doc_no
int64
1
12.6k
doc_text
stringlengths
81
395k
relevant_topic_nos
sequencelengths
0
1
relevant_topic_titles
sequencelengths
0
1
relevant_topic_descriptions
sequencelengths
0
1
relevant_topic_narratives
sequencelengths
0
1
12,401
1  ይሖዋም እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር በወጡ በሁለተኛው ዓመት ሁለተኛ ወር፣ የመጀመሪያ ቀን ላይ በሲና ምድረ በዳ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ሙሴን አነጋገረው። እንዲህም አለው፦ 2  “የእስራኤልን ማኅበረሰብ በሙሉ በየቤተሰባቸው፣ በየአባቶቻቸው ቤትና በስም በተዘረዘሩት ወንዶች ሁሉ ቁጥር መሠረት በግለሰብ ደረጃ ቁጠር። 3  አንተና አሮን ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን በእስራኤል ውስጥ ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉትን ሁሉ በየምድባቸው መዝግቡ። 4  “ከየነገዱ አንድ ሰው ውሰድ፤ እያንዳንዳቸውም ለየአባቶቻቸው ቤት መሪ ይሆናሉ። 5  ከአንተ ጋር የሚቆሙትም ወንዶች ስም የሚከተለው ነው፦ ከሮቤል ነገድ የሸደኡር ልጅ ኤሊጹር፣ 6  ከስምዖን ነገድ የጹሪሻዳይ ልጅ ሸሉሚኤል፣ 7  ከይሁዳ ነገድ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን፣ 8  ከይሳኮር ነገድ የጹአር ልጅ ናትናኤል፣ 9  ከዛብሎን ነገድ የሄሎን ልጅ ኤልያብ፣ 10  ከዮሴፍ ወንዶች ልጆች ይኸውም ከኤፍሬም ነገድ የአሚሁድ ልጅ ኤሊሻማ፣ ከምናሴ ነገድ ደግሞ የፐዳጹር ልጅ ገማልያል፣ 11  ከቢንያም ነገድ የጊድኦኒ ልጅ አቢዳን፣ 12  ከዳን ነገድ የአሚሻዳይ ልጅ አሂዔዜር፣ 13  ከአሴር ነገድ የኦክራን ልጅ ፓጊኤል፣ 14  ከጋድ ነገድ የደኡዔል ልጅ ኤሊያሳፍ 15  እንዲሁም ከንፍታሌም ነገድ የኤናን ልጅ አሂራ። 16  እነዚህ ከማኅበረሰቡ የተመረጡ ናቸው። እነሱም የአባቶቻቸው ነገዶች መሪዎች ማለትም የእስራኤል የሺህ አለቆች ናቸው።” 17  በመሆኑም ሙሴና አሮን በስም የተጠቀሱትን እነዚህን ወንዶች ወሰዱ። 18  እነሱም ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በግለሰብ ደረጃ እንዲመዘገቡ ለማድረግ በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ላይ መላውን ማኅበረሰብ ሰበሰቡ፤ 19  ይህን ያደረጉት ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ነው። እሱም በሲና ምድረ በዳ መዘገባቸው። 20  የእስራኤል የበኩር ልጅ ዝርያዎች የሆኑት የሮቤል ልጆች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በግለሰብ ደረጃ ተቆጠሩ፤ 21  ከሮቤል ነገድ የተመዘገቡት 46,500 ነበሩ። 22  የስምዖን ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በግለሰብ ደረጃ ተቆጠሩ፤ 23  ከስምዖን ነገድ የተመዘገቡት 59,300 ነበሩ። 24  የጋድ ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ 25  ከጋድ ነገድ የተመዘገቡት 45,650 ነበሩ። 26  የይሁዳ ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ 27  ከይሁዳ ነገድ የተመዘገቡት 74,600 ነበሩ። 28  የይሳኮር ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ 29  ከይሳኮር ነገድ የተመዘገቡት 54,400 ነበሩ። 30  የዛብሎን ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ 31  ከዛብሎን ነገድ የተመዘገቡት 57,400 ነበሩ። 32  በኤፍሬም በኩል ያሉት የዮሴፍ ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ 33  ከኤፍሬም ነገድ የተመዘገቡት 40,500 ነበሩ። 34  የምናሴ ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ 35  ከምናሴ ነገድ የተመዘገቡት 32,200 ነበሩ። 36  የቢንያም ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ 37  ከቢንያም ነገድ የተመዘገቡት 35,400 ነበሩ። 38  የዳን ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ 39  ከዳን ነገድ የተመዘገቡት 62,700 ነበሩ። 40  የአሴር ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ 41  ከአሴር ነገድ የተመዘገቡት 41,500 ነበሩ። 42  የንፍታሌም ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ 43  ከንፍታሌም ነገድ የተመዘገቡት 53,400 ነበሩ። 44  ሙሴ ከአሮንና እያንዳንዳቸው የአባቶቻቸውን ቤት ከሚወክሉት ከ12 የእስራኤል አለቆች ጋር በመሆን የመዘገባቸው እነዚህ ናቸው። 45  በእስራኤል ውስጥ ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት እስራኤላውያን ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤት ተመዘገቡ፤ 46  የተመዘገቡትም ሰዎች ጠቅላላ ቁጥር 603,550 ነበር። 47  ይሁን እንጂ ሌዋውያኑ ሌሎቹ እንደተመዘገቡት በየአባቶቻቸው ነገድ መሠረት አልተመዘገቡም። 48  ስለዚህ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 49  “የሌዊን ነገድ ብቻ አትመዝግብ፤ ቁጥራቸውም በሌሎቹ እስራኤላውያን ቁጥር ውስጥ እንዲካተት አታድርግ። 50  ሌዋውያኑን በምሥክሩ የማደሪያ ድንኳን፣ በዕቃዎቹ ሁሉና ከዚያ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ነገሮች ሁሉ ላይ ሹማቸው። እነሱም የማደሪያ ድንኳኑንና ዕቃዎቹን በሙሉ ይሸከማሉ፤ በዚያም ያገለግላሉ፤ በማደሪያ ድንኳኑም ዙሪያ ይሰፍራሉ። 51  የማደሪያ ድንኳኑ ከቦታ ወደ ቦታ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ሁሉ ሌዋውያኑ ይንቀሉት፤ የማደሪያ ድንኳኑ በሚተከልበት ጊዜም ሌዋውያኑ ይትከሉት። ያልተፈቀደለት ማንኛውም ሰው ወደዚያ ቢቀርብ ይገደል። 52  “እያንዳንዱ እስራኤላዊ በየተመደበበት ሰፈር ድንኳኑን ይትከል፤ እያንዳንዱም ሰው ሦስት ነገዶችን ባቀፈው ቡድኑ ውስጥ በየምድቡ ይስፈር። 53   በእስራኤል ማኅበረሰብ ላይ ቁጣ እንዳይወርድ ሌዋውያኑ በምሥክሩ የማደሪያ ድንኳን ዙሪያ ይስፈሩ፤ ሌዋውያኑም የምሥክሩን የማደሪያ ድንኳን የመንከባከብ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።” 54  እስራኤላውያንም ይሖዋ ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ። ልክ እንደዚያው አደረጉ።
[]
[]
[]
[]
12,402
10  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “ሁለት መለከቶችን ለራስህ ሥራ፤ ወጥ ከሆነ ብር ጠፍጥፈህ ሥራቸው፤ መለከቶቹንም ማኅበረሰቡን ለመሰብሰብና ሕዝቡ ከሰፈረባቸው ቦታዎች ተነስቶ እንዲሄድ ምልክት ለመስጠት ተጠቀምባቸው። 3  ሁለቱም መለከቶች ሲነፉ መላው ማኅበረሰብ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ወደ አንተ ይሰብሰብ። 4  አንዱ መለከት ብቻ ከተነፋ ግን የእስራኤል የሺህ አለቆች ብቻ ወደ አንተ ይሰብሰቡ። 5  “ድምፁን እያለዋወጣችሁ መለከቱን ስትነፉ በስተ ምሥራቅ የሰፈሩት ተነስተው ይጓዙ። 6  ለሁለተኛ ጊዜ ድምፁን እያለዋወጣችሁ መለከቱን ስትነፉ በስተ ደቡብ የሰፈሩት ተነስተው ይጓዙ። ከመካከላቸው አንዱ ምድብ ተነስቶ በተጓዘ ቁጥር መለከቱን በዚህ መንገድ ይንፉ። 7  “ጉባኤውን አንድ ላይ በምትሰበስቡበት ጊዜ መለከቶቹን መንፋት ይኖርባችኋል፤ በዚህ ጊዜ ግን ድምፁን እያለዋወጣችሁ መንፋት የለባችሁም። 8  ካህናት የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆች መለከቶቹን ይንፉ፤ መለከቶቹን በዚህ መንገድ መጠቀም በትውልዶቻችሁ ሁሉ ለእናንተ ዘላቂ ደንብ ሆኖ ያገለግላል። 9  “ግፍ ከሚፈጽምባችሁ ጨቋኝ ጠላት ጋር በምድራችሁ ጦርነት ብትገጥሙ በመለከቶቹ አማካኝነት የክተት ጥሪ አሰሙ፤ አምላካችሁ ይሖዋም ያስባችኋል፤ ከጠላቶቻችሁም ያድናችኋል። 10  “እንዲሁም በደስታችሁ ወቅት ይኸውም በበዓላት ወቅቶችና የወር መባቻን ስታከብሩ በሚቃጠሉ መባዎቻችሁ እንዲሁም በኅብረት መሥዋዕቶቻችሁ ላይ መለከቶቹን ንፉ፤ እነሱም በአምላካችሁ ፊት ለእናንተ እንደ መታሰቢያ ሆነው ያገለግላሉ። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።” 11  በሁለተኛው ዓመት ሁለተኛ ወር፣ ከወሩም በ20ኛው ቀን ደመናው ከምሥክሩ የማደሪያ ድንኳን ላይ ተነሳ። 12  እስራኤላውያንም በወጣላቸው የጉዞ ቅደም ተከተል መሠረት ከሲና ምድረ በዳ ተነስተው መጓዝ ጀመሩ፤ ደመናውም በፋራን ምድረ በዳ ቆመ። 13  ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ተነስተው ሲጓዙ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ነበር። 14  ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የይሁዳ ልጆች ምድብ በየምድቡ በመሆን በመጀመሪያ ተነስቶ ተጓዘ፤ የምድቡም አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበር። 15  የይሳኮር ልጆች ነገድ ምድብ አለቃም የጹአር ልጅ ናትናኤል ነበር። 16  የዛብሎን ልጆች ነገድ ምድብ አለቃ የሄሎን ልጅ ኤልያብ ነበር። 17  የማደሪያ ድንኳኑ በተነቀለም ጊዜ የማደሪያ ድንኳኑን የሚሸከሙት የጌድሶን ወንዶች ልጆችና የሜራሪ ወንዶች ልጆች ተነስተው ተጓዙ። 18  ከዚያም ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የሮቤል ምድብ በየምድቡ በመሆን ተነስቶ ተጓዘ፤ የምድቡም አለቃ የሸደኡር ልጅ ኤሊጹር ነበር። 19  የስምዖን ልጆች ነገድ ምድብ አለቃ የጹሪሻዳይ ልጅ ሸሉሚኤል ነበር። 20  የጋድ ልጆች ነገድ ምድብ አለቃ የደኡዔል ልጅ ኤሊያሳፍ ነበር። 21  ከዚያም የመቅደሱን ዕቃዎች የሚሸከሙት ቀአታውያን ተነስተው ተጓዙ። እነሱ በሚደርሱበት ጊዜ የማደሪያ ድንኳኑ ተተክሎ ይቆያል። 22  ቀጥሎም ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የኤፍሬም ምድብ በየምድቡ በመሆን ተነስቶ ተጓዘ፤ የምድቡም አለቃ የአሚሁድ ልጅ ኤሊሻማ ነበር። 23  የምናሴ ልጆች ነገድ ምድብ አለቃ የፐዳጹር ልጅ ገማልያል ነበር። 24  የቢንያም ልጆች ነገድ ምድብ አለቃ የጊድኦኒ ልጅ አቢዳን ነበር። 25  ከዚያም ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የዳን ልጆች ምድብ ለሁሉም ምድቦች የኋላ ደጀን በመሆን በየምድቡ ተነስቶ ተጓዘ፤ የሠራዊቱም አለቃ የአሚሻዳይ ልጅ አሂዔዜር ነበር። 26  የአሴር ልጆች ነገድ ምድብ አለቃ የኦክራን ልጅ ፓጊኤል ነበር። 27  የንፍታሌም ልጆች ነገድ ምድብ አለቃ የኤናን ልጅ አሂራ ነበር። 28  እስራኤላውያን በየምድባቸው በመሆን ተነስተው የሚጓዙበት የጉዞ ቅደም ተከተል ይህ ነበር። 29  ከዚያም ሙሴ የአማቱን የምድያማዊውን የረኡዔልን ልጅ ሆባብን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ እኛ ይሖዋ ‘ለእናንተ እሰጣችኋለሁ’ ወዳለን ምድር ተነስተን መጓዛችን ነው። አንተም ከእኛ ጋር ና፤ ይሖዋ ለእስራኤል መልካም ነገር ለማድረግ ቃል ስለገባ እኛም መልካም ነገር እናደርግልሃለን።” 30  እሱ ግን “አብሬያችሁ አልሄድም። እኔ ወደ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እመለሳለሁ” አለው። 31  በዚህ ጊዜ እንዲህ አለው፦ “በምድረ በዳው የት መስፈር እንዳለብን ስለምታውቅ እባክህ ትተኸን አትሂድ፤ መንገድም ልትመራን ትችላለህ። 32  ከእኛ ጋር የምትሄድ ከሆነ ይሖዋ የሚያደርግልንን መልካም ነገር ሁሉ እኛም በእርግጥ ለአንተ እናደርግልሃለን።” 33  በመሆኑም የሦስት ቀን መንገድ ለመጓዝ ከይሖዋ ተራራ ተነስተው ጉዞ ጀመሩ፤ የሦስት ቀኑን ጉዞ በሚጓዙበት ጊዜም የይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት ለእነሱ የማረፊያ ቦታ ለመፈለግ ከፊት ከፊታቸው ይሄድ ነበር። 34  ከሰፈሩበት ቦታ በሚነሱበት ጊዜ የይሖዋ ደመና ቀን ቀን በላያቸው ይሆን ነበር። 35  ታቦቱ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ሁሉ ሙሴ “ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ፤ ጠላቶችህ ይበታተኑ፤ የሚጠሉህም ሁሉ ከፊትህ ይሽሹ” ይል ነበር። 36  ታቦቱ በሚያርፍበትም ጊዜ “ይሖዋ ሆይ፣ በሺዎች ወደሚቆጠሩት ስፍር ቁጥር የሌላቸው እስራኤላውያን ተመለስ” ይል ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,403
11  በዚህ ጊዜ ሕዝቡ፣ ስለደረሰበት ችግር በይሖዋ ፊት ክፉኛ ማጉረምረም ጀመረ። ይሖዋ ይህን ሲሰማ ቁጣው ነደደ፤ ከይሖዋም የመጣ እሳት በእነሱ ላይ ተቀጣጠለ፤ በሰፈሩ ዳርቻ ያሉትን የተወሰኑ ሰዎችም በላ። 2  ሕዝቡ ወደ ሙሴ መጮኽ ሲጀምር ሙሴ ይሖዋን ተማጸነ፤ እሳቱም ከሰመ። 3  ከይሖዋ የመጣ እሳት በእነሱ ላይ ስለነደደም የዚያ ቦታ ስም ታበራ ተባለ። 4  እስራኤላውያንም በመካከላቸው የነበረው ድብልቅ ሕዝብ ሲስገበገብ ሲያዩ እንዲህ በማለት እንደገና ያለቅሱ ጀመር፦ “እንግዲህ አሁን የምንበላው ሥጋ ማን ይሰጠናል? 5  በግብፅ እያለን በነፃ እንበላው የነበረው ዓሣ እንዲሁም ኪያሩ፣ ሐብሐቡ፣ ባሮ ሽንኩርቱ፣ ቀይ ሽንኩርቱና ነጭ ሽንኩርቱ በዓይናችን ላይ ዞሯል! 6  አሁን ግን ዝለናል። ከዚህ መና በስተቀር ሌላ የምናየው ነገር የለም።” 7  መናው እንደ ድንብላል ዘር ነበር፤ መልኩም ሙጫ ይመስል ነበር። 8  ሕዝቡም ሜዳ ላይ ወጥቶ መናውን ከለቀመ በኋላ በወፍጮ ይፈጨው ወይም በሙቀጫ ይወቅጠው ነበር። ከዚያም በድስት ይቀቅሉት ወይም እንደ ቂጣ ይጋግሩት ነበር፤ ጣዕሙም በዘይት ተለውሶ እንደተጋገረ ጣፋጭ ቂጣ ነበር። 9  ሌሊት በሰፈሩ ላይ ጤዛ በሚወርድበት ጊዜ መናውም በላዩ ላይ ይወርድ ነበር። 10  ሙሴም ሕዝቡ ይኸውም እያንዳንዱ ሰው በድንኳኑ ደጃፍ ላይ ሆኖ ከቤተሰቡ ጋር ሲያለቅስ ሰማ። ይሖዋም እጅግ ተቆጣ፤ ሙሴም በጣም አዘነ። 11  ከዚያም ሙሴ ይሖዋን እንዲህ አለው፦ “አገልጋይህን የምታጎሳቁለው ለምንድን ነው? በፊትህ ሞገስ ያጣሁትና የዚህን ሁሉ ሕዝብ ሸክም በእኔ ላይ የጫንከው ለምንድን ነው? 12  ይህን ሁሉ ሕዝብ የፀነስኩት እኔ ነኝ? ለአባቶቻቸው ለመስጠት ቃል ወደገባህላቸው ምድር እንዳስገባቸው ‘የሚጠባን ሕፃን እንደሚታቀፍ ሞግዚት በጉያህ እቀፋቸው’ የምትለኝ የወለድኳቸው እኔ ነኝ? 13  ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚሆን ሥጋ ከየት ነው የማመጣው? ይኸው እነሱ ‘የምንበላው ሥጋ ስጠን!’ በማለት እያለቀሱብኝ ነው። 14  ይህን ሁሉ ሕዝብ እኔ ብቻዬን ልሸከመው አልችልም፤ ከአቅሜ በላይ ነው። 15  እንዲህስ ከምታደርገኝ እባክህ አሁኑኑ ግደለኝ። በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ ከእንግዲህ መከራ እንዳይ አታድርገኝ።” 16  ይሖዋም መልሶ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል የሕዝቡ ሽማግሌዎችና አለቆች የመሆን ብቃት አላቸው የምትላቸውን 70 ሰዎች ሰብስብልኝ፤ እነሱንም ወደ መገናኛ ድንኳኑ ውሰዳቸውና በዚያ ከአንተ ጋር ይቁሙ። 17  እኔም ወርጄ በዚያ ከአንተ ጋር እነጋገራለሁ፤ በአንተ ላይ ካለው መንፈስ ወስጄ በእነሱ ላይ አደርጋለሁ፤ እነሱም የሕዝቡን ሸክም ብቻህን እንዳትሸከም ይረዱሃል። 18  ሕዝቡንም እንዲህ በለው፦ ‘ሥጋ ስለምትበሉ ለነገ ራሳችሁን ቀድሱ፤ ምክንያቱም በይሖዋ ፊት አልቅሳችኋል፤ ደግሞም “የምንበላው ሥጋ ማን ይሰጠናል? በግብፅ የነበርንበት ሁኔታ የተሻለ ነበር” ብላችኋል። ይሖዋ በእርግጥ ሥጋ ይሰጣችኋል፤ እናንተም ትበላላችሁ። 19  የምትበሉትም ለአንድ ቀን ወይም ለ2 ቀን ወይም ለ5 ቀን ወይም ለ10 ቀን ወይም ለ20 ቀን አይደለም፤ 20  ከዚህ ይልቅ በአፍንጫችሁ እስኪወጣና እስኪያንገፈግፋችሁ ድረስ ወር ሙሉ ትበላላችሁ፤ ምክንያቱም በመካከላችሁ ያለውን ይሖዋን ትታችኋል፤ እንዲሁም “ከግብፅ የወጣነው ለምንድን ነው?” በማለት በፊቱ አልቅሳችኋል።’” 21  ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለ፦ “እኔ በመካከሉ የምገኘው ሕዝብ 600,000 እግረኛ ወንዶች ያሉበት ነው፤ አንተ ደግሞ ‘ሥጋ እሰጣቸዋለሁ፤ ወር ሙሉ እስኪጠግቡ ይበላሉ’ ትላለህ። 22  በጎቹና ከብቶቹ ሁሉ ቢታረዱ እንኳ ይበቃቸዋል? የባሕር ዓሣዎች ሁሉ ቢያዙስ ሊበቃቸው ይችላል?” 23  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን “ለመሆኑ የይሖዋ እጅ አጭር ነው? እንግዲህ ያልኩት ነገር ይፈጸምልህ እንደሆነና እንዳልሆነ ታያለህ” አለው። 24  ሙሴም ወጥቶ የይሖዋን ቃል ለሕዝቡ ተናገረ። እንዲሁም ከሕዝቡ ሽማግሌዎች መካከል 70 ሰዎችን ሰብስቦ በድንኳኑ ዙሪያ እንዲቆሙ አደረገ። 25  ከዚያም ይሖዋ በደመና ወርዶ አነጋገረው፤ በሙሴ ላይ ከነበረውም መንፈስ ወስዶ በ70ዎቹ ሽማግሌዎች ላይ አደረገ። እነሱም ወዲያው መንፈሱ እንዳረፈባቸው እንደ ነቢያት አደረጋቸው፤ ሆኖም ዳግመኛ እንደዚያ አልሆኑም። 26  በዚህ ጊዜ ከሰዎቹ መካከል ሁለቱ በሰፈሩ ውስጥ ቀርተው ነበር። ስማቸውም ኤልዳድና ሞዳድ ነበር። እነዚህ ሰዎች ምንም እንኳ ወደ ድንኳኑ ባይሄዱም ስማቸው ከተመዘገቡት ሰዎች መካከል ስለነበሩ መንፈሱ በእነሱም ላይ ወረደ። በመሆኑም እነሱም በሰፈሩ ውስጥ እንደ ነቢያት ሆኑ። 27  አንድ ወጣትም እየሮጠ በመሄድ “ኤልዳድና ሞዳድ በሰፈሩ ውስጥ እንደ ነቢያት እየሆኑ ነው!” ሲል ለሙሴ ነገረው። 28  በዚህ ጊዜ ከወጣትነቱ ጀምሮ የሙሴ አገልጋይ የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ “ጌታዬ ሙሴ ሆይ፣ እነዚህን ሰዎች ከልክላቸው እንጂ!” ሲል ተናገረ። 29  ሙሴ ግን እንዲህ አለው፦ “ስለ እኔ ተቆርቁረህ ነው? አትቆርቆር፤ የይሖዋ ሕዝቦች በሙሉ ነቢያት ቢሆኑና ይሖዋ መንፈሱን ቢሰጣቸው እንዴት ደስ ባለኝ!” 30  በኋላም ሙሴ ከእስራኤል ሽማግሌዎች ጋር ወደ ሰፈሩ ተመለሰ። 31  ከዚያም ነፋስ ከይሖዋ ዘንድ ወጥቶ ድርጭቶችን ከባሕሩ እየነዳ በማምጣት በሰፈሩ ዙሪያ በተናቸው፤ ድርጭቶቹም የአንድ ቀን መንገድ ያህል በአንድ በኩል፣ የአንድ ቀን መንገድ ያህል ደግሞ በሌላ በኩል በሰፈሩ ዙሪያ ሁሉ ተበትነው ነበር፤ መሬት ላይም ሁለት ክንድ ከፍታ ያህል ተቆልለው ነበር። 32  ሕዝቡም በዚያን ዕለት ቀኑን ሙሉና ሌሊቱን ሙሉ እንዲሁም በማግስቱ ቀኑን ሙሉ ድርጭቶቹን ሲሰበስብ ዋለ። ከአሥር ሆሜር ያነሰ የሰበሰበ አልነበረም፤ የሰበሰቧቸውንም በሰፈሩ ዙሪያ አሰጧቸው። 33  ሆኖም ሥጋውን ገና ሳያኝኩት፣ በጥርሳቸው መካከል እያለ የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፤ ይሖዋም ሕዝቡን ክፉኛ ፈጀ። 34  እነሱም ሲስገበገቡ የነበሩትን ሰዎች በዚያ ስለቀበሯቸው የቦታውን ስም ቂብሮትሃታባ አሉት። 35  ሕዝቡም ከቂብሮትሃታባ ተነስቶ ወደ ሃጼሮት ተጓዘ፤ በሃጼሮትም ተቀመጠ።
[]
[]
[]
[]
12,404
12  ሙሴ ኢትዮጵያዊት ሴት አግብቶ ስለነበር ባገባት ኢትዮጵያዊት ሴት የተነሳ ሚርያምና አሮን ይነቅፉት ጀመር። 2  እነሱም “ለመሆኑ ይሖዋ የሚናገረው በሙሴ አማካኝነት ብቻ ነው? በእኛስ በኩል አልተናገረም?” ይሉ ነበር። ይሖዋም ይህን ይሰማ ነበር። 3  ሙሴ በምድር ላይ ከነበሩ ሰዎች ሁሉ ይልቅ በጣም የዋህ ነበር። 4  ይሖዋም ድንገት ሙሴን፣ አሮንንና ሚርያምን “ሦስታችሁም ወደ መገናኛ ድንኳኑ ውጡ” አላቸው። በመሆኑም ሦስቱም ወጡ። 5  ይሖዋም በደመና ዓምድ ወርዶ በድንኳኑ መግቢያ ላይ በመቆም አሮንንና ሚርያምን ጠራቸው። በዚህ ጊዜ ሁለቱም ወደ ፊት ቀረቡ። 6  እሱም እንዲህ አለ፦ “እባካችሁ ቃሌን ስሙ። አንድ የይሖዋ ነቢይ በመካከላችሁ ቢኖር በራእይ አማካኝነት ራሴን አሳውቀው በሕልምም አነጋግረው ነበር። 7  አገልጋዬን ሙሴን በተመለከተ ግን እንዲህ አይደለም! እሱ በቤቴ ሁሉ ላይ አደራ የተጣለበት ሰው ነው። 8  እኔ እሱን የማነጋግረው ፊት ለፊት በግልጽ እንጂ በእንቆቅልሽ አይደለም፤ እሱም የይሖዋን አምሳል ያያል። ታዲያ አገልጋዬን ሙሴን ስትነቅፉት ምነው አልፈራችሁም?” 9  በመሆኑም የይሖዋ ቁጣ በእነሱ ላይ ነደደ፤ ትቷቸውም ሄደ። 10  ከዚያም ደመናው ከድንኳኑ ላይ ተነሳ፤ በዚህ ጊዜ ሚርያም በሥጋ ደዌ ተመታ እንደ በረዶ ነጭ ሆና ነበር። አሮንም ወደ ሚርያም ዞር ሲል በሥጋ ደዌ ተመታ አየ። 11  አሮንም ወዲያውኑ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይቅርታ አድርግልኝ ጌታዬ! እባክህ ይህን ኃጢአት አትቁጠርብን! የፈጸምነው የሞኝነት ድርጊት ነው። 12  እባክህ፣ ግማሽ አካሉ ተበልቶ የተወለደ ጭንጋፍ መስላ እንድትቀር አታድርግ!” 13  ሙሴም “አምላክ ሆይ፣ እባክህ ፈውሳት! እባክህ!” በማለት ወደ ይሖዋ ጮኸ። 14  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አባቷ ፊቷ ላይ ቢተፋባት ለሰባት ቀን ተዋርዳ ትቆይ አልነበረም? አሁንም ከሰፈር ውጭ ለሰባት ቀን ተገልላ እንድትቆይ ይደረግ፤ ከዚያ በኋላ እንድትመለስ ማድረግ ይቻላል።” 15  ስለዚህ ሚርያም ለሰባት ቀን ከሰፈሩ ውጭ ተገልላ እንድትቆይ ተደረገ፤ ሕዝቡም ሚርያም ተመልሳ እንድትቀላቀል እስኪደረግ ድረስ ጉዞውን አልቀጠለም። 16  ከዚያም ሕዝቡ ከሃጼሮት ተነስቶ በፋራን ምድረ በዳ ሰፈረ።
[]
[]
[]
[]
12,405
13  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “ለእስራኤላውያን የምሰጠውን የከነአንን ምድር እንዲሰልሉ ሰዎችን ላክ። ከእያንዳንዱ የአባቶች ነገድ አንድ አንድ ሰው ይኸውም ከመካከላቸው አለቃ የሆነውን ሰው ትልካለህ።” 3  በመሆኑም ሙሴ ይሖዋ በሰጠው መመሪያ መሠረት ከፋራን ምድረ በዳ ላካቸው። ሰዎቹ በሙሉ የእስራኤላውያን መሪዎች ነበሩ። 4  ስማቸውም የሚከተለው ነው፦ ከሮቤል ነገድ የዛኩር ልጅ ሻሙአ፣ 5  ከስምዖን ነገድ የሆሪ ልጅ ሻፋጥ፣ 6  ከይሁዳ ነገድ የየፎኒ ልጅ ካሌብ፣ 7  ከይሳኮር ነገድ የዮሴፍ ልጅ ይግዓል፣ 8  ከኤፍሬም ነገድ የነዌ ልጅ ሆሺአ፣ 9  ከቢንያም ነገድ የራፉ ልጅ ፓልጢ፣ 10  ከዛብሎን ነገድ የሶዲ ልጅ ጋዲኤል፣ 11  ከዮሴፍ ነገድ መካከል ለምናሴ ነገድ የሱሲ ልጅ ጋዲ፣ 12  ከዳን ነገድ የገማሊ ልጅ አሚዔል፣ 13  ከአሴር ነገድ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፣ 14  ከንፍታሌም ነገድ የዎፍሲ ልጅ ናህቢ 15  እንዲሁም ከጋድ ነገድ የማኪ ልጅ ጌኡዔል። 16  ሙሴ ምድሪቱን እንዲሰልሉ የላካቸው ሰዎች ስም ይህ ነው። ሙሴም ለነዌ ልጅ ለሆሺአ፣ ኢያሱ የሚል ስም አወጣለት። 17  ሙሴ የከነአንን ምድር እንዲሰልሉ ሰዎቹን ሲልካቸው እንዲህ አላቸው፦ “በዚህ አድርጋችሁ ወደ ኔጌብ አቅኑ፤ ከዚያም ወደ ተራራማው አካባቢ ሂዱ። 18  ምድሪቱ ምን እንደምትመስል፣ ነዋሪዎቿም ብርቱ ወይም ደካማ፣ ጥቂት ወይም ብዙ መሆናቸውን እዩ፤ 19  እንዲሁም ምድሪቱ መልካም ወይም መጥፎ መሆኗን ከተሞቹም በግንብ የታጠሩ ወይም ያልታጠሩ መሆናቸውን ተመልከቱ። 20  ምድሪቱም ለም ወይም ደረቅ መሆኗን፣ በዚያም ዛፎች መኖር አለመኖራቸውን አጣሩ። እንዲሁም በድፍረት ከምድሪቱ ፍሬ ጥቂት ይዛችሁ ኑ።” ደግሞም ጊዜው የመጀመሪያው የወይን ፍሬ የሚደርስበት ወቅት ነበር። 21  ስለዚህ ሰዎቹ ወጥተው ምድሪቱን ከጺን ምድረ በዳ አንስተው በሌቦሃማት እስከምትገኘው እስከ ሬሆብ ድረስ ሰለሉ። 22  በኔጌብ በኩል ሽቅብ ሲወጡም ኤናቃውያኑ አሂማን፣ ሸሻይ እና ታልማይ ወደሚኖሩበት ወደ ኬብሮን ደረሱ። ኬብሮን የተቆረቆረችው በግብፅ ያለችው ጾዓን ከመቆርቆሯ ከሰባት ዓመት በፊት ነበር። 23  ወደ ኤሽኮል ሸለቆ በደረሱ ጊዜ የወይን ዘለላዎችን ያንዠረገገ አንድ ቅርንጫፍ ከዚያ ቆረጡ፤ ከሰዎቹም መካከል ሁለቱ በዱላ ተሸከሙት፤ በተጨማሪም ጥቂት የሮማን ፍሬዎችንና የበለስ ፍሬዎችን ያዙ። 24  እስራኤላውያን ከዚያ በቆረጡት ዘለላ የተነሳ ያን ቦታ የኤሽኮል ሸለቆ ብለው ጠሩት። 25  ምድሪቱንም ሰልለው ከ40 ቀን በኋላ ተመለሱ። 26  በቃዴስ ባለው በፋራን ምድረ በዳ ወደሚገኙት ወደ ሙሴ፣ ወደ አሮንና ወደ መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ተመልሰው መጡ። ያዩትንም ሁሉ ለመላው ማኅበረሰብ ተናገሩ፤ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው። 27  ሙሴንም እንዲህ አሉት፦ “ወደላክኸን ምድር ገብተን ነበር፤ በእርግጥም ምድሪቱ ወተትና ማር የምታፈስ ናት፤ የምድሪቱም ፍሬ ይህን ይመስላል። 28  ይሁንና በምድሪቱ የሚኖሩት ሰዎች ብርቱዎች ናቸው፤ በግንብ የታጠሩት ከተሞችም ቢሆኑ በጣም ታላላቅ ናቸው። ደግሞም ኤናቃውያንን በዚያ አይተናል። 29  አማሌቃውያን በኔጌብ ምድር ይኖራሉ፤ ሂታውያን፣ ኢያቡሳውያንና አሞራውያን ደግሞ በተራራማው አካባቢ ይኖራሉ፤ በባሕሩ አካባቢና በዮርዳኖስ ዳርቻ ደግሞ ከነአናውያን ይኖራሉ።” 30  ከዚያም ካሌብ “በድፍረት እንውጣ፤ ድል እንደምናደርግ ምንም ጥርጥር ስለሌለው ምድሪቱን እንወርሳለን” በማለት በሙሴ ፊት የቆመውን ሕዝብ ሊያረጋጋ ሞከረ። 31  ከእሱ ጋር የወጡት ሰዎች ግን “ሰዎቹ ከእኛ ይልቅ ብርቱዎች ስለሆኑ ወጥተን ልንዋጋቸው አንችልም” አሉ። 32  እንዲሁም የሰለሏትን ምድር በተመለከተ ለእስራኤላውያን እንዲህ የሚል መጥፎ ወሬ አወሩ፦ “በውስጧ ተዘዋውረን የሰለልናት ምድር ነዋሪዎቿን የምትበላ ምድር ናት፤ እዚያ ያየናቸውም ሰዎች በሙሉ እጅግ ግዙፎች ናቸው። 33  በዚያም ኔፍሊሞችን ይኸውም የኔፍሊም ዝርያ የሆኑትን የኤናቅን ልጆች አይተናል፤ እኛ ከእነሱ ጋር ስንነጻጸር በእኛም ሆነ በእነሱ ዓይን ልክ እንደ ፌንጣ ነበርን።”
[]
[]
[]
[]
12,406
14  ከዚያም ማኅበረሰቡ ሁሉ ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ፤ ሕዝቡም ሌሊቱን ሙሉ ሲጮኽና ሲያለቅስ አደረ። 2  እስራኤላውያንም በሙሉ በሙሴና በአሮን ላይ ያጉረመርሙ ጀመር፤ መላው ማኅበረሰብ እንዲህ አላቸው፦ “ምነው በግብፅ ምድር ሳለን ሞተን ባረፍነው፤ ወይም ምናለ በዚህ ምድረ በዳ በሞትን! 3  ይሖዋ በሰይፍ እንድንሞት ወደዚህ ምድር ያመጣን ለምንድን ነው? እንግዲህ ሚስቶቻችንና ልጆቻችን ይማረካሉ። ታዲያ ወደ ግብፅ ብንመለስ አይሻለንም?” 4  እንዲያውም እርስ በርሳቸው “መሪ እንሹምና ወደ ግብፅ እንመለስ” ይባባሉ ጀመር። 5  በዚህ ጊዜ ሙሴና አሮን በተሰበሰበው በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ። 6  ምድሩን ከሰለሉት ሰዎች መካከል የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የየፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ 7  ለመላው የእስራኤል ማኅበረሰብም እንዲህ አሉ፦ “ተዘዋውረን የሰለልናት ምድር እጅግ በጣም ጥሩ ምድር ናት። 8  ይሖዋ በእኛ ከተደሰተ ወተትና ማር ወደምታፈሰው ወደዚህች ምድር በእርግጥ ያስገባናል፤ ደግሞም ይህችን ምድር ይሰጠናል። 9  ብቻ እናንተ በይሖዋ ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ ስለምንጎርሳቸው የምድሪቱን ሕዝቦች አትፍሯቸው። ጥላቸው ተገፏል፤ ደግሞም ይሖዋ ከእኛ ጋር ነው። ፈጽሞ አትፍሯቸው።” 10  ይሁን እንጂ መላው ማኅበረሰብ በድንጋይ ሊወግራቸው ተማከረ። ሆኖም የይሖዋ ክብር በመገናኛ ድንኳኑ ላይ ለመላው የእስራኤል ሕዝብ ተገለጠ። 11  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ የሚንቀኝ እስከ መቼ ነው? በመካከላቸው ይህን ሁሉ ተአምራዊ ምልክት እያሳየሁ የማያምኑብኝስ እስከ መቼ ነው? 12  እንግዲህ በቸነፈር እመታቸዋለሁ፤ ደግሞም እደመስሳቸዋለሁ፤ አንተን ግን ከእነሱ ይልቅ ታላቅና ኃያል ብሔር አደርግሃለሁ።” 13  ሙሴ ግን ይሖዋን እንዲህ አለው፦ “እንዲህ ካደረግክ ይህን ሕዝብ በኃይልህ ከመካከላቸው ስታወጣ ያዩ ግብፃውያን መስማታቸው አይቀርም፤ 14  እነሱ ደግሞ የሰሙትን ነገር ለዚህ ምድር ነዋሪዎች ይናገራሉ። እነሱም ቢሆኑ አንተ ይሖዋ በዚህ ሕዝብ መካከል እንዳለህና ፊት ለፊት እንደተገለጥክላቸው ሰምተዋል። አንተ ይሖዋ ነህ፤ ደመናህም በላያቸው ላይ ቆሟል፤ ቀን ቀን በደመና ዓምድ፣ ሌሊት ሌሊት ደግሞ በእሳት ዓምድ ከፊት ከፊታቸው ትሄዳለህ። 15  እንግዲህ ይህን ሕዝብ በሙሉ በአንዴ ብትፈጀው የአንተን ዝና የሰሙ ብሔራት እንዲህ ማለታቸው አይቀርም፦ 16  ‘ይሖዋ ይህን ሕዝብ፣ ሊሰጠው ወደማለለት ምድር ሊያስገባው ስላልቻለ በምድረ በዳ ፈጀው።’ 17  አሁንም እባክህ ይሖዋ እንዲህ በማለት ቃል በገባኸው መሠረት ኃይልህ ታላቅ ይሁን፦ 18  ‘ይሖዋ ለቁጣ የዘገየ፣ ታማኝ ፍቅሩ የበዛ፣ ስህተትንና መተላለፍን ይቅር የሚል፣ በደለኛውን ግን በምንም ዓይነት ሳይቀጣ የማያልፍ እንዲሁም አባቶች ለሠሩት ስህተት በልጆች፣ በሦስተኛና በአራተኛ ትውልድ ላይ ቅጣትን የሚያመጣ ነው።’ 19  ይህን ሕዝብ ከግብፅ አንስቶ እስካሁን ድረስ ይቅር ስትለው እንደቆየህ ሁሉ አሁንም እባክህ፣ የዚህን ሕዝብ ስህተት ታላቅ በሆነው ታማኝ ፍቅርህ ይቅር በል።” 20  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለ፦ “ባልከኝ መሠረት ይቅር እላቸዋለሁ። 21  በሌላ በኩል ግን በሕያውነቴ እምላለሁ፣ መላዋ ምድር በይሖዋ ክብር ትሞላለች። 22  ይሁን እንጂ ክብሬንና በግብፅም ሆነ በምድረ በዳ የፈጸምኳቸውን ተአምራዊ ምልክቶች የተመለከቱት ሆኖም አሥር ጊዜ የተፈታተኑኝና ቃሌን ያልሰሙት ሰዎች አንዳቸውም ቢሆኑ 23  ለአባቶቻቸው የማልኩላቸውን ምድር ፈጽሞ አያዩም። አዎ፣ የናቁኝ ሰዎች አንዳቸውም ቢሆኑ ያን ምድር አያዩም። 24  አገልጋዬ ካሌብ ግን የተለየ መንፈስ እንዳለው ስላሳየና በሙሉ ልቡ ስለተከተለኝ ሄዶባት ወደነበረው ምድር በእርግጥ አስገባዋለሁ፤ ዘሮቹም ያቺን ምድር ይወርሳሉ። 25  አማሌቃውያንና ከነአናውያን በሸለቆው ውስጥ ስለሚኖሩ በነገው ዕለት ተመልሳችሁ በቀይ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳው ሂዱ።” 26  ከዚያም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ 27  “ይህ ክፉ ማኅበረሰብ በእኔ ላይ እንዲህ የሚያጉረመርመው እስከ መቼ ነው? እስራኤላውያን በእኔ ላይ የሚያጉረመርሙትን ሰምቻለሁ። 28  እንዲህ በሏቸው፦ ‘“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ይሖዋ፤ “እናንተው ራሳችሁ ስትናገሩ የሰማሁትን ነገር አደርግባችኋለሁ! 29  ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ሆኗችሁ የተመዘገባችሁትና የተቆጠራችሁት ሁሉ አዎ፣ በእኔ ላይ ያጉረመረማችሁት ሁሉ ሬሳችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል። 30  ከየፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር አንዳችሁም ብትሆኑ በዚያ እንደማኖራችሁ ወደማልኩላችሁ ምድር አትገቡም። 31  “‘“ለምርኮ ይዳረጋሉ ያላችኋቸውን ልጆቻችሁን ግን አስገባቸዋለሁ፤ እናንተ የናቃችኋትንም ምድር በሚገባ ያውቋታል። 32  የእናንተ ሬሳ ግን በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል። 33  እንግዲህ ልጆቻችሁ በምድረ በዳ ለ40 ዓመት እረኞች ይሆናሉ፤ እነሱም የእናንተ የመጨረሻው ሬሳ በምድረ በዳ እስኪወድቅ ድረስ እናንተ ለፈጸማችሁት ታማኝነት የጎደለው ድርጊት መልስ ይሰጣሉ። 34  እኔን መቃወም ምን ማለት እንደሆነ እንድታውቁ ምድሪቱን በሰለላችሁባቸው 40 ቀናት ልክ ይኸውም አንዱ ቀን እንደ አንድ ዓመት ተቆጥሮ፣ ለሠራችኋቸው ስህተቶች ለ40 ዓመት መልስ ትሰጣላችሁ። 35  “‘“እኔ ይሖዋ ተናግሬአለሁ። በእኔ ላይ ተባብሮ በተነሳው በዚህ ክፉ ማኅበረሰብ ላይ በእርግጥ ይህን አደርጋለሁ፦ መጨረሻቸው በዚህ ምድረ በዳ ይሆናል፤ እዚሁም ይሞታሉ። 36  ምድሪቱን እንዲሰልሉ ሙሴ የላካቸውና ስለ ምድሪቱ መጥፎ ወሬ ይዘው በመምጣት መላው ማኅበረሰብ በእሱ ላይ እንዲያጉረመርም ያደረጉት ሰዎች 37  አዎ፣ ስለ ምድሪቱ መጥፎ ወሬ ይዘው የመጡት ሰዎች በይሖዋ ፊት ተቀስፈው ይሞታሉ። 38  ምድሪቱን ለመሰለል ከሄዱት ሰዎች መካከል የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የየፎኒ ልጅ ካሌብ ግን በሕይወት ይኖራሉ።”’” 39  ሙሴም ለእስራኤላውያን በሙሉ ይህን ሲነግራቸው ሕዝቡ እጅግ አዘነ። 40  ከዚያም በጠዋት ወደ ተራራው አናት ለመውጣት ተነሱ፤ እነሱም “ኃጢአት ስለሠራን ይሖዋ ወደተናገረለት ቦታ ለመውጣት ይኸው ዝግጁ ነን” አሉ። 41  ሙሴ ግን እንዲህ አለ፦ “የይሖዋን ትእዛዝ የምትጥሱት ለምንድን ነው? ይህ አይሳካላችሁም። 42  ይሖዋ ከእናንተ ጋር ስላልሆነ አትውጡ፤ በጠላቶቻችሁ ድል ትመታላችሁ። 43  ምክንያቱም አማሌቃውያንና ከነአናውያን በዚያ ይገጥሟችኋል፤ እናንተም በሰይፍ ትወድቃላችሁ። ምክንያቱም ይሖዋን ከመከተል ዞር ስላላችሁ ይሖዋ ከእናንተ ጋር አይሆንም።” 44  እነሱ ግን በትዕቢት ወደ ተራራው አናት ወጡ፤ ሆኖም የይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦትና ሙሴ ከሰፈሩ መካከል ንቅንቅ አላሉም። 45  ከዚያም በዚያ ተራራ የሚኖሩት አማሌቃውያንና ከነአናውያን ወርደው መቷቸው፤ እስከ ሆርማም ድረስ በታተኗቸው።
[]
[]
[]
[]
12,407
15  በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘እንድትኖሩባት ወደምሰጣችሁ ምድር በምትገቡበትና 3  ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ እንዲሆን የሚቃጠል መባም ሆነ ለየት ያለ ስእለት ለመሳል የሚቀርብ መሥዋዕት ወይም የፈቃደኝነት መባ አሊያም በየወቅቱ በምታከብሯቸው በዓላት ላይ የሚቀርብ መባ፣ ከከብታችሁ ወይም ከመንጋችሁ በመውሰድ ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ በምታቀርቡበት ጊዜ 4  መባውን የሚያቀርበው ሰው በአንድ አራተኛ ሂን ዘይት የተለወሰ አንድ አሥረኛ ኢፍ የላመ ዱቄትም የእህል መባ አድርጎ ለይሖዋ ማቅረብ ይኖርበታል። 5  እንዲሁም ከሚቃጠለው መባ ወይም ከተባዕት የበግ ጠቦት መሥዋዕቱ ጋር አንድ አራተኛ ሂን የወይን ጠጅ የመጠጥ መባ አድርገህ ማቅረብ አለብህ። 6  ወይም ከአውራ በግ ጋር በአንድ ሦስተኛ ሂን ዘይት የተለወሰ ሁለት አሥረኛ የኢፍ መስፈሪያ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርገህ አቅርብ። 7  እንዲሁም አንድ ሦስተኛ ሂን የወይን ጠጅ ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው የመጠጥ መባ አድርገህ ማቅረብ አለብህ። 8  “‘ሆኖም ከመንጋው መካከል አንድ ወይፈን የሚቃጠል መባ ወይም ለየት ያለ ስእለት ለመሳል የሚቀርብ መሥዋዕት አሊያም የኅብረት መሥዋዕት አድርገህ ለይሖዋ የምታቀርብ ከሆነ 9  ከወይፈኑ ጋር በግማሽ ሂን ዘይት የተለወሰ ሦስት አሥረኛ የኢፍ መስፈሪያ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርገህ ማቅረብ ይኖርብሃል። 10  እንዲሁም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው የመጠጥ መባ እንዲሆን ግማሽ ሂን የወይን ጠጅ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርገህ ማቅረብ አለብህ። 11  ለእያንዳንዱ በሬ ወይም ለእያንዳንዱ አውራ በግ ወይም ለእያንዳንዱ ተባዕት የበግ ጠቦት ወይም ለእያንዳንዱ ፍየል እንዲሁ መደረግ አለበት። 12  የምታቀርቡት ብዛቱ ምንም ያህል ይሁን ምን ለእያንዳንዱ እንደየብዛቱ እንዲህ ማድረግ ይኖርባችኋል። 13  የአገሩ ተወላጅ የሆነ እያንዳንዱ እስራኤላዊ ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቃጠል መባ የሚያቀርበው በዚህ መንገድ ነው። 14  “‘ከእናንተ ጋር እየኖረ ያለ ወይም ለብዙ ትውልድ በመካከላችሁ ሲኖር የነበረ የባዕድ አገር ሰው ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቃጠል መባ ቢያቀርብ ልክ እናንተ እንደምታደርጉት ያድርግ። 15  የጉባኤው ክፍል የሆናችሁት እናንተም ሆናችሁ አብሯችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው አንድ ዓይነት ደንብ ይኖራችኋል። ይህም በትውልዶቻችሁ ሁሉ ዘላቂ ደንብ ይሆናል። የባዕድ አገሩ ሰው በይሖዋ ፊት ልክ እንደ እናንተ ይታያል። 16  ለእናንተም ሆነ ከእናንተ ጋር ለሚኖር የባዕድ አገር ሰው አንድ ዓይነት ሕግና አንድ ዓይነት ድንጋጌ ይኑር።’” 17  ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 18  “እስራኤላውያንን አናግራቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ወደማመጣችሁ ምድር በምትገቡበትና 19  ከምድሪቱ ማንኛውንም ምግብ በምትበሉበት ጊዜ ለይሖዋ መዋጮ ማድረግ አለባችሁ። 20  ከተፈጨው የእህላችሁ በኩር ላይ የቀለበት ቅርጽ ያለው ዳቦ በማዘጋጀት መዋጮ ማድረግ ይኖርባችኋል። ይህን ማዋጣት የሚኖርባችሁ ከአውድማ ላይ የሚገኘውን መዋጮ በምታዋጡበት መንገድ ነው። 21  በትውልዶቻችሁ ሁሉ፣ ከተፈጨው የእህላችሁ በኩር ላይ የተወሰነውን ለይሖዋ መዋጮ አድርጋችሁ መስጠት ይኖርባችኋል። 22  “‘ምናልባት ስህተት ብትሠሩና ይሖዋ ለሙሴ የተናገራቸውን እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ ሳትፈጽሙ ብትቀሩ 23  ይኸውም ይሖዋ ትእዛዙን ከሰጠበት ዕለት አንስቶ ሥራ ላይ የዋለውንና በትውልዶቻችሁ ሁሉ ጸንቶ የሚኖረውን ይሖዋ በሙሴ በኩል ያስተላለፈላችሁን ትእዛዝ ሁሉ ባትፈጽሙና 24  ይህን ያደረጋችሁት ደግሞ በስህተትና ማኅበረሰቡ ሳያውቅ ቢሆን መላው ማኅበረሰብ አንድ ወይፈን ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቅርብ፤ ከእሱም ጋር በተለመደው አሠራር መሠረት የእህል መባውንና የመጠጥ መባውን እንዲሁም አንድ የፍየል ጠቦት የኃጢአት መባ አድርጎ ያቅርብ። 25  ካህኑም ለመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ያስተሰርያል፤ ኃጢአቱም ባለማወቅ የተፈጸመ ስለሆነና ለሠሩትም ስህተት መባቸውን ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርገው ስላቀረቡ እንዲሁም በይሖዋ ፊት የኃጢአት መባቸውን ስላቀረቡ ይቅር ይባልላቸዋል። 26  ይህም ሕዝቡ ሁሉ ባለማወቅ የፈጸመው ስለሆነ መላው የእስራኤል ማኅበረሰብም ሆነ በመካከላቸው የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ይቅር ይባላል። 27  “‘ማንኛውም ሰው ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራ አንድ ዓመት ገደማ የሆናት አንዲት ፍየል የኃጢአት መባ አድርጎ ያቅርብ። 28  ከዚያም ባለማወቅ በይሖዋ ፊት ኃጢአት በመሥራት የተሳሳተው ሰው ኃጢአቱ ይሰረይለት ዘንድ ካህኑ ማስተሰረያ ያቀርብለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል። 29  ባለማወቅ ከሚፈጸም ነገር ጋር በተያያዘ በእስራኤላውያን መካከል ለሚገኝ የአገሬው ተወላጅም ሆነ በመካከላቸው ለሚኖር የባዕድ አገር ሰው አንድ ዓይነት ሕግ ይኑራችሁ። 30  “‘ይሁን እንጂ ሆን ብሎ ኃጢአት የሚሠራ ሰው የአገሬው ተወላጅም ይሁን የባዕድ አገር ሰው ይሖዋን እንደተሳደበ ስለሚቆጠር ከሕዝቡ ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት። 31  የይሖዋን ቃል ስላቃለለና የእሱን ትእዛዝ ስለጣሰ ያ ሰው ያለምንም ጥርጥር ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት። ጥፋቱ የራሱ ነው።’” 32  እስራኤላውያን በምድረ በዳ ሳሉ አንድ ሰው በሰንበት ቀን እንጨት ሲለቅም አገኙ። 33  ሰዎቹም እንጨት ሲለቅም ያገኙትን ሰው ወደ ሙሴ፣ ወደ አሮንና ወደ መላው ማኅበረሰብ አመጡት። 34  ሰውየው ምን መደረግ እንዳለበት በግልጽ የተቀመጠ ነገር ስላልነበረ በጥበቃ ሥር እንዲቆይ አደረጉ። 35  ይሖዋም ሙሴን “ሰውየው ያለምንም ጥርጥር መገደል አለበት፤ መላው ማኅበረሰብም ከሰፈሩ ውጭ በድንጋይ ይውገረው” አለው። 36  ስለዚህ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት መላው ማኅበረሰብ ሰውየውን ከሰፈሩ ውጭ አውጥቶ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ወገረው። 37  ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 38  “እስራኤላውያን በትውልዶቻቸው ሁሉ በልብሳቸው ጫፍ ላይ ዘርፍ እንዲያደርጉ ንገራቸው፤ ልብሳቸውም ከዘርፉ በላይ ሰማያዊ ጥለት ይኑረው። 39  ‘ይህን ዘርፍ በልብሳችሁ ላይ አድርጉ፤ ምክንያቱም እሱን ስታዩ የይሖዋን ትእዛዛት ሁሉ ታስታውሳላችሁ፤ እንዲሁም ትፈጽማላችሁ። ወደ መንፈሳዊ ምንዝር የሚመራችሁን የገዛ ልባችሁንና ዓይናችሁን አትከተሉ። 40  ይህን መመሪያ የሰጠኋችሁ ትእዛዛቴን በሙሉ እንድታስታውሱና እንድትፈጽሙ ነው፤ ለአምላካችሁም የተቀደሳችሁ ትሆናላችሁ። 41  አምላካችሁ መሆኔን ለማስመሥከር ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። አዎ፣ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’”
[]
[]
[]
[]
12,408
16  ከዚያም የሌዊ ልጅ፣ የቀአት ልጅ፣ የይጽሃር ልጅ ቆሬ ከሮቤል ልጆች አንዱ ከሆነው ከኤልያብ ልጆች ከዳታንና ከአቤሮን እንዲሁም ከሮቤል ልጆች አንዱ ከሆነው ከፐሌት ልጅ ከኦን ጋር በመሆን ተነሳ። 2  እነሱም ከማኅበረሰቡ አለቆች ይኸውም ከጉባኤው መካከል ከተመረጡት ታዋቂ የሆኑ 250 እስራኤላውያን ወንዶች ጋር በማበር በሙሴ ላይ ተነሱ። 3  እነሱም ሙሴንና አሮንን ለመቃወም ተሰብስበው መጡ፤ እንዲህም አሏቸው፦ “ምነው፣ አላበዛችሁትም እንዴ! መላው ማኅበረሰብ እኮ ቅዱስ ነው፤ ሁሉም ቅዱስ ናቸው፤ ይሖዋም በመካከላቸው ነው። ታዲያ በይሖዋ ጉባኤ ላይ ራሳችሁን ከፍ ከፍ የምታደርጉት ለምንድን ነው?” 4  ሙሴ ይህን ሲሰማ ወዲያውኑ በግንባሩ ተደፋ። 5  ከዚያም ቆሬንና ግብረ አበሮቹን ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “ጠዋት ላይ ይሖዋ የእሱ የሆነውን፣ ቅዱስ የሆነውንና ወደ እሱ መቅረብ የሚችለውን ሰው ያሳውቃል፤ እሱ የመረጠውም ሰው ወደ እሱ ይቀርባል። 6  ስለዚህ እንዲህ አድርጉ፦ ቆሬ፣ አንተም ሆንክ ግብረ አበሮችህ በሙሉ የዕጣን ማጨሻዎች ውሰዱ፤ 7  ከዚያም በነገው ዕለት እሳት ካደረጋችሁባቸው በኋላ በይሖዋ ፊት ዕጣን ጨምሩባቸው፤ ይሖዋ የሚመርጠውም ሰው፣ እሱ ቅዱስ ይሆናል። እናንተ የሌዊ ልጆች፣ በጣም አብዝታችሁታል!” 8  ከዚያም ሙሴ ቆሬን እንዲህ አለው፦ “እናንተ የሌዊ ልጆች፣ እባካችሁ አዳምጡ። 9  የእስራኤል አምላክ እናንተን ከእስራኤል ማኅበረሰብ መለየቱ እንዲሁም በይሖዋ የማደሪያ ድንኳን የሚከናወነውን አገልግሎት ትፈጽሙና በማኅበረሰቡ ፊት ቆማችሁ እነሱን ታገለግሉ ዘንድ ወደ እሱ እንድትቀርቡ መፍቀዱ እንደ ቀላል ነገር የሚታይ ነው? 10  ደግሞስ አንተንና የሌዊ ልጆች የሆኑትን ወንድሞችህን በሙሉ ወደ እሱ እንድትቀርቡ ማድረጉ ቀላል ነገር ነው? ታዲያ የክህነት አገልግሎቱንም ለመጠቅለል መሞከር ይገባችኋል? 11  ስለዚህ አንተም ሆንክ አብረውህ የተሰበሰቡት ግብረ አበሮችህ በሙሉ ይሖዋን እየተቃወማችሁ ነው። በአሮን ላይ የምታጉረመርሙት እሱ ምን ስለሆነ ነው?” 12  ከዚያም ሙሴ የኤልያብን ልጆች ዳታንንና አቤሮንን አስጠራቸው፤ እነሱ ግን እንዲህ አሉ፦ “አንመጣም! 13  በምድረ በዳ ልትገድለን ወተትና ማር ከምታፈሰው ምድር ያወጣኸን አይበቃህም? አሁን ደግሞ በእኛ ላይ ፈላጭ ቆራጭ ልትሆን ያምርሃል? 14  ደግሞም ወተትና ማር ወደምታፈስ ምድር አላስገባኸንም፤ ወይም እርሻና የወይን የአትክልት ቦታዎችን ርስት አድርገህ አልሰጠኸንም። ታዲያ የእነዚያን ሰዎች ዓይን ልታወጣ ነው? እኛ እንደሆነ አንመጣም!” 15  ስለዚህ ሙሴ እጅግ ተቆጣ፤ ይሖዋንም እንዲህ አለው፦ “የእህል መባቸውን አትመልከት። ከእነዚህ ሰዎች አንድ አህያ እንኳ አልወሰድኩም፤ አንዳቸውንም ቢሆን አልበደልኩም።” 16  ከዚያም ሙሴ ቆሬን እንዲህ አለው፦ “አንተና ግብረ አበሮችህ በሙሉ ነገ በይሖዋ ፊት ቅረቡ፤ አንተም ሆንክ እነሱ እንዲሁም አሮን መቅረብ ይኖርባችኋል። 17  እያንዳንዱ ሰው የየራሱን የዕጣን ማጨሻ ይያዝ፤ በላዩም ላይ ዕጣን ያድርግበት፤ አንተንና አሮንን ጨምሮ እያንዳንዱ ሰው በይሖዋ ፊት የዕጣን ማጨሻውን ያቀርባል፤ ይህም በአጠቃላይ 250 የዕጣን ማጨሻዎች ማለት ነው፤ እያንዳንዱም የየራሱን የዕጣን ማጨሻ ይዞ ይቀርባል።” 18  ስለዚህ እያንዳንዳቸው የዕጣን ማጨሻቸውን ይዘው መጡ፤ በላዩም ላይ እሳትና ዕጣን አደረጉበት፤ ከዚያም ከሙሴና ከአሮን ጋር በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ቆሙ። 19  ቆሬ፣ ግብረ አበሮቹ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ሙሴንና አሮንን በመቃወም እንዲሰበሰቡ ባደረገ ጊዜ የይሖዋ ክብር ለመላው ማኅበረሰብ ተገለጠ። 20  በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ 21  “በአንዴ ጠራርጌ እንዳጠፋቸው ራሳችሁን ከዚህ ቡድን ለዩ።” 22  እነሱም በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው እንዲህ አሉ፦ “አምላክ ሆይ፣ አንተ የሰው ሁሉ መንፈስ አምላክ ነህ፤ ታዲያ አንድ ሰው በሠራው ኃጢአት የተነሳ በመላው ማኅበረሰብ ላይ ትቆጣለህ?” 23  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 24  “ለማኅበረሰቡ ‘ከቆሬ፣ ከዳታንና ከአቤሮን ድንኳኖች አካባቢ ራቁ!’ ብለህ ንገራቸው።” 25  ሙሴም ተነስቶ ወደ ዳታንና አቤሮን ሄደ፤ የእስራኤል ሽማግሌዎችም አብረውት ሄዱ። 26  ከዚያም ማኅበረሰቡን እንዲህ አላቸው፦ “በኃጢአታቸው ተጠራርጋችሁ እንዳትጠፉ እባካችሁ፣ ከእነዚህ ክፉ ሰዎች ድንኳኖች ራቁ፤ የእነሱ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትንኩ።” 27  እነሱም ወዲያውኑ ከቆሬ፣ ከዳታንና ከአቤሮን ድንኳኖች፣ ከዙሪያቸውም ሁሉ ራቁ፤ ዳታንና አቤሮንም ወጥተው ከሚስቶቻቸው፣ ከልጆቻቸውና ከሕፃኖቻቸው ጋር በድንኳኖቻቸው ደጃፍ ላይ ቆሙ። 28  ሙሴም እንዲህ አለ፦ “እነዚህን ነገሮች ሁሉ የማደርገው ከልቤ አመንጭቼ ሳይሆን ይሖዋ ልኮኝ መሆኑን በዚህ ታውቃላችሁ፦ 29  እነዚህ ሰዎች እንደ ማንኛውም ሰው አሟሟት የሚሞቱ ከሆነና የሚደርስባቸውም ቅጣት በሌሎች ሰዎች ሁሉ ላይ የሚደርስ ዓይነት ከሆነ እኔን ይሖዋ አላከኝም ማለት ነው። 30  ሆኖም ይሖዋ በእነሱ ላይ እንግዳ የሆነ ነገር ቢያደርግና መሬት አፏን ከፍታ እነሱንም ሆነ የእነሱ የሆነውን ነገር ሁሉ ብትውጥ፣ በሕይወት እንዳሉም ወደ መቃብር ቢወርዱ፣ እነዚህ ሰዎች ይሖዋን እንደናቁ በእርግጥ ታውቃላችሁ።” 31  እሱም ይህን ተናግሮ እንደጨረሰ፣ የቆሙባት ምድር ተሰነጠቀች። 32  ምድሪቱም አፏን ከፍታ እነሱን፣ ቤተሰቦቻቸውን፣ የቆሬ የሆነውን ማንኛውንም ሰውና ንብረታቸውን ሁሉ ዋጠች። 33  በዚህ መንገድ እነሱም ሆኑ የእነሱ የሆኑት ሁሉ በሕይወት እንዳሉ ወደ መቃብር ወረዱ፤ ምድርም ተከደነችባቸው፤ ስለዚህ ከጉባኤው መካከል ጠፉ። 34  በዙሪያቸው የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ጩኸታቸውን ሲሰሙ “ኧረ ምድሪቱ እኛንም እንዳትውጠን!” በማለት መሸሽ ጀመሩ። 35  ከዚያም ከይሖዋ ዘንድ እሳት መጥቶ ዕጣን ሲያጥኑ የነበሩትን 250 ሰዎች በላ። 36  በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 37  “የዕጣን ማጨሻዎቹ ቅዱስ ስለሆኑ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ከእሳቱ ውስጥ እንዲያወጣቸው ንገረው። በተጨማሪም እሳቱን ራቅ አድርጎ እንዲበትነው ንገረው። 38  ኃጢአት በመሥራታቸው የተነሳ ሕይወታቸውን የከፈሉት ሰዎች ይዘዋቸው የነበሩት የዕጣን ማጨሻዎች ቅዱስ ስለሆኑ ለመሠዊያው መለበጫ እንዲያገለግሉ በስሱ ይጠፍጠፉ፤ ምክንያቱም በይሖዋ ፊት ስላቀረቧቸው ቅዱስ ሆነዋል። ለእስራኤላውያንም ምልክት ሆነው ያገልግሉ።” 39  ስለሆነም ካህኑ አልዓዛር በእሳት የተቃጠሉት ሰዎች ያቀረቧቸውን የመዳብ የዕጣን ማጨሻዎች ወሰደ፤ ከዚያም መሠዊያውን ለመለበጥ በስሱ ጠፈጠፋቸው፤ 40  ይህን ያደረገውም ይሖዋ በሙሴ በኩል ለእሱ በነገረው መሠረት ነው። ይህም የአሮን ዘር ያልሆነ ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሰው በይሖዋ ፊት ዕጣን ለማጨስ እንዳይቀርብ እንዲሁም ማንም ሰው እንደ ቆሬና እንደ ግብረ አበሮቹ እንዳይሆን ለእስራኤላውያን ማሳሰቢያ እንዲሆን ነው። 41  በማግስቱም መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ “እናንተ ሰዎች የይሖዋን ሕዝብ ገድላችኋል” በማለት በሙሴና በአሮን ላይ ያጉረመርም ጀመር። 42  የእስራኤልም ማኅበረሰብ ሙሴንና አሮንን በመቃወም በተሰበሰበ ጊዜ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ዞር ብሎ ሲመለከት፣ መገናኛ ድንኳኑን ደመና ሸፍኖት አየ፤ የይሖዋም ክብር ተገለጠ። 43  ሙሴና አሮንም ወደ መገናኛ ድንኳኑ ፊት መጡ፤ 44  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 45  “በአንዴ እንዳጠፋቸው ራሳችሁን ከዚህ ማኅበረሰብ ለዩ።” እነሱም በዚህ ጊዜ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ። 46  ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፦ “የዕጣን ማጨሻ ውሰድና ከመሠዊያው ላይ እሳት አድርግበት፤ በላዩም ላይ ዕጣን ጨምርበት፤ ፈጥነህም ወደ ማኅበረሰቡ በመሄድ አስተሰርይላቸው፤ ምክንያቱም ይሖዋ ተቆጥቷል። መቅሰፍቱ ጀምሯል!” 47  አሮን ልክ ሙሴ እንዳለው ወዲያውኑ የዕጣን ማጨሻውን ይዞ ወደ ጉባኤው መካከል እየሮጠ ገባ፤ መቅሰፍቱ በሕዝቡ መካከል ጀምሮ ነበር። በመሆኑም ዕጣኑን በዕጣን ማጨሻው ላይ በማድረግ ለሕዝቡ ማስተሰረይ ጀመረ። 48  እሱም በሞቱትና በሕይወት ባሉት መካከል ቆመ፤ መቅሰፍቱም ቀስ በቀስ ቆመ። 49  በቆሬ ምክንያት የሞቱትን ሳይጨምር በመቅሰፍቱ የሞቱት ሰዎች ብዛት 14,700 ነበር። 50  በመጨረሻም አሮን በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ወደነበረው ወደ ሙሴ ሲመለስ መቅሰፍቱ ቆሞ ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,409
17  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “እስራኤላውያንን አናግራቸው፤ ለእያንዳንዱ የአባቶች ቤት ከእያንዳንዱ የአባቶች ቤት አለቃ ላይ አንድ አንድ በትር ይኸውም በአጠቃላይ 12 በትሮችን ከእነሱ ላይ ውሰድ። የእያንዳንዳቸውንም ስም በየበትራቸው ላይ ጻፍ። 3  ለእያንዳንዱ የአባቶች ቤት መሪ የሚኖረው አንድ በትር ስለሆነ የአሮንን ስም በሌዊ በትር ላይ ጻፍ። 4  በትሮቹን ራሴን ዘወትር ለእናንተ በምገልጥበት በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በምሥክሩ ፊት ለፊት አስቀምጣቸው። 5  ከዚያም እኔ የምመርጠው ሰው በትር ያቆጠቁጣል፤ እኔም እስራኤላውያን በእናንተ ላይ በማጉረምረም በእኔ ላይ እያሰሙ ያሉት ማጉረምረም እንዲያበቃ አደርጋለሁ።” 6  በመሆኑም ሙሴ እስራኤላውያንን አነጋገራቸው፤ አለቆቻቸውም በሙሉ በትሮቹን ይኸውም ለእያንዳንዱ የአባቶች ቤት አለቃ አንድ በትር ማለትም 12 በትሮችን ሰጡት፤ የአሮንም በትር ከእነሱ በትሮች ጋር ነበር። 7  ከዚያም ሙሴ በትሮቹን በምሥክሩ ድንኳን ውስጥ በይሖዋ ፊት አስቀመጣቸው። 8  በማግስቱም ሙሴ ወደ ምሥክሩ ድንኳን ሲገባ የሌዊን ቤት የሚወክለውን የአሮንን በትር አቆጥቁጦ፣ እንቡጥ አውጥቶ፣ አበባ አብቦና የደረሰ የአልሞንድ ፍሬ አፍርቶ አገኘው። 9  ከዚያም ሙሴ በትሮቹን በሙሉ ከይሖዋ ፊት አውጥቶ ወደ እስራኤል ሕዝብ ሁሉ አመጣቸው። እነሱም በትሮቹን አዩ፤ እያንዳንዱም ሰው የራሱን በትር ወሰደ። 10  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለዓመፀኞቹ ልጆች ምልክት ሆኖ እንዲያገለግል የአሮንን በትር መልሰህ ምሥክሩ ፊት አስቀምጠው፤ ይህም የሚሆነው በእኔ ላይ ማጉረምረማቸውን እንዲተዉና እንዳይሞቱ ነው።” 11  ሙሴም ወዲያውኑ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ። ልክ እንደተባለውም አደረገ። 12  ከዚያም እስራኤላውያን ሙሴን እንዲህ አሉት፦ “እንግዲህ መሞታችን ነው፤ በቃ ማለቃችን ነው፤ ሁላችንም ማለቃችን ነው! 13  ወደ ይሖዋ የማደሪያ ድንኳን የሚቀርብ ማንኛውም ሰው ይሞታል! በቃ በዚህ መንገድ ሁላችንም መሞታችን ነው?”
[]
[]
[]
[]
12,410
18  ከዚያም ይሖዋ አሮንን እንዲህ አለው፦ “ከመቅደሱ ጋር በተያያዘ ለሚፈጸመው ማንኛውም በደል አንተ፣ ከአንተም ጋር ወንዶች ልጆችህና የአባትህ ቤት ተጠያቂ ትሆናላችሁ፤ ከክህነታችሁ ጋር በተያያዘ ለሚፈጸመው ማንኛውም በደል አንተ፣ ከአንተም ጋር ወንዶች ልጆችህ ተጠያቂ ትሆናላችሁ። 2  በተጨማሪም በምሥክሩ ድንኳን ፊት ከአንተ ጋር አብረው እንዲሆኑ እንዲሁም አንተንና ወንዶች ልጆችህን እንዲያገለግሉ ከአባትህ ነገድ ይኸውም ከሌዊ ነገድ የሆኑትን ወንድሞችህን አቅርባቸው። 3  ከአንተም ሆነ በአጠቃላይ ከድንኳኑ ጋር በተያያዘ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ይወጡ። ይሁንና አንተም ሆንክ እነሱ እንዳትሞቱ ወደ ቅዱሱ ስፍራ ዕቃዎችና ወደ መሠዊያው አይቅረቡ። 4  እነሱም ከእናንተ ጋር በመሆን ከመገናኛ ድንኳኑና በድንኳኑ ከሚከናወነው አገልግሎት ሁሉ ጋር በተያያዘ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ይወጣሉ፤ ያልተፈቀደለት ማንኛውም ሰው ወደ እናንተ መቅረብ የለበትም። 5  እናንተም በእስራኤል ሕዝብ ላይ ዳግም ቁጣ እንዳይመጣ ከቅዱሱ ስፍራና ከመሠዊያው ጋር በተያያዘ የተጣለባችሁን ኃላፊነት ተወጡ። 6  እኔ ራሴ ወንድሞቻችሁ የሆኑትን ሌዋውያን ከእስራኤላውያን መካከል ወስጄ ለእናንተ ስጦታ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ። እነሱም በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ የሚከናወነውን አገልግሎት እንዲፈጽሙ ለይሖዋ የተሰጡ ናቸው። 7  ከመሠዊያውና በመጋረጃው ውስጥ ካለው ነገር ጋር የተያያዙትን የክህነት ሥራዎቻችሁን የማከናወኑ ኃላፊነት የተጣለው በአንተና በወንዶች ልጆችህ ላይ ነው፤ እናንተም ይህን አገልግሎት ታከናውናላችሁ። የክህነት አገልግሎቱን ለእናንተ ስጦታ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ወደዚያ የሚቀርብ ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሰው ይገደል።” 8  በተጨማሪም ይሖዋ አሮንን እንዲህ አለው፦ “ለእኔ በሚቀርቡት መዋጮዎች ላይ እኔ ራሴ ኃላፊ አድርጌ ሾሜሃለሁ። እስራኤላውያን የሚያዋጧቸውን ቅዱስ ነገሮች ሁሉ ለአንተና ለወንዶች ልጆችህ ድርሻችሁ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ይህም ቋሚ ድርሻችሁ ነው። 9  በእሳት ከሚቀርቡት እጅግ ቅዱስ የሆኑ መባዎች ውስጥ የሚከተሉት የአንተ ይሆናሉ፦ ለእኔ የሚያመጡትን የእህል መባቸውን፣ የኃጢአት መባቸውንና የበደል መባቸውን ጨምሮ የሚያቀርቡት ማንኛውም መባ የአንተ ይሆናል። ይህ ለአንተና ለወንዶች ልጆችህ እጅግ የተቀደሰ ነገር ነው። 10  እጅግ ቅዱስ በሆነ ስፍራ ብላው። እያንዳንዱ ወንድ ይብላው። ይህ ለአንተ የተቀደሰ ነገር ነው። 11  እስራኤላውያን ከሚወዘወዝ መባቸው ሁሉ ጋር መዋጮ አድርገው የሚያመጧቸው ስጦታዎች የአንተ ይሆናሉ። እነዚህን ለአንተ፣ ከአንተም ጋር ለወንዶች ልጆችህና ለሴቶች ልጆችህ ቋሚ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ። በቤትህ ያለ ማንኛውም ንጹሕ የሆነ ሰው ሊበላው ይችላል። 12  “ለይሖዋ የሚሰጡትን ምርጥ የሆነውን ዘይት ሁሉ፣ ምርጥ የሆነውን አዲስ የወይን ጠጅና እህል ሁሉ ይኸውም የፍሬያቸውን በኩራት ለአንተ ሰጥቼሃለሁ። 13  በምድራቸው ላይ መጀመሪያ የደረሰው ለይሖዋ የሚያመጡት ፍሬ ሁሉ የአንተ ይሆናል። በቤትህ ያለ ማንኛውም ንጹሕ የሆነ ሰው ሊበላው ይችላል። 14  “በእስራኤል ውስጥ ቅዱስ ለሆነ ዓላማ የተለየ ማንኛውም ነገር የአንተ ይሆናል። 15  “ከሰውም ሆነ ከእንስሳ ለይሖዋ የሚያቀርቡት የእያንዳንዱ ሕይወት ያለው ነገር በኩር ሁሉ የአንተ መሆን ይኖርበታል። ሆኖም ከሰው በኩር የሆነውን ሁሉ መዋጀት ይኖርብሃል፤ እንዲሁም ርኩስ ከሆነ እንስሳ በኩር የሆነውን ሁሉ መዋጀት ይገባሃል። 16  አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሲሆነው እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት በተተመነለት ዋጋ ይኸውም በአምስት የብር ሰቅል ወጆ ልትዋጀው ይገባል። አንዱ ሰቅል 20 ጌራ ነው። 17  በኩር የሆነውን በሬ፣ በኩር የሆነውን ተባዕት በግና በኩር የሆነውን ፍየል ግን መዋጀት የለብህም። እነዚህ የተቀደሱ ነገሮች ናቸው። ደማቸውን በመሠዊያው ላይ እርጨው፤ ስባቸውን ደግሞ ለይሖዋ ደስ የሚያሰኝ መዓዛ የሚሰጥ በእሳት የሚቀርብ መባ አድርገህ አጭሰው። 18  ሥጋቸው የአንተ ይሆናል። እንደሚወዘወዘው መባ ፍርምባና እንደ ቀኙ እግር ሁሉ ይህም የአንተ ይሆናል። 19  እስራኤላውያን ለይሖዋ የሚያዋጧቸውን ቅዱስ መዋጮዎች በሙሉ ለአንተ፣ ከአንተም ጋር ለወንዶች ልጆችህና ለሴቶች ልጆችህ ቋሚ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ። ይህም በይሖዋ ፊት ለአንተ፣ ከአንተም ጋር ለዘሮችህ የተገባ ዘላቂ የጨው ቃል ኪዳን ነው።” 20  ይሖዋም በመቀጠል አሮንን እንዲህ አለው፦ “አንተ በምድራቸው ውርሻ አይኖርህም፤ በመካከላቸውም ርስት አይኖርህም። በእስራኤላውያን መካከል የአንተ ድርሻም ሆነ ውርሻ እኔ ነኝ። 21  “እንግዲህ የሌዊ ወንዶች ልጆች ለሚያከናውኑት አገልግሎት ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ለሚሰጡት አገልግሎት በእስራኤል ውስጥ ያለውን የማንኛውንም ነገር አንድ አሥረኛ ውርሻ አድርጌ እንደሰጠኋቸው ልብ በል። 22  ከእንግዲህ እስራኤላውያን ወደ መገናኛ ድንኳኑ መቅረብ አይችሉም፤ ከቀረቡ ግን ኃጢአት ሆኖባቸው ይሞታሉ። 23  በመገናኛ ድንኳኑ የሚቀርበውን አገልግሎት ማከናወን ያለባቸው ሌዋውያኑ ራሳቸው ናቸው፤ ሕዝቡ ለሚፈጽመው ስህተት ተጠያቂ የሚሆኑት እነሱ ናቸው። በእስራኤላውያን መካከል በውርስ የሚያገኙት ርስት አይኖራቸውም፤ ይህም በትውልዶቻችሁ ሁሉ የሚቀጥል ዘላቂ ደንብ ነው። 24  ምክንያቱም የእስራኤል ሕዝብ መዋጮ አድርጎ ለይሖዋ የሚያዋጣውን አንድ አሥረኛ ለሌዋውያኑ ውርሻ አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ። እኔም ‘በእስራኤላውያን መካከል በውርስ የሚያገኙት ርስት አይኖራቸውም’ ያልኳቸው ለዚህ ነው።” 25  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 26  “ሌዋውያኑን እንዲህ በላቸው፦ ‘ከእስራኤላውያን ላይ ውርሻችሁ አድርጌ የሰጠኋችሁን አንድ አሥረኛ ከእነሱ እጅ ትቀበላላችሁ፤ እናንተ ደግሞ የአንድ አሥረኛውን አንድ አሥረኛ ለይሖዋ መዋጮ አድርጋችሁ ትሰጣላችሁ። 27  ይህ ለእናንተ እንደ መዋጮ ይኸውም ከአውድማ እንደገባ እህል ወይም ከወይን መጭመቂያ አሊያም ከዘይት መጭመቂያ እንደተገኘ የተትረፈረፈ ምርት ተደርጎ ይታሰብላችኋል። 28  በዚህ መንገድ እናንተም ከእስራኤላውያን ከምትቀበሉት አንድ አሥረኛ ሁሉ ላይ ለይሖዋ መዋጮ ታዋጣላችሁ፤ ከእሱም ላይ የይሖዋን መዋጮ ለካህኑ ለአሮን ትሰጣላችሁ። 29  ከምትቀበሏቸው ስጦታዎች ሁሉ ላይ ምርጥ የሆነውን እንደ ቅዱስ ነገር አድርጋችሁ ለይሖዋ ሁሉንም ዓይነት መዋጮ ታዋጣላችሁ።’ 30  “እንዲህም በላቸው፦ ‘ከስጦታዎቹ ላይ ምርጥ የሆነውን በምታዋጡበት ጊዜ ይህ ለእናንተ ለሌዋውያኑ ከአውድማ እንደገባ ምርት እንዲሁም ከወይን መጭመቂያ ወይም ከዘይት መጭመቂያ እንደተገኘ ምርት ተደርጎ ይታሰብላችኋል። 31  ይህ በመገናኛ ድንኳኑ ለምታከናውኑት አገልግሎት የተሰጠ ደሞዛችሁ ስለሆነ እናንተም ሆናችሁ ቤተሰባችሁ በየትኛውም ቦታ ልትበሉት ትችላላችሁ። 32  ከስጦታዎቹ ላይ ምርጥ የሆነውን መዋጮ እስካደረጋችሁ ድረስ ኃጢአት አይሆንባችሁም፤ የእስራኤላውያንን ቅዱስ ነገሮች ማርከስ የለባችሁም፤ እንዲህ ካደረጋችሁ ግን ትሞታላችሁ።’”
[]
[]
[]
[]
12,411
19  ይሖዋ ሙሴንና አሮንን በድጋሚ እንዲህ አላቸው፦ 2  “ይሖዋ ያዘዘው የሕጉ ደንብ ይህ ነው፦ ‘እንከን የሌለባትና ቀንበር ተጭኖባት የማታውቅ በጥሩ ሁኔታ ላይ የምትገኝ አንዲት ቀይ ላም እንዲያመጡልህ ለእስራኤላውያን ንገራቸው። 3  ለካህኑ ለአልዓዛርም ስጡት፤ እሱም ከሰፈሩ ውጭ ይወስዳትና በፊቱ ትታረዳለች። 4  ከዚያም ካህኑ አልዓዛር ከደሙ ላይ በጣቱ ወስዶ ደሙን በቀጥታ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል። 5  ከዚያም ላሟ ዓይኑ እያየ ትቃጠላለች። ቆዳዋ፣ ሥጋዋና ደሟ ከፈርሷ ጋር አብሮ ይቃጠላል። 6  ካህኑም የአርዘ ሊባኖስ እንጨት፣ ሂሶጵና ደማቅ ቀይ ማግ ወስዶ ላሟ የምትቃጠልበት እሳት ውስጥ ይጨምራል። 7  ከዚያም ካህኑ ልብሶቹን በውኃ ያጥባል፤ ገላውንም ይታጠባል፤ ከዚያ በኋላ ወደ ሰፈሩ መግባት ይችላል፤ ሆኖም ካህኑ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። 8  “‘ላሟን ያቃጠለውም ሰው ልብሶቹን በውኃ ያጥባል፤ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 9  “‘ንጹሕ የሆነ ሰው የላሟን አመድ አፍሶ ከሰፈሩ ውጭ ባለ ንጹሕ ቦታ ያጠራቅመዋል፤ የእስራኤል ማኅበረሰብም ለማንጻት የሚያገለግለውን ውኃ ለማዘጋጀት እንዲውል አመዱን ያስቀምጠው። ይህ የኃጢአት መባ ነው። 10  የላሟን አመድ የሚያፍሰው ሰው ልብሶቹን ያጥባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። “‘ይህም ለእስራኤላውያንና በመካከላቸው ለሚኖር የባዕድ አገር ሰው ዘላቂ ደንብ ሆኖ ያገለግላል። 11  የሞተ ሰው የነካ ማንኛውም ሰው ለሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል። 12  ይህ ሰው በሦስተኛው ቀን ራሱን በውኃው ያንጻ፤ በሰባተኛውም ቀን ንጹሕ ይሆናል። በሦስተኛው ቀን ራሱን ካላነጻ ግን በሰባተኛው ቀን ንጹሕ አይሆንም። 13  የሞተ ሰው የነካና ራሱን ያላነጻ ሰው ሁሉ የይሖዋን የማደሪያ ድንኳን አርክሷል፤ ይህ ሰው ከእስራኤል መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት። የሚያነጻው ውኃ ስላልተረጨበት ርኩስ ነው። አሁንም ከርኩሰቱ አልነጻም። 14  “‘አንድ ሰው በድንኳን ውስጥ ቢሞት ሕጉ ይህ ነው፦ ወደ ድንኳኑ የሚገባም ሆነ ቀድሞውኑም በድንኳኑ ውስጥ የነበረ ሰው ሁሉ ለሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል። 15  መክደኛው ላዩ ላይ ያልታሰረ ክፍት ዕቃ ሁሉ ርኩስ ነው። 16  በሰይፍ የተገደለን ወይም በድንን ወይም አፅምን ወይም መቃብርን የነካ በሜዳ ላይ ያለ ማንኛውም ሰው ለሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል። 17  ለረከሰውም ሰው ከተቃጠለው የኃጢአት መባ አመድ ላይ ወስደው በዕቃ በማድረግ ከወራጅ ውኃ የተቀዳ ውኃ ይጨምሩበት። 18  ከዚያም ንጹሕ የሆነ ሰው ሂሶጵ ወስዶ ውኃው ውስጥ ከነከረ በኋላ በድንኳኑ፣ በዕቃዎቹ ሁሉ፣ እዚያ በነበረው ሰው ሁሉና አፅሙን ወይም የተገደለውን ሰው አሊያም በድኑን ወይም መቃብሩን በነካው ሰው ላይ ይረጨዋል። 19  ንጹሕ የሆነውም ሰው ውኃውን በረከሰው ሰው ላይ በሦስተኛው ቀንና በሰባተኛው ቀን ላይ ይረጨዋል፤ በሰባተኛውም ቀን ከኃጢአት ያነጻዋል፤ ከዚያም ሰውየው ልብሶቹን ይጠብ፤ በውኃም ይታጠብ፤ ማታም ላይ ንጹሕ ይሆናል። 20  “‘ሆኖም የረከሰውና ራሱን ያላነጻው ሰው የይሖዋን መቅደስ ስላረከሰ ይህ ሰው ከጉባኤው መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት። የሚያነጻው ውኃ ስላልተረጨበት ሰውየው ርኩስ ነው። 21  “‘ይህ ለእነሱ ዘላቂ ደንብ ሆኖ ያገለግላል፦ የሚያነጻውን ውኃ የሚረጨው ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ የሚያነጻውን ውኃ የሚነካውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። 22  የረከሰው ሰው የሚነካው ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል፤ ይህን የነካ ሰውም እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።’”
[]
[]
[]
[]
12,412
2  ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ 2  “እስራኤላውያን ሦስት ነገዶችን ላቀፈው ምድባቸው በተሰጠው ቦታ ይስፈሩ፤ እያንዳንዱም ሰው ለአባቶቹ ቤት በቆመው ዓርማ አጠገብ ይስፈር። ፊታቸውን ወደ መገናኛ ድንኳኑ አድርገው ዙሪያውን ይስፈሩ። 3  “በስተ ምሥራቅ ፀሐይ በምትወጣበት አቅጣጫ በየምድቡ የሚሰፍረው ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የይሁዳ ምድብ ይሆናል፤ የይሁዳ ልጆች አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነው። 4  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 74,600 ናቸው። 5  ከእሱም ቀጥሎ የሚሰፍረው የይሳኮር ነገድ ይሆናል፤ የይሳኮር ልጆች አለቃ የጹአር ልጅ ናትናኤል ነው። 6  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 54,400 ናቸው። 7  ከዚያ ቀጥሎ የዛብሎን ነገድ ይስፈር፤ የዛብሎን ልጆች አለቃ የሄሎን ልጅ ኤልያብ ነው። 8  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 57,400 ናቸው። 9  “በይሁዳ ምድብ በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡት በአጠቃላይ 186,400 ናቸው። መጀመሪያ ድንኳናቸውን ነቅለው የሚነሱት እነሱ ይሆናሉ። 10  “ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የሮቤል ምድብ በየምድቡ በመሆን በስተ ደቡብ አቅጣጫ ይስፈር፤ የሮቤል ልጆች አለቃ የሸደኡር ልጅ ኤሊጹር ነው። 11  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 46,500 ናቸው። 12  ከእሱ ቀጥሎ የሚሰፍረው የስምዖን ነገድ ይሆናል፤ የስምዖን ልጆች አለቃ የጹሪሻዳይ ልጅ ሸሉሚኤል ነው። 13  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 59,300 ናቸው። 14  ከዚያ ቀጥሎ የጋድ ነገድ ይስፈር፤ የጋድ ልጆች አለቃ የረኡዔል ልጅ ኤሊያሳፍ ነው። 15  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 45,650 ናቸው። 16  “በሮቤል ምድብ በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡት በአጠቃላይ 151,450 ናቸው፤ በሁለተኛ ደረጃ ድንኳናቸውን ነቅለው የሚነሱት እነሱ ናቸው። 17  “የመገናኛ ድንኳኑ ከቦታ ወደ ቦታ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ የሌዋውያኑ ሰፈር በሌሎቹ ሰፈሮች መሃል መሆን ይኖርበታል። “እነሱም ልክ በሰፈሩበት ሁኔታ እያንዳንዳቸው ቦታቸውን ጠብቀው ሦስት ነገድ ባቀፈው ምድባቸው መሠረት መጓዝ ይኖርባቸዋል። 18  “ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የኤፍሬም ምድብ በየምድቡ በመሆን በስተ ምዕራብ አቅጣጫ ይስፈር፤ የኤፍሬም ልጆች አለቃ የአሚሁድ ልጅ ኤሊሻማ ነው። 19  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 40,500 ናቸው። 20  ከእሱም ቀጥሎ የምናሴ ነገድ ይስፈር፤ የምናሴ ልጆች አለቃ የፐዳጹር ልጅ ገማልያል ነው። 21  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 32,200 ናቸው። 22  ከዚያ ቀጥሎ የቢንያም ነገድ ይስፈር፤ የቢንያም ልጆች አለቃ የጊድኦኒ ልጅ አቢዳን ነው። 23  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 35,400 ናቸው። 24  “በኤፍሬም ምድብ በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡት በአጠቃላይ 108,100 ናቸው፤ በሦስተኛ ደረጃ ድንኳናቸውን ነቅለው የሚነሱት እነሱ ናቸው። 25  “ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የዳን ምድብ በየምድቡ በመሆን በስተ ሰሜን አቅጣጫ ይስፈር፤ የዳን ልጆች አለቃ የአሚሻዳይ ልጅ አሂዔዜር ነው። 26  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 62,700 ናቸው። 27  ከእሱም ቀጥሎ የሚሰፍረው የአሴር ነገድ ይሆናል፤ የአሴር ልጆች አለቃ የኦክራን ልጅ ፓጊኤል ነው። 28  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 41,500 ናቸው። 29  ከዚያ ቀጥሎ የንፍታሌም ነገድ ይስፈር፤ የንፍታሌም ልጆች አለቃ የኤናን ልጅ አሂራ ነው። 30  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 53,400 ናቸው። 31  “በዳን ምድብ የተመዘገቡት በአጠቃላይ 157,600 ናቸው። ሦስት ነገዶችን ባቀፈው ምድባቸው መሠረት መጨረሻ ላይ ድንኳናቸውን ነቅለው የሚነሱት እነሱ ናቸው።” 32  በአባቶቻቸው ቤት መሠረት የተመዘገቡት እስራኤላውያን እነዚህ ነበሩ፤ ወደ ሠራዊቱ ለመቀላቀል በሰፈሩ ውስጥ የተመዘገቡት በአጠቃላይ 603,550 ነበሩ። 33  ሌዋውያኑ ግን ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋር አልተመዘገቡም። 34  እስራኤላውያንም ይሖዋ ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ። እያንዳንዳቸው በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በመሆን ሦስት ነገዶችን ባቀፈው ምድባቸው መሠረት የሰፈሩትም ሆነ ድንኳናቸውን ነቅለው የተነሱት በዚህ መንገድ ነው።
[]
[]
[]
[]
12,413
20  በመጀመሪያው ወር መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ወደ ጺን ምድረ በዳ መጣ፤ ሕዝቡም በቃዴስ ተቀመጠ። ሚርያም የሞተችውም ሆነ የተቀበረችው በዚያ ነበር። 2  በዚያ ለማኅበረሰቡ የሚሆን ውኃ አልነበረም፤ ሕዝቡም ሙሴንና አሮንን በመቃወም በእነሱ ላይ ተሰበሰበ። 3  ሕዝቡም እንዲህ በማለት ከሙሴ ጋር ተጣላ፦ “ምነው ወንድሞቻችን በይሖዋ ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ሞተን ባረፍነው ኖሮ! 4  እኛም ሆንን ከብቶቻችን እዚህ እንድናልቅ የይሖዋን ጉባኤ ወደዚህ ምድረ በዳ ያመጣችሁት ለምንድን ነው? 5  ከግብፅ አውጥታችሁ ወደዚህ መጥፎ ቦታ እየመራችሁ ያመጣችሁን ለምንድን ነው? ይህ ቦታ እህልም ሆነ በለስ፣ የወይን ፍሬም ሆነ ሮማን የሌለበት ነው፤ የሚጠጣ ውኃም የለም።” 6  ከዚያም ሙሴና አሮን ከጉባኤው ፊት ተነስተው ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በመሄድ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ፤ የይሖዋም ክብር ተገለጠላቸው። 7  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 8  “በትሩን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮንም ማኅበረሰቡን ሰብስቡ፤ ዓለቱም ውኃውን እንዲሰጥ በእነሱ ፊት ተናገሩት፤ አንተም ከዓለቱ ውኃ ታፈልቅላቸዋለህ፤ ማኅበረሰቡም ሆነ ከብቶቻቸው እንዲጠጡም ትሰጣቸዋለህ።” 9  ሙሴም ልክ እንደታዘዘው በትሩን ከይሖዋ ፊት ወሰደ። 10  ከዚያም ሙሴና አሮን ጉባኤውን በዓለቱ ፊት ሰበሰቡ፤ እሱም “እናንተ ዓመፀኞች ስሙ! ከዚህ ዓለት ለእናንተ ውኃ ማፍለቅ አለብን?” አላቸው። 11  ሙሴም ይህን ካለ በኋላ እጁን አንስቶ ዓለቱን ሁለት ጊዜ በበትሩ መታው፤ ውኃውም ይንዶለዶል ጀመር፤ ማኅበረሰቡና ከብቶቻቸውም ጠጡ። 12  በኋላም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ “በእስራኤል ሕዝብ ፊት በእኔ ስላልታመናችሁና እኔን ስላልቀደሳችሁ ይህን ጉባኤ እኔ ወደምሰጠው ምድር ይዛችሁ አትገቡም።” 13  ይሖዋ በመካከላቸው ይቀደስ ዘንድ እስራኤላውያን ከእሱ ጋር የተጣሉባቸው የመሪባ ውኃዎች እነዚህ ናቸው። 14  ከዚያም ሙሴ ለኤዶም ንጉሥ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት ከቃዴስ መልእክተኞችን ላከ፦ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ ‘መቼም የደረሰብንን መከራ ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ። 15  አባቶቻችን ወደ ግብፅ ወርደው ነበር፤ እኛም በግብፅ ለብዙ ዓመታት ኖርን፤ ግብፃውያኑም በእኛም ሆነ በአባቶቻችን ላይ በደል ይፈጽሙብን ነበር። 16  በመጨረሻም ወደ ይሖዋ ጮኽን፤ እሱም ጩኸታችንን ሰምቶ መልአክ በመላክ ከግብፅ አወጣን፤ ይኸው አሁን ድንበርህ ላይ ባለችው በቃዴስ ከተማ እንገኛለን። 17  እናም አሁን እባክህ በምድርህ እንለፍ። በየትኛውም እርሻ ወይም በየትኛውም የወይን ቦታ አቋርጠን አንሄድም፤ ከየትኛውም ጉድጓድ ውኃ አንጠጣም። ክልልህን አቋርጠን እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር ሳንል በንጉሡ መንገድ እንሄዳለን።’” 18  ኤዶም ግን “ክልላችንን አቋርጠህ ማለፍ አትችልም። እንዲህ ካደረግክ ወጥቼ በሰይፍ እገጥምሃለሁ” አለው። 19  እስራኤላውያንም መልሰው እንዲህ አሉት፦ “አውራ ጎዳናውን ይዘን እናቀናለን፤ እኛም ሆን ከብቶቻችን ከውኃህ ከጠጣን ዋጋውን እንከፍልሃለን። በእግራችን አልፈን ከመሄድ በስተቀር ሌላ ምንም ነገር አንፈልግም።” 20  እሱ ግን አሁንም “በዚህ ማለፍ አትችልም” ሲል መልስ ሰጠ። ከዚያም ኤዶም ብዙ ሕዝብና ኃያል ሠራዊት ይዞ ሊገጥመው ወጣ። 21  በዚህ መንገድ ኤዶም እስራኤል በክልሉ እንዳያልፍ ከለከለ፤ ስለዚህ እስራኤል ከእሱ ተመለሰ። 22  የእስራኤል ሕዝብ ይኸውም መላው ማኅበረሰብ ከቃዴስ ተነስቶ ወደ ሆር ተራራ መጣ። 23  ከዚያም ይሖዋ በኤዶም ምድር ወሰን ላይ ባለው በሆር ተራራ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ 24  “አሮን ወደ ወገኖቹ ይሰበሰባል። ሁለታችሁም ከመሪባ ውኃ ጋር በተያያዘ በሰጠሁት ትእዛዝ ላይ ስላመፃችሁ ለእስራኤላውያን ወደምሰጣት ምድር አይገባም። 25  አሮንንና ልጁን አልዓዛርን ይዘህ ወደ ሆር ተራራ ውጣ። 26  የአሮንን ልብስ አውልቀህ ልጁን አልዓዛርን አልብሰው፤ አሮንም በዚያ ይሞታል።” 27  በመሆኑም ሙሴ ልክ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ፤ እነሱም መላው ማኅበረሰብ እያየ ወደ ሆር ተራራ ወጡ። 28  ሙሴም የአሮንን ልብስ አውልቆ ልጁን አልዓዛርን አለበሰው። ከዚያም አሮን እዚያው ተራራው አናት ላይ ሞተ። ሙሴና አልዓዛርም ከተራራው ወረዱ። 29  መላው ማኅበረሰብም አሮን መሞቱን አየ፤ በዚህ ጊዜ የእስራኤል ቤት በሙሉ ለአሮን 30 ቀን አለቀሰለት።
[]
[]
[]
[]
12,414
21  በኔጌብ የሚኖረው ከነአናዊው የአራድ ንጉሥ እስራኤላውያን በአታሪም መንገድ እየመጡ መሆናቸውን በሰማ ጊዜ በእነሱ ላይ ጥቃት ሰነዘረ፤ ከመካከላቸውም የተወሰኑትን በምርኮ ወሰደ። 2  ስለዚህ እስራኤል “ይህን ሕዝብ በእጄ አሳልፈህ የምትሰጠኝ ከሆነ ከተሞቻቸውን ጠራርጌ አጠፋለሁ” በማለት ለይሖዋ ስእለት ተሳለ። 3  በመሆኑም ይሖዋ የእስራኤልን ጩኸት ሰማ፤ ከነአናውያንንም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነሱም ሕዝቡንና ከተሞቻቸውን ጠራርገው አጠፉ። ስለሆነም የቦታውን ስም ሆርማ አሉት። 4  እስራኤላውያን ከሆር ተራራ በመነሳት በኤዶም ምድር ዞረው ለመሄድ ስላሰቡ የቀይ ባሕርን መንገድ ይዘው ተጓዙ፤ ከጉዞውም የተነሳ ሕዝቡ ዛለ። 5  ሕዝቡም እንዲህ በማለት በአምላክና በሙሴ ላይ ያማርር ጀመር፦ “በምድረ በዳ እንድንሞት ከግብፅ ያወጣችሁን ለምንድን ነው? ምግብ የለ፣ ውኃ የለ፤ ደግሞም ይህን የማይረባ ምግብ ጠልተነዋል።” 6  በመሆኑም ይሖዋ በሕዝቡ ላይ መርዘኛ እባቦችን ሰደደባቸው፤ እባቦቹም ሰዎቹን ስለነደፏቸው ብዙ እስራኤላውያን ሞቱ። 7  ስለሆነም ሕዝቡ ወደ ሙሴ መጥቶ “በይሖዋና በአንተ ላይ በማማረራችን ኃጢአት ሠርተናል። እባቦቹን ከመካከላችን እንዲያስወግድልን ይሖዋን ተማጸንልን” አለ። ሙሴም ስለ ሕዝቡ ተማጸነ። 8  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የመርዛማ እባብ ምስል ሠርተህ እንጨት ላይ ስቀለው። ማንኛውም ሰው በሚነደፍበት ጊዜ በሕይወት እንዲኖር ምስሉን ማየት አለበት።” 9  ሙሴም ወዲያው የመዳብ እባብ ሠርቶ እንጨት ላይ ሰቀለው፤ አንድ ሰው እባብ ሲነድፈው ከመዳብ ወደተሠራው እባብ ከተመለከተ ይድን ነበር። 10  ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ከነበሩበት ተነስተው በመጓዝ በኦቦት ሰፈሩ። 11  ከዚያም ከኦቦት ተነስተው በምሥራቅ አቅጣጫ በሞዓብ ፊት ለፊት በሚገኘው ምድረ በዳ በኢዬዓባሪም ሰፈሩ። 12  ከዚያ ተነስተው ደግሞ በዘረድ ሸለቆ ሰፈሩ። 13  ከዘረድ ሸለቆ ተነስተው ከአሞራውያን ድንበር ጀምሮ ባለው ምድረ በዳ ውስጥ በሚገኘው በአርኖን ክልል ሰፈሩ፤ ምክንያቱም አርኖን በሞዓብና በአሞራውያን መካከል የሚገኝ የሞዓብ ድንበር ነው። 14  የይሖዋ የጦርነት መጽሐፍ እንዲህ በማለት የሚናገረው ለዚህ ነው፦ “በሱፋ የሚገኘው ዋሄብ፣ የአርኖን ሸለቆዎች 15  እንዲሁም ኤር ወደሚገኝበት አቅጣጫ የሚዘረጋውና የሞዓብን ድንበር የሚያዋስነው የሸለቆዎች ቁልቁለት።” 16  ከዚያም ወደ በኤር ተጓዙ። ይሖዋ ሙሴን “ሕዝቡን ሰብስብ፤ እኔም ውኃ እሰጣቸዋለሁ” ያለው ይህን የውኃ ጉድጓድ አስመልክቶ ነው። 17  በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን ይህን መዝሙር ዘመሩ፦ “አንተ ጉድጓድ፣ ውኃ አፍልቅ! እናንተም መልሱለት! 18  መኳንንት ለቆፈሩት፣ በሕዝቡ መካከል ያሉ ታላላቅ ሰዎች ለማሱት፣በገዢ ዘንግና በራሳቸው በትሮች ላዘጋጁት የውኃ ጉድጓድ ዘምሩለት።” ከዚያም ከምድረ በዳው ተነስተው ወደ ማታናህ ተጓዙ፤ 19  ከማታናህ ተነስተው ደግሞ ወደ ናሃሊኤል፣ ከናሃሊኤልም ተነስተው ወደ ባሞት ተጓዙ። 20  ከባሞትም ተነስተው የሺሞንን ቁልቁል ማየት ወደሚቻልበት በጲስጋ አናት ላይ ወደሚገኘውና በሞዓብ ክልል ወዳለው ሸለቆ ተጓዙ። 21  እስራኤላውያን የአሞራውያን ንጉሥ ወደሆነው ወደ ሲሖን እንዲህ በማለት መልእክተኞችን ላኩ፦ 22  “ምድርህን አቋርጠን እንድናልፍ ፍቀድልን። ወደ የትኛውም እርሻ ወይም ወደ የትኛውም የወይን ቦታ አንገባም። ከየትኛውም ጉድጓድ ውኃ አንጠጣም። ክልልህን አቋርጠን እስክናልፍ ድረስ በንጉሡ መንገድ ቀጥ ብለን እንሄዳለን።” 23  ሲሖን ግን እስራኤላውያን ክልሉን አቋርጠው እንዲያልፉ አልፈቀደላቸውም። ከዚህ ይልቅ ሲሖን ሕዝቡን ሁሉ ሰብስቦ እስራኤልን ለመውጋት ወደ ምድረ በዳው ሄደ፤ ያሃጽ በደረሰ ጊዜም ከእስራኤላውያን ጋር ውጊያ ገጠመ። 24  እስራኤላውያን ግን በሰይፍ ድል አደረጉት፤ ምድሩንም ከአርኖን አንስቶ በአሞናውያን አቅራቢያ እስከሚገኘው እስከ ያቦቅ ድረስ ያዙ፤ ሆኖም ያዜር የአሞናውያን ወሰን ስለሆነ ከዚያ አላለፉም። 25  በመሆኑም እስራኤላውያን እነዚህን ከተሞች ሁሉ ያዙ፤ ከዚያም በአሞራውያን ከተሞች ይኸውም በሃሽቦንና በሥሯ ባሉት ከተሞች ሁሉ መኖር ጀመሩ። 26  ምክንያቱም ሃሽቦን የአሞራውያን ንጉሥ የሲሖን ከተማ ነበረች፤ እሱም ከሞዓብ ንጉሥ ጋር ተዋግቶ እስከ አርኖን ድረስ ያለውን ምድር ከእጁ ወስዶበት ነበር። 27  እንዲህ የሚለውን ቅኔ በመቀኘት የተሳለቁበት በዚህ የተነሳ ነው፦ “ወደ ሃሽቦን ኑ። የሲሖን ከተማ ትገንባ፤ ጸንታም ትቁም። 28  እሳት ከሃሽቦን፣ ነበልባልም ከሲሖን ከተማ ወጥቷልና። የሞዓብን ኤር፣ የአርኖንን ኮረብቶች ጌቶች በላ። 29  ሞዓብ ሆይ፣ ወዮልህ! እናንተ የከሞሽ ሕዝቦች ሆይ፣ ድምጥማጣችሁ ይጠፋል። ወንዶች ልጆቹን ለስደት ይዳርጋል፤ ሴቶች ልጆቹንም ለአሞራውያን ንጉሥ ለሲሖን ምርኮኛ አድርጎ ይሰጣል። 30  በመሆኑም ጥቃት እንሰንዝርባቸው፤ሃሽቦን እስከ ዲቦን ድረስ ይደመሰሳል፤እስከ ኖፋ ድረስ እንደምስሰው፤እስከ መደባም ድረስ እሳት ይዛመታል።” 31  ስለዚህ እስራኤላውያን በአሞራውያን ምድር መኖር ጀመሩ። 32  ከዚያም ሙሴ ያዜርን እንዲሰልሉ የተወሰኑ ሰዎችን ላከ። እነሱም በሥሯ ያሉትን ከተሞች ተቆጣጠሩ፤ በዚያ የነበሩትንም አሞራውያን አባረሩ። 33  ከዚህ በኋላ ተመልሰው ወደ ባሳን የሚወስደውን መንገድ ይዘው ወጡ። የባሳን ንጉሥ ኦግም ከሕዝቡ ሁሉ ጋር በመሆን ኤድራይ ላይ ጦርነት ሊገጥማቸው ወጣ። 34  ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እሱንም ሆነ ሕዝቡን ሁሉ እንዲሁም ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ስለምሰጥህ አትፍራው፤ አንተም በሃሽቦን ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ላይ እንዳደረግከው በእሱም ላይ ታደርግበታለህ።” 35  በመሆኑም ኦግን ከወንዶች ልጆቹና ከሕዝቡ ሁሉ ጋር አንድም ሰው ሳያስቀሩ ሁሉንም ደመሰሱ፤ ምድሩንም ወረሱ።
[]
[]
[]
[]
12,415
22  እስራኤላውያንም ከዚያ ተነስተው በመጓዝ ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ በሚገኘው በሞዓብ በረሃማ ሜዳ ሰፈሩ። 2  የሴፎር ልጅ ባላቅ እስራኤላውያን በአሞራውያን ላይ ያደረጉትን ሁሉ አየ፤ 3  ሞዓብም ከሕዝቡ ብዛት የተነሳ በጣም ፈራ፤ በእርግጥም ሞዓብ በእስራኤላውያን ምክንያት በፍርሃት ታውኮ ነበር። 4  ስለዚህ ሞዓብ የምድያምን ሽማግሌዎች “በሬ በሜዳ ላይ ያለን ሣር ጠራርጎ እንደሚበላ ሁሉ ይህም ጉባኤ በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ጠራርጎ ያጠፋል” አላቸው። በዚያን ጊዜ የሴፎር ልጅ ባላቅ የሞዓብ ንጉሥ ነበር። 5  እሱም የቢዖርን ልጅ በለዓምን እንዲጠሩት መልእክተኞችን ላከ፤ በለዓም የሚኖረው በትውልድ አገሩ ባለው ወንዝ ዳር በምትገኘው በጰቶር ነበር። እንዲህም ብለው እንዲነግሩት ላካቸው፦ “ከግብፅ ወጥቶ የመጣ አንድ ሕዝብ አለ። ይኸው የምድሪቱን ገጽ ሸፍኗል፤ ደግሞም መጥቶ አፍንጫዬ ሥር ሰፍሯል። 6  እነሱ ከእኔ ይልቅ ኃያላን ስለሆኑ እባክህ መጥተህ ይህን ሕዝብ እርገምልኝ። ምናልባትም ድል አድርጌ ከምድሪቱ ላባርራቸው እችላለሁ፤ ምክንያቱም አንተ የባረክኸው ሁሉ የተባረከ፣ የረገምከውም ሁሉ የተረገመ እንደሚሆን በሚገባ አውቃለሁ።” 7  በመሆኑም የሞዓብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎች ለሟርት የሚከፈለውን ዋጋ ይዘው ወደ በለዓም ሄዱ፤ የባላቅንም መልእክት ነገሩት። 8  እሱም “እንግዲህ እዚህ እደሩና ይሖዋ የሚለኝን ማንኛውንም ነገር መልሼ እነግራችኋለሁ” አላቸው። ስለዚህም የሞዓብ መኳንንት በለዓም ዘንድ አደሩ። 9  ከዚያም አምላክ ወደ በለዓም መጥቶ “ከአንተ ጋር ያሉት እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው?” አለው። 10  በለዓምም እውነተኛውን አምላክ እንዲህ አለው፦ “የሞዓብ ንጉሥ የሴፎር ልጅ ባላቅ እንዲህ የሚል መልእክት ልኮብኛል፦ 11  ‘ከግብፅ ወጥቶ የመጣው ሕዝብ የምድሪቱን ገጽ ሸፍኗል። ስለዚህ መጥተህ እነሱን እርገምልኝ። ምናልባትም ድል አድርጌ ከምድሪቱ ላባርራቸው እችላለሁ።’” 12  ሆኖም አምላክ በለዓምን “ከእነሱ ጋር እንዳትሄድ። ሕዝቡ የተባረከ ስለሆነ እንዳትረግመው” አለው። 13  በለዓም በጠዋት ተነስቶ የባላቅን መኳንንት “ይሖዋ ከእናንተ ጋር እንዳልሄድ ስለከለከለኝ ወደ አገራችሁ ሂዱ” አላቸው። 14  በመሆኑም የሞዓብ መኳንንት ተነስተው ወደ ባላቅ ተመለሱ፤ እንዲህም አሉት፦ “በለዓም ከእኛ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ አልሆነም።” 15  ሆኖም ባላቅ ከበፊቶቹ ይልቅ ቁጥራቸው የበዛና ይበልጥ የተከበሩ ሌሎች መኳንንት እንደገና ላከ። 16  እነሱም ወደ በለዓም መጥተው እንዲህ አሉት፦ “የሴፎር ልጅ ባላቅ እንዲህ ይላል፦ ‘እባክህ ወደ እኔ ከመምጣት ምንም ነገር እንዲያግድህ አትፍቀድ። 17  እኔም ከፍ ያለ ክብር አጎናጽፍሃለሁ፤ የምትለኝንም ሁሉ አደርጋለሁ። ስለሆነም እባክህ መጥተህ ይህን ሕዝብ እርገምልኝ።’” 18  ሆኖም በለዓም ለባላቅ አገልጋዮች እንዲህ የሚል መልስ ሰጣቸው፦ “ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላውን የገዛ ቤቱን ቢሰጠኝ እንኳ ከአምላኬ ከይሖዋ ትእዛዝ ወጥቼ ትንሽም ሆነ ትልቅ ምንም ነገር ማድረግ አልችልም። 19  ሆኖም እባካችሁ፣ ይሖዋ ሌላ የሚለኝ ነገር ካለ እንዳውቅ ዛሬም እዚህ እደሩ።” 20  ከዚያም አምላክ በሌሊት ወደ በለዓም መጥቶ እንዲህ አለው፦ “እነዚህ ሰዎች የመጡት አንተን ለመጥራት ከሆነ አብረሃቸው ሂድ። ይሁንና የምትናገረው እኔ የምልህን ብቻ ነው።” 21  ስለዚህ በለዓም በጠዋት ተነስቶ አህያውን ከጫነ በኋላ ከሞዓብ መኳንንት ጋር ሄደ። 22  ይሁን እንጂ በለዓም ጉዞ በመጀመሩ የአምላክ ቁጣ ነደደ፤ የይሖዋም መልአክ በለዓምን ሊቃወመው መንገዱ ላይ ቆመ። በዚህ ጊዜ በለዓም በአህያው ላይ ተቀምጦ እየተጓዘ ነበር፤ ሁለት አገልጋዮቹም አብረውት ነበሩ። 23  አህያዋም የይሖዋ መልአክ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ መንገዱ ላይ መቆሙን ስታይ ከመንገዱ ወጥታ ወደ እርሻ ለመግባት ሞከረች። ሆኖም በለዓም አህያዋን ወደ መንገዱ ለመመለስ ይደበድባት ጀመር። 24  ከዚያም የይሖዋ መልአክ በዚህም በዚያም በኩል በግንብ በታጠሩ ሁለት የወይን እርሻዎች መካከል በሚገኝ ጠባብ መንገድ ላይ ቆመ። 25  አህያዋም የይሖዋን መልአክ ስታይ ግንቡን መታከክ ጀመረች፤ የበለዓምንም እግር ከግንቡ ጋር አጣበቀችው፤ በለዓምም እንደገና ይደበድባት ጀመር። 26  የይሖዋም መልአክ እንደገና አልፎ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ መፈናፈን በማያስችል ጠባብ ቦታ ላይ ቆመ። 27  አህያዋም የይሖዋን መልአክ ስታይ በለዓም ላይዋ ላይ እንዳለ ተኛች፤ በዚህ ጊዜ በለዓም እጅግ ተቆጣ፤ አህያዋንም በዱላው ይቀጠቅጣት ጀመር። 28  በመጨረሻም ይሖዋ አህያዋ እንድትናገር አደረገ፤ እሷም በለዓምን “ሦስት ጊዜ እንዲህ የመታኸኝ ምን አድርጌህ ነው?” አለችው። 29  በለዓምም አህያዋን “ስለተጫወትሽብኝ ነዋ! በእጄ ሰይፍ ይዤ ቢሆንማ ኖሮ እገድልሽ ነበር!” አላት። 30  ከዚያም አህያዋ በለዓምን “እስከ ዛሬ ድረስ በሕይወትህ ሙሉ የተቀመጥክብኝ አህያህ አይደለሁም? ከዚህ በፊት እንዲህ አድርጌህ አውቃለሁ?” አለችው። እሱም “በጭራሽ!” አላት። 31  ከዚያም ይሖዋ የበለዓምን ዓይኖች ገለጠ፤ እሱም የይሖዋ መልአክ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ መንገዱ ላይ ቆሞ አየ። ወዲያውኑም በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደ። 32  ከዚያም የይሖዋ መልአክ እንዲህ አለው፦ “አህያህን ሦስት ጊዜ እንዲህ አድርገህ የመታሃት ለምንድን ነው? መንገድህ ከፈቃዴ ጋር ስለሚቃረን እኔ ራሴ ከጉዞህ ልገታህ መጥቻለሁ። 33  አህያዋ አይታኝ ሦስቱንም ጊዜ ከፊቴ ዞር ለማለት ሞከረች። እሷ ከፊቴ ዞር ባትልማ ኖሮ ምን ይከሰት እንደነበር አስብ! ይሄን ጊዜ አንተን ገድዬህ አህያዋን በሕይወት በተውኳት ነበር።” 34  በዚህ ጊዜ በለዓም የይሖዋን መልአክ እንዲህ አለው፦ “ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ ምክንያቱም አንተ እኔን ለማግኘት መንገድ ላይ እንደቆምክ አላወቅኩም ነበር። አሁንም ቢሆን መሄዴ ጥሩ መስሎ ካልታየህ እመለሳለሁ።” 35  ሆኖም የይሖዋ መልአክ በለዓምን “ከሰዎቹ ጋር መሄዱን እንኳ ሂድ፤ የምትናገረው ግን እኔ የምልህን ብቻ ነው” አለው። በመሆኑም በለዓም ከባላቅ መኳንንት ጋር ጉዞውን ቀጠለ። 36  ባላቅ የበለዓምን መምጣት ሲሰማ በክልሉ ወሰን ላይ በሚገኘው በአርኖን ዳርቻ ባለው በሞዓብ ከተማ ሊቀበለው ወዲያውኑ ወጣ። 37  ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “እንድትመጣ ልኬብህ አልነበረም? ታዲያ ወደ እኔ ያልመጣኸው ለምንድን ነው? ለመሆኑ እኔ አንተን ታላቅ ክብር ማጎናጸፍ የሚያቅተኝ ይመስልሃል?” 38  በለዓምም ባላቅን እንዲህ አለው፦ “ይኸው አሁን ወደ አንተ መጥቻለሁ። ይሁንና ያሻኝን መናገር የምችል ይመስልሃል? እኔ መናገር የምችለው አምላክ በአፌ ላይ የሚያደርገውን ቃል ብቻ ነው።” 39  በመሆኑም በለዓም ከባላቅ ጋር ሄደ፤ ወደ ቂርያትሁጾትም መጡ። 40  ባላቅም ከብቶችንና በጎችን ሠዋ፤ የተወሰነውንም ለበለዓምና ከእሱ ጋር ለነበሩት መኳንንት ላከ። 41  ጠዋት ላይም ባላቅ በለዓምን ይዞት ወደ ባሞትበዓል ወጣ፤ እዚያ ሆኖ ሕዝቡን ሁሉ ማየት ይችል ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,416
23  ከዚያም በለዓም ባላቅን “እዚህ ቦታ ላይ ሰባት መሠዊያዎች ሥራልኝ፤ እንዲሁም ሰባት በሬዎችና ሰባት አውራ በጎች አዘጋጅልኝ” አለው። 2  ባላቅም ወዲያውኑ በለዓም እንዳለው አደረገ። ባላቅና በለዓም በእያንዳንዱ መሠዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቀረቡ። 3  ከዚያም በለዓም ባላቅን እንዲህ አለው፦ “አንተ እዚህ የሚቃጠለው መባህ አጠገብ ቆይ፤ እኔ ግን ልሂድ። ምናልባት ይሖዋ ይገለጥልኝ ይሆናል። እሱ የሚገልጥልኝን ማንኛውንም ነገር እነግርሃለሁ።” በመሆኑም በለዓም ወደ አንድ ገላጣ ኮረብታ ሄደ። 4  በለዓምም ከአምላክ ጋር በተገናኘ ጊዜ “ሰባቱን መሠዊያዎች በመደዳ አቁሜያቸዋለሁ፤ በእያንዳንዱም መሠዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቅርቤያለሁ” አለው። 5  ይሖዋም በበለዓም አፍ ላይ ይህን ቃል አስቀመጠ፦ “ወደ ባላቅ ተመለስና እንዲህ ብለህ ንገረው።” 6  በመሆኑም በለዓም ተመለሰ፤ እሱም ባላቅን ከሞዓብ መኳንንት ሁሉ ጋር በሚቃጠለው መባው አጠገብ ቆሞ አየው። 7  ከዚያም ይህን ምሳሌያዊ አባባል ተናገረ፦ “የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ከአራም፣ከምሥራቅ ተራሮች አመጣኝ፤ ‘ና፣ ያዕቆብን እርገምልኝ። አዎ ና፣ እስራኤልን አውግዝልኝ’ አለኝ። 8  አምላክ ያልረገመውን እኔ እንዴት ልረግም እችላለሁ? ይሖዋ ያላወገዘውንስ እኔ እንዴት ላወግዝ እችላለሁ? 9  ከዓለቶቹ አናት ላይ ሆኜ አያቸዋለሁ፤ከኮረብቶቹም ላይ ሆኜ እመለከታቸዋለሁ። በዚያ እንደ አንድ ሕዝብ ብቻቸውን ሰፍረዋል፤ከሌሎች ብሔራት እንደ አንዱ አድርገው ራሳቸውን አይቆጥሩም። 10  ከብዛቱ የተነሳ እንደ አፈር የሆነውን ያዕቆብን ማን ሊቆጥረው ይችላል?የእስራኤልንስ ሩብ ማን ይቆጥረዋል? የቅኖች ዓይነት አሟሟት ልሙት፤መጨረሻዬም እንደ እነሱ ይሁን።” 11  ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “እንዴት እንዲህ ታደርገኛለህ? እኔ እኮ ያመጣሁህ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ነው፤ አንተ ግን ባረክሃቸው እንጂ ምንም አልፈየድክልኝም።” 12  እሱም መልሶ “እኔ መናገር ያለብኝ ይሖዋ በአፌ ላይ ያስቀመጠውን ብቻ አይደለም?” አለ። 13  ከዚያም ባላቅ እንዲህ አለው፦ “እባክህ፣ እነሱን ማየት ወደምትችልበት ሌላ ቦታ አብረን እንሂድ። እርግጥ ሁሉንም አታያቸውም፤ የምታያቸው በከፊል ብቻ ነው። እዚያ ሆነህ እርገምልኝ።” 14  እሱም በጲስጋ አናት ላይ ወደሚገኘው የጾፊም ሜዳ ወሰደው፤ በዚያም ሰባት መሠዊያዎችን ሠርቶ በእያንዳንዱ መሠዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቀረበ። 15  በለዓምም ባላቅን “እኔ ከእሱ ጋር ለመገናኘት ወደዚያ ስሄድ አንተ እዚሁ የሚቃጠለው መባህ አጠገብ ቆይ” አለው። 16  ይሖዋም ከበለዓም ጋር ተገናኘ፤ በአፉም ላይ ይህን ቃል አስቀመጠ፦ “ወደ ባላቅ ተመለስና እንዲህ ብለህ ንገረው።” 17  በመሆኑም በለዓም ወደ ባላቅ ተመለሰ፤ ባላቅንም በሚቃጠለው መባው አጠገብ ሲጠብቀው አገኘው፤ የሞዓብ መኳንንትም ከእሱ ጋር ነበሩ። ከዚያም ባላቅ “ለመሆኑ ይሖዋ ምን አለ?” ሲል ጠየቀው። 18  በለዓምም ይህን ምሳሌያዊ አባባል ተናገረ፦ “ባላቅ ተነስ፤ አዳምጥ። የሴፎር ልጅ ሆይ፣ ጆሮህን ስጠኝ። 19  አምላክ እንደ ሰው አይዋሽም፤እንደ ሰው ልጅም ሐሳቡን አይለውጥም። እሱ ያለውን አያደርገውም? የተናገረውንስ አይፈጽመውም? 20  እንግዲህ የእኔ ተልእኮ መባረክ ነው፤እሱ እንደሆነ ባርኳል፤ እኔ ደግሞ ልለውጠው አልችልም። 21  ያዕቆብን ለማጥቃት የታሰበን ማንኛውንም አስማታዊ ኃይል ዝም ብሎ አያልፍም፤በእስራኤል ላይ ምንም ዓይነት ችግር እንዲደርስ አይፈቅድም። አምላኩ ይሖዋ ከእነሱ ጋር ነው፤በመካከላቸውም እንደ ንጉሥ ከፍ ባለ ድምፅ ይወደሳል። 22  አምላክ ከግብፅ አውጥቷቸዋል። እሱም ለእነሱ ልክ እንደ ጎሽ ቀንዶች ነው። 23  በያዕቆብ ላይ የሚሠራ ምንም ዓይነት ድግምት የለምና፤በእስራኤልም ላይ የሚሠራ ምንም ዓይነት ሟርት የለም። በዚህ ጊዜ ስለ ያዕቆብና ስለ እስራኤል ‘አምላክ ያደረገውን ተመልከቱ!’ ይባላል። 24  ልክ እንደ አንበሳ የሚነሳው ሕዝብ ይህ ነው፤እሱም እንደ አንበሳ ተነስቶ ይቆማል። ያደነውን እስኪበላ፣የተገደሉትንም ደማቸውን እስኪጠጣ ድረስ አይተኛም።” 25  ከዚያም ባላቅ በለዓምን “እንግዲያው ልትረግመው ካልቻልክ ልትባርከውም አይገባም” አለው። 26  በለዓምም መልሶ ባላቅን “‘እኔ የማደርገው ይሖዋ የሚናገረውን ብቻ ነው’ ብዬህ አልነበረም?” አለው። 27  ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “እባክህ ና፤ እስቲ አሁንም ወደ ሌላ ቦታ ልውሰድህ። ምናልባትም እውነተኛው አምላክ እዚያ ሆነህ እሱን እንድትረግምልኝ ይፈቅድ ይሆናል።” 28  ስለዚህ ባላቅ በለዓምን፣ የሺሞንን ፊት ለፊት ማየት ወደሚቻልበት ወደ ፌጎር አናት ወሰደው። 29  ከዚያም በለዓም ባላቅን “እዚህ ቦታ ላይ ሰባት መሠዊያዎች ሥራልኝ፤ እንዲሁም ሰባት በሬዎችና ሰባት አውራ በጎች አዘጋጅልኝ” አለው። 30  ባላቅም በለዓም እንዳለው አደረገ፤ ከዚያም በእያንዳንዱ መሠዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቀረበ።
[]
[]
[]
[]
12,417
24  በለዓምም ይሖዋ እስራኤልን መባረክ እንደወደደ ሲያይ ዳግመኛ ድግምት ፍለጋ አልሄደም፤ ከዚህ ይልቅ ፊቱን ወደ ምድረ በዳ አቀና። 2  በለዓም አሻግሮ ሲመለከት እስራኤል በየነገዱ እንደሰፈረ አየ፤ ከዚያም የአምላክ መንፈስ በእሱ ላይ ወረደ። 3  በመሆኑም ይህን ምሳሌያዊ አባባል ተናገረ፦ “የቢዖር ልጅ የበለዓም ቃል፣ዓይኑ የተከፈተው የዚያ ሰው ቃል፣ 4  የአምላክን ቃል የሰማው፣ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ራእይ ያየውዓይኖቹ ሳይከደኑ የሰገደው ሰው ቃል ይህ ነው፦ 5  ያዕቆብ ሆይ፣ ድንኳኖችህ፣እስራኤል ሆይ፣ የማደሪያ ድንኳኖችህ እንዴት ያማሩ ናቸው! 6  እንደ ሸለቆዎች፣በወንዝም ዳር እንዳሉ የአትክልት ስፍራዎች በረጅሙ ተዘርግተዋል።ይሖዋ እንደተከላቸው እሬቶች፣በውኃም ዳር እንዳሉ አርዘ ሊባኖሶች ሆነዋል። 7  ከሁለቱም አቁማዳዎቹ ውኃ ይንጠባጠባል፤ዘሩም በብዙ ውኃዎች አጠገብ ተዘርቷል። ንጉሡም ከአጋግ የላቀ ይሆናል፤መንግሥቱም ከፍ ከፍ ይላል። 8  አምላክ ከግብፅ አወጣው፤ለእነሱ ልክ እንደ ጎሽ ቀንዶች ነው። የሚጨቁኑትን ብሔራት ይበላል፤አጥንቶቻቸውንም ይቆረጣጥማል፤ በፍላጻዎቹም ያደቃቸዋል። 9  አድብቷል፤ እንደ አንበሳም ተጋድሟል፤እንደ አንበሳስ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል? አንተን የሚባርኩህ የተባረኩ ናቸው፤የሚረግሙህም የተረገሙ ናቸው።” 10  በዚህ ጊዜ ባላቅ በበለዓም ላይ በጣም ተቆጣ። ባላቅም በንቀት እጆቹን አጨብጭቦ በለዓምን እንዲህ አለው፦ “የጠራሁህ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ነበር፤ አንተ ግን ይኸው ሦስቱንም ጊዜ ባረክሃቸው እንጂ ምንም የፈየድከው ነገር የለም። 11  በል አሁን ቶሎ ብለህ ወደ ቤትህ ሂድ። እኔ እንኳ ታላቅ ክብር ላጎናጽፍህ አስቤ ነበር፤ ይሖዋ ግን ክብር ነፈገህ።” 12  በለዓምም ለባላቅ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ወደ እኔ ለላክሃቸው መልእክተኞች እንዲህ ብዬ ነገሬአቸው አልነበረም? 13  ‘ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላውን ቤቱን ቢሰጠኝ እንኳ ከይሖዋ ትእዛዝ ውጭ በገዛ ፈቃዴ መልካምም ሆነ መጥፎ ነገር ማድረግ አልችልም። እኔ የምናገረው ይሖዋ የሚነግረኝን ብቻ ነው።’ 14  እንግዲህ አሁን ወደ ሕዝቤ ልሄድ ነው። ይልቅስ መጥተህ ወደፊት ይህ ሕዝብ በሕዝብህ ላይ የሚያደርገውን ልንገርህ።” 15  ስለዚህ ይህን ምሳሌያዊ አባባል ተናገረ፦ “የቢዖር ልጅ የበለዓም ቃል፣ዓይኑ የተከፈተው የዚያ ሰው ቃል፣ 16  የአምላክን ቃል የሰማው፣የልዑሉን አምላክ እውቀት የሚያውቀው ሰው ቃል ይህ ነው፤ዓይኖቹ ሳይከደኑ እየሰገደ ሳለሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ራእይ አየ፦ 17  አየዋለሁ፣ አሁን ግን አይደለም፤እመለከተዋለሁ፣ በቅርቡ ግን አይደለም። ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል፤በትረ መንግሥትም ከእስራኤል ይነሳል። የሞዓብን ግንባር፣የሁከት ልጆችንም ሁሉ ራስ ቅል ይፈረካክሳል። 18  እስራኤል ጀግንነቱን ሲያሳይኤዶም ርስቱ ይሆናል፤ሴይርም የጠላቶቹ ርስት ይሆናል። 19  ከያዕቆብም አንዱ ድል እያደረገ ይወጣል፤የተረፉትንም የከተማዋን ነዋሪዎች ሁሉ ያጠፋል።” 20  አማሌቅንም ባየ ጊዜ እንዲህ ሲል ምሳሌያዊ አባባሉን መናገሩን ቀጠለ፦ “አማሌቅ ከብሔራት መካከል የመጀመሪያ ነበር፤ሆኖም በመጨረሻ ይጠፋል።” 21  ቄናውያንንም ባየ ጊዜ እንዲህ ሲል ምሳሌያዊ አባባሉን መናገሩን ቀጠለ፦ “መኖሪያህ አስተማማኝ ነው፤ ጎጆህም በቋጥኝ ላይ የተሠራ ነው። 22  ሆኖም አንድ ሰው ቄይንን ያቃጥላታል። አሦር ማርኮ እስኪወስዳችሁ ድረስ ምን ያህል ትቆዩ ይሆን?” 23  እሱም እንዲህ ሲል ምሳሌያዊ አባባሉን መናገሩን ቀጠለ፦ “አቤት! አምላክ ይህን በሚያደርግበት ጊዜ ማን ይተርፍ ይሆን? 24  ከኪቲም የባሕር ዳርቻ መርከቦች ይመጣሉ፤አሦርንም ያጠቃሉ፤ደግሞም ኤቤርን ያሠቃያሉ። ሆኖም እሱም ፈጽሞ ይጠፋል።” 25  ከዚያም በለዓም ተነስቶ ወደ ስፍራው ተመለሰ። ባላቅም መንገዱን ቀጠለ።
[]
[]
[]
[]
12,418
25  እስራኤላውያን በሺቲም ይኖሩ በነበረበት ጊዜ ሕዝቡ ከሞዓብ ሴቶች ጋር የፆታ ብልግና መፈጸም ጀመረ። 2  ሴቶቹም ለአማልክታቸው ወደተሠዉት መሥዋዕቶች ሕዝቡን ጠሩ፤ ሕዝቡም ከመሥዋዕቱ መብላት እንዲሁም ለእነሱ አማልክት መስገድ ጀመረ። 3  ስለዚህ እስራኤል የፌጎርን ባአል በማምለክ ተባበረ፤ ይሖዋም በእስራኤል ላይ እጅግ ተቆጣ። 4  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እየነደደ ያለው የይሖዋ ቁጣ ከእስራኤል ላይ እንዲመለስ የዚህን ሕዝብ መሪዎች ሁሉ ወስደህ በጠራራ ፀሐይ በይሖዋ ፊት ስቀላቸው።” 5  ከዚያም ሙሴ የእስራኤልን ዳኞች “እያንዳንዳችሁ በፌጎር ባአል አምልኮ የተባበረውን የየራሳችሁን ሰው ግደሉ” አላቸው። 6  ሆኖም ልክ በዚህ ጊዜ አንድ እስራኤላዊ፣ ሙሴና በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ እያለቀሰ ያለው የእስራኤል ማኅበረሰብ በሙሉ እያዩት አንዲት ምድያማዊት ሴት ይዞ ወደ ወንድሞቹ መጣ። 7  የካህኑ የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስ ይህን ሲመለከት ከማኅበረሰቡ መሃል ወዲያው ብድግ ብሎ ጦር አነሳ። 8  ከዚያም እስራኤላዊውን ተከትሎ ወደ ድንኳኑ በመግባት ሁለቱንም ወጋቸው፤ እስራኤላዊውን ወጋው፤ እሷንም ሆዷ ላይ ወጋት። በዚህ ጊዜ መቅሰፍቱ ከእስራኤል ልጆች ላይ ተወገደ። 9  በመቅሰፍቱ የሞቱት ሰዎች 24,000 ነበሩ። 10  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 11  “የካህኑ የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስ በመካከላቸው እኔን የሚቀናቀነኝን ማንኛውንም ነገር በቸልታ ባለማለፉ ቁጣዬ ከእስራኤል ሕዝብ ላይ እንዲመለስ አድርጓል። ስለዚህ እስራኤላውያንን እኔን ብቻ ለምን አላመለካችሁም ብዬ ጠራርጌ አላጠፋኋቸውም። 12  በዚህም የተነሳ ከእሱ ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እንደምገባ ንገረው። 13  ይህም አምላኩን የሚቀናቀነውን ማንኛውንም ነገር በቸልታ ባለማለፉ እንዲሁም ለእስራኤል ሕዝብ በማስተሰረዩ ለእሱና ከእሱ በኋላ ለሚመጡት ዘሮቹ ዘላቂ የክህነት ቃል ኪዳን ሆኖ ያገለግላል።” 14  ከምድያማዊቷ ሴት ጋር የተገደለው ሟቹ እስራኤላዊ የስምዖናውያን አባቶች ቤት አለቃ የሆነው የሳሉ ልጅ ዚምሪ ነበር። 15  የተገደለችውም ምድያማዊት ሴት የጹር ልጅ ኮዝቢ ነበረች፤ ጹር በምድያም ካሉት የአባቶች ቤት ጎሳዎች የአንዱ መሪ ነበር። 16  በኋላም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 17  “ምድያማውያንን አንገላቷቸው፤ እንዲሁም ፍጇቸው፤ 18  ምክንያቱም እነሱ ከፌጎርና ከእህታቸው ከኮዝቢ ጋር በተያያዘ በፈጸሙባችሁ ተንኮል የተነሳ አንገላተዋችኋል፤ ኮዝቢ ከፌጎር ጋር በተያያዘ የተከሰተው መቅሰፍት በመጣበት ዕለት የተገደለች የምድያማዊው አለቃ ልጅ ነች።”
[]
[]
[]
[]
12,419
26  ከመቅሰፍቱ በኋላ ይሖዋ ሙሴንና የካህኑን የአሮንን ልጅ አልዓዛርን እንዲህ አላቸው፦ 2  “ከመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ መካከል ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን በየአባቶቻቸው ቤት ቁጠሩ፤ በእስራኤል የጦር ሠራዊት ውስጥ ገብተው ማገልገል የሚችሉትን ሁሉ ቁጠሩ።” 3  በመሆኑም ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ በሚገኘው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ ላይ ለሕዝቡ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፦ 4  “ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን ቁጠሩ።” ከግብፅ ምድር የወጡት የእስራኤል ልጆች የሚከተሉት ነበሩ፦ 5  የእስራኤል የበኩር ልጅ ሮቤል፤ የሮቤል ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ ከሃኖክ የሃኖካውያን ቤተሰብ፣ ከፓሉ የፓላውያን ቤተሰብ፣ 6  ከኤስሮን የኤስሮናውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከካርሚ የካርማውያን ቤተሰብ። 7  የሮቤላውያን ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 43,730 ነበሩ። 8  የፓሉ ልጅ ኤልያብ ነበር። 9  የኤልያብ ልጆች ደግሞ ነሙኤል፣ ዳታን እና አቤሮን ነበሩ። እዚህ ላይ የተጠቀሱት ዳታን እና አቤሮን ቆሬና ግብረ አበሮቹ በይሖዋ ላይ ባመፁበት ወቅት ከእነሱ ጋር በማበር በሙሴና በአሮን ላይ የተነሱ የማኅበረሰቡ ተወካዮች ነበሩ። 10  ከዚያም ምድር አፏን ከፍታ ዋጠቻቸው። ቆሬም እሳት ወርዶ 250 ሰዎችን በበላ ጊዜ ከነግብረ አበሮቹ ሞተ። እነሱም የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ሆኑ። 11  ይሁንና የቆሬ ልጆች አልሞቱም። 12  የስምዖን ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከነሙኤል የነሙኤላውያን ቤተሰብ፣ ከያሚን የያሚናውያን ቤተሰብ፣ ከያኪን የያኪናውያን ቤተሰብ፣ 13  ከዛራ የዛራውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከሻኡል የሻኡላውያን ቤተሰብ። 14  የስምዖናውያን ቤተሰቦች እነዚህ ሲሆኑ እነሱም 22,200 ነበሩ። 15  የጋድ ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከጸፎን የጸፎናውያን ቤተሰብ፣ ከሃጊ የሃጋውያን ቤተሰብ፣ ከሹኒ የሹናውያን ቤተሰብ፣ 16  ከኦዝኒ የኦዝናውያን ቤተሰብ፣ ከኤሪ የኤራውያን ቤተሰብ፣ 17  ከአሮድ የአሮዳውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከአርዔላይ የአርዔላውያን ቤተሰብ። 18  የጋድ ልጆች ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 40,500 ነበሩ። 19  የይሁዳ ልጆች ኤር እና ኦናን ነበሩ። ሆኖም ኤር እና ኦናን በከነአን ምድር ሞቱ። 20  የይሁዳ ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከሴሎም የሴሎማውያን ቤተሰብ፣ ከፋሬስ የፋሬሳውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከዛራ የዛራውያን ቤተሰብ። 21  የፋሬስ ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ ከኤስሮን የኤስሮናውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከሃሙል የሃሙላውያን ቤተሰብ። 22  የይሁዳ ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 76,500 ነበሩ። 23  የይሳኮር ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከቶላ የቶላውያን ቤተሰብ፣ ከፑዋ የፑዋውያን ቤተሰብ፣ 24  ከያሹብ የያሹባውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከሺምሮን የሺምሮናውያን ቤተሰብ። 25  የይሳኮር ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 64,300 ነበሩ። 26  የዛብሎን ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከሰሬድ የሰሬዳውያን ቤተሰብ፣ ከኤሎን የኤሎናውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከያህልኤል የያህልኤላውያን ቤተሰብ። 27  የዛብሎናውያን ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 60,500 ነበሩ። 28  የዮሴፍ ልጆች በየቤተሰባቸው ምናሴና ኤፍሬም ነበሩ። 29  የምናሴ ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ ከማኪር የማኪራውያን ቤተሰብ፤ ማኪር ጊልያድን ወለደ፤ ከጊልያድ የጊልያዳውያን ቤተሰብ። 30  የጊልያድ ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ ከኢዔዝር የኢዔዝራውያን ቤተሰብ፣ ከሄሌቅ የሄሌቃውያን ቤተሰብ፣ 31  ከአስሪዔል የአስሪዔላውያን ቤተሰብ፣ ከሴኬም የሴኬማውያን ቤተሰብ፣ 32  ከሸሚዳ የሸሚዳውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከሄፌር የሄፌራውያን ቤተሰብ። 33  የሄፌር ልጅ ሰለጰአድ ሴቶች ልጆች ብቻ እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ የሰለጰአድ ሴቶች ልጆች ስም ማህላ፣ ኖኅ፣ ሆግላ፣ ሚልካ እና ቲርጻ ነበር። 34  የምናሴ ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 52,700 ነበሩ። 35  የኤፍሬም ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከሹተላ የሹተላውያን ቤተሰብ፣ ከቤኬር የቤኬራውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከታሃን የታሃናውያን ቤተሰብ። 36  የሹተላ ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ ከኤራን የኤራናውያን ቤተሰብ። 37  የኤፍሬም ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 32,500 ነበሩ። የዮሴፍ ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ። 38  የቢንያም ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከቤላ የቤላውያን ቤተሰብ፣ ከአሽቤል የአሽቤላውያን ቤተሰብ፣ ከአሂራም የአሂራማውያን ቤተሰብ፣ 39  ከሼፉፋም የሼፉፋማውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከሁፋም የሁፋማውያን ቤተሰብ። 40  የቤላ ልጆች አርድ እና ንዕማን ነበሩ፤ ከአርድ የአርዳውያን ቤተሰብ፣ ከንዕማን ደግሞ የንዕማናውያን ቤተሰብ። 41  የቢንያም ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 45,600 ነበሩ። 42  የዳን ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከሹሃም የሹሃማውያን ቤተሰብ። የዳን ቤተሰቦች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ። 43  ከሹሃማውያን ቤተሰቦች በሙሉ የተመዘገቡት 64,400 ነበሩ። 44  የአሴር ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከይምናህ የይምናሃውያን ቤተሰብ፣ ከይሽዊ የይሽዋውያን ቤተሰብ፣ ከበሪአ የበሪአውያን ቤተሰብ፤ 45  ከበሪአ ልጆች፦ ከሄቤር የሄቤራውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከማልኪኤል የማልኪኤላውያን ቤተሰብ። 46  የአሴር ሴት ልጅ ስም ሴራህ ነበር። 47  የአሴር ልጆች ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 53,400 ነበሩ። 48  የንፍታሌም ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከያህጽኤል የያህጽኤላውያን ቤተሰብ፣ ከጉኒ የጉናውያን ቤተሰብ፣ 49  ከየጼር የየጼራውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከሺሌም የሺሌማውያን ቤተሰብ። 50  የንፍታሌም ቤተሰቦች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 45,400 ነበሩ። 51  ከእስራኤላውያን መካከል የተመዘገቡት በጠቅላላ 601,730 ነበሩ። 52  ከዚህ በኋላ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 53   “ምድሪቱ ለእነዚህ በስማቸው ዝርዝር መሠረት ርስት ሆና ትከፋፈል። 54  ተለቅ ላሉት ቡድኖች በዛ ያለ ውርሻ ትሰጣቸዋለህ፤ አነስ ላሉት ቡድኖች ደግሞ አነስ ያለ ውርሻ ትሰጣቸዋለህ። የእያንዳንዱ ቡድን ውርሻ በተመዘገቡት ሰዎች ብዛት ተመጣጥኖ መሰጠት አለበት። 55  ይሁን እንጂ ምድሪቱ መከፋፈል ያለባት በዕጣ ነው። ውርሻቸውንም ማግኘት ያለባቸው በአባቶቻቸው ነገዶች ስም መሠረት ነው። 56  እያንዳንዱ ውርሻ የሚወሰነው በዕጣ ሲሆን በኋላም ውርሻው እንደ ቡድኑ ትልቅነትና ትንሽነት ይከፋፈላል።” 57   ከሌዋውያኑ መካከል በየቤተሰባቸው የተመዘገቡት እነዚህ ነበሩ፦ ከጌድሶን የጌድሶናውያን ቤተሰብ፣ ከቀአት የቀአታውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከሜራሪ የሜራራውያን ቤተሰብ። 58  የሌዋውያን ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፦ የሊብናውያን ቤተሰብ፣ የኬብሮናውያን ቤተሰብ፣ የማህላውያን ቤተሰብ፣ የሙሻውያን ቤተሰብ እና የቆሬያውያን ቤተሰብ። ቀአት አምራምን ወለደ። 59  የአምራም ሚስት ስሟ ዮካቤድ ነበር፤ እሷም የሌዊ ሚስት በግብፅ ለሌዊ የወለደችለት ናት። ዮካቤድም ለአምራም አሮንን፣ ሙሴንና እህታቸውን ሚርያምን ወለደችለት። 60  አሮንም ናዳብን፣ አቢሁን፣ አልዓዛርን እና ኢታምርን ወለደ። 61  ሆኖም ናዳብና አቢሁ በይሖዋ ፊት ያልተፈቀደ እሳት በማቅረባቸው ሞቱ። 62  አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሆኗቸው የተመዘገቡት ወንዶች በአጠቃላይ 23,000 ነበሩ። እነዚህ በእስራኤላውያን መካከል ርስት ስለማይሰጣቸው ከእስራኤላውያን ጋር አልተመዘገቡም። 63  እነዚህም ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ በሚገኘው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ ላይ እስራኤላውያንን በመዘገቡበት ወቅት የመዘገቧቸው ናቸው። 64  ሆኖም ከእነዚህ መካከል ሙሴና ካህኑ አሮን እስራኤላውያንን በሲና ምድረ በዳ በቆጠሩበት ወቅት ተመዝግቦ የነበረ አንድም ሰው አልነበረም። 65  ምክንያቱም ይሖዋ እነሱን በተመለከተ “በእርግጥ በምድረ በዳው ላይ ያልቃሉ” በማለት ተናግሮ ነበር። በመሆኑም ከየፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር አንድም የተረፈ ሰው አልነበረም።
[]
[]
[]
[]
12,420
27  ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ቤተሰቦች የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የጊልያድ ልጅ፣ የሄፌር ልጅ የሆነው የሰለጰአድ ሴቶች ልጆች ቀረቡ። የሴት ልጆቹም ስም ማህላ፣ ኖኅ፣ ሆግላ፣ ሚልካ እና ቲርጻ ነበር። 2  እነሱም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በሙሴ፣ በካህኑ በአልዓዛር፣ በአለቆቹ እንዲሁም በመላው ማኅበረሰብ ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፦ 3  “አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ ይሁንና እሱ በይሖዋ ላይ ለማመፅ ከተባበሩት ከቆሬ ግብረ አበሮች አንዱ አልነበረም፤ እሱ የሞተው በራሱ ኃጢአት ነው፤ ወንዶች ልጆችም አልነበሩትም። 4  ታዲያ አባታችን ወንድ ልጅ ስለሌለው ብቻ ስሙ ከቤተሰቡ መካከል ለምን ይጥፋ? በአባታችን ወንድሞች መካከል ርስት ስጡን።” 5  ስለዚህ ሙሴ ጉዳያቸውን በይሖዋ ፊት አቀረበ። 6  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 7  “የሰለጰአድ ሴቶች ልጆች ትክክል ናቸው። በአባታቸው ወንድሞች መካከል ርስታቸውን ውርስ አድርገህ ልትሰጣቸው ይገባል፤ የአባታቸውም ውርስ ለእነሱ እንዲተላለፍ ማድረግ አለብህ። 8  እስራኤላውያንንም እንዲህ በላቸው፦ ‘አንድ ሰው ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት ውርሱ ለሴት ልጆቹ እንዲተላለፍ ማድረግ አለባችሁ። 9  ሴት ልጅ ከሌለው ደግሞ ውርሱን ለወንድሞቹ ትሰጣላችሁ። 10  ወንድሞች ከሌሉት ውርሱን ለአባቱ ወንድሞች ትሰጣላችሁ። 11  አባቱ ወንድሞች ከሌሉት ውርሱን ከቤተሰቡ መካከል ቅርብ ለሆነው የሥጋ ዘመዱ ትሰጣላችሁ፤ እሱም ርስት አድርጎ ይወስደዋል። ይህም ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለእስራኤላውያን የተደነገገ ደንብ ሆኖ ያገለግላል።’” 12  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደዚህ ወደ አባሪም ተራራ ውጣና ለእስራኤላውያን የምሰጠውን ምድር ተመልከት። 13  ካየኸውም በኋላ እንደ ወንድምህ እንደ አሮን አንተም ወደ ወገኖችህ ትሰበሰባለህ፤ 14  ምክንያቱም ማኅበረሰቡ በጺን ምድረ በዳ ከእኔ ጋር በተጣላ ጊዜ ከውኃዎቹ ጋር በተያያዘ በፊታቸው ሳትቀድሱኝ በመቅረታችሁ ትእዛዜን ተላልፋችኋል። እነዚህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ የሚገኙት የመሪባ ውኃዎች ናቸው። 15  ከዚያም ሙሴ ይሖዋን እንዲህ አለው፦ 16  “የሰው ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆነው ይሖዋ በማኅበረሰቡ ላይ አንድ ሰው ይሹም፤ 17  እሱም የይሖዋ ማኅበረሰብ እረኛ እንደሌላቸው በጎች እንዳይሆን በፊታቸው የሚወጣና የሚገባ እንዲሁም እነሱን መርቶ የሚያወጣና የሚያስገባ ይሆናል።” 18  በመሆኑም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “መንፈስ ያለበትን የነዌን ልጅ ኢያሱን ወስደህ እጅህን ጫንበት። 19  ከዚያም በካህኑ በአልዓዛርና በመላው ማኅበረሰብ ፊት አቁመው፤ በፊታቸውም ሹመው። 20  መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ እንዲሰማውም ከሥልጣንህ የተወሰነውን ስጠው። 21  እሱም በኡሪም አማካኝነት የይሖዋን ፍርድ በሚጠይቅለት በካህኑ በአልዓዛር ፊት ይቆማል። እሱም ሆነ ከእሱ ጋር ያሉት እስራኤላውያን እንዲሁም መላው ማኅበረሰብ በእሱ ትእዛዝ ይወጣሉ፤ በእሱ ትእዛዝ ይገባሉ።” 22  በመሆኑም ሙሴ ልክ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ። ኢያሱንም ወስዶ በካህኑ በአልዓዛርና በመላው ማኅበረሰብ ፊት አቆመው፤ 23  ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት በተናገረውም መሠረት እጆቹን በእሱ ላይ በመጫን ሾመው።
[]
[]
[]
[]
12,421
28  በመቀጠልም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “እስራኤላውያንን እዘዛቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ምግቤን ይኸውም መባዬን ለእኔ ማቅረባችሁን እንዳትዘነጉ። ደስ የሚያሰኝ መዓዛ እንዲሰጡ በእሳት የሚቀርቡት መባዎቼ በተወሰነላቸው ጊዜ መቅረብ አለባቸው።’ 3  “እንዲህም በላቸው፦ ‘ለይሖዋ የምታቀርቡት በእሳት የሚቃጠል መባ ይህ ነው፦ በየቀኑ፣ አንድ ዓመት የሆናቸው እንከን የሌለባቸው ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶችን የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ዘወትር አቅርቡ። 4  አንደኛውን ተባዕት የበግ ጠቦት ጠዋት ላይ፣ ሌላኛውን ተባዕት የበግ ጠቦት ደግሞ አመሻሹ ላይ አቅርቡ፤ 5  ከእነዚህም ጋር ተጨቅጭቆ በተጠለለ አንድ አራተኛ ሂን ዘይት የተለወሰ አንድ አሥረኛ ኢፍ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። 6  ይህም በሲና ተራራ ላይ በወጣው ደንብ መሠረት ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው ዘወትር የሚቀርብ የሚቃጠል መባ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነው፤ 7  ከዚህም ጋር የመጠጥ መባውን ይኸውም ለእያንዳንዱ ተባዕት የበግ ጠቦት አንድ አራተኛ ሂን አቅርቡ። የሚያሰክረውን መጠጥ ለይሖዋ እንደሚቀርብ የመጠጥ መባ አድርጋችሁ በቅዱሱ ስፍራ አፍሱት። 8  ሌላኛውን ተባዕት የበግ ጠቦት ደግሞ አመሻሹ ላይ አቅርቡት። ከእሱም ጋር ማለዳ ላይ የሚቀርበውን ዓይነት የእህል መባና ከእሱ ጋር አብሮ የሚቀርበውን ዓይነት የመጠጥ መባ ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ። 9  “‘ይሁንና በሰንበት ቀን፣ አንድ ዓመት የሆናቸውን እንከን የሌለባቸው ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶች እንዲሁም በዘይት የተለወሰ ሁለት አሥረኛ የኢፍ መስፈሪያ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ ከመጠጥ መባው ጋር ታቀርባላችሁ። 10  ይህ ዘወትር ከሚቀርበው የሚቃጠል መባና ከመጠጥ መባው ጋር በየሰንበቱ የሚቀርብ የሚቃጠል መባ ነው። 11  “‘በየወሩም መባቻ ላይ ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው እንከን የሌለባቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለይሖዋ የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ 12  ለእያንዳንዱ ወይፈን ሦስት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ ለአውራው በግ ደግሞ ሁለት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ 13  ለእያንዳንዱም ተባዕት የበግ ጠቦት አንድ አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ ይኸውም ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ። 14  በተጨማሪም ከእነዚህ ጋር ለአንድ ወይፈን ግማሽ ሂን፣ ለአውራው በግ አንድ ሦስተኛ ሂን እንዲሁም ለአንድ ተባዕት የበግ ጠቦት አንድ አራተኛ ሂን የወይን ጠጅ የመጠጥ መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። ይህም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚቀርብ ወርሃዊ የሚቃጠል መባ ነው። 15  እንዲሁም ከዘወትሩ የሚቃጠል መባና አብሮት ከሚቀርበው የመጠጥ መባ በተጨማሪ አንድ የፍየል ጠቦት የኃጢአት መባ ሆኖ ለይሖዋ መቅረብ አለበት። 16  “‘በመጀመሪያው ወር ከወሩም በ14ኛው ቀን የይሖዋ ፋሲካ ይከበራል። 17  በዚሁ ወር በ15ኛው ቀን በዓል ይሆናል። ለሰባት ቀን ቂጣ ይበላል። 18  በመጀመሪያው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ይሆናል። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም። 19  ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ። እንከን የሌለባቸውን እንስሳት ማቅረብ አለባችሁ። 20  ከእነዚህም ጋር ለአንድ ወይፈን ሦስት አሥረኛ መስፈሪያ፣ ለአውራው በግ ደግሞ ሁለት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። 21  ለሰባቱ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው አንድ አሥረኛ መስፈሪያ ታቀርባላችሁ፤ 22  እንዲሁም ለእናንተ ማስተሰረያ እንዲሆን አንድ ፍየል የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። 23  ለዘወትሩ የሚቃጠል መባ እንዲሆን ጠዋት ላይ ከሚቀርበው የሚቃጠል መባ በተጨማሪ እነዚህን ታቀርባላችሁ። 24  እነዚህንም በተመሳሳይ መንገድ በየቀኑ ለሰባት ቀን እንደ ምግብ፣ ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ እንዳለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ። ይህም ከዘወትሩ የሚቃጠል መባና ከመጠጥ መባው ጋር ይቅረብ። 25  በሰባተኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም። 26  “‘መጀመሪያ የሚደርሰው ፍሬ በሚሰበሰብበት ቀን ለይሖዋ አዲስ የእህል መባ ስታቀርቡ በሳምንታት በዓላችሁ ላይ ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም። 27  ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ 28  ከእነዚህም ጋር ለእያንዳንዱ ወይፈን ሦስት አሥረኛ መስፈሪያ፣ ለአውራው በግ ደግሞ ሁለት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ 29  እንዲሁም ለሰባቱ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው አንድ አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት ታቀርባላችሁ፤ 30  በተጨማሪም ለእናንተ ማስተሰረያ እንዲሆን አንድ የፍየል ጠቦት ታቀርባላችሁ። 31  ከዘወትሩ የሚቃጠል መባና ከእህል መባው በተጨማሪ እነዚህን ታቀርባላችሁ። እንስሳቱም እንከን የሌለባቸው መሆን አለባቸው፤ ከመጠጥ መባቸውም ጋር መቅረብ ይኖርባቸዋል።
[]
[]
[]
[]
12,422
29  “‘በሰባተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም። ይህም መለከት የምትነፉበት ቀን ነው። 2  እናንተም አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤ 3  ከእነዚህም ጋር ለወይፈኑ ሦስት አሥረኛ የኢፍ መስፈሪያ፣ ለአውራው በግ ደግሞ ሁለት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ 4  ለሰባቱ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው አንድ አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት ታቀርባላችሁ፤ 5  እንዲሁም ለእናንተ ማስተሰረያ እንዲሆን አንድ ተባዕት የፍየል ጠቦት የኃጢአት መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ። 6  ይህም በተለመደው አሠራር መሠረት ከሚቀርቡት ከወርሃዊው የሚቃጠል መባና አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባ፣ ከዘወትሩ የሚቃጠል መባና አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባ እንዲሁም ከመጠጥ መባዎቻቸው በተጨማሪ ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነው። 7  “‘በዚሁ በሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ፤ ራሳችሁን አጎሳቁሉ። ምንም ዓይነት ሥራ አትሥሩ። 8  አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው ለይሖዋ የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል። 9  ከእነዚህም ጋር ለወይፈኑ ሦስት አሥረኛ መስፈሪያ፣ ለአውራው በግ ደግሞ ሁለት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ 10  እንዲሁም ለሰባቱ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው አንድ አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት ታቀርባላችሁ፤ 11  ለማስተሰረያ ከሚሆነው የኃጢአት መባ፣ ከዘወትሩ የሚቃጠል መባና አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባ እንዲሁም ከመጠጥ መባዎቻቸው በተጨማሪ አንድ የፍየል ጠቦት የኃጢአት መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ። 12  “‘በሰባተኛው ወር በ15ኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ አትሥሩ፤ ለሰባት ቀንም ለይሖዋ በዓል አክብሩ። 13  እንዲሁም 13 ወይፈኖች፣ 2 አውራ በጎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 14 ተባዕት የበግ ጠቦቶች የሚቃጠል መባ ይኸውም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጋችሁ አቅርቡ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል። 14  ከእነዚህም ጋር ለ13ቱ ወይፈኖች ለእያንዳንዳቸው ሦስት አሥረኛ መስፈሪያ፣ ለ2ቱ አውራ በጎች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው ሁለት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ አቅርቡ፤ 15  እንዲሁም ለ14ቱ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው አንድ አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት አቅርቡ፤ 16  ከዘወትሩ የሚቃጠል መባ እንዲሁም አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባና የመጠጥ መባ በተጨማሪ አንድ የፍየል ጠቦት የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። 17  “‘በሁለተኛው ቀን 12 ወይፈኖች፣ 2 አውራ በጎች እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 14 ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤ 18  ለወይፈኖቹ፣ ለአውራ በጎቹና ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ በተለመደው አሠራር መሠረት በቁጥራቸው ልክ የእህል መባቸውንና የመጠጥ መባዎቻቸውን አቅርቡ፤ 19  ከዘወትሩ የሚቃጠል መባና አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባ እንዲሁም ከመጠጥ መባዎቻቸው በተጨማሪ አንድ የፍየል ጠቦት የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። 20  “‘በሦስተኛው ቀን 11 ወይፈኖች፣ 2 አውራ በጎች እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 14 ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤ 21  ለወይፈኖቹ፣ ለአውራ በጎቹና ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ በተለመደው አሠራር መሠረት በቁጥራቸው ልክ የእህል መባቸውንና የመጠጥ መባዎቻቸውን አቅርቡ፤ 22  ከዘወትሩ የሚቃጠል መባ እንዲሁም አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባና የመጠጥ መባ በተጨማሪ አንድ ፍየል የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። 23  “‘በአራተኛው ቀን 10 ወይፈኖች፣ 2 አውራ በጎች እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 14 ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤ 24  ለወይፈኖቹ፣ ለአውራ በጎቹና ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ በተለመደው አሠራር መሠረት በቁጥራቸው ልክ የእህል መባቸውንና የመጠጥ መባዎቻቸውን አቅርቡ፤ 25  ከዘወትሩ የሚቃጠል መባ እንዲሁም አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባና የመጠጥ መባ በተጨማሪ አንድ የፍየል ጠቦት የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። 26  “‘በአምስተኛው ቀን 9 ወይፈኖች፣ 2 አውራ በጎች እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 14 ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤ 27  ለወይፈኖቹ፣ ለአውራ በጎቹና ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ በተለመደው አሠራር መሠረት በቁጥራቸው ልክ የእህል መባቸውንና የመጠጥ መባዎቻቸውን አቅርቡ፤ 28  ከዘወትሩ የሚቃጠል መባ እንዲሁም አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባና የመጠጥ መባ በተጨማሪ አንድ ፍየል የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። 29  “‘በስድስተኛውም ቀን 8 ወይፈኖች፣ 2 አውራ በጎች እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 14 ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤ 30  ለወይፈኖቹ፣ ለአውራ በጎቹና ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ በተለመደው አሠራር መሠረት በቁጥራቸው ልክ የእህል መባቸውንና የመጠጥ መባዎቻቸውን አቅርቡ፤ 31  ከዘወትሩ የሚቃጠል መባ እንዲሁም አብረውት ከሚቀርቡት የእህል መባና የመጠጥ መባዎች በተጨማሪ አንድ ፍየል የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። 32  “‘በሰባተኛው ቀን 7 ወይፈኖች፣ 2 አውራ በጎች እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 14 ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤ 33  ለወይፈኖቹ፣ ለአውራ በጎቹና ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ በተለመደው አሠራር መሠረት በቁጥራቸው ልክ የእህል መባቸውንና የመጠጥ መባዎቻቸውን አቅርቡ፤ 34  ከዘወትሩ የሚቃጠል መባ እንዲሁም አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባና የመጠጥ መባ በተጨማሪ አንድ ፍየል የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። 35  “‘በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም። 36  አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች የሚቃጠል መባ ይኸውም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤ 37  ለወይፈኑ፣ ለአውራው በግና ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ በተለመደው አሠራር መሠረት በቁጥራቸው ልክ የእህል መባቸውንና የመጠጥ መባዎቻቸውን አቅርቡ፤ 38  ከዘወትሩ የሚቃጠል መባ እንዲሁም አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባና የመጠጥ መባ በተጨማሪ አንድ ፍየል የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። 39  “‘እነዚህም የሚቃጠሉ መባዎች፣ የእህል መባዎች፣ የመጠጥ መባዎችና የኅብረት መሥዋዕቶች አድርጋችሁ ከምታቀርቧቸው የስእለት መባዎችና የፈቃደኝነት መባዎች በተጨማሪ በየወቅቱ በምታከብሯቸው በዓላት ላይ ለይሖዋ የምታቀርቧቸው ናቸው።’” 40  ሙሴም ይሖዋ ያዘዘውን ነገር በሙሉ ለእስራኤላውያን ነገራቸው።
[]
[]
[]
[]
12,423
3  ይሖዋ በሲና ተራራ ላይ ከሙሴ ጋር በተነጋገረ ጊዜ የአሮንና የሙሴ የቤተሰብ ሐረግ ይህ ነበር። 2  የአሮን ወንዶች ልጆች ስም ይህ ነው፦ የበኩር ልጁ ናዳብ፣ አቢሁ፣ አልዓዛርና ኢታምር። 3  የአሮን ወንዶች ልጆች ስም ይኸውም ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉ የተሾሙት ቅቡዕ የሆኑት ካህናት ስም ይህ ነበር። 4  ይሁንና ናዳብና አቢሁ በሲና ምድረ በዳ በይሖዋ ፊት ያልተፈቀደ እሳት ባቀረቡ ጊዜ በይሖዋ ፊት ሞቱ፤ እነሱም ወንዶች ልጆች አልነበሯቸውም። አልዓዛርና ኢታምር ግን ከአባታቸው ከአሮን ጋር በክህነት ማገልገላቸውን ቀጠሉ። 5  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 6  “የሌዊን ነገድ አምጥተህ በካህኑ በአሮን ፊት አቁመው፤ እነሱም ያገልግሉት። 7  ከመገናኛ ድንኳኑ ጋር በተያያዘ የሚያከናውኑትን አገልግሎት በመፈጸም ለእሱም ሆነ ለመላው ማኅበረሰብ ያለባቸውን ኃላፊነት በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ይወጡ። 8  የመገናኛ ድንኳኑን ዕቃዎች በሙሉ በኃላፊነት መቆጣጠርና ከማደሪያ ድንኳኑ ጋር የተያያዘውን አገልግሎት በማከናወን ለእስራኤል ልጆች ያለባቸውን ኃላፊነት መወጣት ይኖርባቸዋል። 9  ሌዋውያኑን ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ ስጣቸው። እነሱ የተሰጡ ናቸው፤ ከእስራኤላውያን መካከል ለእሱ የተሰጡ ናቸው። 10  አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ሹማቸው፤ እነሱም የክህነት ኃላፊነታቸውን ይወጡ፤ ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሰው ወደ መቅደሱ ቢቀርብ ይገደል።” 11  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 12  “በእስራኤላውያን በኩሮች ሁሉ ምትክ ሌዋውያኑን ከእስራኤላውያን መካከል እወስዳለሁ፤ ሌዋውያኑም የእኔ ይሆናሉ። 13  ምክንያቱም በኩር ሁሉ የእኔ ነው። በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ በመታሁበት ቀን በእስራኤላውያን መካከል ያለውን የሰውም ሆነ የእንስሳ በኩር ለራሴ ቀድሻለሁ። እነሱ የእኔ ይሆናሉ። እኔ ይሖዋ ነኝ።” 14  በተጨማሪም ይሖዋ በሲና ምድረ በዳ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 15  “የሌዊን ወንዶች ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶችና በየቤተሰባቸው መዝግብ። አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆነውን ወንድ ሁሉ መዝግብ።” 16  በመሆኑም ሙሴ ይሖዋ በሰጠው መመሪያ መሠረት ልክ እንደታዘዘው መዘገባቸው። 17  የሌዊ ወንዶች ልጆች ስም ይህ ነው፦ ጌድሶን፣ ቀአትና ሜራሪ። 18  የጌድሶን ወንዶች ልጆች ስም በየቤተሰባቸው ይህ ነበር፦ ሊብኒ እና ሺምአይ። 19  የቀአት ወንዶች ልጆች በየቤተሰባቸው አምራም፣ ይጽሃር፣ ኬብሮንና ዑዚኤል ነበሩ። 20  የሜራሪ ወንዶች ልጆች በየቤተሰባቸው ማህሊ እና ሙሺ ነበሩ። የሌዋውያኑ ቤተሰቦች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ነበሩ። 21  የሊብናውያን ቤተሰብና የሺምአያውያን ቤተሰብ የተገኘው ከጌድሶን ነበር። የጌድሶናውያን ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ። 22  አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሆኗቸው የተመዘገቡት ወንዶች በሙሉ ብዛታቸው 7,500 ነበር። 23  የጌድሶናውያን ቤተሰቦች የሰፈሩት ከማደሪያ ድንኳኑ በስተ ኋላ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ ነበር። 24  የጌድሶናውያን የአባቶች ቤት አለቃ የላኤል ልጅ ኤሊያሳፍ ነበር። 25  የጌድሶን ልጆች በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ያለባቸው ኃላፊነት ከማደሪያ ድንኳኑ፣ ከድንኳኑ ጨርቅ፣ ከመደረቢያው፣ ከመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ መከለያ፣ 26  ከግቢው መጋረጃዎች፣ በማደሪያ ድንኳኑ ዙሪያ በሚገኘው ግቢ መግቢያ ላይ ካለው መከለያ፣ ከመሠዊያው፣ ከድንኳኑ ገመዶችና ከእነዚህ ጋር ግንኙነት ካለው አገልግሎት ሁሉ ጋር የተያያዘ ነበር። 27  የአምራማውያን ቤተሰብ፣ የይጽሃራውያን ቤተሰብ፣ የኬብሮናውያን ቤተሰብና የዑዚኤላውያን ቤተሰብ የተገኘው ከቀአት ነበር። የቀአታውያን ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ። 28  አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸው ወንዶች በሙሉ ብዛታቸው 8,600 ነበር፤ እነሱም ቅዱሱን ስፍራ የመንከባከብ ኃላፊነት ነበረባቸው። 29  የቀአት ወንዶች ልጆች ቤተሰቦች ከማደሪያ ድንኳኑ በስተ ደቡብ በኩል ሰፍረው ነበር። 30  የቀአታውያን ቤተሰቦች የአባቶች ቤት አለቃ የዑዚኤል ልጅ ኤሊጻፋን ነበር። 31  ኃላፊነታቸውም ከታቦቱ፣ ከጠረጴዛው፣ ከመቅረዙ፣ ከመሠዊያዎቹ፣ በቅዱሱ ስፍራ ለማገልገል ከሚጠቀሙባቸው ዕቃዎች፣ ከመከለያውና ከእነዚህ ጋር ግንኙነት ካለው አገልግሎት ሁሉ ጋር የተያያዘ ነበር። 32  የሌዋውያኑ ዋና አለቃ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ሲሆን እሱም ከቅዱሱ ስፍራ ጋር በተያያዘ ኃላፊነት የተጣለባቸውን በበላይነት ይከታተል ነበር። 33  የማህላውያን ቤተሰብና የሙሻውያን ቤተሰብ የተገኘው ከሜራሪ ነበር። የሜራሪ ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ። 34  አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሆኗቸው የተመዘገቡት ወንዶች በሙሉ ብዛታቸው 6,200 ነበር። 35  የሜራሪ ቤተሰቦች የአባቶች ቤት አለቃ የአቢሃይል ልጅ ጹሪኤል ነበር። እነሱም ከማደሪያ ድንኳኑ በስተ ሰሜን በኩል ሰፍረው ነበር። 36  የሜራሪ ወንዶች ልጆች የተጣለባቸው ኃላፊነት የማደሪያ ድንኳኑን ቋሚዎች፣ አግዳሚ እንጨቶቹን፣ ዓምዶቹን፣ መሰኪያዎቹን፣ ዕቃዎቹን በሙሉ፣ ከእነዚህ ጋር ግንኙነት ያለውን አገልግሎት ሁሉ 37  እንዲሁም በግቢው ዙሪያ ያሉትን ዓምዶች፣ መሰኪያዎቻቸውን፣ የድንኳን ካስማዎቻቸውንና የድንኳን ገመዶቻቸውን በበላይነት መቆጣጠር ነበር። 38  በማደሪያ ድንኳኑ ፊት ለፊት በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ፀሐይ በምትወጣበት አቅጣጫ የሰፈሩት ሙሴና አሮን እንዲሁም የአሮን ወንዶች ልጆች ነበሩ። እስራኤላውያንን ወክለው እንዲያከናውኑ የተጣለባቸው ግዴታም መቅደሱን የመንከባከብ ኃላፊነት ነበር። ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሰው ወደዚያ ቢቀርብ ይገደላል። 39  ይሖዋ በሰጠው መመሪያ መሠረት ሙሴና አሮን በየቤተሰባቸው የመዘገቧቸው አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሌዋውያን ወንዶች በሙሉ 22,000 ነበሩ። 40  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከእስራኤላውያን መካከል አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸውን በኩር የሆኑ ወንዶች በሙሉ መዝግብ፤ ከቆጠርካቸውም በኋላ ስማቸውን በዝርዝር ጻፍ። 41  ከእስራኤላውያን መካከል በኩር በሆኑት ሁሉ ምትክ ሌዋውያኑን ለይልኝ፤ የሌዋውያኑን የቤት እንስሳትም ከእስራኤላውያን የቤት እንስሳት መካከል በኩር በሆኑት ሁሉ ምትክ ለይልኝ፤ እኔ ይሖዋ ነኝ።” 42  ከዚያም ሙሴ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ከእስራኤላውያን መካከል በኩር የሆኑትን ሁሉ መዘገበ። 43  አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሆኗቸው በየስማቸው የተመዘገቡት በኩር የሆኑ ወንዶች ብዛታቸው 22,273 ነበር። 44  ይሖዋ እንዲህ በማለት ሙሴን ማነጋገሩን ቀጠለ፦ 45  “ከእስራኤላውያን መካከል በኩር በሆኑት ሁሉ ምትክ ሌዋውያኑን ለይ፤ የሌዋውያኑን የቤት እንስሳትም በቤት እንስሶቻቸው ሁሉ ምትክ ለይ፤ ሌዋውያኑ የእኔ ይሆናሉ። እኔ ይሖዋ ነኝ። 46  ቁጥራቸው ከሌዋውያኑ ቁጥር የበለጠውን 273 እስራኤላውያን በኩሮች ለመዋጀት 47  ለእያንዳንዱ ግለሰብ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት አምስት ሰቅል ውሰድ። አንድ ሰቅል 20 ጌራ ነው። 48  አንተም ገንዘቡን ቁጥራቸው ከሌዋውያኑ ቁጥር የተረፈውን ሰዎች ለመዋጀት የተከፈለ ዋጋ አድርገህ ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ ስጥ።” 49  በመሆኑም ሙሴ ቁጥራቸው ከሌዋውያኑ ቁጥር የተረፈውን ሰዎች ለመዋጀት የመዋጃውን ገንዘብ ሰበሰበ። 50  እሱም ገንዘቡን ይኸውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 1,365 ሰቅል ከእስራኤላውያኑ በኩሮች ላይ ወሰደ። 51  ከዚያም ሙሴ በይሖዋ ቃል መሠረት ልክ ይሖዋ እንዳዘዘው የመዋጃውን ገንዘብ ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ ሰጣቸው።
[]
[]
[]
[]
12,424
30  ከዚያም ሙሴ የእስራኤላውያን የነገድ መሪዎችን እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ የሰጠው ትእዛዝ ይህ ነው፦ 2  አንድ ሰው ለይሖዋ ስእለት ቢሳል ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ ራሱን ግዴታ ውስጥ ቢያስገባ ቃሉን ማጠፍ የለበትም። አደርገዋለሁ ብሎ የማለውን ነገር ሁሉ መፈጸም አለበት። 3  “በአባቷ ቤት የምትኖር አንዲት ወጣት ለይሖዋ ስእለት ብትሳል ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ ራሷን በመሐላ ግዴታ ውስጥ ብታስገባ 4  አባቷ ስእለት መሳሏን ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ ራሷን በመሐላ ግዴታ ውስጥ ማስገባቷን ሰምቶ ካልተቃወማት ስእለቶቿ በሙሉ ይጸናሉ፤ እንዲሁም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ የገባችው ማንኛውም ግዴታ ይጸናል። 5  ሆኖም አባቷ ስእለት መሳሏን ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ ራሷን በመሐላ ግዴታ ውስጥ ማስገባቷን ሲሰማ ቢከለክላት ስእለቱ አይጸናም። አባቷ ስለከለከላት ይሖዋ ይቅር ይላታል። 6  “ይሁን እንጂ ይህች ሴት ስእለት ተስላ ወይም ሳታስብበት ራሷን ግዴታ ውስጥ የሚያስገባ ቃል ተናግራ እያለ ባል ብታገባ፣ 7  ባሏም ይህን ቢሰማና በሰማበት ቀን ዝም ቢላት ስእለቶቿ ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ የገባቻቸው ግዴታዎች ይጸናሉ። 8  ሆኖም ባሏ ይህን በሰማበት ቀን ቢከለክላት የተሳለችውን ስእለት ወይም ሳታስብበት ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችበትን ቃል ያፈርሰዋል፤ ይሖዋም ይቅር ይላታል። 9  “ሆኖም አንዲት መበለት ወይም ከባሏ የተፋታች አንዲት ሴት ስእለት ብትሳል ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችባቸው ነገሮች በሙሉ ይጸኑባታል። 10  “ይሁን እንጂ አንዲት ሴት ስእለት የተሳለችው ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ ራሷን በመሐላ ግዴታ ውስጥ ያስገባችው በባሏ ቤት እያለች ከሆነና 11  ባሏም ሰምቶ ይህን ካልተቃወማት ወይም ካልከለከላት የተሳለቻቸው ስእለቶች በሙሉ ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ የገባቻቸው ግዴታዎች ሁሉ ይጸናሉ። 12  ይሁንና ባሏ የተሳለችውን ማንኛውንም ስእለት ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ የገባችውን የትኛውንም ግዴታ በሰማበት ቀን ሙሉ በሙሉ ቢያፈርስባት ስእለቶቹ አይጸኑም። ባሏ ስእለቶቿን አፍርሷቸዋል፤ ይሖዋም ይቅር ይላታል። 13  የትኛውንም ስእለት ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ የገባችውን ግዴታ አሊያም ራሷን ለማጎሳቆል የገባችውን ቃል ባሏ ሊያጸናው ወይም ሊያፈርሰው ይችላል። 14  ሆኖም ባሏ ቀናት እያለፉ ሲሄዱ ጨርሶ ካልተቃወማት ስእለቶቿን በሙሉ ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ የገባችውን ግዴታ ሁሉ አጽንቶታል ማለት ነው። ስእለት መሳሏን በሰማበት ቀን ስላልተቃወማት እንዳጸናቸው ይቆጠራል። 15  ስእለቶቹን ሰምቶ የተወሰኑ ቀናት ካለፉ በኋላ ስእለቶቹን ካፈረሰ ግን የእሷ በደል የሚያስከትላቸውን መዘዞች እሱ ይሸከማል። 16  “ከባልና ከሚስት እንዲሁም ከአባትና በቤቱ ከምትኖር ወጣት ልጁ ጋር በተያያዘ ይሖዋ ለሙሴ የሰጣቸው ደንቦች እነዚህ ናቸው።”
[]
[]
[]
[]
12,425
31  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “ለእስራኤላውያን ምድያማውያንን ተበቀልላቸው። ከዚያ በኋላ ወደ ወገኖችህ ትሰበሰባለህ።” 3  በመሆኑም ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ በምድያም ላይ የሚወስደውን የበቀል እርምጃ ለማስፈጸም ከምድያም ጋር ለሚደረገው ጦርነት ከመካከላችሁ ወንዶችን አስታጥቁ። 4  ከሁሉም የእስራኤል ነገድ ከእያንዳንዱ 1,000 ወንዶችን ወደ ጦርነቱ ላኩ።” 5  ስለዚህ በሺዎች ከሚቆጠሩት እስራኤላውያን መካከል ከአንድ ነገድ 1,000 ወንዶች ተመርጠው በአጠቃላይ 12,000 ወንዶች ለጦርነቱ ታጠቁ። 6  ከዚያም ሙሴ ከየነገዱ የተውጣጡትን አንድ አንድ ሺህ ወንዶች ወደ ጦርነቱ ላካቸው፤ ከእነሱም ጋር የሠራዊቱ ካህን የሆነውን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሃስን ላከው፤ ቅዱስ የሆኑት ዕቃዎችና በጦርነት ጊዜ የሚነፉት መለከቶች በእሱ እጅ ነበሩ። 7  እነሱም ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት በምድያም ላይ ጦርነት ከፈቱ፤ ወንዶቹንም ሁሉ ገደሉ። 8  ከተገደሉትም መካከል ኤዊ፣ ራቄም፣ ጹር፣ ሁር እና ረባ የተባሉት አምስቱ የምድያም ነገሥታት ይገኙበታል። እንዲሁም የቢዖርን ልጅ በለዓምን በሰይፍ ገደሉ። 9  ሆኖም እስራኤላውያን የምድያምን ሴቶችና ትናንሽ ልጆች ማርከው ወሰዱ። በተጨማሪም የቤት እንስሶቻቸውን፣ ከብቶቻቸውን እንዲሁም ንብረታቸውን በሙሉ ዘረፉ። 10  ይኖሩባቸው የነበሩትን ከተሞችና ሰፈሮቻቸውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። 11  ሰውም ሆነ እንስሳ የማረኩትንና የዘረፉትን በሙሉ ወሰዱ። 12  ከዚያም የማረኳቸውን ሰዎችና የዘረፉትን ንብረት በኢያሪኮ፣ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ ላይ ወደሚገኘው ሰፈር ወደ ሙሴ፣ ወደ ካህኑ አልዓዛርና ወደ እስራኤል ማኅበረሰብ አመጡ። 13  ከዚያም ሙሴ፣ ካህኑ አልዓዛርና የማኅበረሰቡ አለቆች በሙሉ ከእነሱ ጋር ለመገናኘት ከሰፈሩ ውጭ ወጡ። 14  ሆኖም ሙሴ ከጦርነቱ በተመለሱት የሠራዊቱ አዛዦች ይኸውም በሺህ አለቆቹና በመቶ አለቆቹ ላይ ተቆጣ። 15  እንዲህም አላቸው፦ “ሴቶቹን በሙሉ እንዴት ሳትገድሉ ተዋችኋቸው? 16  የበለዓምን ቃል ሰምተው እስራኤላውያን በፌጎር በተከሰተው ነገር የተነሳ በይሖዋ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት እንዲፈጽሙ ያሳቷቸውና በዚህም ምክንያት በይሖዋ ማኅበረሰብ ላይ መቅሰፍት እንዲመጣ ያደረጉት እነሱ አይደሉም? 17  በሉ አሁን ከልጆች መካከል ወንዶቹን በሙሉ እንዲሁም ከወንድ ጋር የፆታ ግንኙነት የፈጸሙ ሴቶችን በሙሉ ግደሉ። 18  ሆኖም ከወንድ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጽመው የማያውቁትን ወጣት ሴቶች ሁሉ በሕይወት እንዲተርፉ ልታደርጉ ትችላላችሁ። 19  እናንተም ለሰባት ቀን ከሰፈሩ ውጭ ቆዩ። ከመካከላችሁ ሰው የገደለም ሆነ የሞተ ሰው የነካ ማንኛውም ሰው በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሱን ያንጻ፤ እናንተም ሆናችሁ የማረካችኋቸው ሰዎች ራሳችሁን አንጹ። 20  ማንኛውንም ልብስ፣ ማንኛውንም ከቆዳ የተሠራ ነገር፣ ማንኛውንም ከፍየል ፀጉር የተሠራ ነገር እንዲሁም ማንኛውንም ከእንጨት የተሠራ ነገር ከኃጢአት አንጹ።” 21  ከዚያም ካህኑ አልዓዛር ወደ ጦርነቱ ሄደው የነበሩትን ወንዶች እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ ሙሴን ያዘዘው የሕጉ ደንብ ይህ ነው፦ 22  ‘ወርቁን፣ ብሩን፣ መዳቡን፣ ብረቱን፣ ቆርቆሮውንና እርሳሱን ብቻ 23  ይኸውም እሳትን መቋቋም የሚችለውን ማንኛውንም ነገር በእሳት ውስጥ እንዲያልፍ አድርጉ፤ እሱም ንጹሕ ይሆናል። ያም ሆኖ ለማንጻት በሚያገለግለው ውኃ መንጻት አለበት። እሳትን መቋቋም የማይችሉ ነገሮችን በሙሉ በውኃ ውስጥ እንዲያልፉ ማድረግ አለባችሁ። 24  በሰባተኛውም ቀን ልብሶቻችሁን እጠቡ፤ ንጹሕም ሁኑ፤ ከዚያም ወደ ሰፈሩ መግባት ትችላላችሁ።’” 25  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 26  “የምርኮውን ብዛት ቁጠር፤ ሰዎችም ሆኑ እንስሳት የተማረኩትን ሁሉ ቁጠር፤ ይህንም ከካህኑ ከአልዓዛርና ከማኅበረሰቡ የአባቶች ቤት መሪዎች ጋር አድርግ። 27  ምርኮውንም በጦርነቱ ለተካፈሉት ተዋጊዎችና ለቀረው ማኅበረሰብ ሁሉ እንዲከፋፈል ለሁለት ክፈለው። 28  ለይሖዋም ግብር እንዲሆን በጦርነቱ ከተካፈሉት ተዋጊዎች ላይ ከሰውም ሆነ ከከብት፣ ከአህያም ሆነ ከመንጋ ከ500 አንድ ነፍስ ውሰድ። 29  ለእነሱ ተከፍሎ ከተሰጣቸው ድርሻ ላይ ወስዳችሁ ለካህኑ ለአልዓዛር የይሖዋ መዋጮ አድርጋችሁ ስጡት። 30  ለእስራኤላውያን ተከፍሎ ከተሰጣቸው ድርሻ ላይ ደግሞ ከሰውም ሆነ ከከብት፣ ከአህያም ሆነ ከመንጋ እንዲሁም ከማንኛውም እንስሳ ከ50 አንድ ወስደህ ከይሖዋ የማደሪያ ድንኳን ጋር በተያያዘ ያለባቸውን ኃላፊነት ለሚወጡት ለሌዋውያኑ ስጥ።” 31  በመሆኑም ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ልክ ይሖዋ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ። 32  በውጊያው የተካፈሉት ሰዎች ማርከው ካመጡት ምርኮ ውስጥ የቀሩት 675,000 በጎች፣ 33  72,000 ከብቶች 34  እንዲሁም 61,000 አህዮች ነበሩ። 35  ከወንድ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጽመው የማያውቁት ሴቶች በአጠቃላይ 32,000 ነበሩ። 36  በውጊያው ለተሳተፉት ተከፍሎ የተሰጣቸው ድርሻ በአጠቃላይ 337,500 በግ ነበር። 37  ከበጎቹ መካከል ለይሖዋ ግብር ተደርገው የተሰጡት 675 ነበሩ። 38  ከብቶቹ ደግሞ 36,000 ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል ለይሖዋ ግብር ተደርገው የተሰጡት 72 ነበሩ። 39  አህዮቹ 30,500 ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል ለይሖዋ ግብር ተደርገው የተሰጡት 61 ነበሩ። 40  ሰዎቹ ደግሞ 16,000 ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል ለይሖዋ ግብር ተደርገው የተሰጡት 32 ሰዎች ነበሩ። 41  ከዚያም ሙሴ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ግብሩን ለይሖዋ መዋጮ እንዲሆን ለካህኑ ለአልዓዛር ሰጠው። 42  ሙሴም በጦርነቱ የተካፈሉት ሰዎች ካመጡት ላይ ከፍሎ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ድርሻ ይህ ነው፦ 43  ሙሴ ከፍሎ የሰጣቸው ድርሻ 337,500 በግ፣ 44  36,000 ከብት፣ 45  30,500 አህያ 46  እንዲሁም 16,000 ሰው ነበር። 47  ከዚያም ሙሴ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ለእስራኤላውያን ተከፍሎ ከተሰጣቸው ድርሻ ላይ ከሰውም ሆነ ከእንስሳ ከ50 አንድ ወስዶ በይሖዋ የማደሪያ ድንኳን የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለሚወጡት ሌዋውያን ሰጠ። 48  ከዚያም በሠራዊቱ ክፍሎች ውስጥ የተሾሙት አዛዦች ይኸውም የሺህ አለቆቹና የመቶ አለቆቹ ወደ ሙሴ ቀርበው 49  እንዲህ አሉት፦ “እኛ አገልጋዮችህ በሥራችን ያሉትን ተዋጊዎች ቆጥረናል፤ ከመካከላችን አንድም የጎደለ የለም። 50  ስለዚህ እያንዳንዳችን በይሖዋ ፊት ለራሳችን ማስተሰረያ እንዲሆኑልን፣ ያገኘናቸውን ነገሮች ይኸውም የወርቅ ጌጣጌጦችን፣ የእግር አልቦዎችን፣ የእጅ አምባሮችን፣ የማኅተም ቀለበቶችን፣ የጆሮ ጉትቻዎችንና ሌሎች ጌጣጌጦችን ለይሖዋ መባ አድርገን ማቅረብ እንፈልጋለን።” 51  በመሆኑም ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ወርቁን ይኸውም ጌጣጌጡን ሁሉ ተቀበሏቸው። 52  ከሺህ አለቆቹና ከመቶ አለቆቹ ተቀብለው ለይሖዋ መዋጮ እንዲሆን የሰጡት ወርቅ በጠቅላላ 16,750 ሰቅል ሆነ። 53   በሠራዊቱ ውስጥ ያሉት ወንዶች እያንዳንዳቸው ከምርኮው ላይ ድርሻቸውን ወስደው ነበር። 54  ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ወርቁን ከሺህ አለቆቹና ከመቶ አለቆቹ ተቀብለው በይሖዋ ፊት ለእስራኤል ሕዝብ ማስታወሻ እንዲሆን ወደ መገናኛ ድንኳኑ አስገቡት።
[]
[]
[]
[]
12,426
32  የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች እጅግ በጣም ብዙ ከብት ነበራቸው። እነሱም የያዜር እና የጊልያድ ምድር ለከብቶች የሚስማማ ስፍራ እንደሆነ አዩ። 2  በመሆኑም የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች መጥተው ሙሴን፣ ካህኑን አልዓዛርንና የማኅበረሰቡን አለቆች እንዲህ አሏቸው፦ 3  “የአጣሮት፣ የዲቦን፣ የያዜር፣ የኒምራ፣ የሃሽቦን፣ የኤልዓሌ፣ የሰባም፣ የነቦ እና የቤኦን ምድር 4  ይሖዋ በእስራኤል ማኅበረሰብ ፊት ድል ያደረገው ሲሆን ለከብቶች ምቹ ነው፤ አገልጋዮችህ ደግሞ ብዙ ከብት አላቸው።” 5  አክለውም እንዲህ አሉ፦ “እንግዲህ በፊትህ ሞገስ ካገኘን ይህ ምድር ለአገልጋዮችህ ርስት ተደርጎ ይሰጥ። ዮርዳኖስን እንድንሻገር አታድርገን።” 6  ከዚያም ሙሴ የጋድን ልጆችና የሮቤልን ልጆች እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ እዚህ ተቀምጣችሁ ወንድሞቻችሁ ወደ ጦርነት እንዲሄዱ ትፈልጋላችሁ? 7  የእስራኤል ልጆች ይሖዋ ወደሚሰጣቸው ምድር እንዳይሻገሩ ተስፋ የምታስቆርጧቸው ለምንድን ነው? 8  አባቶቻችሁ ምድሪቱን እንዲያዩ ከቃዴስበርኔ በላክኋቸው ጊዜ ያደረጉት ይህንኑ ነበር። 9  ወደ ኤሽኮል ሸለቆ አቅንተው ምድሪቱን ካዩ በኋላ የእስራኤልን ሕዝብ ይሖዋ ወደሚሰጠው ምድር እንዳይገባ ተስፋ አስቆረጡት። 10  በዚያ ቀን የይሖዋ ቁጣ ነደደ፤ እንዲህም ሲል ማለ፦ 11  ‘ከግብፅ ምድር ከወጡት መካከል 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የማልኩላቸውን ምድር አያዩም፤ ምክንያቱም በሙሉ ልባቸው አልተከተሉኝም፤ 12  ይሖዋን በሙሉ ልባቸው ከተከተሉት ከቀኒዛዊው ከየፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር አንዳቸውም ምድሪቱን አያዩም።’ 13  በመሆኑም የይሖዋ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ በይሖዋ ፊት ክፉ ድርጊት የፈጸመው ያ ትውልድ በሙሉ እስኪያልቅ ድረስ ለ40 ዓመት በምድረ በዳ እንዲንከራተቱ አደረጋቸው። 14  እናንተ የኃጢአተኞች ልጆች ደግሞ ይኸው በአባቶቻችሁ እግር ተተክታችሁ ይሖዋ በእስራኤል ላይ ይበልጥ እንዲቆጣ ታደርጋላችሁ። 15  እንግዲህ እናንተ እሱን ከመከተል ዞር ካላችሁ እሱም እንደገና በምድረ በዳ ይተዋቸዋል፤ እናንተም በዚህ ሁሉ ሕዝብ ላይ ጥፋት ታመጣላችሁ።” 16  በኋላም ወደ እሱ ቀርበው እንዲህ አሉት፦ “እንግዲያው እዚሁ ለከብቶቻችን በድንጋይ ካብ በረት እንሥራ፤ ለልጆቻችንም ከተሞች እንገንባ። 17  ይሁን እንጂ ወደ ስፍራቸው እስክናስገባቸው ድረስ ለጦርነት ታጥቀን በእስራኤላውያን ፊት እንሄዳለን፤ በዚህም ጊዜ ልጆቻችን ከምድሪቱ ነዋሪዎች ተጠብቀው በተመሸጉት ከተሞች ውስጥ ይኖራሉ። 18  እኛም እያንዳንዱ እስራኤላዊ የራሱን ርስት እስኪያገኝ ድረስ ወደ ቤታችን አንመለስም። 19  እኛ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ባለው አካባቢ ርስት ካገኘን ከዮርዳኖስ ማዶና ከዚያ ባሻገር ባለው አካባቢ ከእነሱ ጋር ርስት አንካፈልም።” 20  ሙሴም እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ብታደርጉ ይኸውም በጦርነቱ ለመካፈል በይሖዋ ፊት ታጥቃችሁ ብትነሱ 21  እንዲሁም ጠላቶቹን ከፊቱ እስኪያስወግድ ድረስ እያንዳንዳችሁ የጦር መሣሪያችሁን ይዛችሁ በይሖዋ ፊት ዮርዳኖስን ብትሻገሩና 22  ምድሪቱ በይሖዋ ፊት እስክትገዛ ድረስ በዚያ ብትቆዩ፣ ከዚያ በኋላ መመለስ ትችላላችሁ፤ በይሖዋም ሆነ በእስራኤላውያን ዘንድ ከበደል ነፃ ትሆናላችሁ። ከዚያም ይህች ምድር በይሖዋ ፊት የእናንተ ርስት ትሆናለች። 23  ይህን ባታደርጉ ግን በይሖዋ ላይ ኃጢአት ትሠራላችሁ። ለሠራችሁትም ኃጢአት ተጠያቂ እንደምትሆኑ እወቁ። 24  ስለዚህ ለልጆቻችሁ ከተሞችን መገንባትና ለመንጎቻችሁ በረት መሥራት የምትችሉ ቢሆንም የገባችሁትን ቃል መፈጸም ይኖርባችኋል።” 25  የጋድ ልጆችና የሮቤል ልጆችም ሙሴን እንዲህ አሉት፦ “እኛ አገልጋዮችህ ጌታችን እንዳዘዘን እናደርጋለን። 26  ልጆቻችን፣ ሚስቶቻችን፣ ከብቶቻችንና እንስሶቻችን በሙሉ በጊልያድ ከተሞች ውስጥ ይቆያሉ፤ 27  ሆኖም እኛ አገልጋዮችህ ይኸውም በይሖዋ ፊት ጦርነት ለመግጠም የታጠቅን እያንዳንዳችን ልክ ጌታችን በተናገረው መሠረት እንሻገራለን።” 28  በመሆኑም ሙሴ ለካህኑ ለአልዓዛር፣ ለነዌ ልጅ ለኢያሱና ለእስራኤል ነገዶች የአባቶች ቤት መሪዎች እነሱን በተመለከተ ትእዛዝ ሰጠ። 29  ሙሴም እንዲህ አላቸው፦ “የጋድ ልጆችና የሮቤል ልጆች ይኸውም በይሖዋ ፊት ለጦርነት የታጠቀ እያንዳንዱ ሰው ከእናንተ ጋር ዮርዳኖስን ከተሻገረ፣ ምድሪቱም በፊታችሁ ከተገዛች የጊልያድን ምድር ርስት አድርጋችሁ ትሰጧቸዋላችሁ። 30  ሆኖም የጦር መሣሪያ ታጥቀው ከእናንተ ጋር ካልተሻገሩ በከነአን ምድር በመካከላችሁ ይኖራሉ።” 31  በዚህ ጊዜ የጋድ ልጆችና የሮቤል ልጆች እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ “ይሖዋ ለአገልጋዮችህ የተናገረውን እንፈጽማለን። 32  እኛ ራሳችን የጦር መሣሪያ ታጥቀን በይሖዋ ፊት ወደ ከነአን ምድር እንሻገራለን፤ የምንወርሰው ርስት ግን ከዮርዳኖስ ወዲህ ያለውን ይሆናል።” 33  ስለዚህ ሙሴ ለጋድ ልጆችና ለሮቤል ልጆች እንዲሁም ለዮሴፍ ልጅ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ የአሞራውያንን ንጉሥ የሲሖንን ግዛትና የባሳንን ንጉሥ የኦግን ግዛት ይኸውም በክልሎቹ ውስጥ የሚገኙ ከተሞች ይዞታ የሆነውን ምድር እንዲሁም በዙሪያው ባለው ምድር ያሉትን ከተሞች ሰጣቸው። 34  የጋድ ልጆችም ዲቦን፣ አጣሮት፣ አሮዔር፣ 35  አትሮትሾፋን፣ ያዜር፣ ዮግበሃ፣ 36  ቤትኒምራ እና ቤትሃራን የተባሉትን የተመሸጉ ከተሞች ገነቡ፤ ለመንጎቹም በድንጋይ ካብ በረት ሠሩ። 37  የሮቤል ልጆች ደግሞ ሃሽቦንን፣ ኤልዓሌን፣ ቂርያታይምን፣ 38  ስማቸው የተለወጠውን ነቦን እና በዓልመዖንን እንዲሁም ሲብማን ገነቡ፤ እነሱም መልሰው ለገነቧቸው ከተሞች አዲስ ስም አወጡላቸው። 39  የምናሴ ልጅ የማኪር ልጆች በጊልያድ ላይ ዘምተው ምድሪቱን ያዙ፤ በዚያም ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያን አስወጧቸው። 40  በመሆኑም ሙሴ ጊልያድን ለምናሴ ልጅ ለማኪር ሰጠው፤ እሱም በዚያ መኖር ጀመረ። 41  የምናሴ ልጅ ያኢርም በእነሱ ላይ ዘምቶ የድንኳን ሰፈሮቻቸውን ያዘ፤ እነሱንም ሃዎትያኢር ብሎ ጠራቸው። 42  ኖባህም ዘምቶ ቄናትንና በሥሯ ያሉትን ከተሞች ያዘ፤ እነሱንም በራሱ ስም ኖባህ ብሎ ሰየማቸው።
[]
[]
[]
[]
12,427
33  የእስራኤል ሕዝብ በሙሴና በአሮን መሪነት በየምድቡ በመሆን ከግብፅ ምድር በወጣ ጊዜ የተጓዘው በዚህ መልክ ነበር። 2  ሙሴም በጉዟቸው ላይ ሳሉ ያረፉባቸውን ቦታዎች ይሖዋ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ይመዘግብ ነበር፤ ከአንዱ ስፍራ ተነስተው ወደ ሌላው የተጓዙት በሚከተለው ሁኔታ ነበር፦ 3  በመጀመሪያው ወር ከወሩም በ15ኛው ቀን ከራምሴስ ተነሱ። ልክ በፋሲካ በዓል ማግስት እስራኤላውያን ግብፃውያን ሁሉ እያዩአቸው በልበ ሙሉነት ወጡ። 4  በዚህ ጊዜ ግብፃውያን ይሖዋ በመቅሰፍት የመታቸውን በኩሮቻቸውን ሁሉ እየቀበሩ ነበር፤ ምክንያቱም ይሖዋ በአማልክታቸው ላይ የቅጣት እርምጃ ወስዶ ነበር። 5  በመሆኑም እስራኤላውያን ከራምሴስ ተነስተው በሱኮት ሰፈሩ። 6  ከዚያም ከሱኮት ተነስተው በምድረ በዳው ዳርቻ ላይ በምትገኘው በኤታም ሰፈሩ። 7  በመቀጠልም ከኤታም ተነስተው በበዓልጸፎን ትይዩ ወደምትገኘው ወደ ፊሃሂሮት ተመለሱ፤ በሚግዶልም ፊት ለፊት ሰፈሩ። 8  ከዚያም ከፊሃሂሮት ተነስተው ባሕሩን በማቋረጥ ወደ ምድረ በዳው ሄዱ፤ በኤታም ምድረ በዳ የሦስት ቀን መንገድ ከተጓዙ በኋላ በማራ ሰፈሩ። 9  ከዚያም ከማራ ተነስተው ወደ ኤሊም መጡ። በኤሊም 12 የውኃ ምንጮችና 70 የዘንባባ ዛፎች ነበሩ፤ በመሆኑም በዚያ ሰፈሩ። 10  በመቀጠል ደግሞ ከኤሊም ተነስተው በቀይ ባሕር አጠገብ ሰፈሩ። 11  ከዚያ በኋላ ከቀይ ባሕር ተነስተው በሲን ምድረ በዳ ሰፈሩ። 12  ከሲን ምድረ በዳ ተነስተው ደግሞ በዶፍቃ ሰፈሩ። 13  በኋላም ከዶፍቃ ተነስተው በአሉሽ ሰፈሩ። 14  በመቀጠልም ከአሉሽ ተነስተው በረፊዲም ሰፈሩ፤ በዚያም ሕዝቡ የሚጠጣው ውኃ አልነበረም። 15  ከዚያ በኋላ ከረፊዲም ተነስተው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ። 16  ከሲና ምድረ በዳም ተነስተው በቂብሮትሃታባ ሰፈሩ። 17  ከዚያም ከቂብሮትሃታባ ተነስተው በሃጼሮት ሰፈሩ። 18  በኋላም ከሃጼሮት ተነስተው በሪትማ ሰፈሩ። 19  በመቀጠል ደግሞ ከሪትማ ተነስተው በሪሞንጰሬጽ ሰፈሩ። 20  ከዚያም ከሪሞንጰሬጽ ተነስተው በሊብና ሰፈሩ። 21  ከሊብናም ተነስተው በሪሳ ሰፈሩ። 22  በመቀጠልም ከሪሳ ተነስተው በቀሄላታ ሰፈሩ። 23  ከዚያም ከቀሄላታ ተነስተው በሸፈር ተራራ ሰፈሩ። 24  በኋላም ከሸፈር ተራራ ተነስተው በሃራዳ ሰፈሩ። 25  ከዚያም ከሃራዳ ተነስተው በማቅሄሎት ሰፈሩ። 26  ቀጥሎም ከማቅሄሎት ተነስተው በታሃት ሰፈሩ። 27  ከዚያ በኋላም ከታሃት ተነስተው በታራ ሰፈሩ። 28  ከዚያም ከታራ ተነስተው በሚትቃ ሰፈሩ። 29  በኋላም ከሚትቃ ተነስተው በሃሽሞና ሰፈሩ። 30  ከሃሽሞናም ተነስተው በሞሴሮት ሰፈሩ። 31  ከዚያም ከሞሴሮት ተነስተው በብኔያዕቃን ሰፈሩ። 32  በኋላም ከብኔያዕቃን ተነስተው በሆርሃጊድጋድ ሰፈሩ። 33  ከዚያም ከሆርሃጊድጋድ ተነስተው በዮጥባታ ሰፈሩ። 34  ከዮጥባታም ተነስተው በአብሮና ሰፈሩ። 35  ከዚያም ከአብሮና ተነስተው በዔጽዮንጋብር ሰፈሩ። 36  በኋላም ከዔጽዮንጋብር ተነስተው በጺን ምድረ በዳ በምትገኘው በቃዴስ ሰፈሩ። 37  ከቃዴስም ተነስተው በኤዶም ምድር ወሰን ላይ በሚገኘው በሆር ተራራ ሰፈሩ። 38  እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር በወጡ በ40ኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ካህኑ አሮን ይሖዋ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ወደ ሆር ተራራ ወጣ፤ በዚያም ሞተ። 39  አሮን በሆር ተራራ ላይ በሞተበት ጊዜ ዕድሜው 123 ዓመት ነበር። 40  በከነአን ምድር በኔጌብ ይኖር የነበረው ከነአናዊው የአራድ ንጉሥ የእስራኤላውያንን መምጣት ሰማ። 41  ከጊዜ በኋላም ከሆር ተራራ ተነስተው በጻልሞና ሰፈሩ። 42  ከዚያም ከጻልሞና ተነስተው በጱኖን ሰፈሩ። 43  በመቀጠልም ከጱኖን ተነስተው በኦቦት ሰፈሩ። 44  ከኦቦትም ተነስተው በሞዓብ ድንበር ላይ በምትገኘው በኢዬዓባሪም ሰፈሩ። 45  በኋላም ከኢይም ተነስተው በዲቦንጋድ ሰፈሩ። 46  በመቀጠልም ከዲቦንጋድ ተነስተው በአልሞንዲብላታይም ሰፈሩ። 47  ከአልሞንዲብላታይም ተነስተው ደግሞ በነቦ ፊት ለፊት በአባሪም ተራሮች ሰፈሩ። 48  በመጨረሻም ከአባሪም ተራሮች ተነስተው በኢያሪኮ በሚገኘው በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ ሰፈሩ። 49  በሞዓብ በረሃማ ሜዳ ከቤትየሺሞት እስከ አቤልሺቲም በሚገኘው ስፍራ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ሰፈሩ። 50  ይሖዋ በኢያሪኮ በሚገኘው በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ ላይ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 51  “እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘እንግዲህ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ወደ ከነአን ምድር ልትገቡ ነው። 52  የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ ከፊታችሁ አባሯቸው፤ የተቀረጹ የድንጋይ ምስሎቻቸውንም ሁሉ አጥፉ፤ ከብረት የተሠሩ ሐውልቶቻቸውንም በሙሉ አስወግዱ፤ በከፍታ ቦታዎች ላይ ያሉ ቅዱስ ስፍራዎቻቸውን ሁሉ አፍርሱ። 53   ምድሪቱን ርስት አድርጌ ስለምሰጣችሁ ምድሪቱን ወርሳችሁ በዚያ ትኖራላችሁ። 54  ምድሪቱንም በየቤተሰባችሁ ውርስ አድርጋችሁ በዕጣ ተከፋፈሉ። ተለቅ ላለው ቡድን በዛ ያለውን፣ አነስ ላለው ቡድን ደግሞ አነስ ያለውን ውርስ አድርጋችሁ ስጡት። ሁሉም በወጣለት ዕጣ መሠረት የተሰጠውን ቦታ ይወርሳል። በየአባቶቻችሁ ነገዶች ርስታችሁን ውርስ አድርጋችሁ ትቀበላላችሁ። 55  “‘የምድሪቱን ነዋሪዎች ከፊታችሁ ሳታባርሩ እዚያው ከተዋችኋቸው ግን ዓይናችሁ ውስጥ እንደገባ ጉድፍ እንዲሁም ጎናችሁ ላይ እንደተሰካ እሾህ ይሆኑባችኋል፤ ደግሞም በምትኖሩበት ምድር ያንገላቷችኋል። 56  እኔም በእነሱ ላይ ለማድረግ ያሰብኩትን በእናንተ ላይ አደርግባችኋለሁ።’”
[]
[]
[]
[]
12,428
34  በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “ለእስራኤላውያን ይህን መመሪያ ስጣቸው፦ ‘ወደ ከነአን ምድር ስትገቡ ርስት አድርጋችሁ የምትወርሷት ምድር ይኸውም የከነአን ምድር ከነወሰኖቿ ይህች ናት። 3  “‘በስተ ደቡብ ያለው ወሰናችሁ ከጺን ምድረ በዳ ተነስቶ እስከ ኤዶም ጠረፍ ድረስ ይዘልቃል፤ በስተ ምሥራቅ ያለው ደቡባዊ ወሰናችሁ ደግሞ ከጨው ባሕር ዳርቻ ጀምሮ ያለው ይሆናል። 4  ወሰናችሁ አቅጣጫውን በመቀየር ከአቅራቢም አቀበት በስተ ደቡብ አድርጎ እስከ ጺን ድረስ ይዘልቃል፤ መጨረሻውም ከቃዴስበርኔ በስተ ደቡብ ይሆናል። ከዚያም ወደ ሃጻርአዳር ይሄድና ወደ አጽሞን ይዘልቃል። 5  ወሰኑ አጽሞን ላይ ሲደርስ አቅጣጫውን ቀይሮ ወደ ግብፅ ደረቅ ወንዝ ይሄዳል፤ መጨረሻውም ባሕሩ ይሆናል። 6  “‘ምዕራባዊ ወሰናችሁ ደግሞ ታላቁ ባሕርና የባሕሩ ዳርቻ ይሆናል። ይህ ምዕራባዊ ወሰናችሁ ይሆናል። 7  “‘ሰሜናዊ ወሰናችሁ የሚከተለው ይሆናል፦ ከታላቁ ባሕር አንስቶ እስከ ሆር ተራራ ድረስ ምልክት በማድረግ ወሰናችሁን ከልሉ። 8  ከሆር ተራራም አንስቶ እስከ ሌቦሃማት ድረስ ወሰኑን ምልክት አድርጉ፤ የወሰኑም መጨረሻ ጼዳድ ይሆናል። 9  ወሰኑም እስከ ዚፍሮን ድረስ ይዘልቃል፤ መጨረሻውም ሃጻርኤናን ይሆናል። ይህ ሰሜናዊ ወሰናችሁ ይሆናል። 10  “‘ከዚያም በስተ ምሥራቅ በኩል ወሰናችሁን ከሃጻርኤናን አንስቶ እስከ ሸፋም ድረስ ምልክት አድርጉ። 11  ወሰኑም ከሸፋም አንስቶ ከአይን በስተ ምሥራቅ እስከሚገኘው እስከ ሪብላ ድረስ ይዘልቃል፤ ከዚያም ቁልቁል ወርዶ የኪኔሬትን ባሕር ምሥራቃዊ ዳርቻ አቋርጦ ያልፋል። 12  ወሰኑ ወደ ዮርዳኖስ ይወርድና መጨረሻው ጨው ባሕር ይሆናል። እንግዲህ ምድራችሁ በዙሪያዋ ካሉት ወሰኖቿ ጋር ይህች ናት።’” 13  በመሆኑም ሙሴ እስራኤላውያንን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “ይሖዋ ለዘጠኙ ነገዶችና ለግማሹ ነገድ እንዲሰጥ ባዘዘው መሠረት ርስት አድርጋችሁ በዕጣ የምትከፋፈሏት ምድር ይህች ናት። 14  የሮቤላውያን ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት፣ የጋዳውያን ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ አስቀድመው ርስታቸውን ወስደዋልና። 15  ሁለቱ ነገድና ግማሹ ነገድ በኢያሪኮ አቅራቢያ ከዮርዳኖስ ክልል በስተ ምሥራቅ በፀሐይ መውጫ አቅጣጫ ርስታቸውን አግኝተዋል።” 16  በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 17  “ምድሪቱን ለእናንተ ርስት አድርገው የሚያከፋፍሏችሁ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ ናቸው። 18  ምድሪቱን ርስት አድርጋችሁ ለማከፋፈል ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ አንድ አለቃ ትወስዳላችሁ። 19  የሰዎቹም ስም የሚከተለው ነው፦ ከይሁዳ ነገድ የየፎኒ ልጅ ካሌብ፣ 20  ከስምዖን ልጆች ነገድ የአሚሁድ ልጅ ሸሙኤል፣ 21  ከቢንያም ነገድ የኪስሎን ልጅ ኤሊዳድ፣ 22  ከዳን ልጆች ነገድ አንድ አለቃ ይኸውም የዮግሊ ልጅ ቡቂ፣ 23  ከዮሴፍ ልጆች መካከል ከምናሴ ልጆች ነገድ አንድ አለቃ ይኸውም የኤፎድ ልጅ ሃኒኤል፣ 24  ከኤፍሬም ልጆች ነገድ አንድ አለቃ ይኸውም የሺፍጣን ልጅ ቀሙኤል፣ 25  ከዛብሎን ልጆች ነገድ አንድ አለቃ ይኸውም የፓርናክ ልጅ ኤሊጻፋን፣ 26  ከይሳኮር ልጆች ነገድ አንድ አለቃ ይኸውም የአዛን ልጅ ፓልጢኤል፣ 27  ከአሴር ልጆች ነገድ አንድ አለቃ ይኸውም የሸሎሚ ልጅ አሂሑድ፣ 28  ከንፍታሌም ልጆች ነገድ አንድ አለቃ ይኸውም የአሚሁድ ልጅ ፐዳሄል።” 29  ይሖዋ በከነአን ምድር ለእስራኤላውያን መሬቱን እንዲያከፋፍሉ ያዘዛቸው እነዚህ ናቸው።
[]
[]
[]
[]
12,429
35  ይሖዋ ሙሴን በኢያሪኮ በሚገኘው በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ ላይ እንዲህ አለው፦ 2  “እስራኤላውያንን ከሚወርሱት ርስት ላይ ለሌዋውያኑ መኖሪያ የሚሆኑ ከተሞችን እንዲሰጧቸው እዘዛቸው፤ በከተሞቹም ዙሪያ ያለውን የግጦሽ መሬት ለሌዋውያኑ መስጠት አለባቸው። 3  ከተሞቹ ለእነሱ መኖሪያ፣ የግጦሽ ቦታዎቹ ደግሞ ለከብቶቻቸውና ለዕቃዎቻቸው እንዲሁም ለሌሎች እንስሶቻቸው ይሆናሉ። 4  ለሌዋውያኑ የምትሰጧቸው የከተሞቹ የግጦሽ ቦታዎች ከከተማው ቅጥር በሁሉም አቅጣጫ 1,000 ክንድ ይሆናል። 5  ከተማውን መካከል ላይ በማድረግ ከከተማው ውጭ በምሥራቅ በኩል 2,000 ክንድ፣ በደቡብ በኩል 2,000 ክንድ፣ በምዕራብ በኩል 2,000 ክንድ እንዲሁም በሰሜን በኩል 2,000 ክንድ ለኩ። እነዚህም የከተሞቻቸው የግጦሽ መሬት ይሆናሉ። 6  “ለሌዋውያኑ የምትሰጧቸው ከተሞች ነፍስ ያጠፋ ሰው ሸሽቶ የሚሸሸግባቸውን 6 የመማጸኛ ከተሞችና ሌሎች 42 ከተሞችን ነው። 7  በጠቅላላ 48 ከተሞችን ከነግጦሽ መሬታቸው ለሌዋውያኑ ትሰጧቸዋላችሁ። 8  ከተሞቹን የምትሰጧቸው ከእስራኤላውያን ርስት ላይ ወስዳችሁ ነው። ተለቅ ካለው ቡድን ላይ ብዙ ትወስዳላችሁ፤ አነስ ካለው ቡድን ላይ ደግሞ ጥቂት ትወስዳላችሁ። እያንዳንዱ ቡድን በወረሰው ርስት መጠን ካሉት ከተሞች ላይ የተወሰኑትን ለሌዋውያኑ መስጠት ይኖርበታል።” 9  ይሖዋ በመቀጠል ሙሴን እንዲህ አለው፦ 10  “እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘እንግዲህ ወደ ከነአን ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን ልትሻገሩ ነው። 11  ሳያስበው ሰው የገደለ ሰው ሸሽቶ የሚጠጋባቸው አመቺ የሆኑ የመማጸኛ ከተሞችን ለራሳችሁ ምረጡ። 12  እነዚህ ከተሞች ነፍስ ያጠፋው ሰው በማኅበረሰቡ ፊት ለፍርድ ከመቅረቡ በፊት እንዳይሞት ከደም ተበቃዩ የሚሸሸግባቸው ከተሞች ይሆኑላችኋል። 13  እናንተ የምትሰጧቸው ስድስቱ የመማጸኛ ከተሞች ለዚህ ዓላማ ያገለግላሉ። 14  የመማጸኛ ከተሞች ሆነው እንዲያገለግሉ ከዮርዳኖስ ወዲህ ሦስት ከተሞችን፣ በከነአን ምድር ደግሞ ሦስት ከተሞችን ትሰጣላችሁ። 15  እነዚህ ስድስት ከተሞች ለእስራኤላውያንም ሆነ ለባዕድ አገር ሰው አሊያም በመካከላቸው ለሚኖር ሰፋሪ ሳያስበው ሰው የገደለ ማንኛውም ሰው ሸሽቶ የሚጠጋባቸው ከተሞች ሆነው ያገለግላሉ። 16  “‘ሆኖም ሰውየው ግለሰቡን በብረት መሣሪያ ቢመታውና ቢገድለው ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ነው። ነፍሰ ገዳዩ ያለምንም ጥርጥር መገደል አለበት። 17  ሰውየው ግለሰቡን ሊገድለው በሚችል ድንጋይ ቢመታውና ቢገድለው ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ነው። ነፍሰ ገዳዩ ያለምንም ጥርጥር መገደል አለበት። 18  ሰውየው ግለሰቡን ሊገድለው በሚችል ከእንጨት የተሠራ መሣሪያ ቢመታውና ቢገድለው ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ነው። ነፍሰ ገዳዩ ያለምንም ጥርጥር መገደል አለበት። 19  “‘ነፍሰ ገዳዩን መግደል ያለበት ደም ተበቃዩ ይሆናል። ባገኘው ጊዜ እሱ ራሱ ይግደለው። 20  አንድ ሰው ሌላውን በጥላቻ ተገፋፍቶ ቢገፈትረው ወይም ተንኮል አስቦ የሆነ ነገር ቢወረውርበትና ግለሰቡ ቢሞት 21  አሊያም በጥላቻ ተነሳስቶ በእጁ ቢመታውና ቢሞት መቺው ያለምንም ጥርጥር ይገደላል። እሱ ነፍሰ ገዳይ ነው። ደም ተበቃዩም ነፍሰ ገዳዩን ባገኘው ጊዜ ይገድለዋል። 22  “‘ይሁን እንጂ ሰውየው ግለሰቡን የገፈተረው በጥላቻ ተነሳስቶ ሳይሆን ሳያስበው ከሆነ ወይም ዕቃ የወረወረበት ተንኮል አስቦ ካልሆነ 23  አሊያም ግለሰቡ ሳያየው ድንጋይ ቢጥልበትና ቢሞት ሆኖም ሰውየው ከግለሰቡ ጋር ጠላትነት ባይኖረውና ይህን ያደረገው እሱን ለመጉዳት አስቦ ባይሆን 24  ማኅበረሰቡ እነዚህን ደንቦች መሠረት በማድረግ በገዳዩና በደም ተበቃዩ መካከል ፍርድ ይስጥ። 25  ማኅበረሰቡም ነፍሰ ገዳዩን ከደም ተበቃዩ እጅ ታድጎ ሸሽቶበት ወደነበረው የመማጸኛ ከተማ ይመልሰው፤ እሱም በቅዱስ ዘይት የተቀባው ሊቀ ካህናት እስኪሞት ድረስ በዚያ ይቆይ። 26  “‘ይሁንና ገዳዩ ሸሽቶ ከገባበት የመማጸኛ ከተማ ወሰን ቢወጣና 27  ደም ተበቃዩም ገዳዩን ከመማጸኛ ከተማው ወሰን ውጭ አግኝቶ ቢገድለው በደም ዕዳ አይጠየቅም። 28  ምክንያቱም ሊቀ ካህናቱ እስኪሞት ድረስ በመማጸኛ ከተማው ውስጥ መቆየት ይገባዋል። ሊቀ ካህናቱ ከሞተ በኋላ ግን ገዳዩ ወደ ርስቱ መመለስ ይችላል። 29  እነዚህም በምትኖሩበት በየትኛውም ቦታ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ፍርድ ለመስጠት እንደሚያገለግል ደንብ ይሁኗችሁ። 30  “‘ሰው የገደለ ማንኛውም ሰው ምሥክሮች ከመሠከሩበት እንደ ነፍሰ ገዳይ ተቆጥሮ ይገደል፤ ይሁን እንጂ ማንም ሰው አንድ ግለሰብ በሚሰጠው ምሥክርነት ብቻ በሞት መቀጣት የለበትም። 31  ሞት ለሚገባው ነፍሰ ገዳይ ሕይወት ቤዛ አትቀበሉ፤ ምክንያቱም ያለምንም ጥርጥር መገደል አለበት። 32  እንዲሁም ሸሽቶ ወደ መማጸኛ ከተማው ለገባ ሰው ሊቀ ካህናቱ ከመሞቱ በፊት ወደ ምድሩ ተመልሶ እንዲኖር ለማድረግ ቤዛ አትቀበሉ። 33  “‘ደም ምድሪቱን ስለሚበክል ያላችሁባትን ምድር አትበክሉ፤ ደም ባፈሰሰው ሰው ደም ካልሆነ በስተቀር በምድሪቱ ላይ ለፈሰሰው ደም ስርየት ሊኖር አይችልም። 34  የምትኖሩባትን፣ እኔም የምኖርባትን ምድር አታርክሱ፤ እኔ ይሖዋ በእስራኤል ሕዝብ መካከል እኖራለሁና።’”
[]
[]
[]
[]
12,430
36  ከዮሴፍ ልጆች ቤተሰቦች የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የጊልያድ ተወላጆች የአባቶች ቤት መሪዎች ወደ ሙሴና የእስራኤላውያን የአባቶች ቤት መሪዎች ወደሆኑት አለቆች ቀርበው ተናገሩ፤ 2  እንዲህም አሉ፦ “ይሖዋ ጌታዬን ምድሪቱን ለእስራኤላውያን ርስት አድርጎ በዕጣ እንዲያከፋፍል አዞት ነበር፤ ደግሞም የወንድማችንን የሰለጰአድን ርስት ለሴቶች ልጆቹ እንዲሰጥ ይሖዋ ጌታዬን አዞት ነበር። 3  እነዚህ ሴቶች ከሌሎች የእስራኤል ነገዶች ባሎችን ቢያገቡ የእነሱ ውርስ ከአባቶቻችን ውርስ ላይ ተወስዶ በሚያገቡት ሰው ነገድ ውርስ ላይ ይጨመራል፤ በመሆኑም በዕጣ ከተሰጠን ውርስ ላይ ይቀነሳል። 4  የእስራኤል ሕዝብ የኢዮቤልዩ ዓመት በሚደርስበት ጊዜ የሴቶቹ ውርስ በሚያገቡት ሰው ነገድ ውርስ ላይ ለዘለቄታው ይጨመራል፤ በመሆኑም የእነሱ ውርስ ከአባቶቻችን ነገድ ውርስ ላይ ይቀነሳል።” 5  ከዚያም ሙሴ ይሖዋ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እስራኤላውያንን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “የዮሴፍ ልጆች ነገድ የተናገረው ነገር ትክክል ነው። 6  ይሖዋ የሰለጰአድን ሴቶች ልጆች በተመለከተ እንዲህ ሲል አዟል፦ ‘የፈለጉትን ሰው ማግባት ይችላሉ። ሆኖም ከአባታቸው ነገድ ቤተሰብ የሆነን ሰው ማግባት ይኖርባቸዋል። 7  የትኛውም የእስራኤላውያን ውርስ ከአንዱ ነገድ ወደ ሌላው ነገድ መተላለፍ የለበትም፤ ምክንያቱም እስራኤላውያን እያንዳንዳቸው የአባቶቻቸውን ነገድ ውርስ አጽንተው መያዝ አለባቸው። 8  እስራኤላውያን የቀደሙትን አባቶቻቸውን ውርስ ጠብቀው ማቆየት እንዲችሉ በእስራኤል ነገዶች መካከል ውርስ ያላት የትኛዋም ልጅ የአባቷ ነገድ ተወላጅ የሆነ ሰው ማግባት ይኖርባታል። 9  የትኛውም ውርስ ከአንዱ ነገድ ወደ ሌላው ነገድ መተላለፍ የለበትም፤ ምክንያቱም የእስራኤል ነገዶች እያንዳንዳቸው የየራሳቸውን ውርስ አጽንተው መያዝ አለባቸው።’” 10  የሰለጰአድ ሴቶች ልጆች ልክ ይሖዋ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ። 11  ስለሆነም የሰለጰአድ ሴቶች ልጆች የሆኑት ማህላ፣ ቲርጻ፣ ሆግላ፣ ሚልካ እና ኖኅ የአባታቸውን ወንድሞች ልጆች አገቡ። 12  ውርሻቸው በአባታቸው ቤተሰብ ነገድ ሥር እንደሆነ እንዲቀጥል የዮሴፍ ልጅ የምናሴ ልጆች ቤተሰቦች የሆኑ ወንዶችን አገቡ። 13  ይሖዋ በኢያሪኮ በሚገኘው በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ ላይ ለነበሩት እስራኤላውያን በሙሴ አማካኝነት የሰጣቸው ትእዛዛትና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው።
[]
[]
[]
[]
12,431
4  ይሖዋም ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ 2  “ከሌዊ ልጆች መካከል የቀአትን ወንዶች ልጆች በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤቶች መሠረት ቁጠሩ፤ 3  በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ እንዲሠራ በተመደበው ቡድን ውስጥ ያሉትን ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 50 ዓመት የሆኑትን ሁሉ ቁጠሩ። 4  “የቀአት ወንዶች ልጆች በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ የሚያከናውኑት አገልግሎት ይህ ነው። ይህ እጅግ ቅዱስ የሆነ ነገር ነው፦ 5  ሰፈሩ በሚነሳበት ጊዜ አሮንና ወንዶች ልጆቹ መጥተው ታቦቱን የሚከልለውን መጋረጃ ያወርዱታል፤ የምሥክሩንም ታቦት በእሱ ይሸፍኑታል። 6  በላዩም ላይ ከአቆስጣ ቆዳ የተሠራ መሸፈኛ ይደርቡበታል፤ እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ሰማያዊ የሆነ ጨርቅ ያለብሱታል፤ ለመሸከሚያ የሚያገለግሉትንም መሎጊያዎች በቦታቸው ላይ ያደርጓቸዋል። 7  “ገጸ ኅብስቱ የሚቀመጥበትንም ጠረጴዛ ሰማያዊ ጨርቅ ያለብሱታል፤ በላዩም ላይ ሳህኖቹን፣ ጽዋዎቹን፣ ጎድጓዳ ሳህኖቹንና ለመጠጥ መባ የሚሆኑትን ማንቆርቆሪያዎች ያስቀምጣሉ፤ የዘወትሩም የቂጣ መባ ከላዩ ላይ አይነሳ። 8  ደማቅ ቀይ ጨርቅ ያለብሷቸዋል፤ ከአቆስጣ ቆዳ የተሠራ መሸፈኛም ይደርቡበታል፤ እንዲሁም ለመሸከሚያ የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች በቦታቸው ላይ ያደርጓቸዋል። 9  ከዚያም ሰማያዊ ጨርቅ ወስደው የመብራቱን መቅረዝ ከመብራቶቹ፣ ከመቆንጠጫዎቹና ከመኮስተሪያዎቹ እንዲሁም ዘወትር ዘይት እንዲኖር ለማድረግ ከሚያገለግሉት ዘይት የሚቀመጥባቸው ዕቃዎች ሁሉ ጋር ይሸፍኑታል። 10  መቅረዙን ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር ከአቆስጣ ቆዳ በተሠራ መሸፈኛ ይጠቀልሉታል፤ በመሸከሚያ ሳንቃ ላይም ያስቀምጡታል። 11  የወርቁን መሠዊያም ሰማያዊ ጨርቅ ያለብሱታል፤ ከአቆስጣ ቆዳ የተሠራ መሸፈኛም ይደርቡበታል፤ ለመሸከሚያ የሚያገለግሉትንም መሎጊያዎች በቦታቸው ላይ ያደርጓቸዋል። 12  ከዚያም በቅዱሱ ስፍራ ዘወትር የሚጠቀሙባቸውን መገልገያ ዕቃዎች በሙሉ ወስደው በሰማያዊ ጨርቅ ይጠቀልሏቸዋል፤ ከአቆስጣ ቆዳ የተሠራ መሸፈኛም ይደርቡባቸዋል፤ በመሸከሚያ ሳንቃ ላይም ያስቀምጧቸዋል። 13  “አመዱን ከመሠዊያው ላይ ያስወግዱ፤ መሠዊያውንም ሐምራዊ የሱፍ ጨርቅ ያልብሱት። 14  እንዲሁም በመሠዊያው ላይ ለማገልገል የሚጠቀሙባቸውን ዕቃዎች በሙሉ ይኸውም መኮስተሪያዎቹን፣ ሹካዎቹን፣ አካፋዎቹን፣ ጎድጓዳ ሳህኖቹንና የመሠዊያውን ዕቃዎች በሙሉ በላዩ ላይ ያደርጉበታል፤ ከአቆስጣ ቆዳ የተሠራ መሸፈኛም ይደርቡበታል፤ ለመሸከሚያ የሚያገለግሉትንም መሎጊያዎች በቦታቸው ላይ ያደርጓቸዋል። 15  “አሮንና ወንዶች ልጆቹ ሰፈሩ ከመነሳቱ በፊት በቅዱሱ ስፍራ ያሉትን ነገሮችና የቅዱሱን ስፍራ ዕቃዎች በሙሉ ሸፍነው መጨረስ አለባቸው። ከዚያም የቀአት ወንዶች ልጆች ለመሸከም ይመጣሉ፤ ሆኖም በቅዱሱ ስፍራ ያሉትን ነገሮች መንካት የለባቸውም፤ ከነኩ ግን ይሞታሉ። ከመገናኛ ድንኳኑ ጋር በተያያዘ እነዚህን ነገሮች የማከናወኑ ኃላፊነት የተጣለው በቀአት ወንዶች ልጆች ላይ ነው። 16  “የመብራቱን ዘይት፣ ጥሩ መዓዛ ያለውን ዕጣን፣ ዘወትር የሚቀርበውን የእህል መባና የቅብዓት ዘይቱን የመቆጣጠሩ ኃላፊነት የካህኑ የአሮን ልጅ የአልዓዛር ነው። ቅዱሱን ስፍራና ዕቃዎቹን ጨምሮ የማደሪያ ድንኳኑን ሁሉና በውስጡ ያለውን ነገር በሙሉ የመቆጣጠሩ ኃላፊነት የእሱ ነው።” 17  በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ 18  “የቀአታውያን ቤተሰቦች ነገድ ከሌዋውያን መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ አታድርጉ። 19  እጅግ ቅዱስ ወደሆኑት ነገሮች በመቅረባቸው የተነሳ እንዳይሞቱ፣ ከዚህ ይልቅ በሕይወት እንዲኖሩ ይህን አድርጉላቸው። አሮንና ወንዶች ልጆቹ ገብተው ለእያንዳንዳቸው ሥራቸውንና የሚሸከሙትን ነገር ይመድቡላቸው። 20  ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች ለአፍታ እንኳ ገብተው ማየት የለባቸውም፤ ካዩ ግን ይሞታሉ።” 21  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 22  “የጌድሶንን ወንዶች ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶችና በየቤተሰባቸው ቁጠር። 23  በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ እንዲያገለግል በተመደበው ቡድን ውስጥ ያሉትን ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 50 ዓመት የሆኑትን ሁሉ መዝግብ። 24  የጌድሶናውያን ቤተሰቦች እንዲንከባከቡና እንዲሸከሙ የተመደቡት እነዚህን ነገሮች ነው፦ 25  እነሱም የማደሪያ ድንኳኑን የድንኳን ጨርቆች፣ የመገናኛ ድንኳኑን ጨርቆች፣ መደረቢያውንና ከእሱ በላይ ያለውን ከአቆስጣ ቆዳ የተሠራ መደረቢያ እንዲሁም የመገናኛ ድንኳኑን መግቢያ መከለያ ይሸከማሉ፤ 26  በተጨማሪም የግቢውን መጋረጃዎች፣ በማደሪያ ድንኳኑና በመሠዊያው ዙሪያ ባለው ግቢ መግቢያ ላይ የሚገኘውን መከለያ፣ የድንኳን ገመዶቻቸውንና ዕቃዎቻቸውን በሙሉ እንዲሁም ለአገልግሎቱ የሚውሉትን ነገሮች ሁሉ ይሸከማሉ። የሥራ ምድባቸው ይህ ነው። 27  ጌድሶናውያን የሚያከናውኑትን አገልግሎትና የሚሸከሟቸውን ነገሮች ሁሉ የሚቆጣጠሩት አሮንና ወንዶች ልጆቹ ናቸው፤ እነዚህን ነገሮች ሁሉ የመሸከሙን ኃላፊነት ለእነሱ ትሰጣቸዋለህ። 28  የጌድሶናውያን ቤተሰቦች በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ የሚያከናውኑት አገልግሎት ይህ ነው፤ ኃላፊነታቸውንም የሚወጡት በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር አመራር ሥር ሆነው ነው። 29  “የሜራሪን ወንዶች ልጆችም በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት ትመዘግባቸዋለህ። 30  በመገናኛ ድንኳኑ እንዲያገለግል በተመደበው ቡድን ውስጥ ያሉትን ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 50 ዓመት የሆኑትን ሁሉ ትመዘግባለህ። 31  በመገናኛ ድንኳኑ ከሚያከናውኑት አገልግሎት ጋር በተያያዘ የሚከተሉትን ነገሮች የመሸከም ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል፦ የማደሪያ ድንኳኑን ቋሚዎች፣ አግዳሚ እንጨቶቹን፣ ዓምዶቹን፣ መሰኪያዎቹን፣ 32  በግቢው ዙሪያ ያሉትን ቋሚዎች፣ መሰኪያዎቻቸውን፣ የድንኳን ካስማዎቻቸውን፣ የድንኳን ገመዶቻቸውን እንዲሁም ቁሳቁሶቻቸውንና ከዚህ አገልግሎት ጋር የተያያዙትን ነገሮች ሁሉ ይሸከማሉ። በኃላፊነት የሚሸከሙትንም ዕቃ በስም ጠቅሰህ ትመድብላቸዋለህ። 33  የሜራሪ ወንዶች ልጆች ቤተሰቦች በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር አመራር ሥር ሆነው በመገናኛ ድንኳኑ የሚያገለግሉት በዚህ መሠረት ነው።” 34  ከዚያም ሙሴ፣ አሮንና የማኅበረሰቡ አለቆች የቀአታውያንን ወንዶች ልጆች በየቤተሰቦቻቸውና በየአባቶቻቸው ቤት መዘገቡ፤ 35  በመገናኛ ድንኳኑ እንዲያገለግል በተመደበው ቡድን ውስጥ ያሉትን ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 50 ዓመት የሆኑትን ሁሉ መዘገቡ። 36  በየቤተሰባቸው የተመዘገቡትም በአጠቃላይ 2,750 ነበሩ። 37  ከቀአታውያን ቤተሰቦች መካከል የተመዘገቡትና በመገናኛ ድንኳኑ የሚያገለግሉት በአጠቃላይ እነዚህ ነበሩ። ሙሴና አሮንም ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት መዘገቧቸው። 38  የጌድሶን ወንዶች ልጆችም በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት ተመዘገቡ፤ 39  በመገናኛ ድንኳኑ እንዲያገለግል በተመደበው ቡድን ውስጥ ያሉት ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 50 ዓመት የሆኑት ሁሉ ተመዘገቡ። 40  በየቤተሰቦቻቸውና በየአባቶቻቸው ቤት የተመዘገቡት በአጠቃላይ 2,630 ነበሩ። 41  በመገናኛ ድንኳኑ እንዲያገለግሉ የተመዘገቡት የጌድሶን ወንዶች ልጆች ቤተሰቦች በአጠቃላይ እነዚህ ነበሩ። ሙሴና አሮንም ይሖዋ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት መዘገቧቸው። 42  የሜራሪ ወንዶች ልጆች በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት ተመዘገቡ፤ 43  በመገናኛ ድንኳኑ እንዲያገለግል በተመደበው ቡድን ውስጥ ያሉት ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 50 ዓመት የሆኑት ሁሉ ተመዘገቡ። 44  ከእነሱ መካከል በየቤተሰባቸው የተመዘገቡት በአጠቃላይ 3,200 ነበሩ። 45  ሙሴና አሮን ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት የመዘገቧቸው የሜራሪ ወንዶች ልጆች ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ። 46  ሙሴ፣ አሮንና የእስራኤል አለቆች እነዚህን ሌዋውያን ሁሉ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤቶች መዘገቧቸው፤ 47  እነሱም ከ30 እስከ 50 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ሁሉም ከመገናኛ ድንኳኑ ጋር በተያያዘ እንዲያገለግሉና ሸክም እንዲሸከሙ ተመድበው ነበር። 48  የተመዘገቡትም በአጠቃላይ 8,580 ነበሩ። 49  እነሱም ይሖዋ በሙሴ በኩል ባስተላለፈው ትእዛዝ መሠረት ተመዝግበው ነበር፤ የተመዘገቡትም እያንዳንዳቸው በሚያከናውኑት አገልግሎትና በሚሸከሙት ሸክም መሠረት ነበር፤ እነሱም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ተመዘገቡ።
[]
[]
[]
[]
12,432
5  በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “እስራኤላውያንን የሥጋ ደዌ ያለበትን፣ ፈሳሽ የሚወጣውንና በሞተ ሰው የረከሰን ማንኛውንም ሰው ከሰፈሩ እንዲያስወጡ እዘዛቸው። 3  ወንድም ሆነ ሴት አስወጧቸው። እኔ በመካከላቸው ስለምኖር ሕዝቤ የሚኖርባቸውን ሰፈሮች እንዳይበክሉ ከሰፈሩ አስወጧቸው።” 4  በመሆኑም እስራኤላውያን እንደተባሉት አደረጉ፤ ሰዎቹንም ከሰፈሩ አስወጧቸው። እስራኤላውያን ልክ ይሖዋ ለሙሴ እንደነገረው አደረጉ። 5  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 6  “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት የሰው ልጆች ከሚፈጽሟቸው ኃጢአቶች ውስጥ የትኛውንም ቢሠሩና በይሖዋ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ቢፈጽሙ ይህን ያደረገው ሰው በደለኛ ይሆናል። 7  እሱም የሠራውን ኃጢአት መናዘዝና ለፈጸመው በደል ካሳ አድርጎ ሙሉ ዋጋውን መመለስ አለበት፤ የዚህን አንድ አምስተኛም ይጨምርበት፤ በደል ለፈጸመበትም ሰው ይስጠው። 8  ሆኖም በደል የተፈጸመበት ሰው ቢሞትና ካሳውን የሚቀበልለት የቅርብ ዘመድ ባይኖረው ካህኑ የግለሰቡን በደል ከሚያስተሰርይበት አውራ በግ በስተቀር ካሳው ለይሖዋ ይመለስ፤ የካህኑም ይሆናል። 9  “‘እስራኤላውያን ለካህኑ የሚያቀርቧቸው ቅዱስ መዋጮዎች በሙሉ የእሱ ይሆናሉ። 10  እያንዳንዱ ሰው የሚያቀርባቸው ቅዱስ የሆኑ ነገሮች የእሱ ይሆናሉ። እያንዳንዱ ሰው ለካህኑ የሚሰጠው ማንኛውም ነገር የካህኑ ይሆናል።’” 11  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 12  “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘የአንድ ሰው ሚስት ከትክክለኛው መንገድ ዞር በማለት ለባሏ ታማኝ ሳትሆን ብትቀርና 13  ሌላ ወንድ ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት ቢፈጽም፣ ባሏ ግን ይህን ነገር ባያውቅና ጉዳዩ ተሰውሮ ቢቀር፣ ይህች ሴት በዚህ መንገድ ራሷን ብታረክስም የሚመሠክርባት ሰው ባይገኝና እጅ ከፍንጅ ባትያዝ፣ 14  ባሏም ሚስቱ ራሷን አርክሳ ሳለ የቅናት መንፈስ ቢያድርበትና የሚስቱን ታማኝነት ቢጠራጠር ወይም ደግሞ ራሷን ሳታረክስ የቅናት መንፈስ ቢያድርበትና ታማኝነቷን ቢጠራጠር 15  ሰውየው ሚስቱን ለእሷ ከሚቀርበው መባ ይኸውም ከአንድ አሥረኛ ኢፍ የገብስ ዱቄት ጋር ወደ ካህኑ ያምጣ። ይህ የቅናት የእህል መባ ይኸውም በደል እንዲታወስ የሚያደርግ የእህል መባ ስለሆነ በላዩ ላይ ዘይት አያፍስበት ወይም ነጭ ዕጣን አያድርግበት። 16  “‘ካህኑ ሴትየዋን አምጥቶ ይሖዋ ፊት እንድትቆም ያደርጋል። 17  ከዚያም ካህኑ የተቀደሰ ውኃ በሸክላ ዕቃ ይወስዳል፤ ከማደሪያ ድንኳኑም ወለል ላይ ጥቂት አፈር ወስዶ ውኃው ውስጥ ይጨምረዋል። 18  ካህኑም ሴትየዋ በይሖዋ ፊት እንድትቆም ያደርጋል፤ ፀጉሯንም ይፈታል፤ ለመታሰቢያ የሚሆነውን የእህል መባ ይኸውም የቅናት የእህል መባውን በእጆቿ ላይ ያደርጋል፤ ካህኑም እርግማን የሚያመጣውን መራራ ውኃ በእጁ ይይዛል። 19  “‘ካህኑም ሴትየዋን እንዲህ በማለት ያስምላታል፦ “በባልሽ ሥልጣን ሥር ሆነሽ ሳለ ሌላ ወንድ ከአንቺ ጋር የፆታ ግንኙነት ካልፈጸመ አንቺም ከትክክለኛው መንገድ ዞር ካላልሽና ካልረከስሽ እርግማን የሚያስከትለው ይህ ውኃ ምንም ጉዳት አያድርስብሽ። 20  ይሁንና በባልሽ ሥልጣን ሥር ሆነሽ ሳለ ራስሽን በማርከስ ከትክክለኛው መንገድ ዞር ብለሽ ከሆነና ከሌላ ወንድ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጽመሽ ከሆነ . . . ” 21  ካህኑም ሴትየዋን እርግማን ያለበት መሐላ ያስምላታል፤ እንዲህም ይላታል፦ “ይሖዋ ጭንሽ እንዲሰልና ሆድሽ እንዲያብጥ በማድረግ፣ ይሖዋ በሕዝብሽ መካከል የእርግማንና የመሐላ ምሳሌ ያድርግሽ። 22  እርግማን የሚያመጣው ይህ ውኃ ወደ አንጀትሽ ገብቶ ሆድሽን ያሳብጠው፤ መሃንም ያድርግሽ።” በዚህ ጊዜ ሴትየዋ “አሜን! አሜን!” ትበል። 23  “‘ከዚያም ካህኑ እነዚህን እርግማኖች በመጽሐፍ ይጻፋቸው፤ በመራራውም ውኃ አጥቦ ያጥፋቸው። 24  እርግማን የሚያመጣውን መራራ ውኃም እንድትጠጣ ያድርግ፤ ውኃውም ወደ ሰውነቷ ገብቶ መራራ ሥቃይ ያስከትልባት። 25  ካህኑም የቅናት የእህል መባውን ከሴትየዋ እጅ ላይ ወስዶ በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ይወዝውዘው፤ ወደ መሠዊያውም ያምጣው። 26  ካህኑም ከእህል መባው ላይ አንድ እፍኝ በመውሰድ የመባው መታሰቢያ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጭሰው፤ ከዚያ በኋላ ሴትየዋ ውኃውን እንድትጠጣ ያድርግ። 27  ውኃውን እንድትጠጣ በሚያደርግበትም ጊዜ ሴትየዋ ራሷን አርክሳና በባሏ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ፈጽማ ከሆነ እርግማን የሚያመጣው ውኃ ወደ ሰውነቷ ገብቶ መራራ ሥቃይ ያስከትልባታል፤ ሆዷም ያብጣል፤ ጭኗም ይሰልላል፤ እሷም በሕዝቧ መካከል የእርግማን ምሳሌ ትሆናለች። 28  ይሁንና ሴትየዋ ራሷን ካላረከሰችና ንጹሕ ከሆነች እንዲህ ካለው ቅጣት ነፃ ትሆናለች፤ እንዲሁም መጸነስና ልጆች ማፍራት ትችላለች። 29  “‘እንግዲህ ቅናትን በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው፤ አንዲት ሴት በባሏ ሥልጣን ሥር ሆና ሳለ ከትክክለኛው መንገድ ዞር ብትልና ራሷን ብታረክስ 30  ወይም አንድ ሰው የቅናት መንፈስ ቢያድርበትና የሚስቱን ታማኝነት ቢጠራጠር ሕጉ ይህ ነው፤ እሱም ሚስቱ በይሖዋ ፊት እንድትቆም ያድርግ፤ ካህኑም ይህ ሕግ በሙሉ በእሷ ላይ እንዲፈጸም ያድርግ። 31  ሰውየው ከበደል ነፃ ይሆናል፤ ሚስቱ ግን ስለ በደሏ ትጠየቃለች።’”
[]
[]
[]
[]
12,433
6  በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ለይሖዋ ናዝራዊ ሆነው ለመኖር ልዩ ስእለት ቢሳሉ 3  ስእለት የተሳለው ሰው ከወይን ጠጅና ከሚያሰክር ሌላ መጠጥ መራቅ ይኖርበታል። የወይን ጠጅ ኮምጣጤ ወይም የማንኛውም ዓይነት የሚያሰክር መጠጥ ኮምጣጤ አይጠጣ። ከወይን ፍሬ የተዘጋጀን ማንኛውንም መጠጥ አይጠጣ፤ የወይን ፍሬም ሆነ ዘቢብ አይብላ። 4  ናዝራዊ ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ሁሉ ከወይን ተክል የተዘጋጀን ማንኛውንም ነገር፣ ያልበሰለውን የወይን ፍሬም ሆነ ግልፋፊውን ፈጽሞ መብላት የለበትም። 5  “‘ናዝራዊ ሆኖ ለመቆየት በተሳለበት ጊዜ ሁሉ ራሱን ምላጭ አይንካው። ለይሖዋ የተለየበት ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ የራስ ፀጉሩን በማሳደግ ቅዱስ ሆኖ መገኘት ይኖርበታል። 6  ራሱን ለይሖዋ በለየበት ጊዜ ሁሉ ወደ ሞተ ሰው አይቅረብ። 7  ለአምላኩ ናዝራዊ መሆኑን የሚያሳየው ምልክት በራሱ ላይ ስላለ አባቱ ወይም እናቱ ወይም ወንድሙ ወይም እህቱ ቢሞቱ እንኳ በእነሱ ራሱን አያርክስ። 8  “‘ናዝራዊ ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ሁሉ ለይሖዋ ቅዱስ ይሆናል። 9  ይሁንና አንድ ሰው ድንገት አጠገቡ ቢሞትና ለአምላክ የተለየ መሆኑን የሚያሳየውን ፀጉሩን ቢያረክስ መንጻቱን በሚያረጋግጥበት ቀን ራሱን ይላጭ። በሰባተኛውም ቀን ፀጉሩን ይላጨው። 10  በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶችን ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶችን በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ወደሚገኘው ካህን ያምጣ። 11  ካህኑም አንዱን የኃጢአት መባ ሌላኛውን ደግሞ የሚቃጠል መባ አድርጎ በማዘጋጀት ከሞተ ሰው ጋር በተያያዘ ስለሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል። ከዚያም በዚያ ቀን ራሱን ይቀድስ። 12  ናዝራዊ ሆኖ ለሚቆይበት ጊዜ እንደገና ራሱን ለይሖዋ ይለይ፤ አንድ ዓመት ገደማ የሆነው የበግ ጠቦት የበደል መባ አድርጎ ያምጣ። ሆኖም ናዝራዊነቱን ስላረከሰ የቀድሞዎቹ ጊዜያት አይታሰቡለትም። 13  “‘እንግዲህ ናዝራዊን በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው፦ ናዝራዊ ሆኖ የሚቆይበትን ጊዜ ሲያጠናቅቅ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ እንዲመጣ ይደረግ። 14  በዚያም የሚከተሉትን ለይሖዋ መባ አድርጎ ያቅርብ፦ ለሚቃጠል መባ አንድ ዓመት ገደማ የሆነውን እንከን የሌለበት አንድ የበግ ጠቦት፣ ለኃጢአት መባ አንድ ዓመት ገደማ የሆናትን እንከን የሌለባት አንዲት ጠቦት፣ ለኅብረት መሥዋዕት እንከን የሌለበትን አንድ አውራ በግ፣ 15  በዘይት ከተለወሰ የላመ ዱቄት የተዘጋጁ እርሾ ያልገባባቸው አንድ ቅርጫት የቀለበት ቅርጽ ያላቸው ዳቦዎችና ዘይት የተቀቡ ስስ ቂጣዎች እንዲሁም የእህል መባዎቻቸውንና የመጠጥ መባዎቻቸውን። 16  ካህኑም እነዚህን በይሖዋ ፊት ያቀርባቸዋል፤ የሰውየውን የኃጢአት መባና የሚቃጠል መባም ያቀርባል። 17  አውራውንም በግ በቅርጫቱ ውስጥ ካሉት ቂጣዎች ጋር የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ ለይሖዋ ያቀርበዋል፤ ካህኑም የእህል መባውንና የመጠጥ መባውን ያቀርበዋል። 18  “‘ከዚያም ናዝራዊው ያልተቆረጠውን ፀጉሩን በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ይላጭ፤ ናዝራዊ ሆኖ በቆየበት ጊዜ ያደገውን የራሱን ፀጉር ወስዶ ከኅብረት መሥዋዕቱ ሥር ባለው እሳት ውስጥ ይጨምረው። 19  ናዝራዊው የናዝራዊነት ምልክቱን ከተላጨ በኋላ ካህኑ የአውራውን በግ አንድ የተቀቀለ የፊት እግር፣ ከቅርጫቱም ውስጥ እርሾ ያልገባበት የቀለበት ቅርጽ ያለው አንድ ዳቦ እንዲሁም አንድ ስስ ቂጣ ወስዶ በናዝራዊው መዳፍ ላይ ያድርጋቸው። 20  ካህኑም እነዚህን የሚወዘወዝ መባ አድርጎ በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ይወዝውዛቸው። ይህም ከሚወዘወዘው መባ ፍርምባና መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው እግር ጋር ለካህኑ የተቀደሰ ይሆናል። ከዚህ በኋላ ናዝራዊው የወይን ጠጅ መጠጣት ይችላል። 21  “‘ስእለት የሚሳልን ናዝራዊ በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው፦ ናዝራዊው ስእለት ከተሳለና በናዝራዊነት ከሚጠበቅበት በተጨማሪ ለይሖዋ መባ ለማቅረብ አቅሙ የሚፈቅድለት ከሆነ ለናዝራዊነቱ ሕግ ካለው አክብሮት የተነሳ ስእለቱን መፈጸም ይገባዋል።’” 22  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 23  “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ በላቸው፦ ‘የእስራኤልን ሕዝብ የምትባርኩት በዚህ መንገድ ነው። እንዲህ በሏቸው፦ 24  “ይሖዋ ይባርክህ፤ ደግሞም ይጠብቅህ። 25  ይሖዋ ፊቱን ያብራልህ፤ ሞገሱንም ያሳይህ። 26  ይሖዋ ፊቱን ወደ አንተ ይመልስ፤ ሰላምም ይስጥህ።”’ 27  እኔም እንድባርካቸው ስሜን በእስራኤል ሕዝብ ላይ ያድርጉ።”
[]
[]
[]
[]
12,434
7  ሙሴ የማደሪያ ድንኳኑን ተክሎ በጨረሰበት ቀን የማደሪያ ድንኳኑን ከቁሳቁሶቹ ሁሉና ከመሠዊያው እንዲሁም ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር ቀባው፤ ደግሞም ቀደሰው። እነዚህን ነገሮች በቀባቸውና በቀደሳቸው ጊዜ 2  የእስራኤል አለቆች ማለትም የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች መባ አቀረቡ። ምዝገባውን በበላይነት ሲቆጣጠሩ የነበሩት እነዚህ የየነገዱ አለቆች 3  ስድስት ባለ ሽፋን ሠረገሎችንና 12 በሬዎችን ይኸውም ሁለት አለቆች አንድ ሠረገላ፣ እያንዳንዳቸውም አንድ አንድ በሬ መባ አድርገው ወደ ይሖዋ ፊት አመጡ፤ እነዚህንም በማደሪያ ድንኳኑ ፊት አቀረቡ። 4  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 5  “በመገናኛ ድንኳኑ ለሚከናወነው አገልግሎት እንዲውሉ እነዚህን ከእነሱ ተቀበል፤ ለሌዋውያኑም ለእያንዳንዳቸው ለሥራቸው እንደሚያስፈልጋቸው ስጣቸው።” 6  ስለሆነም ሙሴ ሠረገሎቹንና ከብቶቹን ተቀብሎ ለሌዋውያኑ ሰጣቸው። 7  ለጌድሶን ወንዶች ልጆች ለሥራቸው እንደሚያስፈልጋቸው ሁለት ሠረገሎችና አራት በሬዎች ሰጣቸው፤ 8  ለሜራሪ ወንዶች ልጆች ደግሞ በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር አመራር ሥር ሆነው ለሚያከናውኑት ሥራ እንደሚያስፈልጋቸው አራት ሠረገሎችና ስምንት በሬዎች ሰጣቸው። 9  ለቀአት ወንዶች ልጆች ግን ምንም አልሰጣቸውም፤ ምክንያቱም ሥራቸው በቅዱሱ ስፍራ ከሚቀርበው አገልግሎት ጋር የተያያዘ ሲሆን ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች የሚሸከሙት ደግሞ በትከሻቸው ነበር። 10  አለቆቹም መሠዊያው በተቀባበት ዕለት በምርቃቱ ላይ መባቸውን አቀረቡ። አለቆቹ መባቸውን በመሠዊያው ፊት ባቀረቡ ጊዜ 11  ይሖዋ ሙሴን “በየቀኑ አንድ አንድ አለቃ ለመሠዊያው ምርቃት የሚሆነውን መባውን ያቅርብ” አለው። 12  በመጀመሪያው ቀን መባውን ያቀረበው ከይሁዳ ነገድ የሆነው የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበር። 13  መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤ 14  እንዲሁም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 15  ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣ 16  ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት 17  እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ያቀረበው መባ ይህ ነበር። 18  በሁለተኛውም ቀን የይሳኮር አለቃ የሆነው የጹአር ልጅ ናትናኤል መባ አቀረበ። 19  መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤ 20  በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 21  ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣ 22  ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት 23  እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የጹአር ልጅ ናትናኤል ያቀረበው መባ ይህ ነበር። 24  በሦስተኛውም ቀን የዛብሎን ልጆች አለቃ የሆነው የሄሎን ልጅ ኤልያብ 25  መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤ 26  በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 27  ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣ 28  ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት 29  እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የሄሎን ልጅ ኤልያብ ያቀረበው መባ ይህ ነበር። 30  በአራተኛውም ቀን የሮቤል ልጆች አለቃ የሆነው የሸደኡር ልጅ ኤሊጹር 31  መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤ 32  በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 33  ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣ 34  ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት 35  እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የሸደኡር ልጅ ኤሊጹር ያቀረበው መባ ይህ ነበር። 36  በአምስተኛውም ቀን የስምዖን ልጆች አለቃ የሆነው የጹሪሻዳይ ልጅ ሸሉሚኤል 37  መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤ 38  በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 39  ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣ 40  ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት 41  እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የጹሪሻዳይ ልጅ ሸሉሚኤል ያቀረበው መባ ይህ ነበር። 42  በስድስተኛውም ቀን የጋድ ልጆች አለቃ የሆነው የደኡዔል ልጅ ኤሊያሳፍ 43  መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤ 44  በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 45  ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣ 46  ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት 47  እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የደኡዔል ልጅ ኤሊያሳፍ ያቀረበው መባ ይህ ነበር። 48  በሰባተኛውም ቀን የኤፍሬም ልጆች አለቃ የሆነው የአሚሁድ ልጅ ኤሊሻማ 49  መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤ 50  በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 51  ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣ 52  ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት 53   እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የአሚሁድ ልጅ ኤሊሻማ ያቀረበው መባ ይህ ነበር። 54  በስምንተኛውም ቀን የምናሴ ልጆች አለቃ የሆነው የፐዳጹር ልጅ ገማልያል 55  መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤ 56  በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 57   ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣ 58  ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት 59  እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የፐዳጹር ልጅ ገማልያል ያቀረበው መባ ይህ ነበር። 60  በዘጠነኛውም ቀን የቢንያም ልጆች አለቃ የሆነው የጊድኦኒ ልጅ አቢዳን 61  መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤ 62  በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 63  ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣ 64  ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት 65  እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የጊድኦኒ ልጅ አቢዳን ያቀረበው መባ ይህ ነበር። 66  በአሥረኛውም ቀን የዳን ልጆች አለቃ የሆነው የአሚሻዳይ ልጅ አሂዔዜር 67  መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤ 68  በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 69  ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣ 70  ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት 71  እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የአሚሻዳይ ልጅ አሂዔዜር ያቀረበው መባ ይህ ነበር። 72  በ11ኛውም ቀን የአሴር ልጆች አለቃ የሆነው የኦክራን ልጅ ፓጊኤል 73  መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤ 74  በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 75  ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣ 76  ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት 77  እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የኦክራን ልጅ ፓጊኤል ያቀረበው መባ ይህ ነበር። 78  በ12ኛውም ቀን የንፍታሌም ልጆች አለቃ የሆነው የኤናን ልጅ አሂራ 79  መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤ 80  በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 81  ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣ 82  ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት 83  እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የኤናን ልጅ አሂራ ያቀረበው መባ ይህ ነበር። 84  የእስራኤል አለቆች መሠዊያው በተቀባበት ጊዜ ያቀረቡት የመሠዊያው ምርቃት መባ የሚከተለው ነው፦ 12 የብር ሳህኖች፣ 12 የብር ጎድጓዳ ሳህኖች፣ 12 የወርቅ ጽዋዎች፣ 85  እያንዳንዱ የብር ሳህን 130 ሰቅል፣ እያንዳንዱም ጎድጓዳ ሳህን 70 ሰቅል ይመዝን ነበር፤ ዕቃዎቹ የተሠሩበት ብር በአጠቃላይ፣ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 2,400 ሰቅል ነበር፤ 86  ዕጣን የተሞሉት 12 የወርቅ ጽዋዎች ሲመዘኑ እያንዳንዱ ጽዋ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 10 ሰቅል ነበር፤ ጽዋዎቹ የተሠሩበት ወርቅ በአጠቃላይ 120 ሰቅል ነበር። 87  የእህል መባዎቻቸውን ጨምሮ ለሚቃጠል መባ የቀረቡት ከብቶች በአጠቃላይ 12 በሬዎች፣ 12 አውራ በጎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 12 ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ፤ ለኃጢአት መባ የቀረቡት 12 የፍየል ጠቦቶች ነበሩ፤ 88  ለኅብረት መሥዋዕት የቀረቡት ከብቶች በአጠቃላይ 24 በሬዎች፣ 60 አውራ በጎች፣ 60 ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 60 ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። መሠዊያው ከተቀባ በኋላ የቀረበው የመሠዊያው ምርቃት መባ ይህ ነበር። 89  ሙሴ ከአምላክ ጋር ለመነጋገር ወደ መገናኛ ድንኳኑ በሚገባበት ጊዜ ሁሉ ከምሥክሩ ታቦት መክደኛ በላይ ድምፅ ሲያነጋግረው ይሰማ ነበር፤ እሱም ከሁለቱ ኪሩቦች መካከል ያነጋግረው ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,435
8  ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “ለአሮን ‘መብራቶቹን በምታበራበት ጊዜ ሰባቱ መብራቶች በመቅረዙ ፊት ለፊት ላለው አካባቢ ብርሃን መስጠት ይኖርባቸዋል’ ብለህ ንገረው።” 3  አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት በመቅረዙ ፊት ለፊት ያለው አካባቢ ብርሃን እንዲያገኝ የመቅረዙን መብራቶች ለኮሳቸው። 4  የመቅረዙ አሠራር ይህ ነበር፦ አንድ ወጥ ከሆነ ወርቅ ተጠፍጥፎ የተሠራ ነበር፤ ግንዱም ሆነ የፈኩት አበቦቹ ወጥ ከሆነ ወርቅ ተጠፍጥፈው የተሠሩ ነበሩ። መቅረዙ የተሠራው ይሖዋ ለሙሴ ባሳየው ራእይ መሠረት ነበር። 5  ይሖዋ ሙሴን ዳግመኛ እንዲህ አለው፦ 6  “ሌዋውያኑን ከእስራኤላውያን መካከል ወስደህ አንጻቸው። 7  እነሱንም የምታነጻቸው በሚከተለው መንገድ ነው፦ ከኃጢአት የሚያነጻ ውኃ እርጫቸው፤ እነሱም ሰውነታቸውን በሙሉ በምላጭ ይላጩ፤ እንዲሁም ልብሳቸውን ይጠቡ፤ ራሳቸውንም ያንጹ። 8  ከዚያም አንድ ወይፈንና አብሮት የሚቀርበውን በዘይት ከተለወሰ የላመ ዱቄት የተዘጋጀ የእህል መባ ይወስዳሉ፤ አንተም ለኃጢአት መባ እንዲሆን ሌላ ወይፈን ትወስዳለህ። 9  እንዲሁም ሌዋውያኑን በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ታቀርባቸዋለህ፤ መላውን የእስራኤል ማኅበረሰብ ትሰበስባለህ። 10  ሌዋውያኑን በይሖዋ ፊት በምታቀርባቸው ጊዜ እስራኤላውያን በሌዋውያኑ ላይ እጆቻቸውን ይጫኑ። 11  አሮንም ከእስራኤላውያን መካከል ሌዋውያኑን እንደሚወዘወዝ መባ አድርጎ በይሖዋ ፊት ያቅርባቸው፤ እነሱም ለይሖዋ የሚቀርበውን አገልግሎት ያከናውናሉ። 12  “ከዚያም ሌዋውያኑ በወይፈኖቹ ራስ ላይ እጆቻቸውን በመጫን ለእነሱ ማስተሰረያ እንዲሆኑ አንደኛውን ወይፈን የኃጢአት መባ ሌላኛውን ደግሞ የሚቃጠል መባ አድርገው ለይሖዋ ያቀርባሉ። 13  ሌዋውያኑንም በአሮንና በወንዶች ልጆቹ ፊት እንዲቆሙ ካደረግክ በኋላ እንደሚወዘወዝ መባ አድርገህ ለይሖዋ አቅርባቸው። 14  ሌዋውያኑን ከእስራኤላውያን መካከል ለያቸው፤ ሌዋውያኑም የእኔ ይሆናሉ። 15  ከዚህ በኋላ ሌዋውያኑ በመገናኛ ድንኳኑ ለማገልገል ይመጣሉ። እነሱን የምታነጻቸውና እንደሚወዘወዝ መባ አድርገህ የምታቀርባቸው በዚህ መንገድ ነው። 16  ምክንያቱም እነሱ የተሰጡ ይኸውም ከእስራኤላውያን መካከል ለእኔ የተሰጡ ናቸው። በእስራኤላውያን በኩሮች ሁሉ ምትክ እነሱን ለራሴ እወስዳቸዋለሁ። 17  ምክንያቱም ሰውም ሆነ እንስሳ ከእስራኤላውያን መካከል በኩር የሆነ ሁሉ የእኔ ነው። በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ በመታሁበት ቀን እነሱን ለራሴ ቀድሻቸዋለሁ። 18  ሌዋውያኑን በእስራኤላውያን በኩር ሁሉ ምትክ እወስዳቸዋለሁ። 19  የእስራኤል ሕዝብ ወደ ቅዱሱ ስፍራ በመቅረቡ የተነሳ በመካከሉ መቅሰፍት እንዳይከሰት በእስራኤላውያን ምትክ በመገናኛ ድንኳኑ ያገለግሉና ለእነሱ ያስተሰርዩ ዘንድ ከእስራኤላውያን መካከል ሌዋውያኑን ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ የተሰጡ አድርጌ እሰጣቸዋለሁ።” 20  ሙሴ፣ አሮንና መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ሁሉ ለሌዋውያኑ እንዲሁ አደረጉ። እስራኤላውያንም ይሖዋ ሌዋውያኑን አስመልክቶ ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ። 21  በመሆኑም ሌዋውያኑ ራሳቸውን አነጹ፤ ልብሶቻቸውንም አጠቡ፤ በመቀጠልም አሮን እንደሚወዘወዝ መባ አድርጎ በይሖዋ ፊት አቀረባቸው። ከዚያም አሮን እነሱን ለማንጻት ማስተሰረያ አቀረበላቸው። 22  ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ሌዋውያኑ በመገናኛ ድንኳኑ በአሮንና በወንዶች ልጆቹ ፊት አገልግሎታቸውን ለመፈጸም ገቡ። ይሖዋ ሌዋውያኑን በተመለከተ ሙሴን ባዘዘው መሠረት እንዲሁ አደረጉላቸው። 23  በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 24  “ሌዋውያኑን በተመለከተ የተደረገው ዝግጅት የሚከተለው ነው፦ አንድ ወንድ ዕድሜው 25 ዓመትና ከዚያ በላይ ከሆነ በመገናኛ ድንኳኑ ከሚያገለግለው ቡድን ጋር ይቀላቀላል። 25  ዕድሜው 50 ዓመት ከሞላ ግን ከሚያገለግልበት ቡድን ጡረታ ይወጣል፤ ከዚያ በኋላ ማገልገል አይጠበቅበትም። 26  ይህ ሰው በመገናኛ ድንኳኑ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ያሉትን ወንድሞቹን ሊያገለግል ይችላል፤ ሆኖም በዚያ ማገልገል የለበትም። ሌዋውያኑንና የተጣለባቸውን ኃላፊነት በተመለከተ ማድረግ ያለብህ ይህን ነው።”
[]
[]
[]
[]
12,436
9  ከግብፅ ምድር በወጡ በሁለተኛው ዓመት በመጀመሪያው ወር ይሖዋ ሙሴን በሲና ምድረ በዳ እንዲህ በማለት አነጋገረው፦ 2  “እስራኤላውያን የፋሲካን መሥዋዕት በተወሰነለት ጊዜ ያዘጋጁ። 3  በዚህ ወር በ14ኛው ቀን አመሻሹ ላይ በተወሰነለት ጊዜ አዘጋጁት። ደንቦቹን ሁሉና ሥርዓቱን ሁሉ ተከትላችሁ አዘጋጁት።” 4  በመሆኑም ሙሴ እስራኤላውያን የፋሲካን መሥዋዕት እንዲያዘጋጁ ነገራቸው። 5  እነሱም በመጀመሪያው ወር ከወሩም በ14ኛው ቀን አመሻሹ ላይ የፋሲካን መሥዋዕት በሲና ምድረ በዳ አዘጋጁ። እስራኤላውያንም ሁሉንም ነገር ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት አደረጉ። 6  የሞተ ሰው ነክተው በመርከሳቸው የተነሳ በዚያ ቀን የፋሲካን መሥዋዕት ማዘጋጀት ያልቻሉ ሰዎች ነበሩ። በመሆኑም እነዚህ ሰዎች በዚያ ቀን ሙሴና አሮን ፊት ቀረቡ፤ 7  እንዲህም አሉት፦ “እኛ የሞተ ሰው በመንካታችን የተነሳ ረክሰናል። ይሁንና ከእስራኤላውያን ጋር መባውን በተወሰነለት ጊዜ ለይሖዋ እንዳናቀርብ የምንከለከለው ለምንድን ነው?” 8  በዚህ ጊዜ ሙሴ “ይሖዋ እናንተን በተመለከተ የሚሰጠውን ትእዛዝ እስክሰማ ድረስ እዚያ ጠብቁ” አላቸው። 9  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 10  “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘ከእናንተ ወይም ከመጪዎቹ ትውልዶቻችሁ መካከል ማንኛውም ሰው የሞተ ሰው በመንካቱ ቢረክስ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ ለይሖዋ የፋሲካን መሥዋዕት ማዘጋጀት ይጠበቅበታል። 11  እነሱም በሁለተኛው ወር በ14ኛው ቀን አመሻሹ ላይ ያዘጋጁት። ይህንም ከቂጣና ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉት። 12  ከእሱም ላይ እስከ ጠዋት ድረስ ምንም ማስተረፍ ወይም ከአጥንቱ ውስጥ አንዱንም መስበር የለባቸውም። ፋሲካን በተመለከተ የወጣውን ደንብ ሁሉ ተከትለው ያዘጋጁት። 13  ይሁንና አንድ ሰው ንጹሕ ሆኖ ሳለ ወይም ሩቅ መንገድ ሳይሄድ በቸልተኝነት የፋሲካን መሥዋዕት ሳያዘጋጅ ቢቀር፣ ያ ሰው የይሖዋን መባ በተወሰነለት ጊዜ ስላላቀረበ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ። ይህ ሰው ለሠራው ኃጢአት ይጠየቅበታል። 14  “‘በመካከላችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ካለ እሱም ለይሖዋ የፋሲካን መሥዋዕት ማዘጋጀት አለበት። ይህን በፋሲካው ደንብና በወጣለት ሥርዓት መሠረት ማድረግ አለበት። ለሁላችሁም ማለትም ለባዕድ አገሩም ሰው ሆነ ለአገሬው ተወላጅ አንድ ዓይነት ደንብ ይኑር።’” 15  የማደሪያ ድንኳኑ በተተከለበት ቀን ደመናው የማደሪያ ድንኳኑን ይኸውም የምሥክሩን ድንኳን ሸፈነው፤ ሆኖም ከምሽት ጀምሮ እስከ ጠዋት ድረስ በማደሪያ ድንኳኑ ላይ እሳት የሚመስል ነገር ታየ። 16  ሁልጊዜም እንዲህ ይሆን ነበር፦ ቀን ቀን ደመናው ድንኳኑን ይሸፍነው ነበር፤ ሌሊት ሌሊት ደግሞ እሳት የሚመስል ነገር ይታይ ነበር። 17  ደመናው ከድንኳኑ ላይ በሚነሳበት ጊዜ ሁሉ እስራኤላውያን ወዲያውኑ ተነስተው ይጓዙ ነበር፤ ደመናው በሚቆምበት ቦታ ደግሞ እስራኤላውያን ይሰፍሩ ነበር። 18  እስራኤላውያን ተነስተው የሚጓዙት በይሖዋ ትእዛዝ ነበር፤ የሚሰፍሩትም በይሖዋ ትእዛዝ ነበር። ደመናው በማደሪያ ድንኳኑ ላይ በሚቆይባቸው ቀናት ሁሉ እነሱም በሰፈሩበት ቦታ ይቆዩ ነበር። 19  ደመናው በማደሪያ ድንኳኑ ላይ ረዘም ላሉ ቀናት በሚቆይበትም ጊዜ እስራኤላውያን ይሖዋን በመታዘዝ ባሉበት ይቆዩ ነበር። 20  አንዳንድ ጊዜ ደመናው በማደሪያ ድንኳኑ ላይ የሚቆየው ለጥቂት ቀናት ነበር። እነሱም የሚሰፍሩት በይሖዋ ትእዛዝ ነበር፤ ተነስተው የሚጓዙትም በይሖዋ ትእዛዝ ነበር። 21  አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ደመናው የሚቆየው ከምሽት እስከ ጠዋት ድረስ ብቻ ነበር፤ ጠዋት ላይ ደመናው ሲነሳ እነሱም ተነስተው ይጓዛሉ። ቀንም ሆነ ሌሊት ደመናው በሚነሳበት ጊዜ እነሱም ተነስተው ይጓዛሉ። 22  እስራኤላውያን ደመናው በማደሪያ ድንኳኑ ላይ እስካለ ድረስ ለሁለት ቀንም ይሁን ለአንድ ወር ወይም ረዘም ላለ ጊዜ በሰፈሩበት ይቆያሉ እንጂ ተነስተው አይጓዙም። ደመናው በሚነሳበት ጊዜ ግን ተነስተው ይጓዛሉ። 23  እነሱም የሚሰፍሩት በይሖዋ ትእዛዝ ነበር፤ ተነስተውም የሚጓዙት በይሖዋ ትእዛዝ ነበር። ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ይሖዋ የጣለባቸውን ግዴታ ይወጡ ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,437
1  ይሖዋም ሙሴን ጠርቶ ከመገናኛ ድንኳኑ እንዲህ ሲል አናገረው፦ 2  “እስራኤላውያንን አናግራቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ከእናንተ መካከል ማንኛችሁም ከቤት እንስሳት ለይሖዋ መባ ማቅረብ ከፈለጋችሁ መባችሁን ከከብቶች ወይም ከመንጎች መካከል ማቅረብ አለባችሁ። 3  “‘የሰውየው መባ ከከብቶች መካከል ተወስዶ የሚቀርብ የሚቃጠል መባ ከሆነ እንከን የሌለበትን ተባዕት እንስሳ ማቅረብ ይኖርበታል። መባውን በራሱ ፈቃድ ተነሳስቶ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በይሖዋ ፊት ማቅረብ ይኖርበታል። 4  ለሚቃጠል መባ በሚቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ይጫን፤ መባውም ለሰውየው ማስተሰረያ ይሆን ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል። 5  “‘ከዚያም ወይፈኑ በይሖዋ ፊት ይታረድ፤ ካህናት የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን ያቅርቡት፤ እንዲሁም ደሙን በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በሚገኘው መሠዊያ ጎኖች ሁሉ ላይ ይርጩት። 6  የሚቃጠለውም መባ መገፈፍና መቆራረጥ ይኖርበታል። 7  ካህናት የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆችም በመሠዊያው ላይ እሳት ያንድዱ፤ በእሳቱም ላይ እንጨት ይረብርቡበት። 8  እነሱም ተቆራርጦ የተዘጋጀውን መባ ከጭንቅላቱና ከሞራው ጋር በመሠዊያው ላይ ባለው እሳት ላይ በሚገኘው እንጨት ላይ ይደርድሩት። 9  ሆድ ዕቃውና እግሮቹም በውኃ ይታጠቡ፤ ካህኑም የሚቃጠል መባ ይኸውም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ ሙሉውን በመሠዊያው ላይ ያጭሰው። 10  “‘ሰውየው የሚቃጠል መባ እንዲሆን የሚያቀርበው መባ ከመንጋው ማለትም ከበግ ጠቦቶቹ ወይም ከፍየሎቹ መካከል የተወሰደ ከሆነ እንከን የሌለበትን ተባዕት ያቅርብ። 11  በስተ ሰሜን በኩል ባለው የመሠዊያው ጎን በይሖዋ ፊት ይታረድ፤ ካህናት የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ይርጩት። 12  እሱም ጭንቅላቱንና ሞራውን ጨምሮ እንስሳውን በየብልቱ ይቆራርጠዋል፤ ካህኑም በመሠዊያው ላይ ባለው እሳት ላይ በሚገኘው እንጨት ላይ ይደረድራቸዋል። 13  ሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ ያጥባቸዋል፤ ካህኑም ሙሉውን ያቀርበዋል፤ እንዲሁም በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርገዋል። ይህም የሚቃጠል መባ ማለትም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ ነው። 14  “‘ሆኖም ሰውየው አእዋፋትን ለይሖዋ የሚቃጠል መባ አድርጎ የሚያቀርብ ከሆነ መባውን ከዋኖሶች ወይም ከርግብ ጫጩቶች መካከል ያቀርባል። 15  ካህኑም በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል፤ እንዲሁም አንገቱ ላይ ቦጭቆ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርገዋል። ደሙ ግን በመሠዊያው ጎን ይንጠፍጠፍ። 16  ቋቱንና ላባዎቹንም ከለየ በኋላ ከመሠዊያው አጠገብ በስተ ምሥራቅ በኩል ወዳለው አመድ ወደሚደፋበት ቦታ ይወርውራቸው። 17  ሙሉ በሙሉ ለሁለት ሳይለያየው ክንፎቹን ይዞ ይሰነጥቀዋል። ከዚያም ካህኑ በመሠዊያው ላይ ይኸውም በእሳቱ ላይ ባለው እንጨት ላይ እንዲጨስ ያደርገዋል። ይህም የሚቃጠል መባ ማለትም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ ነው።
[]
[]
[]
[]
12,438
10  በኋላም የአሮን ወንዶች ልጆች ናዳብና አቢሁ እያንዳንዳቸው የዕጣን ማጨሻቸውን አምጥተው በላዩ ላይ እሳት አደረጉበት፤ በእሳቱም ላይ ዕጣን ጨመሩበት። ከዚያም ይሖዋ እንዲያደርጉ ያላዘዛቸውን ያልተፈቀደ እሳት በፊቱ አቀረቡ። 2  በዚህ ጊዜ እሳት ከይሖዋ ፊት ወጥቶ በላቸው፤ እነሱም በይሖዋ ፊት ሞቱ። 3  ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡ ሰዎች መካከል እቀደሳለሁ፤ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከበራለሁ’ ብሏል።” አሮንም ዝም አለ። 4  ሙሴም የአሮን አጎት የዑዚኤል ልጆች የሆኑትን ሚሳኤልንና ኤሊጻፋንን ጠርቶ “ኑ፣ ወንድሞቻችሁን ከቅዱሱ ስፍራ ፊት ለፊት አንስታችሁ ከሰፈሩ ውጭ ወዳለው ቦታ አውጧቸው” አላቸው። 5  ስለዚህ መጥተው ልክ ሙሴ በነገራቸው መሠረት ሟቾቹን ከነቀሚሳቸው ተሸክመው ከሰፈሩ ውጭ አወጧቸው። 6  ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲሁም ሌሎቹን የአሮን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፦ “እንዳትሞቱ እንዲሁም አምላክ በመላው ማኅበረሰብ ላይ እንዳይቆጣ ፀጉራችሁን አታንጨብርሩ ወይም ልብሶቻችሁን አትቅደዱ። ሆኖም ወንድሞቻችሁ ይኸውም መላው የእስራኤል ቤት ይሖዋ በእሳት ለገደላቸው ያለቅሱላቸዋል። 7  የይሖዋ የቅብዓት ዘይት በላያችሁ ላይ ስላለ ከመገናኛ ድንኳኑ ደጃፍ መራቅ የለባችሁም፤ አለዚያ ትሞታላችሁ።” እነሱም ሙሴ እንዳላቸው አደረጉ። 8  ከዚያም ይሖዋ አሮንን እንዲህ አለው፦ 9  “እንዳትሞቱ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ስትገቡ አንተም ሆንክ ከአንተ ጋር ያሉት ወንዶች ልጆችህ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጡ። ይህ ትእዛዝ ለትውልዶቻችሁ ሁሉ ዘላለማዊ ደንብ ነው። 10  ይህም ቅዱስ የሆነውን ከረከሰው ነገር እንዲሁም ንጹሕ ያልሆነውን ንጹሕ ከሆነው ነገር ለመለየት 11  እንዲሁም ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት የሰጣቸውን ሥርዓቶች በሙሉ ለእስራኤላውያን ለማስተማር ነው።” 12  ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲሁም የተረፉትን የአሮን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፦ “ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች የተረፈውን የእህል መባ ወስዳችሁ ያለእርሾ በማዘጋጀት በመሠዊያው አጠገብ ብሉት፤ ምክንያቱም ይህ እጅግ ቅዱስ ነገር ነው። 13  ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች ላይ ይህ የአንተ ድርሻና የወንዶች ልጆችህ ድርሻ ስለሆነ ቅዱስ በሆነ ስፍራ ብሉት፤ ምክንያቱም እንዲህ እንዳደርግ ታዝዣለሁ። 14  እንዲሁም የሚወዘወዘውን መባ ፍርምባና የቅዱሱን ድርሻ እግር አንተም ሆንክ ከአንተ ጋር ያሉት ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ንጹሕ በሆነ ስፍራ ትበሉታላችሁ፤ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች እስራኤላውያን ከሚያቀርቧቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ላይ የአንተ ድርሻና የወንዶች ልጆችህ ድርሻ ሆነው የተሰጡ ናቸው። 15  እነሱም የቅዱሱን ድርሻ እግርና የሚወዘወዘውን መባ ፍርምባ በእሳት ከሚቀርቡት የስብ መባዎች ጋር ያመጣሉ፤ ይህን የሚያደርጉት የሚወዘወዘውን መባ በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ለመወዝወዝ ነው፤ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረትም ይህ ለአንተና ከአንተ ጋር ላሉት ወንዶች ልጆችህ ዘላለማዊ ድርሻ ሆኖ ያገለግላል።” 16  ሙሴም ለኃጢአት መባ የሚሆነውን ፍየል በደንብ አፈላለገ፤ በኋላም ፍየሉ መቃጠሉን ተረዳ። በመሆኑም የተረፉትን የአሮን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን ተቆጣቸው፤ እንዲህም አላቸው፦ 17  “ይህ መባ እጅግ ቅዱስ ነገር ሆኖ ሳለና መባውንም የሰጣችሁ የማኅበረሰቡን ኃጢአት እንድትሸከሙ እንዲሁም በይሖዋ ፊት እንድታስተሰርዩላቸው ሆኖ ሳለ የኃጢአት መባውን በቅዱሱ ስፍራ ያልበላችሁት ለምንድን ነው? 18  ይኸው ደሙ ወደ ቅዱሱ ስፍራ አልገባም። ልክ እንደታዘዝኩት በቅዱሱ ስፍራ ልትበሉት ይገባችሁ ነበር።” 19  በዚህ ጊዜ አሮን ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ እነሱ በዛሬው ዕለት የኃጢአት መባቸውንና የሚቃጠል መባቸውን በይሖዋ ፊት ያቀረቡት እኔ እንዲህ ያለ ነገር ደርሶብኝ እያለ ነው። ታዲያ ዛሬ የኃጢአት መባውን በልቼ ቢሆን ኖሮ ይሖዋ ይደሰት ነበር?” 20  ሙሴም ይህን ሲሰማ ነገሩ አጥጋቢ ሆኖ አገኘው።
[]
[]
[]
[]
12,439
11  ከዚያም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ 2  “እስራኤላውያንን እንዲህ በሏቸው፦ ‘በምድር ላይ ካሉ ሕያዋን ፍጥረታት መካከል እነዚህን መብላት ትችላላችሁ፦ 3  ሰኮናው የተሰነጠቀውንና ስንጥቁም ሙሉ በሙሉ የተከፈለውን እንዲሁም የሚያመሰኳውን ማንኛውንም እንስሳ መብላት ትችላላችሁ። 4  “‘ሆኖም የሚያመሰኩትን ወይም ሰኮናቸው የተሰነጠቀውን እነዚህን እንስሳት መብላት የለባችሁም፦ ግመል የሚያመሰኳ ቢሆንም ሰኮናው የተሰነጠቀ አይደለም። ለእናንተ ርኩስ ነው። 5  ሽኮኮም መብላት የለባችሁም፤ ምክንያቱም የሚያመሰኳ ቢሆንም ሰኮናው የተሰነጠቀ አይደለም። ለእናንተ ርኩስ ነው። 6  ጥንቸልም ብትሆን መብላት የለባችሁም፤ ምክንያቱም የምታመሰኳ ብትሆንም ሰኮናዋ የተሰነጠቀ አይደለም። ለእናንተ ርኩስ ነች። 7  አሳማም መብላት የለባችሁም፤ ሰኮናው የተሰነጠቀና ስንጥቁ ሙሉ በሙሉ የተከፈለ ቢሆንም እንኳ አያመሰኳም። ለእናንተ ርኩስ ነው። 8  የእነዚህን እንስሳት ሥጋ አትብሉ ወይም በድናቸውን አትንኩ። እነዚህ ለእናንተ ርኩስ ናቸው። 9  “‘በውኃዎች ውስጥ ካሉት መካከል እነዚህን መብላት ትችላላችሁ፦ በባሕርም ሆነ በወንዞች፣ በውኃዎች ውስጥ ካሉት መካከል ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ሁሉ መብላት ትችላላችሁ። 10  በውኃዎች ውስጥ ካሉ የሚርመሰመሱ ፍጥረታትና ሌሎች ሕይወት ያላቸው ፍጥረታት ሁሉ መካከል በባሕርና በወንዞች ውስጥ የሚገኙ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ሁሉ ግን ለእናንተ አስጸያፊ ናቸው። 11  አዎ፣ እነዚህን ልትጸየፏቸው ይገባል፤ ሥጋቸውን ፈጽሞ አትብሉ፤ በድናቸውንም ተጸየፉት። 12  በውኃዎች ውስጥ የሚኖሩ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ሁሉ ለእናንተ አስጸያፊ ናቸው። 13  “‘ልትጸየፏቸው የሚገቡ በራሪ ፍጥረታት እነዚህ ናቸው፤ አስጸያፊ በመሆናቸው መበላት የለባቸውም፦ ንስር፣ ዓሣ በል ጭላት፣ ጥቁር ጥምብ አንሳ፣ 14  ቀይ ጭልፊት፣ ማንኛውም ዓይነት ጥቁር ጭልፊት፣ 15  ማንኛውም ዓይነት ቁራ፣ 16  ሰጎን፣ ጉጉት፣ ዓሣ አዳኝ፣ ማንኛውም ዓይነት ሲላ፣ 17  ትንሿ ጉጉት፣ ለማሚት፣ ባለ ረጅም ጆሮ ጉጉት፣ 18  ዝይ፣ ሻላ፣ ጥምብ አንሳ፣ 19  ራዛ፣ ማንኛውም ዓይነት ሽመላ፣ ጅንጅላቴና የሌሊት ወፍ። 20  በአራቱም እግሩ የሚሄድ ክንፍ ያለው የሚርመሰመስ ፍጡር ሁሉ ለእናንተ አስጸያፊ ነው። 21  “‘በአራቱም እግራቸው ከሚሄዱ ክንፍ ካላቸው የሚርመሰመሱ ፍጥረታት መካከል መብላት የምትችሉት ከእግሮቻቸው በላይ በመሬት ላይ ለመፈናጠር የሚያገለግል የሚተጣጠፍ ቅልጥም ያላቸውን ብቻ ነው። 22  ከእነዚህም መካከል የሚከተሉትን መብላት ትችላላችሁ፦ የተለያየ ዓይነት የሚፈልስ አንበጣ፣ ሌሎች የሚበሉ አንበጦች፣ እንጭራሪቶችና ፌንጣዎች። 23  አራት እግር ኖሯቸው ክንፍ ያላቸው ሌሎች የሚርመሰመሱ ፍጥረታት ሁሉ ለእናንተ አስጸያፊ ናቸው። 24  በእነዚህ ራሳችሁን ታረክሳላችሁ። በድናቸውን የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። 25  ከእነዚህ መካከል የማናቸውንም በድን የሚያነሳ ሁሉ ልብሶቹን ይጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 26  “‘ሰኮናው የተሰነጠቀ፣ ስንጥቁ ግን ሙሉ በሙሉ ያልተከፈለ እንዲሁም የማያመሰኳ ማንኛውም እንስሳ ለእናንተ ርኩስ ነው። የሚነካቸውም ሁሉ ርኩስ ይሆናል። 27  በአራቱም እግራቸው ከሚሄዱ ፍጥረታት መካከል በመዳፋቸው የሚሄዱ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ለእናንተ ርኩስ ናቸው። በድናቸውን የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። 28  በድናቸውን የሚያነሳ ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። እነዚህ ለእናንተ ርኩስ ናቸው። 29  “‘ለእናንተ ርኩስ የሆኑት በምድር ላይ የሚርመሰመሱ ፍጥረታት እነዚህ ናቸው፦ ፍልፈል፣ አይጥ፣ ማንኛውም ዓይነት እንሽላሊት፣ 30  ጌኮ፣ ገበሎ፣ የውኃ እንሽላሊት፣ የአሸዋ እንሽላሊትና እስስት። 31  እነዚህ የሚርመሰመሱ ፍጥረታት ለእናንተ ርኩስ ናቸው። በድናቸውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። 32  “‘በሚሞቱበት ጊዜ የወደቁበት ማንኛውም ነገር ይኸውም የእንጨት ዕቃም ሆነ ልብስ ወይም ቆዳ አሊያም ደግሞ በርኖስ ርኩስ ይሆናል። አገልግሎት ላይ የሚውል ማንኛውም ዕቃ ውኃ ውስጥ ይነከር፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም ይነጻል። 33  በሸክላ ዕቃ ውስጥ ከወደቁ ዕቃውን ሰባብሩት፤ በውስጡ ያለውም ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል። 34  እንዲህ ባለ ዕቃ ውስጥ የነበረ ውኃ የነካው ማንኛውም ዓይነት ምግብ ርኩስ ይሆናል፤ በእንዲህ ዓይነቱ ዕቃ ውስጥ የነበረ የሚጠጣ ማንኛውም ዓይነት መጠጥም ርኩስ ይሆናል። 35  በድናቸው የወደቀበት ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል። መጋገሪያ ምድጃም ይሁን አነስተኛ ምድጃ ይሰበር። እነዚህ ነገሮች ርኩስ ናቸው፤ ለእናንተም ርኩስ ይሆናሉ። 36  ምንጭና የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ብቻ ንጹሕ ይሆናሉ፤ ይሁንና በድኑን የነካ ማንኛውም ሰው ርኩስ ይሆናል። 37  በድናቸው በሚዘራ ዘር ላይ ቢወድቅ ዘሩ ንጹሕ ነው። 38  ይሁንና በዘሩ ላይ ውኃ ተደርጎበት ሳለ የበድናቸው አንዱ ክፍል ዘሩ ላይ ቢወድቅ ዘሩ ለእናንተ ርኩስ ይሆናል። 39  “‘እንድትበሉ ከተፈቀደላችሁ እንስሳ አንዱ ቢሞት የእንስሳውን በድን የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። 40  ከበድኑ የበላ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። በድኑን ያነሳ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 41  በምድር ላይ የሚርመሰመስ ማንኛውም ፍጥረት አስጸያፊ ነው። መበላት የለበትም። 42  በሆዱ የሚሳብን ማንኛውም ፍጥረት፣ በአራቱም እግሩ የሚሄድን ማንኛውም ፍጥረት ወይም ብዙ እግሮች ያሉትን በምድር ላይ የሚርመሰመስ ማንኛውም ፍጥረት መብላት የለባችሁም፤ ምክንያቱም አስጸያፊ ናቸው። 43  በምድር ላይ በሚርመሰመስ በማንኛውም ፍጥረት ራሳችሁን አስጸያፊ አታድርጉ፤ በእነሱም ራሳችሁን በመበከል አትርከሱ። 44  እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝና፤ እኔ ቅዱስ ስለሆንኩ እናንተም ራሳችሁን ልትቀድሱና ቅዱስ ልትሆኑ ይገባል። በምድር ላይ በሚንቀሳቀስ በማንኛውም የሚርመሰመስ ፍጥረት ራሳችሁን አታርክሱ። 45  አምላካችሁ መሆኔን ለማስመሥከር ከግብፅ ምድር መርቼ ያወጣኋችሁ እኔ ይሖዋ ነኝና፤ እኔ ቅዱስ ስለሆንኩ እናንተም ቅዱሳን መሆን አለባችሁ። 46  “‘እንስሳትን፣ የሚበርሩ ፍጥረታትን፣ በውኃዎች ውስጥ የሚንቀሳቀስን ማንኛውም ዓይነት ሕያው ፍጡር እንዲሁም በምድር ላይ የሚርመሰመስን ፍጡር ሁሉ በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው፤ 47  ርኩስ የሆነውንና ንጹሕ የሆነውን እንዲሁም ለመብል የሚሆነውንና ለመብል የማይሆነውን ሕያው ፍጡር ለመለየት ሕጉ ይህ ነው።’”
[]
[]
[]
[]
12,440
12  ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘አንዲት ሴት ብታረግዝና ወንድ ልጅ ብትወልድ በወር አበባዋ ወቅት እንደምትረክሰው ሁሉ ለሰባት ቀን ትረክሳለች። 3  ሕፃኑም በስምንተኛው ቀን ይገረዛል። 4  እሷም ከደም ራሷን ለማንጻት ለቀጣዮቹ 33 ቀናት ትቆያለች። የምትነጻባቸው ቀናት እስኪያበቁ ድረስ ምንም ዓይነት ቅዱስ ነገር መንካትም ሆነ ወደ ቅዱሱ ስፍራ መግባት የለባትም። 5  “‘ሴት ልጅ ከወለደች ደግሞ በወር አበባዋ ወቅት እንደምትረክሰው ሁሉ ለ14 ቀን ትረክሳለች። ከደም ራሷን ለማንጻትም ለቀጣዮቹ 66 ቀናት ትቆያለች። 6  ሴትየዋ ወንድ ልጅ ወይም ሴት ልጅ ወልዳ የመንጻቷ ጊዜ ሲያበቃ ለሚቃጠል መባ እንዲሆን አንድ ዓመት ገደማ የሆነው የበግ ጠቦት፣ ለኃጢአት መባ እንዲሆን ደግሞ አንድ የርግብ ጫጩት ወይም አንድ ዋኖስ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ወደ ካህኑ ታመጣለች። 7  እሱም መባዎቹን በይሖዋ ፊት በማቅረብ ያስተሰርይላታል፤ እሷም ከሚፈሳት ደም ትነጻለች። ወንድ ልጅም ሆነ ሴት ልጅ ለወለደች ሴት የሚሠራው ሕግ ይህ ነው። 8  ሆኖም ሴትየዋ በግ ለማቅረብ አቅሟ የማይፈቅድላት ከሆነ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች ታምጣ፤ አንዱ ለሚቃጠል መባ ሌላው ደግሞ ለኃጢአት መባ ይሆናል። ካህኑም ያስተሰርይላታል፤ እሷም ንጹሕ ትሆናለች።’”
[]
[]
[]
[]
12,441
13  ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ 2  “አንድ ሰው በቆዳው ላይ እብጠት፣ እከክ ወይም ቋቁቻ ቢወጣበትና ወደ ሥጋ ደዌነት ቢለወጥበት ወደ ካህኑ አሮን ወይም ካህናት ከሆኑት ወንዶች ልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት። 3  ካህኑም በቆዳው ላይ ያለውን ቁስል ይመረምራል። ቁስሉ ባለበት ቦታ ላይ ያለው ፀጉር ወደ ነጭነት ከተለወጠና ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ከሆነ ይህ የሥጋ ደዌ ነው። ካህኑ ቁስሉን ከመረመረ በኋላ ግለሰቡ ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። 4  ሆኖም በቆዳው ላይ ያለው ቋቁቻ ነጭ ከሆነና ከቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ እንዲሁም በዚያ ቦታ ላይ ያለው ፀጉር ወደ ነጭነት ካልተለወጠ ካህኑ ቁስል የወጣበትን ሰው ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቆይ ያደርገዋል። 5  ከዚያም በሰባተኛው ቀን ካህኑ ሰውየውን ይመረምረዋል፤ ቁስሉ ባለበት ከቆመና በቆዳው ላይ ካልተስፋፋ ካህኑ ሰውየውን ለተጨማሪ ሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቆይ ያደርገዋል። 6  “ካህኑም በሰባተኛው ቀን እንደገና ሰውየውን ይመርምረው፤ ቁስሉ ከከሰመና በቆዳው ላይ ካልተስፋፋ ካህኑ ሰውየው ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል፤ ይህ እከክ ነው። ከዚያም ሰውየው ልብሶቹን ያጥባል፤ ንጹሕም ይሆናል። 7  ሆኖም ሰውየው መንጻቱን ለማረጋገጥ ካህኑ ፊት ከቀረበ በኋላ እከኩ በቆዳው ላይ እየተስፋፋ ከሄደ እንደገና ካህኑ ፊት ይቀርባል። 8  ካህኑም ይመረምረዋል፤ እከኩ በቆዳው ላይ ተስፋፍቶ ከሆነ ካህኑ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። ይህ የሥጋ ደዌ ነው። 9  “አንድ ሰው የሥጋ ደዌ ቢይዘው ወደ ካህኑ እንዲቀርብ ይደረግ፤ 10  ካህኑም ይመረምረዋል። በቆዳው ላይ ነጭ እብጠት ካለና በዚያ ቦታ ላይ ያለውን ፀጉር ወደ ነጭነት ከለወጠው እንዲሁም በእብጠቱ ላይ አፉን የከፈተ ቁስል ካለ 11  ይህ በቆዳው ላይ የወጣ ሥር የሰደደ የሥጋ ደዌ ነው፤ ካህኑም ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። ሰውየው ርኩስ ስለሆነም ለተወሰነ ጊዜ ተገልሎ እንዲቆይ ማድረግ አያስፈልገውም። 12  የሥጋ ደዌው በቆዳው ሁሉ ላይ ቢወጣና የሥጋ ደዌው ካህኑ ሊያየው እስከሚችለው ድረስ ግለሰቡን ከራሱ አንስቶ እስከ እግሮቹ ድረስ ቢያለብሰው 13  እንዲሁም ካህኑ ሲመረምረው የሥጋ ደዌው ቆዳውን ሁሉ አልብሶት ቢያይ ቁስሉ የወጣበት ግለሰብ ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል። ቆዳው ሙሉ በሙሉ ወደ ነጭነት ተለውጧል፤ ሰውየውም ንጹሕ ነው። 14  ሆኖም በቆዳው ላይ አፉን የከፈተ ቁስል በወጣበት በማንኛውም ጊዜ ሰውየው ርኩስ ይሆናል። 15  ካህኑ አፉን የከፈተ ቁስል ካየ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። አፉን የከፈተው ቁስል ርኩስ ነው። ይህ የሥጋ ደዌ ነው። 16  ሆኖም አፉን የከፈተው ቁስል እንደገና ወደ ነጭነት ከተለወጠ ሰውየው ወደ ካህኑ ይመጣል። 17  ካህኑም ይመረምረዋል፤ ቁስሉ ወደ ነጭነት ከተለወጠ ካህኑ ቁስሉ የወጣበት ግለሰብ ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል። ሰውየው ንጹሕ ነው። 18  “አንድ ሰው በቆዳው ላይ እባጭ ቢወጣበትና ቢድን 19  ሆኖም እባጩ በነበረበት ቦታ ላይ ነጭ እብጠት ወይም ነጣ ያለ ቀይ ቋቁቻ ቢወጣ ሰውየው ራሱን ለካህን ያሳይ። 20  ካህኑም ቁስሉን ይመረምረዋል፤ ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ከሆነና በዚያ ቦታ ላይ ያለው ፀጉር ወደ ነጭነት ከተለወጠ ካህኑ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። ይህ በእባጩ ላይ የወጣ የሥጋ ደዌ ነው። 21  ይሁንና ካህኑ ቁስሉን ሲመረምረው በላዩ ላይ ነጭ ፀጉር ከሌለና ከቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ እንዲሁም እየከሰመ ከሆነ ካህኑ ሰውየውን ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቆይ ያደርገዋል። 22  ቁስሉ በቆዳው ላይ እየተስፋፋ መሆኑ በግልጽ የሚታይ ከሆነ ካህኑ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። ይህ ደዌ ነው። 23  ይሁን እንጂ ቋቁቻው ባለበት ከቆመና ካልተስፋፋ ይህ እባጩ ያስከተለው ቁስል ነው፤ ካህኑም ሰውየው ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል። 24  “ወይም አንድ ሰው እሳት አቃጥሎት በሰውነቱ ቆዳ ላይ ጠባሳ ቢተውና ጠባሳው ላይ ያለው ያልሻረ ቁስል ነጣ ያለ ቀይ ወይም ነጭ ቋቁቻ ቢሆን 25  ካህኑ ቁስሉን ይመረምረዋል። በቋቁቻው ላይ ያለው ፀጉር ወደ ነጭነት ከተለወጠና ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ከሆነ ይህ በጠባሳው ላይ የወጣ የሥጋ ደዌ ነው፤ ካህኑም ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። ይህ የሥጋ ደዌ ነው። 26  ይሁንና ካህኑ ሲመረምረው በቋቁቻው ላይ ነጭ ፀጉር ከሌለና ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ እንዲሁም እየከሰመ ከሆነ ካህኑ ሰውየውን ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቆይ ያደርገዋል። 27  ካህኑም በሰባተኛው ቀን ሰውየውን ይመረምረዋል፤ ቁስሉ በቆዳው ላይ እየተስፋፋ መሆኑ በግልጽ የሚታይ ከሆነ ካህኑ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። ይህ የሥጋ ደዌ ነው። 28  ይሁንና ቋቁቻው ባለበት ከቆመና በቆዳው ላይ ካልተስፋፋ እንዲሁም ከከሰመ ይህ ጠባሳው ያስከተለው እብጠት ነው፤ ይህ የጠባሳው ቁስል ስለሆነ ካህኑ ሰውየው ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል። 29  “በአንድ ወንድ ወይም በአንዲት ሴት ራስ ወይም አገጭ ላይ ቁስል ቢወጣ 30  ካህኑ ቁስሉን ይመረምረዋል። ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ከሆነ እንዲሁም በዚያ ቦታ ላይ ያለው ፀጉር ቢጫ ከሆነና ከሳሳ ካህኑ ያ ሰው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል፤ ይህ በራስ ቆዳ ወይም በጢም ላይ የሚወጣ ቁስል ነው። ይህ የራስ ወይም የአገጭ የሥጋ ደዌ ነው። 31  ሆኖም ካህኑ ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ አለመሆኑንና በዚያ ቦታ ላይ ጥቁር ፀጉር አለመኖሩን ካየ ቁስሉ የወጣበትን ሰው ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቆይ ያድርገው። 32  ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቁስሉን ይመረምረዋል፤ ቁስሉ ካልተስፋፋና በዚያ ቦታ ላይ ቢጫ ፀጉር ካልወጣ እንዲሁም ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ 33  ሰውየው ፀጉሩን ይላጭ፤ ቁስሉ ያለበትን ቦታ ግን አይላጨውም። ከዚያም ካህኑ ቁስሉ የወጣበትን ሰው ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቆይ ያደርገዋል። 34  “ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቁስሉ ያለበትን ቦታ እንደገና ይመረምረዋል፤ ቁስሉ በቆዳው ላይ ካልተስፋፋና ከቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ ካህኑ ሰውየው ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ፤ ሰውየውም ልብሶቹን ይጠብ፤ ንጹሕም ይሁን። 35  ሆኖም ሰውየው ከነጻ በኋላ ቁስሉ በቆዳው ላይ እየተስፋፋ መሆኑ በግልጽ ከታየ 36  ካህኑ ይመረምረዋል፤ ቁስሉ በቆዳው ላይ ከተስፋፋ ካህኑ ቢጫ ፀጉር መኖር አለመኖሩን ማየት አያስፈልገውም፤ ሰውየው ርኩስ ነው። 37  ሆኖም ካህኑ ሲመረምረው ቁስሉ ካልተስፋፋና በዚያ ቦታ ጥቁር ፀጉር ከበቀለ ቁስሉ ድኗል ማለት ነው። ሰውየው ንጹሕ ነው፤ ካህኑም ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል። 38  “አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት በቆዳቸው ላይ ቋቁቻ ቢወጣና ቋቁቻው ደግሞ ነጭ ቢሆን 39  ካህኑ ይመረምራቸዋል። በቆዳው ላይ የወጣው ቋቁቻ ደብዘዝ ያለ ነጭ ከሆነ ይህ ቆዳው ላይ የወጣ ጉዳት የሌለው ሽፍታ ነው። ሰውየው ንጹሕ ነው። 40  “አንድ ወንድ ራሱ ቢመለጥና ራሰ በራ ቢሆን ሰውየው ንጹሕ ነው። 41  ሰውየው ከፊት በኩል ቢመለጥና ራሰ በራ ቢሆን ንጹሕ ነው። 42  ሆኖም በራሱ ወይም በግንባሩ ላይ ባለው በራ ላይ ቀላ ያለ ነጭ ቁስል ቢወጣበት ይህ በራሱ ወይም በግንባሩ ላይ የወጣ ሥጋ ደዌ ነው። 43  ካህኑም ሰውየውን ይመረምረዋል፤ በአናቱ ወይም በግንባሩ ላይ ባለው በራ ላይ የወጣው ቁስል ያስከተለው እብጠት ቀላ ያለ ነጭ ከሆነና በቆዳው ላይ ሲታይ የሥጋ ደዌ የሚመስል ከሆነ 44  ሰውየው የሥጋ ደዌ በሽተኛ ነው። ርኩስ ነው፤ በራሱም ላይ ባለው ደዌ የተነሳ ካህኑ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቅ። 45  የሥጋ ደዌ ያለበት ሰው ልብሶቹ የተቀዳደዱ ይሁኑ፤ ፀጉሩም ይንጨብረር፤ አፍንጫው ሥር እስካለው ጢም ድረስ ተሸፋፍኖ ‘ርኩስ ነኝ፣ ርኩስ ነኝ!’ እያለ ይጩኽ። 46  ሰውየው ደዌው በላዩ ላይ ባለበት ጊዜ ሁሉ ርኩስ ይሆናል። ርኩስ ስለሆነም ከሰዎች ተገልሎ መኖር አለበት። መኖሪያውም ከሰፈሩ ውጭ ይሆናል። 47  “ደዌው ከሱፍም ሆነ ከበፍታ የተሠራን ልብስ ቢበክል 48  ወይም የበፍታውንም ሆነ የሱፉን ድር ወይም ማግ አሊያም ቁርበትን ወይም ደግሞ ከቆዳ የተሠራን ማንኛውንም ነገር ቢበክል 49  እንዲሁም ደዌው ያስከተለው ወደ ቢጫነት ያደላ አረንጓዴ ወይም ቀላ ያለ ምልክት ልብሱን፣ ቆዳውን፣ ድሩን፣ ማጉን ወይም ደግሞ ከቆዳ የተሠራውን የትኛውንም ዕቃ ቢበክል ይህ በደዌ ምክንያት የተከሰተ ብክለት ነው፤ ካህኑ እንዲያየው መደረግ አለበት። 50  ካህኑም ደዌውን ይመረምረዋል፤ ደዌው ያለበትም ነገር ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቀመጥ ያድርግ። 51  በሰባተኛው ቀን ደዌውን ሲመረምረው ደዌው በልብሱ፣ በድሩ፣ በማጉ ወይም በቆዳው ላይ (ቆዳው ለማንኛውም ዓይነት አገልግሎት የሚውል ይሁን) ተስፋፍቶ ቢገኝ ደዌው አደገኛ ደዌ ነው፤ ዕቃውም ርኩስ ነው። 52  እሱም ደዌው ያለበትን ልብስ ወይም የሱፍም ሆነ የበፍታ ድር ወይም ማግ አሊያም ደግሞ ከቆዳ የተሠራ ማንኛውም ዕቃ ያቃጥል፤ ምክንያቱም ይህ አደገኛ ደዌ ነው። በእሳት መቃጠል ይኖርበታል። 53   “ሆኖም ካህኑ ሲመረምረው ደዌው በልብሱ ወይም በድሩ አሊያም በማጉ ወይም ደግሞ ከቆዳ በተሠራው በማንኛውም ዕቃ ላይ ካልተስፋፋ 54  ካህኑ ደዌው ያለበትን ነገር እንዲያጥቡት ያዛል፤ ከዚያም እንደገና ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቀመጥ ያደርጋል። 55  የተበከለው ዕቃ በደንብ ከታጠበ በኋላ ካህኑ ይመረምረዋል። ደዌው ባይስፋፋም እንኳ ብክለቱ መልኩን ካልቀየረ ዕቃው ርኩስ ነው። ዕቃው ከውስጡ ወይም ከውጭው ስለተበላ በእሳት አቃጥለው። 56  “ሆኖም ዕቃው በደንብ ከታጠበ በኋላ ካህኑ ሲመረምረው የተበከለው ክፍል ከደበዘዘ ያን ቦታ ከልብሱ ወይም ከቆዳው አሊያም ከድሩ ወይም ደግሞ ከማጉ ላይ ቀዶ ያወጣዋል። 57   ይሁንና ደዌው በልብሱ ወይም በድሩ አሊያም በማጉ ወይም ደግሞ ከቆዳ በተሠራው በማንኛውም ዕቃ ላይ በሌላ ቦታ አሁንም ከታየ ደዌው እየተስፋፋ ነው፤ ስለዚህ በደዌው የተበከለውን ማንኛውንም ዕቃ በእሳት አቃጥለው። 58  ሆኖም በልብሱ ወይም በድሩ አሊያም በማጉ ወይም ደግሞ ከቆዳ በተሠራው በማንኛውም ዕቃ ላይ የተከሰተው ብክለት ስታጥበው ከለቀቀ ዕቃው ለሁለተኛ ጊዜ ይታጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል። 59  “ከሱፍ ወይም ከበፍታ በተሠራ ልብስ አሊያም በድር ወይም በማግ አሊያም ደግሞ ከቆዳ በተሠራ በማንኛውም ዕቃ ላይ የወጣን ደዌ በተመለከተ ዕቃው ንጹሕ ነው ብሎ ለማስታወቅም ሆነ ርኩስ ነው ለማለት ሕጉ ይህ ነው።”
[]
[]
[]
[]
12,442
14  ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “የሥጋ ደዌ ያለበት አንድ ሰው መንጻቱን ለማረጋገጥ ካህኑ ፊት እንዲቀርብ በሚደረግበት ዕለት የሚኖረው ሕግ ይህ ነው። 3  ካህኑ ከሰፈሩ ውጭ ወጥቶ ሰውየውን ይመረምረዋል። የሥጋ ደዌ ይዞት የነበረው ሰው ከሥጋ ደዌው ከዳነ 4  ካህኑ ሰውየው ራሱን ለማንጻት በሕይወት ያሉ ሁለት ንጹሕ ወፎችን፣ የአርዘ ሊባኖስ እንጨት፣ ደማቅ ቀይ ማግና ሂሶጵ እንዲያመጣ ያዘዋል። 5  እንዲሁም ካህኑ አንደኛዋ ወፍ ከወራጅ ውኃ የተቀዳ ውኃ ባለበት የሸክላ ዕቃ ውስጥ እንድትታረድ ትእዛዝ ይሰጣል። 6  በሕይወት ያለችውን ወፍ ደግሞ ከአርዘ ሊባኖስ እንጨቱ፣ ከደማቁ ቀይ ማግና ከሂሶጱ ጋር ወስዶ ከወራጅ ውኃ በተቀዳው ውኃ ላይ በታረደችው ወፍ ደም ውስጥ ይንከራቸው። 7  ከዚያም ራሱን ከሥጋ ደዌ በሚያነጻው ሰው ላይ ሰባት ጊዜ ይረጨዋል፤ ሰውየውም ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል፤ በሕይወት ያለችውንም ወፍ ሜዳ ላይ ይለቃታል። 8  “ራሱን የሚያነጻውም ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤ ፀጉሩንም በሙሉ ይላጭ፤ ገላውንም በውኃ ይታጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል። ይህን ካደረገ በኋላ ወደ ሰፈሩ መግባት ይችላል፤ ሆኖም ለሰባት ቀን ከድንኳኑ ውጭ ይቀመጣል። 9  በሰባተኛው ቀን በራሱ ላይ ያለውን ፀጉር፣ ጺሙንና ቅንድቡን በሙሉ ይላጭ። ፀጉሩን በሙሉ ከተላጨ በኋላ ልብሶቹን ያጥባል እንዲሁም ገላውን በውኃ ይታጠባል፤ ከዚያም ንጹሕ ይሆናል። 10  “በስምንተኛው ቀን እንከን የሌለባቸውን ሁለት የበግ ጠቦቶች፣ አንድ ዓመት ገደማ የሆናትን እንከን የሌለባት አንዲት እንስት የበግ ጠቦት፣ የእህል መባ እንዲሆን በዘይት የተለወሰ ሦስት አሥረኛ ኢፍ የላመ ዱቄትና አንድ የሎግ መስፈሪያ ዘይት ያመጣል፤ 11  ሰውየው ንጹሕ መሆኑን የሚያስታውቀው ካህንም ራሱን የሚያነጻውን ሰው ከመባዎቹ ጋር በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በይሖዋ ፊት ያቀርበዋል። 12  ካህኑም አንደኛውን የበግ ጠቦት ወስዶ ከአንዱ የሎግ መስፈሪያ ዘይት ጋር በማድረግ የበደል መባ እንዲሆን ያቀርበዋል፤ እነዚህንም የሚወዘወዝ መባ አድርጎ በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ይወዘውዛቸዋል። 13  ከዚያም የበግ ጠቦቱን የኃጢአት መባውና የሚቃጠል መባው ዘወትር በሚታረዱበት ቦታ ይኸውም ቅዱስ በሆነ ስፍራ ያርደዋል፤ ምክንያቱም እንደ ኃጢአት መባው ሁሉ የበደል መባውም የካህኑ ድርሻ ነው። ይህ እጅግ ቅዱስ የሆነ ነገር ነው። 14  “ካህኑም ከበደል መባው ደም ላይ የተወሰነውን ይወስዳል፤ ከዚያም ራሱን የሚያነጻውን ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ይቀባል። 15  ካህኑም ከአንዱ የሎግ መስፈሪያ ዘይት ላይ የተወሰነውን በራሱ የግራ እጅ መዳፍ ላይ ያንቆረቁረዋል። 16  ከዚያም የቀኝ እጁን ጣት በግራ እጁ መዳፍ ላይ ባለው ዘይት ውስጥ ይነክራል፤ ከዘይቱም የተወሰነውን በይሖዋ ፊት ሰባት ጊዜ በጣቱ ይረጨዋል። 17  በእጁም መዳፍ ላይ ከቀረው ዘይት ላይ የተወሰነውን ወስዶ ራሱን የሚያነጻውን ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ይቀባል፤ በበደል መባው ደም ላይ ደርቦ ይቀባዋል። 18  ካህኑም በእጁ መዳፍ ላይ የቀረውን ዘይት ራሱን በሚያነጻው ሰው ራስ ላይ ያፈሰዋል፤ ለሰውየውም በይሖዋ ፊት ያስተሰርይለታል። 19  “ካህኑ ለኃጢአት መባ የሚሆነውን እንስሳ ይሠዋል፤ ራሱን ከርኩሰቱ ለሚያነጻውም ሰው ያስተሰርይለታል፤ ከዚያም ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን እንስሳ ያርዳል። 20  ካህኑም የሚቃጠለውን መባና የእህሉን መባ በመሠዊያው ላይ ያቀርባል፤ ለሰውየውም ያስተሰርይለታል፤ እሱም ንጹሕ ይሆናል። 21  “ሆኖም ሰውየው ድሃ ከሆነና ይህን ለማቅረብ አቅሙ ካልፈቀደለት ለራሱ ማስተሰረያ እንዲሆንለት ለሚወዘወዝ መባ አንድ የበግ ጠቦት የበደል መባ አድርጎ ያመጣል፤ በተጨማሪም ለእህል መባ እንዲሆን በዘይት የተለወሰ አንድ አሥረኛ ኢፍ የላመ ዱቄት፣ አንድ የሎግ መስፈሪያ ዘይት 22  እንዲሁም ከሁለት ዋኖሶች ወይም ከሁለት የርግብ ጫጩቶች አቅሙ የቻለውን ያቀርባል፤ አንደኛው ለኃጢአት መባ ሌላኛው ደግሞ ለሚቃጠል መባ ይሆናል። 23  መንጻቱን ለማረጋገጥም በስምንተኛው ቀን እነዚህን ይዞ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በይሖዋ ፊት ወዳለው ወደ ካህኑ ይመጣል። 24  “ካህኑም ለበደል መባ እንዲሆን የቀረበውን የበግ ጠቦትና አንዱን የሎግ መስፈሪያ ዘይት ይወስዳል፤ እነዚህንም የሚወዘወዝ መባ አድርጎ በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ይወዘውዛቸዋል። 25  ከዚያም ለበደል መባ እንዲሆን የቀረበውን የበግ ጠቦት ያርዳል፤ ከበደል መባው ደም ላይ የተወሰነውን ወስዶ ራሱን የሚያነጻውን ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ይቀባል። 26  ካህኑም ከዘይቱ የተወሰነውን በራሱ የግራ እጅ መዳፍ ላይ ያንቆረቁረዋል። 27  በግራ እጁ መዳፍ ላይ ካለው ዘይት የተወሰነውን በቀኝ እጁ ጣት በይሖዋ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል። 28  በእጁ መዳፍ ላይ ካለው ዘይት የተወሰነውን ወስዶ የበደል መባውን ደም በቀባበት ቦታ ላይ ማለትም ራሱን በሚያነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት እንዲሁም በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ይቀባል። 29  ከዚያም በእጁ መዳፍ ላይ የቀረውን ዘይት ራሱን በሚያነጻው ሰው ራስ ላይ ያፈሰዋል፤ ይህን የሚያደርገው በይሖዋ ፊት እንዲያስተሰርይለት ነው። 30  “ካህኑም ሰውየው አቅሙ ፈቅዶ ካመጣቸው ዋኖሶች ወይም የርግብ ጫጩቶች መካከል አንዱን ያቀርባል፤ 31  አቅሙ ፈቅዶ ካመጣቸውም መካከል አንዱን የኃጢአት መባ ሌላኛውን ደግሞ የሚቃጠል መባ አድርጎ ከእህል መባው ጋር ያቀርባል፤ ካህኑም ራሱን ለሚያነጻው ሰው በይሖዋ ፊት ያስተሰርይለታል። 32  “የሥጋ ደዌ የነበረበትን ሆኖም መንጻቱን ለማረጋገጥ የሚያስፈልገውን ነገር ለማቅረብ አቅሙ የማይፈቅድለትን ሰው በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው።” 33  ከዚያም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ 34  “ርስት አድርጌ ወደምሰጣችሁ ወደ ከነአን ምድር በምትገቡበት ጊዜ በምድራችሁ ውስጥ የሚገኝን አንድ ቤት በደዌ ብበክለው 35  የቤቱ ባለቤት ወደ ካህኑ መጥቶ ‘አንድ የሚበክል ነገር ቤቴ ውስጥ ታይቷል’ በማለት ይንገረው። 36  ካህኑም ቤቱ ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ ርኩስ ነው እንዳይል የሚበክለውን ነገር ለመመርመር ወደ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ቤቱ ውስጥ ያለውን ዕቃ በሙሉ እንዲያወጡ ትእዛዝ ይሰጣል፤ ከዚያም ካህኑ ቤቱን ለመመርመር ወደ ውስጥ ይገባል። 37  እሱም ብክለቱ የታየበትን ቦታ ይመረምራል፤ በቤቱም ግድግዳ ላይ ወደ ቢጫነት ያደላ አረንጓዴ ወይም ቀላ ያለ የተቦረቦረ ምልክት ቢታይና ይህም ከላይ ወደ ውስጥ ዘልቆ የገባ ከሆነ 38  ካህኑ ከቤቱ ውስጥ ወደ ደጃፉ ወጥቶ ቤቱን ለሰባት ቀን ያሽገዋል። 39  “ከዚያም ካህኑ በሰባተኛው ቀን ተመልሶ በመምጣት ቤቱን ይመረምረዋል። ቤቱን የበከለው ነገር በግድግዳው ላይ ተስፋፍቶ ከሆነ 40  ካህኑ ትእዛዝ ይሰጣል፤ የተበከሉትም ድንጋዮች ተሰርስረው መውጣትና ከከተማዋ ውጭ ወዳለ ርኩስ የሆነ ስፍራ መጣል አለባቸው። 41  ከዚያም ቤቱ ከውስጥ በኩል በደንብ እንዲፈቀፈቅ ያደርጋል፤ ተፈቅፍቆ የተነሳው ልስንና ምርጊትም ከከተማዋ ውጭ በሚገኝ ርኩስ የሆነ ስፍራ ይደፋ። 42  ባወጧቸውም ድንጋዮች ቦታ ሌሎች ድንጋዮችን ያስገቡ፤ ቤቱም በአዲስ ምርጊት እንዲለሰን ያድርግ። 43  “ድንጋዮቹ ተሰርስረው ከወጡና ቤቱ ተፈቅፍቆ ዳግመኛ ከተለሰነ በኋላ ብክለቱ እንደገና ተመልሶ በቤቱ ላይ ከታየ 44  ካህኑ ገብቶ ይመረምረዋል። ብክለቱ በቤቱ ውስጥ ተስፋፍቶ ከሆነ ይህ በቤቱ ላይ የወጣ አደገኛ ደዌ ነው። ቤቱ ርኩስ ነው። 45  ቤቱ ይኸውም ድንጋዮቹ፣ እንጨቶቹ፣ ልስኑና ምርጊቱ እንዲፈርስ ያደርጋል፤ ከከተማዋ ውጭ በሚገኝ ርኩስ የሆነ ስፍራም እንዲጣል ያደርጋል። 46  ሆኖም ቤቱ ታሽጎ በነበረበት በየትኛውም ቀን ወደዚያ ቤት የገባ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ 47  እዚያ ቤት ውስጥ የተኛ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ እንዲሁም እዚያ ቤት ውስጥ የበላ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል። 48  “ይሁንና ካህኑ መጥቶ ሲያየው ቤቱ ከተለሰነ በኋላ ብክለቱ በቤቱ ውስጥ ካልተስፋፋ ቤቱ ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል፤ ምክንያቱም ብክለቱ ጠፍቷል። 49  ቤቱንም ከርኩሰት ለማንጻት ሁለት ወፎች፣ የአርዘ ሊባኖስ እንጨት፣ ደማቅ ቀይ ማግና ሂሶጵ ይወስዳል። 50  አንደኛዋንም ወፍ ከወራጅ ውኃ የተቀዳ ውኃ ባለበት የሸክላ ዕቃ ውስጥ ያርዳታል። 51  ከዚያም የአርዘ ሊባኖስ እንጨቱን፣ ሂሶጱን፣ ደማቁን ቀይ ማግና በሕይወት ያለችውን ወፍ ወስዶ በታረደችው ወፍ ደምና ከወራጅ ውኃ በተቀዳው ውኃ ውስጥ ይነክራቸዋል፤ ወደ ቤቱም ሰባት ጊዜ ይርጨው። 52  ቤቱንም በወፏ ደም፣ ከወራጅ ውኃ በተቀዳው ውኃ፣ በሕይወት ባለችው ወፍ፣ በአርዘ ሊባኖስ እንጨቱ፣ በሂሶጱና በደማቁ ቀይ ማግ ከርኩሰት ያነጻዋል። 53   በሕይወት ያለችውንም ወፍ ከከተማዋ ውጭ ወደ ሜዳ ይለቃታል፤ ለቤቱም ያስተሰርይለታል፤ ቤቱም ንጹሕ ይሆናል። 54  “ከማንኛውም ዓይነት የሥጋ ደዌ፣ በራስ ቆዳ ወይም በጢም ላይ ከሚወጣ ቁስል፣ 55  በልብስ ወይም በቤት ላይ ከሚወጣ ደዌ፣ 56  ከእባጭ፣ ከእከክና ከቋቁቻ ጋር በተያያዘ 57   አንድ ነገር ርኩስ ወይም ንጹሕ መሆኑን ለመወሰን የሚያገለግለው ሕግ ይህ ነው። የሥጋ ደዌን በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው።”
[]
[]
[]
[]
12,443
15  ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ 2  “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብላችሁ ንገሯቸው፦ ‘አንድ ወንድ ከብልቱ ፈሳሽ የሚወጣ ከሆነ ይህ ፈሳሽ ርኩስ ያደርገዋል። 3  ሰውየው በፈሳሹ የተነሳ ርኩስ ነው፤ ፈሳሹ ከብልቱ እየፈሰሰ ቢሆንም ወይም ብልቱን ቢዘጋው ሰውየው ርኩስ ነው። 4  “‘ፈሳሽ የሚወጣው ሰው የተኛበት አልጋም ርኩስ ይሆናል፤ ይህ ሰው የተቀመጠበት ማንኛውም ነገርም ርኩስ ይሆናል። 5  የሰውየውን አልጋ የነካ ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 6  እንዲሁም ፈሳሽ የሚወጣው ሰው ተቀምጦበት በነበረ ነገር ላይ የተቀመጠ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 7  ፈሳሽ የሚወጣውን ሰው፣ ሰውነት የነካ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 8  ፈሳሽ የሚወጣው ሰው ንጹሕ በሆነ ሰው ላይ ቢተፋ የተተፋበት ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 9  ፈሳሽ የሚወጣው ሰው የተቀመጠበት ኮርቻ ርኩስ ይሆናል። 10  ይህ ሰው የተቀመጠበትን የትኛውንም ነገር የነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እነዚህን ነገሮች የያዘ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 11  ፈሳሽ የሚወጣው ሰው እጆቹን በውኃ ሳይታጠብ አንድን ሰው ቢነካ የተነካው ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 12  ፈሳሽ የሚወጣው ሰው የነካው የሸክላ ዕቃ ይሰበር፤ ማንኛውም የእንጨት ዕቃ ደግሞ በውኃ ይታጠብ። 13  “‘እንግዲህ ፈሳሹ ቢቆምና ሰውየው ከፈሳሹ ቢነጻ ንጹሕ ለመሆን ሰባት ቀን ይቁጠር፤ ልብሶቹን ይጠብ፤ ገላውንም በምንጭ ውኃ ይታጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል። 14  በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶችን ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶችን ይውሰድ፤ እነዚህንም ይዞ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በይሖዋ ፊት በመቅረብ ለካህኑ ይስጥ። 15  ካህኑም አንዱን የኃጢአት መባ ሌላኛውን ደግሞ የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርባቸዋል፤ ካህኑም ስለ ፈሳሹ ለሰውየው በይሖዋ ፊት ያስተሰርይለታል። 16  “‘አንድ ወንድ ዘር ቢፈሰው ገላውን በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 17  የፈሰሰው ዘር የነካውን ማንኛውንም ዓይነት ልብስ ወይም ቁርበት በውኃ ማጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 18  “‘አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር ቢተኛና ዘሩ ቢፈስ ገላቸውን በውኃ መታጠብ አለባቸው፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናሉ። 19  “‘አንዲት ሴት ከሰውነቷ ደም ቢፈሳት በወር አበባዋ የተነሳ ርኩስ እንደሆነች ለሰባት ቀን ትቀጥላለች፤ እንዲሁም እሷን የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። 20  በወር አበባዋ የተነሳ ርኩስ በሆነችባቸው ጊዜያት የተኛችበት ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል፤ እንዲሁም የተቀመጠችበት ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል። 21  አልጋዋን የነካ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 22  እሷ ተቀምጣበት የነበረውን የትኛውንም ነገር የነካ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 23  የተቀመጠችው አልጋ ላይም ይሁን ሌላ ነገር ላይ ሰውየው ያን መንካቱ እስከ ማታ ድረስ እንዲረክስ ያደርገዋል። 24  አንድ ወንድ ከእሷ ጋር ቢተኛና በወር አበባዋ ቢረክስ ሰውየው ለሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል፤ የተኛበት አልጋም ርኩስ ይሆናል። 25  “‘አንዲት ሴት የወር አበባዋ ከሚመጣበት ከተለመደው ጊዜ ውጭ ለብዙ ቀናት ደም ቢፈሳት ወይም በወር አበባዋ ወቅት ከወትሮው ረዘም ላለ ጊዜ ደም ቢፈሳት የወር አበባዋ በሚመጣባቸው ቀናት እንደሚሆነው ፈሳሽ በሚፈሳት ጊዜ ሁሉ ርኩስ ትሆናለች። 26  ፈሳሽ በሚፈሳት ቀናት ሁሉ የተኛችበት አልጋ በወር አበባዋ የተነሳ ርኩስ በሆነችባቸው ጊዜያት እንደተኛችበት አልጋ ይሆናል፤ እንዲሁም የተቀመጠችበት ማንኛውም ነገር በወር አበባዋ ወቅት ርኩስ እንደሚሆን ሁሉ በዚህ ጊዜም ርኩስ ይሆናል። 27  እነዚህን ነገሮች የነካ ማንኛውም ሰው ርኩስ ይሆናል፤ ልብሶቹንም ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 28  “‘ይሁን እንጂ ይፈሳት ከነበረው ፈሳሽ በምትነጻበት ጊዜ ለራሷ ሰባት ቀን ትቆጥራለች፤ ከዚያ በኋላ ንጹሕ ትሆናለች። 29  በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶችን ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶችን ትውሰድ፤ እነዚህንም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ወዳለው ወደ ካህኑ ታመጣቸዋለች። 30  ካህኑም አንዱን ለኃጢአት መባ ሌላኛውን ደግሞ ለሚቃጠል መባ ያደርገዋል፤ ካህኑም የሚፈሳትን ርኩስ ፈሳሽ አስመልክቶ ለሴትየዋ በይሖዋ ፊት ያስተሰርይላታል። 31  “‘በመካከላቸው ያለውን የማደሪያ ድንኳኔን በማርከስ በርኩሰታቸው እንዳይሞቱ በዚህ መንገድ እስራኤላውያንን ከርኩሰታቸው ለዩአቸው። 32  “‘ፈሳሽ የሚወጣውን ወንድ፣ ዘሩ በመፍሰሱ የተነሳ ርኩስ የሆነውን ወንድ፣ 33  በወር አበባዋ ላይ በመሆኗ ርኩስ የሆነችን ሴት፣ ወንድም ሆነ ሴት ከሰውነቱ ፈሳሽ የሚወጣውን ማንኛውንም ሰው እንዲሁም ርኩስ ከሆነች ሴት ጋር የተኛን ወንድ በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው።’”
[]
[]
[]
[]
12,444
16  ሁለቱ የአሮን ወንዶች ልጆች ይሖዋ ፊት በመቅረባቸው የተነሳ ከሞቱ በኋላ ይሖዋ ሙሴን አነጋገረው። 2  ይሖዋም እንዲህ አለው፦ “እኔ ከመክደኛው በላይ በደመና ውስጥ ስለምገለጥ በመጋረጃው ውስጥ ወዳለው ቅዱስ ስፍራ ይኸውም በታቦቱ ላይ ወዳለው መክደኛ ፊት በፈለገው ጊዜ እንዳይገባና በዚህም የተነሳ እንዳይሞት ለወንድምህ ለአሮን ንገረው። 3  “አሮን ወደተቀደሰው ስፍራ በሚገባበት ጊዜ ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ ወይፈንና ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ አውራ በግ ይዞ ይምጣ። 4  ቅዱሱን የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፤ በበፍታ ቁምጣዎቹም ሰውነቱን ይሸፍን፤ የበፍታ መቀነቱንም ይታጠቅ፤ ራሱም ላይ የበፍታ ጥምጥሙን ይጠምጥም። እነዚህ ቅዱስ ልብሶች ናቸው። እሱም ገላውን በውኃ ታጥቦ ይለብሳቸዋል። 5  “ከእስራኤል ማኅበረሰብም ሁለት ተባዕት የፍየል ጠቦቶችን ለኃጢአት መባ፣ አንድ አውራ በግ ደግሞ ለሚቃጠል መባ ይውሰድ። 6  “ከዚያም አሮን ለራሱ የኃጢአት መባ የሚሆነውን ወይፈን ያቅርብ፤ ለራሱም ሆነ ለቤቱ ያስተሰርያል። 7  “ሁለቱን ፍየሎች ወስዶ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በይሖዋ ፊት እንዲቆሙ ያደርጋል። 8  አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥላል፤ አንደኛው ዕጣ ለይሖዋ ሌላኛው ዕጣ ደግሞ ለአዛዜል ይሆናል። 9  አሮንም ለይሖዋ እንዲሆን ዕጣ የወጣበትን ፍየል ያቀርባል፤ የኃጢአትም መባ ያደርገዋል። 10  ለአዛዜል እንዲሆን ዕጣ የወጣበት ፍየል ግን በእሱ አማካኝነት ስርየት እንዲፈጸምበት ከነሕይወቱ መጥቶ በይሖዋ ፊት እንዲቆም ይደረግ፤ ከዚያም ለአዛዜል እንዲሆን ወደ ምድረ በዳ ይለቀቃል። 11  “አሮንም ለራሱ የኃጢአት መባ የሚሆነውን ወይፈን ያቀርባል፤ ለራሱም ሆነ ለቤቱ ያስተሰርያል፤ ከዚያም ለራሱ የኃጢአት መባ የሚሆነውን ወይፈን ያርዳል። 12  “በይሖዋ ፊት ካለው መሠዊያ ላይ የተወሰደ ፍም የሞላበትን ዕጣን ማጨሻና ሁለት እፍኝ ሙሉ ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን ይወስዳል፤ እነዚህንም ይዞ ወደ መጋረጃው ውስጥ ይገባል። 13  እንዳይሞትም ዕጣኑን በይሖዋ ፊት ባለው እሳት ላይ ይጨምረዋል፤ የዕጣኑም ጭስ ከምሥክሩ በላይ ያለውን የታቦቱን መክደኛ ይሸፍነዋል። 14  “ከወይፈኑም ደም የተወሰነውን ወስዶ ከመክደኛው ፊት ለፊት በስተ ምሥራቅ በኩል በጣቱ ይረጨዋል፤ የተወሰነውን ደም ደግሞ ከመክደኛው ፊት በጣቱ ሰባት ጊዜ ይረጨዋል። 15  “ከዚያም ለሕዝቡ የኃጢአት መባ የሚሆነውን ፍየል ያርደዋል፤ ደሙንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ይዞ በመግባት ልክ በወይፈኑ ደም እንዳደረገው በዚህኛውም ደም ያደርጋል፤ ደሙንም ወደ መክደኛውና በመክደኛው ፊት ይረጨዋል። 16  “እስራኤላውያን ስለፈጸሙት ርኩሰት፣ ስለ መተላለፋቸውና ስለ ኃጢአታቸው ለቅዱሱ ስፍራ ያስተሰርይ፤ በእነሱ ዘንድ በርኩሰታቸው መካከል ለሚገኘው ለመገናኛ ድንኳኑም ይህንኑ ያድርግ። 17  “ለማስተሰረይ ወደ ቅዱሱ ስፍራ ገብቶ እስኪወጣ ድረስ ሌላ ማንም ሰው በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ መገኘት የለበትም። እሱም ለራሱ፣ ለቤቱና ለመላው የእስራኤል ጉባኤ ያስተሰርያል። 18  “ከዚያም በይሖዋ ፊት ወዳለው መሠዊያ ይወጣል፤ ለመሠዊያውም ያስተሰርይለታል፤ ከወይፈኑ ደም የተወሰነውን እንዲሁም ከፍየሉ ደም የተወሰነውን ወስዶ በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ያሉትን ቀንዶች ይቀባል። 19  በተጨማሪም ከደሙ የተወሰነውን ወስዶ በመሠዊያው ላይ በጣቱ ሰባት ጊዜ በመርጨት እስራኤላውያን ከፈጸሙት ርኩሰት ያነጻዋል እንዲሁም ይቀድሰዋል። 20  “ለቅዱሱ ስፍራ፣ ለመገናኛ ድንኳኑና ለመሠዊያው ካስተሰረየ በኋላ በሕይወት ያለውንም ፍየል ያቀርባል። 21  ከዚያም አሮን ሁለቱንም እጆቹን በሕይወት ባለው ፍየል ራስ ላይ በመጫን እስራኤላውያን የሠሩትን ስህተት ሁሉ፣ መተላለፋቸውን ሁሉና ኃጢአታቸውን ሁሉ ይናዘዝበታል፤ እነዚህንም በፍየሉ ራስ ላይ ያደርጋል፤ ፍየሉንም ለዚህ በተመደበው ሰው እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰደዋል። 22  ፍየሉም ስህተቶቻቸውን በሙሉ ተሸክሞ ወደ በረሃ ይሄዳል፤ እሱም ፍየሉን ወደ ምድረ በዳ ይሰደዋል። 23  “ከዚያም አሮን ወደ መገናኛ ድንኳኑ ይገባል፤ ወደ ቅዱሱ ስፍራ ሲገባ ለብሷቸው የነበሩትንም የበፍታ ልብሶች ያወልቃል፤ ልብሶቹንም እዚያው ይተዋቸዋል። 24  ገላውንም በቅዱስ ስፍራ በውኃ ይታጠብ፤ ልብሶቹንም ይልበስ፤ ከዚያም ወጥቶ የራሱን የሚቃጠል መባ እንዲሁም የሕዝቡን የሚቃጠል መባ ያቀርባል፤ ለራሱና ለሕዝቡም ያስተሰርያል። 25  የኃጢአት መባው ስብም በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርጋል። 26  “ለአዛዜል ሲል ፍየሉን የለቀቀውም ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤ ገላውንም በውኃ ይታጠብ፤ ከዚያም ወደ ሰፈሩ መግባት ይችላል። 27  “ደማቸው ለማስተሰረያ እንዲሆን ወደ ቅዱሱ ስፍራ የገባው የኃጢአት መባው ወይፈንና የኃጢአት መባው ፍየል ከሰፈሩ ውጭ ይወሰዳሉ፤ ቆዳቸው፣ ሥጋቸውና ፈርሳቸውም በእሳት ይቃጠላል። 28  እነዚህን ያቃጠለው ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤ ገላውንም በውኃ ይታጠብ፤ ከዚያም ወደ ሰፈሩ መግባት ይችላል። 29  “ይህም ለእናንተ ዘላቂ ደንብ ሆኖ ያገለግላል፦ በሰባተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን ራሳችሁን አጎሳቁሉ፤ ምንም ዓይነት ሥራም አትሥሩ፤ የአገራችሁ ሰውም ሆነ በመካከላችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ምንም ዓይነት ሥራ አይሥራ። 30  በዚህ ቀን፣ ንጹሕ መሆናችሁን ለማሳወቅ ለእናንተ ማስተሰረያ ይቀርባል። በይሖዋም ፊት ከኃጢአታችሁ ሁሉ ንጹሕ ትሆናላችሁ። 31  ይህ ሙሉ በሙሉ የምታርፉበት ሰንበት ነው፤ እናንተም ራሳችሁን አጎሳቁሉ። ይህም ዘላቂ ደንብ ነው። 32  “አባቱን ተክቶ በክህነት እንዲያገለግል የሚቀባውና የሚሾመው ካህን ያስተሰርያል፤ እንዲሁም ቅዱስ የሆኑትን የበፍታ ልብሶች ይለብሳል። 33  ለቅዱሱ መቅደስ፣ ለመገናኛ ድንኳኑና ለመሠዊያው ያስተሰርያል፤ እንዲሁም ለካህናቱና ለጉባኤው ሕዝብ በሙሉ ያስተሰርያል። 34  ይህም የእስራኤላውያንን ኃጢአት በሙሉ በዓመት አንድ ጊዜ ለማስተሰረይ የሚያገለግል ዘላቂ ደንብ ይሆናል።” እሱም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት አደረገ።
[]
[]
[]
[]
12,445
17  ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲሁም እስራኤላውያንን በሙሉ እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ ያዘዘው ይህ ነው፦ 3  “‘“ከእስራኤል ቤት የሆነ ማንኛውም ሰው በሬ ወይም የበግ ጠቦት አሊያም ፍየል በሰፈሩ ውስጥ ወይም ከሰፈሩ ውጭ ቢያርድና 4  በይሖዋ የማደሪያ ድንኳን ፊት ለይሖዋ መባ አድርጎ ለማቅረብ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ባያመጣ ያ ሰው በደም ዕዳ ይጠየቃል። ሰውየው ደም አፍስሷል፤ በመሆኑም ይህ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት። 5  ይህም እስራኤላውያን በሜዳ ላይ እየሠዉ ያሉትን መሥዋዕት ወደ ይሖዋ፣ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያና ወደ ካህኑ እንዲያመጡ ነው። እነዚህንም ለይሖዋ የኅብረት መሥዋዕቶች አድርገው መሠዋት አለባቸው። 6  ካህኑም ደሙን በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ባለው የይሖዋ መሠዊያ ላይ ይረጨዋል፤ ስቡንም ለይሖዋ ደስ የሚያሰኝ መዓዛ አድርጎ ያጨሰዋል። 7  ከእንግዲህ ወዲህ፣ አብረዋቸው ምንዝር ለሚፈጽሙት ፍየል የሚመስሉ አጋንንት አይሠዉም። ይህም በመጪዎቹ ትውልዶቻችሁ ሁሉ ለእናንተ ዘላቂ ደንብ ሆኖ ያገለግላል።”’ 8  “እንዲህም በላቸው፦ ‘የሚቃጠል መባ ወይም መሥዋዕት የሚያቀርብ ከእስራኤል ቤት የሆነ ማንኛውም ሰው ወይም በመካከላችሁ የሚኖር ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው 9  ይህን ለይሖዋ ለማቅረብ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ባያመጣ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት። 10  “‘ከእስራኤል ቤት የሆነ ማንኛውም ሰው ወይም በመካከላችሁ የሚኖር የትኛውም የባዕድ አገር ሰው ምንም ዓይነት ደም ቢበላ፣ ደም በሚበላው ሰው ላይ በእርግጥ ፊቴን አጠቁርበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። 11  ምክንያቱም የሥጋ ሕይወት ያለው በደሙ ውስጥ ነው፤ ለራሳችሁም ማስተሰረያ እንዲሆን እኔ ራሴ ደሙን ለእናንተ ስል ለመሠዊያው ሰጥቼዋለሁ፤ ምክንያቱም በውስጡ ባለው ሕይወት አማካኝነት የሚያስተሰርየው ደሙ ነው። 12  እስራኤላውያንን “ማንኛችሁም ደም መብላት የለባችሁም፤ እንዲሁም በመካከላችሁ የሚኖር ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው ደም አይብላ” ያልኳቸው ለዚህ ነው። 13  “‘አንድ እስራኤላዊ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር አንድ የባዕድ አገር ሰው ለመብልነት የተፈቀደ እንስሳ ወይም ወፍ አድኖ ቢይዝ ደሙን ያፍሰው፤ አፈርም ያልብሰው። 14  የሥጋ ሁሉ ሕይወት ደሙ ነውና፤ ምክንያቱም በውስጡ ሕይወት አለ። በዚህም የተነሳ እስራኤላውያንን እንዲህ አልኳቸው፦ “የሥጋ ሁሉ ሕይወት ደሙ ስለሆነ የማንኛውንም ሥጋ ደም አትብሉ። ደም የሚበላ ማንኛውም ሰው ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረጋል።” 15  የአገሬው ተወላጅም ይሁን የባዕድ አገር ሰው፣ ማንኛውም ሰው ሞቶ የተገኘን ወይም አውሬ የቦጫጨቀውን እንስሳ ሥጋ ቢበላ ልብሶቹን ይጠብ፤ በውኃም ይታጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሁን፤ ከዚያም ንጹሕ ይሆናል። 16  ሆኖም ልብሶቹን ካላጠበና ሰውነቱን ካልታጠበ በሠራው ጥፋት ይጠየቅበታል።’”
[]
[]
[]
[]
12,446
18  ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። 3  ትኖሩበት በነበረው በግብፅ ምድር ያሉ ሰዎች እንደሚያደርጉት አታድርጉ፤ እኔ በማስገባችሁ በከነአን ምድር ያሉ ሰዎች እንደሚያደርጉትም አታድርጉ። እንዲሁም እነሱ የሚከተሏቸውን ደንቦች አትከተሉ። 4  ድንጋጌዎቼን ተግባር ላይ አውሉ፤ ደንቦቼንም በመጠበቅ በእነሱ ሂዱ። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። 5  ደንቦቼንና ድንጋጌዎቼን ጠብቁ፤ እንዲህ የሚያደርግ ማንኛውም ሰው በእነሱ አማካኝነት በሕይወት ይኖራል። እኔ ይሖዋ ነኝ። 6  “‘ከመካከላችሁ ማንም ሰው የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ወደ ማንኛውም የቅርብ ዘመዱ አይቅረብ። እኔ ይሖዋ ነኝ። 7  ከአባትህ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ከእናትህም ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። እሷ እናትህ ናት፤ ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። 8  “‘ከአባትህ ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። ይህ አባትህን ለኀፍረት መዳረግ ነው። 9  “‘የአባትህ ልጅም ሆነች የእናትህ ልጅ ወይም በቤት የተወለደችም ሆነች በውጭ፣ ከእህትህ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። 10  “‘ከወንድ ልጅህ ሴት ልጅ ወይም ከሴት ልጅህ ሴት ልጅ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ምክንያቱም እነሱ የአንተው እርቃን ናቸው። 11  “‘የአባትህ ልጅ ከሆነችው ከአባትህ ሚስት ሴት ልጅ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ምክንያቱም እሷ እህትህ ናት። 12  “‘ከአባትህ እህት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። እሷ የአባትህ የሥጋ ዘመድ ናት። 13  “‘ከእናትህ እህት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ምክንያቱም እሷ የእናትህ የሥጋ ዘመድ ናት። 14  “‘ከአባትህ ወንድም ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት በመፈጸም እሱን ለኀፍረት አትዳርገው። እሷ ዘመድህ ናት። 15  “‘ከልጅህ ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። እሷ የልጅህ ሚስት ናት፤ ከእሷ ጋር ግንኙነት መፈጸም የለብህም። 16  “‘ከወንድምህ ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ምክንያቱም ይህ ወንድምህን ለኀፍረት መዳረግ ነው። 17  “‘ከአንዲት ሴትና ከሴት ልጇ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። ከወንድ ልጇ ሴት ልጅም ሆነ ከሴት ልጇ ሴት ልጅ ጋር የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም እነሱን አትውሰድ። እነሱ የእሷ የቅርብ ዘመዶች ናቸው፤ ይህ ጸያፍ ድርጊት ነው። 18  “‘እህቷ ጣውንቷ እንዳትሆን ሚስትህ በሕይወት እያለች ከእህቷ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። 19  “‘አንዲት ሴት በወር አበባዋ ረክሳ እያለች ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ወደ እሷ አትቅረብ። 20  “‘ከጓደኛህ ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት በመፈጸም ራስህን አታርክስ። 21  “‘ከልጆችህ መካከል የትኛውንም ለሞሎክ እንዲሰጥ አታድርግ። በዚህ መንገድ የአምላክህን ስም አታርክስ። እኔ ይሖዋ ነኝ። 22  “‘ከሴት ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ። ይህ አስጸያፊ ድርጊት ነው። 23  “‘አንድ ወንድ ከእንስሳ ጋር የፆታ ግንኙነት በመፈጸም ራሱን አያርክስ፤ ሴትም ብትሆን ከእንስሳ ጋር የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ራሷን ለእንስሳ አታቅርብ። ይህ ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ ነገር ነው። 24  “‘ከእነዚህ ነገሮች በየትኛውም ራሳችሁን አታርክሱ፤ ምክንያቱም ከእናንተ ፊት አባርሬ የማስወጣቸው ብሔራት ራሳቸውን በእነዚህ ነገሮች አርክሰዋል። 25  ስለሆነም ምድሪቱ ረክሳለች፤ እኔም ለሠራችው ስህተት ቅጣት አመጣባታለሁ፤ ምድሪቱም ነዋሪዎቿን ትተፋቸዋለች። 26  እናንተ ግን ደንቦቼንና ድንጋጌዎቼን ጠብቁ፤ ከእነዚህ አስጸያፊ ነገሮች መካከል የትኛውንም ማድረግ የለባችሁም፤ የአገራችሁ ሰውም ሆነ በመካከላችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው እንዲህ ማድረግ የለበትም። 27  ምክንያቱም ከእናንተ በፊት በምድሪቱ ላይ ይኖሩ የነበሩት ሰዎች እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ ፈጽመዋል፤ በዚህም የተነሳ አሁን ምድሪቱ ረክሳለች። 28  እናንተ ግን ምድሪቱን ስለማታረክሷት ከእናንተ በፊት የነበሩትን ብሔራት እንደተፋቻቸው እናንተን አትተፋችሁም። 29  ማንኛውም ሰው ከእነዚህ አስጸያፊ ነገሮች መካከል የትኛውንም ቢፈጽም ይህን የፈጸመው ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ። 30  ከእናንተ በፊት የነበሩ ሰዎች ይከተሏቸው ከነበሩት አስጸያፊ ልማዶች በመራቅ ለእኔ የገባችሁትን ግዴታ ፈጽሙ፤ አለዚያ በእነሱ ምክንያት ራሳችሁን ታረክሳላችሁ። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’”
[]
[]
[]
[]
12,447
19  በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “ለመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ቅዱስ ስለሆንኩ እናንተም ቅዱስ ልትሆኑ ይገባል። 3  “‘ከእናንተ እያንዳንዱ እናቱንና አባቱን ያክብር፤ ሰንበቶቼንም ይጠብቅ። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። 4  ከንቱ ወደሆኑ አማልክት ዞር አትበሉ፤ ወይም ከቀለጠ ብረት ለራሳችሁ አማልክትን አትሥሩ። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። 5  “‘ለይሖዋ የኅብረት መሥዋዕት የምታቀርቡ ከሆነ ተቀባይነት በሚያስገኝላችሁ መንገድ አቅርቡት። 6  መሥዋዕቱም በዚያው ባቀረባችሁበት ዕለትና በቀጣዩ ቀን መበላት ይኖርበታል፤ ተርፎ እስከ ሦስተኛው ቀን የቆየ ካለ ግን በእሳት መቃጠል አለበት። 7  ይሁንና ከተረፈው ላይ በሦስተኛው ቀን ከተበላ ተቀባይነት የሌለው አስጸያፊ ነገር ይሆናል። 8  የበላውም ሰው የይሖዋን ቅዱስ ነገር ስላረከሰ በጥፋቱ ይጠየቃል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት። 9  “‘የምድራችሁን አዝመራ በምትሰበስቡበት ጊዜ በእርሻችሁ ዳር ዳር ያለውን ሙልጭ አድርጋችሁ አትጨዱት፤ የእርሻችሁን ቃርሚያም አትልቀሙ። 10  በተጨማሪም በወይን እርሻህ ላይ የተረፈውን አትሰብስብ፤ በወይን እርሻህ ላይ የወዳደቀውን የወይን ፍሬ አትልቀም። እነዚህን ለድሃውና ለባዕድ አገሩ ሰው ተውለት። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። 11  “‘አትስረቁ፤ አታታሉ፤ አንዳችሁ በሌላው ላይ ሐቀኝነት የጎደለው ድርጊት አትፈጽሙ። 12  በስሜ በሐሰት አትማሉ፤ በዚህም የአምላካችሁን ስም አታርክሱ። እኔ ይሖዋ ነኝ። 13  ባልንጀራህን አታጭበርብር፤ አትዝረፈውም። የቅጥር ሠራተኛውን ደሞዝ ሳትከፍል አታሳድር። 14  “‘መስማት የተሳነውን አትርገም ወይም በዓይነ ስውሩ ፊት እንቅፋት አታስቀምጥ፤ አምላክህን ፍራ። እኔ ይሖዋ ነኝ። 15  “‘ፍርድ አታዛቡ። ለድሃው አታዳላ ወይም ባለጸጋውን ከሌሎች አስበልጠህ አትመልከት። ለባልንጀራህ ፍትሐዊ ፍርድ ፍረድ። 16  “‘በሕዝብህ መካከል እየዞርክ ስም አታጥፋ። የባልንጀራህን ሕይወት ለማጥፋት አትነሳ። እኔ ይሖዋ ነኝ። 17  “‘ወንድምህን በልብህ አትጥላው። የባልንጀራህ ኃጢአት ተባባሪ እንዳትሆን ተግሣጽ በሚያስፈልገው ጊዜ ሁሉ ገሥጸው። 18  “‘የሕዝብህን ልጆች አትበቀል፤ በእነሱም ላይ ቂም አትያዝ፤ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ። እኔ ይሖዋ ነኝ። 19  “‘የሚከተሉትን ደንቦቼን ጠብቁ፦ ሁለት ዓይነት እንስሳትን አታዳቅል። በእርሻህ ላይ ሁለት ዓይነት ዘር አትዝራ፤ ከሁለት የተለያዩ የክር ዓይነቶች የተሠራ ልብስ አትልበስ። 20  “‘አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር ቢተኛና ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት ቢፈጽም፣ ሴቲቱ ደግሞ ለሌላ ወንድ የታጨች ሆኖም ገና ያልተዋጀች ወይም ነፃ ያልወጣች ባሪያ ብትሆን የቅጣት እርምጃ መወሰድ አለበት። ይሁንና ይህች ሴት ገና ነፃ ስላልወጣች መገደል የለባቸውም። 21  ሰውየው የበደል መባውን ይኸውም ለበደል መባ የሚሆነውን አውራ በግ ወደ ይሖዋ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ያምጣ። 22  ካህኑም ሰውየው ለሠራው ኃጢአት የበደል መባ እንዲሆን በቀረበው አውራ በግ በይሖዋ ፊት ያስተሰርይለታል፤ የሠራውም ኃጢአት ይቅር ይባልለታል። 23  “‘እናንተም ወደ ምድሪቱ ብትገቡና ለምግብ የሚሆን ዛፍ ብትተክሉ ፍሬውን ርኩስና የተከለከለ አድርጋችሁ ቁጠሩት። ለሦስት ዓመት ከእሱ መብላት የለባችሁም። ፍሬው መበላት የለበትም። 24  በአራተኛው ዓመት ግን ፍሬው በሙሉ በይሖዋ ፊት የምትደሰቱበት ቅዱስ ነገር ይሆናል። 25  ከዚያም በአምስተኛው ዓመት ፍሬውን መብላት ትችላላችሁ፤ ይህን ካደረጋችሁ ምርታችሁ ይበዛላችኋል። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። 26  “‘ደም ያለበትን ማንኛውንም ነገር አትብሉ። “‘አታስጠንቁሉ ወይም አስማት አትሥሩ። 27  “‘ጆሮ ግንዳችሁ አካባቢ ያለውን ፀጉር አትላጩ ወይም የጢማችሁን ዳር ዳር አትላጩ። 28  “‘ለሞተ ሰው ብላችሁ አካላችሁን አትተልትሉ ወይም ሰውነታችሁን አትነቀሱ። እኔ ይሖዋ ነኝ። 29  “‘ምድሪቱ ዝሙት እንዳትፈጽምና ልቅ በሆነ ምግባር እንዳትሞላ ሴት ልጅህን ዝሙት አዳሪ በማድረግ አታዋርዳት። 30  “‘ሰንበቶቼን ጠብቁ፤ ለመቅደሴ አክብሮት ይኑራችሁ። እኔ ይሖዋ ነኝ። 31  “‘ወደ መናፍስት ጠሪዎች አትሂዱ፤ ጠንቋዮችንም አትጠይቁ፤ እንዲህ ካደረጋችሁ በእነሱ ትረክሳላችሁ። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። 32  “‘በሸበተው ሰው ፊት ተነስ፤ አረጋዊውንም አክብር፤ አምላክህን ፍራ። እኔ ይሖዋ ነኝ። 33  “‘በምድራችሁ አብሯችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ካለ አትበድሉት። 34  አብሯችሁ የሚኖረውን የባዕድ አገር ሰው እንደ አገራችሁ ተወላጅ አድርጋችሁ ተመልከቱት፤ እንደ ራሳችሁ አድርጋችሁም ውደዱት፤ ምክንያቱም እናንተም በግብፅ ምድር ሳላችሁ የባዕድ አገር ሰው ነበራችሁ። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። 35  “‘ርዝመትን፣ ክብደትን ወይም መጠንን ስትለኩ በተጭበረበረ መለኪያ አትጠቀሙ። 36  ትክክለኛ ሚዛን፣ ትክክለኛ የሚዛን ድንጋዮች፣ ትክክለኛ የደረቅ ነገር መስፈሪያና ትክክለኛ የፈሳሽ ነገር መለኪያ ሊኖራችሁ ይገባል። ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። 37  ስለሆነም ደንቦቼን ሁሉና ድንጋጌዎቼን በሙሉ ጠብቁ፤ እንዲሁም ፈጽሟቸው። እኔ ይሖዋ ነኝ።’”
[]
[]
[]
[]
12,448
2  “‘አንድ ሰው ለይሖዋ የእህል መባ የሚያቀርብ ከሆነ መባው የላመ ዱቄት መሆን አለበት፤ በላዩም ላይ ዘይት ያፍስበት፤ ነጭ ዕጣንም ያስቀምጥበት። 2  ከዚያም ካህናት ወደሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆች ያመጣዋል፤ ካህኑም ከላዩ ላይ አንድ እፍኝ የላመ ዱቄትና ዘይት፣ ነጭ ዕጣኑንም በሙሉ ይወስዳል፤ ይህንም አምላክ መላውን መባ እንዲያስበው የሚያደርግ መባ ይኸውም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል። 3  ከእህል መባው የተረፈው ማንኛውም ነገር የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ነው፤ ይህም ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች የተረፈ ስለሆነ እጅግ ቅዱስ ነው። 4  “‘በመጋገሪያ ምድጃ የተጋገረ የእህል መባ የምታቀርብ ከሆነ ከላመ ዱቄት በዘይት ተለውሶ የተጋገረ እርሾ ያልገባበት የቀለበት ቅርጽ ያለው ዳቦ ወይም ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ መሆን ይኖርበታል። 5  “‘መባህ በምጣድ የተጋገረ የእህል መባ ከሆነ በዘይት ከተለወሰ እርሾ ያልገባበት የላመ ዱቄት የተጋገረ መሆን ይኖርበታል። 6  መቆራረስ አለበት፤ ዘይትም አፍስበት። ይህ የእህል መባ ነው። 7  “‘መባህ በድስት የተዘጋጀ የእህል መባ ከሆነ ከላመ ዱቄትና ከዘይት የተሠራ መሆን ይኖርበታል። 8  ከእነዚህ ነገሮች የተዘጋጀውን የእህል መባ ወደ ይሖዋ ማምጣት ይኖርብሃል፤ ወደ መሠዊያው ለሚያቀርበውም ካህን ይሰጠው። 9  ካህኑም አምላክ መላውን መባ እንዲያስበው የሚያደርግ መባ እንዲሆን ከእህል መባው ላይ የተወሰነውን በማንሳት ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል። 10  ከእህል መባው የተረፈው የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ነው፤ ይህም ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች የተረፈ ስለሆነ እጅግ ቅዱስ ነው። 11  “‘እርሾ ወይም ማር ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጋችሁ ማጨስ ስለሌለባችሁ ለይሖዋ ከምታቀርቡት የእህል መባ ውስጥ እርሾ የገባበት ምንም ነገር አይኑር። 12  “‘እነዚህንም የፍሬ በኩራት መባ አድርጋችሁ ለይሖዋ ልታቀርቧቸው ትችላላችሁ፤ ሆኖም ደስ እንደሚያሰኝ መዓዛ ሆነው ወደ መሠዊያው መምጣት የለባቸውም። 13  “‘የምታቀርበው የእህል መባ በሙሉ በጨው መቀመም አለበት፤ የአምላክህ የቃል ኪዳን ጨውም ከእህል መባህ ላይ አይጥፋ። ከማንኛውም መባህ ጋር ጨው አብረህ ታቀርባለህ። 14  “‘መጀመሪያ የደረሰውን ፍሬ የእህል መባ አድርገህ ለይሖዋ የምታቀርብ ከሆነ የደረሰውን ሆኖም ገና እሸት የሆነውን በእሳት የተጠበሰና የተከካ እህል መጀመሪያ ላይ እንደደረሰው ፍሬህ የእህል መባ አድርገህ አቅርብ። 15  በላዩም ላይ ዘይት ትጨምርበታለህ፤ ነጭ ዕጣንም ታስቀምጥበታለህ። ይህ የእህል መባ ነው። 16  ካህኑም ከተከካው እህልና ከዘይቱ የተወሰነውን፣ ነጭ ዕጣኑንም በሙሉ ወስዶ አምላክ መላውን መባ እንዲያስበው የሚያደርግ መባ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ ያጨሰዋል።
[]
[]
[]
[]
12,449
20  ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘ልጁን ለሞሎክ የሚሰጥ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም እስራኤል ውስጥ የሚኖር ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው ይገደል። የአገሩ ሰዎች በድንጋይ ወግረው ይግደሉት። 3  ልጆቹን ለሞሎክ ስለሰጠ እንዲሁም ቅዱሱን ስፍራዬን ስላረከሰና ቅዱሱን ስሜን ስላቃለለ እኔ ራሴ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቁርበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። 4  የአገሩ ሰዎች ሰውየው ልጁን ለሞሎክ በመስጠት የፈጸመውን ድርጊት አይተው እንዳላዩ ቢሆኑና ሳይገድሉት ቢቀሩ 5  እኔ ራሴ በዚህ ሰውና በቤተሰቡ ላይ እነሳባቸዋለሁ። ያንን ሰውም ሆነ ከሞሎክ ጋር ምንዝር በመፈጸም የእሱን ፈለግ የተከተሉትን ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ለይቼ አጠፋቸዋለሁ። 6  “‘አንድ ሰው ከመናፍስት ጠሪዎችና ከጠንቋዮች ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ለመፈጸም ወደ እነሱ ቢሄድ እኔ በዚያ ሰው ላይ በእርግጥ እነሳበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። 7  “‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ስለሆንኩ ራሳችሁን ቀድሱ፤ ቅዱሳንም ሁኑ። 8  ደንቦቼን ጠብቁ፤ እንዲሁም ፈጽሟቸው። የምቀድሳችሁ እኔ ይሖዋ ነኝ። 9  “‘አባቱን ወይም እናቱን የሚረግም ማንኛውም ሰው ይገደል። አባቱን ወይም እናቱን ስለረገመ ደሙ በራሱ ላይ ነው። 10  “‘ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ምንዝር የሚፈጽምን ሰው በተመለከተ እንዲህ ይደረግ፦ ከባልንጀራው ሚስት ጋር ምንዝር የሚፈጽም ሰው ይገደል፤ አመንዝራውም ሆነ አመንዝራይቱ ይገደሉ። 11  ከአባቱ ሚስት ጋር የተኛ ሰው አባቱን ለኀፍረት ዳርጎታል። ሁለቱም ይገደሉ። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው። 12  አንድ ሰው ከልጁ ሚስት ጋር ቢተኛ ሁለቱም ይገደሉ። ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ ድርጊት ፈጽመዋል። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው። 13  “‘አንድ ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱም አስጸያፊ ድርጊት ፈጽመዋል። ስለዚህ ይገደሉ። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው። 14  “‘አንድ ሰው አንዲትን ሴትና እናቷን ቢያገባ፣ ይህ ጸያፍ ድርጊት ነው። ይህ ጸያፍ ምግባር በመካከላችሁ እንዳይቀጥል እሱንም ሆነ እነሱን በእሳት ያቃጥሏቸው። 15  “‘አንድ ሰው ከእንስሳ ጋር የፆታ ግንኙነት ቢፈጽም ይገደል፤ እንስሳውንም ግደሉት። 16  አንዲት ሴት የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ወደ ማንኛውም እንስሳ ብትቀርብ ሴትየዋንም ሆነ እንስሳውን ግደል፤ ሁለቱም ይገደሉ። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው። 17  “‘አንድ ሰው ከእህቱ ማለትም ከአባቱ ሴት ልጅ ወይም ከእናቱ ሴት ልጅ ጋር የፆታ ግንኙነት ቢፈጽምና እርቃኗን ቢያይ፣ እሷም የእሱን እርቃን ብታይ ይህ አሳፋሪ ድርጊት ነው። በሕዝቦቻቸው ልጆች ፊት እንዲጠፉ ይደረጉ። እህቱን ለኀፍረት ዳርጓል። ለፈጸመው ጥፋት ይጠየቅበታል። 18  “‘አንድ ሰው በወር አበባዋ ወቅት ከአንዲት ሴት ጋር ቢተኛና ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት ቢፈጽም እሱም ሆነ እሷ የሚፈሰውን ደሟን ገልጠዋል። ስለሆነም ሁለቱም ከሕዝቦቻቸው መካከል ተለይተው እንዲጠፉ ይደረጉ። 19  “‘ከእናትህ እህት ወይም ከአባትህ እህት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ምክንያቱም ይህ የሥጋ ዘመድን ለኀፍረት መዳረግ ነው። ለፈጸሙት ጥፋት ይጠየቁበታል። 20  ከአጎቱ ሚስት ጋር የተኛ ሰው አጎቱን ለኀፍረት ዳርጓል። ለፈጸሙት ኃጢአት ይጠየቁበታል። ልጅ ሳይኖራቸው ይሙቱ። 21  አንድ ሰው የወንድሙን ሚስት ቢወስድ ይህ አስጸያፊ ድርጊት ነው። ወንድሙን ለኀፍረት ዳርጓል። ያለልጅም ይቅሩ። 22  “‘ትኖሩባት ዘንድ እናንተን የማስገባባት ምድር እንዳትተፋችሁ ደንቦቼንና ድንጋጌዎቼን ሁሉ ጠብቁ፤ እንዲሁም ፈጽሟቸው። 23  ከፊታችሁ አባርሬ የማስወጣቸው ብሔራት በሚመሩባቸው ደንቦች አትሂዱ፤ ምክንያቱም እነሱ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አድርገዋል፤ እኔም እጸየፋቸዋለሁ። 24  በመሆኑም እንዲህ አልኳችሁ፦ “ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ እኔ ደግሞ ወተትና ማር የምታፈሰውን ምድር እንድትወርሷት እሰጣችኋለሁ። ከሕዝቦች የለየኋችሁ አምላካችሁ ይሖዋ እኔ ነኝ።” 25  ንጹሕ በሆነውና ርኩስ በሆነው እንስሳ እንዲሁም ርኩስ በሆነውና ንጹሕ በሆነው ወፍ መካከል ልዩነት አድርጉ፤ እኔ ርኩስ ነው ብዬ በለየሁላችሁ እንስሳ ወይም ወፍ አሊያም መሬት ለመሬት በሚሄድ ማንኛውም ነገር ራሳችሁን አታርክሱ። 26  እኔ ይሖዋ ቅዱስ ስለሆንኩ እናንተም ለእኔ ቅዱስ ልትሆኑ ይገባል፤ የእኔ ትሆኑ ዘንድ ከሌሎች ሕዝቦች ለየኋችሁ። 27  “‘መናፍስት ጠሪ ወይም ጠንቋይ የሆነ ወንድ ወይም የሆነች ሴት ካሉ ይገደሉ። ሕዝቡ በድንጋይ ወግሮ ይግደላቸው። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።’”
[]
[]
[]
[]
12,450
21  ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለካህናቱ ማለትም ለአሮን ወንዶች ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ማንም ሰው ከሕዝቦቹ መካከል ለሞተ ሰው ራሱን አያርክስ። 2  ይሁንና ለቅርብ የሥጋ ዘመዱ ይኸውም ለእናቱ፣ ለአባቱ፣ ለወንድ ልጁ፣ ለሴት ልጁ፣ ለወንድሙ እንዲህ ማድረግ ይችላል፤ 3  እንዲሁም ድንግል ለሆነች፣ ለምትቀርበውና ላላገባች እህቱ ሲል ራሱን ማርከስ ይችላል። 4  ከሕዝቡ መካከል ባል ላገባች ሴት ሲል ራሱን ማርከስና ማዋረድ የለበትም። 5  ራሳቸውን መላጨት ወይም የጢማቸውን ዳር ዳር መላጨት አሊያም ሰውነታቸውን መተልተል የለባቸውም። 6  የአምላካቸው ምግብ የሆኑትን ለይሖዋ በእሳት የሚቀርቡትን መባዎች የሚያቀርቡት እነሱ ስለሆኑ ለአምላካቸው ቅዱሳን መሆንና የአምላካቸውን ስም ከማርከስ መራቅ አለባቸው፤ ቅዱሳን መሆን ይኖርባቸዋል። 7  ዝሙት አዳሪ የሆነችን ይኸውም የረከሰችን ሴት ወይም ከባሏ የተፋታችን ሴት አያግቡ፤ ምክንያቱም ካህኑ ለአምላኩ ቅዱስ ነው። 8  የአምላክህን ምግብ የሚያቀርበው እሱ ስለሆነ ቀድሰው። እናንተን የምቀድሳችሁ እኔ ይሖዋ ቅዱስ ስለሆንኩ እሱም በአንተ ፊት ቅዱስ ሆኖ መገኘት አለበት። 9  “‘የአንድ ካህን ሴት ልጅ ዝሙት አዳሪ በመሆን ራሷን ብታረክስ አባቷን ታረክሳለች። ስለዚህ በእሳት መቃጠል አለባት። 10  “‘ከወንድሞቹ መካከል ሊቀ ካህናት በመሆን በራሱ ላይ የቅብዓት ዘይት የሚፈስበትና የክህነት ልብሶቹን እንዲለብስ የተሾመው ካህን ፀጉሩን ማንጨብረር ወይም ልብሶቹን መቅደድ የለበትም። 11  ወደ ሞተ ሰው አይጠጋ። ሌላው ቀርቶ ለአባቱ ወይም ለእናቱ ሲል ራሱን አያርክስ። 12  ለአምላክ የተወሰኑ መሆንን የሚያሳየው ምልክት ይኸውም የአምላኩ የቅብዓት ዘይት በላዩ ላይ ስላለ ከመቅደሱ መውጣትም ሆነ የአምላኩን መቅደስ ማርከስ የለበትም። እኔ ይሖዋ ነኝ። 13  “‘የሚያገባው ድንግል የሆነችን ሴት መሆን ይኖርበታል። 14  ባል የሞተባትን፣ ከባሏ የተፋታችን፣ የረከሰችን ወይም ዝሙት አዳሪ የሆነችን ሴት አያግባ፤ ሆኖም ከሕዝቡ መካከል ድንግል የሆነችውን ያግባ። 15  እሱን የምቀድሰው እኔ ይሖዋ ስለሆንኩ በሕዝቡ መካከል ዘሩን ማርከስ የለበትም።’” 16  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 17  “አሮንን እንዲህ በለው፦ ‘ከዘርህ መካከል በትውልዶቹ ሁሉ በሰውነቱ ላይ እንከን ያለበት ማንም ሰው የአምላኩን ምግብ ለማቅረብ አይምጣ። 18  እንደሚከተሉት ያሉ እንከኖች ያሉበት ማንም ሰው መቅረብ የለበትም፦ ዓይነ ስውር ወይም አንካሳ አሊያም የፊቱ ገጽታ የተበላሸ ወይም አንዱ እግሩ ወይም አንዱ እጁ የረዘመ 19  አሊያም እግሩ የተሰበረ ወይም እጁ የተሰበረ ሰው 20  አሊያም ጀርባው ላይ ጉብር ያለበት ወይም ድንክ የሆነ አሊያም የዓይን ችግር ያለበት ወይም ችፌ የያዘው አሊያም ጭርት ያለበት ወይም የዘር ፍሬው የተጎዳ አይቅረብ። 21  ከካህኑ ከአሮን ዘር እንከን ያለበት ማንኛውም ሰው በእሳት የሚቀርቡትን የይሖዋን መባዎች ለማቅረብ አይምጣ። ይህ ሰው እንከን ስላለበት የአምላኩን ምግብ ለማቅረብ መምጣት አይችልም። 22  እጅግ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮችና ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች የአምላኩን ምግብ መብላት ይችላል። 23  ሆኖም እንከን ስላለበት ወደ መጋረጃው አይቅረብ፤ ወደ መሠዊያውም አይጠጋ፤ የምቀድሳቸው እኔ ይሖዋ ስለሆንኩ መቅደሴን አያርክስ።’” 24  ስለዚህ ሙሴ ይህን ለአሮን፣ ለወንዶች ልጆቹና ለእስራኤላውያን በሙሉ ነገራቸው።
[]
[]
[]
[]
12,451
22  በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ፣ እስራኤላውያን የሚያመጧቸውን ቅዱስ ነገሮች የሚይዙበትን መንገድ በተመለከተ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና ለእኔ የተቀደሱ አድርገው በለዩአቸው ነገሮች ቅዱስ ስሜን እንዳያረክሱ ንገራቸው። እኔ ይሖዋ ነኝ። 3  እንዲህ በላቸው፦ ‘በትውልዶቻችሁ ሁሉ ከልጆቻችሁ መካከል ረክሶ እያለ እስራኤላውያን ለይሖዋ የተቀደሱ አድርገው ወደለዩአቸው ቅዱስ ነገሮች የሚቀርብ ሰው ካለ ያ ሰው ከፊቴ እንዲጠፋ ይደረግ። እኔ ይሖዋ ነኝ። 4  ከአሮን ልጆች መካከል የሥጋ ደዌ ያለበት ወይም ፈሳሽ የሚወጣው ማንኛውም ሰው ንጹሕ እስኪሆን ድረስ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች መብላት የለበትም፤ የሞተን ሰው በመንካት የረከሰን ሰው የነካ ወይም ከሰውነቱ የዘር ፈሳሽ የሚወጣው 5  አሊያም ርኩስ የሆነን የሚርመሰመስ ፍጡር የነካ ወይም ደግሞ ሊያረክሰው በሚችል በማንኛውም ዓይነት ነገር የረከሰን ሰው የነካ ሰው ከእነዚህ ነገሮች አይብላ። 6  እንደነዚህ ያሉ ነገሮችን የነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ገላውንም በውኃ እስካልታጠበ ድረስ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች መብላት አይችልም። 7  ፀሐይ በምትጠልቅበት ጊዜ ንጹሕ ይሆናል፤ ከዚያ በኋላ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች መብላት ይችላል፤ ምክንያቱም ይህ ምግቡ ነው። 8  በተጨማሪም እንዳይረክስ ሞቶ የተገኘን ወይም አውሬ የቦጫጨቀውን የማንኛውንም እንስሳ ሥጋ መብላት የለበትም። እኔ ይሖዋ ነኝ። 9  “‘ለእኔ የገቡትን ግዴታ ባለመጠበቅ በራሳቸው ላይ ኃጢአት እንዳያመጡና በዚህም የተነሳ ቅዱስ የሆነውን ነገር በማርከስ እንዳይሞቱ የገቡትን ግዴታ መጠበቅ አለባቸው። የምቀድሳቸው እኔ ይሖዋ ነኝ። 10  “‘ያልተፈቀደለት ማንኛውም ሰው ቅዱስ የሆነውን የትኛውንም ነገር መብላት የለበትም። ካህኑ ቤት በእንግድነት ያረፈ ሰው ወይም ቅጥር ሠራተኛ ቅዱስ ከሆነው ነገር መብላት የለበትም። 11  ሆኖም አንድ ካህን በገዛ ገንዘቡ አንድ ሰው ቢገዛ ያ ሰው ከምግቡ መካፈል ይችላል። በቤቱ የተወለዱ ባሪያዎችም ከእሱ ምግብ መካፈል ይችላሉ። 12  የአንድ ካህን ሴት ልጅ፣ ካህን ያልሆነን ሰው ብታገባ በመዋጮ ከተሰጡት ቅዱስ የሆኑ ነገሮች መብላት አትችልም። 13  ይሁንና የአንድ ካህን ሴት ልጅ፣ ባሏ ቢሞት ወይም ብትፋታና ልጅ ባይኖራት እንደ ወጣትነቷም ጊዜ ወደ አባቷ ቤት ብትመለስ ከአባቷ ምግብ መብላት ትችላለች፤ ያልተፈቀደለት ማንኛውም ሰው ግን ከዚያ መብላት የለበትም። 14  “‘አንድ ሰው ቅዱስ ከሆነው ነገር ባለማወቅ ቢበላ የቅዱሱን ነገር ዋጋ አንድ አምስተኛ በመጨመር ቅዱስ የሆነውን መባ ለካህኑ ይስጥ። 15  ካህናቱ፣ እስራኤላውያን ለይሖዋ መዋጮ አድርገው የሰጧቸውን ቅዱስ ነገሮች ማርከስ 16  እንዲሁም ሕዝቡ ያመጣቸውን ቅዱስ ነገሮች እንዲበላና በራሱ ላይ ቅጣት የሚያስከትል በደል እንዲፈጽም ማድረግ የለባቸውም፤ ምክንያቱም የምቀድሳቸው እኔ ይሖዋ ነኝ።’” 17  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 18  “ለአሮን፣ ለወንዶች ልጆቹና ለእስራኤላውያን በሙሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ስእለቱን ለመፈጸም ወይም የፈቃደኝነት መባ ለማቅረብ ሲል የሚቃጠል መባውን ለይሖዋ የሚያቀርብ አንድ እስራኤላዊ ወይም በእስራኤል ውስጥ የሚኖር አንድ የባዕድ አገር ሰው 19  ተቀባይነት እንዲያገኝ ከፈለገ መሥዋዕቱ ከመንጋው፣ ከጠቦቶቹ ወይም ከፍየሎቹ መካከል የተወሰደ እንከን የሌለበት ተባዕት መሆን ይኖርበታል። 20  ተቀባይነት ስለማያስገኝላችሁ እንከን ያለበትን ማንኛውንም ነገር አታቅርቡ። 21  “‘አንድ ሰው ስእለቱን ለመፈጸም ወይም የፈቃደኝነት መባ ለመስጠት ሲል ለይሖዋ የኅብረት መሥዋዕት ቢያቀርብ መሥዋዕቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከከብቶቹ ወይም ከመንጋው መካከል እንከን የሌለበትን ማቅረብ ይኖርበታል። ምንም ዓይነት እንከን ሊኖርበት አይገባም። 22  መባ ሆኖ የሚቀርበው እንስሳ ዕውር ወይም ሰባራ አሊያም ቆራጣ ወይም ደግሞ ኪንታሮት አሊያም እከክ ወይም ጭርት ያለበት መሆን የለበትም፤ እንዲህ ያለውን እንስሳ ለይሖዋ ማቅረብ የለባችሁም ወይም እንዲህ ያለውን መባ ለይሖዋ በመሠዊያው ላይ ማቅረብ የለባችሁም። 23  አንዱ እግሩ የረዘመን ወይም ያጠረን በሬ ወይም በግ የፈቃደኝነት መባ አድርጋችሁ ማቅረብ ትችላላችሁ፤ የስእለት መባ አድርጋችሁ ብታቀርቡት ግን ተቀባይነት አይኖረውም። 24  የዘር ፍሬው ጉዳት የደረሰበትን ወይም የተቀጠቀጠን አሊያም ተሰንጥቆ የወጣን ወይም የተቆረጠን እንስሳ ለይሖዋ ማቅረብ የለባችሁም፤ በምድራችሁ እነዚህን የመሰሉ እንስሳትን ማቅረብ አይኖርባችሁም። 25  እነዚህ ጉድለትና እንከን ስላለባቸው ከመካከላቸው የትኛውንም ከባዕድ ሰው እጅ በመቀበል የአምላካችሁ ምግብ አድርጋችሁ ማቅረብ የለባችሁም። ተቀባይነት አያገኙላችሁም።’” 26  በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 27  “ጥጃ ወይም የበግ ግልገል አሊያም የፍየል ግልገል በሚወለድበት ጊዜ ለሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቆይ፤ ከስምንተኛው ቀን አንስቶ ግን መባ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ሆኖ ቢቀርብ ተቀባይነት ይኖረዋል። 28  ላምን ከጥጃዋ ወይም በግን ከግልገሏ ጋር በአንድ ቀን አትረዱ። 29  “ለይሖዋ የምሥጋና መሥዋዕት የምትሠዉ ከሆነ ተቀባይነት በሚያስገኝላችሁ መንገድ ልትሠዉት ይገባል። 30  መሥዋዕቱ በዚያው ዕለት መበላት ይኖርበታል። ከእሱም ላይ ምንም አስተርፋችሁ አታሳድሩ። እኔ ይሖዋ ነኝ። 31  “እናንተም ትእዛዛቴን ጠብቁ፤ እንዲሁም ፈጽሟቸው። እኔ ይሖዋ ነኝ። 32  ቅዱሱን ስሜን አታርክሱ፤ እኔ በእስራኤላውያን መካከል ልቀደስ ይገባኛል። የምቀድሳችሁ እኔ ይሖዋ ነኝ፤ 33  አምላክ መሆኔን ለእናንተ ለማሳየት ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ነኝ። እኔ ይሖዋ ነኝ።”
[]
[]
[]
[]
12,452
23  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ልታውጇቸው የሚገቡት በየወቅቱ የሚከበሩ የይሖዋ በዓላት ቅዱስ ጉባኤዎች ናቸው። በየወቅቱ የሚከበሩት የእኔ በዓላት የሚከተሉት ናቸው፦ 3  “‘ለስድስት ቀን ሥራ መሥራት ይቻላል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ሰንበት ይኸውም ቅዱስ ጉባኤ ነው። ምንም ዓይነት ሥራ መሥራት የለባችሁም። በምትኖሩባቸው ቦታዎች ሁሉ ይህ የይሖዋ ሰንበት ነው። 4  “‘በተወሰነላቸው ጊዜ ላይ ልታውጇቸው የሚገቡት በየወቅቱ የሚከበሩ የይሖዋ በዓላት ማለትም ቅዱስ ጉባኤዎች የሚከተሉት ናቸው፦ 5  በመጀመሪያው ወር ከወሩም በ14ኛው ቀን አመሻሹ ላይ ለይሖዋ ፋሲካ ይከበራል። 6  “‘በዚህ ወር 15ኛ ቀን ላይ የቂጣ በዓል ለይሖዋ ይከበራል። ለሰባት ቀንም ቂጣ መብላት ይኖርባችኋል። 7  በመጀመሪያው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ታከብራላችሁ። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም። 8  ሆኖም ለሰባት ቀን ያህል ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ታቀርባላችሁ። በሰባተኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ይሆናል። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም።’” 9  በመቀጠልም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 10  “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ የምድሪቱን አዝመራ በምታጭዱበት ጊዜ ከአዝመራችሁ መጀመሪያ የደረሰውን እህል ነዶ ለካህኑ ማምጣት አለባችሁ። 11  እሱም ተቀባይነት እንድታገኙ ነዶውን በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ይወዝውዘው። ካህኑ በሰንበት ማግስት ነዶውን ወዲያና ወዲህ ሊወዘውዘው ይገባል። 12  ነዶው ወዲያና ወዲህ እንዲወዘወዝ በምታደርጉበት ቀን አንድ ዓመት ገደማ የሆነው እንከን የሌለበት ጠቦት ለይሖዋ የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ማቅረብ አለባችሁ። 13  ከዚህም ጋር ሁለት አሥረኛ ኢፍ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። በተጨማሪም አንድ አራተኛ ሂን የወይን ጠጅ ከዚያ ጋር የመጠጥ መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። 14  የአምላካችሁን መባ እስከምታቀርቡበት እስከዚህ ቀን ድረስ ምንም ዓይነት ዳቦም ሆነ ቆሎ ወይም እሸት መብላት የለባችሁም። በምትኖሩበት በየትኛውም ቦታ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህ ዘላቂ ደንብ ነው። 15  “‘ከሰንበት ማግስት ይኸውም ለሚወዘወዝ መባ የሚሆነውን ነዶ ካመጣችሁበት ቀን ጀምሮ ሰባት ሰንበቶችን ቁጠሩ። እነሱም ሙሉ ሳምንታት መሆን አለባቸው። 16  እስከ ሰባተኛው ሰንበት ማግስት ድረስ 50 ቀን ቁጠሩ፤ ከዚያም ለይሖዋ አዲስ የእህል መባ አቅርቡ። 17  ከምትኖሩባቸው ቦታዎች ሁለት ቂጣዎችን ለሚወዘወዝ መባ ማምጣት ይኖርባችኋል። እነሱም ከሁለት አሥረኛ ኢፍ የላመ ዱቄት የተዘጋጁ መሆን አለባቸው። ለይሖዋ የሚቀርቡ መጀመሪያ የደረሱ ፍሬዎች እንደመሆናቸው መጠን እርሾ ገብቶባቸው መጋገር ይኖርባቸዋል። 18  ከቂጣዎቹም ጋር እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸውና እንከን የሌለባቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች፣ አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች አቅርቡ። እነዚህም ከእህል መባቸውና ከመጠጥ መባዎቻቸው ጋር ለይሖዋ የሚቃጠል መባ ማለትም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ ሆነው ይቀርባሉ። 19  እንዲሁም ለኃጢአት መባ እንዲሆን ከፍየሎች መካከል አንድ ግልገል፣ ለኅብረት መሥዋዕት እንዲሆኑ ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶችን አቅርቡ። 20  ካህኑም መጀመሪያ ከደረሱ ፍሬዎች ከተዘጋጁት ቂጣዎችና ከሁለቱ ተባዕት ጠቦቶች ጋር በይሖዋ ፊት የሚወዘወዝ መባ አድርጎ ወዲያና ወዲህ ይወዝውዛቸው። እነዚህም ለይሖዋ የተቀደሱ ነገሮች ናቸው፤ የካህኑም ድርሻ ይሆናሉ። 21  በዚህ ቀን ለእናንተ ቅዱስ ጉባኤ ታውጃላችሁ። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ አትሥሩ። በምትኖሩበት በየትኛውም ቦታ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህ ዘላቂ ደንብ ነው። 22  “‘የምድራችሁን አዝመራ በምታጭዱበት ጊዜ የእርሻችሁን ዳርና ዳር ሙልጭ አድርጋችሁ አትጨዱት፤ የእርሻችሁን ቃርሚያም አትልቀሙ። እነዚህን ለድሃውና ለባዕድ አገሩ ሰው ተዉለት። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’” 23  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 24  “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘በሰባተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን መለከት በመንፋት የሚታሰብ ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ቅዱስ ጉባኤ ታከብራላችሁ። 25  ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ አትሥሩ፤ ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ታቀርባላችሁ።’” 26  በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 27  “ሆኖም የዚህ የሰባተኛው ወር አሥረኛ ቀን የስርየት ቀን ነው። ቅዱስ ጉባኤ አክብሩ፣ ራሳችሁን አጎሳቁሉ እንዲሁም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አቅርቡ። 28  ይህ ቀን በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ለእናንተ ማስተሰረያ የሚቀርብበት የስርየት ቀን ስለሆነ በዚህ ቀን ምንም ዓይነት ሥራ መሥራት የለባችሁም። 29  በዚህ ቀን ራሱን የማያጎሳቁል ማንኛውም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረጋል። 30  በዚህ ቀን ምንም ዓይነት ሥራ የሚሠራን ሰው ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። 31  ምንም ዓይነት ሥራ መሥራት የለባችሁም። በምትኖሩበት በየትኛውም ቦታ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህ ዘላቂ ደንብ ነው። 32  ይህ እናንተ ሙሉ በሙሉ የምታርፉበት ሰንበት ነው፤ በወሩም ዘጠነኛ ቀን ምሽት ላይ ራሳችሁን ታጎሳቁላላችሁ። ሰንበታችሁንም ከዚያ ዕለት ምሽት አንስቶ እስከ ቀጣዩ ቀን ምሽት ድረስ አክብሩ።” 33  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 34  “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘በዚህ በሰባተኛው ወር ከ15ኛው ቀን ጀምሮ ለሰባት ቀን ያህል ለይሖዋ የዳስ በዓል ይከበራል። 35  በመጀመሪያው ቀን ላይ ቅዱስ ጉባኤ ይሆናል፤ እናንተም ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም። 36  ለሰባት ቀን ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ማቅረብ ይኖርባችኋል። በስምንተኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ታከብራላችሁ፤ ለይሖዋም በእሳት የሚቀርብ መባ ማቅረብ አለባችሁ። ይህ የተቀደሰ ጉባኤ ነው። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ አትሥሩ። 37  “‘ለይሖዋ በእሳት የሚቀርበውን መባ ማለትም የሚቃጠለውን መባ፣ ከመሥዋዕቱ ጋር የሚቀርበውን የእህል መባና በየዕለቱ እንዲቀርቡ የተመደቡትን የመጠጥ መባዎች ለማቅረብ ቅዱስ ጉባኤዎች እንደሆኑ አድርጋችሁ የምታውጇቸው በየወቅቱ የሚከበሩት የይሖዋ በዓላት እነዚህ ናቸው። 38  እነዚህ ለይሖዋ ልትሰጧቸው ከሚገቡት በይሖዋ ሰንበቶች ላይ ከሚቀርቡት፣ ከስጦታዎቻችሁ፣ ስእለት ለመፈጸም ከምታቀርቧቸው መባዎችና ከፈቃደኝነት መባዎቻችሁ በተጨማሪ የምታቀርቧቸው ናቸው። 39  ይሁን እንጂ የምድራችሁን ፍሬ በምትሰበስቡበት ጊዜ በሰባተኛው ወር ላይ ከ15ኛው ቀን ጀምሮ የይሖዋን በዓል ለሰባት ቀን ታከብራላችሁ። የመጀመሪያው ቀን ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ሰንበት ይሆናል፤ ስምንተኛውም ቀን ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ሰንበት ይሆናል። 40  በመጀመሪያውም ቀን የተንዠረገጉ ዛፎችን ፍሬ፣ የዘንባባ ዝንጣፊዎችን፣ የለመለሙ ዛፎችን ቅርንጫፎችና በሸለቆ የሚበቅሉ የአኻያ ዛፎችን ውሰዱ፤ በአምላካችሁም በይሖዋ ፊት ለሰባት ቀን ተደሰቱ። 41  ይህን በዓል በየዓመቱ ለሰባት ቀን ለይሖዋ የሚከበር በዓል አድርጋችሁ ታከብሩታላችሁ። በትውልዶቻችሁም ሁሉ ዘላቂ ደንብ አድርጋችሁ በሰባተኛው ወር አክብሩት። 42  ለሰባት ቀን በዳስ ውስጥ ተቀመጡ። በእስራኤል የሚኖሩ የአገሩ ተወላጆች በሙሉ በዳስ ውስጥ ይቀመጡ፤ 43  ይህን የሚያደርጉት እስራኤላውያንን ከግብፅ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ በዳስ ውስጥ እንዲቀመጡ እንዳደረግኩ መጪዎቹ ትውልዶቻችሁ እንዲያውቁ ነው። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’” 44  ስለዚህ ሙሴ በየወቅቱ የሚከበሩትን የይሖዋን በዓላት ለእስራኤላውያን አስታወቀ።
[]
[]
[]
[]
12,453
24  ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “መብራቱ ያለማቋረጥ እንዲበራ ለማድረግ ለመብራቱ የሚሆን ተጨቅጭቆ የተጠለለ ንጹሕ የወይራ ዘይት እንዲያመጡልህ እስራኤላውያንን እዘዛቸው። 3  ከምሽት አንስቶ እስከ ጠዋት ድረስ መብራቱ በይሖዋ ፊት ያለማቋረጥ እንዲበራ አሮን በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ካለው ከምሥክሩ መጋረጃ ውጭ ያስቀምጠው። በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህ ዘላለማዊ ደንብ ነው። 4  ዘወትር በይሖዋ ፊት እንዲሆኑ መብራቶቹን ከንጹሕ ወርቅ በተሠራው መቅረዝ ላይ በቦታ በቦታቸው ያስቀምጣቸው። 5  “አንተም የላመ ዱቄት ወስደህ የቀለበት ቅርጽ ያላቸው 12 ዳቦዎችን ጋግር። እያንዳንዱ ዳቦ ከሁለት አሥረኛ ኢፍ ዱቄት የተዘጋጀ መሆን ይኖርበታል። 6  እነዚህንም በይሖዋ ፊት ባለው ከንጹሕ ወርቅ በተሠራው ጠረጴዛ ላይ ስድስት ስድስት አድርገህ በማነባበር በሁለት ረድፍ ታስቀምጣቸዋለህ። 7  ተነባብሮ በተቀመጠው በእያንዳንዱ ረድፍ ላይም ንጹሕ ነጭ ዕጣን አድርግ፤ ይህም ለምግቡ መታሰቢያ እንዲሆን ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ይሆናል። 8  እሱም በየሰንበቱ ዘወትር በይሖዋ ፊት ይደርድረው። ይህ በእኔና በእስራኤላውያን መካከል ያለ ዘላቂ ቃል ኪዳን ነው። 9  ይህም የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ይሆናል፤ ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች መካከል ለእሱ እጅግ ቅዱስ ነገር ስለሆነ ቅዱስ በሆነ ቦታ ይበሉታል፤ ይህ ዘላቂ ሥርዓት ነው።” 10  በእስራኤላውያን መካከል በእናቱ እስራኤላዊ በአባቱ ግን ግብፃዊ የሆነ አንድ ሰው ነበር፤ በሰፈሩም ውስጥ በእሱና በአንድ እስራኤላዊ መካከል ጠብ ተነሳ። 11  የእስራኤላዊቷም ልጅ የአምላክን ስም መሳደብና መራገም ጀመረ። በመሆኑም ወደ ሙሴ አመጡት። የእናትየውም ስም ሸሎሚት ነበር፤ እሷም ከዳን ነገድ የሆነው የዲብራይ ልጅ ነበረች። 12  እነሱም የይሖዋ ውሳኔ ግልጽ እስኪሆንላቸው ድረስ በጥበቃ ሥር እንዲቆይ አደረጉት። 13  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 14  “የተራገመውን ሰው ከሰፈሩ ውጭ አውጣው፤ የሰሙትም ሰዎች ሁሉ እጃቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት፤ መላው ጉባኤም በድንጋይ ይውገረው። 15  ለእስራኤላውያንም እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ማንኛውም ሰው አምላኩን ቢራገም ለሠራው ኃጢአት ይጠየቅበታል። 16  ስለሆነም የይሖዋን ስም የተሳደበው ሰው ይገደል። መላው ጉባኤም በድንጋይ ይውገረው። የባዕድ አገሩም ሰው የአምላክን ስም ከተሳደበ ልክ እንደ አገሩ ተወላጅ ይገደል። 17  “‘አንድ ሰው የሰው ሕይወት ካጠፋ ይገደል። 18  የቤት እንስሳን የገደለ ሰው፣ ሕይወት ስለ ሕይወት ካሳ አድርጎ መክፈል ይኖርበታል። 19  አንድ ሰው በባልንጀራው ላይ ጉዳት ቢያደርስ ልክ እሱ ያደረሰው ዓይነት ጉዳት በራሱ ላይ እንዲደርስ ይደረግ። 20  ስብራት ስለ ስብራት፣ ዓይን ስለ ዓይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ ይሁን፤ በሰውየው ላይ ያደረሰው ዓይነት ጉዳት በእሱ ላይ እንዲደርስ ይደረግ። 21  እንስሳን መትቶ የገደለ ስለ እንስሳው ካሳ መክፈል ይኖርበታል፤ ሰውን መትቶ የገደለ ግን መገደል አለበት። 22  “‘ለባዕድ አገሩም ሰው ሆነ ለአገሬው ተወላጅ፣ ለሁላችሁም የሚሠራው አንድ ዓይነት ድንጋጌ ነው፤ ምክንያቱም እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’” 23  ከዚያም ሙሴ ለእስራኤላውያን ነገራቸው፤ እነሱም የተራገመውን ሰው ከሰፈሩ ውጭ አውጥተው በድንጋይ ወገሩት። በዚህ መንገድ እስራኤላውያን ልክ ይሖዋ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።
[]
[]
[]
[]
12,454
25  በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን በሲና ተራራ ላይ እንዲህ አለው፦ 2  “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር በምትገቡበት ጊዜ ምድሪቱ ለይሖዋ ሰንበትን ማክበር ይኖርባታል። 3  ስድስት ዓመት በእርሻህ ላይ ዘር ዝራ፤ ስድስት ዓመት ወይንህን ግረዝ፤ እንዲሁም የምድሪቱን ምርት ሰብስብ። 4  ሰባተኛው ዓመት ግን ምድሪቱ ሙሉ በሙሉ የምታርፍበት ሰንበት ይኸውም የይሖዋ ሰንበት ይሁን። በእርሻህ ላይ ዘር አትዝራ ወይም ወይንህን አትግረዝ። 5  በማሳህ ላይ የበቀለውን ገቦ አትጨድ፤ ያልተገረዘውን ወይንህን ፍሬ አትልቀም። ምድሪቱ ለአንድ ዓመት ሙሉ በሙሉ ማረፍ ይኖርባታል። 6  ሆኖም ምድሪቱ በሰንበት እረፍቷ ጊዜ የምታበቅለውን እህል መብላት ትችላለህ፤ አንተ፣ ወንድ ባሪያህ፣ ሴት ባሪያህ፣ ቅጥር ሠራተኛህና አብረውህ የሚኖሩ ባዕዳን ሰፋሪዎች ልትበሉት ትችላላችሁ፤ 7  እንዲሁም በምድርህ ለሚኖሩ የቤትና የዱር እንስሳት ምግብ ይሁን። ምድሪቱ የምትሰጠው ምርት ሁሉ ለምግብነት ሊውል ይችላል። 8  “‘ሰባት የሰንበት ዓመታትን ማለትም ሰባት ጊዜ ሰባት ዓመታትን ትቆጥራለህ፤ ሰባቱ የሰንበት ዓመታትም 49 ዓመታት ይሆናሉ። 9  ከዚያም በሰባተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን ቀንደ መለከቱን ድምፁን ከፍ አድርገህ ትነፋዋለህ፤ በስርየት ቀን የቀንደ መለከቱ ድምፅ በምድራችሁ ሁሉ እንዲሰማ ማድረግ አለባችሁ። 10  ሃምሳኛውን ዓመት ቀድሱ፤ በምድሪቱም ለሚኖሩ ሁሉ ነፃነት አውጁ። ለእናንተ ኢዮቤልዩ ይሆንላችኋል፤ ከእናንተ እያንዳንዱ ወደየርስቱ ይመለሳል፤ ከእናንተም እያንዳንዱ ወደየቤተሰቡ ይመለስ። 11  ሃምሳኛው ዓመት ለእናንተ ኢዮቤልዩ ይሆንላችኋል። ዘር አትዘሩም ወይም ማሳ ላይ የበቀለውን ገቦ አታጭዱም አሊያም ያልተገረዘውን የወይን ፍሬ አትሰበስቡም። 12  ምክንያቱም ይህ ኢዮቤልዩ ነው። ለእናንተም ቅዱስ መሆን ይኖርበታል። ምድሪቱ በራሷ የምታበቅለውን ብቻ መብላት ትችላላችሁ። 13  “‘በዚህ የኢዮቤልዩ ዓመት ከእናንተ እያንዳንዱ ወደየርስቱ ይመለስ። 14  ለባልንጀራችሁ አንድ ነገር ብትሸጡ ወይም ከባልንጀራችሁ እጅ አንድ ነገር ብትገዙ አንዳችሁ ሌላውን መጠቀሚያ አታድርጉ። 15  ከባልንጀራህ ላይ መሬት ስትገዛ ከኢዮቤልዩ በኋላ ያሉትን ዓመታት ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብሃል፤ እሱም ሲሸጥልህ እህል የሚሰበሰብባቸውን የቀሩትን ዓመታት ማስላት ይኖርበታል። 16  ብዙ ዓመታት የሚቀሩ ከሆነ ዋጋውን መጨመር ይችላል፤ የሚቀሩት ዓመታት ጥቂት ከሆኑ ደግሞ ዋጋውን መቀነስ ይኖርበታል፤ ምክንያቱም የሚሸጥልህ አዝመራ የሚሰበሰብበትን ጊዜ አስልቶ ነው። 17  ከእናንተ መካከል ማንም ባልንጀራውን መጠቀሚያ ማድረግ የለበትም፤ አምላክህን ፍራ፤ ምክንያቱም እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። 18  ደንቦቼን ብትፈጽሙና ድንጋጌዎቼን ብትጠብቁ በምድሪቱ ላይ ያለስጋት ትኖራላችሁ። 19  ምድሪቱ ፍሬዋን ትሰጣለች፤ እናንተም እስክትጠግቡ ድረስ ትበላላችሁ፤ በዚያም ያለስጋት ትኖራላችሁ። 20  “‘ሆኖም ‘ዘር ካልዘራን ወይም እህል ካልሰበሰብን በሰባተኛው ዓመት ምን እንበላለን?’ ብትሉ 21  እኔ በስድስተኛው ዓመት በረከቴን እልክላችኋለሁ፤ ምድሪቱም ለሦስት ዓመት የሚበቃ እህል ታፈራለች። 22  ከዚያም በስምንተኛው ዓመት ዘር ትዘራላችሁ፤ እስከ ዘጠነኛውም ዓመት ድረስ ቀድሞ ከሰበሰባችሁት ትበላላችሁ። እህሉ እስኪደርስ ድረስ ቀድሞ የሰበሰባችሁትን ትበላላችሁ። 23  “‘ምድሪቱ የእኔ ስለሆነች መሬት ለዘለቄታው መሸጥ አይኖርበትም። ምክንያቱም እናንተ በእኔ አመለካከት የባዕድ አገር ሰዎችና ሰፋሪዎች ናችሁ። 24  በርስትነት በያዛችሁት ምድር ሁሉ መሬትን መልሶ መግዛት የሚያስችል መብት እንዲኖር አድርጉ። 25  “‘ወንድምህ ቢደኸይና ከርስቱ የተወሰነውን ለመሸጥ ቢገደድ የሚዋጅ የቅርብ ዘመዱ መጥቶ ወንድሙ የሸጠውን መልሶ ይግዛ። 26  አንድ ሰው የሚዋጅለት ቢያጣ ሆኖም እሱ ራሱ ሀብት ቢያገኝና መሬቱን ለመዋጀት የሚያስችል አቅም ቢኖረው 27  መሬቱን ከሸጠበት ጊዜ አንስቶ ያሉትን ዓመታት በመቁጠር ዋጋውን ያስላ፤ የዋጋውንም ልዩነት ለሸጠለት ሰው ይመልስ። ከዚያም ወደ ርስቱ መመለስ ይችላል። 28  “‘ሆኖም መሬቱን ከሰውየው ላይ ለማስመለስ የሚያስችል አቅም ባይኖረው የሸጠው መሬት እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ በገዢው እጅ ይቆያል፤ መሬቱም በኢዮቤልዩ ይመለስለታል፤ እሱም ወደ ርስቱ ይመለሳል። 29  “‘አንድ ሰው በቅጥር በታጠረ ከተማ ውስጥ የሚገኝን መኖሪያ ቤት ቢሸጥ ከሸጠበት ጊዜ አንስቶ እስከ አንድ ዓመት ድረስ የመዋጀት መብቱ እንደተጠበቀ ይቆያል፤ የመዋጀት መብቱ ለአንድ ዓመት ሙሉ እንደተጠበቀ ይቆያል። 30  ይሁንና ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት መልሶ ሊገዛው ካልቻለ በቅጥር በታጠረው ከተማ ውስጥ የሚገኘው ቤት ለዘለቄታው የገዢው ንብረት ሆኖ በትውልዶቹ ሁሉ ይቀጥላል። በኢዮቤልዩ ነፃ አይለቀቅም። 31  ቅጥር በሌላቸው መንደሮች ውስጥ የሚገኙ ቤቶች ግን በገጠራማ አካባቢ የሚገኝ የእርሻ መሬት ክፍል እንደሆኑ ይቆጠራሉ። የመዋጀት መብታቸው እንደተጠበቀ ይቆይ፤ በኢዮቤልዩም ነፃ ይለቀቁ። 32  “‘በሌዋውያን ከተሞች ውስጥ ያሉትን የሌዋውያን ቤቶች በተመለከተ ግን ሌዋውያኑ እነዚህን ቤቶች የመዋጀት መብታቸው ምንጊዜም የተጠበቀ ነው። 33  የሌዋውያን ንብረት ተመልሶ ካልተገዛ የእነሱ በሆነው ከተማ ውስጥ የሚገኘው የተሸጠው ቤት በኢዮቤልዩ ነፃ ይለቀቃል፤ ምክንያቱም በሌዋውያኑ ከተሞች ውስጥ የሚገኙት ቤቶች በእስራኤላውያን መካከል ያሉ የሌዋውያኑ ንብረቶች ናቸው። 34  ከዚህም በላይ በከተሞቻቸው ዙሪያ ያለው የግጦሽ መሬት ዘላለማዊ ርስታቸው ስለሆነ መሸጥ አይኖርበትም። 35  “‘በአቅራቢያህ ያለ ወንድምህ ቢደኸይና ራሱን ማስተዳደር ቢያቅተው አብሮህ በሕይወት ይኖር ዘንድ አንድን የባዕድ አገር ሰውና ሰፋሪ እንደምትረዳ ሁሉ ልትረዳው ይገባል። 36  ከእሱ ወለድ ወይም ትርፍ አትቀበል። ከዚህ ይልቅ አምላክህን ፍራ፤ ወንድምህም አብሮህ በሕይወት ይኖራል። 37  ገንዘብህን በወለድ አታበድረው ወይም እህል ስታበድረው ትርፍ አትጠይቀው። 38  የከነአንን ምድር በመስጠት አምላካችሁ መሆኔን አስመሠክር ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። 39  “‘በአቅራቢያህ የሚኖር ወንድምህ ቢደኸይና ራሱን ለአንተ ለመሸጥ ቢገደድ እንደ ባሪያ እንዲሠራ አታስገድደው። 40  እንደ ቅጥር ሠራተኛና እንደ ሰፋሪ ሊታይ ይገባዋል። እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ያገልግልህ። 41  ከዚያም እሱም ሆነ አብረውት ያሉት ልጆቹ ትተውህ ይሄዳሉ፤ ወደ ዘመዶቹም ይመለሳሉ። እሱም ወደ ቀድሞ አባቶቹ ርስት ይመለስ። 42  ምክንያቱም እነሱ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው ባሪያዎቼ ናቸው። እንደ ባሪያ ራሳቸውን መሸጥ የለባቸውም። 43  የጭካኔ ድርጊት ልትፈጽምበት አይገባም፤ አምላክህን መፍራት ይኖርብሃል። 44  ወንድ ባሪያዎቻችሁና ሴት ባሪያዎቻችሁ በዙሪያችሁ ካሉት ብሔራት የመጡ ይሁኑ፤ ከእነሱ መካከል ወንድ ባሪያ ወይም ሴት ባሪያ መግዛት ትችላላችሁ። 45  በተጨማሪም ከእናንተ ጋር ከሚኖሩት ባዕዳን ሰፋሪዎች እንዲሁም እነሱ በምድራችሁ ከወለዷቸው ቤተሰቦቻቸው መካከል ባሪያዎችን መግዛት ትችላላችሁ፤ እነሱም የእናንተ ንብረት ይሆናሉ። 46  እነሱንም እንደ ቋሚ ንብረት አድርጋችሁ ከእናንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆቻችሁ ማውረስ ትችላላችሁ። ባሪያ አድርጋችሁ ልታሠሯቸው ትችላላችሁ፤ ወንድሞቻችሁ የሆኑትን እስራኤላውያንን ግን በጭካኔ አትግዟቸው። 47  “‘በመካከልህ ያለ የባዕድ አገር ሰው ወይም ሰፋሪ ሀብታም ቢሆንና ከእሱ ጋር ያለው ወንድምህ ደግሞ ደህይቶ ለባዕድ አገሩ ሰው ወይም ሰፋሪ አሊያም ከባዕድ አገሩ ሰው ቤተሰብ መካከል ለአንዱ ራሱን ለመሸጥ ቢገደድ 48  ይህ ሰው ራሱን ከሸጠም በኋላ የመዋጀት መብቱ የተጠበቀ ይሆናል። ከወንድሞቹ አንዱ መልሶ ሊገዛው ይችላል፤ 49  ወይም ደግሞ አጎቱ አሊያም የአጎቱ ልጅ መልሶ ሊገዛው ይችላል፤ አሊያም ደግሞ ማንኛውም የቅርብ ዘመዱ ማለትም ከቤተሰቦቹ አንዱ መልሶ ሊገዛው ይችላል። “‘ወይም ደግሞ ሰውየው ራሱ ሀብት ካገኘ ራሱን መልሶ ሊገዛ ይችላል። 50  እሱም ራሱን ከሸጠበት ዓመት አንስቶ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ያለውን ጊዜ ከገዛው ሰው ጋር በመሆን ያስላ፤ የተሸጠበትም ገንዘብ ከዓመታቱ ብዛት ጋር የሚመጣጠን ይሁን። በዚህ ጊዜ ውስጥ ያሉት የሥራ ቀናት የሚሰሉት የአንድ ቅጥር ሠራተኛ የሥራ ቀናት በሚሰሉበት መንገድ ይሆናል። 51  ገና ብዙ ዓመታት የሚቀሩ ከሆነ እሱን ለመግዛት ከተከፈለው ገንዘብ ላይ የቀሪዎቹን ዓመታት ብዛት ግምት ውስጥ በማስገባት ራሱን የሚዋጅበትን ዋጋ ይክፈል። 52  እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የሚቀሩት ዓመታት ጥቂት ከሆኑ ደግሞ ይህን ለራሱ ያስላ፤ በቀሩት ዓመታት ብዛት ልክም የሚዋጅበትን ዋጋ ይክፈል። 53   ከእሱም ጋር በሚቆይበት ጊዜ ከዓመት እስከ ዓመት እንደ ቅጥር ሠራተኛ ሆኖ ያገልግለው፤ አንተም የጭካኔ ድርጊት እንዳይፈጽምበት ተከታተል። 54  ሆኖም ከእነዚህ መንገዶች በአንዱ ራሱን መልሶ መግዛት ካልቻለ በኢዮቤልዩ ዓመት ነፃ ይለቀቃል፤ እሱም ሆነ ልጆቹ አብረውት ነፃ ይለቀቁ። 55  “‘እስራኤላውያን የእኔ ባሪያዎች ናቸው። እነሱ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው ባሪያዎቼ ናቸው። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።
[]
[]
[]
[]
12,455
26  “‘ትሰግዱላቸው ዘንድ ለራሳችሁ ከንቱ አማልክትን አትሥሩ፤ እንዲሁም ለራሳችሁ የተቀረጸ ምስል ወይም የማምለኪያ ዓምድ አታቁሙ፤ በምድራችሁም ከድንጋይ የተቀረጸ ምስል አታኑሩ፤ ምክንያቱም እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። 2  ሰንበቶቼን ጠብቁ፤ ለመቅደሴም አክብሮት ይኑራችሁ። እኔ ይሖዋ ነኝ። 3  “‘ባወጣኋቸው ደንቦች መሠረት ብትሄዱና ትእዛዛቴን ብትጠብቁ እንዲሁም ብትፈጽሙ 4  ዝናብን በወቅቱ አዘንብላችኋለሁ፤ ምድሪቱም ምርቷን ትሰጣለች፤ የሜዳ ዛፎችም ፍሬያቸውን ይሰጣሉ። 5  ገና እህላችሁን ወቅታችሁ ሳትጨርሱ ወይናችሁን የምትሰበስቡበት ጊዜ ይደርሳል፤ ገና ወይኑን ሰብስባችሁ ሳትጨርሱ ደግሞ ዘር የምትዘሩበት ጊዜ ይመጣል፤ ምግባችሁን እስክትጠግቡ ድረስ ትበላላችሁ፤ በምድራችሁም ያለስጋት ትቀመጣላችሁ። 6  በምድሪቱ ሰላም አሰፍናለሁ፤ እናንተም ማንም ሳያስፈራችሁ ትተኛላችሁ፤ እኔም አደገኛ አውሬዎች በምድሪቱ እንዳይኖሩ አደርጋለሁ፤ በምድራችሁም የጦርነት ሰይፍ አያልፍም። 7  እናንተም በእርግጥ ጠላቶቻችሁን ታሳድዳላችሁ፤ እነሱም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ። 8  አምስታችሁ 100 ሰዎችን ታሳድዳላችሁ፤ መቶዎቻችሁ ደግሞ 10,000 ሰዎችን ታሳድዳላችሁ፤ ጠላቶቻችሁም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ። 9  “‘እኔም ሞገስ አሳያችኋለሁ፤ ፍሬያማ እንድትሆኑና እንድትበዙ አደርጋችኋለሁ፤ ከእናንተ ጋር የገባሁትንም ቃል ኪዳኔን እጠብቃለሁ። 10  እናንተም ያለፈውን ዓመት እህል ገና በልታችሁ ሳትጨርሱ ለዘንድሮው እህል ቦታ ለማግኘት ያለፈውን ዓመት እህል ታስለቅቃላችሁ። 11  የማደሪያ ድንኳኔን በመካከላችሁ እተክላለሁ፤ እኔም አልተዋችሁም። 12  በመካከላችሁ እሄዳለሁ፤ አምላካችሁም እሆናለሁ፤ እናንተ ደግሞ ሕዝቦቼ ትሆናላችሁ። 13  የግብፃውያን ባሪያዎች ሆናችሁ እንዳትቀሩ ከዚያ ምድር ያወጣኋችሁና ቀንበራችሁን ሰብሬ ራሳችሁን ቀና አድርጋችሁ እንድትሄዱ ያደረግኳችሁ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። 14  “‘ይሁን እንጂ የማትሰሙኝ ወይም እነዚህን ትእዛዛት በሙሉ የማትፈጽሙ ከሆነ 15  እንዲሁም ደንቦቼን ችላ የምትሉና ትእዛዛቴን በሙሉ ላለመፈጸም ድንጋጌዎቼን የምትጸየፉ፣ ቃል ኪዳኔንም የምታፈርሱ ከሆነ 16  እኔ ደግሞ እንዲህ አደርግባችኋለሁ፦ ዓይናችሁ እንዲጠፋና ሕይወታችሁ እንዲመነምን የሚያደርግ የሳንባ ነቀርሳና ኃይለኛ ትኩሳት በእናንተ ላይ በማምጣት በጭንቀት እቀጣችኋለሁ። ዘራችሁን የምትዘሩት እንዲሁ በከንቱ ይሆናል፤ ምክንያቱም የሚበሉት ጠላቶቻችሁ ናቸው። 17  እኔም በእርግጥ ፊቴን አጠቁርባችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁም ድል ያደርጓችኋል፤ የሚጠሏችሁም ሰዎች ይረግጧችኋል፤ እንዲሁም ማንም ሳያሳድዳችሁ ትሸሻላችሁ። 18  “‘እነዚህ ሁሉ ነገሮች ደርሰውባችሁም የማትሰሙኝ ከሆነ ለሠራችሁት ኃጢአት ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ። 19  ኃይለኛ የሆነውን ትዕቢታችሁን እሰብረዋለሁ፤ ሰማያችሁን እንደ ብረት፣ ምድራችሁን ደግሞ እንደ መዳብ አደርገዋለሁ። 20  ምድራችሁ ምርቷን ስለማትሰጥና የምድርም ዛፍ ፍሬ ስለማያፈራ ኃይላችሁን እንዲሁ በከንቱ ታባክናላችሁ። 21  “‘ሆኖም እኔን መቃወማችሁን ከቀጠላችሁና እኔን ለመስማት ፈቃደኞች ሳትሆኑ ከቀራችሁ እንደ ኃጢአታችሁ መጠን ሰባት እጥፍ እመታችኋለሁ። 22  የዱር አራዊትን እሰድባችኋለሁ፤ እነሱም ልጆቻችሁን ይነጥቋችኋል፤ የቤት እንስሶቻችሁንም ይበሉባችኋል፤ ቁጥራችሁም እንዲመናመን ያደርጋሉ፤ መንገዶቻችሁም ጭር ይላሉ። 23  “‘እነዚህ ሁሉ ነገሮች ደርሰውባችሁም እርማቴን ባትቀበሉና እኔን መቃወማችሁን ብትገፉበት 24  እኔም እናንተን በመቃወም እመጣባችኋለሁ፤ ለኃጢአታችሁም ሰባት እጥፍ እመታችኋለሁ። 25  ከእኔ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን ስላፈረሳችሁ በላያችሁ ላይ የበቀል ሰይፍ አመጣባችኋለሁ። በከተሞቻችሁ ውስጥ ከተሰበሰባችሁ በመካከላችሁ በሽታ እልክባችኋለሁ፤ እናንተም ለጠላት እጅ ትሰጣላችሁ። 26  የዳቦ እጥረት እንዲከሰትባችሁ በማደርግበት ጊዜ አሥር ሴቶች በአንድ ምድጃ ብቻ ዳቦ ይጋግሩላችኋል፤ ዳቦውንም እየመዘኑ ያከፋፍሏችኋል፤ እናንተም ትበላላችሁ፤ ነገር ግን አትጠግቡም። 27  “‘ይሁን እንጂ በዚህም እኔን ለመስማት ፈቃደኛ ካልሆናችሁና እኔን መቃወማችሁን ከገፋችሁበት 28  በኃይል እቃወማችኋለሁ፤ እኔ ራሴም ለኃጢአታችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ። 29  በመሆኑም የወንድ ልጆቻችሁን ሥጋ ትበላላችሁ፤ የሴት ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ። 30  በከፍታ ቦታዎች ላይ ያሉትን ቅዱስ ስፍራዎቻችሁን አጠፋለሁ፤ የዕጣን ማጨሻዎቻችሁንም አስወግዳለሁ፤ በድናችሁንም አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻችሁ በድን ላይ እከምረዋለሁ፤ እኔም ተጸይፌያችሁ ከእናንተ ዞር እላለሁ። 31  ከተሞቻችሁን ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ መቅደሶቻችሁንም ባዶ አደርጋቸዋለሁ፤ የመሥዋዕቶቻችሁን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ አላሸትም። 32  እኔ ራሴ ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ፤ በዚያ የሚኖሩ ጠላቶቻችሁም በመደነቅ ይመለከቷታል። 33  እናንተንም በብሔራት መካከል እበትናችኋለሁ፤ ሰይፍም መዝዤ አሳድዳችኋለሁ፤ ምድራችሁ ባድማ ትሆናለች፤ ከተሞቻችሁም ይፈራርሳሉ። 34  “‘በጠላቶቻችሁ ምድር ሆናችሁ ምድሪቱ ባድማ ሆና በምትቆይባቸው ጊዜያት ሁሉ የሰንበት ዕዳዋን ትከፍላለች። በዚያን ጊዜ ምድሪቱ የሰንበት ዕዳዋን መክፈል ስላለባት ታርፋለች። 35  ምድሪቱ ትኖሩባት በነበረው ጊዜ በሰንበታችሁ ወቅት ስላላረፈች ባድማ ሆና በምትቆይባቸው ጊዜያት ሁሉ ታርፋለች። 36  “‘ከእናንተ መካከል በሕይወት የሚተርፉትም በጠላቶቻቸው ምድር ልባቸው ተስፋ እንዲቆርጥ አደርጋለሁ፤ የቅጠል ኮሽታ እንኳ ያስበረግጋቸዋል፤ ከሰይፍ እንደሚሸሽ ሰው ይፈረጥጣሉ፤ ማንም ሳያሳድዳቸው ይወድቃሉ። 37  ከሰይፍ እንደሚሸሹ ሰዎች እነሱም ማንም ሳያሳድዳቸው እርስ በርሳቸው እየተደነቃቀፉ ይወድቃሉ። እናንተም ጠላቶቻችሁን መቋቋም ይሳናችኋል። 38  በብሔራት መካከል ትጠፋላችሁ፤ የጠላቶቻችሁም ምድር ትበላችኋለች። 39  ከእናንተ መካከል የሚተርፉትም በሠሩት ስህተት የተነሳ በጠላቶቻችሁ ምድር ይበሰብሳሉ። አዎ፣ በአባቶቻቸው ስህተት የተነሳ ይበሰብሳሉ። 40  ከዚያም የገዛ ራሳቸውን ስህተት እንዲሁም አባቶቻቸው የፈጸሙትን ስህተትና ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ይናዘዛሉ፤ እንዲሁም እኔን በመቃወም ታማኝ ሳይሆኑ መቅረታቸውን አምነው ይቀበላሉ። 41  እኔም እነሱን ወደ ጠላቶቻቸው ምድር በማምጣት እቃወማቸዋለሁ። “‘ምናልባትም ያልተገረዘው ልባቸው በዚያ ጊዜ ትሑት ይሆናል፤ የስህተታቸውንም ዋጋ ይከፍላሉ። 42  እኔም ከያዕቆብ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳንና ከይስሐቅ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስባለሁ፤ እንዲሁም ከአብርሃም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ፤ ምድሪቱንም አስባለሁ። 43  እነሱም ምድሪቱን ትተዋት በሄዱበት ጊዜ ምድሪቱ የሰንበት ዕዳዋን ትከፍላለች፤ ያለእነሱም ባድማ ሆና ትቆያለች፤ እነሱም ድንጋጌዎቼን ችላ ስላሉና ደንቦቼን ስለተጸየፉ የስህተታቸውን ዋጋ ይከፍላሉ። 44  ይህ ሁሉ ቢሆንም ግን በጠላቶቻቸው ምድር በሚቆዩበት ጊዜ ሁሉ እርግፍ አድርጌ አልተዋቸውም፤ ፈጽሜ እስካጠፋቸውም ድረስ አልጥላቸውም፤ እንዲህ ባደርግ ከእነሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ማፍረስ ይሆንብኛል፤ ምክንያቱም እኔ አምላካቸው ይሖዋ ነኝ። 45  አምላካቸው መሆኔን አስመሠክር ዘንድ ብሔራት በዓይናቸው እያዩ ከግብፅ ምድር ካወጣኋቸው አባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ስለ እነሱ ስል አስባለሁ። እኔ ይሖዋ ነኝ።’” 46  ይሖዋ በሲና ተራራ ላይ በሙሴ አማካኝነት በራሱና በእስራኤላውያን መካከል ያስቀመጣቸው ሥርዓቶች፣ ድንጋጌዎችና ሕጎች እነዚህ ናቸው።
[]
[]
[]
[]
12,456
27  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘አንድ ሰው የአንድን ግለሰብ የተተመነ ዋጋ ለይሖዋ ለማቅረብ ልዩ ስእለት ቢሳል 3  ከ20 ዓመት እስከ 60 ዓመት ድረስ ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኝ ወንድ የሚተመነው ዋጋ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል 50 የብር ሰቅል ይሆናል። 4  ሴት ከሆነች ግን የሚተመንላት ዋጋ 30 ሰቅል ይሆናል። 5  ከ5 ዓመት እስከ 20 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ወንድ ከሆነ የሚተመንለት ዋጋ 20 ሰቅል ይሆናል፤ ሴት ከሆነች ደግሞ 10 ሰቅል ይሆናል። 6  ከአንድ ወር እስከ አምስት ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ወንድ ከሆነ የሚተመንለት ዋጋ አምስት የብር ሰቅል ይሆናል፤ ሴት ከሆነች ደግሞ ሦስት የብር ሰቅል ይሆናል። 7  “‘ዕድሜው ከ60 ዓመት በላይ ለሆነ ወንድ ደግሞ የሚተመንለት ዋጋ 15 ሰቅል ይሆናል፤ ሴት ከሆነች 10 ሰቅል ይሆናል። 8  ሆኖም ሰውየው በጣም ድሃ ቢሆንና የተተመነውን ዋጋ መስጠት ባይችል ግለሰቡ ካህኑ ፊት ይቆማል፤ ካህኑም ለሰውየው ዋጋ ይተምንለታል። ካህኑ ስእለት የተሳለውን ሰው አቅም ግምት ውስጥ በማስገባት ለሰውየው ዋጋ ይተምንለታል። 9  “‘ስእለቱ ለይሖዋ መባ ሆኖ መቅረብ የሚችል እንስሳ ከሆነ ለይሖዋ የሚሰጠው ማንኛውም ነገር የተቀደሰ ይሆናል። 10  እንስሳውን በሌላ መተካትም ሆነ መጥፎውን በጥሩ፣ ጥሩውን በመጥፎ መለወጥ አይችልም። እንስሳውን በሌላ እንስሳ መለወጥ ካለበት ግን የመጀመሪያው እንስሳም ሆነ ተለዋጭ ሆኖ የቀረበው እንስሳ የተቀደሱ ይሆናሉ። 11  ሰውየው ያቀረበው እንስሳ ለይሖዋ መባ ሆኖ ሊቀርብ የማይችል ርኩስ እንስሳ ከሆነ እንስሳውን ካህኑ ፊት ያቁመው። 12  ካህኑ እንስሳው ጥሩ ወይም መጥፎ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋ ይተምንለት። ካህኑ የተመነውም ዋጋ ይጸናል። 13  ሆኖም ሰውየው እንስሳውን መልሶ መግዛት ከፈለገ በተተመነው ዋጋ ላይ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ መስጠት አለበት። 14  “‘አንድ ሰው ቤቱን ቅዱስ አድርጎ ለይሖዋ ቢሰጥ ካህኑ ቤቱ ጥሩ ወይም መጥፎ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋ ይተምንለት። የቤቱ ዋጋ ካህኑ የተመነው ዋጋ ይሆናል። 15  ሆኖም ቤቱን ቅዱስ አድርጎ የሰጠው ሰው ቤቱን መልሶ መግዛት ከፈለገ በተተመነው ዋጋ ላይ የገንዘቡን አንድ አምስተኛ ጨምሮ መስጠት አለበት፤ ቤቱም የእሱ ይሆናል። 16  “‘አንድ ሰው ርስት አድርጎ ከያዘው እርሻ ላይ የተወሰነውን ለይሖዋ ቅዱስ አድርጎ ቢሰጥ ዋጋው መተመን ያለበት የሚዘራበትን ዘር መጠን ግምት ውስጥ በማስገባት ይሆናል፤ ለአንድ ሆሜር የገብስ ዘር 50 የብር ሰቅል ይሆናል። 17  ሰውየው እርሻውን ከኢዮቤልዩ ዓመት አንስቶ ቅዱስ አድርጎ ከሰጠ የተተመነለት ዋጋ ይጸናል። 18  ሰውየው እርሻውን ቅዱስ አድርጎ የሰጠው ኢዮቤልዩ ካለፈ በኋላ ከሆነ ካህኑ እስከ ቀጣዩ የኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የቀሩትን ዓመታት ግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋውን ያስላለት፤ ከተተመነውም ዋጋ ላይ መቀነስ አለበት። 19  ሆኖም እርሻውን ቅዱስ አድርጎ የሰጠው ሰው እርሻውን መልሶ መግዛት ከፈለገ በተተመነው ዋጋ ላይ የገንዘቡን አንድ አምስተኛ ጨምሮ መስጠት አለበት፤ ከዚያም እርሻው የእሱ ንብረት እንደሆነ ይጸናል። 20  ሰውየው እርሻውን መልሶ ባይገዛውና እርሻው ለሌላ ሰው ቢሸጥ ሰውየው መልሶ ሊገዛው አይችልም። 21  እርሻው በኢዮቤልዩ ነፃ በሚለቀቅበት ጊዜ ለይሖዋ እንደተሰጠ እርሻ ተቆጥሮ ለእሱ የተቀደሰ ይሆናል። የካህናቱም ንብረት ይሆናል። 22  “‘አንድ ሰው በውርስ ያገኘው ንብረት ክፍል ያልሆነውን በገንዘቡ የገዛውን እርሻ ለይሖዋ ቅዱስ አድርጎ ቢሰጥ 23  ካህኑ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የሚያወጣውን ዋጋ ይተምንለት፤ እሱም የተተመነውን ዋጋ በዚያው ቀን ይስጥ። ይህ ለይሖዋ የተቀደሰ ነው። 24  በኢዮቤልዩ ዓመት እርሻው ለሻጩ ይኸውም ለመሬቱ ባለቤት ይመለሳል። 25  “‘እያንዳንዱ ዋጋ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት መተመን አለበት። አንዱ ሰቅል 20 ጌራ መሆን ይኖርበታል። 26  “‘ይሁንና ማንም ሰው ከእንስሳት መካከል በኩር የሆነውን ቅዱስ አድርጎ መስጠት የለበትም፤ ምክንያቱም በኩሩ የይሖዋ ነው። በሬም ሆነ በግ ቀድሞውንም የይሖዋ ነው። 27  በኩሩ ርኩስ ከሆኑት እንስሳት መካከል ከሆነና በተተመነለት ዋጋ መሠረት ከዋጀው በዋጋው ላይ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ መስጠት አለበት። ሰውየው መልሶ የማይገዛው ከሆነ ግን በተተመነው ዋጋ መሠረት ይሸጥ። 28  “‘አንድ ሰው የራሱ ከሆኑት ነገሮች ውስጥ ያለምንም ገደብ ለይሖዋ የሰጠው ማንኛውም ተለይቶ የተሰጠ ነገር ይኸውም የእሱ ንብረት የሆነ ሰውም ሆነ እንስሳ አሊያም እርሻ ሊሸጥም ሆነ ተመልሶ ሊገዛ አይችልም። ተለይቶ የተሰጠ ማንኛውም ነገር ለይሖዋ እጅግ የተቀደሰ ነው። 29  በተጨማሪም እንዲጠፋ የተበየነበት ማንኛውም ለጥፋት የተለየ ሰው አይዋጅም፤ ከዚህ ይልቅ መገደል አለበት። 30  “‘እርሻው ከሚሰጠው ምርትም ሆነ ዛፉ ከሚያፈራው ፍሬ ውስጥ የምድሩ አንድ አሥረኛ ሁሉ የይሖዋ ነው። ይህ ለይሖዋ የተቀደሰ ነው። 31  አንድ ሰው አንድ አሥረኛ አድርጎ የሰጠውን ማንኛውንም ነገር መልሶ መግዛት ቢፈልግ በዋጋው ላይ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ መስጠት አለበት። 32  ከከብቶቹና ከመንጋው መካከል አንድ አሥረኛው ማለትም በበትሩ ሥር ከሚያልፉት መካከል አሥረኛው እንስሳ ለይሖዋ የተቀደሰ መሆን አለበት። 33  ከዚህ በኋላ እንስሳው ጥሩ ይሁን መጥፎ መመርመር የለበትም፤ በሌላ ሊለውጠውም አይገባም። እንስሳውን በሌላ መለወጥ ካሰበ ግን የመጀመሪያው እንስሳም ሆነ ተለዋጭ ሆኖ የቀረበው እንስሳ የተቀደሱ ይሆናሉ። ተመልሶ ሊገዛ አይችልም።’” 34  ይሖዋ በሲና ተራራ ላይ በሙሴ አማካኝነት ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ትእዛዛት እነዚህ ናቸው።
[]
[]
[]
[]
12,457
3  “‘አንድ ሰው የሚያቀርበው መባ የኅብረት መሥዋዕት ቢሆንና ከከብቶች መካከል ወስዶ የሚያቀርብ ከሆነ እንስሳው ተባዕትም ሆነ እንስት እንከን የሌለበትን በይሖዋ ፊት ማቅረብ ይኖርበታል። 2  እሱም መባ አድርጎ በሚያቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ይጭናል፤ እንስሳውም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ይታረዳል፤ ካህናት የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ይረጩታል። 3  እሱም ከኅብረት መሥዋዕቱ ላይ የተወሰነውን ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርበዋል፤ ይኸውም አንጀቱን የሸፈነውን ስብ፣ በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ በሙሉ፣ 4  ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ማለትም በሽንጡ አካባቢ ያለውን ስብ ያቀርባል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳዋል። 5  የአሮን ወንዶች ልጆችም በመሠዊያው ላይ ይኸውም በእሳቱ ላይ ባለው እንጨት ላይ በሚገኘው የሚቃጠል መባ ላይ ያጨሱታል፤ ይህም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ ነው። 6  “‘ለይሖዋ የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው መባ ከመንጋው መካከል የተወሰደ ከሆነ እንስሳው ተባዕትም ሆነ እንስት እንከን የሌለበትን ያቀርባል። 7  የበግ ጠቦት መባ አድርጎ የሚያቀርብ ከሆነ ይሖዋ ፊት ያቀርበዋል። 8  እሱም መባ አድርጎ በሚያቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ይጭናል፤ እንስሳውም በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ለፊት ይታረዳል። የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ይረጩታል። 9  ከኅብረት መሥዋዕቱ ላይም ስቡን ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርባል። ከጀርባ አጥንቱ አጠገብ ያለውን ላት በሙሉ፣ አንጀቱን የሸፈነውን ስብ፣ በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ በሙሉ ያነሳዋል፤ 10  ደግሞም ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ማለትም በሽንጡ አካባቢ ያለውን ስብ ያነሳዋል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳል። 11  ካህኑም እንደ ምግብ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት እንደሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል። 12  “‘ፍየል መባ አድርጎ የሚያቀርብ ከሆነ ይሖዋ ፊት ያቀርበዋል። 13  እጁንም በራሱ ላይ ይጭንበታል፤ በመገናኛ ድንኳኑም ፊት ይታረዳል፤ የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ይርጩት። 14  ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጎ የሚያቀርበውም እነዚህን ነው፦ አንጀቱን የሸፈነውን ስብ፣ በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ በሙሉ፣ 15  ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ማለትም በሽንጡ አካባቢ ያለውን ስብ ያቀርባል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳል። 16  ካህኑም እንደ ምግብ ይኸውም ደስ የሚያሰኝ መዓዛ እንዳለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሳቸዋል። ስቡ ሁሉ የይሖዋ ነው። 17  “‘ስብም ሆነ ደም ፈጽሞ አትብሉ። ይህም በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለእናንተም ሆነ ለትውልዶቻችሁ ዘላቂ ደንብ ነው።’”
[]
[]
[]
[]
12,458
4  ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘አንድ ሰው ይሖዋ መደረግ የለባቸውም ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን በመፈጸም ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራ እንዲህ መደረግ ይኖርበታል፦ 3  “‘የተቀባው ካህን ኃጢአት ቢሠራና ሕዝቡ በደለኛ እንዲሆን ቢያደርግ ለፈጸመው ኃጢአት እንከን የሌለበትን ወይፈን የኃጢአት መባ አድርጎ ለይሖዋ ያቅርብ። 4  ወይፈኑን ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ወደ ይሖዋ ፊት ያመጣዋል፤ እጁንም በወይፈኑ ራስ ላይ ይጭናል፤ ወይፈኑንም በይሖዋ ፊት ያርደዋል። 5  ከዚያም የተቀባው ካህን ከወይፈኑ ደም የተወሰነ ወስዶ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ይዞ ይገባል፤ 6  ካህኑም ጣቱን ደሙ ውስጥ ነክሮ ደሙን በቅዱሱ ስፍራ መጋረጃ ፊት ለፊት በይሖዋ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል። 7  በተጨማሪም ካህኑ ከደሙ የተወሰነውን ወስዶ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በይሖዋ ፊት የሚገኘውን ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን የሚቀርብበትን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤ ከዚያም የተረፈውን የወይፈኑን ደም በሙሉ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በሚገኘው የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ሥር ያፈሰዋል። 8  “‘ከዚያም አንጀቱን የሸፈነውን ስብና በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ ጨምሮ ለኃጢአት መባ የቀረበውን ወይፈን ስብ በሙሉ ከላዩ ላይ ያነሳል፤ 9  እንዲሁም ሁለቱን ኩላሊቶችና በላያቸው ላይ ያለውን በሽንጡ አካባቢ የሚገኝ ስብ ያነሳል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳል። 10  ይህም ለኅብረት መሥዋዕት ከሚቀርበው በሬ ላይ ከሚነሳው ጋር ተመሳሳይ ይሆናል። ካህኑም የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ እንዲጨሱ ያደርጋል። 11  “‘ሆኖም የወይፈኑን ቆዳ እንዲሁም ሥጋውን በሙሉ ከጭንቅላቱ፣ ከእግሮቹ፣ ከሆድ ዕቃውና ከፈርሱ ጋር 12  እንዲሁም ከወይፈኑ የቀረውን በሙሉ ከሰፈሩ ውጭ ወዳለው አመድ ወደሚደፋበት ንጹሕ የሆነ ቦታ ይወስደዋል፤ በእሳቱ ላይ ባለው እንጨት ላይ አድርጎም ያቃጥለዋል። አመዱ በሚደፋበት ቦታ ላይ ይቃጠል። 13  “‘መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ባለማወቅ ኃጢአት በመሥራቱ በደለኛ ቢሆንና ጉባኤው ግን ይሖዋ አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን መፈጸሙን ባይገነዘብ፣ 14  በኋላም ኃጢአቱ ቢታወቅ ጉባኤው ለኃጢአት መባ የሚሆን ወይፈን ያቅርብ፤ ወደ መገናኛ ድንኳኑም ፊት ያምጣው። 15  የማኅበረሰቡ ሽማግሌዎች በይሖዋ ፊት እጃቸውን በወይፈኑ ራስ ላይ ይጭናሉ፤ ወይፈኑም በይሖዋ ፊት ይታረዳል። 16  “‘ከዚያም የተቀባው ካህን ከወይፈኑ ደም የተወሰነ ወስዶ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ይዞ ይገባል። 17  ካህኑም ጣቱን ደሙ ውስጥ ነክሮ የተወሰነውን በመጋረጃው ፊት ለፊት በይሖዋ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል። 18  የተወሰነውንም ደም ወስዶ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በይሖዋ ፊት የሚገኘውን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤ ከዚያም የተረፈውን ደም በሙሉ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በሚገኘው የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ሥር ያፈሰዋል። 19  ስቡንም በሙሉ አንስቶ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርገዋል። 20  በወይፈኑ ላይ ለኃጢአት መባ እንዲሆን በቀረበው በሌላኛው ወይፈን ላይ እንዳደረገው ሁሉ ያደርጋል። በዚህኛውም ላይ የሚያደርገው ይህንኑ ይሆናል፤ ካህኑም ለእነሱ ያስተሰርይላቸዋል፤ እነሱም ይቅር ይባላሉ። 21  ወይፈኑንም ከሰፈሩ ውጭ እንዲወሰድ ካደረገ በኋላ ልክ የመጀመሪያውን ወይፈን እንዳቃጠለው ሁሉ ይሄኛውንም ያቃጥለዋል። ይህ ስለ ጉባኤው የሚቀርብ የኃጢአት መባ ነው። 22  “‘አንድ አለቃ አምላኩ ይሖዋ መደረግ የለባቸውም ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን በመፈጸም ባለማወቅ ኃጢአት ሠርቶ በደለኛ ቢሆን 23  ወይም ትእዛዙን በመተላለፍ ኃጢአት እንደሠራ ቢያውቅ እንከን የሌለበትን ተባዕት የፍየል ጠቦት መባ አድርጎ ያምጣ። 24  እጁንም በፍየል ጠቦቱ ራስ ላይ ይጭናል፤ እንዲሁም የሚቃጠለው መባ በይሖዋ ፊት ዘወትር በሚታረድበት ስፍራ ያርደዋል። ይህ የኃጢአት መባ ነው። 25  ካህኑም ለኃጢአት መባ ከቀረበው እንስሳ ደም ላይ የተወሰነውን በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤ ከዚያም የተረፈውን ደሙን የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ሥር ያፈሳል። 26  ስቡንም በሙሉ ልክ እንደ ኅብረት መሥዋዕቱ ስብ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርጋል፤ ካህኑም የእሱን ኃጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል። 27  “‘በምድሩ ከሚኖሩ ሕዝቦች መካከል ማንኛውም ሰው ይሖዋ መደረግ የለባቸውም ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን በመፈጸም ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራና በደለኛ ቢሆን፣ 28  በኋላም የሠራውን ኃጢአት ቢያውቅ ለፈጸመው ኃጢአት እንከን የሌለባትን እንስት የፍየል ጠቦት መባ አድርጎ ያምጣ። 29  እጁንም ለኃጢአት መባ በቀረበችው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፤ እንዲሁም ለኃጢአት መባ የቀረበችውን እንስሳ የሚቃጠለው መባ በሚታረድበት ስፍራ ያርዳታል። 30  ካህኑም ከደሙ የተወሰነውን በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤ ከዚያም የተረፈውን ደሙን በሙሉ በመሠዊያው ሥር ያፈሰዋል። 31  ከኅብረት መሥዋዕቱ ላይ ስቡ እንደሚነሳ ሁሉ ከዚህ ላይም ስቡን በሙሉ ያነሳዋል፤ ካህኑም ስቡ ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ እንዲሰጥ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል፤ ካህኑም ያስተሰርይለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል። 32  “‘ሆኖም የኃጢአት መባ አድርጎ የሚያቀርበው የበግ ጠቦት ከሆነ እንከን የሌለባትን እንስት የበግ ጠቦት ማምጣት አለበት። 33  እጁንም ለኃጢአት መባ በቀረበችው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፤ እንዲሁም እንስሳዋን የሚቃጠለው መባ በሚታረድበት ስፍራ የኃጢአት መባ አድርጎ ያርዳታል። 34  ካህኑም ለኃጢአት መባ ከቀረበችው እንስሳ ደም ላይ የተወሰነውን በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤ ከዚያም የተረፈውን ደሙን በሙሉ በመሠዊያው ሥር ያፈሰዋል። 35  የኅብረት መሥዋዕት ሆኖ ከሚቀርበው የበግ ጠቦት ላይ ስቡ እንደሚነሳ ሁሉ ከዚህ ላይም ስቡን በሙሉ ያነሳዋል፤ እሱም በመሠዊያው ላይ ባሉት ለይሖዋ በእሳት በሚቀርቡት መባዎች ላይ እንዲጨሱ ያደርጋል። ካህኑም ሰውየው የሠራውን ኃጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል።
[]
[]
[]
[]
12,459
5  “‘አንድ ሰው ሰዎች የምሥክርነት ቃል እንዲሰጡ ጥሪ እየቀረበ መሆኑን ቢሰማና እሱ መመሥከር እየቻለ ወይም ደግሞ ጉዳዩን አይቶ አሊያም አውቆ ሳለ ሳይናገር ቢቀር በሠራው ጥፋት ይጠየቅበታል። 2  “‘ወይም አንድ ሰው ርኩስ የሆነን ማንኛውንም ነገር ይኸውም ርኩስ የሆነን የዱር አውሬ ወይም ርኩስ የሆነን የቤት እንስሳ አሊያም ርኩስ የሆነን የሚርመሰመስ ፍጥረት በድን ቢነካ፣ ይህን ያደረገው ባለማወቅ ቢሆንም እንኳ ይህ ሰው ርኩስ ነው፤ በደለኛም ይሆናል። 3  ወይም አንድ ሰው ባለማወቅ የሰውን ርኩሰት ይኸውም እንዲረክስ ሊያደርገው የሚችለውን ማንኛውንም ርኩስ ነገር ቢነካና በኋላም ይህን ቢያውቅ በደለኛ ይሆናል። 4  “‘አሊያም ደግሞ አንድ ሰው ነገሩ ምንም ሆነ ምን ክፉ ወይም መልካም ለማድረግ በችኮላ ቢምልና ይህን ያደረገው ባለማወቅ ቢሆን ሆኖም የማለው በችኮላ መሆኑን በኋላ ላይ ቢገነዘብ በደለኛ ይሆናል። 5  “‘ከእነዚህ ነገሮች በአንዱ በደለኛ ሆኖ ቢገኝ በምን መንገድ ኃጢአት እንደሠራ መናዘዝ አለበት። 6  ለሠራው ኃጢአት የበደል መባ ማለትም ከመንጋው መካከል እንስት የበግ ጠቦት ወይም እንስት የፍየል ግልገል የኃጢአት መባ አድርጎ ለይሖዋ ያመጣል። ከዚያም ካህኑ ኃጢአቱን ያስተሰርይለታል። 7  “‘በግ ለማምጣት አቅሙ የማይፈቅድለት ከሆነ ግን ለሠራው ኃጢአት የበደል መባ እንዲሆኑ ሁለት ዋኖሶችን ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶችን ለይሖዋ ያምጣ፤ አንዱ ለኃጢአት መባ ሌላኛው ደግሞ ለሚቃጠል መባ ይሆናል። 8  ወደ ካህኑም ያመጣቸዋል፤ ካህኑም በቅድሚያ ለኃጢአት መባ የሚሆነውን ያቀርባል፤ አንገቱን ሙሉ በሙሉ ሳይቆርጥ ከፊት በኩል አንገቱን በመቦጨቅ ያቀርበዋል። 9  ከኃጢአት መባው ደም ላይ የተወሰነውን በመሠዊያው ጎን ላይ ይረጨዋል፤ የተረፈው ደም ግን በመሠዊያው ሥር ይንጠፈጠፋል። ይህ የኃጢአት መባ ነው። 10  ሌላኛውን ደግሞ በተለመደው አሠራር መሠረት የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርበዋል፤ ካህኑም ለሠራው ኃጢአት ማስተሰረያ ያቀርብለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል። 11  “‘ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች ለማምጣት አቅሙ የማይፈቅድለት ከሆነ ደግሞ ለሠራው ኃጢአት፣ የኃጢአት መባ እንዲሆን አንድ አሥረኛ ኢፍ የላመ ዱቄት መባ አድርጎ ያምጣ። የኃጢአት መባ ስለሆነ ዘይት አይጨምርበት ወይም ነጭ ዕጣን አያድርግበት። 12  ወደ ካህኑም ያመጣዋል፤ ካህኑም አምላክ መላውን መባ እንዲያስበው ለማድረግ ከላዩ ላይ አንድ እፍኝ አንስቶ በመሠዊያው ላይ ባሉት ለይሖዋ በእሳት በሚቀርቡት መባዎች ላይ እንዲጨስ ያደርጋል። ይህ የኃጢአት መባ ነው። 13  ካህኑም ሰውየው ከእነዚህ ኃጢአቶች ውስጥ ለሠራው ለየትኛውም ኃጢአት ማስተሰረያ ያቀርብለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል። እንደ እህል መባው ሁሉ ከመባው የተረፈውም የካህኑ ይሆናል።’” 14  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 15  “አንድ ሰው ለይሖዋ በተቀደሱት ነገሮች ላይ ባለማወቅ ኃጢአት በመሥራት ታማኝነቱን ቢያጎድል ከመንጋው መካከል እንከን የሌለበትን አውራ በግ የበደል መባ አድርጎ ለይሖዋ ያመጣል፤ ዋጋው በብር ሰቅል የሚተመነው እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት ነው። 16  በቅዱሱ ስፍራ ላይ ለፈጸመው ኃጢአት ካሳ ይከፍላል፤ የዋጋውንም አንድ አምስተኛ ይጨምርበታል። ካህኑ ለበደል መባ በቀረበው አውራ በግ አማካኝነት እንዲያስተሰርይለትም ለካህኑ ይሰጠዋል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል። 17  “አንድ ሰው ይሖዋ እንዳይደረጉ ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን በመፈጸም ኃጢአት ቢሠራ፣ እንዲህ ያደረገው ባለማወቅ ቢሆንም እንኳ በደለኛ ይሆናል፤ በሠራውም ጥፋት ይጠየቅበታል። 18  የበደል መባ እንዲሆንም የተተመነለትን ዋጋ ያህል የሚያወጣ እንከን የሌለበት አውራ በግ ከመንጋው መካከል ወስዶ ለካህኑ ያምጣ። ከዚያም ካህኑ፣ ሰውየው ባለማወቅ ለፈጸመው ስህተት ያስተሰርይለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል። 19  ይህ የበደል መባ ነው። በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለፈጸመ በእርግጥ በደለኛ ይሆናል።”
[]
[]
[]
[]
12,460
6  ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “አንድ ሰው በአደራ እንዲይዝ ወይም እንዲያስቀምጥ ከተሰጠው ነገር ጋር በተያያዘ ባልንጀራውን በማታለል ኃጢአት ቢሠራና በይሖዋ ላይ ታማኝነት የማጉደል ተግባር ቢፈጽም አሊያም ባልንጀራውን ቢሰርቅ ወይም ቢያጭበረብር 3  አሊያም ደግሞ የጠፋ ነገር አግኝቶ አላየሁም ብሎ ቢዋሽና ሰውየው ከእነዚህ ኃጢአቶች መካከል አንዱንም እንዳልሠራ አድርጎ በሐሰት ቢምል እንዲህ ማድረግ አለበት፦ 4  ኃጢአት ቢሠራና በደለኛ ሆኖ ቢገኝ የሰረቀውን፣ ቀምቶ ወይም አጭበርብሮ የወሰደውን አሊያም በአደራ ተሰጥቶት የነበረውን ወይም ደግሞ ጠፍቶ ያገኘውን ነገር ይመልስ፤ 5  አሊያም በሐሰት የማለበትን ማንኛውንም ነገር ይመልስ፤ ሙሉ ካሳ ይክፈል፤ የዋጋውንም አንድ አምስተኛ ይጨምርበት። በደለኛ መሆኑ በተረጋገጠበትም ዕለት ለባለቤቱ ይሰጠዋል። 6  በተተመነውም ዋጋ መሠረት እንከን የሌለበትን አውራ በግ ከመንጋው መካከል በመውሰድ የበደል መባው አድርጎ ለይሖዋ ለማቅረብ ወደ ካህኑ ያመጣዋል። 7  ካህኑም በይሖዋ ፊት ያስተሰርይለታል፤ እሱም በደለኛ እንዲሆን ያደረገው ማንኛውም ነገር ይቅር ይባልለታል።” 8  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 9  “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ ‘የሚቃጠል መባ ሕግ ይህ ነው፦ የሚቃጠለው መባ ሌሊቱን ሙሉ እስኪነጋ ድረስ በመሠዊያው ላይ ባለው ማንደጃ ላይ ይቀመጣል፤ እሳቱም በመሠዊያው ላይ ሲነድ ያድራል። 10  ካህኑ ከበፍታ የተሠራውን የክህነት ልብሱን ይለብሳል፤ እርቃኑንም ለመሸፈን ከበፍታ የተሠራውን ቁምጣ ያደርጋል። ከዚያም በመሠዊያው ላይ ከነበረው በእሳት ከነደደው የሚቃጠል መባ የወጣውን አመድ ያነሳል፤ በመሠዊያውም ጎን ያደርገዋል። 11  ከዚያም ልብሱን አውልቆ ሌላ ልብስ ይለብሳል፤ አመዱንም ከሰፈሩ ውጭ ወደሚገኝ ንጹሕ የሆነ ቦታ ይወስደዋል። 12  እሳቱ በመሠዊያው ላይ ዘወትር ይነድዳል። መጥፋትም የለበትም። ካህኑም በየማለዳው እንጨት ይማግድበት፤ በላዩም ላይ የሚቃጠለውን መባ ይረብርብበት፤ የኅብረት መሥዋዕቶቹንም ስብ በላዩ ላይ ያጨስበታል። 13  በመሠዊያውም ላይ ያለማቋረጥ እሳት ይነድዳል። መጥፋትም የለበትም። 14  “‘የእህል መባ ሕግ ደግሞ ይህ ነው፦ እናንተ የአሮን ወንዶች ልጆች በመሠዊያው ፊት ለፊት በይሖዋ ፊት ታቀርቡታላችሁ። 15  ከመካከላቸው አንዱ ለእህል መባ ከቀረበው የላመ ዱቄት ላይ ከነዘይቱ አንድ እፍኝ ያነሳል፤ እንዲሁም በእህል መባው ላይ ያለውን ነጭ ዕጣን በሙሉ ይወስዳል። አምላክ መላውን መባ እንዲያስበውም ለይሖዋ ደስ የሚያሰኝ መዓዛ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል። 16  ከዚያ የተረፈውን አሮንና ወንዶች ልጆቹ ይበሉታል፤ እንደ ቂጣ ተጋግሮ በቅዱስ ስፍራ ይበላል። በመገናኛ ድንኳኑ ግቢ ውስጥ ይበሉታል። 17  ያለእርሾ መጋገር አለበት። ለእኔ በእሳት ከሚቀርቡልኝ መባዎች ውስጥ ይህን ድርሻቸው አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ። እንደ ኃጢአት መባና እንደ በደል መባ ሁሉ ይህም እጅግ ቅዱስ ነገር ነው። 18  የአሮን ዘር የሆኑ ወንዶች ሁሉ ይበሉታል። ይህ ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡ መባዎች ውስጥ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ለእነሱ የሚሰጥ ዘላለማዊ ድርሻ ነው። የሚነካቸውም ነገር ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።’” 19  ይሖዋም በድጋሚ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 20  “አሮን በሚቀባበት ቀን እሱና ወንዶች ልጆቹ ለይሖዋ የሚያቀርቡት መባ ይህ ነው፦ የኢፍ አንድ አሥረኛ የላመ ዱቄት በቋሚነት የሚቀርብ የእህል መባ አድርገው ያቅርቡ፤ ግማሹን ጠዋት፣ ግማሹን ደግሞ ምሽት ላይ ያቅርቡ። 21  በዘይት ከተለወሰ በኋላም በምጣድ ላይ ይጋገራል። ከዚያም በደንብ በዘይት ለውሰህ ታመጣዋለህ፤ የተጋገረውንም የእህል መባ ቆራርሰህ ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ይሆን ዘንድ ለይሖዋ ታቀርበዋለህ። 22  ከወንዶች ልጆቹ መካከል እሱን የሚተካው የተቀባው ካህንም ያቀርበዋል። ሙሉ በሙሉ የሚቀርብ መባም ሆኖ ለይሖዋ እንዲጨስ ይደረጋል፤ ይህም ዘላቂ ሥርዓት ነው። 23  አንድ ካህን የሚያቀርበው እያንዳንዱ የእህል መባ ሙሉ በሙሉ መቃጠል ይኖርበታል። መበላት የለበትም።” 24  ይሖዋ በድጋሚ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 25  “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ በላቸው፦ ‘የኃጢአት መባ ሕግ ይህ ነው፦ ለኃጢአት መባ የሚሆነውም እንስሳ፣ ለሚቃጠል መባ የሚሆነው እንስሳ በሚታረድበት ቦታ በይሖዋ ፊት ይታረዳል። ይህ እጅግ ቅዱስ የሆነ ነገር ነው። 26  ይህን ለኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው ካህን ይበላዋል። በመገናኛ ድንኳኑ ግቢ ውስጥ ቅዱስ በሆነ ስፍራ ይበላል። 27  “‘ሥጋውን የሚነካ ማንኛውም ነገር ቅዱስ ይሆናል፤ ማንም ሰው የእንስሳውን ደም በልብሱ ላይ ቢረጭ ደም የተረጨበትን ልብስ በቅዱስ ስፍራ እጠበው። 28  ሥጋው የተቀቀለበት የሸክላ ዕቃም መሰባበር አለበት። የተቀቀለው ከመዳብ በተሠራ ዕቃ ከሆነ ግን ዕቃው ፍትግ ተደርጎ በውኃ መታጠብ አለበት። 29  “‘ካህን የሆነ ወንድ ሁሉ ይበላዋል። እጅግ ቅዱስ የሆነ ነገር ነው። 30  ይሁን እንጂ በቅዱሱ ስፍራ ለማስተሰረያ እንዲሆን ደሙ ወደ መገናኛ ድንኳኑ የገባ የኃጢአት መባ መበላት የለበትም። በእሳት መቃጠል አለበት።
[]
[]
[]
[]
12,461
7  “‘የበደል መባ ሕግ ይህ ነው፦ ይህ እጅግ የተቀደሰ ነገር ነው። 2  ለበደል መባ የሚሆነውን እንስሳ፣ ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን እንስሳ በሚያርዱበት ቦታ ያርዱታል፤ ደሙም በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ መረጨት ይኖርበታል። 3  ስቡን በሙሉ ይኸውም ላቱን፣ አንጀቱን የሸፈነውን ስብ፣ 4  ሁለቱን ኩላሊቶች፣ በሽንጡ አካባቢ ካለው ስባቸው ጋር ያቅርብ። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳዋል። 5  ካህኑ ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሳቸዋል። ይህ የበደል መባ ነው። 6  ካህን የሆነ ወንድ ሁሉ ይበላዋል፤ ቅዱስ በሆነ ስፍራም መበላት ይኖርበታል። ይህ እጅግ የተቀደሰ ነገር ነው። 7  ስለ ኃጢአት መባው የወጣው ሕግ ለበደል መባውም ይሠራል፤ መባውም በመባው ለሚያስተሰርየው ካህን ይሆናል። 8  “‘ካህኑ ለአንድ ሰው የሚቃጠል መባ በሚያቀርብበት ጊዜ የሚቃጠል መባ ሆኖ ለካህኑ የቀረበው እንስሳ ቆዳ የእሱ ይሆናል። 9  “‘በመጋገሪያ ምድጃ የተጋገረ ወይም በድስት የተዘጋጀ አሊያም በምጣድ የተጋገረ የእህል መባ ሁሉ መባውን ለሚያቀርበው ካህን ይሆናል። መባው የእሱ ይሆናል። 10  በዘይት የተለወሰው ወይም ደረቅ የሆነው የእህል መባ ግን ለአሮን ወንዶች ልጆች በሙሉ ይከፋፈላል፤ እያንዳንዳቸውም እኩል ድርሻ ይኖራቸዋል። 11  “‘አንድ ሰው ለይሖዋ የሚያቀርበውን የኅብረት መሥዋዕት በተመለከተ ደግሞ ሕጉ ይህ ነው፦ 12  ሰውየው መሥዋዕቱን የሚያቀርበው አመስጋኝነቱን ለመግለጽ ከሆነ ከምስጋና መሥዋዕቱ ጋር በዘይት ተለውሶ የተጋገረ እርሾ ያልገባበት የቀለበት ቅርጽ ያለው ዳቦ፣ ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣና በዘይት በደንብ ከራሰና ከተለወሰ የላመ ዱቄት የተጋገረ የቀለበት ቅርጽ ያለው ዳቦ አብሮ ያቀርባል። 13  መባውንም እርሾ ገብቶባቸው ከተጋገሩ የቀለበት ቅርጽ ያላቸው ዳቦዎችና የምስጋና መሥዋዕት አድርጎ ከሚያቀርባቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ጋር አብሮ ያቀርባል። 14  ከዚያም ላይ ከእያንዳንዱ መባ አንድ አንድ በማንሳት ለይሖዋ የተቀደሰ ድርሻ አድርጎ ያቀርባል፤ ይህም የኅብረት መሥዋዕቶቹን ደም ለሚረጨው ካህን ይሆናል። 15  የምስጋና መሥዋዕት እንዲሆኑ ያቀረባቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ሥጋ፣ መሥዋዕቱን ባቀረበበት ቀን መበላት ይኖርበታል። ከዚያ ላይ ምንም ማስቀረትና ማሳደር የለበትም። 16  “‘መባ አድርጎ የሚያቀርበው መሥዋዕት ስእለት ወይም የፈቃደኝነት መባ ከሆነ መሥዋዕቱን ባቀረበበት ቀን መበላት አለበት፤ የተረፈውም በማግስቱ ሊበላ ይችላል። 17  ለመሥዋዕት ከቀረበው ሥጋ ተርፎ እስከ ሦስተኛው ቀን የቆየው ግን በእሳት መቃጠል አለበት። 18  ይሁን እንጂ የኅብረት መሥዋዕት እንዲሆን ያቀረበው ማንኛውም ሥጋ በሦስተኛው ቀን ቢበላ መሥዋዕቱን ያቀረበው ሰው ተቀባይነት አያገኝም። ያደረገውም ነገር አይታሰብለትም፤ ይህ አስጸያፊ ነገር ነው፤ ከዚያም ላይ የበላው ሰው ለፈጸመው ስህተት ይጠየቅበታል። 19  ርኩስ የሆነን ማንኛውንም ነገር የነካ ሥጋ መበላት የለበትም። በእሳት መቃጠል አለበት። ንጹሕ የሆነ ማንኛውም ሰው ንጹሕ የሆነውን ሥጋ ሊበላ ይችላል። 20  “‘ሆኖም ማንኛውም ሰው ርኩስ ሆኖ ሳለ ለይሖዋ ከቀረበው የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ ያ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ። 21  አንድ ሰው ርኩስ የሆነ ነገር ይኸውም የሰውን ርኩሰት ወይም ርኩስ የሆነን እንስሳ ወይም ርኩስ የሆነን ማንኛውንም አስጸያፊ ነገር ቢነካና ለይሖዋ ከቀረበው የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ ያ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ።’” 22  ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 23  “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘ማንኛውንም ዓይነት የበሬ፣ የበግ ጠቦት ወይም የፍየል ስብ አትብሉ። 24  ሞቶ የተገኘ እንስሳ ስብና አውሬ የገደለው እንስሳ ስብ ለሌላ ለማንኛውም አገልግሎት ሊውል ይችላል፤ እናንተ ግን ፈጽሞ እንዳትበሉት። 25  ማንኛውም ሰው ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጎ ከሚያቀርበው እንስሳ ላይ ስብ ቢበላ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ። 26  “‘በምትኖሩበት በየትኛውም ቦታ የወፍም ይሁን የእንስሳ፣ ማንኛውንም ደም አትብሉ። 27  ደም የሚበላ ማንኛውም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ።’” 28  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 29  “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘የኅብረት መሥዋዕቱን ለይሖዋ የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው ከኅብረት መሥዋዕቱ መባ ላይ የተወሰነውን ለይሖዋ ያቀርባል። 30  እሱም ስቡን ከፍርምባው ጋር ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ እንዲሆን በራሱ እጆች ያመጣል፤ የሚወዘወዝ መባ አድርጎም በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ይወዘውዘዋል። 31  ካህኑ ስቡን በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል፤ ፍርምባው ግን የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ይሆናል። 32  “‘ከኅብረት መሥዋዕቶቻችሁም ላይ ቀኝ እግሩን ለካህኑ የተቀደሰ ድርሻ አድርጋችሁ ትሰጣላችሁ። 33  የኅብረት መሥዋዕቱን ደምና ስቡን የሚያቀርበው የአሮን ልጅ የእንስሳውን ቀኝ እግር እንደ ድርሻው አድርጎ ይወስዳል። 34  እስራኤላውያን ከሚያቀርቧቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ላይ የሚወዘወዘውን መባ ፍርምባና የተቀደሰ ድርሻ ሆኖ የቀረበውን እግር እወስዳለሁ፤ ለእስራኤላውያንም ዘላቂ ሥርዓት እንዲሆን ለካህኑ ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ እሰጣቸዋለሁ። 35  “‘ካህናት ሆነው ይሖዋን ለማገልገል በሚቀርቡበት ቀን፣ ለይሖዋ በእሳት ከቀረቡት መባዎች ላይ ለካህናቱ ይኸውም ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ የሚመደብላቸው ድርሻ ይህ ነው። 36  ይሖዋ በቀባቸው ቀን ይህ ድርሻ ከእስራኤላውያን ተወስዶ እንዲሰጣቸው አዟል። ይህ ለትውልዶቻቸው ዘላለማዊ ደንብ ነው።’” 37  የሚቃጠል መባን፣ የእህል መባን፣ የኃጢአት መባን፣ የበደል መባን፣ ለክህነት ሹመት ሥርዓት የሚቀርብ መሥዋዕትንና የኅብረት መሥዋዕትን በተመለከተ የተሰጠው ሕግ ይህ ነው፤ 38  ይህም እስራኤላውያን በሲና ምድረ በዳ መባዎቻቸውን ለይሖዋ እንዲያቀርቡ ባዘዛቸው ቀን ይሖዋ ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ባዘዘው መሠረት የሚፈጸም ነው።
[]
[]
[]
[]
12,462
8  ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “አሮንን፣ ከእሱም ጋር ወንዶች ልጆቹን እንዲሁም ልብሶቹን፣ የቅብዓት ዘይቱን፣ ለኃጢአት መባ የሚሆነውን በሬ፣ ሁለቱን አውራ በጎችና ቂጣ ያለበትን ቅርጫት ውሰድ፤ 3  መላው ማኅበረሰብም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ እንዲሰበሰብ አድርግ።” 4  ከዚያም ሙሴ ልክ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ፤ ማኅበረሰቡም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ተሰበሰበ። 5  ሙሴም ለማኅበረሰቡ “ይሖዋ እንድናደርግ ያዘዘን ነገር ይህ ነው” አላቸው። 6  በመሆኑም ሙሴ አሮንንና ወንዶች ልጆቹን አቀረባቸው፤ በውኃም አጠባቸው። 7  ከዚያም ለአሮን ረጅሙን ቀሚስ አጠለቀለት፤ መቀነቱንም አሰረለት፤ እጅጌ የሌለውን ቀሚስም አለበሰው፤ ኤፉዱንም አደረገለት፤ ኤፉዱንም ተሸምኖ በተሠራው የኤፉዱ መቀነት ጠበቅ አድርጎ አሰረው። 8  በመቀጠልም የደረት ኪሱን አደረገለት፤ በደረት ኪሱም ውስጥ ኡሪሙንና ቱሚሙን አስቀመጠ። 9  ከዚያም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ጥምጥሙን በራሱ ላይ አደረገለት፤ በጥምጥሙም ከፊት በኩል፣ የሚያብረቀርቀውን ጠፍጣፋ ወርቅ ይኸውም ለአምላክ የተወሰኑ መሆንን የሚያሳየውን ቅዱስ ምልክት አደረገለት። 10  ሙሴም የቅብዓት ዘይቱን ወስዶ የማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያሉትን ነገሮች በሙሉ ቀባቸው፤ እንዲሁም ቀደሳቸው። 11  ከዚያም ይቀድሳቸው ዘንድ ከዘይቱ የተወሰነውን ወስዶ በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ በመርጨት መሠዊያውንና ዕቃዎቹን በሙሉ እንዲሁም የውኃ ገንዳውንና ማስቀመጫውን ቀባቸው። 12  በመጨረሻም ከቅብዓት ዘይቱ የተወሰነውን ወስዶ በአሮን ራስ ላይ አፈሰሰው፤ የተቀደሰም ይሆን ዘንድ ቀባው። 13  ከዚያም ሙሴ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት የአሮንን ወንዶች ልጆች አቀረባቸው፤ ረጅሞቹን ቀሚሶችም አለበሳቸው፤ መቀነቶቹንም አሰረላቸው፤ የራስ ቆቡንም ደፋላቸው። 14  ከዚያም ለኃጢአት መባ የሚሆነውን በሬ አመጣ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም እጆቻቸውን ለኃጢአት መባ በሚሆነው በሬ ራስ ላይ ጫኑ። 15  ሙሴም በሬውን አረደው፤ ደሙንም በጣቱ ወስዶ በሁሉም የመሠዊያው ጎኖች ላይ ያሉትን ቀንዶች ቀባ፤ መሠዊያውንም ከኃጢአት አነጻው፤ የቀረውንም ደም መሠዊያው ማስተሰረያ ይቀርብበት ዘንድ መሠዊያውን ለመቀደስ በሥሩ አፈሰሰው። 16  ከዚያም ሙሴ አንጀቱን የሸፈነውን ስብ ሁሉ፣ በጉበቱ ላይ ያለውን ሞራ፣ ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ያለውን ስብ ወስዶ በመሠዊያው ላይ እንዲጨሱ አደረገ። 17  ሙሴም ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ከበሬው የቀረውን፣ ቆዳውን፣ ሥጋውንና ፈርሱን ከሰፈሩ ውጭ በእሳት አቃጠለው። 18  እሱም ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን አውራ በግ አመጣ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም እጆቻቸውን በአውራው በግ ራስ ላይ ጫኑ። 19  ከዚያም ሙሴ አውራውን በግ አረደው፤ ደሙንም በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ረጨው። 20  አውራውንም በግ በየብልቱ ቆራረጠው፤ ቀጥሎም ጭንቅላቱን፣ ብልቶቹንና ሞራውን አጨሰው። 21  ሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ አጠባቸው፤ ሙሴም አውራው በግ በሙሉ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ አደረገ። ይህም ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው የሚቃጠል መባ ነበር። ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነበር። 22  ከዚያም ሁለተኛውን አውራ በግ ይኸውም ለክህነት ሹመት ሥርዓት የሚቀርበውን አውራ በግ አመጣ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ። 23  ከዚያም ሙሴ አውራውን በግ አረደው፤ ከደሙም የተወሰነውን ወስዶ የአሮንን የቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ቀባ። 24  በመቀጠልም ሙሴ የአሮንን ወንዶች ልጆች ወደ ፊት አቀረባቸው፤ ከደሙም የተወሰነውን ወስዶ የቀኝ ጆሯቸውን ጫፍ፣ የቀኝ እጃቸውን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግራቸውን አውራ ጣት ቀባ፤ የቀረውን ደም ግን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ረጨው። 25  ከዚያም ስቡን፣ ላቱን፣ አንጀቱን የሚሸፍነውን ስብ በሙሉ፣ የጉበቱን ሞራ፣ ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ያለውን ስብ እንዲሁም ቀኝ እግሩን ወሰደ። 26  በይሖዋ ፊት ካለው ቂጣዎች ከተቀመጡበት ቅርጫት ውስጥም እርሾ ያልገባበት የቀለበት ቅርጽ ያለው አንድ ዳቦ፣ ዘይት የተቀባ የቀለበት ቅርጽ ያለው አንድ ዳቦና አንድ ስስ ቂጣ ወሰደ። ከዚያም በስቦቹና በቀኝ እግሩ ላይ አደረጋቸው። 27  በመቀጠልም ሁሉንም በአሮን መዳፍና በወንዶች ልጆቹ መዳፍ ላይ አስቀመጣቸው፤ በይሖዋ ፊት እንደሚወዘወዝ መባም ወዲያና ወዲህ ወዘወዛቸው። 28  ከዚያም ሙሴ ከእጃቸው ላይ ወስዶ በመሠዊያው ላይ ባለው በሚቃጠለው መባ ላይ እንዲጨሱ አደረገ። እነዚህም ደስ የሚያሰኝ መዓዛ የሚሰጡ የክህነት ሹመት መሥዋዕት ናቸው። ይህም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነበር። 29  ሙሴም ፍርምባውን ወስዶ በይሖዋ ፊት እንደሚወዘወዝ መባ ወዲያና ወዲህ ወዘወዘው። ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረትም ለክህነት ሹመት ሥርዓት ከሚቀርበው አውራ በግ ላይ ይህ የእሱ ድርሻ ሆነ። 30  ሙሴም ከቅብዓት ዘይቱና በመሠዊያው ላይ ካለው ደም የተወሰነውን ወስዶ በአሮንና በልብሶቹ እንዲሁም ከእሱ ጋር በነበሩት ወንዶች ልጆቹና በወንዶች ልጆቹ ልብሶች ላይ ረጨው። በዚህ መንገድ አሮንንና ልብሶቹን እንዲሁም ወንዶች ልጆቹንና ልብሶቻቸውን ቀደሰ። 31  ከዚያም ሙሴ አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ አላቸው፦ “ሥጋውን በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ቀቅሉት፤ ‘አሮንና ወንዶች ልጆቹ ይበሉታል’ ተብዬ በታዘዝኩት መሠረት ሥጋውንም ሆነ በክህነት ሹመት ሥርዓቱ ቅርጫት ውስጥ ያለውን ቂጣ እዚያ ትበሉታላችሁ። 32  ከሥጋውም ሆነ ከቂጣው የተረፈውን በእሳት ታቃጥሉታላችሁ። 33  ለክህነት ሹመታችሁ ሥርዓት የተመደቡት ቀናት እስከሚያበቁ ድረስ ይኸውም ለሰባት ቀን ያህል በመገናኛ ድንኳኑ ደጃፍ ቆዩ፤ ምክንያቱም እናንተን ካህን አድርጎ መሾም ሰባት ቀን ይፈጃል። 34  ለእናንተ ለማስተሰረይ ዛሬ ያደረግነውን ነገር እንድናደርግ ይሖዋ አዟል። 35  በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ቀንና ሌሊት ለሰባት ቀን ያህል ትቆያላችሁ፤ እንዳትሞቱም ለይሖዋ የገባችሁትን ግዴታ ፈጽሙ፤ ምክንያቱም እንዲህ እንዳደርግ ታዝዣለሁ።” 36  አሮንና ወንዶች ልጆቹም ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት ያዘዛቸውን ነገሮች በሙሉ አደረጉ።
[]
[]
[]
[]
12,463
9  በስምንተኛውም ቀን ሙሴ አሮንን፣ ወንዶች ልጆቹንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠራ። 2  አሮንንም እንዲህ አለው፦ “ለኃጢአት መባ አንድ ጥጃ፣ ለሚቃጠል መባ ደግሞ አንድ አውራ በግ ለራስህ ውሰድ፤ እንከን የሌለባቸው ይሁኑ፤ በይሖዋም ፊት አቅርባቸው። 3  እስራኤላውያንን ግን እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ‘ለኃጢአት መባ አንድ ተባዕት ፍየል፣ ለሚቃጠል መባ ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸውና እንከን የሌለባቸው አንድ ጥጃና አንድ የበግ ጠቦት ውሰዱ፤ 4  የኅብረት መሥዋዕት ሆነው በይሖዋ ፊት እንዲሠዉም አንድ በሬና አንድ አውራ በግ ውሰዱ፤ እንዲሁም በዘይት የተለወሰ የእህል መባ አቅርቡ፤ ምክንያቱም ይሖዋ ዛሬ ለእናንተ ይገለጣል።’” 5  ስለዚህ ሙሴ ያዘዛቸውን ነገሮች በሙሉ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ፊት አመጡ። ከዚያም መላው ማኅበረሰብ መጥቶ በይሖዋ ፊት ቆመ። 6  ሙሴም “የይሖዋ ክብር ይገለጥላችሁ ዘንድ ይሖዋ እንድታደርጉት ያዘዛችሁ ነገር ይህ ነው” አለ። 7  ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፦ “ወደ መሠዊያው ቀርበህ የኃጢአት መባህንና የሚቃጠል መባህን አቅርብ፤ ለራስህና ለቤትህም አስተሰርይ፤ ይሖዋ ባዘዘውም መሠረት የሕዝቡን መባ አቅርብ፤ እንዲሁም ለእነሱ አስተሰርይ።” 8  አሮንም ወዲያው ወደ መሠዊያው ቀርቦ ስለ ራሱ የኃጢአት መባ ሆኖ የሚቀርበውን ጥጃ አረደ። 9  ከዚያም ወንዶች ልጆቹ ደሙን አቀረቡለት፤ እሱም ጣቱን ደሙ ውስጥ በመንከር የመሠዊያውን ቀንዶች ቀባ፤ የቀረውንም ደም በመሠዊያው ሥር አፈሰሰው። 10  ይሖዋ ሙሴን ባዘዘውም መሠረት ከኃጢአት መባው ላይ ስቡን፣ ኩላሊቶቹንና በጉበቱ ላይ ያለውን ሞራ ወስዶ በመሠዊያው ላይ እንዲጨሱ አደረገ። 11  ሥጋውንና ቆዳውንም ከሰፈሩ ውጭ በእሳት አቃጠለው። 12  ከዚያም የሚቃጠል መባ ሆኖ የሚቀርበውን እንስሳ አረደው፤ ወንዶች ልጆቹም ደሙን ሰጡት፤ እሱም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ረጨው። 13  እነሱም የሚቃጠለውን መባ ብልቶች ከነጭንቅላቱ ሰጡት፤ እሱም በመሠዊያው ላይ እንዲጨሱ አደረገ። 14  በተጨማሪም ሆድ ዕቃውንና እግሮቹን አጠባቸው፤ በመሠዊያው ላይ ባለው በሚቃጠለው መባ ላይም እንዲጨሱ አደረገ። 15  በመቀጠልም የሕዝቡን መባ አቀረበ፤ ለሕዝቡ የኃጢአት መባ ሆኖ የሚቀርበውን ፍየል ወስዶ አረደው፤ እንደ መጀመሪያው ሁሉ በዚህኛውም የኃጢአት መባ አቀረበ። 16  ከዚያም የሚቃጠለውን መባ አቀረበ፤ በተለመደውም አሠራር መሠረት አቀረበው። 17  በመቀጠልም የእህል መባውን አቀረበ፤ ከላዩ ላይም እፍኝ ሙሉ አንስቶ ጠዋት ላይ ከሚቀርበው የሚቃጠል መባ በተጨማሪ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ አደረገ። 18  በኋላም ለሕዝቡ የኅብረት መሥዋዕት የሚሆኑትን በሬውንና አውራውን በግ አረዳቸው። ወንዶች ልጆቹም ደሙን ሰጡት፤ እሱም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ረጨው። 19  ከዚያም የበሬውን ስቦች፣ የአውራውን በግ ላት፣ ሆድ ዕቃውን የሸፈነውን ስብ፣ ኩላሊቶቹንና የጉበቱን ሞራ 20  ማለትም ስቡን ሁሉ በፍርምባዎቹ ላይ አደረጉ፤ ስቡም ሁሉ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ አደረገ። 21  ሆኖም አሮን ፍርምባዎቹንና ቀኝ እግሩን ልክ ሙሴ ባዘዘው መሠረት እንደሚወዘወዝ መባ በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ወዘወዛቸው። 22  ከዚያም አሮን እጆቹን ወደ ሕዝቡ በማንሳት ባረካቸው፤ የኃጢአት መባውን፣ የሚቃጠል መባውንና የኅብረት መሥዋዕቶቹን ካቀረበ በኋላ ወረደ። 23  በመጨረሻም ሙሴና አሮን ወደ መገናኛ ድንኳኑ ገቡ፤ ከዚያም ወጥተው ሕዝቡን ባረኩ። በዚህ ጊዜ የይሖዋ ክብር ለሕዝቡ ሁሉ ተገለጠ፤ 24  እሳትም ከይሖዋ ፊት ወጥቶ በመሠዊያው ላይ ያለውን የሚቃጠል መባና ስብ በላ። ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲያይ እልል አለ፤ በግንባሩም መሬት ላይ ተደፋ።
[]
[]
[]
[]
12,464
1  ቤተሰባቸውን ይዘው ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የመጡት የእስራኤል ወንዶች ልጆች ስም የሚከተለው ነው፦ 2  ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ 3  ይሳኮር፣ ዛብሎን፣ ቢንያም፣ 4  ዳን፣ ንፍታሌም፣ ጋድና አሴር። 5  ከያዕቆብ አብራክ የወጡት በጠቅላላ 70 ነበሩ፤ ዮሴፍ ግን ቀድሞውኑም እዚያው ግብፅ ነበር። 6  ከጊዜ በኋላ ዮሴፍ ሞተ፤ ወንድሞቹም ሁሉ ሞቱ፤ ያም ትውልድ በሙሉ ሞተ። 7  እስራኤላውያንም ተዋለዱ፤ በጣም ብዙ ሆኑ፤ ቁጥራቸውም በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረና ኃያል እየሆኑ ሄዱ፤ ከዚህም የተነሳ ምድሪቱን ሞሏት። 8  ከጊዜ በኋላ ዮሴፍን የማያውቅ አዲስ ንጉሥ በግብፅ ተነሳ። 9  እሱም ሕዝቦቹን እንዲህ አላቸው፦ “ይኸው እንደምታዩት የእስራኤል ሕዝብ ከእኛ ይልቅ እጅግ ብዙና ኃያል ነው። 10  እንግዲህ እነሱን በተመለከተ አንድ መላ እንፍጠር። ካልሆነ ግን ቁጥራቸው እየበዛ ይሄዳል፤ ደግሞም ጦርነት ከተነሳ ከጠላቶቻችን ጋር ወግነው እኛን መውጋታቸውና አገሪቱን ጥለው መኮብለላቸው አይቀርም።” 11  በመሆኑም ከባድ ሥራ በማሠራት እንዲያስጨንቋቸው የግዳጅ ሥራ የሚያሠሩ አለቆችን ሾሙባቸው፤ እነሱም ጲቶም እና ራምሴስ የተባሉ ለማከማቻ የሚሆኑ ከተሞችን ለፈርዖን ገነቡ። 12  ሆኖም ይበልጥ በጨቆኗቸው መጠን ይበልጥ እየበዙና በምድሩ ላይ ይበልጥ እየተስፋፉ ስለሄዱ ግብፃውያን በእስራኤላውያን የተነሳ ከፍተኛ ፍርሃት አደረባቸው። 13  በመሆኑም ግብፃውያን እስራኤላውያንን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በባርነት ይገዟቸው ጀመር። 14  የሸክላ ጭቃ በማስቦካት፣ ጡብ በማሠራትና በእርሻ ላይ ማንኛውንም ዓይነት የባርነት ሥራ እንዲሠሩ በማድረግ ሕይወታቸውን መራራ አደረጉባቸው። አዎ፣ ማንኛውንም ዓይነት የባርነት ሥራ በማሠራት በጭካኔ ያንገላቷቸው ነበር። 15  በኋላም የግብፅ ንጉሥ፣ ሺፍራ እና ፑሃ የተባሉትን ዕብራውያን አዋላጆች አነጋገራቸው፤ 16  እንዲህም አላቸው፦ “ዕብራውያን ሴቶችን በምታዋልዱበት ጊዜ በማዋለጃው ዱካ ላይ ተቀምጠው ስታዩ የሚወለደው ልጅ ወንድ ከሆነ ግደሉት፤ ሴት ከሆነች ግን በሕይወት ትኑር።” 17  ይሁን እንጂ አዋላጆቹ እውነተኛውን አምላክ ስለፈሩ የግብፅ ንጉሥ ያላቸውን አላደረጉም። ከዚህ ይልቅ ወንዶቹን ልጆች በሕይወት እንዲኖሩ ይተዉአቸው ነበር። 18  ከጊዜ በኋላም የግብፅ ንጉሥ አዋላጆቹን ጠርቶ “ወንዶቹን ልጆች በሕይወት እንዲኖሩ የተዋችኋቸው ለምንድን ነው?” አላቸው። 19  አዋላጆቹም ፈርዖንን “ዕብራውያን ሴቶች እንደ ግብፃውያን ሴቶች አይደሉም። እነሱ ብርቱዎች ስለሆኑ አዋላጇ ከመድረሷ በፊት በራሳቸው ይወልዳሉ” አሉት። 20  ስለሆነም አምላክ ለአዋላጆቹ መልካም ነገር አደረገላቸው፤ ሕዝቡም እየበዛና እጅግ ኃያል እየሆነ ሄደ። 21  አዋላጆቹ እውነተኛውን አምላክ በመፍራታቸው፣ አምላክ ከጊዜ በኋላ ቤተሰብ ሰጣቸው። 22  በመጨረሻም ፈርዖን ሕዝቡን ሁሉ “አዲስ የሚወለዱትን የዕብራውያንን ወንዶች ልጆች ሁሉ አባይ ወንዝ ውስጥ ጣሏቸው፤ ሴቶቹን ልጆች ሁሉ ግን በሕይወት እንዲኖሩ ተዉአቸው” ሲል አዘዘ።
[]
[]
[]
[]
12,465
10  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ፈርዖን ግባ፤ ምክንያቱም የእሱም ሆነ የአገልጋዮቹ ልብ እንዲደነድን እፈቅዳለሁ፤ ይህን የማደርገውም እነዚህን ተአምራዊ ምልክቶቼን በፊቱ እንዳሳይ 2  እንዲሁም ግብፅን እንዴት አድርጌ እንደቀጣሁና በመካከላቸው ተአምራዊ ምልክቶቼን እንዴት እንዳሳየሁ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ እንድታውጅ ነው፤ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ በእርግጥ ታውቃላችሁ።” 3  በመሆኑም ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ገብተው እንዲህ አሉት፦ “የዕብራውያን አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለመሆኑ ለእኔ ለመገዛት ፈቃደኛ የማትሆነው እስከ መቼ ነው? እንዲያገለግለኝ ሕዝቤን ልቀቅ። 4  አሁንም ሕዝቤን ለመልቀቅ ፈቃደኛ የማትሆን ከሆነ ግን በነገው ዕለት በግዛትህ ላይ አንበጦችን አመጣለሁ። 5  አንበጦቹም ምድሪቱን ይሸፍናሉ፤ መሬቱንም ማየት አይቻልም። እነሱም ከበረዶው ያመለጠውንና የቀረላችሁን ነገር ሁሉ ሙልጭ አድርገው ይበሉታል፤ በመስክ ላይ እየበቀሉ ያሉትን ዛፎቻችሁን በሙሉ ይበሏቸዋል። 6  አንበጦቹ አባቶችህና አያቶችህ በዚህች ምድር ላይ መኖር ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ አይተውት በማያውቁት ሁኔታ ቤቶችህን፣ የአገልጋዮችህን ቤቶች ሁሉና የግብፅን ቤቶች ሁሉ ይሞላሉ።’” እሱም ይህን ከተናገረ በኋላ ፊቱን አዙሮ ከፈርዖን ፊት ወጥቶ ሄደ። 7  ከዚያም የፈርዖን አገልጋዮች ፈርዖንን እንዲህ አሉት፦ “ይህ ሰው ወጥመድ የሚሆንብን እስከ መቼ ነው? አምላካቸውን ይሖዋን እንዲያገለግሉ ሰዎቹን ልቀቃቸው። ግብፅ እየጠፋች እንደሆነ እስካሁን አልተገነዘብክም?” 8  በመሆኑም ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ተመልሰው እንዲመጡ ተደረገ፤ እሱም “ሂዱ፤ አምላካችሁን ይሖዋን አገልግሉ። ይሁንና የሚሄዱት እነማን ናቸው?” አላቸው። 9  በዚህ ጊዜ ሙሴ “ለይሖዋ የምናከብረው በዓል ስላለን ወጣቶቻችንን፣ አዛውንቶቻችንን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንን እንዲሁም በጎቻችንንና ከብቶቻችንን ይዘን እንሄዳለን” አለ። 10  እሱም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተንና ልጆቻችሁን ከለቀኩማ በእርግጥም ይሖዋ ከእናንተ ጋር ነው! መቼም የሆነ ተንኮል እንዳሰባችሁ ግልጽ ነው። 11  ይሄማ አይሆንም! ወንዶቹ ብቻ ሄደው ይሖዋን ያገልግሉ፤ ምክንያቱም የጠየቃችሁት ይህንኑ ነው።” ከዚያም ከፈርዖን ፊት እንዲወጡ ተደረገ። 12  በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንበጦች መጥተው የግብፅን ምድር እንዲወሩና ከበረዶ የተረፈውን በምድሩ ላይ ያለውን ማንኛውንም ተክል ጠራርገው እንዲበሉ በግብፅ ምድር ላይ እጅህን ዘርጋ።” 13  ሙሴም ወዲያው በግብፅ ምድር ላይ በትሩን ሰነዘረ፤ ይሖዋም በዚያን ዕለት ቀኑንና ሌሊቱን ሙሉ በምድሩ ላይ የምሥራቅ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ። ሲነጋም የምሥራቁ ነፋስ አንበጦችን አመጣ። 14  አንበጦቹም በመላው የግብፅ ምድር ላይ መውጣትና በግብፅ ግዛት ሁሉ ላይ መስፈር ጀመሩ። ሁኔታው እጅግ አስከፊ ነበር፤ ከዚህ በፊት ያን ያህል ብዛት ያለው አንበጣ ታይቶ አያውቅም፤ ዳግመኛም ያን ያህል ብዛት ያለው አንበጣ ፈጽሞ አይከሰትም። 15  አንበጦቹም መላውን ምድር ሸፈኑት፤ ምድሪቱም በእነሱ የተነሳ ጨለመች፤ እነሱም ከበረዶው የተረፈውን በምድሩ ላይ ያለውን ተክል ሁሉ እንዲሁም በዛፎች ላይ ያለውን ፍሬ ሁሉ ጠራርገው በሉት፤ በመላው የግብፅ ምድር በዛፎችም ሆነ በመስክ ባሉ ተክሎች ላይ አንድም ለምለም ቅጠል አልተረፈም። 16  በመሆኑም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን በአስቸኳይ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “በአምላካችሁ በይሖዋም ሆነ በእናንተ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁ። 17  ስለሆነም አሁን እባካችሁ ይህን ኃጢአቴን ብቻ ይቅር በሉኝ፤ ይህን ገዳይ መቅሰፍት ከእኔ ላይ እንዲያስወግድልኝም አምላካችሁን ይሖዋን ለምኑልኝ።” 18  እሱም ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ ይሖዋንም ለመነ። 19  ከዚያም ይሖዋ ነፋሱ እንዲቀየር አደረገ፤ ነፋሱም ኃይለኛ የምዕራብ ነፋስ ሆነ፤ ነፋሱም አንበጦቹን ወስዶ ቀይ ባሕር ውስጥ ከተታቸው። በመላው የግብፅ ግዛት አንድም አንበጣ አልቀረም። 20  ሆኖም ይሖዋ የፈርዖን ልብ እንዲደነድን ፈቀደ፤ እሱም እስራኤላውያንን አለቀቀም። 21  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን “በግብፅ ምድር ላይ ጨለማ ይኸውም የሚዳሰስ የሚመስል ድቅድቅ ጨለማ እንዲከሰት እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ” አለው። 22  ሙሴም ወዲያውኑ እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ በመላው የግብፅ ምድር ላይም ለሦስት ቀን ያህል ድቅድቅ ጨለማ ተከሰተ። 23  እነሱም እርስ በርስ አይተያዩም ነበር፤ ለሦስት ቀን ማናቸውም ካሉበት ቦታ ንቅንቅ ማለት አልቻሉም፤ ሆኖም እስራኤላውያን ሁሉ በሚኖሩበት ስፍራ ብርሃን ነበር። 24  ከዚያም ፈርዖን ሙሴን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ሂዱ፣ ይሖዋን አገልግሉ። በጎቻችሁና ከብቶቻችሁ ብቻ እዚሁ ይቀራሉ። ልጆቻችሁም አብረዋችሁ መሄድ ይችላሉ።” 25  ሙሴ ግን እንዲህ አለው፦ “እንግዲያውስ ለመሥዋዕቶችና ለሚቃጠሉ መባዎች የሚሆኑትን እንስሳት አንተው ራስህ ትሰጠንና ለአምላካችን ለይሖዋ መሥዋዕት አድርገን እናቀርባቸዋለን። 26  ከብቶቻችንም አብረውን መሄድ አለባቸው። አምላካችንን ይሖዋን ስናመልክ ከእነሱ መካከል አንዳንዶቹን መሥዋዕት አድርገን ስለምናቀርብ አንድም እንስሳ እዚህ መቅረት የለበትም፤ ደግሞም እኛ ራሳችን ለይሖዋ አምልኮ ምን መሥዋዕት ማቅረብ እንዳለብን የምናውቀው እዚያ ስንደርስ ነው።” 27  ይሖዋም የፈርዖን ልብ እንዲደነድን ፈቀደ፤ እሱም ሊለቃቸው ፈቃደኛ አልሆነም። 28  ስለሆነም ፈርዖን “ከፊቴ ጥፋ! ዳግመኛ ፊቴን ለማየት እንዳትሞክር፤ ፊቴን የምታይበት ቀን መሞቻህ እንደሚሆን እወቅ” አለው። 29  በዚህ ጊዜ ሙሴ “እሺ፣ እንዳልከው ይሁን፤ ዳግመኛ ፊትህን አላይም” አለው።
[]
[]
[]
[]
12,466
11  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በፈርዖንና በግብፅ ላይ አንድ ተጨማሪ መቅሰፍት አመጣለሁ። ከዚያ በኋላ ከዚህ እንድትሄዱ ይለቃችኋል። ደግሞም በሚለቃችሁ ጊዜ አንዳችሁንም ሳያስቀር ከዚህ ያባርራችኋል። 2  እንግዲህ አሁን ወንዶቹም ሆኑ ሴቶቹ ሁሉ ከየጎረቤቶቻቸው የብርና የወርቅ ዕቃዎችን እንዲጠይቁ ለሕዝቡ ንገር።” 3  ይሖዋም ለሕዝቡ በግብፃውያን ፊት ሞገስ ሰጣቸው። ሙሴ ራሱም ቢሆን በፈርዖን አገልጋዮችና በሕዝቡ ፊት በግብፅ ምድር እጅግ የተከበረ ሰው ሆኖ ነበር። 4  ሙሴም እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እኩለ ሌሊት ገደማ በግብፅ መሃል እወጣለሁ፤ 5  በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከፈርዖን የበኩር ልጅ አንስቶ የወፍጮ መጅ እስከምትገፋው ባሪያ የበኩር ልጅ ድረስ በግብፅ ምድር ያለ በኩር ሁሉ ይሞታል፤ የእንስሳም በኩር ሁሉ ይሞታል። 6  በመላው የግብፅ ምድርም ከዚያ በፊት በጭራሽ ሆኖ የማያውቅ ከዚያ በኋላም ፈጽሞ ዳግመኛ የማይከሰት ታላቅ ዋይታ ይሆናል። 7  ሆኖም ይሖዋ በግብፃውያንና በእስራኤላውያን መካከል ልዩነት ማድረግ እንደሚችል እንድታውቁ በእስራኤላውያን ላይ፣ በሰዎቹም ሆነ በእንስሶቻቸው ላይ ውሻ እንኳ አይጮኽም።’ 8  አገልጋዮችህም ሁሉ ወደ እኔ ወርደው ‘አንተም ሆንክ አንተን የሚከተሉ ሰዎች ሁሉ ከዚህ ሂዱልን’ በማለት ይሰግዱልኛል። ከዚያ በኋላም እወጣለሁ።” ሙሴም ይህን ተናግሮ በታላቅ ቁጣ ከፈርዖን ፊት ወጣ። 9  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን “ተአምራቶቼ በግብፅ ምድር ላይ እንዲበዙ ፈርዖን እናንተን አይሰማችሁም” አለው። 10  ሙሴና አሮንም እነዚህን ሁሉ ተአምራት በፈርዖን ፊት ፈጸሙ፤ ሆኖም ይሖዋ የፈርዖን ልብ እንዲደነድን ስለፈቀደ ፈርዖን እስራኤላውያን ከምድሩ እንዲሄዱ ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆነም።
[]
[]
[]
[]
12,467
12  ይሖዋም ሙሴንና አሮንን በግብፅ ምድር እንዲህ አላቸው፦ 2  “ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ ይሆንላችኋል። ከዓመቱም ወሮች የመጀመሪያው ይሆንላችኋል። 3  ለመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ እንዲህ ብላችሁ ንገሩ፦ ‘ይህ ወር በገባ በአሥረኛው ቀን እያንዳንዱ ሰው ለአባቱ ቤት አንድ በግ ይኸውም ለአንድ ቤት አንድ በግ ይውሰድ። 4  ሆኖም ቤተሰቡ ለአንድ በግ የሚያንስ ከሆነ እነሱና የእነሱ የቅርብ ጎረቤቶች በጉን በየቤታቸው ባሉት ሰዎች ቁጥር ልክ ይከፋፈሉት። በምታሰሉበት ጊዜም እያንዳንዱ ሰው ከበጉ ምን ያህል እንደሚበላ ወስኑ። 5  የምትመርጡት በግ እንከን የሌለበት፣ ተባዕትና አንድ ዓመት የሞላው መሆን ይኖርበታል። ከበግ ጠቦቶች ወይም ከፍየሎች መካከል መምረጥ ትችላላችሁ። 6  እስከዚህ ወር 14ኛ ቀን ድረስ እየተንከባከባችሁ አቆዩት፤ መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ጉባኤም አመሻሹ ላይ ይረደው። 7  ከደሙም ወስደው በጉን በሚበሉበት ቤት በር በሁለቱ መቃኖችና በጉበኑ ላይ ይርጩት። 8  “‘ሥጋውንም በዚያው ሌሊት ይብሉት። ሥጋውን በእሳት ጠብሰው ከቂጣና ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉት። 9  የትኛውንም የሥጋውን ብልት ጥሬውን ወይም ቅቅሉን አትብሉ፤ ነገር ግን ጭንቅላቱን ከእግሩና ከሆድ ዕቃው ጋር በእሳት ጥበሱት። 10  እስከ ጠዋት ድረስ ምንም አታስተርፉ፤ ሳይበላ ያደረ ካለ ግን በእሳት አቃጥሉት። 11  የምትበሉትም ወገባችሁን ታጥቃችሁ፣ ጫማችሁን አድርጋችሁና በትራችሁን በእጃችሁ ይዛችሁ መሆን አለበት፤ በጥድፊያም ብሉት። ይህ የይሖዋ ፋሲካ ነው። 12  ምክንያቱም በዚህ ሌሊት በግብፅ ምድር አልፋለሁ፤ ከሰው አንስቶ እስከ እንስሳ ድረስ በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ እመታለሁ፤ በግብፅ አማልክት ሁሉ ላይም የፍርድ እርምጃ እወስዳለሁ። እኔ ይሖዋ ነኝ። 13  ደሙም እናንተ ያላችሁበትን ቤት የሚጠቁም ምልክት ሆኖ ያገለግላል፤ እኔም ደሙን ሳይ እናንተን አልፌ እሄዳለሁ፤ የግብፅን ምድር በምመታበት ጊዜ መቅሰፍቱ መጥቶ እናንተን አያጠፋም። 14  “‘ይህ ቀን ለእናንተ መታሰቢያ ይሆናል፤ እናንተም በመጪዎቹ ትውልዶቻችሁ ሁሉ የይሖዋ በዓል አድርጋችሁ አክብሩት። ይህን ዘላቂ ደንብ አድርጋችሁ አክብሩት። 15  ለሰባት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ። አዎ፣ በመጀመሪያው ቀን ከቤታችሁ እርሾ አስወግዱ፤ ምክንያቱም ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ እስከ ሰባተኛው ቀን ድረስ እርሾ የገባበትን ነገር የሚበላ ማንኛውም ሰው ከእስራኤል መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረጋል። 16  በመጀመሪያው ቀን ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ፤ በሰባተኛውም ቀን ሌላ ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ። በእነዚህ ቀናት ምንም ዓይነት ሥራ መሠራት የለበትም። እያንዳንዱ ሰው የሚበላውን ነገር ከማዘጋጀት ውጭ ሌላ ምንም ነገር አትሥሩ። 17  “‘የቂጣን በዓል አክብሩ፤ ምክንያቱም በዚህ ቀን ሠራዊታችሁን ከግብፅ ምድር አወጣለሁ። እናንተም ይህን ዕለት በመጪዎቹ ትውልዶቻችሁ ሁሉ ዘላቂ ደንብ አድርጋችሁ አክብሩት። 18  በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም ከ14ኛው ቀን ምሽት አንስቶ እስከ ወሩ 21ኛ ቀን ምሽት ድረስ ቂጣ ትበላላችሁ። 19  ለሰባት ቀናት እርሾ የሚባል ነገር በቤታችሁ ውስጥ አይገኝ፤ ምክንያቱም እርሾ ያለበትን ነገር የሚበላ ማንኛውም ሰው የባዕድ አገር ሰውም ሆነ የአገሩ ተወላጅ፣ ያ ሰው ከእስራኤል ማኅበረሰብ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረጋል። 20  እርሾ ያለበት ምንም ነገር አትብሉ። በቤታችሁ ሁሉ ቂጣ ብሉ።’” 21  ሙሴም ወዲያው የእስራኤልን ሽማግሌዎች በሙሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “ሂዱ፣ ለየቤተሰባችሁ የሚሆን ጠቦት መርጣችሁ የፋሲካን መሥዋዕት እረዱ። 22  ከዚያም አንድ እስር ሂሶጵ ወስዳችሁ በሳህን ባለው ደም ውስጥ ከነከራችሁ በኋላ ደሙን በበራችሁ ጉበንና በሁለቱ መቃኖች ላይ እርጩት፤ ከእናንተም መካከል አንድም ሰው እስኪነጋ ድረስ ከቤቱ መውጣት የለበትም። 23  ይሖዋ ግብፃውያንን በመቅሰፍት ሊመታ በሚያልፍበት ጊዜ በበራችሁ ጉበንና በሁለቱ መቃኖች ላይ ያለውን ደም ሲያይ ይሖዋ በእርግጥ በሩን አልፎ ይሄዳል፤ የሞት መቅሰፍቱ ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አይፈቅድም። 24  “እናንተም ይህን ነገር ለእናንተና ለልጆቻችሁ ዘላቂ ሥርዓት አድርጋችሁ አክብሩት። 25  ልክ ይሖዋ በተናገረው መሠረትም ወደሚሰጣችሁ ምድር በምትገቡበት ጊዜ ይህን በዓል አክብሩ። 26  ልጆቻችሁ ‘ይህን በዓል የምታከብሩት ለምንድን ነው?’ ብለው ሲጠይቋችሁ 27  እንዲህ በሏቸው፦ ‘ግብፃውያንን በመቅሰፍት በመታበት ጊዜ በግብፅ ያሉትን የእስራኤላውያንን ቤቶች አልፎ በመሄድ ቤቶቻችንን ላተረፈልን ለይሖዋ የሚቀርብ የፋሲካ መሥዋዕት ነው።’” ከዚያም ሕዝቡ ተደፍቶ ሰገደ። 28  እስራኤላውያንም ሄደው ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዳዘዛቸው አደረጉ። ልክ እንደተባሉት አደረጉ። 29  እኩለ ሌሊት ላይ ይሖዋ፣ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከፈርዖን የበኩር ልጅ አንስቶ በእስር ቤት እስከሚገኘው እስረኛ የበኩር ልጅ ድረስ በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ መታ፤ የእያንዳንዱን እንስሳ በኩርም መታ። 30  ከዚያም ፈርዖን በዚያ ሌሊት ተነሳ፤ እሱ ብቻ ሳይሆን አገልጋዮቹ ሁሉና ሌሎቹ ግብፃውያን በሙሉ ተነሱ፤ ሰው ያልሞተበት አንድም ቤት ስላልነበር በግብፃውያን መካከል ታላቅ ዋይታ ሆነ። 31  እሱም ወዲያውኑ ሙሴንና አሮንን በሌሊት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “ተነሱ፣ እናንተም ሆናችሁ ሌሎቹ እስራኤላውያን ከሕዝቤ መካከል ውጡ። ሂዱ፣ እንዳላችሁት ይሖዋን አገልግሉ። 32  ባላችሁትም መሠረት መንጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ይዛችሁ ሂዱ። እኔን ግን ባርኩኝ።” 33  ግብፃውያኑም “በዚህ ዓይነት እኮ ሁላችንም ማለቃችን ነው!” በማለት ሕዝቡ በአስቸኳይ ምድሪቱን ለቆ እንዲሄድላቸው ያጣድፉት ጀመር። 34  ስለዚህ ሕዝቡ ያልቦካውን ሊጥ በየቡሃቃው አድርጎ በልብሱ ከጠቀለለ በኋላ በትከሻው ተሸከመው። 35  እስራኤላውያንም ሙሴ የነገራቸውን አደረጉ፤ የብርና የወርቅ ዕቃዎችን እንዲሁም ልብሶችን እንዲሰጧቸውም ግብፃውያንን ጠየቁ። 36  ይሖዋም ለሕዝቡ በግብፃውያን ፊት ሞገስ ሰጣቸው፤ በመሆኑም የጠየቁትን ሁሉ ሰጧቸው፤ ግብፃውያኑንም በዘበዟቸው። 37  ከዚያም እስራኤላውያን ከራምሴስ ተነስተው ወደ ሱኮት ሄዱ፤ ልጆችን ሳይጨምር እግረኛ የሆኑት ወንዶች ወደ 600,000 ገደማ ነበሩ። 38  ከእነሱም ጋር እጅግ ብዙ ድብልቅ ሕዝብ እንዲሁም መንጎችና ከብቶች ይኸውም እጅግ ብዙ እንስሳ አብሮ ወጣ። 39  እነሱም ከግብፅ ይዘው በወጡት ሊጥ ቂጣ ጋገሩ። ይህም የሆነው ሊጡ ስላልቦካ ነበር፤ ምክንያቱም ከግብፅ እንዲወጡ የተደረገው በድንገት ስለነበር ለራሳቸው ስንቅ ማዘጋጀት አልቻሉም። 40  በግብፅ የኖሩት እስራኤላውያን የኖሩበት ዘመን 430 ዓመት ነበር። 41  አራት መቶ ሠላሳው ዓመት በተፈጸመበት በዚያው ዕለት መላው የይሖዋ ሠራዊት ከግብፅ ምድር ወጣ። 42  ይህ ሌሊት ይሖዋ ከግብፅ ምድር ስላወጣቸው የሚያከብሩት ሌሊት ነው። ይህ ሌሊት መላው የእስራኤል ሕዝብ በመጪዎቹ ትውልዶች ሁሉ ለይሖዋ የሚያከብረው ሌሊት ነው። 43  ከዚያም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ “የፋሲካው ደንብ ይህ ነው፦ ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው ከፋሲካው አይብላ። 44  ሆኖም አንድ ሰው በገንዘብ የተገዛ ባሪያ ካለው ግረዘው። መብላት የሚችለው ይህ ከሆነ ብቻ ነው። 45  ሰፋሪና ቅጥር ሠራተኛ ከዚያ ላይ መብላት የለባቸውም። 46  በአንድ ቤት ውስጥ መበላት አለበት። ከሥጋውም ላይ የትኛውንም ቢሆን ከቤት ውጭ ይዘህ አትውጣ፤ ከአጥንቱም አንዱንም አትስበሩ። 47  መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ይህን በዓል ማክበር አለበት። 48  በመካከላችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ካለና ለይሖዋ ፋሲካን ማክበር ከፈለገ የእሱ የሆኑት ወንዶች ሁሉ መገረዝ አለባቸው። ከዚያ በኋላ በዓሉን ለማክበር መቅረብ ይችላል፤ እሱም እንደ አገሩ ተወላጅ ይሆናል። ነገር ግን ማንኛውም ያልተገረዘ ሰው ከፋሲካው ምግብ መብላት አይችልም። 49  ለአገሩ ተወላጅም ሆነ በመካከላችሁ ለሚኖር የባዕድ አገር ሰው ሕጉ አንድ ዓይነት ነው።” 50  በመሆኑም እስራኤላውያን በሙሉ ይሖዋ ሙሴን እና አሮንን እንዳዘዛቸው አደረጉ። ልክ እንደተባሉት አደረጉ። 51  በዚሁ ቀን ይሖዋ እስራኤላውያንን ከነሠራዊታቸው ከግብፅ ምድር አወጣቸው።
[]
[]
[]
[]
12,468
13  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “ከእስራኤል ሕዝብ መካከል በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ። ከሰውም ሆነ ከእንስሳ መካከል በኩር የሆነው ወንድ ሁሉ የእኔ ነው።” 3  ከዚያም ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ “ከግብፅ ከባርነት ቤት የወጣችሁበትን ይህን ቀን አስቡ፤ ምክንያቱም ይሖዋ በኃያል ክንድ ከዚህ አውጥቷችኋል። በመሆኑም እርሾ የገባበት ምንም ነገር መበላት የለበትም። 4  ይኸው በዛሬው ዕለት በአቢብ ወር ከዚህ ለቃችሁ እየወጣችሁ ነው። 5  ይሖዋ ለአንተ ይሰጥህ ዘንድ ለቀድሞ አባቶችህ ወደማለላቸው ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር ይኸውም ወደ ከነአናውያን፣ ሂታውያን፣ አሞራውያን፣ ሂዋውያንና ኢያቡሳውያን ምድር ሲያስገባህ አንተ ደግሞ በዚህ ወር ይህን በዓል ማክበር አለብህ። 6  ለሰባት ቀን ቂጣ ትበላለህ፤ በሰባተኛውም ቀን ለይሖዋ በዓል ይከበራል። 7  በእነዚህ ሰባት ቀናት መበላት ያለበት እርሾ ያልገባበት ቂጣ ነው፤ በአንተ ዘንድ እርሾ የገባበት ምንም ነገር መገኘት የለበትም፤ በወሰንህም ውስጥ ሁሉ ምንም እርሾ መገኘት የለበትም። 8  በዚያ ቀን ለልጅህ ‘ይህን የማደርገው ከግብፅ በወጣሁበት ጊዜ ይሖዋ ባደረገልኝ ነገር የተነሳ ነው’ ብለህ ንገረው። 9  የይሖዋ ሕግ በአፍህ ላይ እንዲሆን ይህ በዓል በእጅህ ላይ እንደታሰረ ምልክትና በግንባርህ ላይ እንዳለ መታሰቢያ ሆኖ ያገለግልሃል፤ ምክንያቱም ይሖዋ በኃያል ክንድ ከግብፅ አውጥቶሃል። 10  አንተም ይህን ደንብ በየዓመቱ በተወሰነለት ጊዜ አክብረው። 11  “ይሖዋ ለአንተ ለመስጠት ለአንተም ሆነ ለቀድሞ አባቶችህ ወደማለላችሁ ወደ ከነአናውያን ምድር ሲያስገባህ 12  በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ እንዲሁም የአንተ ከሆነው እንስሳ መካከል በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ለይሖዋ መስጠት አለብህ። ወንዶቹ ሁሉ የይሖዋ ናቸው። 13  የእያንዳንዱን አህያ በኩር በበግ ዋጀው፤ የማትዋጀው ከሆነ ግን አንገቱን ስበረው። ከወንዶች ልጆችህ መካከል በኩር የሆነውን ሁሉ ልትዋጀው ይገባል። 14  “ምናልባት ወደፊት ልጅህ ‘ይህን የምታደርገው ለምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቅህ እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ በኃያል ክንድ ከግብፅ ከባርነት ቤት አወጣን። 15  ፈርዖን እኛን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆን ግትር አቋም በያዘ ጊዜ ይሖዋ ከሰው በኩር አንስቶ እስከ እንስሳ በኩር ድረስ በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ ገደለ። በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ለይሖዋ የምሠዋው እንዲሁም ከወንዶች ልጆቼ መካከል በኩር የሆነውን ሁሉ የምዋጀው ለዚህ ነው።’ 16  ይሖዋ በኃያል ክንድ ከግብፅ ስላወጣን ይህ በዓል በእጅህ ላይ እንዳለ ምልክትና በግንባርህ ላይ እንደታሰረ ነገር ሆኖ ያገልግል።” 17  ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ አምላክ ምንም እንኳ አቋራጭ ቢሆንም ወደ ፍልስጤማውያን ምድር በሚወስደው መንገድ አልመራቸውም። ምክንያቱም “ሕዝቡ ጦርነት ቢያጋጥመው ሐሳቡን ለውጦ ወደ ግብፅ ሊመለስ ይችላል” በማለት አስቦ ነበር። 18  በመሆኑም አምላክ ሕዝቡ በቀይ ባሕር አቅራቢያ ባለው ምድረ በዳ በኩል ዞሮ እንዲሄድ አደረገ። እስራኤላውያንም ከግብፅ ምድር የወጡት የጦርነት አሰላለፍ ተከትለው ነበር። 19  በተጨማሪም ሙሴ የዮሴፍን አፅም ይዞ ነበር፤ ምክንያቱም ዮሴፍ እስራኤላውያንን “አምላክ ፊቱን ወደ እናንተ መመለሱ አይቀርም፤ በመሆኑም አፅሜን ከዚህ ይዛችሁ ውጡ” በማለት በጥብቅ አስምሏቸው ነበር። 20  እነሱም ከሱኮት ተነስተው በምድረ በዳው ዳርቻ ላይ በሚገኘው በኤታም ሰፈሩ። 21  ይሖዋ የሚሄዱበትን መንገድ ይመራቸው ዘንድ ቀን ቀን በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ ከፊት ከፊታቸው ይሄድ ነበር፤ ሌሊት ሌሊት ደግሞ ብርሃን እንዲያገኙ ለማድረግ በእሳት ዓምድ ውስጥ ሆኖ ይመራቸው ነበር፤ በመሆኑም ቀንም ሆነ ሌሊት ይጓዙ ነበር። 22  ቀን ቀን የደመናው ዓምድ ሌሊት ሌሊት ደግሞ የእሳቱ ዓምድ ከሕዝቡ ፊት አይለይም ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,469
14  በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “ወደ ኋላ ተመልሰው በሚግዶልና በባሕሩ መካከል ባለው በበዓልጸፎን ትይዩ በሚገኘው በፊሃሂሮት ፊት ለፊት እንዲሰፍሩ ለእስራኤላውያን ንገራቸው። በበዓልጸፎን ፊት ለፊት በባሕሩ አጠገብ ስፈሩ። 3  ፈርዖንም ስለ እስራኤላውያን ‘ግራ ተጋብተው በምድሪቱ ላይ እየተንከራተቱ ነው። ምድረ በዳው ጋሬጣ ሆኖባቸዋል’ ማለቱ አይቀርም። 4  እኔም የፈርዖን ልብ እንዲደነድን እፈቅዳለሁ፤ እሱም ያሳድዳቸዋል፤ እኔም ፈርዖንንና ሠራዊቱን ድል በማድረግ ለራሴ ክብርን እጎናጸፋለሁ፤ ግብፃውያንም እኔ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ያውቃሉ።” እነሱም ልክ እንዲሁ አደረጉ። 5  በኋላም ለግብፁ ንጉሥ ሕዝቡ እንደኮበለለ ተነገረው። ፈርዖንና አገልጋዮቹም ስለ ሕዝቡ የነበራቸውን ሐሳብ ወዲያው በመቀየር “ምን ማድረጋችን ነው? እስራኤላውያን ባሪያ ሆነው እንዳያገለግሉን የለቀቅናቸው ምን ነክቶን ነው?” አሉ። 6  በመሆኑም ፈርዖን የጦር ሠረገሎቹ እንዲዘጋጁለት አደረገ፤ ሠራዊቱንም ከጎኑ አሰለፈ። 7  ከዚያም 600 የተመረጡ ሠረገሎችንና ሌሎች የግብፅ ሠረገሎችን ሁሉ ይዞ ተነሳ፤ በእያንዳንዱም ሠረገላ ላይ ተዋጊዎች ነበሩ። 8  በዚህ መንገድ ይሖዋ የግብፁ ንጉሥ የፈርዖን ልብ እንዲደነድን ፈቀደ፤ እስራኤላውያን ወጥተው በልበ ሙሉነት እየሄዱ ሳሉ ፈርዖን እነሱን ማሳደዱን ተያያዘው። 9  ግብፃውያኑ ተከታተሏቸው፤ እስራኤላውያን በበዓልጸፎን ፊት ለፊት በባሕሩ አጠገብ ባለው በፊሃሂሮት ሰፍረው ሳሉም የፈርዖን ሠረገሎች፣ ፈረሰኞቹና ሠራዊቱ በሙሉ ደረሱባቸው። 10  ፈርዖን ወደ እነሱ ሲቀርብ እስራኤላውያን ቀና ብለው ተመለከቱ፤ ግብፃውያኑ እነሱን እየተከታተሏቸው ነበር። እስራኤላውያንም ተሸበሩ፤ ወደ ይሖዋም ይጮኹ ጀመር። 11  እነሱም ሙሴን እንዲህ አሉት፦ “እዚህ ምድረ በዳ ውስጥ እንድንሞት ያመጣኸን በግብፅ የመቃብር ቦታ ጠፍቶ ነው? ከግብፅ መርተህ በማውጣት ምን ያደረግክልን ነገር አለ? 12  በግብፅ ሳለን ‘እባክህ ተወን፤ አርፈን ግብፃውያንን እናገልግል’ ብለንህ አልነበረም? እዚህ ምድረ በዳ ውስጥ ከመሞት ግብፃውያንን ብናገለግል ይሻለን ነበር።” 13  በዚህ ጊዜ ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “አትፍሩ። ጸንታችሁ ቁሙ፤ በዛሬው ዕለት ይሖዋ ለእናንተ ሲል የሚፈጽመውን የእሱን ማዳን እዩ። ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያን ዳግመኛ አታዩአቸውም፤ በጭራሽ አታዩአቸውም። 14  ይሖዋ ራሱ ስለ እናንተ ይዋጋል፤ ብቻ እናንተ ዝም በሉ።” 15  በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለምን ወደ እኔ ትጮኻለህ? እስራኤላውያን ድንኳናቸውን ነቅለው እንዲጓዙ ንገራቸው። 16  አንተም እስራኤላውያን በባሕሩ መሃል በደረቅ መሬት እንዲሻገሩ በትርህን አንሳና እጅህን በባሕሩ ላይ ሰንዝር፤ ባሕሩንም ክፈለው። 17  እኔ ደግሞ የግብፃውያን ልብ እንዲደነድን ስለምፈቅድ እስራኤላውያንን ተከትለው ይገባሉ፤ እኔም ፈርዖንን፣ ሠራዊቱን ሁሉ፣ የጦር ሠረገሎቹንና ፈረሰኞቹን ድል በማድረግ ለራሴ ክብርን እጎናጸፋለሁ። 18  ፈርዖንን፣ የጦር ሠረገሎቹንና ፈረሰኞቹን ድል በማድረግ ለራሴ ክብርን በምጎናጸፍበት ጊዜ ግብፃውያን እኔ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ያውቃሉ።” 19  ከዚያም ከእስራኤል ሕዝብ ፊት ፊት ይሄድ የነበረው የእውነተኛው አምላክ መልአክ ከዚያ ተነስቶ ወደኋላቸው ሄደ፤ ከፊታቸው የነበረውም የደመና ዓምድ ወደኋላቸው ሄዶ በስተ ጀርባቸው ቆመ። 20  በመሆኑም የደመናው ዓምድ በግብፃውያንና በእስራኤላውያን መካከል ሆነ። ዓምዱ በአንደኛው በኩል ጭልም ያለ ደመና ነበር። በሌላኛው በኩል ደግሞ ለሌሊቱ ብርሃን ይሰጥ ነበር። ስለሆነም ሌሊቱን ሙሉ አንደኛው ወገን ወደ ሌላኛው ወገን መቅረብ አልቻለም። 21  ሙሴም እጁን በባሕሩ ላይ ሰነዘረ፤ ይሖዋም ሌሊቱን ሙሉ ኃይለኛ የምሥራቅ ነፋስ በማምጣት ባሕሩ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደረገ፤ የባሕሩንም ወለል ወደ ደረቅ መሬት ለወጠው፤ ውኃውም ተከፈለ። 22  በመሆኑም እስራኤላውያን ውኃው በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ቆሞ በባሕሩ መሃል በደረቅ መሬት ተሻገሩ። 23  ግብፃውያኑም እነሱን ማሳደዳቸውን ተያያዙት፤ የፈርዖን ፈረሶች፣ የጦር ሠረገሎችና ፈረሰኞች ሁሉ ተከትለዋቸው ወደ ባሕሩ መሃል ገቡ። 24  በማለዳውም ክፍለ ሌሊት ይሖዋ በእሳትና በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ የግብፃውያንን ሠራዊት ተመለከተ፤ የግብፃውያንም ሠራዊት ግራ እንዲጋባ አደረገ። 25  ሠረገሎቻቸውን መንዳት አስቸጋሪ እንዲሆንባቸው የሠረገሎቻቸውን መንኮራኩሮች አወላለቀባቸው፤ ግብፃውያኑም “ይሖዋ እስራኤላውያንን በመደገፍ ግብፃውያንን እየተዋጋላቸው ስለሆነ ከእስራኤላውያን ፊት እንሽሽ” አሉ። 26  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን “ውኃው በግብፃውያን፣ በጦር ሠረገሎቻቸውና በፈረሰኞቻቸው ላይ ተመልሶ እንዲመጣባቸው እጅህን በባሕሩ ላይ ሰንዝር” አለው። 27  ሙሴም ወዲያውኑ እጁን በባሕሩ ላይ ሰነዘረ፤ ሊነጋጋ ሲልም ባሕሩ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ተመለሰ። ግብፃውያንም ውኃው እንዳይደርስባቸው ለመሸሽ ሲሞክሩ ይሖዋ ግብፃውያኑን ባሕሩ መሃል ጣላቸው። 28  ውኃውም ተመልሶ እስራኤላውያንን ተከትለው የገቡትን የጦር ሠረገሎችና ፈረሰኞች እንዲሁም የፈርዖንን ሠራዊት በሙሉ አለበሳቸው። ከእነሱም መካከል አንድም የተረፈ የለም። 29  እስራኤላውያን ግን ውኃው በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ቆሞ በባሕሩ መሃል በደረቅ መሬት ተጓዙ። 30  በዚህ መንገድ ይሖዋ በዚያ ቀን እስራኤላውያንን ከግብፃውያን እጅ አዳነ፤ እስራኤላውያንም የግብፃውያን ሬሳ በባሕሩ ዳርቻ ላይ ወድቆ ተመለከቱ። 31  በተጨማሪም እስራኤላውያን ይሖዋ ግብፃውያንን የመታበትን ኃያል ክንድ ተመለከቱ፤ ሕዝቡም ይሖዋን መፍራት ጀመረ፤ በይሖዋና በአገልጋዩ በሙሴም አመነ።
[]
[]
[]
[]
12,470
15  በዚያን ጊዜ ሙሴና እስራኤላውያን የሚከተለውን መዝሙር ለይሖዋ ዘመሩ፦ “በክብር እጅግ ከፍ ከፍ ስላለ ለይሖዋ እዘምራለሁ። ፈረሱንና ፈረሰኛውን ባሕር ውስጥ ጣላቸው። 2  አዳኜ ስለሆነልኝ ያህ ብርታቴና ኃይሌ ነው። እሱ አምላኬ ነው፤ አወድሰዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው፤ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ። 3  ይሖዋ ኃያል ተዋጊ ነው። ስሙ ይሖዋ ነው። 4  የፈርዖንን ሠረገሎችና ሠራዊቱን ባሕር ውስጥ ወረወራቸው፣ ምርጥ የሆኑ ተዋጊዎቹም ቀይ ባሕር ውስጥ ሰመጡ። 5  ማዕበሉም ከደናቸው፤ እነሱም እንደ ድንጋይ ወደ ጥልቁ ሰመጡ። 6  ይሖዋ ሆይ፣ ቀኝ እጅህ እጅግ ኃያል ነው፤ ይሖዋ ሆይ፣ ቀኝ እጅህ ጠላትን ያደቃል። 7  እጅግ ታላቅ በሆነው ግርማህ በአንተ ላይ የሚነሱትን ሁሉ ቁልቁል ታሽቀነጥራቸዋለህ፤ የሚነደውን ቁጣህን ትልካለህ፤ እነሱንም እንደ ገለባ ይበላቸዋል። 8  በአፍንጫህ እስትንፋስ ውኃዎች ተቆለሉ፤ ወራጁንም ውኃ ገድበው ቀጥ ብለው ቆሙ፤ ማዕበሉም በባሕሩ ልብ ውስጥ ረጋ። 9  ጠላትም ‘አሳድዳቸዋለሁ! አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ! እስክጠግብም ድረስ ምርኮን እከፋፈላለሁ! ሰይፌን እመዛለሁ! እጄም ታንበረክካቸዋለች!’ አለ። 10  አንተም እስትንፋስህን እፍ አልክ፤ ባሕሩም ከደናቸው፤ እነሱም ኃያል በሆኑ ውኃዎች ውስጥ እንደ አረር ሰመጡ። 11  ይሖዋ ሆይ፣ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስናው ኃያል መሆኑን የሚያሳይ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? የምትፈራና የምትወደስ፣ ድንቅ ነገሮችን የምታደርግ አንተ ነህ። 12  ቀኝ እጅህን ዘረጋህ፤ ምድርም ዋጠቻቸው። 13  የታደግካቸውን ሕዝቦች በታማኝ ፍቅርህ መራሃቸው፤ በብርታትህም ወደ ቅዱስ መኖሪያህ ትመራቸዋለህ። 14  ሕዝቦችም ይሰማሉ፤ ይንቀጠቀጣሉ፤ የፍልስጤም ነዋሪዎችም ምጥ ይይዛቸዋል። 15  በዚያን ጊዜ የኤዶም አለቆች ይሸበራሉ፤ የሞዓብ ኃያላን ገዢዎች ብርክ ይይዛቸዋል። የከነአን ነዋሪዎችም ሁሉ ልባቸው ይከዳቸዋል። 16  ፍርሃትና ድንጋጤ ይወድቅባቸዋል። ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝቦችህ አልፈው እስኪሄዱ ድረስ፣ አንተ የፈጠርካቸው ሕዝቦች አልፈው እስኪሄዱ ድረስ፣ ከክንድህ ታላቅነት የተነሳ እንደ ድንጋይ ደርቀው ይቀራሉ። 17  አምጥተህ በርስትህ ተራራ ላይ ትተክላቸዋለህ፤ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ራስህ ልትኖርበት ባዘጋጀኸው ጸንቶ የተመሠረተ ቦታ፣ ይሖዋ ሆይ፣ እጆችህ በመሠረቱት መቅደስ ትተክላቸዋለህ። 18  ይሖዋ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይገዛል። 19  የፈርዖን ፈረሶች፣ የጦር ሠረገሎቹና ፈረሰኞቹ ወደ ባሕሩ በገቡ ጊዜ፣ ይሖዋ የባሕሩን ውኃ ላያቸው ላይ መለሰባቸው፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን በባሕሩ መሃል በደረቅ መሬት ተሻገረ።” 20  ከዚያም የአሮን እህት ነቢዪቱ ሚርያም አታሞ አነሳች፤ ሴቶቹም ሁሉ አታሞ እየመቱና እየጨፈሩ ተከተሏት። 21  ሚርያምም ከወንዶቹ ጋር እየተቀባበለች እንዲህ ስትል ዘመረች፦ “በክብር እጅግ ከፍ ከፍ ስላለ ለይሖዋ ዘምሩ። ፈረሱንና ፈረሰኛውን ባሕር ውስጥ ጣላቸው።” 22  ከዚያም ሙሴ እስራኤላውያንን ከቀይ ባሕር እየመራ ይዟቸው ወጣ፤ እነሱም ወደ ሹር ምድረ በዳ ሄዱ፤ በምድረ በዳውም ለሦስት ቀን ያህል ተጓዙ፤ ሆኖም ውኃ አላገኙም ነበር። 23  በኋላም ወደ ማራ መጡ፤ ያም ሆኖ በማራ ያለው ውኃ መራራ ስለነበር ሊጠጡት አልቻሉም። የቦታውን ስም ማራ ያለውም በዚህ የተነሳ ነው። 24  በመሆኑም ሕዝቡ “እንግዲህ ምን ልንጠጣ ነው?” እያለ በሙሴ ላይ ማጉረምረም ጀመረ። 25  እሱም ወደ ይሖዋ ጮኸ፤ ይሖዋም ወደ አንዲት ዛፍ መራው። ሙሴም ዛፏን ውኃው ውስጥ ሲጥላት ውኃው ጣፋጭ ሆነ። እሱም በዚያ የሚመሩበት ሥርዓትና ለፍርድ መሠረት የሚሆን መመሪያ አወጣላቸው፤ በዚያም ፈተናቸው። 26  እንዲህም አላቸው፦ “የአምላካችሁን የይሖዋን ቃል በጥንቃቄ ብታዳምጡ፣ በእሱ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ብታደርጉ፣ ለትእዛዛቱ ጆሯችሁን ብትሰጡና ሥርዓቶቹን በሙሉ ብታከብሩ በግብፃውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች አንዱንም በእናንተ ላይ አላመጣም፤ ምክንያቱም እኔ ይሖዋ እፈውሳችኋለሁ።” 27  ከዚያም 12 የውኃ ምንጮችና 70 የዘንባባ ዛፎች ወዳሉበት ወደ ኤሊም መጡ። በዚያም በውኃው አጠገብ ሰፈሩ።
[]
[]
[]
[]
12,471
16  ከኤሊም ከተነሱ በኋላም መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ከግብፅ ምድር በወጣ በሁለተኛው ወር በ15ኛው ቀን በኤሊምና በሲና መካከል ወደሚገኘው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጣ። 2  ከዚያም መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ በምድረ በዳ ሳለ በሙሴና በአሮን ላይ ማጉረምረም ጀመረ። 3  እስራኤላውያንም እንዲህ ይሏቸው ነበር፦ “በግብፅ ምድር በሥጋው ድስት አጠገብ ተቀምጠን ሳለንና እስክንጠግብ ድረስ ዳቦ ስንበላ በነበረበት ጊዜ ምነው በይሖዋ እጅ ሞተን ባረፍነው ኖሮ። እናንተ ግን ይህን ጉባኤ በሙሉ በረሃብ ልትጨርሱት ወደዚህ ምድረ በዳ አመጣችሁን።” 4  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ እኔ ከሰማይ ምግብ አዘንብላችኋለሁ፤ ሕዝቡም ይውጣ፤ እያንዳንዱም ሰው ወጥቶ የሚበቃውን ያህል በየዕለቱ ይሰብስብ፤ በዚህም ሕጌን አክብረው ይመላለሱ እንደሆነና እንዳልሆነ እፈትናቸዋለሁ። 5  በስድስተኛው ቀን የሰበሰቡትን በሚያዘጋጁበት ጊዜ ግን በሌሎቹ ቀናት ከሚሰበስቡት እጥፍ ይሁን።” 6  በመሆኑም ሙሴና አሮን እስራኤላውያንን በሙሉ እንዲህ አሏቸው፦ “ከግብፅ ምድር ያወጣችሁ ይሖዋ መሆኑን በዚህ ምሽት በእርግጥ ታውቃላችሁ። 7  ጠዋት ላይ የይሖዋን ክብር ታያላችሁ፤ ምክንያቱም ይሖዋ በእሱ ላይ ማጉረምረማችሁን ሰምቷል። በእኛ ላይ የምታጉረመርሙት ለመሆኑ እኛ ማን ነን?” 8  ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ምሽት ላይ፣ የምትበሉት ሥጋ ጠዋት ላይ ደግሞ የምትፈልጉትን ያህል ዳቦ ሲሰጣችሁ ይሖዋ በእሱ ላይ ያጉረመረማችሁትን ማጉረምረም እንደሰማ ታያላችሁ። ታዲያ እኛ ማን ነን? ያጉረመረማችሁት በእኛ ላይ ሳይሆን በይሖዋ ላይ ነው።” 9  ሙሴም አሮንን “ለመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ‘ማጉረምረማችሁን ስለሰማ ኑ በይሖዋ ፊት ቅረቡ’ በላቸው” አለው። 10  አሮን ለመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ በተናገረ ጊዜ ሕዝቡ ወደ ምድረ በዳው ዞሮ ቆመ፤ በዚህ ጊዜ የይሖዋ ክብር በደመናው ውስጥ ተገለጠ። 11  በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 12  “የእስራኤላውያንን ማጉረምረም ሰምቻለሁ። እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘አመሻሹ ላይ ሥጋ ትበላላችሁ፤ ጠዋት ላይ ደግሞ ዳቦ ትጠግባላችሁ፤ እኔም አምላካችሁ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ታውቃላችሁ።’” 13  በዚህም መሠረት ምሽት ላይ ድርጭቶች መጥተው ሰፈሩን አለበሱት፤ ጠዋት ላይም በሰፈሩ ውስጥ ሁሉ ጤዛ ወርዶ ነበር። 14  በኋላም ጤዛው ሲተን በምድረ በዳው ላይ እንደ አመዳይ ደቃቅ የሆነ ቅርፊት የሚመስል ስስ ነገር መሬቱ ላይ ታየ። 15  እስራኤላውያንም ባዩት ጊዜ ምን እንደሆነ ስላላወቁ እርስ በርሳቸው “ይህ ነገር ምንድን ነው?” ይባባሉ ጀመር። ስለሆነም ሙሴ እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ እንድትበሉት የሰጣችሁ ምግብ ነው። 16  ይሖዋ እንዲህ ሲል አዟል፦ ‘እያንዳንዱ ሰው የሚበላውን ያህል ይሰብስብ። እያንዳንዳችሁ በድንኳናችሁ ውስጥ ባሉት ሰዎች ቁጥር ልክ ለእያንዳንዱ ሰው አንድ ኦሜር ሰፍራችሁ ውሰዱ።’” 17  እስራኤላውያንም እንደተባሉት አደረጉ፤ ይሰበስቡም ጀመር፤ አንዳንዶቹ ብዙ ሌሎቹ ደግሞ ትንሽ ሰበሰቡ። 18  የሰበሰቡትን በኦሜር ሲሰፍሩት ብዙ የሰበሰበው ምንም ትርፍ አላገኘም፤ ጥቂት የሰበሰበውም ምንም አልጎደለበትም። እያንዳንዳቸው የሰበሰቡት የሚበሉትን ያህል ነበር። 19  ከዚያም ሙሴ “ማንም ሰው እስከ ጠዋት ድረስ ምንም ማስተረፍ የለበትም” አላቸው። 20  እነሱ ግን ሙሴን አልሰሙትም። አንዳንዶቹ ከሰበሰቡት ውስጥ የተወሰነውን አሳደሩት፤ ሆኖም ተልቶ መሽተት ጀመረ፤ በመሆኑም ሙሴ በእነሱ ላይ እጅግ ተቆጣ። 21  በየማለዳው እያንዳንዱ ሰው የሚበላውን ያህል ይሰበስብ ነበር። ፀሐዩ እየበረታ በሚሄድበት ጊዜም ይቀልጥ ነበር። 22  በስድስተኛውም ቀን ሁለት እጥፍ ምግብ ይኸውም ለአንድ ሰው ሁለት ኦሜር ሰበሰቡ። በመሆኑም የማኅበረሰቡ አለቆች በሙሉ መጥተው ሁኔታውን ለሙሴ ነገሩት። 23  በዚህ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ይሄማ ይሖዋ የተናገረው ነገር ነው። ነገ ሙሉ በሙሉ የእረፍት ቀን ይኸውም ለይሖዋ ቅዱስ ሰንበት ይሆናል። የምትጋግሩትን ጋግሩ፤ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፤ የተረፈውን ሁሉ አስቀምጡ፤ እስከ ጠዋትም ድረስ አቆዩት።” 24  እነሱም ልክ ሙሴ ባዘዛቸው መሠረት እስከ ጠዋት ድረስ አቆዩት፤ ምግቡም አልሸተተም ወይም አልተላም። 25  ከዚያም ሙሴ እንዲህ አላቸው፦ “ዛሬ ይህን ብሉ፤ ምክንያቱም ዛሬ የይሖዋ ሰንበት ነው። ዛሬ ሜዳው ላይ አታገኙትም። 26  ስድስት ቀን ትሰበስባላችሁ፤ በሰባተኛው ቀን ይኸውም በሰንበት ቀን ግን ምንም አይገኝም።” 27  ይሁንና ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶቹ በሰባተኛው ቀን ሊሰበስቡ ወጡ፤ ሆኖም ምንም አላገኙም። 28  በመሆኑም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እናንተ ሰዎች ትእዛዛቴንና ሕጎቼን ለማክበር እንቢተኛ የምትሆኑት እስከ መቼ ነው? 29  ይሖዋ ሰንበትን እንደሰጣችሁ ልብ በሉ። በስድስተኛው ቀን ለሁለት ቀን የሚሆን ምግብ የሰጣችሁም ለዚህ ነው። እያንዳንዱ ሰው ባለበት ስፍራ መቆየት አለበት፤ በሰባተኛውም ቀን ማንም ሰው ካለበት ቦታ መውጣት የለበትም።” 30  ሕዝቡም በሰባተኛው ቀን ሰንበትን አከበረ። 31  የእስራኤልም ቤት ምግቡን “መና” አሉት። እሱም እንደ ድንብላል ዘር ነጭ ሲሆን ጣዕሙም ማር እንደተቀባ ቂጣ ነበር። 32  ከዚያም ሙሴ እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ እንዲህ ሲል አዟል፦ ‘ከግብፅ ምድር ባወጣኋችሁ ጊዜ በምድረ በዳ እንድትበሉት የሰጠኋችሁን ምግብ እንዲያዩ ከእሱ አንድ ኦሜር ሰፍራችሁ ለሚመጡት ትውልዶቻችሁ ሁሉ አስቀምጡ።’” 33  በመሆኑም ሙሴ አሮንን “ማሰሮ ወስደህ አንድ ኦሜር መና ጨምርበት፤ ለሚመጡት ትውልዶቻችሁ ሁሉ ተጠብቆ እንዲቆይ በይሖዋ ፊት አስቀምጠው” አለው። 34  አሮንም ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ተጠብቆ እንዲቆይ መናውን በምሥክሩ ፊት አስቀመጠው። 35  እስራኤላውያንም ወደሚኖሩበት ምድር እስከሚመጡ ድረስ ለ40 ዓመት መናውን በሉ። ወደ ከነአን ምድር ድንበር እስከሚደርሱ ድረስ መናውን በሉ። 36  አንድ ኦሜር፣ የኢፍ መስፈሪያ አንድ አሥረኛ ነው።
[]
[]
[]
[]
12,472
17  መላው የእስራኤል ማኅበረሰብም ከሲን ምድረ በዳ ተነስቶ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ከቦታ ወደ ቦታ ሲጓዝ ከቆየ በኋላ በረፊዲም ሰፈረ። ሆኖም ሕዝቡ የሚጠጣው ውኃ አልነበረም። 2  በመሆኑም ሕዝቡ “የሚጠጣ ውኃ ስጠን” በማለት ከሙሴ ጋር ይጣላ ጀመር። ሙሴ ግን “ከእኔ ጋር የምትጣሉት ለምንድን ነው? ይሖዋንስ ለምን ትፈታተኑታላችሁ?” አላቸው። 3  ሆኖም ሕዝቡ ውኃ በጣም ተጠምቶ ስለነበር “እኛና ልጆቻችን እንዲሁም ከብቶቻችን በውኃ ጥም እንድናልቅ ከግብፅ ያወጣኸን ለምንድን ነው?” በማለት በሙሴ ላይ ማጉረምረሙን ቀጠለ። 4  በመጨረሻም ሙሴ “ይህን ሕዝብ ምን ባደርገው ይሻለኛል? ትንሽ ቆይተው እኮ ይወግሩኛል!” በማለት ወደ ይሖዋ ጮኸ። 5  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል የተወሰኑትን ምረጥና የአባይን ወንዝ የመታህበትን በትር ይዘህ ከሕዝቡ ፊት ፊት ሂድ። በትሩን በእጅህ ይዘህ ሂድ። 6  እኔም በዚያ በኮሬብ በሚገኘው ዓለት ላይ ፊትህ እቆማለሁ። አንተም ዓለቱን ትመታዋለህ፤ ውኃም ከውስጡ ይፈልቃል፤ ሕዝቡም ይጠጣሉ።” ሙሴም የእስራኤል ሽማግሌዎች እያዩ እንደተባለው አደረገ። 7  እሱም እስራኤላውያን ስለተጣሉትና “ለመሆኑ ይሖዋ በመካከላችን አለ ወይስ የለም?” በማለት ይሖዋን ስለተፈታተኑት የቦታውን ስም ማሳህ እና መሪባ አለው። 8  ከዚያም አማሌቃውያን መጥተው በረፊዲም እስራኤላውያንን ወጉ። 9  በዚህ ጊዜ ሙሴ ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ሰዎች ምረጥልንና ከአማሌቃውያን ጋር ለመዋጋት ውጣ። እኔም በነገው ዕለት የእውነተኛውን አምላክ በትር በእጄ ይዤ በኮረብታው አናት ላይ እቆማለሁ።” 10  ከዚያም ኢያሱ ልክ ሙሴ እንዳለው አደረገ፤ ከአማሌቃውያንም ጋር ተዋጋ። ሙሴ፣ አሮንና ሁርም ወደ ኮረብታው አናት ወጡ። 11  ሙሴ እጆቹን ወደ ላይ አንስቶ በሚቆይበት ጊዜ ሁሉ እስራኤላውያን ያይሉ፣ እጆቹን በሚያወርድበት ጊዜ ግን አማሌቃውያን ያይሉ ነበር። 12  የሙሴ እጆች በዛሉ ጊዜ ድንጋይ ወስደው ከሥሩ አስቀመጡለት፤ እሱም በድንጋዩ ላይ ተቀመጠ። ከዚያም አሮንና ሁር አንዱ በአንደኛው በኩል፣ ሌላው ደግሞ በሌላኛው በኩል ሆነው እጆቹን ደገፉለት፤ በመሆኑም ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ እጆቹ ባሉበት ጸኑ። 13  በዚህ መንገድ ኢያሱ አማሌቅንና ሕዝቦቹን በሰይፍ ድል አደረገ። 14  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “መታሰቢያ እንዲሆን ይህን በመጽሐፍ ጻፈው፤ ለኢያሱም ‘የአማሌቅን መታሰቢያ ከሰማይ በታች ሙሉ በሙሉ ጠራርጌ አጠፋለሁ’ በማለት ይህን ደግመህ ንገረው።” 15  ከዚያም ሙሴ መሠዊያ ሠርቶ ስሙን ‘ይሖዋ ንሲ’ ብሎ ሰየመው፤ 16  እንዲህም ያለው “እጁ በያህ ዙፋን ላይ ስለተነሳ ይሖዋ ከአማሌቅ ጋር ከትውልድ እስከ ትውልድ ይዋጋል” በማለት ነው።
[]
[]
[]
[]
12,473
18  የምድያም ካህን የሆነው የሙሴ አማት ዮቶር አምላክ ለሙሴና ለሕዝቡ ለእስራኤል ያደረገውን ነገር ሁሉ ይኸውም ይሖዋ እስራኤልን ከግብፅ እንዴት እንዳወጣ ሰማ። 2  የሙሴ አማት ዮቶር የሙሴ ሚስት ሲፓራ ወደ እሱ ተመልሳ በተላከች ጊዜ እሷንና 3  ሁለቱን ወንዶች ልጆቿን ይዞ ተነሳ። ሙሴ “በባዕድ አገር የምኖር የባዕድ አገር ሰው ሆንኩ” ብሎ ስለነበር የአንደኛው ልጅ ስም ጌርሳም ነበር፤ 4  እንዲሁም ሙሴ “ከፈርዖን ሰይፍ ያዳነኝ የአባቴ አምላክ ረዳቴ ነው” ብሎ ስለነበር የሌላኛው ልጁ ስም ኤሊዔዘር ነበር። 5  በመሆኑም የሙሴ አማት ዮቶር ከሙሴ ሚስትና ወንዶች ልጆች ጋር በመሆን የእውነተኛው አምላክ ተራራ በሚገኝበት ምድረ በዳ ሰፍሮ ወደነበረው ወደ ሙሴ መጣ። 6  ከዚያም ዮቶር “እኔ አማትህ ዮቶር፣ ከሚስትህና ከሁለቱ ወንዶች ልጆቿ ጋር ወደ አንተ እየመጣሁ ነው” የሚል መልእክት ወደ ሙሴ ላከ። 7  ሙሴም ወዲያውኑ አማቱን ሊቀበለው ወጣ፤ እሱም ሰገደለት፤ ከዚያም ሳመው። እርስ በርሳቸውም ስለ ደህንነታቸው ተጠያየቁ፤ በኋላም ወደ ድንኳኑ ገቡ። 8  ሙሴም ይሖዋ ለእስራኤል ሲል በፈርዖንና በግብፅ ላይ ያደረገውን ሁሉ እንዲሁም በጉዟቸው ያጋጠሟቸውን አስቸጋሪ ሁኔታዎችና ይሖዋ እንዴት እንዳዳናቸው ለአማቱ ተረከለት። 9  ዮቶርም ይሖዋ እስራኤልን ከግብፅ እጅ በማዳን ለእነሱ ሲል ባደረገላቸው መልካም ነገሮች ሁሉ ተደሰተ። 10  ከዚያም ዮቶር እንዲህ አለ፦ “ከግብፅና ከፈርዖን እጅ ያዳናችሁ እንዲሁም ሕዝቡን ከግብፅ እጅ ነፃ ያወጣው ይሖዋ ይወደስ። 11  ይሖዋ በሕዝቡ ላይ የእብሪት ድርጊት በፈጸሙ ሰዎች ላይ እንዲህ ያለ እርምጃ በመውሰዱ ከሌሎች አማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ አሁን አውቄአለሁ።” 12  ከዚያም የሙሴ አማት ዮቶር የሚቃጠል መባና መሥዋዕቶችን ለአምላክ አመጣ፤ አሮንና የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ከሙሴ አማት ጋር በእውነተኛው አምላክ ፊት ምግብ ለመብላት መጡ። 13  በማግስቱም ሙሴ እንደተለመደው ሕዝቡን በዳኝነት ለማገልገል ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ከጠዋት አንስቶ እስከ ማታ ድረስ እየመጣ በሙሴ ፊት ይቆም ነበር። 14  የሙሴ አማትም ሙሴ ለሕዝቡ የሚያደርገውን ሁሉ ባየ ጊዜ “ይህ ለሕዝቡ እያደረግክ ያለኸው ነገር ምንድን ነው? አንተ ብቻህን ለመዳኘት የምትቀመጠውና ይህ ሁሉ ሕዝብ ከጠዋት እስከ ማታ ድረስ ፊትህ የሚቆመው ለምንድን ነው?” አለው። 15  ሙሴም አማቱን እንዲህ አለው፦ “ምክንያቱም ሕዝቡ አምላክን ለመጠየቅ ያለማቋረጥ ወደ እኔ ይመጣል። 16  አንድ ጉዳይ በሚነሳበት ጊዜ ጉዳዩ ወደ እኔ ይቀርባል፤ እኔ ደግሞ ባለጉዳዮቹን እዳኛለሁ፤ እንዲሁም የእውነተኛውን አምላክ ውሳኔዎችና ሕጎች አሳውቃለሁ።” 17  በዚህ ጊዜ የሙሴ አማት እንዲህ አለው፦ “እያደረግክ ያለኸው ነገር መልካም አይደለም። 18  ይህ ሥራ ለአንተ ከባድ ሸክም ስለሚሆን አንተም ሆንክ ከአንተ ጋር ያለው ይህ ሕዝብ መድከማችሁ አይቀርም፤ ደግሞም ብቻህን ልትሸከመው አትችልም። 19  እንግዲህ አሁን የምልህን ስማ። አንድ ነገር ልምከርህ፤ አምላክም ከአንተ ጋር ይሆናል። አንተ በእውነተኛው አምላክ ፊት የሕዝቡ ተወካይ ሆነህ ታገለግላለህ፤ ጉዳያቸውንም ወደ እውነተኛው አምላክ ታቀርባለህ። 20  ሥርዓቶቹና ሕጎቹ ምን እንደሆኑ በመንገር ማሳሰቢያ ትሰጣቸዋለህ፤ እንዲሁም የሚሄዱበትን መንገድና የሚያከናውኑትን ነገር ታሳውቃቸዋለህ። 21  ሆኖም ከመላው ሕዝብ መካከል አምላክን የሚፈሩትንና ብቃት ያላቸውን እንዲሁም አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የማይፈልጉትንና እምነት የሚጣልባቸውን ሰዎች ምረጥ፤ እነዚህንም የሺህ አለቆች፣ የመቶ አለቆች፣ የሃምሳ አለቆችና የአሥር አለቆች አድርገህ በሕዝቡ ላይ ሹማቸው። 22  እነሱም የተለያዩ ጉዳዮች በሚነሱበት ጊዜ ሕዝቡን ይዳኙ፤ ከበድ ያሉ ጉዳዮች ሲያጋጥሟቸው ወደ አንተ ያምጡ፤ ቀለል ያሉ ጉዳዮችን ግን ራሳቸው ይዳኙ። ሸክሙን እንዲጋሩህ በማድረግ በአንተ ላይ ያለውን ጫና አቅልል። 23  ይህን ነገር ከአምላክ እንደተቀበልከው ትእዛዝ አድርገህ ብትፈጽም ውጥረቱ ይቀንስልሃል፤ እያንዳንዱም ሰው ተደስቶ ወደ ቤቱ ይሄዳል።” 24  ሙሴም ወዲያውኑ አማቱን በመስማት ያለውን ሁሉ አደረገ። 25  ሙሴም ከመላው እስራኤል ብቃት ያላቸውን ወንዶች መርጦ የሺህ አለቆች፣ የመቶ አለቆች፣ የሃምሳ አለቆችና የአሥር አለቆች አድርጎ በሕዝቡ ላይ ሾማቸው። 26  በመሆኑም እነዚህ ሰዎች የተለያዩ ጉዳዮች በሚነሱበት ጊዜ ሕዝቡን ይዳኙ ነበር። ከበድ ያለ ጉዳይ ሲያጋጥማቸው ወደ ሙሴ ያመጡ የነበረ ሲሆን ቀለል ያሉ ጉዳዮችን ግን ራሳቸው ይዳኙ ነበር። 27  ከዚያም ሙሴ አማቱን ሸኘው፤ እሱም ወደ አገሩ ሄደ።
[]
[]
[]
[]
12,474
19  እስራኤላውያን ከግብፅ በወጡ በሦስተኛው ወር በዚያው ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ። 2  ከረፊዲም ተነስተው ወደ ሲና ምድረ በዳ በመምጣት በምድረ በዳው ሰፈሩ። እስራኤላውያን በዚያ ከተራራው ፊት ለፊት ሰፈሩ። 3  ከዚያም ሙሴ ወደ እውነተኛው አምላክ ወጣ፤ ይሖዋም ከተራራው ጠርቶት እንዲህ አለው፦ “ለያዕቆብ ቤት የምትለው፣ ለእስራኤላውያንም የምትነግረው ይህ ነው፦ 4  ‘እናንተን በንስር ክንፎች ተሸክሜ ወደ እኔ ለማምጣት ስል በግብፃውያን ላይ ያደረግኩትን ሁሉ እናንተው ራሳችሁ አይታችኋል። 5  አሁንም ቃሌን በጥብቅ ብትታዘዙና ቃል ኪዳኔን ብትጠብቁ መላው ምድር የእኔ ስለሆነ እናንተ ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ የተመረጣችሁ ልዩ ንብረቶቼ ትሆናላችሁ። 6  እናንተ ለእኔ የካህናት መንግሥትና ቅዱስ ብሔር ትሆናላችሁ።’ ለእስራኤላውያን የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው።” 7  በመሆኑም ሙሴ ሄዶ የሕዝቡን ሽማግሌዎች ጠራ፤ ይሖዋ ያዘዘውንም ይህን ቃል ነገራቸው። 8  ከዚያ በኋላ ሕዝቡ ሁሉ በአንድ ድምፅ “ይሖዋ የተናገረውን ሁሉ ለመፈጸም ፈቃደኞች ነን” ብለው መለሱ። ሙሴም ወዲያውኑ የሕዝቡን ምላሽ ይዞ ወደ ይሖዋ ሄደ። 9  ይሖዋም ሙሴን “ሕዝቡ ከአንተ ጋር ስነጋገር እንዲሰማና ምንጊዜም በአንተ ላይ እምነት እንዲጥል በጥቁር ደመና ወደ አንተ እመጣለሁ” አለው። ከዚያም ሙሴ የሕዝቡን ቃል ለይሖዋ ተናገረ። 10  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ሕዝቡ ሄደህ ዛሬና ነገ ቀድሳቸው፤ እነሱም ልብሳቸውን ይጠቡ። 11  ለሦስተኛውም ቀን ይዘጋጁ፤ ምክንያቱም በሦስተኛው ቀን ይሖዋ ሕዝቡ ሁሉ እያዩ በሲና ተራራ ላይ ይወርዳል። 12  በተራራው ዙሪያ ለሕዝቡ ወሰን አብጅ፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ወደ ተራራው እንዳትወጡ፣ ድንበሩንም እንኳ እንዳትነኩ ተጠንቀቁ። ተራራውን የሚነካ ማንኛውም ሰው ይገደላል። 13  ይህን ሰው ማንም እንዳይነካው፤ ከዚህ ይልቅ በድንጋይ ይወገር ወይም ደግሞ ይወጋ። እንስሳም ሆነ ሰው በሕይወት እንዲኖር አይተውም።’ ሆኖም የቀንደ መለከቱ ድምፅ በሚሰማበት ጊዜ ወደ ተራራው ሊወጡ ይችላሉ።” 14  ከዚያም ሙሴ ከተራራው ወርዶ ወደ ሕዝቡ ሄደ፤ ሕዝቡንም ይቀድስ ጀመር፤ እነሱም ልብሳቸውን አጠቡ። 15  ሕዝቡንም “ለሦስተኛው ቀን ተዘጋጁ። የፆታ ግንኙነት ከመፈጸምም ተቆጠቡ” አላቸው። 16  በሦስተኛውም ቀን ጠዋት ነጎድጓድ መሰማትና መብረቅ መታየት ጀመረ፤ በተራራውም ላይ ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበር፤ ከፍተኛ የቀንደ መለከት ድምፅም ተሰማ፤ በሰፈሩም ውስጥ ያለው ሕዝብ በሙሉ በፍርሃት ተንቀጠቀጠ። 17  በዚህ ጊዜ ሙሴ ከእውነተኛው አምላክ ጋር እንዲገናኙ ሕዝቡን ከሰፈሩ ይዞ ወጣ፤ እነሱም በተራራው ግርጌ ቆሙ። 18  የሲና ተራራ ይሖዋ በእሳት ስለወረደበት ዙሪያውን ጨሰ፤ ጭሱም እንደ እቶን ጭስ እየተትጎለጎለ ይወጣ ነበር፤ ተራራውም ሁሉ በኃይል ተናወጠ። 19  የቀንደ መለከቱም ድምፅ ይበልጥ እየጨመረ ሲመጣ ሙሴ ተናገረ፤ የእውነተኛውም አምላክ ድምፅ መለሰለት። 20  በመሆኑም ይሖዋ በሲና ተራራ አናት ላይ ወረደ። ከዚያም ይሖዋ ሙሴን ወደ ተራራው አናት ጠራው፤ ሙሴም ወጣ። 21  በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ሂድ ውረድ፤ ሕዝቡ ይሖዋን ለማየት ሲሉ አልፈው ለመምጣት እንዳይሞክሩ አስጠንቅቃቸው፤ ካልሆነ ግን ብዙዎቹ ለጥፋት ይዳረጋሉ። 22  ዘወትር ወደ ይሖዋ የሚቀርቡት ካህናትም ይሖዋ እንዳይቀስፋቸው ራሳቸውን ይቀድሱ።” 23  ከዚያም ሙሴ ይሖዋን እንዲህ አለው፦ “አንተ ‘በተራራው ዙሪያ ወሰን አድርግ፤ እሱንም ቀድሰው’ በማለት ስላስጠነቀቅከን ሕዝቡ ወደ ሲና ተራራ መቅረብ አይችልም።” 24  ሆኖም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “ሂድ፣ ውረድና ከአሮን ጋር ተመልሰህ ወደዚህ ውጣ፤ ነገር ግን ካህናቱም ሆኑ ሕዝቡ አልፈው ወደ ይሖዋ ለመምጣት እንዳይሞክሩና እንዳይቀስፋቸው ከልክላቸው።” 25  ስለሆነም ሙሴ ወደ ሕዝቡ ወርዶ ነገራቸው።
[]
[]
[]
[]
12,475
2  በዚያን ጊዜ ከሌዊ ነገድ የሆነ አንድ ሰው የሌዊን ልጅ አገባ። 2  ሴቲቱም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች። ልጁም በጣም የሚያምር መሆኑን ስታይ ለሦስት ወር ደብቃ አቆየችው። 3  ከዚያ በላይ ደብቃ ልታቆየው እንደማትችል ስታውቅ ግን የደንገል ቅርጫት ወስዳ ቅርጫቱን በቅጥራንና በዝፍት ለቀለቀችው፤ ከዚያም ልጁን በቅርጫቱ ውስጥ አድርጋ በአባይ ወንዝ ዳር በሚገኘው ቄጠማ መሃል አስቀመጠችው። 4  እህቱ ግን የሕፃኑ መጨረሻ ምን እንደሚሆን ለማወቅ ራቅ ብላ ቆማ ሁኔታውን ትከታተል ነበር። 5  በዚህ ጊዜ የፈርዖን ሴት ልጅ ገላዋን ልትታጠብ ወደ አባይ ወረደች፤ ደንገጡሮቿም በአባይ ወንዝ ዳር ዳር ይሄዱ ነበር። እሷም በቄጠማው መሃል ቅርጫቱን አየች። ወዲያውኑም ቅርጫቱን እንድታመጣላት ባሪያዋን ላከቻት። 6  ቅርጫቱንም ስትከፍት ሕፃኑን አየችው፤ ሕፃኑም እያለቀሰ ነበር። እሷም “ይህ ልጅ ከዕብራውያን ልጆች አንዱ ነው” አለች፤ ያም ሆኖ ለሕፃኑ አዘነችለት። 7  ከዚያም የሕፃኑ እህት የፈርዖንን ልጅ “ከዕብራውያን ሴቶች መካከል ልጁን እያጠባች የምታሳድግልሽ ሞግዚት ልጥራልሽ?” አለቻት። 8  የፈርዖንም ልጅ “አዎ፣ ሂጂ!” አለቻት። ልጅቷም ወዲያውኑ ሄዳ የሕፃኑን እናት ጠራቻት። 9  የፈርዖን ልጅም ሴትየዋን “ይህን ሕፃን ወስደሽ እያጠባሽ አሳድጊልኝ፤ እኔም እከፍልሻለሁ” አለቻት። በመሆኑም ሴትየዋ ልጁን ወስዳ እያጠባች ታሳድገው ጀመር። 10  ልጁም ባደገ ጊዜ አምጥታ ለፈርዖን ልጅ ሰጠቻት፤ እሱም ልጇ ሆነ። እሷም “ከውኃ ውስጥ አውጥቼዋለሁ” በማለት ስሙን ሙሴ አለችው። 11  ሙሴ በጎለመሰ ጊዜ ወንድሞቹ የተጫነባቸውን ሸክም ለማየት ወደ እነሱ ወጣ፤ ከዚያም ከወንድሞቹ አንዱ የሆነውን ዕብራዊ አንድ ግብፃዊ ሲደበድበው አየ። 12  በመሆኑም ወዲያና ወዲህ ተመልክቶ ማንም አለመኖሩን ካረጋገጠ በኋላ ግብፃዊውን ገድሎ አሸዋ ውስጥ ደበቀው። 13  ሆኖም በማግስቱ ሲወጣ ሁለት ዕብራውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ ተመለከተ። እሱም ጥፋተኛውን “የገዛ ወገንህን የምትመታው ለምንድን ነው?” አለው። 14  በዚህ ጊዜ “አንተን በእኛ ላይ አለቃና ፈራጅ ማን አደረገህ? ግብፃዊውን እንደገደልከው እኔንም ልትገድለኝ ታስባለህ?” አለው። ሙሴም “ይህ ነገር ታውቋል ማለት ነው!” ብሎ በማሰብ ፈራ። 15  ከዚያም ፈርዖን ይህን ነገር ሰማ፤ ሙሴንም ሊገድለው ሞከረ፤ ይሁን እንጂ ሙሴ ከፈርዖን ሸሽቶ በምድያም ምድር ለመኖር ሄደ፤ እዚያም በአንድ የውኃ ጉድጓድ አጠገብ ተቀመጠ። 16  በምድያም የነበረው ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነሱም ውኃ ቀድተው ገንዳውን በመሙላት የአባታቸውን መንጋ ውኃ ለማጠጣት መጡ። 17  ሆኖም እንደወትሮው እረኞቹ መጥተው ሴቶቹን አባረሯቸው። በዚህ ጊዜ ሙሴ ተነስቶ ለሴቶቹ አገዘላቸው፤ መንጋቸውንም አጠጣላቸው። 18  ሴቶቹም ወደ ቤት፣ ወደ አባታቸው ወደ ረኡዔል በተመለሱ ጊዜ አባታቸው “ዛሬ እንዴት ቶሎ መጣችሁ?” ሲል በመገረም ጠየቃቸው። 19  እነሱም “አንድ ግብፃዊ ከእረኞቹ እጅ አዳነን፤ እንዲያውም ውኃ ቀድቶ መንጋችንን አጠጣልን” አሉት። 20  እሱም ልጆቹን “ታዲያ ሰውየው የት አለ? ለምን ትታችሁት መጣችሁ? አብሮን ይበላ ዘንድ ጥሩት” አላቸው። 21  ከዚያ በኋላ ሙሴ ከሰውየው ጋር ለመኖር ተስማማ፤ ሰውየውም ልጁን ሲፓራን ለሙሴ ዳረለት። 22  እሷም ከጊዜ በኋላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ሙሴም “በባዕድ አገር የምኖር የባዕድ አገር ሰው ሆንኩ” በማለት ስሙን ጌርሳም አለው። 23  ከረጅም ጊዜ በኋላ የግብፁ ንጉሥ ሞተ፤ እስራኤላውያን ግን ካሉበት የባርነት ሕይወት የተነሳ መቃተታቸውንና እሮሮ ማሰማታቸውን አላቆሙም ነበር፤ ከባርነት ሕይወታቸው የተነሳ እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙት ጩኸት ወደ እውነተኛው አምላክ ወጣ። 24  ከጊዜ በኋላም አምላክ በመቃተት የሚያሰሙትን ጩኸት አዳመጠ፤ እንዲሁም ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር የገባውን ቃል ኪዳኑን አሰበ። 25  በመሆኑም አምላክ እስራኤላውያንን አየ፤ ያሉበትንም ሁኔታ ተመለከተ።
[]
[]
[]
[]
12,476
20  ከዚያም አምላክ ይህን ቃል ሁሉ ተናገረ፦ 2  “ከግብፅ ምድር፣ ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እኔ አምላክህ ይሖዋ ነኝ። 3  ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ። 4  “በላይ በሰማያት ወይም በታች በምድር አሊያም ከምድር በታች በውኃ ውስጥ ባለ በማንኛውም ነገር አምሳል የተቀረጸን ቅርጽ ወይም የተሠራን ምስል ለራስህ አታድርግ። 5  አትስገድላቸው፤ ተታለህም እነሱን አታገልግል፤ ምክንያቱም እኔ አምላክህ ይሖዋ እኔ ብቻ እንድመለክ የምፈልግና በሚጠሉኝ ሁሉ ላይ በአባቶች ስህተት የተነሳ በልጆቻቸው እንዲሁም በሦስተኛና በአራተኛ ትውልዶቻቸው ላይ ቅጣት የማመጣ አምላክ ነኝ፤ 6  ሆኖም ለሚወዱኝና ትእዛዛቴን ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ታማኝ ፍቅር የማሳይ አምላክ ነኝ። 7  “የአምላክህን የይሖዋን ስም በከንቱ አታንሳ፤ ምክንያቱም ይሖዋ ስሙን በከንቱ የሚያነሳውን ሳይቀጣ አይተወውም። 8  “የሰንበትን ቀን ቅዱስ አድርገህ መጠበቅ እንዳለብህ አትርሳ። 9  ሥራህንና የምታከናውናቸውን ነገሮች በሙሉ በስድስት ቀን ሠርተህ አጠናቅ፤ 10  ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለይሖዋ ሰንበት ነው። በዚህ ቀን አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህም ሆነ ሴት ባሪያህ፣ የቤት እንስሳህም ሆነ በሰፈርህ ውስጥ ያለ የባዕድ አገር ሰው ምንም ሥራ አትሥሩ። 11  ምክንያቱም ይሖዋ ሰማያትን፣ ምድርን፣ ባሕርንና በውስጣቸው ያሉትን ነገሮች ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ ሠርቶ ካጠናቀቀ በኋላ በሰባተኛው ቀን ማረፍ ጀምሯል። ይሖዋ የሰንበትን ቀን የባረከውና የቀደሰው ለዚህ ነው። 12  “አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር። 13  “አትግደል። 14  “አታመንዝር። 15  “አትስረቅ። 16  “በባልንጀራህ ላይ ምሥክር ሆነህ ስትቀርብ በሐሰት አትመሥክር። 17  “የባልንጀራህን ቤት አትመኝ። የባልንጀራህን ሚስት፣ ወንድ ባሪያውን፣ ሴት ባሪያውን፣ በሬውን ወይም አህያውን አሊያም የባልንጀራህ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትመኝ።” 18  ሕዝቡም ሁሉ የነጎድጓዱንና የቀንደ መለከቱን ድምፅ ሰሙ፤ እንዲሁም የመብረቁን ብልጭታና የተራራውን ጭስ ተመለከቱ፤ ይህም በፍርሃት እንዲንቀጠቀጡና ርቀው እንዲቆሙ አደረጋቸው። 19  በመሆኑም ሙሴን “አንተ አነጋግረን፤ እኛም እናዳምጥሃለን፤ ሆኖም እንዳንሞት ስለምንፈራ አምላክ አያነጋግረን” አሉት። 20  ሙሴም ሕዝቡን “አትፍሩ፤ ምክንያቱም እውነተኛው አምላክ የመጣው እናንተን ለመፈተን ይኸውም ዘወትር እሱን በመፍራት ኃጢአት ከመሥራት እንድትቆጠቡ ለማድረግ ነው” አላቸው። 21  ሕዝቡም እዚያው ርቆ ባለበት ቆመ፤ ሙሴ ግን እውነተኛው አምላክ ወዳለበት ጥቁር ደመና ቀረበ። 22  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘ከሰማይ ሆኜ እንዳነጋገርኳችሁ እናንተ ራሳችሁ አይታችኋል። 23  እኔን የሚቀናቀኑ ከብር የተሠሩ አማልክት አይኑሯችሁ፤ ከወርቅ የተሠሩ አማልክትም አይኑሯችሁ። 24  ከጭቃ መሠዊያ ሥራልኝ፤ በእሱም ላይ የሚቃጠሉ መባዎችህን፣ የኅብረት መሥዋዕቶችህን፣ መንጎችህንና ከብቶችህን ሠዋ። ስሜ እንዲታወስ በማደርግበት ቦታ ሁሉ ወደ አንተ እመጣለሁ፣ ደግሞም እባርክሃለሁ። 25  ከድንጋይ መሠዊያ የምትሠራልኝ ከሆነ በተጠረቡ ድንጋዮች አትሥራው። ምክንያቱም ድንጋዮቹን በመሮህ ከጠረብካቸው ታረክሳቸዋለህ። 26  ኀፍረተ ሥጋህ በእሱ ላይ እንዳይጋለጥ ወደ መሠዊያዬ በደረጃ አትውጣ።’
[]
[]
[]
[]
12,477
21  “ለእነሱ የምትነግራቸው ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፦ 2  “ዕብራዊ ባሪያ ከገዛህ ለስድስት ዓመት ባሪያ ሆኖ ያገለግልሃል፤ በሰባተኛው ዓመት ግን ያለምንም ክፍያ ነፃ ይወጣል። 3  የመጣው ብቻውን ከሆነ ብቻውን ነፃ ይወጣል። ሚስት ካለችው ግን ሚስቱም አብራው ነፃ ትውጣ። 4  ጌታው ሚስት ቢያጋባውና ሚስቱ ወንዶች ወይም ሴቶች ልጆችን ብትወልድለት ሚስቱና ልጆቿ የጌታዋ ይሆናሉ፤ እሱም ብቻውን ነፃ ይወጣል። 5  ሆኖም ባሪያው ‘ጌታዬን፣ ሚስቴንና ልጆቼን እወዳለሁ፤ ነፃ መውጣት አልፈልግም’ በማለት በአቋሙ ከጸና 6  ጌታው በእውነተኛው አምላክ ፊት ያቅርበው። ከዚያም ጌታው ወደ በሩ ወይም ወደ መቃኑ አምጥቶ ጆሮውን በወስፌ ይበሳዋል፤ እሱም ዕድሜውን ሙሉ ባሪያው ይሆናል። 7  “አንድ ሰው ሴት ልጁን ባሪያ አድርጎ ቢሸጣት ነፃ የምትወጣው ወንድ ባሪያ ነፃ በሚወጣበት መንገድ አይደለም። 8  ጌታዋ ደስ ባይሰኝባትና ቁባቱ እንድትሆን ባይፈልግ ከዚህ ይልቅ ሌላ ሰው እንዲገዛት ቢያደርግ እሷን ለባዕድ አገር ሰው የመሸጥ መብት አይኖረውም፤ ምክንያቱም ክህደት ፈጽሞባታል። 9  ለወንድ ልጁ እንድትሆን ከመረጣት ደግሞ አንዲት ልጅ ማግኘት የሚገባትን መብት እንድታገኝ ያድርግ። 10  ሌላ ሚስት ካገባም የመጀመሪያ ሚስቱ ምግቧ፣ ልብሷና የጋብቻ መብቷ ሊጓደልባት አይገባም። 11  እነዚህን ሦስት ነገሮች የማያሟላላት ከሆነ ግን ምንም ገንዘብ ሳትከፍል እንዲሁ ነፃ ትውጣ። 12  “አንድ ሰው ሌላውን ሰው መትቶ ቢገድል ገዳዩ ይገደል። 13  ሆኖም የገደለው ሆን ብሎ ባይሆንና እውነተኛው አምላክ ይህ ነገር እንዲሆን ቢፈቅድ ገዳዩ የሚሸሽበት ቦታ እኔ አዘጋጅልሃለሁ። 14  አንድ ሰው በባልንጀራው ላይ እጅግ ቢቆጣና ሆን ብሎ ቢገድለው ይህን ሰው ከመሠዊያዬ አጠገብም እንኳ ቢሆን ወስደህ ግደለው። 15  አባቱን ወይም እናቱን የሚመታ ይገደል። 16  “ማንኛውም ግለሰብ አንድን ሰው አፍኖ ቢወስድና ቢሸጠው ወይም ይህን ሰው ይዞት ቢገኝ ይገደል። 17  “አባቱን ወይም እናቱን የሚረግም ይገደል። 18  “ሰዎች ተጣልተው አንደኛው ሌላውን በድንጋይ ወይም በቡጢ ቢመታውና ተመቺው ባይሞት ከዚህ ይልቅ አልጋ ላይ ቢውል መደረግ ያለበት ነገር ይህ ነው፦ 19  ሰውየው ከአልጋው በመነሳት ከቤት ወጥቶ በምርኩዝ መንቀሳቀስ ከቻለ የመታው ሰው ከቅጣት ነፃ ይሆናል። ተጎጂው ሙሉ በሙሉ እስኪድን ድረስ ከሥራ በመስተጓጎሉ ለባከነበት ጊዜ ብቻ ካሳ ይከፍላል። 20  “አንድ ሰው ወንድ ባሪያውን ወይም ሴት ባሪያውን በበትር ቢመታና እጁ ላይ ቢሞትበት ወይም ብትሞትበት ይህ ሰው የበቀል ቅጣት መቀጣት አለበት። 21  ሆኖም ባሪያው ለአንድ ወይም ለሁለት ቀን በሕይወት ከቆየ የበቀል ቅጣት መቀጣት የለበትም፤ ምክንያቱም ይህ ሰው በጌታው ገንዘብ የተገዛ ነው። 22  “ሰዎች እርስ በርስ ሲታገሉ በአንዲት ነፍሰ ጡር ሴት ላይ ጉዳት ቢያደርሱባትና ያለጊዜዋ ብትወልድ ሆኖም ለሞት የተዳረገ ባይኖር ጉዳት ያደረሰው ሰው የሴትየዋ ባል የጠየቀውን ካሳ መክፈል አለበት፤ ፈራጆቹ የወሰኑበትን ካሳ መክፈል ይኖርበታል። 23  ሆኖም ለሞት የተዳረገ ካለ ሕይወት ስለ ሕይወት፣ 24  ዓይን ስለ ዓይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ፣ እጅ ስለ እጅ፣ እግር ስለ እግር፣ 25  መቃጠል ስለ መቃጠል፣ ቁስል ስለ ቁስል እንዲሁም ምት ስለ ምት እንዲመለስ ማድረግ አለብህ። 26  “አንድ ሰው የወንድ ባሪያውን ወይም የሴት ባሪያውን ዓይን ቢመታና ዓይኑን ቢያጠፋው ለዓይኑ ካሳ እንዲሆን ባሪያውን ነፃ ሊያወጣው ይገባል። 27  የወንድ ባሪያውን ወይም የሴት ባሪያውን ጥርስ ቢያወልቅ ለጥርሱ ካሳ እንዲሆን ከባርነቱ ነፃ አድርጎ ሊያሰናብተው ይገባል። 28  “አንድ በሬ አንድን ወንድ ወይም አንዲትን ሴት ቢወጋና የተወጋው ሰው ቢሞት በሬው በድንጋይ ተወግሮ ይገደል፤ ሥጋውም መበላት የለበትም። የበሬው ባለቤት ግን ከቅጣት ነፃ ነው። 29  በሬው የመዋጋት አመል እንዳለው የሚታወቅ ከሆነና ለባለቤቱም ስለ በሬው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ከነበረ በሬውን ሳይጠብቀው ቀርቶ አንድን ወንድ ወይም አንዲትን ሴት ቢገድል፣ በሬው በድንጋይ ይወገር፤ ባለቤቱም ይገደል። 30  ቤዛ እንዲከፍል ከተጠየቀ ለሕይወቱ መዋጃ የሚሆነውን ዋጋ ይክፈል፤ የተጠየቀውንም ሁሉ ይስጥ። 31  በሬው ወንድ ወይም ሴት ልጅ ቢወጋ የበሬው ባለቤት በዚሁ ድንጋጌ መሠረት ሊፈረድበት ይገባል። 32  በሬው የወጋው አንድን ወንድ ባሪያ ወይም አንዲትን ሴት ባሪያ ከሆነ የበሬው ባለቤት ለባሪያው ጌታ 30 ሰቅል ይሰጠዋል፤ በሬውም በድንጋይ ተወግሮ ይገደላል። 33  “አንድ ሰው ጉድጓድ ከፍቶ ወይም ቆፍሮ ጉድጓዱን ሳይከድነው ቢተወውና አንድ በሬ ወይም አንድ አህያ ጉድጓዱ ውስጥ ቢወድቅ 34  የጉድጓዱ ባለቤት ካሳ መክፈል አለበት። ዋጋውን ለእንስሳው ባለቤት መስጠት ይኖርበታል፤ የሞተውም እንስሳ የእሱ ይሆናል። 35  የአንድ ሰው በሬ በሌላው ሰው በሬ ላይ ጉዳት ቢያደርስና በሬው ቢሞት ሰዎቹ በሕይወት ያለውን በሬ ሸጠው ገንዘቡን ይካፈሉ፤ የሞተውንም በሬ ይካፈሉ። 36  ወይም በሬው የመዋጋት አመል እንዳለበት እየታወቀ ባለቤቱ ሳይጠብቀው ቀርቶ ከሆነ ባለቤቱ በበሬ ፋንታ በሬ ካሳ መክፈል አለበት፤ የሞተውም በሬ የእሱ ይሆናል።
[]
[]
[]
[]
12,478
22  “አንድ ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅና ቢያርደው ወይም ቢሸጠው ለበሬው አምስት በሬዎችን ለበጉ ደግሞ አራት በጎችን ካሳ መክፈል አለበት። 2  (“አንድ ሌባ ሰብሮ ሲገባ ቢያዝና ተመቶ ቢሞት ማንም ስለ እሱ በደም ዕዳ ተጠያቂ አይሆንም። 3  ይህ የሆነው ግን ፀሐይ ከወጣች በኋላ ከሆነ ገዳዩ በደም ዕዳ ተጠያቂ ይሆናል።) “ሌባው ካሳ መክፈል አለበት። ምንም የሚከፍለው ነገር ከሌለው ግን ለሰረቃቸው ነገሮች ካሳ እንዲከፍል እሱ ራሱ ይሸጥ። 4  የሰረቀው ነገር በሬም ሆነ አህያ ወይም በግ በሕይወት እንዳለ በእጁ ላይ ከተገኘ እጥፍ አድርጎ ካሳ መክፈል አለበት። 5  “አንድ ሰው ከብቶቹን በእርሻ ወይም በወይን ቦታ አሰማርቶ የሌላ ሰው እርሻ ውስጥ ገብተው ሲግጡ ዝም ቢላቸው ይህ ሰው ምርጥ ከሆነው ከራሱ እርሻ ወይም ምርጥ ከሆነው ከራሱ የወይን ቦታ ካሳ መክፈል አለበት። 6  “እሳት ተነስቶ ወደ ቁጥቋጦ ቢዛመትና ነዶዎችን ወይም ያልታጨደን እህል አሊያም አዝመራን ቢያወድም እሳቱን ያስነሳው ሰው ለተቃጠለው ነገር ካሳ መክፈል አለበት። 7  “አንድ ሰው ገንዘብ ወይም ንብረት እንዲያስቀምጥለት ለባልንጀራው ቢሰጠውና ገንዘቡ ወይም ንብረቱ ከባልንጀራው ቤት ቢሰረቅ፣ ሌባው ከተያዘ እጥፍ አድርጎ ካሳ መክፈል አለበት። 8  ሌባው ካልተያዘ ግን የቤቱ ባለቤት በባልንጀራው ንብረት ላይ እጁን አሳርፎ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማረጋገጥ በእውነተኛው አምላክ ፊት እንዲቀርብ መደረግ አለበት። 9  አላግባብ በባለቤትነት የተያዘን ንብረት ይኸውም በሬን፣ አህያን፣ በግን፣ ልብስን ወይም ጠፍቶ የነበረን ማንኛውንም ነገር በተመለከተ ‘ይህ ንብረት የእኔ ነው!’ በሚል ክርክር ቢነሳ፣ ሁለቱም ሰዎች ጉዳያቸውን በእውነተኛው አምላክ ፊት ያቅርቡ። አምላክ ጥፋተኛ ነው ብሎ የሚፈርድበት ግለሰብ እጥፍ አድርጎ ለባልንጀራው ካሳ መክፈል አለበት። 10  “አንድ ሰው አህያ ወይም በሬ ወይም በግ አሊያም ሌላ ማንኛውንም የቤት እንስሳ ለባልንጀራው በአደራ ቢሰጥና እንስሳው ቢሞት ወይም ከባድ ጉዳት ቢደርስበት አሊያም ማንም ሰው ሳያይ ተነድቶ ቢወሰድ 11  አደራ ተቀባዩ በባልንጀራው ንብረት ላይ እጁን እንዳላሳረፈ ለማረጋገጥ በይሖዋ ፊት ይማልለት፤ የንብረቱ ባለቤትም መሐላውን መቀበል አለበት። ያም ሰው ካሳ እንዲከፍል አይጠየቅም። 12  እንስሳው ተሰርቆበት ከሆነ ግን ለባለቤቱ ካሳ መክፈል አለበት። 13  በአውሬ ተበልቶ ከሆነ ደግሞ ከአውሬ የተረፈውን ማስረጃ አድርጎ ያቅርብ። አውሬ ለበላው ካሳ መክፈል አይጠበቅበትም። 14  “ሆኖም ማንኛውም ሰው ከባልንጀራው እንስሳ ቢዋስና እንስሳው ባለቤቱ በሌለበት ከባድ ጉዳት ቢደርስበት ወይም ቢሞት የተዋሰው ሰው ካሳ መክፈል አለበት። 15  ጉዳቱ የደረሰው ባለቤቱ አብሮ እያለ ከሆነ ግን ካሳ መክፈል የለበትም። እንስሳው በኪራይ መልክ የተወሰደ ከሆነ የደረሰው ጉዳት በኪራዩ ዋጋ ይሸፈናል። 16  “አንድ ወንድ አንዲትን ያልታጨች ድንግል አባብሎ አብሯት ቢተኛ የማጫዋን ዋጋ ከፍሎ ሚስቱ ሊያደርጋት ይገባል። 17  የልጅቷ አባት ልጁን ለእሱ ለመስጠት ፈጽሞ ፈቃደኛ ሳይሆን ቢቀር ይህ ሰው ለደናግል የሚከፈለውን የማጫ ዋጋ መክፈል አለበት። 18  “መተተኛ ሴት በሕይወት እንድትኖር አትፍቀድ። 19  “ከእንስሳ ጋር የፆታ ግንኙነት የሚፈጽም ማንም ሰው ያለጥርጥር ይገደል። 20  “ለይሖዋ ካልሆነ በቀር ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው ይገደል። 21  “የባዕድ አገር ሰውን አትበድል ወይም አትጨቁን፤ ምክንያቱም እናንተ ራሳችሁ በግብፅ ምድር ሳላችሁ የባዕድ አገር ሰው ነበራችሁ። 22  “መበለቲቱን ወይም አባት የሌለውን ልጅ አታጎሳቁሉ። 23  ብታጎሳቁለውና ወደ እኔ ቢጮኽ እኔ በእርግጥ ጩኸቱን እሰማለሁ፤ 24  ቁጣዬም ይነድዳል። እናንተንም በሰይፍ እገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁ መበለቶች፣ ልጆቻችሁም አባት የሌላቸው ልጆች ይሆናሉ። 25  “ከሕዝቤ መካከል አብሮህ ላለ ችግረኛ ገንዘብ ብታበድር እንደ አራጣ አበዳሪ አትሁንበት። ወለድም አትጠይቁት። 26  “የባልንጀራህን ልብስ መያዣ አድርገህ ብትይዝ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ልትመልስለት ይገባል። 27  ምክንያቱም የሚለብሰው ልብስ ይኸውም ሰውነቱ ላይ የሚጥለው ልብስ እሱ ብቻ ነው፤ አለዚያ ምን ለብሶ ይተኛል? እሱም ወደ እኔ በሚጮኽበት ጊዜ በእርግጥ እሰማዋለሁ፤ ምክንያቱም እኔ ሩኅሩኅ ነኝ። 28  “አምላክን አትራገም፤ በሕዝብህ መካከል ያለውን አለቃም አትራገም። 29  “ከተትረፈረፈው ምርትህና ሞልቶ ከሚፈሰው መጭመቂያህ መባ ለማቅረብ አትሳሳ። የወንዶች ልጆችህን በኩር ለእኔ መስጠት አለብህ። 30  የበሬህንና የበግህን በኩር በተመለከተ ልታደርገው የሚገባህ ነገር ይህ ነው፦ ለሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቆይ። በስምንተኛው ቀን ለእኔ መስጠት አለብህ። 31  “እናንተ ለእኔ ቅዱስ ሕዝብ ሆናችሁ መገኘት አለባችሁ፤ አውሬ ዘንጥሎት ሜዳ ላይ የተገኘን የማንኛውንም እንስሳ ሥጋ አትብሉ። ለውሾች ጣሉት።
[]
[]
[]
[]
12,479
23  “የሐሰት ወሬ አትንዛ። ተንኮል የሚሸርብ ምሥክር በመሆን ከክፉ ሰው ጋር አትተባበር። 2  ብዙኃኑን ተከትለህ ክፉ ነገር አታድርግ፤ ከብዙኃኑ ጋር ለመስማማት ስትል የተዛባ ምሥክርነት በመስጠት ፍትሕን አታጣም። 3  ችግረኛው ሙግት ሲኖረው አታድላለት። 4  “የጠላትህ በሬ ወይም አህያ ሲባዝን ብታገኘው ወደ እሱ ልትመልሰው ይገባል። 5  የሚጠላህ ሰው አህያ ጭነቱ ከብዶት ወድቆ ብታይ ዝም ብለህ አትለፈው። ከዚህ ይልቅ ጭነቱን ከእንስሳው ላይ ለማውረድ እርዳው። 6  “በመካከልህ ያለ ድሃ ሙግት ሲኖረው ፍርድ አታጣምበት። 7  “ከሐሰት ክስ ራቅ፤ እኔ ክፉውን ሰው ጻድቅ እንደሆነ አድርጌ ስለማልቆጥር ንጹሑንና ጻድቁን ሰው አትግደል። 8  “ጉቦ አትቀበል፤ ምክንያቱም ጉቦ አጥርተው የሚያዩ ሰዎችን ዓይን ያሳውራል፤ እንዲሁም የጻድቅ ሰዎችን ቃል ሊያዛባ ይችላል። 9  “የባዕድ አገር ሰውን አትጨቁን። እናንተ ራሳችሁ በግብፅ ምድር ሳላችሁ የባዕድ አገር ሰው ስለነበራችሁ የባዕድ አገር ሰው መሆን ምን ስሜት እንደሚያሳድር ታውቃላችሁ። 10  “ለስድስት ዓመት መሬትህ ላይ ዘር ዝራ፤ አዝመራውንም ሰብስብ። 11  በሰባተኛው ዓመት ግን መሬትህን አትረሰው፤ እንዲሁ ተወው። በሕዝብህ መካከል ያሉ ድሆች ከዚያ ይበላሉ፤ ከእነሱ የተረፈውንም የዱር አራዊት ይበሉታል። በወይን እርሻህም ሆነ በወይራ ዛፍ እርሻህ እንደዚሁ ታደርጋለህ። 12  “ለስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ ሆኖም በሬህና አህያህ እንዲያርፉ እንዲሁም የሴት ባሪያህ ልጅና የባዕድ አገሩ ሰው ጉልበታቸውን እንዲያድሱ በሰባተኛው ቀን ሥራ አትሥራ። 13  “የነገርኳችሁን ነገሮች በሙሉ በጥንቃቄ ፈጽሙ፤ እንዲሁም የሌሎች አማልክትን ስም አታንሱ፤ እንዲህ ዓይነቱ ነገር ከአፍህ ሲወጣ ሊሰማ አይገባም። 14  “በዓመት ሦስት ጊዜ ለእኔ በዓል ታከብርልኛለህ። 15  የቂጣን በዓል ታከብራለህ። በአቢብ ወር በተወሰነው ጊዜ፣ ባዘዝኩህ መሠረት ለሰባት ቀናት ቂጣ ትበላለህ፤ ምክንያቱም ከግብፅ የወጣኸው በዚህ ጊዜ ነው። ማንም ባዶ እጁን ፊቴ አይቅረብ። 16  በተጨማሪም በእርሻህ ላይ በዘራኸው መጀመሪያ በሚደርሰው የድካምህ ፍሬ የመከርን በዓል አክብር፤ ከእርሻህ ላይ የድካምህን ፍሬ በምትሰበስብበት በዓመቱ ማብቂያ ላይ የአዝመራ መክተቻን በዓል አክብር። 17  የአንተ የሆኑ ሰዎች ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ በእውነተኛው ጌታ በይሖዋ ፊት ይቅረቡ። 18  “የመሥዋዕቴን ደም እርሾ ከገባበት ከማንኛውም ነገር ጋር አብረህ አታቅርብ። በበዓሎቼም ላይ የሚቀርቡት የስብ መሥዋዕቶች እስከ ጠዋት ድረስ ማደር የለባቸውም። 19  “በምድርህ ላይ የሚገኘውን መጀመሪያ የደረሰውን ምርጥ ፍሬ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ቤት አምጣ። “የፍየል ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል። 20  “በመንገድ ላይ እንዲጠብቅህና ወዳዘጋጀሁት ስፍራ እንዲያመጣህ በፊትህ መልአክ እልካለሁ። 21  የሚልህን ስማ፤ ቃሉንም ታዘዝ። መተላለፋችሁን ይቅር ስለማይል በእሱ ላይ አታምፁ፤ ምክንያቱም እሱ ስሜን ተሸክሟል። 22  ይሁን እንጂ ቃሉን በጥንቃቄ ብትታዘዝና የምልህን ሁሉ ብታደርግ ለጠላቶችህ ጠላት እሆናለሁ፤ የሚቃወሙህንም እቃወማለሁ። 23  ምክንያቱም መልአኬ በፊትህ ይሄዳል፤ እንዲሁም ወደ አሞራውያን፣ ሂታውያን፣ ፈሪዛውያን፣ ከነአናውያን፣ ሂዋውያንና ኢያቡሳውያን ያመጣሃል፤ እኔም ጠራርጌ አጠፋቸዋለሁ። 24  ለአማልክታቸው አትስገድ፤ ወይም ተታለህ እነሱን አታገልግል፤ የሚያደርጉትን ነገር አታድርግ። ከዚህ ይልቅ አውድማቸው፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውንም ሰባብር። 25  አምላካችሁን ይሖዋን አገልግሉ፤ እሱም ምግብህንና ውኃህን ይባርክልሃል። እኔም ከመካከልህ በሽታን አስወግዳለሁ። 26  በምድርህ ላይ የሚኖሩ ሴቶች አያስወርዳቸውም ወይም መሃን አይሆኑም፤ ረጅም ዕድሜ እሰጥሃለሁ። 27  “አንተ ከመድረስህ በፊት ስለ እኔ ሰምተው ይፈራሉ፤ የምታገኛቸውም ሕዝቦች ሁሉ ግራ እንዲጋቡ አደርጋለሁ። ጠላቶችህም ሁሉ ድል ተመተው ከፊትህ እንዲሸሹ አደርጋለሁ። 28  ከአንተ አስቀድሜ ጭንቀት እልካለሁ፤ ሂዋውያንን፣ ከነአናውያንንና ሂታውያንን ከፊትህ አባሮ ያስወጣቸዋል። 29  ምድሩ ባድማ እንዳይሆንና የዱር አራዊት በዝተው እንዳያስቸግሩህ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከፊትህ አባርሬ አላስወጣቸውም። 30  ቁጥርህ እስኪበዛና ምድሩን እስክትቆጣጠር ድረስ ጥቂት በጥቂት ከፊትህ አባርሬ አስወጣቸዋለሁ። 31  “ወሰንህንም ከቀይ ባሕር አንስቶ እስከ ፍልስጤማውያን ባሕር እንዲሁም ከምድረ በዳው አንስቶ እስከ ወንዙ ድረስ አደርገዋለሁ። ምክንያቱም የምድሩን ነዋሪዎች በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ አንተም ከፊትህ አባረህ ታስወጣቸዋለህ። 32  ከእነሱም ሆነ ከአማልክታቸው ጋር ቃል ኪዳን መግባት የለብህም። 33  በእኔ ላይ ኃጢአት እንድትሠራ እንዳያደርጉህ በምድርህ ላይ መኖር የለባቸውም። አማልክታቸውን ብታገለግል ወጥመድ ይሆንብሃል።”
[]
[]
[]
[]
12,480
24  ሙሴንም እንዲህ አለው፦ “አንተ፣ አሮን፣ ናዳብ፣ አቢሁና 70ዎቹ የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ይሖዋ ውጡ፤ ከሩቅ ሆናችሁም ስገዱ። 2  ሙሴ ብቻውን ወደ ይሖዋ ይቅረብ፤ ሌሎቹ ግን መቅረብ የለባቸውም፤ ሕዝቡም ከእሱ ጋር መውጣት የለበትም።” 3  ከዚያም ሙሴ መጥቶ የይሖዋን ቃል ሁሉ እንዲሁም ድንጋጌዎቹን በሙሉ ለሕዝቡ ነገራቸው፤ ሕዝቡም ሁሉ “ይሖዋ የተናገረውን ቃል በሙሉ ለመፈጸም ፈቃደኞች ነን” ሲሉ በአንድ ድምፅ መለሱ። 4  ስለሆነም ሙሴ የይሖዋን ቃል ሁሉ በጽሑፍ አሰፈረ። በማለዳም ተነስቶ በተራራው ግርጌ መሠዊያና 12ቱን የእስራኤል ነገዶች የሚወክሉ 12 ዓምዶች ሠራ። 5  ከዚያም ወጣት እስራኤላውያን ወንዶችን ላከ፤ እነሱም የሚቃጠሉ መባዎችን አቀረቡ፤ እንዲሁም በሬዎችን የኅብረት መሥዋዕቶች አድርገው ለይሖዋ ሠዉ። 6  ሙሴም ከደሙ ግማሹን ወስዶ በሳህኖች ውስጥ አስቀመጠው፤ ግማሹን ደም ደግሞ በመሠዊያው ላይ ረጨው። 7  ከዚያም የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ወስዶ ድምፁን ከፍ በማድረግ ለሕዝቡ አነበበ። ሕዝቡም “ይሖዋ የተናገረውን ሁሉ ለመፈጸምና ለመታዘዝ ፈቃደኞች ነን” አሉ። 8  በመሆኑም ሙሴ ደሙን ወስዶ በሕዝቡ ላይ ረጨው፤ እንዲህም አለ፦ “በእነዚህ ቃላት መሠረት ይሖዋ ከእናንተ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ደም ይህ ነው።” 9  ሙሴ፣ አሮን፣ ናዳብ፣ አቢሁና 70ዎቹ የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ላይ ወጡ፤ 10  የእስራኤልንም አምላክ አዩ። ከእግሩም ሥር እንደ ሰማይ የጠራ የሰንፔር ንጣፍ የሚመስል ነገር ነበር። 11  እሱም በእስራኤል አለቆች ላይ ጉዳት አላደረሰባቸውም፤ እነሱም እውነተኛውን አምላክ በራእይ ተመለከቱ፤ በሉ፣ ጠጡም። 12  በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣና በዚያ ቆይ። ለሕዝቡ መመሪያ እንዲሆን እኔ የጻፍኩትን ሕግና ትእዛዝ የያዙትን የድንጋይ ጽላቶች እሰጥሃለሁ።” 13  በመሆኑም ሙሴ ከአገልጋዩ ከኢያሱ ጋር ተነስቶ ወደ እውነተኛው አምላክ ተራራ ወጣ። 14  ሽማግሌዎቹን ግን እንዲህ አላቸው፦ “ወደ እናንተ እስክንመለስ ድረስ እዚሁ ጠብቁን። አሮንና ሁር አብረዋችሁ ናቸው። ሙግት ያለው ሰው ቢኖር እነሱ ፊት መቅረብ ይችላል።” 15  ሙሴም ወደ ተራራው ሲወጣ ደመናው ተራራውን ሸፍኖት ነበር። 16  የይሖዋም ክብር በሲና ተራራ ላይ እንዳረፈ ነበር፤ ደመናውም ለስድስት ቀናት ተራራውን ሸፍኖት ነበር። በሰባተኛውም ቀን ከደመናው መሃል ሙሴን ጠራው። 17  ሁኔታውን ይከታተሉ ለነበሩት እስራኤላውያን የይሖዋ ክብር በተራራው አናት ላይ እንዳለ የሚባላ እሳት ሆኖ ታያቸው። 18  ከዚያም ሙሴ ወደ ደመናው ገባ፤ ወደ ተራራውም ወጣ። ሙሴም በተራራው ላይ 40 ቀንና 40 ሌሊት ቆየ።
[]
[]
[]
[]
12,481
25  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “ለእስራኤላውያን መዋጮ እንዲያመጡልኝ ንገራቸው፤ ለመስጠት ልቡ ካነሳሳው ከእያንዳንዱ ሰው መዋጮዬን ትቀበላላችሁ። 3  ከእነሱ የምትቀበሉት መዋጮም ይህ ነው፦ ወርቅ፣ ብር፣ መዳብ፣ 4  ሰማያዊ ክር፣ ሐምራዊ ሱፍ፣ ደማቅ ቀይ ማግ፣ ጥሩ በፍታ፣ የፍየል ፀጉር፣ 5  ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ የአቆስጣ ቆዳ፣ የግራር እንጨት፣ 6  ለመብራት የሚሆን ዘይት፣ ለቅብዓት ዘይትና ጥሩ መዓዛ ላለው ዕጣን የሚሆን በለሳን፣ 7  ለኤፉዱ እንዲሁም ለደረት ኪሱ የሚሆኑ የኦኒክስ ድንጋዮችና ሌሎች ድንጋዮች። 8  ለእኔም መቅደስ ይሠሩልኛል፤ እኔም በመካከላቸው እኖራለሁ። 9  የማደሪያ ድንኳኑንም ሆነ በውስጡ የሚቀመጡትን ቁሳቁሶች ሁሉ እኔ በማሳይህ ንድፍ መሠረት ትሠሯቸዋላችሁ። 10  “ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል እንዲሁም ከፍታው አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦት ከግራር እንጨት ይሠራሉ። 11  ከዚያም በንጹሕ ወርቅ ትለብጠዋለህ። ውስጡንና ውጭውን ትለብጠዋለህ፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ ትሠራለታለህ። 12  አራት የወርቅ ቀለበቶች ትሠራለታለህ፤ ከዚያም ሁለቱን ቀለበቶች በአንዱ በኩል ሁለቱን ቀለበቶች ደግሞ በሌላው በኩል በማድረግ ከአራቱ እግሮቹ በላይ ታያይዛቸዋለህ። 13  ከግራር እንጨት መሎጊያዎችን ትሠራለህ፤ በወርቅም ትለብጣቸዋለህ። 14  ታቦቱን ለመሸከም እንዲያገለግሉ መሎጊያዎቹን በታቦቱ ጎንና ጎን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ ታስገባቸዋለህ። 15  መሎጊያዎቹ በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ እንዳሉ ይቀመጣሉ፤ ከዚያ መውጣት የለባቸውም። 16  የምሰጥህንም ምሥክር በታቦቱ ውስጥ ታስቀምጠዋለህ። 17  “እንዲሁም ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱ ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል የሆነ መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ትሠራለህ። 18  ሁለት የወርቅ ኪሩቦችን ትሠራለህ፤ ወርቁን በመጠፍጠፍም በመክደኛው ጫፍና ጫፍ ላይ ወጥ አድርገህ ትሠራቸዋለህ። 19  በሁለቱ የመክደኛው ጫፎች ላይ ኪሩቦቹን ሥራ፤ አንዱን ኪሩብ በዚህኛው ጫፍ፣ ሌላኛውን ኪሩብ ደግሞ በዚያኛው ጫፍ ላይ ሥራ። 20  ኪሩቦቹ ሁለቱን ክንፎቻቸውን ወደ ላይ በመዘርጋት መክደኛውን በክንፎቻቸው ይከልሉታል፤ እነሱም ትይዩ ይሆናሉ። የኪሩቦቹ ፊት ወደ መክደኛው ያጎነበሰ ይሆናል። 21  መክደኛውንም በታቦቱ ላይ ትገጥመዋለህ፤ የምሰጥህንም ምሥክር በታቦቱ ውስጥ ታስቀምጠዋለህ። 22  እኔም በዚያ እገለጥልሃለሁ፤ ከመክደኛውም በላይ ሆኜ አነጋግርሃለሁ። በምሥክሩ ታቦት ላይ በሚገኙት በሁለቱ ኪሩቦች መካከል ሆኜ እስራኤላውያንን በተመለከተ የማዝህንም ሁሉ አሳውቅሃለሁ። 23  “በተጨማሪም ርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ፣ ከፍታው ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ጠረጴዛ ከግራር እንጨት ትሠራለህ። 24  በንጹሕ ወርቅ ትለብጠዋለህ፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ ትሠራለታለህ። 25  ዙሪያውንም አንድ ጋት ስፋት ያለው ጠርዝ ታበጅለታለህ፤ በጠርዙም ዙሪያ የወርቅ ክፈፍ ታደርግለታለህ። 26  አራት የወርቅ ቀለበቶች ትሠራለታለህ፤ ከዚያም ቀለበቶቹን አራቱ እግሮቹ በሚገኙባቸው አራት ማዕዘኖች ላይ ታደርጋቸዋለህ። 27  ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች እንዲይዙ ቀለበቶቹ በጠርዙ አጠገብ ይሆናሉ። 28  መሎጊያዎቹንም ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ትለብጣቸዋለህ፤ ጠረጴዛውንም በእነሱ አማካኝነት ትሸከማለህ። 29  “ለመጠጥ መባ ማፍሰሻ የሚያገለግሉትን ሳህኖቹን፣ ጽዋዎቹን፣ ማንቆርቆሪያዎቹንና ጎድጓዳ ሳህኖቹን ትሠራለህ። ከንጹሕ ወርቅ ትሠራቸዋለህ። 30  ገጸ ኅብስቱን በጠረጴዛው ላይ ሁልጊዜ በፊቴ ታስቀምጣለህ። 31  “ከንጹሕ ወርቅ መቅረዝ ትሠራለህ። መቅረዙም ወጥ ከሆነ ወርቅ ተጠፍጥፎ የተሠራ ይሁን። የመቅረዙ መቆሚያ፣ ግንድ፣ ቅርንጫፎች፣ አበባ አቃፊዎች፣ እንቡጦችና የፈኩት አበቦች ወጥ ሆነው የተሠሩ ይሆናሉ። 32  በመቅረዙ ጎንና ጎን ስድስት ቅርንጫፎች ይኖራሉ፤ ሦስቱ የመቅረዙ ቅርንጫፎች ከአንዱ ጎን፣ ሦስቱ የመቅረዙ ቅርንጫፎች ደግሞ ከሌላው ጎን የወጡ ይሆናሉ። 33  በአንዱ በኩል ባሉት ቅርንጫፎች በእያንዳንዳቸው ላይ የአልሞንድ አበባ የሚመስሉ ሦስት የአበባ አቃፊዎችን ከእንቡጦቹና ከፈኩት አበቦች ጋር እያፈራረቅክ ትሠራለህ፤ በሌላኛው በኩል ባሉት ቅርንጫፎችም በእያንዳንዳቸው ላይ የአልሞንድ አበባ የሚመስሉ ሦስት የአበባ አቃፊዎችን ከእንቡጦቹና ከፈኩት አበቦች ጋር እያፈራረቅክ ትሠራለህ። ስድስቱ ቅርንጫፎች ከመቅረዙ ግንድ የሚወጡት በዚህ መንገድ ይሆናል። 34  በግንዱ ላይም የአልሞንድ አበባ የሚመስሉ አራት የአበባ አቃፊዎችን ከእንቡጦቹና ከፈኩት አበቦች ጋር እያፈራረቅክ ትሠራለህ። 35  ከግንዱ በሚወጡት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቅርንጫፎች ሥር አንድ እንቡጥ ይኖራል፤ በቀጣዮቹ ሁለት ቅርንጫፎች ሥርም አንድ እንቡጥ ይኖራል፤ በቀጣዮቹ ሁለት ቅርንጫፎች ሥርም እንዲሁ አንድ እንቡጥ ይኖራል፤ ከግንዱ የሚወጡት ስድስቱም ቅርንጫፎች በዚሁ መንገድ ይሠራሉ። 36  እንቡጦቹና ቅርንጫፎቻቸው እንዲሁም የመቅረዙ ሁለመና ንጹሕ ከሆነ አንድ ወጥ ወርቅ ተጠፍጥፈው የተሠሩ ይሆናሉ። 37  ሰባት መብራቶች ትሠራለታለህ፤ መብራቶቹ በሚለኮሱበት ጊዜ ከፊት ለፊቱ ላለው አካባቢ ብርሃን ይሰጣሉ። 38  መቆንጠጫዎቹና መኮስተሪያዎቹ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ይሁኑ። 39  ቁሳቁሶቹ ሁሉ ከአንድ ታላንት ንጹሕ ወርቅ ይሠሩ። 40  በተራራው ላይ ተገልጦልህ ባየኸው ንድፍ መሠረት ተጠንቅቀህ ሥራቸው።
[]
[]
[]
[]
12,482
26  “በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ እንዲሁም ከደማቅ ቀይ ማግ ከተዘጋጁ አሥር የድንኳን ጨርቆች የማደሪያ ድንኳኑን ትሠራለህ። በጨርቆቹ ላይ ኪሩቦችን ትጠልፍባቸዋለህ። 2  የእያንዳንዱ የድንኳን ጨርቅ ርዝመት 28 ክንድ ወርዱ ደግሞ 4 ክንድ ይሆናል። ሁሉም የድንኳን ጨርቆች መጠናቸው እኩል ይሆናል። 3  አምስቱ የድንኳን ጨርቆች አንድ ላይ ይቀጣጠላሉ፤ የቀሩት አምስቱ የድንኳን ጨርቆችም እንዲሁ አንድ ላይ ይቀጣጠላሉ። 4  እርስ በርስ ከተቀጣጠሉት የድንኳን ጨርቆች በመጨረሻው ጨርቅ ጠርዝ ላይ ከሰማያዊ ክር የተሠሩ ማቆላለፊያዎችን ታደርጋለህ፤ እርስ በርስ የተቀጣጠለው ሌላኛው የድንኳን ጨርቅ ከዚህኛው ጋር በሚጋጠምበት የመጨረሻው የድንኳን ጨርቅ ጠርዝ ላይም እንዲሁ ታደርጋለህ። 5  በአንደኛው የድንኳን ጨርቅ ላይ 50 ማቆላለፊያዎችን ትሠራለህ፤ በሌላኛው የድንኳን ጨርቅ ጠርዝ ላይም 50 ማቆላለፊያዎችን ታደርጋለህ፤ ማቆላለፊያዎቹም የሚጋጠሙበት ቦታ ላይ እርስ በርሳቸው ትይዩ ይሆናሉ። 6  ከዚያም 50 የወርቅ ማያያዣዎችን ሠርተህ የድንኳን ጨርቆቹን በማያያዣዎቹ አማካኝነት እርስ በርስ ታጋጥማቸዋለህ፤ በዚህ መንገድ ማደሪያ ድንኳኑ አንድ ወጥ ይሆናል። 7  “በተጨማሪም ለማደሪያ ድንኳኑ ልባስ የሚሆኑ ጨርቆችን ከፍየል ፀጉር ትሠራለህ። አሥራ አንድ የድንኳን ጨርቆችን ትሠራለህ። 8  የእያንዳንዱ የድንኳን ጨርቅ ርዝመት 30 ክንድ ወርዱ ደግሞ 4 ክንድ ይሆናል። የአሥራ አንዱም የድንኳን ጨርቆች መጠን እኩል ይሆናል። 9  አምስቱን የድንኳን ጨርቆች አንድ ላይ ትቀጣጥላቸዋለህ፤ የቀሩትን ስድስቱን የድንኳን ጨርቆች ደግሞ አንድ ላይ ትቀጣጥላቸዋለህ፤ ስድስተኛውን የድንኳን ጨርቅ በድንኳኑ ፊት በኩል ታጥፈዋለህ። 10  እርስ በርስ ከተቀጣጠሉት የድንኳን ጨርቆች በመጨረሻው ጠርዝ ላይ 50 ማቆላለፊያዎችን ትሠራለህ፤ እርስ በርስ የተቀጣጠለው ሌላኛው የድንኳን ጨርቅ ከዚህኛው ጋር በሚጋጠምበት ጨርቅ ጠርዝ ላይም 50 ማቆላለፊያዎችን ታደርጋለህ። 11  ከዚያም 50 የመዳብ ማያያዣዎችን ትሠራለህ፤ ማያያዣዎቹንም ማቆላለፊያዎቹ ውስጥ በማስገባት ድንኳኑን ታጋጥመዋለህ፤ በዚህ መንገድ የድንኳኑ ጨርቅ አንድ ወጥ ይሆናል። 12  ከድንኳኑ ጨርቆች ትርፍ ሆኖ የወጣው እንደተንጠለጠለ ይተዋል። ትርፍ ሆኖ የወጣው ግማሹ የድንኳን ጨርቅ በማደሪያ ድንኳኑ ጀርባ ላይ ይንጠለጠላል። 13  ትርፍ ሆኖ የወጣው አንድ አንድ ክንድ ጨርቅ ድንኳኑን እንዲሸፍን በማደሪያ ድንኳኑ ጎንና ጎን ይንጠለጠላል። 14  “በተጨማሪም ቀይ ቀለም ከተነከረ የአውራ በግ ቆዳ ለድንኳኑ መደረቢያ ትሠራለህ፤ በዚያ ላይ የሚደረግ መደረቢያም ከአቆስጣ ቆዳ ትሠራለህ። 15  “የግራር እንጨት ጣውላዎችን በማገጣጠም ለማደሪያ ድንኳኑ የሚሆኑ አራት ማዕዘን ቋሚዎችን ትሠራለህ። 16  የእያንዳንዱ ቋሚ ቁመት አሥር ክንድ ወርዱ ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል ይሆናል። 17  እያንዳንዱ ቋሚም እርስ በርስ የተያያዙ ሁለት ጉጦች ይኑሩት። ለማደሪያ ድንኳኑ የሚያገለግሉትን ቋሚዎች በሙሉ በዚህ መንገድ ሥራቸው። 18  በስተ ደቡብ በኩል ለሚገኘው ፊቱ በደቡብ አቅጣጫ ላለው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን 20 ቋሚዎችን ትሠራለህ። 19  “ከ20ዎቹ ቋሚዎች ሥር የሚሆኑ 40 የብር መሰኪያዎችን ትሠራለህ፤ በአንዱ ቋሚ ሥር ያሉት ሁለት ጉጦች ሁለት መሰኪያዎች፣ ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱ ቋሚ ሥር ያሉት ሁለት ጉጦችም ሁለት መሰኪያዎች ይኖሯቸዋል። 20  በስተ ሰሜን በኩል ላለው ለሌላኛውም የማደሪያ ድንኳኑ ጎን 20 ቋሚዎችን ሥራ፤ 21  እንዲሁም 40 የብር መሰኪያዎቻቸውን ሥራ፤ በአንዱ ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያዎች፣ ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱም ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያዎች ይኑሩ። 22  በስተ ምዕራብ በኩል ለሚገኘው ለኋለኛው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን ስድስት ቋሚዎችን ትሠራለህ። 23  በማደሪያ ድንኳኑ በስተ ኋላ በኩል የማዕዘን ቋሚዎች እንዲሆኑ ሁለት ቋሚዎችን ትሠራለህ። 24  ቋሚዎቹም ከታች አንስቶ የመጀመሪያው ቀለበት እስከሚገኝበት እስከ ላይ ድረስ ድርብ መሆን አለባቸው። ሁለቱም በዚህ መንገድ መሠራት አለባቸው፤ እነሱም ሁለት የማዕዘን ቋሚዎች ሆነው ያገለግላሉ። 25  ስምንት ቋሚዎችና ከብር የተሠሩ 16 መሰኪያዎች ይኸውም በአንዱ ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያዎች፣ ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱም ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያዎች ይኖራሉ። 26  “ከግራር እንጨት አግዳሚ እንጨቶችን ታዘጋጃለህ፤ በአንዱ ጎን ላሉት የማደሪያ ድንኳኑ ቋሚዎች አምስት አግዳሚ እንጨቶችን፣ 27  በሌላኛው ጎን ላሉት የማደሪያ ድንኳኑ ቋሚዎች አምስት አግዳሚ እንጨቶችን እንዲሁም በስተ ምዕራብ በኩል ባለው በኋለኛው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን ላሉት ቋሚዎች አምስት አግዳሚ እንጨቶችን ታዘጋጃለህ። 28  በቋሚዎቹ መሃል ላይ የሚያርፈው መካከለኛው አግዳሚ እንጨት ከጫፍ እስከ ጫፍ የሚዘልቅ መሆን ይኖርበታል። 29  “ቋሚዎቹን በወርቅ ትለብጣቸዋለህ፤ አግዳሚ እንጨቶቹን የሚሸከሙትን የቋሚዎቹን ቀለበቶች ከወርቅ ትሠራቸዋለህ፤ አግዳሚ እንጨቶቹንም በወርቅ ትለብጣቸዋለህ። 30  የማደሪያ ድንኳኑን በተራራው ላይ ተገልጦልህ ባየኸው ንድፍ መሠረት ትከለው። 31  “ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግ እንዲሁም በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ የበፍታ ድር መጋረጃ ትሠራለህ። በላዩም ላይ ኪሩቦች ይጠለፉበታል። 32  መጋረጃውንም በወርቅ በተለበጡ አራት የግራር እንጨት ዓምዶች ላይ ታንጠለጥለዋለህ። ማንጠልጠያዎቻቸውም ከወርቅ የተሠሩ ይሁኑ። ዓምዶቹም ከብር በተሠሩ አራት መሰኪያዎች ላይ ይቆማሉ። 33  መጋረጃውን ከማያያዣዎቹ በታች ታንጠለጥለዋለህ፤ የምሥክሩንም ታቦት በመጋረጃው ውስጥ ታስቀምጠዋለህ። መጋረጃውም ቅድስቱንና ቅድስተ ቅዱሳኑን ለመለየት ያገለግላችኋል። 34  መክደኛውንም በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ በሚገኘው በምሥክሩ ታቦት ላይ ግጠመው። 35  “ጠረጴዛውንም ከመጋረጃው ውጭ ታስቀምጠዋለህ፤ መቅረዙን በስተ ደቡብ በኩል ባለው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን ከጠረጴዛው ትይዩ ታስቀምጠዋለህ፤ ጠረጴዛውን ደግሞ በስተ ሰሜን በኩል ታስቀምጠዋለህ። 36  ለድንኳኑ መግቢያ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግ እንዲሁም በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ የበፍታ ድር የተሸመነ መከለያ ትሠራለህ። 37  ለመከለያውም አምስት ዓምዶችን ከግራር እንጨት ትሠራለህ፤ በወርቅም ትለብጣቸዋለህ። ማንጠልጠያዎቹም ከወርቅ የተሠሩ ይሆናሉ፤ ለዓምዶቹም አምስት የመዳብ መሰኪያዎችን ትሠራለህ።
[]
[]
[]
[]
12,483
27  “ርዝመቱ አምስት ክንድ፣ ወርዱም አምስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር እንጨት ትሠራለህ። መሠዊያው አራቱም ጎኖቹ እኩል፣ ከፍታው ደግሞ ሦስት ክንድ መሆን አለበት። 2  በአራቱ ማዕዘኖቹ ላይ ቀንዶች ትሠራለታለህ፤ ቀንዶቹም የመሠዊያው ክፍል ይሆናሉ፤ መሠዊያውንም በመዳብ ትለብጠዋለህ። 3  አመዱን ማስወገጃ ባልዲዎችን፣ አካፋዎችን፣ ሳህኖችን፣ ሹካዎችንና መኮስተሪያዎችን ትሠራለህ፤ ዕቃዎቹንም ሁሉ ከመዳብ ትሠራቸዋለህ። 4  ለመሠዊያው እንደ መረብ አድርገህ የመዳብ ፍርግርግ ትሠራለታለህ፤ በፍርግርጉ በአራቱም ማዕዘኖቹ ላይ አራት የመዳብ ቀለበቶችን ትሠራለታለህ። 5  ፍርግርጉንም ከመሠዊያው ጠርዝ ወደ ታች ወረድ አድርገህ ታስቀምጠዋለህ፤ ፍርግርጉም መሠዊያው መሃል አካባቢ ይሆናል። 6  ለመሠዊያው የሚሆኑ መሎጊያዎችን ከግራር እንጨት ትሠራለህ፤ በመዳብም ትለብጣቸዋለህ። 7  መሎጊያዎቹም ቀለበቶቹ ውስጥ ይገባሉ፤ መሠዊያውን በምትሸከሙበትም ጊዜ መሎጊያዎቹ በሁለቱ ጎኖቹ በኩል ይሆናሉ። 8  መሠዊያውንም ባዶ ሣጥን አስመስለህ ከሳንቃ ትሠራዋለህ። ልክ ተራራው ላይ ባሳየህ መሠረት ይሠራ። 9  “የማደሪያ ድንኳኑን ግቢ ትሠራለህ። በስተ ደቡብ በኩል የሚገኘው፣ ፊቱ በደቡብ አቅጣጫ ያለው የግቢው ጎን በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠሩ መጋረጃዎች ይኖሩታል፤ የአንዱ ጎን ርዝመት 100 ክንድ ይሆናል። 10  ግቢው 20 ቋሚዎችና ከመዳብ የተሠሩ 20 መሰኪያዎች ይኖሩታል። በቋሚዎቹ ላይ ያሉት ማንጠልጠያዎችና ማያያዣዎቻቸው ደግሞ ከብር የተሠሩ ይሆናሉ። 11  በስተ ሰሜን በኩል በሚገኘው ጎን ያሉት መጋረጃዎችም ርዝመታቸው 100 ክንድ ይሆናል፤ እንዲሁም 20 ቋሚዎችና ለቋሚዎቹ የሚሆኑ ከመዳብ የተሠሩ 20 መሰኪያዎች ይኖራሉ፤ በቋሚዎቹም ላይ ማንጠልጠያዎችና ማያያዣዎች ይኖራሉ። 12  በስተ ምዕራብ አቅጣጫ በግቢው ወርድ ልክ 50 ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ይኖራሉ፤ አሥር ቋሚዎችና አሥር መሰኪያዎችም ይኖሯቸዋል። 13  በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ በፀሐይ መውጫ በኩል ያለው የግቢው ወርድ 50 ክንድ ነው። 14  በአንዱ በኩል 15 ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ይኖራሉ፤ ሦስት ቋሚዎችና ሦስት መሰኪያዎችም ይኖሯቸዋል። 15  በሌላኛውም በኩል 15 ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ይኖራሉ፤ ሦስት ቋሚዎችና ሦስት መሰኪያዎችም ይኖሯቸዋል። 16  “የግቢው መግቢያ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግ እንዲሁም በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ የበፍታ ድር ተሸምኖ የተሠራ 20 ክንድ ርዝመት ያለው መከለያ ይኑረው፤ አራት ቋሚዎችና ለቋሚዎቹ የሚሆኑ አራት መሰኪያዎችም ይኑሩት። 17  በግቢው ዙሪያ ያሉት ቋሚዎች በሙሉ ከብር የተሠሩ መቆንጠጫዎችና ከብር የተሠሩ ማንጠልጠያዎች ይኖሯቸዋል፤ መሰኪያዎቻቸው ግን ከመዳብ የተሠሩ ይሆናሉ። 18  ግቢው ርዝመቱ 100 ክንድ፣ ወርዱ 50 ክንድ ሆኖ በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠሩ 5 ክንድ ከፍታ ያላቸው መጋረጃዎች ይኖሩታል፤ ከመዳብ የተሠሩ መሰኪያዎችም ይኑሩት። 19  በማደሪያ ድንኳኑ ውስጥ ለሚቀርበው አገልግሎት የሚውሉት ቁሳቁሶችና ዕቃዎች በሙሉ እንዲሁም የድንኳኑ ካስማዎችና የግቢው ካስማዎች በሙሉ ከመዳብ የተሠሩ ይሆናሉ። 20  “አንተም መብራቶቹ ያለማቋረጥ እንዲበሩ ለመብራት የሚሆን ተጨቅጭቆ የተጠለለ የወይራ ዘይት እንዲያመጡልህ እስራኤላውያንን ታዛቸዋለህ። 21  አሮንና ወንዶች ልጆቹ መብራቶቹ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በምሥክሩ አጠገብ ካለው መጋረጃ ውጭ ከምሽት አንስቶ እስከ ጠዋት ድረስ በይሖዋ ፊት እንዲበሩ ያደርጋሉ። ይህ እስራኤላውያን በትውልዶቻቸው ሁሉ የሚፈጽሙት ዘላቂ ደንብ ነው።
[]
[]
[]
[]
12,484
28  “አንተም ለእኔ ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ ወንድምህን አሮንን ከወንዶች ልጆቹ ጋር ከእስራኤላውያን መካከል ለይተህ ትጠራዋለህ፤ አሮንን እንዲሁም የአሮንን ወንዶች ልጆች ናዳብን፣ አቢሁን፣ አልዓዛርንና ኢታምርን ትጠራቸዋለህ። 2  ለወንድምህ ለአሮንም ክብርና ውበት የሚያጎናጽፉትን ቅዱስ ልብሶች ትሠራለታለህ። 3  የጥበብ መንፈስ የሞላሁባቸውን ጥሩ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች ሁሉ አንተ ራስህ ታናግራቸዋለህ፤ እነሱም አሮን ለእኔ ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ እሱን ለመቀደስ ልብሶቹን ይሠሩለታል። 4  “የሚሠሯቸው ልብሶችም እነዚህ ናቸው፦ የደረት ኪስ፣ ኤፉድ፣ እጅጌ የሌለው ቀሚስ፣ በካሬ ንድፍ የተሸመነ ረጅም ቀሚስ፣ ጥምጥምና መቀነት፤ ወንድምህ አሮንና ወንዶች ልጆቹ ካህን ሆነው እንዲያገለግሉኝ እነዚህን ቅዱስ ልብሶች ይሠሩላቸዋል። 5  እነዚህ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ወርቁን፣ ሰማያዊውን ክር፣ ሐምራዊውን ሱፍ፣ ደማቁን ቀይ ማግና ጥሩውን በፍታ ተጠቅመው ይሠሯቸዋል። 6  “ከወርቅ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ ኤፉዱን ያዘጋጃሉ፤ ኤፉዱም ጥልፍ የተጠለፈበት ይሁን። 7  ኤፉዱ ላዩ ላይ የተጣበቁ ሁለት የትከሻ ጥብጣቦች የሚኖሩት ሲሆን እነሱም ኤፉዱን በሁለቱ ጫፎቹ ላይ ያያይዙታል። 8  ኤፉዱ ወዲያ ወዲህ እንዳይንቀሳቀስ ለማሰር የሚያገለግለው ከኤፉዱ ጋር የተያያዘው በሽመና የተሠራው መቀነት ልክ እንደ ኤፉዱ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠራ መሆን ይኖርበታል። 9  “ሁለት የኦኒክስ ድንጋዮችን ወስደህ የእስራኤልን ወንዶች ልጆች ስሞች ትቀርጽባቸዋለህ፤ 10  በትውልዳቸው ቅደም ተከተል መሠረት የስድስቱን ስሞች በአንዱ ድንጋይ ላይ፣ የቀሩትን የስድስቱን ስሞች ደግሞ በሌላኛው ድንጋይ ላይ ትቀርጻለህ። 11  አንድ ቅርጽ አውጪ በድንጋይ ላይ ማኅተም እንደሚቀርጽ ሁሉ የእስራኤልን ወንዶች ልጆች ስሞች በሁለቱ ድንጋዮች ላይ ይቀርጽባቸዋል። ከዚያም በወርቅ አቃፊዎች ውስጥ እንዲቀመጡ ታደርጋለህ። 12  ለእስራኤል ልጆች እንደ መታሰቢያ ድንጋዮች ሆነው እንዲያገለግሉ ሁለቱን ድንጋዮች በኤፉዱ የትከሻ ጥብጣቦች ላይ ታስቀምጣቸዋለህ፤ አሮንም እንደ መታሰቢያ ሆነው እንዲያገለግሉ ስሞቻቸውን በሁለቱ የትከሻ ጥብጣቦች ላይ በይሖዋ ፊት ይሸከማል። 13  አንተም የወርቅ አቃፊዎችን 14  እንዲሁም እንደ ገመድ የተገመዱ ሁለት ሰንሰለቶችን ከንጹሕ ወርቅ ትሠራለህ፤ የተገመዱትንም ሰንሰለቶች ከአቃፊዎቹ ጋር አያይዛቸው። 15  “የፍርዱን የደረት ኪስ የጥልፍ ባለሙያ እንዲሠራው ታደርጋለህ። የደረት ኪሱ ልክ እንደ ኤፉዱ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ መሠራት ይኖርበታል። 16  ለሁለት በሚታጠፍበትም ጊዜ ቁመቱ አንድ ስንዝር፣ ወርዱ ደግሞ አንድ ስንዝር የሆነ ካሬ ይሁን። 17  የከበሩ ድንጋዮችን በአራት ረድፍ በማቀፊያ ውስጥ ታደርግበታለህ። በመጀመሪያው ረድፍ ሩቢ፣ ቶጳዝዮንና መረግድ ይደርደር። 18  በሁለተኛው ረድፍ በሉር፣ ሰንፔርና ኢያስጲድ ይደርደር። 19  በሦስተኛው ረድፍ ለሼም፣ አካትምና አሜቴስጢኖስ ይደርደር። 20  በአራተኛውም ረድፍ ክርስቲሎቤ፣ ኦኒክስና ጄድ ይደርደር። በወርቅ አቃፊዎችም ውስጥ ይቀመጡ። 21  ድንጋዮቹም የእስራኤልን ወንዶች ልጆች ስሞች ማለትም 12ቱን በየስማቸው የሚወክሉ ይሆናሉ። ለ12ቱም ነገዶች ልክ ማኅተም በሚቀረጽበት መንገድ ለእያንዳንዳቸው በየስማቸው ይቀረጽላቸው። 22  “በደረት ኪሱም ላይ ከንጹሕ ወርቅ እንደተሠሩ ገመዶች የተጎነጎኑ ሰንሰለቶችን ትሠራለህ። 23  ለደረት ኪሱም ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተህ ሁለቱን ቀለበቶች ከሁለቱ የደረት ኪሱ ጫፎች ጋር ታያይዛቸዋለህ። 24  ሁለቱን የወርቅ ገመዶችም በደረት ኪሱ ዳርና ዳር ባሉት ጫፎች ላይ በሚገኙት በሁለቱ ቀለበቶች ውስጥ ታስገባቸዋለህ። 25  የሁለቱን ገመዶች ሁለት ጫፎች በሁለቱ አቃፊዎች ውስጥ ታስገባለህ፤ እነሱንም ከኤፉዱ የትከሻ ጥብጣቦች ጋር በፊት በኩል ታያይዛቸዋለህ። 26  ሁለት የወርቅ ቀለበቶችንም ሠርተህ በኤፉዱ በኩል በሚውለው በደረት ኪሱ ውስጠኛ ጠርዝ ላይ ባሉት ሁለት ጫፎች ላይ ታደርጋቸዋለህ። 27  ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችንም ሠርተህ በኤፉዱ በፊት በኩል ከሁለቱ የትከሻ ጥብጣቦች በታች ኤፉዱ በተጋጠመበት ቦታ አካባቢ፣ በሽመና ከተሠራው የኤፉዱ መቀነት በላይ አድርጋቸው። 28  የደረት ኪሱ ከቦታው እንዳይንቀሳቀስ የደረት ኪሱ ቀለበቶች ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ገመድ መያያዝ ይኖርባቸዋል። ይህም የደረት ኪሱ ከመቀነቱ በላይ ከኤፉዱ ላይ ሳይንቀሳቀስ እንዲቀመጥ ያደርገዋል። 29  “አሮን ወደ ቅድስቱ በሚገባበት ጊዜ በይሖዋ ፊት ቋሚ መታሰቢያ እንዲሆን በልቡ ላይ በሚገኘው የፍርድ የደረት ኪስ የእስራኤልን ልጆች ስሞች ይሸከም። 30  ኡሪሙንና ቱሚሙን በፍርድ የደረት ኪሱ ውስጥ ታስቀምጣቸዋለህ፤ አሮን በይሖዋ ፊት ለመቅረብ በሚገባበት ጊዜ በልቡ ላይ መሆን አለባቸው፤ አሮን በይሖዋ ፊት በሚቀርብበት ጊዜ ለእስራኤላውያን ፍርድ መስጫውን ዘወትር በልቡ ላይ ይሸከም። 31  “እጅጌ የሌለውን የኤፉዱን ቀሚስ ሙሉ በሙሉ ከሰማያዊ ክር ትሠራዋለህ። 32  ከላይ በኩል መሃል ላይ የአንገት ማስገቢያ ይኖረዋል። የአንገት ማስገቢያውም ዙሪያውን በሽመና ባለሙያ የተሠራ ቅምቅማት ይኑረው። የአንገት ማስገቢያውም እንዳይቀደድ እንደ ጥሩር አንገትጌ ሆኖ ይሠራ። 33  በታችኛው ጠርዝ ዙሪያ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍና ከደማቅ ቀይ ማግ የተሠሩ ሮማኖችን አድርግ፤ በመሃል በመሃላቸውም የወርቅ ቃጭሎች አድርግ። 34  እጅጌ በሌለው ቀሚስ በታችኛው ጠርዝ ዙሪያ የወርቅ ቃጭል ከዚያም ሮማን፣ የወርቅ ቃጭል ከዚያም ሮማን እያፈራረቅክ አንጠልጥልበት። 35  አሮን በሚያገለግልበት ጊዜ ይህን ልብስ መልበስ አለበት፤ በይሖዋ ፊት ለመቅረብ ወደ መቅደሱ በሚገባበትና ከዚያ በሚወጣበት ጊዜ እንዳይሞት የቃጭሎቹ ድምፅ መሰማት አለበት። 36  “ከንጹሕ ወርቅም የሚያብረቀርቅ ጠፍጣፋ ወርቅ ሠርተህ ልክ ማኅተም በሚቀረጽበት መንገድ ‘ቅድስና የይሖዋ ነው’ ብለህ ትቀርጽበታለህ። 37  እሱንም በሰማያዊ ገመድ በጥምጥሙ ላይ እሰረው፤ በጥምጥሙ ላይ ከፊት በኩል ይሆናል። 38  በአሮን ግንባር ላይ ይሆናል፤ አሮንም አንድ ሰው ቅዱስ ከሆኑ ነገሮች ይኸውም እስራኤላውያን ቅዱስ ስጦታ አድርገው በሚያቀርቧቸው ጊዜ ከሚቀድሷቸው ነገሮች ጋር በተያያዘ ለሚፈጽመው ስህተት ተጠያቂ ይሆናል። በይሖዋም ፊት ተቀባይነት እንዲያገኙ ዘወትር በግንባሩ ላይ መሆን ይኖርበታል። 39  “ከጥሩ በፍታ ረጅም ቀሚስ በካሬ ንድፍ ትሸምንለታለህ፤ እንዲሁም ከጥሩ በፍታ ጥምጥም ትሠራለህ፤ በተጨማሪም በሽመና የተሠራ መቀነት ትሠራለህ። 40  “ለአሮን ወንዶች ልጆችም ክብርና ውበት የሚያጎናጽፏቸውን ረጃጅም ቀሚሶች፣ መቀነቶችና የራስ ቆቦች ትሠራላቸዋለህ። 41  ወንድምህን አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ታለብሳቸዋለህ፤ እንዲሁም ትቀባቸዋለህ፣ ትሾማቸዋለህ ደግሞም ትቀድሳቸዋለህ፤ እነሱም ካህናት ሆነው ያገለግሉኛል። 42  እርቃናቸውን የሚሸፍኑበት የበፍታ ቁምጣም ትሠራላቸዋለህ። ቁምጣውም ከወገባቸው እስከ ጭናቸው የሚደርስ ይሆናል። 43  በደል እንዳይሆንባቸውና እንዳይሞቱ አሮንና ወንዶች ልጆቹ ወደ መገናኛ ድንኳኑ በሚገቡበት ጊዜ ወይም ቅዱስ በሆነው ስፍራ ለማገልገል ወደ መሠዊያው በሚቀርቡበት ጊዜ እነዚህን ልብሶች መልበስ አለባቸው። ይህ ለእሱም ሆነ ከእሱ በኋላ ለሚመጡት ዘሮቹ ዘላለማዊ ደንብ ነው።
[]
[]
[]
[]
12,485
29  “ለእኔ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ እነሱን ለመቀደስ የምታደርገው ነገር ይህ ነው፦ እንከን የሌለበትን አንድ ወይፈንና እንከን የሌለባቸውን ሁለት አውራ በጎች ውሰድ፤ 2  እንዲሁም ቂጣ፣ በዘይት ከተለወሰ ሊጥ የተጋገረ የቀለበት ቅርጽ ያለው እርሾ ያልገባበት ዳቦና ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ ውሰድ። እነዚህንም ከላመ የስንዴ ዱቄት ጋግረህ 3  በቅርጫት ውስጥ ታደርጋቸዋለህ፤ በቅርጫት ውስጥ አድርገህም ከወይፈኑና ከሁለቱ አውራ በጎች ጋር ታቀርባቸዋለህ። 4  “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ታቀርባቸዋለህ፤ በውኃም ታጥባቸዋለህ። 5  ከዚያም ልብሶቹን ወስደህ ረጅሙን ቀሚስ፣ እጅጌ የሌለውን የኤፉዱን ቀሚስ፣ ኤፉዱንና የደረት ኪሱን አሮንን አልብሰው፤ በሽመና የተሠራውን የኤፉዱን መቀነትም ወገቡ ላይ ጠበቅ አድርገህ ታስርለታለህ። 6  ጥምጥሙንም በራሱ ላይ ታደርግለታለህ፤ በጥምጥሙም ላይ ለአምላክ የተወሰኑ መሆንን የሚያሳየውን ቅዱስ ምልክት ታደርጋለህ፤ 7  የቅብዓት ዘይቱንም ወስደህ በራሱ ላይ በማፍሰስ ትቀባዋለህ። 8  “ከዚያም ወንዶች ልጆቹን አምጥተህ ረጃጅሞቹን ቀሚሶች አልብሳቸው፤ 9  አሮንንና ወንዶች ልጆቹን መቀነቱን አስታጥቃቸው፤ የራስ ቆባቸውንም አድርግላቸው፤ ክህነቱም ዘላለማዊ ደንብ ሆኖ የእነሱ ይሆናል። በዚህም መንገድ አሮንና ወንዶች ልጆቹ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉ ትሾማቸዋለህ። 10  “ከዚያም ወይፈኑን በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ታቀርበዋለህ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም በወይፈኑ ራስ ላይ እጆቻቸውን ይጭናሉ። 11  ወይፈኑንም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በይሖዋ ፊት እረደው። 12  ከወይፈኑም ደም ላይ የተወሰነውን ወስደህ በጣትህ በመሠዊያው ቀንዶች ላይ አድርግ፤ የቀረውንም ደም በሙሉ መሠዊያው ሥር አፍስሰው። 13  ከዚያም አንጀቱን የሸፈነውን ስብ ሁሉ፣ በጉበቱ ላይ ያለውን ሞራ፣ ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ያለውን ስብ ውሰድ፤ በመሠዊያውም ላይ እንዲጨሱ አቃጥላቸው። 14  የወይፈኑን ሥጋ፣ ቆዳውንና ፈርሱን ግን ከሰፈሩ ውጭ አውጥተህ በእሳት ታቃጥለዋለህ። ይህ የኃጢአት መባ ነው። 15  “ከዚያም አንዱን አውራ በግ ውሰድ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ይጫኑ። 16  አንተም አውራውን በግ እረደው፤ ደሙንም ወስደህ በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ እርጨው። 17  አውራውንም በግ በየብልቱ ቆራርጠው፤ ሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም እጠባቸው፤ ከዚያም የተቆራረጡትን ብልቶች ከጭንቅላቱ ጋር አሰናድተህ አስቀምጣቸው። 18  አውራውንም በግ ሙሉ በሙሉ በማቃጠል በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ አድርገው። ይህም ለይሖዋ የሚቀርብ የሚቃጠል መባ ይኸውም ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ነው። ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነው። 19  “ከዚያም ሌላኛውን አውራ በግ ትወስዳለህ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ይጭኑበታል። 20  አንተም አውራውን በግ እረደው፤ ከደሙም ወስደህ የአሮንን የቀኝ ጆሮ ጫፍና የወንዶች ልጆቹን የቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጃቸውን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግራቸውን አውራ ጣት ቀባ፤ ደሙንም በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ እርጨው። 21  በመሠዊያው ላይ ካለው ደምና ከቅብዓት ዘይቱ ውሰድ፤ ከዚያም አሮንና ልብሶቹ እንዲሁም ወንዶች ልጆቹና ልብሶቻቸው ቅዱስ እንዲሆኑ በአሮንና በልብሶቹ እንዲሁም በወንዶች ልጆቹና በልብሶቻቸው ላይ እርጨው። 22  “አውራው በግ የክህነት ሹመት ሥርዓት በሚካሄድበት ጊዜ የሚቀርብ ስለሆነ ከአውራው በግ ላይ ስቡን፣ ላቱን፣ አንጀቱን የሚሸፍነውን ስብ፣ የጉበቱን ሞራ፣ ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ያለውን ስብ እንዲሁም ቀኝ እግሩን ውሰድ። 23  በተጨማሪም በይሖዋ ፊት ካለው ቂጣ ከተቀመጠበት ቅርጫት ውስጥ ቂጣውን፣ በዘይት ከተለወሰ ሊጥ የተጋገረውን የቀለበት ቅርጽ ያለው ዳቦና ስሱን ቂጣ ውሰድ። 24  ሁሉንም በአሮን እጅና በወንዶች ልጆቹ እጅ ላይ አስቀምጣቸው፤ ከዚያም በይሖዋ ፊት እንደሚወዘወዝ መባ ወዲያና ወዲህ ወዝውዛቸው። 25  በይሖዋም ፊት ደስ የሚያሰኝ መዓዛ እንዲሆን ከእጃቸው ላይ ወስደህ በመሠዊያው ላይ ባለው በሚቃጠለው መባ ላይ ታቃጥላቸዋለህ። ይህ ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነው። 26  “ከዚያም ለአሮን የክህነት ሹመት ሥርዓት የሚቀርበውን አውራ በግ ፍርምባ ወስደህ በይሖዋ ፊት እንደሚወዘወዝ መባ ወዲያና ወዲህ ወዝውዘው፤ እሱም የአንተ ድርሻ ይሆናል። 27  ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ የክህነት ሹመት ሥርዓት ከቀረበው አውራ በግ ተወስዶ ለሚወዘወዝ መባ የቀረበውን ፍርምባና የተቀደሰ ድርሻ እንዲሆን የተወዘወዘውን እግር ትቀድሳቸዋለህ። 28  ይህም የተቀደሰ ድርሻ ስለሆነ የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ይሆናል፤ ይህም እስራኤላውያን የሚፈጽሙት ዘላለማዊ ሥርዓት ነው፤ ይህ ድርሻ እስራኤላውያን የሚያቀርቡት የተቀደሰ ድርሻ ይሆናል። ከሚያቀርቧቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ላይ ለይሖዋ የሚሰጥ የተቀደሰ ድርሻቸው ነው። 29  “የአሮን ቅዱስ ልብሶችም ከእሱ በኋላ የሚመጡት ወንዶች ልጆቹ በሚቀቡበትና ካህናት ሆነው በሚሾሙበት ጊዜ ይገለገሉባቸዋል። 30  ከወንዶች ልጆቹ መካከል እሱን የሚተካውና በቅዱሱ ስፍራ ለማገልገል ወደ መገናኛ ድንኳኑ የሚገባው ካህን ለሰባት ቀን ይለብሳቸዋል። 31  “ለክህነት ሹመት ሥርዓት የሚቀርበውን አውራ በግ ወስደህ ሥጋውን በተቀደሰ ስፍራ ትቀቅለዋለህ። 32  አሮንና ወንዶች ልጆቹ የአውራውን በግ ሥጋና በቅርጫቱ ውስጥ ያለውን ቂጣ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ይበሉታል። 33  እነሱን ካህናት አድርጎ ለመሾምና ለመቀደስ ማስተሰረያ ሆነው የቀረቡትን ነገሮች ይበላሉ። ሆኖም እነዚህ ነገሮች የተቀደሱ ስለሆኑ ያልተፈቀደለት ሰው ሊበላቸው አይችልም። 34  ለክህነት ሹመት ሥርዓቱ መሥዋዕት ሆኖ ከቀረበው ሥጋና ቂጣ ተርፎ ያደረ ካለ የተረፈውን በእሳት አቃጥለው። የተቀደሰ ስለሆነ መበላት የለበትም። 35  “እኔ ባዘዝኩህ ሁሉ መሠረት ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ በዚሁ መንገድ ታደርግላቸዋለህ። እነሱን ካህናት አድርገህ ለመሾም ሰባት ቀን ይፈጅብሃል። 36  ለማስተሰረያ እንዲሆን የኃጢአት መባ የሚሆነውን በሬ በየዕለቱ ታቀርባለህ፤ ለመሠዊያውም ማስተሰረያ በማቅረብ መሠዊያውን ከኃጢአት ታነጻዋለህ፤ መሠዊያውን ለመቀደስም ቀባው። 37  መሠዊያውን ለማስተሰረይ ሰባት ቀን ይፈጅብሃል፤ እጅግ ቅዱስ መሠዊያ እንዲሆንም ቀድሰው። መሠዊያውን የሚነካ ማንኛውም ሰው ቅዱስ መሆን አለበት። 38  “በመሠዊያውም ላይ የምታቀርበው እነዚህን ይሆናል፦ አንድ ዓመት የሆናቸው ሁለት የበግ ጠቦቶችን በየቀኑ ሳታቋርጥ ታቀርባለህ። 39  አንደኛውን የበግ ጠቦት ጠዋት ላይ ታቀርበዋለህ፤ ሌላኛውን የበግ ጠቦት ደግሞ አመሻሹ ላይ ታቀርበዋለህ። 40  ተጨቅጭቆ በተጠለለ አንድ አራተኛ ሂን ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ አንድ አሥረኛ የላመ ዱቄትና ለመጠጥ መባ የሚሆን አንድ አራተኛ ሂን የወይን ጠጅ ከመጀመሪያው የበግ ጠቦት ጋር ይቅረብ። 41  ሁለተኛውንም የበግ ጠቦት ልክ ማለዳ ላይ ከምታቀርባቸው ጋር ተመሳሳይ ከሆኑ የእህልና የመጠጥ መባዎች ጋር አመሻሹ ላይ ታቀርበዋለህ። ይህን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አድርገህ ታቀርበዋለህ። 42  ይህም እኔ እናንተን ለማነጋገር ራሴን በምገልጥበት በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በመጪዎቹ ትውልዶቻችሁ ሁሉ በይሖዋ ፊት ዘወትር የሚቀርብ የሚቃጠል መባ ይሆናል። 43  “እኔም በዚያ ራሴን ለእስራኤላውያን እገልጣለሁ፤ ያም ስፍራ በክብሬ የተቀደሰ ይሆናል። 44  መገናኛ ድንኳኑንና መሠዊያውን እቀድሰዋለሁ፤ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እቀድሳቸዋለሁ። 45  እኔም በእስራኤል ሕዝብ መካከል እኖራለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ። 46  እነሱም በመካከላቸው እኖር ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው እኔ አምላካቸው ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ያውቃሉ። እኔ አምላካቸው ይሖዋ ነኝ።
[]
[]
[]
[]
12,486
3  ሙሴ የምድያም ካህን የሆነው የአማቱ የዮቶር መንጋ እረኛ ሆነ። እሱም መንጋውን እየመራ ወደ ምድረ በዳው ምዕራባዊ ክፍል ከተጓዘ በኋላ በመጨረሻ ወደ እውነተኛው አምላክ ተራራ ወደ ኮሬብ ደረሰ። 2  ከዚያም የይሖዋ መልአክ በቁጥቋጦ መሃል በሚነድ የእሳት ነበልባል ውስጥ ተገለጠለት። እሱም ትኩር ብሎ ሲመለከት ቁጥቋጦው በእሳት ቢያያዝም አለመቃጠሉን አስተዋለ። 3  ስለዚህ ሙሴ “ይህ እንግዳ ነገር ምን እንደሆነ ለማወቅና ቁጥቋጦው የማይቃጠለው ለምን እንደሆነ ለማየት እስቲ ቀረብ ልበል” አለ። 4  ይሖዋም ሙሴ ሁኔታውን ለማየት ቀረብ ማለቱን ሲመለከት ከቁጥቋጦው መሃል “ሙሴ! ሙሴ!” ሲል ጠራው፤ እሱም “አቤት” አለ። 5  ከዚያም አምላክ “ከዚህ በላይ እንዳትቀርብ። የቆምክበት ስፍራ ቅዱስ መሬት ስለሆነ ጫማህን አውልቅ” አለው። 6  እሱም በመቀጠል “እኔ የአባትህ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ ነኝ” አለው። በዚህ ጊዜ ሙሴ እውነተኛውን አምላክ ለማየት ስለፈራ ፊቱን ከለለ። 7  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “በግብፅ የሚኖረውን የሕዝቤን መከራ በእርግጥ አይቻለሁ፤ አስገድደው በሚያሠሯቸው ሰዎች የተነሳ የሚያሰሙትን ጩኸት ሰምቻለሁ፤ እየደረሰባቸው ያለውንም ሥቃይ በሚገባ አውቃለሁ። 8  እኔም ከግብፃውያን እጅ ልታደጋቸው እንዲሁም ከዚያ ምድር አውጥቼ ወደ ከነአናውያን፣ ወደ ሂታውያን፣ ወደ አሞራውያን፣ ወደ ፈሪዛውያን፣ ወደ ሂዋውያንና ወደ ኢያቡሳውያን ግዛት ይኸውም ወተትና ማር ወደምታፈሰው መልካምና ሰፊ ምድር ላስገባቸው እወርዳለሁ። 9  እነሆ የእስራኤል ሕዝብ የሚያሰማው ጩኸት ወደ እኔ ደርሷል፤ ግብፃውያኑ እነሱን በመጨቆን እያደረሱባቸው ያለውን በደል ተመልክቻለሁ። 10  ስለዚህ አሁን ና፤ ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ፤ አንተም ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ታወጣለህ።” 11  ይሁን እንጂ ሙሴ እውነተኛውን አምላክ “ወደ ፈርዖን የምሄደውና እስራኤላውያንን ከግብፅ የማወጣው ለመሆኑ እኔ ማን ነኝ?” አለው። 12  እሱም በዚህ ጊዜ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ የላክሁህ እኔ ለመሆኔም ምልክቱ ይህ ነው፦ ሕዝቡን ከግብፅ ካወጣሃቸው በኋላ እውነተኛውን አምላክ በዚህ ተራራ ላይ ታገለግላላችሁ” አለው። 13  ሆኖም ሙሴ እውነተኛውን አምላክ “ወደ እስራኤላውያን ሄጄ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል’ ስላቸው እነሱ ደግሞ ‘ስሙ ማን ነው?’ ብለው ቢጠይቁኝ ምን ልበላቸው?” አለው። 14  በዚህ ጊዜ አምላክ ሙሴን “መሆን የምፈልገውን እሆናለሁ” አለው። በመቀጠልም “እስራኤላውያንን ‘“እሆናለሁ” ወደ እናንተ ልኮኛል’ በላቸው” አለው። 15  ከዚያም አምላክ ሙሴን በድጋሚ እንዲህ አለው፦ “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ የሆነው ይሖዋ ወደ እናንተ ልኮኛል።’ ይህ ለዘላለም ስሜ ነው፤ ከትውልድ እስከ ትውልድ የምታወሰውም በዚህ ነው። 16  አሁን ሄደህ የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሰብስብ፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ የሆነው ይሖዋ ተገልጦልኝ እንዲህ አለኝ፦ “እናንተንም ሆነ ግብፅ ውስጥ እየደረሰባችሁ ያለውን ነገር በእርግጥ ተመልክቻለሁ። 17  በመሆኑም እንዲህ አልኩ፦ ግብፃውያን ከሚያደርሱባችሁ መከራ አውጥቼ ከነአናውያን፣ ሂታውያን፣ አሞራውያን፣ ፈሪዛውያን፣ ሂዋውያንና ኢያቡሳውያን ወደሚኖሩባት ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር አስገባችኋለሁ።”’ 18  “እነሱም በእርግጥ ቃልህን ይሰማሉ፤ አንተና የእስራኤል ሽማግሌዎችም ወደ ግብፁ ንጉሥ ሄዳችሁ እንዲህ በሉት፦ ‘የዕብራውያን አምላክ ይሖዋ አነጋግሮን ነበር። በመሆኑም እባክህ ለአምላካችን ለይሖዋ መሥዋዕት ለማቅረብ የሦስት ቀን መንገድ ወደ ምድረ በዳ እንድንጓዝ ፍቀድልን።’ 19  ይሁንና የግብፁ ንጉሥ ኃያል የሆነ ክንድ ካላስገደደው በስተቀር እንድትሄዱ እንደማይፈቅድላችሁ እኔ ራሴ በሚገባ አውቃለሁ። 20  በመሆኑም እጄን እዘረጋለሁ፤ ግብፅንም በመካከሏ በምፈጽማቸው ድንቅ ነገሮች ሁሉ እመታለሁ፤ ከዚያ በኋላ ይለቃችኋል። 21  እኔም ለዚህ ሕዝብ በግብፃውያን ፊት ሞገስ እሰጠዋለሁ፤ በምትወጡበትም ጊዜ በምንም ዓይነት ባዶ እጃችሁን አትሄዱም። 22  እያንዳንዷ ሴት ከጎረቤቷና ቤቷ ካረፈችው ሴት የብርና የወርቅ ዕቃዎችን እንዲሁም ልብሶችን ትጠይቅ፤ እነዚህንም ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቻችሁ ታደርጉላቸዋላችሁ፤ ግብፃውያኑንም ትበዘብዛላችሁ።”
[]
[]
[]
[]
12,487
30  “ዕጣን የሚጨስበት መሠዊያ ትሠራለህ፤ ከግራር እንጨትም ትሠራዋለህ። 2  ርዝመቱ አንድ ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ ሆኖ አራቱም ጎኖቹ እኩል ይሁኑ፤ ቁመቱ ደግሞ ሁለት ክንድ ይሁን። ቀንዶቹም ከዚያው ወጥ ሆነው የተሠሩ ይሆናሉ። 3  ላዩን፣ ሁሉንም ጎኖቹን እንዲሁም ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ትለብጠዋለህ፤ ዙሪያውንም የወርቅ ክፈፍ ትሠራለታለህ። 4  በተጨማሪም በሁለቱ ተቃራኒ ጎኖቹ ላይ ከክፈፉ በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ትሠራለታለህ፤ ቀለበቶቹም መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉት መሎጊያዎች የሚገቡባቸው ይሆናሉ። 5  መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው። 6  ራሴን ለአንተ ከምገልጥበት ከምሥክሩ ታቦት አጠገብ ካለው መጋረጃ በፊት ይኸውም ምሥክሩን ከሚጋርደው መከለያ በፊት ታስቀምጠዋለህ። 7  “አሮንም ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን ያጨስበታል፤ በየማለዳው መብራቶቹን በሚያዘገጃጅበት ጊዜም ዕጣኑ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርጋል። 8  በተጨማሪም አሮን አመሻሹ ላይ መብራቶቹን በሚያበራበት ጊዜ ዕጣኑን ያጨሰዋል። ይህም በትውልዶቻችሁ ሁሉ ዘወትር በይሖዋ ፊት የሚቀርብ የዕጣን መባ ነው። 9  በዚህ መሠዊያ ላይ ያልተፈቀደ ዕጣን ወይም የሚቃጠል መባ አሊያም የእህል መባ አታቅርቡ፤ እንዲሁም በላዩ ላይ የመጠጥ መባ አታፍስሱ። 10  አሮንም በዓመት አንድ ጊዜ በቀንዶቹ ላይ ማስተሰረያ ያድርግ። ለማስተሰረያ ከቀረበው የኃጢአት መባ ላይ የተወሰነ ደም ወስዶ በዓመት አንድ ጊዜ ለመሠዊያው ማስተሰረያ ያደርጋል፤ ይህም በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይደረጋል። ይህ ለይሖዋ እጅግ የተቀደሰ ነው።” 11  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 12  “የሕዝብ ቆጠራ በማካሄድ የእስራኤልን ልጆች በምትቆጥርበት ጊዜ ሁሉ እያንዳንዱ ሰው በቆጠራው ወቅት ለይሖዋ ስለ ሕይወቱ ቤዛ መስጠት አለበት። ይህን የሚያደርጉት በሚመዘገቡበት ጊዜ መቅሰፍት እንዳይመጣባቸው ነው። 13  የተመዘገቡት ሁሉ የሚሰጡት ይህን ነው፦ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት ግማሽ ሰቅል ይሰጣሉ። አንድ ሰቅል ሃያ ጌራ ነው። ለይሖዋ የሚሰጠው መዋጮ ግማሽ ሰቅል ነው። 14  ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ሆኗቸው የተመዘገቡት ሁሉ ለይሖዋ መዋጮ ይሰጣሉ። 15  ለሕይወታችሁ ማስተሰረያ እንዲሆን ለይሖዋ መዋጮ በምትሰጡበት ጊዜ ባለጸጋው ከግማሽ ሰቅል አብልጦ፣ ችግረኛውም ከግማሽ ሰቅል አሳንሶ አይስጥ። 16  ለሕይወታችሁ ማስተሰረያ በመሆን በይሖዋ ፊት ለእስራኤላውያን እንደ መታሰቢያ ሆኖ እንዲያገለግል ለማስተሰረያ የቀረበውን የብር ገንዘብ ከእስራኤላውያን ወስደህ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ለሚቀርበው አገልግሎት ትሰጠዋለህ።” 17  በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 18  “ለመታጠቢያ እንዲሆን ከመዳብ ገንዳና ማስቀመጫውን ሥራ፤ በመገናኛ ድንኳኑና በመሠዊያው መካከል አስቀምጠው፤ ውኃም ጨምርበት። 19  አሮንና ወንዶች ልጆቹም እጃቸውንና እግራቸውን ይታጠቡበታል። 20  ወደ መገናኛ ድንኳኑ በሚገቡበት ወይም ለማገልገልና በእሳት የሚቀርብ መባ ለይሖዋ ለማቅረብ ወደ መሠዊያው በሚቀርቡበት ጊዜ እንዳይሞቱ በውኃ ይታጠባሉ። 21  እንዳይሞቱ እጃቸውንና እግራቸውን ይታጠቡ፤ ይህም ለእሱና ለዘሮቹ በትውልዶቻቸው ሁሉ ዘላለማዊ ሥርዓት ሆኖ ያገልግል።” 22  ይሖዋም እንዲህ በማለት ሙሴን ማነጋገሩን ቀጠለ፦ 23  “አንተም ጥሩ መዓዛ ያላቸውን የሚከተሉትን ምርጥ ቅመሞች ውሰድ፦ 500 ሰቅል የረጋ ከርቤ፣ የዚህን ግማሽ ይኸውም 250 ሰቅል ጣፋጭ ቀረፋ፣ 250 ሰቅል ጥሩ መዓዛ ያለው ጠጅ ሣር፣ 24  እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 500 ሰቅል ብርጉድ እንዲሁም አንድ ሂን የወይራ ዘይት። 25  ከእነዚህም ቅዱስ የቅብዓት ዘይት አዘጋጅ፤ በብልሃት የተቀመመ መሆን ይኖርበታል። ይህም ቅዱስ የቅብዓት ዘይት ይሆናል። 26  “አንተም የመገናኛ ድንኳኑንና የምሥክሩን ታቦት 27  እንዲሁም ጠረጴዛውንና ዕቃዎቹን በሙሉ፣ መቅረዙንና ዕቃዎቹን፣ የዕጣን መሠዊያውን፣ 28  የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያና ዕቃዎቹን በሙሉ እንዲሁም የውኃ ገንዳውንና ማስቀመጫውን በዘይቱ ትቀባለህ። 29  እጅግ ቅዱስ እንዲሆኑም ቀድሳቸው። የሚነካቸው ማንኛውም ሰው ቅዱስ መሆን አለበት። 30  አንተም አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ትቀባቸዋለህ፤ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝም ትቀድሳቸዋለህ። 31  “አንተም ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ትነግራቸዋለህ፦ ‘በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህ ምንጊዜም ለእኔ ቅዱስ የቅብዓት ዘይት ይሆናል። 32  ይህ ማንም ሰው ሰውነቱን የሚቀባው አይደለም፤ እንዲሁም በተመሳሳይ መንገድ በመቀመም እንዲህ ያለ ቅባት ማዘጋጀት የለባችሁም። ይህ የተቀደሰ ነገር ነው። ለእናንተም ምንጊዜም የተቀደሰ ይሆናል። 33  ይህን የመሰለ ቅባት የሚሠራና ያልተፈቀደለትን ሰው የሚቀባ ማንኛውም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ።’” 34  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንተም ጥሩ መዓዛ ካላቸው ቅመሞች ይኸውም ከሚንጠባጠብ ሙጫ፣ ከኦኒካ፣ ከሚሸት ሙጫ እንዲሁም ከንጹሕ ነጭ ዕጣን እኩል መጠን ውሰድ። 35  ከዚያም ዕጣን አድርገህ አዘጋጀው፤ ይህም ዕጣን በብልሃት የተቀመመ፣ ጨው የተጨመረበት፣ ንጹሕና ቅዱስ መሆን ይኖርበታል። 36  ከእሱም የተወሰነውን ወቅጠህ በማላም ራሴን ለአንተ በምገልጥበት በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ባለው ምሥክር ፊት ታስቀምጠዋለህ። ይህም ለእናንተ እጅግ ቅዱስ መሆን ይኖርበታል። 37  በተመሳሳይ መንገድ የተቀመመ ዕጣን ለራስህ ማዘጋጀት የለብህም። ለይሖዋ የተቀደሰ እንደሆነ አድርገህ ልትመለከተው ይገባል። 38  በመዓዛው ለመደሰት ሲል ይህን የመሰለ ዕጣን የሚያዘጋጅ ማንኛውም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ።”
[]
[]
[]
[]
12,488
31  ይሖዋ እንዲህ በማለት ሙሴን ማነጋገሩን ቀጠለ፦ 2  “እንግዲህ እኔ ከይሁዳ ነገድ የሆነው የሁር ልጅ ዖሪ የወለደውን ባስልኤልን መርጬዋለሁ። 3  ደግሞም ጥበብ፣ ማስተዋልና እውቀት በመስጠት በማንኛውም ዓይነት የእጅ ሙያ የተካነ እንዲሆን በአምላክ መንፈስ እሞላዋለሁ፤ 4  ይህን የማደርገው የተለያዩ ንድፎችን እንዲያወጣ፣ በወርቅ፣ በብርና በመዳብ የተለያዩ ነገሮችን እንዲሠራ፣ 5  ፈርጥ የሚሆኑትን ድንጋዮች እንዲቀርጽና በቦታቸው እንዲያስቀምጥ እንዲሁም ከእንጨት ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን እንዲሠራ ነው። 6  በተጨማሪም ከዳን ነገድ የሆነውን የአሂሳማክን ልጅ ኤልያብን ረዳት እንዲሆነው መርጬዋለሁ፤ እኔ ያዘዝኩህን የሚከተሉትን ነገሮች በሙሉ እንዲሠሩ ጥሩ ችሎታ ባላቸው ሰዎች ሁሉ ልብ ውስጥ ጥበብን አኖራለሁ፦ 7  የመገናኛ ድንኳኑን፣ የምሥክሩን ታቦትና በላዩ ላይ ያለውን መክደኛ፣ የድንኳኑን ቁሳቁስ በሙሉ፣ 8  ጠረጴዛውንና ዕቃዎቹን፣ ከንጹሕ ወርቅ የሚሠራውን መቅረዝና ዕቃዎቹን በሙሉ፣ የዕጣን መሠዊያውን፣ 9  የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያና ዕቃዎቹን በሙሉ፣ መታጠቢያ ገንዳውንና መቆሚያውን፣ 10  ጥሩ ሆነው የተሸመኑትን ልብሶች፣ የካህኑን የአሮንን ቅዱስ ልብሶች፣ ወንዶች ልጆቹ ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚለብሷቸውን ልብሶች፣ 11  የቅብዓት ዘይቱንና ለመቅደሱ የሚሆነውን ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን። ማንኛውንም ነገር ልክ እኔ ባዘዝኩህ መሠረት ይሠሩታል።” 12  በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 13  “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እናንተን የምቀድሳችሁ እኔ ይሖዋ መሆኔን እንድታውቁ የሚያደርግ፣ በትውልዶቻችሁ ሁሉ በእኔና በእናንተ መካከል ያለ ምልክት ስለሆነ በተለይ ሰንበቴን ማክበር አለባችሁ። 14  ለእናንተ የተቀደሰ ስለሆነ ሰንበትን አክብሩ። ሰንበትን የሚያረክስ ሰው ይገደል። ማንም ሰው በዚያ ቀን ሥራ ቢሠራ ያ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት። 15  ስድስት ቀን ሥራ መሥራት ይቻላል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ሰንበት ነው። ለይሖዋ የተቀደሰ ነው። በሰንበት ቀን ሥራ የሚሠራ ማንም ሰው ይገደል። 16  እስራኤላውያን ሰንበትን መጠበቅ አለባቸው፤ በትውልዶቻቸው ሁሉ ሰንበትን ማክበር አለባቸው። ይህ ዘላቂ ቃል ኪዳን ነው። 17  በእኔና በእስራኤል ሕዝብ መካከል ያለ ዘላለማዊ ምልክት ነው፤ ምክንያቱም ይሖዋ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ ሠርቶ በማጠናቀቅ ሥራውን ያቆመውና ያረፈው በሰባተኛው ቀን ነው።’” 18  በሲና ተራራ ላይ ከእሱ ጋር ተነጋግሮ እንደጨረሰ የምሥክሩን ሁለት ጽላቶች ይኸውም በአምላክ ጣት የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላቶች ለሙሴ ሰጠው።
[]
[]
[]
[]
12,489
32  በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሙሴ ከተራራው ላይ ሳይወርድ እንደቆየ አየ። በመሆኑም አሮንን ከበው እንዲህ አሉት፦ “እንግዲህ ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣን ያ ሙሴ ምን እንደደረሰበት ስለማናውቅ በል ተነስተህ ከፊት ከፊታችን የሚሄድ አምላክ ሥራልን።” 2  አሮንም “በሚስቶቻችሁ እንዲሁም በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ጆሮዎች ላይ ያሉትን የወርቅ ጉትቻዎች አውልቃችሁ አምጡልኝ” አላቸው። 3  በመሆኑም ሕዝቡ ሁሉ በጆሮዎቻቸው ላይ የነበሩትን የወርቅ ጉትቻዎች እያወለቁ ወደ አሮን ያመጡ ጀመር። 4  እሱም ወርቁን ከእነሱ ወስዶ በቅርጽ ማውጫ ቅርጽ አወጣለት፤ የጥጃ ሐውልትም አድርጎ ሠራው። እነሱም “እስራኤል ሆይ፣ ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው” ይሉ ጀመር። 5  አሮንም ይህን ሲያይ በምስሉ ፊት መሠዊያ ሠራ። ከዚያም ድምፁን ከፍ አድርጎ “ነገ ለይሖዋ የሚከበር በዓል አለ” ሲል ተናገረ። 6  በመሆኑም በማግስቱ በማለዳ ተነስተው የሚቃጠል መባና የኅብረት መሥዋዕት ያቀርቡ ጀመር። ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ። ከዚያም ሊጨፍሩ ተነሱ። 7  በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከግብፅ ምድር መርተህ ያወጣኸው ሕዝብህ ምግባረ ብልሹ ስለሆነ ሂድ፣ ውረድ። 8  እንዲሄዱበት ካዘዝኳቸው መንገድ ፈጥነው ዞር ብለዋል። ለራሳቸውም የጥጃ ሐውልት ሠርተዋል፤ ለእሱም እየሰገዱና መሥዋዕት እያቀረቡ ‘እስራኤል ሆይ፣ ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው’ እያሉ ነው።” 9  ይሖዋም በመቀጠል ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ ግትር መሆኑን ተመልክቻለሁ። 10  እንግዲህ አሁን ቁጣዬ እንዲነድባቸውና እንዳጠፋቸው ተወኝ፤ አንተን በእነሱ ምትክ ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ።” 11  ሙሴም አምላኩን ይሖዋን ተማጸነ፤ እንዲህም አለ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ በታላቅ ኃይልና በብርቱ እጅ ከግብፅ ምድር ካወጣሃቸው በኋላ በሕዝብህ ላይ ቁጣህ የሚነደው ለምንድን ነው? 12  ግብፃውያንስ ‘ቀድሞውንም ቢሆን መርቶ ያወጣቸው ተንኮል አስቦ ነው። በተራሮች ላይ ሊገድላቸውና ከምድር ገጽ ሊያጠፋቸው ፈልጎ ነው’ ለምን ይበሉ? ከሚነደው ቁጣህ ተመለስ፤ በሕዝብህ ላይ ይህን ጥፋት ለማምጣት ያደረግከውን ውሳኔ እስቲ እንደገና አስበው። 13  ‘ዘራችሁን በሰማያት ላይ እንዳሉት ከዋክብት አበዛዋለሁ፤ ለዘላለም ርስት አድርጎ እንዲወርሰውም ለዘራችሁ ለመስጠት ያሰብኩትን ይህን ምድር በሙሉ እሰጠዋለሁ’ በማለት በራስህ የማልክላቸውን አገልጋዮችህን አብርሃምን፣ ይስሐቅንና እስራኤልን አስታውስ።” 14  በመሆኑም ይሖዋ በሕዝቡ ላይ እንደሚያመጣ የተናገረውን ጥፋት እንደገና አሰበበት። 15  ከዚያም ሙሴ ሁለቱን የምሥክር ጽላቶች በእጁ እንደያዘ ተመልሶ ከተራራው ወረደ። ጽላቶቹም በሁለቱም በኩል ተቀርጾባቸው ነበር፤ በፊትም ሆነ በጀርባ ተጽፎባቸው ነበር። 16  ጽላቶቹ የአምላክ ሥራ ነበሩ፤ በጽላቶቹ ላይ የተቀረጸው ጽሑፍም የአምላክ ጽሑፍ ነበር። 17  ኢያሱም ሕዝቡ ይጮኽ ስለነበር ጫጫታውን ሲሰማ ሙሴን “በሰፈሩ ውስጥ የጦርነት ሁካታ ይሰማል” አለው። 18  ሙሴ ግን እንዲህ አለው፦ “ይህ ድምፅ የድል መዝሙር አይደለም፤ ይህ ድምፅ በሽንፈት ምክንያት የሚሰማ የለቅሶ ድምፅም አይደለም፤ ይህ የምሰማው ድምፅ የተለየ መዝሙር ድምፅ ነው።” 19  ሙሴም ወደ ሰፈሩ ሲቃረብ ጥጃውንና ጭፈራውን አየ፤ በዚህ ጊዜ ቁጣው ነደደ። ጽላቶቹንም ከእጁ ወርውሮ በተራራው ግርጌ ሰባበራቸው። 20  የሠሩትንም ጥጃ ወስዶ በእሳት አቃጠለው፤ ሰባብሮም ዱቄት አደረገው፤ ከዚያም በውኃው ላይ በመበተን እስራኤላውያን እንዲጠጡት አደረገ። 21  ሙሴም አሮንን “ይህን ከባድ ኃጢአት ያመጣህበት ይህ ሕዝብ ምን ቢያደርግህ ነው?” አለው። 22  በዚህ ጊዜ አሮን እንዲህ አለ፦ “ጌታዬ አትቆጣ። መቼም ይህ ሕዝብ ወደ ክፋት ያዘነበለ እንደሆነ አንተ ራስህ በሚገባ ታውቃለህ። 23  ስለዚህ ‘ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣን ያ ሙሴ ምን እንደደረሰበት ስለማናውቅ ከፊት ከፊታችን የሚሄድ አምላክ ሥራልን’ አሉኝ። 24  በመሆኑም ‘ወርቅ ያለው ሁሉ አውልቆ ይስጠኝ’ አልኳቸው። ከዚያም ወርቁን እሳቱ ውስጥ ጣልኩት፤ ይህም ጥጃ ወጣ።” 25  በተቃዋሚዎቻቸው ፊት መሳለቂያ እንዲሆኑ አሮን ሕዝቡን መረን ስለለቀቃቸው ሙሴ ሕዝቡ መረን እንደተለቀቀ አስተዋለ። 26  ከዚያም ሙሴ በሰፈሩ መግቢያ ላይ ቆሞ “ከይሖዋ ጎን የሚቆም ማን ነው? ወደ እኔ ይምጣ!” አለ። በዚህ ጊዜ ሌዋውያን በሙሉ በዙሪያው ተሰበሰቡ። 27  እሱም እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እያንዳንዳችሁ ሰይፋችሁን ታጠቁ፤ ከአንዱ በር ወደ ሌላው በር በመሄድና በሰፈሩ ውስጥ በማለፍ እያንዳንዱ ሰው ወንድሙን፣ ጎረቤቱንና የቅርብ ጓደኛውን ይግደል።’” 28  ሌዋውያኑም ሙሴ እንዳላቸው አደረጉ። በመሆኑም በዚያ ዕለት 3,000 ገደማ የሚሆኑ ወንዶች ተገደሉ። 29  ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለ፦ “እያንዳንዳችሁ በገዛ ልጃችሁና በገዛ ወንድማችሁ ላይ ስለተነሳችሁ ዛሬ ራሳችሁን ለይሖዋ ለዩ፤ እሱም ዛሬ በረከትን ያፈስላችኋል።” 30  በማግስቱም ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “ከባድ ኃጢአት ሠርታችኋል፤ እንግዲህ አሁን ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ አንድ ነገር ማድረግ እችል እንደሆነ ለማየት ወደ ይሖዋ እወጣለሁ።” 31  በመሆኑም ሙሴ ወደ ይሖዋ ተመልሶ እንዲህ አለ፦ “ይህ ሕዝብ የፈጸመው ኃጢአት ምንኛ ከባድ ነው! የወርቅ አምላክ ሠርተዋል። 32  ሆኖም አሁን ፈቃድህ ከሆነ ኃጢአታቸውን ይቅር በል፤ ካልሆነ ግን እባክህ እኔን ከጻፍከው መጽሐፍህ ላይ ደምስሰኝ።” 33  ይሁንና ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በእኔ ላይ ኃጢአት የሠራውን ሁሉ ከመጽሐፌ ላይ እደመስሰዋለሁ። 34  በል አሁን ሄደህ ሕዝቡን ወደነገርኩህ ስፍራ እየመራህ ውሰዳቸው። እነሆ መልአኬ ከፊት ከፊትህ ይሄዳል፤ ሕዝቡን በምመረምርበትም ቀን ስለሠሩት ኃጢአት ቅጣት አመጣባቸዋለሁ።” 35  ከዚያም ይሖዋ፣ በሠሩት ጥጃ ይኸውም አሮን በሠራላቸው ጥጃ ምክንያት ሕዝቡን በመቅሰፍት መታ።
[]
[]
[]
[]
12,490
33  በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከግብፅ መርተህ ካወጣኸው ሕዝብ ጋር ከዚህ ተነስተህ ሂድ። ‘ለዘርህ እሰጠዋለሁ’ በማለት ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማልኩላቸውም ምድር ተጓዝ። 2  እኔም ከአንተ አስቀድሜ መልአክ በመላክ ከነአናውያንን፣ አሞራውያንን፣ ሂታውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንንና ኢያቡሳውያንን አስወጣለሁ። 3  ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር ሂዱ። ሆኖም እናንተ ግትር ሕዝብ ስለሆናችሁ በመንገድ ላይ እንዳላጠፋችሁ በመካከላችሁ ሆኜ አብሬያችሁ አልሄድም።” 4  ሕዝቡም ይህን ኃይለኛ ንግግር ሲሰሙ በሐዘን ተዋጡ፤ ከመካከላቸውም ማንም ጌጡን አላደረገም። 5  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘እናንተ ግትር ሕዝብ ናችሁ። ለአንድ አፍታ በመካከላችሁ አልፌ ላጠፋችሁ እችል ነበር። በእናንተ ላይ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እስክወስን ድረስ ጌጣጌጣችሁን አውልቁ።’” 6  ስለዚህ እስራኤላውያን ከኮሬብ ተራራ አንስቶ ጌጣጌጣቸውን ማድረግ ተዉ። 7  ሙሴም የራሱን ድንኳን ወስዶ ከሰፈሩ ውጭ ማለትም ከሰፈሩ ትንሽ ራቅ አድርጎ ተከለው፤ ድንኳኑንም የመገናኛ ድንኳን ብሎ ጠራው። ይሖዋን የሚጠይቅ ማንኛውም ሰው ከሰፈሩ ውጭ ወዳለው የመገናኛ ድንኳን ይሄድ ነበር። 8  ሙሴ ወደ ድንኳኑ ሲሄድ ሕዝቡ በሙሉ ተነስተው በየድንኳናቸው መግቢያ ላይ በመቆም ሙሴ ወደ ድንኳኑ እስኪገባ ድረስ ትክ ብለው ይመለከቱት ነበር። 9  ሙሴ ወደ ድንኳኑ ገብቶ አምላክ ከሙሴ ጋር በሚነጋገርበት ጊዜ የደመናው ዓምድ ወርዶ በድንኳኑ መግቢያ ላይ ይቆማል። 10  ሕዝቡም ሁሉ የደመናው ዓምድ በድንኳኑ መግቢያ ላይ ቆሞ ሲመለከት እያንዳንዳቸው ተነስተው በየድንኳናቸው መግቢያ ላይ ይሰግዱ ነበር። 11  አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር እንደሚነጋገር ይሖዋ ከሙሴ ጋር ፊት ለፊት ይነጋገር ነበር። ሙሴ ወደ ሰፈሩ በሚመለስበት ጊዜ አገልጋዩና ረዳቱ የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ ከድንኳኑ አይለይም ነበር። 12  ሙሴም ይሖዋን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ ‘ይህን ሕዝብ ምራ’ እያልከኝ ነው፤ ሆኖም ከእኔ ጋር ማንን እንደምትልክ አላሳወቅከኝም። ከዚህም በላይ ‘በስም አውቄሃለሁ፤ ደግሞም በፊቴ ሞገስ አግኝተሃል’ ብለኸኝ ነበር። 13  እባክህ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እንዳውቅህና በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንድኖር መንገድህን አሳውቀኝ። እንዲሁም ይህ ብሔር ሕዝብህ እንደሆነ አስብ።” 14  በመሆኑም እሱ “እኔ ራሴ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፤ እረፍትም እሰጥሃለሁ” አለው። 15  ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለው፦ “አንተ ራስህ ከእኛ ጋር የማትሄድ ከሆነ ይህን ቦታ ለቅቀን እንድንሄድ አታድርገን። 16  ታዲያ እኔም ሆንኩ ሕዝብህ በፊትህ ሞገስ እንዳገኘን የሚታወቀው እንዴት ነው? እኔም ሆንኩ ሕዝብህ በምድር ላይ ካሉ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉ የተለየን እንድንሆን ስትል አብረኸን በመሄድህ አይደለም?” 17  ይሖዋም ሙሴን “በፊቴ ሞገስ ስላገኘህና በስም ስላወቅኩህ የጠየቅከውን ይህን ነገር እፈጽማለሁ” አለው። 18  እሱም በዚህ ጊዜ “እባክህ ክብርህን አሳየኝ” አለው። 19  ሆኖም እሱ እንዲህ አለው፦ “እኔ ራሴ ጥሩነቴ ሁሉ በፊትህ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤ ይሖዋ የተባለውንም ስሜን በፊትህ አውጃለሁ። ሞገስ ላሳየው የምፈልገውን ሞገስ አሳየዋለሁ፤ ልምረው የምፈልገውን ደግሞ እምረዋለሁ።” 20  ሆኖም “ማንም ሰው አይቶኝ በሕይወት መኖር ስለማይችል ፊቴን ማየት አትችልም” አለው። 21  በተጨማሪም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “ይኸው አጠገቤ ቦታ አለ። አንተም በዓለቱ ላይ ቁም። 22  ክብሬ በዚያ በሚያልፍበትም ጊዜ በዓለቱ ዋሻ ውስጥ አስቀምጥሃለሁ፤ እስከማልፍም ድረስ በእጄ እጋርድሃለሁ። 23  ከዚያም እጄን አነሳለሁ፤ አንተም ጀርባዬን ታያለህ። ፊቴ ግን አይታይም።”
[]
[]
[]
[]
12,491
34  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ጥረብ፤ እኔም በጽላቶቹ ላይ አንተ በሰበርካቸው በመጀመሪያዎቹ ጽላቶች ላይ የነበሩትን ቃላት እጽፍባቸዋለሁ። 2  አንተም በጠዋት ወደ ሲና ተራራ ወጥተህ በዚያ በተራራው አናት ላይ በፊቴ ስለምትቆም በጠዋት ለመሄድ ተዘጋጅ። 3  ሆኖም ከአንተ ጋር ማንም ሰው አይውጣ፤ ደግሞም በተራራው ላይ በየትኛውም ቦታ ሌላ ማንም ሰው አይታይ። ሌላው ቀርቶ በጎችም ሆኑ ከብቶች እንኳ በተራራው ፊት ለፊት አይሰማሩ።” 4  በመሆኑም ሙሴ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት የመጀመሪያዎቹን የሚመስሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ከጠረበ በኋላ በጠዋት ተነስቶ ወደ ሲና ተራራ ወጣ፤ ሁለቱንም የድንጋይ ጽላቶች በእጁ ይዞ ነበር። 5  ከዚያም ይሖዋ በደመና ውስጥ ወርዶ በዚያ ከእሱ ጋር ሆነ፤ ይሖዋ የተባለውንም ስሙን አወጀ። 6  ይሖዋም በፊቱ እያለፈ እንዲህ ሲል አወጀ፦ “ይሖዋ፣ ይሖዋ፣ መሐሪና ሩኅሩኅ የሆነ አምላክ፣ ለቁጣ የዘገየ፣ ታማኝ ፍቅሩና እውነቱ እጅግ ብዙ የሆነ፣ 7  ታማኝ ፍቅርን ለሺዎች የሚያሳይ፣ ስህተትን፣ መተላለፍንና ኃጢአትን ይቅር የሚል፣ ጥፋተኛውን ግን በምንም ዓይነት ሳይቀጣ የማያልፍ እንዲሁም አባቶች ለሠሩት ስህተት በልጆች፣ በልጅ ልጆች፣ በሦስተኛና በአራተኛ ትውልድ ላይ ቅጣትን የሚያመጣ።” 8  ሙሴም ወዲያውኑ መሬት ላይ ተደፍቶ ሰገደ። 9  ከዚያም እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እባክህ ይሖዋ፣ እኛ ግትር ሕዝብ ብንሆንም በመካከላችን ሆነህ አብረኸን ሂድ፤ ደግሞም ስህተታችንንና ኃጢአታችንን ይቅር በል፤ እንደ ርስትህም አድርገህ ውሰደን።” 10  እሱም መልሶ እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ እኔ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፦ በመላው ምድርም ሆነ በብሔራት ሁሉ መካከል ፈጽሞ ተደርገው የማያውቁ ድንቅ ነገሮችን በሕዝብህ ሁሉ ፊት አደርጋለሁ፤ ለአንተ ስል የማደርገው ነገር የሚያስፈራ ስለሆነ በመካከላቸው የምትኖረው ሕዝቦች ሁሉ የይሖዋን ሥራ ያያሉ። 11  “እኔ ዛሬ የማዝህን ነገር ልብ በል። እኔም አሞራውያንን፣ ከነአናውያንን፣ ሂታውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊትህ አስወጣቸዋለሁ። 12  በምትሄድበት ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳትጋባ ተጠንቀቅ፤ አለዚያ ወጥመድ ይሆንብሃል። 13  ከዚህ ይልቅ መሠዊያዎቻቸውን ታፈራርሳላችሁ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን ትሰባብራላችሁ፤ እንዲሁም የማምለኪያ ግንዶቻቸውን ትቆራርጣላችሁ። 14  ይሖዋ፣ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ አምላክ በመሆኑ የሚታወቅ ስለሆነ ለሌላ አምላክ አትስገድ። አዎ፣ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ አምላክ ነው። 15  ከምድሪቱ ነዋሪዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳትጋባ ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም እነሱ አማልክታቸውን በማምለክ ምንዝር በሚፈጽሙበትና ለአማልክታቸው በሚሠዉበት ጊዜ ከመካከላቸው አንዱ አንተን መጋበዙ አይቀርም፣ አንተም ካቀረበው መሥዋዕት ትበላለህ። 16  ከዚያም ሴቶች ልጆቻቸውን ከወንዶች ልጆችህ ጋር ታጋባለህ፤ ሴቶች ልጆቻቸውም አማልክታቸውን በማምለክ ምንዝር መፈጸማቸው እንዲሁም ወንዶች ልጆችህ የእነሱን አማልክት በማምለክ ምንዝር እንዲፈጽሙ ማድረጋቸው አይቀርም። 17  “ከቀለጠ ብረት አማልክት አትሥራ። 18  “የቂጣን በዓል ታከብራለህ። ልክ ባዘዝኩህ መሠረት ቂጣ ትበላለህ፤ ከግብፅ የወጣኸው በአቢብ ወር ስለሆነ በአቢብ ወር በተወሰነው ጊዜ ላይ ለሰባት ቀን ይህን ታደርጋለህ። 19  “በኩር የሆነ ወንድ ሁሉ የእኔ ነው፤ ደግሞም የመንጋህ በኩር ሁሉ፣ በኩር የሆነ በሬም ሆነ ተባዕት በግ የእኔ ነው። 20  የአህያን በኩር በበግ ዋጀው። የማትዋጀው ከሆነ ግን አንገቱን ስበረው። ከወንዶች ልጆችህ መካከል በኩር የሆነውን ሁሉ ትዋጀዋለህ። ማንም ባዶ እጁን ፊቴ አይቅረብ። 21  “ስድስት ቀን ትሠራለህ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ታርፋለህ። በሚታረስበትም ሆነ አዝመራ በሚሰበሰብበት ወቅትም እንኳ ታርፋለህ። 22  “የሳምንታት በዓልህን መጀመሪያ በደረሰው የስንዴ በኩር አክብር፤ የአዝመራ መክተቻን በዓልም በዓመቱ ማብቂያ ላይ አክብር። 23  “የአንተ የሆነ ሰው ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ የእስራኤል አምላክ በሆነው በእውነተኛው ጌታ በይሖዋ ፊት ይቅረብ። 24  ብሔራትን ከፊትህ አስወጣለሁና፤ ክልልህንም ሰፊ አደርገዋለሁ፤ የአምላክህን የይሖዋን ፊት ለማየት በዓመት ሦስቴ በምትወጣበት ጊዜ ማንም ምድርህን አይመኝም። 25  “የመሥዋዕቴን ደም እርሾ ከገባበት ከማንኛውም ነገር ጋር አድርገህ አታቅርብ። የፋሲካ በዓል መሥዋዕት እስከ ጠዋት ድረስ መቆየት የለበትም። 26  “መጀመሪያ የደረሰውን የአፈርህን ምርጥ ፍሬ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ቤት አምጣ። “የፍየልን ጠቦት በእናቱ ወተት አትቀቅል።” 27  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን “ከአንተም ሆነ ከእስራኤል ጋር ቃል ኪዳን የምገባው በእነዚህ ቃላት መሠረት ስለሆነ እነዚህን ቃላት ጻፍ” አለው። 28  እሱም በዚያ ከይሖዋ ጋር 40 ቀንና 40 ሌሊት ቆየ። እህል አልቀመሰም፤ ውኃም አልጠጣም። እሱም በጽላቶቹ ላይ የቃል ኪዳኑን ቃላት ይኸውም አሥርቱን ትእዛዛት ጻፈ። 29  ከዚያም ሙሴ ከሲና ተራራ ወረደ፤ ሁለቱንም የምሥክር ጽላቶች በእጁ ይዞ ነበር። ከአምላክ ጋር ሲነጋገር ስለቆየ ከተራራው በወረደበት ጊዜ ፊቱ እንደሚያንጸባርቅ አላወቀም ነበር። 30  አሮንና እስራኤላውያን ሁሉ ሙሴን ሲያዩት ፊቱ እንደሚያንጸባርቅ አስተዋሉ፤ ወደ እሱ ለመቅረብም ፈሩ። 31  ሙሴ ግን ጠራቸው፤ በመሆኑም አሮንና የማኅበረሰቡ አለቆች በሙሉ ወደ እሱ መጡ፤ ሙሴም አነጋገራቸው። 32  ከዚያም እስራኤላውያን በሙሉ ወደ እሱ ቀረቡ፤ እሱም ይሖዋ በሲና ተራራ ላይ የሰጠውን ትእዛዝ ሁሉ ሰጣቸው። 33  ሙሴም ከእነሱ ጋር ተነጋግሮ ሲጨርስ ፊቱን በመሸፈኛ ይሸፍን ነበር። 34  ሙሴ፣ ይሖዋ ፊት ቀርቦ ከእሱ ጋር ለመነጋገር ወደ ውስጥ በሚገባበት ጊዜ ግን ከዚያ እስከሚወጣበት ጊዜ ድረስ መሸፈኛውን ያነሳ ነበር። ከዚያም ወጥቶ የተቀበለውን ትእዛዝ ለእስራኤላውያን ይነግራቸው ነበር። 35  እስራኤላውያንም የሙሴ ፊት እንደሚያንጸባርቅ ተመለከቱ፤ ከዚያም ሙሴ አምላክን ለማነጋገር ወደ ውስጥ እስከሚገባበት ጊዜ ድረስ መሸፈኛውን መልሶ ፊቱ ላይ አደረገው።
[]
[]
[]
[]
12,492
35  በኋላም ሙሴ የእስራኤልን ማኅበረሰብ ሁሉ አንድ ላይ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ እንድትፈጽሟቸው ያዘዛችሁ ነገሮች እነዚህ ናቸው፦ 2  ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእናንተ የተቀደሰ ይሆናል፤ ለይሖዋም ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ሰንበት ይሆናል። በዚህ ቀን ሥራ የሚሠራ ማንም ሰው ይገደላል። 3  በምትኖሩበት በየትኛውም ቦታ በሰንበት ቀን እሳት አታቀጣጥሉ።” 4  ከዚያም ሙሴ ለእስራኤል ማኅበረሰብ ሁሉ እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ እንዲህ ሲል አዟል፦ 5  ‘ካላችሁ ነገር ለይሖዋ መዋጮ አምጡ። ልቡ ያነሳሳው ማንኛውም ሰው የሚከተሉትን ነገሮች ለይሖዋ መዋጮ አድርጎ ያምጣ፦ ወርቅ፣ ብር፣ መዳብ፣ 6  ሰማያዊ ክር፣ ሐምራዊ ሱፍ፣ ደማቅ ቀይ ማግ፣ ጥሩ በፍታ፣ የፍየል ፀጉር፣ 7  ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ የአቆስጣ ቆዳ፣ የግራር እንጨት፣ 8  ለመብራት የሚሆን ዘይት፣ ለቅብዓት ዘይትና ጥሩ መዓዛ ላለው ዕጣን የሚሆን የበለሳን ዘይት፣ 9  በኤፉዱና በደረት ኪሱ ላይ የሚቀመጡ የኦኒክስ ድንጋዮችና ሌሎች ድንጋዮች። 10  “‘በመካከላችሁ ያሉ ጥሩ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ሁሉ መጥተው ይሖዋ ያዘዘውን ነገር ሁሉ ይሥሩ፤ 11  እነዚህም የማደሪያ ድንኳኑ ከተለያየ ቁሳቁሱና ከመደረቢያው ጋር፣ ማያያዣዎቹ፣ አራት ማዕዘን ቋሚዎቹ፣ አግዳሚ እንጨቶቹ፣ ዓምዶቹ፣ መሰኪያዎቹ፣ 12  ታቦቱና መሎጊያዎቹ፣ መክደኛው፣ ለመከለያ የሚሆነው መጋረጃ፣ 13  ጠረጴዛው እንዲሁም መሎጊያዎቹና ዕቃዎቹ በሙሉ፣ ገጸ ኅብስቱ፣ 14  የመብራት መቅረዙና ዕቃዎቹ፣ መብራቶቹ፣ ለመብራቱ የሚሆነው ዘይት፣ 15  የዕጣን መሠዊያውና መሎጊያዎቹ፣ የቅብዓት ዘይቱና ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን፣ ለማደሪያ ድንኳኑ መግቢያ የሚሆነው መከለያ፣ 16  የሚቃጠል መባ የሚቀርብበት መሠዊያ እንዲሁም የመዳብ ፍርግርጉ፣ መሎጊያዎቹና ዕቃዎቹ በሙሉ፣ ገንዳውና ማስቀመጫው፣ 17  የግቢው መጋረጃ እንዲሁም ቋሚዎቹና መሰኪያዎቹ፣ ለግቢው መግቢያ የሚሆነው መከለያ፣ 18  የማደሪያ ድንኳኑ ካስማዎችና የግቢው ካስማዎች እንዲሁም ገመዶቻቸው፣ 19  በመቅደሱ ለማገልገል የሚለበሱት በጥሩ ሁኔታ የተሸመኑት ልብሶች፣ የካህኑ የአሮን ቅዱስ ልብሶች እንዲሁም ወንዶች ልጆቹ ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚለብሷቸው ልብሶች ናቸው።’” 20  ከዚያም የእስራኤል ማኅበረሰብ በሙሉ ከሙሴ ፊት ሄደ። 21  ከዚያም ልባቸው የገፋፋቸውና መንፈሳቸው ያነሳሳቸው ሁሉ መጥተው ለመገናኛ ድንኳኑ ሥራና በዚያ ለሚከናወነው ማንኛውም አገልግሎት እንዲሁም ለቅዱሶቹ ልብሶች እንዲሆን መዋጮአቸውን ለይሖዋ አመጡ። 22  ፈቃደኛ ልብ ያላቸው ሁሉ፣ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የደረት ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ ቀለበትና ሌላ ጌጣጌጥ እንዲሁም ሁሉንም ዓይነት ከወርቅ የተሠራ ጌጣጌጥ ይዘው ይመጡ ነበር። ሁሉም የወርቅ መባዎቻቸውን ለይሖዋ አቀረቡ። 23  ደግሞም ሰማያዊ ክር፣ ሐምራዊ ሱፍ፣ ደማቅ ቀይ ማግ፣ ጥሩ በፍታ፣ የፍየል ፀጉር፣ ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ እንዲሁም የአቆስጣ ቆዳ ያላቸው ሁሉ እነዚህን አመጡ። 24  ብርና መዳብ የሚያዋጡ ሁሉ ለይሖዋ የሚሆነውን መዋጮ አመጡ፤ ለመገናኛው ድንኳን ሥራ የሚውል የግራር እንጨት ያላቸውም ሁሉ ይህን አመጡ። 25  ጥሩ ችሎታ ያላቸው ሴቶችም ሁሉ በእጃቸው ይፈትሉ ነበር፤ እነሱም የሚከተሉትን ነገሮች ፈትለው አመጡ፦ ሰማያዊ ክር፣ ሐምራዊ ሱፍ፣ ደማቅ ቀይ ማግ እንዲሁም ጥሩ በፍታ። 26  ጥሩ ችሎታ ያላቸው ልባቸው ያነሳሳቸው ሴቶች ሁሉ የፍየል ፀጉሩን ይፈትሉ ነበር። 27  አለቆቹም በኤፉዱና በደረት ኪሱ ላይ የሚቀመጡ የኦኒክስ ድንጋዮችንና ሌሎች ድንጋዮችን፣ 28  የበለሳን ዘይቱን እንዲሁም ለመብራት፣ ለቅብዓት ዘይቱና ጥሩ መዓዛ ላለው ዕጣን የሚሆነውን ዘይት አመጡ። 29  ልባቸው ያነሳሳቸው ወንዶችና ሴቶች በሙሉ ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት እንዲከናወን ላዘዘው ሥራ የሚውሉ ነገሮችን አመጡ፤ እስራኤላውያኑ ይህን በፈቃደኝነት የሚቀርብ መባ አድርገው ለይሖዋ አመጡ። 30  ከዚያም ሙሴ እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፦ “እንደምታዩት ይሖዋ ከይሁዳ ነገድ የሆነው የሁር ልጅ ዖሪ የወለደውን ባስልኤልን መርጦታል። 31  ደግሞም በማንኛውም ዓይነት የእጅ ሙያ ማስተዋል፣ ጥበብና እውቀት በመስጠት በአምላክ መንፈስ ሞልቶታል። 32  ይኸውም የተለያዩ ንድፎችን እንዲያወጣ እንዲሁም በወርቅ፣ በብርና በመዳብ የተለያዩ ነገሮችን እንዲሠራ፣ 33  ፈርጥ የሚሆኑትን ድንጋዮች እንዲቀርጽና በቦታቸው እንዲያስቀምጥ እንዲሁም ድንቅ የሆኑ ልዩ ልዩ የእንጨት ቁሳቁሶችን እንዲሠራ ነው። 34  አምላክም ለእሱና ከዳን ነገድ ለሆነው ለአሂሳማክ ልጅ ለኤልያብ ሌሎችን የማስተማር ችሎታ ሰጥቷቸዋል። 35  የእጅ ጥበብ ባለሙያ፣ የጥልፍ ባለሙያ እንዲሁም በሰማያዊ ክር፣ በሐምራዊ ሱፍ፣ በደማቅ ቀይ ማግና በጥሩ በፍታ የሚሸምን የጥበብ ባለሙያ ብሎም የሽመና ባለሙያ የሚያከናውኗቸውን ሥራዎች በሙሉ እንዲሠሩ ጥሩ ችሎታ ሰጥቷቸዋል። እነዚህ ሰዎች ሁሉንም ዓይነት ሥራዎች የሚሠሩና ሁሉንም ዓይነት ንድፎች የሚያወጡ ነበሩ።
[]
[]
[]
[]
12,493
36  “ባስልኤል ከኤልያብና ጥሩ ችሎታ ካላቸው ወንዶች ሁሉ ጋር ይሠራል፤ እነዚህ ወንዶች ቅዱስ ከሆነው አገልግሎት ጋር የተያያዘው ሥራ በሙሉ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት እንዴት እንደሚከናወን ማወቅ ይችሉ ዘንድ ይሖዋ ጥበብና ማስተዋል የሰጣቸው ናቸው።” 2  ከዚያም ሙሴ ባስልኤልንና ኤልያብን እንዲሁም ይሖዋ በልባቸው ጥበብን ያኖረላቸውን ጥሩ ችሎታ ያላቸውን ወንዶች ሁሉ ይኸውም ሥራውን ለመሥራት በፈቃደኝነት ራሳቸውን እንዲያቀርቡ ልባቸው ያነሳሳቸውን ሁሉ ጠራ። 3  እነሱም እስራኤላውያን ለቅዱሱ አገልግሎት ሥራ ያመጡትን መዋጮ በሙሉ ከሙሴ ወሰዱ። ሕዝቡ ግን በየማለዳው የፈቃደኝነት መባ ወደ እሱ ያመጣ ነበር። 4  ቅዱሱን ሥራ ከጀመሩም በኋላ ጥሩ ችሎታ ያላቸው ሠራተኞች ሁሉ አንድ በአንድ ይመጡ ነበር፤ 5  ሙሴንም “ሕዝቡ፣ ይሖዋ እንዲሠራ ላዘዘው ሥራ ከሚፈለገው በላይ እያመጣ ነው” አሉት። 6  ስለዚህ ሙሴ በሰፈሩ ሁሉ እንዲህ የሚል ማስታወቂያ እንዲነገር አዘዘ፦ “ወንዶችም ሆናችሁ ሴቶች፣ ከእንግዲህ ለቅዱሱ መዋጮ የሚሆን ተጨማሪ ነገር አታምጡ።” በመሆኑም ሕዝቡ ምንም ነገር ከማምጣት ተገታ። 7  የመጣውም ነገር ሥራውን ሁሉ ለማከናወን በቂ፣ እንዲያውም ከበቂ በላይ ነበር። 8  ጥሩ ችሎታ ያላቸውም ሰዎች ሁሉ በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ የበፍታ ድር፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍና ከደማቅ ቀይ ማግ ከተሠሩ አሥር የድንኳን ጨርቆች የማደሪያ ድንኳኑን ሠሩ፤ እሱም በጨርቆቹ ላይ ኪሩቦችን ጠለፈባቸው። 9  የእያንዳንዱ የድንኳን ጨርቅ ርዝመት 28 ክንድ ወርዱ ደግሞ 4 ክንድ ነበር። ሁሉም የድንኳን ጨርቆች መጠናቸው እኩል ነበር። 10  ከዚያም አምስቱን የድንኳን ጨርቆች አንድ ላይ ቀጣጠላቸው፤ ሌሎቹን አምስት የድንኳን ጨርቆችም እንዲሁ አንድ ላይ ቀጣጠላቸው። 11  ከዚህ በኋላ አንደኛው የድንኳን ጨርቅ ከሌላኛው ጋር በሚጋጠምበት ጠርዝ ላይ ከሰማያዊ ክር ማቆላለፊያዎችን ሠራ። ሌላኛው የድንኳን ጨርቅ ከዚህኛው ጋር በሚጋጠምበት በመጨረሻው የድንኳን ጨርቅ ጠርዝ ላይም እንዲሁ አደረገ። 12  በአንደኛው የድንኳን ጨርቅ ላይ 50 ማቆላለፊያዎችን ሠራ፤ ማቆላለፊያዎቹም ትይዩ እንዲሆኑ ሌላኛው የድንኳን ጨርቅ ከዚህኛው ጋር በሚጋጠምበት የድንኳኑ ጨርቅ ጠርዝ ላይ 50 ማቆላለፊያዎችን ሠራ። 13  በመጨረሻም 50 የወርቅ ማያያዣዎችን ሠርቶ የድንኳኑን ጨርቆች በማያያዣዎቹ አማካኝነት እርስ በርስ አጋጠማቸው፤ በዚህም መንገድ የማደሪያ ድንኳኑ አንድ ወጥ ሆነ። 14  ከዚያም ለማደሪያ ድንኳኑ ልባስ የሚሆኑ የድንኳን ጨርቆችን ከፍየል ፀጉር ሠራ። አሥራ አንድ የድንኳን ጨርቆችን ሠራ። 15  የእያንዳንዱ የድንኳን ጨርቅ ርዝመት 30 ክንድ ወርዱ ደግሞ 4 ክንድ ነበር። አሥራ አንዱም የድንኳን ጨርቆች መጠናቸው እኩል ነበር። 16  ከዚያም አምስቱን የድንኳን ጨርቆች አንድ ላይ፣ ሌሎቹን ስድስት የድንኳን ጨርቆች ደግሞ አንድ ላይ ቀጣጠላቸው። 17  በመቀጠልም አንደኛው የድንኳን ጨርቅ ከሌላኛው ጋር በሚጋጠምበት በመጨረሻው የድንኳን ጨርቅ ጠርዝ ላይ 50 ማቆላለፊያዎችን ሠራ፤ እንዲሁም ከዚህኛው ጋር በሚጋጠመው በሌላኛው የድንኳን ጨርቅ ጠርዝ ላይ 50 ማቆላለፊያዎችን ሠራ። 18  ከዚያም ድንኳኑን በማያያዝ አንድ ወጥ እንዲሆን ለማድረግ 50 የመዳብ ማያያዣዎችን ሠራ። 19  እሱም ቀይ ቀለም ከተነከረ የአውራ በግ ቆዳ ለድንኳኑ መደረቢያ ሠራ፤ እንዲሁም ከአቆስጣ ቆዳ በላዩ ላይ የሚደረብ መደረቢያ ሠራ። 20  ከዚያም የግራር እንጨት ጣውላዎችን በማገጣጠም የማደሪያ ድንኳኑን ቋሚዎች ሠራ። 21  እያንዳንዱ ቋሚ ቁመቱ አሥር ክንድ ወርዱ ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል ነበር። 22  እያንዳንዱ ቋሚም እርስ በርስ የተያያዙ ሁለት ጉጦች ነበሩት። ሁሉንም የማደሪያ ድንኳኑን ቋሚዎች የሠራው በዚህ መንገድ ነበር። 23  በመሆኑም በስተ ደቡብ በኩል ለሚገኘው፣ ፊቱ በደቡብ አቅጣጫ ላለው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን ቋሚዎችን ይኸውም 20 ቋሚዎችን ሠራ። 24  ከዚያም በ20ዎቹ ቋሚዎች ሥር የሚሆኑ 40 የብር መሰኪያዎችን ሠራ፤ በአንዱ ቋሚ ሥር ላሉት ሁለት ጉጦች የሚሆኑ ሁለት መሰኪያዎችን፣ ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱም ቋሚ ሥር ላሉት ሁለት ጉጦች የሚሆኑ ሁለት መሰኪያዎችን አደረገ። 25  በስተ ሰሜን በኩል ላለው ለሌላኛውም የማደሪያ ድንኳኑ ጎን 20 ቋሚዎችን ሠራ፤ 26  እንዲሁም 40 የብር መሰኪያዎቻቸውን ሠራ፤ በአንዱ ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያዎችን፣ በተቀረው በእያንዳንዱም ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያዎችን አደረገ። 27  በስተ ምዕራብ በኩል ለሚገኘው ለኋለኛው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን ስድስት ቋሚዎችን ሠራ። 28  በማደሪያ ድንኳኑ በስተ ኋላ በኩል ባሉት ሁለት ማዕዘኖች ላይ የማዕዘን ቋሚዎች የሚሆኑ ሁለት ቋሚዎችን ሠራ። 29  ቋሚዎቹም ከታች አንስቶ የመጀመሪያው ቀለበት እስከሚገኝበት እስከ ላይ ድረስ ድርብ ነበሩ። ሁለቱን የማዕዘን ቋሚዎች የሠራቸው በዚህ መንገድ ነበር። 30  በመሆኑም ስምንት ቋሚዎች የነበሩ ሲሆን እነሱም ከብር የተሠሩ 16 መሰኪያዎች ነበሯቸው፤ ይህም በእያንዳንዱ ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያ ማለት ነው። 31  ከዚያም ከግራር እንጨት አግዳሚ እንጨቶችን ሠራ፤ በአንዱ ጎን ላሉት የማደሪያ ድንኳኑ ቋሚዎች አምስት አግዳሚ እንጨቶችን፣ 32  በሌላኛው ጎን ላሉት የማደሪያ ድንኳኑ ቋሚዎች ደግሞ አምስት አግዳሚ እንጨቶችን እንዲሁም በስተ ምዕራብ በሚገኘው በኋለኛው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን ላሉት ቋሚዎች አምስት አግዳሚ እንጨቶችን ሠራ። 33  ከዚያም በቋሚዎቹ መሃል ላይ ከጫፍ እስከ ጫፍ እንዲዘልቅ መካከለኛውን አግዳሚ እንጨት ሠራ። 34  ቋሚዎቹንም በወርቅ ለበጣቸው፤ አግዳሚ እንጨቶቹን የሚሸከሙትን ቀለበቶችም ከወርቅ ሠራቸው። አግዳሚ እንጨቶቹንም በወርቅ ለበጣቸው። 35  ከዚያም ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግ እንዲሁም በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ የበፍታ ድር መጋረጃ ሠራ። በላዩም ላይ ኪሩቦች እንዲጠለፉበት አደረገ። 36  ከዚያም ለመጋረጃው ከግራር እንጨት አራት ዓምዶችን ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው፤ ማንጠልጠያዎቻቸውም ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ፤ ለዓምዶቹም ከብር የተሠሩ አራት መሰኪያዎችን አዘጋጀ። 37  በመቀጠልም ለድንኳኑ መግቢያ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግ እንዲሁም በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ የበፍታ ድር የተሸመነ መከለያ ሠራ፤ 38  እንዲሁም አምስቱን ዓምዶችና ማንጠልጠያዎቹን ሠራ። አናታቸውንና ማያያዣዎቻቸውንም በወርቅ ለበጣቸው፤ አምስቱ መሰኪያዎቻቸው ግን ከመዳብ የተሠሩ ነበሩ።
[]
[]
[]
[]
12,494
37  ከዚያም ባስልኤል ከግራር እንጨት ታቦቱን ሠራ። ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል፣ ከፍታው ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል ነበር። 2  ውስጡንና ውጭውንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ ሠራለት። 3  ከአራቱ እግሮቹ በላይ የሚሆኑ አራት የወርቅ ቀለበቶችን ሠራለት፤ ሁለቱን ቀለበቶች በአንድ ጎኑ፣ ሁለቱን ቀለበቶች ደግሞ በሌላኛው ጎኑ በኩል አደረጋቸው። 4  ከዚያም ከግራር እንጨት መሎጊያዎችን ሠራ፤ በወርቅም ለበጣቸው። 5  ታቦቱንም ለመሸከም እንዲያገለግሉ መሎጊያዎቹን በታቦቱ ጎንና ጎን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባቸው። 6  እሱም ከንጹሕ ወርቅ መክደኛውን ሠራ። ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል ወርዱ ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል ነበር። 7  በተጨማሪም በመክደኛው ጫፍና ጫፍ ላይ ከተጠፈጠፈ ወርቅ ሁለት ኪሩቦችን ሠራ። 8  አንዱ ኪሩብ በአንዱ ጫፍ ሌላኛው ኪሩብ ደግሞ በሌላኛው ጫፍ ላይ ነበር። ኪሩቦቹን በሁለቱም የመክደኛው ጫፎች ላይ ሠራቸው። 9  ሁለቱ ኪሩቦችም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ በመዘርጋት መክደኛውን በክንፎቻቸው ከልለውት ነበር። እርስ በርስ ትይዩ ነበሩ፤ ፊታቸውንም ወደ መክደኛው አጎንብሰው ነበር። 10  ከዚያም ከግራር እንጨት ጠረጴዛውን ሠራ። ርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ ከፍታው ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል ነበር። 11  በንጹሕ ወርቅም ለበጠው፤ ዙሪያውንም የወርቅ ክፈፍ ሠራለት። 12  ከዚያም በዙሪያው አንድ ጋት ስፋት ያለው ጠርዝ ሠራለት፤ ለጠርዙም ዙሪያውን የወርቅ ክፈፍ ሠራለት። 13  በተጨማሪም አራት የወርቅ ቀለበቶች ሠራለት፤ ቀለበቶቹንም አራቱ እግሮቹ በሚገኙባቸው አራት ማዕዘኖች ላይ አደረጋቸው። 14  ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች የሚይዙት ቀለበቶች በጠርዙ አጠገብ ነበሩ። 15  ከዚያም ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች ከግራር እንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው። 16  በኋላም በጠረጴዛው ላይ የሚሆኑትን ዕቃዎች ይኸውም ለመጠጥ መባ ማፍሰሻ የሚያገለግሉትን ሳህኖች፣ ጽዋዎች፣ ጎድጓዳ ሳህኖችና ማንቆርቆሪያዎች ከንጹሕ ወርቅ ሠራ። 17  ከዚያም መቅረዙን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ። መቅረዙን ጠፍጥፎ ሠራው። የመቅረዙ መቆሚያ፣ ግንዱ፣ አበባ አቃፊዎቹ፣ እንቡጦቹና የፈኩት አበቦች ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ። 18  መቅረዙ ከግንዱ ላይ የወጡ ስድስት ቅርንጫፎች ነበሩት፤ ሦስቱ ቅርንጫፎቹ ከአንዱ ጎን ሦስቱ ቅርንጫፎቹ ደግሞ ከሌላው ጎን የወጡ ነበሩ። 19  በአንዱ በኩል ባሉት ቅርንጫፎች በእያንዳንዳቸው ላይ የአልሞንድ አበባ የሚመስሉ ሦስት የአበባ አቃፊዎች ከእንቡጦችና ከፈኩ አበቦች ጋር በማፈራረቅ ተሠርተው ነበር፤ በሌላኛው በኩል ባሉት ቅርንጫፎችም በእያንዳንዳቸው ላይ የአልሞንድ አበባ የሚመስሉ ሦስት የአበባ አቃፊዎች ከእንቡጦችና ከፈኩ አበቦች ጋር በማፈራረቅ ተሠርተው ነበር። ከመቅረዙ ግንድ በሚወጡት ስድስት ቅርንጫፎች ላይ የተደረገው ይህ ነበር። 20  በመቅረዙም ግንድ ላይ የአልሞንድ አበባ የሚመስሉ አራት የአበባ አቃፊዎች ከእንቡጦችና ከፈኩ አበቦች ጋር በማፈራረቅ ተሠርተው ነበር። 21  ከግንዱ በሚወጡት በመጀመሪያዎቹ ጥንድ ቅርንጫፎች ሥር አንድ እንቡጥ፣ ቀጥሎ ባሉት ጥንድ ቅርንጫፎች ሥር አንድ እንቡጥ እንዲሁም ቀጥሎ ባሉት ጥንድ ቅርንጫፎች ሥር አንድ እንቡጥ ነበር፤ ከመቅረዙ ግንድ ለሚወጡት ስድስት ቅርንጫፎች እንዲሁ ተደርጎላቸው ነበር። 22  እንቡጦቹም ሆኑ ቅርንጫፎቹ፣ መላው መቅረዙ ከንጹሕ ወርቅ ተጠፍጥፎ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበር። 23  ከዚያም ሰባቱን መብራቶች እንዲሁም መቆንጠጫዎቹንና መኮስተሪያዎቹን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ። 24  መቅረዙን ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር የሠራው ከአንድ ታላንት ንጹሕ ወርቅ ነበር። 25  ከዚያም ከግራር እንጨት የዕጣን መሠዊያውን ሠራ። ርዝመቱ አንድ ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ ሆኖ አራቱም ጎኖቹ እኩል ሲሆኑ ከፍታው ደግሞ ሁለት ክንድ ነበር። ቀንዶቹ ከዚያው ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ። 26  እሱም ላዩን፣ ሁሉንም ጎኖቹን እንዲሁም ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ ሠራለት። 27  መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች እንዲይዙም በሁለቱ ተቃራኒ ጎኖቹ ላይ ከክፈፉ በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠራለት። 28  ከዚያ በኋላ መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው። 29  በተጨማሪም ቅዱሱን የቅብዓት ዘይትና በብልሃት የተቀመመውን ጥሩ መዓዛ ያለውን ንጹሕ ዕጣን አዘጋጀ።
[]
[]
[]
[]
12,495
38  እሱም የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያ ከግራር እንጨት ሠራ። ርዝመቱ አምስት ክንድ፣ ወርዱም አምስት ክንድ ሲሆን አራቱም ጎኖቹ እኩል ነበሩ፤ ከፍታው ደግሞ ሦስት ክንድ ነበር። 2  ከዚያም በአራቱ ማዕዘኖች ላይ ቀንዶቹን ሠራለት። ቀንዶቹም ከዚያው ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ። በመቀጠልም በመዳብ ለበጠው። 3  ከዚህ በኋላ የመሠዊያውን ዕቃዎች በሙሉ ይኸውም አመድ ማጠራቀሚያዎቹን፣ አካፋዎቹን፣ ሳህኖቹን፣ ሹካዎቹንና መኮስተሪያዎቹን ሠራ። ዕቃዎቹን በሙሉ ከመዳብ ሠራቸው። 4  በተጨማሪም ለመሠዊያው ከጠርዙ ወደ ታች ወረድ ብሎ ወደ መሃል አካባቢ እንደ መረብ ያለ የመዳብ ፍርግርግ ሠራለት። 5  መሎጊያዎቹን ለመያዝ የሚያገለግሉትንም አራት ቀለበቶች ከመዳብ ፍርግርጉ አጠገብ በአራቱ ማዕዘኖች ላይ ሠራ። 6  በኋላም መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርቶ በመዳብ ለበጣቸው። 7  ከዚያም መሠዊያውን ለመሸከም እንዲያገለግሉ መሎጊያዎቹን በመሠዊያው ጎኖች ላይ ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባቸው። መሠዊያውንም ባዶ ሣጥን አስመስሎ ከሳንቃዎች ሠራው። 8  ከዚያም የመዳቡን ገንዳና ከመዳብ የተሠራውን ማስቀመጫውን ሠራ፤ ለዚህም በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ በተደራጀ መልክ ያገለግሉ የነበሩትን ሴት አገልጋዮች መስተዋቶች ተጠቀመ። 9  ከዚያም ግቢውን ሠራ። በስተ ደቡብ በኩል ለሚገኘው፣ ፊቱ በደቡብ አቅጣጫ ላለው የግቢው ጎን በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ ርዝመታቸው 100 ክንድ የሆነ መጋረጃዎች ሠራ። 10  ከመዳብ የተሠሩ 20 ቋሚዎችና 20 መሰኪያዎች ነበሩ፤ በቋሚዎቹ ላይ ያሉት ማንጠልጠያዎችና ማያያዣዎቻቸው ደግሞ ከብር የተሠሩ ነበሩ። 11  በተጨማሪም በስተ ሰሜን በኩል ባለው ጎን ያሉት መጋረጃዎች ርዝመታቸው 100 ክንድ ነበር። ሃያዎቹ ቋሚዎቻቸውና 20ዎቹ መሰኪያዎቻቸው ከመዳብ የተሠሩ ነበሩ። በቋሚዎቹ ላይ ያሉት ማንጠልጠያዎችና ማያያዣዎቻቸው ደግሞ ከብር የተሠሩ ነበሩ። 12  በስተ ምዕራብ በኩል ባለው ጎን ያሉት መጋረጃዎች ግን ርዝመታቸው 50 ክንድ ነበር። አሥር ቋሚዎችና አሥር መሰኪያዎች ነበሩ፤ በቋሚዎቹ ላይ ያሉት ማንጠልጠያዎችና ማያያዣዎቻቸው ከብር የተሠሩ ነበሩ። 13  በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ይኸውም በፀሐይ መውጫ በኩል ያለው ጎን ርዝመቱ 50 ክንድ ነበር። 14  በአንደኛው በኩል ያሉት የመግቢያው መጋረጃዎች ርዝመታቸው 15 ክንድ ሲሆን ሦስት ቋሚዎችና ሦስት መሰኪያዎች ነበሯቸው። 15  በሌላኛው በኩል ያሉት የግቢው መግቢያ መጋረጃዎችም ርዝመታቸው 15 ክንድ ሲሆን ሦስት ቋሚዎችና ሦስት መሰኪያዎች ነበሯቸው። 16  በግቢው ዙሪያ ያሉት መጋረጃዎች በሙሉ በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠሩ ነበሩ። 17  የቋሚዎቹ መሰኪያዎች ከመዳብ የተሠሩ ነበሩ፤ በቋሚዎቹ ላይ ያሉት ማንጠልጠያዎችና ማያያዣዎቻቸው ከብር የተሠሩ ሲሆኑ አናታቸውም በብር የተለበጠ ነበር። የግቢው ቋሚዎች በሙሉ ከብር የተሠሩ ማያያዣዎች ነበሯቸው። 18  የግቢው መግቢያ መከለያ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግ እንዲሁም በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ የበፍታ ድር ተሸምኖ የተሠራ ነበር። ርዝመቱ 20 ክንድ ሲሆን ከፍታው ደግሞ ልክ እንደ ግቢው መጋረጃዎች 5 ክንድ ነበር። 19  አራቱ ቋሚዎቻቸውና አራቱ መሰኪያዎቻቸው ከመዳብ የተሠሩ ነበሩ። ማንጠልጠያዎቻቸው ከብር የተሠሩ ሲሆኑ አናታቸውና ማያያዣዎቻቸው ደግሞ በብር የተለበጡ ነበሩ። 20  የማደሪያ ድንኳኑና በግቢው ዙሪያ የሚገኙት ካስማዎች በሙሉ ከመዳብ የተሠሩ ነበሩ። 21  በሙሴ ትእዛዝ መሠረት ተቆጥረው የተመዘገቡት የማደሪያ ድንኳኑ ይኸውም የምሥክሩ የማደሪያ ድንኳን ዕቃዎች የሚከተሉት ናቸው፤ ይህን ያከናወኑት ሌዋውያኑ ሲሆኑ መሪያቸውም የካህኑ የአሮን ልጅ ኢታምር ነበር። 22  ከይሁዳ ነገድ የሆነው የሁር ልጅ የዖሪ ልጅ ባስልኤል ይሖዋ ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። 23  ከእሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነው የአሂሳማክ ልጅ ኤልያብ ነበር፤ እሱም የእጅ ባለሙያና የጥልፍ ባለሙያ እንዲሁም በሰማያዊ ክር፣ በሐምራዊ ሱፍ፣ በደማቅ ቀይ ማግ እንዲሁም በጥሩ በፍታ የሚሸምን የሽመና ባለሙያ ነበር። 24  በአጠቃላይ በቅዱሱ ስፍራ ለተከናወነው ሥራ የዋለው ወርቅ በሙሉ መባ ሆኖ ከቀረበው ወርቅ ጋር ተመጣጣኝ ነበር፤ ይህም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል 29 ታላንት ከ730 ሰቅል ነበር። 25  ከማኅበረሰቡ መካከል ከተመዘገቡት ሰዎች የተገኘው ብር ደግሞ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል 100 ታላንት ከ1,775 ሰቅል ነበር። 26  ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ሆኗቸው ከተመዘገቡት 603,550 ሰዎች መካከል የሆነ እያንዳንዱ ግለሰብ የሰጠው ግማሽ ሰቅል፣ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል ግማሽ ሰቅል ነበር። 27  የቅዱሱን ስፍራ መሰኪያዎችና ለመጋረጃው ቋሚዎች የሚሆኑትን መሰኪያዎች ለመሥራት የዋለው 100 ታላንት ብር ነበር፤ 100 መሰኪያዎች 100 ታላንት ነበሩ፤ ይህም ለእያንዳንዱ መሰኪያ አንድ ታላንት ማለት ነው። 28  ለቋሚዎቹ ከ1,775 ሰቅል ብር ማንጠልጠያዎችን ሠራ፤ አናታቸውንም ከለበጠ በኋላ እርስ በርስ አያያዛቸው። 29  መባ ሆኖ የቀረበው መዳብ ደግሞ 70 ታላንት ከ2,400 ሰቅል ነበር። 30  በዚህም የመገናኛ ድንኳኑን መግቢያ መሰኪያዎች፣ የመዳብ መሠዊያውንና የመዳብ ፍርግርጉን እንዲሁም የመሠዊያውን ዕቃዎች በሙሉ ሠራ፤ 31  እንዲሁም በግቢው ዙሪያ ያሉትን መሰኪያዎች፣ ለግቢው መግቢያ የሚሆኑትን መሰኪያዎች እንዲሁም የማደሪያ ድንኳኑን ካስማዎች በሙሉና በግቢው ዙሪያ ያሉትን የድንኳን ካስማዎች በሙሉ ሠራ።
[]
[]
[]
[]
12,496
39  በቅዱሱ ስፍራ ለማገልገል የሚለበሱትን በጥሩ ሁኔታ የተሸመኑትን ልብሶች ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍና ከደማቅ ቀይ ማግ ሠሩ። ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረትም የአሮንን ቅዱስ ልብሶች ሠሩ። 2  እሱም ኤፉዱን ከወርቅ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ ሠራው። 3  እነሱም ወርቁን በመቀጥቀጥ በስሱ ጠፈጠፉት፤ እሱም ከሰማያዊው ክር፣ ከሐምራዊው ሱፍ፣ ከደማቁ ቀይ ማግና ከጥሩው በፍታ ጋር አብሮ እንዲሠራው ወርቁን እንደ ክር በቀጫጭኑ ሰነጣጠቀው፤ ከዚያም በወርቁ ጥልፍ ጠለፈበት። 4  ለኤፉዱም ላዩ ላይ የሚጣበቁ የትከሻ ጥብጣቦች የሠሩለት ሲሆን ኤፉዱም ከትከሻ ጥብጣቦቹ ጋር የሚያያዘው በሁለቱ ጫፎቹ ላይ ነበር። 5  ኤፉዱ ወዲያ ወዲህ እንዳይንቀሳቀስ ለማሰር የሚያገለግለው ከኤፉዱ ጋር የተያያዘው በሽመና የተሠራው መቀነትም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት እንደ ኤፉዱ ሁሉ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ ተሠራ። 6  ከዚያም የኦኒክስ ድንጋዮቹን በወርቅ አቃፊዎቹ ውስጥ አስቀመጧቸው፤ የእስራኤልን ወንዶች ልጆች ስሞችም ልክ ማኅተም በሚቀረጽበት መንገድ ቀረጹባቸው። 7  እሱም ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለእስራኤል ልጆች እንደ መታሰቢያ ድንጋዮች ሆነው እንዲያገለግሉ በኤፉዱ የትከሻ ጥብጣቦች ላይ አስቀመጣቸው። 8  ከዚያም የደረት ኪሱን የጥልፍ ባለሙያ እንደሚሠራው አድርጎ ልክ ኤፉዱ በተሠራበት መንገድ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ ሠራው። 9  ለሁለት በሚታጠፍበት ጊዜም አራቱም ጎኖቹ እኩል ነበሩ። ለሁለት በሚታጠፍበት ጊዜ ቁመቱም ሆነ ወርዱ አንድ ስንዝር የሆነውን የደረት ኪስ ሠሩ። 10  በላዩም ላይ አራት ረድፍ ድንጋዮችን አደረጉበት። በመጀመሪያው ረድፍ ሩቢ፣ ቶጳዝዮንና መረግድ ተደረደረ። 11  በሁለተኛው ረድፍ ደግሞ በሉር፣ ሰንፔርና ኢያስጲድ ተደረደረ። 12  በሦስተኛው ረድፍ ለሼም፣ አካትምና አሜቴስጢኖስ ተደረደረ። 13  በአራተኛውም ረድፍ ክርስቲሎቤ፣ ኦኒክስና ጄድ ተደረደረ። በወርቅ አቃፊዎችም ውስጥ ተቀመጡ። 14  ድንጋዮቹም 12ቱን የእስራኤል ወንዶች ልጆች ስሞች የሚወክሉ ነበሩ፤ ስሞቹም ልክ ማኅተም በሚቀረጽበት መንገድ ተቀረጹ፤ እያንዳንዱ ስም ከ12ቱ ነገዶች አንዱን የሚወክል ነበር። 15  ከዚያም በደረት ኪሱ ላይ እንደ ገመድ የተጎነጎነ ሰንሰለት ከንጹሕ ወርቅ ሠሩ። 16  በመቀጠልም ሁለት የወርቅ አቃፊዎችንና ሁለት ቀለበቶችን ሠሩ፤ ሁለቱን ቀለበቶችም በደረት ኪሱ ሁለት ማዕዘኖች ላይ አያያዟቸው። 17  በኋላም ሁለቱን የወርቅ ገመዶች በደረት ኪሱ ማዕዘኖች ላይ በሚገኙት ሁለት ቀለበቶች ውስጥ አስገቧቸው። 18  ከዚያም የሁለቱን ገመዶች ሁለት ጫፎች በሁለቱ አቃፊዎች ውስጥ አስገቧቸው፤ በኤፉዱ በፊት በኩል በትከሻ ጥብጣቦቹ ላይ አያያዟቸው። 19  በመቀጠልም ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው በኤፉዱ በኩል በሚውለው በደረት ኪሱ ውስጠኛ ጠርዝ ሁለት ጫፎች ላይ አደረጓቸው። 20  ከዚያም ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው በኤፉዱ ላይ ከፊት በኩል ከሁለቱ የትከሻ ጥብጣቦች በታች፣ መጋጠሚያው አጠገብ፣ በሽመና ከተሠራው የኤፉዱ መቀነት በላይ አደረጓቸው። 21  በመጨረሻም ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት የደረት ኪሱ ከኤፉዱ ላይ ሳይንቀሳቀስ፣ ተሸምኖ ከተሠራው መቀነት በላይ እንዲውል የደረት ኪሱን ቀለበቶች ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ገመድ አያያዟቸው። 22  ከዚያም እጅጌ የሌለውን የኤፉዱን ቀሚስ የሽመና ባለሙያ ሙሉ በሙሉ በሰማያዊ ክር ሸምኖ እንዲሠራው አደረገ። 23  የቀሚሱ አንገት ማስገቢያ ልክ እንደ ጥሩር አንገት ማስገቢያ መሃል ላይ ነበር። የአንገት ማስገቢያውም እንዳይቀደድ ዙሪያውን ተቀምቅሞ ነበር። 24  ከዚያም ሰማያዊ ክር፣ ሐምራዊ ሱፍና ደማቅ ቀይ ማግ አንድ ላይ በመግመድ በታችኛው የቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ ዘርፍ የሚሆኑ ሮማኖችን ሠሩ። 25  በተጨማሪም ከንጹሕ ወርቅ ቃጭሎችን ሠሩ፤ ቃጭሎቹንም በቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ በሮማኖቹ መሃል መሃል አደረጓቸው። 26  ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረትም ለአገልግሎት በሚውለው ቀሚስ የታችኛው ጠርዝ ዙሪያ ቃጭል ከዚያም ሮማን፣ ቃጭል ከዚያም ሮማን እያፈራረቁ አደረጉበት። 27  ከዚያም ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ ከጥሩ በፍታ ረጅም ቀሚስ በሽመና ባለሙያ አሠሩላቸው፤ 28  በተጨማሪም ጥምጥሙን ከጥሩ በፍታ፣ ጌጠኛ የራስ ቆቦቹንም ከጥሩ በፍታ፣ የበፍታ ቁምጣውን በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ 29  እንዲሁም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት መቀነቱን በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍና ከደማቅ ቀይ ማግ ሸምነው ሠሩት። 30  በመጨረሻም የሚያብረቀርቀውን ጠፍጣፋ ወርቅ ይኸውም ለአምላክ የተወሰኑ መሆንን የሚያሳየውን ቅዱስ ምልክት ከንጹሕ ወርቅ ሠሩ፤ አንድ ሰው ማኅተም በሚቀርጽበት መንገድ “ቅድስና የይሖዋ ነው” የሚል ጽሑፍ በላዩ ላይ ቀረጹበት። 31  ከዚያም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት በጥምጥሙ ላይ እንዲውል ለማድረግ ሰማያዊ ገመድ አሰሩበት። 32  የማደሪያ ድንኳኑ ይኸውም የመገናኛ ድንኳኑ ሥራ በሙሉ ተጠናቀቀ፤ እስራኤላውያን ይሖዋ ሙሴን ያዘዘውን ነገር ሁሉ ሠሩ። ልክ እንደታዘዙትም አደረጉ። 33  እነሱም የማደሪያ ድንኳኑን ወደ ሙሴ አመጡ፤ ድንኳኑንና ዕቃዎቹን በሙሉ ማለትም ማያያዣዎቹን፣ አራት ማዕዘን ቋሚዎቹን፣ አግዳሚ እንጨቶቹን፣ ዓምዶቹን፣ መሰኪያዎቹን፣ 34  ለመደረቢያ የሚሆነውን ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳና ለመደረቢያ የሚሆነውን የአቆስጣ ቆዳ፣ ለመግቢያው መከለያ የሚሆነውን መጋረጃ፣ 35  የምሥክሩን ታቦት እንዲሁም መሎጊያዎቹንና መክደኛውን፣ 36  ጠረጴዛውን እንዲሁም ዕቃዎቹን በሙሉና ገጸ ኅብስቱን፣ 37  ከንጹሕ ወርቅ የተሠራውን መቅረዝ እንዲሁም በመደዳ የተደረደሩትን መብራቶቹንና ዕቃዎቹን በሙሉ፣ የመብራቱን ዘይት፣ 38  የወርቅ መሠዊያውን፣ የቅብዓት ዘይቱን፣ ጥሩ መዓዛ ያለውን ዕጣን፣ ለድንኳኑ መግቢያ የሚሆነውን መከለያ፣ 39  የመዳብ መሠዊያውንና የመዳብ ፍርግርጉን እንዲሁም መሎጊያዎቹንና ዕቃዎቹን በሙሉ፣ ገንዳውንና ማስቀመጫውን፣ 40  የግቢውን መጋረጃዎች እንዲሁም ቋሚዎቹን፣ መሰኪያዎቹን፣ ለግቢው መግቢያ የሚሆነውን መከለያ፣ የድንኳኑን ገመዶች፣ የድንኳኑን ካስማዎችና በማደሪያ ድንኳኑ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ለሚከናወነው አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች በሙሉ፣ 41  በመቅደሱ ለማገልገል የሚለበሱትን በጥሩ ሁኔታ ተሸምነው የተሠሩትን ልብሶች፣ የካህኑን የአሮንን ቅዱስ ልብሶች እንዲሁም ወንዶች ልጆቹ ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚለብሷቸውን ልብሶች አመጡ። 42  እስራኤላውያን ሥራውን በሙሉ ያከናወኑት ይሖዋ ለሙሴ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ነበር። 43  ሙሴም ሥራቸውን በሙሉ ሲመለከት ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት እንደሠሩ አየ፤ ከዚያም ባረካቸው።
[]
[]
[]
[]
12,497
4  ሆኖም ሙሴ “‘ይሖዋ አልተገለጠልህም’ ቢሉኝና ባያምኑኝስ? ቃሌንስ ባይሰሙ?” አለው። 2  ይሖዋም “በእጅህ የያዝከው ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። እሱም መልሶ “በትር ነው” አለ። 3  እሱም “መሬት ላይ ጣለው” አለው። እሱም መሬት ላይ ጣለው፤ በትሩም እባብ ሆነ፤ ሙሴም ከእባቡ ሸሸ። 4  በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን “እጅህን ዘርግተህ ጅራቱን ያዘው” አለው። እሱም እጁን ዘርግቶ ያዘው፤ እባቡም በእጁ ላይ እንደገና በትር ሆነ። 5  ከዚያም አምላክ “ይህ የሆነው የአባቶቻቸው አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ ይሖዋ እንደተገለጠልህ እንዲያምኑ ነው” አለው። 6  ይሖዋም በድጋሚ “እባክህ እጅህን ወዳጣፋኸው ልብስ ውስጥ አስገባ” አለው። እሱም እጁን ወዳጣፋው ልብስ ውስጥ አስገባ። ባወጣውም ጊዜ እጁ በለምጽ ተመቶ ልክ እንደ በረዶ ነጭ ሆኖ ነበር! 7  ከዚያም “እጅህን ወዳጣፋኸው ልብስ ውስጥ መልሰህ አስገባው” አለው። እሱም እጁን መልሶ ልብሱ ውስጥ አስገባው። እጁንም ከልብሱ ውስጥ ባወጣው ጊዜ እጁ ተመልሶ እንደ ሌላው የሰውነቱ ክፍል ሆነ! 8  እሱም እንዲህ አለው፦ “ባያምኑህ ወይም የመጀመሪያውን ተአምራዊ ምልክት ችላ ቢሉ እንኳ የኋለኛውን ተአምራዊ ምልክት በእርግጥ አምነው ይቀበላሉ። 9  እንደዛም ሆኖ እነዚህን ሁለት ምልክቶች ባያምኑና ቃልህን ለመስማት ፈቃደኛ ባይሆኑ ከአባይ ወንዝ ውኃ ቀድተህ በደረቁ መሬት ላይ አፍስሰው፤ ከአባይ የቀዳኸው ውኃ በደረቁ መሬት ላይ ደም ይሆናል።” 10  ሙሴም ይሖዋን “ይሖዋ ሆይ፣ ይቅርታ አድርግልኝ፤ እኔ ከዚህ በፊትም ሆነ አንተ አገልጋይህን ካነጋገርክበት ጊዜ ጀምሮ ፈጽሞ አንደበተ ርቱዕ አይደለሁም፤ ንግግር የማልችልና ተብታባ ሰው ነኝ” አለው። 11  ይሖዋም እንዲህ አለው፦ “ለሰው አፍ የፈጠረለት ማን ነው? ሰዎችን ዱዳ፣ ደንቆሮ ወይም ዕውር የሚያደርግ አሊያም ለሰዎች የዓይን ብርሃን የሚሰጥ ማን ነው? እኔ ይሖዋ አይደለሁም? 12  በል አሁን ሂድ፤ በምትናገርበት ጊዜ እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ የምትናገረውንም ነገር አስተምርሃለሁ።” 13  እሱ ግን “ይሖዋ ሆይ፣ ይቅርታ አድርግልኝ፤ እባክህ መላክ የፈለግከውን ሌላ ማንኛውንም ሰው ላክ” አለው። 14  በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቁጣ በሙሴ ላይ ነደደ፤ እንዲህም አለው፦ “እሺ ሌዋዊው ወንድምህ አሮንስ? እሱ በደንብ መናገር እንደሚችል አውቃለሁ። ደግሞም አንተን ለማግኘት አሁን ወደዚህ እየመጣ ነው። በሚያይህም ጊዜ ልቡ በደስታ ይሞላል። 15  ስለሆነም እሱን አነጋግረው፤ ቃላቱንም በአንደበቱ አኑር፤ በምትናገሩበትም ጊዜ ከአንተና ከእሱ ጋር እሆናለሁ፤ ምን ማድረግ እንዳለባችሁም አስተምራችኋለሁ። 16  እሱም አንተን ወክሎ ለሕዝቡ ይናገራል፤ እንደ ቃል አቀባይም ይሆንልሃል፤ አንተም ለእሱ እንደ አምላክ ትሆናለህ። 17  ይህን በትር በእጅህ ይዘህ ትሄዳለህ፤ በእሱም ተአምራዊ ምልክቶቹን ትፈጽማለህ።” 18  ስለዚህ ሙሴ ወደ አማቱ ወደ ዮቶር ተመልሶ በመሄድ “እስካሁን በሕይወት መኖር አለመኖራቸውን አይ ዘንድ እባክህ በግብፅ ወዳሉት ወንድሞቼ ተመልሼ ልሂድ” አለው። ዮቶርም ሙሴን “በሰላም ሂድ” አለው። 19  ከዚያ በኋላ ይሖዋ ሙሴን በምድያም ሳለ “ሂድ፤ ወደ ግብፅ ተመለስ፤ ነፍስህን ለማጥፋት የሚፈልጉት ሰዎች በሙሉ ሞተዋል” አለው። 20  ከዚያም ሙሴ ሚስቱንና ልጆቹን በአህያ ላይ አስቀምጦ ወደ ግብፅ ምድር ለመመለስ ጉዞ ጀመረ። የእውነተኛውን አምላክ በትርም በእጁ ይዞ ነበር። 21  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ግብፅ ከተመለስክ በኋላ፣ በሰጠሁህ ኃይል የምታከናውናቸውን ተአምራት ሁሉ በፈርዖን ፊት መፈጸም እንዳለብህ አትዘንጋ። እኔ ግን ልቡ እንዲደነድን እፈቅዳለሁ፤ እሱም ሕዝቡን አይለቅም። 22  ፈርዖንንም እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ልጄ ነው፤ አዎ፣ የበኩር ልጄ ነው። 23  እንግዲህ ‘እንዲያገለግለኝ ልጄን ልቀቅ’ ብዬሃለሁ። ለመልቀቅ ፈቃደኛ ካልሆንክ ግን ልጅህን፣ አዎ የበኩር ልጅህን እገድላለሁ።”’” 24  ይሖዋም በመንገድ ላይ ባለው የእንግዳ ማረፊያ ስፍራ አገኘው፤ እሱንም ሊገድለው ፈልጎ ነበር። 25  በመጨረሻም ሲፓራ ባልጩት ወስዳ ልጇን ገረዘችው፤ ሸለፈቱን እግሩን ካስነካች በኋላም “ይህ የሆነው አንተ ለእኔ የደም ሙሽራ ስለሆንክ ነው” አለች። 26  ስለሆነም እንዲሄድ ፈቀደለት። እሷም በዚህ ጊዜ በግርዛቱ የተነሳ “የደም ሙሽራ” አለች። 27  ይሖዋም አሮንን “ሙሴን ለማግኘት ወደ ምድረ በዳ ሂድ” አለው። እሱም ሄደ፤ በእውነተኛውም አምላክ ተራራ ላይ አገኘው፤ ከዚያም ሳመው። 28  ሙሴም ይሖዋ እንዲናገር የላከውን ቃል ሁሉ እንዲሁም እንዲፈጽማቸው ያዘዘውን ተአምራዊ ምልክቶች ሁሉ ለአሮን ነገረው። 29  ከዚህ በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው የእስራኤልን ሽማግሌዎች በሙሉ ሰበሰቡ። 30  አሮንም ይሖዋ ለሙሴ የነገረውን ቃል ሁሉ ነገራቸው፤ እሱም በሕዝቡ ፊት ተአምራዊ ምልክቶቹን አደረገ። 31  በዚህ ጊዜ ሕዝቡ አመነ። ይሖዋ ፊቱን ወደ እስራኤላውያን እንደመለሰና ሥቃያቸውንም እንዳየ ሲሰሙ ተደፍተው ሰገዱ።
[]
[]
[]
[]
12,498
40  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2  “በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የማደሪያ ድንኳኑን ይኸውም የመገናኛ ድንኳኑን ትከል። 3  የምሥክሩን ታቦት በውስጡ ካስቀመጥክ በኋላ ታቦቱን በመጋረጃው ከልለው። 4  ጠረጴዛውንም ካስገባህ በኋላ በላዩ ላይ የሚቀመጡትን ነገሮች አስተካክለህ አስቀምጥ፤ መቅረዙንም አስገብተህ መብራቶቹን አብራቸው። 5  ከዚያም ለዕጣን የሚሆነውን የወርቅ መሠዊያ ከምሥክሩ ታቦት በፊት አስቀምጠው፤ ለማደሪያ ድንኳኑ መግቢያ የሚሆነውን መከለያም በቦታው አድርገው። 6  “የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያም በማደሪያ ድንኳኑ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ፊት አድርገው፤ 7  ገንዳውንም በመገናኛ ድንኳኑና በመሠዊያው መካከል አድርገህ ውኃ ጨምርበት። 8  በመገናኛ ድንኳኑም ዙሪያ ግቢ ከልልለት፤ ለግቢውም መግቢያ መከለያ አድርግለት። 9  የማደሪያ ድንኳኑም የተቀደሰ እንዲሆን የቅብዓት ዘይቱን ወስደህ ድንኳኑንና በውስጡ ያሉትን ነገሮች በሙሉ ትቀባቸዋለህ፤ ድንኳኑንም ሆነ ዕቃዎቹን በሙሉ ትቀድሳለህ። 10  የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትም መሠዊያ እጅግ ቅዱስ እንዲሆን መሠዊያውንና ዕቃዎቹን በሙሉ ትቀባቸዋለህ፤ መሠዊያውንም ትቀድሳለህ። 11  ገንዳውንና ማስቀመጫውንም ቀባ፤ ቀድሰውም። 12  “ከዚያም አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ አቅርባቸው፤ በውኃም እጠባቸው። 13  አሮንንም ቅዱስ የሆኑትን ልብሶች ካለበስከው በኋላ ቀባው፤ እንዲሁም ቀድሰው፤ እሱም ካህን ሆኖ ያገለግለኛል። 14  ከዚያም ወንዶች ልጆቹን አቅርበህ ረጃጅሞቹን ቀሚሶች አልብሳቸው። 15  ካህናት ሆነውም እንዲያገለግሉኝ አባታቸውን እንደቀባኸው ሁሉ እነሱንም ቀባቸው፤ መቀባታቸውም ክህነታቸው ለትውልዶቻቸው ሁሉ በዘላቂነት እንዲቀጥል ያስችላል።” 16  ሙሴም ይሖዋ ባዘዘው መሠረት አደረገ። ልክ እንደዚሁ አደረገ። 17  በሁለተኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የማደሪያ ድንኳኑ ተተከለ። 18  ሙሴም የማደሪያ ድንኳኑን ሲተክል መሰኪያዎቹን ከሥር በማስቀመጥ አራት ማዕዘን ቋሚዎቹን አደረገባቸው፤ አግዳሚ እንጨቶቹንም አስገባቸው፤ ዓምዶቹንም አቆማቸው። 19  ከዚያም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት የማደሪያ ድንኳኑን በድንኳኑ ጨርቅ አለበሰው፤ በላዩም ላይ የድንኳኑን መደረቢያ ደረበበት። 20  ቀጥሎም የምሥክሩን ጽላቶች ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አስቀመጣቸው፤ የታቦቱንም መሎጊያዎች አስገባቸው፤ መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አደረገው። 21  ከዚያም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ታቦቱን ወደ ማደሪያ ድንኳኑ አስገባው፤ የመግቢያው መከለያ የሆነውን መጋረጃ በቦታው በማድረግ የምሥክሩን ታቦት ከለለው። 22  በመቀጠልም ጠረጴዛውን በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በስተ ሰሜን በኩል ባለው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን ከመጋረጃው ውጭ አደረገው፤ 23  በላዩም ላይ ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት የተነባበረውን ኅብስት በይሖዋ ፊት አስቀመጠ። 24  መቅረዙንም በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ከጠረጴዛው ትይዩ፣ በስተ ደቡብ በኩል ባለው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን አስቀመጠው። 25  ከዚያም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት መብራቶቹን በይሖዋ ፊት አበራቸው። 26  የወርቅ መሠዊያውንም በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ከመጋረጃው በፊት አስቀመጠው፤ 27  ይህን ያደረገውም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን እንዲጨስበት ነው። 28  ቀጥሎም የማደሪያ ድንኳኑን መግቢያ መከለያ በቦታው አደረገው። 29  ከዚያም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት የሚቃጠለውን መባና የእህሉን መባ በላዩ ላይ እንዲያቀርብበት የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያ በማደሪያ ድንኳኑ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ አደረገው። 30  በመቀጠልም ገንዳውን በመገናኛ ድንኳኑና በመሠዊያው መካከል አደረገው፤ ለመታጠቢያ የሚሆን ውኃም ጨመረበት። 31  ሙሴ እንዲሁም አሮንና ወንዶች ልጆቹ እጃቸውንና እግራቸውን ታጠቡበት። 32  ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ወደ መገናኛ ድንኳኑ በሚገቡበትና ወደ መሠዊያው በሚቀርቡበት ጊዜ ሁሉ ይታጠቡ ነበር። 33  በመጨረሻም በማደሪያ ድንኳኑና በመሠዊያው ዙሪያ ግቢውን ከለለ፤ ለግቢውም መግቢያ መከለያ አደረገለት። በዚህ መንገድ ሙሴ ሥራውን አጠናቀቀ። 34  ደመናውም የመገናኛ ድንኳኑን ሸፈነው፤ የይሖዋም ክብር የማደሪያ ድንኳኑን ሞላው። 35  ደመናው በመገናኛ ድንኳኑ ላይ አርፎ ስለነበርና የይሖዋም ክብር የማደሪያ ድንኳኑን ስለሞላው ሙሴ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግባት አልቻለም ነበር። 36  እስራኤላውያንም በጉዟቸው ወቅት ሁሉ ደመናው ከማደሪያ ድንኳኑ ላይ በሚነሳበት ጊዜ ድንኳናቸውን ነቅለው ይንቀሳቀሱ ነበር። 37  ሆኖም ደመናው ካልተነሳ፣ ደመናው እስከሚነሳበት ቀን ድረስ ድንኳናቸውን ነቅለው አይንቀሳቀሱም ነበር። 38  መላው የእስራኤል ቤት በሚጓዝበት ወቅት ሁሉ ቀን ቀን የይሖዋ ደመና፣ ሌሊት ሌሊት ደግሞ እሳት በማደሪያ ድንኳኑ ላይ ሆኖ ያይ ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,499
5  ከዚያ በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ገብተው እንዲህ አሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ‘በምድረ በዳ በዓል እንዲያከብርልኝ ሕዝቤን ልቀቅ’ ይላል።” 2  ፈርዖን ግን እንዲህ አለ፦ “የእሱን ቃል ሰምቼ እስራኤልን የምለቀው ለመሆኑ ይሖዋ ማነው? እኔ ይሖዋ የምትሉትን ፈጽሞ አላውቅም፤ እስራኤልንም አለቅም።” 3  ሆኖም እነሱ እንዲህ አሉት፦ “የዕብራውያን አምላክ አነጋግሮን ነበር። በመሆኑም እባክህ የሦስት ቀን መንገድ ወደ ምድረ በዳ ተጉዘን ለአምላካችን ለይሖዋ መሥዋዕት ማቅረብ እንፈልጋለን፤ ካልሆነ ግን በበሽታ ወይም በሰይፍ ይጨርሰናል።” 4  የግብፅም ንጉሥ “ሙሴና አሮን፣ ሕዝቡን ሥራ የምታስፈቱት ለምንድን ነው? አርፋችሁ ወደ ጉልበት ሥራችሁ ተመለሱ!” አላቸው። 5  ፈርዖንም በመቀጠል “የምድሩ ሕዝብ ምን ያህል ብዙ እንደሆነ ተመልከት፤ አንተ ደግሞ ሥራ ልታስፈታቸው ነው” አለ። 6  ፈርዖንም በዚያኑ ዕለት የሥራ ኃላፊዎቹንና አሠሪዎቹን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ 7  “ከአሁን በኋላ ለጡብ መሥሪያ የሚሆን ጭድ ለሕዝቡ እንዳትሰጡ። ራሳቸው ሄደው ጭድ ይሰብስቡ። 8  ሆኖም በፊት ይሠሩት የነበረውን ያህል ጡብ ሠርተው እንዲያስረክቡ አድርጉ። ዘና እያሉ ስለሆነ ማስረከብ ከሚጠበቅባቸው ጡብ ምንም እንዳትቀንሱላቸው። ‘መሄድ እንፈልጋለን፤ ሄደን ለአምላካችን መሥዋዕት ማቅረብ እንፈልጋለን!’ እያሉ የሚጮኹት ለዚህ ነው። 9  ለሐሰት ወሬ ጆሯቸውን እንዳይሰጡ ሥራውን አክብዱባቸው፤ እንዲሁም ፋታ አሳጧቸው።” 10  ስለዚህ የሥራ ኃላፊዎቹና አሠሪዎቹ ወጥተው ለሕዝቡ እንዲህ አሉ፦ “ፈርዖን እንዲህ ይላል፦ ‘ከእንግዲህ ጭድ አላቀርብላችሁም። 11  ራሳችሁ ሄዳችሁ ከየትም ፈልጋችሁ ጭድ አምጡ፤ ሥራችሁ ግን በምንም ዓይነት አይቀነስም።’” 12  ከዚያም ሕዝቡ እንደ ጭድ ሆኖ የሚያገለግለውን የእህል ቆረን ለመሰብሰብ በመላው የግብፅ ምድር ተሰማራ። 13  የሥራ ኃላፊዎቹም “እያንዳንዳችሁ ጭድ ይቀርብላችሁ በነበረበት ጊዜ ታደርጉት እንደነበረው ሁሉ አሁንም በየዕለቱ የሚጠበቅባችሁን ሥራ ሠርታችሁ ማጠናቀቅ አለባችሁ” እያሉ ያስገድዷቸው ነበር። 14  በተጨማሪም የፈርዖን የሥራ ኃላፊዎች የሾሟቸው የእስራኤላውያን አሠሪዎች ተገረፉ። እነሱንም “ቀደም ሲል ሠርታችሁ ታስረክቡት የነበረውን ያህል ጡብ ሠርታችሁ ያላስረከባችሁት ለምንድን ነው? ትናንትም ሆነ ዛሬ እንዲህ አላደረጋችሁም” ብለው ጠየቋቸው። 15  በመሆኑም የእስራኤላውያን አሠሪዎች ወደ ፈርዖን ገብተው እንዲህ በማለት እሮሯቸውን አሰሙ፦ “በአገልጋዮችህ ላይ እንዲህ ያለ ድርጊት የምትፈጽመው ለምንድን ነው? 16  ለእኛ ለአገልጋዮችህ ምንም ጭድ አይሰጠንም፤ እነሱ ግን ‘ጡብ ሥሩ!’ ይሉናል። ጥፋቱ የገዛ ሰዎችህ ሆኖ ሳለ እኛ አገልጋዮችህ እንገረፋለን።” 17  እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ እኮ ተዝናንታችኋል፤ አዎ፣ ዘና እያላችሁ ነው! ‘መሄድ እንፈልጋለን፤ ሄደን ለይሖዋ መሥዋዕት ማቅረብ እንፈልጋለን!’ የምትሉት ለዚህ ነው። 18  በሉ አሁን ወደ ሥራችሁ ተመለሱ! ምንም ጭድ አይቀርብላችሁም፤ ሆኖም የሚጠበቅባችሁን ያህል ጡብ መሥራት አለባችሁ።” 19  የእስራኤል አሠሪዎችም “በየዕለቱ ማስረከብ ከሚጠበቅባችሁ ጡብ ምንም ማጉደል የለባችሁም” የሚለውን ትእዛዝ ሲሰሙ ከባድ ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ተረዱ። 20  እነሱም ፈርዖንን አነጋግረው ሲወጡ በዚያ ቆመው ይጠብቋቸው የነበሩትን ሙሴንና አሮንን አገኟቸው። 21  እነሱም እንዲህ አሏቸው፦ “በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት እንድንጠላ ስላደረጋችሁና እንዲገድሉን በእጃቸው ሰይፍ ስለሰጣችኋቸው ይሖዋ ይይላችሁ፤ ደግሞም ይፍረድባችሁ።” 22  በዚህ ጊዜ ሙሴ ወደ ይሖዋ ተመልሶ እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ ሆይ፣ ይህን ሕዝብ ለመከራ የዳረግከው ለምንድን ነው? እኔንስ የላክኸኝ ለምንድን ነው? 23  ፈርዖን በስምህ ለመናገር ወደ እሱ ከገባሁበት ጊዜ አንስቶ ይህን ሕዝብ ይበልጥ ማንገላታቱን ቀጥሏል፤ አንተም ብትሆን ሕዝብህን አላዳንክም።”
[]
[]
[]
[]
12,500
6  በመሆኑም ይሖዋ ሙሴን “አሁን በፈርዖን ላይ የማደርገውን ታያለህ። በኃያል ክንድ ተገዶ ይለቃቸዋል፤ በኃያል ክንድ ተገዶም ከምድሩ እንዲወጡ ያደርጋቸዋል” አለው። 2  ከዚያም አምላክ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እኔ ይሖዋ ነኝ። 3  ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ሁሉን ቻይ አምላክ ሆኜ እገለጥላቸው ነበር፤ ይሖዋ የሚለውን ስሜን በተመለከተ ግን ራሴን ሙሉ በሙሉ አልገለጥኩላቸውም። 4  በተጨማሪም የከነአንን ምድር ማለትም የባዕድ አገር ሰው ሆነው የኖሩባትን ምድር ልሰጣቸው ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ። 5  እንግዲህ አሁን ግብፃውያን በባርነት እየገዟቸው ያሉት የእስራኤል ሰዎች እያሰሙት ያለውን የሥቃይ ጩኸት ሰምቻለሁ፤ ቃል ኪዳኔንም አስባለሁ። 6  “ስለዚህ እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘እኔ ይሖዋ ነኝ፤ ከግብፃውያን ከባድ ሸክም ነፃ አወጣችኋለሁ፤ ከጫኑባችሁም የባርነት ቀንበር አላቅቃችኋለሁ፤ በተዘረጋ ክንድና በታላቅ ፍርድ እታደጋችኋለሁ። 7  የራሴ ሕዝብ አድርጌ እወስዳችኋለሁ፤ አምላካችሁም እሆናለሁ፤ እናንተም ከግብፃውያን ከባድ ሸክም ነፃ የማወጣችሁ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ታውቃላችሁ። 8  ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለመስጠት እጄን አንስቼ ወደማልኩላቸው ምድር አስገባችኋለሁ፤ ርስት አድርጌም እሰጣችኋለሁ። እኔ ይሖዋ ነኝ።’” 9  ከዚያም ሙሴ ለእስራኤላውያን ይህን መልእክት ነገራቸው፤ እነሱ ግን ተስፋ ከመቁረጣቸውና አስከፊ ከሆነው የባርነት ሕይወታቸው የተነሳ ሊሰሙት ፈቃደኞች አልሆኑም። 10  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 11  “ወደ ግብፁ ንጉሥ ወደ ፈርዖን ገብተህ እስራኤላውያንን ከምድሩ እንዲያሰናብታቸው ንገረው።” 12  ሆኖም ሙሴ “እንግዲህ እስራኤላውያን ሊሰሙኝ ፈቃደኛ አልሆኑም፤ ታዲያ የመናገር ችግር ያለብኝን እኔን፣ ፈርዖን እንዴት ብሎ ሊሰማኝ ይችላል?” በማለት ለይሖዋ መለሰ። 13  ይሖዋ ግን እስራኤላውያንን ከግብፅ ምድር ለማውጣት ለእነሱና ለግብፁ ንጉሥ ለፈርዖን ማስተላለፍ ያለባቸውን ትእዛዝ ለሙሴና ለአሮን በድጋሚ ነገራቸው። 14  የአባቶቻቸው ቤት መሪዎችም እነዚህ ናቸው፦ የእስራኤል የበኩር ልጅ የሮቤል ወንዶች ልጆች ሃኖክ፣ ፓሉ፣ ኤስሮን እና ካርሚ ነበሩ። እነዚህ የሮቤል ቤተሰቦች ናቸው። 15  የስምዖን ወንዶች ልጆች የሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጾሃር እና ከአንዲት ከነአናዊት የወለደው ሻኡል ነበሩ። እነዚህ የስምዖን ቤተሰቦች ናቸው። 16  የሌዊ ወንዶች ልጆች በየቤተሰብ የዘር ሐረጋቸው ስማቸው ይህ ነው፦ ጌድሶን፣ ቀአት እና ሜራሪ። ሌዊ 137 ዓመት ኖረ። 17  የጌድሶን ወንዶች ልጆች በየቤተሰባቸው ሊብኒ እና ሺምአይ ነበሩ። 18  የቀአት ወንዶች ልጆች አምራም፣ ይጽሃር፣ ኬብሮን እና ዑዚኤል ነበሩ። ቀአት 133 ዓመት ኖረ። 19  የሜራሪ ወንዶች ልጆች ማህሊ እና ሙሺ ነበሩ። የሌዋውያን ቤተሰቦች በየቤተሰብ የዘር ሐረጋቸው እነዚህ ነበሩ። 20  አምራም የአባቱን እህት ዮካቤድን አገባ። እሷም አሮንንና ሙሴን ወለደችለት። አምራም 137 ዓመት ኖረ። 21  የይጽሃር ወንዶች ልጆች ቆሬ፣ ኔፌግ እና ዚክሪ ነበሩ። 22  የዑዚኤል ወንዶች ልጆች ሚሳኤል፣ ኤሊጻፋን እና ሲትሪ ነበሩ። 23  አሮን የነአሶን እህት የሆነችውን የአሚናዳብን ልጅ ኤሊሼባን አገባ። እሷም ናዳብን፣ አቢሁን፣ አልዓዛርን እና ኢታምርን ወለደችለት። 24  የቆሬ ወንዶች ልጆች አሲር፣ ሕልቃና እና አቢያሳፍ ነበሩ። የቆሬያውያን ቤተሰቦች እነዚህ ናቸው። 25  የአሮን ልጅ አልዓዛር ከፑቲኤል ልጆች መካከል አንዷን አገባ። እሷም ፊንሃስን ወለደችለት። የሌዋውያን የአባቶች ቤት መሪዎች በየቤተሰባቸው እነዚህ ናቸው። 26  ይሖዋ “የእስራኤልን ሕዝብ በቡድን በቡድን በማድረግ ከግብፅ ምድር ይዛችሁ ውጡ” ብሎ የነገራቸው አሮንና ሙሴ እነዚህ ናቸው። 27  የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ለማውጣት የግብፁን ንጉሥ ፈርዖንን ያነጋገሩት ሙሴና አሮን ነበሩ። 28  ይሖዋ በግብፅ ምድር ሙሴን ባነጋገረበት በዚያ ዕለት 29  ይሖዋ ሙሴን “እኔ ይሖዋ ነኝ። የምነግርህን ሁሉ ለግብፁ ንጉሥ ለፈርዖን ንገረው” አለው። 30  ከዚያም ሙሴ ይሖዋን “እኔ እንደሆነ የመናገር ችግር አለብኝ፤ ታዲያ ፈርዖን እንዴት ብሎ ይሰማኛል?” አለው።
[]
[]
[]
[]