዘመናት የተሻገረው ስፖርት አሁንም የአጋርነት ሚናውን እየተወጣ መሆኑን የሰሞኑ ክስተት አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ዓለም በስልጣኔ እንደመራቀቋ የሰው ልጅም በአስተሳሰቡ እንደመምጠቁ የቆዳ ቀለምን መሰረት ያደረገ የዘረኝነት ጥቃት ሊገፋ ያልቻለ ቋጥኝ ሆኗል፡፡ የቆዳ ቀለምን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶችና አስነዋሪ ድርጊት ለዓመታት በስፖርት ሜዳዎችም ጭምር ተንሰራፍተው ታይተዋል፡፡ ሰሞኑን መነሻውን በአንድ ጥቁር ግለሰብ ግድያ ላይ ያደረገውና አሜሪካንን እየናጠ ባለው ተቃውሞም ስፖርት እንደ ትላንቱ ሁሉ ዛሬም ፀያፉን ተግባር በመቃወም ግንባር ቀደም ሆኗል፡፡ ከስፖርቱ ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው የቀድሞ ቦክሰኛ ፍሎይድ ሜይዌዘር በሚኒያፖሊስ በጭካኔ የተገደለውን የ46 ዓመቱን አፍሪካ አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድን የቀብር ስነ-ስርዓት ወጪ እንደሚሸፍን አስታውቋል፡፡ የከባድ ሚዛን ዓለም ቻምፒዮናው ሜይዌዘር በቲውተር ገጹ ላይ ይህንኑ እንዳሰፈረም ነው ዘ ኢንዲፔንደንት በዘገባው ያመላከተው፡፡ የጎልፍ ተጫዋቹ ታይገር ውድስም በተመሳሳይ በሁኔታው ማዘኑን እንዲሁም የሟች ፍሎይድ ቤተሰቦች እንዲበረቱ በትዊተር ገጹ መልዕክት አስፍሯል፡፡ የፖሊሱንም ተግባር ‹‹ያለ ቦታው ኃይልን የተጠቀመና ዕርምጃውም መስመር ያለፈ›› ብሎታል፡፡ አሜሪካዊው የቅርጫት ኳስ ኮከብ ሚካኤል ጆርዳን በበኩሉ በአሜሪካ ያለው ዘረኝነት ስር የሰደደ መሆኑን አስምሮበታል፡፡ ሌሎች የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ተጫዋቾችና ስፖርተኞችም በገንዘብና በሃሳብ ከተጎጂው ቤተሰቦች ጋር መሆናቸውን ከመግለጽ ባለፈ አስነዋሪውን ተግባር በመቃወም አጋርነታቸውን እያሳዩ ይገኛሉ፡፡ የአሜሪካንን ድንበር ያቋረጠውና ወንዝ የተሻገረው ተቃውሞና ለጥቁሮች ወንድማዊ ስሜትን የማሳየቱ ሂደትም በመላው ዓለም እንደቀጠለ ነው፡፡ በአውሮፓ የሚገኙ በርካታ የእግር ኳስ ተጫዋቾች በጨዋታ እንዲሁም በልምምድ ሜዳዎች ላይ በግልና በቡድን በድርጊቱ የተቃውሞ እንዲሁም ከጥቁሮች ጋር የአብሮነት ስሜታቸውን አንጸባርቀዋል፡፡ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠውን የእግር ኳስ ውድድር ከሌሎች ቀድሞ በጀመረው የጀርመን ቡንደስሊጋም ይኸው እንቅስቃሴ ተስተውሏል፡፡ የቦሩሲያ ዶርትመንዱ ተጫዋች ጃደን ሳንቾ ‹‹ፍትህ ለጆርጅ ፍሎይድ›› የሚል ካኒቴራ ከማሊያው ስር በመልበስ ያሳየ ሲሆን፤ ሌሎችም በጉልበታቸው በመንበርከክ ኀዘናቸውን መግለጻቸውን ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡ የተቋረጠውን ሊግ ለመቀጠል በልምምድ ላይ የሚገኙት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾችም በተመሳሳይ ሁኔታ አብሮነታቸውን አሳይተዋል፡፡ 29 የሚሆኑ የሊቨርፑል ተጫዋቾች በሜዳቸው አንፊልድ ከጉልበታቸው በመንበርከክ መልዕክት አስተላልፈዋል፡ ፡ የማንቺስተር ዩናይትድ ተጫዋቾቹ ፓውል ፖግባ እና ማርከስ ራሽፎርድም ድምፃቸውን ካሰሙ ተጫዋቾች መካከል ይገኙበታል፡፡ ፖግባ ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ‹‹ለፍሎይድና ለመላው ጥቁር ማህበረሰብ የንዴት፣ የኀዘን እና የመከፋት ስሜት ተሰምቶኛል፡፡ ጥቁሮች በእግር ኳስ፣ በትምህርት ቤት፣ በሥራና ሁሉም ስፍራ ይህንን ስሜት በየዕለቱ ያስተናግዳሉ፡፡ በመሆኑም ይህ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መቆም አለበት፤ ዛሬውኑ›› ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ እንግሊዛዊቷ የአጭር ርቀት አትሌት ዲና አሸር ስሚዝ፣ የሜዳ ቴኒስ ኮከቧ ሴሪና ዊሊያምስ፣ የፎርሙላ ዋን ሞተር ስፖርት ተወዳዳሪዎች እንዲሁም ሌሎች የስፖርቱ ሰዎችም በሁኔታው መከፋታቸውን በመግለጽ ተቃውሟቸውን የገለጹም የስፖርቱ ዓለም ከዋክብት ናቸው፡፡ አዲስ ዘመን ግንቦት 26/2012ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=33634
[ { "passage": "በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ዘረኝነትንና መድልዎን በመቃወም ድምጻቸውን አሰምተዋል።\n\nአንዳንዶች ዘረኝነት ከጭፍን ጥላቻ የሚመነጭ ይመስላቸዋል። ነገር ግን ሌሎች ሰዎችን የምናስተናግድበት መንገድ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ በርካታ ነገሮች አሉ።\n\nአንዳንዴ ለራሳችን ሳይታወቀን መድልዎ እንፈጽማለን። ይህም ከእምነታችን እና ከባህሪያችንን ሊጻረር ይችላል።\n\nእነዚህ ድርጊቶች ከግል ተሞክሮ፣ ከአስተዳደግ፣ ከባህል፣ ከምናነበው መጻሕፍት እና ከምንሰማው ዜና ይመነጫል።\n\nአሜሪካ ውስጥ ያሉ የፖሊስ ክፍሎች ለራስ የማይታወቅ መድልዎን ለመቅረፍ የሚረዱ መርሐ ግብሮች አሏቸው። ይህም ፖሊሶች ላይ የሚስተዋለውን ዘረኝነት ለመቅረፍ ሁነኛ መንገድ ነው።\n\nፖሊሶች ሲያጠፉ የተለያዩ ማኅበራትና ሕግ አስከባሪዎችም ከተጠያቂነት እንዲያመልጡ ያደርጓቸዋል። ከዚህ ቀደም ከሥራ የተባረሩ ፖሊሶች ጥፋታቸውን በማያውቁ ክፍሎች ዳግመኛ ተቀጥረውም ታይቷል።\n\nይህን ችግር ለመቅረፍ መዋቅራዊ ለውጥ እንደሚሻ፤ በተጨማሪም ሰዎች መድልዎ እንደሚያደርጉ መገንዘብ እንዲንዲችሉ ማድረግ አስፈላጊነት አጽንኦት እተሰጠው ነው።\n\nለራስ የማይታወቅ መድልዎን በተመለከተ ቢቢሲን ጨምሮ በርካታ ተቋሞች ለሠራተኞቻቸው ስልጠና ይሰጣሉ።\n\nአንድ ሰው መተንፈስ እስኪያቆም ድረስ አንገቱ ላይ መቆም እጅግ የከፋ ድርጊት ቢሆንም፤ ለራስ የማይታወቅ መድልዎ እንዲህ አይነቱና ሌላም የተለያየ ቅርጽ አለው።\n\nብዙ ጊዜ እኛና ሌሎችም መድልዎውን ልብ ላንለው እንችላለን።\n\nለመሆኑ ለራስ የማይታወቅ መድልዎን በስልጠና ማስወገድ ይቻላል?\n\nእንዳለብን እንኳን የማናውቀውን መድልዎ መቀነስ ይቻላል? ሙሉ በሙሉ መድልዎን ማስወገድስ?\n\nየመጀመሪያው እርምጃ አድልዎ እንዳለብን ማመን ነው።\n\nካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በዚህ ጉዳይ ላይ ያተከረ ተቋም አለ። በተቋሙ በሚዘጋጅ ፈተና ቃላት ወይም ምስል በስክሪን ላይ ቀርበው በአንዳች መንገድ እንዲያዋቀሩ ይጠየቃሉ።\n\nቃላቱ በጎ ወይም መጥፎም ሊሆኑ ይችላሉ። የሚታዩት ምስሎች የጥቁሮችና የነጮች ናቸው። ብዙ ነጮች በጎ ነገርን ከነጭ ጋር፣ መጥፎ ነገርን ከጥቁር ጋር ያዛምዳሉ።\n\nይህን ፈተና ለብዙዎች አይን ገላጭ ነው። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከ2007 እስከ 2015 በተሠራ ጥናት መሠረት 73 በመቶ ነጮች፣ 34 በመቶ ጥቁሮች እና 64 በመቶ የሌላ ዝርያ ያላቸው ሰዎች ነጭን የሚደግፍና ጥቁር ላይ መደልዎ የሚያሳድር አመለካከት አላቸው።\n\nየአራት ዓመት ሕጻናት ሳይቀር እንዲህ አይነቱ መድልዎ ተስተውሎባቸዋል።\n\nበዝግመተ ለውጥ ለሰው ወይም ስለእንስሳት ያለን አመለካከት ራሳችንን እንድንከላከል ይረዳ ይሆናል። አሁን ግን ወደ መድልዎ ይወስደናል።\n\nየካሊፎርንያ ዩኒቨርስቲው ጄፍሪ ሸርማን \"ከአንድ ቀን በላይ የባህሪ ለውጥ ማምጣት ከባድ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ\" ይላሉ።\n\nነገር ግን አንዳንድ ውጤታማ የለውጥ መንገዶች አሉ።\n\n2012 ላይ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው፤ ከላይ የተጠቀሰውን ፈተና ወስደው ምን ያህል መድልዎ እንደተጫናቸው የተረዱ ሰዎች አሉ።\n\nሰዎቹ ለሁለት ወር ስልጠና ከተሰጣቸው በኋላ መድልዎን በመቀነስ ረገድ አንጻራዊ ለውጥ አሳይተዋል።\n\nአንደኛው የስልጠና መንገድ ስለሆነ ሰው አስቀድሞ የሚቀመጥ ግምትን ማስወገድ ላይ ያተከረ ነው።\n\nየሥነ ልቦና ተመራማሪዋ ፓትሪሽያ ዴቪን፤ ረዥም ጥቁር ሰው ሲታይ “ቅርጫት ኳስ ይጫወታል” ተብሎ ይገመታል። ይህ ግን ማስረጃ ያለው ሳይሆን ጭፍን መድልዎ ነው።\n\nይህን ጭፍን መድልዎ መለወጥ ቀላል አይደለም።\n\nሁሉም ረዥም ጥቁር ሰው ቅርጫት ኳስ እንደማይጫወት ለመረዳት ቢያንስ ሦስት ጥቁር ረዥም ቅርጫት ኳስ የማይጫወቱ ሰዎች ማወቅ እንደሚጠይቅ በማስረጃነት ያቀርባሉ ተመራማሪዋ።\n\nመድልዎን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት... ", "passage_id": "50c8a5d253706a1f92e10256e411a291" }, { "passage": "'ለዘረኝነት እምቢ እንበል' የሚለው ዘመቻ ሶስት የዝንጀሮ ምስሎችን የተጠቀመ ሲሆን የሴሪ ኤ ዋና መቀመጫ በሆነችው ሚላን ከተማ ለእይታ ይቀርባል ተብሏል። \n\nበጸረ ዘረኝነት ላይ የሚሰራ አንድ ግለሰብ ለቢቢሲ ሲናገር '' አሁንም የጣልያን እግር ኳስ ዓለምን አስደምሟል። ሴሪ ኤ ምን እያሰበ እንደሆነ መገመት ከባድ ነው፤ ማንን አማክረው ነው ይህንን የፈጸሙት? ብሏል።\n\n• የሮማ ክለብ ደጋፊዎች በቬይራ ላይ የዘረኝነት ጥቃት አደረሱበት \n\n• ዘረኝነት ሽሽት - ከአሜሪካ ወደ ጋና \n\n''በየሳምንቱ የተለያዩ የእግር ኳስ ተጫዋቾች የዘረኝነት ሰለባ በሚሆኑባት ሀገር ማህበሩ እንዲህ አይነት ተግባር መፈጸሙ እጅግ አሳዛኝና የሚያስቆጣ ቀልድ ነው።'' \n\n''የሴሪ ኤ ተግባር ከቃላት በላይ ነው፤ ዘረኝነትን የሚያበረታታና ለማንም የማይጠቅም እርምጃ ነው። ዘራቸው ከአፍሪካ የሚመዘዝ ተጫዋቾችን እንደ ሰው የማይቆጥር ዘመቻ ነው።'' \n\nባለፈው መስከረም ወር ላይ የኢንተር ሚላኑ የፊት መስመር ተጫዋች ሩሜሉ ሉካኩ በሜዳ ውስጥ እያለ የካግሊያሪ ደጋፊዎች የጦጣ ድምጽ በማውጣት የዘረኝነት ጥቃት የፈጸሙበት ሲሆን እሱም ''እግር ኳስና ደጋፊዎቻችን ወደኋላ እየሄድን ነው'' ብሏል። \n\n•የሮማ ክለብ ደጋፊዎች በቬይራ ላይ የዘረኝነት ጥቃት አደረሱበት \n\nበቅርቡ ደግሞ 'ኮሪዬሬ ዴሎ ስፖርት' የተባለው የጣልያን ጋዜጣ ሮማ እና ኢንተር ሚላን የሚያደርጉትን ጨዋታ 'ጥቁር አርብ' በማለት የሮማው ተከላካይ ክሪስ ስሞሊንግ እና የኢንተር ሚላኑ አጥቂ ሮሜሉ ሉካኩን ምስል የፊት ገጽ ላይ ይዞ መውጣቱ የሚታወስ ነው። \n\n• ዘረኝነት ለእናቶች ሞት ምክንያት እየሆነ ነው?\n\nየአውሮፓ እግር ኳስ ባለሙያ የሆነው ጄምስ ሆርንካስል የጣልያን እግር ኳስ እጅግ አሳፋሪ እየሆነ መጥቷል ብሏል። \n\n'' ሴሪ ኤ ስለዘረኝነት ያለው አመለካከት በጣሙን የተሳሳተ ይመስለኛል፤ ለዚህም ነው ክለቦች በራሳቸው የጸረ ዘረኝነት ዘመቻዎችን ለማካሄድ እየወሰኑ ያሉት።'' \n\nለሴሪ ኤ ዘመቻ የዝንጀሮዎቹን ምስል የሰራው ሰአሊው ሲሞን ፉጋዞቶ በበኩሉ '' ሁሌም ቢሆን በስራዎቼ ዝንጀሮዎችን እጠቀማለሁ፤ ሰዎች ስለዘረኝነት ያላቸውን አስተሳሰብ ለመቀየር እጠቀምበታለው'' ብሏል።\n\nየሴሪ ኤ ዋና ሀላፊ ሉዊጂ ዴ ሴርቮ ደግሞ ''ማንኛውም አይነት የተሳሳተና ሰዎች በተለየ መልኩ እንዲታዩ የሚያደርጉ አስተሳሰቦችን እንቃወማለን፤ ዘረንነት በሊጉ እጅግ እንደተንሰራፋማ እናውቃለን'' ብለዋል።\n\n ", "passage_id": "7dc8c4a10711840d7cf31689c3228a08" }, { "passage": "ዛሬም ድረስ ነገሩ እየባሰበት እንጂ እየተሻሻለ አልመጣም፡፡\n\nበዚህም የተነሳ ጆ ባይደን አዲስ ረቂቅ ሕግ እንዲወጣ አድርገዋል፤ ፊርማቸውንም አኑረውበታል።\n\nየፈረሙበት ረቂቅ ሕግ ኢሲያዊያን ጥቃት እየጨመረ በመምጣቱ ይህንኑ ለመግታት ካስቻለ በሚል ነው፡፡\n\nመቼ ለታ አንድ የታይላንድ ጎልማሳ መሬት ላይ ተገፍትረው ተጥለው ሞተዋል፡፡\n\nበቀደም አንድ የፊሊፒንስ ዝርያ ያለው አሜሪካዊ በሴንጢ ፊቱ ተቆራርጧል፡፡ \n\nባለፈው አንዲት ቻይናዊት ሴት በጥፊ ተመትታ እሳት ተለኩሶበታል፡፡\n\nየዛሬ ዓመት ገደማ በአንድ ምሽት በኢሲያዊያን የውበት ሳሎን ውስጥ ስምንት የኢሲያ ዝርያ ያላቸው ሰዎች ተገድለዋል፡፡\n\nእነዚህ በሙሉ በቅርብ ጊዜ በተለይም የኮቪድን ወረርሽኝ ተከትሎ በአሜሪካ ምድር የደረሱ ጥቃቶች ናቸው፡፡\n\nበቅርብ ወራት ደግሞ ፖሊስ በርካታ ክሶች ደርሰውታል፡፡\n\n በተለይም በቃላት ዝርጠጣና ማንጓጠጥ፣ በድብደባ፣ እንዲሁም መንገድ ላይ በአደባባይ ጭምር የተተፋባቸው ኢሲያዊ መልክ ያላቸው አሜሪካዊያን ለፖሊስ አቤት ብለዋል፡፡\n\nየመብት ተቆርቋሪዎች ይህ የጥላቻ ወንጀል ነው ይላሉ፡፡ በኢሲያዊያን ላይ ጥላቻው የበረታው ደግሞ ኮቪድ ወረርሽኝን ያመጣችሁብን እናንተ ናችሁ ከሚል እሳቤ ስለሚመነጭ ነው፡፡\n\nየአሜሪካ የምርመራ ቢሮ ወረርሽኙ የመጣ ሰሞን በኢሲያዊ መልክ ባላቸው ዜጎች ላይ ጥቃት ሊበረታ እንደሚችል አስጠንቅቆ ነበር፡፡\n\nየ2020 የጥላቻ ጥቃቶች ሪፖርት ለጊዜው ይፋ ባይሆንም በ2019 የጥላቻ ጥቃት አሐዝ ባለፉት 10 ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ከፍ ብሏል፡፡\n\nስቶፕ አፒሄት የተባለ አንድ በመብት ላይ የሚሠራ ቡድን ባለፈው ዓመት ብቻ 3ሺ የሚጠጉ ሪፖርቶች እንደደረሱት ይፋ አድርጓል፡፡\n\n እነዚህ ሁሉ አቤቱታዎች የደረሱት ከኢሲያዊያን ሲሆን መልከ ብዙ ጥቃቶች ከተሰነዘረባቸው በኋላ ለተቋሙ አቤት ያሉ ናቸው፡፡ \n\nየተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም በኢሲያዊያን ላይ የጥላቻ ጥቃቶች አሳሳቢ በሚባል ደረጃ እየጨመሩ ነው ሲል ዘገባ አውጥቷል፡፡\n\nአንዳንድ ግዛቶች ችግሩን ለመቅረፍ የተናጥል እርምጃ ጀምረዋል፡፡ \n\nኒውዮርክ ከተማ ይህን የሚከታተል ልዩ ኃይል ያቋቋመች ሲሆን ባለፈው ዓመት ብቻ 27 ከፍተኛ ጥቃቶች መድረሳቸውን ሰንዳለች፡፡\n\nበኦክላንድ፣ ካሊፎርኒያ ፖሊስ ‹ቻይናታውን› በሚባለው ሰፈር ልዩ ዕዝ (ኮማንድ ፖስት) እስከማቋቋም ደርሷል፡፡\n\nነገሩ እየተስፋፋ በመሄዱ ዕውቅ አሜሪካዊያን ይህ ዘረኝነት ጥቃት እንዲቆም ጥሪ ማቅረብም ጀምረዋል፡፡\n\nእንዴት በአንድ ጊዜ በኢሲያዊያን ላይ ይህ ሁሉ የጥላቻ ጥቃት ሊደርስ ቻለ? ነገሩስ ለምን እያደገ መጣ ለሚለው ብዙ መላምቶች እየተሰነዘሩ ነው፡፡\n\nአሜሪካዊያን በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ሕይወታቸው ስለተመሰቃቀለ ይህን ወረርሽኝ ያመጡት ደግሞ የኢሲያ ሰዎች ናቸው ብለው በተሳሳተ መልኩ መረዳታቸው አንዱ ምክንያት እንደሆነ ይገመታል፡፡\n\nሌሎች ጥናቶች ደግሞ ነገሩን ያባባሱት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ናቸው ይላሉ፡፡\n\nትራምፕ በንግግራቸው ጸረ ቻይና አመለካከቶችና ዘረኝነቶች ይንጸባረቁ ስለነበር፣ በተለይም ወረርሽኙን ‹የቻይና ተህዋሲ› እያሉ ይጠሩት ስለነበር ደጋፊዎቻቸው ኢሲያዊያንን ሲያዩ ደማቸው መፍላት እንደጀመረ ይናገራሉ፡፡\n\nባይደን በበኩላቸው እንዲህ ያሉ ቃላት ጥላቻን ስለሚያነግሱ ማንም ሰው ኮቪድን ‹የቻይና ተህዋሲ› ወይም ‹ኩንግ ፍሉ› በሚል ቃል እንዳይጠቀም የሚከለክል ሕግ ላይ ፈርመዋል፡፡ \n\nይህን ያደረጉትም ነጩ ቤተ መንግሥት በገቡ በመጀመርያው ሳምንት መሆኑ ለነገሩ የሰጡት ቦታ የሚያሳይ ነበር፡፡\n\nበግንቦት 20 ደግሞ ኮቪድ19 ክራይም አክት የተሰኘ ረቂቅ ላይ ፈርመዋል፡፡ \n\nይህ ረቂቅ ለፌዴራል አቃቢ ሕግ በዚህ የኢሲያዊያን ጥላቻ... ", "passage_id": "319eded22c2b190c7d76fdd8974b7a6e" }, { "passage": "«መኪናዬን እያሽከረከርኩ አንድ መንገድ ላይ የትራፊክ መብራት ያዘኝ፤ ቁጭ ብዬ አሰላስል ያዝኩ። ቢጫ ተጠንቀቅ ነው ቀይ ደግሞ ቁም።»\n\nይህች ቅፅበት እግር ኳስን የቀየረች ሆና ተመዘገበች። እንግሊዛዊው አርቢትር ኬኔት ጆርጅ አስተን ይህን ዘዴ ለምን እግር ኳስ ላይ አይተገበርም የሚል ሃሳብ ብልጭ አለለት። \n\nጊዜው በፈረንጆቹ 1960ዎቹ ገደማ፤ 'ኧረ በሕግ' ባይ ያጡ የሁለት እግር ኳስ ቡድን አባላት ቡጢ ገጠሙ፤ ሜዳው የፀብ አውድማ ሆነ። የተጎዱ ወደ ሆስፒታል ተወሰዱ። \n\nይህ የሆነው በፈረንጆቹ 1960 ላይ በቺሊ በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ላይ ነበር።\n\nየሳንቲያጎ አውድማ\n\nበመክፈቻው ጨዋታ ሶቪየት ሕብረትና ዩጎዝላቪያ ጨዋታ ገጠሙ፤ ኧረ ቡጢ ገጠሙ ማለት ይቀላል። \n\nጀርመን እና ጣልያን ያደረጉት ጨዋታም እንዲሁ መፈነካከት የተሞላ ነበር። አጥንቶች ተሰበሩ፤ የአርቢትሩም ፊሽካ የሚሰማ ጠፋ።\n\n'እስቲ ዛሬ እንኳን ሰላማዊ ጨዋታ እንይ' ብለው ሦስተኛውን ቀን የጠበቁ ተመልካቾች በቼኮዝሎቫኪያ እና በስፔን መካከል የተደረገውን ግጥሚያ. . . ይቅርታ. . .ፍልሚያ ሊያዩ ግድ ሆነ፤ አንዳንድ ተጫዋቾች ቡጢው ራሳቸውን አሳታቸው።\n\nአርጀንቲናና ቡልጋሪያም እንዲሁ ሜዳውን ወደ የግብግብ አውድማነት ቀየሩት።\n\n'መች ተለካካንና' ያሉ የሚመስሉት የጣልያንና የቺሊ ብሔራዊ ቡደኖች ታሪክ ፃፉ፤ የሳንቲያጎ አውድማ ተብሎ የሚጠራውን ታሪክ።\n\nቡጢ፣ ካራቴ፣ ጥፊ . . . ብቻ ጨዋታው ደንበኛ በድርጊት የተሞላ (Action) ሲኒማ ሆኖ አረፈው። \n\nጨዋታው በቺሊ 2 ለምንም አሸናፊነት ተቋጨ። አርቢትሩ ግን ከትችት አልተረፉም፤ ኧረ ቡጠም ቀምሰዋል። \n\nዳኛው እንግሊዛዊው ኬኔት ጆርጅ አስተን ነበሩ፤ የቢጫና ቀይ ካርድ ሃሳብ ብልጭ ያለላቸው ግለሰብ።\n\nጊዜው በፈረንጆቹ 1970 ዓ.ም፤ የሜክሲኮ ዓለም ዋንጫ። አርቢትር አስተን 'ግድ የላችሁም አንዲት ሃሳብ አለኝ፤ አድምጡኝ' ሲሉ ተሰሙ።\n\n«እኔኮ የእግር ኳስ ዳኝነት ሳይሆን በሁለት ቦክሰኛ መካከል ያለ አቧቃሽ ነበርኩ» ክስተቱን እንዲህ ነበር የዘከሩት።\n\nኬኔት አስተን\n\n22 ተዋናዮች የሚሳተፉበት ደንበኛ ሲኒማ\n\nአርቢትሩ 1963 ላይ 'አሁንስ በቃኝ ባይሆን ከሜዳ ውጭ ባለው ላግዛችሁ' ብለው የፊፋ ዳኞች ኮሚቴን ተቀላቀሉ። \n\nኮሚቴውን በፕሬዝደንትነት መምራት ዕድሉን ያገኙት አስተን 1966 ላይ ሃገራቸው እንግሊዝ ከአርጀንቲና ስትጫወት የተፈጠረው ነገር ሰቅዞ ያዛቸው። \n\nየዕለቱ አርቢትር ጀርመናዊው ሩዶልፍ ነበሩ፤ ጥፋት ፈፅሟል ያሉትን የአርጀነቲና አምበል ከሜዳ እንዲወጣ አዘዙ፤ አምበሉ ግን አሻፈረኝ አለ።\n\nችግሩ የነበረው ዳኛው ሰፓኒሽ አለመቻላቸው፤ ተጫዋቹ ደግሞ ጆሮው ቢቆረጥ ጀርመንኛም ሆነ እንግሊዝኛ አለመቻሉ ነው። \n\nአስተርጓሚ እስኪመጣ በሚል ለ10 ደቂቃ ያህል ጨዋታው ተቋረጠ። ትርጉሙን የሰሙ የአርጀንቲና ተጫዋቾች ግን 'ፍንክች የአባቢላዋ ልጅ'።\n\nሁኔታው ያልጣማቸው የእንግሊዝ ፖሊሶች ዳኛው ከበው ከሜዳ አሸሿቸው።\n\nየጊዜው የዳኞች ኮሚቴ አለቃ አስተን ወደሜዳ ገብተው ሁኔታውን ካረጋጉ በኋላ ጨዋታው እንዲቋረጥ ሆነ። \n\nይሄኔ ነው ሰውዬው ለዚህ ጉዳይ መላ መዘየድ ግድ ሆኖ የታያቸው፤ የትራፊክ መብራቱ ሃሳብም እውን እንዲሆን መንገድ ተጠረገ። \n\n«እግር ኳስ 22 ተዋናዮች የሚሣተፉበት ዳኛው ደግሞ እንደ አዘጋጅ ሆኖ ማገልገል ያለበት መድረክ ነው» ሲሉ ነበር አርቢትሩ ስለኳስ ያላቸውን እምነት ያንፀባረቁት።\n\n«ስክሪፕት የሌለው፣ መጀመሪያውም መደምደሚያውም ወረቀት ላይ ያልሰፈረ ትዕይንት ሊሆን ይገባል፤ ፍርደ ገምድልነት ግን ሊንፀባረቅበት የማይገባ» ሲሉ አስረግጠዋል። \n\n ", "passage_id": "d01f23cf6de81ef0dff8bd192e163e3f" }, { "passage": "በ2020 በስፖርት ሜዳዎች ላይ የተስተዋሉ የተቃውሞ ምልክቶች\\nፒየር ኤምሪክ ኦባሚያንግ\n\nከሁለት አሥርት ዓመታት በኋላ በ2020 ይህ እውን ሆኖ ታይቷል።\n\nያለፈው የፈረንጆቹ ዓመት [2020] በሁሉም የስፖርት ዘርፎች ያሉ የዓለማችን ስፖርተኛ ዓለምን ለመቀየር ቆርጠው የተነሱበት ነበር።\n\nዘረኝነት ይብቃ ሲሉ ጮኸዋል። ለውጥ ይምጣ ሲሉም ጠይቀዋል።\n\nሴራሊዮናዊው አጥቂ ኬይ ካማራ በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ነው የሚጫወተው። የቀድሞ ክለቡ ከኮሎራዶ ራፒድስ ሚኒሶታ ዩናይትድን ተቀላቅሏል።\n\nጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ እጅ በግፍ መገደሉን ተከትሎ ተቃውሟቸውን ካሰሙ ተጫዋቾች መካከል ነው ካማራ።\n\n\"የልጆቼ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ነው አቋሜን በይፋ እንድገልፅ ያደረገኝ\" ይላል ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ።\n\nኬይ ካማራ\n\nከአሜሪካ አልፎ በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ የሚጫወቱ እግር ኳሰኞች ዘረኝነትን በመቃወም መንበርከክ የጀመሩት በ2020 ነው።\n\nአሜሪካዊቷ የዝላይ ውድድር ክብረ-ወሰን ባለቤት ቶሪ ፍራንክሊን እንደምትለው ስፖርት በሰዎች አስተሳሰብ ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ይችላል።\n\nአልፎም ዘረኝነት ለመዋጋት በሚደረገው ፍልሚያ የስፖርት ሚና የሚናቅ አይደለም ትላለች።\n\n\"እኔ ስፖርት ትልቅ ተፅዕኖ ማምጣት እንደሚችል ነው የማስበው\" ትላለች ፍራንክሊን።\n\n\"በአሜሪካ ባህል ስፖርት ትልቅ ቦታ አለው። በቴሌቪዥን ሰፊ ሽፋን ይሰጠዋል። መገናኛ ብዙሃን ይዘግቡታል። ለዚህ ነው ዘረኝነትን በመቃወም እጃችንን ስናነሳ ለውጥ ልናመጣ እንችላለን የምለው።\"\n\nባለፈው ነሐሴ የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ክለብ ሚልዋውኪ ባክስ ተጫዋቾች ከኦርላንዶ ማጂክ ጋር የነበራቸውን ጨዋታ ጃኮብ ብሌክ የተሰኘው ጥቁር አሜሪካዊ በፖሊስ ጥይት መመታቱን ተከትሎ አንጫወትም ብለው ነበር።\n\nብሌክ በፖሊስ ጥይት በተደጋጋሚ የተመታው በቅርጫት ኳስ ክለቡ ስታድየም አቅራቢያ ነበር።\n\nይህንን ተከትሎ ኤንቢኤ የተባለው የቅርጫት ኳስ አስተዳደር ሌሎችም ጨዋታዎች እንዲሰረዙ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር። \n\nበወቅቱ በአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮች እንዲሰረዙ ተደርጎ ነበር። \n\nየሚያነሳሳ ለውጥ\n\nበአትሌቲክስ ዓለም ትልቁ ውድድር የኦሊምፒክ ጨዋታ ነው። \n\nይህ ውድድር በ2020 ሊካሄድ ዕቅድ ተይዞለት የነበረ ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ይህ ሳይሆን ቀርቷል። \n\nከዚህ ቀደም በነበሩ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በርካታ አትሌቶች ለውጥ ለማምጣት እጃቸውን ወደላይ አንስተው ነበር። \n\nአትሌቶቹ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ለውጦችን የሚጠይቁ ርዕሶችን አንስተዋል።\n\nነገር ግን ባፈለው ዓመት ጥር የኦሊምፒክ ኮሚቴ አዲስ ሕግጋትን አውጥቷል። ሕጉ አትሌቶቹ በኦሊምፒክ መድረክ ላይ ፖለቲካዊ፣ ሐይማኖታዊ፣ አሊያም ከዘር ጋር የተገናኘ መልዕክት ማስተላለፍ አይችሉም ይላል።\n\nኮሚቴው በተለይ ደግሞ በእጅ ምልክት ማሳየትና መንበርከክ ክልክል ነው ብሏል። \n\nፈይሳ ሌሊሳ በሪዮ ኦሊምፒክ\n\nየኦሊምፒክ ሕጎችን አልቀበልም ማለት እንደማይቻልም ኮሚቴው አዲስ ባወጣው መመሪያ ላይ አስቀምጧል።\n\nበ2019 በተካሄደው የፓን አሜሪካን ጨዋታዎች ላይ ተቃውሟቸውን እጃቸውን ከፍ በማድረግ ያሳዩ ሁለት አትሌቶች የ12 ወራት ቅጣት ተላልፎባቸው ነበር።\n\nበኦሊምፒክ ሜዳ ከታዩ ታሪካዊ ተቃውሞዎች መካከል አንዱ አሜሪካዊያኒ ቶኒ ስሚዝና ጆን ካርሎስ በ1968 የሜክሲኮ ኦሊምፒክ ያለ ጫማ፣ በጥቁር ካልሲና ጥቁር ጓንት ሆነው እጃቸውን በማንሳት ተቃውሟቸውን የገለፁበት መንገድ ነው። \n\nአትሌቶቹ በዚህ ድርጊታቸው ዕግድ ተጥሎባቸው ነበር። \n\nሌላኛው ክስተት የታየው በ2016ቱ የሪዮ ኦሊምፒክ ነው። በወቅቱ በማራቶን ውድድር የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት የነበረው ኢትዮጵያዊው ፈይሳ ሌሊሳ ሁለት እጆቹን ወዳላይ በማንሳት በማጣመር የኦሮሞ ተቃውሞን...", "passage_id": "0e82d536aab7c438ef464e3e452a8d81" } ]
4475f876324333f5fe7798bf207f8fcd
a436d05e77ebec652e2df7e593088beb
ኮሚቴው ለፌዴሬሽኖችና የቀድሞ አትሌቶች ድጋፍ አደረገ
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና ለቀድሞ አትሌቶች የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ‹‹የኮቪድ 19 መሰራጨት የዓለምን ስፖርት ቢያጠቃም፣ እንደ ስፖርት እኛም ክፉኛ ብንጎዳም በሥራችን ያሉ ፌዴሬሽኖችን ማገዝ አለብን በሚል ፅኑ አቋም ድጋፉን አድርገናል›› በማለት ትናት መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት ለየፌዴሬሽኖቹ በነፍስ ወከፍ ሃምሳ ሃምሳ ሺ ብር የተሰጠ ሲሆን፤ ለቀድሞ አትሌቶች 200 ሺ ብር እንዲሰጥ መወሰኑን ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል፡፡ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው በስሩ ሃያ አራት ፌዴሬሽኖችና አራት የስፖርት ማህበራት ያሉት ለድጋፉ ከአንድ ነጥብ አራት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉ ታውቋል፡፡ በኦሊምፒክ ኮሚቴው ጽሕፈት ቤት በተካሄደው መግለጫ ላይ የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩርና ምክትል ኮሚሽነሩ አቶ ዱቤ ጅሎ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ባለፈው መጋቢት ወር የሦስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡ አዲስ ዘመን ግንቦት 26/2012
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=33641
[ { "passage": "በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሁሉም ውድድሮች መሰረዛቸው ተከትሎ ክለቦች ካለባቸው የፋይናስ ቀውስ እንዲያገግሙ በማሰብ ፌዴሬሽኑ ለመንግስት አካለት የጠየቀው የገንዘብ ድጋፍ ከምን ደረሰ ?ለወትሮም ደካማ የፋይናንስ መሰረት ላይ የቆሙት ክለቦች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ውድድሮች መሠረዛቸው ለበለጠ የፋይናስ ቀውስ እንዲዳረጉ አድርጓቸዋል። ለተጫዋቾች የወራት ደሞዝ ለመክፈልም ሆነ እንደ ክለብ የመቀጠል አደጋ ውስጥ የሚገኙት ክለቦች ካጋጠማቸው ችግር እንዲያገግሙ በማሰብ የእግርኳሱ የበላይ አካል ፌዴሬሽኑ በስሩ ለሚገኙት ለፕሪምየር ሊግ ሴት እና ወንዶች፣ ከፍተኛ ሊግ ፣ ለአንደኛ ሊግ ክለቦች የገንዘብ ድጎማ ሊያደርግላቸው ይገባል በማለት ለኢፊዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ከሰነድ ጋር የተያያዘ ደብዳቤ ባለፉት ሳምንታት መጠየቁ ይታወሳል። በጎ ምላሽ እንደሚገኝበት ተስፋ የተጣለበት ይህ ጉዳይ እስካሁን መልስ ሳያገኝ መዘግየቱ ክለቦችን የበለጠ አሳስቧል።ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮቻችን ባገኘነው መረጃ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግስት ድጎማ ይገኝበታል የተባለለትን ይህን ጉዳይ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ በሚገባ እየተከታተሉት እንደሆነ የሰማን ሲሆን በቅርቡም የገንዘብ ሚንስቴርም የገንዘቡን ድጋፉን ገቢ እንደሚያደርግ ለክለቦች ለማወቅ ችለናል።በሌላ ዜና በቅርቡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከእግርኳሱ የበላይ አካል ፊፋ የገንዘብ ድጎማ እንዳደረገ ቢገለፅም ፊፋ እስካሁን ለአባል ሀገራቱ ገንዘቡን አከፋፍሎ እንዳልሰጠ ሰምተናል።", "passage_id": "1831fc4bcbe67c056b199633691679ce" }, { "passage": "የኢትዮጵያ ዳኞች እና ታዛቢዎች ሙያ ማኅበር ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ እንዲውል ለጤና ሚኒስቴር የሀምሳ ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍን አበርክቷል፡፡በአለም አቀፍ ደረጃ ስጋት እየሆነ ለብዙዎች ህይወት ማለፍም ጭምር አደጋ እየሆነ የመጣው የኮሮና ኮቪዲ 19 ቫይረስ ሀገራችንም ከገባ ሰንበትበት ብሏል፡፡ ይህን አስከፊ በሽታን ለመከላከል በስፖርቱ ዘርፉ ያሉ ግለሰቦች ድርጅቶች እና ተቋማት ድጋፋቸውን እያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያ ዳኞች እና ታዛቢዎች ሙያ ማኅበርም ለዚህ በሽታ መከላከያ እንዲውል የሀምሳ ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ለጤና ሚኒስቴር ማበርከቱን የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ትግል ግዛው ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግሯል፡፡© ሶከር ኢትዮጵያ", "passage_id": "74102f53973e8d534f354cde864f94d3" }, { "passage": "የውድድሩ አዘጋጅ የሆነው የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን ትናንት ለፌዴሬሽኑ በላከው መልዕክት ውድድሩ ለቀጣዩ አመት መሸጋገሩን አስታውቋል።ይህን ተከትሎም ልምምድ ላይ የነበሩ አትሌቶችና አሰልጣኞችን ከዛሬ ጀምሮ ፌዴሬሽኑ እንደሚያሰናብት ገልጿል።በዓለም አቀፍ ደረጃ ስጋትና ፈተና የሆነው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መስፋፋት ለሻምፒዮናው መራዘም ምክንያት ነው ተብሏል።ኮንፌዴሬሽኑ ሻምፒዮናው ወደ ቀጣዩ ዓመት መተላለፉን ቢያሳውቅም የሚካሄድበትን ትክክለኛ ወር እና ቀን ግን አልገለጸም።ፌዴሬሽኑ በበኩሉ ለቡድኑ አባላት አስፈላጊውን የግብዓትና የሎጅስቲክስ አቅርቦት በማሟላትና ግልፅ ውይይት በማድረግ አትሌቶችና አሰልጣኞቻቸው ያለምንም ችግር ወደየመጡበት እንዲመለሱ እንደሚያደርግም ነው የገለጸው።በትናንትናው ዕለትም ለልዑካን ቡድኑ አባላት በፌዴሬሽኑ የህክምና ባለሙያዎች አማካይነት ስለኮሮና ቫይረስና ተያያዥ ጉዳዮች አጠቃላይ ግንዛቤ በማስጨበጥ፥ ከአትሌቶችና አሰልጣኞች ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠቱንም አብራርቷል።ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!\n", "passage_id": "b8d84220b0cfb54d4a522d31f7d669ca" }, { "passage": "የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖካ) እ.ኤ.አ. በ 2022 ሌሴቶ እንድታስተናግድ ተወስኖ የነበረውን አራተኛውን የአፍሪካ ወጣቶች ውድድር ከሀገሪቱ ነጥቆ ወደ ኢትዮጵያ አዛውሯል፡፡\nሌሴቶ ለውድድሩ በቂ ዝግጅት እያደረገች ባለመሆኑ ውድድሩ ከማሴሩ ወደ አዲስ አበባ መዛወሩን ማህበሩ ስለማሳወቁ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ብሔራዊ ዝግጅት አባል አራያት ራያ ለአል ዐይን እንዳረጋገጡት ኢትዮጵያ ውድድሩን እንድታስተናግድ የተመረጠች ሲሆን ከአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር ጋር በወጪ መጋራት እና መሰል ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡\n“የ 2022 የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች ለኢትዮጵያ አዲስ አበባ ከተማ ተሰጥቷል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ዝግጅት በጥሩ ሁኔታ ለማስተናገድ ቁርጠኛ ነው” ሲል አኖካ በመግለጫው ይፋ አድርጓል፡፡\nውድድሩን እንድታስተናግድ በ2018 ዕድሉ ተሰጥቷት የነበረችው ሌሴቶ በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ላለፉት 2 ዓመታት ምንም ዝግጅት ሳታደርግ ስለመቆየቷ ነው ማኅበሩ የገለጸው፡፡\nከሁለት ዓመታት በኋላ የሚካሔደውን 4ኛውን የወጣቶች ውድድር የተነጠቀችው ሌሴቶ በምትኩ በቂ ዝግጅት በማድረግ ከአራት ዓመታት በኋላ በ2026 የሚካሔደውን 5ኛውን የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች እንድታስተናግድ ተወስኗል፡፡\nየአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች የመላው አፍሪካ ጨዋታዎችን በመተካት በየአራት ዓመቱ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች የሚካሔድ ውድድር ሲሆን ከዚህ ቀደም የተካሔዱትን 3 ውድድሮች ሞሮካ ፣ ቦትስዋና እና አልጄሪያ በቅደም ተከተል አስተናግደዋል፡፡\nኢትዮጵያ ከሁለት ወራት በኋላ በአውሮፓውያኑ ታህሳስ 6 የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር ጉባዔን እንደምታስተናግድም ከአል ዐይን ጋር ቆይታ ያደረጉት በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ብሔራዊ ዝግጅት አባል አራያት ራያ ተናግረዋል፡፡ ለዚህም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ነው የገለጹት፡፡\n", "passage_id": "71ae6a3bf08411890767101849fdbfbd" }, { "passage": "አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ አበረከተ ።የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ3 ሚሊዮን በላይ ብር አበረከተ ።ፌዴሬሽኑ በቀድሞ ሥራ አስፈጻሚ አባላት አማካኝነት በተለያዩ ጊዜያት በተዘጋጁ የገቢ ማሰባሰቢያ ህዝባዊ ሩጫ የተገኘውን ገንዘብ  ነው ትናንት ያስረከበው።ቼኩን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ተረክቧል።ለዚህ አንዱ ተጠቃሽ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበትን አንደኛ ዓመት አስመልክቶ ግንባታው እየተካሄደበት ባለበት አካባቢ በተደረገው ሁሉን ያሳተፈ የሩጫ ውድድርና በተለይ ደግሞ ለሴቶች በተዘጋጀ ሩጫ የተሰበሰበ መሆኑ ነው።የርክክቡ ስነ ስርዓት የተካሄደው ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም 46ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በተጀመረበት ወቅት ነው።የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ቼኩን ባስረከበበት ወቅት እንደገለጸው፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከዳር እስከሚደርስ ፌዴሬሽኑ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል።የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሮማን ገብረስላሴ የቼክ ስጦታውን ተቀብለዋል፡፡ዋና ዳይሬክተሯ ወይዘሮ ሮማን እንደገለጹት ፤ ፌዴሬሽኑ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል።በፌዴሬሽኑ ስም ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል 70 ሚሊዮን ብር ገቢ መደረጉን ያስተዋሱት ወይዘሮ ሮማን፤ የግድቡ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።ፌዴሬሽኑ ለገቢ ማሰባሰቢያ የሚካሄዱ ህዝባዊ ሩጫዎችን በማስተባበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑ ታውቋል-(ኢዜአ) ።", "passage_id": "641efd7ae9b34a4d70cb91b6609164ad" } ]
34478a826f311fbf640d8d4970bff80a
b870ed8398d3514062288bfaf0e31a71
አበረታች ቅመም የተጠቀመው አትሌት ቅጣት ተጣለበት
የኢፌዴሪ ብሄራዊ የጸረ አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት የተከለከለ ንጥረ ነገር መጠቀሙ በተረጋገጠበት አትሌት ላይ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ የሌሎች ሁለት አትሌቶች ጉዳይም እየተጣራ መሆኑን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡ የስፖርት አበረታች ንጥረ ነገር በመጠቀም በውድድር ላይ መሳተፉ በተደረገበት ማጣራት የታወቀው አትሌት የአራት ዓመታት እገዳ ተጥሎበታል፡፡ የቅጣት ውሳኔው የተላለፈበት አትሌት ወንደሰን ከተማ የሚባል ሲሆን፤ እአአ ታህሳስ 01/2019 በቻይና በተካሄደውና ዓለም አቀፍ ደረጃ ባለው ሻንዛቢ ማራቶን በግሉ ተሳትፎ ነበር፡፡ በውድድሩ ወቅት በተወሰደው የደምና የሽንት ናሙና በመጠርጠሩ ምክንያት ላለፉት አምስት ወራት የአበረታች ቅመም መጠቀም አለመጠቀሙን ለማወቅ ማጣራት ሲደረግበት መቆየቱን ጽህፈት ቤቱ የላከው መግለጫ ያሳያል፡፡ አትሌቱ በተደረገበት ተጨማሪ የማጣራት ተግባተርም (Cahinone) የተባለና በስፖርት የተከለከለውን አበረታች ቅመም መጠቀሙ ተረጋግጧል፡፡ በዚህም የኢፌዴሪ ብሄራዊ የጸረ አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት በአትሌቱ ላይ አስተማሪ የሆነ እርምጃ ወስዷል፡፡ በቅጣቱም የአትሌቱ ጥፋት የመጀመሪያ ደረጃ መሆኑን ከግምት በማስገባት እአአ ከየካቲት 01/2020-የካቲት 01/2024 ድረስ በየትኛውም ሃገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ተሳታፊ እንዳይሆን የሚያደርገውን እገዳ ጥሎበታል፡፡ ከእገዳው ባሻገር በቻይናው ውድድር ያስመዘገበው ውጤት እንዲሁም ሽልማቱ እንዲሰረዝም ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑ ታውቋል፡፡ ጽህፈት ቤቱ ሌሎች ሁለት አትሌቶች ላይም ማጣራት እየተደረገ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ አትሌቶቹ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ በግላቸው ተሳትፎ ያላቸው ሲሆን፤ የተከለከሉ የስፖርት አበረታች ንጥረ ነገር መውሰዳቸው ከጥርጣሬ ገብቷል፡፡ በመሆኑም ጉዳዩ ተጣርቶ ተጠቃሚነታቸው ከተደረሰበት የስም ዝርዝራቸውንና የቅጣት ውሳኔያቸው ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አትሌቶች ራሳቸውን ከኮሮና ወረርሽኝ እንዲሁም ከአበረታች ንጥረ ነገር እንዲጠብቁም ጽህፈት ቤቱ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡ ወቅቱ የዓለም ህዝብ ከወረርሽኙ ጋር ግብ ግብ የገጠመበት እንደመሆኑ ውድድሮች መቋረጣቸው ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በሃገሪቷ በየደረጃው የሚደረገው የስፖርት አበረታች ቅመሞች ክትትልና ቁጥጥር ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ አበረታች ቅመሞቹን መጠቀሙ የተረጋገጠበትም ይሁን በተለየ መልኩ የህግ ጥሰት በሚፈጽሙ አትሌቶችና ከጀርባ በመሆን በሂደቱ በሚሳተፉ ግለሰቦች ላይ ጽህፈት ቤቱ የእርምት እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁሟል፡፡ አዲስ ዘመን ግንቦት 30/2012ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=33864
[ { "passage": "ልዩ ፈቃድ ከሌለ በስተቀር እንዳይዘዋወርና እንዳይሸጥ በሕግ ክልከላ የተጣለበትን የኮኬይን አደንዛዥ ዕፅ በማዘዋወር ወንጀል በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ክስ ተመሥርቶበት የነበረው ናይጄሪያዊ በጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ፡፡ሚስተር ማክ ኡጎ ኢዜ የታባለ ናይጄሪያዊ የኮኬይን ዕፅ ለማዘዋወር በማሰብ መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ከብራዚል ሳኦፖሎ ወደ አገሩ ናይጄሪያ ሌጎስ ለመሄድ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለትራንዚት ባረፈበት ወቅት፣ በፀጥታ ሠራተኞች በተደረገበት ፍተሻ መያዙ በክሱ ተገልጿል፡፡ የወንጀል ድርጊቱም በሰውና በሰነድ ማስረጃ ስለተረጋገጠበት፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ወንጀል ችሎት በስምንት ዓመታት ከስድስት ወራት ጽኑ እስራትና በአሥር ሺሕ ብር እንዲቀጣ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ፍርደኛው በውስጥ ሱሪው (ውስጥ) 60 ጥቅልና በሆዱ 37 ጥቅል በድምሩ 97 ጥቅሎች ወይም 2,099.96 ግራም ኮኬይን አደንዛዥ ዕፅ ደብቆ ለማሳለፍ ሲል መያዙን፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ በማስረጃ ማረጋገጡን ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ገልጿል፡፡ ግለሰቡ መርዛማ ዕፆችን ማዘዋወርን በሚመለከት በወጣው አዋጅ ቁጥር 525(1) ሥር የተደነገገውን መተላለፉ በመረጋገጡ ቅጣቱ ተጥሎበታል፡፡ የፈጸመው ድርጊት በፍርድ ቤት ተነቦለት ድርጊቱን መፈጸሙን በማመኑ ፍርድ ቤቱ የዓቃቤ ሕግን፣ የሰውና የሰነድ ማስረጃ መስማት ሳይጠበቅበት ጥፋተኛ በማለት የጠቀሰውን የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡  ", "passage_id": "2397e4ac672d78f7c6388c0f23cc9bef" }, { "passage": "አንድ ታዋቂ ኬንያዊ አትሌት የዶፒንግ ምርመራ ሊያደርጉ ከመጡ የጸረ-ዶፒንግ ባለሙያዎች ለማምለጥ ካምፑን ጥሎ ጠፋ፡፡\nየጸረ-ዶፒንግ ቡድን አባላቱ ምዕራብ ኬኒያ ካፕሳቤት በሚባል አካባቢ ወደ ሚገኝ አንድ የአትሌቲክስ ልምምድ ካምፕ በድንገት ነበር ያመሩት፡፡\nከጥቂት ቆይታ በኋላ ወደ ካምፑ የመጡትን እንግዶች ማንነት ያጣራው አንድ ስመ-ጥር አትሌት በካምፑ ከነበረበት ቤት በመስኮት ዘሎ ከወጣ በኋላ የግቢውንም አጥር በመዝለል እግሬ አውጪኝ ብሎ አምልጧል፡፡\nየኬኒያ አትሌቲክስ ዝነኛ ከመሆኑ ውጭ ማንነቱን ያልጠቀሰው አትሌቱ ቅጣት እንደሚጠብቀው ተገልጿል፡፡\nየሀገሪቱ አትሌቲክስ ከፍተኛ ባለስልጣን ባርናባ ኮሪር እንዳሉት ከአበረታች እጽ ጋር በተያያዘ የጥፋተኝነት ስሜት ያላቸው አትሌቶች ከመርማሪዎች ለማምለጥ ከመሞከር ውጭ አማራጭ የላቸውም፡፡\nባለፉት 5 ዓመታት 60 የሀገሪቱ አትሌቶች ከዶፒንግ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ቅጣቶች ተጥለውባቸዋል፡፡ባለፈው ሳምንት እንኳን ከ20 ዓመት በታች የ800 ሜትር ሻምፒዩኑን አልፍሬድ ኪፕኬተርን ጨምሮ ሁለት የኬንያ አትሌቶች ከዶፒንግ ጋር በተያያዘ እገዳ ተጥሎባቸዋል፡፡\n\nምንጭ፡- ቢቢሲ\n", "passage_id": "a0d415db8ad93063bcbfc80be163a64f" }, { "passage": "የክልል ክለቦች ሻምፒዮና አወዳዳሪ አካል ባለፈው ሐሙስ በተካሄደው የሎጊያ ሰመራ እና ሐረር ቡና ጨዋታ ላይ ከሥነ-ምግባር ውጭ የሆነ ተግባር አሳይተዋል ባላቸው አካላት የጥፋት ውሳኔ አስተላልፏል።በዚህም መሰረት ሰመራ ሎጊያ ከውድድሩ እንዲታገድ ሲወሰን በርከት ባሉ የቡድኑ አባላት ላይ ደግሞ የቅጣት ውሳኔ እና ማስጠንቀቅያ ሰጥቷል። በተጠቀሰው ጨዋታ ላይ ረብሻው እንዲረጋጋ እና ተጫዋቾቻቸው ከፀብ እና ከድብደባ ድርጊት እንዲቆጠቡ ጥረት አድርገዋል የተባሉት የሰመራ ሎግያ አሰልጣኝ መሐመድ ሁሴን በአወዳዳሪው አካል ምስጋና ደርስዋቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ የሰመራ ሎጊያን ውሳኔ በመቃወም በዛሬው ዕለት በነበረበት ጨዋታ ላይ ያልተገኘው ሌላው የአፋር ክልል ተወካይ አሳይታ ከተማም በፎርፌ እንዲሸነፍ አወዳዳሪው አካል ወስኗል። በዚህም አቃቂ ማዞርያ ጨዋታውን በፎርፌ ማሸነፍ ችሏል።ሌላው ውሳኔ የተሰጠበት ጉዳይ ባለፈው ሳምንት ካለ አግባብ ከውድድር ታግጃለው በሚል ቅሬታ አቅርቦ በነበረው ቦዲቲ ከተማ ሲሆን አወዳዳሪው አካል ጉዳዩን ከመረመረ በኃላ ወደ ውድድር እንዲመለስ ወስኗል።ለበለጠ መረጃ አወዳዳሪው አካል ጥፋተኛ ናቸው ላላቸው አካላት የሰጠው የውሳኔ ደብዳቤ ይመልከቱ።", "passage_id": "aefbc3425af4463aed43c8a8bafe6b7c" }, { "passage": "ስፖርተኞች ህገ ወጥ ኃይል-ሰጪ መድኃኒቶችን እንዳይጠቀሙ የወጣውን ህግ ኬንያ አለማክበሯን፣ ዓለማቀፉ የፀረ-ኃይል-ሰጪ መድኃኒት መሥሪያ ቤት አስታወቀ።በዚህም ምክንያት ሪዮ ውስጥ በሚካሄደው የዘንድሮው የበጋ ኦሎምፒክስ ጨዋታዎች የመካፈል ዕድሏ አስጊ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ። የኬንያ ኦሎምፒክስ ኰሚቴ ግን፣ \"ውሳኔውን ይግባኝ እላለሁ\" ብሏል። ", "passage_id": "a692d5f0abc51e358e792660441bc92b" }, { "passage": "ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በቅርቡ ከዳይመንድ ሊግ ውድድር የ5ሺ ሜትር እንደሚሰርዝ ማሳወቁ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎም በተለይ በርቀቱ የታወቁት እና ስኬታማ አትሌቶችንም ያፈሩት የምሥራቅ አፍሪካ ሃገራት ኢትዮጵያ እና ኬንያ በፌዴሬሽኖቻቸው በኩል ተቃውሟቸውን በደብዳቤ አስታውቀዋል። ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውሳኔውን የተመለከተ መግለጫ በተጠናቀቀው ሳምንት መጨረሻ አውጥቷል። መግለጫውም፤ ዓለም አቀፉ ማህበር ከዚህ ቀደም በዳይመንድ ሊግ ይካሄድ የነበረውን የ10ሺ\nሜትር ሩጫ እንዲቀር ያደረገ መሆኑን አስታውሷል። እአአ ከ2020 ጀምሮም የኢትዮጵያ አና\nየአፍሪካ ባህላዊ ሩጫ የሆነውንና በርካታ አትሌቶችም ለራሳቸውና ለሃገራቸው አኩሪ ድል ያስመዘገቡበትን የ5ሺ\nሜትር ሩጫ ከውድድሩ እንደሚቀንስ ማስታወቁ እንደማይደግፍ ነው ያሳየው። የ10ሺ እና 5ሺ ሜትር\nሩጫዎች ከውድድር ውጪ መሆን በቀጣይ በማራቶን ለመወዳደር የሚፈልጉ አትሌቶችን መሸጋገሪያ በማሳጣት ችግር እንደሚፈጥር በመግለጫው ተጠቁሟል። ከ1ሺ500\nሜትር በቀጥታ ወደ ማራቶን ሩጫ ማደግም፣ በዕድሜ እና በተክለ ሰውነት ላይ የጎላ ተጽእኖ ስለሚያሳድር ጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ያሳሰበ ነበር። ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጓል። በዚህም የአፍሪካ አትሌቶች የሚደምቁበት ርቀት ከውድድር ውጪ መሆን ሃገሪቷን እና አትሌቶችን እንደሚጎዳ እንዲሁም በአትሌቲክስ ስፖርት የሚኖረው ተሳትፎም ተጽእኖ የሚያሳድር መሆኑ ተመልክቷል። በመሆኑም ዓለም አቀፉ ማህበር ጉዳዩን በጥሞና እንደገና እንዲያየው አስፈላጊውን ግፊት እንዲያደርግ ወስኗል። በዚህም መሰረት ኮሚቴው በዓለም ደረጃ ስመ ጥር የሆኑ እና በሩጫው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ አትሌቶችን ያካተተ ሃገር አቀፍ ግብረ ኃይል አቋቁሟል። የኮሚቴው አባላትም ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ፣ አትሌት ገብረእግዚአብሄር ገብረማርያም፣ አትሌት ብርሃኔ አደሬ፣ አትሌት መሰረት ደፋር እና አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ናቸው። ይህ ግብረ ኃይልም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር፣ ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ከአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን፣ ከዞን 5 አትሌቲክስ እና ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች፣ከአፍሪካ ህብረት፣ መንግሥታዊ አካላት እንዲሁም መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ የውሳኔ ሃሳቡን የማስቀየር ኃላፊነት ተሰጥቶታል። ጉዳዩንም በቅርበት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ እንዲሁም ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ዋና ሱፐር ኢንቴንዳንት ደራርቱ ቱሉ የሚከታተሉት ይሆናል፡፡ ይህ እንቅስቃሴ ግቡን እንዲመታና የ5ሺ\nእና 10ሺ ሜትር ውድድሮች በቀድሞ ሁኔታ እንዲቀጥሉም የሚመለከታቸው አካላት ለተቋቋመው ግብረ ኃይል አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግም ጥሪ ቀርቧል።አዲስ ዘመን መጋቢት 23/2011በብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "f3014b984b2bfa1bc8ff41d75b3a30b1" } ]
a73b20050af93ea17c6eeff0ce0521b6
24c212eb0cbc2bfc4fa9a396312bd847
ኮቪድ-19 በስፖርት ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ የሚያጠና ኮሚቴ ተቋቋመ
የዓለምን ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታ ወደተለየ አቅጣጫ ያዞረው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በስፖርቱ ዓለም ያሳደረው አሉታዊ ተፅዕኖ ተዘርዝሮ የሚልቅ አይደለም። አንዳች ውድድር በዓለም ላይ እንዳይኖር ከማስገደድ ባለፈ የስፖርቱን ዓለም ሽባ አድርጎታል። ብዙ ታቅዶባቸው፣ብዙም ተለፍቶባቸው ለዓመታት በዝግጅት ላይ የነበሩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች በትልቅ ኪሳራ የሚካሄዱበት ጊዜ እንዲራዘም ግድ ብላል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በዓለም ዙሪያ ከተንሰራፋ ወዲህ በግለሰብ ደረጃ ካልሆነ በስተቀር የትኛውም የስፖርት እንቅስቃሴ ተገድቦ እንደቆየ ይታወቃል። የቫይረሱ ስርጭት በዓለም ዙሪያ እያሻቀበ መሄዱን ተከትሎም ታላላቅ ስፖርታዊ ውድድሮች በቅርቡ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው ይመለሳሉ የሚል ተስፋ የለም። ይሁን እንጂ የዓለማችን ታላላቅ የእግር ኳስ ሊጎች በዝግ ስታድየምም ቢሆን የውድድር ዓመቱን ቀሪ መርሐግብሮች ለማጠናቀቅ በቅርቡ ወደ ውድድር እንደሚመለሱ ተስፋ መስጠታቸው አልቀረም። የዓለም ጤና ድርጅት የሕክምና ባለሙያዎች ግን ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በትልቅ ደረጃ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው እንዳይመለሱ ምክራቸውን ለግሰዋል። በዓለማችን ብሎም በአገራችን በፍጥነት እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት የስፖርት ቤተሰቡ መደበኛ እንቅስቃሴውን ገቶ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ ከጀመረ ሰነባብቷ። የስፖርት ቤተሰቡ ወረርሽኙን ለመከላከል ግንዛቤ ከመፍጠር እስከ ደም ልገሳ፤ ከቁሳቁስ እስከ ገንዘብ ድጋፍ በማድረግ አጋርነቱን አሳይቷል ፤ በማሳየት ላይም ይገኛል። ወረርሽኙ በዓለም ላይ ከተከሰተና ከተስፋፋ ወዲህ የስፖርቱን ዘርፍ ክፉኛ የጎዳው ሲሆን የአገራችንን ጨምሮ በዓለም ላይ በርካታ ታላላቅ ውድድሮች እንዲቆሙ አስገድዷቸዋል። በተለይም ወረርሽኙን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በተወሰዱ እርምጃዎች ስልጠናዎች፣ ውድድሮች ቁመዋል ፤ ስፖርተኛው እና የስፖርት ቤተሰቡ ከፍተኛ የሆነ የስነ ልቦና እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አጋጥሟቸዋል ። በርካታ የስፖርት ክለቦች የመፍረስ አዳጋ ተደቅኖባ ቸዋል፤ አንዳንዶቹም ለስፖርተኞች ወርሃዊ ደመወዝ እስከ መከልከል ደርሰዋል። በመሆኑም የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በወረርሽኙ ወቅት እና ከወረርሽኙ በኋላ ስፖርቱ እንዴት ወደ ነበረበት መመለስ ያስችላል የሚለውን የሚያጠና እና ለመንግሥት የሚያቀርብ ጠንካራ ኮሚቴ መቋቋሙን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጅሎ መናገራቸውን የተቋሙ ይፋዊ የፌስ ቡክ ገፅ ላይ ተዘግቧል። የተቋቋመው ኮሚቴ አብይ እና ቴክኒካል ኮሚቴ ያለው ሲሆን አብይ ኮሚቴው በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ጣሰው የሚመራ ይሆና። ቴክኒካል ኮሚቴው ደግሞ በአቶ ዱቤ ጅሎ እንደሚመራ ታውቋል። ኮሚቴው አጠቃላይ የኮሮና ወረርሽኝ በአገራችን ስፖርት ላይ እያሳደረ ያለውን ጫና እና መፍትሔዎችን በማጥናት ሰነዱን ለመንግሥት የሚያቀርብ ይሆናል። በጥናቱም የሌሎች አገራት ተሞክሮ ምን እንደሚመስል ተካቶ እንደሚቀርብ አቶ ዱቤ አብራርተዋል። ጥናቱን መሠረት በማድረግ መንግሥት ስፖርቱ ለአገራችን ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ፋይዳ ግምት ውስጥ በማስገባት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምክትል ኮሚሽነሩ ገልፀዋል ።አዲስ ዘመን ግንቦት 27/2012ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=33697
[ { "passage": "በ1990 ዓ.ም. በአገር አቀፍ ደረጃ የወጣው የስፖርት ፖሊሲ ሕዝቡ በሚኖርበት፣ በሚማርበትና በሚሰራበት አካባቢ ስፖርት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባው ይደነግጋል። ህብረተሰቡ በሚኖርበት፣ በሚማርበትና በሚሠራበት አካባቢ በስፖርት እንቅስቃሴ ተሳታፊ የሚሆንበት መንገድ መመቻቸት እንዳለበት ያስቀምጣል። ከመንግሥት ተቋማት እስከ ታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል በየደረጃው ኅብረተሰቡ ለሚሳተፍባቸው መድረኮች ትኩረት በማድረግ ልሂቃን (ኤሊቶች) የሚፈጠሩበት ዕድል እንዳለም ፖሊስው ያመለክታል። በሌላ በኩል አምራች ዜጋ ለመፍጠር፣ የኅብረተሰቡ ማኅበራዊ ግንኙነት የሚዳብርበት፣ ከዚያም ሲያልፍ ዜጎች ጤንነታቸውን ለመጠበቅና ለመዝናናት እንዲሁም አካላቸውን ለማጎልበትና አዕምሯዋቸውን ለማበልጸግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ታምኖበታል። የስፖርት ፖሊሲውን መሰረት በማድረግ የሕብረተሰቡን ተሳትፎ በማስፋት ረገድ እየተሄደበት ያለው መንገድ አጥጋቢ አለመሆኑ ተደጋግሞ ይነሳል። በመንግስትም ሆነ በህብረተሰቡ በኩል እንደሚነሳው «ሕዝቡ በሚኖርበት፣ በሚማርበትና በሚሰራበት አካባቢ የስፖርት እንቅስቃሴ ማድረግ አለበት»በሚል በፖሊሲ ደረጃ ቢቀመጥም ወደ ተግባር ከመለወጥ አንጻር ከፍተኛ ክፍተት መኖሩ ይታመናል። በተለይ በመንግስትና በግል ተቋማት ህብረተሰቡ በሚሰራበት ቦታ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ እድል በመፍጠር ረገድ የፍላጎትም ሆነ የግንዛቤ ክፍተቶች እንዳሉ በስፖርቱ አዋቂዎች በኩል ይነገራል። በተቋማት የስፖርቱን ማህበራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳን በመረዳት ስፖርታዊ ክንውኖችን የማዘጋጀት ባህሉ በእጅጉ አናሳ መሆኑም አብሮ ይነሳል። መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በኩል የስፖርቱን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ በመረዳት የስፖርት ፌስቲቫል የማዘጋጀት ልምድ ባለቤት የሆኑ ተቋማት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። ከእነዚህ ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል። የቤተሰብ ስፖርት ፌስቲቫሉ ዘንድሮ ለ5ኛ ጊዜ ከመስከረም 26 ጀምሮ ለአስር ቀናት ያክል «የኋላውን እያደስን የወደፊቱን ለመገንባት እንተጋለን »በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል። የኮርፖሬሽኑ የቤተሰብ ስፖርት ፌስቲቫል በ2002 ዓ.ም እንደተጀመረ መረጃዎች ያመላከታሉ ። ኮርፖሬሽኑ በሚያከናውነው የስፖርት ፌስቲቫል፤ አገር አቀፍ የስፖርት ፖሊሲውን ተግባራዊ ከማድረግ ባሻገር በሰራተኞች መካከል መቀራረብን እንደሚፈጥር ታምኖበታል። የስፖርት ፌስቲቫሉ ጤናው የተጠበቀና አምራች ዜጋን በማፍራት ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ማሳያ መሆኑም ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የቤተሰብ ስፖርት ፌስቲቫል አስተባባሪ አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጥንፉ ሙጬ፤ የስፖርት ፌስቲቫሉ በአገር አቀፍ ደረጃ የወጣውን የስፖርት ፖሊሲ መሰረት በማድረግ የተጀመረ መሆኑን ይናገራሉ። ህዝቡ በሚኖርበትና በሚሰራበት አካባቢ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን ማጉላት እንደሚችል መሰረት ባደረገ መልኩ ተቋሙ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም ይገልጻሉ። እንደ አቶ ጥንፍ ገለጻ፣ ስፖርት በተለይ ደግሞ በሰራተኞች መካከል እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ፣ ጤናው የተጠበቀና አምራች ዜጋን ለማፍራት እንዲቻል፣ የሰራተኞችን አንድነት ለማጠናከር ፋይዳው ግዙፍ መሆኑን ያብራራሉ። በመሆኑም ኮርፖሬሽኑ የቤተሰብ ስፖርት ፌስቲቫሉን እነዚህን ውጤቶች መሰረት በማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እንደጀመረ ይናገራሉ። «ፌስቲቫሉ በየሁለት ዓመቱ ቢደረግ የበለጠ ዝግጅት ተደርጎ በጠንካራና ባማረ ሁኔታ ማከናወን ይቻላል »በሚል አስተዳደሩ ወስኖ በየሁለት ዓመቱ ሊካሄድ እንደቻለም ያስታውሳሉ። የኮርፖሬሽኑ የቤተሰብ ስፖርት በዚህ መልኩ በመቋቋም ባለፉት አስር ዓመታትን መጓዝ ችሏል። በስፖርት ክንውኑ ተቋሙ ውጤታማ መሆን ችሏል? ስንል ጥያቄ ሰንዝረናል። አቶ ጥንፍ ባለፉት አስር ዓመታት በነበረው ስፖርታዊ ክንዋኔ ተቋሙ ውጤታማ መሆኑን ይገልጻሉ። በመጀመሪያ ደረጃ አመራሩና ሰራተኛው መልካም የሆነ ግንኙነት እንዲፈጥሩ አድርጓል። እያደረገም ይገኛል። በአካልም፣ በአዕምሮም የበለፀገ ሰራተኛና አመራር እንዲኖር አስችሏል። ጤናማ ሰራተኛ በመፍጠር ረገድ ውጤት ማምጣት ተችሏል። መታወቅ ያለበት ያለ ጤናማ ሰራተኛ የኮንስትራክሽን ስራ የሚታሰብ እንዳልሆነም ያብራራሉ። የስፖርት ፌስቲቫሉ ሠራተኛውም ሆነ አመራሩን የበለጠ የሚያቀራርብ፣ ሠራተኛው ትርፍ ጊዜውን አዕምሮውንና አካላዊ ብቃቱን የሚያዳብርበት፣ ለተቋሙ ያለውን ወገናዊነት የሚያሳይበት፣ በሌሎች ፕሮጀክቶች ከሚገኙ ሠራተኞች ጋር ለመቀራረብና ለመተዋወቅ መንገድ እየከፈተ እንደሚገኝ ይገልጻሉ። እንደ አቶ ጥንፍ ማብራሪያ፤ የዘንድሮ መድረክ ከእስከ ዛሬው ለየት የሚያደርገው የተሳታፊነቱን ኮታ ለአመራሩ አንድ ሶስተኛውን በመስጠት ዋና ሥራ አስፈጻሚውን ሳይቀር ተሳታፊ ማድረጉ ነው። ስፖርት ፌስቲቫሉ ለአመራሩና ለሰራተኛው እኩል እድል ከመስጠት ባሻገር፤ በሁለቱ አካላት መካከል መቀራረብ እንዲፈጠርና የበለጠ ቀረቤታን መፍጠር እንዲያስችል ነው። ይህን በተግባርም ለመመልከት ተችሏል። የዘንድሮው ውድድር ሴቶችን የበለጠ ተሳታፊ እንዲሆኑ አድርጓል። በመድረኩ ያለፉት ዓመታት ጉዞ ሴቶች ቡድን አልነበራቸውም፤ ዘንድሮ ሁለት ቡድኖች ተቋቁመው በመረብ ኳስና በጠረጴዛ ቴኒስ ስፖርቶች ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ተደርጓል። «የዘንድሮው ፌስቲቫል ልዩ ገጽታው የለውጥ አስተሳሰቦችን ለማስረጽ ጥረት መደረጉ ነው። በውድድሩ ያሉትን ቡድኖች ስያሜን በዚህ ሁኔታ እንዲቃኙ የተደረገ ሲሆን ስያሜዎቹም አሸናፊ፣ ብቁ፣ ታዋቂ፣ ድንቅ፣ ባለራዕይ እና ተስፋ በሚል እንዲሰየሙ ተደርጓል›› ያሉት አስተባባሪው ከዚህ በተጨማሪም ቀደም ሲል ዘርፎች በቡድን ተደራጅተው እርስ በዕርስ የሚያደርጉት ውድድር እንደነበር ተናግረዋል። አደረጃጀቱ እንደ ኮርፖሬሽን ውህደት ባለማምጣቱ አዲስ አደረጃጀት በመፍጠር ወድድሩ እየተካሄደ ሲሆን፤ በመድረኩ የበለጠ መቀራረብና ተቋማዊ ስሜት መፍጠር እንደተቻለ በውድድሩ የአምስትና ስድስት ቀናት ቆይታ ወቅት ለመታዘብ ተችሏል። የስፖርት ፌስቲቫሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቋማዊ ፋይዳውን እያሳደገ መምጣቱን የ5ኛው የቤተሰብ ስፖርት ውድድር እያሳየም ይገኛል። አቶ ጥንፍ ኮርፖሬሽኑ ግዙፍና በርካታ ፕሮጀክቶች ያቀፈ እንደመሆኑ በስፖርት ፌስቲቫሉ ሁሉም ፕሮጀክቶች ተሳታፊ እንዲሆኑ በመስራት የስፖርቱን ግዙፍ ፋይዳ በተቋሙ ምሉእ እንዲሆን ለማድረግ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም አስቀምጠዋል። በ5ኛው የኮርፖሬሽኑ የቤተሰብ ስፖርት ሲሳተፍ ያገኘናቸው በኮርፖሬሽኑ የፋሲሊቲ ሰራተኛ የሆኑት አቶ ዜናው ደነቀው በበኩላቸው፤ የስፖርት ክንውኑን እንደ ኮርፖሬሽኑ ሁሉ ሌሎች ተቋማት ተግባራዊ ማድረግ ቢችሉ ያለውን ፋይዳ ይናገራሉ። «በእኛ ተቋም ያለውን ተሞክሮ በሌሎች የመንግስትና የግል መስሪያ ቤቶች ተግባራዊ ማድረግ ቢቻል፤ በአገር አቀፍ ደረጃ ተጠቃሚ መሆን ይቻላል። ከስፖርቱ የሚገኘውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ማግኘት ይቻላል። በተጨማሪም ኢሊት ስፖርተኞች የሚፈሩበትን አጋጣሚ በማስፋት ረገድ የራሱ የሆነ ድርሻ ይኖረዋል። የአገራችንን ስፖርት በማሳደግ ረገድም የመንግስት ተቋማት ድርሻቸውን እንዲወጡ አጋጣሚውን መፍጠር ይቻላል» ሲል ያብራራል። በኮርፖሬሽኑ የቤተሰብ ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ከአሰልጣኝነት እስከ ዳኝነት የተሻገረ ተሳትፎን ከመጀመሪያው ጀምሮ ሲያደርጉ እንደነበረ የገለፁልን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሰራተኛ የሆኑት አቶ አለማየሁ ገብሬ፤ የኮርፖሬሽኑ ተሞክሮን ሌሎች ተቋማት መውሰድ ቢችሉ ያለውን ነጥብ በማሳት ተመሳሳይ ሃሳብ ይጋራሉ። የቤተሰብ ስፖርቱን ከመጠንሰስ እና ቀጣይነት እንዲኖረው ከማድረግ አካያ በተቋሙ የነበሩና ያሉ አመራሮች ትልቅ ድርሻ እንደነበራቸውም ይናገራሉ። የኮርፖሬሽኑ አመራሮች የስፖርት ፌስቲቫሉ ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ከማደርግ አኳያ ያሳዩት ቁርጠኝነት በተለይ ደግሞ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ትልቅ ስራን መስራታቸውን ያስረዳሉ። አቶ አለማየሁ ዋና ስራ አስፈፃሚው ስፖርታዊ ክንውኑ ቀጣይነት ኖሮት በጠንካራ መስመር እንዲጓዝ ከመስራት ባሻገር፤ በውድድሩ ተጫዋች በመሆን የስፖርቱ ተሳታፊ መሆናቸው የሚያስመሰግናቸው መሆኑን ይገለጻሉ። ስፖርቱ ትኩረት እንዲያገኝ ከማድረግ አኳያም አመራሩ ያሳየው ቁርጠኝነት በሌሎች ተቋማት እንደ አርዓያ ሊወስዱት ይገባል ባይናቸው። ኮርፖሬሽኑም በየሁለት ዓመቱ ይህ የስፖርት ባህል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ እንደሚገባው ያስቀምጣሉ። በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የቤተሰብ ስፖርት ፌስቲቫል ተሞክሮ በሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት መውሰድ ቢቻል ዘርፈ ብዙ ውጤቶች እንደ አገር ማትረፍ እንደሚቻል መመስከር ይቻላል። ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በህብረተሰቡ ዘንድ ትኩረት እንዲሰጠው ፖሊሲ ከመቅረጽ ባሻገር ተግባራዊ እንዲሆን እንደ ኮርፖሬሽኑ ሌሎች ተቋማት መስራት አለባቸው።አዲስ ዘመን  ረቡዕ ጥቅምት 5/2012ዳንኤል ዘነበ ", "passage_id": "6d84cfd7c86d1084995b22e46a54eca8" }, { "passage": " ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ2012 ማብቂያ በጃፓን፣ ቶኪዮ ለሚካሄደው ኦሊምፒክ የሚደረጉ ዝግጅቶችን ለማስተባበር ከተቋቋመ ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር ተወያይተዋል። ብሔራዊ የኦሊምፒክ ኮሚቴው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዝግጅታቸውን ባብራሩበት ወቅት፣ ዓላማቸው ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ለውድድር መላክ ብቻ ሳይሆን፣ በድል እንዲመለሱም ማገዝ እንደ ሆነ አስታውቀዋል።የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለ2020 ኦሊምፒክ ዝግጅት ለኦሊምፒክ ቡድኑ ገቢ ማሰባሰቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የሚታደሙበት ቴሌቶን ሊካሄድ አስቧል፡፡ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከትናንት በስቲያ‹‹ከቶኪዮ እስከ ቶኪዮ›› በሚል ርዕስ ለስፖርት ጋዜጠኞች ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረከ ላይ ፕሬዚዳንቱ ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ተሳትፎ አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነም ገልፀዋል።ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ እንደገለጹት ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ቀድሞ ከነበረው በተለየ መልኩ ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ ነው። ዝግጅቱን የተሟላ ለማድረግ የተለያዩ ኮሚቴዎችን በማዋቀር የገቢ ማሰባሰብ ስራ እየተሰራም ይገኛል፡፡ በቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ የሚመራ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ መዋቀሩንና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚገኙበት ቴሌቶን እንደሚያዘጋጅም ዶክተር አሸብር ጠቁመዋል።የመንግስት የልማት ድርጅቶችና ባንኮች በኦሊምፒክ ውድድሩ አሻራቸውን ያሳርፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም የተናገሩት የኮሚቴው ፕሬዚዳንት ባለሀብቶች እያደረጉት ያለውን ድጋፍ አጠናከረው እንዲሚቀጥሉም ተስፋቸውን ገልፀዋል፡፡በቶኪዮ ኦሊምፒክ ለሚያሸንፉ አትሌቶች ከከዚህ ቀደሙ የላቀና ዳጎስ ያለ የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት እንደሚኖር ዶክተር አሸብር ገልጸዋል። ይህንን አገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት የመገናኛ ብዙሃን አትሌቶችን ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ በማበረታታት ለሚጠበቀው ድል የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጠይቀዋል።በውይይት መድረኩ ከዚህ\nቀደም የኦሊምፒክ ዘገባዎችን\nበአካል ተገኝተው የሰሩ\nአንጋፋ ጋዜጠኞች ልምዳቸውን\nያካፈሉ ሲሆን ኦሊምፒክ\nኮሚቴው ከመገናኛ ብዙሃን\nጋር ያለውን ግንኙነት\nእንዲያሻሽል ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡\nበተለይም ከዚህ ቀደም\nኦሊምፒክን ለመዘገብ የሚጓዙ\nመገናኛ ብዙሃን ተገቢነት\nላይ በርካታ ጥያቄዎች\nየተሰነዘሩ ሲሆን ፕሬዚዳንቱ\nዶክተር አሸብር ከዚህ\nበኋላ በተገቢው መንገድ\nከመገናኛ ብዙሃን ጋር\nተቀራርቦ ለመስራትና የነበሩ\nችግሮችን ለመቅረፍ ቃል\nገብተዋል፡፡ አዲስ ዘመን ጥር 17 ቀን 2012 ዓ.ም ቦጋለ አበበ", "passage_id": "9532f079d2eb406567ac586e61b24847" }, { "passage": "በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው የስፖርት ሴክተር ዓመታዊ ጉባዔ ላይ የአዲስ አበባ ስታዲየም እድሳት ሊደረግለት እንደሆነ ተገልጿል።\nበኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አዘጋጅነት የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት ያካተተ የስፖርት ሴክተር ዓመታዊ ጉባዔ ዛሬ እና ነገ እንደሚከናወን መገለፁ ይታወቃል። በጉባኤው ላይም የቀጣይ የሴክተሩ ስትራቴጂክ ዕቅድ፣ የ2012 ሪፖርት እና 2013 በጀት ዓመት ዕቅድ፣ የተሻሻለው የሀገር አቀፍ ስፖርት ማህበራት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ፣ የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ የተዘጋጀው የማገገሚያ ስትራቴጅክ ሰነድ እና የስፖርት ማህበራት መመዘኛ ስታንዳርድ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።በዛሬው ውሎም ኮሚሽኑ የአዲስ አበባ ስታዲየምን በ2013 ለማደስ ማቀዱን አስረድቷል። ንብረትነቱ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የሆነው ይህ አንጋፋ ስታዲየም ከካፍ በመጡ ገምጋሚዎች ለአህጉራዊ እና ዓለማቀፋዊ ውድድሮች ብቁ እንዳልሆነ መገለፁ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎ ስፖርት ኮሚሽኑ 25 ሚሊዮን ብር ለእድሳት በማውጣት ስታዲየሙን የማብቃት ስራ በ2013 እንደሚሰራ ጠቁሟል። ኮሚሽኑ በገለፃው ወቅት ለእድሳቱ አስፈላጊ ነው የተባለውን 25 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ሚኒስቴር መፍቀዱንም አያይዞ አስረድቷል።ጥቅምት 23 ቀን 1940 የመሰረተ ድንጋይ የተጣለለት ይህ ዕድሜ ጠገብ ስታዲየም ሦስት የፍፃሜ ጨዋታዎችን ጨምሮ 31 የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን እና በርካታ አሕጉራዊ ውድድሮችን ማስተናገዱ አይዘነጋም።", "passage_id": "d140c51986bf101814849c1204f63f3a" }, { "passage": "ምስረታውን በ1985ዓም ያደረገው ኢትዮ ዩናይትድ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለው መከፋፈል መሰረት በኢትዮጵያም በሶስት አሶሴሽኖች ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። በኢትዮጵያ በተለይ በወጣቱ ዘንድ እጅግ ከተስፋፉ ስፖርቶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ የማርሻል አርት ስፖርት በፌዴሬሽን ደረጃ ለመደራጀትም ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን 2003ዓ.ም በወጣው የስፖርት ማህበራት ማቋቋሚያ መመሪያ መሰረትም የድሬዳዋ ኢትዮ ዩናይትድ ኢንተር ናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ሊመሰረት ችሏል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ስር የነበሩት ሶስት\nአሶሴሽኖችም በመጣመር ፌዴሬሽን ያቋቋመ ሁለተኛው ከተማ አስተዳደር ሆኗል። በፌዴሬሽኑ ማቋቋሚያ ጉባኤ ላይም የስፖርት ኮሚሽኑ ተወካይ\nአቶ መኮንን ገብረህይወት የፌዴሬሽኑን ምስረታ አብስረዋል። ተወካዩ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የአሰራር ሂደቱንና ደንቡን\nበተከተለ መልኩ የፌዴሬሽን ምስረታ መካሄዱን አረጋግጠዋል። ፌዴሬሽኑ በስድስት ክፍለ ከተሞች ውስጥ ብቃታቸው የተረጋገጠ 16 ክለቦችን\nያቀፈ፣ በ ‹‹ኤ ላይሰንስ›› ሁለት፣ በ ‹‹ቢ ላይሰንስ›› ስድስት፣ በ ‹‹ሲ ላይሰንስ›› አስር ዳኞች እንዲሁም ከ2-7ኛ ዳን\nያላቸው 16 አሰልጣኞች ያሉት በመሆኑ የማቋቋሚያ ጉባኤ ማድረግ የሚያስችላቸው መሆኑን ጠቁመዋል። በዚሁም መሰረት ስራ አስፈጻሚዎችን\nበመምረጥ ወደ ስራ እንዲገቡ፤ በሂደትም ጽህፈት ቤትና የስፖርት ማዘውተሪያ ገንብተው ከመንግስት ድጎማ እስኪላቀቁ በኮሚሽኑ ቢሮ\nእንዲሁም በትምህርትና ስልጠና ማዕከላት እንዲገለገሉ ፈቃድ ተሰጥቷል። በመጀመሪያው ጉባኤ ላይም አዲስ ፌዴሬሽን እንደመሆኑ ሪፖርት ማቅረብ ባይቻልም ቀጣይ እቅዶች ግን ለጉባየተኛው\nቀርበዋል። በዚህም የክለቦችን ቁጥር አሁን ካለበት ቁጥር ወደ 33 ማሳደግ፣ ጠንካራ ፌዴሬሽን እንዲሆን መስራት፣ ገቢውን በማሳደግ\nከኮሚሽኑ ድጋፍ የሚላቀቅበትን መሰረት መጣል፣ የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላትን ማሳደግ፣ ስፖርተኞችን በሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ\nውድድሮች ማሳተፍ፣ የተለያዩ ቻምፒዮናዎችን በማዘጋጀት ከተማ አስተዳደሩን እንዲሁም ሀገርን ለመወከል የሚችሉ ስፖርተኞችን ማፍራት፣\nበትምህርትና ስልጠና የዳኞችንና አሰልጣኞችን ቁጥር ወደ 100 ማሳደግ እንዲሁም በክትትልና ድጋፍ ላይ ለመስራት መታቀዱ ተገልጿል።\nገለጻውን ያዳመጠው ጉባኤም በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። በመተዳደሪያ ደንቡ ላይም ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ በጉባኤው አባላት ይሁንታ ሊያገኝ\nችሏል።ከተሳታፊዎች በተሰጠው አስተያየትም ስፖርቱ እስከ ወረዳ በመውረድ በይበልጥ እንዲስፋፋ ፌዴሬሽኑ ከክፍለ ከተሞች\nጋር በቅንጅት መስራት እንዳለበት እና ከመንግስት ድጎማ ለመላቀቅ የሚያስችለውን መንገድ ማፈላለግ እንዲሁም የሀብት አሰባሰብ ላይ\nማተኮር እንደሚገባው ተጠቁሟል። በተካሄደው የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫም አቶ በቀለ በዳዳ በ14 ድምጽ በማሸነፋቸው ከቀድሞው የአሶሴሽኑ ፕሬዚዳንት\nኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሲኒየር ሳቦም ተሾመ አበበ የስራ ደንብና መመሪያ ተረክበዋል። አቶ መንሱር ጀማል ምክትል ፕሬዚደንት\nሲሆኑ፤ ወይዘሮ ሰብለወንጌል ቁምላቸው አቃቤ ነዋይ እንዲሁም ሌሎች አራት ግለሰቦች የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በመሆን ተመርጠዋል።\nተመራጮችም በጋራ በመሆን ስፖርቱን ለማሳደግ የሚሰሩ መሆኑን ቃል ገብተዋል። ከማርሻል አርት ስፖርቶች መካከል አንዱ የሆነው ኢንተርናሽናል\nቴኳንዶ እአአ 1966 በጄኔራል ቾይ ሆንግ ሃይ ነው የተመሰረተው። የሁለቱን ኮሪያዎች መነጣጠል ተከትሎም ኢንተርናሽናልና ወርልድ\nቴኳንዶ በሚል ሲከፈል፤ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ በሰሜን ኮሪያ በስፋት ይከወናል። በሲኒየር ማስተር አብዲ ከድር መስራችነትም በኢትዮጵያ\nአሶሴሽኑ እስካሁን ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። በዚህ ወቅት የዓለም አቀፉ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን መቀመጫ በኦስትሪያ ቬና ሲሆን፤\nኢትዮጵያም አባል አገር ናት።አዲስ ዘመን ቅዳሜ የካቲት 21/2012 ብርሃን\nፈይሳ", "passage_id": "f09ec51d75140a7e9ad31d454512eed4" }, { "passage": "የኦሮሚያ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ናስር ሁሴን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሥራቸው በአንድ በኩል የተማረውን የሰው ኃይል ማምረት ሲሆን፤ ማኅበራዊ አገልግሎትን መስጠትም አንዱ ተግባራቸው ነው።ይህ በመሆ ኑም በክልሉ ከማህበራዊ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ በስፖርቱ ላይ የነበረውን ክፍተት ለመሙላትም ሰፊ ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ይናገራሉ። በክልሉ ያሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከስፖርት ጋር ባላቸው እንቅስቃሴ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ከማድረግ አኳያ የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ክፍተት እንደነበረበት፤ የስፖርት እንቅስቃሴውን ሳይንሳዊ መሠረት አስይዞ ለማስ ኬድና የራሳቸውን ክለብ አደራጅተው እንዲሰሩ ለማድረግ የተሰራው ሥራም አናሳ እንደሆነ ኮሚሽነሩ ያብራራሉ። እንደ ኮሚሽነሩ ማብራሪያ፤ በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የኒቨርሲቲዎች የክለብ ባለቤት መሆን ጀምረዋል።እንደ ክልል ሥራውን በተጠናከረ መልኩ በመያዝ አዲስ 30 የአትሌቲክስ ክለብ ይቋቋማል።ከ30ዎቹ ውስጥ በክልሉ የሚገኙ የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እያንዳንዳቸው የአትሌቲክስ ክለብ እንዲያዋቅሩ ይደረጋል። ዩኒቨርሲቲዎቹ የስፖርት ደንቡንና ፕሮፖዛሉን ወስደዋል።በቀጣዩ ወር ውስጥ ክለቦቹ በሙሉ ተደራጅተው ወደ ሥራ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።በዚህ ሂደት አቅጣጫ ማስቀመጥ ብቻ ሳይሆን እንዴት እንደሚያዋቅሩ፣ የሚያስፈልገው በጀትና የመዋቅር አሰራር ተለይቶ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተሰጥቷል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ፕሬዚዳንቶች ከክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ውይይት በማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።በመሆኑም የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአትሌቲክስ ክለብን በማቋቋም ሥራውን ጀምሯል።ሌሎች ዩኒቨርሲ ቲዎችም ይህንን ተሞክሮ ወስደው እንዲሰሩ ለማድረግ ክለብ በማቋቋም ላይ ናቸው። በአዲስ አበባ በጃንሜዳ በተካሄደው የከ ፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውድድር ላይ በክ ልሉ ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች በዚሁ መንፈስ መወዳደር ችለዋል። በአጠቃላይ የከፍተኛ ትም ህርት ተቋማት በማኅበራዊ አገልግሎታቸው ግዴታቸውን እንዲወጡ ከስፖርት ጋር ተያይዞ የሚያስተምሩትን ሳይንስ በተግባር በማሳየት ለአገሪቷ ስፖርት እድገት አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የማድረግ ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ኮሚሽነሩ።አክለውም ‹‹አሁን የተጀመረው በአት ሌቲክስ ስፖርት ዘርፍ ነው።ወደ ፊት በሁሉም የስፖርት አይነቶች የክለብ ባለቤት የሚሆኑበት ሁኔታ ይመቻቻል።አንድ ክለብ የሚያስፈልገውን የሰው ኃይልና ሌሎች ተያያዥ ነገሮችም አብረው ታሳቢ ይደረጋሉ።ይህም በባለሙያዎች ጥናት ተደርጎ ወደ ሥራ ተገብቷል›› ሲሉ በቀጣይ አሰራር ላይ ያላቸውን አስተያየት ሰጥተዋል። ኮሚሽነሩ፤ የስፖርት ፖሊሲው ሁሉም ሰው ጤንነቱን ለመጠበቅ የስፖርት እንቅስቃሴ እንዲያደርግ የሚያዝ ነው በማለት፤ ከዚህ ውስጥ ደግሞ ተሰጥኦ ያላቸው ስፖርተኞች ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑና ተሽለው ሲገኙም እስከ ከፍተኛ ውድድር እንዲደርሱ የሚያዝ መሆኑንና በዚህም መሰረት ከተለምዷዊ ስልጠና ለመላቀቅ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የክለብ ባለቤት ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ኮሚሽነሩ እንደሚሉት፤ በኢትዮጵያ አብዛኛው ስፖርተኛ እንቅስቃሴዎችን የሚሰራው በተለምዶ ነው።ችሎታ ያላቸውና በራሳቸው ተነሳሽነት ልምድ ያካበቱትን ስፖርተኞች ነው በአንድ ላይ በማጣመር እንዲወዳደሩ እየተደረገ ያለው።ይህ አካሄድ ደግሞ ተተኪ አትሌቶችን በማፍራት ረገድ ክፍተት እያመጣ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን በትራክ ላይ በሚካሄደው ውድድር ላይ ውጤት እየቀነሰ ነው። ይህ የሚያሳየውም የስፖርቱ ሳይንሳዊ መሠረቶች ላይ የተሰራው ሥራ አናሳ መሆኑን ነው። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክለብ ባለቤት መሆናቸው በአንድ በኩል ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች በሳይንስ የተደገፈ ሥልጠናን ለመስጠት ያስችላቸዋል።ከዚህም ባሻገር ስፖርተኞች በክለቦቹ ሲታቀፉ ማደሪያና ምግባቸውን ጭምሮ ሌሎች ግብአቶች እንዲሟሉላቸው ይደረጋል።ጎን ለጎን የራሳቸውን ሥራ እየሰሩ ስፖርቱን መስራት ይችላሉ።በአትሌቲክሱ ላይ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሲቃኝ በአገራዊ እድገቱ ውስጥ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ አናሳ በመሆኑ፤ ይህ ተጠናክሮ ከቀጠለ ለአገሪቱ የኢኮኖሚ እድገትም አስተዋጽኦ ይኖረዋል።የአትሌቲክሱ ዘርፍ መጠንከር የውጭ ምዛሪንም ያነቃቃል።ይህንን ለማድረግ ኢትዮጵያ በዓለም አቅፍ ደረጃ ትልቅ አቅም አላት። ‹‹የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክለብ በማ ደራጀታቸው ለአገሪቷ ስፖርት እድገትና ስፖርቱ በኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን ጉልህ አስተዋጽኦ እንዲወጣ ያደርጋሉ።ጎን ለጎንም በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ በውድድር በመድረኮች ላይ የራሳቸውን አርማ ይዘው ስለ ሚገቡ ራሳቸውን ማስተዋወቅ ይችላሉ። ክለቦቹ ስፖርተኞችን ካሰለጠኑና ካሳደጉ በኋላ አትሌቱ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ከፍ ሲል ከሚያገኘው ገቢ ለክለቡ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ይኖራል›› ሲሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክለብ ባለቤት መሆናቸው የሚያስገኘውን ጥቅም አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 11/2011", "passage_id": "b685174b92a001bdbfab79fc9ecad305" } ]
086c95a1ae339991f19b5b45619f6526
30eb40de4b6cb9700e8f81d08acfc01f
በአንድነት ፓርክ፤ ትናንትንም ዛሬንምይመልከቱ
 ሳልፍና ሳገድም፤ አሻግሬ ከማየት ባለፈ ዥንጉርጉሩን የደንብ ልብስ ለብሰው፣ መለዮአቸውን አድርገው፣ መሳሪያቸውን አንግበው በበሩ ላይ ሆነው ሌት ተቀን ከሚጠብቁት ጠባቂዎች አልፌ ከቅጥር ግቢው እገባለሁ ብዬ ላስብ ቀርቶ ተመኝቸው እንኳን አላውቅም፤ ብሔራዊ ቤተ መንግስት። እነሆ ዛሬ በወጣት አስተናጋጆች በአክብሮት በግቢው ዘልቄ ከግር እስከራሱ ለመጎበኘት በቃሁ። ጊዜ ለኩሉ ይል የለ። ፍተሻውን አልፈው ወደ ግቢው ከገቡ በኋላ በቅደም ተከተል የሚጎበኟቸውን እና የማረፊያ ቦታዎችን ሙሉ መረጃ የያዘ መግለጫ (ማፕ) ይሰጥዎታል። አንድሺ ብር ከፍለው ከገቡ በአስጎብኚ (በአስረጅ) ይታገዛሉ። የከፈሉት ሁለት መቶ ብር ከሆነ ግን የተሰጥዎትን አቅጣጫ ጠቋሚ በመጠቀም ይመራሉ። በመግቢያ ላይ በአማርኛና በእንግሊዝኛ በትላልቅ ፊደላት ‹ኢትዮጵያ› ተብሎ ተጽፏል። ፅሁፉ እንደ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ ተሰቅሎ በራሱ ‹‹እባክዎን ወደ ውስጥ ዝለቁ›› የሚል ያህል ይጋብዛል። ጽሁፉን ሲያነቡትም ልብ ይሞላል። እድሜ ጠገብ ከሆኑት ሀገር በቀል ዛፎች የሚነፍሰው ንጹህ አየርም ጎብኚዎችን ለመቀበል ተባባሪ የሆነ ይመስላል። ምድረ ግቢው፣ በውስጡ የተገነቡት የቤቶች የስነ ህንፃ ውበትና ጥበብ፣ ኢትዮጵያ ታላላቅ ተብለው ከሚጠሩ ሀገራት ጋር ስለነበራት ግንኙነት፣ በታሪክ ተሰንዶ የሚታየው ሁሉ ከአዕምሮ በላይ ነው። በቃላት ብቻም የሚታለፍ አይደለም። ታሪክ ይናገራል። የት እንዳለሁ ትገምታላችሁ በሚል። ብዙ አወራሁ፤ ‹አንድነት ፓርክ› ውስጥ ነኝ! በሉ ተከተሉኝ። የፓርኩን የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ ለንግድ ለማረፊያና ለተለያየ አገልግሎቶች የሚውሉ ግንባታዎች፣ የአትክልትና የአበባ ሥፍራዎችን በማዘጋጀት፣ ብቻ በፓርኩ ውስጥ ያስፈልጋሉ የተባሉ ነገሮችን ለማሟላት የሚከናወኑ ተግባራትንም እግረ መንገድ እየተመለከትኩ፣ በሥራው በመሳተፍ ላይ ያሉት የዛሬ ወጣቶች የነገ የዕድሜ ባለጸጋ የታሪክ ተቋዳሽ መሆናቸው ደግሞ ሌላው ድንቅ ታሪክ ነው። የአንድነት ፓርክ በውስጡ ስድስት የቱሪዝም ዋና ዋና መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን፣ እያንዳንዱም ሰፊ ታሪክ ያለው በመሆኑ አለፍ አለፍ እያልኩ የተደመምኩበትንና የታዘብኩትን ብቻ ነው በምናብ በመውሰድ እየሳልኩ የማስተዋውቃችሁ። ወደ ሰው ሰራሽ የጥቁር አንበሳ ዋሻ አመራሁ። ዋሻው ከአለት ድንጋይ ተፈልፍሎ የወጣ እንጂ የእጅ ጥበብ አይመስልም። የዱር እንስሳት መኖሪያ በስፍራው ስለሚገኝ ብቻዬን በዋሻው ውስጥ ለማለፍ አልደፈርኩም። በአጋጣሚ በኤሌክትሪክ ሙያ የተሰማሩ ወጣቶች ለሥራ በውስጡ ሲያልፉ ተከተልኳቸው። በዋሻው መግቢያ ላይ አራት አናብስት አየሁ። ደነገጥኩ። እንደማይደርሱብኝ ስላረጋገጥኩ ፍርሃቴ አልቆየም። እንኳን በአካል በድምጹ ከሚያስፈራው አንበሳ ጋር ከመስተዋት ማዶና ወዲህ በቅርበት ተያየን። ‹‹ማን ይባሉ ይሆን?›› በፓርኩ የሚሰሩት ወጣቶች ወንዱን ቀነኒሳ፣ ሴቶቹን ደግሞ በጥሩነሽና በገንዘቤ ሰየሙልኝ፤ በስያሜው ተሳስቀን ተለያየን፡፡ ዋሻውን አልፌ ወደ ሌላው የታሪክ ሥፍራ ሳመራ በባህላዊ የመድኃኒት ተክል የተሞላ አካባቢ ደረስኩ። ለምች መድኃኒት የሚወሰደው ዳማከሴ፣ ጤና አዳም፣ ጠጅ ሳር፣ ሮዝመሪኖ ሌሎችም እይታን በሚስብ ቦታ ተተክለዋል። ተክሎቹን እንዳለፍኩ ካየኋቸው የነገሥታትና የመሪዎች ፎቶግራፎች መካከል የንግሥት ዘውዲቱን ፎቶግራፍ ማየቴ ለጾታዬ እንዳደላ አድርጎኛል። የስምንተኛው መሪ የዶክተር ዐብይ አህመድ ፎቶ ግራፍ ግን አልተካተተም። የትናንቱን ብቻ እንድናስታውስ ታስቦ ይሆን? አለፍኩት። በጉብኝቴ ውስጥ ‹ላንቺያ› የተባለችው የአፄ ኃይለ ሥላሴ መኪናም ትኩረትን በሚስብ እይታ ቦታ ነበረች። ገና ከፋብሪካ የወጣች እንጂ እድሜ ጠገብ አትመስልም። ባለ8 ማዕዘኑ እና የእንቁላል ቅርጽ ጉልላት ባለው የዳግማዊ ሚኒልክ ቤተመንግሥት ውስጥ ትኩረቴን የሳበው በግድግዳው ውስጥ የተቀበረው ከብረት የተሰራው የድምጽ ማስተላለፊያ ቱቦ ነበር። ምድርና ፎቅ ሆነው በድምጽ መልዕክት የሚለዋወጡበት መሳሪያ መሆኑ ባስጎብኝዋ ሄለን በቀለ ገለፃ ባይደረግልን ኑሮ የውሃ መውረጃ የሚመስለን ጥቂት አንሆንም ነበር። አፄ ሚኒልክና ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ የተለያየ መኝታ ክፍል እንዳላቸው በአስጎብኝዋ ገለጻ ሲደረግልን ቀልደኛ ጎብኚ ደንገጥ ብሎ ‹ለየብቻ ነው የሚተኙት› በማለት ጠየቀ። መልስ ባይገኝም ሳቅ ፈጥሯል። የመጀመሪያው የስልክ ቤትም በዚሁ የሚኒልክ ቤተመንግሥት ውስጥ ይገኛል። ስምንት ሺ ኪሎ ሜትር ይረዝማል ተብሎ በሚገመተው ጠፍር ጣሪያው የተሰራው፣ ሰባት መስኮቶችና 12 በሮች ያሉት፣ እስከ ሶስት ሺ እንግዶች የሚያስተናግደው የግብር አዳራሽ ልዩ ድባብ አለው። ሥራውን ለኪነ ህንጻ ጠቢባን ትቸዋለሁ። በዚህ ክፍል ውስጥ ከዛሬ አምስት አስርት ዓመት በፊት በቀድሞ ተግባረዕድ በአሁኑ እንጦጦ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ተብሎ በሚጠራው ትምህርት ቤት ሲማሩ በትምህርታቸው የላቀ ውጤት በማምጣታቸው ተጋብዘው ከአፄ ኃይለሥላሴ ዲፕሎማና ሽልማት የወሰዱት አቶ ነጋሽ ገብሬ የታሪክ አጋጣሚው ያኔ ለሽልማት አሁን ደግሞ ‹አንድነት ፓርክ› ተብሎ ተሰይሞ ለጉብኝት አብረን ታድመናል። ለአቶ ነጋሽ መታደማቸው ልዩ ስሜት ነበር ያሳደረባቸው። በጉብኝታቸው የተደመሙበትንና በተንቀሳቃሽ ስልካቸው የቀረጿቸውን ወደ ሚኖሩበት አሜሪካን ሜሪላንድ ሲመለሱ ለወዳጆቻቸው ለማሳየት ቸኩለዋል። የማስተዋወቅ ኃላፊነትም እንዳለባቸው አጫውተውኛል። የሌሎች ጎብኚዎችን ስሜትም እየተጋራሁ ስለነበር ‹‹ለካ እንዲህ ነው እንዴ ያረጁ ቤቶችን ነበር የጠበኩት›፣ ‹ጉብኝቱ በግማሽ ሰዓት የሚያልቅ ነበር የመሰለኝ›፣ ‹እድሜ ሰጥቶን ይሄን ማየታችን ዶክተር ዐብይ እግዚአብሄር ይስጠው› የሚሉ በደስታ የሚገለጹ ስሜቶችን ነበር የሰማሁት፤ ከገጽታቸው ያነበብኩት ይህንኑ ነው። በምስል፣ በድምጽና በጽሁፍ ተቀነባብሮ አፈታሪክ በተባለው ክፍል ውስጥ የሚጎበኘው ደግሞ በጽሁፍ ከምገልጽላችሁ በላይ ነው። በአንድነት ፓርክ ውስጥ ከበጎ እስከ ክፋት የተፈጸሙ ነገሮች ቢቀርብልዎትም ታሪክ ነውና ያለፈውን በትዝታ የወደፊቱን ደግሞ በአንድነት ሆነው እንዲቀጥሉ የሚያስተሳስሩ የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ባህልና ወግ የሚያንጸባርቁ እሴቶችም ይገኛሉ፤ አበቃሁ።አዲስ ዘመን ጥቅምት27/2012 ለምለም መንግሥቱ
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=22108
[ { "passage": "እንደተለመደው ባለፈው ረቡዕ በምሳ ሰዓት ወደ ሰራተኞች ክበብ /መዝናኛ/ ሳመራ ለብዙ ዓመታት ለመዝናኛ ክበቡ ግርማ ሞገስ በመሆን ሰራተኛውን ከፀሐይ ከልለው ኦክስጂን ሲመግቡ የአካባቢውን ተፈጥሮ መልኩን ሳይቀይር እንዲቀጥል ብርቱ ትግል ሲያደርጉ የነበሩ ሁለት የፅድ ዛፎች በጋራ ተቃቅፈው ተገንድሰው አገኘኋቸው። ከዘመኑ ሰው የተሻለ በሚመስል ጥምረት በአንድነት ተያይዘው ወደቁ። እንደው ምን ይሆን እንዲህ ያስተሳሰራቸው በሚያሰኝ አብሮነት ተቃቅፈው በሚያስቀና አብሮነት ተያይዘው ከመሬት ደረሱ። እዚያ ቦታ የተገኘሁት፤ ምሳ ለመብላት ነው። ብቻዬን ነኝ፤ ዛፎቹን ስመለከት አንዳች ነገር በውስጤ ተፈጠረ። ዛፎቹ በአብሮነት ከኔ ተሽለዋል። አብረው ኖረው አብረው ተከንብለዋል። እኔ ብቻዬን ዛፎች ግን ሁለት ናቸው። እኔ ቆሜ የወደቁት ዛፎች ከኔ የተሻሉ መሰሉኝ። ውዶቼ ይሄ ነገር እንዴት ነው? ግለኝነታችን፣ መነጠላችን የእርስ በእርስ መደጋገፍና አብሮ የመቆም ልምድና ጥሩ እሴታችን የት ሄደ? ዛፍ ሲወድቅ ብዙው ሰው የየራሱን መላምት ይሰጣል። ትልቅ ዋርካ ሲገነደስ በባህላችን የሚሰጠው ትርጓሜ ይከብዳል። እኔ ግን በመስሪያ ቤቴ የተገነደሱት ትልልቅ የፅድ ዛፎች ከራሴ አስፍቼም ከማህበረሰባችን አሁናዊ ተግባርና ሁነት ጋር አገናኝቼ አየሁት። የኛ መነጣጠል ከነሱ ጥምረት የኛን ግለኛ መሆን ከዛፎቹ በጋራ መውደቅ ጋር አመሳከርኩት። የኛ ሰውነት ከዛፎቹ ዛፍ መሆን ጋር አነካካሁት። የዛፎቹ ዛፍ ሆነው መገኘት አስምሬ፤ የኛ የሰዎቹ ሰው መሆን ላይ ስብዕና መለበስ ላይ ጥያቄ መጠየቅ ፈለኩ። የዛፎቹ ተያይዞ መውደቅ ከዛሬ ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር አዛመድኩ፤ ይህ ንፅፅራዊ ምልከታዬን አሰፋሁት። ከማህበረሰባችን የዛሬ እውናዊ ህይወት ጋር አነፃፀርኩት። ዛሬ ላይ የምናሳየው አብሮ የመቆምና የእርስ በእርስ ትብብር በኖ ታየኝ። የእርስ በእርስ መረዳዳትና አብሮነታችን ተሸርሽሮ ግለኝነት ሰፍኖ ስለራስ እንጂ ስለሌላው ምን አገባኝ ወርሶናል። ኧረ ጉድ ነው! ከዛፎቹ አንሰን ተገኘን ማለት ነው? ተቃቅፈው ፍቅር እስከ ማገዶነት ካሉት፤ አብረን ኖረናል ነገ አልተፈቀደልንም አብረን እንውደቅ ካሉት ዛፎች የማንሻል ነን ማለት ነው። በነገራችን ላይ ዛፎቹ ሳይቀዳደሙ እንደተቃቀፉ በጥላቸው እንዳይደርቅ ለብዙ ዓመታት ጥላ ከለላ የሆኑለት መሬት በክብር ተቀብሏቸዋል። አቤት ዛፎቹ እንደው አንደበት ቢኖራቸው ስንቱን በነገሩኝ። የዛሬን አያድርገው ዛፎቹ ከመገንደሳቸው በፊት በሻይና በምሳ ሰዓት እስሩ ቁጭ ብለን ምሳ በልተን ቡና ስንጠጣ የበዛ ያልረባ ወሬና ጥቂት ቁም ነገር ተለዋውጠናል። የመዝናኛችን ግርማ ሞገስ የነበሩት ዛፎች ከተገነደሱ ቀን ጀምሮ ወደ መዝናኛው ሳመራ አንዳች ነገር የጎደለ ያህል ይሰማኝ ጀምሯል። በእርግጥም ለመዝናኛው ባለውለታ ናቸው። ምን ዋጋ አለው? ከቀናት በኋላ አንድ ፈላጭ ለማገዶነት ሲነርታቸው አየሁ። ዛፎቹ አብረው አድገው አብረው ወድቀው በጋራ ሊማገዱ በሂደት ላይ ናቸው። የክበቡ መዝናኛ ግቢ ውስጥ የጣራን ያህል ተንዠርግገው ዘመናት የቆዩት ዛፎች ስንቱን ሰው ታዝበው ይሆን? ደግነቱ ኢትዮጵያዊ የፅድ ዛፎች ናቸው። ትዝብታቸው አይበዛም፤ እንኳን የፈረንጁ አልሆኑ። የሀበሻ ፅዶች ስለነበሩ ሀሜት የለመዱና ስለሀሜትም ግድ የሌላቸው ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ ገመትኩ እንጂ ስንት ነገር ሰምተው ችለው ይሆን? እድሜ ጠገቦቹ ዛፎች ስንቱን ታዝበው ይሆን! ከስራቸው ተሰይሞ ሰዎችን ያማ፤ ዛፎቹን ተከልሎ የሰው ሀሳብ የቀማ፣ በቡጨቃ ሌላውን ያደማ፤ ጥላቸውን ተጠቅሞ ተገቢ ያልሆነን የሰማና ያሰማ፤ አንዳንዴም ከሰው የተስማማ አይጠፋም። ብቻ ዛፎቹ ቅጠላቸው ረግፎ ከጎረቤት የተዋሱት ሌላ ቅጠል ለብሰው በአብሮነት ዛሬ ድረስ ቆይተው ነበር። ቆዩኝማ ሰሞኑን 200 ሚሊዮን ችግኞች ይተከላል መባሉን ሰምተው እኛን መች በቅጡ ተንከባከባችሁን ብለው እራሳቸውን ከዛፍነት ወደ ማገዶነት በመቀየር ተቃውሞ ማሰማታቸው ይሆን እንዴ? ጠረጠርኩ እዚህ አገር ላይ የማይቃወም እኮ የለም ተቃዋሚነት የሀበሻ ሱሱ ሆኗል። ለነገሩ ፅዶቹን ሀበሻ ናቸው፤ ይሄ ደግሞ ጥርጣሬዬን ያሰፋዋል። ዛፎቹ በሕይወት ዘመናቸው የመዝናኛው የአየር ንብረት ክልል የተዛባ እንዳይሆን ብዙ አስተዋፅኦ አበርክተው ነበር። በተለይ እስሩ ቁጭ ብለው ጢስ ለሚያጤሱት በጥላው ከልሎ የምትለቁት ነገር መልካም ባይሆን እኔ ችዬዋለሁ። እያለ ጢሱን ሲምግ በአንፃሩ ደግሞ ተስማሚውን ሲቸሩ ቆይተዋል። ተያይዘው የወደቁት የፅድ ዛፎቹ ግን የምር አስቀንተውኛል። አብረው የተፈጠረላቸውን እየተቋደሱ ቆይተው አብረው መውደቃቸው የኛ አብሮነት ክፍተት በጉልህ ለማሳየት አያስችልም? ወዳጆቼ። ውይ ትዝ አለኝ፤ እንዴ ፈዘናል፤ ተነጥቀን ዝም ልንለው የማይገባ ብርቱ ጉዳይ ይሄ ነው። ሀበሻ ሆይ አሁን ዘራፍ በል! ተነጥቀሃል። የእውነት ማንነትህ ማሳያ የሆነው የእርስ በእርስ ፍቅርና ህብረትህ ተሸርሽሮ እኛ ግቢ ካለው ዛፍ አንሷል። እኔ ምለው ማነው ግን የቀማን? ማነው የወሰደብን? ኧረ ጎበዝ እናስመልስ ተነሱ። አገር ስትወረር እናብር የለ? ታዲያ በአገሪቱ ኗሪ የሆነው የሰው ልጅ መለያ ባህል ሲሸረሸር ዝም ይባላል። የእርስ በእርስ መተሳሰብ ውዱ እሴታችን የተነጠቅን መሆኑን የሚያሳይ አንድ ትልቅ ማሳያ ከገጠመኜ ላመላክታችሁ ውዶቼ። አንድ ጎረቤት አለኝ፤ የከበረ። የከበረ ስል ገባችሁ ፈራንካ የተራረፈው አስመጪና ላኪ በከተማይቱ ከ10 ያነሱ ቦታዎች ላይ ቪላዎችን እየሰራ የሚያከራይ ነው።እናላችሁ ስግብግብነቱ ደጋግሞ ቢያሳየኝም የሰሞኑ ሁኔታው ግን ለሰውዬው ያለኝን ነገር በሙሉ ወደ ታች ወሰደብኝ። ወደታች ያስኬደኝ ጉዳይማ ወዲህ ነው ውዶቼ። መንግስት ለስራ አጥ ወጣቶች ብሎ የመደበው ስራ አጥ ወገኖቻችን እንዲጠቀሙ የተበጀተ በጀት ሊቀራመት መሞከሩ ነው። ወዳጆቼ ይሄ ሰው ወረዳ ሄዶ መታወቂያ ቀይሩልኝ አለ። ስም ሳይሆን ስራ ነጋዴ የሚለው ወደ ስራ አጥ እንዲቀየር ጠየቀ። ያወቁት ነበርና እንደማይሆን ነግረው ሸኙት። በድብቅ ያደረገው ነበር እና ያው አምላክ ክፉ ስራ አጋላጩ አይጠፋምና ወረዳ ይዞት የሄደው ህፃን ልጁ ውሎዋቸው የት እንደሆነ ለጠየቀችው እናት ወረዳ ለመታወቂያ ቅየራ መሄዳቸውና እንዳልተሳካ አባቱም እንደተናደደ ተናገረ። እናት ይሄኔ ጥያቄዋን አከታተለች። ‹‹የምን የመታወቂያ ቅያሪ ነው?” የሚስት ጥያቄ ሆነ። ይሄኔ አባት አፍረጠረጠው። ስራ አጥ ለማስባል ሄዶ እንዳልተሳካለት። ያንን ለማድረግ ያነሳሳው ደግሞ ለስራ አጥ ብር እንደሚሰጥ በብድር መስማቱና ለጀመረው አዲስ ቤት ማሰሪያው ብር ፈልጎ እንደሆነ ተናገረ። እኔ እንደማፈር ቃጠኝ። በኋላ የድርጊቱ ተዋናይ ይፈር ምን አገባኝ ብዬ ተውኩት። ለቡና የተጠራሁት እኔን እያየች እናት ተሸማቀቀች። አባት ባደረገው ስግብግብነት በጣም አዘነች። ቃል ሳታወጣ በብርቱ ፊትዋን በቁጣ አለበሰችው። እንደው ይሄ አብሮት የነበረው ብላቴና ከሱ ምን ይሆን የሚማረው? ስግብግብነት፤ ገንዘብ አምላኪነት? ሌላ መልካም ነገር ከወላጅ አባቱ ካላየ ከዚህ ልጅ ምን እንጠብቅ? ወገን ይሄ ምን ይሉታል? እንደው ለሰው አለማሰብ ብቻ እኮ አይደለም ከሰው መቀማት ስለሌላው ምን አገባኝ ብሎ እራስን መውደድ ስግብግብነት እንጂ። እኔ ምለው ከዚህ አይነቱ እነዚያ እኛ ግቢ መዝናኛ ውስጥ ወደቁ ያልኳችሁ ዛፎች አይሻሉም? የእውነት በጣም። ለማንኛውም ውዶቼ ዛፎቹን ተክለን የተሻለ ጠቀሜታ እንዲሰጡን ተንከባክበን የምናሳድገው እኛ፤ ሰብዓዊነት ተላብሰን ስለ ሰው ትልቅ ማሰብ የሚጠበቅብን እኛ፤ ከሰው ጋር ተሰልፈን ከሰው ጋር ተጋርተን ሰውነታችንን ከፍ እናድርገው። በስግብግብነት ስብዕናችንን አናጉድለው። ሰው የመሆንን ልዩ መለያችንን በሰው በመሆን እናፅናው አበቃሁ። ቸር ይግጠመን።አዲስ ዘመን ሀምሌ 19/2011(ሻሚል) ", "passage_id": "1cfc169cc3065dbd0a7af595896e3305" }, { "passage": "ፍጥነት እና ክትትል ያልተለያቸው የፓርኮቹ ግንባታ ሂደትና ውጤታቸው ጎብኚዎቹን አስደንቋል። የመገናኛ ብዙሃን አመራሮች እና ባለሙያዎች ፓርኮቹን ለመጎብኘት ሲነሱ፤ ባዩት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ ብሎ የገመተ ባለመኖሩ ሁሉም ተገርመዋል። የፓርኮቹ የግንባታ ፍጥነት ከማስገረሙ በላይ የስራው ውበት ደግሞ እጅግ የሚያስደምም መሆኑን የሚናገሩት የዘ ኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ አቶ ወርቁ በላቸው ናቸው። አቶ ወርቁ የአንድነት፣የሸገርና የእንጦጦ ፓርኮችን ግንባታና የደረሱበትን ደረጃ ተመልክተዋል። የአዲስ አበባ ፓርኮች የፕሮጀክት ግንባታ ፍጥነታቸው ለማመን ይከብዳል ይላሉ ። ሥራው በውጭ ዜጎች ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያውያንም ጭምር የሚከናወን ቢሆንም፤ የግንባታ ፍጥነቱ ታይቶ የማይታወቅ መሆኑን ጠቅሰው፤ በሌሎችም ፕሮጀክቶች ላይ ቢደገም ያስብላል ሲሉ ይገልጻሉ ። የቱሪስት መዳረሻ ይሆናል በማለት እየተገነባ ያለው የእንጦጦ ፓርክ ሙሉ ለሙሉ የሚሰራው በኢትዮጵያውያን ነው። የኢትዮጵያውያን ትጋት የታየበት የፓርኩ ዲዛይን እና ግንባታ ከዓመት በፊት አይቶ አሁን ደግሞ ለጎበኘው ያስደነግጣል። በቦታው ያለእረፍት የተሰራውን ስራ ለመግለፅ እጅግ ያዳግታል። ከመንግስት ጋር ተባብረው የሚሰሩ የግል ባለሃብቶች አሉ። በከተማዋ ትልልቅ የተባሉ አገልግሎት መስጫዎች ‹‹ዋው በርገር›› እና ‹‹ቤሉስ ካፌ››ን የመሳሰሉ እንዲሁም ታዋቂው ‹‹ኩሪፍቱ ሆቴል›› በእንጦጦ ፓርክ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸው ግንባታ እየተካሄደ ይገኛል። አገልግሎት አሰጣጣቸው መሃል ከተማ ላይ በሚያስከፍሉት ዋጋ ሳይሆን፤ መሬቱን ከመንግስት በነጻ በማግኘታቸው እነርሱም በተመጣጣኝ ዋጋ አስፈላጊውን አገልግሎት እንደሚያቀርቡ፤ እነአቶ ወርቁ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጾላቸዋል፤አገልግሎቱንም በአካል ተገኝተውና ተገልግለው አረጋግጠዋል። እንደአቶ ወርቁ ገለፃ፤ አሁን የፓርኩ ደረጃ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት ለመሥጠት የተቃረበ ይመስላል። ይህ ሁሉ ሥራ የተሰራው በዓመታት ሳይሆን በወራት ዕድሜ መሆኑ ጉዳዩን የበለጠ አስገራሚ ያደርገዋል። ከእንጦጦ የቱሪስት መዳረሻ ፓርክ በተጨማሪ የሸገር የወንዝ ልማት ፕሮጀክት አካል የሆነው ሌላኛው የቻይና እና ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ሥራም አፈፃፀሙ በኢትዮጵያ ከተለመደው የፕሮጀክት አፈፃፀም በእጅጉ የተለየ ነው። ፓርኩ የሚሰራው በኢትዮጵያውያን እና በቻይናውያን ትብብር ሲሆን፤ በፓርኩ ሰው ሰራሽ ሃይቅን ጨምሮ አንድነትን የሚያመለክቱ ግንባታዎች፣ የሙዚቃ ኮንሰርት ማዘጋጃ ቦታዎች፣ የቲያትር መመልከቻዎች እና የተለያዩ መዝናኛዎች ተካተውበታል። ሰው ሰራሽ ሃይቅን ጨምሮ ከሌላ ቦታ ተነቅለው የተተከሉ ትልልቅ ዛፎች ታክለውበት ቦታው የተፈጥሮ ገፅታው ማራኪ እንዲሆን የተሰራው ስራ ያስገርማል ይላሉ። አቶ ወርቁ የአንድነት ፓርክም በጣም አስገራሚ ነው። ‹‹ የአንድነት ፓርክ ቦታው ባዶ ሆኖ ገና ለግንባታ ሲታሰብ በአጋጣሚ አይቼው ነበር። እዚህ ጋር የእንስሳት ማቆያ፤ እዚህ ቦታ ላይ ደግሞ ሌላ ነገር ይሰራል ሲባል ተገኝቻለሁ።›› ካሉ በኋላ፤ በአጭር ጊዜ ይህን የመሰለ ሥራ መሰራቱ ከዚህ በፊት ቦታውን አይቶ ለሚያውቅ አሁን በአጭር ጊዜ ውስጥ የታየውን ለውጥ ለማመን የሚከብድ ነው ይላሉ። የእነዚህ ፕሮጀክቶች ውጤታማነት መሰረታዊው ጉዳይ የአስተሳሰብ ለውጥ ነው ያሉት አቶ ወርቁ፤ በቅድሚያ ይቻላል ብሎ ማመን ወሳኝ መሆኑን ይናገራሉ። በከተማዋ ሰው ሰራሽ ሃይቅ መስራት እንደሚቻል ታምኖ መፈጸሙንም በምሳሌነት ይጠቅሳሉ። በከተማዋ የቱሪስት መዳረሻ እና መዝናኛን ለመገንባት በቃል ለዘመናት ተወርቶ ኮሚቴ የተዋቀረ ቢሆንም ለመተግበር አዳጋች ሆኖ ነበር። ካሉ በኋላ፤ አሁን ግን የቱሪስት መዳረሻን መገንባት ተችሏል። የነበሩትን ሃውልቶች ማስጎብኘት ብቻ ሳይሆን አዳዲስ የቱሪስት መስህቦችንም በመሥራት ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል በሥራ የተገለጠ መሆኑን ያብራራሉ። ‹የትኛውም ሰዓት የሥራ ሰዓት ነው።› ብሎ በመትጋት የተገኘ ውጤት ነው። ›› በማለት የተናገሩት አቶ ወርቁ፤ ጠንካራ ግምገማ በማካሄድ በአጭር ጊዜ ምርጥ ሥራ ተሰርቷል። ይህንን ወደ ሌሎች የግንባታ ፕሮጀክቶች እና ወደ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሳይቀር በማስፋት በአገር ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ ይገልፃሉ። በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የኦንላይን ዘርፍ ምክትል ዋና አዘጋጅ አቶ ተሾመ ተፈራም የአቶ ወርቁን ሃሳብ ይጋራሉ። ‹‹እንጦጦ ላይ የተገነባው የቱሪስት መዳረሻ እጅግ ያስገርማል። የአሽከርካሪ ብቻ ሳይሆን የእግረኛ እና የሳይክል መንገዱ በጥሩ መልኩ ተሰርቷል። ቤቶች እየተገነቡ ናቸው። እጅግ ሰፊ ሲሆን፤ ፈረስ መጋለቢያ እና ፈረሶችም አሉ ››ያሉት አቶ ተሾመ፤ የእግር ጉዞ ማድረጊያ እና ማረፊያ በአስደሳች መልኩ መሰራቱንም ይገልጻሉ። ቀጥ ቀጥ ብለው ያደጉ ባህር ዛፎች እና የቦታው ነፋሻነት ህይወት እንደሚያድስ ጠቅሰው፤ ዘመናዊ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት በተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎት ይሰጣሉ። ይሄ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በነፃ እንዲዝናናበት ታስቦ የተገነባው ፓርክ፤ ለከተማዋ ህዝብ እና ለውጭ አገር ጎብኚዎች ‹‹የት ልዋል›› ከሚል ጭንቀት ከመገላገል ባሻገር ለከተማዋም ተጨማሪ ገቢ ለመፍጠር የሚመች ነው።›› ሲሉ ያብራራሉ። የቀድሞ ፖሊስ ጋራዥ አካባቢ ያለው ቦታ አሁን በአስደናቂ መልኩ ተገንብቷል። በጉብኝቱ ሰዓት እንኳ ሰዎች በትጋት እየሰሩ ነው። ከስራ ቀና ብሎ ጎብኚዎችን የሚመለከት ሰራተኛ አልነበረም። ሁሉም ሥራውን ማጠናቀቅ ላይ ማተኮሩ በፊት ይታወቅ የነበረውን ቦታ ገፅታ ሙሉ ለሙሉ መቀየር አስችሏል ይላሉ። የአንድነት ፓርክ በየጊዜው አዳዲስ ነገሮች እየተጨመሩለት ትልቅ ለውጥ እያሳየ ነው። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ የፕሮጀክት አፈፃፀሙ ክትትል የሚደረግበት በመሆኑ ሰራተኞቹም አዲስ ነገር ይዘው የመቅረብ ፍላጎት ስላላቸው ለውጥ ማየት የተለመደ ነው። አንድን ነገር ያዝ ለቀቅ ማድረግ ሳይሆን፤ አጠንክሮ ይዞ ግብ መምታት ላይ ማተኮሩ ስኬታማ እንደሚያደርግ በእነዚህ ፓርኮች ተረጋግጧል። በየጊዜው እየታየ ሥራው አስተያየት ይሰጥበታል። አስተያየቱን ተከትሎ ቀን እና ለሊት ይሰራል። ስለዚህ ሌሎች ፕሮጀክቶችንም የሚመሩ ሰዎች ከእነዚህ ፕሮጀክቶች ትልቅ ልምድ መውሰድ እንዳለባቸውም ነው አቶ ተሾመ የገለፁት። አዲስ ዘመን ሰኔ 16/2012ምህረት ሞገስ", "passage_id": "240091c16f60e146c5bb8a10afbbf95b" }, { "passage": "ዓምና በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ በአንድ ጀምበር ከ350 ሚሊዮን እንዲሁም በክረምቱ መርሃግብር ከአራት ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል በሕንድ ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረ ወሰን ኢትዮጵያ መስበሯ ይታወሳል። ይህንኑ ተግባር በዚህ ዓመት በተሻለ መነቃቃት እና ነገን ታሳቢ ባደረገ ጥንቃቄ ለመድገምም ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቀው እነሆ በዛሬው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከናወነውን የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በደቡብ ክልል ያስጀምራሉ። በዚህ ዓመት በመላው አገሪቱ አምስት ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል በችግኝ ዝግጅቱም በአስተሳሰብም በተግባርም በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተነግሯል።በዚህም የአገሪቷን አረንጓዴ ሽፋን ከማሳደግ ባለፈ የአርሶ አደሩን ህይወት መለወጥ የሚችሉ የፍራፍሬ ዛፎች በስፋት መዘጋጀታቸውን የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ኡመር ሁሴን ገልጸዋል። ከአምስት ቢሊዮኑ ችግኞች 60 በመቶ የሚሆኑት ለምግብነት ሊውሉ የሚችሉ የአትክልትና የፍራፍሬ ተክሎች መሆናቸውን ያስታወቁት ሚኒስትሩ፤ ከቀሪው 40 በመቶ ውስጥ ደግሞ ትልቁ ድርሻ ያላቸው የአገር በቀል ተክሎች መሆናቸውንም ጠቁመዋል። ለዚህም በአገር አቀፍ ደረጃ ከተዘጋጁት 24ሺ የችግኝ ጣቢያዎች በትግራይ ክልል አንድ በመቶ፤ በአማራ ክልል 32 በመቶ፣ በኦሮሚያ ክልል 42 በመቶ እንዲሁም በደቡብ ክልል 25 በመቶ እንደሚሸፍን ተናግረዋል። በችግኝ ተከላ ወቅት የኮቪድ 19 ተጽእኖ ተግዳሮት ሊሆን እንደሚችል የጠቆሙት አቶ ኡመር፤ ሂደቱም ችግኝ በመጫንና በማውረድ፤ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ራስን የመጠበቂያ መሳሪያዎችን በማቅረብና በብዛት ወጣቶችን ተሳታፊ በማድረግ እንደሚካሄድ ገልጸዋል። አቶ ኡመር፤ ችግኝ ለፈጣን ልማት አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት፤ የህዝቡን ኑሮና ለማሻሻል እንዲሁም አገርን ለማበልጸግ እንደሚረዳና ከዛሬው የአረንጓዴ አሻራ ይፋዊ የችግኝ ተከላ ዕለት ጀምሮ ተመሳሳይ የችግኝ ተከላ ዘመቻዎች እንደሚካሄዱና ለዚህም በቂ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል። የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በበኩላቸው ችግኞቹ አገሪቷን በግብርና ኢኮኖሚ መጥቀም የሚችሉ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ እያንዳንዱ ሳይት ላይ ምን ያህል አለ የሚለው በቴክኖሎጂ በመታገዙ ለመንከባከብ እንደሚያግዝና ይህም አምስት ቢሊዮን የመድረሱን ዓላማ ለማሳካት ውጤታማ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።ህዝቡ በየዓመቱ የሚያከናውነው የችግኝ ተከላ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዳይተላለፍ በሚያግዝ ስልት መንግስት ተገቢውን ዝግጅት ማድረጉን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፤ ከይፋዊው የተከላ እለት ጀምሮ እስከ ሀምሌ ወር መጨረሻ ተግባራዊ ክንዋኔው እንደሚቀጥል ተናግረዋል። በመሆኑም ዝናብን ሳይጠብቁ በመስኖ በማልማት ምርታማነትን ማስፋፋትና አገሪቷ ወደ ኋላ በቀረው ግብርናዋ በዘመናዊ መንገድ ታግዛ ውጤታማ እንድትሆን ማድረግ እንደሚገባም ሚኒስትሩ ገልጸዋል። “ችግኝ ከተፋሰስ አጠባበቅ አኳያ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። አገር በቀል የሆኑ የዛፍ አይነቶች ቢተከሉ ምርት ሊሰጡ የሚችሉና አፈሩን መንከባከብን የሚችሉ ስላሉ የዝናብ መጠንን ለመጨመር ያስችላል። ይህም የውሃ በጀት እንዲያድግ ያደርጋል። ከዚህም ባሻገር ደለል በወንዞች ውስጥ አልፎ ወንዞች እንዳይሞሉ ይከላከላል። የተሻለ የምንጭና የከርሰ ምድር ክምችት እንዲኖር ያግዛል። የአካባቢንና የዓለም ሙቀትን ለመቀነስም ያስችላሉ” በማለት ችግኝ ከዛፍነቱ ባሻገር ብዙ ሚና እንዳለው አብራርተዋል። የአረንጓዴ አሻራ ብሄራዊ ኮሚቴ አባል አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፤ በችግኝ ማፊያ ማዕከላት የሚታዩት ተግባራት ጥሩ ደረጃ ላይ መሆናቸውንና ከዚህም በላይ ብዙ ሥራ እንደሚጠበቅ፤ ጅማሮው ያማረ እንደሆነ ሁሉ በዘላቂነት የሚከናወነው ተግባርም እንዲሁ ታሳቢ መደረግ እንዳለበት ተናግሯል። ምርት በተገቢው ሁኔታ ለማግኘት በባለቤትነት እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባና ምርቱን ለተፈለገው ዓላማ ለማዋል ከፍተኛ ጥረት እንደሚያስፈልግ አመላክቷል። የተራቆቱ አካባቢዎችን በማልማት አዳዲስ ምርቶችን የማስተዋወቅ ሥራው ቀጣይነት ያለው እንዲሆን የአረንጓዴ አሻራ ብሄራዊ ኮሚቴ አባላት በሚገባ መስራት እንዳለባቸው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ተናግሯል። ድምጻዊ ስለሺ ደምሴ (ጋሽ አበራ ሞላ) “በባለሙያዎች አማካኝነት የተደረገው ችግኝ የማፍላት ሥራው በመስክ ጉብኝት መልካም ነገሮችን አይተናል። በተለይ የሚተከሉ ችግኞች በዓይነት መብዛታቸው ደግሞ የማህበረሰቡን የአኗኗር ባህሪ መሠረት ያደረጉ በመሆናቸው የአካባቢን ስነምህዳር ከመጠበቅ አልፈው በፋይናንስ በኩል ከፍተኛ ጠቀሜታ ይሰጣሉ። ለመትከል የታሰበውን ቁጥር ለማሳካት ተክሎች ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆኑ በአእምሮ ውስጥ ቀድሞ መትከል ይገባል’’ ይላሉ። እርሳቸውን ጨምሮ ያሉ የኮሚቴ አባላት እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች ይህንን ግንዛቤ ለህብረተሰቡ ማድረስ እንዳለባቸው ድምጻዊ ስለሺ ደምሴ ተናግሯል። በተከላው ላይ የሚደረገው ዘመቻ ኃላፊነት ወስዶ በመንከባከብም ሊቀጥል እንደሚገባ ያመላክታሉ። አዲስ ዘመን ግንቦት 28/2012 አዲሱ ገረመው", "passage_id": "b2464022e5e0160a67da350cc00c734f" }, { "passage": "የአዲስ አበባ ጎዳናዎች አልፎ አልፎ ሽው ሲሉ ከሚታዩት ተሽከርካሪዎች ውጪ በእግረኞች ተሞልተዋል፡፡ ገና ከረፋዱ ከቤታቸው የሚወጡት እናቶች ነጠላቸውን ትከሻቸው ላይ ጣል አድርገው በጥበብ ልብስ ይታያሉ፡፡ ህፃናት በየመንገዱ ይቦርቃሉ፡፡ ወጣቶች በተለየ ሁኔታ ከፀጉር እስከ እግር ጥፍራቸው አምረው ተውበዋል፡፡ ወንዶቹ በትንሽ ርቀት ውስጥ ከአምስት እስከ 10 ብር የሚሸጡ የፕሪም ፍሬ የያዙ እሽጎችን ይገዛሉ፡፡ በየመንገዱ ያሉት እንቅስቃሴዎች ሁሉ በየአቅ ራቢያቸው ወዳሉ አብያተ ቤተክርስቲያናት ይተማሉና እኛም ይህንኑ እየተመለከትን ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ዘለቅን፡፡ ድንገት ታዲያ  ስርዓቱን በምስል የሚያስቀሩ ጎብኚዎች ላይ ዓይናችን አረፈ፡፡በዜግነት ጀርመናዊ በአሁኑ ወቅት ኑሯቸውን በአሜሪካ የከተሙት ቤረንት ባሶሊክ አፍሪካን የሚያውቋት ቢሆንም በኢትዮጵያ ግን የመ ጀመሪያቸው መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ በታሪክ መጽሐፍት ባነበቡት በአገሪቱ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ታሪኮቿ ተደመዋል፡፡ ከአፍሪካ በቅኝ ግዛት ያልተያዘች አስገራሚ አገር ከራሱ አልፎ ለሌሎች ክብር የሚሰጥ አስደናቂ ሕዝብም አላት፡፡ የጥምቀት በዓልም አከባበር ከሚያውቁት በተለየና በታላቅ ድምቀት የሚከበር ሆኖም አግኝ ተውታል፡፡የአገሪቱ የቱሪዝም ዕድገት በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ ማስተዋወቅ ላይ ሰፊ ሥራ ሊሰራ እንደሚገባ ቤረንት ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም ምንም እንኳ እንደ ሆቴል ያሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የተሻለ ነገር ቢታይም ትልቅ አገርና በርካታ ለጉብኝት የሚበቃ ቅርስና ታሪክ ባለቤት በመሆኗ መሠረተ ልማቱ ላይ በትኩረት መሠራት አለበት፡፡ በዚህም በአሁኑ ወቅት በመኪና ላይ የሚያልፈው ሰፊ ጊዜ ለማሻሻል ፈጣን መንገዶች አገልግሎት ቢመቻች የተሻለ ነው፡፡ከአሜሪካ የመጣችው ሌላኛዋ ጎብኚ ጄሪ ካስዋ ናት፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣም የመጀመሪያዋ እንደሆነ ተናግራለች፡፡ በቆየችባቸው ሶስት ሳምንተት በአዲስ አበባ፣ ጎንደር፣ ኣኽሹም፣ ላሊበላና ኦሞ ላይ ከተመለከተቻቸው  የቱሪዝም መስህቦች በተጨማሪ አገሪቱ የሕዝቦቿ ተግባቢነትና መልካምነት ከተፈጥሯዊ ገጽታዋ ጋር ተደማምሮ ፈርጥ አድርገዋታል ስትል ደስታዋን ገልፃለች፡፡ጂሪ፤ አንዳንድ የዓለም አገራት ጥምቀት እንሚያከብሩ ቢታወቅም የኢትዮጵያ ግን የተለየ ሆኖ እንዳገኘችው ትዝብቷን ተናግራለች፡፡እርሷ በምትኖርበት አገር ስለ ኢትዮጵያ ያላቸው ዕውቀት እምብዛም መሆኑን የምታነሳው ጎብኚዋ፤ በጣም ደስ የሚል አስገራሚ አገር፣ ሕዝብና ባህል በመሆኑ ሌሎች እንዲያውቁ ማድረግ ይገባል፡፡ ለዚህም ለዓለም የማስተዋወቅ ሥራ መሠራት አለበት፡፡ በተያያዘ በርካቶቹ ሆቴሎች የሚሰጡት አገልግሎት ጥሩ ቢሆኑም አንዳንዶቹ ላይ ግን ሥራ ያስፈልጋል፡፡ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመጓጓዝ የተወሰነ አስቸጋሪ ሁኔታ እንደተመለከተች በመግለጽም፤ በቀጣይ መሠረተ ልማት ላይ ተጠናክሮ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁማለች፡፡ቅኝታችንን ቀጥለናል ከተለያየ አካባቢ የሚሰበሰቡት ሰዎች ታቦቱን በሃይማኖታዊ ሥነስርዓቶች አጅበው ወደሚሄዱበት ጃንሜዳ አመራን፡፡ በሜዳው ላይ ‹‹ደግሞ ሌላ ደግሞ ሌላ›› የሚሉ የጨዋታ ጥሪዎች ድምጽ ይሰማል፡፡ ፈረስ ግልቢያ፣ የተለያዩ ወጣቶችን ያሳተፉ ጨዋታዎችና ወድድሮች በየቦታው ይታያሉ፡፡ እነዚህን ሁሉ ትዕይንቶች በመመልከት ላይ ያገኘናቸው ሌላኛው ጎብኚ ከጀርመን የጥምቀት በዓልን ለመታደም ከሶሰት ሳምንታት በፊት የገቡት ዶክተር አኪዩሌዲ ማቲኖ ናቸው፡፡በዓሉ በርካቶችን በአንድ ቦታ አሰባስቦ የሚያሳይ ትዕይንት የተሞላበት ሲሉም ዶክተር አኪዩሌዲ አሞካሽተውታል፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ጓደኞች እንዳሏቸው በመግለጽ፤ ምነም እንኳ ለኢትዮጵያ በአካል ሲገኙ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ እንግዳ ቢያደርጋቸውም ወደ አፍሪካ ሲመጡ ግን የመጀመሪያቸው አይደለም፡፡ ከዚህ  በተጨማሪም ስለ ኢትዮጵያ ቀደምት ታሪኮች በተለያዩ ታሪክ መጽሐፎች በማንበባቸው ስለ አገሪቱ ቀድመው እንዲያውቁ እንደረዳቸው አልሸሸጉም፡፡ በመጽሐፎቹ ስለ ጣሊያን ወረራና ከዛም አስቀድሞ ስላሏት ታሪኮችና ከክርስትና ጋር ያላት ግን|ኙነት ሁሉ አንብበዋል፡፡ በዓሉ ከሃይማኖታዊነቱ ባሻገር ቤተሰብ ብሎም ወዳጅ ዘመዶች በአንድ ቦታ ተሰባስበው የሚደሰቱበት፣ የሚያከብሩበትና ለአምላካቸው ፀሎታቸውን የሚያደርሱበት መሆኑ አስደናቂ አድርጎታል፡፡ኢትዮጵያን በቅጡ ለመመልከት ሶስት ሳምንታት ብቻ በቂ ባይሆንም የተመለከቷቸው የቱሪስት መስሀቦች መኖራቸውንም ሳያነሱ አላለፉም፡፡ ትግራይ፣ ጎንደር፣ ባህር ዳር እንዲሁም ሐረር የደረሱባው ስፍራዎች ሲሆኑ፤ በርካታ የአገሪቱ አካባቢዎች በታሪክ የተሞሉ መሆና ቸውንም አንስተዋል፡፡ አገሪቱ ልትጎበኝ የምትገባ በመሆኗ የቱሪዝም ዘርፉን በቀጣይ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ መሥራት ይገባል፡፡ ለዚህም ደግሞ የተረጋጋ ምቹ ሁኔታ መኖሩ ጠቃሚ ቢሆንም ለጎብኚዎች የቪዛ አሰራሮችን ቀላል ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡ ሲመለሱም የተመለከቱትን ለሌሎች እንደሚያጋሩ በመግለጽ፤ ኢትዮጵያውያን ትህትና ለተሞላበት እንግዳ አቀባበላቸውና እርዳታቸው ምስጋናቸውን ቸረዋል፡፡በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ታደለ ጀማል፤ የጥምቀት በዓል ሕዝቦች አደባባይ ወጥተው የሚያከብሩት ነው፡፡ ይህ በመሆኑ ደግሞ ከባህር ማዶ ነዋሪነታቸውን ያደረጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ሁሉ ይታደሙታል፡፡ በዓሉ ታሪካዊነት የተሞላበት፣ አብሮነት እንዲሁም ሕዝቡ በሰላምና ፍቅር በዓመት አንዴ የሚገናኝበት በመሆኑ ሚኒስቴሩ ከተለያዩ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ይሠራል፡፡በዓሉ በመላ አገሪቱ የሚከበር ቢሆንም በርከት ያለ ቁጥር ያለው ጎብኚ ግን የሚበዛባቸው ስፍራዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡ አንዱ አዲስ አበባ ሲሆን፤ ሌላው ደግሞ ጎንደር ነው፡፡ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ በአገሪቱ እጅጉን የበለፀጉ በዓላት፣ ታሪክና ቅርሶች እንዳሏት የማስተዋወቅ ሥራ ይሰራል፡፡ በቀጣይም መንግስት በአሁኑ ወቅት ያለውን የሆቴል አገልግሎት፣ ሪዞርቶች፣ መዝናኛ፣ ሎጆች በየመዳረሻው ያሉ ልማቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር እንደሚሰራ ከፍተኛ ባለሙያው አመላክተዋል፡፡አዲስ ዘመን ጥር 13/2011በፍዮሪ ተወልደ", "passage_id": "21e3c261e90563a2890fc87ab0a9a3aa" }, { "passage": "ከግቢው አጥር ግራና ቀኝ ተፈጥሮዓዊ መስህብ የተላበሱ አለፍ አለፍ ብለው የተተከሉ ችግኞች ይታያሉ። ልምላሜያቸው መፅደቅ መጀመራቸው ያመለክታል። አደራደራቸውም እንዲሁ ለዓይን ይማርካል። በግቢው ውስጥ ያሉ ዛፎች፣ አትክልት፣ ፍራፍሬዎችና አበባዎች መዓዛ ያውዳል። በስርዓት ችምችም ብለው ያደጉት ብዙ አይነት ዛፎች በቦታው ለተገኘ ፍጡር ንፁህ አየር ይመግባሉ። \nከግቢው በስተግራ በተሰናዳው ስፍራ በፕላስቲክ ከረጢቶች ለመትከል የተዘጋጁ ብዙ ዓይነት ዝርያ ያላቸው ችግኞች ከጫፍ እስከ ጫፍ ተሰልፈው ይታያሉ። የቤተሰቡ ኣባላት ችግኞቹን በመንከባከብ ስራ ተጠምደዋል። ይህ በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ነዋሪ የሆኑት የኮማንደር ጥላሁን ፀጋዬ ግቢ ነው። \nለአረንጓዴ አሻራ ማኖር በግለሰብ ደረጃ ከሚተጉ የአረንጓዴ ልማት አርበኞች መካከል ኮማንደር ጥላሁን ፀጋዬ አንዱ ናቸው። ኮማንደር ጥላሁን የዓየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የአረንጓዴ ልማት ቀድመው የጀመሩ የታታሪዎች ምሳሌ ናቸው። በግል ተነሳሽነት ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ ችግኞች\n አፍልቶ በመትከል በግቢያቸው ውስጥ ፅድ፣ ባህር ዛፍ፣ ግራቪሊያ፣ ግራር፣ ዋንዛ፣ ሸውሸዌ፣ ቡና፣ ፓፓያ፣ አቮካዶና የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎች አልምተዋል። \n‹‹የተከልኳቸው ዛፎች የአይኔ ማሳረፊያ ልጆቼ ናቸው›› ኮማንደር ጥላሁን ለተፈጥሮና ለዛፎቹ ያላቸው ጥልቅ ፍቅር የሚያሳዩት እንደ ልጆቻቸው ተንከባክበው ለመጪው ትውልድ የሚያስተላልፉት መተኪያ የሌለው ሃብት መሆኑን ይናገራሉ። ከራሳቸው አልፈው ለማህበረሰቡና ለተለያዩ ድርጅቶች ለዓመታት ችግኞችን አፍልተው በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያቀርቡም ይገልፃሉ። \nተፈጥሮን መጠበቅ እና መንከባከብ ህይወትን ማስቀጠል ነው የሚሉት ኮማንደር ጥላሁን፤ በዚህ ዓመት የተለያዩ ፍራፍሬዎችን ለመትከል ማቀዳቸውንና ችግኞችን ለህብረተሰቡ ለማከፋፈል ማዘጋጀታቸውን ይገልፃሉ። ዛፍ የሰው ህይወት ከሞት የሚታደግ በመሆኑ ሁሉም በግሉ አረንጓዴ ልማት ላይ የጎላ ተሳትፎ ማድረግ የሚገባው መሆኑንም ይጠቁማሉ። \nለ50 ዓመታት ችግኞችን በመትከልና በማልማት የተራቆተ አካባቢ መልሶ እንዲያገግም በማድረግና የእድሜያቸውን አብዛኛው ክፍል በአረንጓዴ ልማት ላይ በማዋል ትልቅ አበርክቶ ያተረፉ ሌላኛው የአረንጓዴ አሻራ አርበኛ ደግሞ አቶ ጌታሁን መብራቴ ናቸው። ባፀደቋቸው ዛፎች ምክንያት ‹‹አባ ዛፉ›› በማለት\n የሚጠሩት የ85 ዓመት እድሜ ባለጸጋ የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪ አርሶ አደር ናቸው። ከላሊበላ ከተማ 42 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከሚገኘው አቡነ ዮሴፍ ቀበሌ (ከአቡነ ዮሴፍ ዝጊት አቦሃይ ጋሪያ ማህበረሰብ ጥብቅ ስፍራ) በቅርብ ርቀት ላይ ልዩ ቦታው እመቤት ዋሻ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነዋሪ ናቸው። \nከደርግ ዘመነ መንግስት ጀምሮ በራሳቸው ተነሳሽት ጉልበታቸውንና ሃብታቸውን በማፍሰስ ለ50 ዓመታት አገር በቀል ዛፎችን በማልማት በመጠበቅ በመሆን በርካታ ቁጥር ያላቸውን ዛፎች አልምተዋል። \nበነዚህ ዓመታት ውስጥ በ30 ሄክታር በተጎዳና በተራቆተ አካባቢ፣ ለሰብል ምርት የሚጠቀሙበትን የግል የእርሻ መሬት ጨምሮ ቁጥቋጦዎችንና የሳር ዝርያ አይነቶችን ሳይጨምር በርካታ የሃገር በቀል ዛፎችን አፅድቀዋል። በተለይ አምጃ፣ አስታ፣ ቀለዋ የተባሉ አገር በቀል ዛፍ ማልማታቸውን ይገልፃሉ። \n‹‹ለዛፍና ለተፈጥሮ ሃብት ልዩ ፍቅር አለኝ። የእድሜን አብዛኛው ክፍል ስተክልና ስንከባከብ የኖርኩት ሊዚያ ነው›› በማለት የሚገልፁት አቶ ጌታሁን፣ የደን ልማት ዋና ትኩረት ያደረጉት እየጠፉ በሚገኙ የአገር በቀል ዛፎች ላይ ነው። ከነዚህም ውስጥ የአካባቢውን ስነ ምህዳር ያስጠበቁት አስታ፣ አምጃ ቀለዋ፣ ቀጋ፣ ኮሶ ሲሆኑ ከዚህ ባለፈ የውጭ ዝርያ የሆኑ ዛፎችን አልምተዋል።\nአዲስ ዘመን ሰኔ 15/2012\nተገኝ ብሩ", "passage_id": "3b7a8f830037b4c3098b515744d24562" } ]
785fdbd629b6989a9b3604b85f73603b
b0f3f15da6770a931ef4b9947ecf883a
ነፃ ጠረጴዛ ፈልጉ!
በጠዋት ነው ቢሮ የገባሁት፤ በወሩ የመጨረሻ ቀናት ላይ ነኝና የሚደርሰኝን ገቢዬን ከወጪዬ ጋር እያሰላሁ ነው:: የቤት ኪራይ፤ የምግብ፤ የትራንስፖርትና ሌሎች ለመኖር አስፈላጊ የሚባሉ ወጪዎችን አሰላለሁ። ደመወዜንም አሰብኩት:: ኦ! አምላኬ ለካስ ደመወዜ ስንት እንደሆነ አላውቅም:: ማሰቡ ስለከበደኝ ተውኩት:: ወጪና ገቢዬን ሳመዛዝን ስላስጨነቀኝ ማሰቡን ለመርሳት ሞከርኩ:: የምር ግን ደመወዛችሁ ስንት እንደሆነ ታውቃላችሁ ወዳጆቼ? እኔ ግን ደመወዜ ስንት እደሆነ አላውቅም:: ”እንዴት?” ካላችሁኝ ምክንያት አለኝ:: ቆዩማ፤ እንዴት ላውቀው እችላለው እኔ ዘንድ ደርሶ አያውቅማ፤ ያልቀረበን ነገር ማወቅ ይከብድ የለ? ከእጄ ሳይደርስ እኮ ነው ተከፋፍሎ የሚያልቀው፤ ሳሳዝን! ሰርቼ፤ ጥሬ ግሬ የማስረክባቸው ብዙ ጠባቂዎች አሉኝ::እኔ ምለው!? እኔ ወጪና ገቢዬን እያሰብኩ ከምጨነቅና ግራ ከምጋባ ሰዎችን ላስቸግር መሰለኝ:: እስኪ አስታውሱኝ ስንት ነበር? የቤት አከራዬ፤ የመስሪያ ቤቴ ሻይ ክበብ፤ የምመላለስባችሁ ታክሲዎች፤ እኔ ሰፈር ያለኸው ባለ ሱቅ፤ የምትቀፍሉኝ ጓደኞቼ፤ እስኪ አንዴ ሰብሰብ በሉና ወርሐዊ ወጪዬን ንገሩኝ:: እኔ ምንም ገቢ የለኝማ:: የተቀበልኩትን መስጠት፤ የተሰጠኝን ለእናንተ ማድረስ ስለሆነ ገቢዬን አላውቅም:: እናንተ ከእኔ የምታገኙት ገቢ ምን ያህል እንደሆነ ደመር.. ደመር አድርጉና ንገሩኝ:: ከወጪ ይልቅ ገቢ መደመር ደስ ይል የለ? አዎን!በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ሰኞ ላይ የሥራ “ሙዴ” ቶሎ አይቆሰቆስም:: ልምድ ይሁን እንጃ ብቻ ሰኞ ዕለት ብሰራም የሰራሁት ለእኔም አያጠግበኝም:: በጠዋት ቢሮዬ ገብቼ ኮምፒዩተሬን መነካካት፤ መረጃዎችን ማየት ቀጠልኩ። በሳምንቱ ውስጥ በምሰራቸው ተግባራት ምንነት ላይ በወጉ እያሰብኩ ቆዬቼ፤ ሥራ ከመጀመሬ በፊት ቡና ጠጥቼ ነቃ ለማለት ወደ ሻይ ክበብ ሄድኩ:: ዛሬ ቀኔን ብሩህ ላደርገው አስቤያለሁ:: ደስ የሚል ቀን ማሳለፍ ፈልጌያለሁ:: ሰላም መናፈሻ ውስጥ የተመለከትኳቸውን ባልደረቦቼን ተቀላቀልኳቸው:: ሙግት ይዘዋል። አንዱ የሌላውን ሐሳብ ይነቅፋል፤ የራሱን ደግሞ ያስከትላል:: የሚከራከሩበት ርዕሰ ጉዳዩ አንድ፤ አተያያቸው ግን ለየቅል ሆኖ ላለመግባባት በሚመስል ሁኔታ በቃላት ይፋለጣሉ:: ጉዳዩ የሰለቸኝ የፖለቲካ ጉዳይ ነው:: መከራከሪያው ወቅታዊ ርዕሰ ጉዳይ ነው:: ይሄ ክርክር ተደጋገመና በየሄድኩበት የሚወራው እሱ ሆነና ሰለቸኝ:: ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚያነሳና የሚጥለው ፖለቲካዊ ጉዳይ ላይ ሆነና አሰለቸኝ:: ወሬው ሁሉ ፖለቲካ የተቀላቀለበት ሆነና እረፍት ፈለኩ:: ቦታዬን የቀየርኩት በምክንያት ነው። ክርክሩን ለመራቅ፤ ተሳካልኝና በቀየርኩት ጠረጴዛ ላይ ሌላ ርዕሰ ጉዳይ ተይዟል:: “ኡፉፉ…ግልግል”፤ እዚህ በሚወራው ሌላ ርዕሰ ጉዳይ ደስ ተሰኘሁ:: ሰሞኑን በወጣ መጽሐፍ ላይ ነው ውይይቱ፤ አጋጣሚ እኔም መጽሐፉን አንብቤው ስለነበር አፍታም ሳልቆይ ሐሳቡ ሲገባኝ መሳተፍ ጀመርኩ:: ትንሽ ሐሳብ እንደተለዋወጥን በመጽሐፉ ላይ ያለ አንድ ርዕሰ ጉዳይ “የሆነ ወገን የሚነካ ነው” መባሉ ከዚያው ከተወያዮች መካከል ተነሳ:: ይሄኔ ጠረጴዛው ላይ ያለው ውይይት መልኩ ሊቀይር እንደሆነ ገባኝና ተከፋሁ:: በተቻለኝ መጠን ርዕሰ ጉዳዩን ልቀይረው ፈለግሁ። አልተሳካልኝም:: ጭራሽ ጉዳዩ ከርሮ የተናገረውን ልጅ ትርጓሜ ተቃራኒ የሆነ ሐሳብ ያለው ነበረና “እነሱ ድሮም…” ማለት ሲጀምር ያዘዝኩትን ቡና ሳልጨርስ ከመቀመጫዬ ተነስቼ መዝናኛ ክበቡን ለቅቄ ወደ ቢሮዬ አመራሁ:: ቢሮዬ ገብቼ ሥራ ከመጀመሬ በፊት የዓለምን አዳር ለማየት ማህበራዊ ገፆችን ከፈትኩ:: ማየት ከሰለቸኝ ርዕሰ ጉዳይ ውጭ የተጻፈ ጽሑፍ፣ ማየት ከመረረኝ ዜና ውጭ ብዙም አዲስ ነገር አጣሁ:: ከፖለቲካ ነፃ የሆነ ምንም ባይኖርም ነፃ የሆነ ሐሳብ ግን ሞልቷል:: የት ሄዶብን ይሆን ነፃ የሆነው ሃሳባችን እንዲህ የሌሎች ሃሳብና አተያይ ጥገኛ ሆነን የቀረነው ጎበዝ!? እንዴት ነፃ መውጣትና በራሳችን መልካም እሳቤ መጓዝ፤ እኛው በምናምንበት በጎ አመለካከት መዝለቅ አቃተን? በጣም ናፈቀኝ፤ የናፈኩት ግን ከአይኔ የራቀ፤ የጠፋብኝ ዘመዴ ወይም ወዳጄ አይደለም:: በጣም አሰኘኝ፤ ያሰኘኝ የምበላው ምግብ ወይም የምጎነጨው ጣፋጭ መጠጥ ግን አይደለም:: የናፈቀኝ ነፃ ጠረጴዛ ነው። መደማመጥ ያለበት፤ ፍሬ ያለው ሐሳብ የሚለዋወጡበት፤ ከፖለቲካዊ ክርክር ነፃ የሆነ ጠረጴዛ፤ ሰዎች ሁሉ የራሳቸውን ሥራ እርግፍ አድርገው መደበኛ “ሥራዬ ፖለቲከኛነት ነው፤ ወሬዬም ከዚያ የማይሻገር” ብለው ከያዙት አሰልቺ ንትርክ ነፃ የሆነ ጠረጴዛ ናፈቀኝ፤አሁን ላይ እኮ ብሶብናል ወገን፤ እንዴት ሁላችንም ፖለቲከኛ ሆነን እንችለዋለን? ግዴለም የምግብና የመጠጥ ማጀቢያችን፤ የጉዞና የአብሮነት ቆይታችን ማጣፈጫ ሌላ መሆኑን ትተን ይሄው ጉዳይ ይሁን፤ ግን እንዴት መሰማማት ተሳነን? ምንም አይነት መደማመጥ በሌለበት የቃላት ልውውጡ ድንበር አልፎ ለጠብ የሚዳርግ እየሆነ ነው:: ታዲያ ይሄ አይሰለችም ወገን? ሃሳብ በመሞገት ማሸነፍ ሳይሆን፤ የራስን ስሜት ብቻ የሚከተሉበትን፤ መግባባት የራቀውን ክርክር ጠላሁ::ነፃ የሆነ ሰው ታውቃላችሁ? ነፃነትን ተጎናጽፎ ንፅት፤ ፅድት ብሎ ህይወቱን የሚመራ ሰው የምታውቁ ከሆነ አገናኙኝ:: አመላክቱኝና ይሄ ሰው ነፃ መሆንን እንዲያጋባብኝ ልወዳጀው፤ እንዴት ይሆን የሚኖረው? ምን አይነት ሐሴት ተጎናፅፎ፤ ምንኛ ከፍ ያለ የመንፈስ እርካታ በውስጡ ናኝቶ? የቱስ አይነት ሐሴት በውስጡ ሰርፆ፤ ሰላም አስገኝቶ ይሆን? ሲያስቀና! እንዲህ ያለ ሰው የማግኘት ህልም አለኝ:: ወዳጆቼ ምሩኝና ላግኘው እባካችሁ! ነገሮችን ሚዛናዊ ሆኖ የሚያይ፤ በስሜት ከመፍረድና ከመወሰን ይልቅ አስልቶ የሚጓዝ ሰው ፈልጉልኝማ፤ ነፃነቱን ተጎናፅፎ ሐሳቡን የሚያራምድ ሰው ተወደደ አይደል? ታዲያ ወዳጆቼ እንዲህ ያለ ሰው መናፈቅ ይነሰኝ? ነፃ የሆነ ባጣ፤ ሁሉም በራሱ ነፃነቱን አጥቶ፤ አርነቱን አስነጥቆ በተገኘበት ዘመን ነፃ የሆነ ሰው መፈለጌ ትክክል አይደለሁ?ነፃ መሆን ውስጣዊ ሰላም ይሰጣል:: ነፃነት ውድ ቢሆንም ሊጎናፀፉት ግድ የሚል የሐሴት መድረክ ነው:: ነፃነት የደስታ ጥግ ላይ የሚያደርስ ብቸኛ መንገድ ነው:: ግን ደግሞ አብዛኞቻችን ነፃነታችንን የምናጣው በኛው በግል ተግባራችን ነው:: ውዶቼ የምናስበውን ነፃነት ነፃ ሆነን ካላሰብነው ነፃነቱ በራሱ ባርነት ነው:: አርነት ውስጥ የማይጎናፀፉት ድል የለም:: አቦ! ከአድልኦ፤ ከበደል፤ ከምቀኝነት ነፃ ያውጣን! አበቃሁ:: ቸር ያሰማን! አዲስ ዘመን ጥቅምት28/2012 ተገኝ ብሩ
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=22165
[ { "passage": "ፈር ቀዳጁ የገበያ ማዕከልየውጭ ገንዘብ መመንዘሪያ (ፎረክስ ቢሮ)በየሳምንቱ ሰርፕራይዝ አለየንፅህና መስጫ (ላውንደሪ)ብዙ መሸመት ያሸልማል የሕፃናት ማቆያ ሱፐርማርኬት፡- ተገልጋዩ ልሹ የሚፈልገውን ዕቃ በመምረጥ (ለምሳሌ የምግብ፣ የቤት ዕቃ፣ የሕፃናት መገልገያ፣ …) የሚገዛበት የችርቻሮ ገበያ ማዕከል ነው፡፡ ሃይፐርማርኬት፡- ዴፓርትመንት ስቶርንና ሱፐርማርኬትን አጠቃሎ የያዘ በጣም ግዙፍ (ሱፐር ስቶር) የገበያ ማዕከል ማለት ነው፡፡ * * *በአገራችን ዴፓርትመንት ስቶር ለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ሱፐርማርኬት ግን ሸዋ ሱፐር ማርኬት “ሱማሌ ተራ” ከተከፈተበት ከ1958 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 50 ዓመታት ያህል ይታወቃል፡፡ ሸዋ ሱፐርማርኬት፣ አምስት የገበያ ማዕከላትን በቦሌ፣ በጦር ኃይሎች፣ በሳር ቤት፣ በሲኤምሲ አካባቢ ከፍቶ ሲሠል ከቆየ በኋላ፣ ሰሞኑን ደግሞ መገናኛ አካባቢ ከቤተልሔም ፕላዛ ፊት ለፊት በዘፍመሽ ግራንድ ሞል (ትልቅ የገበያ ማዕከል) ስድስተኛ ቅርንጫፉን ከፍቷል - “ሸዋ ሃይፐርማርኬት” በሚል፡፡ የሸዋ ሱፐርማርኬት መስራችና ባለቤት ማን እንደሆኑና ከምን ተነስተው እንደከፈቱት ወደ ኋላ ላይ እመለስበታለሁ፡፡ በ3ሺ ካ.ሜ ላይ ባረፈው ሸዋ ሃይፐርማርኬት ሲገቡ፣ መገረምዎና መደነቅዎ አይቀርም፡፡የዕቃዎች ዓይነት፣ ብዛትና ጥራት አጃኢብ ያሰኛል፡፡ በገበያ ማዕከሉ ፈልገው የሚያጡት ነገር የለም፡፡ “ደንበኞቻችን የሚፈልጉትንና መርካቶም ሆነ ሌላ ቦታ ሄደው የሚገዙትን ማንኛውንም ነገር (ምግብ፣ የቤት ዕቃ፣ የሕፃናት መገልገያ …) እዚሁ በአንድ ቦታ እንዲያገኙ አድርገናል” ይላሉ የሸዋ ሃይፐርማርኬት ሼል አስኪያጅ አቶ ግርማይ ዓለማየሁ፡፡ አሁን በምሥራቅ በር እንግባና እንጐብኝ። የነገው አገር ተረካቢ ሕፃናት ጤናማ ሆነው፣ ምቾትና ፍላጐታቸው ተጠብቆ እንዲያድጉ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷል፡፡ ከተወለዱበት ዕለት ጀምሮ የሚያስፈልጋቸው ነገር በዘርፍ በዘርፉ ተዘጋጅቷል። ምግብ፣ የገላ ማጠቢያ፣ መታቀፊያ፣ ልብስ፣ ጡጦ፣ ቅባቶች፣ ሻምፑዎች፣ የንፅህና መጠበቂያ ዳይፐር፣ የገላ መጥረጊያ ዋይፐር፣ ከፍ ሲሉ ደግሞ እንደ የዕድሜያቸው ጫማና ነጠላ ጫማ፣ የተለያዩ መጫወቻዎች፣ አሻንጉሊቶች፣ መኪኖች፣ የተለያየ መጠን ያላቸው አልጋዎች፣ የመመገቢያ ጠረጴዛ፣ ዳዴ ከማለታቸው በፊት የሚጠቀሙበት ጋሪ፣ ግራውንድ ፕላስ ዋን መጫወቻ ቤት፣ … ኧረ ስንቱ! ተዘርዝሮ አያልቅም፡፡ “አራት መደርደሪያ ሙሉ፣ (ከፊትና ከጀርባ ስምንት) ሸቀጦች መዘጋጀታቸው ለሕፃናት የተሰጠውን ትኩረት ያመለክታል” ብለዋል ሼል አስኪያጁ፡፡ ከሕፃናት መደብር ቀጥሎ የጽሕፈት መሳሪያዎች ናቸው ያሉት፡፡ ከትንሿ ነገር እስከ ትልቁ የፋይል ማቀፊያ 300 ዓይነት የጽሕፈት መሳሪያዎች አሉ፡፡ በዳር በኩል በስተግራ ኮስሞቲክስና ሽቶ፣ ጥራት ያላቸው ሞባይሎችና መለዋወጫዎች፣ ልዩ ልዩ የወርቅና የብር ጌጣጌጦች ይታያሉ፡፡ ሸሚዞች፣ የአዲዳስ ጫማዎች፣ ቱታዎችና የስፖርት ትጥቆች፣ … የሚሸጡበት ቡቲክ እየተዘጋጀ ነው፡፡ ከዚያ ፊት ለፊት ደግሞ የተለያየ ዓይነትና መጠን ያላቸው የጉዞ ሻንጣዎች (ላጌጅስ)፣ በፀሐይ ኃይል (ሶላር ሲስተም) የሚሠሩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ አምፑሎችና ኮምፒዩተር አክሰሰሪዎች (ሃርድ ዌርና ሶፍት ዌር) … በወግ በወጉ ተሰትረዋል፡፡ ከቡቲክ ቀጥሎ የዲኤስቲቪ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የተለያዩ መጠን ያላቸው ቴሌቪዥኖች፣ ምድጃዎች፣ ፍሪጆች፣ ማይክሮዌቭ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣ ውሃ ማሞቂያ፣ ጁስ መጭመቂያ፣ ፔርሙሶች፣ ሽንኩርት መፍጫ፣ … ከፊትና ከጀርባ 10 መደርደሪያ ሞልተዋል፡፡ ከዚያ በታች ያሉት የተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ የንፅህና መስጫ ዱቄትና ፈሳሽ ሳሙናዎች (ዲትሬጀንቶች) ናቸው፡፡ ስንዴና ጤፍም ሃይፐር ማርኬት ገብተዋል። ነጭ ጤፍ፣ ማኛ፣ ሠርገኛ፣ ቀይ ጤፍና የስንዴ ዱቄት በ50 ኪሎ እየሆኑ ተሰናድተዋል፡፡ ሌላው የሚገርመው “ትንሿን መርካቶ” የሚመስለው የጥራጥሬና የቅመማ ቅመም ገበያ ነው፡፡ የአገር ውስጥና የውጭ ለውዝ፣ ተልባ፣ የተለያየ ዓይነት ቦሎቄ፣ ፈንዲሻ፣ ማኛ (ማሽ) ምስር፣ ሽንብራ ዱቤ፣ ባቄላ፣ ቡና፣ ምስርና አተር ክክ፣ የቅንጬ እህሎች፣ የተፈጨ ጐመን ዘር፣ አብሽ፣ ዘለላ ሚጥሚጣ፣ ከሙን፣ ኮረሪማ፣ ሄል፣ ቀረፋ … ኧረ ተዘርዝሮ አያልቅም፡፡ ብቻ 70 ዓይነት ጥራጥሬና ቅመማ ቅመም ንፅህናቸው ተጠብቆ በመስተዋት ቤት ተቀምጠው፣ በዲጂታል ሚዛን እየተመዘኑ ይሸጣሉ፡፡ በአዲስ አበባ ታዋቂ የሆኑት የሙልሙል ዳቦ ሠራተኞች፣ እዚያው በገበያ ማዕከሉ የድርጅቱን መሳሪያ በመጠቀም ትኩስ ዳቦና ኬክ በመጋገር ለደንበኞች ያቀርባሉ፡፡ ክሬም ኬክ ግን ሌላ ቦታ ተጋግሮ ይቀርባል፡፡ ሃይፐርማርኬቱን ልዩ የሚያደርገው ጣፋጭ የሶሪያ ኬኮችን እዚያው ጋግሮ ማቅረቡ ነው፡፡ ባቅላባና ኩኪስን ጨምሮ 22 ዓይነት ጣፋጭ ምግቦች ያሰናዳል፡፡ ከዚያው ጐን ደግሞ ትኩስ ፒዛና በርገር ይጋገራል፡፡ በደንበኛው ፍላጐት መሠረት፣ የዶሮ፣ የበሬ፣ የበግ፣ የአትክልት፣ … 26 ዓይነት በርገሮችና ፒዛ ማግኘት ይችላል፡፡ ዓሳም አለ፡፡ ደንበኛው ከፈለገ በቋንጣ፣ ካልፈለገ ትኩሱን “ፊሌቶ አውጡልኝ” ብሎ መውሰድ ይችላል፡፡ የወተት ተዋጽኦዎችም በርካታ ናቸው። የሚያስጐመጅ የሥጋ ዓይነትም አለ፡፡ እንደ ደንበኛው ፍላጐት፣ ንቅል፣ የክትፎ፣ የወጥ፣ የጭቅና፣ የበርገር፣ … ማግኘት ይቻላል፡፡ ዝቅ ሲሉ፣ ፒያሳ አትክልት ተራ የገቡ ይመስልዎታል፡፡ ፒያሳ የሚገኘው አትክልትና ፍራፍሬ በሙሉ፣ በንፅህና ታሽጐ ቀርቧል፡፡ በኪሎ በኪሎ ተመዝነው ተፈጥሮዊ መልክና ጣዕማቸውን ይዘው እንዲቆዩ ፍሪጅ ውስጥና መደርደሪያ ላይ ተለይተው ተቀምጠዋል፡፡ ሃይፐርማኬቱን ልዩ የሚያደርገው ሌላው ነገር ዘመናዊ የሕፃናት ማቆያው ነው፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን ይዘው ዕቃ ፍለጋ የገበያ ማዕከሉን ሲዞሩ፣ ልጆች ሊደክማቸው ይችላል፡፡ ስለዚህ፣ ሞግዚቷ ልጆቹን ተቀብላ፣ መጫወቻ ወደተሟሉለት ማቆያ በመውሰድ እንደየዕድሜያቸው ታዝናናቸዋለች። “ወላጅ ልጆቹን ይዞ ከሠራተኛው ጋር ሊመጣ ይችላል፡፡ ያኔ ልጆቹ እየተጫወቱና እየተዝናኑ እንዲቆዩም ይደረጋል” ብለዋል ሼል አስኪያጁ፡፡ በማቆያው ሲጫወት ያገኘነው ዳኒ ቦጃ 7 ዓመቱ ነው። የ11 ዓመቷ እህቱ ሳሮኒያም አብራው ነበረች፡፡ ልጆቹ ማቆያውን በጣም ወደውታል። “ለልጆች በጣም ጥሩ መጫወቻ ስለሆነ በጣም ደስ ይላል” ብላለች - ሳሮኒያ፡፡ እቃ ለመግዛት ከወንድ ጓደኛዋ ጋር መጥታ በሃይፐርማርኬቱ ውስጥ ያገኘናት ራሔል ግርማም ሾለ ገበያ ማዕከሉ ጠይቄአት፤ “በጣም ደስ ብሎኛል፤ ከጠበቅነው በላይ ነው ያገኘነው፡፡ የምንፈልገው ዕቃ በሙሉ አለ። ከእንግዲህ ወዲያ ዕቃ መግዛት ስንፈልግ ወደዚህ እንመጣለን” ብላለች፡፡ ራሔል ዋጋውም ተመጣጣኝ መሆኑን ተናግራለች፡፡ “ስለ ዋጋው ጉዳይ ከእሱ ጋር (የወንድ ጓደኛዋን ማለቷ ነው) እየተወያየን ነበር፡፡ በሌላ ሱፐርማርኬቶች የምናውቃቸው ዕቃዎች በዚያው ዋጋ እዚህ አሉ፡፡ ስለዚህ ጥሩ ዕድል ነው፤ ብዙ ሳንለፋ ሁሉንም እዚሁ እንገበያለን ማለት ነው፡፡ በጣም ደስ ብሎኛል” በማለት አስተያየቷን ገልጻለች፡፡ እዚያው ያገኘነው ሌላው አስተያየት ሰጪ ማንደፍሮ “የአገራችንም ሆኑ የውጭ እንግዶች ይህን የገበያ ማዕከል በማግኘታቸው በጣም ደስ ብሎኛል። ለአገራችንም ክብር ነው” ብሏል፡፡ የገበያ ማዕከሉ ባንክ ቤት አለው፣ በቅርቡ ደግሞ የንፅህና መስጫው ላውንደሪ ሼል እንደሚጀምር አቶ ግርማይ ተናግረዋል፡፡ “ሌላው ለየት የሚያደርገን ባንካችን ሸዋ ፎሬክስ ቢሮ ነው፡፡ አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና እንደመሆኗ መጠን፣ የውጭ እንግዶችና ቱሪስቶች ይመጣሉ፡፡ እነዚህ የውጭ አገር ደንበኞቻችን ወደዚህ ሲመጡ ዕቃ መግዛት ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን ምንዛሪ በማጣት ይቸገራሉ። መመንዘሪያ ባንክ ፍለጋ እንዳይንከራተቱ ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር በመተባበር ሸዋ ፎሬክስ ቢሮ ከፍተናል፡፡ “ይህን ቢሮ የከፈትነው እኛ የውጭ ምንዛሪ (ዶላር) መቀበል ስለማንችል ነው፡፡ ሁለተኛ ደግሞ ደንበኞች ቼክ ይዘው ሊመጡ ይችላሉ፡፡ ቼኩን አንቀበልም ብለን ደንበኛውን ከምንመልስ፣ “ሸዋ ፎሬክስ” ቼኩን ተቀብሎ ገንዘብ ያለውና የሌለው መሆኑን አረጋግጦ፣ ፈርሞ ይሰጠናል፡፡ ስለዚህ ቼክ ይዘው የሚመጡ ደንበኞችም ይስተናገዳሉ ማለት ነው፡፡ ሌላው አዲስ ነገር ላውንደሪያችን ነው፡፡ ደንበኛው ወደኛ ሲመጣ ልብሶቹ እንዲታጠብለት ይሰጣል፡፡ በቀጠሮው ወይም በሌላ ጊዜ ሲመጣ ደግሞ ልብሶቹን ይዞ ይሄዳል፡፡ ይህ ለየት ያደርገናል” በማለት አስረድተዋል፡፡ ሸዋ ሃይፐርማርኬት ለ350 ሰዎች የመኪና ማቆሚያ አዘጋጅቷል፡፡ የገበያ ማዕከሉ 220 ሠራተኞች ያሉት ሲሆን ሠራተኞቹ ደንበኛ ማለት ምንድነው? ከእኛ ምን ይፈልጋል? እንዴት ነው ማስተናገድ የሚገባን? … በሚሉ ነጥቦች ዙሪያ ስልጠና እንደተሰጣቸው አቶ ግርማይ ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ንብረታቸውን ከሌባ ለመጠበቅና የደንበኞቻቸውን ደህንነት ለማረጋገጥ 58 ካሜራዎችና አንድ የሴኩሪቲ መከታተያ ካሜራ አለ፡፡ ለሸዋ ሃይፐርማርኬት መመሥረት መነሻ የሆኑት ሐጂ ቡሰር አህመድ ናቸው፡፡ ሐጂ ቡሰር፤ ፒያሳ፣ ወደ ሸዋ ዳቦ በሚያወጣው መንገድ በሸቀጣ ሸቀጥ ንግድ ይተዳዳሩ እንደነበር አቶ ግርማይ ይናገራሉ። ከዚያም በ1958 ዓ.ም “ሱማሌ ተራ” አካባቢ የመጀመሪያውን ሸዋ ሱፐርማርኬት ከፈቱ፡፡ ከብዙ ጊዜ ጥረትና ትግል በኋላ ሁለተኛውን ቦሌ አካባቢ “ሸዋ ሾፒንግ ሴንተር”፣ ሦስተኛውን ጦር ኃይሎች አካባቢ፣ ሳር ቤትና ሲኤምሲ አካባቢ ከፈቱ፡፡ ሐጂ ቡሰር በአሁኑ ወቅት በሕይወት የሉም፤ ከስድስት ወር በፊት በሞት ተለይተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ሸዋ ሃይፐርማርኬትን የሚመራው ልጃቸው አቶ ሐሰን ቡሰር ሲሆኑ የታዘዙ ዕቃዎችን ለማስጫን ውጭ አገር ስለሄዱ ልናገኛቸው አልቻልንም፡፡“በኢትዮጵያ የመጀመያ የሆነ በ3ሺህ ካ.ሜ ላይ ያረፈ ሃይፔርማርኬት (የተሟላ የገበያ ማዕከል) ለማዘጋጀት ከፍተኛ ጥረትና ብዙ ሚሊዮን ብሮች የጠየቀን ቢሆንም፤ የሕዝቡን ፍላጐት ለማርካት ቆርጠን ተነስተናል” ያሉት ሼል አስኪያጁ፤ አሁንም ህብረተሰቡ “ይኼ ቀረ፣ ይኼ ጐደለ” ካላቸው ለማሟላት ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ ዓላማችን የሕዝቡን ፍላጐት ማርካት ነው፤ ትልቅ የገበያ ማዕከል እስከሆነ ድረስ ሁሉንም ነገር ማሟላት አለበት ብለዋል፡፡ አንዳንድ ዕቃዎች ለምሳሌ የአሳማ ሥጋ፣ መጠጥና ሲጋራ የለም ተብለው የተጠየቁት ሼል አስኪያጁ፤ “ለጊዜው እነዚህ ነገሮች የሉም። ነገር ግን በምን መልኩ መቅረብ እንዳለባቸው ጥናት እየተካሄደ ነው፡፡ ከዚያም በጥናቱ መሠረት ተፈጻሚነት ያገኛል” ብለዋል፡፡ የገበያ ማዕከሉ ባለፈው ማክሰኞ ተከፍቷል። በዕለቱ የ1,500 ብር ዕቃ ለገዙ ወይም በዕለቱ መጥተው ባይገዙም በቅርቡ ለመግዛት ላቀዱ 250 ደንበኞች የ30 በመቶ ቅናሽ ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በየሳምንቱ በፍጆታ ዕቃዎች ላይ የ “ሰርፕራይዝ” ፕሮግራም መኖሩን ተናግረዋል፡፡ “ለምሳሌ ካሁን ቀደም ያደረግነው ስኳር 20 ብር በሚሸጥበት ወቅት እኛ ግማሽ በግማሽ ቀንሰን በዘጠኝ ብር ሸጠናል። ዘይትም በጣም በተወደደበት ጊዜ እንደዚሁ አድርገናል፡፡ ሰርፕራይዝ የምናደርገውን ነገር አንገልጽም፡፡ “ለምሳሌ ካሁን ቀደም ያደረግነው ስኳር 20 ብር በሚሸጥበት ወቅት እኛ ግማሽ በግማሽ ቀንሰን በዘጠኝ ብር ሸጠናል፡፡ ዘይትም በጣም በተወደደበት ጊዜ እንደዚሁ አድርገናል። ሰርፕራይዝ የምናደርገውን ነገር አንገልጽም፡፡ ‘ዛሬ ይኼ አልፏችኋል፡፡ ለሳምንት ደግሞ?’ ብለን በጥያቄ ምልክት በመተው፣ በሳምንቱ ውስጥ ለኅብረተሰቡ በጣም አስፈላጊ ነው ያልነውን ነገር ሰርፕራይዝ እናደርጋለን” በማለት አስረድተዋል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፡፡ የመጀመሪያዎቹ 10 ከፍተኛ ሸማቾች የሚሸለሙበትም ፕሮግራምም አለ፡፡ “ለደንበኛው አንድ ካርድ ተዘጋጅቶለት ይዞ ይሄዳል፡፡ በየወሩ የገዛቸውን ሸቀጦች ዋጋ እዚያ ላይ ይሞላል፡፡ ያ ይደመርና በወሩ ከፍተኛ ሸማች ለሆኑ 10 ደንበኞች እንሸልማለን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከሼባ ማይልስ ጋር ተነጋግረን የውጭ ጉዞ ሽልማት አዘጋጅተናል፡፡ ደንበኛችን በየጊዜው በሚገዛው እቃ ዋጋ መጠን ነጥብ ይያዝለትና ተጠራቅሞ ዱባይ ወይም ሌላ ቦታ መሄድ ከፈለገ እኛ ወጪውን እንሸፍንለታለን፡፡ ይኼ ደንበኛውን ለማበረታታትና ስለገዛ ብቻ የምንሸልምበት ፕሮግራም ነው፡፡ ሌላው ደግሞ በክፍያ ወቅት ደንበኞቻችን በወረፋ ብዛት እንዳይጨናነቁ 14 የኤሌክትሮኒክስ መክፈያ ቦታ አዘጋጅተናል፡፡ መክፈያዎቹ በኔትወርክ ስለተያያዙ ደንበኛው ሰው ወዳልበዛበት ሄዶ መስተናገድ ይችላል” በማለት አቶ ግርማይ ዓለማየሁ አስረድተናል፡፡በማስፋፊያው ሁለት ተመሳሳይ ሃይፐር ማርኬት ለማቋቋም ታቅዷል፡፡", "passage_id": "eebd3bb25c057e4dba0258dd6c6d3b8d" }, { "passage": "ጎበዝ ይሄን ነገር እንደቀላል እንዳታዩት፡፡ በእርግጥ እኔም እንደቀላል ነበር ሳየው የቆየሁ፡፡ ኧረ እንዲያውም አሁን ልሹ ስፈራ ነበር፡፡ እንዴት ስንት የጥናትና ምርምር ሼል እያለ ሰው ስለመጸዳጃ ቤት ይጽፋል እያልኩ ነበር፡፡ ሳስበው ሳስበው ግን ያጽፋል፡፡ ለነገሩ ጥናትና ምርምር ተብለውም ከመጸዳጃ ቤት ጽሑፍ የማይሻሉ አሉ፡፡ውይ አንዳንድ ጥናት እንዴት እንደሚሰለቸኝ! በጣም ግልጽ የሆነን ነገር እንደትልቅ ግኝት ተደርጎ ይወራል፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ አቀራረባቸው፡፡ የተሰጠው 30 ወይም 20 ደቂቃ ይሆንና ሁሉም መግቢያው አካባቢ ያልቃል፡፡ የጥናቱ የአሠራር ዘዴ፣ የናሙና መረጣ…. እነዚህ እነዚህ እኮ ለጥናቱ (ለወረቀቱ) እንጂ መድረክ ላይ ባይቀርቡ ምን ችግር አለው? የሚፈለገው ግኝቱ አይደል? ለነገሩ አዲስ ግኝት ከሌለው መቼስ ምን ይደረጋል!የመጸዳጃ ቤት ጽሑፍን ከጥናት ጋር አገናኘሁት አይደል? አትናቁት ብያችኋለሁ፡፡ ስንትና ስንት የፈጠራ ሃሳብ ያለበት ነው፡፡ ቆይ ግን ሰው ሃሳብ የሚመጣለት መጸዳጃ ቤት ውስጥ ነው እንዴ? ሳስበው ግን ደራሲዎች ልሹ የመጽሐፋቸውን ሃሳብ የሚያገኙት ከደመናማ ቀን ይልቅ መጸዳጃ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ይሄን ነገር ግን ያለውን የተፈጥሮ ትስስር ምሁራን ሊነግሩን ይገባል፡፡ እኮ የመጸዳጃ አካላት ከአዕምሮ ጋር ግንኙነት ሊኖራቸው? ወይኔ ሳይንቲስት በሆንኩ!ለዚህ ይሆን ግን አንዳንድ ሰዎች እኮ ‹‹መጸዳጃ ቤት ልሂድ›› ለማለት ‹‹እስኪ ትንሽ ልመሰጥ›› የሚሉ አሉ፡፡ ይሄ ነገር እንደመዝናኛም ይቆጠራል ማለት ነው፡፡ ምን ዋጋ አለው የከተሞቻችን መጸዳጃ ቤት እንኳን የሚመሰጡበት የሄዱበትን የተፈጥሮ ጥሪም ሳያስተናግዱ የሚመለሱበት ነው፡፡ እዚያ ውስጥ የሚዝናና ካለ ይሄ ሌላ ተፈጥሮ ነው፡፡እኔ ግን አንድ የምጠረጥረው ነገር(ባካችሁ እንደ ጥናት ያዙልኝ) በማህበራዊ ሕይወታችን ውስጥ በጣም የዋከብን ነን ማለት ነው፡፡ ይሄ ማለት ተረጋግተን የምናስብበት ጊዜ የለንም ማለት ነው፡፡ ለዚህ እኮ ነው አንድ ነገር ስንሠራ አያይዘን ሌላም ነገር እየሠራን ነው፡፡ ለምሳሌ ስልክ እንኳን ስናወራ በጉንጫችን አስደግፈን እየሠራን ነው፡፡ የቢሮ ሼል ከሆነ ‹‹ማውዝ›› ይዘን፣ ሱቅ ውስጥ ከሆነ ዕቃ እያነሳን እያስቀመጥን…. ብቻ የሆነ ነገር እየሠራን ነው፡፡ ይሄ ነገር ግን ‹‹ኢትዮጵያውያን ሼል አይወዱም›› ከሚለው ጋር ይጣረስ ይሆን? ብቻ ግን በሆነ ነገር የዋከብን ነን፡፡ማህበራዊ መገናኛዎችን እንኳን የምናነበው ወይ ከሰው ጋር ሆነን ነው ወይም ጉዞ ላይ ሆነን ነው፡፡ ጉዞ ደግሞ ራሱን የቻለ ሼል ነው፡፡ በሌላ በኩል በተለይም በከተማ ውስጥ ከመጸዳጃ ቤት በስተቀር ብቻችንን የምንሆንበት ዕድል የለም፡፡ ለመመሰጥ ደግሞ ብቻ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ውይ! እኔ ግን አዲስ አበባ ውስጥ የናፈቀኝ ነገር ቢኖር ጸጥ ያለ ቦታ! በቃ ከቤት ውጪ ከሆንን እኮ ስልክ ማውራት የማይታሰብ ሆነ፡፡ያለምንም ምክንያት ‹‹ክላክስ›› የሚያጮህ ሹፌር፣ ያለምክንያት የሚለቀቅ ሙዚቃ… እዚህ ላይ ያለምክንያት ያልኩት ምንም ሙዚቃ የማያስፈልግበት ቦታ ሁሉ ስለሚለቀቅ ነው፡፡ ሙዚቃ የተለመደው መጠጥ ቤት፣ ይሁን ከተባለም ምግብ ቤት፣ በዋናነትም ሲዲ የሚሸጥበት አካባቢ ነው፡፡ አሁን ቡቲክና መጽሐፍ ቤት ውስጥ ሙዚቃ ያስፈልግ ነበር? እሺ እሱም ይሁን! ምናለ አካባቢውን ሁሉ የሚያናውጥ ባይሆን?በነገራችን ላይ አዲስ አበባ ውስጥ የኪራይ ቤት ከሆነ ቤት ውስጥ ሆኖም በነፃነት ስልክ ማውራት አይችልም፡፡ ግድግዳ ለግድግዳ የተደጋገፈ ነው፤ አንዱ ቤት ነው ሁለት በር ያለው፤ ታዲያ ይህ ብቻዬን ነኝ ያሰኛል? እንግዲህ ይህን ውጪ ያጣነውን ጸጥታ መጸዳጃ ቤት ውስጥ ስለምናገኝ ነው መሰለኝ ሃሳብ ይመጣልናል፡፡ «ቀኑ ደመናማ ነበር» ከሚለው የልቦለድ የመጀመሪያ ዓረፍተ ነገር ወደ «መጸዳጃ ቤት ነበርኩ» ልንለወጥ ነው ማለት ነው፡፡በእውነት መጸዳጃ ቤት ውስጥ የሚጻፉ ጥቅሶች እኮ አዝናኝ ብቻ ሳይሆኑ ጥልቅ መልዕክት ያላቸው ናቸው፡፡ አስጠሊታው ነገር ግን አንዳንዶቹ ስድ መሆናቸው ነው፡፡ ከብሄር ጋር የተያያዘ ነገር የሚጻፉት ሌሎች አዝናኝ ጽሑፎችን ጭምር እንዲጠሉ ያደርጋሉ፡፡ የጻፈው ሰው የሚያውቀኝ ሰው የለም ብሎ ይሆናል፤ ዳሩ ግን ምን ፈሪ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ተደብቆ የሚሳደብ የመጨረሻው ፈሪ ነው፡፡ ስድብ ፊት ለፊትም ቢሆን ጥሩ ነው ማለቴ ሳይሆን ግን ይለያያል፡፡ ፊት ለፊት የሚሳደብ ባለጌ ነው፤ ተደብቆ የሚሳደብ ግን ቦቅቧቃ ፈሪ ነው፡፡ሌላው ነውር ነገር ከተቃራኒ ፆታ ጋር ተያይዞ የሚጻፉት ናቸው፡፡ እነዚህ ግን በመስሪያ ቤቶችና በትልልቅ ሆቴሎች ሳይሆን በትንንሽ ሆቴሎችና መጠጥ ቤቶች ውስጥ ነው፡፡ እዚህ ላይ የባሰው ነውር ስልክ ቁጥር የሚያስቀምጡት ናቸው፡፡ የሚያስቀምጡት ራሳቸው ባለቤቶችም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የራሴን ገጠመኝ ልንገራችሁ፡፡ በአንድ መጸዳጃ ቤት ውስጥ በተለጠፈ ስልክ ቁጥር ደወልኩ፡፡ ያነሳችው ሴት ናት፤ ከአጠገቧ ግን የብዙ ሴቶች ድምፅ ይሰማል፡፡ ዋና ዓላማውም የደወለውን ወንድ እያፋዘዙ መቀለድ ነው፡፡ ይቺኛዋ ዘዴ ግን ትንሽ ዘናም አድርጋኛለች፡፡ ወንዶች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ከሴቶች ላይ ስልክ እየተቀበሉ መሟዘዝ ይወዳሉ፡፡ ስለዚህ ለእነርሱ ቅጣት ከሆነ አይከፋም ባይ ነኝ፡፡የመጸዳጃ ቤት ጽሑፍ ስል የሚጻፈውን ብቻ መስሏችሁ ነው? የሚነበበውንም ማለቴ ነው፡፡ የሚነበበውንም ስል ግድግዳው ላይ የተጻፈውን አይደለም፤ ጋዜጣና መጽሔት፡፡ አንዳንድ ሰዎችን ለማድነቅ ‹‹እገሌ እኮ መጸዳጃ ቤት ሲገባ እንኳን ያነባል›› ይባላል፡፡ ይሄ አድናቆት ስህተት ነው፡፡ መጸዳጃ ቤት ውስጥ የሚያነበው ብዙ ሰው ነው፡፡ ችግሩ ሊጠቀምበት ይዞት የገባውን ወረቀት ነው የሚያነበው፡፡ ግን ያንኑም ቢሆን ዝም ብሎ ከሚጥለው ማንበቡ ጥሩ ነው፡፡ መጸዳጃ ቤትም ባይገባ አያነበውም ነበርና!ፈረንጆች ‹‹ከኢትዮጵያውያን ብር መደበቅ ከፈለክ መጽሐፍ ውስጥ አድርገው›› አሉ ተባለ፤ ምናልባት ‹‹ኢትዮጵያውያን እንዲያነቡ ከፈለክ መጽሐፉን መጸዳጃ ቤት አድርገው›› ይሉ ይሆን? ከማለታቸው በፊት ሌላ ቦታም እናንብብ!አዲስ ዘመን ጥር 5/2011ዋለልኝ አየለ", "passage_id": "f83bf44f756649b99e759abe7cc5b789" }, { "passage": "የአገር ጉዳይ ዛሬም ያነጋግራል።እናም ስለሚያሳስቡን ጉዳዮች ሰዓቱ ከረፈደ በኋላ ሳይሆን ዛሬ፣ መነጋገር ለመነጋጋር ያህል ብቻ ሳይሆን ለመግባባት እና አንዳች ጠቃሚ መላ ለመሻት፤ መንገዱ ተጀምሯል።ለዚህኛውም ዙር የአገር ጉዳይ ሦሥት እንግዶች ከአዲስ አበባ ጋብዘናል።“የሁላችንም በሆነች አገር ለሁላችንም የሚበጁ የሕይወት መላዎች” የሚሉ ይመስላል፤ የዛሬዎቹ “የአገር ጉዳይ” ባለተራዎች በወጋቸው።ተወያዮች:- በኢትዮጵያ ጉዳዮች በመጻፍ እና በአገራዊ ውይይቶች በነቃ ተሳትፏቸው የሚታወቁት አንጋፋ ምሁር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም፤ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አንተነህ አሰፋ እና የሕግ ባለሞያው አቶ ተማም አባ ቡልጉ ናቸው። ", "passage_id": "f6c055ca0690d7be51d0e2259f8a5b41" }, { "passage": "ጊዜና ወርቅ እስከ ፍጻሜው የሚጸና ባይሆንም መመሳሰል አላቸው፤ ኹለቱም ውድ ናቸው። ከግል ገጠመኛቸው በመነሳት ይህን የወርቅና የጊዜን ነገር ያነሱት በርናባስ በቀለ፣ ለሁሉም ነገር ጊዜ እንዳለው ሁሉ አሁን ላይ ወርቅ ሆነው ትኩረት አግኝተው ያሉት ራስን ከኮቪድ 19 መጠበቂያ መሣሪያዎች መሆናቸውን ያነሳሉ። በተጓዳኝ የወርቅ ቤቶች ጭር ብለው ለጤና ጉዳይ ሰዉ የመረባረቡን ነገር አንስተው፣ ሕይወትንም ከዛ በማመሳከር በጊዜ ሁሉን መጠቀም ተገቢ ነው ሲሉ እንዲህ ያወጋሉ።ነገሩ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ነው። የሥራ ዘርፏ ንግድ ሆኖ መሥሪያ ቤቷ ደግሞ ወርቅ ቤት (በወርቅ የተሠራ ሳይሆን ወርቅ መሸጫ መደብር) የሆነ አንዷ ወዳጄ ጋር በሥራ ጉዳይ ደውዬ ነበር። ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ‹‹ሥራ እንዴት ነው?›› የሚል ጥያቄ አቀረብኩላት (በቀረብኝ!)። ‹‹ባርኒ ለሼል ዘርፉ ታማኝ ለመሆን ብለን ክፍት አድርገን እንውላለን እንጂ በዚህ ጊዜ ምን ሼል አለ!? (አየር የለም እኮ)›› አለች። አስከትላም፤ ‹‹ጊዜው ሰው በሕይወት ለመቆየት የሚረባረብበት እንጂ የጌጥና የቄንጥ አይደለምና›› አላለችኝም መሰላችሁ!?‹‹ሥራ እና ጊዜ›› በሚል ሐሳብ ጥናታዊ ጽሑፍ ልናዘጋጅ የደወልኩላት አስመሰለችው። ሆሆሆ! እኔ ሾለ ሥራዋ የጠየኳት ወደ ዋናው መልእክቴ ከመግባቴ በፊት ጥሩ መንደርደሪያ ይሆነኛል በሚል ነበር። እርሷ ግን መግቢያዬን ዋና ጉዳዬ አድርጋው ቁጭ! በቃ ምን አለፋችሁ…! ያነሳችው ሐሳብ የስልክ ጥሪው ጭብጥ (አንኳር ወሬ) እስኪመስል ተወያየንበት።ቆይ ግን ‹‹ሥራ እንዴት ነው?›› የሚል በሦስት ቃላት የተዋቀረና ‹‹ደኅና ዋልሽ?›› የማለት ያህል የተለመደ ጥያቄዬ ይህን ሁሉ ያስወራል? ለነገሩ ሰው ልናገር ካለ ከመሬት ተነስቶም ይናገር የለ? ካልሆነም ይህች ወዳጄ የሥራ ዘርፏን ቀይራ መሆን አለበት! ‹‹ወዴት?›› አላችሁኝ? ወደ አውርቶ አደርነት ነዋ! ድሮም አንዳች ትንታኔ የታከለበት ነገር እንደሚመስጣት መች አጣሁት!? እያልኩኝ ማሰብ ጀመርኩኝ።የተግባቦት (Communication) ተማሪ እንደመሆኔ መጠን ከየትኛውም ንግግር በኋላ ራሴን ‹ኦዲት› የማድረግ ልማድ አለኝ። ከራሴው ጋር በመሆን ልሴ ላይ ባደረኩት ጥብቅ ክትትል ራሴን ከቁጥጥር ሾር ማዋል ችያለሁ፤ ስህተቱም እኔው ጋር እንደነበር አስተውያለሁ። እኔ ሾለ ሥራዋ የጠየኳት እንዲያው ሾለ መጠየቅ (just for the sake of asking) እንጂ ከልቤ አልነበረም። እርሷ የምሯን ስትመልስልኝ ልቤ ግን ለመቀበል ዝግጁ አልነበረም (ልቤ የሥራዋን ደኅንነት የጠየቀው ከልቡ አልነበረምና)።አንዳንድ ነገሮቻችን እኮ ስለተለመዱ ብቻ እንጂ በማስተዋል የሚደረጉ አይደሉም። ሰላምታዬ ልሹ ሰላም (ከልብ የሆነ መረጋጋት) የሚያስፈልገው ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ከእንግዲህ እንኳን ወዳጆቼን ሾለ ጤናቸው ስጠይቅ የደውል ጥሪ የምታስተጋባው የቴሌዋ ሴትዮ ልሹ ‹‹ጤና ይስጥልን!›› ስትለኝ ‹‹አብሮ ይስጥልን›› ለማለት ከልብ በሆነ አንዳች ምላሽ የሚኖረኝ ይመስለኛል (እርሷ ባትሰማኝም)።ወደ ወርቅ መንደር ስመልሳችሁ፤ በዚህ ወቅት የገበያ ሁኔታ በእርግጥም ለእነርሱ ከባድ ነው። የሬሳ ሳጥን ነጋዴ ገበያው የሚደራው ሟች የሚበዛበት ወቅት እንደሆነ ሁሉ የወርቅ መደብሮችም ገበያቸው የሚሞቀው ተጋቢዎች የሚበዙበት ወቅት መሆኑን አንባቢዬም አያጣውም። ለነገሩ እንደው ልማድ ሆኖብን እንጂ ለማግባት ደግሞ ምን ወቅት ያስፈልገዋል!? ትዳር በረከት አይደል? ‹የሠርግ ወቅት› እያልን ነገር ማወሳሰቡን ትተን ከዓመት እስከ ዓመት ብንድር ምኑ ጋር ነው ክፋቱ?ይህን ሳስብ እኔ ያገባሁ ጊዜ (ከአንድ ዓመት በፊት) ‹‹በግንቦት ወርማ አታገባም!›› ብለው ሰማዩን ዝቅ ያደረጉ ቤተሰቦቼ ጉዳይ መቼም አይረሳኝም። ‹እንዴ! ለምን!?› ስላቸው፤ ‹በቃ በግንቦት ወር ሠርግ አይደረግማ!›› ብለው ክችች። እኔም ግራ ስለገባኝ ይህ ነገር ከቃሉ ይሆን እንዴ? በሚል እሳቤ ‹ግንቦት› የሚለው ቃል ጥናት (Terminology) ላይ ተጠመድኩኝ። ‹ግንቦት› የሚለው ቃል ‹ግንብ› እና ‹ሞት› የሚሉ ኹለት ቃላት/ድምጾች ጥምረት ይሆን እንዴ? ብዬ አሰብኩኝና ለዚህም አቻ ትርጉም ፈለኩለት። ‹በግንቦት የተጋቡ ሰዎች በግንብ ይሞታሉ (ግንብ-ሞት)› የሚል አንድምታ ይኖረዋል አልኩኝና ደግሞ ምንም አልገጥምልህ ሲለኝ ተውኩት።አዕምሮዬ ሊያርፍ አልቻለምና በመቀጠልም ወሩ የሚጠራበት ቃል ‹ግን› ብሎ ስለሚጀምር መሆን አለበ! ብዬም አሰብኩኝ። በዚህም መሠረት ‹አግብቼ ግን-ብሞት?› የሚል ሐሳብ ሊይዝ እንደሚችል ድምዳሜ ላይ ደረስኩኝ። ደግሞ ለራሴው መልሼ ይህ በፍጹም አይሆንም! አልኩኝ። ‹በመጨረሻም፣ ኤጭ! ጦሴን!› ብዬ ጉዳዩን በጥቅሉ ማሰላሰሉን ተያያዝኩኝ።‹ግንቦት የጋብቻ ወር አይደለም› ይሉኛል፤ እና የፍቺ ወር ነው? ‹በግንቦት ወር መጋባት ደስ አይልም› ይሉኛል፤ እና መፋታት ነው ደስ የሚለው? እሺ! ግንቦት ወር ደርግ የወደቀበት ስለሆነ ነው? እና እርሱስ ቢሆን ከእኔ ትዳር ጋር ምን አገናኘው? የወደቀው ደርግ… የማገባው እኔ በርናባስ…! እኔ ‹ደርጉ› ወይም ‹ደርጋቸው› አይደለሁ!። ሲቀጥል በግንቦት ወር ደርግ ወደቀና እኔ በወሩ መነሳት (በትዳር) አልችልም!? ብዬ ግራ አጋቢዎቼ ግራ እንደተጋቡብኝ እንዳገባሁ አስታውሳለሁ።\nብዙ ሳላደክማችሁ፤ በቃ ለምን እንደምናደርጋቸው የማናውቃቸው ግን ሽንጣችንን ገትረን የምንከራከርላቸው ነገሮች ቁጥራቸው ብዙ ነው። ‹‹ይህ ሰውዬ እያወራ መኻል ፌርማታ ላይ የሚመጡ ሐሳቦች ሁሉ ይወስዱታል እንዴ!?›› ብለኸኝ ይሆናል፤ ግን የግንቦት ወር ከጋብቻና ከሠርግ የጸዳ እንዲሆን በወሩ እየተቃጣ ያለው አሠራር የወርቅ ቤቷ ወዳጄን በቀጥታ ይመለከታታል።‹‹ግንቦት ወር ለትዳር አይሆንም›› ሲሉ በተዘዋዋሪ ‹በግንቦት ወደ ወርቅ ቤት መሄድ ለጤናም ጥሩ አይደለም›› እያሉ ነውና። አይይ…. ግንቦት! በዚህ ጉዳይ ከአንባቢዎቼ ግልጽ መረጃ በአድራሻዬ የሚያደርሰኝ ሰው ከተገኘ ሥሙ የባለውለታዎች ማስታዎሻዬ በደማቅ ብዕር ተጽፎ ይቀመጣል።\nበሌላ በኩል ደግሞ ከወረርሽኙ የተነሳ የሠርግ ቤት ታዳሚዎች ቁጥር ውስን እንዲሆን መደረጉ ሰዎች ወደ ወርቅ ቤት እንዳይሄዱ ተጨማሪ ምክንያት ሳይሆን አይቀርም። ‹እንዴት?› አላችሁኝ? የእኔ ትውልድ ‹ግርግር ውስጤ ነው!› ይል አይደል? ዝምና ጭር ያለ ነገር አይመቸውም። የሕይወቱ ፍልስፍና የተቃኘበት የኑሮው ዘዬ ለውስጠቱ ብዙም ግድ የማይለው ለውጫዊው ነገር (ለገጽታ ግንባታ) ግን ጠብ እርግፍ የሚል ነው።‹‹በኻያ ሰው ፊት ከማገባ ይህ ጊዜ እስኪያልፍ ኻያ ዓመትም ቢሆን መጠበቁ ይቀለኛል›› ያለ ሰው አለ ብላችሁ ታምናላችሁ? ከትዳሩ ይልቅ ሠርጉ፣ ከኑሮውም ይልቅ ግርግሩ የሚያስጨንቀው ተላላ ትውልድ እኮ ነው። ትዳር ማለት የሠርግ ቀን ቪዲዮ ክሊፕና ጭፈራ የሚመስለው ስንት ያልተፈወሰ አግቢ የሞላበት አገር መሰላችሁ? ለነገሩ የተጋቢዎቹ ችግር ብቻ ላይሆን ይችላል፤ የልጆቻቸው የነገ ሕይወት ግድ የማይሰጣቸው ግን ለራሳቸው ሥምና ክብር ሲሉ ሰንጋ ጥለው ሕዝብ ካላበሉ (ተበድረውም ቢሆን) ልጅ የዳሩ የማይመስላቸው ወላጆችም እጅግ ብዙ ናቸው። ብቻ ግን ይህ ሁሉ ተደማምሮ የወዳጄን የሥራ ቦታ (ወርቅ ቤት ሠፈር) ጭር አድርጎታል።በእርግጥ ወርቅ በጣም ተወዳጅና ደስ የሚል ጌጥ ነው፤ ግን ለማጌጥም ጊዜ አለውና በዚህ ወቅት ሰፈሩ ጭር ብሏል። በተለይ ኮቪድ 19 ወደ አገራችን ገና እንደገባ (አሁን እንኳን ተላምዷል /ቤተኛ ሆኗል/ ሕዝቤም ዘንግቷል) ጊዜው የማስክ፣ የአልኮል፣ የሳኒታይዘርና የመሠረታዊ የእህል ፍጆታዎች ነበር። የጊዜው ወርቆችም እነርሱ ነበሩና። አንድ ነገር በራሱ ጥሩ ቢሆንም ውበቱ የበለጠ የሚጎላውና ዋጋ የሚኖረው በጊዜው ውስጥ ነው።ጊዜውን ካልጠበቀ የፍቅር ቃል፣ በጊዜው የሆነ ቁጣ አንዳች ልብን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለው። ወርቅ በዚህ ወቅት ወርቅነቱን አልቀየረም። ግን ፈላጊዎቹ ሰፈር ቀይረዋል። በዚህ ወቅት በጣም የሚያስፈልጋቸው ወርቅ ሳይሆን ሌላ ነገር እንደሆነ ስለተገነዘቡ ወርቅን ፊት ነስተውታል (በወጣቱ ቋንቋ “ላሽ” ብለውታል)። “ወርቃማው ጊዜ (golden time)” የሚባል የተለመደ ሐሳብ አለን አይደል? ምን ለማለት ተፈልጎ ነው? መቼስ ‹በወርቅ የተሠራ ጊዜ› የሚል ምላሽ አልጠብቅም። ‹ወርቃማነት› የሚል ጽንሰ ሐሳብ ሥሙን ያገኘበት ሥረወ-ቃል ባለቤት የሆነው ወርቅ የሚሉት ሼመ-ገናና ማዕድን ልሹ ወርቃማ ጊዜ አለው።ውድ አንባቢ፤ የአውርቶ አደሯ ወዳጄን አሳብ መነሻዬ አድርጌ የባጡንና የቆጡን ስል በትዕግሥት አብረኸኝ በመዝለቅህ ምን እላለሁ? ከልብ የሆነው አክብሮቴ የገባህበት ገብቶ ያግኝህ። ግና ከወርቅ ሰፈሩ ሁኔታ ተነስቼ ለአንተ ለወዳጄ ሙግት ቢጤ አለኝና እንግዲያውስ ተሞገትልኝ።የሁሉም ነገር ውበቱ በጊዜው ውስጥ ከሆነ ታዲያ አንባቢዬ ወርቃማ ጊዜውን እንዴት እያስተዳደረው ይሆን? ብዬ ሾለ አንተ ለማሰብ ጥቂት ጊዜ ወስጃለሁ። ‹ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል› የሚል የአበው አባባል አለን አይደል? ቅሉ ድንጋዩን የሚሰብረው በጥንካሬ ከድንጋይ በርትቶ እኮ አይደለም፤ ያንን የሚያደርግበትን ጉልበት ጊዜ ሰጥቶት እንጂ።ምስኪኑን ሥጋ ለባሽ አንተን ሰማይ ሰቅለው ከአማልክት ጎራ የመደቡህ አንተ ከሌለህ መሬት በፀሐይ ዙሪያ መሽከርከሯን እንደምታቆም የነገሩህ እያሞካሹህ አብረውህ አይዘልቁም። ይህም የሆነው በጊዜው ነውና። ምን እርሱ ብቻ!? የሚገርምህ አሁን ይህንን ጽሑፍ የምታነብበት ዐይንህ ብርሃን የሚደክምበት ጊዜ ይመጣል፤ ጉልበትህም ይከዳሃል። በዙሪያህ ያሉ አድናቂዎችህም እንደ ወርቅ ሰፈሩ ደንበኞች ሄደው ግዛትህ (ዙሪያህ) ጭር የሚልበት ቀን ይመጣል። እባክህን ጊዜ ሳለህ የሕይወት ትርጉም ነገር ግድ ይበልህ።በርናባስ በቀለ፤ የተግባቦት ባለሞያ ሲሆኑ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ላይ ይገኛሉ።ቅጽ 2 ቁጥር 97 መስከረም 2 2012", "passage_id": "e5bbf538b4d79b5eb7c1d2ca2cde6830" }, { "passage": "የኑሮ ውድነት የቁራ ጩኸት፤ የባለጠጎች ኪስ ምች ነው፡፡ ላለው ይጨመረዋል፤ ለሌለው ግን ያለው ይወስድበታል ሕግ ይተገበራል፡፡ የባለጠጎች ኪስ ምች የባለስልጣናትን ወንበር ይነቀንቃል፤ ባለጠጎች ገቢያቸው ዝቅተኛ የሆኑ ዜጎች ፀጋ የሆነውን ሁሉ በገንዘባቸው ሊወስዱት ይችላሉ፤ በገቢያቸው ዝቅተኛ የሆኑ አብዛኞቹ ዜጎች ደግሞ ላበታቸው ዛሬን ብቻ የሚመግባቸው ናቸው፡፡ ወይ በጉልበቱ ወይም በዕውቀቱ፤ የሚነጠቁት ያልጠገቡት እንጀራ የሚመኙትን ነገ እየሠራላቸው አይደለም፡፡ ዕውቀታቸው የባለጠጎችን ካባ ጫፍ የሚነካበት ምኅዳር የለውም፤ በጣም ርቀዋል፤ ጨረታቸው የጓዳ ሚስጥር ስለሆነ ለማንም አሳልፈው አይሰጡም፤ ገባሪዎቻቸው ወደገደል የሚንሻራተት መኪናን የሚያቆሙ ታኮዎች ናቸው፡፡ ጭቃ ላይ ወድቀው ልብሳቸው የማይቆሽሽባቸው ባለጠግነትን ለብሰዋል! ገቢያቸው ዝቅተኛ የሆኑ አብዛኞቹ ሰዎች በቀን 50 ብር እየተከፈላቸው የባለጠጎችን ቤት ሲወለውሉ፣ ሲገነቡ ውለው ፈጣሪ እንደጎረቤት ሳይሆን እንደቤታቸው የማደር ጥበቡን አልነፈጋቸውም፡፡የባለጠጎች እና የዝቅተኛው ማኅበረሰብ የኑሮ ጥግ ሲታሰብ ‹ዋልታ ረገጥ› የሚሏት ትክክለኛ ቃል ቦታዋን የምታገኘው ከዚያ ይመስላል፡፡ የባለጠጎች ሀብት የሚመሠረተው በድሆች ጎልበት እና መበዝበዝ ላይ ነው፡፡ ሀገራችን ባለጠጎችን በርካሽ የሰው ኃይል እያማለለች ነው፡፡ መቼም ሻይ ጠጥቶ ውሎ፤ በሶ በጥብጦ ጠጥቶ የሚያድረው ሠራተኛውን ማኅበረሰብ ረሳሁ የሚል ሀገሬ ላይ ካለ የባለጠጎች ወገን መሆን አለበት፡፡ ሠራተኛው ማኅበረሰብ ቀኑን ሙሉ የሚሠራው ሼል የምግብ ፍላጎቱን መልሶ በዓላትን ለማክበር የሚያስችለውን ጥሪት አያካብትም፡፡ ቆጥቡ የሚሉት ባንኮቻችን ሥሩበት ቢሉ ኑሮ ተቀራራቢ ሕዝብ መፍጠር ይቻል ነበር፡፡ አንድ ሁኑ እየተባለ በሚለፈፍባት አንድ በሆነች ሀገር፣ አንድ የማያደርጉ ሸቀጦች ፈር የለቀቁ ናቸው፡፡ ባለጠጋው ያስወደደውን የታክሲ ኪራይ ለምን ድሀው የሚከፍልባት ሀገር ሆነች? ባለጠጎች ያስወደዱትን ሽሮ፣ ባለጠጎች ያስወደዱትን የገበያ ሥርዓት ድሀው፣ ሠራተኛ ማኅበረሰብ በግዱ እየከፈለው ነው፡፡ አየኸው ወዳጄ ድህነት ለባለጠጎች የሚከፈል ግብር ነው ያልኩት በምክንያት ነው፡፡ልጆችህ የሚፈልጉትን ነገር ማድረግ እንዳትችል በሚያሳምመው ድህነት ውስጥ የባለጠጎች ሥርዓት እንዳይፈጠር የምታደርግበት አቅም አይኖርህም፡፡ ከድህነት ከመውጣት ይልቅ ድህነትን የሚያሰለጥኑብህ ጋር እየተፋለምክ እንድታሸልብ ያደረጉህን መለየት ግድ የሚል ጊዜ ይመስላል፡፡ ከሰሞኑ በሀገሪቱ የሚደረጉ የዋጋ ጭማሪዎች ባለጠግነት እንዲያብብ የሚያደርጉ የድሆችን ተስፋ ጉም እንደመዝገን ሆኖ ታየዋለህ ፡፡ከሰሞኑ አብመድ በባሕር ዳር ከተማ ተዘዋውሮ ባየው መሠረት ጨምሯል የምትለዋ ቃል ብቻ ረክሳ አግኝቷታል፡፡ የታክሲ ዋጋ ጨምሯል፤ ‹‹ለምን?›› ሲባል  ‹ቤንዚን ተወድዷል፤ በዚያ ላይ ለቤንዚን አንድ ቀን ተሰልፈን አንድ ቀን እየሠራን ምን እናተርፋለን?› የሚሉ ምላሾች ያጋጥማሉ፡፡ አስተውሉ ‹ምን እናተርፋለን› ለሚሉት ባለጠጎች የሚታለበው ሕዝባችን ማንን መከታ ያድርግ? አዎ መብቱ ነው የነፃ ገበያ ሥርዓቱ ትራስ ሁኖለታል (የነዳጅ ገበያው በነፃ ገበያው እንደማይመራ ብናውቅም)፡፡ ‹‹ከፈለክ ግባ፤ ጨምሮብኛል ካልክ መውረድ ትችላለህ›› ብለው ቅስም የሚሰብሩ ድምጾች ከረዳትም ከአሽከርካሪም ይሰማሉ፡፡ ‹‹ቸኮልኩ፣ መሄድ አለብኝ፣ ማን አዛዥ አላቸው›› እያለ የሚሳፈረው ሰው ሀሜት የጉድ ነው፡፡ የተነጋገሩ የሚመስሉት የታክሲ ረዳቶች መልስ አያጡም፡፡ ኧረ ፈረሳችን ወዴት ነህ?ባለሱቅ ብለህ የገባህ እንደሆነ ‹‹ሶፍት ጨምሯል አባየ፤ ኧረ መሃረማችንን እናድሰው ጎበዝ፡፡  ‹ቡና ጨምሯል›፣ ‹በኤክሳይዝ ታክሱ ምክንያት ጤፉ ጨምሯል… ምስር ጨምሯል…. ጨምሯል… ባለግሮሰሪ ቤት ‹ቢራ ጨምሯል… ለስላሳ መጠጥም ጨምሯል…›› እንዴ ይሄ ደግሞ ምን ሆነ አልኮልና ለስላሳ መጠጥ ምን አገናኛቸው፡፡ ለራስህ ብቻ አጎረምርመህ እለፍ፡፡ ካለህ መጎንጨት ነው አባየ፤ ከሌለህ የለህም፡፡ሰሞኑን የኤሌክትሪክ የአገልግሎት ዋጋ ተመን መጨመሩን ተከትሎ አካራዮች ‹‹ምድጃ መጠቀም አቁሙ አሉን›› ያሉት የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ሙሉጎጃም አባተ ናቸው፡፡ ከአባዋራው ጋር አራት ልጆችን የሚያሳድጉት ወይዘሮ ሙሉጎጃም የባለቤታቸው ደሞዝ 15 ሺህ ብር ቢሆንም ‹‹ከአየር ላይ ተበትኖ የሚቀር ነው›› ይላሉ፡፡ ቀበሌ 16 ላይ የተከራዩት ሁለት ክፍል ቤት ባለፉት ስድስት ወራት አራት ሺህ ሁለት መቶ ብር ሲከፍሉ ነበር፤ ተቆራርጦ የሚደርሳቸው የባለቤታቸው 10 ሺህ ገዳማ ብር አንጀቷ ተቆረጠ ማለት አይደል፡፡ ልጆቻቸው የትምህርት ቤት ክፍያና ለወሩ ምግብ ፍጆታ ሲሉ ከተረፈችው 6 ሺህ ብር የሚቀራቸው ሁሌም ባለቤታቸው ተሳቅቆ ተበድሮ የሚያልፉት አማራጭ ብቻ ናት፡፡ባለቤታቸው መስክ ወይም ስብሰባ ካልሄዱ ወሩ ከባድ ይሆንባቸዋል፤ ድህነት ከራስህ ሰው ሲነጥል እንዲህ ነው፡፡ የኃይል ክፍያ ጨምሯል ተብለው በአካራያቸው የኤሌክትሪክ ምድጃ ገመዳቸው ተበጥሶባቸው ነበር፡፡ በልመና ከነበረው ኪራይ ላይ 500 ብር እንዲጨምሩ ተደርጎ ሕይወትን ቀጥለዋል፡፡ ሁሌም ግን ሠርተው የሚሰጡት ለማን ነው? ከቤተሰብ የነጠለው ገንዘብን የመፈለግ ጉዳይ ሕይወትን ከማትረፍ በቀር ፍቅር አያሳጣም ወይ? ፍቅር ደግሞ በሀገር ላይ ያለህን፣ በሰዎች ላይ ያለህን ዕይታ ይቀይረዋል፡፡ ሠርተህ ካልተለወጥክ፣ ልትበደር ጠይቀህ ፊት ካበላሹብህ ከማን አግኝተህ ትዋደዳለህ ጃል? አስበው በቀን 50 ብር በላቡ የሚያድረው ሠራተኛማ በዚህ ነበልባል ዘመን ከመንደድ ውጭ ምን በልቶ ያድራል ብሎ ማሰብ ምንኛ ደግነት ነው፡፡", "passage_id": "a35bfecc099d86ed35063470ff05fa52" } ]
b6595143a5bfc7b773e347d18ab4eddd
0891d2ddb29e46baecd847562998e2ca
‘‘ነፃነት… ነፃነት…. ነፃነቴን ስጡኝ”
 አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሁኔታ በአዕምሮዬ ሁለት ሐሳቦች ይመላለሳሉ፤ ነፃነት እና ባርነት። ይህንኑ አወርዳለሁ አወጣለው ፤ ታዲያ በመሐል አንድ ሐሳብ ብልጭ አለልኝ። ከማን ነው ነፃነት የሚመጣው? ባሪያ ያደረገኝ ማን ነው ? ሌላ የሐሳብ መንገድ… ሌላ መልስ ፍለጋ… ለነገሩ አዕምሮ አታስብ አይባል። በዚህ መሐል ነው በአንድ ወቅት ከቡክ ወርልድ ድረ ገጽ ያነበብኩት ታሪክ ትዝ ያለኝ።በድሮ ጊዜ አንድ ታላቅ የነፃነት ታጋይ በተራራማው የሀገሪቱ ክፍል እየተጓዘ በአንድ ማደርያ ቦታ ለተወሰነ ጊዜ ለማሳለፍና ለማረፍ ወሰኖ ጎራ አለ። በዚያ ቤት ውስጥ አንድ የሚያምር ተናጋሪ ወፍ (ፓሮት) በወርቅማ የወፍ ቤት ውስጥ ተቀምጦ “ነፃነት፣ ነፃነት፣ ነፃነት” እያለ ይጮሐል። ድምፁንም ጋራ ሸንተረሩ እያስተጋባው ተመልሶ “ነፃነት … ነፃነት …” በሚል ድምፅ አካባቢው ይሞላል።የነፃነት አርበኛው እንዲህ ሲል አሰበ” በህይወቴ በዚህ ዓለም ስዞር ብዙ የፓሮት ወፎችን በፍርግርግ ብረት ውስጥ ተቆልፎባቸው ሲኖሩ አይቻለሁ። እንደዚህ ወፍ ግን የነፃነት ናፍቆት ያለው በየደቂቃው ነፃነቴን እያለ የሚጮህ አይቼ አላውቅም !” ቀኑን በዚህ ወፍ እየተገረመ ውሎ መምሸት አልቀረም መሸ። የቤቱ ባለቤት በጊዜ እንቅልፍ ወስዶት ቤቱ ጭር እንዳለ ቀኑን በወፉ ሲገረም የዋለው በተፈጥሮው ለነፃነት ታላቅ ክብር የሚሰጠው ሰው አንድ ሐሳብ ብልጭ አለለትና ተነስቶ ወደ ወፉ ቤት በመሄድ የብረት ቤቱን በር ከፈተለት። ወፉ ግን ወደተከፈተለት በር በመቅረብ ፋንታ ወደኋላ እየሸሸ “ነፃነት፣ ነፃነት፣ ነፃነት… “ ሲል ጮኸ፤ አርበኛውም “አሁን በሩ ተከፍቶልሐል፣ ና ውጣ በሰማዩ እንደፈለክ ብረር የነፃነትን አየር ተንፍስ ሁሉም ተኝተዋልና የሚይዝህ የለም፤ አምልጥ አለው” ተናገሪዋ ወፍ ግን ይበልጥ ከመውጫ በሩ እየሸሸ በፍርግርግ ብረቶቹ መታከኩን ቀጠለ ግራ የተጋባው ሰው እጁን ወደወፉ ቤት ሰዶ ሊይዘውና እንዲወጣ ሊረዳው ሞከረ ወፉም ባለ በሌለ ሃይሉ እጁን ቧጨረው ነከሰው እንደዛም ሆኖ ጎትቶ አውጥቶ እንዲበር ለቀቀው እና ክፉኛ የተነከሰው እጁ ህመሙ ቢሰማውም በሠራው መልካም ተግባር ግን ልቡ ረክቶ ተኛ በጠዋት ሲነሳ የተቀበለው የፓሮት ወፉ ድምፅ ነበር “ነፃነት ነፃነት ነፃነት” ይላል አርበኛውም አንድ አለት ላይ ወይም ዛፍ ላይ ተቀምጦ እንደልማዱ እየጮኸ ነው ብሎ እያሰበ ከመኝታው ተነስቶ ወደ ወፉ ቤት ሲመለከት ባየው ነገር ደነገጠ ወፉ በሩ በተከፈተው እስር ቤቱ (ጎጆው) ውስጥ ሆኖ “ነፃነት ነፃነት ነፃነቴን ስጡኝ” ብሎ እየጮኸ ነው።አሁን ባለችው ኢትዮጵያ እየሆነ ያለው ይኸው ነው፤ በተከፈተ በር በሚረዳ እና በሚያግዝ መሪ የመጣውን ሰላም ማጣጣም አቅቶን የምንባክነው። ልክ ከላይ እንዳለችው ፓሮት ከነበርነበት ፍርግርግ ወይ ከእርዳታ አልወጣን፣ አሊያም በራሳችን ጉልበት እንዲያው ፍርግርግ ውስጥ ሆነን በመጋጨት አካላችን ጎዳን እንዲሁም ለነፃነታችን ዋጋ የከፈሉ ሊረዱን የተዘረጉ እጆችን አደማን፤ ጎዳን። እስቲ ወደ ልቦናችን እንመለስ የምንፍልገው ምንድነው? ጭራስ የሌለን ነው? ወይስ የጎደለን? ለሁሉም እንደ ፓሮቷ ከመጮሐችን በፊት እንዲህ ያሉ ጥያቄዎችን እያነሳን እንጠይቅ፤ ታላቁ መጽሐፍ “የጻድቅ አይኖች ወደራሱ ናቸው” ይላል። ይህም ማለት ራስን በመግዛት ራስን ማየት ብዙውን ጥያቄና የምንፈልገውን ሰላም ይመልስልናል።ስለዚህም ለምንጠይቀው ጥያቄ መልሱ ያለው እኛው ጋር መሆኑን መረዳት ይኖርብናል፤ ወዳጆቼ እንደሚታወቀው ነፃነት አንፃራዊና ከእንቅስቃሴ ጋር የተዛመደ ነው። የሰው ልጅ ሲፈጠርም ሆነ ሲኖር ነፃ አይደለም። እድገቱና አኗኗሩ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አጥሮች የተከበበ ነው። ያሻውን፣ የፈለገውን ማድረግ አይችልም። ውስንነት አለበት። አንድም በባህልና በሃይማኖት ሌላው ደግሞ በሰው ሰራሽ ሕግጋት ተጽዕኖ ሥር ነው።በሌሎች ላይ በደል ያደረሰ ሰው ፈፅሞ በነፃነት መኖር አይቻልም። የመኖር መለኪያ ደግሞ ነፃነት ነው። የመሥራት፣ የማደግ ዋልታ ደግሞ ስምምነት ነው። ምድር የሁሉም ቤት ናት። ሰውም ምድርን በጊዜያዊነት ይገለገልበታል። አርሶ፣ ዘርቶ፣ አጭዶ፣ ወቅቶ ይጠቀምበታል። አምርቶ፣ ፈብርኮ፣ ለብሶ፣ አጊጦ ይታይባታል። ተወልዶ፣ አድጎ፣ አግብቶ፣ ወልዶ ተዛምዶ ይኖርባታል። ግን በነፃነት አይኖርም። ምክንያቱም ነፃነት በተፈጥሮ ሳይሆን በፍለጋ የሚገኝ በመሆኑ ነው። ነፃነት ያለ ተጠቃሚነት ባርነት ነው። በድህነት ሥር የሚዳዳ ሰው ነፃ ይሁን አይሁን ትርጉም አይሰጠውም። ለምን የቅድሚያ ቅድሚያ ተጠቃሚ አይደለምና። የነፃነት መለኪያ በስምምነት ላይ የተተከለ ተጨባጭነቱ የተረጋገጠ የተጠቃሚነት ውህደት ድምር ውጤት ነው። ሰው በተፈጥሮና በሰው አዕምራዊ ውጤት የሚገኝ ጥቅም ተጠቃሚ ካልሆነ ነፃነት አልባ ከመሆኑም በላይ የዲሞክራሲ ሥርዓት የለውም። ተጠቃሚነት ባልስፈነበት ዲሞክራሲ ይጎረብጣል። ዲሞክራሲ ከፍላጎት ጋር ካልተጣጣመ ጉዳት ነው። ምክንያቱም ዲሞክራሲ የነፃነት ጥቅም ማስከበሪያ መሣሪያ በመሆኑ ከማህበረሰብ ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል። ፍትሐዊ ጥቅምና ለውጥ ያለፍትሐዊ ነፃነት ዋጋ ቢስ ከመሆነም በላይ የጋርዮሽ ስምምነት መርሆች ያፈርሳል። በጋራ ለመኖርና ለመበልፀግ የጋራ መርሆ ያስፈልጋል። የመርሆች ተፈፃሚነት ማሳያ አንዱ ሰብአዊ ብልፅግና ነው።ሁሉም የተሰጠውን በአግባቡ ቢጠቀም፤ የጎደለ ካለ ከራሱ ለራሱ እየሞላ ምክንያቱም አገር ማለት ጠያቂው (ግለሰብ፣ ማህበረሰብ)፣ ተጠያቂው (መንግሥት)፣ መሬቱ፣ ጋራው፣ ሸንተረሩ… ስለሆነ…. የኮንትራት ህይወቱ እስክታልቅ በነፃነት በሰላም ለሰላም እየኖሩ ማለፍ….. ትውልድ ይመጣል …ትውልድ ያልፋል። መልካም ዕለተ ሰንበት !!አዲስ ዘመን ጥቅም30/2012 አብርሃም ተወልደ
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=22254
[ { "passage": "ወራሪው የፋሺስት ጦር ሀገራችንን በቅኝ ለመግዛት በዘመተበት ወቅት ጀግኖች ኢትዮያውያን አይበገሬነታቸውን በተግባር አሳይተውታል።አዲስ አበባን ማዕከል አድርጎ በቆየበት ጊዜና በየካቲት 12 ቀን 1929 ዓም የሆነው ግን ከሁሉም ይለያል። በዚህች ቀን የግራዚያኒ ጦር ለድሆች ምጽዋት እሰጣለሁ ሲል መኳንንቶችን ሰበሰበ። ይህን አጋጣሚ ለመጠቀም የፈለጉት ወጣቶቹ ሞገስ አስገዶም፣ አብርሀም ደቦጭና ስምኦን አደፍርስም በግራዚያኒ ላይ የእጅ ቦንብ ወርውረው ክፉኛ አቆሰሉት። ይህኔ የድርጊታቸውን አጸፋ ለመመለስ የፈለገው የኢጣሊያ ጦር በከተማው ነዋሪዎች ላይ የጭካኔ በትሩን አሳረፈ። ለሦስት ቀናት በቀጠለው እልቂት ከሳላሳ ሺህ በላይ አረጋውያን፣ ነፍሰጡር እናቶች፣ ጡት ያልጣሉ ህጻናት፣ ወጣቶች፣ አካልጉዳተኞችና ሌሎችንም እያሳደደ በአካፋና በዶማ ጨፈጨፋቸው። የተቀሩትንም በጥይት ደብድቦ በመግደል በቤንዚን አርከፍክፎ አቃጠላቸው። ከተማዋ በደም ተጥለቀለቀች። የንጹሀን ህይወትም በከንቱ አለፈ። እነሆ! ይህ ታሪክ ከተፈጸመ ሰማንያ ሁለት ዓመታት ተቆጠሩ።ይህን አይረሴ ታሪክ በቀላሉ የማይዘነጉት ኢትዮጵያን ግን ዛሬም ቀኑንና ሰማዕታቱን እንዲህ አስበው ውለዋል። ", "passage_id": "8d01a9e78dc68cf518223f6aee12eb61" }, { "passage": "በኢትዮጵያም ይሁን በዓለም ዐቀፍ ነባራዊ ሁኔታዎች የማንነት ጉዳይ አንገብጋቢ ሆኗል። ነገር ግን በኢትዮጵያ ያለው የማንነት አረዳድ በአንድ ነገር ላይ ብቻ የተቸከለ ነው። ቤተልሔም ነጋሽ በሕይወት ገጠመኛቸው እና ንባባቸው የተረዱትን በማጣቀስ የማንነት ጉዳይ ውስብስብ እንደመሆኑ በቀላሉ ለመተርጎም መሞከር እንደማይገባም ያመላክታሉ። ባለፈው ሳምንት ሰሞኑን ወዳለሁበትና ለሥራ ወደ መጣሁበት ፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪካ ስመጣ ከአዲስ አበባ የሚመጣው በረራ ከሚያቆምበት ጆሃንስበርግ አንስቶ 45 ደቂቃ የሚሆነውን የፍጥነት መንገድ ጉዞ የተጓዝኩት የማርፍበት ሆቴል በተጨማሪ ክፍያ ባዘጋጀልኝ መኪናና ሾፌር ነበር። በኢሜይል የበረራ ሰዓቴንና የምቆይበትን ቀን፣ የምፈልጋቸውን አገልግሎቶች፣ የሚጠበቁብኝን ክፍያዎች ከምነጋገራት የሽያጭ ሠራተኛ በቀር ኤርፖርት መጥቶ ስለሚቀበለኝ ሰው መረጃው አልነበረኝም።ከአዲስ አበባ በጠዋት ተነስቼ ከአምስት ሰዓታት በረራ በኋላ ኦሊቨር ታምቦ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሼ፣ ብዙም ያላቆየኝን የኢሚግሬሽን ሰልፍና ጥያቄ ጨርሼ፣ አሰልቺውን ሻንጣ ጥበቃና የጉምሩክ “ምን ይዘሻል” አልፌ መውጫው’ጋ ስደርስ ሥሜን ከአያቴ ሥም ጋር በትልቁ አስጽፈው የቆሙ ሸምገል ያሉ ነጭ ጋር ተገጣጠምኩ። እኔ መሆኔን ገልጬ ቀረብ ስላቸው ቀልጠፍ ብለው ሻንጣዬን የያዘውን ጋሪ ተቀበሉኝ። ቁጥራቸው በርከት ያለ ነጭ የደቡብ አፍሪካ ዜጎች እንዳሉ ስለማውቅ ነጭ ሾፌር ሊቀበለኝ መምጣቱ ብዙም አልደነቀኝ።ባለብዙ ወለሉን የኤርፖርቱን ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ሦስት ወለል በሊፍት ወርደን መኪናቸው ወደቆመበት ስንደርስ፣ በመደዳ የቆሙት እጅግ ዘመናዊ አዳዲስ መኪኖች እያየሁ ተደንቄ ሳላበቃ ሾፌሬ መኪና ጋር ደርሰን እንድገባ ሲከፍቱልኝ አላመንኩም። ፅድት ያለ አዲስ መርሴዲስ መኪና። ከዛ በቃ በአውሮፓ እንደተለመደው ጡረታ ወጥተው አነስተኛ የእንግዳ ማረፊያ ከፍተው የሚሠሩ፣ የሆቴሉ ባለቤት መሆን አለባቸው ብዬ አሰብኩ። በቀስታ አውሮፕላን ማረፊያው ቅጥር ግቢ ለቀን በተንጣለለ በአንድ አቅጣጫ ብቻ ባለ አራት ሰፋፊ መንገድ የፍጥነት ጎዳና መንገዳችንን ስንይዝ ወሬ ተጀመረ። ሾፌሬ ራሳቸውን ሲያስተዋውቁኝ ጡረታ የወጡ ሲቪል ኢንጅነር፣ ሆቴሉን ከወንድማቸው ጋር የከፈቱ፣ ወንድማቸው የአውሮፓውያን ፋሲካ በነበረበት እሁድ ለእረፍት ባለመኖሩ እኔን ለመቀበል መምጣታቸውን ነገሩኝ። የመጣንበትን ዘመናዊ ጎዳና ሳደንቅ በሥራው እንደተሳተፉ እየነገሩኝ፣ ከኢራን እስከ አውስትራሊያ ዛምቢያና ናሚቢያ በሥራ ምክንያት ስላሳለፉት እያጫወቱኝ ከአዲስ አበባ ደብረዘይት የሚሆነውን ከጆሃንስበርግ እስከ ፕሪቶሪያ ዘለቅን።በመንገዳችን ያየሁት ትልቅ “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው” የሚል ከታች ደግሞ አነስ በሚል ጽሑፍ “የክርስቲያኖችን ፓርቲ ምረጡ” የሚል ቢልቦርድ ያጫረብኝ ጥያቄ ውይይታችንን ከግል ልምዳቸው ወደ አገራቸው ደቡብ አፍሪካ ፖለቲካ ወሰደን። ጥያቄዬ የክርስቲያኖችን ፓርቲ ምረጡ ሲል በሃይማኖት ላይ የተመሠረተ ፓርቲ አለወይ የሚል ነበር። ወዲያውም የአገሬ ዘር ተኮር ፓርቲዎች በሐሳቤ እየመጡ። “አይ በሃይማኖት ተደራጅቶ ወይም በዚያ ተጠርቶ ሳይሆን ክርስቲያኖች ተሰባስበው የመሠረቱትን ፓርቲ ምረጡ ማለታቸው ነው” አሉኝ። አልሸሹም ዞር አሉ ነው አልኩ በሆዴ፥ ልክ የእኛ አገር አንዳንድ ፓርቲዎች ብሔር ተኮር አይደለንም ቢሉም በሥራቸውና በስብስባቸው እንዲሁም ትኩረት በሚሰጡባቸው ጉዳዮች ወደ የትኛው ያጋደሉ እንደሆኑ እንደምንረዳው መሆኑ ነው።ሾፌሬ እንዳሉኝ በግንቦት ወር መጀመሪያ በደቡብ አፍሪካ ምርጫ አለ። በዚያው ፖለቲካ ተነስቶ ነጩ ጡረተኛ “ነጻ ስንወጣ” እያሉ ሲያወሩ ትንሽ ግራ ሆነብኝ። ከላይ እንዳልኩት ደቡብ አፍሪካ በርካታ ቁጥር ያላቸው ነጭ ዜጎች እንዳሏት ባውቅም፥ ነጮች ጥቁሮችን በቅኝ ገዙ ከሚለው ዘመኔን ሙሉ ከማውቀው ተረክ ባሻገር ነጭ ከሌላ ነጭ ነጻ መውጣቱን መስማት ትንሽ ለጆሮ ግራ ሆነብኝ። ከዚያ ማንነት ምንድነው የሚለውን ጥያቄ አጫረብኝ። ከአገራችን እውነታ አንፃር በተለይ ባደግኩበት ብዙ ብሔርና ብሔረሰቦች “መጤ” በሚባሉበት ከተማ ተወልዶ ማደግም፣ ቋንቋ መቻልም “የእኛ” የማያስብልበት ሁናቴ በአጠቃላይ እዚህ ነኝ ለማለት የመፈለግን ተፈጥሯዊ ፍላጎትና ነኝ የሚሉትን ማንነት የመከልከል አዝማሚያ አስታወሰኝ። በተለይ ከአንድ በላይ የሆኑ ብሔሮች ቅይጥ በሆነበት ማንነት ምርጫ ነው ወይስ የተጣለ ግዴታ (የእናት ማንነት ለፖለቲካ ወይም ለሌላ ምክያት ሲፈለግ በሚተውበት ሁኔታ) “ንፁኅ እንትን” መባልስ ለራስ ሽንገላ ወይስ በማንነት ቀውስ ውስጥ የመዳከር አባዜ የሚለው ትዝ አለኝ።ከላይ ባስቀመጥኩት ገጠመኝ መነሻነት ግን ከዚህ በፊት በሌሎች አገራት ጉብኝቴ እና የሥራ ጉዞዬ በራሴም ድክመት ጭምር አጋጥሞኝ ከማያውቀው ከሥራ ውጪ ካሉ መደበኛ ከአገሬው ሰዎች ጋር የመወያየት አጋጣሚ ጋር አብሮ ያስታወስኩት ስለማንነት ሲነሳ ለአገራችን ሁኔታ በጣም የሚሥማማ የሚመስለኝ የአንድ ጸሐፊና አሰላሳይ ሥራን በተመለከተ አንዳንድ ሐሳቦችን ለማካፈል በመፈለጌ ነው።አሚን ማአሉፍ በትውልድ ሊባኖሳዊ በዜግነት ፈረንሳዊ የሆነ አረብኛ ተናጋሪ ሆኖ ያደገ ከዛ በፈረንሳይኛ መጻሕፍትን የጻፈና መጽሐፎቹ ከ40 በላይ በሆኑ የዓለማችን ቋንቋዎች የተተረጎሙለት ድንቅ ጸሐፊ ነው። አባቱ መልኪቲ እየተባለ ይጠራ የነበረው የኬልቲክ ማኅበረሰብ አባል የነበረ ሲሆን እናቱ የቱርክ ዝርያ ያላት ግብፃዊት ስትሆን ካቶሊክን የምትከተል ከመሆኗ የተነሳ በሃይማኖታዊ ትምህርት ቤቶች እንዲማር ትወተውት ነበር። አሚን በርካታ መጽሐፎችን ያበረከተ ሲሆን ተጠቃሾቹ እ.አ.አ. በ1983 የታተመው “የመስቀል ጦርነቶች በአረቦች ዐይን”፣ “አፍሪካዊው ሊዮ” (1986)፣ “ሳማርካንድ” (1994)፣ “የብርሃን አፀዶች” (1996)፣ “የታንዮስ አለት” (1994) የተሰኙት ሲሆኑ ለዛሬ አንዳንድ ነጥቦች ለማለት ያሳሳኝና እ.አ.አ. በ1998 የታተመው ደግሞ “በማንነት ሥም፦ ጥቃት እና የሚጠጉበትን መፈለግ” (In the Name of Identity: Violence and the Need to Belong) የተሰኘው መጽሐፉ ነው። መጽሐፉ ማእሉፍ አረቦች በተለይ ለምዕራባዊያን ሥልጣኔና አኗኗር በመጋለጣቸውና ከምዕራቡ ዓለም ጋር በፈጠሩት የተለያየ ግንኙነት ምክንያት የገቡበትን የማንነት ቀውስ የራሱንም አረብ ክርስቲያን ማንነትና ያለፈበትን ልምድ ጨምሮ የተረከበት ነው።በበኩሌ መጽሐፉንና በተለይም ምዕራፍ አንድን መቀመጫውን ኒውዮርክ ያደረገ የምሥራቅ አፍሪካን ወጣቶች በአመራር ላይ ለማሠልጠን የቀረፀው ዝነኛ ፕሮግራም አካል በነበርኩበት ወቅት ለንባብና ለውይይት ከተመረጡ ምዕራፎች አንዱ በመሆኑ ነው ላገኘውና ላውቀው የቻልኩት። አሁን ላለንበት ደረጃ በተለይም ባለፉት ዓመታት ለነበርንበት ማንነትን (ብሔር፣ ዘር፣ ብሔራዊ ማንነት ወዘተ.) የመፈለግና በዚያም ምክንያት ነውጥና ሰላም እጦት ውስጥ መግባትን በሚመለከት የሚያቀርባቸውን ሐሳቦች ስለማደንቅ በአጋጣሚው ጥቂት ነጥቦችን ለማጋራት በመፈለግ ነው።መጽሐፉ በአምስት ዋና ዋና ምዕራፎች የተከፈለ ሲሆን በግርድፍ ትርጉም “ማንነትና መጠጊያ”፣ “ዘመናዊነት ከሌሎች ሲመጣ”፣ “የአርቲፊሻል ዘረኞች ዘመን”፣ “ተንኮለኛውን ማላመድ” እና የቃላት መፍቻ ናቸው። ለዚህ ጽሑፌ ዓላማ የምጠቀመው ግን በመጀመሪያው ምዕራፍ የተጠቀሱ ሐሳቦችን ነው። የተጠቀምኩት መጽሐፍ በባርባራ ብሬይ አማካኝነት ከፈርንሳይኛ ወደ እንግሊዝኛ የተመለሰውንና በፔንጊውን መጻሕፍት አማካኝነት እ.አ.አ. 2000 የታተመውን ኮፒ ነው።\n“ማንነት” ምንድነው?መጽሐፉን በመጀመሪያው ምዕራፍ ጸሐፊው ሐሳቡን የሚጀምረው የቃላትን ኀያልነት በማተት ነው “በጸሐፊነት ያሳለፍኩት ሕይወት ያስተማረኝ አንድ ነገር ቃላቶችን መፍራት እንዳለብኝ ነው። ግልጽ ያሉ ትርጉማቸው የማያሻማ የሚመስሉት በጣም ልንጠነቀቃቸው የሚገባ ሲሆን “ማንነት” የሚለው ቃል ከእነኝህ አንዱ ነው” ካለ በኋላ፥ ቃሉን በአንድ ትርጉም የማጠር ፍላጎትና ዕውቀትም እንደሌለው ጠቅሶ “ራስህን ዕወቅ” ከሚለው የሶቅራጥስ ጥቅስ ጀምሮ እስከ ሲግመንድ ፍሮይድ ቃሉ ወይም ማንነት የሚለው ፅንሰ ሐሳብ ከፍልስፍና መሠረታዊ ጥያቄዎች አንዱ መሆኑን ያትታል። አዲስ አቀራረብና ትርጉም ለማምጣት ሐሳብ የለኝም ቢልም መመለስ የሚፈልገው መሠረታዊ ጥያቄ ወይም ማንሸራሸር የሚፈልገው ሐሳብ ግን “በዘመናችን በርካቶች በሃይማኖት፣ በዘር/ብሔር፣ በብሔራዊ ማንነት ወዘተ. ሥም ወንጀል የሚፈፅሙት ለምንድነው?” የሚለው ነው። ተያይዞ ሌሎች ጥያቄዎች ሲመጡ አንዱ “ይሄ ነገር ከጥንት ዘመን ጀምሮ የነበረ ነው ወይስ አሁን የመጣ?” የሚለው ነው።ማንነት ምንድን ነው የሚለውን ሊጠይቅ የሚሞክረው ከቀላሉ ምሳሌ ነው – ከመታወቂያ፣ የመታወቂያ ካርድ በተለይ በእንግሊዝኛው ማንነት የሚለውን ቃል ካመጣንበት ቃል አንፃር “የማንነት ካርድ” የሚል ቀጥታ ትርጉም ሲኖረው የሚይዘው በተለያዩ ሁኔታዎች የሚለያይ ሆኖ፥ ሥም ከነአያት፣ ፎቶ፣ ምናልባት አንዳንድ አካላዊ መግለጫዎች (ለምሳሌ የዓይንና የፀጉር ቀለም)፣ የባለመታወቂያው ፊርማና አንዳንዴም የጣት አሻራ የዶክመንቱ ባለቤት ሰውየው ለመሆኑ ያለጥርጥር ያስረዳሉ የተባሉትን ሁሉ ያካትታል። እነኝህ መረጃዎች መንትያ ወንድም ወይም እህት እንኳን ቢመጡ በስህተት እሱን እንዳይመስሉን ለማሳወቅ ይረዳሉ የሚባሉ ናቸው። ጸሐፊው እንደሚለው “የእኔ ማንነት ከሌላ ሰው ጋር አንድ ዓይነት ከመሆን የሚከለክለኝ ነገር ነው”። እንደሱ አባባል ይህን ዓይነቱ የማንነት ትርጉም በአንፃራዊ መልኩ የማያሻማ ትርጉም ይሰጣል። ሆኖም ግን የእያንዳንዱ ሰው ማንነት ከላይ በተዘረዘሩት ፓስፖርትም ይሁን መታወቂያ የሚይዛቸው መለያ ባሕርያት ባለፈ በርካታ ዝርዝሮች ያሉት ነው። ለበርካታ ሰዎች ደግሞ ይህ ማንነት የእኔ የሚሉት የሚታመኑት ከሆነ ቡድን የመገኘት ነገርን (allegiance) ያካትታል። ለአንዳንዶች ይህ የሚታመኑለት ቡድን ሃይማኖት ወይም የእምነት ቡድን ነው፤ ከአንድ በላይ ነው። ለሌሎች ተቋም (ፓርቲ)፣ ሙያ ወዘተ. ሊሆን ይችላል።አለፍም ሲል ለሌሎች ጠንካራ ቁርኝት ያላቸው አካል የሚኖሩበት ሰፈር፣ አውራጃ፣ መንደር፣ ጎሳ፣ የእግር ኳስ ቡድን፣ የጓደኛማቾች ማኅበር ወዘተ. ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ቁርኝትና ታማኝነቱ ደረጃው ለእያንዳንዱ አካል መጠኑ የተለያየ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አንዱም የማይረባ ወይም በግለሰብ ሕይወት ላይ ተፅዕኖ የሌለው ሊሆን አይችልም፤ የማንነት አካል ነውና። እንደ ማዕሉፍ እምነት የእነኝህ ነገሮች ቅንብርና ጥንካሬ በየዕድሜያችን የሚለያይ ነው። የትኛውም የማንነታችን መሠረት የሆነ አካል ከሌላው ላይ ፍፁም የበላይነት የለውም። ይልቁንም እንደ ጊዜውና ያለንበት ወቅት በተለያየ መልክ ይገለጻል። ለምሳሌ እምነታችን የተነካ ወይም ጥያቄ ላይ የወደቀ ሲመስለን የእምነት አርበኞች ሆነን ብቅ እንልና ጎልቶ የሚወጣው ማንነታችን ያ ሆኖ ይሳላል። የአፍ መፍቻ ቋንቋችን ወይም የመጣንበት የምንለው ብሔር አደጋ የተደቀነበት ሲመስለን እንዲሁ።ከላይ የተቀመጡት የማንነትና እዚህ ነኝ የምንልባቸው የእምነት፣ የዘር፣ የፖለቲካ ታማኝነት፣ የሆነ ቡድን ደጋፊነት፣ የሆነ ቦታ መወለድ ወዘተ. ከሰው የሚለየን ቢመስልም በብዙ ሌሎች ሁኔታዎች ግን አንድ የሚያደርገንም ጭምር ነው። በየሁሉም ዓይነት ክፍል ከሌሎች በርካታ ሰዎች የምንጋራው ነገር አለንና። ዞሮ ዞሮ ነጥቡ አንዱን ማንነት ወስዶ (እንኳንስ የተቀየጠ ማንነት በበዛበት፣ ደራሲው እንዳለው በአያቶቻችን ጎጆ ማን እንዳለፈ በማናውቅበት) ሰው በዚያ ብቻ እንደሚተነተን ማሰብ ስህተት የሆነውን ያህል፥ ማንነቶቻችን ተጨፍልቀው ሁላችንም ሰው ነን የሚለው አስተሳሰብም ትክክል አለመሆኑን መረዳት። የማንነት ጉዳይ የተወሳሰበና የብዙ ነገሮች ጥርቅም እንዲሁም የሚለዋወጥ እንዲህ በቀላል የማይገለጽ መሆኑን አውቆ የኹለቱ አስታራቂ የሆነ ሰፋ ያለ ትንታኔ መፈለግ የሚጠበቅ የቤት ሥራ ነው።በተረፈ ይህ ጽሑፍ ቁንፅል ቢሆን ጥያቄ ለማጫር ያህል እንደተጻፈ ታስቦ፥ ምናልባት በዝርዝር በሰፊው ሌላ ጊዜ ለመመለስ ቃል በመግባት ከማቆሜ በፊት አንድ ሌላ ሳነበው ትርጉም የሰጠኝ ለእኛ አገር ሁኔታ ተገቢ የመሰለኝን የማዕሉፍን ሐሳብ ላስቀምጥ።“ብዙ የማንነት ክፍሎች ወይም በዘር በእምነት በተቋማት ወይም በመጡበት አካባቢ በርካታ ሚመደቡባቸው አካላት ያላቸው ሰዎች በማንነት ሥም ወንጀል በሚፈፀምባቸው ጊዜያት የሚጫወቱት ሚና አላቸው። እንደ እኔ አረብ፣ ክርስቲያን፣ ሊባኖስ፣ ፈርንሳዊ፣ ካቶሊክ የሆኑቱ እንደዚህ ያሉ ናቸው። ቢያንስ በአንዱ ጎኔ ከሌሎች በርካቶች ምድብ እጋራለሁ በእነሱና በሌሎች በሌላ ጎኔ ከምጋራቸው ጋር ድልድይ ሆኜ ማገልገል፣ የበለጡ ኹለቱ ምድቦች ወደ መረዳት፣ ወደ መተዋወቅ እንዲመጡ ምክንያት ልሆን እችላለሁ። ይህን ማድረግ የምችለው ግን አንደኛውን ማንነት እንድመርጥ የሚያስገድደኝ ወይም በብሔሬ ወይ በሃይማኖቴ አንፃር ብቻ እንድቆም ተፅዕኖ ከሌለ ብቻ ነው።”ቅጽ 1 ቁጥር 25 ሚያዚያ 19 ቀን 2011", "passage_id": "4299fff82ad02438dbd47faaccf4ff6c" }, { "passage": "ከመሬት ወደ ሰማይ የሚተነው ጉም አካባቢውን የተነደፈ ጥጥ አስመስሎታል። በከፊል ጉም የተሸፈነውን የፓርኩን ክፍል የዓይኔ እይታ እስከቻለልኝ አሻግሬ ወደ መመልከት ተሸጋገርኩ። አካባቢው አስደማሚ ገጽታን የተላበሰ ነው። በአረንጓዴ ልምላሜ ከታደለው አካባቢ ሽው የሚለው ንፋስ፤ በንፋሱ ሽውታ እየተገፋ ከጦስኝ ቁጥቋጦዎቹ የሚፈልቀው መልካም መዐዛ ለአፍንጫ ምግብ ነው። የአካባቢው ቅዝቃዜ አንጀት ድረስ ዘልቆ በመግባት መላ ሰውነትን ያንዘፈዝፋል። ብርዱ በስፍራው ቆዩ አይልም። ቢሆንም ግን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን አመራርና ሠራተኞቹን፣ የኪነ ጥበብ ሙያተኞችና የመገናኛ ብዙኃን ሙያተኞች ገና በማለዳው በስፍራው ታድመናል።ከሸዋ\nእስከ ወሎ ያለው የአማራ ወጣትም በስፍራው ቀድሞን ተገኝቷል። «አማራነት ይለመልማል፣ ኢትዮጵያዊነት ይቀጥላል» የሚል ህብረ ዝማሬን እያሰሙ በሚያስገመግም ድምጽ በህብረት የሚተሙትን ወጣቶች መመልከት ልብን በአንዳች የደስታ መንፈስ ይሞላል። እኛም ሆንን ወጣቶቹ በስፍራው የተገኘንበት ምክንያት ከወራት በፊት በእሳት ቃጠሎ ጉዳት በደረሰበት የኢትዮጵያውያን አረንጓዴ ማማ በሆነው ከታላቁ የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ላይ አረንጓዴ አሻራችንን ለማኖር ነው።በወጣቶቹ ትዕይንት የተሳበው ቀልቤ አላረፈምና ትዕይንቱ ከፊት በመሆን ወደ ሚመራው ወጣት ጠጋ ማለትን ወደደኩ። ራሴን አስተዋውቄ ስሙንና ከየት አካባቢ እንደመጣ ጥያቄዬን አቀረብኩለት። ከጎንደር ከተማ መምጣቱንና ስሙም ጋሻው አስናቀ እንደሚባል ነገረኝ። የተከፈተው የንግግር በር እንዳይዘጋ፤ በፍጥነት መርሃ ግብሩ ምን ስሜት ፈጠረብህ ስል? ሰፊ ማብራሪያን ይሰጠኝ ዘንድ ሃሳብ አቀበልኩት። ዕለቱ ከፍተኛ ደስታን የፈጠረበት መሆኑንና በሰሜን ተራራ አናት ላይ በችግኝ ተመስሎ ኢትዮጵያዊ አንድነት የተተከለበት ልዩነት የማይታሰብበት ዕለት ነው ሲል ገለጸልኝ። እኔም እንዴት? ስል በጥያቄ ያዝኩት።እርሱም ጊዜ ሳያጠፋ «በሰሜን ፓርክ በተዘጋጀው የችግኝ መርሃ ግብር ላይ ለመሳተፍ በአንድነት መንፈስ መነሳቱን አሳይቷል። ይሄ ሁኔታ አንድነታችንን የሚያጎለብት ትልቅ አጋጣሚ እንደሆነ ነው የማስበው» ሲል ለችግኝ ተከላ ከዳር እስከ ዳር በነቂስ ወጥቶ የታየው ተሳትፎ ሀገርን ለማልማት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያመላክት መሆኑን ነገረኝ።ከወጣት ጋሻው ጋር የነበረኝን የወግ ምዕራፍ በመዝጋት ሌላ ሃሳብ ሰጪን ፍለጋ ዓይኔን ከግራ ወደቀኝ ማማተር ጀመርኩኝ። ዓይኖቼ ጥቁር በጥቁር ከለበሰች አንዲት ሴት ላይ አረፈ። ጊዜ ሳላጠፋ ከአጠገቧ ተገኘቼ ከስፍራው የመገኘቷን ምክንያት እንድታጋራኝ ጠየኳት። ስሟ መሠረት ቻለው መሆኑን በመግለጽ «ከስፍራው የተገኘነው ሁለት አላማ በመያዝ ነው» ስትል ንግግሯን ጀመረችልኝ። «አንድም በልምላሜ የተሞላች ሀገርን ለልጆቻችንን ለማውረስ የሚያስችል ሥራን ለመስራት። ሌላው ደግሞ ሰኔ 15 ቀን ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ሲታትሩ የተሰዉትን መሪዎቻችንን ለማሰብ ነው» ስትል። መሠረት እንባ ያቀረሩ ዓይኖቿን ከደን ከፈት በማድረግ ስሜቷን ለመቆጣጠር እየሞከረች እንዲህ ስትል ማብራራት ጀመረች፤ «መሪዎቻችን የአማራ ሕዝብ አንገቱን ቀና አድርጎ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ለመውሰድ እስከ ህልፈተ ሕይወታቸው ታግለዋል፤ ሰርተዋል። የሞቱለት ራዕይን ይቀጥላል። የሰሜን ተራሮች ፓርክን የህብረታችን ምሳሌ በማድረግ በአንድነት ለልማት የተነሳንበት ዕለት ነው» ስትል ነበር በችግኝ ተከላው መርሃ ግብሩ ላይ ለመገኘቷ ምክንያቷን እንደሆናት ያወጋችኝ ። በሰሜን ተራራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ለመሳተፍ ከደሴ ከተማ ድረስ እንደመጣ የነገረኝ አቶ መልካሙ ይመር ሌላው የእይታዬ ማረፊያ ነበር። አቶ መልካሙ እንደነገረኝ በሰሜን ተራሮች አናት ላይ ችግኝ ከመትከል ባሻገር፤ መስቀለኛ መንገድ ላይ ያለችውን ሀገራችንን በአንድነት በመቆም ማዳን እንደምንችል ለማሳየት ነው ይላል። የሰሜን ተራሮች ፓርክ የአንድነታችን ማጠንከሪያ ገመድ፣ የብርታታችን ምሳሌ፣ ወድቆ የመነሳቱ ማሳያ እንደሆነ በመግለጽ ነበር የመርሃ ግብሩ አንድምታ ምን ያህል ፋይዳው ከፍ ያለ መሆኑን የገለጸልኝ።ከአቶ መልካሙ ጋር የነበረኝን ቆይታ በመዝጋት አካባቢውን ወደ መቃኘት ተሻገርኩ። በተፈጥሮ መደመምን ፈለኩ። አካባቢው አረንጓዴ ለብሷል። የእሳት አደጋ በቅርቡ ስለመድረሱ ጥያቄን ያጭራል። በተፈጥሮ ሀብቱ ከመደመም ሻገር ስል ደግሞ የአካባቢውን መአዛ ወደማጣጣም ተሻገርኩ። ቅዝቃዜን አሳብሮ ሽው የሚለው ንፋስ ከጦስኝ ቁጥቋጦ የሚፈልቅ መዐዛ ኦህ ….እንዴት ይማርካል። የመልክዓ ምድሩ ገጽታ፤ አፍንጫን ሰርስሮ ልብን ኮርኩሮ የሚገባው የጦስኝ ሽታ፣ የስፍራው በጉም የመሞላቱ ትዕይንት ከሰሜን ተራሮች አስፈንጥሮ ወደ ባሌ ወሰደኝ።ከትውልድ ከተማዬ ጎባ ከተማ መቶ ኪሎ ሜትር ርቆ የዓለም እይታ የሆነውን ሳነቴን በቅጽበት እንዳስብ ያስገደደኝ ስሜት ወረሰኝ። ኢትዮጵያ በሕዝቦቿ ብቻ ሳይሆን በመልክዓ ምድሯም ጭምር የመመሳሰል፣ የመወራረስና የአንድነት ገጽታን የተቸረች ምድር ስለመሆኗ እንዳስብ አስገደደኝ። አጥንት ሰርስሮ በሚገባው የሰሜን ተራሮች ብርድ ሳይበገሩ በርካቶች አሻራቸውን ያሳረፉበት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ወኔን በሰነቀ መንፈስ ከሰዓታት ቆይታ በኋላ ተጠናቀቀ። ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡትን ከሁለት ሺህ በላይ ተሳታፊዎችን ያካተተው መርሃ ግብሩ በመጨረሻም ከ38 ሺህ በላይ ሀገር በቀል ችግኞች መትከል መቻሉ ተሰማ።አዲስ\nዘመን ረቡዕ\nሐምሌ 24/2011  ዳንኤል ዘነበ", "passage_id": "5652ab027328d72b24ab036776b3c447" }, { "passage": "ስለእርሷ መፅናት እልፎች የተዋደቁላት፤ ማህፀነ ለምለሟ አገር ኢትዮጵያ ከዛሬ 124 ዓመት በፊት መቆየቷን የሚፈታተን ሉዓላዊነቷን የሚንድ ከባድ አደጋ ተጋርጦባታል። ይቺ በተደጋጋሚ ከርቀት የሚጎመዧት ተፈጥሮ ያደላት አገር ኢትዮጵያ፤ በልጆቿ አጥንት ታጥራ የኖረች ምድር ቀርበው ሊወርሯት እና ደፍጥጠው ሊገዟት ሽተው ተደጋጋሚ ሙከራ አደረጉባት። ከሙካራም አለፉና እንዳሻን እናድርግሽ አሏት። ብለውም አልቀሩ ከሰሜን\nአቅጣጫ ዘመናዊ የጦር\nመሣሪያ በታጠቀ እብሪተኛ\nየተወጠረው  በጄኔራል ባራቶሪ የተመራው የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር ይቺን ለዘመናት አልደፈር ያለች አገር ተነኮሱ። የማይደፈረውን ደፍሮ ህልውናዋን በመፈታተን ዳር ድንበሯን ተሻገረ። መሪዋ ምኒልክም አገሬን ተዋት ቢልም የወራሪው አመጣጥ ለመመለስ አልነበረምና አሻፈረኝ አለ። በወቅቱ ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ጫፍ አካባቢያቸውን የሚያስተዳድሩ አንዳንድ መሳፍንት በንጉሡ ደስተኛ አልነበሩም። ይሁንና ከንጉሣቸው ተኳርፈው ቅሬታ ውስጥ የነበሩትና የየራሳቸውን ግዛት እያስገበሩ ህዝባቸውን እየመሩ የነበሩት መሳፍንት በአንድ አገር ጥላ ሥር መሆኗቸውን በማመን የንጉሡን አዋጅ፤ አገር ተወርሯል እንዝመት ጥሪን አድምጠው ተቀብለዋል። ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መስከረም 7 ቀን 1888 ዓ.ም ጠላት አገር ሊወርር፤ ሉዓላዊነት ሊደፈር ነውና በሕብረት እንዝመት ባሉ ጊዜ፤ አዋጁን አድምጦ አገር በመወረሩ ያልተቆጣ እና ምላሽ ለመስጠት እራሱን ያላዘጋጀ ዜጋ አልነበረም። ውስጣዊ ቅያሜውን ትቶ አገሩን አስቀድሞ እራሱን ሊሰጥ ንጉሡን አጅቦ ወደ ዓድዋ ዘመተ። የካቲት 23 ቀን 1888 ከየአቅጣጫው በአገር ፍቅር ስሜት ስለ አገሩ ለመዋደቅ ባህላዊ መሣሪያዎችን ታጥቆ ከሰፊ ዝግጅት ጋር ዘመናዊ ጦር መሣሪያ ከታጠቀው የኢጣሊያ ሠራዊት ጋር በወኔ ተፋለመ።  እኩለ ቀን ላይ ዘመናት የሚሻገር የጥቁሮችን አንገት ከፍ ያደረገ የድል ብሥራት ከዓድዋ ታሪካዊ ተራሮች ሥር ለዓለም ደረሰ። ኢትዮጵያውያን በአገር ፍቅር ስሜት እየሸለሉና እየፎከሩ የኢጣሊያንን ሠራዊት ጠራርገው አባረሩ፤ የተቀረውን ማረኩ።በኮተቤ ሜትሮፖሊቲያን ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህሩ ዶክተር አልማው ክፍሌ፤ የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመው ጠላትን ድል ያደረጉበትና አንድነታቸውን ለዓለም ያሳዩበት መሆኑን ይናገራሉ። በጊዜው በተለያዩ መሳፍንቶች የነበሩ የአስተዳደር ቅሬታዎችን ወደጎን በመተው አገርን አስቀድመው በጋራ መዝመታቸው የላቀ የአገር ፍቅር ማሣያ መሆኑን ያስረዳሉ።በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት ኤጀንሲ የዓድዋ በዓልን አስመልክቶ በተዘጋጀው ሴሚናር ላይ ዓድዋን የተመለከተ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡት ዶክተር አልማው፤ ዓድዋ ኢትዮጵያውያን ለጥቁር ህዝብ ያበረከቱት ታላቅ ድል መሆኑን ያነሳሉ። የዓድዋ ድል ኢትዮጵያ እስከ ዛሬ በአንድነት የፀናች አገር እንድትሆን ምክንያት መሆኑንም ይገልፃሉ።የዛሬው ትውልድ በሰከነ\nመንፈስ አባቶቹ ያስረከቡትን\nአገር አንድነት ጠብቆ\nበፍቅር መኖር እንደሚገባው\nይመክራሉ። ኢትዮጵያውያን አለመግባባታቸውን\nበውይይት በመፍታት እንደ\n አገር አንድ ሆነው ዘርፈ ብዙ ድል መቀዳጀት የሚጠበቅባቸው መሆኑን አሳስበዋል። በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህሩ አቶ ዳንኤል ወርቁ በበኩላቸው በሴሚናሩ ላይ ባቀረቡት ዓድዋን በተመለከተው ጥናታዊ ጽሁፋቸው፤ የዓድዋ ድል የኢትዮጵያውያን ታላቅ የትብብርና የአንድነት ማሳያ መሆኑን ይናገራሉ። በወቅቱ የነበሩ መሳፍንቶች ለአገራዊ ጥሪ ከልብ ምላሽ በመስጠትና በመዝመት ለአገራቸው ክብር የተዋደቁበት ታላቅ ገድል መሆኑን አስታውሰዋል። ኢትጵያውያን ተገድደው የገቡበትንና ዝግጅት ያላደረጉበትን ጦርነት አሸናፊ መሆን ያስቻላቸው በአንድነት መቆማቸውና ጥልቅ የሆነ የአገር ፍቅር ስሜት መላበሳቸው እንደሆነ ያስረዱት አቶ ዳንኤል፤ ዓድዋ ከኢትዮጵያ አልፎ በመላው ዓለም ጥቁር ህዝቦች የሚዘከር ታላቅ ድል መሆኑን በማስታወስ፤ የዛሬው ትውልድ ከቀደምት አያቶቹ ሕብረትንና አንድነትን ሊማርና በጋራ አገርን ጠብቆ ሊያቆይ ይገባዋልም ብለዋል። የብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት ኤጀንሲ ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ገረመው ከበደ፤ የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን እራሳቸውን በመክፈል ለትውልድ ያበረከቱት ስጦታ ነው ብለዋል። ዓድዋ ኢትጵያውያን አንድነታቸውን ያረጋገጡበት ልዩ ድል መሆኑንም አውስተዋል። የዛሬው ትውልድም የአንድነት ድር እና ማግ ሆኖ የአገሩን አንድነት ጠብቆ ለለውጥ እንዲተጋ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። አዲስ ዘመን የካቲት 23/2012ተገኝ ብሩ  ", "passage_id": "2518f1276a279dd8dd7259f179678f00" }, { "passage": "ተፈራ ነጋሽ፦ አሁን 13 ዓመት ጨርሼ 14 ዓመት ሊሞላኝ አንድ ወር ይቀረኛል።\n\nያኔ ይህንን ውሳኔ ስትወስን አድናቂዎችህ ምን ይሉ ነበር?\n\nተፈራ ነጋሽ፡-የተለያየ ዓይነት አስተያየት ነበር። የሚደግፉ አሉ። እንደገና ደግሞ በዛው ብቀጥል የሚፈልጉና የራሳቸውን ሐሳብ የሚሰጡም አሉ። እንዲሁ ደግሞ የሚቃወሙም ነበሩ። ዞሮ ዞሮ ውሳኔው ግን የራስ ስለሆነና ሕይወት ስለሆነ፣ መንፈሳዊ ነገር አንተ ለራስህ የሚገለጥልህ ነገር ስለሆነ፣ አንተ የተሰማህን ወይንም ደግሞ የተገለጠልህን ነገር ነው የምትኖረው። \n\nወደ መንፈሳዊ ሕይወት ከገባህ በኋላ የቀድሞ ሥራዎችህን ስትሰማ የሚፈጠርብህ ስሜት ምንድን ነው?\n\nተፈራ ነጋሽ፡- እውነቱን ለመናገር ከሆነ የውሳኔህ ሁኔታ ነው የሚወስነው። እኔ ስወስን ምንም ነገር ሳልጨብጥ አይደለም የወሰንኩት። የሆነ ነገር ገብቶኝ በትክክል መንፈሴ ላይ የተረዳሁት ነገር ስለነበረ፣ ያ የተረዳሁት ነገር ደግሞ ከአእምሮ በላይ የሆነ ትልቅ ስለሆነ፣ ከምንም ነገር ጋር አላነፃፅረውም። እና በቀጥታ ወደዚህ ወደ መንፈሳዊው ዓለም ስመጣ በፊት የነበሩኝ ልምዶች እንዴት እንደሆነ ሳላውቅ ከኔ ተለይተው ነው ያገኘኋቸው። እና ሙዚቃውም ዘፈኑም አብሮ ወዴት አንደሄደም አላውቅም። ፍላጎቱ ጠፍቷል። አሁን የድሮ ሥራዎቼን በምሰማበት ጊዜ እውነቱን ለመናገር ከሆነ ምንም ስሜት አይሰጠኝም።የኔ እስከማይመስሉኝ ድረስ ነው ውስጤ የተለወጠው ልልህ ፈልጌ ነው።\n\n• ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን\n\n• ኦሮምኛ ዘፋኙ ለደስታ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱን አጣ \n\nያንን ድምፅ ስትሰማ፣ ሙዚቃውን ስትሰማ እንደሌላ ሰው ነው የምታስበው?\n\nተፈራ ነጋሽ፡- እውነት ነው፤ ምክንያቱም ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ከሄድን ምን ይላል፣ \"ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው\" ይላል። አዲስ ፍጥረት የሚለው ነገር እውነት ነው። ወደዚህ አዲስ ማንነት ስመጣ ውስጤ ለውጥ ተካሄዷል። በዐይን የማይታይ ግን መለኮት የሚሠራው ውስጣዊ ለውጥ ተከስቷል። ያ ለውጥ ዘፈንን ብቻ አይደለም፤ ሌሎች ማንኛቸውንም ነገሮች በተለይ ኀጥያት ተኮር የሆኑ ነገሮች ወዴት እንደሄዱ አላወቅሁም። \n\nራሴ ነፃ ሆኜ፣ ፍላጎቴ ተቀይሮ፣ ሌላ ሰው ሆኜ ነው ራሴን ያገኘሁት።\n\nለምሳሌ አንድ ነገር ልንገርህ፤ ጫት እቅም፣ መጠጥም እጠጣ ነበር። ግን ይህንን ውሳኔ በወሰንኩ በማግሥቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ነው ትዝ ያለኝ። ውስጤን ሳዳምጠው የለም። ልክ እንደዚህ ዘፈኑም አብሮ ሄዷል። ስለዚህ ይህ ውስጣዊ ለውጥ ነው፤ ይሄ የማንነት ለውጥ ነው።\n\nሥራዎችህ ከውሳኔህ በኋላ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ተከፍተው ሲደመጡ ቅር ይልሃል?\n\nተፈራ ነጋሽ፡- እንደዛ አላስብም፤ ተቃውሞም አላሰማም። ምክንያቱም ሥራዎቹ የብቻዬ አይደሉም። የሙዚቃ ባንዱ፣ ገጣሚያን፣ ዜማ ደራሲያን አሉ። ብቻዬን የሠራሁት ሥራ ስላልሆነ እነኛም ሰዎች መብት አላቸው። ሌላው ቢሰሙም ላለፈው ነገር እኔ አልጠየቅም። የዛን ጊዜ ትክክል ነበርኩ፤ አሁን ደግሞ የበለጠ ትክክል ነኝ። በዛን ወቅት ጥፋት አጥፍቼ ቢሆን አሁን በምሕረት ወጥቼያለሁኝና ያንን ነገር እግዚአብሔር ረስቶልኛል። ወደ ኋላ ተመልሼ ይህ ለምን ሆነ? ለምን ዘፈንኩ? ብዬ አልፀፀትም። በሌላ መንገድ ካየነው ሥራዎቹ ሲሰሙ አንድም ሰዎች መነጋገሪያ ሊያደርጉትና ሰዎች ራሳቸውን ውሳኔ መምረጫ እንዲያደርጉት መንገድ ሊፈጥር ስለሚችል ለምን የኔ ሥራ ተከፈተ፣ በሚዲያ ላይ መደመጥ የለበትም የሚል አቋም የለኝም። \n\n• ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች \n\n• አክሱምና ላሊበላ ለስራዎቹ መስፈርት የሆኑት ዲዛይነር\n\nሰሞኑን ከራይድ ጋር መሥራት መጀመርህን ሰማን፤ እንዴት ወደዚህ ሥራ ልትገባ ቻልክ?\n\nተፈራ ነጋሽ፡- ከዛ በፊትም የተለያየ ሥራ እሠራ... ", "passage_id": "8e06e333a8e578f2494305805b996f49" } ]
ff490b97df1704d73733a1e8f8b2cb40
7e87f7ef3b202a0728b5a33d4f995337
ከፅዳት ሠራተኝነት እስከ አብራሪነት
ህይወት በብዙ ውጣ ውረዶች የተፈተነች ናት። ገሚሶቹ ዛሬን ተቸግረው ነገን በተስፋ ሲያልሙ የተቀሩት ደግሞ በአቋራጭ ለመክበር ድንጋዮችን ሲፈነቅሉ ይስተዋላል። ተስፋን የሰነቁ ሁሉ በመንገዳቸው የሚገጥማቸውን እንቅፋት ገሸሽ በማድረግ የነገ መንገዳቸውን ያመቻቻሉ። ችግር ከጉዟቸው እንዳያደናቅፋቸው ከወዲሁ የሰነቁትን የሞራል ስንቅ በመከላከያነት ይጠቀማሉ። ውጣ ውረዶችን እንዲሁም ከፍታና ዝቅታን የህይወት አንድ አካል አድርጎ በመቁጠር በተስፋ ወደፊት መገስገስን የሚለማመዱት እነዚህ የነገ አላሚዎች መነፅራቸው ስኬትን እንጂ ውድቀትን አይመለከትም።ሁሌም የሚያስቡትና የሚያልሙት ትናንትናቸው አስተማሪ፣ ዛሬያቸው ተስፋ እና ነጋቸው ብሩህ መሆኑን ብቻ ነው። ከፍታ የሚጀመረው ዝቅ ብሎ ከተቀመጠው መወጣጫ መሆኑን ጠንቅቀው የሚያውቁት እነዚህ ግለሰቦች ከግባቸው ለመድረስ ለአፍታም ሲያመነቱ አይስተዋልም። እሾሁን ለቅመው፣ ጠጠሩን ጠርገው፣ አቧራውን አራግፈውና የችግር አጥርን ጥሰው ከፍ ብለው መታየት ቀጣዩ የህይወት ጉዞ መሆኑን በመረዳት ለዚህ ጉዞ ወገባቸውን ጠበቅ አድርገው ይታጠቃሉ። በሀገራችንም ሆነ በአለማችን በተለያዩ ጊዜያት እጅግ ዝቅ ካለ የኑሮ ደረጃ ተነስተው አለምን የሚቀይር ሃሳብ፣ እውቀትና ገንዘብ ያካበቱ በርካታ ግለሰቦችን ታሪክ አይተንም ሰምተንም እናውቃለን።ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የጠቀሙና አንቱታን ያተረፉ ግለሰቦች የስኬት መንገዳቸው ሲመረመር የአንዳንዶቹ ለማመን ሲከብድ ይስተዋ ላል። የስኬታማ ግለሰቦች የራስ ጥረትና ትጋት ተጨምሮበት በሩጫቸው ውሃ ያቀበሏቸው አጋሮ ችም የስኬት መሰላልን የሚያስጨብጡ ተምሳሌቶች ናቸው።ዛሬ ከወደ ናይጄሪያ የተሰማ የአንድ ስኬ ታማ ግለሰብን ታሪክ ልናስነብባችሁ ወደናል። ኢንተለጀንስ ዶት ኮም እንዳስነበበው ግለሰቡ አብራሪ የመሆን ህልሙን የጀመረው ከአውሮፕላን የፅዳት ሰራተኝነት ተነስቶ ሲሆን አሁን ላይ የንግድ አውሮፕላን አብራሪ ለመሆን በቅቷል። የዚህ ስኬታማ ሰው አጭር የስኬት ታሪክ እንደሚከተለው ነው።ናይጀሪያዊው መሀመድ አቡበከር ከዛሬ 24 አመታት በፊት የአውሮፕላን ፅዳት ሰራተኛ ሆኖ ነበር ካቡ ኤር በተባለ ኩባንያ የተቀጠረው። በካዱና ፖሊ ቴክኒክ ለመማር አመልክቶ የትምህርት ማስረጃዎቹን በጊዜው ባለማስገባቱ ተቀባይነት ሳያገኝ የቀረው መሀመድ ምንም እንኳን የስራ ምርጫው ባይሆንም ለረጅም ጊዜ ያለስራ መቀመጥን ባለመምረጥ ነበር በካቡ ኤር ውስጥ ለመቀጠር የወሰነውና በአውሮፕላን የፅዳት ሰራተኝነት ስራ የጀመረው።የመሀመድ ደመወዝ እጅግ ዝቅተኛ ማለትም በቀን 200 የናይጀሪያ ናይራ ወይም 0.5 የአሜሪካን ዶላር በመሆኑ ማንም ሰው በስራው ላይ ይቆያል ብሎ አልገመተም ነበር፤ ነገር ግን ይህ ባለሩቅ ተስፋ ሀልመኛ ወጣት በስራው በመግፋት ብቻም ሳይሆን ውጤታማ ሰራተኛ በመሆን ከጊዜ ቆይታ በኋላ በሜዱግሪ ኤር በግራውንድ ስታፍነት ተቀጠረ።ራሱን በዲሲፕሊን የታነፀና ውጤታማ ሰራተኛ ያደረገው መሀመድ በአቪየሽን ዘርፍ በርካታ እውቀቶችን እንዲያካብት አስቻለው። በቀጣይም መሀመድ በካቦ ኤር የበረራ አባልነት ላይ የማመልከት እድል አግኝቶ ስራውን መስራት ጀመረ። በዚህ ስራም ስምንት አመታትን በወር 17 ሺህ ናይራ ወይም 47 የአሜሪካን ዶላር እየተከፈለው ሰራ። ከዚህ በኋላም በበረራ ተቆጣጣሪነት ወደ ኤሮ ኮንትራክተርስ ተዛወረ።የስራ ታታሪነቱና ፈጣን አዕምሮው በድርጅቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ትኩረትን መሳብ የቻለው መሀመድ ወርሀዊ ደመወዙ በወር ወደ 170 ሺህ ናይራ ወይም 469 የአሜሪካን ዶላር ከፍ አለ። ይህንን ማመን ያቃተው መሀመድ የመጀመሪያ የደመወዝ ክፍያ ቼኩን ሲቀበል ገንዘቡን ለመመለስ ሞክሮ እንደነበር ተገልጿል።የሚያገኘውን ደመወዝ በዋዛ ፈዛዛ ማጥፋት ያልፈለገው መሀመድ ቁጠባ በመጀመር አብራሪ የመሆን ህልሙን እውን ለማድረግ ጉዳዩን ለዋና ዳይሬክተሩ አስረዳ፤ ዳይሬክተሩም የመሀመድን ሃሳብ በመደገፍ ድጋፍ ተደርጎለት በካናዳ የግል አብራሪነት ፈቃድ ለማግኘት ትምህርቱን ጀምሮ በስኬት አጠናቀቀ።መሀመድ ወደ ናይጀሪያ ከተመለሰ በኋላ የንግድ አብራሪነት ፈቃድ መያዝ ቢፈልግም በቂ ገንዘብ ስላልነበረው ይህንን ማሳካት አልቻለም፤ ይሁን እንጂ ችግሩ ይህንን ህልሙን እና ጠንካራ መንፈሱን ሳይጎትተው ወደ ፊት በመገስገስ የድርጅቱን ም/ዋና ዳይሬክተር ድጋፍ በመጠየቅ ታማኝነቱና ስራ ወዳድነቱ በኩባንያው ተጨማሪ ድጋፍ እንዲደረግለት ረዳው።ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ካናዳ በመሄድ የንግድ አውሮፕላን አብራሪነት ስልጠናውን አጠናቆ ወደ ትውልድ ሀገሩ ናይጀሪያ ተመለሰ። ከ24 አመታት ጠንካራና ውጤታማ የስራ ጊዜያት በኋላ መሀመድ በአዝማን ኤር ውስጥ የአውሮፕላን አብራሪ ሆኖ በመቀጠር ህልሙን እውን አደረገ። አሁን መሀመድ በዚህ አየር መንገድ ውስጥ በአብራሪነት ስራውን እየሰራ ይገኛል፡አዲስ ዘመን ኅዳር 1 / 2012 በድልነሳ ምንውየለት
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=22304
[ { "passage": "የሰው\nልጅ ሰው ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ሥራ አለ። መኖሩም ዓለማችን ዛሬ ያለችበት ደረጃና ሁኔታ ላይ እንድትገኝ አድርጓታል። ባጭሩ ዓለማችንን ለዚህ ለአሁን መልኳ ያበቃት ሥራ ሲሆን፤ በተለም ድርጊት ፈፃሚው ወጣቱ ሀይል ነው። በየትኛውም ዘመንና ትውልድ ይሁን መቼ የለውጥ ሀይሉ ወጣቱ ነውና ሥራ ሲነሳ ወጣቱን ማንሳት የግድ ነው። ስለ ሥራ ፈጠራ ሲነሳም እንደዛው። በተለይ\nኢትዮጵያን በመሳሰሉ ታዳጊ አገራት ፈጣን የሕዝብ ቁጥር ዕድገት በመኖሩ የሥራ ፍላጎት ከፍተኛ ሲሆን የሥራ ፈጠራውም ከምን ግዜውም በላይ አጣዳፊና አስፈላጊ ነው። ይሁንና፣ ከሚገኘው የሥራ እድል ጀርባና ከተገኘው የሥራ እድል ተጠቃሚ ሰራተኛ አገር ምን ትጠቀማለች? የሚለው መሰረታዊ ጉዳይ ነው። በበርካታ ድርጅቶች ውስጥ በወጣቶችና የሥራ ሁኔታዎች ላይ ጥናት ያደረጉትና የስነ-ልቦና ምሁር የሆኑት አቶ ሳምሶን ይስሀቅ እንደሚሉት ሥራ “ለሰው ልጅ መሰረታዊ ጉዳይ ነው። ሥራ መያዝም ሰንአዊ መብት ነው። “የሰው ልጅ ሥራ በመስራቱ ለራሱ ከሚያገኘው ጠቀሜታ በላይ ለማህበረሰቡና ለአገሩ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ይበልጣል። ለምሳሌ፤\nሥራ የሌለው ሰው አእምሮው የሚያዘው ተገቢ ባልሆኑ ጉዳዮች ነው፤ ተገቢ ቢሆኑ እንኳን ጊዜያዊ እንጂ ወቅታዊ አይደሉም። ሥራ ከሌለው ጋር ሲነፃፀር ሥራ ያለው ለጭንቀት ተጋላጭነቱ አናሳ ነው። ፈረንጆቹ እንደሚሉት ‘ሥራ የፈታ አእምሮ የዲያቢሎስ መናኸሪያ ነው።’ በቀላሉ ለተለያዩ ሱሶች ይጋለጣል። ሥራ ያለው ሰው፣ ሁሉም ባይሆን፣ ግን ከእነዚህ የራቀ፣ ሓላፊነት የሚሰማው፣ ስለ ስራው የሚያስብ እና ለስራውም የሚጨነቅ፣ ነገን የሚያልም፣ አልባሌ ቦታ ለመዋል ጊዜ የሌለው ነው። ይህ ደግሞ ለጊዜው ላይታወቀን ይችላል እንጂ በአብዛኛው ጥቅሙ ለሀገርና ለአጠቃላይ ማህበረሰቡ ነው።” በጉዳዩ ላይ የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአንድ አገር ላይ ሥራ አጥ ዜጋ አለመኖሩና ሥራ ያለው ቁጥር መብዛቱ አገራዊ ጥቅሙና አኮኖሚያዊ ፋይዳው ከዚህ በመለስ የሚባል አይደለም። ማርክ ሪዲክስ የተባሉ ተመራማሪ “ዋና ዋና” በማለት ያቀረቧቸው ጥቅሞች ያሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል ሰራተኛ የሆነ ዜጋ አንደኛ ሸማች ነው፣ ሁለተኛ አምራች ነው፣ ሦስተኛ ቀዳሚ የገንዘብ ልውውጥ አካል ነው፤ አራተኛ አከፋፋይና ተካፋይ ነው። እንደ ምሁሩ አገላለፅ እነዚህ ደግሞ “ለአንድ ኢኮኖሚ እድገት የጀርባ አጥንት” ናቸው። እንደ\nሪዲክስ ጥናት የስራና ሰራተኛ ጥምረት ከስብጥር የዕድገት ምንጮችም አንዱና ዋነኛው ነው። አዳዲስ ሰዎችን ወደ ስራው ዓለም ማስገባት አዳዲስ ክህሎት፣ እውቀት፣ ልምድ፣ አሰራር ወዘተ ለማግኘት ሰፊ እድልን ለተቋማት ይከፍታል የሚሉን ደግሞ ሚራንዳ ብሩኪንስ ናቸው። እነዚህ የሌሉት ሰራተኛ ወደ ድርጅት ከተቀላቀለ ደግሞ ውጤቱ የዚህ ተቃራኒ እንደሚሆንም ይኸው ጥናት ያስረዳል። በቅርቡ የቻይናን “ቀበቶ እና መንገድ/Belt &\nRoad” ስትራቴጂ\nየገመገሙ አንጋፋ ጋዜጠኛ እና ማህበራዊ ሀያሲ ሀርሌይ ቬግ ሥራ ያላቸውንና የሌላቸውን በንፅፅር ባዩበት ጥናታቸው ውስጥ “ጠቃሚ ነጥቦች” በማለት ካሰፈሯቸው መካከል የሥራ እድል ያገኙ ሰዎች የሥራ እድል ካላገኙት በተሻለ አገርን እየጠቀሙ መሆኑ፤ ሥራ ያላቸው ሰዎች የተለያዩ ወጪዎችን በማውጣት ኢኮኖሚው እንዲስፈነጠር ማድረጋቸው፤ ኢኮኖሚው እንዲያድግና ሌሎች አዳዲስ የስራ እድሎች እንዲፈጠሩ ማድረጋቸው እንዲሁም ለመሰረተልማት መፋጠን ከፍተኛ ሚና ያላቸው መሆናቸው ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው። ለፖለቲካ መረጋጋትም ሆነ ለኢኮኖሚ እድገት ያለውን ቁልፍና የማይተካ ሚና የሚነግሩን ደግሞ የሥራ ፈጠራ ባለሙያና ሥራ ፈጣሪው ምራገሽ ከጅሪዋል (Indian\nInstitute of Management ምሁር) ናቸው።\nእንደ ምራገሽ አስተያየት ሥራ ያለው፣ በትክክልም ስራውን ሰርቶና ውጤታማ ሆኖ የሚውል ሰው በብዙ መልኩ አትራፊ ነው፤ የሞራል ልእልናው ሲበዛ ከፍተኛ፣ በራሱ የሚተማመን፣ የተረጋጋ፣ ፍላጎቱ እየጨመረ ስለሚሄድም ጥሩ ሸማች ነው። ይህ ደግሞ ለኢኮኖሚው መነቃቃት ከፍተኛ እገዛን ያደርጋል። በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ ሀብቱን በማዋል በኩል ጥሩ ኢንቨስተር ነው። ፍላጎቱ ሁሉ በመበጥበጥና ሁከት በመፍጠር ሌሎችን ለመረበሽ ሳይሆን ለማስደሰት ይጥራል። ለህይወቱ ትርጉም ይሰጣል፤ ለመኖሩም ምክንያታዊ ነው። የራሱን\nህይወት መኖር ላይ ያተኩራል። አቶ ሳምሶን ይስሀቅም ከዚሁ ባልተለየ ሁኔታ “ሥራ ያለው ሰው ቤተሰቡንም የሚመራ ሲሆን፤ ይህ ደግሞ ለአገርም ለማህበረሰብም የሚያስገኘው ፋይዳ ቀላል” እንዳልሆነ ይናገራሉ። “ሰዎች ሥራ አጥ በሚሆኑበት ጊዜ ሁከትና አለመረጋጋትን ይፈጥራሉ የሚለው የምራገሽ ጥናት ሥራ አጥ መሆን ሰዎችን ለማንኛውም እኩይ ተግባር ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደርጋል። ከዚህ መረዳት እንደ ሚቻለው ሥራ መፍጠር፤ ዜጎችን የተፈጠረው የሥራ እድል ተጠቃሚ ማድረግና ሰዎች ሰርተው መግባት መቻላቸው ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ባለፈ ፖለቲካዊ ፋይዳም ያለው መሆኑን ነው። ለዚህም\nነው ምሁሩ “መንግስታት አጓጉል ነገር ላይ ገንዘባቸውን ከማፍሰስ ይልቅ ለወጣቶች የሥራ እድል በሚፈጥር መልኩ ማዋል” እንደሚገባቸው አበክረው የሚመክሩት። አቶ ሳሙኤል ይስሀቅም ይህንኑ ሀሳብ በመደገፍ “ለእኩይ ተግባራት የተጋለጠ ነው። ጥፋት ይቀናዋል። ድንጋይ ለመወርወር፣ ንብረት ለማውደም፣ ሁከት ለመፍጠር፣ በሌሎች አላማ ለመነዳት ወዘተ ሲበዛ ቅርብ ነው።” ሲሉ የገለፁት። አያይዘውም “ይነስም ይብዛ ሥራ ያለው ሰው ለፖለቲካው ስጋት መሆኑ ቀርቶ እንደውም አጋዥ ነው የሚሆነው። ምክንያቱም\nበየመንግሥት ተቋማቱ ሲሰራ፣ መንግሥትን ሲያገለግል ነው የሚውለው። ለህብረተሰቡም ቢሆን ይህ ሰው አዎንታዊ አስተዋፅኦ ያደርጋል እንጂ ጎጂ ሊሆን አይችልም። ለዚህም ነው መንግሥታት ሥራ መፍጠሩ ላይ ሊተጉ የሚገባው።” የሺካጎ ዩኒቨርሲቲው ኢኮኖሚስት ራንዳል በርንስ በበኩላቸው ሥራን መፍጠር አጠቃላይ አገራዊ ምርት እንዲጨምር ያደርጋል ይላሉ። እንደ በርንስ አባባል ወጣቶች በሥራ በመጠመዳቸው ብቻ ከሁከትና ረብሻ ይርቃሉ። ይህ ደግሞ የአገር ሀብትና ንብረት እንዳይወድም፤ የሰው ልጅ ህይወት እንዳይጠፋ ያደርጋል። ይህም ለአንድ አገር አጠቃላይ ምርት እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉ ምንም ጥርጥር የለውም።አዲስ ዘመን ግንቦት 12/2011ግርማ\nመንግሥቴ", "passage_id": "d7293f8c3de5a340ee31dd02b73919df" }, { "passage": "ልክ ወደ ምድር በፍጥነት ማስቆልቆል ሲጀምሩ ካፕቴን ያሬድ ጌታቸው በአየር ላይ ለመንሳፈፍ ሙከራ አደረገ። ነገር ግን ካፕቴን ያሬድ ይህንን በሚያደርግበት ሰዓት ኤምካስ የተባለውና አውሮፕላኑን በከፍተኛ ሁኔታ ወደላይ እንዳይወጣ ወይም ወደታች እንዳያሽቆለቁል ለመቆጣጠር ተብሎ የተሰራው ሥርዓት ይህንን ከማድረግ ገታው።\n\nአውሮፕላኑም ወደታች ማሽቆልቆሉን ቀጠለ።\n\n• አደጋው የደረሰበት ቦይንግ 737 የገጠመው ምን ነበር ? \n\nበዚህ ሁሉ ጭንቀት ካፕቴን ያሬድና ረዳቱ አህመድኑር ሞሃመድ መፍትሄ ለማግኘት መታገላቸውን አላቆሙም ነበር። በዚህ ጊዜ አውሮፕላኑ ሙሉ በሙሉ እራሱን በራሱ እያበረረ ነበር።\n\nካፕቴን ያሬድና ረዳቱ የበረራ ቁጥጥሩን በእነሱ እጅ ለማድረግ ከባድ አካላዊ ትግል ማድረግ ነበረባቸው። ሁለቱም የሚችሉትን ያህል ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀረ። \n\nሁሉም ነገር ከቁጥጥር ውጪ ሲሆን ግን አውሮፕላኑ ለበረራ በተነሳ በስድስት ደቂቃዎች ውስጥ በሰዓት 500 ሜትር እየተምዘገዘገ ወደ ምድር ተወረወረ።\n\n149 መንገደኞችንና 8 የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረው ET 302 ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ሲከሰከስ የ35 ሃገራት ዜግነት ያላቸው ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።\n\nከእነዚህ መካከል 32 ኬንያዊያን፣ 18 ካናዳዊያን፣ 18 ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፕሮቶኮል ሻሀድ አብዲሻኩርን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሰራተኞች ይገኙበታል። \n\n• ሁለቱን የአውሮፕላን አደጋዎች የሚያመሳስላቸው ነገር አለ \n\nከአደጋው አምስት ወራት በፊት በኢንዶኔዢያው አውሮፕላን ላይ የደረሰውን አደጋ ለማወቅ በተደረገው የምስለ በረራ ሙከራ ላይ እንደተደረሰበት አውሮፕላኑ ቁልቁል በአፍንጫው ባህር ላይ ሊከሰከስ መሆኑን ያወቁት ከ40 ሰከንዶች ያነሰ ጊዜ ሲቀራቸው መሆኑን ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል።\n\nየኢንዶኔዢያው አውሮፕላን እ.ኤ.አ ኦክቶበር 26 ድረስ ብቻ ስድስት ያህል ችግሮች ገጥመውት ነበር። እነዚህ የገጠሙት ችግሮች በአየር ላይ እያለ ያለውን ፍጥነትና የከፍታ መረጃውን ያካትታሉ።\n\nአውሮፕላኑ ከክንፎቹ እና በአየር ፍሰቱ መካከል ያለውን አቅጣጫ የሚለካውም ችግር ገጥሞት ነበር። አደጋው ከመድረሱ በፊት በነበረው በረራ አብራሪው አስቸጋሪ ሁኔታ ገጥሞት እንደነበር የሚያሳይ ምልክት ልኳል።\n\nየኢንዶኔዢያ አውሮፕላን የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት እንደሚያሳየው አውሮፕላኑ አፍንጫው የመደፈቅ ሁኔታ ሲገጥመው የማስጠንቀቂያ መልዕክት የሚያሳው መሳሪያ በበረራው ጊዜ በሙሉ በርቶ ነበር።\n\nበአደጋውም 198 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።\n\nየአውሮፕላኖቹን ወደ ላይ የመውጣትና የመውረድ ፍጥነት ንባብ እንደሚያመለክተው ሁለቱም አውሮፕላኖች ከፍና ዝቅ እያሉ እንደነበሩና አብራሪዎቹም ይህንን በመቆጣጠር አውሮፕላኖቹ ከፍ ብለው እንዲበሩ ጥረት ሲያደርጉ ነበር።\n\nየኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላኑ ዋና አብራሪ ያሬድ ጌታቸው ችሎታን በተመለከተ አብራሪው ከ8 ሺህ ሰዓታት በላይ የማብረር ልምድ እንዳለው በመጥቀስ \"የሚያስመሰግን ብቃት\" እንዳለው መስክሮለታል።\n\nአደጋው በደረሰበት ዕለትም አብራሪው ያሬድ ጌታቸው ችግር እንደገጠመውና ተመልሶ ለማረፍ ለበረራ ተቆጣጣሪዎች መልዕክት አስተላልፎ ነበር።\n\nከኢትዮጵያ፣ ከአሜሪካ፣ ከፈረንሳይ እና ከአውሮፓ የአየር ትራንስፖርት ባለስልጣን አጣሪ ባለሙያዎች በተሳተፉበት ምርመራ የመጀመሪያ ዙር ውጤት አውሮፕላኑ ለበራ ሲነሳ በትክክለኛ መስመር ለመብረር በሚያስችለው ሁኔታ እንደነበር የገለጸ ሲሆን አብራሪዎቹም አውሮፕላኑን ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለውን ቅደም ተከተል ተግባራዊ ማደረጋቸውን አረጋግጧል።\n\nበአውሮፓውያኑ 2015 ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ለመጀመሪያ ጊዜ... ", "passage_id": "52c02120089dd9eaf2bb39f174a7770f" }, { "passage": "12 ሺ ኪሎ ሜትር ርቀት ያለው ይህ በረራን ለማጠናቀቅም ስድስት ሳምንት ይፈጅባቸዋል ተብሏል። \n\nአራት መቀመጫ ያላት ይህች አውሮፕላን ከተለያየ ስፍራ በተውጣጡ 20 ተማሪዎች ነው የተገጣጠመችው።\n\n•\"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም\" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ \n\n•\"ለአውሮፕላኑ መከስከስ ፓይለቶች ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም\" አቶ ተወልደ ገብረማርያም \n\n\"የዚህ ፕሮጀክት ዋናው አላማ አዕምሯችንን ይቻላል ብለን ካሳመንነው እንደሚቻል ለአፍሪካዊያን ለማሳየት ነው\" በማለት የ17 ዓመቷ ፓይለት ሜጋን ዌርነር ትናገራለች። \n\nታዳጊዎቹ አውሮፕላኗን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሦስት ሳምንታት የፈጀባቸው ሲሆን፤ የውስጥ አካሏን ከደቡብ አፍሪካ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ በመግዛት እንዲሁም በሺህዎች የሚቆጠሩ የውስጥ አካሏን መገጣጠም ችለዋል። \n\n•\"አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ\" የረዳት አብራሪው ጓደኛ \n\n\"አውሮፕሏን ሳያት ማመን አልቻልኩም። በጣም ነው የኮራሁት፤ አውሮፕሏኗን ሳያት ልጄን ነው የምትመስለኝ። በጣም ነው የምወዳት\" በማለት ከጓተንግ ግዛት የመጣችው የ15 ዓመቷ ኪያሞግትስዌ ሲመላ ገልፃለች።\n\nአክላም \"ደስ በሚል ሁኔታ ነው አውሮፕላኗ የምትበረው፤ ዕይታው ልብን የሚሰርቅ\" በማለት ከጆሃንስበርግ ኬፕታውን ከበረሩ በኋላ ተናግራለች። \n\nየአስራ አምስት ዓመቷ አውሮፕላን አብራሪ ይህ ሥራቸው ሌሎችንም እንደሚያነቃቃ ተስፋ አድርጋለች። \"በመጀመሪያ የአካባቢው ማህበረሰብ በጣም ደንግጦ ነበር፤ አውሮፕላን ገጣጥመን ከኬፕታውን ካይሮ ልንበር ነው የሚለውን ዜና ማመን ከብዷቸው ነበር\" የምትለው ታዳጊዋ ውጤቱን ካዩ በኋላ ግን ኩራት እንደተሰማቸው ተናግራለች። \n\nይህንን ፕሮጀክት የጀመረችው የ17 ዓመቷ ሜጋን ስትሆን አንድ ሺ የሚሆኑ ተማሪዎች ፍላጎታቸውን ቢያሳዩም ባደረጉት ማጣራት20 ተማሪዎች ተመርጠዋል። \n\nየአብራሪነት ፍቃድ ካገኙት ስድስቱ ታዳጊዎች አንዷ ሜጋን ስትሆን፤ ግራጫ ቀለም ያላትንና በስፖንሰሮች አርማ የደመቀችውን አውሮፕላንን የማብረር ኃላፊነቱ በስድስቱም ትከሻ ላይ ወድቋል።\n\n ከየቀኑ ትምህርት በተጨማሪ የአብራሪነት ስልጠናዋን የወሰደችው ሜጋን \"የአብራሪነት ፍቃድ ማለት ዲግሪ ማግኘት ማለት ነው\" ትላለች። \n\nየአውሮፕላን አብራሪ አባቷ ደስ ዌርነር አራት ሰዎችን የሚይዝ አውሮፕላን ለመገጣጠም ሦስት ሺ ሰዓታት እንደሚወስድና ለ20 ታዳጊዎችም ሲከፋፈል ሦስት ሳምንታትን እንደሚፈጅ ሞያዊ አስተያየቱን ሰጥቷል።\n\n አንዳንድ የአውሮፕላኑ ክፍሎችና ሞተሩ በሰለጠኑ ሰዎች የተገጠሙ ሲሆን አጠቃላይ አውሮፕላኑ የተገጣጠመው በታዳጊዎቹ ነው።\n\nታዳጊዎቹ በናሚቢያ ካረፉ በኋላ የመጨረሻ መዳረሻቸው ከሆነችው ግብፅ ከመድረሳቸው በፊት በዚምባብዌ፣ ማላዊ፣ ታንዛንያ፣ ኬንያ፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ እንደሚያርፉ ተዘግቧል። \n\n ", "passage_id": "7a673361ba4d71b2ab4d6591e4dae0eb" }, { "passage": "• በንቅለ ተከላ ዕይታው የተመለሰለት ኢትዮጵያዊ ታዳጊ\n\n• ዓይናሞችን ዓይነ ስውር የሚያደርገው እራት\n\nበአደጋው ሕይወቱ ያለፈው ድረስ ሁናቸው በብሔራዊ ዐይነ ሥውራን ማህበር ሥር በሚተዳደረው የወላይታ ዐይነ ሥውራን ትምህርት ቤት ትምህርቱን ተከታትሏል። በዘንድሮ ዓመትም በኮተቤ ሜትሮ ፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በመምህራን ማሰልጠኛ ፕሮግራም በዲፕሎማ ተመርቋል።\n\nባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ ከሌሎች ተመራቂዎች ጋር ሥልጠና ወስደው የሥራ ቦታ ለመመደብ እጣ ይወጣላቸዋል። እጣው ሲወጣም ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ይደርሰዋል። \n\nየተመደበበት ክፍለ ከተማ ከሚኖርበት አቃቂ ክፍለ ከተማ ስለሚርቅ ወደተመደበበት ክፍለ ከተማ ሄዶ እንዲቀይሩት ጥያቄ ያቀርባል። እዚያም አቃቂ ክፍለ ከተማን እንዲጠይቅ ስለነገሩት ወደ ክፍለ ከተማው ያቀናል። \n\nጥያቄውን ለማቅረብ ወዳቀናበት አቃቂ ክፍለ ከተማ 7ኛ ፎቅ ደርሶ ወደ ታች ለመውረድ የአሳንሰሩን ቁልፍ ይጫነዋል። ተከፈተለት። አሳንሰሩ ግን ወለል አልነበረውም፤ 21 ሜትር በሚገመተው የአሳንሰር ጉድጓድ ውስጥ ተምዘግዝጎ ወድቆ ይህንን ዓለም ተሰናበተ።\n\nአቶ ገብሬ እንደሚሉት እስካሁን ለማህበሩ ከደረሱት የሞትና የአካል ጉዳት ሪፖርቶች በአሳንሰር ምክንያት የሞት አደጋ ሲያጋጥም ይህ የመጀመሪያው ነው። \n\n\"አሁን የተፈጠረው አደጋ እንኳንስ ለዐይነ ሥውር ለዐይናማም ቢሆን እጅግ አደገኛ ነው\" የሚሉት አቶ ገብሬ በኮንስትራክሽን ሕግ መሠረት በ2001 ዓ.ም በወጣ የህንፃ ኮድ ላይ ያለውን ደንብና መመሪያ ያጣቅሳሉ። \n\nበመመሪያው ላይ አሳንሰሮች ከውጭም ሆነ ከውስጥ የብሬል ፅሁፍ እንዲኖራቸው እንዲሁም ድምፅ እንዲኖራቸው ይደነግጋል፤ ነገርግን ሃገር ውስጥ የሚገጣጠሙ አሳንሰሮች ይህንን የሚያሟሉ አይደሉም ሲሉ ይኮንናሉ። \n\n\"ከውጭ የሚመጡት አሳንሰሮች ብሬል ተገጥሞላቸው ይመጣሉ፤ ድምፅም አላቸው፤ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ድምፁን ስለማይከፍቱት አይሰሩም\" ይላሉ። በትክክል አገልግሎት የሚሰጡትም በጣም ጥቂቶች እንደሆኑ የታዘቡትን አጋርተውናል።\n\n• \"አካል ጉዳተኛ መሆኔ ጥሩ ደረጃ እንድደርስ አድርጎኛል\"\n\n• የምልክት ቋንቋ በብዛት የሚነገርባት መንደር \n\nምንም እንኳን እርሳቸው ያለ ረዳት ብዙ ጊዜ አሳንሰር ውስጥ የመግባት ልምድ ባይኖራቸውም የገጠማቸው አለ። \n\n\"አሳንሰር ውስጥ ገብቼ የነካኋቸው አብዛኞቹ ቁልፎች አይሰሩም ነበር። የሚሰሩት 9ኛ ፎቅና ምድር ላይ ያለው ብቻ ነበር የሚሰራው፤ እኔ መሄድ የፈለኩት ደግሞ 5ኛ ፎቅ፤ ከላይ ታች ስል በኋላ ላይ በሰዎች እርዳታ ወጣሁ\" ሲሉ ሲንገላቱ የዋሉበትን ቀን ያስታውሳሉ።\n\nከዚህ ቀደምም ዐይነ ሥውራን በመንገድ መቆፋፈር፣ በመኪና አደጋ፣ ከድልድይና ፎቅ ላይ በመውደቅ አደጋ ለሞትና አካል ጉዳት መዳረጋቸውን ይናገራሉ።\n\nበአንድ ወቅት አንድ ዐይነ ስውር የውጭው በረንዳ [ከለላ] ከሌለው የትምህርት ቤት ህንፃ ወድቆ ከባድ አካል ጉዳት እንደደረሰበት ያነሳሉ።\n\nከድልድይ ላይም እንዲሁ ከለላ ባለመኖሩ የአንድ አባት ሕይወት ሲያልፍ በቅርብ ጊዜም የኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪ ውሃ ቀድታ ስትመለስ ከድልድይ ላይ ወድቃ ሕይወቷ እንዳለፈ ይናገራሉ።\n\n\"ቁጥራችን ትንሽ ስለሆነ ነው መሰል ትዝ አንላቸውም\" የሚሉት አቶ ገብሬ አካል ጉዳትን በተመለከተ 'ደረጃው ይለያያል እንጂ ያልተነካ አለ' ለማለት እንደሚቸገሩ ይናገራሉ።\n\nከአባላቶቻቸው በጥቆማ ያገኙትንና ሰኞ እለት ያጋጠመው ይህን አደጋ በተመለከተ ማህበሩ የተለያዩ መረጃዎች እያሰባሰበና የሚመለከተውን አካል ለማነጋገር ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል።\n\nአደጋው በርካቶችን አስቆጥቷል። የህግ ባለሙያዋና የአካል ጉዳተኞች መብት ተሟጋቿ ሎሬት የትነበርሽ ንጉሴም በፌስቡክ እንዲሁም... ", "passage_id": "10456e66ad9be8bfdfb59dab8418d3b1" }, { "passage": " አንድ ሥራ አጥቶ ረጅም ጊዜ የቆየ ሰው ነው አሉ። ሁልጊዜ በራሱ ይማረራል፤ ተምሬ ሥራ አጣሁ።ደህና ነጥብ ኖሮኝ ለሥራ አልታደልኩም ብሎ ብቻ ይማረራልቨ መፈጠሩንና ፈጣሪውን እንዲሁ እያነሳ ይበሳጫል፤ ይበሰጫጫል። አንድ ቀን አሁንም ሥራ ፍለጋ ዘወርወር ሲል በአንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በእሱ የትምህርት መስክ አረጋውያንን ለመንከባከብ የሚል ማስታወቂያ ወጥቶ ይመለከታል። ሄዶም ይመዘገብና ለፈተና ቀነ ቀጠሮ ተቆርጦለት ይመለሳል። ፈተናው በሚሰጥበት ማለዳ ላይ አንድ አዛውንት ወደ ቢሮው መሻገሪያ አካባቢ ቆም ብለው ሰዎች እንዲያሻግሯቸው ይጠይቃሉ። ብዙም አላስተዋላቸውም። በዕለቱ ታዲያ በጠዋት ሮጥ ሮጥ እያለ መንገድ ሊያቋርጥ ሲል አዛውንቱ ያገኙት እና ልጄ እባክህ አሻግረኝ ይሉታል፤ እሱ ግን እሳቸውን ሳሻግር (ፈጠን ብለው ስለማይራመዱ) ሰዓት ያልፍብኛል ብሎ ስላሰበ መልስ ሳይሰጥ ያልፋቸዋል። እሳቸውም አዝነው በቆሙበት ሆነው የሌላ ሰው መምጣት ይጠባበቁ ጀመር። ሌላው ወጣትም እንዲሁ ፈጠን ፈጠን ብሎ ይራመዳል ደግሞ የእጅ ሰዓቱን መለስ አድርጎ ይመለከታል ከሩቅ አስተዋሉት። እኔን ለመጎተት ሰዓትም የለውም መሰለኝ ብለው እያሰቡ ደግሞ ተስፋ ባለመቁረጥ አጠገባቸው ሲደርስ “እባክህ ልጄ” ሲሉት ባልሰማ አለፋቸው። አሁንም አዝነው ሦስተኛውን መጪ መጠባበቅ ቀጠሉ ሦስተኛው ሰውም በተመሳሳይ እየተራመደ ነው፤ አጠገባቸው ደርሶ “ልጄ” ሲሉት እርምጃውን ገታ አድርጎ “አቤት” ብሎ ማድመጡን ቀጠለ። “እባክህን አሻግረኝ” አሉት “እሺ አባቴ ብሎ እጃቸውን ይዞ አሻገራቸው”። የፈተናው ሰዓት ደርሶ ለተፈታኞች የተሰጣቸው ፈተና የነበረው እኛን አዛውንት ማሻገር ነበር እናም የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ወድቀው ሦስተኛው ሰው ማለፉ ተነገራቸው። ምክንያቱም የሚቀጠሩት አዛውንት ሊንከባከቡ ነው፤ ለእነሱ ክብር መስጠትና መንከባከብ የሚችል ፍላጎቱም ያለው ነው የሚያስፈልገው። ይሄንን በየትኛውም ቦታ ላይ ያልተወጣ ሰው እዛም ተቀጥሮ ቢገባ ያለው የውስጥ ባህሪ የታዛዥነት፣ የተንከባካቢነት እና የአዛኝነት ካልሆነ የሚሰው ሥራ ለደመወዝ እንጂ በፍላጎት አይሆንም። ይሄ ደግሞ በሥራ ላይ የሥራ ሰዓት ከመቁጠር ያለፈ ውጤት አያመጣም። ለአዳዲስ ነገርም አያነሳሳም። ሥራን መስራት ከራሥም ኃላፊነት በተጨማሪ ቅንነትን፣ ተነሳሽነትን … ይጠይቃል። ቅን ሰው ከሥራው በላይ ይሰራል። የእኔ ሥራ ይሄ አይደለም ያ ነው እያለ የሚኮፈስ ከሆነ ደግሞ እንኳን የተሻለ ያልተጠበቀ ሥራ ቀርቶ የራሱንም አድምቶ ሊወጣ አይችልም። የጠቅላይ ሚኒስትሩን “እድሳት ከቢሮ እስከ ሀገር” የሚለውን ዶክመንታሪ ፊልም አየሁት። የጠቅላዩን ሀሳበ ሰፊነት እና ትጋት አደነቅሁ። ለወሬ እና ለወሬኛ እንደሳቸው ጆሮውን የደፈነ ብቻ ነው ብዙ አስቦ ብዙ መራመድ የሚችለው። ሌሎችም ይሄንኑ እያደረጉ እንደሆነም አምናለሁ። ይሰራሉ ይተቻሉ። ከተሳሳቱ ይታረማሉ። ከወደፊት ትልማቸው ግን ንቅንቅ አይሉም። እኛም “ትልቅ ነገር እናልማለን፣ ትልቅ ነገር እናስባለን፣ ነገር ግን ከትንሽ እንጀምራለን፤ ያንን በፍጥነት እናሳካለን፣ ወደፈለግንበት እንደርሳለን።” ያሉትን ይዘን መስራት ከጀመርን ከምናስበውም በላይ ውጤት እናመጣለን። ነገር ግን ሥራ ሲሰራ እንቅፋት እንደማይጠፋ ይታመናል፤ እንቅፋት ያደነቃቅፋል። ነገር ግን እንቅፋቱ የከፋ አደጋ እንዳያደርስ መንገድ መንገዱን እያዩ መራመድ ይጠቅማል። የሥራ ያለህ ብሎ ሥራ የሚያማርጥ፣ ሥራ ለመቀጠር ብቻ የሚያስብ ባሰበው መንገድ መቀጠል እንደማይችል ቆም ብሎ ከሌሎች በመማር መንገዱን ማስተካከል ይኖርበታል። ነገር ግን ለሚሰራ መንገድ የጠረገ፣ ያስተካከለ ሥራ ሰራ ነው የሚባለው። መንገዱን አመቻችቶ በዛው መንገድ መቀጠሉ አይቀርምና። አንድ ጸሐፊ “አርፈህ ሥራህን ሥራ” የሚል ጽሑፍ ጽፎ አነበብኩት። እኔም እውነት እኮ ነው ለምን አርፈን ሁላችንም በየተሰማራንበት መስክ ሥራችንን አንሰራም? ለምን ራሳችንን በሥራ አናሸንፍም? ለምን ከመስራት ይልቅ በማውራት እንዲጨበጨብልን እንፈልጋለን? ለምንስ ሥራውን የሚሰራውን ሰው ወይም አካል ስንንቅ ስናንቋሽሽ፣ ስንዘነጥል ስንዘነጣጥል፤ ስንተች እንውላለን? ለምን ለሚሰራ ሰው እንቅፋት ሆነን ለማደናቀፍ እንሞክራለን? ግን ለምን…ለምን… ስል ማሰብ ቀጠልኩ። በኋላ መልስም ባይሆንም እንደመልስ ያሰብኩት\n“ራሳችን ሥራ ስለማንሰራ”\nየሚል ነበር። አንሰራም፤ የተሰራ ሥራ ደግሞ እናጣጥላላለን፣ እናሳንሳለን… ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው እንደሚባለው ማለቴ ነው። ከተሳሳትኩ እንደለመድኩት ጊዜው የይቅርታ ነው በሚለው እሳቤ ይቅር በሉኝ። ግን ለዚህ የሚሆን ብዙ ብዙ ነገር ማንሳት ይቻላል። ሰርቶ ሳይሆን አውርቶ አደሮች መኖራቸውን፤ የሚሰራን አመስግነው ሳይሆን አጥላልተው፤ አጠልሽተው ሕዝብን ለማሳመን የሚጥሩ፤ ሕዝብን ለክፉ ዓላማ ለማነሳሳት ወይ ደግሞ የሰውን ንፁህ ልቦና ለማቆሸሽ የሚሰሩ መኖራቸውን አትዘንጉት። ምን ለማትረፍ ካላችሁ መልሱ ብዙ ነው። ውበት እንደተመልካቹ እንዲሉ። ሁሉም ከራሱ የግል ጥቅም፣ ፖለቲካ፣ ሃይማኖት፣ ዘር፣… ሊነሳ ይችላል። አንዳንዱ ደግሞ ምንም ነገሩ ሳይገባው ሌላው ስላለ ብቻ ይሆናል ለእንቅፋቱ ተባባሪ ለመሆን የሚነሳው። ለዚህ አባባል ምን ማስረጃ አለ የምትሉ ከሆነ ያው በየድረገጹ የምናየው የሚሰነዘረው ሀሳብ ብቻ አንዱና በቂ ምስክር አይደል!። የሚሰራን፣ የሚለፋን፣ የሚጥርን አካል ስም ለማጉደፍ የሚደረገው ሩጫ ሥራ ሰሪዎቹ ከለፉበት ሥራ በላይ በጥበብ የሚደረግ ነው። ግን እኮ ቀላል ነገር አለ፤ እከሌ እከሌት ከሰሯቸው በላይ የሚበልጥ የሚታይ ነገር ሰርቶ የሁሉንም ክብር ወይም ዝና መሰብሰብ ይቻል የለ እንዴ? ይሄ ካለ ታዲያ የግለሰቦችን የተቋማትን ልፋት ሜዳ በሚያስቀር መልኩ ለመተቸት መነሳቱ ምን ያስፈልጋል? ይሄን ማለቴ ግን ምንም ነገር የሰራም ሆነ ያልሰራ አይተቸም ከሚል ሀሳብ ተነስቼ እንዳልሆነ ይያዝልኝ። ትችት አስፈላጊ ነው። እንዲያውም እኮ በእኛ ባህል “የጎረቤት ምቀኛ አታሳጣኝ” የሚባል አባባል አለ። ይሄ ከክፋት የመነጨ አይደለም። ጎረቤት የዋህ፣ አዛኝና ለጋስ… ከሆነ እኔ እራሴን አልችልም። ዕቃም ለመዋስ ከዚያ ቤት ስል፤ ምግብ እነሱ ሰርተዋል ስል እኔ ቤት አልይዝም። ለማደግና ለመሻሻል አልጣጣርም። ስለዚህ በመንፈሳዊ ቅናት በመነሳሳት ሰርቼ ለመብለጥ ለመለወጥ እንዲህ ያለው ጎረቤት ያስፈልጋል ከሚል እሳቤ ይመስለኛል። ደግሞም ነው እንጂ ሰው በራሱ ላይ ጠላት ስጠኝ የሚል ጸሎት አይጸልይም። ትችትም ለሚሰራ ሰው እንዲያውም ያልታየውን እንዲያይ ይበልጥ ያበረታታዋል። ይበልጥ እንዲሰራም ያነሳሳዋል። ይሄ ክፋት ሳይሆን ጥቅም ነው። ነገር ግን ችግሩ የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ለሕዝብና ለሀገር ምንም ያላደረገ ሁሉ እየተነሳ የተሰራን ሥራ፤ የተደረገ ጥረትን ፤ የነገውን ዕቅድ እና ተስፋ አፈር ከድሜ ሲደበላልቀው ማየትም ሆነ መስማት ግን ባይቆጭ ያንገበግባል እንደሚባለው ይሆናል። ይህን ሳነሳ አንድ የረሳሁት ነገር መኖሩ ታወሰኝ። ክፋት አመንጪ የክፋት መርዙን ቢረጭ ብቻውን የትም ሊያደርሰው አይችልም። የክፋትን ሀሳብ ሸማቹ ነው ሌላኛው ክፉ ማለቴ ነው። ጥሬውን ከብስል፣ ደቃቁን ከአንኳር፣ ጣፋጩን ከመራራው መለያ፣ ማገናዘቢያ፣ ማመዛዘኛ የለም እንዴ ብዬ ብጠይቅ ደስ ባለኝ። የሰጪ ብቻ ሳይሆን የተቀባይም ችግር አለ ማለቱ በደፈናው ሳይበቃን አይቀርም። እና የማስተዋል ሚዛን ያስፈልገናል።” አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ አስቀድሞ ነበር መጥኖ መደቆስ” የሚባለው እንዳይሆን ማለቴ ነው። ሰላም!አዲስ ዘመን  መስከረም 18/2012 አልማዝ አያሌው", "passage_id": "8f5e6abcb5d389294f167e33f43ba2fb" } ]
0417a79d8150727f74918efc1e7d288c
e0b83148b34ec3f310e19d7f44621ebd
ተዝናኖታዊ ንባብ ለተሟላ ሰብዕና
የሰው ልጅ የጋራ ባህርያትና ተግባራት ከሆኑት መካከል አንዱ መዝናናት ሲሆን የጋራ ያልሆነው ደግሞ የሚያዝናናው ነገር፣ የሚዝናናበት ፍሬ ነገርና ይዘት ጉዳይና ለዚህም የሚሄድበት ርቀት ነው። ያንዱ መዝናኛ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ (ዋና፣ ብስክሌት መንዳት . . .) ሲሆን ለሌላው ጉብኝት ሊሆን ይችላል። ለአንዱ ምግብ ማብሰል ሲሆን ለሌላው ልብስ ማጠብ፤ ለአንዱ ሰብሰብ ብሎ ማውራት (ካፌም ቢሆን) ሲሆን ለሌላው ሽር ሽር ቢሆን አይገርምም። አሁን አሁን ደግሞ ይህ ቀረህ በማይባል ደረጃ ጥፋት እያደረሰ ባለው ማህበራዊ ሚዲያ (በተለይ ፌስቡክ) ሱስ የተጠመዱ ሰዎች ጉዳይ እያሳሰበ ከመሆኑም በላይ ለተከታዮቹ መዝናኛቸው ሁሉ እሱ እየሆነ መምጣቱ በየጊዜው በሚወጡ ጥናቶች እየገለፁ ነው።ቴዎድሮስ ታደሰ “ሰው በወደደው/ባፈቀረው ይገድፋል” እንዳለው፤ ጉዳዩ የግል ምርጫ ሲሆን፤ እዚህ ልንጨዋወት የፈለግነው ግን ምርጫቸው ንባብ/ማንበብ ስለሆነው ተዝናኞት ነው።“ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!!”፤ “ማንበብ ማበብ ነው።” የሚሉትም ሆኑ ሌሎች እንዳሉ ሆነው የንባብን ማዝናናት ሚና ማውሳት ተገቢ ነው። በእርግጥ ከሥነፅሁፍ አላማዎች አንዱ ማዝናናት ነው። ይሁን እንጂ ይህን የተረዱ ቢኖሩ ጥቂቶች ናቸው። ንባብ ባህል በሆነባቸው አገራት አንድ ሰው በአማካይ በቀን ውስጥ 16 በመቶ ያህል ጊዜውን የሚያሳልፈው በንባብ መሆኑን የሚያወሱ በርካታ ጥናቶች ለአደባባይ ከበቁ ሰንብተዋል። የማቀበያ ክሂል የሆነው ንባብ መረጃ ከሚሰበሰብባቸው አበይት ምንጮች አንዱ ሲሆን ዛሬ ዛሬ ከመረጃ አቀባይነቱ በዘለለ አዝናኝነቱ እየተነገረለት፤ መፃህፍትን ለተዝናኖት የሚያነቡ ሰዎች ቁጥርም በእጅጉ እየላቀ ይገኛል።በተለይ በህፃናት በኩል እየተለመደ የመጣውና ወደ ፊትም ባህል ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ተዝናኖታዊ ንባብ በአንዳንድ አገራት ይሁነኝ ተብሎ ጊዜ፣ በጀትና የሰው ሀይል ተመድቦለት ልምዱን የማጎልበት ስራዎች ሲሰሩ ይታያል። ሌሎችም ልምዱን እየወሰዱ ይገኛሉ። ይህን ጉዳዬ ብሉ እየሰራበት ካለው ኦፕን ዩኒቨርሲቲ ድረ-ገፅ “READING FOR PLEASURE” አምድ የበለጠ መረዳት ይቻላል።ተዝናኖታዊ ንባብን ከሌሎች የንባብ አይነቶች ለየት የሚያደርጉት በርካታ ሁኔታዎች ያሉ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ ምንም አይነት ቦታና ጊዜን አለመምረጡ፣ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሊከናወን መቻሉ፣ ቀስ በቀስ የህይወት አካል እየሆነ መሄዱ፣ ወደ ሂሳዊና ምርምራዊ የንባብ ሂደቶች ማደጉ፣ ከማዝናናት በተጨማሪ በተለያዩ ዘርፎች ሰፊ እውቀትን ማስጨበጡ፣ ከበርካታ የመዝናኛ አይነቶች የተሻለ ሆኖ መገኘቱ፣ አለማችንን የበለጠ ለማወቅና ትስስራችንን ማጥበቁ፣ ወጪ ቆጣቢነቱ፣ ለማህበራዊ ህይወትና መስተጋብር መጠናከርና መጎልበት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ፣ ሌሎችን ለመረዳትና ለመግባባት በከፍተኛ ደረጃ መጥቀሙ፣ አንባቢው ስለሙያው የተሻለ እውቀትና ግንዛቤን ማግኘት መቻሉ እና የመሳሰሉት ናቸው። ይሁን እንጂ እንደ አንዳንድ አጥኚዎች ግኝት ደግሞ የተዝናኖት ንባብ አዞታሪ ከሁሉም በላይ የሚያገኘው ጠቀሜታ ቢኖር በተሟላ ደረጃ ጤነኛ የመሆኑ ጉዳይ ነው። በጉዳዩ ላይ ያጠኑት እንደሚናገሩት ተዝናኖታዊ ንባብ ለጤና መጠበቅ እጅግ አስፈላጊ ከመሆኑም በላይ ያጋጠመ የጤና እክል እንኳን ቢኖር በመፍትሄነት የማገልገሉ ጉዳይ የተረጋገጠ ነው። አቢጌል ፒኔው “WHAT ARE THE BENEFITS OF READING FOR PLEASURE?” በሚል ርእስ ያቀረቡት ጥናት እንደሚያሳየው ተዝናኖታዊ ንባብ ከጭንቀት ይገላግላል፣ አንድ ሰው ጭንቀት ካለበትም በከፍተኛ ደረጃ ይቀንስለታል፣ በእለት ተእለት ህይወታችን የሚያጋጥሙንን ችግሮች እንድንረሳቸውና በእነሱ ከመብሰልሰል እንድናመልጥ ይረዳናል፤ ደረጃ በደራጃ የበሰሉ የሥነጽሁፍ ስራዎችን ወደ ማንበብና መረዳት እንድንሄድ፣ አምስቱን የስሜት ህዋሳቶቻችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ያደርገናል፣ ትክክለኛ፣ ውስጣዊ ሰላም ያለውና ነፃ ደስተኛነት (inner peace and tranquility)ን ያስገኛል፤ ስለራሳችን – ማንነታችንንና ከየት እንደመጣን በውል እንድንገነዘብ ያደርገናል፤ አንባቢ ማህበረሰብና አንባቢ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል፤ እየተደረገ ያለው ጥረት ካለ ያፋጥናል፤ ሃሳብ መቀበልና ሃሳብ መስጠት ላይ ያሉ እንቅፋቶችን ያስወግዳል፤ ወደ ዳበረ የፅሁፍ/መፃፍ ክሂል እንድናመራ ያደርገናል፤ እውቀትን ያበለፅጋል (ከጠቅላላ እውቀት ጀምሮ)፤ በማንኛውም ዘርፍ ያሸጋግረናል፤ በስራ ቦታ የሆነም እንደሆን በስራ ባልደረቦችም ሆነ አለቆች ዘንድ ተወዳጅ፣ ተደማጭና ተከባሪ ያደርጋል፤ የማስታወስ አቅማችንን ይጨምራል፤ የአእምሮ መነቃቃትን ይፈጥራል፤ ብቸኝነት ጥንቡሳሱን ይዞ ገደል ይገባ ዘንድ ያግዛል፤ የተንታኝነት፣ መርማሪነት፣ ሃያሲነት ወዘተ ፍላጎት፣ አቅምና ብቃት እንዲኖረን ያደርጋል፤ ወቅታዊ ያደርጋል፤ በአንድ ጉዳይ ላይ አተኩረን የመስራት ችሎታችንን ያዳብርልናል፤ በራስ መተማመን እንደልብ ነው። እንደ ተመራማሪዋ ግኝት ተዝናኖታዊ ንባብ ሌሎችም በርካታ ፋይዳዎች ያሉት ሲሆን ባጭሩ ሱስ ነው። ከትምህርት ቤት ውጪ ለተዝናኖት ሲሉ መፃህፍትን የሚያነቡ የ16 አመት ልጆች በአብዛኛው የወደፊት ሙያዊ የመሪነት መንበራቸውን ከወዲሁ የሚያረጋግጡ ናቸው። (16-year-olds who choose to read books for pleasure outside of school are more likely to secure managerial or professional jobs in later life.) የሚለውን የእንግሊዝ አገር ጥናት ስንመለከት ደግሞ የተዝናኖት ንባብን የጠቀሜታ ጥጉ የት ድረስ እንደሆነ ጥርት አድርገን እንገነዘባለን።የአሜሪካው “The U.S. National Reading Panel” እንደሚለን ከሆነ ጥሩ አንባቢያን በተዝናኖት ንባብ ውስጥ ያለማቋረጥ እንደሚሳተፉ የሚያሳዩ በርካታ ጥናቶች አሉ። በጥናቶቹም 80 በመቶዎቹም መዝናኛቸው ንባብ እንደሆነም ተመልክቷል።እዚህ ላይ በተደጋጋሚ የሚነሳውና እንደ የተዝናኖት ንባብ ተግዳሮት ተደርጎ የሚወሰደው የአገልግሎትና አቅርቦት ጉዳይ ነው። ተዝናኖታዊ ንባብ የመንግስታትን፣ ተቋማትን፣ ባለሀብቶችን እና የሌሎችን ቀና ትብብር ሁሉ ይፈልጋል። ለምን ቢሉ በተለያዩ መንገዶች በተለያዩ ስፍራዎች የሚነበቡ መፃህፍት ይገኙ ዘንድ የግድ ነውና ነው። ቤተመፃህፍት በብዛት ያስፈልጋሉ፤ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አይነት አሰራር – የሚነበቡ መፃህፍት አቅርቦት ያስፈልጋል፤ በየሆቴሎች፣ ካፌዎች. . . ሁሉ ንባብን የሚያበረታቱ፣ ስለንባብ የቆሙ ጉዳዮች ሊኖሩ ይገባል። የተዝናኖታዊ ንባብ ሱሰኛው በሄደበት ሁሉ የሚያነበው ነገር የሚፈልግ በመሆኑ እጥረትን አይፈልግም። ለዚህም ነው እነ ፊንላንድ (“The Most Literary Nation in The World” የተባለላት)፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝን የመሳሰሉ አገራት በተዝናኖታዊ ንባብ በኩል ምንም አይነት ክፍተት እንዳይፈጠር እየሰሩ የሚገኙት። ትኩረት ለተዝናኖታዊ ንባብ!አዲስ ዘመን ኅዳር 1 / 2012  ግርማ መንግሥቴ
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=22315
[ { "passage": "በትምህርት ቤት ከሚሰጡ የትምህርት ዘርፎች ውስጥ አንደኛውና ዋናው በክፍል ውስጥ የሚሰጠው መደበኛ ትምህርት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከክፍል ውጪ በክበባት በመደራጀት በተጓዳኝ የሚሰጠው ትምህርት ነው። ከጉዳዩ ጋር\nበተያያዘ\nበአገራችን\nትምህርት\nቤቶች\nያለውን\nወቅታዊ\nሁኔታ\nለመረዳት\nበአዲስ\nአበባ\nበተወሰኑ\nትምህርት\nቤቶች\nተዘዋውረን\nከሚመለከታቸውም\nአካላት\nጋር\nቆይታ\nአድርገናል።\nበዳግማዊ ምኒልክ\nአንደኛና\nመለስተኛ\nሁለተኛ\nደረጃ\nትምህርት\nቤት\nየአደረጃጀትና\nትምህርት\nፕሮግራሞች\nክትትል\nምክትል\nርእሰ\nመምህርት\nወይዘሮ\nቅርስነሽ\nየማነ\nእንደነገሩን\nበትምህርት\nቤቱ\nውስጥ\nየተጓዳኝ\nትምህርት\nእንቅስቃሴና\nየተማሪዎች\nተሳትፎ\nበጥሩ\nሁኔታ\nላይ\nይገኛል።«በተለያዩ ዘርፎች የተጓዳኝ ትምህርት ተግባራት ይከናወናሉ። በአጠቃላይ ዘጠኝ ክበባት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል በጤና፣ በኪነጥበብና በበጎ አድራጎት ክበባት ከፍተኛ የመምህራንና ተማሪዎች ተሳትፎ እንዳለ ይናገራሉ። በመመሪያው\nመሠረት\nእያንዳንዱ\nትምህርት\nቤት አስራ ሁለት ክበባት ሊኖሩት ይገባል የሚሉት ምክትል ርእሰ መምህሯ ሆኖም ሦስቱ ማለትም የትራፊክ ደህንነትና ማኔጅመንት፣ የትራንስፖርትና የሰብአዊ መብት ክበቦች ለተማሪዎች ሥልጠና ባለመስጠታቸው እስካሁን ተግባራዊ አለመሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ወይዘሮ ቅርስነሽ እንደሚናገሩት ከሆነ በትምህርት ቤቱ እየተከናወኑ የሚገኙ የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴዎች የተማሪዎችን የተደበቁ እውነተኛ ፍላጎቶችና ችሎታዎች የሚገለጡበት ሲሆን ሲሳተፉ የነበሩ ተማሪዎችም ለፍሬ በቅተዋል። ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት በተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ የሚሳተፉ፣ የሙዚቃ አልበም ያወጡና ሌሎችም አሉ። አሁን ያሉትም በሙሉ ፈቃደኝነትና በከፍተኛ ስሜት ነው የሚሳተፉት። በተለያየ የሙያ ዘርፍ ስኬታማ ለመሆን አቅደውና አልመው እየተሳተፉ ያሉ ተማሪዎች በርካቶች ናቸው።የልዩ ፍላጎት መምህርትና\nየሥርዓተፆታ ክበብ አስተባባሪ\nወይዘሮ አምሳለ ገብረማርያምም\nተመሳሳይ ሃሳብ አላቸው።\nመምህርቷ እንደሚሉት የተጓዳኝ\nትምህርት ያለው ሚና\nቀላል አይደለም፤ የቀለም\nትምህርቱ አጋዥ ነው።\nየተማሪዎችን ሥነ-ምግባርን\nከማነፅም፣ ግንዛቤን ከማስጨበጥም\nሆነ ችሎታቸውን ከማጎልበት\nአኳያ ከፍተኛ ጠቀሜታ\nአለው። በመሆኑም በትምህርት ቤቶች የሚካሄደው የተጓዳኝ ትምህርት ፕሮግራም በሚገባ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል። ሌላው ያነጋገርነው የ8ኛ ክፍል ተማሪና በኪነጥበብ ክበብ በስእል ዘርፍ እየተሳተፈ የሚገኘውን ተማሪ አዶናይ ፍሰሐን ሲሆን በክበቡ ውስጥ በሙሉ ፍቃደኝነት፣ በከፍተኛ ፍላጎትና ፍቅር እንደሚንቀሳቀስ ነግሮናል። ተማሪ አዶናይ እንደሚናገረው ከሆነ የስእል ፍቅር ከልጅነቱ ጀምሮ በውስጡ የነበረ ሲሆን ይህንን ፍላጎቱንም ወደ ተግባር ለመቀየር ያገኘው ቦታ ቢኖር ይህ የኪነጥበብ ክበብ ነው። በመሆኑም በክበቡ በመሳተፍ በትምህርት ቤቱ ውስጥ የተቀመጡ በርካታ ስእሎች አሉት።«እቤቴ መጥታችሁ ብታዩልኝ ደስ ይለኛል» የሚለውና ችሎታው የአባይ ግድብን እስከመሳል ድረስ መሄዱ በአስተባባሪዎቹ የሚነገርለት ተማሪ አዶናይ በሥራው አስተባባሪዎችና የት/ቤቱ እገዛ እንዳልተለየውም ይናገራል። ሁሉም ተማሪ በተጓዳኝ ክበባት እንደየፍላጎቱ በመግባት ሊሳተፍ እንደሚገባም ይመክራል።አጠቃላይ የመስተዳድሩ ትምህርት\nቢሮን አሠራር፣ ክትትልና\nግምገማን በተመለከተም በአዲስ\nአበባ ትምህርት ቢሮ\nየሥርዓተ-ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ የሥራ ሂደት ተገኝተን አነጋግረናል።የሥራ ሂደቱ ተወካይ አቶ አስራት ሽፈራው ጉዳዩን በተመለከተ እንደነገሩን በአሁኑ ሰዓት በትምህርት ቢሮ ደረጃ የክበባት ማንዋል ተዘጋጅቶና ለሁሉም ትምህርት ቤቶች ታድሎ በእሱ መሠረት እየተሰራ ይገኛል። በአጠቃላይም አስራ ሁለት የተጓዳኝ ትምህርት ክበባት ያሉ ሲሆን ተማሪዎችም በእነዚሁ ክበባት እየተሳተፉ ይገኛሉ።በአሁኑ ሰዓት በርካታ የ«ክበብ ይቋቋምልን» ጥያቄዎች ከየመስሪያ ቤቶች ይመጣሉ የሚሉት አቶ አስራት እነዚህን ሁሉ ለማስተናገድ አስቸጋሪ ቢሆንም በተቻለን አቅም ካሉት ክበባት ወደሚቀርባቸው በመመደብ መስተንግዶ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ይናገራሉ።አቶ አስራት ሽፈራው እንደሚሉት ክበባት የትምህርቱ አጋዥ ከመሆናቸውም በላይ የተማሪዎችን ተሰጥኦ ለማውጣት ከፍተኛ ጠቀሜታ አላቸው። አቶ አስራትን ሁሉም ክበባት በትምህርት ቤቶች ተቋቁመው ተማሪዎች እየሳተፉ ናቸው ወይ በሚል ላነሳንላቸው ጥያቄም «ይህን ያላደረጉ እንደሚኖሩ ይጠበቃል፤ ሆኖም ግን በቅርቡ ክትትል በማድረግ ያሉ ክፍተቶች ተለይተው የማስተካል ሥራው ይሰራል።» ሲሉ ሃሳባቸውን አጋርተውናል።አዲስ ዘመን ህዳር 15/2012ግርማ መንግስቴ", "passage_id": "5a9c3cbb66029991f8639aba21adc3a1" }, { "passage": "በመዲናችን\nአዲስ አበባ ተመሳስሎ ያልተሰራ፣ከጎኑ ማታለያ ያልተቀመጠለት፣አለያም ባዕድ ነገር ያልተቀየጠበት አገልግሎት ማግኘት ላሳር ነው። አሁን አሁንማ ቆመው የሚሄዱት ሰዎችም ተመሳስለው የተሰሩ እየመሰሉኝ መጥተዋል። የሚሸመቱ እቃዎችን ተዋቸው። ከአይን እይታ የዘለሉ ማታለያዎችን ጭምር መጠቀም ተክነውበታል። ምነው በዚህ ደረጃ ለማታለያነት የሚያውሉትን (የሚያስቡበትን) አዕምሮ ህብረተሰቡን ቢጠቅሙበት፣ ቢመረቁበት እና የሚለወጡበት ተግባር ቢፈጽሙ ያሰኛል። የሚገርመው በዘላቂነት የሚጠቅም ነገርን መኮረጅ አለመቻላቸው ነው። እንደ ቴክኖሎጂ አይነት እውቀትን ምነው በኩረጃም ማስፋት በተቻለ። ተጠቅመውበት እልፍ ሲልም ተሸልመውበት መንገስ ይችሉ ነበር። ተፈላጊነታቸውም በገበያ ላይ ይጨምራል፡ ምክንያቱም የሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ በአዲስ መልክ መፍጠር ያልተቻሉ ቴክኖሎጂዎችን ለራስ በሚሆን (በሚጠቅም) መንገድ መኮረጅን ይመክራል። ለካ በነካ እጃቸው ነው ሟች ነፍሳቸውን ይማረውና ‹‹መስረቅ ካልተያዙ ሥራ ነው፣ ከተያዙ ግን ወንጀል ነው›› አሉ ተብለው የሚታሙት። ልብ በሉ ሃሜት ነው። አሁን ላይ በእነሱ የማታለያ ማሽኖች ተፈብርኮ ከእኛ የማየት አቅም በላይ ተሸፍኖ ያልቀረበ ቁስ ያለ አይመስለኝም። ህብረተሰባችን በጫንቃው ተሸክሟቸው የሚኖሩ እልፍ አታላዮች ከጓዳ እስከ አደባባይ ሞልተዋል። ምን ህብረተሰቡ ብቻ መንግስት ጭምር እንጂ ተሸካሚው። ከእለት ጉርስ ፈላጊው እስከ አገር ኢኮኖሚ ሾፋሪው ቱጃር ድረስ ማታለል፣ መዋሸት፣ ማጭበርበር በሙያነት ተመርቀውበታል። ከታች እስከ ላይ ያደግንበትን ወግ፣ ባህልና እምነታችንን አስክዶ ትውልዱን የወረረ አደገኛ ተዛማች በሽታ ሆኗል። የሰው ልጅ በዘመን ዥረት መሃል ሲፈስ በአዎንታም ሆነ በአሉታ ለውጦች ማሳየት ተፈጥሯዊ ግዴታ ነው። የሚጠቅሙትን\nበእጁ ጨብጦ የማይጠቅሙትን ከመዳፉ እያራገፈ ሰዋዊ ባህሪን ተላብሶ መገስገስ የእሱ ፋንታ ነው። አሁን ላይ አውሬነት ባህሪያችን ይመራን ይዟል። ሰሞኑን አንዲት ጎረቤቴ ያጫወተችኝን ልንገራችሁ፤ መቼም ሚስጥር ብዬ የነገርኩህን በአደባባይ ለምን አወራኸው እንደማትለኝ ተስፋ አደርጋለሁ። ምክንያቱም የእሷ ልብ ያልቻለውን ሚስጥር እንዴት የእኔ ልብ ይችላልና። ለሁላችንም መቻያውን ይስጠን። ምነው? አሜን፣ አሜን… አይባልም!? እንዴ? ሲሆን ሲሆን ቆሞ ከወገብ ጎንበስ ተብሎ እጅ ተዘርግቶ የሁለት እጅ መዳፍን እስከ መሳም ነበር። ለነገሩ ይሄስ ቢሆን ተመሳስሎ ሳይሰራ ይቀር ብላችሁ ነው?ድሮ ለምርቃት ተብሎ እግር እስኪነቃ ይኬዳል፤ አገልግሎት ይሰጣል። ለሚከወን መልካም ተግባር ምርቃት በሂሳብነት ይከፈላል። በዚያኛው ጫፍ ደግሞ እርግማንም የመብረቅ ያህል ይፈራል፤ ይከበራል፤ ያለ ቦታው አይወረወርም። እርግማን ከማደህየት አልፎ እድሜን ይቀጫል፤ያሣጥራል። እነዚህ ህግጋት ሰጥ ለጥ አድርገው ሀገር ሙሉ ሕዝብ ያስተዳድሩ ነበር። የሰው ልጆች ወንጀል የሚፈሩ እጆች እና ኩነኔ የሚፈሩ አንደበቶች ባለቤት ሆኖ ለእልፍ ዘመናት እንዲኖር አስችለውታል። ዛሬ እርግማንም፣ ምርቃትም፣ እምነትም ረክሰዋል፤ ዋጋ አጥተዋል፤ የአውሬነት ድርጊታችንን የመመከት አቅማቸው ሞቷል። ማን ከቁብ ቆጥሮ ጆሮ ይሰጣቸዋል። ታዲያ እነዚህ ፎርጂድ አልሆኑም ትላላችሁ? እንደ ‹‹ሥድ አደግ›› በሄድኩበት ቀረሁ እኮ። ጨዋታየን አስረሳችሁኝ። እናም እኚሁ ጎረቤቴ ቀጠሉ ‹‹የጤፍ እብቅ ከማበጠር፣ከወፍጮ ሥር ዱቄት ከማቡነን ተገላገልኩ እያልኩ ዘወትር እመርቃለሁ። ዘወትር ሥል በየወሩ ማለቴ ነው። ዱቄትና ደመወዝ ከእኛ ቤት አብረው ይመጣሉ፤አብረው ይሸኛሉ። እንዲህ ነው ኡደታቸው›› ብለው በረዥሙ ተነፈሱ። ቀጥለውም ‹‹ዱቄት ሲቀርለት አይኔም ብርታት ያገኘ መስሎ ይሰማኛል›› ወፍጮ ቤት ድረስ የምሄደው በአይኔ አይቼ ነጭ፣ቀይ፣ማኛ ጤፍ ለመምረጥ ነበር። አሁንስ ሂጀ አላውቅም። እኔም ቀረሁ፣ሥሙም ቀረ፣ጣዕሙም የለ›› አሉኝ። ምነው ሥል ጠየቅኳቸው። እሳቸውም ‹‹ አሁን ላይ ከቤቴ ሁኜ ይሄን ያህል ኪሎ በሚል ነው የማዘው። ጤፍ የበፊት ሥሟንም ቀይራለች። የአሁን መጠሪያዋ ነጭ፣ቀይ ማኛ ሳይሆን አንደኛ ደረጃ፣ሁለተኛ ደረጃ በሚል ሆኗል። የበፊቱን ወዛምና በምጣድ ላይ የሚዘናፈል፣ ለምለሙን እጥፍ አድርገህ ቆርሰህ ሥመህ የምትጎርሰው የጤፍ እንጀራ እግርህ እስኪ ነቃ ድረስ ብትሄድ ለመድሃኒት አታገኝም። ጣዕሟንም ቀይራለች ያልኩህ ለዚህ ነው›› አሉኝ። ጤፍና የወፍጮ ቤት ውሎዋን ተርከህመቋጨት አትችልም። እናም ወተት የመሰለ ነጭ ጤፍ ወይም በዘመኑ አጠራር አንደኛ ደረጃ ጤፍ ብታዝም፣ባታዝም እንጀራው እንደሆነ መናገር አቁሟል። ከምጣዱ የተሰፋውን እንጀራ ለማውጣትም በሠፌድ ያለሰለሰ መማጸንን ይጠይቃል። ወዶ አይምሰልህ። ከወፍጮ ቤት እስከ ምጣድ ድረስ በየደረጃው ለቁጥር የሚታክቱ ሥመ ጤፍ አረሞች ያለፍላጎታቸው ተዋህደው እንዲኖሩ ይደረጋል። በዚህ የተነሳ ጤፍ ማንነቷን ትነጠቃለች። በሀገር ደረጃ የሚስተዋለው የለውጥ እስትንፋስም በወፍጮ ቤቶቻችን አካባቢ ደርሶ የጠፋችውን የጤፍ ጣዕም ለአፍቃሪዎቿ ሊያስመልስ ይገባል። በተመሳሳይ በወፍጮ ቤት ሰፈር ደርሰው የተመለሱ እህሎችን ጤንነት እና ደህንነት በማረጋገጥና በማስጠበቅ መስራት የሚያስችል ጠንካራ አሰራርን መዘርጋት ቢችል ለዜጎች የማይተካ ሚና ያበረክታል። ዜጎች ለዚህ ተግባር ምቹ መደላድል በመፍጠር አጋርነታቸውን እንደሚያሳዩ ጥርጥር የለውም። የሱቅና የመጋዘን ባዕድ ቁስ ማብላያዎች ሥፍር ቁጥር የላቸውም ይባላል። በየወፍጮ ቤቶችም በርካታ ትርክቶች ትሰማላችሁ። ‹‹ደንበኛ ንጉስ ነው›› የሚሉት የግድግዳ ጌጥ ጽሁፎች ከነጋዴዎች አንደበት የተተነፈሱ አይምሰሏቹህ። እንደውም የሚተያዩት እንደ ባላንጣ ነው። በተመሳሳይ ‹‹ደረሰኝ ሳይቀበሉ ሒሳብ አይክፈሉ›› የሚሉትም በነጋዴዎች የተጠሉ ናቸው። በእነዚህ ህግጋቶች ልመራ ሞክሬ የገጠመኝን ላጫውታችሁ። ቀኑን ሙሉ አንዲት እቃ ሸምቼ መመለስ ተስኖኛል። ይልቁንስ ዱላ አትርፋችሁ ልትመለሱም ትችላላችሁ። እነዚህ ትዕዛዛት የገቢዎች ሚኒስቴር ሥሜት እንጂ የነጋዴው ሥሜት አያነባቸውም። አልተዋሃዱትም። አንተ አስተገብራቸዋለሁ፤እኔ መጀመርም እችላለሁ ካልክ አንተ የብርቱዎች ብርቱ ነህ። ክንድህም ኪስህም ብርቱ መሆንአለበት። ሩቅ ማሻገር የሚያስችል። በእርግጥ ይህ እሳቤ እና ድርጊት ከለውጡ በፊትና በኋላ በሚሉ ሁለት ብልቶች ተክፍሎ ሊታይ የሚችል እንደሆነ ከዕለት ኑሯችን በላይ መስካሪ አያሻም። የለውጡን መሪ በሁለት እጇ የጨበጠችው የገቢዎች ሚኒስቴር እንስት በቀላሉ ክንዷ የሚዝል አይመስልም። ይልቁንስ የእኛም ጠጠር መወርወር ዋጋ እንዳለው ተገንዝበን ድርሻችንን ልንወጣ ይገባል። በአገራችን ከሰው ልጆች ክብር በላቀ ደረጃ የገንዘብ ክብር ልቋል። የሰው\nልጅ የሚዛን የልኬት ደረጃው የት እንደነበረ መመርመር ይኖርብናል። መዋደዳችንን፣መከባበራችንን፣መተዛዘናችንን\nፈልገን መልበስ አለብን።ለዚህም በየቀየው የሚገኙ ሽማግሌዎች ትምህርት ቤቶቻችን ናቸው። አትጠራጠሩ የኋላውን ዘንግቶ ወደ ፊት መራመድ የቻለ የትውልድ ሰንሰለት የለም። ለተወሰነ ደቂቃም ቢሆን ጊዜያችሁን ሰጥታችሁ በርከክ ብላችሁ የአገራችሁን ወግና ባህል ከአዛውንቶች ጋር ተጨዋወቱ። ህይወታችሁም ይታደሳል። የሰውን ልጅ በዋጋ የማይተመን የክብር ልክ ማጤን የምትችሉበት ልቦና ይነቃቃል። ሳይበረዝ፣ሳይደለዝ እና ሳይጋነን ተፈጥሯዊ እውነታው ከእነርሱ ጋር ነው። የሰውን\nእምነት የለሽነት ልክ፣ ቅጣባሩ የጠፋውን የነጋዴውን ሥግብግብ ባህሪና አመል፣ የንግግርንና የቃልን ዋጋ ማጣት እንዲሁም የሰው ልጅ ሚዛን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀለለ መምጣት በአይናችን ከምናየው ሀቅ በተጨማሪ በንጽጽር አስረጂዎች ናቸው። ‹‹የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ›› የሚሉት አባቶች አስገዳጅ ህግ ፈርተው አይደለም። መዋሸት፣ መቅጠፍ፣ መካካድ ከነውርነቱም በላይ የተወገዘ ነበር። እንደ ርካሽ ያስቆጥራል። የዘመድ አዝማድን ሥምና ክብር ያሳጣል። የእገሌ ቤተሰብ የሆነው አቶ እገሌ ዋሾ ነው፣ ቃል አያከብርም።‹‹እሱን ያመነና ጉም የዘገነ አንድ ነው›› ከተባለ በዝምድናቸው ቤተሰቡ ያፍራል። በመሆኑም እርምጃ የሚወስድበት ሕግ ሳይሆን ቤተሰብ ነበር። ያውም የማያዳግም ቆራጥ ርምጃ። እነዚህ ሁሉ የአብሮነት ውብ መስተጋብሮች አሁን ላይ አርገዋል አለያም ሰርገዋል። በአጭር ጊዜ መመለስ ካልቻልን የእኛም እጣፋንታ ይሄው ነው። መ…ክ…..ሠ……ም።አዲስ\nዘመን መጋቢት 5/2011በሙሀመድ\nሁሴን", "passage_id": "db3ab666ec0c5f28eea98abca97b6a6d" }, { "passage": "“እ…አብይ ይወርዳል? የትኛው ነብይ ወይም ሟርተኛ ነህ አንተ ደግሞ!” እንዳትሉኝ። ቸኩላችሁ እንዳትበይኑ፤ ጥሎብን ችኩል ፈራጆች ሆነናል። ነገሩን በጥሞና ተመልክቶ መዳኘትና ሚዛናዊ ፍርድ መስጠት ብርቃችን ሆኗል አይደል!? የምናስበውን እንጂ እውነታውን ቀርበን መመርምር ሰልችተናል። አቤት ስንቶችን ባልተገኙበት አውለን ያለተግባራቸው ስም ሰጥተን፣ ያላሰቡትን አስበንና ያላዩትን ቀለም ቀብተን በችኩልነታችን ችካል ሆነንባቸው ይሆን? ዛሬ ዛሬማ እንደልማድ በስሚ ስሚ “ተደረገ” እና “ተባለ”ን ተከትልን የምንነጉድ በመሆናችን ተወራ ብለን መበየን ተክነንበታል። እንዴት ከኛ አርቀን ማስተዋልን ጭራሽ ዘንግተን እርግጠኛ ባልሆንበት ጉዳይ የመንጋ ብያኔ መስጠት ቀልሎናል። ለዛሬ ችኮላችንን የሚያሳይ አንድ ገጠመኜን ላካፍላችሁ ወደድኩ። ጠዋት የመጽሀፍ\nመደርደሪያዬን ተጠግቼ አንድ መጽሀፍ ስፈልግ ጊዜ ወሰደብኝ። ተራ በተራ ከተደረደሩት መካከል ማግኘት አልቻልኩም። ደግሜ ከላይ እስከታች\nፈለግሁ፤ የለም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መጽሀፍ ማዋስ መተው እንዳለብኝ እየተሰማኝ ነው። አንዳንድ ሰው መጽሀፍ ለማንበብ ተውሶ መመለስ\nአይወድም። አሊያም ደግሞ መዋሱን ይረሳዋል መሰለኝ መልስ ካላሉት በራሱ እንደ ጨዋ አመስግኖ የሚመልስ እየጠፋ ነው። እኔ ደግሞ\nየፈለኩትን/የነበረኝን መጽሀፍ ከመደርደሪያዬ ላይ ሳጣ ያናድደኛል። ዛሬም የፈለኩት መጽሀፍ የለም። ማን እንደወሰደው ማስታወስ አልቻኩም።\nበወሰደው ሰው ሳላወቀው አኮረፍኩ። ለስራ በጣም ስለፈለኩት በመጨረሻ አማራጭነት መግዛት እንዳለብኝ ከራሴ ጋር ተስማማሁ። ቁርሴን\nእንደ ነገሩ ቀመስ አድርጌ ከቤቴ ወጣሁ። መጽሀፉ ቆየት ያለ ስለሆነ ይገኛል ብዬ ወዳሰብኩበት ለገሀር አካባቢ ወዳለ መጻሕፍት ቤት\nለማምራት የሜክሲኮን ታክሲ ያዝኩ። ቡልጋሪያ ማዞሪያ ስደርስ አንዲት በዕድሜ ገፋ ያሉ እናት የተሳፈርኩበት\nታክሲ  አስቁመው፤ ባለ 25 ሊትር ቢጫ\nጀሪካን በረዳቱ አጋዥነት ወደ ታክሲው አስገቡ።  በእጆቻቸው በሩንና\nወንበር በመያዝና ዕድሜ የተጫናቸውን እግሮቻቸውን እየጎተቱ፤ በከፊል ተደግፈው ገብተው ከጎኔ አረፍ አሉ። እንደገቡ ሹፌሩ ያውቃቸዋል\nመሰል “እማማ እንዴት አደሩ ሰላም ነዎት? ከየት ነው?” አላቸው። እሳቸውም ቀና ብለው ወደ ሹፌሩ ተመልክተው በፈገግታ፡- “አብደላ\nአንተ ነህ እንዴ? ደህና ነህ አለህ ለመሆኑ …እሰይ! እሰይ! ልጄ በርትተሀላ እቺን ገዛህ፤ ላዳዋን ትተህ፤ ጎበዝ ልጄ እግዛብሄር\nይባርክልህ” ምርቃቱን አከታተሉለት።  እኔም በውስጤ ምርቃቱ ቅቡልነት\nእንዲኖረው ተመኘሁ። ከትላልቅ ሰዎች የሚገኝ ምርቃት የመንፈስ ምግብ አይደል! ደስ ሲል፤ቀጠሉ እማማ፡ “ከየት አልከኝ ልጄ ውሀ ልቀዳ ሄጄ። ይሄው\nአስራ አምስት ቀናችን ውሀ ከጠፋ እነዚህ ሙሰኞች በየቀበሌና በየወረዳው የተሰበሰቡ የመንግሥት ሹመኞች አስቸገሩን። ቆይ መስሎዋቸዋል\nገና ዶ/ር አብይ ይወርዳል። ሹመት ላይ ዘላለም የሚቀመጡ መስሎዋቸው እኮ ነው ሰውን የሚያንገላቱት…” ሰትዬዋ በሚናገሩት ተሳፋሪው\nሁሉ ጆሮ ሰጥቶ ያደምጣቸዋል። በአብዛኛው ተሳፋሪ ትኩረት የተሰጠው አንድ አረፍተ ነገር በተለይ ደጋገሙት “ዶ/ር አብይ ይወርዳል።”\nተሳፋሪው ድምጽ በማውጣት ጭምር አጉረመረመ “…እ..እ..”  በጥያቄ መልክ መሆኑ ነው። ሰው መሪውን ሲወድድ ደስ ይላል። ጠቅላይ ሚኒስትራችን\nበህዝቡ ዘንድ፤ በሰው ዘንድ ያስወደዳቸው ሁሉም ባንድነት የተቀበላቸው የዘመኑ ምርጥ መሪ ስለመሆናቸው ማሳያ የሴትየዋን “ዶ/ር\nአብይ ይወርዳል” የሚለውን ዓረፍተ ነገር መሰማት ተከትሎ በተቀየረው የተሳፋሪዎች የፊት ገጽታ ይበልጥ ተደመምኩ። ሴትዬዋ ቀጠሉ፡ “የወረዳው ሰራተኞች ስራ አይሰሩም። በማይረባ\nወሬ ነው ቀናቸውን የሚጨርሱት፤ ቧንቧ ተበላሸ እባካችሁ ስሩልን ብለን መመላለስ ከጀመርን 10 ቀን አለፈ። አልሰራ ብለውን በስተርጅና\nጀሪካን ተሸክመን እንዞራለን። እንቢ አሉ። የተነገራቸውን መስማት አቁመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶክተር አብይ ይወርዳል! አብያችን\nቀበሌ ድረስ ወርዶ ሁሉንም ያስተካክላል። እስከዚያ እንዳሻቸው ያድርጉን፤ ጉዳቸው ማሾፋቸው እስኪታወቅ ነው አብያችን መቶላቸዋል፤ለካስ ይወርዳል፤ እስከ ቀበሌ ድረስ፤ የሚሉት የጠቅላይ\nሚኒስትሩን አዲስ አሰራር ነው። ተሳፋሪው ከስልጣን ይወርዳል ብለው እሱን እየዘለፉ መስሎት ጆሮውን አቁሞ በቅሬታ እየገላመጣቸው\nእንዳላዳመጠ ነገሩ ሲገባው በፈገግታ እርስ በእርሱ ይተያይ ጀመር። ሴትዮዋ ቀጠሉ፤ ሁሉም ተሳፋሪ በፈገግታ እሳቸውን ነው የሚሰማው፤\n“ የሚናገረውን አልሰማህም ልጄ? ህዝብን አገልግሉ፤ ሀገራዊ ኃላፊነታችሁን ኢትዮጵያዊ አደራችሁን ተወጡ ሲል፤ እሱ የተባረከ ነው!\nቃሉም ተግባሩም የሚያጠገብ፤” እሳቸው የሚያወሩት ሹፌሩን እየተመለከቱ ነው ሌላውን ተሳፋሪ ቁብ ሰጥተው አላዩትም።“አይ እኛን በነገር ካስረጁን ዕድሜያችን ከገፋ በኋላ\nለእናንተ ምርጥ መሪ መጣ። እኛማ ጃጀን። በዚህ ዕድሜያችንም ቢሆን ይሄን ሀገር ወዳድ መሪ ስለሰጠን አምላክን እናመሰግነዋለን።”\nየሴትዮዋ የሰላ ንግግር ጆሮ ያስጥዳል። በመሀል ሹፌሩ ረዳቱን “እንዳትቀበላቸው የሳቸው ተከፍሏል” አለው። ረዳቱ የተቃውሞ ምላሽ\nሠጠ፡-“ኧ ዴች ነው። አብዲ ተቀብያለሁ። ብዙ ነው እስከነ ጀሪካናቸው” አለ። አስር ብር ማለቱ ነበር። ሴትዮዋ፡- “የምን ቋንቋ\nመቀየር ነው ግብዣ ከፍ ሲል ነው የሚጥመው፤ መልስላት ተባልክ መልስ!” ሲሉ በታክሲው ውስጥ የነበርነው ሁላችንም ተሳፋሪዎች በሳቅ\nተንከተከትን።በነገራችን ላይ የቋንቋ አጠቃቀማችን ብዙ ያስተዛዝባል\nአይደል፤ በእርግጥ የረዳቱ ከሹፌር ወይም መሰል የሙያ ባልደረቦቹ ጋር መግባባት የሚችሉበት ቋንቋ መፍጠራቸው ችግር ባይኖረውም፤\nከማንና እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው አለመረዳታቸው ተግባቦትን ያፋልሳል። “አራዶች” የኛ የሚሉት ካራዶቹ ጋር ካልሆኑ ከኔ ቢጤው\nጋር ሊያግባባቸው አይደለም በወጉ ሊያጋጫቸውም ይከብዳል። በየሆቴሉ መዝናኛና አቅጣጫ አመላካች የሆኑ ቦታዎች ላይ የሚለጠፉ ማህበራሰቡን\nወይም ነዋሪውን የዘነጉ የቋንቋ አጠቃቀሞች አብዛኞቹ በእኛ አገር እና ለኛ የተዘጋጁ እኛን ግን የማያግባቡ መሆናቸው ወደፊት የምናየው\nይሆናል።የረዳቱ ከሹፌሩ ጋር የተነጋገረበት የራሱ ቋንቋ እናታችን\nበሰጡት የመልስ ምት ድል ሆነና ሹፌሩ በድጋሚ እንዲመልስላቸው ነግሮት መለሰላቸው። በመጨረሻ ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ አጠገብ ሲደርሱ\nለሹፌሩ እንዲያቆምላቸው ነግረው የምርቃት መዓት አዥጎድጉደውለት ወረዱ። የምን አስር ብር ነው ይህን ምርቃት ለማግኘት ምንስ ቢሰጥ፤\nእናም ወረዳ ምናምን ላይ ያላችሁ አስፈጻሚዎች፤ እባካችሁ በእናንተ አቅም የሚፈታውን የህዝቡን ጥያቄ  እየለያችሁ ፍቱ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እናንተ ዘንድ ከመድረሱ\nበፊት እባካችሁ እናንተ ወደ ህዝቡ ዘንድ ውረዱና አድምጡት፤ ብለዋችኋል እናታችን፤አዲስ ዘመን የካቲት 6/2011", "passage_id": "0b406825e05019e01f1fe5967b35c23c" }, { "passage": "የሰው ልጅ ኑሮ ዛሬን አሳልፎ ትላንት በማድረግ ጉጉትና፣ ትላንትን ሰንዶ አስቀምጦ ለነገ በማቆየት መጠመድ ውስጥ የተቋጠረ ይመስላል። ለዚህም ነው ወደኋላ ታሪክ እና ትዝታ ወደ ፊት ደግሞ ተስፋ በጉልህ የሚታዩት። በዚህ መልኩ የአዲስ አበባን ገጽታ በፎቶ አስቀርቶ የዛሬን ዐይን የሚገልጥ ለነገም ሰነድ የሚያስቀምጥ መድረክ ከኹለት ሳምንት ቀደም ብሎ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ጊቢ ሲካሔድ ነበር።‹‹አዲስን እናንሳ›› (Capture Addis) የተሰኘው ይህ አውደ ርዕይ ከመከፈቱ ቀድሞ ማንኛውም ሰው ፎቶ በማንሳትና በመላክ እንዲሳተፍ ጥሩ ቀርቦ እድሉ ተከፍቷል። ይህንን ተከትሎ ከባለሙያው የተረፈውን ባለሞባይሉ፣ ባለሞባይሉ ያለፈውን ደግሞ ባለሞያው ይዘው ያቆዩትን፣ አቅርበው አዲስ አበባን በፎቶ የሚያስቃኝን አውደ ርዕይ እውን ሊያደርጉ ችለዋል። በማዘጋጃ ጊቢ በተካሔደው ይህ አውደ ርዕይ በቆየባቸው ቀናት ማምሻውን በተከናወኑ የውይይት መድረኮች ደግሞ አዲስ አበባ ከተለያዩ ጥበባት አንጻር ተቃኝታለች።\nአዲስ አበባ ለበርካታ የልብ ወለድ መጻሕፍት መቼት ሆና አገልግላለች። ታድያ ግን ሰፈሮቿ በስም ይጠሩ እንጂ መልካቸውና ገጽታቸው በጉልህ ተቀምጦ አይታይም። ይህን ያነሱት የሥነ ጽሑፍ መምህርና ሃያሲ መሠረት አበጀ፤ አንድ አንባቢ ቀድሞ ወደ ሐሳቡ የሚመጡ ልብ ወለድ መጻሕፍትን ጥራ ቢባል የአብዛኞቹ መቼት አዲስ አበባ ስለመሆኗ ይገልጻሉ።በዓሉ ግርማ፣ ዓለማየሁ ገላጋይ፣ ዘነበ ወላ፣ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር፣ አውግቸው ተረፈ እና ሌሎችም ደራስያን በዚህ ይጠቀሳሉ። ‹‹የደራሲ ግብ አንባቢን በመንፈስ መንጠቅ ነው›› የሚሉት መሠረት፤ መጻሕፍት ተደራሲ ሊያውቀው ከሚችለው በታች መስጠት የለባቸውም ሲሉ ይከራከራሉ። እናም መቼትን በተመለከተ ያለውን አሳድጎ ማቅረብና ፈጠራን ማከል እንዲሁም ገለጻን መጨመር ያሻል ይላሉ።የመሠረት ሌላው ነጥብ፤ ደራስያን ገጸ ባህርያቱን ኳኩለውና አሳምረው፣ ተደራሲ የሚያወቃቸው ያህል እንዲሰማውና በዐይነ ሕሊናው እንዲስላቸው አድርገው ሳለ፣ ለመቼት ግን የዛን ያህል ሲጨነቁ አይታይም። እናም ለመቼት በተለይም ‹‹የት›› ለሚለው፣ ለስፍራው ትልቅ ዋጋ እየተሰጠ እንዳልሆነ ትዝብታቸውን ያስቀምጣሉ።\nየአዲስ አበባ የድህነት፣ የመከራና የሰቆቃ ገጾች እየታዩ የመሻሻሉ ተስፋስ ወዴት አለ ሲሉም ይጠይቃሉ፤ መሠረት። ይህንንም ያሉት ከመቼት አንጻር ብቻ ነው። ‹‹ድርሰት ኃልና ጉልበት ነው። አዲስ ነገር መጨመርና ማነቃቃት ላይ ልንጠቀምበት እንችላለን፤ በዛ መልኩ የሆነ የመቼት ምልከታ ሊኖር ይገባል።›› ብለዋል፤ የሥነ ጽሑፍ መምህርና ሃያሲ መሠረት አበጀ።\n‹‹ሙዚቃ ማህበረሰብን ለማቀራረብና አንድ ለማድረግ ያግዛል።›› ያለው አዲስ አበባን ከሙዚቃ ስፍራነት አንጻር የቃኛት ሙዚቀኛና ፒያኒስት ሳሙኤል ይርጋ ነው። ሙዚቃ በከተማ እድገት ውስጥ የራሱ የሆነ ማህበራዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አለው ያለው ሳሙኤል፤ ይህም እንደ አገር የሚኖረውን አስተዋጽኦ ለማየት ይረዳል ባይ ነው።አዲስ አበባን በተመለከተ እስከ አሁን ሙዚቃ የነበረውን ድርሻ ለማየት የተደረገ ጥናት አለመኖሩን ሳሙኤል ያወሳል። ከተማዋ ለሙዚቃ፣ ሙዚቃው ደግሞ ለከተማዋ ያበረከቱት ነገር ባለመታወቁም፤ ሙዚቀኛውም ሆነ ከተማዋ ሳይናበቡ በየራሳቸው መስመር እንዲሔዱ አድርጓቸዋል።ይህም ሆኖ ታድያ አዲስ አበባ የሙዚቃ ከተማ እንደሚባሉት ሁሉ በዛ ደረጃ ልትጠራ ትችላለች። የተለያዩ ፌስቲቫሎች የሚከናወንባት መሆኗ፣ መገናኛ ብዙኀንን ጨምሮ ከሙዚቃ ጋር የተገናኙ ጉዳዮች ማረፊያም ስለሆነች ነው። በሌላ አገላለጽ አዲስ አበባ የሙዚቃ ማዕከል ነች፤ የሳሙኤል ምልከታ ነው።ነገር ግን ከሌሎች የሙዚቃ ከተሞች የምትለይበት ጉልህ መገለጫ አላት። ይህም ምንም ዓይነት የሙዚቃ ስልት ይዞ ለመጣ ሁሉ ክፍት የሆነችና ብቸኛዋ እድል ያለባት ከተማ ሆና መገኘቷ ነው። ከተለያዩ ከተሞች ሙዚቃን የሚሠሩ ሙዚቀኞች ሳይቀሩ አዲስ አበባ መጥተው ነው ተመልሰው ወደ መጡበት ከተማ ሥራቸውን ይዘው የሚያቀኑት። የሙዚቃ ገበያው በአዲስ አበባ ላይ ማዕከል አድርጓል።ነገር ግን በዛ ልክ አውድ አልተፈጠረባትም፤ ሳሙኤል ይርጋ የሚቆጭበት ነጥብ ነው። የሙዚቃ ስፍራዎች፣ ስቱድዮዎችና ቀን ቀን ሙዚቃ የሚቀርብባቸው መድረኮች የሏትም። ‹‹ሙዚቃውን ለማሳደግ የሚያግዝና ለዛ ታስቦ የተዘጋጀ ስፍራ አይገኝባትም።›› ይላል።በድምሩ ግን ለሙዚቃ ባልተሰጠ ትኩረት የተነሳ ሙዚቃውን ‹‹ዘርፍ›› ብሎ ለመጥራት አስቸጋሪ አድርጎታል። አዲስ አበባም ልታገኝ የሚገባውን ጥቅም ልታገኝ ያልቻለችው በዚህ ምክንያት መሆኑን ሳሙኤል ይገልጻል። ከገቢ አንጻር ሌሎች አገራት ጥቅሙን አይተው ምን ያህል ትኩረት እንደሰጡትና እንደተጠቀሙበት በማንሳት ለአዲስ አበባም በተመሳሳይ እንድትጠቀም፤ እንደ አገር ሙዚቃውንም እንድትጠቅም ከባለሙያዎች ጀምሮ ሁሉም የድርሻውን መወጣጥ አለበት ብሏል።\nበ‹‹አዲስን እናንሳ›› የፎቶ አውደ ርዕይ ክዋኔ ላይ ከቀናት በአንዱ የአዲስ አበባን ትዝታዎች ከኪነ ህንጻ (Architecture) ጋር የሚያያይዝ ውይይት ተደርጓል። በጉዳዩ ላይ ሐሳባቸውን ያጋሩት የኪነ ህንጻ ባለሙያ ማህደር ገብረመድኅን፤ ኪነ ህንጻ የትላንት ትዝታን የሚያቆይ፣ የዛሬን በራሱ መንገድ የሚቀርጽ፣ የነገም ትዝታ ላይ ተጽእኖ ማሳረፍ የሚችል ዐቢይ የኪነጥበብ ዘርፍ ነው ሲሉ ገልጸዋል።የኪነ ህንጻ ለውጥም ከማህበራዊና ፖለቲካዊ ፍልስፍና ጋር ይያያዛልአ አሉ። ፖለቲካዊ እንቅስቃሴውን በተመለከተ ክስተቶች እንዴት ነገሮችን እንዳይመለሱ አድርገው እንደሚቀይሩ ማህደር በማሳያ አስቀምጠዋል። ይህም ለምሳሌ ከ1966 ቀደም ብሎ ታቅዶ የነበረው የከተማ ፕላን ነው። በዚህም ከዓድዋ አደባባይ በቸርችል ጎዳና እስከ ፒያሳ ሊሠራ የታሰበ ሥራ ነበር። ነገር ግን በ1966 የፈነዳው አብዩት እቅዱን አስቀርቶት አካባቢው አሁን ያለውን ገጽ እንዲይዝ አድርጓል። ማህደርም ‹‹በአንድ አብዩት አርክቴክቸሩም ተቀይሯል፤ ትዝታችንንም አብሮ ቀይሮታል።›› ሲሉ ይገልጹታል።ማህበራዊ ኑሮም ተጽዕኖ እንደሚፈጥር ሳይጠቅሱ አላለፉም፤ ይህም በአዲስ አበባ በጉልህ ይታያል። ማህደር እዚህ ላይ በአሁኑ ጊዜ የአዲስ አበባ ኪነ ህንጻ መገለጫ እየሆነ ያለውን ኮንዶሚንየም ቤት ጠቅሰዋል። ኪነ ህንጻ የማህበረሰቡን አኗኗር ከግንዛቤ ያላስገባ ሲሆን ችግሮች እንደሚፈጠሩም ጠቅሰዋል።‹‹ኪነ ህንጻው ለምንፈልገው የኑሮ ሒደት ቦታ ካልሰጠ ማህበረሰቡ የራሱን እርምጃ ይወስድና ግንባታው የታሰበለትን ዓላማ ይቀይሩበታል።›› ይላሉ። እናም ኪነ ህንጻ ለተሠራለት ዓላማ ማገልገል እንዲችል ትውልድና አስተሳሰብን ማግኘት መቻል አለበት። ካልሆነ አገልግሎት ላይ አይውልም፤ የማህደር ገለጻ ነው።ታድያ በዚሁ አንድ ስጋታቸውን አጋርተዋል፤ ይህም ወደፊቱ እንደ ከተማ አዲስ አበባውያን የሚጋሩት ትዝታ ሊቀንስ ይችላል የሚል ነው። በቀደመው ጊዜ የተወሰነ ጋዜጣ፣ ከአንድ ያልዘለለ የቴሌቪዥን ጣቢያ እና ራድዮ እየሰማ የኖረና ያደገው የማህበረሰብ ክፍል፣ የኑሮ ደረጃው ቢለያይ እንኳ ተመሳሳይ ትዝታን የመጋራት እድል ነበረው። አሁን ግን ዲጂታል ቴክኖሎጂ ብዙ አማራጭ በሰጠበት ወቅት ይህ ነገር እንደሚቀንስ ነው ያነሱት።\nአዲስ አበባን የሚወዱ፣ የሚሳሱላትና የሚኖሩባት እንዲሁም በተለያየ ሙያ ውስጥ ያሉ ሰዎች፤ ታዳሚ በሆኑበት በዚህ መድረክ፤ የሚሰጠው አስተያየትም ብዙና ሰፊ ነበር። በውይይት ሰዓት በኪነጥበቡ ዘርፍ ፊልም ለብቻው ከአዲስ አበባ ጋር በተገናኘ በውይይት ርዕስነት አልተጠቀሰም። ሆኖም አስተያየት ከሰጡ የተለያዩ ባለሙያዎች መካከል የመቅረጸ ምስልን ነገር ከአዲስ አበባ ጋር አቆራኝተው ያነሱ አልጠፉም።የፊልም ባለሙያው ሰውመሆን ይስማው (ሶሚክ) አዲስ አባባ ለፊልም ሥራ ምን ያህል አስቸጋሪና ከባድ እንደሆነች ጠቅሷል። አሁን ላይ ይሄ ነው የሚባል የራሷ የሆነ ቀለም የሌላት በመሆኑም የፊልም ባለሙያዎች በመቼት ደረጃ የአሁኗን ሳይሆን የቀደመችውን አዲስ አበባን ከምናብ ጓዳ ፈልፍሎ አውጥቶ በካሜራ ዐይን ማሳየትን ለመምረጥ ይገደዳሉ/ እንገደዳለን ይላል።አንዳች ባህሪ ያለው የከተማ ቀለም፣ አዲስ የሆነ እይታን ማውጣት ይስበኛል የሚለው ሰውመሆን፣ አዲስ አበባ ላይ ያተኮሩ ሥራዎችን ብዙ እንዳላዘጋጀ ይጠቅሳል። ካሜራውን ዝግጁ አድርጎ ለቀረጻ ሲነሳና ‹‹ምን የተለየ ነገር አለ?›› ብሎ ሲጠይቅ፤ አዲስ አበባ ለዚህ አጥጋቢ ምላሽ ሰጥታው እንደማታውቅና መልስ ማግኘት አዳጋች ሆኖበት እንደሚያውቅ ከልምዱ ያለውን ጠቅሷል። ‹‹ስለዚህ አዲስ አበባን በተመለከተ መጻፍ ካለብኝ 1960ዎቹ ነው የምለው። በዛ ዘመን ላይ ሊሆን የሚችለውን በምስል እያሰብኩ ነው የምሠራው።›› ሲል ያክላል።ከዚህ በተጨማሪ ለእይታ አዲስ ነገርን ያመጣሉ የተባሉ አካባቢዎችንና ህንጻዎችን ፈልጎ ማግኘትም አስቸጋሪ ነው። ለዚህም ነው በርከት ያሉ ፊልሞች ትዕይንቶቻቸው ከቤት ውስጥ የሚሆኑት። እንደ ሰው መሆን ገለጻ እንደውም ውጪው ተበላሽቷል፤ ለቀረጻ አስቸጋሪና ምቹ ያልሆነ ነው። ጉራማይሌ መሆኑም ለዚህ ዳርጎታል ባይ ነው።በተመሳሳይ የፊልም ባለሙያ የሆነችው መዓዛ ወርቁ ሐሳቧን ያካፈለችው ከአንድ ገጠመኟ በመነሳት ነው። አንዲት ኡጋንዳዊት ደራሲ አዲስ አበባ ተገኝታ ዙሪያ ገባውን ማየት ፈለገች፤ አንዳች አዲስ ነገር ለማየት በመጓጓት። መዓዛም አዲስ አበባን አስጎበኘቻት፤ ነገር ግን እንግዳዋ ኡጋንዳዊት አልተደነቀችም፤ አዲስ ነገር እንዳላየች ሆነች።\n‹‹ለእኔ አዲስ አበባ ትልቅ ከተማ ናት፤ ለምን አላየቻትም/አልታየቻትም ብዬ አሰብኩ።›› ትላለች መዓዛ። እናም ያቺ ኡጋንዳዊት እንድታይላት የምትፈልጋቸውን ስፍራዎች አሁን ላይ የፊልሞቿ መቼት አንድ አካል አድርጋ ታስቀራቸው ጀመረች። ‹‹በዚህ ትንሽ እርካታ ላገኝ እሞክራለሁ።›› ስትል በአስተያየቷ መካከል ተናግራለች።በተጓዳኝ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚታዩ ፊልሞቸ ላይ አዲስ አበባን በምስል ሰንዶ የማስቀመጥ ሩጫ እንደሚታይ ነው የጠቀሰችው። የአዲስ አበባ መልክ እያደር እየተቀየረና እየተለወጠ ስለሚሔድ።\nየሥነ ጥበብ ባለሙያና በሥነ ጥበብ ተባባሪ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን ‹‹አዲስ አበባ፤ ምናብና ምስል›› በሚል ርዕስ መወያያ ሐሳብ አቅርበው ታዳሚን አነጋግረዋል። ባቀረቡት ሐሳብ ከሚታየው ይልቅ ስፍራን ለመረዳት የምናብን ጥንካሬ አንስተዋል። ለማሳያነት ከአዲስ አበባ ሰፈሮች መካከል የተወሰኑትን እያነጻጸሩ ጠቀሱ።\n‹‹ጨርቆስን በቦሌ ፊት ደረቷን ነፍታ እንድትቆም ያደረጋት ምናብ ነው›› የሚለው ካነሱት ማሳያ መካከል ነው። ለምን ሲባል ስለ ጨርቆስ የሚያነሱ ሰዎች ጨርቆስን በቁሟ (በሚታይ መልኳ) አያይዋትም። ይልቁንም በነዋሪዎቿና በውስጧ ባለ ሙቀትና የሕይወት መስተጋብር ነው የሚመለከቷት። ይህም ስፍራንና አካባቢን በቁሙ እንደማንፈርጅና ይልቁንም ምናብ የላቀውን ስፍራ እንደሚይዝ ያሳዩበት ነጥብ ነው።ይህ ታድያ በጎ ጎን አለውም ብለዋል። ‹‹ድህነታችንን ከወንጀል አርቆ ያቆየው ይህ ምናብ ይመስለኛል።›› ያሉት በቀለ፤ እነዚህ ምናቦች በማህበራዊ ጉዳይም ማህበረሰቡን አቻችለው ያቆዩ ናቸው ሲሉ ምልከታቸውን ገልጸዋል። ይህም ምናባዊነት የሚሰጠው ጠቀሜታ ሆኖ ሊመዘገብ ይችላል።\nበፎቶና በምስል ሲታይ ግን ስፍራን በቁም ማየት ግድ እንደሚል ያነሳሉ። ታድያ አካባቢን በመረዳት ምናባዊነት የጠቀመው ነገር መኖሩ እንዳለ ሆኖ፣ በአንጻሩ ግን ሊሞላ የሚገባ ክፍተት እንዳለና አካባቢን በቁሙ አይቶ ማሻሻል ላይም ትኩረት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።\nከተከናወነ ከአንድ ሳምንት የዘለለው ይህን የፎቶ አውደ ርዕይ ስናነሳ አንዴ ታይቶ የሚጠፋ ክዋኔ እንደማይሆን በማመን የተነሱ ሐሳቦችም ለብዙዎች ቢደርሱ እይታን ሊያሰፉ ይችላሉ ከሚል እይታ አንጻር ነው። ታድያ የ‹‹አዲስን እናንሳ›› የፎቶ አውደ ርዕይ አዘጋጆች መካከል ሐሳቡን ለአዲስ ማለዳ ያካፈለው አክሊሉ ገብረመድኅን፤ በቀጣይም ይህ ክዋኔ እንደሚኖርና ዓመታዊ ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጿል።በዚህ የመጀመሪያ በሆነው ክዋኔ ጥሩ ግብረ መልስ ማግኘታቸውን ያነሳው አክሊሉ፤ በቀጣይ ፎቶ ግራፍ በማንሳት የሚሳተፈውን ባለሙያ እና ባለሙያ ያልሆኑም ሆነው ፍላጎት ያላቸውን ተሳታፊዎች፣ የዳኞች ቁጥር ከፍ እንዲል እቅድ እንደተያዘ፤ እንዲሁም የተሰጠውን የወርክሾፕ ጊዜ ለማፋት እንደታሰበም ጠቅሷል።\nየአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ለአውደ ርዕዩ ቦታ ከመስጠት ጀምሮ በተለያየ መንገድ ዝግጅቱን ደግፏል። ‹‹ቃል የተገባልን ነገር ተፈጽሞ አይተናል›› ያለው አክሊሉ በቀጣይም የከተማ መስተዳደሩ ድግፍ እንደሚኖር ተስፋ እንዳለ ጠቅሷል። በተያያዘም በዚህ ክዋኔ ላይ አስተዋጽኦ ማድረግና አዲስ አበባን ሰንዶ በማቆየትና በማክበር በኩል መሳተፍ ለሚፈልጉ ሁሉ በራችን ክፍት ነው ሲል ጥሪውን አስተላልፏል።ቅጽ 2 ቁጥር 54 ህዳር 6 2012", "passage_id": "796e9dfbc251d17196b9c47aacb12efc" }, { "passage": "ህፃናት በስነ-ምግባር ታንፀው አድገው ነገ በሀገራዊና በራሳቸው ጉዳይ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ከትምህርት ቤት በቀጥታ ከሚቀስሙት ትምህርት ባሻገር፣ ከመፃህፍት፣ ፊልሞችና ከመገናኛ ብዙሃን የሚያገኟቸው መልእክቶች ትልቅ ሚና አላቸው።በተለይ ታሪክን ለልጆች በማስተማርና ማህበራዊ እሴቶችን በማስተላለፍ ረገድ ደግሞ ተረቶች ትልቅ ቦታ ይሰጣቸዋል። የዛሬው እንግዳችን በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር እነዚህን ተረቶችንና ትረካዎችን ለህፃናት በሚመች መልኩ በምስል እያቀናበረ የሚያቀርብ አዲስ የዩቲዩብ ቻናል ከፍቷል፣ ስለ ቻናሉና በህፃናት ዙሪያ ስለሚሰራቸው ስራዎች ከባልደረባችን ስመኝሽ የቆየ ጋር ቆይታ አድርጓል።ይህ በመግቢያው ላይ የሰማችሁት ተረት የተቀነጨበው በቅርብ ጊዜ ከጀርመን የባህል ተቇም ጋር በመተባበር ለህፃናትና ታዲጊዎች ልዩ ልዩ ትረካዎችንና ተረቶችን ከምስል ጋር አቀናብሮ በዩቲዩብ ቻናል አማካኝነት ማቅረብ ከጀመረው 'እነሆ ለልጆች' ቻናል ነው። የዩቲዩብ ቻናሉን የከፈተው ደግሞ ከዚህ በፊት በተለያዩ መፅሃፎቹ፣ የህፃናት የቲያትር ድርሰቶቹና፣ ግጥምን በጃዝ በሚያቀርቡ ዝግጅቶች ላይ ዘና በሚያደርጉ ወጎቹ የምናውቀው በኃይሉ ገ/እግዚአብሔር ነው። በኃይሉን ከ 3 እስከ 12 አመት እድሜ ክልል ላሉ ላሉ ልጆ የተዘጋጀውን ይሄን እነሆ ለልጆች' የተሰኘ የዩቲዩብ ቻናል ለምን እንደጀመረ ጠይቀነው ነበር። የአማርኛ ስነ-ፅሁፍ ምሩቅ የሆነውና ከዚህ በፊት 'ኑሮና ፖለቲካ' እንዲሁም 'መንታ መልኮች' በተሰኙት ለአዋቂዎች ባሳተማቸው መፅሃፎቹ እንዲሁም በግል የፕሬስ ውጤቶች ላይ በሚፅፋቸው መጣጥፎች ይበልጥ የሚታወቀው በኃይሉ፣ የጀርመን የባህል ማእከል ተቋም የልጆች መፅሃፍ አርታኢ ሆኖ ከመስራቱ በተጨማሪ፣ ከተቋሙ ጋር በመተባበር የህፃናት ቲያትሮችን እየፃፈ በእምቢልታ ሆቴል ያሳይ ነበር። ሁለት የህፃናት መፅሃፎችንም አሳትሟል። በኢትዮጵያ የሚኖሩ ህፃናት በየቋንቋቸው በመማራቸው ምክንያት አንድ የሚያደርጉዋቸው ተመሳሳይ ታሪኮች እየሰሙ አይደለም የሚለው በኃይሉ ህፃናት በተለያየ ቇንቇም ቢሆን ተመሳሳይ ተረቶችና ታሪኮችን እንዲሰሙ በማድረግ አንድነት መፍጠር፣ ፍቅርን፣ መተሳሰብና ወንድማማችነትን በተረትና በጨዋታ ማስተማር ይቻላል ብሎ ያምናል። ተመሳሳይ ታሪኮችን በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ለማሳተምም ጥረት እያደረገ ነው። በቀደመው ትውልድ የበርካታ የስነ-ፅሁፍ ውጤቶች ባለቤት የሆኑት ደራሲ ከበደ ሚካኤል ተረቶችን በግጥም ቅርፅ እያደረጉ እንደ ፋኖስና ብርጭቆ ፣ አውራ ዶሮና የአይጥ ግልገል እንዲሁም ብረት ድስትና ሸክላ ድስት የመሳሰሉ ትምህርት አዘል ፅሁፎችን ለልጆች ያቀርቡ ነበር። ለዚህ ትውልድ ግን እንደነዚህ አይነት የልጆችን ስብዕና የሚያንፁ የግጥም ተረቶች እየቀረቡ አይደሉም የሚለው በኃይሉ፣ በዚህ ዙሪያ ብዙ ስራ መስራት እንደሚፈልግም ይናገራል። አሁን የሰማችሁት ድግሞ 'እነሆ ለልጆች' ዩቲዩብ ቻናል ላይ ከሚቀርቡት ዝግጅቶች መሃል 'ከእኛ ቤት ለእናንተ' በሚል ርዕስ ከተሰኘው የተቀነጨበ ነው። ዝግጅቱ እማዋይሽ ስሜ የተሰኘች የበኃይሉ ባልደረባ ከልጆቿ ጋር፣ በተለይ በኮሮና ምክንያት ከቤት መውጣት በማይመከርበት ጊዜ፣ አትክልት ሲንከባከቡ፣ መፅሃፍት ሲያነቡ ወይም የቤት እንስሳትን ንፅህና ሲጠብቁ በማሳየት ልጆች እንዲማሩ የሚያደርግ ነው። ዛሬ የምንሰጣቸውን ነው ነገ ልጆች ላይ የምናየው የሚለው በኃይሉ፣ ከተረቶቹ በተጨማሪ እንደነዚህ አይነት ዝግጅቶች ለልጆች የወደፊት ስነ-ምግባር መሰረት በመሆናቸው የበለጠ መስራት ይጠበቅብናል ይላል። 'እነሆ ለልጆች' ዩቲዩብ ቻናል ገና የጅምር መንገድ ላይ ነው። በአዛውንቶች የሚተረኩ ተረቶችንና በህፃናት በራሳቸው የሚዘጋጁ ዝግጅቶችን ጨምሮ እራሱ የጻፋቸውና ገና ለህትመት ያልበቁ ተረቶቹ በምስል እንዲቀናበሩ ማድረግ በኃይሉ በዩቲዩብ ቻናሉ ሊሰራቸው ከሚያስባቸው ስራዎች ጥቂቶቹ ናቸው። በህፃናት ዙሪያ በቂ ስራ አልተስራም የሚለው በኃይሉ ነገ አገሩን የሚወድ ብቁ ዜጋ ለማፍራት ዛሬ ተባብረን እንስራ ሲል ተመሳሳይ ፍላጎትና ሙያ ያላቸው ሌሎች ሰዎች የነገው ትውልድ በስነ-ፅሁፍ ለማነፅ አብረውት እንዲሰሩ ጥሪ ያቀርባል።", "passage_id": "d0b54cd3e528b802feb2acaf1c8006f1" } ]
ca6f5cf77fedc16587c7bd2f453f5bcd
8f2dcea4c8ff5fb0ab9188b332f8db37
ሙስና በሀገር ህልውና ከደቀነው አደጋ አንጻር መገናኛ ብዙሀን ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩበት እንደሚገባ ተጠቆመ
 በጋዜጣው ሪፖርተርአዳማ፦ መገናኛ ብዙሀን ሙስና በሀገር ህልውና ላይ ፈጥሮት ከነበረው አደጋ አንጻር ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩበት እንደሚገባ የፌደራል የስነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ጸጋ አራጌ “ ስነ ምግባርን በመገንባትና ሙስናን በመከላከል ረገድ የሚዲያ ተቋማት ሚና” በሚል መሪ ሃሳብ በአዳማ ከተማ ትናንት በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ እንዳስታወቁት፤ በሀገሪቱ የተንሰራፋው የሙስና ችግር የሀገሪቱ ዕጣ ፈንታ ላይ ከፍተኛ ተግዳሮት ሆኗል። በቅርቡ ሀገሪቱ የገጠማትና ከፍተኛ ዋጋ ያስከፈላት ችግር ከሙስና ጋር የተያያዘ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ጸጋ፤ ችግሩ በሙስና የተዘፈቀ ስርአትን ለማስቀጠል፣ በሙስና የተሰበሰበን ሀብት ያለ ችግር ለመጠቀም ካለ ከፍ ያለ መፈለግ ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል። ይህ ችግር ለአንድ ተቋም ወይም ለተወሰኑ የመገናኛ ብዙሀን የሚተውት ሳይሆን የሁሉንም የመገናኛ ብዙሀን ንቁ ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑን ጠቁመው፤ ሁሉም ችግሩ ሊያስከትል ከሚችለውና አስከትሎት ከነበረው አደጋ አንጻር ሊመለከቱት ይገባል ብለዋል።ከጋዜጠኝነት ሙያ አንጻር የሙስና ጉዳይ ወቅታዊ መሆኑን ያመለከቱት አቶ ጸጋ፤ ጉዳዩን አጀንዳ በማድረግ መገናኛ ብዙሀን በስፋትና በጥልቀት ሊሄዱበት እንደሚገባ አስታውቀዋል። ወቅታዊነቱም የችግሩ ስፋት እስኪቀንስ ሊቀጥል የሚችል እንደሆነ አመልክተዋል። ኮሚሽኑ ከ2008 ዓ.ም በፊት የማስተማር ፣የመከላከል ፣የመመርመርና የመክሰስ ተቋማዊ ኃላፊነትና ህጋዊ ስልጣን እንደነበረው አመልክተው፤ በአሁኑ ወቅት ተልእኮው በማስተማርና በመከላከል ላይ እንዲያተኩር መደረጉን አስታውቀዋል። የመመርመርና የመክሰስ ስልጣንና ኃላፊነት ለፖሊስና ለአቃቤ ህግ መሰጠቱንም ጠቁመዋል። በሀገሪቱ በተቋሞች መካከል ካለው በአግባቡ ያለመናበብ ባህል አንጻር ለጸረ-ሙስና ትግሉ ስኬት ኮሚሽኑ ስራዎችን በራሱ ተቋማዊ አቅም “ከመነሻ እስከ መጨረሻ” የሚሄድበት ስልጣንና ኃላፊነት ቢሰጠው የተሻለ እንደሚሆን አስታውቀዋል። በአሁኑ ወቅት ኮሚሽኑ ከተሰጠው ተልእኮ አንጻር በአብዛኛው ከምርመራና ከክስ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ስሙ እንደሚነሳ አመልክተው፤ ከምርመራና ከክስ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ከፖሊስና ከአቃቤ ህግ ጋር የተያያዙ ስለመሆናቸው አመልክተዋል። ኮሚሽኑ ቀደም ባሉት ጊዜያት በአብዛኛው ስኬታማ አለመሆኑ የሚነገረው እንደ ተቋም የተሰጠውን ተልእኮ የመወጣት ችግር ስለነበረበት ሳይሆን ከነበረው ሰፊ ጣልቃ ገብነት የተነሳ እንደነበር ገልጸው፤ በተቋሙ ላይ የነበረው ጣልቃ ገብነት ግላዊ ፍላጎትን እስከማስፈጸምና መበቃቀያ እስከመሆን የደረሰ እንደነበር አስታውቀዋል።የመገናኛ ብዙሀን የምርመራ ዘገባዎችን በስፋት በመስራት በጸረ ሙስና ትግሉ ውስጥ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚችሉ ያስታወቁት ኮሚሽኑ፤ መገናኛ ብዙሀን ይህን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ለዚህም ኮሚሽኑ የሙያ ክህሎት ስልጠናዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆኑ ለመስጠት ፈቃደኝ መሆኑን አስታውቀዋል። የምርመራ ጋዜጠኝነት ሙስናን ለመከላከል የሚደረገውን ትግል በማቅለል ከፍ ያለ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አመልክተው፤ የምርመራ ጋዜጠኝነት የኮሚሽኑን ፣ የፖሊስና የአቃቤ ህግን ስራዎች በማቅለል የሚኖረው አዎንታዊ ጠቀሜታ የጎላ ነው ብለዋል። ኮሚሽኑ ከመገናኛ ብዙሀን ጋር በቅንጅት ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ያስታወቁት ኮሚሽነሩ፤ መገናኛ ብዙሀን የሙስና ጉዳይ ችግሩ ለተወሰነ አካል የሚተው አለመሆኑን በአግባቡ ተገንዝበው አብረውት እንዲሰሩ ጠይቀዋል። በውይይት መድረኩ ላይ” ሙስናን ለመዋጋት የመገናኛ ብዙሀን ሚና “በሚል ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡት የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቄ በበኩላቸው፤ መገናኛ ብዙሀን ሙስናን በመከላከል ሂደት ውስጥ ከፍ ያለ ሙያዊ ኃላፊነት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። በቀደሙት ጊዜያት መገናኛ ብዙሀን በብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ ማለፋቸውን ያመለከቱት ዋና ዳሬክተሩ፤ በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሳይቀር በአደባባይ የምርመራ ጋዜጠኝነት ለሀገሪቱ እንደማያስፈልግ ለመናገር የተደፈረበት እውነታ እንደነበር አስታውሰዋል። ይህም ጋዜጠኞች ላይ የነበረው ጫና የቱን ያህል ከባድ እንደነበር ማሳያ ነው ብለዋል።የምርመራ ጋዜጠኝነት ከፍ ካለ ኃላፊነት የሚመነጭ ቁርጠኝነት የሚጠይቅ፣ በሙያው ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ጌታቸው፤ በስራው የሚሰማራው ጋዜጠኛም ከሚያነሳቸው ጉዳዮች ክብደት አንጻር ለአደጋ የሚያጋልጡ እንደሆኑ አመልክተዋል።ይህም ሆኖ ግን ልንገነባው ካለነው የዴሞክራሲ ስርአት አንጻር የምርመራ ጋዜጠኝነት ከፍተኛ ትኩረት የሚፈልግ በመሆኑ መገናኛ ብዙሀን ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩበት እንደሚገባ አመልክተዋል።መገናኛ ብዙሀን እስካሁን በመጡበት ሂደት ከምርመራ ጋዜጠኝነት አንጻር የጀመሯቸው ስራዎች መኖራቸውን አመልክተው፤ ስራዎች በህዝብ በሰፊው ተቀባይነት እንደነበራቸው አስታውቀዋል። እነዚህን ጅማሮች አጠናክሮ በመቀጠል ያለባቸውን ሙያዊ ኃላፊነት መወጣት የሚያስችል የተሻለ ዝግጁነት መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ከፍተኛ ባለሙያዎች እና አመራሮች ተሳትፈዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 27/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=38879
[ { "passage": "ሙስናና የሀብት ብክነትን መከላከል ሳይቻል የሀገሪቷን ሰላም አስተማማኝ ማድረግና ህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚ ማድረግ እንደማይቻል የፌዴራል የፀረ ሙስናና ስነምግባር ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ወዶ አጦ በአዳማ ከተማ በእየተካሄደ ባለው የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች አመታዊ የልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ እንደተናገሩት፤ ሙስና በልማትና በዲሞክራሲያዊ ስርአት ላይ እንቅፋት በመሆን ዜጎችን ለከፋ ድህነት ዳርጓል። እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻም፤ ሙስና ህብረተሰቡን ከፍተኛ ዋጋ ከሚያስከፍሉ ችግሮች ዋነኛው ነው። በሀገሪቷ የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ከዳር ለማድረስ የሙስና ችግሮችን ማጥፋት ለነገ የማይባል ተግባር መሆን ይገባዋል። የመንግስት መስሪያቤቶችና የልማት ድርጅቶች የበላይ ሀላፊዎች ለስነምግባር መከታተያ ክፍሎች ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ የፀረ ሙስናን ስትራቴጂን ነድፎ ወደ ተግባር መሸጋገር አለባቸውም ብለዋል፡፡ በአዳማው መድረክ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች በመቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ በዳግማዊት ግርማ", "passage_id": "3ff6d0476b97f53d765c597c75146c8a" }, { "passage": "የሰማእታት አደራን ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር ኪራይ ሰብሳቢነትና ሙስናን ከምንጩ ማድረቅ እንደሚገባ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ አስታወቁ።ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ፣የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝና የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ከሜቴ አባላት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት ) የትጥቅ ትግል የጀመረበትን የደደቢት በርሃ ትናንት ጎብኝተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ደደቢትን ከጎበኙ በኋላ እንዳስገነዘቡት የስርአቱ አደጋ የሆነውን ኪራይ ሰብሳቢነትና ሙስናን በፅናት በመታገል የሰማእታት አደራን ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር ወቅቱ የሚጠይቀውን መስዋእት መክፈል የግድ ነው።ውድ ታጋዮች ህይወት የሰጡበትን አላማ ለማሳካትና መልካም አስተዳደር ለማስፈን ጸረ ዴሞክራሲ አሰራርን በፅናት መታገል እንደሚገባም አሳስበዋል።የትግሉ ፋና ወጊ በሆነው በደደቢት በርሃ  የተገኙት ለተራ ጉብኝትና ሽርሽር ሳይሆን ” በሺህ የሚቆጠሩ ታጋዮች ህይወት የከፈሉለትን አላማ በማሳካት የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ቃል ለመግባት ነው” ሲሉ አስገንዝበዋል።የትግራይ ቆይታቸው ለየት ያለ ስሜት፣ለየት ያለ ፅናት፣ለየት ያለ የትግል ወኔና ለየት ያለ መስዋእት መክፈል እንደሚያስፈልግ ያዩበትና የተገነዘቡበት ሳምንት እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።ህወሓት ያሳለፋቸውን ውጣ ወረዶችና እልህ አስጨራሽ የትግል ጉዞ አስመልክቶ የትጥቅ ትግሉ በተጀመረበት በደደቢት በርሃ ለተገኙ የአገሪቱ ፕሬዜዳንትና የኢህአዴግ የሥራ አስፈፃሚ ኮሜቴ አባላት የድርጅቱ ነባር ታጋይ አቶ አባይ ፀሃየ፣አቶ ስብሓት ነጋና ሁለት ነባር ሲቪል አባላት ማብራሪያ ተሰጥተዋል።ከነባር ታጋዮቹ መካከል አቶ አባይ ፀሀየ “በጥቂት ተማሪዎች የተጀመረው ትግል ፍሬ አፍርቶ ህወሓት አእላፍን በማሰለፍ ለድል የበቃና እንደወርቅ በእሳት ተፈትኖ ያለፈ ድርጅት ነው” ብለዋል።አቶ ስብሓት ነጋ በበኩላቸው ህልውናውን ለማጥፋት ከተቃጣው መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ ድርጅቱ ራሱን በመከላከል አሁን ለደረሰበት ደረጃ መድረሱን ተናግረዋል።የድርጅቱ ነባር አባል አቶ ካህሳይ ገብረመድህን ከምስረታው ጀምሮ እስካሁን የህዝብ ክንፍ በመሆን በፅናት የታገሉ መሆኑን ገልጸው የላቀ የህዝብ ፍቅር ላለው ድርጅት የበኩላቸውን ድርሻ በብቃት መወጣታቸውን አስታውቀዋል።የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሽሬ ወደ ደደቢት በርሃ ሲያመሩ የየአካባቢው ሕዝብ ደማቅ አቀባበል እድርጎላቸዋል።(ኢዜአ)", "passage_id": "0ba94772d126bf2567566a2521c9d55f" }, { "passage": "አዲስ አበባ፡- የመገናኛ ብዙሃኑ ትክክለኛ መረጃዎችን ለህዝብ በማድረስ ስራ ላይ እንዲጠመዱ በኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ጥሪ አቀረቡ። የመንግስት ረዳት ተጠሪ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ መገናኛ ብዙሃኑ በምክር ቤቱም ይሁን ከአስፈፃሚ አካላት የሚተላለፉ መረጃዎችን በትክክል ከምንጫቸው በማጥራትና ፈልፍሎ በማውጣት ለህዝብ የማድረስ ስራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። እንደ አምባሳደር መስፍን ገለጻ፤ መገናኛ ብዙሃኑ በህዝቡ ውስጥ ያሉ ችግሮችን ያለማጋነንና ያለማሳነስ እንዲሁም ቦታው ድረስ በመሄድ በትክክለኛ መረጃዎች የታገዘ ስራ መስራት አለባቸው። ይህን በማድረጋቸው በአንድ በኩል መንግስት ስራውን በአግባቡ እንዲወጣ ከማገዙም በተጨማሪ በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት ኃላፊነቱን በማይወጣበት ጊዜ ህዝብ የመረጠው ምክር ቤት ተፅዕኖ እንዲፈጥር ያስችላል። ረዳት ተጠሪው፣ ‹‹የማህበራዊ ሚዲያው አገራችን ባጋጠማት ችግር ውስጥ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፣ አገሪቱ አንድነቷ እንዲጠናከር በሚያደርጉ መረጃዎች ላይ ማተኮር አለበት። በየቀኑ ህዝቡን የሚያጋጩ የተሳሳቱ መረጃዎች መተላለፍ የለባቸውም። የዜናዎቹና የመረጃዎቹ ምንጭ በአግባቡ መጣራት ይኖርባቸዋል›› ሲሉ ጠቅሰው፤ለሁሉም የመገናኛ ብዙሃንና የማህበራዊ ሚዲያ ላይ ላሉ አካላት መረጃ በጥራትና በወቅቱ እንዲሁም በትክክለኛ መንገድ ማስተላለፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል። ‹‹መገናኛ ብዙሃን ሰላማችንን ዘላቂ የሚያደርግ፣ የዴሞክራሲ ስርዓትን የሚያጎለብት፣ የአገሪቱን አንድነት የሚያጠናክርና በህዝቦች መካከል ያለውን የቆየ የባህል፣ የቋንቋና የታሪክ ትስስርና አንድነትን ይበልጥ ከፍ የሚያደርግ ስራ ላይ መጠመድ አለባቸው›› ያሉት አምባሳደር መስፍን፣ ልዩነትን ከሚሰብኩና ከሚያባብሱ ግለሰቦችና የፖለቲካ አቋም ካላቸው ጋር የሚደረግ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለአገር አይበጅም ሲሉ ገልጸዋል። ስለዚህ ሚዲያው በዚህ ላይ ትክክለኛ ስራ ቢሰራ ምክር ቤቱ ለሚያደርገው የለውጥ እንቅስቃሴው ሚናው የጎላ እንደሆነም አመልክተዋል። አዲስ ዘመን መጋቢት 10/2011በ ", "passage_id": "50203d486a1ede20b6bbedd70d6159d1" }, { "passage": "በአገሪቱ የመጣውን ፖለቲካዊ ለውጥ ተከትሎ የሚታየውን አለመረጋጋት ግምት ውስጥ በማስገባት አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው በተያዘለት መርሐግብር መካሄድ አለበት ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ አሁን ባለው ሁኔታ ምርጫው መራዘም አለበት የሚል አቋም አላቸው፡፡ በአንጻሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን በተያዘለት የጊዜ መርሐ ግብር ለማካሄድ ሽር ጉድ እያለ ይገኛል፤ በዚህ ስጋትና ተስፋ በተጋረጠበት ምርጫ 2012 የመገናኛ ብዙኃን ሚና ምን ሊሆን ይገባል? ደበበ ኃይለገብርኤል የህግ ቢሮና የናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ የተባሉ ተቋማት “የአገራችን መገናኛ ቡዙኃን ሚና ለዳበረ ዴሞክራሲያዊ ሂደት በኢትዮጵያ” በሚል በቅርቡ ከስድስት ብሮድካስት የመገናኛ ብዙኃን ላይ 88 ዘገባዎችን በናሙናነት በመውሰድ የዳሰሳ ጥናት አካሂደው ነበር፡፡ ጥናቱ በአገሪቱ የመጣውን ፖለቲካዊ ለውጥ ተከትሎ የተከሰቱ ግጭቶችን የሚዲያ ተቋማት በምን መልኩ ዘገቡት የሚለውን ያሳየ እንደነበር በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ትምህርት ክፍል መምህር ፍሬዘር እጅጉ ይናገራሉ። መምህር ፍሬዘር እንደገለፁት፤ የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው መገናኛ ብዙኃኑ የግጭት ዘገባዎችን ሲዘግቡ ወገንተኝነት፣ ስሜታዊነትና ጽንፈኝነት የሚታይባቸው ነበሩ። እንዲሁም ለተፈጠሩ ችግሮች መፍትሄ ከመጠቆም አንጻር አሉታዊምና አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንደነበራቸው አመላክቷል፡፡ በተለይ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱና ተቋማዊ መፍትሄ እንዲያገኙ አቅጣጫ ከመስጠት በተጨማሪ መንግሥትን ተጠያቂ በማድረግና ለዜጎች ወቅታዊ መረጃዎችን በመስጠት በጎ የሆነ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ በጥናቱ ተመላክቷል። በአንጻሩ የሚፈጠሩ ችግሮችን ተባብሮ በመስራትና በመቻቻል መፍታት ያስፈልጋል በሚለው ላይ በስፋት እንደመፍትሄ ወስደው እንዳልሰሩ በጥናቱ መመላከቱን የገለፁት መምህር ፍሬዘር ገልጸው፤ ከዚህ አንጻር መገናኛ ብዙሃኑ ስለትናንትና ግጭት ዘገባዎቻቸው ሲያነሱ፤ እርቅና አንድነትን በሚያመጣ መልኩ አላወሱትም ብለዋል። ከዚያ ይልቅ ውስጣዊ ክፍፍልን በሚፈጥር መልኩና ትናንት በጭቆና ውስጥ ነበርን የሚል ብያኔ በመስጠት የተጠመዱበት ሁኔታ ነበር ይላሉ። በአጠቃላይ ጥናቱ እንደሚያሳየው መገናኛ ቡዙኃኑ ገለልተኛ ተቋም ሆነው ተወዳዳሪና ተገዳዳሪ የሆኑ የተለያዩ አመለካከቶችን ባለማስተናገዳቸው የተለያዩ ቡድኖች፣ አንጃዎች፣ ብሄሮችና ፖለቲካ ፓርቲዎች መታገያና ፕሮፓጋንዳ መንዣ ሜዳ መሆናቸውንና የአገርን ህልውናና የህዝብን ጥቅም እንዳላስቀደሙ በዕለት ተዕለት ትግበራቸው አሻራቸው በግልጽ መቀመጡን ገልጸዋል። መምህር ፍሬዘር እንደገለፁት፤ አንድ ምርጫ ግልጽ፣ ተዓማኒና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ እንዲካሄድ የአንበሳውን ደርሻ ከሚጫወቱ ተቋማት መካከል የመገናኛ ቡዙኃን ሚና አይተኬ ነው። መገናኛ ብዙኃኑ በምርጫ ወቅት በብዙ መልኩ አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ቢችሉም፤ በምርጫው የመጀመሪያ ግባቸው ገለልተኛ ሆነው ከጽንፈኝነትና ስሜታዊነት ተላቀው ትክክለኛና አስተማማኝ መረጃን ለዜጎች በማቅረብ መረጃ ያነገበ ዜጋ መፍጠር ይገባቸዋል። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ፤ የመገናኛ ቡዙኃ ን ለህብረተሰቡ ያላቸውን ወገንተኝነትና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ያላቸውን ቁርጠኝነት ከሚያሳዩበት ወርቃማ አጋጣሚዎች ግንባር ቀደሙ የምርጫ ወቅት ነው ይላሉ። ስለዚህ ምርጫው ፍትሃዊ፣ ነጻና ግልጽ ሆኖ ሀሳቦች በነጻነት ተወዳድረው ህዝብ ያመነበት መንግሥት ወደ ስልጣን እንዲመጣ፤ የመገናኛ ብዙኃኑ ከወገንተኝነት እራሳቸውን አላቀው፣ የሚነቀፈውን በመንቀፍ የሚበረታታውን በማበረታታት፣ ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዮችን ከሚመለከተው አካል ተገቢውን ማብራሪያ በመጠየቅ ለማህኅበረሰቡ ግልጽ በማድረግ ማኅበረሰቡ ምርጫው ላይ እምነት እንዲኖረው እና በነቂስ ወጥቶ እንዲመርጥ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ይናገራሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በካሪኩለም እና ኢንስትራክሽን ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር እንጉዳይ አደመ በበኩላቸው፤ አሁን በአገሪቱ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የመገናኛ ብዙኃኑ በሁለት ጎራ የቆሙ ሲሆን፤ በአንድ ወገን የቆሙት መንግሥት ምንም አይነት ህፀፅ እንደሌለበት በጎ በጎውን ያወራሉ። በሌላኛው ጽንፍ የቆሙት ደግሞ እንከንን ብቻ በማራገብ የመከፋፈል ሥራ ይሠራሉ። ስለዚህ መጪውን ምርጫ በተመለከተ በሁለት ጽንፍ የቆሙት የመገናኛ ብዙኃን ተቀራርበው በመስራት ፍታሃዊ ሆነው የምርጫ ሂደቱን መዘገብ አለባቸው። በዘገባውም የአገርን ህልውና የህዝብን ጥቅም ማስቀደም ይገባቸዋል ይላሉ። በሚዘግቡበት ወቅትም ጥላቻንና ግጭትን በሚያጭር ሁኔታ ሳይሆን ህዝብና ህዝብን በሚያቀራርብ መልኩ መዘገብ እንደሚገባቸው ፕሮፌሰሯ አሳስበዋል። በአገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት\nእንዲጎለብትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን\nመገናኛ ቡዙኃኑ ኃላፊነት\nእንደተጣለባቸው የሚናገሩት መምህር\nፍሬዘር ፤ በምርጫ\nሂደቱ አጨቃጫቂ ጉዳዮች\nሲኖሩ እራሳቸውን ገለልተኛ አድርገው ነገሩን ከስር ከመሰረቱ መርምሮ እውነታውን ለህዝብ በማሳወቅ እና አለመግባባቶች በሰከነ ሁኔታ የሚፈቱበትን መንገድ ማመላከት አለባቸው ይላሉ። መገናኛ ቡዙሃኑም በራቸውን ለአንዱ ክፍት ለሌላው ዝግ ሳያደርጉ ፤የሁሉንም የፖለቲካ ሀይሎች ሀሳብ ማስተናገድ የሚጠበቅባቸው መሆኑን መምህር ፍሬዘር ይናገራሉ። የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ በበኩላቸው፤ የመገናኛ ብዙኃን ከምረጡኝ ቅስቀሳ ጀምሮ ምርጫው ተጠናቆ በህዝብ የተመረጠ መንግሥት ወደ ስልጣን እስኪመጣ ድረስ ያለውን ሂደት ደረጃ በደረጃ ለኅብረተሰቡ መረጃ በመስጠት ግንዛቤ እንዲኖረው ማድረግ አለባቸው። በሌላ በኩልም ከዚህ ቀደም ምርጫ ላይ ተሳትፈው የማያውቁና ወደ መራጭነት የዕድሜ ክልል ለሚቀላቀሉ ወጣቶች ስለምርጫ ስርዓትና ህግ ግንዛቤ መፍጠር ይጠበቅባቸዋል። በምርጫ ቦርድና በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አዋጅ አንቀጽ 44 እና 43 ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው፤ በምርጫ ወቅት የመገናኛ ብዙኃኑ ነጻ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ አምዶችን እየመደቡ እጩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀሳቦቻቸውን ለኅብረተሰቡ እንዲሸጡ ድምጽ ሆነው ማገልግል አለባቸው። ባለፉት አምስት አገራዊ ምርጫዎች ላይ በከፍታም በዝቅታም ውስጥ እያለፉ የተሻለ የምርጫ ዘገባ በመስራት የተሻለ ምርጫ እንዲካሄድ ልምድ ያዳበሩ አንጋፋ መገናኛ ብዙሃን መኖራቸው ይታወሳል። ከምርጫው ከኋላ እየተከተሉ አቃቂር ማውጣትና ጉድለቶቹን ማራገብ ሳይሆን፤ ከፊት እየቀድሙ አቅጣጫ እየሰጡ ሂደቱን መምራትና አደናቃፊ ሁኔታዎችን ከወዲሁ በመቅረፍ ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲካሄድ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ እንደሚገባም ዶክተር ጌታቸው አሳስበዋል። ምሁራኑ እንደሚሉትም፤ መገናኛ\nቡዙሃኑ በምርጫ ሂደቱ\nበከፍተኛ የኃላፊነት ካልዘገቡ\nትናንሽ ግጭቶች ጎልተው\nወደ ቀውስ በመቀየር\nአገር ሊናጋ የሚችልበት\nእድል ሰፊ ነው።\nበአንጻሩ ምርጫው ተቋማቱ\nለአገርና ለህዝብ ጥቅም\nዘብ መቆማቸውን የሚያሳዩበት\nወርቃማ ዕድል በመሆኑ፤\nይህንን አደራ በከፍተኛ\nየኃላፊነት ስሜት መወጣት\nከቻሉ የኢትዮጵያን የፖለቲካ\nታሪክ በመቀየር የዴሞክራሲያዊ\nስርዓት ግንባታ ዋልታን\nየሚተክሉበት አጋጣሚ ላይ\nእንደሚገኙ ምሁራኑ ይናገራሉ።አዲስ ዘመን ታህሳስ 29/2012ሶሎሞን በየነ", "passage_id": "2826b80938ce18817a5d9749ddf1521e" }, { "passage": " -በሃገሪቱ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የመገናኛ ብዙሃን ወቅታዊና ፈጣን መረጃ ለተጠቃሚው በመስጠት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው  የመንግስት  ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ አሳሰቡ።ለሶስት ቀናት በሃዋሳ ከተማ  ሲካሄድ የቆየው የክልል ኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ ተቋማት አመታዊ የጋራ ፎረም ትናንት ተጠናቋል፡፡ሚኒስትሩ በፎረሙ ማጠቃላያ ላይ እንደገለጹት መገናኛ ብዙሃን በፀረ ድህነት ትግሉ የተገኙ ስኬቶችን ብቻ ሳይሆን ድክመቶችን በመጠቆም እንዲስተካከልና የተሻለ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ወቅታዊና ፈጣን  መረጃ ለህዝብ ማድረስ ይገባቸዋል፡፡ህዝቡ የሚያነሳውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመንግስት በማቅረብና  የሚሰጠውን ምላሽ መረጃን ፈጥኖ በማድረስ ሃላፊነታቸውን በብቃት መወጣት   አለባቸው፡፡መገናኛ ብዙሃን ያላቸው ተደራሽነት ከፍተኛ በመሆኑ ስኬትን መሰረት ባደረገና የህዝብን ጥያቄ መመለስ ባስቻለ መልኩ  ማህበራዊ ድረ ገፆችን በመጠቀም ጭምር ጠንካራ መልዕክቶች እንዲተላለፉ  ማድረግ እንዳለባቸው  አሳስበዋል።የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ስራዎችን በመፈተሽና ድክመቶችን በማረም የፌዴራል ስርዓቱን ለማጠናከር በትኩረት መስራት እንደሚገባም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡\" ማንነትን ያከበረች ኢትዮጵያን  ለመመስረትና አንድ ጠንካራ የፌዴራል ስርዓት ለመገንባት ሚዲያው ወጥ  የሆነ መልዕክት በመቅረጽ  በጋራ ማስተላለፍ አለበት\" ሲሉም ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡በፎረሙ ላይ ከሁሉም ክልሎች እና በፌዴራል ደረጃ ካሉ የኮሙዩኒኬሽንና የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት  የተወጣጡ የስራ ሃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል-ኢዜአ ፡፡", "passage_id": "66b5a28fabd2806ba01d87c9b5d9d7d7" } ]
096056600d57553cead695a25fc307d6
42a89dae8ef854cce06d8e6ee0b25d01
የበቆሎ ምርት በሄክታር ከ42 ኩንታል በላይ መድረሱ ተገለጸ
ሰላማዊት ውቤአዳማ፦ በአሁኑ ወቅት ከሦስት ዋና ዋና የግብርናው ዘርፍ መርሐ ግብሮች አንዱ በሆነው የድህነት ቅነሳ የበቆሎ ምርትን በሄክታር 42 ኩንታል ማድረስ መቻሉ ዓለም የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ ጥሩ ሂደት ላይ መሆናችንን እንደሚያሳይ ተገለጸ። የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ ከትናንት በስቲያ በአዳማ ከተማ ለግማሽ ቀን በተካሄደና አጠቃላይ ግብርናው ያለበትን ሁኔታ የዳሰሰ ፓናል ውይይት ላይ እንዳስታወቁት፤ ባለፉት 20 ዓመታት የበቆሎ ምርት ከፍተኛ ዕድገት አሳይቷል።ዕድገቱ በአንደኛውና በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን ጭምር የተገኘ ነው ያሉት ዶክተር ማንደፍሮ፤ እስከ አምና ድረስ በሄክታር የተገኘው 42 ነጥብ 4 ኩንታል መሆኑንም ጠቅሰው፤ በዚህ ዓመት ሲጨመር ደግሞ በሄክታር የሚገኘው የበቆሎ ምርት ከዚህ ከፍ ሊል እንደሚችልም ጠቁመዋል።የምርት ዕድገቱ ምን ያህል ለድህነት ቅነሳ ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነ የሚያመለክት መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው በዓለም ላይ በሄክታር በአማካኝ ያለው የበቆሎ ምርት ዕደገት 58 ኩንታል መሆኑንም ተናግረዋል።እንደ ሀገር በሄክታር የደረስንበት 42 ነጥብ 4 ኩንታል ከዓለም ጋር የሚቀራረብና ዓለም የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ በዚህ ሰብል ጥሩ ሂደት ላይ ነን ማለት የሚያስችል መሆኑን ዶክተር ማደፍሮ ጠቁመው፤ የስንዴ ምርትም ባለፉት አስር አመታት በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉንና አሁን ላይ ከራሳችን አልፈን ወደ ውጪ ለመላክ በዘመቻ መርሐ ግብር መልክ እየሰራን ነው ብለዋል። ‹‹የአሁን ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ መርሐ ግብር የድህነት ቅነሳን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም አመጣጥኖ የሚሄድ ነው›› ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ግብርና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ትልቅ ፋይዳ ያለው በመሆኑ የተጀመረውን ድህነት ቅነሳ ፕሮግራም ተግባራዊ ለማድረግ ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም ጠቁመዋል።የድህነት ቅነሳ መተግበር ሲጀምር የነበረው አጠቃላይ አገራዊ የምርት መጠን 69 ሚሊዮን ኩንታል ብቻ ሲሆን በሁለተኛው 181 ሚሊዮን ኩንታል፣ በሦስተኛው ደግሞ 270 ሚሊዮን ኩንታል መድረሱን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ዘንድሮ ደግሞ 414 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚታሰብና ይህም የምርት አሰባሰብ ሂደቱ በየጊዜው በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መሄዱን ማሳያ ነው ብለዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 27/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=38881
[ { "passage": "በዘንድሮው የመኸር ወቅት 19 ሚሊየን ኩንታል የሰብል ምርት እንደሚጠበቅ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኢዶሳ ጊቢሳ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት ከምርት ስብሰባ በፊት በተሰሩት ግምገማዎች መሰረት ከማሽላ፣ ባቄላና ሰሊጥ ሰብሎች ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ27 በመቶ ብልጫ ያለው ምርት ይጠበቃል፡፡እንደ አቶ ኢዶሳ ገለፃ ክልሉ ከ790,000 ሄክታር በሚሆን መሬት 20 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ አቅዷል፡፡የግብርና ቢሮው የክልሉን ምርታማነት ለማሳደግ ለአምራቾች ሥልጠናዎችን ጨምሮ ከፍተኛ እገዛ ሲያደርግ  እንደነበርና ይህም ውጤታማ እንዳደረገው ታውቋል፡፡ባለፈው ዓመት በድርቅ ተጎድቶ የነበረውን የእርሻ ቦታ አስፈላጊውን የግብርና ግብዓት በማሟላት በዚህ የመኸር ወቅት ከባለፈው ዓመት በ4.5 በመቶ የበለጠ የእርሻ መሬት በሰብል ምርት  የተሸፈነ መሆኑ ተገልጿል፡፡ባለፈው ዓመት በተከሰተው ድርቅ በአጠቃላይ 10.2 ሚሊየን የሚሆን ህዝብ ለድርቅ ተጋላጭ እንደነበረ አቶ ኢዶሳ አስታውሰው፣ በክልሉ ደግሞ 11 ወረዳዎች የድርቁ ተጋላጭ እንደነበሩም ጠቁመዋል፡፡በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዘንድሮ ከሚጠበቀው ምርት የ13 ሚሊየን ኩንታል ምርት ከፍጆታ አልፎ ለገበያ ይቀርባል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከምግብ አቀነባባሪ ፋብሪካዎች ጋር የገበያ ትስስር ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል፡፡ትርጉም -ሰለሞን ተስፋዬ ", "passage_id": "8a08203e8ae99605e4f07586c972b92b" }, { "passage": "በኦሮሚያ ክልል በተያዘው የመኸር ወቅት ከ4 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን የክልሉ የግብርናና ተፈጥሮ ሐብት ቢሮ ገለጸ፡፡የቢሮው የሰብል ልማትና የዕፅዋት ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ሂርጳ ከዋልታ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት በተያዘው የመኸር ወቅት በ6 ነጥብ 06 ሚሊየን ሄክታር ከተዘራው ሰብል 29 በመቶው ለመሰብሰብ እንደደረሰና እስካሁን ከ4 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ከዋና ዋና ሰብሎች ተሰብስቧል፡፡ከተሰበሰበው ምርት 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ያህሉ የስንዴ ምርት እንደሆነና የቦሎቄ እንዲሁም የማሾ ምርቶች ሙሉ በሙሉ መሰብሰባቸውን አቶ ደጀኔ አክው ገልፀዋል፡፡ቢሮው ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ባደረገው ጥረት 3 ሚሊየን 533 ሺህ 414 ኩንታል ማዳበሪያ፣ 581 ሺህ 898 ኩንታል ምርጥ ዘር እንዲሁም 949 ሺህ 616 ሊትር ፀረተባይና ፀረአረም ኬሚካል መጠቀሙን አቶ ደጀኔ ተናግረዋል፡፡በክልሉ ተከስቶ የነበረው የግሪሳ ወፍ በቁጥጥር ስር በመዋሉና የአሜሪካን መጤ ተምች እንዲሁም የዝናብ እጥረት በምርታማነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኗቸው ከፍተኛ ባለመሆኑ በምርታማነት ላይ የጎላ ቅነሳ እንደማይከሰት ይጠበቃል ተብሏል፡፡ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ ምርት እንዳይበላሽ በወቅቱ እንዲሰበሰብ፣ የምርት ብክነትን መቀነስ እንዲሁም ምርትን ወደ ገበያ በማውጣት ሕብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ አርሶአደሩ ይበልጥ መስራ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡በተያዘው የመኸር ወቅት በክልሉ ከለማው የ6 ነጥብ 06 ሚሊየን ሄክታር መሬት 184 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን ዋልታ ሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት ዘግቧል፡፡ ", "passage_id": "f0767fe34ae026c38ce9f07dac25f960" }, { "passage": "በሰሜን ሸዋ ዞን ከ760 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት በመስኖ ለምቶ ለገበያ መቅረቡን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለጸ፡፡ባሕር ዳር፡ ጥር 07/2013 ዓ.ም (አብመድ) በሰሜን ሸዋ ዞን በመጀመሪያው ዙር በለማው የመስኖ እርሻ ከ91 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መሆናቸውን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታውቋል። በመኸር እርሻ ልማቱ የጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተት፣ ከፍተኛ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ፣ በረዶ እና የበርሃ አንበጣ የምርት መቀነስ እዲፈጠር አድርገው ነበር፡፡በዞኑ ግብርና መምሪያ የአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ አጠቃቀም የሥራ ሂደት ተወካይ ድፌ ወንድማገኝ እንደተናገሩት በተፈጥሮ አደጋዎቹ የተፈጠረውን የምርት ቅናሽ ለማካካስ የተጠናከረ የመስኖ እርሻ ልማት እየተከናወነ ነው።በመስኖ ወደ 28 ሺህ 250 ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል። ለዚህም ወደ 36 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እና 5 ሺህ 718 ኩንታል የምርጥ ዘር ግብዓት እየቀረበ መሆኑን አመላክተዋል። በመጀመሪያው ዙር የመስኖ ልማትም 23 ሺህ 187 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን የአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ አጠቃቀም የሥራ ሂደት ተወካዩ ተናግረዋል። ይህም ወደ 82 በመቶ አፈጻጸም እንዳለው ታውቋል።ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ 760 ሺህ 508 ኩንታል ምርት ከለማው መስኖ ለገበያ ቀርቧል። አቶ ድፌ እንዳሉት በዞኑ በመስኖ በስፋት የሚለማው የአትክልትና ፍራፍሬ አይነቶች ናቸው። እንደ ሽንኩርት፣ጥቅል ጎመን፣ ካሮት፣ ቀይሥር፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ቡና፣ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ብርቱካን፣ ፓፓያ፣ ሙዝ እና የመሳሰሉት የግብርና ምርቶች በስፋት ይመረታሉ። ገብስና ሥንዴ በመስኖ ከሚለሙት አዝዕርት መካከል ሲሆኑ ኢትዮጵያ ከውጪ ሀገራት የምታስገባውን የስንዴ ምርት ለመተካት ተስፋ የተጣለበት የቆላ ስንዴ የመስኖ ልማትም በዞኑ ተጀምሯል።በሁለተኛው ዙር የመስኖ ልማት ወደ 13 ሺህ ሄክታር ለማልማት ታቅዷል። እስካሁንም 2 ሺህ 200 ሄክታር ለምቷል ብለዋል አቶ ድፌ። በመስኖ ልማቱ 3 ሚሊዮን 396 ሺህ 512 ኩንታል ምርት ነው ለማግኘት የታቀደው። በዚህም 111 ሺህ 382 አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።ቀደም ብሎ በአርሶ አደሮች ዘንድ የመስኖ አጠቃቀም እንዲሁም የግብርና ግብዓት የመጠቀም ልምድ አናሳ እንደነበር አስታውቀዋል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ሰፊ የግንዛቤ ፈጠራ በመሠራቱና የአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት እየጨመረ በመምጣቱ የመስኖ ልማቱም ሆነ የግብዓት አጠቃቀሙ እያደገ መሆኑን ተናግረዋል።ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር ውኃ መገኛ ነው። ከዚህ በፊት በተሠራ የዳሰሳ ጥናት ወደ 90 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ እንደሚለማ ተገልጿል።የመስኖ ልማቱን ለማሳደግ ከደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ጋር በመነጋገር ጥናት ለመሥራት እንቅስቃሴ ተጀምሯል ብለዋል። በጥናቱ ውጤት ላይ በመመስረትም በዞኑ የተሻለ የመስኖ እርሻ ለደማት እንዲኖር በትኩረት ይሠራል ብለዋል።", "passage_id": "4029061d383eb62df8f43db41f9f0ee1" }, { "passage": "በኩታ ገጠም ማሳ በመዝራትና የግብርና ግብዓት በመጠቀም በምርትና ምርታማነታቸው ላይ ውጤት እያመጡ እንደሆነ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን የኤጀርሳ ለፎ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ።አርሶ አደሮቹ ይህንን ያሉት የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ጣይባ ሀሰን የተመራ ቡድን በወረዳው የሚገኙ በኩታ ገጠም ማሳ የተዘሩ የተለያዩ ሰብሎችን፣ የአርሶ አደር ማሠልጠኛ እና ምርት ማላመድ ሥራዎችን በጎበኙበት ወቅት ነው።በግብርና ባለሙያዎች በሚሠጣቸው ሥልጠና መሠረት የተለያዩ የግብርና ምርት ማሻሻያ ዘዴዎችን መተግበራቸው ውጤታማ እያደረጋቸው እንደሚገኝ አመልክተዋል።ከዚህ በፊት በሄክታር 26 ኩንታል ብቻ ያገኙ የነበሩት አርሶ አደሮቹ እስከ 58 ኩንታል የሚደርስ የስንዴ ምርት እያገኙ እንደመጡ ጠቁመዋል።ከዚህም በተጨማሪ በዚህ ዓመት በወረዳው ለመጀመሪያ ጊዜ በኮምባይነር የስንዴ ምርት መሰብሰብ ጀመረዋል።ሌላው አርሶ አደር ሙለታ ገቢሳ በበኩላቸው ጤፍን በመስመር የመዝራትና ስንዴን በቢቢኤም ማረሻ እንዲሁም የተለያዩ የአፈር መዳበሪያ በጠቀም ምርትና ምርታነታቸው እየጨመረ መሆኑን ይገልጻሉ።በወረዳው የግብርና ባለሙያ የሆኑት አቶ ገመቹ ቡልቶ በበኩላቸው በአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላት ምርጥ ዝርያዎችን የማላመድ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።የዝርያዎቹን ውጤታማነት በማየት ወደ አርሶ አደሩ እንደሚሠራጭም ገልጸዋል።የጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ሽንብራ እና የሌሎች ሰብሎች ምርጥ ዘር ከአየር ንብረቱና ከአካባቢው አፈር ጋር የማላማድ ሥራዎች በማሠልጠኛ ማዕከላቱ እንደሚከናወን ጠቁመዋል።  በኩታ ገጠም ማሳ የመዝራትና እርሻውን የማዘመን ስራ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ለማዳረስ እየተሰራ እንደሚገኝም የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ጣይባ ሀሰን ተናግረዋል።አርሶ አደሩ የሚቀርብለትን የቴክኖሎጂ አማራጭ ተቀብሎ በመተግበሩ ምርታማነቱን እያሳደገ እንደሆነ ተናግረዋል።አርሶ አደሩ ምርታማነቱን በማሳደግ ኑሮውን ከማሻሻል ባለፈ ለአገር ኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የሚያስችለው የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንዲያገኝ ስትራቴጂ ተቀርጾ እንደሚሰራ ወይዘሮ ጣይባ ጠቁመዋል።", "passage_id": "56d08552abd526ba2e47b60eea5baeee" }, { "passage": ". 14 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ በመስኖ እየለማ ነው::አዲስ አበባ፡- የሕዝቡን ፍላጎት ለማሟላትና በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በሃገር ውስጥ ምርት ለመተካት በቆላማ አካባቢዎች ስንዴን በ14 ሺህ አንድ መቶ ሄክታር መሬት በመስኖ የማልማት ተግባር እየተከናወነ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ኡመር ሁሴን በቆላ ስንዴ ልማትና በሌሎች የግብርና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትናንት በመስሪያ ቤታቸው በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት፤ ሚኒስቴሩ የሕዝቡን ፍላጎት ለማሟላት ከውጭ የሚያስገባውን ስንዴ ማስቀረት ብቻ ሳይሆን ስንዴን በብዛትና በጥራት በማምረት ወደ ውጭ ለመላክ ራዕይ ይዟል፡፡ ለዚህም በቆላማ አካባቢዎች ስንዴን በዘመናዊ መስኖ ታግዞ የማልማት ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህን ራዕይ ለማሳካትና ከባለድርሻ አካላት ጋር በባለቤትነት ስሜትና በጠንካራ ቅንጅት ዘንድሮ 32 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እየተሠራ ነው፡፡ እስካሁን ባለው ሂደትም 14 ሺህ አንድ መቶ ሄክታር መሬት የቆላ ስንዴ በመስኖ እየለማ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ ከእነዚህ ውስጥ 11 ሺህ አንድ መቶ ሄክታር የሚሆነው ለምግብነትና ለፋብሪክ፣ ሶስት ሺህ ሄክታር የሚሆነው ደግሞ ለዘር መዘጋጀቱን አብራርተዋል።በአተገባበሩ የቦታ ዝግጅትና አቅርቦት እንዲሁም የዘር ብዜት ችግሮች መሰናክል መሆናቸውን ያስገነዘቡት ሚኒስትሩ፣ ይሁንና አፈፃፀሙ በሁለትና ሶስት አመታት ውስጥ ስንዴን ከውጭ ማስገባትን ለማስቀረት መሰረት በመጣል ረገድ ስኬታማ መደላድል እንደሚፈጠር አመላካች ስለመሆኑንም አብራርተዋል። በመስኖ ልማቱ ላይ የሚስተዋለውን የሃይል አቅርቦት ለማቃለልም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።‹‹በመኸር ምርት\nአሰባሰብ ረገድም ዘንድሮ\nበምርት ከተሸፈነው ከ13\nነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር\nመሬት ውስጥ የደረሰው\n12 ነጥብ 5 ሚሊዮን ወይንም\n93 በመቶ ነው›› ያሉት\nሚኒስትሩ፣ ከዚህም ውስጥ  ምንም እንኳን ከክልል ክልል ልዩነት ቢኖርም 9 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታሩ ወይንም 78 በመቶው ምርት መሰብሰቡንም አብራርተዋል።ቀሪው በቀጣይ ሁለት ሳምንታት እንዲሰበሰብ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው በበርሃ አንበጣና ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ በምርት ብክነት ላይ የደረሰው ጉዳት ዳሰሳዊ ጥናት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የጥናቱ ውጤትም ወደፊት እንደሚገለጽ አስታውቀዋል።የምርት ብክነትን በመከላከል ረገድ በአሰባሰብ ወቅት እስከ 20 በመቶ ምርት እንደሚባክን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ ይህን በመከላከል ረገድም የሜካናይዜሽን አሰራርን የማጎልበት፣ ለአርሶ አደሮች ስልጠና የመስጠትና የምርት ማከማቻ ቦታዎችን የማስፋት ስራዎች በመከናወን ላይ ስለመሆኑ አብራርተዋል። መንግስት የሜካናይዜሽን መሳሪያዎችን ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ መወሰኑ የምርት ብክነትን ለመቀነስና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ መነሳሳትን እየፈጠረ መሆኑንም ገልፀዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 14/2012ታምራት ተስፋዬ ", "passage_id": "2841f94ba4c2100c233e1ec02b089eb6" } ]
fca97ebd842c21e6b46c5d9e339a996e
f091d2faa7a83111f6e1093cb7c62f16
አጫጭር ዜናዎች
የደብረ ብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል በርካታ ምርጥ አትሌቶችን የማፍራት ጉዞ የደብረ ብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል በአማራ ክልል ከሚገኙ ዞኖች የመመልመያ መስፈርቱን አሟልተው የተገኙ አትሌቶችን ወደ ማዕከሉ በማስገባት ማሰልጠን የጀመረው በ2002 ዓ.ም። ማዕከሉ እስከአሁንም ከ360 በላይ አትሌቶችን አሰልጥኖ አብቅቷል። የማዕከሉ ዋና ዓላማ በክልሉ የተሻሉና ወደ ፊትም የተደራጀና ሳይንሳዊ ስልጠና ቢያገኙ ውጤትማ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ የሚታመንባቸውንና የማዕከሉን የመምረጫ መስፈርት አሟልተው የተገኙ ወጣቶችን እያሰለጠነ ክልሉን እና ሀገርን የሚወክሉ አትሌቶችን ማፍራት ነው። ይህንንም መሰረት በማድረግ ማዕከሉ ስልጠና መስጠት ከጀመረበት ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ተከታታይ ዓመታታ በተሰጠ ስልጠና በርካታ ምርጥ አትሌቶችን ማፍራት መቻሉ ተነግሯል። በማዕከሉ 360 አትሌቶች ስልጠናውን መውሰዳቸው የተገለጸ ሲሆን ከዚህ ውስጥም 117 አትሌቶች ወደ ከፍተኛ ክለቦች ገብተዋል፤ 49 አትሌቶች ወደ ብሄራዊ ቡድኑ መግባት ችለዋል፤ 16 አትሌቶች ሀገራቸውን በመወከል በተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግበዋል ተብሏል። የአውሮፓ ቡድኖች እስከ 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ ሊያጋጥማቸው ይችላል ተባለ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች የሚጫወቱ የእግር ኳስ ቡድኖችን እስከ 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ድረስ ሊያሳጣቸው እንደሚችል ተገምቷል። ነገሮችን ለቡድኖቹ ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው ደግሞ ሊጎቹ እንደምንም ተብሎ ቢጠናቀቁ እንኳ ይህን ኪሳራ ማስቀረት አለመቻላቸው ነው። ሊጎቹ በታሰበላቸው ጊዜ መጠናቀቅ የማይችሉ ከሆነ ደግሞ ኪሳራው እስከ 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ከፍ ሊልም ይችላል። የጀርመን ቡንደስሊጋ ትናንት የተጀመረ ሲሆን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ደግሞ በሚቀጥለው ወር አጋማሽ አካባቢ እንደሚጀመር ይጠበቃል። ፈረንሳይ ደግሞ ሊጓን ያቋረጠች ሲሆን የደረጃ ሰንጠረዡን ሲመራ የነበረው ፓሪስ ሴይንት ጀርሜይን አሸናፊ ተብሎ ዋንጫውን አንስቷል። በመላው አውሮፓ የሚገኙ ሊጎችም ይህን ያክል ገንዘብ ላለማጣት ሲሉ ሊጎቻቸውን በተቻለ መጠን ለማስጀመር እየተሯሯጡ ይገኛሉ። ነገር ግን በዚህ መሀል የተጫዋቾች ደህንነት እንዳይረሳ የሚያሳስቡም አልጠፉም።አዲስ ዘመን ግንቦት 11/2012
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=32684
[ { "passage": "የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት (አውስኮድ) አስቀድሞ በኢትዮዽያ ብሔራዊ ሊግ በኋላም በከፍተኛ ሊግ ውድድር ውስጥ ጥሩ ተፎካካሪ በመሆን ቢታወቅም እንዳለው የተጫዋች ጥራት እና ከፍተኛ የገንዘብ አቅም ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደግ ተስኖታል ።በ2009 ላይ በከፍተኛ ሊጉ በነበረው ተሳትፎ በምድብ ሀ አምስተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው አማራ ውሀ ስራ ለዘንድሮ የውድድር አመት በርካታ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ የሚገኝ ሲሆን ከመስከረም መጀመርያ አንስቶ በዛው በባህርዳር ከተማ ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል።ክለቡ ባሳለፍነው የውድድር አመት በነበረው ጉዞ ውስጥ እንደ ክፍተት የተመለከተው ወደ ክለቡ የሚመጡ ተጨዋቾች በተለያዩ ክለቦች ተዟዙረው በመጫወት የሚታወቁ እና በፍላጎት የማይጫወቱ መሆናቸው መሰረታዊ ክፍተት ሆኖ እንዳገኙት ክለቡ አመራሮች ይናገራሉ። ዘንድሮ በነበረው የዝውውር እንቅስቃሴም ካለፈው ትምህርት በመውሰድ የጨዋታ ፍላጎታቸው የተሻሉ ተጫዋቾች ወደ ክለቡ እንደመጡ ተገልጿል፡፡በከፍተኛ ሊግ በ2010 የውድደር አመት በምድብ ሀ የተመደበው አውስኮድ የመጀመርያውን ጨዋታ የቀድሞ ስያሜውን ኢት ውሃ ስፖርት በመቀየር በአዲስ ስያሜ የሚጠራው ኢኮስኮን ባህርዳር ከተማ ላይ የሚገጥም ይሆናል ።", "passage_id": "3615378b1dba2b933b4e41fe5b0bc2a8" }, { "passage": " ደደቢት የውጭ ዜጋ አሰልጣኝ ለመቅጠር እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ክለቡ የፖላንድ እና የፔሩ ዜግነት ያላቸው አሰልጣኞችን ሲቪ እየተመለከተ ሲሆን ከሁለቱ አንዱ የክለቡን ፍላጎት የሚያሟሉ ከሆነ ለሰማያዊው ጦር ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ክለቡ ከአሰልጣኝ ቅጥር ጋር በተያያዘ ሃገር ውስጥ ያሉ አሰልጣኞችን ሊቀጥር የሚችለው ከውጭ ሊያመጣቸው ያቀዷቸው አሰልጣኞች ካልተሳኩ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ እ4ስካሁን የ2 የሃገር ውስጥ አሰልጣኞችን ወረቀት እየተመለከቱ እንደሆነም ታውቋል፡፡ክለቡ ከተጫዋቾች ዝውውር ጋር በተያያዘ እስካሁን ተጫዋቾችን ማስፈረም እንዳልጀመረ ከክለቡ ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ደደቢት ነገ እና ረቡእ የተጫዋቾቹን ኮንትራት የማደስ እንቅስቃሴ እንደሚጀመር የተገለፀ ሲሆን የወጣቱ ተከላካይ አስቻለው ታመነን ኮንትራት ለማራዘም በቃል ደረጃ ከስምምነት መድረሳቸው ታውቋል፡፡ ከራምኬል ሎክ ጋር ስሙ በከፍተኛ ደረጃ የተያያዘው ደደቢት ከተጫዋቹ ጋር እስካሁን ምንም ድርድር እንዳላደረገም አስታውቋል፡፡", "passage_id": "342a6469184c0fa8471870857c585901" }, { "passage": "የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከቦትስዋና ጋር ለሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታ መስከረም 17 ወደ ስፍራው ያመራል፡፡ ጨዋታው የሚደረገው መስከረም 19 ሲሆን በማግስቱ ብሄራዊ ቡድናችን ወደ አዲስ አበባ ይመለሳል፡፡ የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከቡርኪና ፋሶ ጋር ሊያደርገው የነበረው የአለም ከ20 አመት በታች ሴቶች የማጣርያ ጨዋታ መሰረዙን ካፍ አስታውቋል፡፡ ጨዋታው ወደፊት ይካሄድ አይካሄድ ወይም ለኢትዮጵያ ፎርፌ ይሰጥ አይሰጥ የታወቀ ነገር የለም፡፡ የከፍተኛ ሊግ እና ብሄራዊ ሊግ ጨምሮ ሌሎች የውስጥ ውድድሮች በቅርብ ጊዜያት የሚጀመሩ አይመስልም፡፡ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ህዳር 4 ሊጀመር ይችላል ቢባልም እስካሁን አልተረጋገጠም፡፡ ከ17 አመት በታች ፕሪሚር ሊግ ፣ ከፍተኛ ሊግ እና ብሄራዊ ሊጉ እንዴት እና በምን አይነት መልኩ እደሚካሄድም እስካሁን አልታወቀም፡፡ፌዴሬሽኑ እንዳስታወቀው አዲስ ለተቋቋመው ከፍተኛ ሊግ የክለቦች እና የተጫዋቾች ምዝገባ ገና ያልተካሄደ ሲሆን በቅርቡ ምዝገባው ይጀመራል ተብሏል፡፡ከምዝገባው በኋላ ውድድሩ አዲስ በመሆኑ ከክለቦች ጋር ውይይት ተደርጎለት በምን ያህል ዞን እንደሚከፈል ሲወሰን የውድድሩ ደንብ እና ስርአትም ይዘጋጅለታል፡፡", "passage_id": "f91eb7325d0ac3147cb9661405baf01d" }, { "passage": "ሴካፋ በሴካፋ ሲኒየር ቻሌንጅ ካፕ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ከአሰልጣኝ አባላቶቹ ጋር በመሆን ተጨዋቾች የመመልመል ስራ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ህዳር 24 ለሚጀመረው ውድድር በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ምርጫው ተጠናቆ ወደ ዝግጅት እንደሚገቡም ሰምተናል፡፡ (ዳንኤል መስፍን) ፋሲል ከተማፋሲል ከተማ የሴቶች ቡድን በኢትዮዽያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ተሳታፊ መሆኑን ተከትሎ 30 ተጨዋቾችን መልምሎ የመረጠ ሲሆን ዛሬ ባወጣው የአሰልጣኝ ቅጥር መስፈርት መሰረት አሰልጣኝ ተስፋሁን እሸቴን በዋና አሰልጣኝነት ሾሟል፡፡ ቡድኑን ከመመስረት አንስቶ በዝግጅት ወቅት ቡድኑን ሲያሰለጥን የነበረው አሰልጣኝ መካሻው አለም ም/አሰልጣኝ ሆኖ ሲሾም እና የቡድን መሪ በመሆን እንዲመራም ተመርጧል፡፡ የፋሲል ከተማ የሴቶች ቡድን የመጀመርያ ጨዋታውን ሰኞ በአአ ስታድየም ከወጣቶች አካዳሚ ጋር የሚያደርግ ይሆናል። (ዳንኤል መስፍን)አክሊሉ አያናው ለሁለት ክለብ በመፈረሙ ምክንያት ለቅጣት ተዳርጎ የነበረውና ኋላ ላይ ቅጣቱ የተነሳለት ፤ ቆይቶ ደግሞ በድጋሚ እንዲተይ የተወሰነበት አክሊሉ አየነው ጉዳይ በመጨረሻም እልባት አግኝቷል፡፡ ፌዴሬሽኑ ተጫዋቹን መጫወት የሚፈልግበትን ክለብ እንዲመርት በወሰነው ውሳኔ መሰረት አክሊሉ ለኢትዮጵያ ቡና ለመጫወት ምርጫው አድርጓል፡፡  \nስራ አስፈፃሚዎችየኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ አባለት ከጠቅላላ ጉባኤው በኋላ የመጀመርያ ስብሰባቸውን ነገ ያደርጋሉ፡፡ በተለያዮ የሀሳብ ልዩነቶች ውስጥ እንደሚገኙ እና እንደተከፋፈሉ የሚነገረው የስራ አስፈፃሚ አባላት ነገ በሚያደርጉት መደበኛ ስብሰባቸው ምንም መቋጫ ሳይበጅለት ስብሰባው በመበተኑ ምክንያት ብዙ ሲያነጋግር በቆየው የምርጫው አጠቃላይ ሁኔታ ዋና አጀንዳቸው ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። (ዳንኤል መስፍን)አአ ከተማ ዋንጫየአአ ከተማ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከአአ ሲቲ ካፕ ክለቦች በፐርሰት የሚያገኙትን ገቢ በቅርቡ ለየክለቦቹ በየደረጃው አከፋፍሎ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ እና እስካሁንም የዘገየው ከወጪ ቀሪ ያለውን የገንዘብ መጠን ለማስተካከል ጊዜ ስለሚፈልግ እንደሆነ ተገልፆል።በተያያዘ ዜና አአ ከተማ እግርኳስ ፌዴሬሽን በዋናነት በሴቶች እና በወንዶች የሚያወዳድራቸው የውስጥ ውድድሮችን ለመጀመር ቅድመ ሁኔታዎች የጀመረ ሲሆን ህዳር ወር መጨረሻ ላይ ውድድሮቹን ለመጀመር እንዳሰበ ሰምተናል። (ዳንኤል መስፍን)\nኦሮሚያ ዋንጫበኦሮሚያ ዳኞች እና ኮሚሽነሮች ማህበር አዘጋጅነት ከህዳር 5 – 15 ድረስ በዱከም ከተማ አስተናጋጅነት በአምስት ቡድኖች መካከል የሚካሄደው የኦርምያ የአንደኛ ሊግ ቡድኖች የዋንጫ ጨዋታ ባለፈው ማክሰኞ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ተጀምሯል፡፡ በመክፈቻው ጨዋታ ዱከም ከተማ ገላን ከተማን 2-1 ሲያሸንፍ ቢሸፍቱ ከተማ መተሀራ ስኳርን 2-0 ረቷል፡፡  ውድድሩ ዛሬ በአንድ ጨዋታ ሲቀጥል ቢሸፍቱ ከተማ ሆለታ ከተማን 1-0 አሸንፏል። ውድድሩ በዙር የሚካሄድ ሲሆን በአጠቃላይ ውጤት የተሻለ ነጥብ ያስመዘገበ ቡድን የውድድሩ አሸናፊ እንደሚሆን ታውቋል። (ዳንኤል መስፍን)በአምላክ ተሰማኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ በአምላክ ተሰማ በሞሮኮ አስተናጋጅነት በሚካሄደው  የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ጨዋታዎችን እንዲመሩ በካፍ ከተመረጡ ዳኞች መካከል ሆኗል፡፡ በአምላክ ስኬታማ ጊዜ እያሳለፈ በሚገኝበት በዚህ አመት የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ፣ የአለም ከ17 አመት በታች ዋንጫ ጨዋታዎች እና የአለም ዋንጫ ማጣርያዎችን መርቷል፡፡ሲዳማ ቡናየሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር ለማቋቋም ማሰቡን አስታውቋል፡፡ “ደጋፊ ማህበሩን በሚገባ ከማቋቋምም ባለፈ በተጠናከረ መልኩ ለማደራጀት ነው ሀሳባችን፡፡ በቅርቡም ወደ ስራ እነገባለን፡፡ ›› ብለዋል የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ መንግስቱ ሳሳሞ፡፡ (ቴዎድሮስ ታከለ)\nመርሃ ግብሮችየኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ – 3ኛ ሳምንት ቅዳሜ ህዳር 9 ቀን 201009:00 ወልዋሎ ዓ/ዩ ከ ሲዳማ ቡና (አዲግራት)09:00 ወልዲያ ከ ድሬዳዋ ከተማ (ወልዲያ)11:30 ኢትዮጵያ ቡና ከ መከላከያ (አአ)እሁድ ህዳር 10 ቀን 201009:00 አርባምንጭ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ (አርባምንጭ)09:00 ጅማ አባ ጅፋር ከ ፋሲል ከተማ (ጅማ)09:00 ደደቢት ከ ሀዋሳ ከተማ (አአ)09:00 ወላይታ ድቻ ከ አዳማ ከተማ (ሶዶ)11:30 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መቀለ ከተማ (አአ)ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀቅዳሜ ህዳር 09 201009:00 ባህርዳር ከተማ ከ አክሱም ከተማ (ባህርዳር)09:00 ሽረ እንዳስላሴ ከ ኢትዮጵያ መድን (ሽረ)እሁድ ህዳር 10 2010 10:00 አማራ ውሃ ስራ ከ ኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን (ባህርዳር)09:00 የካ ክ/ከተማ ከ ሰበታ ከተማ (አዲስ አበባ)ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዝዮን – 2ኛ ሳምንትቅዳሜ ህዳር 9 ቀን 201009፡00 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ መከላከያ (አአ ስታድየም)እሁድ ህዳር 10 ቀን 201009፡00 ጌዲኦ ዲላ ከ አዳማ ከተማ (ዲላ)09፡00 ሀዋሳ ከተማ ከ ደደቢት (ሀዋሳ)09፡00 ሲዳማ ቡና ከ ድሬዳዋ ከተማ (ይርጋለም)ማክሰኞ ህዳር 12 ቀን 201011፡00 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አአ ስታድየም)ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 2ኛ ዲቪዝዮን – አንደኛ ሳምንትእሁድ ህዳር 10 ቀን 201009፡00 ጥረት ኮርፖሬት ከ ሻሸመኔ ከተማ (ባህርዳር)09፡00 ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ከ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ (አሰላ)ሰኞ ህዳር 11 ቀን 201009፡00 ኢ/ወ/ስ/ አካዳሚ ከ ፋሲል ከተማ (አአ ስታድየም)11፡00 ቂርቆስ ክፍለከተማ ከ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ (አአ ስታድየም)ማክሰኞ ህዳር 12 ቀን 2010 09፡00 ልደታ ክ/ከተማ ከ አአ ከተማ (አአ ስታድየም)09፡00 አርባምንጭ ከተማ ከ ቦሌ ክፍለከተማ (አርባምንጭ)ረቡዕ ህዳር 13 ቀን 201009፡00 ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ከ ኢትዮጵያ ቡና (አአ ስታድየም)አፍሪካሴካፋ ሙሉ መርሀ ግብርከህዳር 24 ጀምሮ በኬንያ አስተናጋጅነት የሚደረገው የሴካፋ ዋንጫ ድልድል ዛሬ ረፋድ ወጥቷል፡፡ የምድብ ድልድልምድብ አንድኬንያ ፣ ሩዋንዳ ፣ ሊቢያ ፣ ታንዛኒያ ፣ ዛንዚባርምድብ ሁለትዩጋንዳ ፣ ዚምባቡዌ ፣ ቡሩንዲ ፣ ኢትዮጵያ ፣ ደቡብ ሱዳንየኢትዮጵያ ጨዋታዎችሰኞ ህዳር 25 ቀን 2010ቡሩንዲ ከ ኢትዮጵያ (8፡00)ዓርብ ህዳር 29 ቀን 2010ደቡብ ሱዳን ከ ኢትዮጵያ (8፡00)እሁድ ታህሳስ 1 ቀን 2010ኢትዮጵያ ከ ዩጋንዳ (10፡00)ማክሰኞ ታህሳስ 3 ቀን 2010ዚምባቡዌ ከ ኢትዮጵያ (10፡00)ሙሉ መርሀ ግብርየአለም ዋንጫ ቋትበሩስያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአለም ዋንጫ ፊፋ 32ቱን ሀገራት በ8 ቋቶች ከፋፍሏል፡፡ ፊፋ ቋቶቹን ያወጣው ሀገራቱ በፊፋ ሰንጠረዥ ባላቸው የብሔራዊ ቡድኖች ወቅታዊ ደረጃ መሰረት ሲሆን የአፍሪካ ሀገራትም በ3ኛ (ቱኒዚያ ፣ ግብፅ ፣ ሴኔጋል) እና 4ኛ (ናይጄርያ ፣ ሞሮኮ) ቋቶች ውስጥ ተመድበዋል፡፡የቻን ቋትየአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) የእጣ ማውጣት ስነስርአት በነገው እለት በሞሮኮ ይካሄዳል፡፡ የአዘጋጅ ኮሚቴው ትላንት ባደረገው ስብሰባም ሀገራቶቹን በአራት ቋቶች ከፋፍሎ ይፋ አድርጓል፡፡ ከምስራቅ አፍሪካ በውድድሩ ላይ የሚካፈሉ ሱዳን ፣ ዩጋንዳ እና ሩዋንዳም በ3ኛው ቋት ላይ ተደልድለዋል፡፡ቋት 1 – ሞሮኮ ፣ አንጎላ ፣ ኮትዲቯር ፣ ሊቢያቋት 2 – ካሜሩን ፣ ጊኒ ፣ ናይጄርያ ፣ ዛምቢያቋት 3 – ኮንጎ ዲ.ሪ. ፣ ዩጋንዳ ፣ ሩዋንዳ ፣ ሱዳን ቋት 4 – ቡርኪና ፋሶ ፣ ኢኳቶርያል ጊኒ ፣ ሞሪታንያ ፣ ናሚቢያ\nኮሳፋ የደቡባዊ አፍሪካ እግርኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (ኮሳፋ) የሚያዘጋጀው የኮሳፋ ከ20 አመት በታች ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያ በውድድሩ ላይ እንድትካፈል ጥሪ ቀርቦላት የነበረ ቢሆንም ምላሽ ባለመስጠቷ የማትካፈል ይሆናል፡፡    የምድብ ድልድሉ ይህንን ይመስላል፡-", "passage_id": "3a940e2fdc7d9b357048738dec096fcc" }, { "passage": "የ2008 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ 2ኛ ዙር በሳምንቱ መጨረሻ ተጀምሯል፡፡ በዚህ ሳምንት የተደረጉትን ጨዋታዎች እና የደረጃ ሰንጠረዦች ከዚህ በታች ይመልከቱ፡-እሁድ ሚያዝያ 16 ቀን 2008ሰሎዳ አድዋ 4-0 ሽረ እንዳስላሴ (አድዋ)ደሴ ከተማ 1-0 ዋልታ ፖሊስ (ደሴ)ትግራይ ውሃ ስራ 1-1 ላስታ ላሊበላ (ውቅሮ)\n \nእሁድ ሚያዝያ 16 ቀን 2008ዳሞት ከተማ 1-2 አምባ ጊዮርጊስ (ፍኖተ ሰላም)አማራ ፖሊስ 1-1 ጎጃም ደብረማርቆስ (ባህርዳር)አዊ እምፒልታቅ 1-2 ዳባት ከተማ (እንጅባራ)አራፊ ቡድን – ደባርቅ\n \nእሁድ ሚያዝያ 16 ቀን 2008አምቦ ከተማ 7-2 ሆለታ ከተማ (አምቦ)ጨፌ ዶንሳ 0-1 ወሊሶ ከተማ (ጨፌ ዶንሳ)ወልቂጤ ከተማ 2-0 አዲስ ከተማ ክ/ከተማ (ወልቂጤ)ቦሌ ገርጂ ዩኒየን 0-3 አራዳ ክ/ከተማ (አበበ ቢቂላ)\n \nእሁድ ሚያዝያ 16 ቀን 2008አምበሪቾ 1-0 ዲላ ከተማ (አምበሪቾ)ቡሌ ሆራ 1-0 ጋርዱላ (ቡሌ ሆራ)ጎፋ ባሬንቾ 0-0 ወላይታ ሶዶ (ጎፋ)ጎባ ከተማ 1-1 ኮንሶ ኒውዮርክ (ጎባ)አራፊ ቡድን – ሮቤ ከተማ\n \nእሁድ ሚያዝያ 16 ቀን 2008ቱሉ ቦሎ 1-0 መቂ ከተማ (ቱሉ ቦሎ)\n-በርካታ የቡታጅራ ተጫዋቾች ህመም ላይ እንደሆኑ ማስረጃ በማቅረባቸው ጨዋታው ለሌላ ጊዜ ተራዝሟል፡፡ቦሌ ክ/ከተማ 4-1 ዱከም ከተማ (አበበ ቢቂላ)የካ ክ/ከተማ 0-1 ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ (አበበ ቢቂላ)\n-አራፊ ቡድን – ልደታ ክ/ከተማ\n \nሞጆ ከተማ 2-2 ሐረር ሲቲ (ሞጆ)መተሃራ ስኳር 5-0 ኢትዮ ሶማሌ ፖሊስ (መተሃራ)ዓሊ ሐብቴ ጋራዥ 2-4 ወንጂ ስኳር (ድሬዳዋ)\nየቢሾፍቱ ከተማ አባላት ወደ ጅግጅጋ ሲያመሩ የመኪና አደጋ የደረሰባቸው በመሆኑ ጨዋታው ለሌላ ጊዜ ተላልፏል፡፡\n ጋምቤላ ከተማ ከ ዩኒቲ ጋምቤላ (ጋምቤላ)አሶሳ ከተማ ከ ከፋ ቡና (አሶሳ)ዩኒቲ ጋምቤላ ከ ሚዛን አማን (ጋምቤላ)–በዚህ ምድብ ሊደረጉ የነበሩ ጨዋታዎች በጋምቤላ ክልል ባለው ወቅታዊ አለመረጋጋት ምክንያት አልተደረጉም፡፡ ይህ ምድብ 1ኛው ዙር ሲጠናቀቅ የነበረው የደረጃ ሰንጠረዥ ይህን ይመስላል፡-\n – ፡ ወደ ማጠቃለያ ውድድር በቀጥታ ለመግባት በሚረዳ ቦታ ላይ የተቀመጡ ቡድኖች– ፡ በጥሩ 3ኝነት ለመግባት የሚረዳ ደረጃ ላይ የሚገኙ ቡድኖች– ፡ ወደ ክልል ሊጎች ለመውረድ በሚያስገድድ ደረጃ ላይ የሚገኙ ቡድኖች", "passage_id": "d4d44da7c3f20aab70368f328091a965" } ]
7a099b232ac855f71d04d73815cdaa61
e44f6ab286a0ed4c2f746d9750dd442c
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ20 ሚሊዮን ብር የሕዳሴ ግድብ ቦንድ ገዛየፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ20 ሚሊዮን ብር የሕዳሴ ግድብ ቦንድ ገዛ
– ለግድቡ በአምስት ወራት ከ888  ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧልበጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን ለማገዝ የ20 ሚሊዮን ብር የቦንድ ግዥ ፈፀመ። የቦንድ ግዢው የግድቡን ግንባታ ለማጠናቀቅ የኅብረተሰቡ ተሳትፎ እንዲያድግ መንግሥት ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ የተደረገ መሆኑን ትናንት በተደረገው የርክክብ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገልጿል። የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን በመወከል ቼኩን ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት ያስረከቡት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ረሻድ ከማል ናቸው። የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት፤ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለተለያዩ ሀገራዊ ልማት ፕሮጀክቶች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታውሰው፤ ለኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚያደርገውን ድጋፍ በልዩ ሁኔታ በመመልከት ሰፊ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህንንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት የሆነው የህዳሴው ግድብ እስኪጠናቀቅ ድረስ ኮርፖሬሽኑ ታሪካዊ አሻራውን ማኖሩን አበክሮ ይቀጥላል።ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ቀደም ባደረጋቸው የገንዘብ አስተዋጽኦዎች ለገበታ-ለሀገር ፕሮጀክት 20ሚሊዮን ብር፣ ለመቄዶኒያ የአረጋዊያን መኖሪያ ግንባታ 5 ሚሊዮን ብር፣ የ COVID-19 ስርጭትን ለመከላከል እየተደረገ ላለው ሀገራዊ ርብርብ 10 ሚሊዮን ብር፣ ባለፉት 6 ወራት የኮርፖሬሽኑ ተከራይ ደንበኞች 50% የቤት ኪራይ ክፍያ እንዲቀነስላቸው በማድረግ 400 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፤ ለገበታ-ለሃገር የተሰጠውን 20 ሚሊዮን ብር ጨምሮ በድምሩ 455 ሚለዮን ብር ገደማ ወጪ በማድረግ ኮርፖሬሽኑ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ እንደሚገኝም አቶ ረሻድ ጠቁመዋል።የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አረጋዊ በርሔ በበኩላቸው፤ የሕዳሴ ግድብ ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ለውጥ ወሳኝ ነው ብለዋል። ኮርፖሬሽኑ ያደረገው ድጋፍ ለሌሎች ተቋማት አርአያ የሚሆን ተግባር እንደሆነ የጠቆሙት ዶክተር አረጋዊ፤ ሁሉም ተቋማትና ዜጎች ተሳትፎአቸውን በማሳደግ ግድቡን ለማጠናቀቅ የሚደረገውን ርብርብ እንዲደግፉም ጥሪ አቅርበዋል።ባለፉት አምስት ወራት ብቻ መላ ኢትዮጵያውያን በአገር ውስጥና በውጪ ከ790 ሚሊዮን ብር በላይ የቦንድ ግዥ ድጋፍ ማደረጋቸውንና በ8100 የገቢ ማስገኛ ፕሮግራምም ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የግድቡ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍቅርተ ታምር ገልጸው፤ ይህም በግድቡ ግንባታ ታሪክ ከፍተኛ አስተዋጽኦ መሆኑን አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 27/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=38880
[ { "passage": "ግዙፉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባገኘው ዋስትና መሠረት ለአዲስ አበባ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ስምንት ቢሊዮን ብር አበደረ፡፡ ባንኩ ብድሩን የሰጠው በአዲስ አበባ የተቀናጀ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፕሮግራም ቀደም ሲል ግንባታቸው ለተጀመሩ ከ140 ሺሕ በላይ ቤቶች ማጠናቀቂያና ዘንድሮ አዲስ ለሚጀመሩ 62,000 ቤቶች በጠቅላላው ለ202,000 ቤቶች መሆኑን፣ የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ኃይሌ ገልጸዋል፡፡ ሚኒስትሩ የአምስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ባለፈው ማክሰኞ ለሕዝብ ተወካዮች ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት፣ 6.3 ቢሊዮን ብር ለአዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት በቀጥታ እንደሚገባና የተቀረው 1.67 ቢሊዮን ብር ደግሞ ለአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ የሚውል ነው፡፡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በ1997 ዓ.ም. ከተጀመረ ጀምሮ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ዋስትና ለአዲስ አበባም ሆነ ለክልሎች ብድር እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ የክልል ኮንዶሚኒየም ፕሮጀክቶች ቀድሞ እንደታሰበው ፈላጊ ሊያገኙ ባለመቻላቸው፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በ2002 ዓ.ም. ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት ተጨማሪ ግንባታ በክልሎች እንዳይከናወን ተደርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለክልሎችና ለአዲስ አበባ የኮንዶሚኒየም ፕሮጀክቶች በዚህ ዓመት ያበደረውን ሳይጨምር፣ በጠቅላላው 13 ቢሊዮን ብር በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ዋስትና መስጠቱን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ባንኩ ከሰጠው ብድር ውስጥ ትልቁ ባለድርሻ ዘጠኝ ቢሊዮን ብር በማግኘት የአዲስ አበባ የኮንዶሚኒየም ፕሮጀክት ቀዳሚ ሲሆን፣ የተቀረውን ክልሎች ተከፋፍለውታል፡፡ ይህ 13 ቢሊዮን ብር እስካሁን ተከፍሎ አለመጠናቀቁን ከሚኒስትሩ ገለጻ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸውም በዚህ ዓመት የቀድሞው ብድር ሦስት ቢሊዮን ብር እንዲመለስ እየተከታተለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሠረት ባለፉት አራት ወራት ውስጥ 843.5 ሚሊዮን ብር ከኦሮሚያ፣ ከደቡብ ክልል፣ ከትግራይና ከአዲስ አበባ አስተዳደር ተሰብስቦ ተመላሽ መደረጉን አስረድተዋል፡፡ በዚህ ዓመት በመጋቢትና በሚያዚያ ወራት ውስጥ የሚተላለፉ ከ70 ሺሕ በላይ ቤቶች መኖራቸውን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ ‹‹በ20/80 እና በ10/90 ቤቶች ፕሮግራም ቀድሞ የከፈለ ወይም የበለጠ የከፈለ ዕጣ ውስጥ ይገባል የሚባል ነገር የለም፡፡ ዕጣ ውስጥ ለመግባት መሠረቱ 20 በመቶውን ማሟላት ወይም 10 በመቶውን ማሟላት ብቻ ነው፤›› ብለዋል፡፡ በ40/60 ቤቶች ፕሮግራም ግን የቤቱን ዋጋ ሙሉ በሙሉ ከከፈሉት በመነሳት እስከ 40 በመቶ የከፈሉ እንዲወዳደሩ የሚደረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡", "passage_id": "9d57105ff7c63bdd1590270497c55317" }, { "passage": "ከንግድ ባንክ የተበደረው ከ200 ቢሊዮን ብር በላይ ነውየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፉት አሥርት ዓመታት ላከናወናቸው የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድሮ መመለስ ያልቻለው የተከማቸ ዕዳ፣ ከፊሉ ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር እንዲዛወር መንግሥት መወሰኑ ታወቀ።ውሳኔውን ያሳለፈው በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሥር የሚገኘውና በቀድሞው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር በኋላም በአሜሪካ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር በነበሩት አቶ ግርማ ብሩ ሰብሳቢነት የሚመራው፣ ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ ኮሚቴ እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል።በውሳኔው መሠረት የኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለያዩ አማራጮች ተበድሮ ለመክፈል ካልቻለው የተከማቸ ዕዳ ውስጥ የተወሰነው ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር እንዲተላለፍ፣ የተቀረው ዕዳም ደረጃ በደረጃ የመክፈል ኃላፊነት ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር እንደሚተላለፍ ለማወቅ ተችሏል።ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አንድ ከፍተኛ ኃላፊ እንዳስረዱት፣ ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር እንዲዘዋወር የተወሰነው ዕዳ በቀጥታ ከባንኩ የተወሰደ ብድር ባለመሆኑ ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር የሚተላለፍ እንደሆነ፣ በዚህ መንገድ የሚስተናገደው ዕዳም ለባንኩ የሚከፈል ሳይሆን መንግሥት በኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ የሚኖረው አዲስ የኢንቨስትመንት ድርሻ እንዲሆን መወሰኑን ገልጸዋል።ይህ የሆነበትም ምክንያት የተወሰነው የኮርፖሬሽኑ ዕዳ መንግሥት ከተለያዩ የገንዘብ ምንጮች ያገኘውን የልማት ፈንድ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመልሶ ማበደር እንዲያስተዳድር በሰጠው ኃላፊነት መሠረት፣ ኤሌክትሪክ ኃይል የተበደረው በመሆኑ ነው። ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ ተበድሮ ያልከፈለው 32 ቢሊዮን ብር በዚህ ዓመት ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር እንዲዘዋወር እንደሚደረግ ኃላፊው ተናግረዋል።የተቀረውና በቀጥታ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንድ ተበድሮ ያልተከፈለው ዕዳ 20 በመቶውን የመክፈል ኃላፊነት፣ ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር ደረጃ በደረጃ እንዲዘዋወር እንደተወሰነም ጠቁመዋል።ኤሌክትሪክ ኃይል ከባንኩ ያገኘው ቀጥታ ብድሮች የመክፈያ ጊዜ መንግሥት በተለያዩ ወቅቶች ባሳለፋቸው ውሳኔዎች በተደጋጋሚ የተራዘሙ በመሆኑ፣ ይኸውም በዋናው ብድር ላይ የሚከፈለውን የወለድ ክፍያ በማናሩ አጠቃላይ የዕዳ መጠኑን ከፍተኛ እንዳደረገው ተገልጿል።በዚህም ምክንያት ዕዳውን መክፈል እንዳልቻለ፣ ከዚህ በተጨማሪም ከአገር ውስጥ ብድር በላይ የሆነ የውጭ ብድር የመክፈል ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ የተከማቸ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ላለፉት በርካታ ዓመታት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድረው ያልመለሱት የዕዳ መጠን ወለድን ጨምሮ 425 ቢሊዮን ብር እንደሆነ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ከጥቂት ወራት በፊት ያወጣው የአገሪቱ አጠቃላይ ዕዳ የሚዘረዝር ሰነድ ያመለክታል።ከዚህ ውስጥ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሲሆን፣ ከተቀረው የዕዳ መጠን ውስጥ አብዛኛው የሚመለከተው የስኳር ኮርፖሬሽንንና የባቡር ኮርፖሬሽንን እንደሆነ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።የገንዘብ ሚኒስቴር የኤሌክትሪክ ኃይልን ዕዳ የመክፈል ኃላፊነት እንዲወስድ መወሰኑ በቀጣዮቹ ዓመታት የሚኖረውን የመንግሥት ወጪ እንደሚያንርና የዋጋ ንረት በኢኮኖሚው የማስከተል አቅም እንዳለው ሪፖርተር ያነጋገራቸው ባለሙያዎች የገለጹ ሲሆን፣ ይኼንን አለማድረግ ደግሞ የኢትዮጵያ የንግድ ባንክን ጤናማነት እንደሚጎዳው አስረድተዋል።", "passage_id": "ef1472107353be6d55161c7bc9ac4813" }, { "passage": "የኢትዮጵያ ሞተርና ኢንጂነሪንግ ኩባንያ አክሲዮን ማሕበር (ሞኤንኮ) ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ የሚሆኑ ሶስት ፒክአፕ መኪኖችን በስጦታ መልክ አበረከተ፡፡በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ዛሬ የተገኙት የገንዘብና ኤኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስትር ዶክትር አብርሃም ተከስተ ግምታቸው 8ነጥብ25 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸው ዘመናዊ ፒክአፕ መኪኖቹን ቁልፍ ከሞኤንኮ ሥራ አስፈፃሚ ተረክበዋል ፡፡በዚሁ ወቅት ዶክተር አብረሃም እንደገለጹት ፤ለሞኤንኮ ምስጋናቸውን ካቀረቡ በኋላ በቀጣይም ኩባንያው ድጋፉን አጠናክሮ እደሚቀጥል እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ሌሎች እንደ ሞኤንኮ ሁሉ የግል ኩባንያዎችም ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ እያበረከቱት ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡መኪኖቹ ግድቡን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለማስገኘት የገቢ ማሳባሰቢያ አማራጮች በመሆን ጉልህ ድርሻ እንደሚኖራቸው ነው የገለጹት ፡፡የሞኤንኮ ሥራ አስፈፃሚ  ክሪስ ዲ ሙይንክ በበኩላቸው ፤ ሞኤንኮ በኢትዮጵያ የትርንስፖርት አገልግሎት ላይ ያለውን አሰተዋጽኦ ከማገዝ ባሻገር የታላቁ ሕዳሴ ግድብ አስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡ኩባንያው ቀደም ሲል 900 ሺህ ብር የሚያወጣ ቶዮታ ያሪስ በስጦታ መልኩ እንዳበረከተና የ23 ሚሊየን ብር ቦንድ ግዢ እንዳከናወነም ሥራ አስፈጻሚው አንስተዋል፡፡ዘንድሮ ለግድቡ ግንባታ ገቢ ማሰባሰቢያ ሁለት ቢሊየን ብር ለማሰባሰብ ታቅዶ እተየሰራ እንደሆነ ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሕዝብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ 11 ሺ የሚሆኑ ወጣቶችና 350 የዘርፉ ባለሙያዎች ቀንና ማታ በግንባታው ላይ እየተሳተፉ እነደሆነ ይታወቃል፡፡የመሰረት ድንጋዩ መጋቢት 24፣ 2003 የተቀመጠው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ አሁን ላይ 54 በመቶ እንደደረሰ መገለጹን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል፡፡\n ", "passage_id": "94c8a0bccd903e8053007dc9a0113a54" }, { "passage": "“ሕዝቡ ለግድቡ ግንባታ የሚችለውን እያደረገ ቢሆንም ሜቴክ ግን ሕዝቡ በእኛ ላይ ያለውን እምነት አሳጥቶናል”\nኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ያለውን ታላቁን የሕዳሴ ግድብ በገንዘብ ለመደገፍ በርካታ አማራጮች ተዘርግተዋል፡፡ የቦንድ ሽያጭ እና የ8100 A የአጭር መልዕክት የድጋፍ ማሰባሰቢያ መንገዶችም ከነዚህ አማራጮች መካከል ናቸው፡፡\nየግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ከ2003 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ወርሃ ሰኔ 2012 ዓ/ም ድረስም ከሃገር ውስጥ የቦንድ ሽያጭ እና ከልገሳ ከ12 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ተሰብስቧል እንደ ግንባታው ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት መረጃ፡፡\nከአል ዐይን አማርኛ ጋር ቆይታ ያደረጉት የጽሕፈት ቤቱ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብርሃም እንደገለጹት ከዳያስፖራ የቦንድ ሽያጭና ልገሳ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሲገኝ ከልዩ ልዩ ገቢዎች ደግሞ ከ244 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል፡፡\nእስካሁን በነበረው የገቢ አሰባሰብ ሂደት በጥቅሉ 13 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገደማ ገንዘብ እንደተሰበሰበም ነው አቶ ኃይሉ የተናገሩት፡፡\nግንባታውን በዐቅማቸው ለመደገፍ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ሁሉ ሲገለገሉበት የነበረው የ8100 A የሞባይል የአጭር መልዕክት ገቢ የማሰባሰቢያ ዘዴ ይህን ገቢ በማሰባሰብ ረገድ የጎላ አስተዋጽኦን አበርክቷል፡፡\nሁሉም የዐቅሙን በቀላሉ እንዲያበረክት በማስቻል ረገድም የማይናቅ ድርሻ ነበረው፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያንና የግንባታው ደጋፊዎችም በዚሁ ዘዴ የድጋፍ እጃቸውን ዘርግተዋል፡፡\nበተጀመረበት አመት 80 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ ያስቻለው አማራጩ በ2008 ዓ.ም ደግሞ 48 ሚሊዮን ብር አስገኝቷል፡፡\n“ሜቴክ ሕዝቡ በእኛ ላይ ያለውን እምነት አሳጥቶናል”አቶ ኃይሉ ሕብረተሰቡ ግንባታውን ለመደገፍ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ የተጀመረው ስራ ከፍተኛ ፈተና ገጥሞት እንደነበር ያነሳሉ፡፡ ይህም የግድቡን የኤሌክትሮ መካኒካልና የሃይድሮ ስቲል ስትራክቸር ሥራ ለመስራት ኃላፊነቱን ተረክኖ የነበረው የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን(ሜቴክ) ኃላፊነቱን በወጉ ካለመወጣቱ እና መስራት የነበረበትን ስራ በወቅቱ በተገቢው መንገድ ባለማጠናቀቁ ነው፡፡ በዚህም ሕብረተሰቡ ከፍተኛ ጥርጣሬ ውስጥ ገብቷል፡፡\n“በተሰራው ስህተት ገንዘባችን ተበላ” የሚል ከፍተኛ ቅሬታ ድጋፍ ሲያደርግ ከነበረው የህብረተሰብ ክፍል ሲቀርብ እንደነበርም ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት፡፡\n“በጽ/ቤቱ የምንሰራ ሰዎች ጋር እየደወሉም ጭምር ‘ገንዘባችንን አከሰራችሁት፣ ጠላቶቻችን እናንተ ናችሁ’” የሚሉ ዛቻዎች ይደርሷቸው እንደነበርም ያስቀምጣሉ ምንም እንኳን ጽህፈት ቤቱ የሚሰበሰበውን ገንዘብ በቀጥታ ወደ ፕሮጀክቱ ገቢ የሚደረግ ቢሆንም፡፡\nከሁለት ዓመት በፊት የተደረገው የአመራር ለውጥ ግን በግድቡ ዙሪያ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታትና የሕዝብን አመኔታ ለመመለስ አግዟል እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም መንግስት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን አከናውኗል፡፡ ተደጋግመው የሚሰሙ የ‘ለግድቡ የተዋጣው ገንዘብ ተበልቷል፣ ለታቀደው ነገር አልዋለም’ መሰል አስተያየቶችን ለማስተካከል የሚያስችሉ ተጠያቂነት የማስፈን ስራዎች መጀመራቸውንም የተናገሩት፡፡\nቀደም ሲል በተጠቀሱት ምክንያቶች ተቀዛቅዞ የነበረው የሕዝብ ተሳትፎ አሁን ላይ ተመልሶ እየተነቃቃ መሆኑን ያነሱት አቶ ኃይሉ በተጠናቀቀው ወርሃ ሰኔ 2012 ዓ/ም ብቻ ከ87 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡\n", "passage_id": "74332553e947dbbc3ea7c3b92c76a120" }, { "passage": "‹‹በሕግም ቢሆን መቀጣት ያለብንን ተቀጥተን እንከፍላለን››የኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽንከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጋር ሕጋዊ ውል በመፈጸም የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ያከራዩ ባለሀብቶች፣ ኮርፖሬሽኑ በገባው ውል መሠረት ክፍያ ሊፈጽምላቸው ባለመቻሉ ከባንክ ለወሰዱት ብድር ማስያዣነት ያዋሏቸው ንብረቶቻቸው ለጨረታ እየቀረቡ መሆኑን ተናገሩ፡፡የኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በሰጠው ምላሽ፣ አከራዮቹ ያቀረቡት ቅሬታ ትክክል መሆኑንና ክፍያ ለመፈጸም መረጋገጥ ያለበት እውነታና ቅደም ተከተል ስላለ እንጂ፣ አከራዮቹ ትክክል መሆናቸውንና በሕግም ቢሆን መቀጣት ያለበትን ተቀጥቶ እንደሚከፍል ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዮናስ አያሌው (ኢንጂነር) ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ከ170 በላይ አባላት እንዳሉት የሚናገረው የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች አከራዮች ማኅበር (ኮማአማ) እንደገለጸው፣ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በመላው ኢትዮጵያ በሚሳተፍባቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶች የኮንስትራከሽን ማሽነሪዎችን የሚጠቀመው ከባለሀብቶች በሚከራያቸው ማሽኖች ነው፡፡ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጀምሮ በመንገድ ግንባታ፣ በስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ፣ በግድቦችና በመስኖ ሥራዎች ላይ ባለሀብቶች የሚያቀርቧቸውን ግዙፍና መለስተኛ የኮንስትራክሽን ማሽኖች ኮርፖሬሽኑ በሕጋዊ ውል እየተከራየ ሲጠቀም ኖሯል ብሏል፡፡ አሁንም ውል እያደሰ በመጠቀም ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡ ምንም እንኳን ባለሀብቶች ክፍያ እየተፈጸመላቸው ማሽነሪዎቹን የሚያቀርብ ቢሆንም፣ ለልማቱ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እያደረጉ እንደሚገኙም ማኅበሩ ጠቁሟል፡፡ቀደም ባሉት ዓመታት ማለትም እስከ 2010 ዓ.ም. ድረስ በተመሳሳይ ሁኔታ መንግሥት ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ክፍያ ሳይፈጽምላቸው ቆይቶ፣ አዲሱ አመራር በተሻለ ሁኔታ ተንቀሳቅሶ ውዝፍ ክፍያውን የፈጸመ ቢሆንም፣ የ2011 ዓ.ም. የካቲት ወርና የ2012 በጀት ዓመት ሙሉ ክፍያ ለአከራዮች እንዳልተፈጸመላቸው አስረድቷል፡፡ክፍያው እንዲፈጸምላቸው በተደጋጋሚ ለኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎች ያቀረቡት ጥያቄ በቂ ምላሽ ሊያገኝ እንዳልቻለ የገለጸው ማኅበሩ፣ ኮርፖሬሽኑ እስከ ሰኔ መጨረሻ ወር ድረስ መክፈል የነበረበት ከ287 ሚሊዮን ብር በላይ እንዳልከፈለ አስታውቋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ በገባው ውል መሠረት ክፍያውን ባለመፈጸሙ ባለሀብቶች ከባንክ በከፍተኛ ወለድ ለማሽነሪዎች ላስያዙት የንብረት ዋስትና ጊዜውን ጠብቀው ክፍያ መፈጸም ባለመቻላቸው፣ ሐራጅ ወጥቶ እየተሸጠባቸው መሆኑን ማኅበሩ ለኮርፖሬሽኑ በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡ መንግሥት ባለሀብቱ ለአገሩ ያደረገውን አስተዋጽኦ ከግምት ውስጥ በማስገባትና በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞችም ከመበተናቸውና ተጨማሪ የሥራ አጥነት ችግር ከመፈጠሩ በፊት፣ ክፍያው ተፈጽሞላቸው ሥራቸውን በገቡት ውል መሠረት በስምምነት እንዲቀጥሉና ለባንክ ያስያዙት ንብረታቸውም ከሐራጅ ሽያጭ እንዲታደግላቸው ጠይቀዋል፡፡ ምንም እንኳን በገቡት ውል መሠረት ወደ ፍርድ ቤት በመሄድ መብታቸውን በሕግ ማስከበር እንደሚችሉ እምነታቸው ቢሆንም፣ ከኮርፖሬሽኑም ሆነ ከመንግሥት ጋር ያላቸው ግንኙነት መልካም የነበረ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት አዲሱ የኮርፖሬሽኑ አመራር ችግራቸው እውነተኛ መሆኑን ፈትሾና አረጋግጦ ክፍያቸውን እንዲፈጽምላቸው ማኅበሩ ጠይቋል፡፡የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች አከራዮች ማኅበር ለመንግሥትና ለኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎች ያቀረበውን የክፍያ ጥያቄ በሚመለከት፣ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዮናስ አያሌው (ኢንጂነር)ን ሪፖርተር አነጋግሯቸው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ኮርፖሬሽኑ አዲሱ አመራር መቀየሩንና አመራር ሲቀያየር ደግሞ መረጃ ማጣራት አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ተቋሙ ከኮንስትራክሽን ዕቃዎች ኪራይ ጋር በተያያዘ ያልተከፈለ የ2009 እና 2010 በጀት ዓመት ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ዕዳ መክፈሉን ገልጸዋል፡፡ ክፍያ መፈጸም ያለበት በቅደም ተከተል መሆን ስላለበት እንጂ፣ ኮርፖሬሽኑ ያለበት ዕዳ  እየተጣራ እንዲከፈልና ከፕሮጀክት ወደ አመራሮች መጥቶና ተጣርቶ የሚከፈልበት ጊዜ እንዳይንዛዛ ተብሎ፣ የፕሮጀክቶች ኃላፊዎች ሥራውን አጣርተው ክፍያ እንዲፈጽሙ ሰርኩላር ማስተላለፋቸውን ዮናስ (ኢንጂነር) ተናግረዋል፡፡ቀደም ባሉት አመራሮች ጊዜ በተፈጸመ የኮንስትራክሽን ዕቃዎች ኪራይ ጋር በተያያዘ፣ ‹‹አከራይና ተከራይ››ን ያካተተ ብዙ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸው ያስታወሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ያንን ዓይነት ክስተት እንዳይደገም እያንዳንዱ ጉዳይ እየተጣራ እንዲከፈል እንጂ ተቋሙ ገንዘብ ስለሌለው እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ በአግባቡ በፕሮጀክት ኃላፊዎች ተጣርቶ የቀረበላቸውን እየከፈሉ መሆኑን ጠቁመው፣ በዚህ መንገድ አልፎ ክፍያ ያልተፈጸመለት ካለ እሳቸው ቢሮ ድረስ ቀርቦ ሊያነጋግራቸው እንደሚችልም አክለዋል፡፡ቀደም ባሉት ዓመታት ከኢትዮጵያ መንገዶች ባሥልጣን ጋር በጋራ ያስተዳድሯቸው፣ የነበሩ ዲስትሪክቶች በአሁኑ ጊዜ መለያየታቸውን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው በሁለቱ ተቋማት መካከል የነበረ የመረጃ መለዋወጥ ሒደትም ጊዜ መውሰዱን ጠቁመው ያም ቢሆን ግን እየከፈሉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ አንዳንድ አከራይ ባለሀብቶች ከባንክ ጋር ችግር እንደገጠማቸው ለተቋሙ በማሳወቃቸው፣ ኮሚቴ በማዋቀር የባንክ ዕዳ እንዲከፈልላቸውና ቀሪው ዕዳ ተጣርቶ እንዲከፈላቸው መወሰኑን ተናግረዋል፡፡ አሁንም በዚያ ደረጃ ላይ የደረሰና የተቸገረ አከራይ ካለ ተጣርቶ ገንዘቡ እስከሚከፈለው፣ አጣዳፊ ችግሩን በማስረዳት እንዲከፈልለት ማድረግ እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡ አንድ ማሽን ያከራየም ሆነ አሥር ማሽን ያራከየ ወይም መቶ ሺሕ ብር ያለውም ሆነ አሥር ሚሊዮን ብር ያለው አከራይ መብታቸው እኩል መሆኑን የተናገሩት ዮናስ (ኢንጂነር)፣ ሁሉም እንደ አመጣጡ እየተጣራ ክፍያ እንደሚፈጸምለት አረጋግጠው የ2012 በጀት ዓመት ክፍያን ግን ወደ ፕሮጀክቶቹ እየሄዱ መቀበል እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ተብሎ ሰርኩላር መተላለፉን አክለዋል፡፡ በየፕሮጀክቱ ያሉ ኃላፊዎች እዚያው አጣርተውና አረጋግጠው ወዲያውኑ እንዲከፍሏቸው በመደረጉ፣ ያለ ምንም መጉላላት መብታቸውን መጠየቅ እንደሚችሉና ተቋሙ በሕግም ቢሆን መቀጣት ያለበትን ተቀጥቶ ክፍያ ሊፈጽምላቸው እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ‹‹እነሱ ከሌሉ እኛም የለንም፤›› ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ የ2012 በጀት ዓመትን እያጣሩ መሆኑንና ይህንንም የሚያደርጉት ደንበኞቻቸውን እንዳያጡ ተጠንቅቀው መሥራት ስላለባቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡", "passage_id": "ce6d47afb4adb7bc624b4e5875ea5049" } ]
36313869fe3e18eb5a11f9a84b2c852b
808c5762711e84121e49097498e5f2df
የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ጠቅላላ ጉባዔ ተራዘመ
በመጪው ጥቅምት ወር በደቡብ ኮሪያ ሴኡል ከተማ ሊካሄድ የነበረው የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ጠቅላላ ጉባዔ በኮሮና ቫይረስ ስጋት መራዘሙ ታውቋል። የሁሉም አገራት ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች የሚሳተፉበት ወሳኝ ጠቅላላ ጉባዔ በመጪው ጥቅምት አጋማሽ ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት ነበር። የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎቹ እንዲሁም ጠቅላላ ጉባዔውን የምታዘጋጀው ደቡብ ኮሪያ የስፖርትና ኦሊምፒክ ኮሚቴ በጋራ በሰጡት መግለጫ ጠቅላላ ጉባዔው የተራዘመው በሁሉም ባለድርሻ አካላት ፍላጎት መሆኑ ታውቋል። እኤአ የ1988 ኦሊምፒክ የሆነችው ሴኡል ከተማ ይህን ታላቅ ጠቅላላ ጉባዔ በመጪው 2021 የፈረንጆች ዓመት እንደምታስተናግድ ይገለፅ እንጂ መቼ እንደሆነ ቁርጥ ያለው ቀን አልተነገረም። ጠቅላላ ጉባዔው የሚካሄድበት እርግጠኛው ቀን ወደ ፊት እንደሚገለፅም ተጠቁሟል። ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎቹ ወሳኝ በሆነው ጠቅላላ ጉባዔ ሃሳባቸውን እንዲያቀርቡ በማህበሩ በኩል ሪፖርቶችና አጀንዳዎች ቀደም ብሎ ተሰጥቷቸው ነበር።‹‹ጠቅላላ ጉባዔው በተያዘለት ጊዜ ባለመካሄዱ ቅር ተሰኝተናል፣ ይሁን እንጂ ዓለም አሁን ካለችበት ወቅታዊ ችግር አኳያ ጠቅላላ ጉባዔውን ማራዘማችን ትክክለኛ ውሳኔ ነው›› በማለት የማህበሩ ፕሬዚዳንት ተወካይ ሮቢን ሚሼል ለዓለም መገናኛ ብዙሃን በተሰራጨው መግለጫ ሃሳባቸውን አስቀምጠዋል። የፕሬዚዳንቱ ተወካይ አክለውም፣ ጠቅላላ ጉባዔውን ለማስተናገድ በዝግጅት ላይ የነበሩት የደቡብ ኮሪያ ስፖርትና ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ ኃላፊዎች ስብሰባውን በታቀደለት ጊዜ ለማስተናገድ ያደረጉትን ጥረትና ስብሰባው ይራዘም ሲባል ሃሳቡን ለመቀበል ላሳዩት ቅንነት ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይም ጠቅላላ ጉባዔው እዚያው ሴኡል ከተማ እንዲካሄድ ከአገሪቱ የስፖርት ኃላፊዎች ጋር ተቀራርበው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል። በኮሮና ቫይረስ ፈጣን ስርጭት የተነሳ በርካቶቹ የዓለማችን አገራት የዜጎቻቸውን እንቅስቃሴ ከመግታት ጀምሮ ዓለም አቀፍ ጉዞዎች ላይ እገዳ እንደጣሉ ይታወቃል። የደቡብ ኮሪያ ስፖርትና ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ሊ ኪ ሁንግ በጠቅላላ ጉባዔው የሚሳተፉ የተለያዩ አገራት የስፖርት ልዑካን ቡድን አባላት የጤናና ደህንነት ሁኔታን ከግምት በማስገባት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተስማሙት መሰረት ስብሰባው እንዲራዘም መደረጉን ገልፀዋል። ጠቅላላ ጉባዔውን በተራዘመው መርሐግብር መሰረት ለማስተናገድም አገራቸው ፍቃደኛ መሆኗን ተናግረዋል። ‹‹ዓለም አሁን የገጠማት ችግር የኦሊምፒክ እንቅስቃሴን ያስቆማል የሚል እምነት የለንም›› ያሉት ፕሬዚዳንቱ በቀጣይ የዓለማችን ስፖርት እጣፋንታ ላይ የሚወስኑ የሁለት መቶ ስድስት አገራት ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎችን ልዑካ ቡድን አባላት ለመቀበልና የተሳካ ጠቅላላ ጉባዔ ለማድረግ እንደሚዘጋጁም ቃል ገብተዋል። ከዚህ ቀደም የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ጠቅላላ ጉባዔ የሚካሄደው በማህበሩ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት መካከል እንዲሁም በማህበሩ የሥራ ባልደረቦች መካከል ነበር። በዚህ ጠቅላላ ጉባዔ እኤአ ከ2014 ወዲህ ማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔውን በሚያካሂድበት ከተማም ትልቅ ዓመታዊ የሽልማት ሥነሥርዓት እንደሚያደርግ ይታወቃል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንቶች በዚህ ጠቅላላ ጉባዔ ተገኝተው ንግግር የሚያደርጉም ሲሆን በዓለማችን ስፖርቶች እንዲሁም ታላላቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ዙሪያ ምክክር ይደረግበታል። ማህበሩ ባለፈው ዓመት ኳታር ዶሃ ላይ ባደረገው ጠቅላላ ጉባዔ የማህበሩ ፕሬዚዳንት ሼክ አሕመድ አል ሳባህ የፍርድ ሂደት መቋጫ እስኪያገኝ ድረስ ሮቢን ሚሼል የማህበሩ ፕሬዚዳንት ተወካይ ሆነው እንዲያገለግሉ መወሰኑ ይታወቃል። ባለፈው ወር ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደው የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች የባህር ዳርቻ የስፖርት ውድድሮች በኮሮና ቫይረስ ስጋት እኤአ እስከ 2023 እንዲራዘም መወሰኑ አይዘነጋም። የዓለምን ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታ ወደተለየ አቅጣጫ ያዞረው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በስፖርቱ ዓለም ያሳደረው አሉታዊ ተፅዕኖ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። አንዳች ውድድር በዓለም ላይ እንዳይኖር ከማስገደድ ባለፈ የስፖርቱን ዓለም ሽባ አድርጎታል። ብዙ ታቅዶባቸው፣ብዙም ተለፍቶባቸው ለዓመታት በዝግጅት ላይ የነበሩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች በትልቅ ኪሳራ የሚካሄዱበት ጊዜ እንዲራዘም ግድ ብሏል። ጃፓን ካለፉት ሰባት ዓመታት በላይ ከፍተኛ ዝግጅት ስታደርግበት የቆየችው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በትልቅ ኪሳራ ለአስራ ስድስት ወራት የተራዘመና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረ ታላቅ የስፖርት መድረክ ነው። ይህን ታላቅ የስፖርት መድረክ ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ እየተናነቀውም ቢሆን ለ2021 ለማራዘም ተገዷል። ኦሊምፒኩን ጨምሮ በርካቶቹ ዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮችና ጉባዔዎች ወደ ቀጣይ ዓመት የተሸጋገሩት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በቁጥጥር ስር ይውላል በሚል ተስፋ ነው። ይሁን እንጂ በዓለም ላይ አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ከተስፋ በስተቀር የቫይረሱ ስርጭት በጊዜ የሚገታ ወይም ፈውስና ክትባት በዚህ ጊዜ እውን ይሆናል የሚያስብል እንዳልሆነ መታዘብ ይቻላል። ይህንን ከግምት ያስገቡት የቶኪዮ ኦሊምፒክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቶሺሮ ሙቶ ኦሊምፒኩ የቫይረሱን ስጋት ለማምለጥ በአሥራ ስድስት ወራት ቢራዘምም ከቫይረሱ ተፅዕኖ ሊያመልጥ እንደማይችል ሰሞኑን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማመልከታቸው ይታወሳል።አዲስ ዘመን ግንቦት 12/2012
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=32747
[ { "passage": "የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ዛሬ ሰኔ 10/2012 ዓ.ም በዙም ቴክኖሎጂ በመታገዝ የቪዲዮ ኮንፍረንስ አካሂደዋል፡፡ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ተጠናቋል፡፡ሙሉ መረጃው የፌዴሬሽኑ ነው1ኛ. የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዚህ ቀደም በየክልሎቹ በመጓዝ ባደረገው ክትትል እና ድጋፍ መሰረት የክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ራሳቸውን እንዲያጠናክሩ እና የተሻለ አደረጃጀት እንዲኖራቸው ለማድረግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ካለው በጀት በመቀነስ የ2ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺህ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ወሳኔ ተላልፏል፡፡ ድጋፉም ክልሎቹ ባላቸው የእግር ኳስ እንቅስቃሴ መሰረት የትግራይ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን፤ የአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን፤ ኦሮሚያ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፤ ደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን፤ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ፌዴሬሽን እያንዳዳቸው የ300 ሺህ ብር ድጋፍ፤ እንዲሁም ቤኒሻንጉል ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን፤ አፋር ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን፤ኢትዮ ሶማሌ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፤ የጋምቤላ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የሀረሬ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን እያንዳንዳቸው የ200 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ እንዲያገኙ ተወስኗል፡፡2ኛ. የኮሮና ቫይረስ ወርርሽኝ በ2012 ሲካሄዱ የነበሩ ውድድሮች እንዲሰረዙ ምክንያት መሆኑ ይታወቃል፡፡በቀጣይ በ2013ዓ.ም የሚጀመሩ የሊግ ውድድሮችን በምን መልኩ ማካሄድ እደሚገባ የሚያጠና እና የመፍትሄ ሀሳብ የሚያቀርብ ኮሚቴ እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡3ኛ. ለ2013 ጠቅላላ ጉባኤ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ከወዲሁ እዲጀመሩ ውሳኔ ተላልፏል፡፡4ኛ. ክለቦች ያለባቸውን የተጫዋቾች ውዝፍ ደመወዝ ከፍለው እስከ ሐምሌ 5/2012ዓ.ም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሪፖርት እንዲያደርጉ ከዚህ ቀደም በተላከላቸው ድብዳቤ የተገለጸላቸው ሲሆን፤ የተጣለባቸውን ግዴታ እሰከ ተጠቀሰው ጊዜ ያልተወጡ ክለቦች የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር ተጫዋቾችን እንዳያዛውሩ እና ውል እንዳያድሱ እንዲደረግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ወስኗል፡፡5ኛ. በጊዚያዊ ጽ/ቤት ኃላፊነት ፌዴሬሽኑን ሲመሩ የቆዩት አቶ ባህሩ ጥላሁን የፌዴሬሽኑ ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ የተወሰነ ሲሆን፤ የክለብ ላይሰንሲንግ ማኔጀር የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ፍራንኮ በክለብ ላይሴንሲንግ ዳይሬክቶሬት ደረጃ እንዲሰሩ ተወስኗል፡፡6ኛ. ለኢትዮጵያ መድን፤ ኢትዮጵያ ቡና፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ አዳማ ከነማ፤ ኒያላ፤ ጉና ንግድ፤ ወንጂ ስኳር፤ ሻሸመኔ ከነማ እንዲሁም ወደ የመን በመጓዝ ለ7ዓመታት ውሃደሰንአ ለተሰኘ ክለብ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በተለያዩ ደረጃዎች ለታዳጊ፤ ወጣት፤ ለኦሎምፒክ እና ዋናው ብሄራዊ ቡድን የተጫወተው ጌታሁን መንግስቱ በአሁን ሰዓት ኑሮውን በጎዳና እየገፋ መሆኑን ለፌዴሬሽኑ በማሳወቁ ለቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች የ50 ሺህ ብር ድጋፍ እንዲደረግለት እና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ካፍ አካዳሚ ውስጥ በቋሚነት ስራ እንዲሰራ ጽ/ቤቱ በሙያው ሚሰራበት ስራ ዘርፍ እንዲፈልግለት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በዛሬ ውሎው ወስኗል፡፡", "passage_id": "c99675e9dd2921c91ee1b82e5e0475cc" }, { "passage": "በፕሬዝዳንቱ እና በሥራ አስፈፃሚዎች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ዛሬ ሊካሄድ የነበረው የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባዔ ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፏል።በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ከጠዋቱ 03:00 ጀምሮ የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔ ለማድረግ ቀጠሮ መያዙ ይታወቃል። ሆኖም ምልዓተ ጉባዔው መሟላቱ ከተረጋገጠ በኃላ በፕሬዝዳንቱ አማካኝነት የመክፈቻ ንግግር ተደርጎ ም/ፕሬዝደንቱ አቶ በለጠ ዘውዴ የ2011 ሪፖርትም ሆነ የ2012 ዕቅድ እኛ የማናውቀው በፕሬዝዳንቱ ብቻ የቀረበ በመሆኑ አንቀበለውም በማለታቸው እንዲሁም አቶ ነጋሲ (የሥራ አስፈፃሚ አባል) ፌዴሬሽኑ የቡድን ሥራ አይሰራም፣ ህግ አይከበርም፣ ግለሰባዊ ነገሮች ይበዛሉ ይህ የሚቀርበው ሪፖርትም አናቀውም በማለታቸው በተጨማሪም የፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈለቀ ዋቄ የኦዲት ሪፖርቱ ማስታወቂያ ወጥቶ ውድድር ይደረግ ሲባል ከፅህፈት ቤቱ እውቅና ውጭ የተካሄደ በመሆኑ እና ሪፖርቱ እና እቅዱም በተመሳሳይ ከእውቅና ውጭ መፈፀም የለበትም በማለት ለጉባዔው አቅርበዋል።ፕሬዝደንቱ ኃይለየሱስ ፍስኃ በበኩላቸው ሁሉም ነገር የተካሄደው ህጉን ደንቡን መሠረት ያደረገ በመሆኑ የጠቅላላ ጉባዔው አባላት በ2011 ሪፖርት እና በ2012 ዕቅድ ዙርያ ሀሳብ ይስጥ በማለት መድረኩን ክፍት አድርገዋል።ከዚህ በኃላ የነበሩት የጉባኤው መንፈሶች እጅግ መግባባት የጎደለው በሥራ አስፈፃሚዎቹ በኩል የሰፋ ልዩነት የነበረበት እና መተማመን ያልሰፈነበት ሆኖ ቀጥሎ በመጨረሻም አሉ የተባሉ ችግሮችን አጣርተው ለቀጣይ ጠቅላላ ጉባዔ የሚያቀርቡ አምስት አጣሪ ኮሚቴ በድምፅ ብልጫ በመምረጥ ጉባዔው ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፏል።የአጣሪ ኮሚቴ አባላትአቶ ዳንኤል ኃ/ሚካኤል\nአቶ ዐቢይ ካሣሁን\nአቶ ገዛኸኝ ታደሰ\nአቶ ሰለሞን\nአቶ ታምሩሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን እንመልሰበታለን", "passage_id": "de16b50be7ecd706433444957ea9f45d" }, { "passage": "የእግርኳስ ፌደሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ አባላትን ጨምሮ ሁሉም የፌደሬሽኑ ጠቅላላ ጉባዔ አባላት በተገኙበት በዚሁ መርሐግብር ላይ የኢፌድሪ ስፓርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩርና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት አቶ አሸብር ወልደጊዮርጊስ በተጋባዥነት ተገኝተዋል።በቅድሚያ የምልዓተ ጉባዔው መሟላቱን በፌደሬሽኑ ዋና ፀኃፊ ኢያሱ መርሐፅድቅ(ዶ/ር) አማኝነት በተደረገው ቆጠራ በጠቅላላ ጉባዔው በድምፅ መሳተፍ ከሚችሉ 146 አባላት ውስጥ 127 አባላት መገኘታቸው ስለተረጋገጠ ስብሰባው እንዲቀጥል ተደርጓል።ጉባዔውን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ አዲሱ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ ስለከወናቸው ተግባሮች አንስተዋል።– የፌደሬሽኑን ፅሕፈት ቤት መዋቅር ለማሻሻል የሪፎርም ጥናት ተጠንቶ ወደ ትግበራ መገባቱ-የረጅም ዓመታት ውጥን የነበረውን የፕሪምየር ሊግ ውድድር በተሳታፊ ክለቦች እንዲመራ ማስቻል-የፌዴሬሽን አሰራርን ለማዘመን በማሰብ በሦስት ቦታ ተበታትንኖ ይሰጥ የነበረውን የፌደሬሽኑን አገልግሎት ለማስቀረት የህንፃ ግዢ መከናወን– ስፖርታዊ ጨዋነት ለማስፈን በርካታ ሥራዎች የተሰሩ ሲሆን በተጨማሪም ከአጋር አካላት ጋር በሦስት ዙር የውይይት መድረክ መዘጋጀቱ– ያለአገልግሎት ለዘመናት የቆየውን የካፍ አካዳሚን ፌዴሬሽኑ ተረክቦ በቅርቡ እድሳ ተደርጓለት ወደ ስራ እንዲገባ እንቅስቃሴ መጀመሩ– ከዓለም አቀፉ ትጥቅ አቅራቢ አምብሮ ኩባንያ ጋር ለብሔራዊ ቡድኑ ነፃ የትጥቅ አቅርቦት ስምምነት መደረሱ-ከዋሊያ ቢራ ጋር ለ4 ዓመታት የሚቆይ አዲስ የ56 ሚልየን ብር የስፖንሰር ሺፕ ውል መፈፀሙ-በሀገሪቱ ከሚገኙ ከተመረጡ 16 የከፍተኛ ትምህርት ተቆማት ጋር በታዳጊዎች ስልጠና ዙርያ የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሞ ለትግበራው እንቅስቃሴ መጀመሩ-የዳኞችን አቅም ለማሳደግ በርካታ ስልጠናዎች መዘጋጀታቸውበጥንካሬ ከተነሱት ባሻገር በድክመትነት በተለይ በስፓርታዊ ጨዋነት ዙርያ እንዲሁም የፌደሬሽኑ ጠንካራ የሆነ የገቢ ምንጭ አለመኖሩ ቀርበዋል።በማስከተል የኢፊዴሪ የስፓርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር አጠር ያለ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።በመቀጠልም በፌዴሬሽኑ ዋና ፀሀፊ አቅራቢነት የጉባዔው ድምፅ ቆጣሪዎችና ቃለ ጉባዔ አጣሪ ግለሰቦችን በእጩነት ቀርበው በአባላት ድምፅ ከተሰጠባቸው በኃላ እንዲፀድቁ ሆኗል።በቀጣይነትም ለጉባዔው አስቀድሞ በተላኩት አጀንዳዎች የፀደቁ ሲሆን ከአጀንዳዎች ውስጥ ተካቶ የነበረው የፌደሬሽኑን መተዳደርያ ደንብ ለማሻሻል የቀረበ ውጥን በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ በነበረው የፊፋ ኮንግረስ የአባላት መተዳደሪያ ደንብ ወጥ እንዲሆን በቀረበው ምክረ ሀሳብ መሠረት ከአጀንዳ ውጭ እንዲደረግ መደረጉም ተያይዞ ተገልጿል።በአጀንዳው መሠረት በቅድሚያ የ2011 እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በፌደሬሽኑ ዋና ፀሐፊ የቀረበ ሲሆን በፕሬዚዳንቱ ንግግር የተነሱ ዐቢይ ጉዳዮችን በጥልቀት ለመዳሰስ ተሞክሯል። በተጨማሪም በዓመቱ ስለገጠሙ ችግሮችና ስለተወሰዱ የእርምት እርምጃዎች ዘለግ ያለ ማብራሪያ ቀርቧል።በመቀጠል በቀረበው ሪፖርት ላይ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳቦችና ጥያቄዎች በሪፖርቱ ዙርያ ቀርበዋል ፤ ከእነዚህ መካከል-በሁሉም የውድድር እርከን ላይ ይታይ ስለነበረው የውድድር መቆራረጥ ማብራሪያ ቢሰጥ-በቀረበው ሪፖርት አብዛኞቹ ችግሮችን ወደ ውጪያዊ አካላት ላይ ለማላከክ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል። ይህም ፌደሬሽኑ እራሱን ገምግሟል ለማለት እጅግ አስቸጋሪ ነው።– ካፍ በትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ዙር አጠቃላይ የግምገማ ሰነድ ባላቀረበበት ሁኔታ ውድድሩ ወደ ባህር ዳር መሸጋገሩ ተቀባይነት የሌለው አሰራር ነው። በእኛ እምነት ፌደሬሽኑ ውስጥ ባሉ አካላት በተጠነሰሰ ሴራ ውድድሩ እንዳይካሄድ ስለተደረገበት አካሄድ ፌደሬሽኑ በይፋ ማብራሪያ መስጠት ይገባዋል።– በሪፖርቱም በፕሬዘዳንቱም ንግግር ላይ አይቮሪኮስትን ማሸነፋችን እግርኳሳችን እያገገመ ስለመሆኑ ማሳያ ተደርጎ መቅረቡ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ አይገፅም።– በእግርኳስ ውድድር ሜዳዎች ላይ እየታየ የሚገኘው ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ለማስወገድ ሁሉም ባለድርሻ አካላትየየድርሻውን ኃላፊነት በጋራ መውሰድ ይገባናል።– በፕሪምየር ሊግ ተካፋይ የሆኑ የተወሰኑ ክለቦች በፌደሬሽኑ አሰራር እና አካሄድ ላይ ጫና ለመፍጠር የሚያደርጉት ጥረት– ዐምና በሊጉ አወዳደሪ አካል ይሰጥ የነበሩ ፎርፌዎች በሊጉ የመጨረሻ ውጤት ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ ስለመኖሩ፤ ስለተዘበራረቀው የተጫዋቾች የዝውውር ሂደት በሪፓርቱ አልተገለፀም። – አጠቃላይ ሪፖርቱም ሆነ ሀሳቦች እየቀረቡ የሚገኙት ሀሳቦች በወንዶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ብቻ የታጠሩ ናቸው፤ የሌሎች ውድድር እርከኖችን ያካተተ አይደለም። የስፓርታዊ ጨዋነት ጉድለቶች በአንደኛ ሊግ ከሚታሰበው በላይ እጅግ ሥር የሰደዱ ናቸው።– የፍትሕ አካላት አሳማኝ ማስረጃ በቀረበበት ሁኔታ እንኳን ተገቢ የሆነ ውሳኔ መስጠት ላይ እጅግ ደካማ አሰራር– ፌደሬሽኑ በሚያዘጋጀው መድረኮችና መርሐ ግብሮች ላይ ምንም እንኳን የጠቅላላ ጉባዔ አባል ብንሆንም ጥሪዎች በቀጥታ አይደርሱንም።– የተጠራው ጉባዔ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጉባኤ ቢሆንም የቀረው ሪፖርት አጠቃላይ በሀገሪቱ ያለውን የእግርኳስ ሁኔታ አይወክልም።– የኮካ ኮላ ውድድር በተመለከተ ክልሎች ያወጧቸው ወጪዎች በተገቢ ሁኔታ ክፍያዎች አልተወራረዱም።– የሪፎርም ጥናት ስለመደረጉ በስፋት ተጠቅሷል። ነገር ግን ከጥናት በዘለለ በተግባር ስለተደረጉ ለውጦች በቂ የሆነ ማብራሪያ በሪፖርቱ አልተካተተም።– የቻን ውድድር ለማካሄድ አቅደን አልተሳካም። በቀጣይ ከዚህ ስህተታችን መማር እንድንችል በነበረው ሂደት ዙርያ ማብራሪያ ቢሰጥበት።– በኮካ ኮላ ውድድር ዙርያ ፌደሬሽኑ የሚያገኘውን ገቢ በቀመር ለክልሎች መከፋፈል ሲገባው እየተደረገ አይደለም። በተጨማሪም አማራና ኦሮሚያ ክልሎች የውድድሩ አሸናፊ በመሆናችን በአህጉር ደረጃ ለሚደረግ ውድድር ተካፋይ የመሆን እድል ብናገኝም በፌደሬሽኑ ቸልተኝነት መሳተፍ ሳንችል ቀርተናል። ይህም ግልፅ ማብራሪያ ይፈልጋል።– በዓመቱ የውድድር አፈፃፀም ላይ በስፖርታዊ ጨዋነት ዙርያ የተሰሩ በጎ እንዲሁም አሉታዊ ችግሮች ካሉ በግልፅነት ማብራሪያ ቢሰጥ።– በጠቅላላ ጉባዔ ሪፖርት አቀራረብ ዙርያ ከጥቃቅን ሀሳቦች ላይ ከማተኮር ይልቅ ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶ መቅረብ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ዙርያ የሪፖርቱ ይዘት ማሻሻያ ያስፈልገዋል።– በሪፖርቱ በጥንካሬነት የቀረቡት ፌዴሬሽኑ እንደ አገልግሎት ሊሰጣቸው የተቋቋሙ ነገሮች እንጂ ይህ ነው የሚባሉ ተግባሮች አይደሉም።– ከአምብሮ ጋር ስለተገባው ውል ሲገለፅ በነፃ የትጥቅ ማቅረብ ስምምነት ተብሎ የተገለፀው ሀሳብ ከዓለም አቀፍ የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ጋር የሚፃረር ነው። ኩባንያው በውሉ ተጠቃሚ ሊሆንበት ስለሚችለው ነገር የተጠቀሰ ጉዳይ የለም፤ ከቀደመው ትጥቅ አቅራቢ ኩባንያ ጋር ስለነበረው ሁኔታም መብራራት ይገባዋል።– የ2011 የውድድር ዘመን በግልፅ ባልተጠናቀቀበት ሁኔታ የ2011 የውድድር ዘመን በሰላም ተጠናቋል ተብሎ ሪፖርት ላይ መቅረቡ ተገቢ አይደለም።– የፌደሬሽኑ አመራሮች ለአንድ አላማ እስከተሰለፋችሁ ድረስ በጋራ በመነባበብ መስራት ይገባችኃል።በተነሱት ሀሳቦች ዙርያ የፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በተለይም አብዛኞቹ ከጉባዔው የተነሱ ጉዳዮች በግብዓትነት የሚወሰዱ መሆናቸውና ሪፖርቱ ደካማ ስለመሆኑ አምነው ማብራሪያ ይሻሉ ባሏቸው ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ሰጥተዋል።“በቅድሚያ መግባባት የሚገባን የአይቮሪኮስቱን ጨዋታ የስታዲየም ለውጥ ጉዳይ ፖለቲካዊ አጀንዳ ለማስያዝ የሚጥሩ ኃይሎች ከፍተኛ ፍላጎት አለ። ሌላው ከፌደሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ አባላት ውስጥ ማንም አባል ውሳኔ የማስቀየር ፍላጎት ያለው ሰው የለም፤ መቐለ የተገኙት ግለሰብ የክለብ ላይሰንሲንግ ባለሙያ ናቸው። እሳቸው ሁኔታውን የተመለከቱት ከክለብ ላይሰንሲንግ እይታ አንፃር ብቻ ነው፤ ነገርግን ሂደቱን በቀጥታ የሚመለከተው የውድድር አስተዳደር አካልን ነው። እኛ መረጃው የደረሰን ከካፍ ኮሙኒኬሽን ክፍል በቀጥታ ነው፤ በተመሳሳይ ባለሙያው አጥሩ አልተጠናቀቀም፤ ከመንገድ ግንባታ ጋር በተያያዘ ያነሳቸው ነጥቦች ነበሩ። ከዚህ አንፃር ቢታይ የተሻለ ነው።”“በስፖርታዊ ጨዋነት ዙርያ የነበረብንን ህመም በግልፅ የሚገልፅ ሪፖርት አላዘጋጀንም። ነገርግን ዘንድሮ በሁለት ሳምንት ውስጥ መጠነኛ መሻሻሎች አይተናል። እውነታው ግን በብሔር ፖለቲካ የተነሳ ሊግ የተቆረጠበት ሀገር ተብለን በዓለም አቀፍ ደረጃ ስማችን እየተሳ ባለንበት የፊፋው ፕሬዚዳንት ኢንፋንቲኖ በዚች ሀገር ላይ 70ኛው የፊፋ ኮንግረስ ስለመደረጉ ጥርጥሬ ገብቷቸው ልዑክ ልከው እንዲደረግ ማጣራት እየተደረገ ባለበት ሁኔታ ብዙ የቤት ስራ አለብን።\nከዚህ ጉባዔ ስንወጣ ክለቦች የየራሳችንን ድርሻ ተወጥተን ብንሄድ ለሀገራዊ መግባባት አምባሳደር መሆን እንችላለን። በተሰሩ መልካም ጅምሮች ላይ ይበልጥ በማበረታታት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጋግዘን መስራት ይኖርብናል።”“እውነት ለመነጋገር የታዳጊ ተጫዋቾችን ማሳደግ ሳይሆን ዋነኛ ዓላማ ድርጅቱን ማስተዋወቅ ነው። በመንግስት አዲስ በተቀመጠው አሰራር መሠረት ትምህርት ሚኒስቴር ታዳጊ ተጫዋቾች ስልጠና በተመለከተ በዋነኝነት በበላይነት የሚመራው ይሆናል። በተመሳሳይ በአህጉራዊ ውድድሩን በሚመለከት ኮካ ኮላ ቃል የገባውን 124ሺህ ብር በወቅቱ መክፈል ባለመቻሉ ሲዘጋጁ የነበሩ ታዳጊዎችን በማይመለከት ገብተን ከራሳችን ለመክፈል ቼክ ብንፅፍም የውድድሩ መጀመርያ ቀን ስለነበር ሳይሳካ ቀርቷል።“ተጨማሪ ስልጠናዎችን ከመስጠት ይልቅ ያለውንን መፈተሽ ይገባናል። በፊፋና ካፍ ግምገማ መሠረት የምንሰጠው ስልጠና ችግር እንዳለበት ተነግሮናል። ለዚህም በመፍትሔነት በጥናት የደረስንበት ያሉትም አሰልጣኞች በአመዛኙ አቅማቸውን በማሳደግ ረገድ ብዙም ጥረት ሲያደርጉ አይታይም። ለዚህም አጠቃጣይ የስልጠናው ስርዓት መፈተሽ ይኖርብታል። ወደ ካፍ ስልጠና ዘለን ከመሄዳችን በፊት የራሳችንን ብሔራዊ የስልጠና ማንዋል አዘጋጅተን መስራት ይኖርብናል ፤ ይህም እስኪዘጋጅ ድረስ ተጨማሪ ስልጠና አንሰጥም”በመጨረሻም ስብሰባው ወደ ምሳ እረፍት ከመበተኑ በፊት የቀረበው ሪፖርት ከተሳታፊዎች በተሰበሰበ ድምፅ ሪፖርቱ በ105 ድጋፍ እንዲፀድቅ ተደርጓል።", "passage_id": "6cc485c9bfd0a2e844c36ef95b62d1b8" }, { "passage": "\nአለምአቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ከትናንት ጀምሮ እያካሄደ ባለው አስቸኳይ ስብሰባ የቶኪዮ 2020 የኦሎምፒክ ውድድርን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍን ጨምሮ ሌሎች አማራጮችን እያየ ይገኛል፡፡\nኮሚቴው የተሰበሰበው እየተስፋፋ የመጣው ኮሮና ቫይረስ በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ላይ ጥላ መጣሉን ተከትሎ ነው፡፡ ኮሚቴው ኮሮና ቫይረስ ሁለት አማራጮችን እንዲያስቀምጥ እንዳስገደደው አስታውቋል፡፡\nኦሎምፒኩ የሚጀመርበትን ሐምሌ 17ን ወደ ኋላ መጎተት ወይንም ወድድሩን በአንድ አመት ወይንም ከዚያ በላይ ወደፊት መግፋት ሲሆን መሰረዝ ግን ችግሩን እንደማይፈታና ማንንም እንደማይጠቅም ኮሚቴው አስታውቋል፡፡ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ “ስለዚህ መሰረዝ አጀንዳ አይደለም”፤ ዝርዝር ውይይቶች በሚቀጥሉት አራት ሳምንታት ይካሄዳሉ ብሏል፡፡\nየኮሚቴው ኦሎምፒኩን ለማስተላለፍ ማሰቡ በአለም አትሌቲክስ፣በአለምአቀፍ ፓራኦሎምፒክ ኮሚቴና በትላልቆቹ ብሄራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴዎች በበጎ ተወስዷል፡፡\nኮሚቴው በከፊልም ቢሆን ሀሳቡን ለመቀየር የወሰነው፣ ከአትሌቶች፣ከፌደሬሽኖችና ከብሄራዊ ኮሚቴዎች የመጣውን ጫና ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የቶኪዮ ኦሎምፒክ አዘጋጆች ግን ወድድሩ በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ እየወተወቱ ይገኛሉ፡፡\n\n\n", "passage_id": "dd9ba197cb508034d684b1fe8606cd94" }, { "passage": " ቦጋለ አበበ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባለፈው ዓመት በቢሾፍቱ ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ወቅት ኮሚቴው የሚተዳደርበትን አዲስ መተዳደሪያ ደንብ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ይህ መተዳደሪያ ደንብ ገና ከመጀመሪያው ውዝግብ ያስነሳና በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት መካከል አለመግባባትን እንደፈጠረ አይዘነጋም። ኮሚቴው ከትንናት በስቲያ በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ ባካሄደው አርባ አምስተኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይም መተዳደሪያ ደንቡን በተመለከተ ከጉባዔው አባላት ጥያቄ አስነስቷል። በተለይም ደንቡ ይፋ ከተደረገ ጀምሮ ተቃውሞ እንዳላት ስትገልፅ የነበረችው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በጉባዔው ላይ ጥያቄዋን ዳግም አንስታለች። በቢሾፍቱው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ይፋ የተደረገው መተዳደሪያ ደንብ የጠቅላላ ጉባዔው አባላትና ስራ አስፈፃሚው እንዲወያይበት በይደር ላይ እንደነበር ያስታወሰችው ደራርቱ፣ ኮሚቴው ከትናንት በስቲያ ባደረገው ጉባዔ ላይ ባቀረበው የ2012 ዓ.ም የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ መተዳደሪያ ደንቡ እንደፀደቀ አድርጎ ማስቀመጡ ተገቢ እንዳልሆነ በመግለፅ ጥያቄ አንስታለች። ‹‹ስራ አስፈፃሚው ባላመነበትና ባልተወያየበት ሁኔታ መተዳደሪያ ሕጉ ፀድቋል፣ መተዳደሪያ ሕጉን በተመለከተ በኮሚቴ እንዲታይ በይደር ተውነው እንጂ አላፀደቅነውም›› ያለችው ደራርቱ በኮሚቴው ውስጥ የተለያዩ ሰዎች በተለይም የፅሕፈት ቤቱ ኃላፊ ተነስተው ሌላ ሰው ሲተካ በተለይም እሷ እንደ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እንዳልተሳተፈች ተናግራለች። የኮሚቴው መተዳደሪያ ደንብ ጉዳይ ባለፈው ሳምንት በሸራተን አዲስ በተካሄደው የብሔራዊ ስፖርት ምክር ቤት ጉባዔ ላይ ለሰብሳቢው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ቀርቦም ባለድርሻ አካላት ከስፖርት ኮሚሽን ጋር ተወያይተውበት ውዝግቡን እንዲፈቱ አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ይታወሳል። የብሔራዊ ስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢው ይህን አቅጣጫ ባስቀመጡበት ሁኔታ ኮሚቴው በእቅድ አፈፃፀሙ ሪፖርት ላይ መተዳደሪያ ደንቡ በዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሕግና ደንብ መሰረት እንደፀደቀ አድርጎ ማቅረቡ ከብሔራዊ ስፖርት ምክር ቤቱ ሕግና ደንብ ጋር እንደሚጣረስ ከደራርቱ በተጨማሪ ሌሎች የጉባዔው አባላትም ጥያቄ አንስተውበታል። በጠቅላላ ጉባዔው በቀረበው ሪፖርት መሰረት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን አደረጃጀት፣ አሰራርና የሰው ሃይል አመራር ለማሻሻል የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስራዎችን እንዳከናወነ የገለፀ ሲሆን፣ በዋናነት በአሰራር ሊሻሻሉ ከሚገባቸው ስራዎች ቀዳሚዎቹ ደንቦችንና መመሪያዎችን በማዘጋጀት ማሻሻል መሆኑን በማመን ኮሚቴው ከዚህ በፊት በጠቅላላ ጉባዔ የፀደቀ ደንብ እንዳልነበረው አስቀምጧል። ሲሰራበት የነበረው ‹‹የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መቋቋሚያና መተዳደሪያ መመሪያ›› በሚል በጠቅላላ ጉባዔ ያልፀደቀና በርካታ ክፍተቶች የነበሩበት መሆኑን በመጥቀስ፣ ኮሚቴው የሕግ ባለሙያዎችን አደራጅቶ የዓለም አቀፉን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ቻርተርና የተለያዩ አገራት ተሞክሮዎችን በማካተት አዲስ መተዳደሪያ ደንብ በስራ አስፈፃሚ ቦርድ ተወያይቶና ግብዓት አክሎበት ለጠቅላላ ጉባዔ በማቅረብ መስተካከል አለባቸው የተባሉትን አስተካክሎ እንዲፀድቅ ማድረጉን ያስቀምጣል። በዚህም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መተዳደሪያ ደንብ ቀርፆ ለዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በመላክ ግብዓት እየጠበቀ እንደሚገኝ ተብራርቷል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ\nፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር\nወልደጊዮርጊስ በጉዳዩ ላይ\nለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት\nማብራሪያ፣ ጠቅላላ ጉባዔው\nመረዳት ያለበት የስፖርት\nምክር ቤቱ ያቀረበው\nየስፖርት ማህበራት ማቋቋሚያ\nመመሪያ ረቂቅና ውይይት\nየሚደረግበት ሃሳብ እንጂ\nፀድቆ መተዳደሪያ የሆነ\nደንብ እንዳልሆነ አስረድተዋል።\nከኦሊምፒክ ጋር ተያይዞ\nእያንዳንዱ የሚተላለፍ ውሳኔ\nየዓለም አቀፉን ኦሊምፒክ\nኮሚቴ ሕግና ደንብ\nመሰረት ባደረገ መልኩ\nእንደሆነ የገለፁት ፕሬዚዳንቱ፣\n‹‹እኛ እዚህ የተቀመጥነው\nየዓለም አቀፉን ኦሊምፒክ\nኮሚቴ ሕግና ደንብ\nለማስፈፀም ነው፣ የኢትዮጵያ\nኦሊምፒክ ኮሚቴ ቀዳሚ\nተግባርም ይህንኑ ማስከበር\nነው፣ ከዚህ የተለየ\nነገር ካለ ለዓለም\nአቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ\nአቅርበን ተቀባይነት ካገኘ\nእኛም እንቀበላለን›› ብለዋል።\nብሔራዊ ስፖርት ምክር\nቤቱ ባቀረበው ረቂቅ\nደንብ ላይ ኦሊምፒክ\nኮሚቴ ሳይሆን ክልሎች፣ፌዴሬሽኖች፣የታወቁ\nየስፖርት ድርጅትና ተቋማት መልስ መስጠት እንዳለባቸው የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፣ እነዚህ የተጠቀሱ ባለድርሻ አካላት በብሔራዊ ስፖርት ምክር ቤቱ ረቂቅ ደንብ ላይ ድምፅ እንዳይኖራቸው መቀመጡን አስረድተዋል። ይህን መቀበል አለመቀበል ደግሞ የእነሱ ድርሻ ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። የስፖርት ማህበራትና ፌዴሬሽኖች፣ ክልሎችና የታወቁ የስፖርት ተቋማትን ከኦሊምፒክ ኮሚቴ አባልነት ያስወጣው ረቂቅ ደንብ መሆኑን ገልፀውም፣ እሳቸው እንደ ኮሚቴው አባልና ፕሬዚዳንት በረቂቅ ደንቡ ላይ እንደማይስማሙበት ተናግረዋል። ‹‹ይሄ እንዲሆን አልፈቅድም፣ ያለክልሎች የኢትዮጵያ ስፖርት ስፖርት አይደለም፣ ያለሕዝብ ተሳትፎ ስፖርቱ ስፖርት ሊሆን አይችልም፣ እነዚህ ትልልቅ ባለድርሻ አካላት የበዪ ተመልካች ሊሆኑ አይገባም›› ሲሉም አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 27/2013", "passage_id": "82a04f598fe58ad5c12b91808119f124" } ]
b47b1d7702e6c139ef56e701f645ec19
4a980366ef66ea523c47939ecb1a465e
ከአካላዊ ውድድር የተነጠለው ስፖርት በቴክኖሎጂ ተጠናክሯል
ስፖርት የማይካተትበት ዘርፍ የለም፤ ቴክኖሎጂም እንዲሁ።ሁለቱም ዘርፎች በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ጋር በመቆራኘት ህይወትን በማቅለል ለዘመናዊው ዓለም የጎላ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ።ከዚህ ባለፈ አንዱ ለሌላኛው ቁልፍ ጉዳይ መከወኑም አልቀረም።በልምድ ይካሄድ የነበረው ስፖርት በሳይንስና ቴክኖሎጂ በመደገፉ፤ ዘመናዊውን ስፖርት ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ለይቶ ማሰብ በዚህ ወቅት አዳጋች ሆኗል።በቴክኖሎጂ የታገዙ ፈጠራዎች መበራከትም የስፖርተኞችን ብቃት በማሳደግ እንዲሁም የስልጠና ሂደቱን በማቃለልም ዘርፉን ትርፋማ ማድረግ ችሏል።የዘመኑ ስትንፋስ የሆነው ቴክኖሎጂ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ስፖርትን ተቀላቅሎ በቁጥር የማይተመኑ ለውጦችን አስገኝቷል።በስፖርት ትጥቅና የስልጠና ቁሳቁስ፣ ውድድሮችን በቀጥታ ለደጋፊዎች በማስመልከት፣ በውድድር ሜዳዎች ተገኝቶ ለመመልከት ትኬት የመቁረጫ አማራጭ፣ የስፖርት ሜዳዎች ሁለገብና ዘመናዊ እንዲሆኑ፣ ከውድድር አጨራረስ እንዲሁም ዳኝነት፣ የስፖርተኞችን መረጃና ውጤትን በመመዝገብ፣ ከዚህ ቀደም የነበረን ውድድርና ብቃት ለመገምገም፣ ስለ ስፖርቱ የሚወጡ አዳዲስ መረጃዎችን ለመከታተል፣ ስፖርተኞችን ከደጋፊዎቻቸው በማገናኘት፣ ንጹህ ስፖርትን ለማካሄድና በስፖርት የሚፈጸሙ የረቀቁ ወንጀሎችን ለማጣራት (ከአበረታች ቅመሞች ጋር በተያያዘ)፣ ከጉዳት ለማገገም (ስፖርት ህክምና)፣ በትልልቅ ጨዋታዎችና ውድድሮች ከአየር ሁኔታ ጋር በተያያዘ ችግር እንዳይገጥም እንዲሁም ዘርፈ ብዙ ግኝቶችንም አበርክቷል። በዋናነት እነዚህ ተጠቀሱ እንጂ ቴክኖሎጂ በእያንዳንዱ ስፖርት ለእያንዳንዱ ሂደት እየተወጣ ያለው አስተዋጽኦ ይዘርዘር ቢባል አዳጋች ነው የሚሆነው።ለአብነት ያህል ግን ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በጉልህ ከታዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል በሁለት ተወዳጅ ስፖርቶች የታዩትና የስፖርት ቤተሰቡን ቀልብ የሳቡትን ማንሳት ይቻላል።በአትሌቲክስ ስፖርት በመሮጫ ጫማ ላይ የነበረው የቴክኖሎጂ እገዛ የሰው ልጅ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች በመሮጥ አዲስ ታሪክ እንዲያስመዘግብ አድርጓል።በቪዲዮ የታገዘ ዳኝነት በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መተግበሩም እስካሁን በእግር ኳሱ ነጥረው ያልወጡ ጉዳዮች እንዲስተዋሉ ያደረጉ ሆነዋል። የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ዓለምን በእጅጉ እያስጨነቀ ባለበት በዚህ ወቅት ደግሞ ቴክኖሎጂ ለስፖርቱ እጅጉን አስፈላጊ መሆኑ በተግባር እየታየ ይገኛል።በተለይ ከስፖርታዊ ውድድሮች መሰረዝና ‹‹ከቤት አትውጡ›› ትዕዛዝ ጋር በተያያዘ ስፖርተኞች እንዲሁም ስፖርት ወዳዶች ቴክኖሎጂን እንደ አማራጭ ይዘውታል።የስፖርት መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ድረ ገጾችም የውድድሮች አለመኖርን ተከትሎ ከዚህ ቀደም የተካሄዱ ውድድሮችን በድጋሚ በማስታወስ ላይ ይገኛሉ።ስፖርተኞች በበኩላቸው በግላቸው የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች በተለያዩ ድረ-ገጾች ለሌላው ህዝብ በማጋራት ላይ ናቸው።አሰልጣኞችም ስፖርተኞች በቤታቸው ሲቆዩ እንዳይዘናጉ በተለያዩ ቴክኖሎጂ አፈራሽ መንገዶች ስልጠናቸውን ቀጥለዋል።የውድድር አዘጋጅ አካላት ደግሞ በአካል ስፖርተኞችን ማፎካከር ባይችሉም በስልኮች ላይ በሚጫን መተግበሪያ ውድድሮችን እያካሄዱ ይገኛሉ።የ ‹‹በቤት ቆዩ›› ቻሌንጆችም በዓለም ላይ እየተበራከቱ መሆኑ በግልጽ የሚታይ ነው። ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያም እየተለመደ ያለ ሲሆን፤ ስፖርተኞች፣ ባለሙያዎች፣ የስፖርት ማህበራት እንዲሁም ስፖርቱን የሚመሩ አካላት የብዙሃን መገናኛዎችንና ድረገጾችን በመጠቀም ህዝቡን ተደራሽ እያደረጉ ናቸው።አሰልጣኞችም በማህበራዊ ድረ-ገጾች ከሰልጣኞቻቸው ጋር ግንኙነት ያደርጋሉ። የስፖርትና የስልጠና ባለሙያዎችም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዴት እንደሚከወን ህብረተሰቡን ግንዛቤ እያስጨበጡና እያነቁም ይገኛሉ።የኢትዮጵያን ስም ከገነኑ አትሌቶች እኩል የሚያስነሳው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ አማካኝነት የሩጫ ውድድር እያካሄደ ይገኛል።‹‹ቨርቹዋል ሬይስ›› የሚሰኘው ይህ የውድድር ዓይነት እየተለመደ ያለና በርካቶች ተሳታፊ እየሆኑበትም ይገኛሉ፡፡በወቅታዊው ሁኔታ ስፖርት ለጊዜውም ቢሆን ከአካላዊ እንቅስቃሴ ጋር መለያየቱን ተከትሎም ከስፖርት ቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ የሚሰሩ ድርጅቶች ገበያቸው እየደራ መሆኑም ተስተውሏል።ፎርብስ በዚህ ጉዳይ ላይ የሰራው ዘገባ፤ ስፖርተኞች በቤት ውስጥ ከመቆየታቸው ጋር በተያያዘ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መከወኛ መሳሪያዎች ፍላጎትና ግዢ ጭማሪ አሳይቷል።በእንግሊዝ የሚገኝ አንድ የስፖርት ቁሳቁስ አምራች ከድረ-ገጹ ጋር በነበረው ቆይታ፤ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ባልታየ መልኩ የፈረንጆቹ 2020 ከገባ በኋላ ጥያቄው መበርታቱን ጠቁሟል።በተለይ የኦሊምፒክ ተሳታፊ አትሌቶች፣ ቡድኖች እና ታዋቂ አትሌቶች ደግሞ ቀዳሚ ፈላጊዎች መሆናቸው ታውቋል። ዘ ኢኮኖሚክስ ደግሞ የዓለም ስፖርት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በወራት ውስጥ ከአካላዊ እንቅስቃሴ ወደ ዲጂታል (በቴክኖሎጂ የታገዘ) መቀየሩን አመላክቷል።ይህ ‹‹ኢ-ስፖርት›› የተሰኘው ውድድር በኮምፒዩተር የሚካሄድ ሲሆን፤ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ የሚያሸልም ነው።በዚህም ምክንያት የተሳታፊዎቹ ቁጥር በእጥፍ እያደገ መሆኑ ተረጋግጧል።ቁጥራዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነም፤ እአአ በ2019 የተሳታፊዎች ቁጥር 443 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፤ ይህም ከ2018 ጋር ሲነጻጸር በ12 ከመቶ ጭማሪ ያሳየ ነው።በዚህ ዓመት ደግሞ በዚህ ጨዋታ ተሳታፊ ከሆኑ ሰዎች አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱም ታውቋል።አዲስ ዘመን ግንቦት 17/2012 ብርሃን ፈይሳ አጫጭር ዜናአትሌቷ እርዳታ አድርጋለች ኢትዮጵያን በኦሊምፒክ፣ በዓለም ቻምፒዮና፣ በዳይመንድ ሊግ እንዲሁም በሌሎች ውድድሮች በ5 እና 10 ሺ ሜትሮች የሜዳሊያ ባለቤት ያደረገችው አትሌት አልማዝ አያና እርዳታ አድርጋለች።አትሌቷ ከባለቤትዋ ጋር በመሆን ከአሁን በፊት የጀመረችውንና ከ30 በላይ የሚሆኑ አቅመ ደካማ አዛውንቶችን ለሁለተኛ ጊዜ የለገሰች ሲሆን፤ ከ50 ለማያንሱ ገቢያቸው አነስተኛ ለሆነና ወደፊት ሀገራቸውን ሊያስጠሩ ለሚጥሩ አትሌቶችም እርዳታውን ማበርከቷን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በድረ ገጹ አስነብቧል።ተረጂዎች እያንዳንዳቸው እንዳንድ ካርቶን ፓስታ፣ 5 ሊትር ዘይት እና 50 ኪሎ ዱቄት አግኝተዋል።ከዚህ ባሻገር የኮሮና ወረርሽኝን (ኮቪድ 19) ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት የሚውል 150 ሺህ ብር ለድጋፍ አስተባባሪው አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ አስረክበዋል።አትሌቷ በጥቅሉ 267ሺ ብር እርዳታ ነው ያደረገችው።ሁለተኛ ዙር የምገባ መርሃ ግብር ተጀመረ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስና እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች እንዲሁም ቢጂአይ ጋር በመሆን ለአንድ ወር የሚቆይ የምገባ መርሃ ግብር ማካሄዳቸው የሚታወስ ነው።አሁን ደግሞ ለአንድ ወር የሚቆይና በአዲስ አበባ ስቴድዮም ዙሪያ የሚገኙ ችግረኞችን የሚያቅፍ ሁለተኛ ዙር የምገባ መርሃ ግብር በይፋ ተጀምሯል።ምገባውን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስና እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች፣ ከኢትዮጵያ ጸረ አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት፣ ከወጋገን ባንክ፣ ከቢጂአይ ኢትዮጵያ እና ከአቶ አብነት ገብረመስቀል ጋር በመተባበጀር የሚካሄድ መሆኑም ታውቋል። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በቀጣዩ ወር ይመለሳል በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጡ የሊግ ውድድሮች እየተመለሱ መሆኑ ይታወቃል።ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆነው ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግም በቀጣዩ ወር የሚቀጥል መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።ባሳለፍነው ሳምንት መጀመሪያ ልምምድ የጀመሩት ክለቦቹ ከ17 ቀናት በኋላ ውድድር የሚጀምሩ መሆኑን የፕሪምየር ሊጉ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሪቻርድ ማስተር አረጋግጠዋል።በሊጉ ከሚሳተፉ 20 ክለቦች ውስጥ ባሉ ተጫዋቾች በተደረገው የኮቪድ 19 ምርመራ በሶስት ክለቦች ውስጥ የሚገኙ ስድስት ተጫዋቾች ላይ መገኘቱም የሚታወስ ነው።አዲስ ዘመን ግንቦት 17/2012
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=33056
[ { "passage": " ጉለሌ ክፍለ ከተማ በከተማ ደረጃ የሚካሄደውን 7ኛውን የተማሪዎች የስፖርት ውድድር ለማስተናገድ ሽር ጉድ እያለ ነው፡፡ ለመላው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተማሪዎች የስፖርት ውድድር ጉለሌ ክፍለ ከተማን ወክለው የሚወዳደሩ ተማሪዎች የሚያደርጉትን የውስጥ ውድድር ምን እንደሚመስል እና ክፍለ ከተማው በከተማ ደረጃ የሚያካሂደውን የተማሪዎች የስፖርት ውድድር ቅድመ ዝግጅት በምን አይነት ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን፤ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ማህበራት ማደራጀት ተሳትፎና የሥልጠና ውድድር ዋና የስራ ሂደት መሪ አቶ ተክለማሪያም ሊጋባ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ተናግረዋል።አቶ ተክለማርያም በ2010 ዓ.ም በተካሄደው የመላ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተማሪዎች የስፖርት ውድድሮች ጉለሌ ክፍለ ከተማ አጠቃላይ የውድድሩ አሸናፊ ሆኖ በማጠናቀቁ፤ ዘንድሮ የሚካሄደውን 7ኛውን የመላ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተማሪዎች የስፖርት ውድድር ክፍለ ከተማው እንዲያዘጋጅ እድል የተሰጠው መሆኑን ይናገራሉ።ለ7ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎች የስፖርት ውድድር ክፍለ ከተማችንን ወክለው የሚወዳደሩ እስፖርተኞችን ለመመልመል የውስጥ ውድድሩ በሶስት ምድብ ተከፍሎ እየተካሄደ መሆኑን በማስረዳት፤ ከ5 እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ በቀኑ የትምህርት መርሀ ግብር የሚማሩ የመንግሥትና የግል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በውድድሩ እንደሚሳተፉና በአንደኛና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በስድስት የስፖርት አይነቶች ማለትም በእግር ኳስ፣ በቅርጫት ኳስ፣ በእጅ ኳስ፣ በጠረጴዛ ቴኒስ እና በአትሌቲክስ የውድድር ዓይነቶች በመካሄድ ላይ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም በአትሌቲክስ፣ በጠረጴዛ ቴኒስና በዳርት በነዚህ በሶስቱ የስፖርት አይነቶች አካል ጉዳተኛ የሆኑ ተማሪዎች የውስጥ ውድድራቸውን እያካሄዱ እንደሆነ ባለሙያው ገልጸዋል።በሶስተኛው ምድብ የሚካሄደው የውስጥ ውድድር እንደ ቦክስ፣ ጂምናስቲክስ፣ ማርሻል አርት፣ ክብደት ማንሳትና መሰል ስፖርቶችን የሚይዝ ሲሆን፤ በነዚህ ስፖርቶች ውድድር ለማካሄድ በጣም አስቸጋሪ መሆኑን ገልፀው፤ በተለያዩ በክፍለ ከተማው በሚገኙ የስልጠና ጣቢያዎች ስፖርተኞችን እርስ በእርስ በማወዳደር፤ ባለሙያዎችንና ቴክኒክ ኮሚቴዎችም በቦታው ተገኝተው ውድድሩን እየተከታተሉ ክፍለ ከተማውን የሚወክሉ ስፖርተኞችን በመመልመል ላይ እንደሆኑ ገልጸውልናል። በአጠቃላይ በከተማ ደረጃ የተማሪዎች የስፖርት ውድድሩ የሚካሄደው በ17 የስፖርት አይነቶች መሆኑን ያስረዳሉ።ባለፈው ዓመት አድርገነው ከነበረው ቅድመ ዝግጅት አንጻር ዘንድሮ የተሻለ ልምድ አለ ለማለት አያስደፍርም። ነገር ግን ካምናው በተሻለ በውስጥ ውድድራችን የሴት ስፖርተኞች ተሳትፎና ተነሳሽነት ጨምሯል። በተለይም ሴት ተወዳዳሪዎች አትሌቲክስና እግር ኳስ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረጋቸው የተሻለ ተሞክሮ ነው። በዚህም በቀጣይ ክፍለ ከተማውን የሚወከሉ ሴት ተተኪ ስፖርተኞችን ያፈራንበት ውድድር ነው። አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የውስጥ ውድድራቸው ወረዳቸውን ወክለው ስለሆነ እያካሄዱ ያሉት በጣም በተጠናከረ መንገድ መሆኑን ገልጸዋል። በተጠናከረ ሁኔታ ባለሙያዎቹም በየውድድር ሜዳው ተመድበው ሁሉንም ጨዋታዎች ትኩረት ሰጥተው በመከታተል ክፍለ ከተማውን የሚወከሉ እስፖርተኞችን በመመልመል ላይ መሆናቸው ከአምናው የተሻለ ጥሩ ተሞክሮ ነው ብለዋል አቶ ተክለማሪያም።በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል የሚካሄደው የተማሪዎች የውስጥ ስፖርት ውድድር በበጀት እጥረትና ርዕሳነ መምህራን ቁርጠኛ አቋም ወስደው ባለመስራታቸው ምክንያት የውስጥ ውድድሩ እየተካሄደ እንዳልሆነ አቶ ተክለማሪያም ጠቁመዋል።\nአቶ ተክለማርያም በክፍለ ከተማው ስር ከሚገኙ 16 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የተወዳዳሪ እስፖርተኞችን ስም ዝርዝር የላኩልን ሶስት ትምህርት ቤቶች ብቻ ናቸው ብለዋል። ሌሎቹ 13 ትምህርት ቤቶች በቶሎ የተወዳዳሪዎችን ስም ዝርዝርና የውስጥ ውድድሩን በያዝነው ሳምንት እንዲጀምሩ ቁርጠኛ አቋም ወስደን ወደታች ወርደን በመስራት ውድድሩን እንዲጀምሩ እናደርጋለን ፤ የበጀት ችግሩንም ከርዕሳነ መምህራን ጋር ውይይት በማድረግ ለመቅረፍ እየሰራን ነው ብለዋል።ተማሪዎች ለባህል ስፖርቱ ፍላጎት አለማሳ የትና በውድድሩም ለመሳተፍ ፍቃደኛ አለመሆን ይታያል። በዚህ ምክንያት የባህል ስፖርቱን በውስጥ ውድድራችን ለማካሄድ ሁሌም ስለምንቸገር ጎን ለጎን ሌሎች የተመልካችን ቀልብ የሚስቡ ስፖርቶችን በማካሄድ ባህላዊ ስፖርት ውድድሮቹን በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄዱ እያደረግን ነው በማለት የውስጥ ውድድሩን ሲያካሂዱ የገጠማቸውን ችግርና ችግሩን ለመፍታት የወሰዱትን የመፍትሄ ሀሳብ አቶ ተክለማሪያም ገልጸውልናል።ከጥንት ጀምሮ ታዋቂና ዝነኛ እስፖርተኞች የትነው መነሻቸውና መፍለቂያቸው ከተባለ ትምህርት ቤት ነው። ነገ ላይም ተተኪ እስፖርተኞች የሚገኙት ከታች ከሰራን ብቻ ነው። ከታች ባለመስራታችን አሁን ላይ ሀገራችን በምትታወቅበት በአትሌቲክስ ስፖርት እንኳን የውጤት ቀውስ ውስጥ እየገባች ነው። ደግሞም ሁሉም ተማሪዎች ዶክተር፣ መሀንዲስ፣ ኢንጂነር፣ መምህር ወ.ዘ.ተ ከመሆን ባለፈ ነገ ሀገራቸውን በዓለም መድረክ እንደ ብርቅየ አትሌቶቻችን ባንዲራዋን ከፍ የሚያደርጉ ተተኪ እስፖርተኞችን ልናገኝ እንችላለን። ባጠቃላይ ተማሪዎች እራሳቸውን ካልባሌ ቦታና ከሱስ የሚያርቁበት፣ ጤናቸውን የሚጠብቁበትና የሚዝናኑበት፣ ከሌሎች ተማሪዎች ልምድ የሚወስዱበትና የእርስበርስ ግንኙነታቸውን የሚያጠነክሩበት ነው። እንዲሁም እኛ ክፍለ ከተማውን ወክለው የሚወዳደሩ ብቃት ያላቸው እስፖርተኞችን የምናገኝበት ውድድር ነው በማለት የውስጥ ውድድሩን ማካሄዳቸው የሚሰጠውን ፋይዳ አቶ ተክለማሪያም ነግረውናል።ጥር 25 ቀን 2011 ዓ.ም የሚጀመረውን የመላ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተማሪዎች የስፖርት ውድድር ለማካሄድ ክፍለ ከተማው እያደረገ ያለውን ቅድመ ዝግጅት እንዲህ ሲሉ አቶ ተክለማሪያም ያብራራሉ፤ መጀመሪያ ውድድሩን አስተዳደሩ በኃላፊነት እንዲቀበለው ግንዛቤ የመፍጠር ሰራ እየተሰራ ነው። በሁለተኛ ደረጃ ለውድድሩ የሚያስፈልገውን በጀት እንዲያዝ አድርገናል። በሶሰተኛ ደረጃ ውድድሩ የተሳካ እንዲሆን የሚያስተባብሩ አበይት ኮሚቴዎችን የማቋቋም ሰራና በክፍለ ከተማው ያሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ኃላፊነታቸውን ቆጥሮ የማስረከብ ስራ ነው የሰራነው። በአራተኛ ደረጃ በክፍለ ከተማው አዘጋጅነት የሚካሄደው የከተማ አቀፉ የስፖርት ውድድር የተሳካ እንዲሆን ከአስሩ ክፍለ ከተማ ባለሙያዎች ጋር በከተማ አስተዳደሩ የውድድር መመሪያዎቹ ላይ ለሶስት ጊዜ ያክል ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።በከተማውና በክፍለ ከተማው ያሉትን የማዘውተሪያ ሥፍራዎችና የስፖርት ሜዳዎችን ለውድድሩ ያለምንም ችግር ለመጠቀም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የጋራ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንገኛለን ብለዋል አቶ ተክለማሪያም።\nእንደ አቶ ተክለማርያም ማብራሪያ ከተማ የተማሪዎች የስፖርት ውድድሩ ሲካሄድ የዳኞችንና የአስተባባሪዎችን የውሎ አበል ክፍያ፣ የዋንጫ ግዢዎች፣ ሽልማቶች እና አስፈላጊ ተያያዢ ቁሳቁሶችንና ወጪችን ከተማ አስተዳደሩ እንደሚያዘጋጅና እንደሚሸፍን ጠቁመዋል።\nበቀስት፣ በኩርቦና ገበጣ ባለ16ና ባለ12 በሶስቱ የባህል እስፖርቶች ብቻ የውስጥ ውድድሮች እየተካሄዱ እንደሆነ፤ በከተማ ደረጃና 3ተኛው ሀገር አቀፍ የተማሪዎች ስፖርት ውድድር በመጭው መጋቢት ወር በመቀሌ ከተማም ሲካሄድ በነዚሁ የስፖርት አይነቶች ብቻ እንደሚካሄድ፤ የባህል እስፖርት ውድድር የሚካሄድባቸውን የመጫዎቻ ቁሶችን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህል ስፖርት ፌዴሬሽን እንደሚያቀርብላቸው አቶ ተክለማሪያም ገልጸውልናል።በአጠቃላይ አዘጋጅ እንደመሆኑ አመራሩ፣ የስፖርት ባለሙያውና ሴክተር መስሪያ ቤቶች ልዩ ትኩረት ሰጥተው በጋራ እየሰራ እንዳሉ፤ ከከተማው ስልጠናና ውድድር ዳይሬክቶሬት ጋራ በቅርበትና በቅንጅት እየሰራ መሆኑ ክፍለ ከተማውም የተሰጠውን ኃላፊነት በሚገባ እየተወጣ እንዳለ፤ ውድድሩንም በተሳካ ሁኔታ እንደሚያካሂድ ያላቸውን ከፍተኛ ግምት አቶ ተክለማርያም ይገልፃሉ።ከባለሙያዎች ጋር በቅርበትና በሰፊው በመስራታቸው ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2010ዓ.ም በተካሄደው የመላው የአዲስ አበባ ነዋሪዎችና ተማሪዎች የስፖርት ውድድር ጉለሌ ክፍለ ከተማ ለተከታታይ አምስትና ከዚያ በላይ ዓመታት ውድድሩን በአንደኛ ደረጃ እንዳጠናቀቀ አውስተው፤ ባለሙያዎችን ያሳተፈ ስራ ከተሰራ ውጤታማ የማይሆንበት ምንም ምክንያት እንደማይኖር ከአሁን በፊት የነበራቸውን ምርጥ ተሞክሮ በመጥቀስ ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ጥር 10/2011ሰለሞን በየነ", "passage_id": "836f74eafda384cd30c38653a31bf7aa" }, { "passage": "የስፖርት ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው በእጅጉ እየጨመረ እንደመጣ ይታወቃል። የዓለም አገራት የስፖርት ሴክተሩን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ በመረዳት ብቻ የሚቆሙ እንዳልሆኑ በዘርፉ ያስመዘገቡት ውጤት ማሳያ ነው። በዓለማችን በበርካታ አገራት ከሌሎች ሴክተሮች ባልተናነሰ መልኩ ለስፖርት ልማቱ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይን በማፍሰስ ስማቸውን በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ብሎ እንዲጠራ ከማድረግ አልፈው ብዙ ማትረፍ ችለዋል፡፡ ለስፖርት ሴክተሩ ትልቅ ትኩረት መስጠት በማህበራዊ ፋይዳው አምራችና ጤናማ ዜጋን በማፍራት\nረገድ ያለውን ውጤት ከመረዳት ይመነጫል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ ትላልቅ ውድድሮች በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ከሚገኘው ድል ጀርባ\nለአገር ፖለቲካዊ ትርፍ ማጣጣም ማስቻሉንም መታዘብ ይቻላል፡፡ ስፖርተኞች ከውድድር ድል በኋላ የሚያገኙት ረብጣ የሽልማት ገንዘብና\nየአገር ኢኮኖሚን በማንቀሳቀስ የሚገኘው ትርፍም ቀላል አይደለም፡፡ የስፖርቱን ዘርፈ ብዙ ፋይዳን በጥልቅ በመረዳት የስኬት ማማ\nላይ የወጡ እንደ ጀርመን ያሉ አገራትን ማንሳት ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለስፖርት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ረገድ ጀርመን\nበግንባር ቀደምነት ተጠቃሽ ናት። ይህች አገር ስፖርቱ በጠንካራ የፋይናንስ መሠረት ላይ ማቆም መቻሏ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መሠረቱን\nሳይለቅ መጓዝ የቻለ አደረጃጀት መፍጠሯ ለስኬቷ ምክንያት ተደርጎ ይነሳል፡፡ የጀርመን መንግሥት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ከሚያፈስባቸው\nዘርፎች ዋነኛው ስፖርት ሊሆን የቻለውም ለዚህ ነው፡፡ ስፖርት በጀርመን ኢኮኖሚ ውስጥ 2 ነጥብ 2 በመቶ ድርሻ ይይዛል። ስፖርቱን በፋይናንስ\nአቅም እንዲጎለብት ከማድረግ በተጓዳኝ፤ ጠንካራ አደረጃጀት የተዘረጋለት ነው። በጀርመን የስፖርት ዘርፍ ይህን መልክ መላበሱ ከዘርፉ\nየሚገኘው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳ እንዲጎላ ማድረጉ ይነሳል። በኢትዮጵያ ለስፖርቱ ዘርፍ የተሰጠውን ትኩረትና ውጤት\nከሌሎች አገራት አንጻር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ በቀደሙት ጥቂት ዓመታት ለስፖርቱ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች፣ ከመንግሥትና ከሌሎች\nባለድርሻ አካላት በኩል ኢትዮጵያ ለስፖርቱ ዘርፍ ተገቢ ትኩረት መስጠቷ ይነገራል፡፡ ለስፖርት ዘርፍ በተገቢው ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶት\nእየተሰራ አለመሆኑንና የዘርፉ እድገት በቁልቁለት ጉዞ ውስጥ መሆኑም በሌላ ወገን ይነሳል። የስፖርት ሴክተሩ ውጤት አልባ መሆኑ\nግን ሁለቱንም ወገኖች እንደሚያስማማ ለመታዘብ ይቻላል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በመንግሥት ደረጃ ይኸው እውነታ ታምኖበት እየተሰራ\nስለመሆኑ በተደጋጋሚ እየተነገረ ይገኛል። በኢፌዴሪ ስፖርት\nኮሚሽን የዕቅድ በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንድሪስ አብዱ፤ በአገሪቱ ባለፉት ሁለት የዕድገትና\nትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመናት ዘርፉ ለአገሪቱ ማበርከት ካለበት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጠቀሜታዎች አንፃር በሚፈለገው\nደረጃ ላይ አለመገኘቱና ውጤቱም በመላ አገሪቱ ተደራሽነት ላይ ክፍተቶች መኖራቸው እንደታመነበት ይናገራሉ:: ለዚህም የስፖርት ሴክተሩን\nመሠረታዊ ችግር በተረዳ መልኩ የ10 ዓመት የስፖርት ሴክተር ስትራቴጂክ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እንዲሆን በኮሚሽኑ በኩል እንቅስቃሴ\nከተጀመረ መሰንበቱን ያስረዳሉ፡፡ ስፖርቱን ወደፊት\nለማራመድ እንቅፋት ከሆኑ መሠረታዊ ምክንያቶች መካከል በዋነኛነት ከአደረ ጃጀት፣ ከፋይናንስ፣ ከሰው ኃይል ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች\nመሆናቸውን የጠቆሙት የኮሚሽኑ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር አቶ እንየው አሊ፤ የ10 ዓመቱ ስትራቴጂክ እቅድ የተጠቀሱትን\nክፍተቶች በጥናት እንዲመልስ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ያስቀምጣሉ፡፡ ስትራቴጂክ ዕቅዱ አገራዊ የስፖርት ሪፎርምን መነሻ በማድረግ\nበስፋት የተዘጋጀ መሆኑንም ይገልፃሉ። በመሆኑም በአገሪቷ ቀጣይ የስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ለውጥና ውጤት ማምጣት እንደሚያስችል\nታምኖበታል፡፡ የስፖርት ሴክተሩ ሪፎርም ፕሮግራም ዘርፍን መለወጥ የሚችሉ ብዙ ያመላከታቸው ነጥቦች እንዳሉም ያስረዳሉ። በዚህም\nከአደረጃጀት ፣ ከፋይናንስ፣ ከሰው ኃይልና ሌሎችም ጉዳዮች አንፃር ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት እንደሚቻል ተስፋ የተጣለበት መሆኑን\nይጠቅሳሉ፡፡ በሪፎርሙ ላይ የሴክተሩ ችግሮች የተለዩ ሲሆን በተመሳሳይ መፍትሄዎች መመላከታቸውንም ያክላሉ። ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ\nተግባራዊ የሚደረገውና ከስፖርት ሪፎርሙ የሚቀዳው የ10 ዓመቱ ስትራቴጂክ እቅድ ዘርፍን የተሻለ እንደሚያደርገውም ያላቸውን እምነት\nይገልፃሉ፡፡ አቶ እንድሪስ በበኩላቸው፤\nበቀጣይ ዓመት ተግባራዊ የሚደረገው ስትራቴጂክ ዕቅድ ትኩረት ያደረጋቸው አንኳር ጉዳዮች መኖራቸውን በመጥቀስ በሴክተሩ በቀጣይ\n10 ዓመታት በትኩረት የሚሰራባቸው ተብለው የቀረቡት ቁልፍ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች እንዳሉ ይናገራሉ:: በመጀመሪያ መንግሥታዊ የስፖርት\nአደረጃጀቶችን የመፈፀም እና የማስፈፀም አቅም በማጎልበት፤ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎችን እና የአሠራር ሥርዓቶችን ተግባር ላይ ማዋል\n፤ ሕዝባዊ የስፖርት አደረጃጀቶችን በዓለም አቀፍ እና በአገር አቀፍ መስፈርቶች መሠረት ማደራጀት የስትራቴጂክ እቅዱ ትኩረት መሆናቸውን\nያስቀምጣሉ:: በሁለተኛ ደረጃ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የማሰልጠኛ ማዕከላት ተደራሽነት፣ ሕጋዊነት እና ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን\nመሠረት በማድረግ በጥራት የሚገነቡበትን ስልት ሥራ ላይ ማዋል ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ያስረዳሉ። በአህጉር እና ዓለም አቀፍ የውድድር\nመድረኮች በተፈጥሮ ብቃታቸውን መሠረት በማድረግ አገራችንን የሚወክሉ እና ውጤታማ የሆኑ ተተኪ ስፖርተኞችን በሳይንሳዊ ስልጠናዎች\nማፍራት ትኩረት ተደርጎ የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑንም ያብራራሉ፡፡ ስፖርት ለማህበራዊ ልማትና ለአገር ብልፅግና ፣ ለሕዝቦች መቀራረብ\n፣ ለገፅታ ግንባታ እና ለቱሪዝም ዕድገት መሣሪያ ሆኖ እንዲያገለግል ትኩረት ሰጥቶ መስራትም የስትራቴጂክ እቅዱ ቁልፍ ጉዳዮች ናቸው።\nበስትራቴጂክ ዕቅዱ የተጠቀሱትን አንኳር ጉዳዮች መሠረት አድርጎ የተዘጋጀው ግብ ወደ ተግባር መቀየር ከተቻለም የስፖርት ሴክተሩ\nውጤታማ መሆን እንደሚችል እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡የባህልና ቱሪዝም\nሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ፤ በአገር አቀፍ የስፖርት ፖሊሲ ባለፉት ሁለት አስር ዓመታት የተመዘገቡ በርካታ አበረታች\nውጤቶች ቢኖሩም የአገራችን የስፖርት ዕድገት ከዕድሜው አኳያ ሲመዘን በሚፈለገው ደረጃ ባለማደጉ ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ ያመላክታሉ።\nበአሁኑ ወቅት መንግሥት ስፖርቱን እንደ አንድ የልማትና ብልፅግና መሣሪያ አድርጎ በመውሰድ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየሰራ እንደሚገኝ\nየሚናገሩት አቶ ሃብታሙ ፤ የስፖርት ዘርፍ በታሪኩ በዚህ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶት እንደማያውቅ ያብራራሉ:: የብሔራዊ የስፖርት ምክር\nቤት በኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ሰብሳቢነትና የበላይ ጠባቂነት መመራቱ መንግሥት ለስፖርቱ ሴክተር የሰጠውን\nትኩረት እንደሚያሳይም ያስቀምጣሉ፡፡ በመሆኑም የስፖርት ዘርፍን ከትናንት በተሻለ መልኩ ዛሬ ትኩረት በማግኘቱ ዕድሉን በአግባቡ\nበመጠቀም ጠንክሮ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡አዲስ ዘመን አርብ ጥር 22/2012ዳንኤል ዘነበ\n", "passage_id": "03113203decaadfcc71b27a06362f673" }, { "passage": "ጥንታዊያኑ ግሪኮች አማልክትን ለማስታወስ ስፖርታዊ ክብረ በዓላትን ያዘጋጁ ነበር።\nበዘጠነኛው ምዕተ ዓመት አካባቢም የሶስቱ ግዛት መሪዎች ጊዜያዊ የተኩስ አቁም አድርገው ነበር። «የተቀደሰ ስምምነት» የሚል ርዕስ\nየተሰጠው ስምምነቱ ስፖርታዊው ክብረ በዓል «ኦሊምፒክ» እስኪጠናቀቅ የነበሩትን ቀናት የሚሸፍን ነበር። ታሪክ ይህንን ሲጠቅስ ሰነዶች ደግሞ የኦሊምፒክ ግብ ለሰላም ግንባታ እንዲሁም\nለወጣቱ ትውልድ ከልዩነት የጸዳ ሰላማዊ ዓለምን ለማሳየት መሆኑን ይጠቁማሉ። ይህ የስፖርት አስኳል ሃሳብ ሲሆን፤ ስፖርታዊ ውድድሮች\nደግሞ መከባበር፣ መረዳዳት፣ አብሮነት፣ ወዳጅነት እና እኩልነት የሚዘመርባቸው መድረኮች ናቸው። ወደ 19ኛው ክፍለ ዘመን መለስ ብንልም በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት (እአአ\nበ1914) የገና ወቅት የእንግሊዝና ጀርመን ጦሮች ትጥቅ ፈተው እንደነበር የጽሁፍ ማስረጃዎችን ማንሳት ይቻላል። ለአንድ ቀን በተካሄደው\nተኩስ አቁም ሁለቱ ተዋጊዎች ሰላማዊውን ጦርነት በመምረጣቸው ዕለቱን በኳስ ጨዋታ ሊያሳልፉም ችለዋል።የሚሊኒየሙን ግብ ለማሳካት ከተቀመጡት መንገዶች መካከልም አንዱ፤ ሰላምን በስፖርት\nለማሳደግ የሚለው ተጠቃሽ ነው። ዩኔስኮም ስፖርትን ተጠቅሞ ዓላማውን ለማሳካት አቅዶ በመስራት ላይ ነው የሚገኘው።     በስፖርት ምክንያት የበረዱ ግጭቶች፤ ከስፖርታዊ ውድድሮች የተነሱ ወዳጅነቶችንም\nዓለም በታሪክ ማህደሯ አስፍራለች። ከጥንታዊው ኦሊምፒክ እስከ አለፈው ዓመቱ የክረምቱ ኦሊምፒክ ድረስም ስፖርት የሰላም ወዳጅና\nመሰረት መሆኑን በተግባር አሳይቷል።  በኢትዮጵያስ፤ ስፖርት «ለሰላምና ወዳጅነት» እየዋለ ነው ወይስ ሚናው ተዘንግቷል?\nይህንን ጥያቄ ይደግፍ ዘንድ አንዳንድ ነጥቦችን እናንሳ። ባለፉት ዓመታት ሃገሪቷ ውስጥ በነበረው ሁኔታ ትልልቅ ውድድሮች ሳይካሄዱ\nቀርተዋል። በስፖርት ማህበራት ይዘጋጁ የነበሩ ሻምፒዮናዎችም ገባ ወጣ ይሉ ነበር። ሁኔታዎችን ተቋቁመው በተካሄዱ ውድድሮች ላይም\nተሳታፊዎቹ እንደሚጠበቀው ሙሉ አልነበሩም።       እንደ ብሄራዊ የኦሊምፒክ ውድድር የሚታየው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች፤ ለ6ኛ\nጊዜ በ2010ዓም መካሄድ ቢኖርበትም እስካሁን አልተካሄደም። በተያዘው ዓመትም ስለመካሄዱ እርግጠኛ መሆን እስካሁን አልተቻለም።\nሌላኛው ዓመታዊና በጉጉት ተጠባቂ ከሆኑት ውድድሮች መካከል የሚጠቀሰው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውድድር፤ ከ2007 በኃላ ተቋርጧል።\nየትምህርት ቤቶች እና የባህል ስፖርቶች  ውድድርም በመሃል ተቋርጠው\nነበር።  የስፖርት ሚና አንድነትና ወዳጅነትን ማሳየት ከሆነ ግጭቶች በመነሳታቸውና አለመረጋጋት\nበመኖሩ ምክንያት ውድድሮች ሊቋረጥ አይገባም። እንዲያውም የግጭትና የአለመግባባትን እሳት እንደ ማጥፊያ መሳሪያ መጠቀም ይቻላል።  አንድ የሚታወቅ እውነት አለ፤ ይህም ብሄራዊ ቡድኖች  በትልልቅ ውድድሮች ላይ የተሳታፊነት ዕድል ሲያገኙ የህዝቡ አትኩሮት በሙሉ\nወደዚያው ይሆናል። አትሌቶች ሮጠው ሲያሸንፉ አሊያም በየትኛውም ስፖርት አሸናፊነት ሲኖር ደግሞ የሃገር ፍቅር ስሜቱ ከምን ጊዜውም\nበላይ የላቀ ይሆናል። በመሆኑም አለመግባባቶችን ለማለዘብ ስፖርትን ይበልጥ ማጉላትና ማድመቅ ጠቃሚ ይሆናል። ፊሊፒንስና ኮሎምቢያ ህጻናትን በፕሮ ጀክቶች በመያዝና በማበረታታት ሰላምን ለማሳደግ\nፕሮጀክት ቀርጸው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ሃገራት ናቸው። ዓላማውም ህጻናት በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወቅት ማሸነፍና መሸነፍን፣ የቡድን\nስሜት እንዲሁም መሪነትን አዳብረው፤ በወደፊት ህይወታቸው ነገሮችን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የሚረዳቸው ይሆናል። ይህም መጪውን\nትውልድ ቅድሚያ ለሰላም እንዲሰጥ የሚያደርግ ነው። ሃገራት በዓለም ላይ ስማቸው ከሚነሳባቸው በርካታ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ስፖርት\nነው። አንድ ቡድን ድል አስመዝግቦ ዋንጫ ሲያነሳ አሊያም አንድ ተወዳዳሪ አሸንፎ ሜዳሊያ ሲያጠልቅ ደስታው የግሉ ብቻ አይሆንም።\nውጤቱ የስፖርተኞች የጥረት ውጤት ቢሆንም የሚወክለው ግን ሃገርን እስከሆነ ድረስ የጋራ ያደርገዋል። እንዲህም ሲሆን፤ በከፍተኛ ደረጃ የብሄራዊ ስሜትንና የአብሮነት አስተሳሰብን\nያነሳሳል። ህዝቡ ስፖርትን የሚወድ እንደመሆኑም በውድድሮች አለመ ግባባቱን ገታ አድርጎ ትኩረቱን ወደዚያው ለማድረግ ያስችላል።\nየተለያዩ መልዕክቶችን በማሰራጨትም ህዝቡ ዘንድ በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ ይቻላል። ይህ የስፖርት ባህሪም ዓለም አቀፋዊ እንደመሆኑ በኢትዮጵያም ኮሽ ባለ ቁጥር ውድድሮች ተቋረጡ ከማለት ይልቅ እንደ መሳሪያ\nመጠቀሙ የተሻለ እንደሚሆን የሚመለከታቸው ሁሉ ሊያስቡበት ይገባል።አዲስ ዘመን የካቲት 18/2011", "passage_id": "95c1de2f14a4c44fae469a58769e25d4" }, { "passage": "የዓለም\nታሪክ ሴቶችን በስፖርት ዓውድ መመዝገብ የጀመረው ዘግይቶ ነው ። በ19ኛው ክፍለ ዘመን ጥቂት ሴቶች በስፖርቱ ተሳትፎ ከማድረጋቸው በፊት ሴት ልጅ በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የመሳተፍ አካላዊ ብቃት የላትም የሚል አመለካከት ነበር። በዚህ የተነሳም ሴቶችን ስፖርት ሜዳ ውስጥ መመልከት እንደ ነውር ይቆጠር ነበር። ይሁንና በጥቂቶች እንዲሁም የተሻለ እሳቤ በነበራቸው ሰዎች ጥረት የሴቶች የስፖርት ተሳትፎ እውን ሆኖ ዛሬ ካለው ነባራዊ ሁኔታ መድረሱን ታሪክ ያወሳል። የኢትዮጵያ ልምድም ከሌላው ዓለም የተለየ አልነበረም። ሴት ልጅን ከጓዳ ብቻ ያዛመደውን ልማድ ለመቅረፍ በርካታ ዓመታት ተቆጥረዋል። ተሳትፎው በሂደት እየጎለበተም በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ስፖርቱን ቋሚ ሥራቸው በማድረግ ከራሳቸው አልፈው ለሌሎችም የሥራ ዕድል እስከ መፍጠር ደርሰዋል። ብቃታቸውም ቢሆን ከኢትዮጵያም ባለፈ በኦሊምፒክም ጭምር ባስመዘገቡት ድል ተመስክሮላቸዋል። በ1990ዓ.ም በወጣው የኢፌዴሪ ስፖርት ፖሊሲ ላይ «ሴቶች በስፖርት እንቅስቃሴ ቀጥተኛ ተሳታፊና በእኩል ደረጃ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል» በሚል ሰፍሯል። በዚህም\nመሰረት ከወንዶች እኩል በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችም ሆነ ሙያዊ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ ተደርጓል። ይህ ብቻውን በቂ ባለመሆኑም በሴቶች እየተመራ ሴቶች ብቻ የሚፎካከሩበት መድረክም ተዘጋጅቶላቸዋል። ሴቶች በስፖርት ተሳታፊ በመሆናቸው በቅድሚያ ጤናቸውን ለመጠበቅ፣ የአካል ብቃታቸውን ለማዳበር እንዲሁም ተፈጥሯአዊና ሰው ሰራሽ ችግሮችን ለመቋቋም ያስችላቸዋል። ከዚህ ባ ሻገር በራስ የመተማመን ብቃታቸውእንዲያድግ፣ በስፖርት ምክንያት እርስ በርስ ያላቸው ግንኙነት እንዲዳብር እና የስፖርት ስነ- ምግባርንና ባህልን እንዲያውቁ የሚረዳቸው መሆኑን በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ናስር ለገሰ ይገልጻሉ። በዚህም\nከ2007ዓ.ም ጀምሮ «የመላ ኢትዮጵያ ሴቶች ጨዋታ» በሚል በየሁለት ዓመቱ ውድድር ይካሄዳል። ውድድሩ ክልሎች የየራሳቸውን የውስጥ ውድድር ካጠናቀቁ በኋላ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄድ ነው። የመጀ መሪያው ውድድር በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አስተናጋጅነት ሲካሄድ፤ ሁለተኛው ደግሞ በሃረር ከተማ ተደርጓል። ሦስተኛው የመላ ኢትዮጵያ ሴቶች ጨዋታም ትናንት በጅግጅጋ ከተማ አስተናጋጅነት መካሄዱን ጀምሯል። ውድድሩ\nበሌሎች ውድድሮች የመሳተፍ ዕድል ያላገኙ ሴት ስፖርተኞች አጋጣሚውን እንዲጠቀሙበት እንዲሁም በመምራት በኩል ያላቸውን የራስ መተማመንም እንዲያሳዩ ይረዳቸዋል። የተሻሉና አገራቸውን መወከል የሚችሉ ስፖርተኞችን ማፍራት የሚቻልበት ነው። የመገናኛ ብዙሃንን ሽፋን ማግኘታቸውም ውጤታማ ስፖርተኞች የሚበረታቱበት እንዲሁም ለክለቦችና ብሄራዊ ቡድኖች የሚታጩበት ዕድልም ያስገኝላቸዋል። ከዚህ ባሻገር ጥቂት ሴት የስፖርት ባለሙያዎች ከአገርም አልፈው በዓለም አቀፍ ደረጃም በመስራት ላይ እንደሚገኙ የሚጠቅሱት ዳይሬክተሩ፤ ከመሰረቱ መስራት ከተቻለ የተሻለ ተሳትፎ እንደሚኖርም ይጠቁማሉ። ነገር\nግን በርካታ ሴት ባለሙያዎች በሌሉ ባቸው ስፖርቶች ላይ ወንዶች እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን፤ በሂደት ሴቶችን በማብቃት ወንዶቹ እንደሚቀነሱም አቶ ናስር ይጠቁማሉ። በመጀመሪያው ውድድር የነበረው የባለሙያዎች ተሳትፎ አናሳ ቢሆንም፤ በሁለተኛው ግን የተሻለ ቁጥር ለመመልከትም ተችሏል። በየውድድሩ መሻሻል እየታየ ሲሆን፤ ይህም በተለያዩ መንገዶች ይረጋገጣል። በክልሎች በኩል የእኔነት ስሜት በማሳደር ላይ እንደሚገኝ ክልሎች ከሚሰጡት ግብረ መልስ ለመረዳትም ይቻላል። ከባለሙያዎች ባሻገር ውድድሩ በየዓመቱ የተሳታፊዎቹን ቁጥር እንዲሁም ውድድር የሚካሄድባቸውን ስፖርቶች እያሳደገ ሲሆን፤ የባህል ስፖርት እንዲሁም መስማት የተሳናቸው በውድድሩ ተሳታፊ እንዲሆኑም ተደርጓል። የተሳታፊዎች ብዛትም እየጨመረ ይገኛል። በመጀመሪያው\n500 ስፖርተኞች ተካፋይ ቢሆኑም በሁለተኛው 700መድረስ ችለዋል። አሁን ደግሞ ከ 2ሺ በላይ ሴት ስፖርተኞች ተሳታፊ ሆነዋል። ሴቶች በስፖርቱ ያላቸው ተሳታፊነት ሲጎለብትም በማህበራዊ ህይወታቸው እንዲሁም በኢኮኖሚው ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ከፍተኛ ይሆናል። ይህንን የሚደግፍም መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን፤ «ስፖርት ለሁለንተናዊ ለውጥ» የሚል ነው። ስፖርቱ ላይ ትኩረት ተደርጎ ሲሰራ ለስፖርቱ ዕድገት እንዲሁም ስፖርታዊ ጨዋነትን ለማንገስ ሚናቸው ከፍተኛ ይሆናል። ህግ ማክበርን እንደሚያስተምሩ የሚጠቁሙት ዳይሬክተሩ፤ ለስህተቶች ላለመጋለጥ በጥንቃቄ እንደሚሰሩም ያረጋግጣሉ። ይህንንም ደግሞ ከዚህ ቀደም በተካሄዱት ውድድሮች ላይ በትክክል ለመገንዘብ ተችሏል። በርካታ የሚያስተምሩት ነገር እንደመኖሩም በስፖርቱ ዕድገት ላይ ከሚያደርጉት አስተዋጽኦ ባሻገር ለውጥ ማምጣት ይችላሉ። ጤንነታቸው ሲጠበቅም በኢኮኖሚው ላይ የራሳቸው የሆነ አስተዋጽኦ ማበርከት ይችላሉ።አዲስ\nዘመን የካቲት 29/2011በብርሃን\nፈይሳ", "passage_id": "2afeac9ed262f305c821f105c1fdf6e6" }, { "passage": "በአገሪቱ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ በስፋት ከሚዘወተሩ ስፖርቶች እግር ኳስ፣ አትሌቲክስ፣ ቦክስ፣ ቦሊቮልና ብስክሌት የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ። ከእነዚህ አንዳንዶቹ ቀደም ባሉት ዓመታት ከአገር ውስጥም አልፎ የኦሎምፒክ ስፖርቶች ተብለው የሚወሰዱበት ወቅት እንደነበር ይታመናል። ከእነዚህ ውስጥ ቦክስና ብስክሌት በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ ይሁንና ስፖርት ከመዝናኛነት አልፎ አዋጪ የቢዝነስ ማዕከል በሆነበት በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ ብዙዎቹ ስፖርቶች በ‹‹ነበር››\nታሪክ ብቻ ይገኛሉ፡፡ ቤን ጀማነህ የብስክሌት ስፖርትን የጀመሩት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያሉ ነበር፡፡ በ1990 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ በተደረገው የ‹‹ማውንቴን›› ብስክሌት ውድድር ላይ\nሦስተኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የብስክሌት ፍቅራቸው እያደገ መጣ፡፡ በ1997 ዓ.ም በአገሪቷ በነበረው የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት ከአገራቸው ተሰድደው ከዓመታት የስደት ቆይታ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ላይ ብስክሌት ስፖርት የሚያዘወትሩ ጥቂት ልጆችን በመሰብሰብ ዛሬ ላይ ከ50 በላይ\nአባላት ያሉትን ቡድን መመስረት ችለዋል፡፡ ማውንቴን ባይክ ( ሮድ ባይክ ኢን ኢትዮጵያ) የሚል ስያሜ ያለው ቡድን በማቋቋም አገር ቤት ካሉት ነባር ስፖርተኞች በተጨማሪ የውጭ አገር ዜጎችን በማሳተፍ ዘወትር እሁድ ከአዲስ አበባ ከተማ ተነስተው ብዙ ኪሎሜትሮችን በማቋረጥ ከውድ እስከ መካከለኛ ወጭ የተደረገባቸውን ብስክሌት በመያዝ ወደ ተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች ይጓዛሉ፡፡ እስካሁን በተደረጉት የብስክሌት ስፖርት እንቅስቃሴዎችም ሱሉልታ፣ ሰንዳፋ፣ ሆለታ፣ ደብረብርሀን፣ ወልቂጤ፣ አገና፣ ቡታጅራና የመሳሰሉት አካባቢዎች የስፖርተኞቹ መዳረሻዎች ሆነዋል፡፡ ይህን የሚያደርጉት እድሜያቸው ከ30ዎቹ እስከ 60ዎቹ የሚጠጉ የቤን ጓደኞች ናቸው፡፡ ስፖርቱ እንዳይረሳ ትልቅ ንቅናቄ መፍጠርና ጤንነትን መጠበቅ የስብስቡ ዓላማ ቢሆንም፤ ጎን ለጎን ትውልዱ ራሱን በስፖርት እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲያሳልፍ ማስቻልም ሌላኛው ዓላማ ነበረ፡፡ ስፖርቱ እንዲያድግ ካላቸው ፍቅር የተነሳ ከቡድኑ ጋር ሆነው ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በብስክሌት ለመጓዝ ተሳትፎ የሚያደርጉትን ስፖርተኞች በነጻ እንደሚያሳትፉና በየመንገዱ ያሉት ወጣቶችም እድሜ ከስፖርቱ ያላገለላቸውን በማየት እንዲሳቡ ለማድረግ አገዥ እንቅስቃሴ መሆኑን ነው ቤን የሚናገሩት፡፡ ቆየት ባሉት ዓመታት ኢትዮጵያ የብስክሌት ስፖርት ወርቃማ ዘመኖችን ማሳለፏን የሚነገሩት ቤን፤ አሁን ላይ ስፖርቱ መዳከሙንና በተለይም መንግሥት የቀደሙ ባለሙያዎችን ሰብስቦ ቢያማክርና ቀደምት ስመ ጥር ስፖርተኞች ልምዳቸውን ለአሁኑ ትውልድ ማስተላለፍ ቢችሉ ስፖርቱ ዳግም ሊያንሰራራ እንደሚችል ይጠቁማሉ፡፡ የብስክሌት መንገድ አሰራርን ጨምሮ ከውጭ የሚመጡ ብስክሌቶች ጥራት መጓደልን አካቶ ስፖርቱ በጥልቀት መዳሰስ እንደሚገባው በስደት በውጭ አገር በቆዩባቸው ወቅቶች ያስተዋሉትን በማስታወስ ተናግረዋል፡፡ ቤን፤ ‹‹የድሮ ትውልድ ከልጅነቱ ጀምሮ በስፖርቱ ንቃት ውስጥ ያለፈው ነው፡፡ በየቦታው ሩጫ፤ በየጫካውም የካራቴ ስፖርት በብዛት ይዘወተር ነበር፡፡ ይህ አሁን ላይ ያለው በውስን ደረጃ ላይ ነው::›› በማለትም አሁናዊውን የብስክሌት ስፖርት ገጽታ ይጠቁማሉ፡፡ የሩጫና የብስክሌት ስፖርት በልምምድ ረገድ ብዙ የሚራራቁ አይደለም በማለት፤ ኢትዮጵያውያን በተፈጥሮ ለሁለቱም ስፖርቶች የሚሆን አቋም እንዳላቸውና እንደ አትሌቲክሱ ብስክሌት ስፖርቱም ቢበረታታ የሚገኘው ውጤት ቀላል እንዳልሆነ ያብራራሉ፡፡ እንደ እርሳቸው ገለፃ፤ ሌሎች አገራት በተለይም እንደ አውሮፓና አሜሪካ ያሉት ለስፖርቱ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ስለሚንቀሳቀሱ በኦሎምፒክ መድረክም ሆነ ሌሎች ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ በምሳሌነታቸው ብቻ ሳይሆን በውጤትም መታጀብ ችለዋል፡፡ በመሆኑም ከውጭ የሚገቡ የአገር አቋራጭ ብስክሌቶች ላይ ቀረጥ ቅናሽ አስተያየት ቢደረግ፤ የቀድሞ ስፖርተኞችና የጤና ቡድኖችን ያሳተፈ ተደጋጋሚ ውድድሮች በሚመለከተው ፌዴሬሽን በኩል ቢካሄድ፣ ለስፖርቱ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ወደ ፌዴሬሽኑ ለመቅረብ ቢሞክሩም መንገዶች ጠባብ ሆነዋል፡፡ ተቀራርቦ መስራት ስፖርቱን ለማሳደግ ትልቅ ሚና እንዳለው በመገንዘብ መንግሥት በአብሮነት ቢሰራ ልምድን ጨምሮ በብዙ መልኩ መተጋገዝም ይቻላል፡፡ የረጅም ጊዜ ልምድን በመጠቀም ለአገሪቷ ብስክሌት ስፖርት እድገት ሙያዊ አበርክቶ እንዲኖር ወደ ፊት ውድድሮችን በማዘጋጀት ተተኪውን ወጣት ትውልድ ለማሳተፍ ጥረቶች ይደረጋሉም ብለዋል፡፡ ስፖርቱ በአንጻራዊነት ይሻል የነበረበትን ዘመን ዳግም ለማደስ ከቡድን አጋሮቹ ጋር በመሆን እንደሚሰሩና የታዳጊ ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ ከውጭ አገር ስፖርተኞች ጋር እየተነጋገሩ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የእዚህ ቡድን አባላት ቢያንስ ከ20 ዓመት\nበላይ በስፖርቱ የቆዩ ስፖርተኞች መሆናቸውንና ትልልቅ ሰዎች ስፖርቱን ቢያዘወትሩት ከጤና አኳያ በርካታ ጥቅሞችን ማግኘት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ እድሜያቸው 50ዎቹ ውስጥ የሚገኘው አቶ ተስፋሚካኤል ገረመው ሌላኛው የቀድሞ ብስክሌተኛ ሲሆኑ፤ በአሁኑ ወቅት ከቡድን አጋሮቹ ጋር በመሆን እድሜ ሳይበግራቸው ረጅም ርቀትን በብስክሌት በመጓዝ ላይ ከሚገኙት ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ ስፖርቱን በ1970 ዓ.ም እንደተቀላቀሉት የሚናገሩት አቶ ተስፋሚካኤል፤ እስከ 1982 ዓ.ም\nድረስ በብስክሌት ስፖርት ከታዳጊዎች እስከ ዋናው ብሄራዊ ቡድን ውስጥ በመሳተፍ የሻምፒዮንነት ድልን እስከመቀዳጀት የደረሱና ድንቅ ብቃትን ማሳየት የቻሉ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በግጭት ምክንያት ውድድሩ ሳይካፈሉ ይቅር እንጂ በ1976 ዓ.ም ለሎሳንጀለስ ኦሊምፒክ በዝግጅት ላይ የነበረውን የወርቃማ ትውልድ ዘመን አባልም ነበሩ፡፡ በውቀቱ ስፖርቱ ከደጋፊዎች ጀምሮ በጥሩ ቁመና ላይ እንደነበርና ከጊዜ በኋላ ግን እየመነመነ መምጣቱን አቶ ተስፋሚካኤል ይናገራሉ። ምንም እንኳን ብስክሌት ከአትሌቲክስ ጀምሮ የኢትዮጵያን ስም በአፍሪካ ሻምፒዮናና በኦሊምፒክ መድረክ ያስጠራ ቢሆንም ዛሬ ላይ ትኩረት በማጣቱ ስፖርት ክለቦችን እስከማፍረስ መደረሱንና ይህም የስፖርቱን መጻኢ እድል አዘቅት ውስጥ ሊከተው እንደሚችል ያሳስባሉ።የትኛውም ስፖርት በትውልድ ቅብብሎሽ ላይ የተመሰረተ መሆን ይገባዋል የሚሉት አቶ ተስፋሚካኤል፤ የእርሳቸው አጋሮች እድሜ ሳይገድባቸው እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ ትውልዱ በማስተዋል እንዲቀበለውና በተራው አገር በዚህ የስፖርት ዘርፍ እንድትጠቀም ማድረግ ተገቢ እንደሆነ ይመክራሉ፡፡ ስፖርቱን ለማስፋፋት ዓለም አቀፍ ይዘት ያላቸውን ውድድሮች ማዘጋጀት ከፌዴሬሽኑ የሚጠበቅ ኃላፊነት መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ ማንም ሰው ለራሱ የጤንነት ጥቅም ሲል ስፖርትን እንደሚያዘወትረው ሁሉ አቶ ተስፋሚካኤልና መሰል ጓደኞቻቸውም እርጅና ከስፖርቱ ሳይገድባቸው በየሳምንቱ ረጅም ኪሎሜትሮችን የመጓዛቸው ምክንያትም ለዚሁ መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስፖርቱ እንዲበረታታና በህብረተሰቡ ዘንድ ስርጸት ለመፍጠር ታስቦ እንደሆነ ያብራራሉ፡፡ ኢትዮጵያ ኦሊምፒክን ጨምሮ በተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮች ከአትሌቲክስ ቀጥሎ ከምትወከልባቸው ስፖርቶች ብስክሌት ይጠቀሳል፡፡ ይሁንና ስፖርቱ በፋይናንስ በተለይም በመወዳደሪያ ብስክሌቶች እጥረት ምክንያት ህልውናው ፈተና ውስጥ መግባቱ ውጤቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑ እንደተጠበቀ፣ በዲፕሎማሲው ረገድ የበኩሉን ድርሻ የሚወጣ ነው፡፡አዲስ ዘመን  ሐምሌ 5/2011አዲሱ ገረመው", "passage_id": "77aab0cf038727e6a72e7b4df51302b5" } ]
f7194beaca147c455aed00644a14fd65
14afffacb7a5601cc006346aab16885d
የሦስት አስርት ዓመታት የቁልቁለት ጉዞ
ኢትዮጵያ በዘመናዊ ስፖርቶች በዓለም መድረኮች መታየት ከጀመረች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ተቆጥሯል። በእነዚህ ዓመት አገሪቱን ሦስት የተለያዩ መንግሥታት መርተዋታል። አንድ መንግሥት የሚከተለው ርዮተ ዓለም በአንድ አገር ላይ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ተጽዕኖ የማሳደሩን ያህል በአንድ አገር ስፖርት ላይም የራሱ የሆነ አሉታዊና አዎንታዊ ተጽዕኖዎችን ማሳረፉ የግድ ነው። አንድ የፖለቲካ ስርዓት በስፖርቱ ላይ ብቻም ሳይሆን የስፖርቱ ዋና ተዋናይ የሆነው ግለሰብ ላይም ተመሳሳይ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍ እርግጥ ነው። የአንድ አገር የፖለቲካ ስርዓት በዲፕሎማሲ፤ በኢኮኖሚ፤ ልማትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያለው ነባራዊ ሁኔታ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ስፖርቱንና ስፖርተኛውን መንካቱ አይቀሬ ነው። ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ገደማ አገራችን የምትከተለው የፖለቲካ ስርዓት በአገሪቱ ስፖርት ላይ የተለያዩ አዎንታዊና አሉታዊ ጎኖችን ማሳደሩ አልቀረም። ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት የነበረው የፖለቲካ ስርዓት ለአገራችን ስፖርት ካበረከታቸው አዎንታዊ ጎኖች አንዱ ከዲፕሎማሲ እውነታዎች አኳያ ይቀኛል። አገራችን ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ከሌሎች አገሮች ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በላቀ መልኩ ማሻሻሏ የሚካድ አይደለም። ይህም በዓለም አቀፍ የስፖርት መድረኮች በተለይም መል ካም ስም ባላት የአትሌቲክስ ስፖርት ኦሊምፒክንና የዓለም ቻምፒዮናን በመሳሰሉ ታላላቅ መድረኮች የነቃ ተሳትፎ እንዲኖራት የራሱን የሆነ አስተዋፅኦ አበርክቷል። ኢትዮጵያ እኤአ ከ1956 ከሜልቦርን ኦሊምፒክ ጀምሮ በኦሊምፒክ መድረኮች ተሳታፊ መሆን ችላለች። ከእዚህ ጊዜ አንስቶ አስራ ሰባት ያህል ኦሊምፒኮች ቢካሄዱም ኢትዮጵያ በሁለቱ ተካፋይ መሆን አልቻለችም ነበር። እኤአ በ1984 አሜሪካ ሎሳንጀለስ ባስተናገደችው የኦሊምፒክ ጨዋታ ኢትዮጵያ በወቅቱ የሶሻሊዝም ርዮተ ዓለም ተከታይ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ በእዚህ ታላቅ መድረክ መካፈል አልቻለችም ነበር። ከአራት ዓመት በኋላም 1988 ላይ የአፓርታይድ ስርዓትን በመቃወም በሲዎል ኦሊምፒክ ላይ አልተገኘችም። ኦሊምፒክን በመሳሰሉ ታላላቅ የስፖርት መድረኮች በፖለቲካ ርዮተ ዓለም ልዩነት የተነሳ መካፈል አለመቻል አንድን አገር ከሜዳሊያ በዘለለ በርካታ ነገሮች እንደሚያሳጣ አያከራክርም። ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ኢትዮጵያ በሁሉም የኦሊምፒክና የዓለም ቻምፒዮናዎች ላይ ቀርታ አታውቅም። በእነዚህ ታላላቅ የስፖርት መድረኮች ሜዳሊያ ከመሰብሰብ ባሻገር መድረኩን ተጠቅማ ገፅታዋን ለመገንባትና ራሷን ለማስተዋወቅ ጠቅሟታልም። በእነዚህ መድረኮች የዘወትር ተሳታፊ መሆኗም የአገሪቱን ስፖርት እንዲነቃቃና ስፖርተኛው ተጠቃሚ እንዲሆን አስችሏል። አንድ ስፖርተኛ ራሱን በኦሊምፒክ መድረክ በማሳየት ዓለም አቀፍ ተጠቃሚነትን እንዲያገኝ ከሌሎች አገራት ጋር ያለን መልካም የሆነ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እዚህ ጋር ቁልፍ ሚና እንዳለው መገንዘብ ይቻላል። ስፖርተኞቻችን የግል ውድድራቸውን በሌሎች አገሮች ለማድረግ ወደ አንድ አገር በቀላሉ ለመግባት መልካም የዲፕሎማሲ ግንኙነት የሚኖረው አስተዋፅኦ ግልፅ ነው። ይህም ስፖርተኞች በተለይም አትሌቶቻችን በተለያዩ ዓለማት ተዟዙረው በስፖርቱ ያላቸውን ተሰጥኦ ተጠቅመው ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ወገኖችና ለአገር ሲተርፉ እንድንመለከት አድርጓል። እዚህ ላይ የአገራችን አቪዬሽን ዘርፉ መዘመንና በበርካታ አገሮች ተደራሽ መሆን ለአትሌቶቻችን እንደ ልብ የፈለጉት አገር በረው የትራንስፖርት ጉዳይ ሳያሳስባቸው ጊዜና ገንዘባቸው ሳይባክን ውድድሮች ላይ እንዲገኙ ማስቻሉ መንግሥት በትራንስፖርት ልማቱ ያከናወነውን ተግባር ዋጋ እንድንሰጠው እንገደዳለን። ስፖርት በዘመናችን ከፍተኛ የገቢ ምንጭ በሆነበት በእዚህ ወቅት አትሌቶቻችን በሌሎች አገሮች ላባቸውን አፍሰው ያመጡትን ገንዘብ አገራቸው ላይ ሠርተው እንዲለወጡበት መንግሥት ቅድሚያ ሰጥቷቸው ሁኔታዎችን በማመቻቸት ወደ ኢንቨስትመንቱ እንዲገቡ አድርጓል። በእዚህም በርካታ አትሌቶቻችን በሆቴልና ሪዞርት እንዲሁም በሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች ግንባር ቀደም ተዋናይ ሆነው እናገኛቸዋለን። ይህም ሁኔታ ስፖርተኞቻችን ወደ አደጉት አገራት ለውድድር ወጥተው ከመቅረት ይልቅ ያገኙትን ይዘው ተመልሰው ከራሳቸው አልፈው ለበርካታ ዜጎት እንጀራ ሲከፍቱ እንድንመለከት አድርጓል። ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ የአንድ ህብረተሰብን አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጤንነትን በመጠበቅ ረገድ ምርታማነትን የሚያጎለብት፥ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ቁልፍ ሚና ያለው የዜጎች መሰረታዊ መብት እየሆነ መጥቷል። ይህን ልብ ያለው የ1990 ዓ.ም የተቀረፀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስፖርት ፖሊሲ በየደረጃው መላውን ህብረተሰብ በስፖርት በማሳተፍ ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት ቀዳሚ ዓላማው አድርጎታል። ለዚህም መላው ህብረተሰብ በሚኖርበት፥ በሚሠራበት እና በሚማርበት አካባቢ በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል በየደረጃው ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር ግልፅ አቅጣጫ አስቀምጧል። የዚህን ፖሊሲ አቅጣጫ ስኬታማ በሆነ መልኩ ተፈፃሚ ለማድረግ የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ፅንሰ ሃሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1996 ዓ.ም በወቅቱ በነበረው የኢፌዴሪ ስፖርት፤ ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ነበር የተጠነሰሰው። የኦሊምፒክና የመላ አፍሪካ ጨዋታዎችን መርህ መነሻ በማድረግ ህብረተሰቡን በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በስፋት በማሳተፍ እና ተጠቃሚነቱን በማጎልበት የበርካታ ባህልና ትውፊቶች ባለቤት የሆኑ ብሔሮችና ብሔረሰቦች በአንድ መድረክ ተገናኝተው የባህል እና ልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ታስቦ ፖሊሲው እንደተቀረፀ የመጀመሪያው የጥናት ሰነድ ላይ ተቀምጧል። ይህም አገራችን በምትከተለው የፌዴራሊዝም ስርዓት ህዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን በማጠናከር በጋራ መግባባት ላይ የተመሰረተ መተሳሰብ እና መቀራረብ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው ታምኖበታል። በዚህም የአገራችን ስፖርት ዜጎችን ተጠቃሚ ከማድረግ አኳያ ተስፋ ሰጪ ምልክቶችን ማየት ተችሏል። ዘመናዊና ግዙፍ ስቴድየሞች በየክልሉ መገንባታቸው፤ አገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት አካዳሚና በተለያዩ ስፖርቶች የወጣት ፕሮጀክቶች መጀመራቸው የአገራችን ስፖርት ባለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት የተጓዘባቸው መንገዶች ናቸው። የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለአገሪቱ ትልልቅ መሠረተ ልማቶችን አስገ ኝቷል፡፡ ለውድድሩ ሲባልም ትልልቅ ስታዲየሞች በክልሎች ተገንብተዋል፡፡ በመገንባት ላይም የሚገኙ በርካታ ናቸው፡፡ በባህር ዳር፣ ሐዋሳና መቐለ የተገነቡት ዘመናዊ ስታዲየሞች ከመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች አልፈው ዓለም አቀፍ ውድድሮችን የሚያስተናግዱ ሆነዋል፡፡ አልፎ ተርፎም ኢትዮጵያ የአፍሪካን ሁለተኛውን ትልቅ የእግር ኳስ ዋንጫ የ2020 አፍሪካን ኔሽን ቻምፒዮን ሺፕ(ቻን) አዘጋጅነት ዕድል እንድታገኝ እነዚህ ስቴድየሞች ካፍን ማሳመን የቻሉበት አጋጣሚ ነበር(ባይሳካም)። ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በየሁለት ዓመቱ የሚካሄዱትን መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ላይ እያሳዩ ያለው ፉክክር ወደ መጋጋል ደረጃ ለመምጣቱ አንዱ ማሳያ፣ ውድድሮችን ለማዘጋጀትና መሠረተ ልማቶችን አሟልቶ ለመገኘት የሚያደርጉት ሽር ጉድ ለዚህ ተጠቃሽ ነው፡፡ በእነዚህ ስቴድየሞች ግንባታ ሂደትም በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድል ከመፈጠሩ ባሻገር በግንታው ዘርፍ በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ሊንቀሳቀስ ችሏል። በዚህም የአገራችን ተቋራጮችን አቅም ከማሳደጉ በተጨማሪ በዘርፉ ትልቅ የእውቀት ሽግግር ሊደረግ ችሏል። ይሁን እንጂ በእነዚህ ስቴድየሞች ግንባታ በብዙ መልኩ የሚነሱ እንከኖች የሉም ማለት አይደለም፡፡ መላ ኢትዮጵያ ጨዋታም ቢሆን ባለፉት ጥቂት ዓመታት የታለመለትን ዓላማ ስቶ ወዳልተፈለገ እኩይ ተግባር መቀየሩና የፖለቲካ መጠቀሚያ መሆኑ የሚካድ አይደለም፡፡ በእነዚህ ዓመታት በአገራችን ስፖርት ከታዩ አንኳር የሆኑ አሉታዊ ጎኖች ዋነኛው ከአትሌቲክስ ስፖርት ውጪ ሌሎቹ ስፖርቶች መዳከማቸውና እድገት አለማሳየታቸው ይጠቀሳል። ለእዚህም በርካታ ምክኒያቶች ይቀመጣሉ። ቀደም ሲል አንድ ክለብ ሲቋቋም ያደገ ወይንም ተከታይ ያለው ስፖርት ብቻ ይዞ መቋቋም አይችልም። ይህ ማለት አንድ እግር ኳስ ክለብ ለማቋቋም ሌሎች ከአምስት ያላነሱ ስፖርቶችን ማቀፍ የሚያስገድድ ሁኔታ ነበር። ይህም አንድ ስፖርት ብቻ ተነጥሎ እንዳያድግና ሌሎች ያላደጉ ስፖርቶች ተያይዘው እንዲያድጉ የሚያስችል ነበር። አሁን ላይ ይህ ዓይነቱ አካሄድ በመቅረቱ በርካታ ክለቦች የፈለጉትን ስፖርት ብቻ ይዘው በመጓዛቸው በርካታ ስፖርቶች ሲወድቁ እንመለከታለን። ቀደም ሲል ኢትዮጵያ ከአትሌቲክስና እግር ኳስ በተጨማሪ ቮሊቦል፤ ቅርጫት ኳስ፤ እጅ ኳስና ሌሎች ስፖርቶች ከሌሎች አገሮች ጋር ተፎካካሪ ነበረች። አሁን ላይ ይህ ገፅታ ተቀይሮ ከእግር ኳስና አትሌቲክስ ውጪ ባሉት ስፖርቶች እንኳን ወደ ውጭ አገር ሄደን ጠንካራ ተፎካካሪ ልንሆን በአገር ውስጥም ጠንካራ እንቅስቃሴ ሲደረግባቸው ለማየት ተቸግረናል። በስፖርት መሰረተ ልማቶች ትላልቅ ፕሮጀክቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተግባራዊ እየሆኑ ቢመጡም በአገራችን ስፖርት መሰረት የሆኑ የተለያዩ ማዘውተሪያ ስፍራዎች ሕንፃና ቤት ተሠርቶባቸው እናገኛለን። ይህም በምንታወቅባቸው በተለይም በእግር ኳስ ከተለያዩ አካባቢዎች የሚወጡ ተጫዋቾችን እንድናጣ ማድረጉ በርካታ የስፖርት ቤተሰቦች የሚስማሙበት ነው። በሌላ በኩል የሚታየው አሉታዊ ጎን ከአገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም ጋር ተያይዞ የሚነሳ ቢሆንም ወደ ፊት ትኩረት ተደርጎ ሊሠራበት የሚገባ አብይ ጉዳይ ነው። ለበርካታ ስፖርቶች መዳከም ዋነኛ ምክኒያት የፌዴሬሽኖች የገንዘብ አቅም ማነስ ነው። መንግሥት ለስፖርት ኮሚሽን ከሚበጅተው ገንዘብ ተመፅዋች ሆነው እንደልብ መራመድ የከበዳቸው አገር አቀፍ ፌዴሬሽኖች ጥቂት አይደሉም። እነዚህ ፌዴሬሽኖች ውድድሮችን ለማካሄድ ስፖርቱን ለማሳደግ አንድና አንድ ችግራቸው የገንዘብ አቅም ነው። እነዚህ ፌዴሬሽኖች የመንግሥት እጅ ከመጠበቅ ይልቅ በራሳቸው የገንዘብ አቅማቸውን ለማጠናከር መሥራት እንዳለባቸው ብዙ ጊዜ ምላሽ ይሰጣል። ይሁን እንጂ እነዚህ ፌዴሬሽኖች ራሳቸውን በገንዘብ የሚያጠናክሩበት አቅም እስኪፈጥሩ ድረስ መንግሥት አሁን ከሚበጅትላቸው ገንዘብ በዘለለ ወጥ የሆነ አደረጃጀት ፈጥሮላቸው ዘላቂ የሆነ መስመር በመዘርጋት በኩል ክፍተቶች አሉ። መንግሥት ለፌዴሬሽኖች ዓሣ ከመስጠት ይልቅ ዓሣ የሚያጠምዱበትን ዘዴ ሊያስተምራቸውና መንገዱን ሊያሳያቸው ይገባል። እስከዚያው ድረስም አሁን የተሠሩት መሰረተ ልማቶች ከጋሪው ፈረሱ የቀደመ እንዳይሆኑ ዓመታዊ በጀታቸው ቢያንስ በርካታ ውድድሮችን በዓመት ውስጥ ማስተናገድ የሚያስችላቸውና በኋላ መሰረተ ልማቱ ተሟልቶ ስፖርቱ ኋላ እንዳይቀር በአንድ ላይ መጓዝ የሚያስችል መላ አልተፈጠረም፡፡ የአገራችን ስፖርት ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ገደማ በእንዲህ ዓይነት የቁልቁለት ጉዞ በመራመድ ዛሬ ላይ ደርሷል። ካለፈው መጋቢት 2010 ወዲህ አገሪቱ በአዲስ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ባሆንም የለውጥ መንገድ ላይ መሆኗ አይካድም፡፡ ይህ የለውጥ ማዕበል በፖለቲካ ውጥረት ውስጥ ገብቶ አገር በማረጋጋት የተጠመደ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ ሊሆን ይችላል የስፖርቱን ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ ሲመለከተው አይስተዋልም፡፡ ሁሉም ነገር ወደ መደበኛው እንቅስቃሴ ሲመለስና የፖለቲካ ውጥረቱ ሲረግብ ግን የስፖርቱን የቁልቁለት ጉዞ ሽቅብ እንዲጓዝ የማድረግ ትልቅ የቤት ሥራ እንደሚጠብቀው ከወዲሁ ማስታወስ ግድ ነው፡፡አዲስ ዘመን ግንቦት 16/2012ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=32985
[ { "passage": "ከፊት ለፊታችን በርካታ ተሽከርካሪዎች ዝግ ብለው ይሄዳሉ፤ ይመጣሉ፤ የመንገድ ግንባታ ተሽከር ካሪዎች፣ከባድ መኪናዎች፣ አውቶቡሶች፣ አውቶሞቢሎች በየዓይነቱ መንገዱን ሞልተውታል፡፡ ተሽከርካሪዎቹ በዝግታ ቢንቀሳቀሱም የሚቀሰቅሱት አቧራ እና ከተሽከርካሪዎቹ የሚያወጠው ጭስ እንድ ላይ ሆኖ አካባቢውን የሚቃጠል አስመስሎታል።በአዲስ መልክ እየተገነባ በመሆኑ ለተሽከርካሪዎች፣ለእግረኞች ፣ለአሽከርካረዎች ይጎረብጣል፡፡ በአንዳንድ ቦታዎች የተቀበሩ ትላልቅ ቱቦዎች ፣በአንዳንዶቹ አካባቢዎች ደግሞ የቱቦዎቹ መስኮቶች ከፍ ብለው ይታያሉ፡፡ መንገዱ በጣም ሰፊና ለተለያዩ አገልግሎቶች እንዲወል ተደርጎ እየተገነባ ይመስላል፡፡ የቃሊቲ ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ግንባታ፡፡እንዲያም ሆኖ መንገዱ አላረፈምም፡፡ አንደኛው የመንገዱ አካል ሲገነባ ሌላው ለተሽከርካሪዎች ክፍት ይደረጋል። ለተሽከርካሪዎች ብዙም የማይመች ቢሆንም አማራጭ ከማጣት የተነሳ አሽከርካሪዎች ይጠቀሙበታል፡፡መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ይህ ከቃሊቲ አደባባይ ቱሉ ዲምቱ  ድረስ የሚሠራው መንገድ አምስት ዋና ዋና ተሻጋሪ ድልድዮችን ያካትታል፡፡ የመንገዱ ርዝመት 11ኪ.ሜ ስፋቱ ደግሞ 50ሜትር ይሆናል፡፡የግንባታው አፈፃፀም ባለፈው በጀት ዓመት 18 ነጥብ 75 በመቶ የደረሰ ሲሆን። የቱሉ ዲምቱ ቂሊንጦ አደባባይ መንገድ እና የቃሊቲ ቀለበት ቱሉ ዲምቱ መንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ 4ነጥብ 7ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞላቸዋል፡፡  በዓይነታቸው ልዩ የሆኑት እነዚህ የመንገድ መሠረተ ልማት ዝርጋታዎች አጠቃላይ 21ኪ.ሜ የሚጠጋ ርዝመት እና  50ሜትር ስፋት ይኖራቸዋል፡፡በቃሊቲ የመንገድ ትራንስፖርት ማሠልጠኛ አካባቢ በመኪና ጥበቃ ሥራ ላይ የተሰማሩት ወጣት መስፍን ተስፋዬ እና ወጣት እስጢፋኖስ ድንቁ መንገዱ ከሚያስተናግደው ተሽከርካሪና ከሚመላለስበት እግረኛ አንፃር በፍጥነት ሊሠራ ይገባው ነበር ይላሉ።የመንገዱ ግንባታ አለመፋጠን አሽከርካሪዎችን ብቻ አይደለም እየጎዳ ያለው፡፡ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ታራሚ ቤተሰቦቻቸውን የሚጠይቁ ወገኖችንም ለችግር እየዳረገ መሆኑን ይጠቁማሉ፡፡ በክረምት ጭቃው፣ በበጋ አቧራው ፈታኝ ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ አቧራው ለጤና ጠንቅ እየሆነ መምጣቱን በመጥቀስ  በፍጥነት እንዲገነባ ይጠይቃሉ፡፡የመንገድ ግንባታውን ለመፋጠን የሚያስችል እንቅስቃሴ በአካባቢው እንደማይታይ ተናግረው፣ ዘወትር ውሃ በቦቴ አመጥቶ  ከማርከፍከፍ ባለፈ ምንም ዓይነት ሥራ አይታይም ይላሉ።የትራፊክ ፍሰቱን በማስተናበር ሥራ ላይ ያገኘናቸውና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ቡድን መሪ ዋና ሳጅን ገብረጻህማ ተሰማ መንገዱ የትራፊክ ፍሰት የሚባዛበት መሆኑን ጠቅሰው፣ ግንባታው እጅግ አዝጋሚ ነው ይላሉ።‹‹መንገዱ በአዲስ መልክ እየተገነባ መሆኑን እናውቃለን፤ ሆኖም በሚፈለገው ፍጥነት እየተሠራ አይደለም›› የሚሉት ዋና ሳጅን ገብረጻህማ፣ ለነዋሪዎች፣ ለነጋዴዎች፣ የተለያዩ ጉዳዮችን ለማስፈጸም ወደ አዲስ አበባ ለሚመጡትም ሆነ ከአዲስ አበባ ወደ ምሥራቁና ደቡቡ ክፍል ለሚጓዙ  እንዲሁም ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ከፍተኛ ችግር መፍጠሩን ይጠቁማሉ፡፡ በመንገዱ ዳርና ዳር የተቀበሩት የፍሳሽ ማስተላለፊያ ቱቦዎች በአግባቡ ባለመደፈናቸው በተለይ በምሽት አደጋ እያስከተሉ መሆናቸወንም ይገልጻሉ፡፡አሽከርካሪው አቶ የሱፍ ሐጂ ከቃሊቲ ባቡር ጣቢያ ጀምሮ እስከ ቱሉ ዲምቱ ባለው መንገድ እየተመላለሱ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጡ  እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡ በመንገዱ ግንባታ መጓተት  ምክንያት ይህን የሥራ ቦታቸውን መቀየራቸውን ይናገራሉ።የሥራ ቦታቸውን ቢቀይሩም የመኖሪያ ቤታቸው በአካባቢው በመሆኑ አቶ የሱፍን ችግሩ አልተለያቸውም፡፡ በተለይም በአካባቢው የተለያዩ ችግሮች ቢያጋጥሙ፤ በመንገዱ አባጣ ጎርባጣ መሆንና የተቆፋፈሩት ዳርቻዎቹ ባለመደፈናቸው ሁሌም እንደሚቸገሩ ይጠቁማሉ፡፡አምቡላንስና የእሳት አደጋ መኪናዎች በቶሎ ደርሰው የአካባቢውን ነዋሪዎች ከአደጋ  ለመታደግ የሚችሉበት አማራጭም የጠበበ መሆኑንም ነው የተናገሩት። በመንገዱ ምቹ አለመሆን የተነሳ በተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት እየደረሰ ለከፍተኛ የጥገና ወጪ የሚዳረጉ መኖራቸውንም አቶ የሱፍ ይገልጻሉ።ወይዘሮ ሱመያ ጀማል እና ዘነበች በቀለ በአካባቢው ቤት ተከራይተው ይኖራሉ፡፡ መንገዱ መኪኖች በብዛት የሚመላለሱበት እና ዕረፍት የሌለው መሆኑን ተናግረው፣ ከመንገዱ የሚነሳው አቧራ እንኳን መንገደኛን ቤቱ የተቀመጠውንም ማስቸገሩን ይጠቁማሉ፡፡ በዚህ የተነሳም የልጆቻቸው ጤንነት አደጋ ላይ እየወደቀ መምጣቱን ይጠቁማሉ።በጉዳዩ ላይ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር መረጃ እንዲሰጡን በስልክ በተደጋጋሚ፣  በአካልም በቢሯቸው ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ስብሰባ ላይ ናቸው በሚል አልተሳካም።አዲስ ዘመን ታህሳስ 30/2011በኃይለማርያም ወንድሙ", "passage_id": "590896c68ca9baf7ed600d120002f015" }, { "passage": "ድልን ለማብሰር ከማራቶን እስከ አቴንስ የሮጠው ግሪካዊው መልዕክተኛ ፊሊፒደስ፣ በባዶ እግሩ 42 ኪሎ ሜትር በመሸፈን ለጥቁሮች ኩራት ለዓለም ህዝብ ትንግርት የሆነው አበበ ቢቂላ፣ ለጥቁሮች መብት ትግል ከኦሊምፒክ ስኬት ይልቅ ሰብዓዊነትን ያስቀደመው ቦክሰኛው መሃመድ አሊ፣ በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት በእንብርክክ ተማጽኖው የአምስት ዓመታትን የእርስ በእርስ ግጭት ማብቂያ ያበጀለት የእግር ኳስ ፈርጥ ዲድየር ድሮግባ፣… ዓለም ካከበራቸው ታሪክም ከጀግኖች መዛግብት ካሰፈራቸው ስፖርተኞች ጥቂቶች ናቸው። ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ ስፖርት በሰው ልጅ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ሰፊውን ድርሻ መያዙ ገሃድ ነው። በዚህ ተወዳጅ ክንዋኔ ላይም በጦርነት አውድ ከሚዋደቁት ባላነሰ በርካታ ጀግኖች ተፈጥረው አልፈዋል፤ በዚህ ዘመንም እየተፈጠሩ ይገኛሉ። ስፖርተኞች ደረታቸውን ለጥይት ነፍሳቸውንም ለአገራቸው መገበር ባይጠበቅባቸውም፤ በእልህ አስጨራሽ ትግል ነጭ ላባቸውን አፍስሰው በሚያገኙት ድል ግን አገራቸውን ያስጠራሉ፣ ባንዲራቸውንም በማውለብለብ ህዝባቸውን ያኮራሉ። ታሪክም ከራሳቸው ይልቅ ህዝባቸውን ያስቀደሙ፤ ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠውም አገራቸውን ያስጠሩትን እነዚህን ጀግኖች እያነሳ ሲዘክራቸው ይኖራል። ለዛሬም ከጀግና ስፖርተኞች መካከል አንዱን 100 ዓመታትን ወደኋላ ተመልሰን እናስታውስ። በአገረ አሜሪካ ከታዩ ስፖርተኞች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳል፤ ጂም ትሮፔ። በኦሊምፒክ ተሳትፎው ያሳየው ቁርጠኝነት አገር ወዳድነቱን የመሰከረ ሲሆን፤ ተግባሩም ለብዙዎችም ትምህርት ሆኗል። እርግጡን የሚያወሳ የልደት የምስክር ወረቀት ባይገኝም አሁን ኦክለሃማ ከተሰኘው የአሜሪካ ግዛት እ.አ.አ በ1887 እንደተወለደ በህይወት ታሪኩ ተጠቅሷል። ትሮፔ በልጅነቱ ከባድ እና ውስብስብ የሆነ ቤተሰባዊ ህይወት የነበረው ሲሆን፤ የመንትያ ወንድሙ እናቱ እንዲሁም የአባቱ ሞት ደግሞ የልጅነት ህይወቱን ይበልጥ ፈታኝ ሊያደርግበት ችሏል። ትምህርቱን ለበርካታ ጊዜ እያቋረጠ እና እየቀጠለ ቢቆይም፤ ፔንሲልቫኒያ በሚገኝ የኢንዱስትሪ ትምህርት ቤት ተማሪ በነበረበት ወቅት ስፖርታዊ ተሳትፎውን ጀምሯል። እንደ እድል ሆኖም በወቅቱ በአሜሪካ ስመጥር በሆኑት የእግር ኳስ አሰልጣኝ ግሌን ስኮቤይ የመሰልጠን አጋጣሚ ተፈጥሮለት ነበር። ነገር ግን በዚያው ዓመት አሰልጣኙ ከዚህ ዓለም በማለፋቸው ከስፖርት ሊርቅ የግድ ሆነበት፤ ከዓመታት በኋላ ኮሌጅ እስኪገባ ድረስም በድጋሚ ወደ ስፖርት አልተመለሰም ነበር። ወደ ስፖርት ከተመለሰ በኋላም በእግር ኳስ እና ቤዝቦል ስፖርቶች ባሻገር በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች መሳተፍ ብቃቱ ተደናቂ አድርጎት ቆይቷል። ከኮሌጅ ቡድን እስከ ክለቦች ድረስም በተለያዩ ውድድሮች ላይ ተሳትፎ ሻምፒዮን ለመሆን ችሏል። በእግር ኳስ ስፖርት የነበረው ብቃት በተለይ የሚደነቅ ይሆን እንጂ በአትሌቲክስ ስፖርቶች ላይ የሚያሳየው ችሎታ ግን የሚያስገርም ነበር። ይህንን ተከትሎም እ.አ.አ በ1912 የስዊድኗ ስቶኮልም አዘጋጅ ለሆነችበት ኦሊምፒክ የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድንን ከሚወክሉት መካከል አንዱ በመሆን ተመረጠ። ወቅቱ የፔንታቶሎን እና ዴክታቶሎን የውድድር ዓይነቶች በኦሊምፒክ የተካተቱበት እንደመሆኑም ቶርፔ የታጨው ለእነዚህ የውድድር ዓይነቶች ነበር። የውድድሩ ዕለት ደርሶም ቶርፔ አስደማሚ ብቃቱን ለዓለም ሊያሳይ ሰዓታት ብቻ ቀሩት። ነገር ግን የእዚያን ዕለት ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ ጫማውን ካስቀመጠበት ሊያገኝ አልቻለም፤ ከፍለጋ በኋላም እንደተሰረቀ አወቀ። በታላቁ የኦሊምፒክ መድረክ መሳተፍ በግሉ ከሚያስገኝለት ክብር በላይ አገሩን መወከል የዜግነት ግዴታው በመሆኑ ተስፋ መቁረጥ የማይታሰብ ነው። በመሆኑም በአጋጣሚው ከመቆጨት ይልቅ አማራጭ ፍለጋውን ተያያዘው። ከቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት ውስጥም አገልግሎት የማይሰጡ ሁለት የተለያዩ ጫማዎችን አገኘ። የውድድር ሰዓቱ እየደረሰ በመሆኑም ጫማዎቹን ሳያቅማማ ለካቸው። አንዱ ጫማ ለእርሱ የማይሆን ሰፊ መሆኑ ሌላ ችግር ነበር። ምን ማድረግ እንዳለበትም አሰበ፤ ያገኘው መላም ሰፊውን ጫማ በሁለት ካልሲዎች ደራርቦ ማድረግ ነበር፤ እናም አደረገው። የእርሱ ባልሆኑት ሁለት ዓይነት ጫማዎችን በነጭ እና ጥቁር ካልሲዎች ተጫምቶም ወደ ውድድር ስፍራው አመራ። በተሳተፈባቸው ሁለት ውድድሮችም ብቃቱን አስመሰከረ። ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለማጥለቅ በቃ። በፔንታቶሎን (ርዝመት ዝላይ፣ ዲስከስ ውርወራ፣ አጭር ርቀት ሩጫ እንዲሁም ትግል) ካደረጋቸው አምስት ውድድሮች መካከል አንዱን ብቻ ተሸንፎ (በጦር ውርወራ) በሰበሰባቸው ነጥቦች ብልጫ አሸናፊ ሊሆን ችሏል። በተሳተፈባቸው የፔንታቶሎን እና ዴክታቶሎን 15 ውድድሮች በድምሩ ስምንቱን በማሸነፍም የቁጥር አንድነትን ማዕረግ ለመጎናጸፍ ችሏል። ቶርፔ በወቅቱ በውድድር አሸናፊነቱ ካጠለቃቸው ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎች ባሻገር ሌሎች ሁለት ሽልማቶችንም ተቀዳጅቷል። የመጀመሪያው ገጸ- በረከት\nበውድድር አዘጋጇ አገር ስዊድን ንጉስ ጉስታቭ አምስተኛ እጅ የተበረከተለት ሲሆን፤ «የዓለም ምርጡ አትሌት ነህ» በማለትም አበረታተውታል። የሩሲያው ኒኮላስ ሁለተኛም ለትሮፔ ሁለተኛውን የማበረታቻ ሽልማት ሰጥተውታል። ነገር ግን ይህ ታሪክ በጋዜጦች ታትሞ ለንባብ የበቃው ትሮፔ ገድሉን ከፈጸመ ከ36 ዓመታት\nበኃላ እ.አ.አ በ1948 ነበር።\nመጽሐፍትም በስሙ ተጽፈው ገበያ ላይ የዋሉት እ.አ.አ በ1952 ነው።\nአትሌቱ ከዓመታት በኋላ በዓለም ላይ ታዋቂ መሆኑ በአሜሪካ ዜጎች ልብ ሰፊ ቦታ አላሳጣውም፤ አሁንም ድረስ ብዙዎች «ጀግናችን» ሲሉ ያወድሱታል። በፔንሲልቫኒያ ግዛትም በስሙ «ጂም ቶሮፔ» በሚል የተሰየመ ከተማ አለው።አዲስ\nዘመን ሚያዚያ 27 ቀን 2011 ዓ.ም ብርሃን\nፈይሳ", "passage_id": "18c14ba7775635036928a87643636857" }, { "passage": "ስፖርት ለጉዳት መንስኤ ነው ባይባልም፤ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ግን ለጉዳት አጋላጭ መሆናቸው ይታወቃል። በዓለም ላይ ከሚዘወተሩ በርካታ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች መካከልም እግር ኳስ፣ መረብ ኳስ እና ቤዝቦል በጉዳት አጋላጭነታቸው ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ። ኢትዮጵያ ስሟን ያስጠራችበትና ከቀዳሚዎቹ ተወዳጅ ስፖርቶች መካከል አንዱ የሆነው አትሌቲክስ ከጉዳት ጋር ያለው ቁርኝት ምን ይመስላል? በዛሬው ዕትምም በአትሌቶች ላይ\nየሚደርሱ ጉዳቶች ምክንያት፣ ህክምናው እንዲሁም በዚህ ዘርፍ በኢትዮጵያ ያለው ተሞክሮ ምን ይመስላል የሚለውን ይዳስሳል። በዚህ አርዕስት ላይ ሙያዊ ማብራሪያ የሰጡንም በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቲክስ ህክምና ከፍተኛ ባለሙያ እንዲሁም በጸረ- አበረታች ቅመሞች ጉዳይ ተጠሪዋ ቅድስት ታደሰ ናቸው። አትሌቲክስ ሰፊና\nበውስጡም በርካታ የውድድር ዓይነቶችን ያቀፈ ስፖርት እንደመሆኑ፤ የተለያዩ ጉዳቶች ይስተናገዳሉ። ከአጭር ርቀት ሩጫ እስከ ሜዳ ተግባራት ባሉት ስፖርቶች አትሌቶች በብዛት ከጡንቻ፣ ከህብለ ሰረሰር፣ ከጅማት፣ ከደም ቧንቧ፣ ከአጥንት … ጋር የተያያዙ ጉዳቶችን ያስተናግዳሉ። ኢትዮጵያ በተለይ የምትታወቀው በሩጫ ስፖርቶች እንደመሆኑ በእግር ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች የሚያመዝኑ ሲሆን፤ ዓይነቱም ከቀላልና መካከለኛ ከፍተኛ ህክምና እስከሚያ ስፈልጋቸው ጉዳቶች ይዘልቃሉ። አንዳንድ የጉዳት ዓይነቶች እረፍት በማድረግና በቀላል ህክምና ሲድኑ፤ ስር የሰደደ ጉዳት ደግሞ ረጅም ጊዜ ሊወስድና እስከ ቀዶ ጥገና ሊደርስም ይችላል። የጉዳት መንስኤዎች እንደ\nጉዳት ዓይነቶቹ የተለያዩ ቢሆኑም፤ ከልምምድ ጋር በተያያዘ በደንብ ባለማሳሰብ፣ በቂ ውሃ ባለመውሰድ፣ በውድድር ላይ፣ በቂ እረፍት ባለማድረግ፣ እንደ ስፖርት ዓይነቱ ከሚጠቀሟቸው ቁሳቁሶች ጋር በተገናኘ፣ ከስነ-ምግብ አለመመጣጠን አሊያም አትሌቶቹ በዓመቱ መጀመሪያ ቅድመ ጤና ምርመራ ካለማድረግ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። ኢትዮጵያ ውጤታማ የሆነችበት የረጅም ርቀት ሩጫ እንደመሆኑ በዚህ ዘርፍ የሚታየው ጉዳት ከጫና ጋር በተያያዘ የሚደርስ ነው። በልምምድና ውድድር ጫና ምክንያትም አትሌቶች በተለይ ስብራትን ለመሰለ ጉዳት ተጋላጭ ይሆናሉ። በመካከለኛ እና አጭር ርቀት ሩጫዎች በአመዛኙ የሚስተዋለው ደግሞ ጡንቻ ላይ ጉዳት እንደሚደርስ ነው። በእርግጥ ከጉዳት በኃላ የሚኖረው የማገገሚያ ጊዜ እንደ አትሌቱ ጉዳት የሚወሰን እንደሚሆን ባለሙያዋ ያስረዳሉ። አትሌቱ የደረሰበት ጉዳት በህክምና ባለሙያዎች ከታየ በኃላ ከመንስኤው በመነሳት የማገገሚያ ጊዜው እንዲሁም የማገገሚያ ዓይነቱ ሊለያይ ይችላል። ከጉዳቱ ክብደት ባለፈም በሴት እና በወንድ አትሌቶች ላይ የሚደርሰው የጉዳት ዓይነት ልዩነት ሊኖረው ስለሚችልም ህክምናውም ሆነ የማገገሚያ ጊዜው ላይ ልዩነት ይኖራል። እንደሚታወቀው ስፖርት በኢትዮጵያ ከሳይንሳዊው መንገድ ይልቅ ወደ ተለምዶአዊ አሰለጣጠን ያደላል። አትሌቲክስ በዚህ ቅድሚያ ተጠቃሽ ሲሆን፤ ባህላዊ ሊባል በሚችል መልኩ አትሌቶች አሰልጥነው እስከ ብሔራዊ ቡድን መድረሳቸውም እሙን ነው። በዚህ መልክ መሰልጠናቸው ሙሉ ለሙሉ ስህተት ነው ሊባል ባይችልም ግን በሳይንሳዊ መንገድ ማሰልጠን ቢቻል የውጤታማነት መንገዱ ሊቀል እንዲሁም ሊደርሱ ከሚችሉ ጉዳቶችና ያለ ዕድሜ ከስፖርቱ የመራቅ ችግር ሊቀረፍ ይችላል። ጉዳትም በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ይገኛል፤ በተለይ በዚህ ወቅት ማሳጅ ቤቶችና ወጌሻዎች በየአካባቢው ተበራክተዋል። በብዛት እንደሚታየው ከሆነም አትሌቶች ጉዳት ሲያስተናግዱ ወደዚሁ መሄድን ምርጫቸው ያደርጋሉ። ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነም፤ አትሌቱ በልምምድ ወቅት ከሚሰራቸው እንቅስቃሴዎች በተጓዳኝ ፊዚዮቴራፒ እና ማሳጅቴራፒ በጉዳት ላይ የራሱ ድርሻ አለው። ከዚህም ባሻገር የስፖርት ህክምና ከስነ-ምግብ እና ስነ-ልቦና ጋርም ተመጋጋቢ ነው። አንዱን ከአንዱ መነጠል ከባድ ቢሆንም፤ አሁን ባለው አሰራር ግን እንደ ሃገር በርካታ የሚጠበቁ ነገሮች አሉ። ከማሳጅና ወጌሻ ጋር በተያያዘ በትምህርት ስርዓት ውስጥ ተካቶና የህክምና ባለሙያዎች ገብተውበት ከመስራት አኳያ በርካታ ክፍተቶች አሉ። ችግሩ በተለይ የሚስተዋለው ደግሞ በክለቦች እና በስልጠኛ ማዕከላት ላይ ነው። ለዚህ ምክንያት የሆነው የግንዛቤ ችግር፤ በስፖርቱ ባለድርሻ አካላትም ትኩረት ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ባለሙያዋ ያመለክታሉ። ቴራፒ ራሱን የቻለ ትልቅ ሙያ ሲሆን፤ በሌላው ዓለም ትምህርቱ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እሰከ ሶስተኛ ዲግሪ የሚሰጥ ነው። እዚህ የሚስተዋለው ባህላዊውን የህክምና ዘዴ በአንዴ ማውጣት ባይቻልም፤ በምን መልኩ መስተካከል ይገባዋል የሚለውም ቁልፍ ጉዳይ ሊሆን እንደሚገባ ባለሙያዋ ያስረዳሉ። ግንዛቤውም ለአትሌቶችና ከአትሌቶች ጋር አብረው ለሚሰሩ አካላት መስጠት አስፈላጊ ይሆናል። ፌዴሬሽኑ ከኃላፊነቶቹ መካከል ለባለ ሙያዎች ስልጠና እና ድጋፍ መስጠት አንዱ እንደሆነ ይታወቃል። በስፖርት ህክምና ላይ እንደ ሃገር ያለው እንቅስቃሴ እዚህ ግባ ባይባልም፤ የሙያ ማሻሻያ ከሚሰጥባቸው ዘርፎች መካከልም አንዱ የስፖርት ህክምና ነው። ከሳምንታት በፊትም በስፖርት ፊዚዮቴራፒና ተጓዳኝ ርዕሶች ላይ ለሶስት ቀናት በባህር ዳር ከተማ ለባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናው 69 ባለሙያዎችን በመያዝ በሁለት ተከፍሎ የተሰጠ ሲሆን፤ የአትሌቲክስ አሰልጣኞች እንዲሁም በክለቦችና ማሰልጠኛ ማዕከላት የሚገኙ የማሳጅና ፊዚዮ ቴራፒ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ነበር። ከዚህ በተጓዳኝ ለጡንቻ እና በነርቭ ጉዳት ተጋላጭ የሆኑ አትሌቶችና ሰልጣኞች በባለሙያዎቹ ህክምና አግኝተዋል። ስልጠናውን የሰጠው በስፔን የሚገኝ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ባለሙያዎች ቡድን በዓመታዊው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር ላይ የመገኘት ልምድ እንዳለው ባለሙያዋ ይጠቁማሉ። ስልጠናውን የሰጡት 33 ባለሙያዎች ሲሆኑ፤ 27 የሚሆኑ በተለያዩ ክሊኒኮች የሚሰሩ ፊዚዮ ቴራፒስቶች እንዲሁም ስድስት የዘርፉ መምህራን ናቸው። የዚህን ዓመት ልዩ የሚያደርገውም ከስልጠናው ባሻገር ከፌዴሬሽኑ እንዲሁም ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በአጭር እና ረጅም ጊዜ ስልጠናዎች ላይ በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ነው። በሃገሪቷ ዘርፉ ያለው እንቅስቃሴ የጎላ አለመሆኑ ዋናው ክፍተት ሲሆን፤ ትምህርቱንም በተሻለ መልኩ በውጪ ሃገራት ነው ማግኘት የሚቻለው። በመሆኑም ልምድ ካላቸው የታወቁ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ትምህርቱ (ስልጠናው) ላይ መስራትና ራሱን የቻለ መስመር ቢዘረጋለት መልካም እንደሚሆን ባለሙያዋ ያመላክታሉ። ያሉትን ጅምሮችም አጠናክሮ በመቀጠል ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ እንዲቻል ባለድርሻ አካላት አጽንኦት መስጠት ተገቢ ነው። እንደሚታወቀው አትሌቲክስ ኢትዮጵያ የምትጠራበት ትልቁ ስፖርት ነው። በመሆኑም ሁሉም አካል ለስፖርት ህክምና አትኩሮት ኖሯቸው፤ ክለቦችና የማሰልጠኛ ማዕከላት በቂና በስርዓት የሰለጠኑ የስፖርት ህክምና ባለሙያዎች ቢኖሯቸው አትሌቶችን ከጉዳት ለመታደግ እንዲሁም የተሻለ ህክምና ለማግኘት ይቻላል። ይህንንም መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ የሚመለከታቸው ሁሉ የበኩላቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል።አዲስ ዘመን ሰኔ 24/2011", "passage_id": "02715ac18a6a7bee6707a6bc4b3d735e" }, { "passage": "ባለፉት አስር ዓመታት በአትሌቲክስ ስፖርት ውስጥ በርካታ ክስተቶች ተስተናግደው አልፈዋል። ለቁጥር የሚታክቱ ክብረወሰኖች ከመሻሻላቸውም ባለፈ በሰው ልጅ ሊደፈሩ ይችላሉ በሚል የማይጠበቁና የማይገመቱ ታሪካዊ ክንውኖችም ታይተዋል። ከእነዚህ መካከል በተለይ በስፖርቱ አጭር ርቀት ውድድር (100ሜትር) እና በረጅሙ ርቀት (ማራቶን) የተመዘገቡት ስኬቶች የሰውን ልጅ አቅም በትክክልም ማሳየት የሚያስችሉ ሆነዋል። ታዲያ በአስሩ ዓመታት ከታዩና ክብረወሰንም ካስመዘገቡ አትሌቶች መካከል የተሻለው ማን ነው? በዚህ ጥያቄ ላይ ተንተርሶ ምርጫውን\nያካሄደው ደግሞ እአአ በ1940 መሰረቱን በአሜሪካ በማድረግ የተቋቋመውና ትኩረቱን በመምና ሜዳ ተግባራት ስፖርቶች ላይ ያደረገው\nመጽሄት ነው። መጽሄቱ እአአ ከ2010-2019 ድረስ ባሉት ዓመታት ከጎዳና ላይ ውድድሮች ባሻገር ባሉት ውድድሮች አስር አትሌቶችን\nበእጩነት በማቅረብ ምርጫውን በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት መጀመሪያ ነበር የጀመረው። በተሰጠው ድምጽ መሰረትም ኬንያዊው የ800 ሜትር\nአትሌት ዴቪድ ሩዲሽያ ተመራጭ ሊሆን ችሏል። በእጩነት ከቀረቡት አትሌቶች መካከል\nአንዱ በአጭር ርቀት የአትሌቲክስ ተጽእኖ ማሳደር የቻለው ጃማይካዊ አትሌት ዩሲያን ቦልት ነው። አሁን ራሱን ከተወዳዳሪነት ያገለለው\nቁመተ መለሎ አትሌት በ100 ሜትር የሸፈነበት 9ሰከንድ ከ63 ማይክሮ ሰከንድ የምንጊዜም የርቀቱ ምርጥ አትሌት ያደርገዋል። በውድድር\nተሳትፎው ከደረጃ ወርዶ የማያውቀው አትሌት አራት የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎችን ከማጥለቅ ባሻገር የዓለም ቻምፒዮን በመሆንም ክብረወሰኑን\nአርቆ የሰቀለ አትሌት መሆኑ ምርጫውን በአሸናፊነት ያጠናቅቃል በሚል ይጠበቅ ነበር። በረጅም ርቀት የመም ላይ ውድድሮች በኢትዮጵያዊያኑ ጀግና አትሌቶች እግር የተተካው እንግሊዛዊ አትሌት\nሞሃመድ ፋራም በእጩነት ከቀረቡት መካከል ነበር። የዓለም ቻምፒዮናው በኦሊምፒክ አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ያሳካ ሲሆን፤ በ5ሺ\nእና 10ሺ ርቀቶች ሃገሩን በተደጋጋሚ ለማስጠራት ችሏል። አትሌቱ ምንም እንኳን ከመም ወደ ጎዳና ላይ ውድድሮች ባደረገው ሽግግር\nእንደሚጠበቀው ውጤታማ ባይሆንም ያለፉት አስር ዓመታት ግን ለእርሱ አስደሳች ነበሩ። ከመም ይልቅ በማራቶን ስሙ የገነነውና የዚህ ወቅት የርቀቱ ቁጥር አንድ አትሌት የሆነው ኬንያዊ ኢሉድ\nኪፕቾጌም ቀዳሚ ተመራጭ ይሆናል በሚል ከሚጠበቁት እጩዎች መካከል ነበር። የዓለም ክብረወሰን ባለቤቱ እንዲሁም ማራቶንን ከ2 ሰዓት\nበታች የመግባት ሙከራውን ያሳካው አትሌት በሮጠበት ጫማ ምክንያት ውዝግቦችን ያስተናግድ እንጂ የጎዳና ላይ ሩጫዎች ንጉስነቱን ማንም\nሊቀማው እንደማይችል ነው አዘጋ ጆቹ ያረጋገጡት። አሜሪካዊያኑ ክርስ ቲያን ቴይለርና አሽተን ኢትን፣ ደቡብ አፍሪካዊው ዋይዴ ቫን ኔኬርክ፣ ፈረንሳ\nዊው ሬናውድ ላቪሌኔ፣ የኳታሩ ሙታዝ ባርሺም እንዲሁም ጀርመናዊው ሮበርት ሃርቲንግም ከአስሩ እጩዎች መካከል ይገኙበታል። ከእጩዎቹ መካከል በተለይ ‹‹የዓለም ፈጣኑ ሰው›› በሚል የሚታወቀው ጃማይካዊ አትሌት አብላጫውን\nድምጽ ያገኛል የሚል ግምት ያግኝ እንጂ አሸናፊ የሆነው ግን ዴቪድ ሩዲሽያ ነው። የለንደንና ሪዮ ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቱ\nእንዲሁም የዴጉና ቤጂንግ የዓለም ቻምፒዮናው አትሌት፣ በተለይ እአአ በ2012ቱ የለንደን ኦሊምፒክ ርቀቱን ያጠናቀቀበት ሁኔታ በአስር\nዓመታት ከማይዘነጉ ትዝታዎች መካከል ቀዳሚው በሚል በዓለም አትሌቲክስ መመረጡ የሚታወስ ነው። አትሌቱን አስደናቂ ከሚያደርጉት ምክንያቶች\nመካከል አንዱ፣ በርቀቱ የዓለም ክብረወሰንን ለሶስት ጊዜያት(1:41.09፣ 1:41.01፣ 1:40.91) መስበር መቻሉ ነው። መጽሄቱ መሰል ምርጫዎችን ማካሄድ የጀመረው እአአ በ1960ዎቹ ሲሆን፣ የመጀመሪያው አሸናፊም ኒውዝላንዳዊው\nፒተር ስኔል ነበር። እአአ የ1970ዎቹን ክብር ደግሞ የሶቬት ህብረት አትሌት የሆነው ቪክቶር ሳኔይቭ ነበር የወሰደው። በ1980ዎቹ\nአሜሪካዊው ካርል ሉዊስ ምርጥ ሲሰኝ፤ የ90ዎቹንም ሌላኛው የሃገሩ ልጅ ሚካኤል ጆሃንሰን አሸናፊ ሆኗል። እአአ ከ2000-2009\nባሉት ዓመታት ምርጥ አትሌትነት ምርጫ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ሲሆን፤ አንበሳው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ቀዳሚ ሊሆን ችሏል። አዲስ ዘመን የካቲት 2/2012ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "c1a3934ef128e2c24bafaf397641a09b" }, { "passage": " በዓለም አትሌቲክስ ታሪክ አስር ሺ ሜትር ውድድር ለኢትዮጵውያን የተለየ ቦታ አለው። የዓለም ሕዝብም ይህን ርቀት የኢትዮጵያውያን የባህል ስፖርት አድርጎ እስከ መቁጠር ደርሷል። ማርሽ ቀያሪው ምሩፅ ይፍጠር በሞስኮ ኦሊምፒክ በርቀቱ ካስመዘገበው ድል አንስቶ ኃይሌ ገብረሥላሴና ቀነኒሳ በቀለ በኦሊምፒክም ይሁን በዓለም ቻምፒዮና ደጋግመው ድል በማድረግ ኢትዮጵያ የርቀቱ ንጉሥ መሆኗን አስመስክረዋል። ከምሩፅ ይፍጠር በኋላ ኢትዮጵያ በርቀቱ ንጉሥ ለማግኘት በርካታ ዓመታትን መጠበቋ ባይዘነጋም ከኃይሌ ገብረሥላሴ ጀምሮ የመጣው የአትሌቲክስ ትውልድ የርቀቱን የኢትዮጵያ የበላይነት አስጠብቆ ቆይቷል። እ.ኤ.አ 2011 ደቡብ ኮሪያ ዴጉ ካስተናገደችው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ወዲህ ግን ኢትዮጵያውያን ካለፉት ስምንት ዓመታት በላይ የርቀቱን ዙፋን ለሌላ አገር አትሌቶች ለማስረከብ የተገደዱበት ሁኔታ ተፈጥሯል። በዴጉው የዓለም ቻምፒዮና አትሌት ኢብራሒም ጀይላን እንግሊዛዊው ሞ ፋራህን መቼም በማይረሳ ሁኔታ ካሸነፈ ወዲህ ኢትዮጵያ በርቀቱ እንደቀድሞዎቹ ጀግኖች አልሸነፍ ባይና እስከ መጨረሻ ታጋይ አትሌት ለዓለም ማሳየት አልቻለችም። ይህም ሞ ፋራህ በርቀቱ በሦስት የዓለም ቻምፒዮናዎችና በሁለት ኦሊምፒኮች እንዲነግሥ ምክኒያት ሆኖታል። በነዚህ ዓመታት ኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋ የጣለችባቸው ወጣትና ባለተሰጥኦ አትሌቶች በብዛት መፈጠር ቢችሉም የፋራህ ተከታይ ሆነው የብርና የነሐስ ሜዳሊያ ከማጥለቅ በዘለለ የርቀቱን ክብር ወደ ቤቱ መመለስ አልተቻላቸውም። ፋራህ ካለፈው የለንደን\nየዓለም ቻምፒዮና በኋላ\nከህመም ውድድሮች ራሱን\nማግለሉን ተከትሎ ዓለማችን\nበአስር ሺ ሜትር\nውድድር አዲስ ንጉሥ\nስትጠብቅ ቆይታለች። ከለንደን\nቻምፒዮና በፊትና በኋላ\nበርቀቱ ትልቅ ተሰጥኦ\nያላቸው ኢትዮጵያውያን ወጣት\nአትሌቶች በብዛት መፈጠራቸውን\nተከትሎ አስር ሺ\nሜትር ዳግም የኢትዮጵያውያን\nአትሌቶች ዙፋን የመሆኛው\nትክክለኛ ጊዜ እንደደረሰ\nበርካቶች ተስፋ አድርገው\nነበር። ከትናንት በስቲያ\nበተጠናቀቀው የዶሃው የዓለም\nቻምፒዮናም የትኛው ኢትዮጵያዊ\nአትሌት የርቀቱን ዘውድ\nእንደሚደፋ በጉጉት ሲጠበቅ\nነበር። ኢትዮጵያ በዚህ\nርቀት ፈጣን ሰዓት\nያላቸው ወጣትና ልምድ\nያካበቱ አትሌቶችን ከማሰለፏም\nበላይ በርቀቱ ያላት\nታሪክ ዳግም ወደ\nድል የምትመለስበት ጊዜ\nአሁን እንደሆነ ብዙዎች እምነት አሳድረው ነበር። ልምድና ብቃት ከድንቅ የሩጫ ክህሎት ጋር የተላበሰው ሐጎስ ገብረሕይወት፣ ቁመተ መለሎው ባለተሰጥኦ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እንዲሁም ጠንካራው አትሌት አንዱዓምላክ በልሁ የርቀቱን ድል የመመለስ ተስፋ የተጣለባቸው አትሌቶች ናቸው። እነዚህ አትሌቶች እንዳላቸው ብቃት ተባብረው የቡድን ሥራ ሠርተው ድሉን ወደ ቤቱ ማምጣት ግን ሳይችሉ ቀርተዋል። ኢትዮጵያም የአስር ሺ ሜትር ድል ከእጇ ከወጣ ይህ አራተኛ የዓለም ቻምፒዮና ሊሆን ችሏል። ለአስር ዓመታት ከእጃችን ለመውጣት የተገደደው የአስር ሺ ሜትር ከዚህ በኋላ ለመመለስ ስንት ዓመት እንደሚፈጅ መገመት አይቻልም። ምክኒያቱም ዶሃ መልካምና የተሻለ አጋጣሚ ነበርና። በርቀቱ ተፎካካሪና ተመሳሳይ ታሪክ ያላት ኬንያም አልተሳካላትም። ያልተጠበቀውና ትኩረት ያልተሰጠው ዩጋንዳዊው አትሌት ጆሹዋ ቺፕቴጌ በዓለም ቻምፒዮና ታሪክ ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት በ26:48.37 አስመዝግቦ ለአገሩ አዲስ ታሪክ ፅፏል። ወጣቱና ወደ ፊት ባይባል እንኳን በቅርቡ ትልቅ ተስፋ እንዳለው ያስመሰከረው ዮሚፍ ቀጄልቻ በርቀቱ ገና ለሁለተኛ ጊዜ ቢወዳደርም 26:49.34 በሆነ ሰዓት የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ማስመዝገብ ችሏል። ይህም ኢትዮጵያ በቻምፒዮናው በሁለት ወርቅ፣አራት ብርና አንድ ነሐስ ሜዳሊያ ከዓለም አምስተኛ ከአፍሪካ ደግሞ ሁለተኛ ሆና እንድታጠናቅቅ አስችሏታል። ባለፈው መጋቢት በዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና በወጣቶች ምድብ ወርቅ ማጥለቅ የቻለው ዩጋንዳዊ ኮከብ ሆኖ ባመሸበት የዓለም ቻምፒዮና የመዝጊያ ውድድር ኬንያዊው ሮኔክስ ኪፕሩቶ 26:50.32 በሆነ ሰዓት የነሐስ ሜዳሊያ ሲያጠልቅ ለድል ሲጠበቅ የነበረው ሐጎስ ገብረሕይወት በ27:11.37 ሰዓት ዘጠነኛ ደረጃን ይዞ መፈፀሙ አስደንጋጭ ነበር። በአንፃሩ የርቀቱን ድል ለመመለስና የቡድን ሥራ ለመሥራት ጥረት ሲያደርግ የነበረው አንዱዓምላክ በልሁ 26:56.71 በሆነ ሰዓት አምስተኛ ደረጃን ይዞ ፈፅሟል።አዲስ ዘመን  መስከረም 27/2012 ቦጋለ\nአበበ", "passage_id": "5ebe622281648a071c818ac6b0df3fb3" } ]
a060178ceb7c8e5b0a79d72d83373cb1
4bd04bb6d2cdcbd8afed2fbdd019ec6b
ስፖርት የአብሮነትና አጋርነት መገለጫ ነው !!
ስፖርት ከአካላዊ እንቅስቃሴና ከመዝናኛነት ባለፈ ማህበራዊ ግዴታን በመወጣት ረገድ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በተለያዩ አጋጣሚዎች ታይቷል፡፡ በተለይም ዓለም በኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ 19) ምክኒያት ጭንቅ ውስጥ በገባችበት በዚህ ወቅት ስፖርትና የስፖርቱ ማህበረሰብ ማህበራዊ ግዴታን በመወጣት ረገድ ትልቅ ስራ እየሰራ ይገኛል።ስፖርት የአብሮነትና አጋርነት መገለጫ የመሆኑን “ሃቂቃ” ባለፉት አምስት ወራት በዘርፉ የተከናወኑ ሰብዓዊ ድጋፎች በቂ ማስረጃ ተደርገውም ይነሳሉ። በሀገራችንም በተመሳሳይ በስፖርቱ ዘርፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አኳያ ሰፊ እንቅስቃሴ እንደሚደረግ መናገር ይቻላል። በዘመነ ኮሮና በስፖርቱ ዘርፍ በኩል ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት ሲደረግ የነበረውን ርብርብ ዘወር ብሎ መመልከቱ ለዚህ እማኝ ይሆናል።በሀገራችን ኮሮናን ለመከላከል ሲደረግና እየተደረገ ባለው ርብርብ የስፖርት ዘርፍም በዚህ እንቅስቃሴ ቀዳሚ ተሰላፊ ነበር። የስፖርት አመራሮች፣ የስፖርት ማህበራት፣ ስፖርተኞች፣ አሰልጣኞች እንዲሁም ደጋፊዎቻቸው፤ መልእክት በማስተላለፍ፣ በየቤታቸው ላሉ ዜጎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማሰራት፣ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ፣ የምግብና ሌሎች መገልገያዎችን በመለገስ እንዲሁም በሌሎች ተግባራት ላይ እየተንቀሳቀሱ ነው። ዘርፉን የሚመራው የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽንም ይህን እንቅስቃሴ በማስተባበር እንዲሁም እንደ አንድ ባለድርሻ አካል በሚጠበቅበት ሁሉ የራሱን ድርሻ በመወጣት ረገድ የነበረው ሚና ደግሞ ግዙፍ ነበር። ኮሚሽኑ ወገናዊነቱን ለመወጣት እየሄደ ያለባቸው ርቀቶች ደግሞ የበለጠ እንዲመሰገንና እንዲደነቅ ያደረገ መሆኑ የተለያዩ አካላት እያነሱ ይገኛሉ። በጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድን በመጋቢት መጨረሻ “ማዕድ ማጋራት” ሲሉ በሰየሙት የድጋፍ መርሃ ግብር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን ከተለያዩ አካላት ጋር በመቀናጀት የጀመረው ተግባር በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል። በስፖርት ኮሚሽኑ አስተባባሪነት ሚያዝያ 17 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም በይፋ የተጀመረው “ማዕድ ማጋራት” መርሃ ግብሩ ስፖርት የአብሮነትና የአጋርነት መገለጫ መሆኑን በተጨባጭ ያሳየ ተግባር እንደሆነ ብዙዎች መስክረውለታል።የስፖርቱን ዘርፍ ወገናዊነት የሚንፀባረቅበት ማህበራዊ ኡደት እንደሆነ በመርሃ ግብሩ 300 የጎዳና ተዳዳሪዎችን ለአንድ ወር ያህል በመመገብ ባከናወነው ተግባር አስመስክሯል።ስፖርት ኮሚሽኑ የተለያዩ የስፖርት ተቋማቱና አጋር ድርጅቶችን አስተባብሮ ለአንድ ወር ያህል ሲያከናውነው የነበረው የምገባ መርሃ ግብር ባሳለፍነው እሁድ ተጠናቋል።የስፖርቱ ማኅበረሰብ በዘመነ ኮሮና ህዝባዊነቱን በተጠናከረ መልኩ ያሳየ መሆኑን የመጀመሪያው ዙር የተጠናቀቀው የምገባ መርሃ ግብር አስረጂ ይሆናል። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን ግን «ስፖርት የአብሮነትና የአጋርነት መገለጫ እንደመሆኑ ማህበራዊ ኃላፊነት የመወጣቱ ተልዕኮ የሚቋጭ ሳይሆን በአዲስ ምዕራፍ የሚጀመር ነው »ሲል ሁለተኛውን ዙር የምገባ መርሃ ግብር መጀመሩን አስታውቋል። በስፖርት ኮሚሽን ፊት አውራሪነት፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከቢጂ አይ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር 300 ጎዳና ተዳዳሪዎችን ለአንድ ወር ያህል በምገባ መርሃ ግብሩ ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውሷል።የስፖርት ቤተሰቡ ወገናዊነት በተግባር የሚያሳየውን መርሃ ግብር በመሆኑ ኮሚሽኑ ሁለተኛ ወር ለማስቀጠል ሌሎች አጋዥ አካላትን በማስተባበር እንዲሁም ድጋፎችን ማሰባሰብ በመቻሉ መርሃ ግብሩ ለቀጣይ አንድ ወርም ተጠናክሮ ሊቀጥል መቻሉ ተነግሯል። በስፖርት ኮሚሽኑ ፊት አውራሪነት ተግባራዊ የተደረገው የምገባ መርሃ ግብር በሁለተኛ ዙር ላይ የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት፣ ወጋገን ባንክ እንዱሁም አቶ አብነት ገብረ መስቀል አጋርነታቸውን ያሳዩበት ሆኗል። ግንቦት 15 ቀን 2012 ዓ.ም አቶ ኤሊያስ ሽኩር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ የብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር ምስጋው አረጋ እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት በአዲስ አበባ ስታዲየም ተጀምሯል። ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር መርሃ ግብሩን ሲያስጀምሩ፤«የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በተወሰዱ እርምጃዎች ስፖርተኛው እና የስፖርት ቤተሰቡ ከፍተኛ የሆነ የስነ ልቦና እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አጋጥሟቸዋል ።ችግሮች ቢያጋጥሙም ስፖርተኛው እና የስፖርቱ ቤተሰብ በአንድ በኩል ከአለው ላይ በመቀነስ ለሌሎች በመደገፍ፤ በሌላ በኩል ሌሎች አካላትን በማስተባበር ወረርሽኙ ሊያስከትለው የሚችለውን ማህበራዊ እና ሰብዓዊ ቀውስ ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛሉ »ሲሉ ዓለም በኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ 19) ምክኒያት ጭንቅ ውስጥ በገባችበት በዚህ ወቅት ስፖርትና የስፖርቱ ማህበረሰብ ማህበራዊ ግዴታን በመወጣት በኩል እያበረከተ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት። አቶ ኤልያስ በሌላ በኩል «በመዲናችን ኗሪ ለሆኑ 300 ጎዳና ተዳዳሪዎች ለአንድ ወር ያህል በምገባ መርሃ ግብሩ ተጠቃሚ ሲደረግ የነበረበት ሁኔታ መቋረጥ እንደሌለበት በማመን ሁለተኛውን ዙር እንዲጀመር ተደርጓል። በመሆኑም ሁለተኛው ዙር የምገባ ፕሮግራም መንግስት የጎዳና ተዳዳሪዎች በዘላቂነት ህይወታቸውን እንዲመሩ እሲኪያመቻች ድረስ በእኛ ደረጃ ለአንድ ወር የምገባ ፕሮግራሙን ለማራዘም ነው »ያሉት። አምባሳደር ምስጋናው አረጋ በበኩላቸው፤ ወረረሽኙን ለመከላከል ከጅምሩ ጀምሮ ቀጣይነት ባለው የስፖርት ቤተሰቦች እያደረጋችሁት ላለው ድጋፍ ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል። በስፖርቱ መስክ የሚገኙ አካላት ለህዝብ ያላቸውን ወገንተኝነት እና ታማኝነት አርዓያነት ያለው ተግባር መሆኑን አመልክተዋል። «ህዝብ ሲኖር ስለሆነ ስፖርት የሚኖረው። ስለዚህ ሁላችንም በአንድ ላይ መቆም የምንችልበት የበለጠ የምንተባበርበት ወቅት በመሆኑ የተጀመሩ ድጋፎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል» ሲሉ ነበር መልዕክታቸውን ያስተላለፉት። በአጠቃላይ በሀገራችን ኮሮናን ለመከላከል ሲደረግና እየተደረገ ባለው ርብርብ የስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ረገድ በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል።የስፖርት አመራሮች፣ የስፖርት ማህበራት፣ ስፖርተኞች፣ አሰልጣኞች እንዲሁም ደጋፊዎቻቸው፤ መልእክት በማስተላለፍ፣ በየቤታቸው ላሉ ዜጎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማሰራት፣ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ፣ የምግብና ሌሎች መገልገያዎችን በመለገስ እንዲሁም በሌሎች ተግባራት ላይ ሲደረጉ የነበሩ እንቅስቃሴዎች ይሄንኑ ይመሰክራሉ።ዘርፉን የሚመራው የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽንም ይህን እንቅስቃሴ በማስተባበር እንዲሁም እንደ አንድ ባለድርሻ አካል በሚጠበቅበት ሁሉ የራሱን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል።ኮሚሽኑ በእርሱ አውራሪነት ተግባራዊ ያደረገው የምገባ መርሃ ግብር ደግሞ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እያደረገ ያለውን አስደማሚ ጥረት መስካሪ ተግባር ነው። በመርሃ ግብሩ 300 የጎዳና ተዳዳሪዎችን ለአንድ ወር በመመገብ የፈፀመውን ሰብዓዊ ተግባር ቀጣይነት ይኖረው ዘንድ፤ ግንቦት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ሁለተኛው ዙር መርሃ ግብር እንዲጀመር በማድረግ «ስፖርት የአብሮነትና አጋርነት መገለጫ ነው !!»የሚለውን አባባል በተጨባጭ፣ በተግባር……እንዲታይ አድርጓልና ሌሎችም ከዚህ ሊማሩ ይገባል ባይነን።አዲስ ዘመን ግንቦት 18/2012ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=33113
[ { "passage": " ከዓለም እስከ አህጉር፣ ከአህጉር እስከ አገር፣ ከአገር እስከ መንደር ከዚያም ማህበረሰብ እስከ ግለሰብ፣ በስፖርት ልቡ ያልተሳበና በፍቅሩ ያልተንበረከከ የለም።ስፖርት ሰላም ፣ፍቅር ፣የአብሮነትና የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የወንድማማችነት ልዩ መገለጫ ነው። ስፖርት ዘር፣ሃይማኖት፣ ፆታና ቀለምን አይለይም።ሁለት የተለያዩ አገራት ያወዳጃል። በአገር ፍቅር ስሜት ያስተሳስራል።ያፋቅራል።በእርግጥ አንዳንዶች ውጤትን ከስፖርታዊ ጨዋነት አስበልጠው የግል ጥቅማቸውን ሲያስቀድሙ ይስተዋላል። ከዚህ በአንፃሩ የግል ፍላጎታቸውን ችላ በማለት በስፖርታዊ ስነ ምግባር የታነፁ መኖራቸው የማይካድ ሃቅ ነው።በአትሌቲክሱ የውድድር ፍልሚያ ኬንያውያን በተለያዩ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ውድድሮች ላይ በርካታ ወገኖችን አስደንቀዋል።አስጭብጭበዋል።በውድድር አሸናፊ ሆነው የታዩትን ያህልም ከአንዴም ሁለት ጊዜ በስፖርታዊ ጨዋነትና ሰብዓዊነት ተግባር የታነፁ ስለመሆናቸውም አስመስክረው የሚሊየኖችን ልብ ሲያሸንፉ ታይተዋል።።የምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር አትሌት ከሰሞኑም ይህን በስፖርታዊ ጨዋነት መርህ የታነፀ ሰብዓዊነት ተግባር ደግሞ አሳይቷል።ትዕይንቱ የተከሰተው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበር የነሃስ ሜዳሊያ በሚሰጠውና ከቀናት በፊት በተካሄደው የናይይጄሪያ ዓለም አቀፍ የ10 ኪሎ\nሜትር የጎዳና ላይ ውድድር ነው።የታሪኩ ባለቤት ሲሞን ቺፕሮት ይባላል።ኬንያዊ የረጅም ሩጫ አትሌት ነው።በዚህ የ10 ኪሎ\nሜትር የጎዳና ላይ ውድድር ሲሳተፍ አራተኛው ሲሆን፣ ከሶስት ዓመት በፊት ደግሞ ባለድል መሆን ችሏል።ባሳለፍነው አመት ደግሞ ሁለተኛ ሆኖ ጨርሷል።ክስተቱ እንዲህ ነው። ሲሞን ቼፐሮት የዘንድሮውን ውድድር እየመራ ለመጨረስ የተወሰኑ ሜትሮች ብቻ ቀርተውታል።ውድድሩን ለሁለተኛ ጊዜ በማሸነፍ የመጀመሪያው የሚሆንበትን ታሪክ ለመፃፍ ማንም ሊያቆመው አይቻለውም።ይሁንና በዚህ ቅፅበት ሌላኛው የአገሩ ልጅና ብርቱ ተቀናቃኙ የሆነው ኬኔት ኪፕኬሞይ ድንገት ሲዝለፈለፍ ይመለከታል።ክስተቱን ያስተዋለው ሲሞን ቼፕሮት ግን የአገሩን ልጅ ጥሎት ለመግባት አልወሰነም።ውድድሩን አሸንፎ አንደኛ የመባል ስሜቱን አላዳመጠም።ውድድሩን ለሁለተኛ ጊዜ በማሸነፍ የመጀመሪያው የሚሆንበት ታሪክ ለመጻፍ አልቸኮለም።አትሌቱ የተፎካካሪውን ውድቀት እንደ መልካም አጋጣሚ ከመጠቀም ይልቅ ብዙዎቹን ባስገረመ መልኩ ሩጫውን በማቋረጥ ጓደኛውን ከወደቀበት ደግፎ አንስቶ ልባዊ ወንድምነቱን በማሳየት በርካታ ወገኖችን አስደምሟል። ሁለቱ አትሌቶችም ቀስ ብለው በመሮጥ ውድድሩን 15ኛ እና\n16ኛ ሆነው የፈፀሙ ሲሆን አንደኛ መውጣት የሚችለው ሲሞንም ተሸንፏል።አትሌቱ ከፊቱ የሚጠብቀውን የወርቅ ሜዳሊያና የአሸናፊነቱን ሽልማት ገንዘቡን በመተውና ይህ ሁሉ ከሰው እንደሚያንስ በማሳብ የፈፀመው መልካም ተግባር በሚሊየን የሚቆጠሩ ልቦችን ማሸናፍ ችሏል።የወርቅ ሜዳሊያውን ትቶ ከወርቅ በላይ የሆነ ጀብዱ በመፈፀም፤ ከወርቅ ሜዳሊያው ይልቅ ሰብአዊነት እንደሚልቅ ለመላው ለዓለም   አሳይቷል።ሜዳሊያ ሳይሆን ልብ ያሸነፈውና በውድድሩ ስፍራ ሆነው ውድድሩን የተመለከቱትን በሺዎች የሚቆጠሩ ብቻም ሳይሆን በአህጉር ዓቀፍ ደረጃ በቴሌቪዥን መስኮት የሚመለከቱትን ያስደነቀ አትሌት ፤ማሸነፍ ማለት ሁሌ አንደኛ መውጣት ማለት አይደለም፤ሁሌ የወርቅ ሜዳሊያ ማግኛት አይደለም። አንዳንዴ ተሸንፈህ አሸናፊ ትሆናለህ፣ መጨረሻ ወጥተህ ክብርን ጀግንነትን ትጎናፀፋለህ አሰኝቷል።‹‹በአንድ ወቅት አባቴ፤ በመንገድህ ላይ የታመመ ሰው ስትመለከት አልፈኸው ጉዞህን አትቀጥል፤ ይልቅ እርዳው፤ ብሎኝ ነበር፤ የአገሬውን ልጅ ወድቆ ስመለከተው ይህ ወደ አእምሮዬ መጣ፤ እናም ለራሴ ሳላስብ ልረዳው ወሰንኩ ››ያለው አትሌቱ፤ መሰል ተግባሩም ለመጪው ትውልድ አርእያነት ያለው ስለመሆኑ ተናግሯል።የአትሌቱ ተግባርም የወርቅ ሜዳሊያ ከማግኘት ይልቅ ወርቃማ ልብ መያዝ ይበልጥ ያነግሳልና ይህም እውነተኛው የስፖርት ጽንሰ ሃሳብ መገለጫ ነው አሰኝቷል። በዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማህበር የናይጄሪያ ተወካይ ማይክ ልቴሟግቦር አትሌቱን ‹፣ጀግናችን››ሲሉ አሞካሽተውታል፡፡ለፈፀመው የሰብዓዊነት አኩሪ ገድልም አንድ ሚሊየን ሽልንግ አበርክተውለታል።የቺፕሮትን ተግባር\nበማወደስ፤ ተረጂው አትሌት\nበበኩሉ፤ ‹‹ሁሉም አትሌት\nይህን መሰል ተግባር\nአይፈፅምም፤ሲሞን መልካም\nሰው ነው፤ በውድድሩ\nእኔን ለማርዳት ያሰው\nመልካምነትም እጅጉን አስድንቆኛል››\nሲል ተደምጧል። አሸንፎ\nሜዳሊያውን ከወሰደው ኢትዮጵያዊ\nበላይ ሲሞን ጀግና\nተብሎ ዘላለማዊ ስምና\nዝናን አትርፏል።አዲስ ዘመን ግንቦት 27/2011 ", "passage_id": "ea9ee4c32daedd909149824d13b5ab5d" }, { "passage": "በእግር ኳሱ የሚስተዋለው ችግር ካልታረመ ውድድርን እስከ ማቆም የደረሰ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ሚኒስቴሩ አስጠነቀቀ። በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር አዘጋጅነት ለሁለት ቀናት «የስፖርት ጨዋነት ምንጮች» በሚል መሪ ቃል ከሚያዚያ 14 እስከ 15 ቀን 2011 ዓ.ም የምክክር ጉባዔ በሸራተን ሆቴል ተካሂዷል። የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው እንደተናገሩት፤ በሀገራችን በስፖርታዊ ሁነቶች ላይ ስፖርታዊ ጨዋነት ሲጓደልና በርካታ ያልተገቡ ድርጊቶች ሲፈጸሙ እየተስተዋለ ይገኛል። በተለይ በእግር ኳሱ ከደጋፊዎች ጋር ተያይዞ የሚስተዋለው መስመር የለቀቀ ባህርይ እየተስተዋለ ነው፡፡ ችግሩ ካልታረመ ውድድርን እስከ ማቆም የደረሰ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል። እንደ ዶክተር ሂሩት ገለጻ ፤ ስፖርት ለሰላም መሆኑ\nቀርቶ ውድድሮች ዘርንና ማንነት መሰረት ባደረገ መልኩ የግጭት ምንጭ እየሆኑ ይገኛሉ። ስፖርት አለ በተባለ ቁጥር ሰው መረበሽ የለበትም። ህዝቡ ተረጋግቶ መኖር መቻል አለበት። ህብረተሰቡ ጨዋታ አለ በተባለ ቁጥር ለከፋ ስነ ልቦና ረብሻ መዳረግ የለበትም፤ አይገባውምም። ስለዚህ በእግር ኳሱ የሚታየው ስፖርታዊ ጨዋነት ችግር እስከሚስተካከል ውድድሩን እስከማቆም የሚደርስ እርምጃ ሊወሰድ የሚችል ይሆናል። ስፖርት ለወንድማማችነት የሚለው ብሂል ተረስቶ፤ በስፖርት ሁነቶች ላይ አጀንዳዎች እየተፈጠሩ እርስ በእርስ ወደ መጠቃቃት የመግባት ሁኔታዎች በስፋት እንደሚስተዋሉ አመልክተዋል። በስፖርት ማህበረሰቡ መካከል መጠራጠርና ጥላቻን ከመዝራት ባሻገር ኢትዮጵያዊ ባህልን፣ እኛነታችንን የሚያዋርድና የስፖርቱን እድገት የሚያቀጭጭ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህ ረገድ ክለቦችና ደጋፊ ማህበራት ሰፊ ስራ መስራት አለባቸው። በተለይ ክለቦችና የደጋፊ ማህበራትን የሚመሩ አካላት ለሚመሩት ወገን አርዐያ ሆነው መገኘት እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል።«ጨዋ ተጫዋች ከጨዋ አሰልጣኝ ይፈጠራል፤ ጨዋ ደጋፊ ከጨዋ የደጋፊ ማህበራት፣ ክለብና የክለብ አመራር ይፈጠራሉ። ወጣቱ የሚማረው በዙሪያ ከሚታዩት ነባራዊ ሁኔታዎች በመሆኑ አመራር ላይ የምትገኙ አባላትና አካላት ተነባቢ መጽሀፍት መሆናችሁን አውቃችሁ መልካም አርዐያ በመሆን ቆርጣችሁ ልትነሱ ይገባል። ባለድርሻ አካላትም በመመካከርና በመወያየት ችግሩን መፍታትና እልባት ለመስጠት መስራት ይገባል» ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የብሄራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ በበኩላቸው፤ ‹‹እግር ኳሱ የሌላ ነገር አጀንዳ መናኸርያ ከማድረጋችን ባሻገር ቂም እያወረስን እንገኛለን። እከሌ ሲያሸንፍ ከስፖርት መርህ ውጭ እከሌ ዘር ተሸነፈ፣ አሸነፈ በሚል ጤናማ ያልሆነ አስተሳሰብ ላይ ደርሰናል። ከስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል የተነሳ ሙሉ ጤና ይዞ መጥቶ ጤናውን አጉድሎ የሚመለስበት ጊዜ ላይ ደርሰናል›› ብለዋል። እንደ አቶ ኢሳያስ ገለጻ ፤ ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት\nእየተደረገ ቢሆንም ይህ በቂ አይደለም። እግር ኳሱን ከዚህ ስፖርታዊ ካልሆነ ተግባር ለመታደግ እንዲህ አይነት ውይይቶች ሊጎለብቱ ይገባል ። የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገብረመስቀል ፤ ‹‹በሀገራችን እግር ኳስ ውስጥ ሥርዓት አልበኝነት እግር ኳሱን እየጎዳው በመሆኑ በርካታ የስፖርት ቤተሰቦችን ከስፖርት ማዘውተሪያ እያራቀ ይገኛል። በጊዜ መስራት የሚገባውን የቤት ስራ ባለመስራታችን ችግሩ እየተባባሰ መጥቶ በዘር ፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት እና በፖለቲካ አመለካከት ያተኮሩ ልዩነቶች እዚም እዛም እየታዩ ይገኛሉ። ስለሆነም ይህ እየተባባሰ የመጣውን ችግር ለመቅረፍ የውይይት መድረኩ የራሱ ድርሻ አለው የሚል እምነት አለኝ» ብለዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 16/2011በ", "passage_id": "70f6c6e6c5695a4670b36a2f580f32b9" }, { "passage": "የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስፖርት ሲታሰብ አንዱ አቅጣጫ ያመዝናል። የአበበ ቢቂላ፤ እሸቱ ቱራ፣ ቶለሳ ቆቱ፣ ፊጣ ባይሳ፣ ኃይሌ ገብረስላሴ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ጌጤ ዋሚ፣ ገዛኸኝ አበራ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ስለሺ ስህን፣ ጥሩነሽ ዲባባና ቤተሰቧ እንዲሁም የበርካቶች መገኛ፤ የኦሮሚያ ክልል። ክልሉ የረጅም ዓመታት የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ስፖርት የጀርባ አጥንት ስለመሆኑም አያጠያይቅም። አሁንም የኦሊምፒክ፣ የዓለም ሻምፒዮና እንዲሁም የበርካታ ውድድሮች ድምቀት እንደሚሆኑ ተስፋ የሚጣልባቸው አትሌቶች በመፍራት ላይ ይገኛሉ። አትሌቲክስና ክልሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው ለማለት የሚያስደፍረውም ለስፖርቱ ምንጭ በመሆኑ ነው። በህዝቡም ዘንድ እንደ ባህል የሚታየው ስፖርቱ፤ አንድ የኢኮኖሚ ምንጭ እስከመሆን ደርሷል። ይህ ከህዝቡ ጋር ከፍተኛ ትስስር ያለው ስፖርት ለባህላዊ ሁነት ማድመቂያ እንዲሁም መልዕክት ለማስተላለፍ ተመራጭ ነው። በኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አድማሱ ዋጋሪ፤ የኢሬቻ በዓል አከባበር ወቅት ወጣቶች የሩጫ፣ የፈረስ ጉግስ እና ሌሎች ውድድሮችን የማድረግ ባህል እንዳላቸው ያስታውሳሉ። ይህም የሚያሳየው ሩጫ የበዓሉ አንድ አካል እንዲሁም የሩጫ ስፖርት ለኦሮሚያ ህዝብም ባህል መሆኑን ነው። በተለይ በዚህ የሽግግር ወቅት በህዝቦች መካከል ጥርጣሬ የበዛበት እንደመሆኑ፤ በሩጫው የሰላምና አንድነትን መልዕክት ለማስተላለፍ እንዳስፈለገ ያስረዳሉ። ትናንት «እሬቻ የሰላምና የአንድነት ተምሳሌት» በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው የሩጫ ውድድርም የዚህ ማሳያ ነው። ከ150 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል ምክንያት በማድረግ እንዲሁም ስለ እሬቻ በዓል ህዝቡ እንዲያውቅና ባህሉን እንዲረዳ ለማድረግ በአዲስ አበባ በተካሄደው የእሬቻ የሰላም ሩጫ ላይ በሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ተገኝቷል። መነሻና መድረሻውን በመስቀል አደባባይ ያደረገው የጎዳና ላይ ሩጫው፤ 10 ኪሎ ሜትር የሸፈነ ነበር። በሩጫው ላይ እንዲሳተፉ ለሁሉም የአትሌቲክስ ክለቦች ጥሪ የቀረበ ሲሆን፤ ከ500 በላይ የሚሆኑ አትሌቶች ከኦሮሚያ፣ ድሬዳዋ፣ አዲስ አበባ፣ ከደቡብ እንዲሁም ከአማራ ክልል ተካፋይ ሆነዋል። በወንዶች መካከል በተካሄደው ውድድር የስሁር ኮንስትራክሽን አትሌቱ በሪሁን አረጋዊ አሸነፊ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ እንዲሁም የ50ሺ ብር ሽልማቱን ወስዷል። ያለፈውን ዓመት በጉዳት ከወድድር ርቆ የቆየው አትሌቱ፤ ብርቱ ተፎካካሪ አለመኖሩ ለአሸናፊነቱ እንደረዳውም ገልጿል። ኃይለማሪያም ኪሮስ እና ደጀኔ ደበላ ደግሞ ከመብራት ኃይል እና ኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ስፖርት ክለብ ሁለተኛ እና ሦስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል። በሴት አትሌቶች በኩልም ኦብሴ አብደታ ከለገጣፎ ለገዳዲ ክለብ አሸናፊ ሆናለች። በግሏ የተሳተፈችው አትሌት መስታወት ፍቅሩ ሁለተኛ ስትሆን፤ የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲዋ አንቻለም ሃይማኖት ሦስተኛ በመሆን የነሃስ ሜዳሊያቸውን አጥልቃለች። ከአንድ እስከ ሦስት ያለውን ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን ያጠናቀቁ አትሌቶችም ከሜዳሊያው ባሻገር፤ የ50ሺ፣ 30 እና 20ሺ ብር ማበረታቻ ተበርክቶላቸዋል። የኦሮሚያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊና የሩጫው ኦርጋናይዘር አቶ ነጋ ቱጂባ፤ ሩጫው ከታሰበው ሰዓት ዘግይቶ ቢጀመርም በመልካም ሁኔታ መጠናቀቁን ይገልጻሉ። የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ በዓለም ደረጃ የገነባው የአትሌቲክስ ስፖርት፤ ከአበበ ቢቂላ ጀምሮ ያለው ታሪክ በርካታ አትሌቶች የወጡት ከኦሮሚያ ክልል መሆኑን ያሳያል። አትሌቲክስ ከኦሮሞ እሴት ጋር ሊያያዝ የሚችል በመሆኑም፤ ኢሬቻና አትሌቲክስን በማገናኘት ህዝቡ በእኔነት ስሜት እንዲደግፈውና እንዲያሳድገው ያደርጋል። በየዓመቱ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓልም ስፖርታዊ ውድድሩ ይበልጥ ውበት የሚሰጠው ይሆናል። የኦሮሚያ ክልል የኢትዮጵያ አትሌቶች ምንጭ ቢሆንም በዚህ ወቅት ግን ውጤቱ እየቀነሰ መምጣቱ ይታያል። የዚህን ምክንያትም በመገምገም ወደ ቀድሞ ስፍራው ለመመለስ ህዝባዊ መሰረት ማስያዝ የግድ ይሆናል። መሰል ውድድሮች በየዞኑ እና ወረዳው ማካሄድ ቢቻል፤ ህዝቡ ስፖርቱንና አትሌቶችን በባለቤትነት ስሜት በመደገፍ ወደ ምንጭነቱ መመለስ እንደሚቻልም ኃላፊው ይጠቁማሉ። በዓሉም በሰላምና በፍቅር ያለ ኃይማኖትና መሰል ልዩነት የሚያከብር በመሆኑ ይህንን አጠናክሮ መቀጠል ለስፖርቱ የራሱን ሚና የሚጫወት ይሆናል። አሁን በ50ሺ ሰው የተጀመረው ውድድር ወደፊትም ተጠናክሮ ለማስቀጠልና ቁጥሩንም ለማሳደግ ጥረት ይደረጋል። ሩጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እንዲሁም ለተሳታፊዎችም ኃላፊው ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አዲስ ዘመን መስከረም 12/2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "e942551dd0fa34e4e889740649e5d299" }, { "passage": "እኔም አመሰግናለሁ። ክልላችን የበርካታ ስፖርቶች ጸጋ ያለው ሲሆን፤ ዘርፉም እንደየትኛውም የልማት ሥራ በስትራቴጂክ ዕቅድ ይመራል። በአንድ በኩል የክልሉ ህዝብ በስፖርቱ ተጠቃሚ የሚሆንበት ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በማድረግ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ለሃገራዊ ዘርፉ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት በሚያስችል አኳኋን እየተንቀሳቀስንም እንገኛለን። በአጠቃላይ 22\nስፖርቶች ሲዘወተሩ፤ ከዚህ መካከል ከክልሉ ልዩ ባህሪ፣ የአየር ንብረትና የቦታ አቀማመጥ አኳያ ምቹ የሆኑት ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሠራለን። እነዚሀም አትሌቲክስ፣ ውሃ ዋና እና ብስክሌት ሲሆኑ፤ የወጣቱ ተሳትፎም እየጨመረ ነው። እንደ ሃገርም ክልላችን ምርጥ ስፖርተኞችን በማበርከት ሲታወቅ፤ ከዓመት ዓመት ዕድገት በማሳየት ላይም ይገኛል። በስፖርት መሰረተ ልማትም በእያንዳንዱ ቀበሌ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ እንዲኖር፣ በወረዳና ዞኖች መካከለኛ ስታዲየሞች እንዲሁም በትልልቅ ከተሞች ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች እንዲገነቡ ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል። ከትልልቆቹ መካከልም የክልሉ መንግሥት የሚያስገነባው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀውና 50ሺ ተመልካቾችን በመያዝ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የባህር ዳር ስታዲየም ይነሳል። በክቡር ዶክተር ሼህ መሃመድ አሊ አላሙዲ የተገነባውና ከሁለት ዓመት በፊት የተጠናቀቀው የወልዲያ ስታዲየምም እንዲሁ። የመጀመሪያው ነገር ፖሊሲውም የሚጠቁመው ስፖርቱን ህዝባዊ ማድረግ ነው። ከዚህ አንጻርም የተሳካልን ህዝቡ ስፖርቱን እንዲመራ እንዲሁም ሀብት በማሰባሰብና በስፖርቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማድረግ ነው። ለምሳሌ መላው የክልላችን አርሶ አደር በክፍያ ለስፖርቱ አስተዋጽኦ ያበረክታል። የመንግሥት ሠራተኛውም ከደሞዙ በፍቃደኝነት ይከፍላል፤ በእርግጥ አሁን መቀዛቀዝ አለ። እንደ አጠቃላይ ግን ከስፖርቱ ልማት ተጠቃሚ የሚሆነው ህዝቡ ራሱ በመሆኑ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደርጋል። ሌላው የሚያኮራው ተግባር የክልላችን ህዝብ በየትኛውም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚያደርገው ድጋፍ ነው። በዚህ ዓመት በስፖርታዊ ጨዋነት የተሻለ ነገር ታይቷል። በአማራና ትግራይ ክለቦች መካከል በነበረው ችግር በራሳቸው ሜዳ እንዳይጫወቱ መደረጉ የሚታወስ ነው። የፌዴራል ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ስፖርት ኮሚሽን፣ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ስፖርት ቢሮዎች፣ ክለቦች እንዲሁም ደጋፊ ማህበራት በቅንጅት ባደረጉት እንቅስቃሴ የሁለቱ ክልል ክለቦች በየሜዳቸው በጨዋነት ሲጫወቱ ቆይተዋል። በክልላችን የተካሄዱት ጨዋታዎችም አስተማማኝ ጸጥታ ነበር። ይህም በዚህ ዓመት ውጤታማ ከሆንባቸው ሥራዎች መካከል ይጠቀሳል። ክልላችን ለአትሌቲክስ ስፖርት በጣም ምቹ ነው፤ ስለሆነም ልዩ ጸጋ ያላቸውን ስፍራዎች ለይተን ስምንት የሚሆኑ የአትሌቲክስ ማዕከላትን በመገንባት ላይ እንገኛለን። የደብረ ብርሃን፣ ቲሊሊ፣ ደጋ ዳሞት፣ ኮን፣ ጉና፣ ደባርቅ፣…\nማዕከላት ተጠቃሽ ሲሆኑ፤ ተስፋ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች ከፕሮጀክት ተመልምለው ይሠለጥኑበታል። ቀደም ብሎ የተቋቋመው የደብረብርሃን ማዕከል በየዓመቱ 40\nታዳጊዎችን በመቀበል የሚያሰለጥንና ብቃት ያላቸው አትሌቶችን እያፈራ ይገኛል፤ ሌሎቹም ወደዚሁ መስመር እየገቡ ነው። በውሃ ዋና ስፖርትም ጸጋው ባለባቸው አካባቢዎች፣ ለምሳሌ ባህርዳር ዙሪያ፣ ጎንደር እና ኮምቦልቻ አካባቢ ክለቦችን በማቋቋም ምርጥ ስፖርተኞችን የማሳደግ ሥራ እየተከናወነ ነው። ሌላው በክልሉ ትልቅ አቅም ያለው የስፖርት ዓይነት ብስክሌት ነው። በባህር ዳር እንደሚታወቀው ብስክሌት ሳይዝ የሚንቀሳቀስ ወጣት የለም። ይህ ደግሞ ትልቅ ዕድል ነው፤ ከዚህ አኳያም ጥረት የሚባል አንድ ክለብ አለን። በቂ ባይሆንም ሌሎች ክለቦችን ለማቋቋም እሠራን እንገኛለን። ስፖርቱ እንዲዘወተርና የክልሉ መገለጫ እንዲሆንም ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር ላይ ነን። እውነት ነው፤ በክልሉ ትልቅ ጸጋ አለ። ከክልሉም አልፎ ለሃገርም ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ስፖርተኞችን ማፍራት ይቻላል። በመሆኑም በቅድሚያ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እያከናወንን ነው። አሁን አሁን ከከተማ ባለፈ በገጠሩ አካባቢም ህበረተሰቡ ለመጓጓዣነት እየተጠቀመ መሆኑ መልካም ዕድል ነው። በመሆኑም ይህንን መለያው እንዲያደርግ ግንዛቤ እያስጨበጥን ነው። ሌላው ከዚህ ቀደም የተቋቋመውን የጥረት ክለብ የማጠናከር ሥራ ነው። በእርግጥ አሁን አሁን አንዳንድ ጥያቄዎች እየተነሱ በውይይት ላይ ነው ያለነው። ጥረት ከአቅም በላይ እንደሆነበትና ወደ ሌላ የልማት ሥራ መዞር ስላለበት ክለቡን ወደ ሌላ እንዲዞርለት አስታውቋል። እኛም ይህ መሆን እንደሌለበትና ክለቡ የህዝብ በመሆኑ የሚከፈለውን ዋጋ ከፍሎ ይዞ እንዲቀጥል አሳስበናል። ሦስተኛው ሥራችን ደግሞ ቁሳቁስ የማሟላት ነው፤ ዘመናዊ ብስክሌቶች አስፈላጊ በመሆኑ ከዚህ ቀደም ገዝተን ነበር። አሁንም በድጋፍ ከፍተኛ ወጪ አውጥተን ከውጭ ዘመናዊ ብስክሌቶችን አስገብተናል። እነዚህ በቂ ናቸው ማለት አይደለም፤ በቀጣይም የሚመለከታቸውን አካላት በማስተባበር ድጋፉን እንቀጥላለን። የውስጥ ውድድሮችን ለማዘጋጀት እንዲሁም ሃገር አቀፍ ውድድሮች ላይ ለምናደርገው ተሳትፎ ትኩረት እንሰጣለን። በዚህ ሂደትም ምርጥ ስፖርተኞችን የማውጣትና የመለየት እንዲሁም ተሳትፎውን የማሳደግ ስራ እየተከናወነ ነው። በዓመቱ በተካሄዱ ሃገር አቀፍ ተሳትፎዎች ያስመዘገብነው ውጤትም መልካም በመሆኑ ደረጃችንን እንዳሻሻልን ማንሳት ይቻላል። ሃገር አቀፍ ውድድሮች ላይ ለመድረስ ከታች መጀመር አስፈላጊ ቢሆንም፤ በወረዳዎችና ዞኖች የገንዘብ እጥረት ስለሚያ ጋጥም የማይሳተፉባቸው አጋጣሚዎች አሉ። በመሆኑም ማስተካከያ ማድረግ እንደ ሚያስፈልግ ለይተናል። ሌላው በአንዳንድ ስፖርቶች ላይ በሚኖረን የውድድር ተሳትፎ በቂ ስፖርተኞችን አለማሳተፍ ይታያል ይህንንም ማስተካከል ይገባናል። እስከአሁን ያልተፈታውና መንግሥትም ትኩረት ቢሰጠው የምለው ስፖርት ከፍተኛ ሀብት የሚጠይቅ እንደ መሆኑ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ብቻ ማሳደግ አይቻልም። በመሆኑም መንግሥት ዘለቄታዊ መፍትሔና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። የስፖርት ፖሊሲውም መከለስ አለበት። ከ20 ዓመት በላይ የቆየ በመሆኑ አሁን ከደረስንበት ደረጃ አኳያ መከለስ ይኖርበታል። ይዘቱ በዚያን ወቅት መልካም ቢሆንም፤ አሁን ስፖርቱ የደረሰበትን እንዲሁም ሃገሪቷ ያለችበትን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የዕድገት ደረጃ ግምት ውስጥ አስገብቶ በድጋሚ መቀረጽ አለበት። ብዙ ጥረት የሚጠይቀው ሌላው ሥራ አደረጃጀትን የሚመለከት ነው። እኔ ወደዚህ ቦታ ከመጣሁ እንኳ ስፖርቱ አንዴ ራሱን ሲችል ሌላ ጊዜ ከሌላው ጋር ሲለጠፍ ቆይቷል፤ ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም። በእርግጥ አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ሁሉ አደረጃጀት መታየት አለበት፤ ነገር ግን ለውጥ በመጣበት ጊዜ ሁሉ ይህንን ማድረግ ሴክተሩን የሚያሳድግ መስሎ አይሰማኝም። በመሆኑም ወጥበት ኖሮት እንዲቀጥል ማድረግና ትኩረት መስጠት ይገባል። የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በያሉበት ከልሎ ማልማትም ያስፈልጋል፤ ለዚህም አስገዳጅ የህግ ማዕቀፍ ያስፈልጋል። የፍቃደኝነት ሥራ ካደረግነው ረጅም ጊዜ ይወስድብናል፤ እንደ ውሃ እና መብራት ማዘውተሪያ ስፍራዎችም አስገዳጅ ማዕቀፍ ሊኖራቸው ይገባል። ይህንንም በፌዴራል ደረጃ እያነሳን እንገኛለን። የመጀመሪያውና ትኩረት ልንሰጠው ያቀድነው የህዝብ አደረጃጀትን ማጠናከር ነው። ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ ህዝባዊ አደረጃጀቶችን የማጠናከርና ባለቤት ሆነው እንዲመሩት ያስፈልጋል። የማዘውተሪያ ስፍራዎች በስታንዳርዱ መሰረት በሁሉም አካባቢ ህጋዊ ሆነው እንዲለሙና እንዲስፋፉ ማድረግም ሌላኛው ነው። የስፖርት ዘላቂነትን ካሰብን ተተኪዎች መኖር ይገባቸዋል። የፕሮጀክት ስልጠናን አጠናክሮ በመያዝና ውጤታማ በሆነ አኳኋን መምራት ስለሚያስፈልግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንሠራለን። ክለቦች ከሌሉ ስፖርተኛን በተናጥል አንቀሳቅሶ ውጤታማ መሆን ያስቸግራል። በመሆኑም በሁሉም ስፖርት ክለቦችን ለማቋቋም ተቋማትን፣ ባለሀብቶችን፣… ለማሳተፍ ጥረት ይደረጋል። የመጨረሻው ደግሞ ሀብት ማሰባሰብ ነው፤ እንደሚታወቀው ስፖርት ከፍተኛ ሀብት የሚፈልግ ዘርፍ ነው። በመሆኑም ይህንን መሸከም የሚችል ሀብት ማሰባሰብ ትኩረት ሰጥተን የምንሠራው ነው።አዲስ ዘመን ሰኔ 17/2011 ", "passage_id": "4445dba796870b36dd5a52fcd576a6cf" }, { "passage": "የጋራ እሴቶቻችንን በማጠናከርና መቻቻልን መርሁ ያደረገ ኢትዮጵያዊነት ማጎልበት በአንዳንድ አካባቢዎች የሚታየው የፀጥታ ችግር መፍትሄ እንደሆነ ትናንት በአዲስ አበባ በተከበረው 13ኛው የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች ይገልፃሉ፡፡\nከዋዜማው ጀምሮ በተለያዩ ባህላዊ ትርኢቶች የተከበረው የዘንድሮ በዓል የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የእርስ በርስ ግንኙነት ለማጠንከር ጉልህ ሚና እንደነበረውና ብዙ የባህል ልምድ ልውውጥ የተካሄደበት መሆኑም የበዓሉ ታዳሚዎች ያመለክታሉ፡፡\nወጣት ከተማ ፈዮ የኮሌጅ ተማሪ ሲሆን ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የመጣ ነው። «በበዓሉ ላይ በመታደሜ የሌሎች ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ባህል የበለጠ እንዳውቅ አድርጎኛል» በማለት ክብረ በዓሉ ያስገኘለትን በጎ ነገር ይገልጻል፡፡«እኛ ኢትዮጵያውያን በባህል የታደልን ህዝቦች ነን›› የሚለው ተማሪ ከተማ፣እነዚህ በጎ ባህሎቻችን እርስ በርስ በመዋዋስ እና በመጠቀም ግንኙነታችን ማጠንከር እንችላለን ይላል፡፡ በተዋበ ባህላዊ ልብስ በክብረ በዓሉ ላይ የተገኘው ተማሪ ከተማ የብዙ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች አገር መሆን ከሁሉም ጠቃሚ ልምዶችና ባህሎችን በመውሰድ ለማህበረሰባዊ ለውጥ መጠቀም እንደሚቻል ያስረዳል፡፡\nየበዓሉ መከበር ጠቀሜታ ሲያስረዳ፣«እዚህ በቆየሁባቸው ቀናት ብዙ ጓደኞችን አፍርቻለሁ፡፡ እኔ ከመጣሁበት ብሄረሰብ ውጭ ከመጡ ጋር ጥሩ መግባባትን ፈጥሬ ወደ እነሱ እንድሄድ ጋብዘውኛል፤ እኔም ጋብዣቸዋለሁ፡፡ ይሄም የእርስ በርስ ግንኙነታችን አጠንክሮልናል» በማለት ያስረዳል፡፡ኢሳያስ መለሰ የኪነ ጥበብ ባለሙያ ነው። «በዓሉን በዚህ መልኩ በጋራ ማክበር ትክክለኛውን ትውፊት ለማሳየት ትልቅ አጋጣሚ ይፈጥራል» በማለት ጠቀሜታን ይገልጻል፡፡ በዚህ መልክ ባህላችንን ይዘን ቀርበን በጋራ ስንቆም ውበታችን ይጎላል፤ በማለት ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን በራሱ የተለየ ውበት መሆኑን ያስረዳል። ኢሳያስ በሀገሪቱ እየታየ ያለው ዘርፈ ብዙ ለውጥ የሚበረታታ መሆኑንና ብሄር፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአንድነት ለለውጡ ዳር መድረስ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባዋል ይላል፡፡ወይዘሮ የሺ ታመነ ከሀረርጌ አካባቢ በዓሉን ለመታደም የመጡ ናቸው። በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ የሀገራችን ክፍሎች እየታየ ያለው የፀጥታ ችግር በማስመልከት ማህበረሰቡም የራሱን ሰላም በመጠበቁ በኩል ድርሻ ሊወስድ ይገባል ይላሉ፡፡\nየበዓሉ ተሳታፊዎች ሰላም የለውጥ መሰረት መሆኑን ማሳወቅ የሚገባ መሆኑን ያስረዳሉ። «እዚህ የተገኘነው ከተለያየ ማህበረሰብ እንደመሆኑ ለመጣንበት ማህበረሰብ ወካይ ነንና የማህበረሰባችን ጥሩ ገፅታ አጉልተን ማሳየት አለብን። የበዓሉ አላማም የእርስ በርስ ትስስራችንን ማጠንከር ነው» ይላሉ።«በአንዳንድ የሀገራችን ክፍሎች የሚታየው የፀጥታ ችግር ለማስቆምና ሰላም ለማስፈን የሁላችንም ተሳትፎ ወሳኝ ነው።» የሚሉት ወይዘሮ የሺ፤ ሰላምን የሚያደፈርሱ አካላትን ነቅቶ መጠበቅ ይገባል ይላሉ፡፡ ወጣቱ ያለ ምክንያት ምንም ነገር ከማድረግ እንዲቆጠብና ሁሌም ምክንያታዊ ሊሆን ይገባል የሚል ምክርም አላቸው፡፡ድምፃዊ አብረሃም አበበ ከደቡብ ክልል ከከንባታና ጠምባሮ ዞን የመጣ ነው፡፡ኢትዮጵያውያን በጋራ በአንድ አላማ በጋራ ስንቆም ያምርብናል፤ አንድነታችንም ከልዩነታችን ከፍ ያለ መሆኑን ይገልፃል። ሀገራችን በለውጥ ሂደት ላይ በሆነችበትና እኛም ጥሩ ተስፋ በሰነቅንበት ወቅት መከበሩ በዓሉ ልዩ ድባብ እንዲኖረው አድርጎታል፡፡ ስለዚህም ማህበረሰቡ ለውጡ የፈጠረለትን መልካም ዕድል ተጠቅሞ ሀገራዊ ዕድገትና ልማት ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት ይላል፡፡ሰላምን ለማስጠበቅ ዋነኛ ድርሻ መውሰድ የሚገባው ህብረተሰቡ መሆኑን የሚናገረው ድምጻዊ አብረሃም፤ ለሰላሙ መጠበቅ ከሚሰሩ የፀጥታ አካላት ጋር በጋራ መቆም የሁሉም ድርሻ ሊሆን ይገባል፡፡ማህበረሰቡም ችግሮችን ለማቃለል መነጋገርና ውይይትን ባህሉ ሊያደርግ ይገባል የሚለው ድምፃዊ አብረሃም፤ በመነጋገር የማይፈታ ችግር የለም ይላል። «አንዱ ብሄረሰብ የሌላውን ብሄረሰብ ባህል ወግ በማክበር፣ በመጠበቅ፣ የእርስ በርስ ግንኙነትን በማጠንከርና መቻቻልን መርህ በማድረግ አንድ ጠንካራ ሀገር መገንባት ወሳኝ ነው በማለት የሀገራዊ አንድነት ፋይዳውን ይጠቁማል።ወጣት መህቡባ ከአፋር ክልል የመጣች የበዓሉ ታዳሚ ናት፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰሙ ወሬዎችና አንዳንድ አሉታዊ አስተሳሰቦች የዚህ በዓል ተሳታፊ በመሆኑ ከሌሎች የብሄረሰብ ተወካዮች ጋር በነበረኝ ቆይታ ሚዛናዊ አስተሳሰብ እንዲኖረኝ አድርጎኛል ትላለች፡፡\n«ኢትዮጵያዊነት ድምቀት ነው» በማለት ኢትዮጵያዊነት የህብር ቀለማት ጥምረት፤ የመቻቻል ማሳያ መሆኑን ትናገራለች፡፡ በጋራ በመቆም ዘርፈ ብዙ ችግሮቻችንን ማቃለል እንደሚቻል ትገልጻለች፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 30/2011ተገኝ ብሩ ", "passage_id": "8669a3d01c3c82b1df789add658030e3" } ]
2c3394fa3ef603b7625578ff018fceb5
1b470bbcfe41888b22972dc4823e2ac7
የእንቁላል ጨዋታ
 ከሦስት ዓመት በፊት ይሆናል። ወደ ሀዋሳ ለሥራ ጉዳይ ከባልደረቦቼ ጋር ተጉዘን በውቧ የደቡብብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ዋና ከተማ መሽገናል። ከተማዋ እንደዛሬው ጭር ሳትል፤ ፍርሀት ሳይነግስባት፤ የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ አገር ጎብኚዎች የሚጎርፉባት፤ ሁሉም የነፃነት ክንፉን ዘርግቶ የሚንሳፈፍባት ነበረች:: ነዋሪዎቿም ቢሆኑ ኢትዮጵያን የሚመስሉ ውብ ድብልቅ ናቸው። አሁንም ጭርሱኑ እንቅስቃሴ የለም ብዬ ባልታበልም። መንፈሷ መታወኩን ሳልናገር ማለፍ ግን ይከብደኛል። ከያዛት ቆፈን ለመውጣት ዳር ዳር የምትል ይመስለኛል። ነገሩ ግን ወዲህ ነው ንትርኩን ሳላበዛ ወደ ጉዳዬ ልግባ መሰለኝ።በወቅቱ በደቡባዊቷ ፈርጥ የከተምኩት በአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ባለቤትነት የሚዘጋጀውን «የታላቁ ሩጫ በሀዋሳ» የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድርን ለመዘገብ ነበር። ታዲያ በዚያን ጊዜ ነው ለዓመታት ከአእምሮዬ ሊወጣ ያልቻለ አስተማሪ ነገር ያጋጠመኝ። በጊዜው ማረፊያችንን ያደረግነው በከተማዋ በሚገኘው በኃይሌ ሪዞርት ነበር። ኃይሌ ሮጦ ብቻ ሳይሆን አልምቶ አንጀት የሚያርስ መሆኑን ያወኩትም ያኔ ሳይሆን አይቀርም። ገጠመኜም ከዚሁ ጀግና ጋር የሚያያዝ ነው። ቀኑ ቅዳሜ ነው። የጎዳና ላይ ሩጫው የሚካሄደው ደግሞ እሁድ ጠዋት ነበር። ቅዳሜ ምሽት ደግሞ ኢትዮጵያውያንንና የውጭ አገር ዜጎችን ያሳተፈ ከፓስታ ብቻ የሚዘጋጅ ጣፋጭ ምግቦች የሚወራረዱበት ‹‹ፓስታ ፓርቲ›› የመክፈቻ መዝናኛ ዝግጅት ነበር። በምሽቱ ከጣፋጭ ምግቦቹ ውጪ ታዳሚዎች የሚሳተፉበት የተለያዩ ጨዋታዎች ነበሩ:: ከዚህ መካከል የኢትዮጵያ ጀግና ኃይሌ ገብረሥላሴ ተመልካችን እንዲያዝናና ከሌሎች ተሳታፊዎች ጋር ውድድር ማድረግ ነበረበት።ጨዋታው እንዲህ ነው። የተወዳዳሪዎቹን ቁጥር የሚስተካከል እንቁላል እና ማንኪያ ተዘጋጅቷል:: ኃይሌን ጨምሮ ተፎካካሪዎቹ ይሄን እንቁላል በማንኪያው ላይ አድርገው በአፋቸው ይይዛሉ። መነሻው እና መድረሻው በተዘጋጀው ስፍራ እንቁላሉን በማንኪያው ይዘው ቀድመው መድረስ ይኖርባቸዋል:: ኃይሌ እንቁላሉን ይዞ ቀድሞ ገብቶ ውድድሩን አሸንፎ ይሆን? የሚለው የእናንተ ጥያቄ እንደሚሆን አልጠራጠርም። ነገሩ ግን ወዲህ ነው።ኃይሌ ውድድሩ ምን እንደሆነ ሲነገረው። ተሳታፊ እንደማይሆን ተናግሮ የተወዳዳሪዎቹንና የታዳሚውን ወሽመጥ ቆረጠው። ለምን አትሉኝም። የሱ መልስ እጅግ በጣም ቀላል ነበር። ‹‹አንድ ጊዜ በልቶ የማያድር ሕዝብ ባለበት መሀል ተፈጥሬ በእንቁላል አልጫወትም›› በማለት በምግብ መጫወት የኑሮውም፣ የባህሉም ሆነ የእምነቱም ሁኔታ እንደማይፈቅድለት ተናግሮ ታዳሚውንም እጅግ አስደንቆና አስተምሮ ከመድረክ ወረደ።በወቅቱ የተከሰተው ሁኔታ አብዛኛዎቻችንን ያስገረመ ነበር። ከድህነት ውስጥ በበቂ ሁኔታ ባንወጣም፤ የኛን ባህል በማያውቁ የውጭ አገር ዜጎች መሀል በመከበባችን እና ፓስታ ፓርቲ ላይ በመሆናችን አዘጋጆቹም እኛን ሊያዝናኑ፤ እኛም በእንቁላል ልንዝናና ቃንጥቶን ፍፁም አቅላችንን ስተን ነበር። በገጠሩ አካባቢ አድጎ የገጠሯን እናት ልፋት፤ የአርሶ አደሩን አባት ድካም የሚያውቀው ብርቱው ጀግናችን ግን ያለው ሀብት እና ዝና ሳያስተው፤ ብልፅግና ልቡን ሳይሰውረው አሁን ደረቱን ነፍቶ ‹‹እኔ በእንቁላል አልጫወትም›› ሲል አዲስ መንገድ አሳየን።ይሄ ክስተት ላለፉት ሦስት ዓመታት የተለያዩ አጋጣሚዎች በተፈጠሩ ቁጥር በህሊናዬ ሲመላለስ ቆይቷል። ዛሬ ደግሞ በምን አጋጣሚ አስታወስከው ካላችሁ ሌላ አንድ ልብ የሚሰብር አሳዛኝ አጋጣሚን እነግራችኋለሁ። ከሦስት ዓመት በፊት ይህ እውቅ እና አስተዋይ ሰው በእንቁላል መጫወት ትክክል አለመሆኑን በአስገራሚ እይታው እና አንደበቱ ቢነግረኝም ይበልጥ እንዳከብረው ያደረገኝ ገፊ ምክንያት ሰሞኑን ያጋጠመኝ ጉዳይ ነው። ነገሩ እንዲህ ነው…የሥራ ባህሪዬ ሆነና በሁሉም የአገሪቷ ክፍል (ከገጠር እስከ ከተማ) የመዘዋወር እና ከሰዎች ጋር የመገናኘት አጋጣሚዬ ሰፊ ነው። ባሳለፍነው ሳምንትም ወደ ሰሜን ሸዋ ምድር የመጓዝ ዕድሉን አግኝቼ ነበር:: ሸዋ ከሥርዓተ መንግሥት ምስረታ ገድሏ ባሻገር በአሁኑ ወቅት እስከ ሦስተኛ ዲግሪ መመረቂያ ጽሑፍ ለማቅረብ የሚጠቅሙ የምርምር የታሪክ እና ሥነ ጽሑፍ ለኢትዮጵያ፣ ለአፍሪካ እንዲሁም ለዓለም የተረፉ የጥበብና የሥልጣኔ ፊትአውራሪ ሰዎች የፈለቁባት ነች። በተለይ ከግእዝ ወደ አማርኛ በርካታ መጽሐፍትን በመተርጎም፤ ከፊደል ገበታ እስከ ታላላቅ መጽሐፍት በመድረስ ለኢትዮጵያውያን ያበረከቱት ተስፋ ገብረሥላሴ፣ንጉስ ሳህለሥላሴ፣አፄ ምኒልክ እና የታሪክ ተመራማሪው እና ምሁሩ ተክለፃዲቅ መኩሪያ የሚጠቀሱ ናቸው።ታዲያ በሸዋ ምድር ቆይታዬ ለማየት ከቻልኳቸው ቦታዎች መካከል የምኒልክ እና የበርካታ ነገስታት መቀመጫ የነበረው የሚገኝበትን ‹‹አንኮበር ቤተ መንግሥት›› አንዱ ነበር። ግዘፍ እንደነሳው ታሪኩ እና ባለውለታነቱ የተረሳ እና እጅግ የሚያሳዝን ማህበረሰብ ያለበት መሆኑን በስፍራው የተገኘ ብቻ ነው የሚረዳው። ሕዝቡንና አካባቢውን አይቶ አይን ባያነባ እንኳን ልብ ማልቀሱ አይቀሬ ነው። ይህን ጉዳይ የሚያስረዳልኝ ደግሞ ቅዳሜ ቀን ገበያ ወጥታ ያገኘኋት የምስኪኗ እናት መከራ ነበር።ይህቺን እናት በገበያ ውስጥ ስዘዋወር ነው ያገኘኋት። የሥራ ባልደረቦቼ አብረውኝ ነበሩ። ግርግር በበዛበት ስፍራ ከፊት ለፊቷ ብጫቂ ጨርቅ ዘርግታ ከአንዲት ትንሽ ድንጋይ ላይ ቁጢጥ አለች:: ነገረ ሥራዋ ትኩረታችንን ስለሳበው ድርጊቷን መከታተል ጀመርን:: ልትለምን አልነበረም። ከያዘችው ቀረጢት ውስጥ በጥንቃቄ ሁለት ትናንሽ ነገሮችን አውጥታ ከዘረጋችው ጨርቅ ላይ አስቀመጠቻቸው። እንቁላሎች ነበሩ። ሁለት እንቁላሎች። ለዚያውም የሚሸጡ እንቁላሎች:: ይቺ እናት አይኗን ወደ ገበያተኛው እያማተረች ገዢዎችን እየተጠባበቀች ነው።ጠጋ ብዬ ስለሁኔታው አነጋገርኳት። የሚያስ ገርመው ደግሞ እዚህ የገበያ ቦታ ለመድረስ ከ10 ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዛለች። ሁለት እንቁላል ለመሸጥ!! በምታገኘው ገንዘብ ደግሞ ጨው ገዝታ ወደ ልጆቿ ትበራለች። ሌላ አስር ኪሎ ሜትር ተጨማሪ:: ትራንስፖርት የማይታሰብ ነው። ጉዞ በእግር ነው። አዛኙ ጓደኛዬ ኪሱ ያለውን አውጥቶ እጁን ዘረጋላት:: ፊቷ በብርሃን ፈካ። ቢያንስ ለሦስት ሳምንት ገበያ መውጣት አይጠበቅባትም። ኑሮዋ እጅጉን ያሳዝናላ።እኔ ደግሞ በሀሳብ ነጎድኩ። ወደ ሃዋሳ። ኃይሌ ሪዞርት። ኃይሌ እንዲህ ይላል ‹‹እኔ በእንቁላል አልጫወትም!!››      አዲስ ዘመን ጥቅምት 16/2012 ዳግም ከበደ
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=21513
[ { "passage": "ሀሳብ አይግባዎ። ተፈጥሯዊውን ስጋ የሚመስል ነገር ግን ከስጋ ነፃ የሆነ ምርት መጥቷል። ምርቱ የስጋ በርገር ወይም ደግሞ የቋሊማ ተመጋቢዎችን ፍላጎት ያረካል ተብሎ ይታሰባል።\n\n• የምግብ ምርጫዎ ስለማንነትዎ ይናገራል?\n\nአትክልት ተመጋቢዎች ስጋ በጤና ላይ ከሚያስከትለውን ጉዳት ለመዳንና ለአካባቢ ጥበቃ ሲሉ ከስጋ ጋር ተለያይተዋል።\n\nየአትክልት ተመጋቢዎች ምርጫ በምግብ ምርት ዘርፍ ውስጥ ስማቸውን ለተከሉ ድርጅቶች ጥሩ የገበያ እድል ፈጥሯል።\n\nስጋን ተክቶ የመጣው ስጋ መሰል ምርት የትክክለኛው ስጋ መአዛ፣ መልክና ይዘት አለው።\n\n• የአየር ንብረት ለውጥ፤ የት ደረስን? \n\nተፈጥሯዊውን ስጋ ይተካል የተባለው ሰው ሰራሽ ስጋ የተሠራው ከአትክልት ምርቶች ነው። በአትክልት ውስጥ ያሉ ፕሮቲኖች ያሉት ሲሆን፤ ቀይ ስር ተጨምቆ የሚወጣው ፈሳሽ እንደ ደም ሆኖ ጥቅም ላይ ይውላል።\n\nቤተ ሙከራ ውስጥ ሰው ሰራሽ ስጋ ከእንስሳት ህዋስ የሚሠሩ ድርጅቶችም አሉ። ሰው ሰራሽ ስጋው በቅርቡ ገበያ ላይ ይውላል ተብሎም ይጠበቃል።\n\n'ጀስት' የተባለ የአሜሪካ ድርጅት በቤተ ሙከራ የተዘጋጀ የዶሮ ስጋ ምርቱን በዚህ ዓመት መጨረሻ ለሽያጭ ያቀርባል ተብሎ ያጠበቃል።\n\n• በቤታችን ውስጥ ያለ አየር የጤናችን ጠንቅ እንዳይሆን ማድረግ ያለብን ነገሮች \n\nእነዚህ ምርቶች ታሳቢ ያደረጉት አትክልት ተመጋቢዎችን ብቻ ሳይሆን ስጋ የሚበሉ ሰዎችን ጭምርም ነው።\n\nመሰል ምርቶች ገበያ ላይ ከመዋላቸው በፊት ጤናማ ስለመሆናቸው ምርመራ ይደረግባቸዋል። አውሮፓ ውሰጥ የምርምር ሂደቱ እስከ ሁለት ዓመት ሊወስድ ይችላል።\n\nሰው ሰራሽ ስጋ አምራቾች ተመጋቢዎችን ያሳምኑ ይሆን? \n\nብዙዎች ቤተ ሙከራ ውስጥ የሚሠራ ስጋ ለመመገብ ፍቃደኛ አይደሉም። በተቃራኒው የስጋው አሠራር ሂደት በግልጽ ከተነገራቸው ሰው ሰራሽ ስጋ መመገብ የሚሹ ሰዎች አሉ።\n\nሰው ሰራሽ ስጋ ከተፈጥሯዊ ስጋ ጋር ተመሳሳይ ስም ሊኖረው ይገባል ወይ? ሌላው አነጋጋሪ ጉዳይ ነው።\n\n'ካትል አሶሴሽን' የተባለ የአሜሪካ ድርጅት ስጋ የሚለው ቃል የተፈጥሯዊ ስጋ ብቻ መጠሪያ መሆን አለበት ሲል ይከራከራል።\n\n• መጠቀም ያቆምናቸው ስድስት የአካል ክፍሎች \n\nአውሮፓ ውስጥ ሰው ሰራሽ ስጋ ተጠቅመው በሚዘጋጁ ምግቦች በሰው ሰራሹ መካከል የመጠሪያ ልዩነት እንዲኖር የማድርግ እቅድ አለ።\n\nፈረንሳይ ተጠቃሚዎችን ግራ ያጋባሉ ያለቻቸውን የሰው ሰራሽ ስጋ ስያሜዎች ለማገድ ወስናለች።\n\nሰው ሰራሽ ስጋ አምራቾች ምርታቸው የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተለ ላለው ተጽዕኖ መፍትሄ እንደሚሰጥ ያምናሉ።\n\nተመራማሪዎች እንደሚሉት ተፈጥሯዊው ስጋ ለ 'ግሪን ሀውስ' ጋዝ ልቀት ምክንያት ነው። ተመራማሪዎቹ ተፈጥሯዊ ስጋ መመገብ ከሚያስከትለው ተጽእኖ ለመዳን ሰው ሰራሽ ስጋ መመገብን ቢደግፉም፤ ሰው ሰራሽ ስጋ በቤተ ሙከራ ውስጥ ለመሥራት የሚያስፈልገው ሀይል ጥያቄ ያስነሳል።\n\nሰው ሰራሽ ስጋ የአርብቶ አደሮች ሕይወት ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተጽእኖ ሌላው ጥያቄ ነው።\n\n ", "passage_id": "67a8c6e0cd62e2d3aa87e91c187e0037" }, { "passage": "የተፈጥሮ ውበታቸውን በጠበቀ መልኩ ስራ ላይ የምታውላቸው የዛፍ አይነቶችን ከየት ታገኛለህ?ሰዎች ዛፎችን ከመኖሪያ ቤትና ከመስሪያ ቤቶች ቆርጠው ይጥሏቸዋል፡፡ ያጫርቱታል፡፡ የእንጨቶችን ባህሪና ውበት ለይቼ ስለማውቅ በየመንገዱና በየአካባቢው አይኔ እንጨቶችን ፍለጋ ይባዝናል፡፡ የተጣሉ የእንጨት ዝርያዎችን የመበስበስና ያለ አግባብ ወድቀው ከመቅረት የማዳን ስራ ነው የምሰራው፡፡ በእግሬ ስጓዝ እንኳን የወደቀና የሚያምር እንጨት ካየሁ አነሳለሁ፡፡ በተፈጥሮዋቸው ውስጥ የራሳቸውን ባህሪ እፈልጋለሁ፡፡ ሶፋ፣ የመስታወት ፍሬም፣ የወንበር እግሮች፣ ጠረጴዛ የመሳሰሉትን ይገኝበታል፡፡ እንዴት ነው ወደዚህ ሙያ የገባኸው?ውስጤ ያለውን ሞያ አውጥቼ እንድጠቀም የረዳኝ እግዚአብሔር ነው፡፡ ከዚህ ስራ ጋር የምተዋወቅበት ምክንያት አልነበረም፡፡ በችግር ምክንያት ቤተሰቦቼን ለመርዳት ብዬ የቀን ስራ ተቀጥሬ በመስራት ነው ነገሮች እዚህ ደረጃ የደረሱት፡፡ ለቤተሰቤ ሁለተኛ ልጅ ነኝ፡፡ ገና 8ኛ ክፍል እያለሁ በ14 ዓመቴ ነው እየተማርኩ ቤተሰቤን ለመርዳት ወደ ቀን ስራ ገባሁት፡፡ በቀን 3 ብር ከ50 ሳንቲም አገኝ ነበረ፡፡ እኔ እና የአሁን ሞያዬ በዚህ ሁኔታ ተጣጥመን እዚህ ደረሰን እንጂ የእኔ ፍላጐት ቦክሰኛ መሆን ነበር፡፡ ኑሮው ግን አልተመቸም… እንኳን ተደባድቤበት… እናም ኑሮ ግራ ሲያጋባኝ ከጓደኞቼ ተደብቄ የ3 ብር ከ50 ሳንቲም ስራዬን ጀመርኩ፡፡ መቼም ይደርስብኝ የነበረው ጫና የሚገርም ነው፡፡ ጓደኞቼ “አንተ ኩሊ፣ ከእኛ ጋር እየተማርክ እንዴት የቀን ስራ ትሠራለህ” እያሉ ያሸማቅቁኝ ነበር፡፡ ግን ለዛሬ ስኬት ያበቃኝ ትናንት ያገኘሁትን ሥራ መስራቴ ነው፡፡ የቀን ስራ ስትል… ምን አይነት ነው?የሰው ቤት አጥር እሰራ ነበር - በቆርቆሮ በእንጨት፡፡ ሲሚንቶ እሸከም ነበር፡፡ ድንጋይ ከመኪና አወርዳለሁ፡፡ ይህን እየሠራሁ ትምህርቴን ጨረስኩ፡፡ ከዛም ተግባረድ ገባሁ፡፡ ከተግባረዕድ በኋላ ነው ወደ እንጨት ስራ የገባኸው?አዎ! ለእንጨት ውበት ያለኝ ፍቅርና አድናቆት የተለየ ነው፡፡ እንጨት ሲማገድ፣ ያለ አግባብ ሲጐሳቆል ደስ አይለኝም፡፡ በጣም አዝናለሁ፡፡ የማይረሳኝ ገጠመኝ አለ፡፡ አንዲት እናት እንጀራ ይጋግራሉ፤ በእንጨት፡፡ ቆሜ ስመለከታቸው በጣም የሚያምረውን እንጨት አንስተው ይማግዱታል፡፡ የእንጨቱ ቅርጽ አፉን ይከፍትና መንታ ምላስ ያለው እባብ ይመስል ነበር፡፡ ስጡኝ ብላቸው ‹‹እየጋገርኩት ያለው ሊጥ ይበላሽ? እንጀራ እየጋገርኩ መሰለኝ›› ብለው ተቆጡ፡፡ ልክፈል ብላቸውም እንኳን እምቢ አሉኝ፡፡ ‹‹ምን ትፈላሰፍብኛለህ!›› ሲሉኝ ዞር አልኩ፡፡ ያንን የመሰለ የእንጨት ውበት ከየትም ላመጣ እንደማልችል ስለማውቅ እንባ ነው የተናነቀኝ፡፡ ውበት ያላቸው የእንጨት ዝርያዎች በተለይ ከየት ታገኛለህ? ከአዲስ አበባ ነው ወይስ…አዲስ አበባ አዲስ አበባ ደግሞ ምን የሚታይ እንጨት አለ፡፡ አርሲ ነገሌ ብትሄጂ የዛፎቹ ተፈጥሮ ያስደንቅሻል፡፡ ጉብጥብጥ ያሉና የተለያዩ አይነት ቅርፆች ያላቸው ዛፎች አሉ፡፡ የሰው ቅርጽ የሚመስሉ አሉ፡፡ ወንድና ሴት፣ ትናንሽ ልጆች፣ የወንድና የሴት ብልት የሚመሳስሉ ሁሉ አሉ፡፡ እዛ አካባቢ ዝግባ፣ ቀረሮ፣ ባህር ዛፍ፣ ግራር የመሳሰሉ ዛፎች አሉ፡፡ አቤት ሲያሳዝንሽ… ደን ልማት ብትይ የአካባቢው ማህበረሰብ እንደ ጉድ ነው አልኩሽ የሚጨፈጭፋቸው፡፡ እንጨቶቹ እንዲሁ ወድቀው ስታያቸው እምባሽ ይመጣል፡፡ ባክነው እንዳይቀሩ እኔ ወደ ህዝብ እይታ አመጣቸዋለሁ፡፡ ደብረብርሃን፣ አክሱም፣ ዝዋይ፣ ጅማ፣ አካባቢ ያሉ እንጨቶችም ድንቅ ጥበብና አፈጣጠር ያላቸው ናቸው፡፡ እኔ በእንጨት ፍቅር ወድቄያለሁ፡፡ የአገር ባህል ቤቶችንም ትሰራለህ?ሌላው ህይወቴ የተመሠረተው በጐጆ ቤቶች ጥበብና ውበት ነው፡፡ በሳር፣ በፊላ፣ በቀርከሃ ጐጆ ቤቶች እሰራለሁ፡፡ በመዝናኛ ቦታዎችና በተለይ በአዲስ አበባ ጥሩ ገቢና መኖሪያ ያላቸው ሰዎች ግቢ ውስጥ ምርጥ ጐጆዎችን ሰርቻለሁ፡፡ እስቲ ከሰራሃቸው መዝናኛ ስፍራዎች ጥቀስልኝ? ያንተ ጐጆዎች የት የት ይገኛሉ?የአፍሪካ ቫኬሽን ክለብ፣ ቦራቲ ሎጂ፣ የሳቫና ሎጅ፣ በአዋሳ የሌዊ ሪዞርት የሚጠቀሱ ሲሆን በላንጋኖ ዙሪያ የሚገኙ ባለሀብቶች ገዝተው የሚያከራይዋቸውና ከነቤተሰቦቻቸው የሚዝናኑበትን ጐጆዎች ዲዛይኑን ከማውጣት ጀምሮ እስከመገንባት ድረስ ሰርቻለሁ፡፡ በአዲስ አበባ ሃያት፣ ሲኤምሲ፣ ቦሌ፣ ፒያሳ እና ሌሎች አካባቢዎች በግለሰቦች መኖሪያ ቤት ውስጥ ጐጆዎችን እንዲሁም ባንኮኒና ባንኮኒ ዙሪያ የሚቀመጡ ወንበሮችን በእንጨት አሳምሬ ሰርቻለሁ፡፡ ሰዎች በአሁኑ ጊዜ ጊቢያቸው ውስጥ ወይንም በሳሎናቸው ውስጥ ጐጆ ቤት እንዲሰራላቸው ይፈልጋሉ፡፡ ለምን መሰለሽ ጐጆ ቤት ሙቀት ሆነ ቅዝቃዜ የአየር ንብረቱን ከመቆጣጠሩ በተጨማሪ የአገር ቤት ስሜት ይፈጥራል፡፡ ከሚያብረቀርቅርና ከተፈጥሮ ውጭ ከሆነ ጌጣጌጥ የበለጠ ያምራል፡፡ ብቻ ደስታ ይሰጥሻል፡፡ የገጠር ድባብ ይፈጥርልሻል፡፡ ይሄው እንግዲህ 18 ዓመት ሙሉ ህይወቴ ሆኗል፡፡ ጐጆ ቤት ለመስራት ወጪው ውድ ነው ይባላል?ተመጣጣኝ ነው፡፡ ውድም ቢሆን እኮ እድሜ ይቀጥላል፡፡ እንዴት መሰለሽ… ጐጆ ቤት ውስጥ ዘና ብሎ መጽሐፉ ማንበብ፣ እረፍት ማድረግ፣ ቡና መጠጣት… በጐጆ ቤቶች ውስጥ የምትተነፍሽው አየር ሁሉ ደስ የሚልና የሚያነቃቃ ነው… የተረጋጋ መንፈስ ይሰጥሻል፡፡ አይንሽን አይሰለቸውም፡፡ በእርግጥ ሳሩና ቀርከሃው ውድ ነው፡፡ እኔ የማስበው እንዴት ተውቦ ይሰራል የሚለውን እንጂ የሚያስወጣኝንና የማተርፈውን አይደለም፡፡ ደግሞ ከየት ነው የምታመጣው ብለሽ ገበያዬን እንዳትዘጊብኝ… ከሩቅ አካባቢ ነው (ሳቅ)አንዱ ጎጆ በምን ያህል ብር ይሠራል?በርግጥ እንደ ሁኔታው ቢለያይም በአማካይ ልነግርሽ እችላለሁ፡፡ ሶስት በአራት የሆነ ጎጆ ስልሳ ሺህ ብር ይሠራል፡፡የጐጆ ቤት ዲዛይኑ የራስህ ነው ወይስ ሰዎች እንዲህ ሥራልን ይሉሃል?ሰዎች ፍላጐታቸውን ይነግሩኛል፡፡ እኔ ደግሞ የዲዛይኑን ውበት በአዕምሮዬ ስዬ እንደዚህ ይሁን እላቸዋለሁ፡፡ እነሱም ይሰሙኛል፡፡ ቦታውን አያለሁ… የሚያመቸውን ዲዛይን መርጬ በሚያምር መልኩ አስውበዋለሁ፡፡እንዴት ነው… ሰው ጐጆ ቤት ይፈልጋል?ዛሬ ዛሬ በጣም ብዙ ጥያቄዎች አሉ፡፡ ሰው መኖሪያ ቤቱን በጐጆዎችና በተፈጥሮ እንጨቶች ማስጌጥ ይፈልጋል፡፡ ግን ያን ያህል ጥቅሙ የገባው አለ ማለቱም ይቸግራል፡፡ ባለሃብቶች አካባቢ ግን ፍላጐት አለ፡፡ ከውጭ የሚመጡ ሰዎች መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ጐጆ ቤትና የእንጨት ስራ ውጤቶች እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ፤ ያሠራሉም፡፡ የውጭ ዜጐችም የመኖርያ ቤታቸውን በር፣ መቀመጫ፣ ጠረጴዛ… የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶችን ወዘተ… በእንጨት ውጤቶች ያሰራሉ፡፡ጎጆዎች ስያሜ አላቸው?አዎ! የሲዳሞ ባህላዊ ጐጆ የሚሰራው በቀርከሃ ሲሆን ውስጣዊ ክፍሉ ግርግዳው ዙሪያውን በወፊጮ (በሰኔል) ይሠራል፡፡የወላይታና የጎጃም በሳር ይሠራል፡፡ የኦሮሚያ አካባቢ በፊላ ይሠራል፡፡ በስርህ ስንት ሰራተኞች ይተዳደራሉ?እንደ ስራው ሁኔታ በየጊዜው ቢለያይም እስከ 50 ጊዜያዊ ሠራተኞችን እቀጥራለሁ፡፡ በስሬ እስከ 15 ባለሞያዎች አሉኝ፡፡የአንተ መኖሪያ ቤትስ… በዚህ መልኩ የተሰራ ነው? ቤቴን በዚህ መልኩ ለመስራት ዲዛይኑን ነድፌ አስቀምጫለሁ፡፡ ግን ሃዘን ላይ ስለነበርኩ እስካሁን አልተሰራም፡፡ አሁን ተረጋግቻለሁ፡፡ በቅርቡ ቤቴን በጐጆና በእንጨት ስራ ውጤቶች አስውቤ በአጭር ጊዜ ውስጥ እጋብዝሻለሁ፡፡ ቤተሰብ መስርተሃል?አዎ ሁለት ልጆች አሉኝ፡፡ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ ባለቤቴ የዛሬ ሦስት ዓመት አካባቢ በካንሰር በሽታ አርፋለች፡፡ ራሴ ያስተማርኳቸው እህትና ወንድሞቼ ከእኔ ጋር ይኖራሉ፡፡ በባለቤቴ ሀዘን ምክንያት አንዳንድ ያሰብኳቸውንም ስራዎች አጓትቻቸው ነበር፡፡ እንግዲህ በቅርቡ የራሴን ቤት በባህላዊ መልኩ ከመገንባት በተጨማሪ በዝዋይ የራሴን የእንጨት ቤት እየከፈትኩ ነው፡፡ ስራዬ ተንቀሳቃሽ በመሆኑ እዚህ አዲስ አበባም የእንጨት ቤት አለኝ፡፡ በዚህ ሁኔታ ነው ያለሁት፡፡ ገቢህ ምን ያህል ነው?ገንዘቡን ተይው ግን እግዚአብሔር ይመስገን ገቢዬ ከፍተኛ ነው፡፡ ጥሩ ገንዘብ ሰርቻለሁ፤ የተሻለ ጊዜ ላይ ነኝ ብልሽ ይበቃል፡፡ ዛሬም እንግዲህ ቀን ከሌሊት እየሰራሁ ነው፡፡ በኮንስትራክሽን ስራም እድገት እያሳየሁ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን ሁሉም መልካም ነው፡፡", "passage_id": "26ca38c9433c1803f569c129b139dcc2" }, { "passage": " መኪና ለማሽከርከር የሚያበቃ ፍቃድ ለማግኘት የበርካታ ሀገራት አሽከርካሪዎች በትንሹ እድሜያቸው 18 እና ከዛ በላይ እንዲሆን ህጎች ያስገድዳሉ፡፡ ይህም ህግ አንድ አሽከርካሪ ለማሽከርከር በሚገባው እድሜና የእውቀት ደረጃ ላይ ሳይደርስ የማሽከርከሪያ ፍቃድ ቢሰጠው አደጋ ሊያስከትል ይችላል ከሚል ስጋት የወጣ ነው ብሎ መገመት ይቻላል፡፡ አንዳንዴ ግን ህጉ የማሽከርከር ብቃት የማይፈቅድላቸው ገና በለጋ እድሜያቸው አውቶሞቢሎችን፣ አውቶብሶችን ከፍ ሲልም ከባድ ተሽከርካሪዎችን ሳይቀር በማሽከርከር አጀብ ያሰኙ አይጠፉም፡፡ ይሁንና እነዚህ ታዳጊዎች ግፋ ቢል ከአስር ዓመት ትንሽ የዘለሉና በመጠኑም ቢሆን ስለመኪና ያውቃሉ ተብለው የሚገመቱ ናቸው፡፡ ገና የአምስት ዓመት ልደታቸውን ሳያከብሩ መኪና የማሽከርከር ብቃት ላይ የደረሱ ህፃናትን ማየት ግን ትንሽ ግራ ያጋ ባል፤ እንግዳ የሆነ ነገር ነው፡፡ ከሰሞኑ ስካይ ኒውስ በድረ ገፁ ለንባብ ያበቃው ፅሁፍም ይህንኑ ያረጋግጣል፡፡ ፅሁፉ እንዳመለከተው፤ ልጆች ከረ ሜላን ጨምሮ ልዩ ልዩ ጣፋጭ ነገሮች ይወ ዳሉ፡፡ ጣፋጭ ነገር እንዲገዛላቸው ደግሞ ወላጆቻቸውን አብዝተው ይወተውታሉ፡፡ እንዲህ ወትውተው ታዲያ ፍላጎታቸውን ካልሞላ ጣፋጭ ነገሯን ለማግኘት የራሳ ቸውን ርምጃ ለመውሰድ ይገደዳሉ። ጥቂት የማይባሉት ከቤተሰብ ሳንቲም በመስረቅ በራሳቸው ጣፋጭ ነገሮች የሚገዙ ሲሆን ፣ አንዳንዶች ደግሞ ወደ ጣፋጭ መሸጫ ሱቆች በመሄድ ጣፋጮቹን እንዲሰጧቸው ባለሱቆቹን ይለምናሉ፡፡ አሜሪካዊው የአራት አመቱ ህፃን ጣፋጭ ነገሮችን ለማ ግኘት የወሰደው ርምጃ ግን ትንሽ የከፋ ነው፡፡ እንደ ፅሁፉ ከሆነ ጅና ስዌንሰን የተሰኘው አሜሪካዊ የአራት ዓመት ህፃን የአያቱን የመኪና ቁልፍ ይሰርቃል፡፡ ግቢ ውስጥ ወደቆመችው አውቶሞቢልም ይጠጋል። የመኪናዋን በር ከፍቶ ሞተር በማስነሳት በጠራራ ፀሃይ መኪናዋን እያከነፈ ጣፋጭ ነገር አገኝበታለሁ ብሎ ወዳሰበበት ቦታ ይሄዳል፡፡ አንድ ጣፋጭ መሸጫ መደብር ወደሚገኝበት የነዳጅ ማደያ ሱቅም ደርሶ መኪናዋን ያቆማታል። ህፃኑ በመንገድ ላይ አውቶሞቢሏን ሲያሽከረክር በአንድም ሰው ላይ ጉዳት ያደረሰ ባይሆንም፣ በመኪናዋ አካል ላይና በመንገድ ዳር በነበሩ የመልእክት ማስቀመጫ ሳጥኖች ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል፡፡ ህጻኑ ሹፌር ከቤቱ ግቢ ያለውን የአትክልት ስፍራ ሲያቋርጥ ከዛፍ ቅርንጫፍ ጋር በመታከኩ በመኪናው የፊት አካል ላይም የመሰርጎድ ምልክት ታይቷል፡፡ ከዛ ውጪ ግን ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስበት መኪናዋን ማቆም ችሏል ሲል ፅሁፉ ገልጿል፡፡አዲስ ዘመን ሰኔ 11/2011 ", "passage_id": "cc61ea49e2d9cf9a71e8827f91592b01" }, { "passage": "ህፃናቱ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እያወሩ መንገዳቸውን ተያይዘውታል። ጨዋታቸው ትኩረቴን ስለሳበው ተከተልኳቸው። ስለተሰጣቸው የትምህርት ቤት የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም)፣ የትምህርት ቁሳቁስና የምገባ ፕሮግራም ነበር የሚጫወቱት። አዲስ ነገር እንደሆነባቸው ከጨዋታቸው በመረዳቴ ጆሮዬን ሰጠሁ። ወንዱ ልጅ የክፍል ጓደኛውን ስም እየጠራ ዩኒፎርሙ የተቀዳደደ እንደነበር ይነግራታል። ምሳም ከእነርሱ ጋር ሲበላ አይቶት እንደማያውቅ ያጫውታታል። ሴቷም በተመሳሳይ በክፍሏ ውስጥ ሴቶችም ወንዶችም ያረጀ የደንብ ልብስ እንደሚለብሱና አንዳንዴ ምሳቸውን እንደሚያካፍሏቸው ነበር ያወራችለት።በዚህ የትምህርት ዘመን ሁሉም የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች አዲስ ዩኒፎርም ስለተሰጣቸውና ምግብም በአንድ ላይ እንዲመገቡ መደረጉ በመንገድ ላይ ሲጨዋወቱ ያገኘኋቸው ተማሪ ዙፋን ንጉሤ እና ባባ ጌታቸው እንዳስደሰታቸው ነበር የነገሩኝ። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኘው አባይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚማሩት ተማሪ ዙፋን እና ባባ የአራተኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ፣ የደንብ ልብስ የሚገዙላቸው ወላጆቻቸው እንደነበሩና ምሳም ቋጥረው እንደሚልኳቸው ነግረውኛል። ዘንድሮ ግን አዲስ ነገር በማየታቸው ተደስተዋል። በተለይ ያስደሰታቸው ሁሉም ተማሪ በእኩል አዲስ ልብስ መልበሱ ነው። የደንብ ልብሳቸውንም ወደውታል። ትምህርት ገና ባለመጀመሩ ስለምገባ ፕሮግራሙ ሊነግሩኝ አልቻሉም። ያነጋገርኳቸው አንዳንድ ወላጆችም የተማሪዎቹን ደስታ ይጋራሉ። የሶስት ልጆች እናት የሆኑት ወይዘሮ መንበረ ወንድሙ ባለቤታቸውን በሞት ካጡ ወዲህ በአነስተኛ የንግድ ሥራ ልጆቻቸውን ማስተዳደር እንደከበዳቸው ይናገራሉ። ዘንድሮ አንደኛ ክፍል ላስመዘገቡት ልጃቸው የደንብ ልብስና የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት የሶስተኛ ክፍል ተማሪ ለሆነው ልጃቸውም ደብተርና እስክሪፕቶ መግዛት ይጠበቅባቸው ነበር። መንግሥት ይህን በማሟላቱ አንድ የኑሮ ጫና እንደተቃለለላቸው ይናገራሉ። መጠነኛም ቢሆን ለማስመዝገቢያ ከሚከፍሉት ወጭ ጋር ከባድ እንደነበር ይገልጻሉ። የምገባ ፕሮግራም መኖሩም በሌሊት ተነስቶ ምሳ መቋጠርና ምን እንደሚቋጥሩ ከመጨነቅ እንደሚያድናቸው ተስፋ አድርገዋል። የአራት ልጆች እናት የሆኑት መምህርት የማታ ከበደ ተማሪዎች ያሉባቸውን ችግሮች ከርሳቸው በላይ የሚያውቅ እንደሌለ ይናገራሉ። እርሳቸውም ቢሆኑ የወር ገቢ ይኑራቸው እንጂ የአራት ልጆቻቸውን ፍላጎት ለማሟላት እንዳልቻሉ ይገልጻሉ። መቀየሪያ የደንብ ልብስ ማሟላት ለእርሳቸው ቅንጦት ነው። የቤት ኪራይ፣ ቀለብና የተለያዩ ወጭዎች ያረጀውን የደንብ ልብስ ለልጆቻቸው ለመቀየር እንኳን ችግር ሆኖባቸዋል። መንግሥት በጣም ዝቅተኛውን ህብረተሰብ ብቻ ሳይሆን እንደርሳቸው አነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ የሆነውንም የመንግሥት ሰራተኛ እንደረዳ ያስረዳሉ። አስተያየት ሰጭዎቹ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያደረገው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ፣ የደንብ ልብስ የማሟላትና የምገባ ፕሮግራም በሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች በተመሳሳይ ቢፈጸም ሀገራዊ ፋይዳው የጎላ ይሆናል። በአዲስ አበባ ከተማ ላይ የሚስተዋለው የተማሪዎች ችግር በተመሳሳይ እዛም እንደሚኖር በመጠቆም ክልሎች ተሞክሮውን ቀምረው በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን በየአካባቢያቸው ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል። በአዲስ አበባ ከተማ የተደረገውን በጎ ነገር የሰሙ የተለያዩ አካባቢ ተማሪዎች እነርሱም ተጠቃሚ ቢሆኑ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት\nቤቶች መሻሻል ፕሮግራም\nዳይሬክቶሬት ክፍል ውስጥ\nየመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት\nመሻሻል ባለሙያ እና የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ተጠሪ አቶ አሸናፊ ጌታቸው የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት ባለመቻልና ምግብ በማጣት ከትምህርት ገበታ የሚቀሩ ልጆች እንዳይኖሩ እንዲሁም ባለፉት ተሞክሮዎች የነበሩትን ትምህርት የማቋረጥ ምጣኔ፣ በትምህርት የመዝለቅንና ሌሎችንም የውጤት ትንተና በማካሄድ ተነሳሽነቱን እንደወሰደ ይገምታሉ። በትምህርት ዘርፉ ከሚያጋጥሙት\nማነቆዎች ምግብ የማያገኙ\nተማሪዎች ችግር አንዱ\nእንደሆነና ችግሩንም ለመቋቋም\nከመንግሥት አቅም በላይ\nእንደሆነ ያወሱት አቶ\nአሸናፊ ከዚህ አንጻር\nበከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ\nአካላት ሲደረጉ የነበሩ\nድጋፎችን አቀናጅቶ ወጥ\nበማድረግ የወሰደውን ተነሳሽነት\nያደንቃሉ። ክልሎችም ትምህርት\nወስደው በተመሳሳይ እንዲተገብሩ\nለማስቻል የከተማ አስተዳደሩ\nየተጠቀማቸውን ዘዴዎች ብቻ ሳይሆን፣ ድጋፉ በአመቱ መጨረሻ በትምህርት ውጤት ላይ ያስገኘውም መሻሻል አብሮ መተንተን ይኖርበታል ብለዋል። አቶ አሸናፊ እንዳስረዱት በተለይ የምገባ ፕሮግራሙ የምግብ ፍላጎትን ብቻ ማሟላት ሳይሆን ህጻናቱ የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ ማድረግ መሆን ይኖርበታል። የምገባ ሥርአቱ እንዴት መመራት እንዳለበት፣ ተጠያቂነትንም የሚያሰፍን፣ በአጠቃላይ በፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲደገፍ በሀገር ደረጃ ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቷል። ረቂቁ በአመራር ደረጃ ባሉ አካላት እጅ ይገኛል። ጸድቆ ሥራ ላይ ከዋለ የምገባ ፕሮግራም መፍትሄ ያገኛል። የትምህርት ቁሳቁስ የማሟላቱ ተግባር ደግሞ እራሱን የቻለ በመሆኑ በፖሊሲው አልተካተተም። የሀገር ኢኮኖሚ አቅም ግምት ውስጥ እንደሚገባ ይናገራሉ። ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ምግብ አጠር በሆኑና በአርብቶ አደሩ አካባቢዎች የምገባ ፕሮግራም እየተካሄደ መሆኑን የሚጠቅሱት አቶ አሸናፊ ክልሎችን በማስተባበር ቁጥራቸው ስምንት መቶ ሺህ የሚጠጋ ተማሪዎች ተጠቃሚ እንደሆኑ አመልክተዋል። በ2010 ዓ.ም በሚኒስቴሩ 289ሚሊየን ብር በጀት ተመድቦ እንደየ ክልሎቹ ተጨባጭ ሁኔታ መከፋፈሉንም አስታውሰዋል። ባለፈው በጀት አመት ላይም በተለይ ከፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ለተፈናቀሉ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፉ በከፍተኛ ሁኔታ መከናወኑን ገልጸዋል። ለትምህርት ዘርፉ የሚደረገው ድጋፍ የትምህርት ጥራትንም ለማሻሻል ፋይዳው የጎላ እንደሆነና በትምህርት ልማቱ ላይ ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ የማገዙ ተግባር ሊጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል።አዲስ ዘመን መስከረም 22/2012 ለምለም መንግሥቱ ", "passage_id": "da1cd3b7a7fac45931c465002352af12" }, { "passage": "ሰዎች በስራና ሌሎች ጉዳዮች በሚጠመዱበት በዚህ ወቅት ምግብን አብስሎና አዘጋጅቶ መመገብ አስቸጋሪ መሆኑ ይታወቃል። በተለይ በከተሞች አካባቢ ኑሮው በውጥረት የተሞላ እንደመሆኑ የተዘጋጁና መሰረታዊ የሆኑ ፍጆታዎችን ጭምር ከገበያ መግዛት በእኛም ሃገር ይሁን በሌላው ዓለም የተለመደ ነው። በቀላሉ ወደ ገበያ አዳራሾች በመሄድ ማብሰል የማያስፈልጋቸውን ምግቦችና መጠጦች በመሸመት መጠቀምም አሁን ላለንበት የአኗኗር ሁኔታ አማራጭ ሆኗል። የታሸጉ ምግቦችን በብዛት መጠቀም ጉዳቱ\nበሂደት የሚያይል መሆኑ በባለሙያዎች ይነገር እንጂ፤ በርካቶች ግን ይጠቀሙታል። ክልከላው የመነጨው ምግቡ ጣዕሙን እንደያዘ ለረጅም ጊዜ ለማቆየት ሲባል ኬሚካሎች ስለሚጨመሩበት እንደሆነም ይነገራል። በተለይ በማሸጊያው ላይ የሚለጠፈው የምግቡን አሊያም የመጠጡን የቆይታ ጊዜ ሳያረጋግጡ መግዛት በጤና ላይ ከባድ እክል ሊያደርስም ይችላል። ይህ\nበባለሙያዎች ዘንድ ይነገር እንጂ አንዳንድ ተጠቃሚዎች ግን «ካላየሁ አላምንም» የሚል ቁማር በህይወታቸው ይጫወታሉ። በእንዲህ ዓይነት ቁማር (ጀብድ) ከሚሳተፉት መካከል አንዱ የሆነው የአሜሪካዋ ሜሪላንድ ነዋሪ ከሰሞኑ መነጋገሪያ ሆኗል። ስኮት ናሽ የተባለው ግለሰብ «የቆይታ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ምግቦች መመገብ እንደሚባለው ለጉዳት ይዳርጋል?» የሚለውን ማውጠንጠን የጀመረው ከሶስት ዓመታት በፊት መሆኑን የኦዲቲ ሴንትራል ድረገጽ ዘገባ ያስነብባል። አስደናቂው ነገርም፤ ሃሳቡን በተግባር አስደግፎ የአፈታሪክ መሰሉ ንግርት ባለቤት ለመሆንም የመሞከሪያ አይጦችን ሳይሆን ህይወቱን ነበር በማስያዣነት ማቅረቡ ነው። ለተግባራዊነቱም በቅድሚያ ከአንድ የገበያ ማዕከል ያረጀ የዕቃ መደርደሪያ ያገኘውንና ተረስቶ ከገበያ ላይ ቆይታ ጊዜው ስድስት ወራትን ያሳለፈ እሽግ የረጋ ወተት በመጠጣት ሙከራወን ጀመረ። የወተቱ ጣዕም መልካም የሚባል አይሁን እንጂ ለህመምም ሆነ ለከፋው ሞት እንዳላጋለጠው አረጋገጠ። በዚህም የታሸጉ ምግቦችን አምራች ድርጅቶች ለምን የቆይታ ጊዜውን በእሽጉ ላይ ይጽፋሉ የሚል ጥርጣሬ አዘል ጥያቄ ማንሳት ጀመረ። ትዝብቱንም «ግልጽ አይደለም፤ የገበያ ላይ የቆይታ ጊዜ ምን ማለት ነው? ከዚህ እስከዚህ ባለው ጊዜ ተጠቀሙ ማለት ትክክል አለመሆኑን ተገንዝቤያለሁ። እንዲያውም ግራ ሊያጋቡን ስለፈለጉ ብቻ ነው ይህንን የሚሉት» ሲል ይገልጻል። እርሱ ይህንን ይበል እንጂ፤ ዕሽግ ምግቦች እና መጠጦች ግን የተመረቱበት እንዲሁም ለምን ያህል ጊዜ መቆየት እንደሚችሉ ማሳሰቢያ መስጠታቸው አስፈላጊ ከመሆኑም ባሻገር ከምርት ጥራት መገለጫዎች መካከል አንዱ ነው። እንደ ጨው፣ የህጻናት ንጽህና መጠበቂያዎችና ሌሎች በቆይታ ሊበላሹ ከሚችሉ ምርቶች በቀር። ስኮት ናሽ ግን ከመጀመሪያ ሙከራው በተረዳው መሰረት ከራሱ አልፎ ላለፈው አንድ ዓመት ቤተሰቦቹንም ጭምር ከገበያ ላይ የቆይታ ጊዜያቸው ሳምንታትና ወራትን ያሳለፉ ስጋ፣ ክሬም እና መሰል ምግቦችን ሲመገቡ መቆየታቸውን ዘገባው ተመላክቷል። በማቀዝቀዣ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ተረስቶ በቆየ የገበታ ቅቤ ምግባቸውን ቢያበስሉም ቤተሰቡ ላይ የደረሰ አንዳችም እክል እንደሌለም ተረጋግጧል። ናሽ በሙከራው ይህንን ያረጋግጥ እንጂ ለረጅም ጊዜ መቆየት በማይችሉ ምግቦች ላይ ግን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ሳይጠቁም አላለፈም። ምግቡ ጠረን ከፈጠረ አሊያም ተፈጥሮአዊ ጣዕሙን ከቀየረ አለመጠቀም አማራጭ እንደሌለውም ያምናል። ከዚህ ባለፈ ግን አምራቾች ተጠቃሚዎች ላይ በሚፈጥሩት ማስፈራሪያ ወደኋላ ማለት እንደሌለባቸውም ያሳስባል። እንዲያውም አምራቾች በጊዜ የገደቡትን ምርት ሻጮችና ተጠቃሚዎች ሲያስወግዷቸው አምራቾቹ ወደ ጥቅም እንደሚቀይሩትም ነው የሚጠቁመው። በማብራሪያውም «የሚበላሹ እና በጤና ላይ ጉዳት የሚያደርሱ የምግብ ዓይነቶች ይኖራሉ፤ አብዛኛዎቹ ግን ፍርሃትን የሚፈጥሩ ብቻ ናቸው» ይላል። ግለሰቡ ይህንን የሙከራ ውጤት በግል ድረ- ገጹ ለዘመናት የቆዩ በጠርሙስና ቆርቆሮ የታሸጉ ምግቦችን ሲጠቀም ለተከታዮቹ ያሳያል። ነገር ግን ተጠቃሚዎች ምቾት የሚነሳቸውን ነገር እንዳይጠቀሙ ከማሳሰብ ወደኋላ አይልም። የእርሱን የሙከራ ውጤት ሙሉ ለሙሉ መቀበል አዳጋች ቢሆንም፤ በእርሱና በቤተሰቡ ህይወት መወራረዱን ድፍረት ወይስ ምን እንበለው? አዲስ ዘመን ሰኔ 24/2011 ", "passage_id": "2bbcb58263148bc5ff642b4b1747292d" } ]
ca5d9ca8e529cd2e2a33f69178d1c0f1
c98eee6b0d2c19f95d55f5bb4e0c9c4f
«እኛ» በ «እኔ» ተተክቶ ይሆን?
 ሰው እራሱን ታዝቦ ያውቃል? መቼም እራሴን ታዝቤያለሁ የሚል ሰው ካለ ቀን በቀን ሰውነቱን የሚታጠብ ሰው መሆን አለበት። ምክንያቱም ቀን በቀን ሰውነቱን ሲታጠብ መወፈሩን፣ መቅጠኑን፣ መቅላቱንና መጠቆሩን ስለሚመለከት ይመስለኛል። ነገር ግን ሰዎች እራቸውን ማለቴ ውስጣቸው ታዝበውት ያውቁ ይሆን? ብዬ አስባለሁ….. ምነው እራስህን ታዝበህ ታውቃለህ? ካላችሁ….አላውቅም ነው መልሴ….ለምን ብትሉ…..እራስን መታዘብ እኮ እራስ ማስጠፋት የሚያደርስ ወቀሳ አለዋ!!መቼም ሰው ስንባል ትዝብት…..ምናምን በጣም ይመቸናል። በተለይ ደግሰን፣ ታመንና በሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ሰዎች ሲቀሩ «ታዝቤሀለሁ» እንላለን። ሕዝብ መሪውን ሲመርጥ ወይም ተወካዩን ሲመርጥ ታዛቢ ያስቀምጣል… (ታዛቢ ሲባል ቁጭ ብሎ ድምፅ ሲሰጥና ሲቆጠር የሚያይ ነው)። በሌላም መንገድ ስናጠፋ…ወይ ጥሩ ስንሰራ የሚታዘበን ሰው አናጣም አይደል…።እስቲ አንዳንድ ሁኔታዎችን እንታዘብ….:: መቼም ርዕሱን አይታችሁ ምን ላወራ እንዳሰብኩ ገምታችኋል? በአሁኑ ወቅት የሚያወራና የሚታዘብ ሰው ከመብዛቱ «እኛነት» ጠፍቶ «እኔ» የሚለው አባባል በአንቀፅ ለብቻው ተከልሎ የመገንጠል ጥያቄ አንስቷል። በአገሪቱ የሞላነው ሰዎች የማናውቀውን የምንነቅፍ፣ በድህነት ውስጥ ሆነን እኔ እበልጥ የምንባባልና ስብሰባና መንገድ መዝጋት ሥራችን ከሆነ ሰነባብቷል።ሰላም ያስጠብቃሉ ተብሎ የተመደቡ ፖሊሶች ቀኑን ሙሉ ስብሰባ እየተቀመጡ በተገላቢጦሽ ሕዝቡ ነው የሚጠብቃቸው አሉ…«አሉ» ነው….። ድንበር ጠባቂ ወታደሮቹም ከድንበር ይልቅ የውስጥ የውስጥ ችግሮችን ሲፈቱ መዋል ዋነኛ ሥራቸው የሆነ ይመስላል፤ ከአገር ግለሰብ ይበልጣል ብለው ሊሆን ይችላል….። እኛ ደግሞ ጥቅም በሌላቸው ሀሳቦች ተከፋፍለንና ተቧድነን መደባደብ ይዘናል….ከየት እንዳመጣነው የማናውቀውን መሬት የኔ ነው…..ውጣ…ውጡ…..ማለት ደመወዝ የሌለው ሥራችን ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል። ድህነት እና ድርቅ ተጋብተው አገሪቱን መውጫና መግቢያ አሳጥተዋት ባለበት ወቅት እኛ ደግሞ በየመንገዱ መኪና እያስቆምን መዝረፍ፣ እህል ማፍሰስ እና እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ ጀብደኝነት ሆኖ ያሸላልመናል። የአንዱ ጉዳት ለሌላኛችን ደስታ ከመሆን አልፎ ርዕዮት ዓለም ሆኖም እያወዛገበም መጥቷል……። እኛ ባለፈ ታሪክ አሁንም ድረስ የምንናቆር ጉዶች ሆነናል… እኮ።በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ሠራተኞች አገልግሎት ከመስጠት ይልቅ ቁጭ ብለው በማህበራዊ ሚድያ በመቧደናቸው ዋና ሥራቸው የሆነውን ሕዝብን ማገልገል አቁመዋል። በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቢሮዎች የፖለቲካ መድረክ ከመሆን አልፈው የአንድ ግለሰብ ሃሳብ ወደ ማራመጃነት አድገዋል። ‹‹ለመንግሥት ሥራ አትልፋ ግን ከወንበርህ አትጥፋ» የምትለዋን አባባል ሙሉ ለሙሉ የሚያሟሉ ሠራተኞችም በየዓመቱ ምርጥ ፈፃሚ እየተባሉ ይሸለማሉ..።(ፈፃሚዎቹ «ከእኛ» አስተሳሰብ ወደ «እኔ» ልጠቀም አስተሳሰብ በመሻገራቸው መሸለማቸውን ልብ በሉ)። ወጣቱ በአገር ጉዳይ ከመከራከርና ከመግባባት ይልቅ በውጭ እግር ኳስ መደባደብን አማራጭ አድርጎ መያዙ በአገር ጉዳይ አያገባኝም መንፈስ ውስጥ ከቶታል..። ይህም ብቻ አይደለም፤ አያድርገውና አገሪቱ በጠላት ብትወረር እንደድሮው ዘምቶ የሚዋጋ ያለ አይመስለኝም… ለምን ብትሉ አሁን ያለነው ሰዎች እኮ «እኔ» ጋር ካልደረሰ ምን አገባኝ ብለን ጥቅልል ብለን የምንተኛ ነን…..ምን እሱ ብቻ አንዳንዶቻችንማ ለጠላት አግዘን ሳንዋጋም እንቀራለን?….። ይህ ዓመት ከገባ ሁለተኛው ወር እየተገባደደም አይደል…. በነዚህ ወራት ውስጥ ብዙ ሁነቶች ተከናውነዋል….በተለይ የድጋፍ፣ የበዓልና የመንገድ መዝጋት ሰልፎች መቼም አይዘነጉም..። የመንገድ መዝጋትን ስናነሳ ያለፈው ሳምንት መንገድ የመዝጋት አባዜያችን ምን ላይ እንደደረሰ ማሳያ ነው። በተለያዩ ከተሞች መንገዶችን በድንጋይ በመዝጋት የአገሪቱን እቅስቃሴዎች ለማገድ የተደረገው ሙከራ ዛሬም ከዚህ በሽታ አለመውጣታችንን የሚያሳይ ነው። ሌላው ደግሞ በመንግሥት ድጋፍ ሰልፎች ላይ የተፎካካሪ ፓርቲ አርማዎች ማየት እየተለመደ መምጣቱ ነው። በተገላቢጦሽ የመንግሥት አርማዎችና የአገሪቱን ሰንደቅ አላማ መያዝ የሚያስደበድብ ወንጀል ሆኗል። መጨረሻውን ያሳምረው እንጂ ወደፊትማ አንድ ግለሰብ ሲደብረው ወይ ሲደሰት በአገር አቀፍ ደረጃ ይከበር ሳይባል አይቀርም..። ሕዝባችን ለምን ወደ ኋላ ተመልሶ ማሰብ ፈለገ ብዬ ወዳጄን ስጠይቀው ምን አለኝ መሰላችሁ «ካለፈው ተምሮ የወደፊቱን ከማስተካከል ይልቅ….ከወደፊቱ በመማር የኋላውን ለማስተካከል እየጣረ ስለሆነ ነው» ብሎ መለሰልኝ….ሳስበው ትክክል ነው..። ለምን ካላችሁ በመገናኛ ብዙኃን ይሁን በግለሰቦች እየተወራ የሚገኘውን ያለፈ ታሪክ ከመማርያነት ይልቅ ታሪኩን ለማስተካከል እየተደረገ ያለውን ትግል ካየሁ በኋላ ነው። ታድያ መቼ ነው የምንለወጠው? መቼ ነው የሰለጠነ ማህበረሰብ የምንፈጥረው? መቼ ነው ያደገ አገር የምንሆነው? ቢባል ….መቼም ይሆናል መልሱ። ምክንያቱም «እኛ»ን አስወግደን «እኔ»ን በመምረጣችን ነዋ።                                                                                                              አዲስ ዘመን ጥቅምት 17/2012 መርድ ክፍሉ
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=21524
[ { "passage": " አበው ሲተርቱ «የቀበጡ ዕለት ሞት አይገኝም» ይላሉ። እውነት ነው፤ የሚያስከትለውና የሚሆነውን ሳያስተውሉና ሳይረዱ ወደ አንድ ነገር ዘው ማለት መጨረሻው መጥፎ መሆኑ አይቀሬ ነው። ብዙዎች ጀግና ለመባል፣ ታዋቂ ለመሆን፣ እንደሚችሉ ለማሳየት፣ በውርርድ አሊያም በሌሎች ምክንያቶች ያለ ጥንቃቄ አንዳች ተግባር ይከውናሉ። ሳያጣሩ የጀመሩት ነገር ስኬታማ ካልሆነም «ቀበጥ» ያሰኛል፤ በእኛ ዘንድ። በመጀመሪያ የጀብድ ለመስራት ብታቅድም መጨረሻዋ ጩኸት እና ስቃይ የሆነን የአንዲት ሴት\nታሪክ\nከሰሞኑ\nኦዲቲ\nሴንትራል\nበድረገጹ\nእንደሚከተለው\nአስነብቧል።\nቻይናዊቷ\nወጣት\nበተንቀሳቃሽ\nምስሎች\nየተለያዩ\nእንቅስቃሴዎችን\nበማድረግ\nበማህበራዊ\nድረገጾች\nበመለጠፍ\nትታወቃለች።\nመጠሪያ\nስሟም\n«ሲሳይድ ገርል ሊትል ሰቨን» የሚሰኝ ሲሆን፤ በዚሁ ተንቀሳቃሽ ምስሏም ጥቂት ተከታዮችን ማፍራት ችላለች። ታዲያ ከዕለታት በአንዱ ቀን ወጣቷ ስትቀብጥ አደገኛ የሆነ ነገር ለመስራት ታስባለች። የምትከውነው ነገር የሚሳካላት ከሆነም የበርካቶችን ትኩረት በመሳብ ተከታዮቿን ለማበራከት እንዲሁም ታዋቂ ለመሆን እንደሚያግዛትም እምነቷ ነበር። ያሰበችውም ምስሏን እየቀረጸች አንድን የባህር እንስሳ በሕይወት እንዳለ መብላት ነው። ለዚህ እንዲሆናት የመረጠችው የባህር እንስሳ ደግሞ «ኦክቶፐስ» በሚል ስያሜው የሚታወቀውን ዓሣ\nነበር።\nዝግጅቷን አጠናቃ ተንቀሳቃሽ ምስሉ እንደጀመረም ወጣቷ ባለ ብዙ እግሩን ፍጥረት በእጇ በመያዝ ወደ\nአፏ\nታስጠጋዋለች።\nበቅጽበት\nውስጥ\nግን\nነገሮች\nተለዋወጡ፤\nዓሣው\nበእግሮቹ\nየአንድ\nጎን\nጉንጯን\nበቁጥጥሩ\nውስጥ\nአስገባ።\nወጣቷም\nድንጋጤ\nሳይታይባት\nለማስለቀቅ\nሙከራ\nማድረግ\nጀመረች።\nእንዲያውም\n«ተመልከቱ ምን\nያህል\nአስቸጋሪ\nእንደሆነ» እያለች ገለጻ ታደርግ ነበር፤ ዓሣው ግን\nፍንክች\nሊል\nአልቻለም።\nእየቆየም\nይበልጥ\nጉንጮቿ\nላይ\nበመለጠፍ\nህመም\nአስከተለባት፤\nመቋቋም\nያልቻለችው\nወጣትም\nመጮህ\nጀመረች።\n«ማስለቀቅ አልቻልኩም፤ በጣም ያማል» እያለች በመጮህ ከዓሣው ጋር የምታደርገው ግብ\nግብም\nአንድ\nጉንጯን\nየሚያሳጣት\nይመስል\nነበር።\nበመጨረሻም\nዓሣውን\nከፊቷ\nማላቀቅ\nብትችልም\nጉንጯ\nላይ\nጥቂት\nጉዳት\nማድረሱ\nአልቀረም።\nበእጇ\nእንደያዘችውም\n«ፊቴን አበላሽቶታል፤ ሆኖም በእቅዴ መሠረት በሚቀጥለው ቪዲዮ የምበላው ይሆናል» ብላለች ለተከታዮቿ። ይህ የባህር ውስጥ ፍጥረት በርካታ እግሮች ያሉት ሲሆን፤ እግሮቹን ከመዋኘት ባሻገር ራሱን ከአደጋ ለመጠበቅም እንደሚጠቀምባቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ለማሽተት፣ ነገሮችን ለመንካት እንዲሁም ለሌሎች ተግባራትም እግሮቹን ይገለገላል። ወጣቷ ያሰበችው ተሳክቶ ኦክቶፐሱን በሕይወት እንዳለ መብላት ባትችልም በደረሰባት ነገር ግን ታዋቂ መሆኗ አልቀረም። ተከታዮቿ ተንቀሳቃሽ ምስሉን በመጋራት በመላው ቻይና ያሰራጩት ሲሆን፤ ይህንን ተከትሎም በአውሮፓ እና\nመላው\nዓለም\nሊዳረስ\nበመቻሉ\nዝናን\nአትርፋለች።\nበርካቶች ግን ተንቀሳቃሽ ምስሉን በመመልከት በሚሰጡት ግብረ መልስ እየተሳለቁባት እንደሚገኝም ነው ኦዲቲ ሴንትራል የጠቆመው። አንድ አስተያየት ሰጪ «ይገባታል፤ ኦክቶፐሱን ልትበላው እንደሞከረችው ነው የበላት» ሲል፤ ሌላኛው ደግሞ «እኔ ኦክቶፐሱን ብሆንና ከእነ ሕይወቴ ልትበላኝ ብትሞክር፤ ተመሳሳይ ነገር አደርግባት ነበር» ብሏል።አዲስ ዘመን ግንቦት 5/2011 ", "passage_id": "67b2d312be0e704875d0c5e18b890208" }, { "passage": "ኢትዮጵያውያን በምን እንታወቃለን የተባለ እንደሆነ ከዓለም እንደቀደመ በምናምነው ስልጣኔ ብቻ አይደለም፡፡ የእኛ በሆኑ ሰዋዊ ሀብቶችም ጭምር ነው፡፡ ለምሳሌ ትህትና፣ ለሰብአዊ ፍጡር የሚሰጥ አክብሮት፣ በማንነት ኩራትና ክብር እንዲሁም ታዛዥነት የኢትዮጵያዊ መገለጫዎች ሆነው ይጠቀሳሉ፡፡ አሁንስ? አሁንማ ሁሉም ነገር ውድ በሆነበት ጊዜ ይኸው እነዚህም ውድ ሆነውብናል፡፡ነገሩን እንደልብ አንጠልጣይ ፊልም ግነት አበዛሁበት መሰለኝ፡፡ እሺ ሳላጋንን፤ «ታዛዥነት ወዴት ገባች?» የሚል መጽሐፍ ይዘጋጅ ይሆን? በጣም ውድ ከሆኑና እየጠፉብን ካሉ ሀብቶቻችን መካከል መታዘዝ አንዱ ይመስለኛል። በአገራችን ያለውን ሁኔታ እያንዳንዱን ስናይ መነሻውም አለመታዘዝ ነው፡፡ አንዱ ጅብ ሌላው ውሻ ሆኖ፤ መንገዱን ባለመታዘዝ እየቀደዱ መሄድ ብቻ፡፡ይሄ ሁሉ ለአገሩ የማይታዘዝ ሰው ግን ቤቱ ገብቶ ልጆቹ እንዲታዘዙት ይፈልጋል? ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስብሰባ ስም የሚወጣው ወጪ አስደንጋጭ እየሆነ መምጣቱንና እንዳላቆመ ተዘግቦ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ስብሰባ ቀንሱ፤ ደንበኛ እናንተን ብሎ መጥቶ በስብሰባ ሰበብ እንዳያጣችሁ፤ ከተሰበሰባችሁም በእረፍት ቀን አድርጉት ሲባሉ፤ ለካ «በአንድ አፍ!» ብለዋል፡፡ከዛ ቅዳሜና እሁድ «ዊኬንድ»ን ከአዲስ አበባ ወጣ ብለው፤ አዳማ ላይ መሰብሰብ፡፡ «ለምን?» አጋጣሚውን ለመጠቀምና አገር ለመጎብኘት፤ የአገር ውስጥ ቱሪዝምን ከፍ ለማድረግ ማለት ነው። የሆነው ሆኖ እንደተቋምም አለመታዘዝ እንዳለ ተገልጾልኛል፡፡ ነገሬ ለምን ከከተማ ተወጣ ሳይሆን፤ በዚህ አካሄድ የአንድ ለአምስት ሳምንታዊ ግምገማ የሚባለው የስብሰባ ዓይነትም ከከተማ ወጣ ተብሎ ይከናወን በሚል ሰበብ፤ ጉዞው እለታዊ እንዳይሆን በመስጋት ነው፡፡ጥሩ! መዋዕለ ነዋይን ከከተማ ወጣ ብሎ ማፍሰስ ተገቢ ነው፡፡ እንግዲህ ወይ ለብቻው በጀት መመደብ ነዋ! አስታውሳለሁ ከዓመት ወይም ከሁለት ዓመት በፊት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች አንዳንድ አላስፈላጊ ወጪዎችን እንዲቀንሱ ተብሎ የኮፍያ፣ ካላንደር ወዘተ የመሳሰሉ የህትመት ወጪዎች እንዲሁም ድግሶች እንዲቀሩ ተብሎ ነበር፡፡ ይህን ባዩ ደግሞ ገንዘብና ኢኮኖሚውን የሚከታተለው ሚኒስቴር ነው፡፡\nተቋማቱ ለዚህ ትዕዛዝ ታዛዥ ነበሩ ወይ? አልነበሩም፡፡ በእርግጥ በጣም ቆጣቢ ይሁኑና፤ እንደእኛ መሥሪያ ቤት በአሥራ ዘጠኝ ሰማንያዎቹ መጨረሻ የተቋማቸውን ዓርማ ይዞ በታተመ ማስታወሻ ደብተር ይጠቀሙ እያልኩኝ አይደለም፡፡ ግን ቢያንስ በጥቂቱ መታዘዝ ጥሩ ነበር፡፡ጭራሽ ስብሰባ ቀንሱ ሲባል ወጪ መጨመር? ጉድ!\nበብዙ እንቅስቃሴዬ መገናኛ የሚሉትንና አንድ ወዳጄ ‹‹መጠፋፊያ እንጂ መገናኛ ሊሆን አይችልም!›› የሚለውን ሰፈር ሳልረግጥ አላልፍም፡፡ እውነቱን ነው! ብዛታችን ቁልጭ ብሎ የሚታየው እዚህ አይደለም እንዴ? ታድያ በዚህ መንገድ ትልልቅ ሰዎች፤ የሚገራው እንደሚፈልግ እንደ ትንሽ ልጅ ሲሆኑ ሳይ ብስጭት እላለሁ፡፡ ይህን ‹በጎ ፈቃደኛ የመንገድ ትራፊኮች› ይናገሩት፡፡ጠዋት ቀድመው የሚወጡትና ጸባያችንን አውቀው ሳይሰለቹ የሚያስተናግዱት እነዚህ ወጣቶች ስንቱን አይተዋል? እንዴት ነፍስ ያወቀ ሰው፤ «መኪና ይበላሃል! አሁን የመኪኖች ተራ ነው፤ ጥቂት ታግሰህ ቁምና ታልፋለህ» ሲባል፤ አሻፈረኝ ይላል? በመስመር ሂዱ፣ ወደዳር አትውጡ፣ እያያችሁ ተሻገሩ፣ ተረጋጉ፣ ስትሻገሩ ዜብራውን የባለስልጣን ቢሮ ምንጣፍ እንደረገጠ ሰው አትጠንቀቁለትና ራመድ በሉ… ይላሉ አስተናባሪዎች፤ ሰሚ ግን የለም፡፡ታዘቡን! ራሳችንን ታዘቡ! መሥሪያ ቤት ቢሄዱ ቁጭ ብሎ እስክርቢቶ እየበሉ የሻይ ሰዓት ለመጠበቅ ነው፤ ከፍ ካለ ለመሰብሰብና ፊርማ ሳይነሳ ለመድረስ፤ ወዲህ ደግሞ ቆም ብለው ከወዳጅ ጋር «እገሌ ፖስት ያደረገውን አየሽ? እንትና ያለውን ሰማሽ?» ሲባባሉ እልፍ የሚለውን ሰዓት ማንም ልብ አይልም። መንገድ ላይ ግን ሯጭ ነን፡፡ ሰዓት እንደረፈደበት፤ ጊዜውን በአግባብ እንደሚጠቀም ሰው «አሁን ደግሞ እኛ እንለፍ እንጂ ምንድን ነው፤ ሰዓት ገደላችሁብንኮ!» ይላል፤ መንገድ አስተናባሪውን እየተቆጣ፡፡ሌላው ቀርቶ ቅጣት እንኳ አይመልሰንም፡፡ እንደልጅ መቆጣትና ተዉ ማለት አንድ ነገር ነው፡፡ መንገዱ ስርዓት እንዲኖረው የሚደክሙት በጎ ፈቃደኛ ትራፊኮች ዱላ ይዘው ‹ዋ!› እያሉ ቢያስፈራሩ እንኳ ሰዉ የሚታዘዝ አይመስለኝም፡፡ ትልቅ ሰው ግን ድሮም እንዲህ ያስቸግራል!?\nበቀደም በኢትዮጵያ ሆቴል በኩል ሳልፍ ‹‹ዝርዝር ነው?›› አለኝ አንድ ወጣት፡፡ ‹‹እናንተ! አላችሁ እንዴ?›› አልኩት…በልቤ፤ ራሴን በአሉታ ነቅንቄለት እያለፍኩ፡፡ አንደኛ ምን ሆኖ ነው እኔን በዝርዝር የጠረጠረኝ? ዝርዝር ፈላጊ እመስላለሁ? ነው ወይስ አስዘርዛሪዎች እንደእኔ ዓይነት ሰው ልከው ነው የሚያዘረዝሩት? የሚለው ጥያቄ ተፈጠረብኝ፡፡ሁለተኛ ደግሞ ድፍረታቸው ገረመኝ፡፡ እንዴት ሰው በቅጣት አይመለስም? ይህን «እንቢ ባይነት» አርበኞች አገርን ለጠላት አንሰጥም ያሉ ጊዜ ያሳዩት ነው፡፡ «ብትገድሉንም ንቅንቅ አንልም፤ አገራችንን ለባንዳና ጠላት አንተውም» ብለው እስከመጨረሻው ታግለውና ሞተው አገር አትርፈዋል፡፡ እነዚህ ወንድሞችና እህቶቻችን ደግሞ ገንዘብ ለማትረፍ «እንቢ» ብለዋል፡፡አሁን የገባኝ ታዛዥነት የሚባል ኢትዮጵያዊና ሰዋዊ ሀብታችን መቀበሩ አልያም መሰረቁ ነው፡፡ የሚገርመው ደግሞ ልጆች ጋር ሳይጠፋ አዋቂዎች ጋር ነው ድራሹ የሌለው፡፡ መንገድ ላይ ተረጋጋ ሲባል፤ ያውም ለራሱ ጥቅም አልሰማ ያለ ጎልማሳ፤ አውቶቡስ ተሳፍሮ ወጣት ልጅ ለትልቅ ሰው ከወንበሩ ካልተነሳ ቁጣው ለጉድ ነው፡፡ ነገሩን አልኩኝ እንጂ በእርግጥ፤ እሾህን በእሾህ ብሎ የማይታዘዝን ባለመታዘዝ መቅጣት ልክ አይደለም፡፡\nግን ትልቅ ሰዎች ምን ነካችሁ ማለት ፈልጌ ነው፡፡ አንድ ሰው ነፍስ ካወቀና ራሱን መግዛት የሚችልበት ደረጃ ከደረሰ፤ ትልቅ ሰው ይባላል፡፡ እና እነዚህ ሰዎች ብርቅዬ ሊሆኑብን ይሆን? አሁን ስለመታዘዝ ለልጅ እንጂ ለትልቅ ሰው የሚነገር መስሎን ያውቃል? ድንቅ የሚለው ግን ረባሽና አስቸጋሪው ትልቅ ሰው መሆኑ ነው፡፡ ይሄኔ ነው ልጅነት ንፍቅ የሚለው፡፡ ሰላም!አዲስ ዘመን ጥር26/2011", "passage_id": "223d5326bf719c41d9c4c667363cf26a" }, { "passage": "እኩለ ቀን ነው ፤ አማራጭ ስለሌለኝ አናት በምትበሳ ፀሐይ መሀል አንድ ወዳጄን ለማግኘት እየተጓዝኩ ነው። እኔ የምለው? ለጸሐይ ቀርበን ነው ወይስ እሷ ወደ እኛ ቀርባ ? ሀይሏ ከመክበዱ የተነሳ ሰውነት የሚያዝል ፣ሃሳብ የሚያስረሳ ነው ብል ማጋነን አይሆንም ብቻ ይህን ሁሉ ውርጅብኝ ተቋቁሜ አይደርሱ የለ የቀጠርኩትን ሰው ወደማገኝበት ቦታ ደረስኩ። በአካባቢው ወደሚገኝ ካፌ ገብቼ አረፍ አልኩ። ብዙም ሳልቆይ አንዲት መልከ መልካም ወጣት ወደ እኔ ቀርባ ምን እንደምፈልግ ጠየቀችኝ። ብዙም ማሰብ ሳያስፈልገኝ ‹‹ውሃ ታመጭልኝ›› እርሷም ቃጠሎዬ ገብቷታል መሰል ለዛውም የቀዘቀዘ አቀረበችልኝ። ጠጣሁት፤ ነብሴ ተመለሰች። ዋናው ነገሬ እንኳን ስለ ፀሐይዋ ማውጋት አልነበረም። እግረ መንገዴን ያስተዋልኩትን እንዲሁ ለመንገር\nያክል እንጂ! የዛሬው ቁምነገሬ ይህን ይመስላል… ለረጅም ጊዜ ተለያይተን ከነበረው ወዳጄ ጋር በቀጠሮ ሰዓት ተገናኝተናል። ከአጭር\nሰላምታ በኋላም ሊያማክረኝ ወደ መጣበት ጉዳይ … እንዲያው ሊያማክረኝ አልኩ እንጂ ያጋጠመውን ሊነግረኝ ወደፈለገው ሃሳብ በቀጥታ\nገብተን መጨዋወት ጀመርን፡፡ ‹‹እኔ የምልህ›› ብሎ ወጉን ሲጀምር በአይኔ ተከትልኩት፤ ቀጠለና ‹‹ውሸት ለካ የእውነት ድምቀቷ\nናት!›› የሚል ጭውውቱን ሲጀምር፤ በተዝናኖት ከተቀመጥኩበት እግሬን፣ እjyንና ቀልቤን እየሰበሰብኩ የወዳጄ አፍ አቅራቢያ ተጠጋሁ፤\nቀጠል አድርጎ ‹‹ባለፈው የሽርክና ስራ ለመስራት አብሬያቸው ጥምረት የመሰረትነውን ልጆች ታወቃቸዋለህ አይደል?›› ሲል ጥያቄውን\nአስከተለ። አንገቴን በአዎንታ እየነቀነኩ እንደማውቃቸው ገለፅኩለት። ‹‹ታዲያ ከሶስታችን መካከል አንዱ ይህንን የስራ ጥምረት አልወደደው\nነበር›› በማለት በዚህም ምክንያት ሊበትናቸው ፣ ጠቅላላ የስራ ግንኙነታቸውን ሊያጠፋው ያላደረው ነገር ያልፈነቀለው ድንጋይ እንዳልነበር\nአረዳኝ…። ‹‹ይህንን\nሰይጣናዊ ምግባሩን ለመከወን ያልተፈጠረ የሃሰት ስንቁን ይዞ ወጣ›› ወጉን እየሰማሁ መሆኔን ለማስረዳት ‹‹እሺ›› ብዬ ቀጣዩን\nበጉጉት እየጠበኩ… ‹‹የማህበራችንን ስም ለማጥፋት ዕቃ የምናቀርብላቸውም የተለያዩ ድርጅቶች እና ከዚህ በኋላ ይሄዳሉ ብሎ ወደሚያስባቸው\nድርጅቶች ጋር በመሄድ የሚሰሩት እንዲያ ነው… እንዲህ ነው … የእነሱ ስራ ችግር አለበት›› እያለ ብቻ ብዙ ስማቸውን እንዳጠፋ\nበንዴት አጫወተኝ። በዚህ ሁሉ የልጁን ወሬ የሚሰሙ ድርጅቶች ለማጣራት በሚል ወደ ምርት ማምረቻችን መምጣታቸውን ገለፀልኝ። ታዲያ\nየሰሙት እና ያዩት ነገር የተቃረነ በመሆኑ ከዚህ በፊት አይተውት በማያውቁት ሁኔታ በደንበኛ ብዛት እንደተጨናነቁ ነገረኝ። ታዘው\nየማያውቁትን ያክል ከአቅማችን በላይ ትዕዛዝ መቀበላቸውን በሃሴት ነገረኝ። ብቻ ምን አለፋችሁ ሊያዋርዳቸው አስቦ ቆንጆ ማስታወቂያ\nሰርቶ እንዳከበራቸው ነገረኝ። የሚገርመው በቅርቡ መኪና ሊገዙ ነው ! በውሸት ሊያጠፋቸው አስቦ መጥቶ ይልቁን አበለጸጋቸው፡፡ በዚህ\nየወዳጄ ጨዋታ መሃል ነው ያነበብኩትን የማስቀመጥበትን አድባር ቦርሳዬን (ፎልደር) ውስጥ ያለ አንድ ጽሑፍ ትዝ ያለኝ።የህዝብ ስነ\nቃሎችን በማደራጀት እንደመማሪያ የሚያቀርብ “ተረት ተረት” በሚል ስሙ የሚጠራው የማህበራዊ የትስስር ገጽ ያገኘሁትን ነው፤ አወጣሁት፤\nተረቱ ሳነበው ወዳጄ ከነገረኝ ጉዳይ ጋር ተዛምዶ አየሁት ፤ ስነ ቃሉ እንዲህ ነው… እሳት፣ ውሃ፣ እውነትና ሃሰት ጓደኞች ነበሩ።ነገር\nግን ሃሰት በዚህ ጥምረት ደስተኛ ስላልነበረ አንድነታቸውን ማበላሸት ፈልጎ እንዲህ አለ “ለምን ወደ አንድ ስፍራ ተጉዘን እያንዳንዳችን\nየራሳችንን ግዛት አንመሰርትም? ስለዚህ ተነስተን አብረን እንጓዝ፡፡”ሁሉም\nበሃሳቡ ተስማምተው ሲሄዱ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሀሰት ወደ ውሃ ጠጋ ብሎ “እሳት ሣሩን፣ ደኑንና ቁጥቋጦውን የሚያቃጥል ቀንደኛ ጠላታችን\nስለሆነ ለምንድነው ከእርሱ ጋር ግዛት ፍለጋ የምንሄደው?” አለው።ውሃም “ታዲያ ምን ብናደርግ ይሻላል?” አለ።ሃሰትም ቀበል አድርጎ\n“ልንገድለው እንደሚገባ ግልፅ ነው።እሳትን የማጥፋት ብቸኛ ኃይል ያለህ ደግሞ አንተ ነህ።እናም ቁጭ ሲል ጠብቀህ እላዩ ላይ ራስህን\nበመርጨት አጥፋው፡፡” አለው።ውሃም “ራሴን መሬቱ ላይ ከረጨሁ ተመልሼ ውሃ መሆን አልችልም፡፡” አለ፡፡ ሀሰትም\n“ችግር የለውም፤ ተረጭተህ እንዳትበታተን የተወሰኑ ድንጋዮች በዙሪያህ አኖርና በኋላ እሰበስብሃለሁ።” አለው።በዚህ ጊዜ ያልጠረጠረው\nእሳት መጥቶ ቁጭ ሲል ውሃው አንድ ጊዜ በላዩ ላይ ሲረጭ ሃሰት ድንጋዮች ዙሪያውን አድርጎ ውሃውን ከሰበሰበውና እሳትን ካስወገዱ\nበኋላ አብረው መጓዝ ጀመሩ።ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሃሰት ውሃውን “ለምን እዚህ ገደል አፋፍ ላይ ቁጭ ብለህ በተፈጥሮ ውበት አትዝናናም?”\nአለው፡፡ ውሃም\nአፋፉ ላይ ቁጭ ሲል ሃሰት ቀስ ብሎ ተነስቶ ውሃ የተቀመጠባቸውን ድንጋዮች ከስሩ ሲለቅማቸው ውሃው በመፍሰስ ተበታትኖ ጠፋ።በመጨረሻም\nሃሰት እውነትን ማጥፋት ነበረበትና ወደ አንድ ትልቅ ተራራ በተቃረቡ ጊዜ ሃሰት እውነትን ከተራራው ግርጌ ቁጭ በል ብሎት ከተራራው\nአናት ላይ ትልቅ አለት ቁልቁል በመልቀቅ እውነትን ሊጨፈልቀው ሲል እውነት ቀልጠፍ ብሎ ማምለጥ በመቻሉ አለቱ ተንከባሎ ሲፈረካከስ\nከውስጡ አልማዝ፣ ወርቅና ልዩ ልዩ የከበሩ ማዕድናት ወጡ።ሃሰትም የእውነትን አስከሬን ሊመለከት በመጣ ጊዜ እነዚህን ሁሉ የከበሩ\nድንጋዮችን አየ፡፡እናም\n“እነዚህ ሁሉ ከየት መጡ?” ብሎ ጠየቀ። እውነትም “ እላዬ ላይ እንዲወድቅ ከላከው አለት ነው የወጡት፡፡” አለው።በዚህ ጊዜ ሃሰት\n“አሁን ደግሞ እኔ ከተራራው ግርጌ ልቀመጥና አንተ አለቱን በላዬ ላይ ልቀቅብኝ፡፡” አለው፡፡እናም\nእውነት ወደ ተራራው ጫፍ ወጥቶ ትልቅ አለት ወደታች በለቀቀ ጊዜ የሃሰት አናት ላይ አርፎ ጨፈላልቆ ገደለው፡፡አየህ\nወዳጄ !ምን እንኳ ሃሰት ቀን የወጣላት፣ የአሸነፈች፣ የተሳካላት ብትመስልም ለጊዜው የተወሰነ ጥፋት ታደርሳለች እንጂ እውነት አትጠፋም።\nይልቅ እውነት በሃሰት የጥፋት መሳሪያ ትለመልማለች ብሎም የመበልጸጊያ መንገዶች ከሃሰት ታገኛለች። ይህ የማህበረሰብ ስነ ቃል ቀድሞ ከወዳጄ ጋር ካነሳሁት\nጉዳይ ጋር እንዴት ይገናኛል? ብለህ ከጠየከኝ፤ ስነ ቃሉም ሆነ ገጠመኜ የሚያሳየው እውነት ፈተና ቢገጥመውም በመጨረሻ አሸናፊ መሆኑን\nየሚያሳይ እንደሆነ እነግርሀለሁ። ሰላም!አዲስ ዘመን ታህሳስ 12/2012አብርሃም\nተወልደ", "passage_id": "ffe9d4c079fd0fdee3604d5f86efc207" }, { "passage": "ኢትዮጵያዊያን\nስንባል ከሌላው ዓለም የተለየ ባህሪ አለን። ይህንን ስላችሁ በባህላችንና በምንኩራበት ግን ደግሞ መድገም ባልቻልነው ታሪካችን የተገኘ\nእንዳይመስላችሁ። ለነገሩ ዛሬ ላይ መቆማችንን ዘንግተን ያለፈውን በመተረክ ብቻ የምንኖር የተለየን ህዝቦች ሳንሆን አንቀርም (የ«ነበር»\nህዝቦች ተብለን ብንጠራ ያስከፋን ይሆን?) ይህ\nየተነጠለ ባህሪያችን ከተቀረው ዓለም እንዳንደርስ የቆመ ግንብ ይመስል መናድ አቅቶን ዘመናትን ኖረናል። አብዛኛው ነገራችን የተንተራሰውም\nእያደር በሚናዱ እውነቶች ላይ ነው። የሚናድ እውነት ታውቃላችሁ? ለመናድ የተለመደው መሬት ስለሆነ በዚህ ላስረዳችሁ። ስትመለከቱት\nየተለየ ያልነበረው መሬት መናድ የሚጀምረው ስትረግጡት ነው። ከናዳው የተረፈው መሬትም ደህና መስሏችሁ ስትቆሙበት ባህሪው ነውና\nእርሱም ደግሞ ይከዳችኋል። እኛም\nእንዲህ ዓይነት ባህሪ ተጠናውቶናል፤ በቀላሉ መናበብም አቅቶናል (ትንሿን ፍሬ ለማግኘት ብዙ ልጣጭ እንደማንሳት ዓይነት)። ነገሬን\nበአጭርና ግልጽ መንገድ ለማስረዳት አንድ ምሳሌ ላቅርብ። አንድ ዕቃ ለመግዛት ወደ ገበያ ወጥታችሁ ከፍለጋ በኋላ አገኛችሁት፤ ነጋዴውንም\nዋጋውን ጠይቁት።«100\nብቻ ነው» ይላችኋል እየተቅለሰለሰ፤ «ኧረ ተወደደ» በሉት፤ ከአፋችሁ ቀበል አድርጎ «እሺ በቃ 90 ውሰዱት» ይላል። «ኧረ አስተያየት\nአድርግበት» ስትሉት ደግሞ ስለመጣበት ሁኔታ፣ ዕቃው ከገበያ ላይ እየጠፋ ስለመሆኑ እንዲሁም ስለ ጥራቱ ጥቂት ካስረዳችሁ በኋላ፤\nበ85 ብር እንድትገዙት ያስማማችኋል። ኮስተር ብላችሁ «የመጨረሻ መሸጫ ዋጋ» ከጠየቃችሁትማ አንገቱን ደፍቶ «የእኔ\nትርፍ ይቅርና በ75 ውሰዱት» ይላችኋል። እመኑኝ አሁንም መወደዱን ነግራችሁ አማራጭ ፍለጋ ሌላ ቦታ እንደምትሄዱ ብትነግሩት፤ እግራችሁን\nከማንሳታችሁ አስቀድሞ ከተማጽኖ ጋር በ50 እና ከዚያ ባነሰ ዋጋ ይሸጥላችኋል(ልፋ ቢለው እኮ ነው)  ወገን እቅጩን ተናግሮ እንደመሸጥ ክርክሩ ጉንጭን ከማልፋት የተሻገረ ምን ጥቅም\nይሰጣል? ለነገሩ ዝም ብሎ የሚገዛው ካገኘ በእጥፎች ከማትረፍ ወደኋላ ስለማይል ነው። ጥሩው ነገር ደግሞ ገዢውም ይህንኑ ስለሚያውቅ\nሳይከራከር አይገዛም(ስንተዋወቅ አንተላለቅ ይመስላል ነገሩ)    እናማ\nአብዛኛዎቻችን በትርኪ ምርኪ እንደተሞላ መጽሐፍ ፍሬ ነገሩን(ለእኛ ደግሞ ማንነታችንን) ለማግኘት ብዙ መገለጥ ያለብን ወደ መሆኑ\nአዘንብለናል። ይህ ባህሪያችንም ከአንዳችን ወደ ሌላችን እየተጋባ እንደ ህዝብ የምንጋራው በሽታ ሆኗል ብል ማጋነን አይሆንም (ህዝብ\nእንዴት በአንዴ ሊታመም ይችላል ግን?)  ኑሯችንም እንደ ነጋዴው ከመጨረሻው መድረስ አቅቶታል፤ እያደር የሚናደው እውነትም\nይህ ነው። ዛሬ ስለ አንድ ሰው ያወቅነው ነገ ተንዶ ደግሞ ሌላ እውነት ብቅ ይላል፤ በሌላኛው ቀን ደግሞ ሌላ እውነት መሳይ እውነት።\nበመንገድም ሆነ ከአንድ ስፍራ በትውልዱ ተማሮ የሚናገር ሰው ገጥሟችሁ ይሆን?  የሌላውን ልጅ አኳዃን ሲወቅስና አሳዳጊውን ሲኮንን እኮ፤ አንዳች እንከን የሚገኝበት\nአይመስልም። ኧረ  የእርሱን ልጆች ስነ-ምግባር አዋቂነት እስክትመለከቱ\nልትጓጉም ትችላላችሁ። ታዲያ አንድ አጋጣሚ ብታገኙ፤ እንዲያ ያደነቃችሁት ሰው በልጆቹ ሲንጓጠጥ እና ከፍና ዝቅ ሲደረግ ታዩት ይሆናል።   ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ስለትውልዱ መበላሸትና በመጤ ባህሎች መጠመድ የሚያወግዝም\nአለ። ታዲያ ለዚህ ምክንያት አድርጎ የሚያነሳው የመገናኛ ብዙሃን እና ትምህርት ቤቶች የሚሰጡት ትምህርት ግብረ ገብነት የጎደለው\nመሆኑን ነው። ነገር ግን እግር ጥሏችሁ ቤቱ ብትገኙ ከእነ ልጆቹ ለ24 ሰዓታት የውጭ ፊልም የሚመለከት ሆኖ ታገኙታላችሁ።  እዚህ የሌላውን ልጅ እየኮነነ ስለ ስነ-ምግባር የሚሰብከው እዚያ የራሱን ልጅ\nእያበላሸ መሆኑ አይገርምም? የየትኛውም ነገር መነሻ ቤቱ ሆኖ ሳለ ሙገሳን ለራስ ወቀሳን ደግሞ ለሌሎች መተው ምን ይባላል? መጣመሙን\nገና ከችግኙ በቁጥጥር ስር ያላዋለውን አናጺው እንዴት ስርዓት ሊያስይዘው ይቻለዋል?     ደግሞ አሉ በየመድረኩ የሃገር ባህል ልብስ ለብሶ፤ ስለ ባህል መበረዝ የሚያብራራ።\nጥንተ ባህሉ ወደ ቤቱ እንዲመለስ ጥረት ማድረጉን እየደሰኮረ፤ ቤቱን ከአውሮፓ በመጡ ዕቃዎች የሚያደረጅ (በልጆቹም «ማሚ እና ዳዲ»\nየሚባለው)።  ስለ\nሃገር ፍቅር የሚያስተምረውን ሰውም አርዓያ ይሆናል ብላችሁ ታሪኩን ብትጠይቁት በኩራት «አንዷ ልጄ አሜሪካ ነዋሪ ናት፣ ሌላኛው\nልጄ ጣሊያን፣…» የሚል ዝርዝር ውስጥ ይገባል(ኩራት በሃገር መሆኑን እየተናገረ የሚኩራራው ግን አውሮፓ ባሉት ልጆቹ ነው)።\nስለ\nስደት መጥፎነት የሚዘምረውስ ቢሆን፤ አስከፊነቱን የሚያሳየው ከተዋቡ ሕንፃዎች መካከል፣ ባማረ መንገድ ላይ ምቾት የሚጎላበት ሰውነቱን\nበዘመናዊ ልብሶች አንቆጥቁጦ አይደለም እንዴ? (በሌላ አነጋገር ተሰደዱ የሚሉ እኮ ነው የሚመስለው) ወገኑ የመሰደድ አስከፊነቱን\nተመክቶ ሃሳቡን እንዲቀይር የማድረግ አቅም ያላቸው ዘፈኖችን ብቻም ሳይሆን ትዕይንቶችን ማሳየትም እኮ አስፈላጊ ነው።  ስለ ዘረኝነት እና አሁን ስለሚታየው ሁኔታ ያሉትን አስታራቂ ሃሳቦች በየመገናኛ\nብዙሃኑ ተገኝቶ ሲደሰኩር እና ትንታኔ ሲሰጥ ቆይቶ ፌስቡክ ላይ «እዚያ እንዲህ አደረጉ፤ እዚህም እንዲህ ተፈጠረ» እያለ ሚሊዮኖችን\nየሚያጭበረብር ምሁር ነኝ ባይም በዝቷል። እዚህ ጥሩ ሲናገር አድንቀነው እዚያ አድናቆታችንን በቅሬታ መሸፈን አዋቂነት ይሆን?\n(ዲግሪያቸውን በማጭበርበር የያዙ እኮ ነው የሚመስለው)።ይህ\nባህሪ በግለሰቦች ብቻም ሳይሆን በተቋማት ላይም እኮ ይንጸባረቃል። ኢትዮጵያ ውስጥ በቅጡ ተደራሽ ያልሆነ እንዲያውም ከዓመታዊ ዕቅዱ\nግማሹን እንኳን ለመፈጸም የሚያቅተው ተቋም በሁለትና ሦስት ዓመታት በምሥራቅ አፍሪካ እዚህ ደረጃ ለመድረስ አስቤ እየሠራሁ ነው\nይላል(ምጸት እኮ ነው)።  ወዳጆቼ\nሆይ ምድሪቷ አንድ ናት፤ ሁለት እግር ቢኖረንም በአንዱ እዚህ በሌላኛው እዚያ መርገጥ አይሆንልንም። ስብዕናም እንዲሁ ነው፤ ሁለትና\nከዚያ በላይ ሊሆን አይችልም፤ እንዲያ ሳይሆን ማስመሰልን ብቻ ሥራችን ካደረግን ግን እየኖርን አይደለም ማለት ነው። በየዕለቱ የሚለዋወጥና\nእንደ አዲስ የሚገለጥ ማንነት መያዝስ ለምን ይጠቅማል። እንደነጋዴው ቢሆንልኝ እጥፍ አተርፋለሁ ካልሆነም በተገኘው እሸጣለሁ ብሎ\nዙሪያ ጥምጥምና አታካች ክርክር ከመግጠምስ፤ እቅጩን መኖር አያዋጣም ትላላችሁ?  አዲስ\nዘመን የካቲት 4/2011በብርሃን\nፈይሳ", "passage_id": "46ea80ef353b3431279b30b15dd89d98" }, { "passage": " እስቲ ዛሬ ስለ ኳስ እናውራ! ከመደበኛው ወጣ እንበላ! ምንም እንኳ እግር ኳስን «ወጣ» ልናደርገው ብንሞክርም ፖለቲካ ካልሆንኩኝ ሲል እያየነው ቢሆንም፤ ይሁን! አንዳንዴ እንደ ርዕስ መቀየሪያ እንጠቀመው። አሃ! ቆዩ እንጂ መግቢያ መች አዘጋጀሁ። እንካችሁማ መግቢያ! መቼ እለት በቴሌቭዥን ካየሁት ዝግጅት ልጀምር፤ ምን የማይታይ አለ! በምላችሁ ዝግጅት ላይ አዘጋጅቱ ለንግግር የጋበዘቻቸው ሰዎች ከተናገሩት ቁምነገር መካከል አንዱ የበለጠ ሳበኝ። ምን አሉ? «አበሾች ለቅሶ ቤት ሰው ለማጽናናት ሲሄዱ ጭራሽ ሃዘን ቀስቅሰው <ታሞ ነበር? እንዴት ሞተ? ብዙ ተሰቃየ?> ወዘተ እያሉ ይጠይቃሉ» አሉ። መቼም እንደ እኛ ለችግር ደራሽ አለ ብለን ባናምንም፤ ማስተዛዘኛ መንገዳችን ግን ጭራሽ ሀዘን የሚቀሰቅስ ሆኖ ተገኘ ማለት ነው። እና ምን ብናደርግ ነበር ጥሩ? ሌላ ሌላ ጉዳይ እያነሳን የታመመውንም ሆነ ሰው የሞተበትን ሰው ከሀዘኑ እንዲወጣ ማስረሳት፤ ማረሳሳት። እና ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው፤  ብለን ብለን የደከመንንና አይገመቴውን ፖለቲካ ለአፍታ ትተን እስቲ ስለኳስ ብናወራ ምን ክፋት አለው? አቤት መግቢያ! እና ግን ለምንድን ነው ከ 18 ዓመት\nበታች የሆኑ ልጆች ስታድየም እንዳይገቡ የማይከለከለው? በተለይ አሁን አሁን «ፖለቲካ የእኔ ነው» ባይ በበዛበት ጊዜ፤ እግር ኳሱም ብሶበት ነው የሚታየው። ያድነኛል ብለው ውጠውት የባሰ አዲስ በሽታ እንደሚፈጥርና ህመሙን እንደሚያብስ «መድኃኒት» ሆነብን፤ እግር ኳስ። አሃ! ጦርነት ሆኗላ! የፖለቲካ እልህ ያለበት ሁሉ በኳስ ሲፈናከት እያየን! ምን ሆነ መሰላችሁ! ስንት ጊዜ የአገራችን እግር ኳስ ሲታማ በጆሮዬ እሰማ የነበርኩ ልጅት ባለፈው ስታድየም መግባት። የት? እርሱን አልነግራችሁም። ያው ችግር የሌለበት ባለመኖሩ አንዱንም ልትገምቱ ትችላላችሁ፤ ግን ከአዲስ አበባ ውጪ መሆኑን ያዙልኝ። ታድያ ወደ ጨዋታው ሜዳ ስንገባ የእንግዳው ቡድን ብቻውን እንጂ አንድም ደጋፊ አልነበረውም። «ውይ! አገር ምድሩ ሰው በሆነበት ጊዜ ደጋፊ ጠፍቶ ነው?» ብል፤ «አይ! ደጋፊዎቹ ጸበኞች ናቸውና እዚህ እንዳትደርሱ ተብለው ነው።» አሉኝ። «እና ይህም እግር ኳስ ሆኖ በዚህም ተከፋፍለናላ!» ስል፤ «ያው የድጋፍ ጉዳይ ነው!» «ጎሽ! እና እነዚህ ያለሜዳቸው የሚጫወቱ ተጫዋቾቹ ብቻቸውን አይፈሩም? ካሸነፉስ ማን ሊጨፍር ነው?» አልኩኝ፤ ድፍረቴኮ! «የምን ማሸነፍ? ማን ፈቅዶላቸው? ጨዋታው ካለቀ በኋላ በሰላም ወደ ማደሪያሽ መግባት አትፈልጊም? ዳኛውም’ኮ ሰው\nነው… ልጆች ይኖሩታል። ይኑርበት እንጂ!» ብለውኝ እርፍ። አሃ! ታድያ በሕይወት ካለ፤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንዲህ ባሉ አጋጣሚዎች ቡድኖች ወጪ ከሚያወጡ ለ«ባለሜዳው» ቡድን\nዝም ብሎ ነጥብ እንዲሰጥ ለምን አይፈቅድም አልኩኝ፤ በልቤ ወይም በሆዴ። ፌዴሬሽኑ ግለሰብ ቢሆን ኖሮ ቀዳሚ ድንጋይ አቀባይና አስወርዋሪ ነገር መስሎ ታየኝ። እንዲህ በማለቴ መቼስ አይከፋውም። ቢከፋውም ይሁን! እንደ ህጋዊ ሰው ስሜት ያለውና ግዑዝ ያልሆነ መሆኑን አረጋግጥበታለሁ። ብቻ ግን ጨዋታው ተካሄደና ይኼው እንግዳውን የተቀበለው ቡድን በሜዳው አንድ ጎል አገባ። ጎሉ እንኳ ኦፍ ሳይድ ነበር፤ ግን ቢሆንስ? እንደውም ለምን በእጁ አያገባም? ውጤቱን የሚወስነው ባለ ሜዳው ነው። ባለሜዳው ባለ አእምሮ ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን ባለ ስሜት ነው። ያውም የእግር ኳስ ስሜት አይደለም… የድብድብ ስሜት። ከዛ በባሰ ልጆች ወደ ሜዳ እንዳይገቡ ይከልከል ያልኩት ደግሞ ለዚህ ነው፤ ስድቡ! ኧረ ስድብ! የስድብ ችሎታችን በዜማና በግጥም ተቀናብሮ ይቀርብ የለ እንዴ? ሰው እንዴት በጋራ እንደ ኅብረ ዝማሬ የስድብ ቃልን በኩራት ይናገራል? በእድሜ ትልልቅ የሆኑ ሰዎችም በሜዳው የዚህ የስድብ ተጋሪ መሆናቸውን ሳይ ደግሞ ጭራሽ አፈርኩ። ነገሩ ለእኔ አዲስ ሆኖብኝ እንደሆነ የገባኝ ደጋግመው ስታድየም ጨዋታ ለመዘገብ የሚገቡ ባልደረቦቼ ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም ማለታቸውን ስመለከት ነው። የሚሆነውን ሁሉ እንደ ጦጣና «ኢትዮጵያዊነት መልካምነት» ብሎ እንደሚያይ ጨዋ ሰው ሆኜ ነበር። በኅብረ ዝማሬ ከሚሳደቡት ደጋፊዎች ተቀብለው ህጻናት የማያውቋቸውን ቃላት እየተቀበሉ ያስተጋባሉ። እነዛን አስጸያፊ የስድብ ቃላት ከሽማግሌና አዋቂዎች አንደበት መስማት ሳያንስ ትርጉሙን ከማያውቁት ልጆች ሲወጣ ደግሞ ሰውነትን ውርር ያደርጋል። ኧረ ምን እየተዘራ ነው? ነገ ምን ሊታጨድ ነው ወገን! ብቻ ግን በስድብና ትክክለኛ ባልሆነ ጎልም ቢሆን ጨዋታው በሰላም አለቀ። ሰላም አንጻራዊ አይደለ? ለካ ደግሞ መውጣትም ፈተና ነው። ጠመንጃ የታጠቁና በቁጥር በርከት ያሉ ፖሊሶች በሩ ጋር ሆነው በመከላከል ተጫዋቾቹ በእንግድነት ከተጫወቱበት ሜዳ ተንከባክበው ይዘዋቸው ወጡ። ኳስ እኛም አገር በስሙ ተጠርታና ወግ ደርሷት ጭራሽ እንዲህ አስፈሪ ትሁን? አሁን ማን ይሙት በአገራችን ከስታድየሞቻችን በላይ አስፈሪ ቀጠናስ አለ? ከስታድየሙ ውጪ የሚታየው የፖሊስ ኃይል ከመብዛቱ የተነሳ አንድ የፖሊስ ክለብ የተጫወተ ነው የሚመስለው። እናላችሁ ወደየማረፊችን ስናቀና አንድ ጉድ ሰማሁ። ለካ ሰብሰብ ብለን ሲያዩን የእንግዳው ቡድን ደጋፊዎች መስለናቸዋል ጥርስ ነክሰውብናል። ጥርስ ይነከሳል ወይ የሚለው ሌላ ጉዳይ ሆኖ ይህን ነገር ከስታድየሙ ስወጣ መስማቴ ጠቀመ እንጂ አስቀድሞ ብሰማ ኖሮ የት ልገባ ነበር? ምንስ ልሆን ነበር? በቃ! ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ስታድየም ከመግባት ይከልከሉ። ስታድየሞቻችንና የሚካሄዱት ጨዋታዎች፤ ወላጆች ልጆችን ይዘው ‹ይህን ቡድን ነው የምደግፈው…› ብለው እንዲያሳዩ፣ የሚደግፉትን ቡድን መለዮ ለብሰው በነጻነትና ያለስጋት እንዲንቀሳቀሱ የሚፈቅድ አይደለም። እንደውም እንደሚባለው ከሆነ መሮጥ የሚችል ሰው ነው ጨዋታ እንዲያይ የሚመከረው! ነጻ ትግል ቢችልም ይመረጣል። ሆድ ያባውን ብቅል እንደ ሚያወጣው ማንነትና ጸባያችንን ኳስዬ እያሳየችን ነው። እንግዳ ተቀባይነት? ኧረ ተውኝ እስቲ! እንግዲህ አንድ ሁለቴ ስታድየም ስመላለስ ነገሩን እለምደው ይሆናል ብዬ በመገመት በቅርቡ ለመድገም አስቤአለሁ። አንዳንድ ነገሮች አልቀየር ካሉና ሌላ አማራጭ ከሌለ ራስን መቀየር አስፈላጊ ነው አይደለ? አዎን! በዚህ ሃሳብ ባልስማማም ትክክል መሆኑን አልክድም። ብቻ ግን እንዳልኩት ስታድየም መግ ባት ከ18 ዓመት\nበታች ለሆኑ ቢከለከል ጥሩ ነው። ቡድኖችም ተተኪ ተጫዋችና ደጋፊ እንጂ ተተኪ ተሳዳቢ ምን ያደርግላቸዋል? ነገሩ ቀላል አልመሰለኝም! እውነቱን ለመናገር የእግር ኳስ ፌደሬሽን የሚባል ነገር የእውነት እንደ ስሙ ካለ መፍትሄው በእጁ ነው ያለው። አሁን ቡድኖች ሳይሆኑ ደጋፊ አለን የሚሉት፤ ደጋፊዎች ናቸው ቡድን ያላቸው። እናት ሉሲ ሰላምን\nፍለጋ ከምትኳትነው በላይ\nእግር ኳስ ወዳጅነትን\nበቀላሉ በመፍጠር አቻ የሌለው\nመሣሪያ ሊሆን ይችል\nነበር። አላለልንም! ኳስ ለሰላም\nከማለታችን በፊት ሰላም\nለእግር ኳሳችን አስፈላጊ\nሆኗል። እንደውም ዘርፉ\nየፈጠረው የሥራ ዕድል\nብዙ ነው፤ በዛ ላይ\nግርማ ሞገስ ያለውና\nሲጠራ የሚያስበረግግ ደመወዝ\nየሚከፈልበት ብቸኛው ትርፍ\nአልባ ዘርፍ መሆኑ\nነው እንጂ ቢቀርስ\nምን እንሆናለን?ወይም\nአንድ ሁለት ዓመት\nዘግቶ የተሻለ መንገድ\nመፈለግ ነው። የእግር\nኳስ ቡድን ደጋፊ\nእንዲኖረው እንጂ ደጋፊ\nቡድን እንዳይፈጥር፣ በብሔርና\nበክልል የተደራጀና በአስተዳደሮች\nየአወቃቀር ተዋረድ ስር በውስጠ\nታዋቂነት ተቀምጦ የእነርሱ\nድንጋይ መወራወሪያ ከመሆን\nእንዲወጣ፤ ከማንም በላይ\nአቅም ያላቸው ልጆች\nዓለም አቀፍ እውቅና\nየሚያገኙበት መድረክ እንዲሆን\nለማድረግ መሰራት አለበት።\nብቻ ይከልከልልን! መጠላላትን\nጠላን። ሰላም!አዲስ\nዘመን ሚያዝያ 13/2011 ", "passage_id": "44564a79ea5e60b7e292217ada4e64f1" } ]
1de5b24bdbea193ca64285fbca601089
ee8dd55e34b77c6fb656c9c8a34fa945
ፍርሃትን ለጉብኝት
 በርካታ ሀገራት ከቱሪዝም ዘርፍ ዳጎስ ያለ ገቢ ለማግኘት ያላቸውን የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ቅርሶች ለጎብኚዎች ክፍት ያደርጋሉ። የጎብኚዎቻቸውን ቁጥር ለመጨመርም ለቱሪስቶች አስፈላጊ ናቸው ብለው ያመኑባቸውን ነገሮች ሁሉ ያሟላሉ። በአሁኑ ወቅት ደግሞ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ቅርሶች የሌላቸው ሀገራት ስማርት ከተሞችን በመገንባትና ለልዩ ልዩ ኮንፍረንሶች በማዋል የቱሪስቶችን ቀልብ በመሳብ ከፍ ያለ ገቢ ማግኘት ጀምረዋል። በየሃገራቱ ያሉ የግል ባለሀብቶችም ተፈጥሯዊ ይዘት ያላቸውን ሪዞርቶችና ቅንጡ ሆቴሎች በመገንባት ከቱሪዝም የሚገኘውን ገቢ እያሳደጉት ይገኛሉ። ቱሪስቶች ወደነዚህ ሪዞርቶችና ቅንጡ ሆቴሎች የሚመጡት ለመዝናናትና ለእረፍት ካልሆነ በስተቀር ለመሳቀቅ አልያም ለመፍራት አይሆንም። ኦዲቲ ሴንትራል ከሰሞኑ ይዞት ብቅ ያለው መረጃ ግን ከዚህ የተለየ ነው። ሰዎች ለመፍራትና ለመሳቀቅ ፍላጎቱ ካላቸው ከኪሳቸው ሰባራ ሳንቲም ሳያወጡ ይልቁንም ተከፍሏቸው ሊጎበኟቸው የሚችሉ አስፈሪ ቤቶች መፈጠራቸውን ጠቁሟል። በሰዎች ላይ የፍርሃት ስሜት የሚፈጥሩ ቤቶች በአንዳንድ ሀገራት ውስጥ ለጉብኝት የሚውሉ መሆናቸው የሚታወቅ ቢሆንም፣ መኬሚ ማኖር የተሰኘው አሜሪካዊ ከሰሞኑ ገንብቶ ለጎብኚዎች ክፍት ያደረገው ቤት በጎብኚዎች ላይ ፍርሃት በመልቀቅ ወደር አልተገኘለትም። ቤቱ በሚፈለገው ልክ በጎብኚዎች እየተዘወተረ ባለመሆኑም በቤቱ ውስጥ የነገሰውን የፍርሃት ድባብ ለአስር ሰዓታት ተቋቁመው ለሚወጡ ሰዎች መኬሚ ማኖር የ20 ሺ የአሜሪካ ዶላር ሽልማት መመደቡ ታውቋል። ለጉብኝት የሚመጣ እያንዳንዱ እንግዳ የመጨረሻው ሰዓት ላይ እስኪደርስና ቤቱን ለቆ እስኪወጣ የአእምሮና የአካል ፈተና የሚገጥመው ሲሆን፣ በቤቱ ውስጥ በሚኖረው የአስር ሰዓታት ቆይታ ከእርሱ ጋር አካላዊ ንክኪ ያላቸው ይሁንና ለንክኪው ምላሽ የማይሰጡ አስፈሪ ተዋንያን መመደባቸው ተገልጿል። ይህንኑ አስፈሪ ቤት በመጎብኘት ለሽልማት የተዘጋጀውን 20 ሺ የአሜሪካ ዶላር ለማፈስ የፈለጉ ተሳታፊዎችም እድሜያቸው ከ21 ዓመት በላይ መሆን እንዳለበት በመረጃው ተጠቁሟል። ቤቱን መጎብኘት የሚፈልጉ የህክምና ኢንሹራንስ ማስረጃ የሚያቀርቡ፣ ስፖርታዊ ቅርፅ ያላቸውና በዚህ ቤት ለመቆየት መስማማታቸውን የሚገልፀውን ባለ አርባ ገፅ ቅፅ ለመፈረም ዝግጁ መሆን ይኖርባቸዋል። ይህንን ቅድመ ሁኔታ ያሟሉ ሰዎች በቅድሚያ ጉብኝቱን በተመለከተ አስተማሪ ቪዲዮ እንዲመለከቱ እንደሚደረግም ተነግ ሯል። በዚህ አስፈሪ ቤት ውስጥ ጎብኚዎች ከገቡ በኋላ 20 ሺ የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ያላቸውን ተስፋና ጉጉት በፍፁም ማሳየት እንደሌለባቸው መኬሚ ይመክራል። ይህን ማድረግ በፍፁም የተከለከለና ከቤቱ ውስጥ የሚያስወጣ መሆኑንም ገልጿል። የተለያዩ ቁልፎች የሚገኙባቸውን አቅጣ ጫዎችና አቅጣጫዎቹ ወዴት እንደሚያመሩ አስፈላጊዎቹ መረጃዎች ሁሉ ለጎብኚዎች የሚገለጹ ሲሆን፣ ጎብኚዎቹ አንድ ጊዜ ቤቱ ውስጥ ከገቡ በኋላ እያንዳንዱን ነገር ማስታወስ የእነሱ ሃላፊነት መሆኑንም አብራርቷል። ‹‹ያዘጋጀሁትን 20 ሺ ዶላር ሽልማት አታሸንፉም›› ሲልም መኬሚ አስጠንቅቋል። የማስፈራሪያ ቤቶች በአብዛኛው በአስፈሪ ድምጾች የታጀቡና በመጠኑ የፍርሃት ስሜት ውስጥ የሚከቱና አንዳንዴም ከጨለማ ጥግ ድንገት የሚዘሉ አክተሮች የሚታዩባቸው ቢሆኑም፣ መኬሚ ማኖር ሸረሪቶችና በረሮዎችን በደም ውስጥ በመንከርና በጎብኚዎች ፊት ላይ እንዲያርፉ በማድረግ እንዲሁም ሌሎችንም ዘግናኝ ድርጊቶችን በመጨመር ነገሮችን አዲስ ለማድረግና የበለጠ አስፈሪ ድባብ ለመፍጠር ጥረት አድርጓል ተብሏል። ይህንኑ ቤት ለማስተዋወቅ የተለቀቀው ቪዲዮም ወደዚህ ቤት የሚመጣን ማንኛውንም ሰው የሚያስጠነቅቅ እንደሆነም ተነግሯል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 18/2012 አስናቀ ፀጋዬ
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=21576
[ { "passage": "የሜጋ ሞሃ አያት\n\nከመታጠቢያ ቤት እየወጣች \"ታምፖን (የወር አበባ መጠበቂያ አይነት) ያለው ሰው ይኖራል?\" ብላ ጠየቀች።\n\nበትኩስ ሻይ ዙሪያ ጨዋታ ይዘው የነበሩት ብዙው የቤተሰቧ አባላት በአንድ ጊዜ ፀጥ አሉ። በሕንድ ደቡብ ያለችው ከታሚል ናዱ ወጣ ብላ የምትገኘው ራሜስዋራም የተሰኘችው ደሴት ላይ በአንድ የሆቴል ክፍል ነበር የታጨቁት።\n\nተፈጠሯዊ ያልነበረው ፀጥታ በሁለት ምክንያቶች በጣም ያስታውቅ ነበር። አንደኛ ዝናቡ መስኮቱን ይደበድብ ስለነበርና ሁለተኛ ደግሞ በሦስት የተለያዩ አህጉራት ላይ የሚኖሩት ቤተሰቦቿ በየቀኑ ዋትሳፕም ላይ እየተገናኙ በአካል ሲገናኙ ግን መቼም ፀጥታ ባለመስፈኑ ነው። \n\nበሆቴሉ አልጋ ላይ ጋደም ብላ የነበረችው አክስቷ ተነስታ የእጅ ቦርሳዋን አነሳች። የወር አበባ መጠበቂያ አወጥታ አቀበለቻት።\n\n\"ይህ ፋርማሲ እስክንሄድ ድረስ ይጠቅምሻል'' አልችና ባዘነ ፊት እያየቻት ''ይህ ምን ማለት እንደሆነ ታውቅያለሽ አይደል?'' ብላ ጠየቀቻት። \n\nሜጋ ግን አላወቀችም ነበር። \n\n\"ቤተ-መቅደስ መምጣት አትችይም ማለት ነው'' አለቻት። \n\nበራሜስዋራም ያለው የፀበል ገንዳዎች ሰዎች በመጠመቅ ለቅድመ ዘር አክብሮት የሚያቀርቡበት ነው\n\nቤተሰባቸው ለእረፍት አልነበረም ወደ ራሜስዋራማ ያቀናው። ይህች ደሴት በጎብኚዎችና በዓሣ አስገሪዎቿ የታወቀች ብትሆንም እነርሱ ግን የተሰባሰቡት ለአሳዛኝ ጉዳይ ነው።\n\nሜጋ የምትወዳት አያቷ ካረፈች ዓመት ሆኗት ነበር። እሷው ነበረች በተለያዩ አህጉራት ላይ ያሉትን የቤተሰቡ አባላትን የምታሰባስበው። \n\nባለፈው ታህሳስ የህልፈቷ ዜና ሲደርሳቸው ሁሉም በፍጥነት አውሮፕላን ተሳፈሩ። \n\nእንደየአካባቢው ቢለያዩም በሒንዱ ባህል በሞት ዙሪያ ብዙ ወጎች አሉ። \n\nሰው ሲሞት የሜጋ ቤተሰብ የሕንድ ደቡብ ሒንዱ ባህልን ነው የሚከተለው። አስክሬኗን ቤታቸው ወስደው በነጭ ጥጥ ከገነዙ በኋላ በትልቅ ኮባ ላይ አስተኝተው ተሰብስበው ፀለዩ። ወንዶቹ አስክሬኑን ለማቃጠል ሲወስዱ ሜጋም አብራ ብትሄድ ትወድ ነበር። \n\nካረፈች በኋላ ለ15 ቀናት ሥጋ አልበሉም ነበር። ከ90 ቀናት በኋላ ደግሞ ልዩ ዝግጅት አደረጉ።\n\nኤርፖርትም እርስ በርሳቸው ተሰነባበተው ለቀጣዩ የሞት ባህል በራሜስዋራም እንደሚገናኙ ቃል ገቡ።\n\nእዚያም ነበር የሜጋ ወንዱ አያት ከሴት አያቷ ቀድሞ የዛሬ 36 ዓመት ሲሞት አያቷ የመጨረሻዎቹን ሥነ-ሥርዓቶች ያስከበረችው። \n\nበቤንጋል ዉሃ ዳርቻ ላይ ያለው ራሜስዋራም ለታሪካዊ ቤተ-መቅደሶቹ የታወቀ ነው። አፈ ታሪኩ እንደሚለው 'ራማ' የተሰኘው የሒንዱ አምላክ እዚያ ነበር 'ሲታ' የተሰኘችውን ሚስቱን ከጠላፊዋ ለማስፈታት ድልድይ ወደ ሽሪላንካ የሠራው። \n\nበሦስቱ የአውሮፕላን ጉዞዎች መካከልና በሚያንገጨግጨው የመኪና ጉዞ እንዳነበበችው ራሜስዋራም በወሳኝ ጊዜያት ነበር የሚኬደው። ሜጋም እራሷን እንደ ሐይማኖታዊ ሰው ቆጥራ ባታውቅም ግን አሁን ከሚጓዙት ሰዎች መካከል አንዷ ሆና እራሷን አግኘችው። \n\nታሚል ናዱ ታዋቂ የሐይማኖታዊ ጉዞ ስፍራ ነው\n\nአያቷ በሞተች በቀጣዮቹ ወራት በራሜስዋራም የሚደረገው የመሰናበቻው የመጨረሻ ምዕራፍ ምን እንደሚመስል ብዙ ታስብ ነበር። \n\nበአክስቷ የሆቴል ክፍል ውስጥ ሆነው ለሞተችው አያቷ የመሰናበቻ የመጨረሻው ክፍል ላይ መገኘት እንደማትችል ሲነገራት ሜጋ እራሷን የመከላከል ስሜት ውስጥ ገባች። \n\nሜጋ በፍጥነት ''በወር አባበዬ ላይ ስላለሁኝ ነው ቤተ-መቅደስ መሄድ የማልችለው?'' ብላ ጠየቀች። \n\nአይኖቿን ቀስ ብላ በማጥበብ አክስቷ የሜጋ አነጋገር በወጣትነቷ ተቀባይነት እንዳልነበረውና አሁን ደግሞ ይበልጥ እንደሌለው በሚገባት መልኩ አየቻት። \n\nሜጋም ወዲያውኑ ''ይቅርታ'' አለቻት። ''ግን እርግጠኛ ነን ይህንን... ", "passage_id": "e95e441af690ae6cce7729686446b63f" }, { "passage": "አላን ባለፉት አስር ወራት የአውሮፓና እስያ ሃገራትን እንዲሁም አውስትራልያ ለመጎብኘት ጉዞ ላይ ነው ያለው። ባለፈው ወር ጃፓን ውስጥ ከደቡባዊ የሳታ ሚሳኪ ጫፍ ተነስቶ ወደ ሰሜናዊው የሶያ ሚሳኪ ፅንፍ በእግሩ እየተጓዘ ነው። \n\nጉዞው እስከ ስድስት ወራት ሊወስድበት እንደሚችል ገምቷል። ጃፓን 25ኛ መዳረሻው ነች።\n\n\"ወላጆቼ ይሄን ያክል ርቀት መጓዝን ምን አመጣው እንዲሉ እንዳደረኳቸው አልጠፋኝም። ለእኔ ግን፤ ከአሁን በኋላ ገና ብዙ ይቀራል\" ይላል የተቀረውን የጉዞ ዕቅዱን እያስታወሰ።\n\nባንድ ወቅት፤ አመሻሽ ላይ በጃፓን በረሃዎች ሲጓዝ ተኩላ ገጠመውና ሳይተናኮለው ተርፏል። ምድረ ጃፓን ተኩላና ድብ የሞላበት አገር ነው። \n\n\"ቻይና ውስጥ በየሄድክበት የፍተሻ ኬላ ስላለ፤ ፓስፖርት ቪዛና የምትቆይበት ቦታ እንዳለህ የሚያስረግጥ ሰነድ ዋናውንና ቅጂውን ማቅረብ ስላለብህ ስጋት ነበረብኝ። ልክ ሻንጋይ እንደደረስኩ ግን፤ ትልቅ ከተማ ስለሆነ ነው መሰለኝ ያ አሰልቺ ፍተሻ አልጠበቀኝም።\" \n\nሻንጋይ የህዝብ ብዛቷን እና የከተማዋን ትልቅነት የሚመጥን ኢንተርኔትንም ይዛ አልጠበቀችውም። \n\nየጉዞው ዓላማ\n\nየጉዞዬ ዓላማ ብዙ ሀገሮችን ለመድረስ እና ባህላቸውን ለማወቅ ነው። በተለይም ከዚህ በፊት ያልተዋወኳቸውን። ከአውሮፓ ውጭ ስለሚኖሩ ህዝቦች የነበረኝ እውቀት ውስን ነበር። አሁን ግን አንዲት ሀገር ላይ ስደርስና አሻግሬ ሌላኛዋን መዳረሻዬን ሳይ እኩል እየሆነ ነው። \n\nበርግጥ ለመጀመሪያ ግዜ አንዲት ሀገር ላይ ስደርስ ሞቅ ያለ ስሜት ነው የሚሰማኝ። ጎብኚዎች የሚሄዱባቸው ቦታዎች፣ ምግቡ፣ የአካባቢው ባህልና ልምዱ ማራኪ ነው። \n\nእንዲህ ላሉት ነገሮች ፍቅሩ ስላለኝ ነው ጉዞውን የማደርገው። ሌላም ግድ የሚለኝ ነገር አለ፤ ሰው ልጆች ግንኙነት። የአንዲት ዓለም ሰዎች ሳለን አስተሳሰባችን እና ችግሮችንን የምንፈታበት ዘዴ ግን የተለያየ ነው። እነዚህን በቅርበት ስታዘብ ደስ ይለኛል።\n\nስለዓለም ያለኝ አመለካከት ከሌላው ሰው ለየት ያለ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ከእያንዳንዳችን መማር የምንችላቸው በርካታ ነገሮች አሉ። በቀጣይነትም መማር እፈልጋለሁ። \n\nጃፓን\n\nስለ ጃፓን ከተራው ሰው የተሻለ እውቀት ያለኝ ይመስለኝ ነበር። ወንድሜ ወደ ጃፓን ከሄደ ይሄው አስር ዓመቱ ነው። እዚያው ቀርቷል። \n\nበባለቤቱና በቤተሰቦቿ በኩል ከሀገሪቷ ጋር በሚገባ መተዋወቅ ጀመርኩ። ከታሪካዊ ቤተ-መቅደሶቻቸው በተጨማሪ ትዕግስታቸው፣ የፈጠራ አቅማቸው፣ ግብረ-ገብነታቸው የሚያስደምም ነው። \n\nሻኲ (ቤዝ-ቦል) ሲጫወቱ ማየትም አስደሳች ነው። አንድን ነገር አሻሽለው ለመስራት፣ ለማስጌጥ፣ ደግመው ለመፍጠር የተፈጠሩ ሰዎች መስለው ነው የሚሰሙኝ።\n\nከደግነታቸው፣ ከዋህነታቸውና ከጋስነታቸው ውጪ ስለምን ላውራ? በተለይ ብቻዬን በማደርገው በዚህ ጉዞ ላይ ሁኜ የማስባቸው እና የማብላላቸው ነገሮች ብዙ ናቸው። ሰዎች ፈገግ ሲሉልኝ፣ ጎንበስ ብለው ሰላምታ ሲያቀርቡልኝ አያለሁ። \n\nጭው ባለው መንገድ ላይ ድጋፍ ቢሆነኝ ብለው የሚጠጣ ይሰጡኛ፣ ልጆች እጃቸውን ያውለበልቡልኛል፣ በእንግሊዘኛ ሊያዋሩኝም ይሞክራሉ። መቼም በጃፓን የውጭ ሰዎችን እምብዛም አያዩም። ልክ ቦሲኒያ፣ ህንድ እና ላኦስ ውስጥ እንደሚገኙት ገጠሮች ጥቁሮችን ማግኘት ከባድ ነው!!! \n\nለዚህም ነው ጃፓንኛ ለመማር የተነሳሳሁት። ከቋንቋ ጋር የሆነ ትስስር አለኝ፤ ጉጉት ይሁን ታታሪ ሁኜ ልሁን አይገባኝም። አዲስ ቋንቋ መማር ግን ደስ ይለኛል። መንገዴ ላይ ከሚገጥሙኝ ልጆች ጋር ሰላምታ መለዋወጥ ደስ ይላል!\n\nማሰላሰል\n\nአንድ መደበቅ እማልፈልገው ነገር ትግርኛ አልችልም። ግን ትንሽ ትንሽ እሰማለሁ። ቤተሰቦቼ እንግሊዘኛ እያስተማሩ ነው ያሳደጉኝ። ምክንያት ነበራቸው 'ቋንቋችን የት... ", "passage_id": "8ca536c51f61df47cea1cb77ac9c2f52" }, { "passage": "ቅንጡዎቹ የአፍሪካ ህብረትና ኢሲኤ አዳራሾች አልተዋወቁም ብዙ ዓለማቀፍ ስብሰባዎችን በማስተናገድ አሜሪካ ትመራለች    ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያ ዓለማቀፍና አህጉራዊ ትልልቅ ስብሰባዎችን እያዘጋጀች ነው። በዚህም አዲስ አበባ የቱሪዝም ኮንፈረንስ ከተማ እየሆነች መምጣቷ ይነገራል፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት እንኳ 7 ሺህ ያህል እንግዶች የተሳተፉበትን 3ኛውን ፋይናንስ ለልማት ኮንፈረንስ በብቃት መወጣቷን፣ ተሳታፊዎች መደሰታቸውንና በአገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት መደነቃቸውን ታዛቢዎች ተናግረዋል፡፡ አገሪቱ በዓለም የቱሪዝም መዳረሻነትና በኮንፈረንስ ቱሪዝም እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ በዘርፉ ባለሙያ የሆኑትን አቶ ቁምነገር ተከተልን አነጋግሬአቸዋለሁ፡፡ ባለሙያው በአዲስ አበባ ሦስት ጊዜ የተሳካ የሆቴል ሾውና ኢትዮጵያ ኤግዚቢሽን ፎረም ያካሄዱ ሲሆን ማይስ (MICE) ኢስት አፍሪካ የተባለ ድርጅት መስርተው፣ በሚቀጥለው ዓመት አጋማሽ 4ኛውን “ሆቴል ሾው አፍሪካ 2016 ፎረም እና ኤክስፖ” ለማካሄድ ዝግጅት እያጠናቀቁ ይገኛሉ፡፡ አቶ ቁምነገር፤የኦዚ ቢዝነስና ሆስፒታሊቲ መስራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር እንዲሁም የሆቴሎች አማካሪም ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ካሏት የቱሪስት ሀብት አኳያ ከዚህ በፊት ይህ ነው የሚባል የሰራቸው ነገር ባለመኖሩ እውቅናው ዘገየ እንጂ በጣም ጥሩ ነው ይላሉ - ባለሙያው፡፡ ቱሪዝም የመዝናናትና የቢዝነስ (ኮንፈረንስ ቱሪዝም) በመባል በሁለት ይከፈላል፡፡ ኮንፈረንስ ቱሪዝም፤ በአሁኑ ወቅት ጊዜ ያለፈበትና ያረጀ አባባል ስለሆነ በማይስ (MICE) አስተሳሰብ ተተክቷል ብለዋል- አቶ ቁምነገር፡፡ እንዴት? ማይስ ደግሞ ምንድነው? በማለት ጠየቅሁ፡፡ ማይስ (MICE) M (meeting) ስብሰባ፣ I ኢንሴንቲቭስ (ማበረታቺያ ማነቃቂያ) C - ኮንፈረንስ/ኮንግረስ እና E ኤግዚቢሽን/ኤቨንት ማለት ነው ሲሉ ማብራሪያቸውን ቀጠሉ፡፡ ስብሰባ ፡- ከ2 ሰዎች ጀምሮ እስከ 1000 ሰዎች የሚያደርጉት የንግድ፣ የቤተሰብ ወይም ማንኛውም የአንድነት ግንኙነቶች ነው፡፡ ኢንሴንቲቭስ ትራቭል (ማበረታቻ፣ ማነቃቂያ፣ ማትጊያ) ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ በዱባይ የኖኪያ ወይም የሳምሰንግ፣ …  ኩባንያ በዓመቱ ባደረገው እንቅስቃሴ አገኛለሁ ብሎ ካቀደው በላይ የላቀ ትርፍ በማግኘቱ ለሰራተኞቹ ወጪ ችሎ ኢትዮጵያ ወይም ወደመረጡት አገር ሄደው እንዲዝናኑ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ከዚህም ጋር ተያያዥነት ያላቸው የሎያሊቲ ጥቅማጥቅሞችን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ኮንፈረንስ ቱሪዝም የሚባለው ከ1000 እስከ 3000 የሚደርሱ ሰዎች የሚሳተፉበት ስብሰባ ነው። ተሳታፊዎቹ ከ3000 ሰዎች በላይ ከሆኑ ኮንግረስ ይባላል፡፡ ለዚህ ነው አንዳንድ ጊዜ MICE እየተባለ የሚጠራው፡፡ ኤግዚቢሽን/ ኢቨንት፤ ኮንሰርት፣ የሃይማኖት ፕሮግራም፣ አነስ ያለ ስብሰባ፣ ሩጫ፣ ቅስቀሳ (ካምፔይን) … ወይም ኤግዚቢሽን ሊሆን ይችላል፡፡ ብዙ ጊዜ ኤግዚቢሽኑን የሚያዘጋጀው ኩባንያ፣ ሌሎች ድርጅቶችና ኩባንያዎች በትርዒቱ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡ የተሳታፊዎቹ ወጪ የሚሸፈነው በተሳታፊው ድርጅት ወይም ኩባንያ ነው፡፡ በኤግዚቢሽኑ የሚሳተፉ ሰዎች የአውሮፕላን ቲኬት፣ በሚቆዩበት ቀን ታስቦ የአልጋ፣ የምግብ፣ … ወጪ በላኪው ኩባንያ ይሸፈናል፡፡ በኤግዚቢሽኑ ለሚቀርቡ ዕቃዎች የአውሮፕላን ኪራይ ድርጅቱ ይከፍላል፡፡ ስለዚህ ተሳታፊዎቹ የተሰጣቸውን ገንዘብ ለማጥፋት አይሰስቱም፣ አይቆጥቡም። እንዲያውም በሚሄዱበት አገር፣ የሚገኝ ረከስ ያለ ነገር ወይም መታሰቢያ ለመግዛት የራሳቸውን ገንዘብ ይዘው ሊጓዙ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ከአገራቸው ይዘው የተነሱትን ዶላር ኤግዚቢሽኑን ባዘጋጀው አገር ያጠፋሉ እንጂ ይዘውት አይመለሱም፡፡ ኮንፈረንስ ቱሪዝም ከማይስ ውስጥ አንድ ዘርፍ ነው፡፡ ኮንፈረንስ ቱሪዝም ብዙ አስቸጋሪ ነገሮች ስላሉት የተለያዩ ዘዴዎችን መጠቀም ያስፈልጋል። ለምሳሌ በቅርቡ በአገራችን የተካሄደው 3ኛው ፋይናንስ ለልማት ኮንፈረንስ እንዴት እዚህ እንደተካሄደ እንይ፡፡ ስብሰባዎች የመንግሥት ኮሚትመንትና የቢዝነስ ሞዴል ስብሰባ በመባል በሁለት ይከፈላሉ። በመንግሥት ኮሚትመንት የሚመጣ ስብሰባ አድካሚና አንዳንድ ጊዜም ወጪ ያለው ነው፡፡ መንግስት፤ “3ኛው ፋይናንስ ለልማት፤በኢትዮጵያ መካሄድ አለበት፡፡” ብሎ የማሳመን ስራ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ ለዚህም ተጨባጭ ስራዎችን መስራቱ የሚታይ ነው፡፡መንግሥት ስብሰባውን ለገጽታ (ኢሜጅ) ግንባታ ጠቃሚ መስሎ ከታየው አስፈላጊውን ሥራ ሰርቶ አንዳንድ ወጪዎችን እሸፍናለሁ ሊል ይችላል፡፡ በዚህ ሁኔታ የገጽታ ግንባታ ሊያገኝ ይችላል፡፡ እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ነገር የገጽታ ግንባታ ሲደረግ የንግድ ትስስሩም ሊመጣ ይችላል፡፡ እንዲሁም ተጨማሪ የኢንቨስትመንት አጋጣሚዎች ይፈጠራሉ፡፡ማይስ (MICE) ማለት የቢዝነስ ስብሰባ ነው። በሌሎች የቱሪዝም ስራዎች የሚገኘው ጥቅም ከማይስ ጋር በፍፁም ሊወዳደሩ ቀርቶ ሊቀራረቡ እንኳ አይችሉም፡፡ ከማይስ የሚገኘው ጥቅም ከሌሎቹ አምስት እጅ ይበልጣል፡፡ ማይስ ትልቅ የገቢ ማግኛ ስለሆነ ኢትዮጵያም ማይስን ጠቃሚዬ ነው፤ ገበያዬ ነው፣ … ብላ አጥብቃ መያዝ አለበት፡፡ ዓለም ማይስ ማይስ ማለት ሲጀምር ብልጦቹ የበለፀጉት አገሮች ትልልቅ የስብሰባ አዳራሾችን፣ (የኮንቬንሽ ቦታዎችን) … ማዘጋጀት ጀመሩ። መሰብሰቢያ ቦታዎችን ስለሰሩ ብቻ ገበያ አይመጣም። ራሳቸውን ማስተዋወቅና መሸጥም አለባቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የመሰረተ ልማት (የመሰብሰቢያ ቦታ) ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ አይገባም፡፡ ቅንጡዎቹ የአፍሪካ ኅብረትና የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ)፣ ሚሊኒየም  አዳራሽ፣ ዓለም የደረሰበት  የቴክኖሎጂ ውጤት (ስቴት ኦፍ አርትስ) የተገጠመለትና 2000 ሰዎች መያዝ የሚችለው የባህርዳር ዘመናዊ አዳራሽ፣ ስታዲየሞች፣ … ሌሎችም አሉ፡፡ የማስተዋወቅ ሥራ ስላልተሰራላቸው እንጂ ቅንጡዎቹ የአፍሪካ ኅብረትና ኢሲኤ አዳራሾች እንደ ትልቅነታቸው በየሳምንቱ ከ1000 እስከ 3000 ስብሰባዎች ማስተናገድ ነበረባቸው፡፡ እንደዚህ ዓይነት አዳራሾች በሌሎች አብዛኛው የአፍሪካ ሀገሮች አይገኙም፡፡ በእነዚህ አዳራሾች በየሳምንቱ 1000 ሰዎች ቢስተናገዱ በትራንስፖርት፣ በአየር መንገዱ፣ በሆቴሉ፣ በሸቀጡ፣ በባህል ዕቃው ግዢ ፣… የሚገኘው የውጭ ምንዛሪ (የገንዘብ ልውውጥ) የትየለሌ ነው፡፡ ይህን የማይስ ትሩፋት የወሰዱት እነዚያው የበለፀጉት አገሮች ናቸው፡፡ በዓለም ላይ ብዙ ትልልቅ ስብሰባዎች የሚካሄዱት የት ነው? ቢባል አሜሪካ ነው፡፡ በአሜሪካስ፤ በየትኛዋ ከተማ ነው? ቢባል አብዛኛው ሰው ኒውዮርክ ወይም ዋሽንግተን ሊመስለው ይችላል፡፡ ሁለቱም አይደሉም፡፡ በረሃ ላይ የተቆረቆረችውና የዓለም ሀብታሞች መዝናኛ የሆነችው ላስቬጋስ ናት፡፡ በዚያች ከተማ 2000፣ 3000፣ 5000፣ 10000፣ … ሰዎች የሚያስተናግዱ አዳራሾች አሉ፡፡ 2000፣ 3000፣ 4000፣ 7000፣ … አልጋዎች ያላቸው ሆቴሎች ናቸው እዚያ ያሉት። ወደ መኝታ ቤት ስትሄድ፣ በዚህ አልፈህ፣ ይህን አቋርጠህ፣ ወደ ግራ ዞረህ፣፣ ወደ ቀኝ ታጥፈህ፣ … ነው ክፍልህን የምታገኘው ተብሎ የምታነበው ካርታ ይሰጥሃል፡፡ በቅርቡ በወጣው መረጃ መሰረት፤ በዓለም ብዙ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች የምታካሂደው አሜሪካ ናት። 2ኛ ጀርመን፣ 3ኛ ፈረንሳይ፣ 4ኛ ስፔይን ናቸው። እነዚህ አገሮች ሥራዬ ብለው በዓለም የሚካሄዱ ስብሰባዎችን የሚከታተል ቡድን ወይም መ/ቤት አላቸው፡፡ መ/ቤቶቹ ስራቸው ስብሰባዎችንና ኤግዚቢሽኖችን ማሳደድ ወይም በየአገሩ የሚካሄዱ ኤግዚቢሽኖችን ፕሮሞት በማድረግ ብዙ ሰዎች እንዲሳተፉ መቀስቀስ ነው፡፡ ኤክስፖ ሲዘጋጅ ሆስትድ ባየርስ (ተጋባዥ ገዢዎች) እናመጣለን፡፡ እነዚህ ሰዎች ስብሰባዎች የት እንደሚካሄዱ የሚወስኑ ናቸው፡፡ የስብሰባ ተሳታፊዎች 10ሺህ ወይም 50 ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ ዓመታዊ የማኔጅመንት ስብሰባው የት መካሄድ እንዳለበት የሚወስኑ የህዝብ ግንኙነትና የማኔጅመንት አባላት አሉ እንበል፡፡ ከአዲስ አበባ ውጭ ስብሰባ ለማካሄድ ወስኖ 1000 ሰው የሚይዝ አዳራሽ እንዲዘጋጅላቸው ሲጠይቁ፣ የህዝብ ግንኙነት ክፍሎች ሎካል ሆስት ባየርስ ይባላሉ፡፡በተመሳሳይ ሁኔታ ቢል ጌትስ ለ2017 አንድ ቢሊዮን ዶላር መድቦ፣ በ500 ሚሊዮን ዶላሩ አፍሪካ ውስጥ ስብሰባ አዘጋጁ ቢል፣ የህዝብ ግንኙነት አባላቱ አፍሪካ ውስጥ ስብሰባ ማድረግ የሚቻለው የት ነው? በማለት ቦታ የሚፈልጉበት ሀገር ወይንም የሚመርጡት በማይስ ኤክስፖ ላይ ነው፡፡ ለዚህም በመጀመሪያ ደረጃ ደቡብ አፍሪካን ያገኛሉ፤ ቀጥሎ ኬንያን፣ ከዚያም ሞሮኮን፡፡ በዚህ ኤክስፖ ላይ የሚካፈሉትን ሀገራት ያገኛሉ፤ ይደራደራሉ፡፡ በእንደዚህ ዓይነቱ ፎረምና ኤክስፖ ላይ ካልተገኘን ሁሉ ነገር ከእጃችን ያመልጣል። ከዚህ በተሻለ ደግሞ በቋሚነት የኤክስፖ አዘጋጁ ሀገር ከፍተኛውን ጥቅም በእጁ ያስገባል፡፡ ገዢዎቹ እኛ በደቡብ አፍሪካ ኤክስፖ የምንሳተፍ ከሆነ፣ የመወዳደር ዕድል ልናገኝ እንችላለን፡፡ ሁለቱን ብናይ መወሰን እንችላለን ብለው አዲስ አበባ አምጥተው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንዲወያዩ፣ እነዚህን ዓለም አቀፍ ሆስት ባየሮች ስናመጣ ወጪያቸውን በሙሉ እኛ እንችላለን፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚዘጋጀው ማይስ ኢስት አፍሪካ 2016፣ ከ50 እስከ 100 የሚደርሱ ባየሮችን እናመጣለን ብለን አቅደናል፡፡ ለምሳሉ ከ50ዎቹ ገዢዎች 5 እንኳ ስብሰባዎች በአዲስ አበባ እንዲካሄድ ቢወስኑ፣ 2000 ተሰብሳቢዎች በቀን 600 ዶላር ሂሳብ  ለ5 ቀን የሚቆዩበትን ወጪ ያደርጋሉ፡፡ በዚህም በቀላል ስሌት ሀገሪቷ የአየር ትኬትን ሳይጨምር ከ30 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ይፈጥርላታል፡፡ ለዚህ ነው የውጪ ምንዛሪን ችግር ፈቺ ቢዝነስ ማይስ መሆን ጀምሯል የሚባለው። ታሪካዊ ቦታዎችን በመጎብኘት የሚደሰቱት ቱሪስቶችና የቢዝነስ (ማይስ) ተሰብሳቢዎችን ብናነፃፅር፣ ቱሪስቶች በቀን 100 ዶላር ሲያጠፉ፣ የማይስ ተሰብሳቢዎች በቀን ከ500 - 600 ዶላር እንደሚያጠፉ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ስለዚህ ማይስ ከ5 እጥፍ በላይ ገቢ የሚያስገኝ አዲሱ የቢዝነስ አቅጣጫ ነው፡፡ ለዚህ ንግድ ደግሞ መሰረታዊ የሚባሉ ቴክኒኮች አሉ፡፡ የመጀመሪያው የመሰብሰቢያ ቦታ (መሰረተ ልማት) ነው፡፡ መሰረተ ልማት የሚባሉት የመሰብሰቢያ ቦታ፣ ሆቴሎች እና የመሳሰሉት ናቸው። በኛ በኩል እነዚህ ችግሮች እየተቀረፉ ነው። ሌላው መንግሥት ራሱን የቻለ የኮንቬንሽን ቢሮ ማቋቋም አለበት፡፡ ይህን ቢሮ አሰራሩ በሚፈቅደው መሰረት ማቋቋም ተገቢ ነው፡፡ ቢሮው ለትርፍ ያልተቋቋመ ይሆናል፡፡ ዘርፉ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ መሆኑን በዚህ የሚቲንግ ኢንዱስትሪ የተጠቀሙ ሀገሮች ልምድ ያሳያል፡፡ የዚህ ቢሮ ወይንም ኤጀንሲ ዋና ተግባራት የሀገሪቱን ዋና ዋና ኤቨንቶች፣ የስብሰባ ኢንዱስትሪ መረጃዎችን ማስተዋወቅ፣ ጥናት ማድረግ፣ አቅጣጫ ማስያዝ ይሆናል፡፡ ይህ ሲሆን የተቀናጀ አሰራርን ይፈጥራል፡፡ በዚህም ውጤታማ መሆን ይቻላል፡፡ሌላው ቴክኒክ ደግሞ ሀገሪቷ ይህንን የሚቲንግ ኢንዱስትሪ በቋሚነት የምታስተዋወቅበት ዓመታዊ ፎረምና ኤክስፖ ማዘጋጀት ነው፡፡ ኤክስፖ ማዘጋጀት የየእለት ውሳኔ የሚፈልጉ ጉዳዮች ከጀርባው ስላሉ፣ በግሉ ዘርፍ የሚሰሩ ስራዎች ናቸው፡፡ እኛም ይህንን መነሳሳት ወስደን በሀገሪቷ የመጀመሪያውን የማይስ ፎረምና ኤክስፖ በ2008 ዓ.ም በመጨረሻው ዓመት አጋማሽ ለመክፈት ዝግጅቱን አጠናቀናል፡፡ ለዚህም አስፈላጊ የሆኑ ፕሮሞሽንና ስምምነቶችን ተፈራርመናል። ይህ የማይስ ፎረምና ኤክስፖ በተለያዩ ወገኖች ድጋፍ የሚሰራ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ቁምነገር፤ተከታታይነት ያለው ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል፡፡   ", "passage_id": "1f1c2f63fbe4f7919d31a4072b079647" }, { "passage": "አንዳንድ ጥንቃቄዎች ከስጋት ይመነጫሉ። ሆኖም ስጋት ባደረበት አካል የሚወሰደው ጥንቃቄ ትክክል ላይሆን አሊያም ሌላኛውን አካል ሊጎዳ ይችላል። እርግጥ ነው ሰውን በእይታ ብቻ መገመት አይቻልም፤ አድራጎቱን እስኪያዩም ደህናውን ከመጥፎው መለየት አዳጋች ነው። በዚህ ስጋት መነሻነትም የሚከተሉት መፍትሄዎች እፎይታን ቢያስገኙም ዳሩ በሌላኛው አካል ደግሞ የቅሬታ ምንጭ ይሆኑ ይሆናል። ከሰሞኑ ከወደ ፔሩ የተሰማውም ይህንን መሰል ጉዳይ ነው። ዜናውን ያሰራጨው ኦዲቲ ሴንትራል የተሰኘው ድረገጽም አንድ ሰው እግሩ ፊት ለፊቱ ከተቀመጠው ጠረጴዛ ጋር በሰንሰለት ታስሮ የሚያሳይ ፎቶ ተያይዟል። ይህን ሲሰሙ ምናልባትም የታሪኩ ባለቤት የሆነው በፎቶው ላይ የሚታየው ሰው እስረኛ አሊያም ወንጀል የሰራ ሰው ሊመስልዎ ይችላል። ነገር ግን ይህ ሰው በችግር ምክንያት ሃገሩን ትቶ ወደ ሌላ ሃገር የተሰደደ ምስኪን ግለሰብ መሆኑን ይሰማሉ። ነገሩ እንዲህ ነው፤ በቬንዙዌላ ባለው ወቅታዊ የፖለቲካና ማህበራዊ ቀውስ በርካቶች ተሰደው ብራዚልን፣ ፔሩን እና ኮሎምቢያን መጠጊያቸው አድርገዋል። ታዲያ ከእነዚህ ስደተኞች መካከል የሆነውና ፔሩን የተጠጋው ላ ፓቲላ (ለደህንነቱ ሲባል ስሙ የተቀየረ) ግለሰብ፤ እህል ሊቀማምስ ከአንድ ምግብ ቤት ጎራ ይላል። ጥቂት ቆይቶ ግን ባለ ምግብ ቤቶቹ ከጠረጴዛው ጋር የተያያዘውን ሰንሰለት ከታፋው አዋደው በቁልፍ ይከረችሙበታል። ሁኔታው ያስፈራውና ያሳዘነው ምስኪን ስደተኛም ነገሩን በፎቶ በማስቀረት ሃገሩ ላለ አንድ ጋዜጠኛ ይልከዋል። ሉዊስ ማርቲኔዝ የተባለው ጋዜጠኛም በፔሩ የሚገኙ ምግብ ቤቶች ስደተኞች ተመግበው ሳይከፍሉ ይሄዱ ይሆናል በሚል ስጋት እግር ከጠረጴዛ (እግር ከወርች ነበር እኛ የምናውቀው) ማሰር ጀምረዋል ሲል በትዊተር ገጹ ይለጥፋል። ከቆይታ በኃላ የባለ ታሪኩን ፎቶ ያጠፋው ቢሆንም በርካቶች ግን ነገሩ ስለገረማቸው ፎቶውን አስቀርተው መነጋገሪያ አድርገውታል። ባለታሪኩ ፓቲላ ስለ ሆነው ነገር ሲያብራራም፤ አጋጣሚው የሆነው የውጪ ሃገር ሰዎችን ከመጥላትና አሳንሶ ከማየት የተነሳ እንደሆነ ነው። በዚሁ ምክንያትም የምግብ ቤቱ ባለቤት ግለሰቡ የተመገበበትን ሂሳብ እስኪከፍል መንቀሳቀስ እንዳይችል ማሰርን ምርጫው እንዳደረገም ገልጿል። ፓቲላም ነገሩን በፎቶ ካስቀረና የምግብ ቤቱን ስም ከያዘ በኃላ ሳይበላ መውጣቱንም ጋዜጣኛው ገልጿል። ጥንቃቄን ስጋት\nይወልደው ይሆናል፤ ነገር\nግን እንደ እኛ የተቸገረን\nመርዳት ከፔሩ ዜጎች\nእሩቅ ሳይሆን አይቀርም።\nለመገልገል ምግብ ቤት የሄደ\nሰውስ ከትዕዛዙ አስቀድሞ\nሰንሰለት ሲቀርብለት ራሱን\nደምበኛ ወይስ እስረኛ\nብሎ ይጠራ ይሆን?አዲስ ዘመን ሰኔ3/2011 ብርሃን\nፈይሳ", "passage_id": "bbc72b1de38842571efba662f8e5db46" }, { "passage": "እንደ ተባልነው አድርገን ወደ ፊት አንድ ሁለት እያልን ተራምደን ድቅድቅ ጨለማ ከዋጠው ክፍል ውስጥ ገባን። ቀጥሎ እንዴት እንደሚንቀሳቀሱ ማሰብ በጣም የሚያስፈራ ነገር አለው። ምክንያቱም ከድቅድቅ ጨለማ ጋር ከመፋጠጥ ውጪ ምንም የሚታይ አንዳች ነገር የለምና፤ ድምፅ ብቻ ነው የሚሰማው። በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛና በጣልያንኛ የሚነጋገሩ ሰዎች ድምፅ በተለያየ ርቀት ይሰማል።\n\nበጨለማ ወዲያ ወዲህ እያሉ ሰዎች ቦታ ቦታቸውን እንዲይዙ የሚያደርጉ አስተናጋጆች አሉ። አንደኛው ወደ እኛ መጥቶ ወንበራችንን እንድንይዝ አደረገ። ሁለት ኢትዮጵያዊያን እና አንድ የውጭ ዜጋ ጠረጴዛ ተጋርተን ተቀመጥን። በድቅድቁ ጨለማ ገፅታችን ምን እንደሚመስል ሳንተያይ ተዋወቅን። የትና ምን እንደምንሰራ እንዲሁም ስለ ብዙ ነገሮች እያወራን ደቂቃዎች ሄዱ።\n\nአስተናጋጁ የሚጠጣ ነገር እንድናዝ ጠይቆ ይዞልን መጣ። ብርጭቋችንን ከጠጴዛ ላይ በዳበሳ ከማንሳትና በውስጡ ያለውን መጠጥ ለማሽተት ከመሞከር ውጭ ምንም ምርጫ አልነበረንም። አሁንም አሁንም ብርጭቋችንን በዳሰሳ እየፈለግን በማንሳት የቀረበልንን እየተጎነጨን ጨዋታችንን ቀጠልን።\n\n• \"እናቴ የሞተችው ኤች አይ ቪ እንዳለብኝ ሳትነግረኝ ነው\"\n\nእዚያ ቦታ ላይ መገኘት ጨለማን እንዲፈሩ፤ አለማየት ሊነገር ከሚችለው በላይ ከባድ እንደሆነ እንዲያስቡ ግድ ይላል። ለቀናት፣ ለዓመታት ብሎም ህይወትን ሙሉ እንዲህ ባለ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ መኖር እጅግ ፈታኝ እንደሆነ አወራን። ይህ የእኔ እጣ ቢሆንስ? የሚል ጥያቄ በእያንዳንዳችን ውስጥ መኖሩ ይሰማል።\n\nአስተናጋጁ ዳግም ወደ እኛ መጥቶ ሾርባ አቅርቦልን ዋናው የምግብ ምርጫችንን ጠይቆን ሄደ። በዳበሳ ማንኪያና ሹካ ከሳሃን እያጋጨን ጨለማም ቢሆን እጅና አፍ አይተጣጡም እንደሚባለው በድቅድቁ ጨለማ ሳናይ አጣጥመን ተመገብን። ቀጥሎም 'ዲዘርት' ኬክ መጣልን። ምንም እንኳ እየበላን፣ እየጠጣንና እየተጨዋወትን ቢሆንም ጨለማው ጭንቅ የሚያደርግ ነገር አለው።\n\nቀጥሎ ደግሞ የተለያዩ ቀርፃ ቅርፅና ሌሎች ነገሮችን እየመጡልን በመዳሰስ እና በማሽተት ምን እንደሆኑ እንድንለይ ተጠየቅን። በዙሪያችን ያለውን ነገር እንደ ዓይነ ስውር በመስማት፣ በመዳሰስና በማሽተት ለመረዳት መሞከራችንን ቀጠልን። በመጨረሻም በአይነ ስውር አስተናጋጆቻችን እየተመራን ከድቅድቁ ጨለማ ክፍል ወጣን።\n\nይህ ለአንድ ሰዓት ተኩል የሚቆይ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የቀረበ ማዕድ የሚዘጋጀው ዓይናሞች የዓይነ ስውራን ህይወት ምን እንደሚመስል ለደቂቃዎችም ቢሆን እንዲሰማቸው ለማድረግ ታስቦ ነው። አይነ ስውራን እንዴት ይህን ወይም ያን ማድረግ ይችላሉ? ለሚሉ ጥያቄዎችም መልስ ለመስጠትና አጠቃላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው።\n\nአቶ ብርሃኑ በላይ የ 'ቱጌዘር ኢትዮጵያ' ሥራ አስኪያጅ ናቸው። የሦስት ልጆች አባት ሲሆኑ ልጆቻቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ገብተው በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ድርጅቶች በመስራት ላይ ይገኛሉ። \n\n• በንቅለ ተከላ ዕይታው የተመለሰለት ኢትዮጵያዊ ታዳጊ\n\nአቶ ብርሃኑ ለ40 ዓመታት ያስተማሩ መምህር ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት 'ማዕድ በጨለማ' ስለ ዓይነ ስውራን ያሉ የተሳሳቱ አመለካከቶችን መለወጥን ያለመ አንድ የድርጅቱ ተግባር ነው።\n\nበጨለማው ማዕድ ላይ ከተካፈሉ በኋላ በሙያዊና በገንዘብ ድጋፍ ከድርጅቱ ጎን የቆሙ በርካቶች እንደሆኑ ይናገራሉ።\n\nነገሩን ለማስፋት በሌሎች አውሮፓ አገራት እንዳሉ ዓይነ ስውራን የሚያስተናግዱባቸው የጨለማ ምግብ ቤት የመክፈት ሃሳብ እንዳላቸውም ይናገራሉ።\n\nድርጅታቸው ሴት ዓይነ ስውራን መጠለያ እንዲያገኙና እንዲማሩ ድጋፍ እንደሚያደርግ፣ ለዓይነ ስውራን የኮምፒውተር እንዲሁም ዓይነ ስውራን እንዴት መንገድ መሪ በትርን መጠቀም እንዳለባቸውም... ", "passage_id": "7f64a86851b1e200cec631f0072d4728" } ]
a2475ddb5ea958fc94bf827bca5aefe6
b51f763bf921b4a573c378567725493d
ሌጣዎችን ብቻ የሚያስተናግደው ቡና ቤት
 ሰዎች መዝናናት ሲፈልጉ ሰብሰብ ማለትን ይመርጣሉ።ሰብሰብ ማለት የተለያዩ ጨዋታዎችን ማምጣት የሚያስችል ሳይሆን ወጪንም ሊቆጥብ ይችላል።ለእዚህም ነው ጉዞ እና የመሳሰሉትን በቡድን የሚደረጉት፤ ድንኳን እየተጣለም ዳንኪራ የሚረገጠው።ጓደኞሞች ተጠራርተው ተቀጣጥረው ተያይዘው መጠጥ ቤት፣ ካፌ ቤት ወዘተ የሚገናኙት በጋራ የሚያደርጉት ጨዋታ ሁሌም የማይገኝ በመሆኑም ጭምር ነው። ኦዲቲ ሴንትራል የተሰኘው ደረ- ገጽ ሰሞኑን ያስነበበን ግን ከዚህ የተለየ ነው።በጃፓን ቶኪዮ የሚገኝ አንድ አነስተኛ ቡና ቤት ሌጣውን የሚመጣን ሰው ብቻ ማስተናገድን ምርጫው አድርጓል።ሂይቶሪ የተሰኘው ይህ ቡና ቤት በሌሎች ቡና ቤቶች የማይመረጥ የራሱን ደንበኞች የሚያስተናግድበት መንገድ አለው፡፡ መረጃው እንዳመለከተው፤ ብቻውን እስከ ሆነ ድረስ የትኛውም ግለሰብ ቡና ቤቱን መገልገል ይችላል።ወደ ቡና ቤቱ በቡድን ሆኖ መግባት ክልክል ነው።ፈቃዱም ሆነ ክልከላው በቡና ቤቱ መግቢያ በር እና በሌሎች ስፍራዎች ላይ በግልጽ ተልጥፏል፡፡ ‹‹ሰብስብ ብላችሁ ዘና ማለት የምትፈልጉ ከሆነ ይህ ቡና ቤት ለእናንተ ዝግጁ አይደለም፡፡›› ያለው መረጃው፣ ይህ ማለት ግን ቡና ቤቷ የብቸኞች ወይም የሌጣዎች ወይም ማህበረሰቡ ያገለላቸው ሰዎች መሰብሰቢያ ነው ማለት አይደለም ይላል፡፡ ቡና ቤቱ ለተገልጋዮቹ ያልተለመደ የተባለ ፖሊሲ ማውጣቱን የሰማችው አንድ የሶራ ኒውስ 24 መገናኛ ብዙሃን ሪፖርተር ማሪኮ በቅርቡ ቡና ቤቱን ጎብኝታለች።ጋዜጠኛዋ ቡና ቤቱ ከምትጠበቀው በላይ አካታች ሆኖ እንዳገኘችውም ተናግራለች።ወደ ቡና ቤቱ እንደገባችም ከስድስት የማያንሱ ተገልጋዮችን ማየቷን ጠቅሳ፣ ሰዎቹ ብቻቸውን እንደገቡ ሰዎች ሆነው እንዳለገኘቻቸው ተናግራለች።ለየብቻቸው ከመሆን ይልቅ ተሰብሰብው ሲጨዋወቱም ተመልክታለች።በአስተናጋጁ አማካይነት ቀረበቻቸውናም አጠገባቸው ተቀመ ጠች። ተገልጋዮቹ ለየብቻቸው ቢመጡም ብዙ ጊዜ አብረው እንደኖሩ ጓደኛሞች እርስ በእርስ ሲያወሩ ትመለከታለች።ማሪኮ መጠጥ አዘዘች፤ ይሁንና ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለበት አላወቀችም።አስተናገጁ ምን እንደተሰማት ተረድቷል፤ ወደ ቡና ቤቱ የመጣሽው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ሲልም ጠየቃት፡፡ ጋዜጠኛዋ ለቀረባላት ጥያቄ ምላሽ ስትሰጥ ሌሎቹ ደንበኞች ጭምር መሳተፍ ጀመሩ፤ ወደ ቡና ቤቱ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዴት ሊመጡ እንደቻሉ ሀሳብ ተለዋወጡ።ማሪኮም በውይይቱ ውስጥ መሳተፍ ቀጠለች።ወደ ቡና ቤቱ የሚመጡ ሁሉ በዚህ አይነት መልኩ እየተቀላቀሉ ተደስተው እንደሚመለሱም ተነገራት።የቡና ቤቱ ባለቤትም ይህን አስቦ ቡና ቤቱን መክፈቱን መረጃው ይጠቁማል። ‹‹ ሰዎች ቡና ቤት መሆን አለበት ብለው በሚያስቡት አይነት ቡና ቤት እኔ እምነቱ የለኝም›› ሲል ለሪፖርተሯ የተናገረው የቡና ቤቱ ባለቤት፣ ቡና ቤቴን እንዴት ባደርገው ከቡና ቤቶች ሁሉ የተለየ ሊሆን ይችላል እያለ ሲያስብ መቆየቱንም ይገልጻል።ቡና ቤቱ አዳዲስ ሰዎች እየመጡ የሚገናኛኙበትና የሚደሰቱባት እንዲሆን ይፈልግ እንደነበርም ይናገራል። ‹‹ቡና ቤቱ እንደገባህ ራስህን ብቸኛ ያረገህ ይመስልሃል፤ በሌሎች የተገለልክም ይመስልሃል፤ በእርግጥም ይመስላል፤ ከዚያም በቡና ቤቱ ከሚገኙት በርካታ ሰዎች ጋር ማውራት ውስጥ ተገባለህ›› ሲል አንዱ ተገልጋይ ይናገራል።ሌላው ተገልጋይ በበኩሉ ‹‹በሌሎች ቡና ቤቶች የማላውቃትን ሴት ለማውራት ብሞክር ሌሎች ድብደባ የሚፈጸምብኝ እየመሰላቸው ይበሳጩብኛል፤ እዚህ ግን ሁላችንም የመሰለንን እንጨዋወታለን፤ ነገሮች ቀለል ያሉ በመሆናቸውም እንደሰታለን›› ሲል የቡና ቤቷን ምቹነት ገልጿል። የሂቶሪ ቡና ቤት የመስተንግዶ ፖሊሲ ማህበራዊነትን የሚጻረር ቢመስልም አዳዲስ ሰዎች ማግኘት የሚቻልበትን ከባቢ ለመፍጠር የራሱን አስተዋጽኦ ያበረክታል።በዚህም ምንም አይነት ግፊት በሌለበት ሁኔታ ሰዎች በራሳቸው ፍላጎት መግባባት የሚችሉበትን መድረክ ለመፍጠር ምቹ ስፍራ ነው ሲል መረጃው ያመለክታል።ይህ ሁኔታ ሲታይ ቡና ቤቱ ከተቀሩት ቡና ቤቶች አንጻር ሲታይ የበለጠ አካታች ነው ሲል መረጃው ያመለክታል፡፡አዲስ ዘመን ጥቅምት 18/2012 ዘካርያስ
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=21578
[ { "passage": "ኩነቱን ማሰብ በራሱ ያስቃል። \n\n5ሺህ እንጀራን የጠቀለሉ መዳፎች ወደ 5ሺህ የተከፈቱ አፎች ሲምዘገዘጉ ማሰብ በራሱ ትን ያስብላል...!\n\nየፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 4 በጊዮን ሆቴል ነው ይህ እንዲሆን ቀጠሮ የተያዘው። \n\nአሰናጆቹ ክስተቱን ከአንድ ቀን የዘለለ ትርጉም እንዲኖረው ጽኑ ፍላጎት አላቸው። \n\nለምሳሌ ቋሚ የጉርሻ ቀን መሰየም ይፈልጋሉ። በኢትዮጰያ የማይቋረጥ ዓመታዊ የመጎራረስ ፌስቲቫል እንዲኖር ያልማሉ። ከፍ ሲልም ጉርሻን በማይዳሰስ ቅርስነት የማስመዝገብ የረዥም ጊዜ ትልምን ሰንቀዋል። \"ጉርሻ ግን አይዳሰስም እንዴ!?\" ብሎ መጠየቅ የተሰነዘረ ጉርሻን ያስከለክል ይሆን?\n\nአዘጋጆቹ የጉርሻ ባሕል በኢትዮጵያ አራት መቶ ዓመታትን ያስቆጠረ ነው ሲሉም ይከራከራሉ።\n\nአንድ የሚያደርገንን ፌስቲቫል ፍለጋ\n\nኢትዮጵያ ውስጥ ኮስተር ብሎ የሚቆጥር ካለ እያንዳንዱ ቀን በዓል ሆኖ ሊያገኘው ይችላል። ይህ በቋንቋና በባሕል ሀብታም የሆነ አገር ሁሉ ባህሪ ነው። \n\n\"እንደ ጉርሻ ግን የሚያግባባን የለም\" ይላል ቅዱስ።\n\n\"...ጉርሻ እኮ አንዱ ለሌላው የማጉረስ ተግባር ብቻ አይደለም፤ በተጠቀለለው እንጀራ ውስጥ ፍቅር አለ፣ መተሳሰብ አለ፣ አክብሮት አለ...።\" ይላል ከአሰናጆቹ ፊታውራሪው ቅዱስ አብረሃም።\n\nሐሳቡ እንዴት እንደተጠነሰሰ ሲያብራራም የሌሎች አገሮችን ዕውቅ ፌስቲቫሎች ከመመልከት የመጣ \"መንፈሳዊ ቅናት የወለደው ነው\" ይላል።\n\n\"ሕንዶች የቀለም፣ ስፔኖች የቲማቲም፣ ጀርመኖች የቢራ ፌስቲቫል አላቸው። እኛ ግን አውዳመት እንጂ የሚያምነሸንሽ አንድም የጋራ ፌስቲቫል የለንም።\" \n\nሐሳቡን ያመነጩት የሥራ አጋሩ አቶ ዘላለም እናውጋው መሆናቸውን ጨምሮ ያስገነዝብና እንዴት አንድ ቀላል የጉርሻ ተግባር አገርን ወደ አንድነት መንፈስ ሊመራ እንደሚችል ማስረዳቱን ይቀጥላል።\n\n\"ጉርሻ ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት አልያም የገቢ መጠንን አይጠይቅም። ሁላችንንም የሚያግባባን ባሕል ነው፤ ለዚህ ነው ልዩ የሚያደርገው። ደግሞም የኢትዮጵያዊያንና የኤርትራዊያን አንጡራ ባህል እንጂ የማንም አይደለም\" ይላሉ ቅዱስ።\n\nለዚህ የጉርሻ አገራዊ ፌሽታ ባሕል ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድጋፍ ማድረጋቸውን አሰናጆቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል።\n\nየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፐብሊክ ዲፕሎማሲ እንግሊዝ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደብዳቤ በመጻፍ የጊነስ የድንቃ ድንቅ መዝገብ ዋና ጽሕፈት ቤት ጉዳዩን እንዲከታተለው ማድረጉን ቅዱስ አብራርቷል። \n\nጊነስ እና ጉርሻ\n\nጊነስ እንዲህ ዓይነቶቹን ኩነቶች በማኅደሩ ለማስፈር ከ 7ሺህ እስከ 22ሺህ ፓውንድ ይጠይቃል። እነ ዘላለም ይህን ሂደት በማጠናቀቅ ላይ ነበሩ።\n\nሁለት የጊነስ የድንቃ ድንቅ መዝገብ ቢሮ ተወካዮች ይህንን የ5ሺህ ሰዎች ጉርሻ ለመታዘብ በቀጣይ ቀናት አዲስ አበባ እንደሚገቡም ይጠበቅ ነበር። ሆኖም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ጉዟቸው እክል ሳይገጥመው አልቀረም። \n\n\"የድጋፍ ደብዳቤዎችን በመላክ ልናሳምናቸው ሞክረን ነበር\" ይላል ዘላለም። ሆኖም መልካም ፍቃዳቸው አልሆነም። ይህ ማለት ግን ጊነስ ኩነቱን አይመዘግበውም ማለት እንዳልሆነ ጨምሮ ያብራራል። \n\n\"አማራጭ አሠራር አለ። ይኸውም ገለልተኛ ተቋም ቀጥሮ፣ ለ50 ጥንዶች በቡድን አንድ-አንድ ታዛቢ በመመደብ፣ ክስተቱን ያለማቋረጥ በቪዲዮ ቀርጾ በጊነስ መዝገብ ይፋዊ ድረ-ገጽ በማኖር ለዕውቅና ሰርተፍኬት ማመልከት ይቻላል። ይህን ካሟላን ዕውቅናው እንደሚሰጡን ቃል ገብተውልናል\" ይላል ዘላለም።\n\nየጉርሻ ታዛቢዎች ነገር እንግዳ ነው። \n\n50 ሰዎች ሲጎራረሱ ከፊት ለፊት ቆመው እያንዳንዷን ጉርሻ ይቆጣጠራሉ። ልክ የተጫዋቾችን እንቅስቃሴ እንደሚቆጣጠር የእግር ኳስ አራጋቢ ዳኛ፤ ከወዳጅ የተቀባበለው ጉርሻ የተቃራኒ ቡድኑን... ", "passage_id": "c48d30a4f9cc6058747020ddfd25d721" }, { "passage": "አከራዬ “ጤፍ ጨመረ፤ ኑሮ ተወደደ” ብለው የቤት ኪራይ ጨመሩብኝ።እኔ የተወደደውን ጤፍ የምበላ አይመስላቸውም መሰለኝ።አዎን! ከስቼ ሲያዩኝ ምግብ የተውኩ መስሉዋቸው ይሆናል።ኮስምኜ ሲመለከቱኝ የኑሮ ክብደት መለከያ ሚዛን መስያቸው ይሆናል።ለሳቸው የከበደው ኑሮ ለኔ የረከሰ ይመስላቸዋል መሰለኝ፤ ብቻ ኑሮ አጠውልጎኝ አንገቴን ሰብሬ ሲያዩኝ የኑሮ መወደድ ምክንያት እኔ መስያቸው ይሆን እንዴ ብዬ አስባለሁ።አከራዬ የኑሮን መወደድ በምን ሊያውቁት ይችላሉ።ምንያም ሱቅ ሄደው የ5 ብር ሻማ 6 ብር ሆነ ሲሏቸው የአራት ሺህ ቤታቸው “ከዛሬ ጀምሮ አምስት ሺህ ሆኗል፡፡” የሚሉት አከራዬ የኑሮ መወደድ ለሳቸው ጭማሪ እንጂ ኪሳራ እንዴት ሊሆን ይችላል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግልምጫቸው ሲጨምርብኝ አጎንብሼ “ሰላም ዋሉ?”\nስል ዝም በማለት ያልፉኝ የነበሩት አከራዬ ማልጎምጎም ሲጀምሩ ጭማሪ አስበው እደሆነ ሊገባኝ ይገባ ነበር።“ጨምሯል” የሚቀላቸው\nተጨምሮብዎታል የሚነዳቸው አከራዬ የሚቀላቸውን ነገር ሲተገብሩ እኔም የቀለለ ቤት ፍለጋ በረፍቴ ቀን ማልጄ ወጥቼ አምሽቼ መግባት\nአዘውትሬያለሁ።ከስራ ወጥቼ ሌላ ኑሮ የሚያቀልል ቤት፤ ለመቆየት የሚበቃ ማረፊያ ለማግኘት ስማስን ረፍት አጥቻለሁ። ውዶቼ የሰሞኑ ትርፍ ስራዬ ቤት መፈለግ ሆኗል።ይህ አጋጣሚ ብዙ\nደላሎች ለማወቅ አጋጣሚ ሆነኝና በአዲስ አበባ የተለያዩ መንደሮች ውስጥ ያሉ ቤት አከራዮች አመልና በተለያየ መልኩ ለኪራይ ያዘጋጁዋቸው\nቤታቸው በደላሎች አስጎብኚነት አዳረስኩ።ከውካዋ …..”ምንድ ነው?” ከውስጥ የአከራይ ቤተሰብ፤ “ተከራይ ይዤ መጥቻለሁ ክፈቱ….”\nከውጭ እኔን ይዘው ይዞሩ የነበሩት ደላሎች ተደጋጋሚ የቃላት ልውውጥ የመሰንበቻዬ ማጀቢያ ሙዚቃዎች ሆነውኝ ከረሙ። ቤት ለመከራየት ስዞር ስንቱን አከራይ ታዘብኩ! “ብቻህን ነህ?”\n“አዎን”፣ “ታመሻለህ?” “አይ” “ትቅማለህ? ታጨሳለህ?” “ኧረ ፈጥሞ”፤ “ብዙ ጓደኛ አለህ?” “አዎን …” የተለያዩ ጥያቄዎች\n፤ብዙ አዎን፤ አንዳንዱ ደግሞ አይ የሚያሰኙ ይጠይቃሉ አከራዮች።አዎን እና አይ አስከትላው እኔ።ብቻ ብዙ የማይገባ ጥያቄና አሰልቺ\nንግግር ይሰማል።ለመግባባት ስደርስ ሌላ ጥያቄ ያስከትላሉ።ይሄን ጥያቄ መሞገት ያምረኛል።ሰው ሆኖ ከሰው ጋር መኖር ክልክል ነው\nባይን እሞግታለሁ።ሰው ሆኖ ሰውን አታቅርብ የሚልን እከሳለሁ።ለዚያውም ራቅ ብዬ።ታዲያ ነግሬያቸው ነው ’ማልፈው።“ሰው ወይም ጓደኞችህ\nማምጣት አይቻልም ሲሉኝ” ተቃውሞዬን ማሰማት እጀምራለሁ፡፡ እኔ ምለው ተከራዮች ጓደኛ የሌላቸው ያህል የተከራይ ጓደኛ አጥብቀው የሚጠሉበት ምክንያት ምን ይሆን? ከሰው\nጋር መኖር ክልክል ነው ማለት እንዴት ይቀላል? ትዳርን መስርቶ፤ ልጅ ወልዶ በደስታ ለመኖር እየታሰበ ለሌላው አያገባኝም በሚል\n“ለባለትዳርና ልጅ ላለው ቤት አላከራይም” እንዴት ይባላል? ትዳሩን የሚያስተዳድሩት እነርሱ፤ ልጁን የሚያሳድጉት እነርሱ፤ ቤተሰቡን\nየሚመግቡት እነርሱ ይመስል።ብቻውን የሚኖር፣ ሰው የማያምረው፣ የማይስቅ የማይጫወት፣ ማህበራዊ ህይወት የራቀና የጠላ ሊያደርጉን\nቆርጠዋል አከራዮች፡፡ ውዶቼ አከራዮች ተከራይ በቤት ላይ እንደዜጋ መብት እንዳለው አስበን እናውቃለን።መሬቱ በምንም መለኪያ የሀገር\nሀብት ነው።ያ ሀብት ደግሞ በአጋጣሚ ወይም በሆነ መንገድ የአከራዩ ሆኖ ተገኘ።ነገር ግን፤ ተከራዩ በሀገሩ ያለን ማንኛውም ሀብት\nበእኩል የማግኘት ኢኮኖሚያዊ መብቱ ነውና ቢያንስ በተከራይነት መብቱ ሳይነጠቅ በሰላም የመኖር ህጋዊ መብት ይኖረዋል።የኑሮ ጉዳይ\nየሰብዓዊ መብት ጉዳይም ነውና አከራይ የተከራይን ሰብዓዊ መብት የማክበር ህጋዊ ግዴታ አለበት።ተከራይም የአከራይ መብት መጠበቅ\nእንዳለበት ሳይዘነጋ፤ እናም ሰው ሆኖ “ሰው አትቅረብ ሰው አትጥራ” ማለት ተገቢነት የለውም።ያራዳ ልጆች እንዲህ አይነቱ ገጠመኝ\nተገቢ ያለመሆኑን መንገር ሲፈልጉ ወይም ሲወርፉ “አይነፋም” ማለት ያዘወትራሉ።እናም ይሄ ተግባር ‘አይነፋም፡፡’ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቅርቡ ባደረጉት የፓርላማ ንግግራቸው “የቤት ኪራይ ጉዳይ በጥናት\nእልባት ይበጅለታል፤” ማለታቸውን በሰማሁ ጌዜ ለተግባራዊነቱ ፍጥነት ጸሎት ጀምሬ ነበር።ምን ዋጋ አለው ጸሎቴ አልሰመረም መሰለኝ፤\nየአጥኚዎቹን ድምፅ እስካሁን መስማት አልቻልኩም።እንደአከራይ ካልሆነ በቀር ተከራይ ሆኖ ይሄን የማይናፍቅ ይኖራል።የኪራይ ገደብ\nተቀምጦ ህጋዊ የሆነ ምቹ ስርዓት ተዘርግቶ ተከራዮች መበዝበዛቸው ቢቆም ምን አለ።የቤት አከራዮችና ደላሎች የሚስማሙበትን ያህል ተከራዮች ከደላሎች ጋር ቢስማሙ የቤት ኪራይ ዋጋ ከመጨመር ይልቅ\nበወረደ ነበር።አቤት የደላሎችና የአከራዮች ፍቅር፤ በነገራችን ላይ ውዴታቸው በጥቅም ላይ የተመሰረተ ነው።ደላላው አዳዲስ ተከራዮችን\nበማቅረብና ዋጋ ከፍ አድርጎ በመንገር የአከራይን ገቢ ማሳደግና አከራይ ደግሞ ተከራይን ቶሎ ቶሎ በመለዋወጥ የደላላውን ገቢ በማሳደግ\nየንግድ ስምምነት አድርገው እቅድ አውጥተው ተከራይን የመበዝበዝ ስራ በጋራ ለመስራት ቃል ኪዳን አስረዋል። የቃላቸውን ያህል ታምነው የማይገኙት ደላሎችም ምግባርና ቃላቸው የተነጣጠለ፤ ተግባርና እውነታቸው የተራራቀ\nሆኗል።ደላሎቹ ቤት ተጠይቀው ሲያወሩ ሲያስተዋውቁ ለጉድ ነው።የቤቱን ሁኔታ በአንደበታቸው ባለ ምርጥ ቃል ሁሉ አጣፍጠው ይናገራሉ።ቤቱ\nየተሰራው ከምርግ ጭቃ ሆኖ አስሩ ቦታ ተነድሎ እየታየ ሳለ በእምነበረድ ተገጥግጦ የተሰራ ነው።የተነደለው ደግሞ በባህሪው ቤቱ ስለሚሞቅ\nለንፋስ መውጫ ሆን ተብሎ የተሰራ ነው፤ በአፈር የተደመደመ ወለል ልስልስ በሆነ ሲሚንቶ ተሰርቶ ነው እያሉ ሲተረተሩ የሚተረትሩትን\nእየሰሙ ከመታዘብ ውጪ ምን ሊባል ይችላል።እኔ ’ምለው ደላላና ውሸት እስከ መቼ ነው አብረው ተከባብረው ወዳጅ ሆነው የሚዘልቁት?\nበነገራችን ላይ ውዶቼ፤ አሁን ላይ ያለው የኑሮ መወደድና የዋጋ ንረት ምክንያት ሸማቹን ከተጠቃሚ ጋር የሚያገናኙት\nደላሎች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ብዙ ማሳያዎችን መጥቀስ ይቻላል።የቤት ኪራይ ጉዳይ አይደል መነሻዬ? እሱን መሰረት አድርጌ አንድ\nገጠመኜን ላንሳ። እዚሁ አዲስ አበባ ከተማ አራት ኪሎ አካባቢ የሚገኝ አንዱ ኮንዶሚኒየም ግቢ ቤት ጥየቃ ገብቼ ከደላሎቹ የተሰጠኝ\nምላሽ ላስከትል።የሚከራይ ቤት መኖሩን የጠየኩት ደላላ መኖሩ ነገረኝ።የዋጋ ጥያቄ ሲያቀርብልኝ የምችለውን ነገርኩት። ባልኩት ዋጋ አሁን ላይ የተያዘ ቤት መኖሩንና እኔ የተሻለ ዋጋ የምከፍል ከሆነ አሁን ያለው ተከራይ ከቤቱ\nባለቤት ጋር በመነጋጋር ማስወጣት እንደሚችል ነገረኝ።የኔን የነገ እጣ አሰብኩት።እሺ ብዬ ተደራድሬው ብገባ ሌላ ከፍ ያለ ተከራይ\nሲመጣ ልቀቅ የማልባልበት ምንም ምክንያት የሌለኝ ተገፍታሪ ነኝና መገፍተርን ጠላሁ። ምቾት ፈልጎ የሰውን ሰላም መንፈግ፤ መደላደልን ተመኝቶ\nድሎትን ከሰው ማራቅ አይከብድም!? የደላሎች ስራ ተጠቃሚን ከአገልግሎት ሰጪ ጋር አገናኝቶ ተገቢ በሆነ መልኩ ገቢ ማግኘት፤ በሰጡት\nልክ መገልገል መሆን ሲገባው ተገቢ ያልሆነ ጥቅም መቃረም አግባብ አይደለም።አገልግሎት ሰጪው ከአገልግሎት ፈላጊው ጋር የሚያገናኝ\nመላ ሲፈጠር ደላላው ምን ይል ይሆን? አከራዩስ “ሰው አይረባህም፤ ብቻህን ከሆንክ፣ እየሳቅህ የማታወራ ከሆነ፤ ከሰው ጋር የማትኖር\nከሆነ ግባ” ማለቱን ሰው ሲያስፈልገው ሰው ከየት ያስገኝለት ይሆን እንጃ? ምድር ለሁላችንም የኪራይ ቤት ናትና እርስ በርስ ሳንበዳደል\nእንለፍባት።ኪራያችን እስኪያበቃ ብንፋቀርባት ትሰፋናለች። አበቃሁ ቸር ያሰማን! አዲስ ዘመን ነሀሴ 17/2011 ተገኝ ብሩ", "passage_id": "99b179bb2697ea564dd7b28d6a7ca3f6" }, { "passage": "በቡናም በመልካም ተሞክሮዎችም ሰዎችን የሚያነቃቃው ወጣት\\nፊልሞን እና ጓደኞቹ ካፌውን ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ሆኖ ሲከፍት ሁሉም ያላቸውን ከኪሶቻቸውን አዋጥተው ወደ ሠላሳ ሺህ ብር ገደማ አሰባስበው ነበር\n\nሙያው በተለይ ወደውጭ አገር የሚላክን ቡና በተገቢው ልኬታ መቁላትን እንዲሁም የጥራት ደረጃውን ለመለየት መቅመስን እንዲካን አስችሎታል።\n\nይህ ከቡና ጋር ያለው ቅርርብ ነው ለአሁን ሥራው መንገድ የጠረገው።\n\n• «ሰው ሲበሳጭ ማስታወሻ እይዝ ነበር» አዲስ ዓለማየሁ\n\n• የ27 አስደናቂ ፈጠራዎች ባለቤት የ17 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ \n\nአሁን ከዕለታዊ ጊዜው ሰፋ ያለውን የሚወስደው በአዲስ አበባ ከተማ ላፍቶ በሚባለው አካባቢ ከጓደኞቹ ጋር በአንድ የቀድሞ መጋዘን የከፈተውን ካፌ ማስተዳደር ነው።\n\nካፌው የአካባቢው ወጣቶች ቡና ከመጠጣት ባሻገር ነፃ የዋይፋይ አገልግሎት የሚያገኙበት፥ ተደርድረው ከተቀመጡ መፅሐፍት ያሻቸውን ተውሰው የሚያነቡበት እንዲሁም በወር አንዴ የሚያነቃቁ ንግግሮችን የሚያደርጉ እንግዶች ተጋብዘው የህይወት ተሞክሯቸውን የሚያጋሩበት እና የጃዝ ሙዚቃ ምሽቶች የሚስተናገዱበት ስፍራ ነው።\n\nቡና ለኢትዮጵያዊያን አነቃቂ መጠጥ ብቻ አይደለም ይላል ፊልሞን፤ የኑሮ ዘይቤም ነው። በተለይ ቀደም ባለው ጊዜ \"የማኅበራዊ ክንውኖች ማዕከል ነበር። ሰዎች ተገናኝተው መረጃ የሚቀባበሉበት፥ ሕይወት የሚከሰትበት መናኸሪያ ነበር። በደስታ በሐዘንም ሰዎችን አንድ አድርጎ የሚያሰባስብ ስርዓት ነበር\" ሲል ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ያስታውሳል።\n\nፊልሞን ይህ ቡና ተፈልቶ፣ ሰብሰብ ብሎ ኃሳብን የመቀያየር ልማድ በከተሞች አካባቢ እየጠፋ መምጣቱ እንደሚያስቆጨው ይገልፃል፤ ከጓደኞቹ ጋር በከፈተው ካፌ እየታጣ ነው የሚለውን ማኅበራዊ ስሜት ለመኮረጅ የሚጥር ይመስላል።\n\nፊልሞን እና ጓደኞቹ ካፌ የከፈቱበት ቦታ ከሁለት ዓመታት ለሚበልጥ ጊዜ ተዘግቶ የከረመ መጋዘን ነበር\n\nመጋዘኑ. . . \n\nአሁን ፊልሞን እና ጓደኞቹ ካፌ የከፈቱበት ቦታ ከሁለት ዓመታት ለሚበልጥ ጊዜ ተዘግቶ የከረመ መጋዘን ነበር።\n\nዝግ በመሆኑም የአካባቢው ነዋሪዎች ቆሻሻ ይጣል እና ይከመርበት፣ ሥራ የሌላቸው ወጣቶችም እርሱ \"አልባሌ\" ያለቸውን ተግባራት ይከውኑበት ነበር። \n\n\"ቦታው ለመጥፎ ነገር የተጋለጠ አካባቢ ነበር\" ይላል።\n\n• \"ትልቅ ዋጋ ተከፍሎበት ዋጋ ያላገኘሁበት ቢኖር ትምህርት ነው\" \n\n• የረሳነውን ነገር የሚያስታውስ መሣሪያ የፈጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች \n\nቦታውን በዚህ መልኩ ቀይሮ አሁን ያለበት ደረጃ ለመድረስ ግን የነበረው ውጣ ውረድ ታዲያ ቀላል አልነበረም።\n\nየመጀመሪያው ፈተና ቦታው ላይ መጋዘኑን ራሱን የመስሪያ ቦታ ለማድረግ ፈቃድ ማግኘት ነበር። \n\n\"በእኛ አዕምሮ ለሁለት ዓመታት ተዘግቶ የቆየን መጋዘን ለሚሰራ ሰው መስጠት ቀላል ውሳኔ የሚሆን ነበር የመሰለን\" ይላል በወቅቱ እርሱ እና ጓደኞቹ የነበራቸውን እሳቤ ሲያስታውስ።\n\nመጋዘኑ በአካካቢው የመንግስት አስተዳደር ባለቤትነት የተያዘ በመሆኑ፣ ከሚመለከተው አካል የመስሪያ ፈቃድ ለማግኘት ሰባት ወራት ገደማ መመላለስን ጠይቆታል።\n\n\"አንደኛው እና ዋናው ችግር እርሱ ነበር፤ ሰዎች እንዲሰሩ መፍቀድ። ለዚያው ኃላፊነቱን ራሳቸው ወስደው፣ ሊመጣ የሚችለውን ኪሳራ ራሳቸው ተጋፍጠው እና በራሳቸው ወጭ እንስራ ላሉ ሰዎች።\"\n\nፈቃዱ ከተገኘም በኋላ ሌሎች ተግዳሮቶች አፍጥጠው መጠበቃቸው አልቀረም። \n\n• የንድፈ ሐሳብ ትምህርትን ወደ ተግባራዊ ዕውቀት ለመለወጥ የሚተጋው የፈጠራ ባለሙያ\n\n• ከባህላዊ ጃንጥላ እስከ እንጀራ ማቀነባበሪያ፡ የ2011 አበይት ፈጠራዎች\n\nለምሳሌ መጋዘኑ ዘለግ ላለ ጊዜ ተዘግቶ እንደመቆየቱ ውሃ እና የኤሌክትሪክ አገልግሎትን የመሳሰሉ አስፈላጊ መሠረተ ልማቶች አልነበሩትም። \n\nእነርሱን ለማሟላትም የተለያዩ...", "passage_id": "0b812586380bf6c2559a3fc0ad6beb89" }, { "passage": "ባለፉት አመታት እየቀነሰ የመጣው ቡና\nበአለም ገበያ ያለው ዋጋ ዘንድሮም በቅርቡ ታይቶ በማያውቅ መልኩ ማሽቆልቆሉን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ይህን ተከትሎም ከዘርፉ መገኘት ያለበት የውጭ ምንዛሬ እየቀነሰ መሆኑንም ይገልጻሉ፡፡ ሀገሪቱ የቡና የውጭ ምንዛሬ እቅዷን ማሳካት እንድትችል በቡና ግብይት ላይ በትኩረት መስራት እንዳለባት የዘርፉ ባለሙያዎች ያስገነዝባሉ፡፡ የኢትዮጵያ ቡናና\nሻይ ግብይት ባለስልጣን የገበያ ልማትና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር አቶ ዳሳ ዳኒሶ ‹‹በእርግጥም አለም አቀፍ የቡና ዋጋ በዚህ አመት በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል፡፡ ባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረበት ዋጋም ከ20 በመቶ\nበላይ ቅናሽ አሳይቷል፡፡›› ሲሉ በመጥቀስ፤ ምክንያቶቹ ውጪያዊና ውስጣዊ ሊባሉ እንደሚችሉ ያመለክታሉ፡፡ ባለፉት 13 አመታት የቡና አለምአቀፍ ገበያ ዋጋ እየቀነሰ መምጣቱንና አሁን ያለው ዋጋም የዛሬ 13 አመትና ከዚያ በፊት ጋር ሲተያይ ይመሳሰላልም ይላሉ፡፡ ዳይሬክተሩ እንደሚሉት፤በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና ቀርቧል፡፡ ገዢዎችም ተረጋግተው የሚገዙበትና ዋጋ የሚቀንሱበት እድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡ ሁለተኛው ውጫዊ ምክንያት አለም አቀፍ የቡና ግብይቱ በጥቂት ከፍተኛ ቡና ቆዪዎችና ቡና ነጋዴዎች ተጽዕኖ ውስጥ መውደቁ ነው፡፡ በዚህ የተነሳም አንድ ኪሎ ቡና ከአንድ ስኒ ቡና ዋጋ በታች እንዲሸጥ ምክንያት ሆኗል፡፡ ‹‹ ከውስጣዊ ምክንያቶች አንዱ በቡና ግብይት የተሰማሩ አካላት የስነ ምግባር ጉድለት ነው። በላኪዎች መካከል የገበያ ሽሚያ ተፈጥሯል፤ በዚህም ከገበያ ዋጋ በታች ዋጋ ዝቅ አድርጎ መሸጥ ችግር እየሆነ መጥቷል፡፡ ይህም በብቃት ተደራድረን የተሻለ ዋጋ የምናገኝበትን እድል አጥብቧል፡፡››ይላሉ፡፡ በቡና ዘርፍ ለአመታት በኃላፊነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በቡናው ኢንቨስትመንት እየሰሩ የሚገኙትና የህብረት ስራ አባት በመባል የሚታወቁት አቶ ሀይሌ ገብሬ፣‹‹የቡናዋን ዋጋያሳነሰችው ራሷ ኢትዮጵያ ናት››ይላሉ፡፡ ስፔሻሊቲ ቡና ተብሎ ከአለም ቡና በተሻለ ዋጋ ላይ ይገኝ የነበረውን ቡና ሸቀጥ /ኮመዲቲ/ ያደረገችውም አገሪቱ መሆኗን ያስረዳሉ፡፡ቡና ከቡና ተደበላልቆ እየተላከ መሆኑን ጠቅሰው፣ በዚህ የተነሳም የኢትዮጵያ ቡና የድሮ ማዕረጉን እያጣ መምጣቱን ይጠቁማሉ፡፡ ቡናው በመደበላለቁ የኢትዮጵያ ቡና መሆኑን ለማወቅ ገዥዎች መቸገራቸውንም ነው ያብራሩት፡፡ አቶ ሀይሌ‹‹ለቡና ዋጋ መውደቅ አንዱ የአለም ሁኔታ ነው፡፡›› ሲሉ አቶ ዳሳ የጠቀሱትን ሃሳብ ተቀብለው፤ዝቅተኛ ደረጃ ያላቸው ቡናዎች በብዛት እየተመረቱ መሆናቸውንና ገዥዎች የኢትዮጵያን ቡና ለቅመምነት ብቻ እየፈለጉት መሆኑን ይገልጻሉ፡፡‹‹ዝቅተኛ ደረጃ ያለው ቡና ደግሞ በርካሽ ዋጋ ነው የሚሸጠው፡፡ የአለም ቡና በብዛት ገበያ መግባትም ሌላው ችግር ነው፡፡›› ይላሉ፡፡ አቶ ዳሳ የላኪዎች የስነ ምግባር ችግር ብለው የጠቀሱትን የግብይት ችግር አቶ ሀይሌም ይጋሩታል፡፡ ‹‹ቡና ዛሬ የኤክስፖርት ሸቀጥ አይደለም፡፡ ለገቢ ሸቀጥ ማስመጫ እንደ እቃ በእቃ ንግድ /ባርተር ትሬዲንግ/ እንዲያገለግል እየተደረገ መሆኑን ያመለክታሉ፡ ፡ እነዚህ ወገኖች የሚያተርፉት በሚልኩት ቡና እንዳልሆነም ጠቅሰው፤ከቡና በሚያገኙት የውጭ ምንዛሪ ብረትና የመሳሰሉትን ሸቀጦች ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባትና በውድ በመሸጥ መሆኑን ይጠቁማሉ፡፡‹‹ይህ አደጋ ነው፤ በዚህ ሁኔታ ኢትዮጵያ ወደፊትም መቆም አትችልም፡፡›› ሲሉም ያስገነዝባሉ፡፡ ‹‹ንግድ መተማመን ይፈልጋል፤ ይሁንና በሀገሪቱ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ገዥዎች ቡና መግዛት አልቻሉም፤ይደርስልናል አይደርስልንም የሚለውም ፈተና ሆኖባቸዋል፡፡›› ሲሉም ይጠቁማሉ፡፡ አቶ ዳሳ መፍትሄዎቹን የአጭርና የረጅም በማለት ይጠቁማሉ፡፡ ከአጭር ጊዜ አኳያ ቀሪዎቹ ወራት በቡና ግብይት ታሪክ ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና ለገበያ የሚቀርብበት እንደመሆኑ በእነዚህ ወራት ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና በማቅረብ እንዲሁም ጥሩ ዋጋ ፍለጋ በሚል ሰበብ ላኪዎች እጅ የሚገኘውን ቡና ወደ ገበያ በማቅረብ ለማካካስ ይሰራል፡፡ ባለፈው አመት የአለም የቡና ዋጋ በቀነሰበት ወቅት መጠን በመጨመር የውጭ ምንዛሬ ግኝቱን ለማሳካት በተደረገው ጥረት በኢትዮጵያ የቡና ኤክስፖርት ታሪክ ትልቁ የሚባለውን 238ሺ ቶን ቡና መላኩን ጠቅሰው፤ ዘንድሮም ይህን ለማድረግ እየተሰራ ነው ይላሉ፡፡ ‹‹ገዥዎች ሀገር ውስጥ ክምችት ሲበዛ የገቡትን ኮንትራት ጭምር በተለያዩ ምክንያቶች ሀገር ውስጥ እንዲዘገይ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡››ያሉት አቶ ዳሳ፣‹‹ይህን ችግር ለመፍታት በእጃችን ያለውን ክምችት ለመላክ ታቅዶ እየተሰራ ነው ሲሉም ይጠቅሳሉ፡፡ አቶ ዳሳ እንዳሉት፤የግብይት ተዋንያኑን ስነምግባር አለመጠበቅ ችግር ለመፍታት ከብሄራዊ ባንክ ጋር በዝቅተኛ ዋጋ የሚሸጡ አካላትን በማስጠንቀቅ እንዲያስተካክሉ ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን፣ይህን በወሳኝ መልኩ ለመከላከል ዝቅተኛ የኤክስፖርት መሸጫ ዋጋ እንዲወሰን ማድረግ የሚያስችል ልምድ ከሌሎች ሀገሮች መገኘቱንና የውሳኔ ሀሳብም ለመንግስት መቅረቡን ያመለክታሉ፡፡ አቶ ዳሳ፣በቡናው ግብይት ዘርፍ ተገቢ ያልሆነውን ተግባር ለማስቆም በአለም ቡና ዋጋ ተመጣጣኝ ነው ተብሎ የሚታሰብ ዝቅተኛ የመሸጫ ዋጋ መወሰን ለእዚህ ተግዳሮት መሸጋሪያ ነው ተብሎ መታሰቡንም አመልክተዋል፡፡ ይህም በየጊዜው የሚከለስና ብዙ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት እንደሚሆን በመግለጽ፡፡ እንደ አቶ ዳሳ ገለጻ፤የእሴት ሰንሰለትን ለመቀነስ፣ከረጅም ጊዜ አኳያ ዘላቂ የገበያ እድል የሚያስገኙ አማራጮችን በመቅረጽ ባለስልጣኑ እየሰራ ነው፡፡ ከእነዚህም አንዱ ‹‹ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ››የሚባል አለም አቀፍ የቡና ጥራት ውድድር ነው፡፡ አቶ ሀይሌ፣ ለሁሉም ነገር ሰላም ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስ፤ገዥዎች የኢትዮጵያን ቡና የሚፈልጉት ከታህሳስ እስከ ሚያዚያ ባሉት ወራት መሆኑን ያስረዳሉ፤ዘንድሮ በእነዚህ ወራት የኢትዮጵያ ሰላም አስተማማኝ ስላልነበረ ገዥዎች ወደ ኬንያና ታንዛኒያ እንዲሁም ወደ ሌሎች ሀገሮች መሄዳቸውን ያመለክታሉ፡፡ የሰላም ማስፈኑ ስራ ላይ በትኩረት እንዲሰራም ያስገነዝባሉ፡፡ የቡና ገበያው በዱሮው መንገድ መፈጸም ይኖርበታል፤ የቡና ግብይት ገዥዎች በሚፈልጉት አይነት እንጂ እኛ በምንፈልገው መንገድ መሆን የለበትም፤ ሲሉም ያመለክታሉ፡፡ በጥናት ላይ ተመስርቶ፣ ተመክሮበትና በባለሙያ ተመርምሮ ስልጠና እየተዘጋጀ ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት እንደሚኖርበት ይገልጻሉ፡፡ አቶ ሀይሌ፤ መንግስት በቡና ገበያ ላይ ያወጣቸውን ህጎች እንደገና ማየትና መከለስ ይኖርበታል፡፡ አሁን አንዳንድ ችግሮችን ለመፍታት በሚል የወጡ የቡና ግብይት ህጎች ኢትዮጵያን ሊያጠፏትም ይችላሉ። ኢትዮጵያ ቡና ከውጭ አስመጥታ ቆልታ እንድትልክ የወጣ ህግ ሀገሪቱን የልዩ ቡና ባለቤትነቷን ሊያሳጣት ይችላል፡፡ ሲሉ ስጋታቸውንም ያመለክታሉ፡፡ አክለውም፤‹‹በአሁኑ ወቅት ስራ ላይ የሌሉትንና ያሉትን በዘርፉ ታዋቂ የሆኑ ባለሙያዎችን በመሰብሰብና አማካሪ በማድረግ በሳል ህግ ማውጣት ይገባል፡፡ የሩጫ ህጎች ለአደጋ ያጋልጣሉ፤ የበሰለና ዘመን የሚሻገር ህግ ያስፈልጋል፡፡ ››ብለዋል፡፡ አቶ ሀይሌ ‹‹ንግድ ገጽታ ነው፤ የቡና ፍላጎት እየሞላ ከመጣ አዳዲስ ፍላጎት ያለበትን ማሰስ ያስፈልጋል፡፡ ጥናት በማድረግ ምን ያህል አቅም እንዳለን አዳዲስ ፍላጎት የት ይገኛል የሚሉና ሌሎችን በማጥናት ገበያ ማፈላለግ ያስፈልጋል፡፡››ይላሉ፡፡ የቡናና ሻይ ግብይት ባለሥልጣን መረጃ እንደሚያመለክተው በ2011 በጀት አመት 300 ሺ 420- ቶን ቡና ለውጭ ገበያ በማቅረብ ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ነበር፡ በዘጠኝ ወራትም 195 ሺ 574 ቶን ቡና በመላክ 706 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ገቢ ይገኛል ተብሎ ታቅዷል፡፡በእነዚህ ወራት 151 ሺ 211 ቶን ቡና በመላክ 498 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ተገኝቷል፡፡አፈጻጸሙም በመጠን 77 በመቶ ሲሆን በገቢ ደግሞ 70ነጥብ 8 በመቶ ነው፡፡ ለአለም ገበያ የሚቀርብ የቡና ግብይት የውጭ ምንዛሬ ምንጭ እንደመሆኑ መንግስት በዚህ ላይ በትኩረት መስራት ይኖርበታል፡፡ የውጭ ምንዛሬውን ላልተፈለገ አላማ የሚያውሉና ግብይቱን የሚረብሹ ህገወጦችን መስመር ማስያዝም ተገቢ ነው፡፡ የቡና ክምችትም ጎጂ እንዳይሆን በጥንቃቄ መመራት ይኖርበታል፡፡ ተጨማሪ የገበያ አማራጮችን መፈለግም ትኩረትን ይሻል፡፡ እነዚህን ማድረግ ከተቻለ ከቡናው ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይቻላል፤ በእነዚህ ላይ ካልተሰራ ግን እንደ ሀገር አደጋ ይከተላል፡፡አዲስ ዘመን ሚያዝያ 29/2011 በ", "passage_id": "7fe3c96a83749e0755208d5420b80ce9" }, { "passage": "ተጠቃሚዎች የማይከፍሉበት ቁርስ ቤት\\nቲሊያ አዲና ልጇ ኤታን በሳምንት ሶስት ቀን ቁርስ ቤቱን ይጎበኛሉ\n\nካፌው በበጎ አድራጎት ድርጅቶች 'ደስ ያላችሁን፣ የምትችሉትን ክፈሉ ባትከፍሉም ችግር የለም' በሚል ብሂል በመላ እንግሊዝ ከተከፈቱ ካፌዎች አንዱ ነው።\n\nበዚህ ካፌ እንቁላል፣ ዳቦ፣ ፖሬጅ ከሻይ ከቡና ጋር ለተጠቃሚዎች ይቀርባል። የብርቱካን ጭማቂም አይጠፋም። ወዲያ ወዲህ ብለው አረፍ ለማለትም ይሁን ጓደኞችን ቀጥሮ ሻይ ቡና ለማለት የነፃው ካፌ ምርጥ ቦታ እንደሆነ ተጠቃሚዎቹ ይናገራሉ። የነፃው ቁርስ ቤት ድባብ ደስ የሚልና አውዳመት አውዳመት የሚል ነው ያሉም አልጠፉም።\n\nየኢንሹራንስ ባለሙያ የሆነው ጋይ ካፌው በሁሉም የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰዎችን እኩል የሚያደርግ ነው ይላል። ምክንያቱም ገንዘብ ጥያቄ ውስጥ ሳይገባ ማንም ወደ ካፌው ሄዶ ሻይ ቡና እያለ መጫወት ይችላልና።\n\n• ኮሎኔል መንግሥቱን ትግል ለመግጠም ቤተ መንግሥት የሄደው ደራሲ\n\n• የደም ሻጮችና ለጋሾች ሠልፍ\n\nየካፌው ደንበኛ የሆኑት ሺላና የስድስት ዓመት ህፃን ልጇ በሳምንት ሁለት ወይም ሶስት ጊዜ ጎራ ይላሉ።\n\n\"አንዳንዴ የምንመጣው ቀለል ያለ ቁርስ ለመብላት ሲሆን አንዳንዴ ደግሞ ገንዘብ ሲያጥረን ነው። ደግሞ እኔም ልጄም እዚህ ጓደኞች አፍርተናል\" ትላለች ሺላ።\n\nካፌውን ለየት የሚያደርገው ተጠቃሚዎች በልተው ጠጥተው ሳይከፍሉ መውጣት የሚችሉበት መሆኑ ብቻ ሳይሆን ተጠቃሚ ራሱን የሚያስተናግድበት መሆኑም ነው።\n\nየካፌው ተጠቃሚዎች ወላጆች ፣ ህፃናት፣ አዛውንት፣ ባለሙያዎች፣ ጎልማሶችና አካል ጉዳተኞችና መሰሎች ናቸው። የካፍቴሪያውን የጋራ ትልልቅ ጠረጴዛዎች ተጋርተው ሰዎች ስለ ተለያዩ ነገሮች እንዲያወሩ የሚጋብዝ ነው የካፌው ሁኔታ።\n\nየዚህ አይነት ካፌዎች የሚከፈቱት የዕለት ምግባቸውን ማግኘት የሚቸግራቸው ሰዎች ማእድ እንዲቋደሱ ነው። ብዙዎቹ ካፌዎች የሚጠቀሙት ሱፐር ማርኬቶች፣ ሬስቶራንቶችና ሌሎች የለገሷቸውን ምግቦች ነው።\n\n", "passage_id": "23e3c769e4f53ea2abd38a4677219779" } ]
235b2aba826e824a5d636f65c8304686
66e0e14f27a08cecb713d5ae9e964fe9
የፌዴሬሽኑ አማራጭ እቅዶችን የመጠቀም እንቅስቃሴ
ይህ ዓመት እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ቢሆን፤ በስፖርቱ ዓለም በተለይ በዚህ ወቅት በርካታ ውድድሮች፣ ጉባኤዎችና ሥልጠናዎች ሊካሄዱ ይችሉ ነበር። ነገር ግን ሳይታሰብ ተከስቶ ዓለምን ባዳረሰው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) ወረርሽኝ ምክንያት ውድድሮች ብቻም ሳይሆኑ በርካታ ጉዳዮች በታቀደላቸው ሁኔታ እንዳይካሄዱ ማድረጉ ግልጽ ነው። ታዲያ የስፖርት ማህበራትና ሌሎች ተቋማት እቅዶቻቸው በዚህ መልኩ አቅጣጫቸውን ሲስቱ ምን ዓይነት አማራጮችን ተጠቀሙ? ከዓመት እስከ ዓመት በሩጫ ላይ ከሆኑና በሥራ ከሚወጠሩ ፌዴሬሽኖች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው። የፌዴሬሽኑ የሥልጠና ጥናትና ምርምር ዳይሬክተሩ አቶ ሳሙኤል ብርሃኑ የሚናገሩት አላቸው። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቻምፒዮናን ጨምሮ የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን፣ የወጣቶች ቻምፒዮና እንዲሁም ሌሎች ውድድሮች ፌዴሬሽኑ በዚህ ዓመት ያላካሄዳቸው የውድድር ዘርፍ እቅዶች ናቸው። በሥልጠና ጥናትና ምርምር ዘርፍ ደግሞ የዚህ ዓመት ዋነኛ እቅድ የነበረው ባለሙያዎችን ማብቃትና መመዘን መሆኑን ዳይሬክተሩ ይገልጻሉ። ዳኞችና አሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ሥልጠናዎችን አግኝተው ደረጃቸውን እንዲያሳድጉ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ባለበት ወቅት ግን የዓለም ትኩሳት የሆነው ጉዳይ በመከሰቱ እንደታሰበው ማስኬድ አልተቻለም ይላሉ። በተለይ ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ወር ድረስ የሥራ ክፍሉ በዚህ ለማሳለፍ ያስቀመጠው እቅድ ወደ መሬት ሳይወርድ ቀርቷል። በዓመቱ ኦሊምፒክና ሌሎች ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ መሳተፍና ብሔራዊ ቡድንን የማዘጋጀት እቅድም ተመሳሳይ ዕጣፈንታ ገጥሞታል። ለብሔራዊ ቡድን የተጠሩ አትሌቶችም ተበትነው ወደየ ቤታቸው ሄደዋል። ይህ ሁሉ ሲሆን ፌዴሬሽኑ ግን ሥራውን ከማቋረጥ ይልቅ ሌሎች አማራጮችን መጠቀምን መርጧል። ዋናው የአትሌቶች ጤንነትና በብቃት መቆየት በመሆኑም የተሻለ ያለውን ተግባር ሲከውን እንደቆየ ዳይሬክተሩ ያስረዳሉ። ፌዴሬሽኑ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ስፖርታዊ ክዋኔዎችን ማካሄድ አዳጋች መሆኑን በመገንዘቡ ቀደም ብሎ ወደ ዝግጅት መግባቱን ይጠቁማሉ። አትሌቶች ሥልጠና ማቋረጣቸውን ተከትሎ ከስፖርቱ እንዳይርቁ እንዲሁም አሰልጣኞችም ከአትሌቶቻቸው በጋራ ያላቸው ግንኙነት እንዳይቋረጥ ምን ማድረግ ይገባል? የሚለውን በማሰብም ነው በቴሌቪዥን ስርጭት በትምህርትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ፕሮግራሞች እንዲተላለፉ የተደረገው። በዚህም የስፖርቱ ባለሙያዎችን በማካተት በሦስት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለስድስት ሳምንታት ለአትሌቶች ጠቃሚ የሆኑ መርሃ ግብሮች ሲተላለፉ ቆይቷል። የመርሃ ግብሩ ይዘትም ሥነ-ልቦና፣ ሥነ-ምግብ፣ ሕክምና፣ ማህበራዊ ግንኙነት፣ የተምሳሌት አትሌቶች መልዕክት፣ የአሰልጣኞች ምክረ ሃሳብ እንዲሁም አትሌቶች በአጠቃላይ ምን ማድረግ ይገባቸዋል የሚለውን ያጠቃለለ ነበር። ከቴሌቪዥን ስርጭቱ ባሻገር በፌዴሬሽኑ ይፋዊ ማህበራዊ ገጽ (ፌስ ቡክ) እንዲሁም በድረገጹ አማካኝነትም አትሌቶችን ተደራሽ ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህ ሂደትም ፌዴሬሽኑ ማድረግ የሚገባውን መልካም ተግባር ማከናወኑን ለመታዘብ ተችሏል። አትሌቶችና ሌሎች ባለሙያዎችም ለዚህ የሚሰጡት ግብረ መልስ ጥሩ ሥራ መሰራቱን የሚያሳይ ነው። አትሌቶች ቤታቸው በሚሆኑበት ወቅት ምን መስራት እንዳለባቸው ግራ ተጋብተው ነበር የሚሉት ዳይሬክተሩ፣ አሰልጣኞች በሚሰጧቸው አቅጣጫ ተጠቃሚ ሆነዋል። በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙና እነዚህን አማራጮች የማያገኙ አትሌቶችን ደግሞ አሰልጣኞች በስልክና በሌሎች መንገዶች በተመሳሳይ እየረዷቸው ይገኛሉ። አሁን ካለው ሁኔታ አንጻር ጥናት መስራትና አትሌቶችን ማግኘት ባይቻልም በተለያዩ መንገዶች ምስጋናቸውን ያደርሳሉ። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምክር የሚጠይቁ አትሌቶች ቁጥር መበራከትም ይህንኑ የሚያመላክት ነው። አሰልጣኞች በበኩላቸው ወትሮ ከነበረው ሁኔታ በተሻለ መልኩ ከፌዴሬሽኑ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያጠናከሩ ሲሆን፤ ግብረመልስ በመስጠትም አጋርነታቸውን እያሳዩ ነው። ከዚህ በኋላም ፌዴሬሽኑ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት ጎን ለጎን መርሃ ግብሩን በአዲስ መልክ የሚያስቀጥልም ይሆናል። የሀገርን ስም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያስጠራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በሚደረገው ርብርብ ቅድሚያ ተሰላፊ መሆኑን በተግባር በማሳየት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። ከዚህ ቀደም በግሉ፣ ከሌሎች ተቋማት ጋር እንዲሁም በአትሌቶቹ አማካኝነት በገንዘብ እንዲሁም በቁሳቁስ የድርሻውን በማድረግ ላይ ይገኛል። አመራሩና ሌሎች ታዋቂ አትሌቶችም ለሕዝቡ መልዕክት በማስተላለፍ ላይ ናቸው። አሁንም ከዚህ በላቀ መልኩ ለመስራት የሚያስችል ተነሳሽነት አለ። እንደሚታወቀው በዚህ ወቅት ውድድሮችና ሌሎች የሥልጠና መርሃ ግብሮች ተቋርጠዋል። በዚህ ምክንያት ፌዴሬሽኑ ቀድሞ የያዛቸውን እቅዶች በመቀየር የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮች ላይ ለማተኮር ማቀዱን ዳይሬክተሩ ይጠቁማሉ። በዚህም ከፌዴሬሽኑ ስፖንሰር ማልታ ጊነስ ጋር በመሆን በቴሌቪዥን የሚተላለፉ መርሃ ግብሮችን በመስራት ላይ ነው። በአንድ ወር ውስጥ ለ16 ቀናት ያህል የሚተላለፈው መርሃ ግብሩ እንደ ቀድሞ በምክረ ሃሳብ ላይ ሳይሆን በተግባር ላይ የተመሰረተ እንደሚሆንም ታውቋል። በአትሌቶች ዘንድ ተምሳሌት የሆኑና ዝነኛ አትሌቶች እንዲሁም ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ሲሆን፤ ተከታታይነት ያላቸው እንቅስቃሴዎች በምን መልኩ እንደሚሰሩ የሚያሳይም ይሆናል። እንቅስቃሴው ከአትሌቶች ጋር ብቻ ሳይሆን ሌላውን ኅብረተሰብም የሚጠቅምም ነው የሚሆነው። ለዚህ የሚሆነው ዝግጅት በመጠናቀቁ በቅርቡ አየር ላይ የሚውልም ይሆናል። በዚህ ወቅት አብዛኛው ኅብረተሰብ ትኩረቱ የመገናኛ ብዙኃን ላይ በመሆኑ፤ ትብብራቸውን እንዳያቋርጡ ይጠይቃሉ። ከቴሌቪዥን ባሻገር በርካቶችን ተደራሽ የሚያደርጉ የመገናኛ ብዙኃን አብሮነታቸውን እንዲያሳ ዩም ጠይቀዋል።አዲስ ዘመን ግንቦት 19/2012 ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=33175
[ { "passage": "የኢፌዲሪ ባህልና ወጣቶች ሚኒስቴር ሂሩት ካሳ (ዶ/ር)፣ የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር፣ አሸብር ወ/ጊዮርጊስ (ዶ/ር)፣ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝደንት፣ የዘጠኙ የክልልና የ2ቱ ከተማ መስተዳድር የስፖርት ኮሚሽን አመራሮች እና እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ እና ስድስት የሥራ አስፈፃሚ አባላት በውይይቱ ላይ ተካፍለዋል።በዶ/ር ሂሩት ሰብሳቢነት በተመራው በዚህ የውይይት መድረክ አቶ ኢሳይያስ ጂራ በ2011 በእግርኳስ የተፈጠሩ ያሉ ችግሮች ምን እንደሆኑ በዝርዝር በማስረዳት እየተፈጠሩ ያሉ አለመግባባቶችን ለመቀነስ እንደመፍትሄ በጊዜያዊነት በሁለት ምድብ የተከፈለ 24 ቡድኖች የሚካፈሉበት ውድድር ማዘጋጀት እንዳስፈለገ ለተሰብሳቢው ገልፀዋል።” ይህ ውሳኔ የተወሰነው ክለቦች ሳይማከሩበት እና ጥናትን መሠረት ያላደረገ መሆኑን በቅወቱም በሥራ አስፈፃሚ ስብሰባ ወቅት አፅኖት ሰጥተን ተናግረን ነበር። ሆኖም እኛ በማናቀው መልኩ የተወሰነ ውሳኔ ነው።” በማለት አንዳንድ የፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚ አባላት መናገራቸውን ተከትሎ በፌዴሬሽኑ አመራሮች መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበረ ሰምተናል።የክልል እግርኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች በተለይ የአማራና የትግራይ እግርኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች በበኩላቸው 24 ቡድኖች ሆነው አማራና ትግራይ ክለቦች እንዳይገናኙ በማለት የተወሰነው ውሳኔን እንደማይቀበሉት፤ እግርኳስ የሠላም እና የማቀራረቢያ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል። አዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጥናት በማስጠናት በውስጥ ውድድር ተካሂዶ በኃላም በኢትዮጵያ ሻምፒዮና ውድድሩ ይጠናቀቅ በማለት ያቀረበው ሀሳብ የሚያስመሰግን ሆኖ ሳለ ፌዴሬሽኑ እንደ መፍትሄ ከመቀበል ይልቅ የራሱን መንገድ መከተሉ ስህተት መሆኑን እና የክልል እግርኳስ ፌዴሬሽኖች ጋር ተቀራርቦ የመስራት ችግሮች እንዳለበት ተናግረዋል። የኦሊምፒክ ፕሬዝደንቱ በበኩላቸው 24 ቡድኖች መሳተፋቸውን እንደማይደግፉ እና ከኦሊምፒክ መርህ አንፃር ክልሎች እና ህዝቦች እንዳይገናኙ ማድረግ ተገቢ አለመሆኑን ገልፀዋል።የመድረኩ ሰብሳቢ በበኩላቸው “ፊፋ ላስቀመጠው ደንብ እና ህግ ተገዢ በመሆን፤ አባል ሀገራቱም ለተቀመጠው መመርያ ተገዢ እንዲሆኑ በማድረግ እያስተዳደረ በመገኘቱ ነው ተፈሪና ተቀባይነት ያለው ተቋም የሆነው። እናተም ላወጣችሁት ደንብ እና መመረያ ተገዢ በመሆን እግርኳሱን መምራት ይገባችኋል።” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።በመጨረሻም በፌዴሬሽኑ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን የሀሳብ ልዩነት በውስጥ እንዲፈቱ፤ በ24 ቡድኖች ለሁለት የተከፈለው ውድድር ለጊዜው እንዲቆም እና ባለ ድርሻ አካላት ክለቦች በተገኙበት ውይይት በማድረግ ዘላቂ መፍትሄ እንዲቀርብ ተወስኗል። ስፖርት ኮሚሽንም ጉዳዩን በጥንቃቄ እንደሚከታተለው ሰምተናል።", "passage_id": "e964f1fbf044458a55ebdf2193bc3446" }, { "passage": "የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኩባንያ ሰሞኑን ስብሰባ ማድረጋቸው ታውቋል።የስብሰባው ዋና አላማ በቀጣይ የኢትዮጵያ ሊጎች የሚጓዙበት መንገድ ላይ መምከር ሲሆን ከኮቪድ-19 ስርጭት መቆጣጠር ከተቻለ በኋላ በምን አይነት አካሄድ ውድድሮች መከናወን ይኖርባቸዋል የሚል ውይይት መደረጉን ሰምተናል። ምናልባትም አሁን እየተከናወነበት የሚገኘው ፎርማት ሊለወጥ እንደሚችልም ተገምቷል።የውይይቱ ዝርዝር ሀሳብ እና ውሳኔዎች በቀጣይ እንደሚገለፁ የሚጠበቅ ሲሆን አንዳንድ ክለቦች እያደረጉት ከሚገኙት የዝውውር እንቅስቃሴ በተቃራኒ አመዛኞቹ ክለቦች የፎርማቱ ሁኔታ ከለየለት በኋላ ወደ ዝውውር ለመግባት እንዳሰቡ ተሰምቷል።በ1936 የተጀመረውና ከአፍሪካ ቀደምት ሊጎች አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ የሊግ ውድድር በምስረታው ዓመታት በአዲስ አበባ ክለቦች ብቻ ሲደረግ ቆይቶ በ1940ዎቹ አጋማሽ በሦስት ከተሞች ደርሶ መልስ የተካሄደ ሲሆን ከስልሳዎቹ እስከ 1989 ድረስ የየክፍለ ሀገራት ሻምፒዮና ተደርጎ በማጠቃለያ ውድድር አሸናፊው እንዲለይ ተደርጓል። ከ1990 ጀምሮ ደግሞ ላለፉት 22 ዓመታት ደግሞ በወጥነት በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ክለቦች በደርሶ መልስ ውድድራቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ።ሶከር ኢትዮጵያ ጉዳዩን እየተከታተለች የሚኖሩትን አዳዲስ መረጃዎች የምናደርሳችሁ መሆኑን እንገልፃለን።", "passage_id": "7b7510143554a0e9077e20299896d6b0" }, { "passage": "ኢትዮጵያ በክለብ ፈቃድ አሰጣጥ ጠንክራ መስራት እንደሚገባት የካፍ ክለብ ፈቃድ አሰጣጥ ማናጀር አስታወቁ። በቀጣዩ የውድድር ዓመት ሁሉም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች የሕጋዊነት ፈቃድ የምስክር ወረቀት ለመጀመር ዝግጅት መጠናቀቁን ፌዴሬሽኑ ገልጿል። ኢትዮጵያ በክለብ ፈቃድ ጠንክራ መስራት እንደሚገባት በተደጋጋሚ ቢገለጽም፤ አሁንም ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ የካፍ ክለብ ፈቃድ አሰጣጥ ማናጀር አህመድ ሃራዝ ማሳሰባቸውን ፌዴሬሽኑ በድረ ገጹ አስነብቧል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም በ2012 ዓ.ም የውድድር ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ የሚሆኑት 16ቱም ክለቦች ለሀገር ውስጥ መወዳደሪያ የሚያገለግል የሕጋዊነት ፍቃድ ማግኘት እንዳለባቸው አስታውቋል። ለዚህም ዝግጅቱ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ እስከ ግንቦት 30/2011ዓ.ም ክለቦች ፊት ለፊት ግምገማ ለማድረግ መታቀዱን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የክለብ ፈቃድ አሰጣጥ ማናጀር አቶ ተድላ ዳኛቸው ጠቁመዋል። ፍቃዱን ለማግኘት ክለቦች አምስት መስፈርቶችን ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው ድረገጹ አስነብቧል። መስፈርቶቹም፤ የመወዳ ደሪያ ቦታ መያዝ፣ የወጣቶች ልማት፣ የሰው ሀብት አስተዳደራዊ መዋቅር፣ የፋይናንስ ሥርዓት (የገቢ እና ወጪ ሥርዓት) እንዲሁም ሕጋዊነት መስፈርት ናቸው። ነገር ግን ሁሉንም መስፈርት በአንዴ ማሟላት ክለቦችን እስከማፍረስ የሚያደርስ በመሆኑ፤ አንዳንድ ነገሮችን በስትራቴጂክ እቅድ በመያዝ ተግባራዊ መድረግ አስፈላጊ እንደሆነም ነው ፌዴሬሽኑ ያረጋገጠው። በተጠናቀቀው ወር በኡጋንዳ ካምፓላ በካፍ ባለሙያዎች ከየሀገራቱ ለተውጣጡ ተወካዮች ሥልጠና ተሰጥቷል። በዚህ ሥልጠና ላይም ሀገራቱ ለሁለት ተከፍለው ከካፍ ክለብ ፈቃድ ኢንስትራክተሮች ጋር ውይይት ተደርጓል። ኢትዮጵያ በተደለደለችበት ምድብ ሁለትም ከናይጄሪያ እና ጋና ኢንስትራክተሮች ጋር ግምገማ እና ውይይቱ ተካሂዷል። በወቅቱም ፌዴሬሽኑ ዕቅዱን ያቀረበ ሲሆን፤ በአህጉር አቀፍ ውድድር ተካፋይ ክለቦች ፍቃድ መሰጠቱም ተጠቁሟል። ይሁን እንጂ በሀገራዊ ፍቃድ ላይ የጥሪ ሂደት ቢተላለፍም ፍቃድ አልተሰጠም። በተጨማሪም የመጀመሪያ ውሳኔ ሰጪ አካል መቋቋሙን፤ በተለይም የሕግ እና የሂሳብ ባለሙያ ያሉት እንደሆነ ተጠቅሷል። የይግባኝ ሰሚ አካሉም ከዚህ በፊት የተቋቋመ ቢሆንም በዚህ ወቅት አባላቱ የሌሉ መሆኑን ተከትሎ በተደራቢነት እንዲሰራ ሃሳብ መኖሩ ተነስቷል። በተሰጠው አስተያየት ላይም ሀገሪቷ ከክለቦች ፈቃድ አሰጣጥ ባሻገር የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው በድጋሚ መደራጀት እንዳለበት ተጠቁሟል። በስትራቴጂክ ፕላን በመጠቀምም ከፕሪሚየር ሊጉ በመቀጠል በከፍተኛ ሊግ እና በተዋረድ ባሉ ሊጎች ላይ መስራት እንደሚገባ ማናጀሩ ገልጸዋል። እስከ ሰኔ 23/2011 ዓ.ም ድረስም የሚታይ ሥራ መከናወን እንዳለበት አሳስበዋል።አዲስ ዘመን ግንቦት 5/2011 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "e010954f00776a95cd5a1adb921aec16" }, { "passage": "(መረጃው የእግርኳስ ፌዴሬሽኑ ነው)ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኮሮና ቫይረስ በዓለም ብሎም በሀገራችን ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ውድድሮች ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጡ እንዲሁም ሀገራችን ላይ እየደረሰ ያለው የወረርሽኝ መጠን እየጨመረ መምጣቱ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ በመሆናችን በቀጣይ የሚደረጉ ውድድሮች መሰረዛችን ይታወቃል፡፡ፊፋ ሚያዚያ 07/2020 በሰርኩላር ቁጥር 1714 ኮቪድ 19 ባቀረበው ምከረ ሀሳብ  ክለቦች እና ተጨዋቾች የኮቪድ 19 አለም አቀፍ ወረርሽኝ ለሁሉም የሰው ዘሮች የመጣ በመሆኑ ከኮንትራት ማስጠበቅ እና ኮንትራትን በስምምነት ከመቀነስ ጋር በተገናኘ ክለቦች እና ተጫዋቾች እግር ኳስ ሰብዓዊነትን የሚያበረታታ በመሆኑ ባጋራ በመመካከር ይህንን ክፉ ጊዜ እንዲወጡት ምክረ ሀሳብ አቅቧል፡፡ በሀገራችን የሚገኙ ጥቂት ክለቦችም ይህንን የፊፋ ምክረ ሀሳብ በመቀበል ተግባራዊ በማድረጋቸው የመጣውን ችግር በጋራ በመፍታት ላይ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ በርካታ ክለቦች የኮቪድ 19 ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ደመወዝ አለመክፈል እንዲሁም  በዲሲፒሊን እና ይግባኝ ሰሚ የተወሰነባቸውን ወሳኔ ተግባራዊ እያደረጉ አለመሆኑን ከሚመጡልን አቤቱታዎች ተረድተናል፡፡በመሆኑም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፒሊን መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 80/1/ መሰረት ክለቦች የተጫዋቾችን፤ የአሰልጣኞች እና የህክምና ባለሙያዎችን መብት በውላቸው መሰረት እንዲያሟሉ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ስለሆነም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክለቦች ያልከፈሉትን ደመወዝ ኮንትራታቸውን በማክበር ወይም ከተጫዋቾች ጋር በመወያየት የደመወዝ እና በዲሲፒሊን የተወሰነላቸውን ክፍያ እሰከ ሐምሌ 5/2012ዓ.ም በመክፈል ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሪፖርት እንዲያደርጉ እያሳሰብን፤ ይህ ተግባራዊ ሳይሆን ቢቀር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቀጣይ እርምጃ ክለቡ ላይ እንደሚወስድ ያሳውቃል ፡፡", "passage_id": "9ab6b419124311624dc3fdafee1ecbe1" }, { "passage": "አዲሱ የፌዴሬሽን የፕሬዝዳንት እና የስራ አስፈፃሚ አባላት ትላንት በነበረው መደበኛ ስብሰባቸው የፌዴሬሽኑ የአሰራር እና አደረጃጀት ችግሮችን የሚፈትሽ እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን  በጥናታቸው እንዲያስቀምጡ አራት ግለሰቦችን በመምረጥ ኮሚቴ አቋቁሟል።ሰኔ 14 የተሰበሰበው አዲሱ የፌዴሬሽን አመራር በፌዴሬሽን ውስጥ ያለውን ልማዳዊ አደረጃጀትና እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም ወደ ለውጥ እንቅስቃሴ ለመግባት በማሰብ የፌዴሬሽኑን አሰራር እና አደረጃጀት ዓለም ወደደረሰበት ዘመናዊ አሰራር ለመቀየር እንዲያስችል አሁን ያለውን ሁኔታ በሚገባ መርምረው በቀጣይ መሆን ስለሚገባው አደረጃጀት የመፍትሄ አቅጣጫ እንዲያስቀምጡ በማሰብ በእግርኳሱ የረዥም አመት ልምዳቸውን ከግምት ባስገባ መልኩ አራት ግለሰቦችን መምረጣቸው ታውቋል።በጥናት ቡድኑ የተካተቱት ግለሰቦች የአአ ከተማ ክለብ ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ፣ የአዳማ ከተማ እግርኳስ ክለብ ስራ አስኪያጅ አቶ አንበሴ መገርሳ፣ ከወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ ተወካይ ባለሙያ አቶ ተሾመ ፣ የፌዴሬሽኑ ምክትል የፅህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ት መስከረም ታደሰ ሲሆኑ ጉዳዮችን እየተከታተሉ እንዲያስፈፅሙ ከፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ በኩል አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ ተመድበዋል።ለዘመናት የሚነሱትን የፌዴሬሽኑን የተዝረከረከ ባህላዊ አሰራርን ስር ነቀል በሆነ መልኩ መፍትሄ ያመጣል ተብሎ በታሰበው በዚህ ጥናት ላይ ተሳታፊ የሆኑት ግለሰቦች ዛሬ 10:00 ላይ በፌዴሬሽኑ ቢሮ በመገናኘት ስብሰባ የሚያደርጉ መሆናቸውን የሰማን ሲሆን ጥናታቸውን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ በዝርዝር ለፌዴሬሽኑ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።", "passage_id": "1ac8465cad5f2a383915e708a65c2146" } ]
8f151b88427816f5e7037b4b6eab67fb
19046af0a58c3d78f9f7d1f503e4bfae
እነ አፋጀሽኝ…
 ‹‹እንዲህ አይነት ጭንቅ ጥብብ ያለ የአፋጀሽኝ ዘመን በእድሜዬ አላየሁም›› አሉ ሼሁ። የተዘባረቀ፤ የተጭበረበረ፤ የተወናገረ፤ የተወሳለተ ዘመን። ‹‹አላህ አላህ›› አሉ መለሱና። ሼሁ የእድሜ ባለጸጋ የተከበሩ አንቱ የተባሉ አባት ናቸው። መካሪ ዘካሪ አስታራቂ በመንደሩ በሰፈሩ በሀገሩም የተከበሩ። ሼሁ መኖሪያ አቅራቢያ አብረው ረዥም ዘመን የኖሩ ጎረቤታቸው ቄስ አሉ። መምሬ ደምሌ። ሁለቱም የብዙ ልጆች አባት ልጅና የልጅ ልጅ ያዩ ናቸው። ቃላቸው እንደ ፈጣሪ ቃል ይከበራል። ደግሞም ይፈራል። ሁለቱም ወደ የቤተ እምነታቸው ሲሄዱ ቦታው ቢለያይም አብረው እያወጉ እየተማከሩ እየተወያዩ ነው የሚሄዱት። አይለያዩም። የሀገር አድባሮች። ለሼሆቹም ለቄሶቹም እድሜና ጤና አብዝቶ ይስጥልን፡፡ ‹‹ቄስ፤ መነኮሳት ሼሆችን የሚያርድ ፤ መስጊድና ቤተክርስቲያን የሚያነድ የሚያጋይ የሚያቃጥል ነፍሰ በላ አውሬ ሕዝቡን ሲጨርሰው በሀገር ሲዘምት ፈጣሪ እንዴት አይቆጣ›› አሉ መምሬ ደምሌ በስጨት ብለው። ሼሁ በረዥሙ የተንዠረገገውን ጺማቸውን በሀሳብ ተውጠው እያልመዘመዙ በሚሰሙት በሚያዩት በሚነገራቸው የሰላም እጦት፤ የዜጎች መገደል፤ የእናቶችና የሕጻናት እንክርት፤ ስደት፤ መጠለያ ማጣት ሁሉ ‹‹አቤቱ በደላችንን ይቅር በለን፤ አላህ›› እያሉ ተንሰቅስቀው ያለቅሳሉ። ያዝናሉ። ‹‹ኧረ ይህች ሀገር እንዲህ አልነበረችም ምን መጣብን›› ይላሉ። አብዝተው ይጨነቃሉ። ይጠበባሉ። ያዝናሉ። ሼሁ የጥንቱ የወሎ ሼሆች ዝየራ ትዝ አላቸውና በለሆሳስ ማንጎራጎር ጀመሩ። በእንዲህ አይነት ዘመን… አይተኙም ይነቋል…፤ መሳሪያውን ስሎ በየጎራው ዘልቋል፤ አሉ። ክፉ ዘመንን የሚያስታውሳቸው ነበር። ለጠቁና ፈጣሪ ለሀገራችን ለሕዝቧ ምህረቱን አብዝቶ ያውርድልን አሉ። ዱአቸውን ቀጠሉ ሼሁ። መለስ ብለው ልመና ዱአ ነው ደጉ የጠፋውን የሚያለማው፤ ጠማማውን የሚያቀናው፤ ክፉውን የሚያገራው፤ ዱአ (ጸሎት) ነው። ሁሉም እንደ የእምነቱ ወደ የፈጣሪው መጸለይ ነው የሚበጀው አሉ ሼህዬ። ‹‹ሌላማ ምን ይባላል መቸስ›› አሉ በቁጨት እየተብሰለሰሉ። መምሬ ደምሌ ከሼሁ ቀበል አድርገው፤ ‹‹ጦቢያ የምትባል ሀገር እንደሁ የሰው ዘር መነሻ፤ እስላም ክርስቲያኑ በአንድ ተፈትሎ፤ በአንድ ተገምዶ፤ በአንድ ተሰድሮ፤ ከጥንት እስከ አሁን የኖረባት ወደፊትም የሚኖርባት እግዚአብሔር የባረካት ሀገርና ምድር ናት። ልጆቿ እሾህና አሜከላ እየሆኑ ሲጥሏት ሲያነሷት ይኖራሉ። ግን ግን አትወድቅም። አትጠፋም። ጠላቶቿ ግን ይጠፋሉ›› አሉና ፊታቸውን ወ ደ ሼሁ አዞሩ መምሬ። በሰርግ በደስታ በፌሽታ በሀዘኑ በበዓሉ አብረን ሁነን፤ አብረን በልተን ጠጥተን ተጫውተን፣ ድረን፣ ኩለን ኖረናል። ዘመናትን ገፍተናል። የወደፊቱን እሱ ያውቃል። እንግዲህ መቸም ተፈርቶ አይሞት፤ ዱአ የበዛ ዱአ ማድረግ ያስፈልጋል መምሬ ሰሙኝ አሉ ሼሁ በተራቸው። መምሬ ቀጠሉ፡፡ ‹‹እንዲህ አይነት መላቅጡ የጠፋ ወንድም ወንድሙን የሚገድልበት ግዜ በሀገራችን አይተን ሰምተንም አናውቅም። በብርቱ አዝነናል። ፈጣሪ ሀዘናችንን አይቶ ምላሽ ይሰጣል። ሀገር መበጥበጥ፤ ሰላሟን ማናጋት ሕዝቡን ሰላም መንሳት፤ መንገድ መዝጋት፤ ቤተ እምነት ማቃጠል ዘር ለይቶ ማጥቃት፤ በሰይጣኖች የተቀነባበረ ሴራ መሆኑን ሕዝበ ሙስሊሙም ሕዝበ ክርስቲያኑም ጠንቅቆ ያውቃል። እንግዲህ እንደየ እምነታችን በእነአፋጀሽኝ ላይ እርግማን አውርደናል›› አሉ መምሬ ደምሌ። ሕዝብን ለመለያየት ደም ለማቃባት እርስ በእርሱ ለማባላት ያሴሩት ሴራ ሁሉ ተበትኖ ይጠፋሉ። ሴራቸው እንደ ጉም እንደ ጠዋት ጤዛ ይበናል። የተመኙትን ወንበር አይቀመጡበትም። የሰበሰቡትን ሀብት አይበሉትም። የተከበረ የሰውኛ ቀብር እንኳን አያገኙም። ኢትዮጵያን እናጠፋለን ብለው ሲነሱ ጸባቸው ከሕዝቧ ጋር ብቻ አይደለም። ጠብቆ አጽንቶ ከፈተናዎች ሁሉ እያወጣ ካኖራት ታላቅ አምላኳ ጋር ነው። ይጠፋሉ። ድህነትን መከራን ከትውልድ ትውልድ ይወርሳሉ። ጉልበታቸውና ሴራቸው ይሰበራል። ዝንተ ዓለም በድህነት በስደት በረሀብ በመከራ እየተገረፉ ተንከራተው ይኖራሉ። መሳሪያ ዎቻቸው ይደነብሻሉ። አይተኩሱም። አይመቱም። ቀኑ ጨለማ ይሆንባቸዋል። ኢትዮጵያ ግን ሴራቸውን ሁሉ እንደጉም አብንና አጥፍታ ተመልሳ ታላቅ የተከበረች ሀገር ትሆናለች። የሚሻለው ባይነኳት ነበር። አምላኳ እጅግ ኃይለኛ ብርቱ የማይንበረከክ የማይተኛ ከነኩት የማይለቅ በቀለኛም ነው። እነአፋጀሽኝ የሼሆቹንና የቄሶቹን እምባና ሀዘን ልኩን አላወቁትም። የአባቶች እምባስ የት ያደርስ ይሆን? አህዛብ ወዮልህ ማለት ይሄኔ ነው። የሚሆነው ይሆን ዘንድ ግድ ነው። ዘመንና ወቅት ይፈራረቃል። ቀንና ሌሊትም እንዲሁ። ኢትዮጵያም ፈተናዎችን ሁሉ አልፋ ታፍራና ተከብራ ለዘለአለም ትኖራለች፡፡አዲስ ዘመን ጥቅምት20/2012 ወንድወሰን መኮንን
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=21738
[ { "passage": "በልጅነቴ ያስተዋልኩትን ሐቅ ልንገራችሁ። ነገሩ እንዲህ ነው። ሰዎች ተሰባስበው፣ እንዲቀናቸው ተመርቀው አደን ይሸኛሉ፡፡ኑሯቸውን በዱርና በገደል ያደርጋሉ፡፡በዚህ ሁኔታ ለወራት በመቆየት በለስ የቀናው አንበሳ በመግደል ጀግና ይሰኛል፡፡በለስ ያልቀናው በርሃብ ሲናውዝ ከርሞ ይመለሳል። ገዳዩም ጀግንነቱን በገበያ ያስመርቃል፤ ያውጃል፡፡የገደለውን የአንበሳ ቆዳ በትከሻው ላይ ይደርባል፤ ፀጉሩንም ቅቤ ይቀባል፡፡ከዚያም ሌሎች ጥቂት የሥጋ ዘመዶቹን አስከትሎ በገበያው መሐል እየተንጎማለለ ስለመፈጠሩ እንኳን በውል የማያውቁት በርካታ ሰዎችን በመንጋ ያስጨፍራል፤ ሲዘፍኑለት ይውላሉ፡፡እርሱም እንደሙሽራ ሲሳምና ሲሸለም የሞራል ግለቱ ጣራ ይነካል፡፡እግር የጣለው ሁሉ እያጨበጨበ አብሮ ይተማል፡፡የእንስሳት መብት ተሟጋች በማያውቃት አገራችን በቀደሙት ጊዜያት የአንበሳ ነፍስ ማጥፋት በመንጋ ያስከብርና በመንጋ ያዘፍን ነበር፡፡አሁን ላይ ይባስ ብሎ የሰው ልጅ ሕይወትን በመንጋ ማጥፋት እና በመንጋ አስክሬን መጎተት በመንጋ ያስከብር ይዟል፡፡በመንጋም ሲያስጨፍር አስተውለናል፡፡ እርግጥ ነው በዚህ የመንጋ እንቅስቃሴ ውስጥ የሀብት ጥሪት የመቋጠር ዕድል ያጋጠማቸው እንዳሉም ሹክሹክታ ይሰማል፡፡በመንጋው በአባልነት ተቀላቅለው የዘመቱ በቀን እስከ 500 ብር ሲቋደሱ፤ በመንጋው ዘመቻ በርካታ ሰው በመውረር ‹‹አራስ ነብር›› ሆነው ለዋሉ ደግሞ እንደዘመቻ አውዱ በበቃኝ ሳንቲም እንዲዘግኑ ይደረጋል መባሉን ከመከራ ቀማሿ ድሬ ሹክ ብለውናል፡፡አጃኢብ ያሰኛል፤ ጆሮ አይሰማው የለ፡፡ይሄ ገንዘብ የሚበቅልበትን ዛፍ አምላክ ይወቀው፡፡ተሠርቶ ያልተገኘ በጂኒ የሚመጣ ገንዘብ ሕዝቡን በመንጋ የጂኒ አመል እንዲኖረው አደረገ፡፡ለመልካም ተግባር ሲሆን የመሰባሰቡና የመደመሩ ጉዳይ ዳገት ይሆንብናል፡፡የእኛ ትውልድ እንዲህ ነው፡፡ቅን መሪዎችን ሳይሆን ቅንቅኖችን የሚሻ፡፡ከአብዮች ሳይሆን ከአባዮች የሚወዳጅ፣ ከሚወዱት ሳይሆን ከሚንቁት ጉልበት ሥር የሚወሸቅ፤ ተራማጅ አስተሳሰብን ያልፀነሰ ጮርቃ ሆኗል፡፡ ቢቆነጠጥና አደብ ቢይዝ አይሻልም ትላላችሁ? ‹‹አገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል›› ነበር ብሂሉ፡፡ታዲያ አገሬ ተባይ ማፍራቷ አርጅታ ይሆን እንዴ? እንጃ አይመስለኝም፡፡ትውልዳችንን ልንፈትሽና ልንመረምር ይገባል፡፡ወቅቱን ጠንቅቆ የሚረዳ ብልጥ ትውልድ ያስፈልግ ይመስለኛል፡፡ዋሽቶ ማስታረቅ እንጂ ዋሽቶ ማጋደል በክብር ሲያስጠራ ከታሪካችን አልሰማንም፤ አልተማርንም፤ ለማንም አይበጅም፡፡ዘመኑን የተነጠቀና ቀልቡ የተገፈፈ ባካኝ በአንዳንዶች አጠራር ‹‹የተረገመ›› ትውልድ እንዲበቅል ቆላ ከደጋ እየባከኑ ደም ሲያራጩ መዋልን ሥራዬ ብለው የተያያዙት በርክተዋል፡፡አዎ አገሪቱ እንዲህ አይነት አዳዲስ የሥራ መስኮች የሚፈጥሩ ሰዎች እንዳሻቸው የሚኖሩባት አገር ሆናለች፡፡የተራ ዜጋውም ጉዳይ ‹‹በሬ ካራጁ ….›› አይነት ሆኗል ወዳጄ፡፡‹‹ከደሙ ንፁህ ነን›› ባይ አፈቀላጤዎችም ወንድም ወንድሙን መግደልና ሲያሸብሩ መዋል እንደ ሥራ ስለመቆጠሩ እየነገሩን ነው፡፡እንደው ማን ይሙት በእኔ ልጅ ደም የእሱን ልጅ እንጀራ የሚያበስል የዋህ ኢትዮጵያዊ ስለመፈጠሩ እንደመስማት የሚያንገሸግሽ ሕመም ምን አለ?፡፡ በእምነት ቅንብብ አጥር ውስጥ በቅሎ እዚህ የደረሰ ኢትዮጵያዊ ‹‹ያልዘራውን የሚያጭድ›› አለመኖሩን መረዳት አያዳግተውም፡፡ የሰው ልጅ በሥራው ልክ ተመዝኖ የሚከፈለው በአንድ ወቅት በዓለም ላይ የበቀለ አረም ተደርጎ ሊታይ ይገባል፡፡ራሱን ዘላለማዊ በማስመሰል የአልማዝ፣ የወርቅና የብር ደረጃዎች እየሰጡ እያንዳንዱን ነገር ‹‹ለእኔ›› እያሉ መስገብገብ የኢትዮጵያውያን ስብዕናም አይደለም፡፡የሰው ልጅ ሕይወት መጥፋት የሚያስጨፍረው አካል መታየት ሲጀምር መላ ሊበጅለት ይገባል፤ ሕመም መለከፉን መረዳት ያስፈልጋል። ነገ ራሱ ተራ ጠባቂ ሟችነቱን ረስቶታል ማለት ነው፡፡‹‹ሆሆይ›› ለካ ነገረ ሥራው ከተቀየረ ዋል አደር ብሏል። የምኑ እንዳትሉኝ፤ ከመኖሪያ ቀያችሁ እስከ ፌስቡክ ሰፈራችሁ የምታዩትንና የምትሰሙትን ወሬና ድርጊት አብጠርጥራችሁ ፈትሹ፡፡‹‹ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር…›› ነው ነገሩ፡፡ከእነ እንትና ሰፈር ዕሳት እየጫሩ በእነ እንትና ሰፈር በ‹‹ቪ ኤይት›› ቄንጠኛ መኪና መንፈላሰስ ዋ! ካላስባለ፣ ነገ ጨዋ ልጅ ከሰፈርህ ቀርቶ ከአብራክህ ሊወጣ አይችልም፡፡የሰውነት ሚዛናችን እያነሰ የእንስሳነት አመላችን እየጎለመሰ ይሄድ ይዟል፡፡ እኔ ለአቅመ ማስተዋል ከደረስኩበት ጊዜ አንስቶ ያስተዋልኩት የሰው ልጅ ሞራል የማጣት ልክ እንደዚህ ጊዜ ሲዘቅጥ አስተውዬ አላውቅም፡፡ምን አልባት የእኔ የማስተዋል ልክ ከሆነ አላውቅም፡፡ኧረ እንደውም ባደግንበት ወግና ባህልማ የሰው ልጅ በሕይወት ሲኖር ከሚያገኘው ክብር የላቀ አስክሬኑ ይከበር ነበር፡፡አብሮን ባደገው የመበቃቀል ክፉ ልማዳችንም ውስጥ ቢሆን እንጥፍጣፊ መከባበር ነበረበት፡፡እንኳንስ ሰውን ያህል ነገር ቀርቶ የእንስሳትም ቢሆን አስክሬን የተመለከተ ሰው ያዝናል፤ ባስ ሲልም በዓይኑ በብረቱ የሰው አስክሬን ወድቆ በድንገት የተመለከተ ሰው ራሱን ለከፍተኛ ፀፀት ይዳርጋል፡፡ምን የሠራሁት ሐጢያት (ክፉ ሥራ ) ቢኖር ይሆን ፈጣሪ ይሄን ያሳየኝ፤ በሚል ነፍሱን እሱ ያጠፋ ያህል ፈጣሪውን በፀፀት ይለምናል፡፡ነፍሱ በፈጣሪው ፊት ትጠየቅ እስከሚመስለው ድረስ ይፀፀታል፡፡‹‹ማረኝ›› ይላል፡፡አሁን አሁን የሚስተዋለው\nድርጊት ግን ለየቅል\nሆኗል፡፡እመኑኝ ታሪክ ዋሽቷል\nወይም ትውልዱ ላሽቋል\nየሚያሰኝ ደረጃ ላይ\nእንገኛለን፡፡በመንጋ ተነስቶ በመዝመት\nየሰው ልጅ ሕይወትን\nማጥፋት በየትኛውም እምነት\nየተወገዘ ብቻ ሳይሆን\nአውሬነት ተደርጎ የሚቆጠር\nተግባር ነው፡፡እንዲህ አይነት\nየአውሬነት ተግባር የመፈፀም\nድፍረት እንዲሁ በአጭር\nጊዜ የሚለመድ ባህሪ\nአይምሰላችሁ፡፡ይህ ትውልድ ጤንነቱ\nሊፈተሽ የሚገባ ይመስለኛል፡፡በማንኛውም\nመመዘኛ ሊያሳምን የሚችል\nአመክንዮ የሚቀርብበት ጉዳይ\nአይደለም፡፡አዲስ\nዘመን\nኅዳር 11/2012 ሙሐመድ ሁሴን", "passage_id": "5185dadf64d68adb195255824800fbd0" }, { "passage": "ወሬው ሁሉ ከሙስናና ምዝበራ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎች ስም ዝርዝር ነው፡፡ ከፖሊስ በወጣው መግለጫ የተጠርጣሪ ስሞች ተሰድረዋል፡፡ የባል ሚስት ልጆች ወንድሞች አክስቶች ጋብቻዎች የሩቅ የቅርብ ዘመድ ውሽሜ ሁሉም በሀብት ተንበሽብሸዋል፡፡ እንዲህ አይነቱ የተቀናጀ የተደራጀ ሕጻናቱን የማያውቁት ሚሊዮን ብር ባለቤት ያደረገ ዘረፋ ጉድ የሚያሰኝ ነው፡፡ የጉድም ጉድ፡፡ ሸማኔው ጊሀጌሎም ስጋ ቆራጩ ወርኬቦ፤ እማማ ይመናሹና አባባ ደቻሳም በሰሙት ነገር ግራ ተጋብተዋል፡፡ አንድ የጎረቤታቸው ልጅ የወጣውን የሰዎቹን ስም ዝርዝር ሲያነብላቸው ፈዘው ቀሩ፡፡\nሆሆይ ሀገሬ ጉድሽ አላልቅ አለ ምን በጀሽ ምንስሽ ተረፈ እንደው ምኑ ነው የቀራቸው? አሉ አዛውንቶቹ፡፡ ሁሉም በአንድ ድምጽ ሌብነትን አወገዙ፡፡ ሌባም ሌቦች፡፡ ሌብነትን ዘረፋን ተጸይፈው ድምጽ አሰሙ፡፡ ሌቦ ሌቦ ነይ የሚለውን ዘፈን ድሮ የዘፈነው ዘፋኝ ማን ነበር ሲሉ ጠየቁ፡፡ ዘመኑ ተፈትልኳል፡፡\nሌቦች እንደ ሰማዩ ጩሉሌ ሙጭልፊት ናቸው አሉ እማማ ይመናሹ፡፡ ከላይ አንዣቦ አንዣቦ ድንገት ጠልፎ እንደሚወስደው፡፡ እንደው የሰው ይቅር መቸም እንደሌለ ቆጥረውታል ሌላ ይቅር ምናለ እግዚአብሔርን ቢፈሩ ኖሮ አሉ ድምጻቸውን ጎላ አድርገው፡፡ ደሞ ብር ካለ በሰማይም መንገድ አለ የሚለው የድሮ ተረት ትዝ አላቸውና ብቻቸውን ሳቁ፡፡ ምን አሳቀሽ ይመናሽ ደቻሳ ጠየቁ፡፡ እንደው ከራሴ ጋር እያወራሁ ነው ደቻሳ ምንም የለም ሲሉ መለሱ፡፡\nእግዜሩም እኮ የእኛ ነገር ግራ ሳያጋባው አይቀርም አሉ አባባ ደቻሳ፡፡ አንዱ ሲባል አንዱ፤ጉድ ጉድ ስንል ሌላ ጉድ የማያባራ ጉድ የሚታይባት፤ የሚሰማባት ሀገር ሆና አረፈች ብለው በዝምታ ተዋጡ፡፡\nአባባ ደቻሳ ከዘራቸውን ደገፍ ብለው ሌቦች ሌብነት ጀግንነት ነው ያሸልማል የተባሉ ይመስላሉ እኮ እንዲህ ሀገር ማራቆት ነውርም አይደለም እንዴ? ሲሉ ጠየቁ፡፡ እግዜሩንም እኮ እንደ ሰው ንቀውታል፤ ምን ያመጣል እያሉ፡፡ አይ ደቻሳ ነገር የተበላሸው እኮ ሕዝቡ አምርሮ ወደ ፈጣሪ ያለቀሰባቸው ግዜ ነው፡፡ ወይ ፍረድ ወይ ውረድ እያለ እሪታውን ከከተማ እስከ ገጠር ሲያቀልጠው ሰምተህ አይተህስ የለም ወይ? አሏቸው፡፡ አዎ ልክ ነሽ ይመናሹ ከሕዝብ የተጣላ ከእግዜር የተጣላ ይባል የለ የሆነውም ይሄ ነው ሲሉ መለሱ፡፡\nባለፈው ሶስት ዓመት በድቅድቅ ክረምት ሕገወጥ ቤት ሰርታችኋል የተባሉ እንዲያም ሆኖ ግብር የመብራት የውኃ ሲከፍሉ የኖሩትን ሰዎች ርሕራሄ በሌለው፣ ጭካኔ በተሞላበት፣ ሰው በተኛበት በትራክተር ያፈረሱና እናት ሕጻን ልጇን እንደያዘች የተደረመሰባትን ስንቱ ያለቀበትን ታሪክ እዚሁ አዲስ አበባ አይተን ሰምተን አልቅሰን ምን አይነት ግዜ መጣ ብለን ነበር፡፡ መንግስት ዜጎቹን በጨለማው ክረምት ቤት ልቀቁ ብሎ ቤታቸውን አፈራርሶ የትም ውደቁ ሲል የዛ ሁሉ ድሀ እንባ ምን ያመጣል ብለው እኮ የማያስቡ ሰዎች ነበሩ አለ ሸማኔው ጊሀ ጌሎ፡፡ የበዛ ግፍ የግፍም ግፍ ነበር ሲፈጸም የነበረው፡፡ ይሄን መሰል ድርጊቶች ናቸው ክብሪት ሆነው ተለኩሰው ሌላ ሌላውም ተጨምሮ ሕዝቡን አስመርረው ዜግነቱን እስኪጠላ አድርሰውት የነበረው ሲሉ መምህር አበበ በረዥሙ ተነፈሱ፡፡\nእነ ሌቦ ሌቦ ነይ በስማቸው ሀምሳ ሶስት ቤት እየያዙ በሚስትና ልጆቻቸው፤ በእቁባቶቻቸው፤ በወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው፤ በአክስትና በአጎት ልጅ ጭምር መሬቱን ቤቱን ሲቀራመቱት በልማት ስም ባለቤትና ባለንብረቶችን እያፈናቀሉ ሲፈነጩ ኖሩ፡፡ እስቲ ምን ያልተዘረፈ ነገር አለ በዚች ሀገር የሚል ጉምጉምታ ከሁሉም ተሰማ፡፡\nበየክፍለ ከተማው መሽጎ የነበረው የመሬት ይዞታ ሹምና ምንዝር ወሮበላ በመንግስት የተወረሱ የቀበሌ ቤቶችን ፋይል እያጠፉ በግለሰብ ስም እያዛወሩ፤ የሀሰት ካርታ እየሰሩ፤ ላሻቸው ሲሰጡ ሲሸጡ፤ ዜጎችን እያፈናቀሉ ትንሽ የካሳ ብር በመስጠት እነሱ በሚሊዮኖች ሲቸበችቡት፤ ሕዝቡ በድሕነት ማቅ ውስጥ እንዲኖር ሲፈረድበት፤ እነሌቦ በፎቅ ላይ ፎቅ፤ በሕንጻ ላይ ሕንጻ፤ በመኪና ላይ መኪና ሲደርቡ፤ይሄ ግፍ ይሄ ወጥ መርገጥ ምን ያመጣል? ብለው ማሰብ ይገባቸው ነበር አሉ አባባ ደቻሳ የመምህርን ንግግር ቀበል አድርገው፡፡ ቀን ሲያዘንብል እግዜሩም አብሮ መከፋቱን ፍርድ መስጠቱን ነው በእድሜያችን ያየነው፡፡ እነሌቦ ይሄም የገባቸው አይመስልም ሲሉ አከሉበት፡፡\nእግዚኦ አንቺ ሀገር መጨረሻሽ ምን ይሆን የሚያሰኙ ብዙ የግፍ ታሪኮች፤ አይደረጉም ተብለው የሚገመቱ ግን ደግሞ የተደረጉ ብዙ ሺህ ተቆጥረው የማያልቁ ግፎች መሰራታቸውን ሕዝቡ በሰፊው ያውቃል፡፡ ጠላ ቤቱ፤ ጠጅ ቤቱ፣ ሰፈሩ፣ መንደሩ፣ ሁሉም ወሬው እኮ ይሄ ነው፡፡ ማታ ማታ መዝናኛ ቦታ የሚሰማውን ለማመን ይከብዳል አሉ ደቻሳ፡፡ ሌብነት ጎሳና ዘር የለውም፡፡ የአማራም፣ የትግሬም፣ የኦሮሞም፣ የደቡብም፣ የሶማሌም፣ የሀደሬም፣ የጉራጌም፣ በሁሉም ብሔሮች ብሔረሰቦች ውስጥ ሌቦች፣ ዘራፊዎች፣ ቀማኞችና ነጣቂዎች ሞልተው ተርፈዋል፡፡ ሌብነት ቀለምና ዘር የለውም፡፡ ሌባ ሌባ ነው፡፡ ሌባም አሉ፡፡\nምሕረት፣ ሀፍረት፣ ይሉኝታን የማያውቁና አይናቸውን በጨው ያጠቡ ደረቅ ዘራፊዎች ገና መቼ ተጋልጠው ወጡና ነው አሉ ሁሉም በአንድነት፡፡ ሌቦ ሌቦ ነይ የሚለው ዘፈን ቢኖር ውይይታቸው የበለጠ ይደምቅ ነበር፡፡\nእነ ሌቦ የራሳቸውን ሰዎች ሲተክሉና ቤት የነበረውን ቤት አልባ ሲያደርጉ፤ ምን ያልተሰራ ስራ አለ፤ የአዲስ አበባ ሹሞች ከቀበሌ ክፍለ ከተማ ምን ያልሰሩት ግፍ አለ ብለሽ ነው አሉ ደቻሳ፡፡ ይሄ ሁሉ ግፍ ሞልቶ ቢፈስ ይኸው ከየት መጣ ሳይባል ድንገተኛ አውሎ ነፋስ እንደ መብረቅ ወርዶ ጉድ አደረጋቸው፡፡ እግዜአብሔር መኖሩን ብቻ ሳይሆን ኃያል መሆኑንም አሳየ አሉ ይመናሹም፡፡ በድንቅ ስራው በመደመም፡፡ ያፈራርሰዋል የሞቀውን ቤት ይሉት አባባል ሆኖ ቢያዩት፡፡ እንዲህ እሳተ ገሞራ አስነስቶ የሚለበልባቸው እግዜሩ እኮ ነው፤ በሰው አድሮ ሌላ እኮ አይደለም አሉ ደቻሳ ደገሙና፡፡\nግፍ እየሰሩ ቤተክርስቲያን ቢሄዱ፤ ምጽዋት ቢሰጡ፤ ቢዘክሩ ከልብ ካልሆነ ምን ያደርጋል አሉ ይመናሹ፡፡ ይውጋህ ይማርህ አይነት መሆኑ ነው፡፡ ገና ብዙ ወደፊት የሚዘረዘሩ የሚፈለጉ ሰዎች መኖራቸውን አትጠራጠሩ፡፡ ይሄ ሁሉ ሲደረግ ሕግና ስርዓት መጥፋቱን፤ ጠያቂ ለምን ባይ አለመኖሩን፤ መካሪ ማጣታቸውን፤ በእብሪት አብጠው ተወጥረው ባሉበት ዙሪያ ገባውን በንዴት የታጀበው የሕዝቡ ቁጣ ብስጭት ንዴት ገንፍሎ ሲወጣ ማንም ሊመክተው አልቻለም እኮ፡፡ ውይይቱ ቀጠለ፡፡ ጨሰ፡፡\nበአባት እናት፣ በትልቅ በትንሽ ልጆች፣ እህቶች፣ ወንድሞች፣ የቅርብና የሩቅም ቢሆን ዘመዳ ዘመዱን በየስማቸው የባንክ ደብተር እየከፈቱ ያለፉበትንና ያልደከሙበትን ሀብት እንዲያከማቹ ማድረግ ለሰሚው ለአድማጩ ግራ ነው፡፡ የእነሌቦ ስራ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ የወደፊቱም ትውልድ ከዚህ አይነቱ ነውረኛ ድርጊት እንዲጠነቀቅ ለማስተማሪያነት እንደሚያገለግል መምህር አበበ ግሩም እምግሩማን በሚል ገለጹ፡፡\nለሕጻን ልጅ በስሙ ባንክ አካውንት ተከፍቶ የሚሊዮኖች ገንዘብ ባለቤት ሆኖ እና አንድ ሰው 53 ቤቶች በስሙ በባለቤትነት ተመዝግቦ መገኘቱን በመስማታቸው ጉድ ጉድ ብለው ሊያበቁ አልቻሉም፡፡ ጆሮ አይሰማው የለ መቼም፤ ሰምተንም ሆነ ገምተን የማናውቀው ገና ብዙ ጉድ እንሰማለን አሉ አባባ ደቻሳና ጎረቤቶቹ በመስማማት፡፡\nሥጋ ነጋዴው ወርኬቦ ነገሩ ብዙም ያስደነቀው አልመሰለም፡፡ እናንተ ሰዎች አሁን ሰዎች ለምን ገንዘብ አገኙ ብላችሁ ነው እንዲህ የምትንጫጩት ሲል ጠየቀ፡፡ መለስ አደረገና እሺ ንገሩን ማነው ገንዘብ የሚጠላው አባባ ደቻሳ? እማማ ይመናሹ? እኛ? አላገኘንም ብላችሁ ነው፤ ሰው የሚለፋው የሚደክመው ሀብት ንብረት ለማግኘት አይደለም እንዴ? ብሎ ሲናገር ሁሉም ፍንድቅ… ፍንድቅ.. ብለው ሳቁ፡፡ አባ ግድየለሽ አንተ ምን አለብህ፤ ሥጋህን በላህ፤ ጠጅህን ጠጣህ፤ ሞቅ ብለህ ገባህ፤ ተኛህ፡፡ ነገም እንደዚሁ ነህ፡፡ ወርኬቦ ሰርቶ መክበርና ዘርፎ መክበር አንድ አይደለም አሉት፡፡ ይህ ሁሉ ሀብት ሀገርና ሕዝብ በመዝረፍ የተገኘ በመሆኑ ነው ሕዝቡ የተቆጣው ሲሉት ወርኬቦ ትንሽ የተረጋጋ መሰለ፡፡ ቀጠለና እኔ ምን አገባኝ፤ እኔም ባገኝ አለቅም ሲላቸው ዳግም በሳቅ ተንከተከቱ፡፡ እኔ ወርኬቦ አንድ የራሴን ሥጋ ቤት እንኳን ብከፍት ዲታ እሆን ነበር አለ ድህነቱ እየቆጨው፡፡ ዶሮ ብታልም ጥሬዋን አሉት፡፡ ታዲያ ሌላ ምን ታልም አላቸው በምላሹ፡፡\nእንዲህ የሙጭልፍቶች ሀገር ሆና ትቅር አሉ እማማ ይመናሹ በንዴት ጦፈው፡፡ የምንሰማው ሁሉ በእድሜያችን ሙሉ ሰምተን የማናውቀው ጉድ ነው፡፡ ሕዝብን ማስተዳደር እንዴት ሀገርን መዝረፍ ሊሆን ይችላል? በማለት አጥብቀው ይደመማሉ፡፡ ከድሀው መቀነት ፈተውና አሰግደደው የሚወስዱ አይን አውጣ ሌቦች፡፡ እነ ሌቦ ሌቦ ነይ፡፡\nበቀበሌ ሌቦች፤ ክፍለ ከተማ ሌቦች፤ በየቢሮው ሌቦች፤ የሰው መሬት ወስደው ካርታ አውጥተው የሚሰጡ ሌቦች፤ ካርታ ሰጪዎቹ ሌቦች፤ ሕዝብን ለማገልገል መንግሥት የመደባቸው መሆኑን ረስተው ሕዝብን የሚዘርፉ የሚያስገድዱ፤ መብቱን ለመጠየቅ ሲሄድ ይሄን ያህል ሺህ ካላመጣህ የጠየከውን አታገኝም ብለው ተደራጅተው ከትንሹ እስከ ትልቁ ድሀውን ጭምር ግጠው የበሉ ያስለቀሱ ሌቦች፤ በድሀው እንባ የሚደሰቱ እርጉማን ፤ ተወው እባክህ ምን ያመጣል? የትስ ቢሄድ የት ይደርሳል? እያሉ ሲሳለቁ የነበሩ ሹምና ምንዝሮች፤ በሕዝብ ላይ የሚፈጸመው ግፍና በደል በዝቶ ጽዋው ሞልቶ ሲፈስ ይኸው ጎርፍ ሆኖ ጠራረጋቸው ሌባ ሁላ አሉ አባባ ደቻሳ፡፡\nበቀደም ስለሌቦቹ ብዙ ከሰሙ በኋላ እማማ ይመናሹ አባባ ደቻሳ ጎረቤቱም ሰፈሩም መንደሩም በሙሉ ክፉኛ ተበሳጭተዋል፡፡ ድሮ እኮ እከሌ የመንግሥት ብር ሰረቀ አጭበረበረ ከተባለ ሀገር ምድሩ ያን ሰው ለማየት ይጠየፈው ነበር፡፡ ያውም እኮ አንድ ሺህ ብር የማይሞላ ብር ካጎደለ፤ ከሰረቀ፡፡ ግዜ የወለዳቸው ሌቦች ደግሞ ድፍን ሀገርን ዘረፉ፡፡ እድሜ ደጉ ብዙ አሳየን አሉ ደቻሳ፡፡\nሌብነት ዘር ቀለም ጎሳ የለውም፡፡ ሌቦች በሁሉም ዘር ውስጥ አሉ፡፡ 82 ብሔረሰብ አንቆጥርም፡፡ የሁሉም ሌባ ሌባ ነው፡፡ ግለሰቦች ናቸው በስግብግብነት ዘረፋ ውስጥ የሚገቡት፡፡ ሕዝብ አይደለም፡፡ ሌቦች ራሳቸውን እንጂ ብሔራቸውን አይወክሉም፡፡ ሌቦች በሕግ የሚጠየቁት በግለሰብ ነታቸው ነው፡፡ ከአማራው፣ ከኦሮሞው፣ ከትግሬው፣ ከሶማሌው፣ ከወላይታው፣ ከጋምቤላው…ወዘተ ስለተወለዱ አይደለም፡፡ ለሌባ ጥብቅና የሚቆም ሕዝብ የለም፡፡ ሌባ ሁላ! ሌቦች የዘመን መርገምቶች እንዴት ተደርጎ የማይሆነውን አሉ ደቻሳ፡፡ ደጉን ዘመን ለሀገርና ለሕዝብ ታምነው የኖሩ፤ ተከብረው ያለፉ ታላላቅ ሰዎች በማስታወስ፡፡ ኧረ መስረቅ ነውር ነው፡፡ ሀገርን መስረቅ ሕዝብን መስረቅ የነውርም ነውር የወንጀልም ወንጀል ነው ደገሙት ደቻሳ፤ ሌባ ሁላ ሌቦች ሲሉ፡፡", "passage_id": "d05a1b9c79a0fc96d924da6b16cdc216" }, { "passage": "የቤተሰቡ አባላት ቀን ቀን እንደፈንድሻ ተበትነው ይውሉና ማታ በትንሿ ሳሎን ሰብሰብ ሲሉ ውሏቸውን ይለዋወጣሉ። በአንድ ገበታም ይመገባሉ። አብሮ መብላት አብሮ መጨዋወት ያፋቅራል፣ ያስተሳስባል፣ ውስጥን ለመተዋወቅም ያግዛል።… ይባል አይደል?። ሁሉም በየፌስቡኩ፣ በየጌሙና ፊልሙ ከተተከለ ቤተሰብም ቤተሰብነቱን ያጣና እንደምንሰማው የዓለም ወሬኛ መሆናችን አይቀሬ ነው።ይሄ በብዙ በተለይ ዘመናዊ ነን በሚሉ ቤተሰቦች እንኳን እየተለመደ መሆኑን ልብ ይሏል። አንዳንዱም የመኝታ ክፍል ይዞ ለብቻ በመሆን ግለኝነት እየመጣ ነው። ከዚህም መለስ ሲል ምን ትዝ አለኝ የኮንዶሚንየም ኑሮ፤ የኮንዶሚንየም በር ከርችሞ ኑሮ ትልቅ ጥያቄ ውስጥ ገብታለች። ሰውና ሰው፤ ጎረቤት ከጎረቤት እየተለያዩ ነው ፤ አንዱ ሲጮኽ ማነው የሚልም ኧረ ጠፋ የሚሉም አስተያየቶች ሰፍተዋል። ብቻ ይሄ ለእኛ አይሆንም፤ አላደግንበትም፣ አልኖርነውም፤ ለመንደር ተልኮ፣ እሳት ጭሮ፣ አብሮ ቦርቆ፣አደራ ተቀብሎ፣ መብላት፣ መጠጣቱ ሁሉም ነገር አብሮ… ተባብሮ ነው።የእኔ ነገር ከቤተሰቡ የውሎ ሪፖርት ወጣሁ – ልመለስ። ከዛ ልጆች የልጅ ተግባራቸውን ፤ ወላጆችም እንደየስራ ድርሻቸውና ፊናቸው ሃላፊነታቸውን ለመወጣት ይሰማራሉ። በዚህ መሀል የዋልያ ቢራ ማስታወቂያ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ አለ።የአራተኛ ክፍል ተማሪው ልጅም ማስታወቂያውን ከመነሻ እስከ መድረሻ ማለቴ እስከ ተሸላሚዎች ምስክርነት ያለውን ቃል በቃል አብሮ ተወጣው። ድንገት «ዋልያ ምንድነው» የሚል ጥያቄ ተነሳ፤ ልጁ ምንም እንደማይስተው ያውቃልና አሁን ይሄ ይጠየቃል በሚል ስሜት ጭምር ኮራ፣ጀነን ብሎ « ቢራ ነዋ! » ማለት ። አባት አሁንም ጥያቄውን ቀጠለ ዳሽንስ? እሱም ቢራ ነው። ማብራሪያም አለው አብሮት «መቶ በመቶ ጥራት ያለው…»ቀጠለ። ልጁ አይፈረድበትም ማታ ማታ በየቀኑ እንደ ዳዊት የደገመው ይሄንኑ ነው። እንዴት ይጥፋው!።«ሀበሻስ » ከሌላ አቅጣጫ የተነሳ ጥያቄ ነበር፤ ይሄም ቢራ ነው።ሁሉም ፈገግ አሉ፤ ልጁ ግን አንድም ነገር አልተሰማውም፤በልጁ አይፈረድም «ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን እነግርሀለሁ» አይደል አባባሉ፤ የእሱ የቅርብ ጓደኛ ቴሌቪዢን የነገረው የቢራ ስም መሆኑን ነው።ቀዝቃዛ ቢራ፣በአረፋ የሞላ ብርጭቆ፤ ግጥም ለውሀ ጥም !? አንድ አይቀመጥም፤ ማን ያልጎመዠ አለ፤ ማለቴ ለሚቀማምሱት ጣዕሙን ላጣጣሙት ትነሱ… ትነሱ..፣ አሁን… አሁን… አይደል የሚያስብለው። በልጆች አእምሮ ደግሞ ምን እንደፈጠረ ያኔ ልጅ በነበርኩበት ወቅት ባየው ኑሮ ዛሬ አስታውሼ እከትበው ነበር።ያኔ ብቸኛው የዶሮ አይን የመሰለው ጠላ፣የማር ጠጅ አይ የኔ ነገር የተረሱትን አነሳሳኋቸው። ወሬን ወሬ ያነሳዋል ማለት እንዲህ ነው።የቢራ ማስታወቂያችን በአገራችን በሰሜን ተራራ የሚገኘው፣ በብርቅየው የዱር እንስሳ ዋልያ ስም የተሰየመው፣…ቢራ እየተባለ ማስታወቂያ ቢሰራ ኖሮ ልጁ ቢያንስ አብሮ የሚያውቀው፣ የሚያጠናው ይኖረው ነበር፤ በምስል ዋልያን ሰሜን ተራራ ላይ ሲጎማለል ቢመለከትም ዋልያ የሚባለው ብርቅዬ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘው እንስሳን በአእምሮው ስለን ባስቀረን ነበር። አሁን ግን እንደምናየው እንደምንሰማው ሆነና ሁሉም ነገር ቢራ። እንድንጠጣ፣ ሽልማትን እያሰብን እንድንሰክር የተጋበዝነው ቢራ በየአይነቱ ነው። ምነው ከልካይ የለም ? ሀይ የሚል ልል አሰብኩና የማስታወቂያ ህግ ፣መመሪያ፣ ደንብ የሚባል የሚዲያ ፖሊሲ አለ ብዬ ልለፈው፤ ግን እኮ እሱም ቢሆን ትውልድን ታዳጊን በሚጎዳ መልኩ እንዳይሆን ማድረጉን ማንን ገደለ አለች አያቴ እኔም ይሄንኑ ደገምኩት። ሀይ የሚል መኖር አለበት ።«ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን እነግርሀለሁ» የሚለውን አባባል እውነትም እውነትነት አለው። ሰው ለካ የሚመስለው ማንንም አይደለም ። በአካል ፣ በመልክ፣ በተክለ ሰውነት ማለቴ አይደለም በባህሪ፣ በአለባበስ ፣በስታይል።ኧረ አንዳንዴ አነጋገርም የሚኮርጅ አይጠፉም። ወጣቱ ልጄ ጸጉሩን በአጭሩ ቆርጦ አበጥሮና በየጊዜው ተስተካክሎ ነው የኖረው ። አሁን አሁን እንግዲህ ዩኒቨርሲቲ በር ላይ ሲደረስ ደግሞ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ለመመሳሰል ተብሎ ይመስ ላል ወይም የዋሉበት ይጋባባት በሚባለው ስታይል ፀጉር ማሳደግ ፣ማንጨባረር እየለመደ መጥቷል። ምነው ማበጠሪያ ሳይጠፋ ልል አሰብኩና ፋሽን ነው የሚለው መልስ እንደሚከተል አስቤ እኔም አለፍኩ። እንዳውም በተለይ ከክልል የመጡት አብዛኛዎቹ ይሄንን እስታይል ተቆጣጥረውታል አሉ። ፀጉር አለማጎፈር እንዳውም አዲስ አበባዎችን «ፋራ» እያስባለም መሆኑን ሰምቼ ፋራነት በዚህ ከሆነ ይሁና አልኩኝ ለራሴ።እየሆነ የማየው አንዳንዱ ነገር ምነው ኢትዮጵያውያን የሌለንን ባህሪ አወጣን ወይንስ ድሮም ባህሪያችን ሲፋቅ እንደሚባለው አይነት ነው ለማለት እከጅላለሁ።ማለቴ ሲፋቅ ሌላ እየሆንን ነው።«ኢትዮጵያውያን ስንፋቅ ሶማሊያ፣ ሶሪያ፣የመን…» ነን እንዴ?\nአያቴ ሁልጊዜም የምትለኝ ነገር እኔም እስከ አሁን ድረስ የማየው ሁሉ አይጥፋብን የሚያሰኝ ነው። አሁን አሁን ግን የሚታየውና የሚሰማው እንደጠፋብን አይነት ስሜት አለው። ደግሞ ይሄ ጥፋት ደመቅ ብሎ የሚታየው «የተማሩ» በሚባሉና በወጣቶቹ አካባቢ ነው።ሰው ያክል ክቡር ፍጡር፣ ታላቅን፣ ሽማግሌን፣ የሀገር መሪ ማዋረድ ፣መስደብ … እንደ ጸያፍ ሳይሆን እንደ ጥሩ እደግልኝ አይነት ምርቃት እየተቆጠረ መሰለኝ ። ክብር ለሚሰጠው ክብር መስጠትን እንጂ መስደብን ማዋረድን ማን አስተማረን? ማን ነገረን? አሁን እንደቀላል «ዴሞክራሲ» የቆጠርነው የኋላ የኋላ ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን እነግርሀለሁ እንዳይሆን እሰጋለሁ። አንዱ ተነስቶ ሌላውን ብሄር፣ ዘር፣ መሪ… የሚዘልፍና የሚሳደብ ከሆነ ማን ማንን ያከብራል፤ የተሰደበው ብቻም ሳይሆን የተሳደበው መዋረዱን አይቶት ይሆን ?ተገንዝቦታል? ሰዎችን ስንሳደብ ስናንጓጥጥ እኮ ድሮስ ማን ያሳደገው ማን ያስተማረው መባባላችን አይቀርም።አንድ ሰው አንድን መጥፎ ድርጊት ሲፈጽም እኮ ወይ ጉድ እከሌ እኮ እንዲህ አደረገ ተብሎ ብቻ አይታለፍም። የማን ልጅ ነው? ከየት ክልል የመጣ ነው?አሁን አሁን ደግሞ ኧረ ብሄሩ ሁሉ ይጠየቃል። ይሄ ታዲያ ግለሰቡን ወይም ቡድኑን ብቻ ሳይሆን የአካባቢው ሰዎችም ፣መሪዎችም… የመጥፎ ምሳሌ ተደርገው እንዲቆጠሩ የሚያደ ርግ ይመስለኛል። አንድን የሀገር መሪ ጸያፍ ስድብ መስደብ እነማን ናቸው ይሄን የተናገሩት? ማን አስተማራቸው? ሲሰደብ ያደገ፣ ከተሳዳቢ ጋር የኖረ ፣ተሳዳቢ ያሳደገው እየተባለ እሱን ሲመሩትና ኮትኩተው ሲያሳድጉት እስከነበሩት ታላላቅ ሰዎች ድረስ ውግዘቱ ይቀጥላል «ማን ከማን ምን ይማራል» እንደሚባለው ይሆናል።አሁን የሚታየውም ክብረ ነክ ነገሮች ለማንም የሚጠቅሙ ሳይሆኑ ኢትዮጵያዊነታችንን እየረሳን ማን ያሳደጋቸው እየተባልን መሆኑን ያሳያሉ። እንግዳ ተቀብሎ እግር አጥቦ፣ ለራሱ ሳይበላ አብልቶና መኝታውን ለቆ እንግዳ ተቀባይ ማህበረሰብ ውስጥ፣ ይሄንን ሲያይ ሲከተል በመጣ ህዝብ መሀል የሀገር መሪን ያክል ለማዋረድ ያልተገባ ስም መስጠት እንደተባለው ጓደኛህን ንገረኝ አይነት ይሆናል። ምክንያቱም በኢትዮጵያውያን ስነምግባር ውስጥ አልተለ መደማ። የኢትዮጵያዊነት መገለጫም አይደለማ። በኢትዮጵያዊነታችን ጉልበት እስከ መሳም ይዘልቃል አክብሮታችን።\nቅሬታዎች፣ ተቃውሞች፣ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነቶች፣ አለመስማማቶች … ይኖራሉ። በፊትም ነበሩ፣ አሁንም ፣ወደፊትም ይኖራሉ። እናስ ይሄንን ቅሬታ የምንገልጽበት መንገዱ ኢትዮጵያዊያን ክብርን በሚያዋርድ መልኩ መሆን አለበት? መታወቂያችን እኮ ዕርቅ ፣ይቅርታ ፣ምህረት ነው። የአጠፋ ይቅርታ ጠይቆ የተበደለ ተክሶ ቀጣይ ህይወት ፣ቀጣይ ኢትዮጵያዊነት ወደፊት ሊሆን ይገባል። ከዚህ ስንወጣ ማንነትህን ንገረኝ እንዳንሆን ከስህተታችን እንማር፣ እንመለስ ። ሰላም!አዲስ ዘመን ጥር 11/2011አልማዝ አያሌው", "passage_id": "0791f5460285713ae2e9a0c40897548e" }, { "passage": "“እ…አብይ ይወርዳል? የትኛው ነብይ ወይም ሟርተኛ ነህ አንተ ደግሞ!” እንዳትሉኝ። ቸኩላችሁ እንዳትበይኑ፤ ጥሎብን ችኩል ፈራጆች ሆነናል። ነገሩን በጥሞና ተመልክቶ መዳኘትና ሚዛናዊ ፍርድ መስጠት ብርቃችን ሆኗል አይደል!? የምናስበውን እንጂ እውነታውን ቀርበን መመርምር ሰልችተናል። አቤት ስንቶችን ባልተገኙበት አውለን ያለተግባራቸው ስም ሰጥተን፣ ያላሰቡትን አስበንና ያላዩትን ቀለም ቀብተን በችኩልነታችን ችካል ሆነንባቸው ይሆን? ዛሬ ዛሬማ እንደልማድ በስሚ ስሚ “ተደረገ” እና “ተባለ”ን ተከትልን የምንነጉድ በመሆናችን ተወራ ብለን መበየን ተክነንበታል። እንዴት ከኛ አርቀን ማስተዋልን ጭራሽ ዘንግተን እርግጠኛ ባልሆንበት ጉዳይ የመንጋ ብያኔ መስጠት ቀልሎናል። ለዛሬ ችኮላችንን የሚያሳይ አንድ ገጠመኜን ላካፍላችሁ ወደድኩ። ጠዋት የመጽሀፍ\nመደርደሪያዬን ተጠግቼ አንድ መጽሀፍ ስፈልግ ጊዜ ወሰደብኝ። ተራ በተራ ከተደረደሩት መካከል ማግኘት አልቻልኩም። ደግሜ ከላይ እስከታች\nፈለግሁ፤ የለም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መጽሀፍ ማዋስ መተው እንዳለብኝ እየተሰማኝ ነው። አንዳንድ ሰው መጽሀፍ ለማንበብ ተውሶ መመለስ\nአይወድም። አሊያም ደግሞ መዋሱን ይረሳዋል መሰለኝ መልስ ካላሉት በራሱ እንደ ጨዋ አመስግኖ የሚመልስ እየጠፋ ነው። እኔ ደግሞ\nየፈለኩትን/የነበረኝን መጽሀፍ ከመደርደሪያዬ ላይ ሳጣ ያናድደኛል። ዛሬም የፈለኩት መጽሀፍ የለም። ማን እንደወሰደው ማስታወስ አልቻኩም።\nበወሰደው ሰው ሳላወቀው አኮረፍኩ። ለስራ በጣም ስለፈለኩት በመጨረሻ አማራጭነት መግዛት እንዳለብኝ ከራሴ ጋር ተስማማሁ። ቁርሴን\nእንደ ነገሩ ቀመስ አድርጌ ከቤቴ ወጣሁ። መጽሀፉ ቆየት ያለ ስለሆነ ይገኛል ብዬ ወዳሰብኩበት ለገሀር አካባቢ ወዳለ መጻሕፍት ቤት\nለማምራት የሜክሲኮን ታክሲ ያዝኩ። ቡልጋሪያ ማዞሪያ ስደርስ አንዲት በዕድሜ ገፋ ያሉ እናት የተሳፈርኩበት\nታክሲ  አስቁመው፤ ባለ 25 ሊትር ቢጫ\nጀሪካን በረዳቱ አጋዥነት ወደ ታክሲው አስገቡ።  በእጆቻቸው በሩንና\nወንበር በመያዝና ዕድሜ የተጫናቸውን እግሮቻቸውን እየጎተቱ፤ በከፊል ተደግፈው ገብተው ከጎኔ አረፍ አሉ። እንደገቡ ሹፌሩ ያውቃቸዋል\nመሰል “እማማ እንዴት አደሩ ሰላም ነዎት? ከየት ነው?” አላቸው። እሳቸውም ቀና ብለው ወደ ሹፌሩ ተመልክተው በፈገግታ፡- “አብደላ\nአንተ ነህ እንዴ? ደህና ነህ አለህ ለመሆኑ …እሰይ! እሰይ! ልጄ በርትተሀላ እቺን ገዛህ፤ ላዳዋን ትተህ፤ ጎበዝ ልጄ እግዛብሄር\nይባርክልህ” ምርቃቱን አከታተሉለት።  እኔም በውስጤ ምርቃቱ ቅቡልነት\nእንዲኖረው ተመኘሁ። ከትላልቅ ሰዎች የሚገኝ ምርቃት የመንፈስ ምግብ አይደል! ደስ ሲል፤ቀጠሉ እማማ፡ “ከየት አልከኝ ልጄ ውሀ ልቀዳ ሄጄ። ይሄው\nአስራ አምስት ቀናችን ውሀ ከጠፋ እነዚህ ሙሰኞች በየቀበሌና በየወረዳው የተሰበሰቡ የመንግሥት ሹመኞች አስቸገሩን። ቆይ መስሎዋቸዋል\nገና ዶ/ር አብይ ይወርዳል። ሹመት ላይ ዘላለም የሚቀመጡ መስሎዋቸው እኮ ነው ሰውን የሚያንገላቱት…” ሰትዬዋ በሚናገሩት ተሳፋሪው\nሁሉ ጆሮ ሰጥቶ ያደምጣቸዋል። በአብዛኛው ተሳፋሪ ትኩረት የተሰጠው አንድ አረፍተ ነገር በተለይ ደጋገሙት “ዶ/ር አብይ ይወርዳል።”\nተሳፋሪው ድምጽ በማውጣት ጭምር አጉረመረመ “…እ..እ..”  በጥያቄ መልክ መሆኑ ነው። ሰው መሪውን ሲወድድ ደስ ይላል። ጠቅላይ ሚኒስትራችን\nበህዝቡ ዘንድ፤ በሰው ዘንድ ያስወደዳቸው ሁሉም ባንድነት የተቀበላቸው የዘመኑ ምርጥ መሪ ስለመሆናቸው ማሳያ የሴትየዋን “ዶ/ር\nአብይ ይወርዳል” የሚለውን ዓረፍተ ነገር መሰማት ተከትሎ በተቀየረው የተሳፋሪዎች የፊት ገጽታ ይበልጥ ተደመምኩ። ሴትዬዋ ቀጠሉ፡ “የወረዳው ሰራተኞች ስራ አይሰሩም። በማይረባ\nወሬ ነው ቀናቸውን የሚጨርሱት፤ ቧንቧ ተበላሸ እባካችሁ ስሩልን ብለን መመላለስ ከጀመርን 10 ቀን አለፈ። አልሰራ ብለውን በስተርጅና\nጀሪካን ተሸክመን እንዞራለን። እንቢ አሉ። የተነገራቸውን መስማት አቁመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶክተር አብይ ይወርዳል! አብያችን\nቀበሌ ድረስ ወርዶ ሁሉንም ያስተካክላል። እስከዚያ እንዳሻቸው ያድርጉን፤ ጉዳቸው ማሾፋቸው እስኪታወቅ ነው አብያችን መቶላቸዋል፤ለካስ ይወርዳል፤ እስከ ቀበሌ ድረስ፤ የሚሉት የጠቅላይ\nሚኒስትሩን አዲስ አሰራር ነው። ተሳፋሪው ከስልጣን ይወርዳል ብለው እሱን እየዘለፉ መስሎት ጆሮውን አቁሞ በቅሬታ እየገላመጣቸው\nእንዳላዳመጠ ነገሩ ሲገባው በፈገግታ እርስ በእርሱ ይተያይ ጀመር። ሴትዮዋ ቀጠሉ፤ ሁሉም ተሳፋሪ በፈገግታ እሳቸውን ነው የሚሰማው፤\n“ የሚናገረውን አልሰማህም ልጄ? ህዝብን አገልግሉ፤ ሀገራዊ ኃላፊነታችሁን ኢትዮጵያዊ አደራችሁን ተወጡ ሲል፤ እሱ የተባረከ ነው!\nቃሉም ተግባሩም የሚያጠገብ፤” እሳቸው የሚያወሩት ሹፌሩን እየተመለከቱ ነው ሌላውን ተሳፋሪ ቁብ ሰጥተው አላዩትም።“አይ እኛን በነገር ካስረጁን ዕድሜያችን ከገፋ በኋላ\nለእናንተ ምርጥ መሪ መጣ። እኛማ ጃጀን። በዚህ ዕድሜያችንም ቢሆን ይሄን ሀገር ወዳድ መሪ ስለሰጠን አምላክን እናመሰግነዋለን።”\nየሴትዮዋ የሰላ ንግግር ጆሮ ያስጥዳል። በመሀል ሹፌሩ ረዳቱን “እንዳትቀበላቸው የሳቸው ተከፍሏል” አለው። ረዳቱ የተቃውሞ ምላሽ\nሠጠ፡-“ኧ ዴች ነው። አብዲ ተቀብያለሁ። ብዙ ነው እስከነ ጀሪካናቸው” አለ። አስር ብር ማለቱ ነበር። ሴትዮዋ፡- “የምን ቋንቋ\nመቀየር ነው ግብዣ ከፍ ሲል ነው የሚጥመው፤ መልስላት ተባልክ መልስ!” ሲሉ በታክሲው ውስጥ የነበርነው ሁላችንም ተሳፋሪዎች በሳቅ\nተንከተከትን።በነገራችን ላይ የቋንቋ አጠቃቀማችን ብዙ ያስተዛዝባል\nአይደል፤ በእርግጥ የረዳቱ ከሹፌር ወይም መሰል የሙያ ባልደረቦቹ ጋር መግባባት የሚችሉበት ቋንቋ መፍጠራቸው ችግር ባይኖረውም፤\nከማንና እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው አለመረዳታቸው ተግባቦትን ያፋልሳል። “አራዶች” የኛ የሚሉት ካራዶቹ ጋር ካልሆኑ ከኔ ቢጤው\nጋር ሊያግባባቸው አይደለም በወጉ ሊያጋጫቸውም ይከብዳል። በየሆቴሉ መዝናኛና አቅጣጫ አመላካች የሆኑ ቦታዎች ላይ የሚለጠፉ ማህበራሰቡን\nወይም ነዋሪውን የዘነጉ የቋንቋ አጠቃቀሞች አብዛኞቹ በእኛ አገር እና ለኛ የተዘጋጁ እኛን ግን የማያግባቡ መሆናቸው ወደፊት የምናየው\nይሆናል።የረዳቱ ከሹፌሩ ጋር የተነጋገረበት የራሱ ቋንቋ እናታችን\nበሰጡት የመልስ ምት ድል ሆነና ሹፌሩ በድጋሚ እንዲመልስላቸው ነግሮት መለሰላቸው። በመጨረሻ ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ አጠገብ ሲደርሱ\nለሹፌሩ እንዲያቆምላቸው ነግረው የምርቃት መዓት አዥጎድጉደውለት ወረዱ። የምን አስር ብር ነው ይህን ምርቃት ለማግኘት ምንስ ቢሰጥ፤\nእናም ወረዳ ምናምን ላይ ያላችሁ አስፈጻሚዎች፤ እባካችሁ በእናንተ አቅም የሚፈታውን የህዝቡን ጥያቄ  እየለያችሁ ፍቱ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እናንተ ዘንድ ከመድረሱ\nበፊት እባካችሁ እናንተ ወደ ህዝቡ ዘንድ ውረዱና አድምጡት፤ ብለዋችኋል እናታችን፤አዲስ ዘመን የካቲት 6/2011", "passage_id": "0b406825e05019e01f1fe5967b35c23c" }, { "passage": "አየህ አንዳንዴ ቁስል ሲደርቅ፤ ጠባሳም አብሮ ይጠፋል። ያኔ ነው የመዘንጋት አባዜ የሚሳፈር። መዘንጋት ደግሞ ‹‹pure›› በሽታ ነው። ህመምህ ሳይድን ሰንበርህ እንኳን ቢጠፋ፤ ማን እንደለጠለጠህ ካላወክ የገራፊህ ወዳጅ ሆነህ፤ ለክፍል ሁለቱ አርጩሜ ጀርባህን እያደነደንክ ትጠብቃለህ። \nእመነኝ ወዳጄ የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም ቢሆንም ቅሉ፤ አባባሉ! ትዝታ ላይ ድር ሲያደራ ያኔ… አንዳንዴ! አንዳንድ ጊዜ ብቻ…የተወጋም ይረሳል። አዳም በስንብት ቀለማት እንዲህ ይላል… ለእያንዳንዱ ሰው የት እንዳለ የሚያሳየው፤ ካርታ እየተሰራ ካልተሰጠው፤ አፉን ሚጥሚጣ ባሞቀው ቁጥር አዋቂ ሊሆንብን ነው…እናማ ወዳጄ የቆምክበትን ካርታ ጎንበስ ብለህ አስተውል። ምናልባት የመዘንጋት አባዜ ተጠናውቶህስ ቢሆን? ግን እኮ መዘንጋት ባይሆንም ሱስም ሊሆን ይችላል። የመቀጥቀጥ፣ የመሰደብ፣ የመሰደድ… አባዜ። \nእናም አንዳንዴ የወጋ ብቻ ሳይሆን የተወጋም ይረሳል። ‹‹መቼ መቼ?›› ካልክ መልሱ ይሄውልህ…. ጠባሳህ ጠፍቶ ትውስታህ በጭጋግ ሲጋረድ፤ የታሪክ ሚዛኑ ተዛብቶ የቆመበት መሬት ሲክድህ…ማስተዋል እርቆህ ከጠላትህ ጋር ትጣባለህ። ቁስልህ ሽሮ ያልተነካህ ቢመስልህ፤ ያን ጊዜ ነው…የተወጋ የሚረሳ። \n‹‹ፍትህ ትወዳለህ ፍትህ እንደጎደለ እያወክ ግን ዝም ትላለህ። አየህ ይሄ አንድ ሰው ሲከፋፈል ነው›› ይልሃል አዳም፤ ጎጥ የሸበበው ሽል ውስጥ ተሸሽገህ መላ ቅጡ ጠፍቶህ ሲያይህ። ቆሜለታለው የምትለው ቀድሞ ሲሞትልህ፤ ፍሬው ሳይደርስ ተስገብግበህ አጨድከው። እናም የቆምክበትን ካርታ ተመልከተው፤ በሳር ውስጥ ካለ እባብ ጋር ወዳጅ መስሎህ ለምደህ ይሆን? \nምን መሰለህ ወንድም ዓለም ምላስም እኮ ያዳልጣል። አንዳንዴ ህሊናም ከራስ ይሸሻል። ታዲያ ሰንበርህ ከውስጥ ተሸፍኖ የጠፋ መስሎ ቢያስትህ፤ ከምኔው ከጠላቶችህ ተወዳጅተህ አዛኞችህን መንከስህ። ሙሾ አውራጅ እንዲህ ትላለች፤ የደረቀውን የእንባ ቀረጢቷን በአይበሉባዋ እያሸች…‹‹ወይ እኛና ዶሮ፤ አሞራና ሞት ሲመጣ መንጫጫት፤ ሲሄድም መርሳት››…ዛዲያማ ወንድሜ ከገባህበት ማቅ ለመውጣት የህሊናህን ድር ጠራርጋት። የማስተዋልህን በር ክፈታት… \n‹‹አህያውን ፈርቶ ዳውላውን›› እንዲሉ… በከሰረ፣ በተንሸዋረረ የጥላቻ ‹‹ቦጠሊቃ›› አውቀህ ያስተኛህው ህሊናህ አንተን ብቻ ሳይሆን ያመነህንም ገደል ሊከት ነው። ‹‹በእንኪያ ሰላምታ›› እውነትህን አርቀህ ቀብረህ ‹‹ስተህ ለማሳት›› ልብህን ምን አበረታው? \nአየህ የተወጋ ሲረሳ… ለተዛባ ፍትህ ቆሜያለሁ ብሎ፤ ንጋትን ለማጨለም ይጣደፋል። ያመነበት ሲሳካ፤ ጉም የዘገነ ይመስለዋል። ትናንቱ እንደ ገደል ማሚቱ ጮሆ ይጠራዋል። ሳይጠጣ እንደሰከረ፣ አሁንም አሁንም እንደሚወላገድ፤ የቆመበት መሬት ስምጥ ገደል እንደሆነ ይታየዋል። ታሪክን ያጨልማል፤ በጭካኔ ተሞልቶ ምስኪን ገበሬን ይከሳል። የእርሱ ያልሆነን ያማትራል…ከአራጁ እየዋለ የበቀለ…በትን መሬት ይክዳል። ለካ የተወጋም ይረሳል….።ከገዳዩ ጋራ አብሮ መሬት ይምሳል። \nአዲስ ዘመን ግንቦት 9/2012\nዳግም ከበደ", "passage_id": "203f9ed28e539b2c365fe517812e41eb" } ]
b91e809768c12e8c3fecd81698d6e003
d3fe25035bb9c528b189a342e6f49656
ኢትዮጵያ 50 ዓመታት የተጠቀመችበትን የንግድ ህግልትቀይር ነው
 ክፍለዮሐንስ አንበርብርአዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ ለግማሽ ክፍለ ዘመን ስትጠቀምበት የነበረውን የንግድ ህግ ከዘመነ ቴክኖሎጂ ጋር የተናበበና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ አዲስ ህግ ልትቀይረው መሆኑን ተገለጸ። አገሪቷ ከምትጠቀምባቸው መድሃኒቶች ውስጥ 80 ከመቶ የሚሆነው በውጭ ምንዛሪ ተገዝቶ ወደ አገር ውስጥ የሚገባ መሆኑም ተገለጸ።የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ድኤታ አቶ ምስጋኑ አረጋ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት ፤ ኢትዮጵያ ግማሽ ክፍለ ዘመን ስትጠቀምበት የነበረው የንግድ ህግ ከዘመነ ቴክኖሎጂ ጋር የተናበበና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ በአዲስ ህግ ልትተካ ነው።አገሪቷ እያካሄደች ያለው የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ መርህ በዋናነት በማክሮ ኢኮኖሚ፣ መዋቅራዊ እና የዘርፍ ማሻሻያ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ጠቁመው ፣ በዚህም በአሁኑ ወቅት ሁለንተናዊ ለውጦችን ለማምጣት ከመቼውም በላይ እየተንቀሳቀሰች መሆኑን አብራርተዋል። እንደ ሚኒስትር ድኤታው ገለፃ፤ እየተደረጉ ካሉ ማሻሻያዎች መካከል 50 ዓመታትን በሥራ ላይ የነበረው የንግድ ህግ ዘመኑ የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ ባገናዘበ መልኩ የማሻሻል እና ህግ ሆኖ የማውጣት ሂደቱ ከጫፍ መድረሱን አብራርተዋል። በአሁኑ ወቅትም የተረቀቀው ህግም ለተወካዮች ምክር ቤት መላኩን ጠቁመው ። ውይይት ከተደረገበትና የተወካዮች ምክር ቤት ይሁንታን ካገኘ በኋላ ወደ ሥራ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ይህም አገሪቱ የጀመረችውን ዕድገት ለማፋጠን እና አቅም በፈቀደ መጠን የንግዱን ማህበረሰብ ጥያቄ ለመመለስ አጋዥ እንደሚሆን አመልክተዋል። የዓለም ማህበረሰብ በአሁኑ ወቅት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ከፍተኛ ግብይት እያካሄደ ይገኛል ያሉት ሚኒስትር ድኤታው፤ የመጠቁ አገራት የንግድ ፈቃዳቸውን ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችንና መረጃዎችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በኦንላይን እያስተናገዱ ይገኛል ብለዋል። ይሁንና ኢትዮጵያ ከዚህ አኳያ እጅጉን ወደ ኋላ የቀረች በመሆኑ እነዚህንና መሰል ጉዳዮችን ታሳቢ ያደረጉ ማሻሻያዎች እየተደረጉ መሆኑን አስታውቀዋል።የኢትዮጵያ የንግድ አካሄድ ሚዛን ያልጠበቀ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ምስጋኑ ፣ በቀጣይ እነዚህን ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ ይሠራል ብለዋል። ለአብነትም አገሪቱ ከምትጠቀምባቸው መድሀኒቶች ውስጥ 80 ከመቶ የሚሆነው በውጭ ምንዛሪ ተገዝቶ ወደ አገር ውስጥ እንደሚገቡ አመልክተዋል። በዘርፉ ሀገር ውስጥ ያሉ አምራቾችን አቅም በማጎልበትና በቁጥር እንዲበዙ በማድረግ ከሀገር ውስጥ ፍጆታ በተጨማሪ ለውጭ ገበያ እንዲያቀርቡ ለማድረግ መንግሥት ከአምራቾች ጋር በቅርበት የሚሠራ መሆኑን ሚኒስትር ድኤታው አረጋግጠዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 25/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=38749
[ { "passage": "የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያን የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት አባልነት አፀደቀ።ምክር ቤቱ ስምምነቱን ዛሬ ባካሄደው ስብሰባው ያጸደቀ ሲሆን ስምምነቱ የዓለም የንግድ ድርጅት ከተመሠረተ ትልቁ የንግድ ስምምነቶች አንዱ ሲሆን፥ በአፍሪካ አንድ ገበያ ለመፍጠር ሙከራ ያደርጋል።ውሳኔው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሚያራምዱት አዕምሮን ለሃሳብ መንሸራሸርና ገበያዎች ለትስስር በመክፈት በአፍሪካ ክልላዊ ውህደትንና ጥብቅ ጥምረት እንፍጠር ከሚለው ራዕይ ጋር ይጣጣማል።የኢትዮጵያ ውሳኔና የፓን አፍሪካን እሳቤ የመደገፍ ታሪካዊ ልምድ የአፍሪካን ውህደት በተሻለ ሁኔታ ወደ እውነታነት ያስጠጋል። (ምንጭ፡- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)", "passage_id": "aef81ad6947966324dd1252f46a2132d" }, { "passage": "አገሪቱ የንግድ ምልክት ምዝገባ በማካሄድ ረገድ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መሆኗን የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ፅህፈት ቤት አስታወቀ።በአገሪቱ ውስጥ ከተመዘገቡ ከ18ሺ200\nየንግድ ምልክቶች ውስጥ 59 ከመቶ በውጭ አገራት የተያዘ መሆኑንም ገልጿል። የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ፅህፈት ቤት\nየንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ ዳይሬክተር ወይዘሮ ትዕግስት ቦጋለ በተለይም ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ አገሪቱ የንግድ ምልክት ምዝገባ በማካሄድና ጥበቃ እንዲደረግለትም የምታደርገው ጥረት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው። የንግድ ምልክት አሰጣጥ 1978 ዓ.ም ጀምሮ በንግድ ሚኒስቴር ሥር የነበረ ሲሆን፤ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ፅህፈት ቤት ስር በአዲስ መልክ የንግድ ምልክት ምዝገባ ተካሂዷል። እስካሁን ባለው የንግድ ምዝገባ ሂደትም 18ሺ200 የንግድ ምልክቶች ምዝገባ የተከናወነ ሲሆን፤ 7ሺ540\nምልክቶች የአገር ውስጥ ሲሆኑ 59 ከመቶ ወይንም 10ሺ699 የንግድ ምልክቶች በውጭ\nአገር የተመዘገቡ ናቸው። እንደ ዳይሬክተሯ ገለፃ፤ የንግድ ስያሜ መያዝና የንግድ ምልክትን መያዝ ልዩነትን አለመረዳት ጭምር እንደሚስተዋል ገልፀዋል። በግንዛቤ ደረጃ በጎላ መልኩ የተሠራበት አይደለም። በመሆኑም እስካሁን ባለው ሂደት የውጭ ንግድ ምልክት ምዝገባ የላቀ ነው። ይሁንና ከባለፈው ዓመት ጀምሮ መሻሻሎች መኖራቸውን አስረድተዋል። ከዚህም በተጨማሪም የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ፅህፈት ቤት በሐዋሳ፣ ጅማ እና ባህርዳር ከተሞች የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ፅህፈት ቤት በመምጣት የንግድ ምልክት ያለማስመዝገባቸው በአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይም ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደሚያሳድርና በዓለም ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመውጣት አስቸጋሪ የሚሆን ነው። በነፃ ገበያ ውድድር ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ሚና ያሳድራል። በተጨማሪም ተቋሙ በክህሎት የዳበረ ባለሙያና ለሥራው በቂ ትኩረት ማነስ ችግሩን አባብሶታል። የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ፅህፈት ቤት ከዓለም አቀፍ ስምምነቶች ውስጥ ሁለቱን ብቻ የፈረመ መሆኑን የጠቆሙት ወይዘሮ ትዕግስት፤ አልፎ አልፎ ዓለም አቀፍ ዝና ያላቸውን ተቋማት የንግድ ምልክት የመጠቀም አዝማሚያ መኖሩን ገልፀዋል። ይሁንና ይህ የራስን ምርትና የንግድ ምልክት የኢትዮጵያ ምርቶች ጎልተው እንዳይወጡና በዓለም ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ ተፅዕኖ ያሳድራል። በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ፅህፈት ቤት ይግባኝ ሰሚ የሆኑት ወይዘሪት እየሩሳሌም ተፈሪ በበኩላቸው፤ ከባለቤትነትና ከንግድ ምልክት ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ቅሬታዎች መኖራቸውን ጠቁመው በዚህ ዓመት ብቻ 60 መዝገቦች ላይ አቤቱታ ቀርቦ ለ46 ውሳኔ\nየተሰጠ ሲሆን ቀሪዎቹ እስከ ሐምሌ 14 ድረስ በቀጠሮ ላይ ናቸው። በዚህ ውስጥም የውጭ ተቋማት ቅሬታ መኖሩን አብራርተዋል። ከኢትዮጵያ አእምሯዊ\nንብረት ፅህፈት ቤት በተገኘው\nመረጃ፤ የንግድ ምልክት\nአንድ ድርጅት የሚሰጠው\nአገልግሎት ከሌላው የሚለይበት\nምልክት ሲሆን፤ አንድ\nየንግድ ምልክት ከወጣ\nበኋላ እስከ ሰባት\nዓመት መጠቀም ይቻላል።\nከዚህን በኋላ በሦስት\nወራት ውስጥ ያለቅጣት፣በቅጣት\nደግሞ በስድስት ወራት\nበአጠቃላይ በዘጠኝ ወራት\nውስጥ የንግድ ምልክቱ\nመታደስ አለበት። በተጨማሪም\nአንድን የንግድ ምልክቶች\nእስከ ሦስት ዓመት\nምንም ሳይሠራበት የተቀመጠ\nከሆነ ውድቅ ይደረጋል።አዲስ ዘመን ቅዳሜ ግንቦት 24/2011ክፍለዮሐንስ አንበርብር ", "passage_id": "f90aa1666341a523b977b05aebdff9b0" }, { "passage": "የአፍሪካ ሀገራት ነጻ የንግድ ቀጠናን ተግባራዊ ለማድረግ ተስማሙ። ስምምነቱ የሀገራቱን ምጣኔ ሀብት በእጅጉ የሚያሳድግና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለዉን የንግድ ልዉዉጥ በእጥፍ ሊያሳድግ የሚችል ስለመሆኑም ተነግሯል።ስምምነቱን 54 የአፍሪካ ሀገራት ሲፈርሙ ኤርትራ ብቸኛዋ እምቢታዋን የገለፀች ሀገር ሆናለች፡፡የአፍሪካ ሀገራት ከአራት አመታት ብርቱ ክርክርና ዉይይት በኋላ ባለፈዉ መጋቢት ወር ላይ በስምምነት የተቋጨዉ የአፍሪካ ሀገራት ነፃ የንግድ ቀጠናን የመመስረት እቅድ ትላንት በናሚቢያዋ መዲና ኒያሚ በተካሄደዉ 35ኛዉ አስቸኳይ የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ በ54ቱ ሀገራት መሪዎች ፊርማ መደምደሚያዉን አግኝቷል።በዘንድሮዉ የመሪዎቹ ጉባኤ ወሳኝና የአህጉሪቱን ምጣኔ ሀብታዊ ትስስር ያጠናክራሉ የተባሉ ዉሳኔዎች ተላልፈዋል።ነፃ የንግድ ቀጠናዉ 1.3 ቢሊየን የሚሆኑትን የአህጉሪቱ ዜጎች የሚያስተሳስርና 3.4 ትሪሊየን ዶላር የሚገመት ምጣኔ ሀብታዊ ቀጠና የሚፈጥር እንደሚሆን ታምኖበታል። በርግጥ አዲሱ ስምምነት የአህጉሪቱን ቀጣይ የልማት ትንሳኤ የሚያበስር እንደሚሆንም ይጠበቃል።መሪዎቹ በትላንትናዉ ዉሳኔያቸዉ ምዕራብ አፍሪካዊቷ ጋና የንግድ ቀጠናዉ መቀመጫ እንድትሆን ዉሳኔ አስተላልፈዋል።የአለም የንግድ ተቋም ከ25 አመታት በፊት በፈረንጆቹ 1994 ከተመሰረተ ወዲህ በግዙፍነቱ ሁለተኛ ነዉ የተባለለት አዲሱ የአፍሪካ ሀገራት ነፃ የንግድ ቀጠና፣ በአህጉሪቱ ሀገራት መካከል የንግድ ትስስርን የሚያጠናክር፣ የአቅርቦት ሰንሰለቶችን የሚያሰፋና የአህጉሪቱን ምጣኔ ሀብት በእጅጉ የሚያሳድግ እንደሚሆን ታምኖበታል።በስምምነቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርና የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱልፈታህ አልሲሲ አፍሪካዊያን እርስ በእርስ በመደጋገፍ አህጉሪቱን ለማልማት ከስምምነት በመድረሳችን የአለም አይኖች ሁሉ ወደ አፍሪካ እንዲዞሩ ሆኗል ብለዋል።የስምምነቱ መፈረም በአህጉረ አፍሪካ ምጣኔ ሀብታዊ እድገት ለማስመዝገብና የህዝቦቿን የዘመናት የልማት ህልም ለማሳካት ብሎም ኑሯቸዉንም በዘላቂነት ለመቀየር ፅኑ መሰረትን የሚጥል ስለመሆኑም አልሲሲ አንስተዋል።የአፍሪካ ሀገራት እርስ በእርሳቸዉ የሚያደርጉት አህጉር አቀፍ የንግድ ትስስር ከሌሎች አህጉራት ጋር ስነፃፀር እጅጉን ዝቅተኛ እንደሆነ ይነገራል። ለአብነት በፈረንጆቹ 2017 የእስያ ሀገራት 59 በመቶ የአዉሮፓ ሀገራትም ቢሆኑ 69 በመቶ ያክሉን የንግድ ልዉዉጥ ያደረጉት እርስ በእርሳቸዉ ነዉ።በአፍሪካ ሀገራት በአንፃሩ በአህጉሪቱ የነበረዉ የእርስ በእርስ የንግድ ልዉዉጥ ከአህጉሪቱ አመታዊ የዉጭ ንግድ 17 በመቶ ያክሉን ብቻ የሚሸፍን ነበር። ይህ መሆኑ ደግሞ ሌሎች የንግድ ቀጠናዎች ባለፉት አስርት አመታት በጋራ በመስራታቸዉ ያስመዘገቡትን ምጣኔ ሀብታዊ ስኬት አፍሪካዊያን ሀገራት እንዳይጋሩት አድርጓቸዉ ቆይቷል።በእርግጥ አፍሪካዊያን ተመሳሳይ የንግድ ትስስሮችን ላለመፍጠራቸዉ እንቅፋቶች እንደነበሩ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ያነሳሉ። በተለይም እንደ መንገድ የመሳሰሉ የመሰረት ልማት ዝርጋታዎች አናሳ መሆን፣ አሳሪና ነፃ ያልሆኑ የድንበር ላይ አሰራሮች፣ ስር የሰደደ ሙስናና በተለያዩ የአህጉሪቱ አከባቢዎች የሚስተዋሉ አለመረጋጋቶችና የሰላም እጦት ዋነኞች ምክኒያቶች ናቸዉ።54 የስምምነቱ ፈራሚ ሀገራት በአብዛኞቹ ምርቶቻቸዉ ላይ የቀረጥ ቅነሳ ለማድረግ ወስነዋል። ይህ ደግሞ እንደ አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ግምት የአሁኑ ነፃ ንግድ ቀጠና መመስረት የአህጉሪቱን ንግድ ከ15 እስከ 25 በመቶ እንዲያድግ ያስችላል። ከዛም በዘለለ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች፣ በተለይም እንደ ሙስናና ዉስብስብ አሰራሮች የሚወገዱ ከሆነ የአህጉሪቱ ንግድ ከተባለዉም በላይ በእጥፍ ኢያድግ ይችላል ተብሎ ይገመታል።በእርግጥ በተለያዩ የአፍሪካ ክፍሎች ተመሳሳይ አላማን ያነገቡ እንደነ ECOWAS፣ EAC፣ SADC እና COMESA የመሳሰሉ ቀጠናዊ ተቋማት የነበሩ ቢሆንም ከምስራቅ አፍሪካዉ EAC ዉጭ ቀሪዎቹ ተቋማት ይህ ነዉ የሚባል የስኬት ታሪክ የላቸዉም። በተለይም በሀገራት መካከል ያለዉ የሀሳብ መለያየት ለዚህ ዋነኛዉ ምክኒያት ነዉ።የአሁኑን ስምምነት ስኬት ይነፍጉታል ከተባሉት ጉዳዮችም የሀገራት የሀሳብ መለያየት አንዱ ነዉ። በተለይም እንደነ ናይጄሪያ ለመሳሰሉት ባለ ግዙፍ ምጣኔ ሀብትና ኢኮሚያቸዉ በነዳጅ ላይ ለተመሰረተ ሀገራት የአሁኑ ስምምነት እምብዛም የጎላ ጥቅም የለዉም። ይህም ለናይጄሪያና መሰሎቿ የስጋት ምንጭ ሆኗል።እንደነ ደቡብ አፍሪካ የመሳሰሉት ሀገራት በአንፃሩ ከስምምነቱ የተሻለ ተጠቃሚዎች እንድሚሆኑ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ገምተዋል።እናም በሀገራት መካከል ያለዉን የተጠቃሚነት ልዩነት መቅረፍና ልዩነቱን ማጥበብ የአዲሱ ስምምነት ፈታኝ ስራ ይሆናል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።", "passage_id": "f6034cd09dc604156c499661f6ebc996" }, { "passage": "ቴሌንና አየር መንገድን የመሰሉ አሉ የሚባሉ የመንግሥት ድርጅቶችን ወደግሉ ዘርፍ ለማዘዋወር ከመወጠን አንስቶ ከጎረቤት ሃገሮች ጋር ያለውን ግንኙነት እስከማጠናከር ድረስ። \n\nየዳይስፖራ ትረስት ፈንድ (የአደራ ገንዘብ እንበለው) እና ለአፍሪካውያን እህት ወንድሞቻችን ቪዛ አየር መንገድ ሲደርሱ መስጠትን ጨምሮ ያሉ ከዚህ በፊት የማናውቃቸው ክንውኖች መታየት ጀምረዋል።\n\n• ጫትን መቆጣጠር ወይስ ማገድ? \n\nበአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማክሮና ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚክስ ምሁሩ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስካሁን ያከናወኗቸው ጉዳዮች መልካም ሆነው ሳለ በምጣኔ ሃብት ጉዳይ አማካሪ ያሻቸዋል ይላሉ። \n\nእውን ጠቅላዩ ወደሥልጣን ከመጡ ወዲህ የምጣኔ ሃብት ፖሊስ ለውጥ አይተናል ወይ? ትልቁ ጥያቄ ነው።\n\n«የምር የሆነ የፖሊሲ ለውጥ የለም ግን ሃሳብ አለ፤ የመለወጥ አዝማሚያ ታያለህ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመጡ ወዲህ ይህ ነው ፖሊሲዬ በዚህ መልኩ ነው የምሄደው ያሉን ነገር የለም። ሃዋሳ በነበረው ጉባዔ (የኢህአዴግ) ላይም የተናገሩት ይሄንኑ ነው። በፊት የነበረው የኢኮኖሚ አስተሳሰብ እንዳለ እንደሚቀጥል ነው ፍንጭ የሰጡት።...»\n\n« ...በአንፃሩ ደግሞ ከዚያ ቀድም ብሎ አንዳንድ ትላልቅ የምንላቸውን የመንግሥት ኩባንያዎች በከፊል ለመሸጥ ሃሳብ እንዳላቸው አሳውቀዋል። ይህ የሚያሳይህ በፊት ከነበረው ለየት ባለ መልኩ ከፈት በማድረግ፤ የመንግሥት ሚና ብቻ ከጎላበት ኢኮኖሚ የግሉም ዘርፍ የሚሳተፍበት ኢኮኖሚ ለመመሥረት ቢያንስ ሃሳብ እንዳላቸው ያሳያል» ይላሉ ፕሮፌሰሩ።\n\n• ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል?\n\nየመንግሥት ድርጅቶችን የመሸጥ ጉዳይ ግን አከራካሪነቱ እንደቀጠለ ነው፤ 'ሃገር መሸጥ ነው' በሚሉና 'እንዲህ ካልሆነ አናድግም' የሚል ሃሳብ በሚያነሱ መካከል።\n\nለፕሮፌሰር አለማየሁ ግን ዋናው ጉዳይ ወዲህ ነው፤ መለየትና ማመቻቸት።\n\n«ወደ ገበያ ተኮር ኢኮኖሚ የምንሄድበት ዋናው ምክንያት ውድድር ለማምጣት ነው፤ ውድድር ለማምጣት ደግሞ መወዳደሪያ ሜዳውን ማስተካከል አለብን። ውድድሩን የሚመራ፤ የሚቆጣጠር አካል ማደርጀት ያስፈልጋል። አለበለዚያ ዝም ብሎ ከመንግሥት ወደ ግል መሄድ፤ 'ሞኖፖሊውን' ከመንግሥት ወደግል መቀየር ነው። የግል ሞኖፖል ደግሞ ተጠያቂነት የለበትም፤ ብሩን የት ያጥፋው የት አይታወቅም፤ የሞራል ኃላፊነትም የለበትም።»\n\nምሁሩ «ምሳሌ ልስጥህ...» ይላሉ፤ «ምሳሌ ልስጥህ፤ ኢትዮ-ቴሌኮም በጣም ደካማ ነው፤ እናውቀዋለን። ሶማሊያ እንኳን ያለው የቴሌኮም አገልግሎት የተሻለ ነው። ኬንያማ አንደርስባቸውም። ስለዚህ እንደ ቴሌኮም ዓይነቱን ምን ማድረግ ነው? በከፊል መሸጥ። ችሎታው ላላቸው፤ ቢቻል ደግሞ አፍሪቃዊ ለሆኑ ድርጅቶች፤ በዚያውም ቀጣናዊ ግንኙነቱን ማጠናከር። እንደዚህ አድርጎ ተወዳዳሪነቱን ማጎልበት። ይህንን ውድድር የሚቆጣጠር ሥርዓት መዘርጋት፤ ከዚያ ለውድድር መክፈት። እንዲህ ነው መሆን ያለበት።»\n\n«አሁን በሌላ በኩል ደግሞ ስትመጣ አየር መንገድ አለ። አየር መንገድ በእኔ እምነት እንኳን ሊሸጥ፤ ለመሸጥ መታሰብ ራሱ የለበትም። ምክንያቱም በጣም ትርፋማ የሆነ ድርጅት ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ በጣም ተወዳዳሪ የሆነ ድርጅት ነው፤ በጣም! ያለው ንብረት ወደ 80 ቢሊዮን ብር በላይ ነው፤ ዕዳው 60 ቢሊዮን ገደማ ነው። ስለዚህ ንብረቱ በአያሌው ይበልጣል። በመንገደኛ የሚያገኘው ገቢ 'ቶፕ' ሰባት ከምትላቸው የአሜሪካ አየር መንገዶች ይበልጣል።»\n\n«ይህ እንግዲህ ኢኮኖሚያዊ መከራከሪያ ነው፤ ወደ ባህላዊው ስትመጣ አየር መንገድ ቅርሳችን ነው፤ ዓለም ላይ ምንም ሳይሳካልን ሲቀር እንኳ አየር መንገዳችን ስኬታማ ነበር፤ ምልክታችን ነው።... ", "passage_id": "1e9e778bd5473925e662bb16e4a042d5" }, { "passage": "በኃይሉ አበራአዲስ አበባ:- የኢንቨስትመንት ህጉ መሻሻል የቴክኖሎጂ ሽግግሩን በማረጋገጥ፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በማሻሻል፣ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት እና ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል በመፍጠር በኩል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከሰሞኑ ከእስራኤል፣ ከእንግሊዝ እና ከአውስትራሊያ ከመጡ ባለሀብቶች ጋር በተሻሻለው የኢንቨስትመንት ህግና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በአዲስ አበባ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሂዷል።በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ መኮንን ኃይሉ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ መንግሥት የኢንቨስትመንት ህጉን በማሻሻል፣ የግሉን ዘርፍ ሚና በማጎልበት እንዲሁም ኢትዮጵያ ከመቼውም በላይ ለቢዝነስ የተሻለችና ምቹ እንድትሆን ከማድረግ አንጻር በትኩረት እየተሰራ ነው። ይህም የውጭ ባለሀብቶችን ተሳትፎ በማሳደግ ኢንቨስትመንቱን እያሳደገው ይገኛል።በሀገራችን በተካሄደው የፖለቲካ ሪፎርም በሌላኛው ጎኑ የኢኮኖሚ መሻሻሎች ማምጣቱን የገለጹት አቶ መኮንን፤ ኢትዮጵያ ያሻሻለችው የኢንቨስትመንት ሕግ በምስራቅ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ደረጃ በኢትዮጵያ ያለው መደላደል ምቹ መሆኑን ግንዛቤ መወሰዱን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ እንድትሆን ከማድረግ አንጻር ባለፉት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አስተባባሪነት እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቢሮ ተሳትፎ ተቋማቶችን ባካተተ መልኩ የንግድና ኢንዱስትሪ፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የባንክና ሌሎች መሰል ነገሮች ጋር በተያያዘ ኢንቨስትመንቱን የማቅለል ስራዎች እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ መኮንንን እንደሚሉት፤ አንክታድ በሚባል ዓለም አቀፍ ሪፖርት በቅርቡ ባወጣው መረጃ ኢትዮጵያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ከምስራቅ አፍሪካ ግንባር ቀደም ላይ ትገኛለች፤ በአፍሪካ ደረጃ ደግሞ ከግብጽ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ኮንጎና ሞሮኮ በመቀጠል በአምስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በመሆኑም በሀገራችን የውጭ እና የሀገር ውስጥ ተሳትፎ የሚያሳድግ እና የግል ዘርፉን ሰፋ ባለ መልኩ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያስችል የኢንቨስትመንት ሕግ ተሻሽሎ መቅረቡ ሀገራችን የበለጠ የወጭ ባለሀብቶች ትኩረት እንዲኖራት ያስችላታል። ይህ ደግሞ ለዜጎቻችን ሰፊ የሥራ እድል ከመፍጠር አንጻር የጎላ እና የላቀ ሚና ይኖረዋል። እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ግኝት እና የቴክኖሎጂ ሽግግሩንም የተሻለ ያደርገዋል፤ ነው ያሉት።የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በበዙ ቁጥር ኅብ ረተሰቡ በሚያገኘው አቅርቦት ከትምህርት ቤት፣ ከሆስፒታሎችና መሰል የመሠረተ ልማት እና የማህበራዊ ተቋማት አገልግሎት እያደጉ የሚመጡ በመሆኑ ለዜጎች የሥራ እድል ፈጠራ ባሻገር የማህበራዊ ተቋማት አገልግሎትን በማሳደግም በቀጥታ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉም ነው አቶ መኮንን የገለጹት።በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ተሳታፊ የነበሩት አቶ አሰፋ፣ መንገሻ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በፀሐይ ኃይል ውሃ የሚያሞቁ መሳሪያዎችን የሚያመርት ፋብሪካ በሰንዳፋ የኢንዱስትሪ ዞን ውስጥ ያቋቋሙ ባለሃብት ናቸው። በእስራኤል ሀገር ከ30 ዓመት በላይ መኖራቸውን የገለጹት አቶ አሰፋ እንደሚሉት፤ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሸን ኢንቨስትመንት ከማሻሻል አንጻር ጥሩ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ነገር ግን ከዋና ኮሚሽኑ ከወጣ በኋላ ያለው የቢሮክራሲ ሁኔታ በጣም መሻሻል ይኖርበታል።አሁን ያለው የኢንቨስትመንት ህግ መሻሻልን ተከትሎ የኢንቨስትመንት የአቀባበል ሁኔታውን ማፋጠን ከተቻለ፣ እስራኤል አነስተኛ አገር ብትሆንም የቴክኖሎጂ ባህር እንደመሆኗ በእርሻ፣ በሶላር እና ሌሎችም በርካታ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ከእስራኤል ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ እንደሚችሉ ነው አቶ አሰፋ የተናገሩት። በፀሀይ ኃይል ውሃ የሚያሞቁ መሳሪያ ማምረቻው ወደ ሀገራችን ቢገባ ያለውን ጠቀሜታና አዋጭነት በማሰብ እና የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት በሚል ቴክኖሎጂውን ማቋቋማቸውን የገለጹት አቶ አሰፋ፤ ፋብሪካውን ካቋቋሙ ስድስት ዓመት እንደሆነውና ምርት ማምረት ከጀመረ አራት ዓመት እንደሆነው ተናግረዋል። ከብዙ ድካምና ውጣውረድ በኋላም በግል መኖሪያ ቤቶች በፔንሲዮኖች፣ በአፓርትመንቶች፣ በሆቴሎች እና ጤናጣቢያ ላይ ሁሉ መግጠም መጀመራቸውን ገልጸዋል። አቶ አሰፋ፣ በእስራኤል ሀገር ሲኖሩ በነበረበት ቅቡጽ በሚባል ኩሚዩናል በሚኖርበት አካባቢ የእርሻ ሂደቱን ታዝበዋል። በሦስት ወር እና በአራት ወር ውስጥ የተለያየየምርት አይነት ይመረትበታል ብለዋል። በሦስት ወር እና በአራት ወር ውስጥ መሬቱ በተለያየ የምርት አይነት ይሸፈናል። ብዙ ሄክታር መሬት በበቆሎ ተሸፍኖ ይታያል፤ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ደግሞ ያንን የዚያ ምርት ተሰብስቦ መሬቱን አለስልሰው በዚያ በቆላ መሬት ላይ የተንጣለለ የስንዴ ማሳ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሲያሰሩ ይታያል፤ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ደግሞ አትክልቶች ሲሰራበት መመልከታቸውን ገልጸዋል። ይሄንን ቴክኖሎጂ በሀገራችን ተግባራዊ በማድረግ ኢትዮጵያን በይበልጥ የአፍሪካ የዳቦ ቅርጫት ማድረግ ይቻላል፤ የስንዴ ቋት መሆን እንችላለን። ቴክኖሎጂውን ደግሞ ለመቀበል እና ወደ ፊት ለማራመድ በሀገራችን በእርሻ ኢንጂነሪንግ የተማሩ ሰዎች በኩል ቴክኖሎጂውን በማስፋፋት ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን በማገናዘብ ከራሳችን አልፈን ለሌላው ሀገር ማቅረብ የሚቻልበትን ሰፊ እድል አለ ብለዋል። በሀገራችን ባሌና አርሲ የስንዴ ሜዳ መሆናቸው እንደሚታወቀው ሁሉ በወሎ እና አፋር ድንበር ላይ ከፍተኛ የስንዴ ምርት ማምረት ይቻላል። በሱማሌ ክልል ገናሌና ሸበሌ ወንዞች አሉ ሜዳው የሰጠ ነው ሰላም እና ደህንነት እስካለ ድረስ ከራሳችን አልፈን ምርቱን ሽጠን ለሌላም ሀገር መቀለብ የሚያስችል አቅም አለ። ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ አይደለችም የሚለውን የውጪ ኢንቨስተሮች እይታ ለመቀየር ኢትዮጵያውያን የሀገራችንን ጥቅም በሚጠብቅ ሁኔታ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በግልጽ በመወያየት እና ግብረመልስ መስጠት ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል። የምርት አይነት ይመረትበታል ብለዋል። በሦስት ወር እና በአራት ወር ውስጥ መሬቱ በተለያየ የምርት አይነት ይሸፈናል። ብዙ ሄክታር መሬት በበቆሎ ተሸፍኖ ይታያል፤ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ደግሞ ያንን የዚያ ምርት ተሰብስቦ መሬቱን አለስልሰው በዚያ በቆላ መሬት ላይ የተንጣለለ የስንዴ ማሳ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሲያሰሩ ይታያል፤ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ደግሞ አትክልቶች ሲሰራበት መመልከታቸውን ገልጸዋል። ይሄንን ቴክኖሎጂ በሀገራችን ተግባራዊ በማድረግ ኢትዮጵያን በይበልጥ የአፍሪካ የዳቦ ቅርጫት ማድረግ ይቻላል፤ የስንዴ ቋት መሆን እንችላለን። ቴክኖሎጂውን ደግሞ ለመቀበል እና ወደ ፊት ለማራመድ በሀገራችን በእርሻ ኢንጂነሪንግ የተማሩ ሰዎች በኩል ቴክኖሎጂውን በማስፋፋት ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን በማገናዘብ ከራሳችን አልፈን ለሌላው ሀገር ማቅረብ የሚቻልበትን ሰፊ እድል አለ ብለዋል። በሀገራችን ባሌና አርሲ የስንዴ ሜዳ መሆናቸው እንደሚታወቀው ሁሉ በወሎ እና አፋር ድንበር ላይ ከፍተኛ የስንዴ ምርት ማምረት ይቻላል። በሱማሌ ክልል ገናሌና ሸበሌ ወንዞች አሉ ሜዳው የሰጠ ነው ሰላም እና ደህንነት እስካለ ድረስ ከራሳችን አልፈን ምርቱን ሽጠን ለሌላም ሀገር መቀለብ የሚያስችል አቅም አለ። ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ አይደለችም የሚለውን የውጪ ኢንቨስተሮች እይታ ለመቀየር ኢትዮጵያውያን የሀገራችንን ጥቅም በሚጠብቅ ሁኔታ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በግልጽ በመወያየት እና ግብረመልስ መስጠት ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን\nታህሳስ 12/2013", "passage_id": "48933cfd926f37a6b1251aab5639163c" } ]
3162b048c7054488da32a450654857de
25fb5df0538f947475c8b3e3b8b97f05
ኮሚሽኑ የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ ለመዋጋት ጠንካራ ሥራዎችን መስራቱን ገለጸ
የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ ለመዋጋት የስፖርት ቤተሰቡንና ባለድርሻ አካላት በማሳተፍና በማስተባበር ጠንካራ ሥራዎችን መስራቱ ተገለጸ። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን በበጀት ዓመቱ የታቀዱ ዕቅዶችና ከተከሰተው የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ አንፃር የተከናወኑ አበይት ተግባራት ትናንት ለማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት ሱፐር ቪዥን ቀርበው ግምገማ ተደርጎባቸዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አረጋይ በዕለቱ እንደተናገሩት፤ በ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ቁልፍና አበይት ዕቅዶችን አውጥቶ በታዳጊ ወጣቶች ስልጠና መርሀ ግብር፣ በማስ ስፖርት (በማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ) በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ልማት፣ በውድድርና ተሳትፎ፣ እና በተቋማዊ ለውጥ ሥራ በሽታው ከመከሰቱ በፊት በርካታ ሥራዎች ማከናወን ተችሏል። አቶ ዮናስ አክለው «ዓለም አቀፍ ስጋት የሆነው ኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ከመደበኛ ሥራው ትይዩ ቫይረሱ ከተከሰተ ጀምሮ በከተማ አቀፍ ደረጃ ወረርሽኙን ለመዋጋት እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ ነበር። የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን በበጀት ዓመቱ የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ ለመዋጋት የስፖርት ቤተሰቡንና ባለድርሻ አካላት በማሳተፍና በማስተባበር ጠንካራ ሥራዎቹን አከናውኗል ሲሉ ገልጸዋል። ኮሚሽኑ የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ ለመዋጋት በከተማ ደረጃ በአብይ ኮሚቴ ውስጥ በመሳተፍ እነዚህን ሥራዎች ሲያከናውን እንደነበር ገልፀው፤ የስፖርት ቤተሰቡንና ባለድርሻ አካላት በማሳተፍና በማስተባበር በገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለከተማ አስተዳደሩ ማስረከባቸው፣ ለታማሚ የሚሆን የቅድመ ቦታ መለየትና ማዘጋጀት፣ ለወገን ወገን በመሆኑ የደም ልገሳ መመደረጉ፣ የኮሮና ቫይረስ ቅድመ መከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰፊ ሥራዎች መሠራታቸው እና በተለይ በቤታቸው ቫይረሱን ለመከላከል የሚኖሩ የጋራ መኖሪያ ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች ቤታቸው አካላዊ ርቀትን ጠብቆ የተሰሩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ከብዙ በጥቂቱ ናቸው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት ዋና አስተባባሪ አቶ ሀይለሰማዕት መርሀጥበብ በበኩላቸው፤ ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸው ተግባራት እጅግ የሚያስደስቱና የሚበረታቱ እንደሆኑ አመልክተዋል።ኮሚሽኑ በቀጣይ የስራ አቅጣጫ ላይ ያሉበትን ክፍተቶች በመሙላት የበለጠ ለውጤት መብቃት እንደሚገባው አስገንዝበዋል። አዲስ ዘመን ግንቦት 4/2012 ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=32176
[ { "passage": "አዲስ አበባ ፣ግንቦት 27 ፣2012 ፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብሄራዊ የኮቪድ19 መከላከልና መቆጣጠር የሚኒስቴሮች ኮሚቴ ዛሬ ከክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና ከከተማ መስተዳድር ከፍተኛ አመራሮች ጋር በወረርሽኙ ስርጭት መስፋፋትና መከላከል  ዙሪያ ውይይት አካሄደ።ከዚያም ባለፈ በውይይቱ የወረርሽኙን ስርጭት ለመቀነስና ለመከላከል እየተደረጉ ባሉ ተግባራት  ተግባራት ላይ  ላጋጠሙ  ችግሮች የመፍትሄ አቅጣጫ ተቀምጧል ።በሀገራችን የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ቢሄድም ህብረተሰቡ አሁንም በከፍተኛ ደረጃ መዘናጋት እንደሚታይበት  በውይይቱ ወቅት ተገምግሟል።ስለሆነም የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸዉና የተከለከሉና አስገዳጅ ሁነቶች ላይ የተጠናከረ ህግ የማስከበር ሂደት እንዲቀጥል አቅጣጫ  መቀመጡም ነው የተገለጸው።የቫይረሱ ስርጭት በመደበኛዉ የህክምና አገልግሎት ላይ ያሉ ባለሙያዎችንም ጭምር እያጠቃ በመሆኑ በህክምና መስጫ ስፍራዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ መወሰድ እንዳለበትና የመከላከያ ግብአቶችም በትኩረት መዳረስ እንዳለባቸው አቅጣጫ ተቀምጧል።ከዚያም ባለፈ በውይይቱ በድንበር አካባቢ ስርጭቱን የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባራት እንዲሁም የማቆያ ቦታዎች አስተዳደር መሻሻል ቢያሳይም አሁንም ጠንካራ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያስፈልግ አፅንኦት መሰጠቱን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።#FBCየዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።", "passage_id": "716212ca88bc783d310016c65aa7a1c0" }, { "passage": "ኮሚሽኑ እንዳለው የወረርሽኙ ስጋት ባለበት ሁኔታ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች መልሰው እንዲጀመሩ ለማድረግ በተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል።\n\nየአገሪቱ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ኤሊያስ ሽኩር እንደተናገሩት በበሽታው ምክንያት የተቋረጡትን ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ከዚህ በላይ እንዲዘገዩ ማድረግ በስፖርት ቤተሰቡ ላይ የሚፈጠረው ጫና ከፍተኛ ነው ብለዋል። \n\nየኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር ሲባል በአገሪቱ ስፖርታዊ ስልጠናዎች፣ ውድድሮች በአጠቃላይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ ተደርጎ ቆይቷል።\n\nበዚህም ሳቢያ የስፖርት ዘርፍ ክፉኛ መጎዳቱን ያመለከተው ኮሚሽኑ፤ ክለቦች የመፍረስ አዳጋ እንደተጋረጠባቸውና የስፖርት ቤተሰቡም የሥነ ልቦና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ መግባታቸውን ገልጿል። \n\nበመሆኑም አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የስፖርት እንቅስቃሴዎችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችንና የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ መሠረት በማድረግ ረቂቅ መመሪያው ተዘጋጅቶ ውይይት ተካሂዷል።\n\nመመሪያው አጠቃላይ የስፖርት እንቅስቃሴዎች በምን ሁኔታ መከናወን እንዳለባቸው የሚያሳይ ሲሆን የስፖርት ተቋማትና ማኅበራት ከሚያካሂዷቸው ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ባህሪ አንጻር አስፈላጊ የጥንቃቄና የአሠራር ሥርዓት ሊያዘጋጁ እንደሚችሉ እንደሚያመለክት ኮሚሽኑ ገልጿል። \n\nበዚህም መሰረት የስልጠናና የውድድር ስፍራዎች ለበሽታው ያላቸውን ተጋላጭነት ባገናዘበ ሁኔታ ደረጃ በደረጃ በግልና በቡድን አነስተኛ ተሳታፊ ቁጥርን ታሳቢ ያደረገ ሊሆን እንደሚገባ ተቀምጧል። \n\nእንዲሁም ወደ ስልጠናና ወድድር የሚገቡ አካላት ምርመራ ማድረግ፣ የንጽህና መጠበቂያዎችን መጠቀምና ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚያገለግሉ ቦታዎች፣ ቁሳቁሶችና መሳሪያዎች ንጽህናቸው ሊጠበቅ እንደሚገባ መመሪያው ጠቅሷል። \n\nባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የእግር ኳስ ውድድርን መልሶ ለማስጀመር እየታሰበ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ውድድሩ ሲጀመር የተመልካቹንና የስፖርተኞቹን ጤና ደኅንነት ያስጠበቀ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎችን ለማከናወን ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። \n\nየኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀ በኋላ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑና በርካታ ሰው የሚታደምባቸው ስፖርታዊ ውድድሮችን የመሰሉ እንቅስቃሴዎች እንዳይካሄዱ መደረጉ ይታወሳል። \n\n ", "passage_id": "366ae60f019c2f68ce5212abe333968c" }, { "passage": "አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 28 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኮቪድ-19 ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ይረዳል የተባለው ሀገር አቀፍ የምርመራ መርሃ ግብር ስኬት የህብረተሰቡ ተሳትፎ መሰረታዊ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ። የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ÷ የወረርሽኙን መስፋፋትና መሰራጨት በመገንዘብ ህብረተሰቡ በትኩረት የመከላከሉን ተግባር ሊፈጽም ይገባል ብለዋል። ሀገር አቀፍ የኮሮና ወረርሽኝ ምርመራ እና የመከላከል ተግባራትን የመፈጸም ንቅናቄ የተጀመረ ሲሆን÷ በዘመቻውም 17 ሚሊየን የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ምርመራ ይደረግላቸዋል ብለዋል። ይህንንም ለማከናወን 200 ሺህ የላብራቶሪ ምርመራዎች እንደሚደረጉ ሚኒስትሯ ገልጸዋል። ኮቪድ 19 ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚረዳ ሀገር አቀፍ የምርመራ እና የመከላከል ተግባር ንቅናቄ ዓላማው የኮሮናን ስርጭት ለመግታት ነው ያሉት ዶክተር ሊያ ÷ ህብረተሰቡ የዘመቻው ዋና ተዋናይ በመሆን እራሱን ቤተሰቡን እና አካባቢውን ከበሽታው የመጠበቅ ድርሻውን ሊወጣና የበሽታው ስርጭት መንስኤ ላለመሆን መጠንቀቅ ይገባል ብለዋል። በዘመቻው በወረርሽኙ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ከግምት ውስጥ በማስገባት በየወረዳው የለይቶ ማቆያ ህክምና መስጫ ተግባራት ከወዲሁ ሊዘጋጁ ይገባልም ነው ያሉት። አያይዘውም በተለይም ህብረተሰቡ ወረርሽኙን ለመቀነስ እና ለመቆጣጠር የፊት ጭንብል ማድረግ እንዲሁም እርቀትን መጠበቅ እና እጅን በአግባቡ በተደጋጋሚ መታጠብ፣ አስገዳጅ ካልሆነ በቀር በቤት መቆየትን ሁሉም ህብረተሰብ ሊተገብረው የሚገባ ተግባር መሆን አለበት ብለዋል። ህብረተሰቡ በ”መ” ህጎች ዙሪያ ማለትም “መታጠብ”፣ “መሸፈን”፣ “መራራቅ” እና “መቆየት” በመተግበር የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። ከዚያም ባለፈ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከናወነው የምርመራ እና የመከላከል ዘመቻ የተሳካ እንዲሆን የህብረተሰቡ ተሳትፎ እና እገዛ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው በመጠቆም ፣በዚህ ዘመቻ መገናኛ ብዙሃን እና የጥበብ ሰዎች የማስተማር ተግባራቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ማለታቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። #FBCየዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።", "passage_id": "e2b1e47d863cecd6bb8f244a344f73ca" }, { "passage": "አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የስፖርቱ ቤተሰብ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ለመግታት ለሚደረገው ጥረት ድጋፍ በማድረግ ላይ ናቸው።የአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ_ፌዴሬሽንም ዛሬ ለኮሮና ቫይረስ መከላከልና ጥንቃቄ የሚውል የ50 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል።ፌዴሬሽኑ የክለብ አሰልጣኞች፣ ስፖርተኞች፣ ባለድርሻ አካላትና አብረውት የሚሰሩ ተቋማትን በማስተባበር በቀጣይ ድጋፎችን ለማከናወን ማቀዱንም አስታውቋል።ሁሉም የስፖርት ቤተሰብ የሚተላለፉ መልዕክቶችን በመተግበር ራሱን፣ ቤተሰቡንና ማህበረሰቡን ከዚህ ቫይረስ እንዲጠብቅም አሳስቧል።ድጋፉን የተቀበሉት የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳዊት ትርፉ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የስፖርት ማህበራት ሰፊ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን ጠቁመው፥ የአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ አባላት ወስነው የ50 ሺህ ብር ድጋፍ በማድረጋቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።ምክትል ኮሚሽነሩ በዚሁ ወቅት በቤታቸው ተቀምጠው ያሉ ነዋሪዎች በተለይ በጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ሰዎች ሳይወጡ በበረንዳቸው ላይ ወጣ ብለው ርቀታቸውን ጠብቀው ራሳቸውን የሚያነቃቁበት እና ከድብርት የሚላቀቁበት የአካል እንቅስቃሴ ቀለል ባለ ሁኔታ በባለሙያ ድጋፍ እንዲሰሩ መመቻቸቱንና ይህም ነገ በተመረጡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንደሚጀመር ተናግረዋል ።", "passage_id": "4fb8883c466f75babee5af167e6784ff" }, { "passage": "የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስራው እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም ኮሚሽኑ ጥሪውን አቅርቧል፡፡የ2012 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ለወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ተግባሩ ልዩ ትኩረት በመሥጠትና ሙሉ የሰው ሃይሉን በማሰማራት ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ወደ ተግባር መግባቱን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እንዳሉት በበዓላት ወቅት የሰው እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ከወትሮው በተለየ መልኩ ስለሚጨምር ይህንን ታሳቢ በማድረግ በገበያና በመዝናኛ ስፍራዎች እንዲሁም በከተማችን በተለያዩ አካባቢዎች የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰትና ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ ኮሚሽኑ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡፡ህብረተሰቡ የፀጥታ ጉዳይ የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝቦ አስፈላጊውን ትብብር እያደረገ እንደሚገኝና ከዚህ ቀደም የተከበሩ ሃይማኖታዊ እና ብሄራዊ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ኮሚሽኑ አስታውሶ አሁንም እንደተለመደው ራሱን ከወንጀል እና ከትራፊክ አደጋ በመጠበቅ ለፀጥታ ሃይሉ የሚያደርገውን ትብብርና የሚሰጠውን ጥቆማ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አቅርቧል፡፡ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት በነፃ የስልክ መስመር 991 እና 816 ወይም በ011-1-11-01-11 መጠቀም እንደሚችል ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡", "passage_id": "1c23e9be4485a0ba64a86ccf512911b3" } ]
cc1994dc2b7d4d40ded99ef3b9793a8b
8a386a521ff85dd418130bbb6c14ce92
የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተናን ለመውሰድ 311 ሺህ 421 ተማሪዎች ተመዝግበዋል
 ዳንኤል ዘነበ አዳማ፦ በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የብቃት መመዘኛ ፈተና ለመውሰድ እስከ አሁን 311 ሺህ 421 ተማሪዎች መመዝገባቸውን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ። በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን ለሚደረገው የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና 500 ሺ ታብሌቶች ተዘጋጅተዋል። በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የተፈታኞች ምዝገባና ውጤት ጥንቅር ዳይሬክተር አቶ ዩሴፍ አበራ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የአጠቃላይ ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ከጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም በኋላ ለመስጠት መርሐግብር ተይዟል። በዚህ መሰረት የተማሪዎች ምዝገባ መደረጉን ገልጸው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ለመውሰድ እስከ አሁን 311 ሺህ 421 ተማሪዎች መመዝገባቸውን አስታውቀዋል። ምዝገባው ከትግራይ ክልል እና ከቤንሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን በስተቀር በሁሉ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካሄዱን የገለጹት ኃላፊው፣ በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ካጋጠመው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ተማሪዎችን ለመመዝገብ እንዳልተቻለ አመልክተዋል። በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ቀደም ሲል ምዝገባ የተጀምረ ቢሆንም ከጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ መቋረጡን አስታውሰው፤ በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎችን ለመመዝገብ የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር እየተሠራ ይገኛልም ብለዋል። በትግራይ ክልል 80 ያህል ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በመተከል ደግሞ እስከ 14 ትምህርት ቤቶች አሉ ተብሎ ይገመታል፣ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች ምዝገባ ከተደረገ ቁጥሩ ይጨምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል። ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ በበኩላቸው፤ መንግሥት በወሰደው ቁርጠኛ አቋም ትምህርት ሚኒስቴር እና ኤጀንሲው በመቀናጀት የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን ለመፈተን መደረግ የሚገባቸው ቅድመ ዝግጅቶች እያጠናቀቁ መሆኑን ገልጸዋል። በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን ለሚደረገው የ12ኛ ክፍል ፈተና 500 ሺ ታብሌቶች መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። በክልሎች ደረጃ የሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ከወዲሁ ለሂደቱ አስፈላጊ የሆኑ መሰረተ ልማቶችን አሟልተው እንዲገኙ ከፌዴራል በወረደላቸው አቅጣጫ መሰረት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ አመልክተዋል። በዘንድሮ አዲስ ቴክኖሎጂ ይዘን ወደ ተማሪዎቻችን የምንቀርብ ከመሆኑ አንጻር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ከኤጀንሲው ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ያስፈልገናል ብለዋል። ባለድርሻ አካላትም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሑሪያ አሊ በበኩላቸው፤ የብሔራዊ ፈተናዎች አሰጣጥ ባህላዊነት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ወጪ፣ ውስብስብ አሠራር፣ ስርቆትና ኩረጃ፣ አድካሚ የሥራ ሂደትና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች አሉበት ብለዋል። ኮምፒውተርን መሰረት ያደረገ የፈተና ሠርዓት መዘርጋት ችግሩን ለመቅረፍ፣ አሊያም ለመቀነስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነም አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 25/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=38751
[ { "passage": "የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በተለይም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ ከሰኔ 27 ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓመተ ምህረት ድረስ ፈተናው ይሰጣል።የ12ኛ ክፍል ፈተና ኮድ 14 የእንግሊዝኛ ፈተና መውጣቱ በመረጋገጡ እና ሌሎች ፈተናዎች ላለመውጣታቸው ምንም ዓይነት ማረጋገጫ ባለመኖሩ እንዲሰረዝ መደረጉን ትናንት ሚኒስትሩ መግለፃቸው ይታወሳል።አሁን የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት እና አሰጣጥ በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ጥበቃ የሚከናወን እንደሚሆንም ነው ሚኒስትሩ የገለፁት።ሀገር አቀፍ ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጥናትና ምርምር ማዕከል አማካኝነት በከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚዘጋጅ ያስረዱት አቶ ሽፈራው፥ ባለሙያዎቹ ተፈታኝ የስጋ ዘመድ እንደሌላቸው ተረጋግጦ በፈተና ዝግጅት እንዲሳተፉ እንደሚደረግም ተናግረዋል።ፈተናው በመቀጠልም በተደራጀ እና ምስጢራዊነቱን በጠበቀ መልኩ የህትመትና የስርጭት ስራው እንደሚከናወንም ነው ያረጋገጡት።በፈተና ስርቆት ተግባሩ ላይ የተሳተፉ አካላትም ህጉ በሚፈቅደው መሰረት አስፈላጊውን ማጣራት በማካሄድ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ እንደሚደረግም ሚኒስትሩ ገልፀዋል።አቶ ሽፈራው ተማሪዎች በቀጣይ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለፈተና ዝግጀት በማድረግ በተጠቀሰው ጊዜ ፈተናውን እንዲወስዱ አሳስበዋል።(ኤፍ ቢ ሲ) ", "passage_id": "172c143d8e7c81e61abef405cc0b045e" }, { "passage": "-በ2008 የትምህርት ዘመን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ የብቃት መመዘኛ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኗል።በዚህም መሰረት በመደበኛ እና በማታ በተፈጥሮ ሣይንስ የትምህርት መስክ ፈተና ወስደው ለወንድ 354 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች ለሴት ደግሞ 340 ያመጡ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።በማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ በመደበኛ እና በማታ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ደግሞ ለወንድ 330 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም ለሴት 320 እና ከዚያ በላይ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ሁሉም የታዳጊና አረብቶ አደር ሴት ተማሪዎች 335 እና ከዚያ በላይ ያመጡ እንደዚሁም ሁሉም የታዳጊ ክልልና የአርብቶ አደር አካባቢ ወንድ ተማሪዎች ከፍተኛ የትምሀርት ተቋማትን ለመቀላቀል 340 እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።በማህበራዊ እና ተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚቀላቀሉ የግል ተፈታኞች ለወንድ 360 እና ከዚያ በላይ ፣ ለሴት ደግሞ 355 እና ከዚያ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።በማህበራዊ ሳይንስ ለታዳጊና የአርብቶ አደር ሴት ተማሪዎች 315 እና ከዚያ በላይ፤ ለወንዶች ደግሞ 320 እና ከዚያ በላይ፤ በተፈጥሮ ሳይንስ ለታዳጊና የአርብቶ አደር ሴት ተማሪዎች ለወንዶች 340 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴቶች ደግሞ 335 እና ከዚያ በላይ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ሆኗል።መስማት ለተሳናቸው የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ለሁለቱም ፆታ 297 እና ከዚያ በላይ ሲሆን፥ በማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ደግሞ ለሁለቱም ጾታ 275 እና ከዚያ በላይ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ሆኗል።ሁሉም አይነስውራን (ወንዶችም ሆነ ሴቶች) 200 እና ከዚያ በላይ  ካስመዘገቡ በመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይመደባሉ። በግልም ሆነ በመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በማታም ሆነ በቀን እንዲሁም በርቀት ትምህርታቸውን መከታተል የሚፈልጉ ተማሪዎች 295 እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።ብሄራዊ ፈተናውን 246 ሺህ 570 ተፈታኞች የወሰዱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 50 በመቶዎቹ 350 እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል።106 ተፈታኞች ደግሞ 600 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 21ዱ ሴቶች ናቸው።በሌላ በኩል የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ከሶስት ቀናት በኋላ ይፋ እንደሚሆን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል።(ኤፍ.ቢ.ሲ)", "passage_id": "2d639957b9e5bd9bc86b6352d8f0096c" }, { "passage": "አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈታኞች ምዝገባ በኦንላይን ተጀምሯል።የኦንላይን ምዝገባውም በየአካባቢያቸው ባሉ ትምህርት ቤቶች መጀመሩን የትምህርት ሚኒስቴር ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ሀረጓ ማሞ ተናግረዋል።ተማሪዎችም በየአካባቢያቸው ባሉ ትምህርት ቤቶች በመገኘት በወቅቱ ምዝገባቸውን እንዲያከናውኑ ዳይሬክተሯ አሳስበዋል።በዛሬው ዕለት የጀመረው ምዝገባውም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚቀጥል ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።በከሮና ቫይረስ ምክንያት ሳይሰጥ የቀረው የ2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ዘንድሮ በኦንላይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።", "passage_id": "eda680c9c5d8c6c6446b661af4fced40" }, { "passage": "የ2011 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ማክሰኞ ነሐሴ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ይፋ ተደረገ፡፡ የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በሰጠው መግለጫ መሠረት፣ ለፈተና ከተቀመጡ 319,264 ተፈታኞች ውስጥ 59 ተማሪዎች ከ600 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡ ከፍተኛው ውጤት ደግሞ 645 መሆኑን ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡በኤጀንሲው ገለጻ መሠረት ከ50 በላይ ውጤት ያመጡት ተፈታኞች 48.59 በመቶ ናቸው፡፡ ተፈታኞች ውጤታቸውን በኤጀንሲው ድረ ገጽና በ8181 የአጭር ጽሑፍ መልዕክት የመፈተኛ ቁጥራቸውን በመጠቀም ማወቅ ይችላሉ ተብሏል፡፡ኤጀንሲው የፈተና ደኅንነት የማስጠበቅ ሥራውን ከዝግጅት ጀምሮ እስከ ውጤት ይፋ ማድረግ ድረስ ለማስቀጠል በመሥራት ላይ መሆኑን አስታውቆ፣ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተናው በተሰጠበት ወቅት ከቀረቡት ሪፖርቶችና ተያያዥ መረጃዎች የተረጋገጠባቸውን 68 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ መደረጉን አስታውቋል፡፡ከዚህም በተጨማሪ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአማራና በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በሚገኙ የተወሰኑ ትምህርት ቤቶች 846 ተፈታኞች በተወሰኑ የትምህርት ዓይነቶች ያገኟቸው ውጤቶች ማጣራት የሚጠይቁ መሆናቸውን ኤጀንሲው ገልጿል፡፡ኤጀንሲው በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የእነዚህ ተፈታኞች ውጤት፣ በተለዩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ ተይዞ ማጣራት እንዲደረግባቸው መወሰኑን አስረድቷል፡፡ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት የተውጣጣ ግብረ ኃይል የማጣራት ሥራውን ያከናውናል ብሏል፡፡ኤጀንሲው ባለድርሻ አካላትና መላው ሕዝብ ባደረጉት ርብርብ እጅግ በተረጋጋ የፈተና ከባቢ ፕሮግራሙን በማሳካቱ፣ የዓመቱ የፈተና አስተዳደር ሥራው መሻሻል ማሳየቱን አስታውቋል፡፡ በፈተና አስተዳደሩ ሒደት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል ላላቸው ለፌዴራልና ለክልል ተቋማት፣ ለፈተና አስፈጻሚዎች፣ ለመላው ተፈታኞች፣ ለወላጆችና በሒደቱ ለተሳተፉ ባለድርሻ አካላት በሙሉ ምሥጋናውን አቅርቧል፡፡የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 6፣ 7፣ 10 እና 11 ቀን 2011 ዓ.ም. መሰጠቱ ይታወሳል፡፡", "passage_id": "e225c605957fef92b561896642a32fe3" }, { "passage": "የ2010 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የፈተና ውጤት እስከ  ቀጣዩ አርብ ድረስ ይፋ እንደሚሆን የሀገር ዓቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል።\nየኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሔር እንደገለጹት ኤጀንሲው የ ፈተናውን  እርማት በማጠናቀቅ መረጃውን በአጭር ጽሁፍ እና በድረ-ገጽ በጥራት ለማሰራጨት ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በጋራ እየተሰራ ነው፡፡ኤጀንሲው እስካሁን የትኛውንም የውጤት ማሳወቂያ ዘዴ በመጠቀም ውጤት እንዳላወጣና ተማሪዎችም በኤጀንሲው ስም በሚወጡ የተሳሳቱ መረጃዎች እንዳይታለሉም ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡\nውጤቱን ይፋ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቃቸውንና እስከ መጪው አርብ ድረስ ውጤቱ እንደተለመደው በኤጀንሲው ድረ-ገፅና በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ይፋ ይደረጋልም፡፡\nተማሪዎች የለፉበት ውጤት እንዳይሳሳት በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ አርአያ የ2010 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል የፈተና ውጤትን ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁም ጠይቀዋል፡፡", "passage_id": "4dc2b940b4d16278dab86a1a4f49fbc5" } ]
5011952b0cf03095ad227da4d4337bf6
e8663d90ba4e1e548c8b57b587d39a11
መገናኛ ብዙሃን በቅርበት አብረውት እንዲሠሩ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ጥሪ አቅረበ
 በኃይሉ አበራአዲስ አበባ፦ መገናኛ ብዙሃን በቅርበት አብረውት እንዲሠሩ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ጥሪ አቀረበ። ተቋማቱ የሚያሰራጯቸው መረጃዎች ተአማኒነት በአግባቡ ሊፈተሸ እንደሚገባ አሳሰበ።የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ እየደረሰ ያለውን ውድመት አስመልክቶ ትናንት በፅሕፈትቤቱ በሰጠው መግለጫ፣ የአካዳሚ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ፅጌ ገብረማርያም እንዳስታወቁት፣ ሀገራችን ለዓለም የሚተርፍ ሀብት ባለቤት ብትሆንም በታሪካችን ሂደት ባስተናገድናቸው የእርስበርስ ጦርነቶችና ግጭቶች የተነሳ ሳንጠቀምበት ቀርተናል ብለዋል።አካዳሚው በተለያዩ ሙያዎች ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ፤ ያካበቱትን እውቀትና ተሞክሮ መሰረት በማድረግ ለሀገርና ለህዝብ የሚጠቅሙ ምክረ ሃሳቦች ሊሰጡ የሚችሉ ምሁራን የሚገኙበት መሆኑን ጠቁመው፣ መገናኛ ብዙሃን ይህንን ሀገራዊ አቅም ለመጠቀም ከተቋሙ ጋር በቅርበት እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።ማንም ዜጋ የመኖር መብት ያለው ቢሆንም፣ በሀገራችን የመኖር መብት ጥያቄ ውስጥ እየገባ መሆኑን አመልክተዋል። ይህ መብት በማንም መወሰድ እንደሌለበትም አሳስበዋል።አካዳሚው በተለይም ከሁለት ዓመታት በፊት በሀገሪቱ ተከስተው የነበሩ አለመረጋጋቶችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የፖሊሲ ግብአቶች እና በመርህ ላይ የተመሰረቱ የተለያዩ ሃሳቦች ሲያቀርብ መቆየቱን አስታውሰዋል። አካዳሚው በመርህ ደረጃ ጥናትን መሰረት ያደረጉ መረጃዎችን ለሀገራዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት እየሰጠ እንደሚገኝ አመልክተዋል። የአካዳሚው የቦርድ አባል ዶክተር ፀደቀ አባተ በበኩላቸው፣ ከጥላቻ፣ ከግል ጥቅም እና የመሳሰሉ አፍራሽ ሁኔታዎችን ከማስወገድ አንጻር የመገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሚና ሊጫወቱ ይገባል ብለዋል።በእለቱ በጽሑፍ በተነበበው የአካዳሚው የአቋም መግለጫ ፣ መንግሥት በሀገራችን የህግ የበላይነት ለማስፈን የሚወስደውን እርምጃ አካዳሚው እንደሚደግፍ ገልጸው ፣ እርምጃውም በሁሉም አካባቢ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፤ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎችም ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ጠይቀዋል።በሶሪያ እና በሊቢያ እና በየመን እንደታየው ሁሉ በሀገራችንም መሰል ቀውስ እንዳይፈጠር ዜጎች ልዩነቶቻቸውን በውይይት ብቻ እንዲፈቱም መልእክት አስተላፈዋል።አካዳሚው ከ177 በላይ አባላት ያሉት መሆኑም በወቅቱ ተገልጿል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 25/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=38753
[ { "passage": "ኢትዮጵያ የሳተላይት ቴክኖሎጂ ስርዓተ-ትምህርት እንድትቀርጽ የህዋ ሳይንስ ተመራማሪዎች ጠየቁ፡፡ህፃናት እና ወጣቶችን ማዕከል ያደረገ የሳተላይት ቴክኖሎጂ ስልጠና በከፍተኛ ትምህርት ደረጃ ሊሰጥ እንደሚገባም የዘርፉ ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡የከዋክብት ተመራማሪ ዶ/ር ጌትነት ፈለቀ በታዳጊ ሀገራት የህዋ ጥናት አስፈላጊነቱ ላይ ጥያቄ ቢነሳም፤ የበለፀጉ ሀገራት ህዋ ሳይንስ ለእድገታቸው ትልቅ ጠቀሜታ እንዳስገኘላቸው ገልጸው፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራት ሳይንሱ በእጅጉ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡ኢንዱስትሪው በኢትዮጵያ እንዲያድግ በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ባይሆኑም በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች የሳተላይት ቴክኖሎጂ ትምህርት ሊሰጥ እንደሚገባ የሚናገሩት የከዋክብት ተመራማሪው፣  ኢትዮጵያ የሳተላይት ቴክኖሎጂ በሚል እራሱን የቻለ ስርዓተ-ትምህርት ተቀርጾ መተግበሩ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን አመልክተዋል፡፡የከተሞች መስፋፋት እና ኢንቨስትመንቶች እየጨመሩ ሲሄዱም በዛው መጠን የመረጃው አስፈላጊነት ከፍ ስለሚል በዘርፉ የተማረ የሰው ሀይል ማመንጨትን ግምት ውስጥ ያስገቡ ተግባራት ማከናወን እንደሚገባም የከዋክብት ተመራማሪው ዶ/ር ጌትነት ፈለቀ አሳስበዋል፡፡መንግስት አስፈላጊ ግብዓቶችን በማቅረብ በሳተላይት ቴክኖሎጂ ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ኢትዮጵያ በዘርፉ ከምስራቅ አፍሪካ ተሻግራ በአፍሪካ ተጠቃሽ ሀገር ለማድረግ መስራት ይጠበቅበታልም ብለዋል፡፡የአንድሮሜዳ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ መጋቢ ሀዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ በበኩላቸው፣ የህዋ ጥናት በዓለም ላይ በፍጥነት እየዘመኑ ካሉ ዘርፎች መካከል ግንባር ቀደም መሆኑን ገልጸው፣  ህፃናት እና ወጣቶችን ማዕከል ያደረገ ስልጠና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ሊሰጥ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡የህዋ ሳይንስን ለሰላማዊ ግልጋሎት መጠቀም ለእድገት እና ብልፅግና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን፤ የህዋ ሳይንስ እርሻን፣ የደን ሽፋንን፣ ውሃና ማዕድናት የሚገኝባቸውን አካባቢዎችን መለየትና መከታተል የሚያስችሉ ተግባራትን መከወን ያስችላሉም ነው የተባለው፡፡እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር፣ የተፈጥሮ አደጋዎች ከመድረሳቸው አስቀድሞ ለመተንበይ እና ደህንነትን ለመጠበቅ እንደሚረዳም ተገልጿል።ኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ ዘርፍ ከበለፀጉ ሀገራት ተሞክሮ በመነሳት የህዋ ኢንዱስትሪውን በመቀላቀል እየሠራችበት ትገኛለች፡፡ኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ ቀደምት የመጠቀ ታሪክ ቢኖራትም አሁን ላይ ግን ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም አንጻር ጀማሪ ስትሆን፤ አፍሪካ ውስጥ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ አልጄሪያ እና ግብጽ ጥሩ ስም ካላቸው ሀገራት መካከል ናቸው።ኢትዮጵያ አሁን ላይ  “ህዋ ለልማት” የሚል የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ትብብር ቢሮ አቋቁማ አበረታች እንቅስቃሴ ማድረጓ ተጠቃሽ ስኬት ነውም ተብሏል።(በደረሰ አማረ)", "passage_id": "2965e2a744b78f680c2aff04db31de49" }, { "passage": " . ከፖለቲከኞችና ነጋዴዎች ነፃ ይሆናልአዲስ አበባ፡- በሙያተኞች የሚመሰ ረተው ኢትዮ ዋርካ መልቲ ሚዲያና ኮምኒኬሽን ሼር ካምፓኒ የጋዜጠኝነት ሙያን ለማሳደግ እንደሚሰራ ተገለጸ። ሚዲያው የጋዜጠኝነትን ሙያ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ከነጋዴዎችና ፖለቲከኞች ተፅዕኖ ነፃ ሆኖ የሚቋቋም መሆኑንም ተጠቁሟል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮምኒኬሽን ትምህርት ክፍል እንዲሁም የኢትዮ ዋርካ የቦርድ ሊቀመንበር ረዳት ፕሮፌሰር መኩሪያ መካሻ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በአገሪቱ ውስጥ ያሉት አብዛኞቹ መገናኛ ብዙሃን የሚመሩትም ሆነ ስራቸው የሚከናወነው ከሙያው ውጪ በሆኑ ሰዎች ነው። ይህም የሙያው ሳይንስ በተጨባጭ ሥራ ላይ እንዳይውል ከማድረጉም ባሻገር ነፃና ገለልተኛ የሆነ ተቋም እንዳይፈጠር ምክንያት ሆኗል። በመሆኑም ባለሙያዎች በአክሲዮን የሚመሰርቱት ይህ ተቋም ከዚህ ቀደም በዘርፉ ይታይ የነበረውን ክፍተት ለመፍታት ይሰራል። «የፖለቲካው ሁኔታ በተቀያየረ ቁጥር የሚቀያየር ሚዲያ ነው ያለው» ያሉት ረዳት ፕሮፌሰር መኩሪያ፤ የአዲሱ ሚዲያ መመስረት ሙያተኞች ዳር ቆመው ከመታዘብ ባለፈ ዘርፉ በተግባር እንዲመሩት ለማድረግ እንደሚያስችል አስረድተዋል። በተለይም በሌሎች ተቋማት ላይ የሚስተዋለውን የፖለቲከኞች ጣልቃገብነት ለማስቀረት አቅም የሚፈጥር መሆኑን አስገንዝበዋል። በተጨማሪም አክሲዮኑ በባለሙያዎች መመስረቱ በፖለቲከኞችና በነጋዴዎች እንዳይጠመዘዝ የሚያደርግ መሆኑን አመልክተዋል። «ሚዲያዎች ትልቁ ችግራቸው የገንዘብ ችግር ነው። በዚህም ምክንያት የነጋዴዎች ወይም የፖለቲከኞች ዓላማ ማስፈጸሚያ ይሆናሉ። ዋርካ ሚዲያ በባለሙያዎች ብቻ በአክሲዮን መመስረቱ ከዚህ ነፃ ያደርገዋል» ብለዋል። ከመስራቾቹ ውስጥ በህትመት ሚዲያ፣ በብሮድካስት ሚዲያ፣ በአይ.ሲ.ቲ እና በመሳሰሉት ሙያዎች ልምድ ያላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል። በቀጣይም በህክምና፣ በምህንድስና፣ በህግና በሌሎችም ዘርፎች ላይ ያሉ ባለሙያዎች ይሳተፉበታል። ዋርካ ሚዲያ ሙያ ላይ ትኩረት አድርጎ ስለሚሰራ በጋዜጠኝነት ሙያ ላይ ‹‹ስፔሻላይዜሽን›› እንዲኖር ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑንም አብራርተዋል። የኢትዮ ዋርካ መልቲ መዲያና ኮምኒኬሽን ሼር ካምፓኒ ሥራ አስኪያጅ አቶ እሸቱ ገለቱ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ሚዲያውን መመስረት ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት ጋዜጠኛው ሙያውን የሚያሳድግበትና ነፃ ሆኖ የሚሰራበት የሚዲያ ምህዳር ለመፍጠር ነው። በየዘርፉ የሚተነትኑ ባለሙያዎችን በማፍራት የአንድ ዘርፍ ተንታኞች እንዲኖሩት ይደረጋል። ከዜና ባለፈ ጥልቀት ያላቸው ትንታኔዎች የሚሰሩበት መሆኑን አመልከተው፤ «ኪነ ጥበብ ከሆነ በኪነ ጥበብ ሰዎች ይተነተናል፤ ኢኮኖሚ ከሆነ የኢኮኖሚ እውቀት ባላቸው ሰዎች ነው፤ ማንም በማይመለከተው እየገባ የሚተነትንበት አይሆንም» በማለት ተናግረዋል። በአገሪቱ ጋዜጣ የሚያትም አንድ ማተሚያ ቤት ብቻ መሆኑ ጋዜጦች በዕለታቸው እንዳይወጡ ያደረጋቸው መሆኑን ያመለከቱት አቶ እሸቱ፣ይህንን ችግር ለመፍታት ያስችል ዘንድ ሚዲያው የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያ ብቻ ሳይሆን ማተሚያ ቤትም የሚኖረው መሆኑን አስረድተዋል። ሚዲያው እንደ ቢቢሲ ያሉ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን ተሞክሮ በመውሰድ ቋሚ የሆኑ ተንታኝ ሠራተኞች እንደሚኖሩ የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፣ በአገሪቱ ውስጥ ለረጅም ዓመት በአንድ ሚዲያ ላይ ያለመቆየትን ችግር የሚቀርፍ መሆኑን አስገንዝበዋል። «ጋዜጠኛ ልምድ የሚኖረው በአንድ ሚዲያ ላይ ለረጅም ዓመት ሲሰራ ነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ይህ ያልተለመደ በመሆኑ ዋርካ ሚዲያ ይህን ለመፍታት የተመሰረተ ነው» ብለዋል። በተጨማሪም በሚዲያና ኮምኒኬሽን የልህቀት እንዲሁም የምር ምርና ሥልጠና ማዕከል የሚኖረው መሆኑን ጠቁመው፣ይህም የጋዜጠኝነት ሥልጠናዎችን ለመስጠት የሚያስችለው መሆኑን ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሰኔ 15/2011ዋለልኝ አየለ\n", "passage_id": "23e18b498c54f19c0c84c8689127c586" }, { "passage": " ጉባዔው ትኩረት ሰጥቶ የጥናት ፅሁፎች ከቀረቡባቸውና ውይይት ከተደረገባቸው ቁም ነገሮች መካከል በኢትዮጵያ ዕውቀት አመንጭ የሆኑ ምርምርና ጥናት የሚካሄዱባቸውን ዩኒቨርሲቲዎች እንዴት መፍጠር ወይንም ማጠናከር ይቻላል? የሚለው አንዱ ነበር።በዚህ ርዕሰ-ጉዳይ የጥናት ፅሁፎችን ያቀረቡ ምሁራን ነበሩ።ከመካከላቸው መለስካቸው አመሃ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚደንት ዶክተር ባይሌ ዳምጤን አነጋግሯል። ቃለ ምልልሱን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡", "passage_id": "120b00fb89d1c00063ba9dbb61b39aa9" }, { "passage": "– በመለስ ፋውንዴሽን ከመላ አገሪቱ የተመረጡ 83 ተማሪዎች የኮምፒተር ሳይንስ ከውጭ አገር በመጡ ምሁራን ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑ ተመለከተ ፡፡በዚሁ ከሓምሌ 1/2008 ዓመተ ምህረት አንስቶ ለአንድ ወር እየተሰጣቸው ያለው ስልጠና ከሁሉም ክልሎች፣ ከአዲስ አበባና ድሬዳዋ አስተዳደሮች በሒሳብ ችሎታቸው የላቀ ውጤት ያመጡ ተመናሪዎች መሆናቸው ተገልጿል ፡፡በአሜሪካን አገር ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪዋን እያጠናች ያለችው በጎ ፈቃደኛ ወጣት ትምኒት ገብሩ ከፋውንዴሽኑ ጋር በመገናኘት ያላትን ዕውቀት ለሀገሯ ልጆች ለማበርከት ከጓደኛዋ ጋር ተማክራ መምጣቷን አስረድታለች ፡፡ተማሪዎቹ ባብዛኛው ኮምፒውተር ነክተው የማያውቁ ቢሆንም ባጭር ጊዜ ኮምፒውተርን ተምረው ስልጠናውን በአግባቡ እየተከታሉ መሆኑን አብራርታለች ፡፡እንደዚሁም ኮምፒውተር ሳይንስ ሰፊ ዕድል እንዳለው አያውቁም ነበር ያለችው ወጣት ትምኒት ፤ዘርፉ ከዘመኑ ጋር የሚሄድ አስፈላጊ ስልጠና እንደሆነ እንዲያውቁ እየተደረገ መሆኑን አስታውቃለች  ፡፡በቀጣይ ዓመትም ተመሳሳይ ስልጠና ለመስጠት ከሌሎች በጎ ፍቃደኞች ጋር እንደሚመጡ ጠቁማ፤ስልጠናው ከመጀመሩ በፊት በኮምፒውተር መጻፍ የማይችሉ ተማሪዎች አስቀድሞ ልምምድ እድርገው ቢዘጋጁ የተሻለ መሆኑን አመልክታለች ፡፡ከሰልጣኛቹ ውስጥ በሐዋሳ ከተማ የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ቤተልሔም ደሳለኝ በሰጠችው አስተያየት የወደፊት ዓላማዋ የህክምና ሳይንስ ዶክተር ለመሆን የነበረ ቢሆንም ስልጠናው ዓላማዋ እንድትቀይር ስለአደረጋት የኮምፒውተር ሶፍትዌር እንጂነር ለመሆን እንደምትፈልግ ገልጻለች  ፡፡ሌላው ከሐረር ከተማ የመጣው የ12ኛ ክፍል ተማሪ መአድን ስይድ በበኩሉ እንዳመለከተው፤ ከዚህ በፊት ስለኮምውተር ሳይንስ ሃሳቡም ዕውቀቱም እንዳልነበረው ገልጾ፤ አሁን ከኮምፒውተር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር በቀጣይ የጠፈር ተመራማሪ በመሆን ሀገሩን በስነ ኮዋክብት ያላትን ደረጃ ከፍ ለማድረግ ማለሙን አስረድቷል ፡፡የስልጠናው ዓላማ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ ከመግባታቸው በፊት ስለኮፒውተር ፕሮግራም  በማለማመድ በሄዱበት ቦታ ለሌሎች ተማሪዎች ዕውቀታቸውን እንዲያካፍሉ መሆኑን ታውቋል ፡፡", "passage_id": "e11f68a495f3636f74e55b1ab240ba6c" }, { "passage": "ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስተዳደር በኋላ ሚዲያና የሚዲያ ቁጥጥር ምን ይመስላል?\\nበሌላ በኩል የሚዲያ አዘጋገቦች ከወገንተኝነት የፀዱ አለመሆናቸው ይህም በማኅበረሰብ መካከል ለሚፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት እንደሆኑ ተደጋግሞ ይነገራል። \n\nለዚህም ከሚጠቀሱ ምክንያቶች አንዱ በሚዲያዎች ነፃ፣ ከወገንተኝነት የፀዳ፣ ሚዛናዊ እና ሙያዊ አዘጋገብ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ቁጥጥር መላላት እንደሆነ ይጠቀሳል። \n\n• የድኅረ ዐብይ ሚዲያ በምሁራኑ ዕይታ \n\n• ብሮድካስት ባለሥልጣን ሥልጣኑ የት ድረስ ነው?\n\nዶ/ር ጌታቸው ድንቁ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ናቸው።\n\nዶ/ር ጌታቸው ለውጡን ተከትሎ ባለፉት ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ ለሚዲያ የተሻለች አገር እንድትሆን ብሮድካስት ባለሥልጣን የተለያዩ ማሻሻያዎችን ሲያደርግ መቆየቱን ይናገራሉ። \n\n\"በሚዲያ ነፃነትና በሚዲያ ሙያ ጎረቤት አገር ኬንያ የተሻለች አገር ናት\" የሚሉት ዶ/ር ጌታቸው ከእነርሱ ልምድ ለመውሰድ የልዑካን ቡድኑን በመምራት እዚህ እኛ የምንገኝበት ኬንያ መጥተው ነበር። \n\nበዚህ አጋጣሚም የቢቢሲን ቢሮ ለመጎብኘት ጎራ ባሉበት ወቅት፤ ከለውጡ በኋላ ያለውን የሚዲያ ዘገባ ይዘትና የቁጥጥር ሥራን አስመልክተን ቃለ ምልልስ አድርገንላቸው ነበር።\n\nጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በአገሪቷ ያለውን የሚዲያ ሁኔታ እንዴት ይገመግሙታል?\n\nከፍተኛ መሻሻል አለ። ከብዝሃነት አንፃር ቁጥራቸው ጨምሯል። መንግሥት በፊት በተለይ ለኤሌክትሮኒክ ሚዲያ ፈቃድ ለመስጠት ፈራ ተባ ይል ነበር። አሁን ግን ቁጥራቸው ጨምሯል። በተለይ በሳተላይት የሚሠራጩ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ለመጀመር የሚፈልጉ ማሟላት የሚጠበቅባቸውን ካቀረቡ ፈቃድ ይሰጣል።\n\nጋዜጦች [በቀጥታ እኛን ባይመለከቱም] ብዙ መፅሔቶችና ጋዜጦች ገበያ ላይ ይታያሉ። ተዘግተው የነበሩ ድረ ገፆችም ተከፍተው የተለያዩ መረጃዎች እያስተላለፉ፤ ሕብረተሰቡ መረጃ የሚያገኝባቸው አማራጮች በዝተዋል።\n\nነገር ግን አሁን በአንገብጋቢነት የሚነሳው የጥራት ችግርና ወገንተኝነት ነው። እንዲህ መሆኑም በሕብረተሰቡ ዘንድ አሉታዊ ተፅዕኖ እያደረሰ እንደሆነ ይነገራል። ባለሥልጣኑ እዚህ ላይ ምን ይላል?\n\nታፍኖ የነበረ ሚዲያና የሚዲያ ምህዳር በሚከፈትበት ጊዜ ወደ ሜዳው መጥተው የሚጫወቱት ሁሉ ሙያዊ በሆነ መንገድ ሥራውን ይሠሩታል ተብሎ አይታሰብም። አንዳንዶች ነፃነቱን ተጠቅመው በኃላፊነት ሲሠሩ፤ አንዳንዶች ደግሞ ለተለያየ ምክንያት ሚዲያውን ይጠቀሙበታል። \n\nለፖለቲካ አላማ ማስፈፀሚያ፣ ለቡድን ዓላማዎች ማስፈፀሚያ እንደሚጠቀሙበት አስበው ይገባሉ። ሲያመለክቱ እንደሱ ቢሉ እኛ ፈቃድ አንሰጣቸውም፤ ሁሉንም ሕብረተሰብ በእኩል እናገለግላለን ብለው ነው ፈቃድ የሚሰጣቸው፤ ፈቃድ ከወሰዱ በኋላ ግን መንሸራተት ያሳያሉ።\n\nወገንተኝነት ከሚዲያ ሙሉ ለሙሉ ይጠፋል ተብሎ ባይታሰብም፤ እኛ አገር እንዳለው ጭልጥ ያለ ወገንተኝነት፤ አንዱን እያሞገሱ፤ አንዱን እያኮሰሱ የሚሠራ ሚዲያ ግን ብዙም የለም። \n\nይህንን የመቆጣጠር ኃላፊነት እኮ የእናንተ ነው። እንዲህ ያደርጋሉ ባለችኋቸው ሚዲያዎች ላይ ምን እርምጃ ወሰዳችሁ? \n\nሁለት ነገሮችን ለማመዛዘን እንሞክራልን። ቸኩለን ወደ እርምጃ አንሄድም። ባንድ በኩል አሁን የተጀመረው የሚዲያ ነፃናትና ተደራሽነት መስፋት፤ የተለያዩ ድምፆች በሚዲያ የመስተናገዳቸው ጉዳይ እንዲቀጥል ስለምንፈልግ፤ አንዴ መስጠት፤ አንዴ መንፈግ እንዳይሆን ቸኩለን ወደ እርምጃ አንገባም። ቢያምም አንዳንድ ነገር መታገስን ይጠይቃል።\n\nእስከምን ድረስ ነው መታገስ የሚቻለው? \n\nይገባኛል እመጣበታለሁ። እና ሁለተኛው ደግሞ ሕብረተሰብ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ የሚዲያ አዘጋገቦች ሲኖሩ፤ ገና ለገና መማር አለብን እያልን ሕብረተሰቡን የሚጎዳ ቀጥተኛ ነገር ሲፈፀም...", "passage_id": "56a97593e61e93be24027eba1c618f19" } ]
4a19b9cbe59ffea7ccb961d07fb66e46
04391ed189555d5cdfcd4a8774625eeb
የጅት ኩንዶው ማዕከል ምስጉን የረድዔት ተግባር
ስፖርት ከአካላዊ እንቅስቃሴና ከመዝናኛነት ባለፈ ማህበራዊ ግዴታን በመወጣት ረገድ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በተለያዩ አጋጣሚዎች ታይቷል። በተለይም ዓለም በኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ 19) ምክኒያት ጭንቅ ውስጥ በገባችበት በዚህ ወቅት ስፖርትና የስፖርቱ ማህበረሰብ ማህበራዊ ግዴታን በመወጣት በኩል እያበረከተ የሚገኘው አስተዋፅኦ እዚሁ አገራችንም ትልቅ ቦታ እንዳለው መታዘብ ይቻላል። ኤርሚያስ ገሰሰ ጂምና ማርሻል አርት ማዕከል ወጣቶችን በጅት ኩን ዶ እንቅስቃሴ ከማብቃት ጎንለጎን የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ይታወቃል። የበጎ አድራጎት ስራ ከማርሻል አርት ስፖርት ጋር አብሮ እንደሚሄድ የሚናገረው ማስተር ኤርሚያስ ወጣቶች ማርሻል አርትን ሲማሩ የስነምግባር ትምህርትም አብሮ እንደሚሰጣቸው ያብራራል። ይህ የስነ ምግባር ትምህርት መገለጫው ደግሞ በጎ ተግባር ነው። 1995 ዓ.ም አካባቢ የተማሪ ቤተሰቦች፣በጎ ፍቃደኞችና ሌሎችም በጋራ ሆነው የስፖርቱን እንቅስቃሴ ሲጀምሩ ገንዘብ በማዋጣት ጎዳና ላይ ያሉ ወገኖችን በምግብ፣ በአልባሳት ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር በዘላቂነት በማቋቋም መደበኛ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እያደረገም ይገኛል። የበጎ አድራጎት ስራውን ከስፖርቱ ባሻገር ለማስፋት በቅርቡ ‹‹ዿጉሜ 5 የበጎ አድራጎት ድርጅት›› በሚል ስያሜ በማሳደግ እውቅና አግኝቶ እየተንቀሳቀሰም ነው። በየዓመቱም የትንሳዔን በዓል ምክኒያት በማድረግ በጎዳና ላይ ያሉ ወገኖችን የመመገብ፣አልባሳትንና ገንዘብ የመስጠት መርሃግብሮችን ያካሂዳል። መማር የሚችሉ እንዲማሩ፣መስራት የሚችሉ እንዲሰሩ ማድረግም አንዱ ተግባሩ ነው። በዚህም የበርካታ ወጣቶችን ሕይወት መለወጥ ተችሏል። ይህ ምስጉን የረድዔት ተግባር በየጊዜው እያደገ ሄዶም ኤርሚያስ ገሰሰ ጂምና ማርሻል አርት ማዕከል ከ‹‹ዿጉሜ 5 የበጎ አድራጎት ድርጅት›› ጋር በመተባበር ባለፈው እሁድ ሃያ ሁለት የጎዳና ልጆችን በማንሳት ማዕድ ከማጋራት ባሻገር መስራት የሚችሉ ወደ ስራ እንዲገቡ፣ ወደ ቤተሰብ የመመለስ ፍላጎት ያላቸው አስፈላጊው ነገር ተሟልቶላቸው እንዲመለሱና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ እስከ ማድረግ የደረሰ የረድዔት ተግባር አከናውኗል። በስፖርቱ የሚሳተፉ ወደ በጎ አድራጎት ድርጅቱ አባልነት እንዲካተቱ በማድረግ ችግርተኛ ወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እየተሰራ መሆኑን የሚናገረው ማስተር ኤርሚያስ አምስት መቶ ያህል አባላት ያሉት የበጎ አድራጎት ድርጅት ከዚህም በላይ የረድኤት ስራዎችን የማከናወን ፍላጎት ቢኖረውም ከጎዳና ላይ የሚያነሳቸውን ልጆች ማሳደሪያ ወይም ማረፊያ ቦታ ትልቁ ችግር እንደሆነ ያስረዳል። ተረጂዎቹ ወጣቶች ቢታመሙም የሕክምና ጉዳይ አሳሳቢ እንደሆነባቸው ገልጿል። በዚህ ረገድ ማንኛውም አካል ቢደግፋቸው ሌሎቹን አስፈላጊ ግብዓቶች ለማሟላት እንደማይከብድም ይናገራል። በተለይም እነዚህ ከበጎ አድራጎት ድርጅቱ አቅም በላይ የሆኑ ችግሮች ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ አሁን ያለንበት አስቸጋሪ ጊዜ እስኪያልፍ ማንኛውም አካል ትብብር እንዲያደርግ ጥሪውን አቅርቧል። ይህም ልጆቹን ከቫይረሱ ተጋላጭነት ከመጠበቅ ባለፈ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር በሚደረገው ርብርብ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ያለውን እምነት ተናግሯል። በቀጣይም ሌሎች ወጣቶችን ከጎዳና ለማንሳት ጥረት እንደሚደረግ ቃል ገብቷል። ባለፈው እሁድ ማዕድ የማጋራት መርሃግብሩ ሲከናወን በስፍራው የተገኙት የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስራ አራት ዋና አስፈፃሚ ወይዘሮ ወይንሸት አስናቀ፣ የስፖርት ማዕከሉና የእርዳታ ድርጅቱ ከወረዳው አስተዳደር ጋር በመሆን መሰል ስራዎችን ከዚህ ቀደምም ሲያከናውን መቆቱን ተናግረዋል። በተለይም በኮሮና ቫይረስ ስጋት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ማዕድ የማጋራት መርሃግብርን ይፋ ካደረጉ ወዲህ የስፖርት ማዕከሉና የእርዳታ ድርጅቱ በጋራ በመሆን ጎዳና ላይ ያሉ ወጣቶችን ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ መስክረዋል። ‹‹በወረዳችን በርካታ ጎዳና ላይ ያሉ ወጣቶች አሉ›› ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ እነዚህን ወጣቶች ማዕድ ከማጋራት ባለፈ ወደ ስራ እንዲሰማሩና እንዲቆጥቡ በማድረግ፣ ወደ ትምህርት እንዲመለሱ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም ወደ ቤተሰባቸው መመለስ የሚፈልጉትን በመመለስ በርካታ ተግባራት መፈፀማቸውን አስታውሰዋል። ሌሎችም ከዚህ ምስጉን ተግባር በመማር ተመሳሳይ የረድዔት ስራዎችን እንዲሰሩ በማድረግ የስፖርትን ማህበራዊ ኃላፊነት በተግባር ማሳየት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። ወረዳው የስፖርት ማዕከሉና የረድዔት ተቋሙ የሚያደርጉትን በጎ ተግባር ለመደገፍም ማደሪን የመሳሰሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል። አዲስ ዘመን ግንቦት 6/2012ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=32321
[ { "passage": "በሆቴሎች ከብርጭቆ አጣቢነት እስከ መስተንግዶነት ሰርቷል፣ በመኪና ጋራዥ ባለሙያ ለመሆን ጥሮም አልተሳካለትም። ተስፋ የቆረጠው መሀመድ አህመድ የለመዳቸው ሱሶች አሸንፈውት ላለፉት አምስት ዓመታት ኑሮውን የመሰረተው ጎዳና ነበር። ከጎዳና ባሻገር ሌላ ሕይወት ይኖረዋል ብሎ ያሰበ አልነበረም። አሁን ግን ታሪኩ ተቀይሯል። ‹‹ከጎዳና ወጥቼ የሞቀ ቤት እኖራለሁ ብዬ አስቤም አቅጄም አላውቅም›› ይላል። ዛሬ በየዕለቱ ጊዜውን በስራ ያሳልፋል። ይህ ደግሞ ጥሩ መነሳሳት እንደፈጠረለት ይናገራል። በጎ ፍቃደኛ ካሊድ ናስርና ወንድሙ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ስለማዕድ ማጋራት ያደረጉትን ጥሪ ተከትለው በራስ ተነሳሽነት በጎ ለማድረግ አቀዱ። በኮሮና ቫይረስ ምክንያት መጠጊያ ያጡ 100 ወጣቶች ማረፊያ፣ መጠለያና መመገቢያ ቦታን አዘጋጅተው አስጠጉ። ከእነዚህ መካከልም ጎዳና የነበሩት መሀመድና ቢኒያም ተጠቃሽ ናቸው። ብዙዎች ጎብኝተው አድናቆትን እንደቸሯቸው ነው የሚናገረው። በጎ ፍቃደኛ ካሊድ እንደሚለው፤ ወጣቶቹ ወደጎዳና እንዳይመለሱ ጥረት እያደረግን እንገኛለን። ‹‹ከጎበኙን መካከል ጉያ ትሬዲንግ በማታው ሽፍት የሚሰሩ 60 ወጣቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ አድርጎልናል። አሁንም ቀሪዎቹን ወጣቶች ስራ ለማስጀመር የተቻለንን እያደረግን እንገኛለን››። በድርጅቱ በተቆጣጣሪነት የሚሰራው ቢኒያም የሺጥላ በእንስሳት ጤና ህክምና ዘርፍ በዲፕሎማ ተመርቆ በመንግስት መስሪያ ቤት በበጎ አድራጎት ድርጅት ተቀጥሮ ሲሰራ ቆይቷል። በኋላም የተሻለ ገቢ ለማግኘትና ህይወትን ለመቀየር በማቀድ ይሰደዳል። ይሁን እንጂ እንዳሰበው አልሆነለትም። ተመልሶ ስራ ሲያፈላልግም አልተሳካለትም። በቀን ስራ ተቀጥሮ ሕይወትን ለማሸነፍ ሲታትር በወረርሽኙ መከሰት ሳቢያ የተቀዛቀዘው ገበያ ለቢኒያም ፈታኝ ጊዜን ይደቅናል። ከስራ ሲቀነስም ማረፊያም ምግብም ተቸግሮ በነበረ ጊዜ ነው ከካሊድ ጋር የተዋወቁት ‹‹እርሱን በማግኘቴ ችግሬን አሳልፌያለሁ፣ ሕይወትን እንደአዲስ ጀምሬያለሁ›› ሲልም ይናገራል። እንደጊዜያዊ ማቆያ ከገቡት መካከል ሆኖ ለወረርሽኙ ሳይጋለጥ፣ የዕለት ጉርስ ሳይቸገር ለማለፍ እንደቻለም ይናገራል። አልፎም በጉያ ትሬዲንግ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንደሆነና ተስፋ እንዲሰንቅ እንዳደረገውም ይመሰክራል። ከሱማሌ ክልል ተፈናቅለው\nበመጠለያ የቆዩትና በድርጅቱ\nየስራ ዕድል የተፈጠረላቸው\nወጣት አሊ አሕመድና\nወጣት ነጃት አህመድ\nጉያ ትሬዲንግ የስራ ዕድል ተጠቃሚ ስላደረጋቸውና ሙያ እንዲለምዱ ዕድል ስላገኙ ደስተኛ መሆናቸውን ይናገራሉ። ከምግብ ርዳታ ጠባቂነትና ከእጅ ወደአፍ ከነበረ ኑሮ ተላቅቀው ሰርተው በማግኘታቸው የመንፈስ እርካታ እንዳገኙ ይጠቁማሉ። ለቀጣይ ሕይወታቸውም ተስፋ እንዲሰንቁ እንዳደረጋቸውም ያክላሉ። የጉያ ማኑፋክቸሪንግ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኢምራን ነጋ እንደሚሉት፤ በአገር ውስጥ የሚገኙ ሆስፒታሎች በቋሚነት በየአመቱ ከ20 ሚሊዮን በላይ ማስክ ይጠቀማሉ። ፕሮጀክቱ ባለሃብቱ ሊሰማሩበት የሚፈልጉት አንድ ዘርፍ ነበረ። ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውና ወደአገር ውስጥም የገባው የኮሮና (ኮቪድ 19) በዋናነት በፍጥነት ወደማምረቱ ለመግባት አስገድዶናል ይላሉ። ወረርሽኙን ለመከላከል መሰረታዊ ፍላጎት ማስክ መሆኑን በመገንዘብ ይህንን ደግሞ በጥራት የሚያመርት ፋብሪካ በማስፈለጉ በአገር ውስጥ ማሽኑን በመትከል ማምረት መጀመራቸውን ነው የሚናገሩት። አሁን ፋብሪካው በየቀኑ በሁለት ፈረቃ ለ20 ሰዓታት ያመርታል። በቀን ውስጥም አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን የአፍ መሸፈኛ ማስክ በከፍተኛ ጥራት እያመረተ ይገኛል ሲሉ አቶ ኢምራን ይጠቁማሉ። ፋብሪካው ለማስክ ምርት ብቻ በሁለት ፋብሪካ 180 ሰራተኞችን መቅጠሩንም ነው የጠቆሙት። የአፍ መሸፈኛ ማስክ ምርት በፍጥነት ለገበያ መድረስ ስለነበረበት ያለውን አማራጭ መጠቀማቸውንና የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካው ምርት ማከማቻ ክፍል የነበረውን የማስክ ማምረቻ ክፍል ለማድረግ መገደዳቸውንም ይጠቅሳሉ። ‹‹ለምርታችን የምናስገባው ጥሬ እቃ ጥራቱ ከፍተኛ፣ የማስክ ምርቱም ለህክምና አገልግሎት መዋል የሚችል ነው። ለዚህም ከኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥርና አስተዳደር ባለስልጣን የሲኦሲ ሰርተፊኬት አግኝተናል፣ ምርቱንም እያስመዘገብን እንገኛለን›› ነው ስራ አስኪያጁ ያሉት። የስራ ምልመላ ለማከናወን ሁለት አይነት መንገድ መከተላቸውን ስራ አስኪያጁ ይናገራሉ። በማስኩ ፕሮጀክት ብቻ ማስታወቂያ በማውጣት በከፍተኛ ደረጃ የተፈጠረውን የሥራ አጥ ቁጥር ለማሟላት መሞከሩንም ይናገራሉ። በጎዳና ተዳዳሪነት ይኖሩ የነበሩ በጎ ፈቃደኛ ወንድማማቾች ተሰባስበው ከሚኖሩ ልጆች ምልመላ ማድረጋቸውንም ነው የሚጠቁሙት። እንደስራ አስኪያጁ ገለጻ፤\nለስራ የተመለመሉት ልጆች\nከፍተኛ የስራ አቅም፣\nየትምህርት ዝግጅትና ጥሩ\nየስራ ሞራል ያላቸው\nቢሆኑም ቀን ዘንበል\nብሎባቸው ጎዳና ወጥተው\nየነበሩ ናቸው። ይህ\nእንደ ድርጅታችን ግዴታችን\nነው ብለን እናምናለን።\nወደፊት ለሚኖሩን የማኑፋክቸሪንግ\nዘርፎች ይህንን አይነት\nየሰራተኛ ምልመላን እንከተላለን። ከሁለት ዓመታት በፊትም ከኦሮሚያ እና ከሶማሌ ክልል ተፈናቃዮችን አሰልጥነን ወደስራ አሰማርተናል። ጉያ ቴክስታይል ማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ በጠቅላላ የኢንደስትሪ ዘርፍ የተሰማራ መሆኑን የድርጅቱ ባለቤት አቶ ሙባረክ ከማል ይናገራሉ። ድርጅታቸው ቀደም ሲል ጨርቃ ጨርቅና መሰል ምርቶች ላይ ተሰማርተው መቆየታቸውን ያስታውሳሉ። ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ ለተፈጠረው ችግር ደራሽ ለመሆን በማሰብ የሜዲካል ሰርጂካል ማስክ ወደማምረት እንደተሸጋገሩ ነው የሚናገሩት። ኮኖናን ለመከላከል ቻይናውያን ችግሩ ሲፈጠር የደገፋቸው እንዳልነበረ ይጠቁሙና፤ ህዝቡ ርብርብ ማድረጉን ያስታውሳሉ:: አምራቾች ወደማስክና ጓንት ምርት ተሸጋግረው አገራቸውን እንደታደጉም ነው የሚገልጹት። ድርጅቱ ከቻይናውያን ልምድ\nበመቅሰም ለወረርሽኙ መከላከል\nስራ ለመስራት መወሰኑንም\nአቶ ሙባረክ ይጠቁማሉ።\nከውጭ ምርት ሳይገባ\nበአገር በቀል ባለሃብት\nችግሩን መቋቋም እንደሚቻል\nለማሳየትና ለባለሃብቶችም ምሳሌ\nለመሆን የማስክ ምርት\nለማምረት መወሰኑን ይናገራሉ። እቅዱ በቀን 10 ሚሊዮን ማስክ ማምረት ነው:: የአገር ውስጥ ፍላጎትን በመሸፈን ወደውጭ ለመላክ አቅደናል:: ይህንን ለማድረግ በአመት እስከ 50 ሚሊየን ዶላርና አራት ሺህ የሰው ሃይል ይጠይቃል። አሁን በቀን አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊየን ማስክ የማምረት አቅም ላይ ደርሰናል። ይህ ማለት የፋብሪካውን አንድ አስረኛውን መሸፈን ችለናል። ያቀድነውን ለማምረት የኢንቨስትመንት ችግር የለብንም ባይ ናቸው አቶ ሙባረክ። ፕሮጀክቱ ሰፊ ቦታ ይፈልጋል። ባለው ነባራዊ ሁኔታም ርቀትን ጠብቆ ማምረት ያስፈልጋል። ስለሆነም የማምረቻ ቦታ በፍጥነት ከመንግስት ማግኘት ይኖርብናል። ወረርሽኙ ጊዜ የማይሰጥ ነው። በመሆኑም የማስክ ማምረቻ ማሽኑን የተከልነው ቀደም ሲል ማከማቻ የነበረው ቦታ ላይ ነው። ቀን የጣላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች የስነ ልቦና ጥንካሬ እንዲያገኙ በማድረግ እንዲህ አይነት የስራ ዕድል ቢፈጠርላቸው ተስፋ ሊሰንቁ ይችላሉ። ይህ አይነት ሁኔታ በእኛ አገር ብዙም አልተሰራም። መስራት ይገባናል ከሚል እሳቤም የተጀመረ ነው።አዲስ ዘመን ሐምሌ 8/2012ዘላለም ግዛው ", "passage_id": "20efa847e3e7635d7baba5ec5a36d1d2" }, { "passage": "ጌትነት ተስፋማርያም ፊታቸው ላይ\nሊፒስቲክ፣\nኩል\nእና\nየውበት\nመጠበቂያ\nክሬሞች\nፈጽሞ\nአይታዩም።\nከዚህ\nይልቅ\nፊታቸው\nላይ\nየሚታየው\nየአልበገር\nባይነት\nወኔ\nእና\nተፈጥሯዊ\nውበት\nነው።\nፀጉራቸውንም\nቢሆን\nእንደወጉ\nይሠሩት\nእንደሆን\nእንጂ\nዛሬም\nነገም\nመተኮስ\nእና\nባማሩ\nጌጦች\nማስዋብ\nየሚያስችል\nጊዜም\nሆነ\nዕድሉ\nየላቸውም።\nምክንያቱም\nዓላማቸው\nየሀገር\nህልውና\nማስከበር\nእና\nወንጀለኞችን\nሥርዓት\nማስያዝ\nነውና፡፡ገደላገደሉን ሲዘሉ፤ ጢሻውን ሲያቋርጡ ነው አብዛኛውን ጊዜያቸውን በግዳጅ ላይ የሚያሳልፉት። ሕብረ- ብሔራዊነትን በአግባቡ በተላበሰው የመከላከያ ሠራዊት ውስጥ የፆታ ልዩነት ሳይገድባቸው በጽናት የቆሙ እንስቶች የሠራዊቱ ብርቱ ክንድ ስለመሆናቸው ደግሞ የሚያውቋቸው ይመሰክራሉ።ወታደር አስደሳች ታከለ እና ወታደር ታሪኬ ኤርሚያስ የመከላከያ ሠራዊትን የተቀላቀሉት ከሐዲያ እና ጋሞ ዞኖች ነው። ሁለቱም እንስቶች የ20 ዓመት የወጣትነት እድሜ ላይ የሚገኙ የ24ኛ ክፍለጦር አባላት ናቸው። በትግራይ ክልል በተደረገው የሕግ ማስከበር ዘመቻ አቧራ ለብሰው ኮቾሮ ቀምሰው አፈር ላይም ጋደም ብለው ያሳለፏቸው በርካታ ቀናት መኖራቸውን አጫወቱን እና ታሪካቸውን በይበልጥ ለመስማት ጓጓን። ግርማ ሞገስ ባለው አረማመዷ ታጅባ ታሪኳን ያወጋችን ሴት ወታደር አስደሳች ታከለ፤ የሕግ ማስከበር ዘመቻው ከጅማሮው አንስቶ ላይ መሳተፏን ነገረችን። በተለይ በአከርና በአካባቢው የነበሩ የጁንታው ቡድን ታጣቂዎችን ለይቶ ለሕግ በማቅረብ እና የአካባቢው ኗሪ ሳይጎዳ ግዳጁን ለማጠናቀቅ ጥረት መደረጉን ታስታውሳለች። በወቅቱ ግን ከበአከር አለፍ ብላ ባለች አንድ ተራራማ ቦታ ላይ ስትደርስ ባጋጠማት የመንሸራተት አደጋ ወድቃ ቀኝ እጇ ላይ ስብራት አጋጠማት።አደጋው የማያላውስ እና ጥዝጣዜውም ከባድ ህመም ያለው ቢሆንም ግን “መሣሪያዬን ለማንም አልሰጥም” ብላ የሚመጣውን ሃይል ለመመከት ዝግጅት ማድረጓ አልቀረም። በመጨረሻም አካባቢውን መከላከያ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ሲቆጣጠረው እርሷም ለህክምና ተወሰደች። እስከ ባህር ዳር\nከተማ ድረስ ተጉዛ\nአስፈላጊውን ህክምና ስትከታተል\nግን ትጥቄን ስጡኝ\nበማለት ከአጠገቧ ሳትነጥል\nማቆየቷን አትዘነጋውም። ዓላማዋ\nቶሎ ተመልሳ የሕግ\nማስከበር እርምጃው ላይ\nለመሳተፍ እንደነበር ነግራናለች።\nአሁን ላይ በመልካም\nጤንነት ላይ መገኘቷን\nበማሳወቅ ልቧ እንደፈቀደው\nዳግም ወደግዳጅ ለመመለስ\nጥያቄ አቅርባለች። በሠራዊቱ ውስጥ ያለው የሴቶች ተሳትፎ የሚያኮራ ነው የምትለው ወታደር አስደሳች፤ 150 ጥይት ታጥቀው ከወንድ እኩል የሚሮጡ እና የተሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት የሚፈጽሙ አባላት እና አመራሮችም ለሌሎች እንስቶች ሁሉ የጽናት ተምሳሌት መሆናቸውን ትገልፃለች። ወታደር ታሪኬ ኤርሚያስ በበኩሏ “በከተማ አካባቢ መኖርና መመለስ ሃሳቤ አይደለም። ዓላማዬ ሁሉ ለሀገሬ መታገል እና ለእናት ሀገሬ መኖር ነው” ትላለች። በሠራዊቱ ውስጥ ያለውን የሴቶች ተሳትፎ ስትገልጽም “ሴት ነኝ ብሎ ወደኋላ የሚሸሽ የለም። ሴቶች በውጊያ መሳተፍ ብቻ ሳይሆን ሠራዊቱንም በማበረታታት ጭምር ጥንካሬያቸውን አሳይተዋል፤ ሴቶች ከባድ መሣሪያ ጭምር ይዘው ለሀገር ህልውና ለህይወታቸውን ሳይሳሱ ተሰልፈዋል” ብላለች። ለሀገሯ አይደለም ደሟን ማፍሰስ ህይወቷንም ልታጣ የምትችልበት አጋጣሚ እንደሚኖር የምትናገረው ወታደር ታሪኬ እርሷም በአከር አካባቢ በነበረ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ብሽሽቷ አካባቢ በጥይት ተመታ ቆስላለች። በቆሰለችበት አጋጣሚ ደም ፈሷት ህመም ቢበረታባትም ግና ወኔዋ ሁሉ መሣሪያዋን ይዛ ግዳጇን ለመቀጠል እንደነበር አትረሳውም።መከላከያ ሠራዊት የህክምና ባለሙያዎች በአካባቢው የመጀመሪያ ዕርዳታ አድርገውላት ለተጨማሪ ህክምና ወደባህርዳር እና ሌሎች ከተሞች የተወሰደችው ወታደር ታሪኬ፤ ህክምናዋን ስታጠናቅቅ ግን፤ ስለዚህ አሁኑኑ ወደ ዘመቻ ልሂድ” ብላ መነሳቷን ነግራናለች። ይሁንና ኢትዮጵያ በርካታ ልጆች ስላሏት ተጨማሪ ሥራ ሲያስፈልግ እንደምትጠራ ተገልፆላት ዝግጅት በማድረግ ላይ ነች። ሠራዊቱ ውስጥ ያሉ በርካታ እንስቶች ዛሬም በድንበር እና በተለያዩ የግዳጅ አካባቢዎቸ የጁንታው ቡድን አመራሮችን ለመያዝ ደፋ ቀና ይላሉ። የሠራዊቱ ፈርጦች መሆናቸውንም በተግባር አሳይተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 4/2013", "passage_id": "eca8f788162d83578e3a1e7ebe749c82" }, { "passage": " ‹‹እስከ ምሽት 5፡30 ድረስ ፊልም እያየሁ ነበር። ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ ግን ዐይኔ ማየት አቁሞ ነበር።›› አለ። በአንዲት ጀንበር ልዩነት የሕይወቱ አቅጣጫ፣ መንገድ እና አካሔዱ የተቀየረበት ጋዜጠኛው ሰለሞን ታምሩ። ገፍቶ ሊያልፍ ያልቻለውን ተራራ ሌላ መንገድ ፈልጎ የማለፍ ጽናትና ጥንካሬ ያለው ወጣት ነው፤ እሱም የሚናገረው ይህንኑ ነው። በብርታቱ ‹አሻራ› የተሰኘ የራድዮን መሰናዶን በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 በየሳምንቱ ሐሙስ ምሽት ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ ለአንድ ሰዓት ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን ያቀርባል። ከአካል ጉዳት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችንም ያነሳል። አዲስ ማለዳም ስለ አሻራ የራድዮን ፕሮግራም፣ የፊታችን ሰኞ ታኅሳስ 20/2012 ስለሚካሔደው ኹለተኛው አሻራ ሽልማት አልፎም ስለግል ሕይወቱ አናግራዋለች። 2002 ላይ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ የነበረው ሰለሞን፣ ከእለታት በአንዱ ማለዳ ዐይኑ ማየት ተስኖት ሲነሳ ድንጋጤና ጭንቀት ፋታ አልሰጡትም። ያ ጊዜ ከባድ እንደነበርና የሆነውን ተቀብሎ አዲሱን የሕይወት ምዕራፍ ለመክፈት ሦስት ዓመታት እንደወሰደበት ያስታውሳል። በ2005 ግን አዲስ ሕይወት የዐይነ ስውራን ማዕከል የብሬል ትምህርት ተማረ። የብሬል ትምህርት የጀመረ ቀን ‹‹ምንም ነገር ማድረግ እንደምችል ያኔ ነው የገባኝ›› ያለው ሰለሞን፣ ዐይናማ በነበረ ጊዜ የነበረውን ሕልምና ሐሳብ ሁሉ የዐይኑ ለማየት መጋረድ እንደማይከለክለው ለራሱ እርግጠኛ ሆነ። ‹‹ሥነ ጽሑፍ ስለምወድ ብሬል ስማር መጀመሪያ ሥራዬን ላስነብብ እችላለሁ ብዬ ነው ያሰብኩት።›› ሰለሞን አለ። ባለጸጋ የነበረን ሰው ሐብቱን ቀምቶ ጎዳና እንዲኖር የማድርገ ያህል ስሜት የተሰማው ቢሆንም፣ ‹‹ግን ከዛኛው ሕይወቴ ይህኛው ስኬታማ ነው። እያየሁ ከኖርኩት ሳላይ የኖርኩት ይበልጣል። ሳላይ ዲግሪ ይዣለሁ፣ ሳላይ በምወደው ሙያ ላይ ነኝ፤ ሳላይ ኮምፕዩተር ተምሬያለሁ። ይህን ሁሉ ራሴ ነኝ ያመጣሁት። ተራራውን ገፍቼ ማለፍ አልችልም፤ ግን ማለፊያ መንገድ አግኝቻለሁ።›› ሲል ይገልጸዋል። ከሦስት ዓመት ቆይታ በኋላ 10ኛ ክፍል ገብቶ ተማረ፤ ዩኒቨርሲቲ መግባትም ቻለ። የየሚወደውን የጋዜጠኝነት እና የራድዮን ሥራ ግን ገና 11ኛ ክፍል እያለ ነው የጀመረው። 2011 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማኅበራዊ ሳይንስ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪውን ተቀበለ። ‹‹ማኅበረሰብ ላይ መሥራት እፈልጋለሁና ገና 11ኛ ክፍል እያለሁ ነው መማር ያለብኝን የመረጥኩት። ገብቼ ሳልንገላታ ጨረስኩ።›› ሲል ያለፈውን ያስታውሳል። ሰለሞን በልጅነትና ከፍ ሲልም በወጣትነት እድሜ ብርታትን ያወቀበት ወጣት ነው። ይህን ብርታት ከእናቴ ወርሻለሁ ባይ ነው። የእርሱና የሦስት እህቶቹ እናት ገነት፣ አራት ልጆቻቸውን ለብቻቸው ያሳደጉና ለልጆቻቸው አረአያ መሆን የቻሉ ሴት መሆናቸውን ሰለሞን ይመሰክራል። ያደርግላቸው ቢያጣ የከፈተውን ሚድያና ፕሮሞሽን በእናቱ ስም አድርጎታል። ገነት ሚድያ እና ፕሮሞሽን። ‹‹በእኔ ውስጥ የእርሷ ስም እንዲነሳ እፈልግ ነበር። የሚድያ እድል ሳገኝ እርሷ ትጠራበት እርሷ ትመስገንት ብዬ ነው።›› ሰለሞን እንዳለው። አዲስ አበባ ፈረንሳይ ለጋሲዮን የተወለደው ሰለሞን፣ ከአካል ጉዳተኝነት ጋር በተያያዘ ለራሱንም ለብዙዎችንም የተረፈ ነው ሲል ዮሴፍ ኃይለማርያምን (ዮሴፍ ምርኩዝ) ያደንቃል። ታድያ በሰፈሩ ዓለምነህ ዋሴ፣ አየለ ማሞ፣ ድምጻዊ ግርማ ተፈራ፣ ኮለኔል ሳህሌ ደጋጎ፣ ጋዜጠኛ ታደሰ ሙሉነህን እያየ ማደጉ ለሙያውና ለኪነጥበብ እንዲቀርብ አንድ ግብዓት ሳይሆነው አልቀረም። ‹‹ስለ ጉዳቴ የሚያወሩልኝ ካሉ ብዬ ፈልጌ ነበር፤ መጀመሪያ ፋና ላይ ነበር፤ አንድ ድምጽ የሚል ፕሮግራም፤ ጥሩ ነገር ያቀርባሉ ግን ከበድ ያሉ ጉዳዮችንም ያነሳሉ። ያንን ስሰማ ቤት ውስት ጓደኞቼ ቀይረው ይሉኛል። ለምን ስላቸው እኛም እንፈራለን፤ በዛ ላይ አንተንም የሚሰማህ ይመስለናል፤ ስለዚህ የሚያዝናናህን ነገር ስማ ይሉኛል።›› ሲል ያስታውሳል። ይህንን ከልቦናው ያላጠፋው ሰለሞን፣ በኢትዮ ኤፍ ኤም ላይ ሥራውን ሲጀምር አዲስ መንገድ ተጠቀመ። አሻራ የራድዮን ፕሮግራም የተጀመረውና አየር ላይ የዋለው ከኹለት ዓመት በፊት ኅዳር 24/2010 ነው። ይህ ሳምንታዊ መሰናዶ ‹‹እኛ ባለ አሻር ትውልድ ነን፣ እናንተስ?›› ሲል ይጠይቃል። የመሰናዶው ዓላማም ቀድሞ ይሠሩ የነበሩትን ከአካል ጉዳት ጋር የተያያዙ ደረቅ ያለ ይዘት ያላቸውን መሰናዶዎች በአዲስ አቀራረብ በተዝናኖት በኩል መፍጠር ነው። ‹‹አድማጭ እየተዝናና እንዲማር ነው ሐሳባችን። ሰው እንዲሰማልን ነው የፈለግነው።›› ይላል ሰለሞን። ስለዚህም ስኬታማ ሰዎችን በመጋበዝ፣ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎችን እና ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ፣ መጽሐፍት በመተረክ፣ የአካል ገዳተኞችን ገጠመኝና የፈተኗቸውን ጉዳዮች አዝናኝ ሆኖ እንዲቀርቡ ያደርጋሉ። በዚህ ታድያ ከአድማጮች የሚያገኙት መልስ መልካም እንደሆነ ሰለሞን ጠቅሷል። ከአካል ጉዳተኞች ይልቅም አካል ጉዳት የሌላቸው አድማጮች በብዛት እንደሚሳተፉ ይጠቅሳል። ‹‹ፕሮግራሙ መዝናኛ ከሆነ ማንም ሰው ይደግፈዋል። ስለ አካል ጉዳተኝነት እንሠራለን አንልም፤ ዝም ብለን ነው የምንሠራው። ርዕስ ሲሰጥ ሰው ይሸሻል። አይቶ ይፍረድ ብለን ነው የምሠራው።›› ሲልም ስለ መሰናዶው ጠቅለል ያለ ሐሳብ አካፍሏል። ታድያ አሻራ የራድዮን መሰናዶን በየሳምንቱ ሲያቀርቡ ደጋፊ እንደሌላቸው ይጠቅሳል። ‹‹አካል ጉዳተኝነት የሚባለውን ይፈሩታል ይጠሉታል፤ እኛ መዝናኛ ይዘናል ብለን ነው የምናዘጋጀው። ያለ ምንም ስፖንሰር ደጋፊ እየሠራን ነው ያለነው።›› ያለው ሰለሞን፤ እንደውም ጣብያውን በእጅጉ አመስግኗል። ገንዘብ ስላላስገቡ እንዲሁም በይዘት ምክንያት የሚቀነሱ መሰናዶዎች ቢኖሩም፤ ገንዘብ አላስገባችሁም ተብለው እንዳልተቀነሱ በመጥቀስ። አካል ጉዳተኝነት ላይ ያተኮሩና መረጃዎችን የሚያቀብሉ መሰናዶዎች ጥቂት ናቸው። ሆኖም የተሻለ ነው። ይሁንና የሕትመት ሥራዎች ግን የሉም ማለት ይቻላል። ሰለሞን ነገሩ ከባድ እንደሆነ ሳይጠቅስ አልቀረም። እንኳንና ለብሬል እንዲሁም የወረቀት ዋጋ መጨመሩ አስቸጋሪ መሆኑንም አንስቷል። ሆኖም የቴክኖሎጂ መኖር ለአካል ጉዳተኞች ችግሩን እንዳቀለለ ይጠቅሳል። በዚህና በሌሎች ምክንያቶችም በአካል ጉዳተኝነት ላይ መሥራት ከባድ ስለመሆኑ ግን አጥብቆ ይገልጻል። ማኅበራትም በዚህ ላይ ተጽእኖ ማሳደር እንዳልቻሉና ይህን ያህል ለውጥ ማምጣት እንዳልሆነላቸው ሲያነሳ፤ ‹‹ማኅበራት ተጽእኖ ሊፈጥሩ አይደለም፤ ተገቢውን መረጃ አይሰጡም።›› የሚለው ሰለሞን፤ ከጥቂቶቹ በቀር አብዛኞቹ ለራሳቸው ጉዳይ ፈልገው ካልሆነ በቀር ጆሮአቸውን ክፍት አድርገው የሚያዳምጡ እንዳልሆኑ ይጠቅሳል። ‹‹አገራችን ላይ እንዳሉ ሌሎች ሽልማቶች ሁሉም የሚያየው እንዲሆን እፈልጋለሁ።›› ይላል ሰለሞን፣ ስለ አሻራ ሽልማት ወደፊት ርዕይ አዲስ ማለዳ ስትጠይቀው። ባለፈው ዓመት ኅዳር 24 ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሔደው ይህ የሽልማት መሰናዶ ዘሚ የኑስ፣ አማረ አስፋው፣ ጋዜጠኛ ደረሰ ታደሰ እና ሌሎች ብዙም ስማቸው ያልተነሳ ነገር ግን በአካል ጉዳት ላይ ትልልቅ ሥራ የሠሩ ሰዎች ተሸላሚ ሆነዋል። ሽልማቱም እንዲህ ያሉ ብዙ ዓመታት ስለ አካል ጉዳተኝነት የሠሩ ሰዎች፣ ማኅበራት፣ ተቋማት፣ ድርጅቶኅ የመሸለም፣ እውቅና የመስጠት፣ ተሰሚ እንዲሆኑ ማጉላትና ድጋ እንዲያገኙ የማሳወቅ ዓላማ አለው። ይህ ሽልማት ቀጣይነት እንዲኖረው ደጋፊ ማስፈለጉ አያጠራጥርም የሚለው ሰለሞን፣ ሽልማቱ ለጊዜው ደጋፊ የሌለው መሆኑን ጠቅሷል። የአምናው የአሻራ ሽልማት መሰናዶ በብዙዎች ድጋፍ የተከናወነ መሆኑን ያወሳው ሰለሞን፣ ዘንድሮ በኹለተኛው የአሻራ ሽልማት ተመሳሳይ ድጋፍ ባይገኝም መጋቢ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁን ጨምሮ፣ ተዋናይ ፍቃዱ ከበደ፣ ኮሜድያን ተፈሪ ብርቄ እና ሌሎችም በነጻ ለማገልገል የፈቀዱ መሆናቸውን ጠቅሷል። ሸገር የብዙኀን ትራንስፖርት ድርጅትም ሦስት ባሶችን በእለቱ እንግዶችን በየአቅጣጫው ለማድረስ እንደመደበላቸው ጠቅሷል። ሰለሞን አሁንም ከሚያስብበት ትልቅነት ለመድረስ ሲል አላረፈም። አሻራ ሽልማት በጎ አድራት ማኅበር ተብሎ እንዲያድግና ተጽእኖ መፍጠር የሚችል እንዲሆን ይመኛል። አሁን ላይ በሙሉ የጋዜጠኝነት ሥራ ላይ የሚገኘው፣ አሻራ የራድዮ ፕሮግራምን በዋና አዘጋጅነት የሚመራውና በኤዲቲንግም ኃላፊነቱን ተቀብሎ የሚያቀናጀው ሰለሞን፣ ህልሙን ለማሳካት ጉዞውን እንደሚቀጥል ለአዲስ ማለዳ ተናግሯል። ተራራውን ከፍቶ ማፍ ቢከብድ እንኳ አዲስ መንገድ መፈለጉን እንደማይተውም ጭምር። ኹለተኛው አሻራ ሽልማት ታኅሳስ 20/2012 ብሔራዊ ቴአትር ይከናወናል። ሰለሞን ይህን ጥያቄ በሽልማቱ መርሃ ግብር ላይ እፎም በየሳምንቱ ባለው የራድዮን መሰናዶ ላይ ያነሳል። ‹‹እኛ ባለ አሻራ ትውልድ ነን፤ እናንተስ?›› ቅጽ 2 ቁጥር 60 ታኅሣሥ 18 2012", "passage_id": "b92d3d3586b474d6b2146a546cffbb37" }, { "passage": "በአፋር ህገ ወጥ መሳሪያን በገንዘብ ተደልሎ አላሳልፍም ያለው ዋና ሳጅን ሲራጅ አብደላ ስራው አርአያነት ያለው ነው በሚል የፈደራል ፖሊስ ኮሚሽን በዛሬው ዕለት እውቀና ሰጥቶታል።ዋና ሳጅን ሲራጅ አብደላ ከፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል መላኩ ፋንታ እጅ የስማርት ስልክ እና የእውቅና ምስክር ወረቀት ተቀብሏል።ምክትል ኮሚሽነሩ ፖሊሱ በሰራው አኩሪ የህግ ማስከበር ስራ አርዓያ በመሆኑ በኮሚሽኑ ስም ምስጋና አቅርበውለታል።ዋና ሳጅን ሲራጅ አርዓያነት ላለው ተግባሩ ከአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድም እውቅና መሰጠቱ ይታወሳል።", "passage_id": "90d815735d178f7da37d0f3638454cf6" }, { "passage": "ምንም እንኳን እያደረሰ ካለው የህይወት መቅጠፍ ተግባር ጋር ባይወዳደርም ኮቪድ ወረርሽኝ ያመጣቸው በርካታ ሰብአዊ ፋይዳ ያላቸው ቁም ነገሮች በአገራት፤ እንደ አጠቃላይም በዓለም ላይ በርካታ ናቸው። ከእነዚህም መካከል አንዱ የአንድ ማህበረሰብ እንደ ማህበረሰብ የሚገለፅባቸው እሴቶቹ ተጠቃሽ ሲሆኑ፤ መተሳሰብ ደግሞ ከሁሉም አንጋፋ፣ ቀዳሚና የአብሮነትና ወሳኝ የህዝቦች የእርስ በርስ ግንኙነት ማሰሪያ ገመድ ነው። በመሆኑም በአገራችን የኮቪድ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ በስፋት ከተስተዋሉት ተግባራት አንዱ ይሄው የመተሳሰብ፣ መረዳዳትና መደጋገፍ የቆየ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበረሰባዊና ባህላዊና የማንነት እሴት ነው። ስለሆነም በየመስኩ፣ ዘርፉና አቅጣጫው ተግባሩ በተግባር ሲረጋገጥ፤ አንዱ የአንዱን ሸክም ሌላው ሲራዳ፤ ሲያቃልልና ወረርሽኙን በጋራ በመከላከል፣ በመቆጣጠርና ከወረርሽኙ ባሻገር ያለውን ተስፋ ሲያለመልም ይታያል። ኮቪድ 19 ይዞት የመጣው ሞትን ብቻ ሳይሆን በአሁኑ ዘመን መስፈርት ከሱ ያልተናነሰውን የኢኮኖሚ ድቀት ጭምር በመሆኑ ችግሩ የአንድና ሁለት ሰዎች ሳይሆን የሁላችንም ነው። በመሆኑም የሁላችንንም የጋራ መፍትሄ ይሻል። ይህም በጥቅል ስያሜው መረዳዳት፤ መደጋገፍ መሆኑ ነው። ይህ መደጋገፍ፣ መረዳዳትና መተሳሰብ ከታየባቸውና አሁንም ድረስ በመዝለቅ እየተስተዋለ ካለባቸው ዘርፎች መካከል አንዱ የኢኮኖሚ አውታር በመሆን የሚታወቀው የንግዱ ዘርፍ በመሆኑ፤ በዘርፉ በርካታ መመሰቃቀሎች ተከስተዋል፤ በርካቶችም ከጨዋታው ውጪ ሆነዋል። የዜጎች ከሥራ መፈናቀል፣ የንግዱ እንቅስቃሴ “ጭራሽ የለም” እስከ መባል ድረስ መቀዛቀዝ… ቀዳሚ ተጠቃሽና በግልፅ የሚታይ ኮቪድ ወለድ ወረርሽኝ ነው። በመሆኑም ከግለሰብ ጀምሮ እስከ መንግሥት ጣሪያ ድረስ የመነጋገሪያ ርእሰ-ጉዳይና ለመፍትሄ ፍለጋውም እያመራመረ የሚገኘው። በቤት፣ ሱቅና መደብሮች ኪራይ ቅነሳ (እስከ ወራት ክፍያ መሰረዝ ድረስ የዘለቀ)፣ የግብርና መሰል ክፍያዎችን መቀነስና የእፎይታ ጊዜን መስጠት፣ ለተጎዱ ተቋማት ድጎማ፣ ድጋፍ፣ ብድር… መፍቀድ፤ ክፍያን ማራዘም ድረስ እርምጃዎች እየተወሰዱ ሲሆን ኢኮኖሚውንና አንቀሳቃሾቹን ከድቀት የመታደግ ሰናይ ተግባር እየተሰራ የሚገኘው። ይሁን እንጂ አልፎ አልፎ ችግሮች የሉም፤ ክፍተቶች በሙሉ ተደፍነዋል ማለት አይደለም። የንግዱ ዘርፍ ከሚንቀሳቀስባቸው ቢዝነሶችና ማከናወኛ ስፍራዎቹ በአብዛኛው የግለሰቦች ህንፃዎች ሲሆኑ እነዚህም በተለይ ኮሮናን በመሳሰሉ ጊዜያት ክፍያቸው ወገብ ያንቀጠቅጣል። በመሆኑም ይመስላል ብዙዎቹ ባለሀብቶች በተለያየ መልኩ ለብዙዎች ምህረት ያደረጉት። ይህንኑ ጉዳይ አስመልክተን በከተማው ተዘዋውረን የተለያዩ አስተያየቶችን ለማሰባሰብ የሞከርን ሲሆን ለየት ብሎ ያገኘነው ወደ አራት ኪሎ አካባቢ ነው። በአራት ኪሎ የሁለት ወር ኪራይን የማሩ የመኖራቸውን ያህል ምንም ያላሉም አሉ። ምንም እንኳን ጉዳዩ የግል ጉዳይ ቢሆንም የጋራ የሚያደርገው ቀደም ሲል እንደጠቀስነው ጉዳዩ ዓለም አቀፍና በማናችንም ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ነው። በድንቅ ሥራ ሀ/የተ/የግ/ማህበር ስር በሚገኘው ድንቅ ስራ ህንፃ ውስጥ የተከራዩ ነጋዴዎችን አግኝተን እንዳነጋገርነው ከሆነ እስካሁን ከሚመለከታቸው አከራዮች ምንም አይነት ሀሳብ የመጣም ሆነ ምን ማድረግ እንዳለባቸው የጠቆመ አካል የለም። በመሆኑም ከበሽታው ስጋት፣ ከገበያው ድቀት በተጨማሪ የኪራይ መክፈሉ ጉዳይ እያስጨነቃቸው መሆኑን ይናገራሉ። በህንፃው ውስጥ የአንደኛው ሱቅ ሥራ አስኪያጅና ስማቸው እንዳይጠቀስ የሚፈለጉት በወር 30 ሺህ ብር ኪራይ የሚጠበቅባቸው ተከራይ እንደሚሉት ከሆነ እስካሁን አንድም ነገር ያናገራቸውም ሆነ ትከፍላላችሁ/አትከፍሉም ያላቸው አካል የለም። ከቃል አልፈው በፅሁፍ ቢያመለክቱም ማንም ትንፍሽ የሚል አልተገኘም። “ከሁሉም እኛን የሚያሳስበን እንዴት አንድ ነገር አይሉንም የሚለው ነው። ምናለበት ቢያወያዩን። ምንም ሳይከፍል ሶስት ወር የሞላው አለ። ሁለት ወር የሆነው አለ። በኋላ አምጣ ቢሉት ከየት ሊያመጣ ነው?” የሚሉት አስተያየት ሰጪው ባለሀብቶቹ ቢያወያዩአቸውና አንድ ነገር ላይ ቢደርሱ ከብዙ ሀሳብ እንደሚገላገሉ ይናገራሉ። “ብንነጋገር እኮ ጥሩ ነው። ወይ በእረጅም ጊዜ ክፍያም ከተስማማን፤ ወይ እንደ ጎረቤት ህንፃ ባለቤቶች ምህረት የሚያደርጉልንም ከሆነ… ብንነጋገር ጥሩ ነው። አሁን ብዙ ሰው እኮ ሀሳብ ገብቶታል። ተጨንቋል።” ሲሉም የህንፃውን አስተዳዳሪዎችና ባለሀብቶች ያሳስባሉ። ሌላው በማርኮ ሚላኖ ሱቅ ውስጥ አግኝተን ያነጋገርናቸው የሱፍ አልባሳትና መጫሚያ ነጋዴ አቶ ኡሽራ ሰይድ ሲሆኑ እንደሚሉት ከሆነ የኮሮና መከሰት እጅግ እጅግ አንገድግዷቸዋል፤ እንደዚህ ዘመንም ተፈትነው አያውቁም። ሰርግ፣ ምርቃት፣ ስብሰባና የመሳሰሉት ባለመኖራቸው ሥራቸው በር መክፈትና በር መዝጋት ብቻ ሆኗል። በአሁኑ ሰዓትም እንኳን ለኪራይ የሚሆን ለግል ወጪ እንኳን እየተንገዳገዱ ነው። እንዲቀንሱላቸውም ተፈራርመው ቢያስገቡም እስካሁን ምንም ምላሽ አላገኙም። ይህ ደግሞ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሮባቸዋል። “ባለሀብቶቹ አንድ ነገር ቢሉን ጥሩ ነው። እነሱም እኛም ሳንጎዳ ቤተሰባዊ ትብብራቸውን እንጠይቃለን” በማለትም ይጠይቃሉ። ምናልባትም ጥሩ አስበውልንም ሊሆን ይችላል አናውቅም ሲልም መልካም ሀሳቡን አካፍሎናል። የአዲስ አበባ መስተዳድርም ያስበናል ብለው እንደሚያስብም ነግሮናል። ሌሎች ከቡና ማፍላት ጀምሮ ያሉትንም አነጋግረን ያገኘነው ተመሳሳይ አስተያየቶችን ሲሆን ሁሉም ከሥራው ውጪ ከመሆናቸው በፊት ባለሀብቶቹ አንድ ነገር ቢሏቸው እንደሚወዱ ነግረውናል። ጉዳዩን በተመለከተ ከሚመለከታቸው ጋር ለመነጋገር ያደረግነው ጥረት አድካሚ ቢሆንም የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑትን አቶ ሙሉጌታ ነጋሽን አግኝተን ያነጋገርናቸው ሲሆን በሥራ ምክንያት ሊሰባሰቡ ባለመቻላቸው ምክንያት ሊወስኑ እንዳልቻሉና ተከራዮች ምንም ሊያሳስባቸው እንደማይገባ ነግረውናል።አዲስ ዘመን ግንቦት 28/2012 ግርማ መንግሥቴ ", "passage_id": "724d7f9d60f09d102f2891f01f81d341" } ]
0488a2fb62ce04e9736c05051373b177
d9a6c910e351136919c0b9932f8b36b6
የአፍሪካ አትሌቲክስ ቻምፒዮና ከኦሊምፒክ ቀድሞ ይካሄዳል
የአፍሪካ አትሌቲክስ ቻምፒዮና ከኦሊምፒክ ቀድሞ ይካሄዳል የኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ 19) በዓለም ላይ በከፍተኛ ፍጥነት መሰራጨቱን ተከትሎ የሁሉም ዓለም አቀፍ የስፖርት መርሃግብሮች ዝብርቅርቅ መውጣቱ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በርካታ ታላላቅ የስፖርት መርሃግብሮችን ዳግም መከለስ አስፈላጊ ሆኗል፡፡ በዚህም መሰረት ክለሳ የተደረገባቸው የተለያዩ መርሃግብሮች ውዝግብ ሲያስነሱ ማየት እየተለመደ መጥቷል፡፡ ከተያዘለት መርሃግብር እንዲራዘም የተደረገው የአፍሪካ አትሌቲክስ ቻምፒዮና በ2021 እንዲካሄድ ከተራዘመው የቶኪዮ ኦሊምፒክ አስቀድሞ እንዲካሄድ የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን ውሳኔ ላይ መድረሱን ከሁለት ቀናት በፊት አሳውቋል፡፡ የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሐማድ ካልካባ በአልጄሪያ የሚካሄደው የአፍሪካ አትሌቲክስ ቻምፒዮና ከቶኪዮ ኦሊምፒክ ከአንድ ወር ቀደም ብሎ እንደሚካሄድ ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡ የዓለም አትሌቲክስ ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት ካልካባ የውድድሩ አዘጋጅ አገርም አዲሱን መርሃግብር የመቀበል ግዴታ እንዳለባት ገልፀዋል፡፡ ካልካባ ቻምፒዮናው ከተራዘመው ኦሊምፒክ በፊት መካሄዱ ለአትሌቶች ጥቅም እንደሚኖረው የገለፁ ሲሆን ውድድሩ በተከለሰው የኦሊምፒክ ማጣሪያ መርሃግብር ውስጥ እንደሚካተት ጠቁመዋል፡፡ ‹‹ውድድሩ የኦሊምፒክ ማጣሪያ(ሚኒማ) ለሚፈልጉ አትሌቶች ጠቃሚ ይሆናል›› ያሉት ካልካባ የዓለም አትሌቲክስ የኦሊምፒክ ማጣሪያ መርሃግብር እስከ ቀጣዩ ዓመት ሰኔ ወር እንዲራዘም ግፊት ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡ በኮሮና ቫይረስ ስጋት የተነሳ የአትሌቲክስ ስፖርት የኦሊምፒክ ማጣሪያ ውድድሮች እስከ መጪው ታህሳስ ወር ድረስ እንዳይካሄዱ የዓለም አትሌቲክስ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ እስከ ተጠቀሰው ጊዜ የሚካሄዱ ማንኛቸውም ውድድሮችና ውጤቶች የኦሊምፒክ ማጣሪያም ይሁን እውቅና እንደማያገኙ ማስጠንቀቁ ይታወሳል፡፡ ይህ የዓለም አትሌቲክስ ውሳኔ በበርካታ ታላላቅ የዓለማችን አትሌቶች የሰላ ትችት ሲሰነዘርበት እንደሰነበተ ይታወቃል፡፡ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት የስፖርቱ ዓለም ካለፉት ሁለት ወራት በላይ እንቅስቃሴው ተገድቦ ቢቆይም ከቅርብ ቀናት ወዲህ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው ለመመለስ ሲፍጨረጨሩ እየተስተዋለ ነው፡፡ ታላላቆቹን አውሮፓ እግር ኳስ ሊጎች ጨምሮ አንዳንድ አገራትም ስፖርታዊ ውድድሮቻቸውን ለማስጀመር ከቫይረሱ ስጋት ነፃ ሳይሆኑ ጥረት እያደረጉ ሲሆን አብዛኞቹ ውድድሮችን በዝግ ስቴድየሞች በማድረግ የውድድር ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት መርሃግብሮቻቸውን ስለመፈፀም እየተጨነቁ ይገኛሉ፡፡ በርካቶቹ የዓለም አቀፍ ውድድሮች ግን ቀደም ሲል ቫይረሱ በቀጣዩ ዓመት ይጠፋል ወይም በቁጥጥር ስር ይውላል በሚል ተስፋ ወደ ቀጣይ ዓመት እንዲዞሩ መወሰናቸው ይታወሳል፡፡ ከነዚህ መካከል በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዘግይቶም ቢሆን በቫይረሱ ስርጭት ስጋት የተነሳ ታላቁን የስፖርት መድረክ ለአስራ ስድስት ወራት እንዲራዘም ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ይህም እንደሌሎቹ ውድድሮች ሁሉ ቫይረሱ በቀጣዩ ዓመት በቁጥጥር ስር ይውላል ከሚል ተስፋ እንጂ በተጨባጭ መረጃና ማስረጃ አልነበረም፡፡ በርካቶቹ ይህን ተስፋ የሙጥኝ ብለው እያንዳንዱ ቀን እንደ ዓመት እየረዘመባቸውም ቢሆን ቀጣዩን ዓመት በጉጉት እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡ የቫይረሱ ስርጭት ግን በተቃራኒው እየቀነሰ ከመሄድ ይልቅ በአስደንጋጭ ፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛል፡፡ ይህንን ያስተዋሉ የጤና ባለሙያዎችም ለአስራ ስድስት ወራት የተራዘመው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በቀጣዩ ዓመት ላይካሄድ እንደሚችል ከወዲሁ እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ የኦሊምፒኩ አዘጋጅ የሆነችው ጃፓን የተላላፊ በሽታዎች ፕሮፌሰር የሆኑት ኬንታሮ ዋታ የቫይረሱ ስርጭት ኦሊምፒኩ በተራዘመበት ወቅት በቁጥጥር ስር ስለመዋሉ አጠራጣሪ በመሆኑ ውድድሩ ላይካሄድ እንደሚችል ስጋታቸውን ለመገናኛ ብዙሃን መግለፃቸው ይታወሳል፡፡ በዓለም ላይ አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ከተስፋ በስተቀር የቫይረሱ ስርጭት በጊዜ የሚገታ ወይም ፈውስና ክትባት በዚህ ጊዜ እውን ይሆናል የሚያስብል እንዳልሆነ መታዘብ ይቻላል፡፡ ይህንን ከግምት ያስገቡት የቶኪዮ ኦሊምፒክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቶሺሮ ሙቶ ኦሊምፒኩ የቫይረሱን ስጋት ለማምለጥ በአስራ ስድስት ወራት ቢራዘምም ከቫይረሱ ተፅዕኖ ሊያመልጥ እንደማይችል ሰሞኑን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማመልከታቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ማስነበቡ ይታወሳል፡፡ የአፍሪካ አትሌቲክስ ቻምፒዮናም ከዚህ የተለየ እድል እንደማይገጥመው ማንም እርግጠኛ አይደለም፡፡አዲስ ዘመን ግንቦት 8/2012ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=32480
[ { "passage": "በኢትዮጵያ አትሌቲክስ አንጋፋውና ያለምንም መቆራረጥ በየዓመቱ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ማክሰኞ ይጀምራል። ዘንድሮ ለ48ኛ\nጊዜ የሚካሄደው ይህ ውድድር ሁሉንም የአትሌቲክስ እና የሜዳ ላይ ተግባራትን አካቶ የሚከናወን ሲሆን፤ ለዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሚኒማ ማሟላት የሚችሉ አትሌቶችም የሚታጩበት መድረክ ነው። ባለፉት ዓመታት ከዚህ ውድድር በርካታ ብርቅዬ አትሌቶች የፈሩ ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን መቀዛዝ እየተስተዋለበት ይገኛል። በተለይ በውጪ ሃገራት ውድድሮች ላይ ተሳታፊ የሆኑ ታዋቂ አትሌቶች በሃገር ውስጥ ውድድሮች አለመታየታቸው በብዙዎች ዘንድ ወቀሳ እንዲሰነዘርበት ያደርጋል። በመሆኑም በዚህ ዓመት በርካታ ታዋቂ አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን፤ አማን ወጤ፣ ጫላ በዮ፣ ዲኖ ስፍር፣ አንዷምላክ በልሁ፣ አባዲ ሃዲስ፣ የኔው አላምረው፣ ሰለሞን ባረጋ፣ አዲር ጉር፣ … በወንዶች በኩል ተሳታፊ የሚሆኑ አትሌቶች ናቸው። በሴቶች በኩልም፤ ደራ ዲዳ፣ ነጻነት ጉደታ፣ በላይነሽ ጉደታ፣ ሱሌ ኡቱራ፣ ብርትኳን ፈንቴ፣ ህይወት አያሌው፣ ፎቴን ተስፋይ፣ ሰንበሬ ተፈሪ፣ አራያት ዲቦ፣… ከተካፋዮቹ ጥቂቶቹ ናቸው። የዚህ ውድድር ዓላማ፤ ለአትሌቶች የሃገር ውስጥ የውድድር ዕድሎችን ከመፍጠርም ባሻገር በክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮችና ክለቦች መካከል ፉክክር ለመፍጠር እንዲሁም ለብሄራዊ ቡድን የሚሆኑ አትሌቶችን ለመምረጥ ነው። ውድድሩን ለማካሄድ ዝግጅቱ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ 2ነጥብ1 ሚሊዮን\nብር በላይ በጀት ተመድቦለታል። ለውድድር የሚሆኑት ቁሳቁሶችና ግብዓቶች ከመሟላታቸውም በላይ ውድድሩን የሚመሩ አደረጃጀቶች መፈጠራቸውንም በፌዴሬሽኑ ጋዜጣዊ መግለጫ በተሰጠበት ወቅት ተጠቅሷል። ማክሰኞ በሚጀመረው ሻምፒዮና ላይም ከዘጠኝ ክልሎችና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች  እንዲሁም ከ36 ክለቦች\nየተወጣጡ አንድ ሺ376 አትሌቶች ተሳታፊ ይሆኑበታል። ይህም ካለፈው ዓመት ሻምፒዮና ጋር ሲነጻጸር በ122 አትሌቶች ብልጫ የታየበት ነው። ውድድሩ የሚመራውም፤ በ80የአትሌቲክስ ዳኞች፣ 45 የፌዴሬሽኑ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ 3 የህክምና ባለሙያዎችና አንድ አምቡላንስ፣ 32 በጎ ፍቃድ አገልጋዮች እንዲሁም ሌሎች ስራዎችን የሚያከናውኑ ሙያተኞች እንደሆነም ታውቋል። የመክፈቻ መርሃ ግብሩ በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ሽፋን የሚሰጠው ሲሆን፤ የማጣሪያ እና የፍጻሜ ውድድሮችም ይካሄዳሉ። ጠዋት ከሚካሄዱ ውድድሮች መካከል የሴቶች አሎሎ ውርወራ እና የወንዶች ሱሉስ ዝላይ ፍጻሜያቸውን ያገኛሉ። በ800፣\n400እና 100 ሜትር የወንድ እና ሴት የማጣሪያ ውድድሮችም ይካሄዳሉ። በኦሊምፒክ ባህል መሰረት የውድድሩ የመክፈቻ ዝግጅት አመሻሹ ላይ የሚካሄድ ሲሆን፤ ውድድሮችም ይኖራሉ። በዚህም መሰረት የሴትና ወንድ የ10ሺ ሜትር የፍጻሜ እንዲሁም የ100ሜትር\nእና 400 ሜትር የግማሽ ፍጻሜ ውድድሮች በሁለቱም ጾታ ይከናወናሉ። በ42ቱ ውድድሮች አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶችም የ2ሺ፣ 1ሺ400 እና 1ሺ\nብር ሽልማት እንደየደረጃቸው የሚያስገኝ ይሆናል። ክብረወሰን ለሚያሻሽሉ እና ከሶስት ወርቅ በላይ ለሚያስመዘግቡ አትሌቶችም 6ሺ ብር ተጨማሪ ሽልማት የሚያገኙ ሲሆን፤ ሁለት ወርቅ ለሚያጠልቁ አትሌቶች ደግሞ 5ሺ\nብር ይሰጣቸዋል። በአጠቃላይ አሸናፊ ለሚሆኑት አተሌቶችም 20ሺ፣ 16ሺ\nእንዲሁም 10ሺ ብር ይበረከትላቸዋል። ውድድሩ እስከ መጪው ግንቦት 04 ቀን\n/2011ዓም ለስድስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፤ የአትሌቲክስ ስፖርት ወዳዱ ህብረተሰብ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝቶ ስፖርቱን እንዲደግፍም በፌዴሬሽኑ ጥሪ ቀርቧል።አዲስ\nዘመን ሚያዚያ 27 ቀን 2011 ዓ.ምብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "c62f6ebc98c2034cb7a51852ca61282a" }, { "passage": " ኢትዮጵያ ለኦሊምፒክ ድል አዲስ ባትሆንም ውጤቷ በአትሌቲክስ ብቻ የተገደበ ስለመሆኑ እርግጥ ነው።ተሳትፎዋም ቢሆን ከቦክስ፣ ብስክሌትና ውሃ ዋና ስፖርቶች ያልዘለለ ነው።ጃፓን በመዲናዋ ቶኪዮ ከአራት ወራት በኋላ በምታስተናግደው የ2020 ኦሊምፒክ ግን ኢትዮጵያ በታሪኳ አዲስ በሆነ ስፖርት ተሳታፊ መሆኗ ታውቋል።ይህ ብስራት የተሰማው ከኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ስፖርት ሲሆን፤ ወጣቱ አትሌት ሰለሞን ቱፋ የታሪኩ ባለቤት መሆኑን አረጋግጧል።ሰለሞን ለዚህ ስኬት እንዲበቃ ከስድስት ዓመታት በላይ በአሰልጣኝነት አብሮት የደከመው ማስተር አዲስ ኡርጌሳም ከዚህ ታሪክ ባለቤትነት ጋር አብሮ ይነሳል።በአፍሪካ ካሉ ስመ ጥር የወርልድ ቴኳንዶ አሰልጣኞች ትልቁ ነው።በዓለም አቀፉ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ደግሞ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ የአሰልጣኞች እና የዳኞች አሰልጣኝ ነው። የአፍሪካ ወርልድ ቴኳንዶ አሰልጣኞች ሊቀመንበር በመሆንም እያገለገለ ነው።ማስተር አዲስ ዑርጌሳ።በ2010/11 የውድድር ዓመት በተሳተፈባቸው ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ውድድሮች ላይ ባልተመቻቸ ሁኔታ በጥቂት ስፖርተኞች ተሳትፎ 5 ወርቅ 2 ብር እና 3 የነሀስ ሜዳሊያዎች በሚያሰለጥናቸው ስፖርተኞች አማካኝነት ለኢትዮጵያ አስገኝቷል።ባለፈው ሪዮ ኦሊምፒክ የማጣሪያ ውድድሮች በሁለቱም ፆታ ያሰለጠናቸው ተወዳዳሪዎች ወደ ታላቁ መድረክ ለማለፍ ከጫፍ ደርሰው ሳይሳካላቸው ቀርቷል።ከሃያ ዓመታት በላይ በስፖርቱ ውስጥ ያሳለፈው ማስተር አዲስ ዛሬ ላይ ህልሙ እውን ሆኖ ታላቁ የስፖርት መድረክ ላይ ደርሷል።በአገራችን ወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ተስፋና ስጋት እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጉዳዮችን ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ እንደሚከተለው ይናገራል። አዲስ ዘመን፡- በዓለም ላይ ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ተከትሎ ኦሊምፒክ ሊራዘም እንደሚችል ስጋት አለ፣ ምናልባት የሚራዘመው ለረጅም ጊዜ ከሆነ እንደ ወርልድ ቴኳንዶ አይነት ብዙ ልፋትና ዋጋ የሚከፈልባቸው የማጣሪያ ውድድሮች ዳግም ወደ ማጣሪያ የሚገቡበት አጋጣሚ ይኖራል? \nማስተር አዲስ፡- አይመስለኝም፤ እስካሁንም እንዲህ የሚል ህግ አላየሁም።ምናልባት ከአንድ ዓመት በላይ የሚራዘም ከሆነ ሊባል ይችል ይሆናል።ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ እስከ መጨረሻው ነገሮችን ሳይመለከቱ ወደዚህ ውሳኔ ይገባሉ የሚል እምነት የለኝም፤ ቢያራዝሙ እንኳን ጥቂት ወራትን ሊሆን ይችላል የሚል ግምት ነው ያለኝ።\nአዲስ ዘመን፡- የኦሊምፒክ ማጣሪያውን አልፋችሁ ትልቅ ደረጃ ላይ ስትደርሱ የነበረው ሂደት እንዴት ነበር? \nማስተር አዲስ፡- ማጣሪያው ወደ 34 የአፍሪካ አገራት የተሳተፉበት ትልቅ ውድድር ነበር።ለአራት ዓመታት ያደረግነውን ዝግጅትም ከ100 በላይ ከሚደርሱ ስፖርተኞች ጋር ተወዳድረን ነው የመዘንነው።እንደሚታወቀው ሰለሞን ሶስቱን ዓመት እስከ አውሮፓ በመጓዝ በተለያዩ ውድድሮች ላይ ነው ያሳለፈው።በቱርክና በፖላንድ ከተሳተፈባቸው ውድድሮች ባሻገር የአፍሪካ ዋንጫንና ፕሬዚዴንሺያል ዋንጫን ጠቅልሎ በመውሰድ በአፍሪካም ኮከብ በመባል ነበር ያጠናቀቀው።ይህም ወደ ማጣሪያው ሲገባ ትልቅ ደረጃን ይዞ በመሆኑ ውጤቱም መልካም ሆኗል፡፡አዲስ ዘመን፡- ቀደም ባሉት ዓመታት በወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ውጤት ይመጣበታል የሚል ብዙም እምነት አልነበረም፣ ይህን አስተሳሰብ ሰብሮ ፈታኝ የሆኑ ማጣሪያዎችን በማለፍ ለኦሊምፒክ ስፖርተኛን ማብቃት ከባድ መሆኑን መገንዘብ አይከብድም፣ ነገር ግን ይህ ስኬት ትልቅ ቦታ ተሰጥቶታል ብለህ ታምናለህ?\nማስተር አዲስ፡- በማጣሪያው ላይ ከሰለሞን ጋር ውድድር ያደረገው ስፖርተኛ በዓመት ውስጥ ከ13 ያላነሱ ውድድሮችን አድርጓል፤ በዓለምና በአፍሪካ ያለው ደረጃም በጣም ጥሩ ነው።ሰለሞን በአንጻሩ ከአራት ያልበለጡ ውድድሮች ላይ ብቻ ተሳታፊ ሆኖ ነው ለአሸናፊነት የበቃው።ይህንን ድል መድገም አይቻልም ነገር ግን የተሰጠው ክብር ብዙም አይደለም።\nአዲስ ዘመን፡- ከዚህ ቀደም በምትሳተፉባቸው ውድድሮች ብዙም ድጋፍ እንደማይደረግላችሁ ይታወቃል።በዚህ ማጣሪያስ ድጋፉ እንዴት ነበር?\nማስተር አዲስ፡- ድሮ ከነበረው በጣም የተሻለ ነበር፤ በተለይ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጥሩ ድጋፍ አድርጎልናል።ፌዴሬሽኑም ያለውን አቅም ተጠቅሟል፤ ከዚህ ቀደም ውድድሮች ሲኖሩብን ለአጭር ጊዜ ነበር ቡድናችንን የምናዘጋጀው አሁን ግን ለረጅም ጊዜ በዝግጅት ላይ እንድንቆይ መደረጉ መልካም ነው።በአንጻራዊነት እንደ አጠቃላይ ያለው ነገር የተሻለ ነው ለማለት ያስችላል።አዲስ ዘመን፡- ማለፋችሁን ተከትሎስ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምን አደረገላችሁ?\nማስተር አዲስ፡- እስካሁን ምንም የተደረገልን ነገር የለም፡፡\nአዲስ ዘመን፡- ከሰለሞን ባሻገር በአፍሪካ ደረጃ ውጤት ያስመዘገቡ ስፖርተኞች ተስፋ ቢጣልባቸውም አሁን ላይ አናያቸውም ምክኒያቱ ምንድነው?\nማስተር አዲስ፡- በእኛ ስፖርት ችግሩ የክለቦች አለመኖር ነው፤ ስለዚህም ወጣቶቹ ስራ ሳይሰሩና ትምህርት ሳይማሩ ስፖርቱ ላይ ብቻ ተሳታፊ እየሆኑ መቆየት አስቸጋሪ ነው።ብዙዎቹ ሰልጣኞች ሌላ ገቢ ስለሌላቸው ከብሄራዊ ቡድን በኋላ ወደ ሌላ ነገር ይሰማራሉ፣ አሊያም ስፖርቱን ይተውታል።ስለዚህም ፌዴሬሽኑ አሁን የመጣው ውጤት ላይ ተመርኩዞ በርካታ ስራዎችን ማከናወንና የማስተዋወቅ ስራ ይጠበቅበታል።በመገናኛ ብዙሃን በኩልም አበረታች የሆኑ ስራዎች በይበልጥ መሰራት ተገቢ ነው።አዲስ ዘመን፡- በኢትዮጵያ እጅግ ተዘውታሪ ከሆኑ ስፖርቶች መካከል የማርሻል አርት ስፖርቶች ተጠቃሽ ናቸው።ነገር ግን በሺዎች ከሚቆጠሩ ተሳታፊዎች ከዓመታት በኋላ ነው አንድ ስፖርተኛ ያገኘነው፤ ምክንያቱ ምንድን ነው?\nማስተር አዲስ፡- ከሩቅ ሆኖ ሲታይ ነገሮች ተመቻችተው ይመስላል፤ ነገር ግን እንደ ሌሎች አገሮች ስፖርቱ ኢንቨስት እየተደረገበት አይደለም።ሌሎች አገራት ዝግጅት የሚያደርጉት ለዓመታት ነው፤ በተለያዩ ውድድሮች ላይም ተሳታፊ በመሆን አቅማቸውን ይፈትሻሉ።እኛጋ ግን በዚያ ደረጃ እየሄደ አይደለም፤ ከስር በርካታ ማሰልጠኛ ማዕከላት ይኑሩ እንጂ ከዚያ የሚወጡትን ሰልጣኞች የሚያቅፍ ክለብ የለም።ለአብነት ያህል ከሰለሞን ጋር ዝግጅት የሚያደርግና በእርሱ ደረጃ የሚገኝ ስፖርተኛ ማግኘት ከባድ ነው።ወደ ሌሎች ክለቦች ሄደንም የወዳጅነት ልምምድ ለማድረግም ለእኛ ከባድ ነው።አዲስ ዘመን፡- በቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ የተለየ እቅድ አላችሁ?\nማስተር አዲስ፡- ከ20 ዓመት በፊት በተካሄደው የሲድኒ ኦሊምፒክ ላይ የመገኘት እድል ገጥሞኝ ነበር፤ ወቅቱ ቴኳንዶ የኦሊምፒክ ስፖርት የሆነበት ስለነበር ተጋባዥ በመሆን ነው የታደምኩት።የዚያኔ ለራሴ በኦሊምፒክ ተሳታፊ እንደምሆን ነግሬው ከዓመታት በኋላ ስኬታማ ሆኛለሁ።አራት ኦሊምፒኮችን ከሞከርኩ በኋላም በአምስተኛው እድል ቀንቶኛል።ወደ ቶኪዮ የምንሄደው ደግሞ ለተሳትፎ ሳይሆን ለማሸነፍ ነው።አዲስ ዘመን፡- የአገራችን በርካታ ፌዴሬሽኖች እንኳን ለ20 ዓመታት የአንድ ዓመት እቅድም ሲያወጡና ሲፈፅሙ አይታዩም፣ አንተ በግልህ ይህን አሳክተሃልና ከዚህ ምን መማር ይቻላል?\nማስተር አዲስ፡- እኔ በተለያዩ አገራት ተዘዋውሬ እንደተመለከትኩት ከሆነ ለአንድ ስፖርት መሰረትም አስፈላጊውም አሰልጣኝ ነው።አሰልጣኞችን ለማብቃት ደግሞ ፌዴሬሽኖች መስራት ይገባቸዋል፤ ምክንያቱም አሰልጣኝ ሁሌም በልጦ መገኘት አለበት።መንግስትም የፌዴሬሽኖች በጀት ላይ ድጎማ ማድረጉ ተገቢ ነው፤ የሚሰሩትንም ማበረታታት ያስፈልጋል።ሌላው ነገር በአህጉር አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ መሆን ነው፤ ከዚያ በኋላ በደረጃ ወደ ዓለም ማውጣት ይቻላል።አዲስ ዘመን፡- እንዲህ አይነት ስኬቶች ሲመዘገቡ ከእውቅናና ማበረታቻ ጋር በተያያዘ ምን መደረግ ይኖርበታል ትላለህ?\nማስተር አዲስ፡- ሁሌም ስለ አንድ ነገር መወራት ያለበት ውጤት ሲመጣ ብቻ መሆን የለበትም።ውጤት ባይመጣም ስፖርተኞች መበረታታት አለባቸው፤ ምክንያቱም በውድድር ዕለት በጥቂት አጋጣሚ ከውጤት ውጪ መሆን ይከተላል።በመሆኑም ውጣ ውረዱና ልፋቱ ሊታይ እንዲሁም ላሉበት ደረጃ በመብቃታቸው ሊበረታቱ ይገባል።ይህ ሲሆን ደግሞ ለቀጣይ መነሳትን ይፈጥራል። \nአዲስ ዘመን፡- ማስተር አዲስ ለሰጠኽን ጊዜ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡\nማስተር አዲስ፡- እኔም አመሰግናለሁ፡፡\nአዲስ ዘመን መጋቢት 14 /2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "e39364e17ec77a5d3d11f0901692fc9e" }, { "passage": "የዘንድሮውን ከ20 ዓመት በታች የዓለም ሻምፒዮና በኬንያ ናይሮቢ ከመካሄዱ በፊት ውድድሩ በሚካሄድበት አካባቢ ያለው የአየር ጥራት እንደሚለካ የዓለም አትሌቲክስ ተቋም አስታውቋል፡፡\nባለሙያዎቹ ፈረንሳይ ሞናኮ ከሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ ትናንት ኬንያ መግባታቸውን ያስታወቀው ተቋሙ “ኩናክ” የተሰኘ የአየር ጥራት መለኪያ መሳሪያ ሻምፒዮናው በሚካሄድበት የካሳራኒ ስታዲየም መተከሉንም ገልጿል፡፡\nመሳሪያው ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ ተተክሎ ነበር፡፡\nይህን ያስታወሰው ሲ.ጂ.ቲ.ኤን አፍሪካ የናይሮቢው የታዳጊዎቹ ሻምፒዮና የአየር ጥራት የሚለካበት የመጀመሪያው ዓለም ቀአፍ ውድድር መሆኑን ዘግቧል፡፡\nሻምፒዮናው በመጪው ሰኔ ወር መጨረሻ የሚካሄድ ነው፡፡\nኬንያ ከሶስት ዓመታት በፊት በዚሁ በካሳራኒ ስታዲየም ከ17 አመት በታች የዓለም ሻምፒዮናን ማስተናገዷ የሚታወስ ነው፡፡\n", "passage_id": "5812a107b5ae2f1f1f7b1c4b2bd0509d" }, { "passage": "የ2019 የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች በይፋ ሊጀመሩ ከሁለት ሳምንት ያነሰ ጊዜ ይቀራቸዋል። ፉክክሮቹ ከመጀመራቸው ቀደም ብሎ የተለያዩ መርሃግብሮች እየወጡ ሲሆን የውድድር ዓመቱ ሁለተኛዋ መዳረሻ ከተማ የሆነችው የቻይናዋ ሻንጋይ የምታስተናግደውን የውድድር አይነትና ብዛት አሳውቃለች። በዚህም መሰረት በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በመካከለኛና ረጅም ርቀት ውድድሮች እንደሚሳተፉ ታውቋል። ሻንጋይ በአጠቃላይ አስራ ስድስት ዓለም አቀፍ ፉክክሮችን ስታሰናዳ በዘጠኙ ፉክክሮች(100፣ 200፣ 400፣ 5000 ሜትሮች፣ 110 ሜትር የዱላ ቅብብል፣400 ሜትር የዱላ ቅብብል፣ከፍታ ዝላይ፣ርዝመት ዝላይና ጦር ውርወራ )ውድድሮች ወንዶች ተሳታፊ ይሆናሉ። ሴቶች በሰባት ውድድሮች ሲፎካከሩ (100፣400፣1500፣3ሺመሰናክል፣ምርኩዝ ዝላይ፣መዶሻ ውርወራና ጦር ውርወራ) ፉክክሩ የሚካሄድባቸው ይሆናሉ። በነዚህ ውድድሮች የ3ሺመሰናክል የዓለም ክብረወሰን ባለቤቷ ኬንያዊት ቢትሪስ ኪፕኮይች፣ የአውሮፓ 5ሺ ሜትር ቻምፒዮን ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድስ አትሌት ሲፈን ሃሰን፣ የአንድ ማይል የቤት ውስጥ የዓለም ክብረወሰን ባለቤቱ ዮሚፍ ቀጄልቻ ተሳታፊ እንደሚሆኑ አይ.ኤኤ.ኤፍ በድረ ገፁ አሳውቋል።እኤአ ከ2020 ጀምሮ ከዳይመንድ ሊግ ፉክክር የሚሰረዘው የ5ሺ ሜትር ውድድር ዘንድሮ ሻንጋይ ላይ በኢትዮጵያውያኑ የቤት ውስጥና ከቤት ውጪ ቻምፒዮኖች እንደሚደምቅ ይጠበቃል። ዮሚፍ ቀጄልቻ በዚህ ውድድር ትልቅ ትኩረት የተሰጠው አትሌት ሲሆን የ2018 የውድድር ዓመትን የአንድ ማይል የቤት ውስጥ የዓለም ክብረወሰን ከሃያ ሦስት ዓመታት በኋላ ማሻሻሉ አይዘነጋም። የውድድር ዓመቱን በ5ሺ ሜትር የዓለማችን ቁጥር ሁለት አትሌት በመሆን ያጠናቀቀው ዮሚፍ ስድስተኛ ሆኖ ካጠናቀቀው የአገሩ ልጅ ሙክታር ኢድሪስ ጋር በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ ብርቱ ፉክክር ያደርጋል። ሙክታር ካቻምና የለንደን የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ላይ የእንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህን የ5ሺ ሜትር የበላይነት አስቀርቶ ቻምፒዮን ከሆነ በኋላ በተለያዩ ውድድሮች ውጤታማ መሆን አልቻለም። ዘንድሮ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ኳታር ዶሃ ላይ የሚካሄድ በመሆኑ የተለያዩ የዓለማችን አትሌቶች በዚህ ታላቅ መድረክ አገራቸውን ለመወከል ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ዮሚፍና ሙክታርም በዓለም ቻምፒዮናው ኢትዮጵያን ለመወከል የሚያበቃቸውን ሰዓት ለማስመዝገብ ከወዲሁ ጠንካራ ፉክክር እንደሚያደርጉ መገመት ይቻላል። አሜሪካዊው የዓለም ቻምፒዮናና የኦሊምፒክ የሜዳሊያ ባለቤት ፖል ቼሊሞ የውድድር ዓመቱን አምስተኛ ደረጃ ይዞ የፈፀመ አትሌት ከመሆኑ አኳያ በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ ቀላል ግምት የሚሰጠው አትሌት አይሆንም። ከዚህ ባሻገር የ2012 የዓለም የቤት ውስጥ የ1500 ሜትር ቻምፒዮን ሞሮኳዊው አብደላቲ ኢጊደር በዚህ ውድድር ጠንካራ ተፎካካሪ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። እነዚህ አትሌቶች በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ እንደሚሳተፉ ይገለፅ እንጂ በቀጣይ ቀናት ሌሎች የርቀቱ ኮከብ አትሌቶችም እንደሚካተቱ ይጠበቃል። በሴቶች መካከል በሚካሄደው የ1500 ሜትር ውድድር ዓመቱን በ5ሺ ሜትር ቁጥር አንድ ሆና ያጠናቀቀችው ሲፈን ሃሰን ከፍተኛ የአሸናፊነት ግምት አግኝታለች። ሲፈን 2014 ላይ በዚሁ የሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ በርቀቱ የመጀመሪያ ውድድሯን ካደረገች ወዲህ ኮከብ ከሆኑ አትሌቶች ተርታ መሰለፍ ችላለች። በርቀቱ አራት የአውሮፓ ቻምፒዮናዎችን ጨምሮ የዓለም የቤት ውስጥ ቻምፒዮናን ከማሸነፏ ባሻገር ከቤት ውጪም በዓለም ቻምፒዮና ሁለት ጊዜ የነሐስ ሜዳሊያ ማጥለቅ ችላለች። በዚህ ውድድር የ2016 የዓለም የቤት ውስጥ ቻምፒዮና የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊዋ ኢትዮጵያዊት ጉዳፍ ፀጋየ ለአሸናፊነት ከታጩ አትሌቶች መካከል ተካታለች። የውድድር ዓመቱን በርቀቱ ሁለተኛ ሆና ያጠናቀቀችው ጉዳፍን ጨምሮ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ዳዊት ስዩም ለሲፈን ፈተና እንደሚሆኑባት ተገምቷል። ዳዊት ስዩም 2016 የዓለም የቤት ውስጥ ቻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ካጠለቀች ወዲህ በርቀቱ ጠንካራ ከሚባ አትሌቶች መካከል አንዷ ሆናለች። የአፍሪካ ቻምፒዮኗ ኬንያዊት ዊኒ ቺቤት ሌላኛዋ ጠንካራ ተፎካካሪ ትሆናለች። ሻንጋይ ላይ ትኩረት ከሳቡ ውድድሮች አንዱ የሆነው የሴቶች ሦስት ሺ ሜትር መሰናክል ይገኝበታል። በዚህ ውድድር ዓመቱን በርቀቱ ቁጥር አንድ ሆና የፈፀመችው ኬንያዊት ቺፕኮይች ያለፈውን ዓመት አስደናቂ ብቃት እንደምትደግም ይጠበቃል። ኮይች ባለፈው የውድድር ዓመት የ2015 የዓለም ቻምፒዮኗን ሄቪን ኪንግን በድንቅ ብቃት ማሸነፍ ችላለች። በዚህ ውድድር ባለፈው ዓመት ሁለተኛ፣አራተኛና አምስተኛ ሆነው ማጠናቀቅ የቻሉ ኬንያውያን የሚያደርጉት ፉክክርም ተጠባቂ ነው።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 24/2011", "passage_id": "bc582014cbc9dbd7ecde1c6cf581b987" }, { "passage": "ታዋቂና ስመ ጥር የአገራችን አትሌቶች የሚሳተፉበትና ለ36ኛ ጊዜ የሚካሄደው የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር ነገ ይካሄዳል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ይህንን ውድድር በተመለከተ ባለፈው ረቡዕ በጽህፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የጎረቤት አገራት አትሌቶች ተጋባዥ ሆነው እንደሚወዳደሩ አሳውቋል። ከስድስት ያላነሱ አጋር የመንግስት መስሪያ ቤት ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በርካታ ውጤታማ፣ ታዋቂና ስመ ጥር አትሌቶች፣ የአትሌት ማናጀሮችና ተወካዮቻቸው እንደሚገኙም ተገልጿል። ከውድድሩም ኢትዮጵያን የፊታችን መጋቢት ወር ዴንማርክ በሚካሄደው 43ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና የሚወክሉ አትሌቶች የሚመረጡ ሲሆን በወጣቶች ከ1ኛእስከ6ኛ የሚጨርሱ አትሌቶች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል። በአዋቂዎች ደግሞ ከ1እስከ5 ያሉት በቀጥታ ያልፉና 6ኛ ተመራጮች ደግሞ ባስመዘገቡት የተሻለ ሰዓት ተለይተው የሚካተቱ ይሆናል። የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር በ1976 ዓ. ም በአዲስ አበባ ጃን ሜዳ «የጃን ሜዳ አገር አቋራጭ ውድድር» በሚል ስያሜ የተጀመረ መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃ ያመለክታል። ውድደሩ ሲጀመር ዋነኛ አላማውን አድርጎ የተነሳው ለዓለም አገር አቋራጭ ውድድር ብቃት ያላቸውን አትሌቶች መምረጥ፣ ተተኪ አትሌቶችን ማፍራትና ለአትሌቶች አገር አቀፍ የውድድር እድል መፍጠር የሚል ነበር። የጃን ሜዳ አገር አቋራጭ ውድድር ቀደም ሲል በ9 ኪሎ ሜትር ወጣት ወንድና ሴቶች ላይ ብቻ ያተኩር የነበረ ሲሆን ቀስ በቀስ በ4፣ በ6፣ በ9 እና በ12 ኪሎ ሜትር ሲካሄድ ቆይቶ በአሁኑ ሰዓት በዓለም አቀፉ የአገር አቋራጭ ሩጫ ውድድር ስታንዳርድ መሰረት አዋቂ ወንድና ሴቶች፣ እንዲሁም ወጣት ወንድና ሴቶች በሚል የ12፣ የ8 እና የ6 ኪሎ ሜትር ውድድሮች በሚል በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ቀደም ባሉት ዓመታት ከ5 ያልበለጡ ክለቦች ብቻ ይሳተፉበት ነበር፤ በአሁኑ ወቅት ግን ከአርባ የማያንሱ ክለቦች የሚሳተፉበት ውድድር ሆኗል። የተወዳዳሪዎች ቁጥርም በየዓመቱ እየጨመረ መሄዱ ይነገርለታል። የጃንሜዳ አገር አቋራጭ ውድድርን ቀደም ባሉት ዓመታት በአሸናፊነት ካጠናቀቁ አትሌቶች መካከል ፤ ወዳጆ ቡልቲ፣ ደረጀ ነዲ፣ መሃመድ ከድር፣ አልማዝ ለማ፣ በላይነሽ በቀለና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ። ሶስት የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያዎችን ያጠለቀውና የዓለም የአምስትና የአስር ሺ ሜትር የክብረወሰን ባለቤቱ ቀነኒሳ በቀለም በመካከለኛው የውድድሩ ዘመን ካሸነፉ አትሌቶች አንዱ ነው። ከቀነኒሳ በቀለ ተጨማሪ ገብረእግዚአብሄር ገብረማርያም፣ የሲቪያ ዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና የ10 ሺ ሜትር አሸናፊዋ ጌጤ ዋሚ፣ አብዮት አባተ፣ ሃይሉ መኮንን እንዲሁም የሲዲኒ ኦሊምፒክ የአምስት ሺ ሜትር አሸናፊው ሚሊዮን ወልዴ ይገኙበታል። በቅርብ ጊዜያት የውድድሩን የአሸናፊነት ዘውድ መድፋት ከቻሉት አትሌቶች መካከል እጅጋየሁ ዲባባ፣ አየለ አብሽሮ፣ መሰለች መልካሙ፣ ገነት ያለው፣ ሙክታር እንድሪስ፣ ህይወት አያሌው፣ ሃጎስ ገብረህይወት እና ሌሎችም ስመጥርና ውጤታማ አትሌቶች ናቸው።አዲስ ዘመን የካቲት 2/2011ቦጋለ አበበ ", "passage_id": "07f5da9fabf651597be391a92bd0aa32" } ]
961296da632878431b7e9a26e599d3f5
2b496ca70b2dec0cc2b42aeb261c5e95
ግንቦት አምስት- የጥቁር ተጫዋቾች የነፃነት ቀን
ግንቦት አምስት ቀን ባለፈው ረቡዕ ነበር። ጥቁር ተጫዋቾች በዓለም ነፃ እንዲወጡ በኢትዮጵያ ውስጥ ታሪክ የተጠነሰሰበትና ታሪካዊው የእግር ኳስ ግጥሚያው የተደረገበት ቀን ነው። ሀሳቡን ያመነጩት፤ ተግባራዊ ያደረጉት ፤ከኢትዮጵያ አልፎ በአፍሪካ አቋርጦ በዓለም አደባባይ እንዲደርስ ጥረት ያደረጉት የጥንቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ማህበረሰቦች ናቸው። ይሄ ነገር ለረጅም ጊዜ ክለቡ አካባቢም አይነሳም ነበር። የኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ነጋሪና ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ(ሊብሮ) በአንድ ወቅት ‹‹ከመሳለሚያ እስከ ፍራንክፈርት- የ32 ዓመት ፈታኝ ጉዞ›› በሚል ካሰፈረው የጥቁር ተጫዋቾች የነፃነት መሰረት ድንጋይ የተጣለበትን የታሪክ አጋጣሚ የሚዳስስ የታሪክ ማስታወሻ የተወሰደውን ፅሁፍ በዛሬው የስፖርት ማህደር አምዳችን ቀንጭበን ለንባብ ለማብቃት ወደድን። ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያውን ጨዋታ ከነጮች ጋር ያደረገው(ከውጭ ሀገር ሰዎች ጋር እንደመጀመሪያ ኢንተርናሽናል ጨዋታ ከተቆጠረ) አራራት ከተባለ የአርመኖች ቡድን ጋር ነው። ጊዜውም በየካቲት 28 ቀን 1928 ዓ.ም ነበር።(በተመሰረተ በሁለት ወሩ)ለሁለተኛ ጊዜ ከነጮች ጋር የተደረገው ግጥሚያ ደግሞ በግንቦት 5 ቀን 1934 ዓ.ም ነው። ይሄ ጨዋታ ከግጥሚያዎች ሁሉ ትልቅ ትርጉም ያለውና በዓለም ያሉ ጥቁር ተጨዋቾችን ነፃ ለማውጣት መሰረት የተጣለበት ቀን ነው። ዛሬ ላይ በርካታ ጥቁር ተጫዋቾች በበርካታ ታላላቅ ክለቦች ተቆጥሮ የማያልቅ ገንዘብ እየተከፈላቸው ለመጫወታቸው መሰረት የሆነችው ይህች ቀን ነች። ጊዮርጊሶች ታሪካዊውን ጨዋታ የተጫወቱት ከጣሊያኑ ፎርቲቲዲዮ ጋር ነበር። ጨዋታውን ለማድረግ ድርድሩ አንድ ዓመት ያህል ፈጅቷል። ጦርነቱ ካለቀ ገና ጥቂት ወር ውስጥ ነው ድርድር የተጀመረው። በአንድ በኩል የሀገሬው ሰው ‹‹እንዴት ሲገድሉን ከነበሩት ጣሊያኖች ጋር እርቅ አድረጋችሁ ኳስ ትጫወታላችሁ?››በሚል ቅሬታና ተቃውሞ ሲደርስ ፤በጣሊያኖች በኩል በኳስ አሳበው አደጋ ቢያደርሱብንስ በሚል ላለመጫወት ብዙ መጓተት ታይቷል። የያኔው ኳስ ጨዋታ ለእርግጫ በጣም የቀረበ መሆኑ ለዚህ ጥርጣሬ መነሻ ነበር። ሁለቱ ቡድኖች ፋሽስቱ ያወጣውን ህግ አፍርሰው ‹‹ጥቁርና ነጭ አንድ ነው›› በሚል ተስማምተው ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ተፈራርመው ተጫወቱ። ይሄ ፊርማ መጨረሻ ላይ ፊፋ ውስጥ ኢትዮጵያ አቅርባው ሁሉም ተስማምቶ የፈረመበት የመጀመሪያው መሰረት ነው። ይሄ ፊርማ በእግር ኳስ ሜዳ ልዩነትን የሚያጠፋ ወንድማማችነትን የሚያሰፍን ነው። የዓለም እግር ኳስ ዛሬ ላይ ለደረሰበት ሁለንተናዊ እድገትም ትልቅ ድርሻ አለው። የዚህ ሀሳብ መነሻ ደግሞ የጊዮርጊስ መስራች የሆኑት አየለ አትናሽና ጆርጅ ዱካስ ናቸው። ሁለቱ በቆዳ ነጭና ጥቁር ናቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ ጣሊያን ህጉን ሲያወጣ መጀመሪያ እንዲለያዩ ማስጠንቀቂያ የሰጠው ለእነርሱ ነበር።ሁለቱ ጀምረው ሌሎች የጊዮርጊስ ሰዎች አቀጣጥለውና ህግ አውጥተው ህጉ በአፍሪካ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደንብ ሆኖ ሲወጣ በመጀመሪያ የተደሰቱትም ሁለቱ መስራቾች ነበሩ። ይህ ዓለም አቀፍ ደንብ ዛሬ ላይ ሆነን ስንመለከተው በቀላሉ እውን የሆነ ሊመስል ይችላል። ይሁን እንጂ ረጅም ጊዜ የፈጀ፣ ብዙ ውጣውረድና ትግል የተደረገበት ነው። በወቅቱ ፊፋ ውስጥ ያሉ እንግሊዞችና ደቡብ አፍሪካ ያሉ አመራሮች ይሄ ጉዳይ በካፍና በፊፋ ላይ እንዳይነሳ አቅምና ተሰሚነታቸውን ተጠቅመው በገንዘብም ጭምር ለመደለል ቢጥሩም ኢትዮጵያ በቀላሉ ጉዳዩን ችላ የምትል አልሆነችም። ጉዳዩን ሲያጣሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ነገሩን አጥብቀው የያዙት የጊዮርጊስ ማህበረሰብ እንደሆኑ ታወቀ። በዚህ የተነሳም ‹‹የጊዮርጊስ ሰዎች ናቸው ያስቸገሩት›› በሚል ጥርስ ተነክሶባቸው ነበር። በርግጥም በየስብሰባው ታላቁ ይድነቃቸው ተሰማ ጉዳዩን በጥብቅ ስለሚያነሱት ግምታቸው ትክክል ነበር። የደቡብ አፍሪካ ነጮች ኬንያ ባለው ‹‹ሚስር አሌክሳንደር›› በተባለ የናይሮቢ ከንቲባ በኩል ክለቡን ለማፍረስ ብዙ መጣራቸውም እዚህ ጋር ሳይነሳ አይታለፍም። ያም ሆኖ ኢትዮጵያኑ በመጨረሻም አሸንፈው ህጉ ጸድቋል። የዚህ ሀሳብ መነሻው ጊዮርጊስ ክለብ ይሁን እንጂ ነገሩ የሀገርን ስም ከፍ የሚያደርግ በዓለም ከክለቦች አንስቶ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተሳተፈበት ታሪካዊ ድል ነው። (ፊፋ ላይ ያቀረበው ፌዴሬሽኑ በመሆኑ)። ጊዮርጊሶች በሀገራቸው ተገልለው የተጫወቱት መሳለሚያ በሚገኘው ኳስ ሜዳ ነው። ለዓለም ጥቁሮች ነጻ መውጣት እና የደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ ከስፖርት እንዲገለል ህጉ የጸደቀው ፍራንክፈርት ላይ በተደረገው የፊፋ ስብሰባ ነው። ያቀረበችው ኢትዮጵያ ስትሆን ተከራካሪው ይድነቃቸው ተሰማ ነበሩ። ይድነቃቸው ከመሳለሚያ እስከ ፈራንክፈርት ባለው ጉዞ ተሳታፊ ናቸው። ለ32 ፈታኝ ዓመታት ትግል ከተደረገ በኋላ ህጉ ጸድቆ ጥቁር ተጫዋቾች ያለምንም ገደብ በየትኛውም የዓለም ክልል እንዲጫወቱ ሆኗል። አዲስ ዘመን ግንቦት 9/2012 ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=32528
[ { "passage": "እኔም አለኝ ቁስል፤ ያንተን የሚመስል የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ሕዝቦች እንኳን ለግንቦት ሃያ በዓል አደረሳችሁ! ግንቦት ሃያ ኢትዮጵያ በታሪኳ ያለፈችባቸውን ዐበይት የታሪክ ምዕራፎች ስናስብ ከምናስታውሳቸው ዕለታት ውስጥ አንዱ ነው። ይህ እለት የኢትዮጵያን ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መልክ አምድር የቀየረ ታሪካዊ ዕለትም ነው፡፤ ይህን በዓል ዛሬ ካለችውና ለወደፊቱም እንገነባታለን ብለን ከምናስባት ኢትዮጵያ አንጻር ማክበር የተሻለ ብቻም ሳይሆን ለሁላችንም የሚበጅ ነው። የወደፊቷን ኢትዮጵያ የተሻለች ለማድረግ አንድ መሠረታዊ ነገር ላይ ተማምነን መነሣት አለብን። በሀገራችን ‹እኔም አለኝ ቁስል፣ ያንተን የሚመስል› የሚል ትልቅ አባባል አለ። ይህ አባባል ለዛሬዋ ኢትዮጵያ የሚጠቅሙ ሁለት ሐሳቦችን አቅፎ ይዟል። የመጀመሪያው ሐሳብ ቁስል የመኖሩን እውነት መግለጹ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የእኛን ቁስል ብቻ ሳይሆን የሌላውንም ቁስል ማየት እንዳለብን ማስረገጡ ነው። በሀገራችን ታሪክ ተፈጥረው በነበሩ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ መዛነፎች ምክንያት የተለያዩ በደሎች በሕዝቦቻችን ላይ ደርሰዋል፡። እነዚህ በደሎችም በሕዝቦቻችን ውስጥ ጠባሳዎችን አሳርፈው፤ ቁስሎችን ትተው አልፈዋል። እነዚህ ቁስሎች በሚገባ ባለመ ታወቃቸው፣ ታውቀውም ባለመታከማቸው በየጊ ዜው እንደ አዲስ እያገረሹ ሀገራችንን ጤና እየነሷት ይገኛሉ። ግንቦት ሃያ እነዚህን ቁስሎች አውቀን የምናክምበት በዓል ሊሆን ይገባል። አንድን ቁስል ለማዳን መጀመሪያ ቁስሉንና የቁስሉን መነሻ በትክክል ማወቅ ይጠይቃልና። ቁስሉን የግድ መለየት እና ማወቅ አለብ የምንልበት ምክንያት ቁስሉን በየጊዜው እየነካካን እንዲያገረሽ ለማድረግ አይደለም ፥ቁስልን በየጊዜው መነካካት እና ማከክ እንዲድን አያደርገውም። አንዲያውም ተባብሶ ጋንግሪን ይሆንና ሌላውን የአካል ክፍል በእጅጉ ይጎዳዋል ቁስልን መነካካት ለሚነካካው ሰው አያመውም እንጂ፣ ለሚነካካበት ሰው ግን ከሕመም ውጭ የሚያተርፈው ነገር የለም። በርግጥ አንዳንድ ሰዎች ቁስልን እያሳዩ ገንዘብ ለማግኘት መለመኛ ማድረግ ይፈልጉ ይሆናል፤ አንዳንድ ቁስልም ለጊዜው ሲያኩት ደስ ይላል፡ ።ያም ቢሆን ግን ለሕመሙ ፈውስ ለቁስሉም መዳን የሚያበረክተው አስተዋጽዖ አይኖርም። ቁስሉን በሚገባ ማወት ያለብን ለሁለት ነገር ነው፡ መጀመሪያ ራሳችንን በቆሰለው ሰው ቦታ ላይ አድርገ የሰውዬው ቁስል እንዲሰማን ያስችለናል። የሰውዬው ቁስል ከተሰማን በሰውዬው ላይ አንፈርድም፣ አንቆጣም፤ በቁስሉ ምክንያት የሚሰሙትን ስሜቶችም በትክክል እንረዳቸዋለን፣ እንታመማቸዋለንም። ሁለተኛው ቁስሉን እናውቅ ዘንድ የሚያስገድደን ምክንያት ቁስሉን በሚገባ አክመን ለማዳን እንድንችል ነው። ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነውና። የማናውቀውን ቁስል ልናክመው አንችልም። ያልታወቀን ቁስል ማከም ሌላ ያልታወቀ በሽታ ማምጣት ነው። የቁስሉ ምንጭ ከታወቀ በኋላም “ ማወቱንስ ዐዉቄአለሁ እጄ አጠረንጂ” በማለት እጃችንን አጣጥፈን መቀመጥ ከንፈር መጠጣ እንጂ ሕክምና አይሆንም። ቁስሉ ይሸር ዘንድ ለመፍትሔውም በጋራ መሥራት አለብን: አዎ! በሀገራችን ተፈጥረው የነበሩትን ቁስሎች በጋራ ዕውቅና ሰጥተን እንደ ሕዝብ በጋራ ለማዳን መነሣት አለብን። ‹እኔም አለኝ ቁስል፤ ያንተን የሚመስል› የሚለው አባባል የሚነግረን ሁለተኛው ጉዳይ እንደ ሕዝብ በደል ያልደረሰበትና ያልቆሰለ ወገን አለመኖሩን ነው። አቁሳይ ገዥዎች እንጂ አቁሳይ ሕዝብ የለም። የሚቆስል ሕዝብ እንጂ የሚቆስል ገዥም የለም፡ ሁላችንም ተበድለናል፤ ሁላችንም ቆስለናል። የእኛ ቁስል የነዚያን የሚመስል ነው፤ የእነርሱም ቁስል የእኛን የሚመስል ነው። ስለዚህም እርስ በርሳችን ዳግም መቋሰል አያስፈልገንም ። ገዥዎቻችን በቂ ቁስል አሳርፈውብናል። አሁን ተጋግዘን መድኃኒቱን መፈለግ አለብን። መነሻችን ‹ያልቆሰለ የለም፣ ስለዚህም ሁሉም መድኃኒት ያስፈልገዋል› የሚል መሆን አለበት። አንዱን ሕዝብ አቁሳይ፤ ሌላውን ሕዝብ ቆሳይ አድርገው የሚያሳዩ አስተሳሰባቸው የተሳሳተ ነው።የሀገራችንን ሕዝቦች የንሮ ሁኔታ፣መሠረታዊ ነገሮችን ለማግኘት ያላቸውን ርቀት፣ የድህነት ወለላቸውንና ለድርቅና ለተፈጥሮ አደጋ ያላቸውን ተጋላጭነት በማየት ብቻ ችግርና መከራ አንድ ያደረጋቸው ሕዝቦች መሆናቸውን ለማወቅ ይቻላል። ድህነት፤ መከራ ፣ጦርነት ረሐብና ቸነፈር በሁላችንም ላይ ጥለውት ያለፉት ጠባሳና ሰንበር አሁንም ይታያል። ይህ ጠባሳና ሰንበር ጀርባው ላይ ያላረፈበት ሕዝብ በዚህች ሀገር የለም ‹እኔም አለኝ ቁስል፣ያንተን የሚመስል› የሚለው አባባላችን በውስጡ ፍቅር፣ መተሳሰብና መተዛዘንን ይዟል።ይህ ደግሞ የሕዝቦች ሁሉ ጠባይ ነው፡፥ ‹አንተም አለህ ቁስል የኔን የሚመስል› አላለም፡።አኔ አንተን አመስላለሁ ነው ያለው። መጀመሪያ ለዚያኛው ወገን ሕመም ነው ዕውቅና የሰጠው። ወገኔ ተታመመብኝ ብሉ ነው የተነሣው። ‹ እኔን፤› እንደሚለው ባሕላችን ‹እኔም እንዳንተ ታምሜያለሁ ፤አብረን መድኃኒት እንፈልግ› ነው የሚለው፡። ሀብት ባያገናኘንም ሕመም አገናኝቶናል ነው የሚለው። እኛንም ከደስታ ይልቅ መከራ፣ ከጤና ይልቅ በሸታ አስተሣሥረውን መኖራቸው እሙን ነው፡ የተክበራችሁ የኢትዮጵያ ሕዝቦች! ታድያ ያለፉት ዘመናት ያቆሰሉን አይበቃንም እንዴ ? ለምን አንድ ሆነን መድኃኒቱን አንፈልግም። እርስ በርሳችን ቁስላችንን እየነካካን እንዲያገረሽና ከማይድንበት ደረጃ እንዲደርስ ለምን እናደርገዋለን? ይህን በዓል ‹በሰው ቁስል እንጨት ስደድ› የሚለውን ትተን ‹እኔም አለኝ ቁስል፣ ያንተን የሚመስል› የምንባባልበት እንዲሆን እመኛለሁ። መልካም በዓል ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራ፣ ተከብራና በልጽጋ ለዘላለም ትኑር!” ፊጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! ግንቦት 19 ቀን 2011 ዓ.ምአዲስ ዘመን ግንቦት 20/2011", "passage_id": "5ae4682b79beb41be0893a3ae04fed0c" }, { "passage": " የካቲት 12 የሰማእታት ቀን ለ83ተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው፡፡የመታሰቢያ በዓሉም ስድስት ኪሎ የሰማእታት መታሰቢያ ሀውልት አደባባይ በሚገኝበት፣ አባት አርበኞችና ሌሎች የከተማዋ ነዋሪዎች እያከበሩት ይገኛሉ፡፡የዛሬ 83 ዓመት በ1992 በፋሺስት ኢጣሊን መሪ በሆነው በግራዚያኒ አማካኝነት ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በግፍ የተገደሉበት እለት ነበር፡፡  ፎቶ ከኢዜአ   ", "passage_id": "4044eb43d937eb54bd97084950fd430f" }, { "passage": "አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 12/2005 (ዋኢማ) – ኢትዮጵያ ለአፍሪካ አንድንት ድርጅት (የአፍሪካ ህብረት) መመስረትና ለአፍሪካ የነጻነት ታጋዮች ያበረከተችው አስተዋጽኦን በሚመለከት ሐምሌ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በቀድሞው የአፍሪካ አንድንት ድርጅት (የአፍሪካ ህብረት) አዳራሽ ጉባዔ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡በኢትዮጵያ የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ማህበር አስተባባሪነት አመቱን ሙሉ የሚካሄደውን የአፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት (የወርቅ ኢዮቤልዩ) በዓልን ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያዊው ንጉሥ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በወቅቱ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረት ያበረከቱትን አስትዋጽኦ ለመዘከር በማሰብ ጉባዔው መዘጋጀቱ ነው የተገለጸው፡፡የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ማህበር ሊቀ-መንበር አቶ ናሁ ሰናይ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የአፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት (የወርቅ ኢዮቤልዩ) በዓል ሲከበር ለድርጅቱ መከበርም ጉልህ ድርሻ የነበራቸው ሰዎች አብረው መታወስ አለባቸው፡፡ ከዚህ ውስጥ ደግሞ ግንባር ቀደሙ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ናቸው ብለዋል፡፡እንደ ሊቀመንበሩ ገለጻ ሐምሌ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ለአፈሪካ አንድነት ድርጅት (የአፍሪካ ህብረት) መመስረት፣ ለሁለት የተከፈለውን ቡድን ለማስማማት የነበረው ሂደት ላይ የዓፄ ኃይለ ሥላሴ ሚና ምን እንደነበር በሰፊው ውይይት እንደሚደረግበት ተናግረዋል፡፡ሊቀመንበሩ አያይዘውም በዚህ ጉባዔ ላይ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ታምቦ ምቤኪ፣ ፕሮፌሰር እንድሪያስ እሸቴ፣ አምባሳደር ብርሃኑ ደሪሳ፣ አቶ ተሾመ ገ/ማርያም፣ ወ/ሮ ሰሎሜ ታደሰ፣ አቶ አብዱል መሃመድ እና የኢትዮጵያ የታሪክ ተመራማሪዎችና ምሁራኖች የውይይቱ መሪ ተሳታፊዎች ሲሆኑ በርካታ ተጋባዥ እንግዶች እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ክፍሌ በበኩላቸው ማህበሩ በ1991 ዓ.ም ሲቋቋም የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አጽመ አስከሬንን በክብር ቦታ ማሳረፍ፣ ለጎበዝና መማር ለማይችሉ ተማሪዎች የትምህርት እድልን ማመቻቸት እንዲሁም በአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሥም ቤተ-መዘክርና ቤተ-ማፃሕፍት ቤት ለመገንባት በሚል ዓላማ እንደተቋቋመ ገልጸዋል፡፡እንደ ኢሬቴድ ዘገባ ሥራ አስኪያጅ ማህበሩ ከተቋቋመ ጀምሮ ለ5 መቶ ተማሪዎች የትምህርት እድልን እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን መንግስት ከያዘው የትምህርት ፖሊሲ አንጻር ወደፊት በሰፊው እንሰራለን፡፡ ለዚህም ወጣቱ ትውልድ ንቁ ታሳትፎ እንዲያደርግ በማለት ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡", "passage_id": "a002eab35c0758065badaac36b132231" }, { "passage": "ዘመናዊው ኦሊምፒክ በተመሰረተበት ወቅት ከጸደቁ ድንጋጌዎች መካከል በግምባር ቀደምትነት የሰፈረው ሃሳብ ‹‹ስፖርት ለሰው ልጆች ሰላምና ሁለንተናዊ ስብዕና መዳበር እንዲውል ማድረግ›› ይላል፡፡ ይህንንም ከምስረታው (እ.አ.አ 1896) ጀምሮ በውድድር ሜዳዎች ሳይወሰን መልካም ያልሆኑ አሠራሮችን በመቃወምና የህብረተሰቡ ትግል አጋር በመሆን ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባሳተመው መጽሔት ላይ ሰፍሯል፡፡ ለአብነት ያህልም እ.አ.አ 1964 ኮሚቴው አፓርታይድን በመቃወሙ ደቡብ አፍሪካን ከቶኪዮ ኦሊምፒክ ተሳትፎ ማገዱን ማስታወስ ይቻላል:: ከዚህም ባለፈ የራሱን ቡድን በማቋቋምም ደቡብ አፍሪካዊያኑ በአፓርታይድ ምክንያት ከሚደርስባቸው ጭቆና እስኪላቀቁ ድረስ መታገሉም ተጠቃሽ ነው፡፡ \nየስፖርት ውድድሮች ሁሉ ራስ የሆነው ኦሊምፒክ ተሳትፎ ዓላማና ግብ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም በተለያዩ ጊዜያት በዓለም ላይ የታዩ ኢ ሰብዓዊ የሆኑ ክስተቶችን በመቃወም፤ የስፖርት መነሻና መድረሻው ሰብዓዊነት መሆኑን አስመስክሯል፡፡ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ሁነቶች ጎን በመቆም ዘመናት የተሻገረው ስፖርት አሁንም የአጋርነት ሚናውን እየተወጣ መሆኑን የሰሞኑ ክስተት አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ዓለም በስልጣኔ እንደመራቀቋ የሰው ልጅም በአስተሳሰቡ እንደመምጠቁ የቆዳ ቀለምን መሰረት ያደረገ የዘረኝነት ጥቃት ሊገፋ ያልቻለ ቋጥኝ ሆኗል፡፡ የቆዳ ቀለምን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶችና አስነዋሪ ድርጊት ለዓመታት በስፖርት ሜዳዎችም ጭምር ተንሰራፍተው ታይተዋል፡፡ ሰሞኑን መነሻውን በአንድ ጥቁር ግለሰብ ግድያ ላይ ያደረገውና አሜሪካንን እየናጠ ባለው ተቃውሞም ስፖርት እንደ ትላንቱ ሁሉ ዛሬም ፀያፉን ተግባር በመቃወም ግንባር ቀደም ሆኗል፡፡ \nከስፖርቱ ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው የቀድሞ ቦክሰኛ ፍሎይድ ሜይዌዘር በሚኒያፖሊስ በጭካኔ የተገደለውን የ46 ዓመቱን አፍሪካ አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድን የቀብር ስነ-ስርዓት ወጪ እንደሚሸፍን አስታውቋል፡፡ የከባድ ሚዛን ዓለም ቻምፒዮናው ሜይዌዘር በቲውተር ገጹ ላይ ይህንኑ እንዳሰፈረም ነው ዘ ኢንዲፔንደንት በዘገባው ያመላከተው፡፡ የጎልፍ ተጫዋቹ ታይገር ውድስም በተመሳሳይ በሁኔታው ማዘኑን እንዲሁም የሟች ፍሎይድ ቤተሰቦች እንዲበረቱ በትዊተር ገጹ መልዕክት አስፍሯል፡፡ የፖሊሱንም ተግባር ‹‹ያለ ቦታው ኃይልን የተጠቀመና ዕርምጃውም መስመር ያለፈ›› ብሎታል፡፡ አሜሪካዊው የቅርጫት ኳስ ኮከብ ሚካኤል ጆርዳን በበኩሉ በአሜሪካ ያለው ዘረኝነት ስር የሰደደ መሆኑን አስምሮበታል፡፡ ሌሎች የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ተጫዋቾችና ስፖርተኞችም በገንዘብና በሃሳብ ከተጎጂው ቤተሰቦች ጋር መሆናቸውን ከመግለጽ ባለፈ አስነዋሪውን ተግባር በመቃወም አጋርነታቸውን እያሳዩ ይገኛሉ፡፡ \nየአሜሪካንን ድንበር ያቋረጠውና ወንዝ የተሻገረው ተቃውሞና ለጥቁሮች ወንድማዊ ስሜትን የማሳየቱ ሂደትም በመላው ዓለም እንደቀጠለ ነው፡፡ በአውሮፓ የሚገኙ በርካታ የእግር ኳስ ተጫዋቾች በጨዋታ እንዲሁም በልምምድ ሜዳዎች ላይ በግልና በቡድን በድርጊቱ የተቃውሞ እንዲሁም ከጥቁሮች ጋር የአብሮነት ስሜታቸውን አንጸባርቀዋል፡፡ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠውን የእግር ኳስ ውድድር ከሌሎች ቀድሞ በጀመረው የጀርመን ቡንደስሊጋም ይኸው እንቅስቃሴ ተስተውሏል፡፡ የቦሩሲያ ዶርትመንዱ ተጫዋች ጃደን ሳንቾ ‹‹ፍትህ ለጆርጅ ፍሎይድ›› የሚል ካኒቴራ ከማሊያው ስር በመልበስ ያሳየ ሲሆን፤ ሌሎችም በጉልበታቸው በመንበርከክ ኀዘናቸውን መግለጻቸውን ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡ \nየተቋረጠውን ሊግ ለመቀጠል በልምምድ ላይ የሚገኙት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾችም በተመሳሳይ ሁኔታ አብሮነታቸውን አሳይተዋል፡፡ 29 የሚሆኑ የሊቨርፑል ተጫዋቾች በሜዳቸው አንፊልድ ከጉልበታቸው በመንበርከክ መልዕክት አስተላልፈዋል፡ ፡ የማንቺስተር ዩናይትድ ተጫዋቾቹ ፓውል ፖግባ እና ማርከስ ራሽፎርድም ድምፃቸውን ካሰሙ ተጫዋቾች መካከል ይገኙበታል፡፡ ፖግባ ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ‹‹ለፍሎይድና ለመላው ጥቁር ማህበረሰብ የንዴት፣ የኀዘን እና የመከፋት ስሜት ተሰምቶኛል፡፡ ጥቁሮች በእግር ኳስ፣ በትምህርት ቤት፣ በሥራና ሁሉም ስፍራ ይህንን ስሜት በየዕለቱ ያስተናግዳሉ፡፡ በመሆኑም ይህ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መቆም አለበት፤ ዛሬውኑ›› ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ እንግሊዛዊቷ የአጭር ርቀት አትሌት ዲና አሸር ስሚዝ፣ የሜዳ ቴኒስ ኮከቧ ሴሪና ዊሊያምስ፣ የፎርሙላ ዋን ሞተር ስፖርት ተወዳዳሪዎች እንዲሁም ሌሎች የስፖርቱ ሰዎችም በሁኔታው መከፋታቸውን በመግለጽ ተቃውሟቸውን የገለጹም የስፖርቱ ዓለም ከዋክብት ናቸው፡፡ \nአዲስ ዘመን ግንቦት 26/2012ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "550c564b74472fc797ee8b1b9d39b489" }, { "passage": "የጥንታዊት ኢትዮጵያ የአርበኞች ማሕበር ተወካይ በበኩላቸው አዲሱ ትውልድ አንድነቱ የተጠበቀ አገር እርሱን ለሚከተለው መጭው ትውልድ ያስተላልፍ ዘንድ ያሉበትን የአደራ ጥሪ ያሰሙበትን ንግግር ጠቅሶ የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ሪፖርት ልኳል። ", "passage_id": "294effa9f38c9c7185e04164cd44b189" } ]
18a483db5cd486c031946f7ebd686e31
ecca94964ee2573c01afae2acf372265
«ተምዘግዛጊው ሚሳኤል» አረፈ!
ከአዲስ አበባ በ110 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኘው ወንጂ ከተማ በእግር ኳሱ በርካታ ተጫዋቾችን ማፍራቷ ይነገርላታል። ይህም ከተማዋ ከምትታወቅበት ጣፋጭ የሸንኮራ አገዳ አምራችነቷ፣ የስኳር ፋብሪካ ማዕከልነቷ ትይዩ የእግር ኳስ ተጫዋቾች መፍለቂያ አሰኝቷታል። የወንጂን ከተማ በእግር ኳሱ ካስተዋወቁት ተጫዋቾች መካከል ደግሞ አንጋፋው ተጫዋች ተስፋዬ ኡርጌቾ ይጠቀሳል። በወንጂ ከተማ ተወልዶ ያደረገው ተስፋዬ፤ በእግር ኳሱ ትልቅ ቦታ መድረስን የልጅነት ህልሙ አድርጎ የተነሳ መሆኑን የቅርብ ወዳጆቹ ይናገሩለታል። ከልጅነቱ ጀምሮ ለእግር ኳስ ልዩ ፍቅር በመያዝ መነሻው ከሰፈር ሜዳ ነበር። በኳሱ የመጓዝ ህልሙ ሩቅ የሆነው የትናንቱ ታዳጊ ተስፋዬ፤ በስፖርቱ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በማጎልበቱ ወደ ክለብ እንዲያድግ አጋጣሚን አገኘ። ከከተማዋ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መሠረት አንዱ የሆነው የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ያቋቋመውን «የወንጂ ስኳር እግር ኳስ ክለብ» ነበር የተቀላቀለው። ተስፋዬ የወንጂ ስኳርን መቀላቀሉ በኳሱ ለሚያልመው ህልሙ፣ ለሰነቀው ተስፋ እውን መሆን መንደርደሪያውን የትውልድ ከተማው ሆነለት። ከክለቡ ጋር የተወሰኑ ጊዜያትን ቆይታ ካደረገ በኋላ የሕይወቱ አቅጣጫ ወደ ሌላ ምዕራፍ ተሸጋገረ። በወንጂ ስኳር እግር ኳስ ክለብ በፈጣንና ጥበብ የተሞላበት እንቅስቃሴ ባለቤትነቱ በአየር ኃይል እግር ኳስ ቡድን እይታ ውስጥ አስገባው። በወቅቱ የአየር ኃይል አሰልጣኝ የነበረው አንጋፋው አሰልጣኝ ሀጎስ ደስታ ልብ በማሸነፍ አሰልጣኙ አየር ኃይልን እንዲቀላቀል አስቻለው። በእግር ኳሱ ትልቅ ደረጃ የመድረስ ተስፋ በልቡ ሰንቆ ወደሜዳ ለሚመጣው ታዳጊ ትልቅ ዕድል ነበር። በአየር ኃይል ቤት ተስፋዬ ምኞቱን መኖር ለመጀመሩ መንደርደሪያው ነበር። በቡድኑ ውስጥ ያሳየው እንቅስቃሴ ክለቡ እንዲደሰትበት ከማድረግ አልፎ፤ ለብሔራዊ ቡድን እንዲጫወት ሀገራዊ ጥሪ እንዲቀርብለት አድርጎታል። በ1983 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን በመመረጥ በግብጽ አዘጋጅነት በተካሄደው 7ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ ችሏል። የወንጂው ፍሬው ተስፋዬ የስኬት ጀንበርን በአጭር ጊዜ ውስጥ መመልከት የቻለ ሲሆን፤ በሜዳ ላይ የሚያሳየው ብቃትና የተላበሰው መልካም ስብዕናው ተደምረው ጉዞው ያማረ እንዲሆን አደረጉት። የወጣት ብሔራዊ ቡድኑ በሻምፒዮናው ላይ ከተሳትፎ መልስ የተስፋዬ የክለብ መዳረሻ ከአየር ኃይል ተወርውሮ ወደ አንጋፋው ቅዱስጊዮርጊስ ላይ አረፈ። በ1983 ዓ.ም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ አንፀባራቂ ታሪክ ባላቸው በኢንስትራክተር መንግሥቱ ወርቁ አማካኝነት ክለቡን ተቀላቀለ። የእግር ኳሱ ጥበበኛ ተስፋዬ ፈረሰኞቹን መቀላቀሉ በኳሱ የስኬትን ቁንጮ ለመቆናጠጥ ትልቅ ዕድል ፈጥሮለታል። በአማካይና የተመላላሽ ቦታዎች ላይ በመጫወት ክለቡን ለስኬት ማብቃት በመቻሉ የክለቡ ደጋፊዎች ዛሬም ድረስ ትልቅ ቦታ እንዲኖራቸው አድርጓል። ከ1983 ዓ.ም እስከ 1992 ዓ.ም ፈረሰኞቹን ማገልገል የቻለው አመለሸጋው ተስፋዬ፤ በቆይታው ከፍተኛ ዝናና ተወዳጅነት አትርፏል። በፈረሰኞቹ ቤት በቆየባቸው የሰባት ዓመታት ቆይታ ውስጥ በ1986 ዓ.ም የአዲስ አበባ ሻምፒዮን ኮከብ ተጫዋችነትን ክብር አግኝቷል። ክለቡ ቅዱስጊዮርጊስ ከ1986 እስከ 88 ዓ.ም የአዲስ አበባ ሻምፒዮናነትን ክብር ሲቀዳጅ ግብ አስቆጣሪ ከሆኑት ተጫዋቾች ጀርባ የእርሱ ሚና ግዙፍ እንደነበር በወቅቱ የነበሩ ተጫዋቾች መስክረውለታል። ከክለቡ ስኬት ተሻግሮም ለሚወዳት ሀገሩ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ተመርጦ በርካታ ጨዋታዎችን ተጫውቶ አሳልፏል። በ1985 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ናይጄሪያን 1ለ 0 ስታሸንፍ ብቸኛዋን ግብ በማስቆጠር ሀገሩን ለድል ያበቃበት አጋጣሚ በአብዛኛው የስፖርት ቤተሰብ ዘንድ ይታወሳል። በብሔራዊ ቡድን ብሎም በክለብ ደረጃ የነበረው እንቅስቃሴ ከክለቡ ተሻግሮ በስፖርት አፍቃሪው ዘንድ ከፍተኛ ተደናቂነት ማትረፍ የቻለ ተጫዋች ነበር። በሀገር ውስጥ የክለብ ፍልሚያዎች በፈረሰኞቹ ቤት በ4 ቁጥር ማሊያ መንገስ ችሏል። በሜዳ ላይ ፈጣንና ድንቅ እንቅስቃሴ የሚያሳይ መሆኑን ተከትሎ «ተምዘግዛጊው ሚሳኤል» የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው ተስፋዬ፤ ከሀገር አልፎ ወደ አውሮፓም አምርቶ በፊንላንድ ሊግ መጫወት ችሏል። በኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ዛሬም ድረስ እንደ ብርቅ በሚታየው የአውሮፓ ሊግ የኳስ ጥበበኛው ተስፋዬ ባህር ተሻግሮ። እግር ኳስን በተጫወተባቸው ዓመታቶች በመሀል ሜዳ የጨዋታ ብቃቱ የብዙዎቹን የእግር ኳስ አፍቃሪዎች እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችን ቀልብ ይስብ የነበረው፤ ተስፋዬ የተጫዋችነት ዘመኑን ቢያበቃም ከኳሱ አልተለየም ነበር። ከተጫዋችነት ወደ አሰልጣኝነት የሕይወቱ አቅጣጫ ተሸጋገረ። በአሰልጣኝነትም ሕይወት በመሰማራት የጌታ ዘሩን የታዳጊ ፕሮጀክት እና የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲንም ክለብን በመያዝ አሰልጥኗል። የሕይወቱን ፍጻሜ ከኳስና ከእናት ሀገሩ ለመነጠል ፍላጎት ያልነበረው ተስፋዬ፤ መኖር ግድ ነበርና በአሜሪካ በስደት በርካታ ዓመታትን አሳልፏል። «ተምዘግዛጊው ሚሳኤል» በገጠመው ህመም ከሚኖርበት አሜሪካ የመጣ ሲሆን፤ በሚወዳት ሀገሩ በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ግንቦት 05 ቀን 2012 ዓ.ም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሕይወቱ አርፏል። በኢትዮጵያ የእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ የራሱን አሻራ ማሳረፍ የቻለው ተስፋዬ የቀብር ሥርዓቱ በትውልድ ከተማው ወንጂ ሸዋ ኪዳነ ምህረት ከትናንት በስቲያ ተፈጽሟል። የተስፋዬ ሞት ብዙዎቹን ያሳዘነም ሲሆን የዝግጅት ክፍላችን በተስፋዬ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ ለወንድሙ ተከተል ኦርጌቾና ለመላው ስፖርት አፍቃሪ እና ለቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች መፅናናትን ይመኛል። አዲስ ዘመን ግንቦት 7/2012ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=32391
[ { "passage": "በ19 ሺህ ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረውና በመብረቅ የተመታው አውሮፕላን አፍንጫው ላይ ጉዳት ቢደርስበትም ፓይለቱ በሰላም መሬት እንዲያርፍ ማድረግ በመቻሉ ብዙዎች በማህበራዊ ሚዲያ እያወደሱት ነው።\n\nየፕሮፍላይት የበበራ ማናጀር የሆኑት ፊል ሊምባ 41 መንገደኞቻቸው በሰላም በመድረሳቸው ደስታቸውን ገልፅዋል።\n\nዳሽ 8-300 የሆነው ይህ አውሮፕላን በሥሪቱ ምክንያት በመብረቁ አፍንጫው ከመጎዳቱ ባሻገር ምንም ጉዳት እንዳልደረሰበት ማናጀሩ ቢገልፁም አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ ግን አውሮፕላኑ ላይ ጉልህ የሚባል ጉዳት ደርሷል ብሏል።\n\nየአየር መንገዱ መግለጫ እንደሚለው እርግጥም አውሮፕላኑ በከባድ ውሽንፍር ተመትቷል። እርግጠኛ ሆኖ በመብረቅም ተመትቷል ለማለት ግን ምርመራ መደረግ አለበት።\n\n• ግብጽዊው አርቲስት አውሮፕላን አብራሪውን እስከወዲያኛው ከሥራቸው አሳገደ \n\n• ታዳጊዎች በገጣጠሟት አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራቸውን አደረጉ\n\n• ደቡብ አፍሪቃ የታንዛኒያ አውሮፕላንን በቁጥጥር ሥር አዋለች\n\n ", "passage_id": "44136dda4c8b61872b4d5758bea76716" }, { "passage": "ከ19 ወራት ያላነሰ ጊዜ የፈጀችውና በሰንዳፋ ዳቢ ጊዮርጊስ ሜዳ ላይ ተንደርድራ ልትበር የነበረችው አነስተኛ አውሮፕላን ባጋጠማት ብልሽት ሳትበር ቀረች፡፡ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ለበረራ ዝግጁ ትሆናለች ተብሏል፡፡ትውልዱ ትግራይ ክልል ዋጅራት አካባቢ ነው፡፡ ያደገው ሐዋሳ ሲሆን የተማረው በአለማያ (ሐሮማያ) ዩኒቨርሲቲ የጤና መኮንንነት ነበር፡፡ ይህን የተማረው አማራጭ ስላጣ እንጂ የልጅነት ሕልሙ አውሮፕላን አብራሪ መሆን እንደነበረ ይናገራል፡፡የ35 ዓመቱ አስመላሽ ዘፈሩ ከ14 ዓመታት በፊት የጤና መኮንን ለመሆን ያስገደደውን አጋጣሚ ለሪፖርተር የገለጸው፣ ለመሥራት አንድ ዓመት ከሰባት ወራት የፈጀችበትን አውሮፕላን ለማብረር እየተዘጋጀ በነበረበት ወቅት ነበር፡፡ አስመላሽ  አውሮፕላን ለማብረር ከልጅነቱ ጀምሮ ሲመኝ ኖሯል፡፡ በትምህርቱ አጥጋቢ ውጤት አምጥቶ ዩኒቨርሲቲ ቢገባም፣ በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ የበረራ ትምህርት የማይሰጥ በመሆኑ የጤና መኮንንነትን ለማጥናት ተገዷል፡፡ ይህም ሆኖ በድሬዳዋ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአብራሪዎች ምልመላ ሲያካሂድ ተመዝገቦ ቢቀርብም፣ ቁመትህ በሚፈለገው ልክ አይደለም ተብሎ ሳይመረጥ መቅረቱን ይናገራል፡፡‹‹ቁመትህ አንድ ሳንቲ ሜትር አጥሯል ተብዬ የአብራሪነት ሕልሜ ሳይሳካ ቀረ፤›› የሚለው አስመላሽ፣ ከ21 ዓመት ዕድሜው ጀምሮ የራሱን አውሮፕላን ሠርቶ የማብረር ፍላጎት እንዳደረበት ተናግሯል፡፡ በዚህ አኳኋን ከጤና መኮንንነት ሙያው ባሻገር የምህንድስና ትምህርት በማታው ክፍለ ጊዜ በመከታተልና ስለአውሮፕላን አሠራር በማጥናት በመጨረሻም ‹‹K-570A›› የሚል ስያሜ የሰጣትንና ሁለት ሰው ማሳፈር የምትችል የድሮ ሞዴል አውሮፕላን ሠርቶ ለማብረር ተቃርቦ ነበር፡፡ ከእናቱ ወይዘሮ ኪሮስ ስም የመጀመርያ የእንግሊዝኛ ፊደል በመውሰድና አውሮፕላኑን ለመሥራት የፈጁበትን 570 ቀናት፣ እንዲሁም ‹‹ኤርክራፍት›› ከሚለው ፊደል የመጀርያውን ተጠቅሞ ለአውሮፕላኑ ስያሜ ሰጥቷል፡፡ባለፈው ሐሙስ ሰኔ 4 ቀን 2007 ዓ.ም. አውሮፕላኗን ከአዲስ አበባ በ40 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ሰንዳፋ ከተማ፣ ዳቢ ጊዮርጊስ በተባለ ሜዳ ላይ አንደርድሮ ለማብረር ዝግጅት በማድረግ ላይ ሳለ፣ ሁለት ጊዜ በተሰበሩበት የአየር መቅዘፊያዎች ምክንያት በረራውን ሳያካሄድ ቀርቷል፡፡ አየር መቅዘፊያውን በጥቂት ቀናት ውስጥ በመሥራት ለሞት አደጋ ሊያጋልጠው የሚችለውን አስፈሪ በረራ በድጋሚ ለመሞከር መወሰኑን አስታውቋል፡፡የመትረፍ ዕድሉ ግማሽ በግማሽ እንደሆነ የሚገልጸው አስመላሽ፣ እስካሁን እልህ አስጨራሽ ጉዞ ማድረጉንና ያለውን ነገር ሁሉ አሟጦ በአቅሙ መሥራት የቻለውን አውሮፕላን ዕውን ማድረጉን በመግለጽ ከማብረር እንደማይመለስ ይፋ አድርጓል፡፡ ለሠራው አውሮፕላን 160 ሺሕ ብር ማውጣቱን፣ ከዚህ አውሮፕላን ውጪ ምንም ነገር እንደሌለው፣ ሙሉ ጊዜውን አውሮፕላን ለመሥራት ሲል ከሥራ ገበታው ራሱን ማግለሉን አስመላሽ ይናገራል፡፡ ከወዳደቁ ቁሳቁሶች፣ 40 የፈረስ ጉልበት ካለው የቮልስ ዋገን ሞተር፣ ከእንጨት፣ ከብረት፣ ከሱዙኪ ሞተር ብስክሌት ጎማዎች፣ ከአልሙኒየምና ከመሳሰሉት ቁሳቁሶች የሠራት አውሮፕላን አንዴ ከበረረች በኋላ ዳግመኛ ስለማትበር ሙዚየም የምትገባ መሆኗን ገልጿል፡፡ የቅርብ ጊዜ ህልሙ ናይጄሪያዊው ወጣት ከውድቅዳቂዎች የሠራትንና በአራት ሜትር ከፍታ ላይ ያበረራትን አውሮፕላን በመብለጥ፣ ተጨማሪ ሜትሮችን ወደ ሰማይ በመንሳፈፍ ለማብረር አቅዷል፡፡እጁን ካፍታታባትና ሙሉ በሙሉ ሜካኒካል በሆነ መንገድ ከምትሠራው አውሮፕላን በተጨማሪ፣ ዲጂታል የሆነና አራት ሰዎችን ማሳፈር የሚችል ዘመናዊ አውሮፕላን የመሥራት ሕልም የሰነቀው አስመላሽ፣ በሰንዳፋ የሠራትን አውሮፕላን ለማበረር ሲሰናዳ የሕይወት አድን ጃኬትም ሆነ ከአየር መዝለያ ፓራሹት አልታጠቀም ነበር፡፡ የሞተር ብስክሌት ሔልሜት በአናቱ ላይ ከማጥለቁ በቀር ለአውሮፕላን አብራሪ የሚመጥን ምንም ዓይነት ቅድመ ዝግጅት አይታይበትም፡፡ ይህ ሁሉ አቅም ስለሌለው እንጂ ሳያስፈልገው ቀርቶ እንዳልሆነ ይገልጻል፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ የሠራት አውሮፕላን በርካታ ማሟላት የሚገባት መሠረታዊ ነገሮች እንደሚቀረም ያምናል፡፡ ይህም ሆኖ አሥር ሜትር ያህል አብርሮ ለማሳረፍ የሚያስችል ዝግጅት ተደርጎባት ነበር፡፡የአስመላሽ አባት አቶ ዘፈሩ፣ ከ90 ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸውና የ11 ልጆች አባት ሲሆኑ፣ አሥረኛው ልጃቸው አስመላሽ ራሱ በሠራው አውሮፕላን እየሩሳሌም እንደሚወስዳቸው ከልጅነቱ ጀምሮ ይነግራቸው እንደነበር ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አስመላሽን ጨምሮ አብዛኞቹ ልጆቻቸው በሰማይ ላይ መብረርን አጥብቀው የሚመኙ፣ የራሳቸውን መኪና ለመሥራት ሲጥሩ የነበሩ መሆናቸውን ገልጸው፣ አንድ ቀን እየሩሳሌምን የመጎብኘት ሕልማቸው በልጃቸው እንደሚሳካ ተስፋቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ልጃቸው በሠራት አውሮፕላንም ከመደሰት በላይ ለአገሩ የሚያኮራ ሥራ መሥራቱን እንደሚያምኑም ገልጸዋል፡፡ ", "passage_id": "24e3e6347199e1a5bdbb7cba1eea852b" }, { "passage": "ኢያሱ መሰለ ሻለቃ ዘላለም\nብዙነህ\nበሰሜን\nአየር\nምድብ\nየአየር\nመከላከል\nእቅድና\nስልጠና\nቡድን\nመሪ\nነው።ዋናው\nየስራ\nድርሻው\nጠላት\nየአየር\nጥቃት\nእንዳያደርስ\nመከላከል\nእና\nየምድር\nኃይሉ\nእንዳይጎዳ\nድጋፍ\nመስጠት\nነው።ሰሜን\nአየር\nምድብ\nከመጣም\nከ17\nዓመት\nበላይ\nሆኖታል።ሻለቃ\nቡዙነህ\nእንደሚያስረዳው\nዶክተር\nአብይ\nወደ\nስልጣን\nከመጡ\nከ2010\nዓ.ም በኋላ ለውጡ\nያልጣማቸው\nኃይሎች\nአዳዲስ\nባህሪ\nአምጥተዋል።ከፌደራል\nመንግስት\nየሚተላለፉ\nመመሪያዎችን\nያለመቀበልና\nሰራዊቱን\nከፋፍሎ\nየመመልከት\nሁኔታዎችም\nይስተዋሉ\nነበር።\nየእነሱን\nሀሳብ\nየማይቀበለውን\nየአየር\nኃይል\nአባል\nየብልጽግና\nፓርቲ  ደጋፊ\nነው በማለት ያጥላላሉ።በዚህ\nሁኔታ ውስጥ እያሉም\nጥቅምት 24 ቀን\n2013 ዓ.ም ከምሽቱ\nአምስት ሰዓት ላይ\nምንም ባላሰቡት ሁኔታ\nመቀሌ በሚገኘው የሰሜን\nአየር ምድብ መኖሪያ\nቤት የተኩስ ሩምታ\nተከፈተ፤ ምንድ ነው\nብለው ሲጠይቁም የሴራው\nተባባሪ የሆኑና ጉዳዩን\nየሚያውቁ አባላት ልምምድ\nነው እያሉ ያዘናጓቸው\nእንደነበር ያስታውሳል።‹‹ሌሊቱን ሙሉ\nሳንተኛ አድረን ልክ\nአስራ ሁለት ሰዓት\nሲደርስ ልዩ ኃይሎች\nወደ ግቢው መግባት\nጀመሩ።በተለይም የአማራና የኦሮሞ\nተወላጅ አባላትን ከቤታችን\nእያወጡ እያመናጨቁና እየገረፉ\nወሰዱን።ወደ ማጎሪያ ቤት\nከወሰዱን በኋላ በብሔር\nከፋፈሉን።ደቡብን ለብቻ ፤\nአማራና ኦሮሞን በአንድ\nላይ አድርገው አጎሩን።ሚሳኤል\nየመተኮስ ልምድና እውቀቱ\nእንዳለኝ  ስለሚያውቁ እኔን ለብቻዬ ወሰዱኝና እንድተኩስላቸውና ከእነርሱ ወገን እንድቆም ጠየቁኝ።እኔ ከምንም በላይ ቃል የገባሁት የሀገሬን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ሕዝቤን ለመጠበቅ ነው፤ ከሀገር በላይ ክብር የለም ፤ ስለዚህ መልሼ ሀገሬን አልወጋም አልኳቸውና 20 ዓመት የታገልኩበትን የትግል ዓላማ በአንድ ቀን እንደማላፈርሰው ነገርኳቸው።ሙያዊ እገዛ አድርግልን ፤ ተኩስልን፤ አሉኝ።እምቢ ስላቸውም በዚህና በዚያ መሳሪያ ደቅነውብኝ አስፈራሩኝ፤ ሰደቡኝም።ከፈለጋችሁ ግደሉኝ አልኳቸው።ከመሃላቸው አንዱ በጥፊ መታኝና ውጣ አለኝ።ከወጣሁ በኋላ ለሚሊሺያዎች አስረከቡኝ።ሚሊሺያዎቹ እግሬን በዱላ ሰባብረው ጣሉኝ፡፡እረ ባካችሁ ተውኝ እያልኩ ብማጸናቸውም ትንሽ እንኳን ሊራሩልኝ አልፈለጉም።ቀጥቅጠው ጥለውኝ ሲሔዱ በዳዴ እየተሳብኩ ቤቴ ገባሁ።ቤት ከገባሁ በኋላም እንደገና መጥተው እንድተኩስላቸው ጠየቁኝ እግሬ መጎዳቱን አሳየኋቸውና እንደማልችል፤ ቃል ኪዳኔንም እንደማላፈርስ ደግሜ ነገርኳቸው።ኮሌኔል በላይ የሚባል ሰው ፈቃደኛ ከሆንኩና ከተኮስኩ እንደሚያሳክመኝ ነገረኝ።እኔ ግን ከፈለግህ ግደለኝ አልኩት።ሚሳኤል ማስወንጨፊያው ሶስት ቦታ ላይ ማለትም መሶቦ፣ አዲግራትና አክሱም ነው ያለው።የሚሳኤሉ ዋና ታርጌት ተዋጊ አውሮፕላኖችን መጣል ነው፤ እስከ 25 ኪሎሜትር ይጓዛል።ወደ ባህር ዳር ይተኩሱት የነበረው ግን ሚሳኤል ሳይሆን ሮኬት ነው።ሮኬቱን ተሽከርካሪ ላይ አጥምደው ቦታ እየቀያየሩ ነበር የሚተኩሱት።ለምሳሌ መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ አካባቢም እየመጡ ይተኩሱ ነበር።አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ወደ ሌላ ቦታ ወስደው ሲተኩሱት ይሰማል።ጦርነቱ እየተባባሰ ሲመጣ ወደ ግንባር ሄዱ።ከዚያም መከላከያ ሰራዊት ከተማውን ሲቆጣጠረው መረጋጋት ጀመርኩ።ምንም አይነት ህክምና ሳላገኝ ማታ ማታ እየታሸሁ አሁን ትንሽ ተሽሎኛል።አድራጎታቸው በጣም ያማል ፤እስከአሁንም አዕምሮዬ ትክክል አይደለም።እህል በማጨድ፣ አንበጣ በማባረር ፣ ኮሮናን በመከላከልና በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ድጋፍ ሲያደርግ የነበረን ሰራዊት ክብሩ ተገፎ ውርደት ደርሶበታል።በተፈጸመብን የጭካኔ ተግባር ምክንያት እስከ አሁን ራሴን እያመመኝ ነው ፤ ጤነኛ አይደለሁም።መከላከያ ሰራዊት ለሀገሩ የገባው ቃል ኪዳን አለ።ሕዝብና መንግስት የሰጠውን ኃላፊነት የመፈጸም አደራ አለበት።ትግል ውስጥ ስገባ ልንሞትም ነው።እኛ እንደሻማ ቀልጠን ሌሎች ብርሃን እንዲወጣላቸው ቃል ገብተናል።በዚህ ቃል ኪዳናችን እንጸናለን፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 29/2012 ዓ.ም ", "passage_id": "70a5fbff9786f76b2c0b9ffb32a2b3cc" }, { "passage": "የሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም አመሻሽ ለኢትዮጵያ መልካም ዜና አላበሰረም፡፡ ከባህር ዳር ከተማ የዶክተር አምባቸውንና የአቶ እዘዝ ዋሴን የግፍ አሟሟት ሲያሰማ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ደግሞ የጀነራል ሰዓረ መኮንን እና የሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራን መስዋዕት አርድቷል፡፡ ውሎ አድሮም የቅዳሜው ምሽት ጦስ የአቶ ምግባሩን ሞት አርድቷል፡፡ የጀነራሎች አስከሬን አሸኛኘት ላይ አዲስ አበባ ከተማ ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች ድርጊቱ አሳዛኝ፣ አሳፋሪና በምንም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ነው የሚገልጹት።አስተያየት ከሰጡን መካከል አቶ ሰለሞን ጽጌ ሜጫ እንደሚያመለክቱት፤ ድርጊቱ በጣም አስነዋሪና የወታደራዊ ስነምግባርን ከሚያውቅ ሰው የማይጠበቅ ብለውታል፡፡ የሞቱት ጀግኖች ሰላም እንዲሰፍን፣ አገሪቱ እንድትለማ ሲታትሩ የነበሩና ለምስራቅ አፍሪካ ሰላም መስፈን መኩሪያ መሆን የሚችሉ እንደነበሩም ይጠቁማሉ፡፡ በእነርሱ ላይ የተፈጸመው ድርጊት በጣም አሳፋሪ ነው ሲሉም ድርጊቱን ይኮንናሉ፡፡ ወታደር ከፖለቲካ አሰራር የተገለለ ነው\nየሚሉት አቶ ሰለሞን፤ ለአገር ሰላም መስፈንና ለህዝብ ደህንነት ዘብ የሚቆም፣ ለሚሰራው አጠቃላይ ሥራም ተጠያቂነት እንዳለበትም ያመለክታሉ፡፡ በመሆኑም የሚፈጽማቸው ተግባሮችን ሁሉ ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ መፈጸም ይጠበቅበታል ባይ ናቸው። ወታደራዊ ስነ ምግባር፣ ደንብና መመሪያም አለው፡፡ በተማረውና በሰለጠነው መሰረት አክብሮ መስራት ይገባዋል ይላሉ፡፡ ከዚህ ባፈነገጠና ከወታደራዊ ስነምግባርና ደንብ ውጪ መፈጸሙ አስነዋሪ ድርጊት የሆነ ከአንድ ወታደር የማይጠበቅ ተግባር ነው ሲሉም ያመለክታሉ፡፡ ሰፊ\nየምርመራ ሥራ በመስራት የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙ ሰዎችን ለይቶ ተገቢና አስተማሪ የህግ እርምጃ መውሰድ አለበት የሚሉት አቶ ሰለሞን፤ የአገር ሰላም ማስፈንና የህዝብን ደህንነት የማስጠበቅ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ በመሆኑ ህዝቡ በየአካባቢው ለሰላሙ ዘብ ሊቆም ይገባል ሲሉም ይገልጻሉ፡፡ እነዚህ ጀግኖች ናቸው። ጀግና ደግሞ አይሞትም፡፡ በርካታ ጀግኖች የተኩ በመሆናቸው አልሞቱም፡፡ እንደ አቶ ሰለሞን ማብራሪያ፤ ጀነራሎቹ ባካበቱት ወታደራዊ ሳይንስ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ታሪክ የሚዘነጋው አይደለም፡፡ ለአገርና ለአህጉር ሰላም መስፈንም ያበረከቱት አስተዋጽኦ የሚደነቅና የሚከበር ነው። ለአገራቸው መስዋዕት ሆነዋል፡፡ መቼም የማይዘነጋ ታሪክ አስመዝግበዋል፡፡ ግን ሌላ ችግር ወይንም ተመሳሳይ ወንጀል እንዳይፈጸም ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም በተቋሙ ውስጥ ያለው አሰራር በደንብ መፈተሽ ይኖርበታል ሲሉም መክረዋል፡፡ ወይዘሮ ስንዳይ አሰፋ፤ ተግባሩ በጣም አሳዛኝ መሆኑን ይጠቁማሉ፡፡ አመራሮቹ በጣም ታታሪ የነበሩ፣ ጥሩ ሰዎችና አገርን ለመገንባት ደፋ ቀና ሲሉ የነበሩ መሆናቸውን ያስታውሳሉ፡፡ ለአገርና ለወገን የሚያስቡ እንደነበሩ በመግለጽም፤ ድርጊቱ ተገቢ እንዳልሆነ ይጠቁማሉ፡፡ ‹‹ለአገር የሚጠቅሙ ሰዎች ላይ እንዲህ አይነት ተግባር መፈጸም ጥሩ አይደለም፡፡ አገሪቱን ወዳልተገባ መንገድ የሚመራ ተግባር ነው›› በማለትም ይገልጻሉ፡፡ ድርጊቱ በምንም አይነት ሁኔታ ተቀባይነት የለውም፡፡ የተሰዉትን መመለስ አይቻልም፡፡አሁን ድርጊቱ ተፈጽሟል፡፡ ግን በትዕግስት ማሳለፍ ያስፈልጋል፡፡ በግልፍተኝነት ተነሳስቶ አገር ማጥፋት አያስፈልግም። በሆደ ሰፊነት ነገሮችን ማሳለፍ ይገባል፡፡ ወደፊት ለመጓዝ መነሳሳት  መፈጠር አለበት። አገርን መገንባት ያስፈልጋል። የአገርን ሰላም ለማስጠበቅ ወጣቱ መነሳሳት ይገባዋል ሲሉም ያመለክታሉ፡፡ የመከላከያ ሰራዊት የተሰዉ ጀነራሎች ሲተገብሩት የነበረውን ፈለግ መከተል ይኖርባቸዋል፡፡ ሰላም የማስከበር ሥራ መቀጠል ይኖርበታል፣ ለአገር ሰላምና ዕድገት መልፋትም መድከምም ይኖርባቸዋል። ህዝቡም ልማቱን ማስቀጠል አለበት፡፡ እንጂ ወደ ጥፋት መንገድ መመራት የለበትም ሲሉም ወይዘሮ ስንዳይ መክረዋል፡፡ አቶ ገብረህይወት ወልደአብእዝጊ፤ የተፈጸመው ድርጊት አገርን የሚለያይ፣ በህዝብ ላይም ከፍተኛ ችግር የሚደቅን መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ ሆን ብለው ያቀነባበሩት የጸረ ሰላም ሃይሎች ድርጊት በመሆኑ ተገቢነት የሌለው ነው ሲሉም ድርጊቱን ይኮንናሉ። እነዚህ ሰዎች የሄዱበት መንገድ በምንም አይነት ሁኔታ ሊሳካ የሚችል አይደለም ባይ ናቸው፡፡ ሰዎቹ ገድለዋል እንደገናም ተገድለዋል፡፡ ይህ ምንም አይነት በጎ ውጤት የለውም የሚሉት አስተያየት ሰጪው፤ የብሄር፣ ብሄረሰቦችን አንድነት ለመናድ፣ እርስ በእርስ ለማጣላት፣ የአገሪቱን በጎ ገጽታ ለማጠልሸት፣ በዓለም ላይ የሚታወቀውን የህዝቡን ሰላማዊ መስተጋብር ለማጥፋት ካልሆነ በስተቀር በእንዲህ አይነት ሁኔታ ስልጣን መያዝ እንደማይቻልም ይናገራሉ። ‹‹እኛ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ተባብረን ጸረ ሳላም ሃይሎችን እናጠፋለን፣ ሰላም እንዲሰፍን ሌት ተቀን እንሰራለን የሚሉት አቶ ገብረህይወት፤ እነርሱ ቢሞቱም የሚተኳቸው በርካታ ጀግኖች ማፍራታቸውን ይጠቁማሉ፡፡ ‹‹እነርሱ ሃላፊነታቸውን ይወጣሉ፣ አገራችንም አትደፈርም›› ይላሉ፡፡ ባለፉት ጊዜያት ለኢትዮጵያ ሲሉ በርካታ ጀግኖች መሰዋታቸውን በመጠቆምም፤ ጀግና እየተፈጠረ ኢትዮጵያ ቀጥላለች፡፡ ህዝቡ አንድነቱን አስከብሮ የአገሩን ሰላም ማስጠበቁንም ይቀጥላል ብለዋል፡ አዲስ ዘመን ሰኔ 20/2011 ", "passage_id": "9c53b18f648a8aaaafea9362f57db53d" }, { "passage": "ካፒቴን ተስፋይ አየር መንገድ የበረራ መምሪያ ኃላፊ በመሆን ለአምስት ዓመታት አገልግለዋል።\n\nካፒቴን ተስፋይ ወላጅ አባታቸው በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት በጁሩንድ (ገንዘብ ሚኒስቴር) ውስጥ የአገር ውስጥ ገቢ ሹም ስለነበሩ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር ነበር።\n\nማይጨው ከተማ ውስጥ የተወለዱት ካፒቴን ተስፋይ፤ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በተንቤንና መቀለ ተከታትለዋል። \n\nየሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በአፄ ዮሐንስ ትምህርት ቤት ተምረዋል። የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ጥሩ ውጤት በማምጣታቸው በ1966 ዓ. ም. ወደ አዲስ አበባ አምርተው ነበር። \n\nወቅቱ ንጉሡ ከሥልጣናቸው ወርደው ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት የተተካበት እና ሁኔታው ያልተረጋጋ ስለነበር ከወንድማቸው ውስ ጋር ቤትጥ ቁጭ ብለው ይውሉ እንደነበር ያስታውሳሉ።\n\nአንድ ቀን አንድ የጎረቤት ልጅ፣ ‘ፓይለት ለመሆን ስልጠና መወስድ የምትፈልጉ ተመዝገቡ’ የሚል ማስታወቂያ መለጠፉን ነገራቸው። \n\nየያኔው ተማሪ ተስፋይ ግን ብዙም ደስተኛ አልነበሩም። ቢሆንም ግን ቁጭ ብሎ ከመዋል ለምን አልሞክርም በሚል ለመወዳደር ማመልከታቸውን ያስታውሳሉ። \n\nበወቅቱ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአብራሪነት ስልጠና ወስዶ ለመቀጠር ካመለከቱት 600 ያህል ወጣቶች በፈተና ተጣርተው መጨረሻ ላይ 8 ልጆች አለፉ። ከእነዚህም መካከል አንዱ ተስፋይ ነበሩ።\n\nበዚሁ መልኩ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራቸውን አሀዱ ብለው ጀመሩ። \n\nካፒቴን ተስፋይ ሥራ ሲጀምሩ ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት የተረፉትን ‘ዲሲ ስሪ’ (ዳኮታ) አውሮፕላን ማብረር መጀመራቸውን ያስታውሳሉ። \n\nበኢትዮጵያ አየር መንገድ የተቀጠረ ጀማሪ አብራሪ ለአንድ ዓመት ረዳት አብራሪ በመሆን መሥራት ስለሚጠበቅበት ረዳት አብራሪ ሆነው አገልግለዋል።\n\nካፒቴን ተስፋይ፤ በአሁኑ ሰዓት ‘ትሪፕል ሰቨን’ (ቦይንግ 777) የሚያበሩ የድርጅቱ አንጋፋ ፓይለት ናቸው። \n\nአውሮፕላን አየር ላይ እንዴት 'መንሳፈፍ' ቻለ?\n\nአውሮፕላን ሰው ጭኖ እንደምን በአየር ላይ መንሳፈፍ ቻለ? በሚል ታዳጊ ልጆች መንደር ውስጥ ይከራከራሉ። አንዱ በክንፍ ታግዞ ነው የሚበረው ይላል። ሌላኛው ደግሞ በሞተር ምክንያት ነው የሚበረው ብሎ ይከራከራል። \n\nቀጥለው ለምን ዘበኛውን አንጠይቅም? በማለት አጠገባቸው የነበሩትን አዛውንት ጠየቁ። የተከራከሩበትን ርዕስና የየራሳቸውን ግምት በማቅረብ፤ አዛውንቱ ማንኛቸው ትክክል እንደሆኑ ፍርድ እንዲሰጧቸው በጽሞና ጠበቁ።\n\nአጋጣሚ ሆኖ ዘበኛው ‘ሁሉንም ነገር አውቃለሁ’ ባይ ስለነበሩ፤ ሁላችሁም ተሳስታችኋል በማለት የሚከተለውን መልስ ሰጡ።\n\nሁለት አጋንንቶች አሉ። አንዱ የመሬት ሁለተኛው ደግሞ የሰማይ በመባል ይከፈላሉ። መሬት ላይ ያለው ጋኔን አውሮፕላንዋን አንደርድሮ ከመሬት ያስነሳትና ‘ያዝ እንግዲህ ተቀበል’ ብሎ ሰማይ ላይ ላለው ጋኔን ያስረክበዋል። ሰማይ ላይ የቆየው ጋኔን ደግሞ አውሮፕላንዋን ይዞ ይበርና ልታርፍ ስትል አንተ ደግሞ በፊናህ ተቀበል ብሎ መሬት ላይ ላለው መልሶ ይሰጠዋል። \n\nአዛውምቱ “መልሱ ይህ ነው። በማታውቁት ነገር ጥልቅ አትበሉ” አሏቸው።\n\nካፒቴን ተስፋይ ይህንን ገጠመኝ አብዱል ከሚባል ጓደኛቸው የሰሙ ዕለት ፈገግ ማለታቸውን ይናገራሉ። \n\nዋናው የአውሮፕላኑ በአየር ላይ ያለ ችግር መንሳፈፍ ምስጢሩ ሞተርና ክንፍ ላይ የሚገኘው ‘ኤሮ ዳይናሚክ’ ነው ሲሉ ለቢቢሲ በአጭሩ መልሰዋል። \n\n45 ዓመታት በሰማይ ላይ\n\nቀደም ሲል በኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንብ መሠረት አንድ ካፒቴን 60 ዓመት ሲሞላው ጡረታ ይወጣል። አሁን ላይ ወደ 65 ዓመት ከፍ እንዲል መደረጉን ካፒቴን ተስፋይ ይገልጻሉ። \n\nበዚህ መሠረት ካፒቴኑ በያዝነው ጥቅምት ወር ውስጥ... ", "passage_id": "3770e500d5049822c369eb2ee0c6dbd3" } ]
cd1d26eb06bf39e7476e73b82224ece4
07df64fca5d4e5b970b1eb0f54cd4e58
የኢትዮጵያ ቨርቸዋል ሩጫ ተካሄደ
ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ያሳደረውን ተፅዕኖ መቀነስና መቀየር ይቻል ዘንድ በኢንተርኔት የታገዘ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት የቨርቿል ሩጫ ተካሄደ። በኢንተርኔት የታገዘ የቀጥታ ቪዲዮ «ቨርቿል ሩጫ» መርሐ ግብር በተሳካ ሁኔታ ከትናንት በስቲያ መካሄዱን የሩጫ አዘጋጁ የታላቁ ሩጫ በዋሽንግተን ዲሲ አስታውቋል። በቨርቹዋል ሩጫ መርሐ ግብሩ ላይ አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ገንዘቤ ዲባባ፣ ስለሺ ስህን፣ ፋጡማ ሮባ፣ ሚሊዮን ወልዴ እና እጅጋየሁ ዲባባ መሳተፋቸው ታውቋል። በውድድሩ አንድ ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ከመላው ዓለም ሆነው ዙም በተሰኘ መተግበሪያ ላይ በኢንተርኔት በቀጥታ እየተያዩ በቤታቸው እና ግቢያቸው ውስጥ ሆነው በመሮጥ እና ሶምሶማ በማድረግ ተሳትፈውበታል ተብሏል። የኢትዮጵያ ቨርቹዋል ሩጫ ዋና አዘጋጅ ዶክተር ጋሻው አብዛ ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት ፤ የኮቪድ-19 በሽታ በዓለም ዙሪያ ከፈጠረዉ የጤና ፈተና ጎን ለጎን፣ በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ኢኮኖሚያዊና ስነ ልቦናዊ ጫና አስከትሏል። በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ይህ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ ረዘም ላለ ጊዜ ቤት ውስጥ ለመቀመጥ ተገደዋል። በመሆኑም የወገኖቻችንን ችግር በተወሰነ መልኩ ማቃለል ይቻል ዘንድ በኢንተርኔት የታገዘ ቨርቿል ሩጫ ማዘጋጀት አስፈልጓል ብለዋል፡፡ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያዊያን በተለይ ደግሞ ወረርሽኙ በበረታባቸው አሜሪካና አውሮፓ የሚገኙ ኢትዮያዊያን ከተለመደው የአኗኗር ዘይቤ በወጣ ሁኔታ ረዘም ላለ ጊዜ ቤት ውስጥ ለመቀመጥ በመገደዳቸው ሥራን እንደ ወትሮው ወጥቶና ነፃ ሆኖ መሥራት አልተቻለም። ስለዚህ በበርካቶች ላይ ስጋትና የአዕምሮ ጭንቀት በመፍጠር ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ዶክተር ጋሻው፤ ጫናውን በተወሰነ ደረጃ ለመቀነስ የሚያግዝ በኢንተርኔት በቤትና ግቢ ውስጥ ሆነው የሚሮጡት የቨርቹዋል ሩጫ ተዘጋጅቶ በስኬት መከናወኑን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ቨርቹዋል ሩጫ ላይ አንጋፋና ብርቅዬ አትሌቶች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መሳተፍ የቻሉ መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ጋሻው ፤ከዝግጅቱ የተገኘው ገቢ በኮቪድ-19 ዙሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚሠሩ ሁለት መንግሥታዊ ያልሆኑና በኢትዮጵያዊያን ለሚመሩ አነስተኛ ድርጅቶች የሚበረከት መሆኑንም ተናግረዋል። በሩጫው ላይ አትሌቶች በያሉበት ቦታ ሆነው በቪዲዮ ተራ በተራ እየሮጡ ለውድድሩ በተዘጋጀ መተግበሪያ ላይ በቀጥታ በማህበራዊ ሚዲያ ከተሳታፊዎች ጋር ሩጫውን አካሄደዋል። ተሳታፊዎችም በቤትና ግቢ ውስጥ እንዲሁም የመሮጫ ማሽን ላይ በመሆን እየሮጡ በስልካቸው፣ በኮምፒዩተርና በሌሎች የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች በመታገዝ አትሌቶችን እየተከተሉ ሮጠዋል። በፌስቡክ እና ዩቲዩብ ላይቭ ላይ ከተለያዩ የዓለም ክፍል የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በተመሳሳይ ሰዓት በአንድ ላይ ሆነው በኢንተኔት በታገዘው ሩጫ ላይ ካሉበት ሆነው መሳተፋቸው ታውቋል። ቨርቹዋል ሩጫ (Virtual Race) የሚባለው ከየትኛውም ቦታ እና አካባቢ በመሆን የሚከናወን ሩጫ ወይንም ፈጠን ያለ የዕርምጃ ውድድር እንደማለት ነው።አዲስ ዘመን ግንቦት 11/2012ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=32673
[ { "passage": "በመጪው ጥቅምት በፖላንድ ጊዲኒያ በሚደረገው የ2020ቱ ግማሽ ማራቶን ውድድር የሚሳተፉ አትሌቶች ለመለዬት ዛሬ የማጣሪያ ሩጫ በሰንዳፋ ተካሂዷል።በማጣሪያው ላይ አስር ወንድና አስር ሴት አትሌቶች መሳተፋቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲከስ ፌዴሬሽን በማኅበራዊ ገጹ አስታውቋል፡፡በዚህ ውድድር የተካፈሉ አትሌቶች አምና በሀገር ውስጥ ከተደረገ ግማሽ ማራቶንና በኢንተርናሽናል ደረጃ ባላቸው ውጤት የተመረጡ መሆኑንም ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡መነሻውን ከበኬ ከተማ ወጣ ብሎ ፍፃሜውን ሰንዳፋ ከተማ ባደረገው የ15 ኪሜ የማጣሪያ ውድድር በሴቶች➊ኛ የለም ዘርፍ የኋላ 50:14.87❷ኛ ነፃነት ጉደታ 50:17.45❸ኛ ዘይነባ ይመር 50:29.80❹ኛ አባ በል የሻነህ 50:38.10❺ኛ መሰረት ጎላ 50:59.13❻ኛ መድህን ገ/ስላሴ 51:14.10በወንዶች➊ኛ ሀይለማርያም ኪሮስ 42:58.55❷ኛ አንዱዓምላክ በልሁ 43:02.36", "passage_id": "253e131424e02e688a0dd22ba0f4b624" }, { "passage": "የኢትዮጵያ\nህክምና ማህበርና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት 4 ኛው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ውድድር ‹‹ለደኅንነታችን እንሩጥ›› በሚል መሪ ቃል እሁድ የካቲት 17 ቀን 2011 ዓ. ም. ይካሄዳል። የውድድሩ ቅድመ ዝግጅትን በተመለከተ በትናንትናው ዕለት በፌደሬሽኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተሰጠው መግለጫ ወቅት የኢትዮጵያ የህክምና ማህበር ፕሬዚዳንት ዶክተር  ገመቺስ ማሞ፤ማህበሩ\nመርሀ ግብሩን ላለፉት ሶስት  ዓመታት ከታላቁ\nሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር እና ከዓመታዊ ሀክምና ጉባኤው ጋር በማቀናጀት ሲያዘጋጅ ቆይቷል። በዘንድሮው ዓመትም ይህንን መርሀ ግብር ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማካሄድ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ዘንድሮ ለ4ተኛ ጊዜ‹‹ለደህንነታችን እንሩጥ››የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ውድድር ይካሄዳል ብለዋል ። የህብረተሰቡን ጤና ተላላፊ  ካልሆኑ በሽታዎች  ለመከላከልና ለመቆጣጠር\nዋነኛ ዘዴዎች መካከል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማጎልበት ጤናን መጠበቅ መሆኑን ማሳወቅ፤ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በሰፊው በመስራት ለአትሌቲክሱ እድገት ድርሻ ማበርከት የውድድሩ አላማ መሆኑን አስረድተዋል።« በውድድሩ 2ሺ ስድስት መቶ ተሳታፊዎች እንደሚኖሩ የገለጹት ዶክተር ገመቺስ፤ከእነዚህ ውስጥ ከአስር ክለቦች የተውጣጡ  100 ሴትና ወንድ አትሌቶች እንዲሁም 2ሺ 500 \nየህክምና ባለሙያዎች ናቸው» ሲሉ አስረድተዋል።  በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑ እንደየ አሸናፊነታቸው የተዘጋጀ የገንዘብና የሜዳሊያ ሽልማት ይኖራል። በሁሉም ጮታ ካታጎሪ ለሚሳተፍ በክለብ ተመዝግበው ለሚወዳደሩ አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለሚወጡ የሜዳሊያ ሽልማት ተዘጋጅቷል። እንዲሁም ከ1ኛ እስከ 6ኛ ለሚወጡት ከ15 ሺ እስከ 1ሺ ብር በየደረጃው የገንዘብ ሽልማት የሚበረከትላቸው ይሆናል። በሁሉም የጾታ ካታጎሪ ለሚሳተፍ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለሚወጡትም የወርቅ፣ብርና ነሀስ ሜዳሊያ እንደሚበረከትላቸው በመግለጫው ላይ ተገልጿል። የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ውድድር መነሻውና መድረሻው መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ በማድረግ እሁድ የካቲት 17 ቀን 2011 ዓ. ም. በድምቀት የሚካሄድ ይሆናል።አዲስ ዘመን የካቲት 14/2011ዳንኤል\nዘነበ", "passage_id": "aff1f0ba806fb939defee3a57dc971ad" }, { "passage": "በመክፈቻው\nዕለት በመም እና በሜዳ ላይ ተግባራት ሀገር አቀፍ ክብረወሰን በመስበር የተጀመረው፤ 48ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል። ከሰዓት በኋላ በሚኖረው መርሃ ግብርም ስድስት የፍጻሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ። ከትናንት በስቲያ በተጀመረው በዚህ ሻምፒዮና ላይ ጠዋት እና አመሻሽ ላይ የተለያዩ የማጣሪያ እና የፍጻሜ ውድድሮች ተካሂደዋል። ጠዋት በተካሄደው የወንዶች ሱሉስ ዝላይ የፍጻሜ ውድድር የመከላከያው አትሌት አዲር ጉር፤ 15 ነጥብ 88 ሜ በመዝለል በራሱ ተይዞ የቆየውን ክብረወሰን አሻሽሏል። የኢትዮጵያ\nንግድ ባንኩ ቡኒኒ አንበሴ እና የሲዳማ ቡናው ጆሴፍ ኦባንግ ደግሞ እርሱን ተከትለው የሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን የያዙ አትሌቶች ሆነዋል። በዕለቱ የተካሄደው ሌላኛው የፍጻሜ ውድድር ደግሞ የሴቶች አሎሎ ውርወራ ነው። በዚህ ውድድር ላይም ዙርጋ ኡስማን ከሲዳማ ቡና፣ አመለ ይበልጣል ከመከላከያ እንዲሁም ሰላማዊት ማሬ ደቡብ ፖሊስ ቀዳሚውን ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል። አመሻሽ ላይም በወንዶች እና ሴቶች የ10ሺ ሜትር ውድድሮች ተካሂደዋል። አስቀድሞ\nበተደረገው የወንዶች ውድድር ላይም በ87 አትሌቶች መካከል ከፍተኛ ፉክክር የተካሄደ ሲሆን፤ ወጣቱ አትሌት ሰለሞን ባረጋ አሸናፊ ሆኗል። አንዱዓለም በልሁ እና አባዲ ሀዲስ ደግሞ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ የብር እና ነሃስ ሜዳሊያ ተሸላሚዎች ሆነዋል። ሌላኛው ከፍተኛ ፉክክር የተካሄደበትና ሀገር አቀፍ ክብረወሰንም የተሻሻለበት ውድድር በሴቶች መካከል የተካሄደው ነው። ታዋቂ አትሌቶችን ጨምሮ ከ54 በላይ አትሌቶች የተሳተፉበትን ውድድርም የትራንስ ክለብ አትሌት የሆነችው ለተሰንበት ግደይ 32 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ ከ13 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት ሸፍናለች። አትሌት\nፀሐይ ገመቹ እና ነፃነት ጉደታ ደግሞ በማይክሮ ሰከንዶች (32:17.20 እና 32:17.82 በሆነ) ተቀዳድመው ውድድራቸውን አጠናቀዋል። ትናንት በሁለተኛው ቀንም የተለያዩ ውድድሮች ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል። በሱሉስ ዝላይ የሴቶች ፍፃሜ ውድድርም፤ የመከላከያዋ አጁዳ ኡመድ፣ የንግድ ባንኮቹ አራያት ዲቦ እና አማር ኡባንግ አሸናፊዎች ሆነዋል። በወንዶች 400 ሜትር ደግሞ አብዱራህማን አብዱ ኦሮሚያ ክልል፣ ኤፍሬም መኮንን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ፣ ሙስጠፋ ኢደኦ ከኦሮሚያ ክልል ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል። በ100\nሜትር የወንድ እና የሴት ውድድሮችም በትናንትናው ዕለት የተፈጸሙ ሲሆን፤ የትኛው አትሌት እንደቀደመ መለየት እስኪያዳግት ድረስ እጅግ ከፍተኛ ፉክክር የታየበትም ነበር። በሴቶች በተካሄደው ውድድርም ወርቄ ኩማሎ ከንግድ ባንክ፣ ሰዓዳ ሲራጅ ከመከላከያ እንዲሁም አቤቤ ከበደ ከኦሮሚያ ክልል በማይክሮ ሰከንዶች ልዩነት ገብተዋል። በወንዶች\nበተካሄደው ውድድር ደግሞ የኤሌክትሪኩ ናታን አበበ፣ የሲዳማ ቡናው ቴዎድሮስ አጥናፉ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልሉ አብዱልሰታር ከማል አሸናፊዎች ሆነዋል። ዛሬ 9 ሰዓት ላይ በሚጀምረው የሶስተኛ ቀን መርሃ ግብር ላይም የወንዶች ዲስከስ ውርወራ፣ የሴቶች የርዝመት ዝላይ፣ የሴትና ወንድ 400 ሜትር መሰናክል እንዲሁም በሁለቱም ጾታ የ800 ሜትር ውድድር የሚካሄድ ይሆናል።አዲስ\nዘመን  ግንቦት 1/2011በብርሃን\nፈይሳ", "passage_id": "0eed3a41c94875c78c0733c3fb33851b" }, { "passage": "ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝጅግት በቦክስ ስፖርት ኢትዮጵያን የሚወክሉ የቡጢ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ ከወዲሁ ዝግጅት ተጀምሯል፡፡ ከትናንት በስቲያ በአዲስ አበባ ስታዲየም የዚሁ ዝግጅት አካል የሆነ ውድድርም ተካሂዷል፡፡ ከዚህ ውድድር የሚመረጡ ስፖርተኞችም ከየካቲት 9 እስከ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር በሚካሄደው የአፍሪካ ቦክስ ቻምፒዮና ላይ በመሳተፍ ወደ ቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚወስዳቸውን ውጤት ለማስመዝገብ የሚፋለሙ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ያዘጋጀው ይህ የብሔራዊ ቡድን\nምርጫ የቦክስ ውድድር በአዲስአበባ ስታዲየም በደማቅ ሁኔታ ሲካሄድ በውድድሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ የቦክስ ተወዳዳሪዎች በሁሉም ኪሎ\nካታጎሪ የተዘጋጁትን ውድድሮች ማሸነፍ ችለዋል።በውድድሩ ከ52 እስከ 75 ኪሎ ግራም ስድስት ጨዋታዎች\nየተደረጉ ሲሆን፣ በ52 ኪሎ ግራም የአዲስ አበባ ፖሊሱ ዳዊት በቀለ ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ቦክሰኛው ያዕቆብ በለጠ ጋር ተገናኝተው\nዳዊት ማሸነፍ ችሏል፡፡ በ57 ኪሎ ግራም የድሬዳዋ ብቸኛ ተወካይ የሆነው አብዱልሰላም አቡበከር ከአዲስአበባ ፖሊሱ ፍቅረሰላም ያደሳ\nጋር ተገናኝተው ብርቱ ፋክክር ቢያደርጉም ፍቅረሰላም ያደሳ አሸናፊ መሆን ችሏል።በ63 ኪሎ ግራም የአዲስ አበባ ፖሊስ ተወዳዳሪ አብርሃም ዓለም የፌዴራል ፖሊሱን ተጋጣሚ ሲያሸንፍ ፤ በተመሳሳይ በ69\nኪሎ ግራም የአዲስ አበባ ፖሊሱ መስፍን ብሩ የፌዴራል ፖሊሱን ቢኒያም ተስፋዬን አሸንፏል። በመጨረሻ በተካሄደው 75 ኪሎ ግራም\nውድድር የአዲስ አበባ ፖሊሱ ተመስገን ምትኩ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ተጫዋች ከሆነውን ባምላኩ ደጉ ጋ ተጋጥሞ በዳኛ ውሳኔ ማሸነፍ\nችሏል።በሌላ በኩል በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል በተካሄደው የ63 ኪሎ ግራም የወዳጅነት ውድድር ኢትዮጵያዊው ካሳሁን ሀይሉ\nእና ቢኒያም ተስፋጋብር ተገናኝተው ካሳሁን ሀይሉ በጠባብ ውጤት አሸንፏል።በውድድሩ በርካታ የቦክስ አፍቃሪያን ተገኝተው የተከታተሉት ሲሆን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሸን ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር ፣\nየኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን አመራሮችና ሌሎች እንግዶች በውድድሩ ቦታ በመገኘት ጨዋታዎችን ተከታትለዋል፡፡ ለአሸናፊዎችም ኮሚሽነር\nኤሊያስ ሽኩር እና ሌሎች እንግዶች የሜዳልያ ሽልማት አበርክተዋል።የውድድሩ ዋና ዓላማ በሴኔጋል\nዋና ከተማ ዳካር ከየካቲት 9/2012 ዓ.ም ጀምሮ የ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ጨዋታ ለሚካሄደው የአፍሪካ ማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያን\nየሚወክሉ ስፖርተኞችን ለመምረጥ ነው። በዚህም መሠረት በውድድሩ አሸናፊ የሚሆኑ ቦክሰኞች በቀጥታ ወደ ዳካር እንደሚያቀኑ ይጠበቃል፡፡አዲስ ዘመን  ጥር 10/2012ቦጋለ አበበ", "passage_id": "0705c1c3e2345c10d3643df3aee2e7c5" }, { "passage": "“ለፋሲል እንሩጥ” በሚል መርህ በደጋፊዎች ማኅበር የተዘጋጀዉ የገቢ ማሰባሰብያ ታላቁ ሩጫ ዛሬ ከ 6000 እስከ 6500 የሚገመቱ የዐፄዎቹ ደጋፊዎች ተሳትፈውበት በጎንደር ከተማ ተከናውኗል።ጎንደር ከተማ ከነበረው ወቅታዊ ሁኔታ እና የመሮጫ ማልያ ሽያጭ የታሰባውን ያህል ገቢ ባለማስገኝቱ በተደጋጋሚ ለማራዘም የተገደደው ይህ ሩጫ በዛሬው ዕለት በተሳካ ሁኔታ ታካሂዷል። ከጠዋቱ 2:00 ላይ የህፃናቶች ሩጫ ተካሂዶ ከ1-10 ለወጡ ህፃናት የቦርሳዎች ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን በአዋቂዎች ቀድመው ሩጫውን ለጨረሱ 1000 ሜዳልያዎች በሽልማትነት ተበርክቶላቸዋል።ከዛሬው ውድድር የሚገኝውን 70 በመቶ ገቢ ለቡድኑ እንደሚያስረክብ የቀረውን 30 በመቶ ደግሞ ለሰራተኛ ደሞዝ እና ለስራ ማስኬጃ እንደሚውል ከቅናት በፊት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።በዘንድሮው የውድድር ዓመት በርካታ የገቢ ማሰባሰቢያዎችን ያደረጉት የዐፄዎቹ የደጋፊዎች ማኅበር ከዛሬው ታላቁ ሩጫ በተጨማሪ የንግድ ትርዒት እና የሙዚቃ ኮንሰርት አዘጋጅተዉ እንደነበር ይታወሳል ።", "passage_id": "419955c29558fabc96dd73ebc53522ed" } ]
95ad2208ea229ea528eb497af03d874b
c906c640a35645044bc92f96bce009a4
በመተከል ዞን እየተወሰደ ባለው የህግ ማስከበር ዕርምጃ የታጠቁ ኃይሎች እጃቸውን እየሰጡ ነው
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ(ኢዜአ):- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን እየተወሰደ ባለው የህግ ማስከበር ዕርምጃ በርካታ የታጠቁ ኃይሎች እጃቸውን ለጸጥታ ኃይሉ እየሰጡ መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ኃይል አስታወቀ።የህግ ማስከበርና የፀጥታውን ዘርፍ በበላይነት የሚመሩት ሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ፤ የጥፋት ቡድኑ በመተከል ዞን በተለይም ቡለንና በቆጂ ወረዳዎች ዜጎችን በመግደል፣ ንብረት የመዝረፍና የማቃጠል አረመኔያዊ ተግባር መፈፀሙን አስታውሰዋል።የተጠናከረ ዘመቻ በማካሄድ በአካባቢው ህግ በማስከበር ሰላምን ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረት በርካታ የታጠቁ ኃይሎች እጃቸውን እየሰጡ መሆኑን ጠቅሰዋል።ታጣቂ ቡድኑ ቀደም ሲል የፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ ስጋት አድሮባቸው መኖሪያቸውን ለቀው የነበሩ ዜጎችም ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆኑን ሌተናል ጀኔራል አስራት ገልጸዋል።ግብረ ኃይሉ አካባቢውን ከተረከበ በኋላ በተለይ ስጋት ተፈጥሮባቸው የነበሩ አካባቢዎችን በማረጋጋት ወደ ተሻለ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረዋል።በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪና የኮማንድ ፖስቱ የፖለቲካና ህዝባዊ ውይይቶች መሪ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በዜጎች ላይ ጥቃት የፈፀመውን ታጣቂ ቡድን የማደን ሥራ መቀጠሉን ገልጸዋል።የተፈፀመውን ጥቃት በመምራትና በማስተ ባበር የተጠረጠሩና ጥቃቱን መከላከል ሲገባቸው ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ አመራሮች ላይ ህጋዊና ፖለቲካዊ ዕርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።የጥፋት ቡድኑን ዓላማ ያልተቀበሉ የጉሙዝ ማህበረሰቦችን ጨምሮ በተለያዩ የማህበረሰብ አካላት ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወት ማጥፋት፣ አካል ማጉደልና ንብረት ማውደም መፈፀሙን አቶ ተስፋዬ ገልጸዋል።ችግሩ እኩይ ዓላማ ያላቸው ኃይሎችን ብቻ የሚመለከት መሆኑን ጠቅሰው፤ “በዘላቂነትመፍትሔ ለማበጀት ግብረ ኃይሉ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በቅንጅት እየሠራ ነው” ብለዋል።ለተፈናቀሉ ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ የማድረስና ወደ ቀዬአቸው መልሶ የማቋቋም ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም አቶ ተስፋዬ ገልፀዋል።በሂደቱ የሰላምና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚያግዙ ህዝባዊ ውይይቶች እንደሚካሂዱም አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 24/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=38672
[ { "passage": "በቤንሻንጉል ጉሙዝ  ክልል  በመተከል  ዞን  በአማራ  ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለውን  ዘርን መሠረት ያደረገ ጭፍጨፋ፣  የፌዴራል መንግሥት ሥራ በዝቶበት ከሆነና ማስቆም ካልቻለ፣ የአማራ ክልል መንግሥት ጥቃቱን ለማስቆምና ሕግ ለማስከበር ዝግጁ መሆኑን ገልጾ፣ ይሁንታን ለማግኘት ሐሳብ ማቅረቡን አስታወቀ፡፡‹‹በመተከል ዞን እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ የቤንሻንጉል ክልል ባለሥልጣናት ቀን ቀን ስብሰባ ላይ ከእኛ ጋር ሲላቀሱ ይውላሉ፡፡ ማታ ማታ ግን ግድያውን ማስቆም አልቻሉም፤›› በማለት የተናገሩት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ናቸው፡፡በመተከል ዞን በአማራ ተወላጆች ላይ ዘር እየተመረጠ በየትኛውም ዓለም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ዘግናኝና ጭካኔ በተሞላበት ድርጊት ሰዎች ሲገደሉ፣ የፌዴራል መንግሥት ግዴታና ኃላፊነቱን ካልተወጣ የአማራ ክልል የፀጥታ ኃይል ዝግጁ እንደሆነ ኮሚሽነር አበረ ለሪፖርተር ገልጸዋል።ኮሚሽነሩ  የችግሩን ቀጣይነት አስመልክተው ሲያብራሩ፣ ከአካባቢው አመራሮች ጋር በተደጋጋሚ ውይይት የተደረገ ቢሆንም፣ ‹‹የችግሩ መንስዔዎች ቀን ቀን አብረውን ስብሰባ ላይ ሲላቀሱ ውለው፣ ማታ ግድያውን ማስቆም የተሳናቸው የሕወሓት ርዝራዦች ናቸው፤›› ብለዋል።‹‹አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች የሚገደሉት አማራ ተብለው ስለሆነ ምናልባት የፌዴራል መንግሥት ሥራ በዝቶበት ከሆነ፣ ለእኛ ይስጠን ብሎ ክልሉ ለፌዴራል መንግሥት ሐሳብ አቅርቧል፤›› ሲሉ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።አንድ ክልል የራሱን የፀጥታ ችግር ማስከበር ካልቻለ የፌዴራል መንግሥት ኃላፊነትና ግዴታ አለበት ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ‹‹አቅጣጫ ያስቀምጥልን፣ ሕዝባችን እንታደግ፤›› ሲሉም የፌዴራሉን መንግሥት ጠይቀዋል።‹‹እንደ ክልል ልናደርግ የምንችለው ወደ ፌዴራል መንግሥት አቤት ማለት ነው፡፡ ነገር ግን አሁንም በአማራ ክልል በኩል የሕዝብን ደኅንነት ለማስጠበቅ ዝግጁ ነን፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡የፌዴራል መንግሥት ከፈቀደ ‹‹የአማራ ክልል የአቅም ውስንነት የለበትም›› ያሉት ኮሚሽነር አበረ፣ በሕወሓት ኃይሎች ላይ እንደተደረገው ዘመቻ ከመከላከያ ጋር በመሆን ሥራውን ለማከናወን ፍላጎት እንዳለ ተናግረዋል፡፡ኮሚሽነሩ አክለውም በአገሪቱ ሕገ መንግሥት መሠረት ሁሉም ኢትዮጵያዊ  ማንም  ይሁን ማን፣ በየትኛውም ቦታ እኩል የመኖር መብት አለው ብለዋል። ‹‹ነገር ግን በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ውስጥ ያሉ የወያኔ ተላላኪዎች ሰው ሲገደል ከመከላከል ይልቅ፣ ለምን ተገደለ ብላችሁ ጠየቃችሁን ብለው ያኮርፋሉ፡፡ እንዲህ ዓይነት አካላት የተሰባሰቡበት የአመራር ቡድን በመሆኑ የሰውን ሕይወት ለመታደግ ሲሠሩ አይታዩም፤›› ብለዋል። የአማራና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በጉዳዩ ላይ እየመከሩ እንደሆነ የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ ‹‹ለችግሩ መፍትሔ ያመጣሉ ብለን እናስባለን፡፡ ነገር ግን እንደ ክልል የፀጥታ ኃይል ትዕዛዝ እየተጠባበቅን እንገኛለን፤›› ብለዋል።", "passage_id": "f2b533b95051db756f9d4476f8907643" }, { "passage": "የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን ክልሉ ውስጥ ያሉ ታጣቂዎች መሣሪያ እንዲፈቱ ያሳሰቡበት ቀነ ገደብ ቢጠናቀቅም እጅ የሰጠ የለም ሲሉ የክልሉ ኮሙኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ አሳውቀዋል።የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ አሁንም በሩ ክፍት ስለሆነ ማንኛውም ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ኃይል ለመንግሥት እጅ ሊሰጥ ይችላል ብለዋል።በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 23 ታጣቂዎች ዛሬ በመተከል ዳንጉር ወረዳ ተደምስሰዋል ሲሉ ኃላፊው ገልፀዋል።\n", "passage_id": "1b3bad3213c4b63e1040f1f0d8e0b1eb" }, { "passage": "የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን በመተከል ዞን የሚንቀሳቀሱ የህወሓት ጥፋት አስፈጻሚ ርዝራዦች እጃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ እስከ አሁን እጅ የሰጠ እንደሌለ የክልሉ ኮሙኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት አሳወቀ።የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ እጅ ለመስጠት የተሰጠው ጊዜ አንድ ሳምንት በመሆኑ አሁንም በተቀሩት ቀናት እነዚህ የጥፋት ሃይሎች እጃቸውን በሰላማዊ መንገድ ይስጡ ሲሉም አሳስበዋል።\n", "passage_id": "a534d403468c8e595f1600921b1e8cb2" }, { "passage": "አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመተከል ዞን በዜጎች ላይ በተደጋጋሚ የሚደርሰው ጭፍጨፋ ሀገርን ለማፍረስ ከሚደረገው እኩይ ዓላማ የተለየ ባለመሆኑ በድርጊቱ የተሰማሩ የጥፋት ተዋንያኖችን በፍጥነት አድኖ ለሕግ የማቅረብ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ።", "passage_id": "e62eefbfb88f5f5b67ae99d1215f6db1" }, { "passage": "በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ ፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን 23 የጸረ ሠላም ኃይሎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የዞኑ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ።የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ኮሎኔል አያሌው በየነኝ ጠቅሶ እንዳስታወቀው ፣ በዞኑ ዳንጉር ወረዳ ልዩ ስሙ ቁጥር 3 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሠላምን ሲያውኩ በነበሩ ኃይሎች ላይ በተወሰደው እርምጃ 23 ጸረ-ሠላም ኃይሎች ተደምስሰዋል ።የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የክልሉ የጸጥታ አካላት በወሰዱት እርምጃ ከተደመሰሱት የጸረ-ሠላም ኃይሎች በተጨማሪ ለጥፋት ሲጠቀሙበት የነበረ ሶስት የጦር መሣሪያ በቁጥጥር ስር ውሏል።በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የጥፋት ቡድን በሠላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጥ በክልሉ መንግሥት ጥሪ መቅረቡን ያስታወሱት ኮሎኔል አያሌው ፣ በተሰጣቸው እድል መጠቀም ካልቻሉ በዋናው ጁንታ ላይ የተወሰደው አይነት የማያዳግም እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።ህብረተሰቡም እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የአካባቢውን ሠላም በተደራጀ መንገድ በመጠበቅ ረገድ የጀመረውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ።አዲስ ዘመን ህዳር\n30/2013", "passage_id": "d7cb4187783600e58e161037eb074f58" } ]
349e2fc3a305e3323bae14796ed2f9e6
2e5a56a38898fa53cc0db39853f93dbd
የበርሊን ማራቶን ላይካሄድ ይችላል
በርካታ የማራቶን የዓለም ክብረወሰኖች የሚሻሻሉበት የበርሊን ማራቶን በዚህ ዓመት የመሰረዝ ወይም የመራዘም እድል ያልገጠመው ብቸኛው ውድድር ነው ማለት ይቻላል። ይህ ታላቅ የማራቶን ውድድር የኮሮና ቫይረስ በዓለም ላይ ከመከሰቱና ከመስፋፋቱ አስቀድሞ መስከረም ወር ላይ በመካሄዱ የሌሎቹ ታላቅ ውድድሮች እጣ ፋንታ ሳይገጥመው ቀርቷል። ያም ሆኖ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እስካሁን የሚያቆመው ባለመኖሩና ወደ ፊትም መፍትሄ ማግኘቱ አጠራጣሪ እየሆነ በመምጣቱ በቀጣዩ መስከረም የበርሊን ማታሪን የመካሄዱ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኗል። የውድድሩ አዘጋጆች ሰሞኑን እንደጠቆሙትም ውድድሩን በተለመደው ወቅት ለማካሄድ እስካሁን ውሳኔ ላይ መድረስ አልቻሉም። ውድድሩን ለማካሄድ ወይም ለማራዘም ውይይት እየተደረገ ሲሆን ውሳኔ ላይ ለመድረስ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው አሳውቀዋል። የጀርመን መንግስት በኮሮና ቫይረስ ስጋት እስከ መጪው ጥቅምት ወር መጨረሻ ከአምስት ሺ ሰው በላይ የሚሰበሰብባቸው ማንኛቸውም መርሃግብሮች ማገዱን ተከትሎ የውድድሩ አዘጋጆች ውሳኔ ላይ ለመድረስ እንደተቸገሩ ጠቁመዋል። እንደ በርሊን ማራቶን ሁሉ ዋነኞቹ የዓለማችን የማራቶን ውድድሮች የሆኑት የቦስተንና የለንደን ማራቶን ውድድሮችም በተመሳሳይ ምክንያት መካሄድ ከነበረባቸው ወቅት የመራዘም እድል እንደገጠማቸው ይታወሳል። የበርሊን ማራቶን አዘጋጆች ውድድሩ ካለው ስፋትና ከሚያሳትፈው የሰው ብዛት አኳያ የሚካሄድበት እድል መኖር አለመኖሩን በማጥናት ላይ የሚገኙ ሲሆን ውሳኔ ላይ ለመድረስም የተወሰነ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው አሳውቀዋል። ለዚህም የውድድሩ አዘጋጆች አሁን ላይ በቫይረሱ ስጋት የተነሳ በሙሉ ሃይላቸው ተገናኝተው መስራት አለመቻላቸው አንዱ እንቅፋት መሆኑን ገልፀዋል። በርካታ የዓለም ክብረወሰኖች የሚመዘገቡበት የበርሊን ማራቶን 2018 ላይ ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ 2፡1፡39 የሆነ አዲስ የዓለም ክብረወሰን በርቀቱ እንዳስመዘገበበት ይታወሳል። ባለፈው መስከረም ደግሞ ቀነኒሳ በቀለ ይህን ክብረወሰን ለማሻሻል በሁለት ሰከንድ የዘገየ ሰዓት ማስመዝገቡ አይዘነጋም። ከቀናት በፊት የወጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት በጀርመን ከ172 ሺ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ከ7600 በላይ የሚሆኑ ሕይወታቸው ማለፉ ታውቋል። ይህም የ2020 በርሊን ማራቶን ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ከማሳደሩ ባለፈ እንዲሰረዝ ወይም እንዲራዘም ሊያደርገው እንደሚችል ስጋት ፈጥሯል። አዲስ ዘመን ግንቦት 9/2012 ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=32529
[ { "passage": " ኢትዮጵያዊው ሹራ ኪጣታ በትናንትናው ዕለት በተደረገው የለንደን ማራቶን ባለ ድል ሆኗል። ሌላኛው የሀገሩ ልጅ ቀነኒሳ በቀለ በውድድሩ እንደማይሳተፍ በዋዜማው ማስታወቁን ተከትሎ የዚህ ውድድር አሸናፊ ይሆናል ተብሎ የተጠበቀው ኬንያዊው የተከታታይ ድሎች ባለቤት ኤልዩድ ኬፕቹጌ ነበር።ሆኖም የ24 ዓመቱ ሹራ ቂጣታ የውድደሩ ግርምት ሆኗል̀። 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ በሆነ ሰዓት ኬንያዊውን ቪንሰንት ኪፕቹምባን አስከትሎ አሸንፈዋል። የሀገሩ ልጆች የሆኑት ሲሳይ ለማ ፣ ሞስነት ገረመው ፣ሙሌ ዋሲሁን እና ታምራት ቶላ ከሶስተኛ እስከ ስድስተኛ ደረጃ ያለውን ስፍራ በመያዝ ተከተለው ገብተዋል። የለንደን ቀዝቃዛ አየር ሁኔታ ውድድሩን ፈታኝ እንዳደረገው ተጠቁሟል።ከ2013 የጎረጎሳዊያን ዘመን ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳያሸንፍ የቀረው የ35 ዓመቱ ኤልዩድ ኪፕቹጌ በቅዝቃዜው ምክንያት ጆሮው መደፈኑን የኃላ ኃላ ደግሞ እንዳያንቀሳቀስ ወደ አገደው ህመም ስሜት ማደጉን በምክንያትነት አቅርቧል።የዛሬ ሁለት ዓመት በተደረገው የለንደን ኦሎምፒክ ላይ ሁለተኛ ወጥቶ የነበረው ሹራ ቂጠታ በበኩሉ ለአሁኑ ድሉ -በውድድሩ ላይ እንደማይሳተፍ በመጨረሻው ሰዓት ያስታወቀውን ቀነኒሳ በቀለን አመሰግኗል።\"ቀነኒሳ ለዚህ ውድድር ሲያግዘኝ ነበር። እንዴት መሮጥ እንዳለብኝም መክሮኛል\" ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል።ከተሳተፋባቸው 13 ማራቶኖች 12ቱን በድል ያጠናቀቀው ኪፕቾጌ በበኩሉ መሸነፉን በጸጋ መቀበሉን በቲዊተር ገጹ አስታውቆ -ወደ ውድድሩ ግን እንደሚመለስ አስታውቋል።በዚሁ ዕለት ቀደም ብሎ በተደረገው የሴቶች ማራቶን ውድድር ኬንያዊቷ ብሪጊድ ኮስጌ 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ በሆነ ጊዜ አሸንፋለች።አሜሪካዊቷ ሳራ ሀል ሁለተኛ ኬንያዊቷ ሳራ ቺፕንጌትች ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን ተቆናጠዋል።የዘንድሮው የለንደን ማራቶን ሊከናወን ቀጠሮ የተያዘለት በሚያዚያ ወር ላይ ነበር። ኮቪድ 19 ሁኔታዎችን በመቀየሩ ወደ ጎረጎሳዊያኑ ጥቅምት ወር ተገፍቷል። ለወትሮው በሺዎች የሚቆተሩ ተሳፊዎችን ይዞ በጎዳናዎች ላይ ይደረግ የነበረው ውድድር ዘንድሮ ሴንት ጀምስ በተሰኘው የከተማዋ መነፈሻን 20 ጊዜ በመዞር ተፈጽሟል።40ሺ ተሳታፊዎች በመረጡት ስፍራ በያሉበት በርቀት ሮጠዋል። ውድድሩን በመጨረሳቸውም ኦፌሴላዊ ሜዳሊያ ይቀበላሉ።የሚያዚያ ውድድር በመሰረዙ ምክንያት ኢኮኖሚያዊ ችግር ለገጠማቸው ግብረሰናይ ድርጅቶችም በሚሊየኖች የሚቆጠር ገንዘብ ይሰባሰባል ተብሏል።ዘገባው የሮይተርስ ነው።-የህንድ ክሪኬት ፕሪሜር ሊግ ተጨዋቾች የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ አምራቾችን የንግድ ምልክት በመለዮቸው ላይ አትመው ለመጫወት ተስማምተዋል።ቅዳሜ በሚጀመረው የውድድር ወቅት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጀምሩ የተዋቀ ሲሆን እርምጃው የወር አበባን በተመለከተ በሀገሬው ዘንድ ያለውን የተሳሳተ ምልከታ ለመዋጋት እንደሚያግዝ ተስፋ ተጥሎበታል።ራጃስታን ሮያልስ የተባለው ቡድን የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ከሚያመርተው ኒኒ ኪባንያ ጋር ስምምነት በመፈጸም የመጀመሪያው ቡድን ሆኗል።«ይሄ ርዕስ በህንድ እና በብዙ የዓለማችን ሀገራት ነውር ነው። ህንድ ውስጥ ጉዳዩን በተመለከተ አጠቃላይ የግንዛቤ ችግር አለ።ወንዶች ብቻ ሳይሆን ወንዶች ላይም » ብለዋል የክለቡ የእንቅስቃሴ(ስምሪት) ሃላፊ ።በደቡብ እስያ ለሚኖሩ ሴቶች፣ በተለይ ለታዳጊ ወጣት ሴቶች- የወር አበባ ጉዳይ የሚያሳፍር እና ምቾት የማይሰጥም ነው።\n ", "passage_id": "a169b507e7fd9c9bd74574731c522b8d" }, { "passage": " በማራቶን የዓለም የሁለት ጊዜ ቻምፒዮኑ ኬንያዊ ኢሉድ ኪፕቾጌ በሳምንቱ መጨረሻ ማራቶንን ከ2ሰዓት በታች የመግባት ሙከራውን በኦስትሪያ ቬና ያደርጋል። ኪፕቾጌ እ.አ.አ በ2018 የበርሊንን ማራቶን የገባበት 2፡01.39 የሆነ ሰዓት የዓለም ክብረወሰን ሲሆን፤ ይህንን በማሻሻል 1ሰዓት ከ59 ደቂቃ የመግባት ሙከራ ያደርጋል። አትሌቱ ለሙከራው እንዲሁም «የሰው ልጅ ዓቅም አይወሰንም» የሚለውን አባባል በተግባር ለማሳየት የሚችልበት አቋም ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል። ናይኪ የተባለው የስፖርት ትጥቅ አምራች የተያዘው ይህ ፕሮጀክት ሙከራውን ከዓመታት በፊት የጀመረ ሲሆን፤ ዛሬ በቬና በያዘው ቀጠሮም ይሳካል የሚል እምነት አሳድሯል። አትሌቱ ለሩጫው ያመቸው ዘንድ ልዩ የመሮጫ ጫማ የተዘጋጀለት ሲሆን፤ ከተማዋም በዛፍ የተከበበችና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ያላት በመሆኑ አትሌቱ ያሰበውን ለማሳካት ይረዳዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት አትሌቱ በጣሊያኗ ሞንዛ ከተማ ባደረገው ሙከራ በ26 ሰከንዶች ዘግይቶ ዓላማውን ማሳካት አልቻለም ነበር፤ አሁን ግን የከተማዋ የቦታ አቀማመጥ እንዲሁም አሯሯጮች የተዘጋጁ በመሆኑ ሰዓቱን እንደሚያሻሽል ተስፋ ተጥሎበታል። ኢሉድ ኪፕቾጌ ሙከራውን በተመለከተ በሰጠው አስተያየትም «ከሁለት ሰዓት በታች የመግባት ሙከራውን ለማድረግ ተዘጋጅቻለሁ። ዝጅግቴም ጥሩ ነበር፤ ይህንንም በተግባር አሳይቼ የሰው ልጅ አቅም ገደብ እንደሌለው አስመሰክራለሁ» ሲል ለኒውስ 24 ገልጿል። ከአትሌቱ ጋር በአሯሯጭነት\nበሙከራው ላይ የሚሳተፉት\n41አትሌቶች የታወቁ ሲሆን\nዘ ዋሽንግተን ፖስትም\nታዋቂዎቹን በስም ጠቅሷል።\nበ1ሺ500 ሜትር\nየዓለም ቻምፒዮን የሆነው\nአሜሪካዊው ማቲው ሴንትሮዊትዝ፣\nበዶሃው የዓለም ቻምፒዮና\nየ5ሺ ሜትር\nየብር ሜዳሊያ ተሸላሚው\nሰለሞን ባረጋ፣ በ3ሺ\nሜትር የዓለም ቀዳሚው\nሰዓት ባለቤት ኡጋንዳዊው\nሮናልድ ሙሳጋላ እንዲሁም\nሌሎች ጠንካራ አትሌቶች\nተካፋይ ይሆናሉ።አዲስ ዘመን ጥቅምት 1/2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "9a110306f18f577fcc7289b9cc971da7" }, { "passage": "የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የወርቅ ደረጃ ከሰጣቸው ታላላቅ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሮች አንዱ የሆነው የፎኮካ ማራቶን ከሳምንት በኋላ በጃፓን ይካሄዳል፡፡ በዚህ ውድድር የሚፎካከሩ የዓለማችን ጠንካራ አትሌቶች ስም ከወዲሁ ይፋ እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን፤ የርቀቱ ኮከቦች የሆኑት ምሥራቅ አፍሪካውያን አትሌቶች የተለመደ የአሸናፊነት ግምት ተችሯቸዋል፡፡እኤአ በ2015 የቤጂንግ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በማራቶን ተከታትለው በመግባት የወርቅና የብር ሜዳሊያ ማጥለቅ የቻሉት ኤርትራዊው ግርማይ ገብረሥላሴና ኢትዮጵያዊው የማነ ፀጋዬ ትልቅ የአሸናፊነት ግምት ከተሰጣቸው አትሌቶች ግንባር ቀደም ናቸው፡፡ግርማይ ገብረሥላሴ በዓለም ቻምፒዮናው በአስራ ስምንት ዓመቱ ሳይጠበቅ ለታላቅ ድል በመብቃት ለኤርትራ በመድረኩ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ ማጥለቁ የሚታወስ ሲሆን፤ በአንፃሩ በርቀቱ የተሻለ ልምድ የነበረው የማነ የብር ሜዳሊውን ለኢትዮጵያ ማስመዝገቡ አይዘነጋም፡፡ ሁለቱ የማራቶን ፈርጦች ከዓለም ቻምፒዮናው በኋላ በትልቅ ውድድር ዳግም ፎኮካ ማራቶን ላይ የሚያደርጉት ፉክክር የሚጠበቅ ይሆናል፡፡የማነ በበርካታ የማራቶን ውድድሮች በማሸነፍ ስማቸው ከሚጠቀስ የዓለማችን ድንቅ የማራቶን አትሌቶች አንዱ ሲሆን፤ ከሁለት ዓመት በፊት በዚሁ በፎኮካ ማራቶን 2:08:48 ሰዓት ማሸነፉ ይታወሳል፡፡ ይህም ሰዓቱ እኤአ 2012 ላይ በሮተርዳም ማራቶን ሲያሸንፍ ካስመዘገበው የራሱ ምርጥ ሰዓት በአራት ደቂቃ የተሻለ ሆኖ ተመዝግቦለታል፡፡ የማነ በዓለም ቻምፒዮናው የብር ሜዳሊያውን ካጠለቀ ወዲህ ጉልበቱ ላይ በገጠመው ጉዳት የ2016 ሪዮ ኦሊምፒክን ጨምሮ በርካታ ውድድሮች ያመለጡት ሲሆን፤ ያለፈውንም ዓመት በጥሩ አቋም ላይ አልነበረም፡፡ ይሁን እንጂ በ2018 ወደ ጥሩ አቋም መመለሱን ባለፈው ሰኔ ወር የኦታዋ ማራቶንን 2:08:52 በሆነ ሰዓት በማሸነፍ አሳይቷል፡፡ግርማይ ገብረሥላሴ በበኩሉ ከዓለም ቻምፒዮናው ድሉ በኋላ በሪዮ ኦሊምፒክ ሌላ ታሪክ ይሠራል ተብሎ ሲጠበቅ ሜዳሊያ ውስጥ መግባት ሳይችል ቀርቷል፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ታላቅ መድረክ አራተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ እንደ ወጣት አትሌት መጥፎ የሚባል አልነበረም፡፡ከኦሊምፒኩ ስድስት ሳምንታት በኋላ በጠንካራው የኒውዮርክ ማራቶን ዳግም ሳይጠበቅ ለድል የበቃው ግርማይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስሙን በርቀቱ ማግነን ችላል፡፡ 2:07:46 የሆነ የራሱ ምርጥ ሰዓት ያለው ግርማይ ባለፉት ሁለት ውድድሮቹ አቋርጦ መውጣቱ ምናልባትም ወደ ጥሩ አቋሙ ካልተመለሰ በዘንድሮው የፎኮካ ማራቶን ከየማነ ጋር የሚጠበቀውን ጠንካራ ፉክክር እንዳያሳይ ስጋት ሊሆን ይችላል፡፡በዚህ ውድድር የማነ ከግርማይ ባሻገር ከሌላ አትሌት ጠንካራ ፉክክር እንደሚገ ጥመው ይጠበቃል፡፡ ይህም ውድድሩ ላይ ከየማነ ቀጥሎ ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት ይዞ የሚወዳደረው ኬንያዊው ቪንሰንት ኪፕሩቶ ሲሆን፤ በርቀቱ 2:05:13 የሆነ የራሱ ምርጥ ሰዓት ያለው አትሌት ነው፡፡\nበሌላ በኩል በዘንድሮው የፎኮካ ማራቶን ትኩረት ሳይሰጠው መታለፍ የሌለበት አትሌት ጃፓናዊው ዩኪ ካዉቺ ነው፡፡ ይህ አትሌት ካለፉት ዘጠኝ የፎኮካ ማራቶን ውድድሮች በስምንቱ ላይ በመሳተፍ ከሌሎቹ አትሌቶች የተሻለ ልምድ ማካበት ችሏል፡፡ ዩኪ ልምድ ማካበቱ ብቻ በውድድሩ አስፈሪ ወይንም ጠንካራ ተፎካካሪ ባያደርገውም በርቀቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያስመዘገበ ያለው ውጤትና ጥሩ አቀም ለምሥራቅ አፍሪካውያኑ አትሌቶች አስፈሪ ያደርገዋል፡፡ ዩኪ በዚህ ውድድር እኤአ በ2011፣2013እና 2016 ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ በሦስቱም ውድድሮች ርቀቱን ከ2፡10 ሰዓት በታች በማጠናቀቅ ጥንካሬውን ማሳየት ችላል፡፡ ዩኪ ምሥራቅ አፍሪካውያን ደጋግመው ያሸነፉትን የቦስተን ማራቶን በቅርቡ ማሸነፉም በአገሩና በደጋፊዎቹ ፊት በሚያደርገው ውድድር ቀላል ግምት እንዳይሰጠው ያደርጋል፡፡", "passage_id": "ba0a2da0290d0ea00dd0d72866a0b83f" }, { "passage": " ኬንያዊው የማራቶን የዓለም ክብረወሰን ባለቤት ኢሉድ ኪፕቾጌ በናይኪ የተያዘውን ከሁለት ሰዓት በታች የመግባት ሙከራ አሳካ። ትናንት በኦስትሪያዋ ቬና በተካሄደው ሙከራ ላይ ኢሉድ ኪፕቾጌ 1፡59፡40 በሆነ ሰዓት በመግባት ዓላማውን ማሳካት ችሏል። አትሌቱ በታሪክ 42ኪሎ ሜትርን ከሁለት ሰዓት በታች የገባ የመጀመሪያው ሰው ይሁን እንጂ ሰዓቱ በዓለም ክብረወሰንነት አይመዘገብለትም። የሰው ልጅ አቅም ወሰን የሌለው መሆኑን ለማሳየት በታዋቂው የስፖርት ትጥቅ አምራች ናይኪ የተያዘው ይህ ፕሮጀክት በአትሌቲክስ ስፖርት ረጅሙን ርቀት ከተለመደው ሁለት ሰዓት በታች ለመግባት የሚያስችል ሙከራ ነው። ለዚህም የዓለም ክብረወሰን ባለቤቱ ኪፕቾጌ የተመረጠ ሲሆን፤ ትጥቅ አምራቹ በሚያደርገው በቴክኖሎጂ የታገዘ ድጋፍ 1ሰዓት ከ59 ደቂቃ ለመግባት ነበር የታቀደው። ለዚህ ሙከራ ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ያላትና ሰዓቱን ለማሟላት የሚያስችል የቦታ አቀማመጥ ያላት ቬና ስትመረጥ፤ ከ41 በላይ የሆኑ አሯሯጮችም ተዘጋጅተው ነበር። ትናትን ጠዋት በተካሄደው ሩጫም አትሌቱ የርቀቱን ግማሽ የሸፈነበት ሰዓት አጠራጣሪ ይሁን እንጂ በአሯሯጮቹ ብርታት 1፡59፡40 በሆነ ሰዓት በመፈጸም ግቡን ሊያሳካ ችሏል። ከሩጫው በኋላም «አሯሯጮቹን ላመሰግናቸው እወዳለሁ፤ ይህንን ሙከራ ተቀብለው አብረውኝ በመሮጣቸው ታሪክ ለማስመዝገብ ችለናል። ይህ በርካቶችን የሚያነሳሳ እና የሰው ልጅ አቅም የሚገደብ አለመሆኑንም ያሳያል። በጣም ደስ ብሎኛል ልጆቼ እና ባለቤቴም ሩጫዬን በመመልከታቸው ተደስቻለሁ» ማለቱን ኢንዲፔንደንት በድረገጹ አስነብቧል። ሙከራው በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ዕውቅና የሌለው መሆኑን ተከትሎ በዓለም ክብረወሰንነት አይመዘገብም። እ.አ.አ በ2018 የበርሊንን ማራቶን የገባበት 2፡01.39 የሆነ ሰዓት የዓለም ፈጣን ሰዓት ሲሆን፤ ከሁለት ዓመት በፊት አትሌቱ በጣሊያኗ ሞንዛ ከተማ ባደረገው ሙከራ በ26ሰከንዶች ዓላማውን አለመሳካቱ ይታወሳል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 2/2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "169d6bee9edecbfefa269a65fb02c866" }, { "passage": "አትሌት ሞስነት ገረመውና ሙሌ ዋስይሁን በመጪው ሚያዝያ በሚካሄደው የለንደን ማራቶን ከዓለም ክብረወሰን ባለቤቱ አትሌት ኢሉድ ኪፕቾጌ ጋር ከሚፎካከሩ አትሌቶች መካከል እንደሚካተቱ አረጋግጠዋል። ሁለቱ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባለፈው ዓመት የለንደን ማራቶን ውድድሩን አራት ጊዜ በተከታታይ ካሸነፈውና የቦታውን ክብረወሰን ከጨበጠው ኬንያዊ አትሌት ኪፕቾጌ ተከትለው በመግባት ሁለተኛና ሦስተኛ ሆነው ማጠናቀቃቸው ይታወሳል። ይህም ባለፈው ዓመት ከአንድ እስከ ሦስት በውድድሩ ማጠናቀቅ የቻሉ አትሌቶች ዘንድሮም የሚፎካከሩበት ዕድል እንዲፈጠር አድርጓል። አምና በውድድሩ አራተኛ፣ ካቻምና ደግሞ ሦስተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ የቻለው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሹራ ቂጣታ ቀደም ብሎ በዘንድሮው የለንደን ማራቶን እንደሚወዳደር ያረጋገጠ አትሌት ነው። ሞስነት ገረመው ባለፈው የለንደን ማራቶን ሁለተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ 2፡02፡55 የሆነውን የዓለም አምስተኛ ፈጣን ሰዓት ማስመዝገብ የቻለ ሲሆን ክረምት ላይ ተካሂዶ በነበረው የዶሃው የዓለም ቻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ማጥለቅ ችሏል። በተመሳሳይ ባለፈው ለንደን ማራቶን ሦስተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ 2፡03፡16 ሰዓት ያስመዘገበው ሙሌ ዋስይሁን የዓለማችን አስራ አንደኛው ፈጣን ሰዓት ባለቤት ነው። እነዚህን ኮከብ አትሌቶች ጨምሮ ሌሎች በርካታ የርቀቱ ጠንካራ አትሌቶች በዘንድሮው ለንደን ማራቶን ተሳታፊ መሆናቸውን ተከትሎ ውድድሩ ከወዲሁ በጉጉት እየተጠበቀ ነው። ‹‹ያለፈው ዓመት ውድድር በተለይም በወንዶች የምንጊዜውም ምርጡ ነበር›› ያለው የኢሊት አትሌቶች ኃላፊ ስፔንሰር ባርደን የዘንድሮው የተሻለ እንደሚሆን ያለውን እምነት ገልጿል። በአምናው ውድድር ሞስነትና ሙሌ ኬንያዊውን ድንቅ አትሌት እስከ አርባ ኪሎ ሜትር ድረስ የፈተኑበት መንገድ ከዚህ ቀደም እንዳልገጠመው የተናገረው ባርደን ዘንድሮ እነዚህ አትሌቶች በተሻለ የራስ መተማመን ሊያሸንፉ የሚችሉበት ዕድል እንዳለ አብራርቷል። ከሦስት ወራት በፊት በቬና ማራቶን አርባ ሁለት ኪሎ ሜትርን ከ2፡00 ሰዓት በታች በማጠናቀቅ የመጀመሪያው የዓለማችን አትሌት የሆነው ኪፕቾጌ ዘንድሮ በለንደን ማራቶን ማሸነፍ ከቻለ አምስት ጊዜ ያሸነፈ ብቸኛው አትሌት በመሆን ተጨማሪ ታሪክ ያኖራል። በዘንድሮው ውድድር የ2017 የዓለም ቻምፒዮና የብር ሜዳሊያ አሸናፊው ታምራት ቶላን ጨምሮ ኬንያዊው ማሪየስ ኪፕሴሬምና ኖርዌያዊው ሶንድሬ ኖርድስታድ ተፎካካሪ መሆናቸው እንደተረጋገጠ አትሌቲክስ ዊክሊ አስነብቧል። በሴቶች መካከል በሚካሄደው ፉክክርም የዓለም ክብረወሰን ባለቤቷና ያለፈው ዓመት የለንደን ማራቶን አሸናፊዋ ኬንያዊት ብሪጊድ ኮስጌ ከትናንት በስቲያ ተሳታፊ መሆኗን ያረጋገጠች ሲሆን በቀጣይ ጊዜዎች ሌሎቹ ተሳታፊዎች ይፋ እንደሚደረጉ ይጠበቃል። አዲስ ዘመን ጥር 7/2012 ቦጋለ አበበ", "passage_id": "eaa1748dbf96270b2511e420391a2253" } ]
788adee6ee5dac6a3824620ea0f82e11
01f73fe2dd71eb57e86861f0d6e6addf
የአበረታች ቅመሞች ቁጥጥር ከጥንቃቄ ጋር ይቀጥላል
የወቅቱ የዓለም ራስ ምታት በሆነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች አንቀላፍተው ቢቆዩም ከሰሞኑ የአውሮፓ ሊጎች ወደ ልምምድ መመለስን ተከትሎ የስፖርቱ ኢንዱስትሪ መነቃቃት ጀምሯል። አሁንም የኮሮና ወረርሽኝ (ኮቪድ 19) ስጋት እንዳለ ቢሆንም ጥንቃቄን በተላበሰ መልኩ ወደ ቀድሞው መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ ጥረቶች እየታዩ ነው። በዚሁ ምክንያት ተቀዛቅዞ የቆየው አበረታች ቅመሞችን መከላከልና የመቆጣጠር ሥራ ነው። ይህ ስፖርትን በተፈጥሯዊው መንገድ ብቻ እንዲካሄድ የማድረግ ጥረት ሊቀዛቀዝ የቻለው በዓለም አቀፍ ደረጃ ውድድሮች መቋረጣቸውን ተከትሎ ነው። ይሁን እንጂ ከዓላማው አንጻር ረጅም ጊዜ መውሰዱና መዘናጋቱ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል። በመሆኑም ዓለም አቀፉ የጸረ አበረታች ቅመሞች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በስሩ ለሚገኙት ብሔራዊ ጽሕፈት ቤቶች መመሪያ ማዘጋጀቱን ከሰሞኑ በድረገጹ አስነብቧል። ይህም በየሀገራቱ የሚገኙ የጸረ አበረታች ቅመሞች ተቆጣጣሪ ጽሕፈት ቤቶች ወደ ቀደመ ሥራቸው እንዲመለሱ የሚያስችል ርምጃ ነው። ኤጀንሲው በወረርሽኙ ምክንያት በዓለም ዙሪያ ሲሰሩ የቆዩት ናሙና የመውሰድና ምርመራ የማድረግ ሂደቶችን የቀነሰና አንዳንድ ሥራዎችንም በጊዜያዊነት ማቋረጡን በዘገባው ተጠቁሟል። ነገር ግን አሁን ወደ ሥራ ለመመለስ እንቅስቃሴ መደረግ እንዳለበት የኤጀንሲው ፕሬዚዳንት ዊቶልድ ባንካ ይገልጻሉ። በኤጀንሲው ስር ካሉ ተቋማት ጋር ከወቅታዊው ጉዳይ ጋር በተያያዘ በቅርበት ሲሰሩና ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል። አሁን ግን ሥራው እንደቀድሞው መቀጠል ያለበት በመሆኑ፤ በቴክኖሎጂ በታገዘና የናሙና አወሳሰዱን በአዲስ መንገድ ማካሄድ ተገቢ መሆኑን ያመላክታሉ። ለዚህ ደግሞ በጸረ አበረታች መድኃኒት ቁጥጥር ላይ የሚሰሩ አካላት አዲስ ነገር ለመፍጠር ርብርብ ላይ ይገኛሉ። የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ኦሊቨር ኒግሊ በበኩላቸው፣ በዚህ ወቅት ናሙናዎችን ከአትሌቶች ለመውሰድ አዳጋች መሆኑን ነው የሚጠቁሙት። ምርመራው መቀጠል የሚገባው አስፈላጊው የጤናና ንጽህና ሁኔታ የተስተካከለ ሲሆን ብቻ ነው። የአትሌቶችና በዙሪያቸው ያሉ አካላት ጤናም ኤጀንሲው ትኩረት የሚሰጠው ቀዳሚ ጉዳይ ነው። ተቋሙ የአትሌቶችን ናሙና በመውሰድ አበረታች መድኃኒት ተጠቃሚነታቸውን በምርመራ መለየት ብቻም ሳይሆን የጤና ግለ ታሪካቸውንም መመዝገብ ሌላው ተግባሩ ነው። ንጹህ ስፖርት ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ግንዛቤ ማስጨበጥም እንዲሁ። በመሆኑም በቀጣይ ሳምንታት ከብሔራዊ ተቋማቱ ጋር በመሆን ሥራው በምን መልኩ መቀጠል ይገባዋል በሚለው ላይ መፍትሄ በማፈላለግ ወደ ሥራ የሚመለስ እንደሆነ አብራርተዋል። የሯጮቹ ሀገር ኢትዮጵያም የኤጀንሲው አባል ሀገር በመሆን ንጹህ ስፖርት እንዲካሄድ ሚናቸውን ከሚወጡት መካከል ትጠቀሳለች። ተሞክሮውን ለሌላው ዓለምም ማጋራት የቻለና በሥራው ምስጉን የሆነ ጽሕፈት ቤትም በአጭር ጊዜ ለማቋቋም መቻሉ ይታወቃል። በመላው ዓለም ባጠላው በዚህ የወረርሽኝ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጸረ አበረታች ቅመሞች ተቆጣጣሪ ጽሕፈት ቤት እንቅስቃሴውን በምን መልኩ እያከናወነ ይገኛል? የሚለውን የጽሕፈት ቤቱ ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል ያስረዳሉ። የተቋሙን ውስጣዊና ውጫዊ እንቅስቃሴ በሁለት የሚከፍሉት ዳይሬክተሩ፤ የኮሮናን ቫይረስ በመከላከል ረገድ ሠራተኞችን የመቀነስና የንጽህና ቁሳቁስን የማዘጋጀት ሥራዎች መከናወናቸውን ይጠቁማሉ። ሁለተኛውና ከተቋሙ ውጪ ከአትሌቶች ጋር በመገናኘት የሚከናወነው ደግሞ ከአበረታች መድኃኒት ቁጥጥር ጋር የተያያዘው ሥራ ነው። ይሁን እንጂ ከአትሌቶች ናሙና መውሰድ በእጅጉ ለንክኪ የሚያጋልጥ በመሆኑ አትሌቶችንም ሆነ በምርመራው ተሳታፊ የሆኑ ባለሙያዎችን ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆኑ በማሰብ ለጊዜው ገታ ተደርጓል። ነገር ግን ሥራውን ሙሉ ለሙሉ ማቆም የማይቻል በመሆኑ ለቫይረሱ አጋላጭ ይሆናሉ የሚል ስጋት ያሳደሩ ሥራዎችን ፎርማት ለመቀየር መሞከሩን ዳይሬክተሩ ይገልጻሉ። በዚህም መሠረት አበረታች ንጥረ ነገር ተጠቃሚ የሆኑ አትሌቶችን የማጋለጥ፣ አትሌቶች ባዮሎጂካል ፓስፖርት ፕሮግራም ሥራን የማጠናከር እንዲሁም ሌሎች ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህ ጊዜ ውድድሮች የተቋረጡ ቢሆንም ስፖርተኞች ግን በየግላቸው በቤታቸው ውስጥ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን አላቆሙም። ይህንን ተከትሎም ከውድድር ውጪ የሚወሰዱ አበረታች ንጥረ ነገሮችን ከመውሰድ እንዲቆጠቡም ያሳስባሉ። በጥቅሉ በጊዜያዊነት ንክኪ ካለባቸው ሥራዎች በቀር ሌሎች ሥራዎች እንደቀጠሉ ሲሆን፤ የአድራሻ ምዝገባቸውን በመደበኛ መልኩ የሚያደርጉ በመሆኑ በዚህ ላይም መዘናጋት አይገባም። ዓለም አቀፉ የጸረ አበረታች መድኃኒቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በመግለጫው ባመላከተው መሠረት፤ ጽሕፈት ቤቱም እንደቀደመው የአትሌቶችን ናሙና ወደመውሰድና መመርመር ሥራው ለመመለስ የሚያስችለውን ሁኔታ እያጠና ይገኛል። እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ከሆነም ስፖርተኞች ከባለሙያዎች ጋር የሚኖራቸውን ንክኪ በሚቀንስና ለበሽታው አጋላጭ በማይሆን መልኩ መፍትሄ እንደተገኘ በቀጥታ ምርመራው የሚጀመር ይሆናል። በብሔራዊ ቡድን፣ በክለብ እና በማሰልጠኛ ተቋማት የተያዙ አትሌቶች እንዲሁም በቡድን ሆነው የሚሰሩ ሰልጣኞች በዚህ ወቅት ልምምድ አቋርጠው በቤታቸው ይገኛሉ። ምንም ዓይነት የቡድን እንቅስቃሴ የማይፈቀድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አትሌቶች በያሉበት አነስተኛ ልምምድ ብቻ የሚያደርጉ ይሁን እንጂ አሁንም እንደ ተቋም አስጊ ሁኔታዎች መኖራቸው አልቀረም። ይህም ወቅታዊውን ሁኔታ ሽፋን በማድረግ የተከለከሉ ንጥረነገሮችን የመጠቀም አዝማሚያ ሊኖር ይችላል የሚል ስጋት ነው። እስካሁን በተጨባጭ የተገኘ መረጃ ባይኖርም በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ እንደ ተቋም ስጋቱ አለ። ከአትሌቶች ባሻገር ከጀርባ በመሆን አጋላጭ የሆኑ አካላት አበረታች ቅመሞችን እንዲጠቀሙ በመገፋፋትና በማሳመን የሕግ ጥሰት የመፈጸም አዝማሚያ ሊኖር ይችላል የሚል ግምት አለ። በመሆኑም ስጋቱን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ሥራዎች በመከናወን ላይ ነው የሚገኙት። በስፖርተኞች በኩል ስለ ጉዳዩ ያለውን ግንዛቤ ለማስፋትም በመገናኛ ብዙኃን በመታገዝ መልዕክቶች በመተላለፍ ላይ ይገኛሉ። በተመረጡ መገናኛ ብዙኃን ላይም የማስታወቂያ እንዲሁም የማንቂያ ሥራዎች እየተካሄዱ መሆኑን የሚጠቁሙት ዳይሬክተሩ በጽሕፈት ቤቱ ድረገጽም መረጃዎችን እያስተላለፉ ይገኛል። ይህም አትሌቱ በሚመቸው መንገድ መረጃ እንዲያገኝ ያስችለዋል። በቀጣይም በመደበኛነት ማስታወቂያዎቹ የሚተላለፉባቸውን የመገናኛ ብዙኃን ቁጥር ለመጨመር ታቅዷል። ሌላው ጽሕፈት ቤቱ በትኩረት እየሄደበት ያለው የሕግ ማዕቀፍ የማሻሻል ሥራ ነው። ኤጀንሲው የጸረ አበረታች ቅመሞች ሕግን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ ስታንዳርዶችን አሻሽሏል፤ በመሆኑም በጽሕፈት ቤቱ በኩል እአአ በ2021 ተግባራዊ የሚሆኑ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎችን ለመከለስ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። በመጨረሻም ዳይሬክተሩ ስፖርተኞችም ሆኑ ሌሎች የሀገሪቷ ዜጎች የሕክምና ባለሙያዎችን ምክር በመተግበር በዓለም ላይ ከተከሰተው ወረርሽኝ ራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ስፖርተኞች፣ የስፖርት ባለሙያዎች፣ የስፖርት አመራሮች እንዲሁም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በበኩላቸው በአበረታች ንጥረ ነገር መከላከልና መቆጣጠር ሥራው ለአፍታ የቆመ ባለመሆኑ መዘናጋት እንዳይኖር ዳይሬክተሩ ያሳስባሉ። ዓለም አቀፉ ኤጀንሲም ሆነ የዓለም አትሌቲክስ ይህ ጊዜ ሲያልፍ ስፖርቱ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በጥንቃቄ እየተመለከቱት ነው። በዚህ መሠረት የሚመለከታቸው አካላት ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። ተጠቃሚነታቸው ከተረጋገጠም ጽሕፈት ቤቱ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እንዲሁም የወንጀል እርምጃ ከመውሰድ ወደኋላ የማይል በመሆኑ ስፖርተኛው በመደበኛ ጥንቃቄው መቀጠል እንዳለበት ዳይሬክተሩ አስቀምጠዋል።አዲስ ዘመን ግንቦት 10/2012ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=32614
[ { "passage": "‹‹የጤና ጉዳቱ በዓለም ጤና ድርጅት ካልተረጋገጠ አቅርቦቱ ይቀጥላል››   አዲስ አበባ፡- ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ፓልም የረጋ የምግብ ዘይት በሂደት ለከፋ የጤና ችግር የሚያጋልጥ መሆኑን በሳይንሳዊ ጥናት የተረጋገጠውንና ከእህል ዘር የሚዘጋጅ ፈሳሽ ዘይት በማቅረብ የህብረተሰቡ ጤና እንዲጠበቅ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በህዳር 19 ቀን፣ 2011 ዓ.ም በላከው ደብዳቤ ያሳወቀውን ምክረ ሀሳብ ምላሽ እየጠበቀ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በበኩሉ የዓለምጤና ድርጅትና በሥሩ ያሉ የምርት ጥራት የሚያረጋግጡ ተቋማትዘይቱ የጤና ጉዳት እንዳለው እስካላረጋገጡ ድረስ ጥቅም ላይ እንደሚውል ገልጿል። በጤና ሚኒስቴር ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አማካሪ ዶክተር ውባየሁ ዋለልኝ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ፓልም የረጋ የምግብ ዘይት በደም ውስጥ የቅባት መጠን እንዲጨምር፣ የኩላሊት ተግባር እንዲቀንስ በማድረግ፣የደም ሥሮችን በማጥበብ፣በሂደትም ከፍተኛ ለሆነ የጤና ጉዳት አጋላጭ መሆኑን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እ.ኤ.አ በ2016 ባካሄደው ሳይንሳዊ ጥናት አረጋግጧል። በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የምግብ ዘይቶች የሚመረቱበት ሂደት አደገኛ መሆኑንም ጥናቱ አመላክቷል ያሉት ዶክተር ውባየሁ ጤና ሚኒስቴር ጥናቱን መሰረት በማድረግ የረጋ የፓልም ዘይት በፈሳሽ እንዲተካና በሀገር ውስጥ ምርት ላይም ተገቢው ቁጥጥርና ክትትል እንዲደረግ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በደብዳቤ ምክረ ሀሳብ ልኮ ምላሹን እየጠበቀ ነው። ጤና ሚኒስቴር ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት በደብዳቤ ያሳወቀው ምክረ ሀሳብ ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዲደርሰው መደረጉንና ሚኒስቴሩ ገበያ ላይ ያለውን ዘይት ዋጋ በማጥናት አምራች ኢንዱስትሪዎች ከእህል ዘር ፈሳሽ ዘይት ማምረት እንዲችሉ የሚደገፉበትን ሁኔታ በማመቻቸት አማራጭ ሀሳብ እንዲያቀርብ አቅጣጫ እንደተሰጠው ዶክተር ውባየሁ አስረድተዋል። ንግድ ሚኒስቴር በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ተልዕኮውን ከተወጣ ምርቱን በሀገር ውስጥ በመተካት እንዲሁም ከኑግ፣ከሱፍ፣ ከተልባ፣ ከበቆሎ፣ ከአኩሪአተር፣ ከሰሊጥና ከሌሎች የቅባት እህል ዓይነቶች የምግብ ዘይት ማምረት ከተቻለ የህብረተሰቡን ጤና መታደግ እንደሚቻል ዶክተሩ ይናገራሉ። በአሁኑ ጊዜ ከእህል ዘር የሚዘጋጅ ፈሳሽ የምግብ ዘይት ምርት በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱንም ጠቅሰዋል። በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት ኢትዮጵያ በየዓመቱ ለዘይት ግዥ የምታወጣውን 450 ሚሊዮን ዶላር ማዳን እንደሚያስችል ጠቁመው፣ ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባው የምግብ ዘይት በ20 ዓመት ጊዜ ውስጥ 330ሺ ቶን መድረሱንም አመልክተዋል። እንደ ዶክተር ውባየሁ ገለፃ የረጋው የፓልም ዘይት የቅባት መጠኑ ከፍተኛ እንደሆነና ቅቤን ለመተካት ሲባል እየተዘጋጀ የሚቀርብ ምርት ነው። በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የምግብ ዘይቶችም የማምረቻ መሣሪያቸው፣የሰው ኃይላቸውና የምርት ግብአታቸው ላይ የጥራት ክትትል ካልተደረገ በአንዳንዶቹ ላይ ጉድለቶች እንደሚታዩ አስረድተዋል። የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ በበኩላቸው እንደገለጹት፣ እየቀረበ ያለው የፓልም የምግብ ዘይት ኢትዮጵያ ባስቀመጠችው አስገዳጅ የጥራት መስፈርት ደረጃ የተረጋገጠ ምርት ነው። አቅርቦቱ አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል የመግዛት አቅም ያገናዘበ ነው ብለዋል። በመሆኑም የረጋው የፓልም ዘይት የጤና ችግር የሚያስከትል መሆኑ በዓለም የጤና ድርጅት እስካልተረጋገጠ ድረስ አቅርቦቱ ይቀጥላል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። መንግሥትም ከተያዘው በጀት ዓመት ጀምሮ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለዘይት፣ለስንዴና ለስኳር ከሚያደርገው ድጎማ ለመውጣት እንቅስቃሴ ጀምሯል።በመሆኑም ምክረሀሳቡ በረጅም ጊዜ ውስጥ ለመተግበር ጥረት እየተደረገ ነው ያሉት አቶ ወንድሙ በኦሮሚያ፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ፣በትግራይ፣በአማራና በሌሎችም በአራት አካባቢዎች ለማምረቻ የሚሆኑ የሼዶች ግንባታ ሥራ መጀመሩንና ባለሀብቶችም በዘርፉ ላይ በስፋት እንዲሰማሩ ሥራዎች ተጀምረዋል። ሚኒስቴሩ ጥራት ያለው ዘይት እንዲቀርብ በጥናት የተደገፈ ሥራ እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። እንደ አቶ ወንድሙ ገለጻ በአሁኑ ጊዜ በሀገር ውስጥ በአነስተኛና በመካከለኛ አማራቾች በወር ሁለት ነጥብ አራት ሚሊዮን ሊትር ዘይት እንደሚቀርብና አቅርቦቱን አምስት በመቶ ይሸፍናል። በነጻ ገበያ መርህ ደግሞ በተለያዩ አቅራቢዎች አምስት ነጥብ አራት ሚሊዮን ሊትር የሚቀርብ ሲሆን፣ ይህም 11በመቶ ይሸፍናል። 40 ሚሊዮን ሊትሩ በመንግሥት ድጎማ ከውጭ የሚገባና 84 በመቶ እንደሚሸፍንና ከፍተኛውን አቅርቦት የያዘው የፓልም ዘይት ነው።አዲስ ዘመን ግንቦት 8/2011በለምለም መንግሥቱ ", "passage_id": "852718d04dba33501f18257e528b8e45" }, { "passage": " ሃይል ሰጪ ዕፅ መጠቀም ከስፖርት እኩል ረጅም ታሪክ ያስቆጠረ ነው። ጥንታውያኑ የግሪክ፤ የሮማ ስፖርተኞች በተለይም በሩጫ፤ በፈረስ ግልቢያና በትግል ስፖርተኞች አንዳቸውን ከሌላቸው ለመብለጥ ሃይል ሰጪ ቅጠላቅጠልና ስራስር ይወስዱ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ። ስፖርቱ ዓይነቱ እየበዛ፤ እየሰፋ፤ ውድድሩ እየረቀቀና እየጠነከረ በመጣ\nቁጥር በእንክብል፤ በፈሳሽ፤ በምግብ መልክም እየተዘጋጀ አትሌቶች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ፤ ሃይል ሰጪ መድሃኒት በተደጋጋሚ እየወሰዱ አልፎ አልፎ ይጋለጡም ነበር።በተፈጥሯዊ አቅምና ብቃት\nከመጠቀም ይልቅ አበረታች ንጥረ ነገርን ምርጫቸው በማድረግ ያገኙትን ሽልማት፤ ክብርና ማዕረግ እንዲሁም ሜዳልያ ተነጥቀውም አንገታቸውን የደፉ፤ በተግባ ራቸው አገራቸውን ጭምር ያዋረዱ በርካቶች ናቸው። አሜሪካዊቷ የሩጫ፤ የዝላይና የዱላ\nቅብብል ስመ ጥር አትሌት ማሪዮን ሉዊስ ጆንሰን፤ እንዲሁም ብስክሌተኞች ስፖርት የቱር ደፍራንስ አሸናፊ ላንስ አርም ስትሮንግን ከአበረታች መድሃኒት (ዶፒንግ) ጋር ተያይዞ ክብራቸውን ከተገፈፉ ስፖርተኞች መካከል ይገኙበታል፡፡ እንደ አገር ሲታሰብም ሩሲያ ከሁሉ ቀድማ በቅሌቱ ስሟ ይነሳል፡፡ በመካከለኛና በረጅም ርቀት\nየአትሌቲክስ ውድድሮች ድንቅ ብቃት በማስመዝገብ የምትታ ወቀው ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኬንያም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከዶፒንግ ቅሌት ጋር ስሟ በእጅጉ እየተዛመደ የመገናኛ ብዙሃንና የስፖርቱ ባለሙያዎች መነጋገሪያ እየሆነች ትገኛለች። ቅሌቱም አገሪቱ በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ መስክ የገነባቸውን የከፍታ ስም በእጅጉ እየናደው ይገኛል። ከቀናት በፊት መገናኛ ብዙሃኑ ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ ከሃምሳ በላይ በዚህ ዓመት ደግሞ 12 የኬንያ አትሌቶች በአበረታች መድሃኒት/ዶፒንግ/ ቅሌት እግድ እንደተጣለባቸው አመላክተዋል። «ኬንያ በዶፒንግ ቅሌት ተመዝጋቢዎች ቁጥር ከአፍሪካ አገራት ቀዳሚ ከዓለም ደግሞ ከሩሲያና ከህንድ ቀጥሎ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች ሲል» የቻይናው የዜና አውታር ዥንዋ አስነብቧል መረጃዎች እንዳመላከቱት ከሆነም ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ስድስት የምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር አትሌቶች ስማቸው ከቅሌቱ ጋር ተነስቷል።ከእነዚህ መካከል ደግሞ ሳሎሜ ጄሮኖ ቀድማ ትጠቀሳለች፡፡ አትሌቱ ባሳለፍነው ወር የተከለከለውን አበረታች ንጥረ ነገር መጠቀሟ በምርምር በመረጋገጡ ከአትልቲክሱ ስፖርት ስምንት አመት እግድ እንደተጣለባት ታውቃል። አትሌቷ መሰል ተግባር ፈፅማለች በሚል ክስ ሲቀርብባትም ከአራት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ታውቋል፡፡ እኤአ በ2012 በናይሮቢ ማራቶን ቀዳሚ\nሆና መግባቷን ተከትሎ በተደረገባት ምርመራ በዓለም አቀፉ ጸረ ዶፒንግ ኤጀንሲ (ዋዳ) የተከለከለ ንጥረ ነገር መውሰዷ በመታወቁ፤ እኤአ 2013 እስከ 2015 የሁለት ዓመት እግድ ተጥሎባት እንደነበርም ይታወሳል። የ36 ዓመቷ አትሌት ከቅጣት መልስ ጥቂት ወራት በኋላ፤ እኤአ 2016 በሃንኦቨር ማራቶን 2 ሰዓት ከ30 ደቂቃ\nከ47 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት የግሏን ምርጥ ሰዓት ያስመዘገበች ሲሆን፤ በዚህ ዓመትን በሳኦፖሎ ማራቶን 2 ሰዓት ከ 37 ደቂቃ\nከ 33 ሴከንድ በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ደረጃ ይዛለች። ከሳሎሜ ጄሮኖ በተጨማሪ የ2016, የሪዮ\nኦሎምፒክ የማራቶን ውድድር የብር ሜዳሊያ ባሌቤቷ ዩኒስ ቺፕኪሩ ኪርዋ፤ ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄደው የዓለም ሻምፒዮና የተሳተፈችው ሳይረስ ሩቶ፤ ከሦስት ዓመት በፊት በተካሄደው የሲንጋፖር ማራቶን ያሸነፈው ፊልክስ ኪርዋ እንዲሁም ባሳለፍነው ዓመት በስፔን ቫሌንሲያ የተካሄደውን የወንዶች ግማሽ ማራቶን ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰን በመስበር ማሸነፍ የቻለው አብርሃም ኪፕቱም ከቅሌቱ ጋር ስማቸው ተነስቷል። እኤአ በ2014 የአፍሪካ 10 ሺ ሜትር\nሻምፒየን ጆይስ ቼፕኪሩይ እና የረጅም ርቀት ሯጩ ጃኮብ ኪቤት በዶፒንግ ቅሌት ጋር በተያያዘ እግድ የተላለፋባቸው ሌሎች የምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር አትሌቶች ሆነዋል፡፡ ጆይስ ቼፕኪሩይ እኤአ በ2011 በአፍሪካ ጨዋታ\n1ሺ500 ሜትር የነሃስ ሜዳሊያ እንዲሁም እኤአ በ2015 የአምስተርዳምና ሆኖሎሉ ማራቶን ማሸነፍ የቻለች ሲሆን፣ በተመሳሳይ ዓመት በቦስተን ማራቶን አስረኛ ደረጃ ይዛ ማጠናቀቁ ይታወሳል። ሌላኛው የዶፒንግ ቅጣት ሰለባ ጃኩብ ኪቤት ካንዳጎር ነው፡፡ አትሌቱ ከሁለት ዓመት በፊት በሳዎል ማራቶን ስድስተኛ እንዲሁም፤ በሃንቡርግና በኢስታንቡል ማራቶን ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ ባሳለፍነው ዓመት በተካሄደው የኢስታንቡል ማራቶን አምስተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ እነዚህን አትሌቶች ዋቢ በማድረግ የኬንያ አትሌቲክስ በዶፒንግ ቅሌት እየታመሰ ስለመሆኑ ያስነበበው የሮይተርሱ የአፍሪካ ስፖርት ጉዳዮች ተንታኝ አይዛክ ኦሙሎ፤ ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኬኒያ በዶፒንግ ቅሌት ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆና ከዓለም ደግሞ ሦስተኛ የመሆኗን ምክንያት አብራርቷል። እንደ ዘገባው ከሆነ፤ ሩሲያ በዶፒንግ ቅሌት ያስመዘገበቻቸው አትሌቶች ቁጥር 87 ደርሷል፤ ይህም ከዓለም ቀዳሚ አድርጓታል። 42 አትሌቶችን ያስመዘገበችው ህንድ ሁለተኛ ደረጃ ይዛለች። ምስራቅ አፍሪካዊቷ የሩጯ አገር ኬንያ ደግሞ 41 አትሌቶችን በስሟ አፅፋለች። ከእነዚህ መካከልም 24 የሚሆኑት ወንዶች ናቸው። ይህ የዶፒንግ ቅሌት ሪፖርት ኬንያ በዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ስፖርት መድረክ ለዓመታት የገነባችውን ገናና ስም በመናድ ረገድ የሚኖረው ጫና በቀላሉ የሚታይ እንዳልሆነ ያመላከተው ዘገባው፤ ጉዳዩም አፋጣኝ መልስ የሚፈልግ ስለመሆኑ አፅንኦት ሰጥቶታል። የኬንያ ፀረ ዶፒንግ ኤጀንሲ የበላይ አለቃ ጃፕተር ራጌት፤«አትሌቶችን በመመርመር፤ ግንዛቤ በማስጨበጥ ተከታታይ የቁጥጥር ስራዎችን ሰርተናል፤ ይሁንና ሪፖርቱ ብዙ መስራት እንዳለብንያመላከተ ነው›› ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል። የዓለም አቀፉ ጸረ ዶፒንግ ኤጀንሲ ላብራቶሪ በአገሪቱ ዋና መዲና በናይሮቢ በመኖሩ በርካታ ምርመራዎች እየተደረጉ መሆናቸውን ጠቁመው፤ በመጪው የዶሃው የዓለም ሻምፒየን ሺፕ ኬንያን እንዲወክሉ የሚመረጡ አትሌቶች እያንዳንዳቸው ቢያንስ አራት ጊዜ ምርመራው እንደሚካሄድላቸው ጨምረው አስታውቀዋል። የኬንያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ጃክሰን ቱዊ በበኩላቸው፤አንዳንድ አትሌቶች ለመታመን ዝግጁ አይደሉም፤ ተግባሩ ኬንያ በዓለም አቀፉ መድረኮች የነበራትን ስም በእጅጉ የሚያጎድፍ ነው፤ ይህን ለማስወገድም ደግሞ የአገሪቱ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እረፍት አይኖረውም» ሲሉም ተደምጠዋል። የሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒየኑ የኬንያው ስመጥር አትሌት ቺብቾጌ ኪኖ በበኩሉ፤ ከሁሉ ተግባራት ቀድሞ አትሌቶች ከዶፒንግ ጋር የመዛመዳቸው ዋነኛ ምክንያትና ስረ መሰረቱን ለይቶ ማወቅ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥቶ ተናግሯል። «ይህም ከመጋረጃው በስተጀርባ ሆነው የአገሪቱን ስፖርትና ባለተሰጥኦ አትሌቶችን እየገደሉ የሚገኙት ባለጭንብል ግለሰቦችስ እነማን ናቸው ከሚለው አንስቶ መስራት ይገባል፤ ግለሰቦቹ እኛ ለዓመታት የገነባነውን ሌጋሲ እንዲሁም ተተኪና ወጣቱን ትውልድ እየገደሉት ነው» የሚለው የ79 ዓመቱ አትሌት፤ግለሰቦቹን በማደን ጥፋተኛውን አካል ለህግ የማቅረቡ ስራ ሳይውል ሳያድር ተግባራዊ መሆን እንዳለበት ነው ያስገነዘበው። የዚህን የሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒየን ሃሳብ ሙሉ በሙሉ የሚስማሙበት የኬንያ አትሌቲክስ ኮሚቴ አባል ባርናባ ኮሪር፤ተደጋጋሚ ቅሌት በኤትሌቲክሱ ላይ መከሰቱ የአገሬው አትሌቲክስ የበላይ አካላት የተከለከለውን ንጥረ ነገር ተጠቃሚዎች በማጋለጥ ረገድ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እንዳልሰሩ የሚያስገነዝብ መሆኑን አብራርተዋል። «የአትሌቲክሱ ስፖርት ከዶፒንግ እስኪነፃ ከመከላከሉ ባሻገር ተጠቃሚዎቹን አነፍንፎ ከማደንና ከማጋለጥ የተለየ ምንም አይነት ሌላ መፍትሄና አማራጭ አይኖርምም ነው ያሉት።አዲስ ዘመን  ሐምሌ 22/2011ታምራት ተስፋዬ", "passage_id": "6bc23a29112d9da0d8dc053f4a118c82" }, { "passage": "አዲስ አበባ፡- በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የምግብ ይዘትን በመከለስና በመለወጥ ለሽያጭ በሚያቀርቡ ግለሰቦች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር እንደቀጠለ ቢሆንም በተጠርጣሪዎች ላይ በቂ የፍርድ ውሳኔ እየተሰጠ አለመሆኑን የአዲስ አበባ አስተዳደር የምግብና ጤና ክብካቤ ባለስልጣን አስታወቀ። የባለስልጣን መስሪያ\nቤቱ ምክትል\nዋና ዳይሬክተር\nአቶ አለማየሁ\nሁንዱማ በተለይ\nለአዲስ ዘመን\nጋዜጣ እንደተናገሩት፤በከተማዋ\nየተለያዩ አካባቢዎች\nምግብን በመከለስና\nይዘቱን በመለወጥ\nለህብረተሰቡ በሽያጭ\nየሚያቀርቡ ህገወጥ\nነጋዴዎች ተበራክተዋል።\nእንደ ዋና\nዳይሬክተሩ ማብራሪያ\nከነሐሴ 2011 አስከ\nጥቅምት 30 ቀን\n2012 ዓም ድረስ\nበከተማዋ የተለያዩ\nስፍራዎች ድርጊቱን\nበሚፈጽሙ ግለሰቦች\nላይ በተደረገ\nአሰሳ በቂ\nየሚባል ማስረጃ\nየተገኘ ቢሆንም\nተጠርጣሪዎቹን ለህግ\nአካል አቅርቦ\nማስቀጣት ያለመቻሉን\nግን ተናግረዋል።\nበተጠቀሱት ጊዚያት በተለያዩ ክፍለከተሞች በባለስልጣኑ ባለሙያዎች በተደረገው ፍተሻ በድርጊቱ መሳተፋቸው የተረጋገጠ 151 እንጀራ ቤቶች ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ሲሆን 55 በሚሆኑት ላይም የማሸግ ዕርምጃ በመውሰድ 45 ሊትር የተከለሰ ሊጥን ለማሰወገድ ተችሏል። በተመሳሳይ ሁኔታ በወፍጮ ቤቶች ላይ በተደረገው ቁጥጥርና ፍተሻ ለ190 ያህሉ ማስጠንቀቂያ በመስጠትና 4 ውፍጮ ቤቶችን በማሸግ 423\nኪሎግራም ጥራቱን ያልጠበቀና ለመፈጨት የተዘጋጀ አህልን ማስወገድ ተችሏል። በከተማዋ በሚገኙ አንዳንድ ዳቦ ቤቶች ላይ በተደረገው ተመሳሳይ ፍተሻም ከምግብነት የተረፉና የደረቁ ዳቦዎችን መልሶ በማዘጋጀት ለሽያጭ ማቅረባቸው በተደረሰባቸው 23 ዳቦ ቤቶች ላይ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ ድርጊቱን የሚከወኑባቸውን 150\nየተለያዩ ቁሳቁሶችን ጭምር በመያዝ ማስወገድ ተችሏል። አቶ አለማየሁ እንደሚሉት በነዚህ ሦስት ወራት እንደተደረገው አሰሳ ሁሉ በተለያዩ ጊዚያት በከተማዋ ተመሳሳይ ድርጊቶች ስለመፈጸማቸው በባለሙያዎች በታገዙ ድንገተኛ ፍተሻዎች ሲረጋገጥ ቆይቷል።ይሁን እንጂ አስካሁን አጥፊዎችን በበቂ ማስረጃዎች አስደግፎ ለህግ አካላት ማቅረብ ያለመቻሉ አጥፊ ግለሰቦች እንዲበራከቱና ድርጊቱ እንዲስፋፋ ምክንያት ሆኗል።እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ይህ ከሆነበት ዋንኛ ምክንያት አንዱ በባለስልጣን መስሪያቤቱ በፍተሻ ተይዘው የሚቀርቡ ማስረጃዎችን ተቀብሎ በላብራቶሪ የሚረጋግጥ አካል ያለመኖሩ ነው። ባዕድ ነገሮች የተቀላቀለባቸውን ምርቶች ለማስመ ርመር የተስማሚነት ምዘና ድርጅትን ጨምሮ ወደ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ቢላክም ምርመራው ግን በምርቱ ላይ ያሉትን ተጨማሪ ይዘቶች ከመጠቆም በተለየ ውህዱ መርዛምነት ወይም ጀሶን መሰል ባዕድ ነገሮች ስለመቀላቀላቸው የሚያመላክት ባለመሆኑ ለክስ ሂደት የሚያግዝ ማስረጃ እንደማይገኝበት ገልጸዋል።ይህ በመሆኑም ተጠርጣሪዎቹ በዋስትና በነጻ እንዲለቀቁ ምክንያት እየሆነ መጥቷል ። አልፎ አልፎ ጀሶና መሰል ባዕድ ነገሮችን በተመለከተ በአንዳንድ ግለሰቦች ላይ የተሰጠው የፍርድ ውሳኔን በተመለከተ ም/ዋና ዳይሬክተሩ ሲናገሩ ውህዱ በባለሙያዎች ፍተሻ አጅ ከፍንጅ በመያዙና በምስክሮች በመረጋገጡ ጭምር መሆኑን አክለው ገልጸዋል። የላቦራቶሬ ምርመራ ከሚያደርጉ ተቋማት የሚገኘ ውን ማስረጃ ለክስ ከመጠቀም ይልቅ የተያዘው ንጥረ ነገር መርዛማ ያለመሆኑ ላይ ብቻ ማተኮሩና ጉዳት አያደርስም የሚል እሳቤ መለመዱም እህልና መሰል ምግቦች ባልተገባ መልኩ እየተከለሱ ለገበያ እንዲውሉ ሰፊ ዕድልን እያበረከተ ነው ብለዋል። ለጉዳዩ የሚሰጠው ትኩረት ማነስና የባለሙያዎች ቁጥር አለመመጣጠን ለባለስልጣን መስሪያቤቱ ችግር ሆኗል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በወረዳና በክፍለከተሞች ላይ የሚስተዋለው የበጀት እጥረትም የቁጥጥር ሂደቱን በታሰበው ፍጥነት ላለመከወን ዕንቅፋት መፍጠሩን ገልፀዋል። ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ በፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ጉዳይ አጣሪ ዳይሬክተር ወይዘሮ ወሰንየለሽ አድማሱ በበኩላቸው የምግብ መከለሱንና የችግሩን ስፋት ከጉዳዩ ማስረጃ ማነስ ጋር ያያይዙታል።ዳይሬክተሯ እንደሚሉት ምግብ ከሌሎች እህል ነክ ጉዳዮች ጋር መቀላቀሉ ብቻ መርዛማ ነው ሊያስብለው አይችልም። ተገኘ የተባለው ውህድ ለጤና ጎጂ መሆኑን የሚያመላክት ማስረጃ በሌለበት አግባብም ተከሳሾችን ወደ ፍርድ ሂደት አምጥቶ ተጠያቂ ለማድረግ አዳጋች ይሆናል። እንደ ወይዘሮ ወሰንየለሽ ገለጻ ጤፍን ከሰጋቱራና ከጀሶ ጋር ቀላቅሎ ማስፈጨት ማሕበራዊ ተጠያቂነት ያለውና ነውር የሚባል ድርጊት ነው።ውህዱ ጉዳት የሚያስከትል ስለመሆኑ በበቂ ማስረጃ ካልተረጋገጠ ግን ግለሰቦቹን በህግ የሚያስጠይቅ አስገዳጅነት ሊኖር አይችልም።እነዚህ መሰረታዊ ጉዳዮች ባልተሟሉበት ሁኔታም የህግ አካላት ግዴታቸውን አልተወጡም ብሎ መውቀስ ተገቢ ያለመሆኑን ጭምር ዳይሬክተሯ ይናገራሉ። ዳይሬክተሯ አያይዘውም በቅርቡ በጸደቀው የመድሀኒት ቁጥጥር አዋጅ ላይ ባዕድ ነገርን አስመልክቶ የሰፈረው ነጥብ በበቂ ሁኔታ ያለመብራራቱን ተናግረዋል።በተቋሙ የአፈጻጸም መመሪያ ለጤና ጎጂ የሚባሉትና መርዛማ የሆኑት ተለይተው ያልተቀመጡ መሆናቸውን የጠቀሱት ወይዘሮ ወሰንየለሽ ተቋሙ ይህን ችግር ለመከላከል በራሱ አቅም የተደራጀ ላቦራቶሪ ሊኖረው እንደሚገባ ገልጸዋል።  በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የምግብ ሳይንስና ስነ-ምግብ ምርምር ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ተሰማ ምግብን ከባዕድ ነገሮች ጋር የመቀላቀል ድርጊት በኢትዮጵያ ብቻ ያለ እንጂ በሌሎች ሀገራት ያልተለመደ ስለመሆኑ ይናገራሉ።ይህ በመሆኑም አስከዛሬ ይህን ቴክኖሎጂ የመጠቀም አጋጣሚው ሳይተገበር ቆይቷል ።በመሆኑም እስከአሁን በነበረው ሁኔታ የላቦራቶሪ ውጤቱ በምግብ ውስጥ የተቀላቀለውን ባዕድ ነገር በአግባቡ ለይቶ ይህ ጀሶ ነው፤ይህ ሰጋቶራ ነው የሚል መረጃን አይሰጥም። ለችግሩ ስፋት ትኩረት በመስጠት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገራችን ተመራማሪዎች ተግባራዊ መሆን በጀመረው የላብራቶሪ አገልግሎት ግን ሰጋቱራና ጀሶ በጤፍ ውስጥ ሲጨመር በእንጀራ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ለውጥ የሚያረጋግጥ ቴክኖሎጂን ይፋ ማድረግ ተችሏል። ለዚህ የላብራቶሪ አገልግሎት የእውቅና ሰርተፍኬት መገኘቱን የተናገሩት አቶ ማስረሻ አስከዛሬ በነበረው ሂደትም ከላቦራቶሪ ባልተሰጠ ማረጋገጫና በምልከታ ብቻ በሚኖር አሰሳ ግለሰቦችን የመያዝ ልምድ እንደነበረ ያስረዳሉ።ይህ ሆኖ ሲገኝ ያለምንም ማስረጃ ሰዎች የሚጠየቁበት አግባብ በመኖሩ በተለመደ ውዥንብር ማህበራዊ ተጽዕኖ ሲፈጠር እንደነበር አስታውሰው፤ይህም አግባብ እንዳልሆነ አስታውቀዋል። በመሆኑም ላቦራቶሪው ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ሲገባ የተቀላቀለውን ባዕድ ነገር በአግባቡ ለይቶ ስለሚያስረዳ አጥፊዎች ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚ ያስችል ገልጸዋል። አዲስ ዘመን ቅዳሜ ታህሳስ 18/2012 መልካምስራ አፈወርቅ", "passage_id": "af3a95d88273fcfb904f6d73d22bc4ff" }, { "passage": "በቅርቡ ተግባረዊ በተደረገው የምግብና የመድኃኒት አዋጅ የአልኮል ማስታወቂያዎችና በተከለከሉ የትንባሆና የሺሻ ምርቶች ዝውውርና ሽያጭ ላይ የሚደረገውን ቁጥጥር ህብረተሰቡ እንዲያግዝ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ጠየቀ።በአንቀጽ 49 በንዑስ አንቀጽ አምስት ደግሞ የሺሻን ምርት ማምረት፣ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት፣ ማከፋፈል፣ ለሽያጭ ማቅረብ ወይም መሸጥ የተከለከለ ነው።በአዋጁ አንቀጽ 60 ንዑስ አንቀጽ አራትና አምስት \"ማንኛውንም የአልኮል ምርት በብሮድካስት አማካኝነት ማስተዋወቅ የተከለከለ መሆኑንና የአልኮል መጠጥን ከሎተሪ ዕጣ ወይም ከሽልማት ጋር በማንኛውም መንገድ በማያያዝ ወይም አልኮልን በቢልቦርድ በማድረግ የማስተዋወቅ ተግባር መከልከሉን\" አስረድተዋል።ኅብረተሰቡ በድርጊቱ ባለመሳተፍ እና የሺሻ ምርት የሚያመርቱ፣ ወደ ሀገር ውስጥ የሚያስገቡ፣ የሚያከፋፍሉ፣ ለሽያጭ የሚያቀርቡ ወይም ሺሻንም ሆነ ማንኛውንም ዓይነት የትምባሆ ምርት የሚያስጨሱ አካላትን በነፃ የስልክ መስመር 8482 ጥቆማ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል።አዋጁ በክፍል ስምንት አንቀጽ 65 ንዑስ አንቀጽ 23 ላይ \"ማንኛውም ሰው የተከለከለ ይዘት ያለው ትምባሆ ወይም በሕገ ወጥ መንገድ የገባን ምርት፣ ሺሻን ወይም የኤሌክትሮኒክ ኒኮቲን መስጫ መሳሪያን ወይም ሌላ ከሲጋራ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ለኒኮቲን መስጫ የሚያገለግል የቴክኖሎጂ ምርት ያመረተ፣ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ ያከፋፈለ፣ ያከማቸ ወይም የሸጠ እንደሆነ ከሦስት ወር እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ እስራት እና ከብር 1 ሺህ እስከ 2 መቶ ሺህ ይቀጣል።(ምንጭ፡-ኢዜአ)", "passage_id": "659bd2457d13515160e0616a5d5e4b5a" }, { "passage": "የኮቪድ-19 ወረርሽ ስርጭት አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ የችግሩን አስከፊነት ከግምት ያስገባ የጥንቃቄ እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡የፀረ ኮቪድ-19 እንቅስቃሴ በትኩረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል የሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ።የቫይርሱ ስርጭት በጎላበት እንደ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ እና በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ላይ የተቀመጡ ደንቦች ተግባራዊ መደረግ አለባቸው ብላዋል።\n", "passage_id": "46a835dad26213fac123c26957f48c59" } ]
63aaefa72e4685a78c07f61f96348365
1e5b708ea52a6dc2098961124a2a4f47
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን አንቀጽ 44 ላይ የነበራትን ተዓቅቦ አነሳች
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ ኢትዮጵያ ወንጀለኞችን አሳልፎ መስጠት (Extradition) የሚደነግገው የተባበሩት መንግሥታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን አንቀጽ 44 ላይ የነበራትን ተዓቅቦ አነሳች። የፌዴራል ሥነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ለዝግጅት ክፍሉ በላከው መግለጫ ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን አንቀጽ 44 ላይ ያላትን ተዓቅቦ አንስታለች ብሏል።ኢትዮጵያ የኮንቬንሽኑን አንቀጽ 44 አስመልክቶ ተዓቅቦ (reservation) እንዳላት የኮንቬንሽኑ ምዕራፍ ሦስት ውስጥ የተመለከተውን የሙስና ወንጀልን ወንጀል አድርጎ መደንገግና ምዕራፍ አራት ዓለም አቀፍ ትብብርን አስመልክቶ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2010 አስከ 2015 ባለው ጊዜ የነበራትን አፈጻጸም ለገምጋሚ አገራት አቅርባ ማስገምገሟን ገልጿል። የአፈጻጸም ግምገማን ተከትሎ ኢትዮጵያ እንድታስተካክል ተሰጥተዋት ከነበሩ ምክረ ሃሳቦች አንዱ ከላይ በተጠቀሰው የኮንቬንሽኑ አንቀጽ ላይ ያላት ተዓቅቦ እንደነበር በመግለጫው ተመልክቷል።በዚህ ግምገማ መሠረት ኢትዮጵያ አንቀጽ 44 ላይ የነበራትን ተዓቅቦ ያነሳች ሲሆን፤ የፕሮቶኮሉን ድንጋጌዎች በሙሉ በማክበር ግዴታዎቿን እንደምትወጣ አረጋግጣለች። አንቀጽ 44 ላይ ያላት ተዓቅቦ መነሳቱን መቀመጫውን ኦስትሪያ ቬና ላደረገው የተባበሩት መንግሥታት የአደገኛ ዕፅ እና ወንጀል መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት (UNODC) እንዳስታወቀችም የኮሚሽኑ መግለጫ አመልክቷል። ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን አባል አገር በመሆን በኮንቬንሽኑ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን ለመተግበር በመስማማት በፊርማዋ አጽድቃ በሕግ አውጪ ፓርላማዋ በአዋጅ ቁጥር 544/1999 ኮንቬንሽኑን በማጽደቅና የሀገሪቱ የሕግ አካል በማድረግ ኮንቬንሽኑን ከሚተገብሩ አገራት መካከል ትጠቀሳለች፡፡ አዲስ ዘመን ታህሳስ 24/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=38673
[ { "passage": "ባለፉት አስር አመታት በስራ ላይ የቆየውን የፀረ ሽብር አዋጅ ለማሻሻል በፌደራል አቃቤ ህግ የህግና ፍትህ ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤ ለወራት ሲያደርግ የነበረውን ጥናት አጠናቆ ተጨማሪ ለማሰባሰብና በባለድርሻ አካላት ለማስተቸት የጥናቱን ውጤት ለውይይት አቅርበዋል፡፡በጥናቱም በ2001 ዓ.ም የፀደቀው የኢትዮጵያ የፀረ ሽብር ህግ በርካታ ክፍተቶች ያሉበት መሆኑ ተመላክቷል፡፡በተለይም የዜጎችን ሰብዓዊም ሆነ ዴሚክራሲያዊ መብቶችን የጣሰና በርካቶችን ለእንግልት የዳረገ ነበረ ተብሏል፡፡በዚህም ጋዜጠኞች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ዋንኞቹ ሰለባዎች እንደነበሩ ተጠቅሰዋል፡፡አተገባበርን በተመለከተ ህጎቹ በዘፈቀደ መተግበራቸውና የፍትህ አካላትም በአግባ ህጎቹን ከማስተግበር አንፃር ከፍተኛ ክፍተት ነበረባቸው ተብለዋል፡፡የብሔራዊ ደህንነት መስሪያ ቤቱ ከህጋዊ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ በዜጎች ላይ አላስፈላጊ ምርመራዎችንና ግንኙነታቸውን ሲጠልፍ እንደነበርና አዋጁ ለተቋሙ የሰጠው ስልጣን የተጋነነ እና አተገባበሩም ክፍተት የነበረበት እንደነሆነ በጥናቱ ተመላክቷል፡፡በተጨማሪም ብሔራዊ ደህንነት መስሪያ ቤቱ በህግ ከተሰጠው ኃላፊነት አልፎ የፖሊስንና የሌሎች የፍትህ አካላትን ኃላፊነትም ያለአግባብ ሲጠቀም ነበር ተብሏል፡፡በሌላ በኩል የፌደራል ፖሊስ አቃቤ ህግ እና ፍርድ ቤቶችም የሽብር ተጠርጣሪዎች ላይ የነበራቸው አያያዝ የተዛባ ስለመሆኑ ተነስተዋል፡፡ፖሊስ በማረሚያ ቤቶች እስረኞች ላይ አላስፈላጊ ድብደባዎችንና እንግልቶችን ሲያደርስ ና ፍርድ ቤቶች ደግሞ የሽብር ክሶች ጊዚያቸው እንዲራዘም በማድረግና ፍትሃዊነት የጎደለውን ፍርድ ሲሰጡ መቆየታቸው በጥናቱ ተዳሰዋል፡፡ዋልታ ያነጋገራቸው የውይይቱ ተሳታፊዎች ጥናቱ ከሞላ ጎደል ችግሮች በጥልቀት የዳሰሰ መሆኑን ገልጸው ለቀጣይ የዲሞክራሲ ግንባታ ህዴትም አስተዋፅኦ የጎላ ይሆናል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ሆኖም በቀጣይ አህጉራዊም ሆኑ አለምዓቀፋዊ ህጎችንና ልምዶችን በመቀመር መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች በቀጣይ ሊካተቱ ይገባዋል ብለዋል፡፡ጥናቱን ያካሄደው የህግና የፍትህ ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤ በቀጣይ ሊወሰዱ ይችላሉ ያላቸውን ሁለት አማራጮች ያቀረቡ ሲሆን እነሱም የፀረ ሽብር ህጉን ሙሉ በሙሉ መሰረዝ አሊያም አዋጁ ያላቸውን ችግሮች ቀርፎ አሻሽሎ ማቅረብ የሚሉ ሃሳቦች ሲሆኑ የውይይቱ ተሳታፊዎች ሃሳብና አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡", "passage_id": "f58b0430d7a2eebfb6f60241204e6ca0" }, { "passage": "ድርጅቶችን በአሸባሪነት የመሰየም ሥልጣን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆን ሲገባው ለሌላ አካል መሰጠቱ አግባብ አለመሆኑንና በረቂቁ ላይ ሊታይ እንደሚገባ የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ በተካሄደ የአስረጅ መድረክ ተጠየቀ። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ፍትህና ዴሞክራሲ እንዲሁም የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ በተዘጋጀ የውይይት መድረክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመወሰን ሥልጣን እንዳለው እየታወቀ በረቂቅ አዋጁ አንቀጽ 21 ንዑስ አንቀጽ 4 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድርጅቶችን በአሸባሪነት እንዲሰይም የውሳኔ ሃሳብ ሲቀርብለት ማስረጃዎችን በመመርመር የውሳኔ ሃሳቡን ለመቀበል ወይም ውድቅ ለማድረግ ይቻላል የሚለው ድንጋጌ አግባብነቱ እንደገና እንዲታይ ተጠይቋል። ከውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቶ ተስፋዬ ዳባ በረቂቅ አዋጁ ላይ ትኩረት ከሚሹ ጉዳዮች ብለው ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል ሽብርተኝነትን የመሰየም ሥልጣን ከሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት መውጣት እንደሌለበት አስምረውበታል። ጉዳዩ እንደገና መታየት አለበትም ብለዋል። አቶ ተስፋዬ አያይዘውም ከዚህ በፊት በሽብርተኝነት ተሰይመው የነበሩ ድርጅቶች የአልሸባብና የአልቃይዳ ጉዳይ እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክርቤት ሽብርተኛ ብሎ የሚሰይማቸው ላይ በረቂቅ አዋጁ እንዲታዩ አስተያየት ሰጥተዋል። ሌላው የቋሚ ኮሚቴው አባል አቶ ዘለቀ መሐሪ ሃሳቡን በማጠናከር በሰጡት አስተያየት ምክርቤቱ የግለሰቦችን፣ቡድኖችንና በአጠቃላይ የዜጎችን ሰብአዊ መብት የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበት ጠቁመው ሽብርተኝነትን የመሰየም ሥልጣን ለምክርቤቱ መሰጠቱ መንግሥት ጉዳዩን በአግባቡ ለመከታተልና ለመቆጣጠር እንደሚያስችለው አመልክተዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ፍትህና ዴሞክራሲ እና የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች ተወካይ ወይዘሮ የሺእመቤት ነጋሽ አሻሚ የሆኑ ቃላትና ትርጉም የሚያስፈልጋቸው እንዲሁም ከመደበኛው የዳኝነት ሥርዓት እና ከሕገመንግሥቱ ጋር አንጻርም በረቂቅ አዋጁ ላይ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ መታየት እንዳለበት አሳስበዋል። ተወካይዋ በረቂቅ አዋጁ ላይ የተቀመጠውን በተለይ የሞት ቅጣትን በተመለከተ በአሁኑ ጊዜ የሞት ቅጣት ውሳኔ ተላልፎባቸው ግን ተፈጻሚ ባለመሆኑ ዜጎች በሥነልቦና እየሞቱና በከባድ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ እንዲሁም በዓለም አቀፍም የሞት ቅጣት ጉዳይ ጥያቄ እየቀረበበት መሆኑን በማስታወስ ጉዳዩ በትኩረት እንዲታይ አስተያየት ሰጥተዋል። በጠቅላይ አቃቤ ሕግ የሕግ ጥናት ማርቀቅና ማጽደቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በላይሁን ይርጋ ከሌሎች የሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር በጋራ ከቋሚ ኮሚቴዎቹ ለቀረቡት የተለያዩ ጥያቄዎችና አጠቃላይ ስለረቂቅ አዋጅ ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ በመስጠት አስረድተዋል። የሞት ቅጣትን በተመለከተ ለተሰጠው አስተያየት አቶ በላይሁን የሞት ቅጣት አንዱ የቅጣት ዓይነት መሆኑንና በተናጠል አዋጅ መቀየር እንደማይቻል ገልጸው፣ የፖሊሲ አቅጣጫ እንደሚያስፈልገው አመልክተዋል። በረቂቅ አዋጁ ላይ ሰኔ19 ቀን 2011ዓ.ም ከባለድርሻ አካላት ጋር መድረክ እንደሚኖርም በቋሚ ኮሚቴዎቹ ተወካይ ተገልጿል። አዲስ ዘመን ሰኔ 13/2011ለምለም መንግሥቱ ", "passage_id": "fa4539c0069d58abfbb0765955d7beed" }, { "passage": "አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 17 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የወንጀል ሕግ ስነ ስርዓትና የማስረጃ ሕግ፤ ሕገ መንግስቱን መሰረት ያደረገና አገሪቷ የፈረመቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ባካተተ መልኩ የሚሻሻል መሆኑን የሕግ ባለሙያዎች ማህበር ገለጸ።", "passage_id": "ec54e8b253a20c0c6c0ce07cb5970e0b" }, { "passage": "ዕለቱ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1963ዓ.ም በዚህ እለት ከቅኝ ግዛቶት ነፃ የወጡ 32 የአፍሪካ አገሮች መሪዎች የአፍሪካን ህብረት ቻርተር የፈረሙበትም ነው። የዛሬውን የአፍሪካን ቀን ምክንያት በማድረግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባን ኪ ሙን ዛሬ ባወጡት መግለጫ፤ ሰብአዊ መብትን ሙሉ በሙሉ ማስከበር የአፍሪካ ህብረት 2063 አጀንዳ ነው ብለዋል።የዘንድሮው የአፍሪቃ ቀን ክብረ በዓል፤ በአጠቃላይ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ፤ በተለይም የሴቶች መብት ከበሬታ እንዲረጋገጥ ትኩረት ይጠይቃል።በሴኔጋል በሚገኘው የተ.መ.ድ. የሴቶች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምእራብ እና መካከለኛ አፍሪካ ክፍሎች የሴቶችን አቅም ለማጎልበት በተነጣጠሩ ፕሮግራሞች ላይ የሚሰሩትን የቤ ዲያሎን (Yébé Diallo) ሳሌም ሰለሞን ማምሻውን በስልክ አነጋግራለች። ዝርዝሩን ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ። ", "passage_id": "5d1cbb30a076bb0c26966bd5982d2bb5" }, { "passage": " “ዘ ሰንትሪ” የተባለውን ይህን የሰብዓዊ መብቶች ቡድን በጋራ የመሠረቱት አሜሪካውያን፥ የፊልም ተዋናዩ ጆርጅ ክሉኒ እና በመብቶች ማስከበር ጉዳይ በንቃት የሚሠሩት ጆን ፕረንደርጋስት ትላንት ዋሺንግተን ዲሲ በተካሄደ ጋዜጣዊ ጉባዔ ላይ ተገኘ ያሉትን ማስረጃ አጋርተዋል።ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።\n", "passage_id": "726862a1f3215ddcf2350add6010cbef" } ]
19189ca3006d35df5bf11d60df2cac3c
2b6bd03e60f85dae7f1464f118acc0f6
የት ሄዱ?
ሁሌም ጠዋት ጠዋት ቁርሴን እየበላሁ ትስስራቸው ጠብቆ ፍቅራቸው ሞቆ አብሮነታቸው ጎልቶ የሚታዩኝ ጥንዶች ዘወትር አገኛቸው ከነበረበት ቦታ አጣኋቸውና ብዙ ጠየቅሁ። በነገራችን ላይ እኛ ግቢ የሰው አይን ማረፊያ መሆናቸውን፤ በሁሉም ዘንድ እውቅና የተሰጣቸው ጥንዶች መሆናቸው ጥያቄ የጠየኩት ሁሉ ስለነሱ ሳነሳ በሚመለሰው መልስ አወቅሁ። አዎን! እንደኔ ሌሎችም መድረሻቸው አሳስቦታል። “የት ሄደው ይሆን?” ብዙ መላ ምቶች አሰብኩ። “ተጣልተው ይሆን?” የዘንድሮ ፍቅር የኢንዶሚን አይነት ነው ቶሎ ሞቆ ቶሎ ደርሶ ተፋፍሞ ወዲያው ጣፍጦ በፍጥነት የሚያልቅ። የእርስ በርስ ቁርኝታችን ላልቶ ማህበራዊ ግንኙነታችን ሻክሮ እንደው ምን ነካን? የሚያስብል ደረጃ ላይ ደርሰናልና መፋቀር፣ ፍቅር ስናይ መገረም፤ መዋደድን ስናስተውል መመሰጥ ተላምደናል። በፍቅር መተሳሰሩ፤ በመውደድ መጣመሩ የሚሰጠውን ልዩ ጣዕም የሚያሳጡን ጉዳዮች በዝተዋልና ደጋግመን ምሬት፤ መስማት መነጣጠል ማየት አዘውትረናል። ፍቅር መገኛው የት ይሆን? ተፋቀሪዎችስ የት ገቡ? ማለታችን በዝቷል። ምን እናድርግ ሰው ከፍቅር ይልቅ ጠብ ቀሎታል። ከአንድነት ይልቅ መነጠል ብቸኝነት ውስጡ ሆኗል።“ሲሄዱም አንድ ላይ ሲጠጡም አንድ ላይ ለየብቻ እንዳላይ..” ያለው ዘፋኝ፤ ማለቴ የስንኙ ባለቤት እነዚህን ጥንዶች አይቶ ይሆን እንዴ? እንጃ ይመስላል፤ ለየብቻ መሆን ፈፅሞ የማይሆንላቸው እነዚያ ጥንዶች ብቻውን የሆነ ሰው ሲያዩ ምን ይሉ ይሆን? አሁን ላይ ብቸኝነት በርክቷልና ተላምደውት እያለፉን ይሆናል እንጂ አስቁመው ለምን ብለው ሁላ የሚጠይቁን ይመስለኛል። በዚህ ፍቅር የኑሮን ያህል በተወደደበት ዘመን ላይ ተገኝተን የእርስ በርስ ግንኙነታችንን አለዘብነው። ከአብሮነት ይልቅ ብቻነት ቀለለን። ሁኔታችን የሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህንን ግጥም “ፈራን ፍቅርን ፈራን” ደጋግሞ ያስነበንባል። አዎን ፈርተናል። መተሳሰርን አብሮነትን ንቀናል። እኔ ምለው? ለብቻ መሆንን የመረጥነው በአብሮነት መኖሩ ሰልችቶን ይሆን እንዴ? በእርግጥ መቀራረባችን አንድ ላይ መሆናችን እኮ አሁንም አለ። ችግሩ ውስጣዊ ጥምረት ነው ከኛ የነጠፈው። እንጂማ “ውዴ፣ ማሬ፣ ከረሜላዬ” መባባሉን በጣም ተክነንበታል። ማፍቀር ቢያቅተን እንዴት የፍቅር ተጓዦችን ማድነቅ ያቅተናል። ፍቅረኞችን ማየት ናፍቃችሁ ታውቃላችሁ? እውነተኛ ጥምረት ማርኳችሁስ ያውቃል? በበጎ ነገር መማረክ በጎነትን ያላምዳል። ፍቅርን መናፈቅ ወደ ፍቅር ጉዞ ሚያደርጉትን መንገድ ያሰምራል። እኔ ግን በእነዚህ ጥንዶች ተጠልፌያለው። አብሮነታቸው ሰምሮ፤ አንድነታቸው ቀጥሎ፤ መተሳሰራቸው ጎልብቶ ማየት ተመኘሁ። “ፍቅር ግን አለ?” ብለው ለሚጠይቁ ሰዎች “አዎን በደንብ ነዋ!” የሚያስብሉ የመውደድና የፍቅር ጥግ የሚያስኮመኩሙ፤ ፍቅርን ከማሳየት በላይ የሚኖሩት አሉ። “ይሄው እዚህ ዘንድ ተመልከቱ!” የሚያስብሉ አንዳንድ የፍቅር መልዕክተኞች አልፎ አልፎ ይገጥሙናል። እኔም አንድ መዝናኛ ውስጥ የሱስ ያህል አብሬ ካላየኋቸው ቅር የሚለኝ፤ ጥምረትና አንድነታቸው የሚያስገርመኝ ፍቅረኛሞች ገጥመውኛል። እንዲያው ጥብቅብቅ ብለው ሲበሉ፤ ሲያወሩ፤ ሲጓዙ አዎን ፍቅር ያስውባል፤ ያሳምራል የሚያሰኙ ጥንዶች ከእይታዬ ሳጣቸው ናፈቁኝ። የመዝናኛው ተጠቃሚ መነጋገሪያ፤ የቤቱ ደንበኛ ሁሉ አይን ማሪፊያ የነበሩት ጥንዶች የት ሄዱ? ስለናፈቁኝ ፍቅረኛሞች፤ ከአይኔ ስለራቁት ጥንዶች ደጋግሜ ማሰቤ ብሎም መጠየቄን አጠናከርኩ። በእርግጥ የጠፉበትን ምክንያት ባውቅም ጥፉ የተባሉበት መንገድ ቅር አሰኘኝ።ትናንት ከአንዱ ባልደረባዬ ጋር ስናወጋ ማዕቀብ ተጥሎባቸው ከቤቱ መጥፋታቸው ተነገረኝ። እርግጥ ነው አንዳንዴ ይሳሳሙ ነበር። መሳሳማቸው ግን በፍቅር ስለሆነ በጠብ ከምንናከሰው ከብዙዎቻችን የነርሱ የተሻለ ነው። እርግጥ ነው አብረው የሆኑ ሳይሆን አንድ የሆኑ ያህል ይጠባበቁ ነበር። ግን ከኛ መገፋፋት የነእርሱ መጣበቅ ይሻላል። እርግጥ ነው በተቀመጡበት ሁሉ በፍቅር አፍ ላፍ ገጥመው ያወሩ ነበር። ግን ከኛ ተደብቆ ከመተማማት እሱ ይልቃል። በማውራታቸው መሀል ከተራ ግንኙነት ያለፈ ጥምረት የሚፈጥር መግነጢሳዊ ሃይል አለ። ሲያወሩ፣ ሲሳሳሙም ሰው አያዩም። ምክንያቱም ፍቅር እውነት እንጂ ሌላ አይታየውም። ፍቅር አይፈራም። በእርግጥ ጨዋነት በሚያጎድል መልኩ፣ ባህልን በማያፋልስ መልኩ ቢያደርጉት መልካም ነበር። ሲሳሳሙ ግን ሁሉም አፍጥጦ ያይ፣ ይመለከታቸው ነበር። መሳሳማቸውን እየተቃወመም ቢሆን እንዳያቋርጡት ይመኝ ነበር። እነሱም ባስተሳሰራቸው ፍቅር ተጠልለው ሌላውን አያዩትም ነበር። ፍቅር እኮ መሸሸጊያ፤ መከለያ ነው። እሱ ውስጥ ተሁኖ ሌላ አይታይም። ፍቅር ያሉበትን አስረሳቸው። እና እነዚህ ጥንዶች ሁሌ ከሚቀመጡበት ቦታ ሳጣቸው ጠየቅሁ። ሁሌም ከሚጓዙበት መንገድ ሳጣቸው የትነታቸውን ለማወቅ ወተወትኩ። “አትምጡ!” ተብለው እንደሆነ ስሰማ ተገረምኩ።“መፋቀራችሁ፣ መጣመራችሁ፣ መዋሃዳችሁ ትክክል ነው። አንዳንዴ ሳታውቁት የምትሳሳሙትን ቢያንስ አቁሙ” ማለት ሲገባ፤ “እዚህ ቤት መሳሳማችሁ ያስከፋቸው ሰዎች ስላሉ ወደዚህ ድርሽ ባትሉ መልካም ነው” መባሉ ግን ተገቢ አይደለም። እናም ተፋቃሪዎቹን ያባረረው መዝናኛ ጠበኞችን ሰብስቦ ሊያውል ማሰቡ ይሆን እንዴ? የት ይሆኑ ግን? ያያቸው አለ? አበቃሁ! ቸር ይግጠመን።አዲስ ዘመን መስከረም 30/2012
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=20466
[ { "passage": "እግር ጥሎዎት ጠብ የተጫረበት አካባቢ ይደርሱ ይሆናል፤ አጠገብዎ ያሉ ሰዎች በነገር አንድ አንድ ሲሉ ቆይተው ጠብ ውስጥ ገብተው አይተውም ሊሆን ይችላል፡፡ በቅርብ ርቀት ጠብ ተነስቶም ሊያዩ ይችላሉ፡፤ ይህ ሁሉ ሲሆን የእርሶዎ አቋም ምንድን ነው? አንዳንዶች ጠብ ሲያዩ እግሬ እውጪኝ ብለው ይፈተለካሉ፡፡‹‹ማምለጥ ነው ለጫማው በሁዋላ ይታስበበታል›› ነው ያለው ማስታወቂያው፤ ‹‹እስከሚጣራ›› እንዳለችው እንስሳም እንደማለት ነው፡፡ ከዚህ አልፈው ሲገላግሉ የሞቱትን፣ የተመቱትን፣ ወይም ስለእነዚህ ተጎጂዎች የሰሙትን እያስታወሱም ወራጅ አለ ብለው እግሬ አውጪኝ የሚሉ በቅርብ ርቀት ሆነው ወሬውን ተቀብለው አቀነባብረው የሚናገሩም ጥቂት አይደሉም፡፡ እነዚህ አይነቶቹ ሰዎች ሲሸሹ መልስ ብለው እንኳ የሚመለከቱ አይደሉም፡፡ እነዚህ ሰዎች አንዳንዴ ትክክል ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የአካል እና የህሊና ጉዳት ሊከሰት ይችላል፤ ጠበኞቹ ደንጋይ መወራወር ቢጀምሩ የማን ያለህ ይላሉ፡፡ ቢታኮሱስ፤ አይጣል ነው፡፡ ምስክርነት መጠራትም አለ፤ ለዚያውም ምን ቅብጥ አርጎ እዚያ ውስጥ አስገባኝ የሚያሰኝ፡፡ የኛ ሀገር ምስክርነት ስራ ያስፈታልና እሱም ሌላው ዳፋ ነው፤ በተከሳሽ በኩል ቅሬታ ካስከተለ ደግሞ ባለጋራ መፍጠር ይከተላል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ትንሽ ቀረብ ብለው ሁኔታውን ይከታተላሉ፡፡ እነዚህ ሁለት ወገኖች በግርግሩ ላለመጎዳት በሚል ነው ራሳቸውን ለመጠበቅ የሚጥሩት፡፡ እነዚህም ልክ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የተጣሉ እናገላግላለን ያሉ የቀመሱት ቡጢ ሊታሰባቸው ይችላል፤ አንተን ማን ገላጋይ አደረገህ? አስደበደብከኝ ብለው ሊማቱ የሚጋበዙ ጠበኞች ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ እስኪዋጣላቸው ድረስ ወይም ገላጋይ እስከሚገባ ድረስ ቆመው መመልከታቸው ጥፋት አይኖረውም፡፡ እነዚህም እንደ ፈርጣጮቹ ገላጋይ ለመሆን ገብተው የተመቱ፣ የተሰደቡ፣ የሞቱም እንዳሉ አስበው ዳር ቆመው መመልከትን ይመርጣሉ፡፤ ምንም እንኳ ሰዎች ሲጋደሉ ቆሞ መመልከት ተገቢ ባይሆንም፣ የእነዚህ ወገኖች ዳር ሆኖ መመልከት ስህተት ነው ብሎ ለመደምደም አያበቃም፡፡ ሌሎች ግን የተከፈለው ዋጋ ይከፈል ብለው ሰው ሲጎዳ እና ሲጋደል ቆመው አይመለከቱም፤ ዘለው ጠበኞቹ መሀል ገብተው ይገላግላሉ፡፤ እኔም አንድ ቀን ተመሳሳይ ችግር ቢገጥመኝ ማን ይደርስልኛል ብለው አስበው ሳይሆን በቃ ሰዎችን መታደግ እንዳለባቸው አምነው ላይሆን ይችላል፡፤ ብቻ ይገላግላሉ ያስታርቃሉ፡፡ በእዚህ አይነት መልኩ ሰዎችን ከአስከፊ አደጋ የታደጉም ጥቂት አይደሉም፡፡ የሚገላግሉት ደግሞ የሚያውቁት ሰው ስለሆነ ብለው ሳይሆን በቃ ሰዎች ተጣልተው የከፋ ጉዳት እንዳይከተል ለማድረግ ነው፡፡ አንዳንዴ ቆሞ መመልከትም ሆነ መገላገል የሚያስከፍለው ዋጋም ይኖራል፡፡ ጠቡ የከፋ እና የሰፋ ሊሆን ይችላል፤ ፓሊስ ተሳክቶለት ይደርስና ለማናቸውም ብሎ በአካባቢው ያለውን ሰው ሁሉ አፍሶ ወደ ማረፊያ ቤት ሊወስድ ይችላል፡፡ መረጃ እስከሚገኝም እስር ላይ መቆየት ይከሰታል፡፡ እነዚህ ወገኖች ይህ ሊሆን እንደሚችል አውቀውም ሳይውቁም ሊሆን ይችላል እርምጃውን የወሰዱት፡፡ ከማገላገሉ ጋር በተያያዘ ምንም ይፈጠር ምን እርምጃቸው ትክክል ነው፡፡ ከእዚህ የከፋም ሊያጋጥም እንደሚችል ጠቅሻለሁ፡፡ በቦክስ መመታት፣ በስለት መወጋት፣ በድንጋይ መመታት፣ መሰደብ፣ ለዛቻ መዳረግ ወዘተ ሊከተል ይችላል፡፡ በምስክርነት መጉላላት ደርሶም ይሆናል፡፡ በግልግል ወቅት ከደረሰ ጉዳት ጋር ተያይዞ መከሰሰም ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ይሄ ይሄ ሁሉ ሁለተኛ ኮሽ ባለበት ቦታ አልገኝም የሚሉ ሰዎች እንዲፈጠሩ ያደርግ ይሆናል፡፡ በመሰረቱ ሰው ሲጣላ እያዩ መሄድ ወይም ዝም ብሎ መመልከት ሰውኛ አይደለም፡፡ ማህበራዊ ሃላፊነትን አለመወጣትም ይሆናል፡፡ በህግ መነጽርም ቢሆን የሚያስኬድ አይመስለኝም፡፡ አካል ሲጎድል ሲጋደሉ ቆሞ ማየት ወይም መሸሽ በህግም የሚያስኬድ አይመስለኝም፡፤ ቤተሰብ፣ ጎረቤት ቀዬ ወዘተ ሰላም እንዲሆን ሃላፊነቱ የፖሊስና የመሳሳሉት የፀጥታ ሀይሎች ብቻ አይደለም፡፡ የእያንዳንዱ ሰው ሃላፈነትም ጭምር ነው፡፡ በማገላገል ወቅት ቆሞ በመመልከት ወቅትም ሆነ በሽሽት ወቅት ካጋጠመ ችግር ጋር በተያያዘ ሊፈጠር የሚችለውን የነግ በኔ አመለካከት ለጊዜው እናቆየውና ሰዎች ማህበራዊ ሃላፊነት ያለባቸው መሆኑን ግን እናስብ፡፡ እያንዳንዱ ሰው ጠብ ሲመለከት መፍትሄ ለማፈላለግ ጥረት ማድረግ ይኖርበታል፡፤ ጠብ እየሰፋ ሄዶ ዳር የቆመውንም መንደር ያለውንም ላይምር ስለሚችል በጊዜ እንዲበርድ ማድረግ ይገባል፡፡ ሲሆን ሲሆን ደግሞ አስታርቆ መሸኘት ወይም ለህግ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ትክክለኛው አካሄድ ነው፡፡ ችግር እንዳይሰፋ የሚያደርግ በመሆኑም ማህበራዊ ሃላፊነትን መወጣት ነው፡፡ የጠቡን ደረጃ መመዝንም ያስፈልጋል፡፡ እነማን ተጣሉ የሚለውን መመልከት ይገባል፡፡ የልጆችን ጸብ መገላገል አያዳግትም፡፡ አስቸጋሪ የሚሆነው ድንጋይ ፣ ስለትና የመሳሰሉትን ጭምር\nይዘው የሚጣሉትን መገላገል ይሆናል፡፡ እሱም ቢሆን መላ ይኖረዋል፡፡ መገላገል አለመቻሎን ካወቁም ሊገላግሉ ይችላሉ ተብለው ለሚታሰቡት መንገርም አንድ መላ ነው፡፡ መሸሽ ወይም ቆሞ መመልከት ግን ትክክል አይደለም፡፡ ቢያንስ ነግ በእኔን\nማሰብ ያስፈልጋል፡፡ ሰዎች\nሲደባደቡ መሸሽ፣ ቆሞ መመልከት፣\nአለመገላገልና አለማስታረቅ ማህበራዊ\nሃላፊነትን መሸሽም ነው፡፡\nለችግር መላ ፋላጊ\nእንጂ ችግር እንዲሰፋ\nእና እንዲፋፋ መፍቀድ\nአይገባም፡፡ ጸብ እያዩ\nእዚያው በጸባላችሁ ማለቱ\nሜዳ ሲቃጠል ተራራ\nይስቃል እንደሚባለውም ሊሆን\nይችላልና ማህበራዊ ሃላፊነትን\nመወጣት ያስፈልጋል፡፡አዲስ ዘመን ሚያዝያ 29/2011", "passage_id": "8e544dda158a61e257f7727ef093e95d" }, { "passage": "የሌላውን ሀገር ባላውቅም በእኛ ሀገር  ግን የማንተገብራቸው በርካታ አባባሎች አሉን። ምሳሌ ጥቀስ ካላችሁኝ ከመነሻዬ ሀሳብ ጋር ከሚቀራረቡት መካከል ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ፣ ሳይቃጠል በቅጠል፤ አስሬ ለካ አንዴ ቁረጥ፤ ሰዶ ማሳደድ ቢያምርህ….. ፤ ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ…..የሚሉት ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው። ብዙ አልተጠቀምንባቸውም  እንጂ   በየመስኩ በየጉዳዩ ብዙ ተረቶች ብዙ አባባሎችና ወጎች  አሉን።ያለሁት ኮተቤ  ከአንድ የዘመዴ ቤት ነው የታመመች ልጇን ለመጠየቅ። ልጅቱ ደግሞ እግሯን  በጀሶ ጠቅልላ መሬት ላይ የተነጠፈ ፍራሽ ላይ ተኝታለች። እንዴ?  ምን ተፈጥሮ ነው? ጠየቅኩ፤ «ወለም ብሏት» ስትይኝ ቀላል መስሎኝ ነበር አልኩ ደንገጥ ብዬ። «እንዳትደነግጡ ብዬ ለሁሉም እንዲሁ ነው ያልኩት። ለነገሩ ዶክተሩ አጥንቷ ብዙም አልተጎዳ፤ በዛ ላይ ልጅ ስለሆነች ቶሎ  ይስተካከላል ብሎኛል» አለች።  ለመሆኑ ምን ሆና ነው?እናቲቱ « አልሰማ ብላ» በማለት ጀምራ ባጭሩ ታሪኩን አወጋችኝ። በአካባቢው ረጅም ጊዜ የወሰደ ሰፊ የመንገድ ሥራ እየተከናወነ ነው። እናም በየቀኑ ወይ ይቆፈራል ወይ ይናዳል ይሄ ሲሆን ግን መንገዱ  በከፊል ለመኪና ይዘጋል። እግረኛው በአንድ ጎን  የግለሰብ አጥር በሌላ  በኩል ደግሞ ገደል በሚያዋስኑት ጠባብ የግራና ቀኝ መንገዶች እየተጠባበቀ ነው የሚጓዘው። አንዳንድ ቦታ ገደሉ ረጅም ስለሚሆን እናት ልጇን በዛ መንገድ እንዳትሄድ  ርቀት ቢኖረውም በአስፋልት ዞራ እንድትመጣ በተደጋጋሚ መክራት ነበር፤ ግን አልሆነም። ከጓደኞቿ መለየት ያልመረጠችው ልጅት ከጓደኛዋ ጋር እንደተያያዙ  ተንሸራተው ከአንዱ ገደል ይወድቃሉ። እንደተነገረኝ ከሆነ ሁለቱም ለከፋ ጉዳት ባይዳረጉም ለቀናት ከትምህርት ገበታቸው መለየታቸው ግን አልቀረም።እንደኔው ሊጠይቁ የመጡ አንዲት እናት «አሁንማ አስተካከሉት እኮ ትናንት የእከሌ አባት አሉ  ስም እየጠሩ ወድቀው ላይሞቱ ነው የተረፉት፤  ዛሬ በደንብ አስተካክለውታል» አሉ በማፅናናት አይነት። ምን ዋጋ አለው ፈጣሪ ባይደርስላት ሞታ አልነበር። ስንት ሰው  በቀን በማታ መከራውን ሲያይ ምን ሰሩ?  ድሮም አንድ ሰው ሞተ፣ መኪና ተገለበጠ ካልተባሉ እንደማይሠሩ ይታወቃል፤ የህዝቡን አቤቱታ መች ሰምተውን ያውቃሉ አለች ዘመዴ ምርር ብላ። እነሱ ወሬያቸውን ቀጠሉ እኔ በሀሳብ ነጎድኩ ግን እውነት እስከ መቼ እሳት እያጠፋን እንኖራለን ?።ተሰናብቼ ወጥቼ ከሃሳቤ ሳልላቀቅ መገናኛ አካባቢ ስደርስ ሻይ ቡና ለማለት መተባበር ህንፃ ላይ ባለ አንድ ካፌ ውስጥ ተቀመጥኩ። ቁልቁል የባቡሩን አካፋይ የቀለበት መንገድ ስመለከት ትኩረቴንም ስሜቴንም የሚስብ ተመሳሳይ  ነገር አስተዋልኩና በጥሞና መከታተል ጀመርኩ። አካባቢውን በደንብ አውቀዋለሁ፤ የጎዳና ላይ ንግድ የተጧጧፈበት ነው። በተለይ አመሻሽ ላይ ያለው ገበያና የሚቀርበው ሸቀጥ «ንግድ ፈቃድ፣ ግብር፣ ቤት ኪራይ» ለምኔ  የሚያሰኝ ነው።  ይሄ ታዲያ  ለወጣቶቹ ነጋዴዎች ከጠባቂዎች ጋር የሚደረገውን  የድብብቆሽ ጨዋታ  በየቀኑ ማሸነፍ ይጠይቃል።  እነዚህ ነጋዴዎች አብዛኞዎቹ በወጣትነት እድሜ ክልል ያሉና ከአዲስ አበባ ውጪ የመጡ በመሆናቸው ባንድ እጃቸው ዱላ በአንደኛው ደግሞ ኮፍያቸውን ይዘው ለሚያሯሩጧቸው የሸገር ጠባቂዎች  የሚረቱ አይደሉም። እንዲያውም አንዳንዶቹ ያንን ኮተት ይዘው እንደዚያ መሮጥ ከቻሉ በዱላ ቅብብል ውድድር ቢሳተፉ እላለሁ።እንግዲህ ልብ በሉ መንግሥት የጎዳና ላይ ንግድን የሚያበረታታ ባይሆንም ወደ ህጋዊ ሥርዓት ለማስገባትና ነባራዊውን ሁኔታ ከግምት በማስገባት በመንገድ ዳርቻ እንዲሸጡ የተፈቀደላቸው ህግ አክባሪ የጎዳና ላይ ነጋዴዎች በየቦታው አሉ። በዚሁ አካባቢ እንኳ ከአደባባዩ  ሁለት መቶ ሜትር ባልሞላ ርቀት አምቼ አጥር ስር በተፈቀደላቸው ቦታ ተወስነው የመኪናና የእግረኛ እንቅስቃሴ ሳያግዱ የሚሠሩ የጎዳና ላይ ነጋዴዎች ቢኖሩም እቃቸውን የሚገዛ  ሸማች የሚደርሳቸው  በአደባባዩ ከሚሯሯጡት  ህገ ወጥ ነጋዴዎች የተረፈው ብቻ ነው። ከታች የምገልጽላችሁ ትእይንት ደግሞ እጣ ሳያወጡ፣ አቦሰም  ሳይጣጣሉ  ጠባቂዎቹና ነጋዴዎች እንዴት  የአባሮሹን ጨዋታ እንደሚጀምሩ ነው።አዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን እግረኛውንና አሽከርካሪውን ለመለየት በከለለው  ብረት ላይ  ደማቅ ሰማያዊ ቀለም ያለው ባለ አርማ ዩኒፎርም የለበሱ የቦሌ  ክፍለ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች ሦስት ሆነው ተደግፈው ያወራሉ። የሚያወሩት ደግሞ ስለ ኑሮ ውድነት ነው። ፎቅ ላይ ሆነህ እንዴት ይሄን አዳመጥክ የሚለኝ ካለ ግምቴ መሆኑን በማስቀደም ለግምቴ መነሻ የሆነኝን  ምክንያት አቀርባለሁ።ከፌስ ቡክ እንደተማርኩት ከሆነ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሰብሰብ ብለው ከታዩ ድንጋይ ውርወራ ሊጀመር በመሆኑ ከአካባቢው መራቅ አልያም ኮፍያ ብጤ ጣል ማድረግ ከተማሪዎቹ ንረታም ሆነ  ሰላማዊና አጥፊን ሳይለዩ ከሚቀጡት ህግ አስከባሪዎች  ራስን ለመታደግ ይረዳል። ተማሪዎቹ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ከሆኑ ስለፍቅር ጓደኛቸው እንደሚያወሩ የሚገመት ሲሆን፣ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች ከሆኑ ስለ ፊልም እንደሚሆን እንገምት። ወደ መንግሥት ሠራተኛው ሲመጣ ጉዳዩ የሚወሰነው በእድሜ አልያም በክፍል ደረጃ ሳይሆን በደመወዝ ይሆንና ባጭሩ ዝቅተኛው ተከፋይ ስለኑሮ ውድነት መካከለኛው ተከፋይ ስለሥልጣንና እድገት ፣ ከፍተኛው አመራር የየእለት ጭውውቱ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያጠነጠነ መሆኑ በዚሁ ፌስ ቡክ ማየት ችያለሁ። የፖለቲካው ነገር ግን ደመወዝም ዕድሜም የሚገድበው አይደለም፤ በተለይ አሁን አሁን።እጅና አፍ አይጠፋፉም ብዬ ከግማሽ ሰዓት ላላነሰ ጊዜ እጄን ከብርጭቆዬ አገናኝቼ ወደ አስፋልቱ ባደረግሁት ማፍጠጥ እነዚያን ስለ ኑሮ ውድነት የሚያወጉ የደንብ አስከባሪዎች የጎዳና ላይ ነጋዴዎቹ እንደ ቀልድ ባጠገባቸው ያልፏቸው ይዘዋል፤ ትንሽ መጠንቀቅ የሚመርጡት ደግሞ ጣደፍ ጣደፍ እያሉ ያልፋሉ፤ ለነገሩ ከአስፋልት ማዶ  የሚያልፉ  ጥንቃቄ  የሚያበዙ  ነጋዴዎችም አሉ።ይህን ጉድ ሳላይ አልነሳም ብዬ ለአንድ ሰዓት ከቆየሁ በኋላ አስራ አንድ ሰዓት ተኩል ሲሆን በርከት ያሉ ደንብ አስከባሪዎች ከየአቅጣጫው በመምጣት ባጠገባቸው እያለፉ ወደ አደባባዩ ገብተው እቃቸውን ከዘረጉት የጎዳና ላይ ነጋዴዎች ጋር የዘወትር አባሮሻቸውን ቀጠሉ። አንዳንዶቹ ሊይዟቸው የሚፈልጉ አይመስሉም ፤ በፍጥነት መሮጥ ይጀምሩና ሊደርሱባቸው ሲሉ ፍጥነታቸውን ይቀንሳሉ።  ለነገሩ «ከልብ ካለቀሱ» የሚለውን አባባላችን  መነሻ  አድርገን ካየነው ምንስ ፈጣን ቢሆን   እቃ ተሸክሞ የሚሮጥን በባዶ ሮጦ መያዝ አለመቻል ተቀባይነቱ እዚህ ግባ የሚባል አይሆንም።  ግን እነዚህ ደንብ አስከባሪዎች የሚሰጣቸው ሥልጠና ምንድነው? ቤት ተሠርቶ፣ አጥር ታጥሮ ሲያልቅ ማፍረስ በአጭሩ መቅጨት የሚችሉትን ለግጭትም ለንትርክም ምክንያት ሲሆን ይታያል።ከዓመታት በፊት አንድ የመኪና ጥገና  የሚሠራ ጓደኛዬ የነገረኝ « የወረዳችን አስተዳደር  21 ዓመት በጋራዥነት ሲያገለግል የነበረውን ግቢ  ከስፋቱ  ጀምሮ ደረጃ አያሟላም ብሎ  እንዲያስፋፉ የማስተካከያ ጊዜ ይሰጣቸዋል።  አስተዳደሩ ምንም እንኳ በህግ የተቀመጠ ነገር ቢናገሩም  በሦስቱም አቅጣጫ በግለሰብ መኖሪያ ቤቶች የተከበበችው  ቦታ ወዴትም እንደማትሰፋ በእርግጠኝነት ያውቁ ነበር። እናም ቀኑ ደርሶ ጋራዡ መስፋት ባለመቻሉ  ተዘጋ» የኔ ጓደኛና ባልደረባው  ከባድ መሳሪያ የማያስፈልጋቸውን ጥገናዎች በየቤታቸውና በየመንደሩ መንገድ እየዘጉ መሥራቱን ቀጠሉበት።  በዛ ሰሞን  እንዴት ነው ያዋጣል? ብዬ ላቀረብኩለት ጥያቄ የሰጠኝ ምላሽ እንዲህ የሚል ነበር  « እኛና መንግሥት ከጋራ ተጠቃሚነት ወደ የጋራ ተጎጂነት ተሸጋግረናል፤ እኛ በጠራራ ጸሀይ በየጎዳናው እየተሽከረከርን ለመሥራት ተገደናል መንግሥት ደግሞ ብታንስም መሰብሰብ የሚችለውን ግብር አጥቷል፤ ድሮ ማወራረድ ስላለ ብዙ ነገሮችን ስንገዛ በደረሰኝ ነበር፤ አሁን ህጋዊ ነጋዴዎች ጋር የሚያስኬደን ጉዳይ የለም፣ ነገሩ ሁሉ አየር በአየር ሆኗል»።  አለኝ እያዘነም ፤እየተናደደም።ምንም እንኳ ህግ መከበር ቢኖርበት  ሰው ከሰላማዊ መንገድ ተገፍቶ ሲወጣና አማራጭ ሲያጣ  ወዴት እንደሚያመራ የሚያሳየን ይመስለኛል። እነዚህ በየታክሲው ላይ የምናያቸው እቤትዎ ድረስ መጥተን ፍሪጅ እናድሳለን፣ ቴፕ፣ ቴሌቪዥን  እንጠግናለን የሚሉ ማስታወቂያዎችም የዚሁ ውጤት ይመስሉኛል። ይሄን ሳይ  ህግና ሥርዓት አክብረው የሚንቀሳቀሱትን  አለመደገፍና አለመንከባከብ ህገ ወጦችን  ማበረታታት፤ ህጋዊው መንገዱንም መግፋት ይሆንብኛል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 20/2011", "passage_id": "89f5dae4825b4812f1864181eed9151f" }, { "passage": "መቼም\nእንግዲህ ይሄ ታክሲ አያሳየኝ የለው! ለነገሩ ይሄኛውን እንኳን ያስተዋልኩት እዚያ ትልቁ ሰማያዊ ተሽከርካሪ ላይ ነው፡፡ ያ ማነው ስሙ ‹‹ፐብሊክ ሰርቪስ›› ማለቴ የመንግሥት ሠራተኞችን ከቤት ወደ መሥሪያ ቤት እና ከመሥሪያ ቤት ወደ ቤት የሚወስደው ሰማያዊው ተሸከርካሪ ማለት ነው(አሁን ተግባብተናል)፡፡ በነገራችን ላይ ወደ ዋናው ጉዳይ ከመግባቴ በፊት እዚህ ተሸከርካሪ ላይ አንድ ያስተዋልኩትን ሌላ ነገር ላስቀድም፡፡ ጠዋት ጠዋት እንኳን መቀመጫ መቆሚያ አይገኝም፤ ማታ ማታ ግን በባዶ ወንበር ነው የሚሄደው፡፡ ለምን ይሆን? እዚሁ ተሽከርካሪ ውስጥ ስጓዝ አንድ ቀልደኛ ሲያወራ የሰማሁት ነገር እውነት ሳይሆን አይቀርም ። እንግዲህ እሱ ሲል እንደሰማሁት ማታ ማታ ባዶ የሚሆነው ብዙ ሰዎች ‹‹ክላስ›› ስላላቸው ነው። ስለሚማሩ ማለት ነው፡፡ ነገሩን\nሲያጣምመው ደግሞ ‹‹ማታ ማታ ወደ ሌላ ክላስ የሚሄዱም አሉ›› ብሎ ፈገግ አሰኝቶን ነበር፡፡ ብቻ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ግን ማታ ማታ የጠዋቱን ያህል የሰው ብዛት የለውም፡፡ ኧረ ጉድ! ይሄ አሁን የነገርኳችሁ አስተውሎት ቀጥሎ ከምናገረው ዋናው ጉዳይ ጋር ለካ ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡ ቆይ ግድለም እንደምንም አገናኘዋለሁ! ምንም እንኳን ብዙ ቀን የማስተውለው ቢሆንም የአንድ ቀኑ ግን የተለየ ሆኖብኝ ነው ዳግመኛ እንዳስብበት ያደረገኝ፡፡ አንድ በዕድሜ አንጋፋ የሚባሉ ሰውዬ ናቸው ይህንን ትውስታዬን የመለሱት። የክፍል ውስጥ ‹‹ሀንድ አውት›› ይዘዋል፡፡ እንግዲህ ሰውዬው እየተማሩ ነው ማለት ነው፤ ሰሞኑን ፈተና ያለባቸው ይመስላል ።የሚያነቡትን የትምህርት አይነትና የትምህርት ደረጃ አላየሁትም(ምናልባት ለዶክትሬትም ሊሆን ይችላል)፡፡ እኔን የገረመኝ በዚህ ዕድሜያቸው እንዴት እስከዶክትሬት ዲግሪ ድረስ አልጨረሱም ብዬ አይደለም(ገና ለመጀመሪያ ዲግሪም ሊሆን ይችላል)፣ ባይጨርሱስ ለምን በዚህ ዕድሜያቸው ይማራሉ ብዬም አይደለም። ግን በዕድሜ ገፋ ያሉ ስለሆነ ብዙም ስላልተለመደ ነገሩን ትኩረት እንዲሰጠውና የሌሎችን ሁሉ እንዳስታውስ ስላደረገኝ ነው ያስገረመኝ። በዚያ\nላይ እኝህ ሰውዬ የታሪክ መጽሐፍ፣ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ወይም ጋዜጦችንና መጽሔቶችን ሲያነቡ ማየት ነበር የሚያመሳስላቸው። አሁንም ልድገመውና ለምን ተማሩ ማለቴ ሳይሆን ኑሮን ለማሻሻል ስለመሰለኝ ነው፡፡ የሰውዬው መነሻ ሆነኝ እንጂ ይሄ ነገር በተደጋጋሚ ያስተዋልኩት ነው፡፡ በትራንስፖርት ጋዜጣና መጽሔት ከሚነበበው ይልቅ ‹‹ሀንድ አውት›› የሚያነብ ነው የሚበዛው፡፡ ጥሩ ነው መነበቡ፤ ዳሩ ግን እውቀት ፍለጋ አይደለም፡፡ ኑሮን ለማሻሻል የሚደረግ ሩጫ ነው፡፡ ካሉበት የሥራ መደብ የተሻለ የሥራ መደብ ለመቀጠር ሲባል ነው፡፡ ይሄን ነገር የሚያጠናክርልኝ አንድ ጓደኛዬ የነገረኝን ገጠመኝ ላጫውታችሁ፡፡ ይህ ገጠመኙን ሲያወራ የሰማሁት ጓደኛዬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪውን እየተማረ ሳለ ነው፡፡ እናም ክፍል ውስጥ አንድ ቀን መምህሩ እንዲህ አላቸው፡፡ ‹‹እስኪ ሳትዋሹ እውቀት ለመጨመር ብላችሁ የምትማሩ እጅ አውጡ›› አለ መምህሩ። ሁሉም ተማሪ እየተያየ ዝም አለ ። መምህሩም ቀጥሎ ይህን ያለበትን ምክንያት አብራራ። ተማሪዎች በተለይም ሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪያቸውን የሚማሩት እውቀት ለመጨመር ሳይሆን ኑሮን ለማሻሻል ብለው ነው፤ የተሻለ ቅጥር ለማግኘትም ነው። መምህሩ ያንን ያለበት ምክንያት ደግሞ ትምህርት ላይ ደካማ ሆነውበት ተናዶ ነው። እውቀት ፍለጋ ስላልሆነ የሚማሩት የሚፈልገውን ያህል አልሆኑለትም፤ አይገባቸውም ማለት ነው። እንደምንም ብለው ወረቀቱን መያዝ ብቻ ነው ፍላጎታቸው። የመምህሩን ነገር እውነት መሆኑን የምናረጋግጠው ደግሞ ይሄው በየመንገዱ በምናየው ነገር ነው፡፡ በየመሥሪያ ቤቱ በሚወራው ወሬ ነው፡፡ እስኪ በየመሥሪያ ቤቱ ልብ በሉ! ሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ የሚማሩት የተሻለ ሥራ ለመቀጠር እንጂ የማህበረሰብ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ለመሥራት አይደለም ። ይሄ እንግዲህ የአገሪቱ የኑሮ ሁኔታ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ቢሆንም ግን እውቀት አለመፈለግን በአገሪቱ የኑሮ ሁኔታ ብቻ የሚወሰን አይደለም፤ ስንፍናውም አለ፡፡ ያንኑም ‹‹ሀውንድ አውቱን›› የማያነብም እኮ አለ፡፡ ይሄን ነገር የሚያጠናክርልኝ አንድ የሰማሁትን ገጠመኝ ልንገራችሁ፡፡ ደራሲ ዓለማየሁ ገላጋዬ በሸገር ኤም ኤም እንግዳ ሆኖ ሲያወራ የሰማሁት ነው፡፡ አንድ አባት አንድን ወጣት ‹‹ለምን አታነብም፣ ለምን አትማርም?›› ብለው ይጠይቁታል፡፡ ‹‹ወጣቱም ምን እየበላሁ ነው የምማረው? ይላቸዋል፡፡ ቃሉ ቢከብድም እንደሰማሁት ልጠቀመውና ‹‹ምን እየበላህ ነው የደደብክ?›› አሉት ይባላል፡፡ እዚህ ላይ ግን ልብ መባል ያለበት ነገር የኑሮ ሁኔታም ቀላል ችግር አይደለም፡፡ ሰው\nስለኑሮ እያሰበ አዕምሮው ነፃ ሊሆን አይችልም ። የሚያስበው ስለነገው ነው፡፡ ይህ ሲሆን ደግሞ መጽሐፍ፣ ጋዜጦችና መጽሔቶች የቅንጦት ይመስሉታል፡፡ ትርፍ ጊዜና ገንዘብ ያለው ሰው የሚያነባቸውና የሚገዛቸው ይመስለዋል፡፡ ለዚህም ነው በአገራችን ጋዜጣና መጽሔት ብዙም አይነበብም የሚባለው፡፡ ድህነት ብቻ ነው ምክንያቱ እንዳንል ደግሞ አሁንም ሌላ አፍራሽ ምክንያት እናገኛለን፡፡ ለዚህ እንደምሳሌ ትምህርት ቤቶች አካባቢ እንሂድ! ብዙ ጊዜ በትምህርት ውጤታማ የሚሆኑት በኑሮ የሚጎሳቆሉ ተማሪዎች ናቸው፡፡ ብዙ ነገር የማይቸግራቸው ተማሪዎች ትምህርት ላይ ትኩረት አያደርጉም፡፡ ምናልባት ይሄም የኑሮ ሁኔታ ይሆን? የድሃ ልጅ ስለሆንኩ ከዚህ ውጭ አማራጭ የለኝም በሚል ትኩረት ስለሚሰጡት ይሆን? ዞሮ ዞሮ ግን ስንፍናም በትልቁ አለ ። ትምህርትን\nለኑሮ ማሻሻያነት መጠቀም ምናልባት የኑሮ ሁኔታ ሊሆን ይችላል፡፡ መጽሐፍ፣ ጋዜጣና መጽሔት አለማንበብ ግን ስንፍና ነው፡ ፡ እንዲያውም ከዚህ የባሰ እኮ ስለውጭ አገር ኳስ፣ ስለፊልም፣ ስለመንደር አሉቧልታ ይወራል አይደል? ትምህርት እንዲህ ለተሻለ ሥራ መፈለጊያ ሲሆን፤ ስኬታም አይሆንም፡፡ ተማሪነታችንን እናስታውስ፡፡ ለፈተና ብለን ቀኑ ሲደርስ ስናነብ ሽምደዳ እንጂ ጽንሰ ሀሳቡ አይገባንም፡፡ ፈተና በሌለበት ሰሞን ስናነብ ግን በጥልቀት ነበር የሚገባን፡፡ ያ ማለት የምናነበው ለእውቀት ነበር እንደማለት ነው፡፡ ሌላም ማሳያ እንጥቀስ፡፡ በአንድ ኮሌጅ በር ላይ ሄዳችሁ ከውስጥ ሲወጡ አሥር ተማሪ አስቁማችሁ ብትጠይቁ ቢያንስ ስምንቱ ‹‹አካውንቲንግ›› ሊሉ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ተማሪዎች የአካውንቲንግ ሳይንስ ፍቅር ይዟቸው አይደለም፤ ወይም የአገሪቱ የምጣኔ ሀብት ላይ እንመራመራለን ብለው አይደለም፤ የተሻለ ቅጥር ያለው እዚያ ላይ ነው ሲባል ስለሚሰሙ ነው ። ይሄ እኮ ግልጽ ነው፡፡ ተማሪዎች 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ጨርሰው የዩኒቨርሲቲ ቅጽ ሲሞሉ ችሎታቸውንና ምኞታቸውን ሳይሆን ‹‹የቱ ነው ቶሎ የሚቀጠርበት?›› ብለው ነው የሚጠይቁ፡፡ ለዚህም ነው ያለፍላጎታቸውና ያለችሎታቸው ገብተው ሲማረሩ የሚሰማው ። ከዚያ በኋላ እንግዲህ ሲመረው በውሃ ቀጠነ ምክንያት ሁሉ ድንጋይ ውርወራ ይጀምራል! ኧረ ጎበዝ ትምህርትን ለኑሮ ብቻ አናድርገው! ለማወቅም እናንብብ! በቃ እውቀት ከሀብት ይበልጣል የሚለው አባባል ውሃ በላው ማለት ነው? አስታውሳለሁ ትምህርት ቤት እያለን ‹‹ከእውቀትና ከሀብት›› እየተባለ እንከራከር ነበር ። ታዲያ ሀብት ይበልጣል ያለ ተማሪ እንደሰነፍ ስለሚታይ አብዛኞቻችን ‹‹እውቀት›› ነበር የምንል፡፡ አሁን ግን ሀብት መባሉ ነው መሰለኝ ። እውቀት ካለ ሀብት ይኖራል የሚለው ግን አስታራቂ ሀሳብ ነው፡፡ ችግሩ ሀብትም ያለእውቀት መሆኑ ነው! ስለዚህ ማወቅ ለሁሉም ይሆናልና ለማወቅም እናንብብ!አዲስ ዘመን የካቲት 10/2011ዋለልኝ\nአየለ", "passage_id": "b6e6d6b1c16bd0e4f7bcf7c68c9624c1" }, { "passage": "አራት\nኪሎ አካባቢ በእግሬ ስንቀሳቀስ የስልጣን ነገር ሽው ይልብኛል፤ ለምንድ ነው? አራት ኪሎ ግር ግር የማይጠፋበት፣ ከባለስልጣን እስከ\nተራው ሰው የሚተራመስበት ስፍራ በመሆኑ ነው እንዳትሉ። እኔን ሲመስለኝ ግን አራት ኪሎ ከፊትም ጀምሮ ለመንግሥት መቀመጫነት የተመረጠችው\nለብዙ ነገር ቅርብ በመሆኗ ነው። በሌላ በኩልም አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ለመግባት ነፍጥና ድምፅ ወሳኝ መሆኑን ያሳየች ቦታም እንደሆነች\nየገቡትን ማየት በቂ ይመስለኛል። ይህንን አውቆ ያከበራት የለም እንጂ … ያው ቀን እስኪወጣላት እየጠበቀችም አልነበር። የሚገርመኝ\nአራት ኪሎን ደርሶ የማይመኛት ሰው የለም፤ የሚያገኟት ጥቂቶች ሆኑ እንጂ።አራት ኪሎ ለመምጣት ዓመታት የዘለቀ ጦርነት መካሄዱን\nሳስብ ቦታው ምን ቢኖረው ነው ብዬ እኔም ለመግባት ጉጉቴ ጨምሯል (መቼም ለስልጣን ቋምጠሀል አትሉኝም)። ግን ግን ስልጣን የሚጠላ\nአለ እንዴ! መቼም እጠላለሁ የሚል ሰው ቢኖር ከስልጣን የወረዱ ብቻ ቢሆኑ ነው። ለምን ቢባሉ በስልጣን ዘመናቸው አራት ኪሎን ተጠቅመዋታልና\nይመስለኛል ምላሹ። አራት ኪሎ ባለስልጣናት የሚመሩባት ብቻም ሳይሆን የሚቀበሩባትም ስፍራ ናት። የማይታይባትም ነገር የለም፤ ሰው\nእንዳሻው ዘሎባት ሲያበቃ ሰፊ ቦታ ይዞ የሚቀበርባት ሲፈልግ ደግሞ አጥሮ የሚቀመጥባት ምድርም ከሆነች ሰነባብታለች…።አራት ኪሎ ተማሪው፣ መምህሩ፣ ደራሲው፣ መጽሐፍ አዟሪው፣ ጋዜጣ ሻጩን ከነ አታሚው፣…\nአቅፋ ይዛለች። እነዚህን ብቻ ሳይሆን የምሁራን መፍለቂያ ተብለው የተከፈቱ ዩኒቨርሲቲዎችም ከትመውባታል ( ዩኒቨርሲቲዎቹ በአሁኑ\nወቅት የምሁራን ሳይሆን የሥራ እጥ መፍለቂያ ሆኑ እንጂ)። ሥራ የሌለው ሰው ሥራ ለማግኘት ከሚያምነው አምላክ ቀጥሎ የሚሳለመው\nስፍራ አራት ኪሎም አይደል። ከአራት ኪሎ በኋላ ነው እንግዲህ የስልጣን አምላክ የሆነውን እንቶኔን ወደ መለመኑ የሚገባው… (እንቶኔ\nየአራት ኪሎ መንግሥት የሚለውን ተክቶ የገባ ነው)። አራት ኪሎን የአገሪቱ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የእምነት መናኸሪያ ወይም አምብርት ያደረጋት ሰው ግን ምስጋና ይገባቸዋል\n(በየተራ እየመጡ የመንግሥታቸው መቀመጫ ያደረጓት ሰዎች ባያባክኗት) ። ገዥዎች ጨካኝ፣ ሩህሩህ፣ ሰጪ እና ነሺ ናቸው። ሲፈልጉ\nበየሰበብ አስባቡ ያበላሉ፣ ያጠጣሉ… ሳይፈልጉ ደግሞ ሰበብ ፈጥረው ያስራሉ፤ ይገርፋሉ… ። እኔን የሚገርመኝ ግን የአራት ኪሎን\nቤተ መንግሥት የረገጠ ሰው ሁሉ እንዴት ተመሳሳይ ይሆናል? ማብላት፣ ማጠጣት፣ መሰብሰብ፣ መግረፍ …(ግርፋቷን ግን የቀመሰ ሰው\nብቻ ነው የሚያውቀው):: ሰሞኑን ቤተመንግሥት መጎብኘት ተጀምሯል ተብሎ ህዝቡ እየጎረፈ ነው፤ ፓርኩን ምን እንደሚመስል ከተመለከተ በኋላም የሰራውን\nመንግሥት ሳይሆን በር የከፈተለትን ሰው እየተደፋ አመስግኗል። እናንተዬ እኛ እኮ ጥሩ አመስጋኞች ነን…በልተን ተመስገን…ተርበን\nተመስገን…ተገርፈን ተመስገን… ከዚያ ደግሞ ‹‹ይህቺንስ ማን አየብኝ›› ብለን ጥቅልል ብለን እንተኛለን። ኧረ አራት ኪሎ እንግባ\nጎበዝ (ኧረ ተው ተው¡)። ምነው እንለመን አላችሁ …ብቻዬን ሁለት መቶ ብር ከፍዬ የማልገባ መሰላችሁ እንዴ። እንደ ድሮው ቢሆን አራት ኪሎ ቤተ\nመንግሥት ለመግባት ነፍጥ አንግቶ ተዋግቶና ብዙ ነፍሶችን መስዋዕት አድርጎ ወይም የምርጫ ኮሮጆ እንደምንም መገልበጥ ያስፈልግ ነበር።\nአሁን ግን ቤተ መንግሥት ለመግባት ሁለት መቶ ብር ብቻ በቂ ነው። አንድ ሺ ብር የከፈለ ደግሞ ለአንድ ቀን አገር ይመራል አሉ!\nአሉ ነው ደግሞ እውነት መስሏችሁ «ገብተን እንምራ» እንዳትሉ!! መቼም አራት\nኪሎ ታሪክ\nአያጣትም አንዳንድ\nከድሮ ጀምሮ\nህዝብ የመምራት\nአቅም አለን\nያሉ አቅም\nያነሳቸው አዛውንቶች\nሰብሰብ ብለን\nሱባኤ ልንገባ\nነው ብለዋል።\n‹‹የት?›› ብትሉ\nአራት ኪሎ\nአደባባይ…ከነፍጥና\nከኮሮጆ ግልበጣ\nውጪ በረሃብ\nቤተ መንግሥት\nይገባል ብለው\nአስበው ይሆን?\nወይስ ቤተ\nመንግሥት ለመግባት\nየሚከፈለውን አንድ\nሺ ብር\nለማግኘት የቀን\nወጪ ቅነሳ\nነው ምግብ\nየሚያቆሙት? እንግዲህ\nጊዜ ያሳየናል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 10/2012መርድ ክፍሉ ", "passage_id": "52b58d0e8d632b0612cb0bb5cdbb9a98" }, { "passage": "ቅዳሜ\nቀትር ላይ ነው፤ ሁለት እብዶችን በአንድነት ማየት ያልተለመደ ቢሆንም በአንዲት ትንሽ የገጠር ከተማ ሶስት እብዶች ጉባኤ ተቀምጠዋል። የእነዚህ እብዶች ካለወትሯቸው በቁም ነገር ማውራታቸውና መደማመጣቸው ደግሞ የጉዳዩን አሳሳቢነትና ክብደት ይናገራል። በእብዶች ታሪክ ያለተፈፀመ እብደት በጤነኛ ነኝ ባዮች እየተፈፀመ በመሆኑ አንዳች የማስተካከያ እርምጃ መወሰድ አለበት። ይላል ድምፁን ከፍ አድርጎ – ራሱን በጨርቅ የጠቀለለውና በጥቁረቱ ገላው ከልብሱ የተማሰለበት ወጣት ከወዲህ ወዲያ እየተራወጠና እጁን እያወናጨፈ ። ንግግሩን\nቀጥሎም አልበዛም እንዴ ? ከምር አሁንስ በጣም አበዙት? የኛም ማንንት መጠበቅ መከበር አለበት እንዴት አይረዱንም ከነሱ የተነጠልነው ስላልተስማማን አይደል እንዴ፤ በቃ! እኛም በነሱ እነሱም በኛ ማንነት፤ ምንነት ስራና እንቅስቃሴ መግባት የለባቸውም፤መግባት የለብንም፤ ድንበራችን መለየት አለበት። ከወደ ቀኝ ጥግ የተቀመጠው ሌላው ባለ አዳፋ ራቁታም ምላሸ መስጠት ጀመረ፤ በጊዜው እርምጃ ባለመውሰዳችን ነገሮች ከእጃችን እየወጡ ነው። በተለይ ባለፉት ሁለት አመታት ማንነታችንም ስራችንም በመጤዎች እየተወረሰ መጥቷል። ለኛ የተረፈን ስማችን ብቻ ነው። በበኩሌ እንደዚህ ባለ አጭር ጊዜ የዚህ አይነት ወረራ ይፈፀምብናል ብዬ አልጠበኩም ነበር። ጀማሪው ተናጋሪ ጥያቄ አቀረበ ሰው ከሰው በምን ይለያል ? በብዙ ነገር በመልክ በፀባይ በሀብት በፆታ በቋንቋ በ….. ስንቱን ልግለፅልህ እኛስ ከሰው በምን እንለያለን ? በምግባር በባህሪ በፀባይ በስራችን ወዘተ… በኛስ መካከል ምን ልዩነት አለ ? በኛ በኩል በደረጃችን ነው እብድ፤ ቀውስ ፤ ወፈፌ፤ ሾጥ ያረገው ፤ ንክ፤ አውቆ አበድ …… ጀማሪ እብድ፤ የለየለት…….. ስንቱን ልንገርህ። እኔ ግን የእኛን መለየት አልቀበለውም እስቲ እያንዳንዱን ነገር በዝርዝር እንየው ራቁታችንን መሄዳችን ከሆነ ዛሬ ሴት ወንዱ የሚንቀሳቀሰው እርቃኑን ነው። ወንዱ ጭራሽ መቀመጫውን እያሳየ ነው የሚሄደው የሚሸጠው ልብስ ሁላ የተተለተለ የተቦጨቀ ሆኖ እያለ ለእኛ ሲሆን ለምን እንደሚኮነንአይገባኝም። ስማችንን ሲያጠፉ እብድ የፈለገውን ያወራል፤ ያሻውን ይናገራል ይላሉ። እውነቱ ግን ሌላ ነው ። ዛሬ ከነሱ መሀል ብቻውን የማያወራ ማን አለ ? የስድቡንማ ነገር ተወው እድሜ ለፌስ ቡክ ይኸው በየቀኑ የስንቱ ዋልጌ ጉድ እየወጣ አይደል። ብታይ እኮ ስድቡ… ትችቱ…. ነቆራው… ዛቻው…. ድንፋታው…… ምን አለፋህ የስድብ ትምህርት ቤት የተከፈተ ነው የሚመስለው። ምን የተከፈተ ብቻ ፤የተስፋፋም ነው የሚመስለው፡፤ጥናት አልተሰራም እንጂ የእያንዳንዱ አበሻ ፌስ ቡክ ቢመረመር ጥራዝ ጥራዝ የስድብ መፅሀፍ የሚወጣው ይመስለኛል። የድሮ እብድ መለያው ድንጋይ ድንጋይና ዱላ ይዞ መሮጡ ነበር። አስበው የዘንድሮ እብድ ምን ድንጋይ ይወረውራል። አላየህም ቡራዩ አላየህም….. የትኛው እብድ ያን ያህል ሰው ገሎ ያውቃል እነሱ ለውጥ መጣ ብጥብጥ፤ ሰላማዊ ሰለፍ ብጥብጥ፤ የድጋፍ ሰልፍ ብጥብጥ፤ ኳስ ጭዋታ ብጥብጥ … ለምሳሌ እኛ መንገድ ዘግተን አናውቅም ቢበዛ ህዝብ ፈርቶን መንገድ ይለቅልን ይሆናል እንጂ። ዛሬ ወጣቱ ሽማግሌው አሮጊቱ ሳይቀር እየተነሳ መንገድ ይዘጋል። አንዳንዱ በድንጋይ ሌላው በእንጨት ፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ብለው ብለው ምናምኑን ሁሉ ሰበስበው እያቃጠሉ በጭስ መንገድ መዝጋትም ጀምረዋል። አይገርምህም ወንድሜ !! ደግሞ ሲላቸው እብድ ከተማ ያቆሽሻል ይላሉ፡፡ እኛ እኮ ጤነኛ ተብዬዎቹ ያቆሸሹትን ከተማ እኛ እንቆሽሽ ይሆናል እንጂ ስናፀዳ ነው የኖርነው። እብድ እንዴት አድርጎ ቆሻሻ ይፈጥራል ? ስለዚህ ስንት ዘመን አስከብረን የኖርነውን እብደት ማንም ወንዝ አመጣሽ ማንም ጊዜ አመጣሽ እንዲነጥቀን መፍቀድ የለብንም። እኛ እኮ ማንም ይመን አይመን አብዛኞቻችን ያበድንበት በቂ ምክንያት አለን ፡፡ ካስፈለገም ከሆስፒታል ፣ ከፀበል ብሎም ከጎረቤት ጭምር መረጃና ማስረጃ ማቅረበ እንችላለን። ተናጋሪው እልህ እየተናነቀው ንግግሩን አቆመ። የጉባኤው ሰብሳቢ ንግግሯን ቀጠለች በርግጥ አለች በርግጥ የሀገሪቱ መሪ የእኛን የእብዶች መብት ማስጠበቅ አለባቸው፤ የመንደር እብዶች ፤ ምሁር ተብዬ የቢሮ እብዶች፤፤የፌስ ቡክ እብዶች ፤ ባጠቃላይ አውቆ እብዶች ከእኛ እንዲለዩ ብሎም በእኛ ስራና ተግባር እንዳይገቡ ማድረግ አለባቸው። ነገር ግን አሁን የተናገርኩት እንዳለና እንደተጠበቀ ሆኖ በሀገሪቱ መሪ ቦታ ሆነን ማሰብ ያለብን ይመስለኛል። በመጀመሪያ ደረጃ ከሞቀ ቤቱ በጠዋት በሰላም ወጥቶ በየመንገዱ በየቢሮው በተለይ በፌስ ቡከ የሚያብደውን መለየት እጅግ አስቸጋሪ ነው። በሁለተኛ ደረጃ ያለባቸውን የጤነኛ እብድ ብዛትም ከግንዛቤ ማስገባት አለብን። በነገራችን ላይ እሳቸው ማለቴ የሀገሪቱ መሪ ስለሙስና፤ ሌቦችና ዘራፊዎች ሲያወሩ ”እንሰራቸው ብንል አንድ ከተማ አይበቃንም” ብለው ነበር አሉ። እንግዲህ ልብ በሉ እሳቸውንም እኛንም ጤና እየነሳ ያለውን በስሜት የሚነዳ እብድ ህዝብ ልሰር ቢሉ ደግሞ ራሷ ሀገሪቱ እምትበቃቸው አይመስለኝም። ምክንያቱም እዚህ ካለው ባልተናነሰ ከውጪ የሚመጣ በሚሊዮን የሚቆጠር ዳያስፖራ እብድም አለባቸውና ነው። ስለዚህ ጥያቄውን መመለስ ያለበት ሌላ ወገን ነው። ሌላ ወገን ስል መጀመሪያ እያንዳንዱ በየቤቱ የራሱን ወፈፌ መያዝ ማስታገስ አለበት። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ እያንዳንዱ አካባቢ ከወፈፌነት ወደ ቀውስነት የተሸጋገሩና በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙትን የመቆጣጠር ብሎም በቤተሰብ ደረጃ የሚደረገውን ክትትል መደገፍ ይጠበቅበታል። ሲሰልስ እያንዳንዱ ክልል በተደራጀና በተቀናጀ አኳኋን የየራሱን ወፈፌ፣ ቀውስ፣ ንክ፣ ባለ ዛርና ባለ ውቃቢ ጭምሮ መያዝ፣ ሀይ ማለት አለበት ። ለዚህ ደግሞ ከፌዴራል መንግስት ጋር በመተባበር ያዘው፣ በለው የሚሉ ምሁራንና አክቲቭስቶች የራሳቸውን ንግግር የሚያዳምጡበት፤ በድረ ገፅ የፃፉትን ራሳቸው የሚያነቡበት በቴክኖሎጂ የታገዘ አዳራሽ መገንባት ያስፈልጋል። ለወጣቶቹም ድንጋይ የሚወረውሩበት ሰፋፊ ሜዳ፤ የሚያቃጥሉት ጎማና መንገድ መዘጊያ ትልልቅ ድንጋይ እንዲሁም የሚዘጋ መንገድም ጨምሮ ማዘጋጀት አለባቸው። ለዚህም በአጭር ጊዜ ውስጥ ይሄንን የሚያሳልጥ ኮሚሽን መቋቋም አለበት። ኮሚሸኑ ደግሞ ከባለስልጣን ወፈፌ፤ ከአክቲቪስት ቀውስ፤ ከወጣት እብድ፤ ከሃይማኖት አባት ንክ፤ ከዳያስፖራ ሾጥ ያረገው፣ ከጋዜጠኛ ጨለፌ ማካተት አለበት። ብላ ንግግሯን አጠናቀቀች። ሶስቱ ሀገር ወዳድ እብዶች የውሳኔና የመፍትሄ ሃሳባቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በፅሁፍ ለማቅረብ ተስማምተው ብእርና ወረቀት ሲያገናኙ “አንተ !!! አትበተንም” የሚል ጠንካራ ድምፅ ሰሙ። የጉባኤው አባላት ድምፁን ተከትለው ከመንገዱ በስተግራ ጥግ አይናቸውን ሲወረውሩ በቆመጥ፣ በክላሽና ካቴና የተደራጁ የክልል ፖሊሶችን ተመለከቱ። በዚች ቅፅበት ሶስቱም የረሱትን የሀገሪቱን መሪ ትልቅ እዳ ለማስታወስ እድል አገኙ፤ ለካስ በሀገሪቱ “የታጣቂ እብዶችም” ነበሩ።አዲስ\nዘመን መጋቢት 3/2011በራስወርቅ\nሙሉጌታ", "passage_id": "5e5646cb2f7f11fb5d66769e4eebf89b" } ]
3fcaa5467aeb2600c6c1d87059a90b90
c34394e48c14cee7a42a8a746ac8208f
«ቀዝቃዛ ቮልካኖ»
መቼም ጆሮ ሰጥቶ ላደመጠ ፣ አይኑን ከፍቶ ለተመለከተ፣ተስፋ ሰንቆ ራዕይ አስቀምጦ ለተጓዘ፣ ቅን ልቦና ያለው ሁሉ፣… በዚህ ዘመን ብዙ ነገሮችን ያስተውላል። ያያል፣ ያደምጣል፤ አእምሮ ያለው ሰው ከሆነ ደግሞ ቁም ነገሮችን ይጨብጣል። የተሳሳተውን ያርማል። አዳዲስ ነገሮች ይማራል ፤ ይሰንቃል። ይሄ ልብ ላለው ነው፤ ለሌለውስ ? ብሎ ለሚጠይቅ ምላሹ ለሁሉም የሚል ይሆናል። ልብ ላጣ ልብ መመለሻ ጊዜ ነው። ነገር ግን ልባችንን ተስፋ ሳይሆን ጥቀርሻ ሸፍነን፤ በብርሀን ሳይሆን በሀምሌ ዳመና ጋርደን ፤ አይናችንን ከፍተን ሳይሆን ጨፍነን አላየንም ፣አልሰማንም፣ አንሰማም ብለን ብቻ ክፋትን የምናስብ ከሆነ እርግጠኛ ሆኖ ለመናገር ነጩ ጥቁር ነው። ያውም ጭግግ ያለ የክረምት ሌሊት። የተስፋ ብርሀን እያየ በብርሀን ውስጥ እየተመላለሰ መሆኑን ለተረዳ ደግሞ ማለዳ የፈነጠቀ ጸሀይ ከፊት ለፊቱ ይታየዋል። ተስፋውም በዚያው ልክ ቦግ ቦግ ይላል። እንግዲህ ጆሮውን ሰጥቶ፣ አእምሮውን ከፍቶ ላደመጠ ብዙ ጣፋጭ ምግቦች አሉ እያልኩ ነው። ካጣጣምኩት አንዱን ጣፋጭ ተቋደሱ ብልስ ታዲያ። እንደእውነቱ ከሆነ መልካም ነገርን ያቋደሰ እንዳውም ይመሰገናል፤ ይመረቃል እና እኔም ይሄው ምርቃት እንደማይነፈገኝ እርግጠኛ ነኝ። ተመርቆ ደስ የማይለው ሊኖር ይችል ይሆን? ብቻ መራቂ አያሳጣን ማለት መልካም ነው። እንዳው የእኔ ነገር ከተነሳሁበት ጉዳይ ጭልጥ ብዬ ወጣሁ እንዴ ልመለስ። ያንን ያደመጥኩትን መልካም ነገር ወደ መንገሩ፤ አልማዝ ከስም በላይ ነው ልል አሰብኩና እውነት ነው አልማዝ ማዕድን ነው። ያውም የከበረ ማዕድን በጥቂቶች እጅ ላይ የሚገኝ ውድ፣ አንፀባራቂ፣ አጓጊ ብቻ አልማዝ ን የሚያውቀው ያውቀዋል ብዬ ባቆምስ። እኔ ከማውቀው በላይ እናንተ የአልማዝን ክብር ፣ ዋጋ ፣ እሱን ለማግኘት የሚደረገውን ልፋት ፤ ልፋት ብቻም ሳይሆን ተፈጥሮም አግዛና ተጋግዛ እኮ ነው አንድን አገር አልማዝ በአልማዝ የምታደርገው። ሀብታም ሀገሮች ናቸው እነ እገሌ የሚባሉት በሌላ አይደለም ከምድር ውስጥ በሚያገኙት ማዕድን አይደል?አንድ ምሁር በተለይ ለእኔ ትልቅ ምሁር ካልኩት ሰው አንደበት የወጣውን ነው።ምሁር መቼም አስተዋይ፣ አርቆ አሳቢ፣ ቅን፣ ሀገርና ወገኑን የሚወድ፣ የሚያከብር፣ ለሀገሩ የቆመ አዋቂ ነው ። ለእኔ እንደዛ ነው የሚሰማኝ። ታዲያ ይሄ ሰው አልማዝ እንዴት ተሰራ የሚለውን በአንድ መድረክ ላይ ቆሞ ያብራራል። እኔም በተመስጦ እያዳመጥኩ ነው። አልማዝ የሚለውን የከበረ ዋጋው እጅግ በጣም ውድ ነገር በሽበሽ ብሎ የማይገኝ በመሆኑ መቼም ማናችንም ብንሆን ለአልማዝ የምንሰጠው ዋጋ ስም እንደማውጣት የቀለለ አይደለም። ስም አውጪዎቹ ቦታ ያለው ክብር ግን ልጆቻቸው እንደዛ የከበረ ማዕድን ተወዳጅ፣ ተፈላጊ፣ አጓጊ እንዲሆኑላቸው በመመኘት ነው። መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ እንደሚባለው አባባል እንደማይሆን አምናለሁ። መልካም መልካሙን ተመኝተው ስም ላወጡት እንዳው ክብር ይገባቸዋል ብልስ ምክንያቱም ዛሬ እኮ ስም የሚወጣው በትርጉም፣ መልካም በመመኘት ሳይሆን አፍ ላይ በቀለለ ሳይሆን ቀረ ብላችሁ ነው? እነ ቲቲ፣ ቡቹ ፣ቶሚ… መጠሪያ ሆነው እነ የውብ ዳር፣ ቆንጅት፣ ሞገስ፣ ነዋይ… አይነቶቹ ሀገር በቀል ስሞች ዳይ ወደ ጓዳ ተብለዋል። ድሮ ድሮ ልጅ ነበር ወደ ጓዳ የሚባለው ያውም እንግዳ ሲመጣ። ልጅስ ምን ሊያደርግ ማን ፈቅዶለት ሳሎን ወጥቶ። ለማንኛውም የዛሬው ጉዳዬ ስም ላይ አይደለምና እናሳድረው።እና እንዲህ ይላል ያ ሰው አልማዝ እንዴት እንደሚገኝ ታውቃላችሁ? ይጠይቃል ደግሞ ማብራሪያውን ሲሰጥ “ አልማዝ በጣም ርቀት ባለው ጥልቅ መሬት ውስጥ ፣እጅግ በጣም ከፍተኛ ሙቀት እንዲሁም እጅግ በጣም ከባድ ግፊት ባለበት ፣ በጣም ረጅም ዘመን ኖሮ የሚወጣ ማዕድን ነው። ይህን ማዕድን እንዴት ማውጣት ይቻላል ከተባለ አልማዝ የሚወጣው ከባድ እሳተገሞራ (ቮልካኖ) ሲፈጠር ያንጊዜ ገንፍሎ ይፈሳል። ያንን አብረቅራቂ ነገር ከቆሻሻው በመለየት ሞርዶና አስተካክሎ በማሳመር ማዕድኑ ይወጣል። ከፈለጋችሁ ከሰልም አልማዝ መሆን ይችላል። እንዴት ካላችሁ አሁን አልማዝ እንዴት እንደሚገኝ ባየነው መንገድ ተጉዞ ። ይሄንን ወደ አገር እንውሰደው ኢትዮጵያም እንደ አልማዝ ናት ።በከፍተኛ ችግር ለረጅም ዓመታት በስቃይ በየዘመኑ በሚፈጠር ውጥረት ስትታመስ ኖራለች። ከባድ ድርቅ ፣ጦርነት፣ መፈናቀል፣ ረሀብ… በመሳሰሉት ተወጥራ ረጅም ዘመናትን አሳልፋለች። አሁን ቀዝቃዛ ቮልካኖ ( እሳተ ጎሞራ) በመውጣቱ ምክንያት መጠነኛ ለውጥ ታይቷል። ይሄ የእሳተ ገሞራው ውጤት ነው።”ይላል። ንግግሩ መሳጭ ነው። አንደበተ ርዕቱና ትሁት ሰው መሆኑን ከአንደበቱ የሚንቆረቆረው ጆሮ ግቡ ንግግሩ ይመሰክራል። ንግግሩን አላበቃም። ቀጠለ “አሁን ያንን አልማዝ መሳይ ለውጥ በመሞረድ ለማስተካከል ጥረት ማድረግ ከሁሉም ይጠበቃል። በደንብ መስራት ከተቻለ አልማዝ ውድ ዋጋ እንደሚያወጣ ሁሉ ለውጡም እጅግ በጣም ውድ የሆነውን የምንናፍቀውን የምናልመውን ብልጽግናን ያመጣል። ይሄ የሚሆነው ታዲያ በአልማዙ መጠቀም ለቻለ ብቻ ነው።” እንግዲህ ይሄን ሀሳብ ከአደመጥኩት ላይ የወሰድኩት በመሆኑ ቃል በቃል አላሳረፍኩትም። ምን አልባት ያጎደልኩት ፣ ያሰፋሁት ካለ እንደክፋት ሳይቆጠርብኝ ይቅርታ ልጠይቅ። በይቅርታና በምህረት ዘመን ጥፋትን ማመን፣ ይቅርታ መጠየቅ ሁለተኛ ላለማጥፋት ግማሽ መንገድ እንደመሄድ ነውና። እንዲህ ከሆነ ቶሎ ቶሎ ስህተቶቻንን እያረምን፣ ጥፋታችንን እያስተካከልንና ከጥፋታችን እየተማማርን የበለጸገች አገር እንገነባለን ። መቼም ብልጽግና የሚለውን ቃል መጥራት በራሱ መበልጸግ ይመስለኛል። ምክንያቱም ብዙ ጊዜ የምናወራቸው፣ የምናደምጣቸው ፣ በየድረ ገጹ የምናነባቸው ተስፋ የሚያስቆርጡ አይነት ነገር ናቸውና። እንዲህ አይነቱ ታዲያ ለመስራትም፣ ለመለወጥም፣ ለመማርም፣ የተሻለ ለማሰብም እድል አይሰጥም። ስለዚህ ስለተስፋና ብልጽግና እናልም።ሰላም!አዲስ ዘመን ጥቅምት 2/2012 አልማዝ አያሌው
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=20668
[ { "passage": "ፀሐይቱ በክራርዋ በመታጅብ በምትደርሳቸው ዜማና ግጥሞች ለውጥንና ፍቅርን ሰባኪ እንደነበረች አድናቂዎቿ ይመሰክራሉ። ጋዜጠኛ ሀብቶም ዮሃንስ በኒዘርላንድስ ነዋሪ ነው። ስለፀሐይቱ የሚያውቀውን አጋርቶናል። ", "passage_id": "d726e88296a6a4daf2930fda8d78cebe" }, { "passage": "አንድ ንጉሥ እጅግ አጥብቆ የሚወደው ፈላስፋ ነበረው። አብሮትየሚጋበዝ፣ የሆነውን የሚሆነውንም ሁሉ የሚያ ማክረው። በጤናና በስምምነት አያሌ ወራት አያሌ ዘመናት ሲኖሩ አንድ ቀን ከገበታ ላይ ለምግብ ተቀምጠው ሳለ ፈላስፋኑ አንስቶ “አዬ!” አለና እጅግ ተከዘ። ወደ ምግቡም እምብዛም ነፍሱ አልፈቀደ። በዚህን ጊዜ ንጉሡ ደንግጦ ያመመው መስሎት “ምነው በደህናህን?” ብሎ ጠየቀው። ፈላስፋኑ እየመላለሰ ‘አዬን’ ብቻ ያዘ። ንጉሡም “ደሞ አመመህን?” ቢለው እንኳን “አላመመኝም” ብሎ መለሰለት። “እንግድያውስ አሁንም አሁንም እየተከዝህ ‘አየ’ የምትለው ምን ብትሆን ነው?” ብሎ መረመረው። ቀጥሎም ‘አዬን’ ብቻ ያዘ። ንጉሡም ገሚሱ ቁጣ በገሚሱ ጭንቀት “እንደዚህ ያለ ምንድር ነው? እባክህን ንገረኝ ምንድር ነው ብልሃቱ?” ብሎ ቢለው፤ “ክፉ ዘመን የሚመጣብን ቢሆን ነው እንዲህ የምሆነው፣ የማዝነው” አለው። የባሰውን ንጉሡ በዚህ ነገር ተጨነቀ። በፍጥነትም ነገሩን እንዲረዳው ፈለገ። ፈላስፋው ግን መልሶ ‘አዬውን’ ያዘ። ተዚህ ወዲህ ንጉሡ አጥብቆ ፈራ። “ እባክህን ውሃ አታርገኝ ንገረኝ” አለው። “እስከ ሦስት ዓመት እንደለመድነው ጊዜ ሁሉ ነው። ቀጥሎ ግን የሚዘንበው ዝናብ እስከ ሦስት ዓመት ድረስ ሰውም ሆነ እንስሳም ሆነ ፍጡር የተባለ ሁሉ ይመርዛል። ውሃን የጠጣ ሁሉ ያብዳል። ወንዙ ምንጩ ባሕሩ ዝናቡ ሲዘንብበት ይመረዛልና። ስለዚህ ውሃ የጠጣ ሁሉ ያብዳል። ተዚህ የበለጠ ምን የሚያሳዝንና የሚያስተክዝ አለ?” ብሎ አረዳው። ንጉሡም እንደ ፈላስፋው አንገቱን ደፍቶ ተራውን ይተክዝ ጀመረ። ቀጥሎ ጥቂት ጥቂት ተንፍሶ “ስማ እንደዚህ ያለ የማይቻል መዓት ሲመጣብን ጊዜ ምን ይበጀናል?” ብሎ አማከረው። “ለዚህማ መቼስ ምን አቅም አለኝ! ያሳየኝ ይህ ነው። ባዋጅ ‘የደህናውን ዝናብ ውሃ ጉድጓድ እያበጀህ አስቀምጥ’ ተብሎ ማስታወቅ ይሻል ይመስለኛል … ለክፉው ዘመን መውጫ እንዲሆን” ብሎ የተቻለውን ምክር መከረ። አዋጁም ሳይውል ሳያድር ተመታ። ከሕዝቡ የፈራ ጉድጓድ ይምስ ጀመር። ነገሩን የናቀ ግን፣ “ተወው! አመሉ ነው። ሁልጊዜም አዋጅ ይመታልና መቼ አንድ ነገር ሆኖ ያውቃል? ደግሞ ያሁኑስ የሚያስደንቅ አዋጅ ነው! ተእግዜር ጋራ ተማክረዋልን? ” እያለ ያፌዝ ጀመር። ከቤተ መንግሥቱ ደሞ ጉድጓድ ሁሉ ተሰናድቶ ተምሶ የደኅናውን ዝናብ አከማቹበት። በቁልፍም ተቆለፈ። የፈሩትም እንደዚሁ አደረጉ። ያ ቀን መድረሱ አልቀረምና ደረሰ። ገና መዝነብ ሲጀምር በየወንዙ በየምንጩ በየባሕሩ ሲጥልበት ጊዜ ተመረዘ። ያን ውሃ የጠጣ ሁሉ ማበድ ጀመረ። ሲል ሲል እብደቱ እየባሰ ሄደ። የእብደት ብዛት እየገነነ ሄደ። ነጋዴ ንግድነቱን ትቶ ወደ ሌላ ሆነ። አራሽም እርሻውን ትቶ ወደ ሌላ ሆነ። ልጅም አባት እየተወ ወደ ሌላ ሆነ። ካህናትም ክህነታቸውን ትተው ወደ ሌላ ሆነ። ቁም ነገር የነበረው ጨዋ ሆነ መኳንንትም ሆነ ሊቃውንትም ውልን ትተው ወደ ሌላ ሆነ። ለእብደቱ ዲካ ጠፋበትና ሁሉም ዝብርቅርቁ ወጣ። ተዚህ ወዲህ በጐራ በጐራ እየተለየ፣ “ነጋሪት ምንድር ነው? ቆሪ እንጨት አይዶለምን? በሉ ነጋሪቱንም ጠፍሩ! መለከቱንም እምቢልታውንም አብጁ!” አሉ። በየጐራው አበጀ። ሁሉም ተተበጀ በኋላ ነጋሪቱን እየጐሸመ፣ መለከቱን እያንጠራራ፣ እምቢልታውን እየነፋ … ሕዝቡ ሁሉ መቸም አብዷልና፣ “ንጉሥ አልነበረነም ወይ? አለ እንጂ! ወዴት ነው? ከግቢው ተቀምጦ ይንፈላሰሳል!” አሉ።ይህንን ሁሉ ንጉሡም ፈላስፋውም ያያሉ ይሰማሉም። ሕዝቡም እንዳልነው ጐራ እየለየ ነጋሪቱን እያስጐሸመ፣ መለከቱን እያንጠራራ፣ እምቢልታውን እያስነፋ፣ “ንጉሣችን ወዴት ነው? በል ሳብ ወደ ግቢ!” እያለ ይስብ ጀመር። ገቢዎች ይኼንን ነገር ባዩ ጊዜ በንጉሡ ታዛዥ የግቢ በር ሁሉ እንዲዘጋ ታዘዘ። እነዝያም እብዶች በደረሱ ጊዜ በሩ ተዘግቶ አገኙ። “ደሞ ዘግቶታልና! አዎን ሊተርፈን? በድንጋይም በዱላም ያን መዝጊያ ተለቀቁበት። ንጉሡም ይኼንን ባየ ጊዜ ለፈላስፋኑ “አንተ! እነዚህ እብዶች ሊገሉን ሊፈጁን ደረሱብን! ምን ይበጀን ትላለህ?” ብሎ አማከረው። “ንጉሥ ሆይ! እኔማ በጉድጓድ ደኅናውን ውሃ እናጠራቅም ለክፉው ዘመን መውጫ እንዲሆን ብየ መክሬ ነበር። ለሕዝቡም ይኼንኑ አስታወቅን ብየ ነበር። ሳይሆን ሲቀርማ ያንኑ የሚያሳብደውን ውሃ ጠጥተን አንድ እንምሰል!” አለ። እነሱም ያንኑ የሚያሳብደውን ውሃ ልጅ ተሾልኮ ይሂድና በቅምጫና ይዞልን ይምጣ ተብሎ ሰደዱት። ሄዶ ይዞ መጣ። እንደ ጠበል ተሻምተው ጠጡ። ወዲያውም አበዱ። ንጉሥም መዝለልና መቀባጠር ጀመረ። ወዲያውም ወደ ግቢው በር ሂዶ፣ “ይኼንን በር ማን አባቱ ነው የዘጋው?” አለ … እርሱ ራሱ ዝጉ ብሎ ሲያበቃ! ወዲያው ብዋ አርገው ከፈቱ። ንጉሡ እየዘለለ እየለፈለፈ እንደነሱ መስሎ በሩን በወጣ ጊዜ የተሰበሰበው ፍጡር ሁሉ መንገድ ለቆ ገለል ብሎ ዳር እስከ ዳር “እልል!” አሉ። ገሚሱ ያልሰማ “ምንድር ነው ነገሩ?” ብለው ሲጠይቁ፣ “ንጉሣችን አብደው ነበር ሽረዋል” ተባለ … ዳር እስከ ዳር እልልታውን አቀለጠው! ክፉውን ዘመን ሁሉ ሲያብዱ ኖሩ። ደኅናው ዘመን ሲገባ ሁሉም እየስፍራው እየሙያው እየደምቡ ገባ። መንግሥቱም አገሩም ሁሉም ረጋ።አዲስ ዘመን ሰኔ 10/2011", "passage_id": "1288af3d9a484b932595b32892d338f3" }, { "passage": "ሦስት ሽህ ኪሎሜትር የከነፈው አቧራ ሜክሲኮና ፍሎሪዳን ጨምሮ በተለያዩ የደቡብ ምሥራቅ ዩናይትድ ስቴትስ አካባቢዎች ላይ እስከሚቀጥለው ሣምንት አጋማሽ ድረስ እንደሚቆይ ተነግሯል።ማዕበሉ በተለይ የመተንፈሻ አካላት መታወክና የልብ ህመም ላለባቸው ሰዎች እጅግ አደገኛ መሆኑን የገለፁት ባለሥልጣናት ሰዉ አፍና አፍንጫውን እንዲሸፍን እየመከሩም ነው። ", "passage_id": "c1f3015b16764c005689d9aa002573b2" }, { "passage": "ሰኔ 7 እና ሰኔ 8 / 2009 ዓ.ም. (ትናንትናና ዛሬ መሆኑ ነው) እንዲያውም ሰሞኑንም ሁሉ ይቀጥላል፤ የሌሊቶቹ ሰማዮች ላይ ፕላኔት ሳተርን ከፀሐይ መውጫና መጥለቂያ አንፃር ጥርት ብላ ትታያለች፡፡ፀሐይ አመሻሹን በምዕራብ ስትጠልቅ ሳተርን በምሥራቅ ብቅ ትላለች፤ ደግሞም በምሥራቅ ብቅ ስትል ሳተርን በምዕራብ ማለዳው ላይ ትጠልቃለች፡፡ ስለዚህም እነዚህ ቀናት የፀሐይና የሳተርን ተቃርኖ ቀናት ተብለው ይጠራሉ፡፡የሰኔ ሰማዮች ለሥነ-ፈለክ አፍቃሪዎችና ተከታታዮች እጅግ የተዋቡና ባለብዙ ሥራ እንደሆነ ነው የሚሰማው፡፡በመሸበትና ሰማዩ የጠራ በሆነበት አካባቢ ያላችሁ ወጣ ብላችሁ ሰማዩን ቃኙት፤ እዚያ ወደ ምሥራቁ ሲያዘነብል ጥርት ብላ የምታይዋት ብሩህ ኮከብ - ኮከብ አይደለችም፤ ፕላኔት ሳተርን እንጂ፡፡ ግሩም ቴሌስኮፕ ያለው ደግሞ ቀለበቶቿንም ለመጎብኘት ዕድሉ ይኖረው ይሆናል፡፡ለማንኛውም ስለመሬታችን የተፈጥሮ አካባቢም ስለሰማዩም የወቅቱን መረጃ የያዘውን የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡ ", "passage_id": "783a63a83f69d0ebd0c10f2751ea0a79" }, { "passage": "ከልጅ እስከ አዋቂ፤ ከሊቅ እስከ ደቂቅ መልዕክቱ ደርሷቸው አጣጥመውታል። እንደ ወጀብ ጠዋት ማታ እየበጠበጣቸው ካለው መጥፎ ዜና ትንሽ እፎይታን ያገኙበት ይመስላል።\n\nየእንዋደድ መልዕክቱ ምናለ ምድር ላይ ቢወርድ፣ ብንዳንስሰው፣ ብንጨብጠው፣ ሁል ጊዜ ብንኖረው ሲሉ የተመኙም ብዙ ናቸው- ዲሽታግናን።\n\nዲሺታግና አዲስ ነጠላ ዜማ ነው። ድምጻዊው ታሪኩ ጋንኪሲ ይባላል። በዩትዩብ ከተለቀቀ የተቆጠሩት ሦስት ሳምንታት ብቻ ናቸው። \n\nበሦስት ሳምንታት ውስጥ ከ3 ሚሊየን በላይ ተመልካቾችን አግኝቷል። በርካቶች በማሕበራዊ ሚዲያ ተቀባብለውታል። \n\nዲሺታግና በተከፈተ ቁጥር ባለበት የማይወዛወዝ ማግኘትም ዘበት ነው። \n\nዲሺታግና \n\nዲሽታግና የአሪ ብሔረሰብ አዲስ ዓመት ወይም ዘመን መለወጫ ነው። ዲሽታግና አብረን እንብላ፣ አብረን እንጠጣ፣ የተጣሉትን እናስታርቅ ፣ ለሌላቸው እንስጥ፣ እንደጋገፍ ማለት ነው።\n\nክብረ በዓሉ \"12 ወራትን በድካም፣ በልፋት፣ በደስታና በሃዘን አሳልፈናል። አሁን ደግሞ 12 ወራት ወደ ፊት ይጠብቀናል። ስለዚህ በጥል ማሳለፍ ሳይሆን በፍቅር ፣ በሰላም፣ በመደጋገፍና ያጡትን በመርዳት እናሳልፍ\" የሚል የመተሳሰብ መልዕክት የሚሰበክበት፤ በተግባርም የሚታይበት ነው።\n\nታሪኩ ሙዚቃውን ለመሥራት የተነሳውም ይህ ፍቅር አዘልና አስታራቂ ባህል ቢኮረኩረው ጊዜ ነው። ታዲያ በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኘው የአሪ ልማት ማሕበር ገፋፊነትም ሳይዘነጋ ነው።\n\n\"ይህንን ሥራ እኛ ብቻ ከምናውቀው ሰው ሁሉ ይወቀው\" ሲል ማሕበሩ ጠርቶ እንዳነጋገረው የሚናገረው ታሪኩ፤ የሙዚቃ ሥራውንም እንደ ማሕበረሰቡ ባህል ተደጋግፈው እንደሠሩት ይናገራል።\n\nማሕበሩ ምንም እንኳን አቅሙ ያልጠና ቢሆንም ለዚህ ሙዚቃ ግን አስተዋፅኦው ከፍተኛ ነበር ይላል ታሪኩ።\n\nየጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ገብሬ ይንቲሶም ድጋፍ ቀላል አይደለም። ግጥሞቹን በማስተካከልና በማረም አግዘውታል።\n\n\"የተሳሳትኩት ነገር ካለ ብዬ ሰግቼ ነበር፤ ፖለቲካ ከሆነ እንዳልጠፋ ብዬ አስቤ ነበር\" ይላል።\n\nበእርግጥ የራሱን ስሜት ለመግለፅ ያህል እንጂ እንዲህ ዓይነት ተቀባይነት አገኛለሁ ብሎ አላሰበም ነበር።\n\n\"እኔ ራሴን የገለፅኩበት ለካስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍቅር ይፈልግ ነበር። እንዲህ ዓይነት ፍቅር ይፈልግ ነበር፤ ተወደደ።\" ይላል።\n\nታሪኩ \"የሰው ልጅ ሲሠራ ያገኛል፤ እኛ ይዘን የመጣነው የለም፤ ወደፊትም ይዘነው የምንሄደው ነገር የለም፤ እስካለን ለምን እንጣላለን? ሲልም ይጠይቃል። በርግጥስ የሚያጣላን ምን ይሆን?\n\nድምጻዊው ለዚህ ሁለት ምክንያቶችን ያስቀምጣል። ራስ ወዳድነትንና ፈጣሪን አለመፍራት።\n\n\"የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈጣሪን የሚፈራ ነው። አሁንም የሚያወጣን ፈጣሪን መፍራት ነው\" ይላል ታሪኩ። \n\n\"ይህችን ምድር የተቀላቀልነው ባዷችንን ነው፤ የምንመለሰውም እንደዚያው\" የሚለው ታሪኩ፤ ከሰውነት የወጡ ተግባራት የሚፈፀሙት ይህንን ማሰብ የዘነጋን ጊዜ እንደሆነ ይናገራል።\n\nድምጻዊው እንደሚለው ራስ ወዳድ የመሆንም ውጤቱ እርስ በርስ መናከስ ነው።\n\n\"ራስ ወዳድ ስትሆኝ ጠባብ ትሆኛለሽ፤ ሰው ትጠያለሽ፣ ከሰው ትርቂያለሽ፤ ጭንቅላትሽ የሚመግበው አንቺ የምታደርጊው ላንቺም ለሰውም እንደሚመች ነው\" ሲል ያስረዳል።\n\n\"እኔን እንኳን ይህችን ሰራህ ብለው 'አንተ ጀማሪ ነህ ከማን ትበልጣለህ' ሲሉ ሞራሌን የሚነኩ አሉ\" የሚለው ታሪኩ፤ ወደዚች አለም መጥተን የምንሄድበት ትኬት እስኪቆረጥ ድረስ ምናለ በፍቅር ብንኖር ይላል።\n\nበስንኞቹም እንዲህ ገልጾታል።\n\n\". . . ያ ባቢሎን እኛን በታተነን \n\nይሄው እስከ ዛሬ የእውነት ፍቅር አጣን . . .\n\nእኔ አና አዳም አንድ አባቴ \n\nአንችና ሄዋን አንዱ አጥንቴ . . .\" \n\nበሙዚቃው ግጥም በአማርኛ... ", "passage_id": "a83b31fba7b51f270f7aa0b71441cf4c" } ]
084adbe590142d2b7afe8ffd2182b24b
35430572a053b74df06f2fa400489660
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሊጉን ለማጠናቀቅ ቆርጠው ተነስተዋል
ዓለምን በአንድነት እያስጨነቀ የሚገኘው ወቅታዊ ጉዳይ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) ወረርሽኝ መሆኑ ይታወቃል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ያስቻለ ፈውስ በዓለም ሳይንቲስቶች፣ የህክምና ጠቢባንም ይሁን በሃያላን አገራት አቅም ማምጣት አልተቻለም። ይህም የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ ከመለወጥ አንስቶ በተለያዩ ዘርፎች ላይ በርካታ አሉታዊ ተፅዕኖው እንዲያርፍ አድርጓል። የስፖርቱ ዓለም በቫይረሱ ስጋት ሳቢያ ብዙ ተጽዕኖ እያስተናገደ ከመሆኑ ባሻገር፤ ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጉን መረጃዎች ያመላክታሉ። በወረርሽኙ ሳቢያ ትልልቅ የስፖርት ውድድሮች በመራዘማቸው፣ በመሰረዛቸው እና በመስተጓጐላቸው ኢንዱስትሪውን ከፍተኛ ገቢ እንደሚያሳጣው የተለያዩ ትንበያዎች አመልክተዋል። የስፖርት ኢንዱስትሪውን በስፖንሰ ርሺፕ የሚደግፉ ትልልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የበጀት ቀውስ ውስጥ መግባታቸው፣ ከትኬት ሽያጭ ከማርኬቲንግና ከተለያዩ ንግዶች የሚገኙ ገቢዎች መቆማቸው ሁሉንም ስፖርት ጎድቷቸዋል፡፡ በተለይ የእግር ኳስ ስፖርት ከፍተኛ ድርሻ የሚይዝ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል። በዚህ ዓመት የእግር ኳሱ ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል ተብሎ ሲጠበቅ ከተላላፊው ቫይረስ ጋር በተያያዘ ገቢው በእጅጉ እያሽቆለቆለ ይገኛል። የስፖርት እንቅስቃሴን ጨምሮ ሌሎች መደበኛ እንቅስቃሴዎችን በቅርብ ጊዜ ማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ ተስፋ ሰጪ ምልክቶች እየታዩ አለመሆኑ፤ በኢንደስትሪው ላይ የሚደርሰው ቀውስ እንዲያሻቅብ እንደሚያደርገው ተነግሯል። የቫይረሱ ስርጭት በዓለም ዙሪያ እያሻቀበ በመሆኑ ታላላቅ ስፖርታዊ ውድድሮች በቅርቡ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው የሚመለሱበት ሁኔታ ጠባብ መሆኑ እየተነገረ ባለበት ወቅት ቢቢሲ ከቀናት በፊት ይዞት የወጣው መረጃ ተስፋ ሰጪ ሆኗል። ቢቢሲ ፤ የዓለማችን ታላላቅ የእግር ኳስ ሊጎች በዝግ ስታድየምም ቢሆን የውድድር ዓመቱን ቀሪ መርሃግብሮች ለማጠናቀቅ በቅርቡ ወደ ውድድር ሊመለሱ መሆኑን ጽፏል። ከዚህ ውስጥ ደግሞ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ግንባር ቀደም ሊሆን እንደሚችል አስነብቧል። የውድድር ዓመቱን ቀሪ መርሃግብሮች ለማጠናቀቅ ማሳባቸውን ጠቅሶ፤ በተለይ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሊጉን ለማጠናቀቅ ቆርጠው ተነስተዋል ሲል አስነብቧል። የዓለም ጤና ድርጅት የሕክምና ባለሙያዎች ግን ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በትልቅ ደረጃ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው እንዳይመለሱ ምክራቸውን መለገሳቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡ የዓለማችን ታላላቅ የእግር ኳስ ሊጎች በዝግ ስታድየምም ቢሆን የውድድር ዓመቱን ቀሪ መርሃግብሮች ለማጠናቀቅ የተለያዩ ሀገራት ሊጎች እንደ አማራጭ እየቀረበ ይገኛል። በዝግ ስታዲየም ውድድሮችን አማራጭን ወደ ተግባር ለመቀየር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ቆርጠው መነሳታቸውን አስነብቧል። የ2020 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት መጋቢት ወር መግቢያ ላይ ነበር የተቋረጠው። ሊጉ የውድድር ዘመኑ ሊጠናቀቅ 92 ጨዋታዎች ይቀሩታል። የቫይረሱ ስርጭት በዓለም ዙሪያ እያሻቀበ መሄዱን ተከትሎም የውድድር ዘመኑን በመደበኛው መልኩ ለማካሄድ ለመመለስ የሚያስችል ተስፋ የለም። የ2020 ውድድር ዘመን 92 ጨዋታዎችን እንዴት እናጠናቅ በሚለው ዙሪያ የሊጉ ክለቦች የቪድዮ ስብሰባ አድርገዋል። በስብሰባው ላይ እንደ ሕክምና ባለሙያዎች ያሉ ያገባቸዋል የተባሉ ሰዎችም ተገኝተው ነበር። ክለቦች ሊጉ በቀላሉ ወደ ውድድር እንደማይመለስ መግባባት ላይ ደርሰዋል። የውድድር ዓመቱን ለማጠናቀቅ የተቀሩትን ውድድሮች በዝግ ስታዲየም ለማድረግ ከስምምነት መድረሳቸውን ቢቢሲ አስነብቧል። በቪዲዮ ስብሰባ ወቅት «የሊጉ ክለቦች ይህን ለማድረግ ደግሞ ቢያንስ 10 ገለልተኛ ሜዳዎች ያስፈልጋሉ ። ገለልተኛ ሜዳዎችን መጠቀም ያስፈለገው ደጋፊዎች ከሜዳ ውጪም ቢሆን እንዳይሰበሰቡ በማሰብ ነው። አልፎም የሚመረጡት ሜዳዎች ከፖሊስና የስፖርት ሜዳዎችን ደህንነት ከሚመረምር አካል ይሁንታ ያገኙ መሆን አለባቸው» መባሉን በዘገባው አስፍሯል። በተጨማሪም ተጫዋቾች በሳምንት ሁለት ጊዜ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ይደርግላቸዋል። በየቀኑ ደግሞ የበሽታው ምልክት ታየባቸው አልታየባቸው የሚለው ይለካል። አልፎም ሜዳዎች በየጊዜው ንፅህናቸው ይጣራል ተብሏል። ተጫዋቾች ከጨዋታ ውጪ ባሉት ጊዜያት ሁሉ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ አለባቸው። በውድድር ስፍራዎች ውስጥም ምግብ መብላትም ሆነ ገላን መታጠብ እንዳይችሉ የሚደረግ መሆኑን አመልክቷል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሊጉን ለማ ጠናቀቅ በገለልተኛ ሜዳ ውድድሮችን ለማድረግ ከስምምነት መድረስ ቢችሉም ከሀገሪቱ መንግስት በኩል የሚኖረውን ተቀባይነት ምን ሊሆን ይችላል ? የሚለው ምላሽ የሚያሻ መሆኑን ዘገባው አንስቷል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን መጋቢት ወር መግቢያ ላይ ነበር በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እንዲቆም የተደረገው። የፕሪሚየር ሊጉ አስተዳዳሪ አካል መንግሥት ይሁንታ ሲሰጥ ብቻ ወደ ሜዳ የሚመለስ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። የውድድር አመቱ የቀሩትን 92 ጨዋታዎች ለመጫወት ከስምምነት ቢደርሱም የሀገሪቱ መንግስት ውሳኔ ምን ሊሆን እንደሚችል የተባለ ነገር አለመኖሩን ዘገባው ጠቅሷል። የዚህ ዓመት ወድድር ይቋረጥ የሚል ሐሳብ ከየትኛውም ክለብ አልመጣም ነበር። በመሆኑም በሁሉም የሊጉ ክለቦች በኩል የተወሰነው ውሳኔ ከመንግስት ድጋፍ የሚያገኝ ከሆነ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መቋጫው በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ሊሆን እንደሚችል ግምቱን አስፍሯል። የእንግሊዝ መንግሥት እንቅስቃሴዎች ቀስ በቀስ ወደነበሩበት እንዲመለሱ ካደረገ በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በዝግ ሜዳ ወደ ውድድር እንደሚመለስ ይጠበቃል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 27/2012ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=31713
[ { "passage": "በአውሮፓ ሀገራት የሚካሄዱ ታላላቅ ሊጎች እና ዓለማቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮች በኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት እየታጠፉ ነው፡፡ የቫይረሱ የስርጭት ማዕከል ከቻይና ወደ አውሮፓ በመቀየሩ በርካታ ስፖርታዊ ሁነቶችና መደበኛ ውድድሮች አንዳንዶቹ ለተወሰኑ ሳምንታት አንዳንዶቹ ደግሞ ላልተወሰነ ጊዜ እየተራዘሙ ይገኛሉ፡፡የጁቬንቱሱ ተጫዋች ዳንኤል ሬጋኒ በቫይራሱ ተይዞ መገኘቱን ተከትሎ ሁሉም የቡድኑ አባላት በማግለያ እንዲቆዩ በማድረግ የተጀመረው የጣልያን ሴሪ ኤ በዝግ ስታዲዬም በመጫወት ተጀመሮ ወደ መቋረጥ ደርሷል፡፡ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግም እንዲቋረጥ ትናንት ውሳኔ ተላልፏል፡፡", "passage_id": "93938d8e757258bdcc08fe5dbce6f6f6" }, { "passage": "ይህንን ያለው በአውሮፓ የሚገኙ ሊጎችን የሚወክለው ማህበር ነው።\n\nየማህበሩ ምክትል ኃላፊ አልቤርቶ ኮሎምቦ እንዳሉት በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተቋረጠው የአውሮፓ ሊግ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብቷል።\n\n‘’አብዛኛዎቹ የማህበሩ አባል ሊጎች በተለይም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች እንዲጀመሩ ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው። ነገር ግን እንደ ቤልጂየም ያሉ ጥቂት አገራት ከነጭራሹ የዘንድሮው ውድድር እንዲሰረዝ ሀሳብ አቅርበዋል’’ ብለዋል።\n\nየእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አርብ ዕለት የወደፊት እርምጃዎችን በተመለከተ ስብሰባ እንደሚያደርግ የሚጠበቅ ሲሆን ዘጠኝ ጨዋታዎች የሚቀሩት ሊግ መቼ ይቀጥል? የሚለው ዋና ርዕስ እንደሚሆን ይጠበቃል።\n\nባለፈው ሳምንት አንዳንድ የጀርመን ክለቦች ወደ ስልጠና መመለሳቸውን ተከትሎ እግር ኳስ ማህበራትና የእግር ኳስ አፍቃሪዎች በተስፋ ተሞልተው ነበር።\n\nአልቤርቶ ኮሎምቦ ግን ዋናው ትኩረታችን መሆን ያለበት ሐምሌ እና ነሀሴ ላይ ጨዋታዎቹን እንዴት ማስቀጠል አለብን የሚለው ላይ ነው፤ ከዛ በፊት ያሉት ወራት ላይ ጨዋታዎችን ማካሄድ የማይታሰብ ሊሆን ይችላል ብለዋል።\n\n‘’በመጀመሪያ የተጫዋቾች ስልጠና መጀመር አለባቸው። በመቀጠል የጨዋታዎቹ አዘጋጆች የደህንነት ማረጋገጫ ስራዎችን ይሰራሉ። ጨዋታዎቹ በዝግ ስታዲየሞች መከናወናቸው የማይቀር ነገር ነው።‘’\n\n‘’እኛ ሀሳብ እናቀርባለን እንጂ የመጨረሻው ውሳኔ ያለው የአገራቱ መንግስት ላይ ነው። የተጣሉት እገዳዎች እንደተነሱ ጨዋታዎችን ከከፍተኛ ጥንቃቄ ጋር በዝግ ስታዲየም እናከናውናለን።‘’\n\nየጣልያን እግር ኳስ ፌደሬሽን እግር ኳስ ተጫዋቾች ሌላው ቢቀር ልምምዳቸውን መስራት እንዲጀምሩ በማሰብ ከመጪው ግንቦት ወር ጀምሮ ተጫዋቾቹ ላይ የኮሮናቫይረስ ምርምራ ማድረግ እንደሚጀምር አስታውቋል።\n\nየአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በበኩሉ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተከሰተውን የሊጎችና ውድድሮች መቋረጥን በተመለከተ በሚቀጥለው ሳምንት ስብሰባ ያደርጋል ተብሏል።\n\n ", "passage_id": "dd9d3851230028e1ed7a2ff7fad4a477" }, { "passage": "ማንችስተር ሲቲ ዛሬ ከአርሰናል ጋር ሊያደርግ የነበረው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ለቅድመ ጥንቃቄ በሚል እንዲራዘም ተደርጓል፡፡\n ከሁለት ሳምንታት በፊት አርሰናል ከኦለምፒያኮስ ጋር ባደረገው ጨዋታ በስፍራው የነበሩት የኦለምፒያኮስ ባለቤት፣ የ52 ዓመቱ ማሪናኪስ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ትናንት በመረጋገጡ ነው ውሳኔው የተላለፈው፡፡\nአርሰናል በጨዋታው እለት በርካታ የክለቡ ተጫዋቾች ከማሪናኪስ ጋር ንክኪ እንደነበራቸው አስታውቋል፡፡ ይሄን ተከትሎ 7 የአርሰናል ተጫዋቾች ተለይተው እንዲቆዩ ተደርገዋል፡፡\nበሌላ ዜና የእንግሊዙ ክለብ ዎልቭስ ነገ በዩሮፓ ሊግ ከኦለምፒያኮስ ጋር ይገናኛል፡፡\nበግሪክ የሚካሄደው ይህ ጨዋታ እንዲራዘም ዎልቭስ ያቀረበው ጥያቄ በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በማህበሩ ውሳኔ ቅሬታ የተሰማው ክለቡ አላስፈላጊ ኃላፊነት እንድንወስድ ተፈርዶብናል ሲል ተቃውሞ ቢያሰማም የማህበሩን ውሳኔ ግን እንደሚያከብር አስታውቋል፡፡\nይሁን እንጂ ሁሉም የኦለምፒያኮስ ተጫዋቾች ከዎልቭስ ቅሬታ በኋላ ዛሬ በተደረገላቸው ምርመራ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡\nከወደ ጣሊያን የተሰማው ዜና ደግሞ፣ የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌደሬሽን ትናንት ባደረገው ስብሰባ ተወዳጁ የሴሪአ ዉድድር ከኮሮና ቫይረስ ስጋት ጋር በተያያዘ ላይጠናቀቅ እንደሚችል አስታውቋል፡፡\nየጣሊያን መንግስት ትናንት ባወጣው መግለጫ መላው በሀገሪቱ የሚካሄዱ ውድድሮች ቢያንስ እስከ መጋቢት 25 እንደሚቋረጡ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡\nፌደሬሽኑ ባወጣው መግለጫ ሴሪአው የማይጠናቀቅ ከሆነ እስከተቋረጠበት ጊዜ ያለው ውጤት የመጨረሻ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል አሊያም የ2019/20 ውድድር ዓመት ሻምፒዮን እንደማይር ገልጿል፡፡\nየሻምፒዮንስ እና ዩሮፓ ሊግ ተወዳዳሪዎችን እንዲሁም 3 ወራጅ ክለቦችን ለመለየት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ሊካሄዱ እንደሚችሉም በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡ በአማራጮቹ ላይ ከቀናት በኋላ በፌደራል ካውንስል ውይይት ተደርጎባቸው ውሳኔ ይተላለፋል፡፡\nበጣሊያን ከዚህ ቀደም ለመጨረሻ ጊዜ ውድድር ተቋርጦ የነበረው በ2004/5 የውድድር ዓመት ነው፡፡ ለመቋረጡ ምክኒያት የነበረው ደግሞ የተወሰኑ ክለቦች ከዳኛ መረጣ ጋር በተያያዘ የገቡበት የሙስና ቅሌት መሆኑ ይታወሳል፡፡\nቢቢሲ እንደዘገበው አሁን ውድድሩ ባለበት እንዲቋረጥ ከተወሰነ በመሪነት ደረጃ ላይ ያለው ጁቬንቲዩስ ሻምፒዮን እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን ያኔ በነበረው ቅሌት ግን በቅጣት ወደ ሴሪቢ እንዲወርድ ተደርጓል፡፡\nእስካሁን በጣሊያን የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 10,150 መድረሱ ሲረጋገጥ 631 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡\nበዓለም ዙሪያ ደግሞ ከ110 በላይ ሀገራት የተዳረሰው ኮሮና ቫይረስ ከ115,800 በላይ ሰዎችን ሲያጠቃ ከ4,200 በላይ የሚሆኑትን ደግሞ ህይወታቸውን ነጥቋል፡፡\n", "passage_id": "f090079b7acb98f4e24a772d79cbf48a" }, { "passage": "አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮሮናቫይረስ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሰኔ 10 ቀን ወደ ውድድር ሊመለስ መሆኑ በዛሬው እለት ተገልጿል።ፕሪምየር ሊጉ ማንችስተር ሲቲ ከአርሰናል እንዲሁም አስቶንቪላ ከ ሼፍልድ ዩናይትድ በሚያደርጓቸው ተስተካካይ ጨዋታዎች እንደሚጀምርም ታውቋል።ከዚያ በመቀጠል ከሰኔ 12 እስከ 14 ደግሞ ሙሉ 10 ጨዋታዎች እንደሚካሄዱም የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።በፕሪምየር ሊጉ ዳግም መጀመር ዙሪያ ክለቦች በውይይት ላይ ናቸው የተባለ ቢሆንም፤ ሁሉም ክለቦች ግን በመርህ ደረጃ ከመስማማት ላይ መድረሳቸውም ነው የተነገረው።የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሊጠናቀቅ 92 ጨዋታዎች የሚቀሩት ሲሆን፥ ሁሉም የሊጉ ውድድሮች በከፍተኛ ጥንቃቄ ደጋፊ ባልተገኘበት በባዶ ስታዲያም እንደሚካሄዱም ተነግሯል።በፕሪምየር ሊጉ ላይ ለሚሳተፉ 2 ሺህ 752 ተጫዋቾችና የስታፍ አባላት በተደረገ ምርመራም እስካሁን 12 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱም ተገልጿል።በፕሪምየር ሊጉ ላይ ለሚሳተፉ ሁሉም ተጫዋቾች እና የስታፍ አባላት በየሁለት ሳምንቱ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ይደረጋል የተባለ ሲሆን፥ ቫይረሱ የተገኘበት ማንኛውም ሰው ራሱን ለ7 ቀናት አግልሎ የመቆየት ግዴታ እንዳለበትም ታውቋል።የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን ሊቨርፑል በ82 ነጥብ ሲመራ፣ ማንቸስተር ሲቲ በ57 ነጥብ 2ኛ፣ ሌሰተር ሲቲ በ53 ነጥብ 3ኛ እንዲሁም ቸልሲ በ48 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።ምንጭ፦ ቢቢሲየዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።", "passage_id": "eeca5c144d026db0f1fe0c15eed3db8a" }, { "passage": "የመድፈኞቹ ተጫዋቾች ራሳቸውን አግልለው በር ዘግተው የተቀመጡት የኦሎምፒያኮስ ባለቤት የሆኑት ኢቫንጀሎስ ማሪናኪስ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ ነው።\n\nአርሰናል እንዳለው ከሆነ ማሪናኪስ ከሁለት ሳምንት በፊት በነበረው አውሮፓ ሊግ ጨዋታ ወቅት በርካታ ተጫዋቾችን አግኝተው ነበር።\n\nየ52 ዓመቱ ማሪናኪስ በኮቪድ 19 [ኮሮናቫይረስ] መያዛቸውን የተናገሩት ማክሰኞ ዕለት ነበር።\n\nኦሎምፒያኮስ በአውሮፓ ሊግ ዎልቭስን ሐሙስ ዕለት የሚያስተናግድ ሲሆን፤ ዎልቭስ ግን አስቀድሞ ጨዋታው እንዲራዘምለት ጠይቆ የነበረ ቢሆንም ተከልክሏል።\n\nየፕሪሚየር ሊግ የበላይ ኃላፊዎች ግን ከእንግዲህ ወዲህ ምንም ዓይነት ጨዋታ የማራዘም ሃሳብ እንደሌላቸው ገልፀው \"አስፈላጊው ጥንቃቄ ሁሉ ተወስዷል\" ሲሉ ተናግረዋል።\n\nብራይተን በበኩሉ ከአርሰናል ጋር ያላቸው ግጥሚያ ቅዳሜ እለት በተያዘለት ሰዓት እንደሚካሄድ አስታውቋል።\n\n\"ተጫዋቾቹ ራሳቸውን ነጥለው የሚያቆዩበት ጊዜ የሚያበቃው ሐሙስ በመሆኑ አደጋው እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው\" ብለዋል።\n\nበዩናይትድ ኪንግደም እስካሁን ድረስ 382 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ስድስት ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።\n\nየኮሮናቫይረስ የስፖርት ውድድሮችን በከፍተኛ ሁኔታ የጎዳ ሲሆን የጣሊያን ሴሪ አ ሲቋረጥ የፈረንሳይና የስፔን ጨዋታዎች በዝግ ስታዲየም እንዲካሄዱ ተወስኗል።\n\nማንችስተር ዩናይትድን፣ ሬንጀርስንና ቼልሲን የሚያሳትፈው የአውሮፓ ዋንጫም በሚቀጥሉት ቀናት በኦስትሪያ እና በጀርመን በዝግ ስታዲየሞች ይካሄዳሉ። \n\nበዩናይትድ ኪንግደም ግን ስፖርት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሲስተጓጎል ይህ የመጀመሪያው ጨዋታ ነው።\n\n ", "passage_id": "b9e340d235aa356c8a9275b629890252" } ]
aa80469b1aeaeecbf46038af5e5d2477
982986101bc0dcb4fb98ac2c435347af
ኦሊምፒክ ኮሚቴ አትሌቶችን እደግፋለሁ አለ
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከውድድር ውጪ ለሆኑ ብሔራዊ አትሌቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተጠሪነቱ ምንም እንኳ ለሁሉም ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ቢሆንም፣ ብሔራዊ አትሌቶችን በሒደት ከገንዘብ ድጎማ ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ እየሠራ መሆኑ ፕሬዚዳንቱ ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ አስታውቀዋል፡፡ ከድጋፉ ባሻገር የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከመከሰቱ በፊት ለአገሮች በሰጠው ነፃ የትምህርት ዕድል ኮታ መሠረት ኤሊት አትሌቶች ዕድሉን እንዲጠቀሙ ለማድረግ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡ ብሔራዊ ተቋማት ችግሩ በአትሌቶች ላይ ሥነ ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዳያሳድር የሚችሉትን እያደረጉ ይገኛሉ። ቀደም ሲል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት አትሌቶችንና መሰል ሙያተኞችን መደጎሙ አይዘነጋም፡፡ አዲስ ዘመን ሚያዝያ 27/2012
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=31712
[ { "passage": "ዓመቱን ሙሉ አትሌቶችን የሚያፋልመው ዳይመንድ ሊግ ውድድር ከአዲሱ የፈረንጆቹ ዓመት 2020 ጀምሮ ስምንት ውድድሮችን እንደቀነሰ አስታውቋል፡፡ የ3ሺ ሜትር መሰናክል እና ረጅሙ የሩጫ ውድድር የሆነው 5ሺ ሜትር እንደማይካሄድም ታውቋል፡፡ ውድድሩ ትኩረቱን በአጫጭር እና መካከለኛ እንዲሁም በሜዳ ተግባራት ላይ የሚያደርግም ይሆናል፡፡ በተያዘው ሳምንት የውድድሩ አዘጋጆች ዕቅዳቸውን ሲያሳውቁ 5ሺ ሜትር አለመካተቱ ተረጋግጧል፡፡ በዚህ ዓመት በዳይመንድ ሊጉ የሚካሄዱት ውድድሮች ቀድሞ ከነበረው 14 አንሶ 12 ብቻ ይሆናል፡፡ ከእነርሱም መካከል ሰባቱ ብቻ የሩጫ ውድድሮች ሲሆኑ ረጅሙ ርቀት ደግሞ 3ሺ ሜትር ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ የሆነውም አዘጋጁ አካል ከአትሌቶች፣ አሰልጣኞች፣ ደጋፊዎች እንዲሁም ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር በተደረገ ምክክር እና ጥናት መሰረት እንደሆነም ፍሎ ትራክ የተባለ ድረገጽ አስነብቧል፡፡ ዓመቱን ሙሉ በአስራ አራት ዙር በተለያዩ ሃገራት ከተሞች በመዘዋወር የሚካሄደው ይህ አትሌቲክስ ውድድር ከአዲሱ ዓመት ጀምሮ ረጅሙን ርቀት እንደሚያስቀር ቀደም ብሎ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ ይህንን ተከትሎም በተለይ በርቀቱ ስኬታማ የሆኑት የምሥራቅ አፍሪካ ሃገራት የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ተቃውሟቸውን ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ ኢትዮጵያም በሃሳቡ እንደማትስማማ በፌዴሬሽኑ አመራሮች በኩል ለዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ማስታወቋ አይዘነጋም፡፡ ይሁን እንጂ ዓለም አቀፉ ማህበር በውሳኔው በመስማማት በርቀቶቹ መሰረዝ ላይ ያለውን ድጋፍ አንጸባርቋል፡፡ ውሳኔው እውን መሆኑን ተከትሎ ከኢትዮጵያ በኩል የተሰማ አስተያየት ባይኖርም ሌሎች አገራት ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡፡ በ3ሺ ሜትር መሰናክል የዓለምን ክብረወሰን የሰበረችው ኬንያዊቷ ባትሪስ ቼፕኮች፤ ውሳኔው ውድድሮቹን እንደ መግደል እንደሚቆጠር ተናግራለች፡፡ በአዲሱ የዳይመንድ ሊግ መርሐግብር መሰረት በሁለቱም ፆታ አስራ ሁለት አስራ ሁለት ውድድሮች ሲካሄዱ የመቶ ሜትር፣ የመቶና መቶ አስር ሜትር መሰናክል፣ አራት መቶ ሜትር፣ አራት መቶ ሜትር መሰናክል፣ ስምንት መቶ ሜትር፣ አንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር፣ ርዝመት ዝላይ፣ ከፍታ ዝላይ፣ ምርኩዝ ዝላይ፣ ጦር ውርወራና መዶሻ ውርወራ ውድድሮች ብቻ የዳይመንድ ሊጉ አካል ይሆናሉ፡፡ አዲስ ዘመን ጥቅምት28/2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "df5b5d1d48000416cbffa53d38f2d214" }, { "passage": "የወቅቱ የዓለም ራስ ምታት በሆነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች አንቀላፍተው ቢቆዩም ከሰሞኑ የአውሮፓ ሊጎች ወደ ልምምድ መመለስን ተከትሎ የስፖርቱ ኢንዱስትሪ መነቃቃት ጀምሯል። አሁንም የኮሮና ወረርሽኝ (ኮቪድ 19) ስጋት እንዳለ ቢሆንም ጥንቃቄን በተላበሰ መልኩ ወደ ቀድሞው መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ ጥረቶች እየታዩ ነው። በዚሁ ምክንያት ተቀዛቅዞ የቆየው አበረታች ቅመሞችን መከላከልና የመቆጣጠር ሥራ ነው። ይህ ስፖርትን በተፈጥሯዊው መንገድ ብቻ እንዲካሄድ የማድረግ ጥረት ሊቀዛቀዝ የቻለው በዓለም አቀፍ ደረጃ ውድድሮች መቋረጣቸውን ተከትሎ ነው። ይሁን እንጂ ከዓላማው አንጻር ረጅም ጊዜ መውሰዱና መዘናጋቱ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል። \nበመሆኑም ዓለም አቀፉ የጸረ አበረታች ቅመሞች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በስሩ ለሚገኙት ብሔራዊ ጽሕፈት ቤቶች መመሪያ ማዘጋጀቱን ከሰሞኑ በድረገጹ አስነብቧል። ይህም በየሀገራቱ የሚገኙ የጸረ አበረታች ቅመሞች ተቆጣጣሪ ጽሕፈት ቤቶች ወደ ቀደመ ሥራቸው እንዲመለሱ የሚያስችል ርምጃ ነው። ኤጀንሲው በወረርሽኙ ምክንያት በዓለም ዙሪያ ሲሰሩ የቆዩት ናሙና የመውሰድና ምርመራ የማድረግ ሂደቶችን የቀነሰና አንዳንድ ሥራዎችንም በጊዜያዊነት ማቋረጡን በዘገባው ተጠቁሟል። ነገር ግን አሁን ወደ ሥራ ለመመለስ እንቅስቃሴ መደረግ እንዳለበት የኤጀንሲው ፕሬዚዳንት ዊቶልድ ባንካ ይገልጻሉ። በኤጀንሲው ስር ካሉ ተቋማት ጋር ከወቅታዊው ጉዳይ ጋር በተያያዘ በቅርበት ሲሰሩና ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል። አሁን ግን ሥራው እንደቀድሞው መቀጠል ያለበት በመሆኑ፤ በቴክኖሎጂ በታገዘና የናሙና አወሳሰዱን በአዲስ መንገድ ማካሄድ ተገቢ መሆኑን ያመላክታሉ። ለዚህ ደግሞ በጸረ አበረታች መድኃኒት ቁጥጥር ላይ የሚሰሩ አካላት አዲስ ነገር ለመፍጠር ርብርብ ላይ ይገኛሉ። \nየተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ኦሊቨር ኒግሊ በበኩላቸው፣ በዚህ ወቅት ናሙናዎችን ከአትሌቶች ለመውሰድ አዳጋች መሆኑን ነው የሚጠቁሙት። ምርመራው መቀጠል የሚገባው አስፈላጊው የጤናና ንጽህና ሁኔታ የተስተካከለ ሲሆን ብቻ ነው። የአትሌቶችና በዙሪያቸው ያሉ አካላት ጤናም ኤጀንሲው ትኩረት የሚሰጠው ቀዳሚ ጉዳይ ነው። ተቋሙ የአትሌቶችን ናሙና በመውሰድ አበረታች መድኃኒት ተጠቃሚነታቸውን በምርመራ መለየት ብቻም ሳይሆን የጤና ግለ ታሪካቸውንም መመዝገብ ሌላው ተግባሩ ነው። ንጹህ ስፖርት ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ግንዛቤ ማስጨበጥም እንዲሁ። በመሆኑም በቀጣይ ሳምንታት ከብሔራዊ ተቋማቱ ጋር በመሆን ሥራው በምን መልኩ መቀጠል ይገባዋል በሚለው ላይ መፍትሄ በማፈላለግ ወደ ሥራ የሚመለስ እንደሆነ አብራርተዋል።\nየሯጮቹ ሀገር ኢትዮጵያም የኤጀንሲው አባል ሀገር በመሆን ንጹህ ስፖርት እንዲካሄድ ሚናቸውን ከሚወጡት መካከል ትጠቀሳለች። ተሞክሮውን ለሌላው ዓለምም ማጋራት የቻለና በሥራው ምስጉን የሆነ ጽሕፈት ቤትም በአጭር ጊዜ ለማቋቋም መቻሉ ይታወቃል። በመላው ዓለም ባጠላው በዚህ የወረርሽኝ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጸረ አበረታች ቅመሞች ተቆጣጣሪ ጽሕፈት ቤት እንቅስቃሴውን በምን መልኩ እያከናወነ ይገኛል? የሚለውን የጽሕፈት ቤቱ ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል ያስረዳሉ። የተቋሙን ውስጣዊና ውጫዊ እንቅስቃሴ በሁለት የሚከፍሉት ዳይሬክተሩ፤ የኮሮናን ቫይረስ በመከላከል ረገድ ሠራተኞችን የመቀነስና የንጽህና ቁሳቁስን የማዘጋጀት ሥራዎች መከናወናቸውን ይጠቁማሉ። \nሁለተኛውና ከተቋሙ ውጪ ከአትሌቶች ጋር በመገናኘት የሚከናወነው ደግሞ ከአበረታች መድኃኒት ቁጥጥር ጋር የተያያዘው ሥራ ነው። ይሁን እንጂ ከአትሌቶች ናሙና መውሰድ በእጅጉ ለንክኪ የሚያጋልጥ በመሆኑ አትሌቶችንም ሆነ በምርመራው ተሳታፊ የሆኑ ባለሙያዎችን ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆኑ በማሰብ ለጊዜው ገታ ተደርጓል። \nነገር ግን ሥራውን ሙሉ ለሙሉ ማቆም የማይቻል በመሆኑ ለቫይረሱ አጋላጭ ይሆናሉ የሚል ስጋት ያሳደሩ ሥራዎችን ፎርማት ለመቀየር መሞከሩን ዳይሬክተሩ ይገልጻሉ። በዚህም መሠረት አበረታች ንጥረ ነገር ተጠቃሚ የሆኑ አትሌቶችን የማጋለጥ፣ አትሌቶች ባዮሎጂካል ፓስፖርት ፕሮግራም ሥራን የማጠናከር እንዲሁም ሌሎች ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህ ጊዜ ውድድሮች የተቋረጡ ቢሆንም ስፖርተኞች ግን በየግላቸው በቤታቸው ውስጥ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን አላቆሙም። ይህንን ተከትሎም ከውድድር ውጪ የሚወሰዱ አበረታች ንጥረ ነገሮችን ከመውሰድ እንዲቆጠቡም ያሳስባሉ። በጥቅሉ በጊዜያዊነት ንክኪ ካለባቸው ሥራዎች በቀር ሌሎች ሥራዎች እንደቀጠሉ ሲሆን፤ የአድራሻ ምዝገባቸውን በመደበኛ መልኩ የሚያደርጉ በመሆኑ በዚህ ላይም መዘናጋት አይገባም።\nዓለም አቀፉ የጸረ አበረታች መድኃኒቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በመግለጫው ባመላከተው መሠረት፤ ጽሕፈት ቤቱም እንደቀደመው የአትሌቶችን ናሙና ወደመውሰድና መመርመር ሥራው ለመመለስ የሚያስችለውን ሁኔታ እያጠና ይገኛል። እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ከሆነም ስፖርተኞች ከባለሙያዎች ጋር የሚኖራቸውን ንክኪ በሚቀንስና ለበሽታው አጋላጭ በማይሆን መልኩ መፍትሄ እንደተገኘ በቀጥታ ምርመራው የሚጀመር ይሆናል። በብሔራዊ ቡድን፣ በክለብ እና በማሰልጠኛ ተቋማት የተያዙ አትሌቶች እንዲሁም በቡድን ሆነው የሚሰሩ ሰልጣኞች በዚህ ወቅት ልምምድ አቋርጠው በቤታቸው ይገኛሉ። ምንም ዓይነት የቡድን እንቅስቃሴ የማይፈቀድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አትሌቶች በያሉበት አነስተኛ ልምምድ ብቻ የሚያደርጉ ይሁን እንጂ አሁንም እንደ ተቋም አስጊ ሁኔታዎች መኖራቸው አልቀረም። \nይህም ወቅታዊውን ሁኔታ ሽፋን በማድረግ የተከለከሉ ንጥረነገሮችን የመጠቀም አዝማሚያ ሊኖር ይችላል የሚል ስጋት ነው። እስካሁን በተጨባጭ የተገኘ መረጃ ባይኖርም በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ እንደ ተቋም ስጋቱ አለ። ከአትሌቶች ባሻገር ከጀርባ በመሆን አጋላጭ የሆኑ አካላት አበረታች ቅመሞችን እንዲጠቀሙ በመገፋፋትና በማሳመን የሕግ ጥሰት የመፈጸም አዝማሚያ ሊኖር ይችላል የሚል ግምት አለ። በመሆኑም ስጋቱን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ሥራዎች በመከናወን ላይ ነው የሚገኙት። \nበስፖርተኞች በኩል ስለ ጉዳዩ ያለውን ግንዛቤ ለማስፋትም በመገናኛ ብዙኃን በመታገዝ መልዕክቶች በመተላለፍ ላይ ይገኛሉ። በተመረጡ መገናኛ ብዙኃን ላይም የማስታወቂያ እንዲሁም የማንቂያ ሥራዎች እየተካሄዱ መሆኑን የሚጠቁሙት ዳይሬክተሩ በጽሕፈት ቤቱ ድረገጽም መረጃዎችን እያስተላለፉ ይገኛል። ይህም አትሌቱ በሚመቸው መንገድ መረጃ እንዲያገኝ ያስችለዋል። በቀጣይም በመደበኛነት ማስታወቂያዎቹ የሚተላለፉባቸውን የመገናኛ ብዙኃን ቁጥር ለመጨመር ታቅዷል። ሌላው ጽሕፈት ቤቱ በትኩረት እየሄደበት ያለው የሕግ ማዕቀፍ የማሻሻል ሥራ ነው። ኤጀንሲው የጸረ አበረታች ቅመሞች ሕግን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ ስታንዳርዶችን አሻሽሏል፤ በመሆኑም በጽሕፈት ቤቱ በኩል እአአ በ2021 ተግባራዊ የሚሆኑ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎችን ለመከለስ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። \nበመጨረሻም ዳይሬክተሩ ስፖርተኞችም ሆኑ ሌሎች የሀገሪቷ ዜጎች የሕክምና ባለሙያዎችን ምክር በመተግበር በዓለም ላይ ከተከሰተው ወረርሽኝ ራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ስፖርተኞች፣ የስፖርት ባለሙያዎች፣ የስፖርት አመራሮች እንዲሁም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በበኩላቸው በአበረታች ንጥረ ነገር መከላከልና መቆጣጠር ሥራው ለአፍታ የቆመ ባለመሆኑ መዘናጋት እንዳይኖር ዳይሬክተሩ ያሳስባሉ። ዓለም አቀፉ ኤጀንሲም ሆነ የዓለም አትሌቲክስ ይህ ጊዜ ሲያልፍ ስፖርቱ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በጥንቃቄ እየተመለከቱት ነው። በዚህ መሠረት የሚመለከታቸው አካላት ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። ተጠቃሚነታቸው ከተረጋገጠም ጽሕፈት ቤቱ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እንዲሁም የወንጀል እርምጃ ከመውሰድ ወደኋላ የማይል በመሆኑ ስፖርተኛው በመደበኛ ጥንቃቄው መቀጠል እንዳለበት ዳይሬክተሩ አስቀምጠዋል።አዲስ ዘመን ግንቦት 10/2012ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "01f73fe2dd71eb57e86861f0d6e6addf" }, { "passage": "አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ታሳቢ ያደረገ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡በወረርሽኙ ምክንያት ከገባበት ችግር እንዲወጣና እንዲነቃቃ ስፖርታዊ ኩነቶችን ማስተናገድ አስተዋፅኦ እንዳለው ታምኖ እየተሠራበት መሆኑን ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር ተናግረዋል፡፡\nዝግጅቶቹን ስኬታማ ለማድረግ በከፍተኛ ጥንቃቄ ዝግጅቱን የሚመራ ዐብይ እና ንዑስ ኮሚቴዎች እንደተቋቋሙም አስታውቀዋል፡፡ ስፖርታዊ ኩነቶቹን ከማስተናገድ ጎን ለጎን የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ የANOCA ጉባኤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሰጠውን ሽልማት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሃገርን መልካም ገፅታ ለተቀረው ዓለም ለማሳየት የሚረዳ በመሆኑ ትልቅ ትርጉም እንደሚሰጠውም አቶ ኤሊያስ መናገራቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡", "passage_id": "16bbf66be56fe275eb7b12d339ca2d7e" }, { "passage": " የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ከትናንት በስቲያ ምሽት አገራቸውንና ህዝባቸውን በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላኮሩ ውጤታማ አትሌቶች እና ባለሙያዎችን ሸልሟል። በካፒታል ሆቴል በተደረገው የሽልማት ስነስርዓት በ2011ዓ.ም መጨረሻና በ2012 ዓ.ም መጀመሪያ ወራት በተካሄዱ በአህጉርና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ተሳትፈው ውጤት ያስመዘገቡ አትሌቶችና ባለሙያዎች ከ20 ሺ እስከ 80 ሺ ብር ሸልሟል። ለዚህም አምስት ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጉ ታውቋል። በሞሮኮ ተካሂዶ በነበረው የመላ አፍሪካ ጨዋታ የወርቅ ሜዳሊያ ላስመዘገቡ\nአትሌቶች 40 ሺ ፣የብር ሜዳሊያ ላመጡ 30 ሺ እንዲሁም የነሐስ ሜዳሊያ ስመዘገቡ 20 ሺ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በዶሀ\nየዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ወርቅ ላመጡ አትሌቶች እና አሰልጣኞች 80 ሺ ፣የብር ሜዳሊያ ላስመዘገቡ 50 ሺና የነሐስ ሜዳያ ላመጡ\n30 ሺ ብር ሽልማት ተበርክቷል። ከመላ አፍሪካ ጨዋታዎች እና ከዓለም ቻምፒዮና ውድድሮች በተጨማሪ በአፍሪካ መስማት የተሳናቸው\nየአትሌትክስ ቻምፒዮና፣ በ6ኛው የአፍሪካ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ቻምፒዮና እና በምሥራቅ አፍሪካ ጤረጴዛ ቴኒስ ቻምፒዮና ተሳትፈው\nውጤት ያስመዘገቡ ስፖርተኞች እና አብረው የተጓዙ የልዑካን ቡድኖች ተሸላሚ ሆነዋል።በዓለምና በአህጉር አቀፍ የስፖርት መድረኮች አገራቸውንና ህዝባቸውን\nላኮሩ አትሌቶችና ባለሙያዎች በመንግሥት ደረጃ እውቅናና ሽልማት መሰጠት ከነበረበት ጊዜ መዘግየቱ ቅሬታ ፈጥሮ የሰነበተ ሲሆን፤\nስፖርተኞችን በዚህ ደረጃ ማበረታታትና መሸለም ለሌላ ትላልቅ የውድድር መድረኮች መነሳሳት እንዲችሉ ያግዛልም ተብሏል።የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ፤መንግሥት በዓለም ቻምፒዮናና በመላ አፍሪካ\nመድረኮች ውጤት በማስመዝገብ አገራቸውንና ህዝባቸውን ላኮሩ አትሌቶች እና ባለሙያዎችን ከምስጋና ጋር ሽልማት ማበርከቱ የሚያስመሰግነው\nመሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያን በመወከል ውጤት የሚያመጡ አትሌቶችን ማበረታትና መሸለሙ በቀጣይ ተጠናክሮ እያደገ የሚሄድ መሆኑን\nየጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ «በቶኪዮ ኦሊፒክም ሜዳሊያ ለሚያመጡ አትሌቶች በጋራ ትላልቅ ሕንፃ የሚገነቡበት ቦታ እንጂ ትንሽ ነገር አይበረከትላቸውም\n» ሲሉ ተናግረዋል። በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፍ አትሌቶች ከወዲሁ ለድል እንዲነሳሱ የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች\nእየተደረጉ መሆኑንም ጠቁመዋል። ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድን ለኦሊምፒክ አንድ ቢሊየን ብር ተጠይቀው ‹‹ለስፖርት\nየምን አንድ ቢሊየን ብር እስከ ሦስት ቢሊየን እንሰበስባለን፣ በቅርቡ የ1ቢሊዮን ብር እራት 1ሺ ሰው እጋብዛለሁ ብለው ቃል መግባታቸውን››\nዶክተር አሸብር ተናግረዋል።የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሸን ኮሚሽነር ኤልያስ ሽኩር በበኩላቸው፤\nየጀግናው አበበ ቢቂላን ድል በቀጣዮቹ ትውልዶች የድል ችቦ ቅብብሎሽ ተከብሮ እና ይበልጥ ጎምርተቶ ለመቀጠሉ ምስጢሩ አትሌቶችን\nለማምጣት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ክለቦች ፣ፌዴሬሽኖችና መንግሥት በቅንጅት ታዳጊዎችን ማዕከል ያደረገ ሥራ መሥራት እንደሚጠይቅ\nአብራርተዋል።አዲስ ዘመን ቅዳሜ የካቲት 7/2012 ዳንኤል ዘነበ", "passage_id": "a516e2583e59b4b14306533de95c4619" }, { "passage": "የዓለም አትሌቲክስ ከዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ምክንያት ከውድድር በመራቃቸው የገንዘብ ችግር ሊገጥማቸው ይችላል ለተባሉ አትሌቶች ድጋፍ እንደሚያደርግ ባለፈው ሚያዝያ መጨረሻ ማሳወቁ ይታወሳል። የዓለም አትሌቲክስ ለዚሁ ድጋፍ እንዲውል አምስት መቶ ሺህ ዶላር ማዘጋጀቱ የሚታወቅ ሲሆን ይህን ድጋፍ ለአትሌቶች ለማድረስ የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንቱ ሴባስቲያን ኮ በሊቀመንበርነት የሚመሩት የባለሙያዎች ቡድን ተቋቋሞ በስድስት ዞኖች በተከፋፈለው የዓለም አትሌቲክስ አባል አገራት የሚገኙ አትሌቶች የሚያቀርቡት የድጋፍ ጥያቄ ተጣርቶ ዕርዳታው መሰጠት ጀምሯል። በዚህም መሠረት መቶ ዘጠና ሦስት አትሌቶች ተለይተው ድጋፉ እንደደረሳቸው ታውቋል። ዕርዳታው የሚሰጣቸው አትሌቶች ከሃምሳ ስምንት የዓለም አትሌቲክስ አባል አገራት ፌዴሬሽኖች የተለዩ ሲሆን እያንዳንዳቸው በመጀመሪያው ዙር ድጋፍ ሦስት ሺህ ዶላር እንደሚደርሳቸው ተጠቆሟል። የድጋፍ ጥያቄውን ለማቅረብ የተሰጠው ቀነ ገደብ ባለፈው የፈረንጆች ግንቦት ሰላሳ ቀን የተጠናቀቀ ሲሆን ሁለት መቶ ስልሳ አንድ አትሌቶች የድጋፍ ጥያቄውን አቅርበው ጉዳዩን የሚመረምረው የባለሙያዎች ቡድን በተቀመጠው መስፈርት መሠረት አጣርቶ መቶ ዘጠና ሦስት አትሌቶች ድጋፉን እንዲያገኙ ውሳኔ አሳልፏል። የባለሙያዎቹ ቡድን ድጋፉን ለመስጠት በዋናነት ከተመለከታቸው መስፈርቶች መካከል አንድ ድጋፍ የሚሻ አትሌት በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ አገሩን ለመወከል የተመረጠ መሆን እንዳለበት፣ ለገጠመው የገንዘብ ችግር አሳማኝ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ ካለፈው የውድድር ዓመት አኳያ የሚያገኘው ገቢ በእጅጉ የቀነሰና ከአበረታች መድሃኒት ተጠቃሚነት ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ክስ ያልቀረበበት መሆን እንደሚገባው ጠቁመዋል። በተጨማሪም በየትኛውም የውድድር\nአይነት በዓለም አትሌቲክስ\nየደረጃ ሰንጠረዥ ከአንድ\nእስከ ስድስት ባለው\nውስጥ ስማቸው የሰፈረ\nአትሌቶች፣ በ2019 በየትኛውም\nየወርቅ ደረጃ ባለው\nየጎዳና ላይ ውድድር\nእስከ ስድስት ባለው\nደረጃ ያጠናቀቁ እንዲሁም\nበ2019 የዳይመንድ\nሊግ ውድድሮች እስከ\nስልሳ ሺህ ዶላር\nድረስ ሽልማት ያገኙ\nአትሌቶች የድጋፍ ጥያቄያቸው\nተቀባይነት እንደሌለው ታውቋል።\nድጋፉን የሚያገኙ አትሌቶች\nወይም አገራት ስም ያልተጠቀሰ ሲሆን ጥያቄያቸው ተመርምሮ ድጋፍ የሚደረግላቸው አትሌቶች በዚህ ሳምንት መጨረሻ ገንዘቡ እንደሚደርሳቸው ተጠቁሟል። የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት እንዲሁም የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፋውንዴሽን ሊቀመንበር ሴባስቲያን ኮ ይህን ድጋፍ ለአትሌቶች ለመስጠት እንደታሰበ በሰጡት መግለጫ ወቅት እንዳስቀመጡት፣ የገንዘብ ድጋፉ ባለፉት ጥቂት ወራት ከውድድር በመራቃቸው ምንም አይነት ገቢ አጥተው የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ለገቡ አትሌቶች ይውላል። እ.ኤ.አ በ1986 በሞናኮው ልዑል አልበርት ሁለተኛ አማካኝነት በአትሌቲክስ ስፖርት ለሚገጥሙ ችግሮች የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ለማከናወን የተቋቋመው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፋውንዴሽን ካለው በጀት ላይ ቀንሶ አትሌቶች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለገጠማቸው ችግር ድጋፍ እንዲውል ማድረጉ ይታወቃል። ድጋፉን ለመስጠት ከተቋቋመው ኮሚቴ መካከል የቀድሞው የኦሊምፒክ የ1500 ሜትር አሸናፊው ሞሮኳዊ አትሌት ሂቻም ኤልግሩዥ፣ የምርኩዝ ዝላይ የዓለም ቻምፒዮኗ ካተሪና ስቲፋኒዲ (የዓለም አትሌቲክስ ኮሚሽንን ወክላ)፣ የዓለም አትሌቲክስ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሱኒል ሳብሃርዋልና ኤቢይ ሆፍማንና ሌሎችም ተካተዋል። ‹‹ሂቻም ኤልግሩዥ ይህን የድጋፍ ሃሳብ በማቅረቡና ልዑል አልበርት ይህን ፕሮጀክት እውን ለማድረግ ላበረከተው ጠንካራ ድጋፍ ላመሰግናቸው እወዳለሁ›› በማለት ሃሳባቸውን ያሰፈሩት ሴባስቲያን ኮ፣ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከዓለም አትሌቶች ጋር በተለያየ መንገድ የቅርብ ግንኙነት እንዳላቸው በመጠቆም ዓለም አቀፍ ውድድሮች በመሰረዛቸው በርካታ አትሌቶች የገቢ ምንጫቸው እንደ ደረቀና የገንዘብ ችግር እንደገጠማቸው አብራርተዋል። በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የዓለም አትሌቲክስ ውድድሮች በእጅጉ መጎዳታቸውን ያስታወሱት ኮ፣ አትሌቶች ገቢያቸው ከውድድር የሚያገኙት ሽልማት እንደመሆኑ በዓመቱ መጨረሻ የተወሰኑ ውድድሮችን በማካሄድ ስፖርቱንና አትሌቶቹን እንዳይዳከሙ የማድረግ ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል። አትሌቶችን ለመደገፍ አሁን ከተያዘው በጀት ባሻገር የስፖርት ቤተሰቡ በሚያደርገው ድጋፍ ተጨማሪ የረድኤት ሥራዎች እንደሚከናወኑም ጠቁመዋል። ልዑል አልበርት ሁለተኛ\nበበኩላቸው ፋውንዴሽኑን ከመሠረቱ\nከሰላሳ አምስት ዓመታት\nበላይ እንደሆነ በማስታወስ\nየፋውንዴሽኑ አላማ አትሌቲክስን\nማበረታታትና ብሔራዊ አትሌቲክስ\nፌዴሬሽኖች እንዲሁም አትሌቶች\nበችግር ጊዜ የገንዘብ\nዋስትና እንዲኖራቸው ማድረግ\nመሆኑን ጠቁመዋል። በዚህም\nመሠረት ፋውንዴሽኑ ባለፉት\nዓመታት ሰላሳ ሚሊየን\nዶላር ለተመሳሳይ አላማ\nእንዳዋለና አሁንም አትሌቶች\nበሚቸገሩበት በዚህ ወቅት\nሊደርስላቸው በመቻሉ የተሰማቸውን\nደስታ ገልፀዋል። ይህ\nድጋፍ አትሌቶች ኦሊምፒክን\nጨምሮ ለዓለም አቀፍ\nውድድሮች የሚያደርጉትን ዝግጅት\nእንዳያቋርጡና በገጠማቸው ችግር\nውጥረት ውስጥ እንዳይገቡ\nሊረዳቸው እንደሚችልም አክለዋል። የቀድሞው የ1500 ሜትር የዓለም ክብረወሰን ባለቤትና የድጋፉ ሃሳብ አመንጪ አትሌት ኤልግሩዤ በበኩሉ፣ የኮሮና ቫይረስ በሁሉም ዓለም ሕዝብ ላይ ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ እንዳሳደረ በማስታወስ ሁሉም የዓለም ሕዝብ ይህን ችግር ለመጋፈጥ በጋራ የሚቆምበት ወቅት አሁን መሆኑን አብራርቷል። የዓለም አትሌቲክና ፕሬዚዳንቱ የድጋፍ ሃሳቡን በቅንነት ስለተቀበሉትም ምስጋናውን አቅርቧል። ዓለም አቀፍ ውድድሮች በመታገዳቸውም በርካታ አትሌቶች ሊደርስባቸው የሚችለውን የኢኮኖሚ ጫና በማሰብ ይህን በጎ ተግባር መፈፀም እንደሚያኮራም ተናግሯል፡፡አዲስ ዘመን ሰኔ 18/2012 ቦጋለ አበበ", "passage_id": "75d675f81bcb7e190c21aebd0b8a2bb8" } ]
d0749959d4d5edf763bf108a42a73620
b64df88ee77d7e21f8a290922665ac3a
ካፍ ለአፍሪካ እግር ኳስ አባል አገሮች የሰጠው ቀነ ገደብ ዛሬ ይጠናቀቃል
አፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ካፍ አባል ሀገራት የተቀመጠላቸው ቀነ ቀደብ ዛሬ ይጠናቀቃል። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠው የየአገሮቹ የውስጥ ሊግ ለማስቀጠልም ሆነ ለማቋረጥ መደረግ ስለሚገባው የጋራ አቋም አገሮች ከየራሳቸው የሊግ አደረጃጀትና ሁኔታ በመነሳት የሚኖራቸውን ሐሳብ በሚያዝያ 19 ቀን 2012 ዓ.ም መጠየቁ ይታወሳል። ለአፍሪካ እግር ኳስ አባል አገሮች በጻፈው ደብዳቤ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የየአገሮቹ የውስጥ ሊግ ካለው ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት መቀጠልም ሆነ መቋረጥ ካለበት አገሮቹ የየራሳቸውን ሐሳብና ዕቅዳችሁን አሳውቁኝ ነበር ያለው፡፡በዕቅዱ መካተት ይኖርባቸዋል ብሎ የጠቀሳቸው ነጥቦች፣ ሊጉ የተጀመረበትና የሚጠናቀቅበት ጊዜ እንዲሁም ሊጉ የሚቀረው የጨዋታ መርሐ ግብርና የቡድኖች የደረጃ ሰንጠረዥ፣ ሊጉ የተቋረጠበት ወር፣ የሚቀረው የጨዋታ ብዛት፣ ቀሪውን ውድድር እናጠናቅቃለን ለሚሉ ሊከተሉት ስላሰቡት የጨዋታ ሥርዓትና ሁኔታ፣ ማስቀጠል አንችልም የሚሉ ካሉም እንዲሁ በዝርዝር ተብራርቶላቸዋል፡፡ ጥቅሙን በሚመለከት ተቋሙ ወደፊት ውድድሮችን ከመምራት ጀምሮ የሚያከናውናቸው ዕቅዶች ከአባል አገሮች ዕቅዶች ጋር እንዳይጋጩ የመፍትሔ አቅጣጫ ማስቀመጥ ይችል ዘንድ መረጃ ለማሰባሰብ እንደሆነ አስገንዝቧል፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ደብዳቤውን ከመላክ ባሻገር አባል ሀገራቱ ውሳኔያቸውን እስከ ሚያዚያ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ እንዲያሳውቁት ነበር ያሳሰበው። ካፍ ሀገራቱ በውስጥ ውድድራቸውን በተመለከተ ውሳኔ የሚያስተላልፍበት ቀን በዛሬው እለት የሚጠናቀቅ ይሆናል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 27/2012
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=31720
[ { "passage": "ዓለምአቀፉ የእግርኳስ አስተዳዳሪ አካል ፊፋ በመጪው ግንቦት በአዲስ አበባ ሊያካሂደው የነበረውን ስብሰባ ማራዘሙን አስታወቀ።የዓለማችን የወቅቱ ስጋት የሆነው የኮርና ቫይረስ (COVID-19) ስርጭት እየተስፋፋ መምጣት እግርኳሱ ላይም በተለያየ መንገድ ተፅዕኖ እየፈጠረ የሚገኝ ሲሆን የተለያዩ የሊግ ውድድሮች እና የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች እየተቋረጡ ይገኛሉ። በዚህ ቫይረስ ስርጭት ስጋት የባው ፊፋም በአዲስ አበባ ግንቦት 28 ቀን 2012 ሊያካሂደው የነበረውን ስብሰባ ወደ መስከረም 8 ቀን 2013 መራዘሙን ይፋ አድርጓል።ፊፋ ጨምሮም የዛሬ ሳምንት ሊያካሂደው የነበረውን መደበኛ ስብሰባም ወደ ሌላ ጊዜ ማዛወሩን አስታውቋል።© ሶከር ኢትዮጵያ", "passage_id": "d93d2199b85656ab22f011a9cad66ed2" }, { "passage": "የ2021 አፍሪካ ዋንጫ ጥር ላይ እንዲካሄድ ተወሰነ\\nየአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ይዘጋጅ የነበረው በወርሃ ሰኔ እና ሐምሌ ላይ የነበረ ሲሆን፤ ግን እነዚህ ወራት በካሜሩን ዝናባማ ስለሚሆኑ ወደ ጥር እንዲዘዋወር ተደርጓል ተብሏል። \n\nይህ ማለት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሚጫወቱ እና ለአፍሪካ ዋንጫ የሚያልፉ ሃገራት ተጫዋቾች እስከ ስድስት የክለብ ጨዋታ ያመልጣቸዋል።\n\nትናንት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን-ካፍ እና የካሜሮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያካሄዱትን ስብሰባ ተከትሎ የካፍ ፕሬዝደንት በትዊተር ገጻቸው ላይ \"የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ከጥር 1 እስከ ጥር 29 ድረስ ይካሄዳል። የጊዜ ለውጡ በአየር ጠባይ ምክንያት በካሜሮን ጥያቄ መሠረት ተቀይሯል\" ሲሉ አስፍረዋል። \n\nየካፍ ምክትል ፕሬዚደንት ቶንይ ባፉኤ በበኩላቸው፤ በቀን ለውጡ ላይ ከካሜሮን ሜትዮሮሎጂ ባለሥልጣናት፣ አሰልጣኞች እና ተጫዋቾች ጋር እንዲሁም የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር በጥልቅ መወያየታቸውን አስረድተዋል። \n\nካሜሮን የ2019 ዋንጫን እንድታዘጋጅ ተመርጣ እንደነበረ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ከስታዲየም ግንባታ እና ከአጠቃላይ ዝግጅት ጋር ተያይዞ የነበራት ዝግጁነት ዘገምተኛ ነው ከተባለ በኋላ ነበር ግብጽ እንድታዘጋጅ እድሉ የተሰጣት።\n\n• «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ \n\n", "passage_id": "772332dfb13f9aa56809b03a3a45a5e8" }, { "passage": " የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር ፔድሮ ሳንቼስ ባሳለፍነው ሰኞ ለጋዜጠኞች አፍሪካ እና አውሮፓን ለአንድ አላማ በጋራ ያስተሳስራል ያሉትን እቅድ ይፋ አድርገዋል። በዚህም ከሁለቱ አህጉራት ሶስት አገራት ይሳተፉበታል ያሉትን የዓለም ዋንጫ ዝግጅት ጥያቄ ለዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር «ፊፋ» ለማቅረብ ማቀዳቸውን ተናግረዋል። ማህበሩ ማመልከቻቸውን ይቀበለዋል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ነው የገለጹት።ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2030 የሚዘጋጀውን የዓለም ዋንጫ ሁለቱ አህጉራት በጋራ እንዲያዘጋጁ አቅደዋል። የዓለም ዋንጫ ውድድሩንም ሞሮኮ፣ ስፔን እና ፖርቹጋል ማሰናዳት እንዲችሉ ለፊፋ ማመልከቻ ለማስገባት ነው ያሰቡት።\n«ሃሳቡን ከሞሮኮው ንጉስ ሞሃመድ ስድስተኛ ጋር ተወያይተንበታል። ይህ ከመሆኑ በፊት ግን እቅዱን ለሞሮኮ መንግስት አሳውቄያለሁ» ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እቅዱ እውን የሚሆን ከሆነ ሁለቱ አህጉራት በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያዘጋጁት ውድድር ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር መሰናዶውን ተከትሎ ከሞሮኮ መንግስት እና ንጉሳውያን ቤተሰቦች ጋር ከመወያየታቸው በፊት የሞሮኮ ፌዴሬሽን የዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት ፊፋ ይፋ በሚያደርገው የዝግጅት ጥያቄ ማመልከቻ ላይ እንዲሳተፍ ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር።መቀመጫውን ፈረንሳይ ውስጥ ያደረገው ዓለም አቀፉ መገናኛ ብዙሃን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ሁኔታውን ለማጣራት የሞሮኮ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳድ ኢዲን ኢል ኦትማኒ ጋር ግንኙነት አድርጎ ለማጣራት ሙከራ ቢያደርግም ሁለቱ አህጉሮች ለማዘጋጀት እቅድ መያዝ አለመያዛቸውን ከማረጋገጥ ተቆጥበዋል። ሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ የዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት አምስት ጊዜ ለፊፋ ማመልከቻ ብታቀርብም ውድቅ ሆኖባታል።በ2022 የሚዘጋጀውን የዓለም ዋንጫ ኳታር የምታሰናዳው ሲሆን፤ በ2026 የሚዘጋጀውን ደግሞ አሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ በጋራ የሚያዘጋጁት ይሆናል። በ2030 ፊፋ ለሚያዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ተመራጭ ለመሆን ከወዲሁ በርካታ አገራት ይፎካከራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በተለይ የደቡብ አሜሪካ እና ብቻቸውን ማዘጋጀት የሚፈልጉ የአውሮፓ አገራት በጨረታው ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።ኡራጓይ፣ አርጀንቲና እንዲሁም ፓራጓይ ከደቡብ አሜሪካ ማመልከቻውን የሚያስገቡ ሲሆን፤ ግሪክ፣ ቡልጋሪያ፣ ሰርቢያ እንዲሁም ሮማኒያ በጋራ ዝግጅቱን ለማሰናዳት ጥያቄ ያቀርባሉ ተብሎ ይታሰባል። አየርላንድ እና እንግሊዝም ፉክክሩ ውስጥ አሉበት። የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር በ2020 ጨረታውን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።በ2030 ገና በርካታ ዓመት የሚቀሩት ቢሆንም ፉክክሩ ግን ከወዲሁ ጀምሯል። አሁን እንደታቀደው አገራት በጋራ የሚያዘጋጁ ከሆነ ከሁለት በላይ አገራት የሚያዘጋጁት የዓለም ዋንጫ የመሆን እድሉ የሰፋ ነው።ዳግም ከበደ", "passage_id": "95725cbc626783703f30d2debc08d88f" }, { "passage": "የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን በአዲስ አበባ ለማድረግ ቀጠሮ ቢይዝም ሃሳቡን መቀየሩ ታውቋል።በአሁኑ ሰዓት በፊፋ የአምስት ዓመት ዕግድ ተጥሎባቸው የነበረው የካፍ ፕሬዝዳንት አህመድ አህመድ ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ትራንዚት ሲያደርጉ ኢትዮጵያ የካፍን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ እንድታስተናግድ መመረጧን ለፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ገልፀው እንደነበር ይታወሳል። ይህንን ተከትሎ ከታኅሣሥ 1-10 ድረስ በአዲስ አበባ ይደረጋል ተብሎ ይታሰበውን ይህን ጠቅላላ ጉባኤ ለማስተናገድ ፌዴሬሽኑ የተለያዩ ሥራዎችን እየከወነ ቢገኝም ጉባኤው አዲስ አበባ ላይ እንደማይደረግ ተገልጿል።የካፍ ኢመርጀንሲ ኮሚቴ እንደገለፀው ከሆነ ተቋሙ ይህንን ውሳኔ የወሰነው በሜዲካል ኮሚቴው በቀረበለት ምክረ ሃሳብ እንደሆነ አስረድቷል። በተለይም በአህጉሪቱ ያለውን የኮቪድ-19 ስርጭት ታሳቢ በማድረግ ጉባዔውን በአካል በመገናኘት ማከናወን አስጊ እንደሆነ በማሰብ ውሳኔው መወሰኑ ተብራርቷል። ከኮቪድ በተጨማሪ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታም እንደ ተጨማሪ ምክንያትነት እንደተያዘ ተጠቁሟል። ይህንን ተከትሎ ፊፋ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን እንዳከናወነው ካፍም ጉባኤውን በቪዲዮ ኮንፍረንስ ለማከናወን ወስኗል።© ሶከር ኢትዮጵያ", "passage_id": "d3368bf15b4e6abb70ff5af0027b2a89" }, { "passage": "በሲምፖዚየሙ ስለ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር፣ አፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት የሚጠይቁ ሀገራት ማሟላት ስላለባቸው ጉዳዮች፣ ስለ ክለብ ውድድሮች፣ ስለ ወጣቶች እግር ኳስ፣ ስለ አጠቃላይ የአህጉሪቱዋ እግር ኳስ እድገት፣ ስለ መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ስለ ቴሌቪዥን መብት እና ተያያዥ ጉዳዮች ምክክር ሲደረግ የአብዛኛውን የተሳታፊ ትኩረት የገዛው ግን አፍሪካ ዋንጫ የሚካሄድበት ወቅትን መቀየር እና የተሳታፊ ሀገራትን ከ16 ወደ 24 ይደረግ ተብሎ የተነሳው ሀሳብ ነበር፡፡ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያውያን የጊዜ አቆጣጠር ጥር ላይ ሲደረግ የነበረውን የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ወደ ሰኔ የመውሰድ አላማ እንዳለቸው በሲምፖዚየሙ የመክፈቻ ቀን የተናገሩት የካፍ ፕሬዝደንት አህመድ አህመድ እንደ ምክንያት ያቀረቡት በአውሮፓ እና በሌሎች አህጉራት የሚጫወቱ አፍሪካውያን ተጨዋቾች ከሚጫወቱበት የክለብ ውድድር አቋርጠው እንዳይመጡ፣ ሁለቱም ወገኖች በዚህ ውድድር ምክንያት እንዳይጎዱ በማሰብ እና ውድድሩ የሚገኘውን የቴሌቭዥን መብት ሽያጭ ገቢ እና ስፓንሰሮችን ከመሳብ አንፃር ከግምት ውስጥ ከማስገባት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከአህመድ በፊት የአፍሪካን እግር ኳስ ለ29 አመታት የመሩት ኢሳ አያቱ ውድድሩ ወደ ሰኔ እንዳይሄድ እንደ ዋነኛ ምክንያትነት ለእግርኳስ ጨዋታ ያልተመቸው የአየር ሁኔታውን አንስተው ሲከራከሩ መቆየታቸው የሚታወስ ቢሆንም አህመድ ግን ለውጥ መምጣት እንዳለበት አምነዋል፡፡የአፍሪካ ዋንጫ ውድድርን ላይ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ እና የኮንፌደሬሽን ዋንጫ የውደድር ጊዜያትም ላይ ለውጥ የማድረግ አላማ ያላቸው የ57 አመቱ አህመድ ከዚህ ቀደም በነበረው አደረጃጀት ወደፊት መጓዝ እንደማይችሉ እና ለውጦች መደረግ እንደሚጀምሩ ተናግረዋል፡፡ከአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ ሃገራት ቁጥር መጨመር ጋር በተያያዘ ከ24 ሃገራት 20 ወይም 21 የአፍሪካ ሃገራት ሲሆኑ 3 ወይም 4 የሚሆኑ ከአፍሪካ አህጉር ውጪ የሚገኙ ተጋባዥ ሃገራት እንዲሆኑ በሲምፓዚየሙ ተነስቷል። የአፍሪካ ዋንጫን ከአህጉሪቱ ውጪ ባሉ ሃገራት ማስተናገድ የሚሉ ሃሳቦችም ሲንሸራሸሩ ነበር።በአፍሪካ ዋንጫ ላይ የተሳታፊ ሀገራትን ቁጥር ከ16 ወደ 24 ካደገ አቅማቸው በእግር ኳሱ ብዙም ያልፈረጠሙ ሀገሮችን በውድድሩ ላይ እንዲሳተፉ ተጨማሪ እድሎችን ከመክፈቱ በላይ ብዙ ጨዋታዎች ባሉ ቁጥር የሚመጡ የቴሌቪዥን እና የስታዲየም ገቢ እንዲሁም ተያያዥ ገቢዎችን ለማግኘት እንደሚጠቅማቸው በማንሳት ነበር፡፡ የካፍ ስራ አስፈፃሚ እና ጠቅላላ ጉባኤ የተነሱ የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ አርብ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡", "passage_id": "fcafecfa5e281e3a92ea4fdf22511be3" } ]
f5776257b0f643ba235b83f1fb8902af
3a6997daa61fb58690997bfb9f80ec3a
የተራዘመው ኦሊምፒክና የዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኖች የገንዘብ ጥያቄ
የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ለአስራ ስድስት ወራት ከመራዘሙ አስቀድሞ የተፈራው ሊደርስ የሚችለው የፋይናንስ ቀውስና ትልቅ የገንዘብ ኪሳራ መሆኑ ይታወቃል።ኦሊምፒኩ እንደተራዘመ ይፋ ከተደረገም በኋላ የአዘጋጇ አገር ጃፓን መንግስትና የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በሚደርሰው ኪሳራና ተጨማሪ ወጪ ዙሪያ ውዝግብ ውስጥ መግባታቸው አልቀረም።ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ገና ከጅምሩ ኪሳራውን ለማካካስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንደሚጋሩት ተስፋ አድርጎ የነበረ ቢሆንም አሁን አጣብቂኝ ውስጥ እየገባ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየወጡ ይገኛል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ትልቅ ባለድርሻ አካል የሆነው የዓለም አትሌቲክስ ከተራዘመው ኦሊምፒክ ገቢ ጋር በተያያዘ ድርድር መጀመሩን አሳውቋል።የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንቱ ሴባስቲያን ኮ በዚህ ጉዳይ ላይ ከዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር ንግግር መጀመራቸውን ከትናንት በስቲያ ይፋ አድርገዋል። የኢንሳይድ ዘ ጌምስ ሃተታ እንደሚያመለክተውም በርካታ ዓለም አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖች ከተራዘመው ኦሊምፒክ ሊያገኙት የነበረውን ገንዘብ መጠየቅ እንደሚጀምሩ ተረጋግጧል።የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውድድሩ በመራዘሙ ምክንያት ብቻ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ውስጥ ገብቶ በሚዳክርበት በዚህ ወቅት ባለድርሻው የሆኑት ታላላቅ ዓለም አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖች ድርሻቸውን ለመጠየቅ ወደ ኋላ አለማለታቸው አስደንጋጭ ዜና ሆኗል። አሁን ድርሻውን የጠየቀው የዓለም አትሌቲክስ ትልቁ ባለድርሻ ሲሆን የዓለም ውሃ ዋና እና የዓለም ጅምናስቲክ ፌዴሬሽኖች በተከታይነት ትልቅ ድርሻ አላቸው።እነዚህ ፌዴሬሽኖች ብቻ ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ቢያንስ እያንዳንዳቸው አርባ ሚሊዮን ዶላር ድርሻ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው እንደማይቀር ታውቋል።ይህም ኦሊምፒክ በመራዘሙ ብቻ በርካታ ውስብስብ ፈተናዎች ውስጥ ለገባው የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖበታል። ‹‹እንደ አብዛኞቹ የኦሊምፒክ ስፖርቶች የዓለም አትሌቲክስም ከኦሊምፒክ የቴሌቪዥን ስርጭት በሚያገኘው ገቢ ላይ ጥገኛ ነው›› ያሉት ሴባስቲያን ኮ ባለፉት አራት ዓመታት ይህን ገቢ ለማግኘት ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመው ይህን ገንዘብ ማግኘት የግድ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ የዓለም አቀፉ ብስክሌት ፌዴሬሽን ከኦሊምፒኩ የሚያገኘው ገቢ ለጊዜው ቢራዘምም እስከ 2020 አጋማሽ ገቢ ሊደረግ እንደሚገባ ከወር በፊት ማሳወቁ ይታወሳል።የዓለም አቀፉ እጅ ኳስ ፌዴሬሽንም ተመሳሳይ ሃሳብ ያንፀባረቀ ሲሆን ሌሎችም በቀላሉ ሃሳብ እንደማይቀይሩ ይጠበቃል።በተለይም የዓለም አትሌቲክስ ኦሊምፒኩ በመራዘሙ በ2021 በአሜሪካ ዩጂን የሚያካሂደው የዓለም ቻምፒዮና ላይ ተፅዕኖ በመፍጠሩና ጥያቄውን በቀላሉ ወደ ኋላ እንደማይመልሰው ተገምቷል።የ2021 ዩጂን የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ከተራዘመው ኦሊምፒክ ጋር የሚካሄድበት ወቅት የሚጋጭ በመሆኑ ወደ 2022 እንዲራዘም መደረጉ ይታወሳል። ላለፉት ሰባት ዓመታት የበለጠ ዝግጅት ሲደረግበት የቆየው የኦሊምፒክ ውድድር መራዘሙ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ማስከተሉ የአዘጋጆቹ ራስ ምታት እንደሚሆን ቀድሞም የታወቀ ነው።ይህ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ የጃፓን መንግስትንም ይሁን ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴን በእጅጉ ሊፈትን እንደሚችል በባለሙያዎች አስተያየት ሲሰጥበት የቆየ ሲሆን ሁለቱ አካላት ኪሳራውን ለማካካስ እንደሚደጋገፉና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ለዚህ እንዲዘጋጁ ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንዲህ አይነት ችግሮች ሲገጥሙት ትልቅ ተቋም እንደመሆኑ የመድህን ዋስትና እንዳለው ይታወቃል።አሁን የገጠመው ግን ካለው የመድህን ዋስትና አቅም በላይ በመሆኑ ነው እዚህ ችግር ውስጥ የተዘፈቀው።ስለዚህ የመድህን ዋስትናው በህጉ መሰረት የሚሸፍነው ኪሳራ እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ ኪሳራውን የሚያካክስበት አንድ ነገር መፈጠሩ የግድ ይሆናል።ይህንን ተጨማሪ ኪሳራ የጃፓን መንግስት እንደሚሸፍን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ቀደም ሲል በተለያዩ አጋጣሚዎች መስማማታቸው ቢገለፅም አሁን የሃሳብ ለውጥ እንዳደረጉ የሚጠቁሙ መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ ውዝግቦች መነሳታቸው ይታወሳል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 29/2012ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=31846
[ { "passage": "በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሁሉም ውድድሮች መሰረዛቸው ተከትሎ ክለቦች ካለባቸው የፋይናስ ቀውስ እንዲያገግሙ በማሰብ ፌዴሬሽኑ ለመንግስት አካለት የጠየቀው የገንዘብ ድጋፍ ከምን ደረሰ ?ለወትሮም ደካማ የፋይናንስ መሰረት ላይ የቆሙት ክለቦች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ውድድሮች መሠረዛቸው ለበለጠ የፋይናስ ቀውስ እንዲዳረጉ አድርጓቸዋል። ለተጫዋቾች የወራት ደሞዝ ለመክፈልም ሆነ እንደ ክለብ የመቀጠል አደጋ ውስጥ የሚገኙት ክለቦች ካጋጠማቸው ችግር እንዲያገግሙ በማሰብ የእግርኳሱ የበላይ አካል ፌዴሬሽኑ በስሩ ለሚገኙት ለፕሪምየር ሊግ ሴት እና ወንዶች፣ ከፍተኛ ሊግ ፣ ለአንደኛ ሊግ ክለቦች የገንዘብ ድጎማ ሊያደርግላቸው ይገባል በማለት ለኢፊዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ከሰነድ ጋር የተያያዘ ደብዳቤ ባለፉት ሳምንታት መጠየቁ ይታወሳል። በጎ ምላሽ እንደሚገኝበት ተስፋ የተጣለበት ይህ ጉዳይ እስካሁን መልስ ሳያገኝ መዘግየቱ ክለቦችን የበለጠ አሳስቧል።ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮቻችን ባገኘነው መረጃ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግስት ድጎማ ይገኝበታል የተባለለትን ይህን ጉዳይ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ በሚገባ እየተከታተሉት እንደሆነ የሰማን ሲሆን በቅርቡም የገንዘብ ሚንስቴርም የገንዘቡን ድጋፉን ገቢ እንደሚያደርግ ለክለቦች ለማወቅ ችለናል።በሌላ ዜና በቅርቡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከእግርኳሱ የበላይ አካል ፊፋ የገንዘብ ድጎማ እንዳደረገ ቢገለፅም ፊፋ እስካሁን ለአባል ሀገራቱ ገንዘቡን አከፋፍሎ እንዳልሰጠ ሰምተናል።", "passage_id": "1831fc4bcbe67c056b199633691679ce" }, { "passage": " የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) የዓለም ስጋት ከመሆኑ አስቀድሞ በስፖርቱ ዓለም ተጠባቂ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ ኦሊምፒክ ነበር። ነገር ግን ሊካሄድ ወራት ብቻ በቀሩትና ሀገራትም ብሔራዊ ቡድናቸውን ማዘጋጀት በጀመሩበት ወቅት መራዘሙ ተሰማ። አጋጣሚውም በተለያዩ አትሌቶች ዘንድ ሁለት ዓይነት ስሜት የፈጠረ ሆኗል። የመጀመሪያዎቹ አትሌቶች የጊዜውን መርዘም ተጠቅመው በ2021ዱ ኦሊምፒክ በተሻለ ብቃት ለመገኘት ዕድል ያላቸው ሲሆኑ፣ ሁለተኛዎቹ ደግሞ በጥሩ አቋም ላይ የሚገኙና ምናልባትም መራዘሙ እክል ሊያስከትልባቸው የሚችሉ ናቸው። ኢትዮጵያም የአትሌቲክስ ቡድኗን መርጣ ልምምድ ለመጀመር ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ በነበረችበት ወቅት ነው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በመራዘሙ አትሌቶች እንዲበተኑ የተደረገው። ከተበተነው ብሔራዊ ቡድን አባላት መካከል የ3ሺ ሜትር መሰናክል አንዱ ሲሆን፤ ይህ ቡድን በዓለም የቤት ውስጥ ቻምፒዮና ውጤታማነቱን ያስመሰከረ ነበር። በኦሊምፒኩ ለአሸናፊነት የሚጠበቀውና ከፍተኛ ግምት ያገኘው ቡድኑና አባላቱ ምን ዓይነት ዝግጅት ሲያደርጉ ቆዩ፣ መራዘሙ ምን አስከተለባቸው እንዲሁም በዚህ ወቅት በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ በሚለው ጉዳይ ላይ የቡድኑ አባላት የሚናገሩት አላቸው። ለቡድኑ ከተመረጡትና ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በምርጥ አቋም ላይ ከነበሩአትሌቶች መካከል አንዱ የዳይመንድ ሊግ አሸናፊው ጌትነት ዋለ ይጠቀሳል። አትሌቱ ኦሊምፒክን ጨምሮ በግሉ ይሳተፍባቸው ለነበሩ ውድድሮች ከአሰልጣኙ ጋር በመሆን ጠንካራ ቅድመ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ይገልጻል። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ ኦሊምፒኩ መራዘሙ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ጎልቶ የሚታየው ጌትነት፤ «አትሌት ባለበት አቋም መጠቀም የሚገባው በወቅቱ ነው» የሚል አመለካከት አለው። የየትኛውም አትሌት አላማ የሆነውን በኦሊምፒክ ሀገርን ወክሎ ድል ማስመዝገብ ካለመቻሉም በላይ ከሚወዱት ሥራቸውም መነጠል ያስከፋል። ነገር ግን ቫይረሱ በመላው ዓለም ሕዝብ ላይ ስጋትና አደጋ በመሆኑ፤ ወቅቱ ይለፍ እንጂ በርትቶ በመስራት ብቃትን መመለስ እንደሚቻል ያምናል። አቋሙ ባለበት እንዲቀጥልም በቤቱ ውስጥ ከቀደመው ጊዜ ያነሰ ልምምድ እየሰራ ጊዜውን በማሳለፍ ላይ ይገኛል። እንደ አጋጣሚ ሆኖ አሰልጣኙ እርሱ በሚኖርበት አቅራቢያ የሚኖር በመሆኑ አልፎ አልፎ በርቀት እየተገናኙ መመሪያዎችን የሚቀበልና በስልክም መረጃ እንደሚለዋወጡ ይጠቁማል። ከዚህ ባለፈ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በመገናኛ ብዙኃን ታግዞ በባለሙያዎች የሚሰጠውን መረጃም ይከታተላል። ሌሎች አትሌቶችም በዚህ መልኩ ከቤታቸው ሳይርቁና ሰዎች በብዛት ባሉባቸው ስፍራዎች ባለመገኘት በአቋማቸው ለመቀጠል እንቅስቃሴ እንዲያደርጉም ጥሪውን ያቀርባል። ኦሊምፒክ በጉጉት ይጠብቀው የነበረውድድርና ከአሰልጣኙም ጋር ልዩ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየ መሆኑን የሚያስታውሰው ደግሞ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ሥልጠናውን ያጠናቀቀውና ሌላኛው የ3ሺ ሜትር መሰናክል ወጣት አትሌት አብረሃም ስሜ ነው። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ይህ ቫይረስ መከሰቱ ቢያሳዝንም በዓለም የመጣ ነገር በመሆኑ የግድ ራስን ከቡድን ልምምድ ማራቅ ተገቢ ነው። የኦሊምፒክ መራዘም አማራጭ የሌለው ጉዳይ ቢሆንም እርሱን በመሰሉና በመልካም አቋም ላይ ለነበሩ አትሌቶች ጉዳት አለው። ይህ ቫይረስ እስኪያልፍ ድረስም ጊዜውን እንደ ማገገሚያ በመጠቀም በአቋሙ ለመቆየት በቤቱ እንቅስቃሴ ማድረግ አላቋረጠም። እንደ ቡድን አጋሩ ጌትነት አብርሃምም የሚኖረው ከአሰልጣኙ ጋር በቅርብ ርቀት አካባቢ በመሆኑ በስልክ ከመገናኘት ባለፈ በአካል ተገናኝቶ ለመወያየትም ዕድል ሰጥቶታል። በአሰልጣኞች እንዲሁም በጤና ባለሙያዎች የሚሰጠውን መመሪያ በጥንቃቄ በመተግበርም እንቅስቃሴውን ቀጥሏል። በየማዕከላቱ የሚሰለጥኑ ታዳጊዎችን ጨምሮ በየክለቡ ያሉ አትሌቶች ተበትነው በየክልሉ ተመልሰዋል። በመሆኑም ጊዜው እስኪያልፍ ድረስ ከእንቅስቃሴ ሳይርቁ እንዲቆዩ መልዕክቱን ያስተላልፋል። በብሔራዊ ቡድን የ3ሺ ሜትር መሰናክል ዋና አሰልጣኙ ተሾመ ከበደ በብሔራዊ ቡድን ከተካተቱ አትሌቶች አብዛኛዎቹ ከእርሱ ጋር የነበሩ በመሆኑ ወጥ የሆነ ልምምድ ላይ እንደነበሩ ያስታውሳል። ከአትሌቶቹ ጋር በመሆን በቤት ውስጥ ቻምፒዮና ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተው ለዓመታዊው ዳይመንድ ሊግ ውድድር እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን፤ የኦሊምፒክ ሚኒማ ለማሟላት ሲሰሩም ነበር። ነገር ግን የኦሊምፒክ መራዘምን ተከትሎ ቡድኑ በመበተኑ አትሌቶች ተፈጥሯዊ የበሽታ መከላከል አቅማቸውን ሊያጎለብት የሚችል ቀላል እንቅስቃሴዎችን እየሰሩ እንዲቆዩ ተደርጓል። ቀድሞ ለአምስት ቀናት ያደርጉ የነበረውን መደበኛ ስልጠና እና ጫና በመቀነስም ክብደት እንዳይጨምሩ ቀላል እንቅስቃሴዎችን በየቤታቸው ይሰራሉ። አሰልጣኞችም በስልክና በሌሎች መንገዶች ከአትሌቶቻቸው ጋር በመገናኘት መስራት ያለባቸውን እየነገሯቸው መሆኑንም ይጠቁማል። የኦሊምፒኩ መራዘም እንደ ሀገር የሚያስከትለው ጉዳት መኖሩን የሚያነሳው አሰልጣኙ፤ እርሱ በሚያሰለጥንበት ርቀት ደግሞ አትሌቶች በጥሩ አቋም ላይ በመቆየታቸው ለኦሊምፒኩም የማሸነፍ ዕድል ነበራቸው። በአንጻሩ መራዘሙ የሚጠቅመው በጉዳት ላይ የቆዩና በወቅቱ በጥሩ አቋም ላይ ያልነበሩ አትሌቶችን ነው። ሁኔታውን ተጠቅመው አቅማቸውን አጎልብተው በመመለስ ብርቱ ተፎካካሪ የመሆን ዕድል ያላቸው በርካቶች እንደመሆናቸው ይህ ጊዜ ሲያልፍ ጠንካራ ሥራ ከአትሌቶች የሚጠበቅ መሆኑንም አሰልጣኙ ያመላክታል። በመጨረሻም አሰልጣኙ አትሌቶች ራሳቸውን ከዚህ ቫይረስ እንዲጠብቁ መልዕክቱን አስተላልፏል። ራሳቸውን ከበሽታ ሊከላከል የሚችልና ያሉበትን አቋም የሚጠብቅ እንቅስቃሴ ከማድረግ በዘለለ ራሳቸውን በጤና መጠበቅ እንዳለባቸውም ምክሩን ይለግሳል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 19/2012", "passage_id": "54bc176b47c4e76254c999d4b9a34bc9" }, { "passage": "ከቀናት በፊት የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና የዓለም አትሌቲክስ ከአስር ወራት ያነሰ ጊዜ የቀሩትን የቶኪዮ ኦሊምፒክ የማራቶንና እርምጃ ውድድሮችን የሚካሄዱበትን ስፍራ ከዋና ከተማዋ ቶኪዮ ለመሰረዝ ሃሳብ አቅርበው ነበር፡፡ ከፍተኛ ሙቀት አትሌቶቹን ሊጎዳቸው እንደሚችል በማሰብ የተነሳው ይህ የስፍራ ለውጥ ሃሳብም በአዘጋጇ ጃፓን ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘ አይመስልም። በቅርቡ በተካሄደው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በኳታር የነበረው የአየር ሁኔታ በተለይ ለማራቶን ስፖርት አስቸጋሪ እንደነበር ይታወሳል። በአየር ሁኔታው ሳቢያ ባልተለመደ መልኩ ውድድሩ በእኩለ ሌሊት እንዲደረግ ቢወሰንም በተለይ በሴቶች በኩል ከተሳተፉት 68 አትሌቶች 28 የሚሆኑት ውድድሩን ማቋረጣቸው እንዲሁም ለጤና መታወክ መዳረጋቸውም አይዘነጋም። ይህም ስፖርቱን በሚመሩት ዓለም አቀፍ አካላት ዘንድ ስጋት ያሳደረ ሲሆን፤ እአአ የ2020ው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በሚካሄድበት ወቅት የሚኖረው የሙቀት መጠን ለጎዳና ላይ ውድድሮች ምቹ እንደማይሆን ተገንዝበዋል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንዲሁም የዓለም አትሌቲክስ በባለሙያዎቻቸው አማካኝነት ባደረጉት ጥናት በሐምሌ ወር በቶኪዮ የሚኖረው ሙቀት ከፍ እንደሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፡፡ ይህም ለማራቶን እና እርምጃ ተወዳዳሪዎች ጤና እክል ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል። በመሆኑም እነዚህ ውድድሮች ከዋና ከተማዋ ቶኪዮ ነፋሻማ አየር ወዳለው ሰሜናዊው የሃገሪቷ ክፍል የማዘዋወር ሃሳብ አቅርበዋል። የውድድር ስፍራውን የለውጥ ሃሳብም ዓለም አቀፎቹን ማህበራት የውድድሩን አዘጋጅ ኮሚቴ እንዲሁም የሚመለከታቸውን አካላት ለማወያየት በተያዘው ወር መጨረሻ ለመገናኘት ቀን ቆርጠው ነበር። ኤኤፍፒ የሃገሪቷን መገናኛ ብዙሃን ዋቢ አድርጎ ባስነበበው ዘገባ መሰረት የውድድሩ አዘጋጆች በዚህ ሃሳብ ደስተኛ አይመስሉም፤ ይልቁንም የውድድር ማስጀመሪያ ሰዓቱ ላይ ለውጥ ማድረግ እንደሚሻል አመላክተዋል። ከመንግስታዊ አካል የተወከሉት ዩሪኮ ኮኬ «በውድድር ስፍራው መለወጥ ሃሳብ አልስማማም» ያሉ ሲሆን፤ መንግስት ዓለም አቀፎቹ ተቋማት ካነሱት ተቃራኒ ሃሳብ በመያዝ ውይይቱ ላይ እንደሚቀርብ ገልጸዋል።ለዚህ እንደ ምክንያት የተነሳውም የለውጡን ሃሳብ ኦሊምፒክ ኮሚቴው በድንገት ማንሳቱን ተከትሎ የሳፖሮ ከተማ ከንቲባዎች ምንም ዓይነት ዝግጅት ያላደረጉ በመሆናቸው ነው። ከዚህም ባሻገር የኦሊምፒኩ አዘጋጆች የማራቶን እና እርምጃ ውድድር በሚካሄድባቸው ስፍራዎች የሙቀት መጠኑን ሊቀንሱ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን እንደሚጠቀሙም ጠቁመዋል። ውድድሩን ለመመልከት ለሚፈልጉ የስፖርቱ ወዳጆች ትኬት የተቆረጠ መሆኑ ደግሞ ሌላ ቀውስ ሊያስከትልባቸው የሚችል መሆኑ አዘጋጆቹን አሳስቧቸዋል። ተወካዩ አክለውም «በርካታ የቶኪዮ ነዋሪዎች ስለ ውድድር ስፍራው ለውጥ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጥያቄ አቅርበዋል። የሃሳቡ አቀራረብም ለመንግስት አካላት እንዲሁም ለስፖርቱ ቤተሰብ ያልታሰበና ድንገተኛም ነው» ብለዋል። አዘጋጆቹ በዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው የጠየቁም ሲሆን፤ ከኮሚቴው የውድድር አስተባባሪ ኮሚሽን ሊቀመንበር ጆን ኮቴስ ጋር ለመነጋገር ማቀዳቸውንም ዘገባው ተመልክቶታል፡፡ ውድድሩን የሚመሩት\nዓለም አቀፍ\nተቋማት ሙቀቱ\nበአትሌቶች እንዲሁም\nበውድድሩ ላይ\nተጽእኖ ማሳደሩ\nእንደማይቀርና በቅድሚያ\nየሚያሳስባቸው የአትሌቶች\nደህንነት መሆኑን\nአስታውቀዋል። ይሁን\nእንጂ ሃሳቡ\nየቀረበው የዓለም\nቻምፒዮናውን መካሄድ\nተከትሎ እንዲሁም\nውድድሩ ሊካሄድ\nዘጠኝ ወራት\nብቻ ሲቀሩት\nነው። ኦሊምፒክ ኮሚቴው ለውድድሮቹ ማካሄጃ ምቹ ይሆናል በሚል የመረጡት፤ ከቶኪዮ በ800ኪሎ ሜትር ርቀት በሆካኢዶ ተራራማ አካባቢዎች የሚገኘውን ሳፖሮ የተባለ ስፍራ ነው። በሰሜናዊው የሃገሪቷ ክፍል የሚገኘው ይህ ስፍራ ውድድሩ በሚካሄድበት ወቅት የአየር ሁኔታው በተሻለ መጠን የሚቀዘቅዝ መሆኑ አትሌቶችን እንደሚረዳቸው ይታሰባል። ስፍራው እአአ 1972 የክረምት ኦሊምፒክ የተካሄደበትም እንደነበር ይታወሳል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 15/2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "75b134abed3dd6d1797ec574bda2a2ad" }, { "passage": "የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውድድሩን ለማራዘም ያስገደደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅቱን በቀጣዩ ሳምንት የሚጀመር በመሆኑ ለዝግጅቱ በቂ ጊዜ እንዲያገኙ በማሰብ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ በፕሪምየር ሊጉ መርሀ ግብር ለውጥ ምክንያት የቀን ሸግሽግ መደረጉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ላልታወቀ ጊዜ መሸጋገሩን ተከትሎ የዘንድሮው ውድድር የመካሄዱ ጉዳይ አጠራጣሪ እንዲሆን አድርጎታል፡፡", "passage_id": "721a9c7b155d5fda1c8c48ac14cca49d" }, { "passage": "የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከውድድር ውጪ ለሆኑ ብሔራዊ አትሌቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተጠሪነቱ ምንም እንኳ ለሁሉም ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ቢሆንም፣ ብሔራዊ አትሌቶችን በሒደት ከገንዘብ ድጎማ ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ እየሠራ መሆኑ ፕሬዚዳንቱ ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ አስታውቀዋል፡፡ ከድጋፉ ባሻገር የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከመከሰቱ በፊት ለአገሮች በሰጠው ነፃ የትምህርት ዕድል ኮታ መሠረት ኤሊት አትሌቶች ዕድሉን እንዲጠቀሙ ለማድረግ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡ ብሔራዊ ተቋማት ችግሩ በአትሌቶች ላይ ሥነ ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዳያሳድር የሚችሉትን እያደረጉ ይገኛሉ። ቀደም ሲል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት አትሌቶችንና መሰል ሙያተኞችን መደጎሙ አይዘነጋም፡፡ አዲስ ዘመን ሚያዝያ 27/2012 ", "passage_id": "982986101bc0dcb4fb98ac2c435347af" } ]
7c3a33a43c8527884df820313c620e7e
c57ef452850e760a86c3743811e5a17b
ቡንደስሊጋው በባዶ ስታዲያም ከ10 ቀናት በኋላ ይጀመራል
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የዓለምን ሕዝብ በአንድ ልብ የጭንቀት ቋት ውስጥ በመክተት የተጽእኖ በትሩን ማሳረፍ ከጀመረ አራት ወራት አለፉት። በወቅቱ በሀገረ ቻይና ውሃን ከተማ የወረርሽኙ መከሰት ሲሰማ ጉዳዩ እንደዋዛ፣ እንደዘበት ነበር የዓለም ሕዝብ ያደመጠው። ኮቪድ 19 መነሻውን በአንድ ሀገር ያድርግ እንጂ የስርጭቱን አድማስ በፍጥነት በመጨመር ዓለምን አዳርሷል። የቫይረሱ መከሰት ዜና ይፋ ሲደረግ ጉዳዬ ያላለውን የዓለም ሕዝብ በአንድ ልብ ትኩረቱና ስጋቱ ኮሮና ከሆነ አራት ወራት አልፈውታል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ሩብ ሚሊዮን ሰዎችን እንደቅጠል ያረገፈው ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ጥረቶች ቢደረጉም ዛሬም መፍትሄ ማግኘት አልተገኘም። በዓለም ሳይንቲስቶች፣ የህክምና ጠቢባንም ይሁን በኃያላን አገራት አቅም ማምጣት አለመቻሉ ደግሞ የተጽእኖውን በትር እንዲበረታ አድርጎታል። ኮቪድ-19 ከሰው ልጆች ሕይወት ባሻገር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ጉዳት ያልዳሰሰው ምድራዊ ኃይል የለም። ወረርሽኝ በእጅጉ ከጎዳቸው ዘርፎች መካከል ስፖርቱ በዋናነት ይጠቀሳል። የስፖርት ኢንዱስትሪውን በስፖንሰር ሺፕ የሚደግፉ ትልልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የበጀት ቀውስ ውስጥ መግባታቸው፣ ከትኬት ሽያጭ ከማርኬቲንግና ከተለያዩ ንግዶች የሚገኙ ገቢዎች መቆማቸው ሁሉንም ስፖርት ጎድቷቸዋል። በተለይ የእግር ኳስ ስፖርት ከፍተኛ ድርሻ የሚይዝ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል። በዚህ ዓመት የእግር ኳሱ ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል ተብሎ ሲጠበቅ ከተላላፊው ቫይረስ ጋር በተያያዘ ገቢው በእጅጉ እያሽቆለቆለ ይገኛል። የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) ወረርሽኝ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር የሚቻል እንዳልሆነ እየወጡ የሚገኙት መረጃዎች የስፖርት እንቅስቃሴን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ማድረግ ይጀመራል የሚል ተስፋ እንዳይጣል አድርጓል። ወረርሽኙ በታላላቆቹ የአውሮፓ ክለቦችን ጨምሮ ሁሉም የስፖርት ዘርፍ ላይ እያሳደረ ያለውን የፋይናነስ ቀውስን እንዲያሻቅብ ያደርገዋል ተብሏል። ከሰሞኑ እየወጡ የሚገኙት መረጃዎች ግን ይሄንን የሚሽሩ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል። በአንዳንድ ሀገራት ላይ ወረርሽኙን መቆጣጠር እየተቻለ መሆኑን ተከትሎ፤ ስፖርታዊ ውድድሮች ሊያደረጉ መሆኑ አስነብቧል። መራሂተ መንግሥት አንጌላ መርኪል በሀገሪቱ የኮሮና ወረርሽኝ እያሳደረ ያለው ተጽእኖ በተመለከተ ከፌዴራል መንግሥቱ ሹማምንቶች ጋር ትናነት በቪዲዮ ኮንፍረንስ ውይይት አድርገዋል። የጀርመን ቦንደንስሊጋው ከአስር ቀን አልያም ከአስራ አምስት ቀናት በኋላ ለማስጀመር የሚያስችለው የስምምነት ሰነድ በውይይቱ ላይ መቅረቡን አመልክቷል። በሀገሪቱ 16ቱም ግዛቶች ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር በመጣመር የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር አመርቂ ውጤት ማምጣታቸው ተከትሎ መንግሥት ጥሏቸው የነበሩ ገደቦችን እንዲነሱ ውሳኔ ሊያስተላልፍ መቻላቸውን ዘገባው አትቷል። መራሄተ መንግሥት አንጌላ መርክል እንደተናገሩት «ጀርመን የቫይረሱን የስርጭት ፍጥነት ለመቀነስ የወጠነችው ግብ በመሳካቱ የንግድ ቦታዎች እንዲከፈቱና ደንበኞቻቸውን ማስተናገድ ይችላሉ። ከዚህም በተጨማሪ ቡንደስሊጋውም እንዲጀመር ተወስኗል» ማለታቸውን ጠቅሶ፤ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ከተቋረጡ የሊግ ውድድሮች ውስጥ አንዱ የሆነው የጀርመን ቡንደስሊጋ በቅርቡ ወደ ውድድር የሚመለስ ይሆናልም ብሏል። ጀርመን እንዲህ ዓይነቱ መረጃ ከተሰሙባቸው ጥቂት ሀገራት ግንባር ቀደም መሆን ያስችላታል የሚለው ዘገባው፤ የጀርመን እግር ኳስ ሊግ ቡንደስሊጋው የፊታችን ግንቦት 1 ወደ ውድድር በመመለስ ያለ ተመልካች ውድድሮቹን አድርጎ ለማጠናቀቅ ዝግጁ እንደሆነ ሲገልጽ መቆየቱን አስታውሷል። ቡንደስሊጋውን እና የሁለተኛ ዲቪዥን ጨዋታዎችን የሚያስተዳደረው የጀርመን እግር ኳስ ሊግ ከ36 ፕሮፌሽናል ክለቦች ጋር ከሳምንት በፊት በነበረው ውይይት የዘንድሮውን የውድድር ዓመት ያለተመልካች የመጨረስ ፍላጎት እንዳለው ከስምምነት ተደርሶ ነበር። የጀርመን እግር ኳስ ሊግ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክርስቲያን ሲፈርት ቦንደንስሊጋው ከአስራ ቀናት በኋላ እንዲጀመር በተላለፈውን ውሳኔ በእጅጉ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። በውድድሩ ተሳታፊ ክለቦች መካከል ውድድሩን መስመር በያዘ መልኩ ለማካሄድ ቀደም ሲል የስምምነት ሰነድ መዘጋጀቱን ሥራ አስፈጻሚው ገልጸው፤ «ግጥሚያዎቹ ከመጀመራቸው በፊት ለሁለት ሳምንታት በለይቶ ማቆያ፤ ምናልባትም በስልጠና ካምፖች ውስጥ እንዲሆኑ ይጠይቃል። በመጀመሪያውና በሁለተኛው ዲቪዚዮን 36 ቡድኖች ውድድራቸውን እንዲጀምሩ የሚደረግ መሆኑ በሰነዱ ተካቷል። ክለቦች የሚደርስባቸውን የምጣኔ ሀብቱን ጉዳት መቀነስ እንዲቻል ከግንዛቤ በማስገባት ነው» ሲሉ አስተያየታቸውን መስጠታቸውን ዘገባው አስፍሯል። ቢቢሲ በዚሁ ዘገባው ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ከተቋረጡ የሊግ ውድድሮች ውስጥ አንዱ የሆነው የጀርመን ቡንደስሊጋ ወደ ውድድር እንዲመለስ መደረጉን ትልቅ ተስፋ ይሰጣል መባሉን የገለጸው ዘገባው፤ የጀርመን ቦንደንስሊጋ በቅርቡ መጀመሩ ስጋትና ቅሬታ ያስነሳ መሆኑንም አያይዞ አመልክቷል። በጀርመን ከሚገኙ ክለቦች አንዱ በሆነው ኮሎኝ ክለብ ተጫዋች የሆኑ ሦስት ተጫዋቾች በኮሮና ተሐዋሲ ተጠቅተዋል። በገለልተኛ ቤተ-ሙከራ ውስጥ ጠቅላላ የቡድኑ አባላት በተደረገላቸው ምርመራ ከሦስቱ በስተቀር ነጻ ተብለዋል። የጀርመን ቡንደስሊጋ የእግር ኳስ ውድድር ለመጀመር ፍቃድ ማግኘቱ አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ቅሬታ መነሳቱን ዘግቧል። የጀርመን ቡንደንስሊጋ በቅርቡ በመመለሱ ቅሬታን ከፈጠረባቸው አካላት መካከል የተለያዩ ክለብ ተጫዋቾች መሆናቸው አያይዞ አንስቷል። ተጫዋቾቹ «ውድድሩ የሚጀምርበት ጊዜ ተፋጠነ» ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል። ዓለም አቀፍ ስጋት ለሆነው የኮሮና ወረርሽኝ ክትባት አልያም መድሃኒት አልተገኘም። የኮሎኝ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች በቫይረሱ መጠቃታቸው በታወቀበት ሁኔታ ወደ ውድድር በቅርቡ መመለስ አደጋው ከፍተኛ ይሆናል። ከዚሁ ትይዩ ደግሞ በሀገሪቱ የሰዎች እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ ባልተፈቀደበት በዚህ ወቅት የጀርመን እግር ኳስ ሊግ አስተዳዳሪዎች ፍቃድ ማግኘታቸው ግርምትን መፍጠሩን አትቷል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 30/2012 ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=31911
[ { "passage": "በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሁሉም የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እና ዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ሌላ ተጨማሪ መግለጫ እስኪወጣ ድረስ እንዲቋረጡ ተወሰነ፡፡\nየአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር 55 አባላት ዛሬ ባደረጉት ስብሰባ ለዩሮ 2020 የወንዶች እና ለ2021 የሴቶች ውድድር የሚደረጉ ማጣሪያዎች እና በሰኔ ወር ሊካሄዱ የታሰቡ የብሄራዊ ቡድን ጨዋታዎችም እንዲቋረጡ መወሰኑን በድረ-ገጹ አስነብቧል፡፡\nበአህጉሩ የወዳጅነትም ይሁን ማንኛውም ጨዋታ ማህበሩ ውሳኔውን እስኪቀለብስ ድረስ መካሄድ እንደማይችል ደንግገዋል፡፡\nበቪዲዮ ኮንፈረንስ ውይይታቸውን ያደረጉት የአህጉሩ እግር ኳስ ገዢ አባላት ሁሉም የ2020/21 የክለቦች የውድድር ዓመት ማብቂያ ጊዜዎችም እንዲራዘሙ ወስነዋል፡፡ ይሁን እንጂ እስከመቼ የሚለው ጥያቄ በማህበሩ ቀጣይ ውሳኔ እንደሚታወቅ ነው የተገለጸው፡፡\nበሌላ የስፖርት ዜና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች እና ተጫዋቾቻቸው የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ድጋፍ እያደረጉ አይደለም በሚል እየተተቹ ነው፡፡\nየብሪታኒያ ፖለቲከኞች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች “የሞራል ክፍተት” አለባቸው ሲሉ ተችተዋቸዋል፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የክለቦቹ እና የተጫዋቾቻቸው ዝምታን መምረጥ የእንግሊዝ እግር ኳስ ምን ያክል የኢኮኖሚክስ ችግር እና የሞራል ቀውስ እንዳለበት ማሳያ ነው ሲሉ አንዳንዶች ትችታቸውን አቅርበዋል፡፡\nቢቢሲ እንደዘገበው የለንደን ከተማ ከንቲባ ሳዲቅ ክሀን “ተጫዋቾች በአሁኑ ወቅት ደሞዛቸውን መለገስ ይጠበቅባቸዋል” ያሉ ሲሆን በተለይ ከፍተኛ ተከፋይ ተጫዋቾች ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡\nየባርሴሎና ተጫዋቾች በሽታው በቁጥጥር ስር እስኪውል የደሞዛቸውን 70 በመቶ ለመለገስ ቃል የገቡ ሲሆን፣ የጁቬንቲዩስ ተጫዋቾች እና አሰልጣኙ ሞሪዚዮ ሳሪ ደግሞ የአራት ወር ደሞዛቸውን መለገሳቸው ይታወቃል፡፡\nበጀርመን ደግሞ እንደ ባየር ሚዩኒክ እና ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ያሉ ክለቦችም ከደሞዛቸው ለመቁረጥ ተስማምተዋል፡፡\n", "passage_id": "51a007f1d10ba65b8d6bab3529327c97" }, { "passage": "የሊግ 1 አሸናፊነት ክሪስቶፍ ጋልቲየርን በሊል ማቆየት አልቻለም። ጁቬንቱሶች አንድሪያ ፒርሎን በማሰናበት በማሲሚሊያኖ አሌግሪ ሊተኩት እየሠሩ ነው። \n\nበጀርመን ዮሃንስ ፍሊክ ከባየር ሙኒክ መነሳት ተመሳሳይ ውሳኔ በሌሎች ክለቦችም ዘንድ እንዲተገበር መንገድ ከፍቷል። \n\nየ2020 - 21 የውድድር ዘመን አቧራ ገና አልሰከነም። ከዚህ በፊት ታይቶ በማያውቅ ሁኔታ ብዛት ያላቸው ታላላቅ አሰልጣኞች ከሥራቸው ሲለቁ ተመልክተናል።\n\nከገንዘብ ነክ ጉዳዮች እስከ አድካሚው ዓመት ያለውን ዝርዝር ሁኔታ የቢቢሲ ሬዲዮ 5 ባለሙያዎች ለምን እንደሆነ ይተነትኑታል። \n\n\"በከፍተኛ ሁኔታ የተፈጠሩ አለመግባባቶች\"\n\nየኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የእግር ኳስ ክለቦችን ፋይናንስ አሽመድምዷል። ኬፒኤምጂ እንደተባለው የገበያ ኩባንያ ከሆነ በአውሮፓ ኃያላኑ 32 ክለቦች ከየካቲት 2020 ጀምሮ 6.1 ቢሊዮን ዩሮ አጥተዋል።\n\nበጀርመን ፍሊክ ባየርን ለቀቀ። ጁሊያን ናጌልስማን በቦታው ተተካ። ጄሲ ማርች ደግሞ አር ቢ ላይፕዚግን በመረከቡ በርካታ ለውጦች ተከታትለው መጡ። ከዚያን ጊዜ ወዲህ በጣሊያን፣ በስፔን፣ በእንግሊዝ እና በፈረንሳይ ያለው ተመሳሳይ ታሪክ ነው።\n\nጀርመናዊው የእግር ኳስ ጋዜጠኛ ራፋኤል ሆኒግስቴይን በቢቢሲ ራዲዮ 5 ቀጥታ ስርጭት ላይ \"መልቀቂያዎቹ የሚያመሳስላቸው በኮቪድ-19 ወቅት ስለ ገንዘብ ብዙ ውስጣዊ ክርክሮችን በመመልከታችን ነው\" ብሏል። \n\n\"ከእነዚህ አሰልጣኞች ብዙዎቹ ለቀዋል። ምክንያቱም ለሌላ ሥራ ለመሰለፍ ሳይሆን ስለበቃቸው ነው\" ሲል ተናግሯል።\n\nአክሎም \"ከዚህ ቀደሙ በተለየ በእነዚህ ትላልቅ ክለቦች ትላልቅ አሰልጣኞች በዚህ ቁጥሮች ሲለቁ አላየንም\" ብሏል።\n\n\"ፍሊክ በተጫዋቾች ዝውውር ላይ ከፍተኛ አለመግባባት ከተፈጠረ በኋላ ነው የለቀቀው። ምክንያቱ ደግሞ ኮቪድ-19 ነው። ፍሊክ የሚፈልገውን ያህል ገንዘብ ሙኒክ ማውጣት አልቻለም። በዚህም አለመግባባቱ ተጀመረ\" ሲል አስረድቷል።\n\nበላሊጋው 2ኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ሪያል ማድሪድ በኬፒኤምጂ ጥናት የአውሮፓ ውዱ ክለብ በመሆን አጠናቋል። ዚዳን ግን በቦርዱ እና በፕሬዚዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ስለመደገፉ አልተሰማውም ሲል የስፔን እግር ኳስ ባለሙያው ጊየም ባላጌ አስታውቋል።\n\nኮንቴ በ11 ዓመታት የመጀመሪያውን የጣሊያን ዋንጫ ለክለቡ ቢያሳካም በኢንተርም ተመሳሳይ ታሪክ ነው ያለው። ምክንያቱም በክለቡ የፋይናንስ ችግር የተነሳ በዚህ ክረምት የደመወዝ ክፍያን በ 20 በመቶ ለመቀነስ ተዘጋጅቷል።\n\nጣሊያናዊው ጋዜጠኛ ጋብሪኤል ማርኮቲ \"ኮንቴ ገንዘብ ፈለገ፤ ጥያቄዎችንም አቀረበ። ነገር ግን አንድ ወይም ሁለት ታላላቅ ተጫዋቾችን ከማግኘት ይልቅ አንድ ወይም ሁለት ታላላቅ ተጫዋቾችን መሸጥ ሊኖርበት ነው\" ብሏል። \n\n\"ስሜቱ ተለውጧል፡፡ ፔፕ ጋርዲዮላ ወይም የርገን ክሎፕን ካልሆንክ እነዚያን ጥያቄዎች ማንሳት በጣም ከባድ ነው\" ይላል፡፡\n\nማርኮቲ አክሎም \"አዳዲስ ተጨዋቾችን ከመግዛት ይልቅ አዲስ አሰልጣኝ ማምጣት ይረክሳል። በግልጽ እንደሚታየው ተያያዥ ምላሽ ስለመኖሩ አይካድም። አብዛኛው ከድህረ ኮሮናቫይረስ ገንዘብ፣ ኢንቨስትመንት እና ኢኮኖሚ ጋር የተያያዘ ነው\" ብሏል፡፡\n\n\"ለዚህም ነው ዚዳን ከማድሪድ የለቀቀው፣ ኮንቴ ኢንተርን የተሰናበተው። ይህ የዝውውር መስኮት ለአሰልጣኞች እና ለተጫዋቾች በጣም የተለየ መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነው\" ሲል ያስረዳል፡፡\n\nአንዳንዶቹ ደክመዋል፣ ሌሎች ደግሞ አዲስ ፈተናዎች አስፈልጓቸዋል \n\nያለፈው ዓመት በወረርሽኙ ከተስተጓጎለ በኋላ በመላው አውሮፓ ያሉ ክለቦች በተጨናነቀ የጊዜ ሰሌዳዎች እንዲጫወቱ ማስገደዱን ተከትሎ ውስጣዊ ውጥረቶች መኖራቸው የተጠበቀ ሊሆን ይችላል፡፡\n\nእንደ ኮንቴ ያሉት አንዳንዶቹም ችግሮች ቢኖሩም፣... ", "passage_id": "46464de49d6b6ca11c9dadd9a2ef6e34" }, { "passage": "በቀጣዩ መስከረም ሊካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት ‹‹የግሬት ኖርዝ ረን›› ግማሽ ማራቶን ውድድር መሰረዙን ተከትሎ ጥቅምት ላይ እንደሚካሄድ የተነገረው የለንደን ማራቶንም ሊሰረዝ እንደሚችል ጥርጣሬ ፈጥሯል:: በእንግሊዝ አገር ከሚካሄዱ የጎዳና ላይ ውድድሮች መካከል ትልቁን ስፍራ የሚይዙት ሁለቱ የማራቶንና ግማሽ ማራቶን ውድድሮች ከኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ 19) ወረርሽኝ ስጋት ጋር በተያያዘ ቀደም ብሎ ከሚካሄዱበት ወቅት እንዲራዘሙ ተደርጎ በቀጣዩ መስከረምና ጥቅምት ወር ሊካሄዱ ቀጠሮ ተይዞ ነበር፡፡ \nዘንድሮ አርባኛ ዓመቱን የያዘው ‹‹ግሬት ኖርዝ ረን›› የግማሽ ማራቶን ውድድር ከመሰረዙ አስቀድሞ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ስልሳ ሺ ተሳታፊዎችን በመያዝ በብሪታኒያ ትልቁ የጎዳና ላይ ውድድር መሆን ችሏል፡፡ ከሰላሳ አንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ከውድድሩ በመሰብሰብ ለበጎ አድራጎት እንዲውል ለማድረግ ታስቦ የነበረ ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ እንዳልተቻለ አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ውድድሩ ሊሰረዝ እንደቻለ የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል:: ውድድሩ ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚደረገውን ጥንቃቄ ከግምት በማስገባት እንዲካሄድ አዘጋጆቹ ከጤና ባለሙያዎች እንዲሁም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅተው በመስራት ጥረት ቢያደርጉም እንዳልተሳካ አሳውቀዋል፡፡ \nበዚህ ታላቅ ውድድር ባለፈው ዓመት እንግሊዛዊው\n የኦሊምፒክ ጥምር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነው አትሌት ሞሐመድ ፋራህ ለስድስተኛ ተከታታይ ጊዜ ሲያሸንፍ ኬንያዊቷ የማራቶን ባለክብረወሰን ብሪጊድ ኮስጌ የውድድሩን ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር ማሸነፏ ይታወሳል፡፡ \nይህ የግማሽ ማራቶን ውድድር መሰረዙን ተከትሎ ጥቅምት ላይ ሊካሄድ የታሰበው ትልቁ የለንደን ማራቶንም ሊሰረዝ እንደሚችል ተገምቷል፡፡ የለንደን ማራቶን እንደወትሮው ቢሆን ባሳለፍነው ሚያዚያ ላይ የዓለማችን የርቀቱ ኮከቦችን ያፋልም ነበር፡፡ በተለይም በወንዶች የማራቶን ባለክብረወሰኑ ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌና የርቀቱ ሁለተኛው ፈጣን አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በዚህ ውድድር የሚያደርጉት ፉክክር በብዙዎች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ ነበር፡፡ ውድድሩ መሰረዝ አለመሰረዙን ግን አዘጋጆቹ የገለፁት ነገር የለም፡፡ \nበርካታ የማራቶን የዓለም ክብረወሰኖች የሚ ሻሻሉበት የበርሊን ማራቶን በዚህ ዓመት የመሰረዝ ወይም የመራዘም እድል ያልገጠመው ብቸኛው ውድድር ነው ማለት ይቻላል፡፡ ይህ ታላቅ የማራቶን ውድድር የኮሮና ቫይረስ በዓለም ላይ ከመከሰቱና ከመስፋፋቱ አስቀድሞ መስከረም ወር ላይ በመካሄዱ የሌሎቹ ታላቅ ውድድሮች እጣ ፋንታ ሳይገጥመው ቀርቷል፡፡ ያም ሆኖ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እስካሁን የሚያቆመው ባለመኖሩና ወደ ፊትም መፍትሄ ማግኘቱ አጠራጣሪ እየሆነ በመምጣቱ በቀጣዩ መስከረም የበርሊን ማራቶን የመካሄዱ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኗል፡፡ \nየውድድሩ አዘጋጆች ባለፈው ወር እንደጠቆሙትም፣\n ውድድሩን በተለመደው ወቅት ለማካሄድ እስካሁን ውሳኔ ላይ መድረስ አልቻሉም፡፡ ውድድሩን ለማካሄድ ወይም ለማራዘም ውይይት እየተደረገ ሲሆን ውሳኔ ላይ ለመድረስ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው አሳውቀዋል፡፡ የጀርመን መንግስት በኮሮና ቫይረስ ስጋት እስከ መጪው ጥቅምት ወር መጨረሻ ከአምስት ሺ ሰው በላይ የሚሰበሰብባቸው ማንኛቸውም መርሐግብሮች ማገዱን ተከትሎ የውድድሩ አዘጋጆች ውሳኔ ላይ ለመድረስ እንደተቸገሩ ጠቁመዋል፡፡ \nእንደ በርሊን ማራቶን ሁሉ ዋነኞቹ የዓለማችን የማራቶን ውድድሮች ከሆኑት አንዱ የቦስተን ማራቶንም በተመሳሳይ ምክንያት መካሄድ ከነበረበት ወቅት የመራዘም እድል እንደገጠመው ይታወሳል፡፡የበርሊን ማራቶን አዘጋጆች ውድድሩ ካለው ስፋትና\n ከሚያሳትፈው የሰው ብዛት አኳያ የሚካሄድበት እድል መኖር አለመኖሩን በማጥናት ላይ የሚገኙ ሲሆን ውሳኔ ላይ ለመድረስም የተወሰነ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው አሳውቀዋል፡፡ ለዚህም የውድድሩ አዘጋጆች አሁን ላይ በቫይረሱ ስጋት የተነሳ በሙሉ ኃይላቸው ተገናኝተው መስራት አለመቻላቸው አንዱ እንቅፋት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ \nበርካታ የዓለም ክብረወሰኖች የሚመዘገቡበት የበርሊን ማራቶን 2018 ላይ ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ 2፡1፡39 የሆነ አዲስ የዓለም ክብረወሰን በርቀቱ እንዳስመዘገበበት ይታወሳል፡፡ ባለፈው መስከረም ደግሞ ቀነኒሳ በቀለ ይህን ክብረወሰን ለማሻሻል በሁለት ሰከንድ የዘገየ ሰዓት ማስመዝገቡ አይዘነጋም፡፡\nአዲስ ዘመን ሰኔ 11/2012\nቦጋለ አበበ", "passage_id": "ed1349c7a3a3792606c14c89ef1f693d" }, { "passage": "በመላው ዓለም ከ200 አገራት በላይ የተዛመተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የዓለምን የስፖርት እንቅስ ቃሴ በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ከቶታል። በወረርሽኙ ሳቢያ ትልልቅ የስፖርት ውድድሮች በመራዘማቸው፣ በመሰረዛቸው እና በመስተጓጐላቸው ኢንዱስትሪውን ከፍተኛ ገቢ እንደሚያሳጣው የተለያዩ ትንበያዎች አመልክተዋል። የስፖርት ኢንዱስትሪውን በስፖንሰ ርሺፕ የሚደግፉ ትልልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የበጀት ቀውስ ውስጥ መግባታቸው፣ ከትኬት ሽያጭ ከማርኬቲንግና ከተለያዩ ንግዶች የሚገኙ ገቢዎች መቆማቸው ሁሉንም ስፖርት ጎድቷቸዋል፡፡በተለይ የእግር ኳስ ስፖርት ከፍተኛ ድርሻ የሚይዝ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል።በዚህ ዓመት የእግር ኳሱ ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል ተብሎ ሲጠበቅ ከተላላፊው ቫይረስ ጋር በተያያዘ ገቢው በእጅጉ እያሽቆለቆለ ይገኛል።የአብዛኛዎቹ የእግር ኳስ ክለቦች ዋነኛ ገቢያቸውን የሚያገኙት ከሶስት ምንጮች ሲሆን፤ ይኸውም ከመገናኛ ብዙሃን የስርጭት መብት፣ ከስፖንሰርና ማስታወቂያዎች እንዲሁም በጨዋታ ወቅት ከስታዲየም የትኬት ሽያጭ እንደሆነ የወርልድ ኢኮኖሚ ፎረም መረጃ ያመላክታሉ።10 በሚደርሱ ሊጎች ያለው ቁጥራዊ መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነም ክለቦቹ ከሚዲያ መብት ብቻ ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያገኛሉ።ይህም ከአጠቃላይ ገቢያቸው 60 ከመቶ ይሸፍናል።በወረርሽኙ ምክንያት የውድድሮች መቋረጥን ተከትሎ ክለቦች ከእነዚህ ምንጮች የሚያስገቡት ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን ያመላክታል።ዴይሊሜይል በዚሁ ዙሪያ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን እንደ ማሳያ በመጥቀስ ያወጣው ይሄንኑ ያጠናክራል።የአለማችን እጅግ ተወዳጅ ከሆኑ ሊጎች በግንባር ቀደምነት የሚጠቀሰው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በወረርሽኙ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳቱን በዘገባው ጠቅሷል። ፕሪምየር ሊጉ ባለፈው ዓመት አዲስ በገባው (ለሶስት ዓመታት) ኮንትራት 12 ቢሊየን ዶላር ከሚዲያ መብት ብቻ ለመሰብሰብ አቅዶ ነበር።እግር ኳሱ አሁን ካለው ቁመና አኳያ እቅዱን ማሳካት የሚቻል አይሆንም ሲል ዘገባው አትቷል።ውድድሩሁለት ወራትን እንኳን ሳያስቆጥር ክለቦቹ ከ60 እስከ 150 ሚሊየን ዶላር ኪሳራ ማስተናገዳቸውን እያስታወቁ ይገኛሉ።በመሆኑም ከቴሌቪዥን መብት ከሚገኝ ገቢ ብቻ እያንዳንዱ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ክለብ 750 ሚሊዮን ፓውንድ ያጣል። ስለዚህም ነው ክለቦቹ ከተጫዋችና አሰልጣኞች ቡድን ባሻገር የሚገኙ ሰራተኞቻቸውን በጊዜያዊነት እያሰናበቱ ይገኛሉ ።የተጫዋቾቻቸውን ደመወዝ ለመክፈል በመቸገራቸውም አንዳንዶች ግማሽ ክፍያ ሌሎች ደግሞ የተወሰነ ቅናሽ በማድረግ እንደሚከፍሉ እያሳወቁ ይገኛሉ።ፕሪሚየር ሊጉ በዚህ ምስቅል ቅል ውስጥ ሆኖ ለማግኘት ያቀደውን ገቢ ማሳካት እንደማይችል ዴይሊ ሜል በዘገባው ተመልክቷል። በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ስፖርታዊ ክንውኖች መቆማቸው እንደ እንግሊዝና የመሳሰሉት ሊጎች ሁሉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ሰለባ መሆኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።ከብሄራዊ ፌዴሬሽኑ መግለጫ በመነሳት በአለማችን ታላላቅ ክለቦች ላይ የተከሰተው የፋይናንስ ቀውስ መንገዱና የኪሳራው መጠን ቢለይም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከችግሩ አለመዳኑን የዘርፍ ሙያተኞች እየተናገሩ ይገኛሉ።በፕሪሚየር ሊጉ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ክለቦች ከኮሮና ቀደም ብሎ በፋይናንስ ቀውስ የሚዋልሉ እንደሆኑ እሙን ነው። የተጫዋቾች ደመወዝ ለመክፈል የነበሩትን ውዝግቦች ወደ ኋላ መለስ ብለን ስናስታውስ ይሄንኑ እውነታ በሚገባ እንረዳለን።በክለቦቹ ላይ ከአስተዳደር፣ ከእቅድ፣ ገቢና ወጪን ያለማመጣጠን ችግሮች በስፋት የሚታዩ እንደሆነ የሚካድ አይደለም።ክለቦቹ ወጪን እንጂ ገቢን መሰረት ያደረገ የፋይናንስ ሥርአት የማይከተሉ በመሆኑ በቀውስ እንዲቆዩ ሆነዋል።የኮሮና ወረርሽኝ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚፈጥረው ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ሲታከልበት«በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ»ይሆናል።የወረርሽኙ ተፅእኖ ከክለቦች አልፎ የፌዴሬሽኖችን አቅም እየፈተነ ስለመሆኑ ከሰሞኑ የወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የገንዘብ ችግር ውስጥ በመግባቱ መንግሥት የገንዘብ ድጎማ እንዲያደርግለት ጥያቄውን በደብዳቤ ማስገባቱን አስታውቋል፡፡የብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እንዳብራሩት፣ «ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግለት ጥያቄ አቅርቧል መልስ እየጠበቀ ነው። ምክንያትም ሁሉም እንደሚያውቀው በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሁሉም ነገር ቆሟል፣ የሁሉም አካላት ትኩረት ቅድሚያ ለሰው ልጆች ሕይወት በሚል ስፖርቱን በሚመለከት ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እያደረጉ እንዳልሆነ ይታወቃል። ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ችግሩን መቋቋም በሚችልበት ቁመና ላይ አይደለም፣ ለዚህም ነው መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግ በደብዳቤ የጠየቅነው»ብለዋል።ሀገሪቱ ከገባችበት ፈተና አንፃር ብሄራዊ ፌዴሬሽኑን የመንግስትን ደጅ መጥናቱ ውጤትያመጣል የሚገመት አይሆንም ተብሏል።በተመሳሳይ የክለቦች እጣ ፈንታ ከዚህ የተለየ እንደማይሆን ከተለያዩ ወገኖች ግምቶች እየቀረቡ ይገኛሉ።ለዚህ እንደ መከራከሪያ በፕሪሚየር ሊጉ የሚሳተፍ አብዛኛዎቹ ክለቦች በመንግስት የሚደጎሙ መሆናቸውን ያነሳሉ። ሀገሪቱ እየገጠማት ካለው የኢኮኖሚ ቀውስ አንፃር መንግስት እንደቀደመው ለክለቦች ከፍተኛ ገንዘብ ስለማውጣቱ አጠራጣሪ ይሆናል ይላሉ።ከዚህ በመነሳት ክለቦችም ሆኑ ፌዴሬሽኑ ከነበረባቸው መጪውን ጊዜ ፈታኝ እንደሚሆንባቸው ሀሳባቸው እየሰነዘሩ ይገኛሉ። የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ከሰሞኑ ይፋ ያደረገው መረጃ ግን በኢትዮጵያን እግር ኳስ መፃኢ ጉዞ ላይ የተስፋ ጭላንጭል የፈጠረ ሆኗል። የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ፤«የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የፊፋ አባል አገራት ለሆኑት 211 ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች የ 150 ሚሊዮን ዶላር አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡በዚህ መሰረት እያንዳንዱ አባል ሀገራት ከሶስት ወራት በፊት የ500 ሺህ ዶላር ከፊፋ ድጋፍ ይደረግላቸዋል »ሲሉ አስታውቀዋል፡፡ፊፋ የሚያደርገው ድጋፍ የአለም እግር ኳስ ከገባበት ቀውስ ያወጣው ይሆን?የሚል ጥያቄ አጭሯል።በኢትዮጵያ ብቻም ሳይሆን በበርካታ ሀገራት በጉጉት የሚጠበቀው ገንዘብ ለማግኘት ፊፋ ቅድመ ሁኔታዎች ማስቀመጡም ተነግሯል።ሀገራት በወረርሽኙ ያደረሰባቸውን ተጽእኖ በተመለከተ በሚያቀርቡት ትንተና ላይ መሰረት ያደረገ ሊሆን ይችላልም ተብሏል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይሄንኑ መሰረት ባደረገ መልኩ ተንትኖ ማቅረብ እንደሚጠበቅበት የዘርፍ ሙያተኞች እያሳሰቡ ይገኛሉ።ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ከክለቦቹ ጋር በሚገባ ተነጋግሮ የደረሰውን የጉዳትና የኪሳራ መጠን አስረጅና ገላጭ በሆነ መልኩ የሚያስረዳ ሰነድ መላክ ይኖርበታል።ብሄራዊ ፌዴሬሽኑም ሆነ ክለቦቹ ከወዲሁ ተቀራርበው መወያየትና ከድጎማው ተቋዳሽ መሆን ይገባቸዋል።ፕሪሚየር ሊጉ፣ብሄራዊ ሊጉ እና እታች የሚገኙት ክለቡች ምን ያህል ቀውስ እንደደረሰባቸው በሚገባ ተንትኖ ማቅረብ ይገባል።ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ በአፋጣኝ ወደ እንቅስቃሴ ካልተገባ «ሰርገኛ መጣ…»አይነት እንዳይሆን ከወዲሁ ነቅቶ መረጃዎችን መከታተልን ይጠይቃል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 23/2012ዳንኤል ዘነበ", "passage_id": "ce9527f694ae0521632b09fca0b44030" }, { "passage": "ቢቢሲ ስፖርት ባገኘው መረጃ መሰረት ሊጉ ከነጭራሹ የሚቋረጥ ከሆነ አልያም ከሊጉ የሚወርዱ ቡድኖች የሚኖሩ ካልሆነ ክለቦቹ ከተገለጸው ገንዘብ ተጨማሪ ሊከፍሉም ይችላሉ።\n\n• የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ በገለልተኛ ሜዳ ሊጠናቀቅ ይሆን?\n\n• ኮሮናቫይረስን ለማሸነፍ ከኢቦላ በሽታ ምን ልምድ መውሰድ ይቻላል?\n\nየፕሪምረየር ሊግ ክለቦች ደግሞ ሊጉን ማስቀጠል በሚቻለበት ሁኔታ ላይ የሚያደርጉትን ውይይት ትናንት አስቀጥለዋል። የ2019/20 ወድድር ዘመን 92 ጨዋታዎች ይቀሩታል። እነዚህን ጨዋታዎች እንዴት እናጠናቅ በሚለው ዙሪያ የሊጉ ክለቦች ላለፉት ሳምንታት የቪድዮ ስብሰባ ሲያደርጉ ነበር።\n\nየፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ደግሞ ሊጉን ለማጠናቀቅ ቆርጠው ተነስተዋል። ይህን ለማድረግ ደግሞ ቢያንስ 10 ገለልተኛ ሜዳዎች ያስፈለጋሉ ነው የሚሉት። ገለልተኛ ሜዳዎችን መጠቀም ያስፈለገው ደጋፊዎች ከሜዳ ውጪም ቢሆን እንዳይሰበሰቡ በማሰብ ነው ተብሏል።\n\nአልፎም የሚመረጡት ሜዳዎች ከፖሊስና የስፖርት ሜዳዎችን ደህንነት ከሚመረምር አካል ይሁንታ ያገኙ መሆን አለባቸው ተብሏል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መጋቢት ወር መግቢያ ላይ ነበር በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እንዲቆም የተደረገው።\n\nሁሉም የሊጉ ክለቦች የቀሩትን 92 ጨዋታዎች ለመጫወት ተስማምተዋል። የዚህ ዓመት ወድድር ይቋረጥ የሚል ሐሳብ ከየትኛውም ክለብ አልመጣም ተብሏል።\n\nየገንዘብ ክፍያው የተጠየቀው የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች በታሰበላቸው ጊዜ ባለመካሄዳቸው ነው። በተጨማሪም ሊጉ የሚቀጥል ቢሆን እንኳን ጨዋታዎቹ ያለ ተመልካች መካሄዳቸውና ከቴሌቪዥን ጣቢያዎች ጋር ስምምነት ከተደረሰበት ጊዜ ውጪ ስለሚካሄዱ ነው።\n\n• በኮሮናቫይረስ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ተፈላጊነታቸው የጨመረ 6 ምርቶች\n\n• በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች\n\nየፕሪምየር ሊግ ዋና ስራ አስፈጻሚው ሪቻርድ ማስተርስ በቅርቡ እንደገለጹት ደግሞ የዘንድሮው ሊግ የሚቋረት ከሆነ ክለቦች በአጠቃላይ እስከ 1 ቢሊየን ፓውንድ ኪሳራ ሊያጋጥማቸው ይችላል።\n\nገለልተኛ ሜዳዎች ላይ ጨዋታዎቹን መቀጠል በሚለው ሀሳብ አንዳንድ ክለቦች አልተስማሙም። የሊጉ ኃላፊዎችም ቡድኖቹን ለማሳመንና በተቻለ መጠን ጨዋታዎቹን በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ለማስጀመር እየሞከሩ ነው።\n\nእስካሁን ዋትፎርድ፣ አስቶን ቪላ እና ብራይተን ጨዋታዎቹን በገለልተኛ ሜዳ ማካሄድ የሚለውን ሀሳብ በይፋ የተቃወሙ ሲሆን በሜዳቸው ደህንነቱ የተጨበቀ ጨዋታ ማካሄድ እንደሚችሉ መንግስትን ማሳመን ይጠበቅባቸዋል።\n\nየሊቨርፑል ከተማ ከንቲባ ደግሞ ጨዋታዎቹ በገለልተኛ ሜዳ ተካሂደውም ሊቨርፑል የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ የሚያነሳ ከሆነ ደጋፊዎች በአንፊል ስታዲየም ዙሪያ ተሰባስበው ደስታቸውን ሊገልጹ እንደሚችሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል።\n\n ", "passage_id": "ea8f984d3218933d38a42ea444e47ce9" } ]
113a0537c5784a5e5d933806ab29d347
d72f0cca261bbd4f4d28a62fa25e7ecb
የአትሌቲክስ አሰልጣኞች የፈታኙ ወቅት ተሞክሮ
የዓለማችን ኮከብ አትሌቶች በዚህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ (ኮቪድ 19) በተስፋፋበት ወቅት በምን ሁኔታ ቀናቸውን እያሳለፉ እንደሚገኙ የስፖርቱን ዓለም ሰዎችና ሌላውን ማህበረሰብ ከማስተማር አኳያ በተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን እያገኘ መሆኑ ይስተዋላል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን የአትሌቲክስ የጀርባ አጥንት የሆኑትና አትሌቶችን ላሉበት ደረጃ ትልቅ ሚና የሚጫወቱት አሰልጣኞች ሥራቸውን በምን መልኩ እያከናወኑ እንደሚገኙ ከሥራቸውና ከቫይረሱ ባህሪ አኳያ ብዙዎች ጥያቄ ሲያነሱ ይስተዋላል፡፡ የዓለም አትሌቲክስም በድረ ገጹ በተለያዩ ዓለማት ቻምፒዮኖችን ያፈሩ አሰልጣኞች በዚህ ወቅት ሥራቸውን በምን መልኩ እየከወኑ እንደሚገኙ የተለያዩ ቅኝቶችን በማቅረብ ሌሎች እንዲማሩበት ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ በዓለም አትሌቲክስ ተሞክሯቸውን እንዲያጋሩ ከተመረጡት አሰልጣኞች መካከል አንዱ ደግሞ የዓለም ሁለተኛው የማራቶን ፈጣን ሰዓት ባለቤቱ ቀነኒሳ በቀለ አሰልጣኝ መርሻ አስራት ናቸው፡፡ አትሌቱ በሦስት ኦሊምፒኮች ተሳትፎው ወርቃማ ታሪክ እንዲጽፍ ከጀርባ በመሆን ከፍተኛውን ድርሻ የተጫወቱት አሰልጣኝ፣ በዚህ የውድድር ዓመት ኮከቡ አትሌት በለንደን ማራቶን የርቀቱን ክብረወሰን እንዲሁም በጃፓኗ ቶኪዮ ለማካሄድ በታሰበው ኦሊምፒክ በማራቶን አራተኛውን ድል ለማስመዝገብ ትልቅ ዝግጅት አድርገው ነበር፡፡ የኦሊምፒኩንና የተጠባቂውን ለንደን ማራቶን መራዘም ተከትሎም ቀነኒሳ ከምንጊዜም ተቀናቃኙና የወቅቱ የማራቶን የዓለም ባለ ክብረወሰን ከሆነው ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ ጋር በተንቀሳሳሽ ምስል የታገዘ ውይይት ማድረጋቸውን ኤንኤን ትሬኒንግ የተባለው ድረገጽ አስመልክቷል፡፡ በዚህም አትሌቶቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በቤታቸው በመሆን የግል እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አሰልጣኞች ዓለም ውጥረት ውስጥ በገባበት በዚህ ወቅት ሥራቸውን በምን መልኩ ይከውናሉ፣ ቀናቸውንስ እንዴት ያሳልፉታል፣ አትሌቶች ከልምምድ እንዳይርቁና ብቃታቸውን ጠብቀው እንዲቆዩ የአሰልጣኞቹ ሚና በምን መልኩ አትሌቶች ጋር እየደረሰ ይገኛል? ለሚለው የአምስትና አስር ሺ ሜትርን ክብረወሰን ለረጅም ዓመት ሳያስደፍር ይዞ የቆየው አትሌት ቀነኒሳ አሰልጣኝ ተሞክሯቸውን ያጋራሉ፡፡ አሰልጣኝ መርሻ የመጀመሪያው ቁም ነገር ዓለም የገጠማትን ይህንን ወጀብ በምን መልኩ ማለፍ ይቻላል? የሚለውን ማሰብ ቀዳሚ እንደሆነ እምነታቸው ነው፡፡ ወረርሽኙ በውድድሮች ላይ እንዲሁም በቡድን በሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ የራሱን አሉታዊ አስተዋፅዖ እንዳሳደረ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ጊዜውን በጥንካሬ ማሳለፍ የግድ ነው ይላሉ፡፡ ሰልጣኞቻቸውም በዚህ መልክ መቆየት እንዳለባቸው ይጠቁማሉ፡፡ በንግግራቸውም ‹‹ሁሉም አትሌቶቼ ጠንካራና በባህሪያቸውም ለሌሎች ምሳሌ መሆን ይገባቸዋል፤ እንደ አሰልጣኝ የምነግራቸውም ይህ ጊዜ ያልፋል ብዬ ነው›› ብለዋል፡፡ ምንም እንኳን በዚህ ወቅት ሁሉም ውድድሮች ከተያዘላቸው መርሐ ግብር ሽግሽግ እንዲደረግባቸውና ሌሎቹም የተሰረዙ ቢሆንም አትሌቶች ልምምዳቸውን ማቆም እንደማይገባቸው አሰልጣኝ መርሻ ይመክራሉ፡፡ አትሌቶች የሚሠሩት እንቅስቃሴም ለጥንካሬ እና አቅምን ለማዳበር የሚረዱ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ ይህንንም ሲያብራሩ ‹‹ለተወሰኑ ጊዜያት ውድድሮች ስለሌሉ ጠንክሮ መሥራት ተገቢ የሆነበት ወቅት ነው፡፡ በመሆኑም በእኔ ስር ለሚሰለጥኑ ሁሉም አትሌቶቼ መሥራት የሚገባቸውን እየጠቆምኳቸው ነው፡፡ ወቅቱ ጥንካሬን የሚያዳብሩበት ነው፤ በደንብ እንዲሠሩም ዕድል ይሰጣቸዋል›› ብለዋል፡፡ ከዓለም አትሌቲክስ ጋር ቆይታ ያደረጉት ሌሎች አሰልጣኞችም በተመሳሳይ ለአትሌቶቻቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የማራቶንና ግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረወሰን ባለቤቶቹ ኬንያዊን ኢሉድ ኪፕቾጌ እና ጆፈሪ ካምዎረር አሰልጣኝ ፓትሪክ ሳንግም ተሞክሯቸውን አጋርተዋል፡፡ በርካታ አትሌቶች በቡድን የሚያሰለጥኑት አትሌቱ ቡድናቸውን የበተኑት ከወር በፊትም ነበር፡፡ በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ታግዘው አትሌቶቻቸውን ቢያገኙም ለውጣቸውን የመመልከት ዕድል አለማግኘታቸው ፈተና እንደሆነባቸው ጠቁመዋል፡፡ ብራዚላዊው አሰልጣኝ ሞራ ኮት አትሌቶች ቀድሞ በነበራቸው መነቃቃት ማቆየት አዳጋች መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ አሰልጣኞችና አትሌቶች መልካም መግባባት ያላቸው ከሆነም በሚያወጧቸው እቅድ መሰረት ባሉበት ሆነው በእንቅስቃሴ ላይ መቆየት ይችላሉ፡፡ ቢሆንም ይህ ጊዜ ሲያልፍ ምን ሊከሰት እንደሚችል ለመገመት አዳጋች መሆኑን አልሸሸጉም፡፡ ‹‹አዲስ ልምድ እንደምናገኝና ይህ ሁኔታ ለበጎ እንደሚሆንም ተስፋ አለኝ›› ይላሉ፡፡ የኒውዝላንድን አትሌቶች ሲያዘጋጁ የቆዩት አሰልጣኝ ዳሌ ስቴቨንሰን በበኩላቸው አትሌቶቻቸውን በስነልቦና እያገዙ እንደሚገኙና በቅርቡ ወደነበሩበት እንደሚመለሱ እየነገሯቸው መሆንኑን ገልጸዋል፡፡ ወቅቱ ወደኋላ የሚመለሱበት ሳይሆን በጥሩ ሞራል እንደ ሙሉ ጊዜ አትሌት ጊዜያቸውን መጠቀም እንዳለባቸውም ምክረሃሳብ ሰጥተዋል፡፡ አሰልጣኞችም አትሌቶቻቸው በምን መልኩ እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለባቸው ማሳየት ተገቢ ነው የሚሉት አሰልጣኙ፤ በአንዳንድ አትሌቶቻቸው መደነቃቸውንም ይናገራሉ፡፡ አትሌቶች በአካባቢያቸው በሚያገኟቸው ቁሳቁስ ስልጠናቸውን እያደረጉ እንደሚገኙና በዚህም እንዲቀጥሉ አሳስበዋል:: ሌላኛው አሰልጣኝ ብራም ሶም አትሌቶች ከሁኔታዎች ጋር ራሳቸውን በማስማማት በዝግጅት ላይ መቆየት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡ ከአትሌቶች ጋር ፊት ለፊት በመተያየት ብቃታቸውን መገምገም ባይቻልም አዲስ ተሞክሮ እንዳስገኘላቸውም አክለዋል፡፡ አዲስ ዘመን ሚያዝያ 28/2012ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=31772
[ { "passage": "አዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ያላትን ስምና ዝና እንዲሁም ውጤት ለማስቀጠል ሲባል በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የተለያዩ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ውድድሮችን ለማድረግ ቅድመ ማጣሪያ ውድድሮችን ማድረግ የተለመደ ተግባር ሆኖ ቆይቷል፡፡ በየዓመቱ ከሚደረጉ ቅድመ ማጣሪያ ውድድሮች አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ይጠቀሳል፡፡ በኦሮሚያ ክልል አሰላ ከተማ ላይ ተተኪ አትሌቶችን ለማግኘት ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች አትሌቶች ክለቦቻቸውን በመወከል ያላቸውን አቅም ማሳየት ከጀመሩ ሰባተኛ ዓመታቸውን ይዘዋል፡፡ ዘንድሮ ለ7ኛ ጊዜ የሚካሄደው ሻምፒዮናው በትናንትናው እለት በአሰላ አረንጓዴው ስታዲየም በይፋ ተጀምሯል።የውድድሩ ውጤታማ አትሌቶች የውድድሩ ዓላማ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲካሄዱ የወጣቶች ውድድር አገራቸውን ወክለው የሚካፈሉ እንደሆነ የተጠቀሰ ሲሆን ፤ቀጣይ ለአገሪቱ አትሌቲክስ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እንደሆነም ጭምር መሆኑን ተነግሯል። የሻምፒዮናው አላማ ይሄንን መልክ የያዘ ቢሆንም ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ከውድድሩ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማግኘት ያለመ ቢሆንም ፤የዕድሜ ተገቢነት ችግር አሁንም ሊፈታ ያልቻለ ጉዳይ እንደሆነ የተለያዩ ባለሙያዎች እየተናገሩ ይገኛሉ።ፌዴሬሽኑም ይህን መቆጣጠር አስቸጋሪ እንደሆነበትና ክልሎችና ክለቦች ሲጠየቁ ክለብ ሲገባ ዕድሜውን እንዲቀንስ ተደርጎ የተመዘገበበትን ሀሰተኛ የሆነ ማስረጃ እንደሚያቀርቡ በተደጋጋሚ ሲነገር ነበር። በዚህ ምክንያት ዕድሜያቸውን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ መሆኑ ይነሳል። ከዚህ በመነሳትም የዘንድሮው የሰባተኛው ከ20 ዓመት በታች የታዳጊዎች ሻምፒዮና ከዚህ ችግር የጸዳ በሆነ መልኩ ተጀምሮ የሚጠናቀቅ ስለመሆኑ ጥያቄን አስነስቷል። ሻምፒዮናው ከትናንት ማለዳ ጀምሮ መካሄድ ጀምሯል።በእለቱ ከተካሄዱ ውድድሮች የስሉስ ዝላይ ሴቶች ከኦሮሚያ ክልል እንደቴ ሮቤ 11.67 ሜትር በመወርወር አንደኛ ስትሆን ፣ ኡጁሉ ኦዶላ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 11.64 በመወርወር ሁለተኛ ፣ ኩለኒ ድሪባ ከኦሮሚያ ክልል 14.54 በመወርወር ሶስተኛ ሆነዋል። ዲስከስ ውርወራ ወንዶች የሲዳማ ቡና ለማ ከተማ 47.44 በመወርወር አንደኛ ሲሆን፣ የመከላከያው ጌታቸው ተመስገን እና የአማራ ክልሉ አየነው ኮሴ 47.23 እና 42.80 በመወርወር ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። በሴቶች ዲስከስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ መሪያምመዊት ፀሀዬ 38 .73 ሜትር በመወርወር አንደኛ ሆናለች። ማርታ በቀለ ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ 34.99 ሜትር በመወርወር ሁለተኛ ፣ ትንጓደድ ተሰማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከንግድ ባንክ 32.89 በመወርወር ሶስተኛ ሆናለች። የወንዶች 10 ሺ ሜትር ሌላው በትናንትናው እለት የተካሄደ ውድደር ሲሆን ጸጋዬ ኪዳኑ 29፡34፡27 ሰዓት በመግባት ከመስፍን ኢንጂነሪንግ አሸናፊ ሲሆን እርሱን ተከትሎ ሚልኬሳ መንገሻ ከሰበታ ከነማ ክለብ 29 ፡35፡65 ሁለተኛ እንዲሁም ወርቅነህ ታደሰ ከኦሮሚያ ክልል 29፡39፡98 ሰዓት አስመዝግቧል።በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም የሚካሄደው ሻምፒዮናው ለቀጣይ አራት ቀናት በድምቀት የሚቀጥል መሆኑን ታውቋል። ከጥር 15 እስከ 19 ቀን 2011 ዓ.ም በሚካሄደው ውድድሩ 9 ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም 34 የተለያዩ_ ክለቦችና ተቋማት ተካፋይ ሆነዋል።አዲስ ዘመን ጥር 16/2011ዳንኤል ዘነበ", "passage_id": "c90b10f6d6ef9e95a9b4a3ed0f3565c4" }, { "passage": " በኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ስፖርት ታሪክ ውስጥ አንቱታን ማትረፍ ችለዋል። የእጅ ኳስ ስፖርትና እርሳቸው የሚነጣጠሉ አለመሆኑን ብዙዎች ይመሰክሩላቸው። ለእጅ ኳስ ስፖርት ጥልቅ ፍቅር ያላቸው ኢንስትራክተር አሰፋ ገለቱ። በእጅ ኳስ ስፖርት በብሄራዊ ቡድን ደረጃ ተጫውተው ከማለፍ ባሻገር በርካታ ወጣት አሰልጣኞችን ማፍራት መቻላቸው ለዚህ ክብር እንዲበቁ አድርጓል። የኢንስትራክተር አሰፋ የስፖርት ህይወት ጅማሮ ከ40 ዓመታት በፊት እንደነበር እንዲህ ይናገራሉ። «ስፖርታዊ እንቅስቃሴን የጀመርኩት በሰፈር ውስጥ ሲሆን ከልጅነት ጀምሮ ንቁ ተሳትፎ አደርግ ነበር። በስፖርቱ የነበረው ተሳትፎ ግን እግር ኳስን ያስቀደመ ነው።›› ኢንስትራክተር አሰፋ ከእግር ኳሱ እኩል ቅርጫት ኳስ እና እጅ ኳስን ይጫወቱም ነበር። በተለያዩ ስፖርቶች ተወጥሮ የነበረው የስፖርት ፍቅር በአንድ አጋጣሚ ነበር ወደ እጅ ኳሱ ብቻ ሊያመዝን እንደቻለ የሚናገሩት፡፡ ‹‹በወቅቱ ከአዲስ አባባ ፖሊስ የእጅ ኳስ ቡድን ጋር በመሆን እጅ ኳስ እጫወት ነበር። ከቡድኑ ጋር አደርገው በነበረው እንቅስቃሴ ከቡድኑ ተጫዋቾች ብሎም አሰልጣኞች በእጅ ኳሱ እንድገፋበት አድርጎኛል። በዚህ ግፊት የአዲስ አበባ ፖሊስ የእጅ ኳስ ቡድንን በመቀላቀል ወደ እጅ ኳስ ስፖርት ሙሉ ለሙሉ መግባት ቻልኩ›› ይላሉ። ኢንስትራክተር አሰፋና እጅ ኳስ በዚህ መልኩ ትውውቅ ካደረጉ በኋላ በበርካታ የከተማ አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ውድድሮች ላይ የመጫወት እድሎችን አገኙ። በእጅ ኳሱ የተጫዋችነት ሂደት ውስጥ ከክለብ ባለፈ እስከ ብሔራዊ ቡድን ውክልና ዘልቋል፡፡ ለኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ብሄራዊ ቡድን በመመረጥ ለአምስት ዓመታት እስከ መጫወትም ደርሰዋል፡፡ ኢንስትራክተር አሰፋ በተጫዋችነት ብቻ 20 ዓመታት ማሳለፍ የቻሉ ሲሆን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ «በተጫዋችነት ዘመኔ የማይቆጩኝን 20 ዓመታትን አሳልፌያለሁ። በስፖርቱ ሀገሬን በመወከል በብሄራዊ ቡድን ደረጃ የተጫወትኩበት እነኚህ ዓመታት ለእኔ ልዩ ኩራቴና ትዝታዎቼ ነበሩ» ሲሉ ያለፈውን የተጫዋችነት ዘመን ያስታውሳሉ፡፡ ለሀገር ክብርና ፍቅር እንዳላቸው ደጋግመው የሚናገሩት ኢንስትራከተር አሰፋ የተጫዋችነት ዘመናቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ አሰልጣኝነት ነበር የተሸጋገሩት። ኢንስትራከተር አሰፋ በእጅ ኳሱ አሰልጣኝ በመሆን በአዲስ መንፈስ እንዴት ብቅ እንዳሉ ሲያስታውሱ፤ «የእጅ ኳስ አሰልጣኝነትን የአዲስ አበባ ፖሊስ እጅ ኳስ ቡድን በመያዝ ነበረ የተጀመረው። ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በርካታ ጊዜያትን ካሳለፍኩኝ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻዬ የነበረው ኦሜድላ ነበር» ይላሉ። የኦሜድላን እጅ ኳስ ቡድን ወደ ማሰልጠኑ መሸጋገራቸው ለስፖርቱ የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ እንዲጨምር እንዳደረገላቸው ይናገራሉ። በኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ታሪክ በተለይ በ70ዎቹ ውስጥ በጥንካሬያቸው ከሚጠቀሱት ክለቦች መካከል ኦሜድላ ዋነኛው ነው። ከክለቡ ጋር በነበራቸው ቆይታ ስፖርቱን ወደ ፊት ማራመድ የሚያስችሉ ስራዎችን ለመስራት እንዳስቻላቸው ኢንስትራክተር አሰፋ ይናገራሉ፡፡ በአሰልጣኝነት ቆይታቸው ጊዜ እየተመዘገቡ ባሉ ውጤቶች ደስተኛ የነበሩት ኢንስትራክተር አሰፋ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የእጅ ኳስ ስፖርት መዳከምና ውጤት አልባ እየሆነ መምጣት በቁጭት እንዲሞሉ ያደረጋቸው ነበር። በወቅቱ ስፖርቱ ረጅም ዓመት እንደቆየ ባለሙያ መፍትሄ መፈለግ እንደሚገባ ለሚመለከተው አካል ሃሳብ እስከ ማቀበል መድረሳቸውን ያስታውሳሉ፡፡ በሃሳብ ብቻ መወሰን ግን አልፈለጉም ነበር ። ከኦሜድላ ክለብ ጋር የነበራቸውን ጉዞ በመግታት መፍትሄው ላይ ወደ ማነጣጠር አዘነበሉ፡፡ ስፖርቱን መሰረት አሳጥቶ ውጤት አልባ ያደረገው የተተኪ ችግር እንደሆነ በማጥናት ታዳጊዎች ላይ መስራት ይጀምራሉ፡፡ በ1990 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ውጤት ያጣውን የእጅ ኳስ ስፖርት ለመታደግ ታዳጊዎችን መሰረት ያደረገውን ተግባር በቁጭት ጀመሩ። ከአዲስ አበባ እጅ ኳስ ፌዴሬሽንና ከሙያ አጋሮቻቸው ጋር በመቀናጀት ታዳጊዎችን በፕሮጀክት ደረጃ በማቀፍ ስልጠናዎችን በስፋት መስጠት ተያያዙት፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥም ውጤታማ ስራዎች ማከናወን ቻሉ፡፡ የኢንስትራክተር አሰፋ ታዳጊዎችን መሰረት ያደረገ ስልጠና በትምህርት ቤቶች ላይ ትኩረት አድርጎ ወደ መስራት ሽግግር ያደረገ ነበር። በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የአንድኛና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን በመመልመል የእጅ ኳስ ስፖርት ወደ ማሰልጠን ነበር የተሸጋገሩት። ኢንስትራክተር አሰፋ ትምህርት ቤቶች ላይ መሰረት በማድረግ በርካታ ታዳጊዎችን አሰልጥነው ማስመረቅ እንደቻሉ ይናገራሉ። «የአምናውን ብቻ ብናስታውስ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ የሆኑ 300 ታዳጊዎችን በፕሮጀክት ደረጃ በማሰልጠን ተመርቀዋል።በዘንድሮ ዓመትም በተመሳሳይ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ከ20 በላይ መንታዎች ሰልጠነው ተመርቀዋል» ሲሉ ይናገራሉ። በእጅ ኳስ ስፖርት ውስጥ ትልቅ አሻራ ማሳረፍ የቻሉት ኢንስትራክተር አሰፋ፤ የስፖርት ህይወት ጉዞን አስደናቂ የሚያደርገው ለስፖርቱ እድገት ታዳጊዎችን መሰረት አድርጎ መስራት እንደሚበጅ በማመን በሰሩት ውጤታማ ተግባር የተቸራቸው ምስጋና ሳያባራ፤ በሀገራችን ባልተለመደ መልኩ መስማት የተሳናቸውን ዜጎች እጅ ኳስ ለማሰልጠን የሚያስችል ንድፈ ሀሳብ በመያዝ መስማት የተሳናቸውን ታዳጊዎች ማሰልጠን መጀመራቸው ነው፡፡ ኢንስትራክተር አሰፋ ለዚህ እንደመነሻ የነበራቸውን አጋጣሚ ሲያስረዱ፤« በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ስልጠና በሚሰጡበት ወቅት የታዘብኳቸው ነገሮች ወደዚህ እንድገባ ያደረጉኝ። ለተማሪዎች እጅ ኳስ ስልጠና በምሰጥበት ወቅት እዛ አካባቢ መስማት የተሳናቸው እኔ የምሰጠውን ስልጠና ቁጭ ብለው ይመለከቱ ነበር። በእነዚህ ታዳጊዎች ተግባር ውስጤ ተነሳሳ። ስልጠናውን ወደ መስጠት ከመሸጋገሬ በፊት ግን ከተማሪዎቹ ጋር ለመግባባት እንድችል የምልክት ቋንቋ መቻል አስፈላጊ ነበር። በመሆኑም ቋንቋውን ለሶስት ወራት ያህል ተማርኩ። በዚህ መሰረት በአዲስ አበባ መስማት የተሳናቸውን ተማሪዎች ከሚያስተምሩ ሶስት ትምህርት ቤቶች ጋር በመነጋገር እንዲሰለጥኑ ማድረግ ችያለሁ» ይላሉ፡፡ ኢንስትራክተር አሰፋ በእጅ ኳስ ስፖርት ውስጥ ያከናወኗቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት ቢሆኑም እሳቸው ዛሬም በአዲስ ወኔ ለመስራት ያሰቧቸው ስራዎች መኖራቸውን ይናገራሉ። «ስፖርት ለእኔ ህይወቴ ነው፤ ልጅነቴን ፣ ወጣትነቴን ከእጅ ኳስ ስፖርት ሳልነጠል አሳልፌያለሁ። ዛሬም ነጭ ፀጉር አብቅዬም ከስፖርቱ መለየት አልሻም። ስፖርቱን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ አማራጭ ያልኳቸውን ተግባራት ለማከናወን አልተኛም» የሚል ጽኑ እምነት አላቸው። ስፖርቱን ለማሳደግ እንደ እርሳቸው ሁሉ በርካታ ባለሙያዎች ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸውና ለዚህ ደግሞ ስፖርቱን ከሚመሩት አካላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ የሚገባ መሆኑን ማስገንዘብ እንደሚፈልጉ ያብራራሉ፡፡አዲስ ዘመን መጋቢት 15/ 2012 ዳንኤል ዘነበ", "passage_id": "181f65790ddfc27c25d67d6cdd582fd3" }, { "passage": "የምሥራቅ አፍሪካውያን የባህል ስፖርት የሆነው በተለይም ለኢትዮጵያ እና ኬንያ የ10ሺ እና 5ሺ ሜትር ሩጫ ታላቅ ትርጉም ያለው ነው። ያሉበት የመልካምድር አቀማመጥና የአየር ጸባይ ለስኬት እንዳገዛቸው በባለሙያዎች ይነሳል። በግልጽ እንደሚታየው ባለፉት ዓመታት በርቀቶቹ በተካሄዱ ውድድሮች የበላይነቱን የያዙት የሁለቱ ሀገራት አትሌቶች ናቸው። ይህ ሁኔታ ደግሞ እንደ ባህል ስፖርት እንዲታይ ምክንያት ሆኗል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን በእነዚህ ርቀቶች የሚካሄዱ ውድድሮች በዓለም ላይ እየተመናመኑ መጥተዋል። የ10ሺ ሜትር ሩጫ በብቸኝነት የሚታየው በዓለም ሻምፒዮና እና ኦሊምፒክ ላይ ብቻ ሲሆን፣ በዳይመንድ ሊግ ይካሄድ የነበረው የ5 ሺ ሜትር ሩጫም ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ እንደማይካሄድ ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር አስታውቋል። ይህም ሀገራቱን ያስቆጣ፤ ቅሬታዎቸውንም በማንሳት ውሳኔውን ለማስቀልበስ የተለያዩ እርምጃዎችን በመወሰድ ላይ ይገኛሉ። ባሳለፍነው ወር በዴንማርክ በተካሄደው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ ጉዳዩን የተቃወሙት ኢትዮጵያ እና ኬንያ በተናጠል የዓለም አቀፉን ማህበር ፕሬዚዳንት ሰባስቲያን ኮን አናግረዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉም ከፕሬዚዳንቱ ጋር ቆይታ አድርጋለች። በውይይቱ ላይ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል የ5ሺህ ሜትር ውድድር አንዱ ሲሆን በሻምፒዮናው ላይ የተካፈሉ አፍሪካውያን አትሌቶችና ደጋፊዎች የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበር ውሳኔን በመቃወም ድምጻቸውን አስተጋብተዋል። በሕይወት ዘመኔ መሮጥ የምፈልገውና ውጤት ለማስመዝገብ የምጓጓው በ5ሺ ሜትር ነበር ያሉት የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አትሌት ኮማንደር ማርቆስ ገነቲ፤ አገራችን የምትታወቅበት የረጅም ርቀት የአትሌቲክስ ስፖርት ከውድድር ውጪ እየሆነ መምጣቱ ልብ የሚሰብርና አሳዛኝ እንደሆነ ገልጸዋል። ነገር ግን ጉዳዩን እስከ መጨረሻው ተከታትለን የምንችለውን በማድረግ በተለይ በሚቀጥለው ዓመት የ5ሺ ሜትር ውድድር ከዳይመንድ ሊግ ውጭ እንዳይሆን እንደማህበር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የምንችለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ነን ይላሉ። ከአፍሪካ ሀገራት በተለይ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ታንዛኒያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሞሮኮና ኡጋንዳ በ10 ሺና በ 5 ሺ ሜትር ሩጫ ለዘመናት በዓለም አደባባይ ላይ ገነው መታየት ችለዋል። ነገርግን እነዚህ ውድድሮች ከጨዋታ ውጪ እየሆኑ መምጣታቸውን ተከትሎ የሀገራቱ አትሌቶች በዓለም መድረክ ውጤት ለማስመዝገብ ችግር ውስጥ ገብተዋል ብለዋል። የ10 ሺ እና 5ሺ ሜትር ርቀቶች ከውድድር ውጪ እየሆኑ መምጣቱ በተለይ የአገራችን አትሌቶች ተወዳድሮ ሚኒማ የሚያሟላበት ውድድር እያገኙ ባለመሆኑ ውጤት እየራቀን ነው ያለው። ከዚህ በፊት በኢንተርናሽናል ውድድር የሚካፈሉ አትሌቶች በኢትዮጵያ ሻምፒዮና ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት ስምንት አትሌቶች ለዓለም አቀፍ ውድድር የሚመርጡት መንገድ ነበር። ነገር ግን የ10ሺ ሜትር ውድድር ቀደም ብሎ ከተለያዩ ውድድር ውጪ እንደሆነ ይታወቃል። እንዲሁም የ5ሺ ሜትር ውድድር እአአ ከ2020 በኋላ ከዳይመንድ ሊግ ለማስወጣት በሂደት ላይ ናቸው። ስለዚህ በዳይመንድ ሊግ ላይ እነዚህ ውደድሮች ካልተካሄዱ ውድድሮቹን ስፖንሰር የሚያደርጋቸው ስለሌለ በሌሎች ውድድሮች ላይ አይካሄዱም ማለት ነው። ይሄ ከሆነ ደግሞ እኛ አፍሪካውያን ውድድሮቹ ውጤት የምናስመዘግብባቸው በመሆኑ አትሌቶቻችን ከውድድር ውጪ እየሆኑ ይመጣሉ። የአፍሪካ መለያ የሆኑት የ5 ሺ እና የ10 ሺ ሜትር የረጅም ርቀት ውድድሮች ከዓለም የውድድር መድረኮች መሰረዛቸው በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ክለቦች በረጅም ርቀት ስፖርት ታቅፈው በሥልጠና ላይ ያሉ አትሌቶች ክለቦች ሊያሰናብቱ ወይም ሊበትኑን ይቸላሉ የሚል ስጋት ተጋርጦባቸዋል ብለዋል። ነጮች በነዚህ ውድድሮች አፍሪካውያንን መቋቋም ስላልቻሉ ቀስበቀስ ስፖርቱን ከተሳትፎ ውጭ እያደረጉ ይገኛሉ ያሉት ኮማንደሩ፤ ጥቁሮች በረጅም ርቀት ውድድሮች ከመንገሳቸው በፊት አውሮፓውያን በርቀቱ ነግሰው እንደነበር ታሪክ ያስረዳል። ነገርግን ጥቁር አፍሪካውያን በተለይ ምሥራቅ አፍሪካዎች ጠንክረው በመስራት እነዚህን ውድድሮች የግላቸው ለማድረግ ችለዋል። ምሥራቅ አፍሪካውያንም ለዘመናት በመፈራረቅ በነዚህ ውድድሮች ገድል መስራት ችለዋል። ስለዚህ የአገራችንና የሌሎች አፍሪካውያን አትሌቶች ከዚህ ታሪክ በመነሳት ነጮች የአጭር ርቀት ሩጫ የግላችን ነው ብለው የሚኩራሩበትን ታሪክ ለመቀየር ጠንክሮ በመስራት በነዚህ ርቀቶች ላይ ዳግም በመንገስ ብቃታቸውን ሊያስመሰክሩ ይገባል። ኮማንደሩ አክለውም፤ የአጭር ርቀት ሩጫ ስልት የሚጠይቅ፣ የተለያዩ መሠረተ ልማቶችና ቁሳቁሶች የሚያስፈልጉት እንደሆነ ይታወቃል፤ ሌሎች አፍሪካውያን ሀገሮች ችግሩን ቀድመው በመረዳት በአጭር ርቀት ሩጫ ተተኪና ተወዳዳሪ አትሌቶችን ለማፍራት ወደታች ወርደው ግንዛቤን በመፍጠር በአጭር ርቀት ሩጫ ላይ ጠንክረው በመስራት በዓለም መድረክ ውጤት እያስመዘገቡ ይገኛሉ። ለአብነትም የአትሌቲክስ ስፖርት ተቀናቃኞችን ጎረቤታችን ኬንያን ብናይ፤ የረጅም ርቀት ሩጫዎች ከውድድር ውጪ እየወጣ መሆኑንና በአጭር ርቀት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት ወደታች ወርደው ግንዛቤውን በመፍጠርና ጠንክረው በመስራት በዓለም መድረክ በተካሄዱ የአጭር ርቀት ውድድሮች ላይ በመሳተፍ፤ በ3ሺ ሜትርና በሌሎች የአጭር ርቀት ውድድሮች የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት እየቻሉ ነው። በተጨማሪም ደቡብ አፍሪካ ናይጀሪያ ሞሮኮ የመሳሰሉ የአፍሪካ ሀገራት የኬንያን ፈለግ በመከተል በአጭር ርቀት ሩጫዎች ላይ ጠንክረው በመስራት ላይ ሲሆኑ፤ ጥሩ ውጤት እያስመዘገቡ መጥተዋል። አገራችን የሌሎች አፍሪካ ሀገሮችን ፈለግ በመከተልና በአጭር ርቀት የተሻለ ውጤትና ልምድ ያላቸውን ሀገሮች አሠራር በመቅሰም፤ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ፣ የስፖርት ማህበረሰቡና የሚመለከታቸው አካላት አንድ ላይ በመሆን ወደታች ወርደው በክልል፣ በዞን፣ በወረዳ እና በቀበሌ ደረጃ ለአትሌቶች ግንዛቤውን በመፍጠር ስፖርተኞች በአጭር ርቀት እንዲፈጠሩ የማድረግ ሥራ መስራት እንዳለባቸው ኮማንደሩ አሳስበዋል። በአትሌቲክሱ\nስናስመዘግብ\nየቆየነው\nውጤት ተጠብቆ እንዲቀጥል በመላ አገሪቱ በአጭር ርቀትና በሌሎች ዘርፎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ለአጭር ርቀት ሩጫ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይኖርበታል። ነገር ግን ርቀቱ አቅምና ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ስልትና ብዙ ድጋፍ የሚያስፈልገው በመሆኑ፤ ፌዴሬሽኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በስፖርቱ ውጤት እንዲመጣ ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል። በአጠቃላይ ሀገራችን የምትታወቅበት የረጅም ርቀት ሩጫዎች ከውድድር ውጪ እየሆኑ መምጣታቸውን ለአትሌቶችና ለስፖርት ማህበረሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ መስራት ያስፈልጋል። ስለዚህ ግንዛቤውን በመፍጠር በርቀቱ ላይ በስፋት ጠንክሮ በመስራት ተተኪና በዓለም መድረክ ተወዳዳሪ የሆኑ ስፖርተኞችን እንደ ሀገር ማፍራት ያስፈልጋል ብለዋል ኮማንደሩ። ኢትዮጵያ ልክ እንደ ማራቶን፣ ግማሽ ማራቶን፣ 10ሺ፣ 5ሺ የመሳሰሉ የስፖርት ዓይነቶች ላይ ጠንከር ያለ ሥልጠናዎች በማድረግና ከታች ጀምሮ ተተኪ ስፖርተኞችን በማፍራት በኩል ያላትን ልምድ በመጠቀም በአጭር ርቀት ሩጫም ጠንክራ ሥራን መስራትና እንደ ሌሎች የአፍሪካ አገራት ውጤት ማምጣት ያለባት በመሆኑ አትሌቶች ወደ አጭር ርቀት ሩጫ በመምጣት ውጤት ለማስመዝገብ መስራት ያለባቸው አሁን ነው። በተጨማሪም 10ሺ እና\n5ሺ ሜትር ሩጫዎች የባህል ስፖርቶቻችን ናቸው ያሉት ኮማንደሩ፤ ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ አትሌት በምን ውድድር መሳተፍ ትወዳለህ ቢባል በ5ሺ\nወይም በ10ሺ ሜትር\nሩጫዎች ነው የሚለው። ምክንያቱም ከጥንት ጀምሮ ብርቅዬ አትሌቶቻችን በዓለም መድረክ በነዚህ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ታሪክ በመስራት የሀገራቸውን ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርገው ማውለብለብ ስለቻሉ። ስለዚህ የመገናኛ\nብዙኃን የስፖርት ቤተሰቡ\nበአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ\nከአትሌቶቹና ከፌዴሬሸኑ ጎን በመሆን\nየአገሪቱ የአትሌቲክስ ስፖርት\nእንዲያድግ መታገል አለበት።\nእንዲሁም የ5ሺ ሜትር\nሩጫ በመጪው ዓመት\nከዳይመንድ ሊግ እንዳይወጣ\nለአንድ ተቋም ብቻ የምንሰጠው\nጉዳይ ስላልሆነ ተቃውሞአችን\nለዓለም እንዲሰማ ሁሉም\nባለድርሻ አካላት በተባበረ\nክንድ የበኩሉን እንዲወጣ\nኮማንደሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 4/2011በሶሎሞን በየነ ", "passage_id": "3b22faa53c14ac23a31d3ed39c507e9b" }, { "passage": "ስልጠናው ብዙ ጊዜ በቃላት ብቻ ታጅቦ ይሰጥ ከነበረው\nበእጅጉ የተሻለ እና በሥራ ላይ ለሚገኙ አካላት እውቀት የሚያስጨብጥ እንደሆነ ነው የምትናገረው፡፡ በተለይ ደግሞ በርካታ የዘርፉ\nተዋናዮች በአንድ መድረክ ላይ ሰፊ ውይይትና ረጅም ቀናትን የወሰደ ምክክር ያደረጉ ሲሆን፤ በቀጣይ ይህን እውቀት በየተቋማቸውና\nበሥራ ላይ የሚተገበር ከሆነ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚመዘገብ ተስፋ ታደርጋለች፡፡ በእርሷ እምነት መሰል ስልጠናዎች መነቃቃትን ከመፈጠርም\nበላይ ክፍተቶችን በሚገባ ለመለየትና ባለድርሻ አካላት በቀጣይ በጋራ በሚያከናውኗቸው ተግባራት ላይ እንዲያተኩሩ ብሎም ለችግሮችም\nመፍትሔ ለማበጀት ዓይነተኛ መንገድ እንደሆነ ትገልጻለች፡፡ ተቋማትም ስልጠናዎችን ለመስጠት ሲያስቡ በተዋቡ\nቃላት እና ‹‹ፓወር ፖይንት›› የታጀበ ድግግሞሽ ወጥተው በተግባር የተደገፈ ስልጠና ቢከተሉ አገሪቱ የምትፈልገውን ለውጥ ለማምጣት\nመሰረት ይጥላል የምትለው ከባቱ ከተማ የመጣችው ወይዘሮ በሻሼ አዮ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት\nማናጅመንት ኢንስቲትዩት ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ጋር በመተባበር 400 ለሚሆኑ ዘርፉን ለሚመሩ አመራሮች፣\nሥራ ተቋጮች፣ አማካሪዎችና የምህንድስና ባለሙያዎች ከጥር 20 እስከ 30 ቀን 2011 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ሲያካሄድ የነበረው ተግባር\nተኮር ስልጠና ትናንት በተጠናቀቀበት ወቅት ነው፡፡ አቶ ሚካኤል አሰፋ በቢሾፍቱ ከተማ የኮንስትራክሽን\nባለሙያ ሲሆን፤ ስልጠናው በብዙ መንገድ ልዩነቶችን የሚያመጣ እንደሆነ ነው የሚናገረው፡፡ በተለይም ደግሞ በተቋራጭ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና\nአማካሪዎች መካከል ያለውን አለመግባባት መቀነስ፤ የኮንስትራክሽን አስተዳደር ለማዘመንና፤ የተንዛዛ የጨረታ ሂደትና የመንግሥት ሀብት\nከብክነት ለመታደግ ትልቅ ሚና ይኖረዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በግንባታ ላይ የሚሳተፉ አካላት የተቀናጀ አሠራር ዘርግተው ለመሥራት\nማሟላት የሚጠበቅባቸውን ብቃትና ታማኝነት ብሎም ተነሳሽነት እንዴት እንደሚመጣ የሚያሳይ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ፕሮጀክቶች\nላይ የዋጋ መዋዠቅ፣የዲዛይን መለዋወጥና የጊዜ ብክነትን ለማስቀረትም ሚናው የላቀ እንደሆነ ይነገራል፡፡ የባሌ ዞን ኮንስትራክሽን ጸህፈት ቤት ኃላፊ አቶ\nሙሎ ዱሬቲ በበኩላቸው፤ ስልጠናው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች እንዳለው ሁሉ በአገሪቱ የሚካሄደው ግንባታና ፖለቲካዊ ውሳኔ የሚፈልጉ አሠራሮችም\nበኮንስትራክሽን ላይ እየፈጠረ ያለውን ጫና የሚያሳይ ነው፡፡ ለዚህም ተጨባጭ መፍትሔ ለመስጠት መከተል ስለሚገባው አሠራር በጉልህ\nየሚያሳይ ነው ይላሉ፡፡ በተለይም ትልልቅ ፕሮጀክቶች እና የከተማ ግንባታዎች በሳይንሳዊ መንገድ እንዴት መካሄድ እንዳለባቸው የሚያሳይ\nስልጠና ሲሆን፤ እንደ አገር ሰፊ ክፍተት ስለመኖሩም ለመረዳት መቻላቸውን ይገልጻሉ፡፡ በዚህም ላይ በሰፊው መሠራት አለበት የሚል\nአቋም አላቸው፡፡ በግንባታ ላይ ያለውን ሙስና ለማፅዳትም መንግሥት\nቁርጠኛ መሆን እንዳለበት በመጠቆም፤ ኮንስትራክሽኑ በተማሩ ሰዎች እየተገነባ ወደ ዘመናዊ መንገድ መሄድ አለበት፡፡ በተለይ ደግሞ\nበቴክኖሎጂ አጠቃቀም ወደ ኋላ የቀረውን አሠራር ለማስተካከልም ሰፊ ኢንቨስትመንት ማካሄድ እንዳለበት ነው የሚጠቁሙት፡፡ በዘርፉ\nላይ ዓመቱን ሙሉ ያለውን ጉድለት ለመሙላት በሚደረገው ኦዲት የማስተካከል ጥረትም አገሪቱ ከፍተኛ ገንዘብ እያጣች መሆኑን በመጠቆም\nሀብት የማዳን ጉዳይ ጊዜ ሊሰጠው የማይገባ እንደሆነ ያሳስባሉ፡፡ በኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ\nየከተሞች ክላስተር አስተባበሪ አቶ አህመድ ቱሳ በበኩላቸው፤ በአገሪቱ ውስጥ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ከአምስት ከመቶ ወደ\n25 በመቶ አድጓል፡፡ ከኢኮኖሚው 36 ከመቶ የሚሸፍን ነው፡፡ ዘርፉ ብዙ ካለመዘመኑም በተጨማሪ ለከፍተኛ ሙስና መጋለጡም አደጋ\nእንደሆነ ይጠቁማሉ፡፡ በኢኮኖሚው ላይ መጫወት ያለበትን ሚና አልተወጣም ይላሉ፡፡ የክልሉ ውሃና ልማት ቢሮ ከ10ሺ በላይ ፕሮጀክቶች\nእንዳሉት የገለጹት አቶ አህመድ፣ በርካቶቹ የህብረተሰቡ ቅሬታ የሚቀርብባቸውና ዘርፈ ብዙ ችግር አለባቸው፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው\nዘርፉ በዘመናዊ መንገድ አለመምራት እና ሙስና ውስጥ መዘፈቁ ማሳያ በመሆኑ በተቀናጀ አሠራር ከዚህ መውጣት እንደሚገባ ይገልጻሉ፡፡የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የኮንስትራክሽን\nፕሮጀክት ማናጅመንት ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር አርጋው አይሻ እንደገለጹት፣ በአገሪቱ ትልቁ ችግር ፕሮጀክቶችን በወቅቱ\nያለማጠናቀቅ ነው፡፡ ከሚገመተው በላይ የዋጋ ንረት ያለበት ዘርፍ ኮንስትራክሽን ዘርፍ በመሆኑ አገሪቱን ፈተና ውስጥ እያስገባት\nነው፡፡ በመሆኑም ስልጠናውን በዚህ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማቃለል ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችንም ወደ ሌሎች ለማስፋፋት እና ለማሳደግ\nሰፊ ዕድል የሚሰጥ ነው፡፡ በአገሪቱ የሚካሄዱ በርካታ ግንባታዎች የጥራት\nደረጃ በጣም የወረደ እንደሆነ የሚናገሩት ዶክተር አረጋው፤ በዓለም ደረጃ አምስት የጥራት ደረጃዎች ያሉ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን\nየጥራት ደረጃ በአንድ እና ሁለት መካከል የሚገኝ ሲሆን፤ ይህም በዓለም መመዘኛ እና የጥራት ልኬት አኳያ በጣም ዝቅተኛ ነው ይላሉ፡፡\nየኮንስትራክሽን የጨረታው ሂደቶችም የአገሪቱ የራስ\nምታት ሆነውባታል፡፡ በውለታ አስተዳደርም ትልቅ ችግር አለበት፡፡ ይህም በአገሪቱ ላይ ትልቅ ጫና ፈጥሯል፡፡  ወደ ከፋ አደጋም ይወስዳታል፡፡ ዘርፉ በብቃት ረገድም የብቃት ጉዳይ ትልቅ\nችግር ያለበት ሲሆን፤ አገሪቱን ዋጋ እያስከፈለ በመሆኑ በማናቸውም ደረጃ ያሉ አካት ብቃቱን ያስመሰከረ ሰው በሥራው ላይ ማሰማራት\nእንዳለባቸው ያሳስባሉ፡፡ ሕንፃ በጥራት እንዲገነባ ብቃት ያለው ሰው ማሠማራትም የአገርን ህልውና በማስቀጠል እና ባለማስቀጠል ላይ\nእንደመወሰን ነው ይላሉ፡፡ በመሆኑም በስልጠና እና በተሞክሮ መጠናከር እና መስተካከል እንዳለበት ዶክተር አርጋው ያሳስባሉ፡፡ አዲስ ዘመን የካቲት 1/2011ክፍለዮሐንስ አንበርብር_", "passage_id": "b8d74fa1a4b4320947d9b4e5fe3a22da" }, { "passage": "ቦጋለ አበበ በኢትዮጵያ የተለያዩ የስፖርት አይነቶችን በማሳደግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ ለመሆን ያስችል ዘንድ በተለያዩ አካባቢዎች የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክቶችን መክፈት ሁነኛው አማራጭ እንደሆነ ታምኖበት ተግባራዊ ከተደረገ ዓመታት ተቆጥረዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በተለያዩ አካባቢዎች የተከፈቱ ፕሮጀክቶችና ማሰልጠኛ ማዕከላት በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ እንዳልሆኑ እየተነገረ ይገኛል። ፕሮጀክቶቹ፣ ማሰልጠኛ ማዕከላቱና ትልልቅ የታዳጊ ወጣቶች አካዳሚዎች ጭምር በትክክለኛው እድሜና በሚፈለገው ደረጃ ተተኪ ስፖርተኞችን እያፈሩ ስለመሆናቸው ደፍሮ መናገር አይቻልም። እነዚህ ፕሮጀክቶች፣ ማሰልጠኛ ማዕከላትና አካዳሚዎች በርካታ ገንዘብ ፈሶባቸው የተገነቡ ቢሆንም ከመሰረተ ልማት ባሻገር ሰልጣኞች የሚፈልጓቸውን የተለያዩ ግብዓቶች ማሟላት ሲቸገሩ ይስተዋላል። ይህም በብዙዎች ዘንድ ከፈረሱ ጋሪው እንደቀደመ ተደርጎ ሲታይ ቆይቷል። እነዚህ የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላት በብዛት ለሰልጣኞች እንደየ ስፖርት አይነቱ የሚያስፈልጉ ምግቦችን በብዛትና በጥራት የማቅረብ  ችግር እንዳለባቸው ሰልጣኞች ዘወትር ቅሬታ ያቀርባሉ። ይህን ለማሟላት የአቅም ችግር እንዳለ ቢታመንም ለስልጠናዎች የሚያስፈልጉ የስፖርት ትጥቆችን በጊዜና በጥራት በማቅረብ ረገድ በርካታ ችግሮች እንዳሉ ማስተዋል ይቻላል። በአሰላ ከተማ የሚገኘው ጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከል ባለፉት ዓመታት ከስፖርት ትጥቅ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ሰልጣኞች በርካታ ችግሮች እንዳሉባቸው ሲገልፁ ቆይተዋል። በተለይም የስፖርት ትጥቆችን በጥራት፣ በተገቢው ጊዜና እያንዳንዱ ሰልጣኝ በሚያስፈልገው መጠን በማቅረብ ረገድ በርካታ ችግሮች እንደነበሩ መዘገባችን ይታወቃል። ቀደም ሲል የማሰልጠኛ ማዕከሉ አመራሮችም ለስፖርት ትጥቅ መግዣ አስፈላጊው በጀት እያለ በጥራትና በሚፈለገው ጊዜ ትጥቁን የሚያቀርብ አካል ጨረታ ወጥቶ እንኳን ማግኘት ከባድ እንደሆነ ሲገልፁ ነበር። የአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ\nአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል\nዋና ዳይሬክተር ዶክተር\nአመንሲሳ ከበደ እና\nሌሎች አመራሮች የስልጠናውን\nሂደት ለመደገፍ ይረዳ\nዘንድ ጥራቱን የጠበቀ\nእና በእያንዳንዱ ሰልጣኝ\nተክለ ሰውነት ልክ\nግዢ እንዲፈፀም በማድረግ\nለሰልጣኞች ጊዜውን የጠበቀ\nየትጥቅ ስርጭት እንዳደረጉ\nበማህበራዊ ገፃቸው ሰሞኑን\nአሳውቀዋል። በዚህም ሰልጣኞች\nየተሰጣቸው ትጥቅ ጥራቱን\nየጠበቀ መሆኑንና በልካቸው መገዛቱን እንዲሁም ጊዜውን ጠብቆ እንደደረሳቸው በመግለፅ ለማዕከሉ አመራሮች ምስጋና እንዳቀረቡ ጠቁመዋል።   ", "passage_id": "7c0b281b4438c545df18fef6a88883dd" } ]
cd43a49aa8dbc57dda79680d3356be1e
4a42253801a00ffc42c86e838d256005
የሊግ ካምፓኒው የሳተው መስመር
የኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ 19) ወረርሽኝ እንደሌሎቹ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ኩነቶች ሁሉ የዓለምን ስፖርት ውጥንቅጡን አውጥቶታል። ታላላቅ የዓለማችን ሊጎች የሚያዙትን የሚጨብጡትን አጥተዋል። በተለይም ወትሮውንም ችግር የማያጣት አፍሪካ የዚህ ገፈት ቀማሽ መሆኗ ነገሩን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚያደርግባት ቀድሞም የተገመተ ነው። በእንደዚህ አይነት አስቸጋሪ ወቅት በሁሉም ረገድ ነገሮችን በብልሃት የሚያልፍ የበሰለ አመራር ሰጪነት ወሳኝ ነው። ለዚህም ሩቅ ሳንሄድ እዚሁ አፍሪካ ውስጥ የቡርኪናፋሶ እግር ኳስ ተሞክሮን መመልከት አንዱ ማሳያ ነው። ቡርኪናፋሶ እንደሌሎቹ የዓለማችንም ይሁን የአፍሪካ አገራት ሰሞንኛ ማህበራዊ ሁኔታዋ ጤነኛ አልነበረም ። አፍሪካ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የኮሮና ቫይረስ ያጠቃቸው ፖለቲከኞች ተመዝግበውባታል። የቡርኪናፋሶ መንግስት ይህ ቫይረስ ተስፋፍቶባቸዋል ብሎ ካወጀባቸው ቦታዎች መካከል የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ይገኙበታል። ጅምናዚየም ፣ የኳስ መጫወቻ ሜዳዎች ለዚህ ተጠቃሽ ከሚባሉት ቦታዎች ውስጥ ይገኛሉ። ስለዚህ ይህንን አደጋ ለመቀነስ እና ለማህበረሰቡ ዋስትና ለመስጠት ሊጉን ሰርዞ የተለያዩ ውሳኔዎችን በዚህ ሳምንት አሳልፏል። የዘንድሮው የውድድር ዓመት እንደማይጠናቀቅ እና በዚሁ ውጤት እንደሚያልቅ፣ ሁሉም ክለቦች በውል ውስጥ የሚገኙ ተጫዋቾቻቸውን ውል እንዲያከብሩላቸው እና እስከውል ማለቂያው ድረስ ደመወዝ እንዲከፍሉ፣ ማንኛውም ክለብ ያለምንም በቂ ምክንያት ምንም አይነት የክለብ አባላት ቅነሳ እንዳያደርግ፣ የትኛውም ተጫዋች ተበደልኩ ቢል ለፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት እንዲያመለክት፣ ከሁሉም በላይ በዘንድሮ 2019 የውድድር ዘመን በኢንተርናሽናል መድረክ አገሪቱን የወከሉት ቡድኖች ማለትም (ራሂሞ ኤፍ ሲ) እና (ሳሊታስ) የተባለው ክለብ በክለቦች ኮንፌዴሬሽን ጨዋታ በሚመጣው ዓመት አገሪቱን እንዲወክሉ አድርጓል። ይህንን ያደረገውም የዘንድሮ ልፋታቸው ሽልማት እንኳን ቢሆን ብሎ በማሰብ ነው ። አሱማ ሲሪማ የቡርኪናፋሶ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ናቸው። ይህንን ውሳኔ ሲወስኑ ሁሉንም እንደሚያስማማ በማሰብ መሆኑን ተናግረዋል። ቡርኪናፋሶን የወከሏት ቡድኖች የተገኙት አምና ባስመዘገቡት ውጤት ነው ። ይህ አንዳንዴ የተቀመጠን ህግ እና አሰራር ወቅቱ በሚፈቅደው ነገር እንደሚጠመዘዝ ማሳያ ነው ። የኢትዮጵያ ሊግ ካምፓኒ ምንም አይነት ቡድን ኢትዮጵያን በኢንተርናሽናል ውድድር አይወክልም የሚል ውሳኔ ከቀናት በፊት አስተላልፏል። ይህ እንደ አገር በድጋሚ ሊጤን የሚገባው ውሳኔ እንደሆነ በርካቶች አስተያየት ሰጥተውበታል። በኢንተርናሽናል ውድድሮች ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉት ቡድኖች ከየትም ወገን ይምጡ የሚወክሉት ሊጉን ነው ። ሊጉ ደግሞ በድግግሞሽ በየዓመቱ ኢትዮጵያን በጥራት የሚወክሉ ቡድኖችን ይፈልጋል። ይህንን ጥራት ለማምጣት ደግሞ የቡድኖችን የኢንተርናሽናል ተሳትፎ መንገድ መቁረጥ ሌላ ፈተና ይዞ እንደሚመጣ ሳይታለም የተፈታ ነው። ይህን መቁረጥ በአንድ ዓመት የኢንተርናሽናል ልምድ በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኝ ተጫዋች ራሱን የማሳየት ተስፋ ማጨለሙ አይቀርም። የክለቦችን የአስተዳደራዊ ዝግጅት ደረጃ ከፍ የማድረግ ልምድ ማ ሳነስም ሌላኛው ኪሳራ ነው። ለምሳሌ ሊጉን እየመራ የሚገኘው ፋሲል ከነማ ዘንድሮ ጥሩ የውድድር ዘመን አሳልፏል። ይህ ማለት ቡድኑ ሊጉ እስከተቋረጠበት ጊዜ ራሱን በሚገባ እያዘጋጀ እንደነበር ማሳያ ነው ። ተከታዮቹ መቐለ 70 እንደርታ እና ቅዱስ ጊዮርጊስም ወደ ውድድሩ የገቡት በተጠና እና የዝግጅታቸውን አቅም ፣ ጥልቀት በሚያሳይ ጥራት ነበር። ከእነዚህ ቡድኖች ውስጥ ወደ ኢንተርናሽናል ውድድር ለመቅረብ ቡድኖች ቢመረጡ እና እንዲወከሉ ቢደረግ ለቡድኖቹ ረዥም የሜዳ ተግባር እና የገንዘብ አቅም ቅድመ ዝግጅት ያገኙ ነበር ። የሊግ ኮሚቴው ውሳኔውን ክለቦች ተስማምተውበት እንዳሳለፈ ቢያሳውቅም ራሱን በሚገባ ሳያዘጋጅ የቀረበ እና የሊግ ካምፓኒው ሊጉ በአጠቃላይ ማግኘት የሚገባውን ጥቅም እንዳያገኝ አድርጎታል። ጉዳዮ ቻምፒዮን የመሆን እና ያለመሆን ጥያቄ አይደለም። በኢንተርናሽናል መድረክ ሊጋችንን የመወከል እና ያለመወከል ጥያቄ ነው። በድግግሞሽ ውስጥ መማር የሚገባው ሊግ ሊማርበት የሚገባውን አንዱን ነጥብ እንደሳተ ብዙዎች ይስማማሉ። እግር ኳሱ ላይ አብዛኛውን ጊዜ የሚወሰኑ ውሳኔዎች የሚሰጡት ጥቅም በአገራዊ መነፀር መታየት ይኖርባቸዋል ተብሎ ይታመናል። ለዚህ ደግሞ ክለቦች ጊዜ ወስደው እንዳያስቡና ፣ ጥናት ያለማድረግ ፣ ማንን ላስደስት የሚለውን አመለካከት አውልቆ አለመጣል ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ይታመናል። የቡርኪናፋሶ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አምና በኢንተርናሽናል መድረክ የተወከሉትን ቡድኖች ዘንድሮም ‹‹እነሱ ናቸው የሚወክሉኝ›› ብሎ ሲወስን ክለቦችን ጊዜ ሰጥቶ በሚገባ አናግሯል። ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትንም በቴሌ ኮንፈረንስ ገንቢ ሐሳብ እንዲሰጡበት አድርጓል። ኘሬዚደንቱ ‹‹እኛ የሚያስጨንቀን የሚመጣው ዓመት የሚሰጠንን ኮታ እንዳናጣው ነው ፣ ምክንያቱም ክለቦቻችን ልምድ እና ተሞክሮ ያስፈልጋቸዋል›› ነበር ያሉት ። ሁለቱ ቡድኖች ዘንድሮ አገሪቱን በኢንተርናሽናል መድረክ ሲወክሉ ፣ ራሂሞ የተባለው ቡድን በቅድመ ማጣሪያ 5ለ1 ተረቶ ነበር ። ከዚህ ሽንፈት በኋላም ሌላ ልምድ እናግኝ ብለው እንደገና ተነጋግረው ፣ ተግባብተው ወካያቸው አድርገውታል። የሊግ ካምፓኒው ውሳኔውን ካሳለፈ በኋላም ቢሆን ስህተቱን አምኗል። ማመን ብቻ ግን በቂ አይደለም። ካለመሳተፍ መሳተፍ ልዩ ዋጋ እንዳለው ተገንዝቦ የተሳሳተውን ውሳኔ የሚያርምበት ቀዳዳ መፈለግ ይኖርበታል።አዲስ ዘመን ግንቦት 1/2012 ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=31988
[ { "passage": "ከአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ጋር እንደሚቀጥል የታወቀው ወልዋሎ ዓ.ዩ ግዙፉን የደደቢት ግብ ጠባቂ በእጁ አስገብቷል። በተጠናቀቀው የውድድር አመት ሊጉን የተቀላቀለው ወልዋሎ በሀገር ውስጥ ግብ ጠባቂዎች ከሚጠቀሙ ጥቂት ክለቦች መካከል አንዱ እንደነበር ይታወሳል። በዚያ ወቅት የቡድኑ ዋነኛ ግብ ጠባቂ የነበረው በረከት አማረ ለብሔራዊ ቡድን እስከመመረጥ ያደረሰውን ብቃት ማሳየት ችሎ ነበር። ሆኖም በሁለተኛው የውድድር አጋማሽ በተለይም በረከት በመከላከያው ጨዋታ በተፈጠረው ግርግር ቅጣት ከተላለፈበት በኋላ ዘውዱ መስፍን እና በአመቱ አጋማሽ ቡድኑን የተቀላቀለው ዮሀንስ ሽኩር ቦታውን ሸፍነው ተጫውተዋል።በሁለቱ ግብ ጠባቂዎች ብቃት ያልረኩ የሚመስሉት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ የውጪ ግብ ጠባቂዎችን ከሚጠቀሙ ክለቦች ተርታ ተቀላቅለዋል። ላለፉት ሁለት የውድድር አመታት በደደቢት የምናውቀው አማራህ ክሌመንት ደግሞ የቢጫ ለባሾቹ ምርጫ ሆኗል። በሁለተኛው ዙር አቋሙ ከቡድኑ ጋር በሚመሳሰል መልኩ የወረደው ጋናዊው ግብ ጠባቂ ደደቢት በመጀመሪያው ዙር ላሳየው ብቃት ትልቅ ሚና በመወጣት በሶከር ኢትዮጵያ የታህሳስ ወር ምርጥ ቡድን ውስጥ መካተት ችሎ ነበር።ግብ ጠባቂው የክለቡ አራተኛ ፈራሚ ሲሆን የኋላ መስመራቸውን በማጠናከር ላይ ትኩረት ያደረጉት  ወልዋሎዎች ከዚህ በፊት የተከላካይ መስመር ተጨዋቾቹን ዳንኤል አድሀኖም ፣ ብርሀኑ ቦጋለ እና ቢንያም ሲራጅን እንዳስፈረሙ ይታወሳል።", "passage_id": "4c0804501ffa2ae56c29085fe626e65e" }, { "passage": "የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ዐቢይ ኮሚቴ ህጋዊ የኩባንያ ዕውቅና አግኝቶ “የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ካምፓኒ” ወደሚለው ስያሜ ተቀይሯል፡፡በአሁኑ ሰዓት በጁፒተር ሆቴሌ የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአንደኛው ዙር የውድድር ዘመን አጋማሽ ግምገማ እየተካሄደ ሲሆን በዛሬው ጉባዔ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ በመክፈቻ ንግግር አስጀምረዋል። ሰብሳቢው በመክፈቻ ንግግራቸው በአንደኛው ዙር ክለቦች ራሳቸው ባቋቋሙት የሊግ ዐቢይ ኮሚቴ እየተመራ ሲሆን ከሁለተኛው ዙር ጀምሮ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዐቢይ ኮሚቴ የሚለው በክለቦች ውይይት መሠረት ወደ ኩባንባነት በመሸጋገሩ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሊግ ካምፓኒ ወደሚል ስያሜ መለወጡን ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ደግሞ የካምፓኒውን መመስረት የሚያረጋግጥ የዕውቅና ሰርተፍኬት መረከባቸውንም በንግግራቸው እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ለታዳሚው ገልፀዋል፡፡የስብሰባው አዳዲስ ጉዳዮች እየተከታተልን እንገልፃለን", "passage_id": "377b348daa1ffd93bb455a037133930c" }, { "passage": "ኢኳቶሪያል ጊኒያዊው ግብ ጠባቂ ፊሊፔ ኦቮኖ ምባንግ ለመቐለ ከፈረሙት ተጫዋቾች መካከል ነው፡፡ ከ2009 ጀምሮ በዋና ቡድን ደረጃ እየተጫወተ የሚገኘውና ለሀገሩ 10 ጨዋታዎቸች ማድረግ የቻለው ምባንግ በሀገሩ ክለቦች ሶኒ ንጉኤማ እና ዴፖርቲቮ ሞኞሞ ከተጫወተ በኋላ በአመዛኙ በተጠባባቂነት ባሳለፈበት የደቡብ አፍሪካው ኦርላንዶ ፓያሬትስ ለሁለት አመታት ቆይቶ ወደ መጀመርያ ክለቡ ሶኒ ንጉኤማ ተመልሶ የተጠናቀቀውን አመት አሳልፏል፡፡የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ሚካኤል አኩፉ ሌላው ለክለቡ የፈረመ ተጫዋች ነው፡፡ ጋና ከሚገኘው የፌይኖርድ አካዳሚ የተገኘው የ29 አመቱ ሚካኤል ባለፉት 10 አመታት በኤሴክ ሚሞሳ ፣ ኤፍ ሲ ፖፓ ፣ አሻንቲ ኮቶኮ እና አልናስር ክለቦች ተጫውቷል፡፡ የጋና ብሔራዊ ቡድን የቻን ስብስብ አባልም ነበር፡፡ለክለቡ የፈረመው ሶስተኛው ተጫዋች አዳም ማሳላቺ ነው፡፡ የ23 አመቱ ጋናዊ የመሀል ተከላካይ በሀገሩ ክለብ ስቲድፋስት 4 የውድድር ዘመናትን ሲያሳልፍ በሊባኖሱ ኢግታሚ ትሪፖሊ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናት አሳልፏል፡፡መቐለ ከተማ በዝውውር መስኮቱ ሰፊ እነንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ሲሆን ከውጪ ዜጎቹ ተጫዋቾች በተጨማሪ በርካታ የሀገር ውሰጥ ተጫዋቾችን ማስፈረም ችሏል፡፡", "passage_id": "0f4bca40f649de9471b33616df839e77" }, { "passage": "የመስመር አማካዩ ከማል ፖርት ሜልቦርን ሻርክስን ለቆ ወደ ሻምፒዮኖቹ ቤንትሊጅ ግሪንስን ተቀላቅሏል፡፡ ከማል ለፖርት ሜልቦርን ሻርክስ ባሳለፍነው የውድድር ዘመን በ28 ጨዋታዎች 10 ግቦችን ሲያስቆጥር 8 ግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፡፡የ24 ዓመቱ ከማል ለድረ ገፁ በሰጠው አስተያየት ከፖርት ሜልቦርን ሻርክስ የተለያየበት ወቅት ትክክለኛው ግዜ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ “በፖርት ሜልቦርን ላለፉት ሶስት ዓመታት ጥሩ ግዜ አሳልፊያለው፡፡ የለቀቀኩበት ግዜ ትክክል ነበር፡፡ የቤንትሊጅ ግሪንስ አጨዋወት ፍልስፍና አደንቃለው፡፡ እንደሚሰማኝ ከሆነ በዚሁ ክለብ ጥሩ የሆነ እግርኳስ መጫወት እችላለው፡፡”የቀድሞ የአውስትራሊያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ከማል በግሉ አስደናቂ የውድድር ዓመት ማሳለፉ ሌሎች ክለቦች የፖርት ሜልቦርን ሻርክስን በር እንዲያንኳኩ አድርጓል፡፡ “ቤንትሊጅ ግሪንስ ሊያስፈርሙኝ እንደሚፈልጉ ሲነግሩኝ በፖርት ሜልቦርንስ በኩል ችግር አልነበረም፡፡ ፖርት ሜልቦርን ቦርድ ፍላጎቴን ተረድተው ወደ ቤንትሊጅ ግሪንስ ሄጂያለው፡፡ ከፖርት ሜልቦርን ጋር የተለያየነውን በስምምነት እና ሰላማዊ መንገድ ነው፡፡”ከማል ለቤንትሊጅ ግሪንስ የመጀመሪያ ጨዋታውን በወዳጅነት ጨዋታ ከሜልቦር ሲቲ ጋር በዝግ ስታዲየም አድርጓል፡፡ ተጫዋቹ አሁንም በኤ ሊግ ክለቦች እይታ ውስጥ አለመግባቱ እንዳበሳጨው ተናግሯል፡፡ “ባለፈው ዓመት ጥሩ አቋም ላይ ነበርኩ፡፡ የኤንፒኤል ቪክቶሪያ ሊግ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ነበርኩ ነገርግን አንድም የኤ ሊግ ክለብ ለሙከራ አልጠራኝም፡፡”የኤ ሊግ ክለብ በሆነው ሜልቦርን ሃርትስ (የአሁኑ ሜልቦርን ሲቲ) ጋር የሶስት ዓመት ቆይታ የነበረው ከማል የኤ ሊግ ክለቦች አሁን ተጫዋቾችን ለመመልመል ወደ ኤንፒኤል ቪክቶሮያ ሊግ መመልከት መጀመራቸው እንደበጎ ጎን ያነሳል፡፡ “በሊጉ ተጫዋቾች ለመመልመል መፈለጋቸው ጥሩ ነው፡፡ የአሁኑ የውድድር ዘመን ጥሩ ተንቀሳቅሼ ወደ ኤ ሊግ ክለብ መዛወር ፍላጎቴ ነው፡፡”አውስትራሊያን በወጣት ብሄራዊ ቡድን ደረጃ የወከለው ከማል ለኢትዮጵያ የመጫወት ፍላጎት እንዳላው በጥቅምት ወር ለሶከር ኢትዮጵያ መግለፁ ይታወሳል፡፡", "passage_id": "6aa04f4a383deacede4f9bdf4043d960" }, { "passage": " ኡመድ ከኢኤንፒፒአይ ጋር የነበረውን ውል በስምምነት ያፈረሰ ሲሆን በሁለት ዓመት ውስጥ ወደ ሶስተኛው ክለብ ማምራት ችሏል፡፡ኡመድ በዓመቱ መጀመሪያ ወደ ነዳጅ አምራቾቹ ኢኤንፒፒአይ በአራት ዓመት ውል ቢያመራም በቂ የመሰል ዕድል መነፈጉ ከክለቡ የመውጫ በር እንዲፈልግ አስገድዶታል፡፡ኡመድ በኢኤንፒፒአይ ቆይታው የኮትዲቯሩ አፍሪካን ስፖርትስ ላይ በካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ ግብ ማስቆጠር የቻለ ሲሆን በ2015/16 የውድድር ዘመን በሊግ ጨዋታ ግብ ማስቆጠር አልቻለም ነበር፡፡የ2006 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ግብ አግቢ የሆነው ኡመድ ለኤል ኤንታግ ኤል ሃርቢ የአንድ ዓመት ውል መፈረሙን የተጫዋቹ ወኪል አብዱልራህማል መግዲ ገልጿል፡፡ ግብፃዊው መግዲ ከኡመድ ባሻገር የሽመልስ በቀለ ወኪል ነው፡፡በ2004 እ.ኤ.አ. የተመሰረተው ኤል ሃርቢ የካይሮ ክለብ ሲሆን ባሳለፍነው የውድድር ዘመን በግብፅ ፕሪምየር ሊግ ሰባተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል፡፡ ክለቡ በቀድሞ የግብፅ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሻውኪ ጋሪብ የሚመራ ነው፡፡ ጋሪብ ከ2004-2011 የሃሰን ሸአታ ምክትል በመሆን ፈርኦኖቹን ያገለገሉ ሲሆን ከ2013-14 ለአንድ ዓመት ቦብ ብራድሊን ተክተው የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ነበሩ፡፡ 30ሺ ተመልካች የመያዝ አቅም ባለው አል ሰለም ስታዲየም የሜዳ ላይ ጨዋታዎቹን የሚያደርገው ክለቡ በግብፅ ጦር ሚኒስቴር ስር የሚተዳደር ክለብ ነው፡፡ኡመድ በግብፅ ቆይታው ለኢትሃድ አልክሳንደሪያ እና ኢኤንፒፒአይ መጫወት ችሏል፡፡", "passage_id": "95c5283884a66a262773d07c1b969c10" } ]
39e58906243ca455f75f386a2ba93c32
992f639de4543547b025498f4591203c
ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ለአትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን አባላቱ ቃል የገባውን ገንዘብ ማስረከብ ጀመረ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለብሔራዊ ቡድን አባላት ቃል የገባውን የአራት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማስረከብ መጀመሩን አስታወቀ። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አመራር ቦርድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ዓለም አቀፍ ውድድሮች በመሰረዛቸው ምክንያት ጥቅማ ጥቅም ለሚያጡ ብሔራዊ አትሌቶች አራት ሚሊዮን ብር ለመደጎም ከሳምንታት በፊት ውሳኔ መተላለፉን አስታውሷል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በወቅቱ በገባው ቃል መሠረት ከሰኞ ግንቦት 3 ቀን 2012 ዓ.ም ማለዳ ጀምሮ ለብሔራዊ አትሌቲክስ ቡድን አባላት ማስረከብ መጀመሩን አስታውቋል። ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርዱ ለ267 ብሔራዊ አትሌቶችና አሠልጣኞች በተናጠል የሚደረጉትን ልምምድና ዝግጅት አጠናክረው መቀጠል ይችሉ ዘንድ፣ ለእያንዳንዳቸው 15 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ከስምምነት ተደርሶ ነበር። በብሔራዊ ቡድን የሚገኙ አትሌቶቹና አሰልጣኞቹ እያንዳንዳቸው ቃል በተገባላቸው መሠረት 15 ሺህ ብር እንዲሁም ሙሉ የስፖርት ትጥቅ ከነመለማመጃው በተዘጋጀው መርሃ ግብር መሠረት እየተረከቡ ይገኛሉ ብሏል። ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የገንዘብ ድጋፉን ለማድረግ ውሳኔ ባስተላለፈበት ወቅት እንደተናገረው ከውሳኔ፤ በዓለም አቀፍና አኅጉር አቀፍ ደረጃ የአትሌቲክስ ውድድሮችና በቡድን የሚካሄዱ ልምምዶች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እንዲቋረጡ ተደርጓል፡፡ በተለይም በብሔራዊ ቡድን ደረጃ በተለያዩ የውድድር ዓይነቶች ማለትም የሜዳ ተግባራትን ጨምሮ ከአጭር ርቀት እስከ ማራቶን 211 አትሌቶችንና 56 ብሔራዊ አሠልጣኞች በድምሩ 267 የአትሌቲክስ ቤተሰቦች ሥነ ልቦናቸው ተጠብቆ ልምምዳቸውን እንዲቀጥሉ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ ፌዴሬሽኑ አምኖበታል፡፡ ሌላው የውጭ የአትሌቲክስ ውድድሮች በመቋረጣቸው በተለይ የአጭር ርቀትና የሜዳ ተግባራት አትሌቶችና አሠልጣኞቻቸው ያገኟቸው የነበሩ ጥቅማ ጥቅሞች በማነሳቸውና በመቀነሳቸው ተቋሙ ከጎናቸው መሆኑን እንዲያረጋግጡ የሞራል ስንቅ ከመሆኑ ባሻገር፣ ለቀጣዩ ኦሊምፒክ ከወዲሁ ተገቢውን ዝግጅትና ተያያዥ ሥራዎችን እንዲያከናውኑ ያለመ ስለመሆኑ ጭምር ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ለቅድመ ማጣሪያው ከ800 ሜትር እስከ ማራቶን ባሉት ርቀቶች ለተመረጡ 91 ብሔራዊ አትሌቶች እንዲሁም ለኦሊምፒክ ዝግጅት አትሌቶችን ላስመረጡ 27 አሠልጣኞች፣ ለ63 የአጭር ርቀትና የሜዳ ተግባራት አትሌቶችና ለ16 አሠልጣኞች፣ ለ57 ተተኪና ወጣት አትሌቶች እንዲሁም ለ13 ተተኪ ወጣት አትሌቶች አሠልጣኞች በገንዘብ ድጋፉ የተካተቱ ሲሆን ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ባወጣው መርሃ ግብር መሠረት ድጋፍ ለማድረግ ቃል የተገባውን ገንዘብና ትጥቅ የሚረከቡ ይሆናል ተብሏል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አመራር ቦርድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ዓለም አቀፍ ውድድሮች መቋረጣቸውን ተከትሎ ለአትሌቶች እያደረገው እንዳለው ድጋፍ ሁሉ ፤ የዓለም አትሌቲክስና ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፋውንዴንሽን በወረርሽኝ ለተጎዱ አትሌቶች የ5 መቶ ሺህ ዶላር ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑን ከሳምንት በፊት ማሳወቁ ይታወሳል። የዓለም አትሌቲከስ ፕሬዚዳንት ሰባስቲያን ኮ እንደተናገሩት ድጋፉን የሚያገኙት በወረርሽኙ ምክንያት ባለፉት ወራት ውድድሮች ባለማድረጋቸው ገቢ ያጡ ፕሮፌሽናል አትሌቶች ነው። ድርጅቱ ድጋፉን የሚያደርገው እኤአ በ2020 እና በ2021 በጀቱ በመቀነስ መሆኑ ነበር ያሳወቀው። አዲስ ዘመን ግንቦት 4/2012 ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=32181
[ { "passage": "  - ባሳለፍነው ዓመት ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት 169 ሚ. ብር ለግሷል  - ዘንድሮ 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ያከብራል    ዳሽን ባንክ በጐርጐራ፣ በወንጪና ኮይሻ ለሚሰሩ ልማቶች የሚውል 30ሚ ብር መለገሱን አስታወቀ፡፡ ባንኩ ከትላንት በስቲያ ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ረፋድ ላይ በዋና መስሪያ ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው ይህ ገንዘብ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ለ “ገበታ ለሀገር” ፕሮጀክት ለሶስቱ ቦታዎች ግንባታና ልማት ላደረጉት ጥሪ የተሰጠ ምላሽ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ እንደገለፁት 30ሚ ብሩ ለጐርጐራ፣ ለወንጪና ለኮይሻ ለእያንዳንዳቸው የ10 ሚ ብር ድጋፍ የተሰጠ ሲሆን በአዲሱ የበጀት ዓመት ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የበጀተው የመጀመሪያው በጀት እንደሆነም ዋና ሥራ አስፈፃማው ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ዋና ሥራ አስፈፃሚው በመግለጫቸው በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሁኔታዎች ለተፈጠሩ ችግሮች ዘርፈ ብዙ ምላሽ ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሰው በአጠቃላይ 169 ሚ. 806ሺ 333 ብር መለገሱንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ከነዚህም መካከል ለኢትዮጵያ ቅርሶች ትረስት 120 ሚ ለፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል 718ሺ 333 ብር፣ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ 1.5 ሚ. ለትግራይ ተፈናቃዮች 10ሚ፣ ለአማራ ተፈናቃዮች 10ሚ ብር፣ ለአምቦ ከተማ ልማት 10 ሚ ብር፣ ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ 10 ሚ ብር ለመልካም አስተዳደር ስራ 20 ሚ ብር ለብሔራዊ አደጋ ስጋት አመራር 5ሚ ብር ለሜሪጆይ ልማት ድርጅት 50ሺህ ብር፣ ለአዲስ አበባ ከተማ ተማሪዎች የደብተር ወጪ 1ሚ.150ሺህ ብርና ለሌሎችም በርካታ ድጋፎች በድምሩ 169ሚ ብር ወጪ ማድረጉን አቶ አስፋው ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ባንኩ በ25 ዓመት ጉዞው የሀገሪቱ የፋይናንስ ምሰሶ ሆኖ በአገር ኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ልማትና በሰዎች የኑሮ እድገት ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ ማሳረፉን የገለፁት ዋና ሥራ አስፈፃሚው በላሊበላ የአየሩን ሁኔታ ለማስተካከልና አካባቢውን ለማልማት ከዛፍ ተከላ ጀምሮ የአካባቢውን ወጣቶች ከቱሪስት እንዳይለምኑ በማድረግ በኩልም በርካታ ስራና ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልፀው ዘንድሮ ባንኩ 25ኛ ዓመቱን በተለያዩ ክብረበዓሎች እንደሚያከብርም ተናግረዋል፡፡ ባንኩ እስካሁን 425 ቅርንጫፎችን በመላው አገሪቱ ከፍቶ ሲሰራ የነበረ ሲሆን በትላንትናው እለት በቤተልና በመርካቶ ሁለት ተጨማሪ ቅርንጫፎችን በመክፈት አጠቃላይ የቅርንጫፎቹን ብዛት ወደ 427 ከፍ ማድረጉም ተገልጿል፡፡  ", "passage_id": "b9e16db59b0d73380f07d72d81c5ca0e" }, { "passage": "የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅትና ለተለያዩ የልማት ሥራዎች ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ አስቧል። በተያዘው ዓመት መጨረሻ በሚካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በመድረኩ ትልቅ ስምና ታሪክ ያላት ኢትዮጵያ በተለያዩ ስፖርቶች ተሳታፊ ትሆናለች። ለዚህ የሚሆነውን ዝግጅት የሚመራ ብሔራዊ የዝግጅት ኮሚቴም በቅርቡ ተዋቅሮ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል። ኮሚቴው እያደረገ ከሚገኘው ዝግጅት መካከልም ለውድድሩ እንዲሁም ሌሎች የልማት ሥራዎች የሚውል አንድ ቢሊዮን ብር ለማሰባሰብ እንዳሰበ ጠቁሟል። ለዚህም ከ12 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የኦሊምፒክ ደጋፊ ማህበር አባላትን በማፍራት፣ የአትሌቶች ሽኝትና ሽልማት እንዲሁም በመድረኩ የአገሪቷን መልካም ገጽታ ለመገንባት ማቀዱን አሳውቋል። ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ቅድመ ዝግጅት\nበማድረግ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ‹‹ከቶኪዮ እስከ ቶኪዮ›› በሚል ርዕስ ከተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመስራት\nላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። በትናንትናው ዕለትም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር በከተማዋ ከሚገኙ\nየግልና የመንግሥት ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ከተውጣጡ ርዕሰ መምህራንና የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል።\nበመድረኩም ላይ የኦሊምፒክ መርሆችና እሴቶች እንዲሁም አገሪቷ ከሜልቦርን እስከ ሪዮ ኦሊምፒክ የነበራት ተሞክሮ ላይ ገለጻ ተደርጓል።\nበቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅት ዙሪያም ከትምህርት ቤቶችና ከማህበረሰቡ ምን ይጠበቃል በሚል ውይይት ተካሂዷል። ውይይቱም የኦሊምፒክ እሴቶችን\nበተማሪዎች ማስረጽ፣ የትምህርት ቤት ማህበረሰብን የኮሚቴው አባል ለማድረግ እንዲሁም ለኦሊምፒኩ ሽኝት የትምህርት ቤት ማህበረሰብ\nተሳታፊ እንዲሆን አልሞ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። በመድረኩ ላይም የዝግጅት ኮሚቴው ሰብሳቢ\nአቶ አባዱላ ገመዳ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል\nኃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳዊት ትርፉ ተገኝተዋል። ዶክተር አሸብር የውይይት መድረኩን\nሲከፍቱ በቀደመው ወቅት የስፖርት እንቅስቃሴ መነሻ የሆኑት ትምህርት ቤቶች በርካታ ውጤታማ አትሌቶችን ማፍራት እንደቻሉ በማስታወስ፣\nስፖርቱን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ እንዲሁም በእኔነት ስሜት ሁሉም ተሳትፎ እንዲያደርግበት ጥሪያቸውን አቅርበዋል። በመድረኩ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የከተማዋ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን እንዲሁም ከየክፍለ ከተማው የትምህርት\nቢሮ የተውጣጡ ተሳታፊዎች በበኩላቸው እንቅስቃሴው የዘገየ መሆኑን ጠቁመዋል። በትምህርት ቤቶች ያለው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ባለመበረታታቱ\nመቀዛቀዝ አሳይቶ የቆየ መሆኑን ያነሱት አስተያየት ሰጪዎች፤ ከዚህ ቀደም እንደነበረው እንዳይሆን ድጋፍ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል።\nአያይዘውም የትምህርት ቤት ማህበረሰብ ለዚህ እንቅስቃሴ ዝግጁ መሆናቸውንና አብረው ለመስራት እንደሚፈልጉም አረጋግጠዋል። የብሔራዊ ኦሊምፒክ ዝግጅት ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳ፤ እንቅስቃሴው ሁለት ዓላማዎች ያሉት\nመሆኑን ይገልጻሉ። የመጀመሪያው ለቶኪዮው ኦሊምፒክ ዝግጅት በማድረግ አገሪቷን የሚያኮራ ሥራ ማከናወን እንዲሁም ለቀጣይ ኦሊምፒኮች\nመነሻ የሚሆን የልማት ሥራ (የብሔራዊ ቡድን ዝግጅት የሚደረግበት ማዕከል ግንባታ) ለማከናወን መሆኑን ጠቁመዋል። ለዚህ የሚሆን\nገቢ ለማሰባሰብም ሰፊ የሕዝብ እንቅስቃሴ በመፍጠር ማህበረሰቡ የዝግጅቱ አካል የሚሆንበትና መሠረተ ልማቱ ላይ የሚሳተፍበት እንደሚሆን\nተናግረዋል። ይህም ከአዲስ አበባ ከተማ የሚጀመር ሲሆን፤ ተማሪዎች ደግሞ በስፋት ተካፋይ እንዲሆኑ ለማድረግ መታሰቡን አብራርተዋል።\nኦሊምፒክ ትውልድ ተሻጋሪ እንቅስቃሴ እንደመሆኑ አዲሱ ትውልድ ባለቤት በመሆን ችቦውን እንዲለኩስ\nለማድረግ በእቅድ ተይዟል። ለዚህም የካቲት 08/2012ዓ.ም ከአዲስ አበባ በመጀመር በአገሪቷ የሚዞር የኦሊምፒክ ችቦ መዘጋጀቱ\nታውቋል። ከዚህ ባሻገር በእንቅስቃሴው ሁሉም የእኔነት ስሜት እንዲኖረውና የኮሚቴው አባል እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ሰብሳቢው አስረድተዋል።\nበቀጣይም ለዚሁ አላማ የሚውልና በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሚዘጋጅ የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት መርሃ ግብር\nእንደሚኖር ይጠበቃል። በዚህም ፕሮግራም ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሳተፉ ሲሆን በመላው አገሪቷ በርካቶች የሚካፈሉበት መሰል\nእቅድም ተይዟል። እቅዱም ከአንድ አካባቢ ብቻ ገንዘብ ማሰባሰብ ሳይሆን ሁሉም ‹‹የራሴ›› የሚለውን አንድ የኦሊምፒክ መንደር እስከ\nመገንባት ይዘልቃል። በኦሊምፒኩ ዝግጅት ዙሪያ ቢሮውና ኮሚቴው አብረው መስራት የጀመሩት ቀደም ብለው እንደሆነ የሚገልጹት\nምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ዳኘው፣ በውይይቱም ለቶኪዮው ኦሊምፒክ ብቻም ሳይሆን ለሌሎችም ኦሊምፒኮች መርሁን ለማስረጽ እንደታሰበ\nተናግረዋል። አሁን ለሚወዳደሩት አትሌቶች አቅምና ጉልበት መሆን እንዲሁም ተተኪ አትሌቶችን መፍጠርም ዋነኛ ዓላማው መሆኑን አብራርተዋል።\nትምህርት ቤቶች በባለሙያ፣ በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲሁም ለስፖርቱ ፍላጎት ያላቸው ታዳጊዎች ያሉበት በመሆኑ መርሆቹንና\nእሴቶቹን ለማስረጽ ምቹ ስፍራዎች መሆናቸውንም አክለዋል። በመሆኑም የካቲት 8 ለተያዘው ቀጠሮ እንደ ትምህርት ቢሮ ዝግጁ መሆናቸውን\nአረጋግጠዋል። አዲስ ዘመን ረቡዕ ጥር 20/2012ብርሃን ፈይሳ ", "passage_id": "2c0c1abd4c9394c5cdce7c65fb412ed4" }, { "passage": "የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ማኅበር ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ የቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል በሀገር ደረጃ ለሚደረገው ጥረት የራሱን ድርሻ እየተወጣ የሚገኘው የኢትዮጵያ ተጫዋችች ማኀበር የተለያዩ ቁሳቁሶችን የማሰባሰቡን ሒደት ከጀመረ ሰነባብቷል። አንጋፋው የቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድም ለዚህ በጎ ተግባር ይረዳ ዘንድ በትናትናው ዕለት ማኀበሩ ለዚህ ዓላማ እንዲውል በከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት 50 ሺህ ብር መለገሱን ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቋል።በቅርቡ የገንዘብም ሆኖ የቁሳቁስ ማሰባሰቡ ሂደት እንደሚጠናቀቅ ከማኀበሩ የሰማን ሲሆን በቀሪዎቹ ቀናት ይህን በጎ ተግባር ለማገዝ የሚፈልጉ ሌሎች አባላት እና የስፖርት ቤተሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ማኀበሩ ጥሪውን አቅርቧል።", "passage_id": "54aa5cbf89b6e22309f60ba052679c83" }, { "passage": "የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ማኅበር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አቅመ ደካሞች እና የጎዳና ተዳዳሪዎች ችግር ውስጥ እንዳይገቡ በማሰብ ያሰባሰበውን ገንዘብ እና ቁሳቁሶችን ነገ ሊያስረክብ ነው።የኮሮና ወረርሽኝ በዓለም እና በሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ ቀውስ ከመፍጠሩ ባሻገር በስፖርቱ ረገድም በውድድሮች እና ስልጠናዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ በመፍጠር ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ያስቆመ ተግባር መሆኑ ይታወቃል።ይህን ተከትሎ የኢትዮዽያ ተጫዋቾች ማኅበር ማኀበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በማሰብ አባላቱ እና የስፖርት ቤተሰቡ አቅም በፈቀደ መጠን ለአቅመ ደካሞች፣ ለጎዳና ተዳዳሪዎች ይውል ዘንድ እርዳታ የማሰባሰብ ዕቅድ አውጥቶ የገንዘብ፣ የምግብ እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ለቀናት ሲያሰባስብ መቆየቱ ይታወሳል። የዚህ በጎ አላማ ማጠቃለያና ነገ (አርብ ሚያዚያ 9) ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚመለከተው አካል የርክክብ መርሐ ግብር እና የነበረውን ሂደት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ አዘጋጅቷል።", "passage_id": "1f9c50f6658b82208c6998867bc414b8" }, { "passage": "በንግድ፣ በሚዲያ እና በሌሎች መስኮች እየተሳተፉ የሚገኙ እንዲሁም የቀድሞ ታዋቂ የብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች የተቋቋመው የአበበ ቢቂላ የጤና ስፖርት ማኅበር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት የሚያግዝ የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።ምስረታውን 2006 ያደረገው ይህ ማኅበር በአውሮፓ፣ በአሜሪካ የኢትዮጵያዊያን የስፖርት ፌስቲቫሎች ለተከታታይ ዓመታት በስኬት በማዘጋጀት ይታወቃል። የአበበ ቢቂላ የጤና ስፖርት ማኅበር በአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ለስፖርት ለሁሉም በሚያዘጋጃቸው የጤና ቡድኖች ውድድሮች ላይም በተደጋጋሚ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡ከዚህ ቀደም በተለያዩ ማኅበራዊ ተግባራት ላይ ድጋፍ በማድረግ የሚታወቀው የአበበ ቢቂላ የጤና ቡድን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያቀረበውን የድጋፍ ጥሪ በመቀበል ግምቱ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ የሆነ የምግብ እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ በዛሬው ዕለት በከተማው አስተዳደር ቅጥር ግቢ በመገኘት ድጋፍ አድርጓል፡፡ በቀጣይነት አባላቱን በማሰባሰብ ቀጣይ ድጋፎችን እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል።", "passage_id": "eb0e6c38e2dabade0ce92789f47a71f8" } ]
c5a742e5fba1f489ca2d6cf330a21896
59cbb6cea81e6e20224432ebd962e39c
ዶፒንግ ቅሌት በምን ይዳኝ?
ጀግናው አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ እኤአ በ2016 መባቻ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆኖ መመረጡን ተከትሎ አበረታች መድሃኒት ተጠቅመው የተገኙ አትሌቶች በስፖርት ህግ ሳይሆን በወንጀል መቅጫ ህግ እንዲጠየቁና ለእስር እንዲዳረጉ መበረታታት እንዳለበት ሲሞግት ነበር። የኢትዮጵያ መንግስትም በዚህ ወንጀል የተሳተፉ አትሌቶች በወንጀል መቅጫ ህግ እንዲጠየቁና ለእስር እስከሚዳርግ ቅጣት እንዲጣልባቸው ማድረጉን ተከትሎ በዓለም ዙሪያ ብዙ ክርክሮች ተነስተው እንደነበር አይዘነጋም። ይህ አከራካሪ ጉዳይ አሁንም መቋጫ አላገኘም። በተለይም ሃይሌ ከቀናት በፊት ከዓለም አቀፉ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ወጣት ሪፖርተሮች ጋር በነበረው የልምድ ልውውጥ በዚህ አቋሙ እንደፀና መግለፁን ተከትሎ በጉዳዩ ላይ የሚነሱ ክርክሮች በርትተው ታይተዋል። በተለያዩ መገናኛ ብዙሃንም ሰፊ ሽፋን እየተሰጠው ይገኛል። በእርግጥ የስፖርቱን ቤተሰብ ለሁለት የከፈለው ‹አበረታች መድሃኒት የተጠቀሙ አትሌቶች በስፖርት ወይንም በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ይዳኙ?› የሚለው ሃሳብ አከራካሪ መሆኑ የግድ ነው። የዓለም አቀፉ ፀረ አበረታች መድሃኒቶች ኤጀንሲ(ዋዳ) አበረታች ንጥረ ነገሮችን በሚጠቀሙ አትሌቶች ላይ ምንም አይነት ምህረት እንደሌለውና እንደማይታገስ ቢታወቅም አትሌቶች በወንጀል መቅጫ ህግ እንዲጠየቁና ለእስር እንዲዳረጉ አይደግፍም። ይሁን እንጂ ኤጀንሲው በራሱ ህግ መሰረት አበረታች መድሃኒት ተጠቅመው የተገኙ አትሌቶችን በቅድሚያ ለአራት ዓመት ከየትኛውም ውድድር በማገድ ያገኙትን ክብር ሁሉ ይነጥቃል። ለሁለተኛ ጊዜ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ አትሌትም ለስምንት ዓመታት ተመሳሳይ ቅጣት ይጣልበታል። ከዚህ ካለፈም ለእድሜ ልክ ከስፖርቱ ይታገዳል። ይህም በቂ ቅጣት ነው ብሎ ያምናል። ሃይሌ ግን ይህ ቅጣት ብቻውን በቂ እንዳልሆነ ያምናል። አበረታች መድሃኒት ተጠቅመው የተገኙ አትሌቶች በስፖርቱ ህግ ብቻ ሳይሆን በወንጀል መቅጫ ሕግ እስከ እስር የሚደርስ ቅጣት ሊጣልባቸው እንደሚገባ ይሞግታል። ለዚህም የተለያዩ ሞጋች ምክንያቶችን ይደረድራል። ‹‹አበረታች መድሃኒት መጠቀም ውድድሮችን ለማሸነፍ ብቻ በማሰብ የተፈፀሙ ተደርጎ መታሰብ የለበትም፣ ሰዎች ቀለል አድርገው ይመለከቱታል›› የሚለው ሃይሌ ወንጀሉ ከስፖርታዊ ኩነትም የበለጠ ትርጉም እንዳለው ያምናል። እንደ ሃይሌ እምነት አንድ አትሌት በአንድ ውድድር ሲያሸንፍ ሁለት ወይም ሦስት መቶ ሺ ዶላር ሽልማት ያገኛል። ይህን ሽልማት በማሰብ አበረታች መድሃኒትም ይጠቀማል፣ ከዚያም ተይዞ ለአራት ዓመት ከውድድር ይታገዳል። አትሌቱ ሽልማቱን እስካገኘ ድረስ ከውድድር መታገዱ ምንም ላይመስለው ይችላል፣ እገዳውን ሲጨርስ ዳግም ተመሳሳይ ጥፋት ይፈፅማል። በሌላው ህብረተሰብ ዘንድም ወንጀል እንደሰራ ላይታሰብ ይችላል። ይሁን እንጂ ይህን ድርጊት የፈፀም አትሌት በወንጀል ቢጠየቅና ለእስር ቢዳረግ በሌላው ማህበረሰብ ዘንድም እንደ‹ሌባ› ሊቆጠርና ሊወገዝ ይችላል። ዳግምም በዚህ ድርጊት ተሳታፊ እንዳይሆን በእርስ ቅጣቱ ሊማር ይችላል። የሃይሌን ሃሳብ ከሚቃወሙት የስፖርቱ ቤተሰቦች መካከል የዓለም አቀፉ ፀረ አበረታች መድሃኒት ኤጀንሲ(ዋዳ) የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሰር ክሬግ ሬዲ አንዱ ናቸው። አበረታች መድሃኒት እንደ አጋጣሚ ተጠቅመው ለሚገኙ አትሌቶች ስፖርታዊ ቅጣቶቹ በቂ መሆናቸውን ያምናሉ። በእርግጥ ሰር ክሬግ አገራት በአትሌቶች ላይ ሳይሆን አበረታች መድሃኒቶችን በማምረት፣ በማሰራጨትና አትሌቶች እንዲጠቀሙ በማድረግ ተሳታፊ የሆኑ ማንኛቸውም ግለሰቦችና ተቋማት በወንጀል ህግ እንዲጠየቁ ዋዳ እንደሚያበረታታም አልዘነጉም። ሃይሌ የአበረታች መድሃኒት ተጠቃሚነት ጉዳይ የኢትዮጵያን አትሌቲክስና የአገሪቱን ባህል ከመጣስ አኳያ ትልቅ ክብደት የሚሰጠው ጉዳይ እንደሆነ ይናገራል። ኢትዮጵያ የምትወስደውን እርምጃ ሌሎች አገራት የግድ ይተግብሩት የሚል አቋም ግን የለውም። በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ቅጣትም መጥፎ ነው ብሎ አያምንም። እያንዳንዱ አገርም በራሱ መንገድ ነገሮችን እንደሚመለከት ይናገራል። ሰር ክሬግ በበኩላቸው እያንዳንዱ አገር የየራሱ የወንጀል መቅጫ ህግ ያለው እንደመሆኑ መጠን ተመሳሳይ ጥፋት ያጠፉ አትሌቶች በየአገራቱ የወንጀል መቅጫ ህግ ይዳኙ ከተባለ ሚዛናዊነት ገደል ይገባል። ይህ ማለት እንደየ አገራቱ የወንጀል መቅጫ ህግ ልዩነት ኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀሉን የፈፀመ አትሌት ሌሎች አገራት ላይ ተመሳሳይ ወንጀል ከፈፀመ አትሌቱ እኩል ቅጣት ሊገጥመውም ላይገጥመውም ይችላል።አዲስ ዘመን ግንቦት 3/2012
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=32125
[ { "passage": " ግዙፉ የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያ ናይኪ በአሜሪካ ፖርትላንድ ኦሪገን ያለውን የአትሌቲክስ ፕሮጀክት መዝጋቱን አስታወቀ። የፕሮጀክቱ አሰልጣኝ የሆነው አልቤርቶ ሳላዛር ከአበረታች መድኃኒት ዓለምአቀፍ ሕግጋቶች መጣስ ጋር ተያይዞ ከሳምንት በፊት ከማንኛውም ስፖርት ለአራት ዓመታት መታገዱ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ ናይኪ ፕሮጀክቱን ለመዝጋት እንደወሰነ ረነርስ ወርልድ ከትናንት በስቲያ ምሽት ዘግቧል። አሰልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር በፕሮጀክቱ የሚያሰለጥናቸውን አትሌቶች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ አበረታች መድኃኒት እንዲጠቀሙ ያደርጋቸዋል በሚል ከስፖርቱ መታገዱን ተከትሎ በፕሮጀክቱ የታቀፉ አትሌቶች ጥያቄ ውስጥ መግባታቸው አልቀረም። የናይኪ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ፓርከር ለረነርስ ወርልድ እንደገለፁት፣ የፕሮጀክቱ አትሌቶች ባልተረጋገጠ አሉባልታ ከአበረታች መድኃኒትተጠቃሚነት ጋር ስማቸው መነሳቱ ያላቸውን እምቅ አቅም ተጠቅመው በልምምድና ውድድሮች ላይ ትኩረት እንዳያደርጉ ተፅዕኖ ስለሚፈጥርባቸው ፕሮጀክቱን መዝጋት አስፈላጊ ሆኗል። ስለዚህም ናይኪ ኩባንያ የፕሮጀክቱን አትሌቶች በሚፈልጉትና ትክክል ነው ብለው በሚያምኑት አሰልጣኝና የሥልጠና ሂደት እንዲከታተሉ በማድረግ ድጋፉን ከውጪ ሆኖ እንደሚቀጥልበት ሥራ አስፈፃሚው ተናግረዋል። የፕሮጀክቱን በርካታ አትሌቶች የሚያሰለጥኑት ፒት ጁሊያን ከአበረታች መድኃኒት ጋር በተያያዘ ስማቸው የማይነሳ ከመሆኑም ባሻገር የዓለም አትሌቲክስ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዳላቸው ይነገራል። የናይኪ ኦሪገን ፕሮጀክት ሲዘጋ የእኚህ አሰልጣኝ ዕጣፈንታ ምን እንደሚሆን የተገለፀ ነገር የለም። በቅርቡ በተጠናቀቀው የዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በአስር ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ ማሸነፍ የቻለው ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻን ጨምሮ የአስርና አንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር ቻምፒዮኗ ትውልደ ኢትዮጵያዊት የኔዘርላንድስ አትሌት ሲፈን ሃሰን የናይኪ ኦሪገን አትሌቲክስ ፕሮጀክት ሰልጣኞች ናቸው። ነገ በሚካሄደው የቺካጎ ማራቶን የሚወዳደሩት አሜሪካውያኑ ጋለን ሩፕና ጆርዳን ሃሴይም የዚሁ ፕሮጀክት ፍሬዎች ናቸው። የሦስት የዓለም ቻምፒዮናዎችና የሁለት ኦሊምፒኮች የአስርና አምስት ሺ ሜትር ቻምፒዮኑ እንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህን በነገው የቺካጎ ማራቶን ለአሸናፊነት የሚጠበቅ የቀድሞ የናይኪ ኦሪገን አትሌቲክስ ፕሮጀክት ውጤት መሆኑ ይታወቃል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆነው የአትሌቲክስ ስፖርት አሠልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን ከቦታ ቦታ ማዘዋወርን\n(Trafficking) ጨምሮ የፀረ-ዶፒንግ እንቅስቃሴውን በማወክ\n(Tampering) እና በተለያዩ የፀረ-ዶፒንግ የሕግ ጥሰቶች ተጠርጥሮ ጉዳዩ በአሜሪካ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (USA­DA) ሲጣራ ቆይቷል። በዚህም መሠረት ግለሰቡ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ለአራት ዓመታት በስፖርቱ ውስጥ እንዳይሳተፍ እገዳ ተጥሎበታል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶችና የስፖርት ባለሞያዎችም ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ ከአሰልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር ጋር የሚኖራቸውን ቀጥተኛም ይሁን ቀጥተኛ ያልሆነ ግንኙነት ማቋረጥ እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት ማሳሰቡ ይታወሳል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 1/2012ቦጋለ አበበ", "passage_id": "ba423af6511abb3fd29996df2ac6a138" }, { "passage": "ዛንግ ዩሃን እ.ኤ.አ በ1993 ሁለት ልጆችን በመግደል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት ፖሊስ ጥፋቱን እንዲያምን እንዳሰቃየውና እንዳስገደደው ተናግሮ ነበር።\n\nዛንግ በቻይና ለ9778 ቀናት፤ በዢያንግዢ ማረሚያ ቤት በስህተት ለረዥም ጊዜ የታሰረ ሰው ሆኖ ተመዝግቧል።\n\nየዛንግን የክስ መዝገብ ዳግም ያንቀሳቀሱት አቃብያነ ህጎች በወቅቱ የሰጠው የእምነት ክህደት ቃል ወጥነት ይጎድለው እንደነበር በመግለጽ ከተፈፀመው ወንጀል ጋርም እንደማይገናኝ ተናግረዋል።\n\nከፍተኛው ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብሎ 27 ዓመት በእስር ቤት ውስጥ ላሳለፈበት ወንጀል በቂ ማስረጃ የለም ብሎ በመወሰኑ በነጻ ተለቅቋል።\n\nታዛቢዎች ቻይና በወንጀል ተጠርጥረውና በስህተት ተፈርዶባቸው በእስር ቤት የሚገኙ ሰዎችን ለመልቀቅ ፈቃደኝነት እያሳየች ነው ሲሉ ተናግረዋል። ይህ ግን የፖለቲከኛ እስረኞችን አይጨምርም ተብሏል።\n\nበቻይና መገናኛ ብዙኀን የቀረበው ምስል እንዳሳየው ዛንግ ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ ከ83 ዓመት እናቱ ጋርና ከቀድሞ ባለቤቱ ጋር ተገናኝቷል።\n\nበቻይና ፖሊስ በተለያዩ ወንጀሎች የተጠረጠሩ ሰዎች ላይ ምርመራ በሚያደርግበት ወቅት ድብደባ እንደሚፈጽም፣ እንደሚያሰቃይ፣ እንቅልፍ እንደሚከለክል፣ በሲጋራ እንደሚያቃጥል፣ ይነገራል።\n\nከዚህ ቀደም በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች በዚህ ሁሉ ውስጥ አልፈው የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ይደረግ ነበር።\n\nእ.ኤ.አ በ2010 ግን የቻይና የሕግ ስርዓት አስገዳጅ የሆነን ምርመራ ለማስቀረት መስራት ጀመረ። \n\nየሞት ፍርድም ቢሆን በቻይና ጠቅላይ ፍርድ ቤት መጽደቅ ያለበት ሲሆን የተፈፀመ ወንጀል ላይ የሚሰጥ ፍርድም በተጠርጣሪው የእምነት ክህደት ቃል ላይ ብቻ እንዳይመሰረት ተወስኗል።\n\nዛንግ ከቀድሞ ሚስቱ፣ ሶንግ ጋር ከመለያየታቸው በፊት ሁለት ወንድ ልጆች ወልደዋል። ሶንግ ድጋሚ ብታገባም የቀድሞ ባለቤቷን ይግባኝ ክስ ግን ትከታተልና ትደግፍ ነበር።\n\n\"የችሎቱን ውሳኔ ስሰማ በጣም ነው ደስ ያለኝ\" ብላለች ሶንግ። ዛንግ በእስር ቤት ላባከናቸው ዓመታት ካሳ እንደሚከፈለው ችሎቱ ወስኗል።\n\n\"ከደንበኛዬ ጋር ስለ ካሳው መጠን እንነጋገርበታለን\" ብለዋል የዛንግ ጠበቃ፣ ዋንግ ፌይ ለቻይና ዴይሊ።\n\nአክለውም \"እንዲህ ዓይነት የሕግ ጥሰት የፈጸሙትንም ተጠያቂ ለማድረግ እቅድ አለን።\" \n\nዛንግ በቁጥጥር ስር የዋለው እ.ኤ.አ በ1993 ሲሆን ሁለት ወጣቶች በናንቻንግ ግዛት ጂያንግዢ ከተማ በውሃ ኩሬ ውስጥ አስከሬናቸው መገኘቱን ተከትሎ ነው።\n\nዛንግ የሟቾቹ ጎረቤት ሲሆን በወቅቱ በግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ ነበር በቁጥጥር ስር የዋለው።\n\nበ1995 የናንቻንግ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ነህ በማለት ሞት የፈረደበት ቢሆንም ነገር ግን ፍርዱ ሁለት ዓመት ከታሰረ በኋላ በእድሜ ይፍታህ ተቀይሮለታል።\n\nዛንግ በምርመራ ወቅት ስቃይ እንደደረሰበት በመግለጽ ነጻ መሆኑን ሲከራከር ነበር።\n\nነገር ግን በወቅቱ ይግባኝ ያለው ጉዳይ ውጤት ሳያስገኝለት ቀርቷል። ከዚያ በኋላ በ2019 መጋቢት ወር ላይ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጉዳዩን ዳግም ለማየት ተስማምቶ ዛንግ በቂ ባልሆነ ማስረጃ እስር ቤት መወርወሩን በመግለጽ ነፃ ነህ ብሎታል።\n\nከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ቲያን ጋንሊን እንዳሉት \"ያገኘናቸውን ማስረጃዎች ከፈተሽን በኋላ የዛንግን ወንጀል የሚያስረዱ ቀጥተኛ ማስረጃዎች ማግኘት አልቻልንም። ስለዚህ አቃቢያነ ህጎቹ ያቀረቡትን ሃሳብ ተቀብለን ዛንግን ነፃ መሆኑን የሚገልጽ ውሳኔ አሳልፈናል።\"\n\nበ1993 ሁለቱን ወጣቶች ማን እንደገደላቸው እስካሁን ድረስ አልታወቀም።\n\n ", "passage_id": "91b019020bb9d0173fbe59580d68b41c" }, { "passage": "እአአ\nበ1980 ሞስኮ ባዘጋጀችው ኦሊምፒክ፤ የ5ሺ ሜትር አሸናፊ ኢትዮጵያዊው አትሌት ምሩጽ ይፍጠር መሆኑ ለዓለም አዲስ ታሪክ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ በዘመናዊው ኦሊምፒክ ከዚያ ቀደም በተካሄዱት 14 መድረኮች አንድም አፍሪካዊ የወርቅ ሜዳሊያ ሳያጠልቅ መቆየቱ ነው። ርቀቱ በበላይነት የተያዘውም በአውሮፓውያን አትሌቶች ሲሆን፤ በተለይ ፊንላንዳውያን በርቀቱ ነግሰው እንደነበር ታሪክ ያወሳል። በ10ሺ ሜትርም በተመሳሳይ የበላይነቱ በአውሮፓውያን አትሌቶች (ለ11 ኦሊምፒኮች) የተያዘ ነበር። እአአ በ1968 ኬንያዊው ናፍታሊ ተሙ እና ኢትዮጵያዊው ማሞ ወልዴ ተከታትለው የወርቅና ብር ሜዳሊያውን እስኪወስዱት ድረስ። የምስራቅ አፍሪካውያኑ አትሌቶች ድል አድራጊነቱን ከተቀላቀሉ በኋላም የደረጃ ሰንጠረዡን ቀዳሚ ስፍራ ሊቆጣጠሩት ችለዋል። ከኦሊምፒክ ባሻገር ባሉ ውድድሮች ላይ የሚታየው ልምድም ከዚህ የተለየ የሚባል አይደለም። ኢትዮጵያ\nለዘመናት ስሟን ያስጠራችበት ይህ የአትሌቲክስ ውድድር ግን ለመጥፋት ጥቂት ቀርቶታል። በርካታ ጀግና አትሌቶች ድል የነሱበት የ10ሺ ሜትር ርቀት በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንዲሁም በኦሊምፒክ ብቻ ከተወሰነ ሰነባብቷል። በዳይመንድ ሊግ ይታይ የነበረው የ5ሺ ሜትር ርቀትም ተመሳሳይ ዕጣ እንደሚደርሰው ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በቅርቡ አስታውቋል። ከጥቂት\nአስርት ዓመታት ወዲህ ሙሉ ለሙሉ በምዕራባውያኑ የበላይነት ተይዞ የቆየው ርቀት በምስራቅ አፍሪካውያኑ አትሌቶች ተወስዷል። ሀገራቱ በዚህ ምክንያት ሙሉ ትኩረታቸውን ወደ አጭርና መካከለኛ ርቀቶች እንዲሁም የሜዳ ላይ ተግባራት እንዲያደርጉም ተገደዋል። ስለዚህም በአፍሪካውያን የተወሰደ ክብራቸውን ለማስመለስ ሀገራትን ማዳከም የመጀመሪያው እርምጃቸው መሆኑ ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው። ውሳኔውን ተከትሎም በርቀቱ በተለይ ውጤታማ የሆኑት ጎረቤታሞቹ ኬንያ እና ኢትዮጵያ ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ። ምንም እንኳን በኬንያ በኩል የመወላወል ነገር እየታየ ቢሆንም፤ ኢትዮጵያ ግን በፌዴሬሽኗ፣ በኦሊምፒክ ኮሚቴዋ እንዲሁም በዝነኛ አትሌቶቿ ትግል ማድረጓን ተያይዛዋለች። መታገሉ በህዝቡ ዘንድ እንደ ባህል የሚታየውን ውድድር ወደ ቀድሞ ክብሩ እንዲመለስ ለማድረግ መልካም ሆኖ ሳለ፤ ሌላ የቤት ስራ የሚሰጥ መሆኑ ግን መዘንጋት የለበትም። ይህም ኢትዮጵያን ለመሳሰሉ ሀገራት ይታወቁበት ከነበረው ርቀት ሌላ አማራጭ እንዲመለከቱ የግድ የሚል መሆኑን ነው። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም በረጅም ርቀት አትሌቲክስ የተጣለውን ውሳኔ ከማስቀልበስ እንቅስቃሴው ባሻገር በሌሎች ርቀቶች ላይ የሚገኙአትሌቶችን መመልከት ይኖርበታል። በተለይ ለአጭር ርቀት እንዲሁም ለሜዳ ላይ ተግባራት ምቹ የሆኑ የአካል ብቃት እንዲሁም የአኗኗር ሁኔታ ላይ በሚገኙ አትሌቶች ላይ ትኩረቱን መጨመር እንደሚገባው በትክክልም የሚጠቁም ነው። በውሳኔው\nመሰረት በረጅም ርቀት የሚካፈሉ አትሌቶች ሁለትና አራት ዓመታትን ጠብቀው መወዳደራቸው የግድ ነው። የፌዴሬሽኑ ስጋት ደግሞ አትሌቶች ዓመታትን ከመጠበቅ ይልቅ ፊታቸውን ወደ ጎዳና ሩጫዎች መመለሳቸው ይጎዳቸዋል የሚል ነው። ይህ ስጋት ትክክለኛ ቢሆንም ግን ከማራቶን ባሻገር በመካከለኛ፣ በአጭር፣ በዝላይ፣ በውርወራ እንዲሁም በእርምጃ ወደ ሚካሄዱ ውድድሮች ፊታቸውን እንዲያዞሩ ማድረግ ተገቢ ነው። ኢትዮጵያ ከኬንያ ስትነጻጸር በታላቁ የኦሊምፒክ መድረክ ሜዳሊያ ያስመዘገበችው፤ በ1ሺ 500 ሜትር፣ በ3ሺ ሜትር መሰናክል፣ በ5ሺ ሜትር እንዲሁም በ10ሺ ሜትር ውድድሮች ብቻ ነው። በአንጻሩ ኬንያ ከእነዚህ ርቀቶች ባሻገር በ400 ሜትር፣ በ400 መሰናክል፣ በ400 ሜትር፣ 800 ሜትር እንዲሁም በጦር ውርወራ ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች። ይህም ኢትዮጵያ ምን ያህል በአንድ አካባቢ ተወስና እንደቀረች የሚያሳይ ሲሆን፤ ኬንያ በበኩሏ ተሳትፎዋን በማብዛቷ ውጤታማ ለመሆኗ ማሳያ ይሆናል። ኢትዮጵያም ሁሌም ከምትነሳባቸው አራትና አምስት ርቀቶች ያላለፈ ዝናዋን በድጋሚ መገንባት የሚቻልበት መንገድ መኖሩን መዘንጋት አያስፈልግም። ለፌዴሬሽኑ እንዲሁም ለኦሊምፒክ ኮሚቴም አካባቢያቸውን እንዲቃኙ በግልጽ የተቀመጠ ማንቂያ ይሆናል። እንደ ነባራዊው ሁኔታ ከሆነ፤ በኢትዮጵያ ባሉ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከወረዳ ጀምሮ አያሌ የታዳጊ ወጣት ፕሮጀክቶች ይገኛሉ። በእነዚህ ፕሮጀክቶችም ከእግር ኳስ ስፖርት በሚስተካከል መልኩ የአትሌቲክስ ስፖርት ስልጠና ይሰጣል። ከዚህ ባሻገር በሀገር አቀፍ ደረጃ አራት የስልጠና ማዕከላት እንዲሁም ሁለት አካዳሚዎች ይገኛሉ። በእነዚህም ውስጥ አትሌቲክስ በከፍተኛ ትኩረት ስልጠና የሚሰጥበት ዘርፍ ነው። በተለያዩ አካባቢዎችም በራሳቸው ጥረት እንዲሁም በግል አሰልጣኞች አትሌት ለመሆን የሚታትሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳጊና ወጣቶች ይገኛሉ። ከእነዚህ\nሰልጣኞች የሚልቁት ደግሞ ትኩረታቸውን በረጅም ርቀት አትሌቲክስ ላይ ያደረጉ ናቸው። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በማትታወቅበት የሜዳ ላይ ተግባራት ያለው ሁኔታ፤ በፍላጎት፣ በግብዓት እንዲሁም በቁሳቁስ እጥረት እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ነገር ግን በተለያዩ ጊዜያት ፌዴሬሽኑ ባደረገው ምልከታም ይሁን ባለሙያዎች እንደሚገልጹት በተለይ በአጭር ርቀት፣ ውርወራ እና ዝላይ ውጤታማ መሆን የሚችሉ ታዳጊዎች የሚፈሩባቸው አካባቢዎች ይገኛሉ። በመሆኑም ማሰልጠኛ ማዕከላት ከእነዚህ አካባቢዎች ወጣቶችን በመመልመል፣ ፌዴሬሽኑም አስፈላጊውን ግብዓት በማሟላት እንዲሁም ተገቢውን ስልጠና እንዲሰጥ በማድረግ ውጤታማነትን መመለስ ይችላል። የኢትዮጵያ\nአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከዓመት በፊት በመላ ሀገሪቷ በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ምልከታ በባለሙያዎቹ ማድረጉ የሚታወስ ነው። ስልጠናው የሚሰጥባቸው ቦታዎች ከባህር ጠለል በላይ የሚገኙበትን በመመልከት እንዲሁም የአኗኗር ሁኔታቸውን በማጥናት ለየትኛው የስፖርት ዓይነት ምቹ ነው የሚለውንም ለይተዋል። በወቅቱ ፌዴሬሽኑ ባስቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት አዳዲስ አትሌቶችን የመመልመል ስራዎች መሰራታቸውን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ አስታውቀው ነበር። በአቅርቦት ላይ የሚታየውን ችግር ለመፍታትም ፌዴሬሽኑ በአነስተኛ ዋጋ ከሚያቀርቡ ከሀገር ውስጥ አምራች ድርጅቶች ጋር በመነጋገር ላይ መሆኑ ተጠቁሞ ነበር። በተለይ እንደየ ሰልጣኙ እድሜ፣ ለውድድርና ለስልጠና በምን ያህል መስፈርት መዘጋጀት ይገባል እንዲሁም ለየክልሎቹ ምን ያህል አቅርቦት ያስፈልጋል በሚለው ላይም ፌዴሬሽኑ ዝግጅት ተደርጓል። በሀገሪቷ\nያሉት አሰልጣኞች ቁጥር ከስልጠናውና ከሰልጣኞቹ ጋር የሚመጣጠን አለመሆኑም ተረጋግጧል። በመፍትሄነትም አሰልጣኞችን ከውጭ ሀገራት ለማስመጣት መታቀዱ በወቅቱ ተገልጾ ነበር። ልምድ ያላቸውን አሰልጣኞች ለማስመጣት በሙከራ መሆኑንና ለኢትዮጵያውያን አሰልጣኞች ልምድና ተሞክሮዎችን እስደሚሰጡም ይጠበቅ ነበር። ይህንን\nስራ ቀድሞ የመጀመሩ አስፈላጊነት አያጠያይቅም፤ ነገር ግን ቀጣይነቱ ላይ ምን እየተሰራ ይገኛል? የሚለው ዋነኛው ጉዳይ ነው። በፌዴሬሽኑ በኩል በዓለም ላይ እየታየ ያለውን ሁነት ተከትሎ መፍትሄ ማበጀት እንዲሁም የጀመሩትን ስራ ከዳር ማድረስ የግድ መሆኑም መዘንጋት የለበትም። ከጥያቄው ባሻገር የተሰጠውን የቤት ስራ ለማከናወን በሙሉ ዝግጁነት መነሳትም አስፈላጊ ነው።", "passage_id": "127551a136af260b2579d72e99514d08" }, { "passage": "ዶክተር ሊ ዌንሊያንግ\n\nየዶክተሩ ሞት ከተሰማ በኋላ የቻይና የማህበራዊ ትስስር መድረክ በሆነው ዌቦ ላይ ዜጎች ከፍተኛ ሐዘናቸውን ሲገልጹ ቆይተው ሁኔታው ወደ ቁጣ ለመቀየር ጊዜ አልፈጀበትም።\n\nበዚህም ምክንያት መንግሥት መጀመሪያ ላይ በሽታውን ለመደበቅ በመሞከርና የወረርሽኙን አስከፊነት በማቃለል ክስ እየተሰነዘረበት ነው።\n\nበዶክትር ሊ ሞት የተፈጠረው ቁጣ እየተባባሰ በቻይና ውስጥ የመናገር ነጻነት ስላለበት ሁኔታ ውይይት እንዲጀመር አድርጓል። \n\nየአገሪቱ ጸረ ሙስና ተቋምም \"ከዶክተሩ ጉዳይ ጋር በተያያዘ\" ምርመራ ማድረግ እንደሚጀምር አሳውቋል።\n\nአንድ የቻይና ድረ ገጽ እንዳለው የሟቹ ዶክተር ባለቤት እርጉዝ ስትሆን ሰኔ ላእ እንደምትወልድ ይጠበቃል። \n\nኮሮናቫይረስ እስካሁን 636 ሰዎችን የገደለ ሲሆን ከ31 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በቻይና ብቻ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። \n\nዶክተር ሊ ዌንሊያንግ ወረርሽኙ በተከሰተበት ዉሃን ከተማ ዉሃን ሴንትራል ሆስፒታል ውስጥ ይሰራ ነበር። \n\nዶክተር ሊ በሆስፒታሉ ውስጥ ይሰራ በነበረበት ወቅት በአንድ እንግዳ ቫይረስ ተጠቅተው የመጡ ሰባት ሰዎችን ያገኛል። ከዚያም በሽታው ከ15 ዓመታት በፊት ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ሆኖ የነበረው 'ሳርስ' ሳይሆን እንደማይቀር ገምቶ ነበር። \n\n• ኢትዮጵያውያን፡ የአስወጡን ድምጽ በጎሉባት የቻይናዋ ዉሃን \n\n• ለመከላከል ብቻ ሳይሆን ስም ለማውጣት ያስቸገረው አዲሱ ቫይረስ \n\nየበሽታውን መከሰት በተመለከተ ለሰዎች በመንገር እንዲጠነቀቁ ምክር የለገሰ ሲሆን ፖሊሶች ቤቱ ድረስ መጥተው ከድርጊቱ እንዲቆጠብ አስጠንቅቀውታል። \n\nፖሊሶቹ በወቅቱ 'ሃሰተኛ መረጃን እያሰራጨህ ህብረተሰቡን እያሸበርክ ነው' ሲሉ ነበር ማስጠንቀቂያውን የሰጡት። \n\nዶክተር ሊ ይህን ማስጠንቀቂያ ከደረሰው ከአንድ ወር በኋላ ግን በሽታው በወረርሽኝ መልክ ተከስቶ ዓለምን ማስጨነቅ ሲጀምር፤ ዶክተር ሊም የበሽታው ሰለባ ሆኖ የሆስፒታል አልጋ ላይ ሆኖ ነበር።\n\nሊ ከሃኪም ቤት ተኝቶ ታሪኩን ይፋ ሲያደርግ ጀግና ተብሎ ተወድሷል። \n\n\"ጤና ይስጥልኝ፤ ሊ ዌንሊያንግ እባላለሁ፣ በዉሃን ማዕከላዊ ሆስፒታል የዓይን ሃኪም ነኝ\" በማላት ይጀምራል የዶክተሩ መልዕክት።\n\nዶክተሩ ይፋ ያደረገው መልዕክት የኮሮናቫይረስ በተከሰተባቸው የመጀመሪያ ሳምንታት ዉሃን ውስጥ ያሉ ባለስልጣናት በሽታውን ለመሸፋፈን ያደረጉትን ጥረት ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው ተብሏል።\n\nታህሳስ ወር ላይ ወረርሽኙ በተከሰተበት ማዕከል ውስጥ ይሰራ የነበረው ዶክተር ሊ በአንድ እንግዳ ቫይረስ ተጠቅተው የመጡ ሰባት ሰዎችን አግኝቶ ነበር ተናግሯል። \n\n• የኮሮናቫይረስ ስጋትና የኢትዮጵያ አየር መንገድ\n\nእንደ አውሮፓዊያኑ ታህሳስ 30 ላይ ዶክተሩ በአንድ የቡድን መልዕክት መለዋወጫ መድረክ ላይ ለሙያ አጋሮቹ ዶክተሮች ስለወረርሽኙ መከሰትና እራሳቸውን ለመጠበቅ የመከላከያ አልባሳትን እንዲጠቀሙ የሚመክር መልዕክት አስተላልፎ ነበር።\n\nከአራት ቀናት በኋላ ከሕዝብ ደህንንት ቢሮ ባለስልጣናት መጥተው አንድ ደብዳቤ ላይ እንዲፈርም ነገሩት። ወረቀቱም ዶክተሩን \"ሐሰተኛ አስተያየቶችን በመስጠት\" ይህም \"በከፍተኛ ሁኔታ ማኅበራዊ ሥርዓትን የሚያናጋ\" መሆኑን በመግለጽ ጥፋተኛ አድርጎ የሚከስ ነበር።\n\nለዶክተሩ የተጻፈው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ\n\n\"በጥብቅ የምናሳስብህ ነገር ቢኖር፡ በዚህ ድርጊትህ በግትርነት የምትገፋ ከሆነና ሕግን ባለማክበር በሕገወጥ ተግባርህ የምትቀጥል ከሆነ ለፍርድ ትቀርባለህ። ገብቶሃል?\" ይላል የቀረበለት ወረቀት። ከስርም ዶክተር ሊ በእጅ ጽሑፉ \"አዎ፤ ተረድቻለሁ\" የሚል ጽሑፍ ሰፍሯል።\n\n\"ሐሰተኛ አሉቧልታዎችን በማሰራጨት\" በሚል ተጠርጥረው ምርመራ ከተደረገባቸው ስምንት ሰዎች ዶክተሩ አንዱ... ", "passage_id": "da75a810bae244788bdacb1d5af1c225" }, { "passage": "የጉዳት መጠናቸው ቢለያይም በስፖርቱ ዓለም ባለሙያዎቹ የሚፈፅሟቸው ስህተቶች በአብዛኛው የሁለት ምክንያቶች ውጤት መሆናቸው ይታመናል። አንዳንዶቹ በውጫዊ ተፅዕኖ ማለትም በደጋፊና በሌሎችም ጫናዎች ሲከሰቱ፤ አብዛኞቹ ደግሞ በስፖርተኞቹ ትኩረት ማጣት ሲከሰቱ ይስተዋላል። የስፖርት ሳይንስ ባለሙያዎች እንደ ሚገልፁት፤ በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር መጠናቀቁ እስካልተረጋገጠ ድረስ አሸናፊ ነኝ ብሎ ደስታውን ማጣጣም ስህተት ነው። ለአብነት እግር ኳስን ስንመለከት በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች የሚፈጠረው አይታወቅምና የጨዋ ታውን መጠናቀቅ የሚያበስረው የዳኛ ፊሽካ እስካልተሰማ «አሸንፌአለሁ» ማለት ሞኝነት ነው። በሰፊ የግብ ልዩነት መምራትም ብቻውን ዋስትና አይሰጥም። ይልቅስ ጨዋታው ሊጠናቀቅ የቀሩ ደቂቃዎችን ታሳቢ ማድረግ የግድ ይላል። በአትሌቲክሱም ቢሆን አንድ አትሌት የመጨረሻዋን መስመር ማለፉን እስካላረጋገጠ ድረስ ማሸነፉን ማረጋገጥ አዳጋች ነው። አንድ አትሌትም አሸናፊ ለመሆን ብቃቱን ከመጠቀም በተጓዳኝ ሌሎች ተግባራትን መከወን ግድ ይለዋል። በተለይ መነሻን እንጂ መድረሻውን ማወቅ ካልቻለ እጅግ ከባድ ዋጋ መክፈሉ አይቀርም። ይህን ጠንቅቆ መረዳት ይኖርበታል። ፊት ያለ ሁሉ መሪ ሳይሆን ተደራቢ ሊሆን ይችላልና የትኛው አትሌት ቀዳሚ ሆኖ እየመራ እንደሚገኝና ጠንቅቆ ማወቅም ግድ ይለዋል። ከሁሉም በላይ ውድድሩ ሊጠናቀቅ የቀሩትን ዙሮች ጠንቅቆ ማወቅ የግድ ይላል። ምክንያቱም በርካታ አትሌቶች የመግቢያ መስመሩን ማለፋቸው እንደ አሸናፊነት በመውሰድ በደስታ ሲፈነጥዙ ከኋላ በነበሩ አትሌቶች ተቀድመው ወርቃማ ዕድላቸውን አሳልፈው ሰጥተዋልና ነው። ከሰሞኑ በኢትዮጵያዊው አትሌት ሃጎስ ገብረሕይወት ላይ የሆነውም ይህ ነው። አትሌቱ ከሳምንት በፊት በተካሄደ የ5 ሺህ\nሜትር ውድድር ብዙ ዙሮችን ሲመራ ቢቆይም በኋላ ለማመን በሚከብድ መልኩ «ዙሩ አልቋል» በሚል በድል አድራጊነት ውድድሩን ሲያቋርጥ ታይቷል። መነሻን እንጂ መድረሻውን ማወቅ ያልቻለው አትሌት ሐጎስ፤ በስዊዘርላንድ በተካሄደው የዳይ መንድ ሊግ ውድድር 4 ሺህ 600 ሜትሮችን እንደሮጠ የመጨረሻ መስመር የደረሰ ሲመስለው በድል አድራጊነት እጁን እያነሳ አሸናፊነቱን ሲገልፅ ሚሊዮኖች ተመልክተውታል። የ25 ዓመቱ\nአትሌት በጊዜያዊ ዝንፈትና ድክመት የፈፀመው ስህተትም የውድድሩን የአሸናፊነት አቅጣጫ ቀይሮቷል። ሐጎስ ዙሩን ሳይጨርስ ያሸነፈ መስሎት ውድድሩን ያቋረጠበትን ምክንያት ሲያስረዳም፤ «የዙሩ የመጨረሻ መግለጫ ደወል ሲደወል አልሰማሁም፤ ውድድሩን እየመራሁ በነበረበት ወቅት ከፊት ለፊቴ አንድ ካሜራማን ነበር፤ በዚያ ምክንያትም ውድድርን በመሪነት ጨርሻለሁ ብዬ አሰብኩና ቆምኩ፤ ተወዛግቤ ነበር፤ ሌሎች ተወዳዳሪዎች አልፈውኝ ሲሮጡ ሳይ እንደገና መሮጥ ጀመርኩ፤ ውድድሩን እንዴት እንደጨረስኩ ባላውቅም ክስተቱ መጥፎ አጋጣሚ ነበር» ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። በአትሌቲክሱ ዓለም መሰል ስህተቶችን በመስራት አሸናፊነቱን አሳልፈው የሰጠው አትሌት ሐጎስ ብቻ ግን አይደለም። ብዙም ባይሆን የኢትዮጵያዊውን ዓይነት የሚያስቆጩ ስህተቶች የሰሩ አትሌቶች አሉ። ከእነዚህ መካከል ደግሞ እስራኤላዊቷ አትሌት ሎናህ ሳልፒተር ከሁሉ ቀድማ ትታወሳለች። አትሌቷ ባሳለፍነው ዓመት በአውሮፓ አትሌቲክስ ሻምፒዮን ሺፕ ውድድር ላይ የመግቢያ መስመሩን ሁለተኛ ሆኗ ማለፏን እንደ አሸናፊነት በመውሰድ በደስታ ስትፈነጥዝ ከኋላዋ የነበሩ አትሌቶች ቀድመዋት በመሄድ ውጤቷን ነጥቅዋታል። አትሌቷ በወቅቱ የውድድሩ የመጨረሻ ዙር መሆኑን የሚጠቁመው የደውል ድምፅ ከማስተዋልና ማዳመጥ ይልቅ ደስታዋን ለማጣጣም በመቸኮሏ አራት መቶ ሜትር እየቀራት ሩጫዋን አቋርጣለች፡፡ ምንም እንኳን ካቋረጠችበት ብትቀጥለም በአንዳች ቅፅበት የሰራችው ስህተት ግን ወርቃማ ዕድሏን አሳልፋ እንድትሰጥና አራተኛ ሆና እንድታጠናቅቅ አስገድዷታል። መስል ሁነቶች በአትሌቲክሱ ላይ ብቻም ሳይሆን በሞተር ሳይክል ውድድር ላይም ሲከሰት ታይቷል። እኤአ በ2012 በተካሄደው በጣሊያን ሞተር\nሳይክል ሻምፒዮን ሺፕ ሪካርዶ ሩሶ አንድ ዙር እየቀረው ለደስታ ጊዜውን ሲመድብ ተቀናቃኞቹ ቀድመውት አሸናፊነቱን በገዛ እጁ አሳልፎ ሰጥቷል። አንደኛ የነበረው ሞተረኛም አስራ አራተኛ ሆኖ ውድድሩን አጠናቋል። ምንም እንኳን እነዚህ ስፖርተኞች በአንዳች ቅፅበት በጥቃቅን ስህተት የፈፀሙት ተግባር ውድ ሽልማቶችና ክብሮችን ቢያሳጣቸውም፤ «የማይሳሳተው የሞተ ነው» እንደሚባለው፤ ተግባራቸው የሚያስተቻቸው አይሆንም። በስፖርቱ ዓለምም ስህተቶቹ ነገም መከሰታቸው አይቀሬ ነው። የስህተቶቹ የጉዳት መጠን ቢለያይም እንኳ፣ ዋናው ቁም ነገር እንዳይደገሙ ማስተካከል፣ነገ እንዳይለመዱም ማቅናትና ማፅናት ነው።አዲስ ዘመን  ሐምሌ 9/2011", "passage_id": "118f9d0732266d99ba67fea07cfcf4a0" } ]
95a0074c4ddf7228c731d07e7cb85416
786bb45a8bd02f3b42c124b346913817
መምህርነት በህፃንነት
የሰው ልጅ የፊት ገፅታ እንደ እድሜውና እንደ ኑሮው ደረጃ ብሎም እንደጤናው ሁኔታ ይለያያል። ሰው ኑሮውን ይመስላል እንዲሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች በአብዛኛው ጎስቆል ያለ የፊት ገፅታን ሲላበሱ በጥሩ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰዎች ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ በፊታቸው ላይ ምቾት ይነበባል። የሰው ልጅ መልኩ ሆዱ ውስጥ ነው የሚባለውም ለዚሁ አይደል። የሰዎች የፊት ገፅታም ቢሆን እንደየእደሜ ደረጃቸው የሚታይ ቢሆንም አልፎ አልፎ ግን ከጤና ችግርና ከተፈጥሮ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ሰዎች በአፍላ የወጣትነት እድሜያቸው ላይ ሆነው የሽምግልና ገፅታ፤ በሽምግልና እድሜ ላይ ሆነው ደግሞ የወጣትነት የፊት ገፅታን ይላበሳሉ። በየሃያ ሁለት ዓመቱ ፊሊፒንሳዊ ወጣት ላይ የታየውም እውነት ይሄው ነው ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ከሰሞኑ ዘግቧል።እንደዘገባው ከሆነ በፊሊፒንስ ቡልካን ፕሮቪንስ በሳን ሆዜ ዴል ሞንቴ መዋእለ ህፃናት መምህር የሆነው ኢያን ፍራንሲስ እድሜው 22 ዓመት ቢሆንም ፣ልክ እንደ እድሜ አቻዎቹ የጉርምስናን የፊት ገፅታ ሊላበስ አልቻለም። አቻዎቹ በአገጫቸውና ባላይኛው ከንፈራቸው ላይ ፂም ሲያበቅሉ እርሱ ግን ለዚህ አልታደለም። ከዚህ ይልቅ በመካከለኛ የክፍል ደረጃ እንዳሉ የታዳጊዎች የፊት ገፅታን ሊይዝ ችሏል። ወጣቱ በጉርምስና እድሜው የልጅ ፊት ገፅታ ቢላበስም ከእድሜ እኩዮቹ ሆነ ከሚያስተምራቸው ህፃናት ደግሞ ሽርደዳ አልገጠመውም። ምን አልባት ከጤና ጋር የተያያዘ ችግር ይሆናል በሚልም የሃኪም ቤት ደጅንም አልረገጠም። ስታንዳርድ ትሩዝ የተሰኘው የሃገሪቱ ሚዲያ እንደዘገበው ከሆነ ፤እድገቱ ሊዘገይና የልጅ ፊት ገፅታን ሊላበስ የቻለው ምን አልባት በህፃንነቱ በተደጋጋሚ በህመም ሲጠቃ ስለነበር እንደሆነ ኢያን አምኗል ብሏል። የመዋለ ህፃናት የመመህርነት መግቢያ ፈተናውንም ያለፈው ከገጠመው የጤና ችግር ጋር ተጋፍጦ እንደሆነ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅትም በመዋእለ ህጻናት ትምህርት ቤቱ የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎችን የሚያስተምር ሲሆን ትምህርት ቤቱም ለክፍል ደረጃው የሚመጥን መሆኑና በተማሪዎች ዘንድም የሚወደድ መሆኑን አረጋግጧል። ኢያን ማግና በበኩሉ ብዙዎቹ የእርሱ ተማሪዎች እርሱን እንደ ታላቅ ወንድማቸው የሚቆጥሩት እንደሆነ ተናግሯል። ይሁንና የህፃንነት ገፅታን የሚያሳየው ፊቱን ለማስረሳትና ራሱን ልክ እንደ መምህር ለመቁጠር ብዙ ጥረቶችን ማድረጉን ይገልፃል። በትክክለኛው የእድሜ ደረጃ ላይ የሚገኝ ወጣት ለመምሰልም ሰፋፊ የትልቅ ሰው ልብሶችንና ሹል የቆዳ ጫማዎችን እንደሚያደርግም ተናግሯል። ‹‹ምንም እንኳን የህጻን ፊት ቢኖረኝም እንደ መመህር አርያ ሆኜ መገኘት ይኖርብኛል›› ሲል ኢያን ለዚሁ ሚዲያ ገልጧል። ‹‹ሳስተምር ኮስተር እላለሁ በዚህ ጊዜ ተማሪዎች ኮስታራ መሆኔን ይረዳሉ›› ሲልም ጨምሮ ተናግሯል። ኢያን ካለው የህፃን ፊት ገፅታ በተጨማሪ ድምፁም የህፃን ልጅ ይመስላል። ቁመቱም 1፡62 ብቻ የሚረዝም ነው። እርሱ እንደሚለው የትምህርት ቤት ጓደኞቹ በእርሱ ላይ የሚቀልዱ ባይሆንም የእርሱ የህፃንነት ቁመና ግን አንዳንድ ጊዜ ከጫካኝ ቀልደኞች ኢላማ ሊያስመልጠው አልቻለም። አዲስ ዘመን መስከረም 20/2012አስናቀ ፀጋዬ
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=19810
[ { "passage": "በጎሮ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝቻለሁ። ሁሉም ተማሪዎች ቀልብን በሚስቡ፣ ሰማያዊና ሮዝ ቀለም ባላቸው ቦርሳዎቻቸው የትምህርት መሳሪያዎቻቸውን በጀርባቸው ተሸክመዋል። ቦርሳዎቹ ዘመናዊ የትምህርት ቁሳቁስ ፣የምሳ ዕቃ እና ሌሎችንም ይዟል። ይሄን ያገኙት ከትምህርት ቤታቸው በስጦታ ነው። የተደረገላችሁ ድጋፍ ምን ስሜት ፈጠረባችሁ ስል ጠጋ ብዬ ለአንዳንዶቹ ጥያቄዬን አቀረብኩላቸው። የሰባተኛ ክፍል ተማሪው መሀመድ ሲራጅ የመማሪያ ቁሳቁስ መያዣ ቦርሳ እና እስካሁን ያልነበረውን የትምህርት መገልገያ ቁሳቁስ በማግኘቱ እንደተደሰተ ይናገራል። እስካሁን በትምህርት በቆየባቸው ዓመታት ከቤተሰቡም ሆነ ከሌላ ቦታ ዘመናዊ ቦርሳ ተበርክቶለት እንደማያውቅ ይገልጻል፡፡‹‹ሁላችንም ተመሳሳይ ደረጃ ያላቸው ቦርሳዎች፣ የትምህርት ቁሳቁስ እንዲኖረን መደረጉና ዩኒፎርም አንድ አይነትና አዲስ መሆኑ ሌላ ወጪ ምንም ሳያሳስበን ወደ ትምህርታችን ብቻ እንድናተኩር ያደርገናል። ለጥሩ ውጤት እንድንተጋ ያግዘናል›› በማለት ዘንድሮ ለመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተደረገው ድጋፍ ለእርሱና ለጓደኞቹ ትርጉም ከፍ ያለ መሆኑን ያስረዳል፡፡ የአምስተኛ ክፍል ተማሪዋ ማርታ ሽመላሽ በበኩሏ፤ በትምህርት ቁሳቁስ ረገድ ሁሉ ነገር የተሟላላት በመሆኑ ስሜቷ በመልካም መንገድ እንደተቀየረ ትገልጻለች፡፡ በትምህርቷም ላይ በንቃት መሳተፍ እንደጀመረች ውጤቷም እየተሻሻለ መምጣቱን ታስረዳለች፡፡ የጎሮ መጀመሪያ ደረጃ\nትምህርት ቤት ርዕሰ\nመምህር አቶ በእደማሪያም\nሙሉጌታም ከአንደኛ እስከ\nስምንተኛ ክፍል ላሉት\nሁሉም ተማሪዎች የተበረከተላቸው\nዘመናዊ ቦርሳ፣ የትምህርት\nቁሳቁስ ድጋፉ የሲኤፍ\nፒኤ እና ሲጂሲኦሲ\nየሚባለው የቻይና ድርጅት\nመሆኑን ይናገራሉ። ይህ\nድጋፍ በአዲስ አበባ\nለተመረጡ 10 ትምህርት\nቤቶች የተደረገም እንደሆነ\nይገልፃሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል\nእርሳቸው የሚመሩት ትምህርት\nቤት የእድሉ ተጠቃሚ  መሆኑ እንዳስደሰታቸው አልሸሸጉም፡፡ ለአራት ሺህ ዘጠና ስድስት ተማሪዎች የድጋፉ ተጠቃሚ መሆናቸው ቤተሰብን ከማገዙ በተጨማሪ በትምህርት ጥራቱ ላይ የሚያሳርፈው አዎንታዊ ተጽዕኖ እንዳለም ይናገራሉ፡፡ በተለይም ከኢኮኖሚ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን ጫና እንደሚቀንስ ያስረዳሉ፡፡ በተማሪዎች መካከልም ጠንካራ የመተጋገዝና የውድድር ስሜት ይፈጥራል፡፡ ርዕሰ መምህሩ የተደረገው ድጋፍ በተለይ በቅርቡ የተጀመረውን የምገባ ስርዓት ቀልጣፋ እንዲሆን ማስቻሉን አንስተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በምግብ ማቅረቢያ ሳህን እጥረት የተነሳ ተማሪዎች ተራ ለመጠበቅ ይገደዱ ነበር ፡፡ ይህ ደግሞ የጊዜ መጓተት ይፈጥር ነበር። አሁን ሁሉም የየራሳቸው ምሳ እቃ ስላላቸው ተራ ሳይጠብቁ በእኩል የመመገብ እድል አግኝተዋል ብለዋል፡፡ በትምህርት ቤቱ የሚገኙና በቅድመ መደበኛ የሚማሩ 1ሺህ 169 ተማሪዎች የድጋፉ ተጠቃሚ አይደሉም ያሉት ርዕሰ መምህሩ እነዚህ ተማሪዎችም የድጋፉ አካል እንዲሆኑ እየሰሩ መሆኑን ይናገራሉ። እንደ መፍትሄም ማህበረሰቡንና የተለያዩ ባለሀብቶችን የማስተባበር ስራ እየተከናወነ ነው። ‹‹ብዙ መደገፍና መረዳት ያለባቸው ቤተሰቦች ለልጆቻቸው ሲሉ እየተጨነቁና እየለፉ ትምህርት ቤት ይልኳቸዋል። መንግስት የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉ ለወላጆች እፎይታን ሰጥቷል›› የሚሉት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አበበ ቸርነት ናቸው፡፡ ቤተሰብ ለልጆቹ ትምህርት የሚያወጣው ከፍተኛ ወጪ የደንብ ልብስ ሲሆን፤ ይሄ ሙሉ ለሙሉ በመንግስት እንዲሸፈን ተደርጓል፡፡ ከዚያ አልፎ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የተማሪዎች ቦርሳ እና የተለያየ የትምህርት መሳሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ እየተደረገ ነው፡፡ በዚህም ተማሪው ተስፋ ሲያገኝ ቤተሰብ እፎይ እያለ ነው፡፡ ድጋፉ በስሜት እንጂ በንግግር የሚገለጥ እንዳልሆነ የሚገልጹት አቶ አበበ፤ ለአስር ትምህርት ቤቶች 23 ሺህ ቦርሳ ከነሙሉ የመማሪያ ቁሳቁሱ መሰራጨቱን አንስተዋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 12/2012ጽጌረዳ ጫንያለው", "passage_id": "60ef88a43e65082c74a4917aff721f1c" }, { "passage": "ድሮ\nድሮ እኛ ተማሪዎች ሳለን ልክ በዛሬዋ ቀን (ሰኞ ሰኞ) የምንከውናት አንዲት ልምድ ነበረችን። የሰልፍ እና ብሄራዊ መዝሙር ስነ-ስርዓትን አጠናቀን፤ ከመማሪያ ክፍላችን እንደገባን ሁላችንም እጆቻችንን ከጠረጴዛው ላይ እንዘረጋለን። መምህራችን አሊያም የክፍል አለቃችን ደግሞ አንድ በአንድ እየዞሩ ይመለከቱናል። በዛሬ ተማሪዎች ዘንድ ይህ ልማድ ስለመኖሩ አላውቅም። በእኛ ጊዜ ግን ይህ የሚደረገው የሳምንቱ በኩር በሆነችው ሰኞ ሁሉም ተማሪ ንጽህናውን በተገቢ መንገድ መጠበቅ አለመጠበቁን ለማረጋገጥ ነበር። የደንብ\nልብስ በስርዓት ታጥቦ መለበሱ፣ ጥፍር መከርከሙ፣ የወንድ ጸጉር መበጠሩ፣ የሴቷም በአግባቡ መጎንጎኑ፣ … ሁሉ ይታይ ነበር። ይህንን አጉድሎ የተገኘም ቅጣት ይጠብቀዋል። ይህ ልማድም አንድም ህጻናት ስለ ንጽህና አውቀው በመተግበር ጤናቸውን እንዲጠብቁ ያደርጋል። ሁለትም ከሰኞ ማለዳ በዚህ መልክ የተጀመረ ሳምንት በንቃትና በጥሩ መንፈስ እንዲቀጥል ለማድረግ ያስችላል። ከሁሉ በላይ ግን ታዳጊዎች ስነ-ስርዓት እንዲማሩና እንዲያውቁ ለማድረግ ያስችላል። ይህንን\nሰዋዊ ልምድ ለከተሞች ብናደርገው ብለን ብናስብስ? እኛ ራሳችንን ፈታሽ አድርገን እንሰይም፤ ከዚያም በሃገራችን የሚገኙ ትልልቅ ከተሞችን ንጽህና በዓይነ ህሊናችን እንፈትሽ። የእናንተን ባለውቅም፤ በእኔ እይታ ግን ንጽህናዋን ባለመጠበቅ፤ ቁንጥጫ፣ አለንጋ አሊያም መንበርከክ የሚከተላት ከተማ መዲናችን አዲስ አበባን ትመስለኛለች። ለምን ቢሉ፤ በነዋሪዎቿ ስርዓት አልባነት ከስሟ በተቃራኒ የምትቆም ንጽህና አልባ ከተማ በመሆኗ ነዋ። መቼም ከትልልቅ መንገዶች እስከ መንደሮች ብናካልል ግማሽ አካሏ ጽዱ ነው የማለት ድፍረት አናገኝም። ስልጣኔዋም በህንጻዎች ይለካ ይሆናል እንጂ በውበት ልትነሳ አትችልም። እስኪ\nለጥቂት ደቂቃዎች በመንገድ ላይ ያለን አካባቢያችንን እናስተውል፤ ከመንገድ ያልወጣንም የምንገኝበትና የምንኖርባቸው አካባቢዎች ምን ይመስላሉ የሚለውን እናስብ። ሰውን ከእንስሳ ያልለዩ መንገዶችና ትርምስ፣ ፈሳሽን ከጠጣር መለየት ተስኗቸው መንገዳቸውን የሳቱ ቦዮችና የፍሳሽ መውረጃዎች፣ እንደ ህጻናቱ የዕቃ ዕቃ ጨዋታ ምኑንም ምኑንም ለጣጥፈው የተዘበራረቁ ህንጻዎች፣ ጥቁረታቸው የውሃነታቸውን አሻራ ያጠፋና የሚረጩት ሽታም የሚተነፍግ ወንዞች፣ ከወዲያ የመኪና ጡሩንባ፣ ከወዲህ የሰው ሁካታ፣ አለፍ ብሎም የሙዚቃና የማሽኖች ጩኸት አቅሏን ያሳቷት፣ ሰዎቿ የቱ ነውር የትኛው ስርዓት መሆኑን ዘንግተው በየጥጋጥጉ የሚጸዳዱ፣ … ከሆኑ ውለው አድረዋል። በልጅነታችን የተማርናቸው ስርዓቶች የት እንደገቡ እንጃ፤ አሁን ሁሉም ነገር ስርዓት አልባ ሆኗል። ከቤታችን የሚወጡት ውጋጆችን አውጥተን ከደጃችን እናከማቻለን(ደግሞ እኮ በዚያ ስናልፍ አፍንጫችንን ሸፍነን ነው!)፣ በተሽከርካሪ ስንጓዝም በኩራት መስኮት ከፍተን ወዲያ እያሽቀነጠርን ነው፣ ከየቤታችን የሚወጡትን ፍሳሾችም ከቦዮችና ወንዞች እናያይዛለን፣…። እኔን የሚገርመኝ እንዲህ በማድረጋችን የምናሳየው ኩራት ነው። ከመንገድ ዳር ያውም በርካታ ወጪ ወራጅ ባለበት ተጸዳድቶ እጁን ኪሱ ከቶ እያፏጨ መንገዱን የሚቀጥል ስንት ኩሩ አለ መሰላችሁ። እንዳይሸታት አፍንጫዋን በደማከሴ ዘግታ ያለ አንዳች እፍረት ቆሻሻ የምትደፋ ስንቷ መሰለቻችሁ። መንገዱን እየጠረጉ አቧራና ሌላውን ደረቅ ውጋጅ በጋሪ ጭነው ከቦይ የሚገለብጡ የመንገድ ጽዳትባለሙያዎችም አሉ። በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ አፍስሰው የገነቡትን ፋብሪካ ተረፈ ምርት (ዕዳ) በወንዞች ላይ የጣሉም ጥቂት አይደሉም። የሚሰራውንና የሚሆነውን ህገወጥነት እየተመለከቱ እንዳላየ የሚያልፉ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች እና ተቋማት በመኖራቸውም ነው ከዚህ የደረስነው። አዲስ አበባን ከሌላው ልዩ የሚያደርጋት ሌላም ባህሪ አላት። የመንገዱ\nግርግር፣ ሽታ እና አቧራ «ሰለቸኝ» ብለው ጥቂት ወደላይ ከፍ ካሉ ሌላ የባሰ ነገር መመልከትዎ አይቀርም። ጣሪያዎች የእቃ ማጎሪያና የዝገት መለያ ናቸው። የተገለገልንበትን ዕቃ በአግባቡ ማስወገድ መቼም አይሆንልንም፤ ብረታ ብረት፣ አሮጌ የቤት ዕቃዎች፣ ጨርቃ ጨርቅና ፕላስቲኮች፣… ሌላም ሌላም መመልከታችሁ አይቀርም። ደግሞ እኮ አናምንም፤ የዚህ ስርዓት አልበኝነት ምክንያትም ሰለባም እኛ ሆነን ሳለን ሌላ አካል እንደፈጠረው ሁሉ እንማርራለን። ነጋራ\nሳያሻን ማከናወን ቢገባንም «አጽዱ» ስንባል «ምን አግብቶኝ» በሚል እንደነፋለን። በነጻነት የመጓዝ መብታችን ከመገደቡም ውጪ ለተለያዩ በሽታዎች ስለመዳረጋችን ዘንግተናል። እንዲህ ባለ አካባቢ የምንሰራው ስራም በነጻ አእምሮ የታገዘ ስላለመሆኑም ማስተዋል ተስኖናል። ወገን፤ አካባቢያችን የእኛነታችን መገለጫ ነው። በዙሪያችን ያሉ ነገሮች ሁሉ ገንቢያችን የመሆናቸውን ያህል ስርዓት አልባ ሲሆን ደግሞ ያፈርሰናል። ቤታችን ጽዱ እንዲሆን የምንጥረውን ያህል፤ አካባቢያችንም ቢጸዳ ጥቅሙ ለራሳችን ነው። እኛ አካባቢያችንን ከመሰልንም፤ አካባቢያችን «ይጽዳ፤ እናጽዳ» ሳይሆን «እንጽዳ» ብለን ብንነሳ መልካም ይሆናል።አዲስ ዘመን ግንቦት 12/2011ብርሃን\nፈይሳ", "passage_id": "36d3c5b0d81e9e612c7eb35a65435793" }, { "passage": "ቢሾፍቱ ተወልዳ ያገደችው ዕልልታ ነጋ 2001 ዓ.ም. ላይ ነበር የህክምና ትምህርት ለመከታተል መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተመድባ ወደዚያው ያቀናችው ።\n\nለሶስት ዓመታት ያህል ትምህርቷን ስትከታተል ብትቆይም ነገሮች እንዳሰበችው እንዳልቀለሉላት ታስታውሳለች።\n\n\"አንዳንድ ሰው ችሎታሽን አቅምሽን ይንቃል፤ በአንድ የትምህርት ዓይነት ብዙ ተማሪዎች ውጤት ተበላሸብን፤ ህክምና ደግሞ በአንድ ኮርስ ከወደቅሽ ለመቀጠል በጣም ይከብዳል፤ ያኔ አስተማሪው 'ለእናንተ ሜዲሲን አይገባችሁም' አለን፤ ሶስት ዓመት ሙሉ ቆይተሽ እንደዚህ ስትባይ በጣም ይሰማል፤ እኔ ደግሞ ከልጅነቴ ጀምሮ ነበር ህክምና መማር የምፈልገው፤ እንደዛ ስባል በጣም ነበር የተናደድኩት፤ ከዚያ ሞራሌ ስለተነካ ቤተሰቦቼን ነግሬያቸው እኔ በቃ እዚህ በፍጹም አልቀጥልም ነበር ያልኩት፤ ግን በህክምና ትምህርት ጨርሼ ተመልሼ ሄጄ እንደማናድደው ነበር ያሰብኩት።\"\n\n•\"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል\" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ \n\n•አዲሷ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማን ናቸው? \n\n•ከኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ እስከ ሣህለወርቅ ዘውዴ\n\nዕልልታ አቅሟን ለማሳየት ቆርጣ ወደ አዲስ አበባ ተመልሳ በቤቴል ሜዲካል ኮሌጅ የህክምና ትምህርቷን እንደ አዲስ ሀ ብላ ጀመረች፤ ግን አሁንም አንድ ነገር አዕምሮዋን ይከነክናት ነበር።\n\n\"አብሬያቸው ስማር ከነበሩ ልጆች ወደ ኋላ መቅረቴ በጣም ነበር የሚሰማኝ\" የምትለው ዕልልታ በጓደኞቿ ጉትጎታ ይህን ስሜት የማሸነፊያ መንገድ አገኘች።\n\n\"የነገርኳቸው ሁሉ 'ያምሻል እንዴ?\" ነበር ያሉኝ\n\n\"እንዲያውም እኔ ዶክተር ብቻ አይደለም መሃንዲስም እሆናለሁ አልኩኝ፤ የነገርኳቸው ሁሉ 'ያምሻል እንዴ?' ነበር ያሉኝ፤ አትችይውም ተይ ይከብድሻል፤ ይቅርብሽ የሚለኝ ብዙ ሰው ነበረ፤ እናቴ ራሱ በጣም ነበረ የተከራከችኝ።\"\n\nዕልልታ የብዙሃኑ ተቃውሞ ቢበረታባትም የሂሳብና የፊዚክስ ትምህርት እንደምትወድ ከሚያውቁት ጓደኞቿን ግን ሙሉ የሞራል ድጋፍ አገኘች። የሲቪል ምህንድስናውን ትምህርት በድፍረት ስትገፋበት ደግሞ አይዞሽ በርቺ የሚላት ሰው እየበዛ መጣ።\n\n\"እኔም ትምህርቱን ወደድኩት፤ ለህክምናው ትምህርት ማንበብና ተግባራዊ ልምምዶችን ማድረግ ይጠበቅብኛል፤ ምህንድስናው ደግሞ በብዛት ካልኩሌሽን (የሂሳብ ቀመር) ነው፤ እሱን ስሰራ ጭንቅላቴ ፈታ ይላል፤ የህክምናው ንባብ ሲበዛብኝ ወደ ምህንድስናው ዞር ብዬ ቀመሩን እየሰራሁ ራሴን አነቃቃ ነበር።\"\n\nአሁን ዕልልታ ይህንን ፈታኝ ጊዜ አልፋ በሰባት ዓመታት ውስጥ ሁለቱንም ጎን ለጎን እያስኬደች በ29 ዓመቷ ባለፈው ዓመት የህክምናና የምህንድስና ዲግሪ ባለቤት ሆናለች።\n\nበትምህርትና በፈተና ወቅት ያሳለፈቻቸውን ከባድና አልህ አስጨራሽ ጊዜያት ሁሉ የምትረታቸው የመጨረሻውን ፍሬ በማሰብ እንደነበር ትናገራለች።\n\n\"በጣም ብዙ ጊዜ 'ምን እንቀልቅሎኝ ነው?' ብዬ አውቃለሁ፤ ለምሳሌ ፈተና በጣም ሲደራረብብኝ ሁለቱንም ለማንበብና ለመስራት ስጥር ውዬ የማድርባቸው ጊዜያት ነበሩ፤ የምህንድስናው ፈተና ብዙ ጊዜ 9 ሰዓት ላይ ነበር የሚሆነው። ስለዚህ የህክምናውን ጠዋት ተፈትኜ እየሮጥኩኝ ወደ ምህንድስናው ነበር የምሄደው፤ በጣም ስልችት ብሎኝ ልተወው እልና መልሼ ግን የመጨረሻውን ድሌን ማሰቤ ነው እንድገፋበት ያደረገኝ።\"\n\n\"ሰው ሳያያኝ ተደብቄ አልቅሼ አውቃለሁ\"\n\nየህክምና ዶክተሯና መሐንዲሷ ዕልልታ ነጋ የህክምናውንን ትምህርት በቀን የሲቪል ምህንድስናውን ደግሞ በማታው ክፍለ ጊዜ ነበር የተማረቸው። ለሁለቱም ጊዜዋን ለማብቃቃት ደግሞ አስቀድሞ መዘጋጀት የሁልጊዜ መርኋ ነው።\n\n\"የፈተና ቀኖች በብዛት ቀደም ብለው ነው የሚወጡት፤ በተለይም የተደራረቡ ፕሮግራሞች ካሉኝ እነሱን ቶሎ... ", "passage_id": "55290efda644d67d2148d616b298ad3f" }, { "passage": " መኪና ለማሽከርከር የሚያበቃ ፍቃድ ለማግኘት የበርካታ ሀገራት አሽከርካሪዎች በትንሹ እድሜያቸው 18 እና ከዛ በላይ እንዲሆን ህጎች ያስገድዳሉ፡፡ ይህም ህግ አንድ አሽከርካሪ ለማሽከርከር በሚገባው እድሜና የእውቀት ደረጃ ላይ ሳይደርስ የማሽከርከሪያ ፍቃድ ቢሰጠው አደጋ ሊያስከትል ይችላል ከሚል ስጋት የወጣ ነው ብሎ መገመት ይቻላል፡፡ አንዳንዴ ግን ህጉ የማሽከርከር ብቃት የማይፈቅድላቸው ገና በለጋ እድሜያቸው አውቶሞቢሎችን፣ አውቶብሶችን ከፍ ሲልም ከባድ ተሽከርካሪዎችን ሳይቀር በማሽከርከር አጀብ ያሰኙ አይጠፉም፡፡ ይሁንና እነዚህ ታዳጊዎች ግፋ ቢል ከአስር ዓመት ትንሽ የዘለሉና በመጠኑም ቢሆን ስለመኪና ያውቃሉ ተብለው የሚገመቱ ናቸው፡፡ ገና የአምስት ዓመት ልደታቸውን ሳያከብሩ መኪና የማሽከርከር ብቃት ላይ የደረሱ ህፃናትን ማየት ግን ትንሽ ግራ ያጋ ባል፤ እንግዳ የሆነ ነገር ነው፡፡ ከሰሞኑ ስካይ ኒውስ በድረ ገፁ ለንባብ ያበቃው ፅሁፍም ይህንኑ ያረጋግጣል፡፡ ፅሁፉ እንዳመለከተው፤ ልጆች ከረ ሜላን ጨምሮ ልዩ ልዩ ጣፋጭ ነገሮች ይወ ዳሉ፡፡ ጣፋጭ ነገር እንዲገዛላቸው ደግሞ ወላጆቻቸውን አብዝተው ይወተውታሉ፡፡ እንዲህ ወትውተው ታዲያ ፍላጎታቸውን ካልሞላ ጣፋጭ ነገሯን ለማግኘት የራሳ ቸውን ርምጃ ለመውሰድ ይገደዳሉ። ጥቂት የማይባሉት ከቤተሰብ ሳንቲም በመስረቅ በራሳቸው ጣፋጭ ነገሮች የሚገዙ ሲሆን ፣ አንዳንዶች ደግሞ ወደ ጣፋጭ መሸጫ ሱቆች በመሄድ ጣፋጮቹን እንዲሰጧቸው ባለሱቆቹን ይለምናሉ፡፡ አሜሪካዊው የአራት አመቱ ህፃን ጣፋጭ ነገሮችን ለማ ግኘት የወሰደው ርምጃ ግን ትንሽ የከፋ ነው፡፡ እንደ ፅሁፉ ከሆነ ጅና ስዌንሰን የተሰኘው አሜሪካዊ የአራት ዓመት ህፃን የአያቱን የመኪና ቁልፍ ይሰርቃል፡፡ ግቢ ውስጥ ወደቆመችው አውቶሞቢልም ይጠጋል። የመኪናዋን በር ከፍቶ ሞተር በማስነሳት በጠራራ ፀሃይ መኪናዋን እያከነፈ ጣፋጭ ነገር አገኝበታለሁ ብሎ ወዳሰበበት ቦታ ይሄዳል፡፡ አንድ ጣፋጭ መሸጫ መደብር ወደሚገኝበት የነዳጅ ማደያ ሱቅም ደርሶ መኪናዋን ያቆማታል። ህፃኑ በመንገድ ላይ አውቶሞቢሏን ሲያሽከረክር በአንድም ሰው ላይ ጉዳት ያደረሰ ባይሆንም፣ በመኪናዋ አካል ላይና በመንገድ ዳር በነበሩ የመልእክት ማስቀመጫ ሳጥኖች ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል፡፡ ህጻኑ ሹፌር ከቤቱ ግቢ ያለውን የአትክልት ስፍራ ሲያቋርጥ ከዛፍ ቅርንጫፍ ጋር በመታከኩ በመኪናው የፊት አካል ላይም የመሰርጎድ ምልክት ታይቷል፡፡ ከዛ ውጪ ግን ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስበት መኪናዋን ማቆም ችሏል ሲል ፅሁፉ ገልጿል፡፡አዲስ ዘመን ሰኔ 11/2011 ", "passage_id": "cc61ea49e2d9cf9a71e8827f91592b01" }, { "passage": "ይሄ ሁሉ የተጀመረው በአንዲት ዕለት ነው፤ የታዳጊዋ አባት ጓደኞቹን ለመጠጥ ጋብዟቸው ነበር። በመጠጥ ኃይል የተገፋፉት ግለሰቦች ቤተሰቦቿ ፊት ይጎነታትሏት ጀመር። አንዳንዶቹም እናቷን ይዘዋት አንደኛው መኝታ ክፍል ውስጥ በተደጋጋሚ ይገቡ፣ ይወጡ ነበር። \n\n• የተነጠቀ ልጅነት \n\nበዚህ የተጀመረው መጎነታተል እዚያ ላይ አላቆመም። አንድ ዕለትም አባቷ ከአንደኛው ጓደኛው ጋር እንድትሆን አድርጎ የአንደኛውን መኝታ ቤት በር ከውጭ ቆለፈባት፤ ሰውየውም ደፈራት። \n\nየልጅነት ዓለሟም በዚህ ተቀጨ፤ ስቃይዋም አንድ ተብሎ ተጀመረ። አባቷ ጓደኞቹም የሆኑም ያልሆኑም ወንዶች ጋር በመደወል ቀጠሮ በመያዝ ገንዘብ እየተቀበል፤ ልጁን ማስደፈር ተያያዘው።\n\nባለሙያዎች እንደሚያምኑት ህፃኗ ቢያንስ በሰላሳ የተለያዩ ወንዶች ተደፍራለች።\n\n• \"በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ\"\n\nከጥቂት ወራት በፊት ከመምህራን በደረሰ ጥቆማ በህፃናት ደህንነት ላይ የሚሰሩ ኃላፊዎች ታዳጊዋን ከትምህርት ቤቷ ወስደው በመጠለያ ቤት ውስጥ አስቀምጠዋታል። በተደረገላትም የህክምና ምርመራ በተደጋጋሚ እንደተደፈረች ማረጋገጥ ተችሏል። \n\nአባቷን ጨምሮ አራት ወንዶችም በቁጥጥር ስር ውለዋል። እነሱም በመድፈር፣ ህፃናትን በወሲብ ንግድ በማሰማራትና በጥቃት ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን ዋስም ተከልክለዋል። \n\nከነዚህ ግለሰቦች በተጨማሪ ፖሊስ አባቷ ያውቃቸዋል ያላቸውና የመድፈርና አካላዊ ጥቃት አድርሰውባታል የተባሉ አምስት ግለሰቦችንም እየፈለገ ነው።\n\nመርማሪዎች ልጅቷን በመድፈር የተጠረጠሩ ሃያ አምስት ወንዶች ስምና ፎቶዎችን ይዘዋል።\n\n• ህንዳዊቷን ዶክተር በቡድን ደፍረው ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩት በፖሊስ ተገደሉ\n\n\"ፊታቸውን አላስታውስም፤ ብዙው ነገር ብዥ ብሎ ነው የሚታየኝ\" ብላለች ታዳጊዋ ጥቃቱን ስለፈጸሙባት ሰዎች ስትጠየቅ። \n\nቤተሰቦቿ በደቡባዊ ህንድ በምትገኝ ጥሩ አቅም ያላቸው ሰዎች በሚኖሩባት ከተማ ቢኖሩም፤ እነሱ ግን ኑሯቸው እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በመስከረም ወር ላይ የታዳጊዋ ጎረቤቶች የሆኑ መምህራን ለትምህርት ቤቱ ኃላፊዎች ልጅቷ ችግር ሊኖርባት እንደሚችል አሳውቀው ነበር።\n\n\"ቤተሰቦቿ አንድ የሆነ ችግር ያለባቸው ይመስለናል፤ ቤቷም ውስጥ ምን እንደሆነ ባናውቅም የሆነ ግራ ግብት የሚል ጉዳይ እየተከናወነ ነው፤ እስቲ ህፃኗን አናግሯት\" ብለው ተናገሩ። \n\nየትምህርት ቤቱ አስተዳደርም ከሴቶች ድጋፍ ቡድን አማካሪ በማምጣት ህፃኗን እንዲያናግሯት አደረጉ። \n\nበመምህራኑና ሰራተኞች ክፍል ውስጥም \"እስቲ ስለ ራስሽና ስለ ቤተሰቦችሽ ትንሽ ንገሪን\" አለቻት አማካሪዋ። \n\nለሰዓታትም ከታዳጊዋ ባወሩበት ወቅት፤ አባቷ ሥራ ስሌለው ሁኔታዎች ፈታኝ እንደሆኑ ተናገረች። የቤት ኪራይም ስላልከፈሉ ከቤት ሊያስወጧቸውም እንደሚችሉ እያለቀሰች በልጅነት አንደበቷ አወራች። \n\nትንሽ ቆይታም በዝምታ ተዋጠች። አማካሪዋ በክፍል ውስጥ ስለሚማሩት የሥርዓተ ፆታ ክፍለ ጊዜና ምን ያህል ህፃናትስ ጥቃት እንደሚደርስባቸው ጠየቀቻት።\n\n• የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት ደፍሮ የገደለን ተጠርጣሪ ስም ይፋ እንዲደረግ ወሰነ \n\n\"እኛም ቤት ጥቃቶች ይደርሳሉ፤ አባቴ እናቴ ላይ ጥቃት ይፈፅማል\" ብላ ምላሽ ሰጠች።\n\nአማካሪዋም \"እስቲ ዘርዘር አድርገሽ ንገሪኝ\" ብላ ጠየቀቻት። አንድ ቀን እናቷን ሊያይ የመጣ ግለሰብ ጥቃት እንዳደረሰባት ተናገረች። እናቷም በአፀፋው ግለሰቡን አስጠንቅቃዋለች አለች። ነገር ግን እሷ በሌለችበት ወቅት እናቷን ሊያዩ የሚመጡ ብዙ ወንዶች መኖራቸውንም አስረዳች። \n\nበተለይም ምሽት ላይ ጠጥተው የሚመጡና እናቷም ላይ ወሲባዊ ጥቃት የሚያደርሱ ወንዶች ቁጥር ብዙ ናቸው አለች።\n\nአማካሪዋም ስለ እርግዝና መከላከያ መድሃኒት ታውቅ... ", "passage_id": "fc3ee7fdd104e8383271f5b98d5e717e" } ]
a43cb76bc94bb7f2eb95b822d433a115
e597523192cc3eb90518f5f9552dc021
የእግር ኳሱ ዓለም ‹‹ፍቅር እስከ መቃብር››
የፍቅር ጉዳይ ሲነሳ በዓለማችን የተለያዩ ጥንዶች በተለያዩ ዘመናት የነበራቸው የሚያስቀና ፍቅር በብዙ ታሪኮች ሲጠቀስ ይታያል፡፡ በአገራችንም ተሰምተው የማይጠገቡ፣ ለበርካቶች ትምህርት የሆኑ ዘመን ተሻጋሪ የፍቅር ታሪኮች አሉ፡፡ ብዙ ጊዜ የልብ ወለድ እንጂ በገሃዱ ዓለም ያሉ ወይም ተከስተው የነበሩ የማይመስሉ የተለያዩ የፍቅር ታሪኮችን ቢያንስ አንድ የሚያውቅ አለ ተብሎ አይታሰብም፡፡ ዘመን አይሽሬው የአገራችን ልብ ወለድ ‹‹ፍቅር እስከ መቃብር›› የሁለት ጥንዶችን የፍቅር ጥግ በማሳየት በብዙዎች ዘንድ የሚረሳ አይደለም፡፡ ከዚያም የተነሳ በውጣ ውረድ የተሞላ፣ ፈተናዎች የበዙበት የፍቅር ሕይወትና ፅናት ‹‹ፍቅር እስከ መቃብር›› የሚል ስያሜ ሲቸረው ማየት የተለመደ ነው፡፡ በስፖርቱ ዓለምም በተለይም በእግር ኳሱ አንድ የፍቅር ታሪክ በርካቶችን ሲያነጋግር ኖሯል፣ እያነጋገረም ይኖራል፡፡ የዚህ ፅኑ ፍቅር ታሪክም በዛሬው የስፖርት ማህደር አምዳችን እንዲህ ይነበባል፡፡ የዚህ ፍቅር ታሪክ መሪ ተዋናይ ቤርናዴት አዳምስ ትባላለች፡፡ ቤርናዴት ዘወትር ማልዳ ትነሳለች። አንድ ሰዓት እንኳን ሳይሞላ ቀኗ ይጀመራል። ቁርሷን ትበላለች፣ ባለቤቷን ለመንከባከብ ራሷን ታዘጋጃለች። ልብስ ትቀይርለታለች። ምግብ ታበስልለታለች። ወደ መፀዳጃ ቤት ትወስደዋለች። ቆሻሻውን ሁሉ ታፀዳለታለች። ጡንቻውን ታፍታታለታለች። ይህ የአንድ ቀን ብቻ ልማዷ አይደለም። ላለፉት ሰላሳ ስምንት ዓመታት አድርጋዋለች። በየዕለቱ ደጋግማዋለች። እስከ መጨረሻው ላታቋርጥም ለራሷ ቃል ገብታለች… ዘመኑ በ1960ዎቹ ፈረንሳይ በጄኔራል ሻርል ደጎል አመራር ሥር ሳለች፣ የመንግሥት ወግ አጥባቂ አስተዳደር እያደር የህዝብ ቅሬታ ሲያስነሳ ነበር። ጥቁሮች ከነጭ ፈረንሳዊያን ጋር በጋብቻ ከተጣመሩ ጉድ የሚባልበት ያ የዘረኝነት ዘመን…። ጥቁሩ ዣን ፒዬር አዳምስ ግን ከነጯ ቤርናዴት ጋር በፍቅር ወደቀ። ወደደችው፣ ወደዳት። አገር ጉድ ይበል ብለው ፍቅራቸውን እስከ ጋብቻ አደረሱት። ገና አማተር ተጫዋች ሳለ ነበር የተዋወቁት። በ1969 አዲስ ዘመን እሁድ ግንቦት 2 ቀን 2012 ዓ.ም ከጋብቻ በኋላ፣ ከፍተኛ ዲቪዚዮን የነበረው ኒም ፕሮፌሽናል ኮንትራት አቀረበለት። ተቀበለው። ዣን-ፒየር እና ቤርናዴት ኑሯቸውን ወደ ኒም ከተማ አዛወሩ። በፍቅር ሲኖሩም ወንድ ልጅ ወለዱ። 1970ዎቹ ለጥንዶቹ አስደሳች ዘመናት ነበሩ። አዳምስ ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጥቁር ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው። ዝና፣ ገንዘብ፣ መሽቀርቀር፣ መደሰት የአዳምስ የዕለት ተዕለት ልማድ ነበር። ቀልድ ያውቃል። ፈገግታ ከፊቱ አይጠፋም። ዝና ሲጨመርበት ደግሞ… አለ አይደል… አብሮ የሚስቅም አይጠፋም። ገና የ10 ዓመት ብላቴና ሳለ አያቱ በመንፈሳዊ ጉዞ ሰበብ ይዘውት ከመጡ በኋላ የሴኔጋሉ ልጅ ፈረንሳይን ቤቴ ብሏል። ፓሪ ሰን ዠርመ እና ኒስን ጨምሮ እስከ 1981 ድረስ በዲቪዚዮኑ ለእውቅ ክለቦች ተጫወተ። 34 ዓመቱ ላይ ጫማውን ሰቅሎ፣ ለቀሪው ህይወቱ ህፃናትን ለማሰልጠን ለትምህርትና ልምምድ ወደ ዲዦ ከተማ አቀና። እዚያም በልምምድ ላይ ሳለ በጉልበቱ ላይ ጉዳት ደረሰበት። የሊጋሜንቱን ህመም ለመገላገል በሊዮን ከተማ በሚገኘው ኤድዋርድ ሄሪዮ ሆስፒታል ምርመራ አደረገ። ጉዳቱ ቀዶ ህክምና እንደሚያስፈልገው በማረጋገጡ ለቀዶ ጥገናው ቀን ተቀጠረ። የቀን ጎዶሎ፣ እ.ኤ.አ መጋቢት 17 ቀን 1982። አዳምስ ቀጠሮውን ጠብቆ ቢመጣም በአገሪቱ የጤና ባለሙያዎች የሥራ ማቆም አድማ አድርገዋል። ህሙማን ብዙ ቢሆኑም ሐኪሞች ጥቂት ነበሩ። የአዳምስ ቀዶ ጥገና አስቸኳይ ባለመሆኑ እንደገና ሊቀጠር ይችል ነበር። ሆኖም ባሉት ባለሙያዎች ጉልበቱ ሊከፈትና ሊጠገን ተወሰነ። አንድ የማደንዘዣ ባለሙያ ብቻ ሥራ ላይ ነበረች። ተለማማጅ ተማሪዎችም አሉ። ህሙማን እንደ ቦኖ ውሃ በየተራ ማደንዘዣ ተሰጣቸው። አዳምስ ተራው ደርሶ አሸለበ። ግን እንደተጠበቀው አልሆነም። ጉልበት ላድን ያለው ህክምና እጅና እግሩን ጨምሮ መላው አካላቱን ከጥቅም ውጭ አደረጋቸው። ከዓይኖቹ ሽፋሽፍት በስተቀር ቢጠሩት እንኳን ፊቱን ዞር ማድረግ ተሳነው። አንደበቱ ተዘጋ፣ በድጋሚ መናገር አልቻለም። የማደንዘዣው ሂደት የህክምና ስህተት ነበረው። ተለማማጆቹ ወደ ሰውነቱ ያስገቧቸው ትቦዎች እንኳን በቅጡ አልተሰኩም። ወደ ሳንባው የተላከው ትቦ የአሰካክ ስህተት ስለነበረው ሳምባዎቹ በቂ ኦክስጅን ባለማግኘታቸው የልቡ ሥራ ተስተጓጎለ። አንጎሉ በቂ ኦክስጂን ባለማግኘቱ ለአደጋ ተጋለጠ። ያ ፈርጣማ ተከላካይ ሰውነቱ ከዳው። መላወስ አቃተው። በዚያች እርጉም ቀን ያለ ድጋፍ ወደ ሆስፒታል ቢገባም፣ በራሱ አቅም ወደ ቤቱ መመለስ አልቻለም። ቤርናዴት ለአምስት ቀን በሆስፒታል እየዋለች፣ እያደረች ጠበቀችው። ፍቅሯ፣ የልጇ አባት፣ የህይወቷ ጓድ ከተኛበት ሳይነሳ ቀረ። ከእንግዲህ በሰው ድጋፍ እንጂ በራሱ አቅም መንቀሳቀስ እንደማይችል ቁርጡን ነገሯት። የህክምና ኃላፊዎች ለአረጋዊያን መንከባከቢያ ማዕከል እንድትሰጠው መከሯት። ለቤርናዴት ይህ የሰነፎች ምክር ነበር። አልተቀ በ ቻቸውም። <<ወደ ቤታችን እወስደ ዋለሁ፣ እዚያም እስከመጨረሻው እንከባከበዋለሁ>> ብላ ወሰነች። በደግ ዘመን ፍቅርን ወዳዩበት ቤታቸው አመጣችው። 2018…፣ ዣን ፒየር አሁንም በህይወት አለ። ዕድሜው ሰባዎቹን አልፏል፡፡ ቤርናዴትም አልሰለቸችም። ዕድሜ ተጭኗት ቆዳዋ ተሽብሽቧል። የዚያ ዘመን ውበቷ ረግፏል። እርጅና ቤት እየሰራባት ነው። ግን እጅ አልሰጠችም። ባሏን መንከባከብ የዕለት ተዕለት ሥራዋ ከሆነ 38ኛ ዓመቷን ልትደፍን ተቃርባለች። ዘመናት ቢያልፉም ታማኟ ሴት ግን ሰው ሥራሽ ስህተት አልጋ ላይ የጣለውን ሸበላ አይኗ እያየ ልትጥለው አልፈቀደችም። የመጀመሪያ ፕሮፌሽናል ክለቡ ከሚገኝበት ኒም ከተማ አቅራቢያ ዣን ፒየር አዳምስ አሁንም ተኝቷል። ዛሬም ቤርናዴት ከጎኑ አለች። ከአደጋው በኋላ በእያንዳንዷ ቀን እንዳደረገችው ሁሉ ዛሬም ማልዳ ትነሳለች። ታጥበዋለች፣ ታለብሰዋለች፣ ትመግበዋለች፣ ከመተኛት ብዛት ጎኑ እንዳይላላጥ ታገላብጠዋለች። አልታከተችም፣ አልሰለቸችም። መልስ ባይሰጣትም ታወራዋለች፣ እ.ኤ.አ በ1969ና 1976 የወለዷቸው ልጆች ላውረንትና ፍሬድሪክ እንደወለዱና ሃያት እንደሆነም አብስራዋለች፡፡ አንድ ቀንም ይነቃል የሚል ተስፋዋ አብሯት አለ፡፡አዲስ ዘመን ግንቦት 2/2012ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=32041
[ { "passage": "ድልን ለማብሰር ከማራቶን እስከ አቴንስ የሮጠው ግሪካዊው መልዕክተኛ ፊሊፒደስ፣ በባዶ እግሩ 42 ኪሎ ሜትር በመሸፈን ለጥቁሮች ኩራት ለዓለም ህዝብ ትንግርት የሆነው አበበ ቢቂላ፣ ለጥቁሮች መብት ትግል ከኦሊምፒክ ስኬት ይልቅ ሰብዓዊነትን ያስቀደመው ቦክሰኛው መሃመድ አሊ፣ በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት በእንብርክክ ተማጽኖው የአምስት ዓመታትን የእርስ በእርስ ግጭት ማብቂያ ያበጀለት የእግር ኳስ ፈርጥ ዲድየር ድሮግባ፣… ዓለም ካከበራቸው ታሪክም ከጀግኖች መዛግብት ካሰፈራቸው ስፖርተኞች ጥቂቶች ናቸው። ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ ስፖርት በሰው ልጅ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ሰፊውን ድርሻ መያዙ ገሃድ ነው። በዚህ ተወዳጅ ክንዋኔ ላይም በጦርነት አውድ ከሚዋደቁት ባላነሰ በርካታ ጀግኖች ተፈጥረው አልፈዋል፤ በዚህ ዘመንም እየተፈጠሩ ይገኛሉ። ስፖርተኞች ደረታቸውን ለጥይት ነፍሳቸውንም ለአገራቸው መገበር ባይጠበቅባቸውም፤ በእልህ አስጨራሽ ትግል ነጭ ላባቸውን አፍስሰው በሚያገኙት ድል ግን አገራቸውን ያስጠራሉ፣ ባንዲራቸውንም በማውለብለብ ህዝባቸውን ያኮራሉ። ታሪክም ከራሳቸው ይልቅ ህዝባቸውን ያስቀደሙ፤ ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠውም አገራቸውን ያስጠሩትን እነዚህን ጀግኖች እያነሳ ሲዘክራቸው ይኖራል። ለዛሬም ከጀግና ስፖርተኞች መካከል አንዱን 100 ዓመታትን ወደኋላ ተመልሰን እናስታውስ። በአገረ አሜሪካ ከታዩ ስፖርተኞች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳል፤ ጂም ትሮፔ። በኦሊምፒክ ተሳትፎው ያሳየው ቁርጠኝነት አገር ወዳድነቱን የመሰከረ ሲሆን፤ ተግባሩም ለብዙዎችም ትምህርት ሆኗል። እርግጡን የሚያወሳ የልደት የምስክር ወረቀት ባይገኝም አሁን ኦክለሃማ ከተሰኘው የአሜሪካ ግዛት እ.አ.አ በ1887 እንደተወለደ በህይወት ታሪኩ ተጠቅሷል። ትሮፔ በልጅነቱ ከባድ እና ውስብስብ የሆነ ቤተሰባዊ ህይወት የነበረው ሲሆን፤ የመንትያ ወንድሙ እናቱ እንዲሁም የአባቱ ሞት ደግሞ የልጅነት ህይወቱን ይበልጥ ፈታኝ ሊያደርግበት ችሏል። ትምህርቱን ለበርካታ ጊዜ እያቋረጠ እና እየቀጠለ ቢቆይም፤ ፔንሲልቫኒያ በሚገኝ የኢንዱስትሪ ትምህርት ቤት ተማሪ በነበረበት ወቅት ስፖርታዊ ተሳትፎውን ጀምሯል። እንደ እድል ሆኖም በወቅቱ በአሜሪካ ስመጥር በሆኑት የእግር ኳስ አሰልጣኝ ግሌን ስኮቤይ የመሰልጠን አጋጣሚ ተፈጥሮለት ነበር። ነገር ግን በዚያው ዓመት አሰልጣኙ ከዚህ ዓለም በማለፋቸው ከስፖርት ሊርቅ የግድ ሆነበት፤ ከዓመታት በኋላ ኮሌጅ እስኪገባ ድረስም በድጋሚ ወደ ስፖርት አልተመለሰም ነበር። ወደ ስፖርት ከተመለሰ በኋላም በእግር ኳስ እና ቤዝቦል ስፖርቶች ባሻገር በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች መሳተፍ ብቃቱ ተደናቂ አድርጎት ቆይቷል። ከኮሌጅ ቡድን እስከ ክለቦች ድረስም በተለያዩ ውድድሮች ላይ ተሳትፎ ሻምፒዮን ለመሆን ችሏል። በእግር ኳስ ስፖርት የነበረው ብቃት በተለይ የሚደነቅ ይሆን እንጂ በአትሌቲክስ ስፖርቶች ላይ የሚያሳየው ችሎታ ግን የሚያስገርም ነበር። ይህንን ተከትሎም እ.አ.አ በ1912 የስዊድኗ ስቶኮልም አዘጋጅ ለሆነችበት ኦሊምፒክ የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድንን ከሚወክሉት መካከል አንዱ በመሆን ተመረጠ። ወቅቱ የፔንታቶሎን እና ዴክታቶሎን የውድድር ዓይነቶች በኦሊምፒክ የተካተቱበት እንደመሆኑም ቶርፔ የታጨው ለእነዚህ የውድድር ዓይነቶች ነበር። የውድድሩ ዕለት ደርሶም ቶርፔ አስደማሚ ብቃቱን ለዓለም ሊያሳይ ሰዓታት ብቻ ቀሩት። ነገር ግን የእዚያን ዕለት ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ ጫማውን ካስቀመጠበት ሊያገኝ አልቻለም፤ ከፍለጋ በኋላም እንደተሰረቀ አወቀ። በታላቁ የኦሊምፒክ መድረክ መሳተፍ በግሉ ከሚያስገኝለት ክብር በላይ አገሩን መወከል የዜግነት ግዴታው በመሆኑ ተስፋ መቁረጥ የማይታሰብ ነው። በመሆኑም በአጋጣሚው ከመቆጨት ይልቅ አማራጭ ፍለጋውን ተያያዘው። ከቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት ውስጥም አገልግሎት የማይሰጡ ሁለት የተለያዩ ጫማዎችን አገኘ። የውድድር ሰዓቱ እየደረሰ በመሆኑም ጫማዎቹን ሳያቅማማ ለካቸው። አንዱ ጫማ ለእርሱ የማይሆን ሰፊ መሆኑ ሌላ ችግር ነበር። ምን ማድረግ እንዳለበትም አሰበ፤ ያገኘው መላም ሰፊውን ጫማ በሁለት ካልሲዎች ደራርቦ ማድረግ ነበር፤ እናም አደረገው። የእርሱ ባልሆኑት ሁለት ዓይነት ጫማዎችን በነጭ እና ጥቁር ካልሲዎች ተጫምቶም ወደ ውድድር ስፍራው አመራ። በተሳተፈባቸው ሁለት ውድድሮችም ብቃቱን አስመሰከረ። ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለማጥለቅ በቃ። በፔንታቶሎን (ርዝመት ዝላይ፣ ዲስከስ ውርወራ፣ አጭር ርቀት ሩጫ እንዲሁም ትግል) ካደረጋቸው አምስት ውድድሮች መካከል አንዱን ብቻ ተሸንፎ (በጦር ውርወራ) በሰበሰባቸው ነጥቦች ብልጫ አሸናፊ ሊሆን ችሏል። በተሳተፈባቸው የፔንታቶሎን እና ዴክታቶሎን 15 ውድድሮች በድምሩ ስምንቱን በማሸነፍም የቁጥር አንድነትን ማዕረግ ለመጎናጸፍ ችሏል። ቶርፔ በወቅቱ በውድድር አሸናፊነቱ ካጠለቃቸው ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎች ባሻገር ሌሎች ሁለት ሽልማቶችንም ተቀዳጅቷል። የመጀመሪያው ገጸ- በረከት\nበውድድር አዘጋጇ አገር ስዊድን ንጉስ ጉስታቭ አምስተኛ እጅ የተበረከተለት ሲሆን፤ «የዓለም ምርጡ አትሌት ነህ» በማለትም አበረታተውታል። የሩሲያው ኒኮላስ ሁለተኛም ለትሮፔ ሁለተኛውን የማበረታቻ ሽልማት ሰጥተውታል። ነገር ግን ይህ ታሪክ በጋዜጦች ታትሞ ለንባብ የበቃው ትሮፔ ገድሉን ከፈጸመ ከ36 ዓመታት\nበኃላ እ.አ.አ በ1948 ነበር።\nመጽሐፍትም በስሙ ተጽፈው ገበያ ላይ የዋሉት እ.አ.አ በ1952 ነው።\nአትሌቱ ከዓመታት በኋላ በዓለም ላይ ታዋቂ መሆኑ በአሜሪካ ዜጎች ልብ ሰፊ ቦታ አላሳጣውም፤ አሁንም ድረስ ብዙዎች «ጀግናችን» ሲሉ ያወድሱታል። በፔንሲልቫኒያ ግዛትም በስሙ «ጂም ቶሮፔ» በሚል የተሰየመ ከተማ አለው።አዲስ\nዘመን ሚያዚያ 27 ቀን 2011 ዓ.ም ብርሃን\nፈይሳ", "passage_id": "18c14ba7775635036928a87643636857" }, { "passage": "ከሁሉ በላይ ዓመታዊው የባህልና ስፖርት አውደፌሽታ አለ። ቁርጥ አለ፤ በቂቤ ያበደ ሽሮ አለ፤ ጎረድ ጎረድ አለ። ቡናው ይንከሸከሻል…እጣኑ ይንቦለቦላል…፤ የአገር ሰው ከዚህ በላይ ምን ይሻል?\n\nይህ አገር ቤት እየኖረ እንግሊዝኛ ለሚቀናው ሰው ‹‹ሶ ዋት?›› የሚያስብል ሊሆን ይችላል። ከአገር ለራቀ ሰው ግን ትርጉሙ ራስ ዳሽን ነው። ለዚህም ነው ለዓመታዊው የሐበሾች ‹‹መካ›› በየዓመቱ በሺዎች የሚተሙት፡፡ ዘንድሮ ተረኛዋ ዙሪክ ነበረች። እጅግ አምሮባት ተኩላ ነበር እንግዶቿን የጠበቀችው።\n\nእርግጥ ነው በነዚህ መድረኮች ላይ ሀበሾቹ የሚገናኙት ለሳቅ ለጨዋታ ነው። የሚጠራሩት ለእስክስታና ፌሽታ ነው። ሆኖም ክትፎና ቁርጥ ቀማምሰው ሲጨርሱ ቡጢ ይቀማመሳሉ። መነሻው ምንም ሊሆን ይችላል። በሐበሾች መንደር ግን ጸብ ጠፍቶ አያውቅም። በዙሪክ ይህ ባይሰተዋልም በስቱትጋርት ሆኗል።\n\n•\"እናቴ ካልመጣች አልመረቅም\" ኢዛና ሐዲስ ከማንችስተር ዩኒቨርስቲ \n\nእንዴት እጅግ የተነፋፈቀ የአገር ልጅ ለያውም በሰው አገር፣ ለያውም ለሳቅ ለጨዋታ ተጠራርቶ ቡጢ እንደሚሰነዛዘር መተንተን የቻለ ሊቅ ለጊዜው አልተገኘም።\n\nብቻ የአገር ልጆች በየዓመቱ ተሰባስበው የ‹‹ፍቅር ቡጢ››ን እንካ ቅመስ-እንቺ ቅመሽ ሲባባሉ ዓመታት አስቆጥረዋል።\n\nለምሳሌ የዛሬ ዓመት የፌሽታው አስተናጅ ስቱትጋርት ነበረች። ቴዲ አፍሮ መጥቶ አፍሮ ተመልሷል፤ ሳይዘፍን። ንብረት ወድሟል። የአዳራሽ መስታወት እንዳልነበር ሆኗል። የጀመርን ፖሊስ ‹‹ኤሎሄ! ዘንድሮ ምን ጉድ ላ'ክብን›› ብሏል። ጸቡ ከእኛም አልፎ ወንድም ኤርትራዊያንን ያሳተፈ ነበር።\n\nየቢራ ጠርሙስ ከአንድ ኢትዮጵያዊ እጅ ተምዘግዝጎ ሌላ ኢትዮጵያ የራስ ቅል ላይ አርፏል። ሀበሾች ሲገናኙ ‹‹አብሿቸው›› ይነሳል መሰለኝ ፍቅራቸው በጸብ ካልደመቀ…። ኢትዮጵያዊያኑ ወደ ዙሪክ የከተሙት ይህንኑ የጸብ ትዝታ ይዘው ነበር። ዙሪክ አላሳፈረቻቸውም። ለሰላሙ ቅድሚያ ሰጥታ አጫውታ፣ አዝናንታ አፋቅራ ሸኝታቸዋለች።\n\nበአሉታዊነቱ ስቱትጋርት እንደ ምሳሌ ተነሳ እንጂ፣ ሮም በ2012 ‹‹የፌዴሬሽኑን ገንዘብ ይዘው ተሰውረዋል›› በሚሉና ‹‹እንዲያውም አዘጋጅተን ከሰርን›› በሚሉት መሀል መራር ጸብ ነበር።\n\nደግነቱ የሮም ጸበኞች ዘንድሮ በዙሪክ ይቅር ለእግዛብሔር ተባብለዋል።\n\nበ2014 ሙኒክ ላይም ምክንያቱ መናኛ የሆነ ዱላ መማዘዝ ነበር።\n\n‹‹ሐበሻ ድሮም አብሮ መብላት እንጂ…አብሮ መሥራት…›› የሚል ተረት የሚያስተርቱ አጋጣሚዎች በርካታ ነበሩ። ሆኖም ይህን ሁሉ ዓመት ከጸብና መወነጃጀል መራቅ ለምን አልተቻለም? የሚለው ጥያቄ ዛሬም ሙሉ በሙሉ ምላሽ አላገኘም።\n\nአንድ ሁለት ምክንያቶችን መዘርዘር ግን ይቻላል። አንዱ በየዝግጅቶቹ ውስጥ የአገር ቤቱ ፖለቲካ የሚያጠላው ጥላ ሰፊ መሆኑ ነው። ሌላው በጎ ፈቃድ እንጂ የአመራር ክህሎት በሌላቸው ሰዎች ትልቅ ድግስ መሰናዳቱ የሚፈጥረው ትርምስ ነው። ሦስተኛው ለጥቅም መንሰፍሰፍ ነው።\n\n•የጄኔራል ደምሴ ቡልቶ ልጅ 'መራር' ትዝታ\n\n‹‹እንዲህ ዓይነቱን ሺህዎች የሚታደሙበት አውደ ፌሽታ ለማሰናዳት ከመቶ እስከ ሁለት መቶ ሺህ ዩሮ ፈሰስ መደረጉ አይቀርም›› ይላሉ ወጪውን የሚያውቁት። ይህንን ወጪ ለመመለስ፣ ብሎም በትርፍ ለመንበሽበሽ አድብቶ የሚጠብቀው ብዙ ነው፤ በዚህ መሀል ትርምስ ይፈጠራል። ከፍተኛ የጥቅም ግጭት ይነሳል።\n\n‹‹ስልጡን አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሰለጠነ መንገድ መነጋገር ይሳናቸዋል። በሰለጠነ መንገድ ሂሳብ ኦዲት አያስደርጉም። በሰለጠነ መንገድ ወጪና ገቢ አያሰሉም። መጨረሻው የማያምረው ለዚህ ይመስለኛል›› ይላል በዓመታት ውስጥ ባየው ነገር ተስፋ ቆርጦ ራሱን ከአዘጋጅነት ተሳትፎ ያገለለ ወጣት ለቢቢሲ።\n\nየዙሪኩ መሰናዶ ግን በሁሉም... ", "passage_id": "b2ef02bf0297971c6d9ceb0634319e8a" }, { "passage": "አውሮፓ ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ የዓለማችን ልጥጥ ክለቦች የሚገኙበት ቢሆንም አደጋ የተጋረጠበት ይመስላል። አደጋው ደግሞ የባለፈው ውድድር ዘመን ቻምፒዮና - ማንቸስተር ሲቲ፤ ይላል የቢቢሲ ስፖርት ተንታኙ ቤን ሱዘርላንድ። \n\n•ጊነስ ዎርልድ ሪከርድስ፡ «ስለተተከሉት ዛፎች ከኢትዮጵያ የደረሰን መረጃ የለም»\n\n•\"የት ይቀርልሃል!? አፈር ድሜ ትበላለህ...!\" ጋሽ አበራ ሞላ\n\nየእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ተወዳጅ እንዲሆን ካደረጉት ጉዳዮች መካከል ዋነኛው ልብ-አንጠልጣይ ፉክክር የሚታይበት መሆኑ ነው። ፈጣን፣ ፈታኝ እና የማይጠበቁ ውጤቶች የሚመዘገቡበት ሊግ ነው። ቢሆንም ይህ ምስል አደጋ ላይ ይመስላል። \n\nበዓመታት ሂደት ሊጉ ስድስት ኃያላን ክለቦች ተብለው የሚታወቁትን አምርቷል። ዩናይትድና ሲቲ፣ ሊቨርፑል፣ አርሴናል እና የከተማ ተቀናቃኙ ቶተንሃም እንዲሁም የምዕራብ ለንደኖቹ ቼልሲ።\n\nአደጋው እዚህ ጋ ነው። በሂደት ስድስቱ ኃያላን ቀርቶ አንድ ኃያል እንዳይሆን የሚል ስጋት። \n\n'እግር ኳስ ከስማለች'\n\nያለፈው ውድድር ዘመን እጅግ ተወዳጅ ያደረገው ሊቨርፑል የሲቲን እግር እየተከተለ ዋንጫ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ነበር። \n\nነገር ግን ሁለቱም ክለቦች የቋመጡለትን ዋንጫ ተቀያይረው አግኝተዋል። ፕሪሚዬር ሊግን የቋመጠው ሊቨርፑል ቻምፒዮንስ ሊግ ሲያነሳ፤ ቻምፒዮንስ ሊግን ለማንሳት የሻተው ሲቲ የሊጉን ዋንጫ ወስዷል።\n\n•ታዳጊዎችን በወሲብ ንግድ በማሰማራት ተከሶ የነበረው ቱጃር አሟሟት ጥያቄን ፈጥሯል \n\nሊቨርፑል የሊጉን ዋንጫ ካነሳ ሶስት አስርት ዓመታት ተቆጥረዋል፤ በአቡ ዳቢ ቱጃሮች የተያዘው ሲቲ ደግሞ ቻምፒዮንስ ሊግ አንስቶ አያውቅም። \n\nሲቲ ዘንድሮ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት ከቻለ ሌላ ታሪክ ይፅፋል። በአንድ ውድድር ዘመን በርካታ ጎሎች በማስቆጠር እና በርካታ ነጥቦች በማምጣት ሲቲ ሪከርዱን ይዟል። \n\nበኤፍ ኤ ዋንጫ ዋትፈርድን 6-0 በመርታት ተመልካችን አጀብ አሰኝተዋል። ይህን ያዩ የኳስ ተንታኞች 'እግር ኳስ ከስማለች' እስከማለት ደርሰዋል። \n\nየፈርናንዲሆ ምትክ ያስፈልጋቸዋል እየተባሉ ሲታሙ የነበሩት ሲቲዎች ባለተሰጥዖው ሮድሪን አስፈርመዋል። በዘመናዊ እግር ኳስ ምርጡ አሰልጣኝ የሚል ስያሜ የተሰጠው ፔፕ ጉዋርዲዮላን የያዙት ሲቲዎች ወደፊትም ተፅዕኖዋቸው እንደሚቀጥል ይገመታል። \n\nየተሻለ የእረፍት ጊዜ ያሳለፉት ሲቲዎች በኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ ሊቨርፑልን መርታት ችለዋል። በአቋምም ሆነ በስነልቡና ጥንካሬ ከሊቨርፑል የተሻሉ ሆነው ነበር የታዩት። \n\nበሌላ በኩል ሌሎች ኃያላን ሲቲን ተቋቁመው የሊጉን ዋንጫ ያነሳሉ ማለት ከባድ ነው። \n\nአርሴናሎች ፔፔን ቢያስፈርሙም፤ ተከላካይ መስመሩ አሁንም ጥገና የሚያሻው ይመስላል። ኪዬራን ቲየርኒን ከሴልቲክ፣ ዴቪድ ልዊዝን ደግሞ ከቼልሲ ማስፈረማቸው ሳይዘነጋ። \n\nአዲስ አሰልጣኝ የቀጠሩት ቼልሲዎች ኤደን ሃዛርድን ለቼልሲ ቢሸጡም በተጣለባቸው ቅጣት ምክንያት ተጫዋች መግዛት አልቻሉም። ይህ ደግሞ ለአዲሱ አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ሁኔታዎችን የሚያከብድበት ይመስላል። \n\nየዩናይትዱ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር ቡድኑን የተቀበለ ሰሞን ድንቅ አቋም ቢያሳይም ወደ መጨረሻ ከበድ ያለ ጊዜ አይቷል። ዩናይትዶች ሊጉን ያሸንፋሉ ተብሎ የተሰጣቸው ግምት ከእስከዛሬው እጅግ ዝቅ ያለ ነው። \n\n•ዘሩባቤል ሞላና በአነቃቂ መንፈስ የታሸው 'እንፋሎት' አልበሙ\n\nታድያ የእነዚህ ኃያላን ቡድኖች እንደ ሲቲ ዝግጁ አለመሆን ለሊጉ አደጋ መሆኑ አይቀርም። እንደ ጣልያን [ጁቬንቱስ ለ8 ተከታታይ ዓመታት ዋንጫ ያነሳበት]፤ እንዲሁም ጀርመን [ባየርንሚዩኒክ ለሰባት ተከታታይ ዓመታት] ሊጎች አጓጊነቱ የወረደ እንዳይሆን ነው ዋነኛው ስጋት። \n\nበየወሩ... ", "passage_id": "ac4b84f42beba8c28a273aa8d4c8757f" }, { "passage": "የኢትዮጵያ\nፕሪሚየር ሊግ የአገሪቱ የእግር ኳስ ደረጃ ነጸብራቅ ነው። በአገሪቱ የእግር ኳስ ጉዞ ላይ ዋናውን ድርሻ መያዙ ይነሳል። ለእግር ኳሱ መውደቅም ሆነ መነሳት ትልቅ ሚና አለው። አገሪቱ በእግር ኳሱ ለሚኖራት ተራማጅ ውጤት ዋልታና ማገር ተደርጎ የሚነሳው ይህ ውድድር፤ የስፖርታዊ ጨዋነት መጉደል በሚል በሽታ ከተጠቃ ሰነባብቷል:: በተለይም\nከቅርብ ዓመታት ወዲህ ችግሩ ፈር ለቋል። ችግሩ በክልል እና በመዲናዋ ስታዲየሞች በመዛመት እግር ኳሱን መልክ አሳጥቶታል። እግር ኳሱን በበላይነት የሚመራው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የውድድሮችን መጀመር ተከትሎ «በስፖርታዊ ጨዋነት ላይ ትኩረት አድርጌ ሠርቻለሁ» በሚል መግለጫና ሪፖርት ቢደጋግምም ያለውና የተባለው በተግባር አልታየም፡ ፡ ወደ ሜዳ ሲገባ የሚደረገውና የሚታየው ሁሉ ተሠራ የተባለው ከዲስኩር ያለፈ አለመሆኑን የሚያመላክት ሆነ። የስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለት ለአገሪቱ የእግር ኳስ ጉዞ እንቅፋት ሆኗል፡፡ «ችግሩ አይጸዳም፤ ጸድቶም አያውቅም» የሚሉ ድምፆችም ጎልተው በመደመጥ፤ በኅብረተሰቡ ዘንድ የቆየውን አብሮ የመኖር እሴት የሚያጠፋ፣ አለፍ ሲልም ለንብረትና ሕይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ የእግር ኳስ ሜዳዎች የጠብ መናገሻ ለመሆናቸው ከሚነሱ በርካታ ምክንያቶች የደጋፊዎች ሥነ ምግባር መጓደል እንደሆነ ይጠቀሳል።«መጠጥ ጠጥቶ ስታዲየም መግባት» የደጋፊዎች ሥነ ምግባር ፈር ለመልቀቁ ዋነኛ ሰበብ ተደርጎም እንደሚወሰድ ይነሳል። ከስፖርታዊ\nጨዋነት ችግር ጀርባ የመጠጥ ጉዳይ አብሮ ለመነሳቱ አዲስ አበባ ስታዲየምን እንደ ማሳያ መጥቀስ ተገቢ ነው። በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታ መኖሩን ከሚያሳብቁ ትዕይንቶች መካከል በስታዲየም ዙሪያ ያለው ሸብረብ ግንባር ቀደሙን ስፍራ ይይዛል። የሸብረቡን ገጽታ የሚያጎሉት ደግሞ በዙሪያው የሚገኙት መጠጥ ቤቶች ናቸው። እነዚህ ቤቶች በተለያዩ ቡድኖች ማልያዎች ባሸበረቁና በቡድን በቡድን ሆነው የቢራ ጠርሙሶች በከበቡ ሰዎች የተጨናነቁ ሆነው ይታያሉ። ወጣቶች፣ ጎልማሶች፣ አዛውንት፤ ለመጠጥ ቤት ያልደረሱ ወይም ከእድሜአቸው ጋር በተያያዘ መጠጥ እንዳይሸጥላቸው በህግ እገዳ የተጣለባቸው ታዳጊዎች ክብ ሠርተው በመጠጣት ከጨዋታው መጀመር በፊት የሚደረግ የደጋፊዎች ሁካታ አላፊ አግዳሚው በስታዲየም ጨዋታ ስለመኖሩ በሚገባ ያስገነዝባሉ። የክለቡን ማንነት በሚያሳብቅ መልኩ በተለያዩ ቀለማት ያሸበረቁ ደጋፊዎች በዚህ ትዕይንት ውስጥ ሆነው መመልከት አዲስ አይደለም። እነዚህ ደጋፊዎች በማወቅ፣ ባለማወቅ፣ በታሪክ አጋጣሚ የሚደግፉት ቡድን የሚጫወትበት ሰዓት ከመድረሱ በፊት በመጠጥ የመድመቅና የመነቃቃቱ ትዕይንት ይከናወናል። ከጨዋታው በፊት ያለው ሁነት በዚህ መልክ ተቃኝቶ ወደ ስታዲየም አብሮ ይገባል። ቆይታውም ከስፖርታዊ ክንውን ወደራቀ፣ ጨዋነት ወደጎደለው አንባጓሮ ሊያቀና እንደሚችል መገመት አያዳግትም። በሜዳ ላይ ያለው እግር ኳስ ይዘነጋል፤ ተረብና ስድብ ይጎላል፤ ጨዋታው ተረስቶ የመጠጥ ቅኔው ወደ ዱላ ከፍ ይላል። አንድ ሁለትዘንግቶ የድብድብ መነሻ የሆኑ የቃላት ዱላዎችን ወደ መወርወር ይሻገራል። በአዲስ አበባ በተደጋጋሚ የሚንጸባረቀው የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር እንደዚህ ዓይነት ስለመሆኑ ሀቅ ነው። ለእዚህ እውነታ ለማሳየት የአዲስ አበባን ስታዲየም ገጽታ እንደ መነሻ ወሰድን እንጂ ችግሩ በሌሎች የክልል ስታዲሞችም ይስተዋላል። ከጊዜ ወደ ጊዜ ደጋፊዎች መጠጥ ጠጥተው ወደ ስታዲየም የመግባት ባህል መጎልበቱ ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መልክ ማጣት ዋነኛው ምክንያት እስከመሆን ደርሷል። ለእዚህም ደግሞ ሰበቡ ስፖርት ስሜትን በመያዙ እንደሆነ ይነገራል። እግር ኳስ በሁለት ተቃራኒ ቡድኖች ውስጥ የሚገኙ 22 ተጫዋቾች ፍልሚያ ሲሆን፤ የእነዚህ ተጫዋቾች የሜዳ ላይ ፍልሚያ አንዳች ዓይነት ስሜት የሚፈጥርና ሰንጎ የሚይዝ እንደሆነ ይታመናል። በተጫዋቾች መካከል የሚደረገው እንቅስቃሴ ተሻጋሪ ስሜትን መፍጠሩ አድማሳዊ ስሜት የሚያሰርጽ ያስብለዋል። አንድ ቡድን የሚያደርገው አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ እንቅስቃሴ ተመልካችን እንደ ሁኔታው ይነዳል። ይሁንና መጠጥ ጠጥቶ የሚገባ ተመልካች ባለበት ግን ከጨዋታው ባሻገር ተመልካቹ የሚነዝረው የስፖርታዊ ክህሎቱ ትዕይንት ሳይሆን አእምሮው ውስጥ የሚላወሰው የመጠጥ ሙቀትና ያልታሰበበት የስሜት መገለጫ ቃል/ቃላት መሆኑ እርግጥ ነው። ታዲያ፤ የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር አንዱ መነሻ ይህ አይነቱ ተግባር በመሆኑ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ መጠጥ ጠጥቶ ወደስታዲየም መግባት የሚከለክል ህግ ማውጣት ይገባዋል ሲሉ የሚጎተጉቱ በርካቶች ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ፤ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑም ሆነ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ችግሩን ቢያውቁትም መፍትሄ ለመፈለግ እንደማይሹ በትችት ይነሳል። ለእዚህ ደግሞ በዋነኛነት የሀገሪቱ እግር ኳስ መሰረቱን የገነባው በቢራ ካምፓኒዎች ድጋፍና አለሁ ባይነት መሆኑ በምክንያትነት ይጠቀሳል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋልያዎቹ የሚደገፈው በቢራ፤ ክለቦች የሚመሰረቱት፤ በቢራ ስፖንሰር የሚሆኑት በቢራ፤ የክለብ ድጋፍም በቢራ፤ በሬዲዮም ሆነ በቴሌቪዥን የሚተላለፉ የስፖርት ፕሮግራሞች ሳይቀር ስፖንሰር የሚደረጉት በቢራ ካምፓኒዎች መሆኑ ከዚህ ሀቅ ጋር ለመጋፈጥ እንዳይቻል፤ ሚዲያው ሳይቀር የድርሻውን እንዳይወጣ አድርጎታል። የችግሩም ደረጃ እንደቀላል ተጠቅሶ እንዲታለፍ እንጂ፤ አንገብጋቢ ጉዳይ ሆኖ ለመነሳት እንዳይችል በጥቅም ሸምቀቆ ተለጉሞ ዓመታትን እንዲጓዝ ተፈርዶበታል። የችግሩ ደረጃ እግር ኳሱን እየጎዳ መሆኑን ለመታዘብ ቢቻልም መፍትሄ ለማበጀት የተሄደ ርቀት አለ ለማለት አያስደፍርም። ደጋፊም ወደስታዲየም ጠጥቶ እንዳይገባ የሚከለክል የህግ አጥር እንዳይበጅለት ይህ የእግር ኳስ ጥገኝነት ገትቶታል የሚሉም አሉ። በርግጥ፤ ከቢራ ካምፓኒዎች ጋር መሥራቱ በአንድ በኩል እግር ኳሱን ለማሳደግ ድጋፍ ያደረጋል። በሌላ በኩል፤ ሕፃናትና ወጣቶች የአልኮል ሰለባዎች እንዲሆኑ የሚያደርጉ ሁኔታዎች እይታዩ ነው። የማስታወቂያ አቀራረቦች በሀገሪቱ ከተደነገገው የማስታወቂያ ህግ ያፈነገጠ ነው። ስፖርቱን በስፖንሰር ለመደገፍ ብሎ ትውልድ በመግደል የሚገኝ ጥቅም ባለመኖሩ የሚመለከተው አካል ከማስታወቂያው ከሚገኘው ገቢ ይልቅ የሀገር ተረካቢ ልጆች ያስፈልጋሉ፤ የ እግር ኳሱ የበላይ አስተዳዳሪ የሆነው የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር ፊፋ የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ክፍለ አህጉራዊ የልማት ቢሮ ከትናንት በስቲያ በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ አስመርቋል። የፊፋው ፕሬዚዳንት ጂያን ኢንፋንቲኖ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ የእግር ኳስ አስተዳዳሪው አካል በማህበሩ አባል አገራት በኩል የእግር ኳስ ልማት ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በአዲስ አበባ የተከፈተው 10ኛው የፊፋ ክፍለ አህጉራዊ የልማት ቢሮ ፊፋ ከሦስት ዓመት በፊት እግር ኳስ በመላው ዓለም እንዲያድግ የጀመረው የእግር ኳስ ልማት ሥራ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ መንግሥትም ቢሮው በአዲስ አበባ እንዲከፈት ላደረገው አስተዋጽኦና ትብብር ትልቅ ምስጋና የሚቸረው መሆኑን ጠቅሰው፤ የአፍሪካ አገራት ላለፉት ሁለት ዓመታት የቀረጿቸው ፕሮጀክቶች ለአህጉሪቷ የእግር ኳስ እድገትና ልማት ወሳኝ ሚና እንደሚኖራቸው፤ ፊፋም ለፕሮጀክቶቹ ስኬት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በበኩላቸው የክፍለ አህጉራዊው ቢሮ መከፈት ፊፋ ከምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ዳንኤል ዘነበ ዳንኤል ዘነበ አገራት ጋር በቅርበት ለመሥራት ያስችለዋል ብለዋል። የቢሮው መከፈት ፊፋ ከአባል አገራቱ ጋር በቅርበት ለመገናኘት እንደሚያግዘውና ለኢትዮጵያ፣ ለምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገራትና ለአፍሪካ አጠቃላይ እግር ኳስ ልማት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የሚለው ሊያሳስበው ይገባል። በእርግጥ የቢራ ስም ከተሸከሙ ክለቦች ፍላጎት ጀርባ የምርት ተጠቃሚና የምርታቸው አፍቃሪ ለማበርከት ማለማቸው ክፉ ሀሳብ እንዳልሆነ እሙን ነው። ብሄራዊ ቡድንንም ሆነ፣ የሊግ ውድድሮችን ስፖንሰር በማድረግ የምርት አገልግሎትን ማስተዋወቁ እንደኃጢያት የሚቆጠር አይደለም። ትልቁ ጉዳይ ግን የቢራ ስም የተሸከሙ ቡድኖች ደጋፊዎችም ሆኑ በቢራ የሚደገፍ ቡድን ደጋፊዎች እግር ኳስና መጠጥ ጠጥቶ መደገፍን ነጥሎ ማየት እስኪያዳግታቸው ቁርኝት ሲፈጥሩ አደጋው አስከፊ ይሆናል ለማለት ነው። እግር ኳሱም ስፖርታዊ ወዙን ያጣል። በአሁኑ ወቅት በተለየ መልኩ በሸገር ደርቢ የፉክክር መንፈስ ላይ እንዳለውና በክልል ስታዲየሞችም እንደሚንጸባረቀው አይነት ሁኔታ በእግር ኳሱ መሰረት ላይ የቢራ ካምፓኒዎች መቆማቸው የፕሪሚየር ሊጉን የስፖርታዊ ጨዋነት ህልውናን ፈተና ውስጥ እንዲገባ ከማድረግ ስለሚሻገር ይሄንን ሀይ የሚል ህግ ተግባራዊ ማድረጉ አማራጭ የለውም። ይሁን እንጂ፤ «ለምን ሲባል?» የሚል ጥያቄ ከተለያዩ አቅጣጫዎች መነሳታቸው አይቀሬ ነው። ስፖርት መዝናኛ ነው፤ ስታዲየም ደግሞ ዘና የሚያስበለው ስሜት መፍጠሪያ ስፍራ። ታዲያ ጠጥቶ መዝናናቱ ኃጢያቱ ምኑ ላይ ይሆን? በሚል ይሄንን ሀሳብ የሚሞግቱ በሌላ ፅንፍ ይከራከራሉ። በሠለጠኑት አገሮችም የሚፈጸመው ይሄው መሆኑን በመጥቀስ ሀሳቡን መሞገታቸው አይቀሬ ነው፡፡ ጠንካራ የክለብ ጨዋታ ለመመልከት ወደ ስታዲየም ሲዘልቁ ፣ በስታዲየሙ ግቢ ውስጥ ካሉ ምግብ ቤቶች በፕላስቲክ ብርጭቆ የተሞሉና የአልኮል መጠናቸው ከ4 ነጥብ 5 እስከ ስድስት በመቶ የሆኑ ቢራዎችን ተጎንጭተው፣ ካስፈለገም ተጨማሪ ቢራ ገዝተው በመግባት ጨዋታ ይኮመኩማሉ፡፡ እንዲያውም ለስታዲየሙ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገቡት በእዚያው ስታዲየም ዙሪያ የሚገኙ ልዩ ልዩ የንግድ ቤቶች መሆናቸው ይነሳል፡፡እነዚህ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ከመዝናኛ ቦታዎች መካከል የሚመደቡ ናቸው:: በእንግሊዝ፣ በጀርመን… እና በመሳሰሉት አገራት ይህ አይነቱ ልምድ ያለና የኖረ እንደሆነም ይጠቅሳሉ። በሀገራችንም\nተመሳሳይ ልምድ ተግባራዊ ማድረጉ እንደክፋት መወሰድ እንደሌለበትም ይሞግታሉ። በዚህ የሀሳብ ማዕበል ውስጥ ያሉ ወገኖች ግን መገንዘብ የሚገባቸው፤ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ የጣሊያን ሴሪ አ፣ የጀርመን ቡንደንስ ሊጋም ሆነ የሌሎች ሊጎች ደጋፊዎችን መቆጣጠር የሚያስችል ጠንካራ ሥርዓት የፈጠሩ ናቸው። ጠንካራ መሰረት ያለው ደጋፊ ማህበራት ናቸው፤ ማን የትኛው ወንበር ላይ እንደተቀመጠ/ እንደሚቀመጥ ሳይቀር ይታወቃል። ቢያጠፋም ተለይቶ የሚቀጣበት መንገድ አላቸው። የሊጋቸው ደረጃ በራሱ የደጋፊዎቻቸውንም ሥነምግባር ደረጃ ይወስናል። ይህ አመክንዮ የሌሎች ተሞክሮ እንደ መሟገቻ የሚያስኬድ አይደለም ተብሎ ይነሳ ይሆናል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በዚህ ሥርዓት ውስጥ የተቃኘ እንዳልሆነ እውነታውን የሚታወቅ ነውና፤ ይህ ግን አያስኬድም። ስለዚህ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ የሚገኙትን መጠጥ ቤቶች በህግ ማዕቀፍ መጎብኘቱና በሥርዓት እንዲመሩ ማድረጉ ለችግሩ መቀረፍ የመጀመሪያው እርምጃ ሊሆን ይችላል የሚሉ ብዙዎች ናቸው። በእርግጥ ከሁለት ዓመት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሀሳቡን በማጠንጠንና በማፅደቅ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ ያሉ ምግብ ቤቶች በስታዲየሙ አካባቢ የአልኮል መጠጥ በመሸጥ ለሚነሱ ሁከትና ረብሻዎች ሁሉ እሳት ለኳሽ እንደሆኑ በመግለጽ፣ ዘወትር ከቀኑ 11፡00 ሰዓት በኋላ የአልኮል መጠጥ ሽያጭ እንዳይፈጽሙ የሚከለክል ሕግ መረቀቁንና ለማፅደቅም በሂደት ላይ እንደነበረ ይታወቃል። በአዲስ\nአበባ ስታዲየም ለሚታየው የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር ይሄ አይነቱ እርምጃ መውሰዱ ዋነኛው ባይሆንም አይነተኛ መፍትሄ ነውና፤ ማዘጋጃ ቤቱ የጀመረውን እንቅስቃሴ ከዳር ማድረስ ይገባዋል። በሌላ ወገን፤ የችግሩ ነጸብራቅ በመዲናዋ ብቻም ሳይሆን በክልል ጨዋታዎች ወቅት በግልጽ ይንጸባረቃል። እዚያም ቢሆን ይሄን መንገድ በአርዓያነት ወስዶ ወደተግባር መሻገር ያስፈልጋል። በዚህ ረገድ መወሰንና ርምጃ ነውሰድ ችግሩን በአንድ ወገን ለማስቀረት ያግዛል። ቀዳዳውንም\nመድፈን ያስችላል። ግን በዚህ ብቻ መወሰን «ግማሽ ተላጭቶ ግማሽ አጎፍሮ» ይሆናል። ምክንያቱም ረብሻንና ሁካታን የሚፈልግ፣ ግብረ ገብ የጎደለው ሰው እኮ ከስታዲየም ዙሪያ በቅርብ ርቀት ከሚገኙ መዝናኛ ቤቶች ጥግብ ብሎ ጠጥቶ ወደስታዲየሙ በመግባት ለመረበሽ ከልካይ አይኖረውም የሚል ሙግት መነሳቱ አይቀርም። በመሆኑም ወደ ስታዲየም የሚገቡ ደጋፊዎች መጠጥ ጠጥተው እንዳይገቡ የሚያስችል፤ ያ ባይሆን እንኳን ሰክረው ወይም ሞቅ ብሏቸው እንዳይገቡ የሚያግድ የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት መተግበር ተገቢ ይሆናል። በደጋፊዎች\nየትኬት አቆራረጥና የፍተሻ ሥርዓት ላይም ቁጥጥርና ክትትል ማካሄዱ ተገቢ ይሆናል። በተለይ ደግሞ የፍተሻ ሥርዓቱን ማስተካከል ችግሩን በበሩ ላይ ስለሚያስቀር የትንፋሽ መመርመሪያ መሳሪያ በስታዲየሙ መግቢያ በሮች ላይ ያስፈልጋል። ምናልባት ይህ ሀሳብ የቅንጦት ነው ካልተባለ፤ ከትራፊክ ፖሊስ ልምድ ወስደን ካንቦሎጆ ሲገባ የአልኮል መጠን በትንፋሽ ተፈትሾ ቢገባ መልካም ነው። ምክንያቱም\nጠጥቶና ሰክሮ ወደውስጥ መግባት ከመኪና ለበለጠ ግጭትና አደጋ ስለሚያጋልጥ በጎ በጎውን መኮረጅ ለእዚህ ጊዜ ይጠቅማል በሚል ሀሳብ የሚያሻግሩ አሉ። በዘላቂነት ደግሞ አጥፊውን፤ ረብሻ የሚያስነሳውን ለመለየት የሚያስችል ካሜራ መግጠምና መጠቀም ሊታሰብበት የሚገባ ነው። በሌላ ወገን፤ ከተቻለ በእግር ኳሱ ውስጥ የቢራ ፋብሪካዎችን ተጽእኖ ከራስ ላይ ማራገፍ ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ ነው። እስቲ ከዚህ እውነታ ጋር የአንዳንድ አገሮችን ተሞክሮ እናንሳ። በስፖርት\nውድድሮች የአልኮል መጠጦች ስፖንሰር እንዳያደርጉ የሚከለክል ሕግ ካላቸው አገራት መካከል ብራዚል ትጠቀሳለች፡፡ የኳስ ከዋክብት መፍለቂያ የሆነችው ብራዚል በስታዲየሞችና በእግር ኳስ ግጥሚያዎች ወቅት የአልኮል ማስታወቂያዎችን ማስነገርና በአካባቢ መሸጥ የተከለከለ መሆኑን እ.ኤ.አ. ከ2003 ጀምሮ የሕግ ክልከላ ተቀምጦበታል፡፡ የኛም አገር ከዚህ አይነቱ አካሄድ ቁርጠኝነት በመማር ከቢራ ካምፓኒዎች ተጽእኖ ራሱን በማላቀቅ የተሳከረውን እግር ኳስ ሊታደገው ይገባል።አዲስ ዘመን የካቲት 6/2011ዳንኤል ዘነበ", "passage_id": "62dd525b0fb826b7420aad94e22b44cc" }, { "passage": "አሮጌውን 2011ዓ.ም ሸኝተን አዲሱን 2012 ዓ.ም ዛሬ አንድ ብለን ተቀብለናል። ባለፉት ሦስት መቶ ስልሳ አምስት ቀናት በኢትዮጵያ ስፖርት ውስጥ መልካም ነገሮችና ተስፋዎች የታዩትን ያህል በእግር ኳሱ ዙሪያ ሊጠቀስ የሚችል አንድም መልካም ነገር አልታየም ማለት መዳፈር ሳይሆን ሀቅ ነው። ስለዚህ 2011 ዓ.ም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ የጨለማ ዘመን ሆኖ አልፏል ቢባል ማጋነን አይሆንም። ይህን ዘመን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ጨለማ ነው ለማለት የተለያዩ ማሳያዎችን ማስቀመጥ እና በአዲሱ ዓመት እንዳይደገሙ ሀሳብ እናቀርባለን፤ ይህ ደግሞ ተገቢ ነው። የስቴድየም ሁከትና ግጭት\nበ2009 ዓ.ም በርካታ ቁጥር ያለው የስቴዲየም ሁከት በተለይም በፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ቢከሰቱም ከብጥብጦቹ ጀርባ እግር ኳስን የሚሻገሩ ገፊ ምክንያቶች እምብዛም እንዳልነበሩ ይጠቀሳል። ከ2009 ወዲህ ግን በልዩ ልዩ ምክንያቶች የሚለኮሱ የስቴድየም ግጭቶችና ረብሻዎች ቁጥር አይሏል። በ2010 የውድድር ዓመት ሐዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ አዲግራት፣ ጅማና ወልዲያ ከተሞች ውስጥ የስቴድየም ሁከትና ግጭቶች ተበራክተው እንደነበር ይታወሳል። በተለይም በውድድር ዓመቱ በወልዲያ ስፖርት ክለብና በመቀሌ ከተማ መካከል ሊደረግ የነበረው የእግር ኳስ ጨዋታ ከመጀመሩ ከሰዓታት በፊት በሁለቱ ቡድኖች ደጋፊዎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ህይወት የጠፋ ሲሆን ንብረት ላይ ዘረፋና ወድመት ተከስቷል። በዕለቱም ማገባደጃ ላይ በመቀሌ ከተማ መንገዶች ላይ ክስተቱን ለመቃወም በርካታ ሰዎች ወጥተው እንደነበር አይዘነጋም። ጨዋታው ካለመካሄዱ በተጨማሪም የግጭቱ አሻራ እስከ ቀጣይ ቀናት ሲሻገርና ከእግር ኳሳዊ ምክንያት ይልቅ ፖለቲካዊ አንደምታው ሚዛን ሲደፋ ታይቷል። የ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ከረብሻዎች ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተለያዩ ክለቦች ላይ የጣለው ቅጣት ግማሽ ሚሊዮን ብር ገደማ መሰብሰብ መቻሉ ግጭቶች በምን ያህል ደረጃ እንደተበራከቱ ማሳያ ነው። ‹‹በእንቁላሉ ጊዜ›› ያልተቀጣው እግር ኳስ 2011 ላይ ከፖለቲካም በላይ ጦዞ ለፀጥታ አስከባሪዎች ፈተና ከመሆን አልፎ እንደ አገር ስጋት የሆነበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ሰላም በራቃቸው የስፖርት ማዘውተሪያዎች መደበኛ የውድድር መርሐ ግብሮች መተማመኛ ማግኘት እየቻሉ እንዳልሆነ ተመልክተናል። በክልል የሚካሄዱ ጨዋታዎች በፖለቲካ ትኩሳት ሳቢያ ተጨማሪ ራስ ምታት እየሆኑ መምጣታቸውን በተለይም በ2011 የውድድር ዓመት ለመታዘብ ተችሏል። በአገሪቱ የደፈረሰው ሰላም ለስፖርቱም ዋናው እርሾ እየሆነ በመታየቱ በተለይ በክልል እግር ኳስ ክለቦች መካከል የሚከናወኑ ጨዋታዎች ከእግር ኳሳዊ ትንቅንቁ ይልቅ የሥጋት ምንጭነታቸው ሲያይል ከማየት የበለጠ ለአገሪቱ እግር ኳስ የጨለማ ዘመን ማስረጃ ማቅረብ አይቻልም። በዚህም የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ መደበኛ ውድድሮች በተያዘላቸው ቀንና ጊዜ እንዳይከናወኑ ምክንያት ሆኗል። በክልል የሚካሄዱ ጨዋታዎች በፖለቲካ ትኩሳት ሳቢያ ተጨማሪ ራስ ምታት እየሆኑ መምጣታቸውን በዚሁ የውድድር ዓመት ለመታዘብ ተችሏል። ለታኅሣሥ 17 ቀን 2011 ዓ.ም. የታሰበው የወላይታ ድቻና የሲዳማ ቡና ጨዋታ አንዱ ማሳያ ሲሆን፣ ሌላው በዚሁ የፖለቲካ ትኩሳት በይደር የቆየው መቐለ 70 እንደርታ ከፋሲል ከተማ፣ እንዲሁም ባህር ዳር ከተማ ከሽረ እንደስላሴና ሌሎችም ይጠቀሳሉ። ክለቦች በክልሉ በተዟዙሮ የሚያደርጉት ጨዋታ ከወጪውም አኳያ ቀድሞውንም ባይደግፉትም ፖለቲካው ባመጣው ጣጣ አንዳንዶቹ እየተዟዟሩ ለመጫወት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቆይተዋል። ቀደም ሲል የወላይታ ድቻና የሲዳማ ቡና የጨዋታ መርሐ ግብር ሲወጣ አንዳችም ተቃውሞ አልነበረም። ይሁንና የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንደሚካሄድ ሲጠበቅ፣ ከሲዳማ ቡና ለፌዴሬሽኑ በተላከ ደብዳቤ ጨዋታውን ወላይታ ድቻ ላይ ሄዶ መጫወት የሚያስችል ሁኔታ ባለመኖሩ ጨዋታው እንዲራዘም ተደርጓል። የመቐለ ከተማና የፋሲል ከተማን ጨዋታ በተመለከተም ፋሲሎች ከሜዳቸው ውጪ ለሚያደርጉት ጨዋታ ዝግጅታቸውን አጠናቀው እንደነበረ፣ ሆኖም ባህር ዳር ከተማ ላይ የሚደረገው የባህር ዳርና የሽረ እንደስላሴ ጨዋታ ፀጥታውን የበለጠ አስተማማኝ ለማድረግ በሚል ከክልሉ የፀጥታ ኃላፊዎች ለፌዴሬሽኑ በቀረበ ጥያቄ መሠረት እንደሆነም በወቅቱ መነገሩ ያታወሳል። በዚሁ ሳቢያ የፋሲል ቡድን ወደ መቐለ የሚያደርገውን ጉዞ ለመሰረዝ መገደዱ ይታወቃል። በእነዚህና በሌሎችም ተያያዥ ምክንያቶች አጣብቂኝ ውስጥ የገባው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የክልል አመራሮችን ማነጋገር የጀመረው ቀደም ሲል ጀምሮ መሆኑ ይታወሳል። ያም ሆኖ ጨዋታዎች መሰረዛቸውና የፀጥታ ስጋት መኖሩ አልቀረም። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ፌዴሬሽኑ በካፍ መርሃግብር መሰረት የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክሉ ክለቦችን ለማሳወቅ ምን ያህል ጥድፊያ ውስጥ እንደገባ በቅርቡ የምናስታውሰው ነው። በስፖርቱ ዓለም የተመልካቾች ነውጠኝነት ምክንያቶች ብዙ መሆናቸውን በስፖርቱ ጥልቅ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች ሲናገሩ ይደመጣል። ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ ወይንም ምጣኔ ሀብታዊ ብሶቶች ስቴዲየም ላይ ሊያጠሉ እንደሚችሉም ይታመናል። በኢትዮጵያ እግር ኳስን የታከከ ግጭትና ሁከት ሲከሰት የመጀመሪያው ባይሆንም 2011 ላይ ቀይ መስመር አልፎ ታይቷል። የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን ስናጤን ደግሞ ከእግር ኳስ ባሻገር ከነዚህ ምክንያቶች ሁሉ ለስፖርት ጠንቅ የሆነ የፖለቲካ አጀንዳ መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ራሳቸው አስተውለውታል። እግር ኳስ ማኅበረሰባዊ መሰረት ከሌለው በስተቀር የጠነከረ የእኔነት ስሜት ሊፈጥር አይቻለውም የሚሉ ተንታኞች ፤ ክለቦች ከማኅበረሰባዊ መሰረታቸው በዘለለ ብሔር ተኮር መልክን እየተላበሱ የመምጣታቸው አዝማሚያ አደገኛ መሆኑን አይክዱትም። ክለቦች ሲቋቋሙ ወይንም ሲዋቀሩ አካባቢያዊ መገለጫ ወይንም ከተማዊ ስያሜ ሊኖራቸው ቢችልም ከብሔር፣ ከዘር ወይንም ከኃይማኖት ጋር በተቆራኘ መልኩ መደራጀት ክልክል መሆኑን የስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ማኅበራት ማደራጃ መመሪያ አንቀፅ 50 ቁጥር 2 ይገልፃል። ነገር ግን ባለፉት ዓመታት ብቻ ፌዴሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ሊጎች የብሔር ስም የተቀጠላላቸው በርካታ ክለቦች ውድድር እያደረጉ ይገኛሉ። እግር ኳሱ ከአንዳንድ ሁከቶች አልፎ እጅግ ወደተደራጀ ነውጠኛነት እያመራ ስለመሆኑ የ2011 ዓ.ም መርሃግብሮች ቁልጭ አድርገው አሳይተውናል። ቀስ በቀስም ወደመቧደን እየተሄደ ራሳችንን መከላከልና ማዘጋጀት አለብን በሚል ደጋፊዎች ራሳቸውን ማደራጀት ከጀመሩ የሚያሰጋ ዓይነት እውነታ ሊፈጠር እንደሚችል በ2011 የውድድር ዓመት ተመልክተናል። በደጋፊዎች መካከል የእኔነቱ መንፈስ ከሮ ከኳስ ወዳጅነት አፈንግጦ በብሔርተኝነት ጎዳና መጓዝ ተጀምሯል። ከዚህ ቀደም ብጥብጡ ተጀምሮ የሚያልቀው ስቴዲየም ነው፤ ከዚያ አያልፍም። አሁን አሁን እየታየ ያለውን ግን ማብራሪያ የማይፈልግ የአደባባይ ሃቅ ነው። ክለቦች የማንነት ማግነኛና የራስ ኩራት መገለጫ መድረኮች እየሆኑ የመምጣታቸውን ሃቅ በየአካባቢው እየጎመራ ከመጣው የዘውግ ብሔርተኛነት ጋር የሚያስተሳስሩትም ጥቂት አይደሉም። ክለቦች መጠሪያው ባይኖራቸውም ከሚመጡበት ክልል ጋር ተያይዞ የእገሌ ብሔር ነው የሚል እምነት አሳድረዋል። ከዚህም በተጨማሪ ክለቦች የተለያዩ የአገሪቱን ክልሎች እንደሚወክሉ መታሰቡ፤ ክልሎች ብሔርን መሰረት አድርገው እንደመዋቀራቸው ብሄርን እንደሚወክሉ ወደመታሰብ አድጓል። ፌዴሬሽኑ ከውይይት የዘለለ ፋይዳ ያለው ነገር እየሰራ እንዳልሆነ የሚጠቁሙ የስፖርት ቤተሰቦች ከዚህም በኋላ ችግሩን ይቀርፋል የሚል እምነት ማሳደር ተቸግረውበታል። ይህንንም በውድድር ዓመቱ በጉልህ ተመልክተነዋል። ሳይጠናቀቅ የተጠናቀቀው ፕሪሚየር\nሊግ አሁን አሁን በአዲስ አበባም ሆነ የክልል ስታደዬሞች ገብቶ ኳስ መታደም የራስን ደህንነት አደጋ ላይ ከመጣል ጋር ይነፃፀር ጀምሯል። ጨዋነት የጎደላቸው ደጋፊዎች፣ ከዳኛ ጋር ቡጢ የሚገጥሙ ተጫዋቾችና የቡድን አባላት፣ እንዲሁም ኢ-ፍትሐዊ የሆኑ ውሳኔዎች የሊጉ መገለጫ ከሆኑ ሰነባብተዋል። የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከስቴድየም ግጭትና ከፌዴሬሽኑ አወዛጋቢ ውሳኔዎች ጋር ተያይዞ ክለቦች የውድድር ዘመኑን ሳይቋጩ ራሳቸውን ከውድድር ያገለሉበት ሆኖም ይታወሳል። ውዝግቦችና አለመግባባቶች በኢትዮጵያ እግር ኳስ ነግሰዋል። መሬት ያልነኩ፣ በእውቀት ያልተዋጁ ውሳኔዎች ሰላማዊውን መድረክ የብጥብጥ ቀጠና አድርገውታል። ሊጉ የሚቀጥልበት አቅም ባለማግኘቱም በተደጋጋሚ ለመቋረጥ ተገዷል። ለዚህም የአገሪቱ ታላላቅ ክለቦች የሆኑት ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ላይ ከፌዴሬሽኑ ጋር የገቡበት ውዝግብ የአዲስ አበባ ክለቦች የራሳቸውን ሊግ ለማቋቋም ውሳኔ ላይ እስከመድረስ ገፍተው እንዲሄዱ አድርጓቸዋል። ያም ሆኖ የአዲስ አበባ ክለቦች የራሳቸውን ሊግ በማቋቋም የጀመርነውን አዲስ ዓመት ይገፉበታል ወይም በተለመደው ፕሪሚየር ሊግ ይቀጥላሉ የሚለው ሃሳብ ጥርት ያለ ድምዳሜ ላይ ሳይደረስበት ወደ አዲሱ የውድድር ዓመት ተሸጋግረናል። ብሔራዊ ቡድኑ (ዋልያዎቹ)\n2011 ዓም የአንድ አገር ሊግ ድክመትና ጥንካሬ የብሔራዊ ቡድኑ መገለጫ እንደሚሆን አሳይቶን አልፏል ማለት ይቻላል። የአገሪቱ ሊግ በግጭትና ፍትሃዊ ባልሆኑ ውሳኔዎች እየታመሰ አይደለም ለወትሮውም ጥሩ ስም የለውም። የሊጉ ደካማነት ብሔራዊ ቡድኑ (ዋልያዎቹ) ላይ ተንፀባርቆ ያለፈበት ዓመት ለመሆኑ ጥቂት ውድድሮችን ለአብነት ማንሳት ይቻላል። ከሁለትና ሦስት ዓመታት በፊት እንደ ጅቡቲ ያሉ የእግር ኳስ ደረጃቸው ከኢትዮጵያ ያልተሻሉ አገራትን በቀላሉ ግማሽ ደርዘን ግብ አስቆጥረን ማሸነፍ እንችል ነበር። አሁን አሁን ይሄም እየከበደን ከአንድ ግብ በላይ ማስቆጠር እየተሳነን እንደመጣ በውድድር ዓመቱ ተመልክተናል። ቀደም ሲል በቻን የምናደርገውን ተሳትፎ አሁን ማድረግ አልቻልንም፣ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ አገራት ከአስራ ስድስት ወደ ሃያ አራት ከፍ ብሎ እንኳን ተሳታፊ መሆን አልቻልንም። ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ እንኳን ሌሴቶን ባህር ዳር ላይ ገጥመን ግብ ማስቆጠር አልቻልንም፣ የመልሱም ጨዋታ ቢሆን አንድ ለአንድ ተለያይተን ወደ ምድብ ድልድል የገባንበት አጋጣሚ ደረት የሚያስነፋ አይደለም። በመጨረሻም እግር ኳሱ በ2011\nየውድድር ዓመት በዚህ ደረጃ ዘቅጦ ፌዴሬሽኑ አዲሱን ዓመት በምን መልኩ መጀመር እንዳለበት በግልፅ ያስቀመጠው ስትራቴጂክ\nእቅድ የለም። ፕሪሚየር\nሊጉ እንዳለፈው ዓመት ተዟዙሮ የመጫወት\nመንገድ ይቀጥል አይቀጥል\nማንም አያውቅም። ከፌዴሬሽኑ\nዝምታ ተነስቶ ግን ሊጉ በነበረበት\nእንዲቀጥል ፍላጎት መኖሩን መገመት ከባድ አይደለም። ይህ ደግሞ ካለፈው ስህተት አለመማር\nብቻም ሳይሆን የአገር ንብረትና የዜጎች ሕይወት የሚጠፋበትን\nመንገድ መፍቀድ ጭምር ነው። ፌዴሬሽኑ\nከዚህ ጉዳይ ይልቅ የተጫዋቾች የደመወዝ\nጣሪያ ጉዳይ አስጨንቆት\nከርሟል። ለዚህም አበጀሁለት\nያለው መላ መልካም ጎን እንዳለው\nሁሉ በርካቶችን ያስማማና\nከትችት ያመለጠ አልሆነም።አዲስ\nዘመን\n  መስከረም\n1 /2012 ቦጋለ አበበ", "passage_id": "c6b9f0e5ca439026fb01026445115345" } ]
324c222bd1fc191bacb4104388f1f603
f8bfcd13a81274d72db376a2884fc4bf
ዩኒቨርሲቲዎቻችን እንደስማቸው
ውብ ጸጉር ያለው ታዳጊ ነው። ለጸጉሩ ያለው ፍቅር ከሴቶችም በላይ ነው። በእንክብካቤ ይይዘዋል። ቢነካካው፣ ቢታጠበው፣ ቢያበጥረው፣ ቢዳስሰው አይጠግብም ።በክረምት ደግሞ አሳድጎ እሱ የሚጨምርበት ንቅናቄ እንዳለ ሆኖ ነፋስ ሽው ሲያደርገው እንደደረሰ የጤፍ ቡቃያ ይዘናፈላል። ሀርነቱ፣ ዞማነቱ ብቻ እንደ እኔ ጸጉር የሚወድን ሰው ብቻ ሳይሆን ጸጉር ለሴት እንጂ እስከሚለው ሰው ድረስ አይን ይስባል። ያማልላል። ይሄ የምላችሁ ልጅ ጸጉር ታዲያ መስከረም ሲጠባ ያው እንደተለመደው የትምህርት ቤት ህግ አለና ይቆረጣል። ባይወድም ግድ ነውና መቼ ይሆን ዩኒቨርሲቲ ገብቼ እንደፍላጎቴ የማደርገው ብሎ እየተነጫነጨም ቢሆን ብቻ የትምህርት ቤቱ ህግ ነው ይታጨዳል ።ለአስር ወራት የትምህርት ጊዜውን ተስተካክሎ ወጣት ወንድ ተማሪ የሚያስመስለውን ጸጉሩን ታጥቦ ከመውጣት በስተቀር ሌላ ምርጫ የለውም ። እንዳው ይሄንን ስል መመስገን የሚገባቸውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ላመስግን። ሁሉም ባይሆኑም ብዙዎች የግል ትምህርት ቤቶች የተማሪዎቻቸውን ጸጉር ፣ ዩኒፎርም እና የሚያደርጉትን ጫማ ጭምር ከስርዓት የወጣ እንዳይሆን ይቆጣጠራሉ።ወንዶቹ ሱሪያቸውን በስርዓት እንዲታጠቁ ያስገድዳሉ።እንዳውም አንድ የትምህርት ቤት ባለቤት በትምህርት ዘመኑ መጀመሪያ ቀን ተማሪዎችን አሰልፎ “እያንዳንዳችሁ ወንዶች ቀበቶ መታጠቅ አለባችሁ ። ሱሪዬን ዝቅ አደርጋለሁ ብትሉ አትገቡም። ወላጆቼ ቀበቶ አልገዙልኝም፣ የለኝም የምትሉ ካላችሁ ሱሪያችሁን በቃጫ ድብን አድርጋችሁ ታስራላችሁ” እንዳላቸው የነገሩኝን አልረሳውም። በእነሱ አባባል ሙድ ቢጤ ቢይዙበትም ለእኔ ግን ትልቅ መልዕክት ትቷል። እንዲህ አይነት ልጆችን ከልጅነታቸው ጀምሮ ስነስርዓት ይዘው እንዲያድጉ የሚያደርጉትን ታዲያ ማመስገን አለብን በሚለው ሁሉም ይስማማል ብዬ አስባለሁ። ነገር ግን ሱሪያቸውን እንደ እጀጠባብ አጣብቀው ከወገባቸው ዝቅ አድርገው ጸጉራቸውን አንጨባረው፣ አንጨፋረውና ቆጣጥረው ወደ ትምህርት ቤት የሚሄዱትን ደግሞ ዝም ብለው የሚቀበሉ ትምህርት ቤቶች እና መምህራን መኖራቸው አይዘንጋ። በቀለም አባትነት የሚቀርፁትን ተማሪ በምንቸገረኝነት የሚመለከቱ ታዲያ መምህራን ናቸው ብሎ መናገር መዳፈር አይሆን ይሆን? እንደ እኔ መምህራን ናቸው ። ተማሪ እየቀረፁ ነው ማለቱ ከበድ አለኝ። ታዲያ ይሄ የስነምግባር ችግር የሚታየው በግል ትምህርት ቤቶች ላይ ብቻ እንዳይመስላችሁ። ምንቸገረኝነቱ በመንግስት ትምህርት ቤቶችም ጎልህ ነው። በነገራችን ላይ የትምህርት ቤት ስነምግባር ተጓደለ ስል ይሄ በተማሪው ብቻ እንዳልሆነ ይያዝልኝ።”ስርዓት አልበኛ” ከምንላቸው ተማሪዎች ባልተናነሰም ስርዓት አልበኛ መምህራንም ብዙ ናቸውና። ተማሪ ከትምህርት እንጂ ከእኔ ስነምግባር ምንአለው እስከሚሉት ድረስ ማለቴ ነው። ከሚያስተምሩት ተማሪ ጋር በጫት ቤት፣ በመጠጥ ቤት የሚጎዳኙ መምህራን መኖራቸው አይዘንጋ። አሁንም እላለሁ ሁሉም መምህራን አይደሉም። በሙያቸው በምግባራቸው አንቱ የተሰኙ፣ የእውነቱ የቀለም አባቶች አሉን። የማንረሳቸው ክፉ አይንካችሁ የምንላቸው፣ ከወላጅ አባት የማይለዩ ብዙ ምስጉን መምህራን አሉን። መቼም የማይረሱ ውለታቸውን እንዴት ልመልስ የሚያሰኙትን መምህራን ኢትዮጵያ አፍርታለችና። አሁንም መምህርነትን እያከበሩና እያስከበሩ ያሉት እነሱ ናቸው። አሁንም እላለሁ እናንተም በራሳችሁ ለራሳችሁ ብቻም ሳይሆን ሌላውንም ከመስመር ወጣ የሚለውን መምህር ጭምር ሃይ በሉ። አበው በአንድ እጅ አይጨበጨብም እንዲሉ በጥቂት ብቁና ሙሉ መምህራን ብቻ ብልሹ መምህራንንና ተማሪን ማረቅ ከበድ ይላል።እዚህ ላይ መምህራኖች ተዳፍሬና ቀዩን መስመር አልፌ ከሆነ ሁሌም ስሳሳትና ሳጠፋ እንደምለው ይቅርታ ይደረግልኝ። ይሁንና ያየሁትን አይቼና የሰማሁትን ሰምቼ እንጂ ልቦለድ እያወራሁ እንዳልሆነ ግን እናንተንም ምስክሮቼ ብዬ እቆጥራለሁ። አነጋጋሪው የስነምግባር ጉዳይ ከተማሪ ወደ መምህራን ሙልጭ አድርጎ ወሰደኝ አይደል፣ ልመለስ ስለተነሳሁበት ወጣት ሀሳብ ።ይሄ ጸጉራማ ወጣት ታዲያ ዘንድሮ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሊገባ ነውና ጸጉሩን እንደ ጉድ አሳድጓል።ዘንድሮ ክረምቱም ያማረ እንደነበረው ዝናብ የጠገበ ለምለም ቡቃያ መስሏል የእሱም ጸጉር ። ክረምቱ ጸጉርም ያሳምራል ልበል? አይቼ በውስጤ ያሰበኩት ነው። አሁንም እንደለመድኩት ጥያቄ ማንሳቴን ግን አልተውኩም። ” ይሄ ጸጉር መፍትሄ የለውም እንዴ?” ስል አነሳሁ ። በሳቅ የታጀበ መልስ ነበር አጸፋው።” ዘንድሮ ጉዞ ወደ ዩኒቨርሲቲ ነው። ተስተካከል ፣ ይሄን ልበስ ፣ያን አትልበስ፣ ደህና እደሪ” ነበር መልሱ። በልጁ አላዘንኩም መለስ ብዬ ያስታወስኳቸው ዩኒቨርሲቲዎቻችንን ነበር። ልጁ ያለው እውነት እኮ ነው አልኩ። የት ነህ? ማንነህ? ምንድነህ?… የሚል ከሌለ ዩኒቨርሲቲዎቻችን እውቀት መገብያ መሆናቸው ይቀርና ልክ የሰማነውን የምናየውን ይሆናሉ። እዚህ ላይ አንድ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ከፍተኛ ባለስልጣን ያሉኝን ላስታውስ። “ዩኒቨርሲቲዎቻችን ቡና የማይጠጡ ልጆችን ተቀብለው ጫት ቃሚ አድርገው ነው የሚያስረክቡት “ብለዋል ። ታዲያ ይሄንን እየሰማና እያየ ያደገ ተማሪ ዩኒቨርሲቲ እንደፈለግኩ የምሆንበት ቦታ ነው ብሎ ቢያስብ ይፈረድበታልን? የልጁን ፍላጎት አስቤ በተለይ ደግሞ የትምህርት ዘመኑ አልቆ ስንገናኝ ይሄ ጸጉር የት ሊደርስ እንደሚችል ዝም ብዬ ስስለው እንደሴቶቹ ወደኋላ ተኝቶ በፖኒተል አስሮ እንደምንገናኘ ሳላሸልብ አለምኩ። ደግሞም ይሆናል ምክንያቱም ሀይባይ የለማ። ይሄ የሚሆነው እስከ አለፈው ዓመት ብቻ ይመስለኛል። ምክንያቱም ቢዘገይም እንኳን ዘንድሮ ላይ ዩኒቨርሲቲዎቻችን ኮስተር ለማለት ማቀዳቸውን ሰምተናልና። ስርዓት አልበኛ ተማሪ አናፈራም፣ ሱሪ ዝቅ፣ ቡጭቅጭቅ …ለተማሪዎቻችን አይመጥንም እያሉ መሆናቸውን ጭምጭምታው ደርሶናል። እኛም ያድርገው እንላለን።ኧረ እንዳውም ደህና ነገር ሲሰማ አይቀይርብን ተብሎ ጸሎትና ዱአ ሁሉ ይደረጋል። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሆነው እንዲገኙ እኛም ይሄንኑ እናደርጋለን ። ይሄንን መነሻዬ አደረግኩት እንጂ ብዙ ኧረ በጣም ብዙ ዩኒቨርሲቲ ገብተን ፀጉራችንን ቆጣጥረን፣ አሳድገን፣ አፍሮ አበጥረን… ብለው የሚያልሙ እንዳሉ አንዘንጋ ። ሁሉም ይሄንን የሚያልሙት ታዲያ ከምን ተነስተው ነው ብለን ብናስብ መልሱ ቀላል ነው። ቀደም ሲል ከገቡ ተማሪዎች ያዩትን ለመድገም ፣ የዕድገት ወይም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የመሆን መለያ አድርገው በማሰብ ይመስለኛል ብል ተሳሳትኩ እንዴ? ከሆነም ይቅርታ። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሪዛቸውና ጸጉራቸው የሚያድገው ለመስተካከል ጊዜ እያጡ የጥናት ሰዓት ይሻማብናል ብለው ይሆናል ብዬ አስባለሁ። በዚህ ሀሳቤ ዙሪያ አንድ የጤና ተማሪ ግን ምን አለኝ” ጸጉር መስተካከል እንዳውም የጥናት ጊዜ ያስገኛል ። ጸጉር መንከባከብ ነው ጊዜ የሚወስደው” አለኝ ።እንዴት? የእኔ ጥያቄ ነበር። በቃ አንድ ልጅ ጸጉሩን ካሳጠረ ጠዋት ፊቱን ሲታጠብ ጸጉሩንም ታጥቦ ንጹህ ይሆናል። ጸጉር ያለው ተማሪ ግን ያንን ጸጉሩን መንከባከብ ይጠበቅበታል ።መስታወት እያየ ማበጠርና ማስተካከል ሁሉ ይኖራል። ይሄ ደግሞ ጊዜውን ይሻማል ። ነገር ግን የጤና ተማሪዎች ከሶስተኛ ዓመት በላይ ሲሆኑ ፀጉር ማሳደግ አይፈቀድላቸውም። አለባበሳቸውም ሆነ ጸጉር አቆራረጣቸው ስርዓት ያለው መሆን አለበት ። ይሄ ግዴታ ነው። የሚያክሙትን ህመምተኛና የሚጎበኙት ታካሚ እምነት ሊጥልበት የሚችል ስርዓት የተከተሉ መሆን አለባቸው ተብሎ ይታመናል” ሲል አስረዳኝ። ይሄ በጣም ጠቃሚና ይበል የሚያሰኝ ሀሳብ ነው። ታዲያ ሌላው ሙያ ላይ እምነት የሚጣልበትና ለሚሰማራበት ሙያ አስፈላጊውን ስነምግባር የተላበሰ ማድረጉ ምነው ከፋን። ስለዚህ ሁሉም ተማሪ ስነስርዓት ያለው አለባበስና የጸጉር አቆራረጥ ይኑረው ነው ሀሳቤ። ይሄ በጣም ጥሩ ነገር ነው በሌላው ዘርፍስ በህብረተሰቡ ዘንድ ተመራጭ ተመስጋኝ ቢሆን የሚያገለግለው ደንበኛ የሚደሰትበት ቢሆን ኧረ እንዳውም ሱሪውን ከፍ አድርጎ ወገቡ ላይ የታጠቀ ወላጆቻችን እንደሚሉት ቆፍጣና ወንድ ቢሆን ምን አለ ። እንዳው ምነው ወንዶቹ ላይ በረታሽ አትበሉኝ። የሴቱም ለዛሬም ባይሆን ብዙ ይባልበታልና በዚሁ ይያዝ። ዘንድሮ ግን ዩኒቨርሲቲዎቻችን የመጥፎ ምሳሌ አንሆንም! እምቢ አሻፈረኝ! ለማለት መዘጋጀታቸውን ወሬ አይደበቅ አይደል ሀሜቱ ሽው ብሎኛል። ቀድሜ ካመሰገንኩ በኋላ ለመውቀስ አይሁን ብዬ እንጂ እውነት ያሰቡትን ከተገበሩት ቀደም ብለን ምስጋና ይድረሳችሁ ማለት ይገባል። ዩኒቨርሲቲዎች ሌላው አሳዳጊዎች ናቸው። ተማሪዎችን በእውቀት አጎልብተው፣ በአእምሮ አደርጅተው፣ ለሀገር ለወገን አሳቢ፣ ሀገር ወዳድ ዜጋ አድርገው ማውጫ ቦታ ናቸው። ታዲያ በተማሪ አያያዛቸው እንደስማቸው ቢሆኑስ? ሰላም!አዲስ ዘመን መስከረም 25/2012አልማዝ አያሌው
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=20092
[ { "passage": " በቅጥር ግቢው በርካታ አውቶቡሶች ቆመዋል:: የተሽከርካሪዎቹ ዝግጁ መሆን የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ለልምድ ልውውጥ ይሁን ለጉብኝት ከግቢው ለመውጣት የተዘጋጁ አስመስሏል:: በ2009 ዓ.ም ወደ ተመሰረተው ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ጊቢ ስንዘልቅ ያስተዋልነው ደግሞ ግቢው ‹‹ቅጥር›› ሊያስብል የሚያስችለው የተጠናቀቀ ስራ አለመኖሩን ነው::በቢሯቸው ያገኘናቸው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ለታ ተስፋዬ እንደሚሉት፤ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ሲቀበል የዘንድሮው ለሶስተኛ ጊዜ ነው:: በ2010 ዓ.ም በመደበኛ ሁለት ሺህ 276 ተማሪዎችን እንዲሁም በተከታታይ እና የርቀት ትምህርት ደግሞ 770 ተማሪዎችን ተቀብሏል::ከአጠቃላይ ተማሪዎቹ መካከልም 186ቱ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ናቸው:: በጥቅሉ በሶስቱም ፕሮግራሞች (በቅድመ ምረቃ፣በድህረ ምረቃና በተከታታይ) ሶስት ሺህ 46 ተማሪዎችን በ36 የትምህርት ዘርፎች ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል:: ዘንድሮ አዲስ የገቡት ተማሪዎች አንድ ሺህ 600 አካባቢ ይሆናሉ፤ እነዚህን ተማሪዎች እንደ ሌሎቹ ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉ የተቀበሏቸው ዝግጅት በማድረግ ነው:: ዩኒቨርሲቲው አዲስ ከመሆኑ የተነሳ የፀጥታ ችግር እንዳያጋጥም ብዙ ዝግጅቶች ከአገር ሽማግሌዎች ጀምሮ የኃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎችና ከከተማው ወጣቶች ጋር በርካታ ተግባሮች ተከናውነዋል::ዶክተር ለታ፣ ‹‹በአሁኑ ወቅት የግቢውን ደህንነት የሚያስጠብቀው የፌዴራል ፖሊስ ነው:: ምክንያቱም ተማሪዎቹን ስንቀበል በአደራ ነውና ደህንነታቸውን መጠበቅ ግድ ይለናል:: የፊቱ የግቢው ፖሊስ ብዙም አቅም አልነበረውም:: ከዚያም የተነሳ እኛም በተለያየ ጊዜ ፌዴራል ፖሊስ ወደ ግቢ ገብቶ ፀጥታውን እንዲያስከብርና ውስጥና ውጭ ያለውን ደህንነት እንዲያረጋግጥልን ጠይቀን ነበር:: መንግስትም ጉዳዩን ስላመነበት ወደ 63 የሚሆኑ የፌዴራል ፖሊስ አባላት መድቦልናል:: እነሱ ከመጡ በኋላም ብዙ ለውጦች ታይተዋል›› ይላሉ:: ዩኒቨርሲቲው አሁንም ሌሎች በርካታ ችግሮት አሉበት የሚሉት ዶክተር ለታ፣ ግቢው አጥርም መግቢያ በርም እንደሌለው ነው የሚጠቁሙት:: በዚህም ምክንያት ተማሪው ከግቢው በማንኛውም ሰዓት የመውጣት እድሉ ሰፊ ነው:: ካፒታል በጀት ለዩኒቨርሲቲው መውረድ የነበረበት ቢሆንም ይህ አልሆነም፤ እንደ ወንበር፣ ፍራሽ ያሉትን ጥቃቅን ነገሮችን ሳይቀር ለመግዛት መንግስትን እንጠይቃለን ሲሉ ያብራራሉ:: እንደ ዶክተር ለታ አባባል፤ ዩኒቨርሲቲው ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎች የሉትም ፤ ከተወሰኑ ተሸከርካሪዎች ውጪ ሙሉ ለሙሉ የሚጠቀመው በኪራይ ነው:: የትራንስፖርቱን ችግር በተመለከተ ለሶስት ዓመት በተከታታይ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል፤ እስካሁን መፍትሄ አልተገኘም:: ግቢ ውስጥ የሚታዩት ወደ ዘጠኝ አውቶቡሶች በኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው:: የመምህራን ደመወዝ እየዘገየ መድረሱም ሌላው ችግር መሆኑን ይጠቁማሉ:: በየ15 ቀኑ ሪፖርት እያደረጉ ነው የሚጠይቁት:: የተማሪዎች የመመገቢያ አዳራሽ እንዲሁም የማደሪያ ክፍሎችንም ማስፋት እንደሚያስፈልግ ይጠቁማሉ::እንደ ዶክተር ለታ\nገለጻ፤ ቤተመጻህፍቱ መፅሐፍት\nእንደልብ የሉትም:: ግዢ\nአካባቢ ችግሮች በመኖራቸው\nመጻህፍት የሚገዛው በለቀማ\nነው:: ግልፅ ጨረታ አውጥቶ ለመግዛት መጻህፍቱን በገበያ አያገኙም:: የውሃ ፓምፕ ቢቃጠል ለመግዛት ብዙ ሂደት መከትልን ይጠይቃል:: ሂደቱ እስከ ስድስት ወር ሊፈጅ ይችላል፤ ይህ በጣም ፈታኝ ጉዳይ ሆኗል:: ስለዚህም ካፒታል በጀት ወደ ዩኒቨርሲቲ መውረድ አለበት በሚል ዩኒቨርሲቲው መንግስትን በተደጋጋሚ ጠይቋል፤ ችግሩ ግን አልተፈታም :: የዩኒቨርሲቲው የጥናት ፣ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ረዳት ፕሮፌሰር ዮሴፍ ሽፈራው ፤ ዩኒቨርሲቲው ሶስት ተልዕኮዎች እንደተሰጡት ይገልጻሉ:: የመጀመሪያው መማር ማስተማር፣ ሁለተኛው ደግሞ ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናቶችን ማካሄድ ሲሆን ሶስተኛው የማህበረሰብ አገልግሎት ወይም ህብረተሰቡን ያሳተፈ አገልግሎት መስጠት እንደሆነ ያብራራሉ:: ‹‹እኛ መኪና መግዛት አልተፈቀደልንም፤ የምርምር ስራ ደግሞ በቂና ምቹ ትራንስፖርት ያስፈልገዋል::›› ሲሉ ጠቅሰው፣ ለአብነትም ከደምቢዶሎ አዲስ አበባ አንድ ናሙና ለመውሰድ ደህንነቱ መጠበቅ እንዳለበት ተናግረው፣ ይህ እንዲሆን ለማድረግ ግን የትራንስፖርት ችግር መሆኖሩን ያመለክታሉ:: ለአካባቢው ህብረተሰብ የሚጠቅም ምርምርና ቴክኖሎጂ ማፍለቅ የሚቻለው በአንኳርነት ሊሟሉ የሚችሉ ጉዳዮች ሲሟሉ ነው የሚሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ መንግስት እዚህ ላይ ትኩረት ቢያደርግ የተሻለ መሆኑን ይናገራሉ:: በዩኒቨርሲቲው በኩል የማህበረሰብ አገልግሎቱን በተነቃቃ መልኩ ለመስራትም ዝግጁ መሆናቸውን ያስረዳሉ::ዩኒቨርሲቲው አሉብኝ ያላቸውን\nችግሮች በተመለከተ ማብራሪያ\nእንዲሰጡን የጠየቅናቸው በሳይንስና\nከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር\nየ11ዱ አዳዲስ\nዩኒቨርሲቲዎች ግንባታ ፕሮጀክት\nዋና ስራ አስኪያጅ\nዶክተር ግርማ መኮንን\n፤ እርሳቸው ወደስራ\nአስኪያጅነቱ ከመጡ ቀናትን\nብቻ እንዳስቆጠሩ ጠቅሰው፣ ዩኒቨርሲቲዎች እያቀረቡ ያሉት የመሰረተ ልማት ችግር ጉዳይ እየተጣራ መሆኑን ይገልጻሉ::‹‹በአሁኑ ወቅት አንዱ ለሰላም መደፍረስ በምክንያትነት የተቀመጠው የዩኒቨርሲቲዎች አጥር አለመኖር መሆኑ በግምገማ ተነስቷል:: ይህን ችግር ለመፍታት በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ምን እየተሰራ ነው ቢባል በአሁኑ ወቅት ለቦታው አዲስ ከመሆኔ ጋር ተያይዞ እርገጠኛ ሆኜ መናገር አልችልም::››\nሲሉ ገልፀው፤ በቅርበት የሚያውቋቸው የሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችን የውሃ ችግር ለመንግስት እንደቀረበ ተናግረዋል:: ማቅረባቸውንና እና ውሳኔም እንደሚሰጥበት እምነታቸው መሆኑን ያብራራሉ:: የደምቢቦሎ ግን እርሳቸው እስከሚያውቁት ድረስ ጥያቄው አልቀረበላቸውም::ዶክተር ግርማ እንደሚናገሩት፤ በጀት ወደዩኒቨርሲቲዎቹ የማውረዱ ነገር ችግር የለውም፤ መንግስት በቀጣይ ርምጃ እየወሰደ ወደዚያ እንዲሄድ ያደርጋል:: ይሁንና የበጀት ወደ ዩኒቨርሲቲዎች መውረድ አለመውረድ ያን ያህል የመሰረተ ልማት ግንባታውን የሚጓትት አይሆንም::በሚኒስቴሩ የምርምርና አካዳሚ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ኤባ ሚጃና በበኩላቸው፤ ተማሪዎች የፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም ኮማንድ ፖስት አያስፈልገንም፤ ሰላማችንን እኛው መጠበቅ እንችላለን ለሚሉት ምላሽ ሲሰጡ እንዳስረዱት፤ በእርግጥም ሰላም እስካለ ድረስ ሌላ ተጨማሪ ጥበቃ በህጉም ቢሆን አያስፈልግም:: ብለዋል:: አሁን በየዩኒቨርሲቲው ሰላም ስለደፈረሰና ከዚህም አልፎ የሰው ህይወት ስለጠፋ ጭምር ነው በመንግስት ተወስኖ ዩኒቨርሲቲዎች በሌላ ሀይል እንዲጠበቁ እየተደረገ ያለው ይላሉ:: ሰላሙ ወደነበረበት የሚመለስ ከሆነ ጥበቃውም እስከዘላለም የሚቀጥል እንዳልሆነና እንደሚነሳም አስገንዝበዋል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 21/2012 አስቴር ኤልያስ", "passage_id": "4a82c93f509498e211ab92a5741fa353" }, { "passage": "በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የተገነቡና አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ከ50 በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ አንዳንዶቹ ሙሉ ለሙሉ ሳይጠናቀቁ ተማሪዎችን በመቀበል ያስተናግዳሉ፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተገንብተው አገልግሎት መስጠት የጀመሩት አብዛኞቹ ዩኒቨርስቲዎች ግን መብራትና ውሃን ጨምሮ በመሰረተ ልማት እጥረት የተነሳ የመማር ማስተማሩን ስራ በአግባቡ ማከናወን አለመቻላቸውን ያማርራሉ፡፡ይህንንም በተመለከተ በህዝብ ተወካዮ ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በእንጅባራ፣ ሰላሌና ጎንደር የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በመገኘት ምልከታ አድርጎ ነበር፡፡ ቋሚ ኮሚቴውም በምልከታው  በየተቋማቱ ችግሮች መኖራቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡የሰው ሀብት ልማትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ክፍሌ ለማ እንደሚሉት፤ ጥናት ያደረጉባቸው ቦታዎች ከግንባታ ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ ለተቋራጭ ገንዘብ በጊዜው አለመከፈልና የግንባታ መጓተት፣ በየተቋማቱ የሚሰጠው የመውጫ ፈተና በተማሪዎች ተቀባይነት ማጣት፣ የመብራት መቆራረጥ፣ የውሃ አቅርቦት ማነስ እንዲሁም በትምህርት ክፍሎች ውስጥ ያለው የብሄር ስብጥር ተመጣጣኝ አለመሆን  በዩኒቨርሲቲዎቹ ለሚነሱ ችግሮች ዋነኛ መንስኤዎች ናቸው፡፡በፌዴራል ደረጃ የተዘጋጁ ዲዛይኖች በፍጥነት አለመሻሻል ለግንባታ መጓተት ምክንያት ነው የሚሉት አቶ ክፍሌ፤ ግንባታዎች ከተያዘላቸው ጊዜ በላይ ተቋራጮች ሲያጓትቱ እርምጃ አለመውሰድና በሌላ በኩል ችግሮቹ ወደ ፍርድ ቤት በሚወሰዱበት ወቅት  አፋጣኝ እርምጃ አለመውሰድ በግንባታ ስራዎች ላይ መጓተት እንደፈጠረ በምልከታው መታየቱን ይጠቁማሉ፡፡ለአዳዲስ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚቀርበው የሃይል አቅርቦት አነስተኛና የተቆራረጠ መሆኑ እና አፋጣኝ መፍትሄ አለመሰጠቱ የማስተማር ስራው ላይ እክል መፍጠሩን በመጥቀስ፤ ለጊዜያዊነት ጀኔሬተር የቀረበ ቢሆንም በእንጅባራና በሰላሌ ጀነሬተሮቹ አገልግሎት እየሰጡ አለመሆኑን በምልከታው መታየቱን ይገልፃሉ፡፡እንደ አቶ ክፍሌ ገለፃ፤ ምልከታ በተደረገባቸው ሁለቱ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች በቂ የቤተ ሙከራ ግብዓቶች ሳይኖሩ ሁሉም ነገር ከተሟላላቸው ዩኒቨርሲቲዎች እኩል የመውጫ ፈተና እንድንፈተን መደረጉ ፍትሀዊ አይደለም የሚል ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ አዳዲስ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ከግንዛቤ የከተተ  የፈተና አሰጣጥ ባለመኖሩም በተማሪዎች ዘንድ ቅሬታ እየተፈጠረ ነው፡፡የተማሪዎች ምደባ የብሄር ስብጥር በጠበቀ መልኩ ቢካሄድ ተማሪዎቹ የሚገጥማቸው የቋንቋም ሆነ የሌላ ማበራዊ ችግር እንደሚፈታ የሚጠቁሙት አቶ ክፍሌ የተወሰኑ ተማሪዎች አንድ ዲፓርትመንት ውስጥ እንዲመደቡ መደረጉ እያጋጠመ ላለው የፀጥታ ችግር መንስኤ መሆኑንም ያመለክታሉ፡፡ በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ያለውን ከፍተኛ የውሃ አቅርቦት ችግር ለመፍታት ለኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ስራው ቢሰጥም እስካሁን ስራው ባለመጀመሩ  ተማሪዎቹ ለችግር መዳረጋቸውን በምልከታው መታየቱን ጠቁመዋል፡፡ ተቋሙ በጊዜያዊነት የሚጠቀምበት ከከተማው የሚመጣው  የውሃ መስመር በብልሽት ምክንያት በመቋረጡ ተማሪዎች ችግር ውስጥ መሆናቸውንም ይናገራሉ፡፡የ11 ዩኒቨርሲቲዎች ግንባታ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ከተማ መስቀላ፤ በአዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሃይል አቅርቦት አነስተኛ በመሆኑ አቅራቢያ ካሉ ከተሞች ሃይል በመሳብ በመጠቀም ላይ እንደሚገኙ ይጠቅሳሉ፡፡ ለዩኒቨርሲቲዎቹ ሃይል ለማሟላት ከመብራት ሃይል አገልግሎት ጋር ውል ተገብቶ ገንዘብ ቢከፈልም እስካሁን ሃይል አለመቅረቡን በመጥቀስ፤ ያለውን ችግር ለመፍታት ስራዎች ቢጀመሩም መዘግየታቸውን ይጠቁማሉ፡፡በአዳዲስ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ጀነሬተር ቢሰጥም አቅራቢው ከዋናው መስመር ጋር የሚያገናኘው ገመድ ዋጋው ጨምሯል ገንዘብ ይጨመርልኝ ማለቱን በመጥቀስ፤ ግዥ ኤጀንሲ ደግሞ ውል በገባው መሰረት ማቅረብ አለበት በማለቱ ገመዶቹ እስኪገዙ መዘግየቱን ይናገራሉ፡፡  የሃይል አቅርቦት ችግሩን ለመፍታት ዘላቂ የሃይል አቅርቦት የሚያስፈልግ ቢሆንም  የኢትዮጰያ ኤሌክትሪክ ሃይል የትራንስፎርመር ችግር ስላለብን ከውጭ ገዝቶ  እስኪያስገባ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ግንባታ የሚያዘገዩቱን ተቋራጮች ውል ሲቋረጥም በአፋጣኝ በአዲስ የማይተኩት በህግ የተያዘው ጉዳይ ሳይጠናቀቅ ለአዲስ መስጠት ስለማይቻል መሆኑን ያመለክታሉ፡፡ የውሃ አቅርቦት ችግሩን ለመፍታት በየክልሎቹ የሚገኙ የውሃ ስራዎች ኢንተርፕራይዞች የውሃ ጉድጓዶች እየተቆፈሩ እንደሚገኙ በመጥቀስ፤ ወደ ተቋማቱ ለማድረስ የበጀት እጥረት እንዳለ ይጠቁማሉ፡፡ በሰላሌ ያለው ጉዳይ የኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ጉድጓዱ ካለበት እስከ ተቋሙ ድረስ ለማምጣት በገጠመው ችግር   ስራው በፍጥነት አለመከናወኑን ያመለክታሉ፡፡የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ እንደሚሉት፤  የሚታዩት ችግሮች በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የሚስተዋል ነው፡፡ የመብራት መቆራረጡ አገራዊ ችግር ነው፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከስድስት እስከ አስራ ሁለት ሜጋ ዋት የሚሆን ሃይል ያስፈልጋል፡፡ መብራት ሃይል  የሚያስፈልገውን ሜጋ ዋት ባለማቅረቡ ምክንያት ከየአካባቢው አንድ ነጥብ አምስት ሜጋ ዋት በመሳብ እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ ለተቋማቱ የተሰጡት ጀነሬተሮችም ችግሩን መፍታት አይችሉም፡፡የመውጫ ፈተና ለማስተግበር በአገሪቱ ሁሉም ተቋም ተመሳሳይ አቅም ላይ መገኘት የለበትም የሚሉት ዶክተር ሳሙኤል፤  የመውጫ ፈተና የሚሰጠው የስራ ገበያውን የሚቀላቀል ተማሪ ቢያንስ ማወቅ ያለበትን ጉዳይ አውቋል ወይ የሚለውን ለመለየት በመሆኑ ይህንን ታሳቢ በማድረግ የሚዘጋጅ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በእርግጥ አዳዲሶቹ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በግብዓትና በሰው ሃይል በደንብ የተደራጁ ባለመሆናቸው እዛ ገብቶ የሚማር ተማሪ የራሱ የሆነ ክፍተት የሚፈጥርበት በመሆኑ የሚካካስበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚገባም ይጠቁማሉ፡፡ዶክተር ሳሙኤል እንደሚሉት የመውጫ ፈተና የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ፣ ለማረጋገጥ፣ ለማጎልበትና ለመቆጣጠር ጠቃሚ ነው፡፡ የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ደግሞ የመምህራን ልማት ስራ ወሳኝ ነው፡፡ በመሆኑም የመምህራን ልማት ላይ ከተሰራ ተማሪውን በመቀየር ጥራት ማምጣት ስለሚቻል  ለዚህ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል፡፡አዲስ ዘመን ጥር 20/2011 ", "passage_id": "d8dd4ccf60aaaddbfb952e4575fc747c" }, { "passage": "በሳምንት ሁለት ቀናት ማለትም ረቡዕና አርብ የ60 ተማሪዎችን ልብስ ያጥባሉ። የተማሪዎቻቸው ንፅህና ተጠብቆና በትምህርታቸው ልቀው ማየት ህልማቸው ነው። ካላቸው አነስተኛ ደመወዝ አንድ ሦስተኛውን ለዚህ በጎ ስራቸው ለማዋል በጅተውታል።\n\n• ሀሁ አስቆጣሪው ጃማይካዊ\n\n• ቀኝ እጇን ለገበሬዎች የሰጠችው ኢትዮጵያዊቷ ሳይንቲስት\n\n• የሙያውን ፈተና ለመጋፈጥ ከከተማ ርቆ የሄደው ሐኪም\n\nየአገሬው ሰው \"ምን ሀጢያት ቢሰራ ነው፤ እንዲህ ያለ እዳው ጎንበስ ቀና የሚለው?\" እያሉ ያጉመተምቱ ነበር- ነገሩ እስከሚገባቸው ነው ታዲያ። ከገባቸው በኋላማ \"አንተ 'እንትፍ ...እንትፍ' ብለህ ከመረቅካቸውም ይበቃል\" ሲሉ ያሞግሷቸዋል።\n\nየሚያውቋቸው \"ጋሸ\" እያሉ ነው የሚጠሯቸው። ሲበዛ ያከብሯቸዋል። \"የእርሳቸውን ነገር ለማውራትም ይከብዳል\" ይላሉ። እንዲያው በአጭሩ \"ለትውልድ ነው የተፈጠሩት\" ሲሉ ይገልጿቸዋል። \n\nተማሪዎቻቸው ከአንድ ክፍል ወደ ሌላ ክፍል ቢሸጋገሩም እርሳቸው የሚያስተምሩበትን አንደኛ ክፍል ላለመልቀቅ ሲሉ \" ምነው እንደ ሊቁ ያሬድ ሰባት ጊዜ በወደቅኩ\" ብለው ይመኛሉ አሉ። \n\nእኝህ ሰው ማን ናቸው?\n\nመምህር ሥዩም ቦጋለ የእንግሊዘኛ መምህር ሲሆኑ በ1998 ዓ.ም ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተመርቀው በመምህርነት እያገለገሉ ይገኛሉ።\n\nከበፊት ጀምሮም በቤተሰብ ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮችን የማየትና ለዚያም መፍትሔ የማፈላለግ ፍላጎት እንደነበራቸው ይናገራሉ። በእርግጥ የእርሳቸው አስተዳደግም የተንደላቀቀ ባለመሆኑ ለችግር ብዙም ሩቅ አይደሉም። \n\nእንዲህ ዓይነት የበጎ ሥራን ማከናወን የጀመሩት አባታቸው በ13 ዓመት እድሜያቸው በሞት ከተለዩ በኋላ ከእርሳቸው በታች ያሉ እህትና ወንድማቸውን የማስተማር ኃላፊነት ከተረከቡበት ጊዜ አንስቶ ነው።\n\n\"እነርሱን በሚፈለገው እውቀትና የሥነ ምግባር ደረጃ ለማብቃት የራሴን ሕይወት ከፍያለሁ፤ የልፋቴን ዋጋም በእነርሱ ማየት ችያለሁ\"ይላሉ። በአሁኑ ሰዓት ደካማ እናታቸውን እየረዱ ይኖራሉ። \n\nየቤት ውስጥ የሚባል ማንኛውንም ሥራ ያከናውናሉ። ምንም የሚቀራቸው የለም። ይሄው ልማድም ጎልብቶ ወደ ሙያቸው እንደመጣ ያስረዳሉ- መምህር ሥዩም።\n\n• የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ \n\nበሚያስተምሩበት አካባቢ ወላጆች እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ ለመቀስቀስ ጋራና ሸንተረሩን ያቋርጣሉ። ሰለቸኝ ደከመኝ አይሉም። ሠርግ፣ ለቅሶ፣ እድር ላይ የአገሬውን ሰው መስለው ይሳተፋሉ። የአገሬው ሰው ቢሆኑም ቀለም ቀምሻለሁ ብለው ግን እራሳቸውን አያመፃድቁም። \n\nከዚያም የማትለያቸውን ማስታወሻ ደብተር አውጥተው የሚሰሟቸውን ቤተሰባዊ ችግሮች እየጠየቁ ይመዘግባሉ። \"ሁሉም ሰው ችግራችንን ይጠይቀናል፤ ግን ከንፈር ከመምጠጥ ባለፈ መፍትሔ የሰጠን የለም\" የሚል ተደጋጋሚ መልስ ነው የሚያገኙት። \n\nአንድ ቀን አንዲት ተማሪ \"ልብሴ ቀዳዳ በመሆኑ፤ የተቀደደ ልብስ ለብሼ ትምህርት ቤት መምጣት አልፈልግም\" ስትል ትምህርት ቤት ላለመግባቷ መልስ የሰጠቻቸውን ያስታውሳሉ።\n\nበወቅቱ የሰሙት ነገር ከእንቅልፋቸው ያባንናቸው ነበር። ይህን ስሜታቸውን ለማስታገስ ቢያንስ ሁለት ተማሪ መርዳት እንዳለባቸው ከራሳቸው ጋር ተነጋግረው ወሰኑ። \n\nልብስ አሰፍተው፣ የትምህርት ቁሳቁስ በሚችሉት አሟሉላት። እርሷም አላሳፈረቻቸውም። ከክፍሏ ቀዳሚ በመሆን ትምህርቷን እንዳጠናቀቀችና እርሳቸው እንደሚሉት ይህች ልጅ በምህንድስና ተመርቃ ሥራ ላይ ትገኛለች።\n\nየእርሷ ለስኬት መብቃት \"ትውልድ እየቀጨጨና እየጠፋ ያለው በእኛ ምክንያት ነው\" ሲሉ ጣታቸውን ወደ የቀለም አባቶች እንዲቀስሩ ምክንያት ሆናቸው። ችግሩ ያለው ከትውልዱ ሳይሆን ከቀራፂው መሆኑን አመኑ። \n\nለዚሁ... ", "passage_id": "b366a4d305ab7479cdd947fb79ed0daa" }, { "passage": "በጎሮ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝቻለሁ። ሁሉም ተማሪዎች ቀልብን በሚስቡ፣ ሰማያዊና ሮዝ ቀለም ባላቸው ቦርሳዎቻቸው የትምህርት መሳሪያዎቻቸውን በጀርባቸው ተሸክመዋል። ቦርሳዎቹ ዘመናዊ የትምህርት ቁሳቁስ ፣የምሳ ዕቃ እና ሌሎችንም ይዟል። ይሄን ያገኙት ከትምህርት ቤታቸው በስጦታ ነው። የተደረገላችሁ ድጋፍ ምን ስሜት ፈጠረባችሁ ስል ጠጋ ብዬ ለአንዳንዶቹ ጥያቄዬን አቀረብኩላቸው። የሰባተኛ ክፍል ተማሪው መሀመድ ሲራጅ የመማሪያ ቁሳቁስ መያዣ ቦርሳ እና እስካሁን ያልነበረውን የትምህርት መገልገያ ቁሳቁስ በማግኘቱ እንደተደሰተ ይናገራል። እስካሁን በትምህርት በቆየባቸው ዓመታት ከቤተሰቡም ሆነ ከሌላ ቦታ ዘመናዊ ቦርሳ ተበርክቶለት እንደማያውቅ ይገልጻል፡፡‹‹ሁላችንም ተመሳሳይ ደረጃ ያላቸው ቦርሳዎች፣ የትምህርት ቁሳቁስ እንዲኖረን መደረጉና ዩኒፎርም አንድ አይነትና አዲስ መሆኑ ሌላ ወጪ ምንም ሳያሳስበን ወደ ትምህርታችን ብቻ እንድናተኩር ያደርገናል። ለጥሩ ውጤት እንድንተጋ ያግዘናል›› በማለት ዘንድሮ ለመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተደረገው ድጋፍ ለእርሱና ለጓደኞቹ ትርጉም ከፍ ያለ መሆኑን ያስረዳል፡፡ የአምስተኛ ክፍል ተማሪዋ ማርታ ሽመላሽ በበኩሏ፤ በትምህርት ቁሳቁስ ረገድ ሁሉ ነገር የተሟላላት በመሆኑ ስሜቷ በመልካም መንገድ እንደተቀየረ ትገልጻለች፡፡ በትምህርቷም ላይ በንቃት መሳተፍ እንደጀመረች ውጤቷም እየተሻሻለ መምጣቱን ታስረዳለች፡፡ የጎሮ መጀመሪያ ደረጃ\nትምህርት ቤት ርዕሰ\nመምህር አቶ በእደማሪያም\nሙሉጌታም ከአንደኛ እስከ\nስምንተኛ ክፍል ላሉት\nሁሉም ተማሪዎች የተበረከተላቸው\nዘመናዊ ቦርሳ፣ የትምህርት\nቁሳቁስ ድጋፉ የሲኤፍ\nፒኤ እና ሲጂሲኦሲ\nየሚባለው የቻይና ድርጅት\nመሆኑን ይናገራሉ። ይህ\nድጋፍ በአዲስ አበባ\nለተመረጡ 10 ትምህርት\nቤቶች የተደረገም እንደሆነ\nይገልፃሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል\nእርሳቸው የሚመሩት ትምህርት\nቤት የእድሉ ተጠቃሚ  መሆኑ እንዳስደሰታቸው አልሸሸጉም፡፡ ለአራት ሺህ ዘጠና ስድስት ተማሪዎች የድጋፉ ተጠቃሚ መሆናቸው ቤተሰብን ከማገዙ በተጨማሪ በትምህርት ጥራቱ ላይ የሚያሳርፈው አዎንታዊ ተጽዕኖ እንዳለም ይናገራሉ፡፡ በተለይም ከኢኮኖሚ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን ጫና እንደሚቀንስ ያስረዳሉ፡፡ በተማሪዎች መካከልም ጠንካራ የመተጋገዝና የውድድር ስሜት ይፈጥራል፡፡ ርዕሰ መምህሩ የተደረገው ድጋፍ በተለይ በቅርቡ የተጀመረውን የምገባ ስርዓት ቀልጣፋ እንዲሆን ማስቻሉን አንስተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በምግብ ማቅረቢያ ሳህን እጥረት የተነሳ ተማሪዎች ተራ ለመጠበቅ ይገደዱ ነበር ፡፡ ይህ ደግሞ የጊዜ መጓተት ይፈጥር ነበር። አሁን ሁሉም የየራሳቸው ምሳ እቃ ስላላቸው ተራ ሳይጠብቁ በእኩል የመመገብ እድል አግኝተዋል ብለዋል፡፡ በትምህርት ቤቱ የሚገኙና በቅድመ መደበኛ የሚማሩ 1ሺህ 169 ተማሪዎች የድጋፉ ተጠቃሚ አይደሉም ያሉት ርዕሰ መምህሩ እነዚህ ተማሪዎችም የድጋፉ አካል እንዲሆኑ እየሰሩ መሆኑን ይናገራሉ። እንደ መፍትሄም ማህበረሰቡንና የተለያዩ ባለሀብቶችን የማስተባበር ስራ እየተከናወነ ነው። ‹‹ብዙ መደገፍና መረዳት ያለባቸው ቤተሰቦች ለልጆቻቸው ሲሉ እየተጨነቁና እየለፉ ትምህርት ቤት ይልኳቸዋል። መንግስት የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉ ለወላጆች እፎይታን ሰጥቷል›› የሚሉት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አበበ ቸርነት ናቸው፡፡ ቤተሰብ ለልጆቹ ትምህርት የሚያወጣው ከፍተኛ ወጪ የደንብ ልብስ ሲሆን፤ ይሄ ሙሉ ለሙሉ በመንግስት እንዲሸፈን ተደርጓል፡፡ ከዚያ አልፎ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የተማሪዎች ቦርሳ እና የተለያየ የትምህርት መሳሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ እየተደረገ ነው፡፡ በዚህም ተማሪው ተስፋ ሲያገኝ ቤተሰብ እፎይ እያለ ነው፡፡ ድጋፉ በስሜት እንጂ በንግግር የሚገለጥ እንዳልሆነ የሚገልጹት አቶ አበበ፤ ለአስር ትምህርት ቤቶች 23 ሺህ ቦርሳ ከነሙሉ የመማሪያ ቁሳቁሱ መሰራጨቱን አንስተዋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 12/2012ጽጌረዳ ጫንያለው", "passage_id": "60ef88a43e65082c74a4917aff721f1c" }, { "passage": "ባደጉት አገራት የመማር ግቡ በጥሩ ድግስ ተመርቆ መጨረስ ሳይሆን በትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኘውን እውቀት ተገቢ በሆነ መልኩ አግኝቶ ስኬታማ መሆን ነው። በዚህ የተነሳ በነዚህ አገራት በምረቃ ወቅት ከሚደረገው ድግስ በምረቃ ወቅት ለሚደረገው የምርምርና የማጠቃለያ ሰርተፊኬት ትልቅ ትኩረት ይሰጣል። በተገላቢጦሽ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተማሪዎች የምርቃት ፕሮግራም ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል። \nበኢትዮጵያ በተማሪዎች መመረቂያ ሰሞን በየቤቱና በየመንደሩ ድንኳን ተተክሎ ከፍተኛ ድግስ ይዘወተራል። ይህም ተማሪዎች ከዩኒቪርሲቲ ትምህርታቸውን ጨርሰው የሚመረቁበትን መሠረት አድርጎ የሚከናወን ሲሆን፤ የምርቃት ሥነ ሥርዓቱና ፕሮግራሙ ግን የተጋነነና ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጣ ነው። ይህ ሁነት ልምድ ሆኖ በመቀጠሉ በዘንድሮው ዓመትም ተመራቂ ተማሪዎች የምርቃታቸውን ቀን በጉጉት እንዲጠብቁ አድርጎ ነበር። ይሁንና የመጨረሻዎቹ የትምህርት ምዕራፍ ላይ ኮሮና በመከሰቱ ትልማቸውን ለሌላ ጊዜ አሸጋግሮታል። \nየኮሮና ተህዋሲ ሥርጭትን ለመከላከል ኢትዮጵያ፣ እንደ አብዛኞቹ አገራት ሁሉ ትምህርት ቤቶችን ከዘጋች ሰንበትበት ብላለች። ወቅቱ በተለይ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ለነበሩ ተመራቂ ተማሪዎች ፈታኝ ነበር። \nፌቨን ለማ በደብረ ብርሃን የኒቨርሲቲ የሲቪል ምህንድስና አምስተኛ ዓመት ተመራቂ ተማሪ ናት። በትምህርቷ ከእርሷ በላይ መስዋዕትነት የከፈሉላትን ቤተሰቦቿ የምርቃት ጋወኑን ለብሳ ለማሳየት ሽር ጉዱን ተያይዛው ነበር። በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የመማር ማስተማር ሂደቱ ከተቋረጠ ወዲህ ግን በቤቷ ውስጥ ሆና በመምህራን የሚሰጠውን ትምህርት በበይነ መረብ እየተከታተለች ትገኛለች። የተሰጣትን የ“ፕሮጀክት” ሥራም ከቡድን አጋሮቿ ጋር በመከፋፈል በመሥራት ጊዜዋን እያሳለፈች ነው። ራሷን ከንባብ ጋርም አወዳጅታለች። \nበኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት መቋረጡ በዘንድሮው ዓመት ተመራቂ እንደመሆኗ ምቾት ባይሰጣትም ከጤና የሚበልጥ ነገር ባለመሆኑ ክስተቱን አምኖ ከመቀበል ውጭ አማራጭ እንደሌላት ተማሪ ፌቨን ትናገራለች። ወደ ቤቷ ከተመለሰች ጊዜ ጀምሮ ከቫይረሱ በመከላከል ረገድ ከቤት ወጥታ እንደማታውቅና ራስን ማግለል ለሌሎችም ድህነት መሆኑን ገልፃለች። ክስተቱ ተፈልጎ የተፈጠር ስላልሆነ ነገሮች ሲረጋጉ ትምህርቱም ምርቃቱም ይደረሳል ብላለች። \nየቫይረሱ ሥርጭት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መምጣቱ ሥጋት የፈጠረባት ተማሪ ፌቨን በአሁን ወቅት በተለይ ቤት ውስጥ ያሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቤተሰቦቻቸውንና ማህበረሰቡን በመጠበቅ ትልቅ ሚና እንዳለባቸው ጠቁማለች። ራሳቸውን ከወረርሽኙ መከላከልና ለሌሎች ሰዎችም ግንዛቤ በመፍጠር እንዲሁም ለድህረ ኮሮና ትምህርት ዝግጁ ሆነው ጊዜያቸውን በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባም አስገንዝባለች። \nበአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የአምስተኛ ዓመት የሜካኒካል ምህንድስና ተማሪ የሆነው ቢኒያም ወርቁ፤ ባልታሰበበት ወቅት ላይ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት በመከሰቱ ለጊዜው ትምህርቱን አቁሞ በቤቱ እንዲቆይ ሆኗል። ወቅቱ በተለይ ለምርቃት አፋፍ ላይ ደርሰው ለነበሩት ውስን ተማሪዎች የሥነ ልቦና ጫና ቢያሳድርም ለሰው ልጅ ቀዳሚውና አስፈላጊ ጉዳይ ጤና በመሆኑ የሆነውን ሁሉ መቀበል ግድ ሆኖበታል። ለዚሁ ሲባል የተወሰደውን እርምጃም በመቀበል ነገን አሻግሮ በተስፋ እየጠበቀ ይገኛል። \nተማሪ ቢኒያም ትምህርት የማቋረጥ ውሳኔ ከተላለፈ በኋላም ትምርህት ነክ የሆኑ መጻህፍትን በማንበብ ጊዜውን እያሳለፈ ይገኛል። ለመደበኛ ትምህርት አጋዥ የሆኑ መጻህፍትንና ጽሁፎችን መከታተሉ ደግሞ በቀጣይ ለሚኖረው የመጨረሻዎቹ የትምህርት ክፍለ ጊዜያት ለንድፈ ሀሳባዊ ትምህርቶች እንግዳ እንዳይሆንና የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንደሚያግዘውም ተናግሯል። \nለመመረቅ የሚያበቃ ዝግጅት እየተደረገ ባለበት ወቅት ትምህርት ማቆም ነገን በተስፋ ለሚጠብቅ ተማሪ የሞራል ስብራት ይፈጥራል የሚለው ተማሪ ቢኒያም፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ወደ ቤተሰብ መሸኘታቸው ተገቢ ቢሆንም፤ ለተማራቂ ተማሪዎች ትኩረት ተሰጥቶ እዚያው እንዲቆዩ ማድረግ አሊያም የተለየ ሁኔታ ፈጥሮ በዚሁ ዓመት እንዲመረቁ ማድረግ ያስፈልግ እንደነበርም ጠቁሟል።\nቢሆንም ጉዳዩ ከጤና ችግር ስለማይበልጥ ውሳኔውን ጠብቆ መፃኢውን ጊዜ መጠበቅ እንደሚበጅ ተናግሯል። ተማሪዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሳይሆኑ ቤተሰብን በመርዳትና ግንዛቤ የማስጨበት በጎ ሥራ ላይ ተሰማርተው ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉም መክሯል።\nበደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአምስተኛ ዓመት የሲቪል ምህንድስና ተመራቂ ተማሪ መቅደስ ሃይማኖት በበኩሏ፤ “በተቻለኝ መጠን ከቤት ላለመውጣት እና ለማጥናት እሞክራለሁ፤ ትምህርት ተቋርጦ ወደ ቤታችን ስንመለስ መፈፀም የሚጠበቅብንን ነገሮች ተነግሮን ነው የተመለስነው። ተመራቂ ተማሪዎች እንደመሆናችን መጠን ጥያቄ ሲኖረን ደግሞ መምህር እና አማካሪዎቻችንን በኢሜል እና በስልክ የማግኘት ዕድል አለን” ትላለች። \nየመመረቂያ ጽሁፍ በማዘጋጀት የምርቃታችንን ቀን እየቆጠርን በተስፋ ስንጠብቅ ነበር የምትለው ተማሪ መቅደስ፤ በወቅቱ ትምህርት ተቋርጦ ወደ ቤት ሂዱ ሲባሉ መከፋቷንና በጊዜ ሂደት የቫይረሱ ሥርጭት እየተስፋፋ መምጣቱ ደግሞ ውሳኔው ትክክል እንደነበር ተገንዝባለች። የትምህርት መረጃዎችን በተገቢው መንገድ በማግኘት ቀሪውን የትምህርት ጊዜ በስኬት ለማጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት እያደረገች መሆኗንም አስታውቃለች። \nተማሪዎቹ እንደሚሉት አሁን ትኩረት የሚሻው ከምረቃው ይልቅ ከፊታችን የተደቀነው በሽታ ነው። ይህንን በሽታ መከላከል ከተቻለ ከዚያ በኋላ ጥሩ ጊዜ ይመጣል። ይህ ደግሞ ከምረቃም በላይ የነገ ተስፋችንን የሚያለመልም በመሆኑ መከላከሉ ላይ ትኩረት ልንሰጥ ይገባል። \nየተማሪዎች የቀለም ወላጆች የሆኑ መምህራንም በዚህ ወቅት ለተማሪ ልጆቻቸው የሚሰጡት ውድ ጊዜና እውቀት ሊያጠናክሩ ይገባል።\nአዲስ ዘመን ሰኔ 5/2012አዲሱ ገረመው", "passage_id": "61d66285664dbaa277f73e487044c1ff" } ]
35922e9c5cdf76d2092268ba544e85c4
2c81c81cfb23db86bd5f82a05385e9a5
አራት ሺህ ሜትሩ “ቁርጥ”
 ወዳጄ ነገ ከቻልክ እንቅልፍ እንዳወስድህ። የሀገርህን ውብ ገፅታ፤ የህዝብህን ድንቅ ባህል ወጥተህ ታደም።ወዳጄ የቁርስ ጉዳይ አያሳስብህ የምትታደመው “እንካ ብላልኝ፤ በሞቴ ይህቺን ደህሞ ተረጎንጭልኝ” የሚል ህዝብ በደገሰው ድንቅ ባህል ነው። በባህሉ ባለሙያዎች በልዩ መልኩ የተዘጋጀ ቁርጥ ተዘጋጅቶልሀል።የኦሮሞ ጭኮ ማለት ንፁህ ቅቤ እየቆረጥክ መላፍ በለው።ይሄ ድንቅ የሆነ ማህበረሰብ “ናልኝ በሞቴ ብላ፤ ይህቺን ድገም” ብሎ ሊያጎርስህ ተዘጋጅቷል።“ቁርጡን” እየቆረጥክ በአይኖችህ አይጠገቤ የሆኑ የባህል ትርኢቶች፣ መዋደድን የሚሰብኩ ልዩ ልዩ ሁነቶችን አይተህ ትደመማለህ።አዎን ወዳጄ ነገ ሸገር ላይ የሚከበረውን ድንቅ ባህል፤ አዲስ ላይ የሚጥለቀለቀውን ማራኪ ውበት፤ ፊንፉኔ ላይ የሚታየውን ፍቅር ተቋደስ።ኢሬቻን በመታደም በብዙ ተጠቀም! ቀጣዩን አመት በጉጉት እንድትጠብቅ የሚያደርግህ የበዛ መደመም ይገጥምሀል።አብሮህ የሚኖረውን ማህበረሰብ ድንቅ እሴት፤ የእርስ በዕርስ መዋደድና ፍቅር ትመለከታለህ።እስርህ ሆኖ ያማታውቀውን አስደናቂ ማንነት፤ አብሮህ ሆኖ ያልተላመድከውን ልዩ ክስተት ኢሬቻ ላይ ታገኘዋለህ። የሀገርህን ድንቅ ውበት፤ የህዝብህን የማይነጥፍ ድንቅ ባህል፤ የወገንህን የ አብሮነት ጥምረት ትኮመኩማለህ። ወዳጄ ይሄን ጥሩ ገጠመኝ እንዳታልፍ፤ አብረህ ተቀላቅለህ የባህሉና የበዓሉ ባለቤት ሆነህ ፍቅርን ተላመድ።ድንቁን የሀገሬን ሰው በባህል ልብሱ አጌጦ፤ ለአምላኩ ምስጋናውን ሲያደርስ ተመልከት።ደግነቱን፣ ቀናነቱን፣ የአብሮ መኖር ጥልቅ ፍቅሩንና ህብረቱን የሚገልፅበትን ልዩ እሴቱን ታደም።በአመት አንዴ ኦሮሞ በሚያከብረውን ታላቅ የባህል መድረክ ላይ ተገኝተህ ከታላቅ ህዝብ ጋር ዋል። አይንህ በተመለከተው ነገር ላይ ሁሉ ይደመማል።የባህል አልባሳቱን አይቶ ያደንቃል፤ የማህበረሰቡን ልዩ ልዩ ትስስራዊ መገለጫዎችን አይቶ ይደመማል።አንተ ብቻ እዚያ ቦታ ተገኝተህ ወገንህን ለማየት ያብቃህ እንጂ የምትናፍቀው ልዩ ገጠመኝ ይጠብቅሀል።“ቁርጥ” ስልህ የአገሬ ሰው ጥርስህን የሚያደክም በትግል የምታኝከው አይደለም። እየሰለቀጥህ የምታሻምደው የቅቤ ልውስ እንጂ፤ ጣዕሙ ስታስበው ምራቅ የሚያስውጥ ቁርጥ ነው። ኢትዮጵያ ድንቅ ሀገር ናት። ህዝቦችዋም የተዋቡ፤ የዚህችን ውብ ሀገር አስደናቂ ባህሎችና ማራኪ ገፅታ አይኑን ገልጦ ላስተዋለው ልቡን ከፍቶ ላሰበ ያ’ጅባል። ከራስ አስከ እግሯ፤ ከፊት እስከ ጀርባዋ ላስተዋለ ይደመማል። ተነግሮ የማያልቅ ተዳስሶ የማይደረስ ባህልና ትውፊት ባለቤት ናት ሀገሬ፤ ኢሬቻም ከእነዚህ ሀገራዊ ድንቅ ባህላዊመገለጫዎች አንዱ ክብረ በዓል ነው።በጋው መሬቱን በፀሀዩ ሰነጣጥቆ አፈሩን እንደ ዱቄት ሊበትነው ሲቃረብ፤ ክረምቱ ደርሶ የተራበውን መሬት በዝናብ አርሶ፤ የደረቀውን መሬት ድጋሚ ህይወት ይዘራ ዘንድ፤ ድጋሚ ምድሩ ይለመልም ዘንድ ወቅቱን ይረከባል።ክረምት የህይወት መቀጠያ፤ የመኖር ዋስትና ውሀ መፍለቂያና የዝናም ምንጭ ነውና በብርቱ ይናፈቃል። በዚህ ወቅት ኦሮሞ ልዩ ባህል አለው።የክረምቱን መምጣት ተከትሎ የሚያከብረው አምላኩን በክረትም ከሚገኝ መልካም ነገር እነዲያጎናፅፈው የሚለምንበት በክረምት ከመጣ ክፋት እንዲጠብቀው የሚማፀንበት፤ ኢሬቻ ተፈጥሮን ገርቶ፣ ምድርን አለምልሞ፣ ጤናን ጠብቆ ሀገርን አንፆ ላቆመ አምላክ ምስጋና የሚቀርብበት ድንቅ የኦሮሞ ትውፊታዊ በዓል ነው።የኢሬቻ ፍልስፍናው የሰዎችን አንድነትና መጠናከር የሚሰብክ፤ ፍቅር፤ ሰላም የሚያፀና፤ አብሮ መኖርንና መተጋገዝን የሚነግር መሆኑ ተናፋቂ በዓል ያርገዋል።ነገ ይህንን ክብረ በዓል መዲናችን ልታስተናግድ ወገብዋን አስራ ለበዐሉ ስርዐት በመትጋት ላይ ትገኛለች።በዚህ ክብረ በዓል ላይ በመገኘት አንተነትህን ከፍ አድርግ፤ በዚህ የሚሊዮኖች ስበስብ ላይ ታድመህ ባህል የፋፋቴ ያህል ሻኣ…ብሎ ሲወርድ ሁሉንም ሲያረሰርስ ተመልከት። ባህል በራሱ የሚያንፀው የሚያቀናው ብዙ ጉዳይ አለ። ባህል የሚያወርሰው የበዛ ትርፍ መቋደስ የሚሰጠው ትልቅ ችሮታ ነው። የሌላ ’ምትለው አንድም ነገር የለም።መልካም ነገርን ሲመለከት የራስን ማድረግ መልካምነት ነው።“የአንተ ነው” ተብሎ የተሰጠህን ነገር “የእኔ አይደለም” ብሎ መግፋት ደግሞ ከባድ ጉዳይ፤ ነው፡፡ ኢሬቻ የሀገርህ ትሩፋት ከመሆን አልፎ የተባባሩት መንግስታት ደርጅት በዓለም ቅርስነት ሊመዘግበው ከጫፍ ላይ ደርሷል። አንተ የኔ አይደለም ብትል ይከብደብሀል። የአንዱን ባህል በሌላው መከበሩ፤ የአንዱ በጎ ነገር ሌላው ዘንድ ደርሶ በጎነት ማላበሱ፤ ፍቅርን መጨመሩ እጅጉን የሚወደድ ጉዳይ ነው።እኛ ኢትዮጵያዊያን ብዙነታችንን አክብርን፤ የእርስ በእርስ ትስስራችን አጠንክርን መሄድ ወደፊት መጓዝ እንዳለብን ስያንፅ ያቆየን ባህላችን አይደል? የሚያስውበን የሚያስተሳስረን ድንቅ እሴታችን አይደል? ድንቅ ባህላችንን ከፍ አድርገን በጋራ ከፍታ ላይ እንድንደርስ መንገድ ሊሆነን የሚችል ብዙ ትሩፋት አለን።በዚያ ማትረፍን እንጂ መጉደልን እንዴት ልናስበው እንች ላለን? ባህል በማህበረሰብ የረጅም ጊዜ ልምድ የሚዳብር የማህበረሰቡ መገለጫ ነው።ያንን ባህል ተወልዶ፤ በዚያው ተኮትኩቶ አድጎ የፈጠረውን በጎ ተፅዕኖ ለሌላው የሚተርፍ አገር አቅኚ ከሆነ ያ ባህል መልካምነቱ አይካድም።የሚሰጠው ጥቅምና የበዛ ትርፍ ባትራፊው የኔ ነው ባይነት ላይ ይወሰናል።በጎ ነገርን የጋራ ማድረግ ከጋራ የከበደ ብልጠት፤ ከመውደድ ከፍ ያለ መጋመድ ይፈጥራል። አዎን፤ የሀገሬ ልጆች! እኛ ኢትዮጵያውያን የችግሮቻችን መፍትሄ ያለው በእኛው እጅ ላይ ነው። ተቀራርበን እንነጋገር፣ እንግባባ እንደራደር።የሚለያየን ነገር ይቀረፋል፤ ልዩነታችን የሰፋ ቢሆን እንኳን ተቀብለን አንደኛችን የሌላውን አክብረን በልዩነት ውስጥ በፍቅር እናድራለን። አንድ አመለካከት ሀገርን ቀይሮ አያውቅም።አንድነት ፍቅርና ህብረት እንጂ፤ የኢሬቻን የአንድነት ጥሪ አብሮ የመቆምን ባህል አብረን በማክበር አብረን በማስዋብ እናፅናው።ያ ነው ኢትዮጵያዊነት! የተሟላ፤ እርስ በርስ የሚያስተሳስር ሙሉ የሆነ ውብ ባህል አለን።የጎደለው የሚሞላው ያለውን በማጉደል አይደለም። ሀገር የሚለወጠው በሰፊ ሀሳብ ነው። ሀገር ማለት የክብርህ መጎናፀፈያ፤ የችግርህ መከለያ ጥላ ናት። ለራሳችን ብለን ሀገራችንን እንውደድ! ለሀገራችን በጎ እንመኝ።የህዝቦችዋን መቀራረብ የሚያጠናክር መንገድ መፈለግ የሚያለያይ ከመፈለግ እጅጉን ይቀላል ወዳጄ።በህብረት ውስጥ የምታገኘው በጎ ተግባር ውጤቱ የጭኮ ያህል ይጥ ማል።በአብሮነት ከቆምን፤ የእርስ በርስ ፍቅራችን ከደረጀ እመነኝ ያኔ ከፍታ ላይ እንገኛለን። ከፍታ ላይ የሚያደርሰው ደግሞ ፍቅር ብቻ ነው። አብሮነታችን በአብሮነት የታነፀ ውብ ጉዳይ ነው።“የእነሱ” የምንለው ምንም ነገር የለም። የኛ፤ የጋራችን፤ የሁላችን የምንለው የበዛ ነገር አስተሳስሮናል።የእጆችህን ጣቶች እያቸው ወዳጄ የተለያየ ቅርፅ፤ የራሳቸው ቁመትና ተግባር አላቸው። አንድ ላይ ሆነው ግን የተቃና ተግባር ይከውኑልሀል።ይሄ ትልቅ ሚስጥር ነው ወዳጄ፤ በጥልቀት ከተረዳኸው ብዙ የሚነግር፤ ባህሏን በመጠበቅ የእርስ በርስ ግንኙነታችንን በማጠናከር “ሀገሬ ክብሬ” የምንላትን ሀገር እንገንባ። ትውልድን ፍቅር በማስተማር በባህሉ የታነፀ፤ የሀገር ፍቅር የገባው፤ የህዝብ ጥቅም የሚያስቀድም ቀና እናድርግ። ለትውልዱ ሳናቋርጥ ፍቅርን መስበክ እንልመድ።በፍቅር የታነፀ ሀገሩን የሚወድ ትውልድ መግሪያው ይህ መንገድ ብቻ ነውና፤ በፍቅር ጥላ ስር ተቻችሎ ማደርና ተባብሮ ማደግ ደስታና ሀሴት ለሁሉም ይዳረሳል። በፍቅር የተጋሩት የከፋ ነገር እንኳን የለዘበ ክፉ ነው እንጂ ፅልመት የለውም። ታደም ያልኩህ የኢሬቻ በዓል የተዋበ ባህሉን ከየአቅጣጫው አቅርቦ የሚያስኮመኩምህ ደጉ ወገኔ ውበቱንና ፍቅሩን እንድታይበት ነው።በፍቅር ደግፎ የዛሬ መገኛህ ላይ ያደረሰንህ ውብ ባህል እድትመለከት አብረህም እንደትቋደስ መፈለጌ ነው ውትወታዬ፤ የሀገርህን ውብ ባህል አውቀህ ለሌላው መተረክ ትችል ዘንድ የማህበረሰብህን ባህል፤ የወገንህ ክብረ በዓል በማስጌጥ አብረህ ዋል። የበዛ ክብረ በዓልና ባህል የታደለች ሀገር ላይ መፈጠር በራሱ ትልቅ እድል ነው ያልኩህም በዚሁ ምክንያት ነው።የተዋበ ነገር ለመዋዋስ፤ የተጓደለን ለመሙላት በብዙ ልዩነት ውስጥ በተጋመደ አንድነት ማለፍ ትልቅ ጥቅም አለው።የራቀን ነገር እኳን አቅርቦ የኔነት ስሜት መፍጠር መልመድ በጎ ነው። ይሄ ግን የቅርብ ቅርብህ ነው። የራስህ፤ አንድነት ላይ ቆሞ ስለ አንድ ሀገር ማሰብ የላቀ ምጥቀት ነው።ቀለመ ብዙ፤ ባህለ ስብጥር መሆን መልካም ነው። የዚህችን ሀገር ተዓምራዊነት ለመረዳት ተዓምረኛ ወይም የመጠቅህ መሆን አይጠበቅብህም ወዳጄ፤ ውበት ሞልቶ የሚፈስባት፤ የተዋበ ባህል ያለት ለመሆኑ በጓዳህ ያሉትን፤ በስርህ ያሉትን ባህልና እሴቶችዋን ተመልከት።የሀገሪቱ ውበት መገለጫ የሆኑ ልጆችዋ የየራሳቸው ልዩ ባህል ስያንፀባርቁ ተመልክተህ ብዙ ትማራለህ። በህብረት የቆሙት ልጆቿ የየራሳቸው መልካም እሴት ተላብሰው፤ ባህልና ማንነታቸውን በተለየየ መልኩ በመግለፅና በአንድነት ቆመው የሚያስጌጧ ውብ ሀገር መሆኗን ለመስከር ባህላዊ ክብረ በዓላቸውን መታደም በቂ ነው። እዚህች ሀገር ላይ መፈጠርህን በራሱ ትልቅ አድል ነው ያልኩህ የሚገባህ ሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ድንቅ ነገር ስትረዳ ነው።ተዟዙረህ የምታየው በረከት የተትረፈረፈ ሆኖ ታገኘዋለህ።እርግጥ ሀገሪቱ ያላት የበዛ በረከት ልጆች ተረድተው መጠቀሙ ላይ ገና ብዙ ቢቀራቸውም፤ የበዛው ሀብትቷ ግን ሳይነኩትም ብዙ መሆኑ ያስታውቃል።የሰጡትን አጥፎ የሚመልሰው፤ የዘሩበት አለምልሞ የሚያበቅለው ለሙ መሬት ጠረኑ ይናፍቃል። ይሄንን የምትረዳው ስትርቅ ነው ወዳጄ፡፤ የሀገር ፍቅር እና ክብር ማጣጣም የሚቻለው ከጉያዋ ሲርቁ ነው።ሀገር ጥላ ነው፤ የክፉ ቀን መሸሸጊያ፤ ባህል ደግሞ የማህበረሰብ መገለጫ፤ ባህላችንን በበጎ ተጠቅምን የጋራ መቆሚያ አውድ ማድረጉ የእኛ የምንለው ነገር እንዲበዛ ያደርግልናል።ቸር ይግጠመን!አዲስ ዘመን መስከረም 23/2012ተገኝ ብሩ
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=19977
[ { "passage": "ሱራ ሽቅብ ሽቅብ ያቃስታል። ግዝፈቱ ያስጨንቀዋል። ልብስ አይበቃውም። የጫማው ቁጥር 48 ነው። የትከሻው ስፋት የሰውነቱ ግዝፈት የቁመቱ ርዝመት የሰማይ ስባሪ አስመስለውታል። አባ ግድየለሽ ሱራ ወግ ጨዋታ ይወዳል። ሰው አያስቀይምም። ውፍረቱ አስፈሪ አስደንጋጭ ነው።የሰፈሩ ሰው ልጆች\nሲያለቅሱና ሲረብሹ ዋ ሱራን ነው የምንጠራው ሲባሉ ያውቁታልና በፍርሀት ርደው ጭጭ ነው የሚሉት። ሲደሰትም ሲከፋም ሱራ የአላህ\nልጅ፤ የአላህ ወዳጅ የሚለው ነገር አለው። ለወላጆች ምነው ምነው ሕጻናቱ እንዲጠሉኝ እንዲፈሩኝ ባታደርጉ ምን አደረኳችሁ ይላል\n– ሱራ። በዛ ቁመቱና ውፍረቱ\nሲንጎማለል ሲታይ የሞላለት ቱጃር ይመስላል። ጫማ ሰፊው ሱራ በቀን ሰርቶ ከሚያገኘው ውጭ ምንም የለውም። እጁ ሲያጥር ደምበኞቹ\nከሆኑት ሴቶች ይበደራል። የድሀ ገንዘብ አታድርገኝ ይላሉ – እማማ ጌጤ። ከቀናት በኋላ ሴቶቹ\nከች ይሉና ብር መልስ ይሉታል። አንተ ሱራ ስማ እንጂ የተበደርከውን አታመጣም፤ አላበዛኸውም እንዴ እያሉ ሴቶቹ ወገባቸውን ሲነቀንቁበት\nይጨነቃል። ሂጂ እዛው ምን ወገብሽን ትሰብቂያለሽ ይላል ሱራ፤ ሶርሷራው። ተናገር ምንድነው ሂጂ እዛው አንተ አይደለህም እንዴ ስንቱን\n… ይሉታል። ኧረ በሕግ አምላክ ስሜን አታጥፉ አልደረስኩባችሁም ይላል እንደ ማፈር ብሎ።ጫማው መስፊያ ጎን\nያሉት እማማ ጌጤ ይቺ ሙጢ አሁን እውነት ሱራ ቢጠጋት ትተርፋለች፤ ሹል አፍ ሙጢ እንደው መቀላመድ ትወዳለች ልጄ አሉና አጉተመተሙ።\nየመንደሩ ሴቶቹ የተቦተረፈ ጫማቸውን ይዘው ስፋልን እያሉ የሚወስዱት ለሱራ ነው። ብዙ የሴት ወዳጆች አሉት። አንዳንዶቹ የሚበላው\nቋጠር አድርገው ያመጡለታል። አላህ እናንተን ባይጥልልኝ ኖሮ ምን እሆን ነበር ይላል ሱራ። ሱራ የሰማይ ስባሪው ሲሉት እናንተ ኮስማኖች\nበልታችሁ አይጠጋችሁ፤ ነገር ስትበሉ ውላችሁ ታድራላችሁ ፤ታዲያ ሱራ ምን ያድርጋችሁ ይላል። መኖሪያ ቤቱ የቀበሌ ቤት ነች። ግን ማንንም\nአያስገባም። ቤት ውሰደን ሱራ ሲሉት ደሞ ምን ቀራችሁ፤ ከእኔ ቤት ምን ጉዳይ አላችሁ ይላል። ቤት እየመጡ እሱ ሲሰራ እየተቀመጡ\nበዚህ መዘዝ ድሮ ምን እንደመጣበት ሱራ ሲያስታውሰው ይዘገንነዋል። ራሱ አብስሎ ይመገባል። አንዳንዴ በጎርናና ድምጹ ያንጎራጉራል።\nሱራ የአላህ ወዳጅ… የአላህ ልጅ እያለ። ተናግረው ሊያናግሩት ሲነካኩት አሁን ከእኔ ምን ታገኛላችሁ ተውኝ ስራ የላችሁም ይላል።\nጫማ መስፋቱን ይቀጥላል። ይህን ዝምታ የወረሰው በደርግ ዘመን ከደረሰበት ችግር በመነሳት ነው። በማያውቀው ነገር ሊሞት ነበር።\nጫማ የሚሰፋባት አንዲት ክፍል የኪራይ ቤት ነበረችው። ከበውት የሚውሉ የሚያመሹም ነበሩ።ፖለቲካ አይወድም። እሱ ጋ የሚገቡና የሚወጡት\nወጣቶች በዛን ዘመን ኢህአፓዎች ነበሩ። ወረቀት የሚበትኑ፤ ግድግዳ ላይ ቀለም የሚቀቡ፤ በቀይ ቀለምና በቀይ ጨርቅ ሀገሩን የሚያሸበርቁ።\nበፌስታል አምጥተው ሱራ የማያውቀውን እቃ ወረቀት ምናምን አመጣን ሱራየ ይቺ እዚህ ጋ ትቀመጥ ሲሉት ሱራ በመጡ ሰአት ተመልሰው\nይወስዱታል እያለ ጫማውን መስፋት ይቀጥላል። የሚያውቀው ነገር የለውም ምስኪኑ ሱራ። እቃቸውን አይነካም። ተጠራጥሮም አይሸፍንም።\nበል ሲለው ያንጎራጉራል። ሱራ የአላህ ወዳጅ የአላህ ልጅ የምትለዋ ቃል ከአፉ አትጠፋም። በዚህ ይታወቃል። ጊዜው 1969ዓ.ም ነው። አዲስ አበባ መርካቶ\nአካባቢ። ሀገር ምድሩ ታምሷል። አንድ ቀን ቀበሌው የኢሕአፓ ወጣቶችን እያሳደደ ማሰር ሲጀምር እንዴ እነሱማ ተሰብስበው የሚውሉት\nሱራ ጫማ ሰፊው ቤት ነው የሚል ጥቆማ አብዮት ጠባቂዎች ይሰጣሉ። ይታሰር ተብሎ ጠመንጃ ተሸክመው ሱራ ጋ ይሄዳሉ። ሱራ አይሞቀው\nአይበርደው አባ ግዴለሽ። እንደውም ቤቱ ይከበብ ተብሎ ከውጭ ብዙ ጥበቃዎች ይከቡታል። ሱራ ጫማውን አቀርቅሮ ይሰፋል። መሳሪያ ደግነው\nዘው ብለው ገቡ። እጅ ወደ ላይ አሉት። ሱራ የአላህ ወዳጅ አለና ጠመንጃው ምን ያደርጋል ለአንድ ድሀ ጫማ ሰፊ የእኔ እጅ ስራ\nይዟል ለምንድነው እጄን ወደላይ የማደርገው በእንጀራዬ ለምን መጣችሁ ይላቸዋል። ና ውጣ አንተ ኢህአፓ አሉት። ሱራ መለሰ ምንድነው\nኢሕአፓ አላቸው። እሱንማ አንተ ታውቃለህ በደምብ ትመልሳለህ አሁን እስረኛ ነህ ና ውጣ ቀበሌ እንሂድ አሉት። ተውኝ ቢል ማን ሰምቶት።\nእያመረሩ ሄዱ። ሌሎች ሱራ ቀበሌ ሂድላቸውና ቃልህን ስጥ ምን ትሆናለህ አሉት። ሱቁን ቆለፈና በብዙ አብዮት ጠባቂዎች ታጅቦ የሠማይ\nስባሪው ሱራ ቀበሌ ጽህፈት ቤት ገባ። ግቢው ውስጥ እሱ ጋ ገባ ወጣ ከሚሉት ወጣቶች ውስጥ የታሰሩ እንዳሉ አየ። ጮክ አለና ምን\nሰርቃችሁ ነው የተያዛችሁት አላቸው። አብዮት ጥበቃዎቹም ወጣቶቹም ሳቁ። ሱራ ለምርመራ ገባ። ጠያቂዎቹን ያውቃቸዋል። የጫማ ደምበኞቹ\nናቸው። ጫማቸው ሲቀደድ የሚሰፋላቸው።ሱራ አንተም አሉት። ተገረመና ምን አላቸው።\nኢህአፓ አሉት። ምንድነው የምትሉት እሱን ሰውየ አላውቀውም። ቅድምም አብዮት ጥበቃዎቹ እንደሱ አሉኝ። የእኔ የጫማ ደምበኛ አይደለም።\nአሰርቶ አያውቅም። እኔም አላውቀውም አላቸው። ሱራ የአላህ ወዳጅ የአላህ ልጅ አለ ሰው በተሰበሰበበት። እስኪጣራ ታስረህ ትቆያለህ አሉት። ክፉኛ አዘነ።\nአላህ እንደ ስራየ ይስጠኝ፤ በተንኮል ለወነጀሉኝም ፍርዱን ይስጥ አለ- ደገመና። እስር ቤቷ ውስጥ ግዙፉ ሱራ አንገቱን አዝምሞ\nገባ። ታሳሪው በተጨናነቀው ቤት ውስጥ ለሱራ ተጣበው ቦታ ሰጡት። ግድግዳውን ደገፍ ብሎ እንደቆየ ድብን አድርጎ እንቅልፍ ወሰደው።\nማንኮራፋት ጀመረ።ቢጠሩት መች ሰምቶ። ለሊቱን እነዛን ልጆች\nወደማይታወቅ ስፍራ ወስደዋቸዋል። ሲነቃ ልጆቹ የሉም። የሰፈሩ ሰው ሱራ ቀበሌ መታሰሩን ሲሰማ በእጅጉ አዘነ። ከፊሉ አሽሟጠጠ።\nደሞ ሱራ ብሎ ፖለቲከኛ እያለ። ጠጅ ቤት መነጋገሪያ ሆነ። ሱራ ታሰረ— ሱራ ታሰረ — ባዩ በዛ። የሰፈሩ ሰው ጫማ የሚሰፋላቸው\nሴቶች እየተጋገዙ ምግብ ያቀብሉት ጀመር። ቀለብ የማያገኙት እስረኞች ረሀባቸው ጠፋ። ሱራ ሱራ አሉት አቤት አላቸው። እንኳን ታሰርክ\nእንዲያውም መውጣት የለብህም አሉት። ተንከትክቶ ሳቀ። አንተ በመታሰርህ እስር ቤቱ ምግብ በምግብ ሆነ ሲሉት ቀበል አደረገና እኔ\nፖለቲካ አላውቅም። ጫማ ሰፊ ነኝ። እኔን በሀሰት በወነጀሉኝ ሰዎች ላይ አላህ ፍርድ ይስጥ፤ ሱራ የአላህ ወዳጅ የአላህ ባሪያ አለና\nአይኖቹ በእምባ ተሞሉ። አይዞህ ሱራ አሉት። አይዞህ አይዞህ ሱራ። ለሊት በቀበሌያቸው አካባቢና ዙሪያ የቀለጠ ተኩስ\nተሰማ። እስረኞቹ በተኙበት ይሰማሉ። ሱራ አላህ –አላህ ይላል። የመትረየሱ ድምጽ ተረረረረረም ሲል ሱራ አላህ ድረስ፤ የታሰሩት\nልጆች አውጣን አውጣን ሆነ። አይነጋ የለም በጭንቅ ነጋ። ጠዋት ለሽንት ሊወጡ ሲሉ ሱራ ነበር የቀደመው። ያገኛቸውን ሰዎች ምንድነው\nጉዱ አላቸው። መጥተው ፈጅተውን ሄዱ፤ አመለጡ አሉት። እነማን ናቸው አላቸው – ሱራ። ኢህአፓዎቹ ናቸዋ አሉት። ሰው ተጎዳ ብሎ\nጠየቀ። ምን ሰው ተረፈ ብለህ ነው። በቀደም አንተን ከሱቅህ አስረው ያመጡህ በሙሉ ሞተዋል አሉት። ምን አለ ሱራ ደንግጦ። ደገመና\nሱራ የአላህ ወዳጅ የአላህ ልጅ። እቺ ኢህአፓ የምትሏት አላህ ነች እንዴ አለ ሱራ። ሰዎቹ በሳቅ አሽካኩ። ሱራ ሱራ።ወንድወሰን መኮንንአዲስ ዘመን የካቲት 19/2012", "passage_id": "45ce0bb182143b58cebebdfdf922ef5d" }, { "passage": "እኛ ኢትዮጵያውያን ለጊዜ ያለን አመለካከት እና ከልባችን ምት እኩል የሚጓዘው የጊዜ ቀመር ፍሰቱ ለየቅል በመሆኑ ይህው በየዕለቱ “…የሀበሻ ቀጠሮ…” እያልን እንተርታለን። ከተረት ያለፈ መሻሻል ብናሳይም ባናሳይም፤ ለውድ ጊዜ ዋጋ ብንሰጥም ባንሰጥም፤ ጊዜ የለኝም በሚል የውሸት ብንጨናነቅም ባንጨናነቅም፤ ብንተርትም ባንተርትም ጊዜ እንደሁ ያው ጊዜ ነውና ላፍታ እንኳ ሳይዘናጋ ይነጉዳል። እኛም ከጊዜው እኩል ያለምንም እረፍት\nአንዳንዴም በብዙ እረፍት ውስጥ ሆነን “ቢዚ ነኝ” በሚል ፈሊጥ ተሸብበን አለን። በእርግጥ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለምናባክናቸው\nሽርፍራፊ ሰኮንዶች፣ ደቂቃዎች፣ ሰዓታት፣ ቀናት፣ ሳምንታት፣ ወራትና ዓመታት ለምን ብለን አንጠይቅም። ብንጠይቅም ብዙ ሺህ ውጫዊና\nበጣም ጥቂት ደግሞ ውስጣዊ ምክንያቶችን መደርደር እንችላለን። ይሁንና ምክንያቶቹ ያለፈውን ውድ ጊዜ አይመልሱልንም። እኛም ባለፈው\nጊዜ ስንቆጭ አንታይም። ሌላው ቀርቶ የቀጠሮ ሰዓታችንን ባለማክበር\nላጠፋነው የሌሎች ሰዎችን ጊዜ እንኳን ይቅርታ አንጠይቅም። ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ ያው እንደተለመደው የትራንስፖርት እጥረቱን፣\nየመንገድ መዘጋጋቱን፣ የአስፓልቱን መቆፋፈርና መሰል የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ ምክንያቶችን በማከታተል የተለመደ አይደል “የሀበሻ\nቀጠሮ እኮ ነው…” እያልን እንተርታለን። እኔ እምለው ተረት ባይኖር ግን እኛ\nኢትዮጵያውያን እንዴት እንሆን እንደነበር አስባችሁታል?… ነገራችን ሁሉ እኮ የሚደምቀው በተረትና ምሳሌያዊ አነጋገራችን ነው።\nእስኪ አስቡት ሲቸግረንም፣ ሲከፋንም፣ ሲደላንም፣ መንግስት ቢቀያየርም፣ ለውጥ ቢመጣም ባይመጣም፣ ለውጡ ቢቀጥልም ቢደናቀፍም የምንተርተው\nተረት አናጣም። ባስ ካለም በግልፅ ማስተላለፍ ያልፈለግነውን ጉዳይ በሙዚቀኞቻችን አማካኝነት በዜማ እንለዋለን። ትንሽ ግር እና ግርም የሚለኝ ግን ተረቶቻችን ሁሉ “…አለ” አማራ ሲተርት በሚለው ማሰሪያ አንቀፅ\nመቋጨቱ ነው። እውነት ግን ተረትን ለአማራ ብቻ የሰጠው ማን ይሆን?…እውነት እንነጋገርና ተረትን የተረተው አማራ ብቻ ነው?…\n“ይህማ ምን ጥያቄ አለው አዎና” አላችሁ… ካላችሁ እሺ ተስማምቻለሁ። መስማማቴ እንዳለ ይሁንና ስለዚህ ስለተረት ነገር በሌላ ጊዜ\nእንድመለስበት ቀጠሮ ልያዝና ልቀጥል፤ጉዳያችንስ ቢሆን ቀጠሮ እና የጊዜ አጠቃቀማችንም አይደል… አዎ አብዛኞቻችን ለጊዜ የምንሰጠው ዋጋ\nእጅግ የወረደ እና የሳሳ ከመሆኑም በላይ የተለያዩ ተግባራትን በተገቢው ጊዜ ባለመከወናችን ዋጋ እንከፍላለን። በአብዛኛው አገልግሎት\nፈልገን በሄድንበት ሁሉ በጊዜው የሆነ ፈጣን ምላሽ አናገኝም። ይህ ደግሞ “ያለወቅቱ የዘነበ ዝናብ ለጥፋት እንደሆነ ሁሉ በጊዜውና\nበሰዓቱ ያልተሰጠ ምላሽም ረብ የለሽ ይሆናል።እናላችሁ አሁን አሁን አየሩን የያዘው የለውጥ ሽታ ሽታ ብቻ ሆኖ እንዳይቀር ሁላችንም የበኩላችንን\nለመወጣት የተለመደውን የአበሻ ቀጠሮ ትተን የፈረንጁን ብንይዝ ምን ይለናል… ምክንያቱም በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚሰጡት\nአገልግሎት እጅግ የዘገየ ከመሆኑም በላይ እርካታን የማይፈጥር እና ባለጉዳዩን የሚያንገላታ ነው። እኔ የምላችሁ…“ደንበኛ ክቡር\nነው” የሚለው አባባል ከአባባልነት አልፎ ተግባር ላይ የሚውለው መቼ እና የት ይሆን…አሁን አሁንማ ከህዝብ ቁጥሩ በላይ በዝተው የተትረፈረፉ እጅግ በርካታ ጉዳዮች ያሉ ይመስል በየቀበሌው\nተኮልኩለው ጠዋት ብርዱን ቀን ፀሐይና አቧራውን እየጠጡ ኃላፊን እና የኃላፊዎችን ውሳኔ የሚጠባበቁ ዜጎች አሉ። ታዲያ እነዚሁ ዜጎች\nጉዳያቸውን ለማስፈፀም በሄዱበት ሁሉ ከጉዳዩ የገዘፈ ቀጠሮ ተሸክመው ይመለሳሉ። ቀን ቆጥረው ቀጠሮ አክብረው ሳይታክቱ ወደ ጉዳያቸው ቢጓዙም አለቃ የለም። ፀሐፊዋ ስትጠየቅ መልስ\nአትሰጥም። ብትሰጥም ዘንቦ አባርቆ ካባራ በኋላ “ዛሬ አይገቡም ነገ ከነገ ወዲያ ተመለሱ” በማለት ተራዋን ሌላ ቀጠሮ ትሰጣለች።\nመድረስ አይቀርም የፀሐፊዋ ቀጠሮም ይደርስና ጉዳዬ ቢሳካ ብለው አሁንም ይጓዛሉ፤ ይመላለሳሉ ዳሩ ምን ዋጋ አለው፤ እንደተለመደው\nአለቃው የሉም ስብሰባ ናቸው ይባላል። አለፍ ካለም ኃላፊው ቦታውን ለቀዋል ይባሉና እርፍ። ይሄኔ ነገሩ ሁሉ ከዜሮ ይጀምርና ጉዳዮ\nእንደ አዲስ መታየት ይጀምራል። ታዲያ እንደዚህ አይነቱ ውጣ ውረድ ህብረተሰቡን ከማማረር አልፎ ተስፋ እንዲቆርጥና መንግስት ላይ\nያለውን እምነት እንዲሸረሽር ያደርገዋል። ከዚህም ባለፈ እዚህም እዚያም የሚነሱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ወቅታዊና\nፈጣን ምላሽ ካለመስጠት ጋር ተያይዞ የሚሰጠው የበዛ ቀጠሮ ነው። ይህ ደግሞ ህገወጥ የሆኑ ተግባራት ጭምር ህጋዊ የሆኑ ያስመስላል።\nህጋዊ የሚመስሉ ህገ ወጥ ተግባራትን ስርዓት ለማስያዝ እና እርምጃ ለመውሰድም ዘግይተን እንነሳለን። በዚህም “ጅብ ካለፈ ውሻ ይጮሃል”\nነውና ነገሩ ለብዙ ጉዳዮች ከዘገየነው በላይ በብዙ እጥፍ የሕይወት፣ የንብረትና የታሪክ ዋጋ ከፍለናል እየከፈልንም ነው። እንግዲህ ሕይወት አጭር አንደመሆኗ ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም፤ ብንችል ከዘመኑ መፍጠን አልያም ከጊዜ\nጋር እግር በእግር ተከታትለን በመጓዝ ሁሉን በጊዜውና በሰዓቱ ልንከውን ይገባል። ካልሆነ ግን መሽቶ በነጋ ቁጥር የምናጠፋው ጊዜ\nእና የምንሰጠው የበዛ ቀጠሮ በኢኮኖሚያችንም ሆነ በማህበራዊ ሕይወታችን ትልቅ ዋጋ ያስከፍለናል።ከዚህም በላይ በዓለማችን በየዕለቱ የምንመለከታቸውና የምንሰማቸው አዳዲስ ነገሮች አንዱ በአንዱ ላይ\nተነባብሮ ከአቅማችን በላይ ይሆኑና ከጫወታ ውጭ ያደርጉናል። ይህ ደግሞ ድምፃዊቷ እንዳዜመችው “አልበዛም ወይ ድንዛዜው ቴክኖሎጂው\nበላይ በላይ…” ይሆንና ነገሩ በተሻለ ጊዜ የተሻለና የቀለጠፈ ስራ ካልሰራን እንዲሁም ከዘመነው ዘመን ጋር ካልተፎካከርን ነገሩ\nሁሉ “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” ይሆንና የምንመኘው ለውጥ እንደናፈቀን ይቀራል።ታዲያ ለዚህ\nሁሉ መፍትሔው ጊዜን በአግባቡ ከመጠቀም ባለፈ ከአገልጋይነት ስሜት በመነጨ መልካምነትና አንድነትን በማጣመር በተሰማራንበት ስራ\nሁሉ ውጤታማ ለመሆን መውተርተር የግድ ይለናል። በመጨረሻም ዘመን ተሻጋሪ በሆኑት ስራዎቹ የሚታወቀው አንጋፋው ድምፃዊ ዶክተር ጥላሁን\nገሰሰ ስለቀጠሮ ባዜመው ዜማ ልሰናበት “አርቆ ማሰቢያ እያለን አዕምሮ እንደምን ተሳነን ለማክበር ቀጠሮ”አዲስ ዘመን የካቲት 2/2012 ፍሬህይወት አወቀ", "passage_id": "e315b14a6cf015cc809e642fcc81f511" }, { "passage": "ድንገት\nእግር ከጣለኝ አንድ ስፍራ በተገኘሁበት፤ ከልጅነቴ ጀምሮ ስሰማው የኖርኩትንና አድጌም ትዝታው ያለቀቀኝን ዘፋኝ በአካል አገኘሁት። እጅግ\nከመደሰቴ የተነሳ ዝለል ዝለል ነበር ያለኝ (እንደ ልጅነቴ)። ተማር ልጄ፣ አዲስ አበባ ቤቴ፣… የማደንቀው አቀንቃኝ አለማየሁ እሸቴ፤ የምወዳቸው ዘፈኖች ናቸው። ታዲያ የምወደውን ሰው ሳገኝ አጋጣሚውን ተጠቅሜ በትንሿ የእጅ ስልኬ ምስላችንን አስቀረሁ። ለዘመን ምስጋና ይድረሰውና የሚወዱትን፣ የሚያደንቁትን ሰውም ሆነ የትኛውንም ነገር ከስልካችን ማከማቸት አስችሎናል። አለማየሁ እሸቴን ልጅ እያለው አባቴ የሚዘፍንበት ቦታ ድረስ ወስዶኝ አይቸው ነበር። ግን ፎቶ ለመነሳት አልቻኩም፤ ምክንያቱም በጊዜው የፎቶ ካሜራ የሚገኘው ፎቶ ቤት አሊያም አንበሳ ግቢ ነበር። ገጠመኜ ልጅነቴን፤ ልጅነቴም ሌሎች ትውስታዎቼን አከታተለብኝ እኮ(ነገርን ነገር ያነሳዋል አይደል የሚባለው)።አንበሳ ግቢም ብዙ ትዝታዎች አሉኝ፤ እንዲያውም የሚበዙት የልጅነቴ ፎቶዎች እዚያ የተነሱ ናቸው (ከአንበሳ ጋር አለመሆኑ ግን ይታወቅልኝ)። የዚያኔ አብዛኛዎቹ ፎቶ አንሺዎች እዚያ ስለሚገኙ የመስክ ፎቶ ለመነሳት ወደ ስድስት ኪሎ መሄድ የግድ ነበር (ያውም በሳምንቱ ታጥቦ ለሚደርስ ፎቶ)። መቼም የዛሬ ልጆች ይሄንን ሲሰሙ ይደነቁ ይሆናል፤ ያው ካሜራ በእጃቸው ነዋ። ፎቶ ቤትም ቢሄዱ በደቂቃዎች ውስጥ ፎቷቸውን ከእጃቸው ማስገባት ይቻላል። በእኛ ጊዜ ግን አንድ ፎቶ ሳምንት ይፈጅበታል፤ አንዳንዴም ሲታጠብ ሊበላሽና ሊጠቁር ይችላል።እንዲያም ሲሆን አማራጭ የለም የሆነውን ከመቀበል በቀር። መቼም በእኔ ዕድሜ ያለ ሰው አንበሳ ግቢ ብዙ ትዝታ አይጠፋውም። ስድስት ኪሎ ከሚለው የአካባቢው መጠሪያ በላይም «አንበሳ ግቢ» ሚለው ስሙ በእኛ ዘንድ(በዘመኑ ልጆች ለማለት ነው) ይበልጥ ይታወቃል። ምክንያቱም ቅዳሜና ዕሁድ ለልደት ወይም ለሽርሽር ቤተሰብ አዘውትሮ የሚጓዘው ወደዚያው ነበር። የሐምሌ 19 እና ብሄረ ፅጌ መናፈሻም የወቅቱ መዝናኛዎች መሆናቸውን አልዘነጋሁም። በአንድ ልደቴን ፎቶ ለመነሳት ከቤተሰቦቼ ጋር ወደ አንበሳ ግቢ አቀናን። ፎቶ እንደ ቀልድ ስለማይገኝም ያሉንንና ፎቶ ብንነሳባቸው የምንላቸውን አዳዲስ ልብሶች በሻንጣ ይዘናል። አንበሳ\nግቢ ስንደርስም ብዙ እንደኛ ከቤተሰቡ ጋር ፎቶ ለመነሳት በመጡ ሰዎች ተጨናንቋል። እኛም ፎቶ ለመነሳት የሚሆነንን ስፍራ ብንፈልግም የሰዉ መብዛት ሊያፈናፍነን ስላልቻለ እስኪጨርሱ መጠባበቅ ያዝን። ከፊት ለፊታችን ያለው ፎቶ አንሺም የሚያነሳቸውን ሰዎች፤አንዴ አበባ እያስያዘ… አንዴ ጥድ ስር እየከተተ… ሲሻው ደግሞ ሳር ላይ እያንከባለለ ሲያነሳቸው ቆይቶ «ብርሃን ስለበዛበት ፊልሙ ተቃጠለ» የሚል ምላሽ ሰጥቶ ድጋሚ ለማንሳት ይዘጋጃል። በሌላ ጥግ ያለው ፎቶ አንሺ ደግሞ ልብሳቸውን እየቀያየሩ «እንዲህ አንሳን…ደግሞ እንደዚህ ሆነን…›› በሚሉ የአንድ ቤተሰብ አባላት ትዕዛዝ ተሰላችቷል። ተነሺዎቹ\nበያዙት ልብስ ሁሉ ለመነሳት ቆርጠው የመጡ በመሆናቸው የድካም ስሜትም አይታይባቸውም። የታከተው ፎቶ አንሺም የያዘው ፊልም መሙላቱን ሲነግራቸው የቤተሰቡ ንዴት እስከ መተናነቅ አድርሷቸው ነበር። እኛም በተራችን ፎቶ አንሺያችንን ይዘን ወደ ተለቀቀው ስፍራ አመራን። ፎቶ አንሺውም 30 ፎቶ ብቻ እንደሚያነሳንና በፍጥነት እንድንዘጋጅ ነገረን። ሁላችንም ቀድመን በየትኛው ልብስ እንነሳ በሚል ሃሳብ ውስጥ ገብተን ከሻንጣው አንዱን ስናነሳ ሌላውን ስንጥል ረጅም ጊዜ ፈጀን። እንደምንም ከመራረጥን በኋላ አንዳንዶቻችን ቆመን፤ ሌላኛዎቻችን ከቆሙት ስር በርከክ እያልን ለፎቶው ተዘጋጀን። ያው\nየድሮውን ካሜራ ታውቁት የለ፤ አንዴ «ብልጭ» ብሎ ምስሉን እስኪይዝ መንቀሳቀስ አይፈቀድም። አንድ ሁለት ፎቶዎች እንደተነሳን ግን አንድ ሰው «ልጆቹን እግራችሁ ላይ አስደግፋችሁ፣ አበባ አስይዛችው፣ ጥዱ አናት ላይ አስቀምጣች… ለምን አትነሱም» የሚል ሃሳብ ሰነዘረ። ይህንን የሰሙት እናትና አባቴም ምክሩን ተቀብለው ሲያቅፉን፤ እሽኮኮ ሲያደርጉን፣ ደግሞ ሌላ የሚመች ቦታ ፍለጋ በሚል ግቢውን በመዞር የደከምነው አይረሳኝም። ያኔ እኮ ፎቶ ለመነሳ ፕሮግራም ተይዞ፣ ልብስ ተሸክፎ፣ ቤተሰብ ተሰባስቦ፤ አንዳንዴም የቤት እንስሳ ተይዞ ነበር። አረንጓዴ\nየሆነ እና አበባ በብዛት የሚገኝነት የአትክልት ስፍራ ማግኘትም የግድ ይላል (እንደ አሁኑ እያቀናበረ በሌለንበት የሚያኖረን ቴክኖሎጂ አልነበረማ)። ከዚያማ በዕድሜ፣ በቁመት አሊያም እንደ ቤተሰቡ ሁኔታ አግድም በሰልፍ አሊያም ፊትና በኋላ ከፍና ዝቅ እያሉ መነሳት ነው። አሁንማ ሁሉም ተለውጧል፤ ወደ ፎቶ ቤት የሚኬደው መታጠብ ላለበት ፎቶ ሲሆን ብቻ ነው (በዚህ ምክንያት አልበም ከየቤቱ አልጠፋ ይሆን?)። ጊዜውም የ«የሰልፊ ስቲክ» ነው፤ ፎቶ ለመነሳት በእጃችን ላይ ያሉትን ስልኮች መጠቀም አሊያም በእንጨት መሳዩ መቀሰሪያ ራሳችንን እያየን ምስላችንን ማስቀረት ነው። በዚህ ወቅት አንበሳ ግቢ የሚኬደውም አንበሳ እና ሌሎች እንስሳቶችን ለመጎብኘት እንጂ በዋናነት ፎቶ ለመነሳት አለመሆኑን ሳስብ «አይ ጊዜ» ያሰኘኛል።አዲስ ዘመን መጋቢት 9/2011መርድ\nክፍሉ", "passage_id": "935fffc442519a3fbd06f507427a9d27" }, { "passage": "ተሰልፈን ቆመናል አምባሳደር አካባቢ ታክሲ ተራ።ታክሲዎች ተሳፋሪውን ተራ በተራ እየጫኑ ወደ መድረሻቸው ይጓዛሉ።ተሳፋሪው ሌላ ታክሲ እስኪመጣ ይጠብቃል።አንድ ከፍ የለ ድምፅ በሰልፍ የቆመውን ተሳፋሪ ትኩረት ስቧል።ሁሉም ወደ ተሰማው ድምፅ አማተረ።አንድ ወጣት አንዲት ህፃን ልጅ አቅፎ ተሳፋሪውን ቀረበና በእጁ የያዘውን በፕላስቲክ ማሸጊያ የተለበጠ ወረቀት ላይ የተፃፈ ጽሁፍ ድምፁን ከፍ አድርጎ ያነባል፡፡የተለያዩ ጎዳናዎች ላይ በተደጋጋሚ የሚሰማ ምልዕክት አይነት የመሰለው አይንና ጆሮው መለሰ። ልጁ ቀጥሏል፤\nወረቀቶችን ይዞ ድመፁን ከፍ አድርጎ ያነባል። “ከተፋቀርን አባይ ይገደባል እኛም እንጠግባለን። እባካችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርስ\nተፋቀሩ ያኔ ኢትዮጵያ ከፍ ትላለች፡፡” ሰውየው ከፍ ባለ ድምፅ ይናገራል። ይሄን እዚያ ለመሳፈር የቆመው ሁሉ ጆሮ ሰጥቶ ይሰማው\nጀምር፡፡ከሰውየው አንደበት የሚፈልቁ ቃላት የተመጠኑና ሁሉም ሰው ሊያዳምጣቸው የሚገቡ በመሆናቸው እንዲቀጥሉ\nተመኘሁ።ታክሲ ለመያዝ ተጣድፌ የነበርኩትን ያህል፤ ታክሲ እንዲዘገይ ተመኘሁ።ሰውየው በፈገግታ ተሞልቶ ስለ ፍቅር ታላቅነት ይሰብካል።“እባካችሁ\nተዋደዱ ያኔ ለውጥ ይመጣል ተከባበሩ ያኔ ድል ይመጣል….” ስለ ፍቅርና መዋደድ ስለ አብሮነትና ፍቅር በማይጠገብ አንደበቱ ያስረዳል።\nእናንተዬ ፍቅርን የሚሰብክ አንደበት፣ እድገት የሚያፀና ምክር፣ ህብረትን የሚሰብክ ንግግር ምንኛ ይጥማል።ታክሲ መጣና ተሳፈርኩ።\nስራ ረፍዶብኝ ነበረና ቦታውን ሳልወድ ለቀኩ።ሰውየው ግን ከአይምሮዬ አልጠፋም ደጋግሞ ይታሰበኛል።ይህ ሰው ስለዚህ ጉዳይ እንዲናገር\nምን አነሳስቶት ይሆን? የጎደለን ፍቅር መሆኑ ከኛ ከፍ ባለ ሁኔታ ገብቶት መንገርስ ላይ ያደረሰው ምን ይሆን? ብዙ አሰብኩ፤ እዚያው\nቦታ ሆኜ የጎደለን ፍቅርና መተሳሰብ እንጂ እውነትም አባይ አይደለም ችግርና መከራችንም መገደብ እንችላለን የምር!!።ስለ ፍቅር\nብለን እርስ በርስ ብንተጋገዝ ስለ ሀገር ፍቅር ብለን ለሀገራችን በጎ ካበረከትን ምን ሊጎለን ይችላል?ምንም! ለራሴ መልስ ሰጠሁ፡፡ታክሲ ውስጥ ረዳቱ\nሒሳብ ሲለኝ ከሄድኩበት ሰመመን ተመለስኩ።አውጥቼ ሁለት ብር ሰጠሁት።“አምስት ብር ነው፡፡” እ…ከሁለት ወደ አምስት ብር ያደገው\nከመቼ ጀምሮ ነው? አትነጫነጭ ሁሉም ከፍሏል። “በአቋራጭ ነው የምሄደው ጨምር።” ሹፌሩ በመሀል ረዳቱን ለማገዝ ቃላት መወርወር\nጀመረ። “አንተ ሰው ስራ አይደል እንዴ ምን እያልክ ነው ለምን ገባህ እየተናገርን አይደል የጫንክ” ተሳፋሪውን ዞር\nብዬ አየሁ ፊቱን ሁሉም ቅጭም ሲያደርግብኝ መኪናው ሙሉ በኔ ያኩረፈ መሰለኝ፤ አውጥቼ ሰጠሁ።እስክሰጠው ድረስ በስድብ እያጥረገረገኝ\nነበር። ኦህ! አምላኬ ትግስቱን ስጠኝ ትርፍ ከፍዬም ተሰድቤም ከባድ ነው።ሰልፉ ቦታ ወደነበረው ሰው በሀሳብ ተመለስኩ።“ እርስ\nበርስ እንከባበር እንዋደድ፣ ፍቅር አተን ነው የተቸገርነው እባካችሁ እንፋቀር፡፡” ንዴቴ ረገበ።ስለፍቅር ብዬ ዝም አልኩ።እኛ ግን ምን ነካን።ፍቅራችን\nየት ገባ።ረዳቱና ሹፌሩ ግን ያንን ሰው ሰምተውት ይሆን ሲጭኑ እዚያ ቦታ ነበሩና ሳይሰሙት አይቀሩም።ችግሩ አያደምጡትም…። ወዳጄ\nስላለን ብቻ የፈለግነው አንበላም እኮ አረ እንዋደድ ተዉ…። አብዝቶ መስገብገብ ምንድነው እንዴ? ሆድ ልክ አልባ ይመስል ሰውን\nመበደል፣ ሰውን መግፋት የሰውን መሰብሰብ አስጭኖና ቋጥሮ መቃብር ይዞ ላይሄዱት ነገር ኧረ ነውር ነው…!!።ሰው ከተዋደደ በደህነቱ\nንፁህ ህሊናውን ይዞ ሊሰፈር የማይችል ደስታን ይጎናፀፋል።ህሊና ቢስ ከሆነ ግን ሰው ከሚለው ስብዕና የራቀ ክፉ አውሬ ከመሆን አይድንም።\nበክፉ ስራው ሰዎችን ክፉኛ ያቆስላል፣ ከሚታሰበው በላይ ክፋትን ይለምድና ለሰዎች ሴራን ይጎነጉናል ስለሌላው አይጨንቀውም ስለማንም\nአይገደውም።ይህ ሰው እያደረ ‹‹ሰው ጤፉ›› ነው።ሰውየው ግን አይቶናል\nፍቅር በማጣታችን መቸገራችን ከኛ በላይ ገብቶት ጎዳና ላይ መስበክ ተያይዞታል… እንደው በዚህ በጎ ተግባሩ እስከ መቼ ይቀጥል ይሆን?\nታድሎ።ውስጡ የሚሰማው ሰላምስ ምን ያህል ይሆን? እኔ ምለው ሰላም ግን ይሰፈራል። ምን ያህል ነው ክብደቱ? ኦህ! ይከብዳል አቻ\nየሌለው ነገር በምን ሊሰፈር ይችላል።ሰውየው ውስጡ ያ ሰላም ሳስበው ቀናው። ወዳጄ ደስታህ ከእጅህ\nእንዳይወጣ ባንተ ሰው እንዲደሰት ትፈልጋለህን? ውስጥህ ሰላም ከሆነ ባትበላ ረሀቡ አይቀፈድድህም፣ ባትለብስ የሰው ፍቅር ትሞቃለህ፣\nበሰው ክብር ምቾት ይሰማሀል።የትም ጋደም ብትል ለሽ… ብለህ የሚያስቀና እንቅልፍ ትተኛለህ።ሰዎች ብዙ ጊዜ ስግብግብ የሚሆኑት ፈፅሞ\nቢያገኙም በማይጠቀሙበት አግኝተውም በማይደሰቱበት መሻታቸው ላይ ነው። ይሰበስባል፣ ላይ በላይ ደራርቦ ከምሮም ከልክ በላይ ያደልባል\nእድሜውን ሙሉ ያለ እረፍት የሱ ያልሆነን የማይገባውን የሌሎችን እየነጠቀ ባለው ላይ እየጨመረ ቀዶ እንኳን የማይጨርሰው ሀብት ያከማችና\nሰላሙን ያጣል።ሰውየው ግን ከየት\nተልኮልን ይሆን “ተፋቀሩ ተዋደዱ” ያለው ፍቅር ከኛ መንጠፉ ምን ያህል ቢገባው ነው።ፍቅር አተን እንጂ ምን ይጎለን ነበር።በተጓዘበት\nበደረሰበት ሁሉ የሚሰብከው መልካም ነገር ስንቶቻችን ይሆን ጆሮ ሰጥነት የምንሰማው ምን ያህሎቻችንስ ነን ከልብ የምናዳምጠው።ዛሬ ላይ የምነሰማው\nመልካም ነገር ጎሎ ሳንፈልግ የሚቀርበን መጥፎ ዜና በተበራከተበት ለሁሉ ጉዳት መፍትሄ የሚሆነው ፍቅር ማጣታችን ዋንኛው ምክንያ\nነው።ፍቅር ውስጥ የማይፈታ ችግር የማይታለፍ ፈተና የለም።መከባበር ውስጥ የማያስችል ጉዳይ የማያግባባ ሀሳብ አይኖርም ግን በተቃራኒው\nከኛ ፍቀር ከራቀ ጥላቻ ቦታውን ይወርስና የማያርቅብን ጉዳይ አይኖርም፡፡አዲስ ዘመን የካቲት 30/2012ተገኝ ብሩ", "passage_id": "e637ae7ddadabed4d44b390722c63ad5" }, { "passage": "ግቢው ንፁህ ነው፡፡ ዙሪያውን የተለያዩ ቀለማት (አረንጓዴ፣ሰማያዊ፣ነጭ) ባላቸው የከበሩ ማዕድናት ተውቦ ሲያዩት ልብን በሐሴት ይሞላል፡፡ በስተግራ በኩል ግድግዳው ላይ የተለያዩ ባህላዊ አልባሳትና ቅርፃ ቅርፆች ተደርድረዋል፡፡ ጥግ ላይ የቡና ማፍያ መደብ አለ፡፡ መኻሉ ቡና መጠጫ በርጩማ ተደርድሯል፡፡ ፊት ለፊት ያሉት በመስተዋት ያሸበረቁ ሁለት ክፍሎች ከከበሩ ማዕድናት የተሠሩ ጌጣጌጦች (ጅውለሪ) የሚሸጡባቸው ናቸው፡፡ ፎቅ ላይ የአርት ጋለሪ አለ፡፡ይህ አሁን ያስቃኘኋችሁ ግቢ፣ ዛሬ ከ11 ሰዓት ጀምሮ ተመርቆ የሚከፈት ሲሆን በተለምዶ አትላስ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከኡራኤል ወደ ቦሌ ሲሄዱ ከ‹‹2000 ሐበሻ ሬስቶራንት›› ፊት ለፊት የሚገኘው የአብዘር ኢሳያስ ትሬዲንግ የከበሩ ማዕድናትና ጌጣጌጦች ባህላዊ አልባሳት ቅርፃ ቅርፅ… ጋለሪ ነው፡፡የዓለምን ኦፓል ገበያ የተቆጣጠረው የአውስትራሊያ ኦፓል ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የወሎ ኦፓል ዓለም ገበያ ውስጥ ሰብሮ መግባት ችሏል። ኦፓሉ ከማማሩም በላይ ያንፀባርቃል፡፡ የተለያዩ የኦፓል ዓይነቶች በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ይገኛሉ። በሰሜን ሸዋ የሚገኘው ኦፓል በተለምዶ ‹‹ቸኮሌት ኦፓል›› ይባላል፡፡፡ በአፋር ክልልም ተገኝቷል፡፡ የዛሬ 5 ዓመት ገደማ የወሎውን ኦፓል ሲያዩት በጣም ወደዱት፡፡ ኢትዮጵያ ያልተነካ የማዕድን ሀብት ስላላት በዚህ ዘርፍ ለመሰማራት ወሰኑ፡፡ጥናት ለማድረግ ወደተለያዩ አገራት በመሄድ በኦፓል ኤግዚቢሽኖች ተሳተፉ፡፡ ከዚያም የውጪውን የገበያ ሥነ- ሥርዓት አዩ፡፡ በዚህ ጊዜ የበከበሩ ማዕድናት ሥራ አዋጪና በዓለም ተፈላጊ መሆኑን ተገንዝበው፣ ወደ ሥራው መግባታቸውን የአብዘር ኢሳያስ ትሬዲንግ  መሥራች ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢሳያስ አበበ ይናገራሉ፡፡ አብዘር ኢሳያስ ትሬዲንግ ላለፉት 10 ዓመታት በኮምፒዩተር፣ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ በቲኬትና አስጎብኚነት፣ ወደ ኋላም በማዕድን ኤክስፖርትነት ሊሰራ የቆየ ድርጅት ነው፡፡ በአሁን ወቅት የድርጅቱ ራዕይ ኢትዮጵያ ያሏትን የከበሩ ማዕድናት ማስተዋወቅና የገጽታ ግንባታ መሆኑን አቶ ኢሳያስ ይናገራሉ፡፡ ከገጽታ ግንባታው አንዱ ቱሪስቶችን ወደ አገሪቷ መሳብ ነው፡፡ የዚህ ጋለሪ መከፈት በጣም ለሚቸኩሉ፤ አንድ ቀን ወይም ግማሽ ቀን ብቻ ለሚቆዩ ቱሪስቶች በአንድ ግቢ ውስጥ አምስት ዓይነት አገልግሎት ማግኘት በጣም ጥሩ አማራጭ ነው ይላሉ አቶ ኢሳያስ፡፡ ‹‹የሚቸኩሉ ቱሪስቶች ሽሮ ሜዳ፣ ጥቁር አንበሳ አካባቢ ወይም መርካቶ ለመዘዋወር ጊዜ አይኖራቸውም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቪዛ ካርዳቸውን ሊነጠቁ፤ ፓስፖርታቸውን ሊጠፋ፣… ይችላል፡፡ እኛ ጋ ግን ደህንነታቸው ተጠብቆ ባህላዊ ቡና እየጠጡና ሥዕል እየተመለከቱ አምስት ዓይነት አገልግሎት ያገኛሉ›› ብለዋል፡፡ ድርጅቱ በአንድ ግቢ ከሚሰጣቸው 5 ዓይነቶች አገልግሎቶች አንዱ የባህል ዕቃዎች (ሱቬኒር)፣ ቅርፃ ቅርፅ፣ የባህል አልበሳት፣ የስጦታ ዕቃዎች ናቸው። ሌላው አገልግሎት፣ ማዕድናትን በተለያዩ መልኩ አለስልሶና (ፖሊሽ አድርጎ) እሴት ጨምሮ መሸጥ ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ የአርት (ሥዕል) ጋለሪ ነው፡፡ ‹‹ብዙ ቱሪስቶች አርት (ሥዕል) ይወዳሉ፡፡ ምስላቸው ወዲያው ተሠርቶ እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች ጥሩ ጥሩ ቤቶች እየሠሩ ነው፡፡ ቤታቸው ውስጥ የሚሰቀሉ ጥሩ ጥሩ ሥዕሎች ይፈልጋሉ፤ ይገዛሉ፡፡ ለዚህ ነው የታዋቂ አርቲስቶችን ጋለሪ ያዘጋጀነው›› በማለት ገልጸዋል፡፡ ሌላው ዝግጅት የአገራቸውን ባህል የሚያስተዋውቁበት የጀበና ቡና ሥነ-ሥርዓት ነው። በቡናው ዝግጅት ላይ ለቁርስ የሚሆን አበሻ ዳቦ፣ ጭኮ፣ ዳቦ ቆሎ፣ አምባሻ፣ ፈንዲሻ… ይቀርባል። አምስተኛው አገልግሎት አስጎብኚ ድርጅት (ቱር ኤንድ ትራቪል) ነው፡፡ በዚህ ሥራ፣ የተለያዩ የአገሪቱን ውብና ታሪካዊ ቦታዎች ያስተዋውቃሉ፤ የመኪና ኪራይም ያቀርባሉ፡፡ ጋለሪው በሚመረቅበት ዕለት የከበሩ ማዕድናት ወርክሾፕ ለሕዝብ ክፍት ሆኖ የሚታይ ሲሆን ‹‹ማዕድናቱ እንዴት ነው የሚቀረፁትና የሚለሰልሱት ጌጣጌጦች እንዴት ነው የሚሰሩት፣ የሚለውን ጥያቄ ይመልሳል፡፡ በዚሁ የመክፈቻ ዕለት የሥዕል ወርክሾፕም ይታያል፡፡ አርቲስቶች አንዴት ነው የሚሥሉት ለሚለው ጥያቄ አርቲስቶች በቀጥታ ሲሰሩ የሚታዩበት (Live) ወርክሾፕ ይቀርባል፡፡ ቱሪስቶች ቡና እየጠጡ ሥዕል ሲሳል ማየት፣ ምስላቸውን ማሠራት ወይም እንዲህ አይነት ነገር ሳልልኝ ሊሉ ይችላሉ›› በማለት አቶ ኢሳያስ አስረድተዋል፡፡ የጋለሪው መከፈት ኢትዮጵያ ያላትን 42 ዓይነት የከበሩ የተፈጥሮ ማዕድናትን ማስተዋወቅ ነው ያሉት አቶ ኢሳያስ፣ “ባለሀብቶች በዚህ ዘርፍ ኢንቨስት ቢያደርጉ ጥቅሙ ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ ‹እናተም ትጠቀማላችሁ፣ ለአገሪቷም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ታስገኛላችሁ፤ ለበርካታ ዜጎችም የሥራ ዕድል ትፈጥራላችሁ፡፡ ስለዚህ ባለሀብቶች ሆይ! ይህን ያልተነካ ድልብ የተፈጥሮ ሀብት ዘርፍን እንደ አንድ ምቹ አጋጣሚ (ኦፖርቹኒቲ) ተመልከቱ የሚል መልዕክትም አለው” በማለት አብራርተዋል፡፡ በማንኛውም ዘርፍ ችግሮች እንዳሉት ሁሉ በማዕድን ዘርፍም መኖሩን የጠቀሱት አቶ ኢሳያስ፣ “አሁን የከበሩ ማዕድናት ማምረቻ የለንም፤ ገበሬዎቹ አምርተው የሚሰጡንን ኤክስፖርት ስለምናደርግ የምርት እጥረት አለ፡፡ ሌላው ደግሞ አምራቾች የዓለምን ዋጋ በትክክል ስለማያውቁ፣ ሁሉንም ምርት በተገኘው ዋጋ ይተምናሉ። ስለዚህ እኛም ቦታ ተረክበን ወደ ማምረት ለመግባት እንቅስቃሴ ጀምረናል” ብለዋል፡፡ አቶ ኢሳያስ ለወደፊት ሁለት ዕቅዶች አሉኝ ይላሉ። “ኢትዮጵያ የወርቅ ማዕድን ካላቸው አገሮች አንዷ ናት። ወርቅ ኤክስፖርት ታደርጋለች፡፡ ብርና ወርቅን በከበሩ ማዕድናት ብናስጌጣቸው (ብንጨምርባቸው) ወርቅን ከምንሽጥበት ሦስትና አራት እጥፍ ዋጋ ሊያወጡ  ይችላል፡፡ የወርቁን እሴት ይጨምረዋል፡፡ የተወሰኑ የከበሩ ማዕድናት ዋጋቸው ከወርቅ በላይ ነው፡፡ ስለዚህ ኤክስፖርት ለማድረግ የጌጣ ጌጥ (የጅውለሪ) ኢንዱስትሪ (ፋብሪክ) መክፈት እፈልጋለሁ፡፡ ሌላው ደግሞ በእጅ የተሰሩ መስቀሎች ያላቸው ወርቆች ዋጋቸው ውድ ነው። ወርቆቹ ላይ የተለያዩ የከበሩ ማዕድናት በማድረግ ደረጃውን የጠበቀ ጌጣጌጥ ወደ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ ካናዳ፣ ኤክስፖርት ማድረግ የወደፊት ዕቅዴ ነው” ሲሉ ገልፀዋል፡፡ የአብዘር ኢሳያስ ትሬዲንግ ለ50 ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡ ባለሀብቱ፣. የተከበሩ ማዕድናትን ይዘው በዓለም 1ኛ በሚባለው በአሜሪካ አሪዞና ግዛት ቱሳይና በዴንቨር፣ በአውሮፓ፣ በፈረንሳይ፣ በጀርመን፣ በቻይና ሆንግኮንግ፣ በቅርቡ ደግሞ በታይላንድ ኤግዚቢሽኖች በመሳተፍ የኢትዮጵያን የከበሩ ማዕድናት እያስተዋወቁ መሆኑን አቶ ኢሳያስ አበበ ተናግረዋል፡፡   ", "passage_id": "f41ca63f510d57af44ee1eee5e400368" } ]
f7f048a51b303f6e8317d26538aebf11
8ddc44e3491fe2866267c4b7798aa23c
የታክስ ውስጥ ጥቅሶች
በተለምዶ ጥቅስ ሲባል፤ በመደበኛ አጠቃቀም ከመጻሕፍት (ቅዱሳን መጻሕፍት፣ የምርምር እና የሣይንስ መጻሕፍት፣ የታሪክ ድርሳናት እና የልብ ወለድ ድርሰቶች) የሚታወቁ እና ለምንናገርበት ወይም ለምንጽፈው ጉዳይ ማጠናከሪያ ሆነው የሚጠቀሱ እና ባለቤት ያላቸውን ነው፡፡ ነገር ግን ጥቅስ ተናጋሪው ወይም ጸሐፊው ሳይታወቅ ሀሳብን በተቃውሞ ወይም በድጋፍ የማኅበረሰቡን ሥሜት ሲገልፁ ይስተዋላል፡፡ለዚህ ተግባር ከሚጠቀሱት ደግሞ የመፀዳጃ ቤቶች /በተለይ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት/ እና የታክሲ ውስጥ ጥቅሶች በዋናነት ይነሳሉ፡፡ እነዚህ ጥቅሶች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የጥናት እና ምርምር ርዕሰ ጉዳይ በመሆን በርካታ ጥናቶች ተካሂዶባቸዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ደግም በማኅበራዊ ሚዲያዎች የመወያያ ሀሳብ እየሆኑ መቅረብ ጀምረዋል፡፡ እኛም በዚህኛው አውድ የተወሰኑትን ጀባ ብለናል፡፡ ከታክሲ ሥራ ጋር የተያያዙ ጥቅሶች ዘመን መፂሄት መስከረም 2012 አባይ ፈለቀ
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=19999
[ { "passage": "ግብር አጭበርባሪዎች በማኅበራዊ ሚዲያ 'ፖስት' ሊታደኑ ነው\\nየማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በገጻቸው ላይ የሚለጥፉትን ፎቶግራፍና የግል መረጃ ዝርዝር (ፕሮፋይል) በማየት ግብር የከፈሉና ያልከፈሉ እንደሚለዩ ተገልጿል። \n\nድንጋጌው ባለፈው ሳምንት ከግብር ክፍያ ጋር በተያያዘ የወጣው ሕግ አካል ነው።\n\nየሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የፈረንሳይ የመረጃ ደህንነት ክፍል ሕጉ እንደሚያሰጋቸው ተናግረዋል። \n\nሕጉን ያፀደቀው ምክር ቤት፤ እርምጃው የዜጎች ራስን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ ጫና ሊያሳድር ቢችልም፤ ድንጋጌው የሚተገበርበት ቅድመ ሁኔታዎች አሉ ብሏል።\n\nከቅድመ ሁኔታዎቹ አንዱ በሚስጥራዊ ይለፍ ቃል (ፓስወርድ) የተቆለፉ ገጾችን ሰብሮ አለመግባት ሲሆን፤ የግብር ክፍያ ክፍሉ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ለሕዝብ ይፋ የተደረጉ መረጃዎችን መጠቀም ግን ይችላል። \n\nየፈረንሳይ መንግሥት የዜጎቹን የድረ ገጽ እንቅስቃሴ የሚቃኝበት የሦስት ዓመት እቅድ ነድፏል። ግብር ያልከፈሉ ሰዎችን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚለጥፉት መረጃ ማግኘት የዚሁ እቅድ አካል ነው።\n\nየፈረንሳይ የመረጃ ደህንነት ክፍል የሦስት ዓመት እቅዱ ሕጋዊ አግባብነት ቢኖረውም፤ ግብርን በተመለከተ የወጣው ድንጋጌ የዜጎችን ነፃነት ይጋፋል ብሏል።\n\nየበጀት ሚንስትሩ ጄራልድ ዳርማኒን በበኩላቸው \"አጭበርባሪዎችን የምንገታበት አንድ መንገድ ነው\" ሲሉ ሕጉን ገልጸውታል።\n\n\"በዚህ ዓመት ፈረንሳይ አልኖርኩም ብለሽ፤ ኢንስታግራም ላይ የፈረንሳይ ፎቶዎችን ብትለጥፊ ችግር አለ ማለት ነው\" ሲሉ ለ 'ለ ፊጋሮ' ጋዜጣ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።\n\n• 17 ታካሚዎችን የመረዘው ዶክተር\n\n• ፈረንሳይ ኩሽና ውስጥ ተሰቅሎ የተገኘው ሥዕል ብሔራዊ ሐብት ነው አለች\n\n• ኩባንያው በደረሰበት ጫና ሂጃብ መሸጥ አቆመ \n\n", "passage_id": "26dda250f6b366212ea6e602e7557dcf" }, { "passage": " የኢትዮጵያ ገቢዎች ባለሥልጣን “ሁላችንም ኃላፊነታችንን እንወጣ!” በሚል መሪ ቃል ለ7ኛ ጊዜ የግብርና ቀረጥ ሳምንት እያከበረ ነው፡፡ገቢ የህልውናችን መሰረት ስለሆነ ህብረተሰቡ ስለግብር፣ ታክስና ቀረጥ ያለውን ግንዛቤ ከፍ በማድረግ ርእሰ ጉዳዩ አድርጐ እንዲወያይባቸው ከጥር 23 እስከ የካቲት 1 ቀን የሚቆይ የአንድ ሳምንት መርሐ ግብር ቀርፆ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን የባለሥልጣኑ የትምህርትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ገልፀዋል፡፡ዳይሬክተሩ አቶ ኤፍሬም መኮንን ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ የግብርና ታክስ ግንዛቤ ለመፍጠር የአንድ ሳምንት ትምህርት ይበቃል ማለት ሳይሆን ይህች አገር ማደግ ካለባት፣ የታከስ አሰባሰቧ መሻሻል አለበት፤ ህብረተሰቡም በግብር አሰባሰብ ረገድ ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ በመነጋገርና በመመካከር ሁሉም የጋራ ኃላፊቱን እንዲወጣና መነጋገሪያ ርእስ እንዲያደርገው ለማስገንዘብ ነው ብለዋል፡፡ ባለሥልጣኑ የተለያዩ ፕሮግራሞች ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ ነው ያሉት አቶ አፍሬም፤ ከሚዲያ ተቋማት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ ከወጣቶችና ሴቶች አደረጃጀትና አባላት፣ ከከፍተኛ ግብር ከፋዮች፣ ከመካከለኛ ግብር ከፋዮችና ከአነስተኛ ግብር ከፋዮች፣ ከጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ አንቀሳቃሾችና ከጉምሩክ አስተላላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም የተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በግብር አሰባሰብ ረገድ የሰሯቸውን ክንውኖች የሚያሳይ ኤግዚቢሽን ጥር 27 የተከፈተ ሲሆን  እስከ የካቲት 1 ይቆያል ተብሏል፡፡ በዋና ዋና የመዲናይቱ ጐዳዎች በመኪና ቅስቀሳ ማድረጋቸውንና ስለግብረና ቀረጥ ሳምንት በሚዲያዎች እንዳስተላለፉ፤ ክንውኑ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን ክልሎችም ከደንበኞቻቸው ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡400 ከሚደርሱ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ጋር ባደረጉት ውይይት፤ ባለሥልጣን መ/ቤቱ እያደረገ ያለው የለውጥ ሥራዎች ጥሩ ቢሆኑም ይበልጥ መሻሻል እንዳለባቸው ጠቅሰው፤ የግብር ጉዳይ የሁላችንም ስለሆነ ባለሥልጣኑ ለህብረተሰቡ እየሰጠ ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርትና ቅስቀሳ ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡የስፖርት አዘጋጆች የአየር ሰዓት ገዝተው ስፖርት የሚተነትኑበትና ዲጄዎች ሙዚቃ እያሰሙ የሚውሉባቸው ኤፍኤም ራዲዮች ሞልተው ሳለ፣ ገቢዎች ባለስልጣንን የሚያህል ትልቅ መ/ቤት በሳምንት በቲቪ የ20 ደቂቃ፣ በራዲዮ የ30 ደቂቃ ፕሮግራም ብቻ ማቅረቡ በቂ አይደለም፤ ሰፊ የአየር ሰዓት ሊኖረው ይገባል በማለትም አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ከፍተኛ የሠራተኛ ጥሎ መውጣት (Turn over) ከሚታይባቸው መ/ቤቶች አንዱ የገቢዎች ባለሥልጣን መሆኑን የጠቆሙት ከፍተኛ ግብር ከፋዮች፤ ልምድ ያላቸው ሙያተኞች ሲለቁ አዲስ ማሰልጠን ጉዳት ስላለው መ/ቤቱ የሠራተኞቹን አያያዝ (ክፍያ፣ ጥቅማ ጥቅም…) እንዲፈትሽ፤ የሠራተኞች አገልግሎት አሰጣጥ ተመሳሳይ ስላልሆነ መ/ቤቱ ራሱን እንዲፈትሽ፤ የተመላሽ ገንዘብ ክፍያ መዘግየትም እንዲስተካከል ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡ “ወደ ታክስ መረቡ የገባን አለን፤ ብዙ ነጋዴዎች ግን አልገቡም ስለዚህ የንግዱ ሜዳ ፍትሐዊ አይደለም፤ ኦዲት አራት ዓመት ያህል ሰለሚዘገይ ወደኋላ ሄዳችሁ ወለድ ትጠይቁናላችሁ፣ የአገልግሎት አሰጣጡ ተመሳሳይ ስላልሆነ ውስጣችሁን ብታዩ ጥሩ ነው፤ …” በማለት በመ/ቤቱ ያዩትን ድክመቶች መጠቆማቸውን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡አወያዮቹ ለተነሱት አስተያየቶች ከመድረክ በሰጡት ምላሽ፣ በአገልግሎት አሰጣጡ ብዙ መሻሻሎች ቢኖሩም ድክመቶች እንዳሉባቸው አምነዋል፡፡ የአገልግሎት አሰጣጡን የተሻለ ለማድረግ የእናንተና የሁሉም ደጋፍ ያስፈልገናል ያሉት አወያዮቹ፤ ማንኛውም ሰው አገልግሎት ፍለጋ ወደ ተቋሙ ሲመጣ ማሟላት የሚገባውን ግዴታዎች አሟልቶ መቅረብ አለበት፤ ያላሟላው ነገር ኖሮ አሟልቶ አንዲመጣ ሲነገረው “አገልግሎት አሰጣጡ ፈጣን አይደለም” ማለት አይችልም፡፡በመ/ቤቱና በአገልግሎት ፈላጊዎች መካከል ግልፅነት ሊኖር ይገባል ያሉት ኃላፊዎቹ፤ ደንበኛን ያጉላላ፣ የሚለግም… ሠራተኛ ካለ መጠቆምና ማሳወቅ እንዳለባቸው ገልፀዋል። የኦዲት መዘግየትንና ወለድን በተመለከተ በሰጡት ምላሽ፣ በግብር ሕጉ መሰረት መጀመሪያ የሚደረገው አምንሃለሁ፣ የሠራኸውን ሳትደብቅ ክፈል የሚል ስለሆነ፣ ነጋዴው “እኔ ሰርቼ ያገኘሁት ይሄ ነው” ብሎ የሰጠውን እንደሚቀበሉ ተናግረዋል፡፡ ነጋዴው ያለበትን ግብር በትክክል ካሳወቀ፣ ኦዲት የሚደረገው በፍጥነትም ሆነ ቆይቶ ቢሆን ለውጥ እንደሌለው ጠቅሰው፣ ግብሩን አሳንሶ የከፈለ ሰው በኦዲት ሲደረስበት ግብራቸውን ለሚያሳንሱ ሌሎች ሰዎችም ማስተማሪያ እንዲሆን መቀጫው ከፍ ያለ ነው ብለዋል፡፡ድርጅቱ ኦዲት ለማድረግ  የሚያስጠረጥረው ደግሞ የተጋነነ ትርፍ ወይም የተጋነነ ኪሳራ ነው። የእኛም ሠራተኛ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ግብር ሲያሳንስ ወይም ከፍ ሲያደርግ ሕገ-ወጥነትን መከላከል የምንችለው በጋራ ስለሆነ ለመ/ቤቱ ማሳወቅ ያስፈልጋል በማለት ኃላፊዎች ምላሽ እንደሰጡ ታውቋል፡፡አንዳንድ ዓመታዊ ገቢያቸው ከ100ሺ በታች የሆኑ የ“ሐ” ነጋዴዎች፤ አገር ውስጥ ገቢ ግብር እየጫነብን መሥራት አቅቶናል፤ ከዚህ ኑሮ በሰው አገር ተሰድዶ መኖር ይሻላል በማለት የሚኮበልሉ አሉ ወይም አየር በአየር ሕገ ወጥ ንግድ ውስጥ የሚገቡ እየበረከቱ ስለሆነ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ይላሉ ተብለው የተጠየቁት አቶ ኤፍሬም፤ እነዚህ ነጋዴዎች የሂሳብ ባለሙያ መቅጠር ስለማይችሉ የሽያጭ መዝገብ እንዲይዙ አይገደዱም፡፡ ግብራቸው የሚተመነው በግምት ነው፡፡ ግምት ደግሞ ከፍም ዝቅም ሊል ሰለሚችል ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ሰለዚህ “ግብር በዛብኝ” እያሉ ከማማረር የየእለት ሽያጫቸውን በደብተር መዝግበው ቢይዙ መ/ቤቱን ከማማረር ይድናሉ፡፡ ያለ አግባብ ግብር ተጣለብኝ የሚል ሰው በ10 ቀናት ወይም በ30 ቀናት ውስጥ ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ቅሬታ ቢያቀርብ ይታይለታል፡፡ ብዙ ሰዎች ቅሬታ አቅርበው እውነታው ታይቶ ወደ ሥራቸው ተመልሰዋል በማለት አብራርተዋል፡፡  ", "passage_id": "c0cb1ddb60b14e7dfc5e9e22c94c67d3" }, { "passage": "ድሮ\nድሮ “ውድ” ለወዳጅ የሚጻፍ የደብ ዳቤ መክፈቻ ቃል ነበር:: ዛሬ ደግሞ ለነፍስ ለቀረበ ወዳጅ የሚሰጥ የቁልምጫ ስም ነው:: ፍቅረኛንና የትዳር አጋርን ውዴ ማለት ግድ ነው:: ጆሮ አስፍስፎ ይጠብቃላ! የቃሉ ፍቺ አንድም ተወዳጅ አንድም በቀላሉ የማይገኝ (ብዙ ዋጋ የሚያስከፍል) ማለት ነው:: ጨዋታችን በቃሉ ሁለተኛ ብያኔ ዙሪያ ነው:: ብዙ ገንዘብ የሚያስወጡ (ውድ) ነገሮችን ስለሚወዱ ሰዎች እናወጋለን:: ውድ\nነገሮችን ትወዳላችሁ ? ወይም ውድ ነገሮችን የሚወዱ ሰዎች ገጥመዋችሁ ያውቃሉ? ውድ ነገርን መውደድ ጤናማ ሰዋዊ ባህሪ ነው ልትሉ ትችላላችሁ። ነገር ግን መጠን አለው። ምንም ነገር ቢሆን ልኩን ሲያልፍ ችግር መሆን ይጀምራል። በያዝነው ሳምንት አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ በተላለፈ ወንጀል ነክ ፕሮግራም መጠን ባለፈ የግዢ ሱስ ምክንያት የትዳር አጋሯ ሳያውቅ ከፍተኛ ብድር ውስጥ ተዘፍቃ ቤታቸው በሐራጅ ተሸጦ ባለቤቷንና መንታ ልጆቿን ጥላ ለእስር የተዳረገች እንስት ታሪክ ቀርቦ ነበር። ባለታሪኳ ለዚህ የበቃችው ማንም ሰው እንደ አቅሙ በየቀኑ የሚፈጽመው ግዢ እርሷ ግን አቅሟ የማይፈቅደውን ነገር ሁሉ ሱስ ሆኖባት እየተበደረች በመግዛቷ ነው። ውድ ነገርን መውደድም ቅጥ ሲያጣ ሱስ ይሆናል። ውድ ወዳዶችን መተዋወቅ ትፈልጋላችሁ ? እነሱን በአካል ማግኘት በጣም ቀላል ነው። ሰንደይ ማርኬት ላይ ሦስት መቶ ብር የሚሸጥ ሱሪን የከተማው ታዋቂ ሞል ገብተው ያለክርክር በአንድ ሺህ ብር ሲገዙ ታገኟቸዋላችሁ። በሚንቀሳቀሱበት ቦታ ሁሉ ዓይኖቻቸው ለየት ያለ ጫማ፣ ልብስ፣ መነጽርና የእጅ ስልክ ላይ ያርፋሉ። ደግሞ አይተው ዝም አይሉም። ጠጋ ብለው በጣም ያምራል ! ከየት ገዛኸው ? ከውጭ ተልኮልህ ነው ? ይመቻል ? እያሉ ጥያቄ ይደረድራሉ። ባስ ሲልም ትሸጠዋለህ ? ብለው በዋጋ ለመደራደር አያመነቱም። ለዓመታት የተለዩትን ሰው ድንገት ሲያገኙት እንዴት ነህ ? በማለት ፈንታ ጫማና ልብስህ ያምራል ማለት ይቀናቸዋል። የራሳቸው\nያልሆኑ ቢላ ቤቶችና ዘመናዊ መኪናዎች ፊት ተደንቅረው ወይም ባጋጣሚ ባገኟቸው ዝነኞች ጉያ ተሸጉጠው ፎቶ መነሳት ሆቢያቸው ነው። የየትኛውም ሃይማኖት ተከታይ ይሁኑ ለአምልኮት የሚሄዱት እጅግ የተዋበ ሕንፃ ወዳለው ማምለኪያ ስፍራ ነው። አንድ ነገር ውድ ከሆነ ታዋቂ ብራንድ ነው ብለው ያስባሉ። ዝነኞች ከፍተኛ ክፍያ ተከፍሏቸው የሚያስተዋውቋቸውን የንግድ ምል ክቶች እነርሱ ያለምንም ክፍያ በኩራት ገላቸው ላይ በቋሚነት ይነቀሷቸዋል። የማይታ\nወቅ የንግድ ምልክት ያለው አዲስ ልብስ መግዛት አይፈልጉም። ልምዱ ያላቸውን ቡቲኮች አስቸ ግረው ታዋቂ የሆኑ ብራንዶችን በውድ ዋጋ ከሰል ባጅ ተራ ያስመጣሉ። የብራንድ ነገር ውስጣቸው ነው። ደብዳቤው ብራንድ በሆነ ወረቀት ይጻፍ እንጂ ከሥራ መሰናበ ታቸው አያስጨንቃቸውም። ሁለት ሦስት ቅያሬ ልብስ ከሚኖራቸው ይልቅ ዳጎስ ያለ ዋጋ ያለው አንድ ብራንድ የሆነ ልብስ ቢኖራቸው ይመርጣሉ። ጉልት ገበያ ብትወስዷቸው እንኳን ብራንድ ቲማቲምና ድንች ከመፈለግ ወደኋላ አይሉም። የቀብር\nስነስርዓት ላይ እንኳን ከአጉል ልማ ዳቸው አይቆጠቡም፤ ኀዘኑን ረስተው ሳጥኑ ላይ በማፍጠጥ ብራንድ መሆኑንና አለመሆኑን ያጣራሉ። በአንድ ወቅት አንድ ናይጄሪያዊ አባቱን እጅግ ውድና ቅንጡ በሆነ የቤት መኪና መቅበሩ ዓለምን አስገርሞ ነበር። ያለጥርጥር ይህ ናይጄሪያዊ ከውድ ወዳዶች አንዱ ነው። ውድ ነገር ትኩረታቸውን ይስበዋል። እነዚህን ሰዎች የማድመጥ ዕድል ከገጠማችሁ በአሜሪካን አገር ባለ 18 ካራት የወርቅ መጸዳጃ ቤት ስለመሠራቱና ለጎብኚዎች ክፍት ተደርጎ ረዥም ጊዜ ሳይወስዱ እንዲጠቀሙ በት ሊደረግ እንደሆነ ይነግሯችኋል። ወይም\nደግሞ በዓለም ላይ ለአንድ ቀን አዳር በሚያስከፍለው ዋጋ ውድ የሆነው ሆቴል ጄኔቫ ውስጥ የሚገኘው ፕሬዚዳንት ዊልሰን ሆቴል መሆኑንና በዚህ ውድ ሆቴል የሚገኙት አስር ክፍሎች ለአንድ አዳር 65 ሺህ ዶላር እንደሚከፈልባቸው እየተደነቁ ይነግሯችኋል። ቀንቷቸው አንዳች ነገር ከገዙ ስልክ በመደወል የሚያውቁትን ሰው ሁሉ ካላገኘንህ ይላሉ። ለምን አላችሁኝ ? ሾው ለማሳየትና ስለዋጋው ሌክቸር ለማድረግ ነዋ ! ኪሳቸው በድርቅ ሲመታ ደግሞ ሳይነጋ ቅባቱ ሻይ ቤት ሄደው ዳቦ በሻይ እየነከሩ ይበሉና ቀትር ላይ ካልዲስ ካፌ በረንዳ ላይ ተኮፍሰው ይታያሉ። ሲያገኙም ሲያጡም ያውቁበታል አይደል ! አይ … ሱስ ! አዲስ ዘመን ግንቦት 16/2011የትናየት\nፈሩ", "passage_id": "cd2fc855879828ca01c091102cb1060a" }, { "passage": " በእውቀቱ ስዩም በ“እንቅልፍ እና ዕድሜ” ልብወለድ መጽሀፉ የኢትዮጵያው ንጉስ ሹማቸውን ‹‹…ከዛሬ ጀምሮ ሕዝቡ ያለውን ቃል አሰባስቦ በግጥም ብቻ እንዲያወራ ንገር፡፡ አሻፈረኝ እምቢ ብሎ ቤት የማይመታ ነገር የሚናገር ቤቱ ይወረስበታል ብለህ ተናገር፡፡›› (ገጽ21) ብለው አዋጅ እንዲታወጅ ያደርጋሉ፤ ታዲያ ‹‹ይህ በሆነ በሁለተኛው ቀን አንድ ገበሬ ግማሽ ቀን ሲያርስ ውሎ ወደ ቤቱ ከገባ በኋላ መደቡ ላይ ተደላድሎ ተቀምጦ በግራ እጁ አመዳም እግሩን በቀኝ እጁ ሆዱን እያከከ፤‹‹ኧረ ምሳ›› አለ ባል‹‹የበላኸውሳ!›› አለችው፡፡›› (ገጽ 22) ባልና ሚስቱም ቤት ለመምታት በሚል ያልፈለጉትን ሲያወሩ፣ አለመግባባት ውስጥ ይገባሉ፡፡ ንጉሱም ደርሰው ሲጠይቁ፤ አስሮ ገረፈኝ ብላ በግጥም ታስረዳቸዋለች፡፡ ንጉሡም፡-‹‹ሚስቱን የገረፈ አስከፋሽኝ ብሎይጠበቅበታል እንዲከፍላት ካሳ›› አሉ በልባቸው፡፡ ግን ቤት እንደማይመታ ሲያውቁ ሌላ ይፈልጉ ጀመር፡፡‹‹ሚስቱን የገረፈ አስከፋሽኝ ብሎያለምንም ምህረት ይሰቀል ተገድሎ!›› ካሉ በኋላ ፍርዱን አስፈጽመው ባጀብ ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡›› (ገጽ 23) ይለናል፡፡ ሰሞንኛ ማስታወቂያዎቻችን ያለ ግጥም ማስታወቂያ መስራት አይቻልም የተባሉ ይመስል ከመልዕክቱ ይልቅ ቤት ለመምታት መከራቸውን ሲበሉ ይታያሉ፡፡ ማስታወቂያ ሰሪዎችም ቤት በመምታት አባዜ ለመለከፋቸው ማሳያ የበእውቀቱ ምሳሌ በልክ የተሰፋች ትመስለኛለች፡፡ ከቤት መታ አልመታ አባዜ ስንወጣ ደግሞ ከአንድ አመት በፊት ባህልንና የህብረተሰቡን ኑሮ ያላገናዘበ ማስታወቂያ በቴሌቪዥን መስኮት ድንገት ሰማሁ፣ ምናልባት በደንብ አላደመጥኩት ይሆናል ብዬም ድጋሚ ለመስማት እጠብቅ ጀመር። ያው የማስታወቂያዎቻችን ነገር የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ ነውና በድጋሚ ሲተላለፍ ጆሮዬን ሰጥቼ አደመጥኩት፤ አንዲት ወጣት የምስራች ነጋሪ ይመስል ጮክ ብላ ለተሰበሰቡት ሰዎች እንዲህ ትላለች፤ ‹‹እንደ ወጥ ባሉ ቆሻሻዎች የመነቸኩ ልብሶችን …..›› ወጥ ከመቼ ወዲህ ነው ከቆሻሻነት የተመደበው? ወጥን ያህል ክቡርና የኢትዮጵያዊያን መደበኛ ምግብ ቆሻሻ ማለትስ ተገቢ ነው? አሁን ልጆች (ታዳጊ ህጻናት) ልብሳቸውን ወጥ ቢነካባቸው ቆሻሻ ነካኝ ወይስ ወጥ ነካኝ እንዲሉ ነው የተፈለገው?... የሚሉት ሀሳቦች ውስጤን ስለረበሹት በፌስ ቡክ ገጼ ላይ ‹‹ወጥ ምግብ እንጂ ቆሻሻ አይደለም…››የሚል ርዕስ ሰጥቼ ፃፍኩበት፡፡ ታዲያ ማስታወቂያውም ምክንያቱን ባላወቅሁት ሁኔታ ቶሎ ተቀየረና እንዲህ በሚል “ተሻሽሎ” ቀረበ፡፡ ‹‹በወጥ የመነቸኩ ልብሶችን….›› ለዚህም ነው በቴሌቪዥንና በሬዲዮ ጣቢያዎች የሚተላለፉት ማስታወቂያዎቻችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው በሚል የራስ ወዳዶች መርህ መመራት የጀመረው የሚል እምነት በውስጤ ማሳደር የጀመርኩት፡፡ ይህ ለምን ሆነ? እነዚህ ማስታወቂያዎች እንዴትስ የአየር ሰዓት ሊፈቀድላቸው ቻለ? መልስ የለኝም፡፡መገናኛ ብዙኃን ሀገርን በመገንባትም ሆነ ሕብረተሰብን በማነጽ ረገድ ትልቅ ሚና እንዳላቸው ግልጽ ነው፣ በሰለጠነው አለም ልጆች የሚያዩት ብቻ ጣቢያ እንዳለ መስማቴን አስታውሳለሁ ( “ሳያዩ ያመኑ…” እንዲል መጽሃፉ ሄጄ ባላይም የተነገረኝን አምኛለሁ)፣ በእኛ ሀገር ግን እንኳን ለልጆች ብቻ ተብሎ ጣቢያ ሊከፈትና ለአዋቂዎቹም የተከፈቱት ጣቢያዎች አዋቂዎቹን አልመጥን ብለው አለመግባባትን እያስነሱ ይገኛሉ፡፡ በዚህች እድሜ የማይለዩ ጣቢያዎች ባሉባት ሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ለህፃናትና ታዳጊዎች ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ይታመናል፡፡ ግደይ ገብረኪዳን በቅርቡ “አብዮት የሤራ ንድፈ ኃሳብ” በሚል ርዕስ ባወጣው መጽሐፉ (ገጽ 18) ላይ የመገናኛ ብዙሃንን ሚና እንዲህ ይገልጸዋል፤ ‹‹መገናኛ ብዙኃን የማህበረሰብ ቀራጮች ወይም መሃንዲሶች ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በመገናኛ ብዙሃን ቦታ የማይሰጠው እውነታ ሕልውና አይኖረውም፡፡ ዘመናዊው ግለሰብ ከሚያውቀው በላይ የአመለካከቱንና እምነቱን ስፋትና ጥልቀት የሚወስኑት አምኖ የሚከተላቸው መገናኛ ብዙሃን ናቸው፡፡ የመገናኛ ብዙሃን ዴስክ የዘመናዊው ዓለም የመስበኪያ መድረክ ወይም አውደ ምህረት ነው፡፡›› መገናኛ ብዙሃን ለሕብረተሰቡ ባላቸው የእለት ተለት ቅርበትና በሕብረተሰቡ በኩል ያላቸውን በጎ ምላሽ መሰረት አድርገው መልካምም ሆነ ተገቢ ያልሆነ መልዕክቶችን ቢያስተላልፉ ተቀባይነታቸው ያንኑ ያህል የጎላ ነውና የደራሲውን ሀሳብ እጋራለሁ፡፡ታዲያ ሰሞኑን በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ‹‹በቢራ ማስታወቂያ የሬዲዮና ቲቪ ጣቢያዎች ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው›› በሚል ርዕስ ያነበብኩት ዜና የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንን ማስጠንቀቂያ “ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ ይሉት ፈሊጥ ሆነብኝ፣ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የቢራ ማስታወቂያዎቹ የአየር ሰዓታቸውን ከጨረሱና ማስተላለፍ የፈለጉትን ነገር ሁሉ ለህዝቡ ካደረሱ በኋላ የሚተላለፉባቸው ጣቢያዎች ስህተታቸውን እንዲያስተካክሉ ማስጠንቀቅ ምን ይሉት ቀልድ ይሆን? ጣቢያዎቹ ከዚህስ በኋላ አለማስተላለፍ ይችሉ ይሆናል፡፡ ታዳጊ ህጻናት አዕምሮ ውስጥስ የተቀረጸውን በምን ማውጣት ይቻል ይሆን? ባለስልጣን መስሪያ ቤቱስ ማስጠንቀቂያ ሊሰጥባቸው የሚገባቸውና ታዳጊ ህጻናትን ከግምት ያላስገቡት ማስታወቂያዎችስ የቢራ ማስታወቂያዎች ብቻ ናቸው? ሌሎች ማስታወቂያዎች ስለ ታዳጊ ህጻናት የሚመጥኑ ሆነው ይሆን? በሚዲያዎቻችን ላይ ህጻናቱን ያካተቱት ማስታወቂያዎች ለታዳጊ  ህጻናቶች ምን ያስተምሩ ይሆን? እነዚህ ማስታወቂያዎችስ ላይ ማስጠንቀቂያ ሊሰጥበት አይገባም ነበር? ማስታወቂያዎቻችን ወደ ታዳጊ ህጻናቱ አዕምሮ ውስጥ በቀላሉ በመግባት ዕዳቸውን ለምስኪኑ ቤተሰብ አስተላልፈው አላለፉም?ለጥያቄዎቻችን መልስ ይሆነን ዘንዳ በቅርብ ጊዜ ታይተው የአየር ሰዓታቸውን ከጨረሱ ማስታወቂያዎችንን አንዱን መዝዤ ለማሳየት እሞክራለሁ፤ ማስታወቂያው የሰንሴሽን ኮንዶም ሲሆን በዚህ ማስታወቂያ አንድ ወጣት በመዝናኛ ስፍራ ውስጥ ሆኖ ሁለት ፍቅረኛሞችን ይመለከታል፣ ወዲያውኑ ስልኩን አንስቶ ወደ አንዲት ሴት (ፍቅረኛው ወይም ሚስቱ) “ናፈቅሽኝ” ብሎ የጽሁፍ መልዕክት እንደ ላከ፣ ሴቲቱም መልሳ “ናፈቅኸኝ” ብላ ትመልስለታለች፣ ይሄን ጊዜ ወደ ቤቷ ይሄድና ሲያንኳኳ ብቅ ስትል፤ ‹ያን ጊዜ ሰነሴሽን › የሚል ድምጽ ይመጣና ማስታወቂያው ያበቃል፡፡ በዚህ ጉዳይም በፌስ ቡክ ገጼ ላይ ጻፍኩ፣ ከአንባቢ ጋር ተወያየንበት፤ ከሁሉም ተወያዮች ግን ውስጤን የነካኝ ከአንዲት እናት በውስጥ መስመር (inbox) የተላከልኝ መልዕክት ነበር፡፡ እንዲህ ይላል፤ ‹‹አንተ ይህን ስትጽፍ ሰሞኑን እኔ ቤት ውስጥ የተፈጠረውን ነገር ሳላካፍልህ ማለፍ አልቻልኩምና ይህን ጽሁፍ በውስጥ መስመር ልሰድልህ ተገደደድኩ። ነገሩ እንዲህ ነው፡- ከሳምንት በፊት መስሪያ ቤት ሆኜ ልጄ ናፈቀኝና ሰራተኛዬ ጋር ደውዬ፣ ልጄን አገናኚኝ” አልኳት፡፡ ስልኩን ሰጠችው፣ ልጄ ሦስት አመት ከስምንት ወሩ ነው፡፡ ናፈቅሽኝ ሲለኝ እኔም “በጣም ነው የናፈቅኸኝ አልኩት፡፡ ይሄን ጊዜ ያልጠበኩትን ነገር ከልጄ ጣፋጭ አንደበት ሰማሁ፡፡ ‹‹ማሚ ያን ጊዜ ሰንሴሽን” አለኝ…. ታዲያ ይሄ ማስታወቂያ በህብረተሰቡ ውስጥ አልገባም? የዚህስ ማስታወቂያ ጥላ በየቤቱ አጥልቶ አላለፈም? እነዚህ ማስታወቂያዎችስ ታዳጊ ህጻናትን ከግምት ውስጥ ያላስገቡ አይደሉም? የገንዘብ ጥቅምን ብቻ ታሳቢ በማድረግ በህዝብ ዘንድ ቅሬታን ሊያስነሱስ አይችሉም? ሳይቃጠል በቅጠል ነውና ነገሩ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በቢራ ማስታዎቂያዎች ላይ ብቻ ዘግይቶ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ በሌሎች ማስታወቂያወችም ላይ ያለ አንዳች መዘግየት ይሰጥ ዘንድ እንደ ዜጋ ላስታውሰው እሻለሁ፡፡", "passage_id": "f5c02dcb226caa2dbf688ec12c4da7c2" }, { "passage": "13 ሺህ የሚሆኑ ደግሞ ጉዳዮን በማስመልከት ችማማንዳ ፌስቡክ ገጿ ላይ ላሰፈረችው ፅሁፍ በተለያየ መንገድ ምላሽ ሲሰጡ ሦስት ሺህ አስተያየቶችም ተሰጥተዋል።\n\nባለፈው ሃሙስ ፓሪስ ላይ በተደረገ የቀጥታ ስርጭት ቃለ-ምልልስ ነበር ቺማማንዳ ከጋዜጠኛዋ ጥያቄው የቀረበላት።\n\nየቺማማንዳ መልስ \"በጣም በሚያስገርም መልኩ ያነባሉ\" የሚል ነበር። መፅሃፏ በናይጄሪያ ብቻም ሳይሆን በመላው አፍሪካ እንደሚነበብም ጨምራ ገልፃለች።\n\nበምርጥ ፀሃፊነቷ ዓለም ለሚያውቃት፣ በርካታ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ላገኘቸውና በአሜሪካና በአውሮፓ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት ለተሰጣት ቺማማንዳ የዚህ አይነት ጥያቄ ማቅረብ የጋዜጠኛዋን ዝግጅት ከማድረግ ይልቅ ግምቷን ይዛ ወደ ቃለ መጠይቁ መግባቷን አጋልጧል።\n\nጋዜጠኛዋ ፈረንሳይ ውስጥ ስለ ናይጄሪያ የሚነገረው ሁሉ ስለ ቦኮ ሃራምና ብጥብጥ ብቻ እንደሆነ በመጥቀስ ጥያቄዋን መሰረት ለማስያዝም ጥራ ነበር።\n\nጋዜጠኛዋ ስለ ናይጄሪያ ሥነ-ፅሁፍና የንባብ ባህል ግምቷን መሰረት አድርጋ ያቀረበችው ጥያቄ የፈረንሳይ ህዝብን ገፅታ የሚያበላሽ እንደሆነ ቺማማንዳ ተናግራለች።\n\nበጋዜጠኛዋ የተበሳጩ ናይጄሪያዊያን እውቅ ፀሃፊ ዎሌ ሾይንካ፣ ቺንዋ አቼቤንና ቤን ኦርኪን በመጥቀስ ስለ ናይጄሪያ የሥነ-ፅሁፍ ከፍታ ለማስታወስ ተገደዋል።\n\nበዚህ ዘመን አንብቦ ከመዘጋጀት ይልቅ ግምቱንና የራሱን ውስን የዓለም አተያይ መሰረት አድርጎ የሚሰራ ጋዜጠኛ መኖር አሳዛኝ እንደሆነ አስተያየታቸውን የሰጡም በርካቶች ናቸው።\n\nከቺማማንዳ መፅሃፎች አሜሪካና እና ፐርፕል ሄቢስከስን መጥቀስ ይቻላል።\n\n\"ዊ ሹድ ኦል ቢ ፌሚኒስትስ\" የሚለው የቴድ ኤክስ ንግግሯ ደግሞ ወደ መፀሃፍ ተቀይሮ ስዊድን ውስጥ ለ16 ዓመት ልጆች በሙሉ ተሰጥቷል። \n\nየንግግሩን ሃሳብ ቢዮንሴም በአንድ ዘፈኗ አካታዋለች።\n\n ", "passage_id": "86a3ebb4b43279127f3cebcb330b2ff4" } ]
0012a8763d6f5bb58290c93249b38779
b13c6fb00ac903f9d14d20ac0e6a3e3f
ኮሚሽኑ ኮቪድ 19ን ለመከላከል የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል
የዓለም ህዝብ ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) የሚያስከትለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለመቋቋምና ለመከላከል መተጋገዝ አስፈላጊ መሆኑ ተደጋግሞ ይነገራል። በዚህም ምክንያት የተለያዩ አካላት በዓይነት፣ በገንዘብ እንዲሁም ባለሙያዎችም በጉልበታቸው ጭምር ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። የስፖርት ዘርፍም በዚህ እንቅስቃሴ ቀዳሚ ተሰላፊ መሆኑ ታይቷል። የስፖርት አመራሮች፣ የስፖርት ማህበራት፣ ስፖርተኞች፣ አሰልጣኞች እንዲሁም ደጋፊዎቻቸው፤ መልእክት በማስተላለፍ፣ በየቤታቸው ላሉ ዜጎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማሰራት፣ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ፣ የምግብና ሌሎች መገልገያዎችን በመለገስ እንዲሁም በሌሎች ተግባራት ላይ እየተንቀሳቀሱ ነው። ዘርፉን የሚመራው የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽንም ይህን እንቅስቃሴ በማስተባበር እንዲሁም እንደ አንድ ባለድርሻ አካል በሚጠበቅበት ሁሉ የራሱን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል። ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተሰማበት ጊዜ አንስቶ የመንግስትን አቅጣጫ በመከተል የተለያዩ እርምጃዎችንም ወስዷል። በቅድሚያም ህዝቡን በብዛት በማሳተፍ ቫይረሱን በማሰራጨት ረገድ ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችል ስጋት የሚያሳድሩ የእግር ኳስና ሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮችን ማቋረጥ ነው። በቀጣይም በየክለቦቹ እንዲሁም በማሰልጠኛ ተቋማት ያሉ ሰልጣኞች ወደ የአካባቢያቸው በመሄድ ራሳቸውን በየቤታቸው እንዲያቅቡ ማድረግ ነው። በቀጣይም የቶኪዮ ኦሊምፒክ ብሄራዊ ቡድኑን አባላት መበተንን ጨምሮ የተለያዩ የቡድን እንቅስቃሴዎች በስፖርቱ ዘንድ እንዳይካሄዱ ማገድ ነው። ከዚህ በኋላም ስፖርተኞችና ማህበራት በግላቸውና በቡድን ከሚያደርጉት እገዛ ባሻገር በስሩ ያሉትን አካላት በማስተባበርና በማቀድ እየሰራ ይገኛል። ኮሚሽኑ በዋናነትም አራት ተግባራትን በመለየት ኃላፊነቱን እየተወጣ እንዳለም ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ገልጸዋል። ይኸውም የገንዘብ ድጎማ፣ በስፖርት ቤተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጥ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በመገናኛ ብዙሀን ማስተላለፍ እንዲሁም የማሰልጠኛ ተቋማት ቫይረሱን ለመዋጋት በሚደረገው እንቅስቃሴ አንድ አካል እንዲሆን የማድረግ ትብብር ነው። የገንዘብ ድጎማውን ተከትሎም የስፖርት ማህበራት በግላቸው ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በኮሚሽኑ አስተባባሪነት ከአገር አቀፍ ስፖርት ማህበራትና የአትሌቶች ማህበር ጋር በመሆን የተደረገውን የሶስት ሚሊየን ብር ድጋፍ ጨምሮ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስና እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን፣ የወጣቶች ስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ በጥቅሉ ወደ 15 ሚሊዮን የሚሆን ብር ለብሄራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስረክቧል። አቅም ለሌላቸው ዜጎች የሚውሉ የምግብና የንጽህና ቁሳቁሶችንም በተመሳሳይ ገቢ ማድረግ ተችሏል። ለህብረተሰቡ እንዲሁም ለስፖርት ቤተሰቡ ግንዛቤ በማስጨበጥ ረገድም የተለያዩ ስራዎች ተከናውነዋል። ታዋቂና ተጽእኖ ፈጣሪ የስፖርት ሰዎችን በመጠቀም ተደራሽነታቸው ሰፊ በሆኑ የመገናኛ ብዙሃን ትምህርታዊ ማስታወቂያዎች እየተላለፉም ይገኛል። ሌሎች ስፖርተኞችም በተመሳሳይ በግላቸውና በቡድን በመሆን ግንዛቤ በማስጨበጥ ላይ ይገኛሉ። ከዚህ በተጓዳኝ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ቫይረሱን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት በመሆኑ ኮሚሽኑ በመገናኛ ብዙሃን ለማስተላለፍ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለአትሌቶች የሚሰጠው ምክርና አቅጣጫም ለዚህ ተጠቃሽ ነው። የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚንና የጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከልን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የስልጠና ማዕከላትን ከቫይረሱ ጋር በሚደረገው ጦርነት በተፈለጉ ጊዜ እንዲያገለግሉ ዝግጁም ተደርጓል። ሌላው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ይፋ የተደረገው የምገባ መርሃ ግብር ነው። በዚህም 300 ለሚሆኑ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያና ሌሎች አካባቢዎች ለሚገኙ ጎዳና ተዳዳሪዎች ለአንድ ወር የሚቆይ የምገባ መርሃግብር ነው። በቀጣይም ኮሚሽኑ በምን መልኩ መደገፍ እንዳለበት ከስፖርት ማህበራትና ተጠሪ ከሆኑት ተቋማት ጋር ውይይት በማድረግ ጉድለት ያለባቸው ቦታዎችን በመለየት ድጋፉን የሚቀጥል መሆኑን ኮሚሽነሩ አረጋግጠዋል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 22/2012ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=31441
[ { "passage": "አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ሲጀመሩ አስፈላጊው የኮቪድ 19 መከላከያ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የኢፊዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ።በትናንትናው ዕለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ስፖርታዊ እንቅስቀሴ ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ እንዲነሳ መወሰኑን ተከትሎ የኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ ዱቤ ጅሎ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል ፡፡በኢትዮጵያ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ሲባል ስፖርታዊ ስልጠናዎች፣ ውድድሮች በአጠቃላይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ መደረጉ ይታወቃል ፡፡የኢፊዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጅሎ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች መፈቀዳቸውን አስመለክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።በመግለጫቸው አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የስፖርት እንቅስቃሴዎችን ወደ ነበረበት ለመመለስ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን እና የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ መሠረት በማድረግ የኢፊዴሪ ስፖርት ኮሚሽን በአዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ለሚመለከተው አካል ፍቃድ እንዲሰጥ መቅረቡን ገልጸዋል።በዚህም ፕሮቶኮሉን መነሻ በማድረግ እና የጤና ሚኒስቴር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ምክረ ሀሳብ መሰረት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲጀመሩ ተወስኗል ብለዋል ፡፡ነገር ግን ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ሲጀመሩ አስፈላጊው የኮቪድ -19 መከላከያ መንገዶች እና ጥንቃቄዎች ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡በተለይም ስልጠናዎች እና ውድድሮች ከመጀመራቸው በፊት ከማዘውተሪያ ዝግጅት ፣ የሰው ሀይል ቁጥር እና ሌሎች አስፈላጊ የመከላከያ ግብዓቶች መሟላታቸው ሊረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል ፡፡የሀገር አቀፍ ስፖርት ማህበራት ስፖርቱን ሲያስጀምሩ በኮሚሽኑ እና በጤና ሚኒስቴር የወጣውን መመሪያ በየደረጃው ስራ ላይ እንዲውል ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸው መጠቆማቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።ይህን የሚከታተልም የብሔራዊ ኮሚቴ ፣የጤና እና የፀጥታ ኮሚቴ ተቋቁሞ አስፈላጊው ክትትል ይደረጋል ብለዋል ፡፡በተዋረድም በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮችም ኮሚቴዎች ተቋቁመው ክትትል እና ድጋፍ እንደሚደረግ አስታውቀዋል ፡፡መመሪያውን ተላልፎ የሚገኝ አካል ላይም አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድ አሳስበዋል ፡፡ከዚህ ባሻገር ኮሚሽኑ ስፖርቱን በአሠራር እና በአደረጃጀት ለማስተካከል እና ውጤታማ ለማድረግ ሀገር አቀፍ የስፖርት ሪፎርሙን መሠረት በማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰራ በመግለጫቸው አንስተዋል ፡፡", "passage_id": "d36f7e4dd93305b694e2a6e735528a28" }, { "passage": "አዲስ አበባ፡- ለኮቪድ 19 መከላከል ሥራ እስካለፈው ዓርብ ድረስ ወደ 180 ተቋማትና 400 ሚሊዮን የሚደርስ ብር በድጋፍ መሰብሰቡን የአገር አቀፍ ኮቪድ 19 ዋና ግብረ ኃይል ኮሚቴ አባልና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ድጋፍ ለማድረግ የሚደረገው ርብርብ የሚበረታታ ቢሆንም የተገኘው ድጋፍ ግን አነስተኛ እንደሆነ አመልክተዋል።ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፤ እስካለፈው ዓርብ ድረስ ወደ 180 ተቋማት ድጋፍ አድርገዋል። ከእነዚህም ውስጥ መቶ ያህሉ የመንግሥት ተቋም ሲሆኑ፣ 80ዎቹ ደግሞ የግል ተቋማት ናቸው። ከእነዚህ መካከል የማምለኪያ ቤተ ክርስትያኖች፣ ኮሌጆች፣ የግለሰብ መኖሪያዎችና የተለያዩ ሕንፃዎቻቸውን ለዚህ ለድንገተኛ ወረርሽኝ ለይቶ ማቆያነት ይዋል ብለው መስጠታቸውንም ገልጸዋል። ከዚህ አንጻር የመላው ሕዝብ ርብርቡ “ጥሩ ነው ማለት ይቻላል “ ብለዋል።‹‹በገንዘብ ደረጃም እስከአሁን ድረስ በፌዴራል ደረጃ የተቋቋመው ኮሚቴ እጅ የገባ 400 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ገንዘብ ተሰብስቧል›› ያሉት ጠቅላይ ዓቃቤ ህጓ፣ ከዚህ ውጪም የእህል ፣ የንፅህና መጠበቂያ እቃዎችን እና የሌሎችም ዓይነት ድጋፎች በአዲስ አበባም ሆነ በክልል ደረጃ መሰብሰባቸውን አስታውቀዋል። ‹‹የተደረገውም ድጋፍ ሲደማመር የሚናቅ ሳይሆን የሚያስመሰግን ነው›› ብለዋል። \n‹‹ ወረርሽኙ በባህሪው የሚፈልገው ብዙ ነገር ነው። ለምሳሌ ሕንፃ በስጦታ አግኝተናል ሕንፃውን ማግኘት በራሱ በቂ አይደለም። ወደ ሕንፃው የምናመጣው ሰውሌላ ድጋፍ ይፈልጋል። የምግብ ፣ የልብስ፣ የንጽ ሕና መጠበቂያ እቃዎችን .. ወዘተ ። ለእነዚህና መሰል ድጋፎች ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ያስፈልጋል። ‹‹እነዚህን ሁሉ ከግምት ስናስገባ የሚያስፈልገው እርዳታ ከፍ ያለ እንደሚሆን መገመት አይከብድም ከዚህ አንጻር እስካሁን የተሰበሰበው ድጋፍ ገና ትንሽ ነው ለማለት ያስደፍራል ›› ሲሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ህጓ አመልክተው፤ ‹‹በተለይ በገንዘብ በኩል የተሰበሰበው ገና ትንሽ ነው ›› ብለዋል። ከምንም በላይ ካለንበት ችግር ለመውጣት ትልቁ አቅም ስለበሽታው ምንነት በአግባቡ ተረድተን መከላከሉ ላይ በርትተን መስራት ነው ። ይህ ደግሞ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነትና ግዴታ ጭምር ነው። በእርግጥም የእግዚአብሄር ኃይል እንደተጠበቀ ሆኖ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የወጡትን ህጎችና መመሪያዎች በመቀበል ራስን ለህጎቹና መመሪያዎቹ በታማኝነት ተገዥ ማድረግ ለመከላከሉ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለውም ገልጸዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 13/2012 አስቴር ኤልያስ", "passage_id": "b45df7e2f25738dd3725fbab66cc7164" }, { "passage": "በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል አቅመ ደካሞችን ለመርዳት ማኀበሩ ለስፖርት ቤተሰቡ የድጋፍ ጥሪ አቅርቧል።የጤና ባለሙያዎች የሚያስተላልፉትን መልዕክት እንጠብቅ የሚለው ማኅበሩ ጎን ለጎን የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች የሌላቸውን የጎዳና ተዳዳሪዎችን (አቅመ ደካማዎችን) ለመደገፍ የማኅበሩ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት እና ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ማኀበራዊ ኃላፊነታችንን እንወጣ ሲሉ እያንዳንዳቸው በግል 300 ሳሙና ለመለገስ የወሰኑ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ይህን በጎ ተግባር ለማገዝ የሚፈልጉ ሌሎች አባላቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሒሳብ ቁጥር ተጠቅመው መደገፍ እንደሚችሉ ተገልጿል፡-© ሶከር ኢትዮጵያ", "passage_id": "cd22c2e8e84fb0e429f787d1b8ff8b58" }, { "passage": " በመላው ዓለም የኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ-19) ለመዋጋት የሚደረገው ርብርብ እንደቀጠለ ነው። በኢትዮጵያም የስፖርት ቤተሰቡ ተሳትፎ ገና ከጅምሩ አበረታች የሆነ መንገድ ያሳየ ሲሆን፤ እውቅ ስፖርተኞችና የስፖርት ማህበራት ድጋፋቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦችና ተጫዋቾች በገንዘብና በዓይነት ድጋፋቸውን በመስጠት ላይ ካሉት መካከል በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ። የሃዲያ ሆሳዕና እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞችና የጽህፈት ቤት ሰራተኞች የደመወዛቸውን 50 በመቶ መስጠታቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል። በዚህም 443 ሺ 366 ብር ስርጭቱን ለመቆጣጠር ለሚቋቋመው ግብረ ኃይል አበርክቷል። የጅማ አባጅፋር እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች እና አጠቃላይ የክለቡ ሠራተኞች 130 ሺ ብር ድጋፍን አድርገዋል። የድሬዳዋ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾችና አባላት በበኩላቸው ሙሉ ደመወዛቸውን ለዚሁ ዓላማ እንዲውል ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ታውቋል። የሲዳማ ቡናው አጥቂ አዲስ ግደይ፣ የመከላከያው አጥቂ ሀብታሙ ወልዴ፣ የጅማ አባጅፋሩ አማካይ ንጋቱ ገብረስላሴ፣ የሃላባ ከተማው ልመንህ ታደሰ እና የጅማ አባጅፋር ተከላካይ መላኩ ወልዴ በጋራ ለትውልድ ከተማቸው አጋሮ በጥሬ ዕቃ ድጋፋቸውን አድርገዋል። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች 80 ሺ ብር የሚገመት የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ማስረከባቸውን ለማወቅ ተችሏል። ከዚህ በተጨማሪም ቆሼ ተብሎ ወደ ሚጠራው ስፍራ በመጓዝ ለ541 አቅመ ደካሞች ርዳታ ሰጥተዋል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ኮሚሽኑን ጨምሮ በስሩ የሚገኙ የስፖርት ማህበራት ድጋፋቸውን አጠናክረው ከቀጠሉት መካከል ይገኛሉ። በከተማው የውሹ ፌዴሬሽን 45 ሺ 800 ብር በከተማ ደረጃ ለተቋቋመው ኮሚቴ የሚውል ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ስፖርት ኮሚሽነር አበርክቷል። ከዚህም ውስጥ በስራ አስፈፃሚው ውሳኔ ፌዴሬሽኑ 20 ሺ ብር፣ 15 ሺ 800 ብር እና የምግብ ግብዓቶች ከክለብ አሰልጣኞች እንዲሁም የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ማስተር ፍሬህይወት ሽታዬ በግላቸው 10 ሺ ብር አበርክተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽንም በስሩ ያሉ ማዕከላትን እስከ ታችኛው የወረዳ መዋቅር ድረስ ለቅድመ መከላከልና መቆጣጠር ለሚያስፈልጉ ተግባራት ሁሉ እንዲውሉ መወሰኑ ይታወቃል። ከዚህ መካከል አንዱ የሆነው የጃን ሜዳ ስፖርት ማዕከል በጊዜያዊነት ወደ አትክልት ተራነት ተዘዋውሮ ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል።አዲስ ዘመን መጋቢት 27/2012ዳንኤል ዘነበ", "passage_id": "c7359f79daf14553b513a2b8d155ceab" }, { "passage": "አዲስ አበባ ፦ የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን በመከላከል ረገድ በሁሉም ዘርፍ እየተሰራ ያለውን ውጤታማ ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ ። ወረርሽኙን መንግሥት ብቻውን መከላከል የማይችል በመሆኑ ህዝቡ ከመንግሥት ጎን ተሰልፎ በሽታውን እንዲከላከል አሳሰቡ:: \nየኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተቋቋመው ብሄራዊ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ትናንት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በተለያዩ ንዑስ ኮሚቴዎች ሲሰሩ የቆዩ ሥራዎችን በመገምገም በቀጣይ መሰራት ባለባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጧል። \nኮሚቴው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም፣ በጤና፣ በኢኮኖሚ፣ በትራንስፖርት፣ በቴክኖሎጂ፣ በውጭ ጉዳይ ላይ እና በሽታውን ለመከላከል እየተደረገ ካለው የድጋፍ አሰባሰብ ጋር ያሉ ሥራዎችን በሚመለከት ሪፖርት አድምጧል ። \nበወቅቱም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፤ በመንግሥት በኩል ግንዛቤ የመፍጠር ሥራዎች እና በሽታውን ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደው ለውጥ የመጣ ቢሆንም አሁንም በሚፈለገው ልክ እንዳልሆነ ተናግረዋል። \nለአብነትም የገበያ እና የትራንስፖርት አጠቃቀም ላይ ያለውን የህዝብ ጭንቅንቅ በማንሳት በሽታው የከፋ አደጋ ሳያስከትል በፍጥነት ማረምና ማስተካከል እንደሚገባ አመልክተዋል ። \nየጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው፤ የላቦራቶሪ መመርመሪያ አቅምን ማሳደግ በመቻሉ አዲስ አበባን ጨምሮ በክልሎች 24 ላብራቶሪ እና 27\n መመርመሪያ መሳሪያ ስለ መኖሩ ጠቁመዋል።\nበቤት ለቤት ልየታ እስካሁን 3 ነጥብ 6 ሚሊዮን ቤቶች መጎብኘታቸውን እና በቤት ለቤት ልየታ አዲስ አበባ፣ ትግራይ እና አሮሚያ ክልሎች ጥሩ እንደፈጸሙ አስታውቀዋል ። \nእስከ ዛሬ ድረስ 133 በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ስለመገኘታቸው እና ከእነዚህ ውስጥ 66 ሰዎች ከቫይረሱ ስለማገገማቸው ተናግረዋል።\nየገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በበኩላቸው ወረሽኙን ለመከላከል 15 ቢሊዮን ብር የበጀት ሽግሽግ እንደተደረገና በአጠቃላይ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ከ2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ሀብት የማሰባሰበ ሥራ እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል ።\nበመደበኛ የነበረው 15 ሚሊዮን ተረጂ በኮቪድ-19 ምክንያት 15 ሚሊዮን ተጨምሮበት 30 ሚሊዮን ህዝብ እርዳታ የሚያስፈልገው በመሆኑ ይሄንን ችግር ለመፍታት በአዲስ አበባና በክልሎች የምግብ ባንክ መቋቋሙን አስታውቀዋል ።\nየሀብት ማሰባሰብ ንዑስ ኮሚቴ በክልል እና በፌዴራል እስካሁን ከ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር መድረሱን እና 40 ሚሊዮን የሚሆን ደግሞ በአይነት መገኘቱን የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል አስታውቀዋል። የምግብ ክምችት እና ስርጭት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።\nየኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም በበኩላቸው ፤በቦሌ አየር ማረፊያ በኩል ወደ አዲስ አበባ በቀን በአማካኝ የሚገቡ ሰዎች ቁጥር 30 ሰው ብቻ መሆናቸውን እና በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ለ14 ቀናት የሚገቡ ስለመሆናቸው ገልፀዋል።\nአየር መንገዱ በጭነት አገልግሎት ጥሩ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንና በአትክልትና አበባ እንዲሁም በስጋ ምርቶች ላይ የትራንስፖርት ፍላጎት መጨመሩ ለአየር መንገዱ ገቢ እያስገኘ መሆኑን ጠቁመዋል። \nጠቅላይ ሚኒስትሩ የእያንዳንዱን ዘርፍ የስራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ካደመጡ በኋላ በሰጡት የሥራ መመሪያ፤ ኮቪድ-19 በመከላከል ረገድ በሁሉም ዘርፍ እየተሰራ ያለው ውጤታማ ሥራ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል ። \nከጤና አንፃር ከኮቪድ-19 ውጪ ያሉ በሽታዎችንም በእኩል ሁኔታ የሚሰሩበት ሁኔታ መፍጠር እንደሚያስፈልግ አመልክተው ለዚህም የተቋማትን ምላሽ የመስጠት አቅምን መፈተሽ እንደሚገባ ተናግረዋል።\nአየር መንገዱ ከሌሎች አገሮች አንፃር ይሄ ነው የሚባል ድጋፍ ሳይደረግለት ራሱን ችሎ መቆሙን አድንቀው ፤ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ማዕከል መሆኗን ያረጋገጠ ስለመሆኑም ገልፀዋል።\nአየር መንገዱ አገሪቱ በክፉ ጊዜ የምትጠቀምበት ብቸኛ አማራጭ በመሆኑ አቅሙን አጎልብቶ እየሰራ ያለውን ውጤታማ ሥራ ማጠናከር ይገባዋልም ብለዋል።\n‘’በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የመዘናጋት ሁኔታዎች ይስተዋላል’’ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት የወሰዳቸውን ርምጃዎች በትክክል ማድረስ እንደሚገባና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከመንግሥት ጎን ቆሞ ወረርሽኙን እንዲከላከል ጥሪ አቅርበዋል።\nህግ አስከባሪዎች የወጣውን አዋጅ በትክክል ማስተግበር እንዳለባቸውና ዜጎችም ለህግ ተገዥ እንዲሆኑ በማሳሰብ ጥቃቱን መንግሥት ብቻውን ሆኖ መመከት የሚችል ባለመሆኑ ህዝቡ ከመንግሥት ጎን ተሰልፎ በሽታውን እንዲከላከል መልዕክት አስተላልፈዋል።\nበትራንስፖርት በኩል ያለውን ችግር ለመፍታት የመንግሥት ተቋማት ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 24/2012", "passage_id": "1afbf787e8cabc4c7b0a37f24ba1c5e1" } ]
7c34f74c12242599e16f33349d00b40f
c6132eb1ae8632b1cb425d11c6f98a83
የጃፓን መንግሥትና የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውዝግብ
የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ለአስራ ስድስት ወራት በመራዘሙ ምክንያት የአዘጋጅ አገሯ ጃፓን መንግሥትና የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ገና ከጅምሩ በርካታ ውስብስብ ችግሮች ውስጥ መዘፈቃቸው ሲነገር ቆይቷል። የኦሊምፒክ ውድድሩ በዓለም ላይ ከፍተኛ ስጋት በፈጠረው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር ተያይዞ ወደ ቀጣዩ ዓመት መራዘሙ ግድ መሆኑ ከታመነበት ወቅት አንስቶ አዘጋጆቹ በርካታ ፈተናዎችን መጋፈጣቸው የማይቀር ሆኗል። በተለይም ላለፉት ሰባት ዓመታት የበለጠ ዝግጅት ሲደረግበት የቆየው የኦሊምፒክ ውድድር መራዘሙ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ማስከተሉ የአዘጋጆቹ ራስ ምታት እንደሚሆን ቀድሞም የታወቀ ነው። ይህ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ የጃፓን መንግሥትንም ይሁን ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴን በእጅጉ ሊፈትን እንደሚችል በባለሙያዎች አስተያየት ሲሰጥበት የቆየ ሲሆን ሁለቱ አካላት ኪሳራውን ለማካካስ እንደሚደጋገፉና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ለዚህ እንዲዘጋጁ ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንዲህ ዓይነት ችግሮች ሲገጥሙት ትልቅ ተቋም እንደመሆኑ የመድህን ዋስትና እንዳለው ይታወቃል። አሁን የገጠመው ግን ካለው የመድህን ዋስትና አቅም በላይ በመሆኑ ነው እዚህ ችግር ውስጥ የተዘፈቀው። ስለዚህ የመድህን ዋስትናው በሕጉ መሠረት የሚሸፍነው ኪሳራ እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ ኪሳራውን የሚያካክስበት አንድ ነገር መፈጠሩ የግድ ይሆናል። ይህንን ተጨማሪ ኪሳራ የጃፓን መንግሥት እንደሚሸፍን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ቀደም ሲል በተለያዩ አጋጣሚዎች መስማማታቸው ቢገለፅም አሁን የሃሳብ ለውጥ እንዳደረጉ የሚጠቁሙ መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ ውዝግቦች ተነስተዋል። የዓለም አቀፍ ኮሚቴው ፕሬዚዳንት ቶማስ ባኽ ሰሞኑን ከአንድ የጀርመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ እንደጠቆሙት፣ ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ከጃፓን መንግሥት ጋር በተስማማው መሠረት ለሚደርሰው በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች የሚገመተውን ኪሳራ ለመሸፈን የራሱ ድርሻ አለው። ተጨማሪ የተባለውን ኪሳራ የመሸፈን ግዴታ ያለበት ደግሞ የጃፓን መንግሥት ነው። ይህን ስምምነት ሁለቱ አካላት እአአ 2013 ላይ እንዳደረጉ ቢገለፅም የጃፓን ካቢኔ አባላት ዋና ፀሐፊው ዮሺሂዴ ሱጋ ስምምነቱ እንዳልተደረገ አስተባብለዋል። ይህንንም ተከትሎ በሁለቱ አካላት መካከል ውዝግብ የተፈጠረ ሲሆን ተጨማሪ የተባለው ኪሳራ እስከ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል የጃፓኑ ክዮዶ ኒውስ ዘግቧል። የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ አዘጋጅ ቃል አቀባይ ማሳ ታካያ በበኩላቸው የጃፓን መንግሥት፣ የኦሊምፒኩ አዘጋጅ ኮሚቴና ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውድድሩ በመራዘሙ ሊገጥሙ የሚችሉ እንቅፋቶችን በጋራ እንደሚወያዩና መፍትሄ እንደሚያስቀምጡ ተናግረዋል። ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ብቻ የጃፓን መንግሥትን ጨምሮ በርካታ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ውስጥ እንደሚገቡ ቀደም ሲል ተዘግቧል። የጃፓኑ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴም ገና ከመጀመሪያው ከፍተኛ ኪሳራ ሊገጥም እንደሚችል መናገሩ ይታወሳል። ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለዚህ ኪሳራ ስጋት ሰላሳ ሦስቱንም ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኖች የሚመለከት መድህን የገባ ቢሆንም በቂ እንደማይሆን ታምኖበታል። ፕሬዚዳንቱ ቶማስ ባኽም ኦሊምፒኩ መራዘሙን በገለፁበት ወቅት ከባድ ኪሳራ እንደሚኖር በማመን ሁሉም ባለድርሻ አካላት መስዋዕትነት መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ለመጠቆም ሞክረዋል። ከባዱን መስዋዕትነት ማን እንደሚከፍልና ጫናው በየትኛው ወገን ትከሻ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ግን ከመጀመሪያውም ግልፅ አልነበረም። አሁን ላይ ገና ኦሊምፒኩ አስራ አምስት ወራት ገደማ እየቀሩትም ሁለቱ አካላት ውድድሩ በመራዘሙ የገጠማቸውን ውስብስብ ችግሮች ከመፍታት ይልቅ ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ባለው ጉዳይ ላይ መነታረ ክ ጀምረዋል። የተለያዩ ተንታኞች እንደሚናገሩት ከሆነ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በዓለም ላይ ሙሉ ለሙሉ እስከ ቀጣዩ ዓመት በቁጥጥር ስር ካልዋለ ኦሊምፒኩ በተራዘመበት 2021ም ላይካሄድ ይችላል። ከዚህም በዘለለ የመሰረዝ ዕድል ሊገጥመው ይችላል። ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ብቻ በሚገጥመው ኪሳራ ትልቅ ውዝግብ የሚነሳ ከሆነ ከነጭራሹ ከተሰረዘ የሚገጥመው ኪሳራም በቀላሉ የሚሰላ እንደማይሆን ይታመናል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 17 / 2012 ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=31115
[ { "passage": "የኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ 19) በዓለም ላይ በከፍተኛ ፍጥነት መሰራጨቱን ተከትሎ የሁሉም ዓለም አቀፍ የስፖርት መርሐግብሮች እንዲቋረጡ አድርጓቸዋል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ተከትሎ የስፖርቱ ዓለም ካለፉት ሁለት ወራት በላይ ተቋርጦ እንዲቆይ አድርጎታል። የውድድሮቸ መቋረጥና መርሐ ግብሮች መራዘማቸውን ተከትሎ የስፖርቱን ኢንዱስትሪ ክፉኛ እንደጎዳው ዓለም አቀፍ ጥናቶች ከወዲሁ ያመላክታሉ። ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በመቆማቸው ምክንያት የሚደርሰውን ኪሳራ በመጠኑም ቢሆን ለማዳን ውድድሮችን በዝግ ስታዲየም ማድረግ አማራጭ ተደርጓል። ከቫይረሱ ስጋት ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆን ባይችሉም ታላላቆቹን አውሮፓ እግር ኳስ ሊጎች ጨምሮ አንዳንድ አገራትም ስፖርታዊ ውድድሮቻቸውን ከሰሞኑ አስጀምረዋል። ውድድሮችን በዝግ ስቴድየሞች በማድረግ የውድድር ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት መርሐግብሮቻቸውን ለማጠናቀቅ ጨዋታዎችን እያደረጉ ይገኛሉ። \nበአውሮፓ እግር ኳስ ሊጎች የተወሰደውን መፍትሔ የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተግባራዊ ሊያደርገው እንደሚችል ቢቢሲ ዘግቧል። የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሰባስቲያን ኮዬ ፤ የአትሌቲክስ ስፖርት ሲመለስ በባዶ ሜዳዎች ሊካሄድ እንደሚችል ማስጠንቀቃቸውን መሰረት ያደረገው ዘገባው፤ «በታላላቆቹን አውሮፓ እግር ኳስ ሊጎች ከሰሞኑ እንደተመለከትነው ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮችም በቅርቡ ሊመለሱ ይችላሉ »ሲል አስነብቧል የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቲክስ ስፖርት ሲመለስ በባዶ ሜዳዎች ሊካሄዱ እንደሚችሉ ከማስገንዘብ በተጨማሪ ፤ውድድሮች ስለሚመለሱባቸው ሁኔታዎች በተመለከተ ሃሳብ መስጠታቸውን አመልከቷል። በዚሁ ላይም «ዓመታዊው የዳይመንድ ሊግ እንዲሁም የተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች ሁኔታዎች ከተገመገሙ በኋላ በመጪው ነሐሴ አጋማሽ እንዲካሄዱ እቅድ ተይዟል። በነሐሴ እንዲካሄዱ እቅድ የተያዘላቸው አስራ አንዱ የተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች በዝግ ሜዳ ይሆናሉ » ሲሉ መናገራቸውን ጽፏል። \nቢቢሲ በዘገባው ፕሬዚዳንቱ በተለይ ጌምስ ለተባለው ድረገፅ በሰጡት ማብራሪያ «በመጪዎቹ ቅርብ ጊዜያት የሚካሄዱ ውድድሮች ላይ ለደህንነት ስንል ልንደራደርባቸው የማይገቡ ጉዳዮች አሉ። በተደጋጋሚ በጤና ባለሙያዎችም ሆኑ በአካባቢው ማህበረሰብ የተነገረንን ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ያስገባና ችላ የማንላቸውም ናቸው። ሁላችንም ቢሆን ይህ የረዥም ጊዜ መፍትሔ ነው ብለን አናስብም። ስፖርታዊ ውድድሮች ያለታዳሚ ይጠፋሉ። ሆኖም በአሁኑ ወቅት የአትሌቲክስ ውድድሮችን ለመመለስ መክፈል ያለብን መስዋዕትነት ይሄ ነው» ሲሉ መናገራቸውን በዘገባው አካቷል።አዲስ ዘመን ግንቦት 11/2012ዳንኤል ዘነበ", "passage_id": "7880ef43a81ab343f810d54366a6043d" }, { "passage": "የድንገተኛ ክፍሎች በኮሮናቫይረስ ህሙማን በመጣበባቸው ምክንያት ከባድ የጤና ችግር ያለባቸውን ሌሎች ህሙማንን ለማከም እንዳልቻሉ ባለስልጣናት ተናግረዋል። \n\nአንድ የኮሮናቫይረስ በሽታ ምልክቶችን የሚያሳይ በሽተኛ ይዞ የነበረ አምቡላንስ በመጨረሻ የሚቀበለው እስኪያገኝ ድረስ ቁጥራቸው በርካታ ወደ ሆኑ ሆስፒታሎች ሄዶ እንደመለሱት ተነግሯል። \n\nበመጀመሪያ ላይ የቫይረሱን ስርጭት እንደተቆጣጠረችው ሲነገርላት የቆየችው ጃፓን ዛሬ ቅዳሜ በወጣ አሃዝ መሰረት በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ከ10 ሺህ አልፏል። \n\nጃፓን ውስጥ እስካሁን ድረስ ከ200 ሰዎች በላይ በኮቪድ-19 ወረርሸዕኝ ምክንያት የሞቱ ሲሆን በበሽታው ክፉኛ የተጠቃችው ደግሞ ዋና ከተማዋ ቶኪዮ እነደሆነች ተነግሯል። \n\nበከተማዋ ውስጥ በሌሎች መደበኛ ሥራዎች ላይ ተመድበው ይሰሩ የነበሩ አጠቃላይ የቀዶ ህክምና ዶክተሮች በአገሪቱ የጤና ሥርዓት ላይ የተፈጠረውን ጫና ለማቅለል ሲሉ በበሽታው በተጠረጠሩ ሰዎች ላይ በሚደረገው የምርመራ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል። \n\nየሐኪሞቹ ማኅበር ምክትል ለሮይተርስ እንደገለጹት አባሎቻቸው እያደረጉ ያለው \"የአገሪቱ የህክምና ሥርዓትን በሚፈጠርበት ጫና ከመንኮታኮት ለመከላከል ነው\" ብለዋል።\n\nየጃፓን መንግሥትም አሽከርካሪዎች በቀጥታ መጥተው ምርመራ የሚያገኙበትን መንገድ በማመቻቸት ያለውን መመርምር አቅም ከፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ተነግሯል። \n\nበቅርብ ሳምንታት ውስጥ ጃፓን ሌሎች አገራት ውስጥ ከተካሄደው የበሽታው ምርመራ ያነሰ ቁጥር ያለውን ብቻ ያደረገች ሲሆን፤ ይህም የበሽታውን መስፋፋት ለመከታተል አስቸጋሪ እንዳደረገው ባለሙያዎች አመልክተዋል። \n\nኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ያወጣው መረጃ እንደሚጠቁመው ጃፓን ባለፈው ወር ያደረገችው ምርመራ ደቡብ ኮሮያ ካደረገችው 16 በመቶውን ብቻ ነው። \n\nደቡብ ኮሪያ ሰፊ የኮሮናቫይረስ ምርመራን በማድረግ በሽታውን በቁጥጥር ስር ማዋል የቻለች ሲሆን፤ በወቅቱ የጃፓን መንግሥት መጠነ ሰፊ ምርመራ ማካሄድ \"የሃብት ብክነት ነው\" ሲሉ አጣጥለውት ነበረ። \n\n ", "passage_id": "21a48f797040560373de69c99d5489c8" }, { "passage": " ቦጋለ አበበ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባለፈው ዓመት በቢሾፍቱ ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ወቅት ኮሚቴው የሚተዳደርበትን አዲስ መተዳደሪያ ደንብ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ይህ መተዳደሪያ ደንብ ገና ከመጀመሪያው ውዝግብ ያስነሳና በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት መካከል አለመግባባትን እንደፈጠረ አይዘነጋም። ኮሚቴው ከትንናት በስቲያ በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ ባካሄደው አርባ አምስተኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይም መተዳደሪያ ደንቡን በተመለከተ ከጉባዔው አባላት ጥያቄ አስነስቷል። በተለይም ደንቡ ይፋ ከተደረገ ጀምሮ ተቃውሞ እንዳላት ስትገልፅ የነበረችው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በጉባዔው ላይ ጥያቄዋን ዳግም አንስታለች። በቢሾፍቱው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ይፋ የተደረገው መተዳደሪያ ደንብ የጠቅላላ ጉባዔው አባላትና ስራ አስፈፃሚው እንዲወያይበት በይደር ላይ እንደነበር ያስታወሰችው ደራርቱ፣ ኮሚቴው ከትናንት በስቲያ ባደረገው ጉባዔ ላይ ባቀረበው የ2012 ዓ.ም የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ መተዳደሪያ ደንቡ እንደፀደቀ አድርጎ ማስቀመጡ ተገቢ እንዳልሆነ በመግለፅ ጥያቄ አንስታለች። ‹‹ስራ አስፈፃሚው ባላመነበትና ባልተወያየበት ሁኔታ መተዳደሪያ ሕጉ ፀድቋል፣ መተዳደሪያ ሕጉን በተመለከተ በኮሚቴ እንዲታይ በይደር ተውነው እንጂ አላፀደቅነውም›› ያለችው ደራርቱ በኮሚቴው ውስጥ የተለያዩ ሰዎች በተለይም የፅሕፈት ቤቱ ኃላፊ ተነስተው ሌላ ሰው ሲተካ በተለይም እሷ እንደ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እንዳልተሳተፈች ተናግራለች። የኮሚቴው መተዳደሪያ ደንብ ጉዳይ ባለፈው ሳምንት በሸራተን አዲስ በተካሄደው የብሔራዊ ስፖርት ምክር ቤት ጉባዔ ላይ ለሰብሳቢው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ቀርቦም ባለድርሻ አካላት ከስፖርት ኮሚሽን ጋር ተወያይተውበት ውዝግቡን እንዲፈቱ አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ይታወሳል። የብሔራዊ ስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢው ይህን አቅጣጫ ባስቀመጡበት ሁኔታ ኮሚቴው በእቅድ አፈፃፀሙ ሪፖርት ላይ መተዳደሪያ ደንቡ በዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሕግና ደንብ መሰረት እንደፀደቀ አድርጎ ማቅረቡ ከብሔራዊ ስፖርት ምክር ቤቱ ሕግና ደንብ ጋር እንደሚጣረስ ከደራርቱ በተጨማሪ ሌሎች የጉባዔው አባላትም ጥያቄ አንስተውበታል። በጠቅላላ ጉባዔው በቀረበው ሪፖርት መሰረት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን አደረጃጀት፣ አሰራርና የሰው ሃይል አመራር ለማሻሻል የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስራዎችን እንዳከናወነ የገለፀ ሲሆን፣ በዋናነት በአሰራር ሊሻሻሉ ከሚገባቸው ስራዎች ቀዳሚዎቹ ደንቦችንና መመሪያዎችን በማዘጋጀት ማሻሻል መሆኑን በማመን ኮሚቴው ከዚህ በፊት በጠቅላላ ጉባዔ የፀደቀ ደንብ እንዳልነበረው አስቀምጧል። ሲሰራበት የነበረው ‹‹የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መቋቋሚያና መተዳደሪያ መመሪያ›› በሚል በጠቅላላ ጉባዔ ያልፀደቀና በርካታ ክፍተቶች የነበሩበት መሆኑን በመጥቀስ፣ ኮሚቴው የሕግ ባለሙያዎችን አደራጅቶ የዓለም አቀፉን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ቻርተርና የተለያዩ አገራት ተሞክሮዎችን በማካተት አዲስ መተዳደሪያ ደንብ በስራ አስፈፃሚ ቦርድ ተወያይቶና ግብዓት አክሎበት ለጠቅላላ ጉባዔ በማቅረብ መስተካከል አለባቸው የተባሉትን አስተካክሎ እንዲፀድቅ ማድረጉን ያስቀምጣል። በዚህም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መተዳደሪያ ደንብ ቀርፆ ለዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በመላክ ግብዓት እየጠበቀ እንደሚገኝ ተብራርቷል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ\nፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር\nወልደጊዮርጊስ በጉዳዩ ላይ\nለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት\nማብራሪያ፣ ጠቅላላ ጉባዔው\nመረዳት ያለበት የስፖርት\nምክር ቤቱ ያቀረበው\nየስፖርት ማህበራት ማቋቋሚያ\nመመሪያ ረቂቅና ውይይት\nየሚደረግበት ሃሳብ እንጂ\nፀድቆ መተዳደሪያ የሆነ\nደንብ እንዳልሆነ አስረድተዋል።\nከኦሊምፒክ ጋር ተያይዞ\nእያንዳንዱ የሚተላለፍ ውሳኔ\nየዓለም አቀፉን ኦሊምፒክ\nኮሚቴ ሕግና ደንብ\nመሰረት ባደረገ መልኩ\nእንደሆነ የገለፁት ፕሬዚዳንቱ፣\n‹‹እኛ እዚህ የተቀመጥነው\nየዓለም አቀፉን ኦሊምፒክ\nኮሚቴ ሕግና ደንብ\nለማስፈፀም ነው፣ የኢትዮጵያ\nኦሊምፒክ ኮሚቴ ቀዳሚ\nተግባርም ይህንኑ ማስከበር\nነው፣ ከዚህ የተለየ\nነገር ካለ ለዓለም\nአቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ\nአቅርበን ተቀባይነት ካገኘ\nእኛም እንቀበላለን›› ብለዋል።\nብሔራዊ ስፖርት ምክር\nቤቱ ባቀረበው ረቂቅ\nደንብ ላይ ኦሊምፒክ\nኮሚቴ ሳይሆን ክልሎች፣ፌዴሬሽኖች፣የታወቁ\nየስፖርት ድርጅትና ተቋማት መልስ መስጠት እንዳለባቸው የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፣ እነዚህ የተጠቀሱ ባለድርሻ አካላት በብሔራዊ ስፖርት ምክር ቤቱ ረቂቅ ደንብ ላይ ድምፅ እንዳይኖራቸው መቀመጡን አስረድተዋል። ይህን መቀበል አለመቀበል ደግሞ የእነሱ ድርሻ ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። የስፖርት ማህበራትና ፌዴሬሽኖች፣ ክልሎችና የታወቁ የስፖርት ተቋማትን ከኦሊምፒክ ኮሚቴ አባልነት ያስወጣው ረቂቅ ደንብ መሆኑን ገልፀውም፣ እሳቸው እንደ ኮሚቴው አባልና ፕሬዚዳንት በረቂቅ ደንቡ ላይ እንደማይስማሙበት ተናግረዋል። ‹‹ይሄ እንዲሆን አልፈቅድም፣ ያለክልሎች የኢትዮጵያ ስፖርት ስፖርት አይደለም፣ ያለሕዝብ ተሳትፎ ስፖርቱ ስፖርት ሊሆን አይችልም፣ እነዚህ ትልልቅ ባለድርሻ አካላት የበዪ ተመልካች ሊሆኑ አይገባም›› ሲሉም አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 27/2013", "passage_id": "82a04f598fe58ad5c12b91808119f124" }, { "passage": "በቻይና ከወር በፊት የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተከትሎ በዓለም ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ መስተጋብር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየተፈጠረ እንደሚገኝ ተደጋግሞ ተነግሯል፡፡ ይህ ገዳይ ወረርሽኝ በዓለም ስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ያሳደረው አሉታዊ ተፅዕኖ ተጋኖ አይነገር እንጂ በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ኩነቶች ላይ ካሳደረው ተፅዕኖ የባሰ እንጂ ያነሰ እንዳልሆነ በርካታ ማሳያዎች መውጣት ጀምረዋል፡፡ በእርግጥ በዚህ ቫይረስ ምክኒያት ቻይናን ጨምሮ በበርካታ አገራት ዓለማቀፋዊ ውድድሮች የተሰረዙ ቢሆንም የዓለም ህዝብ ትኩረት ከአምስት ወር በኋላ በቶኪዮ የሚካሄደው የ2020 ኦሊምፒክ ላይ ነው፡፡ የኦሊምፒክ ውድድሩን በበላይነት የሚመሩት አካላት ግን ታላቁን የስፖርት መድረክ መሰረዝ ወይም የሚካሄድበትን ጊዜ ማራዘም የማይታሰብ መሆኑን ከሳምንታት በፊት ሲናገሩ ነበር፡፡ በቫይረሱ ስጋት ምክኒያት የቶኪዮ ኦሊምፒክ ምንም አይነት አደጋ እንዳላንዣበበት አፅኖት ሰጥተው መግለጫ ሲያወጡም ከርመዋል፡፡ ይሁን እንጂ የቫይረሱ ስርጭት ከመቀነስ ይልቅ በበርካታ አገራት እየተስፋፋ መሄዱን ተከትሎ የኦሊምፒክ አዘጋጆቹ ስጋት ውስጥ እንደገቡ የሚጠቁሙ መረጃዎች መውጣት ጀምረዋል፡፡ የቀድሞው የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዚዳንት ዲክ\nፖንድ በኮሮና ቫይረስ ስጋት የቶኪዮ ኦሊምፒክ በተያዘለት ጊዜ እንደሚካሄድ እርግጠኛ ሆኖ ለመወሰን ዓለም አቀፍ ኮሚቴው እስከ መጪው\nሰኔ ድረስ እንደሚታገስ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ አሁንም ድረስ የኮሚቴው አባል የሆኑት የቀድሞ የውሃ ዋና ተወዳዳሪ ፖንድ በቫይረሱ\nሳቢያ ብዙ መጥፎ ነገሮች እየተፈጠሩ እንደሚገኙ በማስታወስ ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ውድድሩ ሁለት ወር እስኪቀረው ድረስ ስጋት እንደማይኖርበትና\nአስፈላጊው ነገር ሁሉ መሟላቱን ማረጋገጥ እንዳለበት ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡ ከዚያ በኋላም ቶኪዮ ውድድሩን እንደምታካሂድ\nወይም እንደሚሰረዝ፣ ካልሆነም እንደሚራዘም ውሳኔ ላይ መድረስ እንደሚቻል ፖንድ ገልፀዋል፡፡ ከሳምንት በፊት የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ ከጃፓናዊቷ የሜዳ ቴኒስ ኮከብ ተጫዋች ናኦሚ ኦሳካ ጋር በመሆን\n‹‹በስሜት አንድ እንሁን›› የሚለውን የውድድሩን መሪ ቃል በተንቀሳቃሽ ምስል ለዓለም ሲያስተዋውቁ ታይተዋል፡፡ በዚህ ወቅት የዓለምን\nህዝብ በስሜት አንድ ያደረገው ጉዳይ ግን ከኦሊምፒኩ ይልቅ የኮሮና ቫይረስ ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ የቅርብ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት\nበኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ዙሪያ 75 ሺ ሰዎች ተጠቅተዋል፡፡ ከሁለት ሺ በላይ ሰዎች በዚሁ ቫይረስ ሳቢያ ሕይወታቸው ያለፈም\nሲሆን ቫይረሱ በሃምሳ የዓለም አገራት ተሰራጭቷል፡፡ የዚሁ ወረርሽኝ መነሻና ክፉኛ ተጎጂ የሆነችው ቻይና ፕሬዚዳንት ዢ ጂፒንግ\n‹‹ሰይጣኑ ቫይረስ›› ብለው እንደጠሩት ሁሉ የቫይረሱ ስርጭት በአስደንጋጭ ሁኔታ እየተስፋፋ የዓለም ተመራማሪዎችም ፈውሱን የማግኘት\nጥረት ተጨባጭ ተስፋ እንዳላመጣ እየተስተዋለ ይገኛል፡፡ ይህም የዓለምን ምጣኔ ሀብት በተያዘው 2020 ሩብ ዓመት ብቻ 280 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ እንደሚያደርስ በጥናት\nተጠቁሟል፡፡ ይህም እ.ኤ.አ ከ2009 ወዲህ የመጀመሪያ ይሆናል፡፡ በቫይረሱ ስርጭት ከቻይና ቀጥላ በሁለተኛነት የተቀመጠችው ጃፓን\nውስጥ ከሰባት መቶ ያላነሰ ሰው በቫይረሱ መጠቃቱ ተዘግቧል፡፡ የቅርብ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ግን 3700 ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸውንና\nየኦሊምፒክ ውድድሩ ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች ዋነኛ ከሆነው ዮኮሃማ ቤዝ ቦል ስቴድየም ከሦስት ኪሎ ሜትር ባነሰ ርቀት ላይ በሚገኝ\nስፍራ ላይ በመገለል እንደተቀመጡ ታውቋል፡፡ ይሁን እንጂ ጃፓን በቀጣዩ ወር በአርባ ሰባት ግዛቶቿ ለ121 ቀናት የሚዞረውን የኦሊምፒክ\nችቦ ለመለኮስ ተዘጋጅታለች፡፡ የኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴው መሪ ቶሺሮ ሙቶ የኦሊምፒክ ውድድሩን ለማስተናገድ ምንም ስጋት እንደሌለ\nቀደም ብለው ቢፎክሩም አሁን አሁን ስጋት ውስጥ እንደገቡ በግልፅ በአገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ተናግረዋል፡፡ በግልፅ የቫይረሱ ስጋት\nውድድሩን ያስቀረዋል ባይሉም በኦሊምፒኩ የሞቀ ዝግጅት ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ሊከልስ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ በቫይረሱ ስጋት የተነሳ ቶኪዮ የኦሊምፒክ ውድድሩን የመሰረዝ አዝማሚያ ባይታይባትም ባለፈው ሳምንት በተካሄደው\nየቶኪዮ ማራቶን ከአትሌቶች በስተቀር ሕዝብ እንዳይሳተፍ አድርጋለች፡፡ ከሁለት ቀናት በፊትም የጃፓን የኦሊምፒክ ሚኒስትሯ ሴኮ ሃሺማቶ\nበአገሪቱ ፓርላማ በጉዳዩ ዙሪያ በቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ ሲሰጡ፣ ቶኪዮ ውድድሩን በ2020 ለማካሄድ ከዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ\nኮሚቴ ጋር ውል እንደገባ በማስታወስ በውሉ መሰረት ውድድሩን እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የማራዘም እድል እንዳለ አስረድተዋል፡፡\nይሁን እንጂ ውድድሩ በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ የተቻለውን ሁሉ ለማድረግ እየተሞከረ መሆኑን ሚኒስትሯ አብራርተዋል፡፡የኦሊምፒኩ አዘጋጅ ኮሚቴ ውድድሩን ለማካሄድ የልብ ልብ የተሰማቸው ወቅቱ በጋ እና ከፍተኛ ሙቀት የሚኖርበት\nከመሆኑ ጋር ተያይዞ የኮሮና ቫይረስ ልክ እኤአ 2003 ላይ የሳርስ ወረርሽኝ በበጋ ወራት ሊጠፋ እንደሚችል ተስፋ አድርገው መሆኑን\nመረጃዎች ወጥተዋል፡፡ ይሁን እንጂ የሳርስ ወረርሽ ለምን በበጋ ወራት እንደሚጠፋ አሁንም ድረስ በህክምናው ዓለም ግልፅ ማስረጃ እንደሌለ የሚናገሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ በሚኒሶታ ዩኒቨርስቲ የህክምና\nተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ሚካኤል ኦስተርሆልም አንዳንድ የኮሮና ቫይረስ አይነቶች ከክረምት ወራት ይልቅ በበጋ እንደሚስፋፉ በመጠቆም\nየኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴው ባዶ ተስፋ መሆኑን ከታይም መፅሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አረጋግጠዋል፡፡ ጃፓን ለዓመታት የለፋችበት የኦሊምፒክ ዝግጅት ከንቱ ከሚቀርና\nቫይረሱ ይዞ ከሚመጣው አደጋ አንዱን መምረጥ ያለባት ወቅት ላይ ትገኛለች፡፡ የኦሊምፒክ ውድድሩ ቢሰረዝ ወይም የቦታ ለውጥ ቢደረግበት\nጃፓን የሚገጥማትን ኪሳራ ያሰሉ የምጣኔ ሀብት ምሁራን ቀላል እንዳልሆነ ይናገራሉ፡፡ ለውድድሩ 25 ቢሊየን ዶላር ወጪ እንደሚሆን\nየታሰበ ሲሆን የመሰረዝ ወይም የቦታ ለውጥ የሚደረግበት ከሆነ ቀድሞ ከታሰበው በአራት እጥፍ ሊያስወጣ እንደሚችል ቢቢሲ ሰሞኑን\nባስነበበው ዘገባ አትቷል፡፡ ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ በዘለቀው የዘመናዊው ኦሊምፒክ ታሪክ ታላቁ የስፖርት መድረክ በጦርነት ካልሆነ\nበስተቀር በሌላ ምክኒያት ተራዝሞ ወይም ተሰርዞ አያውቅም፡፡ ነገር ግን ኦሊምፒክ የአሁኑን ያህል ከባድ ፈተና ገጥሞት ያውቃል ለማለትም\nአይቻልም፡፡አዲስ ዘመን አርብ የካቲት 27/2012 ቦጋለ አበበ", "passage_id": "3b406149853ba1ba565927d02432214e" }, { "passage": "የዓለም ህዝብን በአንድ የጭንቀት ቋጥ ውስጥ ባስገባው የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት በስፖርቱ ዘርፍ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ማሳደሩ ይነገራል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በሀገሪቱ የኮሮና ወረርሽኝ በስፖርቱ ላይ እያሳደረ ያለውን ጫና የሚዳስስ ውይይት ከሀገር አቀፍ ፌዴሬሽኖች ጋር አድርጎ ነበር። የሁሉም ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ውቅር የሆነው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከሀገር አቀፍ ፌዴሬሽኖች ጋር ካደረገው ውይይት መነሻነት እንዲሁም ፌዴሬሽኖቹም በሰጡት ጥናት መሰረት አንድ ውሳኔ አስተላልፏል። «ብሔራዊ ፌዴሬሽኖችን የገንዘብ ድጋፍ ይደረግላቸው ። ከዚህ በተጓዳኝ የገንዘብ አቅም የሌላቸው ስፖርቶችና ስፖርተኞች ወቅታዊ ብቃታቸው እንዳይወርድ ዕገዛ ይደረግላቸው» ሲል ነበር። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ትናንት በመደበኛ የፌስቡክ ገጹ ፤« የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገባውን የገንዘብ ድጎማ ማክሰኞ ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚያስረክብ አስታወቋል። \nበኢትዮጵያ የተለያዩ ስፖርቶችን ለማሳደግና ለማስፋፋት የተቋቋሙ ከ26 በላይ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ዓለም አቀፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ ከማናቸውም ዓይነት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተቆጥበዋል፡፡ በኅብረተሰቡ ዘንድ በስፋት የሚዘወተሩት ስፖርቶች ከሚመሩ ፌዴሬሽኖች በቀር ብዙዎቹ በወረርሽኙ ምክንያት ከቢሮ ይልቅ ቤት ውስጥ መዋል ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡ ኦሎምፒክ ኮሚቴው የብሄራዊ ፌዴሬሽኖችን ምክረ ሐሳብን መነሻ በማድረግ ቃል የተገባውን ገንዘብ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነሩ እና ምክትል ኮሚሽነሩ በተገኙበት ርክክቡ የሚደረግ ይሆናል ብሏል። ኦሎምፒክ ኮሚቴው ሥነ ሥርዓቱን መገናኛ ብዙሃን በስፍራው ተገኝተው መረጃውን በመከታተል ለህዝብ ተደራሽ ያደርጉለት ዘንድ ጥሪውን በመደበኛ ማህበራዊ ፌስቡክ ገጹ አስፍሯል። \nሕጋዊ ሰውነት አግኝተው በአገሪቱ በመንቀሳቀስ ላይ ከሚገኙ ብሔራዊ ፈዴሬሽኖች የኢትዮጵያ አትሌቲክስና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ካልሆኑ ሌሎቹ በአጠቃላይ ከመንግሥት ቋት በሚለቀቅላቸው አነስተኛ በጀት የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ መንግሥት ከሚመደብላቸው በጀት ይልቅ ከስፖርት ኮሚሽንና ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተሻለ የገንዘብ ድጎማ እንደሚደረግላቸው የሚናገሩት ብሔራዊ ፌዴሬሽኖቹ፣ ስፖርት በቂ ፋይናንስ ታክሎበት ካልሆነ በስተቀር ብሔራዊ በሚለው ስያሜ ብቻ ትርጉም ያለው እንቅስቃሴና ውጤት ማስመዝገብ እንደማይችል ጭምር ያምናሉ፡፡ የፌዴሬሽኖቹ አመራሮችም የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለወትሮ በዓመት አንድ ጊዜ እንደ አስፈላጊነቱ ይሰጥ የነበረው የሙያ ማሻሻያ ኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ በወረርሽኙ ምክንያት ስለመቋረጡ ጭምር ይናገራሉ፡፡\nአዲስ ዘመን ግንቦት 25/2012ዳንኤል ዘነበ", "passage_id": "7e5e36b2bb400322dbc8ac93c3165d71" } ]
2a97e0aad4fa0ad56a585fd391b23a5b
709a028eb5f4d4950942dd58fb048c92
የአውሮፓ አትሌቲክስ ቻምፒዮናና ዳይመንድ ሊግ
በርካታ ዓለም አቀፍ ውድድሮች በተሰረዙበትና በተራዘሙበት በዚህ ወቅት እንደሚካሄድ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው የአውሮፓ አትሌቲክስ ቻምፒዮና ከመሰረዝ እንዳልዳነ ታውቋል፡፡ በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ እኤአ ከሐምሌ 25 እስከ 30 በቻርሌቲ ስቴድየም ሊካሄድ ታስቦ የነበረው ቻምፒዮና በኮሮና ቫይረስ ስጋት እንደተሰረዘ አዘጋጆቹ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ አሳውቀዋል፡፡ ውድድሩን በተያዘለት ጊዜ ለማካሄድ የተቻለው ሁሉ ጥረት ቢደረግም በአሁኑ ወቅት ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ በፈረንሳይ መሰብሰብ የተከለከለ በመሆኑ የውድድር አዘጋጅ ኮሚቴው፣ የአውሮፓ አትሌቲክስ ማህበርና የፈረንሳይ አትሌቲክስ ባለስልጣናት ውድድሩን ለመሰረዝ እንደተገደዱ አሳውቀዋል:: እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስም የፈረንሳይ የጤና ኮሚሽን በአትሌቶችና በተመልካቾች ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ከግምት ያስገባ ጥናት ማድረጋቸው ታውቋል:: የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ጂን ጋርሺያ ለመገናኛ ብዙኃን እንደገለፁት፣ ውድድሩን ለማካሄድ እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ ጥረት የተደረገ ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቷል:: «በርካታ ውድድሮች በተሰረዙበት ሰዓት ለአትሌቶች በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ሰዓት አንድ የሚያስደስት ነገር ለማድረግ አስበን ነበር» ያሉት ፕሬዚዳንቱ ውድድሩን ከቫይረሱ ስጋት ነፃ ለማድረግ የስቴድየሞች ተመልካች የመያዝ አቅም በግማሽ እንዲያንስ ለማድረግ ጥረት መደረጉን አብራርተዋል፡፡ ውድድሩን ከመሰረዝ ይልቅ ወደ ቀጣዩ ዓመት እንደ አማራጭ ታስቦ እንደነበረ የተናገሩት ግራሺያ የቫይረሱ ስጭት ምናልባት እስከ ቀጣይ ዓመትም ካልተገታ ማራዘሙ አማራጭ እንደማይሆን ታምኖበት ውሳኔ ላይ እንደደረሰ ገልፀዋል፡፡ ለውድድሩ ከአስራ ስምንት ሚሊዮን ዶላር በላይ በጀት የተያዘ ሲሆን ሊገጥም የሚችለውን ኪሳራ ለማዳን የአገሪቱ መንግሥት ዋስትና እንደሚሰጥ ታውቋል:: የአውሮፓ አትሌቲክስ ማህበር ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ከወር በፊት ውድድሩ በተያዘለት ጊዜ መካሄድ የሚችልበትን መንገድ ማጥናት እንደሚገባ የጠቆመ ሲሆን ውድድሩ በተያዘለት ጊዜ ካልተካሄደ የሚራዘምበት ዕድል እንዲፈጠር ፍላጎት ነበረው፡፡ ያም ሆኖ አዘጋጆቹ ከማራዘም ይልቅ ለመሰረዝ ተገደዋል፡፡ በዚሁ በአውሮፓ በርካታ ከተሞች ይካሄዱ የነበሩ የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች በተያዘላቸው መርሃግብር መሠረት እንደማይካሄዱ የተገለጸ ሲሆን የሚካሄዱበት አዲስ መርሃግብር ከዓለም አትሌቲክስ ጋር በመወያየት እንደሚገለፅ ተጠቁሟል፡፡ ከግንቦት መጨረሻ አንስቶ በአስራ አራት የተለያዩ የዓለማችን ከተሞች የሚካሄዱት የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች የፓሪስና የዩጂን ዳይመንድ ሊጎችን ጨምሮ በርካቶቹ መራዘማቸው ታውቋል፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ በኖርዌይ ኦስሎ የሚካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ቢራዘምም አዘጋጆቹ በምትኩ አዲስ የውድድር አማራጭ ማቅረባቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ «የማይቻል» የተባለው ውድድር በኦስሎ አዘጋጆች ሲታቀድ በኤግዚቢሽን መልኩ በዝግ ስቴድየም እንደሚሆን ተገልጿል፡፡ ውድድሩን ማህበራዊ ርቀትን በመጠበቅና የኮሮና ቫይረስ የሚፈልገውን ጥንቃቄ ተግባራዊ በሚያደርግ መልኩ ለማካሄድ የታሰበ ሲሆን በኖርዌያን የሜዳ ተግባራት አትሌቶች መካከል የዓለም ክብረወሰን የሚሻሻልበት ይሆናል ተብሏል፡፡ በተለይም ኖርዌያዊው የርዝመት ዘላይ ካርልስተን ዋርሆልም እንዲሁም የምርኩዝ ዘላዮቹ ሞንዶ ዱፕሌንቲስና ሪናውድ ላቪሌኒ የሚያደርጉት ፉክክር ተጠባቂ እንደሚሆን ተገምቷል፡፡ ለአንድ ሰዓት ያህል የሚካሄደው ውድድር በኖርዌይ የሕዝብ ቴሌቪዥን ጣቢያ በቀጥታ እንደሚተላለፍ ተጠቁሟል፡፡ ይህ የኖርዌይ ውሳኔ ከኮሮና ቫይረስ ስጋት ጋር ተያይዞ ለብዙዎች የማይመስል ቢሆንም የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሴባስቲያን ኮ ጭምር አድናቆታቸውን ገልጸውለታል፡፡ አዲስ ዘመን ሚያዝያ 18/2012ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=31149
[ { "passage": "የዓለም አትሌቲክስ የፕላቲነም ደረጃ በሚሰጠው የቶኪዮ ማራቶን እስካሁን ከተደረጉ 13 ውድድሮች በወንዶች 4 በሴቶች 6 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡ የቦታው ክብረ ወሰን የተያዘው ግን በኬንያውያን አትሌቶች ነው፡፡\nበመጪው የአውሮፓውያኑ መጋቢት 1 በሚጀመረው በዚህ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያኑ ብርሃኑ ለገሰ እና ሩቲ አጋ ያሸንፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የዓለም አትሌቲክስ ዘገባ ያሳያል፡፡\nብርሃኑ ለገሰ በ2019 ቶኪዮ ላይ ርቀቱን በ2፡04፡48 በማጠናቀቅ ሲያሸንፍ በዚሁ አመት በርሊን ማራቶን ላይ ኤሉድ ኪፕቾጌን 2፡02፡48 በሆነ ሰዓት ተከትሎ ገብቷል፡፡ ይህም ምርጥ የግል ሰዓት ሆኖ ተመዝግቦለታል፡፡ሆኖም በቶኪዮው ውድድር ልክ እንደ ብርሃኑ ሁሉ ርቀቱን ከ2 ሰዓት ከ05 ደቂቃ በታች የገቡ ስምንት አትሌቶች መኖራቸው ፉክክሩን ከፍ እንደሚያደርገው ይጠበቃል፡፡\nየዱባይ ማራቶን አሸናፊው ጌታነህ ሞላ፣ሲሳይ ለማ፣አሰፋ መንግስቱ እና ኃይሌ ለሚ ኢትዮጵያውያን የብርሃኑ ተቀናቃኞች ናቸው፡፡የውድድሩ የሁለት ጊዜ አሸናፊ ኬንያዊው ዴክሰን ቹምባ በተመሳሳይ የአሸናፊነቱን ቅድመ ግምት አግኝቷል፡፡የዓለም ሻምፒዮና የነሃስ ሜዳሊያ ባለቤቱ አሞስ ኪፕሩቶ እና ቤዳን ካሮኪምም የውድድሩ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡\nልክ እንደ ብርሃኑ ሁሉ ኢትዮጵያውያኑ ሴት አትሌቶችም በፉክክሩ ይጠበቃሉ፡፡ የውድድሩ የባለፈው ዓመት አሸናፊ ሩቲ አጋ ክብሯን ለማስጠበቅ እንደምትሮጥ ይጠበቃል፡፡ሩቲ 2፡20፡40 ነበር ርቀቱን ያጠናቀቀችው፡፡ ከ2 ዓመት በፊት በበርሊን ማራቶን 2፡18፡34 በመግባት ሁለተኛ ወጥታ ነበረ፡፡ ሰዓቱም ምርጥ የግል ሪከርዷ ነው፡፡\nየውድድሩ የ2015 እና 2018 አሸናፊዎቹ ብርሃኔ ዲባባ እና ትርፌ ጸጋዬ ሩቲን ለመፎካከር ቅድመ ግምትን አግኝተዋል፡፡ ብርሃኔ ባሳለፍነው ወር ስፔን ቫሌንሺያ ላይ ሶስተኛ ስትወጣ የገባችበት 2፡18፡46 ምርጥ የግል ሰዓቷ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በውድድሩ የኢትዮጵያ የግማሽ ማራቶን የክብረ ወሰን ባለቤት ሰንበሬ ተፈሪም ትሳተፋለች፡፡\nየቶኪዮ ማራቶን ከባድ ፉክክር የሚጠበቅበት ብቻም ሳይሆን የተሻለ ሰዓት የሚያስመዘግቡ ጃፓናውያን አትሌቶች ለኦሎምፒክ የሚመለመሉበት ነው ተብሏል፡፡\n", "passage_id": "d15ffe2ac0bf7fe94a03944f0f1b5f8e" }, { "passage": "በፖርትላንዱ የዓለም አዳራሽ ውስጥ ሻምፒዮና ውድድር በሴቶቹ 3,000 ሜትር ውድድር አሸናፊዋ ልማደኛዋ ገንዘቤ ዲባባ እንደምትሆን ሳይታለም የተፈታ ነበር።​በተመሳሳይ ርቀት የወንዶቹን ድል የተቀዳጀው ደግሞ ወጣት ዮሚፍ ቀጄልቻ ነው። ሁለቱም በየግላቸው ያስመዘገቧቸው ሰዓቶችም የሚናቁ አልሆኑም፥ የገንዘቤ 8 ደቂቃ ከ 47 ነጥብ4 - 3 ሴኮንድ ሲሆን የዮሚፍ 7 ደቂቃ ከ 57 ነጥብ 2 - 1 ሴኮንድ ሆኗል።ሁለቱም የኢትዮጵያ አትሌቶች በመጪው ግንቦት ዩጂን ኦሪጎን በሚካሄደው የዳያመንድ ሊግውድድር ለመሳተፍ ተመልሰው እንደሚመጡ ይጠበቃል።ኤዲ ኢዛርድ የተባለ የ 54 ዓመት ኮሜዲያን፥ 27 ማራቶኖችን በ 27 ቀናት ውስጥ ሮጧል።አርቲስቱ ይህን ያደረገው ኔልሰን ማንዴላ የመጀመሪያው የደቡብ አፍሪካ ጥቁር ፕሬዘዳንትከመሆናቸው በፊት ለ 27 ዓመታት በእሥር መቆየታቸውን ለማስታወስ ነው ተብሏል።አስቂኙ አርቲስት በጠቅላላው የሮጠው 707 ማይሎችን ሲሆን በውሃ ጥም ማረሩና ቆዳው መቆሳሰሉተስተውሏል። ኤዲ ኢዛርድ አጋጣሚውን የስፖርት ፕሮግራሞችን ለማስፋፊያ ገንዘብ ማሰባሰቢያነትም ተጠቅሞበታል።በእለቱም ከደጋፊዎቹ ከአንድ ሚሊዮን ፓውንድ በላይ መሰብሰብ ችሏል። ሰሎሞን ክፍሌ ዝርዝሩን አጠናቅሮ አቅርቦታል፣ ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል በመጫን ያድምጡ። ", "passage_id": "fdf4a3cca18ab20bc8cc7c655e95ddd8" }, { "passage": "የምሥራቅ አፍሪካውያን የባህል ስፖርት የሆነው በተለይም ለኢትዮጵያ እና ኬንያ የ10ሺ እና 5ሺ ሜትር ሩጫ ታላቅ ትርጉም ያለው ነው። ያሉበት የመልካምድር አቀማመጥና የአየር ጸባይ ለስኬት እንዳገዛቸው በባለሙያዎች ይነሳል። በግልጽ እንደሚታየው ባለፉት ዓመታት በርቀቶቹ በተካሄዱ ውድድሮች የበላይነቱን የያዙት የሁለቱ ሀገራት አትሌቶች ናቸው። ይህ ሁኔታ ደግሞ እንደ ባህል ስፖርት እንዲታይ ምክንያት ሆኗል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን በእነዚህ ርቀቶች የሚካሄዱ ውድድሮች በዓለም ላይ እየተመናመኑ መጥተዋል። የ10ሺ ሜትር ሩጫ በብቸኝነት የሚታየው በዓለም ሻምፒዮና እና ኦሊምፒክ ላይ ብቻ ሲሆን፣ በዳይመንድ ሊግ ይካሄድ የነበረው የ5 ሺ ሜትር ሩጫም ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ እንደማይካሄድ ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር አስታውቋል። ይህም ሀገራቱን ያስቆጣ፤ ቅሬታዎቸውንም በማንሳት ውሳኔውን ለማስቀልበስ የተለያዩ እርምጃዎችን በመወሰድ ላይ ይገኛሉ። ባሳለፍነው ወር በዴንማርክ በተካሄደው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ ጉዳዩን የተቃወሙት ኢትዮጵያ እና ኬንያ በተናጠል የዓለም አቀፉን ማህበር ፕሬዚዳንት ሰባስቲያን ኮን አናግረዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉም ከፕሬዚዳንቱ ጋር ቆይታ አድርጋለች። በውይይቱ ላይ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል የ5ሺህ ሜትር ውድድር አንዱ ሲሆን በሻምፒዮናው ላይ የተካፈሉ አፍሪካውያን አትሌቶችና ደጋፊዎች የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበር ውሳኔን በመቃወም ድምጻቸውን አስተጋብተዋል። በሕይወት ዘመኔ መሮጥ የምፈልገውና ውጤት ለማስመዝገብ የምጓጓው በ5ሺ ሜትር ነበር ያሉት የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አትሌት ኮማንደር ማርቆስ ገነቲ፤ አገራችን የምትታወቅበት የረጅም ርቀት የአትሌቲክስ ስፖርት ከውድድር ውጪ እየሆነ መምጣቱ ልብ የሚሰብርና አሳዛኝ እንደሆነ ገልጸዋል። ነገር ግን ጉዳዩን እስከ መጨረሻው ተከታትለን የምንችለውን በማድረግ በተለይ በሚቀጥለው ዓመት የ5ሺ ሜትር ውድድር ከዳይመንድ ሊግ ውጭ እንዳይሆን እንደማህበር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የምንችለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ነን ይላሉ። ከአፍሪካ ሀገራት በተለይ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ታንዛኒያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሞሮኮና ኡጋንዳ በ10 ሺና በ 5 ሺ ሜትር ሩጫ ለዘመናት በዓለም አደባባይ ላይ ገነው መታየት ችለዋል። ነገርግን እነዚህ ውድድሮች ከጨዋታ ውጪ እየሆኑ መምጣታቸውን ተከትሎ የሀገራቱ አትሌቶች በዓለም መድረክ ውጤት ለማስመዝገብ ችግር ውስጥ ገብተዋል ብለዋል። የ10 ሺ እና 5ሺ ሜትር ርቀቶች ከውድድር ውጪ እየሆኑ መምጣቱ በተለይ የአገራችን አትሌቶች ተወዳድሮ ሚኒማ የሚያሟላበት ውድድር እያገኙ ባለመሆኑ ውጤት እየራቀን ነው ያለው። ከዚህ በፊት በኢንተርናሽናል ውድድር የሚካፈሉ አትሌቶች በኢትዮጵያ ሻምፒዮና ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት ስምንት አትሌቶች ለዓለም አቀፍ ውድድር የሚመርጡት መንገድ ነበር። ነገር ግን የ10ሺ ሜትር ውድድር ቀደም ብሎ ከተለያዩ ውድድር ውጪ እንደሆነ ይታወቃል። እንዲሁም የ5ሺ ሜትር ውድድር እአአ ከ2020 በኋላ ከዳይመንድ ሊግ ለማስወጣት በሂደት ላይ ናቸው። ስለዚህ በዳይመንድ ሊግ ላይ እነዚህ ውደድሮች ካልተካሄዱ ውድድሮቹን ስፖንሰር የሚያደርጋቸው ስለሌለ በሌሎች ውድድሮች ላይ አይካሄዱም ማለት ነው። ይሄ ከሆነ ደግሞ እኛ አፍሪካውያን ውድድሮቹ ውጤት የምናስመዘግብባቸው በመሆኑ አትሌቶቻችን ከውድድር ውጪ እየሆኑ ይመጣሉ። የአፍሪካ መለያ የሆኑት የ5 ሺ እና የ10 ሺ ሜትር የረጅም ርቀት ውድድሮች ከዓለም የውድድር መድረኮች መሰረዛቸው በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ክለቦች በረጅም ርቀት ስፖርት ታቅፈው በሥልጠና ላይ ያሉ አትሌቶች ክለቦች ሊያሰናብቱ ወይም ሊበትኑን ይቸላሉ የሚል ስጋት ተጋርጦባቸዋል ብለዋል። ነጮች በነዚህ ውድድሮች አፍሪካውያንን መቋቋም ስላልቻሉ ቀስበቀስ ስፖርቱን ከተሳትፎ ውጭ እያደረጉ ይገኛሉ ያሉት ኮማንደሩ፤ ጥቁሮች በረጅም ርቀት ውድድሮች ከመንገሳቸው በፊት አውሮፓውያን በርቀቱ ነግሰው እንደነበር ታሪክ ያስረዳል። ነገርግን ጥቁር አፍሪካውያን በተለይ ምሥራቅ አፍሪካዎች ጠንክረው በመስራት እነዚህን ውድድሮች የግላቸው ለማድረግ ችለዋል። ምሥራቅ አፍሪካውያንም ለዘመናት በመፈራረቅ በነዚህ ውድድሮች ገድል መስራት ችለዋል። ስለዚህ የአገራችንና የሌሎች አፍሪካውያን አትሌቶች ከዚህ ታሪክ በመነሳት ነጮች የአጭር ርቀት ሩጫ የግላችን ነው ብለው የሚኩራሩበትን ታሪክ ለመቀየር ጠንክሮ በመስራት በነዚህ ርቀቶች ላይ ዳግም በመንገስ ብቃታቸውን ሊያስመሰክሩ ይገባል። ኮማንደሩ አክለውም፤ የአጭር ርቀት ሩጫ ስልት የሚጠይቅ፣ የተለያዩ መሠረተ ልማቶችና ቁሳቁሶች የሚያስፈልጉት እንደሆነ ይታወቃል፤ ሌሎች አፍሪካውያን ሀገሮች ችግሩን ቀድመው በመረዳት በአጭር ርቀት ሩጫ ተተኪና ተወዳዳሪ አትሌቶችን ለማፍራት ወደታች ወርደው ግንዛቤን በመፍጠር በአጭር ርቀት ሩጫ ላይ ጠንክረው በመስራት በዓለም መድረክ ውጤት እያስመዘገቡ ይገኛሉ። ለአብነትም የአትሌቲክስ ስፖርት ተቀናቃኞችን ጎረቤታችን ኬንያን ብናይ፤ የረጅም ርቀት ሩጫዎች ከውድድር ውጪ እየወጣ መሆኑንና በአጭር ርቀት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት ወደታች ወርደው ግንዛቤውን በመፍጠርና ጠንክረው በመስራት በዓለም መድረክ በተካሄዱ የአጭር ርቀት ውድድሮች ላይ በመሳተፍ፤ በ3ሺ ሜትርና በሌሎች የአጭር ርቀት ውድድሮች የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት እየቻሉ ነው። በተጨማሪም ደቡብ አፍሪካ ናይጀሪያ ሞሮኮ የመሳሰሉ የአፍሪካ ሀገራት የኬንያን ፈለግ በመከተል በአጭር ርቀት ሩጫዎች ላይ ጠንክረው በመስራት ላይ ሲሆኑ፤ ጥሩ ውጤት እያስመዘገቡ መጥተዋል። አገራችን የሌሎች አፍሪካ ሀገሮችን ፈለግ በመከተልና በአጭር ርቀት የተሻለ ውጤትና ልምድ ያላቸውን ሀገሮች አሠራር በመቅሰም፤ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ፣ የስፖርት ማህበረሰቡና የሚመለከታቸው አካላት አንድ ላይ በመሆን ወደታች ወርደው በክልል፣ በዞን፣ በወረዳ እና በቀበሌ ደረጃ ለአትሌቶች ግንዛቤውን በመፍጠር ስፖርተኞች በአጭር ርቀት እንዲፈጠሩ የማድረግ ሥራ መስራት እንዳለባቸው ኮማንደሩ አሳስበዋል። በአትሌቲክሱ\nስናስመዘግብ\nየቆየነው\nውጤት ተጠብቆ እንዲቀጥል በመላ አገሪቱ በአጭር ርቀትና በሌሎች ዘርፎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ለአጭር ርቀት ሩጫ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይኖርበታል። ነገር ግን ርቀቱ አቅምና ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ስልትና ብዙ ድጋፍ የሚያስፈልገው በመሆኑ፤ ፌዴሬሽኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በስፖርቱ ውጤት እንዲመጣ ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል። በአጠቃላይ ሀገራችን የምትታወቅበት የረጅም ርቀት ሩጫዎች ከውድድር ውጪ እየሆኑ መምጣታቸውን ለአትሌቶችና ለስፖርት ማህበረሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ መስራት ያስፈልጋል። ስለዚህ ግንዛቤውን በመፍጠር በርቀቱ ላይ በስፋት ጠንክሮ በመስራት ተተኪና በዓለም መድረክ ተወዳዳሪ የሆኑ ስፖርተኞችን እንደ ሀገር ማፍራት ያስፈልጋል ብለዋል ኮማንደሩ። ኢትዮጵያ ልክ እንደ ማራቶን፣ ግማሽ ማራቶን፣ 10ሺ፣ 5ሺ የመሳሰሉ የስፖርት ዓይነቶች ላይ ጠንከር ያለ ሥልጠናዎች በማድረግና ከታች ጀምሮ ተተኪ ስፖርተኞችን በማፍራት በኩል ያላትን ልምድ በመጠቀም በአጭር ርቀት ሩጫም ጠንክራ ሥራን መስራትና እንደ ሌሎች የአፍሪካ አገራት ውጤት ማምጣት ያለባት በመሆኑ አትሌቶች ወደ አጭር ርቀት ሩጫ በመምጣት ውጤት ለማስመዝገብ መስራት ያለባቸው አሁን ነው። በተጨማሪም 10ሺ እና\n5ሺ ሜትር ሩጫዎች የባህል ስፖርቶቻችን ናቸው ያሉት ኮማንደሩ፤ ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ አትሌት በምን ውድድር መሳተፍ ትወዳለህ ቢባል በ5ሺ\nወይም በ10ሺ ሜትር\nሩጫዎች ነው የሚለው። ምክንያቱም ከጥንት ጀምሮ ብርቅዬ አትሌቶቻችን በዓለም መድረክ በነዚህ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ታሪክ በመስራት የሀገራቸውን ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርገው ማውለብለብ ስለቻሉ። ስለዚህ የመገናኛ\nብዙኃን የስፖርት ቤተሰቡ\nበአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ\nከአትሌቶቹና ከፌዴሬሸኑ ጎን በመሆን\nየአገሪቱ የአትሌቲክስ ስፖርት\nእንዲያድግ መታገል አለበት።\nእንዲሁም የ5ሺ ሜትር\nሩጫ በመጪው ዓመት\nከዳይመንድ ሊግ እንዳይወጣ\nለአንድ ተቋም ብቻ የምንሰጠው\nጉዳይ ስላልሆነ ተቃውሞአችን\nለዓለም እንዲሰማ ሁሉም\nባለድርሻ አካላት በተባበረ\nክንድ የበኩሉን እንዲወጣ\nኮማንደሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 4/2011በሶሎሞን በየነ ", "passage_id": "3b22faa53c14ac23a31d3ed39c507e9b" }, { "passage": "በታሪክ አጋጣሚ ቀደም ባሉት ዓመታት በተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች ወንድና ሴት አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች በተመሳሳይ ውድድር ላይ ሲሮጡ መመልከት የተለመደ ነው። ‹‹ወንዶች የሚሮጡትን ርቀት ሴቶች መሮጥ አይችሉም›› የሚል አስተሳሰብ በነበረበት ዘመን በተመሳሳይ ውድድር ላይ ሴቶች ከወንዶች ያነሰ ርቀት ለመሮጥ ይገደዱ ነበር። እንዲያውም በአንዳንድ ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ላይ ወንዶች በሚሮጡበት ርቀት ሴቶች እንደማይወዳደሩ ከታሪክ መረዳት ይቻላል። ለምሳሌ ያህል በታላቁ የዓለማችን የስፖርት መድረክ ኦሊምፒክ ማራቶን አንጋፋና ምናልባትም ከመጀመሪያ አንስቶ የሚካሄድ የውድድር አይነት ቢሆንም ሴቶች በርቀቱ መወዳደር የጀመሩት ዘግይተው ነው።በኦሊምፒክ መድረክ ብቸኛው የጎዳና ላይ ውድድር በሆነው ማራቶን ወንዶች መሳተፍ የጀመሩት እኤአ 1896 ላይ ነው። የሴቶች ማራቶን የኦሊምፒክ ውድድር ውስጥ የተካተተው ግን ዘጠና ዓመታትን ዘግይቶ በ1984 ኦሊምፒክ ነበር። ከማራቶን በተጨማሪም በርካታ በተለይም ረጅም ርቀት ውድድሮች በኦሊምፒክም ይሁን በዓለም ቻምፒዮና ሴቶችን ማካተት የጀመሩት ዘግይተው ነው። ይሁን እንጂ በዘመናዊው የአትሌቲክስ ዓለም ሴቶች ወንዶች በሚወዳደሩበት ርቀት ሙሉ በሙሉ ለማለት በሚያስችል ደረጃ ተወዳዳሪ ናቸው።ከአታካቹ ማራቶን አንስቶ እስከ ተለያዩ የጎዳና ላይ ውድድሮች ሴቶች ወንዶች የሚሮጡትን ርቀት በመሮጥ ብቃታቸውን አስመስክረዋል። ርቀቶቹን ሮጠው  ለማጠናቀቅ የሚፈጅባቸው ሰዓት ከተፈጥሮ ጋር በተያያዘ ከወንዶች የዘገየ ቢሆንም የትኛውንም ርቀት ሴቶች አይሮጡም ብሎ የሚያምን ሰው ፈልጎ ማግኘትም ከባድ የሚመስልበት ዘመን ላይ ተደርሷል። ይሁንና ሴቶች በአገር አቋራጭ ውድድሮች ላይ ከወንዶች ያነሰ ርቀት እንዲሮጡ መደረጉ በአትሌቲክሱ ቤተሰቦች መከራከሪያ አጀንዳ ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል።እንግሊዛዊቷ የቀድሞ የአገር አቋራጭ ቻምፒዮና የሜዳሊያ ባለቤት አትሌት ጆ ፓቬይ «በአገር አቋራጭ ውድድሮች ሴቶች ከወንዶች ባነሰ ርቀት መወዳደራቸው የፆታ እኩልነትን አያሳይም» የሚል አስተያየት ከሁለት ዓመት በፊት ለስካይ ኒውስ መስጠቷን ተከትሎም የአገር አቋራጭ ውድድር አዘጋጆች ከአትሌቲክስ ቤተሰቡ ጋር ሙግት ገጥመው እንደነበር ይታወሳል። በርካታ የስፖርቱ ባለሙያዎችና የውድድር አዘጋጆችም በጉዳዩ ላይ ሲሟገቱ ይስተዋላል። አገር አቋራጭ ውድድሮች በየዓመቱ በተለያዩ ከተሞች በተለይም በአውሮፓ ይካሄዳሉ። የዓለም አትሌቲክስም በየሁለት ዓመቱ የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና ያዘጋጃል። በእነዚህ ውድድሮች ሴትና ወንድ አትሌቶች በእኩል ርቀት ሲወዳደሩ አይታይም። እኤአ ከ2017 በፊት በዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና የሚካሄደው ፉክክር በአራት አይነት መንገድ ተከፍሎ ነው። የመጀመሪያው አዋቂ ወንዶች የሚወዳደሩበት የአስራ ሁለት ኪሎ ሜትር ውድድር ሲሆን አዋቂ ሴቶች ስምንት ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ርቀት ላይ ብቻ ተፎካካሪ ነበሩ። በወጣት ወንዶች መካከል የሚካሄደው ውድድር ደግሞ ስምንት ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ወጣት ሴቶች ስድስት ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ፉክክር ያደርጋሉ። እነዚህ ርቀቶች በዓለም ቻምፒዮናም ይሁን በግል አገር አቋራጭ ውድድሮች በብዛት የተለመዱ ናቸው። አልፎ አልፎ ግን በዓለም ቻምፒዮናም ይሁን በግል ውድድሮች እንደየሁኔታው ወንዶች ከሴቶች እኩል ርቀቶችን የሚሮጡበት አጋጣሚ ሲፈጠር ይታያል። ለአብነት ያህልም በ2017 በዩጋንዳ ካምፓላ ተካሂዶ የነበረው የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮናን ማንሳት ይቻላል። በዚህ ቻምፒዮና ለመጀመሪያ ጊዜ አዋቂ ሴቶችና ወንዶች እኩል አስር ኪሎ ሜትር የሸፈነ ውድድር ማድረጋቸው ይታወሳል። «ታዲያ ሴቶች በዚህ ውድድር ከወንዶች እኩል መሮጥ እየቻሉ አነስተኛ ርቀት እንዲሮጡ መደረጋቸው ለመጪው ትውልድ ምን አይነት መልዕክት ያስተላልፋል?» የሚል ከጾታ እኩልነት አኳያ ጥያቄ የሚያነሱ ቁጥራቸው ብዙ ነው።በምስራቅ ለንደን የአትሌቶች ማህበር አባል የሆነችው ማዑድ ሆድሰን በዚህ ውድድር የጾታ እኩልነት መረጋገጥ ካለበት ሴትም ወንድም እኩል ርቀት መሮጥ አለባቸው የሚል አቋም ይዛ ባለፉት ዓመታት ስትከራከር ቆይታለች። ይህን ሃሳቧንም በርካቶች ደግፈውታል። ሆድሰን በጉዳዩ ላይ ለራነርስ ዌብ ከዓመታት በፊት እንደገለፀችው፣ በአገር አቋራጭ ውድድሮች ሴትና ወንድ እኩል ርቀት እስካልሮጡ ድረስ መጪው የአትሌቲክስ ትውልድ በሩጫው ዓለም ሴትም ወንድም እኩል መሆናቸውን ሊረዳ አይችልም። ወንዶች ከፍ ያለውን ርቀት መሮጣቸው በአገር አቋራጭ ውድድሮች የሴቶቹ ፉክክር ከወንዶቹ ያነሰ የሚመስል ትርጉም ይሰጠዋልም ትላለች። ሆድሰን በዚህም ሳታበቃ በጉዳዩ ላይ አንድ መፍትሄ ለማምጣት በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ፊርማ አሰባስባ በቀናት ውስጥ ከአንድ ሺ በላይ ተከታዮችን አግኝታለች። ይህ ሃሳብ በፌስ ቡክ ገፅም«አይ ወዝ ኦር አም ራነር» በሚል በተፈጠረ የቡድን ገፅም በርካታ ወንዶች የደገፉት ሲሆን ብዙ ተከታዮች አግኝቶ መነጋገሪያነቱ እየጨመረ መጥቷል።አዳጋች በሆነው የአገር አቋራጭ ውድድር አትሌቶች በጭቃ፤ በዳገትና ቁልቁለት አልፎ አልፎም በበረዶ ይፈተናሉ። ይህን ከግምት የሚያስገቡ በርካታ ሰዎች ሴቶች በውድድሩ እንደ ወንዶች ረጅም ኪሎ ሜትር መሮጥ አይችሉም የሚል አስተሳሰብ እንዲይዙ ያደርጋቸዋል። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ግን ሴቶች በሌሎች ፈታኝ በሚባሉ ማራቶንና ግማሽ ማራቶን ውድድሮች ላይ ከወንዶች እኩል ርቀት ሮጠው ከሚያስመዘግቡት የሰዓት ልዩነት የተጋነነ አያስመዘግቡም። በቢኬት ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስና ባዮሜካኒክስ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ብሬን ሃንሌይ ጥናታዊ ፅሁፍ ግን በአገር አቋራጭ ውድድር ሴቶች ከወንዶቹ ባልተናነሰ ተመሳሳይ ርቀት መወዳደር እንደሚችሉ ይጠቁማል። ጥናቱ ልክ እንደ ወንዶቹ የሴቶቹም ውድድር መጀመሪያ ላይ ቀዝቃዛ ፉክክር የሚታይበት ቢሆንም መጨረሻው በፉክክር የታጀበ እንደሚሆን አረጋግጧል። አብዛኞቹ የውድድር አዘጋጆች ግን ሴቶች በዚህ ውድድር ከወንዶች እኩል ርቀት ቢሮጡ መጨረሻው በፉክክር እንደማይታጀብና አሰልቺ እንደሚሆን ስለሚያምኑ ሴቶች አነስተኛ ርቀት እንዲወዳደሩ ያደርጋሉ የሚል ክርክር ይነሳል። ይህ ግን ዞሮ ዞሮ ከፆታ እኩልነት ጋር ባይያያዝ እንኳን በርካታ ወጣት አትሌቶችን ወደ ውድድሩ እንዳይመጡ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል መላ ምቶች ይቀመጣሉ። ይህም ርቀቱ በረዘመ ቁጥር በርካታ አትሌቶች እንደ ጎዳና ላይ ረጅም ርቀት ውድድሮች ሁሉ የመወዳደራቸው አጋጣሚ ሰፊ ይሆናል የሚል ነው።የአርባ ስድስት ዓመቷ ጆ ፓቬይ አትሌቲክስን ካቆመች በርካታ ዓመታት ቢቆጠሩም ሴቶች በአትሌቲክሱ ዓለም አስደናቂ ታሪኮችን ከወንዶች እኩል መስራታቸውን በማስታወስ በአገር አቋራጭ ውድድሮችም ከወንዶች እኩል ርቀት መሮጥ እንዳለባቸው ከስካይ ኒውስ ጋር በነበራት ቆይታ ገልፃለች። «ለበርካታ ዓመታት በአስቸጋሪው የማራቶን ውድድር ሴቶች ከወንዶች እኩል ርቀት ሲወዳደሩ ቆይተዋል፤ በአገር አቋራጭ ውድድሮች እኩል ርቀት ያለመሮጣቸው ሴቶች ከወንዶች እኩል አቅም የላቸውም የሚል አመለካከትን ይፈጥራል» በማለትም ፓቬይ አቋም ይዛለች።የማራቶን ባለክብረወሰኗና የቀድሞ የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮኗ አትሌት ፓውላ ራድክሊፍ ሰሞኑን በጉዳዩ ላይ በማህበራዊ ሚዲያው የሚደረገውን ክርክር ተቀላቅላ ‹‹ርቀቶች መመሪያ ናቸው፣ የአገር አቋራጭ መወዳደሪያ ቦታዎች ጥሩ ከሆኑ በሁለቱም ፆታ ተመሳሳይ ርቀት ቢሮጥ ችግር የለውም፣ የውድድሩ ተፈጥሯዊ ባህሪ ሆኖ አንዳዶች አጭር ርቀት መሮጥ ሲፈልጉ ሌሎች ረጅም መሮጥ ሊፈልጉ ይችላሉ፣ ወንድም ሴትም ተመሳሳይ ርቀት መሮጥ እንደሚችሉ ግን አምናለሁ›› በማለት ፅፋለች። የአገር አቋራጭ ውድድር አዘጋጆች ይህ ልዩነት ለምን እንደተፈጠረ አሳማኝ ምክንያት ማቅረብ ባይችሉም በተለምዶ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ በመሆኑ ብቻ አሁን ላይ እየተገበሩት እንደሚገኙ ይታመናል። ይህ ግን በአንዳንድ የስፖርት ቤተሰቦች የፆታ ልዩነት እንዳለ ለማሳየት ሆን ተብሎ የተደረገ ሳይሆን የሴቶቹን ፉክክር ረዘም ላለ ሰዓት መመልከት ስለማይፈለግ ነው የሚል ትችት ይቀርባል። የእንግሊዝ አገር አቋራጭ ውድድር ማህበርም ይህ ልዩነት በተለምዶ አሰራር የመጣ መሆኑን በማመን በአገር አቀፍ ውድድር ላይ ሴቶች ከወንዶች እኩል ርቀት መሮጥ እንዳለባቸው ሲከራከርና ተፅዕኖ ሲያሳድር ቆይቷል። በዚህም የእንግሊዝ አትሌቲክስ ማህበርን ድጋፍ ማግኘት ችሏል። የእንግሊዝ አትሌቲክስ ማህበርም ጥያቄውን ወደ ፊት በማምጣት የተለያዩ ሙግቶችን ሲያደርግ ቆይቷል። ለረጅም ጊዜ ጉዳዩ የተዘነጋና ተድበስብሶ ያለፈ ቢመስልም የእንግሊዝ አትሌቲክስ ማህበር ከቀናት በፊት ዳግም ጉዳዩን በማንሳት በጥናት ጭምር አስደግፎ እየተሟገተ ይገኛል። አትሌቲክስ ማህበሩ በፈጠረው ተፅዕኖ በአገሪቱ በሚደረጉ የአገር አቋራጭ ውድድሮች ላይ ለውጦች ማምጣት ቢችልም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ የውድድር አዘጋጆችን ለማሳመን ተጨማሪ ስራዎች ይቀሩታል። ለዚህም የአውሮፓ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ላይ የሰራውን ጥናት ሰሞኑን ይፋ አድርጓል። 2016 ላይ ከሃምሳ አንድ የአውሮፓ አገራት አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ሰላሳ ሰባቱ ለጥናቱ ምላሽ የሰጡ ሲሆን ከሰላሳ ሰባቱ ሃያ አንዱ ሴቶችና ወንዶች በአገር አቋራጭ ውድድሮች እኩል ርቀት መሮጥ አለባቸው የሚል እምነት እንዳላቸው ጠቁሟል። አገር አቋራጭ ውድድር እንደ ረጅም ርቀት ውድድሮች ሁሉ በስፋት የሚታወቁት ምስራቅ አፍሪካውያኑ ኢትዮጵያና ኬንያ ቢሆኑም በጉዳዩ ላይ የተነሳው ሙግት ከወደ ምዕራባውያኑ መሆኑ አስገራሚ ነው። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር የነበሩትና አሁን የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ዱቤ ጂሎ በአንድ ወቅት ከአዲስ ዘመን ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያለውን አቋም አሳውቀው ነበር። አቶ ዱቤ ይህ በሴቶችና በወንዶች አገር አቋራጭ ውድድሮች ላይ ያለው የመወዳደሪያ ርቀት በተለምዶ ሲሰራበት ስለመጣ እንጂ ሴቶች ወንዶች የሚሮጡትን ርቀት መሮጥ ስለማይችሉ የተፈጠረ እንዳልሆነ ያብራራሉ። የርቀቱ ልዩነት የመጣው ቀደም ሲል በውድድሩ ደንብ ላይ የተቀመጠ በመሆኑ እንጂ ከጤናም አኳያ ይሁን ከሌሎች ነገሮች ሴቶች በአገር አቋራጭ ውድድር ከወንዶች ያነሰ ርቀት እንዲሮጡ የሚያደርጋቸው ምንም አይነት አሳማኝ ምክንያት እንደሌለ ገልፀው ነበር። «ሴቶች ከወንዶች እኩል በአገር አቋራጭ ውድድር መሮጥ አለባቸው፤ ማራቶንም ይሁን ግማሽ ማራቶን እኩል እስከ ሮጡ ድረስ በአገር አቋራጭም እኩል ርቀት መሮጥ አለባቸው፤ ይህ ካልሆነ ማራቶንም እኩል ኪሎ ሜትር መሮጥ የለባቸውም» በማለትም አቶ ዱቤ ሃሳባቸውን ሰንዝረው ነበር። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ ጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድሮችን በክልሎችና በክለቦች መካከል እንደሚያካሂድ ይታወቃል። በነዚህ ውድድሮች ወንዶቹም ሴቶቹም እኩል ርቀት የሚሸፍን ውድድር እንዲያካሂዱ ማድረግ ይቻላል ያሉት አቶ ዱቤ፣ ይህን ጥያቄ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለዓለምአቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ሊያቀርብ እንደሚችልም ጠቁመዋል። ከዚያም ዓለምአቀፍ ማህበሩ አሁን ያለውን ህግ አሻሽሎ በተመሳሳይ ርቀት እንዲወዳደሩ ከፈቀደ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም በእኩል ርቀት ውድድሮቹን ለማካሄድ የሚያግደው ነገር እንደሌለ አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013 ዓ.ም ", "passage_id": "45eada520b80135f2da51e6ad708b565" }, { "passage": "በ25 ዓመታት የውድድር ዘመኑ፤ በርካታ የኦሊምፒክና የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ሜዳሊያዎችን እንዲሁም 27 የዓለም ክብረወሰኖችን በእጁ አስገብቷል። በረጅም ርቀት የመም ተወዳዳሪዎችም ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል፤ ከገጹ ፈገግታ የማይነጥፈው ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ። በስድስት ዓለም ቻምፒዮናዎች ተሳትፎው አራት የወርቅ፣ ሁለት የብርና አንድ የነሃስ በጥቅሉ ሰባት ሜዳሊያዎችን ለሃገሩ አበርክቷል። እአአ 1993 የስቱትጋርት ቻምፒዮና የመጀመሪያ ተሳትፎው ሲሆን፤ በ10ሺ ሜትር የወርቅ በ5ሺ ሜትር ደግሞ የብር ሜዳሊያ ነበር ያጠለቀው። ከሁለት ዓመታት በኋላም ጉተንበርግ በተዘጋጀው ቻምፒዮና በ10ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያውን መድገም ችሏል። በአቴንስ እና ሴቪላ በተካሄዱት ውድድሮችም በተመሳሳይ የወርቅ ሜዳሊያውን የግሉ አድርጓል። እአአ የ2001 የኤድመንተን ቻምፒዮና የመጀመሪያውን የነሃስ ሜዳሊያ ሲወስድ፤ በመድረኩ የመጨረሻ ተሳትፎውን ያደረገበት የፓሪሱ ቻምፒዮናም አትሌቱን በብር ሜዳሊያ ነው ያሰናበተው። አሁን ኃይሌ ራሱን ከውድድሮች ካገለለ ዓመታትን አስቆጥሯል። ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነት መንበሩን በቃኝ ብሎ ቢያስረክብም አገራቸውን ወክለው ለመሮጥ ከተዘጋጁ አትሌቶች ጎን አይጠፋም። በስድስት ጊዜ የዓለም ቻምፒዮና ተሞክሮውን ነገ በሚጀምረው የኳታር የዓለም ቻምፒዮና ኢትዮጵያን ለሚወክሉ አትሌቶች እንደሚከተለው ያካፍላል። «ዓለም ቻምፒዮናን፤ በዓለም ላይ ያሉ ምርጥ አትሌቶች የሚሳተፉበት መሆኑ ለየት ያደርገዋል። በዳይመንድ ሊግ እና ሌሎች ውድድሮች ላይ የሚገኙት ጥቂቶች ሊሆኑ ይችላሉ፤ በዓለም ቻምፒዮና ግን በዓለም ላይ ‘አሉ’ የተባሉ አትሌቶች የሚሰባሰቡበት ነው»። ጠንካራ አትሌቶች\nየሚገናኙበትና የምርጦች\nምርጥ የሚመረጥበትም\nይኸው ውድድር\nበመሆኑ በአትሌቶች\nዘንድ በልዩነት\nይታያል። አትሌቶች\nሃገራቸውን የሚወክሉበት\nእንዲሁም ሃገራት\nባስመዘገቡት ውጤት በዓለም\nአቀፉ የአትሌቲክስ\nፌዴሬሽኖች ማህበር\nደረጃ የሚያገኙበት\nበመሆኑም፤ ስፖንሰር\nአድራጊ ተቋማትም\nጭምር ከፍተኛ\nትኩረት እንደሚሰጡት አንጋፋው አትሌት ይጠቁማል። ሃገሩን ወክሎ\nበጥረቱ ውጤት ካስመዘገበባቸው\nቻምፒዮናዎች ሁሉ እስካሁንም\nከትውስታው ያልተሰረዙ\nገጠመኞችም አሉት።\n«ከተካፈልኩባቸው ቻምፒዮናዎች\nሁሉ እስካሁንም\nየማዝንበት አጋጣሚ\nየደረሰው በስቱትጋርት\nነው። እአአ የ1993ቱ\nቻምፒዮና በ5ሺ\nሜትር አሸናፊነት\nአምልጦን የብር ሜዳሊያ\nነበር ያገኘነው»\nሲል ቁጭቱን\nይናገራል። ገጠመኞቹ\nእነዚህ ብቻም አይደሉም\nኃይሌ ይቀጥላል፤\n«እአአ 2001 ኤድመንተን\nላይ እኔና አሰፋ\nመዝገቡ ማሸነፍ\nበምንችለው ውድድር\nላይ የፈጸምነው\nስህተት ነው። በተለይ\nእኔ ለአምስተኛ\nጊዜ አሸናፊ\nእንደምሆን በማመኔ\nመዘናጋት አሳይቼ\nነበር፤ ባልተጠበቀ\nሁኔታ ግን አንድ\nኬንያዊ አትሌት\nአሸነፈን። ይህም እስካሁን\nእንደ እግር እሳት\nነው የሚለበልበኝ»\nበማለት በድንገት\nከመሃላቸው ፈትልኮ\nወርቁን ስላጠለቀው\nጥርሰ ፍንጭቱ\nኬንያዊ አትሌት\nቻርልስ ካማቲ ያስታውሳል። ከተካፈለባቸው ቻምፒዮናዎች ሁሉ አንጋፋውን አትሌት በተለየ የሚያስደስተው እአአ 1995 በስዊድን ጉተንበርግ የነበረው ተሳትፎ ነው። በዚህ ውድድር ላይ የመጨረሻውን 200ሜትር፤ የወቅቱ ጠንካራ አትሌቶች ከነበሩት፤ ፖል ቴርጋት፣ ካሊድ ካህ እና ሳላ ኢሱ ለማምለጥ ያደረገው ጥረት ያስደስተዋል። አጨራረሱን ሲያስታውስም ምናልባት ከ800ሜትር ሯጮች በላይ የፈጠነ እንደነበር ነው የሚገልጸው። ከትውስታው መልስም\nነገ በዶሃ በሚጀመረው\nቻምፒዮና ስለሚሳተፈው\nየኢትዮጵያ ብሄራዊ\nቡድን አስተያየት\nሰጥቷል። ከዳይመንድ\nሊግ ውድደሮች\nበመነሳት በወንድም\nበሴትም በተለይ\nበ10ሺ ሜትር\nጥሩ ጥሩ አትሌቶች\nአሉ። በዚህ ውድድር\nላይ ግን ብልጠት\nበጣም አስፈላጊ\nነገር ነው። በተለይ\nየመጨረሻዎቹ ሜትሮች\nላይ የተለየ\nነገር ካላደረጉ\nልፋታቸው ሁሉ ገደል\nነው የሚገባው።\nየመጨረሻው 100ሜትር\nቀላል አይደለም\nበጣም ብዙ ነገር\nነው የሚያበላሸው፤ በመሆኑም እዚህ ላይ አእምሯቸውንና ሰውነታቸውን መጠቀም አለባቸው። ብልጠት ካልታከለበት ሰውነት ብቻውን አሸናፊ አያደርግም፤ ብልጥ ከሆኑ ግን ሰውነትም ቢደክም ማሸነፍ ይቻላል በማለት የይቻላል ተምሳሌቱን ይናገራል። ቡድኑ ወደ ዶሃ ከመጓዙ ከሁለት ቀናት አስቀድሞም የብዙዎች ተምሳሌት የሆነው አትሌቱ ልምምድ በሚያደርጉበት አዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝቶ ምክርና ተሞክሮውን አካፍሏል። «ውድድር ‘እንዲህ ነው፤ እንዲያ ነው’ አይባልም ሁሉም የሰራውን ነው የሚያመጣው። ስታዲየሙ የሚያቀዘቅዝ መሳሪያ ስለተገጠመለት እዚህ ካለው አየር የተለየ አይሆንም። ከዚህ ባለፈ በአትሌቶችም ሆነ አሰልጣኞች መካከል አብሮነት አስፈላጊ ነው፤ የእናንተ አብሮ መሆን ብዙ ነገር ይቀይራል። የእናንተ በጋራ መስራት ከውጤትም በላይ ነው፤ ህዝቡም የሚፈልገው ይሄንኑ ነው። ሁሌም ሩጫ ስትሮጡ መጠንቀቅ ያለባችሁ የመጨረሻዎቹን 500 እና 600ሜትሮች ነው። ሌላውን ርቀት ሳትጨናነቁና ሳትፈሩ ዘና ብላችሁ ሸፍኑ። በመካከለኛ ርቀትም ቢሆን ሩጫውን ማንበብ የግድ ነው፤ መዘናጋት አያስፈልግም» ሲልም አስገንዝቧል። ቀጥሎም፤ «አንዳችሁ ለሌላችሁ ውጤት አስፈላጊ እንደሆናችሁ እንዳትዘነጉ። ልብ አድርጉ፤ አሰልጣኞችም ሆናችሁ አትሌቶች ‘እኔ ውጤት ላምጣ እንጂ ስለሌላው አያገባኝም’ ማለት የለባችሁም። ሌላው ማስታወስ ያለባችሁ እናንተን የሚመለከቱ ብዙ ሺ ታዳጊዎች አሉ፤ ውጤት ሁለተኛ ነገር ነው ዋናው እርስ በእርሳችሁ የምታሳዩት ስነ-ምግባር ነው። እናንተ ውጤት ስላመጣችሁ ብቻ መደሰት ሳይሆን ሌላውንም መደገፍ በተመሳሳይ አስፈላጊ ነገር ነው። አሰልጣኞች፣ የቡድን መሪዎችና ቴራፒስቶችም ከልምምዱ ባሻገር ስነ-ምግባር ላይም ማተኮር አለባችሁ»ም ብሏል። በመጨረሻም ለብሄራዊ ቡድኑ መልካም ውድድር እንዲሆን ተመኝቷል።አዲስ ዘመን  መስከረም 15/2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "50f62ba170ff10bda28e8097fbd8bf73" } ]
0b53e5584199d63e553f453282c9e8c2
9244288241948d956f1e17db20f07627
ማዕድ የማጋራት ብሄራዊ ጥሪና የስፖርቱ ማኅበረሰቡ ምላሽ
ኃያላኑን አገሮች ጨምሮ የዓለም ሳይንቲስቶች ከሁሉም በፊት ትኩረታቸውን በአንድ ነገር ካደረጉ አራት ወራት አለፈ።በቻይና ውኃን ግዛት በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መባቻ ለተከሰተውና በምህፃረ ቃሉ ኮቪዲ 19 የሚል መጠሪያ ላገኘው ኮሮና ቫይረስ።ወረርሽኙ ዘር፣ ቀለም፣ ትንሽና ትልቅ ሳይለይ ሁሉንም በማጥቃት የአለም ህዝብ በፍርሃት አቁማዳ ውስጥ እንዲገባ ካደረገ አራት ወራቶች አልፈዋል። በእነዚህ ወራት የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት የቻለ ምድራዊ ኃይል አልተገኘም። የአለም ሀያላን አገራት ከምድር ተሻግረን ጨረቃ ላይ እንወጣለን ሲሉ እንዳልተመፃደቁ፤ የኮሮና ወረርሽኝ ከቤታቸው ራሱ እንዳይወጡ አደረጋቸው። ሀገራቱ የወረርሽኙን ስርጭት በቶሎ የመቆጣጠር አቅም በማጣታቸው በአራት ወራት ብቻ ከሁለት መቶ ሺህ ሰዎች በላይ ህይወት ተቀጠፈ። የአለም ህዝብን እንደ ቅጠል ከማርገፍ በተጨማሪ በተለያዩ የንግድ ተቋማት ላይ ይህ ቀረሽ የማይባል ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውስ አስከትሏል። የኮቪድ 19 ስርጭት በማይታመን ፍጥነት ከመጨመር በተጓዳኝ መድሃኒት አልባ በመሆኑ ሀገራት ትኩረታቸውን ሁሉ ቅድመ መከላከል ላይ መስራትን መርጠዋል። ኢትዮጵያም የአለም ሀገራትን በአንድ ልብ እያስጨነቀ ካለውን ጠላት ህዝቦቿን ለመታደግ በብሄራዊ ደረጃ መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችሉ ሥርዓቶችን በመዘርጋት እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች። መንግስት የወረርሽኙ ባህሪ ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ አቋም አኳያ ስርጭቱ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚቸል በመገንዘብ ለህዝቡ ጥሪ በማድረግ የጋራ ተሳትፎን ያማከለ እንቅስቃሴ ሲደረግ ቆይቷል። በዚህ ተግባር ላይ የተለያዩ አካላት ተሳትፏቸውን ባሳዩበት ተግባር ላይ በስፖርቱ ዘርፍ ባሉ አካላት በኩል አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት የነበራቸው ተሳትፎ ትልቅ እንደነበር ለመታዘብ ተችሏል። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ከታወቀበት ከመጋቢት መጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ በቡድንም ሆነ በተናጠል ለወረርሽኙ መከላከያ የሚውል የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ ነበር ይሄንኑ ያስመሰከሩት። የስፖርቱን ተቋማት ከሚመሩት አካላት ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከወራት በፊት መንግስት ላቀረበው ጥሪ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ያሳዩት ተሳትፎ ዳግም ማሳየተቻው ተነግሯል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በጋራ ለማሸነፍ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ከሳምንታት በፊት የማዕድ ማጋራት ብሔራዊ ጥሪን አድርገው ነበር። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ከቢ. ጂ አይ ኢትዮጵያ በጋራ በመሆን በሳምንቱ መጨረሻ ላይ አንድ መርሃ ግብር ይፋ አድርገዋል። የስፖርቱ ተቋማት በኩል ይፋ የተደረገው መርሃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ያቀረቡትን «የማዕድ ማጋራት ብሄራዊ ጥሪ»ን እውን ያደርጋል ተብሏል። መጋቢት መጨረሻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ “ማዕድ ማጋራት” ሲሉ በሰየሙት መንገድ መንግስት የኮሮና ወረርሽኝ የከፋ ጉዳት ቢያደርስ በየቤቱ ምግብ ለማድረስ አቅሙም ሆነ መንገዱ ስለማይኖረው፤ ሰዎች በምግብ እጦት እንዳይጎዱ አንድ ቤተሰብ በቀን አንድ ምግብ ሌላ ቤተሰብ ለማቅረብ ዝግጅት እንዲደረግ እና እንደቤተሰብ ምክክር እንዲደረግ ሲሉ ነበር ያሳሰቡት። የጠቅላይ ሚኒስቴሩን ጥሪ ተከትሎ በርካቶቸ ምላሽ ሰጥተዋል። የስፖርት ተቋማቱ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት ሰሞኑን ይፋ ያደረጉት የምገባ መርሃ ግብር ይሄንኑ መሰረት አድርጓል። በዚህ መርሃ ግብር 300 የጎዳና ተዳዳሪዎችን ለአንድ ወር ያህል እንደሚመግብ ተነግሯል። የስፖርቱ ን ማኅበረሰብ ህዝባዊነት የሚያረጋግጥ መሆኑ የተነገረለት መርሃ ግበር ሚያዝያ 17 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲጀመር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እንደተናገሩት፤ የኮሮና ቫይረስ ወደ ሀገራችን ከገባ ጀምሮ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የስፖርቱ መንግስታዊ እና ህዝባዊ አደረጃጀቶች፣ ታዋቂ አትሌቶች፣ የደጋፊ ማህበራት፣ በአጠቃላይ የስፖርት ቤተሰቡ ህብረተሰቡን በማንቃት እና ኢኮኖሚያዊ ጫናውን ለመቋቋም የሚያግዝ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን መወጣታቸውን አስታውሰዋል። የስፖርቱ ማኅበረሰብ ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥልና የምገባ መርሃ ግብሩ መጀመር ለዚሁ ማሳያ ይሆናል ብለዋል። የጎዳና ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን በተወሰነ መልኩ ለማገዝ አንድ ወር የሚቆይ የምገባ መርሃ ግብሩ ይሄንኑ ሚና መሰረት ባደረገ መልኩ መጀመሩን የተናገሩት አቶ ኤልያስ፤ በስታዲየም ዙሪያ መርሃ ግብሩ እንዲደረግ የተመረጠበትን ምክንያት መኖሩን አመልክተዋል።« በወቅታዊ የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ስርጭቱን ለመቆጣጠር ሲባል በተለይ ስታዲየም ዙሪያ የሚገኙ ባር እና ሬስቶራንቶች መዘጋታቸው እና በአካባቢው ያለው እንቅስቃሴ መቆሙ ይታወቃል። ሬስቶራንቶች መዘጋታቸውን ተከትሎ ከሬስቶራንቶች ተመላሽ የሚሆኑ ምግቦችን ይጠቀሙ የነበሩ የጎዳና ተዳዳሪዎችም ሆነ በስታዲየም አካባቢ የተለያዩ ነገሮችን በመሸጥ ይተዳደሩ የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል። በመሆኑም ጊዜው የከፋ ችግር ላጋጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እጃችን የምንዘረጋበት፤ የጋራ መከራችንን በመተጋገዝ የምናልፍበት መሆኑን በማመን እና ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ነው »ሲሉ አብራርተዋል። አቶ ኤልያስ በመጨረሻ የተጀመረው ተግባር የሚቋረጡ ሳይሆን በቀጣይም እነዚህ ወገኖቻችን በዘላቂነት ህይወታቸውን ሊመሩበት በሚችሉ ጉዳዮች ላይ የስፖርት ቤተሰቡ በሙሉ አቅሙ የሚደግፍ መሆኑን አመልክተዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የቢጂ አይ ኢትዮጵያ አመራሮች በጋራ በመሆን ባስተላለፉት መልዕክት ደግሞ፤ የምገባ መርሃ ግብሩ በቀጣይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። «በአሁኑ ሰዓት የገጠመንን ፈተና ለማሸነፍ ለመንግስት ብቻ የሚተው ባለመሆኑ ሁሉም በአቅሙ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል »ያሉት ደግሞ፤ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ናቸው። ሚኒስትሯ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የምገባ ፕሮግራም ለሌሎች ድርጅቶች እና ባለሀብቶች አርዓያነት ያለው ተግባር መሆኑም ገልጸዋል። በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያቀረቡትን የማዕድ ማጋራት ብሔራዊ ጥሪ ተከትሎ የስፖርት ቤተሰቡ እና አመራሩ በዚህ በጎ ተግባር መሳተፉ ሊያስመሰግነው እንደሚገባ አመልክተዋል። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ከቢ. ጂ አይ ኢትዮጵያ በጋራ በመሆን ሚያዚያ 17 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ይፋ ያደረጉት መርሃ ግብር ለአንድ ወር ያህል የሚዘልቅ ይሆናል። በመርሃ ግብሩ 300 ሰዎች ተጠቃሚ የሚሆኒ ሲሆን ተመጋቢዎቹ በቀን 2 ጊዜ እንዲመገቡ ይደረጋል። የተጠቃሚዎች ዝርዝር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 7 የሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት አማካኝነት ተለይተው እንዲቀርቡ የተደረጉ ናቸው። ለምገባ ፕሮግራሙ ከ800 ሺ ብር በላይ ወጪ የሚደረግ መሆኑ ታውቋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 20/2012 ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=31281
[ { "passage": "‹‹ማዕድን›› ማጋራት የርህራሄነት ሀብታምነት እንጂ የቁስ ባለፀጋነት ጉዳይ አለመሆኑን ተረድቻለሁ። በወረርሽኙ ጦስ ምክንያት ገቢያቸው የነጠፈባቸውና ተንጠፍጥፎ የዕለት ጉርስ የቀራቸው ወገኖች ጭምር የማዕድን ማጋራት ዘመቻ መቀላቀላቸው የትርፍ ጉዳይ እንዳልሆነ ከቋንቋም በላይ ነው። የስሜት፣ የሐሳብ አንድነት፣ የልብ መውደድ ጉዳይ ነው፤ ወገንን ከስቃይ ማዶ አሻግሮ ነገን የማየት ተስፋ። በዚህ ሰዓት የዚህ ዘመቻ አካል የሆናችሁ ኢትዮጵያውያን ለእናት አገር ጥሪ ምላሽ በመስጠታቸው ሊመሰገኑ እንደሚገባ ድጋፍ የተደረገላቸው አካላት ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም ዜጎች ይናገራሉ። \nየማዕድ ማጋራቱ ጉዳይ ዓላማን የመጋራት ጉዳይ፣ ብሶትን የመካፈል ጉዳይ፣ ራባቸውን የማስታገስ ጉዳይ እንጂ የፖለቲካ ስሌት አይደለም። ለወገን ርሃብና ችግር መድረስ ፖለቲከኝነት ከሆነም እሰየው። የማዕድ ማጋራት ጉዳይ አብሮ አረንቋውን የመሻገር ጉዳይ፣ ከውሃ ሙላት የማሻገር ጉዳይ እንጂ የትርፍ መወርወር ጉዳይ አይደለም። \nየወረርሽኙ ብትር ቀጥሏል። የማዕድ ማጋራቱም ጉዳይ እንዲሁ። የሕጻናትን ልብ የሚያንጠለጥል ለቅሶ ላለመስማት፣ የእናትን ልብ የሚሰብር ትካዜ ላለማየት ገንዘብ መታደልን ሳይሆን ቅን ልብ መታደልን እንደሚጠይቅ አሳይተውናል። ዛሬ የዚህ ዓይነት ታሪክ ተቋዳሾችን የቅን ልብ ባለቤቶች ‹‹እኔም ስለወንድም እና እህቶቼ ያገባኛል›› የሚል ቅን ምላሽና እጃቸውን ለወገኖቻቸው ስለዘረጉ የህጻናት ማሳደጊያ ልጆች አወጋችኋለሁ። \nነገሩ እንዲህ ነው። ወላጅ አልባነት በአንድ እንዲከትሙ አድርጓቸዋል። መወለድ ሳይሆን መዋደድ እህትና ወንድም አድርጓቸዋል። ፍቅርን፣ አንድነትን፣ መዋደድን፣ መከባበርን ሲሰበኩ አድገዋል። የራሳቸውን አሳዳጊና ተንከባካቢ እናት፣ የሌሎችን ተንከባካቢ አክስት፣ እህል ውሃ ያሰባሰባቸውን እኩዮቻቸውን እህትና ወንድም፣ የጧት ጠያቂና ፈቃጃቸውን አባት አድርገው አድገዋል፤ ከ14 ዓመታት በላይ አብረው ኖረዋል። \nበዚህ ሁኔታ ያደጉት የኤስ ኦኤስ ልጆች መልካ ምነትና ደግነትን ከኢትዮጵያዊነታቸው ባሻገር በደግነት ከወለዷቸው ከአባታቸው ከፕሮፌሰር ሃርማን ግማይነር እና ማዕድ ማጋራትን ሰው የመሆንን አንድ ሚዛን ከሚያስቀድሙት ጠቅላይ ሚንስትራቸው ዶክተር አብይ አህመድ በመውረስ ‹‹በመተባበር፣ በመደጋገፍ ይሄን አስቸጋሪ ወቅት እናልፈዋለን›› በሚል ከየተበተኑበትና ከያሉበት የተለያየ የዓለም ክፍል በአላማ ጽናት ባሰባሰባቸው ‹‹የኤስ ኦ ኤስ የቀድሞ ልጆች ማህበር በኢትዮጵያ›› አማካኝነት ያሰባሰቡትን 120 ሺህ ብር የተለያዩ የዕለት መጠቀሚያ ቁሳቁሶች (ዘይት፣ ሩዝ፣ መኮሮኒ፣ ሳሙና፣ ፓስታና ዱቄት) በመግዛት ለ77 አቅመ ደካማ ወገኖቻቸው ለአንድ ወር ቢሆናቸው ሲሉ በዕለተ ሰንበት ግንቦት 23 በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስረክበዋል። በሕጻናት መንደር ሰው መሆንና መዋደድን ለምደው ማደጋቸው የሕጻናት ብሶትና የእናቶች መቸገር ከስጋቸው ዘልቆ አጥንታቸውን ይሰረስራቸዋል። መተጋገዝ ለአቅመ ሀብታም መድረስን አይጠይቅም ባይ ናቸው። ከአንደበታችሁ ከልባችሁ ስሙ። \nየማህበሩ ሊቀመንበር አቶ እዮብ በቀለ እንደተናገሩት፣ በመላው ዓለምም ሆነ በኢትዮጵያ በተከሰተው የኮቪዲ 19 ወረርሽኝ ምክንያት በርካታ ወገኖች ከሥራ ተለያይተዋል። በዚህ የተነሳም ሥራ ሠርተው ራሳቸውንና ልጆቻቸውን መግበው ማደር እየተቸገሩ ይገኛሉ። በመሆኑም ‹‹ወገኖቻችንን እና እህቶቻችንን ለማሰብ›› የተገናኙበት ፕሮግራም እንደሆነ ይገልፃሉ። ‹‹የወገኖቻችን ችግር የእኛ ችግር ነው፣ ሲርባቸው ይርበናል፤ ሲጠማቸው ይጠማናል›› ሲሉ ክፉ ጊዜን እጅ ለእጅ ተያይዘን እንሻገር። ለስጦታ ቅንነት እንጂ ሀብት አይወስነውም፤ ያለንን በመስጠት ለወገኖቻችን የምንደርስበት፣ ሰው የመሆናችን ሚዛን የሚሰፈርት፣ አዛኝ ልብ እንዳለን የምንታይበት፣ ያለንን በማካፈል ታላቅነትን የምንጎናፀፍበት ጊዜ በመሆኑ ወገኖቻችንን ልንደርስላቸው ይገባናል ሲሉ ጥሪቸውን አስተላልፈዋል። ለዚህ የተቀደሰ ተግባር በአጭር ጊዜ 120 ሺህ ብር በማበርከት እጃቸውን የዘረጉ የማሳደጊያ እህት ወንድሞቻቸውን በማመስገን ድጋፋቸው የወገኖቻችን ችግር እስኪቃለል ድረስ እንዲቀጥል ተማጽነዋል። \nየማህበሩ አባል የሆነው አቶ ሃይለሚካኤል ዋስይሁን እንደተናገሩት በኤስ ኦ ኤስ ሕጻናት ማሳደጊያ ክፉ ደጉውን ተምረው በማሳለፍ ራሳቸውን ችለው የሚኖሩ እህት ወንድሞቻቸው ጋር በእንዲህ ዓይነት ደግ የማዕድ ማጋራት ተግባር በመገናኘታቸው አመስግነዋል። በማህበራዊ ሚዲያ ጥሪ ከያሉበት ቀና ምላሽ የሰጡትን የማህበሩ አባላት እሰየው ድጋፋችሁ ለወገናችሁ ደርሷል ብለዋል። ማህበራዊ ሚዲያን ለሰብዓዊነት ተግባር እንጂ ለአረመኔነት ተግባር አታውሉ፤ ለወገን ለመድረስ ሰውነትን እንጂ ሀብታምነትን አትጠብቁ ሲሉ ከሕጻናት መንደር አድገው ለሕጻናት ችግር ለመድረስ ከሚጥሩት ልምድ እንዲቀስሙ መክረዋል። \nበአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 12 ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሸለመ ታደሰ በበኩላቸው እነዚህ ተስፋ ያላቸው ወጣቶች የወቅቱ ችግር በወገናቸው ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ አሳስቧቸው የአቅማቸውን በማበርከታቸው ምስጋና ችረዋል። ከእነዚህ ወጣቶች በጎ ተግባር ሌሎች የሚማሯቸው በርካታ ቁም ነገሮች አሉ። በወረዳው ከሰባት ሺህ 730 በላይ ነዋሪዎች በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ እንደሚገኙ ተለይተው የወገናቸውን ድጋፍ የሚሹበት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። ስለዚህ በወረዳው በሰባት ቀጠናዎች በተዘጋጁ መጋዘኖች ወጣቶች፣ ባለሀብቶች፣ አርሶ አደሮች እና አጠቃላይ ሕብረተሰቡ የአቅሙን በማበርከት ላይ መሆኑን በመግለጽ አመስግነዋል። \nአቶ ሸለመ እንዳሉት፤ ከዚህ የባሰ ጊዜ የሚመጣ ከሆነ ወገኖቻችን ለከፋ ጉዳት እንዳይጋለጡ ድጋፋችንን አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል። በእንዲህ አይነት ቅንነትና ርህራሄ የተሞላበት ተግባር ሰው የሆነ ሁሉ እንዲሳተፍ በወረዳው ስም ጥሪያቸውን አስተላፈዋል። በመጨረሻም ‹‹በሕክምና ባለሙያዎቻችንና በመንግሥታችን በኩል የሚተላለፉ መልዕክቶችን ሳይዛነፉ በመተግበር ከወረርሽኙ ራሳችንን፣ ቤተሰቦቻችንን እና ወገኖቻችንን ልንጠብቅ ይገባል።አዲስ ዘመን ሰኔ 5/2012ሙሐመድ ሁሴን", "passage_id": "854583c935b760e3ee8e0d0f86c2e20c" }, { "passage": "የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የዓለም ወቅታዊው ሁኔታ፤ የሰውን ልጅ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ፣ አስተሳሰብና ልማድ እንዲቀየር ምክንያት ሆኗል፡፡ በዚህ መንስኤነትም አካላዊና አእምሯዊ ጤናን ከመጠበቅና ከማዝናናት ባለፈ ከፍተኛ ገንዘብ የሚዘዋወርበት ስፖርትም በቀድሞ ቁመናው ላይ እንዳይገኝ ሆኗል፡፡ በዘርፉ በዓለም ደረጃ እአአ በ2011 ከተገኘው ገቢ በ45 በመቶ የላቀ ትርፍ ከሁለት ዓመታት በፊት መገኘቱን ወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም ያመላክታል፡፡ ይህ እአአ በ2018 የተገኘው 471ቢሊዮን ዶላር በዚህ ዓመት በእጅጉ ሊያድግ እንደሚችልም አመላካች ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ባልተጠበቀ ሁኔታ ተከስቶ መላውን ዓለም ባዳረሰው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ምክንያት እንቅስቃሴው ሊገታ ችሏል፡፡ እንደ ሌላው ዓለም ሁሉ የኢትዮጵያ ስፖርትም መዳከም አሳይቷል፡፡ በእንቅስቃሴው መገታት በስፖርተኞች፣ ክለቦች፣ ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ አወዳዳሪዎችና ሌሎች ባለድርሻዎች መካከል የነበረው ሰንሰለት በቫይረሱ ተጠቅቷል፡፡ በጥቂት ውድድሮች ሽልማት በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብና የውጭ ምንዛሪ ለሀገር ያስገኙ ከነበሩ አትሌቶች፤ ‹‹ነገ ያልፍልኛል›› በሚል እሳቤ ከኑሮ ጋር እስከሚታገሉት ጀማሪ ስፖርተኞች ድረስ የጉዳቱ ሰለባ ሆነዋል፡፡ ከአቅማቸው በላይ የሆኑትም ከበጎ ፈቃደኞች ተደጓሚ ሆነዋል፡፡ የስፖርት ማህበራትም ከውድድሮችና ስፖንሰሮች ማግኘት የሚገባቸውን ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡ ይህንን አሳሳቢ ሁኔታ\nያጤነው የኢፌዴሪ ስፖርት\nኮሚሽንም ወረርሽኙ በዘርፉ\nላይ ያሳደረውን ጫና\nበማመዛዘን እንዲሁም በተወሰነ\nመልኩ የሚያገግምበትን ሁኔታ\nለማመቻቸት የሚረዳ ሥራ\nበማከናወን ላይ ይገኛል፡፡\nበጉዳዩ ላይ ለአዲስ\nዘመን ጋዜጣ ማብራሪያ\nየሰጡት ምክትል ኮሚሽነር\nዱቤ ጂሎ፤ ከኮሮና\nቫይረስ ወረርሽኝ ጋር\nበተያያዘ እንደ ንግድ ሁሉ ስፖርትም ጉዳት ያስተናገደ ዘርፍ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ስፖርተኞች ቀድሞ የሚያገኙትን ገቢ ማግኘት ባለመቻላቸው፣ ክለቦች የመፍረስ አደጋ የተደቀነባቸው በመሆኑ መሰል ጉዳዮችን ከግምት በማስገባት ከመንግሥት ማገገሚያ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ እንዲለቀቅ ጥያቄ መቅረቡንም ይገልጻሉ፡፡ ኮሚሽኑ ለመንግሥት ያቀረበው\nየዳሰሳ ጥናት ‹‹ኮሮና\nቫይረስ በስፖርቱ ልማት\nላይ ያሳደረው ተጽእኖ\nየማገገሚያ ስልት›› የሚል\nሲሆን፤ ጥናቱ የተከናወነውም\nየሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ\nበመቀመር ጭምር ነው፡፡\nበዚህም እንግሊዝ፣ ናይጄሪያ፣\nኬንያ እና የመሳሰሉት\nሀገራት በወረርሽኙ ወቅት\nለማገገሚያ የተጠቀሙትን ስልት\nለመዳሰስ መሞከሩንም አመላክተዋል፡፡\nየኢትዮጵያ ስፖርት ሕዝባዊ\nመሠረት ያለው እንደመሆኑ\nበስፖንሰርና በስታዲየም ገቢ\nከሚያገኙት ገንዘብ ባለፈ\nለከተማ ክለብ ስፖርተኞች\nደመወዝ የሚከፈለው ከሕዝብ\nከሚሰበሰበው ታክስ ነው፡፡\nይህም ማለት አብዛኛውን\nገንዘብ የሚሸፍነው መንግሥት\nነው፡፡ ከወቅቱ ነባራዊ\nሁኔታ ጋር በተያያዘ\nውድድሮችን ማካሄድ ባለመቻሉ\nበዘርፉ ያለው  እንቅስቃሴ\nአስቸጋሪ ሆኗል፡፡ ይህንን ጊዜ ለመሻገርም ከስፖርት ማህበራቱ ጋር በመተባበር ስትራቴጂ በመንደፍና ጥያቄውን ለመንግሥት በማቅረብ ኮሚሽኑ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ ጥናቱ ስፖርተኞች በምን መልክ ወደሥልጠናና ውድድር ይመለሱ፣ እንዴትስ ፈቃድ ይሰጣቸው የሚለውን በመነሻነት መያዙንም ነው ምክትል ኮሚሽነሩ የሚጠቅሱት:: እንደ ኮሚሽንም ሀገር አቀፍ የስፖርት ማህበራቱ መርሃ ግብራቸውን እንዲያቀርቡም መመሪያ ተላልፏል፡፡ በኢትዮጵያ ስፖርት የሚንቀሳቀሰው የገንዘብ መጠን በውል አይታወቅም፡፡ ይህም መሰል ጥናቶች ላይ ተጽእኖ ማሳደሩ አይቀርም፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ፌዴሬሽን ይብዛም ይነስም በስፖንሰር የሚያገኙት ገቢ ይኖራል፤ ሆኖም በዓመት ይህን ያህል ይገኛል የሚለው በውል አይታወቅም፡፡ ለአብነት ያህል የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኢንተርናሽናል እና የሀገር ውስጥ ስፖንሰሮች ቢኖሩትም ከወቅታዊው ሁኔታ ጋር በተያያዘ በትክክል ለማወቅ የሚቻልበት ሁኔታ አዳጋች ነው፡፡ ቢሆንም ቅድመ በግምቶችን በማስቀመጥ ጥናቱ መከናወኑንም ነው ምክትል ኮሚሽነሩ ያስረዱት፡፡ የኮሮና ወረርሽኝ የስፖርቱን\nዘርፍ ሙሉ በሙሉ\nጎድቷል፤ እንቅስቃሴዎችንና ውድድሮችን\nገድቧል፡፡ በስፖርተኞችና ሀገራትም\nላይ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ\nችግሮችን አስከትሏል፤ ይህም\nአደጋ ነው፡፡ ነገር\nግን ይህ ጊዜ\nያልፋል በሚል ተስፋ\nሁሉም በአንድነት እየተጠባበቀ\nይገኛል፡፡ መንግሥትም ሁኔታዎችን\nበማገናዘብ ምላሽ ይሰጣል\nየሚል ተስፋ አለ፤\nይህን ወቅት በመሻገርም\nስፖርቱን ወደነበረበት የስፖርት\nቤተሰቡም ወደ ተመልካችነቱ\nየሚመለስበት ጊዜ ሩቅ\nአይሆንም፡፡ በመሆኑም ይህንን\nጊዜ በጋራ ለማለፍ\nራስን ከቫይረሱ መጠበቅ\nእንዲሁም የአካል ብቃት\nእንቅስቃሴ በማድረግ እንዲቆዩም\nምክትል ኮሚሽነሩ መልዕክታቸውን\nአስተላልፈዋል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 15/2012ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "238790f6962b11e39b556fdfe12c1add" }, { "passage": "እግር ኳስ በመዝናኛነቱ እንዲቀጥል ሰላማዊ የውድድር መድረክ መፈጠሩ የግድ ነው። ስኬታማ ሊግ ለመመልከት ደግም ጊዜና ገንዘቡን ወጪ አድርጎ፣ ፀሐይና ብርድ ሳይበግረው፣ተስፋ አስቆራጩን ሰልፍ ተቋቁሞ ስታድየም የሚገኘው የስፖርት ቤተሰብ የአደጋገፍ ስርዓትና ስፖርታዊ ጨዋነት ወሳኝነት አለው።ወጥ የውድድር መርሃ ግብር እጦት፤የዳኝነት ውሳኔ አሰጣጥ ችግር እንዲሁም ደጋፊዎች፤ የተጫዋቾችና የአሰልጣኞች ስፖርታዊ ጨዋነት ምግባር ችግር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መገለጫ መሆን ከጀመሩ ዋል አደር ብለዋል።\nየወንድማማችነትና የመግባባት ምሳሌ የሆነው ንፁህ እግር ኳስ ተብክሏል። የስታድየም ድምቀትና ለእግር ኳሱ ውበት ዋና ተዋናይ የሆኑ ደጋፊዎች የአደጋገፍ ስርአት ተለውጧል።ከስታድየሞቻችን የሚሰሙት ህብረ ዝማሬዎች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየደበዘዙ በአንፃሩ አፀያፊ ስድቦችና ፀብ አነሳሽ ድርጊቶች ጎልተው ተሰምተዋል፤ታይተዋል።በእግር ኳስ ሁነት ማሸነፍና መሸነፍ ያለና ወደፊትም የሚኖር መሆኑ ተረስቷል።\nይህን ተከትሎ በሚነሱ ግርግሮች ስጋትም ስታድየሞቻችን ለህፃናት፣በእድሜ ለገፉ ሰዎች፣ሴቶችና ለአካል ጉዳተኞች ምቾት የሚነሱ ሆነዋል።አዳዲስ ተመልካችን ለመመልከት እስኪያቅትም የካምቦሎጆው መንደር ለእንግዶቹ በሩን የዘጋ መስሏል።ይሁንና በተለይ ባለፈው ዓመት የፕሪሚየር ሊጉ መገለጫዎች እስኪመስሉ የተስተዋሉና የአገሪቱን እግር ኳስን መቀመቅ የሚከቱ እክሎች በዘንድሮው የሊግ ውድድር እንዳይስተዋሉ ሊጉም ካለፉት ጊዜያት በተሻለ በስፖርታዊ ጨዋናት የታጀበ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ብዙ ደክሟል።\nየኢትዮጵያ እግር ኳስ የፌዴሬሽኑ አዲስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጂራ በየክልሉ እየዞሩ ስፖርታዊ ጨዋነትን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ከከተማ አስተዳደሮች ጋር ተወያይተዋል።ክለባትና የደጋፊ ማህበራትም በየፊናቸው የየበኩላቸውን ተወጥተዋል።ክለቦች ተጨዋቾቻቸውን በስነ ምግባርና በእውቀት በማነጽ ረገድ የቤት ስራቸውን እንዲወጡ ተደርጓል። ከሳምንት በፊት በአዳማ ከተማ በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ የስፖርት ቤተሰቡን ያሳተፈ ውይይትም ተካሂዶ ነበር ።ይሁንና በስድስተኛው ስምንት የሊጉ መርሃ ግብር ፌዴሬሽኑም ሆነ የስፖርት ቤተሰቡ ጥረት ከንቱ ሆኖ የተለያዩ መድረኮች የተካሄዱ ስብሰባዎችም ፍሬ አልባ ሆነው ታይታል።በእለቱ በቅድሱ ጊዮርጊስና በሃዋሳ ከተማ መካከል ሊካሄድ በነበረው ጨዋታ ቀደም ሲል ለስፖርታዊ ጨዋነት ምክንያት ሆነው የሚቀርቡ ፤የዳኛ ውሳኔ አሰጣጥ ጉድለት፤ አሊያም ዳኞችን ውሳኔ አምኖ አለመቀበል፤ክብር የሚነኩ ዘለፋዎች፣የተጫዋቾችና አሰልጣኞች ለፀብ የሚያነሳሱ ድርጊቶች አልተስተዋሉም።ይልቅስ የስፖርታዊ ጨዋናት ጉድለቱ ጨዋታው ከመጀመሩ ቀድሞ የተከሰተ እንደመሆኑ ሌላ የግጭት መነሾ ተስትውላል። ከጨዋታው መጀመር 25 ደቂቃ ቀድሞ በደጋፊዎች መካከል የተካሄደው አምባጓሮም በርካታ የስፖርት ቤተሰቡን አባላት ለጉዳት ዳርጓል።ክስስቱም ጨዋታውን ለመታዳም ወደ ሜዳ የገቡ ደጋፊዎች ስሜት ክፉኛ አሳዝኗል፣አንገት አስደፍቷል።\nአስር ሰዓት ላይ መጀመር የነበረበት ጨዋታ እስከ ምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ድረስ ቢጠበቅም የኋላ ኋላ በተለይ ሃዋሳ ከተማዋዎች ጨዋታውን ለማካሄድ ባለመፈለጋቸው ሳይካሄድ ቀርቷል።ከብጥብጡ በኋላ ለክስተቱ ዋነኛ ምክንያት ሆኖ የቀረበው፤ በእለቱ ለእንግዳ ደጋፊዎች የተዘጋጀው የመቀመጫ ስፈራ አናሳ ሆኖ መቅረቡ ነው የተባለ ሲሆን፤ይህ ግን ብቻውን ለክስተቱ አሳማኝና በቂ ምክንያት ነበር ብሎ ለመናገር አያስደፍርም። ምክንያቱም የቦታ ጥያቄ ከሆነም በውይይት መፍታት ሲቻል ድንጋይ የሚያወራውር አንዳችም ምክንያት ይኖራል ተበሎ አይታሰብም።\nምንም እንኳን በእለቱ የግጭቱ ቀስቃሽ የሆኑ ደጋፊዎችን በውል መለየት ቢያስችግርና ቅድሚያ ጥፋተኛ የነበረው ማነው የሚለውን አጣርቶ ውሳኔ የሚያሳልፈው የሊግ ኮሚቴው በእለቱ በስታዲየሙ አንድ አቅጣጫ የተስተዋለው ግጭትና በሜዳው ክልል የነበረው ድብድብ በእጅጉ የሚያሳፍ፤ የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግም ስርዓቱን የሚያስጠብቅለት እንደሌለ የሚመሰክር ሆኖ ታይቷል።ከሁሉም በላይ በእንግዳ ክለብ ደጋፊዎች በአግባቡ መለየትና ከአደጋ መከላከል የማያስችል አጥር መኖሩም ጉዳቱን ከባድ አድርጎታል።በተለይ የድንጋይ ውርውራውን ተከትሎ ሸሽተው ወደ ሜዳው ክልል በገቡ የሃዋሳ ደጋፊዎችና በቅዱስ ጊዮርጊስ ስትዋርትቶች መካከል የተፈጠረው ግብ ግብ እጅጉን የሚያሳዝን ሆኖ ታይታል።ይሁንና ስታዲየሙን ከአፍ እስከ ገደፉ የሞሉት የፈረሰኞቹ ደጋፊዎች ከምንም በላይ ለስፖርታዊ ጨዋነት በመገዛት ወደ ፀብ አለመመራትና ሜዳ ወደነበሩት የሃዋሳ ደጋፊዎች አለመግባታቸውም በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አሰጥቷቸዋል።\nየስታድየሙን ፀጥታ ለማስከበር የሚመደቡ የፖሊስ ኃይሎች ቀደም ሲል ከነበረው ታሪክ ጋር ሲነፃፃር ችግሮችን በውይይት ከመፍታት ይልቅ ዱላን አማራጭ አድርገው አለመታየታቸው በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አሰጥቷቸዋል።\nበአጠቃላይ አንድ እርምጃ ፈቀቅ ማለት በተሳነው እግር ኳሳችን መሰል ክስተቶች መመልከት የሚቆመው እንዲሁም ሊጉን ስነስርዓት የማስጠበቅ ኃላፊነት ያለባቸው የስፖርት ቤተሰቦች ይህኑ ተግባራቸውን በአግባቡ የሚወጡት መቼ እንደሆን ለመረዳት አዳጋች ሆኗል።ከሁሉም በላይ በቅዱስ ጊዮርጊስና በሃዋሳ ከተማ መካከል ሊካሄድ ከነበረው ጨዋታ ቀድሞ የተከሰተው የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ግን ሊጉ ዘንድሮም ስርዓቱን የሚያስከብርለት ማጣቱን አሳይቷል።የሊጉን ስነስርዓት ለማስጠበቅ ከስፖርት ቤተሰቡም በላይ ከባድ ኃላፊነት ያለበት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተለይም ጠንካራ ህግጋትን በማስተላለፍ ረገድ ከባድ የቤት ስራ እንዳለበት አመላክቷል።\nይህን መሰሉ የስታድየም ብጥብጥና ሁከት በጊዜ መፍትሄ ካልተበጀለት፤ ነገሮች ፈራቸውን ሳይለቁ አስቀድሞ ነገሮችን ማስተካከልና መስመር ማስያዝ ካልተቻለ ከዚህም በከፋ ሁኔታ ወደ መቀመቅ መውረዳችን ሳይታለም የተፈታ ይሆናል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 9/2011ታምራት ተስፋዬ", "passage_id": "a584f5aadc30450c16fe4134c39a5306" }, { "passage": " ስፖርት በባህሪው ተጽእኖ ፈጣሪ እንደመሆኑ በቀላሉ መልዕክትን ሊያስተላልፍና ንቅናቄ ሊፈጥር እንደሚችል እሙን ነው። ይህ በመሆኑም ዓለም በአንድነት ከተላላፊው ቫይረስ ጋር እያደረገ ባለው ፍልሚያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል። በኢትዮጵያም የስፖርት ማህበራት፣ ክለቦች፣ ስፖርተኞችና ሌሎች ባለሙያዎች የበኩላቸውን ማበርከት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ሉሲዎቹም በዋና አሰልጣኛቸው ብርሃኑ ግዛው አስተባሪነት የድርሻቸውን ለመወጣት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ። እንደ ሀገር የመጣውን ፈተና ለመመከት የሚደረገውን እቅስቃሴ ለማገዝ በቅድሚያ የተነሱት የዋናው ሴት ብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች ነበሩ። ነገር ግን የገንዘቡን መጠን በመመልከት ለ20 እና 17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን፣ የንግድ ባንክ ሴቶች ክለብ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች እንዲሁም ደጋፊዎች ጥሪ አቅርበው ተቀባይነት ማግኘታቸውን አስተባባሪው አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ይገልጻል። በመገናኛ ብዙሃን የተደረገውን ጥሪ ተከትለው ብዙዎች ሚናቸውንለመወጣት እንቅስቃሴውን በመቀላቀላቸው ገንዘብ ማሰባሰቡን በቀጣዩ ሳምንት መጀመሪያ ሙሉ ለሙሉ በማጠናቀቅ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴ ገቢ የሚደረግም ይሆናል። የገንዘብ ማሰባሰቡ ስራ ተጫዋቾች በውድድሮች ተሳታፊ በመሆን ሃገራቸውን ከመወከል ባሻገር ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ያስችላቸዋል። ከዚያ ባሻገር ግን ተጫዋቾች ተጽእኖ የመፍጠር አቅማቸውን በመጠቀም ደጋፊዎችንና ህዝቡን ማነሳሳትን ዓላማው ያደረገ መሆኑንም አሰልጣኙ ይጠቁማሉ። ለማሰባሰብ የታቀደው የገንዘብ መጠን 100ሺ ብር ሲሆን እስካሁን የተዋጣው ከ55ሺ ብር በላይ ደርሷል፤ በቀጣይ ቀናትም እቅዱን ለማሳካት ጥረት ይደረጋል። ከድጋፉ ባሻገር ኢትዮጵያን ጨምሮ ዓለምን እያናወጠ ያለው ቫይረስ ማለፉ አይቀርምና ካለፈ በኋላ ላለመቸገር ተጫዋቾች ላይ መስራት ተገቢ ነው። በዚህ ላይም የግንዛቤ ችግር መኖሩን ያነሳው አሰልጣኙ ‹‹ በስፖርቱ ውስጥ ሆነን ኃላፊነታችንን ተወጥተናል፤ በዚያ ልክ ግን በየደጃችን ትንሽ እንቅስቃሴ የመስራትና የስፖርት ቁሳቁሶችን በማዘጋጀት በግል የመስራት ልምድ ችግር አለብን። ሁሌም አሰልጣኞችን እንጠብቃለን። ይህ ሁኔታ ካለፈ በኋላ ስፖርቱ አንዳይቀዛቀዝና እንደ አዲስ ከዜሮ ጀምረን ውጤት እንዳናጣ የትኛውን ስራ መቼ መስራት አንዳለበን አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን እያደረገን ነው። ይህ የበለጠ ጥሩ ይሆናል ብለን አንጠብቃለን፤ እኛ አንደ ባለሙያ ከምንሰጣቸው ባለፈ ተጫዋቾቹ ተዘናግተው ስራቸው ላይ ወደ ኋላ እንዳይሉ እየሰራን እንገኛለን›› ሲል ያብራራል። በዚህ ሁሉም ቤቱ እንዲቆይ በተደረገበት ወቅት ስፖርተኞች እንደ ቀድሞው ልምምዳቸውን ለመስራት ከባድ ይሆንባቸዋል። ባደጉት ሃገራት አሰልጣኞች ተጫዋቾቻቸውን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዘው ክትትል ያደርጉላቸዋል። ተጫዋቾቹም ከቤታቸው ሆነው በየግላቸው የሚያደርጉትን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በተንቀሳቃሽ ምስል ለዓለም በማጋራት ላይ ይገኛሉ። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት ግን ይህ የተለመደ ካለመሆኑም ባለፈ በምን መልኩ መስራት እንደሚቻል ግንዛቤውም የለም። ለዚህም አሰልጣኞች በማህበራዊ ትስስር ዘዴዎችን በመጠቀም (በቴሌግራም) ከተጫዋቾቻቸው ጋር ግንኙነት እንደሚያደርጉ አሰልጣኙ ያስረዳል። በዚህም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዴት መስራት እንደሚችሉ ግንዛቤ በመፍጠር ላይ ይገኛሉ። ቴክኒካዊ የሆኑ የስልጠና ክፍሎችንም በተለያዩ የአሰልጣኝነት ስልጠናዎች ባገኟቸው ልምዶች ታግዘው ለተጫዋቾቻቸው ያጋራሉ። ከዚህ በተጓዳኝ ተጫዋቾች በመገናኛ ብዙሃን በሚሰሙትና በሚመለከቱት በመረበሽና በመጨነቅ ስነ-ልቦናቸው እንዳይጎዳ ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ለማሳወቅ የአሰልጣኞች ቡድኑ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ለሉሲዎቹም ሆነ ለዋልያዎቹ, ባለውለታ እንደመሆኑ በዚህ ወቅት ስፖርት፤ ህዝቡ ሚናውን በመወጣት ከጎኑ መሆኑን ማሳየት አለበት። ዝናብ፣ ብርድና ጸሃይ ሳይል ቡድኑን ሲደግፍና እንዲሁም ወደ ውጪ ሃገራት ሲጓዝ ከጎኑ የነበረውን ህዝብ በዚህ ወቅት የማጽናናትና የማረጋጋት ግዴታ እንዳለበት አሰልጣኙ ይገልጻል። የስፖርቱ ቤተሰብ ህዝቡ በቫይረሱ ተጠቂ እንዳይሆን እንዴት መጠንቀቅ እንደሚገባው ከማስተማር ባሻገር በግልና በቡድን የሚያደርገው አስተዋጽኦ በቂ ነው የሚል እምነት የሌለው አሰልጣኙ፤ ከዚህ በላይ አስፈላጊ መሆኑን አመላክቷል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 3/2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "40d2f498b59fb0bf9cf0548e21a15c61" }, { "passage": "የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስፖርት ሲታሰብ አንዱ አቅጣጫ ያመዝናል። የአበበ ቢቂላ፤ እሸቱ ቱራ፣ ቶለሳ ቆቱ፣ ፊጣ ባይሳ፣ ኃይሌ ገብረስላሴ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ጌጤ ዋሚ፣ ገዛኸኝ አበራ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ስለሺ ስህን፣ ጥሩነሽ ዲባባና ቤተሰቧ እንዲሁም የበርካቶች መገኛ፤ የኦሮሚያ ክልል። ክልሉ የረጅም ዓመታት የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ስፖርት የጀርባ አጥንት ስለመሆኑም አያጠያይቅም። አሁንም የኦሊምፒክ፣ የዓለም ሻምፒዮና እንዲሁም የበርካታ ውድድሮች ድምቀት እንደሚሆኑ ተስፋ የሚጣልባቸው አትሌቶች በመፍራት ላይ ይገኛሉ። አትሌቲክስና ክልሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው ለማለት የሚያስደፍረውም ለስፖርቱ ምንጭ በመሆኑ ነው። በህዝቡም ዘንድ እንደ ባህል የሚታየው ስፖርቱ፤ አንድ የኢኮኖሚ ምንጭ እስከመሆን ደርሷል። ይህ ከህዝቡ ጋር ከፍተኛ ትስስር ያለው ስፖርት ለባህላዊ ሁነት ማድመቂያ እንዲሁም መልዕክት ለማስተላለፍ ተመራጭ ነው። በኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አድማሱ ዋጋሪ፤ የኢሬቻ በዓል አከባበር ወቅት ወጣቶች የሩጫ፣ የፈረስ ጉግስ እና ሌሎች ውድድሮችን የማድረግ ባህል እንዳላቸው ያስታውሳሉ። ይህም የሚያሳየው ሩጫ የበዓሉ አንድ አካል እንዲሁም የሩጫ ስፖርት ለኦሮሚያ ህዝብም ባህል መሆኑን ነው። በተለይ በዚህ የሽግግር ወቅት በህዝቦች መካከል ጥርጣሬ የበዛበት እንደመሆኑ፤ በሩጫው የሰላምና አንድነትን መልዕክት ለማስተላለፍ እንዳስፈለገ ያስረዳሉ። ትናንት «እሬቻ የሰላምና የአንድነት ተምሳሌት» በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው የሩጫ ውድድርም የዚህ ማሳያ ነው። ከ150 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል ምክንያት በማድረግ እንዲሁም ስለ እሬቻ በዓል ህዝቡ እንዲያውቅና ባህሉን እንዲረዳ ለማድረግ በአዲስ አበባ በተካሄደው የእሬቻ የሰላም ሩጫ ላይ በሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ተገኝቷል። መነሻና መድረሻውን በመስቀል አደባባይ ያደረገው የጎዳና ላይ ሩጫው፤ 10 ኪሎ ሜትር የሸፈነ ነበር። በሩጫው ላይ እንዲሳተፉ ለሁሉም የአትሌቲክስ ክለቦች ጥሪ የቀረበ ሲሆን፤ ከ500 በላይ የሚሆኑ አትሌቶች ከኦሮሚያ፣ ድሬዳዋ፣ አዲስ አበባ፣ ከደቡብ እንዲሁም ከአማራ ክልል ተካፋይ ሆነዋል። በወንዶች መካከል በተካሄደው ውድድር የስሁር ኮንስትራክሽን አትሌቱ በሪሁን አረጋዊ አሸነፊ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ እንዲሁም የ50ሺ ብር ሽልማቱን ወስዷል። ያለፈውን ዓመት በጉዳት ከወድድር ርቆ የቆየው አትሌቱ፤ ብርቱ ተፎካካሪ አለመኖሩ ለአሸናፊነቱ እንደረዳውም ገልጿል። ኃይለማሪያም ኪሮስ እና ደጀኔ ደበላ ደግሞ ከመብራት ኃይል እና ኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ስፖርት ክለብ ሁለተኛ እና ሦስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል። በሴት አትሌቶች በኩልም ኦብሴ አብደታ ከለገጣፎ ለገዳዲ ክለብ አሸናፊ ሆናለች። በግሏ የተሳተፈችው አትሌት መስታወት ፍቅሩ ሁለተኛ ስትሆን፤ የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲዋ አንቻለም ሃይማኖት ሦስተኛ በመሆን የነሃስ ሜዳሊያቸውን አጥልቃለች። ከአንድ እስከ ሦስት ያለውን ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን ያጠናቀቁ አትሌቶችም ከሜዳሊያው ባሻገር፤ የ50ሺ፣ 30 እና 20ሺ ብር ማበረታቻ ተበርክቶላቸዋል። የኦሮሚያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊና የሩጫው ኦርጋናይዘር አቶ ነጋ ቱጂባ፤ ሩጫው ከታሰበው ሰዓት ዘግይቶ ቢጀመርም በመልካም ሁኔታ መጠናቀቁን ይገልጻሉ። የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ በዓለም ደረጃ የገነባው የአትሌቲክስ ስፖርት፤ ከአበበ ቢቂላ ጀምሮ ያለው ታሪክ በርካታ አትሌቶች የወጡት ከኦሮሚያ ክልል መሆኑን ያሳያል። አትሌቲክስ ከኦሮሞ እሴት ጋር ሊያያዝ የሚችል በመሆኑም፤ ኢሬቻና አትሌቲክስን በማገናኘት ህዝቡ በእኔነት ስሜት እንዲደግፈውና እንዲያሳድገው ያደርጋል። በየዓመቱ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓልም ስፖርታዊ ውድድሩ ይበልጥ ውበት የሚሰጠው ይሆናል። የኦሮሚያ ክልል የኢትዮጵያ አትሌቶች ምንጭ ቢሆንም በዚህ ወቅት ግን ውጤቱ እየቀነሰ መምጣቱ ይታያል። የዚህን ምክንያትም በመገምገም ወደ ቀድሞ ስፍራው ለመመለስ ህዝባዊ መሰረት ማስያዝ የግድ ይሆናል። መሰል ውድድሮች በየዞኑ እና ወረዳው ማካሄድ ቢቻል፤ ህዝቡ ስፖርቱንና አትሌቶችን በባለቤትነት ስሜት በመደገፍ ወደ ምንጭነቱ መመለስ እንደሚቻልም ኃላፊው ይጠቁማሉ። በዓሉም በሰላምና በፍቅር ያለ ኃይማኖትና መሰል ልዩነት የሚያከብር በመሆኑ ይህንን አጠናክሮ መቀጠል ለስፖርቱ የራሱን ሚና የሚጫወት ይሆናል። አሁን በ50ሺ ሰው የተጀመረው ውድድር ወደፊትም ተጠናክሮ ለማስቀጠልና ቁጥሩንም ለማሳደግ ጥረት ይደረጋል። ሩጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እንዲሁም ለተሳታፊዎችም ኃላፊው ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አዲስ ዘመን መስከረም 12/2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "e942551dd0fa34e4e889740649e5d299" } ]
d22555101296306d5f0fdaf9e5dd78c5
cc41fe609d4ceb7bef911a1285183aa4
የመሬትና የብድር አጠቃቀም ችግር በወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ጫና ማሳደሩ ተገለጸ
ዋቅሹም ፍቃዱአዲስ አበባ፡- የመሬትና የብድር አጠቃቀም ችግር በወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ጫና ማሳደሩን የአሶሳ ከተማ ከንቲባ አስታወቁ። በበጀት ዓመቱ ለ1ሺህ 117 ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር አቅዶ በሩብ ዓመቱ 543 ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠሩን ገለጹ ።የከተማው ከንቲባ አቶ ዑመር መሀመድ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት ፣ አሶሳ ከተማ ከሁሉም የአገሪቱ ክፍል የሚመጡ የብሔር ብሔረሰቦች መናኸሪያ በመሆኗ በርካታ ወጣቶች ስራ ፍለጋ ወደ ከተማይቱ ይመጣሉ። የከተማ መስተዳድርም ያለምንም አድሎ አቅም በፈቀደ መጠን የስራ ዕድል ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል። ለወጣቶቹ የብድር አቅርቦት ሲመቻች አንዳንድ ወጣቶች ሰርተው ከመለወጥ ይልቅ ያገኙትን ገንዘብ ይዘው የመሰወር እንዲሁም የመጥፋት ሁኔታ ያሳያሉ ያሉት ከንቲባው ፣ በተመሳሳይ መልኩ አንዳንዶቹም ምንም እንኳ እንደሌሎቹ ገንዘብ ይዘው ባይጠፉም በአግባቡ ሰርተው ከተለወጡ በኋላ የተበደሩትን ገንዘብ ሳይመልሱ ተጨማሪ ብር የመጠየቅ ሁኔታዎች አሉ ብለዋል ። ይህ ደግሞ ሌሎች አዳዲስ ስራ ፈላጊዎች በአግባቡ እንዳይስተናገዱ አሉታዊ ተጽዕኖ እያደረገ መሆኑን አመልክተዋል። ከተማ መስተዳድሩ ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ቢሆንም ፣በከተማው የስራ ቦታ እጥረት መኖሩን አመልክተዋል ። ያለውም ቢሆን ለህገ ወጥ ወረራ የተጋለጠ በመሆኑ ችግሩን ለማቃለል እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ። የብድር አቅርቦትም ቢሆን ምናልባት ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተያይዘው እጥረት እንዳለም የጠቆሙት ከንቲባው ፣ በቀጣዩ ከፌዴራልም ሆነ ከክልሉ ለከተማይቱ ወጣቶች የሚመደበው በጀት በአግባቡ ስራ ላይ እንዲውል ልዩ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግም አስረድተዋል። በከተማው የመሬት ወረራ ትልቁ ራስ ምታት እንደሆነ ጠቁመው ፣ ወጣቶች የተሰጣቸውን የስራ ቦታ በአግባቡ ሰርተውበት ከተለወጡ በኋላ ለቀጣዩ ስራ ፈላጊ ከመልቀቅ ይልቅ አንዳንድ ወጣቶች የወሰዱትን መሬት ለሌሎች አሳልፈው እንደሚሸጡና የተሸጠው መሬትም ለስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል ከመፍጠር ይልቅ ለህገ ወጥ መኖሪያ ቤት ግንባታ እንደሚውል ከተማ መስተዳድሩ ባደረገው ክትትልና ግምገማ እንደ ደረሰበት ከንቲባው አክለው ገልጸዋል። እንደ እርሳቸው ገለጻ አሶሳ ከተማ ለስራም ሆነ ለኑሮ ምቹ በመሆኗ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ አዳዲስ ፊቶችን፣ በተለይ ወጣቶችን በከተማይቱ ማየት እየበዛ መጥቷል። ወደ ከተማው የሚመጡ ሰዎች አሶሳ አገራቸው እንደሆነች በማመንና በመተማመን ስለሚመጡ የከተማ አስተዳደሩም እነዚህ ወጣቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ አቅዶ እየሰራ ይገኛል። እስካሁንም የስራ እድል ከተፈጠረላቸው ወጣቶች መካከልም ግማሾቹ ከሌሎች አከባቢ የመጡ ናቸዉ። አቶ ዑመር ከብድር አጠቃቀም ጋር የተስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ለስራ ቁርጠኛ የሆኑና ሰርተው ለመለወጥ ጽኑ ዓላማ ያላቸውን ወጣቶች በጥንቃቄ እንዲመለመሉ በማድረግ በዋስ ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሰሩ ጠቁመው፣ በመሬት አጠቃቀም ዙሪያም ጠንካራ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት ችግሩን ለመፍታት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን አመልክተዋል ። አዲስ ዘመን ታህሳስ 22/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=38531
[ { "passage": "አዲስ አበባ፡- በሴቶች ስራ ፈጠራ ልማት ፕሮጀክት የብድርና የስልጠና አገልግሎት ሴቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የከተሞች ስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ጥሪ አቀረበ፡፡የኤጀንሲው ዳይሬክተር አቶ ዘነበ ኩሞ እና የሴቶች ስራ ፈጠራ ልማት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዮሃንስ ሰለሞን ትናንት  በቢሯቸው በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ፕሮጀክቱ የሚሰጠው የስልጠና እና የብድር አገልግሎት ለስራ ፈጣሪ ሴቶች ትርፋማነት ያግዛል፡፡በፕሮጀክቱ ሴት ስራ ፈጣሪዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ያቀረቡት አስተባባሪው ፣ በፌዴራል ከተሞች የስራ እድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ስር የሚገኘው የሴቶች ኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ፕሮጀክት ከዓለም ባንክና ከተለያዩ መንግስታት የተገኘ የረዥም ጊዜ ብድር እየተተገበረ የሚገኝ  መሆኑንም አስረድተዋል፡፡አቶ ዘነበ እንደገለጹት፤ የፕሮግራሙ የመጀመሪያ ክፍል 2005 ዓ.ም የጀመረ ሲሆን፤ ታህሳስ 2010 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ነበር፡፡ የፕሮጀክቱ ውጤታማነት የዓለም ባንክ ባደረገው ግምገማ መሰረት የብድር ገንዘቡ ሙሉ ለሙሉ ስራ ላይ መዋሉ፣ ውጤታማ፣ ተግባራዊ ለውጥ ያስገኘና የተሰጠው ብድር 98 ነጥብ ሰባት በመቶ ተመላሽ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡በመጀመሪያው የፕሮጀክቱ ክፍል ከ28 ሺ በላይ አገልግሎት ፈላጊ ስራ ፈጣሪ ሴቶች ተመዝግበው 16 ሺ ያህሉ ስልጠና ወስደዋል፡፡ ከ2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ለ10 ሺ ስራ ፈጣሪዎች ሴቶች ተሰጥቷል፡፡ በዚህም በአማካይ 256ሺ ብር አንድ ስራ ፈጣሪ ሴት ብድር የወሰደች ሲሆን፤ 55 ነጥብ ሰባት በመቶ የሰው ሃይል የመቅጠር አቅማቸው እንዲያድግ እና የድርጅታቸው ትርፍ ደግሞ በ44 ነጥብ 77 በመቶ እንዲጨምር እገዛ አድርጓል፡፡ በፕሮጀክቱ ከ12 አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማትና ከልማት ባንክ የብድሩ ፋይናንስ ቀርቧል፡፡የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ዮሃንስ ሰለሞን የፕሮጀክቱን ውጤታማነት በመመልከት የጃፓን መንግስት 50 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም የጣሊያን መንግስት 15 ሚሊዮን ዩሮ በብድር መስጠታቸውን ጠቅሰው፣ በዚህም ፕሮጀክቱ ለሁለት ዓመታት እንዲራዘም መደረጉን ጠቁመዋል፡፡በተገኘው ተጨማሪ የብድር ድጋፍ ከዚህ ቀደም ፕሮጀክቶቹ ይተገበር ከነበረባቸው አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር፣ ሐዋሳ፣ መቀሌ እና አዳማ በተጨማሪ በጎንደር፣ አክሱም፣ አሰላ እና ዲላ ከተሞች በቀጣይ አገልግሎቱ እንደሚሰጥም አስታውቀዋል፡፡ የፕሮጀክቱ ብድር እስከ 36 ወር (ሶስት ዓመት) ድረስ ተመላሽ እንደሚሆን ተናግረው፣ የዓለም ባንክ ከአገር ውስጥ አንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ጋር በጋራ በመሆን የተበዳሪዋን ፍላጎትና አቋም በመመዘን ያለማስያዣ ለማበደር ያካሄዱት የሙከራ ጥናት ተስፋ ሰጪ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ለሙከራ ያህልም ለ15 ስራ ፈጣሪ ሴቶች ብድር በመስጠት መጀመሩንም ገልጸዋል፡፡የፕሮጀክቱ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ከተሞች እና ከከተሞቹ እስከ 50 ኪሎ ሜትር ዙሪያ የሚገኙ አካባቢዎች የሚገኙ ስራ ፈጣሪ ሴቶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡ የፕሮጀክቱን ስራ ፈጠራና የስራ ስልጠናውን ገና ወደ ስራ መግባት የሚፈልጉ ሴቶችም መውሰድ እንደሚችሉ ተመልክቷል፡፡ 8658 በነጻ የስልክ መስመር በመደወል ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት እንደሚቻል ተጠቁሟል፡፡አዲስ ዘመን ጥር 18/2011በሰላማዊት ንጉሴ", "passage_id": "d2699985898d28d1c294e3b2deee32ed" }, { "passage": " አዲስ አበባ፡- ውድ የሆነውን የከተማ መሬት ሀብት ቆጥሮ ለማወቅ እና ለማሳወቅ የተጀመረው የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ የሰለጠነ የሰው ሃይል እጥረት እየፈተነው መሆኑን የፌዴራል የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት፣ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ገለጸ፡፡ የኤጀንሲው\nየህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን\nየስራ ኃላፊ አቶ\nአራጌ ክብረት በተለይ\nለአዲስ ዘመን ጋዜጣ\nዝግጅት ክፍል እንደተናገሩት፤\nበአገራቱ በዋነኝነት በደቡብ፣\nበኦሮሚያ፣ በአማራና በትግራይ\nክልሎች ባሉ በ18\nትላልቅ ከተሞች ህጋዊ\nካዳስተር መገንባት ተጀምሯል፡፡\nከከተማዎቹ መካከል ባህርዳር፣\nሀዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ ዲላ፣\nአርባምንጭ፣ ደብረማርቆስ፣ ጎንደር፣\nደብረብርሃን፣ ትግራይ፣ አክሱም፣ ሽሬ፣ አዲግራትና መቀሌ ተጠቃሾቹ ሲሆኑ፤ በእነዚህ ከተሞች በእኩል ደረጃ ባይሆንም ስራው እየተሰራ ይገኛል፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ሰፊ ስራ ተሰርቷል፡፡ ህጋዊ ካዳስተር መተግበሩ\nየመልካም አስተዳደር እና\nሌሎችም ውስብስብ ችግሮችን\nየሚያስቀር፤ ብልሹ አሰራሮችን\nበተለይም ሙስናን ከስር\nመሰረቱ ለማድረቅ የሚረዳ\nመሆኑን የተናገሩት አቶ አራጌ፤ ባለ ይዞታዎች ሙሉ በሙሉ በመሬቱ ላይ ዋስትና እንዲኖራቸው የሚያግዝ እና ዓለም አቀፍ ስታንዳርዱን የጠበቀ ሰርተፍኬት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ያም ሆኖ ግን ህጋዊ ካዳስተር የመገንባት ሥራው እንዳይፋጠን የሰለጠነ የሰው ሃይል ችግር ማነቆ ፈጥሯል፡፡ እንደ አቶ አራጌ\nገለፃ፤ ካዳስተሩ በሁሉም ከተሞች እኩል እንዳይተገበሩ ዘርፉ የሚፈልገው የሰለጠነ የሰው ሃይል እጥረት ከማጋጠሙም ባሻገር የቅየሳ መሳሪያዎች አለመሟላት፣ የቴክኖሎጂ የግብዓት አቅርቦት በተፈለገው መጠን አለመገኘት እንዲሁም በአገሪቱ ያሉ ወቅታዊ ችግሮች ሥራው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠሩ መሆኑን ጠቁመዋል።ህጋዊ ካዳስተር ዜጎች\nተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማገዝ\nጎን ለጎን መንግሥት\nከመሬት ሊያገኝ የሚገባው\nጥቅም የበለጠ ለማጠናከር፤\nለኢንቨስትመንት እና ለቱሪዝም ምቹ ለማድረግ እንዲሁም ከተሞች በራሳቸው ገቢ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ የሚያስችል መሆኑን አቶ አራጌ ተናግረዋል።እያንዳንዱ ምዝገባ በቴክኖሎጂ የተደገፈ፤ በቀጥታ ባለይዞታዎች እንዲሁም ባለሙያዎች የሚሳተፉበት፤ ምንም አይነት የሙስና ክፍተት የማይፈጥር መሆኑንም ገልፀዋል።የዝግጅት ክፍሉ በካዳስተሩ ምን ያህል መሬት መመዝገቡን አስመልክቶ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፤ አቶ አራጌ የተጠናቀቀ መረጃ እንደሌላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 20/2012ወርቅነሽ ደምሰው", "passage_id": "162ccaf690acbf27423c6d8d054427eb" }, { "passage": "አዲስ አበባ ፣ ሀምሌ 28/2005 (ዋኢማ) – ወጣቱ ትውልድ የህገወጥ ደላሎች ሰለባ እንዳይሆን በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ሁለም ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳሰበ ።በአሁኑ ወቅት በሃገር ሰርቶ መለወጥ የሚያስችሉ አማራጮች በርካታ ቢሆኑም ፥ በህገወጥ ደላሎች ተታለው ከቤታቸው በመውጣት ለከፋ አካላዊና ስነልቦናዊ ችግር የሚጋለጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መጥቷል ።ሚኒስትሩ አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ አገሪቷ ከድህነት ለመላቀቅ በፈጣን የልማት ጎዳና ውስጥ ብትገኝም ፥ አምራቹን ሃይል እየተፈታተነ ያለውን የህገወጥ ደላሎችን ከንቱ ተስፋ ለመታገል የታየው ቅንጅታዊ አሰራር በቂ ያለመሆኑን ሚንስትሩ አስረድተዋል ።እንደ ፋና ዘገባ ይህንን ሁኔታ በቀጣይ በመቅረፍ ዜጎች በሃገራቸው ሰርተው የሚለወጡበትን ሁኔታ ማመቻቸትና ህገወጦችን መቆጣጠሩ ላይ ትኩረት መስጠት ይገባልም ብለዋል ።", "passage_id": "a229b1ce9114f79ccf416b4a71a1d5ff" }, { "passage": "በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወጣቶችን ወደ ሥራ ለማስገባት መንግስት ከመደበው 10 ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ የገንዘብ ብድር 5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ስራ ላይ መዋሉን የከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ አስታወቀ።የኤጀንሲው የኢንተርፕራይዞች ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በቀለ መንግስቱ በድሬዳዋ ከተማ የወጣቶችን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው በተመለከቱበት ወቅት እንዳሉት፣ መንግስት 10 ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ የገንዘብ ብድር መድቦ በሀገሪቱ የሚገኙ ሥራ አጥ ወጣቶችን ወደ ሥራ ለማስገባት የተቀናጀ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነው፡፡በመሆኑም በየክልሉ ከሚገኙ ተቋማት ጋር በመሆን በገጠርና በከተማ የሚገኙ ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 24 ዓመት የሆኑ ወጣቶች አዋጭ በሆኑ የሥራ ዘርፎች ላይ ሥልጠና አግኝተውና ክትትልና ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጉን ገልጸዋል።/ኢዜአ/", "passage_id": "95cc3c30b3782e8fc9d68fa37cf7bd74" }, { "passage": "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ነው ሲሉ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ገለጹ።ምክትል ከንቲባው ትናንት ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ጋር ተወያይተዋል።ከተማ አስተዳደሩ የወጣቶችን የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑንም ገልጸዋል።በውይይቱ ወቅት ወጣቶች የሥራ ማጣት፣ የመሥሪያ ቦታና ሼዶች፣ የወሳኝ ኩነቶችና የመታወቂያ አሠጣጥ ችግሮች እንዲሁም የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ ጥያቄዎችን አንስተዋል።ወጣት ፎዚያ ናስር የመሥሪያ ቦታ፣ የሼዶችና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ችግሮች አሉብን መንግስት ሊፈታልን ይገባል ብላለች።በቅርብ ላሉ ኃላፊዎች ችግራችንን ብንናግርም በቅርቡ ይፈታል ከማለት ውጭ ያመጡልን መፍትሄ የለም ነው ያለችው።ወጣት ቢኒያም ከበደ በበኩሉ የመልካም አስተዳደር ችግር አለብን፣ የመኖሪያ ቤት ጥያቄ እየተፈታልን አይደለም ጥያቄዎቻችንን ለሚመለከተው አካል ብናቀርብም ምላሽ እያገኘን አይደለም ብሏል።በጥቃቅንና አነስተኛ ብንደራጅም በአግባቡ ሥራ አላገኘንም ያለው ወጣት አስረስ ጌታነህ ደግሞ መንግስት ትኩረት እንዲሠጣቸው ጠይቋል።ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን እያከናወነ ነው ብለዋል።ሼዶች በማን እንደተያዙ በማጣራት ላይ ነን፣ የማጣራቱ ስራ ሲጠናቀቅ ለሚመለከታቸው ሰዎች ይተላለፋሉ ያሉት ምክትል ከንቲባው የሼዶችን ጉዳይ በማጣራቱ ስራ ህብረተሰቡ ጥቆማ በመስጠት እንዲሳተፍ ጠይቀዋል።ስለ መኖሪያ ቤት ለተነሳው ጥያቄም በከተማዋ የማጣራት ስራ በመስራት ለደሃ ደሃ የህብረተሰብ ክፍሎች የመስጠቱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።ሼዶች፣ የቀበሌ ቤቶች፣ ሱቆችና የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለህብረተሰቡ ሲተላለፉ በግልጽ ነዋሪውን በማሳተፍ ለተገቢው ሰው ይተላለፋሉ ሲሉም አክለዋል።የመልሶ ማልማት ስራም ዜጎችን ሳያፈናቅል በያሉበት የሚከናወን ይሆናል፣ የግብር አሰባሰብን ፍትሃዊ የማድረግና ወጣቶችን ማዕከል ያደረጉ ስራዎችም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው።ኢንጂነር ታከለ በከተማዋ የዛሬውን ጨምሮ ከስድስት ክፍለ ከተሞች ወጣቶች ጋር ውይይት አካሂደዋል።(ኢዜአ)", "passage_id": "65b3abbaf7485d07cd52b6e77cb12299" } ]
f84f419f074bb0e5b03b1af828fb9ad4
54bc176b47c4e76254c999d4b9a34bc9
በኦሊምፒክ መራዘም የ3ሺ ሜትር መሰናክል አትሌቶች ምን አሉ?
የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) የዓለም ስጋት ከመሆኑ አስቀድሞ በስፖርቱ ዓለም ተጠባቂ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ ኦሊምፒክ ነበር። ነገር ግን ሊካሄድ ወራት ብቻ በቀሩትና ሀገራትም ብሔራዊ ቡድናቸውን ማዘጋጀት በጀመሩበት ወቅት መራዘሙ ተሰማ። አጋጣሚውም በተለያዩ አትሌቶች ዘንድ ሁለት ዓይነት ስሜት የፈጠረ ሆኗል። የመጀመሪያዎቹ አትሌቶች የጊዜውን መርዘም ተጠቅመው በ2021ዱ ኦሊምፒክ በተሻለ ብቃት ለመገኘት ዕድል ያላቸው ሲሆኑ፣ ሁለተኛዎቹ ደግሞ በጥሩ አቋም ላይ የሚገኙና ምናልባትም መራዘሙ እክል ሊያስከትልባቸው የሚችሉ ናቸው። ኢትዮጵያም የአትሌቲክስ ቡድኗን መርጣ ልምምድ ለመጀመር ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ በነበረችበት ወቅት ነው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በመራዘሙ አትሌቶች እንዲበተኑ የተደረገው። ከተበተነው ብሔራዊ ቡድን አባላት መካከል የ3ሺ ሜትር መሰናክል አንዱ ሲሆን፤ ይህ ቡድን በዓለም የቤት ውስጥ ቻምፒዮና ውጤታማነቱን ያስመሰከረ ነበር። በኦሊምፒኩ ለአሸናፊነት የሚጠበቀውና ከፍተኛ ግምት ያገኘው ቡድኑና አባላቱ ምን ዓይነት ዝግጅት ሲያደርጉ ቆዩ፣ መራዘሙ ምን አስከተለባቸው እንዲሁም በዚህ ወቅት በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ በሚለው ጉዳይ ላይ የቡድኑ አባላት የሚናገሩት አላቸው። ለቡድኑ ከተመረጡትና ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በምርጥ አቋም ላይ ከነበሩአትሌቶች መካከል አንዱ የዳይመንድ ሊግ አሸናፊው ጌትነት ዋለ ይጠቀሳል። አትሌቱ ኦሊምፒክን ጨምሮ በግሉ ይሳተፍባቸው ለነበሩ ውድድሮች ከአሰልጣኙ ጋር በመሆን ጠንካራ ቅድመ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ይገልጻል። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ ኦሊምፒኩ መራዘሙ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ጎልቶ የሚታየው ጌትነት፤ «አትሌት ባለበት አቋም መጠቀም የሚገባው በወቅቱ ነው» የሚል አመለካከት አለው። የየትኛውም አትሌት አላማ የሆነውን በኦሊምፒክ ሀገርን ወክሎ ድል ማስመዝገብ ካለመቻሉም በላይ ከሚወዱት ሥራቸውም መነጠል ያስከፋል። ነገር ግን ቫይረሱ በመላው ዓለም ሕዝብ ላይ ስጋትና አደጋ በመሆኑ፤ ወቅቱ ይለፍ እንጂ በርትቶ በመስራት ብቃትን መመለስ እንደሚቻል ያምናል። አቋሙ ባለበት እንዲቀጥልም በቤቱ ውስጥ ከቀደመው ጊዜ ያነሰ ልምምድ እየሰራ ጊዜውን በማሳለፍ ላይ ይገኛል። እንደ አጋጣሚ ሆኖ አሰልጣኙ እርሱ በሚኖርበት አቅራቢያ የሚኖር በመሆኑ አልፎ አልፎ በርቀት እየተገናኙ መመሪያዎችን የሚቀበልና በስልክም መረጃ እንደሚለዋወጡ ይጠቁማል። ከዚህ ባለፈ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በመገናኛ ብዙኃን ታግዞ በባለሙያዎች የሚሰጠውን መረጃም ይከታተላል። ሌሎች አትሌቶችም በዚህ መልኩ ከቤታቸው ሳይርቁና ሰዎች በብዛት ባሉባቸው ስፍራዎች ባለመገኘት በአቋማቸው ለመቀጠል እንቅስቃሴ እንዲያደርጉም ጥሪውን ያቀርባል። ኦሊምፒክ በጉጉት ይጠብቀው የነበረውድድርና ከአሰልጣኙም ጋር ልዩ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየ መሆኑን የሚያስታውሰው ደግሞ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ሥልጠናውን ያጠናቀቀውና ሌላኛው የ3ሺ ሜትር መሰናክል ወጣት አትሌት አብረሃም ስሜ ነው። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ይህ ቫይረስ መከሰቱ ቢያሳዝንም በዓለም የመጣ ነገር በመሆኑ የግድ ራስን ከቡድን ልምምድ ማራቅ ተገቢ ነው። የኦሊምፒክ መራዘም አማራጭ የሌለው ጉዳይ ቢሆንም እርሱን በመሰሉና በመልካም አቋም ላይ ለነበሩ አትሌቶች ጉዳት አለው። ይህ ቫይረስ እስኪያልፍ ድረስም ጊዜውን እንደ ማገገሚያ በመጠቀም በአቋሙ ለመቆየት በቤቱ እንቅስቃሴ ማድረግ አላቋረጠም። እንደ ቡድን አጋሩ ጌትነት አብርሃምም የሚኖረው ከአሰልጣኙ ጋር በቅርብ ርቀት አካባቢ በመሆኑ በስልክ ከመገናኘት ባለፈ በአካል ተገናኝቶ ለመወያየትም ዕድል ሰጥቶታል። በአሰልጣኞች እንዲሁም በጤና ባለሙያዎች የሚሰጠውን መመሪያ በጥንቃቄ በመተግበርም እንቅስቃሴውን ቀጥሏል። በየማዕከላቱ የሚሰለጥኑ ታዳጊዎችን ጨምሮ በየክለቡ ያሉ አትሌቶች ተበትነው በየክልሉ ተመልሰዋል። በመሆኑም ጊዜው እስኪያልፍ ድረስ ከእንቅስቃሴ ሳይርቁ እንዲቆዩ መልዕክቱን ያስተላልፋል። በብሔራዊ ቡድን የ3ሺ ሜትር መሰናክል ዋና አሰልጣኙ ተሾመ ከበደ በብሔራዊ ቡድን ከተካተቱ አትሌቶች አብዛኛዎቹ ከእርሱ ጋር የነበሩ በመሆኑ ወጥ የሆነ ልምምድ ላይ እንደነበሩ ያስታውሳል። ከአትሌቶቹ ጋር በመሆን በቤት ውስጥ ቻምፒዮና ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተው ለዓመታዊው ዳይመንድ ሊግ ውድድር እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን፤ የኦሊምፒክ ሚኒማ ለማሟላት ሲሰሩም ነበር። ነገር ግን የኦሊምፒክ መራዘምን ተከትሎ ቡድኑ በመበተኑ አትሌቶች ተፈጥሯዊ የበሽታ መከላከል አቅማቸውን ሊያጎለብት የሚችል ቀላል እንቅስቃሴዎችን እየሰሩ እንዲቆዩ ተደርጓል። ቀድሞ ለአምስት ቀናት ያደርጉ የነበረውን መደበኛ ስልጠና እና ጫና በመቀነስም ክብደት እንዳይጨምሩ ቀላል እንቅስቃሴዎችን በየቤታቸው ይሰራሉ። አሰልጣኞችም በስልክና በሌሎች መንገዶች ከአትሌቶቻቸው ጋር በመገናኘት መስራት ያለባቸውን እየነገሯቸው መሆኑንም ይጠቁማል። የኦሊምፒኩ መራዘም እንደ ሀገር የሚያስከትለው ጉዳት መኖሩን የሚያነሳው አሰልጣኙ፤ እርሱ በሚያሰለጥንበት ርቀት ደግሞ አትሌቶች በጥሩ አቋም ላይ በመቆየታቸው ለኦሊምፒኩም የማሸነፍ ዕድል ነበራቸው። በአንጻሩ መራዘሙ የሚጠቅመው በጉዳት ላይ የቆዩና በወቅቱ በጥሩ አቋም ላይ ያልነበሩ አትሌቶችን ነው። ሁኔታውን ተጠቅመው አቅማቸውን አጎልብተው በመመለስ ብርቱ ተፎካካሪ የመሆን ዕድል ያላቸው በርካቶች እንደመሆናቸው ይህ ጊዜ ሲያልፍ ጠንካራ ሥራ ከአትሌቶች የሚጠበቅ መሆኑንም አሰልጣኙ ያመላክታል። በመጨረሻም አሰልጣኙ አትሌቶች ራሳቸውን ከዚህ ቫይረስ እንዲጠብቁ መልዕክቱን አስተላልፏል። ራሳቸውን ከበሽታ ሊከላከል የሚችልና ያሉበትን አቋም የሚጠብቅ እንቅስቃሴ ከማድረግ በዘለለ ራሳቸውን በጤና መጠበቅ እንዳለባቸውም ምክሩን ይለግሳል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 19/2012
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=31209
[ { "passage": " ብስራቱን ለመንገር የመጀመሪያውን ማራቶን ከአቴንስ እስከ ስፓርታ የሮጠው ወታደሩ ፊዲፒደስ ከ30 ሰዓታት በላይ ፈጅቶበታል። ከዘመናት በኋላ ደግሞ 42 ኪሎ ሜትሩ በሁለት ሰዓት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሆኗል፡፡ ነገር ግን በቅርቡ ከዚህም በታች በሆነ ሰዓት መግባት እንደሚቻል ኬንያዊው አትሌት አረጋግጧል። ይህንን ሃሳብ በመያዝ ሲንቀሳቀስ የቆየው ናይኪ የተባለው የስፖርት ትጥቅ አምራችም በጫማዎቹ አማካኝነት ርቀቱ እስካሁን በሰው ልጅ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅበት ሁኔታ ከሁለት ሰዓት በታች መግባት እንደሚቻል አሳይቷል። ነገር ግን የማራቶን ሰዓት እዚህ ከመድረሱ ናይኪም በዘመን አመጣሽ ጫማዎቹ ሳይራቀቅ በፊት ፊዲፒደስ ርቀቱን በምን ሸፈነው በማለት የታሪክ ማህደርን ማገላበጥ አስፈላጊ ይሆናል። ሩጫ መለያዋ የሆነው ኢትዮጵያም የተከበረውን የኦሊምፒክ መንደር አሃዱ ያለችው በምን መልኩ ነው ለሚለውም ታሪክን መለስ ብሎ ማስታወስ በቂ ነው። ባለሙያዎች «ተፈጥሮአዊ ሩጫ» ሲሉ የሚጠሩትና በተለምዶ በባዶ እግር መሮጥ ለማራቶን ስፖርት መሰረት ነው ለማለት ይቻላል። በዘመነው ዓለም የማይታሰበው የባዶ እግር ሩጫ በአፍሪካ እና በደቡባዊው አሜሪካ ግን እስካሁንም በስፋት ይስተዋላል። በኢትዮጵያም ይህ አሯሯጥ የተለመደ ቢሆንም ምርጫ በማጣት (ከድህነት ጋር በተያያዘ ምክንያት) አሊያም በአስገዳጅ ሁኔታ የሚከወን ስለመሆኑ ዋቢ መጥቀስ አያሻም። በአንጻሩ ከሃብት ማማ ላይ በሚገኙት ምዕራባዊያን ዘንድ ይህ ዓይነቱ ሩጫ ጥቅሙን በመረዳት ይዘወተራል። ከጊዜ ወደ ጊዜም እየታወቀና እየተስፋፋ የመጣ የአሯሯጥ ዓይነት ሆኗል። በተለይ በሃይቅና ውቅያኖስ ዳርቻዎች እንዲሁም በሳር በተሸፈኑ መስኮች ላይ ባዶ እግርን መሮጥ እያደገ ያለ ተግባር ነው። በዚህ የሩጫ ዓይነት ስሙ ጎልቶ የሚነሳው ኢትዮጵያዊው ታላቅ አትሌት አበበ ቢቂላ ቢሆንም ከእርሱ አስቀድመውም ሆነ በዚያው ዘመን በርካቶች ባዶ እግራቸውን በውድድሮች ላይ ይካፈሉ ነበር። ከታዋቂዎቹ መካከልም ደቡብ አፍሪካዊቷ የሁለት ጊዜ የሃገር አቋራጭ ሻምፒዮና ዞላ ቡድ፣ አውስትራሊያዊው የ1ሺ500 ሜትር እና 800 ሜትር አትሌት ኸርብ ኤሎት እንዲሁም እንግሊዛዊው የ3 ማይል ሻምፒዮን ብሩች ቱሎህ ጥቂቶቹ ናቸው። ጀግናውን አትሌት ከሌሎቹ ልዩ የሚያደርገውም በባዶ እግር ቀርቶ በጫማም የማይደፈረውንና እህል ውሃ የማያሰኘውን ማራቶንን በመሮጡ ነው። እርግጥ ነው ከረጅም ዓመታት በኋላም ሌላ ኢትዮጵያዊ አትሌት በዚህ መልክ 42 ኪሎ ሜትሮችን በማቋረጥ ዓለምን አጀብ ማሰኘት ችሏል። ከሰው ልጅ ስልጣኔ እና የአኗኗር ሁኔታ ጋር በተያያዘ የሰው ልጅ ሩጫን በባዶ እግሩ አሊያም ከድብ እና ከሌሎች እንስሳት ቆዳ በሚሰራ ጫማ ሲከውነው እንደነበረ ጥንታዊያን ታሪኮች ያስረዳሉ። ግሪካዊያንም በጥንታዊው ኦሊምፒክ ጭምር በሩጫ ብቻም ሳይሆን በተለያዩ ስፖርቶች የሚካፈሉ ተወዳዳሪዎች ባዶ እግራቸውን ነበር የሚቀርቡት። እንደሌላው ዘርፍ ሁሉ የስፖርት ቁሳቁሶችም ከዘመን ጋር እየዘመኑና በረቀቁ ቴክኖሎጂዎች ታግዘው እየተካሄዱ ይገኛሉ። ለዚህም በቅርቡ ኬንያዊው አትሌት ኢሉድ ኪፕቾጌ በ1ሰዓት ከ59 ደቂቃ ከ40ሰከንድ በሆነ ሰዓት ማራቶንን የሮጠበትን ጫማ ማንሳት ይቻላል። ናይኪ ቫፖርፍላይ የተባለው ይህ የመሮጫ ጫማ ከተፈጥሮአዊው አቅም ባሻገር አትሌቶችን ወደፊት በማፈናጠር ተጨማሪ ፍጥነት የሚሰጥ ነው። በርካቶች ግን 250 ዶላር ዋጋ የተተመነለት ናይኪ ቫፖርፍላይን በህግ ከሚያስቀጣው የአበረታች ቅመሞች ተጠቃሚነት ለይተው አያዩትም። ይህ ከዘመናዊው ዓለም ጋር ከመራመድ እና ከተፈጥሯዊው ልማድ ጋር የመቀጠል እሳቤም የአትሌቲክስ ቤተሰቡን ከሁለት የከፈለ አድርጎታል። በተፈጥሯዊ መንገድ በባዶ እግር መሮጥ ግን ላለንበት ወቅት የማይመጥን ተግባር ተደርጎ ይወሰድ እንጂ የጤና ባለሙያዎች እንዲተገበር የሚመክሩት የአሯሯጥ ዓይነት ነው። ሳይንስም በባዶ እግር መሮጥን ከጉዳት ማገገምን ጨምሮ በርካታ ጥቅሞችን እንደሚያስገኝ ያረጋግጣል። ነገር ግን ተግብሮት ለማያውቅ ሰው በመጀመሪያ ፈታኝ እንደሚሆን እና የሚሮጡበትን ስፍራ ደህንነትም አስቀድሞ ማረጋገጥ እንደሚገባም ያሳስባል። የመጫሚያዎች ምቾት ከሳምባ፣ ከአእምሮ፣ ከደም ዝውውር እንዲሁም ከነርቭ ጋር ይያያዛል። በመሆኑም ከባድ፣ ጠባብ፣ ከተረከዛቸው ከፍ ያሉ፣… ጫማዎች ያደረገውን ሰው ምቾት ከመንሳት ባሻገር ጤናም ላይ ተያያዥ እክሎችን ማድረሱ አይቀርም። በመሆኑም አልፎ አልፎም ቢሆን ባዶ እግርን መጓዝ እና መሮጥን መለማመድ ጠቃሚ ይሆናል። የደም ዝውውርን ለማስተካከል ተመራጭ መንገድ ሲሆን፤ በተለይ ለልብ ህመም እንዲሁም በደም ውስጥ የሚኖሩ መርዘኛ ንጥረ ነገሮችን ለማስወገድ እንደሚረዳ ተመራማሪዎች በሳይንስ ጆርናሎች ያሳተሟቸው ጽሁፎች ያስነብባሉ። በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ዳንኤል ሊበርማን እንደሚገልጹት ከሆነ፤ (cushioned\nshoes) በመባል የሚታወቁትን የስፖርት ጫማዎች የሚያዘወትሩ አትሌቶች ተረከዛቸው በመዶሻ የመቀጥቀጥን ያህል ጉዳት ይደርስባቸዋል። በመሆኑም አሰልጣኞች አንዳንዴም አትሌቶቻቸውን ባዶ እግራቸውን በሳር ላይ እንዲሮጡ ቢያደርጉ፤ የእግራቸውን ጤንነት ከመንከባከብም በላይ ከደረሰባቸውም ጉዳት እንዲያገግሙ እንደሚረዳቸው ያስረዳሉ። በጫማ መሮጥ በባዶ እግር ከመሮጥ ይልቅ የኦክስጅን ፍጆታን በሁለት እጅ ይጨምራል፤ ይህም አትሌቱ (ሯጩ ግለሰብ) ከሚያወጣው ጉልበት የሚያያዝ በመሆኑ በሚሸፍነው ርቀት ላይ የራሱን ተጽእኖ ማሳረፉ አይቀርም። በእግር ጤንነት፣ ሚዛን፣ ነርቮችን በማነቃቃት፣ የእግር ቅርጽ እና እድገት ላይም በጫማ እና ያለጫማ እንቅስቃሴ ማድረግ ሚናው ይለያያል። በተለይ ደግሞ በሽንጥ፣ ባት፣ ተረከዝ፣ ቁርጭምጭሚት፣ ጅማት፣ አጥንት እና ጡንቻዎች ጤና ላይ የራሱን አሻራ ያሳርፋል። ከዚህ ባሻገር ሰው ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ቁርኝትም በማስፋትና ተፈጥሮን በመንከባከብ ረገድ የራሱን ስነ-ልቦናዊ በረከት ያስገኛል።አዲስ ዘመን ጥቅምት24/2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "721145480b76984363e8a73c5bcf2259" }, { "passage": "በታሪክ አጋጣሚ ቀደም ባሉት ዓመታት በተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች ወንድና ሴት አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች በተመሳሳይ ውድድር ላይ ሲሮጡ መመልከት የተለመደ ነው። ‹‹ወንዶች የሚሮጡትን ርቀት ሴቶች መሮጥ አይችሉም›› የሚል አስተሳሰብ በነበረበት ዘመን በተመሳሳይ ውድድር ላይ ሴቶች ከወንዶች ያነሰ ርቀት ለመሮጥ ይገደዱ ነበር። እንዲያውም በአንዳንድ ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ላይ ወንዶች በሚሮጡበት ርቀት ሴቶች እንደማይወዳደሩ ከታሪክ መረዳት ይቻላል። ለምሳሌ ያህል በታላቁ የዓለማችን የስፖርት መድረክ ኦሊምፒክ ማራቶን አንጋፋና ምናልባትም ከመጀመሪያ አንስቶ የሚካሄድ የውድድር አይነት ቢሆንም ሴቶች በርቀቱ መወዳደር የጀመሩት ዘግይተው ነው።በኦሊምፒክ መድረክ ብቸኛው የጎዳና ላይ ውድድር በሆነው ማራቶን ወንዶች መሳተፍ የጀመሩት እኤአ 1896 ላይ ነው። የሴቶች ማራቶን የኦሊምፒክ ውድድር ውስጥ የተካተተው ግን ዘጠና ዓመታትን ዘግይቶ በ1984 ኦሊምፒክ ነበር። ከማራቶን በተጨማሪም በርካታ በተለይም ረጅም ርቀት ውድድሮች በኦሊምፒክም ይሁን በዓለም ቻምፒዮና ሴቶችን ማካተት የጀመሩት ዘግይተው ነው። ይሁን እንጂ በዘመናዊው የአትሌቲክስ ዓለም ሴቶች ወንዶች በሚወዳደሩበት ርቀት ሙሉ በሙሉ ለማለት በሚያስችል ደረጃ ተወዳዳሪ ናቸው።ከአታካቹ ማራቶን አንስቶ እስከ ተለያዩ የጎዳና ላይ ውድድሮች ሴቶች ወንዶች የሚሮጡትን ርቀት በመሮጥ ብቃታቸውን አስመስክረዋል። ርቀቶቹን ሮጠው  ለማጠናቀቅ የሚፈጅባቸው ሰዓት ከተፈጥሮ ጋር በተያያዘ ከወንዶች የዘገየ ቢሆንም የትኛውንም ርቀት ሴቶች አይሮጡም ብሎ የሚያምን ሰው ፈልጎ ማግኘትም ከባድ የሚመስልበት ዘመን ላይ ተደርሷል። ይሁንና ሴቶች በአገር አቋራጭ ውድድሮች ላይ ከወንዶች ያነሰ ርቀት እንዲሮጡ መደረጉ በአትሌቲክሱ ቤተሰቦች መከራከሪያ አጀንዳ ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል።እንግሊዛዊቷ የቀድሞ የአገር አቋራጭ ቻምፒዮና የሜዳሊያ ባለቤት አትሌት ጆ ፓቬይ «በአገር አቋራጭ ውድድሮች ሴቶች ከወንዶች ባነሰ ርቀት መወዳደራቸው የፆታ እኩልነትን አያሳይም» የሚል አስተያየት ከሁለት ዓመት በፊት ለስካይ ኒውስ መስጠቷን ተከትሎም የአገር አቋራጭ ውድድር አዘጋጆች ከአትሌቲክስ ቤተሰቡ ጋር ሙግት ገጥመው እንደነበር ይታወሳል። በርካታ የስፖርቱ ባለሙያዎችና የውድድር አዘጋጆችም በጉዳዩ ላይ ሲሟገቱ ይስተዋላል። አገር አቋራጭ ውድድሮች በየዓመቱ በተለያዩ ከተሞች በተለይም በአውሮፓ ይካሄዳሉ። የዓለም አትሌቲክስም በየሁለት ዓመቱ የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና ያዘጋጃል። በእነዚህ ውድድሮች ሴትና ወንድ አትሌቶች በእኩል ርቀት ሲወዳደሩ አይታይም። እኤአ ከ2017 በፊት በዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና የሚካሄደው ፉክክር በአራት አይነት መንገድ ተከፍሎ ነው። የመጀመሪያው አዋቂ ወንዶች የሚወዳደሩበት የአስራ ሁለት ኪሎ ሜትር ውድድር ሲሆን አዋቂ ሴቶች ስምንት ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ርቀት ላይ ብቻ ተፎካካሪ ነበሩ። በወጣት ወንዶች መካከል የሚካሄደው ውድድር ደግሞ ስምንት ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ወጣት ሴቶች ስድስት ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ፉክክር ያደርጋሉ። እነዚህ ርቀቶች በዓለም ቻምፒዮናም ይሁን በግል አገር አቋራጭ ውድድሮች በብዛት የተለመዱ ናቸው። አልፎ አልፎ ግን በዓለም ቻምፒዮናም ይሁን በግል ውድድሮች እንደየሁኔታው ወንዶች ከሴቶች እኩል ርቀቶችን የሚሮጡበት አጋጣሚ ሲፈጠር ይታያል። ለአብነት ያህልም በ2017 በዩጋንዳ ካምፓላ ተካሂዶ የነበረው የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮናን ማንሳት ይቻላል። በዚህ ቻምፒዮና ለመጀመሪያ ጊዜ አዋቂ ሴቶችና ወንዶች እኩል አስር ኪሎ ሜትር የሸፈነ ውድድር ማድረጋቸው ይታወሳል። «ታዲያ ሴቶች በዚህ ውድድር ከወንዶች እኩል መሮጥ እየቻሉ አነስተኛ ርቀት እንዲሮጡ መደረጋቸው ለመጪው ትውልድ ምን አይነት መልዕክት ያስተላልፋል?» የሚል ከጾታ እኩልነት አኳያ ጥያቄ የሚያነሱ ቁጥራቸው ብዙ ነው።በምስራቅ ለንደን የአትሌቶች ማህበር አባል የሆነችው ማዑድ ሆድሰን በዚህ ውድድር የጾታ እኩልነት መረጋገጥ ካለበት ሴትም ወንድም እኩል ርቀት መሮጥ አለባቸው የሚል አቋም ይዛ ባለፉት ዓመታት ስትከራከር ቆይታለች። ይህን ሃሳቧንም በርካቶች ደግፈውታል። ሆድሰን በጉዳዩ ላይ ለራነርስ ዌብ ከዓመታት በፊት እንደገለፀችው፣ በአገር አቋራጭ ውድድሮች ሴትና ወንድ እኩል ርቀት እስካልሮጡ ድረስ መጪው የአትሌቲክስ ትውልድ በሩጫው ዓለም ሴትም ወንድም እኩል መሆናቸውን ሊረዳ አይችልም። ወንዶች ከፍ ያለውን ርቀት መሮጣቸው በአገር አቋራጭ ውድድሮች የሴቶቹ ፉክክር ከወንዶቹ ያነሰ የሚመስል ትርጉም ይሰጠዋልም ትላለች። ሆድሰን በዚህም ሳታበቃ በጉዳዩ ላይ አንድ መፍትሄ ለማምጣት በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ፊርማ አሰባስባ በቀናት ውስጥ ከአንድ ሺ በላይ ተከታዮችን አግኝታለች። ይህ ሃሳብ በፌስ ቡክ ገፅም«አይ ወዝ ኦር አም ራነር» በሚል በተፈጠረ የቡድን ገፅም በርካታ ወንዶች የደገፉት ሲሆን ብዙ ተከታዮች አግኝቶ መነጋገሪያነቱ እየጨመረ መጥቷል።አዳጋች በሆነው የአገር አቋራጭ ውድድር አትሌቶች በጭቃ፤ በዳገትና ቁልቁለት አልፎ አልፎም በበረዶ ይፈተናሉ። ይህን ከግምት የሚያስገቡ በርካታ ሰዎች ሴቶች በውድድሩ እንደ ወንዶች ረጅም ኪሎ ሜትር መሮጥ አይችሉም የሚል አስተሳሰብ እንዲይዙ ያደርጋቸዋል። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ግን ሴቶች በሌሎች ፈታኝ በሚባሉ ማራቶንና ግማሽ ማራቶን ውድድሮች ላይ ከወንዶች እኩል ርቀት ሮጠው ከሚያስመዘግቡት የሰዓት ልዩነት የተጋነነ አያስመዘግቡም። በቢኬት ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስና ባዮሜካኒክስ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ብሬን ሃንሌይ ጥናታዊ ፅሁፍ ግን በአገር አቋራጭ ውድድር ሴቶች ከወንዶቹ ባልተናነሰ ተመሳሳይ ርቀት መወዳደር እንደሚችሉ ይጠቁማል። ጥናቱ ልክ እንደ ወንዶቹ የሴቶቹም ውድድር መጀመሪያ ላይ ቀዝቃዛ ፉክክር የሚታይበት ቢሆንም መጨረሻው በፉክክር የታጀበ እንደሚሆን አረጋግጧል። አብዛኞቹ የውድድር አዘጋጆች ግን ሴቶች በዚህ ውድድር ከወንዶች እኩል ርቀት ቢሮጡ መጨረሻው በፉክክር እንደማይታጀብና አሰልቺ እንደሚሆን ስለሚያምኑ ሴቶች አነስተኛ ርቀት እንዲወዳደሩ ያደርጋሉ የሚል ክርክር ይነሳል። ይህ ግን ዞሮ ዞሮ ከፆታ እኩልነት ጋር ባይያያዝ እንኳን በርካታ ወጣት አትሌቶችን ወደ ውድድሩ እንዳይመጡ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል መላ ምቶች ይቀመጣሉ። ይህም ርቀቱ በረዘመ ቁጥር በርካታ አትሌቶች እንደ ጎዳና ላይ ረጅም ርቀት ውድድሮች ሁሉ የመወዳደራቸው አጋጣሚ ሰፊ ይሆናል የሚል ነው።የአርባ ስድስት ዓመቷ ጆ ፓቬይ አትሌቲክስን ካቆመች በርካታ ዓመታት ቢቆጠሩም ሴቶች በአትሌቲክሱ ዓለም አስደናቂ ታሪኮችን ከወንዶች እኩል መስራታቸውን በማስታወስ በአገር አቋራጭ ውድድሮችም ከወንዶች እኩል ርቀት መሮጥ እንዳለባቸው ከስካይ ኒውስ ጋር በነበራት ቆይታ ገልፃለች። «ለበርካታ ዓመታት በአስቸጋሪው የማራቶን ውድድር ሴቶች ከወንዶች እኩል ርቀት ሲወዳደሩ ቆይተዋል፤ በአገር አቋራጭ ውድድሮች እኩል ርቀት ያለመሮጣቸው ሴቶች ከወንዶች እኩል አቅም የላቸውም የሚል አመለካከትን ይፈጥራል» በማለትም ፓቬይ አቋም ይዛለች።የማራቶን ባለክብረወሰኗና የቀድሞ የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮኗ አትሌት ፓውላ ራድክሊፍ ሰሞኑን በጉዳዩ ላይ በማህበራዊ ሚዲያው የሚደረገውን ክርክር ተቀላቅላ ‹‹ርቀቶች መመሪያ ናቸው፣ የአገር አቋራጭ መወዳደሪያ ቦታዎች ጥሩ ከሆኑ በሁለቱም ፆታ ተመሳሳይ ርቀት ቢሮጥ ችግር የለውም፣ የውድድሩ ተፈጥሯዊ ባህሪ ሆኖ አንዳዶች አጭር ርቀት መሮጥ ሲፈልጉ ሌሎች ረጅም መሮጥ ሊፈልጉ ይችላሉ፣ ወንድም ሴትም ተመሳሳይ ርቀት መሮጥ እንደሚችሉ ግን አምናለሁ›› በማለት ፅፋለች። የአገር አቋራጭ ውድድር አዘጋጆች ይህ ልዩነት ለምን እንደተፈጠረ አሳማኝ ምክንያት ማቅረብ ባይችሉም በተለምዶ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ በመሆኑ ብቻ አሁን ላይ እየተገበሩት እንደሚገኙ ይታመናል። ይህ ግን በአንዳንድ የስፖርት ቤተሰቦች የፆታ ልዩነት እንዳለ ለማሳየት ሆን ተብሎ የተደረገ ሳይሆን የሴቶቹን ፉክክር ረዘም ላለ ሰዓት መመልከት ስለማይፈለግ ነው የሚል ትችት ይቀርባል። የእንግሊዝ አገር አቋራጭ ውድድር ማህበርም ይህ ልዩነት በተለምዶ አሰራር የመጣ መሆኑን በማመን በአገር አቀፍ ውድድር ላይ ሴቶች ከወንዶች እኩል ርቀት መሮጥ እንዳለባቸው ሲከራከርና ተፅዕኖ ሲያሳድር ቆይቷል። በዚህም የእንግሊዝ አትሌቲክስ ማህበርን ድጋፍ ማግኘት ችሏል። የእንግሊዝ አትሌቲክስ ማህበርም ጥያቄውን ወደ ፊት በማምጣት የተለያዩ ሙግቶችን ሲያደርግ ቆይቷል። ለረጅም ጊዜ ጉዳዩ የተዘነጋና ተድበስብሶ ያለፈ ቢመስልም የእንግሊዝ አትሌቲክስ ማህበር ከቀናት በፊት ዳግም ጉዳዩን በማንሳት በጥናት ጭምር አስደግፎ እየተሟገተ ይገኛል። አትሌቲክስ ማህበሩ በፈጠረው ተፅዕኖ በአገሪቱ በሚደረጉ የአገር አቋራጭ ውድድሮች ላይ ለውጦች ማምጣት ቢችልም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ የውድድር አዘጋጆችን ለማሳመን ተጨማሪ ስራዎች ይቀሩታል። ለዚህም የአውሮፓ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ላይ የሰራውን ጥናት ሰሞኑን ይፋ አድርጓል። 2016 ላይ ከሃምሳ አንድ የአውሮፓ አገራት አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ሰላሳ ሰባቱ ለጥናቱ ምላሽ የሰጡ ሲሆን ከሰላሳ ሰባቱ ሃያ አንዱ ሴቶችና ወንዶች በአገር አቋራጭ ውድድሮች እኩል ርቀት መሮጥ አለባቸው የሚል እምነት እንዳላቸው ጠቁሟል። አገር አቋራጭ ውድድር እንደ ረጅም ርቀት ውድድሮች ሁሉ በስፋት የሚታወቁት ምስራቅ አፍሪካውያኑ ኢትዮጵያና ኬንያ ቢሆኑም በጉዳዩ ላይ የተነሳው ሙግት ከወደ ምዕራባውያኑ መሆኑ አስገራሚ ነው። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር የነበሩትና አሁን የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ዱቤ ጂሎ በአንድ ወቅት ከአዲስ ዘመን ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያለውን አቋም አሳውቀው ነበር። አቶ ዱቤ ይህ በሴቶችና በወንዶች አገር አቋራጭ ውድድሮች ላይ ያለው የመወዳደሪያ ርቀት በተለምዶ ሲሰራበት ስለመጣ እንጂ ሴቶች ወንዶች የሚሮጡትን ርቀት መሮጥ ስለማይችሉ የተፈጠረ እንዳልሆነ ያብራራሉ። የርቀቱ ልዩነት የመጣው ቀደም ሲል በውድድሩ ደንብ ላይ የተቀመጠ በመሆኑ እንጂ ከጤናም አኳያ ይሁን ከሌሎች ነገሮች ሴቶች በአገር አቋራጭ ውድድር ከወንዶች ያነሰ ርቀት እንዲሮጡ የሚያደርጋቸው ምንም አይነት አሳማኝ ምክንያት እንደሌለ ገልፀው ነበር። «ሴቶች ከወንዶች እኩል በአገር አቋራጭ ውድድር መሮጥ አለባቸው፤ ማራቶንም ይሁን ግማሽ ማራቶን እኩል እስከ ሮጡ ድረስ በአገር አቋራጭም እኩል ርቀት መሮጥ አለባቸው፤ ይህ ካልሆነ ማራቶንም እኩል ኪሎ ሜትር መሮጥ የለባቸውም» በማለትም አቶ ዱቤ ሃሳባቸውን ሰንዝረው ነበር። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ ጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድሮችን በክልሎችና በክለቦች መካከል እንደሚያካሂድ ይታወቃል። በነዚህ ውድድሮች ወንዶቹም ሴቶቹም እኩል ርቀት የሚሸፍን ውድድር እንዲያካሂዱ ማድረግ ይቻላል ያሉት አቶ ዱቤ፣ ይህን ጥያቄ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለዓለምአቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ሊያቀርብ እንደሚችልም ጠቁመዋል። ከዚያም ዓለምአቀፍ ማህበሩ አሁን ያለውን ህግ አሻሽሎ በተመሳሳይ ርቀት እንዲወዳደሩ ከፈቀደ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም በእኩል ርቀት ውድድሮቹን ለማካሄድ የሚያግደው ነገር እንደሌለ አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013 ዓ.ም ", "passage_id": "45eada520b80135f2da51e6ad708b565" }, { "passage": "በአትሌቲክስ ስፖርት ዝና እና ክብሯን የገነባችው ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችንም አግኝታበታለች። ስፖርቱ አንድ የስራ ዘርፍ በመሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት አትሌቶችን ያቅፋል። አትሌቶችም በዓለም አቀፍ ውድድሮች ሲሳተፉ ከውጤት ባሻገር የውጭ ምንዛሪን በማስገኘት የሀገሪቷን ኢኮኖሚ ያግዛሉ። በሚያፈሱት መዋዕለ ነዋይም ለበርካቶች የስራ እድል ፈጥረዋል። \nእንደሚታወቀው በዚህ ወቅት ይህ ዘርፍ እንደሌሎች ስፖርቶች ሁሉ ለውድድር ዝግ ሆኗል። ማልዶ ለልምምድ ይወጣ የነበረውና በዓመት ውስጥ ተደጋጋሚ ውድድሮች ላይ ተሳታፊ የነበረው እረፍት የለሽ አትሌትም ከተላላፊው ቫይረስ ጋር ተያይዞ ከቤት ውሏል። በብሄራዊ ቡድን የተያዙ፣ በተለያዩ ክለቦች የተካተቱ እንዲሁም የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ተቋማት ሰልጣኝ የሆኑ አትሌቶችም እንዲበተኑ ተደርጓል። በግላቸው የሚሰለጥኑትም ቢሆን እንደ ቀድሞው ከመኖሪያቸው ርቀው የማይጓዙበት ሁኔታ ተጋርጦባቸዋል። \nለአንድ ዓመት የተራዘመውን ኦሊምፒክ ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ ቻምፒዮናዎች ላይ ተሳታፊ ለመሆን በብሄራዊ ቡድን የተካተቱ አትሌቶች ደግሞ ከሌሎች በተለየ ሁለት አማራጮችን ያስተናግዳሉ። \nየመጀመሪያው ለተላላፊው የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ላለመሆን በሚደረገው የቤት ውስጥ ቆይታ ከልምምድ በመራቃቸው የአቋም መውረድን ማስተናገድ ነው። ሌላኛው ደግሞ የውድድሮችን መራዘም እንደ መልካም እድል በመጠቀም በተደጋጋሚ ውድድር ላይ ያሳለፉ አትሌቶች እንደ ማገገሚያ ጊዜ በመመልከት በተሻለ ብቃት ለመመለስ የራሳቸውን ጥረት ማድረግ ነው። \nበእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ስፖርተኞች ከስፖርቱ ላለመራቅ ምን ማድረግ አለባቸው፣ ፌዴሬሽኑስ ሚናውን በምን መልኩ እየተወጣ ነው ለሚለው በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቲክስ ህክምና ከፍተኛ ባለሙያና እና የጸረ አበረታች ቅመሞች ተጠሪዋ ቅድስት ታደሰ ከአዲስ ዘመን ጋር ቆይታ አድርገዋል። \nየመጀመሪያው ነገር ስነ-ልቦና መሆኑን ባለሙያዋ ይገልጻሉ።በዓለምና በሃገር በመጣው በዚህ ቫይረስ ምክንያት በቤታቸው እስኪቆዩ ድረስ ኦሊምፒክን ጨምሮ ለዚህ የውድድር ወቅት በዝግጅት ላይ የነበሩ አትሌቶች በጥሩ አቋም ላይ ነበሩ። በዚህም ምክንያት አቋማቸው እንዳይወርድና ጂምናዚየሞችም በመዘጋታቸው በቤት ውስጥ የተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ይገደዳሉ። ከትንፋሽ ጋር በተያያዘ ያለውን ደግሞ የሰዎች ንክኪ በሌለበት በግላቸው ጫካ አካባቢ መስራት ይችላሉ። ይህም ወቅታዊ ብቃታቸው እንዳይወርድ እንጂ ለውድድር በሚደረግ ልክ አይሆንም። \nይህ እንዲሆን ደግሞ አስቀድሞ እንደተገለጸው ዋናው ነገር በመልካም ስነ-ልቦና ላይ መገኘት መሆኑን ይጠቁማሉ። በማብራሪያቸውም ‹‹የሰው ልጅ በተፈጥሮው በጭንቀት ወቅት ሰውነቱ በሚሰጠው ግብረመልስ የተለያዩ ቅመሞችን ስለሚያመነጭ ለውጥረትና ለመደበት ስሜት ይጋለጣል። አትሌትሌቲክስ የሙሉ ጊዜ ስራው የሆነው አትሌትም ውድድሮች ከሌሉ በእንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ውስጥ ሊገባ ይችላል። ይህ እንዳይከሰትም አትሌቶች ራሳቸውን በስነ-ልቦና ማዘጋጀት ይገባቸዋል›› ሲሉ ያስረዳሉ ባለሙያዋ። ሁኔታዎችን አእምሮ ሲቀበል ሌሎች አካላትን ማዘዝ ስለሚቻል ስነ-ልቦና የመጀመሪያውና ዋነኛው ጉዳይ ነው።\nከዚህ ባሻገር በአትሌቲክስ ስፖርት የሚፈራው ነገር ክብደት መጨመር ነው። በክብደት ተወስነው እንደሚካሄዱት የቦክስና የማርሻል አርት ስፖርቶች ሁሉ የረጅም ርቀት በአትሌቲክስም ክብደት መጨመር የራሱ አደጋ ይኖረዋል። በመሆኑም የቡድን እና ጫና ያላቸውን ልምምዶችን በማስቀረት ሰውነትን ባለበት እንዲቆይና የብቃት መዋዠቅ እንዳይከተል የሚያደርግ መሆን እንዳለበት ባለሙያዋ ያስገነዝባሉ። \nአመጋገብ ላይም አትሌቶች የራሳቸውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል፤ አመጋገብ ከሚወጣው ኃይል ጋር ተመጣጣኝ መሆን ይኖርበታል። በዚህ ወቅት ቀለል ያሉ ልምምዶችን እየሰሩ እንደ ወትሯቸው የሚመገቡ ከሆነ ግን ሰውነት ያንን ለማስተናገድ ስለሚከብደው የክብደት መጨመር ይከሰታል። በመሆኑም ይህንን መከታተልና ከቻሉ በየዕለቱ ያሉበትን ሁኔታ በመመዝገብ ማስታወሻ እንዲይዙ ይመከራል። የዓለም አትሌቲክስም በየወቅቱ የሚያወጣውን መረጃ መከታተልም አስፈላጊ ነው። \nበዚህ ሂደት ሊዘነጋ የማይገባው ዋናው ነገር በቤት ውስጥ የሚሰሩ ማሳሳቢያዎችና ሌሎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ንጹህ አየር ባለበት ስፍራ መሆኑን ማረጋገጥ ነው። \nሰው የማይበዛበትና ነፋሻማ አየር ባለበት ስፍራ ቢንቀሳቀሱ ደግሞ የተሻለ ይሆናል። እንደ ዓለም አትሌቲክስ መረጃ ከሆነ አትሌቶች በተለይም የረጅም ርቀት ሯጮች ትንፋሻቸው የዳበረ በመሆኑ ከሌላው በተለየ ተጋላጭነታቸው የሰፋ ይሆናል። \nበመሆኑም ራሳቸውን ለየት ባለመልኩ መጠበቅ ይኖርባቸዋል። ፈሳሽ በብዛት መውሰድና በሽታን ሊቋቋሙ የሚችሉ ምግቦችንም ከዚህ ቀደሙ በተሻለ ሁኔታ ማዘውተርና በዓለም የጤና ድርጅት እንዲሁም ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ከመሳሰሉ ተቋማት የሚወጡ መረጃዎችን መከታተል ለአትሌቱ ጠቃሚም ነው። ምክንያቱም አብዛኛው የማህበራዊ ትስስር ገጾችን የሚጠቀም እንደመሆኑ መረጃዎችን የሚያገኙበት መንገድ በራሱ ጎጂ ሊሆን ይችላል። \nይህንንና መሰል ግንዛቤዎችን ከማስጨበጥ አንጻር ባለሙያዎች አትሌቱን በአካል ለማግኘት አዳጋች በመሆኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተለያዩ ስራዎችን እንደጀመረም ባለሙያዋ ይጠቁማሉ። የፌዴሬሽኑ አመራሮች ባደረጉት ውይይት አትሌቱ ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ክልሎችም የሚገኝ እንደመሆኑ ሁሉንም ተደራሽ ለማድረግ በቴሌቪዥንና በሬዲዮኖች መልዕክቶችን ማስተላለፍ የተሻለ አማራጭ ሆኖ አግኝቶታል። በመሆኑም ሰፊ ሽፋን ካላቸውና ከክልል የመገናኛ ብዙሃን ጋር በመተባበር፤ አትሌቱ ልምምዱን እንዴትና በምን ሁኔታ መስራት እንዳለበት በባለሙያዎች ግንዛቤ የሚሰጥ ይሆናል። \nከዚህ ባሻገር ከወቅታዊው ሁኔታና ከቫይረሱ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን፣ ስነ- ምግብ፣ ስፖርታዊ ስነ-ልቦና፣ የስፖርት ህክምና፣ የመረጃ ክትትል ምን መምሰል አለበት የሚሉና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ነባራዊ ሁኔታውን ባገናዘበ መልኩ ለአትሌቱ እንዲደርስ ይደረጋል። በዚህ ሁሉ ሁኔታ ውስጥ ግን መዘንጋት የሌለበት ዋነኛ ጉዳይ አበረታች ቅመም መሆኑን ያሳስባሉ። \nይህንን ግንዛቤ የሚሰጡትም በስፖርቱ ላይ ለረጅም ጊዜ ያሳለፉ ባለሙያዎች እና ኦሊምፒክን ጨምሮ በተለያዩ መድረኮች ላይ ስኬታማ የሆኑ አንጋፋና ተምሳሌት አትሌቶች ሲሆኑ፤ መልእክቶችን፣ ምክሮችንና በተግባር የታገዙ እንቅስቃሴዎችንም ለአትሌቶች የሚያስተላልፉ ይሆናል። ከፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት እንዲሁም ከስልጠና ጥናትና ምርምር ክፍል ጋር በመሆንም በተለያዩ የማህበራዊ ገጾች መልእክቶችን ለማስተላለፍም በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኙ ባለሙያዋ ጨምረው ገልጸዋል።\nአዲስ ዘመን ሚያዝያ 5/ 2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "1dee20ef7f798a5f4f9393c780beb163" }, { "passage": "ይህ ዓመት እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ቢሆን፤ በስፖርቱ ዓለም በተለይ በዚህ ወቅት በርካታ ውድድሮች፣ ጉባኤዎችና ሥልጠናዎች ሊካሄዱ ይችሉ ነበር። ነገር ግን ሳይታሰብ ተከስቶ ዓለምን ባዳረሰው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) ወረርሽኝ ምክንያት ውድድሮች ብቻም ሳይሆኑ በርካታ ጉዳዮች በታቀደላቸው ሁኔታ እንዳይካሄዱ ማድረጉ ግልጽ ነው። ታዲያ የስፖርት ማህበራትና ሌሎች ተቋማት እቅዶቻቸው በዚህ መልኩ አቅጣጫቸውን ሲስቱ ምን ዓይነት አማራጮችን ተጠቀሙ? ከዓመት እስከ ዓመት በሩጫ ላይ ከሆኑና በሥራ ከሚወጠሩ ፌዴሬሽኖች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው። የፌዴሬሽኑ የሥልጠና ጥናትና ምርምር ዳይሬክተሩ አቶ ሳሙኤል ብርሃኑ የሚናገሩት አላቸው። የኢትዮጵያ\nአትሌቲክስ ቻምፒዮናን ጨምሮ የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን፣ የወጣቶች ቻምፒዮና እንዲሁም ሌሎች ውድድሮች ፌዴሬሽኑ በዚህ ዓመት ያላካሄዳቸው የውድድር ዘርፍ እቅዶች ናቸው። በሥልጠና ጥናትና ምርምር ዘርፍ ደግሞ የዚህ ዓመት ዋነኛ እቅድ የነበረው ባለሙያዎችን ማብቃትና መመዘን መሆኑን ዳይሬክተሩ ይገልጻሉ። ዳኞችና አሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ሥልጠናዎችን አግኝተው ደረጃቸውን እንዲያሳድጉ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ባለበት ወቅት ግን የዓለም ትኩሳት የሆነው ጉዳይ በመከሰቱ እንደታሰበው ማስኬድ አልተቻለም ይላሉ። በተለይ ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ወር ድረስ የሥራ ክፍሉ በዚህ ለማሳለፍ ያስቀመጠው እቅድ ወደ መሬት ሳይወርድ ቀርቷል። በዓመቱ\nኦሊምፒክና ሌሎች ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ መሳተፍና ብሔራዊ ቡድንን የማዘጋጀት እቅድም ተመሳሳይ ዕጣፈንታ ገጥሞታል። ለብሔራዊ ቡድን የተጠሩ አትሌቶችም ተበትነው ወደየ ቤታቸው ሄደዋል። ይህ ሁሉ ሲሆን ፌዴሬሽኑ ግን ሥራውን ከማቋረጥ ይልቅ ሌሎች አማራጮችን መጠቀምን መርጧል። ዋናው የአትሌቶች ጤንነትና በብቃት መቆየት በመሆኑም የተሻለ ያለውን ተግባር ሲከውን እንደቆየ ዳይሬክተሩ ያስረዳሉ። ፌዴሬሽኑ\nከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ስፖርታዊ ክዋኔዎችን ማካሄድ አዳጋች መሆኑን በመገንዘቡ ቀደም ብሎ ወደ ዝግጅት መግባቱን ይጠቁማሉ። አትሌቶች ሥልጠና ማቋረጣቸውን ተከትሎ ከስፖርቱ እንዳይርቁ እንዲሁም አሰልጣኞችም ከአትሌቶቻቸው በጋራ ያላቸው ግንኙነት እንዳይቋረጥ ምን ማድረግ ይገባል? የሚለውን በማሰብም ነው በቴሌቪዥን ስርጭት በትምህርትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ፕሮግራሞች እንዲተላለፉ የተደረገው። በዚህም የስፖርቱ ባለሙያዎችን በማካተት በሦስት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለስድስት ሳምንታት ለአትሌቶች ጠቃሚ የሆኑ መርሃ ግብሮች ሲተላለፉ ቆይቷል። የመርሃ ግብሩ ይዘትም ሥነ-ልቦና፣ ሥነ-ምግብ፣ ሕክምና፣ ማህበራዊ ግንኙነት፣ የተምሳሌት አትሌቶች መልዕክት፣ የአሰልጣኞች ምክረ ሃሳብ እንዲሁም አትሌቶች በአጠቃላይ ምን ማድረግ ይገባቸዋል የሚለውን ያጠቃለለ ነበር። ከቴሌቪዥን ስርጭቱ ባሻገር በፌዴሬሽኑ ይፋዊ ማህበራዊ ገጽ (ፌስ ቡክ) እንዲሁም በድረገጹ አማካኝነትም አትሌቶችን ተደራሽ ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህ\nሂደትም ፌዴሬሽኑ ማድረግ የሚገባውን መልካም ተግባር ማከናወኑን ለመታዘብ ተችሏል። አትሌቶችና ሌሎች ባለሙያዎችም ለዚህ የሚሰጡት ግብረ መልስ ጥሩ ሥራ መሰራቱን የሚያሳይ ነው። አትሌቶች ቤታቸው በሚሆኑበት ወቅት ምን መስራት እንዳለባቸው ግራ ተጋብተው ነበር የሚሉት ዳይሬክተሩ፣ አሰልጣኞች በሚሰጧቸው አቅጣጫ ተጠቃሚ ሆነዋል። በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙና እነዚህን አማራጮች የማያገኙ አትሌቶችን ደግሞ አሰልጣኞች በስልክና በሌሎች መንገዶች በተመሳሳይ እየረዷቸው ይገኛሉ። አሁን ካለው ሁኔታ አንጻር ጥናት መስራትና አትሌቶችን ማግኘት ባይቻልም በተለያዩ መንገዶች ምስጋናቸውን ያደርሳሉ። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምክር የሚጠይቁ አትሌቶች ቁጥር መበራከትም ይህንኑ የሚያመላክት ነው። አሰልጣኞች በበኩላቸው ወትሮ ከነበረው ሁኔታ በተሻለ መልኩ ከፌዴሬሽኑ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያጠናከሩ ሲሆን፤ ግብረመልስ በመስጠትም አጋርነታቸውን እያሳዩ ነው። ከዚህ\nበኋላም ፌዴሬሽኑ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት ጎን ለጎን መርሃ ግብሩን በአዲስ መልክ የሚያስቀጥልም ይሆናል። የሀገርን ስም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያስጠራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በሚደረገው ርብርብ ቅድሚያ ተሰላፊ መሆኑን በተግባር በማሳየት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። ከዚህ ቀደም በግሉ፣ ከሌሎች ተቋማት ጋር እንዲሁም በአትሌቶቹ አማካኝነት በገንዘብ እንዲሁም በቁሳቁስ የድርሻውን በማድረግ ላይ ይገኛል። አመራሩና ሌሎች ታዋቂ አትሌቶችም ለሕዝቡ መልዕክት በማስተላለፍ ላይ ናቸው። አሁንም ከዚህ በላቀ መልኩ ለመስራት የሚያስችል ተነሳሽነት አለ። እንደሚታወቀው\nበዚህ ወቅት ውድድሮችና ሌሎች የሥልጠና መርሃ ግብሮች ተቋርጠዋል። በዚህ ምክንያት ፌዴሬሽኑ ቀድሞ የያዛቸውን እቅዶች በመቀየር የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮች ላይ ለማተኮር ማቀዱን ዳይሬክተሩ ይጠቁማሉ። በዚህም ከፌዴሬሽኑ ስፖንሰር ማልታ ጊነስ ጋር በመሆን በቴሌቪዥን የሚተላለፉ መርሃ ግብሮችን በመስራት ላይ ነው። በአንድ ወር ውስጥ ለ16 ቀናት ያህል የሚተላለፈው መርሃ ግብሩ እንደ ቀድሞ በምክረ ሃሳብ ላይ ሳይሆን በተግባር ላይ የተመሰረተ እንደሚሆንም ታውቋል። በአትሌቶች ዘንድ ተምሳሌት የሆኑና ዝነኛ አትሌቶች እንዲሁም ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ሲሆን፤ ተከታታይነት ያላቸው እንቅስቃሴዎች በምን መልኩ እንደሚሰሩ የሚያሳይም ይሆናል። እንቅስቃሴው ከአትሌቶች ጋር ብቻ ሳይሆን ሌላውን ኅብረተሰብም የሚጠቅምም ነው የሚሆነው። ለዚህ የሚሆነው ዝግጅት በመጠናቀቁ በቅርቡ አየር ላይ የሚውልም ይሆናል። በዚህ\nወቅት አብዛኛው ኅብረተሰብ ትኩረቱ የመገናኛ ብዙኃን ላይ በመሆኑ፤ ትብብራቸውን እንዳያቋርጡ ይጠይቃሉ። ከቴሌቪዥን ባሻገር በርካቶችን ተደራሽ የሚያደርጉ የመገናኛ ብዙኃን አብሮነታቸውን እንዲያሳ ዩም ጠይቀዋል።አዲስ\nዘመን ግንቦት 19/2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "66e0e14f27a08cecb713d5ae9e964fe9" }, { "passage": " 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በኳታር ዶሃ ተካሂዶ ባለፈው እሁድ ምሽት ተጠናቋል፡፡ ኢትዮጵያም በተለያዩ ርቀቶች ሰላሳ ሰባት አትሌቶችን አወዳድራ በሁለት ወርቅ፣አራት ብርና አንድ ነሐስ ሜዳሊያ ከዓለም አምስተኛ ከአፍሪካ ሁለተኛ በመሆን አጠናቃ ልዑካን ቡድኑ ዛሬ ወደ አገሩ ተመልሷል:: ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው ውጤት ከፍተኛ የሚባል ቢሆንም ማግኘት የሚገባት ወይም ማግኘት የምትችለው ውጤት ከስልጠናና ዝግጅት፣ ከቴክኒክና ከታክቲክ እንዲሁም ከሌሎች ችግሮች ጋር ተደማምሮ በርካታ ሜዳሊያዎች ቀልጠው ቀርተዋል:: ከነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹን መመልከት ለቀጣይ የአትሌቲክሱ ውጤት ማማር ጠቃሚ ይሆናል፡፡ በቻምፒዮናው የመጀመሪያ ዕለት በተካሄደው የሴቶች የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያን የወከሉት ሦስቱም አትሌቶች ውድድሩን ከአስራ አምስት ኪሎ ሜትር በላይ መግፋት እንዳልቻሉ ይታወሳል፡፡ ለዚህ በብዛት እንደምክንያት ሲቀርብ የነበረው በዶሃ ያለው ከፍተኛ ሙቀትና ወበቅ ነው፡፡ ይህ ግን ብዙዎችን የሚያስማማ እንዳልሆነ ባለፉት ቀናት ተመልክተናል:: በዚህ ውድድር ኢትዮጵያውያን በማራቶን ያላቸው አቅምና ችሎት ወርቅ ቢቀር ብርና ነሐስ ለማስመዝገብ በቂ መሆኑን በድፍረት መናገር ይቻላል፡፡ ከነዚህ ሜዳሊያዎች መካከል አንዱን እንኳን ማስመዝገብ ሳይቻል ቀልጠው የቀሩት በዶሃ ከፍተኛ ሙቀት ሳይሆን በዝግጅት ችግር መሆኑን ማስቀመጥ ይቻላል:: በስፍራው የነበረው የሙቀት መጠን ምንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆን ለሁሉም አገራት ተወዳዳሪዎች እኩል ነው፡፡ እኩል ባይሆን ኖሮ ከኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጋር ተመሳሳይ አቅም ያላቸው ኬንያውያን ውድድሩን ባላሸነፉ ነበር:: ወትሮውንም ቢሆን የማራቶን ቡድኑ ዝግጅት ግልፅ አልነበረም፡፡ አዲስ አበባና አካባቢዋ ላይ ዝጅግት አድርጎ በዶሃ ከፍተኛ ሙቀት ማራቶንን መሮጥ ያስከተለው ውጤትም እንደሆነ ይታመናል:: በዚህ ርቀት ቀልጠው የቀሩት ሜዳሊያዎች በቂ ዝጅግት ባለማድረግ እንጂ በዶሃ አስቸጋሪ ሙቀት ምክኒያት እንዳልሆነ በወንዶች ማራቶን የተመዘገበው አስደናቂ ውጤት ማሳያ ነው፡፡ ሌላው በሴቶች አምስት ሺ ሜትር የተመዘገበው ውጤት ነው፡፡ በዚህ ርቀት የኦሊምፒክና የዓለም ቻምፒዮኗ አልማዝ አያና በመጨረሻ ሰዓት በጉዳት ምክንያት ከውድድር ውጭ መሆኗን ተከትሎ የወርቅ ሜዳሊያ ማስመዝገብ አደጋ ውስጥ ገብቶ ነበር:: ያምሆኖ ኢትዮጵያን የወከሉ ወጣት አትሌቶች ከሜዳሊያ ውጭ ይሆናሉ የሚል ግምት አልነበረም፡፡ አስር ሺ ሜትርን ሮጣ የአምስት ሺ ሜትር ማጣሪያ አድርጋ ከተደጋጋሚ ድካም በኋላ ለድል የበቃችው ኬንያዊቷ ሔለን ኦቢሪ ካላት ልምድና አቅም አኳያ ለኢትዮጵያውያን ወጣት አትሌቶች ቀላል እንደማትሆን ግልፅ ነው፡፡ ያም ሆኖ ኢትዮጵያውያን በርቀቱ ካላቸው እምቅ አቅምና ታሪክ አኳያ በጀርመን አትሌት ሳይቀር ተቀድመው ከሜዳሊያ ውጭ ይሆናሉ ብሎ ማመን ከባድ ነው:: በዚህ ውድድር እነዚህ ወጣቶች ላይ በቂ ዝግጅት እንዳልተደረገና የቡድን ሥራ እንዳልተሰራ ግልፅ ነው፡፡ አንዳንዴ ውጤት ሊበላሽና ላይቀና እንደሚችል ከግምት ውስጥ በማስገባት አትሌቶቹን ተወቃሽ ከማድረግ ማለፍ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን በዚህ ርቀት ከቻምፒዮኗ ሔለን ኦቢሪ የበለጠ ድንቅ ብቃት በአስር ሺ ሜትር አሳይታ የብር ሜዳሊያ ያጠለቀችው ለተሰንበት ግደይ አለመሰለፏ የሚያስቆጭ ነው፡፡ አንዳንዴ አገርን ወክሎ በዓለም አቀፍ ውድድሮች ተሳታፊ ሲኮን ከራስ ውጤት ባሻገር አገርን ማስቀደም ያስፈልጋል የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ በአንድ ርቀት ለመወዳደር የሄደ አትሌት ሁሉ የመወዳደር ግዴታ የለበትም፡፡ ለተሰንበት ግደይ በአስር ሺ ሜትር ያሳየችውን ብቃት ተከትሎ በአምስት ሺ ሜትር ከሚወዳደሩት አትሌቶች ቀንሶ ጥሩ አቅም ያላትን ማሰለፍ ቢቻል ወርቅ ባይመጣ እንኳን ሜዳሊያ ውስጥ የመግባት ዕድል ይኖር ነበር፡፡ በእርግጥ ይሄን አድርጎ ውጤት ባይመጣ ሌላ የአስተዳደራዊ ቀውስ መፍጠሩ እንደማይቀርና የተቀነሰው አትሌት አሜን ብሎ እንደማይቀበል ግልፅ ነው፡፡ እዚህ ላይ ግን ለአገር ውጤት ማማር ሲባል አደጋ ቢኖረውም ደፋር አስተዳደራዊ ውሳኔ ያስፈልጋል፡፡ በወንዶች አስር ሺ ሜትር የወቅቱ ኮከብ የሆኑትና ፈጣን ሰዓት ማስመዝገብ የቻሉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ቢሆኑም የርቀቱ የወርቅ ሜዳሊያ ያለፉትን ስምንት ዓመታት ጨምሮ በቀጣይ ሁለት ዓመታት በአጠቃላይ ለአስር ዓመታት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ማድረግ አልቻሉም፡፡ ደካማ የቡድን ሥራና አለመቀናጀት በተለይም በውድድር ዓመቱ አስደናቂ ብቃት ሲያሳይ የነበረውን ሐጎስ ገብረሕይወትን ከሜዳሊያ ውጭ አድርጎታል፡፡ በዚህ ርቀት ከኢትዮጵያውያን አኳያ ታሪኩም ብቃቱም የሌላቸው ዩጋንዳውያን ሲነግሱ ዮሚፍ ቀጄልቻ ወጣት እንደመሆኑ መጠን የብር ሜዳሊያ ማስመዝገቡ ሳይደነቅ አይታለፍም፡፡ ያም ሆኖ ሐጎስ ገብረሕይወትና አንዱዓምላክ በልሁን የመሳሰሉ ጠንካራ አትሌቶች ይዞ የወርቅ ሜዳሊያ አለማስመዝገብ አስቆጪነው:: እነዚህ አትሌቶች የተቀናጀ የቡድን ሥራ ሠርተው እንዲተጋገዙ ከመጀመሪያው መሥራት ቢቻል በርቀቱ ከብር ሜዳሊያም በላይ ማስመዝገብ የሚቻልበት ዕድል ሰፊ ነበር፡፡ እንደ አጠቃላይ በቻምፒዮናው ከዚህ ቀደም በታሪክ ያልነበሩ እንደ ሦስት ሺ ሜትር መሰናክል አይነት ውጤቶች ማምጣት ቢቻልም የነበሩንን እየለቀቅን የመሄድ አዝማሚያ ወደ ፊትም ቢሆን ብዙ ሜዳሊያዎችን ሊያቀልጥብን እንደሚችል በጊዜ ማየቱ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ አዲስ ዘመን  መስከረም\n28/2012 ቦጋለ አበበ", "passage_id": "2ea9f73dea0795061dc2f5fa0f4eaa1f" } ]
1b49b04e2c22f69c691ac5f085d855b8
31430e6b6122d55b4e12362e084163ed
የሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር የ4 ሚሊዮን ብር ሽያጭና የገበያ ትስስር እንደሚፈጠር ተገለጸ
አዲሱ ገረመው አዲስ አበባ፡- የ2013 በጀት ዓመት የ4 ሚሊዮን ብር ሽያጭና የገበያ ትስስር እንደሚፈጥር የፌዴራል የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ አስታወቀ። ከተሳታፊዎች ውስጥ 50 በመቶዎቹ ሴቶች መሆናቸው ተጠቆመ ። ኤጀንሲው ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በ2013 በጀት አመት አንደኛው ዙር የሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሀገር አቀፍ ኤግዚቢሽንና ባዛር ‹‹ዘላቂነት ያለው የገበያ ትስስር ለስራ ዕድል ፈጠራና ለኢንተርፕራይዞች ልማት መሰረት ነው ›› በሚል መሪ ቃል ከታህሳስ 22 እስከ ታህሳስ 28 ቀን 2013 ዓ.ም በጀሞ አንድ አደባባይ ትራፊክ መብራት ፊትለፊት ለሰባት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ይሆናል። የ4 ሚሊዮን ብር ሽያጭና የገበያ ትስስር እንዲሚፈጥርም ይጠበቃል። በኤግዚቢሽንና ባዛሩ ላይ ከሁሉም ክልሎችና ከተሞች የተውጣጡ 202 የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች 10 አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የሚሳተፉ ሲሆን፤ ሴቶች 50 በመቶ እና አካል ጉዳተኛ ሦስት በመቶ በማሳተፍ ምርትና አገልግሎታቸው ከ20ሺ በላይ በሚሆን ተጠቃሚ የህብረተሰብ ክፍል እንዲጎበኝ ይደረጋል ብሏል ። ባዛሩ ከተለያዩ ክልሎችና አካባቢዎች የተሰባሰቡና በልዩ ልዩ ዘርፎች የተሰማሩ ብቁና ተወዳዳሪ ኢንተርፕራይዞችንና አንቀሳቃሾችን የሚያሳትፍ ሲሆን፤ በአንድ ማዕከል በማገናኘት በሚፈጠረው ትውውቅና የልምድ ልውውጥ በመካከላቸው ጤናማ የውድድር ስሜት ለማቀጣጠል እንደሚያስችልም “ኤጀንሲው አመልክቷል ። ባህላዊና ዘመናዊ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ምርት ውጤቶች፣ ባህላዊና ዘመናዊ የቆዳ አልባሳትና የቆዳ ምርት ውጤቶች፣ ባህላዊ የዕደ-ጥበባትና ቅርጻ-ቅርጽ ሥራዎችና ውጤቶች፣ የብረታብረት፣ የእንጨት ሥራና የኢንጅነሪንግ ስራዎችና ውጤቶች፣ የአግሮ-ፕሮሰሲንግ ምርቶች እና የከተማ ግብርና ውጤቶች፣ የቴክኖሎጂ ውጤቶችና የፈጠራ ስራዎች፣ ፈሳሽ ሳሙና፣አልኮል፣ሳኒታይዘር፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል/ማስኮች/፣ እና ሌሎችም ምርቶች በኤግዚቢሽንና ባዛሩ እንደሚቀርቡ አስታውቋል። የአዲስ አበባ ነጋዴ ሴቶች ማህበር፣ የሴቶች ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ፕሮግራም፣ ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ማዕከል፣ ፋሽን ዲዛይን አሶሴሽን፣ የሴቶች ራስ አገዝ ድርጅት፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በዕደ ጥበብ ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችና ሌሎችም ተሳታፊ ኢንተርፕራይዞች እንደሚሆኑ ጠቁሟል። ሁነቱ የተሞክሮ ልውውጥና የንግድ ልማት ግንዛቤ ከማዳበሩም ባሻገር፤ ኢንተርፕራይዞች ከተጠቃሚው ህብረተሰብ ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት ዘላቂ የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል ምቹ አጋጣሚ ይሆንላቸዋል። ምርቶቻቸውንና አገልግሎታቸውን ለተጠቃሚዎች በቀጥታ በመሸጥም ተጠቃሚ እንደሚሆኑም እጀንሲው አስታውቋል ።አዲስ ዘመን ታህሳስ 22/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=38532
[ { "passage": " አራተኛው ዲፕሎማቲክ ባዛር ዛሬ ከረፋዱ 4፡00 ጀምሮ በተባበሩ መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ (ECA) ይከፈታል፡፡ በባዛሩ የተለያዩ አገር ምግቦች፣ የባህል አልባሳት፣ የስጦታ እቃዎች፣ መጠጦችና ህፃናት የሚዝናኑበት ጥግ መሰናዳቱን አዘጋጆች ገልፀዋል፡፡ ከ62 አገራት በላይ በሚካፈሉበት ከዚህ ባዛር የሚገኘው ገቢ በእናቶች ልማትና በተጋላጭ ህፃናት ዙሪያ ለሚሰሩ የእርዳታ ድርጅቶ ገቢ ይደረጋል የተባለ ሲሆን ከዚህ በፊት በተካሄዱት ሶስት የዲፕሎማቲክ ባዛሮች የተሰበሰቡ ገቢዎች በትግራይና በኦሞ ለሚገኙ በእናቶችና ህፃናት ላይ የሚሰሩ 26 ፕሮጀክቶች ድጋፍ መዋሉም ተገልጿል። ባለፈው ዓመት ከባዛሩ 3.9 ሚ. ብር የተገኘ ሲሆን ከዛሬው ባዛር 4 ሚ. ብር እንደሚጠበቅም አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡ ወደ ባዛሩ ለመግባት ለአዋቂዎች 50 ብር፣ ለህፃናት ደግሞ 10 ብር እንደሚከፈል ተገልጿል፡፡ ባዛሩን ሄኒከን ቢራ፣ አዲስ ኢንተርናሽናል ካተሪንግ፣ ኖርዲክ ሜዲካሌ ኬር፣ ካፒታል ሆቴል፣ ማሪዮት ሆቴል፣ ኬንያ አየር መንገድ፣ ራዲሰን ብሉ ሆቴል፣ ራማዳ ሆቴልና ገልፍ አየር መንገድ ስፖንሰር እንዳደረጉትም ታውቋል፡፡", "passage_id": "0e4cce56a7d9cae016b44af8650ee0a7" }, { "passage": "አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአርሲ ዞን የመጀመሪያው የግብርና ባዛርና የገበያ ትስስር ኤግዚቪሽን እየተካሄደ ይገኛል።በመርሃ ግብሩ የግብርና ውጤቶች፣ ቴክኖሎጂዎች፣ ግብአቶች ከአምራቹ ወደ ገዢው በቀጥታ የሚቀርቡበት ነውም ተብሏል።አምራቾች ቀጥታ ለሸማቾች ምርቶቻቸውን ማቅረባቸውም የሽያጭ ሰንሰለቱን በማሳጠር የዋጋ ውድነትን የሚቀንስ እንዲሁም ለአርሶ አደሩ የገበያ ትስስርን የሚፈጥር መሆኑን የአርሲ ዞን ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አባቡ ዋቆ ተናግረዋል።በተጨማሪም ሃላፊው መርሃ ግብሩ በዞኑ ለመጀመሪያ ጊዜ መዘጋጀቱን ገልፀው፤ ከዚህ በፊት ይነሱ የነበሩ የገበያ ትስስር ችግሮችን ይፈታል ብለዋል።በግብርና ባዛርና ኤግዚቢሽኑ የግብርና ቴክኖሎጂ አምራቾች፣ የፀረ አረምና ፀረተባይ አምራች ኩባንያዎች፣ ማህበራት እና አርሶ አደሮች ምርቶቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን በዞኑ የሚገኙ ወረዳዎችም ተሳታፊ ሆነዋል።መርሃ ግብሩ ለ3 ቀናት ይቀጥላልም ነው የተባለው።በአፈወርቅ እያዩ", "passage_id": "6fc4bd7ada086b3ba843360336a1d54f" }, { "passage": "በኢትዮጵያ ያሉ የዲፕሎማት ሚስቶች ቡድን በሚቀጥለው ቅዳሜ ዓመታዊውን የበጎ አድራጎት ባዛር በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡፡ ከ25 ዓመት በፊት የተመሰረተው የዲፕሎማት ሚስቶች ቡድን፣ ከየአገሮቻቸው እያስመጡ የሚሸጧቸውን የተለያዩ ቁሶች ገቢ፣ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚውል የዘንድሮው የቡድኑ ፕሬዚዳንት በአፍሪካ ህብረት የአሜሪካ አምባሳደር ባለቤት ዶ/ር ሊላይ ስላሴ ገልጸዋል፡፡ ሴቶቹ ባዛሩን የሚያዘጋጁት በየተራ በተለያዩ ኤምባሲዎች ግቢና በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እንደነበር የጠቀሱት ፕሬዚዳንቷ፣ በባዛሩ የሚሳተፉ የአገር ውስጥና የውጭ እንግዶች ቁጥር እየጨመረ ስለሄደ፣ ሁሉንም ለማሳተፍ ከ2002 ጀምሮ ባዛሩ በሚሌኒየም አዳራሽ እየተካሄደ መሆኑንና ባለፈው ዓመት ከ10ሺህ በላይ ሰዎች መጎብኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ዓመት የባዛሩን ማዘጋጃ ስፍራ ክፍያና የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች በሙሉ ስፖንሰሮቻችን ስለሸፈኑልን ከመቶ ፐርሰንት ትርፍ ጋር ከባዛሩ ያገኘነውን ከሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር በላይ በመላ አገሪቷ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ከ25 በላይ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሰጥቶናል ብለዋል፡፡ ሚስ ኤሪካ አሸር የድጋፍ ጠያቂ ድርጅቶች ፕሮፖዛል አጣሪ ኮሚቴ ኃላፊ ሲሆኑ በየዓመቱ ከመላው የአገሪቱ ክፍሎች፣ በርካታ የተለያዩ የድጋፍ ጥያቄዎች እንደሚቀርቡላቸው ጠቅሰው “የቅድሚያ ትኩረት የሚሰጣቸው ለሴቶች፣ ለህፃናትና በኢትዮጵያ እጅግ ተጠቂ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ለሚያደርጉ በጎ አድራጊ ድርጅቶች ነው” ብለዋል፡፡ የዲፕሎማት ሚስቶቹ ባለፉት ዓመታት የመማሪያ ክፍል ጥበት ላለባቸው ት/ቤቶች፣ የመማሪያና የመፀዳጃ ክፍሎች ግንባታ፣ ለቁሳቁስና ለመጻሕፍት መግዣ እንዲሁም ለክሊኒኮች የማዋለጃ አልጋና የሕክምና መሳሪያዎች ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ የውሃ እጥረት ላለባቸው ማህበረሰቦች የውሃ ጉድጓድ ማስቆፈራቸውን፣ መኖሪያ ለሌላቸው አረጋውያን ቤት መስጠታቸውን፣ ለጎዳና ተዳዳሪዎች የምክርና የሕይወት ክህሎት መስጫና ከስጋ ደዌ በሽታ ለዳኑ አረጋዊ ሴቶች የሽመና ማዕከል ማቋቋማቸውን፣ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኛ ሕፃናት ለቀዶ ሕክምና አገልግሎት ድጋፍ ማድረጋቸውን የዘንድሮው የቡድኑ ተወካዮች አስረድተዋል፡፡ የዛሬ ሳምንት በሚሌኒየም አዳራሽ ከጧቱ 4 እስከ 10 ሰዓት በሚቆየው ባዛር፣ ከ60 በላይ ኤምባሲዎችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃሉ ያሉት ፕሬዚዳንቷ፤ ከአምናው የበለጠ ገቢ ለማሰባሰብ ማቀዳቸውን ተናግረዋል፡፡ የባዛሩ ተሳታፊዎች በአገራቸው የታወቀና ለየት ያለ ነገር ይዘው በመቅረብ ይሸጣሉ ያሉት ዶ/ር ሊላይ፤ የተለያዩ ጌጣ ጌጦች፣ የየአገሮቹ ምግቦች፣ መጠጦችና የተለያዩ ምርቶች ይቀርባሉ ብለዋል፡፡ በዚሁ ቡድን ድጋፍ የተደረገላቸው ከ20 በላይ የማህበረሰብ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን አቅርበው እንደሚሸጡም ታውቋል፡፡ የባዛሩ መግቢያ ትኬት ከሕዳር 1 እስከ 12 ድረስ በሂልተን ሆቴል ከጧቱ 4 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ለአዋቂዎች በ30 ብር፣ ለሕፃናት በ10 ብር እየተሸጡ ነው፡፡ ", "passage_id": "0db8408c0ec717c8aa6b49ab8527cec1" }, { "passage": "በኢትዮጵያ የዲፕሎማቲክ ሚስቶች ቡድን አባላት፣ በየዓመቱ የገቢ ማሰባሰቢያ ባዛር የሚያካሂዱ ሲሆን፣ የዘንድሮው ባዛር በመጪው ሳምንት ቅዳሜ ሕዳር 29፣ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ የማቲሪክስ ፕሮጀክት የሥራ ኃላፊዎች ባለፈው ረቡዕ በሂልተን ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በየዓመቱ በርካታ የውጭ አገር ዜጎችና ኢትዮጵያውያን በአንድ ጥላ ስር የሚገናኙበት ብቸኛው ትዕይንት እንደሆነ ጠቅሰው፣ ለአንድ ቀን በሚቆየው በዚህ ባዛር ላይ ዘጠኝ ሺህ ያህል ተሳታፊዎች እንደሚታደሙበት ገልጸዋል፡፡ በባዛሩ ላይ 60 ኤምባሲዎች የየአገሮቻቸውን ምግብ፣ ባህል፣ የመታሰቢያ ዕቃዎችና የሥነ ጥበብ ቅርፆች የሚቀርቡበት ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ባዛር 4.2 ሚሊዮን ብር ተሰብስቦ፣ በማትሪክስ ፕሮጀክት አማካይነት ለትርፍ ላልተቋቋሙ ድርጅቶችና ለበጎ አድራጎት ማኅበራት መከፋፈሉን ኃላፊዎቹ ተናግረዋል፡፡ ፕሮጀክት ማትሪክስ የሴቶችን፣ የሕፃናትና እጅግ ጎስቋላ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ፍላጎት ለማሟላት የዲፕሎማቲክ ሚስቶች ያቋቋሙት ማህበር ሲሆን ከባዛሩ የሚሰበሰበው ገንዘብ መቶ ፐርሰንት ለበጎ አድራጎት ተግባር ለተቋቋሙ ድርጅቶችና ማኅበራት እንደሚሰጥ ኃላፊዎቹ ገልጸዋል፡፡ ቀደም ባሉ ጊዜያት ከተካሄዱ ባዛሮች የተሰበሰበው ገንዘብ፤ ተጠቃሚ ከሆኑ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችና ማኅበራት መካከል ለአብነት፡- ኔክስት ዲዛይን ኮሌጅ፣ ኢየሩሳሌም አጠቃላይ ት/ቤት፣ ክብረ የአረጋውያን ምግባረ ሰናይ ድርጅት፣ ምስጋና ቻይልድ፣ የስኳር ሕመም ላለባቸው ሰዎች ድጋፍ የሚያደርግ ድርጅት፣ … ጥቂቶቹ ናቸው፡፡  ", "passage_id": "bc7c653208a406d33beaf1742f8b45db" }, { "passage": "በምሥራቅ አፍሪካ በዓይነቱና በይዘቱ ልዩ የሆነው 9ኛው አዲስ ቢውልድ ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ግብአቶችና ቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን ከመጪው ሐሙስ መስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 ቀን 2011 በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ኤግዚቢሽኑን አስመልክቶ ከትናንት በስቲያ በሳፋየር ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ኤግዚቢሽን፣ ኢትኤል አድቨርታይዚንግና ኮሙኒኬሽን ከኮንስትራክሽን ሚ/ርና ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጁ ሲሆን፣ 91 ኩባንያዎች በ20 ያህል የግንባታ ግብአትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ እንደሚሳተፉ ታውቋል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከቻይና፣ ከጀርመን፣ ከግሪክ፣ ከኢጣሊያ፣ ከቱርክ፣ ከዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ የተውጣጡ ኩባንያዎች በኤግዚቢሽኑ እንደሚሳተፉ የጠቀሱት የኢቴኤል አድቨርታይዚንግና ኮሙኒኬሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሃይማኖት ተስፋዬ፣ ኩባንያዎቹ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የግብአት አቅርቦትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ከፍተኛ ዕድገት ላይ የደረሱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ከተሳታፊዎቹ 90 በመቶ ያህሉ የውጭ አገራት ኩባንያዎች ሲሆኑ 16ቱ ደግሞ ከአገር ውስጥ እንደሆኑ የጠቀሱት የኢትኤል ማኔጂንግ ዳይሬክተር፣ ይህ በዓይነትና በይዘቱ ከፍተኛ የሆነው ኤግዚቢሽን አገራችን በዕድገት ግስጋሴ ላይ የምትገኝ መሆኗን በአካል በማየት ለመገንዘብ ያስችላል፤ ለኢንቨስትመንት መስፋፋትም መልካም ዕድል ከመፍጠሩም በላይ የአገራችንን መልካም ገጽታ ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ግምት ይሰጠዋል ብለዋል፡፡ ኤግዚቢሽኑ፣ ለአገር ውስጥ የዘርፉ ተዋናዮችና ለሌሎች አካላት የገበያ ትስስርና የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ፣ በዓለም ላይ ኢንዱስትሪው የደረሰበትን የምጥቀት ደረጃ ለመገንዘብ ያስችላል ያሉት ወ/ሮ ሃይማኖት፤ ከሀገራችን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፈጣን ዕድገትና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የመገንባት ሀገራዊ ራዕይ አንፃር፣ እየገጠመን ያለውን የጥራት፣ የዋጋ፣ የጊዜና የደህንነት ችግሮችን በመቅረፍ ረገድ ሰፊ የትምህርት ማዕድ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡ አገራችን ሰፊ የሆነ የተፈጥሮ ሀብት ያላትና የምርቱ ፈላጊዎችም ቢኖሩ፣ ባለሀብቶች ዘመናዊ የማምረቻ ቴክኖሎጂ ስለማይጠቀሙ፣ 82 ከመቶ የሴራሚክ ውጤቶችን የምናስገባው ከውጭ አገር ነው ያሉት በኮንስትራክሽን ሚ/ር የኮንስትራክሽን ምክር ቤትና የባለድርሻ አካላት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ንጉሴ፤ 18 በመቶ የሚያመርቱ ጥቂት አምራቾች ቢኖሩም የአመራረት ዘዴው ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ስለሆነ የምርቱ ፈላጊዎች የውጪውን ይመርጣሉ በማለት አስረድተዋል፡፡ የአቅም ግንባታ መፍጠርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማምጣት የመስሪያ ቤቱ ትኩረት በመሆኑ ከኢትኤል አድቨርታይዚንግና ኮሙኒኬሽን ጋር ተባብረን እንሰራለን ያሉት አቶ ሳሙኤል፤ የገበያ ትስስር ለመፍጠርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ የኮንስትራክሽን ኤግዚቢሽን በማዘጋጀት የብዙ ዓመት ልምድ ካለው የግል ድርጅት ኢትኤል ጋር መተባበር ጠቃሚ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች ምን ችግር አለባቸው? እንዴት ክፍተቱን መሙላት ይቻላል? … በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፊ የፓናል ውይይት ይደረጋል ብለዋል፡፡   ", "passage_id": "87081d9cc7685447fc9a820da97b0c56" } ]
be0454755e017aa3d93b5dbe74382487
3e7abc4b9373e017c91a86544fde8cd1
የመቀሌ ከተማ በአስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት ላይ እንደምትገኝ ተገለጸ
እፀገነት አክሊሉአዲስ አበባ፦ የመቀሌ ከተማ በአስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት ላይ እንደምትገኝ የከተማው ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስታወቀ ። በህብረተሰቡ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ ያሳደረው የገንዘብ ቅያሪም ባንኮች ሥራ ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በ14 ቀናት ውስጥ እንዲፈጸም ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።ከከተማዋ ኮሙኒክሽን ጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በከተማዋ በቤተ እምነቶችና በሌሎች ቦታዎች ላይ ተሰብስቦ የተገኘ ሰው ይገደላል፣ ታፍሶ ወደበረሃ ይወሰዳል እየተባለ ከፍተኛ ውዥንብር ይነዛ ነበረ፤ ሆኖም በትናንትናው እለት የማርያምን ወርሃዊ በዓል ለማክበር ህዝቡ በመቀሌ ከተማ እነዳማርያም ቤተክርስቲያን በብዛት በመገኘት በተረጋጋ ሁኔታ ለአሉባልታዎች ጆሮ ባለመስጠት ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ፈጽሟል። በከተማዋ የገበያ ስፍራዎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሁም ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ወደቀድሞ ስራቸው እየተመለሱ ነው፤ ህዝቡም ምንም ሳይሸበር በሰላማዊ መንገድ ወጥቶ የፈለገውን ጉዳዩን ፈጽሞ ተገበያይቶ ቤቱ እንዲገባ የማድረጉም ስራ እየተሰራና ውጤትም እየታየበት ይገኛል። በከተማዋ ክፍለ ከተሞችንና ወረዳዎችን የማደራጀት ስራዎች እየተከናወኑ ነው ያለው መረጃው፣ እስከ አሁን ለስድስቱም ክፍለ ከተሞች አመራር የመምረጥ ስራ ተጠናቋል። በእነዚህ ክፍለ ከተሞች ውስጥ ላሉ ቀበሌዎች ደግሞ 20 አባላት ያሏቸው ካቢኔዎች ተደራጅተዋል፤ እነሱም የወረዳ አመራሮችን የመረጡ ሲሆን በትናንትናው እለት የአይደር ክፍለ ከተማ አመራር ተመርጧል። ከዚህ ቀደም 88 በመቶ የሚሆነው የመንግስት ሰራተኛ ወደ ስራው ለመመለስ ሪፖርት አድርጎ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ሪፖርት ካደረጉት ውስጥ ምን ያህሉ በስራ ገበታቸው ላይ ተገኙ የሚለውን ለማጣራት የታህሳስ ወርን የስራ አፈጻጸም በመሰራት ላይ መሆኑን የገለጸው መረጃው ፤ ስራው እንደተጠናቀቀም ውጤት እንደሚገለጽ ተብራርቷል። በሌላ በኩልም የመቀሌ ከተማ ንግድ ምክር ቤት እንደ አዲስ ተቋቁሞ የንግዱ ማህበረሰብ ህዝቡን ለማገልገል ስራዎች ወደነበነሩበት እንዲመለሱ የራሳቸውን ጥረት እያደረጉ ሲሆን በተለይም ከወልድያ መቀሌ ያለው መንገድ ክፍት መደረጉ በከተማዋ ያለው የንግድ እንቅስቃሴ ሞቅ እንዲል ብሎም ከዚህ ቀደም እጅግ ዋጋቸው ንሮ የነበሩ የእህል ምርቶች ዋጋ እንዲቀንሱ ማስቻሉን መረጃው ያመለክታል። “ባለፈው አንድ ወር ከተማው ትርምስምሱ ወጥቶ ፤ የታክሲ ታሪፍ ፣ መጫኛና ማውረጃ ቦታዎች በውል እስካለመታወቅ ደርሰው ነበር ፤ አሁን ላይ ግን እነዚህ ሁሉ ነገሮች በሚገባ ተስተካክልውና ወደቦታቸው ተመልሰዋል፤ የትራፊክ ፖሊሶችም ወደመደበኛ ስራቸው ገብተው ህግ እያስከበሩ ነው” ብላል። በሌላ በኩልም የትራፊክ ፍሰቱን አውኮ የነበረው የጸጥታ ሁኔታ እንዲሁም የነዳጅ እጥረት በአሁኑ ወቅት መፈታት ስለቻለ ከባጃጅ ጀምሮ ታክሲና ሌሎች የትራንስፖርት አማራጮች ወደስራ ገብተዋል ያለው መረጃው፣ ህብረተሰቡም ይህንን በመገንዘብ ከአላስፈላጊ ውዥንብሮች ራሱን ጠብቆ ሊንቀሳቀስ እንደሚገባም አመልክቷል። የከተማዋ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትም ከተማዋ ላይ በብዛት ተቆልሎ የሚገኘውን ቆሻሻ በማንሳትና የጽዳት ስራዎችን የመንገድ ዳር የማስዋብ ተግባራትን እያከናወነ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን የራሱን ሚና እየተጫወተ መሆኑ መረጃው አመልክቷል። የጁንታው ቡድን ከወህኒ ቤት ፈትቶ የለቀቃቸው የህግ ታራሚዎች በከተማዋ ላይ ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ ስጋት ጋርጠው እንደነበር ያስታወሰው መረጃው ፣ አሁን የክልሉ ፖሊስና መከላከያ ሰራዊት በተቀናጀ ሁኔታ በሰሩት የህግ ማስከበር ስራ ከተማዋ ከእለት እለት መረጋጋት እያሳየች ትገኛለች። “ መንግስት ይሄዳል መንግስት ይመጣል ይህ ደግሞ ምንም አዲስ ነገር የለውም፤ ትግራይ ክልል ላይም የተከሰተው ይኸው ነው፤ አንዳንዶች ግን ለውጡን ለመቀበል ተቸግረዋል፤ አብዛኛው ህዝብ ግን የተቀየረውን መንግስት ደግፎ ሰላሙ ተረጋግጦ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ እየጠየቀ ነው፤ በዚህ መካከል ግን ህወሓት ተመልሶ ክልሉን ያስተዳድራል በማለት በህዝቡ ላይ ጥርጣሬን የሚነዙ አሉ ህብረተሰቡ ይህንን ተረድቶ ወደ ኋላ ሳይሆን ወደፊት እየሄደ ልማቱን ማስቀጠል እንደሚኖርበት አሳስቧል። በተያያዘ ዜና ተቋርጦ የነበረውን የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ ከታህሳስ 21/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለ14 ቀናት እንዲከናወን ብህራዊ ባንክ መወሰኑ ተገልጿል።የገንዘብ ኖቶ ቅየራው ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ እንደሚከናወን ያስታወቀው ባንኩ በብር መቀየሩ ሂደት የነበሩ መመሪያዎችና አሠራሮች እንደተጠበቁ መሆናቸውንም አስታውቋል።ከባንክ በጥሬ ገንዘብ የሚወጣው የገንዘብ መጠን ላይ በተሻሻለው መመሪያ ላይ በተቀመጠው መሠረት ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን ከ100 ሺ እስከ 1ነጥብ 5 ሚሊዮን አሮጌ ብር ያላቸው የመቀየሪያው የጊዜ ገደብ የህግ ማስከበሩ ዘመቻ ከመጀመሩ በፊት የተጠናቀቀ በመሆኑ ብር መቀየር የሚችሉት ከ100ሺህ ብር በታች ያላቸው መሆናቸውን ባንኩ ጠቁሟል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 22/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=38541
[ { "passage": "ከተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ጎን በመቆም የከተማቸውን ሰላም ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የሽሬ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። የህወሓት የጥፋት ቡድን በህዝቡ ላይ በተለያዩ መንገዶች ሲያደርሰው የነበረው ብዙዎቹ ግፍና ጫና በአማርሮ እንደነበር  ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። “ህልውናችሁ የህወሓት ቡድን ብቻ ነው፣ ህወሓት ከሌለ ትግራይና ህዝቧ አይኖርም” በማለት ጁንታው ሲያደናግር እንደነበር  ኢዜአ ያነጋገራቸው የሽሬ ከተማ ተናግረዋል። የህወሓት ታጣቂ ቡድን ይባስ ብሎ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ የትግራይ ህዝብ መከታ እና የልማት አጋር የነበረውን የሰሜን ዕዝ በማጥቃት የጭካኔውን ጥግ ማሳየቱንም ነው ነዋሪዎቹ የጠቀሱት። ድርጊቱ በሃይማኖትም የተወገዘ ከሰብዓዊነትም የወጣ እኩይ ተግባር መሆኑን የሽሬ ከተማ ነዋሪው መልዕከ ሰላም ገብረዋህድ ገብረማርያም ገልጸውልናል። “የሰውን ልጅ ያውም ወገንን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል ለአሞራና ጅብ የሰጠ የህወሓት ቡድን የትግራይ ህዝብ ወኪል ነኝ ቢል ማንም የሚሰማው የለም” ብለዋል። የትግራይ ህዝብ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር እጅ እና ጓንት ሆኖ አብሮ እየበላ፣ ተዛምዶና ተዋልዶ የኖረ ስለመሆኑም አንስተዋል። ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ ሃጂ ሙሃመድ ሙርሃን ሲራጅ፤ “የመከላከያ ሠራዊት የህዝብ ልጅ እንጂ ወራሪም ጠላትም አለመሆኑን የትግራይ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃል” ብለዋል። ሠራዊቱ የአርሶ አደር አዝመራ ሲሰበስብ፣ አንበጣ ሲያባርር እና በብዙ አጋጣሚዎች አብሮነቱን በተግባር ያሳየ የትግራይ ህዝብ ቤተሰብ መሆኑንም ጠቅሰዋል። “ይህንን የህዝብ አጋር የሆነ ሠራዊት ላይ ጥቃት የፈጸመው የህወሓት የጥፋት ቡድን የትግራይ ህዝብ ጠላት መሆኑን በግልጽ አሳይቷል፤ በቁጥጥር ሥር ውሎ በህግ ተጠያቂ መሆን ይኖርበታልም” ብለዋል ሃጂ ሙሃመድ። በጥፋት ተግባር የተሰማራው የህወሓት ቡድን በፈፀመው ወንጀል በህግ ተጠያቂ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ህዝቡ በየአካባቢው ሰላሙን በማረጋገጥ ልማቱን እንዲያስቀጥል ጊዜያዊ አስተዳደር መቋቋሙ ተገቢ መሆኑንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ከጊዜያዊ አስተደደሩ ጋር በመሆን ለከተማው ሰላምና ልማት በጋራ እንደሚሰሩም ነዋሪዎቹ አረጋግጠዋል። በተለይ ወጣቶች ለከተማቸው ብሎም ለአገራቸው ሰላም የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል። በሽሬ ከተማ በአሁኑ ወቅት ሰላማዊ እንቅስቃሴ መኖሩን በስፈራው የተገኘው የኢዜአ ሪፖርተር አረጋግጧል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን የተሾሙት ዶክተር ሙሉ ነጋ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ በህዝብ ምርጫ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ በማቋቋም ላይ ይገኛሉ።", "passage_id": "31e1108910ee665f2c05bf9d09e3d2fc" }, { "passage": "ላለፉት በርካታ ዓመታት በግንባታ ላይ የነበረውና በ2009 መጨረሻ ወራት በተሻለ የግንባታ ደረጃ ጨዋታዎች ማዘጋጀት የጀመረው የትግራይ ስታዲየም በመጨረሻው የግንባታ ደረጃ ደርሷል።በዓመቱ መጀመርያ መቐለ 70 እንደርታ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ከማከናወኑ በፊት መጠነኛ ግንባታዎች የተደረገለት ይህ ስታዲየም በዚህ ወቅት የበርና መስኮት ሥራዎች፣ የድህንነት ካሜራ፣ የሽንት ቤት እና መታጠብያ ቤት ስራዎች እና ሌሎች ተጨማሪ ስራዎች እየተሰሩለት ሲገኙ በቀጣይ ወራትም ሌሎች ግንባታዎች እንደሚኖሩ ከትግራይ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ወ/ሮ ካሕሱ ዜናዊ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል።እንደ ወ/ሮ ካሕሱ ዜናዊ ገለፃ በመጨረሻ ከሚሰሩት የጥላ እና ወንበር ገጠማ ውጪ ያሉት አጠቃላይ ሥራዎች በቀጣይ ወራቶች ለማጠናቀቅ እየተሰራ እንደሆነ ገልፀው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እንደተፈለገው በፍጥነት መሰራት እንዳልተቻለም ተናግረዋል። “እስከ መጨረሻ ላለው ግንባታ ውል አስረናል፤ አሁን ከዚህ ቀደም መጠናቀቅ እየነበረባቸው ያላለቁ ስራዎች በመስራት እንገኛለን። የመፀዳጃ ቤት እና የድህንነት ካሜራ ስራዎች በመሰራት ይገኛሉ። የተቀሩት ስራዎች እንዳይጠናቀቁም የኮሮና ቫይረስ ምክንያት የምንፈልጋቸው እቃዎች በጊዜው ማግኘት አልቻልንም። በቀጣይ የተጀመሩት የመኪና ማቆምያ እና የሦስት በአንድ ትንሿ ስታዲየም እንዲሁም የአጥር ሥራዎች ይሰራሉ። ሌላም ካፍ በሰጠን መመርያ መሰረት ደረጃውን የጠበቀ የመጫወቻ ሜዳ መብራት እንገጥማለን። ” ብለዋል።ወ/ሮ ካሕሱ አክለውም ስታዲየሙ ካፍ ባስቀመጠው መመርያ መሰረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው የመጨረሻው ምዕራፍ A እና B በሚል የግንባታ ምዕራፎች ከፍለው ለመጨረስ በመንቀሳቀስ እንደሚሆኑ ገልፀዋል።በሀገሪቱ ከሚገኙ ምቹ የመጫወቻ ሜዳ ካላቸው ስታዲየሞች አንዱ የሆነው የትግራይ ስታዲየም በዚህ ወቅትም መጠነኛ ጥገናዎች እየተደረጉለት ይገኛሉ።", "passage_id": "d658c53f6ea87b9f09526d9b6b2050b1" }, { "passage": "የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከሾማቸው ኃላፊዎች መካከል አንዱ የሆኑት የመቀሌ ከተማ ከንቲባ አቶ አታኽልቲ ኃይለሥላሴ በከተማዋ የተለያዩ የመሠረታዊ አገልግሎቶች ሥራ መጀመራቸውን ለቢቢሲ ገለጹ።ግጭቱን ተከትሎ ለሳምንታት ተቋርጠው የነበሩት የውሃ፣ የኤሌክትሪክ፣ የጤናና የአየር ትራንስፖርት አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ መጀመራቸውን የገለፁት ከንቲባው፤ የባንክ አገልግሎት ግን በሁለት ቀን ውስጥ የሚያስፈልጋቸውን ዝግጅት አጠናቀው አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ሲሉ ተናግረዋል።ባንኮች ከዚህ ቀደም በወረቀት አገልግሎት የሰጡበት አሰራር ስለነበር እርሱን ወደ ሲስተም ውስጥ እስኪያስገቡ ድረስ የአገልግሎት መስጫ ጊዜው መዘግየቱንም አብራርተዋል።በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በትግራይ ክልል የጸጥታ ኃይሎችና በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት መካከል የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ ለ40 ቀናት ያህል በክልሉ የኤሌትሪክ፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች ተቋርጠው ቆይተዋል። በእነዚህ ጊዜያት በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች የስልክ፣ መብራት፣ ኢንተርኔት ባንክና የመሳሰሉት ለዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ወሳኝ የሆኑ አገልግለቶች ከሥራ ውጪ ሆነው ነበር። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ከአንድ ወር በላይ ከሥራ ገበታቸው ርቀው የነበሩ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ከሰኞ ታህሳስ 05/2013 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ገበታቸው ላይ እንዲገኙ ባቀረበው ጥሪ መሰረት፣ በርካታ ግለሰቦች ወደ ሥራ ገበታቸው የተመለሱ ቢሆኑም በየቢሮው በርካታ የወደሙ ነገሮች በመኖራቸው እነዚያን የማስተካከል እና የመመዝገብ ሥራ እየሰሩ መሆናቸውን ከንቲባው ጨምረው አስታውቀዋል።ከመቀለ አዲስ አበባ በአውሮፕላን ለሚደረግ ጉዞ በኢንተርኔት አማካይነት ትኬት ለመቁረጥ አሁንም እንደማይቻል የተጠየቁት ከንቲባው ከኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ጋር በተያያዘ ይህ መፈጠሩን ገልፀው ድርጅቱ የተለያዩ መፍትሄዎችን እያመቻቸ ነው ብለዋል።ከአዲስ አበባ ትኬት በማስቆረጥ መገልገል እንዲሁም ከእሁድ ጀምሮ ከመቀለ በሚዘረጋ ሲስተም አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።አቶ አታኽልቲ ከከተማዋ ነዋሪ ጋር በየደረጃው እየተወያዩ መሆኑን አመልክተው፣ በየደረጃው የክፍለ ከተማ እና የቀበሌ ምክር ቤቶችንም እያቋቋሙ መሆኑን ተናግረዋል።\"በዋነኛነት የፀጥታው እንዲጠበቅ የምንፈልገው በማኅበረሰቡ ነው\" ያሉት ከንቲባው፣ \"ያ እስኪሆን ድረስ ግን የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ኃይል ከሚመለከተው የመስተዳድር አካል ጋር በመቀናጀት ፀጥታውን በማስከበር ላይ ነው\" ብለዋል።በከተማዋ አልፎ አልፎ ዘረፋ እንደሚስተዋል የተናገሩት ከንቲባው ተጨማሪ የፀጥታ ኃይል የሚመደብበት እና ሕዝቡ ድጋፍ በሚፈልግበት ወቅት መረጃ የሚሰጥበትን መንገድ በማመቻቸት ላይ መሆናቸውን ይናገራሉ።በዋነኛነት ከፀጥታ አካሉ እና በኅብረተሰቡ መካከል እንደ ድልድይ ሆነው እንዲያገለግሉ ከኅብረተሰቡ ውስጥ በሥነ ምግባራቸው የተመሰከረላቸው እና ማኅበረሰቡ እኛን ሊጠብቁን እና ሊከላከሉ ይችላሉ ብሎ ላመነባቸው ወጣቶች በጎ ቃደኞች ምልመላ ተደርጎ ገለጻ በመሰጠት ላይ መሆኑን ገልፀዋል።\"እስካሁን ድረስ በየዕለቱ መልካም የሚባል ለውጥ እየታየ ነው\" የሚሉት ከንቲባው የንግድ ቤቶች፣ የመንግሥት የአገልግሎት ተቋማት እንዲሁም የሰዎች እንቅስቃሴ ወደ መደበኛው ሁኔታ እየተመለሰ መሆኑን አስረድተዋል።በመቀለ ከተማ የመንግሥት ወታደሮች በወሰዱት የሕግ ማስከበር እርምጃ ተገድለዋል ስለተባሉ የከተማዋ ነዋሪዎች የተጠየቁት አቶ አታኽልቲ፣ እርሳቸው ይህንን ኃላፊነት የተረከቡት በቅርቡ መሆኑ እና ከተረከቡበት ቀን አንስቶም ከዝርፊያ እና አለመግባባት ጥቆማዎች ውጪ የሞት መረጃ እንዳልመጣላቸው ጠቅሰው በተሻለ የክልሉን ፀጥታ የሚያስተባብሩ አካላት በጉዳዩ ላይ ምላሽ ቢሰጡ ተገቢ መሆኑን ገልፀዋል።የከተማዋ ነዋሪዎች ስልካችን ይጠለፋል የሚል ስጋት እንዳላቸው በተመለከተ ተጠይቀውም በዚህም ጉዳይም መረጃ እንደሌላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።ባለፈው ጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ የፌደሬሽን ምክር ቤት የክልሉ አስተዳደር እንዲፈርስ ከወሰነ በኋላ የተሰየመው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ሥራው ከጀመረ ቀናት ተቆጥረዋል። ክልሉን ያስተዳድር በነበረው ህወሓትና በፌደራል መንግሥቱ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ለወራት ከዘለቀ በኋላ በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኘው የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ላይ በክልሉ ልዩ ኃይል ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ለሳምንታት የዘለቀ ወታደራዊ ግጭት መካሄዱ ይታወሳል። በዚህም ወቅት የስልክ፣ የመብራትና ሌሎች መሠረታዊ አገልግሎቶች ለሳምንታት ተቋርጠው የቆዩ ሲሆን የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት የክልሉን ዋና ከተማ መቆጣጠሩን ተከትሎ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ክልሉ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እንዲመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን ተገልጿል። በትናንትናው ዕለትም በአዲግራትና ውቅሮ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው የመብራት አገልግሎት መመለሱን የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል በማኅበራዊ ድረገፁ ላይ አስታውቋል።ድርጅቱ አክሎም የሽሬ፣ አክሱምና አድዋ ከተሞች ኃይል እንዲያገኙም እየሰራ መሆኑንና በጥቂት ቀናት ውስጥ የኃይል አቅርቦቱ ሥራ እንደሚጀምር ይጠበቃል።", "passage_id": "0251a9a2d4c931f52476720a5584c9b3" }, { "passage": "በጅግጅጋ ከተማ እና በአጎራባች ዞን ከተሞች በዛሬው እለት አንፃራዊ ሰላም መሰፈኑን የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አስታውቋል፡፡ከዋልታ ጋር ቆይታ ያደረጉት በሚኒስትሩ የኢንዶክትርኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጄነራል መሀመድ ተሰማ የመከላከያ ሰራዊቱ ወደ ጅግጅጋ ከገባ በኋላ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ገልጸዋል፡፡በዛሬው ዕለት ዝርፊያም ሆነ የጥይት ድምፅ በከተማዋ አልተሰማም ያሉት ሜጄር ጄነራሉ አንዳንድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ስራ መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡በከተማዋ የሚገኙ የንግድ ተቋማት ሙሉ በሙሉ ስራ እንዲጀምሩ ከኡጋዞች እና አካባቢ ነዋሪዎች ጋር ውይይት እየተደረገ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ የውሃ፣ መብራትና የመሳሰሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ስራ እንዲጀምሩ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡መከላከያ ሰራዊቱ ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በመሆን ከጅግጅጋ በተጨማሪ በጎዴ፣ ደጋሀቡር እና ሌሎች የዞን ከተሞች መረጋጋት ለማስፈን እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡በተፈጠረው ግጭት ወቅት የተፈፀመው ዝርፊያ የማጣራት እና የመለየት ስራ እየተካሄደ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡   ", "passage_id": "14429e66d9968558d1f28eb2957e8fe2" }, { "passage": "  - የመጀመሪያው 12 ሺህ ኩንታል የእርዳታ ስንዴ ደርሷል  - የተቋረጠው መብራት ትናንትና አገልግሎት ይጀምራል ተብሎ ነበር  - “ከጊዜያዊ የክልሉ አስተዳደር ጋር የማረጋጋት ስራ እየሰራን ነው” (ትዴፓ)   መቀሌ ወደ ቀድሞ ሰላማዊ እንቅስቃሴዋ እየተመለሰች መሆኑን የፈንቅል እና የትግራይ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ትዴፓ) ሃላፊዎች ገለጹ።  ለትግራይ የሰብአዊ ድጋፍ እየቀረበ ሲሆን ከ16 ሚሊየን ብር በላይ የወጣበት የእርዳታ ስንዴና መድኃኒት ወደ ትግራይ እየተጓጓዘ ሲሆን ከነገ ጀምሮ መከፋፈል ይጀምራል ተብሏል። የመጀመሪያው ዙር 12 ሺህ ኩንታል የእርዳታ ስንዴ መቀሌ መግባቱም ተገልጿል።መንግስት ከጥቅምት 24 ምሽት ጀምሮ የህወሃትን አጥፊ ቡድን ለህግ ለማቅረብ የጀመረውን እርምጃ ተከትሎ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የዘለቀችው መቀሌ  በአሁኑ ሰዓት ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እየተመለሰች ነው ተብሏል። ህዝቡ ወደ ውጪ መውጣት ጀምሯል፤  ካፌዎች ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ ነው ሲሉ የፈንቅል ንቅናቄ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይስሃቅ ወልዳይ በመቀሌ የሚገኝ አባላቸውን ጠቅሰው ነግረውናል።  አቶ ይሰሃቅ አክለውም  በቀጣይም ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ፣ የስልክና የባንክ አገልግሎት ይጀመራል መባሉን ተከትሎ ህዝቡ በደስታና በተስፋ መሞላቱን ገልጸዋል። ህዝቡ ከመከላከያ ሰራዊቱና ከጊዜያዊ የክልሉ አስተዳደር ጋር በመሆን የህወሃት የጦር መሳሪያ ማከማቻዎችን፣ የህወሃትን አላማ ለማሳካት ሲላላኩ የነበሩ ባንዳዎችንና ሌሎች የጥፋት ሴራዎችን እያጋለጠ እንደሚገኝ  ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል።ፈንቅል በቀጣይ በጦርነቱ ምክንያት ለችግር የተጋለጡትንና አስቸኳይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የክልሉን ነዋሪዎች ለመደገፍ የእርዳታ ድርጅቶችን አጋር በማድረግ እንደሚሰራ እና ከተማዋን የማረጋጋት ስራ ለመስራት እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።የትዴፓ ሊቀመንበር አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ “ህወሃት አጥፍቶ ለመጥፋት የተነሳ የጥፋትና የጭካኔ ቡድን ነው ያሉ ሲሆን ጁንታው ቡድን ሁሉንም መሰረተ ልማቶች በማፈራረስና በማውደም የትግራይ ህዝብ በጨለማና በችግር እንዲኖር አድርጎት ቆይቷል ብለዋል። ህውሃት ህዝቡን ለ27 ዓመት ያፈነውና የተጨቆነው ሳያንስ አሁን በቅርቡም “ልትወረር ነው ልትወጋ ነው፤ ልታልቅ ነው” የሚል የባሰ ስጋትና ጭንቀት ውስጥ አስገብቶት የቆየ በመሆኑ አሁን በመከላከያ ሰራዊት መረጋጋት እያገኘ መሆኑን መቀሌ የሚገኙ አባሎቻችን ገልፀውልናል ብለዋል።  እንደ እርሳቸው ገለፃ፤ መብራት በመጥፋቱ ወፍጮ የሚባል ነገር አልነበረም፣ አሁንም መብራት፣ የባንክ አገልግሎት ስራ አልጀመረም፣ መድሃኒትም የለም። ሕዝቡ እነዚህን አገልግሎቶች ሳያገኝ በመቆየቱ በችግር ውስጥ በመሆኑ መንግስት እነዚህን መሰረተ ልማቶች በሌሎች የትግራይ አካባቢዎች ስራ እንዳስጀመረ ሁሉ በመቀሌም በፍጥነት ያስጀምራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።ሰሞኑን መቀሌ የደረሰውን የእርዳታ ስንዴም በተመለከተ የተሰራውን ስራ አድንቀው በሴፍትኔት ለሚኖረው አብዛኛው የትግራይ ህዝብም ሆነ ተሯሩጦና ያገኘውን ሰርቶ የእለት ጉርሱን ለሚያገኘው ሁሉ ከፍተኛ ችግር ሆኖ በመቆየቱ ተጨማሪ ድጋፍ ያስፈልጋል ያሉት ዶ/ር አረጋዊ፤ ፓርቲያቸው ከጊዜያዊው የክልሉ አስተዳደር ጋር በመተባበር የማረጋጋትና እርዳታ የሚያገኝበትን መንገድ በመፈለግ በኩል ከፍተኛ ስራ ይሰራል ብለዋል። ", "passage_id": "8264770a72ac46f542d46618bb7b04ec" } ]
2db81eca975adbf5daa09559c11c31c5
c8fbe02c95e54c69ff124b6c97535312
በሬሳ ሳጥን ውስጥ መቆየት ያሸልማል
ጎበዝ የሬሳ ሳጥን ስትመለከቱ ምን ይሰማችኋል። አንዳንዶች ሟች ዘመድ ወዳጆቻቸውን ሊያስቡ ይችላሉ። አንዳንዶች ደግሞ ሞት አጠገባቸው የደረሰ ይመስላቸውም ይሆናል። አይደለም የሬሳ ሳጥን የሬሳ መኪና ሊፍት ሊሰጣቸው ሲቆም የሚሸሹም አጋጥመውኛል። የሚሪላንዱ ቲም ፓርክ ግን ጥንዶች በሬሳ ሳጥን ውስጥ ለበርካታ ሰአታት ሊቆዩ የሚችሉበትን ውድድር እያዘጋጀ ነው። በውድድሩ እንዲሳተፉ የሚጠበቁት ጥንዶች በሬሳ ሳጥን ውስጥ ለ30 ሰአታት እንዲቆዩ ይደረጋል። ውድድሩ የሚካሄድበት ስፍራም በጣም ያልተለመደ ነው። የሬሳ ሳጥኖቹ ስድስት ሰንደቅ አላማዎች የሚደረጉባቸው ሲሆን ፣ፍቅረኞች ፣ ጓደኛሞች፣ የቤተሰብ አባላት፣ወዘተ የሆኑ ስድስት ጥንዶች እንዲሳተፉ የሚደረግበት መሆኑን ዩፒአይ ሰሞኑን የለቀቀው መረጃ ያመለክታል። ጥንዶቹ በቀን ለሰላሳ ሰአት ከፈረንጆቹ መስከረም 27 ቀን ከጠዋቱ 4 ሰአት አንስቶ እስከ መስከረም 28 ቀን 10 ሰአት ድረስ በሬሳ ሳጥኑ ውስጥ መቆየት ይኖርባቸዋል። ጥንዶቹ በቆይታቸው ፓርኩ ስራ ላይ በሚሆንባቸው ሰአቶች በፓርኩ አቅራቢያ ጓደኛ ሊጠብቃቸው ይችላል።ፓርኩ ከተዘጋ በኋላ ግን ብቻቸውን እንዲሆኑ ይደረጋል።ይህ የሆነበት ምክንያት የጨለማው ወቅት አስፈሪ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ የሚኖራቸውን ስሜት ለመፈተን ተፈልጎ ይመስላል። ተወዳዳሪዎቹ በውድድሩ ወቅት ስማርት ስልኮችን እንዲይዙ አይፈቀድላቸውም። ይህ ብቻም አይደለም ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስንም መያዝ አይኖርባቸውም። እነዚህ ቁሳቀስ መያዝ የሚችሉት በተፈቀደላቸው የእረፍት ጊዜ ብቻ ይሆናል። ‹‹ መጸዳጃ ቤት ለመጠቀምና ምግብ ለመብላት ከተፈቀደው ጊዜ ውጪ በተለያየ ምክንያት ከሬሳ ሳጥኑ የወጣ ተወዳዳሪ ከውድድሩ ውጪ እንደሚደረግ ፓርኩ አስጠንቅቋል። ተወዳዳሪዎቹ ሰው ሰራሽ ጭጋግና መብረቅ እንደሚለቀቅባቸውም ተጠቁሟል። የፎቶግራፍ ፍላሾችና ከባድ የአየር ሁኔታ እንዲሚጠብቃቸውም ታውቋል። ይህን ሁሉ ፈተና አልፈው ለውድድሩ ከተያዘው 30 ሰአት በኋላ የሚገኙ ጥንዶች እያንዳንዳቸው 600 ዶላር የሚሸለሙ ይሆናል። አዲስ ዘመን  መስከረም 13/2012 ዘካርያስ
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=19038
[ { "passage": "ታራሚው ሰባት አመት ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኝ ሲሆን በማረሚያ ቤት ቆይታው የአዕምሮ ህመም እንዳለበት ተረጋግጦ ህክምና እየወሰደ እንደነበር አቶ ተመስገን ያስረዳሉ።\n\nግለሰቡ በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ ግንቦት 17፣ 2013 ዓ.ም ሆዴን አመመኝ ብሎ ወደ አርባ ምንጭ ሆስፒታል የመጣ ሲሆን አቶ ተመስገን ከፍተኛ ህመም ላይ እንደነበር ይናገራሉ።\n\nየህክምና ባለሙያዎች በርካታ ጥያቄዎች ሲያቀርቡለት ሚስማሮችን ይውጥ እንደነበር ምላሽ ሰጥቷል። \n\nየታራሚውን ቃል በመስማት በአስቸኳይ ራጅ (ኤክስሬይ) እንዲነሳ የተደረገ ሲሆን ውጤቱም ባዕድ ነገሮች ሆዱ፣ አንጀቱ ውስጥ መኖራቸውን አሳየ።\n\nአቶ ተመስገን እንደሚሉት ባዕድ ነገሮቹ ከመኖራቸውም በላይ ተባብሶ አንጀቱ ሙሉ በሙሉ እየዘጋ መሆኑ ከታዬ በኋላ ቀዶ ህክምና እንዲገባ ተደርጓል። \n\nቀዶ ህክምናው በሚካሄድበት ወቅት ውስጡ ላይ ጨጓራውን ጨምሮ በተለይም የአንጀቱን ክፍል እንደበሳሳውና በጥንቃቄ ከጨጓራውም ከአንጀቱም መለቀም እንደነበረበት አቶ ተመስገን ይገልጻሉ።\n\nበቀዶም ህክምናውም ወደ ሰላሳ የሚሆኑ በአብዛኛው ሚስማሮች፣ አራት የሚሆኑ እስክርቢቶዎች፣ መርፌ፣ የተለያዩ ክሮች፣ ከሚስማርም ወፈር ያለ ብረትም ሆድ እቃው ውስጥ ተገኝቷል።\n\nበቀዶ ህክምናም ከወጣለት በኋላ ኤክስሬይ እንዲነሳ እንደገና የተደረገ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ባዕድ ነገሮቹ መውጣታቸውንም የህክምና ባለሙያዎቹ ማረጋገጥ ችለዋል።\n\nከቀዶ ህክምናው በኋላ ታማሚው በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ቢቢሲ አቶ ተመስገንን የጠዬቀ ሲሆን \"አሁን ያለበት ሁኔታ በጣም በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለው ምናልባት ቀጣይ የሆነ ምርመራ ሊያስፈልግ ይችላል። ምናልባት እየዋጠ የነበረው በጣም ሹልና ስለታም ቁሶች ስለነበር በርካታ የሰውነቱን ክፍሎች ጎድቶ ሊሆን ይችላል።\"ብለዋል \n\nበተለይም ጉሮሮውና ጨጓራ አካባቢ ላይ ቁስለት ፈጥሮ ከነበር ሌሎች ምርመራዎች እንደሚያስፈልግ አፅንኦት የሰጡ ሲሆን ካገገመም በኋላ ሌሎች ተጨማሪ ምርመራዎች እንደሚደረግም ተናግረዋል።\n\nበተጨማሪ ደግሞ የስነ ልቦና ህክምናም እንደሚያስፈልገው ያስረዳሉ። \n\nኃላፊው ለቢቢሲ እንደገለፁት ታራሚው ማረሚያ ቤት ከመግባቱ በፊት የአዕምሮ ህመም ታሪክ እንደሌለው ነው።\n\n ማረሚያ ቤት ከገባ በኋላ የአዕምሮ ህመምተኛ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ከዚህ በፊት ምንም ችግር እንደሌለበት ስራ አስኪያጁ የግለሰቡን ጓደኛ ዋቢ አድርገው ተናግረዋል።\n\n ", "passage_id": "80bda72f7ad4d0a7980fb58d87bf75c7" }, { "passage": "ሬሳ ሳጥኑ ከግብፅ የተዘረፈው በ 'አረብ ስፕሪንግ' አብዮት ወቅት የነበረ ሲሆን ኒው ዮርክ ለሚገኘው ሜትሮፖሊታን ሙዚየም ቅርሱን ሲገዛ፤ ከግብፅ ተዘርፎ የተወሰደ መሆኑን እንዳላወቀ ተገልጿል።\n\n• አሜሪካ ከግብፅ የተሰረቀውን የወርቅ ሬሳ ሳጥን መለሰች\n\n• ላሊበላ፡ የመፍትሔ ያለህ የሚለው ብሔራዊ ቅርስ\n\n• 31 ኢትዮጵያውያን ከኖርዌይ ተባረሩ\n\nሙዚየሙ፤ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ እንደተሠራ የሚገመተውን የሬሳ ሳጥን ለግብፅ ባለሥልጣኖች ማስረከቡ የሚታወስ ነው።\n\nእንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2011 ግብፅ ውስጥ አብዮት ሲቀጣጠል፤ ሬሳ ሳጥኑ ሚንያ ከሚባለው አካባቢ ተዘርፎ፤ በዱባይ በኩል ወደ ጀርመን ከዛም ወደ ፈረንሳይ ተወስዷል።\n\nከዚያም ሀሰተኛ መረጃዎችን በመጠቀም በዓለም አቀፉ የሥነ ጥበብ ደላሎች አማካኝነት አሜሪካ ኒዮርክ ለሚገኘው ሜትሮፖሊታን ሙዚየም መሸጡን ባለሥልጣናት ተናግረዋል።\n\nሬሳ ሳጥኑ ውስጥ ኔደጅማንክህ የተባሉት እና ሔሪሻፍ የተባለው አማልክት ቄስ የደረቀ አስክሬን እንደሚገኝበት ተገልጿል።\n\n'ኔጀማንክህ' በመባል የሚታወቀው እና በወርቅ የተለበጠው የሬሳ ሳጥን ተሰርቆ በሕገ ወጥ መንገድ ከግብፅ የወጣው በአውሮፓዊያኑ 2011 ነበር።\n\nየአስክሬን ሳጥኑ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአንደኛው ክፍለ ዘመን በ4 ሚሊየን ዶላር ከፐርሺያኖች መገዛቱ ተነግሯል። \n\nሙዚየሙ 1971 ሐሰተኛ የውጭ ንግድ ፈቃድ እና ሀሰተኛ መረጃዎች እንደቀረቡለት እና ሳያውቁ እንደተገዛ አቃቤ ሕግ ለአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።\n\nባለሥልጣናቱ እንዳሉት ጥንታዊ የሆነው የአስክሬን ሳጥን በአውሮፓዊያኑ 2011 ተሰርቆ እስከሚወሰድ ድረስ በግብፅ ሚንያ ክልል ከ2000 ዓመታት በፊት ተቀብሮ ነበር የቆየው።\n\n ", "passage_id": "19852daee74f97072a13ef7253a4ee58" }, { "passage": "በኢኳዶር ሕዝብ እጭቅ ባለባት ከተማ ጓያኪውል እጥረቱ ከፍተኛ በመሆኑ መንግሥት 4 ሺህ የሬሳ \"ሳጥኖችን\" (የሬሳ ካርቶኖችን) ለማከፋፈል ተገዷል።\n\nየሬሳ መርማሪዎች ምርመራ ከጨረሱ በኋላ የሬሳ ሳጥን ያለህ እያሉ ሲሆን የቀብር አስፈጻሚዎችም ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተቸግረው ቆይተዋል።\n\nበዚች የኢኳዶር ትልቅ ከተማ ከሦስት ሚሊዮን ሰዎች በላይ ይኖራሉ። በርካታ ሰዎች በኮሮናቫይረስ እየሞቱም ነው። ምንም እንኳ ይፋዊው የሟቾች ቁጥር 180 ብቻ ነው ቢልም ይህ አሐዝ ትክክል እንዳልሆነ ብዙዎች ያምናሉ። \n\nፕሬዝዳንት ሌኒን ሞሬኖ ይህ ቁጥር ተመርምረው ኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸው የሞቱትን ብቻ የሚመለከት ነው ብለዋል። የአገሪቱ በቀን የመመርመር አቅም ዝቅተኛ በመሆኑ ዜጎች በቫይረሱ መያዛቸው ሳይታወቅ እየሞቱ እንደሆነ ይገመታል። \n\nይህቺ ጓያኪውል የምትባለው ከተማ የወደብ ከተማ ስትሆን በሽታው የተነሳባት የኢኳዶር ከተማ ናት። የከተማዋ ነዋሪዎች በየመንገዱ ሬሳ እየተጣለ እንደሆነና መንግሥት ቶሎ ቶሎ ሬሳዎችን እያነሳ እንዲቀብር ሲጠይቁ ነበር። \n\nበርታ ሳሊናስ የተባለች አንዲት ነዋሪ ለቢቢሲ-ስፓኒሽ ክፍል በቅርቡ እንተናገረችው የእህቷ እንዲሁም የእህቷ ባል ሬሳ ከቤት ለማውጣት አራት ቀናት ወስዷል። \n\nለጊዜው በፕላስቲክ አንሶላ ሬሳዎቹን ጠቅልለን ለማቆየት ተገደን ነበር ብላለች ሳሊናስ ለቢቢሲ።\n\nኢኳዶር የሕዝቧ ብዛት 17 ሚሊዮን ሲሆን እስካሁን 3ሺህ 465 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋግጧል። የጓያኪውል ከተማ ከንቲባ ራሳቸው በቫይረሱ ተይዘው የአልጋ ቁራኛ ናቸው።\n\n ", "passage_id": "f2156919f4fa48b5b49e0839e300fb0a" }, { "passage": "ባርኔየር ብራሰልስ ሆነው ባደረጉት ንግግር አሁንም ቢሆን ብሪታንያ ካለ ምንም ሥምምነት መውጣቱን ለማስወገድ የምትችልበት ተስፋ አለ ብለዋል። ይሁንና ብሪታንያ ያሏት አማራጮች ውሱን መሆናቸውን ገልፀዋል። የብሪታንያ ምክር ቤት ቴሬሳ May ከአውሮፓ ህብረት ጋር ለሁለት ዓመታት ያህል ከተነጋገሩ በኋላ የተደረሰውን ሥምምነት ቢቀበል እንደሚያዋጣው ነው ዋናው ተደራዳሪ የመከሩት።እስካሁን ባለው ጊዜ የብሪታንያ ምክር ቤት ሥምምነቱን ሦስት ጊዜ አልተቀበለውም። ቴሬሳ May ለአርተኛ ጊዜ ድምፅ እንዲሰጥበት ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።", "passage_id": "f42a08a02b15c765f4bdc01dc8f0c08d" }, { "passage": "ከዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ ወደ ሰሜን ማዘጋጃ በሚወስደው በላይ ዘለቀ ጎዳና ጥቂት እንደተጓዙ በስተቀኝ በኩል አንድ ደሴት ላይ ሁለት ዓይነት ፖሊሶች ይገኛሉ፡፡መጀመርያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን (ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ) ቀጥሎ ደግሞ የብዙ ኢትዮጵያውያን እንባና ደም የፈሰሰበት የፌዴራል ወንጀል ምርመራ መምሪያ ማዕከል (ማዕከላዊ) ይገኛል፡፡በኢትዮጵያ ከ40 ለሚበልጡ ዓመታት የሰቆቃ ማዕከል ሆኖ የቆየው ማዕከላዊ በመጨረሻ ሰሞኑን ሙዚየም እንደሚሆን ተነግሯል፡፡የኢሕአዴግ ሊቀመንበር አቶ ኃይለ ማርያም ዳሳለኝ ከኢሕአዴግ ብሔራዊ ድርጅቶች ሊቃነ መናበርት ጋር በጋራ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ፣ ማዕከላዊ ከዚህ በኋላ የምርመራ ማቆያ ሥፍራ ሆኖ እንደማይቀጥልና ሙዚየም ሆኖ እንደሚያገለግል ተናግረዋል፡፡የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ኮማንደር መብራቱ ተስፋ ሚካኤል ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ማዕከላዊ ሙዚየም እንደሚሆን በይፋ ሲነገር ቢሰማም ነገር ግን እስካሁን የወረደ መመርያ የለም፡፡ አሁንም የተጠርጣሪዎች ማቆያ ሆኖ እያገለገለ ነው ብለዋል፡፡‹‹የቢሮ ጥበት ስላጋጠመው የወንጀል ምርመራ ክፍል ባምቢስ አባባቢ፣ የፎረንሲክ ክፍሉ ደግሞ ኢምግሬሽን አካባቢ ቢሮ ተከፍቶላቸው እየሠሩ ነው፡፡ ማዕከላዊ ግን አሁንም ማቆያ ሆኖ እያገለገለ ነው፤›› ሲሉ ኮማንደር መብራቱ ገልጸዋል፡፡ በሁለተኛው የጣሊያን ወረራ ወቅት በጣሊያን ዲዛይነሮችና ኮንትራክተሮች የተገነባው ማዕከላዊ፣ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ‹‹የፖሊስ ሠራዊት ልዩ ምርመራ›› ተብሎ ይጠራ እንደነበር መዛግብት ይገልጻሉ፡፡ማዕከላዊ ገብተው በሚደረግባቸው ምርመራ ስቃይ በቀመሱ የመሬት ሥሪት ባለሙያዎች ግምት፣ የማዕከላዊ ጠቅላላ የቦታ ስፋት ስምንት ሺሕ ካሬ ሜትር ይጠጋል፡፡በማዕከላዊ የተካሄደው ግንባታ በተለይ በጣሊያን ዘመን የተካሄደው ድንጋይ በድንጋይ ሲሆን፣ በውስጡ የምርመራና የማጎሪያ ክፍሎችን ያጨቀ ነው፡፡ አቶ ግርማይ አብርሃ ሐምሌ 2002 ዓ.ም. ‹‹የሚያነቡ እግሮች›› በሚል ርዕስ ባሳተሙት መጽሐፍ ላይ እንደገለጹት፣ እስረኞች ወዳሉበት ግቢ ለመድረስ ሦስት ቢሮዎችን ማለፍ ግድ ይላል፡፡ ሦስተኛውን በር አቋርጦ የገባ ሰው ሁለት የተከለሉ ግቢዎች መኖራቸውን ይመለከታል፡፡ የላይኛውና የታችኛው ግቢ እየተባሉ የሚጠሩት እነዚህ እስር ቤቶች በድምሩ 21 ክፍሎች የያዙ ናቸው፡፡የላይኛው ግቢ ከ800 በላይ እስረኞች ይታጎሩበት የነበረ ባለ 12 ክፍሎች ግቢ ነው፡፡ በአንድ ጊዜ ስምንት ሰዎች ብቻ የሚያስተናግዱ አራት መፀዳጃ ቤቶችና ሁለት ሰዎች የሚይዝ መታጠቢያ ቤት ያለው እስር ቤት ነው፡፡ የታችኛው ግቢ ደግሞ በ1971 ዓ.ም. በላይኛው ግቢ ቅርፅ የተሠራና በ1973 ዓ.ም. ከላዩ ላይ ተጨማሪ ቤት የተገነባለት ዘጠኝ ክፍሎች ያሉት ድፍን ግቢ ነው፡፡በማዕከላዊ እያንዳንዱ የእስረኛ ክፍል ባለብረት መዝጊያና ባለወንፊት የብረት መስኮት እንዲኖው ሆኖ የተሠራ ነው፡፡ በላይኛው ግቢ የእንጨት ንጣፍ ካላቸው ከአንድ እስከ ስድስት ቁጥር በስቀተር ሌሎቹ የሲሚንቶ ወለል ያላቸው መሆኑን አቶ ግርማይ በመጽሐፋቸው አስፍረዋል፡፡ በተለይ በ1970ዎቹ መጨረሻ አካባቢ በወታደራዊው መንግሥት ትዕዛዝ የመንግሥት ኮንትራክተሮች የነበሩት ለአብነት ሕንፃ ኮንስትራክሽን፣ ባቱ ኮንስትራክሽን፣ ኪቤአድና የመሳሰሉት ተቋማት በጋራ ተጨማሪ ክፍሎችን እንደገነቡ ሪፖርተር ያሰባሰበው መረጃ ይጠቁማል፡፡ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በማዕከላዊ ምርመራ እየተደረገበት አራት ወራት ከ26 ቀናት ቆይቷል፡፡ ጋዜጠኛ ጌታቸው ያየውን ለሪፖርተር ሲገልጽ፣ ማዕከላዊ በዋናነት ሦስት ክፍሎች አሉት፡፡ የመጀመርያው ሳይቤሪያ ይባላል፡፡ ሳይቤሪያ በምርመራ ወቅት የሚቆይበት ሥፍራ ሲሆን፣ ከመሬት በታች ዝቅ ያሉ ክፍሎች አሉት፡፡ ሳይቤሪያ የተባለበት ምክንያት ተጠርጣሪዎች በብዛት ሲገቡ የሚሞቅ፣ የተመርማሪዎች ቁጥር ሲያንስ ደግሞ እጅግ የሚቀዘቅዝ ሥፍራ በመሆኑ ነው፡፡  ሳይቤሪያ ዘጠኝ ክፍሎች ሲኖሩት፣ ክፍል ቁጥር ስምንት በአራት ተከፍሎ አንድ ሰው ለብቻው የሚታሰርበት ጨለማ ቤት ነው፡፡‹‹ሳይቤሪያ ዘግናኙ ክፍል ሲሆን፣ ቁጥር ስምንት ደግሞ ለሕይወት አደገኛ ነው፤›› ሲል ጋዜጠኛ ጌታቸው ይገልጸዋል፡፡ ጋዜጠኛ ጌታቸው እንደሚለው ማዕከላዊ ሰው በሕይወት እወጣለሁ ብሎ የማያስብበት እጅግ አደገኛ ሥፍራ ነው፡፡ ይህ ነው እንግዲህ በስምንት ሺሕ ካሬ ሜትር ያህል ቦታ ላይ አርፎ፣ በጣሊያን ኮንትራክተሮች መሠረቱ ተጥሎ፣ በወታደራዊ መንግሥትና በኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት ማሻሻያ ተደርጎበት የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ሕይወት የበላው፣ አሰቃቂ አካል ጉዳት ያደረሰው፣ በአሰቃቂ ድብደባና ማሰቃያ ዘዴዎች የኢትዮጵያውያንን ልብ የሰበረ የሰቆቃ ማዕከል፡፡አቶ ግርማይ አብረሃ በመጋቢት 2006 ዓ.ም. ‹‹ከደርግ ማኅደር›› በሚል ርዕስ ባሳተሙት መጽሐፍ ላይ ደግሞ የማሰቃያ ዘዴዎችን ተንትነዋል፡፡ በተለይ በአለንጋ፣ በኤሌክትሪክ ሽቦ፣ በአጠና፣ የውስጥ እግር እስከሚበጣጠቅ ድረስ መግረፍ፣ በተበከለ ውኃ መድፈቅ፣ አስሮና አንጠልጥሎ ማቆየት፣ እግር በጩቤ እየቆራረጡ እንዲነፈርቅ ማድረግ፣ እንቅልፍ መከልከል፣ በወንድ ብልት ውኃ ወይም አሸዋ የተሞላ ጠርሙስ ማንጠልጠል፣ በሴቶችም ላይ እጅግ አሰቃቂ ኢሰብዓዊ ጉዳት ማድረስ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ክፍሎቹ በተለያዩ ተውሳኮች ከመሞላታቸው በላይ ብርሃንና  ንፋስ የማይገባባቸው በመሆኑ ሞትን እንደሚያስናፍቅ ይናገራሉ፡፡ በእነዚህ ዘግናኝ ማሰቃያዎች በወታደራዊውም ሆነ በኢሕአዴግ የሥልጣን ዘመን በርካታ ሰቆቃ መድረሱ በተለያዩ መዛግብቶች ከመመዝገቡ ባሻገር ቋሚ በርካታ ምስክርነት ሰጪዎችም አሉ፡፡ይህ ማዕከላዊ ተቋም በመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች እንዲዘጋና ወደ ሙዚየምነት እንዲዛወር መወሰኑ ብዙኃኑን ያስደሰተ ቢሆንም፣ ይህንኑ አሰቃቂ የምርመራ ዘይቤ በሌሎች ነባርና አዳዲስ ምርመራ ቦታዎች ላለመካሄዱ መንግሥት በይፋ ዋስትና እንዲሰጥ የሚጠይቁም በርካታ ናቸው፡፡ጋዜጠኛ ጌታቸው እንደሚያሳስበው ይህ አደገኛ ቦታ በንጉሡ፣ በወታደራዊውና በኢሕአዴግ ዘመን የዜጎች የሰቆቃ ቦታ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ሌላው ትውልድ እንዲያየው መደረጉ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ድብደባና ስቃይ በሌሎችም እስር ቤቶች የሚታይ በመሆኑ እንደሚያሳስበው ይናገራል፡፡ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ታሪካዊ ዳራውንና የዲዛይኑን ሁኔታ ለመረዳት በርካታ የታሪክ ምሁራንና አርክቴክቶችን ለማነጋገር ቢሞከርም፣ የተሟላ መረጃ አልተገኝም፡፡ አስፈሪውና ዘግናኙ ማዕከላዊ እንደ ታላቅ ወንድሙ የአዲስ አበባ ወህኒ ቤት መዘጋቱ መልካም ሆኖ በሌሎች ቦታዎች እንዳያቆጠቁጥ የሚሠጉ በርካቶች ናቸው፡፡ በአዲስ አበባ የማዕከላዊን ያህል አሰቃቂ የነበረው፣ የማዕከላዊ ታላቅ የሚባለው የአዲስ አበባ ወህኒ ቤት (ከርቸሌ) ነው፡፡ከርቸሌ ከጣሊያን ወረራ በፊት የተገነባ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመርያው መደበኛ እስር ቤት ነው፡፡ አቶ ግርማይ በመጽሐፋቸው እንዳብራሩት፣ ከርቸሌ ለመጀመርያ ጊዜ ሕጋዊ መሠረት ይዞ እንዲሠራና ተጠሪነቱ ለአገር ግዛት ሚኒስቴር እንዲሆን የተደረገው በ1936 ዓ.ም. ነው፡፡ከርቸሌ በአጠቃላይ 400 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ስፋት የነበረው ሲሆን፣ በውስጡ የብዙ ኢትዮጵያውያንን ልብ የሰበረው ‹‹ዓለም በቃኝ›› ጎልቶ ይነሳል፡፡ ከዓለም በቃኝ በተጨማሪ የቀጠሮ ክልል፣ የፍርደኛ ክልል፣ የፍትሐ ብሔር ክልልና የሴቶች ክልል  ይገኛሉ፡፡ እስረኞች ከሚገኙባቸው ከእነዚህ ክልሎች በተጨማሪ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፣ የሙስሊሞች መስጊድና የተለያዩ አገልግሎት መስጫዎች አሉ፡፡ከእነዚህ ሁሉ ዘግናኙ ዓለም በቃኝ የተሰኘው ማሰቃያ ሲሆን፣ በዚህ ቦታ በርካታ ተስፈኞች ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ የአካልና የመንፈስ ስብራትም የደረሰባቸው በርካቶች ናቸው፡፡ይህ አዲስ አበባ ወህኒ ቤት ያለበት ቦታ ለአፍሪካ ኅብረት ማስፋፊያ ያስፈልጋል ተብሎ እስር ቤቱ ሙሉ ለሙሉ ተነስቷል፡፡ በውስጡ የነበሩት እስረኞችም ወደ ተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ተዘዋውረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በምርመራ ስም የሚደረግ ኢሰብዓዊ የምርመራ ዘዴ እንዲቀር፣ ዕውቀትን መሠረት ያደረገ ለሰብዓዊ መብቶች ትኩረት የሚሰጥ ሥልት ተግባራዊ እንዲደረግ የሚጠይቁ በርካቶች እንደ መሆናቸው፣ መንግሥት ሌሎች ማሰቃያዎችን ይዝጋ፣ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ምርመራ ይጀመር ይላሉ፡፡ እርግጥ ሆኖ ማዕከላዊ ከሦስት መንግሥታት በኋላ ሙዚየም የሚሆን ከሆነ ማን ያስተዳድረዋል? የሚለው ጥያቄ ለአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብረ ፃዲቅ ሐሰሳ በሪፖርተር ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር፡፡እሳቸውም ሙዚየም የመሆኑን ዜና ከሚዲያ እንደሰሙ፣ ሙዚየሙ በፌዴራል ይተዳደር? ወይስ በአዲስ አበባ? የሚለው ጉዳይ በቀጣይ የሚታይ እንደሚሆን በመግለጽ ዝርዝሩን ለመናገር እንደሚቸገሩ ገልጸዋል፡፡ ", "passage_id": "5d5ccf0679c9d495497a4f29354bbb93" } ]
1565812f10a6db02c5f4ee53d3073b05
5e414daaaf06110cffcbf1e860041df3
የኮሮና ቫይረስ የፈጠረው የእግር ኳሱ ዓለም ፈተና
በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሚያንቀሳቅሰው የስፖርት ዓለም ላይ በመጣው ፈተና ምክንያት በእጅጉ እየተጎዱ ካሉት ዘርፎች መካከል እግር ኳስ አንዱ ሆኗል።በርካቶችን በአንድነት በማሰባሰብና በአንድ ስፍራ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾች ከሚገኙባቸው መዝናኛዎች መካከል አንዱ የሆነው ስፖርት ለቫይረሱ እጅግ አጋላጭ ሁኔታን እንደሚፈጥር ታምኖበታል።በመሆኑም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በቅድሚያ ያለ ደጋፊ እንዲካሄድ ቀጥሎም ሙሉ ለሙሉ ሊቋረጥ ችሏል።ይህ ደግሞ እንደሌላው የኢኮኖሚ ዘርፍ ሁሉ ኪሳራን እንዲያስተናግድ አስገድዶታል። እአአ በ2018 የስፖርቱ ዘርፍ 471 ቢሊዮን ዶላር ነበር ያስመዘገበው፤ ይህም እአአ ከ2011 ጋር ሲነጻጸር በ45 በመቶ ጭማሪ አሳይቶ ነበር።አሁን ግን የስፖርቱ ሰንሰለት በኮቪድ 19 ምክንያት ተቋርጧል፤ ስፖርተኞች፣ ክለቦች፣ ሊጎች፣ ጨዋታዎችንና ውድድሮችን የሚያሰራጩ መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ሌሎች የስፖርቱ አካላት እንደ ድሮ መንቀሳቀስ አልቻሉም።ከዚህ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው ደግሞ ተወዳጁ የእግር ኳስ ስፖርት ቢሆንም፤ በዚህ ዓመት ገቢው ይጨምራል በሚል ቢጠበቅም ከተላላፊው ቫይረስ ጋር በተያያዘ ውድድሮች በመቋረጣቸው ገቢው በእጅጉ እያሽቆለቆለ ይገኛል። በዚህ ስፖርት እያንዳንዶቹ ክለቦች የየራሳቸው የሆነ መለያና አሰራር ቢኖራቸውም ዋነኛ ገቢያቸውን የሚያገኙት ከሶስት ምንጮች ነው።ይኸውም ከመገናኛ ብዙሃን የስርጭት መብት፣ ከስፖንሰርና ማስታወቂያዎች እንዲሁም በጨዋታ ወቅት ከስታዲየም የትኬት ሽያጭ ከሚገኝ ገቢ ነው።10 በሚደርሱ ሊጎች ያለው ቁጥራዊ መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነም ክለቦቹ ከሚዲያ መብት ብቻ ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያገኛሉ።ይህም ከአጠቃላይ ገቢያቸው 60 ከመቶ የሚሸፍን መሆኑን ወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም በዘገባው ያመላክታል። ተወዳጁና በዓለም ላይ ከፍተኛ ተመልካች ያለው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ባለፈው ዓመት አዲስ በገባው (ለሶስት ዓመታት) ኮንትራት 12 ቢሊየን ዶላር ከሚዲያ መብት ብቻ ለመሰብሰብ አቅዶ ነበር።ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ ይህንን ማሳካት የሚቻል አይመስልም፤ ምክንያቱም ከተቋረጠ ሁለት ወራትን እንኳን ሳያስቆጥር ክለቦቹ ከ60 እስከ 150 ሚሊየን ዶላር ኪሳራ ማስተናገዳቸውን እያስታወቁ ነው። እንደ ዴይሊሜይል ዘገባ ከሆነም ከቴሌቪዝን መብት ከሚገኝ ገቢ ብቻ እያንዳንዱ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ክለብ 750 ሚሊየን ፓውንድ ያጣል። በዚህም ምክንያት ክለቦቹ ከተጫዋችና አሰልጣኞች ቡድን ባሻገር የሚገኙ ሰራተኞቻቸውን በጊዜያዊነት እያሰናበቱ ነው።የተጫዋቾቻቸውን ደመወዝ ለመክፈል በመቸገራቸውም አንዳንዶች ግማሽ ክፍያ ሌሎች ደግሞ የተወሰነ ቅናሽ በማድረግ እንደሚከፍሉ እያሳወቁ ነው።በተያዘው ወር መጀመሪያ ላይም ሊጉ ሃያዎቹ ክለቦች ከተጫዋቾች ደመወዝ 30 በመቶ ለመቀነስ የተጫዋቾቻቸውን ስምምነት እንዲጠይቁ ማሳወቁን ጎል ዶት ኮም አስነብቧል።በስምምነቱ ማንቸስተር ዩናይትድ የመጀመሪያው ክለብ ሲሆን ተቀናሽ የሚሆነው ገንዘብ ቫይረሱን ለመከላከል ለሚደረገው ትግል ገቢ እንዲደረግም ወስነዋል። የፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ማህበር በበኩሉ ክለቦች አቅሙ ካላቸው ሙሉ ክፍያ ለተጫዋቾች እንዲሰጡ፤ ካልቻሉ ግን የክለቦቻቸውን የፋይናንስ ኪሳራ እንዲጋሩ ለአባላቱ ጥሪውን አቅርቧል። ይህ በዓለም የመጣው አስቸጋሪ ሁኔታ በኢትዮጵያም መስተናገዱ አይቀርም።በተለይ የሊጉ ክለቦች በአብዛኛው በመንግስት የሚደጎሙ እንደመሆኑ ጠንካራ ፋይናንስ ያላቸው ክለቦች ያቃታቸውን ይወጡታል ማለት አስቸጋሪ ነው።በእንግሊዝና በሌሎች ሊጎች የታየው የደመወዝ ቅነሳም በኢትዮጵያ ክለቦችም እየታየ ይገኛል፡፡ የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደግሞ በዚህ ረገድ ቀዳሚው ሆኗል።ፕሪምየር ሊጉን ዘንድሮ የተቀላቀለው ክለቡ በኮሮና ቫይረስ በተቋረጠው ሊግ ምክንያት ሊፈጠር የሚችለውን የፋይናንስ ጫና ለመቀነስ በማሰብ ተጫዋቾች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ላለመውሰድ መወሰናቸውን ሶከር ኢትዮጵያ በዘገባው አስነብቧል። በቀጣይም የክለቦችና ተጫዋቾች ገቢ በምን ዓይነት ሁኔታ ይቀጥላል የሚለው የወቅቱ ፈተና እንደሚሆን ነው የሚጠበቀው፡፡አዲስ ዘመን ሚያዝያ 10/2012
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=30594
[ { "passage": "ዘመናዊ ስፖርቶች በኢትዮጵያ መታወቅና መዘውተር ከጀመሩ አንድ ምዕተ ዓመት የሚጠጋ እድሜ ማስቆጠራቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ። ይሁንና ከረጅም እድሜያቸው ጋር ሲነፃፀር እድገታቸውና ለህብረተሰቡ እያበረከቱ ያለው ፋይዳ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ይገለጻል። ለዚህም የስፖርቱ ዘርፍ የአደረጃጀትና አመራር፤ የአቅም ውስንነት ማለትም የሠለጠነ የሰው ኃይል፤ ዘመናዊና ሳይንሳዊ ሥልጠናና ማዕከላት፤ የስፖርት ፋሲሊቲ ግብዓትና የፋይናንስ እጥረት እንዲሁም የአመለካከትና አቅጣጫ ችግሮች በዋና ዋና ምክንያትነት ይጠቀሳሉ። የአገሪቱ ስፖርት ልማት የትኩረት አቅጣጫም ሰፊውን የህብረተሰብ ክፍል በስፖርት በማሳተፍ ምርጥ ስፖርተኞችን ማፍራትን ታሳቢ ያደረገ አልነበረም። ከዚህ ይልቅ በተለያየ መንገድ በራሳቸው ጥረት ብቅ ያሉትን በማሰባሰብ በውድድር ስፖርቶች ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴ ማካሄድን ምርጫው ያደረገ ነው። ምርጥና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት የሚያስችል ሰፊ መሰረት ስላልነበረውም ውጤቱ በየጊዜው ብልጭ ድርግም ሲል ቆይቷል። ለዚህም ህብረተሰቡ በስፖርት የሚያደርገው ተሳትፎ ውስን መሆን፤ የትምህርት ቤቶች ስፖርት መዳከም፤ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ትጥቅና መሳሪያዎች በበቂ ሁኔታ አለመኖር፤የሠለጠኑ ባለሙያዎች የሥልጠና ሥርዓትና ማዕከላት አለመኖር በምክንያትነት ይጠቀሳሉ። እነዚህን የአገሪቱ ስፖርት ልማት ሁነኛ ችግሮች ለማስወገድና በአዲስ አስተሳሰብና አቅጣጫ ለመምራትም የዘርፉን አደረጃጀት የተጠናከረ፤ በፖሊሲ አቅጣጫ የሚመራና የህዝብ መሰረት ያለው ለማድረግ ፖሊሲ ተቀርጿል። ፖሊሲውም የትኩረት\nአቅጣጫዎች ተቀምጠውለት፤ የማስፈፀሚያ ስልቶች ተዘጋጅተውለትና አስፈፃሚ አካላት ተዋቅረውለት ሥራ ላይ ከዋለ ሁለት አስርት ዓመታትን አስቆጥሯል። በእነዚህ ሁለት አስርት ዓመታትም ምንም እንኳን ሙሉ በሙሉ ውጤታማ አፈፃፀም አልነበረውም ብሎ መናገር ባያስደፍርም ስኬታማ ውጤት አምጥቷል ማለት ፈፅሞ አይቻልም። አፈፃፀሙ በተለይ በአትሌቲክሱ ውጤታማ ከመሆን ውጪ በእግር ኳሱ ማሳየት አልቻለም። እንደሚታወቀው እግር ኳስ እጅግ ተወዳጅ ስፖርት ከሆነባቸው አገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት። ዜጎቿም ለእግር ኳስ ያላቸው ፍቅርና ክብር እጅጉን የላቀና ከመዝናኛነቱም አልፎ ከዕለት ኑሯቸው ጋር የተቆራኘ ነው። አገሪቱ የክለባቸውን ጨዋታ ለመታደም የምሽትና የሌት ብርድ የቀን ሃሩር ሳይበግራቸው በስታዲየም በሮች ፊት ለፊት ረዥም ሰልፎችን ከሚሰለፉት ደጋፊዎች ባሻገር የምርጥ ተጫዎቾች ባለቤትም ነች። ክልጅነት ጀምሮ\nበየመንደሩ ባዶ እግራቸውን ኳስ የሚጫወቱ፤ በልበ ሙሉነት እርሳቸውን ለስፖርቱ ፍቅር አሳልፈው የሰጡ፤ ለእግር ኳስ ፍቅር የሚታመኑ ተጫዋቾች ሀብታምም ነች። በዚህ መልክ እግር ኳስ በፍቅር በሚወደድባት አገር የአገሪቱ እግር ኳስ ልማት ሲነፃፀር ግን እዚህ ግባ ተብሎ የሚወራ ታሪክና ውጤት የለውም። የእግር ኳስ ልማት አጀንዳም ፈር ሳይዝና በእቅድ፣ በሥልጠናና በባለሙያ መደገፍ አቅቶት በእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ብቻ ባለበት እየረገጠ ዓመታትን ማሳለፉንም የዘርፉ ባለሙያዎቹ ይመሰክራሉ። ከሰሞኑ ታዲያ ይህን የአገሪቱን እግር ኳስ ልማት ከተኛበት የሚቀሰቅስ ተግባር እውን ሆኗል። የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር ፊፋ ለምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ የሚውለውን ክፍለ አህጉራዊ ልማት ቢሮ በአዲስ አበባ ከፍቶ አስመርቋል። በሥነ ሥርዓቱ ላይም የስፖርት ኮሚሽነር ርስቱ ይርዳው፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው እንዲሁም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን አባል ሀገራት ተወካዮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተውበታል። የአዲስ አበባ የፊፋ ክፍለ አህጉራዊ የልማት ቢሮ በሴኔጋልና በደቡብ አፍሪካ ከከፈታቸው ክፍለ አህጉራዊ ቢሮዎች ቀጥሎ ሦስተኛው ሲሆን፤ ቢሮው ካሉት የሥራ ክፍሎች በተጨማሪ የእግር ኳስ ልማት ኃላፊ፣ የፕሮጀክት አስተባባሪ፣ የቴክኒክ፣ የዳኞች እንዲሁም የፋይናንስና ሥነ ምግባር ኦፊሰሮች ክፍሎችንም አካቷል። ከአንድ ዓመት በፊት ሊከፈት ታቅዶ በተለያዩ ምክንያቶች እውን ሳይሆን የቆየው ይህ ቢሮ፤ የቀጠናው እግር ኳስ አባል አገራት ከፊፋ ጋር በቅርበት በመስራት የእግር ኳስ ልማት ስትራቴጂዎቻቸውንና ግቦቻቸውን እንዲያሳኩ ማድረግ ዋነኛው ዓላማው ያደረገ ነው። አዲስ ዘመን\nጋዜጣ መሰል አህጉራዊ ቢሮዎች በኢትዮጵያ መከፈት ለአገሪቱ እግር ኳስ ልማት ምን አስተዋፆኦ ያደርጋል? ከዚህ ተጠቃሚ ለመሆንስ ምን ተግባራት መከናወን አለባቸው? የሚሉትን ጥያቄዎች በማንሳት ባለሙያዎችን አነጋግሯል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምሀር ረዳት ፕሮፌሰር ወንድሙ ታደሰ እንደሚገልፁት፤ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን (ፊፋ) ዋነኛ ተልዕኮ የእግር ኳስ ልማት ነው። ፊፋ የሚከተለው የስፖርት ልማት ፕሮግራም በታዳጊዎች ላይ መሰረቱን ያደርጋል፤ በእድሜ የተከፋፈለ የልማት ሥልጠና ሥርዓት ይከተላል። ይህን ዓላማ የሚያስፈፅሙለትም የየአህጉሪቱ ብሄራዊ ፌዴሬሽኖች ናቸው። የአንድ አገር የስፖርት ልማትም እንደ እድገት ደረጃው በዚህ አግባብ መራመድና መሥራት አለበት። ከዚህ ውጪ ውጤታማ መሆን አይቻለውም። «ይህ በሆነበት እኛ የምንከተለው የእግር ኳስ ልማት የለም፤ አለ ከተባለውም፤የት ነው ያለው» ሲሉ የሚጠይቁት ረዳት ፐሮፌሰር ወንድሙ፤ ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት በ1987 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ልማትን የሚመለከቱ ጥናቶች ቢሠሩም፣ ዛሬም ድረስ በዚህ ላይ ተመስርቶ የሚሠራ የለም›› ይላሉ። «የአገሪቱ ስፖርት ፖሊሲ የስፖርት ልማትን ለማገዝ የተቀመረ ቢሆንም፤ ፖሊሲውን በአግባቡ የሚያስፈፅም፤ ካልሆነም እንዴት ነው ተግባራዊ የሚደረገው ብሎ የሚጠይቅ የለም፤ በዚህም ምክንያት በአገሪቱ የስፖርት ልማት አልተሠራበትም»ይላሉ። እንደ ረዳት ፐሮፌሰሩ ገለፃ፤ በአገሪቱ የስፖርት ልማት አጀንዳ ተዘርግቶ የተሠራ ሥራ የለም። የስፖርት ልማት አስፈፃሚዎችም ቢሆኑ ቢሮ ተቀምጠው የሚሠሩ ናቸው። በስፖርት ልማት ታዳጊዎች እየሠለጠኑ ነው ቢባልም፣ ታች ተወርዶ ሲቃኝ ተጨባጭ ውጤት አይታይም። ስፖርት አካዳሚዎችን የሚመግቡ ማዕከላት ከክልል እስክ ወረዳ ድረስ የሉም። ብሄራዊ አካዳሚውን የሚቀላቀሉትም ቢሆኑ በስፖርት ልማት አጀንዳ ተቀርፀው የመጡ አይደሉም። ይልቅስ በየክልሉ በሚካሄዱ ውድድሮች ላይ ተመርጠው የሚቀላቀሉ ናቸው። በአገሪቱ የስፖርት ልማት አጀንዳ ተዘርግቶ ባለመሠራቱም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወቅታዊ ሁኔታ፤ ክለቦቻችን በአግባቡ ማዋቀር አለመቻላችን የአገሪቱ እግር ኳስ በተለይ የፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብርም በሳይንሳዊ ቀመር ሳይሆን በግምት የሚሠራባት መሆኑን መመልከት በተጨማሪነት በቂ ምስክር ይሰጣል።«ይህ በሆነበት የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር ፊፋ ለምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ የሚውለውን ክፍለ አህጉራዊ ልማት ቢሮ መክፈቱ አቅጣጫዎችን ለማመላከት፤ በተለይም የአገሪቱን የስፖርት ፖሊሲ ተከትለን እንድንጓዝ ከፍተኛ እገዛ ይኖረዋል»የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ከዚህም ባሻገር የገንዘብ ድጋፍ በተለይም ለተጨዋች፤ ለአሠልጣኝ ለክለቦች የቴክኒክ ድጋፍ ለማግኘት ሁነኛ ፋይዳ እንዳለው ያመላክታሉ። ይህን መልካም እድል ለመጠቀም ቀድሞ መገኘት እንደሚያስፈልግ የሚያስገነዝቡት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤«ቢሮውን ዓይን ዓይኑን ማየት ሳይሆን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ማቀድ፤ ከአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የታዳጊዎች ልማት አጀንዳን መዘጋጀትና በጊዜ ቀመር የተዋቀረ እቅድ በመንደፍ መድረስ የሚፈለግበት ደረጃ ማስቀመጥ የግድ ይላል›› ሲሉም ይጠቁማሉ። በአገሪቱ የስፖርት ፖሊሲ ላይ የስፖርት ልማት አጃንዳዎች በአግባቡ የተመላከቱ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ለውጥ ማምጣት ከተፈለገ የፖሊሲውን የልማት አጀንዳዎች በመቃኘት ይህን ለማስፈፀም መጣር እንደሚያስፈልግ ያስገነዝባሉ። አስፈፃሚ አካላትን በሚመለክትም «በኢትዮጵያ የስፖርት ልማት አጀንዳ የማነው» የሚለው የታወቀ አልመሰለኝም የሚሉት ረዳት ፐሮፌሰሩ፤ የስፖርት ልማት አጀንዳ ቁጥር አንድ የመንግሥት ስለመሆኑ ይገልፃሉ። እንደ ረዳት ፐሮፌሰሩ ገለፃ፣ መንግሥት በስፖርቱ ልማት በሚኖረው ተሳትፎ ላይ የአመለካከት ችግሮች ይስተዋላሉ። የተማረውም ያልተማረው መንግሥት ስፖርት አካባቢ መድረስ የለበትም ሲሉ ይደመጣል። ይሁንና ለአብነት የስፖርት ማዘውተሪያ፤ ስታዲየም፣ አካዳሚ፣ ጅምናዚየም የሚገነባው በፌዴሬሽኖች ሳይሆን በመንግሥት ነው። ይህ እንደመሆኑ መንግሥት በስፖርት ልማት ዋነኛ ባለድርሻ ነው። ይህ እንደመሆኑም\nመንግሥት የበኩሉን ኃላፊነት ይበልጥ መወጣት ይኖርበታል። የኮተቤ ሜትሮ ፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምህር አቶ ሲያምረኝ በርሄ፤ ኢትዮጵያ የስፖርት ልማት ፖሊሲ እንዳላት ጠቅሰው፤ ይህን በማስፈፀም ረገድ በተለይ በእግር ኳሱ ልማት ምንም አለመሥራቱን ይስማሙበታል። እንደ አቶ ሲያምረኝ ገለፃ፤ በእግር ኳስ ልማት ታዳጊዎችን በመስፈርት በመመልመልና አሠልጣኞችን በማሠልጠን የማሠልጠኛ መመሪያ በማዘጋጀት ከሳይንስ ጋር ለመጓዝ ተሞክሯል። ይሁንና ስፖርቱን በበላይነት ከሚመሩ አስፈፃሚዎች ትኩረት አለመስጠትና የእግር ኳስ ልማቱን የውድድር ሥራ አድርጎ ብቻ ከማሰብ በመነጨ የአመለካከት ችግር የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት አልተቻለም። ከታዳጊዎች በተጓዳኝ በወጣቶች ደረጃም የተከናወነ ተግባር የለም። ይህ በሆነበት ውጤት መጠበቅ የማይታሰብ ነው። ለዚህም ውጤቱ በቂ ምስክር ይሰጣል። ይህ በሆነበት ፊፋ አህጉራዊ ቢሮውን በአዲስ አበባ የመክፈቱ አንድ ምክንያት«የአገሪቱ ስፖርት ልማት በተለይም እግር ኳሱን በበላይነት የሚመሩ አካላት መንግሥትን ጨምሮ ተኝታችኋል ተነሱ የሚል ደውል የሚያሰማ ነው» የሚሉት አቶ ሲያምረኝ፤ ዓላማውም ማነቃቃት፤ ማበረታታትና አገሪቱ ያላትን እምቅ አቅም እንድትጠቀም መቀስቀስ መሆኑን ነው ያመላከቱት። ከዚህ በተጓዷኝ «ኢትዮጵያ በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ካፍ መስራችነትም ሆነ በዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር ፊፋ አባልነት ለስፖርቱ እድገት ካበረከተችው አስተዋፅኦ አኳያ ለአገሪቱ እውቅና እንደመስጠት እረዳዋለሁ» የሚሉት አቶ ሲያምረኝ፤ እርምጃውም አገሪቱ ያላትን እምቅ አቅም ከግምት ያስገባ መሆኑንም ይገልፃሉ።«አገሪቱ ያላትን እምቅ አቅም ለመጠቀም የተወሰኑ ማስተካከያዎችና ድጋፎች ከተደረጉ ኢትዮጵያ በእግር ኳስ ስፖርት ከታወቁ አገራት ተርታ መሰለፍ እንደምትችል የሚያሳዩ ምልክቶች አሉ» የሚሉ አቶ ሲያምረኝ፤ በዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር /ፊፋ/ አህጉራዊ ቢሮውን በመዲናዋ መክፈትም ተቋሙ በአገሪቱ ላይ የፀና እምነት እንዳለው ምስክር የሚሰጥ መሆኑንም እንደሚያስገነዝብ ይጠቅሳሉ። በአህጉራዊው ቢሮ መከፈትም፤ የሥልጠና የማማከርና ሌሎች ድጋፎችን ለማግኘት እድል የሚሰጥ በመሆኑም አገሪቱ ይህን መልካም አጋጣሚ ሳይውል ሳያድር መጠቀም እንዳለባት የሚያስገነዝቡት አቶ ሲያመረኝ፤ ይህን «ከአገሪቱ ለውጥ ጋር የመጣ መልካም እድል በቀላሉ ከማሳልፍ ይልቅ ከፌዴሬሽን ጀምሮ ትምህርት ሚኒስቴርም በትምህርት ቤቶች እንዲሁም ሌሎችን ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ጥረት ማድረግ አለባቸው ነው»ያሉት። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፤ የክፍለ አህጉራዊው ቢሮ መከፈት ተቋሙ ከኢትዮጵያ፣ ከምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ አባል አገራት ጋር ያለውን ቀረቤታ ይበልጥ ለማሳደግ በእግር ኳስ ልማት የተሻሉ ሥራዎች እንዲሠሩ መልካም አጋጣሚን እንደሚፈጥር ያረጋግጣሉ። ፌዴሬሽኑ በአሁኑ\nወቅት በአገሪቷ እግር ኳስ ውስጥ ያሉ ችግሮችን በመለየትና ጥናት በማድረግ ላይ መሆኑን ያስገነዘቡት ፕሬዚዳንቱ፤ የተቋሙ ቢሮ በመዲናዋ መኖርም በጅምር ላይ ያሉ የእግር ኳስ ልማት ሥራዎችን ዳር ለማድረስ አንድ እርምጃ ስለመሆኑ ነው ያስረዱት። በምርቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር ፊፋ ፕሬዚዳንት ጂያን ኢንፋንቲኖ እንደገለጹት፤ ተቋሙ የዓለም እግር ኳስ እድገት የተሟላ እንዲሆን የአፍሪካን እግር ኳስ ማሳደግ ወሳኝ ነው፤ ለዚህም ፊፋ ከአፍሪካ ጋር በትብብር እየሠራ ነው። እ.ኤ.አ በ2016 ፊፋ በጀመረው «የፊፋ ፎርዋርድ የልማት መርሃ ግብር» እግር ኳስ በመላው ዓለም እንዲያድግ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። አዲስ አበባ የተከፈተው ለምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ የሚውለው ክፍለ አህጉራዊ ልማት ቢሮም የእዚሁ ሥራ አንዱ ማሳያ ነው። የአፍሪካ አገራት ላለፉት ሁለት ዓመታት የቀረጿቸው የእግር ልማት ፕሮጀክቶች ለአህጉሪቷ የእግር ኳስ እድገት ወሳኝ ሚና እንደሚኖራቸው ያመላከቱት ፕሬዚዳንቱ፤ ተቋማቸውም ለፕሮጀክቶቹ ስኬት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡ ከቢሮው መከፈት በተጓዳኝ ተቋማቸው በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ያለውን ሙስና ለመዋጋት፣ በስታዲየሞች ጸጥታና ደህንነት እንዲሁም በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እግር ኳስን ለማስፋፋት የሚያስችል የጋራ ስምምነት ከአፍሪካ ህብረት ጋር መፈራረሙን አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን የካቲት 12/2011ታምራት ተስፋዬ", "passage_id": "c2d2198d9c85d19c123d2d37a8ac2709" }, { "passage": "የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የዓለም ወቅታዊው ሁኔታ፤ የሰውን ልጅ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ፣ አስተሳሰብና ልማድ እንዲቀየር ምክንያት ሆኗል፡፡ በዚህ መንስኤነትም አካላዊና አእምሯዊ ጤናን ከመጠበቅና ከማዝናናት ባለፈ ከፍተኛ ገንዘብ የሚዘዋወርበት ስፖርትም በቀድሞ ቁመናው ላይ እንዳይገኝ ሆኗል፡፡ በዘርፉ በዓለም ደረጃ እአአ በ2011 ከተገኘው ገቢ በ45 በመቶ የላቀ ትርፍ ከሁለት ዓመታት በፊት መገኘቱን ወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም ያመላክታል፡፡ ይህ እአአ በ2018 የተገኘው 471ቢሊዮን ዶላር በዚህ ዓመት በእጅጉ ሊያድግ እንደሚችልም አመላካች ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ባልተጠበቀ ሁኔታ ተከስቶ መላውን ዓለም ባዳረሰው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ምክንያት እንቅስቃሴው ሊገታ ችሏል፡፡ እንደ ሌላው ዓለም ሁሉ የኢትዮጵያ ስፖርትም መዳከም አሳይቷል፡፡ በእንቅስቃሴው መገታት በስፖርተኞች፣ ክለቦች፣ ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ አወዳዳሪዎችና ሌሎች ባለድርሻዎች መካከል የነበረው ሰንሰለት በቫይረሱ ተጠቅቷል፡፡ በጥቂት ውድድሮች ሽልማት በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብና የውጭ ምንዛሪ ለሀገር ያስገኙ ከነበሩ አትሌቶች፤ ‹‹ነገ ያልፍልኛል›› በሚል እሳቤ ከኑሮ ጋር እስከሚታገሉት ጀማሪ ስፖርተኞች ድረስ የጉዳቱ ሰለባ ሆነዋል፡፡ ከአቅማቸው በላይ የሆኑትም ከበጎ ፈቃደኞች ተደጓሚ ሆነዋል፡፡ የስፖርት ማህበራትም ከውድድሮችና ስፖንሰሮች ማግኘት የሚገባቸውን ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡ ይህንን አሳሳቢ ሁኔታ\nያጤነው የኢፌዴሪ ስፖርት\nኮሚሽንም ወረርሽኙ በዘርፉ\nላይ ያሳደረውን ጫና\nበማመዛዘን እንዲሁም በተወሰነ\nመልኩ የሚያገግምበትን ሁኔታ\nለማመቻቸት የሚረዳ ሥራ\nበማከናወን ላይ ይገኛል፡፡\nበጉዳዩ ላይ ለአዲስ\nዘመን ጋዜጣ ማብራሪያ\nየሰጡት ምክትል ኮሚሽነር\nዱቤ ጂሎ፤ ከኮሮና\nቫይረስ ወረርሽኝ ጋር\nበተያያዘ እንደ ንግድ ሁሉ ስፖርትም ጉዳት ያስተናገደ ዘርፍ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ስፖርተኞች ቀድሞ የሚያገኙትን ገቢ ማግኘት ባለመቻላቸው፣ ክለቦች የመፍረስ አደጋ የተደቀነባቸው በመሆኑ መሰል ጉዳዮችን ከግምት በማስገባት ከመንግሥት ማገገሚያ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ እንዲለቀቅ ጥያቄ መቅረቡንም ይገልጻሉ፡፡ ኮሚሽኑ ለመንግሥት ያቀረበው\nየዳሰሳ ጥናት ‹‹ኮሮና\nቫይረስ በስፖርቱ ልማት\nላይ ያሳደረው ተጽእኖ\nየማገገሚያ ስልት›› የሚል\nሲሆን፤ ጥናቱ የተከናወነውም\nየሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ\nበመቀመር ጭምር ነው፡፡\nበዚህም እንግሊዝ፣ ናይጄሪያ፣\nኬንያ እና የመሳሰሉት\nሀገራት በወረርሽኙ ወቅት\nለማገገሚያ የተጠቀሙትን ስልት\nለመዳሰስ መሞከሩንም አመላክተዋል፡፡\nየኢትዮጵያ ስፖርት ሕዝባዊ\nመሠረት ያለው እንደመሆኑ\nበስፖንሰርና በስታዲየም ገቢ\nከሚያገኙት ገንዘብ ባለፈ\nለከተማ ክለብ ስፖርተኞች\nደመወዝ የሚከፈለው ከሕዝብ\nከሚሰበሰበው ታክስ ነው፡፡\nይህም ማለት አብዛኛውን\nገንዘብ የሚሸፍነው መንግሥት\nነው፡፡ ከወቅቱ ነባራዊ\nሁኔታ ጋር በተያያዘ\nውድድሮችን ማካሄድ ባለመቻሉ\nበዘርፉ ያለው  እንቅስቃሴ\nአስቸጋሪ ሆኗል፡፡ ይህንን ጊዜ ለመሻገርም ከስፖርት ማህበራቱ ጋር በመተባበር ስትራቴጂ በመንደፍና ጥያቄውን ለመንግሥት በማቅረብ ኮሚሽኑ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ ጥናቱ ስፖርተኞች በምን መልክ ወደሥልጠናና ውድድር ይመለሱ፣ እንዴትስ ፈቃድ ይሰጣቸው የሚለውን በመነሻነት መያዙንም ነው ምክትል ኮሚሽነሩ የሚጠቅሱት:: እንደ ኮሚሽንም ሀገር አቀፍ የስፖርት ማህበራቱ መርሃ ግብራቸውን እንዲያቀርቡም መመሪያ ተላልፏል፡፡ በኢትዮጵያ ስፖርት የሚንቀሳቀሰው የገንዘብ መጠን በውል አይታወቅም፡፡ ይህም መሰል ጥናቶች ላይ ተጽእኖ ማሳደሩ አይቀርም፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ፌዴሬሽን ይብዛም ይነስም በስፖንሰር የሚያገኙት ገቢ ይኖራል፤ ሆኖም በዓመት ይህን ያህል ይገኛል የሚለው በውል አይታወቅም፡፡ ለአብነት ያህል የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኢንተርናሽናል እና የሀገር ውስጥ ስፖንሰሮች ቢኖሩትም ከወቅታዊው ሁኔታ ጋር በተያያዘ በትክክል ለማወቅ የሚቻልበት ሁኔታ አዳጋች ነው፡፡ ቢሆንም ቅድመ በግምቶችን በማስቀመጥ ጥናቱ መከናወኑንም ነው ምክትል ኮሚሽነሩ ያስረዱት፡፡ የኮሮና ወረርሽኝ የስፖርቱን\nዘርፍ ሙሉ በሙሉ\nጎድቷል፤ እንቅስቃሴዎችንና ውድድሮችን\nገድቧል፡፡ በስፖርተኞችና ሀገራትም\nላይ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ\nችግሮችን አስከትሏል፤ ይህም\nአደጋ ነው፡፡ ነገር\nግን ይህ ጊዜ\nያልፋል በሚል ተስፋ\nሁሉም በአንድነት እየተጠባበቀ\nይገኛል፡፡ መንግሥትም ሁኔታዎችን\nበማገናዘብ ምላሽ ይሰጣል\nየሚል ተስፋ አለ፤\nይህን ወቅት በመሻገርም\nስፖርቱን ወደነበረበት የስፖርት\nቤተሰቡም ወደ ተመልካችነቱ\nየሚመለስበት ጊዜ ሩቅ\nአይሆንም፡፡ በመሆኑም ይህንን\nጊዜ በጋራ ለማለፍ\nራስን ከቫይረሱ መጠበቅ\nእንዲሁም የአካል ብቃት\nእንቅስቃሴ በማድረግ እንዲቆዩም\nምክትል ኮሚሽነሩ መልዕክታቸውን\nአስተላልፈዋል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 15/2012ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "238790f6962b11e39b556fdfe12c1add" }, { "passage": "የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በመላው ዓለም በሚካሄዱ ስፖርታዊ ዉድድሮችና እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አሳድሯል፡፡\nበቫይረሱ ምክንያት እግርኳስን ጨምሮ ስፖርታዊ ዉድድሮች እና ልምምዶች በመቋረጣቸው ስፖርተኞች በቤታቸው ለመቀመጥ ተገደዋል፡፡ በተለይ ደግሞ በርካታ ተከታታዮች ያሉት ተወዳጁ የእግር ኳስ ስፖርት ኮቪድ-19 ጠባሳውን ያሳረፈበት ዋነኛው ዘርፍ ነው፡፡\nበኢትዮጵያም በየትኛውም ሊግ የሚካሄዱ ዉድድሮች ከተቋረጡ ሰነባብተዋል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሳምንት በፊት ባወጣው መግለጫ፣ የ2012 ሁሉም የሊግ ውድድሮች እንዲሰረዙ ዉሳኔ ማሳለፉ ደግሞ ግማሽ ያክል ዉድድሮች የሚቀሩት ስፖርቱ በያዝነው ዓመት ፍሬ አልባ ሆኖ እንዲቋጭ ግድ ብሏል፤ ሻምፒዮንም ወራጅም የለም፡፡ የተጫዋቾች ልፋትና ክለቦች ያፈሰሱት ገንዘብም መና ቀርቷል፡፡\nይህ እንዳለ ሆኖ ቀጣይ ውድድር እስኪጀመር ስፖርተኞች፣ በተለይም እግር ኳስ ተጫዋቾች ጊዜያቸውን እንዴት ያሳልፋሉ የሚለው አንዱ ዋነኛ ጥያቄ ነው፡፡\nይህ ወቅት በመላው ዓለም ለሚገኙ ስፖርተኞች እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ ሜዳ ላይ ልምምድ መስራት እና መቧረቅ የለመዱ ስፖርተኞች ቤታቸው እንዲቀመጡ ሲገደዱ ለከፍተኛ ስነልቦናዊ እና ስነ-አካላዊ ችግር እንደሚጋለጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ ተጽእኖው በእግር ኳስ ተጫዋቾች ላይ ደግሞ ይበልጥ እንደሚበረታ የማንችስተር ዩናይትድ ክለብ የቀድሞ ሳይኮሎጂስት ቢል ቤስዊክ፣ በኮሮና ምክንያት ዉድድሮች ከመቋረጣቸው ጋር በተያያዘ በሰጡት ሙያዊ አስተያየት፣ ተናግረዋል፡፡\nበመሆኑም እግር ኳስ ተጫዋቾች በቤት ዉስጥ በግልም ይሁን ከቤተሰብ ጋር የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ቢያደርጉ ወደ ዉድድር በሚመለሱበት ወቅት እንዳይቸገሩ ይረዳቸዋል፡፡ ወትሮውንም በታታሪነቱ የሚታወቀው የቅዱስ ጊዮርጊሱ ተጫዋች አብዱልከሪም መሀመድ በዚሁ ጉዳይ ለአል ዐይን አማርኛ ሀሳቡን እና ልምዱን አካፍሏል፡፡\nተጫዋቹ በአሁኑ ጊዜ፣ ሊጉ ከተቋረጠ በኋላ ከካምፕ ወጥቶ፣ በሲዳማ ዞን ወንዶ ገነት ከቤተሰቡ ጋር ጊዜውን በማሳለፍ ላይ ይገኛል፡፡ ባለበት ሆኖ ታዲያ የተለመደውን ስፖርታዊ እንቅስቃሴውን ከማድረግ አልተቆጠበም፡፡ ጊቢዉን ለስፖርት አመቺ በሆነ መልኩ አሰናድቶ፣ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን በማሟላት በየእለቱ ስፖርት መስራቱን ቀጥሏል፡፡\nሜዳ ላይ ካለው ጽናት እና ፍጥነቱን እንደጠበቀ ሙሉ ጨዋታውን ያለድካም ከማድረጉ ጋር በተያያዘ “ተርሚኔተር” በሚል ቅጽል ስሙም የሚታወቀው አብዱልከሪም ለብዙ ተጫዋቾች ተምሳሌት እንደሚሆን የቡድን አጋሮቹም ይመሰክራሉ፡፡\nተጫዋቹ ከአል ዐይን አማርኛ ጋር በስልክ ባደረገው ቆይታ ተጫዋቾች በቤታቸው በሚገኙበት በዚህ ጊዜ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ጤናቸውን ከመጠበቅ ባለፈ ለቀጣይ የዉድድር ጊዜ በአካል እና በስነልቦና ዝግጁ እንዲሆኑ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡ ከስፖርት ባለፈ ቤት ዉስጥ ከቤተሰባቸው ጋር የተለያዩ ስራዎችን ቢሰሩ ስነልቦናዊ ደህንነታቸውን ሊጠብቁ እንደሚችሉም የራሱን ተሞክሮ በማንሳት ይመክራል፡፡\nበበጎ አድራጎት ስራም ላይ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኘው አብዱልከሪም መሀመድ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ከ3 ሳምንታት በፊት በትውልድ ስፍራው ወንዶ ገነት ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ በማድረግ ፈሳሽ ሳሙና፣ ሳኒታይዘር እና ለእጅ መታጠቢያነት የሚያገለግሉ የዉሃ ሮቶዎችን አድሏል፡፡\nአብዱልከሪም አሁን ከሚጫወትበት የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በተጨማሪ በክለብ ደረጃ ለኢትዮጵያ ቡና፣ ሲዳማ ቡና እና ሀዋሳ ከነማ ክለቦች በፕሮፌሽናል ተጫዋችነት ማገልገሉ ይታወቃል፡፡\nተጫዋቹ ካሸነፋቸው ሽልማቶች መካከል በ2010 ዓ.ም የውድድር ዘመን በምርጥ ተጫዋችነት ዘርፍ ያሸነፈው የኢቢሲ አዋርድ እንዲሁም በዚያው ዓመት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የዓመቱ የፕሪሚየር ሊጉ ምርጥ ተጫዋችነት ሽልማቶች ይጠቀሳሉ፡፡\n", "passage_id": "44f2797da0dc6d1d422aa0aef77c3e10" }, { "passage": "ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 30/2012 ዓ.ም (አብመድ) የኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፋዊ ስጋት መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ካወጀበት ጊዜ ጀምሮ መዝናኛው በጥቁር መጋረጃ ተጠቅልሏል፡፡ የዓለምን ቀልብ በመሳብ የሚታወቁት ስፖርታዊ ውድድሮች አንዳንዶቹ ወደ ሚቀጥለው ዓመት ሲሸጋገሩ አንደንዶቹ ደግሞ ባሉበት ተሰርዘዋል፡፡ የሁለቱም ዕጣ ፈንታ ያልገጠማቸው ገና ውሳኔ ላይ ያልደረሱ ውድድሮችም አሉ፡፡በአውሮፓ ከሚገኙ አምስት ታላላቅ ሊጎች መካከል የፈረንሳይ ሊግ አንድ ውድድር ተቋርጧል፡፡ የሀገሪቱ እግር ኳስ የበላይ ጠባቂ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መክሮ ደረሰኩበት ባለው ውሳኔ መሠረት የዓመቱ የሊጉን አሸናፊ፣ በቻምፒዮንስና አውሮፓ ሊጎች ተሳታፊ ቡድኖችን፣ ወደ ታችኛው ሊግ የሚወርዱና በዓለም አቀፉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ሰለባ የሆነው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቆሞ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ከሞሰኑ ደግሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውድድሩ አሸናፊም ሳይኖረው በውድድሩ ሂደት የተለወጠ ነገር ሳይኖር ጨዋታዎች ሙሉ ለሙሉ እንዲቋረጡ ውሳኔ ላይ ደርሷል፡፡ ይህ ውሳኔ ደግሞ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡", "passage_id": "ce5be75e01ec86dc98e4319c1f071491" }, { "passage": "የኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ 19) በዓለም ላይ በከፍተኛ ፍጥነት መሰራጨቱን ተከትሎ የሁሉም ዓለም አቀፍ የስፖርት መርሐግብሮች እንዲቋረጡ አድርጓቸዋል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ተከትሎ የስፖርቱ ዓለም ካለፉት ሁለት ወራት በላይ ተቋርጦ እንዲቆይ አድርጎታል። የውድድሮቸ መቋረጥና መርሐ ግብሮች መራዘማቸውን ተከትሎ የስፖርቱን ኢንዱስትሪ ክፉኛ እንደጎዳው ዓለም አቀፍ ጥናቶች ከወዲሁ ያመላክታሉ። ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በመቆማቸው ምክንያት የሚደርሰውን ኪሳራ በመጠኑም ቢሆን ለማዳን ውድድሮችን በዝግ ስታዲየም ማድረግ አማራጭ ተደርጓል። ከቫይረሱ ስጋት ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆን ባይችሉም ታላላቆቹን አውሮፓ እግር ኳስ ሊጎች ጨምሮ አንዳንድ አገራትም ስፖርታዊ ውድድሮቻቸውን ከሰሞኑ አስጀምረዋል። ውድድሮችን በዝግ ስቴድየሞች በማድረግ የውድድር ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት መርሐግብሮቻቸውን ለማጠናቀቅ ጨዋታዎችን እያደረጉ ይገኛሉ። \nበአውሮፓ እግር ኳስ ሊጎች የተወሰደውን መፍትሔ የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተግባራዊ ሊያደርገው እንደሚችል ቢቢሲ ዘግቧል። የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሰባስቲያን ኮዬ ፤ የአትሌቲክስ ስፖርት ሲመለስ በባዶ ሜዳዎች ሊካሄድ እንደሚችል ማስጠንቀቃቸውን መሰረት ያደረገው ዘገባው፤ «በታላላቆቹን አውሮፓ እግር ኳስ ሊጎች ከሰሞኑ እንደተመለከትነው ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮችም በቅርቡ ሊመለሱ ይችላሉ »ሲል አስነብቧል የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቲክስ ስፖርት ሲመለስ በባዶ ሜዳዎች ሊካሄዱ እንደሚችሉ ከማስገንዘብ በተጨማሪ ፤ውድድሮች ስለሚመለሱባቸው ሁኔታዎች በተመለከተ ሃሳብ መስጠታቸውን አመልከቷል። በዚሁ ላይም «ዓመታዊው የዳይመንድ ሊግ እንዲሁም የተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች ሁኔታዎች ከተገመገሙ በኋላ በመጪው ነሐሴ አጋማሽ እንዲካሄዱ እቅድ ተይዟል። በነሐሴ እንዲካሄዱ እቅድ የተያዘላቸው አስራ አንዱ የተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች በዝግ ሜዳ ይሆናሉ » ሲሉ መናገራቸውን ጽፏል። \nቢቢሲ በዘገባው ፕሬዚዳንቱ በተለይ ጌምስ ለተባለው ድረገፅ በሰጡት ማብራሪያ «በመጪዎቹ ቅርብ ጊዜያት የሚካሄዱ ውድድሮች ላይ ለደህንነት ስንል ልንደራደርባቸው የማይገቡ ጉዳዮች አሉ። በተደጋጋሚ በጤና ባለሙያዎችም ሆኑ በአካባቢው ማህበረሰብ የተነገረንን ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ያስገባና ችላ የማንላቸውም ናቸው። ሁላችንም ቢሆን ይህ የረዥም ጊዜ መፍትሔ ነው ብለን አናስብም። ስፖርታዊ ውድድሮች ያለታዳሚ ይጠፋሉ። ሆኖም በአሁኑ ወቅት የአትሌቲክስ ውድድሮችን ለመመለስ መክፈል ያለብን መስዋዕትነት ይሄ ነው» ሲሉ መናገራቸውን በዘገባው አካቷል።አዲስ ዘመን ግንቦት 11/2012ዳንኤል ዘነበ", "passage_id": "7880ef43a81ab343f810d54366a6043d" } ]
bf1158e325e73dfeefb6e109f63d436e
e10eb64dc6d136aecb7fc5a3a35fdabe
የስፖርት ማኅብረተሰቡ- ማኅበራዊ ኃላፊነት የመወጣት ሰብዓዊው መንገድ
የዓለም ሕዝብ ሁሉ ጭንቀትና ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከትንሽ እስከ ትልቅ፣ ከሀብታም እስከ ድሃ፣ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ዋነኛ ትኩረቱ እንዲሆን ካስገደደ ስድስት ወራት ተቆጠሩ፡፡ የቫይረሱ ስርጭት በእነዚህ ወራት እንደ ሰደድ እሳት ያላዳረሰው የዓለም ክፍል ስለመኖሩ አጠራጣሪ ሆኗል፡፡ ሀገራት ዓለም በጋራ የገጠማት ጦርነት በድል ለመወጣት የሚያስችል መፍትሄ ለማበጀት ጥረት ማድረጉን ተያይዘውታል። የቫይረሱ ማንነትና፣ ምንነት ፈጣን መፍትሄ ማበጀት የሚያስችል አልሆነም። በእርግጥም የኮሮና ወረርሽኝ በዓለም ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ መስተጋብር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ብቻ ነውን? በእኔ እሳቤ አዎንታዊ እንዳለው መካድ ንፍግነት ይሆናል! የኮሮና ቫይረስ ዓለምን እንደጎዳት ባለበት ደረጃ ባይሆንም በጎ መልኮችን ይዞ መምጣቱን በድፍረት መናገር ይገባል። ዓለም ከገባችበት የጋራ ማዕጥ ለመውጣት ከሚደረግ ጉዞ የሚቀዳው «ሰውነትን» ያስቀደሙ ደጋግ እጆችን፤ ኅብረተሰቡ ከተጋረጠበት አደጋ ለመታደግ ሰብአዊነትን አርግዘው የሚወለዱ ድጋፎችን በዘመነ ኮሮና ሊበረክቱ ችለዋል። በዓለም አራቱም አቅጣጫዎች ሰብአዊነትን ባስቀደመ መልኩ ሲደረጉና እየተደረጉ ያሉ ድጋፎችን ብሶባቸው ታዝበናል። በተለያዩ መስኮች እንፋሎቱ ሳይበርድ የቀጠለው ልግስና ከስፖርቱ መስክ ያለውን ሁኔታ መመልከቱ ይበጃል። ስፖርት ሰላም፣ ፍቅር፣ የአብሮነትና የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የወንድማማችነት ልዩ መገለጫ ነው። ስፖርት ዘር፣ ሃይማኖት፣ ፆታና ቀለምን አይለይም። በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ የስፖርታዊ እንቅስቃሴ አስኳል ሃሳብ ወዳጅነትና መተሳሰብ መሆኑ ይታወቃል። በታሪክ ገጾች እንደሰፈረውም በሰው ልጅ ታሪክ ባጋጠሙ በጎም ሆኑ መጥፎ ክስተቶች ስፖርት በአጋርነት ተሳትፏል። ስፖርታዊ ክንዋኔዎች ሰላምንና አንድነትን የሚሰብኩ እንደመሆናቸው በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በመግባት ሚናቸውን ሲወጡም ኖረዋል። ስፖርት ሰብአዊነትን ያነገበ የልግስና ማዕድ መሆኑን ዘመነ ኮሮና በተጨባጭ አሳይቶናል። የቫይረሱ ስጋትነት በዓለም አቀፉ የጤና ተቋም ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ፤ ውድድሮችን ከማቋረጥና ከመሰረዝ ባለፈ የስፖርቱ ተዋንያን በተናጥልም ሆነ በተቋማዊ ደረጃ አበርክቷቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። በእግር ኳስ ጠቢብነታቸው ዓለም የመሰከረላቸው ተጫዋቾችና ስመ ጥር አሰልጣኞችም፤ ለደጋፊዎቻቸው መልእክት ከማስተላለፍና ገንዘብ ከመለገስ ባሻገር ሆቴሎቻቸውን ለህክምና አገልግሎት እንዲውሉም ጭምር መስጠታቸው ይታወሳል። በሀገራችን በተመሳሳይ የስፖርቱ ለጋስነትና ሰብአዊነት መገለጫ ያደረጉ ተግባራት ዛሬም እንደ ትናንቱ በዘመነ ኮሮና ከነበረው ብሶበት አለኝታነቱን እያሳየ ይገኛል። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ከታወቀበት ከመጋቢት መጀመሪያ አንስቶ በስፖርቱ ማህበረሰብ ጠንካራ እንቅስቃሴ በማድረግ አጋርነቱን በፈጠነና በቀደመ መልኩ ያሳየው። በስፖርት ቤተሰቡ በቡድንም ሆነ በተናጠል ለወረርሽኙ መከላከያ የሚውል የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ ከመንግስት ጎን በመቆም ወገን ላይ የተደቀነውን አደጋ በአንድነት ለመመከት ህዝባዊነቱን ማሳየት ችሏል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የድጋፍ መሠባሰብ ጥሪ ተከትሎ የስፖርቱ ማህበረሰብ ተሳትፎ በተጠናከረ መልኩ መቀጠሉን ለመታዘብ ችለናል። ከመከላከያ ስፖርት ክለብ አካባቢ የተሰማው ዜና ይሄንኑ ያስረዳል። የመከላከያ ስፖርት ክለብ አዋቂ ወንዶች እና ሴቶች እግር ኳስ ቡድን እና ኮቺንግ አባላቱ 211 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል። የስፖርት ክለቡ ለኮረና ቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር እንዲውል በከተማ አስተዳደሩ ለተቋቋመ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ኮሚቴ ነበር ገንዘቡን ያስረከበው። «የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባቀረበው የድጋፍ ጥሪ መሠረት የኮቪድ -19 ለመግታት በሚደረገው ርብርብ የበኩላችንን ለመወጣት ነው» ሲሉ ነበር የስፖርት ክለቡ አባላት በስፖርቱን ማህበረሰብ ዘንድ ሰብአዊነትን ባስቀደመ መልኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እየተደረገ ያለውን ተሳትፎ ያመላከቱት። የሀገር ዳር ድንበር ህልውና ከሆነው የስፖርቱ ክለብ በተመሳሳይ፤ በስፖርቱ የሰብአዊነት ልግስናው ተጠናክሮ የመቀጠሉን ሁኔታ የጠዋት ጎህ አትሌቶች የልማት መረዳጃ ተግባርም ይነሳል። በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ድል በማድረግ የሀገራችንን ሰንደቅ አላማ በማወለብለብ ስሟና ዝናዋን ከፍ ባደረጉት አትሌቶች የተቋቋመው ዕድሩ 200 ሺህ ብር ድጋፍ በማድረግ አጋርነታቸውን አስመስክረዋል፡፡ የአትሌቶቹ የመረዳጃ ዕድር አባላት አስተባባሪዎች ኮማንደር አትሌት ጌጤ ዋሚ፣ አትሌት ተስፋዬ ቶላ፣ አሰልጣኝ ንጋቱ ወርቁ ፣ ዶክተር በዛብህ ወልዴ እና ወይዘሮ አይናዲስ ተስፋዬ ድጋፍ ለማድረግ የመሻታቸውን ሚስጥር በጋራ እንዲህ አጋርተዋል። «ዓለም ብሎም ሀገራችን በጭንቅ ተውጣለች። ህዝባችንም በሲቃ ተኮራምቷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኮረና ቫይረስ መከላከል ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ እኛም የዜግነት ግዴታችን ለመወጣት የገንዘብ ድጋፍ ልናደርግ ወደናል። ኢትዮጵያዊነታችን የሚደምቀው በዚህ በጭለማና በጭንቅ ወቅት ስንረዳዳና ስንተጋገዝ በመንፈስና በፀሎት አብረን ከማህበረሰባቸን ጎን ስንቆም ነው» የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ከሆኑ አትሌቶች ልግስና ወረድ በማለት እንደ መቋጫ አንድ ክስተት ስንጠቅስ፤ በኢትዮጵያ የወንዶችና የሴቶች ብሔራዊ ቡድኖች አሠልጣኞች እንዲሁም የስፖርቱ ሙያተኞች የተደረገ ልግስና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ከስፖርቱ ቤተሰብ በኩል እየተደረገ ያለውን ልግስና የሚያሳየው ሁነት ነው። እነዚህ አካላት ህዝብን ለመታደግ በሚደረገው ርብርብ በየአቅጣጫው 120 ሺህ ብር መሰብሰብ ችለዋል። ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ለኢንጂነር ታከለ ኡማ አስረክበዋል፡፡ ይህ ተግባር በአጠቃላይ ከስፖርት ማኅብረተሰቡ ዘንድ የተንፀባረቁትን ወገናዊ ድጋፎችንና ችግርን በአንድነት ለመመከት እየተደረገ ካለው ጥረት በመነሳት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከፈጠረውና ካሳደረው አሉታዊ ተጽእኖ ጎን ለጎን የፈጠረው በጎ መልክ ስለመኖሩ የሚያስገነዝብ ይሆነናል። በስፖርት ማኅብረተሰቡ አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ ማኅበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ጉዞ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እሙን ነው።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 9/2012 ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=30621
[ { "passage": "የስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ይታወቃል። ይኸውም ስፖርቱን ከማስፋፋት ይልቅ ወደ ማገድ፣ ህዝቡንም ከማቀራርብ ይልቅ ወደ ማራራቅ የሚመራ መሆኑ ታይቷል። አሳሳቢ የሆነውን ይህንን የስፖርታዊ ጨዋነት ችግርም በጥናት የመለየት ስራ ሲሰራ ቆይቷል። የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽንም ከፌዴሬሽኑ ጋር በመተባበር በሳይንሳዊ መንገድ ችግሮቹ እንደተለዩ በተለያዩ መድረኮች ተገልጿል። በተለየው መንስኤና የመፍትሄ አቅጣጫ መሰረትም መግባባት ላይ የሚያደርስ ግኝት በመያዝ በየደረጃው ከባለድርሻ አካላት ጋር የግንዛቤ ማስጨበጥ እና ሁሉም የየራሱን ሚና እንዲጫወት አቅጣጫ በማስቀመጥ ወደ ስራ መገባቱን፤ በኮሚሽኑ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ናስር ለገሰ ይገልጻሉ። ወደ ስራ ከተገባ በኃላም በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል የሚለውን ለማወቅም ከሰሞኑ በአዳማ ከተማ መድረክ ተዘጋጅቷል። በመድረኩም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አጠቃላይ አፈጻጸሙን እንዲሁም የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ሚናውን በምን መልኩ እንዳከናወነ ሪፖርት መቅረቡን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። በቀረበው የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት መሰረትም የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት ካለፈው ዓመት አንጻር መቀነሱ ታይቷል። ችግሮቹ ፖለቲካዊ ይዘትም ስለነበራቸውም ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ከላይ እስከታች የተሳተፉበት ነበር። በተለይም በአማራ እና ትግራይ ክልሎች መካከል የነበረውን ችግር በመፍታት ክለቦች በሜዳቸው እንዲጫወቱ መደረጉ በመልካም ጎን ተነስቷል። በተለይ የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ስፖርታዊ ጨዋነትን በማስፈን ረገድ የተሻለ በመሆኑ በመድረኩ ከተገኙ አካላት ምስጋና ተችሮታል። ክለቡ በተለይ ከመቀሌ ሰባ እንደርታ ጋር በነበራቸው ጨዋታ በራሳቸው ተነሳሽነት ኃላፊነት ለመውሰድ ያሳዩት ዝግጁነት እንዲሁም ደጋፊዎች ሰላምን ለማስፈን የሚያደርጉት ጥረት ተደንቋል። ሌሎችም የክለቡን አርዓያ በመከተል የውድድር ስፍራዎች የስጋት ቀጠና ሳይሆን፤ ህብረተሰቡ ያለ ሃሳብ የሚዝናናበት ስፍራ እንዲሆን ጥሪ መቅረቡንም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። ስፖርታዊ ጨዋነትን ለማስፈን ተጨባጭ ስራ የሚሰሩ የመኖራቸውን ያህል ጠንክረው መስራት እንደሚገባቸው የታዩ መኖራቸውም ተመልክቷል። በአንድ ክልል ውስጥ ሆነውም ያልተፈታ ችግር ያለባቸው መኖራቸውም ተጠቅሷል፤ ለአብነት ያህልም በሃዋሳ ከተማ እና ወላይታ ድቻ፣ በኮምቦልቻ እና ደሴ ከተማ መካከል እንዲሁም በትግራይ ባሉ የክለብ ደጋፊዎች መካከል አለመግባባቶች መኖራቸውም ተጠቅሷል። ይህም ችግሩን ከመቀነስ ባሻገር ሙሉ ለሙሉ እንዳይፈታ አድርጎታል። አሁንም ያልተሰሩ ቀሪ ስራዎች መኖራቸው የተነሳ ሲሆን፤ ስፖርታዊ ጨዋነትን ለማስፈን ያልተዳሰሱ መንገዶች መኖራቸውም ከመግባባት ላይ ተደርሷል። በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰራር ላይም ችግሮች መኖራቸውም ተስተውሏል። የፌዴሬሽኑ ጽህፈት ቤት በቂ የሰው ኃይል እንዲኖረው ከማድረግ ጀምሮ ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴዎችን በድጋሚ የማደራጀት እንዲሁም አሰራሩን የመፈተሽ ስራም አስፈላጊ ነው። በመሆኑም ይህንኑ ከክለቦች ጋር የጋራ ለማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ አቶ ናስር ያብራራሉ። ፌዴሬሽኑ ውሳኔዎችን ተከትሎ የሚመጣውን ቅሬታ ለማስቀረት በሰነድ ደረጃ አሳድጎ ለሚመለከታቸው አካላት በማሰራጨት ላይ ይገኛል። ፌዴሬሽኑ ሌሎች ችግሮችንም በአሰራር ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑም ተመልክቷል። ይህንኑ በየደረጃው ግንዛቤ በማስጨበጥ የህግ ክፍተት እንዳይኖርም ተጨማሪ ስራዎችን ማከናወን እንዳለባቸው ተመልክቷል። ሌላው የደጋፊዎችን ግንዛቤ በማሳደግና ደጋፊዎች የአባልነት መታወቂያ እንዲያገኙ የማድረግ ስራ አስፈላጊ መሆኑም ተነስቷል። የጸጥታ አካሉም አጠቃላይ የውድድር ቦታን ደህንነት በማስጠበቅ እና የውድድር ሁኔታን አስቀድሞ በማወቅ ቅድመ ሁኔታ በማድረግ ለትንኮሳ የሚገቡትን በመፈተሽ፣ በመለየትና የማውጣት ላይ እንዲሰሩ። በዚህ ስራ ላይ የጸጥታ ክፍሉ በሌሎች ላይ ጉዳት ላለማድረስ በሚያደርገው ጥረት በራሱም ላይ ችግር እየደረሰ መሆኑ የተሰመረበት ጉዳይ ሆኗል። በክለቦች ዘንድ አጥፊዎችን በማጋለጥ ላይ ችግር ስላለ ለስፖርቱ እድገት ሲባል በዚህ ላይ ጠንካራ ስራ መሰራት አለበት። በመገናኛ ብዙሃን ዘንድም ለስፖርታዊ ጨዋነት መስፈን ጉልህ ሚና ያላቸውን ያህል ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ በማሰራጨት አባባሾች መኖራቸውም ተነስቷል። በመሆኑም ተቀራርቦ በመስራት ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ ነው። በመድረኩ ቀጣይ የትኩረት\nአቅጣጫዎችም ተቀምጠዋል፤ በዚህም\nሁሉም አቅዶ በስፖርታዊ\nጨዋነት መስፈን ላይ\nመስራት እንደሚገባ መጠቆሙን\nአቶ ናስር ይገልጻሉ።\nበስፖርቱ ጥራት ላይ\nመስራት እንደሚገባ፤ በዳኞች\nአቅም በማሳደግ፣ በስፖርተኞች\nምልመላ፣ የክለብ ተጫዋቾች\nክፍያ ወጥነት፣ አድሎአዊ\nከሆነ አሰራር በመውጣት፣\nጸጥታ ክፍሉም ጠንክሮ\nእንዲሰራ፣ የተሻለ ስራ\nየሰሩ ክለቦች ተሞክሮም\nሌሎች እንዲጋሩ፣ … ከስምምነት\nላይ ተደርሷል።አዲስ ዘመን ግንቦት\n26/2011 ", "passage_id": "b96570e382d186f19c30ddf844a5ce4e" }, { "passage": "ዘመናዊ ስፖርት ወደ ኢትዮጵያ ከገባ አንድ ምዕተ ዓመት ሊያስቆጥር መቃረቡን ሰነዶች ያሳያሉ። ይሁን እንጂ ስፖርት በኢትዮጵያ በዕድሜው ልክ እንዲሁም ከዓለም ነባራዊ ሁኔታ አንጻር መድረስ ካለበት ስፍራ እንዳልደረሰ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል። ስፖርት የአንድ ሀገር እድገት መለኪያ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ቢሆንም፤ በኢትዮጵያ የህዝቡን ጥቅምና ፍላጎት አስጠብቋል ለማለት አያስደፍርም። ለስፖርቱ እድገትም ሆነ መዳከም ድርሻ ያላቸው የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም ስፖርቱን የሚመሩ አካላት ጥንካሬና ብቃት ግን ወሳኝነት እንዳለው ይታመናል። ይሁን እንጂ እስካሁንም ድረስ በዚህ አቅጣጫ ሳይሆን በራሳቸው ጥረት የተሻለ ብቃት ያሳዩትን ስፖርተኞች በውድድር ላይ ማሳተፍ ላይ ያተኮረ አካሄድ እየተተገበረ ይገኛል። ስፖርትን ለልማት ከማዋል ይልቅ ውድድሮችን ብቻ ኢላማ ያደረገ አካሄድም ስፖርቱ በሚፈለገው ልክ እንዳያድግ ያደረገ ገፊ ምክንያት ሆኖ በተደጋጋሚ ይነሳል። የአገራችን ስፖርት ከየት ተነስቶ ወደ የት ማምራት እንዳለበት የሚያሳይ የስፖርት ፖሊሲ አቅጣጫ በ1990 ዓ.ም ተቀርጿል። ነገር ግን በፖሊሲው በተቀመጠው ልክ በተጨባጭ ስኬታማ የሆነ ሂደት ባለማሳየቱ በአሰራሩ ላይ ፍተሻ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት በጥናት ላይ የተመረኮዘ ብሄራዊ የስፖርት ሪፎርም በቅርቡ በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን መዘጋጀቱ ይታወቃል። በሪፎርሙ ምክረ ሃሳብ መሰረትም መመሪያዎች በመከለስና በመሻሻል ላይ ይገኛሉ። ሪፎርሙ ካመላከታቸው ነጥቦች መካከል አንዱ የሆነው አደረጃጀቱን የሚመለከት ሲሆን፤ በተለይ መንግስታዊው አካል ላይ ክፍተት መኖሩን አመላክቷል። በኢትዮጵያ 30 የሚሆኑ የስፖርት ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች ይገኛሉ። ከፌዴራል እስከ ቀበሌ ባለው አደረጃጀትም በጥቅሉ 397 ፌዴሬሽኖችና የስፖርት ማህበራት እንዳሉ ይታመናል። ከእነዚህ ማህበራት መካከል ራሳቸውን ችለው ከመንግስት ድጎማና ድጋፍ የተላቀቁት ግን ሁለቱ ብቻ ሲሆኑ፤ አትሌቲክስና እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች በዋናነት ይጠቀሳሉ። የተቀሩት እስካሁንም የመንግስትን ድጎማ የሚጠብቁ በሁለት እግራቸው ያልቆሙ ሲሆኑ፤ በግላቸው የሚያደርጉት እንቅስቃሴም አነስተኛና የተገደበ ነው። ለዚህና ለስፖርቱ አለማደግ በዋናነት እንደ ምክንያት የሚያነሱትም በመንግስት በኩል የሚመደብላቸውን አነስተኛ የበጀት ድጎማ ነው። ነገር ግን የየስፖርት ዓይነቱን በኃላፊነት የሚመሩትና በየደረጃው የሚገኙ የስፖርት ማህበራት (ፌዴሬሽኖች) ካሉባቸው ችግሮች ባሻገር ከራሳቸው ድክመት የተነሳ ስፖርቱ እንዲዳከም ምክንያት እንደሆነ ይታመናል። አሁን ባለው ሁኔታ ፌዴሬሽኖቹ ራሳቸውን ከተረጂነት ነጻ ለማውጣት ያላቸውን እድል ተጠቅመው ለውጥ ለማምጣት የሚፍጨረጨሩት ጥቂቶች ናቸው። መልካም ተሞክሮ ካላቸው ሌሎች ፌዴሬሽኖች ልምድ ለማግኘት የሚችሉበት መንገድም ዝግ መሆኑ ይስተዋላል። አንዳንድ ስፖርቶች በህዝቡ ዘንድ በቅጡ ያልታወቁና ተደራሽነታቸውም በአሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን በማህበር ታቅፈው የመንግስትን በጀት ለብክነት የሚዳርጉም አሉ። በአንጻሩ መልካም ድልና የተሻለ ውጤት ሊመዘገብባቸው የሚችሉ ስፖርቶች ደግሞ እንቅስቃሴያቸው የተገደቡ ሆነዋል። ሌሎች ደግሞ በተወሰኑ አካላት ተሸብበው እድገታቸው ቀጭጮ እንዲቀር ሆነዋል። ስፖርቱ በህዝቡ ዘንድ ተስፋፍቶ ጥቅም የሚገኝበት እንዲሁም በሀገር ደረጃ ውጤት እንዲመዘገብበት ካስፈለገም እነዚህ ችግሮች በቅድሚያ ሊቀረፉ እንደሚገባ ብዙዎች ይስማማሉ። በመሆኑም ሀገር አቀፉን የስፖርት ማህበራት ማቋቋሚያ መመሪያ ማሻሻል አስፈልጓል። ባለፈው ሳምንት ኮሚሽኑ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተሻሻለው መመሪያ ረቂቅ በኮሚሽኑ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን አልዩ ለተሳታፊዎቹ የቀረበ ሲሆን አስተያየትም ተሰጥቶበታል። በገለጻው ላይ እንደተመላከተው ከሆነም ለመመሪያው መሻሻል አስፈላጊ የሆኑት ምክንያቶች፤ በሪፎርሙ የተሰጠው ምክረ ሃሳብ፣ የማህበራዊ ወቅታዊ አቋም፣ ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት እንዲሁም የስፖርት ምክር ቤቱ የውሳኔ አቅጣጫ ናቸው። የማህበራቱን አሰራሮችና አደረጃጀቱን በመፈተሽ ተገቢውን መስፈርት አሟልተው እንዲሄዱ ማድረግም አላማው ነው። አብዛኛዎቹ ማህበራት ተገቢውን መስፈርት ሳያሟሉ የማህበር ስያሜ ብቻ በመያዝ እውቅና አግኝተው የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው ውጤታማ መሆን አልቻሉም፤ በመሆኑም ዳግም ዕውቅና ማግኘት አስፈልጓቸዋል። መሆኑም ማሻሻያው የተለያዩ ሂደቶችን ተከትሎ ሊዘጋጅ ችሏል። ይኸውም ነባሩን መመሪያ መሰረት በማድረግ፣ የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ በመዳሰስ፣ ዓለም አቀፍ አሰራሮችን በመመልከት እንዲሁም ያጋጠሙ ተጨባጭ ሁኔታዎችን በመውሰድ መሆኑንም በመድረኩ ተጠቁሟል። በስራውም የኮሚሽኑ፣ የተለያዩ ፌዴሬሽኖች እንዲሁም የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ባለሙያዎች ተሳታፊዎች ነበሩ። መመሪያው ከያዛቸው ሃሳቦች መካከል አደረጃጀትና ስያሜን የሚመለከት ሲሆን፤ በክልል ያሉ ፌዴሬሽኖች ‹‹አሶሴሽን›› ከዚያ በታች ያሉት ደግሞ ‹‹ኮሚቴ›› በሚል ቢጠሩ ለአሰራር አመቺ እንደሚሆኑ ተመልክቷል። የፌዴሬሽን ማቋቋሚያ መስፈርትን በተመለከተም የቡድንና የግል ስፖርቶችን በራሳቸው አሰራር መሰረት እውቅና የሚያገኙበት ሁኔታም ተካቷል። በዚህም የቡድን ስፖርቶች የሚያወዳድሯቸው ቢያንስ ስድስት ክለቦች ሊኖሯቸው እንደሚገባ፤ በአርት ስፖርቶች 10 ማዕከላት እንዲሁም በግል ስፖርቶች 250 የተመዘገቡ ስፖርተኞች ሊኖሩ ይገባል። ደረጃውን የጠበቀ የውድድርና የስልጠና ቁሳቁስ መኖሩ ሲረጋገጥ፣ የሀብት ምንጭ ሲኖራቸው እና የሂሳብ አያያዝ ሥርዓት የዘረጉ ሊሆኑም ይገባቸዋል። የሀገር አቀፍ ስፖርት ፌዴሬሽኖች የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት እጩ አቀራረብ፣ የመምረጫ መስፈርት እንዲሁም ተግባርና ኃላፊነትም በመመሪያው ተካቷል። በዚህም የኮሚቴዎቹ የስራ ዘመን አራት ዓመት ብቻ ሲሆን፣ በድጋሚ የሚመረጡትም ለአንድ የስራ ዘመን ብቻ ይሆናል። ይህም ቀድሞ በተለያየና በተበታተነ ሁኔታ ይከናወን የነበረው ምርጫ አንድ የኦሊምፒክ ጨዋታ በተጠናቀቀ ሶስትና አራት ወራት ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ምርጫ እንዲከናወን የሚያስገድድ ነው። ከዚህ ጋር የተካተተው መመሪያም የትኛውም የስራ አስፈጻሚ ሊያገለግል የሚችለው በአንድ ስፖርት ላይ ብቻ መሆኑን የሚያመለክት ነው። የማህበራት ፈቃድ አሰጣጥ፣ እድሳትና መፍረስን በተመለከተም በምን መልኩ ይከናወናል የሚለውን የተሻሻለው የመመሪያ ረቂቅ በዝርዝር አስቀምጧል። የኦሊምፒክና ፖራሊምፒክ ኮሚቴዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ስፖርት ማህበር እንዲሁም የጤና ስፖርት ማህበር በበኩላቸው የተለያዩ ስፖርቶችን አቅፈው የሚያካሂዱ ማህበራት እንደመሆናቸው ከሌላው የተለዩ መሆናቸውም ተገልጿል። በመመሪያው ዝግጅት ላይ ተሳታፊ የነበሩትና ገለጻውን ያደረጉት የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አልዩ ምላሽ የተነሱ ሃሳቦች ላይ ምላሽ ሰጥተዋል። መድረኩ የተዘጋጀው ግብዓት ለመሰብሰብ እንደመሆኑ በተለያዩ አካላት ዘንድ የተለያዩ እይታዎች ይፈጠራሉ። በመሆኑም ጠቃሚ የሆኑትን ለማካተት ያስችላል፤ የስፖርቱ አደረጃጀት በምን መልክ ሊቃኝ ይገባል በሚለው ላይ ጠቃሚ ሃሳቦች እንጂ ፍላጎቶችን ለማስተናገድ እንደማይቻልም አሳስበዋል። አደረጃጀቶቹ ያሉባቸውን ክፍተቶች በመሙላት አደረጃጀቱን ለማጠናከር ይቻላል፤ ስለዚህም የተሰጡት ግብረ መልሶች በሰነዱ የሚካተቱ ይሆናል። በተጨማሪም መድረኩ የተዘጋጀው በምክር ቤት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በመሆኑ መንግስት ወደፊትም ለማህበራቱ እገዛና ድጋፍ ከማድረግ ወደኃላ እንደማይልም አመላክተዋል። በኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዱቤ ጂሎ በበኩላቸው ይህ የቀረበው ረቂቅ መመሪያ ወደ ክልሎች ወርዶ የራሳቸውን ደንብና መመሪያ እንዲያወጡ የሚደረግ መሆኑን ገልጸዋል። ማህበራቱ የየራሳቸውን መመሪያና ደንብ ካዘጋጁ በኋላም በዚህ ላይ ተመስርተው ክልሎች በስታንዳርዱ መሰረት የሚተዳደሩ ይሆናል፤ በመሆኑም በመድረኩ የተንጸባረቁ ሃሳቦች ጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል። አዲስ ዘመን ሐምሌ 25 ቀን 2012 ዓ.ምብርሃን ፈይሳ ", "passage_id": "6d433d0150840ea67e532f9662178373" }, { "passage": " ከዓመታት በፊት የስፖርት አበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) ተጠቃሚነት ጉዳይ ጎልቶ የሚሰማ የዓለም ዜና ነበር። በርካታ አትሌቶችና ሃገራትም ስፖርት ላይ ጥቁር ነጥብ በጣለው በዚሁ ምክንያት ለዕገዳ እና ቅጣት ተዳርገዋል። ኢትዮጵያን የመሳሰሉ ሃገራትም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው ይታወሳል።በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ ለዓመታት የተከናወነው ሥራ በርካታ መሻሻል ቢያሳይም፤ ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ይታመናል፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የጸረ-አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት ዋነኛው የጉዳዩ ተዋናይ ይሁን እንጂ፤ የስፖርት ህገ-ወጥነትን የመከላከልና የመቆጣጠር ጥረቱን ከሌሎች ተቋማት ጋር በህብረት እያከናወነ ይገኛል። ከቀናት በፊትም ሁለተኛውን የጸረ-አበረታች ቅመሞች የባለ ድርሻ አካላት ጉባኤ አካሂዷል። በመድረኩ ላይም ባለድርሻዎቹ በተጠናቀቀው ዓመት ያከናወኑትን እንዲሁም የአዲሱ ዓመት ዕቅዳቸውን አስታውቀዋል። ከአበረታች መድሃኒት ጋር በተያያዘ በተለይ የሚነሳው የአትሌቲክስ ስፖርት መሆኑ ይታወቃል። ኢትዮጵያም በዚህ ስፖርት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሻለ ተሳትፎና ውጤት ያላት እንደመሆኑ ትኩረት የሚደረገው በዚህ ስፖርት ላይ ነው። በመድረኩም ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተጠናቀቀው ዓመት ክንውኖቹን እንዲሁም የእዚህ ዓመት ዕቅዱን አቅርቧል። ፌዴሬሽኑ ከጽህፈት ቤቱ ጋር በቅርበት የሚሰራ ሲሆን፤ የመገኛ ቦታ አድራሻ፣ ቅድመ ውድድር የጤና ምርመራ እንዲሁም በምርመራ ላይ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ላይ በጋራ ሲሰሩ መቆየታቸው ተነስቷል። አበረታች ቅመሞች ተጠቃሚነትን ለመከላከል አትሌቶች እንዴት በተፈጥሯዊ መንገድ ብቃታቸውን ማሳደግ ይችላሉ? በሚልም ስልጠና ተሰጥቷል። በዚህም ኢትዮጵያዊ ይዘት ያላቸውና በሽታን ሊከላከሉ የሚችሉ የምግብ ዓይነቶች እንደየ ርቀቱ ተዘጋጅቶ እንዲያውቁት እየተደረገ ነው። የምክር አገልግሎት ለአትሌቶች፣ አሰልጣኞች እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎች በመስጠት ረገድ በዓመቱ 84 ባለሙያዎችን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል። በዓለም አቀፉ ተቋም የሚከለከሉ ቅመሞች ዝርዝርንም ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስ ተደርጓል። በዓመቱ በተካሄዱ ሃገር፣ አህጉር እና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ለሚካፈሉ አትሌቶች እንዲሁም ድጋፍ ሰጪ አካላትም የግንዛቤ ማስጨበጫ በፌዴሬሽኑ ሲሰጥ መቆየቱም ተጠቁሟል። በተያዘው ዓመትም ፌዴሬሽኑ እአአ በ2020 ለሚካሄደው የጃፓን ኦሊምፒክ ከወዲሁ የተለያዩ ስራዎች እያከናወነ እንዳለ ተጠቅሷል። የአትሌቶችን አጠቃላይ መረጃ በአንድ ቋት ለመያዝ፣ የስፖርት ስነ- ምግብና ህክምና ስርዓትንም ለማጠናከር ታስቧል። የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችንም ማስፋት፣ በየጊዜው የሚቀየሩ ህጎችን ተከታትሎ ለተገቢው አካል ማሳወቅ እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከርም ታቅዷል። በክብደት ማንሳት ስፖርት በ12ኛው የሞሮኮ ራባት የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ የብሄራዊ ቡድኑ ገጠመኝም በመድረኩ ተንጸባርቋል። በዚህ ስፖርት ከዚህ ቀደም በተካሄደ ውድድር በርካታ የአበረታች ቅመም ተጠቃሚዎች መገኘታቸውን ተከትሎ ስፖርቱ በልዩ ሁኔታ የሚታይ ሆኗል። ፌዴሬሽኑ ግን ከዚህ በተቃራኒ በቀድሞው አካሄድ ነበር ቡድኑን ይዞ ወደ ውድድሩ ያቀናው። በዚህ ምክንያትም ከውድድር ውጪ ሊሆን ችሏል። በመሆኑም ፌዴሬሽኑ በዓለም አቀፉ ህግ መሰረት ለመንቀሳቀስ የተለያዩ ስራዎች በመተግበር ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። የተሟላ ስፖርተኞችን መኖሪያና ስልጠና አድራሻ በመመዝገብ ለዓለም አቀፉ አካል በማሳወቅ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ሌሎች መሰል ህጎችን ወደ ተግባር ለመለወጥ እየተራመደ ይገኛል። ከዚህ ቀደም ከአበረታች ቅመም ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ መድሃኒቶቹ በግልጽ የሚሸጥ መሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ ነበር። ሁለት መድሃኒት መሸጫ መደብሮችም በዚሁ ምክንያት መታገዳቸው የሚታወስ ነው። በመሆኑም መድሃኒት መሸጫ መደብሮች ከጽህፈት ቤቱ ጋር በቅርበት የሚሰሩ ባለድርሻ አካል ሆነዋል።ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያ ፋርማሲዎች ማህበር ጉዳዩን እንዳስጠና በመድረኩ ላይ ተገልጿል። ዳሰሳዊ ጥናቱም በአምስት ክፍለ ከተሞች ላይ በሚገኙ ፋርማሲዎች በሚሰሩ 336\nባለሙያዎች ላይ ነው የተደረገው። በዚህም ስለ አበረታች መድሃኒት ምን ያህል ዕውቀት አላቸው የሚለውን ለማየት እንደተሞከረው ከፍተኛ የዕውቀት ክፈተት መኖሩ ተረጋግጧል። አትሌቶች በዓለም አቀፉ የጸረ አበረታች ቅመሞች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ(ዋዳ) የተከለከሉ መድሃኒቶችን ስለመፈለጋቸው በተደረገው መጠይቅም 33ነጥብ4 በመቶ የሚሆኑት «አዎ» የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ከእነዚህ ውስጥ ስምንት የሚሆኑት ቢያንስ በሳምንት ለአንድ ጊዜ ሌሎቹ ደግሞ በወራት ውስጥ ይህ ዓይነት ጥያቄ ይቀርብላቸዋል። ከዚህ በመነሳትም ወደፊት የፋርማሲ እና የጤና ባለሙያዎች ላይ ከፍተኛ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ሊከናወን እንደሚገባ በመድረኩ ተመላክቷል። በመደበኛ ትምህርት ካሪኩለም በውስጥ ቢካተትም፤ በፋርማሲ ትምህርት ካሪኩለም ውስጥ ግን አለመኖሩም ነው የተጠቆመው። በመሆኑም ባለሙያዎች ስለጉዳዩ እንዲረዱ ለማድረግ ጽህፈት ቤቱ በዚህ ላይ መስራት ይገባዋል። እንደ ሙያ ማህበርም የኢትዮጵያ ፋርማሲ ትምህርት ቤቶች ህብረት የሚሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። ከህክምና ሙያ ማህበራት ጋር በመስራትም የህክምና ባለሙያዎች መድሃኒት ሲያዙ ይህንን ነገር ከግምት ማስገባት ይቻላል። ዓለም አቀፉ የጸረ አበረታች ቅመሞች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የሚያወጣውን የተከለከለ መድሃኒት ዝርዝር በየመደብሩ እና ጤና ተቋማት መኖር እንዳለበትም ተነስቷል። በተጨማሪ በዓለም ላይ ከጦር መሳሪያ ቀጥሎ በህገወጥ መንገድ የሚዘዋወረው መድሃኒት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ እንደ ሃገር ከፍተኛ ቁጥጥር ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነም አጽንኦት ተሰጥቷል። በኢትዮጵያ ብሄራዊ የጸረ አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል፤ በ2011ዓም በባለድርሻ የተከናወኑ ተግባራትን በግብዓትነት መያዝ በዚህ ዓመት የተጠናከረ ስራ ለመስራት እንደሚያግዝ ይገልጻሉ። በመሆኑም በየጊዜው በመገናኘትና የጋራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መስራት ተገቢ ይሆናል። በቀጣይም ከሌሎች የሙያ ማህበራት ጋር ለመስራት ፎረሞችን የማቋቋም ዕቅድ ተይዟል። በዚህ የህብረት እንቅስቃሴም ፎረሞቹ የራሳቸውን ግብዓት በመስጠት እንዲሁም የድርሻቸውን በመወጣት አወንታዊ ስራ ማከናወን እንደሚቻል ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን መስከረም 12/2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "383f0f9db4b4ffb790053c119b71c8ae" }, { "passage": "ስፖርት ከአካላዊ እንቅስቃሴና ከመዝናኛነት ባለፈ ማህበራዊ ግዴታን በመወጣት ረገድ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በተለያዩ አጋጣሚዎች ታይቷል። በተለይም ዓለም በኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ 19) ምክኒያት ጭንቅ ውስጥ በገባችበት በዚህ ወቅት ስፖርትና የስፖርቱ ማህበረሰብ ማህበራዊ ግዴታን በመወጣት በኩል እያበረከተ የሚገኘው አስተዋፅኦ እዚሁ አገራችንም ትልቅ ቦታ እንዳለው መታዘብ ይቻላል። \nኤርሚያስ ገሰሰ ጂምና ማርሻል አርት ማዕከል ወጣቶችን በጅት ኩን ዶ እንቅስቃሴ ከማብቃት ጎንለጎን የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ይታወቃል። የበጎ አድራጎት ስራ ከማርሻል አርት ስፖርት ጋር አብሮ እንደሚሄድ የሚናገረው ማስተር ኤርሚያስ ወጣቶች ማርሻል አርትን ሲማሩ የስነምግባር ትምህርትም አብሮ እንደሚሰጣቸው ያብራራል። ይህ የስነ ምግባር ትምህርት መገለጫው ደግሞ በጎ ተግባር ነው። 1995 ዓ.ም አካባቢ የተማሪ ቤተሰቦች፣በጎ ፍቃደኞችና ሌሎችም በጋራ ሆነው የስፖርቱን እንቅስቃሴ ሲጀምሩ ገንዘብ በማዋጣት ጎዳና ላይ ያሉ ወገኖችን በምግብ፣ በአልባሳት ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር በዘላቂነት በማቋቋም መደበኛ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እያደረገም ይገኛል። የበጎ አድራጎት ስራውን ከስፖርቱ ባሻገር ለማስፋት በቅርቡ ‹‹ዿጉሜ 5 የበጎ አድራጎት ድርጅት›› በሚል ስያሜ በማሳደግ እውቅና አግኝቶ እየተንቀሳቀሰም ነው። በየዓመቱም የትንሳዔን በዓል ምክኒያት በማድረግ በጎዳና ላይ ያሉ ወገኖችን የመመገብ፣አልባሳትንና ገንዘብ የመስጠት መርሃግብሮችን ያካሂዳል። መማር የሚችሉ እንዲማሩ፣መስራት የሚችሉ እንዲሰሩ ማድረግም አንዱ ተግባሩ ነው። በዚህም የበርካታ ወጣቶችን ሕይወት መለወጥ ተችሏል። \nይህ ምስጉን የረድዔት ተግባር በየጊዜው እያደገ ሄዶም ኤርሚያስ ገሰሰ ጂምና ማርሻል አርት ማዕከል ከ‹‹ዿጉሜ 5 የበጎ አድራጎት ድርጅት›› ጋር በመተባበር ባለፈው እሁድ ሃያ ሁለት የጎዳና ልጆችን በማንሳት ማዕድ ከማጋራት ባሻገር መስራት የሚችሉ ወደ ስራ እንዲገቡ፣ ወደ ቤተሰብ የመመለስ ፍላጎት ያላቸው አስፈላጊው ነገር ተሟልቶላቸው እንዲመለሱና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ እስከ ማድረግ የደረሰ የረድዔት ተግባር አከናውኗል። \nበስፖርቱ የሚሳተፉ ወደ በጎ አድራጎት ድርጅቱ አባልነት እንዲካተቱ በማድረግ ችግርተኛ ወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እየተሰራ መሆኑን የሚናገረው ማስተር ኤርሚያስ አምስት መቶ ያህል አባላት ያሉት የበጎ አድራጎት ድርጅት ከዚህም በላይ የረድኤት ስራዎችን የማከናወን ፍላጎት ቢኖረውም ከጎዳና ላይ የሚያነሳቸውን ልጆች ማሳደሪያ ወይም ማረፊያ ቦታ ትልቁ ችግር እንደሆነ ያስረዳል። ተረጂዎቹ ወጣቶች ቢታመሙም የሕክምና ጉዳይ አሳሳቢ እንደሆነባቸው ገልጿል። በዚህ ረገድ ማንኛውም አካል ቢደግፋቸው ሌሎቹን አስፈላጊ ግብዓቶች ለማሟላት እንደማይከብድም ይናገራል። በተለይም እነዚህ ከበጎ አድራጎት ድርጅቱ አቅም በላይ የሆኑ ችግሮች ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ አሁን ያለንበት አስቸጋሪ ጊዜ እስኪያልፍ ማንኛውም አካል ትብብር እንዲያደርግ ጥሪውን አቅርቧል። ይህም ልጆቹን ከቫይረሱ ተጋላጭነት ከመጠበቅ ባለፈ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር በሚደረገው ርብርብ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ያለውን እምነት ተናግሯል። በቀጣይም ሌሎች ወጣቶችን ከጎዳና ለማንሳት ጥረት እንደሚደረግ ቃል ገብቷል። \nባለፈው እሁድ ማዕድ የማጋራት መርሃግብሩ ሲከናወን በስፍራው የተገኙት የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስራ አራት ዋና አስፈፃሚ ወይዘሮ ወይንሸት አስናቀ፣ የስፖርት ማዕከሉና የእርዳታ ድርጅቱ ከወረዳው አስተዳደር ጋር በመሆን መሰል ስራዎችን ከዚህ ቀደምም ሲያከናውን መቆቱን ተናግረዋል። በተለይም በኮሮና ቫይረስ ስጋት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ማዕድ የማጋራት መርሃግብርን ይፋ ካደረጉ ወዲህ የስፖርት ማዕከሉና የእርዳታ ድርጅቱ በጋራ በመሆን ጎዳና ላይ ያሉ ወጣቶችን ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ መስክረዋል። ‹‹በወረዳችን በርካታ ጎዳና ላይ ያሉ ወጣቶች አሉ›› ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ እነዚህን ወጣቶች ማዕድ ከማጋራት ባለፈ ወደ ስራ እንዲሰማሩና እንዲቆጥቡ በማድረግ፣ ወደ ትምህርት እንዲመለሱ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም ወደ ቤተሰባቸው መመለስ የሚፈልጉትን በመመለስ በርካታ ተግባራት መፈፀማቸውን አስታውሰዋል። ሌሎችም ከዚህ ምስጉን ተግባር በመማር ተመሳሳይ የረድዔት ስራዎችን እንዲሰሩ በማድረግ የስፖርትን ማህበራዊ ኃላፊነት በተግባር ማሳየት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። ወረዳው የስፖርት ማዕከሉና የረድዔት ተቋሙ የሚያደርጉትን በጎ ተግባር ለመደገፍም ማደሪን የመሳሰሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል። አዲስ ዘመን ግንቦት 6/2012ቦጋለ አበበ", "passage_id": "04391ed189555d5cdfcd4a8774625eeb" }, { "passage": "የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግሥት የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣ አዋጅ ቁጥር 1097/2011\nመሠረት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የስፖርት ሥራዎችን እንዲመራ ስልጣን ተሰጥቶታል። ሚኒስቴሩ በአዋጁ የተሰጠውን ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት በማድረግ ባለፉት ሦስት ወራት እንቅስቃሴ አድርጓል። በዋነኛነት ትኩረት የተደረገው ስፖርታችን የት ላይ ነው? መንግሥታዊ አደረጃጀቱ ስፖርቱን እንዴት እየመራው ይገኛል? ስፖርቱን እንዴት ያያል? በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? የሚለውን ለመመልከት በቂ ጊዜ መውሰድ ነበረብን። በዚህ ምልከታ ውስጥ የስፖርቱ ጉዞ ቁልቁል መሆኑን መረዳት ችለናል። በዚህ ውስጥ ግን ጠንካራ ተግባራት የሉም ማለት አልነበረም። ስፖርቱን ለማንቀሳቀስ በተለየ መልኩ ሥራዎች ተሠርተዋል። ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞችን ከመገንባት፤ የስልጠና ማዕከላትን ከማቋቋምና ከማስፋፋት አኳያ ያለውን እንደማሳያ መውሰድ ያስፈልጋል። ደረጃቸውን የጠበቁ አካዳሚዎችና ማጠልጠኛ ማዕከላት፤ በፌዴራል ደረጃ የኢትዮጵያ ወጣት ስፖርት አካዳሚ እና የአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ተቋቁሞ ስልጠና እንዲሰጥ ተደርጓል። በክልሎች በተመሳሳይ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል (በትግራይ ማይጨው፤ በአማራ ደብረ ብርሃን፤ በኦሮሚያ በቆጂና ሱሉልታ፤ በደቡብ ሃገረ ሰላም ወዘተ. ተገንብተዋል። በእነዚህ ተቋማት በሀገር አቀፍ ደረጃ 2 ሺህ 682 የምርጥ (ኤሊት) ስፖርተኞችና 47 ሺህ 278 ታዳጊ ወጣቶች በፕሮጀክት በመሰልጠን ላይ ይገኛሉ። በስታዲየም ግንባታ ረገድ በተመሳሳይ የሚዘረዘሩ ሥራዎች እንዳሉ ድብቅ አይደለም። ስለዚህ፤ ፖሊሲውን መሰረት በማድረግ ከተሠሩ ሥራዎች አንጻር መንግሥት የሚታማ አልነበረም። ስታዲየሞችንም ሆነ የስልጠና ማዕከላትን ማስፋፋት ብቻውን ስፖርቱን የሚያሳድግ አይሆንም። ፖሊሲውን አውቆና ተገንዝቦ ተግባራዊ የማድረግና ሌሎች መሰረታዊ ችግሮች እንዳሉበት መካድ አይቻልም። ‹የፖሊሲ አፈጻጸም ችግር አለ› የተባለውን እጋራዋለሁ። በሀገራችን የስፖርት ፖሊሲ የወጣው በ1990 ዓ.ም ነው። በየደረጃ ያሉት የጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች ቢጠየቁ ፖሊሲውን በቅጡ አያውቁትም። በአብዛኛው ህብረተሰብ ዘንድም ይታወቃል ማለት አይቻልም። ፖሊሲውን ያወቀው መንግሥታዊም ሆነ ህዝባዊ አካል በፖሊሲው ውስጥ የተቀመጡትን ጉዳዮች በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ አላደረገም። የስፖርት ፖሊሲው ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ 21 ዓመት አስቆጥሯል። ነገር ግን የት ደረሰ ተብሎ አልተገመገመም። አልተከለሰም። ከፖሊሲው በተጓዳኝ የሚጠቀሱ በርካታ ችግሮች ያሉ ሲሆን፤ የስፖርቱ መንግሥታዊ አደረጃጀት (ከፌዴራል ጀምሮ እስከ ወረዳ) ቁመና ጠንካራ አለመሆን፤ የስፖርቱ ህዝባዊ አደረጃጀት ስፖርትን በአግባቡ ለመምራት በሚያስችል ቁመና ላይ አለመገኘት። ይህም የስፖርት ምክር ቤቶች፣ ብሄራዊና ክልላዊ ፌዴሬሽኖች፣ ቡድኖች ወይም የህብረተሰብ ኮሚቴዎች ጠንካራ መሰረት አለመኖር፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የስፖርት ህዝባዊ መሠረት አለመያዝ። ማለትም፤ በትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች፣ በመስሪያ ቤቶች፣ በመኖሪያ አካባቢዎች፣ በአገር መከላከለያና በፖሊስ ሠራዊት… ወዘተ. ያለው አደረጃጀት ጠንካራ አለመሆን ስፖርቱን አንቀው የያዙት ችግሮች ናቸው። የስፖርት አደረጃጀቱ ቁመናው እንደ ዕድሜው አይደለም። ዘመናዊ ስፖርት ወደ ሀገራችን ከገባ ከ75 ዓመት በላይ ያስቆጠረ ቢሆንም፤ ዕድሜውን የሚመጥን ቁመና ላይ አይደለም። ይሄ ማለት፤ አንድ ሰው ከ70 ዓመት በላይ ከኖረ ሊኖረው የሚገባ ዕውቀት፤ ግንዛቤ፤ ነገሮችን የማመዛዘን ደረጃ ከ16 ዓመት ታዳጊ ጋር በእጅጉ ልዩነት አለው። በተቋምም ደረጃ ከተመለከትነው ተመሳሳይ ነው። ስለዚህ በየደረጃው የሚገኙ ፌዴሬሽኖች እንደ ዕድሜያቸው ናቸው ወይ? አይደሉም። የኢትዮጵያን የስፖርት አደረጃጀት፤ የፌዴ ሬሽኖችን አደረጃጀት ከሌሎች ሀገራት ከኬኒያ፤ ሞሪሺየስ፤ ናይጄሪያ፤ አልጄሪያ፤ ሩዋንዳ፤ እና ከመሳሰሉት ጋር ስናወዳድር የት ነን እኛ? ካልን እታች ነን። ይህም በሀገራችን ከፍተኛ የሆነ የማስፈጸም አቅምና የትኩረት ውስንነት በመኖሩ ነው። በእርግጥ አደረጃጀት ታክቲክ ነው፤ ስትራቴጂ አይደለም። ሆኖም፤ አደረጃጀቱ የህዝብን መገኛ መሰረት በማድረግ ከታች ከወረዳ ደረጃ ትኩረት አድርጎ መሥራት ሲገባ በዚህ መልኩ አልተሠራም። ምክንያቱም ህዝብ ያለው፤ ስፖርተኛው፤ ሜዳ፤ በስፖርቱ ተሰጥኦ ያለው ሰው የሚገኘው በቀበሌ ደረጃ መሆኑ ግልጽ ነው። የስፖርቱ ዕድገት መሰረት ተብሎ በተጠቀሰው በቀበሌ ደረጃ ጠንካራ አደረጃጀት አለ ከተባለ ግን የለም። ደካማ ነው። ከፍተኛ የማስፈጸም አቅም ችግር በመኖሩ ስፖርቱ ይሄ መልክ ሊኖረው ችሏል። የተጠሪነቱን ሁኔታ ለዚህ እንደ ማሳይ መጥቀስ ተገቢ ነው። ስፖርቱ ተጠሪነቱ አንዴ ከአንዱ ይሆናል። ሌላ ጊዜ ከሌላው ይለጠፋል… ወጥ ሆኖ እንዲዘልቅ አልተደረገም። በየደረጃው ያሉ የስፖርት መዋቅሮች፤ ፌዴሬሽኖች፤ ወዘተ. የወቅቱ ቁመናቸው ዕድሜያቸውን የሚመጥን አይደለም። ከአደረጃጀት ጋር ተያይዞ ያለውን ጉድለት በሚገባ ተገንዝቦ ወደ ሥራ መግባት ያስፈልጋል። ስፖርቱን የሚመራው ህዝባዊ አደረጃጀቱ እንደሆነ በፖሊሲው ተቀምጧል። ህዝባዊ አደረጃጀት የሚባለው፤ ኦሎምፒክ ኮሚቴ፤ ፌዴሬሽኖቹ፤ ክለቦቹ፤ እንዲሁም የስፖርት ምክር ቤቶች ናቸው። በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ የስፖርት ምክር ቤቶች የት ናቸው? ስፖርቱን በአግባቡ መምራት በሚችሉበት ቁመና አይገኙም። በፌዴራል ደረጃ የስፖርት ምክር ቤት ተቋቁሞ ወደ ሥራ የገባው በ60ዎቹ አካባቢ ቢሆንም፤ በፌዴራል ደረጃ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ጠፍተዋል። ብሄራዊ የስፖርት ምክር ቤት በ2011 ዓ.ም ነው ገና እንደአዲስ የተቋቋመው፤ በክልሎችም ተመሳሳይ ሁኔታ ይንጸባረቃል። በዓመት አንዴ፤ አሊያም ሁለቴ መሰብሰብ አለባቸው። ለአራትና አምስት ዓመታት ያልተሰበሰቡ የክልል ስፖርት ምክር ቤቶች አሉ። መገንዘብ የሚያስፈልገው በአንድ ሀገር ውስጥ ስፖርትን በበላይነት ከሚመሩ አካላት አንዱ የስፖርት ምክር ቤት ነው። ለስፖርቱ ህልውና የሆነው ይህ ምክር ቤት አለመኖሩ ትልቅ ችግር ነው። ስለዚህ ጠንካራ የስፖርት ምክር ቤት አለመፈጠር ስፖርቱ ህዝባዊ መሰረቱን እንዲያጣና አሁን ለሚገኝበት ደረጃ ምክንያት ሆኖ ይቀርባል። የስፖርት ምክር ቤት እንዲዳከም መንግሥት ፍላጎት አለው የሚል እሳቤ የለኝም። በሀገር አቀፍ ደረጃ ለስፖርት ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት ግን በእጅጉ አነስተኛ ነው። ከ83 ዓ.ም በፊት በ14 ክፍለ ሀገራት ጠንካራ የስፖርት ምክር ቤቶች ነበሩ። የየራሳቸው ዓመታዊ ውድድር ያከናውናሉ። የመላው ኢትዮጵያ ውድድሮች በስፖርት ምክር ቤት ስር ይደረጉ ነበር። ስፖርቱን በዋነኛነት የሚመራው አወዳዳሪ አካል ምክር ቤቱ ነበር። መንግሥታዊውንና ህዝባዊውን አካላት አቀናጅቶና ሚናቸውን ለይቶ አንድ ላይ እንዲጓዙ አድርጓል። በመሆኑም ስፖርቱም ህዝባዊነትን ተላብሶ በመጓዝ ውጤታማ ነበር። በአሁን ወቅት ግን፤ የመንግሥታዊና የህዝባዊ አካሉ ሚና ተደበላልቋል። በመንግሥታዊ አካሉ ስፖርቱን ከማልማት ይልቅ ስፖርቱን ለመምራት ዝንባሌ ይስተዋላል። በመገናኛ ብዙሃን የሚነገሩ ዜናዎችን ቆም ብለን ብናስብ፤ የስፖርት ውድድሮቸ ስለመደረጋቸው በተደጋጋሚ ይሰማል። ስንት ሜዳ ተስፋፋ፤ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስንቱ ሰው ተሳትፏል፤ በትምህርት ቤት ውስጥ የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት በአግባቡ ይሰጣል… የሚሉ ዘገባዎች ኢሚንት ናቸው። ትኩረት ያደረገው ውድድር በመምራት ላይ እንጂ በስፖርት ልማት ላይ አይደለም። መንግሥታዊ አካሉ የስፖርት ልማት የማከናወን ኃላፊነትን እንጂ፤ የመምራቱን ስልጣን ለስፖርት ምክር ቤቶች ነው የሚሰጠው፤ የመንግሥት ሚና በፖሊሲና በስትራቴጂ በማስደገፍ የህግ ማዕቀፍ በማ ውጣት በበጀትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ስፖርት ምክር ቤቶቹን፤ የኦሎምፒክ ኮሚቴን፤ ክለቦችን መደገፍ ነው። በበላይነት መሥራት የሚገባቸው ስፖርት ምክር ቤቶችና ፌዴሬሽኖች ናቸው። መንግሥታዊ አካሉ ፌዴሬሽኖችን በራሱ አምሳል ቀርጾ አስቀምጧቸዋል። በሀገ ራችን 28 ፌዴሬሽኖች ይገኛሉ። የቱ ነው ራሱን የቻለው? መንግሥታዊ አደረጃጀቱ ራሱን አላበቃም፤ አልቻለም። አብዛኛዎቹ ፌዴሬሽኖች ስትራቴጂ የላቸውም። ከክልል ጋር የሚያገናኛቸው መዋቅር በሚፈለገው ደረጃ አልተዘረጋም። ከፌዴራል ጋር ብቻ መንጠልጠሉ ውጤት አያመጣም። የታመመውን ስፖ ርት ማዳን ይቻላል። ችግሮቹ በትክክል በመኖራቸው ላይ መተማመን መቻሉ የመጀ መሪያው ደረጃ ነው። ይህ ከሆነ ህዝባዊ አደረጃጀቱም ሆነ መንግሥታዊው ወደሌሎች ጣቱን መጠቆም የለበትም፤ ወደ ራሱ መመልከት ይገባዋል። ስፖርቱ ህዝባዊ መሰረት እንዲይዝ፤ አደረጃጀቱ ጠንካራ መሰረት እንዲኖረው ማድረግ ይገባል። በፖሊሲው ላይ፤ “ህዝቡ በሚኖርበት፤ በሚሠራበት፤ በሚማርበት አካባቢ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ማመቻቸት ይገባል፤ ይጠበቃል” ይላል። ነገር ግን፤ ህዝቡ በሚገባ ራሱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ቢሻ ለመሥራት የሚችልበት ሜዳ የለም። ከማዘውተሪያ ስፍራ ጋር ተያይዞ ያሉትን ጉድለቶች መሙላት ያስፈልጋል። ባለሀብቱም በስፖርቱ ሊሳተፍ ይገባል። ክለቦችን በማቋቋም፤ ማዘውተሪያ ቦታዎችን በመገንባት፤ ወዘተ. መሳተፍ ከቻለ ስፖርቱን በተባበረ ክንድ ማዳን ይቻላል። በትምህርት ቤቶች ስፖርቱን ማጠንከር፤ በከፍተኛ ተቋማት ያለውን ሁኔታ ተገንዝቦ መሥራት ይገባል። የኢትዮጵያን የስፖርት ችግር በሚፈታ መልኩ እያስተማሩ እንዳልሆነ ግልጽ እውነት ነው። ስለዚህ በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው ትምህርት በአግባቡ መሆን ይገባዋል። በሌላ ወገን፤ የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል የስፖርት ዘርፉን እየጎዳ በመሆኑ የአገሪቱ ስፖርት የሚመራበት ወጥ የሕግ ማዕቀፍ የለም። ስለዚህ ስፖርቱን ለመምራት የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ይገባል። የስፖርት አካዳሚዎችና ማዕከላትም ስፖርቱን በሚፈለገው እንዲደግፉ ማጠናከር ይገባል። በአገራችን ስፖርት ከተጀመረ ረጅም ዕድሜ አስቆጥሯል። ስፖ ርት የአገራችንን ስም፤ ዝናና ክብር ከፍ ሲያደርግ ቆይቷል። ነገር ግን፤ ስፖርታችን በጥሩ ቁመና ላይ አይደለም። ለዘርፉ ያለው አመለካከት፤ እሳቤ ለሚጠበቅበት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ የሚመጥን አይደለም። ስፖርት ለኢኮኖሚው ያለው ፋይዳ፤ ስፖርት ማህበራዊ ትስስርን ለመፍጠር ያለውን ጠቀሜታ፤ ስፖርት ለፖለቲካው ያለውን አስተዋጽኦ በሚገባ መረዳትና አመለካከትን ማስተካከል ያስፈልጋል። የኛ ስፖርት ሰላምንና ልማትን ማገዝ ተስኖት ራሱ አጋዥ ይፈልጋል።ስፖርታችን ውስብስብ ችግሮች ያሉበት እና ጊዜ የሚፈልግ ቢሆንም ማስተካከል ይቻላል። ዋናው ጉዳይ በይቻላል መንፈስ መሥራቱ ነው። ሚዲያው ትልቅ ኃላፊነት አለበት። ስለዚህ ሁላችንም የበኩላችንን በብቃት ከተወጣን የአገራችንን ስፖርት ማስተካከል ይቻላል።ሁላችንም የየድርሻችንን በብቃት እንወጣ፤ ይህ አገራዊ ጥሪ ነው። እኔም አመሰግናለሁ!አዲስ ዘመን ሚያዝያ 2/2011ዳንኤል ዘነበ", "passage_id": "6f7df1523ec430992651745bae94e00f" } ]
7004703c5675339f68245554721d8e21
c2116d9c852f65fce77b7b7a9de24ef3
‹‹ፋሲል ከነማ›› – የትውልድ ቅብብሎሽ አርማ!
 በአገራችን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በእግር ኳሱ ትልቅ ተፅዕኖ እያሳደሩ ከመጡ ክለቦች አንዱ ፋሲል ከነማ ስለመሆኑ ማረጋገጫ አያስፈልግም። ክለቡ የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ መሆኑን ካረጋገጠ ወዲህ በጥቂት ዓመታት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋልታና ማገር የሆኑ በርካታ ተጫዋቾችን ከማበርከት ባለፈ በፕሪሚየር ሊጉ የዋንጫ ተፎካካሪ በመሆን በተደጋጋሚ ዓመታት ጥንካሬውን አሳይቷል። በቁጥርም በውበትም የእግር ኳሱን ቤተሰቦች ያስደመሙ ደጋፊዎችን በማበርከትም ካምቦሎጆን ካደመቁ ጥቂት ክለቦች መካከል አንዱ ሆኗል። የውብ ደጋፊዎች ባለቤት የሆነውን ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ከብዙ በጥቂቱ በዛሬው የስፖርት ማህደር አምዳችን እንደሚከተለው ለመመልከት ወደድን።1960 ዓ.ም ጎንደር ከተማ ላይ የያኔ ወጣቶች በአገሪቱ የነበሩ ትልልቆቹን የእግር ኳስ ቡድኖች (አሥመራ ቡድን፣ ሸዋ ቡድን፣ አየር ኃይል ቡድን፣…) እያሰቡ፤ አንድ ትንሽ የእግር ኳስ ቡድን በራሳቸው ጥረት መሰረቱ። በጨርቅ ኳስ የተጀመረው የእግር ኳስ ቡድን ስብስብ ብዙ የተለየ እንቅስቃሴ ሳያድርግ ስድስት ዓመታት ተቆጠሩ። ስብስቡ የሰፈር ጨዋታዎችን ከማካሄድ ሳይሻገር ኢትዮጵያ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ አስተናገደች። ሕዝባዊ አብዮት። የ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት የአገሪቱን ፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ መዋቅሮች ብቻከገጽ 20 የዞረሳይሆን ማህበራዊ መዋቅሩንም ቀየረው። የለውጡ አካል የነበረችው ጎንደር፤ በሥር ነቀል ሂደቱ ውስጥ ስታልፍ በከተማው ውስጥ ከስድስት ዓመታት በፊት የተመሰረተው የእግር ኳስ ቡድን እንደዘመኑ መንፈስ አዲስ የቡድን ስያሜ ያዘ። ‹‹ትግል ፍሬ የእግር ኳስ ቡድን›› ተሰኘ። አሁን ጊዜው 1967 ዓ.ም ሆኗል።የትግል ፍሬ የእግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾች በአብዛኛው የቀበሌ 16 በተለምዶ ‹‹ቸቸላ›› ተብሎ የሚጠራው ሰፈር ልጆች ናቸው። በጊዜ ሂደት ግን ከየአቅጣጫው ቡድኑን የተቀላቀሉት የከተማዋ ወጣቶች አልጠፉም። መካሻ፣ አባቡ፣ ሰጠኝ፣ አራጋው፣ … የትግል ፍሬ እግር ኳስ ቡድን ሞተር ነበሩ። በእግር ኳስ ያበደ ልባቸው በፖለቲካ ለመቅለጥ ጊዜ አልፈጀበትም። አብዛኛዎቹ የቡድኑ አባላት በኢህአፓ የፖለቲካ መስመር ተጠለፉ። እንደዘመኑ መንፈስ፤ ህብዑ ገቡ። ይህም ሆኖ ትግል ፍሬ የእግር ኳስ ቡድን ከአቻዎቹ ጋር የእግር ኳስ ግጥሚያ ከማካሄድ አልቆመም። የግጥሚያ ሜዳው በየጊዜው ይቀያየር ነበር። ጎንደር ሆስፒታል ግቢ ውስጥ በተለምዶ ‹‹ኳስ ሜዳ›› ተብሎ በሚጠራው ሜዳ፣ ፋሲለደስ መዋኛ ግቢ ፊት ለፊት (ዛሬ ላይ ፋሲለደስ ስታዲየም ተብሎ የተሰየመው)፣ ፋሲለደስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ፣ … የእግር ኳስ ውድድሮች በተዘጋጁ ቁጥር ትግል ፍሬ የእግር ኳስ ቡድን ተሳታፊ ነበር።የደርግ ምህረት የለሽ ቅጣት በኢህአፓ ወጣቶች ላይ እየበረታ ሲመጣ፣ የመላኩ ተፈራ ፈርዖናዊ እብሪት በጎንደር አደባባዮች ላይ ናኘ። ከተማዋ በደም አበላ ታጠበች። ትግል ፍሬ የእግር ኳስ ቡድን ቅርቃር ውስጥ ገባ። የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋቾች መመናመን ጀመሩ። ያም ሆኖ የቀይ ሽብር ዘመን አልፎ እንኳ ቡድኑ አልከሰመም። መደብዘዙ ግን አልቀረም።ትግል ፍሬ የእግር ኳስ ቡድን ‹‹ዓለም የለምም›› ሳይባል ዓመታት ነጐዱ። ደርግ በድራማዊ አጀብ እንደተከሰተው፤ በትራጄዲ ሁነት ተሰናበተ። ትግል ፍሬ እንደ አጀማመሩ ባይሆንም ቡድኑ በሥም ደረጃ ይንቀሳቀስ ነበር። ከደርግ ውድቀት በኋላ ግን ትግል ፍሬ በስምም ከሰመ። ለሁለት ዓመት ብቻ። 1985 ዓ.ም የትግል ፍሬ ተከታይ ትውልድ በአዲስ መንፈስ ‹‹ፋሲል›› በሚል ሥያሜ የእግር ኳስ ቡድን ተቋቋመ። ፋሲል ከነማ የሚለው ስያሜ የሽግግር መንግሥቱ ጊዜ ካበቃ በኋላ በተፈጠረው የከተሞች አደረጃጀት የመጣ ስያሜ መሆኑ እዚህ ላይ ይነሳል።1985 እና ከዛ በኋላ የነበሩ ዓመታት እንደ ቀዳሚዎች ዓመታት ከፖለቲካና ኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች አኳያ ለጐንደር ፈታኝ ጊዜያት ነበሩ። ማህበራዊ ቀውሶች በተጨማሪነት ቢስተዋሉም በእግር ኳስ ረገድ ግን ጥሩ መነቃቃት ነበር። ዛሬ ላይ ‹‹ታየ በላይ ሆቴል›› የተገነባበት ቦታ ‹‹ሜክሲኮ ሜዳ›› ይባል ነበር። በዚህ መለስተኛ ሜዳ በመሬት አርድ የእግር ኳስ ደጋፊዎች የታጀበ የእግር ኳስ ውድድር መርሃ ግብሮች ይካሄዱ ነበር። አራዳ፣ ውሃ ልማት፣ ፖሊ፣ ኳሊበር፣ ኒያላ፣ ኢዲዲሲ … የተሰኙ የእግር ኳስ ቡድኖች ቀንደኛ ተፋላሚዎች ነበሩ። ከእነዚህ ቡድኖች ውስጥ የተሻለ የመጫወት ጥበብ ያላቸው ተጫዋቾች ለፋሲል እግር ኳስ ቡድን መጋቢ በመሆን አገልግለዋል። የያኔው ፋሲል ከ‹‹ሜክሲኮ›› ጨዋታ ከፍ ባለ መልኩ ከወረዳ የእግር ኳስ ቡድኖች ጋር ይጫወት ነበር። ‹‹ፋሲል ከነማ የትውልዶች ቅብብል ውጤት ነው›› የሚባለውም ለዚህ ነው።የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አደረጃጀትና የአሰራር ዝግመታዊ ለውጥን ተከትሎ ፋሲል ከነማ ለዓመታት በከተማ ደረጃና በብሔራዊ ሊግ ደረጃ ሲጫወት ቆይቶ፤ በ2008 የውድድር ዘመን ብሄራዊ ሊጉን በበላይነት በማጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፕሪሚሪ ሊግ ተሳታፊ ለመሆን በቃ። የትውልድ ቅብብሎሽ በታየበት በዚህ የታሪክ ሂደት መሰረት ክለቡ 50 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ አንጋፋ ክለብ ነው።‹‹ፋሲል ከነማ በትውልዶች ቅብብል የቆመ የከተማችን እግር ኳስ ክለብ ነው›› የሚለው አቋም የክለቡ ደጋፊዎች የጋራ ምልከታ ነው። በተለይም ክለቡ በብሔራዊ ሊግ ቆይታው በነበረበት የገንዘብ እጥረት የተነሳ ፈታኝ ጊዜያትን አሳልፏል። በ2008 ዓ.ም የብሔራዊ ሊጉ የውድድር ዘመን ፋሲል ምድቡን በበላይነት እየመራ እንኳን ከተማ አስተዳደሩ ለክለቡ የበጀተው በጀት በዓመቱ አጋማሽ አልቆ ነበር። በክለቡ ስም የንግድ ትርዒት (ባዛር) እና የሙዚቃ ዝግጅት (ኮንሰርት) በማዘጋጀት ገቢ በማሰባሰብ፤ በጐንደር ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ፤ በከተማው ወጣቶችና አጋር የስፖርቱ ቤተሰቦች ጥረት እንዲሁም ዳሽን ቢራ ፋብሪካ በሰጠው ገንዘብ ዓመቱን እንደምንም ቆይቶ ብሔራዊ ሊጉን በድል በማጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ለመቀላቀል በቃ።ለብዙዎቹ የአገሪቱ እግር ኳስ ተከታታዮች ክስተት በሆነ መልኩ የፋሲል ከነማ ስኬታማ የሚባል ጉዞ ያለ ደጋፊው ማዕበል የሚታሰብ አልነበረም። የክለቡ ደጋፊዎች ፋሲል ከነማን እንደ አንድ የጎንደር የታሪክ አካል አድርገው ይመለከቱታል። ከዚህ ምልከታቸው በመነሳት ለክለቡ የሚያደርጉትን ድጋፍ ማቀጣጠያ ዘዴያቸውም ታሪክ ነው። ‹‹የጎንደር ክብሯ ታሪኳ ነው›› የሚሉት የክለቡ ደጋፊዎች፤ የፋሲል ከነማ ክለብ ዋና መለያ ‹‹አፄዎቹ›› ሆኗል። በፖለቲካ አፈና፣ በማህበራዊ ሕይወት ብክነትና በኢኮኖሚ መገፋት ተበታትነው የነበሩት የጎንደር ከተማና አካባቢዋ ወጣቶች ፋሲል ከነማ ምክንያት ሆኗቸው በአንድነት ጥላ ስር ተገናኝተዋል። በፋሲለደስ ስታዲየም፤ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና ጓዶቹ ስማቸው እየተነሳ ተዘምሮላቸዋል። አርበኛ ጐቤ መልኬ ታስቦበታል። ዛሬ ላይ ፋሲል ከነማ በአገሪቱ ቀዳሚ የደጋፊ ሃብታም ከሚባሉ ክለቦች አንዱ ብቻ ሳይሆን ጠንካራ ተፎካካሪም ሆኗል። የድጋፍ መሰረቱ የሰፋውን ያህል ግን የገቢ አቅሙን ማሳደግ አልቻለም። ትላንት፣ ዛሬም ሆነ ነገ ዘመናዊ አደረጃጀትና ዘላቂ የገቢ/ስፖንሰር ምንጭ ዕጥረት የክለቡ ፈተና ሆነው ይቀጥላሉ። ፋሲል ከነማ ካስቆጠረው ዕድሜና ከመጣበት የታሪክ ሂደት አኳያ በአደረጃጀት ተገቢ በሚባል ደረጃ ላይ ይገኛል ማለት ስህተት ይሆናል። በየዘመኑ ግን ህያው የሕዝብ ድምፅ በመሆን የትውልድ ቅብብሎሽ አርማ ሆኖ አገልግሏል። እያገለገለም ነው።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 11 ቀን 2012 ዓ.ም ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=30665
[ { "passage": "ባሕር ዳር፡ መስከረም 09/2013ዓ.ም (አብመድ)  ዘመነ ኢሕአዴግ ‘ከተደገፈው የተነቀፈው፣ ከሠራው ያፈረሰው፣ ከሰበሰበው የበተነው፣ ካቀራረበው ያራራቀው፣ ካፋቀረው ያጣላው ይበዛል’’ ይሉታል፡፡ ‘‘ኢትዮጵያዊነት እንዲሸረሸር፣ ዘረኝነት እንዲስፋፋ፣ አንድነት እንዲቀበርም ሠርቷል’’ ተብሎም ይወቀሳል፡፡ በዘመነ ኢሕአዴግ ኢትዮጵያውያን ከአንድነታቸው ይልቅ ልዩነተቻው ከፍ ብሎ እንዲታያቸው እና ‹‹እኛ›› ከማለት ይልቅ ‹‹እኔ›› ማለት እንዲቀድምባቸው እንደተደረገ ይህም በኪነ ጥበቡ ውስጥም እንደገባ ሐያሲዎች ይናገራሉ፡፡ወታደራዊው መንግሥት ኃይልን በዋና መሣያነት ቢጠቀምም በኢትዮጵያዊነት ግን ለድርድር ተቀምጦ እንደማያውቅ ይገለጻል፡፡ ለኢትዮጵያ እንድነትና ለመንግሥቱ አብዮት ደግሞ ኪነ ጥበብን በሚገባ ይጠቀምበት ነበር፡፡ ለዚህም ይሆነው ዘንድ በየክፍለ አገራቱ ጠንካራ የሆኑ የኪነ ጥበብ ቡድኖች እንዲመሠረቱ አድርጎ ነበር፡፡ በዚያነው ‘‘የሕዝብ ለሕዝብ’’ አገራዊ ሥራው ዓለምን እየዞረ የኢትዮጵያን ብዝኃነትና አንድነት ያስተዋወቀ የሥርዐቱ ወቅት የኪነ ጥበብ ጉልላት እንደነበር ብዙዎች ይስማማሉ፡፡በደርግ ዘመነ መንግሥት ጊዜ በአማራ ክልል ሦስት ታላላቅ የኪነ ጥበብ ቡድኖች ተቋቁመው አጀብ ያስባሉ የጥበብ ሰዎች ተፈጥረዋል፡፡ ወሎ ላልይበላ፣ ግሽ ዓባይና ፋሲለደስ የባህል ቡድኖች ስማቸው ከፍ ብሎ ከሚነሱት የባህል ቡድኖች ነበሩ፡፡ ዛሬ የፋሲለደስ የባሕል ቡድንን ጉዞ ለመቃኜት ወደድን፡፡የቀድሞው ፋሲለደስ ባህል ኪነት የአሁኑ ፋሲለደስ ባህል ቡድን በኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ታሪክ ዝናቸው ከፍ ካሉ የኪነ ጥበብ ቡድኖች መካከል ከግንባር ቀደሞቹ ይገኝበታል፡፡በዚህ የኪነ ጥበብ ቡድን አስደናቂ የጥበብ ሰዎች ተገኝተውበታልና፡፡ በዘመነ ደርግ የአገሪቱ የባህል ሚኒስቴር የኪነ ጥበብ ዘርፉ እንዲያድግ ፍላጎት ነበረው፡፡ ይህን ጥበብ ከፍ ለማድረግም ከወትሮውም በቡድን ሳይደራጅ በተሰጥዖ ጥበብ በሚንቆረቆርበት የጎንደር ክፍለ አገር የበለጠ ለማዳበር የኪነ ጥበብ ቡድን ለመመሥረት ታሰበ፡፡ኪነ ጥበብ በጎንደር ዘመን ጀምሮ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጠው እንደነበር ይነገራል፡፡ ከጎንደር ነገሥታት መካከል ዮሐንስ ሦስተኛ የጥበብ ፍቅር ስለነበራቸው ‘‘የጥበብ ሰዎችን ወደቤተ መንግሥት እያሰባሰቡ በጥበብ ይመሰጡ ነበር’’ ይባላል፡፡ ይህ ጥበብ ሲወርድ ሲወራረድ ቀጥሏል፡፡ በዘመነ ኃይለሥላሴም የፖሊስ ኪነት በመባል በጎንደር ከፍ ያለ የኪነ ጥብብ ድግስ ይደገስ እንደነበር ይነገራል፡፡ የዙፋን ዘመን አልቆ የደርግ ዘመን ተተካ፡፡ የወቅቱ የባህል ሚኒስቴር ታወቂውን አውላቸው ደጀኔን በመላክ ጎንደር ላይ አንድ የጥበብ ቡድን እንዲመሠረት ወሰነ፡፡አውላቸው ደጀኔ ከታዋቂው የባህል ሙዚቀኛ ጋሽ ይርጋ ዱባለ ጋር በመሆን በመጠጥ፣ በሠርግ፣ በዓመት በዓልና በተለያዩ አጋጣሚዎች እየተገኙ ከያኒያንን ማሰባሰብ ጀመሩ፡፡ ዘጠና የሚሆኑ አዝማሪዎችንም ሰብስበው በበጎ ፈቃደኛነት በማኅበር አደራጇቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል ከማሲንቆ ተጫዋችነት ባለፈ በድምጽ የሚያንጎራጉሩና ውዝወዜ የሚችሉ 33 ሰዎች ተመርጠው በአውላቸው አማካኝነት ስልጠና ይሰጣቸው ጀመር፡፡ በአጭር ጊዜም ‘‘ታግሎ አታጋይ’’ በሚል ስያሜ በ1969 ዓ.ም የኪነት ቡድን ተመሠረተ፡፡ ከያንያኑም በጥቂት ጊዜያት ከበርካታ ሰዎች ጋር የመላመድና ሙያውን የማጎልበት ዕድል ገጠማቸው፡፡ የመወዝ ጉዳይ ግን ለኪነት ቡድኑ ፈታኝ ነበር፡፡ይህ የኪነት ቡድን አንድነትን ከሚያጠናክሩና ኢትዮጵያዊነትን ከሚሰብኩ የሙዚቃ ሥራዎች በተጨማሪ የቲያትር ሥራዎች በመሥራት በአጭር ጊዜ ውስጥ አንቱታን አተረፈ፡፡ የኪነት ቡድኑ በተመሠረተ በሁለት ዓመቱ ጅግጅጋ ላይ በተዘጋጄው የእናት አገር ጥሪ በዓል ላይ ተሳታፊ ነበር፡፡ በዚህ በዓልም አንደኛ በመሆን ተሸላሚ መሆን ቻለ፡፡ዕድገቱ ከፍ እያለ ሄደ፡፡ ከጥቂት ዓመታት በኃላ ስሙን ‘የራስ ደጀን ኪነት’ ወደሚል ቀዬረ፡፡ የኪነት ቡድኑ በርካታ መልካም የሚባሉ ሥራዎችን ቢሠራም የአባላቱ ዘመናዊ ትምህርት አለመማር ኪነቱን ይፈትነው ነበር፡፡ የኪነት ቡድኑ ዘመናዊ ትምህርት እንዲቀስሙ የባህል ሚኒስቴር ጋሽ ቀለመወርቅ ደበበን ወደጎንደር ላከ፡፡ ጋሽ ቀለመወርቅ ደበበ በተለያዩ አውራጃዎች ተዝዋውረው 32 ሰዎቸን መረጡ፡፡ የተመረጡትን የጥበብ ሰዎች ለዘጠኝ ወራት ተውኔት፣ ሙዚቃና ሌሎች ስልጠናዎችን ሰጥተው ሕዳር 2 ቀን 1976ዓ.ም አስመረቁ፡፡ በዚህ ጊዜ የኪነት ቡድኑ ስሙ የበለጠ የታወቀበትን ‘ፋሲለደስ ኪነት’ የሚል ስያሜ ያዘ፡፡የኪነት ቡድኑ በጋሽ ቀለመወርቅ ደበበ የተደረሰ ‘መረዋ’ የተሰኜ ተውኔት አዘጋጅቶ አሰብን ጨምሮ በያኔው የኢትዮጵያ ክፍለ ሀገራት በመዘዋወር በማቅረብ ስሙን ከፍ አድርጓል፡፡ የኪነት ቡድኑ የመጀመሪያ የተውኔት ሥራው ‘ጎራው ብቅ በል’ የሚል እንደነበር ታሪኩ ያሳያል፡፡ ከዚህ ተውኔት በመቀጠል ‘ቢሮ›› የተሰኜው ተውኔት ከጎንደር ውጪ ለአራት ወራት በአስራ አንድ ክፍለ ሀገራት ተዘዋውሮ በማሳዬትም በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፎ ነበር፡፡በዚህ የኪነት ቡድን ጋሽ ይርጋ ዱባለ፣ ታማኝ በዬነ፣ አሰፉ ደባልቄ፣ እንዬ ታከለ፣ አበበ ብርሃኔ፣ አበበ በለው፣ ሡራፌል ተካ፣ ሳሊህ አብደላ እና ሌሎችም እንቁ ሰዎች ወጥተውበታል፡፡ ይህ የኪነት ቡድን ዕድሜው የሰነበተው ግን ኢሕአዴግ ሥልጣነ መንበሩን እስኪረከብ ድረስ ነበር፡፡ ኢሕአዴግ ስልጣኑን እንደያዘ አብዮተኛን ሲኮንን ‘‘ጥበበኞችም የአብዮቱ ፍሬዎች ናቸው’’ በሚል ቡድኑን አፈረሰ፣ የኪነ ጥበብ ሰዎችም በነጻነት እንዳይንቀሳቀሱ ተደረገ፡፡ ልብ ይበሉ ፍቅርና ኢትዮጵያዊነትም መጎዳት የጀመረው እዚህ ላይ መሆኑ ይነገራል፡፡ በነገራችን ላይ ሙዚቀኞች አልበም ሲያወጡ ስለእናት ሀገር አንድ ሙዚቃ ማካተት በደርግ ዘመነ መንግሥት የኪነ ጥበብ ሰዎች ግዴታ እንደነበር ይነገራል፤ ብዙዎቹ በዚህ ዘመን የሚደመጡ ሀገራዊ ስሜት ያላቸው ሙዚቃዎች ውልደትም ያኔ ነው፡፡የክራርና የድምጽ ተጫዋቹ፣ የዜማና የግጥም ደራሲውና የቀድሞው የጎንደር ባህል ማዕከል ሥራ አስኪያጅ ጋሽ ስለሺ መስፍን ከአብመድ ጋር በነበራቸው ቆይታ ‘‘የኪነት ቡድኑ ምንም እንኳን አብዮቱ እንዲቀጣጠል ታስቦ የተቋቋመ ቢሆንም የአገር ፍቅር እንዲጎለብት ከፍተኛ ድርሻ ነበረው’’ ብለዋል፡፡ ‘‘ፋሲለደስ በመፍረሱ የአገር ፈቅር ስሜትና የጥበብ ሥነ ምግባርቀንሷል’’ ነው ያሉት፡፡ በዚህ ዘመን የፈረሰው ፋሲለደስ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ስለነበሩ ነው የአገር ፍቅር ስሜቱና ጥበቡ እንዲንሸራተት የሆነው፡፡ ‘‘ደርግለጥበብ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ነበር’’ ያሉት ጋሽ ስለሺ በዚህ ዘመን ግን ኪነ ጥበብ መቀዛቀዙን እንደታዘቡ ነግረውናል፡፡ ‘‘የኪነት ቡድኖችን ማፍረስ ሳያንሳቸው ማሲንቆ የያዘ ሁሉ እንዲያፍርና ከጥበብ እንዲርቅ ይደረግ ነበር’’ ነው ያሉኝ፡፡ እንዲህ መሆኑ አሁን ላይ ዘመን ተሸጋሪ የኪነ ጥበብ ሥራዎች እንዳይሠሩና አቅም የነበራቸው ሰዎች ተሸማቅቀው እንዲቀሩ እንዳደረገ ተናግረዋል፡፡የባህል ተጫዋቾች በመቀነሳቸውና በመሸማቀቃቸው ባህል እንዲበረዝ ምክንያት መሆኑንም ያስረዳሉ፡፡ ‘በዚያ ዘመን የተሠሩ የጥበብ ታሪኮች እንዲጠፉ ተደርገዋል’’ ነው ያሉት ጋሽ ስለሺ፡፡ ደርግ ሥርዓቱ አስፈሪ ቢሆንም ስለአገር ፍቅር ይሠራ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡ በእርግጥ ደርግ ጥበቡ ከአገር ፍቅሩ ጎን ለጎን አብዮቱን ለማቀጣጠል ስለተጠቀመበት ያስተቸዋል፡፡ በየክፍለ አገራቱ የሚገኙ የኪነት ቡድኖች እርስ በርስ እየተገናኙ የባህል ትውቅቅ ያደርጉ እንደነበር ያስታወሱት ጋሽ ስለሺ በዚያ ዘመን የነበሩ ባህላዊ ጭውውቶች አሁን ላይ እንደጠፉም ተናግረዋል፡፡ከዓመታት ቆይታ በኋላ በጎንደር ግንቦት 19/2008 ዓ.ም ‘‘ፋሲለደስ የባሕል ቡድን’’ ተብሎ እንደገና ተቋቁሟል፡፡ ለዚህም የሙዚቃ ባለሙያው ሡልጣን ኑሪ ታላቅ ድርሻ ነበረው፡፡ ይህ ቡድን በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ መልካም የሚባሉ ሥራዎች ቢሠራም ያልተበረዘውን ባህል በመሥራት ረገድ ግን ክፍተት እንዳለበት ነው ጋሽ ስለሺ የነገሩኝ፡፡ ያልተበረዘውን ባህል ለማቅረብም የባህል ቡድኑ ገጠር ሄደው ባህሉን እንዲያዩ እንደተደረገ ሥ ነቃል፣ ዜማና ውዝዋዜ እንዲያዩና እንዲያመጡ እየተደረገ መሆኑንም ሰምቻለሁ፡፡ ቀደም ባለው ጊዜ የኪነ ጥበብ ሰው እንደጦር ሠራዊት ጥንቃቄ ያደርግ እንደነበር ያስታወሱት ጋሽ ስለሺ ለዓመታት ትኩረት ስለተነፈገው የኪነ ጥበብ ሥነ ምግባሩ እንደቀነሰ ነው የተናገሩት፡፡ የጥበብ ሰው ለጥበብና ለማኅበራዊ ግዴታ መሥዕዋት መሆን እንዳለበትም ይመክራሉ፡፡ የደከመውን የጥበብ አብዮት ለመመለለስ በትኩረት መሥራት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ ‘‘በጥበብ ያደገ ሰው አገራዊ ፍቅሩ ከፍ ያለ ነው፤ ጥበብንና አገሩን የማድመቅ ዕድሉም ከፍ ያለ ነው’’ ብለዋል፡፡ መንግሥትም ለሥራው ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡ ባህሉን ያልጠበቀ ሙዚቃና ማናቸውም የኪነ ጥበብ ሥራ መገሰጽ እንዳለበትም መክረዋል፡፡የአሁኑ የፋሲለደስ የባህል ቡድን ዋሽንት ተጫዋች፣ የዜማና የግጥም ደራሲና ድምጻዊ አስፋው መለሰ ‘‘ከድሮው የተሻለ ነገር አሁን ላይ አለ፤ ከድሮው ያልተሸለ ነገርም አሁን ላይ አለ፤ አሁን ላይ መሣሪያው ያደገ ነው፤ ይህ የተሻለው ነው፡፡ የድሮው ትክክለኛ ባህሉን ይሠራ ነበር፤ አሁን ላይ እንዲቀዬጥ ሆኗል፤ ይህ ደግሞ ያልተሻለው ምሳሌ ነው’’ ብሏል፡፡ በመካከል ላይ ተቋርጦ መቆዬቱ የባህል ጨዋታዎች እንደነውር እንዲቆጠሩ ማድረጉንም አንስቷል፡፡ ተተኪው ትውልድ ባህሉን እንዳያውቅ መደረጉንም እንዲሁ፡፡ ‘‘ኪነጥበብ አገር አፈራሽም አገር ሠሪም ነው’’ ያለው አስፋው ከሌሎች ጋር ሳይሆን ራሱን የቻለ ተቋም ሆኖ የኪነ ጥበብ ሰው እንዲመራው መደረግ እንደሚገባውም አሳስቧል፡፡", "passage_id": "8570e489e8e9e47657594c9a881494e4" }, { "passage": "እንየው ካሳሁን የፋሲል ከነማ የመጀመርያ ፈራሚ በመሆን ለዝግጅት ወደ ባህርዳር አቅንቶ ቡድኑን ተቀላቅሏል።ያለፉትን ሁለት ዓመታት በወልዋሎ ጥሩ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ ሊጉ ካለቀ በኋላ ከተለያዩ የሊጉ ትላልቅ ክለቦች ጋር ስሙ እየተነሳ ቢቆይም በመጨረሻም ለቀጣይ የአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ በስፋት በዝውውሩ እንደሚሳተፉ የሚጠበቁት ፋሲል ከነማዎች ማረፍያውን አድርጓል።ለፌዴራል ፖሊስ ፣ አዲስ አበባ ከተማ እና ወልዋሎ የተጫወተው ይህ ተጫዋች በዚህ ዓመት መጀመርያ ለኦሊምፒክ ብሄራዊ ቡድን መመረጡ ሲታወስ ለመጀመርያ ተሰላፊነትም ከሰዒድ ሐሰን ጋር ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል።", "passage_id": "b925497a95eb1939766b34cd6e6a6aa1" }, { "passage": "የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን ለፋሲል ከነማ ምስጋና አቅርቧል።ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ከሊግ ካምፓኒው ጋር በመሆን የ2012 የኢትዮጵያ የሊግ ውድድሮች እንደሰረዙ መወሰኑ ይታወሳል። ከዚህ ውሳኔ ጎን ለጎንም ክለቦች ለተጨዋቾቻቸው እስከ ኮንራት መገባደጃ ድረስ ደሞዝ እንዲከፍሉ ማሳሰቡ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግርኳስ ተጨዋቾች ማህበር ክለቦች ለተጨዋቾች ደሞዝ በአግባቡ እንዲከፍሉ ጥሪ በማድረግ በጊዜው ለተጨዋቾቻቸው ደሞዝ የከፈሉትን የወንዶች እና የሴቶች ፕሪምየር እንዲሁም የከፍተኛ ሊግ ክለቦችን ማመስገኑ ይታወሳል። ትላንትናም ይህ ማህበር ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ፋሲል ከነማን አመስግኖ ደብዳቤ ልኳል።ደብዳቤው ይህንን ይመስላል", "passage_id": "ff019c73b2bd9ac941588964465b3895" }, { "passage": "የረጅም ዓመት የቅዱስ ጊዮርጊስ የልብ ደጋፊ ነው። በሁሉም የፈረሰኞቹ ደጋፊዎች ዘንድም የሚከበር እና የሚወደድ ነው። ባለው የሙዚቃ ተሰጥኦ የሚወደውን ክለብ የሚያወድሱ በርከት ያሉ ዜማዎችን ሠርቷል። የዛሬው የደጋፊዎች ገፅ አምዳችን እንግዳ የሙዚቃ ባለሙያው እዮብ እድሉ (እዮባ ሳንጃው) ነው።ድምፃዊ ፣ የሙዚቃ መሳርያ ተጫዋች ፣ የሙዚቃ አቀናባሪ ፣ የግጥም ፀሐፊ ሁለገብ የሙዚቃ ባለሙያ ነው። ከልጅነት እስከ ዕውቀት የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊ ነው። በተሰጠው ፀጋ ለሚወደው ክለቡ የተለያዩ የሙዚቃ ስራዎችን በመስራት የክለቡን ታሪክ ፣ ጉዞ ፣ ስኬት እና ወጣ ውረድ አሁን ላለው ትውልድ ለወደፊትም ጭምር እያስተላለፈ ይገኛል። በዛሬ የደጋፊዎች ገፅ አምዳችን የረጅም ዓመት የቅዱስ ጊዮርጊስ የልብ ደጋፊ የሆነው እና በስራዎቹ ተወዳጅነትን ያተረፈው እዮብ እድሉን አቅርበናል። መልካም ቆይታቅዱስ ጊዮርጊስ እግርኳስን ለሚወድ ሰው ስሙ ሩቅ አይደለም። በሬድዮ የምሰማው ነገር እና ትልልቅ ሰዎች የሚያወሩት ስሰማ ያጓጓኝ ነበር። ስታድየም ደግሞ ሄጄ ሳየው የእኔነት ስሜቱ ተጋብቶብኛል። ህፃን ሆነንም ኳስ ስንጫወት የጊዮርጊስን መለያ በሹራብ ‘V’ አስረተን የምንለብሰው ፣ ታላላቆቻችንም የሚያደርጉት ነገር ከሰው መሀል ነጥሎ ጊዮርጊስን እንድንሳብ አድርጎናል። እኔም በባህሪዬ ለየት ያለ ነገር ስለሚማርከኝ በእነዚህ በእነዚህ ምክንያቶች ጊዮርጊስን መደገፍ ልጀምር ችያለሁ።አዎ በ1988 ላይ የአንደኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ ነው ፤ የጊዮርጊስ ወጣት ቡድን ከአየር መንገድ ጋር ሲጫወት ነበር የተመለከትኩት። ሆኖም ግን በተከታታይ ስታድየም እየገባው ኳስ ማየት የጀመርኩት 1994 ወይም 1995 ጀምሮ ነው። በጣም የሚገርም 1991 ላይም የመጀመሪያውን የፕሪምየር ሊጉን የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ቡናን የሸገር ደርቢ ጨዋታን ለማየት ችዬ ነበር። ያ ማለት ጊዮርጊስ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድግ ያደረገውን የመጀመሪያ ጨዋታ ማለት ነው። እንደሚታወቀው 1987 እና 1988 ጊዮርጊስ ቻምፒዮን ሆኖ 1989 ላይ ለብሔራዊ ቡድን ሄደው የጠፉ የዋና ቡድን ተጫዋቾች ነበሩ ፣ ለወጣት ቡድንም ሄደው የጠፉ ተጫዋቾች ነበሩ። በዚህ ምክንያት ከየትምህርት ቤቱ በሰበሰባቸው ተጫዋቾች ነበር የተጫወተው። በዚያ ዓመት ቡና ጊዮርጊስን 4-0 ሁሉ አሸንፎ ቻምፒዮንም ሆኖ ነበር። ቀጣዩ ዓመት ላይ ጊዮርጊስ እስከ ድሬዳዋው ጨዋታ ምንም ሳይሸነፍ መምጣት ችሏል። 1990 ላይ ኤልፓ ነበር ቻምፒዮን የሆነው። ከዚያ ነው 1991 ላይ የሊጉ መክፈቻ ላይ ጊዮርጊስ እና ቡና የተገናኙት። ያኔ እንደውም ትዝ ይለኛል ስታድየሙ ውስጥ የቡና ደጋፊዎች በመሐሙድ አህመድ ዜማ ‘እንዴት ይረሳል እንዴት ይረሳል ተረሳሽ ወይ ?’ ብለው ሲያዜሙ በጊዮርጊስ ደጋፊዎች በኩል ደግሞ በእሳቱ ተሰማ ዘፈን ‘ወደ ኋላ እየሄድሽ በሀሳብ ከማለም ፤ ቀኑ እንዳይመሽብሽ ትናንት ዛሬ አይደለም’ የሚል ምልልስ ነበር። በዚያ ጨዋታ ጊዮርጊስ 4-1 አሸንፎ የጨፈርንበትን በደንብ አስታውሳለሁ። ክፍለ ሀገር ደግሞ እየሄድኩ ማየት የጀመርኩት ከ1999 አካባቢ ጀምሮ ነው።በእርግጥ ሙያተኞች ሆነው በሙያቸው ጊዮርጊስን የሚያገለግሉ ደጋፊዎች ድሮም ነበሩ ፤ አሁንም ብዙ አሉ። ሙዚቃ በባህሪው የሚታይ እና የሚገዝፍ ስለሆነ የኔ ተጋነነ እንጂ ከሌሎች ደጋፊዎች የተለየ ነገር አድርጊያለው ብዬ አላስብም። ነገር ግን ለጥበብ ካለኝ ፍቅር አንፃር እግር ኳስም ያው ጥበብ አይደል ? አንዳንዴ መስራትም መብላትም እንደመፈለግ ዓይነት ፤ እንደዛ ሆነብኝ እና እግርኳሱን ከጊዮርጊስ ጋር አያያዝኩት እና በሙያዬ ለጊዮርጊስ አንድ ነገር ማበርከት አለብኝ ብዬ ጀመርኩኝ። ደግሞም የተለያየ ሙያ እያላቸው እኮ ለክለቡ በምን መንገድ ማበርከት እንዳለባቸው ያላወቁ ሰዎችም ይኖራሉ ፤ ለእነዛ ሰዎችም ምሳሌ ለመሆን ነው። ለኔ ሙዚቃ ስራዬ ነው። ማንኛውንም የሙዚቃ ስራዬን እንደምሰራው ነው የጊዮርጊስንም ስራ የምሰራው። እኔ ባለኝ ነገር በሙያዬ ነው እየሰራሁ ያለሁት። ይህ ደግሞ ከክለቤም አልፎ ለሀገርም ጭምር ትልልቅ አርቲስቶችም ተሳተፉበት ከእስከ ዛሬ ስራዎቼ በተለየ አኳኋን የተለየ ስራ እየተሰራ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየደረሰ ይገኛል።በሙዚቃ ደረጃ የሰራሁዋቸው ከ25 በላይ ናቸው። ለ80ኛ ዓመት ክብረ በዓል ተብሎ ደግሞ የተለመዱ እና አዳዲስ 10 የሚሆኑ ስራዎችን ሰርቻለሁ። በተጨማሪም ስታድየም ውስጥ እየተቀባበልን የምንዘምራቸው በአልበም ያልተካተቱ ከ15 በላይ ዜማዎችም አሉ። እኔ ሁሌም ቁጥራቸውን አላስበውም። ብዙ ሰው መሰጠት የሚለውን ነገር ሲያስበው መጉደል ያለ ይመስለዋል ፤ እኔ ግን እንደዛ አላስብም። እንደውም እርካታው በቃላት የማይገለፅ ነው። ያንን ስለማስብ እና ይህንን ስሜትም ስለምወደው ነው ሁሌም ስለመስራት የማስበው። ወደፊትም የምወደውን ክለቤን በሙያዬ ለማገልገል ሳልታክት የምችለውን ሁሉ በደስታ አደርጋለው። ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደታላቅነቱም እንደቀደምትነቱም እኔ ካደረኩለትም በላይ የሚገባው ክለብ ነው። እንደውም ያደረኩት በጣም ትንሽ ብዬ ነው የማስበው።እንግዲህ ይህንን የሚሉ ሰዎች የራሳቸው ምልከታ ይኖራቸዋል። እኔ ደግሞ እንደ አንድ ደጋፊ የምመለከተውን ነው መናገር የሚኖርብኝ። አብዛኛው ደጋፊ ስራውን ትቶ ፣ ቤተሰቡን ትቶ ፣ ገንዘብ አውጥቶ ፣ ጊዜውን ሰውቶ ፣ ዕውቀቱን ሰጥቶ ነው የሚመጣው ፤ እግርኳስን ከማየት አንፃር ብቻ። እኔ ጊዮርጊስን በማየት የማገኘውን ደስታ ማንም ሰው ፣ የትኛውም ኃይል አይሰጠኝም። እኔ ስታድየም የምመጣው ለራሴ ብዬ የትም ብሄድ የማላገኘውን ይህንን ደስታ ለማግኘት ስል ነው። አብዛኛው ደጋፊም እንደዚህ ብሎ ነው የሚመጣው። የጊዮርጊስ ብቻ ሳይሆን የትኛውም ደጋፊ ጓደኞቹንም አይቶ ይሁን በቴሌቭዥንም አይቶ የሚመጣው ለመደገፍ ነው። ይህን ስል ግን ከደጋፊነት ወደ ተደጋፊነት የሚያሸጋግሩ መስመሮች አይኖሩም ብዬ አላስብም። ነገር ግን አብዛኛውን ደጋፊ አይወክሉም። ቢበዛ 2% ቢሆን ነው ፤ እሱንም እርግጠኛ ሆኜ ሳይሆን የለም ብዬ መደምደም ስለማልችል ነው። አፌን ሞልቼ መናገር የምችለው ግን የየትኛውም ክለብ ደጋፊ መጀመሪያ የሚመጣው እግርኳሱን ብሎ መሆኑን ነው።በመሀከላችን ያለው ርቀት እንደተጠበቀ ሆኖ መስመራችንን ግን ማጥራት አለብን ብዬ አስባለሁ። ለምሳሌ በደጋፊ እና በደጋፊ መካከል ያለው ልዩነት እና አንድነት በግልፅ መቀመጥ መቻል አለበ። በዳኞች እና በክለቦች መካከል ፣ በክለቦች እና በክለቦች መካከል ፣ በተጫዋቾች እና በክለቦች መካከል ፣ በክለቦች እና በደጋፊዎች መካከል ፣ በክለቦች እና በጋዜጠኞች መካከል ፣ በድጋፊዎች እና በደጋፊዎች መካከል ፣ በጋዜጠኞች እና በደጋፊዎች መካከል ፣ በጋዜጠኞች እና በጋዜጠኞች መካከል ያለው ግንኙነት ሁሉ መጥራት አለበት ብዬ አስባለሁ። ይሄንን በሚገባ ካላጠራን በቀር አሁንም እግርኳሳዊ ያልሆኑ ምክንያቶች መፈጠራቸው የሚቀር አይመስለኝም። ሁሉም ነገር እግርኳሳዊ የሚሆነው አወቃቀሩንም እግርኳሳዊ ስናደርገው ነው። ይሄንን ለማድረግ ደግሞ ተነሳሽነቱ ሊኖር እንደሚገባ አስባለሁ።አዎ ‘ሀ’ ብለን ጀምረናል። ሰዉ ልዩነቶችን ማስታረቅ አንድ መሆን ይመስለዋል። ለምሳሌ ‘እኛ እና ቡና አንድ ነን’ ሲባል ወይም ቡናዎች ‘እኛ እና ጊዮርጊስ አንድ ነን’ ሲሉ እሰማለሁ። ይሄ የተሳሳተ አባባል ነው። አንድ አይደለንም። አንድ ብንሆንማ የተለያየ ክለብ አንደግፍም ነበር። ነገር ግን በልዩነታችን ተከባብረን እንደ አንድ መቆም እንችላለን። በተለያዮ ሜዳዎች የሚፈጠሩ እግርኳሳዊ ያልሆኑ ያልተገቡ ነገሮች መቀረፍ አለባቸው። ማንም ሰው ወደ ስታዲየም መጥቶ ያለ ስጋት በእግርኳሱ ተዝናንቶ፣ የሚወደውን ክለብ ባማረ ዜማ ደግፎ በደስታ መጥቶ በደስታ መመለስ አለበት። ይህንንም አስመልክቶ ከሌሎች ክለቦች ደጋፊዎች ጋር የተነጋገርኳቸው ልሰራቸው ያሰብኳቸው ስራዎች አሉ። ወደፊት የሚወጣ ይሆናል። ዞሮዞሮ ሙዚቃ ትልቅ ጉልበት ያለው በመሆኑ ይህን ተጠቅመን ሜዳዎቻችን ሰላማዊ አየር የምንተነፍስበት እንዲሆኑ ማድረግ አለብን።እንደሰው መቼም ፍላጎታችን ብዙ ነው። በእነባርሴሎና እና በእነማድሪድ ደረጃ ያሉ ክለቦችም የራሳቸው ፍላጎት ይኖራቸዋል። እኔም ክለቤ እዛ ደረጃ ይደርሳል ብዬ ተስፋ ያለኝ ሰው ነኝ። ለክለቤ ከዛሬ ለነገ ፣ ከነገው ደግሞ ከነገ ወዲያው ይሻላል ብዬ በክለቤ ላይ ትልቅ ዕምነት የምጥል ደጋፊ ነኝ። ክለቤን እንደ ልጄ ነው የማየው። ልጄ ኢንጂነርም ዶክተርም ሁሉንም ነገር ቢሆንልኝ ደስ ይለኛል። ባይሆንልኝም ግን ልጄ ነው። መጀመሪያ በእኔ እና በክለቡ መካከል ያለው ወዳጅነት ይበልጣል ብዬ ነው የማስበው። ከዚያ በኋላ ቀጣዮቹ በሀገር ፣ በክፍለሀገር ፣ በአህጉር አልፎም በዓለም ደረጃ ያሉ ስኬቶች ይመጣሉ ብዬ ነው የማስበው።በጣም ይከብዳል። አስጨፋሪ ስትሆን ስሜትህን ከመግለፅ ትቆጠባለህ። ስሜትህ ሰዎች ላይ ይጋባል፤ በክፉም ይሁን በጥሩ። እኔ በተሻለ መጠን ስሜቴን መቆጠብን ነው የምመርጠው። በጣም የሚያስደስትም የሚያሳዝንም አጋጣሚ ሲኖር ስሜቴን እቆጣጠራለሁ። እና ይሄ ጥያቄ ቢያልፈኝ እመርጣለሁ። ለእኔ ሁሉም ተጫዋቾች መልካም ናቸው። ከስብስብ አንፃር ግን ከ2005 እስከ 2007 የነበረውን ጊዮርጊስ በጣም እወደዋለሁ። ጥሩ ስብስብ ነበር ፤ ከታች የመጡ እነ ዮናታን ብርሀነ ፣ መስፍን ኪዳኔ ፣ ምንተስኖት አዳነ ፣ ታደለ መንገሻ ፣ ዘሪሁን ታደለ ፣ ኤልያስ ማሞ ጊዮርጊሳዊ መሰላሉን የጠበቁ ተጫዋቾችም የነበሩበትም ስለነበር በጣም እወደዋለው።አፌን ሞልቼ እናገራለሁ። ለኔ ምርጡ አሰልጣኝ ሚኬል ክሩገር ነው። አንዴ ልምምድ ሜዳ ላይ የለመድናቸውን ሦስት ድርድር ያላቸው (4-4-2/4-3-3) አሰላለፎችን ለምን እንደማይጠቀም ስጠይቀው ‘ኢትዮጵያዊያን ተጫዋቾች የፊትነስ ደረጃቸው ዘጠና ደቂቃ የሚያጫወታቸው አይደለም። ባለሦስት ድርድር አሰላለፍ ከሆነ አንድ ተጫዋች በአማካይ 45 ስኴር ሜትር መሸፈን ይኖርበታል። አራት ከሆነ ግን ወደ 33 ትቀንሰዋለህ ተጫዋቹም ትንፋሸን እንዲቆጥብ ይረዳዋል’ አለኝ እና ‘አሁን ካሉት ተጫዋቾች ውስጥ በፊትነስ እና በፍጥነት የተሻለ የምትለው ማነው ?’ አለኝ። ‘አሉላ ግርማ’ አልኩት። አሉላን ጠራውና ከአንደኛው ጎል ጫፍ እስከሌላኛው ጎል ጫፍ አስሮጠው። ቀጥሎ ‘ኳስ እየገፋህ ሂድ’ አለው። ኳስ እየገፋ በ20 ወይ በ21 ሰኮንዶች ደረሰ። ‘ይሄ ማለት ዳንኤል አልቬስ የሚፈጅበት ሰዓት ነው’ አለኝ። ከዛ ‘ይዘህ ተመለስ’ አለው። ሲመለስ ደግሞ ከአንድ ደቂቃ በላይ ፈጀበት። ‘ይሄ ደግሞ ዓለም ላይ ያሉ ዝቅተኛ ተመላላሾች ፍጥነት ነው።’ ብሎ አስረዳኝ። ምንአልባት ቀርቤ ስላየሁትም የማየውም ነገር ጥሩ ስለነበር ይሆናል ክሩገር ለኔ ምርጡ አሰልጣኝ ነበር።\nወንድሜ የቤቱ ታላቅ ነው። በእርግጥ አብረን አላደግንም። ምንአልባት አብረን አድገን ቢሆን ማናችንም የቤተሰቦቻችን ነፀብራቅ እንደመሆናችን እሱን ከማየት እሱ ወደሚወደው ክለብ ላዘነብል እችል ነበር። አብረን አለማደጋችን በራሴ መንገድ የምወደውን ክለብ አግኝቻለው። ከወንድሜ ጋር በጣም የምንቀራረብ በየጊዜው የምንገናኝ ከወንድምነትም ባሻገር ጓደኛሞችም ነን። እኛ ቤት ብዙ ነን ግን እኔ እና እሱ ልዩ ቅርበት ነው ያለን ፤ ልደታችን ራሱ አንድ ቀን ላይ ነው። የሚገርመው ግን በብዙ ፍላጎቶቻችን ብዙ ልዩነቶች አሉት። በአውሮፓ ሊጎች ውስጥ ራሱ በድጋፋችን ሁሉም ጋር የተለያየን ነን። ይሄን ነገር እወደዋለው ፤ እንደውም በጣም ነው ደስ የሚለኝ። እንጂ ሌላ ተቃርኖ የለንም።ይሄ የዓለም ችግር ነው። ችግር አንተ ላይ ብቻ ሲሆን ይከብዳል። ችግር የጋራ ሲሆን ግን ችግርነቱ ባይቀርም ይቀላል። እኛ ላይ ብቻ የመጣ ነገር አይደለም። በፈጣሪዬ ዕምነት አለኝ ፤ የተሻለ ነገ እንደሚመጣ። ናፍቆታችንን እና የዓይን ርሀባችንን እናስታግሳለን። ይህንን ደግሞ የምለው ለእኛ ደጋፊዎች ብቻ አይደለም ፤ ለሁሉም የእግርኳሱ ደጋፊ ነው። እግርኳሱ አካባቢ ላሉ ዳኞች ፣ አሰልጣኞች ጋዜጠኞች ለሁሉም በእግርኳሱ አነሰም በዛም አሻራ ላላቸው በሙሉ ነው። ዓለም ከዚህ በላይ ተፈትናም ታውቃለች እና እንደተለያየን ከነሙሉ ነገራችን እንድንገናኝ የተሻለ ጊዜ እስኪመጣ ባላችሁበት ቆዩ ነው የምለው። ለሀገራችንም ሠላም እመኛለሁ።", "passage_id": "35b8c946db1167e9b26aff27f91fe89f" }, { "passage": "በቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ እና ዋናው ቡድን ተጫውቶ አሳልፏል፡፡ በፍጥነትም ባሳየው ድንቅ አቋም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መመረጥም ችሏል፡፡ ዘንድሮ ለድሬዳዋ ከተማ ፈርሞ ሊጉ እስከ ተቋረጠበት ጊዜ ድረስ ጥሩ ቆይታ የነበረው የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ፍሬዘር ካሳ የዛሬው የዘመናችን ከዋክብት ገፅ ተጋባዥ ነው፡፡ትውልድ እና ዕድገቱ አዲስ አበባ ፒያሳ በተለምዶ ገዳም ሰፈር አካባቢ ቢሆንም ኳስን መጫወት የጀመረው በጃን ሜዳ ነው፡፡ ብዙ የታዳጊ ቡድኖች እና ክለቦች ለልምምድ የሚጠቀሙበት እና በርካታ ተጫዋቾችን ያፈራው ጃን ሜዳ ለዛሬው ዕንግዳችንም መሠረት ጥሎለት አልፏል፡፡በዚሁ ሜዳ ላይ በአሰልጣኝ ፈለቀ በሚሰለጥነው ‘ሂሳብ’ በተሰኘ የስልጠና ቡድን ውስጥ የልጅነት የኳስ ህልሙን የጀመረ ሲሆን ዕድሜው እየበሰለ ሲመጣ 2005 ለንግድ ባንክ የታዳጊ ቡድን የነበረውን ምልመላ በማለፉ ወደ ቡድኑ ገብቶ የአንድ ዓመት ቆይታን ብቻ አድርጎ 2006 ላይ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ‘ቢ’ ቡድን 2007 ደግሞ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ቡድን በማደግ መጫወት ችሏል።በፈረሰኞቹ በታዳጊነት ዕድሜው ከዓመት ዓመት ፈጣን ዕድገትን እያሳየ በመምጣቱ በ2008 ግማሽ ዓመት ላይ ወደ ዋናው ቡድን አድጎ ክለቡን በሚገባ አገልግሏል፡፡ ከ2009 ጀምሮ በቋሚነት በክለቡ የመሀል እንዲሁም የመስመር ተከላካይነት ቦታ ላይ ሲሰለፍ የነበረው ተጫዋቹ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2010 ተጠርቶ መጫወትም ችሏል፡፡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የተለያየበት ምክንያት ዛሬም ድረስ እንደሚቆጨው የሚናገረው ፍሬዘር ካሳ ዘንድሮ ወደ ድሬዳዋ ካመራ በኃላ በክለቡ መልካም የሚባል ዓመትን ሊጉ እስከ ተቋረጠበት ጊዜ ድረስ ሲያሳልፍ ከአሰልጣኝ ስምኦን አባይ መልቀቅ በኃላ በአሰልጣኝ ፍሰሀ ጥዑመልሳን የተከላካይ አማካይነት ስፍራ ላይ እንዲጫወት የተለየ ሚና የተሰጠው ይህ ወጣት ተጫዋች አዝናኝ ጥያቄን ባዘለው የዘመናችን ክዋክብት ገፅ የዛሬው ዕንግዳችን ነው፡፡ጊዮርጊስ ይከብዳል ፤ ያው ለሁሉም ነገር ራስን ማዘጋጀት ነው። በክለቡ ብዙ ተጫዋቾች ሲኒየር ከመሆናቸውም የተነሳ ብዙ ነገር ነበር ከእኔ ሚጠበቀው። ከባድ ነው። ያው ግን ከገባህበት በኃላ ያለውን ነገር ስታየው እየለመድከው ስለምትመጣ እኔ አሁን የታዳጊነት ጊዜ ጀምሮ ስለነበረ የነበርኩበት ያሉትን ነገሮች በአንዳንድ ጓደኞቼ እና ተጫዋቾች ምክንያት እየለመድኩ እንድመጣ አድርጎኛል፡፡ በዚህ ደረጃ ከብዶኛል ብዬ አላስብም እንደመጀመሪያ የሚከብድ ነገር ይኖራል፡፡ ከዚያ በኃላ ግን ከሚነግሩህ ነገር እና በምታሳየው ጥሩ ነገር እየቀለለህ ይመጣል። እና ከሰራህ ምንም ነገር ማለፍ ትችላለህ ያን ነገር በነበረኝ ጊዜ አይቼበታለሁ፡፡በዕርግጥ እኛ ከለመድንበት የአጨዋወት ዘይቤ ዓይነት ወጣ ያለ ነው። ኮሮናው አስቸጋሪ ስለነበር ጥሩ ነገር እያሳየው መቋረጡ ትንሽ ይከብድ ነበር። ከተቋረጠ በኃላ ግን አብዛኛዎቹን ጊዜ ማሳልፈው ቤት ውስጥ ነበር። ግን ጠዋት ጠዋት ብዙ ጊዜ ስፖርቴን እሰራለሁ። ባይቻልም ጊቢ ውስጥ ባለው ነገር መስራት የምትችለውን ያህል ትሰራለህ። ከዛ በተረፈ ቤተሰቦቼ ጋር ነበረ የማሳልፈው ፤ ፊልምም አያለሁ። አሁን ላይ ደግሞ ትንሽ ይሄን ሰፋ ሳደርገው ከፍቅረኛዬ ጋር ባህርዳርም እየመጣው ከሷ ጋር አሳልፍ ነበር። እና ደግሞ እዚህም የተሻለ ነገር ስለነበረ በባህርዳር ጥሩ ነገር መስራትም ችያለሁ። ያለው የአየሩ ሁኔታ ጥሩ ስለሆነ ለመስራት እና ለመንቀሳቀስም ምቹ ስለሆነ እዚህ ለማሳለፍ ነው የተገደድኩት እና ብቻ ወጣ ያለ ነገር ነው፡፡ የምናሳልፈው ነገር ትንሽ ይከብዳል ግን መቻል ነው፡፡ኡ በጣም ከባድ ነው፡፡ የመጣውን ነገር ትችለዋለህ አሁን ካቆምን ወደ ስድስተኛ ወራችን ገብተናል ያለ ኳስ አንድ ቀን እንኳን ማሳለፍ ይከብዳል፡፡ ግን ይሄ በሀገር ደረጃ የመጣ ስለሆነ ያለህ አማራጭ በቃ እንደጊዜው መሆን ነው፡፡ እና በጣም ከባድ ጊዜ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆንም ከዚህ በኃላ ከባድ ጊዜዎች ይምጡ አይምጡ አናውቅም። ፈጣሪ ነው እንግዲህ የሚያውቀው ብቻ የተሻለውን ጊዜ ያምጣልን ነው የምለው፡፡በእርግጥ እንደዚህ እሆናለሁኝ ብዬ አላስብም። እግር ኳስ ተጫዋች ባልሆን ምን ልሆን እንደምችል አላስብም ፤ አስቤውም አላውቅም። ግን ያው ፈጣሪ ያለልኝን ነበር የምሆነው።እኔ አሁን ለምሳሌ አብሬ ከተጫወትኳቸው አሁን ከእነአስቻለው ታመነ ፣ ሳልሀዲን በርጊቾ እንን ደጉ ደበበ በየጊዜው አብሬያቸው ተጫውቻለው፡፡ ግን በቃ በይበልጥ ከአስቻለው እና ሳልሀዲን ጋር አብሬ በመጫወቴ ደስተኛ ነኝ። ትንሽ ጊዜም ቢሆን አብሬ በማሳለፌ እና ለእኔ ትልቅ ነገር ነው ከእነሱ አይቼም ሰርቼም ነው ያለፍኩት። በቀጣይም ከአስቻለው ታመነ ጋር ብጫወት ደስተኛ ነኝ፡፡እኔ በዚህ ደረጃ ይከብደኛል ያልኩት ተጫዋች የለም። እኔ ሁልጊዜ የተሻለ ነገርን ሰራለሁ ብዬ ስለማስብ ይከብደኛል ብዬ ማስበው ተጫዋች የለም ከብዶኝም አያውቅም እስከ አሁን፡፡ለእኔ ሁለት ሦስት ልጆች አሉ ግን በይበልጥ ምንተስኖት አዳነ ነው በጣም ምስጢረኛዬ። ሳልሀዲን በርጌቾም በጣም ጓደኛዬ ነው። ግን ምንተስኖት ይቀርበኛል። እንደወንድምም እንደጓደኛም ነው። እሱን ነው በተሻለ የማማክረው፡፡ለጊዜው ከቤተሰብ ጋር ነው ኑሮዬ። ፍቅረኛ ግን አለችኝ። አሁን ከጊዜ በኃላ እግዚአብሔር ከፈቀደ ከእሷ ጋር በትዳር እጣመራለሁ ብዬ ከማስባት ፍቅረኛዬ ጋር ነው አሁን ያለሁት። አምላክ ከፈቀደ ወደ ፊት አብረን እንኖራለን፡፡በእግር ኳስ ሁለቴ አዝኛለሁ። አንድ በጊዮርጊስ እያለሁ ቻምፒዮስ ሊግ ስምንት ውስጥ ለመግባት ይመስለኛል ከሳንዳውንስ ጋር ስንጫወት የወደቅንበት እና ሁለተኛ ደግሞ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የወጣውበት ጊዜ በህይወቴ ያዘንኩባቸው ጊዜያቶች ናቸው፡፡ ዛሬም ለመልቀቄ ይሄ ነው የምለው ነገር የለም።ደስተኛ የሆንኩበት በ2009 በግሌ በቅዱስ ጊዮርጊስ የተሳካ ዓመት አሳልፌያለሁ ብዬ የማስብበት ጊዜ ነበር። ትልልቅ ስም ካላቸው ጋር የተጫወትኩበት ነበር፤ ቢያንስ እዛ በነበርኩበት አንድ ታሪክ ፅፌያለሁ ብዬ የማስብበት ደስተኛም የነበርኩበት ነው ያ ጊዜ፡፡እኔ እንኳን በዚህ ደረጃ ምግብ አላማርጥም። ግን ያው ስፖርትን በምሰራ ሰዓት መጠቀም ያለብኝን ማለትም እንደ ፓስታ፣ ሩዝ እና አትክልት ነገሮችን አዘወትራለሁ። ግን ከዛ ውጪ ቤት ውስጥ ያገኘሁትን ነው የምጠቀመው። ችግር የለውም ምግብ ላይ፡፡በዚህ ደረጃ እንኳን አለኝ ብዬ አላስብም። እንደማንኛውም ሰው ከጓደኞቼ ጋር ስሆን መሳቅ መጫወት እወዳለሁ። በተለይ ከምንተስኖት ጋር ስሆን በቃ ዝም ብዬ ነው የምስቀው፤ ስለሚያስቀኝ እስቃለሁ። ሜዳ ውስጥ ስሆን ግን የሚቀይረኝ ነገር አለ፤ ያው ውጤት ከመፈለግ አንፃር። ከሜዳ ውጪ ዝምተኛ ባህሪ ስላልኝ ሜዳ ውስጥ አንዳንድ ሰው ስቀየርበት ይገረማል። በልዩነት የማነሳው ባህሪ ግን የለኝም፡፡(ሳቅ) …አዎ ሁለት ስሞች አሉኝ። አንዱ “ኒኖ” ነው አንዱ ደግሞ “ስፔን” ነው፡፡ ስፔን የሚለውን አዳነ ግርማ ነው ያወጣልኝ። አብዛኛዎቹም አዳነ ባወጣልኝ ስም ነው የሚጠሩኝ። ትንሽ ፈን ያደርጋል አወጣጡ። አንዴ ጊዮርጊስ እያለን ክፍል ውስጥ ቁጭ ብለን ስፖርት ዜና በቴሌቪዥን ተሰብስበን እያየን ብዙ ነን፤ አዳነም ነበረ… ይህን ሳስበው አሁንም ስቃለሁ። እያየን ጋዜጠኛው እንዲህ አለ ኢትዮጵያዊያን ብስክሌተኞች በስፔን የነበራቸውን ውድድር አጠናቀው መጡ ብሎ እየነተነ ነው። ‘እንዴ ከሚመጡ አይጠፉም እንዴ’ ብዬ ስሜታዊ ሆኜ ነበር የተናገርኩት። አዳነም ‘የት ነው የሚጠፉት? ስፔን? አለኝ’ በቃ በዛ ነገር ተሳቀብኝ። ከዛ ስፔን ብሎ መጥራት ጀመረ። በዛው ቀረ። አልፎ አልፎ ኒኖ በምትባለውም እጠራለሁ። ቶሬስን በጣም ነበር የምወደው። አንድ የሰፈር ልጅ ነው ኒኖ ብሎ ያወጣልኝ፡፡ከእግር ኳስ ውጪ ከጓደኞቼ ጋር ሳሳልፍ ማለት ቁጭ ብዬ አብሬያቸው ስጫወት ደስ ይለኛል። ፊልምም አያለሁ። ያው እነዚህ እነዚህን ሳደርግ ያዝናናኛል፡፡", "passage_id": "64ebd46da82ea6aa898f293959f2c0c2" } ]
b01ff77cac89bade19a4a87609aaeef2
b59dfc697e8e88156204e7b196042fb3
ኦሊምፒክን በተመለከተ አማራጭ እቅድ አልተቀመጠም
በአስከፊው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት ለአስራ ስድስት ወራት የተራዘመው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ አሁንም ከአንድ ዓመት በላይ እየቀረው ከቫይረሱ ስጋት ነፃ መሆን አልቻለም። የቫይረሱ ስርጭት ከመሻሻል ይልቅ እየባሰበት መሄዱ ከአስራ ስድስት ወራት በኋላም የመቆሙ ነገር ጥርጣሬ ውስጥ እንዲገባ አድርጓል። ይህም የቀጣዩን ዓመት ኦሊምፒክ ስጋት እንዲኖርበት ከማድረግ ባሻገር በርካታ ጥያቄዎች እንዲነሱ ሆኗል። በተለይም ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከዚሁ ስጋት ጋር በተያያዘ ኦሊምፒኩን ዳግም የማራዘም ወይም ሌላ አማራጭ እቅድ መያዙን በርካቶች እየጠየቁ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ የኦሊምፒኩ ቃል አቀባይ ማሳ ታካያ ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ውድድሩን በቀጣዩ ዓመት ከማካሄድ ውጪ ሌላ አማራጭ እንዳላስቀመጠ ከጃፓን ጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው መግለጫ ጠቁመዋል። ‹‹ኦሊምፒኩ በተራዘመበት ወቅት እንዲካሄድ እየሰራን ነው፣ በዚህ መሰረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፣ አሁን ላይ መናገር የምችለው ይህን ብቻ ነው›› በማለትም ቃል አቀባዩ ኦሊምፒኩን ዳግም የማራዘምም ይሁን የመሰረዝ ሃሳብ እንደሌለ አስረድተዋል። ቃል አቀባዩ በጀርመኑ እለታዊ ጋዜጣ ዳይ ዌልት ኦሊምፒኩ የመሰረዝ ወይም የመራዘም እድል እንዳለው ተጠይቀው በቀጥታ ምላሽ አልሰጡም። ወዲያው ግን የኦሊምፒክ አዘጋጆቹና የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ኦሊምፒኩን የመሰረዝም ይሁን የማራዘም ምንም አይነት ሃሳብ እንደሌለ ለመገናኛ ብዙሃን ለመጠቆም ሞክረዋል። ከተራዘመው የጉዞና የሆቴል ጉዳይ፣ የስቴድየም መግቢያ ትኬቶችና በአጠቃላይ ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ሊገጥም የሚችለውን ኪሳራ በተመለከተ ጥያቄ ተነስቷል። ይህ ኪሳራ ከሁለት እስከ ስድስት ቢሊየን የጃፓን የን እንደሚሆን ግምቶች ቢሰጡም አሁንም ትልቁ ጥያቄ የኪሳራው መጠን ምን ያህል ነው? ማንስ ይከፍለዋል? የሚል ነው። የዓለም አቀፍ ኮሚቴው ፕሬዚዳንት ቶማስ ባኽ ተቋማቸው በመቶ ሚሊየን ዶላሮች ሊከስር እንደሚችል የጠቆሙ ሲሆን ጃፓንም አዘጋጅ አገር እንደመሆኗ ሊገጥማት የሚችለው ኪሳራ በቀላሉ የሚታይ አይሆንም። ቶኪዮ ኦሊምፒኩን ለማስተናገድ አስራ ሁለት ቢሊየን የን ማውጣቷን ትናገራለች። ባለፈው ዓመት የታተመው የአገሪቱ መንግስት ኦዲተር ሪፖርት እንደሚያመለክተው ግን ወጪው በሁለት እጥፍም ሊልቅ ይችላል። ከዚህ ገንዘብ ውስጥ ግን አምስት ነጥብ ስድስት ቢሊየን የሚሆነው በግል ባለሃብቶች ወጪ የተደረገ ሲሆን ቀሪው በአገሪቱ መንግስት ነው። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውድድሩ ወደ 2021 እንዲዘዋወር ውሳኔ ላይ ከደረሰ ወዲህ በቫይረሱ ስጋት በአስተናጋጇ ጃፓን ቶኪዮን ጨምሮ በሰባት ከተሞች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል። ከቀናት በፊት የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱትም በኮሮና ቫይረስ በጃፓን ከስድስት ሺ በላይ ሕዝቦች ሲጠቁ ከመቶ በላይ የሚሆኑት ሕይወታቸውን አጥተዋል። ኦሊምፒኩ እስከሚካሄድ ገና አስራ ስድስት ወራት የቀሩት ቢሆንም የቫይረሱን ስርጭት በነዚህ ጊዜያት በቁጥጥር ስር ማዋል ካልተቻለ ኦሊምፒኩ አሁንም ከስጋት ውጪ ሊሆን እንደማይችል የቶኪዮ ኦሊምፒክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቶሺሮ ሙቶ መናገራቸው ይታወሳል። ‹‹በዚህ ወቅት ማንም በእርግጠኝነት ቫይረሱን በቁጥጥር ስር አውላለሁ የሚል እምነት የለውም፣ ስለዚህ የተራዘመው ኦሊምፒክ ከቫይረሱ ስጋት ነፃ ይሆናል ብለን ለመናገር ይቸግረናል›› በማለትም ሃሳባቸውን አጠናክረዋል። በቫይረሱ ስጋት ኦሊምፒኩን ከአንድ ዓመት በላይ ለማራዘም እንደተወሰነ ያስታወሱት ስራ አስፈፃሚው፣ ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በዚህ ወቅት ለተራዘመው ኦሊምፒክ ጠንክሮ ከመዘጋጀት ውጪ ሌላ ነገር ሊያደርግ እንደማይችል አስረድተዋል። ይሁን እንጂ የሰው ልጅ እስከዚያው ቫይረሱን በቁጥጥር ስር ያውላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልፀዋል። የተራዘመው ኦሊምፒክ ዘንድሮ ሊካሄድ በታቀደበት ተመሳሳይ ወቅት እንዲካሄድ ከመወሰኑ ውጪ በየትኛው ቀን እንደሚካሄድ ቁርጥ ያለ ቀን አልተቀመጠለትም። ይህንንም ለመወሰን ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተለየ አማራጭ እስካሁን እንዳልተመለከተ አስረድተዋል። ከዚህ ይልቅ ኦሊምፒኩን ቀጣይ ዓመት ላይ በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ የተቻለውን ሁሉ ጥረት ማድረግ የሚቻልበትን አማራጭ ታሳቢ በማድረግ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ዓለምን እያስጨነቀ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ በቀጣዮቹ አስራ አምስት ወራት በቁጥጥር ስር እስካልዋለ ኦሊምፒኩ ቢካሄድም የደበዘዘ እንደሚሆን ከወዲሁ ግምታቸውን የሚያስቀምጡ ተበራክተዋል። በተለይም ውድድሮች በሚካሄዱባቸው ስቴድየሞች የሚታደሙ ተመልካቾች ጉዳይ በታላቁና ደማቁ የስፖርት መድረክ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ እንዳይጨምር ያሰጋል። ለበርካታ ወራት በቫይረሱ ስርጭት ምክንያት የዓለም ሕዝቦች ራሳቸውን ለመጠበቅ የፊት ጭምብል የማድረግና ማህበራዊ ርቀትን የመጠበቅ ልም ምድ ውስጥ ገብተዋል። ታላቁን የስፖርት መድረክ በስቴ ድየም ተገኝቶ መመልከት የሚቻልበት እድል ቢኖር እንኳን ደጋፊዎች ከዚህ ረጅም ልማድ ሳይወጡ ውድድሮችን ለመመልከት እንደሚገደዱ ይጠበቃል። ይህም በስቴድየም ወንበሮች ተራርቆ ከመቀመጥ ጋር ተያይዞ የተመልካቾች ቁጥር በእጅጉ እንደሚቀንስ ይታመናል። ይህም በኪሳራ ላይ የሚገኙትን የውድድሩ አዘጋጆች ከትኬት ሽያጭ ጋር በተያያዘ ለሌላ ኪሳራ እንደሚዳርጋቸው ያሰጋል። ከደጋፊዎች ጋር በተያያዘ እንደቀድሞው የአገራቸውን ሰንደቅ አላማ አንግበው በስቴድየም በአንድ ላይ ተሰብስበው ማየት ብርቅ ሊሆን ይችላል። ደጋፊዎች የአገራቸው አትሌቶች ሲያሸንፉ እንደተለመደው በደስታ ተቃቅፈው የሚያነቡበት፣ አብረው ፎቶ ግራፍ የሚነሱበትና በጋራ ተሰብስበው ደስታቸውን የሚገልፁበት አጋጣሚ ብርቅ ሊሆን ይችላል። ይህ በአንድ አገር አትሌቶች መካከልም ይሁን በተለያዩ አገራት አትሌቶች መካከል የተለመደ የመጨባበጥ፣ ተቀራርቦ የመደናነቅና ‹‹ተቃቅፎ እንኳን ደስ ያለህ›› የመባባል የስፖርታዊ ጨዋነት መገለጫዎች ቅንጦት እንዳይሆኑም ያሰጋል። ይህ ሁሉ ስጋትና እንቅፋት የተደገነበት የቶኪዮ ኦሊምፒክን በተመለከተ በተራዘመበት ጊዜ ከማካሄድ ውጪ አዘጋጆቹ ሌላ አማራጭ እቅድ እስኪያጡ ድረስ ተጨንቀዋል። ይህም የዓለም አቀፉን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ያህል ትልቅ ተቋም ከወዲሁ የሰላ ትችት እንዲሰነዘርበት እያደረገ ይገኛል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 12 /2012
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=30712
[ { "passage": "የኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ 19) በዓለም ላይ በከፍተኛ ፍጥነት መሰራጨቱን ተከትሎ የሁሉም ዓለም አቀፍ የስፖርት መርሐግብሮች እንዲቋረጡ አድርጓቸዋል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ተከትሎ የስፖርቱ ዓለም ካለፉት ሁለት ወራት በላይ ተቋርጦ እንዲቆይ አድርጎታል። የውድድሮቸ መቋረጥና መርሐ ግብሮች መራዘማቸውን ተከትሎ የስፖርቱን ኢንዱስትሪ ክፉኛ እንደጎዳው ዓለም አቀፍ ጥናቶች ከወዲሁ ያመላክታሉ። ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በመቆማቸው ምክንያት የሚደርሰውን ኪሳራ በመጠኑም ቢሆን ለማዳን ውድድሮችን በዝግ ስታዲየም ማድረግ አማራጭ ተደርጓል። ከቫይረሱ ስጋት ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆን ባይችሉም ታላላቆቹን አውሮፓ እግር ኳስ ሊጎች ጨምሮ አንዳንድ አገራትም ስፖርታዊ ውድድሮቻቸውን ከሰሞኑ አስጀምረዋል። ውድድሮችን በዝግ ስቴድየሞች በማድረግ የውድድር ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት መርሐግብሮቻቸውን ለማጠናቀቅ ጨዋታዎችን እያደረጉ ይገኛሉ። \nበአውሮፓ እግር ኳስ ሊጎች የተወሰደውን መፍትሔ የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተግባራዊ ሊያደርገው እንደሚችል ቢቢሲ ዘግቧል። የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሰባስቲያን ኮዬ ፤ የአትሌቲክስ ስፖርት ሲመለስ በባዶ ሜዳዎች ሊካሄድ እንደሚችል ማስጠንቀቃቸውን መሰረት ያደረገው ዘገባው፤ «በታላላቆቹን አውሮፓ እግር ኳስ ሊጎች ከሰሞኑ እንደተመለከትነው ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮችም በቅርቡ ሊመለሱ ይችላሉ »ሲል አስነብቧል የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቲክስ ስፖርት ሲመለስ በባዶ ሜዳዎች ሊካሄዱ እንደሚችሉ ከማስገንዘብ በተጨማሪ ፤ውድድሮች ስለሚመለሱባቸው ሁኔታዎች በተመለከተ ሃሳብ መስጠታቸውን አመልከቷል። በዚሁ ላይም «ዓመታዊው የዳይመንድ ሊግ እንዲሁም የተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች ሁኔታዎች ከተገመገሙ በኋላ በመጪው ነሐሴ አጋማሽ እንዲካሄዱ እቅድ ተይዟል። በነሐሴ እንዲካሄዱ እቅድ የተያዘላቸው አስራ አንዱ የተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች በዝግ ሜዳ ይሆናሉ » ሲሉ መናገራቸውን ጽፏል። \nቢቢሲ በዘገባው ፕሬዚዳንቱ በተለይ ጌምስ ለተባለው ድረገፅ በሰጡት ማብራሪያ «በመጪዎቹ ቅርብ ጊዜያት የሚካሄዱ ውድድሮች ላይ ለደህንነት ስንል ልንደራደርባቸው የማይገቡ ጉዳዮች አሉ። በተደጋጋሚ በጤና ባለሙያዎችም ሆኑ በአካባቢው ማህበረሰብ የተነገረንን ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ያስገባና ችላ የማንላቸውም ናቸው። ሁላችንም ቢሆን ይህ የረዥም ጊዜ መፍትሔ ነው ብለን አናስብም። ስፖርታዊ ውድድሮች ያለታዳሚ ይጠፋሉ። ሆኖም በአሁኑ ወቅት የአትሌቲክስ ውድድሮችን ለመመለስ መክፈል ያለብን መስዋዕትነት ይሄ ነው» ሲሉ መናገራቸውን በዘገባው አካቷል።አዲስ ዘመን ግንቦት 11/2012ዳንኤል ዘነበ", "passage_id": "7880ef43a81ab343f810d54366a6043d" }, { "passage": "ቦጋለ አበበበኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋት ለአስራ ስድስት ወራት የተራዘመው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ወረርሽኙ መፍትሄ ባያገኝም እንደሚካሄድ እርግጠኛ የሚያደርጉ ማሳያዎችን አዘጋጆቹ ይፋ ሲያደርጉ ሰንብተዋል፡፡ ይሁን እንጂ በውድድሮች ለመሳተፍ ወደ ቶኪዮ የሚያቀኑ አትሌቶችና የስፖርት ቤተሰቦች ከወረርሽኙ ስጋት ጋር በተያያዘ ማሟላት ስለሚጠበቅባቸው መስፈርቶች ወጥ የሆነ ህግ በማውጣት ረገድ አዘጋጆቹ ለረጅም ጊዜ እንደተቸገሩ ይታወቃል፡፡ ይህም የቶኪዮ ኦሊምፒክ የመሰረዝ እድል ይገጥመዋል የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ አሳድሮ ነበረ፤ይሁንና አዘጋጆቹ ከወረርሽኙ ስጋት ጋር በተያያዘ ተቸግረውበት የነበረውን ህግ ሰሞኑን ይፋ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡ ወራትን ከፈጀ ምክክር በኋላ ሃምሳ አራት ገፅ የያዘ ሪፖርት ይፋ ያደረጉት የኦሊምፒኩ አዘጋጆች ወረርሽኙ በቀጣይ ሰባት ወራት ውስጥ መፍትሄ ባያገኝ እንኳን ኦሊምፒኩ መካሄድ የሚችልባቸውን ከጤና ጋር የተያያዙ ሕግና ደንቦች ይፋ አድርገዋል፡፡ በዚህም አትሌቶችም ይሁኑ ተሳታፊዎች መደበኛ የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረጋቸው እንደማይቀር ያስቀመጡ ሲሆን፣ ከወረርሽኙ ስጋት ጋር በተያያዘ የሚቀመጡ ገደቦችን የጣሰ ማንኛውም አትሌት የሚቀጣበትን ሕግ እንዳረቀቁ አስታውቀዋል፡፡ ውድድሩን ለመከታተል ወደ ቶኪዮ የሚያቀኑ የስፖርት ቤተሰቦች ለይቶ የማቆያ ጉዳይ እንደሚመለከታቸው የተገለፀ ሲሆን፣ ወረርሽኙን ለመከላከል ከሚያስፈልጉ የጥንቃቄ ርምጃዎች መካከል የአፍ ጭንብል ማጥለቅና አለመጨባበጥን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚገደዱም ተጠቁሟል፡፡ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ ቶሺሮ ሙቶ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ጥብቅ የመከላከል ርምጃዎች ተግባራዊ እንደሚሆኑ ጠቁመው፣ ይህ የኦሊምፒኩን ድባብ የተለየ ቢያደርገውም በደማቅ ሁኔታ እንደሚከናወን ያላቸውን እምነት ለመገናኛ ብዙሃን ገልፀዋል፡፡ ከየትኛውም አገር ወደ ቶኪዮ የሚያቀኑ አትሌቶች ጃፓን እንደደረሱ የኮቪድ-19 ምርመራ ይደረግላቸዋል፤ በኦሊምፒክ መንደር በሚኖራቸው ቆይታም በአራት ወይም አምስት ቀናት ልዩነት ተመሳሳይ ምርመራ ይደረግላቸዋል፡፡ በተለያዩ ምርመራዎች ወረርሽኙ የሚገኝባቸውን አትሌቶች በተመለከተም የማገገሚያ ማዕከል እንደሚኖር ተጠቁሟል፡፡ ይሁን እንጂ አትሌቶች በውድድር ወቅት በወረርሽኙ ቢጠቁ የውድድር ሕጎች ላይ ስለሚያሳድረው ተፅዕኖ የተገለፀ ነገር የለም፡፡ አትሌቶች ከውድድርና ልምምድ ውጪ የአፍ መሸፈኛ ጭምብል የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ተጠቁሟል፤ ድምፅን ከፍ አድርጎ ማውራትና ከሌሎች ጋር ንኪኪ መፍጠር እንደማይችሉ ተገልጿል፡፡ ለዚህም እያንዳንዳቸው በቅድሚያ ለነዚህ ሕጎች ተገዢ እንደሆኑ የሚያረጋግጡበት የስነምግባር ደንብ እንደሚፈርሙ ታውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሁሉም አገራት የስፖርት ልዑካን ቡድኖች ውድድሮቻቸውን እንዳጠናቀቁ በፍጥነት አገሪቱን ለቀው መውጣት እንዳለባቸውና ውድድሮች ከተጠናቀቁ በኋላ ለጉብኝት ወይም ለሽርሽር ተጨማሪ ቀናትን በጃፓን መቆየት እንደማይቻል ተገልጿል፡፡ የተቀመጡትን ሕግና ደንቦች ጥሰው የተገኙ አትሌቶች ወይም የስፖርት ቤተሰቦች ምን አይነት ቅጣት እንደሚጠብቃቸው እስካሁን የተቀመጠ ነገር ባይኖርም አዘጋጆቹ ከዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር በዚህ ጉዳይ ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ የተቀመጡት ደንቦች ስፖርት መዝናኛ እንደመሆኑ በመጠኑም ቢሆን የማስጨነቅ ባህሪ እንዳላቸው ቢታመንም ሕጎቹን እንደ ወንጀል መቅጫ ሕግ መመልከት ሳይሆን ለጥንቃቄ ሲባል የተወሰዱ እንደሆኑ መገንዘብ አስፈላጊ እንደሚሆን አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡ ሕግና ደንቦቹን አትሌቶችና ልዑካን ቡድኖች በአግባቡ እንዲገነዘቡ በቡድን መሪዎች በኩል የተለያዩ ማብራሪያዎችና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ይፈጠራሉ፤ስቴድየም ገብተው ውድድሮችን የሚመለከቱ የስፖርት ቤተሰቦችን ቁጥር ለመወሰን ወቅቱ ሲደርስ የወረርሽኙ ስርጭት በዓለም ላይ የሚኖረውን ነባራዊ ሁኔታ መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡ በኦሊምፒኩ ለመታደም ወደ ቶኪዮ የሚያቀኑ የስፖርት ቤተሰቦች ለሁለት ሳምንታት በለይቶ ማቆያ እንዲቀመጡ ማድረግ እንደማይቻል የገለፁት አዘጋጆቹ፣ ሌሎች አማራጮችን እንደሚጠቀሙ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ የወረርሽኙ ክትባት እንደተገኘና በርካታ አገራትም በግዢ ሂደት ላይ እየተረባረቡ መሆኑ እየተሰማ ቢሆንም፣ ኦሊምፒኩ እስከሚካሄድበት ወቅት ድረስ ለዓለም ሕዝብ ሊዳረስ ስለማይችል የኦሊምፒኩ አዘጋጆች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ውድድሩን በታሰበው ጊዜ ማካሄድ የግድ እንደሆነ አምነው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ የወረርሽኙን ስጋት ለመቅረፍ በሚደረጉ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች የኦሊምፒክ አዘጋጆች ምን ያህል ወጪ እንደሚጠብቃቸው ቁርጥ ያለ መረጃ ባይኖርም፣ ባለፈው ሳምንት የወጡ ሪፖርቶች እስከ አንድ ቢሊየን ዶላር ሊፈጅ እንደሚችል አመላክተዋል፡፡ ኦሊምፒኩን በታቀደው ጊዜ ማካሄድ ካልተቻለና የመራዘም እድል ከገጠመው ደግሞ አዘጋጆቹ ቀደም ብለው ከያዙት በጀት እስከ ሁለት ቢሊየን ዶላር ድረስ ተጨማሪ ወጪ ሊያወጡ እንደሚችሉ በቅርብ የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013", "passage_id": "59e014c49aaf9951044da734cee2ec85" }, { "passage": " የመላው ዓለም ሕዝብ ትኩረትና ጭንቀት በሆነው የኮሮና ቫይረስ ፈጣንና አስደንጋጭ ስርጭት የተነሳ መደበኛ እንቅስቃሴዎች በብዙ የዓለማችን አገራት ተገተዋል። የስፖርቱ ዓለም በቫይረሱ ስጋት ሳቢያ ብዙ ለውጦችን ከማስተናገድ አልፎ ሽባ ሆኗል። የስፖርት መገናኛ ብዙኃንም በአንድ ጉዳይ ላይ ብቻ በማጠንጠን ቆመዋል። ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የሁሉም የስፖርት ቤተሰብ ልብ አንጠልጣይ ጉዳይ ከሆነ ሰንብቷል። ዓለም በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ሆና የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውድድሩን በተያዘለት ጊዜ ለማካሄድ ድርቅ ማለቱ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። ያም ሆኖ የዓለም አቀፍ ኮሚቴውን ደረቅ አቋም የሚፈታተን አዲስ ዜና ከየአቅጣጫው ብቅ ማለቱ ትልቅ ተፅዕኖ መፍጠሩ አልቀረም። በተለይም ካናዳና አውስትራሊያን የመሳሰሉ አገራት ከቀናት በፊት ራሳቸውን ከኦሊምፒክ እንዳገለሉ መግለፃቸውን ተከትሎ ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ከግትር አቋሙ እየተለሳለሰ እንዲመጣ አስገድዶታል። ፈረንሳይና እንግሊዝን የመሳሰሉ አገራትም ዓለም አቀፍ ኮሚቴው በአስቸኳይ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ መጠየቃቸውን ተከትሎ ኦሊምፒኩ ላይ ለውጥ ስለመኖሩ በርካቶችን እርግጠኛ ያደረገ ነበር። የኦሊምፒክ ትልቁ ባለድርሻ አካል የዓለም አትሌቲክስ ከቀናት በፊት የቶኪዮ ኦሊምፒክ እንዲራዘም ጥያቄ ማሳቱን ተከትሎም በቅርቡ አዲስ ነገር እንዲጠበቅ አድርጓል። የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሴባስቲያን ኮ ኦሊምፒኩ ወደ 2021 የሚሸጋገር ከሆነ በኦሬገን አሜሪካ በተመሳሳይ ወቅት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረውን የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ወደ ሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ ሙሉ በሙሉ ፈቃደኛ እና ዝግጁ መሆናቸውን ለኮሚቴው ባስገቡት ‹‹ውድድሩ ለሌላ ጊዜ ይተላለፍልን›› መጠየቂያ ደብዳቤያቸው ማረጋገጣቸውም ኦሊምፒኩ እንደሚራዘም ያረጋገጠ ርምጃ ነበር። ይህ ሁሉ ተፅዕኖ የተፈጠረበት የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴም እየመረረውም ቢሆን ውድድሩን ወደ 2021 ለማስተላለፍ ያስገደደውን የማይቀር ውሳኔ ማሳለፉን አሳው ቋል። የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤና የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባኽ ከትናት በስቲያ ምሽት ባደረጉት የቪዲዮ ኮንፍረንስ ከቫይረሱ ስርጭት ጋር በተያያዘ ያለውን አደጋ ከግምት በማስገባት ኦሊምፒኩ ወደ 2021 እንዲራዘም ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን አሳውቀዋል። ኦሊም ፒኩ ወደ 2021 መሸጋገሩ ይጠቀስ እንጂ በየትኛው ወቅት እንደሚካሄድ የተገለፀ ነገር የለም። ያም ሆኖ የበጋ ኦሊምፒክ እንደመሆኑ መጠን በቀጣይ ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ላይ ሊካሄድ እንደሚችል ተገምቷል። ይህንን ውሳኔ ተከትሎም የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ከጦርነት ውጪ ባሉ ምክንያቶች በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተላለፈ ሊሆን ችሏል። ኦሊምፒክ ከጤና ስጋት ጋር የተያያዘ ባይሆንም በተለያዩ ጊዜዎች የመራዘም፣የመሰረዝና የቦታ ለውጥ ሲደረግበት ታይቷል። እኤአ የ1916 የበጋ ኦሊምፒክ በጀርመን በርሊን ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት በአንደኛ የዓለም ጦርነት ሳቢያ ተሰርዟል። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅትም የ1940 የክረምት ኦሊምፒክና የ1944 የበጋ ኦሊምፒክ ውድድሮች የመሰረዝ ዕድል ገጥሟቸዋል። እኤአ የ1976 የክረምት ኦሊምፒክም በዴንቨር ኮሎራዶ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የኮሎራዶ ግዛት ሕዝብ ለውድድሩ የሚወጣውን ወጪ በመቃወሙ ውድድሩ የቦታ ለውጥ ተደርጎበት በአውስትራሊያ ኢንስብረክ ለመካሄድ ተገዷል። ዩ ኤስ ኤ ቱዴይ በወቅቱ እንደዘገበው የኮሎራዶው ኦሊምፒክ የቦታ ለውጥ እንዲደረግበት ውሳኔ ላይ የተደረሰው ውድድሩ ከመካሄዱ ከሦስት ዓመታት አስቀድሞ ነበር። ይህም ከጥንት ጀምሮ የኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ የቦታ ለውጥ ለማድረግ ቢያንስ ከሁለት ዓመት በፊት ውሳኔ ላይ መደረስ ይኖርበታል። የሪዮ 2016 ኦሊምፒክም ከመድረሱ ከዓመታት በፊት የዚካ ቫይረስ ስጋት መሆኑ ቢታወቅ ሊሰረዝ፣ሊራዘምና የቦታ ለውጥ ሊደረግበት ይችል እንደነበር በርካቶች አስተያየት ሲሰጡ ይስተዋላል። የዚካ ቫይረስ የሪዮ ኦሊምፒክ ስጋት መሆኑ የታወቀው ውድድሩ ከመካሄዱ ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ መታወቁ የቫይረሱ ስርጭት ያን ያህል ስጋት ካለመሆኑ ጋር ተደምሮ የመሰረዝ፣ የመራዘምና የቦታ ለውጥ ሳይደረግበት ለመቅረቱ ዋነኛ ምክንያት መሆኑን የሚያብራሩም ጥቂት አይደሉም። ዘንድሮም ከአራት ዓመት በኋላ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ከጥር ጀምሮ በቻይና በተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ተመሳሳይ አደጋ ሊራዘም በቅቷል። አዲስ ዘመን መጋቢት 17/2012 ", "passage_id": "ba98f9daf5ec70deee510e34ba8b92b6" }, { "passage": " እኤአ ታኅሣሥ 31 ቀን 2019 በቻይና ዉሃን ከተማ የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን የዓለም የጤና ድርጅት ማስታወቁን ተከትሎ የቻይና መንግሥት በአፋጣኝ የቫይረሱን ስርጭት በአጭሩ ለመቅጨት እርምጃ ወደ መውሰድ ገብቶ ነበር። የቫይረሱን ስርጭት እንደተባለው በቀላሉ ለመቆጣጠር ሳይቻል ቀርቷል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭቱ ወረርሽኝ ደረጃ መድረሱን ተከትሎ በዓለም ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ መስተጋብር ላይ አደጋ ጥሏል። የስፖርቱ ዓለም በቫይረሱ ስጋት ሳቢያ ብዙ ለውጦችን ከማስተናገድ አልፎ ቆሞ ቀር ለመሆን ተገዷል፡፡ የስፖርት መገናኛ ብዙኃንም እስከ ትናንት በስቲያ ድረስ መካሄድ አለማኬዱ ያለየለት ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ብቻ የዜና ግብዓታቸው የሆነ መስሏል፡፡ ዓለም በእንዲህ ዓይነት አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውድድሩን በተያዘለት ጊዜ ለማካሄድ ለረጅም ጊዜ ደረቅ አቋም መያዙ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል፡፡ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣትና የአንድ ሀገር ስጋት ከመሆን ወደ ዓለም አቀፍ ስጋትነት እያደገ መምጣት ነገሮችን እንዲቀየሩ አድርጓል፡፡ በኦሊምፒክ መድረክ የሚሳተፍ አገራት «በመድረኩ እንሳተፍ» ወደሚል ውሳኔ ላይ እንዲደርሱም አድርጓል። የ2020 ኦሊምፒክ መካሄድ የለበትም የሚሉ ሀሳቦች ቀስ በቀስ መነሳታቸውም ውድድሩ ይራዘም የሚሉ ድምጾች ከቀን ወደ ቀን ብዛትና ጉልበት እንዲያገኙ አቅም ፈጥሮላቸዋል፡፡ የኦሊምፒክ መድረኩ የማይራዘም ከሆነ ስፖርተኞቻችንን ለአደጋ አናጋልጥም፣ ዓለም በጭንቅ ውስጥ እያለች ከሚካሄደው የ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ይቅርብን ያሉ እንደ ካናዳ ያሉ አገራት ራሳቸውን እስከማግለል ደርሰዋል። የካናዳን እግር በመከተል እንደ አውስትራሊያ ያሉ አንዳንድ አገራት ተመሳሳይ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል፡፡ የኢትዮጵያም የተሳትፎ ጉዳይ በአንድ ልብ ውሳኔ መስጠት ሳይቻል ቀርቶ ከፍተኛ ውዝግብ እስከማስነሳት የደረሰ ነበር። «የኢትዮጵያ አትሌቶች በውድድሩ ለመሳተፍ አንድ ላይ ሆቴል ገብተው ዝግጅት መጀመር አለባቸው የለባቸውም» በሚል በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መካከል ብርቱ የሆነ እሰጣ አገባ መፈጠሩ አይዘነጋም፡፡ ይሁን እንጂ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከቀናት በፊት የቶኪዮ ኦሊምፒክ ለአንድ ዓመት ማራዘሙን ተከትሎ በሁለቱ አካላት መካከል የነበረው የሃሳብ ልዩነት መቋጫ አግኝቷል፡፡ በኢትዮጵያ ስፖርት አመራሮች መካከል ሰሞነኛው ውዝግብ ዓለም አቀፉ ኮሚቴ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የረገበ ይምሰል እንጂ ነገ እንደ አዲስ አለመነሳቱን በርካቶች ይጠራጠሩታል፡፡ በሁለት ጎራ የተቧደኑ የስፖርት አመራሮች ውዝግብ ከየት ተነሳ?ብለን በመጠየቅ ወደ ኋላ መለሰ ብለን የተፈጠረውን ጉዳይ እንመርምር። ጥር 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አዱላላ ሪዞርት፣የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በዝግ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጠርቷል። ወቅቱ ደግሞ የዓለም አገራት በታላቁ የኦሊምፒክ መድረክ የሚኖራቸውን ተሳትፎ በጎ መልክ ለማስያዝ ሽርጉድ እያሉ የሚገኙበት ነው። የኦሊምፒክ ኮሚቴ በዝግ ስብሰባ የቶኪዮ ኦሊምፒክን መሠረት ያደረገ ውሳኔን ይዞ ከመምጣት ይልቅ፤ «የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው የሥራ አመራር ቦርድ የአገልግሎት ዘመንና ተቋሙን በዋና ጸሐፊነት እንዲመራ፣ የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው የሥራ አመራር ቦርድ የቆይታ ጊዜ ከአራት ዓመት ወደ ስምንት ዓመት እንዲሻሻል ተደርጓል» የሚል ነበር። የኦሊምፒክ ኮሚቴ ይሄንኑ ውሳኔውን ተከትሎ ኮሚቴው ስፖርቱን ለማሳደግ የያዘውን ወንበር የሥልጣን ጊዜውን ለማሳደግ እየተውተረተረ መሆኑን አሳዛኝ እንደሆነ ከተለያዩ አካላት ትችቶች ሲሰነዘሩበት ነበር። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከዚህ ውስጥ አንዱ ሲሆን፤ ጉባዔው ውሳኔ ያሳለፈባቸው ጉዳዮች ተገቢነት ላይ ‹‹አልተስማማሁም›› ሲል ተቃውሞውን አሳውቋል፡፡ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የፌዴሬሽኑን ሀሳብ በመደገፍ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ሊታረም እንደሚገባ እስከ ማስገንዘብ ደርሶም ነበር። በዚህ መልክ የሚደረግ ሙግት ስፖርቱን መሠረት በማድረግ እንዲህ ዓይነት የሀሳብ ተቃርኖዎች የሚበረታቱ ቢሆንም፤ የስፖርቱ አመራሮች በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በመውጣት የሚሰጧቸው ምላሾችና የቃላት ልውውጦች ስፖርቱን መሠረት ያደረጉ አልነበሩም። በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ እና በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ በኩል በወቅቱ ይሰጧቸው በነበሩት ቃለ ምልልሶች ይሄንኑ በሚገባ የሚያንፀባርቁ ነበሩ። ስፖርቱን የሚመሩ ሌሎች አመራሮች የሚሰጡ አስተያየቶች ተመሳሳይ የነበሩ ሲሆን፤ ይህም ስፖርቱን መሠረት ያደረገ ቅራኔ አለመሆኑን በተጨባጭ መገንዘብ ያስችላል። ከስፖርቱ አመራሮች ውዝግብ ጀርባ ያለው ሴራ እንዳለ ሆኖ በክስተቱ ብዙዎችን ማስቆጣቱን የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነበር። የስፖርት አመራሮቹ ሲወዛገቡበት የነበረበት ወቅት ለቁጣው ትልቁን ድርሻ ይወስዳል። የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅት ዙሪያ ከማተኮር ይልቅ፤ ባልተገባ ትርምስና ሽኩቻ ስፖርቱን ለመጥቀም ወይስ ለመጉዳት? ያስባለም ነበር። በዚህ ደረጃ ቅሬታን ካስነሳ በኋላ በሁለቱ ጎራ የነበረው ፀብ በይደር እንዲቆይ በማድረግ ተቋማቱ ትኩረታቸውን ወደ ኦሊምፒክ ለማድረግ ቃል ገብተው ነበር፡፡ ስፖርቱን የማሸበሩ ዜና ግን ዳግመኛ ጥር 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ተፈጥሯል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቶኪዮ 2020 አሊምፒክ ላይ ለሚደረገው ዝግጅትና ተሳትፎ በሚመለከት ባለድርሻ አካላትን ጋር ያዘጋጀው የምክክር መድረክ ለዚህ እንደመነሻ ሆኗል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ‹‹በመድረኩ እንድንሳተፍ መልዕክት አልደረሰኝም›› ሲል ብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ትልቁን ባለድርሻ አካል ሳያሳትፍ የውይይት መድረክ መዘጋጀቱ ቅር መሰኘቱን አስታውቋል። አጋጣሚውም የሁለቱ ተቋማት ቁርሾ ለኦሊምፒክ እየተደረገ ያለው ዝግጅት በተናጠል እንዲሆን በር ከፍቷል፡፡ «በዝሆኖች ፀብ የሚጎዳው ሳሩ ነው» እንደሚባለው በስፖርቱ አመራሮች ሽኩቻ አገሪቷ ዋጋ እንዳትከፍል መፍትሄ መስጠት አስፈላጊ ቢሆንም በዝምታ ታልፏል፡፡ የአመራሮቹ ቁርሾ መፍትሄ አለማግኘቱን ተከትሎ መጋቢት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በሰጠው መግለጫ ፤ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በተያዘለት መርሐ ግብር መሠረት እንደሚካሄድ ገልጿል፡፡ በዚህ መሠረት አትሌቲክሱን ጨምሮ ለቶኪዮ 2020 የተመረጡ ብሔራዊ አትሌቶች ዝግጅት መጀመር እንዳለባቸው አስታወቀ። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ደግሞ ፤ «የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መፍትሔ ሳያገኝ ብሔራዊ አትሌቶችን በሆቴል አሰባስቦ ዝግጅት ማድረጉ አደጋ አለው» ሲል አስገነዘበ። ለብሔራዊ አትሌቶች የተደረገው ጥሪን ኃላፊነት የጎደለው እንደሆነ በመሞገት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ውሳኔ ፊት ለፊት ተጋፈጠ። የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አቋም እንደፀና የኦሊምፒክ ኮሚቴ ውሳኔው ተገቢና የማይቀለበስ መሆኑን አቋም በመያዝ ፍጥጫ ውስጥ ገቡ። በመጨረሻም ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ እንዲሰረዝ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ማስታወቁ ተከትሎ፤ በስፖርት አመራሮቹ መካከል የተፈጠረው ግብ ግብ ረገበ። ይህ ሽኩቻ እንዳለፉት ጊዜያቶች ተዳፈነ እንጂ አልጠፋም፡፡ ነገ እንደረመጥ የሚቆሰቁሰው አንድ አካል እንደሚኖር ሁለቱ አካላት አንዴ ሲሻኮቱ አንዴም ተስማማን እያሉ ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ እንደሚባለው መሆናቸውን ማስታወስ በቂ ነው፡፡ ለዚህም የሁለቱም ተቋሞች የበላይ የሆነው ስፖርት ኮሚሽን ኦሊምፒክ ሲመጣ ሳይሆን ከወዲሁ የሚስማሙበትን መንገድ መፈለግ እንዳለበት ይታመናል፡፡ በግለሰቦች ፍጥጫና የግል ፍላጎት ትልቁ የአገር ገፅታ ኦሊምፒክ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ የነገ ሳይሆን የዛሬ ጉዳይ ነው፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 18/2012 ዳንኤል ዘነበ", "passage_id": "c2c19c50dfe36b2204fac2582e0ac2fc" }, { "passage": "ቦጋለ አበበ ጃፓን ከሰባት ዓመታት በላይ ብዙ የለፋችበት የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅት ካለፈው ዓመት ጀምሮ የዓለም ሕዝብ የጤና ጠንቅ በሆነው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለአስራ ስድስት ወራት ተራዝሞ ዘንድሮ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለታል። ኦሊምፒኩ በተራዘመው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደሚካሄድም እርግጠኛ ሆነው የውድድሩ አዘጋጆች መናገር ከጀመሩ ሰነባብተዋል። የተለያዩ አገራትም በአዘጋጆቹ ተማምነው የስፖርት ልዑካን ቡድኖቻቸውን እያዘጋጁ ይገኛሉ።የዓለም አቀፉን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጨምሮ የውድድሩ አዘጋጆች አሁንም ድረስ ውድድሩ እንደሚካሄድ እርግጠኛ የሆኑት ወረርሽኙ ኦሊምፒኩ እስኪቃረብ አንድ መፍትሄ ያገኛል በሚልና በሙከራ ላይ የሚገኙትን የተለያዩ ክትባቶች ተማምነው ነው። ያም ሆኖ ሰሞኑን እየወጡ የሚገኙ መረጃዎች ወረርሽኙ እየቀነሰ ከመሄድ ይልቅ በፍጥነት እየተስፋፋ እንደሚገኝ ያመላክታሉ። ጃፓን ውድድሩን በምታካሂድበት ወቅት ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ከአገሪቱ ዜጎች በበለጠ ብዙ ቁጥር ያላቸው እንግዶች ስጋት ሊሆኑ እንደሚችሉ የገመተች ቢሆንም፣ በተቃራኒው ራሷ ጃፓን የእንግዶቿ ስጋት ልትሆን እንደምትችል በቅርብ የወጡ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው።ወረርሽኙ ለዓለም ስጋት ከሆነ ወዲህ ኦሊምፒኩን በዋናነት የምታስተናግደው ከተማ ቶኪዮ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ በቫይረሱ የተጠቁ አስር ሺህ ሰዎች የተገኙባት ሆናለች። ይህም በቀጣዩ ክረምት በሚካሄዱት የኦሊምፒክና የፓራሊምፒክ ውድድሮች ላይ ዳግም ተመሳሳይ ስጋት እንዲፈጠር ያደረገ ሲሆን በብዙዎች ዘንድ ጥያቄ እየተነሳበት ይገኛል።ኦሊምፒኩ ሊካሄድ ስድስት ወራት በቀሩበት በዚህ ወቅት ባለፈው ሐሙስ ብቻ ቶኪዮ በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ ስምንት መቶ ሃያ ሁለት ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባት ከተማ ሆናለች። ይህም ወረርሽኙ በሀገሪቱ ከተከሰተበት ወቅት ወዲህ የታየ ከፍተኛው ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል። የቶኪዮ ከተማ አስተዳዳሪ ዩሪኮ ኮኢኬ ከጃፓን ታይምስ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስም የቶኪዮ የጤና ተቋማት ከአቅማቸው በላይ ሕመምተኞችን እያስተናገዱ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ‹‹ሆስፒታሎች ተዘግተዋል፣ በዚህ ወሳኝ ወቅት በቅርቡ መሰረታዊ አገልግሎት መስጠት ሊያቆሙም ይችላሉ›› በማለትም በከተማዋ ያለውን ሁኔታ ገልፀዋል።ቶኪዮ ወረርሽኙ ከተከሰተ ወዲህ እስካለፈው ሳምንት መጨረሻ ብቻ ሃምሳ ሁለት ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁባት ከተማ ስትሆን አምስት መቶ ያህል ሰዎችም ሕይወታቸው አልፏል። በአጠቃላይ በጃፓን ደግሞ እስካፈው ሰኞ ድረስ በአማካይ ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ እየተጠቁ እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፤ እስካሁን ከሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መሞታቸው ታውቋል።የቶኪዮ ተላላፊ በሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል ዳይሬክተር ኖሮዪ ኦማጋሪ በበኩላቸው ‹‹የቫይረሱ ሥርጭት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ ከዚህ የበለጠ ብዙ ሰዎች በቫይረሱ እንዳይጠቁ ጠንካራ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው›› በማለት ለአገሪቱ ጋዜጣ ተናግረዋል።ጥቂት ቀናት በቀሩት የፈረንጆቹ አዲስ ዓመትና የገና በዓል አከባበር ወቅት በርካታ የአውሮፓ አገራት የወረርሽኙን ሥርጭት ለመቀነስ ጠንካራ መመሪያዎችን ከማውጣት ባሻገር በአገር አቀፍ ደረጃ እንቅስቃሴዎችን እስከ መግታት ደርሰዋል። ይህን በመመልከትም ጃፓን በአንፃራዊነት የተሻለ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ የሚናገሩ አሉ። ከቀናት በፊት የእንግሊዝ መንግሥት የጤና ቢሮ ሃላፊ ክሪስ ዊቲይ በአይነቱ ልዩ የሆነና በፍጥነት የመዛመት ባህሪ ያለው የኮቪድ-19 ቫይረስ በአገሪቱ እንደተገኘ ለዓለም ጤና ድርጅት ጭምር በማሳወቅ ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰቡ ይታወቃል። በአገሪቱ የቫይረሱ ሥርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በአዲስ ዓመትና በገና በዓል ዋዜማዎች ወቅት በሚደረጉ መዝናኛዎች ላይ ጠንካራ እግድ አስቀምጠዋል። መዲናዋ ለንደንን ጨምሮ ቫይረሱ በስፋት በተሰራጨባቸው የደቡብ እንግሊዝ ከተሞችም ጠንካራ የተባሉ ገደቦች ተጥለዋል።አስቀድሞ በቫይረሱ ከፉኛ የተጠቃችው ጣሊያንን ጨምሮ ኔዘርላንድስና ጀርመን እስከ አዲሱ ዓመት ድረስ ማንም ከቤቱ እንዳይወጣ እግድ አስቀምጠዋል። አውስትራሊያም ከገና በዓል በኋላ ተመሳሳይ እርምጃ እንደምትወስድ መረጃዎች ጠቁመዋል። በቅርቡ በቤልጂየም ብራሰልስ የተካሄደውን የአውሮፓ ሕብረት ስብሰባ ከተካፈሉ በኋላ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑዔል ማክሮንና የስሎቫኪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኢጎር ማቶቪች እንዲሁም ሌሎች የአገር መሪዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ይታወቃል። ባለፈው ዓመት በቫይረሱ ሥርጭት ስጋት የገባቸው የኦሊምፒክ አዘጋጆች ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ታላቁን የስፖርት መድረክ ለማራዘም መገደዳቸው ይታወቃል። በዚህም የተነሳ አዘጋጅ ኮሚቴው ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊየን ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ከወር በፊት አሳውቋል። ወረርሽኙ ዳግም በከፍተኛ ሁኔታ ማገርሸቱን ተከትሎም የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ላይ ጥያቄ ተነስቷል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባኽን ጨምሮ የተለያዩ ሃላፊዎች ግን አሁንም ውድድሩን በጥንቃቄ ለማካሄድ ሃሳብ አለወጡም።ቶኪዮ በኦሊምፒኩ ወቅት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በምትወስደው እርምጃ ከዘጠኝ መቶ ስልሳ ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ እንደምታደርግ የተዘገበ ሲሆን፣ የውድድሩ አዘጋጆች ቫይረሱን ለመዋጋት ከአገሪቱ መንግሥት ጋር በየጊዜው ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ። በኦሊምፒኩ የሚሳተፉ አትሌቶችና የስፖርት ልዑካን ቡድኖች የፊት ጭምብል ማጥለቅና ርቀትን መጠበቅ እንደሚገባቸው አዘጋጆቹ በቅርቡ ጠቁመዋል፤ ከውድድሩ በኋላ በጃፓን የሚቆዩበት ጊዜ አጭር እንደሚሆንም አሳውቀዋል።እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ቻይናና ሩሲያን የመሳሰሉ የተለያዩ አገራት ለወረርሽኙ መፍትሄ ይሆን ዘንድ የተለያዩ ክትባቶችን በማምረት የተሳካ ሙከራ እንዳደረጉ መናገር ከጀመሩ ሰንብተዋል። ክትባቱ በምን አይነት ፍጥነት ለዓለም ሕዝብ ተዳርሶ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ከስጋት ነፃ በሆነ መልኩ ይካሄዳል የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው። በኦሊምፒኩ ለመሳተፍ ወደ ቶኪዮ የሚያቀኑ ከቫይረሱ ነፃ የሆኑ አትሌቶች ክትባቱን ለማግኘት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል አይሰጣቸውም የሚሉ ጥያቄዎችም ከወዲሁ እየተነሱ ይገኛሉ።የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባኽ ባለፈው ወር በጃፓን ባደረጉት ጉብኝት ወቅት የተሳካ የኮቪድ-19 ክትባት ተገኘ መባሉን ተከትሎ እንኳን ስፖርተኞች የስፖርቱ አፍቃሪዎች ስቴድየም ገብተው የኦሊምፒክ ውድድሩን ካለ ስጋት እንደሚመለከቱ እርግጠኛ ሆነው ሲናገሩ ተደምጠዋል።የጃፓን መንግሥትና የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አትሌቶች የወረርሽኙን ክትባት እንዲያገኙ የተለያዩ ጥረቶችን እያደረጉ ይገኛሉ። ከዚህ ባሻገር በኦሊምፒኩ የሚሳተፉ አትሌቶችና የስፖርት ቤተሰቦች ወረርሽኙን ለመከላከል የተለያዩ ጥብቅ መመሪያዎችን ማክበር እንደሚገባቸው ቀደም ሲል አዘጋጆቹ አሳውቀዋል።ባለፈው ዓመት ወረርሽኙ በኦሊምፒኩ አዘጋጅ ጃፓንም ይሁን በሌሎች አገራት እንዲህ እንዳሁኑ ባልጠነከረበት ወቅት ለመራዘም የተገደደውን ይህን ውድድር፣ ዘንድሮ ወረርሽኙ ‹‹ክትባት ተገኝቶለታል›› እየተባለም መልኩን እየቀያየረ የብዙዎች ስጋት በሆነበት ጊዜ እንዲካሄድ መወሰን ለብዙዎች አልተዋጠም። ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴውም ይሁን የጃፓን መንግሥት ውድድሩን ለማካሄድ እርግጠኛ ሆነው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙትም ኦሊምፒኩ ካልተካሄደ የሚደርስባቸውን ትልቅ ኪሳራ በማስላት ሊሆን እንደሚችል ትችቶች ይሰነዘራሉ።ኦሊምፒኩ ባለፈው ዓመት መካሄድ ሲገባው ወደ ዘንድሮ በመራዘሙ ብቻ ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊየን ዶላር ኪሳራ እንዳደረሰ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ይህን ኪሳራ ለመሸፈን የቶኪዮ ከተማ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊየን ዶላር ወጪ እንዳደረገ ተዘግቧል፤ የውድድር አዘጋጅ ኮሚቴው አንድ ቢሊየን ዶላር ወጪ አድርጓል። ቀሪውን ሰባት መቶ ሚሊየን ዶላር ደግሞ የጃፓን መንግሥት እንደሚሸፍን ታውቋል። ኦሊምፒኩ ከመራዘሙ አስቀድሞ አስራ ሦስት ቢሊየን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቅ ተገልጿል።በዘንድሮው ዓመት ሳይካሄድ ከተራዘመ ወይም ከተሰረዘ ቀድሞ ከተያዘለት በጀት እስከ አራት እጥፍ ኪሳራ ሊያደርስ እንደሚችል መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013", "passage_id": "1dd6701861055b016f1ec03cf6a04fb5" } ]
fd03ba4834cc67e8f982fc141e737229
8e56a815cdee7aabfdbd7ad0612069df
የአውሮፓ እግር ኳስና ኮሮና ቫይረስ
በአሁኑ ሰዓት ተቋርጦ የሚገኘው የአውሮፓ እግር ኳስ ከዚህ በኋላ በዝግ ስታዲየሞች እንዲደሚካሄድ ግልጽ ቢሆንም መቼ የሚለው ጥያቄ ግን ምላሽ እንዳላገኘ በአውሮፓ የሚገኙ ሊጎችን የሚወክለው ማህበር አስታወቀ። የማህበሩ ምክትል ኃላፊ አልቤርቶ ኮሎምቦ እንዳሉት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተቋረጠው የአውሮፓ ሊግ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብቷል። «አብዛኛዎቹ የማህበሩ አባል ሊጎች በተለይም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች እንዲጀመሩ ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው። ነገር ግን እንደ ቤልጂየም ያሉ ጥቂት አገራት ከነጭራሹ የዘንድሮው ውድድር እንዲሰረዝ ሀሳብ አቅርበዋል» ብለዋል። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዓርብ ዕለት የወደፊት እርምጃዎችን በተመለከተ ስብሰባ እንደሚያደርግ የሚጠበቅ ሲሆን ዘጠኝ ጨዋታዎች የሚቀሩት ሊግ መቼ ይቀጥል? የሚለው ዋና ርዕስ እንደሚሆን ይጠበቃል። ባለፈው ሳምንት አንዳንድ የጀርመን ክለቦች ወደ ስልጠና መመለሳቸውን ተከትሎ እግር ኳስ ማህበራትና የእግር ኳስ አፍቃሪዎች በተስፋ ተሞልተው ነበር። አልቤርቶ ኮሎምቦ ግን ዋናው ትኩረታችን መሆን ያለበት ሐምሌ እና ነሐሴ ላይ ጨዋታዎቹን እንዴት ማስቀጠል አለብን የሚለው ላይ ነው፤ ከዛ በፊት ያሉት ወራት ላይ ጨዋታዎችን ማካሄድ የማይታሰብ ሊሆን ይችላል ብለዋል። «በመጀመሪያ የተጫዋቾች ስልጠና መጀመር አለባቸው። በመቀጠል የጨዋታዎቹ አዘጋጆች የደህንነት ማረጋገጫ ስራዎችን ይሰራሉ። ጨዋታዎቹ በዝግ ስታዲየሞች መከናወናቸው የማይቀር ነገር ነው። እኛ ሀሳብ እናቀርባለን እንጂ የመጨረሻው ውሳኔ ያለው የአገራቱ መንግስት ላይ ነው። የተጣሉት እገዳዎች እንደተነሱ ጨዋታዎችን ከከፍተኛ ጥንቃቄ ጋር በዝግ ስታዲየም እናከናውናለን» ሲሉ ተናግረዋል። የጣልያን እግር ኳስ ፌደሬሽን እግር ኳስ ተጫዋቾች ሌላው ቢቀር ልምምዳቸውን መስራት እንዲጀምሩ በማሰብ ከመጪው ግንቦት ወር ጀምሮ ተጫዋቾቹ ላይ የኮሮና ቫይረስ ምርምራ ማድረግ እንደሚጀምር አስታውቋል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በበኩሉ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተከሰተውን የሊጎችና ውድድሮች መቋረጥን በተመለከተ በሚቀጥለው ሳምንት ስብሰባ ያደርጋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 9/2012
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=30623
[ { "passage": "በዚህ ዓመት ሊካሄድ የነበረው የአውሮፓ ዋንጫ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወደ ሚቀጥለው ዓመት መዛወሩ ተገለጸ፡፡ ዜናውን ቀድሞ ያበሰረው የኖርዌይ እግር ኳስ ማህበር እንደገለጸው ውድድሩ እ.አ.አ በ2021 እንዲካሄድ ተወስኗል፡፡ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ባደረገው አስቸኳይ ውይይት ነው ውሳኔው የተላለፈው፡፡ ውሳኔው የአውሮፓ ሊጎች እንዲጠናቀቁ እድል ይሰጣል ተብሏል፡፡ የአውሮፓ ዋንጫ በአውሮፓውያኑ ከፊታችን ሰኔ 12 እስከ ሀምሌ 12 ሊካሄድ የነበረ ቢሆንም በ 2021 ከሰኔ 11 እስከ ሀምሌ 11 ይካሄዳል፡፡\nየአውሮፓ ዋንጫ እንዲሁም ከ21 ዓመት በታች ውድድሩም ወደ ሚቀጥለው ዓመት የተሸጋገሩ ውድድሮች ናቸው፡፡\nየአውሮፓ ዋንጫ የሴቶች ውድድር ደግሞ በሚቀጥለው ዓመት የወንዶቹ ውድድር ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚካሄድ መርሃ ግብር ወጥቶለታል፡፡\nበኮሮና ቫይረስ ምክንያት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በፈረንጆቹ እስከ ሚያዚያ አራት ድረስ የማይካሄድ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የስፔን ላሊጋ በተመሳሳይ በፈረንጆቹ እስከ ሚያዚያ አራት ውድድሮቹ አይካሄዱም፡፡\nበአውሮፓ ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ የተበራከተባት ጣሊያንም ሊጓ ብቻ ሳይሆን ብዙ ክንውኖችም ተዘግተዋል፡፡በፈረንሳይም አሁን ላይ የሊግ አንድ ጨዋታዎች እየተካሄዱ አይደለም፡፡ የጀርመን ቡንደስሊጋ ደግሞ እስከ ሚያዚያ ሁለት 2020 ድረስ ውድድሮች አይኖሩትም፡፡\nምንጭ፡- ቢቢሲ\n", "passage_id": "8ccba2aa67f4f7f71324acf7bd3782ba" }, { "passage": "በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር በሚኖር ቅርብ ግንኙነት እና ንክኪ እንዲሁም ታማሚው በሚስልበት ወቅት በአየር ላይ በሚለቀቁ ጠብታዎች (droplets) አማካኝነት የሚተላለፈውን ቫይረስ ስርጭት ለመቆጣጠር የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም ወደተለያዩ ሃገራት እንዳይዛመት ለመከላከል አልተቻለም። በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥም ኢትዮጵያን ጨምሮ 133 ሃገራትን ሲያዳርስ ከ138,000 በላይ ሰዎችን አጥቅቶ ለ5000 ሰዎች ህይወት ማለፍ ምክንያት ሆኗል። የዓለም የጤና ድርጅት በመጀመሪያ በዓለምአቀፍ የጤና ስጋት ደረጃ ያስቀመጠው በሽታም ወደ ዓለምአቀፍ ወረርሺኝነት (Pandemic) ተቀይሯል።ከዓለማችን ህዝብ ከግማሹ በላይ የሚከታተለው እግርኳስም እንደማንኛውም የህይወት ክፍል የዚህ ወረርሺኝ ተፅዕኖ እንዲያርፍበት ሆኗል። በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች በየስታዲየሙ እየተገኙ የሚከታተሏቸው ጨዋታዎችም ለቫይረሱ ስርጭት የተመቸ ሁኔታን ሊፈጥሩ የሚችሉ እንደመሆናቸው የየሃገራቱ የጤና ጥበቃ ተቋማትና ውሳኔ ሰጪ ሰዎችን ትኩረት መሳባቸው አልቀረም። ወረርሺኙ ከተነሳባት ቻይና ጀምሮ የተለያዩ ሃገራት ክለቦች፣ ሊጎች፣ የእግርኳስ ማህበሮች፣ ብሎም እስከ ዓለምአቀፉ የእግርኳስ ማህበር ፊፋ ድረስ ከጤና ተቋማቱ ጋር በመተባበር ስርጭቱን ለመከላከል እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ።የቫይረሱ መነሻ የሆነችው ቻይና በየካቲት ወር ጀምሮ ታህሳስ ላይ የሚጠናቀቀውን የቻይና ሱፐርሊግ የሚጀመርበትን ቀን ላልተወሰነ ጊዜ አራዝማለች። ሃገሪቱ የቫይረሱን ስርጭትና የአዳዲስ ተጠቂዎችን ቁጥር በተወሰነ መልኩ ለመቆጣጠር ብትችልም ውድድሩ ግን እስካሁን ድረስ አልተጀመረም። ከእግርኳስ ሊጉ በተጨማሪም በቻይና ሊደረጉ የታሰቡ የእስያ ቻምፒዮንስ ሊግ፣ የሴቶች እግርኳስ የኦሎምፒክ ማጣሪያ፣ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ የፒጂኤ የጎልፍ ውድድር፣ የፌድካፕ የቴኒስ ውድድር፣ የቻይና ግራንድ ፕሪ የሞተርስፖርት ውድድር እና የተለያዩ የቶክዮ ኦሎምፒክ የማጣርያ ውድድሮችን ጨምሮ በርካታ ስፖርታዊ ኩነቶች ተሰርዘዋል፣ ተሸጋግረዋል፣ ወይንም ወደ ሌላ አዘጋጅ ሃገር ተቀይረዋል። ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታም ባለፉት ሶስት ወራት ህዝብ የሚሰበሰብባቸው ስፖርታዊ ውድድሮች በቻይና እንዳይከናወኑ ተደርጓል።የእግርኳስ ደረጃቸው ከፍተኛ የሆኑ ሃገራት በሚገኙባት አውሮፓም የእግርኳሱ ባለድርሻ አካላት የቫይረሱን ስርጭት በመከላከል እና የእግርኳስ ካሌንደሩን ለመጠበቅ፣ ውድድሮች የሚያመነጩት ገቢም እንዳይነጥፍ በማድረግ ተፃራሪ ምርጫዎች ውስጥ የተለያዩ ውሳኔዎችን ሲያሳልፉ ቆይተዋል። የአውሮፓ እግርኳስ ማህበርም የቻምፒዮንስ ሊግ እና ዩሮፓ ሊግ ውድድሮች የሚጠናቀቁበትን ሂደት እና የ2020 የአውሮፓ ዋንጫ ዕጣፈንታን ለመወሰን አባል ሃገራቱን በመሰብሰብ በመወያየት ላይ ይገኛል። የአውሮፓ ዋንጫን ከማራዘም፣ የውድድሩን አዘገጃጀት እና ቅርፅ መቀየር፣ አልፎም የቻምፒዮንስ እና ዩሮፓ ሊግ ውድድሮችን እስከመሠረዝ ድረስ ያሉ እርምጃዎችም ሊወሰዱ እንደሚችሉ ይጠበቃል።ከአውሮፓ ሃገራት ውስጥ በወረርሺኙ ክፉኛ የተጠቃችው ጣሊያን የእግርኳስ ውድድሮቿ በዝግ ስታዲየም እንዲደረጉ የወሰነችው ቀደም ብላ ነበር። ከጣሊያን በመቀጠልም ፈረንሳይ ከ1000 ሰዎች በላይ የሚገኙባቸው ስፖርታዊ ኩነቶች በዝግ እንዲሆኑ ስታደርግ ስፔን፣ ቤልጂየም፣ ጀርመን እና ሌሎች ሃገራትም ይህንኑ ለመተግበር ወስነዋል። የእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር እና ፕሪምየር ሊጉ ግን ውድድሮችን እንደቀድሞው ለማስኬድ በመወሰን መርሃግብሮችን ሲያስቀጥሉ ተስተውሏል። በነዚህ ሃገራት ክለቦች የሚጫወቱ ተጫዋቾች፣ አሠልጣኞች እና የክለብ አመራሮች በቫይረሱ መያዝ፣ የበርካታ ክለቦች አባላትም በከፊልም ሆነ በሙሉ በመለያ ክፍሎች (Isolation Rooms) እና በቤት ውስጥ ራስን በመለየት (Self Isolation) ላይ መሆናቸው ግን ሃገራቱ ሊጎቻቸውን በጊዜያዊነት ቢያንስ እስከ ሚያዝያ ወር ድረስ እንዲያቋርጡ አስገድዷቸዋል።የሃኖቨር 96ቱ ተከላካይ ቲሞ ሁበርስ፣ የቼልሲው አማካይ ካለም ሃድሰን-ኦዶይ፣ የሳምፕዶሪያው አጥቂ ማኖሎ ጋቢያዲኒ፣ የጁቬንቱሱ ዳኔሌ ሩጋኒ፣ የአርሰናሉ አሠልጣኝ ሚኬል አርቴታ፣ የኦሊምፒያኮስ እና ኖቲንግሃም ፎረስት ክለቦች ባለቤት ኢቫንጀሎስ ማሪናኪስ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው በምርመራ ከተረጋገጡ የእግርኳስ ሰዎች ውስጥ ይጠቀሳሉ።በሃገረ አሜሪካ የእግርኳስ ውድድሩ ሜጀር ሊግ ሶከር ለአንድ ወር ያህል እንዲቆም ሲደረግ ከቅርጫት ኳስ እና አሜሪካን ፉትቦል ጀምሮ የቴኒስ እና የጎልፍ ውድድሮች፣ የቦክስ ግጥሚያዎች፣ የሞተር ሬሲንግ፣ ቤዝቦል፣ የፈረስ ውድድር፣ የኮሌጅ ፉትቦል እና ሌሎች በርካታ ስፖርታዊ ውድድሮች፤ ከዚህም አልፎ እንደ WWE ሬሲሊንግ ያሉ ስፖርታዊ የመዝናኛ ዝግጅቶች በከፊል እንዲቆሙ ሆኗል።ዓለምአቀፍ ስፖርታዊ ዝግጅቶችን ስንመለከት ደግሞ የ2020ው የቶክዮ ኦሊምሊክ እስካሁን 701 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች እና 10 ከበሽታው ጋር የተያያዙ ሞቶች በተመዘገቡባት ጃፓን እንደመካሄዱ በርካታ አካላት ስጋታቸውን እየገለፁ ቢሆንም ዓለምአቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ግን ውድድሩን ቀድሞ በተቀመጠው መርሃግብር ለማድረግ እንደተዘጋጀ ገልጿል። ኮሚቴው በመግለጫው ብሏል።በአውሮፓ የሚገኙ ክለቦች ባለፉት ሳምንታት በደጋፊ ፊትም ሆነ በዝግ ስታዲየም ውድድሮችን እያከናወኑ ሲቆዩ የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ይከላከላል ብለው ያሰቧቸውን ልምዶች ሲተገብሩ ቆይተዋል። አብዛኛዎቹ ክለቦች ተጫዋቾቻቸው ከደጋፊዎች ጋር ፎቶ ለመነሳትም ሆነ ፊርማቸውን ማኖር እንዳይገናኙ የከለከሉ ሲሆን በርካታዎቹም ከእግርኳሳዊ ኩነቶች (ልምምዶች እና ጨዋታዎች) ውጪ ሌሎች የቡድኑ አባላትን ከህብረተሰቡ ጋር የሚያገናኙ ዝግጅቶችን እና የስታዲየም ጉብኝቶችን አግደዋል፤ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ሰራተኞች ውጪ ሌሎች ሰዎች በስታዲየሞች እና የልምምድ እና ቴክኒካል ስፍራዎች ላይ እንዳይገኙም አድርገዋል። እንደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ያሉ ውድድሮች ደግሞ ከጨዋታ በፊት የሚደረገውን የተቃራኒ ቡድን ተጫዋቾች እጅ መጨባበጥ የከለከለ ሲሆን ተጫዋቾችን አጅበው ወደ ሜዳ የሚገቡ ህፃናቶች ልምድም ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆም ሆኗል። ክለቦችም የሊጉን መሪነት በመከተል በልምምድ ሜዳዎች እና በክለብ ቢሮዎች ዙሪያ እጅ መጨባበጥ እንዳይኖር አድርገዋል።ስለ ኮቪድ-2019 ወረርሽኝ መረጃ የሚሰጡ ፖስተሮችን በስታዲየም በመለጠፍ፣ በስታዲየም ስክሪኖች ላይም ትምህርታዊ የሆኑ ምስሎች እንዲተላለፉ በማድረግ ተመልካቾች ስለ በሽታው እንዲያውቁ እና ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጥረት ያደረጉ ክለቦችም ነበሩ። በስታዲየም እና የልምምድ ስፍራዎች የፀረ-ቫይረስ እና ፀረ-ባክቴሪያ ኬሚካል ርጭት ማከናወን እና የእጅ ማጠብያ አልኮሎችን በእነዚህ ቦታዎች በማስቀመጥ ህብረተሰቡ እንዲጠቀም ማድረግ በሽታውን ለመከላከል በክለቦች የተወሰዱ እርምጃዎች ነበሩ። ክለቦቹ ማንም ደጋፊ እንደ ሳል፣ ትኩሳት፣ የጉሮሮ ህመም እና ትንፋሽ ማጠር አይነት ምልክቶችን የሚያሳይ ከሆነ ጨዋታዎችን ለመመልከት ወደ ስታዲየሞች እንዳይመጣ ሲማፀኑም ተስተውሏል።የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ከ70 ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸው ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም እንዳይመጡ ለማገድ እንቅስቃሴ እያደረገም እንደነበር ተሰምቷል። ይህም የሆነው እነዚህ አረጋውያን በበሽታው የመያዝ እና ከተያዙም በኋላ ወደ ከፍተኛ ህመም፣ አልፎም እስከ ሞት የመድረሳቸው ዕድል ከሌላው የህብረተሰብ ክፍል አንፃር ከፍተኛ በመሆኑ ነው። በእንግሊዝ በተለይም ለአርሴናሉ አሠልጣኝ ሚኬል አርቴታ ለቫይረሱ መጋለጥ ተጠያቂ ነው የተባሉትን ከጨዋታ በፊት እና በኋላ የሚደረጉ ፕሬስ ኮንፈረንሶችንም ላልተወሰነ ጊዜ ለማቆም በዕቅድ ደረጃ ተይዟል።የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት በሃገራችን የመጀመሪያውን በላብራቶሪ የተረጋገጠ የኮቪድ-2019 ተጠቂ ይፋ አድርጓል። ይህ ታካሚው ከሳምንት በፊት ከቡርኪና ፋሶ ወደ ሃገራችን የገባ የ48 ዓመት ጃፓናዊ ዜጋ እንደሆነ እና በለይቶ ማከሚያ ማዕከልም በህክምና እየተረዳ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ ጨምሮ አስታውቋል።በሃገራችን የሚኖረው ትክክለኛ የቫይረሱ የስርጭት መጠን ምናልባትም በቀጣይ ሳምንታት ግልፅ እየሆነ የሚመጣ ይሆናል። የበሽታው ስርጭት ከፍተኛ ስጋት ላይ የሚጥል ከሆነም ህብረተሰቡን ከህመሙ ለመጠበቅ ሲባል በርካታ እርምጃዎች ሊወሰዱ ይችላሉ። በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ደጋፊ በሜዳ ተገኝቶ ይከታተላቸዋል ከሚባሉ ውድድሮች የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግም ሆነ በዝቅተኛ እርከን ላይ የሚገኙት ሊጎቻችን የእነዚህ እርምጃዎች አንድ አካል ሊሆኑ የሚችሉበት ዕድል ሰፊ ነው። ከላይ የገለፅናቸው የዓለማችን ክለቦች፣ ሊጎች እና የእግርኳስ ማህበራት በሽታውን ለመከላከል የወሰዷቸው እርምጃዎች በአመዛኙ በሃገራችን ተግባራዊ ለመሆን ቢችሉም ከነባራዊ ሁኔታችን አንፃር ከአቅም በላይ የሚሆኑ እንደሚኖሩም ግልፅ ነው።በቂ መፀዳጃ ቤት እና እጅ መታጠቢያ እና ንፁህ የአየር ዝውውር እንኳን የሌላቸው የሃገራችን ስታዲየሞች ዋነኛ የቫይረሱ ስርጭት ማዕከሎች እንዳይሆኑ ቅድመ-ጥንቃቄዎችን ማድረግ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በቂ የጤና መሰረተ ልማት እና ጠንካራ የፋይናንስ ክንድ ያላቸውን ሃገራት ተሞክሮ ከሃገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብም ጨዋታዎችን በዝግ ስታዲየም ከማድረግ አንስቶ እግርኳሳዊ ውድድሮችን እስከማቋረጥ ድረስ የተለያዩ አስፈላጊ እርምጃዎችን የምንወስድባቸው የራሳችን ልኬቶች (thresholds) ያስፈልጉናል። ክለቦች፣ አዲሱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የጋራ ኩባንያ እና ፌዴሬሽኑም ከጤና ተቋማቶቻችን ጋር በመወያየት ሊከሰት ለሚችል ማንኛውም የጤና ስጋት ተገቢውን ውሳኔ እንዲያስተላልፉበት የሚረዳቸውን ቅድመ-ዝግጅት ቢያደርጉ እንመክራለን።", "passage_id": "b5f26c995b47fd1ffa0bea6b1a65cd43" }, { "passage": " ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪመየር ሊግ አዲስ ውሳኔ ካላስተላለፈ በቀር በተያዘው ወር መጨረሻ ዳግም ወደ ውድድር ለመመለስ ማቀዱ ይታወቃል፡፡ ይህንን ተከትሎም ማንቸስተር ዩናይትድ ከቀናት በኋላ ልምምድ ይጀምራል:: ታዲያ ተጫዋቾች ከአቋማቸው ላለመውረድ በቤታቸው ሆነው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ ማተኮራቸውን በተለያዩ ጊዜያት ለደጋፊዎቻቸው በሚያጋሩት ተንቀሳቃሽ ምስል ያስመለክታሉ፡፡ ይህ ሁኔታም ቀድሞ ለረጅም ሰዓታት አብረዋቸው ያሳልፉ ለነበሩትና አሁን ግን በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች መልዕክት ለሚለዋወጡት አሰልጣኞች መልካም መሆኑን የቀያዮቹ አሰልጣኝ ኦሊጉነር ሶልሻየር ለኢቭኒንግ ስታንዳርድ ገልጸዋል፡፡ ተጫዋቾች ጤናቸውንና አቋማቸውን በመጠበቁ ሂደት ቤተሰቦቻቸውም እንዲያግዟቸው ጭምር ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በርካታ ስፖርታዊ ክንዋኔዎች መታገዳቸውን ተከትሎ ስፖርተኞች ከቤታቸው እንዳይወጡ በመከልከላቸው በቤታቸው ሆነው በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ እንዲያሳልፉ አስገድዷቸዋል፡፡ በተንቀሳቃሽ ምስል ሁሉም ከገዳዩ ቫይረስ ራሱን እንዲጠብቅ መልእክት በማስተላለፍና ቫይረሱን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ድጋፍ ከማድረግ ባለፈም በቤታቸው ውስጥ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በምን መልኩ እንደሚሰሩ ለሌሎች በማስመልከት ላይም ይገኛሉ፡፡ ከተራዘሙ ውድድሮች መካከል አንዱ ኦሊምፒክ እንደመሆኑ በብሄራዊ ቡድን የተካተቱ ስፖርተኞችም ለአንድ ዓመት በምን መልኩ ብቃታቸውን ጠብቀው መቆየት እንደሚችሉ ልምዳቸውን እያካፈሉ ይገኛሉ፡፡ እንግሊዛዊቷ የሁለት ጊዜ የወርልድ ቴኳንዶ የዓለም ቻምፒዮናዋ ጃዴ ጆንስ ለኦሊምፒኩ በተሻለ ብቃት ለመመለስ በአንድ ዓመት መራዘሙን እንደ መልካም አጋጣሚ የምትመለከተው መሆኑን ትገልጻለች፡፡ ውድድሮች፣ የልምምድ አካዳሚዎች እንዲሁም ጂምናዚየሞች በዚህ ወቅት የተዘጉ ቢሆንም በቤት ውስጥ ልምምድ በማድረግ በስፖርቱ የሶስት ጊዜ ቻምፒዮን በመሆን ታሪክ ለመስራት እየተዘጋጀችም ትገኛለች፡፡ ከዚህም ባሻገር ወቅቱን እንደማገገሚያ ጊዜ በመውሰድ ያለመዘናጋት ልምምድ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን እንደገለፀች ዘ ጋርዲያን በዘገባው አስነብቧል፡፡ ሌላኛዋ ዋናተኛም በተመሳሳይ የራሷንና የሌሎችን ህይወት አደጋ ላይ ላለመጣል በቤቷ መሆንን አማራጭ የሌለው መሆኑን ታምናለች፡፡ የአምስት ጊዜ ኦሊምፒክ ቻምፒዮናዋ ኬት ሌዴኪ ከሲኤንኤን ጋር በነበራት ቆይታ ከዓመት በኋላ በሚካሄደው ኦሊምፒክ በደካማ አቋም ላለመሳተፍ ልምምዱን በጎረቤቶቿ መዋኛ ገንዳ ላይ አጠናክራ መቀጠሏን ገልጻለች፡፡ በእርግጥ ለ800 ሜትር ነጻ ዋና ቻምፒዮናዋ ልምምድ የምታደርግበት ገንዳ በቂ ባይሆንም ከአቋሟ ዝንፍ ብላ ላለመገኘት ስትል በልምምድ ላይ ትቆያለች፡፡ አንጋፋው ህንዳዊ የስፖርት ጋዜጠኛ ሮሂት ብሪጅናዝ በበኩላቸው ስፖርቱ ሲመለስ የተሻለ ነገር ማግኘት ይሻል ይላሉ፡፡ በቤት ውስጥ መቆየት አስፈላጊ በሆነበት በዚህ ወቅት ውድድሮች ባይኖሩም ከዚህ ቀደም የተካሄዱ ውድድሮችን እንዲሁም ዘጋቢ ፊልሞችን በመመልከት እያሳለፉ መሆኑን ዘ ስቴር ታይምስ አስነብቧል፡፡ በኢትዮጵያም ከዚህ ቫይረስ መስፋትን ተከትሎ ክለቦች፣ ማሰልጠኛ ማዕከላት እንዲሁም ብሄራዊ ቡድኖች ስፖርተኞቻቸውን እንዲበትኑ ተደርጓል:: ስፖርተኞቹ በቡላቸው ባላቸው አቅም ቫይረሱን ለመቆጣጠር በሚደረገው ርብርብ ከደጋፊዎቻቸውና በተናጥል በመሆን ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ብቃታቸውን ጠብቀው ለመቆየት ምን እያደረጉ እንደሆነ መረዳት አልተቻለም፡፡ ስፖርተኛ ሁሌም ብቁና ዝግጁ ሆኖ መገኘት ያለበት እንደመሆኑ ከሌሎች ተሞክሮ በመውሰድ ይህንን በቤት ውስጥ የማሳለፍ ወቅት አቅማቸው በቻለ መጠን ዝግጅታቸውን ማከናወን ተገቢ መሆኑን የስፖርት ባለሙያዎችም ይመክራሉ፡፡ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽንም ስፖርተኞች በየግላቸው ጊዜውን እንዲያሳልፉና መመሪያዎችን መከተል እንደሚገባቸው በመግለጫው ጠቁሟል፡፡ በሌላ በኩል በአትሌቲክስ ስፖርት የምትታወቀው ኢትዮጵያ አትሌቶች ከአበረታች መድሃኒት የጸዳ ጊዜ ማሳለፍ እንደሚገባቸው ተመልክቷል፡፡ ብሄራዊ የጸረ አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት አትሌቶች ሳይዘናጉ ራሳቸውን እንዲጠብቁና በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ያልተገባ ጥቅምን ለማግኘት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የህግ ጥሰት በሚፈጽሙት ላይ የእርምት እርምጅ ይወሰዳል፡፡ ከዚህ ቀደም ይከናወን የነበረው የአትሌቶችን ናሙና የመውሰድና የመመርመር ሂደትም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ጽህፈት ቤቱ አሳስቧል፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 24/2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "21899956b5d85efbc79462ca38c89e30" }, { "passage": "ኦስትሪያ፣ ክሮኤሺያ፣ ስዊትዘርላንድ፣ ስፔን፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን ኮሮናቫይረስን ሪፖርት ያደረጉ አገራት ሲሆኑ፤ 'ወደ አገራችን የገባው ከጣሊያን በመጡ ሰዎች ነው' ብለዋል። \n\nአፍሪካዊቷ አገር አልጄሪያም ከጣሊያን ኮሮናቫይረስ መዛመቱን አሳውቃለች። \n\nኑሮውን በብራዚል ያደረገው ግለሰብም ቫይረሱን ከጣሊያን ወደ መኖሪያ አገሩ በመውሰድ በላቲን አሜሪካ የመጀመሪያው ኮሮናቫይረስ ሊመዘገብ ችሏል። \n\nበጣሊያን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 300 የደረሱ ሲሆን 11 ሰዎች በቫይረሱ ሞተዋል። \n\nየጣሊያን ጎረቤት አገራት ከጣሊያን ጋር የሚያዋስናቸውን ድንበር ሊዘጉ ይችላሉ የሚል መላ ምት በስፋት ቢነገርም፤ የፈረንሳይ፣ ጀርመን እና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ድንበርን ክፍት በማድረግ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ጥረት እንደሚያደርግ አሳውቀዋል። \n\nበቁጥር ከፍ ያሉ የአውሮፓ አገራት ወደ ጣሊያን ሲጓዙ መውሰድ ስላለባቸው ቅድመ ጥንቃቄዎች ዜጎቻቸውን እያስጠነቀቁ ይገኛሉ። \n\nበኮሮናቫይረስ ምክንያት ሊካሄዱ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩ የጣሊያን እግር ኳስ ጨዋታዎች በዝግ ስታድየም እንዲካሄዱ ተወስኗል። \n\nከጣሊያን ወደ ብራዚል የተጓዘው የ61 ዓመት አዛውንት ቫይረሱ እንደተገኘበት ተረጋግጧል።\n\nየሳኦ ፖሎ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ፤ ወደ ብራዚል የተመለሰው ታዋቂው የብራዚል ካርኒቫል ዝግጅት እየተከናወነ በነበረበት ወቅት ነበር። ለካርኒቫል በዓል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ብራዚል እና ሳኦ ፖሎ ይተማሉ በዚህም ቫይረሱ ተሰራጭቶ ከሆነ ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት እጅግ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል። \n\nእስካሁን በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 78064 ሲሆን በቻይና ብቻ ወደ 2715 ሰዎች በቫይረሱ ሞተዋል። \n\n ", "passage_id": "9007de210fb97e24341ab4e9aa86b702" }, { "passage": "ስፖርት አንድ ትልቅ ማሕበራዊክንውን ነው።በተለይ በዚህ ዘመን ስፖርት ትልቅ የገቢ ምንጭም ነው፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገራችን በተለይም በእግር ኳሱ መንደር እየተከሰቱ የመጡ ሁከቶችን ተከትሎ ስፖርትና ፖለቲካን ምን አገናኛቸው? በሚል በርካታ የስፖርት ቤተሰቦች ሙግት ሲገጥሙ ይታያል፡፡ በአንድ ወገን ስፖርትና ፖለቲካ አይገናኙም የሚሉ ሞጋቾች ፖለቲካና መንግሥት በስፖርቱ አካባቢ መድረስ የለባቸውም የሚል አቋም ሲያንፀባርቁ ይስተዋላል፡፡ በሌላ በኩል ስፖርት ብቻም ሳይሆን ሁሉም ነገር ፖለቲካ መሆኑን የሚያስቀምጡ ወገኖች ስፖርት ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ ሊሆን እንደማይችል ያስቀምጣሉ፡፡ከዚህ በተለየ መልኩ ስፖርት በመሰረታዊ ፅንሰ ሃሳቡ ከፖለቲካ ነፃ መሆን እንዳለበት ወይም ነፃ ቢሆን ይመረጣል፣ ነገር ግን ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ እንደማይሆን በርካታ ማሳያዎችን የሚያስቀምጡ ምሁራን በርካታ ናቸው፡፡ስፖርት በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ሁነኛ የፖለቲካ መሳሪያ ሆኖ ማገልገል እንደቻለ ማስተዋል ይቻላል፡፡ስፖርት በጥሩ ከተጠቀምንበት ምላሹ ጥሩ እንደሚሆን ሁሉ ለመጥፎ ፖለቲካ አላማ ከተጠቀምንበት በተቃራኒው የሚያስከትለው ጉዳት በቀላል የሚታይ እንዳልሆነ ከታሪክ ማህደሮች መማር ይቻላል፡፡ ለዚህም በዓለማችን በሩቅና በቅርብ ዓመታት ስፖርት ከፖለቲካ ጋር እንዴት እየተሳሰረ እንደመጣ የተለያዩ አጋጣሚዎችንና የአገራትን ተሞክሮ በመዘርዘር መመልከት ይቻላል፡፡አሜሪካበሃያሏ አገር አሜሪካ እጅግ ተወዳጅና ሰፊ ተቀባይነት ባለው የአሜሪካን እግር ኳስ ውስጥ ስፖርት በበርካታ አጋጣሚዎች ከፖለቲካ ጋር ሲተሳሰር ማየት የተለመደ ነው፡፡ በአሜሪካ እግር ኳስ ውስጥ የሚሳተፉ ሃብታምና ዝነኛ ጥቁር ተጫዋቾች በአሜሪካዊያን ጥቁሮች ላይ የሚደረገውን የዘር መድልዎ በመቃወም ከጨዋታ በፊት የአሜሪካ ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመር መንበርከካቸው ዛሬ የመጣ ነገር አይደለም፡፡ በአሜሪካ እግር ኳስ ብቻም ሳይሆን በቅርጫት ኳስና ሌሎች ስፖርቶች ላይ የሚሳተፉ ታዋቂ ጥቁር ስፖርተኞች አሁንም ተመሳሳይ ነገር ሲያደርጉ ይታያል፡፡ ይህ የጥቁር ተጫዋቾች ተቃውሞ የዋይት ሃውስን በር እያንኳኳም ተፅዕኖ ማሳረፍ ሲችል በግልፅ ታይቷል፡፡ በቅርብ ሰሞን እንኳን የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ይህን የተጫዋቾችን ድርጊት በመቃወም ስቴድየም ጥለው ለመውጣት እስከ መገደድ የደረሱበት አጋጣሚ ይታወሳል፡፡ስፔንበስፔን ታላቁ ውድድር ላሊጋ የዓለማችን ሃያል የእግር ኳስ ክለቦች ባርሴሎናና ሪያል ማድሪድ በሚጫወቱበት ወቅት የሚፈጠረው ድባብ ከስፖርት ይልቅ ወደ ጦርነት የሚያደላ መሆኑን የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ያውቁታል፡፡ ጨዋታው በተገንጣዩ የካታላን ግዛት ወኪል ባርሴሎናና በማእከላዊያን ወኪል ሪያል ማድሪድ መካከል የሚደረግ መሆኑ እያንዳንዱ ጨዋታ ከፖለቲካ ትኩሳት ነፃ ሆኖ አያውቅም፡፡ የባርሴሎናው የተከላካይ መስመር ተጫዋች ጄራርድ ፒኬ በአንድ ወቅት ‹‹ከአሁን በኋላ ካታላን ለሚባል አገር እንጂ ስፔን ለሚባል አገር አልጫወትም›› ብሎ በአደባባይ ማወጁ ጨዋታው የሚካሄድበትን ድባብ ይገልጻል። ከስፔን ሳንወጣ በሁለቱ የማድሪድ ክለቦች ሪያል ማድሪድና አትሌቲኮ ማድሪድ መካከል የሚደረገው ጨዋታም ስፖርታዊ አይደለም። ፍጹም የፖለቲካ መንፈስ የሚንጸባረቅበት ነው። በአምባገነኑ ጀነራል ፍራንኮ ዘመን ከሪያል ማድሪድ ይልቅ አትሌቲኮ ማድሪድ መንግሥታዊ ድጋፍ ያገኝ ነበር ተብሎ ስለሚታመን የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ዘወትር ከፖለቲካ ተፅዕኖ ወጥቶ አያውቅም።ደቡብ አፍሪካኔልሰን ማንዴላ በአፓርታይድ ስርዓት ምክንያት የተቃቃረውን ደቡብ አፍሪካዊ ሁሉ አንድ ያደረጉት የራግቢን ስፖርት ተጠቅመው ነበር። ማዲባ ደቡብ አፍሪካ የዓለም ራግቢ ዋንጫን አዘጋጅ የነበረችበትን መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው የራሳቸውን የተለየ መርሐግብር በማውጣት ቡድናቸውን እያበረታቱ ደቡብ አፍሪካ ብታሸንፍም ባታሸንፍም በስፖርት አማካኝነት የአገሪቱ ህዝብ ወደ አንድ ሊመጣ እንደሚችል ቀድመው ተረድተዋል፡፡ የነፃነት ታጋዩ እድል ሲቀናቸው ቡድናቸው ዋንጫ ወሰደ፡፡ ይህም የተቃቃረው ህዝብ በደስታ ስሜት ቂሙን ረስቶ ተቃቅፎ በአንድ ላይ ይቅር የሚባባልበትን አጋጣሚ እንዲፈጠር አደረገ፡፡የነፃነት ታጋይና የሰላም አባት የሆኑት ማንዴላም በዓለም አቀፉ የስፖርት መድረክ ለሰው ልጆች ነፃነትና መብት ባደረጉት ትግል፣ ስፖርታዊ ውድድሮች በረጅሙ ዘመን የእርሳቸውና ሕዝባቸው እልህ አስጨራሽ የፀረ-አፓርታይድ የነፃነት ተጋድሏቸው ወቅት ‹‹ሰላማዊ የትግል ስልት›› መሆኑን ላሳዩበት ፖለቲካዊ ብቃታቸው በተሰጣቸው ዓለም አቀፍ ሽልማት ላይ ባደረጉት ንግግር ‹‹ ስፖርት ዓለምን ለመቀየርና ህዝቦችን አንድ ለማድረግ ትልቅ ሃይል አለው›› በማለት ገልፀውታል፡፡እንግሊዝና አርጀንቲናታላላቆቹ የእግር ኳስ አገራት እንግሊዝና አርጀንቲና በዓለም ዋንጫም ይሁን በሌሎች አጋጣሚዎች ሲጫወቱ ከኳስነቱ ይልቅ ፖለቲካነቱ እንደሚያመዝን በተደጋጋሚ ታይቷል፡፡ እኤአ በ1982 ለአስር ያህል ሳምንታት በፎክላንድ ደሴቶች ምክንያት ሁለቱ አገራት የገጠሙት የውጊያ ታሪክ አሁንም ድረስ በሰላማዊው ጦርነት በኳስ ሜዳ ይከተላቸዋል፡፡ ከፍተኛ የሆነ ጦርነት ውስጥ ገብተው የነበሩት ሁለቱ አገራት ሲገናኙ ከኳሱ ውጤት ጀርባ የሚመነዘር ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ይራመዳል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ኳሳዊ ሽንፈት የክብር፣የማንነት፣የሐገር፣የፖለቲካ ጉዳይ በመሆኑ ነው። በይበልጥ የሁለቱ አገራት የኳስ ፉክክር መክረር የጀመረውም ከጦርነቱ በኋላ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሴኔጋልና ፈረንሳይፈረንሳይ ባስተናገደችው የዓለም ዋንጫ በመክፈቻው ጨዋታ በሴኔጋል አንድ ለዜሮ መሸነፏ ከኳሱ ውጤት ይልቅ ፖለቲካዊ አንደምታው ትልቅ እንደነበር ይታወሳል፡፡ሴኔጋል ፈረንሳይን አሸነፈች፣ አፍሪካውያን ሁሉ በአንድ እግር ቆመው አጨበጨቡ፣ጨፈሩ፡፡ ምክንያቱም ሴኔጋል በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ውስጥ ወድቃ ነበር። ስለዚህ የሴኔጋል ፈረንሳይን ማሸነፍ ከኳስ በላይ ሊተረጎም የቻለ የመላውን አፍሪካውያን ስነልቦና የቀየረ ፖለቲካዊ አንድምታ ነበረው ማለት ነው፡፡ቻይናቻይና በ2050 አካባቢ የዓለምን እግር ኳስ መቆጣጠር እንደምትፈልግ ይታወቃል፡፡ለዚህም በመላው ቻይና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕጻናት እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የስፖርት አካዳሚዎች ተከፍቶላቸው ከሕጻንነታቸው ጀምሮ ተመልምለው የኳስ ስልጠና እየወሰዱ ነው። የቻይና ክለቦች ልጆቻቸው ብቁ እስከሚሆኑ ድረስ የዓለምን ቀልብ ለመሳብ ከስፔን እና እንግሊዝ ተጫዎቾችን እጅግ ውድ በሆነ ዋጋ እየገዙ የሚወስዱት ስፖርትን ብቻ አስበው እንዳልሆነ ብዙዎች ይመሰክራሉ፡፡ አንድ አገር በዓለም ላይ የበላይነትን ለማሳየት ስፖርትም አንዱ አማራጭ መሆኑ ቻይናውያን ዘግይተውም ቢሆን ገብቷቸዋል፡፡ ጀርመንጀርመን ከሌላ አገር ጋር ገጥማ ስትሸነፍ በኳስ ብቻ የተሸነፈች አይመስልም፡፡ ይህም የሆነው ጀርመናውያን በኳስ የሚመጣ ሽንፈትን የክብር፣የፖለቲካና የስነልቦና ሽንፈት አድርገው ስለሚመለከቱት መሆኑ ይገለፃል፡፡ ይህንን የሚያደርጉት ኳስ የፖለቲካ ዋና መሳሪያ እንደሆነ በአግባቡ ስለሚረዱ መሆኑንም የሚናገሩ በርካታ ናቸው፡፡አሜሪካና ኢራንየ1998ቱ በፈረንሳይ አስተናጋጅነት የተካሄደው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ በዓለም አቀፉ የፖለቲካ መድረክ ስፖርት ለሰላም፣ ለወንድማማችነት፣ ለአንድነት … ወዘተ ያለው አዎንታዊ ፋይዳ በግልፅ የታየበት መድረክ ሆኖ ነበር ያለፈው። በአንድ ምድብ ተደልድለው የተገናኙት በጥንታዊ ስልጣኔዋ የምትታወቀው ኢራን ከዘመናችን ሃያሏ አገር አሜሪካ ጋር ነበር። እነዚህ ሁለት የፖለቲካ ባላንጣ አገሮች በአንድ ቡድን ተደልድለው የተገናኙበትን ጨዋታና ፉክክር ‹‹የጨዋታዎች ሁሉ እናት›› በማለት ነበር የአሜሪካው እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት በአጭር ቃል የገለጹት፡፡ በወቅቱም ስለ ሁለቱ አገራት ጨዋታ የዘገቡ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን፣ የሁለቱ አገራት ፖለቲከኞች፣ ዲፕሎማቶች፣ የእግር ኳስ ባለሙያዎችና ተንታኞች ጨዋታው ከስፖርታዊ ውድድር ባለፈ ጠንከር ያለ ፖለቲካዊ አንድምታ እንዳለው ሲዘግቡ ቆይተዋል፡፡ ከእግር ኳስ ፉክክሩ ባሻገር ፖለቲካዊ አንድምታው ጎልቶ በተነገረበት በዚህ የአሜሪካንና የኢራን ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ፣ ሁለቱ አገሮች በስፖርቱ መድረክ ለሰላምና ለመልካም ግንኙነት ያላቸውን አዎንታዊ ፍላጎትና ስሜት የገለጹበት መልካምና ልዩ አጋጣሚ ሆኖ ይታወሳል፡፡በተጨማሪም የሁለቱ አገሮች ደጋፊዎች በውድድሩ ወቅት ያሳዩት ሰላማዊነትና ስፖርታዊ ጨዋነት ‹‹ስፖርት ለሰላም፣ ለፍቅር፣ ለአንድነት፣ ለትብብር፣ ለወንድማማችነት›› የሚለውን የስፖርት መርህ ከፍ አድርጎ ለዓለም ሕዝብ ያሳየ ነበር። ጥቂት የማይባሉ የሁለቱ አገራት እግር ኳስ አፍቃሪያንና ደጋፊዎች አንድ ጉንጫቸውን በአሜሪካን አንድ ጉንጫቸውን ደግሞ በኢራን ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት በማስዋብ የእግር ኳስ ስፖርት በአገሮችና በሕዝቦች መካከል መቀራረብና ሰላም እንዲፈጠር የሚያስችል መድረክ መሆኑን በተግባር ለዓለም አሳይተውበታል። ይህን የወቅቱን እውነታ ያስተዋለው የኢራኑ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆነው አፍሺህን የእግር ኳስ ስፖርት አገራትን በሰላምና በፍቅር መንፈስ ለማስተሳሰር ያለውን ጉልበት እንዲህ በማለት ነበር የገለጸው ‹‹ይህችን ዓለም በአንድ ላይ ለማምጣት ሁለት ነገሮች ብቻ ቁልፍ ናቸው፣ እነሱም እግር ኳስና ፍቅር ይባላሉ››፡፡ማጠቃለያየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ የነበሩት ባንኪሙን በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እ.ኤ.አ ግንቦት 11 ቀን 2011 ዓ.ም\n‹‹ስፖርት ለሰላምና ለልማት ያለው አስተዋጽዖ›› በሚል ባደረጉት ንግግራቸው እንዳረጋገጡት፤ ስፖርት በዓለም አቀፍ ደረጃ የአገሮችን ድንበር ተሻግሮ የዘር፣ የጎሳና የኃይማኖት ልዩነቶች ሳይገድበው፣ የዓለም አቀፍ ቋንቋ መሆን እንደቻለና ስፖርታዊ ውድድሮች ለሰው ልጆች ሰላም፣ አንድነትና እድገት እየተጫወቱ ያለውን ቁልፍ ሚና መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ስፖርታዊ ውድድሮች የሰላም፣ የወንድማማችነትና የፍቅር መድረክ ናቸው ቢባሉም አልፎ አልፎም ቢሆን የዘረኝነት መንፈስ የሚንጸባረቅባቸው፣ የሌሎችን ክብርና ነፃነት የሚጋፋ ኃይማኖታዊ መልዕክቶች፣ ፖለቲካዊ ተቃውሞች፣ ጠብና ግጭት ድረስ የሚዘልቁ ክስተቶችን ማስተናገዳቸው አልቀረም።እንግሊዝና አርጀንቲና፣\nየላቲን አሜሪካኖቹ የኤልሳልቫዶርና\nሆንድራስ በእግር ኳስ ጨዋታ\nምክንያት የተፋጠጡበትንና ጦር የተማዘዙበት አጋጣሚዎች ሲታሰቡ\nየስፖርቱ መድረክ አልፎ\nአልፎም ቢሆን የፖለቲካ\nአጀንዳዎች እንደማያጣው ያስገነዝበናል።አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሰኔ 22/2011ቦጋለ አበበ", "passage_id": "38f48767cc66dc61e9c6ff1dae46b8ab" } ]
e7dda6658291e3196108f7035175a384
c7490cbc30ca4cde47f18370fb5ddfa6
የተወዳጁ ስፖርት በመሰናክል የተዋጀው መንገድ
በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፋት ከሚዘወተሩ የስፖርት አይነቶቸ በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል ። በተለያዩ አገራት ከፍተኛ ተቀባይነትን ማግኘት የቻለው የዳርት ስፖርት መነሻው ጥንታዊቷ ግሪክ እንደሆነች የታሪክ ድርሳናት ይናገራሉ። በግሪክ ወታደራዊ ተቋማት ውስጥ የዳርት ስፖርት በተለየ ሁኔታ ይዘወተር ነበር። በአጭር ጊዜም በአገሪቱ የሚኖረው ሌላው ማህበረሰብ አውቆት በስፋት ወደ ማዘውተር መሸጋገሩ ይነገራል፤ የዳርት ስፖርት፡ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በስፋት ወደ መዘውተር ሊሸጋገር የቻለውም በዚህ ሂደት ውስጥ አልፎ ነው። ዳርት አካልንና አዕምሮን የሚያነቃቃ ባህሪ የተላበሰ ስፖርት ሲሆን፤ የማሰብ ችሎታን የማሳደግ አቅም ያለው መሆኑ ስፖርቱን ተወዳጅ እንዲሆን አድርጎታል። ስፖርቱ መነሻውን ግሪክ ያድርግ እንጂ በአሁኑ ወቅት አድማሱን በማስፋት በተለያዩ አገራት በመዘውተር ላይ ይገኛል። ኢትዮጵያ ስፖርቱ መዳረሻውን ካደረገባቸው አገራት መካከል አንዷ ናት። ስፖርቱ በአገሪቱ መዘውተር ከጀመረ ረጅም ጊዜ እንዳስቆጠረም መረጃዎች ያመላክታሉ። የስፖርቱ መዘውተር የጀመረበት ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም በሚፈለገው የዕድገት ደረጃ ላይ እንደማይገኝ ይስተዋላል። ስፖርቱ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ሃይማኖት፣ የዘርና ቀለም ልዩነት ሣይገድበው ማንኛውም ሰው አካሉንና አዕምሮውን ለማዳበር፤ ጤናውን ለመጠበቅ፣ በመስኩም ተወዳዳሪ ለመሆን የሚሳተፍበት ስፖርት ቢሆንም፤ በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች እየተዝወተረ እንደማይገኝ ለስፖርቱ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ወቀሳ ሲሰነዝሩ ይስተዋላል። ለዳርት ስፖርት እንደሌሎች የስፖርት አይነቶች ትኩረት አለመሰጠቱም ምክንያት ተደርጎ ይነሳል። የኢትዮጵያ ዳርት ፌዴሬሽን ጽፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጥላሁን አላምረው፤ ስፖርቱ በሚፈለገው ደረጃ እንዳያድግ ከበጀት እጥረት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች ዋነኛ ምክንያት መሆናቸውን ይናገራሉ። ይህም ስፖርቱን በብዙ መልኩ ጎድቶታል። የኢትዮጵያ ዳርት ፌዴሬሽን የዓለም አቀፍ ዳርት ፌዴሬሽን (WDF) አባል መሆኑን ተከትሎ እ.ኤ.አ በ2017 በጃፓን በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ውድድር ኢትዮጵያ የመሳተፍ ዕድሉን አግኝታ ነበር። ለአገራችን የዳርት ስፖርት ይህ አጋጣሚ ትልቅ ቢሆንም ፌዴሬሽኑ ባለበት የበጀት ውስንነት ምክንያት ብሔራዊ ቡድኑን በዚህ መድረክ ላይ ለማሳተፍ ሳይቻል መቅረቱን እንደ ማሳያ ያስቀምጣሉ። በአገሪቱ የዳርት ስፖርት በሚፈለገው ደረጃ እንዳይጓዝ የተለያዩ ፈተናዎች እንቅፋት ቢሆኑበትም፤ ፌዴሬሽኑ ኃላፊነቱን ለመወጣት እየሠራ መሆኑን አቶ ጥላሁን ያነሳሉ። ስፖርቱን ከማስተዋወቅ፣ ከማስፋፋት አኳያ በርካታ ሥራዎችን በተለየ መልኩ በማከናወን ውጤታማ መሆንም እንደሚቻልም ይጠቁማሉ። ለዚህም በአገር አቀፍ ደረጃ የውድድር መድረኮችን እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም አማራጭ ተደርጎ እንደተወሰደም ያመለክታሉ። ለአብነትም በኢትዮጵያ ዳርት ፌዴሬሽን አማካኝነት የሚዘጋጀው አገር አቀፍ የዳርት ቻምፒዮና ስፖርቱ በህብረተሰቡ ዘንድ ተወዳጅና ተዘውታሪ እንዲሆን ባለፉት ዓመታት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በአገር አቀፍ ደረጃ፣ ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የሚሳተፉበት ዓመታዊ የዳርት ቻምፒዮና ስፖርቱን ከማስተዋወቅ፣ ተወዳጅና ተዘወታሪ ከማድረግ ባሻገር ታዋቂ ስፖርተኞችን ከማፍራት አኳያ አበረታች ውጤትም ማግኘት መቻሉን አብራርተዋል። የውድድር መድረኩ ለስፖርቱ ውጤታማነት ያለውን አስተዋጽኦ ለመጨመር በዘንድሮው ዓመትም ቻምፒዮናው የሚቀጥል ይሆናል። የኢትዮጵያ ዳርት ቻምፒዮና ለ14ኛ ጊዜ በመጪው ሰኔ በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ለማካሄድ ዝግጅት ሲደረግ የቆየ ሲሆን፤ በዓለም ዓቀፍ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ሻምፒዮናው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ነው ያመላከቱት። ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የስፖርቱን እንቅስቃሴ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እንዲህ አይነት ውድድሮችን በማዘጋጀት የሚወሰን አለመሆኑን ያነሳሉ። በማንኛውም ደረጃ የሚካሄዱ የዳርት ውድድሮች፣ ግጥሚያዎችና ጨዋታዎች ወጥ በሆነ መንገድ የሚመሩት ሥራዓቶችን በማበጀት እየተሰራ ይገኛል። ስፖርቱን ትክክለኛውን መስመር እንዲይዝ የሚያደርገውን ማንዋሉ በዘርፉ ባለሙያዎች በተዘጋጀና ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን ባካተተ መልኩ የተዘጋጀ መሆኑ ውጤቱ የተሻለ እንዲሆን ያደርገዋል ሲሉ አስገንዝበዋል። በኢትዮጵያ ስፖርቱ ተወዳጅ ቢሆንም፤ እየተኬደበት ያለው መንገድ መሰናክል የበዛበት መሆኑን በመጨረሻ ያነሱት፤ ኃላፊው፤ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑም በቀጣይ የውድድር አማራጮችን መፍጠር ያስፈልጋል። በመሆኑም የዳርት ስፖርትን የበለጠ ተወዳጅና ተዘውታሪ ከማድረግ፣ ከማዘመን፣ ስፖርታዊ ጨዋነትን ከማስፈን፣ የመረጃ አያያዝ ሥርዓትን ከማቀላጠፍ፣ በክልል ፌዴሬሽኖች፣ ማህበራትና ሌሎች ክበባት መካከል የጋራ ግንዛቤን ከማዳበር አንፃር ሰፊ ሥራዎቸን ለመሥራት ዕቅድ መያዙን አስታውቀዋል። የዓለምን ህዝብ ሥጋት ውስጥ የከተተው የኮሮና ቫይረስን በመቆጣጠር በሀገራችን መደበኛ እንቅስቃሴ መጀመር ሲቻል ፌዴሬሽኑ እነዚህና መሰል ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራ በማስገንዘብ ሐሳበቸውን ቋጭተዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 13/2012ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=30805
[ { "passage": "ስፖርት ጤንነትን ከመጠበቅና ከመዝናኛነት ባለፈ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው ክንዋኔ መሆኑ ይታወቃል። በተለይ አሁን አሁን እያደገና እየሰፋ የመጣው ስፖርትን ለማህበራዊ ኃላፊነትና በጎ ተግባራት ማዋል ዋናውና ተጠቃሽ ዘርፍ ሲሆን፤ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው ተቀባይነት ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በቀላሉ የህዝብ ንቅናቄን ለመፍጠር እንዲሁም ዓላማን ለማሳካት መቻሉም ውጤታማነቱ በተለያዩ መድረኮች እየታየ ነው። የኮትዲቯራውያን ኩራትና መለያ የሆነው ተወዳጁ የእግር ኳስ ተጫዋች ዲድየር ድሮግባ «የእርዳታው ንጉስ» የሚል ተጨማሪ መጠሪያ ተሰጥቶታል። ይህ ስም የተበረከተለት ደግሞ የበጎ አድራጎት ድርጅት በማቋቋም በሚያደርገው መጠነ ሰፊ እርዳታ ነው። ድሮግባን የመሳሰሉ ሌሎች ስፖርተኞችም ተመሳሳይ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን በመክፈት እንዲሁም ተጽዕኖ አሳዳሪነታቸውን በመጠቀም በዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይሳተፋሉ። በዚህም በተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለተጎዱ፣ በበሽታ ለሚሰቃዩ፣ መሰረተ ልማት ለሚያስፈልጋቸው እንዲሁም ወላጅ አልባ ህጻናትን በመደገፍ ምስጉን ለመባል ያስቻላቸውን ተግባራት ያከናውናሉ። ስፖርት የገቢ ምንጭ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፤ የውድድር አዘጋጆች፣ ክለቦችና ተጫዋቾች ከሚያገኙት ረብጣ ገንዘብ ለበጎ አድራጎት ሥራዎች ማካፈልን ባህል እያደረጉት ይገኛሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ዓለማት የበጎ አድራጎት ሥራን ለማከናወን የወጠኑ ውድድር አዘጋጆች የተለያዩ ውድድሮችን ማዘጋጀታቸው እየተለመደ መጥቷል። የውድድር አዘጋጆቹ የተለያዩ ታዋቂ አትሌቶችን በመጋበዝና በማሳተፍ ህዝቡን የማነቃቃትና ገንዘብ የማሰባሰብ እንዲሁም መልዕክት የማስተላለፍ ሥራ ያከናውናሉ። በቅርቡ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሃዋሳ ከተማ ያከናወነውም ይኸው በጎ አስተሳሰብ ነው። የኢትዮጵያ አንድ መገለጫ እየሆነ ያለው ተቋም ዓመታዊ ውድድሮችን በማዘጋጀት ይታወቃል። ከእነዚህ መርሃ ግብሮቹ መካከል አንዱ በሃዋሳ ከተማ የሚካሄደው የግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር ሲሆን፤ በዘንድሮው የሩጫ ውድድር ላይም 200 አትሌቶች፣ 200 ጤናቸውን ለመጠበቅ የሚሮጡና የውጭ ሀገር ዜጎች፣ 700 ህጻናት በጥቅሉ 4ሺ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳታፊዎች ነበሩ። ከውድድሩ በተጓዳኝም የተለያዩ መልዕክቶች የተላለፉበት እንዲሁም በጎ ተግባራት የተከናወኑበት መርሃ ግብሮች ተካትተዋል። በተለይ በዚህ ወቅት በሀገሪቱ ባሉ ውሃማ ስፍራዎች ላይ የተጋረጠው አደጋ የህልውናም ጭምር መሆኑ ይታወቃል። በደለል መሞላትና በቆሻሻዎች መበከል የሃዋሳ ሐይቅ እየተጋፈጠው ያለው አንዱ ችግር በመሆኑ «የሃዋሳ ሐይቅን እንጠብቅ» የሚል መልዕክት ተላልፎበታል፤ የሩጫው ተሳታፊዎችም ከውድድሩ መካሄድ አስቀድሞ የጽዳት ዘመቻ አካሂደዋል። የውጭ ሀገራት ዜጎች እንዲሁም የከተማ ነዋሪዎች በተሳተፉበት እንቅስቃሴ በርካታ ኪሎ ግራሞችን የሚመዝን ቆሻሻ ተወግዷል። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የከተማዋን የቱሪስት መስህብ የመጨመር ሥራ ሌላኛው የውድድሩ ዓላማ ነበር። በዚህም በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎችን በሩጫ ውድድሩ ላይ ለማሳተፍ ተችሏል። የቀድሞው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አንጋፋው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ፤ በርካታ መልዕክቶችን ይዞ በደመቀ ሁኔታ የተካሄደ ውድድር መሆኑን ይገልጻል። ከሃዋሳ ሐይቅና ከግብር መክፈል ጋር በተያያዘ መልዕክቶች የተላለፉበት ነበር። ሃዋሳ ያለ ሐይቁ አሁን ባለችበት ሁኔታ ልትገኝ እንደማትችል የሚጠቁመው ኃይሌ፤ ለማንም ሰው የማይተውና ሁሉም ተባብሮ ሊጠብቀው የሚገባ መሆኑንም ይጠቁማል። ከከተማው ወደ ሐይቁ የሚገቡትን ቆሻሻዎች ህዝቡ እየተከታተለ ሊያስወግድ እንደሚገባ፤ ካልሆነ ግን ሌሎች ሐይቆች ላይ የተከሰተው ሁኔታ እጣ ፋንታው እንደሚሆንም አሳስቧል። ከዚህ በተጨማሪ በውድድሩ ላይ በርካታ የውጭ ዜጎች መሳተፋቸው በቱሪዝም በኩል የራሱን አስተዋጽኦ የሚያበረክት ሲሆን፤ ከተማዋን ምቹ በማድረግ የቱሪስቶች ቁጥር እንዲበራከትና ከዚህም ተጠቃሚ ለመሆን እንደሚቻል አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ይጠቁማል። የበርካታ ብርቅዬ አትሌቶች ማፍሪያ ከሆነችው በቆጂ በርካታ ስመጥር አትሌቶችን በመመልመል አሁን ላሉበት ያደረሱትና የበቆጂ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል አሰልጣኝ ስንታየሁ እሸቱ በውድድሩ ላይ በተጋባዥ እንግድነት ተገኝተው ዕውቅና ከተሰጣቸው በኋላ በውድድሩ ላይ በመሳተፋቸው የተሰማቸውን ደስታ ሲገልፁ« ከሀገር ውስጥ አልፎ በርካታ የውጭ ሀገራት ዜጎችን ያሳተፈው ውድድር፤ ስፖርቱ የሚያድግበት እንዲሁም የውጭ ሀገራት ዜጎች ስለ ኢትዮጵያዊያን የሚያውቁበትና በትክክል የሚገነዘቡበት ነው። በመሆኑም ይህ ዓይነቱ እንቅስቃሴ ለኢትዮጵያ ወሳኝ ነው» ብለዋል፡፡አዲስ ዘመን የካቲት 7/2011ብርሃን\nፈይሳ", "passage_id": "015ad8c3835eb7e3e2b1cc91b937a4e2" }, { "passage": " ‹‹አንዱ በር ቢዘጋብኝ\nሌላኛውን አንኳኳለሁ›› ታሪካቸውን ሲያወሱ በተደጋጋሚ የሚያነሱት አባባል ነው። ባልተሳካው ሁሉ ተስፋ እየቆረጡ\nወድቆ አለመቅረትን ተሞክሯቸው በግልጽ ይመሰክራል። ስለስፖርት ፍቅር ብዙ በሮችን አንኳኩተው ቢዘጋባቸውም ደግመው ከማንኳኳት ሰንፈው\nአያውቁም፤ የዛሬው የአዲስ ዘመን ስፖርት ገጽ እንግዳችን ኢንስትራክተር ታደሰ ይርጋ። ትውልዳቸው በ1957 ዓ.ም በደሴ ሲሆን፤\nከልጅነታቸው ጀምሮ ድፍረት እንዲሁም የሀገርና የባንዲራ ፍቅር በውስጣቸው እንዲሰርጽ የቤተሰቦቻቸው አስተዳደግ ተጽእኖ ያሳደረባቸው\nመሆኑን ያስታውሳሉ። ስፖርትን በአትሌትነት፣ በመምህርነት፣ በአሰልጣኝነት፣ በአካል ብቃት ኢንስትራክተርነት፣ በማሳጅ እና ፊዚዮቴራፒስት\nእንዲሁም የስፖርት ቁሳቁስ ፈጣሪነት ተላብሰው እስካሁንም ቀጥለዋል። በሕይወታቸው ለተስተ ናገደ ውጣ ውረድ ቦታ ሳይሰጡ ሁሌም ለአዲስ\nነገር የሚተጉት ኢንስትራክተር ታደሰ ይርጋ ለስፖርት ቤተሰቡ አስተማሪ የሆነውን ተሞክሯቸውን ያጋሩ ዘንድ ጋበዝናቸው። አዲስ ዘመን፡- ወደ ስፖርቱ ዓለም ለመግባት መነሻ የነበረውን ሁኔታ እንዴት ያስታውሱታል?አቶ ታደሰ፡- አስተዳደጌ ድፍረት እንዲኖረኝ የሚያደርግ በመሆኑ በስፖርት መሳተፍ የጀመርኩት በልጅነቴ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን የተከታተልኩበት የንጉስ ሚካኤል ትምህርት ቤት የሰውነት ማጎልመሻ መምህሬም እገዛ ያደርጉልኝ ነበር። ከዚያ በኋላ የተማርኩባቸው የቅዳሜ ገበያ፣ ሆጤ፣ አሰብ እና ወይዘሮ ስህን ትምህርት ቤቶች ውስጥም ችሎታዬን ማዳበር ችያለሁ። በኮተቤ መምህራን ኮሌጅም የስፖርት ሳይንስ ትምህርት አጥንቻለሁ። አዲስ ዘመን፡- ከዚያስ በኋላ\nበስፖርቱ ዓለም የቀጠሉበት መንገድ ምን መልክ ነበረው?አቶ ታደሰ፡- የኮሌጅ ትምህርቴን ካጠናቀቅኩ በኋላ በጤናና ሰውነት ማጎልመሻ መምህርነት ነበር ወደ ወሊሶ ያቀናሁት። በእርሻ ቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ በነበረኝ ቆይታም የተለያዩ ሥራዎችን ከማከናወን ጎን ለጎን አምቦ ላይ በተካሄደ ውድድር በአጭር ርቀት ተሳትፌ ጥሩ ውጤት አስመዝግቤያለሁ። ከቆይታ በኋላ በተዘዋወርኩበት የደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ በሥራዬ ዕውቅናን አትርፌያለሁ። ይህም ከአካባቢ በቀላሉ በሚገኙ ቁሳቁስ ለተለያዩ ስፖርቶች የሚሆኑ ማዘውተሪያዎችን አዘጋጅቼ ተማሪዎችን በማሰልጠን ነው። 30 የሚሆኑ ተማሪዎችን ጂምናስቲክ በማሰልጠንም በወሊሶ ስታዲየም የእግር ኳስ ጨዋታ ሲካሄድ ትርኢት እናሳይም ነበር። በአጋጣሚ ወደ አዲስ አበባ በመጣሁበት ወቅት የምርኩዝ ዝላይ ውድድር በመመልከቴ በውስጤ መነሳሳት ተፈጠረ። ሁኔታዎች አልጋ በአልጋ ባይሆኑም ተማሪዎቼን ከማሰልጠን በተጓዳኝ ራሴን ለውድድር ማዘጋጀት ጀመርኩ፤ የሚገርመው ተማሪዎች እኔን ሲመለከቱ ፍላጎት አድሮባቸው ነበር። ጊዜው ደርሶም በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቻምፒዮና ምርኩዝ ዝላይ ውድድር ተሳትፌ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚና የብሔራዊ ቡድን ተመራጭ ሆኛለሁ። ከተማሪዎቼ መካከል በዚሁ ስፖርት ያሰለጠንኳቸውን አምስት ልጆችም በራሴ ወጪ የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ውድድር ላይ አሳትፌ በነበራቸው ውጤት ሦስቱን ለብሔራዊ ቡድን አብቅቻለሁ። አዲስ ዘመን፡- እርሶና የእርሶ\nተማሪዎች በብሔራዊ ቡድን ተሳትፏችሁ በየትኛው ውድድር ሀገርን ወከላችሁ?አቶ ታደሰ፡- በወቅቱ በተደረገው ተጽእኖ የሚገባንን እንኳን ሳይሰጠን በዓለም አቀፍ ውድድርም መካፈል አልቻልንም። የእኔ ህልም አሰልጣኝና ተወዳዳሪ በመሆን የሀገሬን ባንዲራ በውድድር መድረክ በኩራት ማውለብለብ በመሆኑ ብዙ ጥረት አደርግ ነበር። ነገር ግን በሚኒማ ማሟያ ውድድር የዘለልኩት ከፍታ በትክክል ባለመመዝገቡ በተነሳ አለመግባባት እንዲሁም ለስፖርቱ በሚሰጠው አነስተኛ ግምት ተሳትፎዬ ሳይሳካ ቀረ። እኔም የደረሰብኝን ተጽእኖ የሚያሳዩ ጽሑፎችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በማውጣት እታገል ነበር። አዲስ ዘመን፡- ከዚህ ሁኔታ\nበኋላስ ወደ መምህርነቱ ተመለሱ ወይስ በስፖርቱ ቀጠሉ?አቶ ታደሰ፡- በመምህርነት ወደ ወሊሶ ነበር የተመለስኩት፤ ተማሪዎችን ከማሰልጠን ጎን ለጎን የአካባቢውን ነዋሪዎች የማስ ስፖርት አሰራም ነበር። ነገር ግን በወቅቱ በርካታ ፈተናዎችን ለማሳለፍ ተገደድኩ። የመጀመሪያው በአውሮፓ ለሚካሄድ ሥልጠና በወጣ ማስታወቂያ መሠረት ሁሉንም መስፈርት እያሟላሁ እንዳልሳተፍ መደረጌ ነው። ከቆይታ በኋላ ደግሞ በአመለካከቴ ምክንያት ቀድሞ ከማስተምርበት ትምህርት ቤት ወደ ሌላ እንድዘዋወር ተደረገ፤ ደመወዜ ከመታገዱም በላይ ያለ ጥፋቴ እንድታሰር ተደርጎ ብዙ እንግልት ደርሶብኛል። ከተፈታሁ በኋላ ወደ ተመደብኩበት አካባቢ ስሄድም ተመሳሳይ ነገር ነበር የጠበቀኝ፤ ነገር ግን መምህር የዘራውን ዘር የትም ማግኘቱ አይቀርምና በቀድሞ ተማሪዎቼ እገዛ ነገሮች ተቃለው ነበር። ቢሆንም ብዙም ሳልቆይ ወደ አዲስ አበባ መጣሁ። አዲስ ዘመን፡- የአዲስ አበባ\nቆይታዎስ እንዴት ነበር?አቶ ታደሰ፡- አዲስ አበባ ከመግባቴ ነበር ወደ ሥራ የገባሁት። በቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት በነበረኝ ቆይታም ስፖርትን ከማስተማር በተጓዳኝ በርካታ ሥራዎችን አከናውኛለሁ። ከእነዚህ መካከል አንዱ 16 ስፖርቶችን በአንድ ሊያሰራ የሚችል ሜዳ ማዘጋጀት ነው። ይሁን እንጂ በትምህርት ቤቱ የሠራተኛ ማህበር ሊቀመንበር በመሆኔ በድጋሚ ፈተናዎችን ማስተናግድ የግድ ሆነ። ለሠራተኛው መብት በመታገሌ ከሥራ ከመባረሬም በላይ በክስ ረጅም ሂደት አሳልፌያለሁ። በሁለተኛው እስርም እስካሁን በግልጽ የሚታይ የአካል ጉዳት ደርሶብኛል። አዲስ ዘመን፡- ከነዚህ ፈተናዎች\nበኋላ የማሳጅና ፊዚዮቴራፒ እንዲሁም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አሰልጣኝነት ሥራ መጀመሩ ከባድ አልነበረም?አቶ ታደሰ፡- ለሀገሬ በምርኩዝ ዝላይ የተሻለ ነገር ማስመዝገብ እችላለሁ ባልኩበት ወቅት እንዳሰብኩት ሳይሆንልኝ ቀረ። በብዙ ፈተና የታጀበውን ማስተማርም አቆምኩ። ነገር ግን አንዱ በር ሲዘጋብኝ ሌላውን ከማንኳኳት ወደኋላ ባለማለት እነዚህን ሙያዎች በትምህርት ለማዳበር ቻልኩ። ከስፔን በመጡ ባለሙያዎችም ሥልጠናዎችን በመውሰድ እውቀቴን ለማስፋት ችያለሁ። በዚህ ወቅትም በዚሁ ሙያ የተጎዱ ሰዎችን በመርዳት ላይ እገኛለሁ። አዲስ ዘመን፡- ከዚያ በኋላ\nወደ አትሌቲክስ ስፖርት አልተመለሱም?አቶ ታደሰ፡- በ2009 ዓ.ም በምርኩዝ ዝላይ ለብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ልጠራ ችያለሁ። ሥልጠናም የጀመርኩት በምን መልኩ፣ በምን ያህል ጊዜ አትሌቶችን የት ማድረስ እችላለሁ በሚለው ላይ ፕሮፖዛል በመቅረጽ ነው። ማሰልጠኑን ስጀምርም ቡድኑ ውስጥ የነበሩት አራት አትሌቶች፤ ቢሰራባቸው የተሻለ ብቃት ማሳየት እንደሚችሉ ተገነዘብኩ። ከሰልጣኞቹ መካከል በተለይ አንዱ የነበረው ችሎታና በልምምድ ወቅት የሚያሳየው ብቃት ክብረወሰን መስበር እንደሚችል የሚያመለክት ነበር። ይሁን እንጂ ከውድድር በፊት ልምምድ ሲያደርግ ጉዳት ደርሶበት በማገገም ላይ ሳለ ፌዴሬሽኑ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞች ምርጫ ደንብን ማሻሻሉ ተሰማ። ብዙ አትሌቶችን ያስመረጠ አሰልጣኝ ቡድኑን ይመራል በሚለው አሠራርም ቡድኑን ከዚያ በላይ ይዤ መቆየት አልቻልኩም። በዚህ ዓመት ደግሞ በፖላንድ ይካሄድ በነበረ የወጣቶች ቻምፒዮና ላይ ብሔራዊ ቡድኑን በፊዚዮቴራፒ ለማገዝ በድጋሚ ተጠርቼ ነበር፤ ነገር ግን በኮሮና ምክንያት ውድድሩ ተራዘመ። አዲስ ዘመን፡- አሁንስ ምን\nእያከናወኑ ይገኛሉ?አቶ ታደሰ፡- አሁን ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የመተንፈሻ አካላት እንቅስቃሴዎችን በማከናወን ህመሙን ለመቋቋም ይቻላል በሚል ፕሮፖዛል አዘጋጅቼ እየተንቀሳቀስኩ ነው። ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት በማቅረብም ምላሽ እስኪሰጠኝ በመጠባበቅ ላይ እገኛለሁ። በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ላይ በመቅረብም በምን መልክ እንቅስቃሴው ይከናወናል የሚለውን ለሕዝቡ እያደረስኩ ነው ያለሁት። አዲስ ዘመን፡- የአካል ብቃት\nማከናወኛና ለፊዚዮቴራፒ የሚጠቅሙ መሣሪያዎችን በራስዎ ማዘጋጀትዎ የተለየ ያደርጎታል፣ ይህን ችሎታ እንዴት አዳበሩት?አቶ ታደሰ፡- የማየውን ነገር ማሻሻልና መፍትሄ ሰጪ የሆኑ ፈጠራዎችን ማከናወን ያስደስተኛል። እስር ቤት እያለሁ በርካታ የስፖርት ዲዛይኖችን አዘጋጅ ነበር። አሁንም ቤቴ ቁጭ ብዬ ከመስራት አልቦዝንም። ለአብነት ያህል በሀገሪቷ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እጥረት አለ፤ ይህንን ሊፈታ የሚችልና በጠባብ ስፍራ ሊሰራ የሚችል የማዘውተሪያ ሃሳብ አለኝ። ለሥራዬ የሚያግዙኝን የሕክምና መሣሪያዎችና ሌሎች የስፖርት ሥልጠና ቁሳቁስም በአካባቢዬ ከማገኛቸው ቀላል መሣሪያዎች አዘጋጃለሁ። መንግሥት ዕድሉን ቢያመቻችልኝ ለሀገሬ መከወን የምችላቸውና ነገ ሀብት ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ሥራዎች አሉኝ። ከሀገር ባለፈ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊያሳውቀን የሚችሉ የፈጠራ ሃሳቦችና ዲዛይኖችም በወረቀት ላይ አስፍሬያለሁ። ሁሌም ያለኝን ነገር ለሀገሬ ከማበርከት ወደኋላ ብዬ አላውቅም። ሃሳቦቼን ወደ ተግባር ለመለወጥና በሙያዬ ሕዝብን ለመርዳትም ታላቅ ፍላጎት አለኝ። አዲስ ዘመን፡- አቶ ታደሰ\nለሰጡን ጊዜ ከልብ እናመሰግናለን። አቶ ታደሰ፡- እኔም\nአመሰግናለሁ።አዲስ ዘመን ሐመሌ 20/2020  ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "c48b37d48157e023e260a3c109e24abe" }, { "passage": " ልምምድን አድምቶ በመስራትና በጥንካሬ በመቆየት የመጨረሻዋን መስመር በቀዳሚነት መርገጥ ዋጋው ከደስታም ይልቃል። ሃገርን ማስጠራት እንዲሁም ክብርን መቀዳጀት ደግሞ የስኬታማነት ክፍያው ነው። እንደ አትሌቶቹ ሁሉ፤ ልምምድን በትጋት መልሶ መላልሶ መስራት የግድ ነው፤ በየትኛውም ስፖርት ከውጤት ማድረሱም እውነት ነው። ባሉበት ስፖርት በታማኝነት ጊዜን፣ ጉልበትንና አቅምን አሟጦ መጠቀምም አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ስኬትን ከተቀዳጁበት አንድ ስፖርት ወደ ሌላ በመሸጋገር በድጋሚ ውጤታማ መሆን ይቻላል? ከተጫዋችነት አሊያም ከአትሌትነት ወደ አሰልጣኝነት እንዲሁም ወደ አማካሪነትና ሌሎች ስራዎች መሸጋገር የተለመደ ነው። ጫማ ሰቅሎ የቦክስ ጓንት ማጥለቅ፣ ከመም ወደ እግር ኳስ ሜዳ መሸጋገር እንዲሁም ጓንት ሰቅሎ የበረዶ ላይ ገና ጨዋታ ዱላን ማንሳት ግን አደናጋሪ ነው። ዋናው ጥያቄም እውን እጅግ በተለያዩ ሁለት ስፖርቶች በቀላሉ ስኬታማነትን ማግኘት ይቻላል? የሚለው ይሆናል። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ጥናት ማድረግን ቢጠይቅም፤ ለዛሬ ከአንዱ ወደ ሌላኛው ስፖርት የተሸጋገሩ ስፖርተኞችን እናንሳ። «በርካታ ዋንጫዎችን አንስቻለሁ፤ አሁን ግን ቀበቶ ማግኘት እፈልጋለሁ» በሚል ነበር የተነሳው። ይህ የሁለት ክብሮች ናፋቂ የእንግሊዝን ብሄራዊ ቡድንን ለ14ዓመታት በተለይ የታወቀበትን ክለብ ማንቸስተር ዩናይትድን ደግሞ ለ12ዓመታት ያገለገለው ሪዮ ጋቪን ፈርዲናንድ ነው። በአራት ክለቦች ሁለት አስርት ዓመታትን በተጫዋችነት ያሳለፈው ፈርዲናንድ፤ በእንግሊዛውያን ዘንድ የምንጊዜም ተወዳጅነትን ካተረፉ ተጫዋቾች መካከል ተጠቃሽ ነው። ስድስት የፕሪምየር ሊግ፣ አንድ የቻምፒዮንስ ሊግ፣ አንድ የፊፋ የክለቦች እንዲሁም ሌሎች ዋንጫዎችን ጨምሮ በርካታ ክብሮችንም በግሉ እና በቡድን አግኝቷል። በ39ዓመቱ የእግር ኳስ ሜዳን ሲሰናበት ግን የቦክስ መፋለሚያ ሪንግን እያሰበ ነበር። በሰቀለው ጫማ ምትክም ጓንት ማጥለቁ መነጋገሪያ አድርጎታል፡፡ በፕሮፌሽናል ቦክሰኛነት በከባድ ሚዛን ለመሳተፍ በሳምንት ከ4-5 ቀናት ልምምድ እንደሚያደርግም አስታወቀ። ነገር ግን በፕሮፌሽናል የቦክስ ማህበር በኩል «ብቁ ነህ» የሚል ማረጋገጫ ማግኘት ሳይችል ቀረ። በዚህ ምክንያትም ማዘኑን «ቦክስ ሰውነት ብቻም ሳይሆን ጠንካራ ልብ ነው የሚፈልገው» ሲል ነበር የገለጸው። የእግር ኳስ ተንታኝ የሆነው አንጋፋው ተጫዋች እንዲያም ቢሆን ፈቃዱን ለማግኘት ጥረቱን እንደማይተውና ጠንክሮ እንደሚሰራ አረጋግጧል። ጃማይካዊው የዓለም ፈጣኑ ሰው ደግሞ ከመም በቀጥታ ወደ እግር ኳስ ማንከባለል የገባ ስፖርተኛ ነው። የሰው ልጅ በዚህን ልክ ይፈጥናል ተብሎ ባይጠበቅም በአጭር ርቀት አትሌቲክስ አዲስ ታሪክ ያስመዘገበው ቁመተ መለሎውና ቀልደኛው ዩሲያን ቦልት ስምንት የኦሊምፒክ ሜዳሊያዎችን ጠራርጎ በመውሰድ ስኬታማ ነው። ቦልት 100 ሜትርን በ9ሰከንድ ከ58 ማይክሮ ሰከንድ፣ 200ሜትርን ደግሞ 19ሰከንድ ከ19ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት የዓለምን ክብረወሰን አርቆ የሰቀለ አስደናቂ አትሌት ነው። ቦልት ከታወቀበት አትሌቲክስ ባሻገር እግር ኳስን እጅግ የሚወድ እንዲሁም የሚመኘውም ስፖርት ነው። የእንግሊዙ ማንቺስተር ዩናይትድ ክለብ ደጋፊ የሆነው አትሌቱ የቀያዮቹ ሴጣን ተጫዋች የመሆን ህልም እንዳለውም ይናገር ነገር። እአአ ከ2017ቱ የለንደን የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በኋላም ከአትሌቲክስ ስፖርት ወጥቶ ወደ እግር ኳስ መግባቱን አሳወቀ። የእግር ኳስ ልምምዱን በቅድሚያ የጀመረው በኖርዌይ ክለብ ሲሆን፤ የዓለምን ክብረወሰን ያስመዘገበበትን 9.58 የሚያስታውስ ማሊያ ይለብስ ነበር። ከቆይታ በኋላም የአውስትራሊያውን ሴንትራል ኮስት ማሬነርስ የተባለውን ክለብ ተቀላቀለ፤ በመጀመሪያው የወዳጅነት ጨዋታም ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ቻለ። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ከስፖርት ህይወት ሙሉ ለሙሉ ወጥቶ ወደ ንግድ መግባቱን ይፋ አደረገ። ለበርካታ ጊዜያት ጾታዊ ጥርጣሬ ውስጥ በመግባት አስቸጋሪ ጊዜን መግፋት የግድ የሆነባት ደቡብ አፍሪካዊቷ አትሌት ካስተር ሰመኒያም በቅርቡ ከአትሌቲክስ ስፖርት እግር ኳስን እንደመረጠች አስታውቃለች። በተክለ ቁመናዋ ምክንያት በርካታ ፈተናዎችን ለመጋፈጥ የተገደደችው የ800 ሜትር የኦሊምፒክ ቻምፒዮናዋ ሰመኒያ ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ያወጣውን ደንብ ተከትሎ በክስ ሂደት መቆየቷ ይታወሳል። ነገር ግን እሰጣ አገባው እንዳሰበችው ሆኖ ባለመጠናቀቁ፤ በልጅነቷ ታንከባልል እንደነበር ወደ ገለጸችው ኳስ ገብታለች። በሃገሯ የሚገኝን ክለብ የተቀላቀለችው ተጫዋቿ አዲሱ የጨዋታ ዘመን እስኪጀመር በልምምድ ላይ የምትቆይ መሆኗን ተከትሎ «ይሻላል» ባለችው እግር ኳስ ያላትን ብቃት ማስመስከር አልቻለችም። ከሰሞኑ በተሰማ ሌላ ዜና ደግሞ የቀድሞው ግብ ጠባቂ ፒተር ቼክ በጓንቱ ፋንታ የበረዶ ላይ ገና ጨዋታ ዱላ ወደ ማንሳት መሸጋገሩን አስታውቋል። በተለይ በሰማያዊዎቹ እና በመድፈኞቹ ቤት ቆይታው የሚታወቀው ግብ ጠባቂው ጓንቱን ከሰቀለ በኋላ በቀድሞ ክለቡ ቼልሲ የቴክኒክ አማካሪ በመሆን እያገለገለ ይገኛል። ከዚህ ስራው ጎን ለጎንም በልጅነቱ የተጫወተውንና የሚወደውን ይህንን ስፖርት ተቀላቅሏል። እንደ ግብ ደጀንነቱ ሁሉ በዚህ ስፖርትም ስኬታማ መሆን አለመሆኑም ጊዜ ምላሽ ይሰጥበታል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 3/2012ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "0d3a92bfdf79b699d7eb03245ba05d17" }, { "passage": "ቦጋለ አበበ የባህል ስፖርት ከሰው ልጅ የአኗኗር ዘይቤ አንጻር በየአካባቢው የሚያከናውናቸው ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አንዱ ነው። ባህል የአንድ ህብረተሰብ ልዩ ልዩ ማህበራዊ መተዳደሪያ ስርዓቶችን፤ የሀዘንና የደስታ ስሜት፤ መገለጫ የሆኑ ልዩ ልዩ ስነ ቃሎች፤ ጭፈራዎች ዳንኪራና አልባሳትን ያካተተ ሲሆን ሲጠቃለል የሕዝቦች ማህበራዊ ህይወት ማሳያና የማንነት መገለጫ ነው። የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ማሳተፍ የሚችሉና ብሔር ብሔረሰቦች የበለጠ እንዲቀራረቡ፤ የመከባበርና የመቻቻል ባህላቸውንም እንዲያዳብሩ በማድረግ ጉልህ ሚና አለው። የባህል ስፖርት የሰው ልጅ በተፈጥሮ በለገሰው ነገር ህልውናውን ለማኖር በሚያደርገው የዕለት ተለት ውጣ ውረድና እንቅስቃሴ አማካኝነት የተፈጠረ ማህበራዊ ጨዋታና እንቅስቃሴ ነው። የባህል ስፖርት በአዝጋሚ ለውጥ ከህብረተሰቡ እድገት ጋር እያደገና እየዳበረ የመጣ የህብረተሰብ ወጉና ማዕረጉ የሱነቱ መገለጫ ከሆኑ ቅርሶቹ ውስጥም አንዱና ዋነኛው ነው።ከክርስቶስ ልደት በፊት በ6ኛው እና 7ኛው ክፍለ ዘመን በተለያዩ አካባቢዎች፤ በመንደር፣ በቤተሰብና በደብር የተመሰረተ የባህል ስፖርት ጨዋታ በኢትዮጵያ ይካሄድ እንደነበረ የባህል ስፖርቶች የውድድር ሕግ በሚል ሰኔ 2oo6 ዓ.ም በባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ተዘጋጅቶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል ድጋፍ የታተመው መፅሐፍ ያስረዳል። በዓለም አቀፍ ደረጃ «ሆኪ» ተብሎ የሚታወቀውን የገና ጨዋታ ኢትዮጵያውያን ከሶስት ሺ ዓመት በፊት ይጫወቱት እንደነበር የዓለም ሆኪ ፌዴሬሽን በድረ-ገጹ ከአራት ዓመት በፊት ያሰፈረው ፅሁፍ ያስረዳል። ያም ሆኖ ሆኪ አሁን ያለበት ደረጃና የእኛው የገና ጨዋታ ለንጽጽር እንኳን የማይበቃ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ማንም መናገር ይችላል። የሆኪ ስፖርት መነሻው ከገና ጨዋታ መሆኑን ከጨዋታዎቹ ፍጹም መመሳሰል ተነስቶ መገመት ከባድ አይሆንም። ነገር ግን ይህን ተወዳጅ ስፖርት በኢትዮጵያ ማበልጸግና ዓለምአቀፋዊ ይዘቱን ማጎልበት ባለመቻሉ ምዕራባውያኑ የግላቸው አድርገው አሁን ላይ መነሻ የሆነው የገና ጨዋታ በሆኪ ተውጦ እናገኘዋለን።የገና ጨዋታ በኢትዮጵያ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ይዘት ያለው፣ ከጥንት ጀምሮ የነበረ ጨዋታ እንደሆነ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ መምህር ካህሳይ ገብረእግዚአብሔር የተባሉ የታሪክ ተመራማሪና ደራሲ፤ ስለ ገና ጨዋታ ታሪካዊ አጀማመር ሁለት ትውፊቶች ተደጋግመው እንደሚነገሩ አስቀምጠዋል። ክርስቶስ ሲወለድ እረኞች ከመላዕክት ጋር አብረው እንደዘመሩና በወቅቱም የገና ጨዋታ መጫወት እንደጀመሩ አንደኛውን ትውፊት በመጥቀስ ያስረዳሉ፡፡ሁለተኛው ትውፊት ደግሞ ከሰብዓ ሰገሎች ጋር የሚገናኝ ነው፡፡ ንጉስ ሄሮድስ የሚባለው የዘመኑ ንጉሥ አዲስ የሚወለደው ህጻን የበለጠ ዝናና ክብር እንደሚያገኝ የሰማው ትንቢት ስላስደነገጠው በዚያን ጊዜ የተወለዱ ወንድ ህጻናት በሙሉ እንዲገደሉ ትዕዛዝ ሰጥቶ እያሳደደ ያስገድል እንደነበር ይወሳል። ሄሮድስ ታዲያ ክርስቶስ ሊወለድ መሆኑ ተነግሮት ስለነበር የት እንደሚወለድና ስለ አጠቃላይ ሁኔታው በቅርበት ለማወቅ በመፈለጉ አንድ ሰላይ የሰብዓ ሰገል ዓይነት ልብስ አስለብሶ፣ ከእነሱ ጋር እንዲቀላቀል ይልካል፡፡ ሰላዩ ከሰብዓ ሰገል ጋር ተቀላቅሎ ጌታ ወደሚወለድበት ሥፍራ ሲጓዙ፣ ይመራቸው የነበረው ኮከብ ድንገት ቀጥ ይላል፡፡ ይኼኔ ተጠራርተው መሃላቸውን ሲፈትሹ፣ ሰላዩን እንዳገኙት ይኸው ትውፊት ያስረዳል፡፡ ከዚያም ሰብዓ ሰገል ሰላዩን ይገድሉና ራሱን ቆርጠው እንደ አሁኑ የገና “ሩር” እየተቀባበሉ ተጫወቱበት ይላል – ሁለተኛው ትውፊት፡፡ ከዚያም በመነሳት የገና ጨዋታ ተፈጠረ ይላሉ፤ የታሪክ ተመራማሪው፡፡ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ትውልድ ከትውልድ እየተቀባበለ፣ እስከ አሁን የቀጠለው የገና ጨዋታ፤ በየዓመቱ በታህሣሥ ወር በተለይ በኢትዮጵያ የገጠሩ ክፍል እረኞች በድምቀት ይጫወቱታል። ከክርስቶስ ልደት\nበኋላም\nበተለያዩ\nጊዜያት\nበወቅቱ\nነግሰው\nበነበሩ\nየኢትዮጵያ\nነገስታት\nጊዜ፤\nበመሳፍንት፤\nበሹማምንቱ፤\nበሎሌዎች፤\nበሕዝቡ\nመካከል\nበሰንበትና\nበአውድ\nዓመት\nየባህል\nስፖርት\nጨዋታዎች\nበከፍተኛ\nሁኔታ\nውድድርና\nፉክክር\nበማድረግ\nይዝናኑበት\nእንደነበር\nበተለያዩ\nጽሁፎች\nተገልጿል።በአፄ ቴዎድሮስ\nእና\nበአፄ\nሚኒልክ\nዘመነ\nመንግስታት\nወቅት\nበራሳቸው\nንጉሶቹ\nአዘጋጅነትና\nዳኝነት\nበከፍተኛ\nሁኔታ\nየባህል\nስፖርት\nጨዋታዎች\nይካሄዱ\nነበር።\nአፄ\nቴዎድሮስ\nየኢትዮጵያኖችን\nጥንካሬና\nጀግንነት\nለውጪ\nአገር\nዜጎች\nለማሳየት\nየኢትዮጵያ\nጎበዝ\nታጋዮችን\nከውጪ\nአገር\nከመጡ\nዜጎች\nጋር\nበራሳቸው\nዳኝነት\nየትግል\nውድድር\nበማወዳደር\nላሸነፉ\nኢትዮጵያኖች\nልዩ\nልዩ\nሽልማቶችን\nይሸልሙ\nእንደነበርም\nየታሪክ\nድርሳናት\nይነግሩናል።\nአፄ\nሚኒሊክ\nደግሞ\nየራሳቸው\nየገና\nተጫዋቾች\nበማደራጀት\nከእቴጌ\nጣይቱ\nቡድን\nጋር\nየገና\nጨዋታ\nውድድር\nያደርጉ\nነበር።\nእቴጌ\nጣይቱም\nበስማቸው\nየከፈቱትን\nሆቴል\nለማስተዋወቅ\nየገበጣ\nጨዋታ\nአዘጋጅተው\nያጫውቱ\nነበር።በአሁኑ ወቅትም በገጠር የሚኖረው አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ አካላዊ ብቃቱን ከሚያዳብርባቸውና መንፈሳዊ እርካታን ከሚጎናፀፍባቸው እሴቶች መካከል የሱነቱ መለያ፤ ባህልና ልምዱን ወግና ማዕረጉን ከሚገልጽባቸው መንገዶች አንዱ የባህል ስፖርት ነው። በተለይም የተዳከመ አዕምሮውንና የዛለ አካሉን የሚያነቃቃባቸውና የሚያፍታታባቸው፤ በትርፍ ሰዓቱና በበዓላት ቀናት ማህበራዊ ግንኙነቱን የሚያጠናክርበት መሳሪያው የባህል ስፖርት ነው። አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች የባህል ስፖርቶች በተለይም በበጋው ወራት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ውድድሮች ይካሄዳሉ። የክርስቶስ ልደት ወይንም የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ እረኞች የገና ጨዋታን ከታህሳስ ጀምሮ እስከ ጥር ከዚያም እስከ ክረምቱ መግቢያ ይጫወቱ እንደነበርም የቀድሞ አባቶች ይናገራሉ።በተለይም የገና\nጨዋታ\nበከፍተኛ\nሁኔታ\nየሚካሄደው\nመኸር\nበተሰበሰበበት\nአካባቢ\nለጥ\nባለ\nሜዳ\nከሰዓት\nበኋላ\nሩሩ\nለዓይን\nመታያት\nእስከተቻለበት\nጊዜ\nድረስ\nጨዋታው\nይካሄድ\nነበር።\nጨዋታው\nየሚካሄደው\nበሁለት\nየቡድን\nአባቶች\nአማካኝነት\nእያንዳንዱ\nተወዳዳሪ\nየተለየ\nስም\nእያስመረጡ\nወደ\nቡድናቸው\nይቀላቀላሉ።\nይህም\nየሚሆነው\nሁለት\nቡድኖች\nከአንድ\nመንደር\nወይም\nቀበሌ\nከሆነ\nብቻ\nነው።\nሌላው ከፍተኛ የውድድር ዓይነት ደግሞ የቡድን አባቶች የተመደበው ደብር ከደብር፤ የላይ አምባ ከታች አምባ፤ የአንዱ ቀበሌ ከሌላው ቀበሌ ከሆነ ብቻ ነው። እንዲሁም ባገቡና ባላገቡ መካካል ተካፍለው የጨዋታውን ዓይነት በስምምነት የሚፈጸምም ነው። በዚህ የጨዋታ ዓይነት ለመንደር ወይም ለደብር ገናን ለመጫወት የፈለጉ ሁሉ የሚሳተፉበትና ለቡድኑ መግባት የሚችሉት የተጫዋቾች ቁጥር ማዕቀብ የሌለውና ሊበላለጥ የሚችል የትርምስ የገና ጨዋታ ሲሆን፤ አንድ ተጫዋች ሲወጣና ሲገባም በቡድኑ አባላት የማይጠየቅበት ነው። በቡድን አባቶች በምርጫ የሚጫወቱ ሌላው ገና ግን አንዱ በጨዋታው ተጎድቶ ቢወጣ ወይም አዲስ ለመግባት ቢፈልግ ለቡድኑ አባት ለጎበዝ አለቃ ወይም ለአጫዋቾች ተናግሮ ሲፈቀድለት የሚገባበት ነው። የገና ጨዋታን ይጫወቱበት የነበረው ዱላ ከጫፉ ቀለስ ያለ የእንጨት ገና ሲሆን የመጫወቻ ሩር (ጥንግ) ከቆዳ ወይም ከዛፍ ስር ድቡልቡል አድርጎ በማዘጋጀት በመምታት፤ በማንከባለልና በመለጋት ነበር የሚካሄደው። አለባበሳቸውም ጉልበት ላይ የሚቀር ሱሪ፤ እጀ ጠባብ፤ ከወገቡ ላይ የሚጠመጠም ድግ ነበር ለብሰው የሚጫወቱት። በአንዳንድ አካባቢ የገና ጨዋታ በሚደረግበት ጊዜ አንድ የጎበዝ አለቃ ከአማካሪዎቹ ጋር ከመሃል ሜዳ አቆራቋዥና ጨዋታውን የሚመሩ አራት የድንበር ጠባቂዎች ይደረግለት ነበር። የጨዋታው ፍፃሜም በግብ ወይም በነጥብ የሚለይ ነው።የገና ጨዋታ ብዙ አይነት ውድድር ይደረግበት ነበር። ለምሳሌ ያህልም ቁርቁዝ፤ ሙጭ፤ ቀልቦ መለጋትና አፍሶ መለጋት ይጠቀሳሉ። አፍሶ መለጋት ከባድ የአውዳመት ጨዋታ ሲሆን አፍሶ በመለጋት የሚጫወቱት ነው። ህግና ሚና በሚከበርበት ጊዜ ደግሞ ቀልቦ መለጋት ጨዋታ ላይ ይውላል። ሙጭ ጨዋታ በመጥረግ ብቻ እንጫወት ብለው በስምምነት ያገኙትን የሰውንም እግር ሆነ ጥንጉን በመጥረግ የሚጫወቱት ነው። ቁርቁዝ የተባለው አጨዋወት ህግን በመከተል በሚናህ በማለት ጥንጓን በኃይል ሳይጫወቱ ወይም ሳይመቱ በማንከባለል ብቻ የሚጫወቱት ጨዋታ ነበር።በቀድሞው የገና ጨዋታ ጊዜ ጨዋታው የሁሉም መሆኑን ለመግለጽ «በገና ጨዋታ የለም ሎሌ ጌታ፤ በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ» እየተባለ በሚደርሰው አደጋ ምንም አይነት ቂም መያዝና አደጋ መፍጠር ወይም ጠብ በማያስከትል መንገድ ይካሄድ እንደነበርም ይወሳል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 29/2013", "passage_id": "ec36bd6289b1b9caf3f797a1c747ac74" }, { "passage": "አትሌቲክስ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ስፖርታዊ የውድድር መድረኮች በውጤታማነት ስሟን ለዓለም ያስተዋወቀችበትና ገናናነትን ያተረፈችበት መሆኑን ብዙዎችን የሚያስማማ ሀቅ ነው።ኢትዮጵያና አትሌቲክስ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች እንደመሆናቸውም ብርቅዬ አትሌቶቿ በዓለማችን ትልቁ የስፖርት መድረክ በኦሊምፒክና በሌሎችም ሻምፒዮናዎች ወርቅ ተለይቷቸው አያውቅም።\nከአትሌቲክስ ልዩ ልዩ ውድድሮች መካከል ደግሞ የረጅምና መካከለኛ ርቀት ሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ተጠቃሽ ውጤት ያስመዘገቡባቸው የውድድር ፈርጆች ናቸው።በተለይም በረጅም ርቀት በዓለም ትኩረት ያገኘችበትና ኩራትን የተጎናጸፈችበት ስለመሆኑ የአትሌቶቻችን ድሎች ማሳያዎች ናቸው ።አትሌቶቻችን በዓለም አቀፍ ውድድሮች ከአንድ እስከ ሦስት ተከታትለው በመግባት ዓለምን ያስደመሙባቸው ወቅቶች በርካታ ናቸው።በዚህ ረገድ በሲድኒ ኦሊምፒክ የታየው ወርቃማ ታሪክ «አረንጓዴው ጎርፍ»ን (green flood ) ማስታወስ በቂ ምስክር ይሆናል።\nምንም እንኳን በዚህ ምልክ በተለይም ቀደም ባሉት ዓመታት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ የረጅምና መካከለኛ ርቀት ሩጫ ውድድሮች ፈርጥ መሆን ቢችሉም አሁን ግን ይህ የቀደመ ውጤታማነታቸው አብሯቸው አለመሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች ይታያሉ።\nለዚህ የውጤት መራቅም በተለይ በአህጉርም ሆኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዓመታትን ጠብቀው እስካልሆነ በአምስትና አስር ሺ ሜትር የሚካሄዱ ውድድሮች በእጅጉ መቀንስ፣ በምክንያትነት ይጠቀሳል። ይሁንና በአሁኑ ወቅት የጎዳና ውድድሮች መበራከታቸውን ተከትሎ በርካታ አትሌቶች ለአምስትና አስር ሺ ሜትር ውድድር የሚረዳ ልምምድ ከመስራት ይልቅ ለጎዳና ውድድሮች ትኩረት በመስጠት ወደዚያው መፍለሳቸው ዋነኛው ችግር ሆኖ ይጠቀሳል።አዲስ ዘመን ጋዜጣም በመም ውድድሮች በተለይ የአምስትና አስር ሺ ሜትር የኢትዮጵያን የቀድሞ ስምና ክብር በማስመለሱ ሂደት በአሁኑ ወቅት ዋነኛ ተግዳሮት የሆነውን የአትሌቶች ለጎዳና ውድድር ትኩረት መስጠት እና ወደ ጎዳና ውድድሮች መፍለስን እንዴት በመከላከል ውጤታማ መሆን ይቻላል ሲል የዘርፉ ባለሙያዎች አነጋግሯል።ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አትሌቲክስ ክለብ ዋና አሰልጣኝ ንጉሴ ተፈራ፤ቀደም ባሉት ዓመታት በዓለም አቀፍ ደረጃ በአምስት እና አስር ሺ ሜትር ውድድሮች የዓለም ትኩረት ማረፊያ የነበረችው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በርቀቱ ያላት ስምና ክብር በቀድሞው ልክ አለመሆኑን ይስማሙበታል።\nየዚህም ዋነኛ ምክንያት በሙሉ ለማለት በሚያስደፍር መልኩ አገሪቱ በርቀቱ የነበራትን ክብር ነገ ከነገ ወዲያ አስጥብቀው ይቀጥላሉ የተባሉ አትሌቶች ጭምር ወደ ጎዳና ውድድሮች ፈልሰዋል የሚሉት አሰልጣኙ፤አሁን ከአልማዝ አያና ውጪ በርካታ አትሌቶች በጎዳና በተለይ በማራቶን ውድድር መጠመዳቸውን ይጠቅሳሉ።ይህም ሁሉም ግላዊ ፍላጎቱን ወደ ማርካት ማድላቱና ገንዘብ ላይ በማተኮሩ የተፈጠረ መሆኑን የሚገልፁት አሰልጣኙ፤ ሁሉም ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ማናጀሮች ትኩረት የሚሰጡት፣ አሰልጣኞችም የሚያሰለጥኑት አትሌቶችን ለጎዳና ውድድር ለማብቃት መሆኑን ይገልፃሉ።\nበተለይ ማናጀሮችና አሰልጣኞች አንድን አትሌት ነገ ስለሚካሄድ የጎዳና ውድድር እንጂ በቀጣይ ወራት ስለሚካሄድ ትላቅ አህጉር አቀፍ ሻምፒዮና ላዘጋጀው የሚል ሀሳብ የላቸውም» የሚሉት አሰልጣኙ፤አትሌቶቹ ወደ ጎዳና ውድድር እንዲያዘነብሉ በማድረጉ በኩል አብዛኛው ችግር ያለው አሰልጣኞቹ ዘንድ መሆኑን ያሰምሩበታል።‹‹የገንዘብ ጉዳይ ከሆነ ገንዘቡ በትራክ ውድድሮች ላይም አለ ›› የሚሉት አሰልጣኙ፤ በአግባቡ ከተሰራበት የትራክ ውድድርም ገንዘብ እንዳለውና ለዚህም ቀነኒሳ በቀለ፤ደራርቱ ቱሉ እነ ስለሺ ስህን የመሳሰሉ አትሌቶች በትራክ ውድድር ትልቅ ገንዘብ ሲያገኙ እንደነበር በማሳያነት በመጥቀስ ያብራራሉ።\nየአገሪቱን የቀደመ የረጅም ርቀት እውቅና እና ክብር መልሶ ለማስቀጠል የመም ውድድር አትሌቶችን በልዩነት መያዝ ይገባል የሚሉት ዋና አሰልጣኝ ንጉሴ፣ ለዚህም ራሱን የቻለ ህግ መውጣት እንዳለበት ነው የሚጠቁሙት፡፡ይህ እስካልሆነ ድረስ ነገም ከዚህ የከፋ አደጋ ውስጥ እንደምንወድቅ አልጠራጠርም»ይላሉ።እንደ ዋና አሰልጣኙ ገለፃ፤ በአሁኑ ወቅት ዓለም አቀፍ ውድድር በተቃረበ ቁጥር የጎዳና ተወዳዳሪ አትሌቶችን ወደ መም ለማምጣት ሲሞከር ይስተዋላል።ይሁንና በዚህ ዓይነት አካሄድ ውጤታማ ለመሆን መዳከር አግባብ አይደለም። እንደ የውድድሩ ባህሪም የሚገኘው ውጤትም ለየቅል የሆነውም ለዚሁ ነው።አንድ ሻምፒዮና ሲደርስ አትሌቶች ቢያንስ ከሦስት ወራት ቀድመው ማንኛውንም የጎዳና ውድድር ከማድረግ እንዲቆጠቡ ማድረግ እስካልተቻለ ድረስ አትሌቶች ከመም ውድድሮች ይልቅ ጉዳናን ምርጫቸው ከማድረግ እንደማይ ቆጠቡ ተናግረው፣ይህ አካሄድ የመም ውድድር አትሌቶችን እስከማሳጣት እንደሚደርስም ነው የሚያስገነዝቡት።ዋና አሰልጣኙ ይህን ችግር ለመፍታት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም አቅጣጫ ማስቀመጥ እንደሚኖርበት፣ለዚህም አዲስ አሰራር መተግበር የግድ እንደሚለው ይጠቁማሉ፡፡ ለአብነት ጎዳና ላይ የነበሩ አትሌቶች ከተወሰነ ወር በፊት ወደ ትራክ እንዳይመጡ፤የመም ተወዳዳሪ አትሌቶችም ከጎዳና ውድድር እንዳይመረጡ የሚገድብ ህግ መተግበር እንዳለበት ያስገንዝባሉ።አሰልጣኝ ሙልዬ እያዩም ኢትዮጵያ በተለይ በረጅም ርቀት የመም ውድድሮች የነበራት ዝና መደብዘዙን ይስማሙበታል።የዚህም ዋነኛ ምክንያት የጎዳና ውድድሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት እየተሰጣቸው መምጣቱ መሆኑን ያሰምሩበታል።\nእንደ አሰልጣኝ ሙልዬ ገለፃ፤በአሁኑ ወቅት ከ27 ሺ 800 በላይ የጎዳና ውድድሮች በየዓመቱ ይካሄዳሉ። እነዚህ ውድድሮችም ከጊዜ ወደ ጊዜ አዝናኝነታቸው ተመራጭ እየሆነ በመምጣቱም አዘጋጅ አገራት የአትሌቶቹን ቀልብ በእጅጉ መቆጣጠር ከመቻላቸውም በተጨማሪ ፣በተለይ በቱሪዝም ዘርፉ ለገቢ ምንጭነት እየተጠቀሙት ይገኛሉ።ይህ እንደመሆኑ ኢትዮጵያን በርቀቱ የመወከል አቅም ያላቸው ወጣት አትሌቶች ጭምር ወደ ጎዳና እየፈለሱ መሆናቸውን የሚያረጋግጡት አሰልጣኝ ሙልዬ፤ይህ ማለት ግን የውድድሮቹ መብዛት አትሌቶቹን ወደ ጎዳና ስቧቸዋል አሊያም ማናጀሮቻቸው በሚያሳድሩባቸው ጫና ወደ ጎዳና ውድድር ሄደዋል ለማለት እንደማያስደፍር ያስቀምጣሉ።አትሌቶች ከትራክ ውድድር ይልቅ ለጎዳና ውድድሮች ቅድሚያ እንዲሰጡ በአሰልጣኝና ማናጀሮቻቸው በኩል ጫና ይደርስባቸዋል የሚለውን አስተያየት አሰልጣኙ አይስማሙበትም፡፡ይህ ማለት ለግል ጥቅማቸው ሲሉ አትሌቶችን ለጉዳት በሚዳርግ መልኩ ለረጅም ጊዜያት ከሳምንት እስከ ሳምንት በአስፋልት ውድድር ሙሉ ስልጠና የሚሰጡ አንዳንድ ማናጀሮች የሉም ማለት እንዳልሆነም ይጠቁማሉ።\nአትሌቶች ወደ ጎዳና ውድድሮች የሚፈልሱት በማናጀሮቻቸው ገፋፊነት ብቻም ሳይሆን በአብዛኛው በግል ውሳኔ ቀደም ሲል የነበሩ አትሌቶችን በመመልከት ነው የሚሉት አሰልጣኙ፤አትሌቶችም በውድድር በመካፈላቸው ብሎም ካሸነፉ የሚያገኙት ጥቅም ከፍተኛ በመሆኑም የጎዳና ውድድሮችን እንዲመርጡ እያስገደዳቸው መሆኑን ያስገነዝባሉ።አሰልጣኙ በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ትላልቅ መድረኮች የአምስት እና አስር ሺ ሜትር ሩጫ የምስራቅ አፍሪካውያን መድመቂያ ነው፤ ኢትዮጵያውያንም የዚህ ድምቀት ፈጣሪዎች ናቸው፡፡ ይሁንና ይህ ትዕይንት አሁን ደብዝዟል ከማለት የቀደመውን ስምና ዝናችንን እንዴት መመላስ እንችላለን የሚለውን መመለስ ይገባል ሲሉ ያመለክታሉ።\nለዚህም በቀዳሚነት የመም ውድድር አትሌቶችን እንዴት በብቃት ማፍራት እንዲሁም ወደ ጎዳና የፈለሱትን በምን መልኩ ፊታቸውን እንዲያዞሩ ማድረግ ይቻላል የሚለውን የሚመለስ ተግባር መፈፀም እንደሚገባ ይጠቁማሉ።«ይህን ለማድረግ በቀዳሚነት በትራክ ውድድር የሚሳተፉ አትሌቶች የሚያገኙትን ጥቅም ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል›› የሚሉት አሰልጣኙ፤አትሌቶች ወደ ጎዳና የመውጣታቸው ምክንያት ህይወታቸውን ለመደጎም መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ይህን ችግር ለመፍታትም በመም ውድድር ለሚካፈሉት ከፍ ያለ ሽልማት ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ በመጠቆም፣ይህ ሲሆንም ተተኪ አትሌቶች ማግኘት እንደሚቻል ያመለክታሉ።ከዚህም ባሻገር በዚህ ዘርፍ ፍላጎት ያላቸውን ልጆች ማፍራት እንደሚገባ በመጠቆም፣ ለዚህም የተመረጡት ልጆች ቀጣይነት ባለው መልኩ ህይወታቸውን መምራት የሚያስችላቸው ራሱን የቻለ ፕሮጀክት መቅረጽ እንደሚያስፈልግም ይገልጻሉ።\nእንደ አሰልጣኙ ገለፃ፤ትራክ ላይ የሰራ አትሌት ውድድር ለማግኘት አንድና ሁለት ዓመት መጠበቅ ግድ ይለዋል።ከዚህ ባንፃሩ የጎዳና ውድድሮችን ቶሎ ቶሎ ማግኘት ይችላል።ይህ በሆነበት የጎዳና ውድድር መምረጡ አይቅሬ ነው።በመሆኑም መሰል ችግሮችን ለመፍታት የውድድር ተደራሽነት መስፋት ያስፈልጋል፡፡ በመም ውድድሮች በተለይ በአምስትና አስር ሺ ሜትር የኢትዮጵያን የበላይነት የውጤት ክብር ለማስቀጠል ውድድሮችን በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ በማዘጋጀት ተደራሽነቱን ማስፋት ያስፈልጋል። ምንም እንኳን የጎዳና ላይ ሩጫዎች ተበራክተው የትራክ ውድድር ቢያንስ ሁለቱን ለማስታረቅ አትሌቶቹ ራሳቸውን ሳይጎዱ የሚካፈሉባቸው የልምምድ ዓይነቶችን ማዘጋጀትም የተሻለ ውጤት ማምጣት ይቻላል።\n«የጎዳና ላይ ውድድር የግል ህይወትን ማሻሻያ እንጂ ለክብር እና ለአገር ተብሎ የሚሮጥበት አይደለም» የሚሉት አሰልጣኝ ማሙዬ፤ከሁሉም በላይ አትሌቶች ለአገርና ለክብር ያላቸውን ስሜት በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር በድጋሚ እንዲያ ረጋግጡ ግንዛቤ የማስረፅ ተግባር ማከናወን እንደሚገባም ይገልጻሉ።የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዚዳንትና ተወካይ አትሌት ስለሺ ስህን፤ በአሁኑ ወቅት የአስርና አምስት ሺ ሜትር የመም ውድድሮች ከቀደመው ጊዜ አንፃር ሲታይ በእጅጉ መቀነሳቸውን ጠቅሶ፣ ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል ለማለት እንደማያስደፍር አሁንም ትልልቅ ውድድሮች እንዳሉ ያብራራል።የግል ጥቅም አትሌቶቹ ወደ ጎዳና ለመውጣታቸው ምክንያት እንደማይሆን የሚናገረው አትሌት ስለሺ፣ በመም ውድድሮች ላይ ውጤታማ መሆን ከማራቶን ባልተናነሰ በስፖንሰር፤በዳይመንድ ሊግ የመመረጥ እና ሌሎችም ረብጣ ሽልማቶች የሚያስገኝበት ሁኔታ እንዳለም ያስረዳል።ለዚህም አሁንም በመም ውድድር አልማዝና እና ገንዘቤ እንዲሁም ሰለሞን ባረጋ እየሮጡ መሆናቸውን በአብነት ይጠቅሳል።\n‹‹እርግጥ ነው ማራቶን ጥቅም ሊኖረው ይችላል።ይሁንና ማራቶን በመጪዎቹ የአትሌቲክስ ዕድሜዎች የሚደረስበት ውድድር ነው›› የሚለው አትሌት ሰለሺ፤ ከጎዳና ውድድሮች በተለይም አንድ ጊዜ ማራቶን ላይ ገብቶ ሁለትና ሦስት ዓመታት ከቆዩ በኋላ ጨርሶኑ መጥፋት ጉዳት እንጂ ጥቅም እንደሌለውም ነው ያብራራው።በአሥርና አምስት ሺ ላይ የሚቆይ አትሌት ወደ ማራቶን ሲሄድ ውጤታማ መሆን እንደሚ ችልና በተለይ ወጣት አትሌቶች በልጅነት ዕድሜያቸው ወደ ማራቶን ከሚገቡ በመም ውድድሮች ላይ ብዙ ዓመታት መስራት ቢችሉ ውጤታማ ስለመሆናቸው ጥርጥር ሊገባቸው እንደማይገባም ይጠቁማል።\nእንደ አትሌት ስለሺ ገለፃ፤ይህን ችግር ለመፍታት በቀዳሚነት አትሌቶች ቸኩለው ወደ ጉዳና መውጣታቸው ስህተት እንደሆነና በቀጣይ የሩጫ ህይወታቸው ውጤታማነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳርፍ ጠንቅቀው እንዲረዱት ግንዛቤ ማስጨበጥ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ዓይነት ውድድር ውስጥ ለማለፍ እንደማይጠቅም በውድድሩ ቢያልፉም ውጤታማ እንደማይሆኑ ማስረዳት ይገባል፡፡ በመም ውድድሮች በስለው ወደ ጎዳና ውድድሮች ቢሄዱ የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆኑ ማስገነዘብ የግድ ይላል።ከሁሉም በላይ የአገር ፍቅር ስሜት የሚባለው እንዲሰርፅባቸው ማድረግ ይገባል።አንድ አትሌት ወደ ጎዳና የሚወጣው በአሰልጣኝ አሊያም ማናጀሩ ከፍተኛ ጫና እያሳደረበት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ መሆኑን የሚመሰክረው አትሌት ስለሺ፤እነዚህ ገንዘብ ተኮር የሆኑ አሰልጣኝና ማናጀሮችን መቆጣጠር እንደሚያስፈልግ ይናገራል፡፡ይህን ችግር መፍታትም የፌዴሬሽኑ ኃላፊነት መሆኑን ይናገራል።\nየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ ዱቤ ጅሎ፤በዓለም አቀፍ ደረጃ የመም በተለይ የአሥርና አምስት ሺ ሜትር ውድድሮች እየቀነሱ መምጣታቸውን ጠቅሶ፣ ፌዴሬሽኑም ራስ ምታት እንደሆነበት ይገልጻል፡፡ በተጠቀሱት ውድድሮች ሚኒማ ለማሟላት አትሌቶች ወደተለያዩ አገራት በመላክ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እየከፈለ መሆኑንም ይገልፃሉ።ከመልክዓ ምድር ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ዓለም አቀፉ ፌዴሬሽን የሚያስቀም ጠውን ሚኒማ ማሟላት አይቻልም፤ይህ እንደመሆኑ ፌዴሬሽኑ አትሌቶችን በመምረጥ ወደ ተለያዩ አገራት በመውሰድ እያወዳደረ መሆኑንም ያስረዳሉ።\nየረጅም ርቀት ውድድሮች እያበቃላቸው፤ የጎዳና ላይ ውድድሮች እየተበራከቱ መምጣታቸውና ሽልማታቸውም እየገዘፈ በመሆኑ አሰልጣኞች፤ ማናጀሮች እንዲሁም አትሌቶች ወደ ጉዳና እየፈለሱ መሆናቸውን ፌዴሬሽኑንም እንደሚያሳስበው ያስረዳሉ።ይህ ችግር እያደር በመባባሱም ፌዴሬሽኑ በተለይ አጭር ርቀት ላይ እንዴት እንስራ የሚለውን አቅጣጫ እስከመከተል እንዳደረሰው የሚገልፁት አቶ ዱቤ፤ፌዴሬሽኑም ክልሎችና ክለቦችን በመደገፍ የትራክ አትሌት የማይጠፋበት ሁኔታ እንዲፈጠር የበኩሉን እያደረገ መሆኑንም ነው ያስረዱት።አሁን የመም ውድድሮችን የሚሳተፉ አትሌቶችን ለመለየትና ለማብቃት እንቅፋት ከሆኑት መካከል አንደኛው የመወዳደሪያ ቦታ እጥረት መሆኑንም የሚያስረዱት አቶ ዱቤ፤በቀጣይ የመም ውድድር ራጮችን ፍፅሞ ከማጣት ቀድሞ መሰል የመወዳደሪያ ቦታ እጥረቶች መስተካከል እንደሚገባ ይናገራሉ፡፡ለዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የየበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ያቀርባሉ።\nየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ስፖንሰር አድራጊ ተቋማትን ፈልጎ እንዲሁም የአገር ውስጥ ውድድሮችን በማዘጋጀት ተወዳዳሪ አሸናፊዎች የተሻለ ጥቅማ ጥቅም የሚያገኙበትን አሰራር መዘርጋት እንዲሁም ለትራክ ተወዳዳሪዎች የሚሰጠውን ሽልማት ከፍ ለማድረግ መስራት እንደሚገባ ይጠቁማሉ።ታምራት ተስፋዬ", "passage_id": "29de9c359db0ea3019780eda698c1526" } ]
88c6524c7dfabb9118ba2b29e71287da
7c62f1e6db6c324efffae8cba53943df
ኢትዮጵያዊቷ የ5 ሺህ ሜትር ሯጯ አትሌት መሰረት ደፋር
በመንግሥት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ለመከላከል እያደረገ ለሚገኘው ርብርብ እንዲጠቀምበት ህንፃዋን በጊዜያዊነት አበረከተች። አትሌቷ ህንፃውን የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሆኑት ወ/ሮ አዳነች አበቤ፣ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም፣ በኢትዮጵያ ጤና ኢንስቲቲዩት እንዲሁም የጤና ተቋማት ዝግጁነት እና ለይቶ ማቆያ ዋና አስተባባሪ የሆኑት አቶ ኢሳያስ አገኘሁ ጨምሮ የተለያዩ የመንግሥት ሹማምንቶች በተገኙበት አስረክባለች። አትሌት መሰረት ደፋር በወቅቱ እንደተናገረችው፤ ከዚህ ህብረተሰብ መሐል የተገኘሁ ሰው ነኝ። እኔም ሆንኩ የኢትዮጵያ ህዝብ ጤና ስንሆን ነው ሁላችንም አብረን በሰላም ሰርተን የምንኖረው። ይህን ህንፃ እኔ እና ባለቤቴ ቴዲ እንገንባው እንጂ የኛ ብቻ አይደለም። ከኛ ጋር በሃሳቡ አብሮ የሮጠ የጤና ችግር ሲገጥመኝ አብሮ የታመመ የተጨነቀልኝ፤ በስፖርቱ ዓለም ለነበረኝ ያማረ ጉዞ በሙሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ከጎኔ ሆኖ ሁሉን የተካፈለኝ የሀገሬ፣ የወገኔ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ህንፃ ነው ብላለች። ህንፃው አገሬንና ወገኔን በእንዲህ አስቸጋሪውን ጊዜ ካላገለገለና ካልጠቀመ ዋጋ እንዳለው የሚቆጠር አለመሆኑን ገልፃለች አያደርግም። በመሆኑም የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተደረገ በሚገኘው ተግባር እንዲውል ህንፃውን በጊዜያዊነት ማስረከቧን ተናገራለች። እኛ ኢትዮጵያኖች ደግሞ አኗኗራችን በመረዳዳት፣ በመደጋገፍ፣ አብሮ በመኖርና በመብላት፣ የተሳሰር ነው። በሽታው «ደግሞ እነዚህን የማይወድ ክፉ በመሆኑ እኛም የገጠመን እባካችሁ አብሮ የመኖር አብሮ ሁሉን የመጋራት ልምዳቸንን ገታ በማድረግ ከመንግሥት ጤና ተቋማት የሚሰጡንን መመሪያዎች በመተግበር አስቸጋሪውን፣ ክፉ ጊዜ መሻገር አለብን »ብላለቸ። የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሆኑት ወ/ሮ አዳነች አበቤ በበኩላቸው፤ በእውነት መሰረት እና ባለቤቷ አቶ ቴድሮስ ህንፃው ገና ሥራ ሳይጀምር ለእንዲህ አይነት የተቀደሰ አላማ እንዲውል መስጠታቸው የሚደነቅ ተግባር ነው። ለንግድ ሥራ ተገንብቶ ሥራውን “ሀ” ብሎ ሲጀምር ለበጎ ሥራ የዋለ ወይም በበጎ ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው የአትሌት ህንፃ ይመስለኛል። ይህን ማድረግ መቻል ደግሞ ትልቅ መባረክና ለሌሎችም አርአያ ጭምር መሆኑን አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ማህበር ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ማህበር ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ያሰባሰቡትን ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ። በማህበሩ አባላት ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ይውል ዘንድ ከፕሪምየር ሊግ እና ከከፍተኛ ሊግ ቡድን ተጨዋቾች ያሰባሰቡትን ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ዕርዳታ ከትናነት በስቲያ ለድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አስረክበዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የመስተዳድሩ እና የስፖርት ኮሚሽን ከፍተኛ ሃላፊዎች እንደዚሁም ደግሞ የየክለቡ ካፒቴኖች እና የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች አመራሮች በአዲስ አበባ ስታድየም በተገኙበት በእዚህ የገንዘብ ርክክብ ፕሮግራም ላይ ማህበሩ ይሄን ለወገን ደራሽ ወገን ነው በሚል መርህ ኮረና ቫይረስን መነሻ አድርጎ ለሰራው ሥራ ከመስተዳደሩ ከስፖርት ኮሚሽንና ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ ምስጋና ቀርቦለታል። የመልካም ቤተሰብ – ተምሳሌት በስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን እና በስዊዝ ዋናው ሱፕር ሊግ ስኬታማ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ታዳጊ ተጫዋቾች ሲነሳ በጥሩ ምሳሌነት ማረን ሃይለሥላሴ እና ቅዱስ ሃይለሥላሴ ይጠቀሳሉ። ታዳጊዎቹ ከወላጆቻቸው ጋር በመሆን ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ በቋሚነት ለሚረዱት የከለላ እግርኳስ ክለብ ታዳጊዎች እና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ኑሮ ለከበዳቸው የምግብ ፍጆታ ድጋፍ አድርገዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 13/2012ዳንኤል ዘነበኢትዮጵያዊቷ የ5 ሺህ ሜትር ሯጯ አትሌት መሰረት ደፋር በመንግሥት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ለመከላከል እያደረገ ለሚገኘው ርብርብ እንዲጠቀምበት ህንፃዋን በጊዜያዊነት አበረከተች። አትሌቷ ህንፃውን የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሆኑት ወ/ሮ አዳነች አበቤ፣ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም፣ በኢትዮጵያ ጤና ኢንስቲቲዩት እንዲሁም የጤና ተቋማት ዝግጁነት እና ለይቶ ማቆያ ዋና አስተባባሪ የሆኑት አቶ ኢሳያስ አገኘሁ ጨምሮ የተለያዩ የመንግሥት ሹማምንቶች በተገኙበት አስረክባለች። አትሌት መሰረት ደፋር በወቅቱ እንደተናገረችው፤ ከዚህ ህብረተሰብ መሐል የተገኘሁ ሰው ነኝ። እኔም ሆንኩ የኢትዮጵያ ህዝብ ጤና ስንሆን ነው ሁላችንም አብረን በሰላም ሰርተን የምንኖረው። ይህን ህንፃ እኔ እና ባለቤቴ ቴዲ እንገንባው እንጂ የኛ ብቻ አይደለም። ከኛ ጋር በሃሳቡ አብሮ የሮጠ የጤና ችግር ሲገጥመኝ አብሮ የታመመ የተጨነቀልኝ፤ በስፖርቱ ዓለም ለነበረኝ ያማረ ጉዞ በሙሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ከጎኔ ሆኖ ሁሉን የተካፈለኝ የሀገሬ፣ የወገኔ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ህንፃ ነው ብላለች። ህንፃው አገሬንና ወገኔን በእንዲህ አስቸጋሪውን ጊዜ ካላገለገለና ካልጠቀመ ዋጋ እንዳለው የሚቆጠር አለመሆኑን ገልፃለች አያደርግም። በመሆኑም የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተደረገ በሚገኘው ተግባር እንዲውል ህንፃውን በጊዜያዊነት ማስረከቧን ተናገራለች። እኛ ኢትዮጵያኖች ደግሞ አኗኗራችን በመረዳዳት፣ በመደጋገፍ፣ አብሮ በመኖርና በመብላት፣ የተሳሰር ነው። በሽታው «ደግሞ እነዚህን የማይወድ ክፉ በመሆኑ እኛም የገጠመን እባካችሁ አብሮ የመኖር አብሮ ሁሉን የመጋራት ልምዳቸንን ገታ በማድረግ ከመንግሥት ጤና ተቋማት የሚሰጡንን መመሪያዎች በመተግበር አስቸጋሪውን፣ ክፉ ጊዜ መሻገር አለብን »ብላለቸ። የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሆኑት ወ/ሮ አዳነች አበቤ በበኩላቸው፤ በእውነት መሰረት እና ባለቤቷ አቶ ቴድሮስ ህንፃው ገና ሥራ ሳይጀምር ለእንዲህ አይነት የተቀደሰ አላማ እንዲውል መስጠታቸው የሚደነቅ ተግባር ነው። ለንግድ ሥራ ተገንብቶ ሥራውን “ሀ” ብሎ ሲጀምር ለበጎ ሥራ የዋለ ወይም በበጎ ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው የአትሌት ህንፃ ይመስለኛል። ይህን ማድረግ መቻል ደግሞ ትልቅ መባረክና ለሌሎችም አርአያ ጭምር መሆኑን አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ማህበር ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ማህበር ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ያሰባሰቡትን ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ። በማህበሩ አባላት ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ይውል ዘንድ ከፕሪምየር ሊግ እና ከከፍተኛ ሊግ ቡድን ተጨዋቾች ያሰባሰቡትን ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ዕርዳታ ከትናነት በስቲያ ለድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አስረክበዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የመስተዳድሩ እና የስፖርት ኮሚሽን ከፍተኛ ሃላፊዎች እንደዚሁም ደግሞ የየክለቡ ካፒቴኖች እና የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች አመራሮች በአዲስ አበባ ስታድየም በተገኙበት በእዚህ የገንዘብ ርክክብ ፕሮግራም ላይ ማህበሩ ይሄን ለወገን ደራሽ ወገን ነው በሚል መርህ ኮረና ቫይረስን መነሻ አድርጎ ለሰራው ሥራ ከመስተዳደሩ ከስፖርት ኮሚሽንና ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ ምስጋና ቀርቦለታል። የመልካም ቤተሰብ – ተምሳሌት በስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን እና በስዊዝ ዋናው ሱፕር ሊግ ስኬታማ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ታዳጊ ተጫዋቾች ሲነሳ በጥሩ ምሳሌነት ማረን ሃይለሥላሴ እና ቅዱስ ሃይለሥላሴ ይጠቀሳሉ። ታዳጊዎቹ ከወላጆቻቸው ጋር በመሆን ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ በቋሚነት ለሚረዱት የከለላ እግርኳስ ክለብ ታዳጊዎች እና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ኑሮ ለከበዳቸው የምግብ ፍጆታ ድጋፍ አድርገዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 13/2012
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=30808
[ { "passage": "በመጪው የፈረንጆቹ ወር የመጀመሪያው ዕለት በሚካሄደው የቶኪዮ ማራቶን የአምናዎቹ አሸናፊዎች በድጋሚ ተሳታፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። በዓለም ላይ ስመጥር ከሆኑትና የዓለም አትሌቲክስም የፕላቲኒየም ደረጃ ከሰጣቸው የጎዳና ላይ ውድድሮች መካከል አንዱ የሆነውን የቶኪዮ ማራቶንን ኢትዮጵ ያዊያኑ አትሌቶች እንደሚያደምቁትም ይጠበቃል። የአትሌቶቹ የግል ፈጣን ሰዓትም በሁለቱም ጾታ ቀዳሚ መሆኑ ደግሞ ፉክክሩ በአንድ ሃገር አትሌቶች መካከል ስለሚያደርገው፤ ውድድሩን ይበልጥ አጓጊም ያደርገዋል። አትሌት ብርሃኑ ለገሰ በወንዶች ምድብ የሚመራ ኢትዮጵያዊ ሲሆን\nቀዳሚው ፈጣን ሰዓትም የግሉ ነው። የአምናው የዚህ ውድድር ባለ ድል ርቀቱን ለማጠናቀቅ የፈጀበት 2:04:48 የሆነ ሰዓት ቢሆንም፤ከስምንት\nወራት በፊት በተካፈለበት የበርሊን ማራቶን 2:02:48 በመግባት የራሱን ሰዓት አሻሽሏል። ይህም ከባዱንና ረጅሙን የማራቶን ውድድር\nከ2 ሰዓት ከ05 በታች የሆነ ሰዓት ካስመዘገቡ ስምንት ምርጥ አትሌቶች ተርታ የሚያሰልፈው ነው። ብርሃኑ በፈጣን ሰዓቱ እንዲሁም\nበቦታው ባለው ልምድ ታግዞ ዘንድሮም አሸናፊ የመሆን ከፍተኛ ቅድመ ግምትን ያግኝ እንጂ፤ ፈተና ሊሆኑበት የሚችሉ አትሌቶችም በውድድሩ\nተካተዋል። ውድድሩን ሊያከብዱት አሊያም በአሸናፊነት ሊያጠናቅቁ ይችላሉ በሚል\nከሚጠበቁት አትሌቶች መካከል አንዱ የሃገሩ ልጅ ጌታነህ ሞላ ነው። 2:03:34 ደግሞ አምና የዱባይ ማራቶንን በቀዳሚነት ያጠናቀቀበት\nእንዲሁም በቶኪዮ ማራቶን ተሳታፊዎች መካከል ሁለተኛው ፈጣን ነው። አትሌት ሲሳይ ለማም ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሲሆን፣ በበርሊን ማራቶን\nብርሃኑ ለገሰን ተከትሎ የገባበት ሰዓት 2:03:36 የግሉ ፈጣን ነው። በአንድ ደቂቃ ልዩነት የሚከተሉት አሰፋ መንግስቱ እና ሃይሌ\nለሚም በተመሳሳይ በውድድሩ መሳተፋቸውን ያረጋገጡ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ናቸው። ኬንያዊያኑ ዲክሰን ቹምባ፣ ቱቲስ ኢክሩይ፣ አሞስ\nኪፕሩቶ እንዲሁም ባህሬናዊው አል ሃሰን አል አባስም ቀላል ግምት የማይሰጣቸው አትሌቶች ናቸው። እንደ ወንዶቹ ምድብ ሁሉ የሴቶቹን ምድብ የምትመራውም የአምናዋ የዚህ ውድድር አሸናፊ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት\nሩቲ አጋ ናት። ሩቲ የርቀቱን የመጨረሻ መስመር የረገጠችው 2:20:40 በሆነ ሰዓት ሲሆን፤ የግሏን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበችው\nግን እአአ በ2018ቱ የበርሊን ማራቶን (2:18:34) ነው። ይህም በውድድሩ ከሚካፈሉት አትሌቶች ቀዳሚዋ ያደርጋታል። ከአትሌቷ\nጋር በውድድሩ የሚሰለፉት የሃገሯ ልጆችም እአአ በ2015 እና 2018 የቶኪዮ ማራቶን አሸናፊ የነበረችው ብርሃኔ ዲባባ እንዲሁም\nእአአ የ2014 ባለ ድሏ ትርፌ ጸጋዬም ከቀዳሚዎቹ የአሸናፊነት ተገማች ይጠቀሳሉ። በማራቶን ሰፊ ልምድና አቅም ያላቸው፤ ትእግስት\nግርማ፣ አዝመራ ገብሩ፣ ሹሬ ደምሴ፣ ማርታ ለማ፣ ሱቱሜ አሰፋ እና ሰንበሬ ተፈሪም በኢትዮጵያ በኩል ተሳታፊ የሚሆኑ አትሌቶች ናቸው።\nየቶኪዮ ማራቶንን በዳይሬክተርነት የሚመሩት ታዳኪ ሃያኖ\nውድድሩ በሁለት መልክ የሚካሄድ መሆኑን ይጠቁማሉ። የመጀመሪያው ምድብ 2ሰዓት ከ03 ደቂቃና ከዚያ በታች በሆነ ሰዓት ለመግባት\nፍላጎት ላላቸው አትሌቶች ነው። ሁለተኛው ደግሞ ከ2:04:40-2:05:30 በሆነ ሰዓት ሩጫቸውን በሚያጠናቅቁ አትሌቶች መካከል\nየሚካሄድ ነው። በዚህ ውድድር ውጤታማ የሚሆኑ አትሌቶችም ከወራት በኋላ በሚካሄደው የቶኪዮው ኦሊምፒክ ቲኬት ለመቁረጥ የሚያስችላቸው\nነው። በመሆኑም በርካታ ጃፓናዊያን አትሌቶች በእድሉ የሚጠቀሙ ይሆናል ሲሉም ዳይሬክተሩ ያብራራሉ።አዲስ ዘመን ቅዳሜ ጥር 30/2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "5071499c7bb784cefddf5e2f5cf5bec0" }, { "passage": "የረጅም ርቀትና የአገር አቋራጭ ንጉሱ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከረጅም ጊዜ ጉዳት ተመልሶ የማራቶን የዓለም ክብረወሰንን ለመስበር ተቃርቧል። ትናንት በተካሄደው የበርሊን ማራቶን ቀነኒሳ ርቀቱን 2፡01፡41 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ በጀርመኗ መዲና ለሁለተኛ ጊዜ ነግሷል። ቀነኒሳ እ.አ.አ በ2016 የበርሊን ማራቶን ሲያሸንፍም የዓለም ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት አስመዝግቦ እንደነበረ ይታወሳል። ቀነኒሳ እ.አ.አ ለመጀመሪያ ጊዜ 2015 የፓሪስ ማራቶንን የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር ካሸነፈ ወዲህ በርቀቱ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት አትሌት ቢሆንም በተደጋጋሚ በሚገጥመው ጉዳት ውድድሮችን አቋርጦ ለመውጣት ሲገደድ ታይቷል። ለረጅም ጊዜ ከጉዳቱ ለማገገም ሲጥርም በርካታ ውድድሮች አምልጠውታል። ያምሆኖ ትናንት ከወደቀበት ተነስቶ ታሪክ መስራት እንደሚችል በማሳየቱ የዓለም መገናኛ ብዙኃንን ቀልብ ስቧል። በኳታር ዶሃ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ኢትዮጵያ እስከ ትናንት ድረስ የጠበቀችውን ውጤት ማምጣት ባለመቻሏ ቅር የተሰኙ የስፖርት ቤተሰቦችም በቀነኒሳ ድል ተፅናንተዋል። በኬንያዊው ድንቅ አትሌት ኢሉድ ኪፕቾጌ ተይዞ የሚገኘው የዓለም የማራቶን ክብረወሰን 2፡01፡39 ሲሆን ይህን ክብረወሰን ሌላ አትሌት እንደማይደፍረው ሲነገር ቆይቷል። ቀነኒሳ በትናንቱ ውድድር ምናልባትም ውሃ አንስቶ ለመጠጣት ያባከናት ሽርፍራፊ ሰከንድ ዋጋ አስከፈለችው እንጂ ይህን ክብረወሰን ማሻሻል እንደሚችል አስመስክሯል። ከቀነኒሳ ጎን ለጎን የዘንድሮው የበርሊን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የነገሱበት ሆኗል። ቀነኒሳን ተከትሎ ብርሃኑ ለገሰ 2:02:48 በሆነ የራሱ ምርጥ ሰዓት ሁለተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ሲሳይ ለማ በ2:03:36 ሰዓት ሦስተኛ ሆኗል። በሴቶች መካከል በተካሄደው ውድድርም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል። እሸቴ በክሪ የኢትዮጵያን ክብረወሰን 2:20:14 በሆነ ሰዓት በማሻሻል ጭምር ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ የቀድሞ የዓለም ቻምፒዮኗ ማሬ ዲባባ 2:20:21 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆናለች። ኬንያዊቷ ሳሊ ቺፕየጎ 2:21:06 ሰዓት ሦስተኛ፣ ሔለን ቶላ በ2:21:36 ሰዓት አራተኛ ሆነው ውድድሩን ጨርሰዋል። በውድድሩ ትልቅ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቷት የነበረችው የቀድሞ የኦሊምፒክና የዓለም ቻምፒዮኗ አትሌት መሠረት ደፋር እስከ ሰላሳ ኪሎ ሜትር ገደማ ከመሪዎቹ ተርታ ሆና ብትታገልም ደረጃ ውስጥ ገብታ ማጠናቀቅ አልቻለችም።አዲስ ዘመን  መስከረም 19/2012 ቦጋለ\nአበበ", "passage_id": "bab702c661a4cb7ff3acbe61468e4ddb" }, { "passage": "አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ለተሰንበት ግደይ የ”ሞመንት ኦፍ ዘ መንዝ” አሸናፊ ሆነች፡፡አትሌት ለተሰንበት ግደይ መስከረም 27፣2013 ዓ.ም ስፔን ቫሌንሺያ ተካሂዶ በነበረው የ5 ሺህ ሜትር ውድድር ክብረወሰን ማሻሻሏን ተከትሎ የፈረንጆቹ ኦክቶበር ወሩ አሸናፊ ተብላለች፡፡የ22 ዓመቷ ለተሰንበት ርቀቱን ለማጠናቀቅ የፈጀባት ጊዜ 14 ደቂቃ ከ6 ሰከንድ ከ62 ማይክሮሰከንድ መሆኑ ይታወሳል፡፡ይህን ተከትሎም በሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን የሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ማሻሻል ችላ ነበር፡፡ከዚህ ቀደም ከ12 ዓመታት በፊት በ14 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ ከ15 ማይክሮሰከንድ በሆነ ጊዜ ጥሩነሽ ዲባባ የርቀቱ ክብረ ወሰን ባለቤት እንደነበረች ይታወሳል፡፡", "passage_id": "a5f9cf94c518cf5445ecc22f8429d163" }, { "passage": "የቱርክ አትሌቶች ኤልቫን አብይ ለገሠ እና ጋምዜ ቡሉት የተከለከለውን አበረታች መድሃኒት በመጠቀም ከውድድሮች ታገዱ።ትውልዷ ኢትዮጵያ ሆኖ ለቱርክ የምትሮጠው አትሌት አብይ ለገሠ ከ2007 እአአ ጀምሮ ያገኘችውን ሽልማት በሙሉ ትነጠቃለች።በሮም ማራቶን በኢትዮጵያዊቷ ራሃማ ቱሣ የተመራው ጠንካራ ቡድን ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከታትሎ ገባ።በፕራግ ግማሽ ማራቶን ደግሞ ኬንያዊቷ ጆስሊን ጆፕኮስፒ ለ4ኛ ጊዜ የዓለምን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈች።በኢትዮጵያ አዲስ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ተመረጠ።ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡ ", "passage_id": "0ce7258e8ec207f5d24c1a5074554a8a" }, { "passage": "ኢትዮጵያዊቷ ኮከብ አትሌት አልማዝ አያና ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ ወደ ልምምድ ለመመለስ ጥረት ማድረግ ከጀመረች ሰነባብታለች፡፡ ከጉዳት አገግማ ባለፈው ወር ዩጂን ዳይመንድ ሊግ ላይ በሦስት ሺ ሜትር ያደረገችው ተሳትፎ ውጤታማ አልነበረም። ይህም አልማዝ ከዘጠና ስድስት ቀናት በኋላ በኳታር ዶሃ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና አትደርስም የሚል ስጋት ፈጥሯል። ይሁን እንጂ አልማዝ ለዓለም ቻምፒዮናው ለመድረስ ልምምድ እያደረገች እንደምትገኝ ከዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ድረ ገፅ ጋር ሰሞኑን ባደረገችው ቃለ ምልልስ ተናግራለች፡፡ የአልማዝ አያና\nአሰልጣኝና ባለቤት ሶሬሳ ፊዳ ከወራት በፊት ለአዲስ ዘመን እንደገለፀው አትሌቷ ጉልበቷ ላይ በደረሰባት ጉዳት ለአንድ ዓመት ያህል ከውድድር ርቃ የነበረ ሲሆን ከጉዳቷ ለማገገም የጅምናዚየም ልምምድ ስትሰራ ቆይታለች፡፡ አልማዝ በሁለቱም እግሮቿ ላይ\nበገጠማት ጉዳት የተለያዩ ቀዶ ጥገናዎችን ያከናወነች ሲሆን ቀስ በቀስ ወደ ልምምድ መመለስ እንዳለባት ዶክተሮቿ መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ዝግጅቷን በተለመደው የአምስትና አስር ሺ ሜትር\nርቀቶች ላይ በማድረግም በዓለም ቻምፒዮናው ኢትዮጵያን ወክላ ለመሮጥ ትልቅ ፍላጎት እንዳላት ተናግ ራለች፡፡ የዓለም የአስር ሺ ሜትር ክብረወሰን ባለቤት፤ የኦሊምፒክና የዓለም ቻምፒዮናዋ አልማዝ በ2017 የውድድር ዓመት ለአስራ አንድ ወራት ያህል ከውድድር ርቃ ብትቆይም የለንደን አትሌቲክስ ቻምፒዮና ላይ በአስር ሺ ሜትር\nየወርቅ፤ በአምስት ሺ ሜትር\nደግሞ የብር ሜዳሊያ ማጥለቋ ይታወሳል። በዚያ የውድድር ዓመት የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የዓመቱ ምርጥ አትሌቶች ሽልማት አሸናፊ መሆን የቻለችው አልማዝ ምንም እንኳን በውድድር ዓመቱ ከለንደን ቻምፒዮና ሁለት ውድድሮች ውጪ መካፈል ባትችልም ከጉዳት ተመልሳ በአጭር ጊዜ ዝግጅት አስር ሺ ሜትሩን 30:16.32 በሆነ\nየዓመቱ ፈጣን ሰዓት ማሸነፏ አድናቆትን አስገኝቶላታል። በ2016 የውድድር ዓመት የአትሌቲክሱ ዓለም ከተመለከታቸው ድንቅ አትሌቶች መካከል አንዷ አልማዝ አያና ነበረች። በሪዮ ኦሊምፒክ በአስር ሺ ሜትር\n29:17.45 የሆነ የዓለም ክብረወሰን በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳሊያ ያጠለቀችው አልማዝ በአምስት ሺ ሜትርም የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት ስትሆን የዳይመንድ ሊግ\nአጠቃላይ አሸናፊም ጭምር ነበረች። በዚያ የውድድር ዓመት በሮም ዳይመንድ ሊግ ላይ በአምስት ሺ ሜትር\n14:12.59 የሆነ ሁለተኛው የዓለማችን ፈጣን ሰዓት ማስመዝገቧም በውድድር ዓመቱ የሚጠቀስ ታላቅ ስኬቷ ነበር። አልማዝ በሪዮ ኦሊምፒክ በተለይም በአስር ሺ ሜትር\nስታሸንፍ ለሃያ ሦስት ዓመታት በቻይናዊቷ ዋንግ ጁአ ተይዞ የቆየውን የዓለም ክብረወሰን በአስራ አራት ሰከንዶች ማሻሻሏ ኢትዮጵያውያንን ብቻም ሳይሆን የዓለም አትሌቲክስ አፍቃሪን ጮቤ አስረግጧል። አልማዝ በወቅቱ አስር ሺ ሜትርን ለመጀመሪያ ጊዜ\nበሮጠችበት የሄንግሎ የመመዘኛ ውድድር ላይ ያስመዘገበችው 30:07 ሰዓት በርቀቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በሮጠች አትሌት የተመዘገበ ፈጣን ሰዓት ሆኖም ተይዟል። አልማዝ አያና በ2017 የለንደን አትሌቲክስ ቻምፒዮና በአስር ሺ ሜትር የወርቅና በአምስት ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ ካሸነፈች ወዲህ ግን ብቅ ያለችው በተለመደው የመም ውድድር ሳይሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት የኒው ዴልሂ ግማሽ ማራቶን ውድድር ነው። አልማዝ የመም ውድድር ጉዞዋን ሳትቋጭ ወደ ግማሽ ማራቶን የመጣችበት ምክንያት ግልፅ ነው። አምስትና አስር ሺ ሜትር የመም ውድድሮች ከዓለም መጥፋታቸው አልማዝ ወደ ጎዳና ላይ ውድድሮች ፊቷን እንድታዞር ያደረጋት እውነታ እንደሆነ ይታመናል። ያም ሆኖ ግን ይህች ድንቅ ኢትዮጵያዊት አትሌት ለመጀመሪያ ጊዜ በግማሽ ማራቶን ራሷን ፈትሻ 1፡07፡11 በሆነ ሰዓት ቀዳሚ ሆና ፈፅማለች። አልማዝ በለንደኑ የዓለም ቻምፒዮና በተለይ ደግሞ በሪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ ካለ አንድ ወርቅ ከመሰናበት እንደታደገችው ሁሉ በ2017 ግማሽ ማራቶን ውድድሮች ወንዶች ያስመዘገቡት እዚህ ግባ የማይባል ውጤት በሴቶች እንዳይደገም አድርጋለች። ከዴልሂ ግማሽ ማራቶን ውድድሯ ወዲህም ካለፈው አንድ ዓመት በላይ በጉዳት የትኛውም ውድድር ላይ ሳትታይ ቀርታለች።አዲስ ዘመን  ሐምሌ 22/2011", "passage_id": "7cde991eb4e3ca2b33fe419234c4cd6e" } ]
312f6330d11b67565093840c5afa2a91
c7440b35c4d40c37250e289c6ca75e58
ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ቫይረስን ከመዋጋት አኳያ
ዓለምን በአንድነት እያስጨነቀ የሚገኘው ወቅታዊ ጉዳይ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ መሆኑ ይታወቃል። ታዲያ በዚህ ቫይረስ ላለመጠቃት አሊያም በቶሎ ለማገገም ከሚረዱ ጉዳዮች መካከል አንዱና ዋነኛው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ነው። በየዕለቱ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ማዘውተር አዕምሮን ከጭንቀት ነፃ ከማድረጉም በላይ አካላዊ ጤንነትን ለመጠበቅና በሽታ የመቋቋም አቅምን ለመገንባት እንዲሁም በቶሎ ከጉዳት ለማገገም ያለው ጠቀሜታ በቁጥር የሚተመን አይደለም። ይህንንም ጥናቶችና የዘርፉ ባለሙያዎች ይስማሙበታል። ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ትምህርት ቤቱ በኩል በሚያዘጋጀው ህትመት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል መደረግ ካለባቸው ነገሮች መካከል አንዱ በሽታን የመከላከል አቅምን ማጎልበት መሆኑን ይጠቁማል። ሰውነት በሽታን የመከላከል አቅሙን እንዲያሳድግ ከሚያደርጉ ዋነኛ መንገዶች አንዱ ደግሞ አካላዊ እንቅስቃሴ ማዘውተር ነው። የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በመደበኛነት ማካሄድ ከልብ፣ ከደም ግፊት፣ ከሰውነት ክብደት መጨመር እንዲሁም በርካታ በሽታዎች ሊከላከል ይችላል። በተፈጥሯዊ መንገድ በሽታ የመከላከል ችሎታን የመጨመርና በጤናማ ሁኔታ እንዲቆይ ያስችላል፤ በመሆኑም እንደ ወቅታዊው ወረርሽኝ ላሉ በሽታዎች መፍትሔ መሆኑን ይመክራል ጽሑፉ። በየቀኑ ለግማሽ ሰዓት ያህል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማካሄድ በቫይረስ ከሚመጡና ገዳይ ከሆኑ በሽታዎች የሚታደግ መሆኑን የሚያረጋግጡት ደግሞ የጥናትና ምርምር ዩኒቨርሲቲ በሆነው (UIUC) ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ጄፍሪ ዉድስ ናቸው። ተመራማሪው የስፖርትና ጤና ሳይንስ ከሆነ ጆርናል ጋር ባደረጉት ቆይታ እአአ በ2000 ያደረጉትን ጥናት ዋቢ በማድረግ አካላዊ እንቅስቃሴ በሽታ የመከላከል አቅምን እንደሚያሳድግ በእንስሳት ላይ ማረጋገጣቸውን ያስረዳሉ። በኮሮና ቫይረስ ላይ እስከአሁን የተረጋገጠ ጥናት ባለመኖሩና አዲስ እንደመሆኑ እርግጥ የሆነ ነገር መናገር ባይቻልም፤ አካላዊ እንቅስቃሴን በጥንቃቄና የጤና ባለሙያዎች የሚመክሯቸውን የመከላከያ መንገዶች እየተገበሩ መሥራት ግን እጅግ ጠቃሚ መሆኑንም ያስገነዝባሉ። በቨርጂኒያ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ቤት ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ዢን ያን በበኩላቸው የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማድረግ በሳንባ ውስጥ የሚከሰቱ ህመሞችን አስቀድሞ መከላከልና መቀነስ እንደሚያስችል በጥናት መረጋገጡን ያስረዳሉ። እያንዳንዷ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የበሽታ መከላከል አቅምን በማሳደግ በኮሮና ቫይረስ መጠቃትን ለመቀነስ የሚችልበት ሚና እንዳለው በቁጥራዊ መረጃ አስደግፈው ለኒውሮ ሳይንስ ድረገጽ ገልጸዋል። ስፖርት ከበሽታ የመከላከል አቅምን ከመፍጠሩ ጎን ለጎን ‹‹በቤት ቆዩ›› ለሚለው መመሪያም ደጋፊ ሊሆን የሚችል ቁልፍ ጉዳይ ነው። ይኸውም አብዛኛው ሰው ከቤቱ ሳይወጣ እንዲሁም ከአካባቢው ሳይርቅ እንዲቆይ የሚያደርገው የእንቅስቃሴ ገደብ ስነ-ልቦናዊና አካላዊ ተጽእኖ ማድረሱ አይቀሬ ነው። ታዲያ በዚህ ሁኔታ አካላዊ ክብደት ከመጨመር ባሻገር ጭንቀትን ተከትሎ የሚከሰቱና ድምፅ አልባ ለሆኑ በሽታዎች አጋላጭ ነው። በመሆኑም ስፖርተኞች ብቻም ሳይሆኑ ማንኛውም ሰው በቤቱም ሆነ ባለበት ስፍራ በተቻለው አቅም ሰውነትን ማንቀሳቀስና ማፍታታት አስፈላጊ ነው። በመሆኑም በሌሎች ዓለማት ባለሙያዎችና ተቋማት በስፋት በቤት ውስጥ መሠራት የሚችሉ የእንቅስቃሴ ዓይነቶችን ያፈራሉ። ዘርፈ ብዙ የሆነውን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጠቀሜታ ከግንዛቤ ያስገቡ አካላት በኢትዮጵያም እየሠሩ ይገኛሉ። በእርግጥ እንቅስቃሴው በጅማሬ ላይ ያለ ቢሆንም፤ አበረታች ነገር ግን ስፖርታዊ ማህበራትና ሌሎች አካላትን ጨምሮ የበርካቶች ኃላፊነት እንደመሆኑ ሁሉም የበኩሉን ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ ጠቋሚ ነው። በህዝባዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ረገድ ፈርቀዳጅ በመሆን የሚጠቀሰው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን በዚህ ወቅትም አበተታች ሥራ እያከናወነ ነው። ኮሚሽኑ በተለይ በጋራ መኖሪያ አካባቢ በመገኘት በባለሙያዎቹ አማካኝነት አካላዊ እንቅስቃሴ አካሂዷል። ነዋሪውም በእንቅስቃሴው ተካፋይ ከመሆኑ ባለፈ በቀጣይም በምን መልኩ ከቤቱ ሳይወጣ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ ግንዛቤ ያገኘበት ነው። ሌላው ኢትዮጵያን ለዘመናት እያስጠራ ከዚህ የደረሰው የአትሌቲክስ ስፖርት ነው። ፌዴሬሽኑ በሃገሪቷ ከፍተኛ ሽፋን ባላቸውና ተደራሽም በሆኑ የመገናኛ ብዙሃን ታግዞ በሺዎች ለሚቆጠሩ አትሌቶቹ በቤት ውስጥ ምን ማከናወን እንደሚገባ እያስገነዘበ ይገኛል። ይህም ጠቃሚ መልዕክቶችንና ሳይንሳዊ ትንታኔዎችን ያቀፈ በመሆኑ ከአትሌቶች ባሻገር ህዝቡም ጠቃሚ መረጃ ሊያገኝበት ያስችላል። በአፍሪካ ቀዳሚና በዓለምም ስመ ጥር ከሆኑ የጎዳና ላይ ሩጫዎች መካከል ተጠቃሽ የሆነው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያም በተመሳሳይ በዚህ ወቅትም ህዝቡ ከስፖርት መራቅ እንደሌለበት ትምህርት በመስጠት ላይ ይገኛል። ተቋሙ በዩቲዩብ ገጹ መርሐ ግብሮችን በማዘጋጀት ለግማሽ ሰዓት የሚቆይ እንቅስቃሴ በምን መልኩ እንደሚካሄድ በባለሙያዎች እያሳየ ይገኛል። ይህ ይበል የሚያሰኝ ሥራም ከስፖርታዊ አካላት ባለፈ ሁሉም ተሳታፊ ሊሆንበት የሚገባ መሆኑን በማስገንዘብ በኩልም ዘርፈ ብዙ ሥራዎች መከናወን ይኖርባቸዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 14/2012ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=30882
[ { "passage": "በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር በሚኖር ቅርብ ግንኙነት እና ንክኪ እንዲሁም ታማሚው በሚስልበት ወቅት በአየር ላይ በሚለቀቁ ጠብታዎች (droplets) አማካኝነት የሚተላለፈውን ቫይረስ ስርጭት ለመቆጣጠር የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም ወደተለያዩ ሃገራት እንዳይዛመት ለመከላከል አልተቻለም። በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥም ኢትዮጵያን ጨምሮ 133 ሃገራትን ሲያዳርስ ከ138,000 በላይ ሰዎችን አጥቅቶ ለ5000 ሰዎች ህይወት ማለፍ ምክንያት ሆኗል። የዓለም የጤና ድርጅት በመጀመሪያ በዓለምአቀፍ የጤና ስጋት ደረጃ ያስቀመጠው በሽታም ወደ ዓለምአቀፍ ወረርሺኝነት (Pandemic) ተቀይሯል።ከዓለማችን ህዝብ ከግማሹ በላይ የሚከታተለው እግርኳስም እንደማንኛውም የህይወት ክፍል የዚህ ወረርሺኝ ተፅዕኖ እንዲያርፍበት ሆኗል። በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች በየስታዲየሙ እየተገኙ የሚከታተሏቸው ጨዋታዎችም ለቫይረሱ ስርጭት የተመቸ ሁኔታን ሊፈጥሩ የሚችሉ እንደመሆናቸው የየሃገራቱ የጤና ጥበቃ ተቋማትና ውሳኔ ሰጪ ሰዎችን ትኩረት መሳባቸው አልቀረም። ወረርሺኙ ከተነሳባት ቻይና ጀምሮ የተለያዩ ሃገራት ክለቦች፣ ሊጎች፣ የእግርኳስ ማህበሮች፣ ብሎም እስከ ዓለምአቀፉ የእግርኳስ ማህበር ፊፋ ድረስ ከጤና ተቋማቱ ጋር በመተባበር ስርጭቱን ለመከላከል እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ።የቫይረሱ መነሻ የሆነችው ቻይና በየካቲት ወር ጀምሮ ታህሳስ ላይ የሚጠናቀቀውን የቻይና ሱፐርሊግ የሚጀመርበትን ቀን ላልተወሰነ ጊዜ አራዝማለች። ሃገሪቱ የቫይረሱን ስርጭትና የአዳዲስ ተጠቂዎችን ቁጥር በተወሰነ መልኩ ለመቆጣጠር ብትችልም ውድድሩ ግን እስካሁን ድረስ አልተጀመረም። ከእግርኳስ ሊጉ በተጨማሪም በቻይና ሊደረጉ የታሰቡ የእስያ ቻምፒዮንስ ሊግ፣ የሴቶች እግርኳስ የኦሎምፒክ ማጣሪያ፣ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ የፒጂኤ የጎልፍ ውድድር፣ የፌድካፕ የቴኒስ ውድድር፣ የቻይና ግራንድ ፕሪ የሞተርስፖርት ውድድር እና የተለያዩ የቶክዮ ኦሎምፒክ የማጣርያ ውድድሮችን ጨምሮ በርካታ ስፖርታዊ ኩነቶች ተሰርዘዋል፣ ተሸጋግረዋል፣ ወይንም ወደ ሌላ አዘጋጅ ሃገር ተቀይረዋል። ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታም ባለፉት ሶስት ወራት ህዝብ የሚሰበሰብባቸው ስፖርታዊ ውድድሮች በቻይና እንዳይከናወኑ ተደርጓል።የእግርኳስ ደረጃቸው ከፍተኛ የሆኑ ሃገራት በሚገኙባት አውሮፓም የእግርኳሱ ባለድርሻ አካላት የቫይረሱን ስርጭት በመከላከል እና የእግርኳስ ካሌንደሩን ለመጠበቅ፣ ውድድሮች የሚያመነጩት ገቢም እንዳይነጥፍ በማድረግ ተፃራሪ ምርጫዎች ውስጥ የተለያዩ ውሳኔዎችን ሲያሳልፉ ቆይተዋል። የአውሮፓ እግርኳስ ማህበርም የቻምፒዮንስ ሊግ እና ዩሮፓ ሊግ ውድድሮች የሚጠናቀቁበትን ሂደት እና የ2020 የአውሮፓ ዋንጫ ዕጣፈንታን ለመወሰን አባል ሃገራቱን በመሰብሰብ በመወያየት ላይ ይገኛል። የአውሮፓ ዋንጫን ከማራዘም፣ የውድድሩን አዘገጃጀት እና ቅርፅ መቀየር፣ አልፎም የቻምፒዮንስ እና ዩሮፓ ሊግ ውድድሮችን እስከመሠረዝ ድረስ ያሉ እርምጃዎችም ሊወሰዱ እንደሚችሉ ይጠበቃል።ከአውሮፓ ሃገራት ውስጥ በወረርሺኙ ክፉኛ የተጠቃችው ጣሊያን የእግርኳስ ውድድሮቿ በዝግ ስታዲየም እንዲደረጉ የወሰነችው ቀደም ብላ ነበር። ከጣሊያን በመቀጠልም ፈረንሳይ ከ1000 ሰዎች በላይ የሚገኙባቸው ስፖርታዊ ኩነቶች በዝግ እንዲሆኑ ስታደርግ ስፔን፣ ቤልጂየም፣ ጀርመን እና ሌሎች ሃገራትም ይህንኑ ለመተግበር ወስነዋል። የእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር እና ፕሪምየር ሊጉ ግን ውድድሮችን እንደቀድሞው ለማስኬድ በመወሰን መርሃግብሮችን ሲያስቀጥሉ ተስተውሏል። በነዚህ ሃገራት ክለቦች የሚጫወቱ ተጫዋቾች፣ አሠልጣኞች እና የክለብ አመራሮች በቫይረሱ መያዝ፣ የበርካታ ክለቦች አባላትም በከፊልም ሆነ በሙሉ በመለያ ክፍሎች (Isolation Rooms) እና በቤት ውስጥ ራስን በመለየት (Self Isolation) ላይ መሆናቸው ግን ሃገራቱ ሊጎቻቸውን በጊዜያዊነት ቢያንስ እስከ ሚያዝያ ወር ድረስ እንዲያቋርጡ አስገድዷቸዋል።የሃኖቨር 96ቱ ተከላካይ ቲሞ ሁበርስ፣ የቼልሲው አማካይ ካለም ሃድሰን-ኦዶይ፣ የሳምፕዶሪያው አጥቂ ማኖሎ ጋቢያዲኒ፣ የጁቬንቱሱ ዳኔሌ ሩጋኒ፣ የአርሰናሉ አሠልጣኝ ሚኬል አርቴታ፣ የኦሊምፒያኮስ እና ኖቲንግሃም ፎረስት ክለቦች ባለቤት ኢቫንጀሎስ ማሪናኪስ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው በምርመራ ከተረጋገጡ የእግርኳስ ሰዎች ውስጥ ይጠቀሳሉ።በሃገረ አሜሪካ የእግርኳስ ውድድሩ ሜጀር ሊግ ሶከር ለአንድ ወር ያህል እንዲቆም ሲደረግ ከቅርጫት ኳስ እና አሜሪካን ፉትቦል ጀምሮ የቴኒስ እና የጎልፍ ውድድሮች፣ የቦክስ ግጥሚያዎች፣ የሞተር ሬሲንግ፣ ቤዝቦል፣ የፈረስ ውድድር፣ የኮሌጅ ፉትቦል እና ሌሎች በርካታ ስፖርታዊ ውድድሮች፤ ከዚህም አልፎ እንደ WWE ሬሲሊንግ ያሉ ስፖርታዊ የመዝናኛ ዝግጅቶች በከፊል እንዲቆሙ ሆኗል።ዓለምአቀፍ ስፖርታዊ ዝግጅቶችን ስንመለከት ደግሞ የ2020ው የቶክዮ ኦሊምሊክ እስካሁን 701 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች እና 10 ከበሽታው ጋር የተያያዙ ሞቶች በተመዘገቡባት ጃፓን እንደመካሄዱ በርካታ አካላት ስጋታቸውን እየገለፁ ቢሆንም ዓለምአቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ግን ውድድሩን ቀድሞ በተቀመጠው መርሃግብር ለማድረግ እንደተዘጋጀ ገልጿል። ኮሚቴው በመግለጫው ብሏል።በአውሮፓ የሚገኙ ክለቦች ባለፉት ሳምንታት በደጋፊ ፊትም ሆነ በዝግ ስታዲየም ውድድሮችን እያከናወኑ ሲቆዩ የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ይከላከላል ብለው ያሰቧቸውን ልምዶች ሲተገብሩ ቆይተዋል። አብዛኛዎቹ ክለቦች ተጫዋቾቻቸው ከደጋፊዎች ጋር ፎቶ ለመነሳትም ሆነ ፊርማቸውን ማኖር እንዳይገናኙ የከለከሉ ሲሆን በርካታዎቹም ከእግርኳሳዊ ኩነቶች (ልምምዶች እና ጨዋታዎች) ውጪ ሌሎች የቡድኑ አባላትን ከህብረተሰቡ ጋር የሚያገናኙ ዝግጅቶችን እና የስታዲየም ጉብኝቶችን አግደዋል፤ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ሰራተኞች ውጪ ሌሎች ሰዎች በስታዲየሞች እና የልምምድ እና ቴክኒካል ስፍራዎች ላይ እንዳይገኙም አድርገዋል። እንደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ያሉ ውድድሮች ደግሞ ከጨዋታ በፊት የሚደረገውን የተቃራኒ ቡድን ተጫዋቾች እጅ መጨባበጥ የከለከለ ሲሆን ተጫዋቾችን አጅበው ወደ ሜዳ የሚገቡ ህፃናቶች ልምድም ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆም ሆኗል። ክለቦችም የሊጉን መሪነት በመከተል በልምምድ ሜዳዎች እና በክለብ ቢሮዎች ዙሪያ እጅ መጨባበጥ እንዳይኖር አድርገዋል።ስለ ኮቪድ-2019 ወረርሽኝ መረጃ የሚሰጡ ፖስተሮችን በስታዲየም በመለጠፍ፣ በስታዲየም ስክሪኖች ላይም ትምህርታዊ የሆኑ ምስሎች እንዲተላለፉ በማድረግ ተመልካቾች ስለ በሽታው እንዲያውቁ እና ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጥረት ያደረጉ ክለቦችም ነበሩ። በስታዲየም እና የልምምድ ስፍራዎች የፀረ-ቫይረስ እና ፀረ-ባክቴሪያ ኬሚካል ርጭት ማከናወን እና የእጅ ማጠብያ አልኮሎችን በእነዚህ ቦታዎች በማስቀመጥ ህብረተሰቡ እንዲጠቀም ማድረግ በሽታውን ለመከላከል በክለቦች የተወሰዱ እርምጃዎች ነበሩ። ክለቦቹ ማንም ደጋፊ እንደ ሳል፣ ትኩሳት፣ የጉሮሮ ህመም እና ትንፋሽ ማጠር አይነት ምልክቶችን የሚያሳይ ከሆነ ጨዋታዎችን ለመመልከት ወደ ስታዲየሞች እንዳይመጣ ሲማፀኑም ተስተውሏል።የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ከ70 ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸው ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም እንዳይመጡ ለማገድ እንቅስቃሴ እያደረገም እንደነበር ተሰምቷል። ይህም የሆነው እነዚህ አረጋውያን በበሽታው የመያዝ እና ከተያዙም በኋላ ወደ ከፍተኛ ህመም፣ አልፎም እስከ ሞት የመድረሳቸው ዕድል ከሌላው የህብረተሰብ ክፍል አንፃር ከፍተኛ በመሆኑ ነው። በእንግሊዝ በተለይም ለአርሴናሉ አሠልጣኝ ሚኬል አርቴታ ለቫይረሱ መጋለጥ ተጠያቂ ነው የተባሉትን ከጨዋታ በፊት እና በኋላ የሚደረጉ ፕሬስ ኮንፈረንሶችንም ላልተወሰነ ጊዜ ለማቆም በዕቅድ ደረጃ ተይዟል።የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት በሃገራችን የመጀመሪያውን በላብራቶሪ የተረጋገጠ የኮቪድ-2019 ተጠቂ ይፋ አድርጓል። ይህ ታካሚው ከሳምንት በፊት ከቡርኪና ፋሶ ወደ ሃገራችን የገባ የ48 ዓመት ጃፓናዊ ዜጋ እንደሆነ እና በለይቶ ማከሚያ ማዕከልም በህክምና እየተረዳ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ ጨምሮ አስታውቋል።በሃገራችን የሚኖረው ትክክለኛ የቫይረሱ የስርጭት መጠን ምናልባትም በቀጣይ ሳምንታት ግልፅ እየሆነ የሚመጣ ይሆናል። የበሽታው ስርጭት ከፍተኛ ስጋት ላይ የሚጥል ከሆነም ህብረተሰቡን ከህመሙ ለመጠበቅ ሲባል በርካታ እርምጃዎች ሊወሰዱ ይችላሉ። በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ደጋፊ በሜዳ ተገኝቶ ይከታተላቸዋል ከሚባሉ ውድድሮች የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግም ሆነ በዝቅተኛ እርከን ላይ የሚገኙት ሊጎቻችን የእነዚህ እርምጃዎች አንድ አካል ሊሆኑ የሚችሉበት ዕድል ሰፊ ነው። ከላይ የገለፅናቸው የዓለማችን ክለቦች፣ ሊጎች እና የእግርኳስ ማህበራት በሽታውን ለመከላከል የወሰዷቸው እርምጃዎች በአመዛኙ በሃገራችን ተግባራዊ ለመሆን ቢችሉም ከነባራዊ ሁኔታችን አንፃር ከአቅም በላይ የሚሆኑ እንደሚኖሩም ግልፅ ነው።በቂ መፀዳጃ ቤት እና እጅ መታጠቢያ እና ንፁህ የአየር ዝውውር እንኳን የሌላቸው የሃገራችን ስታዲየሞች ዋነኛ የቫይረሱ ስርጭት ማዕከሎች እንዳይሆኑ ቅድመ-ጥንቃቄዎችን ማድረግ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በቂ የጤና መሰረተ ልማት እና ጠንካራ የፋይናንስ ክንድ ያላቸውን ሃገራት ተሞክሮ ከሃገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብም ጨዋታዎችን በዝግ ስታዲየም ከማድረግ አንስቶ እግርኳሳዊ ውድድሮችን እስከማቋረጥ ድረስ የተለያዩ አስፈላጊ እርምጃዎችን የምንወስድባቸው የራሳችን ልኬቶች (thresholds) ያስፈልጉናል። ክለቦች፣ አዲሱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የጋራ ኩባንያ እና ፌዴሬሽኑም ከጤና ተቋማቶቻችን ጋር በመወያየት ሊከሰት ለሚችል ማንኛውም የጤና ስጋት ተገቢውን ውሳኔ እንዲያስተላልፉበት የሚረዳቸውን ቅድመ-ዝግጅት ቢያደርጉ እንመክራለን።", "passage_id": "b5f26c995b47fd1ffa0bea6b1a65cd43" }, { "passage": "የወቅቱ የዓለም ራስ ምታት በሆነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች አንቀላፍተው ቢቆዩም ከሰሞኑ የአውሮፓ ሊጎች ወደ ልምምድ መመለስን ተከትሎ የስፖርቱ ኢንዱስትሪ መነቃቃት ጀምሯል። አሁንም የኮሮና ወረርሽኝ (ኮቪድ 19) ስጋት እንዳለ ቢሆንም ጥንቃቄን በተላበሰ መልኩ ወደ ቀድሞው መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ ጥረቶች እየታዩ ነው። በዚሁ ምክንያት ተቀዛቅዞ የቆየው አበረታች ቅመሞችን መከላከልና የመቆጣጠር ሥራ ነው። ይህ ስፖርትን በተፈጥሯዊው መንገድ ብቻ እንዲካሄድ የማድረግ ጥረት ሊቀዛቀዝ የቻለው በዓለም አቀፍ ደረጃ ውድድሮች መቋረጣቸውን ተከትሎ ነው። ይሁን እንጂ ከዓላማው አንጻር ረጅም ጊዜ መውሰዱና መዘናጋቱ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል። \nበመሆኑም ዓለም አቀፉ የጸረ አበረታች ቅመሞች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በስሩ ለሚገኙት ብሔራዊ ጽሕፈት ቤቶች መመሪያ ማዘጋጀቱን ከሰሞኑ በድረገጹ አስነብቧል። ይህም በየሀገራቱ የሚገኙ የጸረ አበረታች ቅመሞች ተቆጣጣሪ ጽሕፈት ቤቶች ወደ ቀደመ ሥራቸው እንዲመለሱ የሚያስችል ርምጃ ነው። ኤጀንሲው በወረርሽኙ ምክንያት በዓለም ዙሪያ ሲሰሩ የቆዩት ናሙና የመውሰድና ምርመራ የማድረግ ሂደቶችን የቀነሰና አንዳንድ ሥራዎችንም በጊዜያዊነት ማቋረጡን በዘገባው ተጠቁሟል። ነገር ግን አሁን ወደ ሥራ ለመመለስ እንቅስቃሴ መደረግ እንዳለበት የኤጀንሲው ፕሬዚዳንት ዊቶልድ ባንካ ይገልጻሉ። በኤጀንሲው ስር ካሉ ተቋማት ጋር ከወቅታዊው ጉዳይ ጋር በተያያዘ በቅርበት ሲሰሩና ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል። አሁን ግን ሥራው እንደቀድሞው መቀጠል ያለበት በመሆኑ፤ በቴክኖሎጂ በታገዘና የናሙና አወሳሰዱን በአዲስ መንገድ ማካሄድ ተገቢ መሆኑን ያመላክታሉ። ለዚህ ደግሞ በጸረ አበረታች መድኃኒት ቁጥጥር ላይ የሚሰሩ አካላት አዲስ ነገር ለመፍጠር ርብርብ ላይ ይገኛሉ። \nየተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ኦሊቨር ኒግሊ በበኩላቸው፣ በዚህ ወቅት ናሙናዎችን ከአትሌቶች ለመውሰድ አዳጋች መሆኑን ነው የሚጠቁሙት። ምርመራው መቀጠል የሚገባው አስፈላጊው የጤናና ንጽህና ሁኔታ የተስተካከለ ሲሆን ብቻ ነው። የአትሌቶችና በዙሪያቸው ያሉ አካላት ጤናም ኤጀንሲው ትኩረት የሚሰጠው ቀዳሚ ጉዳይ ነው። ተቋሙ የአትሌቶችን ናሙና በመውሰድ አበረታች መድኃኒት ተጠቃሚነታቸውን በምርመራ መለየት ብቻም ሳይሆን የጤና ግለ ታሪካቸውንም መመዝገብ ሌላው ተግባሩ ነው። ንጹህ ስፖርት ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ግንዛቤ ማስጨበጥም እንዲሁ። በመሆኑም በቀጣይ ሳምንታት ከብሔራዊ ተቋማቱ ጋር በመሆን ሥራው በምን መልኩ መቀጠል ይገባዋል በሚለው ላይ መፍትሄ በማፈላለግ ወደ ሥራ የሚመለስ እንደሆነ አብራርተዋል።\nየሯጮቹ ሀገር ኢትዮጵያም የኤጀንሲው አባል ሀገር በመሆን ንጹህ ስፖርት እንዲካሄድ ሚናቸውን ከሚወጡት መካከል ትጠቀሳለች። ተሞክሮውን ለሌላው ዓለምም ማጋራት የቻለና በሥራው ምስጉን የሆነ ጽሕፈት ቤትም በአጭር ጊዜ ለማቋቋም መቻሉ ይታወቃል። በመላው ዓለም ባጠላው በዚህ የወረርሽኝ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጸረ አበረታች ቅመሞች ተቆጣጣሪ ጽሕፈት ቤት እንቅስቃሴውን በምን መልኩ እያከናወነ ይገኛል? የሚለውን የጽሕፈት ቤቱ ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል ያስረዳሉ። የተቋሙን ውስጣዊና ውጫዊ እንቅስቃሴ በሁለት የሚከፍሉት ዳይሬክተሩ፤ የኮሮናን ቫይረስ በመከላከል ረገድ ሠራተኞችን የመቀነስና የንጽህና ቁሳቁስን የማዘጋጀት ሥራዎች መከናወናቸውን ይጠቁማሉ። \nሁለተኛውና ከተቋሙ ውጪ ከአትሌቶች ጋር በመገናኘት የሚከናወነው ደግሞ ከአበረታች መድኃኒት ቁጥጥር ጋር የተያያዘው ሥራ ነው። ይሁን እንጂ ከአትሌቶች ናሙና መውሰድ በእጅጉ ለንክኪ የሚያጋልጥ በመሆኑ አትሌቶችንም ሆነ በምርመራው ተሳታፊ የሆኑ ባለሙያዎችን ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆኑ በማሰብ ለጊዜው ገታ ተደርጓል። \nነገር ግን ሥራውን ሙሉ ለሙሉ ማቆም የማይቻል በመሆኑ ለቫይረሱ አጋላጭ ይሆናሉ የሚል ስጋት ያሳደሩ ሥራዎችን ፎርማት ለመቀየር መሞከሩን ዳይሬክተሩ ይገልጻሉ። በዚህም መሠረት አበረታች ንጥረ ነገር ተጠቃሚ የሆኑ አትሌቶችን የማጋለጥ፣ አትሌቶች ባዮሎጂካል ፓስፖርት ፕሮግራም ሥራን የማጠናከር እንዲሁም ሌሎች ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህ ጊዜ ውድድሮች የተቋረጡ ቢሆንም ስፖርተኞች ግን በየግላቸው በቤታቸው ውስጥ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን አላቆሙም። ይህንን ተከትሎም ከውድድር ውጪ የሚወሰዱ አበረታች ንጥረ ነገሮችን ከመውሰድ እንዲቆጠቡም ያሳስባሉ። በጥቅሉ በጊዜያዊነት ንክኪ ካለባቸው ሥራዎች በቀር ሌሎች ሥራዎች እንደቀጠሉ ሲሆን፤ የአድራሻ ምዝገባቸውን በመደበኛ መልኩ የሚያደርጉ በመሆኑ በዚህ ላይም መዘናጋት አይገባም።\nዓለም አቀፉ የጸረ አበረታች መድኃኒቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በመግለጫው ባመላከተው መሠረት፤ ጽሕፈት ቤቱም እንደቀደመው የአትሌቶችን ናሙና ወደመውሰድና መመርመር ሥራው ለመመለስ የሚያስችለውን ሁኔታ እያጠና ይገኛል። እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ከሆነም ስፖርተኞች ከባለሙያዎች ጋር የሚኖራቸውን ንክኪ በሚቀንስና ለበሽታው አጋላጭ በማይሆን መልኩ መፍትሄ እንደተገኘ በቀጥታ ምርመራው የሚጀመር ይሆናል። በብሔራዊ ቡድን፣ በክለብ እና በማሰልጠኛ ተቋማት የተያዙ አትሌቶች እንዲሁም በቡድን ሆነው የሚሰሩ ሰልጣኞች በዚህ ወቅት ልምምድ አቋርጠው በቤታቸው ይገኛሉ። ምንም ዓይነት የቡድን እንቅስቃሴ የማይፈቀድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አትሌቶች በያሉበት አነስተኛ ልምምድ ብቻ የሚያደርጉ ይሁን እንጂ አሁንም እንደ ተቋም አስጊ ሁኔታዎች መኖራቸው አልቀረም። \nይህም ወቅታዊውን ሁኔታ ሽፋን በማድረግ የተከለከሉ ንጥረነገሮችን የመጠቀም አዝማሚያ ሊኖር ይችላል የሚል ስጋት ነው። እስካሁን በተጨባጭ የተገኘ መረጃ ባይኖርም በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ እንደ ተቋም ስጋቱ አለ። ከአትሌቶች ባሻገር ከጀርባ በመሆን አጋላጭ የሆኑ አካላት አበረታች ቅመሞችን እንዲጠቀሙ በመገፋፋትና በማሳመን የሕግ ጥሰት የመፈጸም አዝማሚያ ሊኖር ይችላል የሚል ግምት አለ። በመሆኑም ስጋቱን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ሥራዎች በመከናወን ላይ ነው የሚገኙት። \nበስፖርተኞች በኩል ስለ ጉዳዩ ያለውን ግንዛቤ ለማስፋትም በመገናኛ ብዙኃን በመታገዝ መልዕክቶች በመተላለፍ ላይ ይገኛሉ። በተመረጡ መገናኛ ብዙኃን ላይም የማስታወቂያ እንዲሁም የማንቂያ ሥራዎች እየተካሄዱ መሆኑን የሚጠቁሙት ዳይሬክተሩ በጽሕፈት ቤቱ ድረገጽም መረጃዎችን እያስተላለፉ ይገኛል። ይህም አትሌቱ በሚመቸው መንገድ መረጃ እንዲያገኝ ያስችለዋል። በቀጣይም በመደበኛነት ማስታወቂያዎቹ የሚተላለፉባቸውን የመገናኛ ብዙኃን ቁጥር ለመጨመር ታቅዷል። ሌላው ጽሕፈት ቤቱ በትኩረት እየሄደበት ያለው የሕግ ማዕቀፍ የማሻሻል ሥራ ነው። ኤጀንሲው የጸረ አበረታች ቅመሞች ሕግን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ ስታንዳርዶችን አሻሽሏል፤ በመሆኑም በጽሕፈት ቤቱ በኩል እአአ በ2021 ተግባራዊ የሚሆኑ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎችን ለመከለስ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። \nበመጨረሻም ዳይሬክተሩ ስፖርተኞችም ሆኑ ሌሎች የሀገሪቷ ዜጎች የሕክምና ባለሙያዎችን ምክር በመተግበር በዓለም ላይ ከተከሰተው ወረርሽኝ ራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ስፖርተኞች፣ የስፖርት ባለሙያዎች፣ የስፖርት አመራሮች እንዲሁም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በበኩላቸው በአበረታች ንጥረ ነገር መከላከልና መቆጣጠር ሥራው ለአፍታ የቆመ ባለመሆኑ መዘናጋት እንዳይኖር ዳይሬክተሩ ያሳስባሉ። ዓለም አቀፉ ኤጀንሲም ሆነ የዓለም አትሌቲክስ ይህ ጊዜ ሲያልፍ ስፖርቱ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በጥንቃቄ እየተመለከቱት ነው። በዚህ መሠረት የሚመለከታቸው አካላት ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። ተጠቃሚነታቸው ከተረጋገጠም ጽሕፈት ቤቱ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እንዲሁም የወንጀል እርምጃ ከመውሰድ ወደኋላ የማይል በመሆኑ ስፖርተኛው በመደበኛ ጥንቃቄው መቀጠል እንዳለበት ዳይሬክተሩ አስቀምጠዋል።አዲስ ዘመን ግንቦት 10/2012ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "01f73fe2dd71eb57e86861f0d6e6addf" }, { "passage": "በአትሌቲክስ ስፖርት ዝና እና ክብሯን የገነባችው ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችንም አግኝታበታለች። ስፖርቱ አንድ የስራ ዘርፍ በመሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት አትሌቶችን ያቅፋል። አትሌቶችም በዓለም አቀፍ ውድድሮች ሲሳተፉ ከውጤት ባሻገር የውጭ ምንዛሪን በማስገኘት የሀገሪቷን ኢኮኖሚ ያግዛሉ። በሚያፈሱት መዋዕለ ነዋይም ለበርካቶች የስራ እድል ፈጥረዋል። \nእንደሚታወቀው በዚህ ወቅት ይህ ዘርፍ እንደሌሎች ስፖርቶች ሁሉ ለውድድር ዝግ ሆኗል። ማልዶ ለልምምድ ይወጣ የነበረውና በዓመት ውስጥ ተደጋጋሚ ውድድሮች ላይ ተሳታፊ የነበረው እረፍት የለሽ አትሌትም ከተላላፊው ቫይረስ ጋር ተያይዞ ከቤት ውሏል። በብሄራዊ ቡድን የተያዙ፣ በተለያዩ ክለቦች የተካተቱ እንዲሁም የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ተቋማት ሰልጣኝ የሆኑ አትሌቶችም እንዲበተኑ ተደርጓል። በግላቸው የሚሰለጥኑትም ቢሆን እንደ ቀድሞው ከመኖሪያቸው ርቀው የማይጓዙበት ሁኔታ ተጋርጦባቸዋል። \nለአንድ ዓመት የተራዘመውን ኦሊምፒክ ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ ቻምፒዮናዎች ላይ ተሳታፊ ለመሆን በብሄራዊ ቡድን የተካተቱ አትሌቶች ደግሞ ከሌሎች በተለየ ሁለት አማራጮችን ያስተናግዳሉ። \nየመጀመሪያው ለተላላፊው የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ላለመሆን በሚደረገው የቤት ውስጥ ቆይታ ከልምምድ በመራቃቸው የአቋም መውረድን ማስተናገድ ነው። ሌላኛው ደግሞ የውድድሮችን መራዘም እንደ መልካም እድል በመጠቀም በተደጋጋሚ ውድድር ላይ ያሳለፉ አትሌቶች እንደ ማገገሚያ ጊዜ በመመልከት በተሻለ ብቃት ለመመለስ የራሳቸውን ጥረት ማድረግ ነው። \nበእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ስፖርተኞች ከስፖርቱ ላለመራቅ ምን ማድረግ አለባቸው፣ ፌዴሬሽኑስ ሚናውን በምን መልኩ እየተወጣ ነው ለሚለው በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቲክስ ህክምና ከፍተኛ ባለሙያና እና የጸረ አበረታች ቅመሞች ተጠሪዋ ቅድስት ታደሰ ከአዲስ ዘመን ጋር ቆይታ አድርገዋል። \nየመጀመሪያው ነገር ስነ-ልቦና መሆኑን ባለሙያዋ ይገልጻሉ።በዓለምና በሃገር በመጣው በዚህ ቫይረስ ምክንያት በቤታቸው እስኪቆዩ ድረስ ኦሊምፒክን ጨምሮ ለዚህ የውድድር ወቅት በዝግጅት ላይ የነበሩ አትሌቶች በጥሩ አቋም ላይ ነበሩ። በዚህም ምክንያት አቋማቸው እንዳይወርድና ጂምናዚየሞችም በመዘጋታቸው በቤት ውስጥ የተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ይገደዳሉ። ከትንፋሽ ጋር በተያያዘ ያለውን ደግሞ የሰዎች ንክኪ በሌለበት በግላቸው ጫካ አካባቢ መስራት ይችላሉ። ይህም ወቅታዊ ብቃታቸው እንዳይወርድ እንጂ ለውድድር በሚደረግ ልክ አይሆንም። \nይህ እንዲሆን ደግሞ አስቀድሞ እንደተገለጸው ዋናው ነገር በመልካም ስነ-ልቦና ላይ መገኘት መሆኑን ይጠቁማሉ። በማብራሪያቸውም ‹‹የሰው ልጅ በተፈጥሮው በጭንቀት ወቅት ሰውነቱ በሚሰጠው ግብረመልስ የተለያዩ ቅመሞችን ስለሚያመነጭ ለውጥረትና ለመደበት ስሜት ይጋለጣል። አትሌትሌቲክስ የሙሉ ጊዜ ስራው የሆነው አትሌትም ውድድሮች ከሌሉ በእንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ውስጥ ሊገባ ይችላል። ይህ እንዳይከሰትም አትሌቶች ራሳቸውን በስነ-ልቦና ማዘጋጀት ይገባቸዋል›› ሲሉ ያስረዳሉ ባለሙያዋ። ሁኔታዎችን አእምሮ ሲቀበል ሌሎች አካላትን ማዘዝ ስለሚቻል ስነ-ልቦና የመጀመሪያውና ዋነኛው ጉዳይ ነው።\nከዚህ ባሻገር በአትሌቲክስ ስፖርት የሚፈራው ነገር ክብደት መጨመር ነው። በክብደት ተወስነው እንደሚካሄዱት የቦክስና የማርሻል አርት ስፖርቶች ሁሉ የረጅም ርቀት በአትሌቲክስም ክብደት መጨመር የራሱ አደጋ ይኖረዋል። በመሆኑም የቡድን እና ጫና ያላቸውን ልምምዶችን በማስቀረት ሰውነትን ባለበት እንዲቆይና የብቃት መዋዠቅ እንዳይከተል የሚያደርግ መሆን እንዳለበት ባለሙያዋ ያስገነዝባሉ። \nአመጋገብ ላይም አትሌቶች የራሳቸውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል፤ አመጋገብ ከሚወጣው ኃይል ጋር ተመጣጣኝ መሆን ይኖርበታል። በዚህ ወቅት ቀለል ያሉ ልምምዶችን እየሰሩ እንደ ወትሯቸው የሚመገቡ ከሆነ ግን ሰውነት ያንን ለማስተናገድ ስለሚከብደው የክብደት መጨመር ይከሰታል። በመሆኑም ይህንን መከታተልና ከቻሉ በየዕለቱ ያሉበትን ሁኔታ በመመዝገብ ማስታወሻ እንዲይዙ ይመከራል። የዓለም አትሌቲክስም በየወቅቱ የሚያወጣውን መረጃ መከታተልም አስፈላጊ ነው። \nበዚህ ሂደት ሊዘነጋ የማይገባው ዋናው ነገር በቤት ውስጥ የሚሰሩ ማሳሳቢያዎችና ሌሎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ንጹህ አየር ባለበት ስፍራ መሆኑን ማረጋገጥ ነው። \nሰው የማይበዛበትና ነፋሻማ አየር ባለበት ስፍራ ቢንቀሳቀሱ ደግሞ የተሻለ ይሆናል። እንደ ዓለም አትሌቲክስ መረጃ ከሆነ አትሌቶች በተለይም የረጅም ርቀት ሯጮች ትንፋሻቸው የዳበረ በመሆኑ ከሌላው በተለየ ተጋላጭነታቸው የሰፋ ይሆናል። \nበመሆኑም ራሳቸውን ለየት ባለመልኩ መጠበቅ ይኖርባቸዋል። ፈሳሽ በብዛት መውሰድና በሽታን ሊቋቋሙ የሚችሉ ምግቦችንም ከዚህ ቀደሙ በተሻለ ሁኔታ ማዘውተርና በዓለም የጤና ድርጅት እንዲሁም ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ከመሳሰሉ ተቋማት የሚወጡ መረጃዎችን መከታተል ለአትሌቱ ጠቃሚም ነው። ምክንያቱም አብዛኛው የማህበራዊ ትስስር ገጾችን የሚጠቀም እንደመሆኑ መረጃዎችን የሚያገኙበት መንገድ በራሱ ጎጂ ሊሆን ይችላል። \nይህንንና መሰል ግንዛቤዎችን ከማስጨበጥ አንጻር ባለሙያዎች አትሌቱን በአካል ለማግኘት አዳጋች በመሆኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተለያዩ ስራዎችን እንደጀመረም ባለሙያዋ ይጠቁማሉ። የፌዴሬሽኑ አመራሮች ባደረጉት ውይይት አትሌቱ ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ክልሎችም የሚገኝ እንደመሆኑ ሁሉንም ተደራሽ ለማድረግ በቴሌቪዥንና በሬዲዮኖች መልዕክቶችን ማስተላለፍ የተሻለ አማራጭ ሆኖ አግኝቶታል። በመሆኑም ሰፊ ሽፋን ካላቸውና ከክልል የመገናኛ ብዙሃን ጋር በመተባበር፤ አትሌቱ ልምምዱን እንዴትና በምን ሁኔታ መስራት እንዳለበት በባለሙያዎች ግንዛቤ የሚሰጥ ይሆናል። \nከዚህ ባሻገር ከወቅታዊው ሁኔታና ከቫይረሱ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን፣ ስነ- ምግብ፣ ስፖርታዊ ስነ-ልቦና፣ የስፖርት ህክምና፣ የመረጃ ክትትል ምን መምሰል አለበት የሚሉና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ነባራዊ ሁኔታውን ባገናዘበ መልኩ ለአትሌቱ እንዲደርስ ይደረጋል። በዚህ ሁሉ ሁኔታ ውስጥ ግን መዘንጋት የሌለበት ዋነኛ ጉዳይ አበረታች ቅመም መሆኑን ያሳስባሉ። \nይህንን ግንዛቤ የሚሰጡትም በስፖርቱ ላይ ለረጅም ጊዜ ያሳለፉ ባለሙያዎች እና ኦሊምፒክን ጨምሮ በተለያዩ መድረኮች ላይ ስኬታማ የሆኑ አንጋፋና ተምሳሌት አትሌቶች ሲሆኑ፤ መልእክቶችን፣ ምክሮችንና በተግባር የታገዙ እንቅስቃሴዎችንም ለአትሌቶች የሚያስተላልፉ ይሆናል። ከፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት እንዲሁም ከስልጠና ጥናትና ምርምር ክፍል ጋር በመሆንም በተለያዩ የማህበራዊ ገጾች መልእክቶችን ለማስተላለፍም በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኙ ባለሙያዋ ጨምረው ገልጸዋል።\nአዲስ ዘመን ሚያዝያ 5/ 2012 ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "1dee20ef7f798a5f4f9393c780beb163" }, { "passage": "በእግር ኳሱ የሚስተዋለው ችግር ካልታረመ ውድድርን እስከ ማቆም የደረሰ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ሚኒስቴሩ አስጠነቀቀ። በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር አዘጋጅነት ለሁለት ቀናት «የስፖርት ጨዋነት ምንጮች» በሚል መሪ ቃል ከሚያዚያ 14 እስከ 15 ቀን 2011 ዓ.ም የምክክር ጉባዔ በሸራተን ሆቴል ተካሂዷል። የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው እንደተናገሩት፤ በሀገራችን በስፖርታዊ ሁነቶች ላይ ስፖርታዊ ጨዋነት ሲጓደልና በርካታ ያልተገቡ ድርጊቶች ሲፈጸሙ እየተስተዋለ ይገኛል። በተለይ በእግር ኳሱ ከደጋፊዎች ጋር ተያይዞ የሚስተዋለው መስመር የለቀቀ ባህርይ እየተስተዋለ ነው፡፡ ችግሩ ካልታረመ ውድድርን እስከ ማቆም የደረሰ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል። እንደ ዶክተር ሂሩት ገለጻ ፤ ስፖርት ለሰላም መሆኑ\nቀርቶ ውድድሮች ዘርንና ማንነት መሰረት ባደረገ መልኩ የግጭት ምንጭ እየሆኑ ይገኛሉ። ስፖርት አለ በተባለ ቁጥር ሰው መረበሽ የለበትም። ህዝቡ ተረጋግቶ መኖር መቻል አለበት። ህብረተሰቡ ጨዋታ አለ በተባለ ቁጥር ለከፋ ስነ ልቦና ረብሻ መዳረግ የለበትም፤ አይገባውምም። ስለዚህ በእግር ኳሱ የሚታየው ስፖርታዊ ጨዋነት ችግር እስከሚስተካከል ውድድሩን እስከማቆም የሚደርስ እርምጃ ሊወሰድ የሚችል ይሆናል። ስፖርት ለወንድማማችነት የሚለው ብሂል ተረስቶ፤ በስፖርት ሁነቶች ላይ አጀንዳዎች እየተፈጠሩ እርስ በእርስ ወደ መጠቃቃት የመግባት ሁኔታዎች በስፋት እንደሚስተዋሉ አመልክተዋል። በስፖርት ማህበረሰቡ መካከል መጠራጠርና ጥላቻን ከመዝራት ባሻገር ኢትዮጵያዊ ባህልን፣ እኛነታችንን የሚያዋርድና የስፖርቱን እድገት የሚያቀጭጭ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህ ረገድ ክለቦችና ደጋፊ ማህበራት ሰፊ ስራ መስራት አለባቸው። በተለይ ክለቦችና የደጋፊ ማህበራትን የሚመሩ አካላት ለሚመሩት ወገን አርዐያ ሆነው መገኘት እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል።«ጨዋ ተጫዋች ከጨዋ አሰልጣኝ ይፈጠራል፤ ጨዋ ደጋፊ ከጨዋ የደጋፊ ማህበራት፣ ክለብና የክለብ አመራር ይፈጠራሉ። ወጣቱ የሚማረው በዙሪያ ከሚታዩት ነባራዊ ሁኔታዎች በመሆኑ አመራር ላይ የምትገኙ አባላትና አካላት ተነባቢ መጽሀፍት መሆናችሁን አውቃችሁ መልካም አርዐያ በመሆን ቆርጣችሁ ልትነሱ ይገባል። ባለድርሻ አካላትም በመመካከርና በመወያየት ችግሩን መፍታትና እልባት ለመስጠት መስራት ይገባል» ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የብሄራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ በበኩላቸው፤ ‹‹እግር ኳሱ የሌላ ነገር አጀንዳ መናኸርያ ከማድረጋችን ባሻገር ቂም እያወረስን እንገኛለን። እከሌ ሲያሸንፍ ከስፖርት መርህ ውጭ እከሌ ዘር ተሸነፈ፣ አሸነፈ በሚል ጤናማ ያልሆነ አስተሳሰብ ላይ ደርሰናል። ከስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል የተነሳ ሙሉ ጤና ይዞ መጥቶ ጤናውን አጉድሎ የሚመለስበት ጊዜ ላይ ደርሰናል›› ብለዋል። እንደ አቶ ኢሳያስ ገለጻ ፤ ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት\nእየተደረገ ቢሆንም ይህ በቂ አይደለም። እግር ኳሱን ከዚህ ስፖርታዊ ካልሆነ ተግባር ለመታደግ እንዲህ አይነት ውይይቶች ሊጎለብቱ ይገባል ። የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገብረመስቀል ፤ ‹‹በሀገራችን እግር ኳስ ውስጥ ሥርዓት አልበኝነት እግር ኳሱን እየጎዳው በመሆኑ በርካታ የስፖርት ቤተሰቦችን ከስፖርት ማዘውተሪያ እያራቀ ይገኛል። በጊዜ መስራት የሚገባውን የቤት ስራ ባለመስራታችን ችግሩ እየተባባሰ መጥቶ በዘር ፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት እና በፖለቲካ አመለካከት ያተኮሩ ልዩነቶች እዚም እዛም እየታዩ ይገኛሉ። ስለሆነም ይህ እየተባባሰ የመጣውን ችግር ለመቅረፍ የውይይት መድረኩ የራሱ ድርሻ አለው የሚል እምነት አለኝ» ብለዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 16/2011በ", "passage_id": "70f6c6e6c5695a4670b36a2f580f32b9" }, { "passage": "ስፖርት ጤንነትን ከመጠበቅና ከመዝናኛነት ባለፈ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው ክንዋኔ መሆኑ ይታወቃል። በተለይ አሁን አሁን እያደገና እየሰፋ የመጣው ስፖርትን ለማህበራዊ ኃላፊነትና በጎ ተግባራት ማዋል ዋናውና ተጠቃሽ ዘርፍ ሲሆን፤ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው ተቀባይነት ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በቀላሉ የህዝብ ንቅናቄን ለመፍጠር እንዲሁም ዓላማን ለማሳካት መቻሉም ውጤታማነቱ በተለያዩ መድረኮች እየታየ ነው። የኮትዲቯራውያን ኩራትና መለያ የሆነው ተወዳጁ የእግር ኳስ ተጫዋች ዲድየር ድሮግባ «የእርዳታው ንጉስ» የሚል ተጨማሪ መጠሪያ ተሰጥቶታል። ይህ ስም የተበረከተለት ደግሞ የበጎ አድራጎት ድርጅት በማቋቋም በሚያደርገው መጠነ ሰፊ እርዳታ ነው። ድሮግባን የመሳሰሉ ሌሎች ስፖርተኞችም ተመሳሳይ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን በመክፈት እንዲሁም ተጽዕኖ አሳዳሪነታቸውን በመጠቀም በዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይሳተፋሉ። በዚህም በተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለተጎዱ፣ በበሽታ ለሚሰቃዩ፣ መሰረተ ልማት ለሚያስፈልጋቸው እንዲሁም ወላጅ አልባ ህጻናትን በመደገፍ ምስጉን ለመባል ያስቻላቸውን ተግባራት ያከናውናሉ። ስፖርት የገቢ ምንጭ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፤ የውድድር አዘጋጆች፣ ክለቦችና ተጫዋቾች ከሚያገኙት ረብጣ ገንዘብ ለበጎ አድራጎት ሥራዎች ማካፈልን ባህል እያደረጉት ይገኛሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ዓለማት የበጎ አድራጎት ሥራን ለማከናወን የወጠኑ ውድድር አዘጋጆች የተለያዩ ውድድሮችን ማዘጋጀታቸው እየተለመደ መጥቷል። የውድድር አዘጋጆቹ የተለያዩ ታዋቂ አትሌቶችን በመጋበዝና በማሳተፍ ህዝቡን የማነቃቃትና ገንዘብ የማሰባሰብ እንዲሁም መልዕክት የማስተላለፍ ሥራ ያከናውናሉ። በቅርቡ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሃዋሳ ከተማ ያከናወነውም ይኸው በጎ አስተሳሰብ ነው። የኢትዮጵያ አንድ መገለጫ እየሆነ ያለው ተቋም ዓመታዊ ውድድሮችን በማዘጋጀት ይታወቃል። ከእነዚህ መርሃ ግብሮቹ መካከል አንዱ በሃዋሳ ከተማ የሚካሄደው የግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር ሲሆን፤ በዘንድሮው የሩጫ ውድድር ላይም 200 አትሌቶች፣ 200 ጤናቸውን ለመጠበቅ የሚሮጡና የውጭ ሀገር ዜጎች፣ 700 ህጻናት በጥቅሉ 4ሺ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳታፊዎች ነበሩ። ከውድድሩ በተጓዳኝም የተለያዩ መልዕክቶች የተላለፉበት እንዲሁም በጎ ተግባራት የተከናወኑበት መርሃ ግብሮች ተካትተዋል። በተለይ በዚህ ወቅት በሀገሪቱ ባሉ ውሃማ ስፍራዎች ላይ የተጋረጠው አደጋ የህልውናም ጭምር መሆኑ ይታወቃል። በደለል መሞላትና በቆሻሻዎች መበከል የሃዋሳ ሐይቅ እየተጋፈጠው ያለው አንዱ ችግር በመሆኑ «የሃዋሳ ሐይቅን እንጠብቅ» የሚል መልዕክት ተላልፎበታል፤ የሩጫው ተሳታፊዎችም ከውድድሩ መካሄድ አስቀድሞ የጽዳት ዘመቻ አካሂደዋል። የውጭ ሀገራት ዜጎች እንዲሁም የከተማ ነዋሪዎች በተሳተፉበት እንቅስቃሴ በርካታ ኪሎ ግራሞችን የሚመዝን ቆሻሻ ተወግዷል። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የከተማዋን የቱሪስት መስህብ የመጨመር ሥራ ሌላኛው የውድድሩ ዓላማ ነበር። በዚህም በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎችን በሩጫ ውድድሩ ላይ ለማሳተፍ ተችሏል። የቀድሞው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አንጋፋው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ፤ በርካታ መልዕክቶችን ይዞ በደመቀ ሁኔታ የተካሄደ ውድድር መሆኑን ይገልጻል። ከሃዋሳ ሐይቅና ከግብር መክፈል ጋር በተያያዘ መልዕክቶች የተላለፉበት ነበር። ሃዋሳ ያለ ሐይቁ አሁን ባለችበት ሁኔታ ልትገኝ እንደማትችል የሚጠቁመው ኃይሌ፤ ለማንም ሰው የማይተውና ሁሉም ተባብሮ ሊጠብቀው የሚገባ መሆኑንም ይጠቁማል። ከከተማው ወደ ሐይቁ የሚገቡትን ቆሻሻዎች ህዝቡ እየተከታተለ ሊያስወግድ እንደሚገባ፤ ካልሆነ ግን ሌሎች ሐይቆች ላይ የተከሰተው ሁኔታ እጣ ፋንታው እንደሚሆንም አሳስቧል። ከዚህ በተጨማሪ በውድድሩ ላይ በርካታ የውጭ ዜጎች መሳተፋቸው በቱሪዝም በኩል የራሱን አስተዋጽኦ የሚያበረክት ሲሆን፤ ከተማዋን ምቹ በማድረግ የቱሪስቶች ቁጥር እንዲበራከትና ከዚህም ተጠቃሚ ለመሆን እንደሚቻል አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ይጠቁማል። የበርካታ ብርቅዬ አትሌቶች ማፍሪያ ከሆነችው በቆጂ በርካታ ስመጥር አትሌቶችን በመመልመል አሁን ላሉበት ያደረሱትና የበቆጂ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል አሰልጣኝ ስንታየሁ እሸቱ በውድድሩ ላይ በተጋባዥ እንግድነት ተገኝተው ዕውቅና ከተሰጣቸው በኋላ በውድድሩ ላይ በመሳተፋቸው የተሰማቸውን ደስታ ሲገልፁ« ከሀገር ውስጥ አልፎ በርካታ የውጭ ሀገራት ዜጎችን ያሳተፈው ውድድር፤ ስፖርቱ የሚያድግበት እንዲሁም የውጭ ሀገራት ዜጎች ስለ ኢትዮጵያዊያን የሚያውቁበትና በትክክል የሚገነዘቡበት ነው። በመሆኑም ይህ ዓይነቱ እንቅስቃሴ ለኢትዮጵያ ወሳኝ ነው» ብለዋል፡፡አዲስ ዘመን የካቲት 7/2011ብርሃን\nፈይሳ", "passage_id": "015ad8c3835eb7e3e2b1cc91b937a4e2" } ]
9f8a8d2d2ea30d31d305651baf1b9735
6aefcf1f956bdd3db8e17f245d84e6db
በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነቡ ስምንት ትምህርት ቤቶች ለርክክብ ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ
 መሀመድ ሁሴንአዲስ አበባ፡- በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት አማካኝነት በመገንባት ላይ የሚገኙ ግንባታቸው ከዚህ ቀደም ተጠናቆ ለአገልግሎት ከበቁ ትምህርት ቤቶች ተጨማሪ የስምንት ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጠናቆ ለርክክብና ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን ጽሕፈት ቤቱ አስታወቀ። የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ፋንታ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የሚያስገነባቸው የትምህርት ተቋማት ፕሮጀክቶች በአብዛኛው በመጠናቀቅ ላይ ናቸው። ከዚህ ቀደም ግንባታቸው ተጠናቀው ስራ ከጀመሩት በተጨማሪ የስምንት ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጠናቆ ለርክክብና ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል። ግንባታቸው ተጠናቆ ርክክብ የሚፈጸምባቸው ትምህርት ቤቶች በአፋር ክልል ዱብቲ፣ በጋምቤላ አኝዋክ ዞን፣ በቤኒሻንጉል ክልል አሶሳ እና መተከል ዞን ፣ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ዞን 02 እና 06 ቀበሌዎች፣ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ደባርቅ ከተማ እና ዋግኸምራ ዞን ሳህላ ሰለምት ወረዳ የተገነቡ መሆናቸውን አመልክተዋል።ግንባታቸው ቀድመው የተጠናቀቁና ርክክባቸው ተፈጽሞ ስራ የጀመሩት አምስት ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ፤ በአማራ ክልል ጎንደር ሎዛ ቀበሌ፣ ደቡብ ወሎ ጦሳ ፈላና ቀበሌ (አልብኮ ወረዳ)፣ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሊበን ጭቋላ ቀበለ (ቢሾፍቱ አካባቢ)፣ ምዕራብ ጉጂ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞን ውጫሌ ወረዳ ጃቴ ቀበሌ (ሙከጡሪ አካባቢ) የሚገኙት መሆናቸውንና አሁን ላይ ተማሪዎችን ተቀብለው በማስተናገድ ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል። በተጨማሪም ግንባታቸው እስከ ታህሳስ 30/2013 ባለው ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቁ አራት ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፤ ትምህርት ቤቶቹም በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሸካ ዞን፣ ጌዲኦ ዞን፣ ደቡብ ኦሞ እና በኦሮሚያ ክልል ሐዊ ጉዲና ወረዳ ሐሮ ቢሊቃ ቀበሌም እንደሚገኙ አስታውቀዋል። በአዲስ አበባ የተሰራው የሕጻናት ማሳደጊያ፣ በሰበታ ከተማ የሚገኘውን ማየት የተሳናቸው ትምህርት ቤት እና በተለያዩ ክልሎች የተገነቡትን ክፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ገንብቶ ለማጠናቀቅ ጽህፈት ቤቱ እስካሁን 760 ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጉንአስታውቀዋል። ገንዘቡም ከተለያዩ የውጭ አገራት ረጂ ድርጅቶች የተገኘ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህ ዓመትም 10 ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት እቅድ ተይዞ የአምስቱ የግንባታ ቦታ መለየቱን የጠቀሱት አቶ ሙሉቀን፤ የእነዚህ ፕሮጀክቶች ወጪ የሚሸፈነውም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከመደመር መጽሀፍ ሽያጭ ያገኙትንና ለጽህፈት ቤቱ ባበረከቱት ገንዘብ መሆኑን አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 21/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=38455
[ { "passage": "አዲስ አበባ፤ በቦሌ አራብሳ በ150 ቀናት እንዲጠናቀቁ ታቅዶ የተጀመሩ 15 የኮንዶሚኒየም ህንጻዎች ጥራታቸውን ጠብቀው በፍጥነት እየተገነቡ መሆኑን እና በሐምሌ ወር መጨረሻ ቀለም ተቀብተው እንደሚጠናቀቁ የልደታ ቤቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት አሳውቋል። በአዲስ አበባ ቤቶች የልደታ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አረጋ አባተ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ከቤቶቹ ውስጥ 224ቱ ስቱዲዮ፣ 423ቱ\nባለአንድ መኝታ፣ 454ቱ ደግሞ\nሁለት መጥታ እንዲሁም 69ኙ የንግድ ቤቶች\nናቸው። የካቲት ወር ውስጥ የተጀመሩት የኮንዶሚኒየም ቤቶች በፍጥነት እና በጥራት እየተገነቡ ስለመሆናቸው ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል። ቤቶቹ በሐምሌ ወር መጨረሻ ከነቀለም ቅባቸው ተጠናቀው ለተጠቃሚዎች ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ግንባታዎቹ አሁን 66 ነጥብ 2 በመቶ ላይ ናቸው። እንደ አቶ አረጋ ከሆነ፣ ቤቶቹ እየተገነቡ የሚገኙት ቦሌ አራብሳ ሲሆን፣ በካሳ ክፍያ ምክንያት እስከ 2011 ዓ.ም አጋማሽ ሳይገነቡ የቀሩት ናቸው። በመሆኑም ሲጠናቀቁ በቀጥታ እጣ ውስጥ ገብተው ለተጠቃሚ ይተላለፋሉ። በግንባታው ላይ የእነ ቶሎ ቶሎ ቤት አይነት የጥራት ችግር እንዳይፈጠር ካለፉት ጊዜያት በበለጠ ትኩረት ተሰጥቷል። አንዱ ኮንትራክተር ጋር ግብአት እጥረት ሲፈጠር ከሌላው እየወሰደ እንዲጠቀም በማድረግ በፍጥነት እንዲሰሩ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ተደርጎባቸዋል። የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጋሻው ተፈራ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢንጂነር ሰናይት ዳምጠው ዛሬ በግንባታ ቦታዎቹ ተገኝተው አስፈላጊውን መመሪያ ይሰጣሉ። እስከአሁንም ኢንጂነሯ ቤቶቹ በጥራት እና በፍጥነት እንዲጠናቀቁ አስፈላጊውን መመሪያ እየሰጡ ክትትል አድርገዋል። እንደ አዲስ አበባ ቤቶች ልማት ጽህፈት ቤት መረጃ ከሆነ፣ እየተገነቡ የሚገኙት 1ሺ170 ቤቶች ከሌሎች ቤቶች ጋር አንድ ላይ ለ20/80 የኮንዶሚኒየም ቤቶች በእጣ መልክ ለነዋሪዎች ይተላለፋሉ።አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሰኔ\n8/2011", "passage_id": "503ff43e41b8b29223301551c0fff3f7" }, { "passage": "• አብዛኞቹ ት/ቤቶች የትምህርት ቢሮ ያወጣውን መመሪያ አያሟሉም • ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ስጋት አለባቸው። • ለተማሪዎች 50 ሚ. ማስክ ይመረታል ቢባልም እስከ አሁን የተመረተው ከ6 ሚ. አይበልጥም። • ከዚህ ጊዜ በላይ ተማሪዎቻችንን በቤት ውስጥ ማስቀመጥ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል - ጠ/ሚኒስትሩ • በዘንድሮ የተማሪዎች ምገባ መርሀግብር፤ 400ሺ ተማሪዎች ተካተዋል። • በሁሉም የመንግስት ት/ቤቶች የተማሪዎች ክሊኒክ ይቋቋማል ተብሏል።    በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር የተዘጉ ት/ቤቶችን ለማስከፈት እየተደረገ ያለው ዝግጅት  አጥጋቢ አለመሆኑን የሚጠቁሙት አስተያየት ሰጪዎች፤ በቂ ዝግጅት ባልተደረገበት ሁኔታ ት/ቤቶቹን መክፈት የበሽታውን ስርጭት ይበልጥ እንደሚያባብሰው ገልፀዋል።አብዛኛዎቹ የመንግስት ት/ቤቶች የአዲስ አበባ ት/ቢሮ ያወጣውን ባለ 54 ነጥብ መስፈርት እንደማያሟሉም የተገለፀ ሲሆን። ት/ቢሮው በበኩሉ፤ ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እያጠናቀቅን ነው ብሏል። ትምህርት ሚኒስቴር በአገሪቱ የሚገኙ ትምህርት ቤቶቸን በ 3 ደረጃዎች ለመክፈት ባስተላለፈው መመሪያ መሰረት፤ በተለያዩ የአገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎች ያሉ ት/ቤቶች ጥቅምት 9 ቀን/2013 የተከፈቱ ሲሆን በክልል ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ደግሞ በመጪው ሰኞ ጥቅምት 16 ቀን/2013 ይከፈታሉ፡፡ የ8 12 ክፍል ተማሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ በመጪው ሰኞ ትምህርታቸውን እንደሚጀምሩ ተገልጿል ።በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ይከፈታሉ ተብሏል ።የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላት ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ፤ በከተማዋ የሚገኙ ት/ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ለመቀበል ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኙኛ አብዛኛዎቹ ት/ቤቶች በተጠቀሰው ጊዜ ዝግጅቶቻቸውን አጠናቀው ተማሪዎቻቸውን ለመቀበል እንደሚችሉ ተናገረዋል። የትምህርት ቢሮው ትምህርት ቤቶቹን በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች ለየትምህርት ቤቶች የማከፋፈል ስራ እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል። በከተማዋ በሚገኙ ት/ቤቶች የተማሪዎች ክሊኒክ እንደሚቋቋምና በክፍሎቹን የፀረ ተዋስያን ኬሚካል  ርጭት ስራ መከናወኑን ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ት/ቢሮው ትምህርት ቤቶች ስራ ለማስጀመር ያስችላል በሚል ያወጣውን ባለ 54 ነጥብ መስፈርቶች የአብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች የማያሟሉ መሆኑንና በተለይም ተማሪዎቹን ርቀታቸውን ጠብቀው ለማስተማር የወጣውን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ የማይቻል እንደሆነ የግል ት/ቤት  ባለንብረቶችና ኃላፊዎች ይናገራሉ ።ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ  አንድ የግል ት/ቤት ርዕሰ መምህር እንደገለጹት በከተማዋ የሚገኙ አብዛኞቹ የግል ትምህርት ቤቶች በአነስተኛ  ሥፍራ ላይ የተሰሩ የትምህርት ቢሮው ያወጣውን “እያንዳንዱን የመማሪያ ክፍል 40 ካሬ ሜትር መሆን ይኖርበታል” የሚለውን መመሪያ ያልተገበሩ በመሆኑ ተማሪዎችን በተባለው መሰረት ርቀታቸውን አስጠብቆ ለማስተማር እንደማይቻል ተናግረዋል። ትምህርት ቤቱ ያቋቋመው የኮቪድ፣ ኮሚቴ ት/ቤታቸውን በአንደኛ ዙር ግምገማ አይቶ እንደነበር የተናገሩት ርዕሰ መምህሩ የፀረ ተዋሲያን ኬሚካል ርጭት ለመጀመሪያ ዙር ማከናወናቸውን በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች በአሁኑ ወቅት በገበያው ተፈላጊ በመሆናቸው አንደ ልብ አገልግሎቱን ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል ብለዋል። የሳውዝ ዌስት ፕሪፓራቶሪ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ፈለቀ ፤እንደተናገሩት፤ት/ቤታቸው ት/ቢሮው ያወጣውን መስፈርቶች በሟሟላት ትምህርት ለመጀመር የሚያስችለውን ዝግጅት እያከናወነ እንደሆነ ጠቁመው፤የመማሪያ ክፍሎችን የማጽዳቱና የጸረ ተህዋሲያን ኬሚካል ርጭት የመጀመሪያ ዙር ማከናወናቸውን ገልጸዋል። በአንድ ክፍል ውስጥ ከ18-20 ተማሪዎች ተቀብለው ለማስተማር በቂ ክፍሎች እንዳሏቸውም ተናግረዋል። የአቡነ ጎርጎሪየስ ት/ቤት ወይራ ቅርንጫፍ ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ አሜጋ በበኩላቸው ለአዲሱ ትምህርት ዘመን ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሆኑና ክፍሎቹን ከተህዋሲያን የማጽዳቱን ሰራ ለመተግብር ከአንድ ተቋም ጋር ውል መፈራረማቸውን ነግረውናል።ለተማሪዎቹም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል በወላጆች የሚዘጋጅ እንደሆነም ጠቁመውናል።በግል ትምህርት ቤቶች የሥራ ኃላፊዎችና ባለንብረቶች  እየተነገረ ያለውን ጉዳይ አብዛኛዎቹን ት/ቤቶች እንደማይወክልና በተባለው ደረጃ ዝግጅት እያደረጉ እንዳልሆነ የሚናገሩት  አንድ  የግል ት/ቤት  መምህር “ይህ የሕይወት ጉዳይ ነው” ትምህርት ቤቶች በሚሉት ደረጃ እየተዘጋጁ እንዳልሆነ ላረጋግጥላችሁ እችላለሁ። ባለፈው ዓመት በኮቪድ ሳቢያ ሙሉ ክፍያ ከተማሪዎቻቸው እንዳይጠይቁ መመሪያ የወጣባቸው ት/ቤቶች በከፍተኛ ኪሳራ ላይ እንደወደቁ እየተናገሩ ባለበት በዚህ ወቅት፤ ሌላ ተጨማሪ ወጪዎችን የሚያስወጣ ተግበር ያከናውናሉ የሚል እምነት የለኝም። በአብዛኛው ትቤቶች  ውስጥም የሚታየው ይሄው ነው ብለዋል። ት/ቢሮ ይህን ችግር ለመቅረፍ ያወጣው መመሪያና መስፈርት በአግባቡ እየተተገበረ መሆኑን ለማረጋገጥ ጥብቅ ክትትል ሊያደርግ ይገባዋል ሲሉም መምህሩ ተናግረዋል።የትምህርት ቤቶቹ ዝግጅት ሁኔታ ምን እንደሚመስል በቃኘናቸው ሁለት የመንግስት ት/ቤቶች ውስጥ ያየነው ሁኔታ ት/ቤቶቹ ከኮሮና ወረርሽኝ በኋላ ተማሪዎቻቸውን ለመቀበል የሚያስችል የተለየ ዝግጅት እያደረጉ አለመሆናቸውንነው የሚጠቁም ነው። በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኝው የሰላም በር አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፤ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል የግንባታ ስራ መጀመሩን ብንመለከት ግንባታው በጊዜ ገደቡ ተጠናቆ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ ይሆናል የሚል እምነት የለንም በተመሳሳይ ሁኔታ ካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ አንድነት አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተገኝተን ባደረግነው  ቅኝት፤ት/ቤቱ ምንም ዝግጅት አለማድረጉንና 1200 ተማሪዎቸን ለመቀበል ቀደም ሲል ካሉት የመማሪያ ክፍሎች ውጪ ሌላ ግንባታ አለመከናወኑን ለማወቅ ችለናል ። የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ባንታየሁ ግርማ እንደነገሩን ት/ቤቱ ከፍተኛ የመጸዳጃ ቤት ችግር እንዳለበትና ለትምህርት ቤቱ አጠቃላይ ተማሪዎች ያለው የመጸዳጃ ቤት አንድ ጉድጎድ ብቻ መሆኑን ገልጸውልናል ይህ ሁኔታም ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸውና መንግስት ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አሳስበዋል ት/ቤቱን የጸረ ተህዋሲያን ኬሚካል ርጭት ስራ እንደተከናወነለት ጠቁመው ድጋሚ የሚደረግበትን ጊዜም እንደማያውቁ ነግረውናል።ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አንድ የአዲስ አበባ ት/ቢሮ ሰራተኛ እንደሚሉት ትምህርት ቢሮ ያወጣውን መስፈርት የሚያሟሉ ት/ቤቶች በጣም ጥቂት መሆናቸው  አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች ብዙዎቹን ነገሮችን ወደፊት እናሟላለን በሚል ሁኔታ ትምህርት  ለመጀመር የሚችሉበትን መንገድ እየፈለጉ እንደሆነ ነግረውናል። ይህ ባለበት ሁኔታ ልጆቻችንን ወደትምህርት ቤት መላክ ለአደጋ መጋበዝ ነው የሚሉ ወላጆች ጉዳዩ በሚገባ ትኩረት እስኪያገኝ ድረስና በየትምህርት ቤቶቹ ያለው ዝግጅት በቂ መሆኑ እስካልተረጋገጠ ድረስ ልጆቻችንን ወደትምህርት ቤት አንልቅም የሚሉ ወላጆች መንግስት በጉዳዩ ላይ ትኩረት ይሰጥበት ይላሉ፡፡የሕብረተሰብ ጤና ባለሙያ  ዶክተር አብርሀም ተስፋዬ ይህን የወላጆች ስጋት  በእጅጉ አይጋሩትም  ልጆቹ በዚሁ ወረርሽን ሳቢያ ከትምህርታቸው ተፈናቅለው እቤት በመዋላቸው ሳቢያ ከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና ተፈጥሮባቸዋል የሚሉት ባለሙያ ራሳቸውን ከበሽታው ለመከላከል የተለያዩ  ጥንቃቄዎችን  በማድረግ  ልጆቹን ወደ ትምህርት ገበታቸው መላክ ይገባል ብለዋል ልጆች ከትምህርት ገበታቸውና ከጓደኞቻቸው ተለይተው ረዘም ላለ ጊዜ መቆየታቸው በራሱ የሚያመጣው ከፍተኛ የሥነ ልቦና ጫና እንዳለ የሚገልጹት ዶ/ር አብርሃም ይህ ሁኔታ እየቀጠለ ከሄደ ደግሞ ልጆቹን ለከፋ የጤና ችግር ሊያጋልጣቸው ይችላል ስለዚም  ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በደንብ ተወያይተው እና ጥንቃቄን ተግባራዊ እንዲያደርጉ መክረው ልጆቻቸውን  ወደ ትምህርት ቤት መላክ ይኖርባቸዋል ብለዋል። ትምህርት ሚኒስቴር የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች ሁለት ሁለት ለሁሉም ተማሪዎች  በነፍስ ወከፍ ለማከፋፈል አቅድ ነድፎ፣ 50 ሚሊዮን የአፍና የአፍንጫ  መሸፈኛ ጭንብሎች እንዲመረቱ ለአዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ስራው ቢሰጥም  እስከ አሁን ድረስ የተመረተው ከ6 ሚሊዮን የማይበልጥ እንደሆነና በተሠጠው የጊዜ ገድብም ምርቱን አጠናቆ ለማስረከብ እንደማይችል ውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመውናል። ይህ የሆነበት ምክንያት ፓርኩ ለሰራተኞች የሚከፍለው ደሞዝ አነስተኛ በመሆኑና ከፍተኛ የሠራተኛ መልቀቅ ስለሚያጋጥም እንደሆነም ምንጮች ጠቁመውናል። ስለ ጉዳዩ ለማወቅ የኢንዱስትሪያል ፓርኩን ስራ አስኪያጅ አቶ ፍጹም ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ሳይሳካልን ቀርቷል።  በተያያዘ ዜናም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከኮሮና ወረርሽኝ በኃላ ለተከፈተው የትምህርት ዘመን እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ ለመላው የኢትዮጵያ ተማሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡“ከዚህ ጊዜ በላይ ተማሪዎቻችንን በቤት ውስጥ ማቆየት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። በተማሪዎቻችን ላይ ሥነልቡናዊ ጫና ያሳድራል፤ አንዳንድ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመተው በሌሎች አልባሌ መስኮች እንዲሠማሩ ያደርጋቸዋል፤ መጥፎ ሱስ ውስጥ ያስገባቸዋል። በአንድም በሌላም መንገድ ያለ እድሜ ጋብቻን ያበረታታል፤ በወላጆች ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና ያሳድራል፤ የቤት ውስጥ ጥቃት ቁጥሩ እንዲያሻቅብ ያደርጋል። ስለዚህም የተሻለው መፍትሔ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ትምህርትን መጀመር ሆኖ አግኝተነዋል። ኮሮናንና መሰል ሀገራዊ ችግሮችን የሚያጠፋ ትውልድ ማግኘት የሚቻለውም በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ጭምር መማርና መመራመር የሚችል ትውልድ በመፍጠር ነው።” ብለዋል ጠ/ሚኒስትሩ፡፡“አስፈላጊ የሆኑ የንጽሕና ቁሳቁሶችን፣ የመታጠቢያና የመጸዳጃ ቦታዎችን፣ ርቀትን ለመጠበቅ የሚያስችሉ የመማሪያ ክፍሎችን፣ በተቻላቸው መጠን ትምህርት ቤቶች እንዲያሟሉ እየተደረጉ ነው። የትምህርትና የጤና ቢሮዎች፣ ፖሊሶችና ወላጆች እነዚህን ነገሮች እንዲከታተሉ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። በየትምህርት ቤቶች አስፈላጊ ነገሮች እንዲሟሉ ወላጆች፣ የበጎ አድራጎት ተቋማትና ባለሀብቶች ማኅበራዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ አቀርባለሁ።” ብለዋል በመግለጫቸው፡፡", "passage_id": "98a0934e66ea15068ceb65eb30d41ae8" }, { "passage": "ቀዳማዊት እመቤቷ ትናንት በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ለሚገነባው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡\nበሥነ-ሥርዓቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤቷ እንደተናገሩት ፣የሚገነባው ትምህርት ቤት በተለያዩ ክልሎች ከሚገነቡት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አንዱ ነው።ለትምህርት ቤቱ ግንባታ የሚውለው በ20 ሚሊዮን ብር ወጪ በኢፌዴሪ ቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት እንደሚሸፈን ታውቋል።\nየትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል እንደገለጹት፤ የትምህርት ቤቱ ግንባታ ተጠናቆ ተማሪ እንዲቀበል የከተማዋ ህዝብ የተለመደውን ድጋፉን ማበርክት ይጠበቅበታል።የከተማዋ የአገር ሽማግሌዎች ተወካይ አቶ አረጋይ አየለ በከተማዋ ተጨማሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመገንባት ቀዳማዊት እመቤቷ በአካል ተገኝተው የመሰረት ድንጋይ በማኖራቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀዋል።\n/ኢዜአ/አዲስ  ዘመን  ጥር 7/2011", "passage_id": "71c0bac0c7bed31914f944b68eb9b54f" }, { "passage": " በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ሙሉ ወጪ የተገነባው ደባርቅ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የግንባታ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በቀጣይ ወር ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ፡፡በ13 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ይህ ትምህርት ቤት 18 የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መፅሀፍት፣ ቤተ ሙከራዎች፣ የአስተዳደር ህንፃ፣ መጸዳጃ ቤትና ክሊኒክ ያሟላ ነው፡፡የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ፈንታ እንዳሉት፣ በቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የተገነባው ዘመናዊ ትምህርት ቤት በከተማው የሚታየውን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ችግር የሚፈታ ነው ፡፡የትምህርት ቤቱ ግንባታ ዘመን ተሻጋሪ እና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ጥራት ያላቸውን የግንባታ ቁሳቁሶች ከመጠቀም ጀምሮ ተገቢ የሆነ የባለሙያ ክትትል ተደርጎለታል ተብሏል፡፡የክልሉ ትምህርት ቢሮ ችግሩን በመረዳት እድሉን በመስጠቱ በከተማ አስተዳደሩ ተማሪዎችና መምህራን ስም ምስጋና ያቀረቡት የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ትምህርት ቤቱ አዲስ በመሆኑ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበርና ሌሎች ግብአቶችን ለማሟላት ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ግብአት ለማሟላት በሚደረገው ጥረት የሚመለከተው የመንግስት ተቋም፣ የአካባቢው ማህበረሰብና በውጭ ሀገር የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ድጋፍ እንዲያደርጉም የትምህርት ጽህፈት ቤቱ ጥሪ አቅርቧል:: ", "passage_id": "8f045f410a2b665f9eae29c8c7e7045f" }, { "passage": "የመጀመሪያው ዙር የ1997 ዓ.ም. የኮንዶሚኒየም ቤት ተመዝጋቢዎችና እስከ 11ኛው ዙር ዕጣ ያልወጣላቸው ተመዝጋቢዎች፣ አሁን በግንባታ ላይ ካሉት ቤቶች ሁሉም እንደሚደርሳቸው ተገለጸ፡፡በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ የቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ እንደገለጸው፣ እስከ 11ኛው ዙር የኮንዲሚኒየም ቤቶች ዕጣ የወጣላቸው የከተማው ነዋሪዎች 176 ሺሕ ናቸው፡፡ በመጀመሪያው ዙር የተመዘገቡ ነዋሪዎች ከ900 ሺሕ በላይ ነበሩ፡፡ በ2005 ዓ.ም. በዳግም ምዝገባ አብዛኞቹ ነባር ተመዝጋቢዎች የቤት ምዝገባቸውን ደረጃ በማሻሻል በአዲሱ የአመዘጋገብ ሥርዓት ውስጥ የገቡ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ቀድሞ የተመዘገቡበትን በማደስ እስከ 11ኛው ዙር ድረስ ዕጣ የወጣላቸው መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ቀሪዎቹ ደግሞ አሁን በመገንባት ላይ ካሉ ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንደሚደርሳቸው፣ የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሽመልስ ታምራት ተናግረዋል፡፡አቶ ሽመልስ፣ ምክትል ሥራ አስኪያጇ ወይዘሮ አፀደ ዓባይ፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ የአንድ ማዕከል አስተባባሪ አቶ መንበረ አስመረና የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ብርሃኔ ገብረፃዲቅ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፣ በ11ኛው ዙር ዕጣ ከወጣባቸው 30,634 ቤቶች ውስጥ 19,047 ዕጣ የወጣላቸው ሰዎች ብቻ ቀርበው ተዋውለዋል፡፡ 16,0203 ሰዎች ቁልፍ ተረክበዋል፡፡ አብዛኞቹ ሰዎች የመዋዋያ ቅጽ የወሰዱ ቢሆንም፣ 1,953 ሰዎች ግን አለመቅረባቸውንም ኃላፊዎቹ አስታውቀዋል፡፡ በመሆኑም እስከ ኅዳር 19 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ ቀርበው ካልተዋዋሉ የማይስተናገዱና ቀሪዎቹ ቤቶች በድጋሚ ዕጣ እንደሚወጣባቸውም አሳውቀዋል፡፡ ነገር ግን በፍርድ ቤት ክርክር ላይ የነበሩ፣ በግዳጅ ላይ የነበሩ የመከላከያና የፀጥታ አባላት ግን በቀረቡ ጊዜ የሚስተናገዱ መሆናቸውን ኃላፊዎቹ አስታውቀዋል፡፡ዕጣ የወጣላቸው ሰዎች ስማቸውን በጋዜጣ ላይ በማየት ሊዋዋሉ ሲሄዱ ‹‹የእናንተ አይደለም›› እየተባሉ ስለሚመለሱ፣ በአንድ መስኮት መስተንግዶ ሁሉንም የቤት ውል የሚፈጽሙ የአስተዳደሩ ሠራተኞች ስለሚያደርሱት በደል ጥያቄ የቀረበላቸው ኃላፊዎቹ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡እንደ ኃላፊዎቹ ገለጻ፣ ነዋሪዎቹ በጋዜጣ ላይ የታተመውን ስማቸውን በማየት ወደ እነሱ ቢመጡም በሞክሼነት የቀረቡ እንጂ ትክክለኛና እስከ እናታቸው ስም ድረስ የተረጋገጠ ዕድለኞች እንዳልተመለሱ አስረድተዋል፡፡ በ11ኛው ዙር ዕጣ የወጣባቸው የጋራ ቤቶች መሠረተ ልማቶቻቸው የተሟሉ ቢሆኑም፣ ጥቂት የቀሩት ግን እየተሠሩና በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ቤቶቹ እየተሰነጣጠቁ ስለመሆናቸው፣ የመሠረተ ልማቶች ችግር እንዳለባቸው የሚገለጸው የተጋነነ መሆኑን የገለጹት ኃላፊዎቹ፣ ከኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት በስተቀር ሁሉም ከሞላ ጎደል እየተሳካ መሆኑን ተናግረዋል፡፡በ11ኛው ዙር ዕጣ ወጥቶባቸው የተረፉ ከ3,000 በላይ የ10/90 ቤቶች ስላሉ በድጋሚ ለ2005 ዓ.ም. ተመዝጋቢዎች በዕጣ እንደሚተላለፉ ኃላፊዎቹ ገልጸዋል፡፡ የ10/90 ፕሮግራም ከዚህ በኋላ እንደሚቆምም አክለዋል፡፡በ10ኛው ዙር ዕጣ የወጣባቸው ቤቶች ለዕድለኞች የተላለፉ ቢሆንም፣ መሠረተ ልማቶች ባለመሟላታቸው ግለሰቦቹ መቸገራቸውን በሚመለከት ለቀረበው ጥያቄ፣ ለማስተካከል እየተሠራ መሆኑን አቶ ሽመልስ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸው ወይም ‹‹የደሃ ደሃ›› ለሚባሉት ነዋሪዎች አስተዳደሩ ቤቶችን በመሥራት ለማከራየት ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፣ 5,000 ቤቶችን ለመገንባት የተዘጋጀ መሆኑንና የመጀመሪያዎቹ 2,000 ቤቶች ግንባታ በታኅሳስ ወር 2009 ዓ.ም. እንደሚጀምርም አስረድተዋል፡፡", "passage_id": "531d08c17f3970e22ce6eb290b94fb0c" } ]
b8de3d7acbf2cdd29da93cac53507882
2aa5575f8d5d40c720c48d572bcadc14
ህብረተሰቡ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን በመጠቀም የጤና ባለሙያዎችን እንዲያግዝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቀረቡ
አዲስ አበባ ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ህብረተሰቡ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን በአግባቡ በመጠቀም የጤና ባለሙያዎችን እንዲያግዝ ጥሪ አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር በማሻቀብ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።በአሁኑ ወቅት የጽኑ ሕሙማን ክፍል ያለውን ዐቅም ሁሉ አሟጦ እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁመው ፥ በዚህ ወቅት የጥንቃቄ እርምጃዎችን ቸል ማለት እንደማይገባም አሳስበዋል። ህብረተሰቡ የራሱን ሕይወት እንዲታደግ የሌሎችንም ሕይወት እንዲያተርፍም ጥሪ አቅርበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 21/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=38454
[ { "passage": "የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች አጠቃቀም ላይ ተገቢ ጥንቃቄ መወሰድ እንዳለበት የሕብረተሰብ ጤና ሳይንስ ልዩ ሐኪም አሳሳቡ። በሽታው የጥንቃቄ መርሆዎችን ተግባራዊ በማድረግ ከመከላከል ውጭ ምንም ልላ አማራጭ እንደሌለው አስታወቁ። \nልዩ ሐኪሙ ዶክተር መኮንን አይችሉም በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ከአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች አጠቃቀም ላይ በጣም ግራ የሚያጋቡ ነገሮች ይታያሉ ። አንዳንዶች አፍና አገጫቸውን ሸፍነው አየር እንዳያጥራቸው በሚመስል መልኩ አፍንጫቸው ሳይሸፈኑ የሚተው አሉ ይህ ትክክል አይደለም ብለዋል።\nየጭንብል ዋናው ጥቅም አፍና አፍንጫ ለመሸፈን መሆኑን የገለፁት ዳሬክተሩ፣ አላማውም ቫይረሱ ወደ አፍና አፍንጫችን እንዳይገባ ወይም እንዳይወጣ አፍኖ ለማስቀረት እንደሆነም አመልክተዋል። \nበሕክምናው ጥቅም ላይ የሚውሉት ‘ኤን 90 ወይም ሰርጂካል ማስክ’ ተብለው የሚጠሩት ጭንብሎች የአፍንጫችን ግድግዳ ላይ ጠበቅ አድርገው የሚይዙ ብረት ወይም ላስቲክ ያላቸው በመሆኑ ጫን በምንልበት ጊዜ ጠበቅ አድርገው የሚይዙ ናቸው መሆናቸውን ጠቁመዋል። \nይህ የሆነው አፍና አፍንጫን በደንብ መሸፈን እንዲቻል ነው የሚሉት ዶክተሩ፤ ቫይረሱ ወደ ሰውነት ሊገባ የሚችልባቸው ዋና መንገዶች ሦስት ሲሆን፤ አፍንጫ፤ አፍና ዓይን ናቸው። ሰዎች አፍና አፍንጫቸውን በደንብ በመሸፈን ለዓይናቸውም መነጽር እንዲኖራቸው ይመከራል ብለዋል። \nየኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ደረጃ በንክኪ የሚተላለፍ ቫይረስ መሆኑን ጠቁመው፤ በምናስልና በምናነጥስበት ጊዜ በውሃ አዘል ጠብታዎች ጋር የሚወጣው ቫይረስ በአፍ፤ በአፍንጫና ወደ ዓይናችን በሚደርስበት ጊዜ አሽተን ወደ ውስጥ ልናስገባ እንችላለን ሲሉም ተናግረዋል። \nበሽታው በዋናነት የመከላከያ ዜዴዎቹ የአፍና የአፍንጫ ጭንብሎችን መጠቀም፤ እጅ በውሃና በሳሙና በደንብ መታጠብ፤ አለመጨባበጥ፤ አለመሳሳም፤ አለመተቃቀፍ፤ አለመነካካትና ርቀት መጠበቅ መሆናቸው አብራርተዋል። \nከአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች በአብዛኛው እንዲጠቀሙ የሚመከረው ለሕክምና ባለሙያዎች ነው፤ አስገዳጅ ሁኔታዎች ሲኖሩ ሰዎች እንዲጠቀሙበት ይደረጋል የሚሉት ዶክተሩ፤ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ በደንብ እንደተቀመጠው ህዝብ በሚበዛበት አካባቢ ማንኛውም ሰው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች መጠቀም አስፈላጊ ነው ብለዋል፡ ፡ \nየአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች ከተጠቀምንባቸው በኋላ መቃጠል ወይም መቀበር ያለባቸው ነገሮች ናቸው እንጂ በየሜዳ ላይ የሚጣሉ መሆን እንደሌለባቸው ጠቁመው። በድራማ ላይ እንደምናያቸው አንዳንዱ ጭምብሉንና የእጅ ጓንቱን አውልቆ ሜዳ ላይ የሚጠልበት ሁኔታ ስህተት መሆኑ መክረዋል። እያንዳንዱ ሰው ለተጠቀመበት ነገር ኃላፊነቱን መውስድ እንዳለበት በመጠቆም፤ የተጠቀመበትን ወደ ማስወገጃ ቦታዎች በመውስድ ጉድጓድ ቆፍሮ መቅበር እጀግ አስፈላጊ መሆኑ አመልክተዋል። \nበየጊዜው እንደዚህ አይነት ወረርሽኞች፤ በተለይ ዓለም አቀፍ ወረርሽኞች ዓመታትን እየጠበቁ እንደሚከሰቱ የሚገልፁት ዶክተሩ፤ በእነዚህን ዓለም አቀፍ ወረርሽኞች ብዙ ጊዜ በሽተኛውን ሆስፒታል አስተኝቶ አክሞ ማዳን አይቻልም። \nለምሳሌ ኤች አይ ቪ ማየት ይችላል። በሽታ መድኃኒት የሌለው መሆን ትልቁ ሰው ማድረግ ያለበት የጤና ባለሙያዎች ምክር መውስድና መቀበል፣ መንግሥት የሚያስተላልፋቸውን ትእዛዛት በመፈፀም እራስን ከበሽታው መከላከል ብቻ መሆኑን አስረድተዋል። በሽታው በጥንቃቄ መርሆዎችን ተግባራዊ በማድረግ ከመከላከል ውጭ ምንም አማራጭ እንደልለው አጽኖት ሰጥተው የሚገልፁት ዶክተሩ፤ ‹‹ ከባለሙያዎች የሚነገሩ ምክረ ሐሳቦች ተግባራዊ በማድረግ፤ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች በሚገባ ቦታ ላይ በመጠቀም፤ እጆቻችን በውሃና ሳሙና ማጽዳት ይኖርብናል። ይህ ተግባር ማንም ሊከውንልን የማይችለው፤ እኛ የምንሰራው ነገር በመሆኑ በደንብ በማክበር በሽታውን መከላከል እንችላለን። ሳይቃጠል በቅጠል እንደሚባል አሁን የጀመረነው በጥንቃቄ የመከላከል ሥራ አጠናክረን በሽታውን መከላከል ይኖርብናል ብለዋል ››አዲስ ዘመን ግንቦት 10/2012ወርቅነሽ ደምሰው", "passage_id": "336a0eaaefe58549cca79bbb570b9116" }, { "passage": "አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የሐዋሳ እና አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች 50 ሚሊየን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎችን በማምረት ለትምህርት ሚኒስቴር ማቅረብ ጀመሩ40 ሚሊየን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎች ከሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ እንዲሁም 10 ሚሊየን ደግሞ ከአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለትምህርት ሚኒስቴር የሚቀርቡ ሲሆን የመጀመሪያው 5 ሚሊየን ጭምብልም ርክክብ ተከናውኗል፡፡የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርከ በመገኘት የመጀመሪያውን ዙር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎች መረከባቸውን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።", "passage_id": "903151f2b782270020f2e4f06c97ef64" }, { "passage": "ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኮሮና ቫይረስ የሚያስከትለውን ሀገራዊ ችግር ለማለፍ በችግሩ መጠን መዘጋጀት እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል፡፡\nጠቅላይ ሚነስትሩ በዛሬው እለት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ነገ ለሚከበረው የእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡\n“ይህ ያለንበት ወቅት ለኛ የተለየ ወቅት ነው፤ኮሮና ያለ ጦር መሳሪያ አለማችንን ወሯል፡፡ በሀገራችን ብዙዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤አንዳንዶችም ህይወታቸውን አጥተዋል”ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወረርሽኙ እስካሁን ካስከተለው የማህበራዊና ኢኮኖሚ ችግሮች ባሻገር ወደፊት የሚያስከትለው የስነልቦና ተጽእኖ እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡\nጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “አሁን ከገጠመን የበለጠ ችግር እንዳይገጥመን እስከምን ድረስ መዘጋጀት እንዳለብን” መንግስትና ህዝብ በአንድ ልብ መስራት አለበቸው ብለዋል፡፡\nጠቅላይ ሚኒስትሩ ክርስቲያኖች በአሉን በሚያከብሩበት ወቅት አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ለቫይረሱ አጋላጭ ከሆኑ ድርጊቶች እንዲታቀቡም በመልእክታቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡\nጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሁሉም የሚገባውን ከሰራ የችግሩ ጊዜ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል ማሸነፍ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡\nመንግስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ለአምስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ ዘዋጅ በማወጅ የተለያዩ እግዶችን አውጦቶ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡\nበኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ሶስት ሰዎች ሲሞቱ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 105 ደርሷል፡፡\n\n\n\n", "passage_id": "99fbab408e3f838cb5dea0efa1f3e3d3" }, { "passage": "አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ የተላኩ የቻይና የህክምና ባለሙያዎችን ቡድን አመሰገኑ።ዶክተር ሊያ በፌስ ቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ የህክምና ባሉሙያዎቹ በወረርሽኙ ቁጥጥር ላይ ያላቸውን የዳበረ ልምድ በማካፈል አስቸኳይ የህክምና ግብአቶችን እንደሚያቀርቡ አስታውቀዋል።በዚህ ወሳኝ ጊዜም የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያ ላሳየው አጋርነት በጤና ሚኒስቴር እና በራሴ ስም ማመስገን እወዳለሁ ብለዋል።በተያያዘ ዜና ዶክተር ሊያ ታደሰ አካላዊ ርቀት መጠበቅ እርስ በእርሳችን ከመረዳዳትና በደግነት ከመተሳሰብ ሊያግደን እንደማይገባም አንስተዋል።የጤና ባለሙያዎች፣ በጤና ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞች፣ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ እና በለይቶ ማቆያ ቆይተው የወጡትን ማግለል ትክክለኛ ያልሆነ ተግባር በመሆኑ መደጋገፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።", "passage_id": "c8b782ed6de756c13a1f9c9b82c254df" }, { "passage": "አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፌደራልና ከክልል ኮሙዩኒኬሽን አመራሮች እንዲሁም ከክልል ጤና ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን አመራሮች ጋር ተወያዩ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ ከኮሙዪኬሽን ቢሮ አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር በኮሮናቫይረስ ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር ላይ መምከራቸውን አስታውቀዋል።በመድረኩም በኮሮናቫይረስ (በኮቪድ -19) ግንዛቤ ላይ እና ዕውቀትን የማሳደግ ጥረቶች ላይ መወያየታቸውን አስታውቀዋል።በየደረጃው ለሚገኘው ሕዝብ ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃዎችን በማስተላለፍ የማረጋጋት ሚናን ከመጫወት አንፃር የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ወሳኝ ድርሻ አላቸው ብለዋል።የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ማስረጃን መሰረት ያደረገ መረጃን በማሰራጨት ለመከላከል እና ስርጭቱን ለመግታት የማይተካ ሚና እንዳላቸውም አስታውቀዋል።በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ የፌደራል እና የክልል ኮሙዪኬሽን አመራሮች እንዲሁም የክልል የጤና ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።", "passage_id": "46c8eccf14dc7302d8028d44b2df6aa7" } ]
eb2df538fb0157813930823abbee19c9
877f90401cd7c14c35cd7c65fabf2ce4
ቂም በቀል በቁራዎች
ሰዎች በልዩ ልዩ ጉዳዮች በተለይ እነርሱ በማያምኑባቸው ምክንያቶች ቤተሰቦቻቸውን አልያም የቅርብ ወዳጆቻቸውን በሞት ሲነጠቁ በከባድ ኀዘን ውስጥ ይወድቃሉ። ዘመዳቸው ወይም የቅርብ ወዳጃቸው ሕይወቱ ሆን ተብሎ በግለሰብ እጅ ያለፈ ከሆነም አሟሟቱን በማሰብ በንዴት ይበግናሉ። በቂም በቀል ተነሳስተውም የገዳዩን ሕይወት እስከማጥፋትም ይደርሳሉ። በእኛም ሀገር ቀደም ሲል እንደነበረው አይብዛ እንጂ አሁንም ድረስ በተለይ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ላይ በዚህ መልኩ ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ የሟች ቤተሰቦች ደም ለመመለስ በሚል በቂም በቀል ተነሳስተው በገዳይ ቤተሰቦች ላይ እርምጃ ይወስዳሉ። ይህ ጉዳይ እንደባህል ተቆጥሮ ዛሬም አልፎ አልፎ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ ገዳዩ ዘመድ እንኳን ባይኖረው ልጁን እስከመግደል የሚደረስበት ሁኔታም ይፈጠራል። ይህ የቂም በቀል ተግባር ታዲያ በሰዎች ሕይወት ውስጥ የሚታይና የተለመደ ቢሆንም፤ በእንስሳት በተለይም በአእዋፋት በኩል አለ ቢባል ግን ትንሽ ያስገርማል። ኦዲቲ ሴንትራል የተሰኘው ድረገፅ ከሰሞኑ ያወጣው መረጃም ልክ እንደሰው ሁሉ አእዋፍም በቂም በቀል ተነሳስተው ጥቃት ሊያደርሱ እንደሚችሉ ያሳያል። እንደዘገባው ከሆነ፤ ላለፉት ሦስት ዓመታት በሕንድ ማድሃያ ፕራዴሽ ግዛት ነዋሪ የሆነው ግለሰብ ህልም የሚመስል ግን እውነተኛ ሕይወትን ከቁራዎች ጋር አሳልፏል። በቀን ሠራተኝነት የሚተዳደረውና ሱሜላ በተሰኘች መንደር ነዋሪው ሺቫ ኪዋት እርሱ ባልተረዳው መልኩ ከቁራዎቹ ጋር ያጋጠመው ችግር ከሦስት ዓመት በፊት እንደነበር ያስታውሳል። ከዕለታት በአንዱ ቀን በመንገድ ላይ ሲጓዝ አንዲት ቁራ በብረት መረብ ውስጥ ተጣብቃ ይመለክትና ወደ እርሷ ቀረብ ይላል። ይሁንና ቁራዋን ከተጣበቀችበት መረብ ውስጥ ለማላቀቅ ጥረት ቢያደርግም ሳይሳካለት ቀርቶ ቁራዋ እጁ ላይ ትሞታለች። ይህ ሲሆን የተመለከቱት ሌሎች ቁራዎችም ምንአልባት የቁራዋን ሕይወት የቀጠፈው እርሱ ሳይሆን አይቀርም በሚል ሁሌም ቁራዋ በሞተችበት አካባቢ ሲያልፍ ጥቃት ያደርሱበታል። ጥቃታቸውንም አንዴ በቡድን ሌላ ጊዜ ደግሞ በተናጠል ያካሂዱበታል። ከዚህ ጊዜ ጀምሮም ኪዋት ከቁራዎቹ ሹል መንቁርና ስል ጥፍር ጥቃት ለመሸሽ ሁሌም ልምጭ ይዞ መንቀሳቀስ ይጀምራል። ኪዋት «ቁራዋ የሞተችው እጄ ላይ ነው፤ ቁራዎቹ ሃሳቤን መረዳት ቢችሉ ኖሮ ቁራዋን ልረዳት እንደነበር እገልፅላቸው ነበር» ሲል ለታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ገልጿል። «ራሴን ለመከላከል ልምጭ እጠቀማለሁ፤ ይመስለኛል ቁሯዋን የገደልኳት እኔ መስያቸዋለሁ» ሲልም ተደምጧል። ኪዋት እንደተናገረው፤ እርሱ ብቻ የጥቃቱ ኢላማ መሆኑንና ቁራዎቹ ከሌሎች ሰዎች ጋር ምንም ዓይነት ችግር እንደሌለባቸው እስኪያውቅ ድረስ የቁራዎቹን ጥቃት በደንብ እንዳላጤነው ተናግሯል። ቁራዎቹ እርሱን ለማጥቃት በአናቱ ላይ ሲያንዣብቡ በእርሱ ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት ለመመልከት በርካታ ሰዎች በየቀኑ በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ እስከመሰባሰብም ደርሰዋል። ብዙዎቹ በጉዳዩ የተገረሙ ሲሆን፤ ሌሎቹ ደግሞ ድርጊቱን «ድንገተኛና አስደንጋጭ» ሲሉ ገልፀውታል። ከኪዋት ጎረቤቶች ውስጥ አንዱ «ቁራዎቹ ኢላማቸውን እንዳዩ ልክ እንደ ተዋጊ ጄቶች ዝቅ ብለው በመብረር ጥቃቱን በኪዋት ላይ ያደርሳሉ» ሲል የቁራዎቹን ድንገተኛ ጥቃት ገልጿል። በባራካቱላህ ዩኒቨርሲቲ በወፎች ባህሪ ዙሪያ ጥናት ያካሄዱት ፕሮፌሰር አሾክ ኩማር በበኩላቸው፤ ቁራዎች የማስታወስ ችሎታቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው፤ በተለይ በእነርሱ ላይ ጉዳት ያስከተሉትን እንደማይዘነጉ ተናግረዋል። የበቀል ሃሳባቸው ልክ እንደሰዎች የተወሳሰበ ባይሆንም፤ በሚያስቆጣቸው ጉዳይ ላይ በቡድን ወይም በተናጠል የማጥቃት ባህርይ እንዳላቸውም ጠቁመዋል። በመሰረታዊነት ቂም የሚይዙ በመሆናቸው ኪዋት ያገጠመው ችግርም ይኸው መሆኑን አመልክተዋል።  አዲስ ዘመን  ጳጉሜን 5 /2011 አስናቀ ፀጋዬ
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=17594
[ { "passage": "ጽጌረዳ ጫንያለው በአገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች ግጭቶች ገደብ አልባ ሆነው ለአገርና ለሰው ደህንነት ችግር ሲሆኑ ታይተዋል። ለዚህ መንስኤው በርካቶች ቢሆኑም ዋነኞቹ ግን የመርህ፣ የህግና የተሳሳቱ ትርክቶች መሆናቸውን ምሁራን ይገልጻሉ። በደብረብረሃን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው ተሰማ እንደሚናገሩት፤ በየቦታው የሚነሱት ግጭቶች መሰረታቸው በርካታ ቢሆንም በዋናነት የምናነሳቸው ግን የመርህ፣ የህግና የተሳሳቱ ትርክቶችን ነው። የፖለቲካው ማኒፌስቶ ከትርክት ጋር ተዋቅሮ ማህበረሰቡ የነበረውን መተሳሰብ እንዲያጣና እርስ በእርስ እንዳይተማመን አድርጎታል። በተለይም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርዓት ከመፈክሮች የተቀዳ የ1960ዎቹ የግራዘመም አስተሳሰብን ያነገበ በመሆኑ ቋንቋና ባህል ሳይቀር ጨቋኝ ተጨቋኝ መደብ ተሰጥቶት አጠላልቷል። በተለይ ከ1983 ዓ.ም በኋላ በአለው እንቅስቃሴ በባህረ ሰላጤው አካላት ድጋፍ ፣ በአሜሪካ እገዛ ፣በህውሓትና በኦነግ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያን የፖለቲካ መርህ የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክት መድረክ ከማድረጉም በላይ የህገመንግሥት መነሻ እንዲሆን አድርጎታል። የኢፊዴሪ ህገመንግሥት መግቢያው ላይ ‹‹የተዛባ ግንኙነታችንን›› የሚል አንቀጽ አለው። ይህ ደግሞ በህዝብ መካከል የተዛባ ግንኙነት እንዳለ በግልጽ የሚሰብክ ሲሆን፤ ተበደልኩ ባይ እንዲስፋፋ፣ ቆዛሚ እንዲበራከትና ድንኳን ጥሎ ለ30ና 40 ዓመት እንዲቀመጥ በማድረግ ዛሬ ድረስ ግጭቶች በየቦታው እንዲነሱ መሰረት ጥሏል። በክልሎች የሚወጡ ህገመንግሥቶች ሳይቀሩ ግጭቶች ህግ መንግሥታዊ መሰረት ኖሯቸው እንዲከወኑም አድርጓል። ስለዚህም ክልሎች ተወላጁን እንጂ ሌላ የአገሪቱ ነዋሪ አይመለከታቸውም። ስለዚህ የመኖር መብትን ስለሚነፈጉ በሚችሉት ሁሉ ሲታገሉ ግጭቱ ተፋፍሞ በአገርና በሰው ላይ አደጋዎች እንዲደርሱ ይሆናሉ ይላሉ።የተሳሳቱ ትርክቶች በመጽሐፍና በማጣቀሻ መጽሐፍት መልኩ መቅረባቸውና ተማሪዎች እንዲማሩባቸው መደረጉ አንዱ የግጭቶች መንስኤ እንደሆነ የሚያነሱት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ በተለመደ ሞግዚነት ክልሎች ስለሚተዳደሩም ስልጣናቸውን ላለመነጠቅ ሲሉ ትርክቱን እውነት በማስመሰል ያስፈጽማሉ። በዚህም ሃሳቦቹ አገር የጋራ ነው የሚለው እንዳይታሰብ፤ የእኔ ክልል ስለሆነ ከዚህ ውጣ እንዲበዛ፤ ወደፊት አገር የጋራ ይሆናል የሚባል ሃሳብ ሲቀርብ ይህንን የሚፈራው ባለስልጣን አገር እንዳይረጋጋ አይፈልግምና የውጪ ጣልቃ ገብነት እንዲፋፋምና ጥላቻ ቦታ እንዲያገኝ ማድረጉን ይናገራሉ። እንደ ረዳት ፕሮፌሰሩ ገለጻ፤ ግጭት ንግድ መሆኑም ሌላው መንስኤ ነው። መሳሪያ አምራቹ ጠመንጃውን ለመሸጥ፤ ባለስልጣኑ ስልጣኑን ለማቆየት፤ የኢኮኖሚ ተጠቃሚው ባለቤትነቱን ለማረጋገጥ ግጭትን በንግድ መልኩ ይተገብረዋል። ለዚህ ደግሞ ትርክቶች የመርህና የህግ ስህተቶች ዋነኛ መሳሪያ ሆነውታል። በኮተቤ መልቲፖሊታል ዩኒቨርሲቲ የህግና ታሪክ መምህሩ ዶክተር አልማው ክፍሌ በበኩላቸው፤ አሁን የሚነሱት ግጭቶች መሰረታቸው እንግሊዝና ጣሊያን ናቸው። እነርሱ የተባረሩት በህዝባዊ አንድነትና በማዕከላዊ መንግሥቱ ጠንካራ አሠራር በመሆኑ ማዕከላዊ መንግሥቱ እንዲዳከም ብዙ ዘሮችን ተክለዋል። አንድነት የሚባል ሃሳብ እንዳይኖርም በብሔርና በጆግራፊያዊ አቀማመጥ ከፍለው እርሷቸውን ተክለዋል። ጣሊያን በአምስት ዓመት ቆይታው የሠራውን ሥራና እንግሊዝ በጆግራፊያውዊ አቀማመጥ ከፋፍላ ኡጋዴንን ወደ ሱማሌ፣ ቤኒሻንጉልንና ጋንቤላን ወደ ሱዳን አድርጋ አስቀምጣ የሄደችውን ነው ህውሓት ያስቀጠለው ይላሉ። ከ30 ዓመት በላይ ግጭቶቹ መልካቸው በእነዚህ አካላት ሲቀየር አንድነትና ባህሎች ተሰባብረዋል። በባህል ዳኝነት የሚፈቱ ችግሮችም ጠፍተዋል። ከዚያ ይልቅ በጠመንጃ የሚዳኙ ብዙ ግጭቶች እንዲኖሩ ዕድል ሰጥቷል። አሁንም ማዕከላዊ መንግሥቱን ብቻ ሳይሆን የሰዎችን ደህንነት የሚፈትን ግጭት በየቦታው የመፈጠሩ መንስኤ የጣሊያንና የእንግሊዝ አስተሳሰብ በህውሓት ተግባሪነት እየቀጠለ መጓዙ ነው። በተለይም የመርህ ፣ የህግ ችግርና የተሳሳቱ ትርክቶች በአገር ላይ ዋጋቸው እንዲልቅ መሆኑ ብዙ አደጋዎችን እንድናስተናግድ እንዳደረጉን ይገልጻሉ። ‹‹መቼም ቢሆን የፈረንጅ ወዳጅ የለንም›› የሚሉት ዶክተር አልማው፤ አሁን መንግሥት በሚያደርገው የህግ ማስከበር ሥራ ብቻ ቢጠቀስ የውጭ ሚዲያዎች ሳይቀሩ አሉታዊ ጎኖችን ብቻ ሲያሳዩ ይታያሉ። ጸረ መንግሽትም እንደሆኑ ተመልክተናል። አገራቱም ቢሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ በጥቅምና በስልጣን የተጋጨ ቡድንን በመሸሸግና ድጋፍ በማድረግ ትርምስ የሚፈጥሩ ናቸው። ስለዚህም አገር ውስጥ ካሉ የመርህ ፣ የህግ እና የተሳሳቱ ትርክቶች ትግበራ በተጨማሪ ለግጭቶቹ መንስኤ የሆኑት የአንዳንድ የውጭ አገራት በማይመለከታቸው መግባት መሆኑን ይናገራሉ። የስልጣን ጥማትና የገንዘብ ፍቅር ለግጭት መንስኤ ብቻ ሳይሆን እንዳይቆሙ ጭምር የሚያደርግ መሆኑን የሚጠቁሙት የህግ መምህሩ፤ ለስልጣን ያለው ስግብግብነት ከገንዘብና ከሰው ህይወትም በላይ መሆኑ ነገሮች ቀላል እንዳይሆኑ በር ከፍቷል። የህዝብ ለውጥ የእነርሱ ጉዳይ እንዳይሆንም አድርጓል። ስልጣን እንዲቆይ አንድነት ላይ ጠመንጃ ይነሳል፤ አገር አፈርሳለሁ ይባላል። ስለሆነም የግጭቶቹ መንስኤ ለስልጣንና ለገንዘብ ፍቅር ሲባል የሚደረግ ግብግብ፤ በብሔርና ኃይማኖት ሽፋንነት መተግበሩ እንደሆነ ያስረዳሉ። ሌላው የርዕዮት ዓለም መለያየት ሲሆን፤ በምሥራቁ ድጋፍና ፍልስፍና የሰከረው ኢትዮጵያን በሶሻሊዝም ወይም በኮሚኒዝም እይታ ማሳደግ መፈለግና በምዕራባውያን ርዕዮት ዓለም አገሪቱ እንድትቃኝ የሚፈልገው ደግሞ ካፒታሊስትና ሚክስድ ኢኮኖሚ ተከታይ እንድትሆን መሥራቱ የሃሳብ መለያየቶችን አምጥቶ ግጭቶችን ፈጥሯል። በአስተሳሰብ ልዩነታቸውም ግጭቶች ዘላቂ መፍትሔ እንዳይኖራቸው አድርጓል ይላሉ። አስተዳደራዊ በደል፣ ፍትሐዊ ያልሆነ ተጠቃሚነት ሌላው የግጭቶች መነሻና እንዳይቆሙ ያደረገ ጉዳይ መሆኑንም ያነሳሉ። አሁን አገሪቱ ባለችበት ሁኔታ መፍትሄው ወታደራዊ ዕርምጃ እንደሆነ የሚጠቁሙት ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው፤ ችግሮቹ የባህል ውጤት፣ የሌሎች ጣልቃ ገብነት፣ የስልጣን ጥማት፣ የኢኮኖሚ ልዩ ተጠቃሚነት ጉዳይ በመሆናቸው በውይይት ለምፍታት ዘግይቷል። ስለሆነም አሁን መንግሥት እያደረገ ያለውን ተግባር መቀጠል አለበት። ከዚያ ጎን ለጎን የህውሓትን እውር አመለካከት ያነገቡ የቀድሞ አመራሮች ብቃት ባላቸው ኢትዮጵያዊነትን መተካት ይኖርባቸዋል። ‹‹ቃል ያፈርሳል ቃል ያጸናል›› እንደሚባለው ስልጣን የያዘው የብልጽግና አመራሮችም ከቃላት ጦርነት ወጥተው በኢትዮጵያ የጋራ ራዕይ ላይ መወያየት ፣ ምን እናድርግ ላይ መመካከር አለባቸው። ከእስር የተለቀቁ ጸሐፍት፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም እልህ እንዳይገቡ ማድረግ ላይም መሥራት ይገባል። ምክንያቱም ጉዳዩ የስልጣን ሳይሆን አገርን ማዳን ነውና ይላሉ። ግጭቶቹ በተዘራው ዘር ምክንያት በቀላሉ ዘላቂ መፍትሔ አያስገኙም። ብዙ ሥራዎች ይፈልጋሉ። ስለሆነም በየቦታው የሚጠፋውን እሳት በመተባበር ማድረግ ያስፈልጋል። የፌዴራል መንግሥቱ ብቻውን የሚያደርገው ነገር በቂ ስላልሆነ በሰሜኑ ላይ እንደሆነው ሁሉ ክልሎች ድጋፍ ሊያደርጉለት ይገባል። የብሔር ፖለቲካውም ገደብ አንዲኖረው መሰረት መጣል አለበት። ወታደራዊ ዕርምጃ፣ የፖለቲካ መፍትሔና የትርክት ለውጥ እንዲሁም የመርህና የህግ ስህተቶችን ማረምም ይገባል። ሊሂቃኑ በሚናገሩት ሳይሆን በሚሆኑት ህዝብን ወደ መልካም ጎዳና መውሰድ ሲችሉ መፍትሔዎች እንደሚመጡ ይናገራሉ። እንደ ዶክተር አለማው ገለጻ ደግሞ፤ መፍትሔው እውነተኛ ፌዴራሊዝምን በአገሪቱ ላይ መተግበር፤ የተመረጠ መንግሥት እንዲኖር ማድረግ፤ ህገመንግሥቱ አብሮነትን በሚያስተናግድበት መልኩ፣ በእውነተኛ ዴሞክራሲ ተቃኝቶ እንዲረቀቅ ማስቻል ነው። የአናሳው ብሔረሰብ መብት እንዲከበር በህግ መፍቀድና ልዩነትን በልኩ ማስተናገድ፤ አስታራቂና ነውጠኛ ሆኖ ለመቀጠል የሚፈልግ ኃይልን ማስወገድም፤ በዴሞክራሲያዊ መርህ ላይ የተመሰረተ አገር መፍጠር፤ ከተወሰኑ ባለስልጣናት የአጤሬራ አመራር ስርዓት መውጣት፤ የአመራር ጤናማነትን ማረጋገጥ፤ ህዝባዊ ደጀኖችን ማስፋት መፍትሔ ይሆናሉ። ሌላው መፍትሔ የፍትህ አካሉና ተቋማት ነጻ እንዲሆኑ መፍቀድ፣ የውጭ ጣልቃ ገብነቶችና ፈተናዎች እንዳይንሰራፉ ዜጋነኝ የሚል ሁሉ መረባረብ፤ ፍትሐዊ የሆኑ አሠራሮችን እውን ማድረግ ነው። በኢትዮጵያ ፖለቲካና ወታደራዊ ታሪክ ውስጥ በርካታ ግጭቶች ተከስተዋል። በተለይም ከአደዋ በኋላ በአንድነት ምክንያት ድል የተደረጉት ጣሊያኖች ከ40 ዓመት በኋላ ሲመለሱ የክልል መንግሥታት ከፌዴራሉ በላይ እንዲፈረጥሙና ስልጣን እንዲይዙ አግዞ የማዕከላዊ መንግሥትን አቅም እንዲሰልብ በማድረጉ ግጭቶቹ ህይወት እንዲበሉ፣ ሰው እንዲያደሙ ሆነዋል። ማዕከላዊ መንግሥቱንና አንድነትን በመግደል ክልሎች የፈረጠመ ጉልበት ኖሯቸው አገርን እንዲያተራምሱም አድርጓቸዋል። በቀጣይ አገር ጉልበት እንድታገኝ ጅምሮች አሉና እነርሱን ማስቀጠል ተገቢ ነው። አገሪቱ ከዚህ የባሱ ችግሮችን በአንድነትና በትብብር ያለፈች በመሆኗ አሁንም ህግና መርህን ማስተካከል የተሳሳቱ ትርክቶች ወደፊት በሚያራምድ መልኩ መቃኘት እንዲችሉ ማድረግ የሁሉም ኃለፊነት መሆኑን ሁለቱም ምሁራን ይናገራሉ።አዲስ ዘመን ታህሳስ 26/2013", "passage_id": "d7a0711f7fa58ee900eb29238cca5397" }, { "passage": "  - “እርስ በርስ መሰባበሩ የትም አያደርሰንም” - ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ - “የታገልነው በወጣቶች ላይ ሞት እንዲቆም ነበር፤ አሁንም ትግላችን ይሄው ነው” - የመከላከያ ሚ/ር ለማ መገርሳ - “በወንጀሉ የተሳተፉትን ለቅመን ለህግ እናቀርባለን” - የ ኦሮሚያ ክልል ም/ርዕሰ መ ስተዳድር የአክቲቪስትና ኦ ኤም ኤን ዳይሬክተር ጀዋር መሀመድ ‹‹የግል ጠባቂዬ ሊወሰድብኝ ነው›› የሚል የማህበራዊ ድረ ገጽ መልዕክትን ተከትሎ በተፈጠረው ተቃውሞና ግጭት የሞቱ ዜጎች ቁጥር 78 መድረሱን መንግስት  ሕይወት መግለፁ የሚታወቅ ይህን ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ውይይት በኦሮሚያ ዞኖችና ወረዳዎች እየተካሄደ ነው፡፡ በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ፣ የኦሮሚያ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ሽመልሽ አብዲሳ ከአባ ገዳዎች፣ ሃያ ሲንቆዎችና የአገር ሽማግሌዎች ጋር በአዳማና በሃረር ውይይት አድርገዋል፡፡ የአዳማውን ውይይት በንግግር ያስጀመሩት ጠ/ሚ፤ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፤ “ያሉንን ልዩነቶችና ጥያቄዎች በመወያየትና በመነጋገር መፍታት እየተቻለ፣ ባልተገባ አካሄድ የሰው ሕይወትን ወደ ሚያጠፋ ክስተት በመገባቱ በእጅጉ አዝናለሁ” ካሉ በኋላ ይህን ችግር ለመሻገር ምን ማድረግ እንዳለብን እንድትመክሩን እንፈልጋለን” ብለዋል፡፡ የመጀመሪያውን እድል አግኝተው ሀሳባቸውን ያጋሩት የሃገር ሽማግሌ፤ ‹‹አገራችን ተረጋጋች፤ ወደ ሰላም እየተመለስን ነው ባልንበት በዚህ ወቅት በመካከላችን የሌለን ልዩነት ፈጥረው ጉዟችንን ሊያደናቅፉ የፈለጉ አሳፋሪዎች ናቸው ችግር የፈጠሩት እነሱ ናቸው ማፈር የለባቸው›› ብለዋል፡፡ ‹‹ሕዝባችን የራሱ ስነ ምግባርና ባህል አለው›› ያሉት የሃገር ሽማግሌው ህዝባችን ከዚህ በኋላ ‹‹ይሄ አይነቱ ግርግር እንዲቆም ይፈልጋል፤ መቆም አለበት›› ብለዋል፡፡ ‹‹ብሄር ብሄረሰቦች በሚኖሩባትና በፈጣሪ በተባረከችና በተመረጠች አገር እንዲህ ያለውን ቀውስ ከእንግዲህ ማየት አንፈልግም፤ መንግስት በቀጥታ ሕግ ማስከበር ካለበት እኛም ጎረቤት ለጎረቤት እየተመካከርን፣ አካባቢያችንን በንቃት መጠበቅ አለብን” ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል›› - የአገር ሽማግሌው፡፡አንዲት የውይይቱ ተሳታፊ እናት በበኩላቸው፤‹‹ይሄን ችግር ለማስቆምና ከእንግዲህ እንዳይደገም ለማድረግ እናቶች ትልቅ ሃላፊነት አለብን፤ ልጆቻችን በጊዜ ወደ ቤት መግባታቸውን፣ አዋዋላቸውን… መቆጣጠር አለብን፡፡ ልጆቻችንን እኩያን በገንዘብ እየገዙና እያታለሉ መጠቀሚያ እንዲያደርጓቸው መፍቀድ የለብንም፤ ቤተሰብ ልጆቻችንን በሚገባ መቆጣጠር አለብን፣ ይሄን የማድረግ መብትም አለን” ሲሉ ለወላጆች ምክርና ማሳሰቢያ አስተላልፈዋል፡፡ ሌላው የአገር ሽማግሌ ደግሞ እንዲህ ብለዋል፡፡ ‹‹በለውጡ አመራር የኦሮሞ ሕዝብ ያገኘው ድል ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ የኦሮሞ ሕዝብ አገር መምራት እንደሚችል ለአለም እያሳየን ባለንበት በዚህን ወቅት ወደ ኋላ ተመልሰን ራሳችንን በራሳችን ለመስበር ስንታገል ምን ይባላል? ይሄ በመሆኑ በእጅጉ አዝናለሁ›› ብለዋል፡፡ በትግል ሂደት ውስጥ ችግሮች እንደሚፈጠሩ፤ ነገር ግን ከችግር መውጫዎችን ሁሌም መተለም እንደሚያስፈልግ በመግለጽም፣ እንደ መንግስት አመራሩ እርስ በእርስ እንዲፈታተሽና እንዲገማገም፣ አባ ገዳዎችና ሕብረተሰቡም ወደ ራሱ በስክነት እንዲመለከት የአገር ሽማግሌው መክረዋል፡፡ ‹‹ሁሉም ተነስቶ አክቲቪስት ልሁን እያለ ነው፤ በዚህ እውነቱን ለመናገር እኛም ሕዝባችንም ግራ ተጋብተናል›› ያሉት የአገር ሽማግሌው፤ ‹‹ሁላችንም በተረጋጋ መልኩ ወደ ውስጣችን እንመልከት፤ የአገር ሽማግሌዎችም ሕዝባችንን መምከር አለብን›› ብለዋል፡፡ በየጊዜው አባገዳዎች፣ የአገር ሽማግሌዎችና ተሰማኒት ያላቸው አካላት ሕዝቡን በማወያየት መምከር እንዳለባቸው ያሳሰቡት ደግሞ ሌላው የውይይቱ ተሳታፊ የአገር ሽማግሌ ናቸው፡፡ ለውጡ በፈተና የተሞላ መሆኑን በመስቀል አደባባይ የሰኔ 16 ቀን 2010 የድጋፍ ሰልፍ ላይ ከተወረወረውና ለሰዎች ሞት ምክንያት ከሆነው ጥቃት ጀምሮ በለውጡና በለውጥ ሃይሎች ላይ የተቃጡ ያሏቸውን ጥቃቶች የዘረዘሩት ሌላው የሃይማኖት አባት፤ ለእነዚያ ሙከራዎች ተገቢና አስተማሪ የሕግ ቅጣት ባለመፈፀሙ የሕግ የበላይነት ላልቷል፣ ይህም ለቀውስ ፈጣሪዎች እድል ፈጥሯል ብለዋል። አክለውም፤ “እኛ ሽማግሌዎች ተወልደን ባደግንበትና ባረጀንበት አገር ለምን በየጊዜው እንሳቀቃለን?” ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ ‹‹የለውጥ ሃይሉ የኦሮሞ ሕዝብ ገጽታ ነው›› ያሉት ሌላኛው አስተያየት ሰጪ የሃይማኖት አባት፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማትን ባገኙ ባገኘ ማግስት ለምን ይሄ ተፈጠረ?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ‹‹እኛ አሁንም ቢሆን እርስ በእርስ መከባበርና አንድነታችንን ማጠናከር አለብን›› ሲሉም ምክር ለግሰዋል፡፡ በመንግስት ላይ እስከ ዛሬ ሲሞከሩ በነበሩ የጥቃት መልክ ያላቸው ሙከራዎች ላይ ተገቢው እርምጃ ቢወሰድ ኖሮ፣ ይሄ ችግር ባላጋጠመ ነበር ያሉት ሌላው የአገር ሽማግሌ፤ አሁንም መንግስት ከምንጊዜውም በላይ የሕግ የበላይነትን ማስከበር አለበት” ብለዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ም/ርእሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው፤ በኦሮሞ ሕዝብ መካከል ልዩነትን ለመፍጠር የሚሰሩትን አንታገስም፤ እያስተካከልን መሄድ አለብን፤ ከእንዲህ አይነቱ ቀውስ እርስ በርስ መጠፋፋት እንጂ ሌላ ትርፍ የሚያገኝ አካል አይኖርም” ሲሉ አስረድተዋል፡፡  ከዚህም የባሱ ችግሮችን እየተወያየን ፈትተን እዚህ ደርሰን ነበር፡፡ አሁን የተፈጠረው ችግር በእጅጉ አሳፋሪ ነው” ብለዋል - ም/ርዕሰ መስተዳድሩ አስገንዝበዋል፡፡ ‹‹በተለይም ሕዝብን በሃይማኖት በመከፋፈል ለማጫረስ የተደረገው ሙከራ ትልቅ ቁስል ጥሎ ያለፈ ድርጊት ነው›› ያሉት አቶ ሽመልስ፤  በዚህ ድርጊት የተሳተፉ አካላትን እያንዳንዳቸውን ለቅመን ለሕግ እናቀርባለን፣ ይሄን እንደምናደርግ ለሕዝባችን ቃል እንገባለን›› ብለዋል፡፡ የሃገር ሽማግሌዎች የሕዝቡን ልብ ወደነበረበት የመመለስና የማረጋጋት ተግባር እንዲያከናውኑም ጠይቀዋል አቶ ሽመልስ፡፡ የአገር ሽማግሌዎች የተፈጠረውን ችግር በማረጋጋት ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና በማቅረብ ንግግራቸውን የጀመሩት የመከላከያ ሚኒስትሩ ለማ መገርሳ፤ “ከምሁራኖችና ከሽማግሌዎች ጋር በሕዝባችን ጉዳይ እየተመካከርን እየተረዳዳን ነበር ስንሰራ የቆየነው፣ በዚህ ሂደትም እስካሁን ያገኘናቸው ውጤቶች ብዙ ናቸው፣ ነገር ግን ይሄን በበጎ የማይመለከቱ ለማደናቀፍ የሚሰሩ በርካቶች ናቸው፤ ይህ በሆነበት ተመካክረን መስራት ሲገባን ወደ መጠላለፍ መሄዳችን ተገቢ አይደለም›› ብለዋል፡፡ ‹‹የታገልነው በወጣቶች ላይ ሞት እንዲቆም ነበር፤ ከዚህም በኋላ ትግላችን ይሔው ነው›› ያሉት ለማ መገርሳ፤ ‹‹አሁንም ቢሆን በግልጽ በፊት ለፊት መመካከር አለብን›› ብለዋል፡፡ ‹‹በአመራሩ ላይ ችግር ካለም በግልጽ ሊነገረን ይገባል›› የተነገረንንም ለማስተካከል ዝግጁ ነን፤ ነገር ግን በመገዳደል የሚሆን ነገር የለም” ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡ ‹‹ከምንናገረው በላይ ለዚህች ሃገርና ሕዝቧ እየሰራን ያለነውን ስራ ፈጣሪ ይገልጥላችሁ ከማለት ውጪ ብዙ ማለት አልፈልግም›› በሚል ንግግራቸውን የጀመሩት ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው፤ “ከዚህ በፊት የነበሩ አመራሮች በኛ ትግል ብቻ ከስልጣን የወረዱ የሚመስላቸው  የቀድሞ አመራሮች አሉ፤ ይሄ ስህተት ነው፤ የኛ ትግል ብቻ ሳይሆን የፈጣሪ ስራም በውስጡ እንዳለ ማመን አለብን” ብለዋል፡፡ በቅርቡ ‹‹መደመር›› በሚል ርዕስ የጻፉት መጽሐፍ መቃጠሉ መቀደዱ ተገቢ አለመሆኑን የገለፁት ጠ/ሚኒስትሩ ሀሳብ የሌላቸው ሀሳብ ማቃጠል የለባቸውም፤ ሀሳቡን አይተው ካልተስማማቸው ሌላ ሀሳብ ማምጣት ነበረባቸው” ሲሉ ኮንነዋል፡፡ ‹‹በየሄድንበት አለም እናንተ ሀሳብ አላችሁ እያለ እያደነቀን ነው፤ እኛ ግን እርስ በእርስ እየተሰባበርን ነው ያለነው›› ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፤ “በዚህ መንገድ መሄድ ደግሞ የትም አያደርሰንም፤ ሕዝባችን ከዚህ በፊት የከፈለው መስዋዕትነት ይበቃዋል፤ ለምን ሌላ ዋጋ እንዲከፍል እናደርገዋለን” በማለትም ሁሉም ወደ ቀልቡ እንዲመለስ ጠይቀዋል፡፡ ‹‹ይሄን መንግስት በሁለት ቀን አመፅ እናፈርሰዋለን የሚሉ ሰዎችን ሰምቻለሁ፤ እጅግ ነው የማዝነው፤ እነዚህ ሰዎች እንዲህ ያለ አቅም ካላቸው ባለፉት 27 ዓመታት ሕዝባችን ሲቸገር የት ነበሩ? ለምን ከአገር ጥለው ጠፉ? ወይስ ኦሮሞ ሲያስተዳድር ነው ነገሩ የተገለጠላቸው፤ ይሄ አይጠቅምም፤ እርስ በእርስ መሰባበር የትም አያደርሰንም፤ መናናቁ የትም አያደርሰንም›› ብለዋል - ጠ/ሚኒስትሩ። ‹‹ለጀዋር ባለፈው 1 ዓመት ከ6 ወር ጥበቃ የምናደርግለት እኛ ነን፤ ልንገለው ብንፈልግ ለምን እናስጠብቀዋለን? ልናስረው ብንፈልግ ለምን እናስጠብቀዋለን? መንግስት’ኮ ጀዋርን የመጠበቅ ሃላፊነት የለበትም፤ እንዲህ መታሰብ የለበትም” ብለዋል ጠ/ሚኒስትሩ፡፡ በወለጋ ካለው ችግር ጋር በተያያዘም ለበርካታ ጊዜ ሽማግሌ መላኩን ነገር ግን የታጠቀው ቡድን እምቢ በማለቱ ችግሩ በሰላም ሊፈታ አለመቻሉን አያይዘው ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም ከአገር ሽማግሌዎች፣ ከአባገዳዎች፣ ከየአካባቢው ከሚገኙ ቄሮዎችና ቃሬዎች ምሁራን ጋር ውይይት በተከታታይ እንደሚደረግም ገልፀዋል፡፡ ጠ/ሚሩና የመከላከያ ሚኒስትሩ ከአዳማው ውይይት ቀጥሎ ያመሩት በቀውሱ ወቅት ከፍተኛ ጉዳትና ሁከት ወደተከሰተበት ሃረርና አካባቢው ነበር፡፡ በሃረር ጨለንቆ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የአካባቢው የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ሴቶችና ወጣቶች በተገኙበት በተደረገው ውይይትም በዋናነት ለቀውሱ መነሻ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሃሳቦች ከተሳታፊዎች ተነስተዋል፡፡ “በተለይ ጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም ሌሊት ለምን የአክቲቪስት ጀዋር መሃመድን ጥበቃዎች ማንሳት ተፈለገ? ጀዋርን ለመግደል ሙከራ ተደርጓል የሚል ወሬ ነው የሰማነው፤ ለምን ይህ ይሆናል? ከወጣቶቻችን ላይ መቼ ነው ሞት የሚያበቃው” የሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎችም በስፋት ቀርበዋል፡፡ አንድ የሃገር ሽማግሌም፤ ‹‹ነፃነት ካገኘን ሰላም ማግኘት አለብን፤ የነጻነት መገለጫው ሰላም ነው፣ ነፃነት አለን የምንለው ሰላም ስናገኝ ነው ስለዚህ ሁላችሁም ሰላም አውርዱ” ሲሉ አሳስበዋል፡፡ የተፈጠረው ግጭትና ልዩነትም በውይይት እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡ ከተወያዮቹ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በቅድሚያ ማብራሪያ የሰጡት የመከላከያ ሚኒስትሩ ለማ መገርሳ፤ ከአክስቲቪስት ጀዋር መሀመድ ጋር በውይይት በመተራረምና በምክክር ሲሰራ መቆየቱንና ለወደፊትም ይሄኛው የመመካከርና የመተራረም መንገድ የሚቀጥል መሆኑን በመጠቆም፤ ለተፈጠረው ችግር የመጀመሪያ መነሻ በሆኑ አካላት ላይ ተጣርቶ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም አስገንዝበዋል፡። ‹‹ሰዎች ሊያውቁት የሚገባው ይሄን ወንድማችንን ልናጠፋው ብንፈልግ፣ ወደዚህ አገር እንዲገባ ባልጋበዝነው ነበር፣ እንዲጠፋ ብንፈልግ ኖሮ እኛ ራሳችን ጥበቃ መድበንለት አናስጠብቀውም ነበር›› ያሉት ለማ መገርሳ፤ “መንግስት ጀዋርን ሊያጠፋው ይፈልጋል የሚባለው ፈጽሞ የማይሆን ነው” ብለዋል፡፡ አክለውም “ብንሳሳትም መተራረምና መመካከር ይገባናል እንጂ መጠፋፋት የሕዝባችንን ትግል ያዳክመዋል እንጂ አያጠናክረውም፡፡ ለዚህም የኦሮሞ የፖለቲካ ልሂቃን በጋራ የምንመካከርበት መድረክ ፈጥረን አብረን እየሰራን ነው” ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ውስጥ የሚነሱ በርካታ ነገሮች መኖራቸውን ያመላከቱት ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በበኩላቸው፤ ‹‹ዐቢይ የኦሮሞን ትግል ረስቷል፣ የኦሮሞን ጉዳይ ረስቷል፣ የሚል ወሬ ይነዛል፤ ነገር ግን ይሄን ለወደፊት ፈጣሪ ይፈርደዋል፤ በሌላ ወገንም ዐቢይ የኦሮሞ የበላይነት ሊያመጣ ነው የሚል ቅሬታ ይቀርባል” ብለዋል፡። አላማቸው ለሁሉም የምትሆን፤ ሁሉንም በእኩል የምታስተናግድ አገርን መገንባት መሆኑንም ጠ/ሚኒስትሩ በዚሁ መድረክ ላይ በአፅንኦት አስገንዝበዋል። ለዚህም የ‹‹መደመር›› ሀሳብን በመጽሐፍ አትመው ለሕዝብ ትችት ማቅረባቸውንና ይሄን መጽሐፍ አንብቦ ሃሣብ ማዋጣት፣ ወይም አይሆንም የሚል የሃሳብ ሙግትን በማምጣት ሀገር መገንባት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡ ሌላው ጠ/ሚኒስትሩ በዚህ ንግግራቸው ያነሱት፣ የኢህአዴግ ፈርሶ አዲስ ውህድ ፓርቲ የመመስረት ጉዳይ ነው፡፡ ‹‹ሰዎች ለምን ኦዲፒን ለማፍረስ ፈለጋችሁ እያሉን ነው፤ እነዚህ ሰዎች መገንዘብ ያለባቸው ይሄን ህዝብ ሲጨቁንና ሲገርፍ የኖረን ድርጅት፣ ያ ድርጅት የሚመራበት ሃሳብ፣ አደረጃጀቱን ማፍረስ ትግላችንን ወደፊት የማሻገር ውጤት ነው ያለው›› ብለዋል ጠ/ሚኒስትሩ፡፡ ‹‹ደርግ ፈርሶ ነው ሌላው የራሱን የገነባው፤ እኛም ለኛ የሚሆነውን ሃሳብና አደረጃጀት የነበረውን አፍርሰን ነው የምንገነባው፣ ድርጅቱንና ሃሳቡን የምናፈርሰውም ለዚሁ ነው›› ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፤ “የነበረውን ድርጅት እናፈርሳለን፣ የራሳችን እንገነባለን፤ የህዝባችንን ጥያቄም እንመልሳለን” ብለዋል፡፡ የአፋን ኦሮሞ የፌደራል የስራ ቋንቋ የመሆን ጉዳይም እየተሰራበት መሆኑን ጠ/ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡ የጃዋር ጉዳይም በተመለከተ “እኛ እንኳን ጃዋርን እኛን ለመግደል ሲሞክሩ የነበሩትንም ለመግደል አልሞከርንም፤ አልፈለግንም” በማለት ጃዋርን ለማጥፋት የተባለው ሃሰተኛ ወሬ መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ ሰዎች ሲያጠፉም ህግ አለ፤ በህግ ነው የሚጠየቁት እንጂ ሌላ የተንኮል እርምጃ አይወሰድባቸውም ብለዋል ጠ/ሚኒስትሩ፡፡ ከሀረር በተጨማሪም ጠ/ሚኒስትሩና የመከላከያ ሚኒስትሩ በአምቦ ከተማ ተመሳሳይ ውይይት ከሀገር ሽማግሌዎቻችና የህብረተሰቡ ተወካዮች ጋር ማድረጋቸውም ታውቋል፡፡ በዚህ ውይይት ላይ መሳተፍ አለብን ያሉ ወጣቶችም በአደባባይ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ", "passage_id": "2e87d5e7f8ddce7fd43c30b7da287ae5" }, { "passage": " እርቅ የፈጸሙበት ጉዳይ አለመታወቁ እያነጋገረ ነው ሰሞኑን በሃይማኖት አባቶች አሸማጋይነት የአማራና የትግራይ ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እርቅ የፈጸሙ ሲሆን ጉዳዩ ያልተገለፀ ስምምነትም ተፈራርመዋል፡፡ የህወሓት ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤልም ሆኑ የብአዴን ም/ሊቀመንበር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፤ በሁለቱ ክልሎች መሃከል በጥርጣሬ የመተያየት አዝማሚያ መፈጠሩን ጠቁመው፣ ይህም የሆነው በራሳቸው በፖለቲከኞቹ ስህተት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ “ህዝብ አልተጋጨም አልተጣላም፤ ችግሩ ያለው እኛ ጋ ነው” ያሉት የክልሎቹ መሪዎች፤ ”እኛ ፖለቲከኞች የሚጠበቅብንን ባለመስራታችን ለዚህ አሳዛኝ የታሪክ ምዕራፍ በቅተናል” ብለዋል፡፡ ሁለቱ መሪዎች ለእርቅና ስምምነቱ ፈቃደኛ ሆነው እርቅ በማውረዳቸው የሽምግልና ቡድኑ  ምስጋና ያቀረበላቸው ሲሆን ፖለቲከኞች ችግሮቻቸውን በእርቅ መፍታት መጀመራቸው የአገሪቱ ፖለቲካ እየተለወጠ መምጣቱን ጠቋሚ ነው ሲሉ  አስተያየት የሰጡ ወገኖች አሉ፡፡  አዲስ አድማስ ያነጋገራቸው ፖለቲከኞችና ምሁራን ደግሞ በዚህ አይስማሙም፡፡ ያልተግባቡት በምን እንደሆነ ባልተገለጸበት ሁኔታ የመሪዎቹ እርቅ መፍጠር ውጤት ያመጣል ብለው እንደማያምኑ ይገልጻሉ፡፡  በዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ በሁለቱ መሪዎች መካከል የተደረሰው ስምምነት በምን ጉዳይ ነው የሚለው በግልፅ ለህዝብ ይፋ አለመደረጉ ጥርጣሬዎች እንዲቀጥሉ በር ከፋች ነው፤ ከዚህ ቀደምም እንዲህ ዓይነት ድርድር ተደርጎ አልሰመረም ብለዋል - ከአንድ አመት በፊት በጠገዴ ጉዳይ የተደረገውን ስምምነትና እርቅ በማስታወስ፡፡  “አሁን የተደረገው ቁስሉን የመጠገን እንጂ በሽታውን ከስር መሰረቱ ማከም አይደለም” የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ “ማን ነው የታረቀው? በምን ጉዳይስ ነው የታረቀው? የሚለው መልስ የለውም” ይላሉ፡፡ የዶ/ር ቴዎድሮስን ሃሳብ የሚጋሩት የአረና ትግራይ ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ ጎይቶም ፀጋዬ በበኩላቸው፤ በመጀመሪያ ለግጭት የዳረጋቸው ጉዳይ ምንድን ነው? በምን መልኩ ፈትተውት ነው የታረቁት? ሲሉ ይጠይቃሉ። የግጭቱና ያለመግባባቱ ምክንያት ባልተገለፀበትና በምን ሁኔታስ እርቁ እንደተቋጨ ባልታወቀበት ሁኔታ ሁለቱ መሪዎች መጨባበጣቸው ከሚዲያ ፍጆታ ባለፈ  ውጤት ያመጣል የሚል እምነት እንደሌላቸው ይናገራሉ፡፡ በሁለቱም በኩል የግዛት (መሬት) ይገባኛል ጥያቄ ባለበትና ምላሽ ባልተሰጠበት፤ የተፈናቀሉ ወገኖች መፍትሄ ባላገኙበት፤ በሁለቱም ወገን ያሉ የፖለቲካ ልሂቃን ፅንፍ ይዘው ባሉበት ሁኔታ የተደረገው እርቅ ምን ዓይነት ነው? ሲሉ ጉዳዩ ለሳቸውም ግራ አጋቢ እንደሆነ አቶ ጎይቶም ይገልፃሉ፡፡ “እኔ እስከሚገባኝ ድረስ የፀባቸው መነሻ የስልጣን ሽኩቻ ነው” የሚሉት አቶ ጎይቶም፤አሁን ያደረጉት እርቅ እንግዲህ በስልጣን ሽኩቻ አንጣላም የሚል ከሆነም የእርቁ ስምምነት በግልፅ ተነግሮ ህዝብ ከመደነጋገር  መውጣት አለበት ብለዋል፡፡ የተፈጠረው አለመግባባት ግን በህዝብ መሃከል አለመሆኑን አቶ ጎይቶም ያሰምሩበታል፡፡በሁለቱ አካላት መካከል ያለውን ችግር በንግግርና በእርቅ ለመፍታት መሞከሩ መልካም መሆኑን የገለጸው ወጣቱ ፖለቲከኛና ጦማሪ ዮናታን ተስፋዬ፤ ችግሩ ግን ሁለቱ አካላት ብቻ ከሚፈቱት በላይ ሆኗል የሚል እምነት እንዳለው ይገልጻል፡፡ በዚህ እርቅ ውስጥ በወልቃይትና ራያ እንዲሁም ሌሎች አካባቢ ያሉ የፖለቲካ ልሂቃን ቢካተቱ ቢያንስ ወደ መፍትሔው መድረስ ይቻል ነበር የሚለው ዮናታን፤የሁለቱ አካላት ዋነኛ ግጭት የመሬት ሳይሆን የፖለቲካ ቁጭት ነው ይላል፡፡ በአሁኑ ወቅት ህዝቡን ከማንም በላይ ማንቀሳቀስ የሚችሉት አክቲቪስቶች ለጉዳዩ ቀና አመለካከት ከሌላቸው መሪዎቹ ምንም ያህል ቀና ቢሆኑም ዋጋ የለውም የሚለው ዮናታን፤ ለዚህ መፍትሔው እነዚህ ተጽእኖ ፈጣሪ አካላትን በጨዋታው ማሳተፍ ነው ብሎ እንደሚያምን ተናግሯል፡፡  ሁለቱ የፖለቲካ ሃይሎች ባለፉት 28 አመታት እጅና ጓንት ሆነው ሲሰሩ የኖሩ መሆናቸውን የጠቀሱት የአብን  የህዝብ  ግንኙነት ሃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ በበኩላቸው፤ ከዚህ አንፃር የአዴፓ ወይም የአብን ሳይሆን የህዝቡ ጥያቄ ሳይመለስ የመሪዎቹ መጨባበጥ መሬት ላይ ያለውን ሃቅ አይቀይረውም ብለዋል፡፡ ዋነኛው የአማራ ህዝብ ጥያቄ የፖለቲካ ውሣኔ የተወሰደበት ታሪካዊ ርስቱ እንዲመለስለት ነው የሚሉት አቶ ክርስቲያን፤ ሁለቱ መሪዎች እነዚህን ጥያቄዎች የት አድርሰዋቸው ነው የተስማሙት ሲሉ የስምምነቱ ፍሬ ሃሳብ በግልጽ መቀመጥ እንዳለበት ያመለክታሉ፡፡  የአረና ሊቀ መንበር አቶ አብርሃ ደስታ ግን የተለየ ሃሳብ ነው ያላቸው፡፡ “ሁለቱ አካላት አስቀድሞም ቢሆን ለጦርነት የተዘጋጁ መስለው የሚቀርቡት ህዝብን ለማታለል ነው፤ ህዝብ ሰግቶ ከእነሱ ጋር እንዲቆም፣ የህዝብ ተቃውሞ ወደ እነሱ እንዳይዞር ነው እንጂ ብአዴንና ህወሓት አብረው እንደሚሠሩ አስቀድሞም ይታወቃል” ያሉት አቶ አብርሃ፤ወትሮም ቢሆን ያን ያህል አለመግባባት በድርጅቶቹ መሃከል አለመኖሩን ይናገራሉ፡፡ “መሪዎቹ ለፖለቲካ ፍጆታ እየተጣሉ ቢታረቁም በአማራና በትግራይ ህዝብ መካከል መቼውንም ግጭት አይኖርም፤ ሠላም ይሠፍናል” ብለዋል አቶ አብርሃ፡፡ በሁለቱ ክልሎች መካከል ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት በዋናነት ሁለቱ አካላት ብቻ ሳይሆኑ ጉዳዩ ይመለከተኛል የሚሉ የፖለቲካ ልሂቃን፣ አክቲቪስቶች እንዲሁም ህዝቡ የተሳተፉበት ውይይትና መግባባት ተደርጐ ነው እርቅ መከናወን ያለበት የሚሉት የዩኒቨርሲቲ መምህሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ በአጠቃላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ነው ብሔራዊ እርቅ መፈጠር ያለበት ብለው እንደሚያምኑ ይገልጻሉ፡፡   “ወደ ትክክለኛው መፍትሄ እንሂድ ከተባለ የምንጣላው መሬት ስለጠበበን ሳይሆን በስልጣን ሽኩቻ ስለሆነ ዋነኛ መግባባቱ መፈጠር ያለበትም በስልጣን ሽኩቻው ጉዳይ ነው” ይላሉ፤ዶ/ር ቴዎድሮስ፡፡ በመጀሪያ ገለልተኛ የሆነ የመፍትሄና እውነት አፈላላጊ ኮሚሽን ተቋቁሞ ምርመራና ማጣራት ተደርጎ በሚያቀርበው ሪፖርት ላይ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ተሰባስበው መክረው ከተስማሙ በኋላ ነው እርቅ የሚሰምረው የሚሉት አቶ ክርስቲያን በበኩላቸው፤ለብሔራዊ እርቅም መደላደል የሚሆነው በመጀመሪያ የፍትህ መስፈን ነው ብለዋል፡፡ የሁለቱ ክልል ርዕሰ መስተዳደሮች ከእርቁ በኋላ በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ ሁለቱም ከእንግዲህ ለሰላም እንሰራለን ብለዋል፡፡ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፤ “በኛ በኩል የሚጀመር ግጭትም ሆነ የሚተኮስ ጥይት የለም” ሲሉ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በበኩላቸው፤ “ለሰላም እሰራለሁ ይሄ ቃሌ ነው፤ባህርዳር ስሄድም አይቀየርም” ብለዋል፡፡  ", "passage_id": "2dd1a02a821ed8c5789330380c60333a" }, { "passage": " የዘንድሮው ክረምት ከበድ ባለ ብርድ ታጅቦ የሀገሪቱን ጫፍ እስከ ጫፍ በዝናብ ያጠግባት ይዟል! እሰየው ነው አሁን ባለንበት ደረጃ ዝናብ ማለት ህይወት ነውና። ሰበብ ሳይኖር እንኳ ዋጋው ዕለት ከዕለት እየጨመረ ዜጎቻችንን እያማረረ ያለው ኑሯችን ድርቅ ቢጨመርበት ደግሞ ምን ሊያደርገን ይችላል የሚለውን ማሰብ በራሱ ይዘገንናል። ወቅቱ ነውና በተለይ ወርሐ ነሐሴ ሰማይ ምድሩ ጨልሟል። ይናፍቀን የነበረው ጉምም አለፍ አለፍ ብሎ እየታየ ነው። የጀመርነውን የአረንጓዴ ልማት አጠናክረን ከቀጠልን ደግሞ ከዚህም በላይ ጉም ከዚህም በላይ ደመናና ዝናብ እንደምንበሸበሽ አያጠራጠርም። በርትተን አሻራችን ማሳረፉ ላይ እንበርታ! ጨለማው ነሐሴ ጳጉሜን አስከትሎ ሲያልፍ ደግሞ ብርሃናማው መስከረም ብዙ ሀገራዊ ተስፋዎችን ይዞ ብቅ ይላል። የዚህ አዲስ ዓመት መቀበያ ዋና አጀንዳ ደግሞ እርቅና ይቅርታ መሆኑ እየተሰማ ነውና በጣም ደስ ይላል። የሰላምና አብሮነት መሰረት ነውና ከእርቅ በላይ የሚናፈቅ ምን አጀንዳስ ይኖራል? ለዚህም ነው በርዕሳችን ጨለማ የሆኑትን ቂም በቀልንና ጥላቻን ከነሐሴ ጋር ወደ ኋላ ጥለን የአዲሱን ዓመት መባቻ መስከረምን በእርቅ ልንቀበል እንደርደር ማለታችን! እርቅ የትናንትን ጠባሳ ሽሮ ነገን ብሩህ ማድረጊያ ፍቱን መድሃኒት ነው። እርቅ የአብሮ የመኖር ሚስጥርና የጀግኖች ተግባር ነው። የክርስትና፣ እስልምናና ዋቄ ፈታም ሆነ ሌሎች እምነቶች ጉልህ ሥፍራ ከሚሰጧቸው ነገሮች ቀዳሚው እርቅ እንደሆነም ከማናችንም የተሰወረ አይደለም። ዛሬያችንን መልካም አድርገን ለቀጣይ ትውልድ የተሻለች ሀገር ማስረከብ የምንችለውም በረባ ባልረባው እየተነታረክንና ቂም እየቋጠርን ሳይሆን ይቅር እያልንና እርቅ እየፈጠርን መጓዝ ስንችል ብቻ መሆኑም የአደባባይ ሀቅ ነው። እውነት ነው እንኳን እንደ ሀገር 100 ሚሊዮን ሆነን ይቅርና በየቤታችንና በየተቋማችን ባለን ማህበራዊ መስተጋብር በየቀኑ የሚያጋጩንና የሚያጣሉን ነገሮች ብዙዎች ናቸው። በሌላ አነጋገር ግጭትና የሰው ልጆች ህይወት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ስለሆነም እርቅን የህይወት መመሪያ ማድረጉ ቤተሰብን፣ ተቋምንና ሀገርን ለማስቀጠል ቁልፍ ሚና አለው ማለት ነው። ለዘመናት የዘለቅንበት ፖለቲካችን ደግሞ ከእርቅ ይልቅ ጥላቻን፤ ነገሮችን ተነጋግሮ ከመፍታት ይልቅ ተቧድኖና ነፍጥ መዞ መጠቃቃትን ያስተማረን ነው። የመንግሥትነት ሥልጣን እየተያዘ የመጣውም አንዱ አሸናፊ አንዱ ተሸናፊ በሆኑበት መንገድ ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ሳንወድ የተጣቡን በርካታ ቁርሾዎችና ግጭቶች ነበሩ፤ አሁንም አሉ። ይሁንና በተለይም በኢትዮጵያ\nከነፈሰው መልካም የለውጥ\nአየር ጋር ተያይዞ\nበዶ/ር አብይ\nየሚመራው መንግሥት ለዘመናት\nየዘለቅንበትን የቂምና የጥላቻ\nእርሾ የሚሻር አዲስ\nመንገድ አስተዋውቆናል። ፍቅር፣\nይቅርታና መደመር የሚል!\nበክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን\n ዶክተር አብይ አህመድ የተለያዩ ንግግሮች ውስጥም ይቅር እንባባል፣ እንፋቀር፣ እንደመር ኢትዮጵያን ወደ ቀድሞ ክብሯ እንመልሳት የሚሉ ሐሳቦች ተደጋግመው የሚሰሙትም መጪው ዘመን ብሩህና ተስፋ ሰጪ የሚሆነው ይቅርታ ተደራርገንና ቂምን ሽረን በእርቅ ስንዘልቅ በመሆኑ ነው። ስለ እርቅ ሲወራ ሊተኮርበት የሚገባው ጉዳይ እርቅ ጽናትን የሚጠይቅና ጀግኖች ብቻ ሊከውኑት የሚችል ቅዱስ ተግባርን መሆኑን ነው። በእርቅ ሂደት ካልነኩኝ አልነካም የሚል ብሂል ቦታ የለውም። ከዚህ ይልቅ ተነክቼም ሆነ ተጎድቼም ይቅር እላለሁ የሚል ጽናትን መላበስን ይጠይቃል። ስለሆነም ዳመናማውና ጭጋጋማውን ክረምት ሸኝተን ብርሃናማውን መስከረምና መጪውን የ2012 አዲስ ዓመት ለመቀበል ስንንደረደር በጓደኛ፣ በቤተሰብ በተቋምና በአገር ደረጃ ይቅር መባባልን የየዕለት ተግባራችን አድርገን ሊሆን ይገባል እንላለን! አዲስ ዘመን ነሃሴ 11/2011", "passage_id": "5c87f8142508cba6788a5317dff95142" }, { "passage": "በዚሁ 2012 ዓ.ም መጀመሪያ በሦስተኛው ቀን አንድ ስልጠና ላይ የመገኘት ዕድል አግኝቼ ነበር፡፡ ስልጠናው የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ዕቅዱን ለመገናኛ ብዙኃን ማስተዋወቅና በሙያቸው እገዛ እንዲያደርጉ የሚያግዝም ነበር፡፡ በስልጠናው በጤናው ዘርፍ ያሉ ፈተናዎችንና መልካም አጋጣሚዎች ተብራርተውበት ነበር፡፡ በተለይም የሱስ መስፋፋትን ለመግታት ቢሮው ያቀደውንና ችግሩን ለመከላከል የሚወሰደው እርምጃ ይበል ያሰኛል፡፡\nለአብነት ማንኛውም አጫሽ በሆቴል ቤት፣ በመዝናኛ ቦታዎች፣ በትራንስፖርት ጣቢያዎች፣ በመስሪያ ቤቶችና ሕዝብ በሚሰበሰብበት ማንኛውም ቦታ ሲጋራ ማጨስ የሚከለክለውን ሕግ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ማጨስ የሚቻለውም ከእነዚህ ቦታዎች 10 ሜትር ርቀት ላይ ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ከ10 ሜትር ሲርቅ ወደ ሌላ መሥሪያ ቤትና ሕዝብ ወደ ሚሰበሰብበት የሚደርስ ከሆነ ማጨስ አይቻልም፡፡ ሲያጨስ ቢገኝ በአዋጁ መሠረት ቅጣት ይተላለፍበታል፡፡\nብዙዎቻችን በተግባር እንዲፈጸም የተጫወትነው ሚና የጎላ ባለመሆኑ አሁንም ተጠቂዎች ሆነናል፡፡ የዘርፉ ምሁራን ከአጫሹ ይልቅ ሲጨስ የሚሸተው ሰው ላይ ጉዳቱ ከፍ እንደሚል ይገልጻሉ፡፡ በወቅቱ ሰልጠናውን የሰጡን የክልሉ የጤና ጥበቃ ቢሮ ባለሙያዎች ሱስን ለመዋጋት ከምንጊዜውም በተለየ በትኩረት እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል፡፡ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችም ሕጉና መመሪያው በሚፈቅደው ልክ የአመለካከት ለውጥ በማምጣት እና እየተከታተሉ በማጋለጥ እገዛ እንዲያደርጉ ተጠይቀዋል፡፡\nስልጠናውን በወሰድኩ ወር ባልሞላ ጊዜ ከሥራ ባልደረቦቼ ጋር ለሥራ ወደ ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አቀናሁ፡፡ በብሔረሰብ አስተዳድሩ ርዕሰ ከተማ ኬሚሴ በቅርብ ርቀት ላይ ወደ ምትገኘው የደዋ ጨፋ ወረዳ ቢላቻ ቀበሌ ነው፤ ለዚህ ትዝብት መነሻ የሆነ ጉዳይ የገጠመኝ፡፡\nበቀበሌዋ በርከት ያሉ ማሳዎች በጫት ተክል ተሸፍነዋል፡፡ ሁሉንም እየቃኘሁ የበለጠ ወደ ገጠሩ ስጠጋ ለዓይኔ አዲስ የሆነ ነገር በየጓሮዎቹ ተዘርቶ ተመለከትኩ፡፡ ቅጠሉ ሰፋፊ ነው፡፡ ጥቅል ጎመን ይመስላል ነገር ግን ከጥቅል ጎመን ጋር ስለምንተዋወቅ ጥቅል ጎመን እንዳልሆነ ለራሴ አረጋገጥኩ፡፡ አካሄዴ ለሌላ ተግባር ቢሆንም የዚያን አዝርዕት ስምና ጥቅም ሳላውቅ መመለስ ግን አልፈለኩም፡፡ ጓሮዎችን እየቃኘሁ በርከት ያሉ ቤቶች ወደ ተሠሩበት አካባቢ ተጠጋሁ፡፡\nከቤቶቹ በር በአልጋና ሸራ የተሰጣ ተድበልብሎ የተሠራ ቅመም ነገር ተመለከትኩ፡፡ ይሄም ትኩረቴን ሳበኝ፡፡ መጀመሪያ የሄድኩበትን ተግባር ስፈጽም ድቡልቡሉን እና በጓሮው የተዘራውን ተክል ምንነት ጠየኩ፡፡ ተድበልብሎ የተሰጣውን ቅመም መሰል ነገር በደንብ እንዲደርቅ የሚያገላብጥ አንድ ወጣት “ትንባሆ ይባላል” አለኝ፡፡ የእውነት ደንግጫለሁ ጆሮዬን አላመንኩም ምን? አልኩት በአደነጋገጤ ግርምት ፈጥሮበት ፈገግ እያለ፡፡ “ትንባሆ ይባላል ትንባሆ አታውቅም?” እንዴ አለኝ፡፡ እረ አውቃለሁ፡፡ የት አገኘኸው? አልኩ አከታትዬ፤ የልጁ እናት ከኩሽና እየወጡ “ከጓሮ ነው እንጂ ከዬት ይገኛል አሉ፡፡” እሳቸውም ፈገግ እያሉ፡፡\nያ ሰፊው ቅጠልም ትንባሆ እንደሆነ እዛው በቆምኩበት አረዱኝ፡፡ እና ትንባሆ ማምረት ይቻላል ማለት ነው እዚህ አካባቢ? “ታዲያ ተችሎ ነዋ እዚህ ይህን ያገኘኸው አሁን እንዳውም ገበያው ጥሩ ስለሆነ ሌላ አትክልት ከመትከል ይህን መትከል ያዋጣል፡፡ አንዷን ጥቅል እስከ 15 ብር ድረስ ስለምንሸጣት ጥሩ ገበያ ነው ያለው” አለኝ፡፡ “የሚሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ” እንዲሉ አበው ሲጋራ እና ሌሎች አደገኛ ሱሶችን የሚጠቀም ሰው እንዳይኖር እንሠራለን ያለው የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ እንጀቴን በላው፡፡\nበአካባቢው በርካታ አርሶ አደሮች ትንባሆን ይዘሩታል፡፡ ከምርቱም ከመሸጥ ባለፈ ራሳቸውም ያጨሳሉ፡፡ በስፍራው ያገኘኋቸው አርሶ አደሮች እንደነገሩኝ ለትንባሆ አዲስ የሆነ ሰው በጥርሱ ሲነክስ ሰክሮ እስከመውደቅ ይደርሳል፡፡ የት ወስደው እንደሚሸጡትም ጠይቄ ነበር፡፡ ከተማ ወስደው ለነጋዴዎች እንደሚያስረክቡ ነገረውኛል፡፡ ይህ አይደለም የገረመኝ አርሶ አደሮቹ ትንባሆውን በጥርሳቸው ሲይዙ ለሥራ እንደሚያነቃቃቸውና ፈጣን እንዲሆኑ እንደሚያደርጋቸውም ነግረውኛል፡፡ “ለጤና ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም” ሲሉም በድፍረት ይናገራሉ፡፡", "passage_id": "f3893fcb5734a40069b0c7c0b0118ef4" } ]
1ac54b635f36ba4c23854a44067e8ac8
dca1c624b5554a6d6d019edd8b3606d6
ቦርዱ ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ የሚያደርጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ እንደሚገኝ ገለጸ
ሶሎሞን በየነአዲስ አበባ:- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መጪውን ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ የሚያደርጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ እንደሚገኝ ገለጸ።የቦርዱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስኪያጅ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ቦርዱ ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ቀደም ሲል ከተካሄዱ ምርጫዎች በእጅጉ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ሆኖ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ ይገኛል። ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ባለፉት ከተካሄዱ ምርጫዎች በእጅጉ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ሆኖ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርጉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የምርጫ ቁሳቁሶች 90 በመቶ ተገዝተው መጠናቀቃቸውን ያመለከቱት ስራ አስኪያጇ፣ የተገዙት የምርጫ ቁሳቁሶቹና ህትመቶች ከዚህ በፊት ምርጫ ከተደረገባቸው ቁሳቁሶችና ህትመቶች በእጅጉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እንደሆኑ አስታውቀዋል።የድምጽ መስጫ ወረቀቶቹና የመራጭ ካርዶቹ ደግመው መታተም የማይችሉ፣ ከተነካኩ የሚያስታውቁ፣ የራሳቸው የሆነ ቀሪ ያላቸው፣ ኮፒ ለመደረግ የሚያስቸግሩ እንዲሁም የድምጽ መስጫ ሳጥኖቹ አስተማማኝና መራጩ ድምጽ ሲሰጥ በነጻነት ለመስጠት የሚያስችል መከለያዎች ያሉት እንደሆነም ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ላይ ሲስተዋሉ የነበሩ የተለያዩ ማጭበርበሮችን የሚያስቀሩ የምርጫ ቁሳቁሶች መዘጋጀታቸውንም አመልክተዋል። ምርጫውን በህጉ መሰረት ለማከናወን የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት መጠበቂያ ፕሮሲጀር መዘጋጀቱን የጠቆሙት ወይዘሪት ሶሊያና ፤ ይህም ምርጫው በህጉ መሰረት ተከናውኗል አልተከናወነም ብሎ ለመለየት የሚቻልበት እድል እንዲኖር የሚያደርግና የድምጽ ቆጠራው የምርጫ ሂደቱን ተከትሎ መከናወን አለመከናወኑን ለመለየት እንደሚረዳም አስታውቀዋል። ቦርዱ ከዚህ ቀደም እንደነበረው አሰራር ለይስሙላ የተዋቀረ ሳይሆን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ባላቸው፣ የትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል ባልሆኑና ገለልተኛ በሆኑ የቦርድ አባላት እንደ አዲስ የተዋቀረ መሆኑን ጠቁመው ፤ ቦርዱ ሪፎርም ከተደረገ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ባለው የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት በተቻለ መጠን ጠንካራና ፍትሃዊነት ያላቸውን ውሳኔዎችን እየሰጠ ይገኛል ብለዋል። በውሳኔ አሰጣጡ በኩል የተአማኒነት ችግር ወይም ጥያቄ እንደሌለበት የጠቆሙት ወይዘሪት ሶሊያና፣ ቦርዱ ይሄንን ጠንካራ፣ ፍትሃዊና ተአማኒ የሆነ የውሳኔ አሰጣጥ አቅሙን ይዞ ወደ ምርጫው እንደሚገባ አስታውቀዋል። ይህም ለምርጫው ተአማኒ መሆን የራሱን አስተዋጽዖ እንደሚያበረክት ተናግረዋል። ለምርጫው የተገዙ ቁሳቁሶችና ምርጫውን ለማካሄድ የተነደፉ የአሰራር ስርዓት በተቻለ መጠን ምርጫውን ተአማኒ እንደሚያደርጉት ወይዘሪት ሶሊያና ገልጸው፤ መጪው ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ከዚህ በፊት ከተካሄዱት ምርጫዎች ለየት የሚያደርገው ምርጫው የሚካሄደው በምርጫ ህጉ የነበሩ ማነቆዎች ተስተካክለውና የቦርድ አመራሩ አደረጃጀትም በአዲስ መልኩ ተዋቅሮ መሆኑን አመልክተዋል። ይህም ምርጫው ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 21/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=38456
[ { "passage": "አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ የሚውል የመራጮች ምዝገባ ሰነዶች ህትመትና የቁሳቁሶች ግዥ መጀመሩን አስታወቀ።ምርጫ ቦርድ ለቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ከሚያደርጋቸው ዝግጅቶች መካከል አንዱ የሆነውን የመራጮችን ምዝገባ ዘመናዊ እና ተአማኒ የሚያደርግ የህትመት ስራ እንዲጀመር በትላንትናው እለት በዱባይ ስምምነት ተፈራርሟል።የዚህ የህትመት ውል አላማም የምርጫው ሂደት አለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ እና አዲሱ የምርጫ ህግ ላይ የተቀመጡትን መስፈርቶች ያሟላ እንዲሆን የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።እንዲሁም በምርጫ ሂደቱ ሊፈጠሩ የሚችሉ ስህተቶችን ለመቀነስና እና ማጭበርበርን ለማስወገድ የሚረዳ እንዲሆን እንዲሁም ለምርጫ አስፈጻሚዎች ለመረዳትና ለማስፈጸም ቀላል እንዲሆን ለማድረግ ያስችላል ነው የተባለው።ስምምነት የተፈጸመበት የህትመት ስራ ከዚህ በፊት ከነበሩትና ሀገር ውስጥ ከሚደረጉ ህትመቶች የተለየ መሆኑም ተመላክቷል።በዚህ መሰረትም ህትመቱ የመራጮች መመዝገቢያ መዝገቡም ሆነ የምዝገባ ማረጋገጫ ካርድ የራሳቸው የደህንነት ማረጋገጫ ያላቸውና ሊጭበረበሩ እና ሊባዙ የማይችሉ መሆናቸው ነው የተገለጸው።የመራጮች ካርድ ቀሪ ያለው ሆኖ የሚዘጋጅና መራጮች ጋር ያለው ካርድ ቀሪ የምርጫ አስፈጻሚዎች ጋር የሚቀር መሆኑ በምዝገባ ወቅት ሊፈጠር የሚችል ማጭበርበርን ማስቀረት እንደሚያስችልም ተጠቁሟል።ከዚህ ባለፈም እያንዳንዱ መራጭ በመራጮች ካርድ አማካኝነት የራሱ የሆነ ልዩ መለያ ቁጥር ያለው ሲሆን፥ ሁሉም ሰነዶች በአምስት ቋንቋ ማለትም፣ በአማርኛ፣ በአማርኛ/ትግርኛ፣ በአማርኛ/አፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ/ሶማሊኛ እንዲሁም በአማርኛ/ አፋርኛ የሚታተሙ ይሆናል።ህገ ወጥ የሆነ የምርጫ እቃዎች አግባብ ባልሆነ እጅ እንዳይወድቁ እቃዎቹ የሚታሸጉበት ልዩ ቁሳቁስ ለመራጮች ምዝገባም ሆነ ለድምጽ መስጫ የሚውል መሆኑ ተገልጿል።ከዚህ በተጨማሪም የህትመት ሂደቱ ጋር አብሮ የሚከናወነው ግዥ ጥቅል የሆነ ለመራጮች ምዝገባ የሚያስፈልግ ቁሳቁስ፣የማጭበርበር ሙከራ ካለ ሊያጋልጥ የሚችል የፕላስቲክ ቦርሳ እና የአጠቃቀም ስልጠናን እንደሚያካትት ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።ይህንን ህትመት የሚያከናውነው ድርጅት ለኬንያ ፣ ለኡጋንዳ፣ ለማላዊና ለዛምቢያ የምርጫ ሰነዶችን በማተም የሚታወቅና የምርጫ ስራዎችን በልዩ ሁኔታ የሚሰራ ተቋም መሆኑ ተጠቁሟል።", "passage_id": "a5717d7c2e44358a5747b654926092c0" }, { "passage": "አዲስ አበባ:- በአገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ በተፈጠረው ማህበራዊ ቀውስ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት አገር አቀፍ ምርጫውን ማካሄድ እንደማይቻል ገለፀ።\nሀገራዊ ምርጫውን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ለማከናወን ቦርዱ ተገቢ ጥረት እያደረገ በሚገኝበት ወቅት ባለፉት ሳምንታት በአገሪቱ የኮሮና ቫይረስ በመከሰቱ እንቅስቃሴዎች በመቋረጣቸው በመጋቢትና ሚያዝያ 2012 ዓ.ም መጠናቀቅ ያለባቸው\n በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ በማሳደሩ ምርጫውን ማካሄድ አይቻልም።\nቦርዱ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ምርጫውን ማካሄድ የማይቻል መሆኑን በመረዳት የወረርሽኙ ሥጋት ተወግዶ ሁኔታዎች ሲመቻቹ እንደገና ግምገማ በማድረግ አዲስ የምርጫ ኦፕሬሽን እቅድና የጊዜ ሰሌዳ በማውጣት እንቅስቃሴውን የሚያስጀምር እንደሚሆን ገልጿል፡፡\nቦርዱ ባደረጋቸው ምክክሮችና የዳሰሳ ጥናት ላይ በግልጽ የተለዩ፣ በኮቪድ 19 የማይስተጓጎሉ፣ የቦርዱን የምርጫ አፈጻጸም ዝግጁነት የሚጨምሩና ተቋሙ ወደ መደበኛ ተግባሩ እንዲመለስ ምርጫን ለማስፈጸም የሚያስችል ሁኔታን የሚፈጥሩ ተግባራትን እያከናወነ መቆየት እንዳለበት መወሰኑ ተጠቅሷል፡፡\nበህገ መንግስቱ በተቀመጠው መሰረት በሥራ ላይ የሚገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስልጣን ጊዜው ከሚያበቃበት አንድ ወር አስቀድሞ ቦርዱ አጠቃላይ ምርጫውን ማድረግ የማይችል መሆኑን ተገንዝቦ፣ የሚሰጠው ውሳኔ ቢኖር ለመነሻነት ያገለግለው ዘንድ ይህ ውሳኔ እንዲሁም ቦርዱ ያደረገው የዳሰሳ ጥናት ሰነድ ለህዝብ ተወካዮች እንዲተላለፍለት ተወስኗል፡፡ \nምንጭ፡- ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንአዲስ ዘመን መጋቢት 23/2012\nበጋዜጣው ሪፖርተር", "passage_id": "4e6d69c037e59553579c10851a520b09" }, { "passage": "አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተጽዕኖንና ስርጭትን በመከላከል ሃገራዊ ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችል መመሪያ እያዘጋጀ መሆኑን ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።መመሪያው ሁሉንም የምርጫ ሂደቶች ያካተተ መሆኑንም ነው የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ያስታወቁት።በመመሪያው ዝግጅት ላይ የህግ ባለሙያዎችን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ምክረ ሃሳብ ተካቶበት እንደሚዘጋጅም ነው የተገለፀው።ለመመሪያው ዝግጅት ግብአት ለማሰባሰብና የመፍትሄ ሃሳቦችን ለማካተት ዛሬ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር መክሯል።በምክክሩ በተለይ ፓርቲዎቹ ተንቀሳቅሰው በሚሰሩባቸው ገጠራማ አካባቢዎች በወረርሽኙ ዙሪያ ያለው ግንዛቤ ደካማ መሆኑንና የጥንቃቄ እርምጃዎች እየተወሰዱ አለመሆኑን አስተያየት ሰጪዎቹ ጠቁመዋል።በተለይ የምርጫው ጊዜ ሲቃረብ የፓርቲዎቹ እንቅስቃሴም ስለሚጨምር ከወዲሁ የግንዛቤ ማስጨበጫና ፈጣን የመረጃ ፍሰት ዘዴ ሊኖር ይገባልም ነው ያሉት።በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል ስድስተኛው የሃገራዊ ምርጫ ሰሌዳ ረቂቅም በውይይቱ ቀርቧል።በዚህም የመራጮች ምዝገባ ከጥር ወር መጨረሻ እስከ የካቲት ወር መጨረሻ፣ የእጩዎች ምዝገባ ከየካቲት መጀመሪያ እስከ የካቲት አጋማሽ እንዲሁም ከዚሁ ጋር ተያይዞ ፓርቲዎች ቅሬታና አቤቱታቸውን የሚያቀርቡበት ወቅት ከየካቲት ወር መጀመሪያ እስከ የካቲት መጨረሻ ለማድረግ ታቅዷል።በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው መሰረት የምረጡኝ ቅስቀሳ ወቅት ከየካቲት ወር መጨረሻ እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ እንዲሁም ድምፅ አሰጣጥ ከግንቦት መጨረሻ እስከ ሰኔ አጋማሽ ድረስ ይሆናል።ከምርጫው ወቅት ጸጥታ ጋር በተገናኘው የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚታየው የሰላም መደፍረስና የዜጎች ህይወት መጥፋት ሊገታ ይገባልም ብለዋል። በምርጫው ሂደት ላይም እንቅፋት እንዳይፈጥር መንግስት ከወዲሁ መፍትሄ ሊያበጅ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። በሰላማዊት ካሳ", "passage_id": "5651f9ba9d3d97dd4b4b733fb7c4d40b" }, { "passage": " የአገሪቱን ህግና ደንብ አክብረው በህጋዊነት መንገድ ለሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚያደርግላቸውን ድጋፍና ክትትል እያጠናከረ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች በበኩላቸው በቀጣዩ አመት የሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ነፃና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቦርዱ በጠንካራ የሰው ሃይል መደራጀት እንዳለበት አሳስበዋል።የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነጋ ዱፌሳ ለኢዜአ እንደተናገሩት ቦርዱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በየዓመቱ ለስራ ማስኬጃ ከሚያደርገው የፋይናንስ ድጋፍ ባሻገር ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል።በምርጫ ወቅትም አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመቀመርና የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ በማገናዘብ ለፖለቲካ ፓርቲዎች የፋይናንስ ድጋፍና የፖለቲካ አላማና ፕሮግራሞቻቸውን ለህብረተሰቡ የሚያስተዋውቁበት ነፃ የአየር ሰዓት እየሰጠ ነው።አቶ ነጋ በሌሎች አገራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሚያከናውኑት የምርጫ ቅስቀሳ የመገናኛ ብዙሃን የአየር ሰዓት በከፍያ የሚገኝ  ቢሆንም በኢትዮጵያ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ የአየር ሰዓት ድልድል በነጻ መፈቀዱን አስታውሰዋል።ፓርቲዎች መንግስታዊና  መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በሚያጋጥሟቸው ችግር ሁሉ ቦርዱ በቅርበት እየተከታተለ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አብራርተዋል።በሌላ በኩል ቦርዱ በየሁለት አመቱ ጠቅላላ ጉባኤ በማያደርጉ፣ የምርጫ ህግጋቶችን በማያከብሩና በውጭ ኦዲተር ገቢና ወጪያቸውን ለቦርዱ ሪፓርት በማያደርጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አስታውቀዋል።አቶ ነጋ እንደገለፁት በአገር አቀፍ ደረጃ በህጋዊ መንገድ ከሚንቀሰቀሱ 74 አገር አቀፍና የክልል የፖለቲካ ድርጅቶች 18ቱ ሙሉ በሙሉ የምርጫ ቦርድን መመሪያ በማሟላታቸው የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።ቀሪዎቹ 56ቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ የቦርዱን የስነ-ምግባር ደንብ ሙሉ በሙሉ ያላሟሉ በመሆናቸው በቅርብ ድጋፍና ክትትል እያደረገላቸው ነው።ቦርዱ የምርጫ መተዳደሪያ አዋጁን፣ የስነ ምግባር ደንቡንና ሌሎች ከምርጫ ጋር የተያያዙ ህጎችን ባላከበሩ ሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ባለፈው አመት ፈቃዳቸውን እስከ መሰረዝ የሚደርስ እርምጃ መውሰዱን አስታውሰዋል።በዚህም መሰረት ቦርዱ የኦሮሞ ነፃነት ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ፓን አፍሪካኒስት ፓርቲና የኢትዮጵያ ሶማሊ ልማትና ዲሞክራሲ ፓርቲ በ2005 ዓመተ ምህረት ከህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲነት መሰረዙን አስታውቀዋል።አቶ ነጋ እንዳሳሰቡት ፓርቲዎች ውህደት ሲፈጥሩ እንዲሁም የስምና የአድራሻ ለውጥ ሲያደርጉ በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት ይፋ ከማድረጋቸው በፊት ለቦርዱ ማስታወቅ ይጠበቅባቸዋል።በአገር አቀፍ ደረጃ በህጋዊ መንገድ 74 አገር አቀፍና ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ።", "passage_id": "a7857f81f30d2ca5e7b37f65662155a8" }, { "passage": "በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሲያካሂድ የነበረውን የምርጫ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።ፓርቲው ለዝግጅት ክፍሉ ትናንት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ምርጫ ቦርድ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ መደረጉን ተከትሎ ምርጫው ላይ በንቃት ለመሳተፍ እና ምርጫው ሰላማዊ፣ ነፃ እና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሲያደርግ የነበራቸውን ዝግጅቶች አጠናቆ ወደትግበራ እየገባ ነው። ለምርጫው ሲያደርግባቸው ከቆየባቸው ዝግጅ ቶች መካከል አባላት እና ደጋፊዎች በምርጫ እንቅስቃሴ ወቅት ሊመሩበት የሚገባ የምርጫ ሥነ-ምግባር መመሪያ ይፋ መሆኑን አመልክቷል። ይህ መመሪያ ቀጣዩ ምርጫ ለሀገራችን ሰላም እና መረጋጋት እንዲሁም ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ፋይዳ ከግምት በማስገባት የተዘጋጀ መሆኑን ያመለከተው መግለጫው፣ መመሪያው ለአባላት እና ደጋፊዎች ታትሞ እንደሚሰራጭ አስታውቋል፡፡ በመመሪያው ዙሪያ ሥልጠናም እንደሚሰጥ ጠቁሟል።ሌላው ዝግጅት ሲደረግበት የቆየው ተግባር የዕጩ ምልመላ ሲሆን፣ ኢዜማን በቀጣዩ ምርጫ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤቶች የሚወዳደሩት ዕጩዎች ከዛሬ ጥር 1 ጀምሮ መታወቅ ይጀምራሉ ብሏል። ኢዜማን ወክለው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ ሰዎችን ከአባላት መካከል በተቀመጠው መስፈርት እና ለምርጫ ወረዳው ጠቅላላ ጉባዔ በሚያቀርቡት ንግግር መሰረት የሚለዩበት ሥነ ሥርዓት በየምርጫ ወረዳዎቹ ከዛሬ ጥር 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚደረግም ጠቁሟል። ይህ ሥነ ሥርዓት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው ሰሌዳ መሰረት የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ.ም ለሚጀመረው የዕጩዎች ምዝገባ አስቀድሞ የዕጩዎችን ዝርዝር አውቀን እንድንጠብቅ የሚያስችል ነውም ብሏል።ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወርሃዊ ቋሚ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥበት መርሃ ግብር የሚያዘጋጅ መሆኑን ያስታወቀው መግለጫው፣ በየወሩ በቋሚ ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ በሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት እና የሚመለከታቸው ክፍሎች ከሚያደርጉት ገለፃ በተጨማሪ ጋዜጠኞች በሀገራችን እና በኢዜማ ጉዳይ ላይ እንዲብራሩላቸው የሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ ጥያቄ ማንሳት እንደሚችል ገልጿል።ሰኞ ጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫው የሚሰጥበት ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል።", "passage_id": "2ee3108796fe28598efa9e502b88e48a" } ]
524db682bbc78ef68c712ba44ad20234
85fabd60d2f0bc03b8aae8f9e4a84f37
“በኢትዮ-ሱዳን ድንበር የተፈጠረውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየተሰራ ነው” አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
 በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ በኢትዮ- ሱዳን ድንበር አካባቢ የተፈጠረውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። በዚህ ሳምንት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 328 ዜጎች ወደ አገራቸው መመለስ መቻሉን ገለጹ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስወቁት ፤ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የድንበር ውዝግብ በአሁኑ ወቅት ውጥረቱ ቀንሷል።ችግሩ እንዲፈጠር ያደረጉት ቀጠናው እንዳይረጋጋ የሚፈልጉ ኃይሎች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ የሱዳን የተወሰኑ ልሂቃኖችም ከእነዚህ ኃይሎች ጋር መወገናቸውን አመልክተዋል።“እነዚህ ኃይሎች በግልጽ የሚታወቁ ናቸው” ያሉት ቃል አቀባዩ፣ በትርምሱ የራሳቸውን አጀንዳ ለማስፈጸምና ጥቅማቸውን ለማስከበር ያለሙ መሆናቸውን አስታውቀዋል።እነዚህ ኃይሎች ለሱዳን ህዝብም ሆነ ለቀጠናው ጠቃሚ አለመሆናቸውን መንግሥት በተለይ ለሱዳን ህዝብ መልዕክት የማስተላለፍ ሥራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።ጎን ለጎንም እነዚህን ኃይሎችን የማጋለጥ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው፣ ችግሮቹን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች መቀጠላቸውን ገልጸዋል።በመግለጫቸው በትግራይ ክልል መረጋጋት መስፈኑንና ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ጠቁመዋል ።አንዳንድ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ክልሉ ላይ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በሃቀኝነት መዘገብ እንዳልቻሉ አስታውቀዋል።እነዚህ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ጉዳዩን በሚመለከት እየተከተሉት ያለው አካሄድ ትክክል ባለመሆኑ ሊታረሙ እንደሚገባም ጠቁመዋል። የውጭ ኢንቨስትመንትን አስመልክቶም የእስራኤል፤ የህንድ፣ የዱባይ፣ የቻይናና የቱርክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት አመራጮችን ለመጠቀም ፍላጎት መሳየታቸውን አመልክተዋል። “በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አማካኝነትም ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባቸው ውጭ አገራት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ናቸው” ብለዋል።በተለይ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎች ወደ አገራቸው ለመመለስ የተለያዩ ጥረቶች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህ ሳምንት ብቻ 328 ዜጎች ወደ አገራቸው መመለስ መቻሉን ገልጸዋል። ከእነዚህ ውስጥ 286ቱ ከሳዑዲ አረቢያ የተቀሩት ከሊባኖስ መመለሳቸውን ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 21/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=38465
[ { "passage": "፡- ‹‹ኢትዮጵያ ለሱዳን ህዝብ ሰላም አበክራ መስራቷን ትቀጥላለች›› ሲል የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ 68ኛው የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ የኢፌዴሪ የውጭ\nጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው ትናንት ለጋዜጠኞች እንደገለጹት ፤ ኢትዮጵያና ሱዳን\nጠንካራ ኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ትብብር ያላቸው ሀገራት ናቸው፡፡ ሱዳን ባለፉት ወራት በገጠማት ቀውስ ሱዳናውያን በሰላማዊ መንገድ ልዩነታቸውን እንዲፈቱ ኢትዮጵያ ድጋፍ ስታደርግ ቆይታለች፡፡ በተለይም በተቃዋሚዎች (በለውጥ ሃይሎች) እና በወታደራዊ ምክር ቤት መካከል በቅርቡ ተከስቶ የነበረውን ልዩነት ለማጥበብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ካርቱም በማቅናት የሱዳን የፖለቲካ ሃይሎች ልዩነታቸውን በሰላማዊ መንገድ በውይይት እንዲፈቱ አስማምተው መምጣታቸውንም አስታውሰዋል፡፡ እንደ አቶ ነቢያት ገለፃ፤ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰየሙት አምባሳደር መሃሙድ ድሪር ከነፃነት ሃይሎች እና ወታዳራዊ ሽግግር መንግስቱ ጋር በተናጥል ባደረጉት ውይይት በተወሰኑ ነጥቦች ላይ መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡ ከተግባቡባቸው መካከል ሁለቱ ወገኖች ድርድራቸውን ከማቋረጣቸው በፊት በሽግግር መንግስቱ አወቃቀር ስልጣን እና ሃላፊነት ዙሪያ ደርሰውበት ወደ ነበረው ስምምነት እንዲመለሱ ማድረግ ላይም ውይይት መካሄዱን ቃል ዓቀባዩ ተናግረዋል፡፡ በሉዓላዊ ምክር ቤት ምስረታ እና ሌሎች ጠቃሚ ጉዳዮች ዙሪያ ተቋርጦ የነበረው ውይይት በበጎ መንፈስ ልዩነቶችን ለማጥራት እንዲቀጥል ለማግባባት ጥረት የተደረገ መሆኑን ያመለከቱት ቃል አቀባዩ፤ ሁለቱም ወገኖች ጠብ አጫሪ ከሆኑ ንግግሮች እንዲታቀቡ፤ የፖለቲካ እስረኞችን እንዲፈቱና በሁለቱ ወገኖች መካከል የመተማመን መንፈስ እንዲጠነክር፣ የነፃነት/የለውጥ ሃይሎችም የህዝብ እምቢተኝነት ጥሪያቸውን እንዲያረግቡ ውይይት መካሄዱን አብራርተዋል፡፡ 68ኛው የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የገለጹት አቶ ነቢያት፣ በጉባኤው በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት የሚካሄድ ሲሆን፤ የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚም በሱዳን ጉዳይ ላይ እንደሚመክር ጠቁመዋል፡፡ የኢጋድ አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ በሱዳን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ውይይት የሚካሄድ ሲሆን፤ ኢትዮጵያም የኢጋድ ሊቀመንበር በመሆኗ ሪፖርት ታቀርባለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በ68ኛው ጉባኤ የደቡብ ሱዳን ጉዳይም ውይይት የሚካሄድበት መሆኑን ጠቁመው፤ ከአንድ ወር በፊት በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ የተካሄደው 67ኛው የኢጋድ ጉባኤ ላይ ለስድስት ወር የተሰጠው የቅድመ ሽግግር ጊዜ በአንድ ወር ውስጥ ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ እና ችግሮች ካሉም አስፈላጊውን ድጋፍ ለመስጠት ውይይቱ እንደሚካሄድም አመልክተዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የጀርመኑ አቻቸው ባደረጉላቸው ጥሪ መሰረት እ.አ.አ ከሰኔ 21 እስከ 25 ቀን 2019 ድረስ በጀርመን ይፋዊ ጉብኝት የሚያደርጉ መሆኑንም ቃል አቀባዩ አመልክተዋል፡፡ ጉብኝቱ በኢትዮጵያና በጀርመን የጋራ ጉዳዮች ላይ መምከርን ማዕከል ያደረገ መሆኑን እና በሁለቱ አገራት ከፍተኛ አመራሮች በተደረሰው ውሳኔ መሰረት የጋራ ኮሚሽን እንዲቋቋም በጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚስተር ሄኮ ማስ እና በአቶ ገዱ አማካኝነት የፊርማ ሥነሥርዓት እንደሚካሄድ ገልፀዋል፡፡ የወቅቱ ሊቀመንበር የሆነችው ግብፅ የአፍሪካ ህብረት ሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤትን በሱዳን ጉዳይ ላይ ለመምከር ስብሰባ የጠራች ሲሆን፤ ሰኔ 13 ቀን በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ቃል ዓቀባዩ አቶ ነቢያት ተናግረዋል፡፡ አዲስ\nዘመን ሰኔ 12/2011 ", "passage_id": "d447c6f595f874ec833935b6f5c1a058" }, { "passage": "በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ያለው የድንበር ጉዳይ ባሉ የሁለትዮሽ ስምምነቶች እና የጋራ የድንበር መድረኮች አማካኝነት በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ አሳሰቡ። ከሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የብሔራዊ ድንበር ኮሚሽን ተቀማጭነታቸው በሱዳን ለሆኑ ዲፕሎማቲክ ሚሽኖች፣ ቆንስላዎች እና የዓለምአቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ገለጻ አድርጓል። በዚህም ወቅት፣ አምባሳደር\nይበልጣል ከዳግልሽ ተራራ በስተሰሜን ከሰፈራ እና ከእርሻ መሬት ጋር  በተያያዘ\nየተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት\nሁለቱን ሀገራት የሚያስማማ\nየመፍትሔ ሃሳብ እንዲመጣ\nየሚደነግገው እና በሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች\nእ.ኤ.አ. ሐምሌ 18 ቀን\n1972 የተደረገው የማስታወሻ ልውውጥ ከፍ ያለ ፋይዳ እንዳለው\nአስታውቀዋል።በ1972ቱ የማስታወሻ ልውውጥ በተቀመጠው መሰረት የጉዊን መስመርን ዳግም ማካለል ከመጀመሩ በፊት ከዳግልሽ ተራራ በስተሰሜን ከእርሻ መሬት እና ሰፈራ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት የጋራ ልዩ ኮሚቴው ሁለቱን ሀገራት የሚያስማማ የመፍትሔ ሃሳብ ያካተተ ሪፖርት ለጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ማቅረብ እንደሚኖርበት አመልክተዋል።የጋራ ልዩ ኮሚቴው ሁለቱን ሀገሮች የሚያስማማ የመፍትሔ ሃሳብ ለማቅረብ ስምንት ዙር ስብሰባዎችን ቢያካሂድም ኃላፊነቱን ገና እንዳላጠናቀቀ ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ-ሱዳን ድንበር የጋራ ልዩ ኮሚቴ ስራ ባልተጠናቀቀበት ሁኔታ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በጥቅምት ወር መጨረሻ ህግ ለማስከበር ወደ ትግራይ ክልል ያደረገውን ስምሪት እንደ መልካም አጋጣሚ መጠቀሙን አምባሳደር ይበልጣል አመልክተዋል። በዚህም የሱዳን ሰራዊት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቆ በመግባት ንብረት ከመዝረፉ፣ ወታደራዊ እና የእርሻ ካምፖችን ከማቃጠሉ ባሻገር በኢትዮጵያውያን ላይ እስራት፣ ጥቃት እና ግድያ መፈጸሙ እንዲሁም በሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ማፈናቀሉን አስታውቀዋል ፤ ይህ የ1972 የማስታወሻ ልውውጥን በግልጽ የጣሰ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።በሁለቱ እህትማማች ሀገራት ጸንቶ ከቆየው አጋርነት እና ትብብር መንፈስ በተቃረነ መልኩ የሱዳን ሰራዊት አጋጣሚውን በመጠቀም\n የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ   ሰራዊት ለቋቸው የወጣ ካምፖችን መቆጣጠሩን\nጠቁመዋል።ሱዳን በችግር ውስጥ በነበረችበት ጊዜ ሁሉ ኢትዮጵያ ከሱዳን ህዝብ ጎን መቆሟን ያስታወሱት አምባሳደር ይበልጣል፤ ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይዋ በተጠመደችበት ወቅት ከሱዳን ሰራዊት የደረሰባት ጥቃት የሚገባት እንዳልሆነ አመልክተዋል።የማስተካከያ እርምጃ በፍጥነት ካልተወሰደ፣ ታይቶ የማይታወቀው የሱዳን ሰራዊት ተግባር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ብሎም የጋራ ድንበሩን ዳግም የማካለሉን ስራ የሚያወሳስብ እና ለሁለቱ ሀገራት ህዝቦች እንዲሁም ለቀጠናው ከፍ ያለ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው አስታውቀዋል።የኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ልዩነቱን ሁለቱ ሀገራት በገቧቸው ስምምነቶች እና ባሉ የጋራ የድንበር መድረኮች መሰረት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል። ለችግሩ ዘላቂ እልባት ለመስጠት ፣ የሱዳን ሰራዊት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፈጸመውን ወረራ በመቀልበስ በ1972ቱ የማስታወሻ ልውውጥ በተቀመጠው መሰረት ወደ ቅድመ-ኖቬምበር 2020 (እ.ኤ.አ.) መመለስ እንዳለበት አስታውቀዋል።ከዚህም በተጨማሪ ወደ ድንበር ዳግም ማካለል ከመገባቱ በፊት የጋራ ልዩ ኮሚቴው በ1972 የማስታወሻ ልውውጥ መሰረት ከዳግሊሽ ተራራ በስተሰሜን ከሰፈራ እና እርሻ መሬት ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ሁለቱን ሀገራት የሚያስማማ የመፍትሔ ሃሳብ የማቅረብ ስራውን ማጠናቀቅ እንዳለበት አመልክተዋል ።የጋራ ድንበሩን ዳግም ለማካለል ሁለቱ ሀገራት ያቋቋሟቸው የጋራ የድንበር ኮሚሽን፣ የጋራ የቴክኒክ የድንበር ኮሚቴ፣ እና የጋራ ልዩ ኮሚቴ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እና ስራቸውን እንዲያጠናቅቁ ማድረግ ተገቢ እንደሆነ ጠቁመዋል ።", "passage_id": "6695d2a28da370b035b3aaac016b2d35" }, { "passage": "በካርቱም እየተካሔደ በሚገኘው ሁለተኛው የኢትዮ-ሱዳን ድንበር የጋራ ከፍተኛ የፖለቲካ ኮሚቴ ውይይት ላይ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተለያዩ የሁለትዮሽ ጉዳዮችን የተመለከተ ንግግር አድርገዋል፡፡\nከጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የሱዳን ወታደራዊ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ በተደራጀ መልኩ ጥቃት እየፈጸሙ ስለመሆናቸው አቶ ደመቀ በንግግራቸው አንስተዋል፡፡ ይህ ማለት በትግራይ ክልል የተፈጠረው ቀውስ ሳምንት እንኳን ሳይሞላው ነው የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት መፈጸም የጀመረው፡፡\nአቶ ደመቀ በንግግራቸው “ከባድ የጦር መሳሪያዎችን እና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም የሱዳን ጦር የተደራጁ ጥቃቶችን እየፈጸመ መሆኑን እየተመለከትን ነው” ብለዋል፡፡ በዚህም “የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የግብርና ምርቶች ተዘርፈዋል ፤ ካምፖቻቸው ወድመዋል እንዲሁም የራሳቸውን የእርሻ ምርት እንዳያጭዱ ተደርገዋል” ያሉት አቶ ደመቀ በርካታ ንጹሀን ስለመገደላቸው እና ስለመቁሰላቸውም ገልጸዋል፡፡ እናም በድንበር አከባቢዎች የተከሰተው የቅርብ ጊዜ ክስተት የኢትዮጵያን መንግስት ክፉኛ እንዳሳሰበው ነው በንግግራቸው ያካተቱት፡፡ ም/ጠ/ሚኒስትር እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ይህ ሁኔታ በሰሜን ዳግልሽ ተራራ አካባቢ ያለውን ሁኔታ ባለበት ለማቆየት የደረስናቸውን ስምምነቶች አደጋ ላይ እየጣለ ነው” በማለት ስጋታቸውንም ገልጸዋል፡፡\n“በድንበር አካባቢ ባሉ ማህበረሰቦች መካከል መልካም ግንኙነትን ለመፍጠር ፣ የድንበር ጉዳዮችን ለመፍታት እና ሰላምን እና ደህንነትን ለማስጠበቅ” ባለፈው ግንቦት ወር አዲስ አበባ ላይ ፍሬያማ ውይይት ተደርጎ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡ ይሁንና “በቅርብ ጊዜ የተመለከትነው ሁኔታ በሁለታችን ሀገራት መካከል ካለው መልካም ግንኙነት ጋር የሚጻረር ነው” ሲሉም የተፈጠረውን ድርጊት አውግዘዋል፡፡\nስለሆነም ከዚህ ቀደም የነበሩትን አሰራሮች በመተግበር መፍትሄ መፈለግ ለጋራ የድንበር ጉዳዮች ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ብቸኛው መንገድ መሆኑን ነው የጠቀሱት፡፡ አቶ ደመቀ አክለውም “አላስፈላጊ ውጥረትን መፍጠር በድንበር አከባቢ ያለውን ሁኔታ ከማባባስና ትርጉም የለሽ ስጋት ከመፍጠር ባሻገር በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦቻችንን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚያደናቅፍ እንደሆነ እናምናለን” ብለዋል፡፡\n“ሁልጊዜም የኢትዮጵያ እና የሱዳን ግንኙነት ምልክት በሆነው ወንድማዊ ትብብር እና ቁርጠኝነት” ችግሮችን መፍታት እንደሚቻል ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል፡፡\nአሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ መንግሥት ፣ በሁለትዮሽ ፣ በቀጣናዊ እና ዓለማቀፋዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ ከሱዳን መንግስት ጋር በቅርበት ለመስራት ጽኑ አቋም እንዳለውም አረጋግጠዋል፡፡\nየሱዳን መንግሥት በትግራይ ክልል በነበረው የሕግ ማስከበር ሂደት ድጋፍ ማድረጉን በመግለጽ ለዚህም አቶ ደመቀ መኮንን ምስጋና አቅርበዋል፡፡\n", "passage_id": "b44afd76605ed26e59d3048830ac3654" }, { "passage": "አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከትግራይ ክልል ወደ ሱዳን በገቡ ኢትዮጵያውያን ዙሪያ የኢትዮጵያ መንግስት ከሱዳን መንግስት ጋር በሁሉም መስክ ተባብሮ እየሰራ መሆኑን በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ገለፁ።በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ከስካይ ኒውስ የአረብኛ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል።በዚህም መንግስት በትግራይ ክልል የጀመረው ሕግ የማስከበር እርምጃ ጥቂት ወንጀለኞችን ለህግ ለማቀረብ የሚደረግ ዘመቻ መሆኑን አስታውቅዋል።ይህም ማንኛዉም መንግስት የሚያደርገዉ እንደሆነ የገለፁት አምባሳደሩ ማንም መንግስት ህግ እየተጣሰ ቁጭ ብሎ የሚያይበት ሁኔታ እንደሌለ ገልጸዋል።የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ በሚገኘው እርምጃ ምክንያት ችግሩ አካባቢያዊ ሊሆን የሚችልበት እድል እንደሌለ ጠቅሰዋል።በህግ ማስከበረ ሂደት ከቀያቸዉ ተፈናቀለው ወደ ሱዳን የገቡ ኢትዮጵያውያን በተለይም የምዕራቡ ትግራይ ክፍል ሙሉ በሙሉ ሰላም የተረጋገጠ በመሆኑ በቅርቡ ወደ ቀያቸው እንደሚመለሱ አረጋግጠዋል።ከዚህ ጋር በተያየዘ ከሱዳን መንግስት ጋር በሁሉም መስከ በትብብር እየሰሩ መሆኑንም አምባሳደሩ አስገንዝበዋል።", "passage_id": "70639e5c4f1de399e381296c592e7f09" }, { "passage": "የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤትና የሚኒስትሮች የጋራ ምክር ቤት ሀገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የድንበር ውዝግብ በተመለከተ ወደ ጎረቤት ሀገራት ጉብኝት እንዲደረግ መወሰኑን አስታወቀ፡፡\nየሀገሪቱ ባለሥልጣናት ወደ ካይሮ፣አስመራ፣ጁባና ሳዑዲ አረቢያ በመሄድ ጉዳዩን እያስረዱ ነው ተብሏል፡፡ በዚህም መሰረት የሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤቱ አባል ሌፍተናንት ጄነራል ሻምሰዲን ካባሺ በደቡብ ሱዳን፣ የሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤቱ ምክትል ሊቀመንበር ሌፍተናንት ጄነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ ወደ ኤርትራ፣ የሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤቱ አባል ሌፍተናንት ጄነራል ኢብራሂም ጃቢር ወደ ቻድ፣ መሐመድ ፋኪ ሱሌማን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ጉብኝት አድርገዋል፡፡\nየሀገሪቱ ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦማር ቀመረዲን፣ የስለላ ኃላፊው ጄነራል ጃማል አዲን ኦማር ፣የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ፋይሳል መሐመድ ሳሊህ እና የሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤቱ አባል ሌፍተናንት ጄነራል ሻምስ ኢል ዲን ካባሺ ዛሬ ወደ ካይሮ አቅንተዋል፡፡\nየኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ማክስኞ ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “ኢትዮጵያ ይህንን ችግር ማጉላት ያልፈለገችው ጉዳዩን ቀጠናዊ ላለማድረግ ነው” ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን ሱዳን ግን ባለሥልጣኖቿን ወደ ተለያዩ ሀገራት መላኳን ቀጥላለች፡፡\n“በጉዳዩ ላይ ሱዳንን የሚገፉ ሌሎች ከጀርባ ያሉ አካላት ስላሉ የነሱን ካርድ ላለመጫወት ነበር ዝም ያልነው ፣ ይህ ግን እንደፍርሀትና እንደመወላወል መቆጠር የለበትም” ሲሉ አምባደር ዲና መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ በትናንትናው ዕለት ድንበር አካባቢ ከሀገሪቱ ጦር ጋር ቆይታ ያደረጉት የሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤቱ ሊቀመንበር ሌፍተናንት ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ፣ “ከጀርባችን ማንም የለም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡\nሌፍተናንት ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ለሀገሪቱ መከለከያ ሰራዊት አመራሮችና አባላት መመሪያ መስጠታቸው ተዘግቧል፡፡ ሊቀመንበሩ በድንበር አካባቢ ባደረጉት ጉብኝት ቦታው የሱዳን በመሆኑ ከዚህ ስፍራ አንወጣም ማለታቸውን የሱዳን ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡\nየሱዳን ጦር ድንበር ጥሶ የኢትዮጵያን ግዛት መቆጣጠሩን የገለጸው የኢትዮጵያ መንግስት ፣ ሱዳን ከሰላማዊ መንገድ ውጭ የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንድታቆም በተደጋጋሚ ጠይቋል፡፡ በድንበር ጉዳይ ስምምነት ላይ መድረስ እንዲቻል ሱዳን የ1972ቱን (እ.ኤ.አ) ስምምነት እንድታከብር እና ከያዘችው መሬት ወጥታ ወደ ቀድሞ ስፍራዋ እንድትመለስ ኢትዮጵያ አሳስባለች፡፡ ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር ዘመቻ መጀመሯን ተከትሎ በተፈጠረው ክፍተት ፣ ዘመቻው ከተጀመረ ከ 6 ቀናት በኋላ ሱዳን በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ወደ ኢትዮጵያ ዘልቃ መግባቷን የኢትዮጵያ መንግስት ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ በዚህም የንጹሃን ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በርካታ ንብረትም ወድሟል ነው የተባለው፡፡\n", "passage_id": "0adb871c23320a3b3295941c12d0ae6c" } ]
fc8b0678f5fba8360725682e416e1991
f808482971c9194089aaa4d0c11afee5
አስከፊውን ጊዜ በብልሃት የማለፍ ጅምር
የዓለም ሕዝብ ሁሉ ጭንቀትና ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከትንሽ እስከ ትልቅ፣ ከሀብታም እስከ ድሃ፣ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ዋነኛ ትኩረቱ እንዲሆን ካስገደደ ሰንብቷል፡፡ የቫይረሱ ስርጭት እንደ ሰደድ እሳት ያላዳረሰው የዓለም ክፍል የለም፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዓለም ሕዝቦች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ከቫይረሱ ቢያገግሙም የሟቾች ቁጥር ይህ ነው በማይባል ፍጥነት እየጨመረ ይሄዳል:: ከሁሉም በላይ በቫይረሱ ስጋት በየቤቱ የከተመው የዓለም ሕዝብ ጭንቀትና ድብርት ውስጥ እንዲገባ ማስገደዱ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እየሆነ ይገኛል፡፡ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የዓለምን ሕዝብ ያጠቃው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያልገባበበት ቤት፣ ያላንኳኳው በር የለም፡፡ ከዓለም ታላላቅ አገራት መሪዎች እስከ ተራው ሕዝብ፣ ከዝነኛ ሰዎች እስከ ሕፃናትና አዛውንት ድረስ የዚህ አስከፊ ወረርሽኝ ተጠቂ ሆነዋል፡፡ ቫይረሱን ለመቋቋም በሽታን የመመከት ከፍተኛ አቅም ያላቸው የስፖርቱ ዓለም ሰዎች ሳይቀሩ በዚህ ወረርሽኝ ተለክፈዋል፣ ሕይወታቸውን ያጡም ጥቂት አይደሉም፡፡ የስፖርት ቤተሰቡ በቫይረሱ ስርጭት ስጋት የዓለም ታላላቅ የስፖርት መድረኮች ተቆልፈውበት ሁነኛ የመዝናኛ አማራጩን አጥቶ በየቤቱ ቆዝሟል፡፡ የስፖርቱዓለም ታላላቅ ከዋክብትም ረብጣ ገንዘብና ዝናቸው ከደጃፋቸው እንዲወጡ አቅም አልሆናቸውም፡፡ ይሄ ክፉ ጊዜ እስኪያልፍ ሁሉም በየቤቱ እንዲቆይ ማድረግ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የተሻለ አማራጭ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅትና መንግሥታት በየጊዜው ሲወተውቱ ይታያሉ፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ኢኮኖሚያቸው ዝቅተኛ የሆኑ አገራት ዜጎች የተሻለ የመዝናኛ አማራጭና በየቤቱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚቸገሩ መሆናቸው ከጭንቀትና ድብርት ጋር ተያይዞ ለሚመጣው ቀውስ ተጋላጭ እንደሚሆኑ ይታመናል፡፡ ይህ አስቸጋሪ ጊዜ እስኪያልፍ ከስፖርቱ አኳያ ማህበረሰቡ በያለበት ሆኖ እንቅስቃሴዎችን እንዲያደርግ መላ መዘየድ እንደሚያስፈልግ ግልፅ ነው፡፡ ለዚህም የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ትናንት የወሰደው ርምጃ አንድ ምሳሌ ይሆናል፡፡ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ግቢ እና በረንዳዎች ላይ ርቀትን በመጠበቅ ቀለል ያሉ የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በመስራት ኅብረተሰቡ ከኮሮና ቫይረስ እራሱን እንዲጠብቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል፡ በአዲስ አበባ ከተማ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ባሉ በረንዳ ላይ ቀለል ያሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በማካሄድም ግንዛቤ ፈጥሯል:: በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ሳቢያ በአዲስ አበባ ከተማ ሁሉም የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎች ዝግ መሆናቸው ይታወሳል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ከፊት ኮርነር ስፖርት ጋር በመቀናጀት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በረንዳ ላይ ነዋሪዎች በተገኙበት ተገቢውን ርቀት በመጠበቅ የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሰርተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አረጋይ፣ «የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር በቤታቸው ተወስነው ያሉ ነዋሪዎች በቤታቸው ሆነው ቀለል ያሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ከጭንቀት እና ከድብርት ተላቀው ጤናማ ኑሮ እንዲኖሩ ያስፈልጋል» ማለታቸውን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት መረጃ ያመለክታል፡፡ ኅብረተሰቡም የማህበራዊና አካላዊ ርቀቱን ጠብቆ በዚህ ጊዜ በመጠኑ አካላዊ አዝናኝ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ያለጭንቀት ጤናውን በመጠበቅ ይህን አስከፊ ጊዜ ማለፍ እንደሚኖርበት ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል፡፡ በቀጣይም በሌሎች የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ኅብረተሰቡ የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲሰራ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑን ኮሚሽነር ዮናስ ተናግረዋል። በአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ፕሮግራም ላይ ከነዋሪዎች በተጨማሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አመራሮች ኮሜዲያን እና የስፖርት ባለሙያዎች ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 30/2012 ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=30017
[ { "passage": " ኦ ሊምፒክ ከጤና ስጋት ጋር የተያያዘ ባይሆንም በተለያዩ ጊዜዎች የመሰረዝና የቦታ ለውጥ ሲደረግበት ታይቷል፡፡ እኤአ የ1916 የበጋ ኦሊምፒክ በጀርመን በርሊን ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት በአንደኛ የዓለም ጦርነት ሳቢያ ተሰርዟል:: በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅትም የ1940 የክረምት ኦሊምፒክና የ1944 የበጋ ኦሊምፒክ ውድድሮች የመሰረዝ እድል ገጥሟቸዋል:: እኤአ የ1976 የክረምት ኦሊምፒክም በዴንቨር ኮሎራዶ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የኮሎራዶ ግዛት ሕዝብ ለውድድሩ የሚወጣውን ወጪ በመቃወሙ ውድድሩ የቦታ ለውጥ ተደርጎበት በአውስትራሊያ ኢንስብረክ ለመካሄድ ተገዷል፡፡ ዩ ኤስ ኤ ቱዴይ በወቅቱ እንደዘገበው የኮሎራዶው ኦሊምፒክ የቦታ ለውጥ እንዲደረግበት ውሳኔ ላይ የተደረሰው ውድድሩ ከመካሄዱ ከሦስት ዓመታት አስቀድሞ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ኦሊምፒክ በታሪክ ተራዝሞ የሚያውቅበት አጋጣሚ አልነበረም:: ዓለም በአሁኑ ወቅት እየተሸበረችበት በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት ግን የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ለአሥራ ስድስት ወራት ሲራዘም በታሪከ የመጀመሪያው ለመሆን በቅቷል፡፡ ይህም ለዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴና ለውድድሩ አዘጋጆች አዲስ ተሞክሮ ብቻ ሳይሆን አዲስ ፈተና ይዞ መምጣቱ አልቀረም፡፡ ይህን አዲስ ፈተናም ለመጋፈጥና ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮችን ከወዲሁ ለማስተካከል ዓለም አቀፍ ኮሚቴውና አዘጋጆቹ ከወዲሁ ሌት ከቀን እየሰሩ እንደሚገኙ ሰሞኑን ገልፀዋል፡፡ የኦሊምፒክ ስፖርቶች ዳይሬክተሩ ክሪስቶፍ ዱቢ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ‹‹ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ውስብስብ ብቻ ሳይሆን አዲስ ፈተና ገጥሞናል›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከጃፓን መንግሥት ጋር በመሆን ይህን ፈተና ለመወጣትና አሁን ዝግጁ የሆኑ ነገሮችን ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ ተግባራዊ እንዲሆኑ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡ ይህም ማለት ኦሊምፒኩ ከመራዘሙ አስቀድሞ በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ ዝግጁ የነበሩ የኦሊምፒክ መንደሮችን፣አርባ አንድ ዋነኛየውድድር ቦታዎች፣ ከአርባ ሺ በላይ የሆቴል ክፍሎች፣ከሁለት ሺ በላይ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን እንዲሁም አገልግሎትና በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ ቁሶችን ለማቅረብ የተደረጉ ውሎችን መልክ ማስያዝና ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ ተግባራዊ የሚሆኑበትን አቅጣጫ የማስቀመጥና መልክ የማስያዝ ሥራዎች ከወዲሁ እየተሰሩ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የዓለምን እንቅስቃሴ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሽባ ያደረገው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ነገሮችን መልክ ለማስያዝ በሚያደርገው እንቅስቃሴ አሁንም ፈተና እየሆነ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ አልሸሸጉም፡፡ ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ከተጠቀሱት ፈተናዎች በተጨማሪ ሌሎችም እንቅፋቶች ይኖሩበታል:: ከውድድር ጋር በተያያዘ ለኦሊምፒኩ አስፈላጊውን መስፈርት (ሚኒማ) በተለያዩ ስፖርቶች አሟልተው የነበሩ በሺ የሚቆጠሩ አትሌቶች መስፈርታቸው ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ ለሚካሄደው ኦሊምፒክ ይስራ አይስራ እርግጠኞች አይደሉም፡፡ በኦሊምፒክ ለመሳተፍ በየትኛውም ስፖርት አንድ አትሌት መስፈርቶችን ማሟላት የግድ ይለዋል፡፡ ከአስራ ስድስት ወር በፊት መስፈርት ያሟላ አትሌት ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ ያሟላል ወይም አሁን ያለውን አቋም ይዞ ይቆያል ማለት አይቻልም፡፡ የተራዘመው ኦሊምፒክ ሲቃረብ አትሌቶች ዳግም መስፈርት አሟልተው ይወዳደሩ ማለት ደግሞ ሌላ ጣጣ ይዞ ይመጣል፡፡ ዛሬ መስፈርቱን ያሟላ አትሌት ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ ዳግም ላያሟላ ይችላል፡፡ ስለዚህ ይህን ጉዳይ ለማስተካከል ራሱን የቻለ ትልቅ የቤት ሥራ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ይሁን እንጂ የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ኃላፊው ኪት ማክኮኔል አሁን መስፈርቱን ያሟሉ አትሌቶች ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ መስፈርታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ይቆያል ብለዋል፡፡ ይህ በራሱ ግን ኋላ ላይ ጭቅጭቅ አለማስነሳቱን እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ ከሰላሳ ሦስት ዓለም አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖች ከአስራ አንድ ሺ በላይ አትሌቶች መስፈርቱን አሟልተው ለውድድር እየተዘጋጁ ባሉበት ሁኔታ ኦሊምፒኩ መራዘሙ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን በኦሊምፒክ እግር ኳስ ውድድር የሚሳተፉ የወንድ ተጫዋቾች እድሜ ከሃያ ሦስት እስከ ሃያ አራት መሆን እንዳለበት ይታወቃል፡፡አሁን ኦሊምፒኩ በመራዘሙ በርካታ ተጫዋቾች ከዚህ እድሜ ሊያልፉ መቻላቸው ሌላው ፈተና ይሆናል፡፡ ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴም ይህን ጉዳይ መልክ ለማስያዝ ጉዳዩ ከሚመለከተው ፊፋ ጋር በቅርቡ ውይይት ለማድረግ እንዳሰበ ተጠቁሟል፡፡ ኦሊምፒኩን በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ለማስተላለፍ የተዋዋለው የአሜሪካን ኩባንያ ኦሊምፒኩ በሚካሄድበት ወቅት ከምንም በላይ የሚጠብቀው የኤንቢኤና ሌሎች ታላላቅ የአሜሪካን ቅርጫት ኳስ ውድድሮች ስለሚኖሩበት የፍላጎትና የጥቅም ግጭቶች ሊፈጠር ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ አንዱን ወገን በቢሊዮን ዶላሮች ኪሳራ ላይ ሊጥል ስለሚችል ከባድ ፈተና እንደሚሆን ይታመናል:: በተመሳሳይ ከዚህ ዓመት የተላለፉ በርካቶቹ ዓለም አቀፍ ውድድሮች የሚካሄዱበት መሆኑ ሌላ ጣጣ ይዞ መምጣቱ አይቀሬ ነው፡፡ በነዚህ ወራት ከሚካሄዱ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች መካከል የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናና የዓለም ውሃ ዋና ቻምፒዮና ዋነኞቹ ቢሆኑም ውድድራቸውን ለመሰረዝ ፍቃደኛነታቸውን መግለፃቸው ይታወቃል፡፡ ይህ አበረታችና ለዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተስፋ የሰጠ ቢሆንም በነዚህ አካላት መካከል ተጨማሪ የውል ስምምነት እንደሚኖር ይጠበቃል፡፡ ይህ ምናልባትም ሌሎቹ ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኖችም ለኦሊምፒክ ቅድሚያ እንዲሰጡ ማነሳሳት ቢችልም ወቅቱ በጣም ከፍተኛ ሙቀት የሚኖርበት መሆኑ ለውድድሮች አስቸጋሪ እንደሚሆን ስጋት አሳድሯል:: ምንም ይሁን ምንም ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ብቻ የጃፓን መንግሥትን ጨምሮ በርካታ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ውስጥ እንደሚገቡ ቀደም ሲል ተዘግቧል፡፡ የጃፓኑ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴም ገና ከመጀመሪያው ከፍተኛ ኪሳራ ሊገጥም እንደሚችል ተናግሯል፡፡ ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለዚህ ኪሳራ ስጋት ሰላሳ ሦስቱንም ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኖች የሚመለከት መድህን የገባ ቢሆንም በቂ እንደማይሆን ታምኖበታል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ቶማስ ባኽም ኦሊምፒኩ መራዘሙን በገለፁበት ወቅት ከባድ ኪሳራ እንደሚኖር በማመን ሁሉም ባለድርሻ አካላት መስዋዕትነት መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ለመጠቆም ሞክረዋል:: ከባዱን መስዋዕትነት ማን እንደሚከፍልና ጫናው በየትኛው ወገን ትከሻ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ግን ዛሬ ላይ ቆሞ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 28/2012 ቦጋለ አበበ", "passage_id": "a6817872051fa117ab913c4d9ad9c3f2" }, { "passage": "ለአንድ አገር ስፖርት ውጤታማነት ማንሰራሪያና የትንሳኤ ማብሰሪያ መላና ምክንያት ከሆኑት ውስጥ በተለይ በዋና ከተሞች የሚካሄዱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተጠቃሾች ናቸው። የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን በአዲሱ ዓመት – የዓመታት ቁጭቴን በእርካታና በተስፋ ለመሙላት እንዲሁም ለስፖርቱ ትንሳኤ የምችለውን ለማከናወን ቆርጬ ተነስቻለሁ” ብሏል፡፡ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ጋር ቆይታ ያደረጉት አቶ ዮናስ አረጋይም የኮሚሽኑን ተግባራትና መፃኢ ተስፋ አብራርተዋል፡፡ አዲስ ዘመን፡- የከተማ አስተዳደሩ\nበ2011 ዓ.ም በስፖርቱ ዘርፍ ካከናውናቸው ተግባራት መካከል እንደ ስኬት ያስመዘጋባቸው ምን ምን ጉዳዮች ነበሩ? አቶ ዮናስ፡- በስኬት ደረጃ ያስቀመጥናቸው አምስት ጉዳዮች ናቸው፡፡ የመጀመሪያው አጠቃላይ መዋቅሩን ከታች እስከ ላይ እንዲለወጥ\nአድርገነዋል፡፡ የማያስፈልጉ መዋቅሮችን አስነስተናል፡፡ የተሻሉ መዋቅሮችን ደግሞ ወደፊት እንዲሄዱ አድርገናል፡፡ ለምሳሌ፤ የማያስፈልገው\nአንዱ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ነው፡፡ እሱን አንስተን ኮንስትራክሽን ቢሮ ይመለከተዋል ብለን ሰጥተነዋል፡፡ ስፖርት ኮሚሽኑ የማዘውተሪያ\nስፍራ ያስፈልገናል የሚል ጥያቄ ማቅረብ እንጂ፤ መሐንዲስ በሌለበት የማዘውተሪያ ግንባታ ማካሄድ አይደለም፡፡ ኮሚሽኑ በስፋት የስፖርት ከፍተኛ ባለሙያዎች አልነበሩትም፡፡ ስለዚህ\nከሚሽኑ በሚያስተዳድራቸው እንደ ራስ ኃይሉ፤ አበበ ቢቂላ፤ ጃንሜዳ፤ አራት ኪሎ ሥልጠና ማዕከላት ሁለት ሁለት ከፍተኛ ባለሙያዎች\nእንዲመደቡ አድርገናል፡፡ እነዚህ ማዕከላትም አብዛኞቹ ስፖርትንና የስፖርትን ሥራ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ሆኗል፡፡ ይህም በተሻለ\nደረጃ ተተግብሯል፡፡ የማያሰሩ ማነቆዎች የተባሉትን በጠቅላላ በባለሙያ በተደገፈ ጥናት ፈትሸን ለማየት ጥረት አድርገናል፡፡ ከዚህ\nጋር ተያይዞ ለውጥ ባደረግንበት ልክ የሰው ሃይላችንን የመደልደል ሥራም ሠርተናል፡፡ የዚህ ውጤትም የስፖርት ኮሚሽን ከዚህ በፊት\nየነበረውን እንደ ልብ እንዳይሠራ ያደረገውን አሠራር ለማረምና አዲስ አበባ ያጣቸውን የስፖርት ማዕከልነቷን ለመመለስ ነው፡፡ ይህንን\nትኩረት አድርገን ስንሰራም በመዋቅሩ ዙሪያ ምን መደረግ አለበት ብለን ከፍተኛ ግምገማ አድርገናል፡፡ ሌላኛው፤ እንደ መንግሥትም ሊበራታታ የሚገባው ጉዳይ በቀደመው አደረጃጀት የወጣቶች ጉዳይና ስፖርት በጋራ የነበረ\nሲሆን፤ ስፖርት ራሱን ችሎ ይሂድ የሚል መዋቅር የመጣውም በዚህ ዓመት ነው፡፡ ሁለተኛው፤ የስኬት ተግባር የማዘውተሪያ ሥፍራን የተመለከተ ነው፡፡ ምንም እንኳን የአዲስ አበባን ጥያቄ በሚመጥን\nመልኩ ተመልሷል ባይባልም ትናንት የነበሩትንና ያደሩትን ውዝፍ ሥራች ግን ማገባደድ ችለናል፡፡ ለምሳሌ፤ የአበበ ቢቂላ ስታዲየም\nየረጅም ጊዜ የግንባታ ችግር ነበረበት፡፡ የማስፋፊያ ችግር ነበረበት፡፡ ከተማዋንም የሚመጥን አልነበረም፡፡ አሁን ግን ከተማዋን\nበሚመጥን መልኩ የወንበር፤ የትራክና የጣራ ሥራዎች ተጠናቅቀው አጠቃላይ ሥራው ወደ 95 በመቶ ያህል አልቋል፡፡ ከ105 ሚሊዮን\nብር በላይም ወጭ ተደርጎበታል፡፡ ከህዳሴ ግድብ እኩል የተጀመረው የሜዳ ቴኒስና የዓለም አቀፍ መዋኛ ገንዳውም በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀንና ሌሊት\nእየተሠራ እንዲጠናቀቅ ተደርጓል፡፡ የቀረን ውሃ መሙላትና መሞኮር ብቻ ነው፡፡ ሁለቱም የመዋኛ ስፍራዎች፤ ማለትም የህፃናቱም የአዋቂውም\nተጠናቅቀዋል፡፡ ይህም ከ500 ሚሊዮን በላይ ወጭ ተደርጎበታል፡፡ ከዚህ በፊት የተጀመሩትን ሥራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ከማድረግ\nአኳያ በርካታ ሥራዎች የተሰሩበት ወቅት ነበር፡፡ እዚህ ላይ ሊታሰብ የሚገባው ቁምነገር ግዙፍ የሆኑ ሜጋ ፕሮጀክቶችን መሥራት አይደለም\nትልቁ ነገር፤ ዋናው ነገር ተደራሽ በሆነ ሁኔታ አነስ አነስ ያሉ ማዘውተሪያ ቦታዎችን መሥራት ነው የሚያዋጣው፤ በመሆኑም፤ በ2012\nዓ.ም የምንሰራቸው እንዳሉ ሆነው በአፈጣኝ ግን በ117ቱም ወረዳዎች የጥርጊያ ሜዳ መሥራት አለብን ብለን ተነስተን 61 ቦታዎች\nተሳክተውልናል፡፡ አዲስ አበባ የነበራትን ነባር ሜዳ በማጣት ነው እንጂ የምናሳልፈው አዲስ ሜዳዎች ሲጨመሩ ብዙም የተለመደ አልነበረም።\nይህ በሁለተኛው የዕቅድና ትራንስፎርሜሽን ዘመን ያልሠራነውን ነው በዚህ ዓመት ማሳካት የቻልነው፡፡ ከዚህ ውጭ 63 ቦታዎች የይዞታ\nማረጋገጫ ካርታም አስወጥተናል፡፡ አንዳንዱ ቦታ ካርታ ስለሌለው ማንም ባዶ ቦታ ሲያይ መጥቶ ይገነባል፡፡ ይህ እንዲቀርም ተደርጓል፡፡\nሦስተኛው፤ የታዳጊዎችን ፕሮጀክቶች ከአዲስ አበባና\nከኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በዝርዝር እንዲገመገሙ አድርገናል፡ ፡ ገልለተኛ አካላቱ ፕሮጀክቱን ሲያጠኑ እስከዛሬ\nበነበረው አሠራራችን ላይ ችግር እንደነበር አመላክተዋል፡፡ በእርግጥ የተወሰኑ ፕሮጀክቶች የተሻሉ መሆናቸውም ታይቷል፡፡ በድምር\nውጤቱ ግን በአዲስ መንገድ መሄድ እንዳለብን ያመላከቱ ናቸው፡፡ ወደ 132 የሚሆኑ ጣቢያዎች ላይ በነበሩ እንቅስቃሴዎች ከአራት\nሺህ አምስት መቶ  በላይ ልጆች የታቀፉበት ሥራ ግን በስኬት\nየሚታይ ነው፡፡ እነዚህም አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ ስለዚህ ታዳጊዎች ላይ በአዲስ ዓመት አዲስ ሐሳቦች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡\nበተመረጡ ቦታዎች ላይ ብቻ ለመስራት ነው ዕቅድ የተያዘው፤ በዚህ ዓመት በዘጠኝ የስፖርት ዓይነቶች እስከ ሦስት ዓመት ድረስ ካልሰራን\nመወዳደሩ አይጠቅምም የሚል አቋም ላይ ነን፡፡ በነገራችን ላይ፤ አዲስ አበባ ላለፉት ስድስት ዓመታት ከስፖርት ማዕከልነቷ ወጥታ\nበአገር አቀፍ ውድድሮች ስድስተኛና ሰባተኛ ደረጃ ነበር ይዛ የምታጠናቅቀው፤ ስህተታችንን ስላወቅን በትክክል በሰራነው ላይ ብቻ\nበመሳተፍ ያልሰራነውን በመተው ጥራት ላይ ት ኩረት ማድረግ ጀምረናል፡፡ በአራተኛ ደረጃ፤ ለአጠቃላይ ባለሙያዎች ሠፋፊ ዓለም አቀፍ ይዘታቸውን\nየጠበቁ ሥልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡ የመጨረሻና ትልቁ ሥራ ደግሞ የማስ ስፖርትን የማጠናከሩ ተግባር ነው፡፡ ስፖርት መሰረቱ ማስ ስፖርት\nነው። ይህም በኢትዮጵያ የስፖርት ፖሊሲ ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ማስ ስፖርት ባህል ሆኖ እንዲቀጥልም የተሻለ ሥራ ተሠርቷል፡፡\nአዲስ ዘመን፡- እነዚህን\nስኬታማ ተግባራት ስታከናውኑ ምንም ሳንካ አልነበረም ማለት ነው? አቶ ዮናስ፡- ቀላል የማይባሉ ችግሮች ነበሩብን፡፡ መዋቅር ሲስተካከል በክፍለ ከተማ ላይ በስፖርት የሰለጠኑ ብቻ ናቸው የስፖርት\nዘርፍ ዳይሬክተር መሆን ያለባቸው ስንል በማኔጅመንትና በኢኮኖሚክስ የጨረሱ ነበሩ የተመደቡት፤ ይህንን ለማስተካከል ችግር ፈጥሮ\nነበር፡፡ በሌላ በኩል፤ ታዳጊዎች ላይ አሁንም ቀላል የማይባሉ ማነቆዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ፦ አንዱ ችግር የእድሜ ማጭበርበር ነው፡፡\nአሾልኮ የሚያስገባውም የሚገባውም ትስስር ያላቸው ናቸው፡፡ ልምምድ በአግባቡ ያለመስራት፤ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በተሻለ ፍጥነት\nየፍፃሜ ሥራዎችን አለማከናወን፣ በቢሮ በኩል ደግሞ ትጥቅ አለማድረስ፤ አበልና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ማዘግየት፤ እልፍ ሲል ደግሞ\nየጥራት ጉድለቶችም እንዳሉ አስተውለናል፡፡ በፈፃሚዎች መካከል ያሉ ድክመቶችም ተስተውለዋል፡፡ ከዚህ ውጭ አዲስ አበባ ላይ የማዘውተሪያ\nሥፍራ ችግር ቀላል አይደለም፡፡ በተለይ በልማት ምክንያት ተነሽ በሆኑ አካባቢዎች አንድ ስንዝር መሬት እንኳን ማግኘት ችግር ነበር፡፡\nማስ ስፖርቱን ቁልፍ ጉዳይ አድርጎ አለመግምገም እንዲሁ እንደ ክፍተት የሚታይ ነው፡፡ እንደ ካርኒቫልና ፌስቲቫል ከማየት በዘለለ\nበእያንዳንዱ ወረዳ ላይ እንዲተገበር በማድረግ ረገድ ችግር አለ፡፡ የመጨረሻው አንዱ ችግር የአዲስ አበባ ስታዲየም ጉዳይ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ሁሉም ክልሎች ስታዲየም አላቸው፡፡\nበፌዴራል የሚተዳደር ስታዲየም የላቸውም፡፡ የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን መሥራት ያለበት በስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ ነው እንጂ ክልሎች\nበሚሰሩት ጉዳዮች ላይ መካተቱ ስፖርቱን ያዳክመዋል የሚል እምነት ነው ያለኝ፤ እኛም የአዲስ አበባ ስታዲየም ሜዳው ይሰጠን ብለን\nአመልክተናል፡፡ ይህንን እየጠበቅን ነው፡፡ በተለይ በስታዲየሙ ዙሪያ ያለው የአልኮል መጠጥ ንግድ ቤቶች በስፖርቱ ላይ ከፍተኛ ማነቆ\nእንዲፈጠር አድርገዋል፡፡ በመሆኑም ስታዲየሙን ተረክበን አልምተን ለከተማዋ ማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሰጥ እናደርጋለን፡፡ ይህ\nሲሆን ደግሞ የሚገጥመውን የፋይናንስ ችግር ለመቅረፍ ያግዛል፡፡ አዲስ ዘመን፡- ወርሐዊው\nየማስ ስፖርት ተሳትፎ ለፖለቲካ ፍጆታ እንጂ ስፖርታዊ መሠረት የለውም የሚሉ አካላት አሉ። አርስዎ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ይላሉ?\nስፖርታዊ ክንዋኔውስ ከታለመለት ዓላማ አንፃር ምን ያህል ውጤታማ ነበር? አቶ ዮናስ፡- በመሰረቱ ስፖርት ከዘር፤ ከሃይማኖትና ከፖለቲካ የፀዳ ነው፡፡ የኦሊምፒክ ውድድሮችን ብዙ ጊዜ በከተማችን ውስጥ\nስናካሄድ ቆይተናል፡፡ ስፖርትን የሚያጠናክረው ሠላም ነው፤ የሚያፈርሰውም የሰላም እጦት ነው። አገራችን ውስጥ በሚፈጠር ችግር የስፖርቱ\nቤተሰብ ለሰላሙ አቅም ካልሆነ ስፖርት ምንም አይጠቅመንም፡፡ ስፖርት ለአገራችን አንድነትና ፍቅር ጠንካራ የሆነ መሠረት መፍጠሪያ\nነው፡፡ ኦሊምፒክን የመሰረተው እኮ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የፈጠራቸው ችግሮች ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ ኦሊምፒክ ውድድር አይደለም።\nአሁን አሁን የውድድር መልክ ያዘ እንጂ አንድነትና ፍቅር የሚገለፅበት መድረክ ነበር፡፡ ስለዚህ የማስ ስፖርቱ በህዝባችን ውስጥ\nእንዲሰርፅ ማድረግ አንድነትን ማጠናከሪያ እንጂ በሌላ እይታ የሚታይ አይደለም፡፡ ስፖርቱ ያቀራርባል እንጂ የፖለቲካ ተልዕኮ አይደለም፡፡\nበአሁን ወቅት በስፖርት ቤት የገባው አንዱ ነገር ዘረኝነት ነው፡፡ ለዚህ ነው “ዘረኝነት ይብቃ” የሚል መሪ\nቃል/ሞቶ እየተጠቀምን ያለነው፤ ስፖርት የፖለቲካው ትኩሳት ጥሩ ሲሆን ጥሩ የምንሆንበት፤ መጥፎ ሲሆን መጥፎ የምንሆንበት አካሄድ\nአይደለም፡፡ ፖለቲካው ጥሩም ሳይሆን ወደ ሠለም መመለሻ አቅም መሆን አለበት፡፡ ስፖርት ሠላም ነው ካልን ሰላም የሚያደፈርሱ ሃይሎችንም\nከእኩይ ተግባራቸው የሚያወጣ ነው፡፡ ትኩሳትን የሚያበርድ እንጂ ለመንግሥትና ለህዝብ ራስ ምታት መሆን የለበትም፡፡ ከዚህ አንፃር፤ ምንም የፖለቲካ አጀንዳ የለውም። የፖለቲካ አመራሮች በማስ ስፖርት ላይ ተገኙ ማለት አጀንዳው\nፖለቲካ ነው ማለት አይደለም። መቀራረብና መፈቃቀር ግን አጀንዳው ነው፡፡ ሁሉም ተጋግዘው ነው እየሠሩ ያሉት፤ የሚተላለፈው መልዕክት\nእንዴት መሥራት እንዳለብን የሚጠቁም ነው፡፡ የስፖርት ቤተሰቡም የመገኘትም ያለመገኘትም መብት አለው፡፡ የማስ ስፖርት መርሐ ግብር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ዓላማውን እያሳካ ነው፡፡ በማህበረሰቡ ዘንድ\nመቀራረብ ፈጥሯል፡፡ ሰዎች በጉጉት እንዲጠብቁት ሆኗል፡፡ የተሳታፊዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። ከጤና አኳያም ብዙ\nሰው ባህል አድርጎት እየተሳተፈበት ነው፡፡ የማስ ስፖርት ከጀመርን በኋላ 21 ወረዳዎች በተጠናከረ መልኩ እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ አዲስ ዘመን፡- በመዋቅር ለውጡ ስፖርት ኮሚሽን ራሱን ችሎ\nእንዲቆም ቢደረግም ተጠሪነቱ ግን ለወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባሪያ ቢሮ መሆኑ አሉታዊ ተጽዕኖ አይኖረውም? አቶ ዮናስ፡- ክልሎች የተለያየ አደረጃጀት ይኖራቸዋል፡፡ አዲስ አበባ ላይ አሁን ባለው ሁኔታ ለስፖርቱ ትልቅ ትኩረት ከተሰጠው\nተጠሪነቱ ለከንቲባው መሆን አለበት የሚል እምነት አለኝ። ይህንንም ምክትል ከንቲባው በተገኙበት በዓመታዊ ግምገማ ላይ ተናግሬያለሁ፡፡\nአሁንም ራሱን ችሎ እየሄደ ነው ለማለት ግን የሚጎድለን ነገር የለም፡፡ ቡድን መሪ፣ ዳይሬክተሮችና አመራሩ ነው ወሳኙ፡፡ ሥራውን\nአጠናቅቆ የመሥራት አቅም ካለ የተጠሪነቱ ጉዳይ አያሳስብም፡፡ ስለዚህ በአሁኑ ወቅት ራሱን የቻለ ተቋም ነው ብለን እየመራን ነው፡፡\nከድጋፍ ጋር በተያያዘ ግን ከከንቲባው ጽህፈት ቤት ጋር መሠራት አለበት የሚል አቋም ነው ያለኝ፤ ይህም የሚወሰነው እንደ አመራር\nሚና ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡ አዲስ ዘመን፡- ኮሚሽኑ በአዲሱ\nዓመት በዋናነት ምን ምን ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ ሊሠራ አቀደ? አቶ ዮናስ፡- ከሚሽኑ የራሱ ስትራቴጂክ ዕቅድ አለው፡፡ ዋና ፍኖተ ካርታውም መነሻው ከዚህ ነው። የስትራቴጂክ ዕቅዱ ዋና\nራዕይ “አዲስ አበባ ላይ ያለው ትውልድ በተክለ ሰውነትም ሆነ በአዕምሮው የዳበረ፤ በአስተሳሰቡ የተሻለ ጠንካራ ዜጋ በስፖርት ዘርፉ\nመገንባት” ነው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ በአገራዊ ጥሪዎች ላይ ከዓለም የጎላ ተወዳዳሪነት መንፈስን ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡\nበዚህ አዲስ ዓመት የጥርጊያ ሜዳዎቻችንን ማስፋፋት፣ ጥርጊያ ሆነው የተሰሩትን ደግሞ ወደ ሣር ማሸጋገርና ወጣቶችን\nአደራጅተን የተሻለ ሥራ ለመሥራት አቅደናል፡፡ 32 ሦስት በአንድ የሆኑ ሜዳዎችን መስራትም አንዱ ዕቅድ ነው። የተጀመሩትን ፕሮጀክቶች\nሙሉ ለሙሉ እንዲጠናቀቁ ማድረግም ሌላኛው ሥራ ነው፡፡ ሌለኛው ደግሞ የተለዩ የማዘውተሪያ ሥፍራዎችን የመረከብና የማከል ሥራ ነው፡፡\nየማስ ስፖርቱን በተጠናከረ መልኩ በማስቀጠል በሁሉም ወረዳ ተግባራዊ ማድረግ የኮሚሽኑ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ\nነው፡፡ የታዳጊ ፕሮጀክቶችን በተመረጡ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ላይ በሚታይና በሚቆጠር ሥራ ላይ ትኩረት እናደርጋለን፡፡ ለዚህም\nለትምህርት ቤቶች በር እንከፍታለን፡፡ ዋናው ነገር በተመረጡ ስፖርቶች ብቻ ውድድር እያደረግን በአዲሱ ዓመት አዲስ አበባ የስፖርት\nማዕከልነቷን እንድትመልስ ማድረግ ነው፡፡ ለዚህም የስፖርቱን ቤተሰብ አቅም ከመገንባት አኳያም የተጀመሩትን ተግባራት እናስቀጥላለን፡፡\nአዲስ ዘመን፡- የከተማ አስተዳሩ በስፖርቱ ዘርፍ ከሌሎች ዓለም\nአቀፍ እህት ከተሞች ጋር ተሞክሮ የመቅሰም ልምድ ካለው ቢጠቅሱልኝ፤ አቶ ዮናስ፡- እስካሁን አለነበረም፡፡ ከአሁን በኋላ ለመጀመር ግን ከተለያዩ አገራት አምባሳደሮች ጋር ተናጋግረናል፡፡\nየአርጀንቲና፣ የጃፓን፣ የፈረንሳይና የኮሪያ ተጠቃሾች ናቸው። ስለዚህ በ2012 ዓ.ም ከእህት ከተሞች ጋር በከተማ አስተዳደሩ አማካኝነት\nትስስር ፈጥረን በማስ ስፖርትና በታዳጊዎች ላይ እንሠራለን፡፡ ከሚበልጡን ለማማር ዕቅድ ይዘናል፡፡ አዲስ ዘመን፡- አዲስ አበባ የአገሪቷ ርዕሰ መዲና ሆና ሳለች\nዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም ማጣቷ ለምንድነው? ወደፊትስ ምን ታስቧል? አቶ ዮናስ፡- ስታንዳርዱ በምን ደረጃ ነው መሆን ያለበት የሚለው ነገር እንዳለ ሆኖ፤ በአጠቃላይ ግን ባዳ መሆናችንን\nያሳያል፡፡ ምክንያቱም “የአዲስ አበባ ስታዲየም ለምንድነው ደረጃውን ያላሟላው?” የሚለውን ነገር አናውቀውም፡፡ ከሚመለከታቸው አካላት\nጋር አብረን ሆነን በምክክር እንዳንሠራ ችግር አለ፡፡ በግብረ መልሶች ላይ ከኮሚሽነሮች ጋር ተቀምጠን አልተወያየንም፡፡ ነግር ግን፤\nበዚህ ዙሪያ በርከታ ሥራ መሥራት እንዳለብን እረዳለሁ፡፡ ችግሩ እንዳይደገምም እየሠራን ነው፡፡ አዲስ ዘመን፡- የባህል ስፖርቶችን በከተማዋ እንዲስፋፉ ለማድረግስ\nምን እየተሠራ ነው? አቶ ዮናስ፡- በቅርቡ አምቦ ላይ በተደረገው የባህል ስፖርት ውድድሮች በከተማ ደረጃ የተሻለ አፈፃፀም ታይቷል፡፡\nበቀጣይም ከባህልና ቱሪዝም ጋር በመተባበር ሥልጠና እንዲሰጥና የባህል ስፖርቱን አጠናክረን መሄድ እንዳለብን ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡\nበአዲሱ ዓመት ከምንሠራቸው ተግባራትም አንዱ ትውልዱ አገሩን እንዲወድ በባህል ስፖርት ላይ ትኩረት ማድረግ ነው፡፡ ነባር የሆኑ\nየባህል ስፖርቶች እንዳይጠፉ ግን በከተማዋ ላይ በርካታ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው፡፡ አዲስ ዘመን፡- ለሰጡኝ ሰፊ ማብራሪያ አመሰግናለሁ! አቶ ዮናስ፡- እኔም በጣም አመሰግናለሁ!አዲስ ዘመን መስከረም 2/2011አዲሱ ገረመው ", "passage_id": "a9110a474f2eb59073e6aad97829a75a" }, { "passage": "እአአ\nበ1980 ሞስኮ ባዘጋጀችው ኦሊምፒክ፤ የ5ሺ ሜትር አሸናፊ ኢትዮጵያዊው አትሌት ምሩጽ ይፍጠር መሆኑ ለዓለም አዲስ ታሪክ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ በዘመናዊው ኦሊምፒክ ከዚያ ቀደም በተካሄዱት 14 መድረኮች አንድም አፍሪካዊ የወርቅ ሜዳሊያ ሳያጠልቅ መቆየቱ ነው። ርቀቱ በበላይነት የተያዘውም በአውሮፓውያን አትሌቶች ሲሆን፤ በተለይ ፊንላንዳውያን በርቀቱ ነግሰው እንደነበር ታሪክ ያወሳል። በ10ሺ ሜትርም በተመሳሳይ የበላይነቱ በአውሮፓውያን አትሌቶች (ለ11 ኦሊምፒኮች) የተያዘ ነበር። እአአ በ1968 ኬንያዊው ናፍታሊ ተሙ እና ኢትዮጵያዊው ማሞ ወልዴ ተከታትለው የወርቅና ብር ሜዳሊያውን እስኪወስዱት ድረስ። የምስራቅ አፍሪካውያኑ አትሌቶች ድል አድራጊነቱን ከተቀላቀሉ በኋላም የደረጃ ሰንጠረዡን ቀዳሚ ስፍራ ሊቆጣጠሩት ችለዋል። ከኦሊምፒክ ባሻገር ባሉ ውድድሮች ላይ የሚታየው ልምድም ከዚህ የተለየ የሚባል አይደለም። ኢትዮጵያ\nለዘመናት ስሟን ያስጠራችበት ይህ የአትሌቲክስ ውድድር ግን ለመጥፋት ጥቂት ቀርቶታል። በርካታ ጀግና አትሌቶች ድል የነሱበት የ10ሺ ሜትር ርቀት በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንዲሁም በኦሊምፒክ ብቻ ከተወሰነ ሰነባብቷል። በዳይመንድ ሊግ ይታይ የነበረው የ5ሺ ሜትር ርቀትም ተመሳሳይ ዕጣ እንደሚደርሰው ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በቅርቡ አስታውቋል። ከጥቂት\nአስርት ዓመታት ወዲህ ሙሉ ለሙሉ በምዕራባውያኑ የበላይነት ተይዞ የቆየው ርቀት በምስራቅ አፍሪካውያኑ አትሌቶች ተወስዷል። ሀገራቱ በዚህ ምክንያት ሙሉ ትኩረታቸውን ወደ አጭርና መካከለኛ ርቀቶች እንዲሁም የሜዳ ላይ ተግባራት እንዲያደርጉም ተገደዋል። ስለዚህም በአፍሪካውያን የተወሰደ ክብራቸውን ለማስመለስ ሀገራትን ማዳከም የመጀመሪያው እርምጃቸው መሆኑ ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው። ውሳኔውን ተከትሎም በርቀቱ በተለይ ውጤታማ የሆኑት ጎረቤታሞቹ ኬንያ እና ኢትዮጵያ ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ። ምንም እንኳን በኬንያ በኩል የመወላወል ነገር እየታየ ቢሆንም፤ ኢትዮጵያ ግን በፌዴሬሽኗ፣ በኦሊምፒክ ኮሚቴዋ እንዲሁም በዝነኛ አትሌቶቿ ትግል ማድረጓን ተያይዛዋለች። መታገሉ በህዝቡ ዘንድ እንደ ባህል የሚታየውን ውድድር ወደ ቀድሞ ክብሩ እንዲመለስ ለማድረግ መልካም ሆኖ ሳለ፤ ሌላ የቤት ስራ የሚሰጥ መሆኑ ግን መዘንጋት የለበትም። ይህም ኢትዮጵያን ለመሳሰሉ ሀገራት ይታወቁበት ከነበረው ርቀት ሌላ አማራጭ እንዲመለከቱ የግድ የሚል መሆኑን ነው። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም በረጅም ርቀት አትሌቲክስ የተጣለውን ውሳኔ ከማስቀልበስ እንቅስቃሴው ባሻገር በሌሎች ርቀቶች ላይ የሚገኙአትሌቶችን መመልከት ይኖርበታል። በተለይ ለአጭር ርቀት እንዲሁም ለሜዳ ላይ ተግባራት ምቹ የሆኑ የአካል ብቃት እንዲሁም የአኗኗር ሁኔታ ላይ በሚገኙ አትሌቶች ላይ ትኩረቱን መጨመር እንደሚገባው በትክክልም የሚጠቁም ነው። በውሳኔው\nመሰረት በረጅም ርቀት የሚካፈሉ አትሌቶች ሁለትና አራት ዓመታትን ጠብቀው መወዳደራቸው የግድ ነው። የፌዴሬሽኑ ስጋት ደግሞ አትሌቶች ዓመታትን ከመጠበቅ ይልቅ ፊታቸውን ወደ ጎዳና ሩጫዎች መመለሳቸው ይጎዳቸዋል የሚል ነው። ይህ ስጋት ትክክለኛ ቢሆንም ግን ከማራቶን ባሻገር በመካከለኛ፣ በአጭር፣ በዝላይ፣ በውርወራ እንዲሁም በእርምጃ ወደ ሚካሄዱ ውድድሮች ፊታቸውን እንዲያዞሩ ማድረግ ተገቢ ነው። ኢትዮጵያ ከኬንያ ስትነጻጸር በታላቁ የኦሊምፒክ መድረክ ሜዳሊያ ያስመዘገበችው፤ በ1ሺ 500 ሜትር፣ በ3ሺ ሜትር መሰናክል፣ በ5ሺ ሜትር እንዲሁም በ10ሺ ሜትር ውድድሮች ብቻ ነው። በአንጻሩ ኬንያ ከእነዚህ ርቀቶች ባሻገር በ400 ሜትር፣ በ400 መሰናክል፣ በ400 ሜትር፣ 800 ሜትር እንዲሁም በጦር ውርወራ ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች። ይህም ኢትዮጵያ ምን ያህል በአንድ አካባቢ ተወስና እንደቀረች የሚያሳይ ሲሆን፤ ኬንያ በበኩሏ ተሳትፎዋን በማብዛቷ ውጤታማ ለመሆኗ ማሳያ ይሆናል። ኢትዮጵያም ሁሌም ከምትነሳባቸው አራትና አምስት ርቀቶች ያላለፈ ዝናዋን በድጋሚ መገንባት የሚቻልበት መንገድ መኖሩን መዘንጋት አያስፈልግም። ለፌዴሬሽኑ እንዲሁም ለኦሊምፒክ ኮሚቴም አካባቢያቸውን እንዲቃኙ በግልጽ የተቀመጠ ማንቂያ ይሆናል። እንደ ነባራዊው ሁኔታ ከሆነ፤ በኢትዮጵያ ባሉ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከወረዳ ጀምሮ አያሌ የታዳጊ ወጣት ፕሮጀክቶች ይገኛሉ። በእነዚህ ፕሮጀክቶችም ከእግር ኳስ ስፖርት በሚስተካከል መልኩ የአትሌቲክስ ስፖርት ስልጠና ይሰጣል። ከዚህ ባሻገር በሀገር አቀፍ ደረጃ አራት የስልጠና ማዕከላት እንዲሁም ሁለት አካዳሚዎች ይገኛሉ። በእነዚህም ውስጥ አትሌቲክስ በከፍተኛ ትኩረት ስልጠና የሚሰጥበት ዘርፍ ነው። በተለያዩ አካባቢዎችም በራሳቸው ጥረት እንዲሁም በግል አሰልጣኞች አትሌት ለመሆን የሚታትሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳጊና ወጣቶች ይገኛሉ። ከእነዚህ\nሰልጣኞች የሚልቁት ደግሞ ትኩረታቸውን በረጅም ርቀት አትሌቲክስ ላይ ያደረጉ ናቸው። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በማትታወቅበት የሜዳ ላይ ተግባራት ያለው ሁኔታ፤ በፍላጎት፣ በግብዓት እንዲሁም በቁሳቁስ እጥረት እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ነገር ግን በተለያዩ ጊዜያት ፌዴሬሽኑ ባደረገው ምልከታም ይሁን ባለሙያዎች እንደሚገልጹት በተለይ በአጭር ርቀት፣ ውርወራ እና ዝላይ ውጤታማ መሆን የሚችሉ ታዳጊዎች የሚፈሩባቸው አካባቢዎች ይገኛሉ። በመሆኑም ማሰልጠኛ ማዕከላት ከእነዚህ አካባቢዎች ወጣቶችን በመመልመል፣ ፌዴሬሽኑም አስፈላጊውን ግብዓት በማሟላት እንዲሁም ተገቢውን ስልጠና እንዲሰጥ በማድረግ ውጤታማነትን መመለስ ይችላል። የኢትዮጵያ\nአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከዓመት በፊት በመላ ሀገሪቷ በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ምልከታ በባለሙያዎቹ ማድረጉ የሚታወስ ነው። ስልጠናው የሚሰጥባቸው ቦታዎች ከባህር ጠለል በላይ የሚገኙበትን በመመልከት እንዲሁም የአኗኗር ሁኔታቸውን በማጥናት ለየትኛው የስፖርት ዓይነት ምቹ ነው የሚለውንም ለይተዋል። በወቅቱ ፌዴሬሽኑ ባስቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት አዳዲስ አትሌቶችን የመመልመል ስራዎች መሰራታቸውን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ አስታውቀው ነበር። በአቅርቦት ላይ የሚታየውን ችግር ለመፍታትም ፌዴሬሽኑ በአነስተኛ ዋጋ ከሚያቀርቡ ከሀገር ውስጥ አምራች ድርጅቶች ጋር በመነጋገር ላይ መሆኑ ተጠቁሞ ነበር። በተለይ እንደየ ሰልጣኙ እድሜ፣ ለውድድርና ለስልጠና በምን ያህል መስፈርት መዘጋጀት ይገባል እንዲሁም ለየክልሎቹ ምን ያህል አቅርቦት ያስፈልጋል በሚለው ላይም ፌዴሬሽኑ ዝግጅት ተደርጓል። በሀገሪቷ\nያሉት አሰልጣኞች ቁጥር ከስልጠናውና ከሰልጣኞቹ ጋር የሚመጣጠን አለመሆኑም ተረጋግጧል። በመፍትሄነትም አሰልጣኞችን ከውጭ ሀገራት ለማስመጣት መታቀዱ በወቅቱ ተገልጾ ነበር። ልምድ ያላቸውን አሰልጣኞች ለማስመጣት በሙከራ መሆኑንና ለኢትዮጵያውያን አሰልጣኞች ልምድና ተሞክሮዎችን እስደሚሰጡም ይጠበቅ ነበር። ይህንን\nስራ ቀድሞ የመጀመሩ አስፈላጊነት አያጠያይቅም፤ ነገር ግን ቀጣይነቱ ላይ ምን እየተሰራ ይገኛል? የሚለው ዋነኛው ጉዳይ ነው። በፌዴሬሽኑ በኩል በዓለም ላይ እየታየ ያለውን ሁነት ተከትሎ መፍትሄ ማበጀት እንዲሁም የጀመሩትን ስራ ከዳር ማድረስ የግድ መሆኑም መዘንጋት የለበትም። ከጥያቄው ባሻገር የተሰጠውን የቤት ስራ ለማከናወን በሙሉ ዝግጁነት መነሳትም አስፈላጊ ነው።", "passage_id": "127551a136af260b2579d72e99514d08" }, { "passage": "እአአ የ1964ቱ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በታሪኳ ተሳታፊ የሆነችበት ሶስተኛው ኦሊምፒክ ነው። ታላቁ አትሌት አበበ ቢቂላ በኦሊምፒክ ማራቶን ለራሱ እና ለአገሩ ሁለተኛውን፣ በውድድሩ ደግሞ ብቸኛውን ሜዳሊያ ያገኘበትም ነበር። አሁን ደግሞ ጃፓን ከሃምሳ ስድስት ዓመታት በኋላ ኦሊምፒክን በምድሯ ለማስተናገድ ወራት ብቻ የቀሩበት ጊዜ ላይ እንገኛለን። በዚህ ታላቅ የስፖርት መድረክም የተሻለ ታሪክ ለማስመዝገብ ኢትዮጵያ በተለየ ትኩረት በመንቀሳቀስ ላይ ትገኛለች። በታላቁ የኦሊምፒክ መድረክ ከውጤታማነት ባሻገር ተሳትፎም ክብርን ያስገኛል። በውጤታማነት ድርብ ክብርን ለመጎናጸፍ ደግሞ ትኩረት፣ ጥረትና ጽናት አስፈላጊ መሆናቸው ይታመናል።በኦሊምፒክ መድረክ የአገሪቷን ስም በተደጋጋሚ ያስጠራው እንዲሁም ከፍተኛውን የውጤታማነት\nስፍራ የሚይዘው የአትሌቲክስ ስፖርት ነው። ኢትዮጵያ ደግሞ በዚህ ስፖርት በተመዘገቡ ሜዳሊያዎች አማካኝነት ከውጤታማዎቹ አገራት\nመካከል 36ኛ ስፍራ ላይ ትገኛለች። ነገር ግን በዚህ መድረክ ውጤታማ ያደረጓት አትሌቶች የኋላ ታሪክ ቢጠና በግላቸው የሚያደርጉት\nጥረትና ጽናት ሰፊውን ድርሻ ይይዛል። በመሆኑም መንግስት የተሻለ ትኩረት በመስጠት ውጤታማነቱን ለማሳደግና ለማገዝ እየተንቀሳቀሰ\nመሆኑን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አስታውቋል። ለዚህም የመጀመሪያው ርምጃ አትሌቶች የዝግጅት ጊዜያቸውን በትኩረት እንዲያሳልፉ በተሻለ\nስፍራ እንዲያርፉ ማድረግ ነው። በመሆኑም የዝግጅት ኮሚቴው ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ባደረጉት ውይይት\nለውድድሩ የተመረጡ አትሌቶች ካምፓቸውን ከፍተኛ ደረጃ ካላቸው ሆቴሎች መካከል በአንዱ እንዲያደርጉ አቅጣጫ ተሰጥቷል። በዚህም መሰረት\nበኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጥሪ የተደረገላቸው አትሌቶች ተሰባስበው ወደ ልምምድ እንደሚገቡ ተገልጿል። ከዚህ ቀደም በብሄራዊ\nቡድን የታቀፉ አትሌቶች የላብ መተኪያ ወጪ እጅግ አናሳ መሆኑ በቅሬታ መልክ የሚነሳ ነበር። ይህንንም ለመቅረፍ በመንግስት በኩል\nበተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ለታዋቂ አትሌቶች 50ሺ ብር ደሞዝ እንዲያገኙ እንዲሁም ለሌሎች ጀማሪ አትሌቶች 10ሺ ብር በየወሩ የሚከፈላቸው\nይሆናል። በልምምድ ግብዓት እንዲሁም ትጥቅ በኩልም ችግር እንዳይገጥማቸው እየተሰራ መሆኑም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአትሌቲክስ\nፌዴሬሽን ጋር በመሆን ከትናንት በስቲያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጧል። ዝግጅቱን በበላይነት\nየሚመራው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከስፖርት ማህበራትና ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር በመሆን ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅ በማድረግ ላይ\nእንደሚገኝ ይታወቃል። ለዝግጅቱም የቶኪዮ ብሄራዊ ዝግጅት ኮሚቴ እንዲሁም የቶኪዮ ኦሊምፒክ ቴክኒክ ኮሚቴ በሚልም ሁለት ኮሚቴዎችን\nአዋቅሯል። ብሄራዊ ኮሚቴው በቀድሞ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ የሚመራ ሲሆን፣ ትኩረቱን በሃብት አሰባሰብ፣\nየልማት ስራዎች፣ የደጋፊ አባላት ላይ እንዲሁም በስፖርተኞች ሽኝትና አቀባበል ላይ ያደርጋል። በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል\nኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጂሎ የሚመራው የቴክኒክ ኮሚቴው ደግሞ ከተለያዩ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በአትሌቶችና አሰልጣኞቻቸው ምርጫ ላይ\nየሚሰራ ይሆናል። በዚህም መሰረት\nአትሌቲክስ ፌዴሬሽን እጩ አትሌቶችንና አሰልጣኞቻቸውን ከቀናት በፊት አሳውቋል። በማጣሪያ ውድድር ላይ ያሉት የቦክስና ወርልድ ቴኳንዶ\nስፖርቶችን ጨምሮ ከውሃ ስፖርቶችና ብስክሌት ፌዴሬሽኖችም ጋር ኮሚቴው በትብብር በመስራት ላይ ይገኛል። ቀደም ብሎ ወደ ዝግጅት\nምዕራፍ በመግባት ላይ የሚገኘው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በበኩሉ 90 አትሌቶችንና 15 አሰልጣኞችን በማጨት ወደ ልምምድ ለመግባት\nበመንደርደር ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። ብሄራዊ ቡድኑ በሶስት ምዕራፍ የተከፈለ ዝግጅት የሚያደርግ ሲሆን፤ በመጨረሻም 50 አትሌቶች\nወደ ቶኪዮ የሚጓዙ ይሆናል። ለጊዜው በተሳትፎ ደረጃ የተያዘው ከ800ሜትር እስከ እርምጃ ባሉት ርቀቶች ቢሆንም ሚኒማውን ማሟላት\nከተቻለ በ400ሜትርም ተሳታፊ የመሆን እድል እንደሚኖር ተጠቁሟል።የቴክኒክ ኮሚቴው\nቀድሞ ዝርዝራቸው ይፋ የተደረጉትን አሰልጣኞች የተመረጡበት መስፈርትም በርካታ አትሌቶችን በማስመረጥ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ውድድሮች\nባላቸው ልምድ መሆኑን ገልጿል። የአትሌቶች የምርጫ መስፈርት ደግሞ እአአ በ2019 ባስመዘገቡት ሰዓት መሰረት በመምረጥ በስራ አስፈጻሚ\nኮሚቴው የጸደቀ መሆኑ ተብራርቷል። ለኦሊምፒክ የሚደረገው\nዝግጅት አገርን ለማስጠራት የሚደረግ እንደመሆኑ በሁሉም አካላት ዘንድ በተለይም በአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች\nበኩል ያለው አለመግባባትን ከወደ ጎን በመተው ለውጤታማነት በጋራ መስራት አስፈላጊ መሆኑ በመግለጫው ተጠቁሟል።አዲስ ዘመን አርብ የካቲት 13/2012ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "b91076268f89ce5d1de2ac6ab4f9b259" }, { "passage": "የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የዓለም ወቅታዊው ሁኔታ፤ የሰውን ልጅ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ፣ አስተሳሰብና ልማድ እንዲቀየር ምክንያት ሆኗል፡፡ በዚህ መንስኤነትም አካላዊና አእምሯዊ ጤናን ከመጠበቅና ከማዝናናት ባለፈ ከፍተኛ ገንዘብ የሚዘዋወርበት ስፖርትም በቀድሞ ቁመናው ላይ እንዳይገኝ ሆኗል፡፡ በዘርፉ በዓለም ደረጃ እአአ በ2011 ከተገኘው ገቢ በ45 በመቶ የላቀ ትርፍ ከሁለት ዓመታት በፊት መገኘቱን ወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም ያመላክታል፡፡ ይህ እአአ በ2018 የተገኘው 471ቢሊዮን ዶላር በዚህ ዓመት በእጅጉ ሊያድግ እንደሚችልም አመላካች ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ባልተጠበቀ ሁኔታ ተከስቶ መላውን ዓለም ባዳረሰው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ምክንያት እንቅስቃሴው ሊገታ ችሏል፡፡ እንደ ሌላው ዓለም ሁሉ የኢትዮጵያ ስፖርትም መዳከም አሳይቷል፡፡ በእንቅስቃሴው መገታት በስፖርተኞች፣ ክለቦች፣ ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ አወዳዳሪዎችና ሌሎች ባለድርሻዎች መካከል የነበረው ሰንሰለት በቫይረሱ ተጠቅቷል፡፡ በጥቂት ውድድሮች ሽልማት በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብና የውጭ ምንዛሪ ለሀገር ያስገኙ ከነበሩ አትሌቶች፤ ‹‹ነገ ያልፍልኛል›› በሚል እሳቤ ከኑሮ ጋር እስከሚታገሉት ጀማሪ ስፖርተኞች ድረስ የጉዳቱ ሰለባ ሆነዋል፡፡ ከአቅማቸው በላይ የሆኑትም ከበጎ ፈቃደኞች ተደጓሚ ሆነዋል፡፡ የስፖርት ማህበራትም ከውድድሮችና ስፖንሰሮች ማግኘት የሚገባቸውን ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡ ይህንን አሳሳቢ ሁኔታ\nያጤነው የኢፌዴሪ ስፖርት\nኮሚሽንም ወረርሽኙ በዘርፉ\nላይ ያሳደረውን ጫና\nበማመዛዘን እንዲሁም በተወሰነ\nመልኩ የሚያገግምበትን ሁኔታ\nለማመቻቸት የሚረዳ ሥራ\nበማከናወን ላይ ይገኛል፡፡\nበጉዳዩ ላይ ለአዲስ\nዘመን ጋዜጣ ማብራሪያ\nየሰጡት ምክትል ኮሚሽነር\nዱቤ ጂሎ፤ ከኮሮና\nቫይረስ ወረርሽኝ ጋር\nበተያያዘ እንደ ንግድ ሁሉ ስፖርትም ጉዳት ያስተናገደ ዘርፍ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ስፖርተኞች ቀድሞ የሚያገኙትን ገቢ ማግኘት ባለመቻላቸው፣ ክለቦች የመፍረስ አደጋ የተደቀነባቸው በመሆኑ መሰል ጉዳዮችን ከግምት በማስገባት ከመንግሥት ማገገሚያ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ እንዲለቀቅ ጥያቄ መቅረቡንም ይገልጻሉ፡፡ ኮሚሽኑ ለመንግሥት ያቀረበው\nየዳሰሳ ጥናት ‹‹ኮሮና\nቫይረስ በስፖርቱ ልማት\nላይ ያሳደረው ተጽእኖ\nየማገገሚያ ስልት›› የሚል\nሲሆን፤ ጥናቱ የተከናወነውም\nየሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ\nበመቀመር ጭምር ነው፡፡\nበዚህም እንግሊዝ፣ ናይጄሪያ፣\nኬንያ እና የመሳሰሉት\nሀገራት በወረርሽኙ ወቅት\nለማገገሚያ የተጠቀሙትን ስልት\nለመዳሰስ መሞከሩንም አመላክተዋል፡፡\nየኢትዮጵያ ስፖርት ሕዝባዊ\nመሠረት ያለው እንደመሆኑ\nበስፖንሰርና በስታዲየም ገቢ\nከሚያገኙት ገንዘብ ባለፈ\nለከተማ ክለብ ስፖርተኞች\nደመወዝ የሚከፈለው ከሕዝብ\nከሚሰበሰበው ታክስ ነው፡፡\nይህም ማለት አብዛኛውን\nገንዘብ የሚሸፍነው መንግሥት\nነው፡፡ ከወቅቱ ነባራዊ\nሁኔታ ጋር በተያያዘ\nውድድሮችን ማካሄድ ባለመቻሉ\nበዘርፉ ያለው  እንቅስቃሴ\nአስቸጋሪ ሆኗል፡፡ ይህንን ጊዜ ለመሻገርም ከስፖርት ማህበራቱ ጋር በመተባበር ስትራቴጂ በመንደፍና ጥያቄውን ለመንግሥት በማቅረብ ኮሚሽኑ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ ጥናቱ ስፖርተኞች በምን መልክ ወደሥልጠናና ውድድር ይመለሱ፣ እንዴትስ ፈቃድ ይሰጣቸው የሚለውን በመነሻነት መያዙንም ነው ምክትል ኮሚሽነሩ የሚጠቅሱት:: እንደ ኮሚሽንም ሀገር አቀፍ የስፖርት ማህበራቱ መርሃ ግብራቸውን እንዲያቀርቡም መመሪያ ተላልፏል፡፡ በኢትዮጵያ ስፖርት የሚንቀሳቀሰው የገንዘብ መጠን በውል አይታወቅም፡፡ ይህም መሰል ጥናቶች ላይ ተጽእኖ ማሳደሩ አይቀርም፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ፌዴሬሽን ይብዛም ይነስም በስፖንሰር የሚያገኙት ገቢ ይኖራል፤ ሆኖም በዓመት ይህን ያህል ይገኛል የሚለው በውል አይታወቅም፡፡ ለአብነት ያህል የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኢንተርናሽናል እና የሀገር ውስጥ ስፖንሰሮች ቢኖሩትም ከወቅታዊው ሁኔታ ጋር በተያያዘ በትክክል ለማወቅ የሚቻልበት ሁኔታ አዳጋች ነው፡፡ ቢሆንም ቅድመ በግምቶችን በማስቀመጥ ጥናቱ መከናወኑንም ነው ምክትል ኮሚሽነሩ ያስረዱት፡፡ የኮሮና ወረርሽኝ የስፖርቱን\nዘርፍ ሙሉ በሙሉ\nጎድቷል፤ እንቅስቃሴዎችንና ውድድሮችን\nገድቧል፡፡ በስፖርተኞችና ሀገራትም\nላይ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ\nችግሮችን አስከትሏል፤ ይህም\nአደጋ ነው፡፡ ነገር\nግን ይህ ጊዜ\nያልፋል በሚል ተስፋ\nሁሉም በአንድነት እየተጠባበቀ\nይገኛል፡፡ መንግሥትም ሁኔታዎችን\nበማገናዘብ ምላሽ ይሰጣል\nየሚል ተስፋ አለ፤\nይህን ወቅት በመሻገርም\nስፖርቱን ወደነበረበት የስፖርት\nቤተሰቡም ወደ ተመልካችነቱ\nየሚመለስበት ጊዜ ሩቅ\nአይሆንም፡፡ በመሆኑም ይህንን\nጊዜ በጋራ ለማለፍ\nራስን ከቫይረሱ መጠበቅ\nእንዲሁም የአካል ብቃት\nእንቅስቃሴ በማድረግ እንዲቆዩም\nምክትል ኮሚሽነሩ መልዕክታቸውን\nአስተላልፈዋል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 15/2012ብርሃን ፈይሳ", "passage_id": "238790f6962b11e39b556fdfe12c1add" } ]
18019dc8dacaad11667167c7539ca6b1
936cf6c1b06d1d1678fc4cc0fee04050
ከፓራጓይ ሰማይ ሥር-የወደቀው የብራዚላዊው እግር ኳስ ኮከብ ዝና
ዳንኤል ዘነበ በዓለም ዙሪያ በማራኪነቱ፤ በአዝናኝነቱም ሆነ በልብ ሰቃይነቱ ወደር አልተገኘለትም፣ ዘመናዊው የእግር ኳስ ስፖርት። ለእግር ኳስ ፍቅር በከፍተኛ ደረጃ ባለቤት በመሆን ረገድ ብራዚላውያንን የሚስተካከል ስለመኖሩ እርግጠኛ መሆን እንደማይቻል ይነገራል፡፡ ብራዚል ብዙ ሚሊዮን የእግር ኳስ ስፖርት ፍቅር ያለው ሕዝብ ባለቤት ብቻም አይደለችም። ብራዚል የእግር ኳስ ክዋክብቶችን በማፍራት ተጠቃሽ ናት። በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ ተጫዋቾችን በማፍራት ነጥፋ አታውቅም። የብራዚላውያን የኳስ ጥበበኛነትን ዓለም አምኖ እንዲቀበል ካደረጉ የዘመናቸን ድንቅ ተጫዋቾች መካከል ሮናልዲንሆ ጎቾ ዲ አሲስ ሞሬራ!! ሮናልዲንሆ ጎቾ በተጫዋችነት ዘመኑ የሰራቸው ገድሎች «ዘመናዊ እግር ኳስ እንግሊዝ ውስጥ ተወልዶ ብራዚል አደገ» እስኪባል ድረስ ሀገሩን ብሎም ዓለምን በማስደመም ስሙን መትከል ችሏል። በዓለም ዋንጫ መድረክ ብቻም ሳይሆን ሌሎች መድረኮች ላይ በሜዳ ላይ በሚያሳያቸው እንቅስቃሴዎች፣ አብዶዎች ከስፖርት ቤተሰቡ ልብ ትዝታው ዛሬም የሚነሳለት ድንቅ ጥበበኛ፤ እኤአ በመጋቢት 1980 በብራዚል በደቡብ ብራዚል ፖርት ኤሌግሪ ተወለደ። እግር ኳስ ወዳድ ከሆነ ቤተሰብ የተገኘው ጎቾ ኳስን በ8 ዓመቱ ኳስ ከሰፈሩ ልጆች ጋር በፖርት አሌግሪ የባህር ዳርቻ በማንከባለል ነበር የጀመረው። ሜዳው ላይ በዕድሜው አነስተኛው ልጅ እሱ ሲሆን፤ በችሎታው የሰውን ዓይን በቀላሉ መማረክ የሚችልና ብዙዎች ከዓይን ያውጣህ ማስባል የጀመረው ያኔ ገና ነበር። ሮናልዲንሆ እስከ 13 ዓመቱ ከሰፈሩ በዘለለ ለትልልቅ ክለቦችም ሆነ ለታዳጊ መጫወት አልቻለም። ውሎው የባህርዳርቻ ነበር። በ13 ዓመቱ ግን አንድ ነገር ተከሰተ፣የወንድሙ ክለብ የሆነው የግሪሚዩ መልማዮች ጎበዝ ተጫዋቾችን ሊመለምሉ የነ ሮናልዲንሆ ሰፈር ደረሱ። ለምልመላው ይረዳቸው ዘንድም ተጫዋቾችን ለሁለት ከፍለው ግጥሚያ እንዲያደርጉ አዘዙ። ክፍፍሉም ፍትሃዊ እንዲሆን በሰፈር አደረጉት። የላይኛው ሰፈር ልጆችና የታችኛው ሰፈር ልጆች። ጨዋታው ተጀመረ። ልክ እንደተጀመረ ሮናልዲንሆ ተከላካዮችን አተራምሶ አስደናቂ ጎል አስቆጠረ። ከደቂቃዎች በኋላም የግል ብቃቱን ተጠቅሞ ሌላ ጎል ደገመ። ውጤቱም 23 ለ 0 ነበር። የሚገርመው 23ቱንም ጎሎች ያስቆጠረው ሮናልዲንሆ ጎቾ ዲ አሲስ ሞሬራ ነው። መልማዮቹ ወደ ካምፓቸው ሲመለሱ አንድ ሳቂታ ልጅ አስከትለው ተመለሱ። ሮናልዲንሆም ከወንድሙ ጋር አንድ ክለብ ውስጥ የመጫወት ዕድል አገኘ። ሮናልዲንሆ ለታዳጊዎቹ ሮቤርቶ ደግሞ ለዋናው ቡድን፡፡ ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ወንድሙ ሮቤርቶ በደረሰበት ጉዳት ከኳስ ተሰናበተ። ሮናልዲንሆ ወንድሙ ባጋጠመው ነገር ቢያዝንም ኳስ ከመጫወት ግን ለደቂቃም አልቦዘነም። በግሪሚዩ የእግር ኳስ ካምፕ ውስጥ ኳስን ጓደኛው አደረጋት። ቀኑን ሙሉ ውሎው ከኳስ ጋር ሆነ። ከጓደኞቹ ቀድሞ ልምምድ ቦታ መገኘት እንዲሁም ከሁሉም በኋላ መውጣት ባህሪው ሆነ። ይህ ታታሪነቱ ወደ ታላላቅ የዓለማችን ክለቦች አምርቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ በእግር ኳሱ ዓለም እስከዛሬም የማይዘነጉ ተዓምሮችን መፍጠር ቢያስችለውም ዝናና ገንዘብ ይዞት የሚመጣውን ጣጣ እንዲቋቋም አላደረገውም፡፡ ውሎና አዳሩ በየጭፈራ ቤቱ ሆነ፡፡ አብዝቶ መዝናናት ከድህነት ሕይወት ያስመለጠውን ኳስ አስረሳው፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥም ሆኖ ግን ዓለምን በእግር ኳስ ጥበቡ ማስደመም ለእሱ ቀላል ነበር፡፡ በታላቁ ኤልክላሲኮ ታሪክም ከማራዶና በኋላ በተቃራኒ ደጋፊዎች ሜዳ የተጨበጨበለት ተጫዋች እስከመሆን ደረሰ፡፡ በኳሱ ተዝናንቶበታል፣ ተመልካቹንም አዝናንቶበታል፡፡ ይህ ሁሉ ግን ከአምስት ዓመታት በላይ እንዲዘልቅ አብዝቶ መዝናናቱ አልፈቀደለትም:: ብራዚላውያን ለዚህ ዘመን ድንቅ ኮከባቸው ያላቸው ጥልቅ ስሜት ዛሬም እንደ አዲስ እየተቀሰቀሰ በትዝታው አብረው ሲደሰቱና ሲኮሩ ይሰተዋላሉ። ብዙዎች ጥበቡን ሳይጠግቡ የእግር ኳስ ሕይወቱ በአጭሩ ሊቀጭ ችሏል፡ ፡ እኤአ 2002 ከብራዚል ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫን ማንሳት ችሏል። ሮናልዲንሆ የ2005 ባለንደኦር [የዓለም ኮከብ ተጫዋች ሽልማት] አሸናፊ ነበር። በኳስ ሕይወት ስኬትና ዝናንን በመጨበጥ አድናቆትን ማትረፍ የቻለው ሮናልዲንሆ በ800 ሺህ ዶላር ዋስ ሆቴል እንዲታሠር ታዘዘ ይላል የቢቢሲ ዘገባ። ሮናልዲንሆና ወንድሙ ፓራጓይ ውስጥ ሃሰተኛ ፓስፖርትና ሌሎች ሰነዶች ይዘው ተገኝተዋል በሚል በፖሊስ ሊያዙ ችለዋል። ወንድማማቾቹ በወቅቱ እንዲለቀቁ ይግባኝ አመልክተው የነበረ ቢሆንም ሰሚ ጠፍቶ ከአንድ ወር በላይ እሥር ቤት ውስጥ ለመሰንበት ተገደዋል። ብራዚላዊው የእግር ኳስ ጠቢብ ሮናልዲንሆ ጎቹ እና ወንድሙ ፓራጓይ ከሚገኘው እሥር ቤት ተለቀው ውሳኔ እስኪሰጣቸው ድረስ ሆቴል ታስረው እንዲቆይ ውሳኔ ተላልፏል። በተጨማሪ እያንዳንዳቸው 800 ሺህ ዶላር ዋስ ጠርተው የፓራጓይ ዋና ከተማ አሱንሲዮን የሚገኝ ባለ አራት ኮከብ ሆቴል ውስጥ እንዲቆዩ ትዕዛዝ ተላልፎባቸዋል ሲል ዘግቧል። በብራዚላዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሮናልዲንሆ ጎቾና ወንድሙ ላይ ውሳኔውን ያስተላለፉት ዳኛ ገንዘቡ ጫን ያለ እንዲሆን የተደረገው ግለሰቦቹ ሀገር ጥለው እንዳይጠፉ በማሰብ መሆኑን አስገንዝበዋል። «የ40 ዓመቱ የእግር ኳስ ሰው ሮናልዲንሆና ወንድሙ አሲስ እኛ ሃሰተኛ ሰነድ መሆኑን አላወቅንም ነበር »ሲሉ ቢሟገቱም፤ ጠበቃቸውም «የወንድማማቾቹ እሥር ሕገ-ወጥ ነው» ሲል ቢከራከርም ውሳኔው ተፈጻሚ ከመሆን አላዳናቸውም ሲል ቢቢሲ ዘገባውን ቋጭቷል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 2/2012 ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=30124
[ { "passage": "ክሮሺያዊው ሉካ ሞድሪች በ2018 የውድድር አመት በክለቡ ሪያል ማድሪድ እና በሀገሩ ብሄራዊ ቡድን ውስጥ ባበረከተው የላቀ አስተዋፅዎ የባሎን ዶር ሽልማትን ተቀዳጅቷል፡፡የ33 አመቱ የመሀል ሜዳ ኮከብ ባለፉት አስር አመታት ከሊዮኔል ሜሲ እና ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ውጪ የባሎን ዶር ሽልማትን ያሸነፈ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል፡፡", "passage_id": "90671ef3792314228cb229c73e4f338e" }, { "passage": "የቀድሞው የአርጀንቲና ኮከብ ተጫዋች እና በኋላም የአገሩ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበረው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ያረፈው ቤቱ ውስጥ ሳለ በልብ ችግር እንደሆነ ተገልጿል። \n\nማራዶና በዚህ ወር መጀመሪያ አካባቢ በአንጎሉ ውስጥ ላጋጠመው የደም መርጋት የተሳካ ቀዶ ሕክምና ተደርጎለት የነበረ ሲሆን በተከታይነትም ከአልኮል ሱስ ለመላቀቅ ሕክምና ይደረግለታል ተብሎ ነበር። \n\nየዓለማችን የምንጊዜም ታላላቅ ተጫዋቾች ከሚባሉት አንዱ የሆነው ማራዶና አርጀንቲና እአአ በ1986 የዓለም ዋንጫ ባለቤት ስትሆን የቡድኑ አምበል የነበረ ሲሆን ድንቅ ችሎታውንና የታወቀባቸውን የኳስ ጥበቡን በማሳየት ዓለምን አስደምሞ ነበር። \n\nበተለይ በወቅቱ አርጀንቲና ከእንግሊዝ ጋር ባደረገችው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ላይ እሱ \"የእግዜር እጅ\" ያላትና ዳኞች ሳያዩ በእጁ ያስቆጠራት ግብ ዘወትር ትታወሳለች። \n\nበተጨማሪም ለስፔኑ ባርሴሎናና ለጣሊያኑ ናፖሊ ቡድኖች በአውሮፓ ውስጥ የተጫወተ ሲሆን፤ በጣሊያን ሴሪ አ ውስጥም ሁለት ጊዜ ዋንጫ ለማንሳት በቅቶ ነበር። \n\nየአርጀንቲና እግር ኳስ ማኅበር የማራዶና ሞት በተሰማ ጊዜ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባወጣው መግለጫ \"በጀግናችን ሞት በጣሙን አዝነናል\" በማለት \"ሁልጊዜም በልባችን ውስጥ ትኖራለህ\" ብሏል። \n\nማራዶና ለአገሩ አርጀንቲና በአራት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ በተደረጉ 91 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 34 ግቦችን አስቆጥሯል። \n\nማራዶና የተከለከሉ አበረታች መድኃኒቶችንና ዕጽ በመጠቀም ስሙ በተደጋጋሚ ሲነሳ የቆየ ሲሆን ከስፖርትም እገዳ ተጥሎበት ነበር። \n\nማራዶና ፕሮፌሽናል እግር ኳስን ከዛሬ 23 ዓመት በፊት በ37 ዓመት ዕድሜው ያቆመ ሲሆን፤ በአርጀንቲና ውስጥ ያሉ ቡድኖችን በአሰልጣኝነት ከመራ በኋላ የአገሩን ብሔራዊ ቡድንንም በማሰልጠን ለዓለም ዋንጫ አብቅቷል። \n\nከዚያም በኋላ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ እና በሜክሲኮ ውስጥ የሚገኙ ቡድኖችን በተለያዩ ጊዜያት አሰልጥኖ ህይወቱ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ደግሞ የአገሩን አንድ ቡድን በማሰልጠን ላይ ነበር። \n\nየማራዶና አድናቂዎች ሐዘናቸውን ሲገልጹ\n\n ", "passage_id": "814a86171aa2740764db5ff673cbabdf" }, { "passage": "በማርሴሎ ቢዬልሳ ቤተ-ዕውቀት ውስጥ ከሌሎች የበለጠ አስተዋጽኦ ያደረጉት ሉዊ ቫን ሃል ሳይሆኑ አይቀርም፡፡ ቫን ሃል በቅርብ ዘመናት የዓለም ትልልቅ የእግርኳስ ክለቦች በሆኑት ባየር ሙኒክ፣ ባርሴሎና፣ አያክስና ማንችስተር ዩናይትድ አሰልጥነዋል፡፡ ከአሰልጣኙ የቀደመ የአጨዋወት ምርጫ አንጻር የሚወደድ አቀራረብ እንዳልነበረው ብዙ የተወራለትና በ2014ቱ የብራዚሉ ዓለም ዋንጫ ሶስተኛ ደረጃን ያገኘውን የሆላንድ ብሄራዊ ቡድንም መርተዋል፡፡ ከማንችስተር ዩናይትድ ውጪ ቫን ሃል ትልልቅ ቡድኖችን ለሃገር ውስጥና ለዓለምአቀፍ ድሎች በማብቃት ተክነዋል፡፡ በአያክስ ቆይታቸው ልምድ በሌላቸው ወጣቶች ያዋቀሩትን ቡድን ለተከታታይ የቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ አድርሰው በአንዱ ድል አድርገዋል፡፡ ከእነዚህ አንጸባራቂ ስኬቶች በኋላ ቫን ሃል በ2009 የአልክማር ከተማ ክለብ የሆነውን ኤ.ዚ.አልማርን ለማሰልጠን ተስማሙ፡፡ በዚሁ ዓመት ሊደረግ ቀርቶ ሊታሰብ እንኳ የሚከብደውን የኤሬዲቪዚዬ ዋንጫ ወደ ትንሹ ክለብ አመጡ፡፡ ይህን ታሪካዊ ድል ለማሳካት አያክስን፣ አይንድሆቨንን፣ ፌይኖርድንና ኤፍ.ሲ.ትዌንቴን የመሳሰሉ የሃገሪቱ ኃያላን ክለቦችን ጫና መቋቋም ነበረባቸው፡፡በ1995 በአያክስ እና በጣልያኑ የወቅቱ ታላቅ ቡድን ኤሲ ሚላን መካከል የተካሄደውን የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ማርሴሎ ቢየልሳ ደግመው-ደጋግመው አይተውታል፤ በዘላቂነት የሚያዩትም ይመስለኛል፡፡ ይህን ስለማድረጋቸው እርግጠኝነት ይሰማኛል፡፡ በቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ታሪክ አራት የፍጻሜ ጨዋታዎች ባስተናገደው የኧርነስት ሃፔል ስታዲየም የሉዊ ቫንሃል አያክስ ያሳየው የአጨዋወት ዘይቤ እና ማርሴሎ ቢዬልሳ በቅርብ ዓመታት በቺሊ ብሄራዊ ቡድን እንዲሁም በአትሌቲክ ቢልባኦ ክለብ ቆይታቸው በፎርሜሽኖች ላይ እንዲኖር የሚሹት ዋላይነት እንዲሁም ፍሰቱን የጠበቀ የተጫዋቾች እንቅስቃሴያዊ ቦታ አያያዝ ላይ ያላቸው አቋም ማራኪነት ተመሳስሎ አለው፡፡ከጊዜያት በኋላ በቢዬልሳ ተቀባይነት ያገኘው ሐሳብ ቀድሞ በአያክሶች በተግባር የታየ ነበር፡፡ ኤድጋር ዳቪድስ እና ሮናልድ ደቦር በ1-3-3-3-1 ፎርሜሽን መሃል ሜዳ ላይ ከፍራንክ ራይካርድ ፊት በመሐል አማካይነት እንደሚሰለፉ ይጠበቅ ነበር፡፡ እዚህ ላይ በፎርሜሽኖች አሰያየም የግብ ጠባቂውን መስመር መጥቀስ የግድ ይላል፡፡ በሶሥት የመሃል ተከላካዮች የተዋቀረው የአያክሶች የኋላ ክፍል ፍራንክ ደቦር፣ ማይክል ሬይዚገርንና ዳኒ ብሊንድን አካቷል፡፡ ከዚህ የተከላካይ መስመር ሁለቱ መደበኛ የመሃል ተከላካዮች ሲሆኑ አንደኛው ግን የጠራጊነት ሚና የሚወጣ ተከላካይ ነበር፡፡ ይህ የተከላካይ ክፍል በከፍተኛ መግባባት ላይ ተመስርቶ ጠንካራ ጥምረት በመፍጠር በጨዋታ ወቅት የሜዳውን ስፋት የማጥበብ ኃላፊነት በአግባቡ ይወጣ ዘንድ ሁሌም ይጠበቅበት ነበር፡፡በመከላከል የጨዋታ ሒደት ወቅት የመስመር አማካዮች ወይም በሜዳው ስፋት የሚጫወቱ አማካዮች  ወደኋላ እየተመለሱ በሶስት የመሃል ተከላካዮች እና በግራና ቀኝ የሜዳው ቁመት መስመሮች መካከል የሚኖረውን ጥልቅ ክፍተት የመሸፈን ኃላፊነት እንዲወጡ ማሰብ አዲስ አይደለም፤ ቀድሞም ሲተገበር የሰነበተ አጨዋወት ነው፡፡ በሌላ ሁኔታ ከሁለቱ የመስመር አማካዮች አንደኛው ወደኋላ ሲያፈገፍግ በሦስት ተከላካዮች የተዋቀረው የተከላካይ ክፍል የአደረጃጀት መዋቅሩን ሳያዛንፍ ያለምንም እንከን ወደ ሌላኛው መስመር ይጠጋል፡፡ ይህም በአራት ተጫዋቾች የሚከላከል ክፍል ይፈጥራል፡፡ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ በዊጋን ቆይታቸው ይህንኑ ታክቲካዊ ሽግሽግ ከተጫዋቾቻቸው ይጠብቁ ነበር፡፡ ለዚህኛው የመከላከል ሽግግር ሉዊስ ቫን ሃል የፈጠሩት ስልት የተለየ ነው፡፡ ሁለቱ የመሃል አማካዮች (ዳቪድስ እና ደቦር) ወደኋላ በማፈግፈግ የተጋጣሚ ቡድን የመስመር አማካዮችን እግር በእግር እየተከታተሉ የመከላከል አደረጃጀቱ አካል ይሆናሉ፡፡ ይህኛው ስልት በሶስቱ የመሃል ተከላካዮች የእርስ በእርስ እንቅስቃሴያዊ አደረጃጀት መካከል የመለጠጥ ችግር እንዳይከሰት ያግዛል፡፡ ጥበቱን እንደጠበቁ እንዲጫወቱም ይረዳቸዋል፡፡ይህ የቫንሃል የተከላካይ ክፍል አጨዋወት እስከዛሬም ድረስ ልዩ እና ለመተግበር ቀላል ሆኖ  የተገኘው በበቂ ምክንያት ነው፡፡ ከሶሥቱ አማካዮች ሁለቱ የመሃለኛው ሜዳ ቦታቸውን ለቀው ወደኋላ ስለሚሄዱ መሃሉ ክፍል ላይ ክፍተት ይፈጠራል፡፡ ከዚህኛው ወሳኝ የሜዳ ክልል ተጋጣሚን በአንድ ተጫዋች ብቻ የመጋፈጥ አደጋ ያስከትላል፡፡ በርካታ የግብ ዕድሎች የሚመነጩት ከየትኛውም ቡድን አማካይ ክፍል መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ ሉዊስ ቫን ሃል በ10-ቁጥር ሚና በአጥቂ አማካይነት የሚሰለፈውን ያሪ ሊትማነን ወደኋላ አፈግፍጎ ከፍራንክ ራይካርድ ጎን እንዲጫወት በማድረግ በመከላከል የጨዋታ ሒደት አያክሶች በጥምር ተጫዋቾች የሚመራ የአማካይ ክፍል እንዲኖራቸው አደረጉ፡፡ከ1-3-3-3-1 ወደ 1-5-4-1፣ ከመሃል አማካይነት ወደ መስመር ተከላካይነት፣ ከተለምዷዊ አሰላለፍ ወደ አዲስ ሚና…ምስል፦ ከሚላን ጋር በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ የአያክስ የማጥቃት ፎርሜሽን (ግንቦት 24-1995)ምስል፦ ከሚላን ጋር በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ የአያክስ የመከላከል ፎርሜሽን (በግንቦት 24-1995)\nበጨዋታ ወቅት ብዙ እንቅስቃሴ ይደረግበታል ተብሎ የሚታሰበውን የተወሰነ የሜዳ ክፍል (Position-Slot) መለዋወጥ በራሱ ቀልብ የሚስብ ሐሳብ ነው፡፡ ይህንን እግርኳሳዊ ሐሳብ እኔ ራሴ ከጥቂት ዓመታት በፊት በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ቤቱ ዋና አሰልጣኝ ሳለሁ በሥራ ላይ አውዬዋለሁ፡፡ ለዚህ መጽሃፍ ግብዓት ይሆኑኝ ዘንድ ከተለያዩ ጉዞዎቼ የሰበሰብኳቸው መረጃዎች በዋና አሰልጣኝነት በተሳተፍኩበት ሥራ ለአንድ ዓላማ የሚቆም ቡድን ከመሥራት የሚገኘውን ትምህርት ይበልጥ ግልጽ አድርጎልኛል፡፡ ይህ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ቡድን አሰልጣኝነት ተመክሮዬ ብዙዎች በእግርኳስ ሊያገኙ የማይችሉትን አዳዲስ ሐሳቦችን በተግባር ለመሞከርና ለመፈላሰፍ እድል ሰጥቶኛል፡፡ ሁኔታዎች አመቻችቶልኛል፡፡ ከሁሉም በላይ እግርኳስ የምመለከትበትን አተያይ እንድቀይር እና በሐሳብ እምነት ስለማሳደር እንዳስብ ትምህርት ሆኖኛል፡፡ከማንም ሰው በላይ የማርሴሎ ቢዬልሳ መሰረታዊ ሐሳቦችና የዕምነት መርሆዎች የዚህን መጽሃፍ ፍሬ ነገሮች ለማጠናቀር ረድቶኛል፡፡ ይሁን እንጂ መጽሃፉ በአሰልጣኙ ፍልስፍና ዙሪያ ያጠነጠነ የግል አረዳዴ ትርጉም በመሆኑ በውስጡ የሚቀርቡት ናሙናዎች በሙሉ በእኔ ልምድ በተሻለ ያወቅኋቸው አልያም በቅርብ የተረዳኋቸው\nናቸው፡፡ ከቢዬልሳ ጋር ከሰሩ ሰዎች ጎን ተቀምጬ ለማውጋት ብዙ ሃገራትን ዞሬያለሁ፤ ከእርሱ ሥር በተጫዋችነትም ሆነ በረዳትነት ያሳለፉ ባለሙያዎችን ፍለጋ ያላዳረስኩት ቦታ የለም፡፡ በእርሱ ዙሪያ ወይም በአጋዥነት አብረው ያሳለፉ ዕድለኞችን በየስፍራው ላገኝ ጥሬያለሁ፡፡ በሃሜትና በጭምጭምታ ወሬ የአርጀንቲናዊውን ስም በክፉ ለማንሳት ከማይወዱ ታማኝ ተከታዮቹ ጋር ስለ ንጹህ የእግርኳስ አጨዋወት አውርቻለሁ፤ የእርሱን የጨዋታ ሥልት ከጥቅም ውጪ ስለሚያደርግ ታክቲካዊ መፍትሄም ብዙ ሰምቻለሁ፡፡በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከራሴ የሆነ አዲስ ያበረከትኩት ሐሳባዊ አስተዋጽኦ እንደሌለኝ እንድታውቁልኝ እፈልጋለሁ፡፡ በውስጡ ከቀረቡ አስገራሚ የአጨዋወት ሐሳቦች ውስጥ አንዳቸውም የእኔ አይደሉም፡፡ ተመሳሳይ ዕምነት ካላቸው በርካታ ታላላቅ አሰልጣኞች የተለያዩ ሐሳቦችን ወስጄ አንድ ላይ ከማሰባሰብ ባለፈ ያደረግሁት የተለየ ነገር የለም፡፡ መጽሃፉን ለማዘጋጀት በተደረገው ጥረት ሐሳቦቹን በጥልቀት የመረዳትና ወሰውሰብ ያሉትንም ለመፍታት የሚያስችል ከፍተኛ ልምድ የማግኘት አጋጣሚ ፈጥሮልኛል፡፡ ሁሌም በቢዬልሳ ታክቲካዊ አስተሳሰብ ዙሪያ የሚደረጉት እግርኳሳዊ ውይይቶች በንድፈ ሐሳብ ደረጃ እንዲጠናቀሩ ይደረጋል፡፡ ይህ መጽሐፍ ትኩረቱን ለውይይት በሚቀርቡት ሐሳቦች ዙሪያ እንጂ በተወያዮቹ ማንነት ላይ አያደርግም፡፡\nመጽሃፉ እግርኳስ እና እግርኳስ ላይ ብቻ ያጠነጥናል፤ የሐሳባውያኑን ግለሰባዊ የአደባባይ ስብዕናን መዳሰስ የመጽሃፉ ዓላማ አይደለም፡፡ ይህ መጽሐፍ ከሌሎች ሥራዎች የበለጠ በህይወቴ ተፈላጊ እንደሚሆን እና የታለመለትን ግብ እንደሚመታ እምነቴ ነው፡፡ አንባቢዎችም በመጽሃፉ ውስጥ የተካተቱትን እግርኳሳዊ ሐሳቦችና መመሪያዎች ላትቀበሏቸው ትችሉ ይሆናል፡፡ በተጻራሪ ሁኔታ እግርኳስን የምታዩበትን መነጽር በመቀየር ረገድ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጥሮባችሁ በማርሴሎ ቢዬልሳ ፍልስፍና ማዕቀፍ ውስጥ ያሉት ሐሳቦች ሊገለጥላችሁም ይችላል፡፡ የቢየልሳ ተከታዮች በሆኑት ታማኝ ደቀመዛሙርቱ ፔፕ ጓርዲዮላ፣ ማውሪዚዮ ፖቼቲኖ፣ ሄራርዶ ማርቲኖ፣ ሆርሄ ሳምፓውሊ፣ ኤድዋርዶ ቤሪዞ፣…በተጓዙበት የሐሳብ ፈለግ እናመራም ይሆናል፡፡ ያኔ እኔም እናንተም “ቢየልሲስታ” ሆንን ማለት ነው፡፡", "passage_id": "c68074d98dd968534d78052743bb86a7" }, { "passage": "የቅርብ ጓደኛውና ለአመታትም አብሮት የተጫወተው ቲየሪ ሄንሪ \"ለኔ ብዙዎች ኒኮ ብለው በሚያስቡትና በኒኮ መካከል የሰማይና የምድር ያህል መራራቅ አለ\" በማለት ምስክርነቱን ሰጥቷል።\n\nበእግር ኳስ የዝና ጣራ ላይ ደርሶ የነበረው ኒኮላስ አኔልካ ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጫውቷል። የአውሮፓ ሻምፒዮንሺፕ፣ ሻምፒዮንስ ሊግ፣ ፕሪሚየር ሊግን ከሁለት ክለቦች ጋርና ኤፍ ኤ ዋንጫንም አራት ጊዜ አሸንፏል።\n\nሆኖም የእግር ኳስ ህይወቱ አልጋ ባልጋ አልነበረም፤ ከብሄራዊ ቡድን እንዲሁም ከዌስት ብሮም ክለብ ተባሯል። \n\nበተደጋጋሚም በበርካታ ተቃውሞች፣ ማዕቀብና ሌሎች አወዛጋቢ ጉዳዮችም በተደጋጋሚ ስሙ ሲጠራ ነበር። \n\nየ41 አመቱ አኔልካ ታሪኩን በራሱ አንደበት ለኔትፍሊክስ ተናግሯል። ወደኋላ ዘወር ብሎ ስኬቶቹንና አወዛጋቢ ስለተባሉ ጉዳዮችም ሆነ ቀጥተኛነቱ ምን ያህል እንዳስከፈለው ተናግሯል።\n\nሪያል ማድሪድን ጠላሁት\n\nኒኮላስ አኔልካ ሪያል ማድሪድ በነበረበት ወቅት\n\nአኔልካ ገና በ17 አመቱ ነበር ለታላቁ ቡድን አርሴናል የፈረመው። ወቅቱም በጎርጎሳውያኑ 1997 ነበር። አርሰናል በ1997ና በ1998 የፕሪሚየር ሊግና የኤፍ ካፕ ዋንጫዎችን እንዲያሸንፍ ትልቅ ሚና ተጫውቷል።\n\nወደ አርሰናል የመጣውም ድንቅ ችሎታውን በተረዱት አሰልጣኙ አርሴን ቬንገር አማካይነት ነበር። \n\nከቬንገርም ጋር ስላላቸው ግንኙነት \"አርሴን ቬንገር ከኔ ጎን ነበር። ከጎንህ ሆኖ የሚደግፍህ ሰው እንዳለ ሲሰማህ ያለ የሌለህን ትሰጣለህ\" ብሏል።\n\nነገር ግን በጎርጎሳውያኑ 1999 አኔልካ በ29.75 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ሪያል ማድሪድ ተዛወረ።\n\n\"ሪያል ማድሪድን ስቀላቀል ኮከብነት ምን ማለት እንደሆነ ተረዳሁ እናም ጠላሁት\" ይላል።\n\nሪያል ማድሪግ እግሩ ከረገጠባት ወቅት ጀምሮ ምን ያህል ውጥረት እንደገጠመውም ፊልም ላይ ይታያል። ይኸም ከመልበሻ ክፍል ይጀምራል።\n\n\"ተቀምጬ እያለሁ አንድ ተጫዋች ይመጣና ቦታዬ ነው ብሎ ያስነሳኛል፣ ሌላ ቦታ ስቀይርም እንዲሁ ሌላኛው እንዲሁ እያሉ አስነሱኝ\" ይላል።\n\nአኔልካ ለአምስት ወራት ያህል አንድም ግብ አላስቆጠረም፤ የሆነ ወቅትም ላይ አልለማመድም ብሎም በመቃወምም አቁሞ ነበር\n\n\"እንደ ውሻ ነው የቆጠሩኝ\" በማለት ምሬቱን አጋርቷል።\n\nበአጠቃላይ ሪያል ማድሪድ ላይ የነበረውንም ወቅት \"መስዋዕትነት መከፈል የሚገባቸው ጉዳዮች ነበሩ እሱን ደግሞ ገና ታዳጊ በመሆኔ አልተረዳሁትም\" ብሏል።\n\nለሪቨርፑል ደጋፊዎች ማወቅ ያለባችሁ መቆየት እፈልግ ነበር \n\nኒኮላስ አኔልካ ሊቨርፑል በነበረበት ወቅት\n\nበጎርጎሳውያኑ 2002 አኔልካ ሊቨርፑልን ተቀላቀለ። ፈረንሳያዊው አሰልጣኝ ጄራል ሁልየር ጋር ግቡቡነት ነበራቸው ተብሏል። \"ለኔ ምርጥ ክለብ ነውም\" ይላል።\n\nነገር ግን በመንፈቁ ማብቂያ ወቅት አሰልጣኙ አኔልካ በሊቨርፑል እንዲቀጥል አልፈለጉም።\n\nአኔልካን ማኔጅ የሚያደርጉት ወንድሞቹ ሌላ ክለብም እየፈለጉ መሆናቸው አሰልጣኙን አላስደሰተም።\n\nአኔልካ በዚህ ይፀፀታል።\n\n\"የሊቨርፑል ደጋፊዎች እኔ መቆየት እንዳልፈለግኩ ነው የተሰማቸው፤ ሁኔታው እንደዛ አይደለም። ያ ወቅት ለኔ አሳዛኝ ነው። ታላላቅ ነገሮችን ማከናወን የምችልበት ክለብ ነበር\" ብሏል።\n\nፀረ- ሴም አይደለሁም \n\nምናልባት በአኔልካ የእግርኳሰኝነት ህይወት ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብ ያስከተለው በዌስት ብሮም ውስጥ የነበረው ቆይታ ነው።\n\nግብ ሲያስቆጥር ደስታውን ለማሳየት ቄኔሌ የተባለውን ምልክት ማሳየቱ ነበር ከፍተኛ ውግዘት ያደረሰበት። \n\nምልክቱን ፈረንሳያዊው ኮሜዲያን ዱዮዶን ምባላ ሲጠቀምበት ይታያል። ይህ ግለሰብ በፀረ ሴማዊነቱ የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡም ፌስቡክ አግዶታል።\n\n ይህንንም ተከትሎ አኔልካ አምስት ጨዋታዎች ታገደ፤ 80 ሺህ ፓውንድም... ", "passage_id": "b9b1e8c33e3d810f65de271c71f55e56" }, { "passage": "ከዓለም ረዥሙ የቀድሞው የእግር ኳስ ተጫዋች ሮማኒያዊው ጆርጅ ሙሬሳን በ6.3 ሴንቲ ሜትር የሚያጥረው የ23 አመቱ ታኮ፤ የታዋቂው የቦስተን ሴልቲክስ ከቋሚዎቹ አስራ አምስት ተጫዋቾች አንዱ ለመሆንም ጥረት ላይ ነው።\n\n• የደቡብ አፍሪካ ባሕር ጠላቂዎች በኬንያ አስክሬን ፍለጋ ላይ ሊሰማሩ ነው \n\n• የካቶሊክ ቄሶች ማግባት ይፈቀድላቸው ይሆን?\n\n• በአሜሪካዊቷ ፖሊስ የፍርድ ሂደት ምስክርነት የሰጠው የዐይን እማኝ ተገደለ\n\nሴልቲክስ ታኮ ፎልን የመረጠበት ምክንያትም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቡ እንደሆነም ተገልጿል።\n\nበሴኔጋሏ መዲና ዳካር የተወለደው ታኮ፤ ወደ አሜሪካ የሄደው በ16 ዓመቱ ሲሆን፤ በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሴንትራል ፍሎሪዳ ቅርጫት ኳስ ይጫወት ነበር።\n\nታኮ ለቢቢሲ እንደተናገረው፤ ዩኒቨርስቲው ውስጥ ብዙዎች ሙያውን እንዲያሳድግ ድጋፍ አድርገውለታል።\n\nታዳጊ ሳለ ብዙም ስለ ቅርጫት ኳስ እንደማያውቅ ይናገራል። ጊዜውን ያሳልፍ የነበረው ካርቱን ፊልሞች በማየት ነበር። የአያቱ ቅርጫት ኳስ መውደድ ስፖርቱ ላይ ፍቅር እንዲያሳድር አድርጎታል።\n\nወደ አሜሪካ ከሄደ በኋላ ሙሉ ትኩረቱን ወደ ቅርጫት ኳስ አድርጓል። ጉዞው ግን አልጋ በአልጋ አልነበረም።\n\n\"ቅርጫት ኳስ መጫወት አልችልም ነበር። ብዙ ነገር መማር ይጠበቅብኝ ነበር። እድለኛ ሆኜ ብዙ ሰዎች ራሴን እንዳሻሽል ረድተውኛል\" ይላል።\n\nሂውስተን አንድ ዓመት ከቆየ በኋላ ወደ ቴኒሲ፣ ጂዎርጂያ እና ፍሎሪዳ አቅንቷል። በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሴንትራል ፍሎሪዳ ሁለት ዓመት ቆይቷል።\n\n\"አንድ ሴኔጋላዊ ታዳጊ ነበርኩ። ቅርጫት ኳስ መጫወት የጀመርኩትም ከስድስት ዓመት በፊት ነበር። ኤንቢኤ ውስጥ ለመጫወት ብዙ ለፍቻለሁ። በጣም እድለኛ እንደሆንኩ ይሰማኛል። ቅርጫት ኳስ ሕይወቴ ነው። አንድ ቀን እንኳን ሳልጫወት ባልፍ አዝናለሁ\" ሲል ይናገራል።\n\n ", "passage_id": "01032eb5e445c086250ec35cb7a45475" } ]
4f8419d9ac2daf6e9a4ea5a355c83689
40d2f498b59fb0bf9cf0548e21a15c61
ሉሲዎቹ ድጋፍ ለማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው
ስፖርት በባህሪው ተጽእኖ ፈጣሪ እንደመሆኑ በቀላሉ መልዕክትን ሊያስተላልፍና ንቅናቄ ሊፈጥር እንደሚችል እሙን ነው። ይህ በመሆኑም ዓለም በአንድነት ከተላላፊው ቫይረስ ጋር እያደረገ ባለው ፍልሚያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል። በኢትዮጵያም የስፖርት ማህበራት፣ ክለቦች፣ ስፖርተኞችና ሌሎች ባለሙያዎች የበኩላቸውን ማበርከት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ሉሲዎቹም በዋና አሰልጣኛቸው ብርሃኑ ግዛው አስተባሪነት የድርሻቸውን ለመወጣት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ። እንደ ሀገር የመጣውን ፈተና ለመመከት የሚደረገውን እቅስቃሴ ለማገዝ በቅድሚያ የተነሱት የዋናው ሴት ብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች ነበሩ። ነገር ግን የገንዘቡን መጠን በመመልከት ለ20 እና 17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን፣ የንግድ ባንክ ሴቶች ክለብ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች እንዲሁም ደጋፊዎች ጥሪ አቅርበው ተቀባይነት ማግኘታቸውን አስተባባሪው አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ይገልጻል። በመገናኛ ብዙሃን የተደረገውን ጥሪ ተከትለው ብዙዎች ሚናቸውንለመወጣት እንቅስቃሴውን በመቀላቀላቸው ገንዘብ ማሰባሰቡን በቀጣዩ ሳምንት መጀመሪያ ሙሉ ለሙሉ በማጠናቀቅ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴ ገቢ የሚደረግም ይሆናል። የገንዘብ ማሰባሰቡ ስራ ተጫዋቾች በውድድሮች ተሳታፊ በመሆን ሃገራቸውን ከመወከል ባሻገር ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ያስችላቸዋል። ከዚያ ባሻገር ግን ተጫዋቾች ተጽእኖ የመፍጠር አቅማቸውን በመጠቀም ደጋፊዎችንና ህዝቡን ማነሳሳትን ዓላማው ያደረገ መሆኑንም አሰልጣኙ ይጠቁማሉ። ለማሰባሰብ የታቀደው የገንዘብ መጠን 100ሺ ብር ሲሆን እስካሁን የተዋጣው ከ55ሺ ብር በላይ ደርሷል፤ በቀጣይ ቀናትም እቅዱን ለማሳካት ጥረት ይደረጋል። ከድጋፉ ባሻገር ኢትዮጵያን ጨምሮ ዓለምን እያናወጠ ያለው ቫይረስ ማለፉ አይቀርምና ካለፈ በኋላ ላለመቸገር ተጫዋቾች ላይ መስራት ተገቢ ነው። በዚህ ላይም የግንዛቤ ችግር መኖሩን ያነሳው አሰልጣኙ ‹‹ በስፖርቱ ውስጥ ሆነን ኃላፊነታችንን ተወጥተናል፤ በዚያ ልክ ግን በየደጃችን ትንሽ እንቅስቃሴ የመስራትና የስፖርት ቁሳቁሶችን በማዘጋጀት በግል የመስራት ልምድ ችግር አለብን። ሁሌም አሰልጣኞችን እንጠብቃለን። ይህ ሁኔታ ካለፈ በኋላ ስፖርቱ አንዳይቀዛቀዝና እንደ አዲስ ከዜሮ ጀምረን ውጤት እንዳናጣ የትኛውን ስራ መቼ መስራት አንዳለበን አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን እያደረገን ነው። ይህ የበለጠ ጥሩ ይሆናል ብለን አንጠብቃለን፤ እኛ አንደ ባለሙያ ከምንሰጣቸው ባለፈ ተጫዋቾቹ ተዘናግተው ስራቸው ላይ ወደ ኋላ እንዳይሉ እየሰራን እንገኛለን›› ሲል ያብራራል። በዚህ ሁሉም ቤቱ እንዲቆይ በተደረገበት ወቅት ስፖርተኞች እንደ ቀድሞው ልምምዳቸውን ለመስራት ከባድ ይሆንባቸዋል። ባደጉት ሃገራት አሰልጣኞች ተጫዋቾቻቸውን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዘው ክትትል ያደርጉላቸዋል። ተጫዋቾቹም ከቤታቸው ሆነው በየግላቸው የሚያደርጉትን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በተንቀሳቃሽ ምስል ለዓለም በማጋራት ላይ ይገኛሉ። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት ግን ይህ የተለመደ ካለመሆኑም ባለፈ በምን መልኩ መስራት እንደሚቻል ግንዛቤውም የለም። ለዚህም አሰልጣኞች በማህበራዊ ትስስር ዘዴዎችን በመጠቀም (በቴሌግራም) ከተጫዋቾቻቸው ጋር ግንኙነት እንደሚያደርጉ አሰልጣኙ ያስረዳል። በዚህም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዴት መስራት እንደሚችሉ ግንዛቤ በመፍጠር ላይ ይገኛሉ። ቴክኒካዊ የሆኑ የስልጠና ክፍሎችንም በተለያዩ የአሰልጣኝነት ስልጠናዎች ባገኟቸው ልምዶች ታግዘው ለተጫዋቾቻቸው ያጋራሉ። ከዚህ በተጓዳኝ ተጫዋቾች በመገናኛ ብዙሃን በሚሰሙትና በሚመለከቱት በመረበሽና በመጨነቅ ስነ-ልቦናቸው እንዳይጎዳ ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ለማሳወቅ የአሰልጣኞች ቡድኑ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ለሉሲዎቹም ሆነ ለዋልያዎቹ, ባለውለታ እንደመሆኑ በዚህ ወቅት ስፖርት፤ ህዝቡ ሚናውን በመወጣት ከጎኑ መሆኑን ማሳየት አለበት። ዝናብ፣ ብርድና ጸሃይ ሳይል ቡድኑን ሲደግፍና እንዲሁም ወደ ውጪ ሃገራት ሲጓዝ ከጎኑ የነበረውን ህዝብ በዚህ ወቅት የማጽናናትና የማረጋጋት ግዴታ እንዳለበት አሰልጣኙ ይገልጻል። የስፖርቱ ቤተሰብ ህዝቡ በቫይረሱ ተጠቂ እንዳይሆን እንዴት መጠንቀቅ እንደሚገባው ከማስተማር ባሻገር በግልና በቡድን የሚያደርገው አስተዋጽኦ በቂ ነው የሚል እምነት የሌለው አሰልጣኙ፤ ከዚህ በላይ አስፈላጊ መሆኑን አመላክቷል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 3/2012 ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=30194
[ { "passage": " የ2020 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያና ማጣሪያ ጨዋታዎች ድልድል ይፋ ተደርጓል። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ሴት ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) በቅድመ ማጣሪያና ማጣሪያ ጨዋታዎች የሚገጥሙትን ቡድን አውቀዋል። ሉሲዎቹ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ከጅቡቲ ብሔራዊ ቡድን ጋር የፊታችን ሚያዚያ አራት ቀን የሚያደርጉ ሲሆን ጅቡቲን በደርሶ መልስ ጨዋታ ድምር ውጤት የሚያሸንፉ ከሆነ በመጨረሻው የማጣሪያ ጨዋታ ከሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚጫወቱ ይሆናል። በአሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመራው\nየኢትዮጵያ ሴት ብሔራዊ ቡድን ለ2020 የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከወዲሁ ለውድድሩ ትኩረት በመስጠት ከፍተኛ ስራዎችን እየሰራ\nየሚገኝ ሲሆን አሰልጣኙ ቡድኑን ለአፍሪካ ዋንጫ ማሳለፍ ካልቻሉ ራሳቸውን ከአሰልጣኝነት ስራ እንደሚያገሉ መግለፃቸው ይታወሳል።\nለመጀመሪያ ጊዜ ሰላሳ ሁለት አገራትን\nየሚያሳትፈው የ2020 የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 2018 ተካሂዶ ከነበረው ውድድር አስራ ሁለት አገራትን ጨምሮ ሲካሄድ ዘንድሮ\nየመጀመሪያው ይሆናል። ይሁን እንጂ ይህን ውድድር የሚያዘጋጀው አገር እስካሁን አልታወቀም።ካፍ የ2020 የሴቶችን የአፍሪካ ዋንጫ\nሞሮኮ እንድታዘጋጅ ፍላጎት እንዳለው የተለያየ መረጃ እየወጣ ይገኛል።ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከበጀት እጥረት ጋር ተያይዞ የ2020 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫን እንደማታዘጋጅ\nከተገለጸ ወዲህ የአፍሪካ እግር ኳስን በበላይነት የሚመራው ካፍ ደቡብ አፍሪካ ውድድሩን እንድታዘጋጅ ጥሪ ቢያቀርብላትም ለ2023\nየሴቶች ዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት ፉክክር ውስጥ በመግባቷና የዓለም ዋንጫውን ለማዘጋጀት ከፍተኛ ስራ ውስጥ በመገኘቷ ጥያቄውን ውድቅ\nማድረጓ ይታወቃል። ካፍ የ2020 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫን አዘጋጅነት ጥያቄ በቅርቡ የመላው የአፍሪካ ጨዋታዎችን በድምቀት ወደ አዘጋጀችው\nሞሮኮ ፊቱን በማዞር ጥያቄ ሊያቀርብ እንደተዘጋጀ ታውቋል። ሞሮኮ የ2020 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫን የምታዘጋጅ ከሆነ ሉሲዎቹ ከጅቡቲ አቻቸው ጋር በሚያደርጉት\nጨዋታ የአፍሪካ ዋንጫ ትኬታቸውን በቀላሉ የሚቆርጡበት እድል ሰፊ ይሆናል። የጅቡቲ ብሔራዊ ቡድን ከአራት ሳምንት በፊት ተካሂዶ\nበነበረው የመካከለኛና ምስራቅ አፍሪካ(ሴካፋ) ዋንጫ ላይ ከዩጋንዳ፣ኬንያና ኢትዮጵያ ጋር ተደልድሎ በኬንያ 13ለ0፣ በዩጋንዳ\n12ለ0 እንዲሁም በኢትዮጵያ 8 ለ 0 ተሸንፎ በውድድሩ በአጠቃላይ ሰላሳ አንድ ግቦች በማስተናገድ አንድም ግብ ሳያስቆጥር መቅረቱ\nይታወሳል። ይህም ሉሲዎቹ በቅድመ ማጣሪያው ጨዋታ በቀላሉ አሸንፈው ወደ ቀጣዩ ማጣሪያ እንደሚያልፉ ከፍተኛ ግምት እንዲሰጣቸው አድርጓል።\nእኤአ 1991 ላይ በተጀመረው የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ላይ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ 2002 ተሳታፊ\nመሆን ብትችልም በውድድሩ ከምድብ ጨዋታዎች ማለፍ እንዳልቻለች ይታወሳል። 2004 ላይ ዳግም ተሳታፊ በመሆን አራተኛ ደረጃን ይዛ\nያጠናቀቀችበት ውጤት በታሪክ ትልቁ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ በመድረኩ የተሳተፈችው 2012 ላይ ነው። ዘንድሮ ግን ከስምንት ዓመታት\nበኋላ ወደ መድረኩ የመመለስ ትልቅ ተስፋ ሰንቃለች።አዲስ ዘመን አርብ ህዳር\n26/2012 ቦጋለ አበበ", "passage_id": "32816ef5eb105c385ccff5fa9eb80d0d" }, { "passage": "በአሰልጣኝ ሰላም ዘርአይ የሚመራው ቡድኑ ለ36 ተጨዋቾች ጥሪ በማድረግ ዞላ ኢንተርናሽናል ሆቴል ማረፊያውን በማድረግ በወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ሜዳ ልምምዱን እያደረገ ይገኛል፡፡ ቡድኑ በቀጣይ የማጣርያ ዙር ናይጄርያን እስከሚገጥምበት ህዳር ወር መጨረሻ ድረስ እንዴት ባለ ሁኔታ እንደሚቆይ ለማወቅ ልምምዳቸውን ወደሚሰሩበት ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ባቀናንበት ወቅት ቡድኑ አስቀድሞ ጥሪ ከተደረገላቸው 36 ተጫዋቾች መካከል14 ተጨዋቾች ሲቀነሱ ከወጣቶች አካዳሚ 15 አመት በታች ቡድን እና ከደደቢት 4 ተጨዋቾችን በመጨመር በጥቅሉ 25 ተጨዋቾችን በመያዝ ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል።ስለ ቡድኑ ቀጣይ ቆይታ እና ዝግጅት አስመልክቶ አሰልጣኝ ሰላም ዘራይ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት እስከ ጨዋታው መዳረሻ ተሰባስቦ እንደማይቆይ ገልጸዋል፡፡ ” ተጫዋቾቹ ከዚህ በኋላ በደንብ እስክናውቃቸው ድረስ ከእኛ ጋር ለአንድ ሳምንት የሚቆዩ ይሆናል፡፡ በመቀጠል ለሁለት ሳምንት ወደ ቡድኖቻቸው አምርተው እንዲዘጋጁ ካደረግን በኋላ ተመልሰው ጥሪ ተደርጎላቸው ለአንድ ሳምንት ሆቴል ገብተው በሚቆዩበት ወቅት የወዳጅነት ጨዋታዎች አድርገን ተመልሰው ወደ ክለብ ውድድሮች እንዲገቡ እናደርጋለን፡፡ የጨዋታው መቃረቢያ ሲደርስ ደግሞ ለሦስት ሳምንት ያህል ወደ መደበኛ ዝግጅት እንገባለን፡፡” ብለዋል፡፡አሰልጣኝ ሰላም የኬንያው ጨዋታ መቅረቱ በቡድኑ ላይ የሚያሰከትለው ተፅዕኖም አብራርተዋል፡፡  “የነበረን የዝግጅት ወቅት አነስተኛ በመሆኑ ልንቸገር እንችላለን ብለን አስበን ስለነበር እንደ ጠቀሜታ እንወስደዋለን፡፡ የዛኑ ያህል ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች አለማድረጋችን ጉዳት ቢሆንም አሁን ለቀጣዩ ጨዋታ በበቂ ሁኔታ እንድንዘጋጅ እድል ሰጥቶናል፡፡”የኢትዮዽያ ከ17 አመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በአንደኛው ዙር ማጣርያ ከናይጄርያ አቻው ጋር የመጀመርያ ጨዋታውን ህዳር ወር መጨረሻ ላይ (ቀኑ አልታወቀም) የሚያደርግ ይሆናል።", "passage_id": "d91bf1ab47679fec1fddf69c5efac790" }, { "passage": "የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት እንዲረዳቸው ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።በቅርቡ ከቡሩንዲ ጋር የመጀመርያ ዙር ጨዋታውን የሚያደረገው ብሔራዊ ቡድኑ ከሁለት ሳምንት በፊት ፍሬው ኃይለ ገብርኤል እና ህይወት አረፋይኔን በዋና እና ምክትል አሰልጣኝነት መቅጠሩ የሚታወስ ሲሆን ለጨወቻው የሚያደርገውን ዝግጅት ከታህሳስ 25 ጀምሮ እንደሚያከናውንም ይጠበቃል።ፌዴሬሽኑ ይፋ ያደረገው የተጫዋቾች ዝርዝርግብ ጠባቂዎች\nዓባይነሽ ኤርቄሎ (ሀዋሳ ከተማ)፣ እምወድሽ ይርጋሸዋ (አዳማ ከተማ)፣ ምህረት ተሰማ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)ተከላካዮች\nናርዶስ ጌትነት (አዳማ ከተማ)፣ ናርዶስ ጌትነት (አዳማ ከተማ)፣ ታሪኳ ደቢሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ብዙዓየሁ ታደሰ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ማህደር ባዬ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ፍሬወይኒ ገብረፃድቅ (ኤሌክትሪክ)አማካዮች\nእመቤት አዲሱ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ የምስራች ላቀው (አዳማ ከተማ)፣ ገነት ኃይሉ (አዳማ ከተማ)፣ ዙፋን ደፈርሻ (ሀዋሳ ከተማ)፣ እፀገነት ግርማ (ጌዴኦ ዲላ)፣ አረጋሽ ካልሳ (መከላከያ)፣ ሲሳይ ገብረዋህድ (መከላከያ)፣ ማህሌት ታደሰ (አቃቂ ቃሊቲ)፣ ብርቄ አማረ (አቃቂ ቃሊቲ)አጥቂዎች\nሳራ ነብሶ (አዳማ ከተማ)፣ ነፃነት መና (ሀዋሳ ከተማ)፣ ሥራ ይርዳው (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ረድኤት አስረሳኸኝ (ጌዴኦ ዲላ)፣ አይዳ ዑስማን (መከላከያ)፣ ዮርዳኖስ ምዑዝ (መቐለ 70 እንደርታ)", "passage_id": "bce99b744f601060b8d851779f9116b8" }, { "passage": "በአሰልጣኝ በኃይሏ ዘለቀ የሚመራው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን መጋቢት 23 ቀን 2007 ለመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ማጣርያ ከካሜሩን አቻው ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ 40 ተጫዋቾችን ጠርቷል፡፡ሉሲዎቹ ዝግጅታቸውን ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የሚጀምሩ ሲሆን የኢትዮጰያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግም ለአንድ ወር ያህል ይቋረጣል ተብሏል፡፡ለሉሲዎቹ የተመረጡት 40 ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡-    ", "passage_id": "8b6de7f5c9a4a9e8fee19b0ce456b27a" }, { "passage": "በህንድ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም የሴቶች ከ17 ዓመት ዋንጫ ውድድር ለመሳተፍ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረገ የሚገኘው ብሔራዊ ቡድኑ ከዩጋንዳ ጋር ላለበት የመልስ ጨዋታ ልምምዱን እየሰራ ይገኛል።በአሰልጣኝ ሳሙኤል አበራ (ዋና) እንዲሁም በአሰልጣኝ ሰርካዲስ እውነቱ (ረዳት) አሰልጣኝነት እየተመራ ያለው ብሔራዊ ቡድኑ ከሳምንት በፊት ወደ ካምፓላ አቅንቶ በዩጋንዳ 2-0 መሸነፉ ይታወሳል። ቡድኑ ከሜዳ ውጪ የደረሰበትን ሽንፈትን ቀልብሶ ወደ ቀጣይ ዙር ለማለፍም ከአንድ ሳምንት (ረቡዕ) በፊት የመልሱን ጨዋታ ወደሚያደርግበት ባህርዳር አምርቶ ልምምዶችን እያከናወነ ይገኛል።ቡድኑ ባህር ዳር ከደረሰ በኋላ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በቀን ሁለት ጊዜ ከዛ በኋላ ደግሞ በቀን አንድ ጊዜ የልምምድ መርሐ ግብሮችን እያከናወነ ይገኛል። ዛሬም ከ4 ቀናት በኋላ ላለበት ወሳኝ ጨዋታ ለ2 ሰዓታት የቆየ ልምምድ ከ9 ሰዓት ጀምሮ አከናውኗል። በልምምዱም ቡድኑ ለ2 ተከፍሎ የግማሽ እና የሙሉ ሜዳ ግጥሚያዎችን ሲያደርግ ተስተውሏል። በዋናነት ግን ተጨዋቾቹ ግብ የማስቆጠር ችሎታቸው እና ስልታቸው እንዲጎለብት ግብ ላይ ያተኮረ ስልጠናዎች ሲሰጡ ታይቷል።ከቡድኑ ጋር በተያያዘ 2 ተጨዋቾች በአዲስ መልክ ጥሪ ቀርቦላቸው ስብስቡን ዛሬ ተቀላቅለዋል። በዚህም አረጋሽ ካልሳ እና ገነት ኃይሉ ትላንት ወደ ባህር ዳር አምርተው ዛሬ ከአጋሮቻቸው ጋር ልምምድ መስራት ጀምረዋል። ከሁለቱ ተጨዋቾች በተጨማሪ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግብ ጠባቂ የሆነችው ምህረት ተሰማ ነገ ቡድኑን ልትቀላቀል እንደሆነ ታውቋል። ከዚህ ውጪ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦላቸው ቡድኑን ለቀው የነበሩት ቤተልሄም በቀለ እና ነፃነት ፀጋዬ ዛሬ ዳግም ቡድኑን ተቀላቅለው ልምምድ እየሰሩ ታይቷል።በሶሊያና ሆቴል መቀመጫውን አድርጎ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ዋና ስታዲየም እና መለስተኛ ስታዲየም ልምምዱን እየሰራ የሚገኘው ቡድኑ ትላንት 9 ሰዓት ሽምብጥ የሴቶች ፕሮጀክት ከተባለ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አከናውኖ በሰፊ ጎል አሸንፏል።", "passage_id": "ea3af1fb17ad0acffa94000d884b034f" } ]