category
large_stringclasses
7 values
headline
large_stringlengths
10
171
text
large_stringlengths
1
26.4k
url
large_stringlengths
13
180
lang
large_stringclasses
16 values
health
ኮሮናቫይረስ፡ ኮቪድ-19 በሁለተኛው ዙር የከፋ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል- ተመራማሪዎች
ብዙ አገራት በኮሮናቫይረስ በመጀመሪያ ዙር ክፉኛ ተጠቅተው መቆጣጠር ቢችሉም ወረርሽኙ ድጋሚ አገርሽቶ እየፈተናቸው ነው። ከዚህ ቀደም ተከስተው የነበሩ ወረርሽኞች ተሞክሮ እንደሚያሳየው በድጋሚ ሊያገረሽ ይችላል። ከ100 ዓመት በፊት ተከስቶ ቢያንስ 50 ሚሊዮን ህዝብ እንደጨረሰ የሚነገርለት ስፓኒሽ ፍሉ፣ ከመጀመሪያውም ሆነ ከሦስተኛው ጊዜ በላይ ሁለተኛው ዙር የከፋ ጉዳት አድርሷል። የኮሮናቫይረስም ተመሳሳይ ሂደት ሊከተል እንደሚችል ሳይንቲስቶች እያስጠነቀቁ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/53839161
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ከሚያዙት መካከል 63 በመቶው ምልክት አያሳዩም
በአሁኑ ወቅት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተይዘው የሚገኙ ሰዎች ውስጥ 63 በመቶው ምልክት የማያሳዩ እንደሆኑ ተገለፀ። ዛሬ የጤና ሚኒስቴርና ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተገለፀው አሁን ላይ አዲስ አበባ በስርጭቱ ቀዳሚ ሰትሆን፣ ኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው ከሐምሌ እና ነሐሴ በላይ አሁን ላይ ወደ ፅኑ ሕሙማን የሚገቡ ታማሚዎች ብዛት እየጨመረ መጥቷል። በመግለጫው ላይ በኢትዮጵያ ያለውን የቫይረሱን ስርጭት ለማወቅ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደ የአንድ ወር አገር አቀፍ የምርመራ ዘመቻ ከ73 በመቶ በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መለየታቸው ተገልጿል። 1.4 በመቶ የሚሆኑት በሆስፒታል የሚገኙ ታማሚዎች በፅኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ እንደሚገኙም ተመልክቷል። የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዳይሬክተር አስቻለው አባይነህ እንዳሉት በኢትዮጵያ ሁሉም ወረዳዎች ቢያንስ አንድ በኮቪድ የተያዘ ሰው ሪፖርት አድርገዋል። በዚሁ መግለጫ ላይ እስካሁን በኢትዮጵያ በቫይረሱ ከሚያዙት 57 በመቶ የሚሆኑት እድሜያቸው ከ15-34 ሲሆን ከሟቾች ውስጥ ደግሞ 51.9 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ መሆኑን ተገልጿል። ምክትል ዳይሬክተሩ አክለው እንደገለፁት በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተይዘው ለህልፈት የሚበቁ ሰዎች ምጣኔ 1.52 በመቶ ነው። አሁን ላይ የምርመራ መጠን የቀነሰ ቢሆንም ቫይረሱ የሚገኝባቸው እና ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑም ተመልክቷል። ባለፉት ሁለት ሳምንት ውስጥ እንደአገር ያለው የቫይረሱ ስርጭት 10 ነጥብ 4 በመቶ መሆኑም ተገልጿል። አዲስ አበባ ከተማ፣ ኦሮሚያ ፣ ትግራይ ፣ አማራ ፣ ደቡብ እና ሲዳማ ክልሎች በቅደም ተከተል ከፍተኛ የቫይረሱ ተጠቂዎች የተገኙባቸው ስለመሆኑም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡ የጤና ሚኒስትርዋ ዶ/ር ሊያ በበኩላቸው ርቀትን ሳይጠብቁና ማስክ ሳያደርጉ አገልግሎት መቀበልም ሆነ መስጠት ለቫይረሱ ተጋላጭነትን ስለሚጨምር ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል። ቸልተኝነት እና መዘናጋት አሁንም በሰፊው እንደሚስተዋል በመግለጽ ይህ ዋጋ ስለሚያስከፍል ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል በቫይረሱ ሊያዝ ስለሚችል ጤናውን ከመጠበቅ ሊዘናጋ እንደማይገባም ነው ሚኒስትሯ ያስጠነቀቁት። በቫይረሱ የሞት ምጣኔ በኢትዮጵያ 1.52 በመቶ ፣ በአፍሪካ 2.4 በመቶ ፣ በዓለም ደግሞ 2.8 በመቶ መሆኑንም በመግለጫው ወቅት ተገልጿል። በአጠቃላይ በኢትኦጵያ 89 ሺህ 860 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ፤ የ1,365 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 43,149 ከበሽታው አገግመዋል።
https://www.bbc.com/amharic/54612587
amh
health
የሰሞኑ ጉንፋን መሰል ህመም የኮሮናቫይረስ ሊሆን ስለሚችል ምርመራ ማድረግ እንደሚገባ ተመከረ
በኢትዮጵያ አዲስ የኮሮናቫይረስ ማዕበል በመከሰቱ ሰሞኑን የተስተዋለው ጉንፋን መሰል ህመም የሚያሳው ምልክት ከኮሮናቫይረስ ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ ህመሙ ያላባቸው ሰዎች ምርመራ እንዲያደርጉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መከረ። ከዚሁ ጋር ተያይዞም ባለፉት ሳምንታት በኢትዮጵያ ውስጥ የታየው በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር በአገሪቱ አዲስ የወረርሽኙ ማዕበል መከሰቱን እንደሚያሳይ ተቋሙ ገልጿል። ሰሞኑን የተከሰተውን 'ጉንፋን መሰል' ወረርሽኝን በማስመልከት መግለጫ ያወጣው ተቋሙ እንዳለው በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአዲስ አበባ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ባደረገው የመስክ ቅኝትና የናሙናዎች ምርመራ ከ59 እስከ 86 በመቶው ላይ ኮቪድ-19 እንደተገኘባቸው አመልክቷል። ጨምሮም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በጤና ተቋማት የኮሮናቫይረስ ምርመራ ካደረጉ 55 ሺህ 562 ሰዎች ውስጥ 25 ሺህ 191 ያህሉ ላይ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን ገልጿል። እንዲሁም በመላው አገሪቱ ከታኅሣሥ 15 እስከ 21/2014 ዓ.ም ድረስ ባሉት ሰባት ቀናት ውስጥ የኮቪድ ምልክት ታይቶባቸው ምርመራ ካደረጉ 83 ሺህ 237 ሰዎች ውስጥ 29 ሺህ 279 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው ተገኝተዋል። ይህም በኢትዮጵያ ውስጥ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ያለው በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ምጣኔ ተከታታይ ጭማሪ አሳይቷል። በዚህም መሠረት ከሁለት ሳምንት በፊት የነበረው የ5 በመቶ ምጣኔ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቶ ሐሙስ (ታኅሣሥ 21/2014 ዓ.ም) ላይ ወደ 36 በመቶ ከፍ ማለቱን ተቋሙ አመልክቷል። በዚህም ሳቢያ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዳለው እየታየ ያለው የወረርሽኙ መስፋፋት በአገሪቱ አዲስ የኮቪድ-19 ማዕበል መከሰቱን እንደሚያመለክት ገልጿል። ተቋሙ ጨምሮም ሰሞኑን ከሚስተዋለው "ጉንፋን መሰል" ህመም ጋር የሚታዩት ምልክቶች ከኮቪድ-19 ምልክቶች ጋር ተመሳሳይ በመሆናቸው ሳይዘናጉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ መመርመር እንደሚገባ መክሯል። በአሁኑ ወቅት የኮሮናቫይረስ ስርጭት በዓለም ዙሪያ በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመረ በመሆኑ ይህ ክስተት ኢትዮጵያ ውስጥም መስተዋሉን በመግለጽ ምልክቶች የታዩባቸው ሰዎች ምርመራ እንዲያደርጉ መክሯል። የተቀረው ሕብረተሰብም የኮሮናቫይረስ መከላከያ መንገዶችን በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ እራሱንና ሌሎችን ከወረርሽኑ እንዲጠብቅ መክሯል። የኮሮናቫይረስ በኢትዮጵያ መኖሩ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ አስከ ሐሙስ ታኅሣሥ 21/2014 ዓ.ም ድረስ ከ4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተመርምረው ከ415 ሺህ በላይ ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፣ 6 ሺህ 926 ደግሞ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን አጥተዋል። በሽታውን ለመከላከል የሚረዳው ክትባት በአገሪቱ መሰጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የተከተቡ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ካላት አጠቃላይ ሕዝብ አንጻር ይህ አሃዝ ዝቅተኛ እንደሆነ ይነገራል። የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር የተለመዱትን የመከላከያ ዘዴዎች በአግባቡ ዘወትር ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ባለሙያዎች እየመከሩ ሲሆን ክትባት መውሰድም እንደሚገባ ያሳስባሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-59840260
amh
health
የአፍሪካ አገራት ግዜው ያለፈበት የኮቪድ ክትባትን እንዳያስወግዱ ተጠየቁ
የዓለም ጤና ድርጅት የመጠቀሚያ ግዜያቸው ያለፈ የኮሮናቫይረስ ክትባት በእጃቸው የሚገኝ የአፍሪካ አገራት ክትባቱን ከማስወገድ እንዲቆጠቡ አሳሰበ። አገራቱ ቀጣይ መመሪያዎች እስኪሰጡ ድረስ የመጠቀሚያ ግዜያቸው ያለፈባቸውን ክትባቶችን ይዘው እንዲያቆዩ ተጠይቀዋል። ማላዊ እና ደቡብ ሱዳን በሚያዚያ ወር አጋመሽ ላይ 70 ሺህ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ክትባቶችን ለማስወገድ ማሰባቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው የዓለም የጤና ድርጅት ይህን ማሳሰቢያ የሰጠው። ማላዊ 16 ሺህ የአስትራ ዜኔካ ብልቃጦችን፤ ደቡብ ሱዳን ደግሞ 59 ሺህ ተመሳሳይ ብልቃጦችን ለማስወገድ አስበዋል። የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ (ሲዲሲ) ግን ምንም እንኳን ክትባቶቹን ለመጠቀም የተቀመጠው ግዜ ቢያልፍም ክትባቶቹ ጥቅም ላይ መዋል እንደሚችሉ ገልጾ ነበር። በዓለማችን ያሉ ሌሎች ክትባቶች ከተመረቱ ጀምሮ እስከ 36 ወር ድረስ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሲሆን የኮቪድ ክትባት ግን አዲስ መሆኑን ተከትሎ ነው ለምን ያህል ግዜ ውጤታማ ሆኖ መቆየት እንደሚችል ገና ያልተለየው። እነዚህ ግዜያቸው ያለፈባቸውን ክትባቶች ጥቅም ላይ የማዋል ውሳኔ የሚሰጠው በብሔራዊ የመድሃኒት ተቆጣጣሪዎች እንደሆነ የቢቢሲ የጤና ጉዳዮች ዘጋቢ ርሆዳ ኦዲያምቦ ታብራራለች። የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ዋና ዳይሬክተር ማክሰኞ ዕለት በሰጡት መግለጫቸው ላይ፤ "ለአባል አገራት የማቀርበው ጥሪ ቢኖር፤ እኛ ክትባቱን አስተባብረን ለማቅረብ የራሳችንን ድርሻ እየተወጣን ነው፤ እናንተም ክትባቶቹን በመጠቀም የድርሻችሁን ተወጡ" ሲሉ ተማጽነዋል። የኮሮናቫይረስ ክትባትን በአፍሪካ በሚፈለገው ፍጥነት እስካሁን ማድረስ ያልተቻለ ሲሆን፤ ለዚህም የአቅርቦት እጥረት እንዲሁም ስለ ክትባቱ ጥርጣሬዎች መኖራቸው እንደ ምክንያት ይነሳሉ።
https://www.bbc.com/amharic/56855661
amh
health
ቀይ መስቀል በሰሜን ኢትዮጵያ የመድኃኒት እና የሕክምና መገልገያ እጥረት አሳስቦኛል አለ
በሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት ተከትሎ በአካባቢው የመድኃኒት እና የሕክምና መገልገያ መሳሪያዎች አቅርቦት አለመኖር በእጅጉ እንዳሳሰበው ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ። አንድ ዓመት ካለፈው ጦርነት ጋር ተያይዞ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች የሚገኙ የሕክምና ተቋማት ውድመት የገጠማቸው ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በአሁኑ ወቅት የአስፈላጊ አቅርቦቶችን ችግር እንደገጠማቸው ተነግሯል። "የሕክምና አገልግሎት አቅራቢዎች መሠረታዊ ግብዓቶችን እያገኙ አይደለም፤ እንዲሁም በአንዳንድ መሠረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል" ብሏል ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (አይሲአርሲ) ጥር 09/2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ። ቀይ መስቀል የመድኃኒት እና ሕክምና መስጫ መሳሪዎች እጥረት ከጤና መሠረተ ልማት ውድመቶች ጋር ተደማምሮ የጤና አገልግሎት አቅርቦትን እጅግ አስቸጋሪ አድርጎታል ይላል። ቀይ መስቀል በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ፤ "ሰዎች ለመኖር የሚያስፈልጋቸውን መሠረታዊ ነገር ከመከልከል" ጋር የሚስተካከል ነው ብሏል። አይሲአርሲ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱን የበለጠ ተጎጂ በሆኑት ላይ ትኩረት እያደረኩ ነው በሏል። "የሕክምና አቅርቦቶች በመቀነሳቸው ምላሽ የመስጠት አቅማችንን ተገድቧል" ያለው ቀይ መስቀል፤ ጦርነት፣ የደኅንነት እጦት እና ገደቦች የሰብዓዊ እርዳታውን ፈተና ውስጥ ከከተቱት ምክንያቶች መካከል ቀዳሚ መሆናቸውን በትናንቱ መግለጫው አስታውቋል። "በአማራ ክልል አንዳንድ ሆስፒታሎች በመድኃኒት እጥረት ምክንያት ተዘግተዋል" ሲሉ በአማራ እና አፋር ክልሎች የቀይ መስቀል ተወካይ ሚቻ ዌዲኪንደ ተናግረዋል። "ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያለባቸው ሰዎች በየዕለቱ እየሞቱ ነው። የጤና ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆናቸው፤ ውሃ ወይም መብራት ስለማይኖራቸው እናቶች በቤት ውስጥ እየወለዱ ነው" ብለዋል የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የአማራ እና አፋር ክልል ተወካይ። ከአማራ እና አፋር በተጨማሪ በትግራይ ክልልም ከፍተኛ የሆነ መድኃኒት እና የሕክምና ቁሳቁሶች እጥረት መኖሩ ቀይ መስቀል በመግለጫ ተመልክቷል። "በትግራይ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ እንደ ጓንት፣ የቀዶ ሕክምና ቁሳቁሶች እና ሰውነት ውስጥ የሚገቡ የሕክምና ቱቦዎች ሳይቀሩ እየታጠቡ ዳግም ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ ነው" ሲሉ በኢትዮጵያ የቀይ መስቀል የጤና አስተባባሪ አፖሎ ባራሳ። ከላይ የተጠቀሱት አይነት ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ መዋል ያለባቸውን የጤና መሳሪያዎችን ዳግም መጠቀም፤ ለኢንፌክሽን የመጋለጥ እድልን ያሰፋል ይላሉ ተወካይዋ። በአንዳንድ አካባቢዎች ታካሚዎች የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶችን ከመውሰዳቸውም በተጨማሪ ሐኪሞች የሰዎችን ቁስል ለማጽዳት ጨው ለመጠቀም መገደዳቸውን ጭምር አፖሎ ባራሳ ይገልጻሉ። ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት በፍጥነት የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ የበኩላቸውን እንዲወጡ በመግለጫው ጠይቋል። ኮሚቴው ከኢትዮጵያ የቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመሆን እአአ 2021 ላይ በአማራ፣ በአፋር፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች ለሚገኙ 130 የጤና ተቋማት ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል። በዚህም ወደ 120 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ድጋፉን ማግኘታቸውን በመግለጫው አመልክቷል። የቀይ መስቀል ኮሚቴ እያደረገ ካለው የሕክምና ድጋፍ በተጨማሪ በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉ አካባቢዎች ያለው የምግብ እና የኑሮ ሁኔታ ያሳስበኛልም ብሏል። ኮሚቴው በስድስት ወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በአማራ ክልል ላልይበላ ከተማ እንዲሁም በመቀለ ከተማ ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል። በመጨረሻም ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ጨምሮም በቅርቡ ንጹሃን ዜጎችን ለጉዳት የዳረገ ግጭት መኖሩ አሳስቦኛል ብሏል። ኮሚቴው የግጭቱ ተሳታፊዎች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ሕግጋቶችን እንዲያከብሩ ጠይቋል። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የሕዝብ መገልገያ መሠረተ ልማቶች ላይ በተለይም የሕክምና ተቋማት ላይ ዘረፋና ውድመት መፈጸሙ የተለያዩ መንግሥታዊና የተራድኦ ድርጅቶች ያወጧቸው ሪፖርቶች አመልክተዋል። የጤና ተቋማት በገጠማቸው ችግርና በመድኃኒትና በሕክምና መገልገያዎች አለመኖር ምክንያት በአካባቢዎቹ ያሉ ነዋሪዎች ከባድ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች ለአደጋ መጋለጣቸው እተነገረ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-60041869
amh
health
አንድ ውሻ በዝንጀሮ ፈንጣጣ መያዙን የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ
አንድ ውሻ ከባለቤቱቶቹ በተላለፈ የዝጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ መጠቃቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የበሽታው ስርጭት ሰዎች በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ ራሳቸውን ከቤት እንስሳቶቻቸውም ጭምር ማግለል እንዳለባቸው የሚያሳይ እንደሆነም የጤና ሃላፊዎቹ አስታውቀዋል። ሌሎች እንስሳትን የመበከል አደጋን ለመቀነስ ቆሻሻን በጥንቃቄ ማስወገድ እንደሚያስፈልግ የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል። ውሾች በሽታውን ወደ ሌሎች ውሾች ወይም ወደ ሰዎች ያስተላልፉ እንደሆነ የሚያረጋግጥ መረጃ እስካሁን እንደሌለም ባለሞያዎች ገልጸዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ በቆዳ-ለቆዳ ንክኪ እና ሰዎች ጨርቆችን ጨምሮ አልጋ ወይም ፎጣ በቫይረሱ ​​​​ከተያዘ ሰው ጋር በጋራ ሲጠቀሙ የሚተላለፍ በሽታ ነው። በአሁኑጊዜ በዓለም ዙሪያ ወደ 35,000 የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን አብዛኛዎቹ በአውሮፓ፣ በሰሜን እናበደቡብ አሜሪካ ይገኛሉ ። እስካሁን ከበሽታው ጋር በተያያዘ 12 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። የአለም የጤና ድርጅት ባለፈው ሃምሌ ወር ውስጥ ነበር የዝንጀሮ ፈንጣጣን አለማቀፍ የጤና አደጋ ሲል ያወጀው። የመጀመሪያው የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ከሰው ወደ ውሻ የተላለፈው በፓሪስ ከተማ ሁለት አንድ ላይ በሚኖሩ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ወንዶች ቤት ውስጥ ነው። ግለሰቦቹ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምልክቶች ማሳየት ከጀመሩ ከ 12 ቀናት በኋላ ነበር በውሻቸው ላይም ምልክቶችን ማየት የጀመሩት። ባለሞያዎች ያደረጉት የዘረመል ትንታኔ እንደሚያሳየው ውሻውን ያጠቃው ቫይረስ ግለሰቦቹን ካጠቃው ጋር ቫይረስ ጋር ተመሳሳይ ነው። የውሻው ባለቤቶችም ውሻው አብሯቸው ሲተኛ እንደነበር ተናግረዋል። በአለም የጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምላሽ ሰጪ ቡድን ውስጥ የቴክኒካል ስራዎች መሪ የሆኑት ዶ/ር ሮሳምንድ ሉዊስ “ይህ ከዚህ በፊት ሪፖርት ያልተደረገ ብሎም ለመጀመሪያ ግዜ የመዘገበ ወደ ውሻ ያጋጠመ ስርጭት ነው ብለን እናምናለን’’ ብለዋል። በተቋሙ የድንገተኛ የጤና አደጋዎች ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር ማይክ ራያን “ጉዳዩ ያልተጠበቀ አይደለም” ብለዋል። ነገር ግን በሽታው ከአንድ ዝርያ ወደ ሌላው መዘዋወሩ እጅግ እንደሚያሳስባቸውም ተናግረዋል። አክለውም አንድ በሸታ ወደ አዲስ የእንስሳ ከተላለፈ በኋላ እንደሚላመድ ብሎም እና በውስጡም ወደ አዲስ ዝርያ እንዲለወጥ እድል እንደሚሰጥ ተናግረዋል። “ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ያጋጠመ ስርጭት ነው። ስለሆነም ውሾች ሊበከሉ ይችላሉ ማለት ነው። ነገር ግን ውሻው ሌሎች ውሾችን ሊበክል ይችላል ወይም ወደ ሰዎች ያስተላልፋል ማለት አይደለም’’ ሲሉ የአለም የጤና ድርጅት የዓለም አቀፍ ተላላፊ በሽታዎች ስጋት ዝግጁነት ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ሲልቪ ብሪያንድ ተናግረዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣን ለመከላከል በመላው አለም ያለው የክትባት አቅርቦት እስካሁን ድረስ ውስን ነው። ባለፈው ሳምንት ብቻ በበሽታው ተይዘው ሪፖርት የተደረጉ ሰዎች ቁጥር በ 20 በመቶ ጭሯል። ይህም ከሳምንት በፊት ከነበረው በ20 በመቶ ብልጫ አለው። እስካሁን አብዛኛው በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሲታይ ወንድ የተመሳሳይ ጾታ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cqlk1nd5877o
amh
health
ጠላፊዎች የታዋቂ ሰዎችን የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና ፎቶ እንለቃለን ሲሉ ዛቱ
የበይነ መረብ ጠላፊዎች የታዋቂ ሰዎችን የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና ሂደት የሚያሳይ መረጃ እንለቃለን ሲሉ ዝተዋል። ጠላፊዎቹ የታካሚዎችን የበፊትና የአሁን ፎቶ በመልቀቅ 'ጉድ እንሠራቸዋለን' እያሉ ነው። 'ዘ ሆስፒታል ግሩፕ' የተሰኘውና በታዋቂ ሰዎች ዘንድ እውቅና ያለው ድርጅት ጠላፊዎቹ ክፍያ ካልተፈፀማቸው መረጃዉን እንደሚያሾልኩ ዝተዋል ሲል አረጋግጧል። ድርጅቱ ይህን ጉዳይ ለሚመለከተው ክፍል አሳውቅያለሁ ብሏል። ሪቪል [REvil] በተሰኘ ስማቸው የሚታወቁት ጠላፊዎቹ 'ሚስጢራዊ የሆኑት' እኚህ ፎቶዎች ለተመልካች ብዙም ደስታ የሚሰጡ አይደሉም ብለዋል። ጠላፊዎቹ በኮምፒውተር ልኬት 900 ጊጋባይት መጠን ያላቸው ፎቶዎች እጃችን ገብተዋል እያሉ ነው። ዘ ሆስፒታል ግሩፕ በዩናይትድ ኪንግደም ቀዳሚው የክብደት ቅነሳና የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ሆስፒታል ነው። ክብደት መቀነሻ ቀዶ ሕክምና፣ ጡት ማሳደግ፣ የጡት ጫፍ ማስተካከል እንዲሁም አፍንጫ ማረም ሆስፒታሉ በ11 ክሊኒኮቹ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶቹ መካከል ናቸው። ሆስፒታል በቀደመው ጊዜ በታዋቂ ሰዎች አማካይነት ማስታወቂያ ይሠራ ነበር። ነገር ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ይህንን ማድረግ አቁሟል። በፈረንጆቹ 2009 'ቢግ ብራዘር' የተሰኘው የሰዎችን የዕለተ ተለት ሕይወት የሚያስቃኝ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አባል የነበረችው አይዝሊን ዘ ሆስፒታል ግሩፕ ሄዳ ጡቷን እንዳሳደገች ተናግራ ነበር። ታዋቂዋ ዘፋኝ ኬሪ ካቶና፣ ተዋናይት ቲና ማሎንና የቴሌቪዥን ኮከቡ ጆዊ ኤሴክስ ወደ ሆስፒታሉ ጎራ ብለው ሕክምና ካገኙ ታዋቂ ሰዎች መካከል ናቸው። ሆስፒታሉ ደንበኞቹን ስለተፈጠረው ጉዳይ በኤሜይል አማካይነት ማሳቁንና በጣም ከባድ ሚስጥር ያላቸው ሰዎች አደጋ ላይ ሊሆኑ እንደሚችሉ እንደነገራቸው በለቀቀው መገለጫ አስታውቋል። ጠላፊዎቹ እንለቃን ያሉት የአሁንና የቀድሞ ገፅታ የሚያሳይ ፎቶ የታካሚዎችን ማንነት ላያጋልጥ ይችላል ተብሏል። ቢቢሲ ያነጋገረው አንድ ደንበኛ ሚስጢራዊ ፎቶዎቹ በጠላፊዎች እጅ ወድቆ እንዳይሆን ስጋት እንዳለው ይናገራል። ሳይመን ሄይልስ የተሰኘው ደንበኛ ወደ ሆስፒታሉ ሄዱ ደረቱን አስቀንሶ መጥቷል። ነገር ግን ኩባንያው ጠላፊዎቹ ገንዘብ ስለመጠያቃቸው እንዳላሳወቀው ተናግሯል። "መረጃዎቻችን በጠላፊዎች እጅ ወድቀው ሊሆን እንደሚችል ተነግሮናል። ነገር ግን ዝርዝር መረጃ አልደረሰንም" ይላል። በዓለም ዙሪያ ያሉ ጠላፊዎች መረጃ ከመዘበሩ በኋላ በምትኩ ገንዘብ ይጠይቃሉ። ይህ በሳይበር ቋንቋ 'ራንሰምዌር' ይባላል። የመረጃ መረብ ደህንነት መሥሪያ ቤቶች መረጃቸው በጠላፊዎች የተወሰደባቸው ድርጅቶች ገንዘብ እንዳይከፍሉ ይመክራሉ። መረጃ መዝባሪዎች በፈረንጆቹ 2020 ብቻ 25 ቢሊዮን ዶላር እንደመዘበሩ ይነገራል። በዓለም በጣም ታዋቂ ከሆኑ መረጃ ጠላፊዎች መካከል ሪቪል አንዱ ነው። ከዚህ በፊትም ሁለት ትላልቅ ድርጅቶችን ጠልፎ ገንዘብ ተቀብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55465727
amh
health
ኮሮረናቫይረስ፡ ብዙ ተስፋ የተጣለበት የኦክስፎርድ ክትባት አስተማማኝነቱ 70 በመቶ ነው ተባለ
በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የበለጸገው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሰዎችን 70 በመቶ ከቫይረሱ መጠበቅ ያስችላል ተባለ። ይህ የክትባቱ ውጤት ይፋ የሆነው የክትባቱ ውጤታማነትን ለመፈተሽ የተካሄደው ጥናት ውጤት መታወቁን ተከትሎ ነው። የኦክስፎርድ ክትባት አስተማማኝነቱ 70 በመቶ ነው መባሉ በባለሙያዎች ዘንድ የተለያየ ስሜትን ፈጥሯል። ከዚህ ቀደም ይፋ የተደረጉት የፋይዘር እና ሞደርና ክትባቶች አስተማማኝነት 95 በመቶ መሆኑ ይታወሳል። ይሁን እንጂ የኦክስፎርድ ክትባት ከሁለቱ ክትባቶች አንጻር ዋጋው ርካሽ መሆኑ እንዲሁም ኦክስፎርድ ሰራሽ ክትባትን ማጓጓዝ እና ማከማቸት ከሁለቱ ክትባቶች አንጻር እጅግ ቀላል መሆኑ በመልካም ጎኑ ተጠቃሽ ሆኗል። በዚህም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የኦክስፎርድ ክትባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት አስቀድሞ 100 ሚሊዮን የኮሮናቫይረስ ክትባት ብልቃጦችን ለመግዛት ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጋር ውል አስሯል። ይህ ማለት ለ50 ሚሊዮን ሰዎች የሚበቃ ነው። ሰዎች ክትባቱን በሶስት ሳምንት ልዩነት ሁለት ጊዜ ይወስዱታል ተብሏል። የዩኬ ጤና ጥበቃ ኃላፊ ማት ሃንኮክ ለቢቢሲ፤ "ይህ ወደ ተለመደ አይነት ሕይወት ለመመለስ አንድ እርምጃ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ነዋሪነታቸው በዩናይትድ ኪንግደም እና ብራዚል የሆኑ 20 ሺህ ሰዎች ላይ የኦክስፎርድ ክትባት ሙከራው ተከናውኗል። የክትባቱን ሙከራ በበላይነት እየመሩ የሚገኙት ፕሮፌሰር አንድሩ ፖላርድ በክትባቱ ውጤት እጅግ ደስተኞች ነን ሲሉ ለቢቢሰ ተናግረዋል። የዩናትድ ኪንግደም መንግሥት 4 ሚሊዮን ክትባቶች ተረክቧል። 96 ሚሊዮን ብልቃጦችን ደግሞ በቅርቡ ከአምራቹ ይቀበላል ተብሏል። ክትባቱ ግን የመድሃኒት ተቆጣጠሪዎችን ይሁንታ ሳያገኝ ለሰዎች አይሰጥም። መድሃኒት ተቆጣጣሪዎች የክትባቱን አቅም ለመፈተሽ እና ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደማያስከትል ለማረጋገጥ ቢያንስ ሳምንታት ያስፈልጋቸዋል። በዩናይትድ ኪንግደም ክትባቱን በቅድሚያ ከሚያገኙት መካከል እድሜያቸው የገፉ ሰዎች፣ የአረጋውያን መኖሪያ ውስጥ የሚኖሩ አዛውንቶች እና የተቋማቱ ሰራተኞች፣ የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም እድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ የሆናቸው አዛውንቶች ተጠቃሽ ናቸው።
https://www.bbc.com/amharic/news-55042382
amh
health
በመቀለ የሚገኘው ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል አገልግሎት መስጠት ማቆሙ ተነገረ
በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ የሚገኘው ዋነኛው ሪፈራል ሆስፒታል በገጠመው የግብዓት ችግር ምክንያት ለታካሚዎች ይሰጥ የነበረውን አግልግሎት ማቋረጡን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ተናገሩ። ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በገጠመው የመድኃኒት አቅርቦት ችግር፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጥ እና በሌሎች ተደራራቢ ችግሮች ምክንያት ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን አገልግሎት መስጠት ማቆሙን የሆስፒታሉ ቴክኒካል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ክብሮም ገብረሥላሴ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ትግራይ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ የእርዳታ አቅርቦቶችን ጨምሮ መሠረታዊ አቅርቦቶች በመቋረጣቸው ምክንያት በክልሉ ውስጥ በርካታ ሰዎች በምግብና በህክምና አቅርቦት እጦት ምክንያት ለችግር መጋለጣቸውን ዓለም አቀፍ ተቋማት መግለጻቸው ይታወቃል። ከተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ከፍተኛ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት የሚመጡ በርካታ ህሙማንን ያስተናግድ የነበረው ሆስፒታሉ፤ የገጠመው ችግር ከአቅም በላይ በመሆኑ አገልግሎት ማቋረጡ ተነግሯል። ሃያ ወራት ባስቆጠረው ጦርነት ውስጥ የህክምና መገልገያዎችና መሠረታዊ አቅርቦቶች ተቋርጠውበት የቆየው ዓይደር ሆስፒታል፣ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ሆኖ ህሙማንን ለማከም ሲጥር መቆየቱን የገለጹት ኃላፊው፣ አሁን ላይ ግን አገልግሎት መስጠት የማይችልበት ደረጃ መድረሱን ገልጸዋል። ሆስፒታሉ በመድኃኒት አቅርቦት እጦት እና በህክምና መሳሪያ ችግር ምክንያት የሚሰጠው አገልግሎት ሲቆራረጥ ቆይቷል የሚሉት ዶክተር ክብሮም “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ማደንዘዣ መድኃኒት ስለሌለ፣ ለድንገተኛ ታካሚዎች ብቻ ህክምና ስንሰጥ ቆይተናል” ብለዋል። “አሁን ደግሞ የመብራት አገልግሎት ስለተቋረጠ ኦክስጅን አምርተው የሚሰጡን ተቋማት ሥራቸውን አቁመዋል። ሆስፒታሉ ሲሰጠው የነበረው የኦክስጅን አገልግሎት ከተበላሸ አንድ ዓመት አልፎበታል” ብለዋል። ከዚህ ባሻገር የነዳጅ አቅርቦት እንደሌለ የሚናገሩት ዶክተር ክብሮም፣ የሆስፒታሉ ሠራተኞች ደሞዝ ከተከፈላቸው ረጅም ጊዜ በመሆኑ በሥራ ገበታቸው ላይ ለመገኘት እና ለታካሚዎች አገልግሎት መስጠት እንዳልተቻሉ ገልጸዋል። ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድንና ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር አብዛኞቹ የክልሉ ጤና ተቋማት በጦርነቱ ምክንያት መውደማቸው እና አገልግሎት መስጠት ከማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ገልጸው እንደነበር ይታወሳል። በአሁኑ ጊዜ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ከቀላል የድንገተኛ ህክምና ውጪ አግልግሎት እንደማይሰጥና በተለይ ቀናቸው ሳይደርስ ለሚወለዱ ህጻናት እርዳታ መስጠት እንደማይችል ዶክተር ክብሮም ለቢቢሲ ገልጸዋል። የሆስፒታሉ ሐኪሞች ከአንድ ዓመት በላይ ደሞዝ ሳይከፈላቸው ሲሰሩ ቢቆዩም፣ አሁን ላይ ራሳቸውንም ሆነ ቤተሰቦቻቸውን መርዳት ባለመቻላቸው ከባድ ችግር ውስጥ ሆነ አስከ መለመን የደረሱ እንዳሉ ቢቢሲ ባለፈው ዘግቦ ነበር። በመቀለ ዩኒቨርስቲ ስር የሚገኘው የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በመቀለና በአካባቢው ለሚገኙ ነዋሪዎች የህክምና አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ 3600 ያህል ሠራተኞች እንዳሉት ከሆስፒታሉ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ለበርካታ ወራት ወደ ትግራይ የሚገባው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ተቋርጦ ከቆየ በኋላ ባለፈው መጋቢት የፌደራሉ መንግሥት የተኩስ አቁም ካወጀ በኋላ የምግብና መሠረታዊ አቅርቦቶች ወደ ክልሉ መግባት መጀመራቸው ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cqv26jlzx2vo
amh
health
በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ በሕንድ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ
በሦስተኛ የኮሮናቫይረስ ማዕበልን ውስጥ የምትገኘው ሕንድ በዋና ከተማዋ ኒው ዴሊሂ እንዲሁም በፋይናንስ ማዕከልዋ ሙምባይ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። ትላንት ማክሰኞ በአገሪቱ 37 ሺህ 379 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን በሳምንት ውስጥ የአምስት እጥፍ ጭማሪ አሳይቷል። ባለሙያዎች የመጨመሩ ምክንያት ኦሚክሮን የተባለው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ነው ብለዋል። በቫይረሱ ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ አንድ ሦስተኛው የሚሆኑት በዴሊሂ እና ሙምባይ የሚኖሩ ሲሆን ይህም በከተሞቹ የሚያዙ ሰዎች በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ እንደሆነ አመላካች ተደርጓል። በዚህም ሳቢያ የሁለቱ ከተሞች አስተዳደር የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት የሰዓት እላፊ ገደብን ጨምሮ ሌሎች ገደቦችን ይፋ አድርገዋል። የሕንድ የክትባት ግብረ ኃይል ኃላፊ ዶ/ር ኤንኬ አሮራ ሦስተኛው የወረርሽኙ ማዕበል በአገሪቱ መጀመሩን ገልፀው "ሙሉው ማዕበሉ በአዲሱ ዝርያ... ኦሚክሮን ምክንያት የመጣ ይመስላል" ሲሉ ለአገሪቷ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። አገሪቱ እስካሁን ከ1 ሺህ 700 በላይ በኦሚክሮን የተያዙ ሰዎችን ሪፖርት አድርጋለች። ከዚህ መካከል ዋና ከተማዋ ሙምባይ 568 ሰው በመመዝገብ ከፍተኛ ቁጥር የያዘች ሲሆን ዴልሂ 382 ሰዎች በመመዝገብ ሁለተኛ ላይ ተቀምጣለች። የዴልሂ የጤና መሥሪያ ቤት ኃላፊ ሳትየንዳር ጃይን በከተማው ውስጥ 81 በመቶው የኮቪድ ምርመራዎች በኦሚክሮን የተያዙ ሰዎችን እንደሚያመላክቱ ተናግረዋል። በዴልሂ የሚገኘው እና ከሕንድ ዋና ዋና ሆስፒታሎች አንዱ የሆነው የመላው ሕንድ የህክምና ሳይንስ ኢንስቲትዩት የተሰኘው ሆስፒታል ለዶክተሮች የክረምት ፈቃድ የመስጠት ተግባሩን መሰረዙ ተዘግቧል። እየጨመረ የመጣው በቫይረስ የመያዝ ምጣኔ ሕንድ በሚያዝያ እና በግንቦት ወር ያጋጠማትን አስከፊ ሁለተኛ ማዕበል የሚያስታውስ ነው የተባለ ነው። በዚያ ወቅት ማዕበሉ የመጨረሻ ጫፍ ሲደርስ በየቀኑ በአማካይ ወደ 400,000 የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ ይያዙ ነበር። በመላ አገሪቱ ያሉ ሆስፒታሎች የአልጋ እና ህይወት አድን ኦክሲጅን እጥረት የገጠማቸው ሲሆን በክፍት ቦታዎች ላይ የጅምላ የቀብር ሥነ ሥርዓቶችን ለማከናወን አስገደዷቸው ነበር። ያ ሁኔታ ቀንሶ ለበርካታ ወራት በቀን ከ10,000 በታች የሆኑ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ነበር። ሆኖም አሁን በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እንደገና ሲያሻቅብ የግዛት መንግሥታት እገዳዎችን መጣል ጀምረዋል። የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ እንደሚያመለክተው በኦሚክሮን የተያዙ ሰዎች ከሌሎች ዝርያዎች ጋር ሲነጻፀር የሆስፒታል ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ዝቅተኛ ናቸው፤ ነገር ግን በቫይረሱ የመያዝ መጠን መጨመር ሆስፒታሎች ላይ ጫና ስለሚፈጥር ባለሙያዎች ጥንቃቄ ማድረግን ይመክራሉ። ትላንት ማክሰኞ በዴልሂ ከተማ ባለሥልጣናት በእረፍት ቀናት የሚደረጉ ሁሉንም ወሳኝ ያልሆኑ ተግባራት የሚከለክል ገደብ አውጥተዋል። ዋና ከተማዋ ባለፈው ሳምንት የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና ሲኒማ ቤቶች እንዲዘጉ እንዲሁም የምሽት የሰዓት እላፊ ገደብ ጥላለች። የእረፍት ቀናት ወይም የሳምንት መጨረሻ ላይ የሚተገበረው የሰዓት እላፊ ገደብ የታወጀው የከተማው ዋና አስተዳዳሪ አርቪንድ ኬጅሪዋል ቫይረሱ ከተገኘባቸው ከሰዓታት በኋላ ነው። በሕንድ ውስጥ ከአዋቂዎች 63 በመቶ ያህሉ ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሲሆን ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቢያንስ የመጀመሪያውን ክትባት ወስደዋል። ሕንድ እስካሁን ከ34 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 482 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ በኮሮናቫይረስ መሞታቸውን ሪፖርት አድርጋለች። ባለሙያዎች ግን ትክክለኛው ቁጥር ከዚህ የበለጠ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ያስቀምጣሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-59860044
amh
health
ከኢቦላ ያገገመው ሐኪም፡ “የምሞት መስሎኝ ነበር”
ኡጋንዳ በአሁኑ ወቅት የተከሰተውን ገዳዩን የኢቦላ በሽታ ለመቆጣጠር እየታተረች ትገኛለች። ኢቦላን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት በበሽታው ተይዞ የነበረው ሐኪም “የምሞት መስሎኝ ነበር” ይላል። በዚህ ዘገባ ስለ ኢቦላ ቫይረስ ማወቅ የሚገባዎ በሙሉ ተብራርቷል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c6pj5kre7pzo
amh
health
ተጨማሪ ዘጠኝ የኮቪድ-19 ምልክቶች ይፋ ሆኑ
ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች ላይ ተጨማሪ ዘጠኝ ምልክቶች ተጨመሩ። እነዚህ ምልክቶች ከዚህ በፊት የነበሩትን የሚያሰፉና ተጨማሪ ነገሮችን ከግምት ውስጥ የሚያስገቡ ናቸው። የዩኬ የጤና ደህንነት ኤጀንሲ ባዘጋጀው አዲስ መመሪያ ውስጥ የጉሮሮ ህመም፣ የጡንቻ ህመም እና 'ተቅማጥ' ከተካተቱት አዳዲስ የኮሮረናቫይረስ ምልክቶች መካከል ናቸው። ይህ መመሪያ የወጣው ወረርሽኙ ከተከሰተ ሁለት ዓመታት ካለፈው በኋላ ሲሆን እንግሊዝ ውስጥ ደግሞ ይደረግ የነበረው የነጻ ምርመራ ከተቋረጠ ከቀናት በኋላ ነው። ነገር ግን የዩኬ የጤና ደህንነት ኤጀንሲ ባስተላለፈው የማስጠንቀቂያ መልእክት አዳዲሶቹ ምልክቶች ከጉንፋን ብዙም ያልተለዩ መሆናቸውን አሳስቧል። ከዚህ በፊት የሚታወቁት የኮቪድ-19 ምልክቶች ትኩሳት፣ የማያቆም ሳል፣ የሽታ እና የመቅመስ ስሜቶቻችን መጥፋት እንዲሁም ድካም የሚጠቀሱ ናቸው። ወረርሽኙ ባጋጠመበት የመጀመሪያዎቹ ወራት ወቅት የስርጭቱን አካሄድ መረዳትና ምልክቶቹን መለየት ከባድ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን ዓለም ስለቫይረሱ ማወቅ ከሚገባው አብዛኛውን ነገር አውቋል። የዓለም ጤና ድርጅትም ቢሆን ከረጅም ጊዜ በፊት ምልክቶች ብሎ ያስቀመጣቸው ነገሮች በርካታ ናቸው። ነገር ግን ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ትክክለኛ ምልክቶቹ የትኞቹ ናቸው እንዲሁም ምን አይነት ምልክቶችን የሚያሳይ ሰው ነው ምርመራ ማድረግ ያለበት የሚሉት ጥያቄዎች መከራከሪያ ሆነው ቆይተዋል። ለምሳሌ ራስ ምታት የኮሮናቫይረስ ምልክት ተደርጎ ሊቆጠር የሚችል ቢሆንም ራሱን ያመመው ሰው በሙሉ ግን የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረግ አይችልም። ምክንያቱም ራስ ምታት ከኮሮናቫይረስ ውጪ በበርካታ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል። ትኩሳት፣ ሳል፣ ማሽተት ማቆም አልያም ጣእም ማጣት በርካቶችን የማያከራክሩ ምልክቶች ሲሆኑ አሁን ላይ ደግሞ ዘጠኝ ተጨማሪ ምልክቶች እንዲጨመሩ ተደርጓል። እነዚህም ትንፋሽ ማጠር፣ ድካም፣ የሰውነት መላሸቅ፣ ራስ ምታት፣ የጉሮሮ ሕመም፣ ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ [ንፍጥ]፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ተቅማጥ እና አጠቃላይ የጤንነት ስሜት ማጣት ናቸው። ዩኬ ውስጥ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 4.9 ሚሊየን የደረሰ ሲሆን መንግስት በነጻ ሲያከናውነው የነበረው ምርመራም ባሳለፍነው ሳምንት ተጠናቋል። የዩኬ የጤና ደህንነት ኤጀንሲ እንደሚለው ሰዎች አሁንም ቢሆን በተቻላቸው መጠን ከቤታቸው ላለመውጣት መሞከርና ከሌሎች ሰዎች ጋር ያላቸውንም ንክኪ መቀነስ አለባቸው። በተለይ ደግሞ እነዚህን ምልክቶች የሚያሳይ ሰው ምርመራ ማድረግና እራሱን ከሰዎች መለየት እንዳለበት ኤጀንሲው አሳስቧል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60992822
amh
health
ኮሮናቫይረስ ፡ አሜሪካ የኮቪድ-19 ምልክት የማያሳዩ አይመረመሩም የሚለውን ውሳኔ ቀለበሰች
ባለፈው ወር አሜሪካ የኮቪድ-19 ምልክት የማያሳዩ ሰዎች ምርመራ ማድረግ የለባቸውም የሚል አወዛጋቢ ውሳኔ አስተላልፋ ነበር። አሁን ግን ይህ ውሳኔ በጤናው ዘርፍ አመራሮች መቀልበሱ ተገልጿል። የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ተቋም [ሲዲሲ] እንዳለው በሽታው ካለበት ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው በአጠቃላይ መመርመር አለባቸው። ተቋሙ ከዚህ ቀደም የነበረው አሠራር ነሐሴ ላይ ለውጥ ተደርጎበት የነበረ ቢሆንም ምርመራን በተመለከተ ወደ ቀድሞው መርህ ተመልሷል። አወዛጋቢ የተባለው ውሳኔ የተላለፈው ያለሳይንቲስቶች ምክረ ሐሳብ ነው ተብሏል። ኒው ዮርክ ታይምስ የጠቀሳቸው ምንጭ እንዳሉት፤ ውሳኔው በሲዲሲ ድረ ገጽ መለጠፉን ባለሙያዎች ተቃውመዋል። ሮይተርስ እንደዘገበው፤ በርካታ የአሜሪካ ግዛቶች ውሳኔውን አንቀበልም ብለዋል። ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተሉ ያሉ እንደሚሉት በአወዛጋቢው ውሳኔ ውስጥ የፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ እጅ ሊኖርበት ይችላል። ምርመራ የሚያደርጉ ሰዎችን ቁጥር በመቀነስ ሪፖርት የሚደረጉ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎችን አሃዝ ለመቀነስ አስበው እንደሆነም ተጠቁሟል። ፕሬዝዳንቱ ሰኔ ላይ የምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ደጋፊዎቻቸውን “ባለሥልጣኖችን እባካችሁ ምርመራ ቀንሱ ብያቸዋለሁ” ማለታቸው ይታወሳል። አንድ የዋይት ሐውስ ባለሥልጣን የፕሬዘዳንቱ ንግግር “ቀልድ ነበር” ብለዋል። በሌላ በኩል የሲዲሲ አመራሮች ውሳኔው የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እንደሌለው ገልጸዋል። ለውጡ ወቅታዊውን የኅብረተሰብ ጤናን የተመረኮዘ ነው ሲሉም ለሮይተርስ ተናግረዋል። የቀድሞው ውሳኔ መቀልበሱ ባለሙያዎችን አስደስቷል። የተላላፊ በሽታዎች ማኅበር ፕሬዘዳንት የሆኑት ቶማስ ፋይል "ሲዲሲ ሳይንስን መሠረት ወዳደረገ ምርመራ መመለሱ ለኅብረተሰብ ጤና መልካም ዜና ነው። ከወረርሽኙ ጋር የምናደርገውን ትግልም ያግዛል” ብለዋል። ሲዲሲ ውሳኔውን መቀልበሱን በተመለከተ “የበሽታውን ምልክት የማያሳዩ ሰዎችን እንዲሁም በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን መመርመር ያስፈልጋል” ብሏል። በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር በስድስት ጫማ ርቀት ቢያንስ ለ15 ደቂቃ የተገናኙ ሰዎች የበሽታውን ምልክት ባያሳዩም እንዲመረመሩ ተቋሙ ይመክራል። በአሜሪካ በአሁኑ ወቅት ወደ 7 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። ይህም በመላው ዓለም በሽታው ከተገኘባቸው የሰዎች ብዛት አንድ አምስተኛው ነው። በወረርሽኙ ሳቢያም 200,000 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ ይህም ከዓለም አገራት ከፍተኛው ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-54216398
amh
health
ፋይዘር የኮሮናቫይረስ ማከሚያ መድኃኒቱን ታዳጊ አገራች እንዲያመርቱት ፈቀደ
ፋይዘር በሙከራ ደረጃ ያለውን የኮሮናቫይረስ ማከሚያ እንክብል መድኃኒቱን ታዳጊ አገሮች እንዲሠሩት እና እንዲያከፋፍሉት ፈቀደ። የአሜሪካው መድኃኒት አምራች ፋይዘር በ95 ታዳጊ አገራት እንክብል መድኃኒቱ እንዲመረት የተስማማው የተባበሩት መንግሥታት ከሚደግፈው ሜድስንስ ፔሸንት ፑል ድርጅት ጋር በመጣመር ነው። ድርጅቱ የኮሮናቫይረስ ማከሚያ መድኃኒቱን ከሠራ በኋላ 53 በመቶ ለሚሆነው የዓለም ሕዝብ ያዳርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ስምምነቱ እንደ ብራዚል ያሉ በከፍተኛ ሁኔታ ቫይረሱ የተስፋፋባቸው አገራትን አያካትትም። መድኃኒቱ ለሕመም ተጋላጭ የሆኑ ጎልማሶች በጽኑ በሽታ እንዳይያዙ እንደሚከላከል ፋይዘር አስታውቋል። መድኃኒቱ በታዳጊ አገራት እንዲመረት መፍቀዱ "የመድኃኒቱን ተደራሽነት ያሰፋዋል" ሲል ገልጿል። በታዳጊ አገራት ከሚመረተው መድኃኒት ፋይዘር የባለቤትነት (ሮያሊቲ) ክፍያ አይወስድም። ወረርሽኙ ለዓለም አስጊ ሆኖ እስከቀጠለ ድረስ በሁሉም አገራት ትርፍ እንደማይሰበስብም ይፋ አድርጓል። ፋይዘር ለኮቪድ-19 ማከሚያ እየሠራ ያለው ፓክሎቪድ የተባለ መድኃኒት ነው። ይህም በከፍተኛ ሁኔታ ለሕመም ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ሞትና ሆስፒታል የመግባት እድልን በ89 በመቶ ይቀንሳል ተብሏል። የሜድስንስ ፔሸንት ፑል ኃላፊ ቻርልስ ጎሬ እንዳሉት መድኃኒቱ በታዳጊ አገራት እንዲመረት ፍቃድ መሰጠቱ መልካም ነው። "ይህ መድኃኒት በተለይም አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት ሕይወት ያድናል" ብለዋል። መድኃኒቱን እንዲሠሩ ፈቃድ ካገኙ አገራት አብዛኞቹ በአፍሪካ እና እስያ ይገኛሉ። እንደ ብራዚል፣ ቻይና፣ ሩስያ፣ አርጀንቲና እና ታይላንድ ያሉ ክፉኛ በወረርሽኙ የተጎዱ አገራት በስምምነቱ አልተካተቱም። የኮሮናቫይረስ ሕክምና እንዲሁም ክትባቱን ተደራሽ ለማድረግ ይህ እርምጃ በቂ እንዳልሆነ ባለሙያዎች ተችተዋል። ፋይዘርን ጨምሮ ሌሎችም የኮቪድ-19 ክትባት አምራቾች የባለቤትነት መብታቸውን አንስተው፤ ክትባቱ በሌሎች አገራት እንዲመረት ፈቃድ እንዲሰጡ ቢጠየቁም አሻፈረኝ ብለዋል። ዶክተርስ ዊዝአውት ቦርደርስ ባወጣው መግለጫ፤ ፋይዘር ለታዳጊ አገራት የሰጠው ፈቃድ የኮሮናቫይረስ መድኃኒት በመላው ዓለም እንዲደርስ እንደማይረዳ ተችቷል። "ወረርሽኙን መግታት ከፈለግን የኮሮናቫይረስ ማከሚያ መድኃኒት ለሁሉም ሰው፣ በሁሉም አገር መዳረስ አለበት" ሲሉ የድርጅቱ የሕግ አማካሪ ዩአንክዮንግ ሁ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም መርክ የተባለው መድኃኒት አምራች ድርጅት ሞልኑፒራቪር የተባለ የኮሮናቫይረስ መድኃኒቱ ከሜድስንስ ፔሸንት ፑል ጋር በጥምረት ለማምረት ተስማምቷል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59315766
amh
health
ሦስት ልጆቻቸው ዐይነ ስውር ከመሆናቸው በፊት ዓለምን እየዞሩ ያሉት ቤተሰቦች
የኢዲት እና የሴባስቲያን ልጆች አንድ ቀን አይነ ስውር ይሆናሉ። ከአራት ልጆቻቸው ሦስቱ በዘር የሚተላለፍ እና በሂደት የዐይን ብርሃንን የሚያሳጣ በሽታ ተገኝቶባቸዋል። በመሆኑም ወላጆች ችግሩ ከመከሰቱ በፊት በልጆቻው ላይ ትውስታ ለማስቀመጥ በርካታ የዓለም ክፍልን በመዘዋወር ለማሳየት ወስነዋል። በሽታው ምንም አይነት ምልክት አይታይበትም። ሰዎች ከውልደታቸው ጀምሮ ይዘውት የሚመጡት ነገር ነው። ይህ ችግር በልጆቻቸው ላይ እንደተከሰተ ያወቁት እነዚህ ካናዳውያን ቤተሰቦች የአንድ ዓመት ጉዞ ማድረግ ከጀመሩ ስድስት ወር ሆኗቸዋል። በስድስት ወር ጊዜ ውስጥም በሦስት አህጉራት ስድስት አገራትን ጎብኝተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c723g4z20eeo
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ የዕድሜ ባለጠጋዎቹ ጥንዶች በእንክብካቤ ማዕከል ውስጥ ተሞሸሩ
በዊልቲሸር በሚገኝ የአረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከል ውስጥ የሚኖሩ የ85 ዓመት አዛውንት 91 ዓመት የሞላቸውን ፍቅረኛቸውን በማዕከል ውስጥ አግብተዋል። ይህ የዕድሜ ባለፀጋዎቹ ጋብቻ ሊፈፀም የቻለው የአካባቢው አስተዳደር በሰጠው ልዩ ፍቃድ መሆኑም ተነግሯል። ሁለቱ ጥንዶች ፒተር ስሚርለስ እና ጄን ሮብሰን የጋብቻ ስነ ስርዓታቸውን ከዚህ ቀደም ብለው ለማድረግ ያሰቡ ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለማራዘም ተገደዋል። ሆኖም ከፈረንጆቹ ገና በኃላ የፒተር የጤንነት ሁኔታ እያሽቆለቆለ ሲመጣ ሀኪማቸው የሰርግ ስነ ስርዓቱ በፍጥነት እንዲከወን መክሯቸዋል። ይህንንም ተከትሎ ጥንዶቹ በዊልቲሸር፣ ፑተር በሚገኝ ሴደር በተሰኘ የእንክብካቤ ማዕከል ውስጥ ጋብቻቸውን ለመፈፀም በቅተዋል። ሁለቱ ጥንዶች በፍቅር 26 ዓመታት ቆይተዋል። "የመጀመሪያውን የ'ላግባሽ' ጥያቄ ያቅረበልኝ ከ 25 ዓመታት በፊት ቢሆንም 'ለምን እንጣደፋለን?' ብዬዋለው" የሚሉት አዲሷ የዕድሜ ባለጠጋ ሙሽራ "ይህ መቼም የሚሆን አይመስልም ነበር" ሲሉ ገልፀዋል። የጥንዶቹ የጋብቻ ስነ ስርዓት ከመፈፀሙ አስቀድሞ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ሁኔታ በተመለከተ ምልከታ የተደረገ ሲሆን ቫይረሱን ለመከላከል የሚረዱ የጥንቃቄ መንገዶች መተግበራቸውም ተገልፃል።
https://www.bbc.com/amharic/56249351
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ በአውስትራሊያ የተከሰተው አዲሱ ዙር ወረርሽኝ ከለይቶ ማቆያ ሆቴሎች ጋር የተገናኘ ነው ተባለ
በአውስትራሊያዋ ከተማ ቪክቶሪያ የተከሰተው አዲሱ ዙር ወረርሽኝ ከለይቶ ማቆያ ሆቴሎች ጋር የተያያዘ መሆኑ ተገልጿል። ከሌላ አገራት የተመለሱ መንገደኞች ራሳቸውን ለይተው ባቆዩባቸው ሆቴሎች ወረርሽኙ መነሳቱም በምርመራ ተጣርቷል። በዚህ ምርመራ እንደተገኘው የሆቴሉ አጠቃላይ ሰራተኞችም ያልተገባ ስልጠና ወስደዋል ተብሏል። የአውስትራሊያ ሚዲያ እንደዘገበው የሆቴሉ ጠባቂዎች ጭምብልም ሆነ ሌሎች የመከላከያ ቁሳቁሶችን ማድረግ አስፈላጊ አይደለም፤ አካላዊ ርቀታችሁን እስከጠበቃችሁ ድረስ የሚል ምክር ተሰጥቷቸዋል። ይህንንም ተከትሎ ቪክቶሪያ ላይ አዲስ ዙር ወረርሽኝ ተከስቷል፤ ከተማው እንቅስቃሴዋ እንዲታገድ ትዕዛዝ ተላልፏል። በሌላኛዋ ከተማ ሜልቦርን እንዲሁም ጥብቅ የተባለ የእንቅስቃሴ ገደብ ለስምንት ሳምንታት ተጥሎባታል። በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ በቪክቶሪያ 282 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 25ቱ ሞዋል። ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮም ከፍተኛ እንደሆነም ተገልጿል። መጋቢት መጨረሻ ላይ የአውስትራሊያ ፌደራል መንግሥት በሌላ አገራት የሚኖሩ ዜጎቹ ሲመለሱ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ መግባት አለባቸው የሚል ውሳኔን አስተላልፏል። ይህንንም ተግባራዊነት የሚያስፈፅሙት የተለያዩ ከተማ አስተዳዳሪዎች ናቸው። በሜልቦርን የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ቤን ሃውደን እንዳሉት በአሁኑ ሰዓት የተከሰተው አዲሱ ዙር ወረርሽኝ ውስጥ 99 በመቶው ከውጭ አገራት ከመጡ መንገደኞች ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል። ስለ መንገደኞቹ ማንነትም ሆነ የትኞቹ ሆቴሎች እንደሆኑ ዝርዝር መረጃ አልተሰጠም። ምርመራው ሆቴሎች ለይቶ ማቆያዎቻቸውን እንዴት እያስተዳደሩ እንደነበርም በምርመራው በጥልቀት እየታየ ነው ተብሏል፤ ይህም ለወደፊቱ ለይቶ ማቆያዎች በማሻሻያነት ግብአት እንዲሆን ነው። ለይቶ ማቆያዎቹ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን መግታት ሳይሆን የበለጠ ማስፋፊያ ሆነዋልም ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-53798545
amh
health
በአውስትራሊያ በምርመራ ማዕከል ስህተት ብዙዎች ኮሮናቫይረስ እንደሌለባቸው ተነገራቸው
በአውስትራሊያ ሲድኒ ውስጥ በሚገኝ የምርመራ ማዕከል በተፈጠረ ስህተት ምክንያት ኮሮናቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ከቫይረሱ ነጻ ናችሁ ተባሉ። በሲድኒ በርካቶች በወረርሽኙ እየተያዙ ቢሆንም በምርመራ ማዕከሉ ስህተት ሳቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቫይረሱ እንደሌለባቸው ተነግሯቸዋል። ስህተቱ የተፈጠረው በፈረንጆች ገና ሰሞን ነው። ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ናሙና ሲፈተሽ በተፈጠረ የመረጃ ስህተት ሳቢያ ውጤቱ የተሳሳተ መሆኑም ተገልጿል። አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ኦሚክሮን መስፋፋት ከጀመረ ወዲህ በአውስትራሊያ በወረርሽኙ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። ብዙ ሰዎች ምርመራ እያደረጉ መሆኑ የመረጃ መጨናነቅ መፍጠሩም ተጠቁሟል። ቫይረሱ እያለባቸው የለባችሁም የተባሉት ሰዎች በዓመት በዓል ሰሞን ቫይረሱን ወደ ወዳጅ ዘመዶቻቸው አስተላልፈው ሊሆን እንደሚችል ተሰግቷል። ሲድፓዝ የተባለው የምርመራ ማዕከል ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ ጠይቋል። ወደ 886 ሰዎች የምርመራ ውጤታቸው የተሳሳተ የሆነው ባልተጠበቀ ሁኔታ ምርመራ ያደረጉ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ መሆኑን ቤተ ሙከራው ገልጿል። 400 ሰዎች የገና ዕለት ቫይረሱ እንደሌለባቸው ቢነገራቸውም በነጋታው ግን ትክክለኛ ውጤታቸው ተገልጾላቸዋል። ከእነዚህ ሰዎች በኋላ ተጨማሪ 486 ሰዎች ቫይረሱ ቢኖርባቸውም በስህተት የለባችሁም መባላቸውን ምርመራ ማዕከሉ ይፋ አድርጓል። የሰዎች ናሙና በዲጂታል መንገድ ይመረመር እንደነበረና ከሰሞኑ ግን በሰው ኃይል ምርመራ መደረግ በመጀመሩ የተፈጠረ ክፍተት እንደሆነ ተገልጿል። ከዚህ በኋላ ወደ ዲጂታል ምርመራ እንደሚመለሱም አክለዋል። ስታፋኒ ኮሎና የተባለች የሲድኒ ነዋሪ ቫይረሱ እያለባት የለብሽም ከተባለች በኋላ ከቤተሰቦቿ ጋር እንደተገናኘችና ቫይረሱን አስተላልፋባቸው ሊሆን እንደሚችል ተናግራለች። የጤና ሚኒስትሩ ብራድ ሀዛርድ ስህተቱ የተፈጠረው ምርመራ የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር በጣም በመጨመሩ ነው ብለዋል። የቫይረሱ ስርጭት ከጨመረ ወዲህ በየቀኑ ምርመራ የሚደረግላቸው ሰዎች ቁጥር ከ117,000 ወደ 145,000 አድጓል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59810496
amh
health
ኮሮረናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ጽኑ ህሙማን ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት አሻቀበ
የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የጽኑ ታማሚዎች ቁጥር ከአንድ ሺህ ማለፉን ተገለጸ። የጤና ሚኒስቴርና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ሐሙስ ሚያዝያ 07/2013 ዓ.ም ባወጣው ዕለታዊ የወረርሽኙ መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በበሽታው በጽኑ የታመሙ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 031 መድረሱን አመልክቷል። ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀ ከአንድ ዓመት በኋላ ባሉት ሦስት ወራት፤ ማለትም ባለፉት ጥር፣ የካቲትና መጋቢት ውስጥ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ቀስ በቀስ እያሻቀበ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን የኢትዮጵያ የጤና ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ሲገልጹ ነበር። የወረርሽኙ በማኅበረሰብ ደረጃ መስፋፋቱ አሳሳቢ ከመሆኑ በተጨማሪ በወረርሽኙ ሳቢያ በጽኑ የሚታመሙና ለሞት የሚዳረጉ ሰዎችም ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ከወራት በፊት ምርመራ ከሚያደርጉ ሰዎች መካከል ቫይረሱ ይገኝባቸው የነበሩት ከአምስት መቶ ብዙም ሳይርቅ በመቶዎቹ የሚቆተሩ የነበረ ሲሆን አሁን ግን በየቀኑ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው ተይዘው ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪም በበሽታው ክፉኛ ታመው የጽኑ ህሙማን ክትትልና ድጋፍን የሚሹ ሰዎች ቁጥር ከአምስት መቶ በታች ሆኖ ለረጅም ጊዜ የቆየ ሲሆን፤ ባለፉት ሁለት ወራት ግን አሃዙ ከአምስት መቶ አልፎ አሁን ከአንድ ሺህ በላይ ደርሷል። በተመሳሳይ በየቀኑ በበሽታው ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአስራዎቹ የሚቆጠር ሆኖ ለረጅም ጊዜ ቆይቶ አሁን ግን ከሃያዎቹ አስከ ሰላሳዎቹ የሚደርሱ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ እየተመዘገበ ነው። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙና የጽኑ ህሙማን ህክምናና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያና የኦክስጂን እጥረት እያጋጠመ መሆኑ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገልጾ የነበረ ሲሆን ቁጥሩ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ችግሩን የበለጠ ያባብሰዋል። ተቋሙ በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ዕለት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ የባለሙያ ድጋፍና እንክብካቤ የሚሹ ሰዎች ቁጥር "የህክምና ማዕከላት ማስተናገድ ከሚችሉት አቅም በላይ" እየሆነ መምጣቱን ጨምሮ ገልጿል። በዚህም ሳቢያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ ታምመው በህክምና ተቋማት ድጋፍ ለማግኘት ለሚመጡ ህሙማን አገልግሎት የሚውሉ "የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) እና የኦክስጅን እጥረት እያጋጠመ ነው" ሲል ገልጿል። የኮሮናቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን በተለይም ሳንባን የሚያጠቃ ሲሆን በበሽታው ክፉኛ ለተጠቁ ጽኑ ህሙማን ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ (ቬንትሌተር) እና ኦክስጂን ህይወታቸውን ለመታደግ ለሚደረገው ጥረት በእጅጉ አስፈላጊ ናቸው። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ የታመሙ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ በአሁኑ ወቅት በአገልግሎት ላይ የሚገኙት የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ ቬንትሌተሮች ቁጥር ከ500 ብዙም የበለጡ እንዳልሆኑ ሲገለጽ ቆይቷል። በየዕለቱ በበወረርሽኙ በጽኑ ታመው ድጋፍ የሚሹት ህሙማን ቁጥር በመቶዎች ከመቆጠር አልፎ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሺህ በላይ መድረሱ የጤና ተቋማት ለህሙማኑ እንክብካቤና ድጋፍ ለመስጠት ችግር እየገጠማቸው መሆኑ ቀደም ሲል መገለጹ ይታወሳል። በተለይም በወረርሽኙ በጽኑ ታመው የቬንትሌተርና የኦክስጂን ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ህሙማን ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ የነፍስ አድን አገልግሎቱን መስጠት ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ከደረሰ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ሊያሻቅብ ይችላል። በአሁኑ ወቅት በመላው አገሪቱ በየዕለቱ የሚመዘገበው በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የገለጸው ኢንስቲትዩቱ፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በወረርሽኙ ሳቢያ የጽኑ ህሙማን የህክምና አገልግሎት የሚፈልጉ ህሙማንና ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር "አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል" ይገኛል ብሏል። ሐሙስ ዕለት በወጣው የበሽታው ዕለታዊ ሪፖርት መሠረትም 33 ሰዎች በኮቪድ-19 በሽታ ምክንያት መሞታቸው ተገልጿል። በዕለቱ 8 ሺህ 878 ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸው 2 ሺህ 149ኙ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ ቀደም ሲል በበሽታው ተይዘው ከነበሩት መካከል ደግሞ 1 ሺህ 288 አገግመዋል። አስካሁን በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ 236 ሺህ 554 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3 ሺህ 285 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 175 ሺህ 879 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56755324
amh
health
ኖርዌይ ፡ በአንድ ዋሻ ውስጥ ሲዝናኑ የነበሩ ሰዎች በጭስ ታፍነው ሆስፒታል ገቡ
በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ውስጥ በሚገኝ በአንድ ከመሬት በታች ባለ ዋሻ ውስጥ ተሰባስበው እየተዝናኑ ከነበሩ ሰዎች መካከል ከ20 የሚበልጡት በካርበን ሞኖክሳይድ ጭስ ታፍነው በመመረዛቸው ሆስፒታል መግባታቸው ተነገረ። ግለሰቦቹ ሊገኙ የቻሉት በአካባቢው ቅኝት ሲያደርጉ የነበሩ ፖሊሶች በዋሻው ውስጥ ከነበሩት መካከል የተወሰኑት ራሳቸውን ስተው ወደ ጎዳና በመውጣት ወዲያ ወዲህ ሲሉ ካገኟቸው በኋላ ነው። ከዚህም በኋላ ሌሎቹ ጓደኞቻቸው በጭሱ ታፍነው ከዋሻው ውስጥ በመውጣታቸው አምቡላንስ ተጠርቶ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ ተደርጓል። ባለስልጣናቱ የፓርቲው ታዳሚዎችን ለመመረዝ ያበቁት ወደ ዋሻው ይዘው ከገቡት አነስተኛ ጄኔሬተር በሚወጣ ጭስ ምክንያት ነው ብለው ያምናሉ። በጭሱ የመመረዝ ጉዳት ካጋጠማቸው 25 ሰዎች መካከል ሁለቱ በዋሻው ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ለማውጣት ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ፖሊሶች ናቸው። ግለሰቦቹ አሁን ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተም "እድለኞች ናቸው፤ የሁሉም የጤና ሁኔታ እየተሻሻለ ነው። በጤናቸው ላይ ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም" ሲሉ በኦስሎ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ዋና ሐኪም ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ከ20 በላይ ሰዎች በጭስ በታፈኑበት በዚህ ዝግጅት ላይ 200 የሚደርሱ ሰዎች ታድመውበት እንደነበር የኦስሎ ፖሊስ አስታውቋል። በተጨማሪም ታምመው ወደ ሆስፒታል ከገቡት የፓርቲው ታዳሚዎች ውጪ ያሉት ማቅለሽለሽ፣ የራስ ምታት፣ ራስን የመሳት ስሜት ካጋጠማቸው ወደ ሐኪም ቤት እንዲሄዱ ፖሊስ መክሯል። ፖሊሶች በአደጋው ስፍራ ከመድረሳቸው በፊት ከዋሻው ወጥቶ የሄደ የዝግጅቱ ታዳሚ እንዳለው በስፍራው በነበረው የታፈነ አየር ምክንያት በተደጋጋሚ ወደ ውጪ እየወጣ አየር ሲወስድ ነበር። የኦስሎ ፖሊስ በዋሻው ውስጥ ስለተካሄደው ዝግጅት ቀድሞ ጥቆማ የደረሰው ቢሆንም በወቅቱ ለምን እርምጃ መውሰድ እንዳልቻለ ምርመራ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/news-53967065
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ በሜክሲኮ ሆስፒታል የኮቪድ-19 ክትባቶች ተሰረቁ
በሜክሲኮዋ ሞሬሎስ ግዛት በሚገኝ ሆስፒታል የኮቪድ-19 ክትባቶች ተሰርቀዋል ተብሏል። ይህንንም ተከትሎ የአገሪቱ ጦር ምርመራ ከፍቷል። ሜክሲኮ ይህንንም ስርቆት ለመመርመርና ጥፋተኞቹንም በቁጥጥር ስር ለማዋል በመላው አገሪቷ ጦሯን አሰማርታለች። በዋናነትም በአገሪቷ አድራጊና ፈጣሪ ከሆኑት የማፊያ ቡድን እጅ ክትባቶቹም እንዳይገባ ስጋት ስለፈጠረም ነው ሰራዊቱ የተሰማራው። "ስርቆቱ ምናልባት የተፈፀመው ታማኝ ባልሆነ የሆስፒታሉ የክትባት ቡድን አባል ሊሆን ይችላል" የሚል መግለጫም ከመንግሥት በኩል ወጥቷል። የተዘረፈው የክትባት መጠን አልተጠቀሰም። ሜክሲኮ 129 ሚሊዮን ህዝቦቿን በነፃ ክትባት ለመክተብም ቃል ገብታለች። በአለም አቀፍ ደረጃ በወረርሽኙ ክፉኛ ከተጠቁ አገራት አንዷ የሆነቸው ሜክሲኮ 140 ሺህ ዜጎቿንም በቫይረሱ አጥታለች። ይህም አሃዝ ከአለም አራተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ ሶኖራ በምትባለው ግዛት ታጣቂዎች አንድ ሆስፒታል ውስጥ በመግባት ለኮሮናቫይረስ ህሙማን የሚውል የማገዣ መሳሪያ መተንፈሻ (ኦክስጅን) መዝረፋቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው አስነብቧል። ዘራፊዎቹ በሆስፒታሉ ሰራተኞች ላይ ጥይት ከደገኑ በኋላ ኦክስጅኑ የት እንደሚቀመጥ ጠይቀዋቸዋል። በመቀጠልም ሶስት ኦክስጅን የተሞላበት መሳሪያና አራት የኦክስጅን ማስቀመጫን ይዘው ሄደዋል ተብሏል። በአገሪቱ ውስጥ የኦክስጅን ስርቆት በሌላለ አካባቢም እንዲሁ የተከሰተ ሲሆን በቅርቡም የተሰረቀ 44 የኦክስጅን መሳሪያዎችን የያዘ የከባድ ጭነት መኪና ሜክሲኮ ከተማ አቅራቢያ ተይዟል። በርካታ ዜጎች ህሙማን ቤተሰቦቻቸውን በየቤቶቻቸው እንዲያቆዩ በተገደዱበት ወቅት የማገዣ መሳሪያ መተንፈሻ (ኦከስስጅን)ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። አገሪቷ ባጋጠማት ከፍተኛ የኮሮናቫይረስ ህሙማንም ቁጥር ሆስፒታሎች ሞልተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55745361
amh
health
የጉሮሮ ካንሰር ለምን የአርሲ እና የባሌ አካባቢ ማህኅረሰብን በተለየ ያጠቃል?
የጉሮሮ ካንሰር፣ ገዳይ ከሆኑ የካንሰር ዓይነቶች መካከል አንዱ ነው። በተለያዩ የዓለማችን አገራት በጉሮሮ ካንሰር የሚጠቁ ሰዎች ቢኖሩም ከሌሎች በተለየ ግን ስርጭቱ ሰፋ ብሎ የሚታይባቸው አካባቢዎች መኖራቸውን ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። እነዚህ አገራትም በምሥራቅ እና በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በእስያ የሚገኙ አገራት ናቸው። ኢትዮጵያም የጉሮሮ ካንሰር በስፋት ከሚስተዋልባቸው አገራት መካከል ትገኛለች። ምንም እንኳ እርግጠኛው የጉሮሮ ካንሰር መነሻ ምክንያቶች እነዚህ ናቸው ተብሎ ባይበየኑም፣ በበርካታ አገራት የአልኮል መጠጥን የሚያዘወትሩ፣ በሲጋራ ሱስ የተጠመዱ ሰዎች በጉሮሮ ካንሰር እንደሚጠቁ ጥናቶች ያሳያሉ። በተጨማሪም የሚፋጁ ምግቦች እና መጠጦችን የሚያዘወትሩ ለጉሮሮ ካንሰር የመጋለጥ ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን እነዚህ ጥናቶች ጠቁመዋል። ካንሰር ምንድን ነው? ካንሰር ሰውነታችን ውስጥ ያሉ ሴሎች ያለ አግባብ ሲበዙ የሚፈጠር በሽታ ነው። ይህ ያለ አግባብ የሴሎች መባዛት፣ ሰውነት ላይ እብጠት ይፈጥራል። ይህ እባጭም በጊዜ ሂደት እያደገ የሚሄድ ነው። ዶ/ር ጂልቻ ድሪባ የካንሰር ስፔሻሊስት እና በበሽታው ዙሪያ የተለያዩ ጥናቶችን በመስራት ላይ ይገኛሉ። "ካንሰር ከተፈጠረበት የአካላችን ክፍል በመነሳት እየተስፋፋ የሚሄድ ሲሆን፣ የሰውነታችንን ምግብም ይሻማል። በዚህ ሂደትም በሙሉ ሰውነታችን ላይ በመስፋፋት ሕይወትን እስከ ማሳለፍ ይደርሳል" ይላሉ ዶ/ር ጂልቻ። ስለጉሮሮ ካንሰርም ሲያብራሩ በኢትዮጵያ ከሌሎቹ የአገሪቱ አካባቢዎች በተለየ በአርሲ እና በባሌ ተስፋፍቶ እንደሚገኝ ይናገራሉ። እርሳቸውም የባሌ እና የአርሲን ማኅበረሰብን በስፋት እየጎዳ የሚገኘውን ይህንን የጎሮሮ ካንሰር ላይ አራት ጥናቶችን ይፋ አድርገዋል። የአርሲን እና የባሌን ማኅበረሰብን ለምን? ይህ የካንሰር ዓይነት የጉሮሮ ቱቦን የሚያጠቃ ሲሆን 'የጎሮሮ ካንሰር' በመባል ይታወቃል። ኢትዮጵያ ውስጥም በተወሰኑ አካባቢዎች ብቻ ላይ ይስተዋላል። "በአገር ደረጃ በዚህ የካንሰር ዓይነት ተይዘው በብዛት ወደ ሆስፒታል የሚመጡ ሰዎች በተለይ ከባሌ እና ከአርሲ አካባቢ ነው። እኔም በዚህ ጉዳይ ላይ ለዓመታት ጥናት ሳደርግ ቆይቻለሁ። ምሥራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ቡታጅራ እና ስልጤ አካባቢዎችም እንደ አርሲ እና ባሌ ባይሆንም ይህ በሽታ ከሚታይባቸው አካባቢዎች መካከል ናቸው።" ይህ የካንሰር ዓይነት ለምን በእነዚህ ሁለት አካባቢዎች በስፋት ይከሰታል? እንደ ዶ/ር ጂልቻ ጥናት ከሆነ ዋናው ምክንያት በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩት ማኅበረሰቦች አዘውትረው ከሚመገቡት ምግብ ጋር የሚያያዝ ነው። "ለዚህ የካንሰር ዓይነት ጥናቶች እንደምክንያት የሚጠቅሱት ሁለት ነገሮች አሉ። እነርሱም አልኮል እና ትኩስ [የሚፋጁ] ምግቦችን መመገብ ናቸው። በአርሲ እና በባሌ አካባቢ ደግሞ አልኮል ብዙም የማይዘወተር ነገር ነው። ስለዚህ ምክንያቱ ሊሆን የሚችለው የሚመገቡት ምግብ ነው ማለት ነው" ይላሉ። ልክ በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ሰዎች እንጀራ በየዕለቱ እንደሚመገቡት ሁሉ በባሌ እና በአርሲ ማኅበረሰብ ባህላዊ ምግብ የሆነው ገንፎ የዚህ ካንሰር መነሻ መሆኑን የሚያሳዩ ብዙ ማስረጃዎች እንዳሉ ዶ/ር ጂልቻ ይናገራሉ። "የእነዚህ አካባቢ ነዋሪዎች በብዛት ገንፎ ይመገባሉ። ገንፎ ደግሞ በባህሪውም በባህልም ትኩሱን ነው የሚበላው። ይህ ደግሞ በጊዜ ሂደት ለዚህ የካንሰር ዓይነት እንድንጋለጥ ያደርጋል ማለት ነው" በማለት ስለዚህም እንደመፍትሄ ሰዎች ይህንን ምግብ ሲመገቡ አቀዝቅዘው እንዲበሉ ባለሙያው ይመክራሉ። በተጨማሪም በአመጋገብ ልማድ ምክንያት ለዚህ የጤና ችግር ተጋላጭ የሆኑ አካባቢ ነዋሪዎችን የአመጋገብ ሥርዓትን መቀየር አስፈላጊ መሆኑንም ዶ/ር ጂልቻ ጠቅሰዋል። ባለሙያው ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ገንፎ በየዕለቱ መመገብ ለጉሮሮ ቱቦ ካንሰር የመጋለጥ እድልን እነደሚያሰፋ ይገልጻሉ። ይህ የጉሮሮ ቱቦ ካንሰር ምን ያህል አስከፊ ነው? ዶ/ር ጂልቻ እንደሚሉት ይህ የካንሰር ዓይነት ከሌሎች የካንሰር ዓይነቶች አንጻር ለማከም የሚያስቸግር እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ሕይወትን ሊያሳጣ የሚችል ነው። "አሁን አሁን ብዙ የካንሰር ዓይነቶችን ማዳን እየተቻለ ነው። የጎሮሮ ቱቦ ካንሰር ግን በጣም አስከፊ ነው። አንዴ ከያዘ ተመልሶ የዳነን ሰው ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው" ይላሉ። "በየጎሮሮ አካባቢ ቀዶ ሕክምና ለማድረግ እንኳ በጣም አስቸጋሪ ነው። በቱቦ አካባቢ ያሉት ሌሎች የሰውነታችን አካላት በጣም ወሳኝ ናቸው። ልባችን የሚገኘው በዚያ አቅራቢያ ነው። ሳንባችንም እንደዚሁ። ከዚያ በተጨማሪ ትልቁ የደም ቧንቧ፣ አኦርታ የሚባለውም የሚገኘው በዚሁ አካባቢ ነው። ስለዚህ ይህ ካንሰር ከያዘ ቶሎ ወደ እነዚህ የአካል ክፍሎች ይስፋፋል ማለት ነው" በማለት የሚያስከትልውን ውስብስብ ችግር ይገልጻሉ። ስለዚህ ይህ የካንሰር ዓይነት አንዴ ከያዘን ረዥም ጊዜ ሳይሰጥ በወራት ጊዜ ውስጥ ሊገድል ይችላል ይላሉ። የዚህ ካንሰር ዓይነት ምልክቶች ምን ምንድን ናቸው? በዚህ ካንሰር ዓይነት የተያዘ አንድ ታማሚ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያየው ምልክት የደረት ማቃጠል ነው። ይኹን እንጂ ብዙ ሰዎች ይህ ምልክት የቀላል ሕመሞች ምልክት አድርገው ስለሚያስቡ ወደ ሆስፒታል ከመሄድ ይልቅ፣ አቅልለው በመመልከት የጨጓራ መድኃኒት እንደሚወስዱ በጥናታቸው ማረጋጋጣቸውን ይናገራሉ። "በዚህ የካንሰር ዓይነት የተያዘ ሰው ደረቱ አካባቢ የማቃጠል ስሜት ከመሰማት ባሻገር፣ በሂደት ምግብ መዋጥ ሊያስቸግረው ይችላል። መጀመሪያ ላይ ጠጣር ምግቦችን ከዚያ ደግሞ ፈሳሽ፣ መጨረሻ ላይ ምራቁን ጭምር መዋጥ ይቸገራል። ከዚያም ክብደቱ በጣም ይቀንሳል" ይላሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-61445937
amh
health
ሕንድ ፡ በአንድ ሆስፒታል ላይ በተከሰተ የእሳት አደጋ 10 አራስ ሕፃናት ሞቱ
ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት በሕንድ አንድ ሆስፒታል ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የሆስፒታሉ ሠራተኞች ህይወት ለማትረፍ የቻሉትን ቢያደርጉም አስር አራስ ሕፃናት ህይወት ማለፉ ተነገረ። የእሳት አደጋ ተከላካዮች በምዕራባዊው ማሃራሽትራ ግዛት ወደምትገኘው የብሃንዳራ አካባቢ ሆስፒታል እሳቱን ለመቆጠጠር ከመድረሳቸው በፊት ሰባት ሕፃናትን ከእሳት አደጋው ማትረፍ ተችሏል። የሕንድ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ "ልብ የሚያቆስል አሳዛኝ ክስተት" ሲሉ አደጋውን ገልጸዋል። የእሳት አደጋው የተከሰተው አርብ ሌሊት ለቅዳሜ አጥቢያ መሆኑን የሆስፒታሉ ኃላፊዎች የገለጹ ሲሆን መንስኤው ምን እንደሆነ እስካሁን ያልታወቀ ነገር የሌለ ሲሆን ምርመራ እየተደረገ ይገኛል። በእሳቱ ሳቢያ በሆስፒታሉ ውስጥ የተከሰቱት ተከታታይ ፍንዳታዎች የነፍስ አድን ሥራውን ማሰናከሉን የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በሥራ ላይ የነበረች አንዲት ነርስ ከሆስፒታሉ አዲስ የተወለዱ አራስ ህጻናት እንክብካቤ ክፍል ውስጥ ጭስ ሲወጣ ካየች በኋላ ለባለስልጣናት ማስታወቋን ተናግራለች። የአካባቢው የቀዶ ጥገና ሐኪም ፕራሞድ ካንዳቴ እንደገለጹት "የሆስፒታሉ ባለሥልጣናት ሰባት ህፃናትን ቢያድኑም 10 ህጻናት ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ሞተዋል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በደረሰባቸው ሐዘን ከሟች ቤተሰቦች ጎን መሆናቸውን በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል። የሕንድ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሚት ሻህ ስለአደጋው እንዳሉት "ቃላት የማይገልጹት የማይጠገን ጉዳት ነው" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55581634
amh
health
ኮሮናቫይረስ ፡ አሜሪካ የዩናይትድ ኪንግደም መንገደኞች ኮቪድ እንዲመረመሩ የሚያስገድድ ደንብ አወጣች
አሜሪካ ከዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የሚመጡ የሁሉም አየር መንገድ ተሳፋሪዎች በ72 ሰዓታት ውስጥ ከኮቪድ- 19 ነፃ መሆናቸውን ማሳየት አለባቸው አለች። ይህ ውሳኔ የተላለፈው በዩኬ በተገኘው አዲስ የኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት ነው። በመሆኑም ከመጭዎቹ ሁለት ቀናት በኋላ መንገደኞች የላብራቶሪ ምርመራ ውጤታቸውን የሚያሳይ የጽሁፍ ማስረጃ ለአየር መንገዶች ማሳየት አለባቸው ተብሏል። የአሜሪካ የበሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል (ሲዲሲ) መንገደኞች ምርመራ እንዲያደርጉ የወሰነው ለአዲሱ የቫይረስ ዝርያ ምላሽ ለመስጠት የኒው ዮርክ ከተማ ለዓለም አቀፍ ተጓዦች የለይቶ ማቆያ ሕግ ማስተዋወቋን ተከትሎ ነው። ሲዲሲ እንዳለው መንገደኞች በ'ፒሲአር' ወይም እንግዳ አካል ወደ ሰውነታችን ስለመግባቱ የሚጠቁሙ ሞለኪዩሎች [አንቲጂን] ምርመራ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን ማረጋጋጥ አለባቸው። በአዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ምክንያት ሌሎች አገራትም ድንበሮቻቸውን ከዩኬ ለሚነሳ በረራ ዝግ አድርገዋል። ይሁን እንጂ ዩኬም በቫይረሱ ፈጣን ስርጭት ሳቢያ የበርካታ እንግሊዛዊያን የውጭ አገር ጉዞ ክልከላን ጨምሮ ሌሎች ጥብቅ ገደቦችን ለመጣል ተገዳለች። አሜሪካ ወረርሽኙ በተከሰተ መጀመሪያ አካባቢ አብዛኞቹ የውጭ አገር ዜጎች ወደ አገሯ እንዳይገቡ ካገደች በኋላ፤ የአሜሪካ አየር መንገዶች ወደ ዩኬ እና አውሮፓ የሚያደርጉት በረራ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሰዋል። አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በጣም ገዳይ ስለመሆኑ ወይም ቫይረሱ ለክትባቱ የተለየ ምላሽ እንደሚሰጥ የሚያሳይ መረጃ እንደሌለ የጤና ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ነገር ግን ከነባሩ ቫይረስ በ70 በመቶ የመሰራጨት ዕድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ተነግሯል። ዩናይትድ እና ዴልታ አየር መንገድም በዩኬ በረራዎች ላይ ያሉ ሁሉም ተሳፋሪዎች ምርመራ እንዲያደርጉ እንደሚጠይቁ ያስታወቁት ሐሙስ ዕለት ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/news-55447031
amh
health
ኢትዮጵያ በአገር አቀፍ ደረጃ በበሽታ የሚሞቱ ሰዎችን መጠን ለማወቅ መመሪያ አዘጋጀች
ኢትዮጵያ በአገር አፍ ደረጃ በበሽታ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎችን መጠን ለማወቅ የሚያስችል የቅኝት መመሪያ ማዘጋጀቷን ቢቢሲ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ካገኘው መረጃ መረዳት ችሏል። በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የሞት መጠን ለማወቅ የሚያስችል የቅኝት መመሪያ ለማዘጋጅት መነሻ የሆነው የኮሮኖቫይረስ ወረርሽኝ መሆኑም ተገልጿል። መመሪያወው በማህበረሰቡ ውስጥ በበሽታ የሚሞቱ ሰዎችን ጭምር ማካተት እንደሚኖርበት ታምኖ የአገሪቱን የሞት መጠን የሚያሳውቅ መመሪያ ተዘጋጅቷል ተብሏል። በተለይም እንዲህ አይነት ወረርሽኞች ሲከሰቱ የሞቱን መጠን በትክክል ለማወቅ፣ ከዚህ ቀደም የነበረውን የሞት መጠን ለመገምገም፣ በሽታው የትኛውን የማህበረሰብ ክፍል በፆታ፣ በእድሜና ሌሎች መስፈርቶች አስመልክቶ የትኛውን አካል ነው እያጠቃ ነው የሚለውን በተመለከተ መመሪያው ምላሽ ይሰጣል ተብሏል። መመሪያው ይፋ የተደረገው ግንቦት 11፣ 2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ነው። መመሪያው ይፋ መሆኑን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የጤና ክስተቶች ቅኝትና ምላሽ መስጠት ዳይሬክቶሬት የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ሞት ዳሰሳ እና ምላሽ መስጠት ቡድን አስተባባሪ ወ/ሮ ሮዚና ታሪኩ ከመረጃዎች አሰባሰብና መለኪያ ጋርም ተያይዞ ወሳኝ የሚባሉ ጉዳዮች በመመሪያው መካተታቸውን አስታውቀዋል። መመሪያው መጠናቀቁን አስመልክቶ አዳማ በነበረው ዝግጅት ላይ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ እንደተናገሩት መመሪያው የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ጉዳት ሳያደርሱ ለመከላከልና ለመቆጣጠር አስፈላጊ ነው ብለዋል። መመሪያውን በማዘጋጀቱ በኩል የጤና ሚኒስቴር ባለሙያዎች፣ የክልሎች የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር እና የአጋር ድርጅት ተወካይ ባለሙያዎች ተሳትፎ ማድረጋቸውም ከመረጃው መረዳት ተችሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57188529
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ የሟቾች ቁጥር 500,000 መድረሱ ‘ልብ ሰባሪ ምዕራፍ ነው’- ባይደን
አሜሪካ በኮሮናቫይረስ ምክንያት 500,000 ዜጎቿን ማጣቷን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለህዝቡ ንግግር አድርገዋል። "እንደ አንድ ህዝብ እንዲህ ዓይነቱን ጭካኔ የተሞላበት ዕጣ ፈንታ መቀበል አንችልም። በሀዘኑ መቆዘምን መከልከል አለብን" ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ፣ ምክትል ፕሬዚዳንቱ እና የትዳር አጋሮቻቸው ከንግግሩ በኋላ በኋይት ሃውስ በነበረው የሻማ ማብራት ሥነ-ስርዓት ወቅት የህሊና ፀሎት አድርገዋል፡፡ አሜሪካ ከ 28.1 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ በመያዛቸውም በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ ሆናለች። ፕሬዝዳንቱ "ዛሬ ሁሉም አሜሪካውያን እንዲያስታውሱ እጠይቃለሁ፡፡ ያጣናቸውን እና ወደ ኋላ የተውናቸውን ዳግም አስታውሱ" ሲሉ አሜሪካኖች ኮቪድን በጋራ እንዲዋጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በፌደራል መንግሥቱ ሥር የሚገኙ ሁሉም ቦታዎች ላይ ለሚቀጥሉት አምስት ቀናት የአገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ባይደን አዝዘዋል፡፡ ጆ ባይደን በኋይት ሃውስ ተገኝተው ንግግራቸውን የከፈቱት፣ በኮቪድ-19 የደረሰው አሜሪካውያን ሞት ከአንደኛው በዓለም ጦርነት፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት እና በቬትናም ጦርነት ከሞቱት ሰዎች ድምር ቁጥር የበለጠ መሆኑን በመጥቀስ ነው። "ዛሬ በእውነት አስከፊ እና ልብ ሰባሪ ምዕራፍ ነው- 500,071 ሰዎች ሞተዋል" ብለዋል፡፡ በመቀጥለም "ብዙ ጊዜም እንደ ተራ አሜሪካዊ ሰዎች ሲገለጹ እንሰማለን። እንደዚህ ዓይነት ነገር የለም። ምንም ተራ ብሎ ነገር የለም፡፡ ያጣናቸው ሰዎች እጅግ የተለዩ ነበሩ፡፡ በአሜሪካ የተወለዱ ወደ አሜሪካ የተሰደዱ ናቸው" ብለዋል። "ብዙዎቹም የመጨረሻ እስትንፋሳቸውን በአሜሪካ ወስደዋል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ጆ ባይደን ሚስታቸው እና ሴት ልጃቸው በጎርጎሮሳዊያኑ 1972 በመኪና አደጋ የተገደሉ ሲሆን ወንድ ልጃቸው ደግሞ በ 2015 በካንሰር ህይወቱ ማለፉን በማንሳት የራሳቸውንም የሃዘን ተሞክሮ ጠቅሰዋል። "ለእኔ በሀዘን ውስጥ ያለው መንገድ ዓላማን መፈለግ ነው" ብለዋል። ባይደን በወረርሽኙ ላይ የወሰዱት እርምጃ ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተለየ ነው። ትራምፕ በአደገኛው ቫይረስ ተጽዕኖ ላይ ጥርጣሬ ያሳደሩ እና የቫይረሱ ስርጭትን ለመከላከል ጭምብሎችን መልበስ እና ሌሎች እርምጃዎችን ፖለቲካዊ አድርገውት እንደነበር ይነገራል፡፡ ባይደን ስልጣኑን ከመረከባቸው ከአንድ ቀን በፊት 400,000 አሜሪካውያን በቫይረሱ ምከንያት የሞቱበትን ክስተት አስበው ውለዋል፡፡ በሌላ በኩል በዋሽንግተን በብሔራዊ ካቴድራል ደወሎች 500 ጊዜ ተደውሏል- በወረርሽኙ ህይወታቸው ላለፈው ለአንድ ሺህ አሜሪካዊ አንድ ጊዜ ማለት ነው፡፡ በኮሮቫይረስቫይረስ የተያዙት አሜሪካውያን ቁጥር በሁለተኛ ደረጃ ከያዘች ህንድ (11 ሚሊዮን) እና ብራዚል (10.1 ሚሊዮን) ጋር ሲነፃፀር በእጥፍ የሚበልጥ ነው፡፡ ብራዚል በ 244,000 የሟቾችን ቁጥር ሁለተኛ ስትሆን ሜክሲኮ 178,000 ሰዎችን አጥታ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ "ከአስርተ ዓመታት በኋላ በመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን ምክንያት የደረሰውን የብዙዎች ሞት በሃገሪቱ ታሪክ ውስጥ እንደ ታላቅ ታሪካዊ ምዕራፍ ይገልጹታል" ሲሉ የበሽታ መከላከያ ባለሙያው ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ለሲ.ኤን.ኤን ገልጸዋል። "አስገራሚ ቁጥር ነው። ከአንድ ዓመት በፊት ግማሽ ሚሊዮን አሜሪካውያን በዚህ በሽታ ሕይወታቸውን ያጣሉ የሚል ግምት አልነበረኝም" ብለዋል በብራውን ዩኒቨርሲቲ የኅብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት ዲን የሆኑት ዶ/ር አሺሽ ጅሃ። "በዚህች ሀገር ውስጥ ብዙ አቅም፣ ብዙ ሀብት አለን ... የምንከላከለው ስለነበር መከሰት አልነበረበትም፡፡ አሁን እዚህ ደርሰናል፡፡ የምንሰጠው ምላሽ የተሳሳተባቸውን መንገዶች ሁሉ ማንፀባረቅ ያለብን ይመስለኛል" ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል፡፡ የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው ትንበያ መሠረት ቢያንስ 90,000 የሚሆኑ ተጨማሪ አሜሪካውያን እስከ ሰኔ 1 ቀን ድረስ በቫይረሱ ይሞታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በግምቱ መሠረት በግንቦት መጨረሻ ቫይረሱ በየቀኑ 500 ገደማ አሜሪካውያንን እንደሚገድል ይገምታል። በአሁኑ ወቅት በየቀኑ ወደ 2,000 የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ እንደሚሞቱ ይገመታል። በየቀኑ ወደ 1.6 ሚሊዮን የሚጠጋ ክትባት ለአሜሪካዊያን እየተሰጠ በመሆኑ ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎች መጠን ለ40ኛ ተከታታይ ቀናት ቀንሷል፡፡ ሆኖም ባለሙያዎች በአገሪቱ ውስጥ እየጨመረ በሄደው አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ የሟቾችን ቁጥር ሊጨምር ይችላል በሚል አሳስቧቸዋል፡፡ አኃዞች ቢሻሻሉም በኮሮናቫይረስ ምክንያት የአሜሪካኖች በሕይወት የመኖር ዕድሜን በአንድ ዓመት ቀንሷል ሲል የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል ባለፈው ሳምንት አስታውቋል፡፡ በቫይረሱ እጅግ በተጎዱትና በቁጥር አናሳ በሆኑት ማህበረሰቦች ዘንድ ደግሞ ለውጡ ከፍተኛ ነው ተብሏል። በህይወት የመኖር ዕድሜያቸው በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰባቸው ጥቁር ወንዶች ሲሆኑ ከጥር እስከ ሰኔ 2020 ባለው ጊዜ ብቻ በሦስት ዓመት ቀንሷል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ የሂስፓኒኮች በህይወት የመኖር ዕድሜ በ 2.4 ዓመት ቀንሷል፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-56156450
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ ሕንድ ዕድሜያቸው ከ18 በላይ ለሆኑ ዜጎቿ የኮቪድ ክትባት ልትሰጥ ነው
ሕንድ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ የክትባት መርሀ ግብሯን በስፋት ማዳረስ ጀምራለች። ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሁሉም አዋቂዎች በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ወር የመጀመሪያ ቀን ላይ ክትባቱን መውሰድ እንደሚጀምሩ ተገልጿል። ነገር ግን በሕንድ በበርካታ ግዛቶች የክትባት እጥረት መኖሩ ችግር ሊሆን እንደሚችል የተገመተ ሲሆን ተጨማሪ ክትባቶችን መንግሥት ከየት ሊያቀርብ እንደችሚል የተገለጸ ነገር የለም። የሕንድ መንግሥት ባለፈው ሳምንት እንዳለው 27 ሚሊዮን የክትባት ብልቃጦች ብቻ ነበር ያሉት። ይህ ማለት ደግሞ አሁን አገሪቱ ዜጎቿን እየከተበችበት ካለው ፍጥነት አንጻር ለ9 ቀናት ብቻ የሚበቃ ነው ማለት ነው። ሕንድ በአሁኑ ሰዓት የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ዕድሜያቸው ከ45 ዓመት በላይ የሆኑ ዜጎቿን በበርካታ ግዛቶች እየከተበች ሲሆን የክትባት እጥረት ግን እንዳጋጠመ ተገልጿል። ጥቂት በማይባሉ ግዛቶችም ክትባቱን ለመስወድ የመጡ ሰዎች ሰይከተቡ መመለሳቸው ተዘግቧል። እንደ ሴረም ያሉ ትልልቅ የክትባት አቅራቢ ድርጅቶች በመላው ዓለም ያለውን የክትባት ፍላጎት ማርካት እንደከበዳቸውና ክትባቱን ለማምረት የሚውሉ ጥሬ እቃዎች እጥረት እንዳጋጠማቸውም ገልጸዋል። ይህም የሆነው አሜሪካ ክትባቱን ለማምረት የሚውሉ ጥሬ እቃዎች ወደሌላ አገራት እንዳይላኩ በማገዷ ነው። በሕንድ ክትባቱ ሲሰጥበት የነበረው መንገድ በመንግሥት ቁጥጥር ስር ነበር፤ ነገር ግን መንግሥት ሕጉን በመቀየር ላይ ነው። ይህ ለውጥም የክትባት ምርት እና አቅርቦትን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምረው ታምኖበታል። የሕንድ የክትባት አምራቾች አገሪቱ ከሚያስፈልጋት 50 በመቶ የሚሆነውን ለማዕከላዊ መንግሥት ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ቀሪው 50 በመቶ ደግሞ በግዛቶችና በነጻ ገበያ ዋጋው የሚወስ ይሆናል። መጀመሪያ ላይ በሕንድ ሶስት ክትባቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ፈቃድ አግኝተው ነበር። ሁለቱ ክትባቶች በሕንድ ክትባት አምራች ድርጅቶች ሴረም ኢንስቲትዩትና ባራት ባዮቴክ የተዘጋጁ ሲሆን ሶስተኛ ደግሞ የሩሲያው ስፑትኒክ ቪ ነው። መንግሥት ግን በሌሎች አገራት ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ ተጨማሪ ክትባቶቸ በሕንድም ይጀመራሉ ብሏል። በተጨማሪም መንግሥት ለሁለቱ የሕንድ ክትባት አምራች ድርጅቶች 600 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጓል። ሕንድ ከያዝነው ወር ጀምሮ እስካሁን በየቀኑ ቢያንስ 200 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙባት እንደሆነ ሪፖርት አድርጋለች። በሕንድ ከአንድ ዓመት በፊት በየቀኑ 93 ሺ ሰዎች ነበር የሚያዙት። የሟቾችም ቁጥር ቢሆን አየጨመረ ነው። ትናንት ሰኞ ዕለት ብቻ በሕንድ 1 ሺ 619 ሰዎች በኮሮረናቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸው እንዳለፈ መንግሥት አስታውቋል።
https://www.bbc.com/amharic/56797854
amh
health
ኢራን የሕዝብ ቁጥሯን ለማሳደግ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን ማቅረብ አቆመች
ኢራን የሕዝብ ቁጥሯን ከፍ ለማድረግ በሚል በመንግሥት ሆስፒታሎች ውስጥ ይቀርብ የነበረው የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት አቅርቦትን ውስን አደረገች። በዚህም በመንግሥት በሚተዳደሩ ሆስፒታሎች ውስጥ እርግዝና በጤናቸው ላይ እክል ለሚያስከትልባቸው ሴቶች ብቻ የእርግዝና መከላከያዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ በወንዶች ላይ ይደረግ የነበረው ቫሴክቶሚ የተባለው ቀዶ ህክምና እንዳይካሄድ ተደርጓል። ነገር ግን የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎቶቹ በግል ሆስፒታሎች ውስጥ እንደሚሰጡ ታውቋል። የኢራን መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ የሚመዘገበው ዝቅተኛ የወሊድ መጠንና እየጨመረ የመጣው እድሜያቸው እየገፋ የሚሄድ ሰዎች ቁጥር አሳስቦታል። የኢራን አመታዊ የሕዝብ ቁጥር እድገት በአንድ በመቶ እየቀነሰ ሲሆን፤ በቶሎ ርምጃ ካልተወሰደ አገሪቱ በሚቀጥሉት 30 ዓመታት ውስጥ በርካታ በእድሜ የገፉ ዜጎች ካላቸው አገራት ተርታ ውስጥ እንደምትገባ የአገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል። ከሁለት ዓመት በፊት ኢራን የሕዝብ ብዛቷ 1.4 በመቶ ማስመዝገቧ ተገልጾ ነበር። ይህ አሃዝ በጎረቤቷ ኢራቅ ውስጥ 2.3 በመቶ ሲሆን ባላንጣዋ ሳኡዲ አረቢያ ደግሞ 1.8 በመቶ የሕዝብ ቁጥር እድገት ማስመዝገባቸውን የዓለም ባንክ መረጃ ያመለክታል። የአገሪቱ መንግሥት የዜና ተቋም የሆነው ኢርና እንደዘገበው ጋብቻ እና በጋብቻ ውስጥ የሚወለዱ ልጆች ቁጥር ቀንሷል፤ ለዚህም ምክንያቱ ኢኮኖሚያዊ ጫና እንደሆነ አመልክቷል። ግንቦት ወር ላይ የጤና ጥበቃ ምክትል ሚኒስትሩ ሰይድ ሐሚድ ባራካቲ እንደተናገሩት በኢራን ውስጥ ያለው የጋብቻ መጠን በአስር ዓመት ውስጥ በ40 በመቶ ቀንሷል። "በዚሁ የምንቀጥል ከሆነ በሚቀጥሉት 30 ዓመታት ውስጥ በዕድሜ የገፉ በርካታ ሕዝብ ካላቸው አገራት አንዱ እንሆናለን" ብለዋል ምክትል ሚኒስትሩ። እንደ አውሮፓዊያኑ በ1979 የተካሄደው እስላማዊ አብዮትን ተከትሎ የሕዝብ ቁጥሯ በከፍተኛ መጠን ጨምሮ ነበር። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ውጤታማ የሕዝብ ብዛት መቆጣጠሪያ ፖሊሲ በመከተሏ አሁን የታየው ውጤት መመዝገቡ ተገልጿል። የአገሪቱ የበላይ መሪ የሆኑት አያቶላህ አሊ ኻሚኒ ሕዝቡ በርካታ ልጆች እንዲኖሩት ሲያበረታቱ ቆይተዋል። እንደ እሳቸው ፍላጎት ኢራን አሁን ካላት 80 ሚሊዮን ሕዝብ ወደ ግማሽ የሚጠጋ ጭማሪ አድርጋ ቁጥሩ ወደ 150 ሚሊዮን ከፍ እንዲል ይሻሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-53044858
amh
health
“የጥርሴ ቢጫ መሆን ሕልሜን አመከነው”
በልጅነት ፍሎራይድ የበዛበትን ውሃ መጠቀም የጥርስ ቀለምን ወደ ቢጫ እንዲቀየር እና እንዲበልዝ ያደርጋል። ይህ ሁኔታም ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ውስጥ ያጋጥማል። ፍሎራይድ የጥርስን የላይኛውን ክፍል በመጉዳት ቀለሙ እንዲቀየር እና እንዲሸራረፍ ምክንያት ይሆናል። በዚህም ሳቢያ በርካታ ሰዎች በጥርሳቸው ቀለም እፍረት እና መገለል ይገጥማቸዋል። የወደፊት ዕቅዳቸው ተሰናክሎብናል የሚሉም አሉ። የታንዛኒያዋ አሩሻ በውሃ ውስጥ ከፍተኛ የፍሎራይድ መጠን ካለባቸው ስፍራዎች መካከል አንዷ ስትሆን፣ እዚያ የአሩሻ ነዋሪ የሆኑ ሁለት ወጣት ሴቶች ስለገጠማቸው ችግር ይናገራሉ። ሁለቱ ወጣቶች በጥርሳቸው ቀለም መቀየር ምክንያት መድሎ እንደሚደርስባቸው ገልጸዋል። መፍትሔ ይኖረው ይሆን የጥርስን ቀለም የሚቀይረውን ከፍተኛ የፍሎራይድ መጠን ያለውን ውሃ ማጣራት እጅግ ከባድና ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ነው። አሁን ግን ቀላል የውሃ ጣሪያ ዘዴ ተፈጥሯል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c4n023lnxdqo
amh
health
በኢንግላንድ ኮኖናቫይረስ የሚመረመሩ ልጆች ቁጥር ጨምሯል
ኮሮናቫይረስ በዋነኛነት የሚጎዳው አረጋውያንን መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ። ሕፃናት ለበሽታው ተጋላጭ ናቸው? የሚለው ጥያቄ መነሳቱ ግን አልቀረም። ኢንግላንድን እንደ ማሳያ ብንወስድ በአገሪቱ የኮቮድ-19 ምርመራ የሚያደርጉ ልጆች ቁጥር በዚህ ወር ጨምሯል። ከተመረመሩት መካከል አንድ በመቶው ብቻ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። በመጀመሪያዎቹ የመስከረም ሳምንታት ከ200,000 በላይ እድሜያቸው ከዘጠኝ ዓመት በታች የሆነ ታዳጊዎች ተመርምረዋል። ይህም ካለፉት ወራት አንጻር ሦስት እጥፍ ይሆናል። ጥናት እንደሚያሳየው ልጆች ከአዋቂዎች አንጻር ለበሽታው የመጋለጥ እድላቸው ጠባብ ነው። ሆኖም ግን ሕፃናት በሽታውን ያስተላልፋሉ? ለሚለው ጥያቄ አሁንም ቁርጥ መልስ አልተገኘም። የኢንግላንድ አሃዝ እንደሚጠቁመው፤ ምርመራ የሚያደርጉ ከ40 ዓመት በታች ያሉ ግለሰቦች ቁጥር ጨምሯል። አብላጫውን ድርሻ የሚይዙት በ20ዎቹ እድሜ ክልል ያሉት ናቸው። ምርመራ የሚያደርጉ ልጆች ቁጥር የጨመረው ኢንግላንድ ውስጥ ተቋርጦ የነበረው ትምህርት በመጀመሩ ነው። የተመርማሪዎች ቁጥር መናር የቤተ ሙከራ ውጤት እንዲዘገይ አድርጓል። ከሚመረመሩት ታዳጊዎች መካከል ኮቪድ-19 የሚገኝባቸው አንድ በመቶው ብቻ ናቸው። በሌላ በኩል ከጎልማሶች 3.5% ቫይረሱ ይገኝባቸዋል። ይህ ቁጥር በ20ዎቹ እና በ30ዎቹ እድሜ ክልል ያሉትንም ያካትታል። ለምን የሚመረመሩ ልጆች ቁጥር ጨመረ? የብርድ እንዲሁም ጉንፋን ምልክት የሚያሳዩ ልጆች ከሌሎች ታዳጊዎች ጋር መቀላቀል ጀምረዋል። ኢንግላንድ ወደ ቀዝቃዛ ወቅት እየገባቸው እንደመሆኗ የተለያዩ የመተንፈሻ አካሎች ህመሞች ይቀሰቀሳሉ። የእነዚህ በሽታዎች ምልክት ደግሞ ከኮሮናቫይረስ ጋር ተቀራራቢ ነው። ስለዚህም የኮሮናቫይረስ ምርመራ የሚያደርጉ ልጆች ቁጥር ንሯል። በእርግጥ ልጆች በቫይረሱ ቢያዙም በጠና አይታመሙም። ጃማ ፔዲያትሪክስ የሚባለው የዩናይትድ ኪንግደም የጥናት ቡድን ከ20 ዓመት በታች ያሉ ታዳጊዎች ለወረርሽኙ የመጋለጥ እድላቸው 44% ነው። በተለይም ከዓሥር ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት እምብዛም ለበሽታው አይጋለጡም። ቡድኑ ከምሥራቅ እስያ፣ አውሮፓና ሌሎችም የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ 21 አገሮች ውስጥ የተካሄደ ጥናትን ዳሷል። በጥናቱ 42,000 ሕጻናት እና 270,000 አዋቂዎች ተሳትፈዋል። ጥናቱ ልጆች በሽታውን ወደ ሌላ ሰው ያስተላልፋሉ? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ አላገኘም። ልጆች በበሽታው ከተያዙ ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ። ሳል ከሌላቸው ወይም በጠና ካልታመሙ ምናልባትም በሽታውን አያስተላልፉ ይሆናል የሚል መላ ምት አለ። ስለዚህም በሽታውን የማሰራጨት መጠን ምን ያህል ለበሽታው ተጋልጠዋል? ምን ያህል ቫይረስ ተሸክመዋል? ከምን ያህል ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸው? በሚሉት ጥያቄዎች ይወሰናል። ቫይረሱ በልጆችና በጎልማሶች ምን ያህል እንደተሰራጨ ለማወቅ በበሽታው ከተያዙ ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች ላይ የዳሰሳ ጥናት እንደሚያስፈልግ አጥኚዎቹ ጠቁመዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54309062
amh
health
ዩኬ በ11 የአፍሪካ አገራት ላይ ጥላ የነበረውን የጉዞ ዕቀባ አነሳች
የዩኬ መንግሥት ከአዲሱ ኦሚክሮን የኮቪድ ተህዋሲ ዝርያ ጋር በተያያዘ በ11 የአፍሪካ አገራት ላይ ጥላ የነበረውን የጉዞ ዕቀባ ማንሳቷን አስታወቀች፡፡ አገራቱም አንጎላ፣ ቦትስዋና፣ ኢስዋቲኒ፣ ሌሴቶ፣ ማላዊ፣ ሞዛምቢክ፣ ናሚቢያ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዛምቢያ እና ዚምባብዌ ናቸው፡፡ እነዚህ አገራት በዩኬ የጎዞ ዕቀባ የተጣለባቸው ባለፈው ኅዳር ወር የኦሚክሮን ተህዋሲ ዝርያ ከዚሁ ደቡባዊ አፍሪካ አካባቢ መገኘቱን ተከትሎ ነበር፡፡ የዩኬ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሳጂድ ጃቪድ እንዳሉት ዕቀባውን ማንሳት ያስፈለገው ተህዋሲው አሁን በስፋት በሌሎች ቦታዎችም መሰራጨቱ ስለተረጋገጠ በነዚህ አገራት ላይ ጫና አድርጎ መቆየቱ ትርጉም ስለሌለው ነው፡፡ ሚኒስትሩ ለዩኬ ፓርላማ እንዳብራሩት፣ የኮቪድ ተህዋሲ አዲሱ ዝርያ ኦሚክሮን በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ሳይቀር ገብቶ እያለ፣ እንዲሁም በሌሎች በርካታ የአውሮጳ አገራት መዛመቱ እየታወቀ እነዚህን ዐሥራ አንድ የአፍሪቃ አገራት በዕቀባ ዝርዝር ማቆየት ትርጉም አልባ ነው፡፡ ለወረርሽኝ ተጋላጭ አደገኛ አካባቢ በሚል ከተዘረዘሩ አገራት ወደ ዩኬ የሚገቡ ተጓዦች ለ10 ቀናት ራሳቸውን ለይተው መንግሥት ባዘጋጃቸው ሆቴሎች መቆየት ይኖባቸዋል፡፡ ወጪውን የሚችሉትም ተጓዦቹ ይሆናሉ፡፡ ከዚህ ቀደም በርካታ ተጓዦች ለሆቴል ቆይታ ብዙ ገንዘብ ወጪ እንዲያደርጉ መገደዳቸው ቅሬታ ፈጥሮባቸው እንደነበር ሲዘገብ ነበር፡፡ በዩኬ ከአዲሱ የኦሚክሮን የኮቪድ ዝርያ ጋር በተያያዘ አንድ ሰው መሞቱ የተዘገበው ትናንት ነበር፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-59662930
amh
health
በሽታን በሚከላከሉ ክትባቶች መካከል ለምን ልዩነት ተፈጠረ?
የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት አንድን ሰው እስከ ምን ያህል ጊዜ ከበሽታው ሊከላከል እንደሚችል ማንም እርግጠኛ አይደለም። አንዳንድ ክትባቶች እስከ እድሜ ልክ በሽታን የመከላከል አቅም ሲኖራቸው ሌሎች ደግሞ በተወሰነ ጊዜ የተገደበ የመከላከል አቅምን ያዳብራሉ። ይህ ልዩነት እንዴት ሊፈጠር ቻለ? ይህ ቪዲዮ ምላሽ አለው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cyrdrpjd6d2o
amh
health
አንሶላችንን መቀየር ያለብን በምን ያህል ቀናት ልዩነት መሆን አለበት?
ነገሩ በአደባባይ አይወራም የሚሉ ብዙ ናቸው። ግን የአንሶላ ቅያሪ ጉዳይ የሁላችንንም ደጅ ያንኳኳል። ብዙዎች በምን ያህል ቀናት አንሶላ ይቀየር? በሚለው ቁጥር ላይ አይስማሙም። እርስዎ ግን በምን ያክል ጊዜ አንሶላዎ ይቀይራሉ/ ያጥባሉ? አንሶላ በምን ያህል ቀናት ልዩነት መቀየር አለበት የሚለውን ከጤና ጋር የሚያስተሳስሩ አሉ። ስለጉዳዩ ጥናት የሠራችው ዩናይትድ ኪንግደምን እንደ ማሳያ እንውሰድ። አንሶላ በየስንት ቀኑ ይቀየር ለሚለው ጥያቄ የተሰጠው መልስ በጥናቱ በተሳተፉ 2 ሺህ 250 ዜጎች መካከል የአቋም ልዩነት እንዳለ ጠቁሟል። ግማሽ ያህሉ ወንደላጤዎች አንሶላቸውን ለአራት ወር እንዳላጠቡ ተናግረዋል። 12 በመቶው ደግሞ አንሶላ የሚያጥቡት ትዝ ሲላቸው ነው። ይህም ከአራት ወራት ሊበልጥ ይችላል። የሥነ ልቦና ባለሙያ፣ ኒውሮሳይንቲስትና የእንቅልፍ ተመራማሪዋ ዶ/ር ሊንዚ ብሮውኒንግ "ይሄ ትክክል አይለም" ትላለች። ከሴተላጤዎች 62 በመቶዎቹ በየሁለት ሳምንቱ አንሶላ እንደሚቀይሩ ይናገራሉ። የተወሰኑት ደግሞ በየሦስት ሳምንቱ። አንሶላ መቀየር ለምን ይጠቅማል? አንሶላ በየሳምንቱ ወይም በየሁለት ሳምንቱ መቀየር አለበት ትላለች ዶ/ር ሊንዚ። ይህ የሚደረገው ለንጽህና ሲባል ነው። ከሰውነታችን የሚወጣውን ላብ የሚሰበስበው አንሶላችን እንደመሆኑ በላብ ተጠቅልሎ መተኛት ያስቸግራል። "ላብ አንሶላን ያሸታል፣ ይጨመድደዋለም" ትላለች ዶክተሯ። ስንተኛ ምቾት እንዲሰማን በአካባቢያችን ነፋሻማ አየር ቢኖር ይመረጣል። አንሶላ አለመቀየር የሚያስከትለው በላብ ተዘፍቆ መተኛትን ብቻ አይደለም። ከሰውነታችን ላይ የሚነሱ ሙት ህዋሳት እንቅልፋችንን እንዲያስተጓጉሉትም ያደርጋል። ስንተኛ ከቆዳችን ላይ ሙት ህዋሳት ይወድቃሉ። ይህም አንሶላችን ላይ ይሰበሰባል። አንሶላ በቀናት ልዩነት የማንቀይር ከሆነ እነዚህን ሙት ህዋሳት አናስወግድም ማለት ነው። "አንሶላችንን ቶሎ ቶሎ የማናጥብ ከሆነ ሙት ህዋሳት አንሶላው ላይ ይከማቻሉ" ትላለች ዶክተር ሊንዚ። ችግሩ በዚህ ብቻ አያከትምም። ማይት የሚባሉ ጥቃቅን ነፍሳት ህዋሳቱን ለመመገብ አንሶላችን ላይ ይሰበሰባሉ። ይህም ለቆዳ በሽታ ያጋልጣል። በእንቅልፍ ወቅት ምቾትም ይነሳል። አንሶላ በምን ያህል ጊዜ ይቀየር? ዶክተሯ እንደምትለው፣ አንሶላ ከተቻለ መቀየር ያለበት በየሳምንቱ ነው። ግን በቀዝቃዛ ወቅት ከሳምንት ጥቂት አለፍ ሊልም ይችላል። ከሁለት ሳምንት በላይ አንሶላ ሳይቀይሩ መቆየት ግን አስጊ እንደሆነ ታስጠነቅቃለች። ስንተኛ እጃችን በመጠኑም ቆሽሾ እንደመሆኑ አንሶላ ማቆሸሻችን አይቀርም። ከትንፋሻችን የሚመወጣውም አየር ሁሌ ንጹህ አይደለም። አንዳንዶች ከመተኛት በፊት ሰውነት መታጠብ አንሶላ እንዳይቆሽሽ ይረዳል ቢሉም ሁነኛው መፍትሄ አንሶላ መቀየር እንደሆነ ባለሙያዎች ይመክራሉ። ቶሎ አንሶላ የማንቀይረው ለምንድን ነው? መልሱ እንደየሰዉ ይለያያል። መግቢያችን ላይ የጠቀስነው የዩናይትድ ኪንግደም ጥናት እንደሚለው ግን፣ 67 በመቶ የአገሪቱ ዜጎች አንሶላ ቶሎ ቶሎ የማይቀይሩት ስለሚረሱት ነው። 35 በመቶው ግድ አይሰጣቸውም። 22 በመቶው ንጹህ ተለዋጭ አንሶላ አያገኙም። 38 በመቶ ያህሉ ደግሞ አንሶላ በየጊዜው መታጠብ አለበት ብለው አያስቡም። ዶ/ር ሊንዚ፣ መኝታ ቤት እንደተቀደሰ ስፍራ ሊጠበቅ ይገባል ትላለች። "መኝታ ቤት የምንወደው ቦታ መሆን አለበት። ወደ መኝታ ቤት ስንገባ በደስታ ልንሞላም ይገባል።" እንቅልፍ የማጣት ችግር ያለባቸው ታካሚዎቿን ከምትመክራቸው ነገሮች መካከል አንሶላችሁን አጽዱ የሚለው አንዱ ነው። "ንጹህ አንሶላ አንጥፈን ስንተኛ ምቾት ይሰማናል። ደስ ይለናል። እንረጋጋለን።"
https://www.bbc.com/amharic/news-61330283
amh
health
ኮቪድ-19፡የትራምፕ ታዳጊ ልጅ በኮሮናቫይረስ ተይዞ እንደነበር ተገለፀ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የ14 ዓመት ልጅ፣ ባሮን በኮሮናቫይረስ ተይዞ እንደነበር እናቱ፣ ቀዳማዊት እመቤት ሜላንያ ትራምፕ ገልፃለች። በአሁኑ ወቅት ግን ተመርምሮ ነጻ መሆኑንም አስረድታለች። ሚላንያ ልጇ ባሮን ተመርምሮ በኮሮናቫይረስ መያዙን ስታውቅ "የፈራሁት ደረሰ" ማለቷን ትናገራለች። ፕሬዝዳንት ትራምፕና ባለቤታቸው ሜላንያ እንዲሁም ሌሎች የዋይት ሐውስ ሰራተኞች በኮሮናቫይረስ ተይዘው የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት አገግመዋል። ልጇ በቫይረሱ ተይዞ የነበረበት ወቅት እነሱም ታመው ከነበረበት ጊዜ ጋር ተመሳሳይ መሆኑንም ሜላንያ ትራምፕ በዋይት ሃውስ ድረ-ገፅ አስፍራለች። ሜላንያ ስለ ልጇ በቫይረሱ መያዝ ይፋ ማውጣቷን ተከትሎም የምረጡኝ ቅስሳ ላይ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ትራምፕ "ለአጭር ጊዜ ቫይረሱ ይዞት ነበር" ሲሉ የልጃቸውን የጤና ሁኔታ በአዮዋ ለተሰበሰበው ደጋፊያቸው ተናግረዋል። "መያዙን ሁሉ የሚያውቅ አይመስለኝም፤ ምክንያቱም ገና ታዳጊ ስለሆነ እና የመከላከል አቅሙ ጠንካራ በመሆኑ በቀላሉ መክቶታል" ብለዋል። አክለውም " ባሮን መልከ መልከ መልካምና ነጻ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። የልጃቸውንም ከኮሮናቫይረስ በቀላሉ ማገገምም እንደ ምክንያት በመጥቀስ አሜሪካ ትምህርት ቤቶቿችን በቅርቡ ልትከፍት ይገባል ሲሉም ሞግተዋል። በርካታ የመምህራን ማህበራት ግን በአሁኑ ሰዓት ትምህርት ቤቶች መከፈት እንደሌባቸውና በርካታ መምህራን በተማሪዎች ሊጠቁ ይችላሉም እያሉ ነው። በአዮዋ ለተሰበሰው ደጋፊዎቻቸውም "ባሮን በኮሮናቫይረስ መያዙ ተነገረን። ከሁለት ሰኮንዶች በኋላ ተሻለው። አሁን ነፃ ነው አልተባለም? ተብሏል። ሰዎች በኮሮናቫይረስ ይያዛሉ፣ ይሻላቸዋል። ልጆችን ትምህርት ቤት መልሱ" ብለዋል። በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የአለም መነጋገሪያ ሆነው የነበሩት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻቸው ተመልሰዋል። ፕሬዚዳንቱ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ከተነገረ ሁለት ሳምንታት ባልሞላ ጊዜም ውስጥ ነው በሺዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን በፍሎሪዳ፣ ሳንፎርድ ከአዳራሽ ውጭ በነበረው የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ላይ የተገኙት። ደጋፊዎቻቸው የተለመደውን "አራት ተጨማሪ አመታትን ይምሩ" በማለት የዘመሩላቸው ሲሆን ፤ በዝግጅቱ ላይ የተገኙትም ደጋፊዎች ሙቀታቸው እየተለካና ጭምብል እየተሰጣቸው ወደተዘጋጀው ቦታ አቅንተዋል። ደጋፊዎቻቸው ፕሬዚዳንቱ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ወቅት በመምጣታቸው ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል። በኮሮናቫይረስ ክፉኛ የተጠቃችው አሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 7.8 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን 216 ሺህ ዜጎቿንም መነጠቋን ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54544014
amh
health
አሜሪካዊያን ከ20 ቀን በኋላ የኮቪድ ክትባት መከተብ ይጀምራሉ ተባለ
የአሜሪካ የኮሮናቫይረስ ክትባት መርሐግብር ቢሮ ኃላፊ የመጀመርያው አሜሪካዊ ተከታቢ በዲሴምበር 11 (ታኀሣሥ 2) ክትባት ሊያገኝ እንደሚችል ጠቆሙ። ይህም ማለት የመጀመርያው ተከታቢ የኮቪድ ክትባት ለመውሰድ ከ20 ቀናት ያነሰ ጊዜ ነው የቀረው ማለት ነው። ኃላፊው ዶ/ር ሞንሴፍ ስሎይ ለሲኤንኤን እንደተናገሩት መሥሪያ ቤታቸው እያቀደ ያለው ይህ ክትባት ከሚመለከተው መሥሪያ ቤት ፍቃድ ባገኘ በ24 ሰዓታት ውስጥ ክትባቱን ወደ ጤና ጣቢያዎች ለማጓጓዝ ነው። ይህም ክትባቱን ወደ ዜጎች ለማድረስ አንዲትም ሰኮንድ እንዳትባክን ለማድረግ ነው። አሜሪካ በአሁን ሰዓት ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ፍጥነት በተህዋሲው ወረርሽኝ እየተጠቃች ነው። አሁን በተህዋሲው የተያዙት አሜሪካዊያን ቁጥር ከ12 ሚሊዮን ማለፉ ብቻ ሳይሆን በቀን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 200ሺ አካባቢ መጠጋቱ አገሪቱን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷታል። ወረርሽኙ አሜሪካ ከገባ ወዲህ 255ሺ ዜጎች ሕይታቸውን አጥተዋል። በዚህን ያህል ቁጥር ተህዋሲው ነፍስ ያጠፋበት ሌላ አገር የለም። ፋይዘር የተባለው እውቅ የመድኃት አምራች ኩባንያ ከጀርመኑ ባዯንቴክ ጋር በመሆን ላመረተውን መድኃኒት የእውቅና ጥያቄን ለሚመለከተው ክፍል ያቀረበው ባለፈው አርብ ነበር። ፋይዘርና አጋሩ ያመረቱት የክትባት ዓይነት የፈውስ ምጣኔው 95 ከመቶ ነው ተብሏል። አንድ ሰው ከኮቪድ ተህዋሲ ለመጠበቅ ይህን ክትባት በተለያየ ጊዜ ሁለት ጠብታ መውሰድ ይኖርበታል። ፋይዘርና አጋሩ እስከዚህ እስከያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ብቻ 50 ሚሊዮን የሚሆን ጠብታ ለማምረት ሁሉን ዓቀፍ ዝግጅቱን አጠናቋል። ይህም ማለት የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ሊገባደድ አንድ ወር ገደማ ብቻ ነው ስለቀረው በአንድ ወር 50 ሚሊዮን ጠብታ ያመርታል ማለት ነው። የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር የአማካሪዎች ምክር ቤት ልዩ ኮሚቴ በዲሴምበር 10 ይህን ክትባት ፍቃድ በመስጠት ጉዳይ ላይ ስብሰባ ይቀመጣል። ይህ ማለት ከ17 ቀናት በኋላ ነው የሚሆነው። ዶ/ር ስሎይ የሚሉት ታዲያ ይህ ኮሚቴ በተሰበሰበና መድኃኒቱ የምርት ይሁንታን ባገኘ በነገታው ክትባቶች ወደ ጤና ጣቢያዎች ይደርሳሉ። ሞዴርና የተሰኘው ሌላው የመድኃኒት አምራች በበኩሉ እንደ ፋይዘር ሁሉ የፈውስ ምጣኔው 95 ከመቶ የሆነ ሌላ ክትባት መሥራቱን ይፋ አድርጓል። ሞዴርና እንደ ፋይዘር ሁሉ በሚቀጥሉት ሳምንታት እውቅናና ፈቃድ እንዲሰጠው ማመልከቻ ያስገባል ተብሎ ይጠበቃል። ሀብታም አገራት ከነዚህ ሁለት ኩባንያዎች ጋር የመድኃኒት ምርት ስምምነት እያደረጉ ነው። ድሀ አገራት በዚህ ረገድ እጣ ፈንታቸው ምን ሊሆን ይችላል የሚለው አሁንም እያነጋገረ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/55040023
amh
health
የለንደኑ ነዋሪ የመጀመሪያው በ3ዲ የታተመ ሰው ሰራሽ ዓይን ሊተከልለት ነው
የለንደን ከተማ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ በ3ዲ የታተመ ሰው ሰራሽ ዓይን ለመጀመሪያው ጊዜ ሊተከልለት ነው። ስቲቭ ቬርዜ ለንደን ከተማ በሚገኘው የሞርፊልድ የዓይን ሆስፒታል በ3ዲ ቴክኖሎጂ የታተመው ዓይን ይተከልለታል። አዲሱ ዓይን ከዚህ ቀደም ከነበረው ሰው ሰራሽ ዓይን የበለጠ ተፈጥሯዊ እንደሚመስል ተስፋ ተደርጓል። በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ለታካሚዎች ሰው ሰራሽ ዓይን ለመግጠም ይፈጅ የነበረውን የስድስት ሳምንታት ጊዜ የ3ዲ ቴክኖሎጂው በግማሽ ይቀንሳዋል ተብሏል። ምንም እንኳ ይህ ሰው ሰራሽ ዓይን የማየት ችሎታን ባይመልስም የተፈጥሮ ዓይን ስለሚመስል የሰዎችን በራስ መተማመን ከፍ ያደርጋል ተብሏል። ዕድሜ በ40ዎቹ ውስጥ የሚገኘው ቬርዜ "ከ20 ዓመቴ ጀምሮ ሰው ሰራሽ ዓይን ያስፈልገኝ ነበር። . . . ከቤቴ ስወጣ በመስታወት ውስጥ ዓይኔን እመለከታለሁ። እናም የማየው አያስደስተኝም" ብሏል። "አዲሱ ዓይን ድንቅ ይመስላል። በ3ዲ ዲጂታል ማተሚያ ቴክኖሎጂ በመሠራቱ የተሻለ ይሆናል" ብሏል። ለአንድ ግለሰብ ሰው ሰራሽ ዓይን ከመተከሉ በፊት በዓይኑ ልክ ሰው ሰራሸ አይኑ መቀረጽ ይኖርበታል። በ3ዲ የታተመ ሰው ሠራሽ ዓይን የማምረት ሂደትን ከሁለት እስከ ሦስት ሳምንታት ይቀንሳል። የመጀመሪያ ቀጠሮው ግማሽ ሰዓት ብቻ እንደሚወስድም ተገልጿል። በሞርፊልድስ የዓይን ሆስፒታል የዓይን ሕክምና አማካሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ማንዲፕ ሳጎ ሙሉ በሙሉ ዲጂታል በሆነው የሰው ሰራሽ ዓይን በማግኘታቸው ባልደረቦቻቸው "ደስተኛ" ነበሩ ብለዋል። "መጪው ሙከራ የዚህን አዲስ ቴክኖሎጂ ጥቅም በተመለከተ ጠንካራ ማስረጃዎችን እንደሚሰጠን ተስፋ እናደርጋለን። ለታካሚዎች ምን ያህል ልዩነት እንዳለው ያሳያል" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/59427030
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ ስፔን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በማገርሸቱ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል አዘዘች
የስፔን መንግሥት በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ በወረርሽኙ ክፉኛ በተጠቁት በመዲናዋ ማድሪድና አካባቢዋ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል አዘዘ። አዲስ በተጣለው ገደብም ወሳኝ የሆነ ጉዞ ማድረግ ከሌለባቸው በስተቀር ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ጥለው እንዲወጡ አይፈቀድላቸውም። ይሁን እንጅ የማድሪድ ክልል መንግሥት የእንቅስቃሴ ገደቡ ሕጋዊ አይደለም ብሏል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ በስፔን በቫይረሱ ከተያዙት 133 ሺህ 604 ሰዎች መካከል ከሲሶ በላይ የሚሆነው የተገኘው በማድሪድ ነው። በዚህም መሰረት ረቡዕ ዕለት አብዛኞቹ የስፔን የክልል ባለሥልጣናት፤ ከ100 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የሚገኙባቸው አካባቢዎች ሦስት መመዘኛዎችን ካሟሉ ገደብ እንዲጣልባቸው ድምፅ ሰጥተዋል። ሦስቱ መመዘኛዎች፤ ከ100 ሺህ ነዋሪዎች ውስጥ 500 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ካሉ፣ 35 በመቶ የሚሆኑት የበሽታው ታማሚዎች ፅኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ ከገቡ እና ከሚደረገው ምርመራ በ10 በመቶው ላይ ቫይረሱ ከተገኘበት የሚሉ ናቸው። በዚህ መስፈርት መሰረትም ከ100 ሺህ ነዋሪዎች 780 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ያሉባት ማድሪድ፤ መመዘኛውን አሟልታለች ተብሏል። ይሁን እንጅ አዲስ የተጣለው ገደብ መቼ ተግባራዊ እንደሚሆን አልታወቀም። ገደቡን ለመጣል ድምፅ ያልሰጠው በወግ አጥባቂው ተቃዋሚ ፓርቲ የሚመራው የማድሪድ ክልል መንግሥት ግን የእንቅስቃሴ ገደቡ ሕጋዊ አይደለም ብሏል። የክልሉ የጤና ኃላፊ ኢንሪኪው ሩይስ እስኩደሮ 'የማስጠንቀቂያና የሚረብሽ መልዕክት' በመላክ ማዕከላዊ መንግሥቱን ከሰዋል። የማድሪድ መንግሥት በከተማዋና አካባቢዋ የእንቅስቃሴ ገደብ ከመጣል ይልቅ፤ በ45 ዋና ዋና የጤና ተቋማት አካባቢዎች ገደቡን በመጣል የቫይረሱን ሥርጭት ለመቆጣጠር ነበር ምርጫው ያደረገው። ይሁን እንጅ ገደቦቹ በከተማዋ በአብዛኛው በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ነዋሪዎች ያሉባቸውን አካባቢዎችን ይበልጥ ይጎዳል በሚል አከራካሪ ነበሩ። ከዚህ ቀደም የእንቅስቃሴ ገደቡን በመቃወም በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች አደባባይ መውጣታቸው ይታወሳል። የስፔን ማዕከላዊ መንግሥት ግን "ከዚህ ቀደም የተጣሉት ገደቦች በቂ አልነበሩም" በማለት በመላ ከተማዋ የሚደረግ አላስፈላጊ እንቅስቃሴ እንዲቆም አሳስበዋል። የእንቅስቃሴ ገደቡ ተግባራዊ ሲደረግ የማድሪድ ድንበሮች ወሳኝ ወይም አስፈላጊ የሆነ ጉዞ ለሌላቸው ጎብኝዎች ዝግ ይሆናሉ። ድንበሯን እንዲያቋርጡ የሚፈቀደው ለሥራ ፣ ለሕክምና እና ለሸመታ እንደሆነም ተነግሯል። መናፈሻዎችና የመጫወቻ ሜዳዎችም ይዘጋሉ። ከስድስት በላይ ሰዎች አንድ ላይ መሰባሰብም አይችሉም። በስፔን ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን፤ እስካሁን ከ31 ሺህ 411 ሰዎች በላይ በቫይረሱ ሕይወታቸው አልፏል። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ፤ እስካሁንም ከ748 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። የዓለም ጤና ድርጅት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በአውሮፓ አገራት ወረርሽኙ 'በአስጊ ሁኔታ' እየተስፋፋ መሆኑን አስታውቋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54367505
amh
health
ኮሮናቫይረስ ፡ ባንነካካ፣ ባንተቃቀፍ፣ ባንሳሳም በጤናችን ላይ የሚጎድል ነገር ይኖር ይሆን?
ያለፈው የፈረንጆች ዓመት በጥቅሉ ካየነው መልካም ዓመት አልነበረም። አራራቀን እንጂ አላቀራረበንም። ለመሆኑ ባንተቃቀፍ ምን ይቀርብናል? ትዝ ብሎንስ ያውቃል? ለምን አልተጨባበጥኩም ብሎ የከፋውስ አለ? ለነገሩ ልጆችንን አቅፎ መሳም፣ ፍቅረኛችንን መሳም፣ ባሎቻንን ማቀፍ. . . እንዴት አንናፍቅም? በዓለም ላይ በርካታ ሰዎች የፈረንጆቹን 2020 የማኅበራዊ መራራቅ ዓመት ብቻ ሳይሆን ቤት ተከርችሞብን የታሸግንበት ዝጋታም ዓመት ሆኖ ነው እያበቃ ያለው። ከኮቪድ-19 መከሰት በፊት ማንም ሰው መቼስ ወደፊት መጨባበጥ ይከለከላል፣ መተቃቀፍ ያስቀስፋል ብሎ ያሰበ ይኖራል ተብሎ አይገመትም። ለመሆኑ አለመተቃቀፋችን አለመጨባበጣችን የራሱን ችግር ይዞ ብቅ ይል ይሆን? ተመራማሪዎች አዎ ይላሉ። መነካካት ተራ ነገር አይደለም። በፍቅር መነካት ወይም መታቀፍ ሕጻን ሳለን የመጀመርያ ቋንቋችን ነው። ፍቅርን የምንማርበት ቋንቋ። መግቢያቢያችን። ደግነትን፣ ሰው መውደድን፣ ለሆነ ፍጡር እምነታችንን መስጠትን የምንሰለጥነው በእቅፍ ትምህርት ቤት ውስጥ ነው። በጊዜ ሂደት ረስተነው ይሆናል እንጂ ድሮ ድሮ ካልታቀፍን ብለን አልቅሰናል። ካላመናችሁ እናታችሁ ጋር ደውሉ። ለዕድገታችንም እንደ እናት ጡት ወተት ሁሉ መታቀፍ አስተዋጽኦ ነበረው። በጊዜ ሂደት ክደውን ነው እንጂ. . . ። "የሰዎች ተቀራርቦ መነካካት የዋዛ ነገር አይደለም። ማኅበራዊ ሙጫ ማለት ነው። አስተሳስሮናል። ከምንወደው ሰው ጋር ገምዶናል። እንደ ሰው የሚያቀራርበን አንድ ነገር ቢኖር ይኸው ነው" ይላሉ ዴቪድ ሊንደን። ዴቪድ 'ዘ ኒው ሳይንስ ሂዩማን ኢንዲቪጁዋሊቲ' ደራሲ ናቸው። በዚህ የንክክኪ ሳይንስ ውስጥ ብዙ አጥንተዋል። "የመነካካት ነገር እና ፋይዳው እምብዛምም አልተጠናም። ቸል ያልነው፤ ገሸሽ ያደረግነው ጉዳይ ሳይሆን አይቀርም" ይላሉ ደራሲ ዴቪድ። ለመሆኑ ሌሎችን ሰዎችን ስንነካ አእምሯችን ውስጥ ምንድነው የሚፈጠረው? አንዳንድ ጥናቶች መነካት፣ መታቀፍ፣ ልክ ሕመም ማስታገሻን የመውሰድ ያህል ፈውስ ይሰጣል ይላሉ። ይህ የተጋነነ አረፍተ ነገር ከመሰላችሁ፣ አንድ ሕጻን ልጅ ሲነካ እንዴት እንደሚሆን ለማየት ሞክሩ። አንድ ሕጻን ልጅ በእናቱ ጭንቅላቱ ቢዳበስ የልብ ምቱ መረጋጋት ይጀምራል። ይህን ያሉት በሕጻናት አንጎል [ኒውሮሳይንስ] ላይ ተመራማሪ የሆኑት ሬቤካ ስላተር ናቸው። አንዳንድ ጥናቶች ይህንን ነገር ከዚህም በላይ ገፋ ያደርጉታል። ለምሳሌ ክብደታቸው ከአማካይ በታች ሆነው የተወለዱ ልጆች በእናቶቻቸው ሲነካኩና ሲታቀፉ መጠናቸው እየተስተካከለ እንደሚመጣ ተደርሶበታል። የዝግመተ ለውጥ ተመራማሪ ሮቢን ደንበር እንደሚሉት የሰው ልጅ ከእንሰሳት ጋር ከሚያመሳስሉት ነገሮች አንዱ ንክኪና ለዚያ የሚሰጠው ትርጉም ነው። የሰው ልጅ ያለበት የነ ዝንጀሮና ዝርያቸው ጨምሮ አጥቢዎች በሕይወት ዘመናቸው 20 ከመቶውን የሚያሳልፉት እርስ በርሳቸው በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በመነካካት ነው። ከዝርያቸው ጋር ወዳጅነታቸውን የሚገልጹትም በብዛት በንክኪ ነው። ለምሳሌ አንድን ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ስንነካ በመዳፋችን ያለው የነርቭ ብልጭታ ለጭንቅላታችን 'ከአዲስ ሰው ጋር አዲስ ግንኙነት እየፈጠርክ ነው' የሚል መልዕክት ያደርስለታል። ያ ስሜት ደግሞ ብዙ እጢዎች መልካም የሰውነት ፈሳሾችን እንዲያመነጩ ያደርጋል። በንክኪ ውስጥ አእምሯችን ዘና ይላል፤ በተለይም ደግሞ አብረነው በንክኪ እየተግባባነው ያለውን ሰው የምናምነው ሲሆን እፎይታን ይመግበናል ይላሉ እኚሁ ተመራማሪ። ከመነካካት ጋር የነበረን የመጀመሪያ ቁርኝት ፈዋሽ ብቻ ሳይሆን ስሜትን ሰቅዞ የሚይዝ ነው። መጀመሪያ የሳምናትን ኮረዳ፣ መጀመሪያ የዳበስነውን መልከ መልካም ልጅ፣ የመጀመሪያ የፍቅር ግንኑነቶች ሁሌም በአእምሯችን የማይጠፉት ከንክኪ በሚያገኙት ኃያል የተነሳ ነው። ለመሆኑ መነካካት ይህን ያህል ትርጉም ካለው አለመነካካት ምን ሊያደርገን ይችላል? መነካት፣ መታቀፍ ይህን ያህል አእምሯችን ላይ በጎ ተጽእኖ አለው ብለናል። ያረጋጋናል፣ ያስደስተናል፣ ሕይወታችንን እንድንወዳት ያደርገናል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሕመማችንን ያስወግድልናል። አልተጋነነም። በንክኪ ደዌ ይፈወሳል። የንክኪ ሕክምና ያለውም ለዚህ ሳይሆን ይቀራል? አሁን እንዳትነካኩ፣ እንዳትጨባበጡ፣ እንዳትስሙ ስንባል ሳናውቀው የሆነ ነገራችን እየተጎዳ ነው። "እርግጥ ነው አትነካኩ በተባልን ማግስት ሕመም አልጀመረንም። ራሳችንን አልሳትንም፣ መፈጠራችንን አልጠናል ይሆናል. . ." ይላሉ ደራሲው ሊንደን። . . . ነገር ግን ከሰው ጋር የነበረን የቁርኝት ገመድ ለእኛ ባይታየንም ተበጥሷል፤ በስሜት ተለያይተናል። ቀስ በቀስ መጎዳታችንን ሳናውቀው ተጎድተናል።" ለምሳሌ አንዳንድ እንሰሳትን በፍጹም እንዳይነካኩ ብንከለክላቸው ወዲያውኑ ሊታመሙ ይችላሉ። ታመሙ የምንለው በመንፈስ ብቻ ሳይሆን በአካልም ጭምር ነው። በጭንቀት ይወጠራሉ፤ አዳዲስ የአውሬነት ባህሪን እያሳዩ ሊመጡ ይችላሉ። በጊዜ ሂደት ደግሞ ጤናቸው እየተቃወሰ ሊመጣ ይችላል። እስከመሞትም ሊያደርሳቸው ይችላል። ወረርሽኙ የገባ ሰሞን፣ በተለይ ደግሞ ብዙ አገሮች ማኅበራዊ መራራቅን ግዴታ ባላደረጉበት ወቅት እንኳ ብዙ ሰዎች ከሰዎች ጋር መቀራረብን፣ መነካካትን እንደናፈቁ ይናገሩ ነበር። አሁን ዓለም እንዲህ በተራራቀበት ጊዜ ይህ ሁኔታ ሲብስበት ምን ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ነው። ምናልባት ነገሩን ትተነዋል። ቅርርቦሽንና ፋይዳውን የምናስብበት ጊዜ እንኳን አጥተን ይሆናል። ሕይወት እያራወጠን ዘንግተነው ይሆናል። ያ ማለት ግን ውስጣችን አልተጎዳም ማለት አይደለም። ጎልድስሚዝ ዩኒቨርስቲ በቢቢሲ ራዲዮ ፎር በኩል አንድ ጥናት አድርጎ ነበር። በጥናቱ በ110 አገሮች የሚኖሩ 40ሺህ ሰዎች ተጠይቀው ነበር። 20ሺህ የሚሆኑት መተቃቀፍን እጅግ አድርገው መናፈቃቸውን አምነዋል። መነካትን መናፈቅ ከባድ ናፍቆት ነው። ታዲያ ምን ተሻለ? ፕሮፌሰር ስሌተር እንደሚሉት ከሆነ ከዚህ በኋላ በሰዎች መካከል ተህዋሲው ቢጠፋ እንኳን ከተህዋሲው በፊት እንደነበረው ጊዜ ንክኪዎች አይኖሩም ይላሉ። ሰዎች በመጨባበጥ ውስጥ የሚለዋወጡት ወዳጅነት እንደነበረው አይዘልቅም ነው የሚሉት። ነገር ግን የዝግመተ ለውጥ ተመራማሪና ሳይኮሎጂስት ሮቢን ደንበር ይህ ነገር አያሳምናቸውም። እሳቸው የሚያምኑት ወዳጅነትና መነካካት ሰዋዊ ነው። ሰዋዊ ባህሪ ደግሞ እንዴትም ቢሆን ካቆመበት ይቀጥላል። መዳፋችን የውስጠኛው አካሉ ሲፈጠር ራሱ እንዲነካ፣ እንዲዳስስ ተደርጎ ነው። የነርቮቹ ብዛት የሚያመላክቱትም ያንኑ ነው። እኛ ባናውቀውም ሰውነታችን ልክ እንደ ጥልፍልፍ የኤሌክትሪክ ገመድ ያለ ነው። ንክኪ ቶሎ ብሎ ወደ አእምሮ መልዕክት ይልካል። ስለዚህ ያለ መነካካት ጤናችን ልክ አይመጣም። በሚወዱት ሰው መነካትን የመሰለ የአእምሮ ፈውስ የለም። ለረዥም ጊዜ በናፈቅነው ሰው እቅፍ ውስጥ የመግባትን ያህል ደስታ የለም። በናፈቅነውና በምንወደው ሰው እቅፍ ውስጥ ለሰከንዶች መቆየት ትንሽዬ የገነት ጎጆ ውስጥ ገብቶ የመውጣት ያህል ነው። "አንድ ሰው ስለእናንተ የሚሰማውን በትክክል ለማወቅ የምትፈልጉ ከሆነ . . . የሚነግሯችሁን ከመስማት ይልቅ እንዴት እንደሚነካችሁ ስሜቱን ለመረዳት ሞክሩ" ያላሉ ባለሙያው። ብዙ ሰዎች ከልጅነታቸው ጋር በነበራቸው የእናት ፍቅር ውስጥ ምን ትዝ ይላችኋል ሲባሉ፤ እናታቸው ፀጉራቸውን ስትነካካቸው የነበራቸው ስሜትን በይበልጥ ያስታውሳሉ። ለምን? የፈረጆቹ 2021 ዳግም የምንተቃቀፍበት ዘመን ይሆን ይሆን?
https://www.bbc.com/amharic/news-55421935
amh
health
ኮሮናቫይረስ ፡ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተናገሩ
በኮሮናቫይረስ ተይዘው ሆስፒታል የገቡት የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ደህና መሆናቸውንና ቀጣዮቹ ቀናትም ለጤንነታቸው ወሳኝ መሆናቸውን ተናግረዋል። ፕሬዚደንቱ ይህን ያሉት ጤንነታቸውን አስመልክቶ የሚወጡ የተለያዩ መረጃዎችን ተከትሎ ቅዳሜ ምሽት በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት ነው። የፕሬዚደንቱ ሐኪምም ትራምፕ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ እና ሕክምናውን ከጀመሩ አንስቶ ለውጥ እንዳሳዩ ተናግረዋል። ሐኪማቸው ዶ/ር ኮንሊ በሰጡት መግለጫ ላይ ፕሬዚደንቱ ከተጋረጠባቸው አደጋ ሙሉ ለሙሉ ባይላቀቁም፤ የሕክምና ቡድኑ ግን በሁኔታቸው ተስፋ እንዳለው ተናግረዋል። ከሰዓታት በፊት ትራምፕ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት ላይ ያለ ከረቫት የሱፍ ኮት በሸሚዝ ለብሰው ታይተዋል። በንግግራቸውም በዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ በዋልተር ሪድ ብሔራዊ ወታደራዊ ሕክምና ማዕከል የሚሰሩ ዶክተሮችና ነርሶችን አመስግነዋል። "እዚህ ስመጣ ደህና አልነበርኩም ፤ አሁን ላይ ግን እየተሻለኝ ነው" ብለዋል ትራምፕ። የሚቀጥሉት ቀናት ወሳኝ እንደሆኑ ገልፀው፤ " በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ምን እንደሚፈጠር እናያለን" ብለዋል። ፕሬዚደንቱ በኮቪድ-19 መያዛቸውን በትዊተር ገፃቸው ለሕዝብ ይፋ ያደረጉት ባሳለፍነው አርብ ነበር። ይህም የምረጡኝ የቅስቀሳ ዘመቻቸውን ያቋረጠባቸው ሲሆን ከምርጫው በፊት አዲስ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ለመሰየም መሞከራቸው ላይም ጥርጣሬን አሳድሯል። ትራምፕ በከሮናቫይረስ ተይዘው ሆስፒታል ከገቡ ሁለተኛ ቀናቸውን ይዘዋል። ስለ ትራምፕ ጤንነት የምናውቃቸው ነገሮች ቅዳሜ ዕለት ጠዋት የፕሬዚደንቱ ሐኪም ዶ/ር ኮንሊ በሰጡት መግለጫ ለፕሬዚደንቱ ተጨማሪ ኦክስጅን አለመሰጠቱንና ለ24 ሰዓታትም ትኩሳት እንዳልነበራቸው ተናግረዋል። ይሁን እንጅ ፕሬዚደንቱ ለመጭዎቹ 'ጥቂት ቀናት' በሆስፒታሉ እንደሚቆዩ ዋይት ሃውስ ገልጿል። ዶ/ር ኮንሊ ስለትራምፕ የጤንነት ሁኔታ ሲናገሩም ተስፋ እንዳላቸው ገልፀው፤ ከሆስፒታል ሊወጡ የሚችሉበትን ጊዜ ግን አልገለፁም። ሆኖም የዋይት ሃውስ ቺፍ ኦፍ ስታፍ (የቢሮ ኃላፊ) ማርክ ሚዶውስ፤ ፕሬዚደንቱ የማገገም ሂደት ላይ እንዳልነበሩ ጠቅሰው፤ ጤንነታቸው ላይ ያላቸውን ስጋት ገልፀዋል። ፕሬዚደንቱ ላለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የበሽታው ወሳኝ ምልክቶች እንደታዩባቸው በመግለፅም ቀጣዮቹ 48 ሰዓታት አስጊ እንደሚሆኑ አክለዋል። የ74 ዓመቱ ትራምፕ እድሜያቸውና የሰውነታቸው ክብደታቸው ግዙፍ የሚባሉ ዓይነት በመሆናቸው ለኮቪድ-19 ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ ሰዎች ይመደባሉ። እስካሁን በሙከራ ላይ ያለ መድሃኒት እና የፀረ ቫይረስ መድሃኒት እየወሰዱ ነው። ሐኪማቸው ቅዳሜ እለት በሰጡት መግለጫ ፕሬዚደንቱ ኦክስጅን ይወስዱ ነበር ወይ? ተብሎ በተደጋጋሚ ለተነሳላቸው ጥያቄ " በዚህ ሰዓት እየወሰዱ አይደለም ፤ አሁን ሁላችንም እዚህ ባለንበት ሰዓት ኦክስጅን አልተገጠመላቸውም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ይሁን እንጅ በርካታ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ፕሬዚደንቱ አርብ ዕለት ሆስፒታል ከመግባታቸው በፊት በዋይት ሃውስ ኦክስጅን ተገጥሞላቸው እንደነበር ዘግበዋል። ቅዳሜ ምሽት በተሰጠው መግለጫ ግን የሕክምና ቡድኑ ትራምፕ 'ሬምዲሲቫየር' የተሰኘውን መድሃኒት ሁለተኛውን ዶዝ መጨረሳቸው ተገልጿል። ከሰዓቱንም በደህና ሁኔታ ሲያሳልፉ ነበር ተብሏል። ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕም በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ እና በዋይት ሃውስ እረፍት እያደረጉ መሆናቸው ተነግሯል። የምርጫ ዘመቻውስ? ፕሬዚደንት ትራምፕ በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ "ዘመቻውን በተጀመረበት መንገድ ለማጠናቀቅ በቅርቡ እመለሳለሁ ብየ አስባለሁ" ሲሉ ተስፋቸውን ገልፀዋል። የፕሬዚደንቱ የምርጫ ዘመቻ ቡድን ትራምፕ ወደ ምርጫ ዘመቻው መመለስ እስከሚችሉ ድረስ ባላቸው ፍጥነት ቅስቀሳውን እንደሚቀጥል አስታውቋል። በመሆኑም አሁን ላይ የፕሬዚደንቱ ወንድ ልጆች ዶናልድ ጀር እና ኤሪክ እንዲሁም ምክትል ፕሬዚደንቱ ማይክ ፔንስ ዘመቻውን ያስቀጥላሉ ተብሏል። የዘመቻው ቃል አቀባይም የመጀመሪያው ዝግጅት ሰኞ የሚካሄደው 'ቨርቹዋል'[ ኦንላይን] ሰልፍ እንደሆነ ለፎክስ ኒውስ ተናግረዋል። አርብ ዕለት ተመርምረው ከቫይረሱ ነፃ የሆኑት ምክትል ፕሬዚደንት ፔንስ የዴሞክራቲክ ምክትል ፕሬዚደንት እጩ ካማላ ሃሪስ ጋር ረቡዕ ክርክር ለማካሄድ ፕሮግራም ይዘዋል። የዴሞክራቲኩ ጆ ባይደንም ዘመቻቸውን ቀጥለዋል። ቅዳሜ እለትም 'ቨርቹዋል' ዝግጅት አሰናድተዋል። ትራምፕ ለወባ በሽታ ፈዋሽነቱ የሚታወቀውን ሀይድሮክሲክሎሮኪውን መድኃኒትን በተደጋጋሚ ሰዎች እንዲወስዱ ሲወተውቱ ነበር። ከዚህ በፊት ይህንኑ መድኃኒት እንደወሰዱትና ጥሩ እንደሆነም ተናግረው ያውቃሉ። አሁን እርሳቸው ሀይድሮክሲክሎሮኪውንን ወስደው ይፈወሱ ይሆን ወይ የሚለው የጠላትም የወዳጅም ጥያቄ ሆኗል። ትራምፕ አሁን የሚወስዱት መድኃኒት ረምዴስቪር የተባለ ጸረ-ቫይረስ መድኃኒት ነው። ይህ መድኃኒት በኢቦላ ፈዋሽነቱ ይታወቃ። የትራምፕ በተህዋሲው መያዝን ተከትሎ ሴናተሮችና ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣናት እንዲሁም ረዳቶቻቸው ምርመራ ማድረግ ጀምረዋል። እስከአሁን ምክትል ፕሬዝዳንቱና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተህዋሲው እንደሌለባቸው ተረጋግጧል። ሆኖም የቀድመው የፕሬዝዳንቱ አማካሪ ኬሌያን ኮንዌይ፣ ሁለት የሪፐብሊካን ሴናተሮች ማይክ ሊ እና ቶም ቲሊስ ቫይረሱ ተግኝቶባቸዋል። የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ጉዳዮች ሥራ አስኪያጅ ቢል ሰቴፒን በተመሳሳይ ቫይረሱ ተገኝቶበታል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54406747
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ የፊት መከለያ መሳሪያ ያመረቱት የሥነ ሕንጻ ባለሙያ
አቶ አሸናፊ ዘመቻ በሙያቸው የሥነ ሕንጻ ባለሙያ ናቸው። ለሥራቸው የሚያግዟቸውን የተለያዩ ነገሮችም ዲዛይን በማድረግ ይሰራሉ። ለዚሁ ስራቸውም እንዲረዳቸው በሚል የ3ዲ ፕሪንተር ያላቸው ሲሆን በዚያም የተለያዩ ባሕላዊ የሆኑ እቃዎችን፣ መብራቶችን ለማተም ይገለገሉበታል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ላይ ከተከሰተ ጀምሮ በቅርበት ጉዳዩን ሲከታተሉ እንደነበር የሚገልፁት አቶ አሸናፊ፣ በወቅቱ ወረርሽኙ ስጋት ውስጥ ከትቷቸው እነደነበር ያስታውሳሉ። በወቅቱ ከመደናገጥ ይልቅ ምን ዓይነት አስተዋፅኦ ላበርክት የሚል ሃሳብ ይዘው ዙሪያቸውን ሲቃኙ ባላቸው 3ዲ ፕሪንተር የተወሰነ አገለግሎት መስጠት እንደሚችሉ አሰቡ። ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከቻይና አልፎ አውሮፓ፣ አሜሪካ እንዲሁም አፍሪካን ሲያዳርስ ግለሰቦችንም ሆነ የሕክምና ባለሙያዎችን ለቫይረሱ እንዳይጋለጡ ለማድረግ በሙያቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሲያስቡም ባላቸው ሕትመት መሳሪያ የፊት መሸፈኛ መስራት እንደሚችሉም ማስተዋላቸውን ይናገራሉ። ቻይና ላይ ቫይረሱ መከሰቱ በተሰማበት ወቅት ጀምሮ ጉዳዩ ያሳስባቸው እንደነበር ለቢቢሲ የሚናገሩት አቶ አሸናፊ፣ በወቅቱበአገር ውስጥ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ዋጋ በፍጥነት መናሩ እንዲሁም የአቅርቦት ችግር መኖሩ ማስተዋላቸው ምን ማድረግ አለብኝ ወደሚል ጥያቄ እንደመራቸው ይገልጻሉ። 3ዲ ፕሪንተር ካላቸው እና በእንግሊዝ አገር ከሚገኙ ሌሎች ባለሙያዎች ጋር በኢንተርኔት ላይ በነጻ የሚገኙ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም ለአገራቸው የሚጠቅም ነገር ለማበርከትም አቀዱ። በዚህ የፊት መሸፈኛ የሕክምና ባለሙያዎችም ሆኑ ሌሎች ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ፊታቸውን የሚከልሉበትን መሳሪያ ከበይነ መረብ ላይ በመመልከት ሰሩ። እርሳቸው በ3ዲ ፕሪንተር ተጠቅመው ያመረቷቸውን የፊት መከለያዎች፣ ለሆስፒታሎችና ለሕክምና ባለሙያዎች በነጻ ሲሰጡ የፊት መከለያ መጠቀም በስፋት በባለሙያዎች ዘንድ አለመለመዱን ያስታውሳሉ። መጀመሪያ ላይ ያመረቷቸውን የፊት መከለያዎች በነጻ ለተወሰኑ ሆስፒታሎችና የሕክምና ባለሙያዎች ለግሰዋል። በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታሎች፣ እንዲሁም በግል ለሚያውቋቸው ሕክምና ባለሙያዎች በነጻም በሽያጭም መስጠት የጀመሩት አቶ አሸናፊ፣ ይህ የሕክምና ባለሙያዎች ፊታቸውን ሙሉ በሙሉ የሚከልሉበትን (ፌስ ሺልድ) መሳሪያ በበርካታ ባለሙያዎች ዘንድ ፍላጎትን በመፍጠሩ በክፍያ ለማቅረብ ተነጋገሩ። ይህንን የፊት መከለያ ማንም የ3ዲ ፕሪንተር ያለው ግለሰብ በቀላሉ በሚጫኑ ሶፍት ዌሮችን በመጠቀም ማተም የሚችል ቢሆንም ህትመቱ ግን ዘገምተኛ በመሆኑ በብዛት ለማዳረስ አስቸጋሪ እንዳደረገው ይገልጻሉ። በአገር ውስጥ 3ዲ ፕሪንተር ያለው ግለሰብ ቁጥር አነስተኛ መሆኑን የገለፄት አቶ አሸናፊ ዘመቻ፣ ለህትመት የሚያገለግለው ቁስ በቀላሉ አለመገኘቱ ደግሞ ሌላ ፈታኝ ነገር ነበር። ፊትን የሚሸፍነው ማይካ በቀላሉ ገበያ ላይ የሚገኝ ቢሆንም እርሱን አቅፎ የሚይዘው ፍሬም ግን በ3ዲ ፕሪንተር መታተም እንዳለበት ጨምረው ያብራራሉ። ይህ መሸፈኛውን የሚያቅፈው ፍሬም ፀጉር ላይ እንደሚቀመጥ ቲያራ ዓይነት ሲሆን፣ ተበስቶ የፊት መሸፈኛውን እንዲታሰርበት ይደረጋል። በ3 ዲ ፕሪንተር ላይ ለማተም ይጠቀሙበት የነበረው ቁስ አንዴ ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ እንደማያገለግል የሚናገሩት አቶ አሸናፊ፣ ልጠቀምበት ቢባል እንኳ በቀላሉ ባክቴሪያ እንደሚስብ በተጨማሪም የአቅርቦት እጥረት መኖር ፈታኝ ማድረጉን ያስረዳሉ። ይህ የፊት መከለያ ማይካ ከቻይና እንደሚገባ የሚገልፁት ባለሙያው፣ ነገር ግን ግንባር ላይ የሚያርፈው የፊት መሸፈኛ አካሉ ስፖንጅ መሆኑን ይገልጻሉ። ይህ ደግሞ በቀላሉ ባክቴሪያን ስለሚይዝ በየጊዜው በፀረ ተህዋሲያን ኬሚካል ለማጽዳት አስቸጋሪ መሆኑን አብራርተዋል። ነገር ግን ይህንን ከ3ዲ ፕሪንተር ውጪ መስራት አስፈላጊመሆኑን እንዲሁም በአገር ውስጥ በቀላሉ በሚገኝ ቁስ ቢሰራ መልካም መሆኑን ማስተዋላቸው የራሳቸውን የፊት መሸፈኛ ዲዛይን አድርገዋል። በዚህም ወቅት መሳሪያው ዳግም ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጎ ቢሰራ መልካም መሆኑን ማስተዋላቸውንም ይገልጻሉ። በዚህም የተነሳ የሰሩት የፊት መሸፈኛ ዳግም ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን፣ ፊትን የሚከላከለው ማይካ ደግሞ በትንፋሽ አማካኝነት በቀላሉ ጭጋግ አይለብስም ሲሉ ያብራራሉ። እርሳቸው የሰሩት የፊት መከለያ ወጥ የሆነ ከፕላስቲክ የተሰራ ሲሆን ተቆርጦ በሌዘር ውስጥ እንደሚገባ ገልፀዋል። ለማጽዳት በሚፈለግበትም ወቅት ተፈትቶ በኬሚካል በቀላሉ ለማጽዳት እንዲቻል ተደርጎ መሰራቱን ያስረዳሉ። እነዚህ መሳሪያዎች ለየት የሚያደርጋቸው በቀላሉ ተፈታትተው መገጣጠማቸው ብቻ ሳይሆን፣ አገር ውስጥ በቀላሉ ከሚገኙ ቁሶች መሰራታቸውም ሌላው ለየት የሚያደርጋቸው ነገር መሆኑን ይገልጻሉ። አቶ አሸናፊ የሰሩት የፊት መሸፈኛ ቅርፁን ጠብቆ እንዲቆይ እና በቀላሉ እንዳይሰብ ተደርጎ መሰራቱን ጨምረው ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/54635973
amh
health
ረመዳን፡ ጾም በሰውነታችን ውስጥ የሚያስከትለው ለውጥና የሚሰጠው ጥቅም
ታላቁ የረመዳን ጾም ወቅት እነሆ ተጀምሯል። በመላው ዓለም በሚገኙ ሙስሊሞች ዘንድ በጉጉት የሚተበቀው ይህ ወቅት ቀኑ በጾም ምሽት ላይ ደግሞ ከቤተሰብና ከዘመድ ጋር ተሰብስቦ በአንድነት ማፍጠር የተለመደ ነው። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ዓለማችን በገጠማት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአንድ ላይ ተሰብስቦ ሐይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶችን መካፈልና ከተለያዩ ሰዎች ጋር መሰባሰብ እንዲቀር ይመከራል። ስለዚህም በሐይማኖት አባቶች የሚሰጠውን ምክር ተግባራዊ በማድረግ ይህንን ቅዱስ የጾም ወቅት እራሳችንንና ሌሎችን በመጠበቅ ልናሳልፈው ይገባል። በወረርሽኙ ምክንያት ምዕመናን ቀደም ሲል ሲያከናውኗቸው የነበሩ የጋር ሥርዓቶችን ማድረግ ባይችሉም፤ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ከቅርብ የቤተሰብ አባላቸው ጋር የተለመደውን ሥርዓት መፈጸም ይችላሉ ተብሏል። መጾም ታላቅ መንፈሳዊ ጸጋ እንደሚያስገኝ የሐይማኖት አባቶች ይናገራሉ። ከዚህ ባሻገር ደግሞ የጤና ባለሙያዎች ጾም ከሚያስገኘው መንፈሳዊ በረከት በተጨማሪ ለአካላዊ ጤንነት የሚሰጠው ጠቀሜታ አለው ይላሉ። ዝርዝሩን እነሆ. . . በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ረመዳንን በጾም ያሳልፋሉ። ጀንበር ወጥታ እስክትጠልቅ ድረስ። ሰውነታችን ከጾም ጋር የሚተዋወቀው ለመጨረሻ ጊዜ ምግብ ከቀመስን ከስምንት ሰዓታት በኋላ ነው። ይህም ማለት አንጀታችን ከተመገብነው ምግብ የሚያገኛቸውን ንጥረ ነገሮች በሙሉ አሟጦ ከጨረሰ በኋላ ነው የሚሆነው። ከዚህ በኋላ ሰውነታችን ተስፋ ይቆርጥና ፊቱን ጡንቻችንና ጉበታችን ውስጥ ወደተከማቸ ጉሉኮስ ያዞራል። የተቀረው የሰውነታችን አካል ጉልበት የሚያገኘውም ከዚህ የመጠባበቂያ 'ግምጃ ቤት' ከሚያገኘው ኃይል ይሆናል ማለት ነው። ከጡንቻና ከጉበት የጉሉኮስ ክምችት ሲያልቅ ሰውነታችን ሌላ አማራጭ ስለማይኖረው ስብን (Fat) ማቃጠል ይጀምራል። ከዚህ በኋላ ሙቀትና ጉልበትን የሚያገኘውም ከሌላ ሳይሆን ስብን በማቃጠል ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ ታዲያ መልካም ነገሮች ይከሰታሉ። የሚቃጠለው ስብ በመሆኑ ክብደት መቀነስ፣ የኮሌስትሮል መጠን መውረድ ይኖራል። የስኳር መጠናችን በዚህ ወቅት ዝቅ ማለቱ አይቀርም። ሆኖም በደማችን ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን ስለሚቀንስ ድካምና መዛልን ያስከትልብናል። ይህን ተከትሎ መጠነኛ ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽና መልካም ያልሆነ የአፍ ጠረን ሊከተል ይችላል። ይህ የሚሆነው በረሀብ ምክንያት ሆዳችንን ሲሞረሙረንና ያለ ምግብ መቆየቱ ለሰውነታችን እየከበደው ሲመጣ ነው። ከ3-7ኛ ቀን፤ ሰውነታችን በፈሳሽ እጥረት የሚጎዳበት ጊዜ ሰውነታችሁ ጾሙን እየተለማመደ ሲመጣ በውስጣችን የሚገኘው የስብ ክምችት እየተሰባበረ ራሱን ወደ የደም ስኳርነት (Blood sugar) ይለውጣል። የምንወስደው ፈሳሽ መጠን እየቀነሰ መምጣቱ በሰውነታችን ውስጥ ያለው ፈሳሽ ወደመሟጠጥ (ዲሃይድሬሽን) ስለሚያመራ በ"ማፍጠሪያ" ሰዓትና ከዚያም በኋላ ባለው የሌሊቱ ክፍለ ጊዜ በርከት ያሉ ፈሳሾችን መውሰድ ይመከራል። በጾም መግደፊያ ሰዓት የምትወስዱት የምግብ መጠን ጉልበት ሰጪ የሆኑ ተመጣጣኝ ምግቦችን ማግኘት ይኖርበታል። በፕሮቲን ከበለጸጉ ምግቦች ባሻገር ጨው እና በርከት ያለ ውኃ ከሌሎች የተመጣጠኑ ምግቦች ጋር ማግኘት ለሰውነታችን መልካም ሁኔታን ይፈጥራል። ከ8ኛ-15ኛ ቀናት በዚህ ጊዜ ሰውነታችን ጾሙን ተላምዶታል። በዚህም የተነሳ ድካምና መዛሉ እንደመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም። ዶክተር ራዚን ማህሩፍ የአኔስቴሺያና የጽኑ ሕሙማን ሕክምና አማካሪ ናቸው። በኬምብሪጅ አዴንብሩክ ሆስፒታል ውስጥ ነው የሚሠሩት። እርሳቸው እንደሚሉት በዚህ ጊዜ ጾሙ ለሰውነታችን ሌላም በጎ ጎን ይዞ ይመጣል። ለምሳሌ በሌላው ጊዜ በርከታ ያለ ካሎሪ ያላቸው ምግቦችን የምንወስድ ከነበረ ሰውነታችን ሥራዎችን በአግባቡ ለመፈፀም ፈተና ውስጥ ይወድቅ ነበር። ወይም ደግሞ እክል ይገጥመዋል። በጾም ጊዜ ግን ይህ ሁኔታ ይስተካከላል። "ምክንያቱም የካሎሪ ክምችት ስለማይበዛበት ሰውነታችን ወደ ሌሎች ሥራዎች ትኩረቱን ያደርጋል" ይላሉ ሐኪሙ። ለዚህም ነው "ጾም ኢንፌክሽን በመዋጋትና ጤናን በመመለስ አስተዋጽኦ የሚኖረው።" ከ16ኛ- 30ኛ ያሉ ቀናት በረመዳን ሁለተኛው ምዕራፍ (ከ15ኛው ቀን ጀምሮ) ሰውነት ሙሉ በሙሉ ጾሙን ይላመዳል። በዚህ ጊዜ እነ ደንዳኔ፣ ጉበት፣ ኩላሊት እንዲሁም ቆዳ ሁሉም ራሳቸውን በማጽዳት ሂደት (ዲቶክሲፊኬሽን) ውስጥ ነው የሚሆኑት። ዶክተር ማህሩፍ እንደሚሉት በዚህ ወቅት ጤና ተመልሶ፣ ሰውነታችን የቀድሞውን ጉልበቱን የሚያገኝበትና የማስታወስ አቅምና ትኩረት የማድረግ ብቃት ወደ ቀድሞው ሁኔታ የሚመለስበት ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ሰውነታችን ጉልበት ለማግኘት ወደ ፕሮቲን መሄድ አይኖርበትም። ይህ የሚሆነው ብዙውን ጊዜ ረሀብ ሲሰማንና ሰውነታችን ከጡንቻዎቻችን እየቀሰመ የሚወስደውን ምግብ ማደን ሲጀምር ነው። በዚህ መንገድ የሚቀጥለው ግን ለቀናትና ለሳምንታት በተከታታይ ስንጾም ነው። የረመዳን ጾም የሚጸናው የየዕለቱ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ብቻ ስለሆነ ሰውነታችን ጉልበት ከምግብ እንዲያገኝ የ"ኢፍጣር" ሰዓት ዕድል ይሰጠዋል። ፈሳሽም እንደልብ ያገኛል። ይህ ጡንቻዎቻችን ውስጥ ያለን ክምችት ለመጠባበቂያነት ያቆይልናል። የተወሰነ ኪሎ እንድንቀንስም ይረዳናል። ይህም ለሰውነት መልካም ነገር ነው። ጾም ጤናን ይጎዳል? የካምብሪጁ አዲንብሩክ ሆስፒታል ሐኪም ዶክተር ማሕሩፍ ምላሻቸው "እንደሁኔታው" የሚል ነው። እንደርሳቸው አመለካከት በርከት ያሉ ሁኔታዎች ጾምን ለሰውነታችን ጎጂም ጠቃሚም ሊያደርጉት ይችላሉ። ጾም ለሰውነታችን መልካም የሚሆንበት አንዱ ምክንያት መቼ ምን መብላት እንዳለብን ትኩረት እንድናደርግ ስለሚያስችለን ነው። ሁለተኛው ክብደታችንን መቆጣጠርና፣ የካሎሪ መጠን መወሰን ስለሚያስችል ነው። ለወር ያህል መጾም እምብዛምም የሚያመጣው የጤና እክል ባይኖርም ከዚያ በኋላ ግን ለተከታታይ ጊዜ ያለማቋረጥ መጾም ግን አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ሐኪሙ ሳይጠቁሙ አያልፉም። እንደ ሐኪሙ ማብራሪያ ያለማቋረጥ መጾም በቋሚነት ኪሎ ለመቀነስ አይረዳም። ምክንያቱም ከሆነ ጊዜ በኋላ ሰውነታችን ስብን ወደ ጉልበት መቀየር ያቆምል። ከዚያ ይልቅ ፊቱን ወደ ጡንቻዎቻችን ነው የሚያዞረው። ይህ ደግሞ ጤናማ አይደለም። ምክንያቱም ሰውነታችን ከሆነ ወቅት በኋላ "በመራብ ስሜት" ላይ ስለሚቆይ ነው። ሐኪሙ እንደሚሉት ከረመዳን ውጭ መጾም ቢያስፈልግ እንኳ በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ እያፈራረቁ መጾም በመደዳ ለተከታታይ ቀናት ከመጾም እጅግ የተሻለ ጤናማ ተግባር ነው። "ረመዳን በአግባቡ ከተጾመና በቂ ፈሳሽ በቀን ውስጥ ማግኘት ከተቻለ፣ ጠቃሚ የጡንቻ ክምችቶች ሳይቃጠል ኪሎ መቀነስ ስለሚያስችል የጤና በረከትም ያስገኛል" ይላሉ እኚሁ ሐኪም።
https://www.bbc.com/amharic/news-44128047
amh
health
በእስራኤል ጭንቅላታቸው ተጣብቆ የተወለዱ መንትዮች በቀዶ ህክምና ተለያዩ
ጭንቅላታቸው ተጣብቆ የተወለዱ የአንድ ዓመት መንትዮች በእስራኤል ያልተለመደ በተባለለት ቀዶ ሕክምና ተለያይተው ለመጀመሪያ ጊዜ ለመተያየት በቁ። ባለፈው ሳምንት በቢርሼባ ከተማ በሶሮካ የሕክምና ማዕከል 12 ሰዓታት የፈጀውን ቀዶ ህክምና ለማከናወን የወራት ዝግጅት ተደርጓል። በደርዘን የሚቆጠሩ የእስራኤል እና የሌሎች ሃገራት ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል። በስም ያልተጠቀሱት መንትያ እህትማማቾች ከህክምናው በኋላ በጥሩ ሁኔታ እያገገሙ ነው ተብሏል። "በራሳቸው እየተነፈሱ እና እየተመገቡ ነው" ሲሉ የሶሮካ የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና ክፍል ኃላፊ ኤልዳድ ሲልበርስተይን ለእሥራኤሉ ቻናል 12 ተናግረዋል። በዓለም ላይ 20 ጊዜ ብቻ የተደረገው ይህ መሰል ቀዶ ህክምና በእስራኤል ሲደረግ የመጀመሪያው ነው። ቀዶ ህክምናው ከመደረጉ ከወራት በፊት የሲሊኮን ከረጢቶች ወደ ጭንቅላታቸው ገብተው በጊዜ ሂደት ቆዳቸው እንዲለጠጥ ተደርጓል። የራስ ቅሎቹ እንደገና ከተሠሩ በኋላ ተጨማሪ ቆዳቸው የራስ ቅላቸውን እንዲሸፍን ጥቅም ላይ ውሏል። የመንትዮቹ የ 3ዲ ምናባዊ እውነታን የሚያሳይ ዝግጅት መደረጉንም የሶሮካ ዋና የነርቭ ቀዶ ህክምና ባለሙያ የሆኑት ሚኪ ጊዶን ተናግረዋል ። አክለውም "ደስተኛ ያደረገን ሁሉም ነገር እንዳሰብነው መሆኑ ነው" ብለዋል። ከአንድ ዓመት በፊት የተወለዱት ልጆች ወደፊት ሙሉ በሙሉ መደበኛ ሕይወት ይመራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58459656
amh
health
ኮሮናቫይረስ ፡ ሳሙና ወይስ ፀረ-ቫይረስ ፈሳሽ? - የኮቪድ-19 ፀር ማነው?
ውሃን ሳሙና እንደ ዘንድሮ ከብረው አያውቁም ብንል ማጋነን አይሆንም። በውሃና ሳሙና መሪነት ስንቱ ኮሮናቫይረሰን ከመዳፉ ጠራረገ። እርግጥ ነው ሳሙናና ውሃ ለመዳፋችን ብርቅ አይደሉም። እንዲህ በሕይወታችን አስፈላጊ ይሆናሉ ብሎ የተነበየ ካለ ግን እሱ ሐሰተኛ ነው። ውሃና ሳሙና አሁን ከነርቫችን ጋር ተናኝተዋል። ሳናስበው ሁላ መታጠብ ጀምረናል። ኮሮናቫይረስን ለመዋጋት ብዙ መሣሪያ ታጥቀናል። ጭምብል ቢሉ ጓንት፤ ራስን ማግለል ቢሉ በጸረ ተህዋስ ቫይረስን መግደል። ከሁሉም በላይ ቀላሉ መሣሪያ ግን እጅን በሳሙና እሽት አድርጎ መታጠብ ነው። ኮሮናቫይረስ ገዳይ ወረርሽኝ ነው ተብሎ ወርሃ የካቲት ላይ ሲታወጅ የጤና ሰዎች አዲሱን ቫይረስ እንዴት እንደምትከላከከሉ እንንገራችሁ ብለው ብቅ አሉ። እንዲህም አሉ፤ የመጀመሪያውና የመጀመሪያው እጅን መታጠብ ነው። ለዚያውም በሳሙና። ከተገኘ ሞቅ ባለ ውሃ። ቢያንስ ለ20 ሰከንድ መታጠብ። በኢትዮጵያዊው ዶ/ር ቴድሮስ የሚመራው የዓለም ጤና ድርጅት እጃችን እንዴት መታጠብ እንደምንችል የሚያሳይ ምስል ሠራ። ይኸው ይህ በቫይረስ የሚተላለፈውን ወረርሽኝ ስድስት ወር አለፈው። በርካታ ከተሞች ተዘግተው ተከፈቱ። እንደገና የተዘጉም አሉ። ሰዓት እላፊም ያወጁም መቶዎች ናቸው። ቫይረሱ ግን እንዲህ በቀላሉ አልተበገረም። ለዚህም ነው አሁንም እጃችሁን ታጠቡ እየተባለ የሚመከረው። ነገር ግን እጃችንን በአግባቡ እየታጠብን አይደለም የሚሉ ቅሬታቸው አሁንም ይደመጣሉ። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ የተሠራ አንድ ጥናት የሕክምና ማዕከሎችን ከሚጎበኙ 1 ሺህ ሰዎች 1 በመቶ ብቻ ናቸው በአግባቡ እጃቸውን የታጠቡት ይላል። እውን ውሃና ሳሙና ቫይረሱን ሙልጭ አድርገው ያጠፋሉ? በደንብ ነዋ! ይላሉ የቦስተን ማሳቹሴትስ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ቶማስ ጊልበርት። ባለሙያው እንደሚሉት ኮሮናቫይረስ የተሠራበት የኬሚካል ውህድ በትንሽ ሳሙናና ሙቅ ውሃ ብትንትኑ ይወጣል። "ቫይረሶች ቅባታማ ባህሪ ያለው ሽፋን ያላቸው ናቸው። ይህ ቅባትነት ያለው ሽፋን ውስጥ ያለውን ዋና ቫይረስ የሚከላከል ነው። ይህ ሽፋን በሳሙናና ውሃ መሰበር ይችላል። ሽፋኑ ተሰበረ ማለት ውስጥ ያለው ቫይረስ ተጋለጠ ማለት ነው። ይህ ደግሞ ቫይረሱን ያጠፋዋል" ይላሉ ባለሙያው። “ከዚህ በኋላ በውሃና ሳሙና መታጠብ አያስልፍግም የሚባልበት ጊዜ ቅርብ ነው ብዬ አላስብም።” “መጀመሪያን እጅዎን ያርጥቡ፤ ከዚያ ሳሙናው አረፋ ከሰራ በኋላ ቢያንስ ለ20 ሰከንዶች ያህል እጅን ማሸት ነው“ ሲሉ ባለሙያው ይመክራሉ። ጊልበርት እንደሚሉት ሳሙናው የቫይረሱን ሽፋን ሰብሮ ለመግባት 20 ሰከንድ ይበቃዋል። ሙቅ ውሃ ከታከለበት ደግሞ ሳሙናውን ሥራውን በፍጥነት እንዲያከናውን ያግዘዋል። በኬንት ዩኒቨርሲቲ የሞለኪዩላር ሳይንስ ምሁር የሆኑት ፕሮፌሰር ማርቲን ሚካየሊስ ደግሞ ውሃ ብቻውን የቫይሱን ሽፋን ለመስበር በቂ አይደለም ይላሉ። “ኩሽና ውስጥ ስናበስል ዘይት እጃችንን ከነካው በውሃ ብቻ ለማስለቀቅ እንደሚከብደን ሁሉ የኮሮናቫይረስን ለማግኘት ሳሙና የግድ ነው።“ ነገር ግን የውሃና ሳሙና ድል በእንግሊዝኛው ሳኒታይዘር እየተባለ ከሚጠራው ፀረ-ተህዋስ ፈሳሽ ጋር ሲምታታ ይስተዋላል። ዘንድሮ ሳኒታይዘርና ጭምብል ረስቶ ከመውጣት ሞባይል ስልካችንን ረስቶ መውጣት የተሻለ ነው። ነገር ግን ባለሙያዎቹ ሳኒታይዘር ለችግር ጊዜ ነው መሆን ያለበት ይላሉ። ቤት ውስጥ ውሃና ሳሙና ካለ ሳኒታይዘር መጠቀም አይመከርም። ጊልበርት በትንሽዬ ብልቃጥ ሳኒታይዘር ይዞ መንቀሳቀስ አይከፋም ይላሉ። ነገር ግን እኔን ብትጠይቁኝ ይላሉ ባለሙያው “እኔን ብትጠይቁኝ የምመርጠው ውሃና ሳሙና ነው።” እጃችንን ምን ያክል እንታጠብ? ወረርሽኙ የጀመረ ሰሞን በርካታ አገራት ዜጎቻቸው በየጥቂት ሰዓቱ እጃቸውን እንዲታጠቡ ይመክሩ ነበር። ቤት ብትውሉ እንኳ እጃችሁን መታጠብ እንዳትረሱ የሚል መልዕክት መስማት የተለመደ ነበር። ፕሮፌሰር ጊልበርት ግን ቤት የምንውል ከሆነ አስር ጊዜ እጅን መታጠብ አስፈላጊ አይደለም ባይ ናቸው። ቢሆንም ሽንት ቤት ከተጠቅምን በኋላም ሆነ ማዕድን ከማዘጋጀትችንና ከመቁረሳችን በፊትና በኋላ እጅን መታጠብ ግድ ይላል። ባለሙያው በጭራሽ እንድነዘጋ አይፈልጉም። እጃቸውን በተደጋጋሚ መታጠብ ያለባቸው ሰዎች አሉ። ለምሳሉ ቤታቸው ውስጥ የኮቪድ-19 ታማሚ የሚንከባከቡ ሰዎች ውሃና ሳሙና ወዳጃቸው ሊሆን ይገባል። አሊያም ቫይረስ ሊኖርባቸው ይችላሉ የተባሉ ዕቃዎችን የነኩ ሰዎችን በጣም ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። መኖሪያ ቤታችሁ ብዙ ሰዎች ካሉም እጅን በተደጋጋሚ መታጠብ ይመከራል። አንድ ጥናት ሰዎች ቫይረሱ ያለበት ሰው ወይም ዕቃ ከነኩ ወዲያውኑ እጃቸውን መታጠባቸው በጣም አዋጭ መሆኑን ይጠቁማል። አንዳንድ ሰዎች ከዚህ በፊት ከምንጠቀመው ሳሙና ይልቅ ፀረ-ተህዋስ ሳሙናዎች የበለጠ ኮቪድ-19ኝን ይከላከላል በማለት ሲጠቀሙ ይስተዋላሉ። ይሁንና እንደ ሚካየሊስ ከሆነ የትኛውም ሳሙና የኮሮናቫይረስ አምጪ ተህዋስን የመግደል አቅም አለው። ሁለቱም ባለሙያዎች ኮሮናቫይረስን ከመዳፋችን ጠራርጎ ለማጥፋት የግድ ለመጠጥ የሚሆን ንፁህ መጠቀም እንደሌለብን ይመክራሉ። የውሃ አቅርቦት በቂ ባልሆነባቸው የዓለማችን ክፍሎች በውሃና በሳሙና በቀላሉ እጅን መታጠብ ቀላል ላይሆን ይችላል። የዶክተር ቴድሮስ መሥሪያ ቤት በቅርቡ ያወጣው አንድ ጥናት እንደሚያሳየው በዓለማችን ከአምስት ትምህርት ቤቶች ሁለቱ ብቻ ናቸው በቂ የውሃ አቅርቦት ያላቸው። ይህ ጥናት የተሰራው ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፊት ነው። ሌላው አስገራሚ የኮሮናቫይረስ ተፅዕኖ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን መቀነሱ ነው። ለምሳሌ የኢንፍሉዌንዛ በሽታ ከሌላው ጊዜ በተለይ ዘንድሮ እጅግ ቀንሷል። ባለፈው ዓመት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መጋቢትና ነሐሴ ወር ላይ ቢያንስ 700 ሰዎች በጉንፋን ነክ በሽታዎች በጠና ይታመሙ ነበር። ዘንድሮ ግን አንድ ሰው ብቻ ነው መሰል በሽታ የታየበት። ለዚህም ደግሞ ዋነኛው ምክንያት ሰዎች አካላዊ ንክኪ መቀነሳቸው ነው። ወጣም ወረደ ኮሮናቫይረስ ክትባት እስኪገኝለት ድረስ እጅ መታጠባችን፤ ንክኪ መቀነሳችንን መቀጠሉ አዋጭ ነው። መቼም ሚሊዮኖች የተጠቁበት፤ አእላፍ ያለቁበትን በሽታ በዓይናችን እያየን መዳፈሩ አዋጭ አይደለም።
https://www.bbc.com/amharic/news-54003869
amh
health
በኮቪድ ወረርሽኝን ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የተሻለ ቆጥበዋል
ዓለም አቀፉን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተከትሎ በዩናይትድ ኪንገደም ከስድስት ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ወጪያቸውን በመቀነስ የተሻለ ገንዘብ ቆጥበው መገኘታቸውን እንድ ጥናት አመላከተ። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝነት ተከትሎ በርካቶች ሥራ አጥ አልያም በእዳ ተዘፍቀው ቁጠባቸውን ያጡ እንዳሉት ሁሉ፤ በወረርሽኙ ምክንያት ወጪያቸውን ቀንሰው ቁጠባቸውን የጨመሩ ሰዎች አሉ ብሏል ኤልሲፒ የተባለው የፋይናንስ አማካሪ ድርጅት የሰራው ጥናት። እንደ ጥናቱ ከሆነ፤ በወረርሽኙ ወቅት የትራንስፖርት ወጪ መቀነስ፣ ለመዝናናት የሚደረግ ጉዞ መገደቡ እና ለምግብ ይወጣው የነበረው ወጪ መቀነሱ ከስድስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ሰዎች ቁጠባቸው እንዲጨምር ካደረጉ ምክንያቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። ሰዎች ወረርሽኙን ተከትሎ የተዋወቀው ከቤት ሆኖ መስራት እንዲቀጥል የሚደረግ ከሆነ የመሰል ሰዎች የቁጠባ መጠን ሊጨምር እንደሚችል ጥናቱ አመላክቷል። የቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ ፍጆት እና ልጆች በቤት በመቆየታቸው ተያይዘው የሚመጡ ወጪዎች የቁጠባ መጠን እንዲቀንስ ካደረጉ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል። በአጠቃላይ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ዝቀተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች ክፉኛ ተጎድተዋል። በዩናይትድ ኪንገደም ብቻ 9 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ስርጭት ምክንያት ገቢያቸው በመቀነሱ ቋሚ ወጪያቸውን ለመሸፈን ብድር መውሰዳቸውን የአገሪቱ ብሔራዊ ስታስቲክስ ድርጅት ይፋ አድርጓል። ኤልሲፒ የተባለው የፋይናንስ አማካሪ ድርጅት የሰራው ጥናት እንዳሳየው ከወረርሽኙ መከስት ወዲህ የተሻለ ቆጥበው የተገኙት እድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ናቸው። ጥናቱ እንዳመላከተው ከሥራ ገበታቸው ያልፈተናቀሉት እድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ የሆኑት ሰዎች የትራንስፖርት እና ለሽርሽር የሚያወጡት ወጪ በከፍተኛ መጠን ቀንሷል። ሪፖርቱ ጭማሪ የታየበት ቁጠባ ብድር ለመሸፈን እና በጥሩታ ወቅት ወጪን ለመሸፈን ሊውል ይችላል ብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56229284
amh
health
ዕድሜያቸው 40 የሞላ እና ጥቁር ወንዶች ሊያውቁት የሚገባ የካንሰር ዓይነት
ለበርካቶች ፕሮስቴት ሲባል ሁለቱ የወንድ ልጅ የዘር ፍሬዎች አካባቢ ወይም የዘር ፍሬ ከረጢቱ ውስጥ ያለ አካል እንደሆነ ነው የሚያስቡት። የኩላሊት፣ የፕሮስቴት፣ የሽንት ፊኛ እና ቧንቧ ቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ፍፁም ሠለሞን ግን ፕሮስቴት ከሽንት ፊኛ በታች ያለ አካል ነው ይላሉ። እንደ ዶ/ሩ ገለጻ ከሆነ ፕሮስቴት በወንድ ልጅ ብልት እና ፊኛ መካከል የሚገኝ እጢ ነው። ፕሮስቴት የዘር ፈሳሽ የማመንጨት ጥቅም አለው። የወንድ ልጅ የዘር ፈሳሽ ወደ ውጪ ሲፈስ ሰባ በመቶ ያህሉን የሚያመነጨው ፕሮስቴት መሆኑን ዶ/ር ፍፁም ያብራራሉ። የወንድ ልጅ የዘር ፈሳሽ ሀዋስ የሚዋኘው እንዲሁም ምግቡን የሚያገኘው ከዚህ ፈሳሽ መሆኑን አክለው ይጠቅሳሉ። ታድያ የፕሮስቴት ችግር ያለበት ወንድ የዘር ፈሳሹ ወደ ውጪ መፍሰሱን ትቶ የሚመለሰው ወደ ፊኛው ነው። ስለዚህ ይላሉ ዶ/ር ፍፁም ፕሮስቴት፣ የዘር ፈሳሹ ወደ ፊኛ እንዳይመለስ እና ወደ ውጪ እንዲወጣ ይረዳል። ፕሮስቴት ልክ እንደ ምራቅ አመንጪ እና ታይሮይድ እጢዎች ሁሉ እጢ (ግላንድ) ነው። የፕሮስቴት እጢ የሚገኘው ወንድ ላይ ብቻ ነው። እንደ ዶ/ር ፍፁም ገለጻ በየትኛውም የሰውነታችን ክልፍ ላይ ካንሰር ሊከሰት ይችላል፣ ስለዚህም ፕሮስቴትም ለካንሰር  ይጋለጣል። በዓለም ላይ ከስምንት ወንዶች መካከል አንዱ በሕይወት ዘመኑ በፕሮስቴት ካንሰር ይያዛል። ፕሮስቴት አጥቢ እንስሳት ላይ በሙሉ የሚገኝ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስም ካንሰሩ ከሰው ውጪ የታየው ውሾች ላይ ብቻ ነው። 80 በመቶ ያህሉ ፕሮስቴት ካንሰር ቀስ ብሎ የሚያድግ እንዲሁም ህመም ሳያስከትል ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ነው። በብዛት የፕሮስቴት ካንሰር በመጀመሪያ ከፕሮስቴት እጢ ላይ ተወስኖ ይቆይና ከባድ ጉዳት በማያስከትል መልኩ ቀስ እያለ የሚያድግ ችግር ነው። ለፕሮስቴት ካንሰር አጋላጭ ከሆኑ ምክንያቶች መካከል አንዱ እድሜ ነው። እድሜያቸው ከ50 በላይ የሆኑ፣ ጥቁር ወንዶች እንዲሁም በቤተሰባቸው ውስጥ የፕሮስቴት ካንሰር የተያዘ ሰው የሚገኝ ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ። የዩናይትድ ኪንግደም ተመራማሪዎችም እድሜያቸው 40 የሞላቸው ወንዶች በየዓመቱ ቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመክራሉ። ዶ/ር ፍፁም በበኩላቸው ፕሮስቴት ካንሰር ከ40 ዓመት በታች በሆኑ ሰዎች ላይ የመገኘት እድሉ እጅጉን በጣም አነስተኛ መሆኑን ይናገራሉ። እድሜያቸው ከ20 እስከ 30 የሆነ ወንዶች በፕሮስቴት የመያዝ እድላቸው አንድ በመቶ ብቻ ነው። ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው የፕሮስቴት ካንሰር የሚከሰተው እድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ በሆናቸው ወንዶች ላይ ነው ይላሉ ዶ/ር ፍፁም። አፍሪካውያን ከነጮች አንጻር ሲታይ በዚህ ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ተመሳሳይ የቤተሰብ ታሪክ ያላቸው ግለሰቦች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። ወንድም፣ አባት፣ አያት እንዲሁም አጎቱ በፕሮስቴት ካንሰር የተያዘበት ግለሰብ የተጋላጭነት ዕድሉ ሰፊ ነው። ከቅርብ ቤተሰብ መካከልም አባቱ በዚህ ካንሰር የተያዘ እና አያቱ የተያዘ ወንድ እኩል የተጋላጭነት ልክ እንደሌላቸው ዶ/ር ፍፁም ያብራራሉ። አባቱ ወይንም ወንድሙ በፕሮስቴት ካንሰር የተያዘ ወንድ፣ ከአጠቃላይ ሕዝቡ ከሁለት እና ሦስት እጥፍ በላይ ተጋላጭ ነው። ሌላኛው መታየት ያለበት በቤተሰብ ውስጥ ካንሰር የተያዘው ሰው በስንተኛው ዕድሜው ላይ ተገኘበት የሚለው ወሳኝ ነጥብ መሆኑን ዶ/ር ፍፁም ያብራራሉ። ይህንንም ሲያብራሩ ከ65 ዓመት በታች የፕሮስቴት ካንሰር የተገኘበት አባት፣ ልጁ ለካንሰሩ የመጋለጥ ዕድሉ ከፍተኛ ይሆናል ሲሉ ያስረዳሉ። ይህም ማለት ልጁ እስከ 5 እጥፍ ድረስ የተጋለጠ ነው። ሌላኛው ደግሞ ይላሉ ዶ/ር ፍፁም፣ አባቱ እና አያቱ በፕሮስቴት የተጠቁ እና አባቱ ብቻ የተያዘ ልጅን ብናወዳድር፣ ይህ ሁለቱም የቤተሰብ አባላት የተያዙበት ግለሰብ የበለጠ ተጋላጭ ነው ይላሉ። የዘረመል እክል (ጄኔቲክ ሚውቴሽን) ላይ እክል ካለ የበለጠ ለዚህ ካንሰር ያጋልጣል። ካንሰር በአብዛኛው ሲታይ ህዋሱ በተነሳበት አካል ወይንም ስፍራ ከመጠን በላይ ይራባል። ከዚያም በመቀጠል ባለበት አካል ላይ ብቻ ተገድቦ ሳይቀመጥ ወደ ሌላ የአካል ክፍል ይሰራጫል። ፕሮስቴት ካንሰር ተገቢውን ሕክምና በተገቢው ሰዓት ካላገኘ የሽንት ፊኛን ሊያፍን ያችላል። የፕሮስቴት እጢ ከተራባ በኋላ ፕሮስቴት አጠገብ ያሉ የሽንት ቧንቧ እና ፊኛ ላይ ይዛመታል። ከዚያም አልፎ በደም ስር ተሰራጭቶ ወደ ጀርባ ይሄዳል። ፕሮስቴት ካንሰር ብዙ ጊዜ በደም ስር አድርጎ ወደ ጀርባ፣ አከርካሪ አጥንት እና ሆድ ውስጥ ወዳሉ ንፍፊቶች ይሰራጫል። የፕሮስቴት ካንሰርን ለመከላከል አመጋገብን ማስተካከል ዋነኛው መፍትሄ ነው። አትክልት እና ፍራፍሬ የበዛበት፣ ዓሳ፣ የዓሳ ዘይት፣ ኦሊቭ ኦይል ያለው ምግብ መመገብ ለመከላከል ይረዳል። ከእነዚህ በተጨማሪ አረንጓዴ ሻይ እነዲሁም ቫይታሚን ዲ መጠቀም የመከላከል አቅምን ያጎለብታል። የፕሮስቴት ካንሰር አብዛኛውን ጊዜ ቀስ ብሎ የሚያድግ በመሆኑ፣ ከጀመረበት አንስቶ ለመሰራጨት እና ሕይወትን አደጋ ላይ ለመጣል ረዥም ጊዜ ይወስድበታል። ስለዚህም ቢያንስ በዓመት ወይንም በሁለት ዓመት አንዴ ቅድመ ምርመራ ማድረግ ጠቃሚ ነው። በተለይ ለካንሰሩ የመጋለጥ ዕድላቸው የሰፋ የቤተሰብ ታሪክ ያላቸው፤ ቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራሉ። ቅድመ ምርመራ ለመጀመር የተለያዩ አገራት፣ የተለያዩ መመርያዎች እንዳላቸው የሚናገሩት ዶ/ር ፍፁም፣ አንድ ሰው እድሜው ከ50 አስከ 55 ዓመት ሲሆን ቅድመ ምርመራ እንዲያደርግ ይመከራል። ተመሳሳይ የቤተሰብ ታሪክ ያለው ግለሰብ ደግሞ እድሜው ከ40 አስከ 45 ላይ እያለ ምርመራውን ቢጀመር መልካም መሆኑን ገልፀዋል። “ቢያንስ ቢያንስ በየሁለት ዓመቱ ቅድመ ምርመራ ማድረግ ይመከራል” ሲሉ ያክላሉ። ከሁሉ በፊት በቤተሰብ ውስጥ ያለን የፕሮስቴት ካንሰር ታሪክን ማወቅ እንዲሁም ወደ አርባዎቹ የእድሜ ክልል ሲገባም በተወሰ ጊዜው ውስጥ ምርመራ ማድረግ ችግሩ ካለ ስር ሳይሰድ ለማከም ይረዳል። ምርመራው ተደርጎ የፕሮስቴት ካንሰር መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ የተለያዩ ዓይነት ሕክምናዎች እንዳሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ከእነዚህም ውስጥ በቀዶ ሕክምና ካንሰሩን ማውጣት፣ የጨረር ሕክምና ወይንም ደግሞ የወንድ ልጅ ቴስቴስትሮን ካንሰሩን በዋነኛነት ስለሚመግብ በሰውነት ውስጥ ያለውን የቴስቴስትሮን መጠንን ለመቀነስ ሕክምና ይሰጣል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cndxlne6nk9o
amh
health
የኮቪድ ወረርሽኝ ትልቅ አደጋ ነው - ኪም ጆንግ ኡን
በሰሜን ኮሪያ በፍጥነት እየተዛመተ ያለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለሀገሪቱ "ትልቅ አደጋ" ነው ሲሉ መሪዋ ኪም ጆንግ ኡን መናገራቸውን የመንግሥት ሚዲያዎች ዘግበዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮናቫይረስ ሞት መመዝገቡን ያስታወቀችው ሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም በያዝነው ሳምንት ቅዳሜ ዕለት ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሁለንተናዊ ትግል እንዲደረግ ጠይቀዋል። ባለስልጣናቱ በያዝነው ሳምንት ሃሙስ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው መረጋገጡን አስታውቀዋል። ባለሙያዎች በበኩላቸው አሁን ተያዙ የተባሉት የመጀመሪያ እንዳልሆኑና ለተወሰነ ጊዜ እየተዛመተ ነበር ይላሉ። በሰሜን ኮሪያ ወረርሽኙ ከፍኛ ሊሆን እንደሚችልና አስከፊ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋትም ጭሯል። 25 ሚሊዮን ነዋሪዎቿ በክትባት መርሃ ግብር እጥረት እና በደካማ የጤና አጠባበቅ ስርአት ምክንያት ለአደጋ የተጋለጡ መሆናቸውም ተገልጿል። ባለፉት ሳምንታት ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በማይታወቅ ትኩሳት እንደተጠቁ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ቅዳሜ እለት ዘግበዋል። የሃገሪቱ የመመርመር አቅምም የተገደበ በመሆኑ በኮቪድ-19 ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም። ይህ አኃዝ አርብ እና ሐሙስ ከፍተኛ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ይህም ሁኔታ በሰሜን ኮሪያ እየተከሰተ ስላለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አንዳንድ ፍንጮችን ይሰጣል ተብሏል። "የከፋው ወረርሽኝ በአገራችን ላይ የወደቀ ትልቅ አደጋ ነው" በማለት መሪው መናገራቸውን የኬ ሲ ኤንኤ የዜና ወኪል ዘግቧል። ኪም ለዚህ ችግር መንስኤ ያሉትን የቢሮክራሲ ቀውስ እና የህክምና ብቃት ማነስ እንደሆነ ጠቁመው እንደ ጎረቤት ቻይና ካሉ ሀገራት ምላሽ መማር እንደሚቻልም ጠቁመዋል። ከሚያዝያ ወር ጀምሮ 27 ሰዎች ትኩሳት ካጋጠማቸው በኋላ መሞታቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል። በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ በኦሚክሮን ልውጥ ከሞተው አንድ ሰው በስተቀር እነዚህ ግለሰቦች ኮቪድ- 19 ተይዘው ነበር ወይ ስለሚለው ጉዳይ ሪፖርቶቹ ያሉት ነገር የለም።
https://www.bbc.com/amharic/news-61454622
amh
health
‘የዓለም ምርጧ የጽዳት ባለሙያ’ ለምንድን ነው በነጻ አገልግሎት የምትሰጠው?
አውሪ ካታሪና እጅግ የቆሸሸ ቤት ስታጸዳ የተቀረጸው ቪዲዮ በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት ተሰራጭቷል። አሁን በመላው ዓለም ቤቶችን በነጻ እያጸዳች ነው። በዓለም ምርጧ የጽዳት ባለሙያ ነኝ የምትለው አውሪ “በጣም የቆሸሸ ነገር የሥራዬን ውጤትነት ለማየት ስለሚረዳኝ እመርጠዋለሁ” ትላለች። ለምን እና ለማን ነው የጽዳት አገለግሎቷን በነጻ የምትሰጠው?
https://www.bbc.com/amharic/articles/cjq7xddndv1o
amh
health
ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች ሥራውን ማቋረጡን አስታወቀ
የፈረንሳዩ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ኤምኤስኤፍ ሠራተኞቹ ትግራይ ውስጥ ከተገደሉ በኋላ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የሚያከናውነውን ሥራ ማቋረጡን ገለጸ። ሰኔ 17/2013 ዓ.ም ትግራይ ክልል ውስጥ ለሥራ እየተጓዙ ሳለ ማንነታቸው ባልታወቁ ጥቃት ፈጻሚዎች የተገደሉት የእርዳታ ድርጅቱ ሠራተኞች ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንዷ ደግሞ የስፔን ዜግነት ያላት ናት። ድርጅቱ እንዳለው በሠራተኞቹ ላይ በተፈጸመው ጭካኔ የተሞላበት ግድያ ዙሪያ አስቸኳይ ምርመራ እንዲደረግና በክልሉ ውስጥ የእርዳታ ሠራተኞች ደኅንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ እንዲፈቀድ ጠይቋል። በሠራተኞቹ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም ኤምኤስኤፍ በትግራይ ክልል ማዕከላዊና ምሥራቃዊ ክፍል በሚገኙት አቢ አዲ፣ አዲግራትና አክሱም ውስጥ የሚያከናውነውን ሥራ ማቋረጡን አስታውቋል። ነገር ግን ከእነዚህ አካባቢዎች ውጪ ባሉ ሌሎች አካባቢዎች አባላቱ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ነዋሪዎች ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ሥራቸውን ማከናወን እንደሚቀጥሉ ገልጿል። "በባልደረቦቻችን ላይ ግድያው ከተፈጸመ ሁለት ሳምንት ሊሆነው ቢቃረብም ማንም ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን የሌለ ሲሆን በተጨማሪም በግድያው ዙሪያ ስላለው ሁኔታ ምንም ግልጽ ያለ ነገር የለም" ሲሉ የድርጅቱ ኃላፊ ቴሬሳ ሳንክሪስቶቫል ተናግረዋል። ጨምረውም በባልደረቦቻቸው ላይ በተፈጸመው ግድያ ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ ምርመራ አድርገው ምን እንደተከሰተና ተጠያቂው ማን እንደሆነ ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። በዚህም ሳቢያ "በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ በጣም ከባድ ነገር ግን አስፈላጊ የሆነውን በበርካታ የትግራይ አካባቢዎች የምናካሂዳቸውን ሥራዎቻችንን ለማቋረጥ ወስነናል" ብለዋል። የእርዳታ ሠራተኞቹ ሰኔ ወር አጋማሽ ላይ በትግራይ ክልል ውስጥ በጉዞ ላይ እንዳሉ የነበራቸው ግንኙነት መቋረጡንና በተከታዩ ቀን የሁለቱ ኢትዮጵያውያንና የስፔናዊቷ አስከሬን ይጓዙበት ከነበረው መኪና ጥቂት ሜትሮች ራቅ ብሎ መገኘቱንም የድንበር የለሽ ሐኪሞች በወቅቱ ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቶ ነበር። በጥቃቱ የተገደሉት የህክምና እርዳታ ድርጅቱ ባልደረቦች በየካቲት ወር ላይ በድርጅቱ በረዳት አስተባባሪነት ሥራ የጀመረው የ31 ዓመቱ ዮሐንስ ሃለፎም፣ በግንቦት ወር ለግብረ ሰናይ ድርጅቱን መሥራት የጀመረው የ31 ዓመቱ ሹፌር ቴድሮስ ገብረ ማሪያም እና ለዓመታት በድንገተኛ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪነት የሠራችው የ34 ዓመቷ ስፔናዊት ማሪያ ኽርናንዴዝ ናቸው። አስካሁን ድረስ ለሦስቱ የድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን ሠራተኞች ግድያ ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን የሌለ ሲሆን ስለግድያው የወጣ ምንም አይነት ተጨመሪ መረጃ የለም። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግድያውን ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ የተሰማውን ሐዘን ገልጾ፤ ጥቃቱ የተፈጸመው አቢ አዲ ተብሎ በሚጠራ "ህወሓት በሚንቀሳቀስበት አካባቢ" መሆኑን አመልክቷል። ጨምሮም እንዲህ አይነቱን "ኃላፊነት በማይሰማው ቡድን የሚፈጸምን ጥቃት ለማስቀረት የእርዳታ ድርጅቶች በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ወታደራዊ እጀባ እንዲደረግላቸው መንግሥት ያቀረበው ጥሪ ትክክል መሆኑን ያመለክታል" ብሏል። ከመንግሥት ሠራዊት ጋር ለስምንት ወራት በጦርነት ውስጥ የቆየው የህወሓት ኃይልም በበኩሉ በእርዳታ ሠራተኞቹ ላይ የተፈጸመውን ግድያ አውግዞ ድርጊቱ በመንግሥት ወታደሮች የተፈጸመ ነው ሲል ገልጾ ነበር። ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) በትግራይ ክልል ውስጥ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት በመደገፍና በማቋቋም እንዲሁም የህክምና ድጋፍ ለሚሹ ሰዎች እርዳታን እያደረገ ያለ ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው። ድርጅቱ በባልደረቦቹ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም አገልግሎቱን አሁን ለማቋረጥ በወሰነባቸው አካባቢዎች ውስጥ ለሚገኙ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች የተለያየ አይነት የጤና አገልግሎቶች ሲያርብ መቆየቱን ገልጿል። የአገልግሎቱ መቋረጥም በርካታ ሰዎች ከረድኤት ድርጅቱ ሲያገኙት የነበረውን የሰብአዊና የጤና ድጋፎችን እንዲያጡ ያደርጋቸዋል ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57714392
amh
health
ኮሮናቫይረስ ፡ ሲሼልስ የኮቪድ -19 ክትባት መስጠት ጀመረች
በርካቶች ለመዝናናት የሚመርጧት አፍሪካዊቷ ደሴታማ አገር፣ ሲሼልስ የኮሮናቫይረስ ክትባት መስጠት መጀመሯን አስታወቀች። ይህንን በማድረግም ከጊኒ ቀጥላ ሁለተኛዋ አፍሪካዊት አገር ሆናለች። ጊኒ የሩሲያውን ስፑትኒክ ቪ ክትባት አነስተኛ ዶዝ ያገኘችው ባለፈው ወር ነበር። የሲሼልስ ፕሬዚደንት ዋቨል ራምካላዋን ዕሁድ እለት የመጀመሪያውን ክትባት በቀጥታ ቴሌቪዥን ሥርጭት እየታዩ ተከትበዋል። ፕሬዚደንቱ "የተሰማኝ ልክ እንደማንኛውም ክትባት ነው" በማለት ሌሎች ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ አበረታተዋል። ደሴታማዋ አገር ሲሼልስ ቻይና ያበለፀገችውን ክትባት ከተባበሩት አርብ ኤምሬትስ 50 ሺህ ዶዝ [መጠን] በእርዳታ አግኝታለች። ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ዛሬ የጤና ባለሙያዎች መከተብ እንደሚጀምሩ እና ከዚያ በኋላ ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ክትባቱን እንደሚወስዱ ተናግረዋል። ይህ ሲጠናቀቅም ክትባቱ ለሌሎች ሕዝቦቿ ይዳረሳል ተብሏል። አገሪቷ ከሁለት ወር እስከ ሦስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ካሏት 98 ሺህ ሕዝብ 70 በመቶውን ለመከተብ አቅዳለች። ይህንን ለማሳካትም በአንድ ቀን 1 ሺህ ሰዎችን መከተብ ይጠይቃል። ሲሼልስ እስካሁን 508 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የመዘገበች ሲሆን ያስተናገደችው አንድ ሞት ብቻ ነው። ይሁን እንጂ ባለሥልጣናት በቅርቡ የታየው የቫይረሱ ሥርጭት አስግቷቸዋል። ቅዳሜ ዕለት ብቻ በአገሪቷ 57 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55614499
amh
health
በአፍሪካ ኮቪድ-19ን እንዴት መቆጣጠር ተቻለ?
አፍሪካ ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአማካይ እየቀነሰ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች የቫይረሱ ስርጭት የቀነሰባቸው ምክንያቶች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። ባለሙያዎቹ በምክንያትነት ከጠቀሷቸው መካከል የአህጉሪቷ ነዋሪዎች ወጣት መሆናቸው፣ ሞቃታማ የአየር ንብረት፣ ከዚህ ቀደም የዳበረ በሽታ የመከላከል አቅም መኖሩ እና በከተማ ቀመስ አካባቢዎች ጥቂት ሕዝብ መኖሩ ይጠቅሳሉ። የዓለም ጤና ድርጅት ተገቢው ጥንቃቄ ካልተደረገ እስከ 190,000 ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ ብሎ መላ ምት ቢያስቀምጥም በርካታ የአፍሪካ አገሮች የወረርሽኙን ስርጭት መቆጣጠር ችለዋል። አህጉሪቱ እንዴት በሽታውን መቆጣጠር እንደተቻለ በተደረገው የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች ውይይት ላይ እንደተገለጸው ወረርሽኙ በሌሎች የዓለም ክፍሎች ካሳየው የተለየ ባህሪ በአፍሪካ ታይቷል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍረካ ኃላፊ ዶ/ር ማቲሺዲሶ ሞይቲን ጨምሮ ሌሎችም ባለሙያዎች በተገኙበት ውይይት እንደተጠቀሰው ከሆነ፤ የወረርሽኙ ስርጭት ሲጀመር እንቅስቃሴ ላይ ገደብ መጣሉ ውጤት አሳይቷል። ከሌሎች አህጉሮች አንጻር አፍሪካ ውስጥ ገደብ የተጣለው ቀድሞ ነበር። ይህም በርካታ አገሮች ላይ የምጣኔ ሀብት ጫና ማሳደሩ አልቀረም። በአፍሪካ አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት ወጣቶች ናቸው። ኮሮናቫይረስ በግንባር ቀደምነት የሚያጠቃው ደግሞ አረጋውያንን ነው። የአውሮፓ አገራትን በማነጻጸሪያነት ብንወስድ፤ ሰዎች እድሜያቸው ሲገፋ አረጋውያን ማቆያ ውስጥ ይገባሉ። በአፍሪካ ግን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይኖራሉ። ይህ አኗኗር የበሽታውን ስርጭት ከቀነሱ ምክንያቶች አንዱ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎቹ ተናግረዋል። ሌላው ምክንያት በርካታ ሰዎች በከተማ ስለሚኖሩ በሽታው ወደ ገጠር እንዳይሰራጭ መገታቱ ነው። የመሠረተ ልማት ዝርጋታው ውስን በመሆኑም ሰዎች ከቦታ ቦታ እንዳልተዘዋወሩ ተጠቅሷል። ዶ/ር ማቲሺዲሶ እንዳሉት፤ ከዚህ ቀደም እንደ ኢቦላ ያሉ ወረርሽኞችን ለማስወገድ የተደረገው እንቅስቃሴ ኮቪድ-19ን በመከላከል ረገድ ጠቃሚ ሆኗል። ሆኖም ግን ወረርሽኙ በአህጉሪቱ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ለመፈተሽ ጥናት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። በአፍሪካ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 34,000 ሞተዋል። አንድ ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54294584
amh
health
ኮሮናቫይረስ ፡ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ100 በላይ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተነገረ
በሲዳማ ክልል በሚገኘው የሐዋሳ ኢንዱስትሪ መንደር ውስጥ ከ100 በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የክልሉ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶ/ር ማቴ መንገሻ ለቢቢሲ ገለፁ። ክልሉ ባለፉት 12 ቀናት በኢንዱስትሪ መንደሩ ባደረገው ምርመራ የኢንዱስትሪ መንደሩ ሠራተኞች በኮሮናቫይረስ መያዛችን ያረጋገጠ ሲሆን፤ ቫይረሱ በተለይ በሁለት ማዕከላት (ሼዶች) ውስጥ ተስፋፍቶ እንደሚገኝ ዶ/ር ማቴ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በኢንደስትሪ ፓርኩ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱን ያረጋገጡት አንድ ሠራተኛ ከ12 ቀን በፊት ታሞ በፓርኩ በሚገኝ ክሊኒክ ለሕክምና በመሄዱና ምልክቶቹ የኮሮናቫይረስ መሆናቸው በመረጋገጡ ጥቆማ ደርሷቸው መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ ግለሰብ እንዲሁም ከባሕር ማዶ የመጡ የድርጅቱ ሠራተኛ ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች ሲመረመሩ ከ100 በላይ ሰዎች ተይዘው መገኘታቸውን ለቢቢሲ አስረድተዋል። እንደ ዶ/ር ማቴ ከሆነ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ንክኪ አላቸው ተብሎ ከሚታመኑ ሰዎች በአጠቃላይ ናሙና እየተወሰደ ነው። ከፍተኛ ንክኪ አለው ተብሎ የተገመተው አንድ ሼድ ሲሆን ስምንት መቶ ያህል ሠራተኞች እንዳሉት ገልፀው፤ ሁሉንም ሠራተኞች ለመመርመር ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል። "በአባታችን ቀብር ላይ ሆነን የእናታችንን ሞት ሰማን" በድሬዳዋ ከሃያ በላይ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በኮቪድ-19 ተያዙ ቻይና ዜጎቿን ለኮሮናቫይረስ የባሕል መድኃኒት እንዲወስዱ ለምን ታበረታታለች? ዶ/ር ማቴ አክለውም ከሁለተኛው ሼድ ግን ሙሉ በሙሉ አለመወሰዱን ተናግረዋል። በቫይረሱ ከተያዙት ሠራተኞች መካከል የውጭ አገር ዜጎች፣ የሰው ኃይል አስተዳደር ላይ የሚሰሩ ሠራተኞችና፣ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ግንኙነት የነበራቸው ኦፕሬተሮች መሆናቸውን ጨምረው ገልፀዋል። እነዚህ በቫይረሱ ተይዘው የሚገኙት ሰዎች የኢንዱስትሪ ማዕከሉ ውስጥ ባሉ በሁለት ሼዶች ውስጥ ሚሰሩ እንደሆኑ ተናግረዋል። "በኢንደስትሪ ፓርኩ ያለውን ስርጭት ተቆጣጥረናል ማለት ይቸግረና" ያሉት ዶ/ር ማቴ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውንና ንክኪ ያላቸውን ለመለየት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። የክልሉ ኮሮናቫይረስ መከላከል ባለሙያዎች በኢንዱስትሪ ፓርኩ ያለውን ንክኪ ለመለየት፣ ግንዛቤ ለማስጨበጥና ትምህርት መስጠት ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህ በተሻለ ግን የቫይረሱን ስርጭት ባለበት ለማቆም ከኢንደስትሪ ፓርኩ ጋር በመነጋገር ቫይረረሱ በስፋት የታየበት ሼድ ለተወሰነ ገዜ ሥራ እንዲያቆምና ሠራተኞች ራሳቸውን ለይተው እንዲቀመጡ ለማድረግ ቢታሰብም ውጤታማ አለመሆናቸውን ተናግረዋል። ዶ/ር ማቴ አክለውም እስከ ዛሬ ድረስ በሲዳማ ክልል 13 የሕክምና ባለሙያዎች እና ሁለት ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተናግረዋል። በኮቪድ-19 ከተያዙት የሕክምና ባለሙያዎች መካከል ወደተለያየ ስፍራ ሄደው ራሳቸውን ለቫይረሱ ያጋለጡ፣ በሚሰሩባቸው ተቋማት አካባቢ ባለ የጥንቃቄ ጉድለት እንዲሁም የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት በመኖሩ የተነሳ የተጋለጡ እንደሚገኙበት አብራርተዋል። የሲዳማ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተሩ በክልሉ እስካሁን ድረስ 452 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ገልፀው፤ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘም አምስት ሰዎች መሞታቸውን ገልፀዋል። የሐዋሳ የሚገኘው ኢንዱስትሪያል ፓርክ በአገሪቱ ካሉ መሰል ተቋማት መካከል ከትልልቆቹ ጋር የሚመደብ ሲሆን በውስጡ የተለያዩ ምርቶችን የሚያመርቱ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተቋማት ይገኙበታል። ፓርኩ በአሁኑ ጊዜ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች ያሉበት ሲሆን ከጥቂት ዓማት በፊት ተከፍቶ ሥራውን በጀመረበት ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ በውስጥ ያሉት ሁሉም ፋብሪካዎች ሥራ ሲጀምሩ ከ60 ሺህ በላይ ሠራተኞችን ይቀጥራል ተብሎ እምነት ተጥሎበት ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/news-53719605
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ የውጭ አገር ተጓዦች የኮቪድ-19 ምርመራ ለማድረግ ፈተና ሆኖባቸዋል
አገራት ድንበሮቻቸውን በጥንቃቄ እየከፈቱ ባሉበት በአሁኑ ወቅት የአየር በረራ መጀመርን ተከትሎ በወጡ አዳዲስ ደንቦች ምክንያት ተጓዦች ከኮቪድ-19 ተህዋሲ ነጻ መሆናቸውን በምርመራ እንዲያረጋግጡ ይገደዳሉ። በኢትዮጵያ ይህንን ምርመራ በማድረግ ውጤት ከሚሰጡ ተቋማት መካከል የሆነውና አብዛኞቹ የውጭ አገር ተጓዦችን የሚያስተናግደው ተቋም የምርመራ ፈላጊዎች ቁጥርና አገልግሎቱ ተመጣጣኝ እንዳልሆነ ተገልጋዮች እየተናገሩ ነው። የአየር በረራ አገልግሎት ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ በመቆየቱ ለወራት ሲጠባበቁ የነበሩ ተጓዦች ይህንን ምርመራ ለማድረግ ከባድ ፈተና ሆኖብናል ይላሉ። ምክንያቱ ደግሞ ምርመራውን የሚያከናውነው ተቋም የወሰደውን ናሙና ውጤት ለማሳወቅ ቢያንስ 48 ሰዓታትን ይፈልጋል። አገራት ደግሞ ተጓዦች ከመሳፈራቸው በፊት ምርመራ እንዲያደርጉ የሚፈልጉበት የሰዓት ገደብ ከ48 ሰዓት እስከ 96 ሰዓት እንደየአገሩ ይለያያል። ምርመራውን ከብዙ ጥበቃ በኋላ ባለፈው አርብ ዕለት ማድረግ የቻሉ ተጓዦች ውጤት አልደረሰም በመባላቸው በረራቸውን ለመሰረዝ እንደተገደዱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ክሊኒኩ ለተመርማሪዎች ውጤት የሚሰጠው የጉዞው ዕለት ወይም ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ በ10 ሰዓት ብቻ ነው። በዚህም ምክንያት የጉዞ ቀን፣ የሚጓዙበት አገር የምርመራ ደንብና የክሊኒኩ ውጤት መስጫ ዕለት ለማጣጣም ፈታኝ እንደሆነ ተጓዦቹ ጠቅሰዋል። ቢቢሲ ሰኞ ማለዳ ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ምርመራ በሚሰጠው ተቋም ደጃፍ ላይ ተሰልፈው ያገኛቸው ተጓዦች ተቋሙ ስለምርመራው በቂ መረጃ እንዳልሰጣቸው፣ በረራቸውን በተደጋጋሚ ለመሰረዝ እንደተገደዱና ላልተጠበቀ ወጪና መጉላላት እንደተዳረጉ ገልጸዋል። አገልግሎቱን ፈልገው ወደተቋሙ የሄዱ ሰዎች ለቢቢሲ እንደገለጹት ምርመራውን የሚያደርገው ላቦራቶሪ ሥራውን የሚያስኬድበት ግልጽ አሰራር እንዳልዘረጋም ተናግረዋል። አገልግሎት ፈላጊዎች የሚስተናገዱት በቅድሚያ በኢሜይልና በስልክ ከተመዘገቡና የጉዞ ትኬታትና የፓስፖርታቸውን ቅጂ ከሰጡ በኋላ ነው የሚል ማስታወቂያ በክሊኒኩ ደጃፍ ላይ የተለጠፈ ቢሆንም፤ በክሊኒኩ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ የተጠቀሱት የስልክ መስመሮች ከአገልግሎት ወጪ ናቸው አልያም ተዘግተዋል። የኢሜይል ምላሽም ከክሊኒኩ ማግኘት አልተቻለም። የቢቢሲ ዘጋቢዎችም ይህንኑ ማረጋገጥ ችለዋል። የክሊኒኩ ሠራተኞች በበኩላቸው ሰዎች ከተመዘገቡ በኋላ በራሳቸው ምክንያት ሊቀሩ ስለሚችሉ ይህንን የቅድመ ምዝገባ አሰራር ትተን ሰዎች እንደ አመጣጣቸው ማስተናገድ ጀምረናል ይላሉ። ሰኞ ማለዳ በስፍራው ተሰልፈው ከነበሩ ተጓዦች ቢቢሲ እንደተረዳው አንዳንዶቹ ተገልጋዮች እሑድ ከቀትር ጀምሮ ለረዥም ሰዓት አገልግሎቱን ለማግኘት በዝናብ ተሰልፈው የጠበቁ ቢሆንም "አሁን ደክሞናል ከዚህ በላይ አናስተናግድም" በሚል እንዲበተኑ ተደርገዋል። ሌሎች ደግሞ ነገ በአዲስ መልክ አንሰለፍም በሚል ቅሬታ በማንሳታቸውና የክሊኒኩን በር አናዘጋም በማለታቸው ስም ዝርዝራቸው ተጽፎ በቀጣይ ቀን ቅድሚያ ተሰጥቷቸው እንደሚስተናገዱ ቃል እንደተገባላቸው ተናግረዋል። ክሊኒኩ በዚህ መንገድ ተገልጋዮቹን ካሰናበተ በኋላ የተወሰኑ ሰዎችን "አሾልኮ እንዳስገባና አገልግሎት እንደሰጣቸው" በቦታው ነበርኩ ያሉ እማኝ ተናግረዋል። በአካባቢው የሚገኙ የመኪና አስተናባሪዎችና የጎዳና ተዳዳሪዎች የችግሩን ስፋት በመረዳት በጠዋት ወረፋ በመያዝ ሰልፋቸውን እስከ 200 ብር እየሸጡ እንደሚገኙ ተገልጋዮች ይናገራሉ። የምርመራ አገልግሎት ሰጪው ተቋም በርካታ ለምርመራ የሚመጡ ሰዎች በሚስተናገዱበት በአንደኛው ቅርንጫፉ በሁለት ነርሶችና በሁለት ናሙና ሰብሳቢዎች ብቻ አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሆነና የሚሰጠው ምርመራው አገልግሎቱን ከሚፈልገው ሰው ጋር ተመጣጣኝ እንዳልሆነ ቢቢሲ ለመታዘብ ችሏል። የቢቢሲ ዘጋቢ ሰኞ ማለዳ በስፍራው እንደተመለከተ የአገልግሎት ደረሰኝ ወረቀት ማተሚያ ማሽን ብልሽት ገጥሟል በሚልም ክሊኒኩ ለግማሽ ሰዓት ያህል ሥራውን አቁሞ ነበር። ክሊኒኩ ምንሊክ ሆስፒታል አካባቢና ቡልጋሪያ ባሉት ቅርንጫፎቹ የምርመራ አገልግሎት ይሰጣል ቢባልም የሌሎች ቅርንጫፎቹ ተገልጋዮች ከሌሎች ቅርንጫፎች ይልቅ ወደ አንደኛው ክሊኒክ በብዛት ሄደው ምርመራ ለማግኘት እየጣሩ ነው። "ወደ ሌላ ቅርንጫፍ ሄደን እድላችንን እንሞክር ስንላቸውም መልስ አይሰጡንም፣ መረጃ እንኳን ማግኘት ብርቅ ነው" ይላሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ተገልጋይ። ሰኞ በዚህ ቅርንጫፍ ረዣዥም ሰልፎች የነበሩ ሲሆን በምንሊክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው የክሊኒኩ ቅርንጫፍ ግን የተገልጋዩ ቁጥር አነስተኛ ሆኖ ታይቷል። ክሊኒኩ ተመርማሪዎችን አንድ ሺህ ሦስት መቶ ሃያ ብር ለአገልግሎቱ ካስከፈለ በኋላ ውጤቱን የሚሰጠው ከ48 ሰዓታት በኋላ እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ቅርንጫፉ ብቻ ነው። ጠዋት በረራ ያላቸው ሰዎች ውጤት ስለማይደርስላቸው በብዛት ለድጋሚ የትኬት ማስቀየሪያ ወጪ፣ እንዲሁም ለሌላ አዲስ ምርመራ ወጪ እየተዳረጉ መሆናቸውን ቢቢሲ ካናገራቸው ሰዎች ለመረዳት ችሏል። ቢቢሲ ምርመራውን ከሚሰጠው የኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላቦራቶሪስ ምላሽ ለማግኘት በማስታወቂያ ሰሌዳቸው ላይ ባሰፈሩት የስልክ አድራሻ በተደጋጋሚ ቢደውልም ቁጥሩ ስለማይሰራ መልስ ማግኘት አልቻለም።
https://www.bbc.com/amharic/news-53638908
amh
health
ከበርካታ ሕጻናት ሞት በኋላ በ4 የሕንድ ምርት በሆኑ ሽሮፖች ላይ ማስጠንቀቂያ ወጣ
በርካታ ቁጥር ያላቸው ሕጻናት ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ የሕንድ ምርት በሆኑ አራት የሽሮፕ አይነቶች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ። የዓለም ጤና ድርጅት ዓለም አቀፍ ማስጠንቀቂያውን ያወጣው በአፍሪካዊቷ ጋምቢያ የ66 ሕጸናት ሕልፈት ከሽሮፖቹ ጋር ሳይገናኝ አይቀርም ከተባለ በኋላ ነው። ሽሮፖቹ ለከፍተኛ የኩላሊት ጉዳት እና ለ66 የሕጻናት ሞት ምክንያት ሳይሆኑ አይቀርም ብሏል የዓለም ጤና ድርጅት። የዓለም ጤና ድርጅት ወላጆች ለልጆቻቸው ከመስጠት መቆጠብ አለባቸው ያላቸው ሽሮፖች ፕሮመታዚን ኦራል ሶሉሽን (Promethazine Oral Solution)፣ ኮፌክስማሊን ቤቢ ካፍ ሲረፕ (Kofexmalin Baby Cough Syrup)፣ ማኮፍ ቤቢ ካፍ ሲረፕ (Makoff Baby Cough Syrup) እና ማግሪፕ ኤን ኮልድ ሲረፕ (Magrip N Cold Syrup) የሚባሉት ናቸው። እነዚህ የሕጻናት ሽሮፖችን ያመረተው ማይደን ፋርማሱቲካልስ የሚባል የሕንድ ኩባንያ ሲሆን፤ ለሽሮፖቹ የደኅንነት ማስረጃ ማቅረብ አለመቻሉን የዓለም ጤና ድርጅት ጨምሮ አስታውቋል። አምራቹ ኩባንያ በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም። ቢቢሲም ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም። የሕንድ ባለሥልጣናት በበኩላቸው ሽሮፖቹ ለሕጻናቱ ሞት ምክንያት መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲሰጣቸው የዓለም ጤና ድርጅትን መጠየቃቸው ተገልጿል። ሽሮፖቹን መጠቀም በተለይ በሕጻናት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ወይም ሞትን ሊያስከትል እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅት ሽሮፖቹ የጤና ጉዳት እንደሚያስከትሉ ማወቅ የቻለው የጎብኚዎች መዳረሻ በሆነችው በጋምቢያ በተለይ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ከፍተኛ የኩላሊት ጉዳት የሚያጋጥማቸው ሕጻናት ቁጥር መጨምሩን ተከትሎ ነው። ይህን ተከትሎ የአገሪቱ መንግሥት ዜጎች ፓራሲታሞል ሽሮፖችን መጠቀም በማቆም በምትኩ የሚዋጥ ኪኒኒ እንዲጠቀሙ አሳስቧል። የጋምቢያ ጤና ኃላፊዎች ባለፈው ወር ትክክለኛውን ቁጥር ሳይጠቅሱ በርካታ ሕጻናት ሕይወታቸው አልፏል ብለው ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት በሽሮፖቹ ላይ በተደገረ ምርመራ ዳይታይለን ግላይኮል እና ኢታይለን ግላይኮል የተሰኙ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ንጥረ ነገሮች ተገኝተዋል። እነዚህ ንጥረ ነገሮች መርዛማ ሲሆኑ የሆድ ሕመም፣ ትውከት፣ ተቅማጥ፣ ራስ ምታት እና ለሞት የሚዳርግ ከፍተኛ የኩላሊት ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ረቡዕ መስከረም 25/2015 ዓ.ም. በጄኔቭ ንግግር ሲያደርጉ፤ “የእነዚህ ጨቅላ ሕጻናት ሕልፈት ለወላጆቻቸው ልብ የሚሰብር ነው” ብለዋል። የሕንድ ማዕከላዊ የመድኃኒት ጥራት ተቆጣጣሪ ድርጅት ሽሮፖቹ ለጋምቢያ ብቻ መላካቸውን ለዓለም ጤና ድርጅት መግለጹን ኤአፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። ምንም እንኳ እነዚህ አራት የሕጻናት ሽሮፕ አይነቶች የተሰራጩት በጋምቢያ ብቻ ነው ቢባልም መደበኛ ባልሆነ የገበያ ስንሰለት ወደ ተቀሩት ጎረቤት አገራትም ሳይሰራጩ አይቀርም ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪም የዓለም ጤና ድርጅት አምራቹ ሽሮፖቹ ውስጥ የተገኙትን መርዛማ ኬሚካሎች በሌሎች ምርቶቹ ላይ በመጠቀም ሕንድ ውስጥ እና ወደተቀረው ዓለም ልኮ ሊይሆን ይችላል ብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c29eg84k0gko
amh
health
በኮቪድ-19 ማዕከላት የሚሠሩ የጤና ባለሙያዎች የተገባልን ቃል አልተፈጸመም አሉ
በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሥር በሚተዳደሩ እና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በተቋቋሙ የሕክምና መስጫዎች ውስጥ የሰሩ እና የሚሰሩ የሕክምና ባለሙያዎች በተለያየ ጊዜ የተገባላቸው ቃል እንዳልተፈጸመ በመግለጽ ቅሬታቸውን አቀረቡ። ኮሮናቫይረስ ወረርሽን በኢትዮጵያ መገኘቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ መንግሥት በሕክምና ባለሙያዎችን ላይ የሚኖረውን ጫና ከግምት በማስገባት ከባለሙያዎቹ ጎን እንደሚቆም አስታውቆ ነበር። በዚህ መሠረትም የሚንስትሮች ምክር ቤት ግንቦት 14/2012 ዓ. ም ባካሄደው 83ኛ መደበኛ ስብሰባ የኮቪድ-19 ወረርሽንን በመከላከል እና የህክምና አገልግሎት በመስጠት በቀጥታ ለሚሳተፉ የጤና ባለሙያዎች ልዩ አበል እንዲከፈላቸው ውሳኔ ማሳለፉን ባለሙያዎቹ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ምክር ቤቱ እንደሙያቸው እና ሥራቸው ሁኔታ ከ1ሺህ150 ብር ጀምሮ እስከ 300 ብር በየቀኑ እንዲከፈላቸው ነው የወሰነው። በዚህ መሠረትም በፌደራል ደረጃ የሚተዳደሩት እንደ ኤካ ኮተቤ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል እና ሚሊኒየም ሆስፒታል ያሉት የጤና ተቋማት እና አንዳንድ ክልሎች ወሳኔውን መሠረት በማድረግ ለባለሙያዎቻቸው ልዩ አበል እንደከፈሉ ባለሙያዎቹ አስታውቀዋል። ሆኖም በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሥር ከሚተዳደሩ ጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች መከካከል የተወሰኑት የኮሮናቫይረስ ህክምና መስጫ ማዕከል ሆነው እያገለገሉ ቢሆንም ለባለሙያዎች እስካሁን ምንም ዓይነት ከፍያ እንዳልተፈጸመ የጤና ባለሙያዎቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ግንቦት አጋማሽ መመሪያው ከወጣ በኋላ የባለሙያ እና የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የአበል ዝርዝር በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ደረጃ አልወጣ ሲል ጠብቀን መታገል ጀመርን" ሲሉ ለቢቢሲ የተናገሩት በጉለሌ ክፍለ ከተማ የጉቶ ሜዳ ኮቪድ -19 ማዕከል ሠራተኛ የሆኑት አቶ ዲኖ ጀማል ናቸው። ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ ከእያንዳንዱ የኮቪድ -19 ህክምና ማዕከል 3 ተወካይ በመምረጥ አቤቱታቸውን ለተለያዩ የመንግሥት ተቋማት አስገብተዋል። ወኪሎቻቸውን ያላሳወቁትን ሳይጨምር 1158 ሠራተኞች ወኪሎቻቸውን መርጠው ልዩ አበሉ ለምን እንዳልተከፈላቸው መጠየቃቸውን ገልጸዋል። ኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያ ገባ ተብሎ ሰዉ በሚሸሽበት ወቅት ጭምር ሙያዊ ግዴታ በሚል ወደ ሥራ መግባታቸውን የገለጹት የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ባልደረባ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚሰሩ ጤና ባለሙያዎች ተወካይ የሆኑት አቶ ከድር ሳሊህ ናቸው። . ኮቪድ-19 ያስተጓጎለው የኢትዮጵያ የካንሰር ህክምና . በኢትዮጵያ በአስክሬን ምርመራ ኮቪድ-19 መገኘቱ ምን ያመላክታል? "ሁሉም እኛን ማሞካሸት ጀመረ። በመሃል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኮቪድ -19 ላይ ለሚሰሩ ልዩ አበል ይከፈል አለ። እኛ ሙያዊ እና ሰብዓዊነት ነው ያስገባን። ክፍያ አይተን አይደለም። አንዳንድ ቦታ ይከፈላል ሌላ ቦታ አይከፈልም" ብለዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ጠቅላላ ሐኪም በበኩላቸው በኮሮናቫይረስ ማዕከል ከአምስት ወር በላይ እንደሠሩ እና አሁን ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውን አስታውቀዋል። መጀመሪያ ላይ ህብረተሰቡ በነበረው ፍራቻ እና በተለያየ ምክንያት ብዙዎች ከቤት እና ለተወሰነ ቀን ብቻ ከሥራ ቦታቸው እንዲሠሩ በተደረገበት እና ትርፍ ክፍያ ባልነበረበት ወቅት ጭምር መሥራት መጀመራቸውን ገልጸዋል። ሆኖም ሥራ ጀምረው ከሁለት ወራት በኋላ ተግባራዊ እንዲሆን የወጣው መመሪያ ተባግባራዊ አለመሆኑ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው አስታውቀዋል። "ማህበረሰቡ ባለሙያው ብዙ ክፍያ እንዳለው ነው የሚያውቀው። የማይከፍሉ ከሆነ ማህበረሰቡ ማወቅ አለበት። ቢከፍሉን ጥሩ ነው። የማይለከፍሉ ከሆነ ግን አንከፍልም ግን እናመሰግናለን የሚል ደብዳቤ ቢሰጠን። ከህክምና ጣቢያው ስወጣ በግሌ የሚያስጠሉ ፈተናዎች ነበሩት። 'የት ነበርሽ?' ምናምን የሚሉት ነገሮች ትንሽ ቅስም ይሰብራል" ብለዋል ሐኪሟ። እንደ አዲስ አበባ ጤና ቢሮ ልዩ አበሉ ባይከፈልም በፌደራል ስር በሚገኙ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከላት እና በአንዳንድ ክልሎች ተግባራዊ መደረጉን ግን እነዚህ ባለሙያዎች ገልጸዋል። "አዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሄደው ያነጋገሩ ባልደረቦች አሉ። እነሱ ግን በቃ እንደማይገባን ነገሩን ያሉት። በጀት የለንም አሉ። በጀት ከሌለ መጀመሪያም ውሳኔው (የሚንስተሮች ምክር ቤት) አይፈቅድም" ብለዋል። ውሳኔውን መሠረት በማድረግ ጤና ቢሮው ክፍያውን እንዲፈጽምላቸው በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም ተገቢውን ምላሽ አላገኙም። ክፍያው ሁለት ቢሊዮን ብር ገደማ ስለሚሆን እንደሚክብዳቸው፤ ከኮቪድ-19 ማዕከላት ውጭ ያሉት ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውን ጭምር በመግለጽ እነሱን ስለማያካትት ለአፈጻጸም አመቺ አይደለም ተብሎ ከጤና ቢሮው እንደተመለሰላቸው አቶ ዲኖ አስታውቀዋል። የጤና ጥበቃ ሚንስትር ደግሞ ጉዳዩ እንደማይመለከተው እንዳስታወቃቸው እና ለከተማው ካቢኔ ደብዳቤ አስገብተው ምላሽ እየተጠባበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል። የሚንስትሮች ምክር ቤት በመመሪያው ያወጣው በኮሮናቫይረስ የተያዙን የሚያክሙ፣ በለይቶ ማቆያ ህክምና በመስጠት ላይ የሚገኙ፣ ቀጥታ ተጋላጭ ሆኑ ባለሙያዎች በሚል በዝርዝር ለይቶ ማስቀመጡን ገልጸዋል። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ግን አሠራሩን በመቀየር ቢሮ የሚሠሩትን ተጠቃሚ በማድረግ ሌላ ውሳኔ ተግባራዊ መደረጉን ኮንነዋል። 'የወጣው ውሳኔ ሁሉንም ባያካትትም ሁሉም የህክምና ባለሙያ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ ነው' በሚል ቢሮ ውስጥ ያሉትንም ለመጥቀም የሚመስል ሁሉንም የሚያካትት አሠራር ለመፍጠር መሞከሩን አቶ ከድር አስታውቀዋል። ስለ ጉዳዩ ለሲቪል ሰርቪስ ያቀረቡት ቅሬታ ደግሞ 'ካልተስማማችሁ መልቀቅ ትችላላችሁ ብዙ ሥራ የሚፈልግ ባለሙያ አለ' በሚል ምላሽ አንደተሰጣቸውም ገልጿል። የጤና ባለሙያዎቹ ሌላ ቅሬታ ደግሞ የቤት ጉዳይ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ተገንብተው የተጠናቀቁና በግንባታ ላይ ያሉ በርካታ ቤቶች መኖራቸውን ጠቅሶ፤ በራሳቸውም ሆነ በባለቤቶቻቸው ስም ቤት እንደሌላቸው የሚገልጽ ማስረጃ እንዲያቀርቡ መጠየቁን አስታውሰዋል። መረጃውን ለሟሟላትም ውጣ ውረድ በማሳለፍ በተሰጣቸው ጥቂት ቀናት መረጃውን ማስገባታቸውን ገልጸዋል። ዕጣ እንደሚወጣላቸው በተነገራቸው ሰሞን የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተፈጠረው ችግር ምክንያት መደናቀፉን አስታውቀዋል። ምላሽ እንገኛለን በሚል ቢጠብቁም የቀድሞው ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከቦታቸው ተነስተው ወደ ሌላ ቦታ ተቀይረዋል። . የያዘዎት ጉንፋን ወይስ ኮሮናቫይረስ መሆኑን እንዴት መለየት ይችላሉ? . በለይቶ ማቆያ ያሉ የጤና ባለሙያዎች መሠረታዊ ፍላጎታችን እየተሟላ አይደለም አሉ . በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በኋላ የተሰጣቸው ምላሽ 'ዳታ' ለመስብሰብ ነው የሚል ነበር። ቤት እናገኛለን በሚል መረጃ ለማቅረብ ተሯሩጠው 'ለዳታ ነው' መባላቸው ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ጠቅሰዋል። መጀመሪያ ተስፋ ስለተሰጣቸው እንጂ ያሰቡት ባይሆንም ቃል ከተገባ ደግሞ ሊፈጸም ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል። ሰኔ 2012 ዓ. ም የጤና ባለሙያው በሦስት ቀን ውስጥ በራሳቸው እና በትዳር አጋራቸው ስም ቤት እንደሌላቸው የሚገልጽ ማስረጃ አምጡ መባላቸውን አቶ ዲኖ ገልጸው "አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ለህክምና ባለሙያዎች ቤት ሊሰጥ ነው ሁሉ ብለዋል" ሲሉ ተናግረዋል። "አንዳንድ ታካሚዎች ቤት ተሰጣችሁ ደስ ብሎናል እስከሚሉ ድረስ። እኛ ላይ የማታለል ሠራ ነው የሰረቡን" ብለዋል። በራሳቸውም ሆነ በትዳር አጋሮቻቸው ስም ቤት እንደሌላቸው የሚያሳይ ማስረጃ አስገብተው ዕጣው ሊወጣ አካባቢ በአርቲስት ሃጫሉ ሞት ምክንያት ዘገየ ሲሉ ያስታወሱት አቶ ከድር ናቸው። ከህክምና ቦታቸው ወጥተው ሰዎች ከኮቪድ-19 ማዕከላት በመምጣታቸው ብቻ እያገለሏቸው እና በአጭር ቀናት ውስጥ ያስገቡትን ማስረጃ "ለዳታ ነው። ምን ያህል ቤት እንደሌላችሁ ለማወቅ ነው እንጂ ቤት ይሰጣችኋል አልተባለም" መባሉ እንዳሳዘናቸውም አስታውቀዋል። የህክምና ዶክተሯ በበኩላቸው "ቤት እንሰጣለን ብለው ወከባ ፈጠሩ። እንደ ግለሰብ ሳይሆን እንደ ጤና ባለሙያ ግን ከቤት ውጣ የተባለ ሃኪም አለ። በኮቪድ-19 ጊዜ ቤት ልንሰጥ ነው ብለው የኑሮ ውድነት እንዲመጣ፤ ጤና ባለሙያዎች የሚከራየውን ቤት በእጥፍ እንዲጨመረበት ነው ያደረጉት። ይከፈላቸዋል በሚል ብቻ የኑሮ ውድነት እንዲጨምርበት ተደርጓል" ብለዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉት ጠቅላላ ሐኪም የገቢ ግብር እስካሁን እንዳልተነሳ እና በየትኛውም ህክምና ተቋም የሚከፈለው 'ዲዩቲ' (የሥራ) አበል አንኳን በአግባቡ እንዳልተከፈላቸው አስታውቀዋል። "ሁሉም የህክምና ባለሙያዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ናቸው ከተባለም ይህ መሸፈን ያለበት በጤና መድህን ነው። ቤተሰቦቻችን እየተከፈላችሁ ነው። ቤተሰብ እና ጓደኞቻችን የት አደረጋችሁት እያሉ ነው። እነሱ ባወጡት ህግ ነው የጠየቀውነው። ለምን ይሸራርፉታል በሚል። ህዝቡ በአዋጁ እየተጠቀማችሁ ነው እያለ ነው። ቤተሰብም ጓደኛም ግብርም ቀርቶላችኋል ይላል" ብለዋል አቶ ከድር። ይህም ሆኖ ግን እስካሁን የገቢ ግብር ቅነሳውም ቢሆን ተግባራዊ አለመደረጉን ጠቁመዋል። ቢቢሲ በመጨረሻም ለባለሙያዎቹ ምላሽ ካላገኛችሁ ምን ለማድረግ አስባችኋል? በሚል ላቀረበላቸው ጥያቄ የሚከተለውን መልሰዋል። "ሥራ ለማቆም አላሰብንም። ባለሙያው ሥራ እንዳያቆም ነው ተወካይ የተላከው። ተወካዮች ኮሚቴ መረጡ። እነሱ ናቸው የሚንቀሳቀሱት። ኮሚቴዎቹ ሥራም እየሠሩ ነው። በሚዲያ እያሳወቅን ነው ህዝቡ እንዲያውቅልን። በኮሚቴም በአባላትም ደረጃ ወደፊት ወደ ፍርድ ቤት ልናመራ እንችላለን የሚል ሃሳብ ነው ያለው" ያሉት አቶ ዲኖ ናቸው። "አገራዊ እና ሙያዊ ግዴታ ነው። እኔ ሥራ ባቆም የሚሞቱ ሰዎች አሉ። ይሄ ባለሙያው ምሎ የወጣበት ስለሆነ ሥራ ማቆም አይችልም። አመጽም አይኖርም። እየተረገጥክ ጥቅመህን አሳልፈን እንድትኖር ነው የሚያደርጉት" ያሉት ደግሞ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሐኪም ናቸው። ዶ/ር ሙሉጌታ እንዳለ በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ናቸው። እንደ ዶ/ር ሙሉጌታ ከሆነ ልዩ አበሉን ለማስፈጸም መመሪያ ከወጣ በኋላ አፈጻጸም ላይ ችግር ገጥሟቸዋል። በመጀመሪያው የልዩ አበሉ የተፈቀደው የኮቪድ -19 ማዕከላት ውስጥ ለሚሠሩ እና በመከላከል ላይ ለሚሳተፉ ባለሙያዎች በሚል ነው። እንደ ምክትል ኃላፊው ከሆነ ግን በዚህ ውስጥ ሁሉም የጤና ሠራተኞች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እየተሳተፉ ነበር አሁንም በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። በዚህ ምክንያት ለማስፈጸም አስቸግሮናል ይላሉ። በተጨማሪም ደግሞ ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በራሳቸው አውድ እንዲጠቀሙበት መመሪያው እንደሚፈቅድ ገልጸው የተለያዩ አማራጮችን በመውሰድ ለመተግበር ሙከራ መደረጉን አስታውቀዋል። ሆኖም ሙከራዎቹ ጥቂት ሠራተኞችን ብቻ የሚጠቅሙ ሆነው ተገኝተዋል ይላሉ። "መሬት ላይ ስናወርደው ጽዳቱም፣ ሹፌሩም ድንገተኛ ክፍል የሚሠራው ይገባዋል። ተመላላሽ ህክምና፣ ቀዶ ጥገና ክፍል፣ ማዋለጃ የሚሠሩና ሁሉም ላይ ያሉ ሠራተኞቻችን ከኮቪድ -19 ጋር ተጋፍጠው እየተከላከሉ እየሠሩ ነው። እንተግብረው ካልን ደግሞ ለሁሉም ነው መተግበር ያለብን" ሲሉ ያስረዳሉ። ሌላው ደግሞ ለትግበራ ያስቸገረው የበጀት ጥያቄ ነው። "የከተማ አስተዳድሩ ላይ ትልቅ ወጪ አለ። ከተማ አስተዳደሩ ያንን መሸከም የሚችል አይደለም" ብለዋል። ከዚህ በተሻለ አማራጭ ተደርጎ የተወሰደው ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ ከገባበት ወቅት አንስቶ በከተማ መስተዳድሩ በጤና ዘርፍ ለሚሠሩ ባለሙያዎች በሙሉ የግብር ቅነሳ ማድረግ ነው። "ሁሉም የጤና ዘርፍ ሰራተኞች ራሳቸውም አደጋ ላይ ጥለው ነው እየሠሩ ያሉት። ኮቪድ-19 ላይ ቅዳሜ እና እሁድ ገብተው የሚሠሩ አሉ። ገብተው የሚያድሩ አሉ። ይሄንን የትርፍ ሰዓት ክፍያቸውን እንሰጣለን" ሲሉ ተናግረዋል ። አክለውም "ከተማ መስተዳድሩ ታክስ ቅነሳ ወይም ራሱ መስተዳድሩ ታክሱን ይከፍላል ማለት ነው። ስለዚህ ኮቪድ-19 ከጀመረበት ከመጋቢት ጀምሮ ኮቪድ-19 ከስጋትነት እስከሚወጣበት ድረስ ሁሉም የጤና ሠራተኞቻችን ያንን ከግብር ተቀንሶላቸው መስተዳድሩ ራሱ እየሸፈነ በዚያ መንገድ እናስተናግድ ተብሎ ተወሰነ" ብለዋል። መመሪያው ሲወጣ መጀመሪያ ድንገተኛ የአደጋ መቆጣጠር ዘርፍ ላይ የሚሠሩ የተወሰኑ ሠራተኞችን ብቻ ታሳቢ አድርጎ እንደነበር ዶ/ር ሙሉጌታ አስታውቀው፤ የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረ ሲሄድ ብዙ ባለሙያዎችን ከማሳተፉም በላይ መመሪያዎችም መቀያየራቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ኮሮናቫይረስ ላይ የሚሠሩ ሠራተኞች ቁጥር መጨመርም ሌላው ምክንያት ነው። ቸግሩን ለመቅረፍ ከሠራተኞች ጋር በተደጋጋሚ መወያየታቸውን አንስተው "ብዙ የጤናው ዘርፍ ሠራተኛ በውሳኔው ላይ ጥሩ እይታ እንዳለው ነው ያየነው" ብለዋል። ሆኖም ቅሬታዎች መኖራቸውን ጠቁመው ጤና ቢሮው የወሰደውን እርምጃ ሌሎችም (ክልሎች እና ጤና ጥበቃ) የመከተል ነገር እንዳለ መመልከታቸውን ጠቁመዋል። ከዚህ በተቃራኒ ሁላችንም ለአደጋ ተጋልጠን በምንሠራበት ለጥቂቶች ብቻ መከፈል የለበትም የሚሉ ጥያቄዎች መነሳታቸውን በተመለከተ፤ "እኛም አደጋ ላይ ወድቀን እየሠራን ለጥቂቶች ብቻ እየተከፈለ ታሳቢ አለመደረጉ ተገቢ አይደለም ብለው ደግሞ በተቃራኒው የሚጠይቁ አሉ። የግድ ኮቪድ-19 ማከሚያ ቦታ ብቻ ነው ወይ እኛም እየተጋፈጥን ነው የሚሉ አሉ" ሲሉ አስረድተዋል። ገቢ ግብርን በተመለከተ ደግሞ በከተማ መስተዳድሩ ሥር በሚገኙ ሁሉም ጤና ተቋማት መረጃ የማሰባሰብ ሥራ መከናወኑን አስታውቀው በጥቂት ቀናት ውስጥ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል። ህክምና ባለሙያዎቹ ቤት ይሰጣችኋል ተብለን በተገባልን ቃል መሠረት አልተፈጸመልንም ለሚለው ቅሬታቸውም ምላሻውን እንደሚከተለው ሰጥተዋል። "ቤት ይሰጣል የሚል እንደ መስተዳደርም እንደ ቢሮም የለም። መረጃ ሊሰበሰብ ቤት ያለውን እና የሌለው የጤና ባለሙያ መረጃ እንዲያዝ ከተማ መስተዳደሩ መጠየቁን ነው እኔ የማውቀው። መረጃውን ጠይቁ አለ መረጃውን ሰብስበን ልከናል። ቤት ይሰጣቸዋል የሚል ነገር ግን የለም" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54744135
amh
health
"በረሃብ ምክንያት ከሥራ ገበታቸው የሚቀሩ የጤና ባለሙያዎች አሉ" አይደር ሪፈራል ሆስፒታል
በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ የሚገኘው ዋነኛ የሕክምና ተቋም አይደር ሪፈራል ሆስፒታል በቀን ከ4 እስከ 6 አስክሬኖች የሚሸኝበት ደረጃ እንደደረሰ ለቢቢሲ ገለጸ። በመድኃኒትና ሕክምና አገልግሎት እጥረት ከሞቱት መካከል የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች እንደሚገኙበትም አስታውቋል። ቢቢሲ ያነጋገረው የሆስፒታሉ የነርሲንግ አገልግሎት ኃላፊ ቴዎድሮስ ካህሳይ ከጦርነቱ በፊት ከትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች ለሚመጡ ታካሚዎች አገልግሎት ይሰጥ የነበረው ሆስፒታል አሁን ግን እጅግ መዳከሙን ገልጿል። ከአንድ ዓመት በላይ በሆነው የሰሜኑ ጦርነት ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል እና ከዓለም ተቆራርጣ ባለችው ትግራይ ክልል በሕክምና ቁሳቁሶች፣ መድሃኒቶችን እና የሰብዓዊ እርዳታዎች እጥረት በርካቶች ለከፋ ችግር መዳረጋቸው ሲዘገብ ቆይቷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በትግራይ የጤና ማዕከላት በአስፈላጊ መድኃኒት እጥረት ሳቢያ ሥራ ማቆማቸውን ያስታወቀ ሲሆን በትግራይ ክልል የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች በበኩላቸው ህፃናትን ጨምሮ ህሙማን በከፍተኛ መድኃኒት እጥረት ምክንያት እየሞቱ መሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማድረስ ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን አስታውቆ፤ የትግራይ ኃይሎች ከማንኛውም ጥቃት እንዲታቀቡና በኃይል ከያዟቸው የአጎራባች አፋር ክልል አካባቢዎች እንዲወጡ ጠይቆ ነበር። ይህንን ተከትሎም የትግራይ ኃይሎች የተኩስ አቁም እንዳደረጉና ከአፋር ክልል ኤረብቲ መውጣታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ሳምንት ደግሞ የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ህወሓት ከአፋር ክልል ሙሉ ለሙሉ ለመውጣት ዘላቂ፣ ያልተገደበ፣ ወቅታዊ እና በቂ የሆነ እርዳታ ማቅረብን ጨምሮ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል። ቀደም ሲል የተደረገውን ስምምነት ተከትሎም ከሁለት ሳምንት በፊት የዓለም ምግብ ፕሮግራም 47 ምግብና ነዳጅን ጨምሮ የተለያዩ ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ትግራይ ማድረሱን ገልጿል። አለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ መድኃኒቶች፣ የህክምና መገልገያዎችና የምግብ እርዳታ የጫኑ መኪኖቹ ከስድስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሜ መጋቢት 24፣ 2014 ወደ ትግራይ መግባታቸውን አስታውቋል። አሜሪካም በሰሜን ኢትዮጵያ ለተከሰተው ችግር የሚውል 313 ሚሊየን ዶላር የሚገመት የሰብዓዊ እርዳታ ማድረጓን ከትናንት በስቲያ አስታውቃለች። የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል የነርሲንግ አገልግሎት ኃላፊው ቴዎድሮስ ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ ለሆስፒታሉ ሲሰጥ የነበረው ድጎማ እና የሕክምና ቁሳቁስ አነስተኛ እንደነበር አስታውሰው ላለፈው አንድ ዓመት ግን ሆስፒታሉ ካለምንም በጀት እየሠራ እንደሆነ ተናግሯል። " በአሁኑ ሰዓት 30 በመቶ በሚሆን አቅም ነው አገልግሎት እየሰጠን ያለነው፤የመድሃኒት ክምችታችን ወደ 10 በመቶ ወርዶ ነበር። ከዓለም ጤና ድርጅት የመጣ እርዳታ ተጨምሮበት ክምችቱ ወደ 20 በመቶ ደርሶ ነበር። ነገር ግን ይህ ለሆስፒታሉ የተሰጠው መድሃኒት ያለቀው በሁለት ሳምንት ውስጥ ነው" ይላል። ኃላፊው እንደሚሉት ድጋፍ የተደረጉላቸው መድሃኒቶች በዓይነትም እጅግ አነስተኛ እንደነበር ጠቁመዋል። ኃላፊው እንደ ካንሰር፣ ደም ግፊት ላሉ ስር የሰደዱ በሽታዎች ምንም ዓይነት መድሃኒት አለመግባቱን በመግለፅም ለሳንታት ታይቶ የነበረው የሆስፒታሉ አገልግሎት መሻሻል ተመልሶ መውረዱን አክለዋል። ለላብራቶሪ የሚውሉ ግብዓቶች ፣ መድሃኒቶች፣ ማሽኖችን ማንቀሳቀሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ፣ ተኝተው ለሚታከሙ የሚቀርብ ምግብ ፣ ለሠራተኞች የሚከፈል በሌለበት መስራትም አስቸጋሪ አንደሆነ ቴዎድሮስ ገልጿል። "በረሃብ ምክንያት ከሥራ ገበታቸው የሚቀሩ ባልደረቦቻችን አሉ" በሆስፒታሉ ድንገተኛ ክፍል ውስጥ ነርስ የሆነው ገብረይ አቢዩ " ሰዎች ለሕክምና መጥተው እያየናቸው ሕይወታቸውን ሲያጡ እጅግ እናዝናለን" ይላል። የሆስፒታሉ ሠራተኞች በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ሆነው እየሠሩ እንደሆነ የሚናገረው አቶ ገብረይ "በረሃብ ምክንያት ከሥራ ገበታቸው የሚቀሩ ባልደረቦቻችን ግን አሉ" ይላል። "ከባድ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው ሰዎች ሙያዊ ድጋፍ ፈልገው ሲመጡ ምንም ሳይደረግላቸው ሲቀር ሥራ ቦታ ብቻ ሳይሆን ቤት ሄደህም ሰላም አታገኝም። ለሊት ተኝተህ ወደ ህሊናህ የሚመጣ ብዙ ነገር አለ። ሕጻናት መጥተው በኦአርኤስ ወይም በሌላ ትንሽ ነገር ሕይወታቸውን ማትረፍ እየተቻለ ይህ ባለመኖሩ ስታጣቸው በጣም ከባድ ነው። እጆችህን አጣጥፈህ ነው ቆመህ የምታየው። ልብህን የሚያደማ እንጂ ደስ ብሎህ የምትሠራው ሥራ አይደለም።" ሲሉ በሆስፒታሉ ያለውን ችግር ያስረዳሉ። ችግሩ ይህ ብቻ አይደለም፤ ድርብርብ ነው። የትራንስፖርት አገልግሎት ባለመኖሩም ለ11 ወራት ደሞዝ ያልተከፈላቸው ሠራተኞች እስከ 2 ሰዓት የሚወስድ መንገድ በእግር ተጉዘው ሆስፒታሉ እንደሚደርሱ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የጤና ባለሙያዎች ይገልጻሉ። "የጤና ባለሙያዎችም በሕክምና አገልግሎት እጦት ሕይወታቸው አልፏል" ቴዎድሮስ እንደሚለው የመድኃኒትና የሕክምና አገልግሎት እጥረት የታካሚዎችን ሕይወት ብቻ ሳይሆን የጤና ባለሙያዎችንም ሕይወት እየቀጠፈ ነው። "በዚህ ሁለት ወር 2 ነርሶች ሞተውብናል። መዳን ይችሉ ነበር፤ ግን መድኃኒት ማግኘት አልቻሉም። በተለይ አንደኛዋ ነርስ ኤምአርአይ ማሽኑ እየሠራ ስላልሆነ በሽታዋን በግልጽ ማወቅ አልተቻለም። በዚህ ምክንያት ሕመሟ ጸንቶ ሞታለች። ሁለተኛው ነርስ ደግሞ ሊወስደው የሚገባ መድኃኒት እዚህ ሆስፒታል ስለሌለ ያጣነው ባልደረባችን ነው። አሁን በቀን እስከ 4 አልፎም እስከ 6 አስክሬን ከዚህ ሆስፒታል ይሸኛል። ከዚህ በፊት ግን በሁለት ወይም ሦስት ቀን አንድ ሬሳ ነበር የሚወጣው" ይላል። በሕክምና እጦት ምክንያት ሕይወታቸው ከሚያልፍ የጤና ባለሙያዎች መካከል አብዛኞቹ የክሮኒክ በሽታዎች ተጠቂ መሆናቸውንም ኃላፊው ገልጿል። ትግራይ ባለው የጥሬ ገንዘብ እጥረት ምክንያት ሆስፒታሉ ለሚሰጠው አግልግሎት ከታካሚዎች የሚጠይቀው ገንዘብም እጅግ ዝቅተኛ ክፍያ [ከቀድሞው ከ90 በመቶ ያነሰ) ነው። "በሆስፒታሉ የማይገኙ መድኃኒቶችን ከውጭ ለመግዛት የተቸገሩ ሰዎች፣ ከሩቅ የትግራይ አካባቢ መጥተው መመለሻ ያጡ ሰዎች፣ የሞቱ ቤተሰቦቻቸውን አስክሬን ለመውሰድ የሚቸገሩ ሰዎችን ማየት የሠራተኞቹን ልብ በሐዘን ይሰብራል" ብሏል። ለታካሚዎችና ለተወሰኑ ሠራተኞች ይቀርብ የነበረ ምግብ ላለፉት 10 ቀናት ውስጥ ስለተቋረጠ እስከ 240 ታካሚዎች ወደ ቤታቸው እንደተሸኙም አክሏል። ከዚህ ቀደምም የአይደር ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ባወጡት መግለጫ በቀዶ ህክምና ወቅት የሚያስፈልጉ በደም ስር የሚሰጡ (intravenous fluids) እና የሰመመን መስጫ መድኃኒቶች ባለመኖራቸው ቀዶ ህክምና ማድረግ አለመቻላቸውን ነው። በተደጋጋሚ የሚከሰተው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እና ያልተሟላ የኦክስጂን አቅርቦት ለታካሚዎች ሞት ምክንያት ነው ብለዋል። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልል መሰረታዊ የሚባሉ አገልግሎቶች መብራት፣ ውሃ፣ ስልክ፣ ትራንስፖርትና የባንክ አገልግሎቶች ተቋርጠው ይገኛሉ። ባለፈው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ ተከስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሺዎችን በመቅጠፍና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀል መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ አድርሷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለው ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልገው ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ገልጿል። አስራ ስምንት ወራት ያስቆጠረው ይህ ጦርነት እንዲቋጭ አሜሪካን ጨምሮ የአፍሪካ ሕብረትና ሌሎች አጋሮች ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ከሰሞኑ የኢትዮጵያ መንግሥትና የትግራይ ኃይሎች ለሰብዓዊነት ሲባል የተኩስ አቁም ያወጁ ሲሆን ይህም ለሰላም በር ሊከፈትና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማብቃት ወደሚያስችል ውይይት መሄድ እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል።
https://www.bbc.com/amharic/news-61132952
amh
health
መንግሥት በትግራይ ክልል ረሃብ አለ መባሉን አጣጣለ
በትግራይ ክልል ረሃብ እንደሌለ የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ተናገሩ። ረቡዕ ዕለት በትግራይ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ ከጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር ለጋዜጠኞች በተሰጠ ማብራሪያ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር የሰብዓዊ ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። የተባበሩት መንግሥታት በቅርቡ በትግራይ ክልል ያሉ ነዋሪዎች በረሃብ ቋፍ ላይ ናቸው የሚል መግለጫ ያወጣ ሲሆን የከፋው የ1977ቱ ረሃብ ሊደገም እንደሚችል አስጠንቅቋል። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ በትግራይ ክልል በረሃብ ሰዎች እየሞቱ ነው የሚለውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሪፖርትን በመጥቀስ ከጋዜጠኞች ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ምትኩ ምላሽ ሰጥተዋል። በአንዳንድ ሪፖርቶች በኮረም ኦፍላ ወረዳ በረሃብ ሞተዋል ተብሎ የወጣ ሪፖርት እንዳለ ጠቁመው "ሐሰት ነው" ብለዋል ኮሚሽነሩ። "አካባቢው ሰላማዊ ነው" ያሉት አቶ ምትኩ በትግራይ ክልል በሚሰሩ አንዳንድ ድርጅቶች ሆን ብሎ የተደረገ ነው በማለትም ወንጅለዋል። በተጨማሪም "መንግሥት በክልሉ ውስጥ ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ እየተጠቀመ ነው" የሚሉ በሚዲያም ሆነ በተለያዩ አካላት የወጡ ሪፖርቶችን ያጣጣሉት አቶ ምትኩ በአብዛኛው የትግራይ ክልል እርዳታ በመስጠት የሚንቀሳቀሱት አጋር ድርጅቶች ናቸው ብለዋል። በእነዚህ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የአርዳታ ድርጅቶች አስፈላጊውን እርዳታ ለማቅረብ አቅሙም እንዳላቸው ጠቁመዋል። የፌደራሉ መንግሥት በአብዛኛው በምዕራብ ትግራይ ሁመራ፣ ማይካድራና ሌሎች አካባቢዎችን ጨምሮ በ40 ወረዳዎች ውስጥ በዋነኝነት የእርዳታ አቅርቦቱ ስርጭት እንደሚያከናውን አመልክተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ረሃብ (ፋሚን) ብሎ ለማወጅ ሦስት ዓለም አቀፍ መስፈርቶች በአንድነት መሟላት እንዳለባቸው አቶ ምትኩ ጠቁመዋል ይህ ሁኔታ በትግራይ እንዳልተከሰተ ተናግረዋል። ኮሚሽነሩ መስፈርቶች ብለው የጠቀሷቸው በአንድ አካባቢ 20 በመቶ ቤተሰቦች የምግብ እጥረት ሲገጥማቸውና ለመኖር አሰቸጋሪ ሲሆን፣ ከ30 በመቶ በላይ ህፃናት በከፍተኛ የምግብ እጥረት ሲሰቃዩ እና ረሃብ ከአስር ሺህ ነዋሪዎች መካከል በየቀኑ ከሁለት ሰው በላይ ሲገድል የሚል ነው። አሁን ባለው ሁኔታ 20 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ የምግብ እጥረት እንዳጋጠመው ነው ሪፖርቶች የሚያሳዩት ቢሉም "በክልሉ ምንም አይነት የምግብ እጥረት የለም ምክንያቱም 91.3 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ በአምስት እርዳታ ድርጅቶች እየተረዱ ይገኛሉ" ብለዋል አቶ ምትኩ። የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ እርዳታ ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ ባለፈው ሳምንት ለቢቢሲ እንደተናገሩት በትግራይ ክልል ውስጥ በአሁኑ ጊዜ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ እንደተጋለጡ በመግለጽ የከፋ ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል መናገራቸው ይታወሳል። ከዚህም በተጨማሪ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አበበ ገብረ ህይወት በቅርቡ በሰጡት ቃለ መጠይቅ አርሶ አደሮች እንዳያርሱ ተከልክለዋል ያሉትም ጉዳይ በጋዜጠኞች የተነሳ ሲሆን ይህ ተፈፅሟል ወይ? ለሚለው ጥያቄ አቶ ምትኩ በምላሹ "ሐሰት ነው" በትግራይ ክልል 70 በመቶ የሚሆነው አካባቢ ታርሷል ብለዋል። አቶ ምትኩ ይህንን ያሉት የግብርና ሚኒስቴርን ዋቢ በማድረግ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የተሻሻለ ዘርና ማዳበሪያም በክልሉ እንደተከፋፈለ በዚሁ አጋጣሚ አስረድተዋል። ምክትል የትግራይ አስተዳደሩ ይህንን ቢናገሩም ከሚዲያ ጋር ለሁለተኛ ጊዜ በነበራቸው ቆይታ ይህንን ማስተካከላቸውን አቶ ምትኩ ለጋዜጠኞቹ ገልፀዋል። የሰብዓዊ እርዳታን በተመለከተ በክልሉ ውስጥ እስካሁን ለ4.5 ሚሊዮን ሕዝብ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ እርዳታዎች በመጀመሪያው ዙር፣ በሁለተኛውና በሦስተኛው ዙር ለ5.2 ሚሊዮን ሕዝብ እርዳታ መቅረቡን አቶ ምትኩ ይናገራሉ። በዚህም መሰረት ኮሚሽነሩ እንደሚሉት በ5.4 ቢሊዮን ብር የሚገመት 170 ሺህ 798 ሜትሪክ ቶን ስንዴ ለክልሉ ተከፋፍሏል። በመጀመሪያውና በሁለተኛው ዙር የተከፋፈለውን የምግብ ወጪ 70 በመቶ መንግሥት የሸፈነ ሲሆን ሰላሳ በመቶውን ደግሞ አጋሮች ሸፍነዋል ተብሏል። በሦስተኛው ዙር ግን መንግሥትን ጨምሮ ስድስት አካላት ማለትም የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ ወርልድ ቪዥን፣ ኬር ኢንተርናሽናል፣ ሪሊፍ ሶሳይቲ ኦፍ ትግራይ፣ ፉድ ፎር ሃንግሪ እርዳታ እያደረሱ እንደሚገኙም ተጠቁሟል። እነዚህ የአጋር ድርጅቶች 84.9 በመቶ የትግራይ ወረዳዎችን በመሸፈን 91̄.3 በምግብ አቅርቦትና ስርጭት አያደረሱ እንደሚገኙም ተነግሯል። መንግሥት በእነዚህ አካባቢዎች ላይ ቁጥጥር በማድረግ፣ እርዳታው እንዲሰራጭ ምቹ ሁኔታንም ለመፍጠር ከአጋሮች ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑንም አቶ ምትኩ ጠቁመዋል። የተለያዩ የሰብዓዊ አርዳታ አጋሮች በክልሉ 5.2 ሚሊዮን ወይም ደግሞ 90 በመቶ የሚሆነው የክልሉ ሕዝብ አስቸኳይ የሰብዓዊ አርዳታ ያስፈልገዋል ቢሉም አቶ ምትኩ በበኩላቸው ከነዚህ ውስጥ 1 ሚሊዮን 10 ሺህ 752 ሰዎች የሴፍቲ ኔት ፕሮግራም ተጠቃሚ ናቸው፤ እንዲሁም 40 ሺህ 336 ደግሞ ኤርትራውያን ስደተኞች ናቸው ብለዋል። እነዚህ የጠቀሷቸው ፕሮግራሞች "የራሳቸው ፈንድ አላቸው" አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸውም ጋር በቅንጅት ሊታዩ እንደማይገባም ይናገራሉ። ሆኖም አቶ ምትኩ በክልሉ እርዳታ ለማቅረብ ተግዳሮቶች እንዳሉ የጠቆሙ ሲሆን፤ በአንዳንድ አካባቢዎች ውጊያና ተኩስ በመኖሩ የፀጥታውና የደኅንነት ሁኔታውን ስጋት ላይ መጣሉን ጠቁመው በዚህም የወታደሮች እጀባ ያስፈልጋል ብለዋል። በሌላ በኩል አስቸኳይ መጠለያና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች እጥረት ሌሎችም ችግሮችም እንዳሉ ጠቁመዋል። "ምግብ ነክ ባልሆኑ ቁሶች እርዳታ ላይ ከፍተኛ የሚባል ክፍተት አለ" የሚሉት አቶ ምትኩ ለዚህም በዋነኝነት የሚያነሱት አጋሮች እየሸፈኑ ያሉትም 33 በመቶ ወጪውን መሆኑን ነው። ከዚህም በተጨማሪ በክልሉ ውስጥ ያሉ ተፈናቃዮችን በተመለከተ፤ አቶ ምትኩ በክልሉ ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎች ሦስት አማራጮች የቀረበላቸው ሲሆን ሰላማቸው በተረጋገጡ አካባቢዎች ተፈናቃዮች በፈቃዳቸው ዓለም አቀፉን ድንጋጌ መሰረት ባደረገ መልኩ ወደመጡበት እንዲመለሱ፣ በሁለተኛ ደረጃ አካባቢያቸው ያልተረጋጋ ከሆነም የቅርብ ቤተሰብና ዘመዶች ካሏቸው ከእነሱ ጋር እንዲቆዩ፣ ሁለቱን ማድረግ ካልተቻለ ደግሞ በመጠለያዎች እንዲቆዩ የሚል ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ በምዕራብ ትግራይ የተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆችን በተመለከተ ምላሽ የሰጡት አቶ ምትኩ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት አርባ አባላት ያሉት ኮሚቴ መቋቋሙን አመልክተዋል። እነዚህን ተፈናቃዮች የክረምት ወር ከመጀመሩ በፊት ወደመጡባቸው ቦታዎች ለመመለስ እቅድ የተያዘ ሲሆን ኮሚቴውም የአማራ ክልል ፕሬዚዳንትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዚዳንቶችንም በአባልነት እንዳካተተ ተጠቁሟል። በክልሉ የጤና ሥርዓትን በተመለከተ በትግራይ የጤና ሥርዓቱን ወደነበረበት ለመመለስ የጤና ሚኒስቴርና የተለያዩ ኤጀንሲዎች እየሰሩ ነው የተባለ ሲሆን ይህንንም ለማከናወን አንድ ግብረ ኃይል መሰማራቱን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል። የተለያዩ የጤና ባለሙያዎች ከብሔራዊ ተቋማት ተሰማርተው የክልሉን የጤና ቢሮ እየረዱ እንደሚገኙም ተገልጿል። የክልሉን ጤና ሥርዓት ከመመለስ ጋር በተያያዘ ዋነኛ የተባለውም ሥራ የጤና ተቋማቱ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በክልሉ 55 በመቶ የሚሆኑት ሆስፒታሎች እንዲሁም 52 በመቶ የጤና ተቋማት አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ሚኒስትሯ ተናግረዋል። አገልግሎት በሚሰጡ ሆስፒታሎችም ሆነ የጤና ማዕከላት 95 በመቶ የሚሆኑት የጤና ባለሙያዎች በየቀኑ አገልግሎት መስጠት መቀጠላቸውን የጠቆሙት ሚኒስትሯ፤ የቀሩት የጤና ተቋማት ላይ የደረሰባቸው ጉዳት ተግመግሞ መልሰው እንዲቋቋሙና አገልግሎት እንዲጀምሩ ከፌደራል መንግሥት በኩል ለ14 ሆስፒታሎችና 58 የጤና ማዕከላት ገንዘብ ተመድቧል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ አስፈላጊ የሚባሉ የጤና ቁሳቁስ ግብዓቶች እንደ አልትራ ሳውንድ፣ ቬንትሌተር፣ ማይክሮስኮፖች መላኩን የገለፁት ሚኒስትሯ፤ እስካሁንም ባለው ከ310.8 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ መድኃኒቶችና ሌሎች ግብዓቶች ወደ ክልሉ መላኩን አስረድተዋል። በአጠቃላይ በክልሉ ለጤና አገልግሎት አስፈላጊ ግብዓቶች 215 ሚሊዮን ብር ተመድቦ አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል ተብሏል። ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) መጋቢት ወር ላይ ባወጣው መግለጫ በትግራይ ክልል በሚገኙ የህክምና ተቋማት ላይ ሆን ተብሎ ዘረፋ እና ጥቃት ተፈጽሟል ሲል ገልፆ ነበር። ድርጅቱ በዚሁ መግለጫው አንዳንዶቹ ዘረፋዎች የተፈፀሙት በወታደሮች ጭምር ነው ያለ ሲሆን 13 በመቶ የሚሆኑ የጤና ተቋማት ብቻ በአግባቡ እየሰሩ ነው ማለቱ የሚታወስ ነው። በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የጤና ተቋማትን አገልግሎት ከማስጀመር ጋር ተያይዞ ተንቀሳቃሽ የጤና የህክምና አገልግሎትን መመለስ ከፍተኛ ክፍተት እንዳለ ሚኒስትሯ ተናግረዋል። ተቋማቱ በውስን ደረጃም አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን በተለይም እናቶችና ህፃናት ላይ አተኩሮ የክትባትና ሌሎች የህክምና አገልግሎት በተለያዩ ወረዳዎች እየተሰጡ ይገኛሉ ብለዋል። ከዚህም ጋር በተያያዘ በባለፉት ሁለት ወራት ከ75 ሺህ የሚበልጡ ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ የምግብ እጥረት ያጋጠማቸው ህፃናት ወደ ጤና ማዕከላትና ተንቀሳቃሽ የህክምና መስጫ ማዕከላት መምጣታቸውን ሚኒስትሯ ተቋማቱን ዋቢ አድርገው ተናግረዋል። ከነዚህም መካከል 4 በመቶዎቹ ለከፋ የምግብ እጥረት የተጋለጡ ሲሆን አስፈላጊው የህክምና እንክብካቤና አገልግሎት አግኝተዋል ያሉት ሚኒስትሯ፤ በአጠቃላይ አገልግሎት በሚሰጡት የጤና ተቋማት 409 ሺህ የክልሉ ነዋሪዎች በባለፉት ወራት አገልግሎት እንዳገኙም ተገልጿል። ክልሉ በርካታ የአምቡላንስ አገልግሎቶቹን ከማጣቱ አንፃር በአሁኑ ጊዜ ሚኒስቴሩን ጨምሮ ከሌሎች አካላት በተገኘ እርዳታ 58 አምቡላንሶች አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ የተጠቆመ ሲሆን፤ ከዚህም በተጨማሪ 65 ጥገና ላይ ሲሆኑ ሌሎቹንም በተጨማሪነት ለማግኘት ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል። በተጨማሪም ተፈናቃዮች ባሉበት ቦታ አስፈላጊ የሚባሉ የጤና አገልግሎቶች በነፃ እየተሰጡ እንደሆነ ሚኒስትሯ ተናግረዋል። ይህንንም ለማገዝ በጤና ሚኒስቴር አማካኝነት ተጨማሪ ባለሙያዎችን በማሰማራትና ጊዜያዊ የጤና ማዕከላትን በማቋቋም እየተረዱ እንደሚገኙም ተነግሯል። በዚህ ጦርነት የተደፈሩ ሴቶችን አስፈላጊ ህክምና ለመስጠት የሥነ አዕምሮ ህክምናን ጨምሮ የማማከር ሥራ የሚሰሩ ባለሙያዎች በስድስት ከተሞች ድጋፍ እየሰጡ ይገኛሉ ብለዋል። በክልሉ የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የክልሉ የጤና ቢሮ ከ28 አጋሮች ጋር እየሰሩ ነው ቢባልም እንደዚያም ሆኖ በርካታ ችግሮች ተደቅነዋል ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/57417533
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ ኮሮናቫይረስ ውሸት ነው ብሎ የሚያምነው ጎልማሳ ባለቤቱ በበሽታው ተቀጠፈች
ብራየን ሊ ይባላል፡፡ በፍሎሪዳ ውስጥ ታክሲ ነጂ ነው፡፡ ለረዥም ጊዜ ኮሮና የሚባል ነገር የለም፤ ፍጹም ቅጥፈት ነው ሲል ነበር፡፡ ይህን የሚለው ግን ለጨዋታ ድምቀት ሳይሆን የምሩን ነበር፡፡ እንዲያውም ወደ ፌስቡክ እየወጣ ሰዎች በዚህ እልም ያለ ውሸት እንዳይታለሉ ይሰብክ ነበር፡፡ ባለቤቱ ኤሪን ትባላለች፡፡ ወይም ‹ትባል ነበር› ማለቱ ይሻላል፡፡ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወተወን አጥታለች። ለብራይን ይህ ትልቁ ቅጣት ሆኖበታል፣ ዛሬ፡፡ ብራይንም ሆነ ባለቤቱ ኤሪን በበይነ መረብ የሚሰራጩ መላምቶች ሰለባ ሆነው ቆይተዋል፡፡ ‹ኮሮና ብሎ ነገር የለም፡፡ ካለም ጉንፋን ነው፤ ካለም 5ጂ ቴክኖሎጂ የፈጠረው ነገር ነው› ሲሉ ነበር የሚያምኑት፡፡ ለዚህም ይመስላል ቫይረሱ ከተገኘባቸው በኋላ እንኳን ሐኪም የሚላቸውን ነገር ለመስማት ያልፈቀዱት፡፡ ሁለቱም ግንቦት ላይ ነበር የታመሙት፡፡ ብራይን በለስ ቀንቶት አገገመ፡፡ ሚስቱ ግን አሸለበች፤ 46 ዓመቷ ነበር፡፡ ብራይን በሐምሌ ወር ላይ የቢቢሲ እንግዳ ነበር፡፡ ቢቢሲ ያኔ በኮቪድ-19 ዙርያ በሚሰሩ መላምቶችና የሴራ ወሬዎች ዙርያ አንድ ዘገባ እየሰራ ነበር፡፡ ያን ጊዜ የብራይን ሚስት አልሞተችም ነበር፡፡ ሆኖም በጽኑ ሕሙማን ማገገምያ ክፍል ገብታ ትተነፍስ የነበረው በቬንትሌተር ነበር፡፡ ኤሪን በፍሎሪዳ ፓስተር ነበረች፡፡ ጤናዋ ግን መልካም የሚባል አልነበረም፡፡ አንደኛ አስም ነበረባት፤ ሁለተኛ የእንቅልፍ እጦት ያሰቃያት ነበር፡፡ ባሏ ባደረሰባት የአስተሳሰብ ተጽእኖ ምክንያት እና በወቅቱ በቫይረሱ ዙርያ በነበራቸው እምነት ምክንያት ጥንቃቄ እንዳላደረጉ ነው የሚናገረው ብራያን፣ ለቢቢሲ፡፡ ስለዚህ ቫይረሱ እንደያዛቸው ቢያውቁም ሁለቱም ሥራቸውን ቀጥለው ነበር፡፡ እሷም ፓስተርነቷን፣ እሱም ሹፍርናውን፡፡ እሷ አልጋ ከያዘች ወዲህም ቢሆን ብራይን መደንገጥ በነበረበት ደረጃ አልደነገጠም፡፡ መድኃኒት ግዛ ሲባል በመድኃኒቶቹ እምነት ባይኖረውም እያቅማማም ቢሆን ታክሲው እያሽረከረ ይሄዳል፡፡ በጉዞው ላይ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አያደርግ? ማኅበራዊ ርቀቱን አይጠብቅ፡፡ ለነገሩ ሁለቱም ግንቦት ላይ የታመሙ ጊዜ ራሱ ቶሎ ሐኪም ለማየት አልሄዱም፡፡ በብዙ ጥርጣሬና ማመንታት ነበር ምርመራ ያደረጉት፡፡ አለባችሁ ሲባሉም አልደነቃቸውም፡፡ ምክንያቱም ኮሮናቫይረስ ብሎ ነገር የለም ብለው በውስጣቸው ያምኑ ስለነበረ፡፡ ብራይን አሁን ለቢቢሲ እንደተናገረው ‹ያን ጊዜ ሰው የሚለኝን ሰምቼ ቢሆን ኖሮ…› የሚል ጸጸት አድሮበታል፡፡ ‹‹ቫይረሱ እውነት ነው፡፡ ሰዎችን በተለያየ ደረጃ ቢያጠቃም ኮቪድ-19 ሐቅ መሆኑን አምኛለሁ፡፡ አሁን ወደኋላ ሄጄ የምቀይረው ነገር ግን የለም፡፡ አሁንን መኖር ነው የሚኖርብኝ፤ አሁን ላይ ለወደፊት የተሻለ ምርጫ እያደረጉ ከመኖር ሌላ ምን ማድረግ እችላሁ?›› ብሏል ለቢቢሲ፡፡ ‹‹ባለቤቴ ላትመለስ ሄዳለች፡፡ አንዳንድ ጊዜ ትናፍቀኛለች፡፡ ወደ ተሻለ ዓለም ተሸጋግራለች ብዬ ማመን ነው የምመርጠው፡፡ ›› ይላል ብራይን፡፡ ብራይን እንደሚለው እሱም ሆነ ሟች ባለቤቱ ቫይረሱ ሐሰት ነው ሲሉ ምን ማለታቸው እንደሆነ በግልጽ ለመናገር ይከብደዋል፡፡ መጀመርያ አካባቢ 5ጂ ያመጣው መቅሰፍት ነበር የሚመለስላቸው፡፡ ቀጥለው ደግሞ እንዲሁ መንግሥታት ሕዝቦቻቸውን ለማታለል የፈጠሩት አድርገው መውሰድ ጀመሩ፡፡ ይህን እምነት ያዳበሩት ደግሞ በፌስቡክ ላይ በሚያነቡት ነገር ነው፡፡ ‹‹እውነቱን ለመናገር እኛ በዋናነት ይመስለን የነበረው መንግሥት ሕዝቡን ለማስቀየስና በሌላ ጉዳይ ወጥሮ ለመያዝ የፈጠረው ወሬ እንጂ ቫይረሱ የምር አይመስለንም ነበር፡፡ ብራይን ባለቤቱ ጽኑ ሕሙማን ማገገምያ ከገባች በኋላ ወደ ፌስ ቡክ ተመለሰና ‹‹በኛ ይብቃ፣ ትውልድ ይዳን›› ብሎ መጻፍ ጀመረ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም ድረስ ቫይረሱ ፈጠራ ነው፤ ወሬ ነው ብለው ከልባቸው ያምናሉ፡፡ ቢቢሲ ባለፈው ግንቦት በሰራው አንድ ጥናት በርካታ ሰዎች 5ጂ የቴሌኮሚኒኬሽን የስልክ መስመሮች ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ በሕክምና ባለሞያዎቸ ላይ እንዲሁ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ በጤና ተቋማትም ላይ እንዲሁ፡፡ የብዙዎቹ የተሳሳተ እምነት ተኮትኩቶ ያደገው ታዲያ በማኅበራዊ ሚዲያ ነው፡፡ የፌስቡክ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ሲናገር እንዲህ ዓይነት አሳሳች መረጃዎች ሲመጡ ፌስቡክ እርምጃ ይወስድባቸዋል፡፡ ለምሳሌ ባለፉት ወራት 7 ሚሊዮን የሚሆኑ ከቫይረሱ ጋር የተያያዙ ሐሳዊ መረጃዎች ከገጹ እንዲወገዱ አድርገናል ብሏል፡፡ ሆኖም ተቺዎች ፌስቡክ ሐሳዊ መረጃዎችን ለማጥፋት ዳተኛ ነው ይላሉ፡፡ ቫይረሱ አሁን በመላው ዓለም 24 ሚሊዮን ሰዎችን አዳርሷል፡፡ የ800ሺህ ሰዎችን ሕይወት ነጥቋል፡፡ ይህ ሁሉ ግን ሐሰትና የተቀነባበረ ወሬ የሚመስለው ሰው ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ እውነታው ግን ሌላ ነው፡፡ አሁንም ሚሊዮኖች ኮቪድ-19 ብሎ ነገር የለም፤ ወይም መንግሥታት የፈጠሩት ቅንብር ነው ብለው ነው የሚያስቡት፡፡ በተለይም ከክትባት ጋር በተያያዘ ብዙ መላምቶች ማኅበራዊ ሚዲያውን አጥለቅልቀውታል፡፡ ቢልጌትስ የሕዝብ ቁጥርን ለመቀነስ የዘየደው ነው ከሚለው ጀምሮ፣ ገንዘብ በክትባት መልክ ለማፈስ የተፈጠረ በሽታ ነው ብለው ዛሬም ሚሊዮኖች ያምናሉ፡፡ ብዙዎች እንደ ብራያን የሚወዱትን እስኪያጡ ድረስ ከዚህ ቅዥብርብር እምነታቸው ንቅንቅ የሚሉ አይመስሉም፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-53900470
amh
health
ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን በተለያዩ ክልሎች ውስጥ ሥራውን ማቋረጡን ገለጸ
ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) በተጣለበት ዕገዳ መሠረት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የሚያከናውናቸውን ሥራዎቹን ማቋረጡን አስታወቀ። የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ እንዳለው ከኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ የተጣለበትን የሦት ወራት ዕገዳን በማክበር በአማራ፣ በጋምቤላ፣ በሶማሌና በደቡብና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ክልል ውስጥ ያለውን ሥራውን አቁሟል። ድርጅቱ በተጠቀሱት አካባቢዎች ያለውን ሥራውን ቢያቋርጥም "በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ ጉጂ፣ በደቡብ ክልልና በደቡብ ምሥራቅ ትግራይ ውስጥ የህክምናና የሰብአዊ እርዳታ አገልግሎቱን ይቀጥላል" ብሏል። የእገዳ ትዕዛዙ ከተሰጠው በኋላ የሚደረገው ምርመራ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚሰጠውን የህክምናና የሰብአዊ እርዳታ ሥራዎችን ጨምሮ ሁሉንም ተግባራቱን ለሦስት ወራት ማቋረጡን አስታውቋል። በዚህም መሠረት ኤምኤስኤፍ ባሉት ክሊኒኮች ውስጥ የነበሩ ታካሚዎች በአጭር ማስጠንቀቂያ እንዲወጡ መደረጉንና አንድ ሺህ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞቹ ከቤታቸው ሆነው እንዲጠባበቁ እንዲሁም ሁሉም በሚባል ደረጃ የውጭ አገር ዜጋ የሆኑ ሠራተኞቹ ከአገሪቱ እንዲወጡ መደረጋቸውን አመልክቷል። ድርጅቱ እነዳለው የሚያካሂደው የህክምናና የሰብአዊ እርዳታ ሥራ እንዲያቋርጥ የታዘዘው በአገሪቱ ያለው የተለያየ አይነት የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎት ከፍተኛ በሆነበት ጊዜ መሆኑን ገልጿል። የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ሥራውን ማከናወን ባቆመባቸው በምዕራብና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ውስጥ ያለው ሁኔታ ለሕዝቡም ሆነ ለእርዳታ ሠራተኞች አደገኛና ተለዋዋጭ ነው ሲል ገልጿል። በሶማሌና በአማራ ክልል ለተለያዩ ችግሮች የተጋለጡ ሰዎች እንዲሁም በጋምቤላ ውስጥ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ሁኔታ እንደሚያሳስበው የድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድኑ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል። ድርጅቱ ከሦስት ወራት በፊት ትግራይ ውስጥ ስለተገደሉት ሠራተኞቹ ጉዳይ አስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደም ሆነ ስለግድያው ሁኔታ ምንም ግልጽ ያለ ነገር እንደሌለና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተደረገ ስላለው ምርመራ የሚያደርግውን ክትትል መቀጠሉን ገልጿል። ኤምኤስኤፍ የባልደረቦቹን ግድያ ተከትሎ በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙት ማዕከላዊና ምሥራቃዊ ዞኖች ውስጥ ሲያከናውን የነበረውን እንቅስቃሴ ማቋረጡ ይታወሳል። ድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን በኢትዮጵያ ውስጥ ለ37 ዓመታት ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከክልል መስተዳድሮች ጋር በመተባበር በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች በገለልተኝነትና በሰብአዊነት የህክምና ድጋፍ ሲሰጥ መቆየቱን አመልክቷል። ድርጅቱ የሚሰጠውን ሰብአዊ አገልግሎት ለመቀጠል ያለውን ፍላጎት ገልጾ ለዚህም የተጣለበት ዕገዳ እንዲነሳና ሥራውን ለመቀጠል ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ መሆኑንም ገልጿል። የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በቅርቡ በአገሪቱ ይሰሩ የነበሩ ሦስት የበጎ አድራጎት ተቋማትን ማገዱን መግለጹ ይታወሳል። በዚህም መሠረት የሆላንድ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን፣ ኖርዌጂያን ሪፊዩጂ ካውንስል እና አል ማክቱም ፋውንዴሽን ለሦስት ወራት እገዳ እንደተጣለባቸው አስታውቆ ነበር። የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ሦስቱ የውጭ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ከመንግሥት በሰጣቸው ፍቃድ በተለያዩ የሰብዓዊ ተግባራት ላይ ተሰማርተው ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሶ፤ ኤጀንሲው በሚያደርገው ክትትል መሠረት ድርጅቶቹ ከተቋቋሙለት አላማ ውጪ ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው እግዱ እንደ ተጣለባቸው አመልክቷል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58519813
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ ጳጳሳቷን በኮቪድ-19 እያጣች ያለችው የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንደ ሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉዳትና ጫና ያሳረፈባቸው የእምነት ተቋማት በጣም ጥቂት ናቸው። በባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ በሰርቢያና ሞንቴኔግሮ የሚገኙ የቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ ኃላፊዎችን በኮሮናቫይረስ አጥታለች። የቤተክርስቲያኗ ኃላፊዎች ከኮሮናቫይረስ መከሰት በኋላ በተለመደው መንገድ የአምልኮና ሌሎች አገልግሎቶችን በመቀጠላቸው ለወረርሽኙ መዛመትና ለሞቱ ምክንያት እንደሆነ ታዛቢዎች ይናገራሉ። ባለፉት ወራትም በቤተ ክርስቲያኗ የተከሰተው ተከታታይ ሞት አስደንጋጭ ሆኗል። የቤተ ክርስቲያኗ አመራሮች በኮሮናቫይረስ የታመሙም ሆነ የሞቱ ቢኖሩም በአሁኑ ወቅት ቤተክርስቲያኗ በአብዛኛው ሰርቢያውያን ዘንድ የህይወታቸው ማዕከል ናት። በሰርቢያ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የማስተማር ሥራውን በወረርሽኙ ምክንያት በበይነ መረብ እንዲያደርጉ መመሪያ ቢወጣም ቤተክርስቲያኗ የቁርባን ሥርዓቷን አልተወችም። የአገሪቱ መንግሥት ወረርሽኙን ለመቆታጠር ከአምስት በላይ ሰዎች በአንድ ቦታ ላይ እንዳይሰባሰቡ ያስተላለፈውን ትእዛዝ በመተላለፍ ቤተ ክርስቲያኗ የአምልኮ ሥነ ሥርዓት ማካሄዷን ቀጥላለች። "ምንም እንኳን የምዕመናን ቁጥር በተወሰነ መልኩ መቀነስ ቢያሳይም አሁንም ቢሆን በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያኖች የሚደረገው የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት አልተስተጓጎለም፤ በየጊዜው ይደረጋል" በማለት የእምነት ጉዳዮች ተንታኝ ዜልጅኮ ኢንጃክ ይናገራሉ። "በሰርቢያውያን ዘንድ ቤተ ክርስቲያኗ ትልቅ ክብር አላት። ከአገሪቷም ሆነ ከየትኛው ብሔራዊ ተቋማት በበለጠ ትልቅ ክብር አላት" ይላሉ ተንታኙ። "በባልካን አገራትም ሆነ በምሥራቅ አውሮፓ የአስተዳደር ሥርዓት፣ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች፣ ርዕዮተ ዓለማትም ሆነ መንግሥት በተደጋጋሚ ቢቀያየርም ሕዝቡ በፖለቲካውም ሆነ በምጣኔ ሀብቱ ይህ ነው የሚባል ማሻሻያ አላሳየም። ለሕዝቡ ቋሚና ዋነኛዋ ነገር ቤተ ክርስቲያኗ ናት" በማለትም ያስረዳሉ። ሆኖም ሁለት ትልልቅ ጳጳሳት የቀብር ሥነ ሥርዓት ጋር ተያይዞ በቤተ ክርስቲያኗ አሰራር ላይ ትችቶች እየተሰሙ ነው። በሞንቴግሮ መዲና ፖዶጎሪጋ ለቅስተኛ ምዕመናን የኤጲስ ቆጶስ አምፊሎሂጄ ራዶቪች አስከሬን እጅና ግንባር በመሳምና በመሳለም ሲሰናበቱ ነበር። ኤጲስ ቆጶሱ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ህይወታቸው ከማለፉ በፊት የእምነት ተግባራት "የአምላክ ክትባት" ናቸው ብለው ነበር። ለቀስተኛ ምዕመናን በቤልግሬድ ሴይንት ሳቫ ቤተክርስቲያን የተካሄደውን ፓትርያርክ ኢሪነጅ የቀብር ሥነ ሥርዓት በርቀት እንዲከታተሉት ተደርገዋል። ሆኖም ከቀብራቸው በፊት በነበረው የፓትርያርኩ የስንብት ሥነ ሥርዓት ላይ መመሪያዎች አልተከበሩም ተብሏል፤ የእምነቱ ተከታዮች የሬሳ ሳጥኑ ላይ የተገጠመውን መስታወት በመሳምና በመሳለምም ክብራቸውን ሲገልፁም ነበር። በነበረውም የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ቁርባኑ ሲፈፀም የነበረው በአንድ ማንኪያ እንደሆነም ተገልጿል። ይህም ሁኔታ ለኮሮናቫይረስ የማጋለጥ እድሉም ከፍተኛ እንደሆነም የተላላፊ በሽታዎች አጥኚ ዶክተር ጁሪክ ለቢቢሲ ሰርቢያ ተናግረዋል። ቤተ ክርስቲያኗ ሥነ ሥርዓቷንና አሰራሯን እንድታሻሻልና ካልሆነም መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ባለሙያው ጥሪ አድርገዋል። ዶክተር ጁሪክ በተጨማሪም ስብሰባዎች የታገዱበት መመሪያ ወጥቶ ባለበት ሰዓት በቤተ ክርስቲያኗ ለምን ይህ ተግባራዊ እንደማይሆን ይጠይቃሉ። "ሕግና መመሪያዎች ለአንዳንዶች ተግባራዊ እንደማይደረግ መጥፎ መልዕክትን አስተላልፏል። ይህ ሁኔታ መመሪያዎችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ በተጠየቀው ሕዝብ ዘንድ አመኔታን ያሳጣልም" ይላሉ። ከፓትርያርኩ የስንብት ፕሮግራም ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ የወረርሽኙ መዛመት ሊኖር ይችላል በሚልም የጤና ባለሙያዎች ዝግጅት እያደረጉ ነው። በቅርብ ቀናት ውስጥ በሰርቢያ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱንም በመጥቀስ ሁኔታው የሚያሳዝን ነው ተብሏል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ቩሲክ በበኩላቸው "ሁላችንም ቢሆን ኃላፊነታችን ካልተወጣን ለሚያሳዝን ከፍተኛ አደጋ መጋለጣችን አይቀርም" በማለት አስጠንቅቀዋል። ቤተ ክርስቲያኗ አገልግሎት መቀጠሏን በማስመልከት ምንም ከማለት የተቆጠበች ቢሆንም የቤተ ክርስቲያኗ ኃላፊዎችም ሆኑ ቁሶች ከቅዱስ ሲኖዶሱ አቅጣጫ እንዲቀመጥላቸው እየጠበቁ መሆኑን አሳውቀዋል። ምንም እንኳን የፓትርያርኩን ሞት እንዲሁም የኤጲስ ቆጶስ ዴቪድን ሆስፒታል መግባት ተከትሎ አገልግሎት የሚሰጡ ኃላፊዎች ቁጥር ቀንሷል። ነገር ግን አሁንም ዝርዝር አቅጣጫ ይሰጣል በሚል እየተጠበቀ ነው ያለው። እስከዚያው ግን ቤተ ክርስቲያኗ ፓትርያርኳን ለማስታወስ የምታደርገውን የሰባት ቀን እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች ቀጥለዋል። በዚህ ሳምንት መጨረሻ አርብ በነበረው ስነ ስርአትም ቄሶች ጭምብል አላጠለቁም ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/news-55120402
amh
health
ኮሮናቫይረስ ፡ በሞባይል ስክሪን ላይ የምናሳልፈው ጊዜና የዓይናችን ጤና በኮቪድ-19 ዘመን
ኮሮናቫይረስ ያስከተለውን የእንቅስቃሴ እገዳ ተከትሎ የሰዎች በስልክና በኮምፒውተር ስክሪን ላይ ያላቸው የቆይታ ጊዜ የጨመረ በመሆኑ ለዓይናቸው ደኅንነት መጠበቅ የ"20-20-20" ደንብን እንዲለማመዱ አንድ የዓይን ጤና በጎ አድራጎት መክሯል። 'ፋይት ፎር ሳይት' ለ20 ደቂቃዎች ስክሪን ላይ አንዳች ነገር እያደረጉ ከቆዩ በኋላ 20 ጫማ ርቀት ላይ ያለን ነገር ለ20 ሰከንድ መመልከት ይመክራሉ። ከ2,000 ሰዎች መካከል ግማሾቹ ከኮቪድ-19 መከሰት በኋላ ከፍ ያለ ጊዜን ስክሪን ላይ እያጠፉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አንድ ሦስተኛው (38 በመቶ) የሚሆኑት የዓይን ችግራቸው መባባሱን አንድ ጥናት አመልከቷል። የዓይን ሐኪሞች ደግሞ እርዳታ ለሚገፈልጉ ሰዎች ሁሌም ክፍት ሆነው ቆይተዋል ሲል የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ገልጿል። ነገር ግን በ2 ሺህ ጎልማሶች ላይ የተደረገው ጥናት እንዳመለከተው በቫይረሱ መያዝን ወይም ማሰራጨትን በመፍራት ከአምስቱ ውስጥ አንዱ ከወረርሽኙ በፊት እንደነበረው የዓይን ምርመራ የማድረግ ዕድሉ አነስተኛ ነው ብሏል። የጥናቱ ተሳታፊዎች እንዳሉት የማንበብ ችግር፣ እንዲሁም ራስ ምታት፣ በተወሰነ የጭንቅላት ክፍል ላይ የሚከሰት ከባድ የራስ ምታት [ማይግሬን] እና ደካማ የማታ ዕይታ እንዳለባቸው ሪፖርት አድርገዋል። ሰዎች መደበኛ የዕይታ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ማስታወስ እንደሚያስፈልግ እና "አብዛኞቹ የዓይን ሐኪሞች የእንቅስቃሴ ገደብ በተጣለባቸው ወቅቶችም ለቀጠሮ ክፍት ሆነው ቆይተዋል" ተብሏል። የፋይት ፎር ሳይት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሽሪን ክራውስ "የዓይን ችግር ከሚያስከትሉ ጉዳዮች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ቀደም ብሎ በመለየትና የመከላከል ዘዴዎችን በመተግበር ሊወገዱ ይችላሉ። መደበኛ የዓይን ምርመራዎች ብዙውን ጊዜ ምልክት የሌላቸውን የዕይታ ችግሮች ለይተው ማወቅ ያስችላሉ" ብለዋል። በየመካከሉ ቀላል ዓይንን ከስክሪን ዕይታ ዞር በማድረግ እረፍት ማግኘት ዓይን ላይ የሚፈጠር ጫናን ለመከላከል ይረዳል ሲል የበጎ አድራጎት ድርጅቱ አመልክቷል። የዓይን ሐኪሞች ቀጠሮዎች ተፈቅደዋል በመንግሥት መመሪያ መሠረት ሰዎች በዕገዳ ወቅትም ቢሆን ለህክምና ቀጠሮ ከቤት መውጣት እና "ጉዳትን፣ ህመምን ወይም የመጎዳት አደጋን ማስወገድ" ይችላሉ ይላል። የዓይን ህክምና ኮሌጅ አባላት ማንኛውም የዕይታ ለውጥ ወይም ችግር ላጋጠማቸው ሰዎች በእገዳው ጊዜ የዓይን እንክብካቤ መስጠቱን መቀጠል አለባቸው ብሏል። መደበኛ ቀጠሮዎችም "አቅም በፈቀደ መጠንና ለህሙማን ጥቅም እስከሆነ ድረስ" በቀላሉ ሊመቻቹ ይገባል ይላል መመሪያው። የዓይን ህክምና ክሊኒክ አማካሪ ፓራምዴፕ ቢልኩ እንደተናገሩት የኮሌጁ ጥናት የተወሰኑ ሰዎች በመጀመሪያው ዕገዳ ወቅት ዕይታቸው መታወኩን አስተውለዋል። "ብዙ ሰዎች በስክሪኖች ፊት ብዙ ጊዜ ማሳለፋቸው ዕይታ ችግራቸውን እንዳባባሰው እንደሚያምኑ ያደረግነው ጥናት አሳይቷል" ብለዋል። "መልካሙ ዜና እንዲህ ያሉት ችግሮች በዕይታ ላይ ዘላቂ ጉዳት የማያስከትሉ መሆናቸው ነው። ሆኖም ግን ዕይታዎ እንደተዳከመ ከተሰማዎት ወይም ዓይኖችዎ ሲቀሉ ወይም ህመም ሲሰማዎ በቅርብዎ የሚገኙ የዓይን ሐኪሞችን በስልክ ወይም በድረገጽ ላይ በማግኘት ማማከር ያስፈልጋል" ሲሉ ገልጸዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የጤናና ደኅንነት ሕግ አሠሪዎች ሠራተኞች በቀን ከአንድ ሰዓት በላይ ለሥራ ስክሪን መጠቀም ካለባቸው ለሠራተኞቻቸው የዓይን ምርመራ ማድረግ አለባቸው። በበጋ ወቅት ቢያንስ 10,000 ያህል ሰዎች በብሪታንያ አስፈላጊ የሆነ የዓይን እንክብካቤ እንዳላገኙ ተልጿል። አስከፊው ጉዳይ የሮያል ብሔራዊ ዓይነ ስውራን ኢንስቲትዩት በወረርሽኙ ወቅት ሆስፒታል መሄድን በመፍራት አንዳንድ ሰዎች ዕይታቸውን የማጣት አደጋ ተጋርጦባቸዋል የሚል ስጋት እንዳለው ተናግሯል። የሮያል ኮሌጅ የዓይን ህክምና ባለሙያዎች ቃል አቀባይ "በዕይታቸው ላይ ከፍተኛ ለውጥ የተመለከቱ ሰዎች የዓይን ሐኪም ምክር መጠየቁ እና ለውጦቹ የዓይን ሐኪም ተጨማሪ ምርመራ የሚፈልግ መሆኑን መወሰን አስፈላጊ ነው" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55631982
amh
health
በርካታ ልጆች ከመጠን ካለፈ ውፍረት ጋር በተገናኘ በስኳር በሽታ እየተያዙ ነው
በዩናይትድ ኪንግደም በሁለተኛው ዓይነት የስኳር ህመም የሚጠቁ ህፃናት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ የጤና ባለሙያዎችን እንዳሳሰባቸው አንድ የበጎ ድርጅት አስጠንቅቋል። ህፃናቱ የስኳር ህመም ተጠቂ ያደረጋቸው ከመጠን ያለፈ ውፍረት እንደሆነና ይህም ከኑሮ ውድነት ጋር በተገናኘ ያለው ደካማ የአመጋገብ ስርዓት መሆኑንም የዩናይትድ ኪንግደም የስኳር ህመምተኞች ማህበር አስታውቋል። በተለይም የኑሮ ውድነቱ በከፍተኛ መጠን ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ ጤናማ የሚባሉ የምግብ አይነቶች በመወደዳቸው የበለጠ ሁኔታውን ሊያባብሰው እንደሚችልም ተገልጿል። በተለይም የኑሮ ዝቅተኛነት በሚስተዋልባቸው የእንግሊዝና ዌልስ አካባቢዎች ጫናው ከፍተኛ መሆኑንም መረጃዎች ይጠቁማሉ። በሁለተኛው ዓይነት የስኳር ህመም ከተጠቁ አስሩ ወስጥ አራቱ የኑሮ ዝቅተኛነት ከሚስተዋልባቸው አካባቢዎች ነው። ይህም አሃዝ የኑሮ ከፍተኛነት በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች ከ19ኙ አንዱ እንደሚጠቃ ያሳያል። በእንግሊዝ ዕድሜያቸው ለትምህርት ከደረሱ ህፃናት መካከል ከአስሩ አንዱ ከመጠን ያለፈ ውፍረት አለው። ከመጠን በላይ ውፍረት በሁለተኛው ዓይነት የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል። በተጨማሪም ከዘር  እንዲሁም ከቤተሰብ ታሪክ ጋር በተገናኘ በህመሙ የመጠቃት እድል አለ። የስኳር በሽታ ምንድነው? -       የስኳር በሽታ ሰዎች በደም ውስጥ ከመጠን በላይ ስኳር (ግሉኮስ) እንዲኖራቸው ያደርጋል። -       በአንደኛው አይነት ስኳር የተጠቁ ሰዎች በሰውነታቸው ውስጥ ኢንሱሊን አያመነጩም። -       በሁለተኛው ዓይነት ስኳር ህመም የተጠቁ ደግሞ የማይጠቅም ወይም በቂ ያልሆነ ኢንሱሊን ሰውነታቸው ያመነጫል። በእንግሊዝ እና በዌልስ የህጻናት የስኳር ህመም ክፍል ውስጥ ህክምና ከሚያገኙ ህፃናት መካከል በሁለተኛው የስኳር ህመም የሚጠቁ ህፃናት ቁጥር ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ከ 50 በመቶ በላይ መጨመርን ያሳያል ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/clkvvp011kno
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ ኮቪድ-19 ገና አልሰለቸንም- የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ
ዓለም የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባትን ወደማግኘት እየተቃረበ ቢሆንም የኮሮናቫይረስ መከላከያዎችን ማላላት የለበትም ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊው አሳሰቡ። ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮናቫይረስ አሁንም የዛሬ ስምንት ወር እንደነበረው አስጊ ወረርሽኝ መሆኑን እንደቀጠለ ነው ብለዋል። በመላው ዓለም በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1.2 ሚሊዮን ደርሷል። በፓሪስ እየተካሄደ ባለው የሰላም ጉባዔ ላይ "በኮቪድ-19 ታክቶን ይሆናል ነገር ግን እርሱ ገና አልሰለቸንም" ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም። "የአውሮፓ አገራት እየታገሉ ነው ነገር ግን ስርጭቱን ለማቆም የተወሰዱት እርምጃዎች እንዲሁም ቫይረሱ ምንም ለውጥ አላሳየም" ሲሉም አክለዋል። ከቅርብ ቀናት ወዲህ በኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ላይ የተሻሉ ግኝቶች እየታዩ መጥተዋል። ሰኞ ዕለት ፋይዘር እና ባዮንቴክ እየሰሩት ያለው ክትባት በተደረገለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍተሻ 90 በመቶ የመከላከል አቅም እንዳለው አረጋግጠናል ብለዋል። ረቡዕ ዕለት ደግሞ የሩስያ ተመራማሪዎች የሰሩት የመከላከያ ክትባት 92 በመቶ ውጤታማ መሆኑን አስታውቀዋል። ነገር ግን ሁለቱም ክትባቶች የሚደረግላቸውን የቁጥጥር ፍተሻ ማለፍ አለባቸው ተብሏል። ዶ/ር ቴድሮስ ገና ደህንነቱ እና ውጤታማነቱ መፈተሽ ባለበት ክትባት ላይ መተማመን አደገኛ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል። "ክትባት በፍጥነት ያስፈልጋል፣ ነገር ግን እጃችንን አጣጥፈን ቁጭ አንልም" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/54920166
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ጽኑ ህሙማንን የሚከታተሉ ሐኪሞች ስጋትና ጭንቀት
በኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮናቫይረስ መገኘቱ ከታወቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ቀን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ገለጸ። ትናንት ሐሙስ በተደረገ ምርመራ በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ከፍተኛው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች አሃዝ ተመዝግቧል። በዚህም ምርመራ ከተደረገላቸው 8,055 ሰዎች መካከል በሽታው በ2,057 ሰዎች ላይ መገኘቱን ኢኒስቲቲዩቱ ያወጣው መረጃ አመልክቷል። ይህ ማለት ከተመረመሩት 100 ግለሰቦች ውስጥ 26 ወይም 25.5 በመቶው የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል በማለት "በማኅበረሰብ አቀፍ የምርመራ ዘመቻ ወቅት እንኳን ይህን ያህል ከፍተኛ ቁጥር አልተመዘገበም" ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም በኮቪድ-19 ክፉኛ ታመው በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ክትትል የሚደረግላቸው ሰዎች ቁጥርም ከዚህ በፊት ከተመዘገበው በበለጠ ከፍተኛው ቁጥር ላይ ደርሷል። በዚህም ሐሙስ ዕለት 600 ሰዎች በጽኑ የታመሙ ሰዎች እንዳሉ ተገልጿል። ከሰሞኑ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ "በአስደንጋጭ ሁኔታ" እየጨመረ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር እና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የሰጧቸው መግለጫዎች ያመለክታሉ። ቢሆንም ግን ወረርሽኙ እየፈጠረ ያለውን ከባድ አደጋ ከግንዛቤ በማስገባት ተገቢውን የመከላከያ ጥንቃቄ "ከማድረግ ይልቅ መዘናጋት በሰፊው እንደሚታይ" ቢቢሲ ያናገራቸው የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። በርካታ ቁጥር ያለው ሕዝብ የተሳተፈባቸው የተለያዩ ስብሰባዎችና ዝግጅቶችን የታዘቡት የጤና ባለሙያዎች ችግሩ ሕብረተሰቡ ጋር ብቻ ሳይሆን መንግሥት የጤና ሚኒስቴር የሚያስቀምጣቸውን የኮሮናቫይረስ መከላከያ መመሪያዎች "ለማስፈፀም ተነሳሽነት ይጎድለዋል" አስብሏቸዋል። ይህንንም ተከትሎ ከጊዜ ወደ ጊዜ የበሽታው መስፋፋት እጨመረ ባለፉት ሳምንታት ውስጥ በወረርሽኙ የሚያዙ፣ በጽኑ የሚታመሙና ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ከመድረሱ ባሻገር የጤና ተቋማት ህሙማንን ለማስተናገድ ፈተና እየገጠማቸው ነው። በዚህም ሳቢያ በመላው አገሪቱ በጽኑ ለታመሙ ሰዎች አጅጉን አስፈላጊ የሆኑት የኦክስጅንና የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) እጥረት በመከሰቱ በርካታ የኮቪድ-19 ታማሚዎች ህይታቸውን እንዲያጡ ሊያደርግ እንደሚችል ስጋት ፈጥሯል። "በአንድ ጊዜ በርካታ ኦክስጅን የሚፈልጉ ህሙማን ወደ ህክምና ተቋማት ይመጣሉ" የሚሉት ዶ/ር ብሩክ አለማየሁ ኦክስጂን ባለመኖሩ ብቻ ህሙማን ወደ ቤታቸው ለመመለስ የሚገደዱበት ጊዜ ላይ መደረሱን ይናገራል። "በርካታ ሰዎች በግላቸው የኦክስጂን ሲሊንደር እየገዙ ወደ ቤታቸው እየገቡ ነው" በማለት፣ ሆስፒታል አልጋ ይዘው የሚታከሙም ቢሆኑ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ ለማግኘት ረዥም ወረፋ እንደሚጠብቁ ይገልጻሉ። በኮቪድ-19 ተይዘው በቤታቸው ውስጥ እራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ ከሚደረጉት ባሻገር ወደ ህክምና ተቋማት የሚመጡ ህሙማንን የመቀበል አቅማቸው እየተሟጠጠ መሆኑንም አልሸሸጉም። በኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል የጽኑ ህክምና ክፍል ኃላፊ ዶክተር ህሩይ አርዓያ ለፋና እንደተናገሩት ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ወደ ማዕከሉ የሚመጡ የቫይረሱ ታማሚዎች ቁጥር እንዲሁም ወደ ጽኑ ህክምና ክፍል የሚገቡ ታካሚዎች ቁጥር እያሻቀበ ነው ብለዋል። የሚሊኒየም ኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ዳይሬክተር ዶክተር ውለታው ጫኔ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ወደ ማዕከላቸው ከሚመጡ ሕሙማን መካከል ከ75 በመቶ በላይ ኦክስጅን የሚፈልጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። በማዕከሉ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር መበርከቱን ገልፀው "በመካኒካል ቬንትሌተር እጥረት ምክንያት የማንቀበላቸው ህሙማን ይኖራሉ" ብለዋል። ዶ/ር ውለታው ጨምረውም የኦክስጅን እጥረት ስለገጠማቸው ድጋፉን ፈልገው የሚመጡ ሁሉንም ጽኑ ህሙማን ማስተናገድ አለመቻላቸውን ገልፀዋል። የጽኑ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ ነው ዶ/ር ብሩክ ዓለማየሁ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ መጨመር እያሳየ መምጣቱን እነዳስተዋሉ የጠቆሙ ሲሆን፤ ዶ/ር ውለታው ጫኔም በበኩላቸው በተለይ ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት በኮቪድ-19 በጠና ታምመው ወደ ማዕከላቸው የሚመጡ ሰዎች በመርከቱን ተናግረዋል። በየተቋማቱ ለህሙማን አልጋ በመጥፋቱ አስቸጋሪ ሁኔታ መፈጠሩን የሚናገሩት ዶ/ር ብሩክ፣ ይህም በህክምና ባለሙያዎች ላይ ጫና መፍጠሩን አስረድተዋል። እርሳቸው እንደሚሉት ኮቪድ-19 የተያዙ ሕሙማን እየበዙ በመምጣታቸው በሌላ የሕክምና ክፍል ያሉ አልጋዎችን እስከ መሻማት ተደርሷል። ዶ/ር ብሩክ በሚሰሩበት ህክምና ተቋም ከዚህ በፊት አንድ ታካሚ በኮቪድ-19 ተይዞ ኦክስጂን ባያስፈልገው እንኳን ተኝቶ ህክምና እንዲያገኝ ይደረግ እንደነበር አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት ግን አስተኝቶ ለማከም ህሙማኑ ኦክስጅን የሚያስፈልጋቸው መሆን አለመሆኑ ይወስነዋል ይላሉ። "አሁን የምናስተኛቸው ታካሚዎች በሙሉ ኦክስጂን ፈላጊዎች ናቸው።" እንደ ዶ/ር ብሩክ ከሆነ ሁሉም ተኝተው የሚታከሙ ሰዎች ኦክስጂን የሚፈልጉ መሆናቸውን ገልጸው፤ በአሁኑ ጊዜም የኦክስጂን ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል ብለዋል። ይህንን ሲያብራሩም በአሁኑ ጊዜ ተኝተው የሚታከሙ ህሙማን በሙሉ ኦክስጅን ፈላጊ ሲሆኑ የሚፈልጉት የኦክስጅን መጠን ከፍተኛ መሆኑን አመልክተዋል። "ከአምስት እና ከአስር ሊትር በላይ መጠን ያለው ኦክስጂን፣ የመተንፈሻ መሳሪያ ድጋፍ የሚፈልጉ ህሙማን ቁጥር ጨምሯል።" ይህ የግብአት እጥረት በተወሰኑ ተቋማት ላይ ብቻ የታየ ሳይሆን ዶ/ር ብሩክ እንደሚሉት የኮቪድ-19 ህሙማንን በተለይ በሚያክሙት በሚሌኒየም እና ኤካ ኮተቤ ሆስፒታሎች ጭምር እንደሚስተዋል ከባልደረቦቻቸው ተረድተዋል። በተጨማሪም በግል ሆስፒታሎች የረር፣ ቤተዛታ፣ ሃሌሉያ የሚሰሩ ባለሙያዎችም ተመሳሳይ ነገሮችን ማስተዋላቸውን እንደነገሯቸው ይጠቅሳሉ። ዶ/ር ብሩክ እርሳቸው የሚሰሩበት ተቋም ከፍተኛ የኦክስጂን ተጠቃሚ ህሙማንን መቀበል የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱንም ይናገራሉ። ይህ የኦክስጂን እጥረት በአዲስ አበባ እና በክልል በሚገኙ ሆስፒታሎች እንደሚስተዋል የሚናገሩት ዶ/ር ብሩክ፣ ችግሩን ለመቅረፍ የጤና ሚኒስቴር የተለያዩ እርምጃዎችን ለመውሰድ እንቅስቀሴ እያደረገ መሆኑን እንደሚያውቁ አስረድተዋል። ዶ/ር ብሩክ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቀነስ ከተቀመጡ መመሪያዎች ሁሉ ቢያንስ ቢያንስ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አጠቃቀምን መጨመር በወረርሽኙ ስርጭት ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጣ ይመክራሉ። የበሽታው መስፋፋት ከዚህም በላይ እንዳይጨምር በግለሰብ ደረጃ የመከላከያ እርምጃዎችን ከመውሰድ ባሻገር በርካታ ሰዎች የሚሰበሰቡባቸውን ዝግጅቶችና ሥነ ሥርዓቶችን በተመለከተ የተቀመጡ መመሪያዎችን አጠናክሮ ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ነው ሲሉ አሳስበዋል። አዲስ የኮቪድ-19 ዝርያ ተከስቶ ይሆን? ዶ/ር ብሩክ በሚሰሩበት እና በሌሎች የኮቪድ-19 ህክምና በሚሰጥባቸው ተቋማት የሚሰሩ ባልደረቦቹ ለኮሮናቫይረስ ታማሚዎች መጨመር አንዱ ምክንያት የጥንቃቄ ጉድለትና መዘናጋት ነው ይላሉ። በዚህ ወቅት እንዲህ በሽታው እንዲንሰራፋ ያደረገው ሌላም ምክንያት ሊኖር እንደሚችል ጥርጣሬ አላቸው። "ደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ ውስጥ እንደተደረገው በቫይረሱ ላይ ጥናት ቢደረግ አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ሊኖር ይችላል" ሲሉ ይሰጋሉ። ይህንንም ሲያስረዱ መጀመሪያ ላይ በኮቪድ-19 ተይዘው እና ታመው ወደ ህክምና ተቋማት ከሚመጣ ሰዎች መካከል ህመሙ የሚጠናባቸው በጣም አነስተኛ ቁጥር ያላቸው እንደነበሩ ይጠቅሳሉ። በተጨማሪም በአንድ ቤተሰብ ውስጥ አንድ ሰው ታሞ ሌሎች የቤተሰብ አባላት ሳይታመሙ ይገኙ እንደነበርም አስታውሰው፤ ምልክት የማያሳዩ ህሙማን ቁጥርም በርካታ እንደነበሩ ጠቅሰዋል። አሁን ግን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መታመማቸው፣ በእድሜም ሲታይ በርካታ ወጣቶች በበሽታው መያዛቸውና ወደ ህክምና ተቋማት መጥተው አልጋ መያዛቸውን ማስተዋላቸውን ይናገራሉ። ከዚህ በፊት በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቢኖሩም በሚሰጣቸው ህክምና በፍጥነት የማገገም ይታይባቸው እንደነበር የገለጹት ዶ/ር ብሩክ፣ በዚያን ወቅት አልጋ ይዘው የሚቆዩ ሰዎች ቁጥር በጣም አነስተኛ ነበር ይላሉ። በአሁኑ ጊዜ የቫይረሱ የመተላለፍ አቅም እና የመግደል አቅሙ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው "በእርግጥ ጥናት ያስፈልገዋል፤ በእኔ እይታ አዲስ ዓይነት የቫይረስ ዝርያ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት አለኝ" ብለዋል። ጨምረውም በዚህ ወቅት ከአንድ ቤተሰብ ሁለት ሦስት ሰው የሚታመምበት እና አልጋ የሚይዝበት አጋጣሚ ተደጋጋሚ መሆኑን ዶ/ር ብሩክ ዓለማየሁ ይናገራሉ። ለበሽታው እንዲህ በአሳሳቢ ሆኔታ መስፋፋት ሁሉም ሰው ማድረግ ያለበት የመከላከያ ጥንቃቄን አለመተግበር መሆኑን ዶ/ር ውለታው ጫኔ እና ዶ/ር ብሩክ ዓለማየሁ የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። በአዲስ የወረርሽኙ ዝርያ ተከስቶ ሊሆን ይችላል የሚለው የዶ/ር ብሩክ ጥርጣሬ እነዳለ ሆኖ፤ ሁለቱም የህክምና ባለሙያዎች እዚህ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ተገቢው ምርመራ መደረግ እንዳለበት ይናገራሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-56442845
amh
health
እንግሊዛዊው 35 ኪሎግራም የሚመዝኑ ኩላሊቶቹ በቀዶ ህክምና ተወገዱለት
በአንግሊዝ ነዋሪ የሆነ አንድ ግለሰብ ሁለቱም ኩላሊቶች በከፍተኛ ደረጃ ትልቅ መሆናቸውን ተከትሎ እንዲወጡለት መደረጉን ሐኪሞች ተናገሩ። የ 54 ዓመቱ ዋረን ሂግስ በአጠቃላይ 35 ኪሎ ግራም የሚመዝኑትን የአካል ክፍሎቹን ለማስወገድ የሁለት ሰዓት ቀዶ ጥገና አድርጓል። ግለሰቡ ኩላሊቶቹ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ትልቅ ከመሆናቸው የተነሳ ክብረ ወሰንም ይዟል ተብሏል የአንድ ወድ ልጅ አባት የሆነው እና ፖሊሲስቲክ የተባለ የኩላሊት በሽታ ያለበት ግለሰቡ "በየትኛውም መንገድ ቢለካ" ትልቅ ኩላሊት ያለው በመሆን ክብረ ወሰን እንደሚሰብር ሐኪሞቹ እንደነገሩት አስታውቋል። በሆዱ መጠን ላይ ያለውን ልዩነት "አስገራሚ ነው" ብሏል። ከእንግሊዟ ዊንድሶር የመጣው ሂግስ ትልቁ የቀኝ ኩላሊቱ 15 ኪሎ ሲመዝን ተጨማሪ 5 ኪሎ የሚመዝን ፈሳሽም በላዩ ላይ ነበር ብሏል። ቀደም ሲል በዓለም ላይ ትልቅ የነበረው ኩላሊት በሕንድ በቀዶ ጥገና የተወገደው እና 7.4 ኪ.ግ የሚመዝነው እንደሆነ ይታመን ነበር። "የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ሁሉንም አረጋግጦ ነበር። እናም አዎ በእያንዳንዱ መለኪያ ክብረ ወሰኑን አሻሽለነዋል።" ብሏል። "ርዝመቱ በሚለካበት ጊዜ፣ ከያዘው ፈሳሽ ጋር ሲመዘን እና ፈሳሹ ከተወገደ በኋላም አሻሽዬዋለሁ።" ያለው ግለሰቡ ሆኖም "ይህ የምኮራበት ነገር አይደለም።" ይላል ፒኬዲ በኩላሊት ውስጥ ሲስቲክ የሚባሉ ትናንሽ ፈሳሽ የተሞሉ ከረጢቶች እንዲፈጠሩ ያደርጋል። ከአምስት ዓመት በፊት በውርስ የሚመጣው ህመም ኩላሊቶቹ ከሚገባው በላይ አምስት እጥፍ እንዲያድጉ አድርጓቸዋል ሲሉ ዶክተሮቹ ተናግረዋል። ኩላሊቶቹ ሳንባውን፣ ሆዱን እና ልቡን መጉዳት ስለጀመሩ "ሕይወት አድን" ቀዶ ጥገና መደረጉ አስፈላጊ መሆኑ እንደተነገረው ሂግስ አስታውቋል። በተጨማሪ ትልቅ የሆድ እብጠት እንዲኖረው ምክንያት ሲሆን እብጠቱ ከሐምሌው ቀዶ ጥገና በኋላ "አስደናቂ" ለውጥ አምጥቷል ብሏል። ግለሰቡ በአሁኑ ወቅት ወደ ጂምናዚየም የተመለሰ ሲሆን በሚቀጥለው ዓመትም በኤሌክትሪክ ብስክሌት ትሪያትሎን (ሩጫ፣ ዋና እና ሳይክልን ያካተት ውድድር) ላይ ለመወዳደር በጉጉት እየተጠበቀ ነው። የቀድሞው የሂሳብ ባለሙያው በየሁለት ቀኑ የዲያሊሲስ ማድረጉ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰበት መሆኑን ጠቅሷል። "በዲያሊሲስ ማለፍ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መግለጽ አልችልም" ብሏል። በሚቀጥለው ዓመት ለኩላሊት ንቅለ ተከላ ብቁ ለመሆን በመዝገቡ ውስጥ እንደሚገባ ተስፋ ያደርጋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58825476
amh
health
ኮሮናቫይረስ ፡ በየደቂቃው በዓለም ዙሪያ ኮቪድ-19 የሚይዛቸውና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርን የሚያሳይ ካርታ
ከቻይናዋ ሁቤይ ግዛት ተነስቶ ሰው ከማይኖርበት አንታርክቲክ ውጪ ሁሉንም የዓለማችንን አህጉራትን ያዳረሰው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአሁኑ ወቅት የምድራችን ዋነኛ የጤና ስጋት ሆኗል። ኮቪድ-19 በመባል የሚታወቀው ይህ ወረርሽኝ የመተንፈሻ አካልን የሚያጠቃ ሲሆን፤ መጀመሪያ ትኩሳት ቀጥሎም ደረቅ ሳል ከሳምንት በኋላ ደግሞ የትንፋሽ ማጠርን ያስከትላል። እስካሁን በቫይረሱ ከ186 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የተያዙ ሲሆን ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል። በበሽታው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተያዙና ከሞቱ ከአንድ ዓመት በኋላ የተለያዩ አይነት ክትባቶች ተገኝተው ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ለሰዎች እየተሰጡ ይገኛሉ። ነገር ግን አሁንም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም፣ የእጅን ንጽህና በተደጋጋሚ መጠበቅና በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በሽታውን ለመከላከል ዋነኞቹ መንገዶች መሆናቸውን ባለሙያዎች አጥብቀው ይመክራሉ። በየደቂቃው በዓለም ዙሪያ ባሉ አገራት ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ፣ ከበሽታው የሚያገግሙና በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎችን አሃዝ ቀጥሎ ከተቀመጠው ዝርዝር ላይ ይመልከቱ። የኮሮናቫይረስ ሁለት ዋነኛ ምልክቶች ከፍተኛ ትኩሳትና ደረቅ ሳል ናቸው። በአንዳንድ ታማሚዎች ላይ እነዚህ ምልክቶች ወደ ትንፋሽ ማጠር ይወስዳሉ። ደረቅ ሳል ሲባል በጣም ጠንካራ የሆነ አንዳንድ ጊዜ ለአንድ ሰዓት የሚቆይ ነው። ከዚህ በፊት ደረቅ ሳል ካለብዎ የኮሮናቫይረስ ሳል በጣም ለየት ያለና ከባድ መሆኑን ማስተዋል ይችላሉ። ከፍተኛ ትኩሳት የሚባለው ደግሞ የሰውነት ሙቀት መጠን ከ37.8 ዲግሪ ሴልሲየስ ሲልቅ ነው። ይህ ትኩሳት ሰውነት እንዲግል ወይም ደግሞ ከፍተኛ ብርድና መንቀጥቀጥ እንዲሰማን ያደርጋል። ከእነዚህ ሁለቱ ዋነኛ ስሜቶች ባለፈ ራስ ምታትና ተቅማጥ አንዳንድ የበሽታው ታማሚዎች ያሳይዋቸው ምልክቶች ናቸው። የማሽተትና የመቅመስ አቅም ማጣትም ምልክቶች ሆነው ተመዝግበዋል። ምልክቶቹ ቫይረስ ሰውነት ውስጥ በገባ በአምስት ቀናት ሊታዩ ይችላሉ። የዓለም ጤና ድርጅት ዘገባ ምልክቶቹ እስከ 14 ቀናት ድረስ ሳይታዩ ሊቆዩ እንደሚችሉ ያስረዳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-51868474
amh
health
ሰዎች ለምን ራሳቸውን ስለማጥፋት ያስባሉ?
ራስን ማጥፋት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ትልቅ የሞት መንስኤ የሚታይ ጉዳይ ነው። በመላው ዓለም በሚገኙ ወጣቶች ዘንድም ሶስተኛው ትልቁ የሞት መንስኤ ራስን ማጥፋት ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ቢያንስ 700 ሺህ ሰዎች ራሳቸውን የሚያጠፉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከሶስት አራተኛው በላይ የሚሆኑት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች እንደሆነ ከኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ድረ-ገፅ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። በምስራቅ አፍሪካ አገራትም ራስን የማጥፋት አኃዝ በዓመት ከ100 ሺህ ህዝብ ከ5.02-15.71 እንደሚደርስ የተባበሩት መንግሥታትን ዋቢ አድርጎ ማህበሩ ከጥቂት ወራት በፊት ባወጣው ጽሁፍ አመልክቷል። በኢትዮጵያ ያለው አመታዊ ራስን የማጥፋት መጠን መካከለኛ እንደሆነ የሚጠቅሰው በድረ-ገጹ የወጣው ፅሁፍ በዓመት ከ100,000 ህዝብ 9.63 ሲሆን ይህም ማለት በየቀኑ 30 ሰዎች ራሳቸውን ያጠፋሉ ማለት ነው። እዚህ ጋር በጉዳዩ ላይ በቂ በሚባል ደረጃ ጥናቶችና ምርምሮች አለመደረጋቸው እንዲሁም ማህበረሰቡ ስለ ጉዳዩ ያለው እውቀት ዝቅተኛ መሆኑና እንደ ችግር የሚወራ ባለመሆኑ የበርካቶች ሞት መንስኤ ሳይወራ ወይም ተደብቆ ያልፋል። አንድ የቤተሰብ አባል እራሱን ሲያጠፋ ማህበረሰቡ ሰዎች ምን ይሉኛል? በሚል ፍራቻ የሞቱን መንስኤ ይደብቃል አልያም ሌላ ምክንያት ለመስጠት ይሞክራል። ይህ ደግሞ ችግሩን ይበልጥ ያባብሰዋል። ስለጉዳዩ በግልጽ አለመወራቱ አንድ ሰው እራሱን ሲያጠፋ ሰዎች ለምን ብለው እንዳይጠይቁና ከሌሎች ተሞክሮዎች እንዳይማሩ ያደርጋቸዋል። በጅማ ዩኒቨርሲቲ የስነ አእምሮ መምህር የሆኑት ዶክተር ኤሊያስ ገብሩ እንደሚሉት ምንም እንኳን በቂ በሚባል ደረጃ ጥናቶች ባይሰሩም በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሐይማኖቶች ጠንካራ አማኞች ባሏቸው አገራት እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ ነው። ለዚህ ደግሞ ዋነኛ ምክንያቱ በእስልምናም ሆነ በክርስትና ሐይማኖቶች እራስን ማጥፋት እንደ ሀጢያት መቆጠራቸው ነው። በሌላ በኩል ራስን ማጥፋት በሁሉም ሐይማኖቶች መከልከሉ ሰዎች እራሳቸውን ሲያጠፉ የተጎጂ ቤተሰቦች ጉዳዩን ለሰዎች እንዳያጋሩና እንዲደብቁት ያደርጋቸዋል። በአጠቃላይ የኮቪድ-19 ወረርሽን ተከትሎ እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር በአሳሳቢ ደረጃ ጨምሮ እንደነበር የሚገልጹት ዶክተር ኤልያስ ፣ ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ውስጥ ይፋዊ የሆነ ጥናት ባይካሄድበትም እንደ ባለሙያ ሲታይ ግን ቀላል የማይባሉ ሰዎች ወረርሽኙን ተከትሎ እራሳቸውን ስለማጥፋት አስበዋል፣ ሞክረዋል አልያም ራሳቸውን አጥፍተዋል ይላሉ። ''እኔ ባለሁበት አካባቢ እንኳን 7 የሚሆኑ ወጣቶች በሁለት ወር ውስጥ እራሳቸውን አጥፍተው ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ሰዎች የማያወሯቸውና ሌሎች ሰዎች ሊሰሟቸው የማይችሉ በርካታ ሞቶች ሊመዘገቡ እንደሚችሉ መገመት ቀላል ነው'' ሰዎች እራሳቸውን ወደማጥፋት የሚገፋቸው ምንድነው? ባለሙያው እንደነገሩን እራሳቸውን ከሚያጠፉ ሰዎች ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት ጊዜያዊም ሆነ ቀጣይነት ባለው የስነ አእምሮ ጤና መቃወስ ተጠቂ ናቸው። ስለዚህ እራስን ማጥፋት አልያም ስለማጥፋት ማሰብ አብዛኛውን ጊዜ ከስነ አእምሮ ጤና ጋር የተያያዘ ነው ማለት እንችላለን። ለመሆኑ የትኞቹ የአእምሮ ጤና መቃወሶች ናቸው ሰዎች ራሳቸውን እንዲያጠፉ አልያም እራሳቸውን ስለማጥፋት እንዲያስቡ የሚያደርጋቸውን ስንል ለዶክተር ኤልያስ ጥያቄ ሰነዘርን። ''በተለይ ከፍተኛ ድብርትና ጭንቀት ሰዎችን ወደዚህ መስመር የሚገፉ ዋነኛ መንስኤዎች ናቸው። እነዚህን የአእምሮ ጤና እክሎች በአግባቡ መረዳትና ማከም ስንችል እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ እንችላለን።" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ከፍተኛ ድብርት ምክንያት የሌለው ጭንቀት፣ የባዶነት ስሜት፣ ደጋግሞ እራስን መውቀስ፣ ምንም የማልጠቅም ሰው ነኝ እያሉ ማሰብ፣ ተስፋ መቁረጥ፣ የሚረዳኝ ሰው የለም ብሎ ማሰብ፣ ከባድ ድካምና አቅም ማጣት፣ የእንቅልፍ መዛባት (ብዙ መተኛት አልያም እንቅልፍ ማጣት)፣ ስራና የግል ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማጣት እንዲሁም የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋነኛ ምልክቶቹ ናቸው። በሌላ በኩል ከባድ ጭንቀት በዋነኛነት የወደፊቱን ነገር ካለማወቃችን ጋር ተያይዞ ምን ይፈጠር ይሆን እያልን የምንጨነቀው ነው። በአንድ ጊዜ ስለብዙ ነገሮች አብዝቶ መጨነቅ፤ ነገን እንዴት ነው የምሆነው ብሎ ሌሎች ስራዎችን ትቶ ቁጭ ብሎ ማሰብና ሕይወታችንን እስከ ማወክ ሊደርስ ይችላል። እነዚህ የአእምሮ ጤና እክሎች ደግሞ በሰዎች የስራ ሕይወት፣ ትምህርት፣ የፍቅር ግንኙነት እንዲሁም ከቤተሰብና ጓደኞች ጋር የሚኖረንን ግንኙነት በእጅጉ ያበላሸዋል። ከባድ ጭንቀትና ከባድ ድብርት አብዛኛውን ጊዜ ተያይዘው የሚመጡ ነገሮች ሲሆኑ በአግባቡና በጊዜ ካልታከሙ ደግሞ ሰዎችን እራስን ማጥፋት ወደሚለው ጎዳና ሊመሩ ይችላሉ። የትኞቹ የማህበረሰብ አባላት ተጋላጭ ናቸው? ዶክተር ኤልያስ እንደሚሉት ከእድሜ አንጻር አፍላ እድሜያቸው ላይ የሚገኙ ወጣቶችና በአርባዎቹና ሀምሳዎቹ ውስጥ የሚገኙ ጎልማሶች አካባቢ እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር ከፍ ይላል። በተለይ በአስራዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ታዳጊዎች ማንነታቸውን ማወቅ የሚጀምሩበትና በርካታ የሕይወት ጥያቄዎችን መመለስ የሚጀምሩበት ወቅት መሆኑ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። ''ታዳጊዎች ላይ የምናያቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ። ታዳጊዎች 20 ዓመት እስከሚሞላቸው ድረስ እራሳቸውን የሚያገኙበት፣ ማንነታቸውን የሚቀርጹበት ጊዜ እንደመሆኑ ብዙ ጊዜ ግራ መጋባት ውስጥ ሊከታቸው ይችላል። ከትምህርት፣ ከቤተሰብ ግንኙነት፣ ከጓደኞች እንዲሁም ከተቃራኒ ጾታ ግንኙነት አንጻር ብዙ አይነት መቀያየሮችና ግራ መጋባቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ'' እነዚህን መቀያየሮችና እራስን የማግኘት ሂደት ውስጥ ደግሞ ታዳጊዎች ስሜታዊ መሆን፣ ራሳቸውን መቆጣጠር አለመቻል፣ ቶሎ ተስፋ መቁረጥ እንዲሁም ማንም ሰው አይረዳኝም ብሎ ማሰብ ውስጥ ይገባሉ። ታዳጊዎች በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ ሲሆኑ ብዙ ነገሮችን ይሞክራሉ፤ ይጠይቃሉ። እነሱ በሚገባቸውና በሚረዱት ልክ መልስ የማያገኙ ከሆነ ደግሞ የህይወት ትርጉሙ ሊጠፋባቸውና ከዚህ ሁሉ ጭንቀት ብገላገልስ የሚል አስተሳሰብ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ። ''ይህ የእድሜ ክልል ከማህበረሰቡ ከፍተኛ ክትትልና ተጽዕኖ የሚደረግበት ነው። በተጨማሪ ደግሞ በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ታዳጊዎች ከጓደኞቻቸውና ከቤተሰባቸው ጋር ያላቸው መስተጋብር ከራሳቸው በላይ ትልቅ ቦታ የሚሰጡት ነገር ነው። በአጭሩ በዙሪያቸው ባሉ ሰዎች በቀላሉ ተፅእኖ ውስጥ ይገባሉ። በራሳቸው ብዙ ነገሮችን መወሰን አይችሉም''ይላሉ። ይህንን ተከትሎ አንድ አስጨናቂና ከእነሱ ቁጥጥር ውጪ የሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው በቶሎ ተስፋ የመቁረጥና ራስን ወደ ማጥፋት ሊያመሩ ይችላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ይህ የእድሜ ክልል ጥቂት የማይባሉ የአእምሮ ህመሞች እራሳቸውን የሚገልጡበት ወቅት ነው። በዘር የሚመጡት ህመሞችም ሆነ ሌሎች የአእምሮ ህመሞች በትክክል ህመም ሆነው መታየት የሚጀምሩት በዚህ እድሜ ውስጥ ነው። ሌላ መረሳት የሌለበት ጉዳይ ብለው ዶክተር ኤልያስ ያነሱት ጉዳይ ደግሞ ወጣቶች በዚህ እድሜ ክልል ውስጥ ሲሆኑ በራሳቸውም ሆነ በጓደኞቻቸው ገፋፊነት ወደተለያዩ ሱሶች ውስጥ መግባታቸው አስተዋጽኦ እንዳለው ነው። ከታዳጊዎች ጋር በተገናኘ በተለይ ወላጆችና ማህበረሰቡ በእዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ልጆችን በአግባቡ መረዳትና በተቻለ መጠን ድጋፍ ማድረግ ያለበት ወቅት እንደሆነ ዶክተር ኤልያስ ያሳስባሉ። ''እነዚህ ታዳጊዎች የራሳቸው ፈቃድ እንዳላቸውና በራሳቸው ነገሮችን ማመዛዘን እንደሚችሉ ማህበረሰቡ መረዳት አለበት። ያለአግባብ አዳዲስ ነገሮችን እንዳይሞክሩ መከልከልና ከፍተኛ ቁጥጥር ማድረግ እንዲያውም ወዳልሆነ ውሳኔ እንዲሁም ባህሪ ነው የሚገፋቸው'' ይላሉ። አክለውም '' በህይወታቸው የራሳቸውን መንገድ እንዲያገኙ መደገፍና ትክክለኛውን አካሄድ ማሳየት ነው እንጂ በጭፍን መከልከልና እኛ የምንለውን ነገር ብቻ አድርጉ ማለት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። በዚህ እድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ታዳጊዎች ነጻነትና እምነት ወሳኝ ናቸው'' በማለት ያስረዳሉ። ታዳጊዎች አእምሯቸው እያደገና ጥያቄዎችን መጠየቅ ሲጀምሩ በተለይ ከሃይማኖት፣ ትምህርት፣ የፍቅር ግንኙነትና የወደፊት እቅዶች ጋር በተያያዘ ብዙ ግራ መጋባት ውስጥ ይወድቃሉ። ቤተሰብና ማህበረሰቡ ይህንን ተረድቶ ተገቢውን ድጋፍ ባላደረገላቸው ቁጥር ነገሮች እንዳሰቡት ሳይሆኑ ሲቀሩ በቶሎ ተስፋ መቁረጥና እጅ መስጠት ውስጥ ይገባሉ። ሌላኛው ራስን በማጥፋት ትልቅ ቁጥር የሚመዘገብበት የእድሜ ክልል የጎልማሶች ነው። በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ብዙውን ጊዜ በህይወታቸው ባደረጓቸው ነገሮች ደስተኛ አለመሆንና ቁጭት ይስተዋልባቸዋል። ''ወደ ኋላ መለስ ብለው ህይወታቸውን የመቃኘትና ሀዘን ውስጥ መግባት ይስተዋላል። በውሳኔዎቻቸው መጸጸትና ከፍተኛ ጭንቀትና ድብርት ውስጥ መግባትም ይታይባቸዋል'' የማህበረሰብ ኃላፊነት ዶክተር ኤልያስ እንደሚሉት ሰዎች ራሳቸውን ሊያጠፉ የሚችሉት አልያም ራሳቸውን ስለማጥፋት የሚያስቡት በሁለት ዋነኛ ምክንያቶች ነው። የመጀመሪያው ከላይ በተጠቀሱት ሌሎች የአእምሮ ጤና መታወክ ምክንያት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ድንገተኛ የሆነ አሳዛኝ ወይም አስደንጋጭ ክስተት ሲያጋጥም ነው። ''በሆነ አጋጣሚ ከሰዎች ጋር ሲጣላ ወይም የሚያስጨንቅ ነገር ሲያጋጥማቸው በቃ እኔ ብሞት ይሻለኛል። ምንም የማልጠቅም ሰው ነኝ የሚሉ ሰዎች ስናገኝ በቀላሉ ማለፍ የለብንም። ጓደኞችም ሆነ ቤተሰቦች ቀርበው ለምን መሞት እንደሚፈልግ ወይም ብዙ ጊዜ ስለመሞት ያስብ እንደሆነ መጠየቅና መረዳት አለባቸው። መርዳት በሚችሉት ሁሉ መንገድ ለመርዳት መጣር ኃላፊነታቸው ነው'' ''በማህበረሰባችን ውስጥ እንደ ቀልድ የሚባሉ ለምሳሌ ፈጣሪዬ ውሰደኝ በቃ፤ የኔ ሕይወት ትርጉም የለውም አይነት ንግግሮችን ሰዎች ሲያዘወትሩ በጊዜያዊ ንዴት ውስጥ ሆነው ነው ወይስ የምር መሞት ይፈልጋሉ ብለን ማጣራት አለብን'' ሲሉ ያሳስባሉ። በሌላ በኩል ከዚህ በፊት እራሱን ለማጥፋት ሞክሮ የሚያውቅ ሰው ከሆነ ቤተሰብም ሆነ ሌሎች የቅርብ ሰዎች ሁሌም ቢሆን በንቃት መጠበቅ አለባቸው። ግለሰቡ ከሌላ ጊዜው በተለየ መልኩ የጸባይ መለዋወጥ፣ ዝምታ፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ጭንቀት የሚያበዛ ከሆነ ቀረብ ብሎ መጠየቅና በግልጽ ማውራት እጅግ ጠቃሚ እንደሆኑ ባለሙያው ያስረዳሉ። የሚወዱትን ሰው ያጡ ሰዎች፣ ሀብት ንብረታቸው የጠፋባቸው ሰዎች ወይም ከፈተና የወደቁ ተማሪዎች እራስን ስለማጥፋት የማሰብ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ሊከታተሏቸው ይገባል። ለምሳሌ አንድ ፈተና የወደ ተማሪ ወደ ሱቅ ሄዶ ገመድ አልያም በረኪና ለመግዛት ቢሞክር ባለሱቆች እንኳን የተማሪውን የፊት ሁኔታ ማጤንና ለምን እየገዛው እንደሆነ መጠየቅ አለባቸው።
https://www.bbc.com/amharic/news-61192480
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ የአውሮፓ ሕብረት አስትራዜኔካ የተሰኘው ክትባት የደም መርጋት አያመጣም እያለ ነው
ኮቪድ-19 እንዲከላከል ተብሎ የተሠራው የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባት የደም መርጋት አደጋን ይጨምራል የተባለው ሃሰት ነው ሲል የአውሮፓ ሕብረት አስታወቀ። መግለጫውን ያወጣው የአውሮፓ ሕብረት የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ነው። ባለሥልጣኑ እንደሚለው የደም መርጋት የታየባቸው የተከተቡ ሰዎች ቁጥር ካልተከተቡ ሰዎች ቁጥር ጋር ተመሳሳይ ነው። የአውሮፓ ሕብረት ይህን ማለት ያሻው ዴንማርክና ኖርዌይን ጨምሮ አንዳንድ ሃገራት ክትባቱን ለዜጎቻቸው መስጠት ማቆማቸውን ተከትሎ ነው። ሃገራቱ ክትባቱን መስጠት ያቆሙት ጥቂት ሰዎች ከተከተቡ በኋላ የደም መርጋት ምልክት አሳይተዋል ተብሎ ነው። አንድ የ50 ዓመት ጣልያናዊ ክትባቱን ከወሰደ በኋላ 'ዲፕ ቬይን ትሮሞቦሲስ' [ከደም መርጋት ጋር ተያያዥነት ያለው] የተሰኘ በሽታ ታይቶበት ሞቷልም ተብሏል። "በአሁኑ ወቅት ክትባቱና የደም መርጋት ግንኙነት እንዳላቸው የሚያሳይ ነገር የለም። የደም መርጋትም የክትባቱ ጎንዮሽ ጉዳት አይደለም" ብሏል የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲ። "ክትባቱ ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል። ስለዚህ ታዩ የተባሉትን ጉዳቶች እየመረመርን ክትባቱን መስጠት እንቀጥላለን" ብሏል ኤጀንሲው። ኤጀንሲው እንደሚለው አውሮፓ ውስጥ ክትባቱን ከወሰዱ አምስት ሚሊዮን ሰዎች መካከል 30 ሰዎች የደም መርጋት ምልክት ታይቶባቸዋል። አስትራዜኔካ በቃል አቀባዩ አማካይነት የክትባቱ ደህንነት በብዙ ምርምርና ፈተና የተረጋገጠ ነው ብሏል። በዩናይትድ ኪንግደም የመድኃኒት ተቆጣጣሪው ባለሥልጣን ክትባቱን ከደም መርጋት ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚያሳይ ምንም መረጃ የለም ብሏል። ስለዚህ ሰዎች በተጠየቁ ጊዜ ሄደው ክትባቱን እንዲወስዱ እንመክራለን ይላል። "የደም መርጋት ክትባት ባይኖርም የሚከሰት ነገር ነው። አዲስ ነገር አይደለም። እስካሁን ድረስ 11 ሚሊዮን የአስትራዜኔካ ክትባቶች ዩኬ ውስጥ ተሰጥተዋል" ይላሉ የባለሥልጣኑ ሠራተኛ የሆኑት ፊል ብራያን። በክትባት መዘግየት ምክንያት ችግር ላይ የነበረው የአውሮፓ ሕብረት አሁን ደግሞ አስትራዜኔካ ክትባትን በተመለከተ የሚሰራጩ ያልተረጋገጡ ዜናዎች ማነቆ ሆነውበታል። የአውሮፓ ሕብረት አሁን ፊቱን ወደ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ወደተሰኘውና አንድ ጊዜ ብቻ ወደሚሰጠው ክትባት ማዞር የፈለገ ይመስላል። "ደህንነታቸው ይበልጥ አስተማማኝ የሆኑ ክትባቶች ወደ ገበያው እየመጡ ነው" ብለዋል የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኧርስላ ቮን ደር ለየን። ከዚህ አልፎ ኖቫክስ የተሰኘው ክትባት ዋናውን የኮቪድ ዝርያ በመከላከል ረገድ 96 በመቶ አዲሱን ዝርያ ደግሞ 86 በመቶ ውጤታማነት ማሳየቱ ተነግሯል። ዴንማርክና ናሮዌይ የአስትራዜኔካን ክትባት መስጠት ሙሉ በመሉ ሲያቆሙ ኦስትሪያና ጣሊያን ደግሞ አንዳንድ ብልቃጦችን ማስወገድ ይዘዋል። ኢስቶኒያ፣ ላትቪያ፣ ሊቱኔያ እንደ ላግዘምበርግ ልክ እንደ ኦስትሪያ ለጊዜው የተወሰኑ የአስትራዜኔካ ክትባቶችን መስጠት አቁመዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56369967
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡አማዞን ወደ 20 ሺህ የሚጠጉ ሰራተኞቹ በኮሮና እንደተያዙ አስታወቀ
አማዞን ኩባንያ 19 ሺህ 816 ሰራተኞቹ በኮሮናቫይረስ እንደተያዙ ገልጿል። ይህ ቁጥር ከመጋቢት ወር ጀምሮ የተመዘገበ ሲሆን በአሜሪካ ያሉት ሰራተኞቹም ናቸው። በአጠቃላይ ኩባንያው 1.37 ሚሊዮን ሰራተኞች ያሉት ሲሆን በኮሮናቫይረስ የተያዙትም ከአጠቃላይ ሰራተኞቹ ቁጥር ጋር ሲሰላ 1.44 በመቶ ነው ተብሏል። የኩባንያው ሰራተኞች፣ የሰራተኛ ማህበራትና ኃላፊዎችም የሰራተኞችን ደህንነት አደጋ ላይ ጥሏል በሚልም ኩባንያው ከፍተኛ ትችት እየቀረበበት ነው። ሆኖም ኩባንያው በበኩሉ በቫይረሱ የተያዙት ሰራተኞች ቁጥር ከተጠበቀው በታች ነው ብሏል። ኩባንያው ባወጣው መግለጫም በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ከግምት ውሰት በማስገባት 33 ሺህ 952 ሰራተኞቹ በቫይረሱ እንደሚያዙ ጠብቆ እንደነበር አስታውቋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በርካታ ኩባንያዎች ለተወሰነ ጊዜ ስራቸውን ቢያቆሙም አማዞን በበኩሉ የትኞቹንም ቅርንጫፎች አልዘጋም። በዚህ ወረርሽኝ ወቅትም ትርፋማ ከሆኑት ኩባንያዎች አንዱ መሆን ችሏል። አገራት ወረርሽኙን ለመግታት በሚል ያወጧቸውን መመሪያዎች ተከትሎ በርካቶች ቤታቸው በመቀመጣቸው የበይነ መረብ (ኢንተርኔት) ግብይይት ሁነኛ አማራጭ ሆኗል። ይህም ሁኔታ ለግዙፉ ኩባንያ አማዞንና በአለም አንደኛ ለሆነው ባለቤቱ ጄፍ ቤዞ በትርፍ ላይ ትርፍ ሆኖለታል። በባለፉት ሶሰት ወራትም ውስጥ ኩባንያው 40 በመቶ ሽያጩ ጨምሯል። ከመጋቢት እስከ ሰኔ ወራት ባሉትም 88.9 ቢሊዮን ዶላር ሽያጭን ሲያስመዘግብ፣ ከዚህም ውስጥ 5.2 ቢሊዮን ዶላሩ ትርፍ ነው። ኩባንያው ከተመሰረተበት ከጎሮጎሳውያኑ 1994 ጀምሮም እንዲህ አይነት ትርፍ አስመዝግቦ አያውቅምም ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54389476
amh
health
በኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ዶሮዎችን የገደለው በሽታና የተጣለው የገበያ እግድ
ከሰሞኑ የዶሮ እርባታ ማዕከል በሆነችው በቢሾፍቱ፣ በአዲስ አበባና በአንዳንድ አጎራባች አካባቢዎች በተከሰተ ያልታወቀ የዶሮ በሽታ በበርካታ ሺህ የሚቆጠሩ ዶሮዎች መሞታቸውን ተከትሎ የግብርና ሚኒስቴር ዶሮና የዶሮ ውጤቶች ለገበያ እንዳይቀርቡ ሰኔ 03/2014 ዓ.ም እግድ ጥሏል። በአንዳንድ የዶሮ እርባታ ጣቢያዎች ውስጥ መቶ በመቶ በሚባል ሁኔታ ዶሮዎችን ገድሏል የተባለው ያልታወቀ የዶሮ በሽታ፣ ምንነትና መፍትሔ እስኪገኝ ድረስ ዶሮ፣ ጫጩቶችና እንቁላሎች ከተለያዩ ክልሎች ማጓጓዝ አይቻልም። በተጨማሪም ዶሮ አርቢዎች ዶሮና የዶሮ ውጤቶችን ለገበያ ማቅረብ እንደማይችሉ የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና የእንስሳት ሃብት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በተለይ በሽታው በዋነኝነት በተከሰተባቸው በቢሾፍቱ፣ በአዲስ አበባና በአጎራባች አካባቢዎች ዶሮና የዶሮ ውጤቶችን ማጓጓዝ እንዲሁም ከውጭም ማስገባትም ሆነ ወደ ውጭ መላክ አይቻልም። በሽታው በተከሰተባቸው ስፍራዎች ብቻ ተወስኖ እንዲቀርና ወደሌሎች አካባቢዎች እንዳይዛመት የእንቅስቃሴው ገደብ እንደተጣለ የሚናገሩት ዶክተር ፍቅሩ፣ ለተለያዩ ክልሎችም የየራሳቸውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። በአሁኑ ጊዜ መጀመሪያ ላይ እንደነበረው የዶሮዎች ሞት እየተከሰተ እንዳልሆነና የመቀነስ አዝማሚያ እንዳሳየ የሚናገሩት ሚኒስትር ዲኤታው ሆኖም ሙሉ በሙሉ አለመገታቱን አመልክተዋል። ይህንንም ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የተፈለፈሉ ጫጩቶች፣ እንዲሁም የደረሱ እንቁላሎች ለገበያ እንዳይውሉ እግድ በመጣሉ በርካታ ዶሮ አርቢዎች ለችግር ተጋልጠናል ብለዋል። የዶሮ በሽታው የተከሰተው ከሳምንት በፊት ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ የተሻሻለ የዶሮ እርባታ ያላቸው በሚባሉት ስፍራዎች በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱና በአጎራባች አካባቢዎች መሆኑን ከግብርና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያስረዳል። የበሽታው መዛመትም ከቢሾፍቱ እስከ አዳማ ባለው ኮሪደር በስፋት ተከስቶ የነበረ መሆኑንም ብርሃኑ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎችና አቀናባሪዎች ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ምንም እንኳን የዶሮ በሽታዎች በተደጋጋሚ ቢከሰቱም በሽታው በፍጥነት የመተላለፍና የመዛመት ባህርይ በማሳየቱ እንዲሁም በገባባቸው የዶሮ እርባታ ማዕከላት በብዛት እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ዶሮዎችን መግደሉን ዶክተር ፍቅሩ ይናገራሉ። በተለይም ያጠቃው አነስተኛ እና መካከለኛ የዶሮ እርባታ ማዕከላትን ሲሆን ሁሉም ዶሮዎች ያለቁባቸው ማርቢያዎችም ታይተዋል። እስካሁን ባለው መቶ ሺህ ወይም ከዚያ በላይ ዶሮዎች ሞተዋል ተብሎ የሚገመት ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተጣራ መረጃ ላይ እንዳልደረሰና ገና ስለሁኔታ ግምገማም እያደረገ ነው። “በዚህ አይነት ፍጥነት መዛመቱና ዶሮዎችን በከፍተኛ ሁኔታ መግደሉ ስጋት ፈጥሯል። ዝም ከተባለም ከአንድ እርባታ ማዕከል ወደ ሌላ እርባታ ማዕከል የመዛመት ሁኔታ ሲያሳይ ወደ እንቅስቃሴ ገደብ ገብተናል” ይላሉ ዶክተር ፍቅሩ። ከሰሞኑ የተከሰተው ያልታወቀ የዶሮ በሽታ ትልልቅ የዶሮ ማርቢያዎችን ያላጠቃ ቢሆንም፣ እነዚህ ማዕከላትም ቢሆን ዶሮና የዶሮ ግብዓቶች ማጓጓዝም ሆነ መሸጥ አይችሉም። የእንስሳት ህክምና ባለሞያ የሆኑት ዶክተር ደመቀ ወንድማገኝ መንግሥቴ፣ በሽታው በአነስተኛና በመካከለኛ ዶሮ እርባታ ማዕከል ያስከተለውን ከፍተኛ ሞት በማየት ክስተቱ ከበድ ያለ ሊሆን እንደሚችል ይጠቅሳሉ። በሽታው ሁሉንም አይነት ዶሮዎች፣ ጫጩቶችን ጨምሮ መጠነ ሰፊ ሞት በማድረሱና ሰፊ ቦታ በመሸፈኑ የዶሮ በሸታ ወረርሽኝ ሊባል እንደሚችል ዶክተር ደመቀ ያስረዳሉ። አቶ ብርሃኑ በበኩላቸው በሽታው እያጠቃ ያለው በበለጠ የእንቁላል ዶሮዎችን እንደሆነና ጫጩቶችን ወይም የሥጋ ዶሮዎችን እየገደለ እንዳልሆነ ይገልጻሉ። እስካሁን ስለበሽታው የታወቀ ነገር ስለሌለ ምንነቱን ለመለየት የግብርና ሚኒስቴር የምርምር ሥራዎችን በዋነኝነት እያከናወነ ይገኛል። ሆኖም በተደረገው ዳሰሳና ከበሽታው ባህርይ በመነሳት በንክኪ ስለሚተላለፍ በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱና በኦሮሚያ ክልል የዶሮና የዶሮ ውጤቶች ገቢም ሆነ ወጪ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ ውሳኔ ተላልፏል። ለዚህ ውሳኔ ምክንያቱም አንዳንድ አርቢዎች ዶሮዎች ሲታመሙባቸው ከማስወገድ ይልቅ የመሸጥ ሁኔታ በመታየቱና በሌሎች ስፍራዎች ተዛምቶ በአጠቃላይ በአገሪቱ የዶሮ እርባታ ዘርፍን እንዳይጎዳ በሚል የተወሰደ እርምጃ እንደሆነ ሚኒስትር ዲኤታው ይጠቅሳሉ። አቶ ብርሃኑ በበኩላቸው ጠበቅ ያለና ሙሉ እገዳ ነው የተጣለው ያሉ ሲሆን፣ እሳቸውም ሲጠቅሱ በኢትዮጵያ ደረጃ ከክልል ወደ ክልል ዶሮና የዶሮ ግብዓቶችን እንቁላልና ጫጩቶችን ማጓጓዝ አይቻልም። ከዶሮና የዶሮ ውጤቶች በተጨማሪ ከዶሮ ጋር ንክኪ የሚኖራቸውን መገልገያዎችን መኖን ጨምሮ ማጓጓዝ እንደተገደበ ያስረዳሉ። ከዚህ ባለፈ ዶሮ፣ ጫጩቶች፣ ቄቦች፣ የዳበረ (የለማ) እንቁላል ከውጭ አገራትም እንዳይገቡ እንዲሁም ወደ ውጭ እንዳይላኩ እገዳው ይከለክላል። ለገበያ ማቅረቡም ሆነ የእንቅስቃሴ ገደቡ በሽታው ተለይቶ በቁጥጥር ስር እስኪውል ድረስም የሚቀጥል እንደሚሆን በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ተገልጿል። ባለፈው ሳምንት የሞት መጠኑ ከፍተኛ የነበረ ቢሆንም፣ ባለፉት ቀናት ግን ጋብ የማለት ምልክት እንዳሳየም ሚኒስትር ዲኤታው ዶ/ር ፍቅሩ፣ አቶ ብርሃኑ እንዲሁም ዶክተር ደመቀ ያስረዳሉ። “ሞት ቆሟል ማለት በሽታው አይዛመትም ማለት ስለማይቻል፣ ምን አይነት ተፅእኖ እንደሚያመጣ ስለማይታወቅ፤ የኅብረተሰብ ጤና ጉዳይም ስለሚኖረው ያንን ማጣራት ያስፈልጋል” ይላሉ ዶክተር ደመቀ። ሆኖም በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱና አጎራባች አካባቢዎች ያሉ ዶሮ አርቢዎች ምርቶቻቸውን ማጓጓዝ እና ለገበያ ማቅረብ ባለመቻላቸው ለከፍተኛ ኪሳራ ተዳርገናል ይላሉ። በተለይም አቶ ብርሃኑ እንደሚናገሩት አብዛኞቹ አነስተኛ የዶሮ አርቢዎች በመሆናቸው ከዶሮ ምርታቸው በሚያገኙት ገቢ ላይ ጥገኛ በመሆናቸው ከፍተኛ ጉዳት አስከትሎባቸዋል። በዶሮዎች ላይ ከተከሰተው በሽታ ጋር በተያያዘ በተጣለው ገደቡ ምክንያት ባለፈው ሳምንት ውስጥ ብቻ 40 ሺህ የሚሆኑ ጫጩቶች በአንድ የእርባታ ስፍራ ተቀብረዋል ይላሉ። አቶ ብርሃኑ እንደሚሉት አንዳንድ ማዕከላት ዋነኛ ተግባራቸው ጫጩት እያስፈለፈሉ መሸጥ ስለሆነ ይህም በሺዎች የሚቆጠሩ ጫጩቶች ያስፈለፈለው ማዕከል ማጓጓዝ ባለመቻሉ ለማስወገድ ተገዷል። ሌላኛው አቶ ብርሃኑ የሚጠቅሱት የዶሮ እርባታና ማቀናበሪያ ማዕከል መፈልፈል የነበረባቸው 50 ሺህ እንቁላሎች እንደያዘ በመቆየቱ ከጥቅም ውጪ እንደሚሆን ነው። በተጨማሪም ከውጭ አገራት በዶላር ከፍተኛ ክምችት አስገብተው እንቁላል መፈልፈልና መሸጥ ቢኖርባቸውም እነዚህ ማዕከላት ይህንን ማድረግ ባለመቻላቸው ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጋቸውንም ያስረዳሉ። በርካታ የዘር እንቁላሎችም ከጥቅም ውጪ በመሆናቸው ይህ ሁኔታ አርቢዎችን በተለይም አነስተኛ አርቢዎችን ከሥራ እያስወጣ መሆኑንም ይገልጻሉ። ሌላኛው የሚያነሱት ችግር እነዚህ አርቢዎች ከሚያገኙት ገቢ መኖ መግዛት ባለመቻላቸው፣ እገዳው በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ዶሮዎቹ በረሃብ ያልቃሉ የሚል ስጋትም ተጋርጦባቸዋል። “ዶሮዎቹ ከበሽታው በበለጠ በረሃብ ሊያልቁ ይችላሉ” ይላሉ አቶ ብርሃኑ። የአገሪቱን ከሃምሳ በመቶ በላይ የሆነ የእንቁላል አቅርቦት የሚይዙት አነስተኛ አርቢዎች ናቸው የሚሉት አቶ ብርሃኑ፣ ከሞቱ በላይ ምርት አለመሸጥ ከፍተኛ ጉዳት ስላላው ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ያስረዳሉ። “ነገ ከነገ ወዲያ የእነዚህ የዶሮ እርባታ ማዕከላት ዕጣ ፈንታ ምንድን ነው?” ሲሉም ይጠይቃሉ። ቅሬታቸውንም ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን በአጭር ጊዜም መፍትሄ ያገኛል የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። በርካታ አባሎቻቸውም ከፍተኛ ቅሬታ እያነሱ ሲሆን አፋጣኝ ጥናት ተደርጎ በሽታው ከተለየና ሌላ ችግር የማያስከትል ከሆነ የጥንቃቄ እርምጃዎች እየተወሰዱ ወደ ሥራ የሚመለሱበት ሁኔታ እንዲፈጠር እንደሚፈልጉ አመልክተዋል። ለአቶ ብርሃኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጣላቸው የእንቅስቃሴ ገደቦች ከባድ የሚባሉ መሆናቸውን ነው። በተጨማሪም በሽታው የከፋ ስጋት እንደማይደቅን ከሚጠቅሷቸው ምክንያቶች ዋነኛው ወደ ሰው አለመተላለፉን ነው። የበሽታው ምንነት በአሁኑ ወቅት እየተመረመረ ቢሆንም ሚኒስትሩም ሆነ አቶ ብርሃኑ በሽተኛ ዶሮዎችን ሲንከባከቡ ከነበሩ ግለሰቦች እንዲሁም በማዕከላቱ ከተደረገው አሰሳ ወደ ሰው እንደማይተላለፍ ነው። በሽተኛ ዶሮዎችን ሲንከባከቡ የነበሩ ግለሰቦች ምንም አይነት የህመም ምልክት አላሳዩም። ሌላኛው አቶ ብርሃኑ የሚጠቅሱት ምክንያት በአንዳንድ የእርባታ ማዕከላት አቅራቢያቸው ያለው ማዕከል በበሽታ ቢጠቃም ወደሌሎች አለመዛመቱ ሌላው የሚጠቅሱት ምክንያት ነው። በተጨማሪም በባለፉት ሦስት እና አራት ቀናት ሞት እንዳልተከሰተ፣ በሽታውም የለም በሚባልበት ደረጃ ላይ እንዳለ እንዲሁም በትልልቅ የማራቢያ ማዕከላት ባለመከሰቱ መሆኑ ሌላኛው በጎ ምልክት ነው ይላሉ። በአነስተኛና መካከለኛ ደረጃ ላይ ባሉ ጣቢያዎች መከሰቱ የጥንቃቄ መላላት (ባዮ ሴኩሪቲ ደካማ) መሆን ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል ሲሉም ይጠቁማሉ። “በሽታ አለ። ዶሮ ሁልጊዜም ከበሽታ ጋር ነው የሚኖረው። ለሰው ጤና ጉዳት የማያመጣ ከሆነ ሌላውን በክትባትም እየተቋቋምን መኖር እንችላለን። ለምሳሌ ኒውካስትል የሚባለው የዶሮ በሽታ 70 አስከ 80 በመቶ ገዳይ ነው። ይህም ተመሳሳይ በሽታ ከሆነ ማዕከላቱ ጥንቃቄ እያደረጉ ወደ ሥራ መመለስ ይኖርባቸዋል። አሁን በርካታ ጉዳቶች እየደረሱ ናቸው” ይላሉ። ሚኒስትሩ የተጣሉት ገደቦች ከባድ ነው በሚለው አይስማሙም “ከባዱ ነገር ዶሮዎቹ ማለቃቸው ነው” ይላሉ። ምንነቱ ያልታወቀው በሸታ በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ የማርቢያ ማዕከላት ተዛምቶ ዶሮዎችን ቢጨርስስ? ብለው የሚጠይቁት ሚኒስትር ዲኤታው በአጠቃላይ የዶሮ እርባታና ማቀናበር ሥርዓቱን ሊገድል ይችላል ይላሉ። ሆኖም በዶሮ አርቢዎች ላይ ያለውን ተፅእኖና ኪሳራ እንደሚረዱ ገልጸዋል። “ወደን ሳይሆን ከመጥፎው የተሻለ መጥፎን መምረጥ ነው። ለጊዜው እንቁላሉንም ሽያጩንም ያዝ አድርገው እኛ ደግሞ የተከሰተባቸው ቦታዎች ላይ እርምጃ ወስደን ከተቆጣጠርን በኋላ የተሻለ ነገር ይኖራል” ይላሉ። እንዲህ አይነት እርምጃዎች በበርካታ አገራት የሚወሰዱ የተለመዱ አሰራሮችም መሆናቸውንም አፅንኦት ይሰጣሉ። ለዶክተር ደመቀም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጣለው እገዳ ሳይንሱን ተከትለው ነው ይላሉ። የትኛውም አገር ላይ ወረርሽኝ ሲያጋጥም እንቅስቃሴ መገደብ የተለመደ መሆኑን የሚጠቅሱት ዶክተር ደመቀ፣ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦችን ይጠቅሳሉ። መሥሪያ ቤቱ በንክኪ መዛመትን ለመግታት እንቅስቃሴን መገደብን በዚህም ሕዝቡንም ሆነ የዶሮ እርባታ ማዕከላትን ለመጠበቅ፣ እንዲህ አይነት እርምጃ በበርካታ አገራት ተግባራዊ ይደረጋል ይላሉ። ሆኖም ሳይንሱ ይህንን ቢልም በኢትዮጵያ አንድምታ አብዛኛው ዶሮ አርቢ መኖና የተለያዩ መገልገያዎች የሚገዛው ከቢሾፍቱ ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ በሽታ ያልገባባቸው አካባቢዎች በመኖና በሌሎች መገልገያዎች ጥገኛ ስለሚሆኑ በሎጂስቲክ መቋረጥ ምክንያት ችግር ውስጥ እንደሚገቡም ያስረዳሉ። ሆኖም ይላሉ ዶክተር ደመቀ “እንዲህ አይነት ውሳኔዎች ሲወሰኑ በጣም መጥፎ ከሚባለው፣ የተሻለውን መጥፎ መምረጥ የሚለውን አሰራር ተከትሎ ነው።" ዶክተር ደመቀ እንደሚያስረዱት የዶሮ በሽታ ወረርሽኝ አለ የሚባለው ከሁለት በላይ የሆኑ የዶሮ እርባታ ማዕከላትን ሲያጠቃ ነው። በዚህም ወቅት የተከሰተው በሽታ በርካታ ማዕከላትን ማጥቃቱ ወደ አጎራባች አካባቢዎች መዛመቱ የዶሮ ወረርሽኝ ሊባል ይችላል ይላሉ። ከዚህ በፊት አጋጥሞ ቢያውቅም በዚህ ደረጃ እንዳልነበርና መለስ ያሉ የዶሮ መሞት መጠን እንደነበረና የተወሰነውንም መርጦ እንዳጋጠመ ያወሳሉ። ዶክተር ፍቅሩም በአንዳንድ የዶሮ እርባታ ማዕከላት መቶ በመቶ ዶሮዎቹን በመጨረሱ ወረርሽኝ ነው ለማለት እንደሚያስችል ያስረዳሉ። ወረርሽኝ በሚያጋጥምበት ወቅት እንቅስቃሴዎችን መገደብን ጨምሮ ሌሎች እርምጃዎች እንደሚወሰዱ የሚናገሩት አቶ ብርሃኑ፣ ወረርሽኝ ነው ተብሎ የሚታሰብ ከሆነ በፍጥነት መለየት እንዳለበት ያስረዳሉ። “የዶሮ እርባታ ዘርፉ በቋፍ ላይ ነው” የሚሉት አቶ ብርሃኑ በርካታ ችግሮች ያሉበትና እድገት የማያሳይ ነው የሚሉትን ዘርፍ ሊያቀጭጨው እንደሚችልም ያስጠነቅቃሉ። አሁን ባለው ሁኔታም ላይነሳ ከሚወድቅበት ደረጃ ላይ በመሆኑ እግዱ ላላ ሊል ይገባል ይላሉ። ወረርሽኝ ተከስቶ እንደማያውቅ የሚናገሩት አቶ ብርሃኑ በ1997ም ‘በርድ ፍሉ’ ነው በሚል እሳቤ በርካታ ዶሮዎች መገደላቸውን አስታውሰው። የላብራቶሪ ውጤቱ ግን ወረርሽኝ እንዳልሆነ በማሳየቱ የተወሰደው ትክክለኛ እርምጃ እንዳልነበር ያወሳሉ። በዚህም ወቅት ተመሳሳይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ የሚናገሩት ሥራ አስኪያጁ በሽታው ታውቆ ለዚያ የሚሆን ትክክለኛ እርምጃ ቢወሰድ ችግር እንደሌለውም ያስረዳሉ። ነገር ግን “በአሁኑ ወቅት ውጤቱ ባልታወቀበትና አመላካች ሁኔታዎች ብዙ ወረርሽኝ በማይመስሉበት ሁኔታ” ወደ እገዳ እርምጃ መገባቱ ትክክል እንዳልሆነም አፅንኦት ይሰጣሉ። የዶሮ እርባታ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣ ዘርፍ ነው የሚሉት ዶክተር ፍቅሩ፣ ይህም እንዳይጎዳ ስለ በሽታው ምንነት በማያሻማ መልኩ ውጤቱ አስኪታወቅ ድረስ ገደቡ የሚቀጥል ሲሆን፣ አሁን በተያዘው ሁኔታ ረጅም ጊዜ ሊቆይ እንደማይችልም ያስረዳሉ። የዶሮ አርቢዎች ማኅበር በተጨማሪ የሚያነሱት ቅሬታ በግብርና ሚኒስቴር እየተላለፉ ያሉ ውሳኔዎች ማኅበሩን ያገለሉ መሆናቸውን ነው። ማኅበሩ እንደ ዋና ባለ ድርሻ አካል በምርምሮቹና በመፍትሄዎቹ ላይ ተሳታፊ ቢሆን ለመከላከያ እርምጃውም የተሻለ ግብዓት እንዲሁም በተቀላጠፈ ጊዜ ቶሎ ውጤት ላይ ለመድረስ ይቻላል ብለው ያምናሉ። ከተከሰተው የዶሮ በሽታ ጋር በተያያዘ ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጣ ግብረ ኃይል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አቋቁሟል። ግንዛቤ የማስጨበጥ እንዲሁም በሸታው በተከሰተባቸው ስፍራዎች የክትትል ሥራ፣ ምርምሮች፣ ምላሽ የመስጠት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። በርካታ ዶሮዎች በየጢሻው ተጥለው በመገኘታቸው በሽታው እንዳይስፋፋና በድጋሚ እንዳይከሰት እነዚህን የሞቱ ዶሮዎችን አሰባስቦ የማስቀበርና የማቃጠል ሥራዎች እየተሰሩ ነው። በሽታው በተከሰተባቸው ስፍራዎች ሌላ በሽታ ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ኬሚካል የመርጨት ተግባር እየተከናወነ ነው። ትልልቆቹ የዶሮ እርባታ ማዕከላትም የደኅንነት አጠባበቃቸውን በማሳደግ በዚያው ምርቶቻቸውን እንዲይዙ ተደርጓል። የዶሮ እርባታ ማዕከላት ላይ በሽታዎች የመከሰት ነገር የተለመደ መሆኑን የሚናገሩት ዶክተር ፍቅሩና ዶክተር ደመቀ፣ በሽታዎች ሲከሰቱ ሊያደርሷቸው የሚችሉ ጉዳቶችን በተመለከተ አስቀድመው መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄዎች (የባዮ ሴኩሪቲ ደኅንነት) ቢኖርም አንዳንዶች በትክክል ተግባራዊ እንደማያደርጉ ይናገራሉ። በተጨማሪም ኬሚካሎችና የጽዳት ግብዓቶች (ዲስኢንፌክታንት) የማይጠቀሙ፣ ክትባትም ጊዜውን ጠብቀው በአግባቡ የማይሰጡ የእርባታ ማዕከላት ሲኖሩ በሽታዎች እንደሚከሰቱ ጠቅሰው፣ በአሁኑ ወቅት ጥንቃቄዎችን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። በተጨማሪም ዶክተር ፍቅሩ ለአርቢዎች የሚመክሩት በአካባቢያቸው የሞቱና የተጣሉ ዶሮዎች ካሉ በአግባቡ ማስወገድ፣ የኬሚካል ርጭትም ካለ ያንን ማከናወን ከተሰማራው ግብረ ኃይል ጋር በከላከል ሥራው ላይ እንዲሳተፉ መክረዋል። ኅብረተሰቡም ቢሆን ጥቆማ እንዲያደርግ የሚመክሩት ዶክተር ፍቅሩ፣ በተባባረ መንገድም በፍጥነት ለመቆጣጠርና ለማጥፋት ይረዳል ይላሉ። በተለያዩ መንገዶች እየወጡ ያሉ መረጃዎች ኅብረተሰቡን ዶሮና እንቁላል ከመመገብ ፍርሃት ውስጥ የሚከቱ ናቸው የሚሉት አቶ ብርሃኑ በበኩላቸው፣ ለሰው ጤና አስጊ ባልሆነበት ሁኔታ ለመረጃዎች ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ይላሉ። “ይሄንን ያህል የሚያስፈራ ነገር የለም። ነገር ግን በደንብ ያልታወቀ ጉዳይ ደግሞ እንዲህ አድርጉ ማለት አይቻልም። ምንም አይነት የገጠመ ወይም ሪፖርት የተደረገ የለም። ነገሮችን እስከምናውቅ ብሉ አትብሉ ልንል አንችልም” ይላሉ ዶክተር ፍቅሩ በበኩላቸው። ዶክተር ደመቀ ሕዝቡ ዶሮንም ሆነ የዶሮ ተዋፅኦ የሚጠበቅበት መንድ አብስሎ ስለሆነ፣ በደንብ ማብሰልና ንፅህናውን የመጠበቅ ሁኔታ ካለ ተጠቃሚውን የሚያሰጋ ነገር ሊኖር ይችላል ብለው እንደማያስቡ ያስረዳሉ። ሆኖም በአጠቃላይ ባለሙያው የሚያስተላልፉት መልዕክት የዶሮ እርባታ ወደ ኢንዱስትሪ ሊያድግ እንደሚችል ጠቅሰው፣ ይህም የራሱ ችግር ስለሚያመጣ ተገቢ የሆነ የዶሮ በሽታ መከላከልና መቋቋም ሥራ በተገቢው መንገድ መሰራት እንዳለበት ነው። ይህንንም የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትም ሆነ የግል ሴክተሩ አንድ ላይ ሆነው ፕሮግራም ቢቀርጹ ጥሩ ነው በማለት መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c4nlzg7pry9o
amh
health
የአውስትራሊያው ምክትል ጠ/ሚ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ዩኬ አቅንተው በኮቪድ ተያዙ
የአውስትራሊያው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም አቅንተው በኮቪድ መያዛቸው አሜሪካ በደረሱ ወቅት ተረጋገጠ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ባርናቢ ጆይስ በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ጉብኝት ባደረጉት ወቅት በቫይረሱ ሳይያዙ እንዳልቀሩ ተናግረዋል። አክለውም በአሁኑ ሰዓት እራሳቸውን ለይተው እንደሚገኙና ቀለል ያሉ ጉንፋን መሰል ምልክቶችን እንዳስተዋሉ ገልጸዋል። ባርናቢ ጆይስ ረቡዕ ዕለት ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ከመጓዛቸው አስቀድመው በዩናይትድ ኪንግደም በነበራቸው ቆይታ የካቢኔ ሚኒስትር ከሆኑት ዶሚኒክ ራብ እና ግራንት ሻፕስ ጋር ተገናኝተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ እስካሁን ድረስ ለቫይረሱ ስርጭት ምን ያክል ስጋት እንደሆኑ አልታወቀም። እስካሁን ድረስ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር አብረው እየተጓዙ ካሉ የልዑክ ቡድን አባላት መካከል በቫይረሱ የተያዘ አልተገኘም። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚሉት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ሲሄዱ ተመርምረው ኮሮናቫይረስ እንደሌለባቸው አረጋግጠው የነበረ ቢሆንም ልክ አሜሪካ ሲደርሱ ግን ድካምና እግራቸው አካባቢ የመዛል ስሜት አስተውለዋል። ከዚህ በኋላ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለ10 ቀናት እራሳቸውን አግልለው እንደሚቆዩ የተገለጸ ሲሆን ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ሊያደርጉት የነበረውም ውይይት ተሰርዟል። ባርናቢ ጆይስ ከአውስትራሊያ መገናኛ ብዙኀን ጋር ባደረጉት ቆይታ ለገና በዓል ለንደን ውስጥ አንዳንድ እቃዎችን ለመግዛት ወደ ትልልቅ የገበያ ማዕከላት ማቅናታቸውን ያልደበቁ ሲሆን በርካታ ሰዎችም ትከሻ ለትከሻ ተጠጋግተው እንደነበር አስረድተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ከፍተኛ ስልጣን ላይ የሚገኙ የአውስትራሊያ ኃላፊ ናቸው። የአውስትራሊያው መከላከያ ሚኒስትር ባሳለፍነው ዓመት ወደ አሜሪካ ጉዞ ካደረጉ በኋላ በቫይረሱ መያዛቸው የሚታወስ ነው። አውስትራሊያ እስካሁን ድረስ በወረርሽኙ ምክንያት ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች መሞታቸውን ያስታወቀች ሲሆን ይህም ካደጉት አገራት ጋር ሲነጻጸር በጣም ዝቅተኛ ቁጥር ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-59574514
amh
health
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ተመዘገቡ
በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረጉ የኮሮናቫይረስ ምርመራዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ተገለጸ። በየዕለቱ የሚደረጉ የኮሮናቫይረስ ምርመራዎችን መሠረት በማድረግ ማክሰኞ ታኅሣሥ 13/2014 ዓ. ም በጤና ሚኒስቴር በኩል የወጣው መረጃ እንዳመለከተው 2,323 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ይህ አሐዝም ከዚህ በፊት በአንድ ቀን ከተመዘገቡት በጣም ከፍተኛው ነው። በየዕለቱ በ24 ሰዓት ይፋ የተደረጉ ቀደም ያሉ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ዕለታዊ አሐዝ ከ500 እስከ 1000 ባለው መካከል የቆየ ነበር። የማክሰኞ ዕለቱ ሪፖርት እንዳመለከተው 2,323 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው በዕለቱ ምርመራ ካደረጉ 10,016 ሰዎች መካከል ነው። እስካሁን በአገሪቱ በወረርሽኙ መያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 379,379 የደረሰ ሲሆን፣ ትናንት ለተመዘገበው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር ምክንያቱ ምን እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር እስካሁን የሰጠው መረጃ የለም። እስካሁን በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ከነበሩ መካከል 351,168 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ 6,877 ሰዎች በወረርሽኙ ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በዓለም ዙሪያ ክትባት እየተሰጠ ቢሆንም፤ በቅርቡ የተከሰተው ኦሚክሮን የተባለው አዲስ ዓይነት ዝርያ የበሽታውን የመስፋፋት ፍጥነትና አደገኝነት እንዳባባሰው የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል። ይህ መጀመሪያ ላይ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መገኘቱ የተነገረው ኦሚክሮን በርካታ ሰዎች ላይ እየተገኘ ሲሆን አገራት በሽታውን ለመቆጣጠር ጥብቅ እርምጃ እየወሰዱ ነው። ይህ የወረርሽኙ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለመገኘቱ በጤና ባለሥልጣናት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።
https://www.bbc.com/amharic/news-59730317
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ በኦክስፎርዱ የክትባት ሙከራ ላይ አንድ ሰው ቢሞትም የደህንነት ስጋት የለበትም ተባለ
በአስትራዜኔካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በጥምረት እየበለጸገ የሚገኘው የኮሮናቫይረስ ክትባት ላይ ሙከራ በሚደረግባት ብራዚል የአንድ በጎ ፈቃደኛ ሕይወቱ ማለፏን ተከትሎ ክትባቱ ምንም አይነት የድህንነት ስጋት እንደሌለበት ተገለጸ። የብራዚል ጤና ባለስልጣን ከሙከራው ጋር በተያያዘ ሕይወቱ ስላለፈው በጎ ፈቃደኛ ምንም አይነት መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ቡድን በበኩሉ በጉዳዩ ላይ ጥንቃቄ የተሞላበት ምርመራ እንደሚደረግና ክትባቱ ግን ምንም አይነት የደህንነት ስጋት እንደሌለበት አስታውቋል። ቢቢሲ ባገኘው መረጃ መሰረት ደግሞ በጎ ፈቃደኘው ክትባቱን አልወሰደም። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየተሰራ የሚገኘው ክትባት ላይ ከሚሳተፉት በጎ ፈቃደኞች መካከል ግማሽ የሚሆኑት ብቻ ሲሆን ክትባቱን እንዲወስዱ የተደረገው ቀሪዎቹ ደግሞ ማረጋገጫ የተሰጠው የማጅራት ገትር ክትባት ነው የተሰጣቸው። የሙከራው ተሳታፊ በጎ ፈቃደኞችም እራሳቸው የሚሰጣቸው የኮሮረናቫይረስ ክትባት ይሁን የማጅራት ገትር የሚያውቁት ነገር የለም። ይህ የሚደረገውም በገዛ ፈቃዳቸው ነው ተብሏል። ግዙፉ የመድሀኒት አምራች አስትራዜኔካ በበኩሉ በእያንዳንዱ የግለሰብ የሙከራ ሂደት ላይ አስተያየት እንደማይሰጥና ሙከራው ሲካሄድ ግን አስፈላጊው ጥንቃቄና የደህንነት እርምጃዎች መወሰዳቸውን አስታውቋል። ''ሁሉም ወሳኝ የጤና ሁኔታዎች በጥንቃቄ ተመርምረዋል፤ ከግምት ውስጥም ገብተዋል። ሙከራውም ሆነ የምርምር ሂደቱ ምንም አይነት አሳሳቢ ነገር አልተገኘባቸውም፤ የሚመለከታቸው ኃላፊዎችም ሂደቱን እንዲከታተሉት አድርገናል'' ብሏል። በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ ተስፋ ከተጣለባቸው የክትባት ሙከራዎች መካከል ይሄኛው በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን በቅርቡ ለገበያ እንደሚበቃም ይጠበቃል። እስካሁን ደረጃ አንድና ደረጃ ሁለት የሙከራ ሂደቶችን በስኬታማነት ያጠናቀቀው ይኸው ክትባት ደረጃ ሶስትን ለማጠናቀቅ ደግሞ በዩኬ፣ ብራዚልና ሕንድ በበጎ ፈቃደኞች ላይ ሙከራውን እያካሄደ ይገኛል። ባሳለፍነው ወር በዩኬ ይካሄድ የነበረው ሙከራ የጎንዮሽ ጉዳት ሊኖረው ይችላል በሚል ተቋርጦ የነበረ ሲሆን ከቀናት በኋላ ግን ሙከራውን ለማከናወን ምንም ስጋት እንደሌለ በመገለጹ ሂደቱ በድጋሚ እንዲጀመር ሆኗል። የብራዚል ጤና ባለስልጣን በጎ ፈቃደኛው ሕይወቱ ስለማለፉ ከትናንት በስትያ መስማቱን አስታውቋል። የብራዚል መገናኛ ብዙኃን በበኩላቸው ሕይወቱ ያላፈችው ግለሰብ የ28 ዓመት የህክምና ባለሙያ እንደሆነና ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ሕይወቱ እንዳለፈች ዘግበዋል። ይህ ክትባት ሙሉ ፈቃድ የሚያገኝ ከሆነ ብራዚል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ብልቃጦችን ለመግዛት ወስናለች። በአገሪቱ እስካሁን 5.3 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከአሜሪካና ሕንድ በመቀጠል በዓለማችን ሶስተኛው ከፍተኛ ቁጥር ነው። የሟቾች ቁጥር ደግሞ እስካሁን 155 ሺ መድረሱ ተረጋግጧል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54641714
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ የአሜሪካውያን የኮቪድ-19 ክትባት ምርጫ ለምን የተለያየ ሆነ?
አሜሪካ ሦስት ክትባቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ የፈቀደች ሲሆን ሰዎች የሚፈልጉትን እየመረጡ ነው። ሦስቱም የኮቪድ-19 ክትባቶች በቫይረሱ መያዝና ተይዞ ሆስፒታል መግባትን እንዲሁም ሞትን በመከላከል ረገድ ውጤታማ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ የጤና ባለሥልጣናት ለዜጎች የሚሰጠው የተሻለው ክትባት ነው ብለዋል። ቢሆንም ከጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ይልቅ ፋይዘር እና ሞደርና ክትባቶችን የሚመርጡ ብዙዎች ናቸው። በመጋቢት መጀመሪያ የዲትሮይት ከንቲባ ማይክ ዱጋን የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባትን ውድቅ አድርገው በአሜሪካ የቀረቡት ሌሎች ሁለት ክትባቶች የተሻሉ መሆናቸውን ለከተማዋ ነዋሪዎች ጠቁመዋል። በጋዜጣዊ መግለጫቸው ወቅት "የዲትሮይት ከተማ ነዋሪዎች የተሻለውን እንዲያገኙ የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ" ብለዋል። የጤና ባለሙያዎች አስተያየት ከሰጡ በኋላ ከንቲባው ክትባቱ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ ስለመሆኑ "ሙሉ እምነት አለኝ" በማለት ገልጸዋል። እንደ ዱጋን ሁሉ አንዳንድ አሜሪካውያን ስለ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት እና ስለ አጠቃላይ ውጤታማነቱ ጥያቄ አንስተዋል። የጤና ባለሥልጣናት ግን እነዚህ ቁጥሮች ሙሉውን ገጽታ እንደማያሳዩ አስጠንቅቀዋል። አንዳንዶች ጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን ከመውሰድ ሳይከተቡ ቢዘገዩ እንደሚመርጡ ይናገራሉ። አንድ የዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ ለቢቢሲ ሲናገሩ "የክትባት ቀጠሮ በነበረኝ ጊዜ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን እየሰጡ እንደሆነ ስለሰማሁ ሰርዤዋለሁ። ያንን ክትባት በጭራሽ አልወስድም" ብለዋል። እንደ ዶ/ር ማይክል አንድራሲክ ያሉ የጤና ባለሥልጣናት ማንኛውንም ፈቃድ ያገኘ ክትባት መውሰድ ጥሩ መሆኑን አሜሪካውያንን ለማሳመን እየሞከሩ ነው። "በአንድ በኩል ሰዎች ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጥ በመሆኑ በጣም ተደስተዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ውጤታማነቱን በተመለከተ ብዙ ግራ መጋባት አለ። ይህ ደግሞ ጥሩ አይደለም" ሲሉ በፍሬድ ሃች የክትባትና ተላላፊ በሽታ ክፍል ከፍተኛ የሳይንስ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር አንድራሲክ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአሜሪካ ተቆጣጣሪዎች አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጠውን ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት በይፋ ያጸደቁት በየካቲት ነው። ይህም ፍቃድ ያገኘ የመጨረሻው ክትባት አድርጎታል። አዲስ የኤም አር ኤን ኤ ክትባት ቴክኖሎጂን ከሚጠቀሙት እና ሁለት ጊዜ ከሚሰጡት ከፋይዘር እና ከሞዴርና ክትባቶች በተለየ መልኩ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ጉዳት እንዳያደርስ የተደረገ ቫይረስን ይጠቀማል። ከዚያ የኮሮናቫይረስን ዘረ መል በከፊል ወደ ሰውነት ይወስዳል። ይህም ሰውነት አደጋውን ለይቶ እንዲያውቅ እና ኮሮናቫይረስን ለመዋጋት እንዲዘጋጅ ያደርጋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በክትባቱ ላይ እምነት እንዳላቸው አሳይተዋል፡፡ በዚህ ወር ለአሜሪካኖች ከቀረበው በእጥፍ 100 ሚሊዮን ተጨማሪ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባቶች እንደምታዝ አስታውቀዋል። የብሔራዊ አለርጂ እና ተላላፊ በሽታዎች ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ በበኩላቸው በአሜሪካ የሚገኙ ሁሉም ክትባቶች ጥሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባትም "ደካማ ክትባት አይደለም" ብለዋል። አሳሳቢው ነገር ከሙከራዎች የሚወጣው የውጤታማነት መረጃ መለያየት ነው። የጤና ባለሥልጣናት ሦስቱም ክትባቶች መቶ በመቶ ቫይረሱን የመከላከል አቅም አላቸው ሲሉ አሳስበዋል። የፋይዘር እና የሞደርና ክትባቶች አዳዲሶቹ የቫይረሱ ዝርያዎች ከመስፋፋታቸው በፊት የተሞከሩ ሲሆን አዳዲሶቹ ዝርያዎች በሙከራዎች ላይ ልዩነት ይፈጥራሉ። በተጨማሪም የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) ሁሉም ክትባቶች ከዓመታዊው የጉንፋን ክትባት የበለጠ ውጤታማ ናቸው ሲል ይገልጻል። እንደ ዶ/ር አንድራስክ ከሆነ "ዋናው ነገር ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን፣ ሞደርና እና ፋይዘር ከባድ በሽታን በመከላከል፣ ሆስፒታል መተኛትን በመቀነስ፣ ከፍተኛ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን በመቀነስ ወይም መሞትን በመከላከል በማይታመን ሁኔታ ውጤታማ ናቸው።" የማኅበረሰብ ጤና ተሟጋቾች እንደሚሉት ከሆነ ሌላው የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ጠቃሚ ጎን በአሜሪካ ውስጥ ብቸኛው አንድ ጊዜ የሚሰጥ ክትባት መሆኑን ነው። ራቅ ወዳሉ እና ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ ቦታዎችም ለማሰራጨት የበለጠ ምቹ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ያንን ክትባት ብቻ ወደ አካባቢዎቹ መላክ መገለልን ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አለ። አክለውም "ሁሉም ክትባቶች ለሁሉም ሊደርሱ ይገባል ብዬ አስባለሁ። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን ወደ ገጠር እና ድሃ ማኅበረሰቦች የመላክ ምክንያታዊነት በእንክብካቤ ተደራሽነት ምክንያት ነው ብዬ አስባለሁ" ብለዋል ዶ/ር አንድራስክ። እንደ ዶ/ር አንድራስክ ያሉ የማኅበረሰብ አመራሮች እና የጤና ባለሙያዎች በክትባቱ ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ ለማስፋፋት እና የተሳሳተ መረጃን ለመከላከል ጥረት እያደረጉ ነው። በአሜሪካ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 ሲሞቱ "የእኔ ተራ ሲደርስ ማንኛውንም ክትባት እወስዳለሁ" ይላሉ። ሌሎቹ አሳሳቢ ጉዳዮችስ ምንድን ናቸው? ዩ ኤስ ኮንፈረንስ ኦፍ ካቶሊክ ቢሾፕስ የተባለው እና በአሜሪካ የሚገኘውን ቤተክርስትያን የሚወክለው ጉባኤ በክትባቱ ዙሪያ "የሞራል ስጋት" መኖሩን መግለጹ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። የስጋቱ ምንጭ ጽንስ በማስወረድ ከሚገኙ ሕዋሶች ክትባቱ ተመርቷል መባሉ ነው። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኢቦላ ክትባትን ለማዘጋጀት የዋለውን ተመሳሳይ ዘዴ ተጠቅሟል። በተጨማሪም የትኛውም የኮቪድ -19 ክትባት ምንም ዓይነት የሰው ህዋሳትን አልያዘም። ጉባኤው ምርጫ እስካለ ድረስ ካቶሊኮች አማራጭ ክትባቶች መውሰድ እንዳለባቸው መክሯል። በአሜሪካ ጉባኤ የተሰጠው ምክር ከቫቲካን አቋም ጋር የሚቃረን ይመስላል። ምክንያቱም ቫቲካን እንዲህ ያሉት ክትባቶች "ከሞራል አንጻር ተቀባይነት አላቸው" ስለምትል ነው። ሌሎች የካቶሊክ መሪዎችም የቤተክርስቲያኗ አባላት ከዚህ ክትባት መራቅ አለባቸው የሚለውን ሐሳብ እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል። የሐርትፎርድ ሊቀ ጳጳስ እና ሌሎች የአካባቢው የሐይማኖት አባቶች በሰጡት መግለጫ ሁሉም ነዋሪዎች ለራሳቸው ጤና እና ለጋራ ጥቅም ሲሉ "ማንኛውንም ክትባት ለመቀበል የህሊና ነፃነት ሊሰማቸው ይገባል" ሲሉ ተናግረዋል። እንደ ዶሮ በሽታ እና ሩቤላ ያሉ ሌሎች ብዙ ክትባቶች በተመሳሳይ መልኩ የተሠሩ ቢሆንም የካቶሊክ መሪዎች ስለ ለጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ያሰሙት ስጋት በአንዳንድ አሜሪካውያን ዘንድ ጥርጣሬ እንዲጨምር አድርጓል። ስጋቶችን የሚጋፈጠው የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ብቻ አይደለም። አሜሪካ ጥቅም ላይ እንዲውል ለመፍቀድ እየተዘጋጀችበት የሚገኘው የኦክስፎርድ-አስትራዛኔካ ክትባት ከደም መርጋት ችግር ጋር በተያያዘ የአውሮፓ አገራት ታግዶ ነበር። የአውሮፓ ሕብረት የመድኃኒት ተቆጣጣሪ ባሥልጣን ክትባቱ "ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ ነው" ብሎ መግለጹን ተከትሎ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን እና ስፔን ክትባቱን መጠቀም መጀመራቸውን ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56498267
amh
health
የቬትናም ፖሊስ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዳግም ጥቅም ላይ ሊውሉ የነበሩ ኮንዶሞች ያዘ
የቬትናም ፖሊስ ከ320ሺህ በላይ ታጥቦ ዳግም ጥቅም ላይ ሊውል የነበረ ኮንዶም መያዙን አስታወቀ። የቬትናም የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከሆነ ኮንዶሞች ሊሸጡ የነበረው በኮንዶሞቹ ጥራት ላይ ጥያቄ ለማያነሱ ግለሰቦች ነው። ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ታጥበው ዳግም ጥቅም ላይ ሊውሉ በተዘጋጁ ኮንዶሞች የተሞሉ ሻንጣዎች ምስል በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ተሰራጭቷል። ፖሊስ እንዳለው ከሆነ ሕገ-ወጥ ኮንዶሞቹ የተያዙት በአገሪቱ ደቡባዊ አቅጣጫ በአንድ መጋዘን ውስጥ ተከማችተው ነው። የመጋዘኑ ባለቤት ነች የተባለችው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋሏ ተዘግቧል። ጥቅም ላይ የዋሉት ኮንዶሞች ከታጠቡ በኋላ የወንድ ልጅ ብልት ቅርጽ ባለው አንጨት ላይ ይለጠጡ እና ዳግም ታሽገው ለገበያ ይቀርባሉ ተብሏል። በቁጥጥር ሥር የዋለችው የመጋዘን ባለቤት በአንድ ኪሎ ግራም ኮንዶም 0.13 ዶላር ተስማምታ ወደ ሥራው መግባቷን ለፖሊስ ቃሏን ሰጥታለች። ጥቅም ላይ ውለው ዳግም ለገበያ የሚቀርቡት ኮንዶሞች ዋጋ እንዲሁም ጥቅም ላይ የዋሉ ኮንዶሞች እንዴት እንደሚሰበሰቡ የተባለ ነገር የለም።
https://www.bbc.com/amharic/news-54295812
amh
health
ኔዘርላንድ ከ12 አመት በታች ላሉ ታዳጊዎች የፈቃድ ሞትን ፈቀደች
የኔዘርላንድ መንግሥት በማይድን በሽታ የተጠቁ ታዳጊዎች በፈቃድ ሞት ወይም በእንግሊዝኛው ዩቴኔዥያ (euthanasia) ተግባራዊ እንዲሆን ከሰሞኑ ፈቅዷል። ታዳጊዎች ብሎ የጠቀሰው ከአስራ ሁለት አመት በታች የሆኑ ህፃናትን ሲሆን የጤና ሚኒስትሩ ሁጎ ደ ጆንጌም ይህ ህግ "መቋቋም በማይችሉትና ተስፋ በሌለው ሁኔታ የሚሰቃዩ" ህፃናትን ይታደጋቸዋል ብለዋል። በኔዘርላንድ የፈቃድ ሞት ከአስራ ሁለት አመት በላይ ለሆኑ ታዳጊዎች የሚፈቀድ ሲሆን ይህም የሚፈፀመው ከህመምተኞችና የቤተሰቦች ፈቃድ ሲገኝ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ከአንድ አመት በታች ያሉ ህፃናትን በማይድን በሽታ ከተጠቁና በቤተሰብ ፈቃድ እስከተገኘ ድረስ እንዲሞቱ ይፈቀዳል። በ አንድ አመትና በ12 አመት መካከል የሚገኙ በማይድን በሽታ እየተሰቃዩ የሚገኙ ታዳጊዎችን በተመለከተ ምንም ህግ ያልነበረ ሲሆን የአሁኑ ይፈቀድ የሚለው ጥያቄም አገሪቷን በሚመሯት አራት ጥምር ፓርቲዎች መካከል ከፍተኛ ውዝግብን ፈጥሯል። ለወራትም ያህል የፓርላማ አባላቱ ሲነታረኩ ነበር። በተለይም ወግ አጥባቂው የክርስቲያን ፓርቲዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተቃውመውታል። ሆኖም በመጨረሻ የፈቃድ ሞት ይፈቀድ የሚለው አሸንፎ ህግ እንዲሆን ፀድቋል። ከዚህ በኋላ ህጉን በተግባር ላይ ለማዋልም መመሪያዎች እንደሚወጡ የጤና ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የዚህ ህግ መቀየር አስፈላጊ መሆኑንም አንድ በባለሙያዎች የቀረበ ጥናት ማስረጃ ነው ይላሉ የጤና ሚኒስትሩ። በዚህ ጥናት መሰረት አዲሱ ህግ በአመት አስር የሚሆኑ በማይድን በሽታ የሚሰቃዩ ህፃናትን ህይወት ይቀይራል። በስራ ላይ ያሉት ህጎች ሙሉ በሙሉ ይቀየራሉ ማለት እንዳልሆነ የጠቀሱት የጤና ሚኒስትሩ ነገር ግን ፍቃድ ያለው የፈቃድ ሞት ዶክተሮች ቢያከናውኑ ከመከሰስ ይከላከልላቸዋል። በተሻሻለው ህግ መሰረትም ከ12 አመት በላይ ያሉ ታዳጎጊዎች የቤተሰብ ፈቃድ፣ ከፍተኛና መቋቋም የማይችሉት ህመምና ይህንን ተግባር ማከናወን የፈቀዱ ሁለት ዶክተሮች መስፈርቶች መሟላት አለባቸው። እነዚህ ህጎችም በሚቀጥሉት ወራት ተግባራዊ ይሆናሉ። የፈቃድ ሞት በኔዘርላንድ ህግ ሆኖ የፀደቀው በጎሮጎሳውያኑ 2002 ሲሆን ከወራት በኋላም ቤልጅየም በመፍቀድ ተከትላታለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-54544006
amh
health
ዐይናችንን ሊጎዱ እና ዕይታችንን ሊያጨልሙ የሚችሉ አራት ምክንያቶች
የህመም አለመኖር ጤንነትን አያረጋግጥም ይባላል። ፍጹም ጤነኛ እንደሆኑ እያሰቡ ድንገት በአንዱ የሰውነት ክፍልዎ ላይ ስር የሰደደ በሽታ እንዳለ ማወቅ ሌላ ህመም ነው። ከ23 ዓመታት በፊት ሥራ የጀመሩት የዐይን ህክምና ስፔሻሊሰቱ ዶክተር ዮናስ ጥላሁን እንዲህ አይነት አጋጣሚዎችን ተመልክተዋል። “አንዳንድ ታካሚዎች ‘ድንገት ጠዋት ተነስቼ አንዱ ዐይኔን ሳሸው ጠፋ’ ይላሉ” በማለት አልፎ አልፎ ስለሚያጋጥማቸው ነገር ይናገራሉ። ዐይን በድንገት ሊጠፋ ይችላል? መልሱን እንመለሰበታለን! ከዚያ በፊት ዐይናችንን ስለሚጎዱ እና የዕይታ መጠናችንን ስለሚቀንሱ ምክንያቶች እናውራ! ዐይንን የሚጎዱ በርካታ ምክንያቶች አሉ። እኛ ግን ዶክተር ዮናስ ጥላሁን የነገሩን አራት ምክንያቶች ብቻ እንመልከት። ዶክተር ዮናስ ዐይን በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ባሉ የጤና ችግሮች ምክንያት ሊጎዳ የሚችልበት አጋጣሚዎች እንዳሉ ያስረዳሉ። እንደ ስኳር እና ደም ግፊት ያሉ በሽታዎች በቀጥታ የዐይን ጤንነት ላይ ጉዳት በማድረስ እስከ ዐይነ ስውርነት ሊደርሱ ይችላሉ። የአሜሪካ በሽታ መቆጣጠር እና መካለከል ማዕከል ወይም ሲዲሲ እንደሚለው የስኳር በሽታ ከዐይን ጋር የተሳሰሩ የደም ቧንቧዎች ላይ ጉዳት በማድረስ የዕይታ መጠናችን እጅግ እንዲያሽቆለቁል ወይም ሙሉ በሙሉ እንዲጠፋ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ከዚህም ባሻገር በክትባት በቀላሉ ሊወገዱ በሚችሉ ችግሮች ምክንያት ዐይን በከፋ ሁኔታ ሊጎዳ እንደሚችልም ነው ዶክተር ዮናስ የሚናገሩት። “እንደ ኩፍኝ ያሉ በሽታዎች ክትባት ካልተወሰደ ጠበሳ በማምጣት ዐይንን እስከማጥፋት ይደርሳሉ” የሚሉት የዐይን ስፔሻሊስቱ “በተመጣጠነ ምግብ፣ ቫይታሚን ኤ እጥረት የዐይን ብሌን መቁሰል አጋጥሟቸው ብዙ ህጻናት ዐይናቸውን ሊያጡ የሚችሉበት ሁኔታ አለ” ብለዋል። በሌላ በኩል በህጸናት ዐይን ላይ “መንሸዋረር” የመሰሉ ችግሮችን ችላ ብሎ ማለፍ በዕይታቸው ላይ ከፍ ያለ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችልም ጠቁመዋል። የዐይን ንጽህናንን ባለመጠበቅ ደግሞ እንደ ትራኮማ ያሉ በሽታዎች ተከስተው “ውለው አድረው” የዐይን ብርሃንን ሊያሳጡ የሚችሉ ሲሆን የዐይን በሽታ ከቤተሰብ ሊወረስበት የሚችልበት አጋጣሚም አለ። በጤና ምክንያት የሚመጡ የዐይን ችግሮችን ምርመራ በማድረግ የከፋ ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት ሊደረስባቸው ይችላል። ስኳርን የመሳሰሉ በሽታዎች ያሉባቸው ሰዎች እና በቤተሰብ ውስጥ የዐይን ችግር እንዳለ ከታወቀ የዐይን ምርመራን በቋሚነት ማድረግ ይመከራል። ለህጻናት ደግሞ የተመጣጠነ ምግብ መስጠት እና ክትባቶችን እንዲወስዱ ማድረግ እንደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሁሉ ለዐይናቸውም ጠቃሚ መሆኑን ነው ይላሉ ዶክተር ዮናስ። ህጻናት ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ ዐይናቸው ላይ “ነጭ ነገር ጣል ካለ”፣ ሳያለቅሱ እንባ ከፈሰሰ፣ የዐይን መጠን መለያየት ካለና ዐይናቸውን ደጋግመው ካሹ ወደ ህክምና ተቋማት እንዲሄዱ ዶክተር ዮናስ ይመክራሉ። የቫይታሚን ኤ እና ኦሜጋ 3 ይዘት ያላቸው ምግቦችን ማዘውተር የዐይን ጤናን በእጅጉ ይጠብቃሉ። እንደ ፓፓያና ማንጎ ያሉ ፍራፍሬዎችን፣ እንደ ቆስጣና ጎመን ያሉ አትክልቶችን እንዲሁም አሳን ማዘውተር ለዐይን ጤና ጠቃሚ ነው። የዐይን ስፔሻሊስቱ “በስክሪን ላይ የሰዎች ዐይን ተተክሎ በመዋሉ የተነሳ፣ የዐይን ጤና መታወክ ደርሶ ሰዎች ወደ ሆስፒታል መመላለሳቸው መጨመሩ ይታያል” ይላሉ። በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ከሞባይል እና ከኮምፒውተር ጋር ያለን ቁርኝት እየጨመረ በመሄዱ የተነሳ፣ በዲጂታል ቁሶች ምክንያት የሚመጡ የዐይን ውጥረቶች (Digital Eye Strain/Computer Vision Syndrome) በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። እንደ ሐኪሙ ገለጻ በቀን በስክሪኖች ላይ ያለ ቆይታ ከ2 ሰዓታት ከዘለለ ረጀም የስክሪን ቆይታ ተብሎ የሚገለጽ ነው። ማን ያውቃል?! ከሞባይሉ ጋር ቁርኝት ላለው ግለሰብ በቀን ለሁለት ሰዓት መጠቀም እጅግ ትንሽ ሊሆን ይችላል። ቢቢሲ በአንድ ወቅት የተመለከተው ሪፖርት በ20 ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሰዎች ስክሪን ላይ የሚያጠፉት ጊዜ መጨመሩን ያመላክታል። ሪፖርቱ ከ5 እስከ 16 ዓመት ያሉ ህጻናት በቀን በአማካኝ 6 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ስክሪን ላይ እንደሚያጠፉ ይጠቁማል። ታዲያ ዐይንን ለረጅም ሰዓት ስክሪን ላይ ማንከራተት ጊዜያዊ ችግሮችን እንደሚያስከትል ነው ዶክተር ዮናስ የሚያስረዱት። ይህም የዐይን ብዥታ፣ መወጠር፣ መቅላት፣ ማሳከክ፣ መደረቅ፣ ማቃጠል እንዲሁም ቶሎ መድከም፣ እንቅልፍ እንቅልፍ ማለትና ራስ ምታትን ያካትታል። ሐኪሙ አንዳንድ ጥናቶችን ዋቢ በማድረግ ረጅም የስክሪን ቆይታ ህጻናት ላይ የዕይታ ችግር (Short-sightedness) ሊፈጥር እንደሚችል ተናግረዋል። መፍትሄው ምንድን ነው? ስክሪን በምንጠቀምበት ጊዜ “የሃያ ሃያ ሕግ”ን መተግበርን ዶክተር ዮናስ ይመክራሉ። “የሃያ ሃያ ሕግ” እንደ ኮምፒውተር፣ ሞባይል ወይም ቴሌቪዢን ያሉ ቁሶችን ለ20 ደቂቃ ከተጠቀምን በኋላ ለ20 ሰኮንድ ሥራ በማቆም 20 ጫማ ወይም 6 ሜትር ርቀት አካባቢ በመመልከት ዐይንን የማሳረፍ ሕግ ነው። ይህም ቀላል የሚመስል ቢሆንም ለዐይን ጠቃሚ መሆኑን ነው የሚያስረዱት። መነጽርን ከተገኘበት ቦታ “ለስክሪን፣ ለፀሐይ አልያም ለዝነጣ” መሸመት ለዐይናችን ጤና ጠንቅ ሊሆን ይችላል። ዶክተር ዮናስ “አንዳድ መነጽሮች ጠቃሚነታቸው የተረጋገጠ አይደለም። አንዳንዶች ደግሞ ጎጂም ሊሆኑ ይችላሉ” ያሉ ሲሆን፣ ለምሳሌ ሰማያዊ ብርሃኖችን ያጣራሉ በሚል እና ለኮምፒውተር በሚል በውድ ዋጋ የሚሸጡ መነጽሮችን በምሳሌነት ይጠቅሳሉ። “እርግጥ ኮምፒውተር ለመጠቀም መነጽር አይጠቅምም እያልኩ አይደለም። በሐኪም ምርመራ ታይቶ የሚጠቅምባቸው አስፈላጊ እና የግድም የሚሆንባቸው ጊዜያት አሉ” ይላሉ። ከዚያ ውጪ ግን አንዳንዶቹ የ‘ሳይት’ ቁጥራቸው ከተጠቃሚው ዐይን ጋር ባለመናበቡ ምክንያት ዐይን ላይ ጫና ይፈጥራሉ። ለፀሐይ ወይም ለዝነጣ በሚል የሚሸመቱት ደግሞ “ዐይናችን እንደጨለመ ስለሚቆጥር የዐይን ብሌናችን ይሰፋል።” የዐይን ብሌን መስፋት ደግሞ ዐይናችን ለጎጂ እና አላስፈላጊ ጨረር እንዲጋለጥ ያደርገዋል። ዕድሜ ከሚያዳክማቸው የሰውነት ክፍሎች አንዱ ዐይን ነው። በተለይ እድሜ ከአርባ ሲሻገር ዐይን ይደክማል። የዕይታ መጠን እየቀነሰ ይሄዳል። ዶክተር ዮናስ የዚህን ምክንያት ሲያስረዱ ዐይን ጉልበቱን የሚያስተካክልበት፣ ቅርጽ የሚቀይርበት ጡንቻዎች እያረጁ ስለሚሄዱ ነው ይላሉ። በወጣትነት ዘመን ብሌን ለርቀት፣ ለመካከለኛ እና ለቅርበት ዕይታ የሚሰጠው ቀላል ምላሽ ዕድሜ ሲገፋ ለመታዘዝ ይደክማል። በዚህ ጊዜ አጋዥ መነጽሮች ሊያስፈልጉ ይችላሉ። በሌላ በኩል ዕድሜ ሲገፋ ሞራ (Cataract) የተሰኘው የዐይን ክፍል “ጉም በመያዝ” ብርሃን ለማስተላለፍ ይቸገራል። ይህም “ጭጋግ የሆነ ዕይታ ሊያመጣ ይችላል። በተወሰነ ደረጃ በመነጽር ሊረዳ ይችላል። ግን እየገፋ ሲሄድ ደግሞ በቀዶ ህክምና ብቻ የሚስተካከል ሊሆን ይችላል” ይላሉ - የዐይን ህክምና ስፔሻሊስቱ። በዕድሜ ምክንያት ዐይን ላይ የሚመጡ ችግሮች አንዳንዶቹ በህክምና መመለስ የሚችሉ ሲሆን፣ ሌሎቹ ደግሞ ህክምና ላይመልሳቸው ይችላል። ዶክተር ዮናስ “ሰዎች ዐይናቸው ሥራ እንዳቆመ ድንገት ሊያውቁ ይችላሉ እንጂ ዐይን ድንገት አይጠፋም” ይላሉ። ቀደም ብሎ የነበረ እና በህክምና ያልታየ ችግር በሂደት ዐይንን እስከ ማሳወር ሊያደርስ ይችላል። በተለይ “የዐይን ብርሃን ሌባ” ተብሎ የሚታወቀው ግላኮማ ምንም ምልክት ሳይሰጥ ለረጅም ጊዜ የዐይን ነርቭን ጎድቶ ሥራውን ሊያቆም ይችላል። ለዚህ ነው ሰዎች ከ40 ዓመት ዕድሜ በኋላ በየዓመቱ የጤና ምርመራ ማድረግ እንዲያደርጉ የሚመከረው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cgl2841vzd7o
amh
health
የቬትናም ፖሊስ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዳግም ጥቅም ላይ ሊውሉ የነበሩ ኮንዶሞች ያዘ
የቬትናም ፖሊስ ከ320ሺህ በላይ ታጥቦ ዳግም ጥቅም ላይ ሊውል የነበረ ኮንዶም መያዙን አስታወቀ። የቬትናም የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከሆነ ኮንዶሞች ሊሸጡ የነበረው በኮንዶሞቹ ጥራት ላይ ጥያቄ ለማያነሱ ግለሰቦች ነው። ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ታጥበው ዳግም ጥቅም ላይ ሊውሉ በተዘጋጁ ኮንዶሞች የተሞሉ ሻንጣዎች ምስል በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ተሰራጭቷል። ፖሊስ እንዳለው ከሆነ ሕገ-ወጥ ኮንዶሞቹ የተያዙት በአገሪቱ ደቡባዊ አቅጣጫ በአንድ መጋዘን ውስጥ ተከማችተው ነው። የመጋዘኑ ባለቤት ነች የተባለችው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋሏ ተዘግቧል። ጥቅም ላይ የዋሉት ኮንዶሞች ከታጠቡ በኋላ የወንድ ልጅ ብልት ቅርጽ ባለው አንጨት ላይ ይለጠጡ እና ዳግም ታሽገው ለገበያ ይቀርባሉ ተብሏል። በቁጥጥር ሥር የዋለችው የመጋዘን ባለቤት በአንድ ኪሎ ግራም ኮንዶም 0.13 ዶላር ተስማምታ ወደ ሥራው መግባቷን ለፖሊስ ቃሏን ሰጥታለች። ጥቅም ላይ ውለው ዳግም ለገበያ የሚቀርቡት ኮንዶሞች ዋጋ እንዲሁም ጥቅም ላይ የዋሉ ኮንዶሞች እንዴት እንደሚሰበሰቡ የተባለ ነገር የለም።
https://www.bbc.com/amharic/news-54295812
amh
health
ለ78 ጊዜ የኮቪድ ምርመራ አድርጎ 'ፖዘቲቭ' የሆነው ግለሰብ
ቱርካዊው ሙዛፈር ካያሳን የደም ካንሰር ህመምተኛ ሲሆን ከዓመት በፊት ባደረገው ምርመራ የኮሮናቫይረስ እንዳለበት ሲነገረው ተስፋ ቆርጦ ነበር። ነገር ግን ኮቪድ ከነበረበት የካንሰር ህመም ጋር ተደምሮ የከፋ ችግር ሳያስከትልበት ወራት ተቆጥረው ከዓመት በላይ ሆኖታል። ኮቪድ-19 የያዛቸው አብዛኞቹ ሰዎች ለጥቂት ሳምንታት ከታመሙ በኋላ አገግመው ከቫይረሱ ነጻ ይሆናሉ፤ የተወሰኑት ተደግሞ በሚፈጠርባቸው የጤና እክል ለሞት ሊዳረጉ ይችላሉ። የሙዛፈር ግን የተለየ ነው፤ ባለፉት 14 ወራት ለ78 ጊዜ ምርመራ አድርጎ አስካሁን ድረስ ፖዘቲቭ ነው። ከዚህ አንጻር በኮቪድ ተይዞ ለረጅም ጊዜ ቫይረሱ ከሰውነቱ ሳይጠፋ የቆየ የመጀመሪያው ሰው ሳይሆን አይቀርም።
https://www.bbc.com/amharic/news-60458640
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ የኮቪድ-19 ውጤትን በ30 ደቂቃ ውስጥ ማወቅ ሊቻል ነው
ኮቪድ-19ን በደቂቃዎች ውስጥ የሚለይ ምርመራ በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የመለየት ስራን በእጅጉ ያሳድጋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ተናገረ። አምስት ዶላር ብቻ የሚያስወጣው ይህ ምርመራ ሃብታም ባልሆኑ እና የጤና ባለሙያዎችና የላብራቶሪ እጥረት ባለባቸው አገራት የኮቪድ-19 ሕሙማንን ለመለየት በእጅጉ ይረዳል ተብሏል። መመርመሪያውን ከሚያመርቱ ድርጅቶች ጋር የተደረገ ስምምነት በስድስት ወር ውስጥ 120 ሚሊዮን መመርመሪያዎችን ለማምረት ያስችላል። ይህንን እርምጃ የጤና ድርጅቱ የበላይ ኃላፊዎች "ጉልህ ሚና የሚጫወት" ብለውታል። በበርካታ አገራት ምርመራ ከተደረገ በኋላ ውጤት ለማወቅ የሚፈጀው ጊዜ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የሚያርጉትን ትግል ጎድቶት ቆይቷል። እንደ ሕንድና ሜክሲኮ ባሉ ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ በተሰራጨባቸው አገራት በፍጥነት መርምሮ ውጤቱን ማወቅ አለመቻል የወረርሽኙን የመስፋፋት ፍጥነት ትክክለኛ ምስል ማሳየት አልቻለም ሲሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ይህ አዲሱ "ተንቀሳቃሽ እና ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ" መመርመሪያ ውጤትን ከ15 እስከ 30 ደቂቃ ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ሰኞ እለት በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ግን የኮሮናቫይረስን ውጤት ለማወቅ ሰዓታት ካልሆነም ቀናት እንደሚፈጅ ይታወቃል። አቦት እና ኤስዲ ባዮሴንሰር የተባሉ መድሃኒት አምራቾች ከቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን 120 ሚሊዮን መመርመሪያዎችን ለማምረት ስምምነት መድረሳቸውን ዶ/ር ቴድሮስ ጨምረው ገልፀዋል። በዚህ ስምምነት መሰረት የሚመረቱ መመርመሪያዎች በቫይረሱ በጣም የተጎዱ የላቲን አሜሪካ አገራትን ጨምሮ ለ133 አገራት ይሰጣል ተብሏል። "ይህ በተለይ ከፍተኛ ስርጭት ባለባቸው አካባቢዎች የመመርመር አቅም ላይ ትልቅ እመርታ የሚፈጥር ነው" ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ። አክለውም "ላቦራቶሪ በሌላቸውና ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ወይንም ምርመራውን ለማካሄድ በቂ የሰለጠነ ባለሙያ በሌለበት አካባቢ የመመርመር አቅምን ያሰፋል።''
https://www.bbc.com/amharic/54336434
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ የአውሮፓ አገራት በአስትራዜኒካ ክትባት ጉዳይ ለሁለት ተከፍለዋል
የአውሮፓ አገራት አስትራዜኒካ ክትባትን ለሕዝባቸው በማደልና ባለማደል ጉዳይ ለሁለት እንደተከፈሉ ናቸው፡፡ ኦክስፎርድ አስትራዜኒካ ክትባት የደም መርጋትን አስከትሏል የሚለው መረጃ ነው አገራቱን እያወዛገባቸው ያለው፡፡ የተወሰኑ አገራት ክትባቱን መስጠት እንደቀጠሉ ሲሆን አንዳንድ አገራት ግን ነገሮች እስኪጠሩ በሚል ያዝ አድርገውታል፡፡ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ስፔንና ጣሊያን የአውሮፓ ኅብረት ክትባቱን ፈትሾ ችግር የለውም የሚል ሪፖርት ካልሰጠን ለሕዝባችን አናድልም ብለው አቋም ወስደዋል፡፡ ነገር ግን እነ ፖላንድና ቤልጂየም ክትባቱን ለሕዝባቸው መስጠታቸውን እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ የአውሮፓ ሜዲካል ኤጀንሲ አስትራዜኒካ ክትባት በእርግጥም የደም መርጋት ያስከትላል ወይ የሚለውን እየመረመረ ሲሆን ነገ ሐሙስ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ትናንት ማክሰኞ የአውሮፓ ሜዲካል ኤጀንሲ በሰጠው መግለጫ ክትባቱ የከፋ የጎንዮሽ ጉዳት እንደሌለው እና ክትባቱን ካለመውሰድ፣ መውሰዱ የተሻለ እንደሆነ እንደሚያምን ተናግሮ ነበር፡፡ የኤጀንሲው ኃላፊ ኤመር ኩክ እንዳሉት የደም መርጋት የተከሰተው ከጠቅላላው ክትባት ወሳጅ እጅግ በተወሰኑ ሰዎች ሲሆን ይህም መከተብን ተከትሎ ስለመሆኑ ገና አልተጣራም ብለዋል፡፡ "ማሳሰብ የምፈልገው ነገር ቢኖር ደማቸው ረጋ የተባሉት ሰዎች ክትባቱን በመውሰዳቸው ነው ያ የሆነው የሚለው ገና አልተረጋገጠም" ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ የኤጀንሲውን አስተያየት 'ተስፋን የሚሰጥ' ብለውታል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ የዓለም ጤና ድርጅት የሊቃውንት ቡድን ትናንት ማክሰኞ በጉዳዩ ላይ አንዳች ውሳኔ ላይ ለመድረስ ተሰብስቦ የነበረ ሲሆን የደም መርጋቱ ክትባቱን ከመውሰድ ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ መረጃ ማግኘት አልቻልኩም ብሏል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት እንዳለው አገራት ክትባቱን መስጠት ማቆም አይጠበቅባቸውም፡፡ ክትባቱን መስጠቱ ነው የሚበጀው ሲል መክሯል፡፡ በታላቋ ብሪታኒያ እስከአሁን ወደ 11 ሚሊዮን ሰዎች ቢያንስ አንዲት ቀንጣት አስትራዜኒካ ክትባትን መውሰዳቸው ተረጋግጧል፡፡ ከ11 ሚሊዮን ዜጎች እስከአሁን የደም መርጋትም ሆነ ሞት ስለመመዝገቡ መረጃ የለም፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ 13 የአውሮጳ አገራት ክትባቱ ‹ለማንኛውም ይቆየን› ብለው እደላውን ያቆሙ ሲሆን ይህን እርምጃ በመውሰድ ረገድ ዴንማርክን የቀደማት የለም፡፡ ከዴንማርክ ሌላ ኖርዌይ አይስላንድ ጀርመን ፈረንሳይ ጣሊያን፣ ሳይፕረስ ስፔን ላቲቪያና ስዊድን ተመሳሳይ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል፡፡ ከትናንት በስቲያ ሰኞ ጀርመን ፈረንሳይና ጣሊያን የአውሮፓ ሜዲካል ኤጀንሲን ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ እንደሆኑ ይፋ አድርገዋል፡፡ ሁሉም የአውሮፓ አገራት የአውሮፓ ሜዲካል ኤጀንሲን ግምገማ ተከትሎ አስትራዜኒካ ክትባትን ለሕዝቦቻቸው ማደላቸውን ይቀጥላሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-56425426
amh
health
ኮቪድ ያሰራጨው የቬትናም ዜጋ አምስት ዓመት ተፈረደበት
አንድ ቬትናማዊ ግለሰብ የኮቪድ-19 መመሪያዎችን በመጣስ እና ቫይረሱን በማሰራጨት ወንጀል ተከስሶ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የአምስት ዓመት እስር ተፈረደበት። ሊ ቫን ትሪ አደገኛ እና ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ የሚተላለፍ በሽታን በስምንት ሰዎች ላይ በማሰራጨት ወንጀል ጥፋተኛ መሆኑን ተከትሎ ነው ፍርድ ቤቱ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈበት። ግለሰቡ ኮቪድ ካስያዛቸው ሰዎች መካከል አንድ ግለሰብ ህይወቱ አልፏል ተብሏል። እስከ ቅርብ ጊዜያወት ድረስ ቬትናም የኮሮናቫይረስ ስርጭትን በመቆጣጠርና ጥብቅ መሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ ስኬታማ አገር ነበረች። ነገር ግን ከባለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ አዲሱ ዴልታ የተሰኘው የቫይረሱ ዝርያ በአገሪቱ መከሰቱን ተከትሎ በርካቶች በቫይረሱ እየተያዙ ነው። እስካሁን ድረስም በቬትናም ከ530 በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 13ሺህ 300 ሰዎቸው ደግሞ ሕይወታቸው አልፏል። ነገር ግን ከዚህ ቁጥር አብዛኛው የተመዘበው ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ መሆኑ ነገሮች ምን ያክል አሳሳቢ ስለመሆናቸው ማሳያ ነው ተብሏል። በስርጭት ደረጃ ደግሞ ሆ ቺ ሚኒ ከተማ ውስጥ በርካቶች በቫይረሱ ተይዘዋል። በሰኔ ወር መጀመሪያ አካባቢ ጥፋተኛ የተባለው የ28 ዓመቱ ሊ ከሆ ቺ ሚኒ ከተማ ተነስቶ ወደ ትውልድ አካባቢው ካ ማው ግዛት በሞተር ሳይክል ተጉዟል። ካ ማው ከደረሰ በኋላ ደግሞ ስለ ጉዞ ታሪኩ እና ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ለተጠየቀው ጥያቄ ሀሰተኛ መረጃ ሰጥቷል፤ በተጨማሪም እራሱን መለየት ሲገባው ይህንን መመሪያ ተግባራዊ አላደረገም። የአካባቢው ባለስልጣናት ከወራት በፊት እንዳስታወቁት ማንኛውም ተጓዥ ወደ ካ ማው ግዛት ሲገባ እራሱን ለ21 ቀናት ላይቶ ማቆየት ግዴታ ነው። ከትንሽ ቆይታ በኋላ ሊ የኮቪድ19 ምርመራ ሲደረግለት በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ ሲሆን በወቅቱም ቫይረሱን ለቤተሰቡ አባላት እንዲሁም ለህክምና የሄደበት የጤና ማዕከል ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎችን አስይዟል። ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ከሰማ በኋላ ሊ አምስት ዓመት እስራት እና 880 ዶላር መቀጮ ፈርዶበታል።
https://www.bbc.com/amharic/58463475
amh
politics
አዲሱ ክልል አራት ዋና ከተሞች እንዲኖሩት ማድረጉ የሚኖረው አንደምታ
በይፋ ተመሰረተ የወራት ዕድሜ ያለው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል አዲስ የከተሞች ማዕከላትን ለመስተዳደሩ ተቋማት ለማደራጀት ወስኗል። ሌሎቹ ክልሎች ማዕከላቸውን በአንድ ዋና ከተማ አድርገው ቢሮዎቻቸው በአንድ ስፍራ ላይ እንዲዋቀሩ በማድረግ ይታወቃሉ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ግን ከሌሎቹ በተለየ ለየት ያለ አደረጃጀትን ለመከተል መርጧል። በዚህም ከትናንት በስተያ ረቡዕ ሐምሌ 27/2014 ዓ.ም. የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል አራት ዋና ከተሞች እንዲኖሩት የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ለክልሉ ምክር ቤት አቅርቧል። ይህ ረቂቅ ሕግ የሚጸድቅ ከሆነ በክልሉ ካሉ ስድስት ዞኖች በአራቱ የዞን ከተሞች የክልሉ መስተዳደር ዋና ዋና አካላት መቀመጫ ይሆናሉ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል አካል የነበሩት ስድስት ዞኖች ተባብረው የመሠረቱት ክልል ነው። በረቂቁ መሠረትም ቦንጋ የፖለቲካ እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳደሩ ጽህፈት ቤት መቀመጫ ትሆናለች። ተርጫ የክልሉን ምክር ቤት መቀመጫ፣ ሚዛን አማን የዳኝነት መዋቅሩ የሚገኝበት እንዲሁም ቴፒ የብሔረሰቦች ምክር ቤት መቀመጫን ይይዛሉ። ሥራ አስፈጻሚ ቢሮዎች ደግሞ በአራቱም ከተሞች ፍትሃዊ ሆነው ይመደባሉ ተብሏል። ይህ አዲስ የክልል አደረጃጀት የተለያዩ ሃሳቦች እየተሰነዘሩበት ነው። አንዳንዶች የክልሎችን ሥራና ሃብት በአንድ ከተማ ላይ ብቻ በማከማቸትን በማፍሰስ ከሌሎች ከተሞች በበለጠ አንድ ከተማ ብቻ በላቀ ሁኔታ እንዲያድግና ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያደርገውን አሰራር ይለውጣል ሲሉ ይደመጣል። ሌሎች ደግሞ ይህ የክልል መስተዳደር ተቋማትን በተለያዩ ከተሞች ውስጥ እንዲቀመጡ ማድረግ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚፈልጉ ነዋሪዎችን ለወጪ እና እንግልት ከመዳረጉ ባሻገር፣ በክልሉ ተቋማት መካከል በቅርበት በትብብር የመስራት ዕድልን ከማጓደል ባሻገር አባካኝ ሊሆን ይችላል በማለት ስጋታቸውን ይገልጻሉ። አቶ ደያሞ ዳሌ ቀደም ሲል በደቡብ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ይሰሩ የነበሩ የፖለቲካ ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ ናቸው። ይህ የክልሉ አስተዳደር እቅድ የክልሉን ነዋሪዎች ሊያጉላላ ይችላል ሲሉይናገራሉ። የክልሉ መንግሥት ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ያቀደው “በፖለቲካዊ ውሳኔ” ነው የሚሉት አቶ ደያሞ፤ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ አንድ ክልል ከአንድ በላይ ከተማ ሲኖረው ታይቶ እንደማይታቅ በማስታወስ ነው። ጨምረውም እንዲህ አይነቱ ልምድ ያለው በሰለጠኑት አውሮፓ አገራት ውስጥ ነው ይላሉ። “እንዴት ተግባራዊ ያደርጉታል የሚለውን ባለቤቶቹ ናቸው የሚያውቁት። ይህም ወደፊት የምናየው ይሆናል። ወጪው ከፍተኛ ይሆናል” ይላሉ አቶ ደያሞ። ረቂቅ ሕጉ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን ለመስጠትም ሆነ፤ አገልግሎት ለማግኘት ለከፍተኛ ወጪ የሚዳርግ ነው የሚሉት አቶ ደያሞ አራቱ ከተሞቹም የተመረጡበት መስፈርትም ግልጽ አይደለም ይላሉ። “አራቱ ከተሞች በምን ተመረጡ? ትላልቅ ስለሆኑ ነው የተመረጡት ወይስ ከዞኖች ተወጣጥተው ነው? ያልደረሳቸው ከተሞች ቅሬታስ እንዴት ይፈታል?” ሲሉ ይጠይቃሉ። የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ማሞ በበኩላቸው፤ በክልሉ ያሉ ነዋሪዎችን ፍላጎት ለማማከል ሲባል ከዚህ ውሳኔ ላይ መደረሱን ይናገራሉ። ይህ ክልል ሲመሰረት ማዕከላዊ ከተማው ማን ይሆናል የሚለው ብዙ አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኖ ነበር ይላሉ አቶ ፀጋዬ። “አንዳንድ ከተሞች ማዕከላዊ ከተማው እኛ ጋር ካልሆነ ክልሉን አንቀላቀልም የሚል አቋም ይዘው ስለነበር፤ በወቅቱ የነበረው አመራርም ሆነ ክልሉ ሲመሰረት የነበረው አመራር ከአንድ በላይ የማዕከል ከተማ ይኖራል በሚል ተነጋግረው ነበር” ይላሉ። “ሰው ሳይጉላላ እና ሥራ ሳይጎዳ እንዴት አድርገን ነው ብዘሃ ከተሞችን የምንፈጥረው በሚለው ላይ ተነጋግረን አጠናቀናል” ይላሉ። አንድ ነዋሪ ጉዳይ ለማስፈጸም ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ ሳይጓዝ ጉዳዩን ባለበት መጨረስ የሚያስችሉ ጉዳይ ማስፈጸሚያ ቢሮዎችም ታስበዋል ይላሉ። “ከአንድ ቢሮ ወደ ሌላ ቢሮ የሚሸጋገሩ ተግባራት ካሉ፤ አገልግሎቱን የሚሰጡ ላይዘን ጽ/ቤቶች አብረን ለመፍጠር ነው ያሰብነው” ይላሉ። በክልሉ የመንግሥት ተወካይ የሆኑት አቶ ፀጋዬ፤ ክልሉ አራት መዲናዎች እንዲኖሩት መደረጉ ተጨማሪ ወጪ ያስከትላል የሚል እምነት የለንም በማለት ይናገራሉ። “ለምሳሌ አንድ ቢሮ በጀት ቢፈልግ ለፋይናንስ ቢሮ ወረቀት ይልካል እንጂ፣ በአካል ወደ አንድ ከተማ መጥቶ ገንዘብ አይወስድም፤ ስለዚህ የተለየ ወጪ አይኖርም” በማለት ያስረዳሉ። በየትኛው ከተማ ምን አይነት ቢሮዎች ይኑሩ የሚለው ቀድሞ በስምምነት የተደረሰበት እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ፀጋዬ፤ “በዚህ ከተማ ይህ ቢሮ ይኑር የተባለው በስምምነት እንጂ በሳይንሳዊ ምክንያት አይደለም” ይላሉ። የክልሉ ምክር ቤት ረቂቅ አዋጁን ተወያይቶ ካጸደቀው በኋላ ተግባራዊ መደረግ እንደሚጀምር አቶ ፀጋዬ ገልጸዋል። ይህ በአገሪቱ ካሉ ሌሎች ክልሎች በተለየ ሁኔታ የተደራጀው የአዲሱ ክልል አስተዳደር መዋቅር ድጋፍም ጥያቄም ከተለያዩ ወገኖች እየተነሱበት ነው። ነገር ግን ከክልሉ ብዝሃነት አኳያ ማዕከሉን በአንድ ስፍራ አድርጎ የእድገትም ሆነ ሌሎች ዕድሎችን በአንድ ከተማ ላይ ከማከማቸት ይልቅ በተለያዩ ስፈራዎች መሆኑን በአዎንታ የሚመለከቱት አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የክልሉ የመንግሥት ሥራዎችና አገልግሎቶችን በተለያዩ ስፍራዎች ላይ እንዲሆኑ መደረጋቸው ለሕዝቡ እንግልት፣ በክልሉም ላይ ከፍተኛ ወጪን ሊያስከትላል የሚችል ነው ይላሉ። ቢሆንም ግን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ያስተዋወቀው አዲስ የከተሞችና የአስተዳደር ተቋማት አወቃቀር ሊኖረው የሚችለው ጥቅምም ሆነ የሚገጥመው ተግዳሮት ወደ ፊት የሚታይ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cxe5p05ylvlo
amh
politics
ሩሲያ ዩክሬን ድንበር ላይ ወታደር እያሰፈረች ያለችው ለምንድነው?
ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ሩሲያ ባልተለመደ ሁኔታ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ድንበር ማስጠጋቷ አዲስ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ፍርሃት ፈጥሯል፡፡ ሩሲያ በበኩሏ ዜጎቼን ለመታደግ ነፍጥ ላነሱ ተገንጣይ ቡድኖች እገዛ አደርጋለሁ ብላለች፡፡ አንድ የሩሲያ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣን እንዲያውም ‹ሞስኮ በምሥራቅ ዩክሬን ሩስኪ ተናጋሪ የሆኑ ተገንጣዮችን ለመደገፍ ሁሉንም እገዛ ታደርጋለች› ብለዋል፡፡ ባለሥልጣኑ ጨምረውም ዩክሬን በተገንጣዮቹ ላይ እጇን ካነሳች ደግሞ ሞስኮ ሳታወላውል ጦር ታዘምታለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በሩሲያ የሚደገፉ ተገንጣዮች በምሥራቅ ዩክሬን ከመንግሥት ጋር ግጭት ውስጥ ከገቡ ሰነባብተዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ሩሲያ ወታደሮቿን ወደዚያው ድንበር ማስጠጋቷን ገፍታበታለች፡፡ ባለሥልጣኑ ዲምትሪ ኮዛክ ሩሲያ ዜጎቿን የመጠበቅ ግዴታና ኃላፊነት አለባት ብለዋል፡፡ ‹‹ሁሉም ነገር የሚወሰነው በዩክሬን ጠብ አጫሪነት መጠን ነው› ሲሉም ሊወሰድ ስለሚታሰበው እርምጃ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ እኚሁ ባለሥልጣን ዩክሬን በሩሲያ ተናጋሪ ሕዝቦች ላይ እጇን ካነሳች ምናልባትም የዩክሬን መጨረሻ ሊሆን ይችላል ሲሉ ነገሩ የት ድረስ ሊሄድ እንደሚችል አስገንዝበዋል፡፡ ዩክሬን ላይ ከተኮስን እግር ላይ ሳይሆን ፊት ላይ ነው የሚሆነው ሲሉም በወታደራዊ ቋንቋ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡ ሩሲያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ድንበር ብታስጠጋም ለክፋት እንዳልሆነ ስትናገር ነበር የቆየችው፡፡ የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ጄን ወደ ድንበር የተጠጉ የሩሲያ ወታደሮች ብዛት በ2014 ከነበሩት በላይ ናቸው ብለዋል፡፡ ሩሲያ በዚህ ዓመተ ምሕረት ዩክሬንን መውረሯ አይዘነጋም፡፡ ዋይት ሐውስ ጉዳዩን አሳሳቢ ብሎታል፡፡ አንድ በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች እየተጋራ የሚገኝ ተንቀሳቃሽ ምሥል ሩሲያ ከባባድ መሣሪያዎችን ወደ ዩክሬን ድንበር ስታመላልስ የሚያሳይ ነው፡፡ በዩክሬን ወታደሮችና በሩሲያ የሚደገፉት ምሥራቅ ተገንጣዮች መካከል በዶንባስ ግዛት ወታደራዊ ግጭቶች ባለፉት ወራት ጨምረው ነበር፡፡ ባለፈው ሐሙስ አንድ የዩክሬን ወታደር በግጭት መሞቱ በዚህ ዓመት የተገደሉ ወታደሮችን ቁጥር 25 አድርሶታል፡፡ ባለፈው ዓመትም በተመሳሳይ በግጭቱ 50 ወታደሮች ሞተው ነበር፡፡ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲመር ዘለኔስኪ ሐሙስ ወታደራቸው ከተገደለ በኋላ አካባቢውን መጎብኘታቸው ሌላ ውጥረት ፈጥሯል፡፡ ያንኑ ቀን ሐሙስ ነገሮች መስመር እንዳያልፉ በሚል የጀርመኗ መራሒተ መንግሥት አንግላ ሜርክል ወደ ፑቲን ስልክ መተው ነገር እናብርድ ሲሉ ተማጽነዋል፡፡ ሜርክል ሩሲያ ወታደሮቿን ከድንበር ዘወር እንድታደርግ ነበር ቪላድሚር ፑቲንን የጠየቁት፡፡ በ2014 ሩሲያ የዩክሬን አካል የነበረችውን ክሪሚያ ግዛትን በኃይል በቁጥጥር ሥር ማድረጓ ይታወሳል፡፡ ይህ ክስተት ምዕራባዊያንን ፍጹም ያስደነገጠ ነበር፡፡ የሩሲያን ወረራ ተከትሎም የአውሮጳ ኅብረትና አሜሪካ በሩሲያ ላይ ከባድ ያሉትን ማዕቀብ ጥለው ቆይተዋል፡፡ ይህን የሩሲያን ወረራ ተከትሎ እነዚህ ተገንጣዮች በዶንባስ ክልል የዶኔስክ እና ሉሃነስክ ግዛትን ተቆጣጥረዋል፡፡ በዶንባስ በአመዛኙ የሩስኪ ተናጋሪዎች ናቸው የሚበዙት፡፡ ሩሲያና ዩክሬን በነበራቸው የተራዘመ ግጭት ቢያንስ 14ሺ ወታደሮች እንደሞቱ ይገመታል፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-56686722
amh
politics
በፖሊስ የተገደለው ጥቁር አሜሪካዊ ቤተሰቦች 15 ሚሊዮን ዶላር ሊከፈላቸው ነው
የአሜሪካዋ ኮሎራዶ ክፍለ ግዛት ባለሥልጣናት ከፖሊስ ጋር በነበረ እሰጣገባ ምክንያት የተገደለው ጥቁር አሜሪካዊ ቤተሰቦች 15 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንደሚከፈላቸው አስታውቀዋል። የ23 ዓመቱ ኢላይጃህ ሸነን ማክሌይን በፈረንጆቹ 2019 አውሮራ በምትባል ሥፍራ ነው ሕይወቱ ያለፈው። ግለሰቡ ሕይወቱ ከማለፉ ከሶስት ቀናት በፊት ሶስት ፖሊሶች አስቁመውት አደገኛ ማደንዘዣ መደኃኒት ሰጥተውት ነበር። የሟች ቤተሰቦች ባለፈው ዓመት ክስ መሥርተው ፖሊስ ለኢላይጃህ ሞት ኃላፊነቱን እንዲወስድ ሲጠይቁ ነበር። የኮሎራዶ ክፍለ ግዛት በስህተት በተፈፀመ ሞት አማካይነት ይህን ያክል ገንዘብ ለከሳሽ ስትከፍል የመጀመሪያዋ ነው። የኢላይጃህ እናት ሺና የሕግ አማካሪ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው እናቱ ሕዝቡ ባሳያቸው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውንና የልጃቸው ሞት "ከባድ ለውጥ ለሚያስፈልገው" ፖሊስ እንደምክንያት እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል። በሟች ቤተሰብ በፖሊስ መካከል የተገባው ስምምነት ምን እንደሚያካትት እስካሁን ይፋ አልተደረገም። የኢላይጃህ ጉዳይ ይበልጥ ትኩረት ያገኘው ምንም ዓይነት መሣሪያ ሳይታጠቅ ባለፈው ዓመት በፖሊስ የተገደለው ጆርጅ ፍሎይድ ክስተት አሜሪካን ካናወጠ በኋላ ነው። ወጣቱ ኢላይጃህ ነሃሴ 24/2019 ዴንቨር ውስጥ በምትገኘው አውሮራ ካለ አንድ ጎዳና ላይ ብቻውን ሲራመድ ሶስት ፖሊሶች ያስቆሙታል። አንድ ተጠርጣሪ እያፈላለጉ ያሉት ፖሊሶች በተሰጣቸው ጥቆማ መሠረት ኢላይጃህ "ተጠርጣሪውን መስሎን ነበር" ሲሉ ተናግረው ነበር። ሶስቱ ፖሊሶች ኢላይጃህ ታጥቆ እንደሆን ለመፈተሽ ቢሞክሩ ወጣቱ ግን እንዳይነኩት በመፈለግ ይሸሻል። ከፖሊስ ካሜራ ላይ የተገኘው ምስል እንደሚያሳየው ኦቲዝም ያለበት ኢላይጃህ "እኔ ከቤት ብዙ አልወጣም፤ እባካችሁ ብዙ አትቅረቡኝ" እያለ ነበር። ነገር ግን የፖሊስ መኮንኖቹ በግድ ይዘውት ከመሬት ያጣብቁታል። የኢላይጃህ ቤተሰብ ፖሊስ አላስፈላጊና ከመጠን በላይ የሆነ ኃይል ተጠቅሟል፤ ይህ ሲሆን ልጃችን እያስመለሰ ነው፤ መተንፈስ አቃተኝ እያለ ነበር ሲሉ ከሰዋል። ፖሊሶቸ ተጨማሪ እርዳታ ከጠሩ በኋላ 500 ግራም ኬታሚን የተባለ አደንዛዥ መድኃኒት እንደወጉት ተነግሯል። ከሶስት ቀናት በኋላ የኢላይጃን አእምሮ ሙሉ በመሉ መሥራት አቆመ። ከሁለት ዓመታት በኋላ ሶስቱ ፖሊሶችና መድኃኒቱን የወጉት ሁለት የሕክምና ሰዎች በ23 መዝገቦች ተከሰዋል። የጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰቦች ተመሳሳይ ክስ ፖሊስ ላይ መሥርተው 27 ሚሊዮን ዶላር እንደተከፈላቸው ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59364201
amh
politics
የአንጎላ “የሰላም መሃንዲስ” በ79 ዓመታቸው አረፉ
በማዕድን የበለጸገችውን አንጎላን ለአራት አስርት ዓመታት ያህል የገዙት ሁለተኛው የአንጎላ ፕሬዝዳንት ሆሴ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ በ79 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የአገሪቱ መንግሥት አስታወቀ። ዶሳንቶስ ስፔን ውስጥ የልብ ህመም በሽታ ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው ሕይወታቸው አልፏል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶስ ሳንቶስ በአውሮፓውያኑ 2000 መጀመሪያ ላይ በአንጎላ ለረጅም ጊዜ ሲካሄድ የቆየውን የእርስ በርስ ጦርነት በመቋጨት ታሪክ ይዘክራቸዋል። ለዚያም ነው ደጋፊዎቻቸው “የሰላም መሃንዲስ” እያሉ የሚጠሯቸው። ነገር ግን በሥልጣን ዘመናቸው በተፈጸሙ መጠነ ሰፊ ሙስና እና የሰብዓዊ መብት ረገጣ ምክንያት በርካቶችም የሚተቿቸው አልጠፉም። ዶስ ሳንቶስ በቀድሞዋ የሶቭየት ኅብረት በፔትሮሊየም ምህንድስና ዲግሪያቸውን ያገኙት በአውሮፓውያኑ 1969 ነበር። የመጀመሪያው የአንጎላ ፕሬዚዳንት አንቶኒዮ አጎስቲንሆ ኔቶ ከሞቱ ከአስር ዓመታት በኋላ ሁለተኛው ፕሬዚዳንት በመሆንም አንጎላን መርተዋል። ሥልጣን ሲቆናጠጡ ገና የ37 ዓመት ወጣት ነበሩ። ከቅኝ ግዛት ነጻነቷን በአውሮፓውያኑ 1975 የተጎናጸፈችው አንጎላ ከአራት ዓመታት በኋላ የፖርቹጋል ቅኝ ግዛትን የተዋጉት የዶስ ሳንቶስ ኤምፒኤልኤ እና ዩኒታ በሚባሉ ቡድኖች በተፈጠረው ቁርሶ አገሪቷ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ገባች። ለ27 ዓመታት የዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነትም አገሪቷን አፈራረሳት። በጦርነቱ ወደ 500 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ሞተዋል ተብሎ ይታመናል። በተጨማሪም በዚህ ጦርነት የውጭ አገራት ኃይሎች ተሳታፊ ሆነዋል። በአፓርታይድ የነጮች አገዛዝ ስር የነበረችው ደቡብ አፍሪካ ወታደሮች አማጺው ዩኒታ የተሰኘውን ቡድን እንዲደግፉ ስትልክ፣ የኩባ ኃይሎች ደግሞ ለመንግሥት ወግነው ጣልቃ ገብተዋል። ዶስ ሳንቶስ ሶቭየት ኅብረት እስትክትፈርስ እንዲሁም የቀዝቃዛው ጦርነት ማክተሚያ ድረስ በማርክሲስት ርዕዮተ ዓለም ላይ ያተኮረ የአንድ ፓርቲ መንግሥትን መርተዋል። ኤምፒኤልኤ እና ዩኒታ የሰላም ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ ግን ሁኔታዎች መቀየር ጀመሩ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cndx7ykr3pko
amh
politics
የታይዋን ፓርላማ አባላት የአሳማ ስጋ በመወርወር ተቃውሟቸውን ገለፁ
የታይዋን የተቃዋሚ ፓርላማ አባላት የአሳማ ስጋ በመወርወርና በቡጢም በመደባደብ ተቃውሟቸውን ገልፀዋል። ከአሜሪካ የሚገባው የአሳማ ስጋ ምርት ጋር የተያያዘው መመሪያ ቀለል ብሏል በሚልም ነው ፓርላማው ውስጥ ይህ የተፈጠረው። በቅርቡም የታይዋን መንግሥት ከአሜሪካ እንዲገባ የፈቀደው የአሳማ ስጋ ራክቶፓሚን የሚባል ሱስ የሚያስይዝና በታይዋንና በአውሮፓ ህብረት የታገደ ንጥረ ነገር የያዘ ነው ተብሏል። ንጥረ ነገሩ ለጤና ስጋትም እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ታይዋንም ለአሳማ ስጋዎች ጥቅም ላይ እንዳይውል ከልክላዋለች። ገዢው ፓርቲው በበኩሉ ይህን ክስ ያስተባበለ ሲሆን ምክንያታዊ ወደሆኑ ንግግሮችም እንዲመለሱ ጠይቋል። እንዲህ አይነት ቁጣዎችና ድብድቦች ለታይዋን ፓርላማ አዲስ አይደሉም። የታይዋን ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ ኩዎሚንታ (ኬኤምቲ) ፓርቲ የአሳማ አንጀትና ስጋ በባልዲ ይዘው ወደ ፓርላማ በማምጣትና በመወርወር ጠቅላይ ሚኒስትር ሱ ሴንግ ቻንግ ጥያቄና መልስ እንዳያካሂዱም ለማድረግ ሞክረዋል። የአሳማ አንጀት መወርወር ብቻ ሳይሆን በተቃዋሚው ፓርቲ ኬኤምቲና ቼን ፖ ዌይ በተባለው ፓርቲ አባላት መካከልም ቡጢ እንደተሰነዘረም ሮይተርስ የዜና ወኪል አስነብቧል። ገዢው ዲሞክራቲክ ፕሮግረሲቭ ፓርቲ "አፀያፊ ተቃውሞ" በሚል ያወገዘው ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ምግብ መባከኑና ፓርላማውም በመጥፎ ጠረን መታወዱን የማይገባ ተግባር ነው ብሎታል ። ፓርላማው ወደ ምክንያታዊ ክርክር እንዲገባም ጥያቄ ቀርቧል። የታይዋን ፕሬዚዳንት ትሳይ ኢንግ ከአሜሪካ የሚገባውን የአሳማ ስጋ ምርት በማስመልከት የተጣለውን መመሪያ ያቀለሉት ነሐሴ ወር ላይ ሲሆን፤ ከጥር ጀምሮም ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። ውሳኔው አሜሪካን ሲያስደስት የታይዋን ተቃዋሚዎች ግን ህዝቡ ላይ ሊያስከትለው የሚችለውን የጤና እክል በማንሳት ተግባራዊ እንዳይሆን ይሞግታሉ። ከዚህ ቀደምም በርካታ ሰልፈኞች ተቃውሟቸውን ገልፀው ነበር። ሱስ ያስይዛል የሚባለው ራክቶማፖን በታይዋል፣ በቻይናና በአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ለሰው ልጅና ለእንስሳት ከሚያስከትለው የጤና ስጋት ጋር ተያይዞም እግድ ተጥሎበታል። ዩዋን የተባለው የታይዋን ፓርላማ ቡጢ መሰነዛዘር፣ ፀጉር መጎተት፣ የውሃ ፕላስቲክ መወርወርንም በአመታት ውስጥ አስተናግዷል። በተለይም ከሶስት አመት በፊት የመሰረተ ልማት ፍሰት ላይ በተነሳ ክርክር የፓርላማ አባላቱ ወንበር አንስተው ሲወራወሩ ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/news-55106409
amh
politics
ትግራይ ፡ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም (አምባዬ) መስፍን
በትግራይ ውስጥ የተከሰተውን ወታራዊ ግጭትን ተከትሎ በተፈላጊነት የስም ዝርዝራቸውን ካወጣው ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍን በአገሪቱ የጸጥታ ኃይሎች ረቡዕ ጥር 05/2013 ዓ.ም መገደላቸው ተገልጿል። አቶ ስዩም መስፍን ከፍተኛ የህወሓት አመራር ሆነው ከሃያ ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና በቻይና የአገሪቱ አምባሳደር ሆነው የሰሩ ሲሆን ከህወሓት የትጥቅ ትግል ጀምሮ ከፍተኛ ተጽእኖ የነበራቸው ግለሰብ እንደነበሩ ይነገራል። ስዩም (አምባዬ) መስፍን ስዩም መስፍን በ1940ዎቹ መጀመሪያ ትግራይ ውስጥ አዘባ ተብሎ በሚጠራ የአጋሜ አውራጃ ቀበሌ ነው የተወለዱት። የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲ ግራት ከተማ አግአዚ ትምህርት ቤት በመከታተል፤ በባሕር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የዲፕሎማ ምሩቅ ናቸው። ከፍተኛ ትምህርታቸውን ለመቀጠል ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የገቡት አቶ ስዩም፤ በዩኒቨርሲቲው የትግራይ ተማሪዎች ማኅበርን ካቋቋሙት መካከል አንዱ ናቸው። በ1965 ዓ.ም ማኅበሩ በድብቅ ወደ ተመሰረተው የትግራይ ብሔር የፖለቲካ ቡድንነት ሲሸጋገር ስዩም ፓርቲውን ከመሰረቱት ሰባት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች አንዱ ነበሩ። የንጉሡ ሥርዓት መውደቅን ተከትሎ በርካታ ወጣቶች የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በመመስረት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ፤ የትግራይ ብሐር ፓርቲ አባላትም "የትግራይ ሕዝብ ጥያቄዎች በትጥቅ ትግል ነው የሚፈቱት" በማለት ጠመንጃ አንስተው ትግል ለመጀመር ወደ ትግራይ በረሃማ አካባቢዎች ሄዱ። አቶ ስዩም መስፍንም የዚህ ውሳኔ አካል ሆነው ከጓዶቻቸው ጋር ወደ ትግራይ አቀኑ። ስዩም - በትጥቅ ትግል የትግራይ ሕዝብን ጥያቄዎች ለመመለስ ትጥቅ ትግል እንዲጀመር ከተወሰነ በኋላ የንቅናቄው አመራር በሦስት የተለያዩ መንገዶች የተሰጠውን ዓላማ እንዲፈጽም ተወሰነ። አንዱ ቡድን ወደ ደደቢት በረሃ በመሄድ የትጥቅ ትግሉ መጀመርን ይፋ እንዲያደረግ፣ ሁለተኛው ወደ ኤርትራ በመሄድ የትጥቅ ትግል ተሞክሮ እንዲወስድ፣ ሦስተኛው ደግሞ በከተማ ውስጥ ፖለቲካዊ ሥራዎች እንዲመራ ተደረገ። በዚህም አቶ ስዩም መስፍን ወደ በረሃ በመሄድ የትጥቅ ትግሉን ከጀመሩት አስራ አንድ ሰዎች መካከል አንዱ ነበሩ። ቤተሰባቸው አምባዬ ብሎ መጠሪያ ስም ያወጣላቸው አቶ ስዩም፤ ወደ ትጥቅ ትግል ከሄዱ በኋላ ግን ሁሉም ስማቸውን ሲቀይሩ አብረዋቸው ከነበሩት ጓዶች መካከል አንዱ የሆነው ታጋይ ስሑል 'ስዩም' የሚለውን ስም ሰጣቸው። በ1970ዎቹ አጋማሽ ድርጅቱን ከሚመሩት አንዱ በመሆን የተመረጡት አቶ ስዩም፤ አድያቦ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከመንግሥት ሠራዊት ጋር በተደረገው ከባድ ውጊያ ጭንቅላታቸውን ተመትተው ኤርትራ ውስጥ ህክምና እንደተደረገላቸው "ጽናት" በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ሰፍሯል። ታጋይ መሓሪ ተኽለ (ሙሴ) ከኤርትራ ህወሓት ወደ ሚመራው የትጥቅ ትግል ከተቀላቀሉት ጥቂት ቀደምት ታጋዮች በመንግሥት ተይዞ በሽረ እንዳሥላሴ ከታሳረ በኋላ፤ ስዩም ሙሴን ጨምሮ የታሰሩትን ታጋዮች ለማስፈታት የተዘጋጀውን "የሙሴ ኦፕሬሽን" ለመፈጸም የአዕምሮ ህመምተኛ በመምሰል ስለላ ላይ ተሰማርተው እንደነበር ታሪካቸው ያትታል። ስዩም- የህወሓት መልዕከተኛ አቶ ስዩም ከ1969 ዓ.ም መጨረሻዎቹ ጀምሮ የህወሓት የውጭ ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው ለ15 ዓመታት በሱዳን የሰሩ ሲሆን፤ በካርቱም ቆይታቸውም ስማቸው ወደ 'ሙሳ' ተቀይሮ እንደነበረም ይነገራል። አቶ ስዩም በ1983 ዓ.ም ከመለስ ዜናዊና ከብርሃነ ገብረክርስቶስ ጋር በመሆን በለንደን ከመንግሥት ጋር ሲደረግ በነበረው ድርድር ላይ ተሳትፈዋል። ህወሓት/ኢህአዴግ የደርግ ሥርዓትን ጥሎ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር የወቅቱ የሱዳን ፕሬዝደንት የነበሩት ኦማር አልበሽር ባዋሷቸው አውሮፕላን ከሌሎች ጓዶቻቸው ጋር ወደ አዲስ አበባ በሚጓዙበት ጊዜ የቴክኒክ ችግር አጋጥሟቸው ነበር። በዚህ ምክንያት አውሮፕላኑ ከባድ አደጋ እንደገጠማት በተረዱ ጊዜ ለ17 ዓመታት የመሩት ትግል በድል ተጠናቆ ማየት አለመቻላቸው ከባድ ድንጋጤ ውስጥ ከቷቸው እንደነበር ይነገራል። ነገር ግን የፈሩት ሳይደርስ በሰላም አዲስ አበባ ገቡ። ስዩም - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በህወሓት መሪነት ኢህአዴግ የአገሪቱን ሥልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ አንስቶ አቶ ስዩም መስፍን ለ20 ዓመታት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን በቁልፍ የመንግሥት ሥልጣን ላይ ቆይተዋል። ከኢትዮ ኤርትራ የድንበር ጦርነት ማብቃት በኋላ በ1993 ዓ.ም በህወሓት አመራሮች መካከል ክፍፍል ሲፈጠር አቶ ስዩም ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጎራ ከተሰለፉት መካከል አንዱ ነበሩ። ከድንበር ጦርነቱ ጋር በተያያዘ በዓለም አቀፍ የግልግል ፍርድ ቤት ለደም አፋሳሹ ጦርነት ዋነኛ ምክንያት የነበረችው ባድመን ለኤርትራ ወስኖ እያለ ለኢትዮጵያ እንደተወሰነ አድርገው በቴሌቪዥን መግለጫ በመስጠት ሕዝብ የድጋፍ ሰልፍ እንዲወጣ በማድረጋቸው በተአማኒነታቸው ላይ ዘወትር የሚጠቀስ ጠባሳ ጥሏል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ በዙሪያዋ ካሉ ጎረቤት አገራት ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖራት ለማድረግ አስችለዋል ቢባልላቸውም፤ ከኤርትራ ጋር ግን የድንበር ግጭቱ ሳይፈታ እንዲቆይ በማድረግ ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ያደረጉት ጥረት የለም ተብለው ይተቻሉ። በተጨማሪም ህወሐት በኢሕአዴግ ውስጥ በነበረው ጠንካራ የበላይነት ወቅት በአገሪቱ ውስጥ ለተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂ ናቸው ተብለውም ይከሰሳሉ። በሌላ በኩል አቶ ስዩም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በቆዩባቸው ዓመታት የእስያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸው እንዲያፈሱ ከፍተኛ ጥረት ያደርጉ እንደነበረ ይነገራል። በዚህም ምክንያት የሚኒስትርነት ቦታቸውን ሲለቁ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ለስድስት ዓመታት ሰርተዋል። ስዩም - ከለውጡ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ አቶ ስዩም ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተመልሰው ማገልገል ጀምረው ነበር። ነገር ግን በተመደቡበት ክፍል ደስተኛ እንዳልሆኑ በመግለጽ ወደ መቀለ እንደሄዱ ይነገራል። በፌደራል መንግሥቱና በህወሐት መካከል የተፈጠረው መካረር በበረታበት ወቅት፤ አቶ ስዩም በተለያዩ አጋጣሚዎች በመገናኛ ብዙሃን ላይ በመቅረብ ጠቅላይ ሚኒስትሩን አጥብቀው ሲተቹ ቆይተዋል። በአንድ ቃለ ምልልሳቸውም የኖቤል ኮሚቴ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጠው የሠላም ኖቤል ሽልማት ላይ እየተወዛገበ መሆኑን በመግለጽ ሽልማቱን ለማንሳት እያሰበ መሆኑን በመግለጻቸው መነጋገሪያ ሆነው ነበር። የሽልማት ኮሚቴውም በእንዲህ አይነቱ ጉዳይ ላይ እንዳልተነጋገረና አንድ ጊዜ የተሰጠ የኖቤል ሽልማት እንደማይመለስ ማብራሪያ መስጠቱ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ሠራዊት የክልሉን ዋና ከተማ መቀለን በቁጥጥር ስር ከማስገባቱ ቀደም ብሎ እስካለው ጊዜ ድረስ አቶ ስዩምና የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች በከተማዋ የቆዩ ሲሆን፤ ከዚያ በኋላ ግን ከተማዋ ወጥተው ወደ ተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች መሄዳቸው ተነግሮ ነበር። የእስር ማዘዣ ከወጣባቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ የነበሩት አቶ ስዩም መስፍንና ሌሎች ጓዶቻቸው ያሉበት ቦታ በጸጥታ ኃይሎች ተከቦ እጅ እንዲሰጡ የቀረበላቸውን ጥሪ ባለመቀበል ጥር 05/2013 ዓ.ም በተወሰደባቸው እርምጃ መገደላቸውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሰጠው መግለጫ አሳውቋል። መቀለ በኢትዮጵያ ሠራዊት እጅ ውስጥ መግባቷን ተከትሎ ከነበሩት ጥቂት ቀናት ውጪ የህወሓት አመራሮች ለየትኛውም የመገናኛ ብዙሃን ምንም አይነት መግለጫ ሰጥተው ስለማያውቁ ስለተገደሉት አመራሮቹ ከቡድኑም ሆነ ከሌላ ወገን የተሰማ ነገር የለም።
https://www.bbc.com/amharic/news-55663925
amh
politics
በእስር ላይ ያሉ የኦነግ አመራሮች በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ተገለጸ
በእስር ላይ የሚገኙ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ ጠበቃቸው ለቢቢሲ ተናገሩ። በእስር ላይ የሚገኙ የኦነግ አመራሮችን ከሚወክሉት ጠበቆቻቸው መካከል አንዱ የሆኑት ቱሊ ባይሳ፤ የረሃብ አድማ ላይ የሚገኙት ሚካኤል ቦረን፣ ኬነሳ አያና፣ ዳዊት አብደታ፣ ለሚ ቤኛ፣ ገዳ ገቢሳ እና በቴ ኡርጌሳ የተባሉት የኦነግ አመራሮች መሆናቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። እንደ ጠበቃው ከሆነ የተያዙበት ሁኔታ ሕጋዊ አይደለም በሚል ላለፉት አምስት ቀናት በረሃብ አድማ ላይ የቆዩት አመራሮቹ በአገር ሽማግሌዎች ተማጽኖ የረሃብ አድማቸውን ለማቆም ተስማምተው የነበረ ቢሆንም ወደ ሆስፒታል ተወስደው አስፈላጊው የሕክምና መሳሪያ የለም ተብሎ ወደ እስር ቤት ከተመለሱ በኋላ በረሃብ አድማቸው መቀጠላቸውን አስረድተዋል። "የረሃብ አድማውን ለማቆም ከአገር ሸማግሌዎች የቀረበላቸውን ተማጽኖ ተቀብለው ነበር። ነገር ግን ምግብ መውሰድ ከመጀመራቸው በፊት ወደ ሆስፒታል መወሰድ ነበረባቸው። ይሁን እንጂ በፌደራል ፖሊስ ሆስፒታል አስፈላጊ የሆነ የሕክምና መሳሪያ የለም በመባሉ ወደ ቡራዩ ፖሊስ ጣቢያ እንዲመለሱ ተደርገዋል። አሁንም በረሃብ አድማ ላይ ናቸው" ብለዋል ጠበቃ ቱሊ ባይሳ። የኦነግ አመራሮች በእስረኞች ላይ ያለውን አግባብ የሌለው አያያዝ በመቃወም የረሃብ አድማ እያደረጉ መሆኑን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በትናንትናው ዕለት ረቡዕ የካቲት 3፣ 2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። እስረኞቹ በአግባቡ እንደማይያዙና "እንግልትና ጥሰት ይፈጸምባቸዋል" ያለው መግለጫው ምግብ፣ ውሃና ሌሎች መሰረታዊ ሰብዓዊ አገልግሎቶችንም መነፈጋቸውንም አክሏል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች ምግብ በማቆማቸው "በጤንነትና አጠቃላይ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ደህንነት በየቀኑ እየተጎዱ ነው" ብሏል መግለጫው ጠበቆችም ሆኑ የቤተሰብ አባላት እስረኞቹን ማግኘት ፈጽሞ አስቸጋሪ እንደሚሆንባቸው የሚናገሩት ጠበቃው የእስረኞቹን ሁኔታም ከደንበኞቻቸው ሳይሆን ታስረው ከሚለቀቁ ከሌሎች ሰዎች በተዘዋዋሪ የሚሰሙበት አጋጣሚዎች መኖራቸውን ይናገራሉ። "እኛ (ጠበቆች) ከባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ጀምሮ እስካሁን አግኝተናቸው አናውቅም" በማለት ጠበቆች ከደንበኞቻቸው ጋር ከተገናኙ ወራቶች መቆጠራቸውን ያስረዳሉ። ኦነግ በመግለጫውም የእስረኞቹ ቤተሰቦች እንዳይጠይቋቸው እንደሚከለከሉና አልፎ አልፎም ትንኮሳም እንደሚደርስባቸው በትናንትናው መግለጫ ሰፍሯል። ጠበቃ ቱሊ እንደሚሉት ዐቃቤ ሕግ የኦነግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በሆኑት ሚካኤል ቦረን እና ኬነሳ አያና ላይ የማቀርበው ክስ የለኝም ብሎ መዝገባቸውን ከዘጋ አንድ ዓመት ቢያልፈውም አሁንም ሁለቱ ግለሰቦች በእስር ላይ እንደሚገኙ ያስረዳሉ። ለሚ ቤኛ እና ዳዊት አብደታ የተባሉት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ደግሞ በፍርድ ቤት በነጻ የተሰናበቱ ናቸው ይላሉ ጠበቃው። "ዐቃቤ ሕግ ይግባኝ ጠይቆ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረስ ተከራክረን ነጻ የወጡ ሰዎች ናቸው። ፖሊስ ግን በሕገ-ወጥ መንገድ ይዟቸው ይገኛል" በማለት ቱሊ ያስረዳሉ። እንደ ጠበቃው ከሆነ የኦነግ ቃል አቀባይ በሆኑት በቴ ኡርጌሳ እና የፓርቲው አመራር በሆኑት ገዳ ገቢሳ ደግሞ እስከነ ጭራሹ ክስ አልተመሰረተባቸወም፤ ሲከናወንባቸው የነበረው የወንጀል ምርመራ ተቋርጧል። ኮሎኔል ገመቹ አያና እና የኦነግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አብዲ ረጋሳ ከትናንት በስቲያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት ፍርድ ቤቱ በነጻ ቢያሰናብታቸውም ዐቃቤ ሕግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብሎ ግለሰቦቹ እንዳይለቀቁ አድርጎ አስቀምጧል ይላሉ። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ በትናንትናው መግለጫ ላይ" መንግሥት የኦነግ አመራሮችን በሕገ-ወጥ መንገድ በማሰር እና በእስር ቤቶች ውስጥ በማስቀመጥ እያሰቃየ ይገኛል" ብሏል። ባለስልጣናቱ በኦነግ ለቀረበባቸው ክስ ምላሽ አልሰጡም። መግለጫው አክሎም በእስር ላይ ያሉ አመራሮቹ በቡራዩ ፣ ሰበታ እና ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያዎች ታስረው እንደሚገኙ አመልክቷል። "የተያዙበት ሁኔታ ከሞራልም ከሕግም ውጪ ነው" ክስ ያልተመሰረተባቸውን፣ በፍርድ ቤት በነጻ የተሰናበቱና በሕግ መሠረት በእስር ላይ መቆየት የማይገባቸውን ከእስር ለማስፈታት "ሪፖርት ያላደረግንበት ቦታ የለም።" በማለት ጠበቃው ቱሊ ይናገራሉ። "ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አሳውቀናል። አካልን ነጻ ማውጣት መዝገብ አስከፍተናል። . . . ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት አድርገናል" ይላሉ። ቢቢሲ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጉዳዩን በተመለከተ ያነጋገረው አካል ስለመኖሩ ለመጠየቅ ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ጠበቃው ደንበኞቻቸው "የተያዙበት ሁኔታ ከሞራልም ከሕግም ውጪ ነው። . . . ከባድ ወንጀል ነው እየተፈጸመባቸው ያለው። ጉዳዩን ለቤተሰብም ማስረዳት በጣም አስቸጋሪ ሆኖብናል።" ይላሉ። አብዛኞቹ የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች ሁከትና ሽብርተኝነትን በማነሳሳት ተከሰው ከሁለት ዓመት በላይ በእስር ላይ ይገኛሉ። አንዳንዶቹ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቢያስተላልፍም በእስር ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል። መንግሥት በቅርቡ ለሚካሄደው አገራዊ ምክክር መንዱን ለማመቻቸት በሚል በእስር ላይ የነበሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ከእስር ፈትቷል። ኦነግ ለአገራዊ ምክክሩ እንዳልተጠራ የገለጸ ሲሆን በዚህም ምክክር ለመሳተፍም አመራሮቹ እንዲፈቱ እየጠየቀ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-60329476
amh
politics
ሰሜን ኮሪያ፡ ታመዋል ሲባሉ የነበሩት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ድንገት ተከሰቱ
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ታመዋል ከሚለው ጀምሮ፣ አብቅቶላቸዋል፣ ሞተዋል እየተባለም ብዙ ይወራባቸው ነበር፡፡ ድንገት በፓርቲ ስብሰባ ተከስተው መመርያ ሰጥተዋል፣ ትናንት፡፡ ሰሜን ኮሪያ ትልቅ አደጋ ከፊቷ ተደቅኗል ያሉት ኪም ሕዝቡ በተጠንቀቅ እንዲሆን አዘዋል፡፡ ትልቅ አደጋ እየመጣ ነው ያሉት ኪም አደጋዎቹ በዋናነት ሁለት መሆናቸውን አውስተዋል፡፡ አንዱ ኮሮና ቫይረስ ሲሆን ሌላው ደግሞ አውሎ ንፋስ ነው፡፡ ኪም ከሰሞኑ ጠፍተው ስለነበር የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ስለነበረ ምናልባት ሞተው ይሆን? ሲባል ነበር፡፡ ሰሜን ኮሪያ እስካሁን አንድም ሰው በኮቪድ-19 አልተያዘብኝም ስትል ታስተባብላለች፡፡ አይበለውና ወረርሽኙ ወደዚያች አገር ቢገባ ባላት ደካማ የጤና መሰረተ ልማት ከፍተኛ አደጋ ሊያጋጥማት ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡ ይህ በእንዲህ ሳለ ባቪ የሚሰኝ አደገኛ አውሎ ነፋስ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሰሜን ኮሪያን ሊመታት ይችላል ተብሎ ተሰግቷል፡፡ የፖሊትቢሮ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ኪም በስብሰባው ላይ ንግግር እያደረጉ ሲያጨሱ ይታዩ ነበር፡፡ በዚህ ንግግራቸው ኮቪድን በተመለከተ አንዳንድ ችግሮች ተስተውለዋል ብለዋል፡፡ ምን ማለታቸው እንደሆነ ግን የሚያውቅ አልተገኘም፡፡ ፒዮንግያንግ ለረዥም ጊዜ ወረርሽኙ እኔ ጋ ድርሽ አላለም ስትል እያስተባበለች ቆይታለች፡፡ ነገር ግን ይህን የሰሜን ኮሪያን አስተያየት ብዙዎች በጥርጣሬ ነው የሚመለከቱት፡፡ አንድም በቫይረሱ የተጠቃ ሰው የለም ስትል የነበረው ሰሜን ኮሪያ በቫይረሱ አጠባበቅ ዙርያ ችግሮች ታይተዋል ማለቷ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል፡፡ ሰሜን ኮሪያ ከጥርጣሬ የተነሳ አንዲት የድንበር ከተማ ሰዎች ተገለው እንዲቀመጡ ያደረገች ሲሆን ነገር ግን ከዚህ የዘለለ ስለተያዘ አንድም ሰው ተጠቅሶ አያውቅም፡፡ ኪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ክብደት እየጨመሩ ስለሆነ በወጣትነታቸው ሊቀጠፉ ይችላሉ የሚሉ ስጋቶች በስፋት ይሰነዘሩ ነበር፡፡ በቅርቡም ለእህታቸው ኪም ዮ ጆንግ በርከት ያሉ ሥልጣኖችን ሰጥተዋት ነበር፡፡ ይህንን ሁኔታ እንደ ኑዛዜ የወሰዱት ሚዲያዎችም ነበሩ፡፡ ሰሜን ኮሪያ 25 ሚሊዮን ዜጎች አሏት፡፡ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎቿ የረሀብ አደጋ ገጥሟቸዋል ይላል የተባበሩት መንግሥታት፡፡ የረባ የንግድ ግንኙነት ከአገራት ጋር ያልመሰረተችው ሰሜን ኮሪያ ከቻይና ጋር የምታደርገው ንግድ ወሳኝ ተደርጎ ይታሰባል፡፡ ይህም በኮሮና ምክንያት እክል ገጥሞታል፡፡ በፒዮንግያንግ መቀመጫቸውን ያደረጉ በርካታ ግብረሰናይ ድርጅቶችና የኤምባሲ ሰራተኞች አገሪቱን ለቀው እንደወጡ ተዘግቧል፡፡
https://www.bbc.com/amharic/53915684
amh
politics
በጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሰየሙት ዐቢይ አሕመድ ማን ናቸው?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በተመሰረተው ምክር ቤት አማካይነት ለቀጣይ አምስት ዓመታት አገሪቱን እንዲመሩ ተሰይመዋል። አገሪቱ ውስጥ ተከሰተን ፖለቲካዊ ቀውስን ተከትሎ ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን ተከትሎ ነበር ዐቢይ አሕህመድ (ዶ/ር) የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ኃላፊነት ተረከቡት። ባለፉት ሦስት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት ዐቢይ አሁን ለሙሉ የሥልጣን ዘመን ኃላፊነቱን ትተረክበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማን ናቸው? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ስልጣን የመጡት ከሦስት ዓመታት ገደማ በፊት በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ነበር። በወቅቱ ኢትዮጵያ ወደ የእርስ በእርስ ግጭት ለመግባት ከጫ ደርሳለች ተብሎ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣናቸውን እንደተረከቡ ታሪካዊ የሚባሉ የለውጥ እርምጃዎችን ወስደዋል፤ አንዳንዶቹ ለውጦችም በኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት ይሆናሉ ተብለው የማይታሰቡ ነበሩ። ኢትዮጵያ ዘወትር ዜጎች ሃሳባቸውን በነጻናት እንዳይገልጹ ታደርጋለች፣ ተቃዋሚዎች የሚታሰሩባት እና ለተቃውሞ አደባባይ በሚወጡ ዜጎች ላይ የማያዳግም እርምጃ የምትወስድ አገር ናት እየተባለች በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በተደጋጋሚ የምትተች አገር ነበረች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ግን ይህ ሁሉ ተቀየረ። ከኤርትራ ጋራም ሰላም ወረደ። ለዚህ ጥረታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ2019 የሰላም ኖቤል ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእርሳቸው በፊት ሥልጣን ላይ ከነበሩት እና "ጠላት" ከሚባሉት ጋር ለመገናኘት እንዲሁም ስላም ለማውረድ ቁርጠኛ መሆናቸው ተስተውሏል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አባት ሐምሌ 2011 ላይ ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ "ከሁሉም ጋር ጓደኛ የሆነ ልጅ ነው" ሲሉ ልጃቸውን ገልጸው ነበር። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ማን ናቸው? ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኦሮሞ ሕዝብ የተገኙ የኢትዮጵያ መሪ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ያመጣቸው ለሦስት ዓመታት የዘለቀው ተቃውሞ በኦሮሚያ ውስጥ መሠረት ያደረገ ነበር። ለዓመታት በዘለቀው ታውሞ በርካቶች ተገድለዋል በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል። ተቃዋሚዎች ከሚያነሷቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ እና ዋነኛው የኦሮሞ ሕዝብ የኢትዮጵያ ትልቁ ብሔር ሆኖ ሳለ ሕዝቡ ከአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ለዓመታት ተገሎ ቆይቷል የሚል ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ወደ ስልጣን ሲመጡ ይህ መቀየር ጀመረ። ዐቢይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከመሾማቸው በፊት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) አካል የሆነው የኦሮሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኢህዴድ) ሊቀመንበር ተደርገው ተሹመው ነበር። ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሦስት አስርት ዓመታት ገደማ የኢትዮጵያ ፖለቲካን ተቆጣጥሮ የቆየውን ኢሕአዴግ በማክሰም ብልጽግና የተሰኘና ከቀድሞው ገዢ ፓርቲ ሰፋ ያለ መሰረት ያለውን ፓርቲ መስርተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት በኢሕአዴግ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ ሆኖ የቆየው ህወሓት ብልጽግና ፓርቲን ለመቀላቀል አልፈለገም። የ44 ዓመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ክርስቲያን እና ሙስሊም ከሆኑ ወላጆች የተገኙ ሲሆን የተወለዱት ደግሞ በአሉአባቦራ ኦሮሚያ ነው። ዐቢይ አሕመድ በውትድርና ሕይወታቸው አስከ ሌፍተናንት ኮሎኔል ማዕረግ ለመድረስ ችለዋል። ከዚያም የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ የተባለው ተቋምን መስርተው ይመሩም ነበር። በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ያደርግ በነበረው መንግሥት ውስጥ፤ ይህ ተቋም በአገሪቱ የሚደፈጸሙ የሳይብር - ሴኩሪቲ ጥቃቶችን መከላከል ዋና ዓላማው ነበር። በተከታይነት ደግሞ ዐቢይ የአገሪቱ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ሆነው ተሾሙ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙም በኋላ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር በሚገኘው የቴሌኮም ዘርፍ ውስጥ ሌሌች እንዲሰማሩ በመፍቀድ ዘርፉን ለማዘመን ቃል ገብተዋል። ቁልፍ እውነታዎች፡ ዐቢይ አሕመድ ኦሮሞ ከሆኑት ሙስሊም አባላታቸው እና አማራ ከሆኑት ክርስቲያን እናታቸው በአጋሮ ከተማ ተወለዱ። ዐቢይ ገና በአስራዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ እያሉ ደርግን መታገል ጀምሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሰላም እና ደኅንነት ጥናት የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቀብለዋል። የማስተርስ ዲግሪያቸውን ደግሞ 'በትራንስፎርሜሽናል ሊደርሺፕ' ከለንደኑ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ግሪንዊች አግኝተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ኦሮምኛ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎችን ይናገራሉ። እአአ 1995 ላይ በሩዋንዳ የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ኃይል አባል ሆነ አገልግለዋል። 1999 ላይ የኢትዮጵያን የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲን አቋቁመዋል። የኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቦርድ አባል ሆነውም አገልገለዋል። 2002 ላይ የኦሮሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅትን (ኦህዴድ) በአባልነት ተቀላቅለው 2007 ላይ የፓርቲው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል መሆን ችለዋል። 2008 ላይ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። 2010 ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። 2011 ላይ ኢሕአዲግ አንዲከስም ተደርጎ የልጽግና ፓርቲን መሠረቱ። 2012 ላይ ከጎረቤት አገር ኤርትራ ጋር ሰላም እንዲሰፍን ላደረጉት ጥረት የኖቤል የሰላም ሽልማትን ተሸለሙ። 2013 ላይ በትግራይ ኃይሎች ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ መገደዳቸውን አስታወቁ። የኖቤል የሰላም ሽልማት ጠቅላይ ሚንሰትር ዐቢይ ከኤርትራ ጋር የደረሱት የሰላም ስምምነት በሁለቱ አገራት መካከል ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀውን ጦርነትም ሰላምም የሌለበት ሁኔታን የቀየረ ነበር። ይህ ተግባራቸውም የ100ኛው የኖቤል ሽልማት አሸናፊ እንዲሆኑ አደርጓቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦስሎ የኖቤል ሽልማታቸውን ሲቀበሉ የሚከተውን ንግግር አድርገው ነበር። "ጦርነት ለመቀስቀስ የሚያስፈልገው የተወሰኑ ሰዎች ብቻ ነው። ሰላም ለመገንባት ግን መንድር እና ሕዝብ ያስፈልጋል። "ለእኔ ሰላምን መንከባከብ ማለት ዛፍ እንደመትከል እና ማሳደግ ነው። ዛፎች ለማደግ ጥሩ አፍር እና ውሃ እንደሚፈልጉት ሁሉ፤ ሰላምም ያልተቋረጠ ትጋት፣ ያልተቆጠበ ትዕግስት እና ቁርጠኝነትን ይጠይቃል።" ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማታቸውን ከተረከቡ በኋላ በአገሪቱ የተከሰተውን "ሞት እና መፈናቀል" ምክንያት በማድረግ የኖቤል ኮሚቴው የሰጠውን ሽልማት እንዲሰርዝ ጥያቄ ያቀረቡ ነበሩ። ይህን ተከትሎም የኖርዌይ ኖቤል ኮሚቴው መግለጫ ለማውጣት ተገዶ ነበር። ኮሚቴው በመግለጫው ለጠቅላይ ሚንስትሩ የኖቤል ሽልማት መስጠቱ ትክክል አልነበረም ብሎ እንደማያስብ አስታውቋል። መደመር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ 'መደመር' የሚለው ቃል በበርካቶች ዘንድ ጥቅም ላይ ሲውል የቆየ ቃል ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን ችግር መፍታት የሚያስችል አካሄድ እንደሆነ ይናገራሉ። መደመር የተሰኘው የጠቅላይ ሚንስትሩ መጽሐፍም በአማርኛ እና በኦሮምኛ ቋንቋዎች ከታተመ በኋላ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ኮፒ መሸጡ ተነግሯል። 280 ገጽ እና 16 ምዕራፎች ያሉት መጽሐፉ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ፍልስፍና ያትታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዘር የተከፋፈለችው ኢትዮጵያን በአንድነት ስሜት እንድትቆም ይሻሉ፤ በተመሳሳይ ብዝሃነት እንዲከበር ይሻሉ። ጠቅላይ ሚንስትሩ ፍልስፍና የተለያዩ ወይም የሚቃረኑ ሃሳቦችን አንድ ላይ በማምጣት መግባባት ላይ መድረስ ይቻላል የሚል መሠረት አለው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እአአ 2017 ላይ በደኢህዴን ስበሰባ ላይ "አንድ አማራጭ ነው ያለን። ይህም አንድ መሆን ነው፤ መተባበር እና እርስ በእርስ መተጋገዝ ብቻ ሳይሆን መኖር እንዲቻለን አንድ መሆን አለብን። ሌላኛው አማራጭ መገዳደል ነው" ሲሉ ተናግረዋል። የትግራይ ቀውስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትግራይ ኃይሎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ መገደዳቸውን ያስታወቁት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ላይ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከዚህ ውሳኔ እንዲደርሱ ያደረገው ምክንያት የህወሓት ኃይሎች የአገር መከላከያ ሠራዊት አንድ አካል በሆነው የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ መሆኑን ተናግረዋል። "ስለዚህ የፌደራሉ መንግሥት ወታደራሚ አማራጭ እንዲወስድ ተገዷል" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ። በጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተዳደር እና በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ቅራኔ ከለውጡ በኋላ ለርካታ ወራት ቆይቷል። የስልጣን ሽኩቻ፣ ምርጫ እና የተወሰዱ ፖለቲካዊ የለውጥ እርምጃዎች በሁለቱ ወገን መካከል አለመግባባት እንዲፈጠር ካደረጉ ምክንያቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። ለሦስት አስርት ዓመታት ገደማ ህወሓት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አድራጊ ፈጣሪ ኃይል ሆኖ ቆይቷል። የህወሓት አመራሮች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ግን ከስልጣን ተገፍተናል ሲሉ ይከሳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለውጥና ማሻሻያዎችን ሲያደርጉ የህወሓት ኃይሎች ግን ደስተኛ አልነበሩም፤ ይህም ፖለቲካዊ ቀውስ አስከተለ። የህወሓት አመራሮች የጠቅላይ ሚንስትሩን ፈጣን የለውጥ እርምጃ ስልጣንን ለማማከል የሚደረግ ጥረት እንደሆነ እና የኢትዮጵያን የፌደራል ሥርዓት ለማፍረስ የሚደረግ ጥረት እንደሆነ አድርገው ይመለከቱታል። ቀጠናዊ ተጽእኖ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአጭር የሥልጣን ዘመናቸውን አለመግባባት በተፈጠረባቸው ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በማሸማገል ተልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። በሱዳን ከአል-በሽር መወገድ በኋላ የአገሪቱ ሠራዊትና ተቃዋሚዎች ወደ ድርድር እንዲመጡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። ይህም ድርድር በሱዳን ሠራዊቱና እና ሲቪሎች ሥልጣን ተጋርተው አገሪቷ በሽግግር መንግሥት እንድትመራ አስችሏል። ጂቡቲ እና ኤርትራም ዲፕሎማሲያዊ ግነኙነታቸውን እንዲሰያሻሽሉ ጥረት አድርገዋል። ሶማሊያ እና ኬንያም በሚጋጩበት የባሕር ጠረፍ ዙሪያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለቱን አገራት አሸማግለዋል። ይህን ብቻም ሳይሆን የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር እና የአማጺያኑ መሪ ሬክ ማቻር ከስምምነት እንዲደርሱ የተቻላቸውን አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትግራይ እየተወሰደ ያለውን ወታደራዊ እርምጃ "ሕግ የማስከበር እርምጃ ነው" ቢሉትም ከሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ከእርዳታ አቅርቦት አንጻር ምዕራባውያንና ዓለም አቀፍ ተቋማት በመንግሥታቸው ላይ ተለያዩ ግፊት እያደረጉ ነው። ቢሆንም ግን መንግሥታቸው ከአማጺያኑ ጋር ድርድር እንደማይደረግ እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ በተደጋጋሚ አሳስበዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55097999
amh
politics
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ በፈቃዳቸው ሥልጣን ለቀቁ
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ለተከታታይ ሳምንታት ሲካሄድ በቆየውና እሁድ ዕለት ካርቱም ውስጥ የተደረገውን ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ለቀቁ። በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ባለፈው ጥቅምት ወር የተካሄደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ ከጦር ሠራዊቱ ጋር የተደረሰውን የሥልጣን ክፍፍል በመቃወም ነበር አደባባይ ሲወጡ የነበሩት። ተቃዋሚዎች ሥልጣን ወደ ሕዝቡ ተመልሶ አገሪቱ ሙሉ በሙሉ በሲቪል መሪዎች እንድትደታዳር የሚጠይቁ መፈክሮችን ሲያሰሙ ነበር። ነገር ግን ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ ትናንት እሁድ ሁለት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ተገድለዋል። በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣናቸው ከተወገዱ ከስድስት ሳምንታት በኋላ ወደ ኃላፊነታቸው ተመልሰው የነበሩት የጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ የሥልጣን መልቀቅ ውሳኔ የሱዳን መንግሥት ሙሉ ለሙሉ በጦር ሠራዊቱ ቁጥጥር ስር እንዲገባ ያደርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ ሥልጣን መልቀቃቸውን በተመለከተ በቴሌቪዥን ቀርበው ባደረጉት ንግግር፣ "የአገሪቱ አጠቃላይ ህልውና ከባድ አደጋ ላይ" መሆኑን ገልጸዋል። በሥልጣን ቆይታቸው ሱዳን "ወደ አደገኛ ሁኔታ" ውስጥ እንዳትገባ ለማድረግ የቻሉትን እንዳደረጉ፣ ነገር ግን "አስፈላጊው ሁሉ ጥረት ቢደረግም ስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም" ስለዚህም "የተሰጠኝን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ኃላፊነት ሱዳንን ወደ ሲቪሊ አስተዳደር ለማሸጋገር ለሚችል ሰው ለመልቀቅ ወስኛለሁ" ብለዋል። ትናንት እሁድ በተደረገው ወታደራዊውን አስተደደር በሚቃወም ሰልፍ ላይ የፀጥታ ኃይሎች ሁለት ሰዎችን መግደላቸውን የፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ የሕክምና ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የተቃውሞ ላይ ፖሊስ ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝና ጥይት ተኩሶ ቢያንስ አምስት ሰዎች መገደላቸውን የዶክተሮች ቡድን የገለጸ ሲሆን ካለፈው ጥቅምት ወር ወዲህ በፀጥታ ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 56 መድረሱን ሮይተርስ ዘግቧል። ሱዳን ውስጥ ለሳምንታት በቀጠለው የተቃውሞ ሰልፍ የፀጥታ ኃይሎች የሚወስዱት አደገኛ እርምጃ በእጅጉ እንዳሳሰባትና እርምጃ እንደምትወስድ አሜሪካ በሳምነቱ ማብቂያ ላይ አስጠንቅቃ ነበር። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን እንዳሉት የሱዳን የፀጥታ ኃይሎች በተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ እየወሰዱ ያለውን እርምጃን በተመለከተ የሚወጡ ሪፖርቶች በጣሙን እንዳሳሰባቸው በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ ገልጸዋል። ባለሥልጣኑ ጨምረው መንግሥታቸው በተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን አደገኛ የኃይል እርምጃ እንደሚያወግዘውና ሱዳን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሲቪል አስተዳደር እንዳትሸጋገር እንቅፋት በሆኑት ላይ ደግሞ አሜሪካ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቀዋል። እሁድ ዕለት ካርቱም ውስጥ በቀጠለው የተቃውሞ ሰልፍ ላይም የፀጥታ ኃይሎች ወታደራዊ አስተዳደርን በመቃወም አደባባይ የወጡ በሺዎች በሚቆጠሩ ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጋዥ ተኩሰዋል። መንግሥት ተቃውሞውን ለመቆጣጠር ከሰልፉ ቀደም ብሎ የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ ያደረገ ሲሆን፣ ወደ ካርቱም የሚያመሩ ዋነኛ መንገዶችና ድልድዮች ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የታጠቁ ፖሊሶችን በማሰማራት እንዲዘጉ አድርጎ ነበር። ባለፈው ጥቅምት ወር ጄኔራል አብዱል ፋታህ አልቡርሐን በሲቪሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ላይ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ካደረጉ ወዲህ የእሁዱ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ 12ኛው ሲሆን ለአዲሱ የፈንጆች ዓመት ደግሞ የመጀመሪያው ነው ተብሏል። እሁድ ጠዋት ተቃዋሚዎች በሱዳን ጦር ሠራዊት መሪዎች ላይ ለወራት ሲያሰሙት የነበረውን ተቃውሞ ለመቀጠል ወደ አደባባይ መውጣት ሲጀምሩ አንስቶ የኢንርኔት አገልግሎት መቋረጡን በዓለም ዙሪያ የኢንተርኔት አገለግሎትን የሚከታተለው ኔትብሎክስ አስታውቋል። ለወራት የቀጠለው የተቃውሞ ሰልፍ አስተባባሪዎች እንደሚሉት ዋነኛ ጥያቄያቸው ጦር ሠራዊቱ ሥልጣን በሲቨሎች ለሚመራ መንግሥት አስረክቦ ከመሪነት መንበሩ ገለል እንዲል ነው። ተቃዋሚዎቹ ባለፈው ሳምንት በካርቱም አቅራቢያ በምትገኘው ኦምዱርማን ከተማ ውስጥ በተካሄዱት ተመሳሳይ ሰልፎች ላይ የፀጥታ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ በተገደሉት አምስት ሰልፈኞች ሞት ቁጣቸው ጨምሯል። ከሞቱት በተጨማሪ በተለያዩ የሱዳን ከተሞች ውስጥ በተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ ፖሊስ በተከሰው አስለቃሽ ጋዝና ጥይት ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች መቁሰላቸው ተዘግቧል። ሱዳንን ሰላሳ ዓመታት ለመጠጋ ጊዜ በፈላጭ ቆራጭነት የመሩት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር በሕዝባዊ ተቃውሞ ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ አገሪቱ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ በተቃውሞ ስትናጥ ቆይታለች። ከአልበሽር ከሥልጣን መወገድ በኋላ ሥልጣን በአገሪቱ ጦር ሠራዊትና በሲቪል ፖለቲከኞች መካከል ተከፋፍሎ የሽግግር መንግሥት ቢቋቋምም ሁለቱ ወገኖች ሳይስማሙ ተቃውሞው ቀጥሎ ቆይቷል። ሕዝባዊውን ለውጥ የመሩት ኃይሎች ጦር ሠራዊቱ ከአገሪቱ የመንግሥት ሥልጣን ውጪ ሆኖ ሲቪል አስተዳደር እንዲቋቋምና ሱዳን በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት እንዲኖራት ግፊትና የተቃውሞ ሰልፎች ሲያደርጉ ቆይተዋል። ነገር ግን በአገሪቱ የሽግግር ሲቪል መሪዎችና በወታደሮች መካከል ያለው አለምግባባት እየተባባሰ ሄዶ ባለፈው ጥቅምት ወር የሽግግር መንግሥቱ ሊቀመንበር የነበሩት ጄነራል አል ቡርሐን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክን በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት አስወግደው ነበር። ከሦስት ዓመት በፊት በተደረሰውና ባልተከበረው የሥልጣን ክፍፍል ስምምነት መሠረት የሱዳን የሽግግር መንግሥት መሪ ጄነራል አል ቡርሐን ሥልጣናቸውን ለሲቪል ፖለቲከኞች ማስረከብ የነበረባቸው መፈንቅለ መንግሥት ባደረጉ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ኅዳር ወር ላይ ነበር። ጄነራሉ መፈንቅለ መንግሥት ያካሄዱት ፖለቲከኞች ሰላማዊ ሰዎችን በፀጥታ ኃይሎች ላይ እያነሳሱ በመሆናቸው የእርስ በርስ ጦርነት እንዳይከሰት ለመከላከል ነው ሲሉ የእርምጃቸውን ተገቢነት ገልጸው ነበር። ጄነራሉ ሱዳን አሁንም በሽግግር ሂደት ላይ እንደሆነችና አገሪቱን ወደ ሲቪል አስተዳደር ለማሻገር ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸው ከሁለት ዓመት በኋላ ምርጫ እንደሚካሄድ አመልክተዋል። ጄነራል አልቡርሐን በአገር ውስጥና ከዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ በደረሰባቸው ጫና ምክንያት በመፈንቅለ መንግሥት ያነሷቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክን ወደ መንበራቸው ቢመሉሱም ተቃውሞው አሁንም እንደቀጠለ ነው። ለወራት ወታደራዊውን መንግሥት በመቃወም በሱዳን ጎዳናዎች ላይ ድምጻቸውን ሲያሰሙ የቆዩ ሱዳናውያን በጦር ኃይሉ ላይ እምነት ስለሌላቸው ጄነራሎቹ ከመንግሥታዊ አስተዳደር ሥልጣን እንዲገለሉ እየጠየቁ ነው። ጥቅምት ወር ላይ በጄነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሐን የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ቀውስ ያባባሰው ሲሆን፣ አገሪቱ ወደ ዴሞክራሲ እንድትሸጋገር የሚጠይቁ ተቃዋሚዎች ጦር ኃይሉ በሕዝባዊ ትግል የመጣውን ለውጥ ጠልፏ በሚል ይከሳሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-59854349
amh
politics
ሱዳን የመፈንቅለ መንግሥት 'ሞካሪዎቹ በሙሉ' በቁጥጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀች
ሱዳን የተሞከረውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ማክሸፏንና "ተሳታፊዎቹ በሙሉ" በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀች። የሱዳን መንግሥት ቃል አቀባይ ለአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን እንደተናገሩት የመንግሥት ግልበጣ ሴራውን የወጠኑት ከሁለት ዓመት በፊት ከሥልጣን ከተወገዱት ከኦማር አል ባሽር ጋር ግንኙነት ያላቸው መሆናቸውን ገልጸዋል። የመንግሥት ግልበጣ ሙከራውን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ካርቱም እና በቅርበት በምትገኘው ኦምዱርማን ውስጥ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዳለና በናይል ወንዝ ላይ ያለው ግዙፉ ድልድይ ተዘግቶ እንደነበር ተዘግቧል። ወደ ካርቱምና ወደ ወደቦች የሚወስዱት ጎዳናዎች ተዘግተዋል። የመፈንቅለ መንግሥቱ ሞካሪዎች የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን የሚገኙበትን ህንጻ ለመቆጣጠር ሙከራ ማድረጋቸውን የፈንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ ዘግቧል። የሱዳን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው ማክሰኞ ማለዳ በአገሪቱ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መክሸፉን ይፋ ያደረገው። የመንግሥት ቃል አቀባይ የሆኑት መሐመድ አል ፋኪ ሱሌይማን በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው የተጠረጠሩ አካላት ላይ ምርምራ እንደሚደረግባቸው ተናግረዋል። የመንግሥት ግልበጣውን የሞከሩት ሰዎች በኡምዱርማን የሚገኘውን የአገሪቱን ብሔራዊ ሬዲዮ ጣቢያን ለመቆጣጠር ሙከራ ተደርጎ ነበር። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከካርቱም የተቀረፁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች አውራ መንገዶች ላይ ከባድ መሳሪያ የታጠቁ ወታደሮች የመኪናውን ፍሰት ሲቆጣጠሩ ታይተዋል። በካርቱም ለዛሬ ሊካሄድ የታቀደ የተቃውሞ ሰልፍ የነበረ ሲሆን የመከላከያ ኃይሉ የከተማዋን የፀጥታ ሁኔታ አጠናክሮታል። ሱዳን ፕሬዝዳንት አል ባሽር እኤአ በ2019 ሚያዚያ ወር ላይ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ የሚመራ የሽግግር መንግሥት እየተዳደረች ትገኛለች። የቀድሞውን መሪ ለሦስት አስርት ዓመታት ያህል ከቆዩበት ሥልጣን እንዲወገዱ ምክንያት የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ የጀመረው የዳቦ እና የነዳጅ ዋጋ መጨመሩን ተከትሎ ነበር። አል ባሽር ከስልጣን የተነሱት ለወራት የዘለቀ የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ ሲሆን ራሳቸውን ወደ ስልጣን ያመጣቸውን የ1989 መፈንቅለ መንግሥት በሚመለከት የፍርድ ሂደታቸውን እየተከታተሉ ነው። የመፈንቅለ መንግሥቱ መከራውን ተከትሎ ሁኔታውን ለመቆጣጠር መንግሥት እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑ ተነግሯል። የመንግሥት ግልበጣው በማን እንደተሞከረ እስካሁን የተባለ ነገር የለም። በሽግግር መንግሥቱ ውስጥ ጉልህ ሚና ባላቸው ወታደራዊና ሲቪል አመራሮች መካከል በየወቅቱ አለመግባባትና ውጥረት በተደጋጋሚ ሲከሰት መቆቱ ይነገራል። ከሲቪል አመራሮች መካከል ዋነኛ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ከአንድ ዓመት በፊት ካርቱም ውስጥ በመኪናቸው እተጓዙ ሳለ መንገድ ላይ በተጠመደ ፈንጂ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው እንደነበር ይታወሳል። አገሪቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነት የመሩት ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ ከሁለት ዓመት በፊት በአገሪቱ ሠራዊት፣ በሲቪሎች እና ተቃውሞውን በመሩት ቡድኖች መካከል የሥልጣን ክፍፍል መደረጉ ይታወሳል። በዚህም ሲቪሉን በመወከል የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታውን አብደላ ሐምዶክ ያዙ ሲሆን ከሠራዊቱ በኩል ደግሞ የአገሪቱ ሉአላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር በመሆን አብዱል ፋታህ አልቡርሐን ከፍተኛውን ቦታ ይዘዋል። የሱዳን መንግሥት ዜና ወኪል ሱና የአገሪቱን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጠቅሶ እንደዘገበው ከተሞከራው መፈንቅለ መንግሥት በኋላ በአገሪቱ ያለው ሁኔታ በመንግሥት ቁጥጥር ስር መሆኑን አመልክቷል። አል በባሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ሱዳን ውስጥ በርካታ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች እንደነበሩ ሪፖርት ተደርጓል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የደኅንነት ሁኔታ እየተዳከመ የመጣው ወታደራዊ መሪዎቹ ሥልጣን የሚያስረክቡበት ወቅት ለማስተጓጎል ነው ሲሉ ተቺዎች ይናገራሉ። በሜጀር ጄነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሐን የሚመራው ኃያሉ የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ለሲቪሎች ሥልጣኑን በመጪው ኅዳር እንዲያስተላልፍ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለታል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58636107
amh
politics
እስራኤል የረጅም ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሯ አሰናብታ አዲስ መረጠች
የእስራኤል ፓርላማ ለረጅም ዓመታት በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትርነት መንበር ላይ የቆዩት ቤንያሚን ኔታኒያሁ የሚተኩ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መረጠ። አዲሱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት በሁለት ዓመት ውስጥ በተደረጉ አራት ምርጫዎች ምክንያት ውዝግብ የተጫነውን የእስራኤልን ሕዝብ አንድ ለማድረግ ቃል ገብተዋል። ናፍታሊ ቤኔት ከ12 ዓመታት በኋላ በእልህ አስጨራሽ ፍልሚያ ከስልጣን ገሸሽ የተደረጉትን ቤንያሚን ኔታንያሁ ተክተዋል። እሁድ በኢየሩሳሌም ፓርላማ ውስጥ በተደረገው ክርክርም ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚስተር ኔታንያሁ "ተመልሰን እንመጣለን" በማለት ቃል ገብተዋል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም መንግሥታቸው ለሁሉም ሕዝብ ጥቅም እንደሚሰራ ገልፀው በተለይም በትምህርት፣ በጤና እና አሳሪ የሆኑ አሰራሮችን በማሻሻል ላይ እንደሚያተኩርም ተናግረዋል። ትላንት እሁድ በተደረገው ድምፅ የመስጠት ሂደትም የአንድ ድምፅ ብልጫ (60 ለ 59) በማግኘት ያሸነፈው የቀኝ አክራሪ ብሔረተኛው ክንፍ በእስራኤል ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የተባለለትን የፓርቲዎች ጥምረት በመመስረት አገሪቱን ይመራል። የያሚና ፓርቲ መሪ የሆኑት ቤኔት በሥልጣን መጋራት ስምምነቱ መሰረት እስከ መስከረም 2023 እኤአ ድረስ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገለግላሉ። በቀጣይ ላሉት ሁለት ዓመታት ደግሞ የለዘብተኛ ፓርቲው መሪ ያሺር አቲድ ስልጣኑን ተረክበው ይመራሉ። በእስራኤል ታሪክ ለረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ የቆዩት ኔታኒያሁም የፓርቲያቸው መሪ ብሎም በምክር ቤቱ የተቃዋሚ መሪ ሆነው ይቀጥላሉ። የፓርላማ አባላቱ ለአዲሱ የጥምረት መንግሥት ድምጽ ከሰጡ በኋላ ኔታንያሁ ወደ ቤኔት በመሄድ እጃቸውን ሲጨብጧቸው ታይተዋል። የ49 ዓመቱ ቤኔት በንግግራቸው ላይ "ይህ የልቅሶ ቀን አይደለም። በዲሞክራሲያዊ መንገድ የመንግሥት ለውጥ ተደርጓል። ይኸው ነው። ማንም ሰው ፍርሃት እንዳይሰማው የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን። እና ዛሬ ማታ ይህንን ደስታ ለማክበር ላሰባችሁም፤ እኛ ጠላቶች አይደለንም፣ አንድ ሕዝብ ነን በሌሎች ህመም ላይ አትጨፍሩ" ሲሉ ተሰምተዋል። የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ቃል አቀባይ በበኩላቸው "ይህ የእስራኤል ውስጣዊ ጉዳይ ነው። አቋማችን ሁል ጊዜ ግልፅ ነው፣ የምንፈልገው የፍልስጤም መንግሥት በ1967 ድንበሯ ከነ ዋና ከተማዋ ኢየሩሳሌም ጋር ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ጋዛን የሚቆጣጠረው የእስላማዊው ቡድን ሀማስ በበኩሉ "ይህ የወረራ እና የቅኝ ግዛት ኃይል ነው፤ መብታችንን ለማስመለስ በኃይል እንቃወማለን" ብለዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ቢደን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን ለቤኔት ገልፀው "የመቀራረብ እና ዘላቂ" የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር በጉጉት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57455830
amh
politics
የተባበሩት መንግሥታትበሁከት በምትናጠው ሄይቲ አነስተኛ የጦር መሳሪያ ሽያጭን አገደ
በተደራጁ ወሮበሎች ጥቃት በከፍተኛ ሁከት እና ግጭት በምትናጠው ሄይቲ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አነስተኛ የጦር መሳሪያዎች ሽያጭ ክልከላን በሙሉ ድምፅ ወሰነ። ውሳኔው የመንግሥታቱ ድርጅት አባል አገራት መንግሥታዊ ላልሆኑ አካላት ቀላል የጦር መሳያዎችን እና ጥይቶችን መሸጥ እንዲከለክሉ ይጠይቃል። ነገር ግን የጦር መሳሪያ ሽያጭ ላይ ሙሉ እገዳ በአገሪቷ ላይ እንዲጣል የቀረበው ሃሳብ በቻይና ውድቅ ተደርጓል። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በመዲናዋ ፖርት ኦ ፕሪንስ ብቻ 89 ሰዎች ተገድለዋል። የረድዔት ድርጅቶች በአሁኑ ጊዜ በሄይቲ ያሉ አካባቢዎችን ለመድረስ አደገኛ ነው ይላሉ። ቅዳሜ ሐምሌ 09/ 2014 ዓ.ም. የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዳስታወቀው ከሐምሌ 1 አስከ 5 ባለው ጊዜ ውስጥ በወሮበሎች ቡድን ጥቃት 234 ሰዎች ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል ብሏል። "አብዛኞቹ ሟቾች ወይም ተጎጂዎች በእነዚህ ቡድኖች ውስጥ ተሳታፊ ባይሆኑም የጥቃቱ ኢላማ ሆነዋል” በማለት የተባበሩት መንግሥታት ቃል አቀባይ ጄረሚ ሎሬንስ ተናግረዋል። በተጨማሪም ለጽህፈት ቤታቸውም የወሲባዊ ጥቃት ሪፖርቶች እንደደረሳቸውም አክለዋል። በሜክሲኮና በአሜሪካ አማካኝነት የቀረበው የተባበሩት መንግሥታት የጦር መሳሪያ ሽያጭን የሚከለክለው የውሳኔ ሃሳብ ባለፈው አርብ ተቀባይነት አግኝቷል። ውሳኔው በሄይቲ የወሮበሎች ቡድን መሪዎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ ግለሰቦች ላይ የጉዞና የንብረት እገዳ ማዕቀብ እንደሚጣል ያሳያል። እንዲሁም በሄይቲ ተቀማጭነቱን ያደረገው የተባበሩት መንግሥታት ልዩ የፖለቲካ ተልዕኮ ተቋምን የሚቆይበትን ጊዜ ለአንድ ዓመት ያራዝመዋል። ከዓመት በፊት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ጆቬኔል ሞይስ በቅጥረኞች ከተገደሉ በኋላ በሄይቲ የወሮበሎች ጥቃት በሰፊው ተንሰራፍቷል። ከቅርብ ቀናት ወዲህም በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች የቤንዚን አቅርቦቱ ወደነበረበት እንዲመለስ አፋጣኝ እርምጃ መወሰድ አለበት ሲሉ ጎማዎችን እያቃጠሉ እንዲሁም መንገዶችን እየዘጉ ነው። የሄይቲ ዋና የነዳጅ ማከማቻ ባለፈው ሳምንት የነበረውን ከባድ የወሮበሎች ጥቃት ተከትሎ ሥራውን ለማቆም ተገዷል። የቫርሬክስ የነዳጅ ማከማቻ በሁለት ተቀናቃኝ ቡድኖች መካከል ፍልሚያ በሚደረጉባት በሲቴ ሶሌይል ከተማ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን ሥራውን ማቆሙ በአገሪቱ የነዳጅ እጥረት አስከትሏል። በሄይቲ ያለው ድህነት እንዲሁም ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ በርካታ ዜጎች ወደ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ እና አሜሪካ እየተሰደዱ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cl5ny8v2x70o
amh
politics
ስለኮቪድ-19 የጻፉትን ተከትሎ ትዊተር የአወዛጋቢዋን አሜሪካዊት ፖለቲከኛ ገጽ አገደ
ትዊተር የአወዘጋቢዋን አሜሪካዊት ፖለቲከኛ ማርጆሪ ቴይለር ግሪን የግል ገጽ ማገዱን አስታወቀ። የሪፐብሊካ ፓርቲ አባልና የአሜሪካ ሕግ አውጪ ገጻቸው የታገደባቸው የትዊተርን ሕግጋት በመተላለፋቸው፣ በተለይ ደግሞ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን አስመልክተው የሚለጥፉት መልዕክት አደጋ ሊያስከትል የሚችል በመሆኑ ነው ሲል ድርጅቱ ገልጿል። ትዊተር ከዚህ በፊት የፖለቲከኛዋን ገጽ አራት ጊዜ በጊዜያዊነት ማገዱ የሚታወስ ነው። የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክርት ቤት አባል የሆኑት ማርጆሪ ቴይለር ግሪን ኩባንያው "የአሜሪካ ጠላት ነው" ሲሉ ገጻቸው በመዘጋቱ የተሰማቸውን በጠንካራ ቃላት ገልፀዋል። ቴሌግራም በተሰኘው የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ላይ ረዘም ያለ መግለጫ የለጠፉት ፖለቲከኛዋ "ማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች እውነቱን ማፈን አይችሉም" ብለው ትዊተር "የኮሚዩኒስት አብዮትን እያገዘ ነው" ሲሉ ወቅሰዋል። ምንም እንኳ የአዋዘጋቢዋ ፖለቲከኛ የግል ገጽ ይዘጋ እንጂ ኦፊሴላዊ የኮንግረስ ገጻቸው ግን አሁንም እየሰራ ሲሆን፣ እዚህ ገጽ ላይ መልዕክት የሚለጥፉት ለሥራው የተመደቡ ሙያተኞች ናቸው። የ47 ዓመቷ ማርጆሪ ቴይሌር ግሪን ባለፈው ቅዳሜ "አሜሪካ ውስጥ በርካታ ክትባት የወሰዱ ሰዎች እየሞቱ ነው" ሲሉ ያልተረጋገጠ ወሬ ማጋራታቸው ነው ገጻቸውን እንዲዘጋ ያደረገው። የጆርጂያ ግዛት ሕዝብ እንደራሴዋ ከትዊተር የታገዱት የኮሮናቫይረስ የተሳሳተ መረጃ ፖሊሲን "በተደጋጋሚ በመጣሳቸው ነው" ሲሉ የትዊተር ቃል አቀባይ ለቢቢሲ በጽሑፍ አሳውቀዋል። ቃል አቀባዩ እንደሚሉት ኩባንያው አራት ጊዜ ሕግ ጥሰው የሚገኙ ሰዎችን ገጽ በጊዜያዊነት ያግዳና ቆይቶም በቋሚነት ሊያግድ ይችላል። "ሰዎች በተደጋጋሚ ጥፋት አጥፍተው ሲገኙ ገፃቸውን እስከወዲያኛው እናግዳለን" ብለዋል አፈ ቀላጤው። ባለፈው የአሜሪካ ምርጫ ድምፅ አግኝተው ወደ ዋሺንግተን የመጡት ግሪን በአወዛጋቢ ድርጊታቸው ይታወቃሉ። የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ቀንደኛ ደጋፊ የሆኑት ግሪን፤ ትራምፕ ባለፈው ምርጫ አልተሸነፉም ምርጫው ተጭበርብሮ እንጂ ከሚሉት መካከል ናቸው። አልፎም ሴትየዋ 'ኪውኤነን' ከተባለው የነጭ አሜሪካዊያን የሴራ ፅንሰ ሐሳብ አራማጅ ድርጅት ጋር ስማቸው ሲያያዝ ይሰማል። ፖለቲከኛዋ፤ ምንም እንኳ አገራቸው አሜሪካ በቫይረሱ ምክንያት 825 ሺህ ሰዎች ብታጣም ቫይረሱን ለመከላከል የሚደረጉ እርምጃዎችን አጥብቀው በመቃውም ይታወቃሉ። የክትባቶችን የመከላከል አቅም በተደጋጋሚ ሲወቅሱ የሚደመጡት ማርጆሪ ቴይለር ግሪን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አልጠቀመም ብለው የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ውስጥ ግርግር እስከመፍጠር ደርሰው ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/news-59856595
amh
politics
ቤተ መንግሥታቸው በተቃዋሚዎች የተወረረው የሲሪላንካ ፕሬዚዳንት ከሥልጣን ሊለቁ ነው
ተቃዋሚዎች የሲሪላንካውን ፕሬዚዳንት ቤተ መንግሥት ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ ፕሬዚዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ አስታወቁ። ተቃዋሚዎቹ በደረሱበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ ፕሬዚዳንቱ በቅጥር ግቢው ውስጥ አልነበሩም። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በመዲናይቱ ኮሎምቦ አደባባይ ወጥተው ፕሬዚዳንት ራጃፓክሳ ሥልጣናቸውን እንዲያስረክቡ ጠይቀዋል። ይህም በአገሪቱ በኢኮኖሚ አስተዳደር እጦት ምክንያት ለወራት ከዘለቀው የተቃውሞ ሰልፍ በኋላ መሆኑም ተዘግቧል። ፕሬዚዳንት ራጃፓክሳ ከቀናት በኋላ ሥልጣን ይለቃሉ ተብሏል። ከእሳቸው በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዊክሬሜሲንጌ ከሥልጣን ለመልቀቅ ተስማምተዋል። የፓርላማው አፈ-ጉባዔ ፕሬዚዳንቱ ከሥልጣን ለመልቀቅ የወሰኑት “በሰላማዊ መንገድ የሥልጣን ርክክብ እንዲኖር ነው” ሲሉ ሕዝቡም “ሕግ እንዲያከብር” ጠይቀዋል። የፕሬዚዳንቱ ውሳኔ በከተማዋ ውስጥ ከፍተኛ ፈንጠዝያን ፈጥሯል፤ በርካቶችም ርችቶችን በተኮስ ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። በትናንትናው ዕለት ተቃዋሚዎች የፕሬዚዳንቱን መኖሪያ ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ አሜሪካ የአገሪቱን የምጣኔ ሀብት ችግር ለመፍታት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ የሲሪላንካ አመራሮችን ጠይቃ ነበር። በፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት ለተቃውሞ ወጥታ የነበረች ፊዮና ሲርማና የተባለች ግለሰብ “ፕሬዚዳንቱን እና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከሥልጣን በማስወገድ ለሲሪላንካ አዲስ ዘመን የምንቀዳጅበት ጊዜ አሁን ነው” ስትል ተናግራለች። “ቀደም ብለው ከሥልጣን ባለመውረዳቸው በጣም አዝኛለሁ፤ ምክንያቱም ቀደም ብለው ቢሰናበቱ ምንም አይነት ውድመት ባልደረሰም ነበር” ስትል ለሮይተርስ ዜና ወኪል አስረድታለች። በቅዳሜው ተቃውሞ በርካታ ዜጎች የቆሰሉ ሲሆን፣ የኮሎምቦ ዋና ሆስፒታል ቃል አቀባይ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደተናገሩት ሦስት ሰዎች በጥይት ተመትተው ህክምና እየተደረገላቸው ነው። ሲሪላንካ በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እየተናጠች ሲሆን በአገሪቱ በ70 ዓመታት ውስጥ ያልታየ በተባለው አስከፊ የኢኮኖሚ ቀውስ ምግብ፣ ነዳጅ እና መድኃኒት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት እየታገለች ነው። የአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ተመናምኖ ያለቀ ሲሆን፣ ለግል ተሽከርካሪዎች ቤንዚን እና ናፍታ ሽያጭ ላይ እገዳ ተጥሏል። ከዚህም ጋር ተያይዞም ነዳጅ ለማግኘት ለቀናት በርካቶች ረጃጅም ሰልፎች ላይ ታይተዋል። የቅዳሜው ያልተለመደ ክስተት በሲሪላንካ ውስጥ ለወራት የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ማክተሚያ ይመስላል። በፕሬዚዳንት ራጃፓክሳ መኖሪያ ቤት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአገሪቱን ሰንደቅ አላማ የያዘ ሕዝብ መፈክሮችን በማሰማት አጥሩን ጥሰው ገብተዋል። ከስፍራው የወጣ ቪዲዮ ተቃዋሚዎች በግቢው ውስጥ ሲዘዋወሩ እና በፕሬዚዳንቱ የመዋኛ ገንዳ ውስጥ ሲዋኙ፣ ሌሎች ደግሞ የፕሬዚዳንቱን እቃዎች ሲበረብሩ እንዲሁም አንዳንዶች የቅንጦት መታጠቢያ ቤታቸውን ሲጠቀሙ ያሳያል። ቅንጡ የሚባለው የፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት እና  22 ሚሊዮን ሕዝብ ነዋሪ ያሳለፈው የመከራ ወራት ልዩነት ተቃዋሚዎች በዝምታ ሊያልፉት አልፈለጉም። “መላው አገሪቱ እንደዚህ አይነት ችግር ውስጥ ባለበት ወቅት ሰዎች የተሸከሙት ጫና ለማስተንፈስ ወደዚህ መጥተዋል። በዚህ ቤት ውስጥ ያለውን የቅንጦት ሁኔታ ስንመለከተው ለአገር ለመስራት ጊዜ እንደሌላቸው ግልፅ ነው” በማለት ቻኑካ ጃያሱሪያ የተባሉ ግለሰብ ለሮይተርስ ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2xvxp2p85o
amh
politics
ትራምፕ የካፒቶል ሂል አመጽን እንዲያወግዙ ቢጠየቁም ፍቃደኛ አልነበሩም ተባለ
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አመጸኞች ካፒቶል ሂልን በኃይል ጥሰው ሲገቡ እርምጃውን ከማውገዝ ይልቅ ክስተቱን ዋይት ሃውስ ሆነው በቴሌቪዥን መስኮት መከታተልን መርጠዋል ተባለ። ሪፓብሊካኑ አደም ኪንዚንግለር፤ ትራምፕ አመጸኞቹን እንዲያወግዙ ልጆቻቸው እና አማካሪዎቻቸው “ቢለምኗቸውም” ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል ሲሉ ክስተቱን እየመረመረ ላለው ኮሚቴ ተናግረዋል። “ምንም አይነት እርምጃን አለመውሰድን መርጠዋል” ሲሉ የሪፓብሊካን ፓርቲ አባሉ ኪንዚንግለር በዲሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ለሚመራው ኮሚቴ ተናግረዋል። የካፒቶል ሂል አመጽን እየመረመረ የሚገኘው ኮሚቴ ትራምፕ ሁከቱን ለማስቆም ለሕግ አስከባሪ አባላትም ይሁን ለብሔራዊ ደኅንነት አማካሪዎቻቸው ስልክ እንዳልደወሉ ተነግሮታል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዋይት ሃውስ ባለው መመገቢያ ክፍል ከ2 ሰዓት በላይ የዘለወቀውን የፎክስ ኒውስ ዘገባ ሲከታተሉ ነበር ተብሏል። የቨርጂኒያው ዴሞክራት ፓርቲ አባል ኤልይን ሉሪያ፤ “የፕሬዝዳንት ትራምፕ ከፍተኛ አማካሪዎች እና የቤተሰብ አባላት ከየትኛውም የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሚጠበቀውን እንዲያደርጉ ቢለምኗቸውም ትራምፕ መመገቢያ ክፍል ውስጥ ቁጭ ብለው ጥቃቱ ሲፈጸም በቴሌቪዥን መስኮት ሲከታተሉ ነበር” ብለዋል። ትራምፕ አመጹን ለማስቆም እርምጃ ከመውሰድ የተቆጠቡት “በስልጣን ላይ ለመቆየት ያላቸውን የግል ፍላጎት” ለማሳካት ነው ተብሏል። ትናንት ሐሙስ ሐምሌ 14/2014 ዓ.ም. በአሜሪካ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋቋመው ኮሚቴ ከአንድ ዓመት በፊት የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶል ሂልን በኃይል ሲወሩ በነበሩት 187 ደቂቃዎች ዶናልድ ትራምፕ ምን ሲያከናውኑ ነበር የሚለውን ለመለየት ለ8ኛ ጊዜ ምስክሮችን ሰምቷል። ከሁለት ዓመት ገደማ በፊት በአሜሪካ የተደረገውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጆ ባይደን ማሸነፋቸውን ተከትሎ የሕዝብ እንደራሴዎች የባይደንን የምርጫ ውጤት ለማረጋገጥ ስበሰባ ላይ ሳሉ፤ የትራምፕ ደጋፊዎች ወደ ሕንጻው በኃይል በመግባት የሕዝብ እንደራሴዎችን ስብሰባ አውከዋል። ትራምፕ ምንም አይነት ማስረጃ ሳያቀርቡ በአውሮፓውያኑ 2020 የተካሄደው ምርጫ የተጭበረበረ ነው በማለት ሽንፈታቸውን አልተቀበሉም። ይህ በአሜሪካ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋቋመው ኮሚቴ፤ ሪፐብሊካኑ ትራምፕ፤ በዴሞክራቱ ጆ ባይደን የደረሰባቸውን ሽንፈት ለመቀልበስ ሕጋዊ ያልሆኑ እርምጃዎችን ወስደዋል የሚል ክስ ለመመስረት የሚያስችለውን መረጃ እያስባሰበ ነው። በቀጣይ 2024 በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ እንደሚሳተፉ ያመላከቱት ትራምፕ፤ ጉዳያቸውን እየመረመረ የሚገኘውን ኮሚቴ አጥብቀው ይተቻሉ። ትራምፕን እየመረመረ የሚገኘው ኮሚቴ እስካሁን የተቀበላቸውን ምስክርነቶች ይዞ ትራምፕ ላይ ‘የኮንግረሱን ይፋዊ ሥራ ማደናቀፍ’ እና ‘የአሜሪካን ሕዝብ ለማጭበርበር ማሴር’ የሚሉ ክሶችን መመስረት ይቻላል ሲል ምክረ ሃሳብ አቅርቧል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cyd473p0ljpo
amh
politics
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ምርጫና ቀጠናዊ አንደምታው
እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከ2012 እስከ 2017 የሶማሊያ ስምንተኛው ፕሬዝዳንት የነበሩት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በድጋሚ ተመርጠዋል። በሦስት ዙር በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 214 አብላጫ ድምጽ በማግኘት፣ ሞሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆን አሸንፈው ሥልጣነ መንበሩን ተረክበዋል። በሥልጣን ዘመናቸው፣ በሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን፣ አልፎም ሶማሊያ ከአፍሪካ ቀንድ አገራት እንዲሁም ከምዕራቡ ዓለም አገራት ጋርም እርቀ ሰላም እንድታወርድ እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል። ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በ2017 በድጋሚ ሲወዳደሩ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆ እንደረቷቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ መልሰው ሥልጣኑን ከፈርማጆ ተረክበዋል። በኮቪድ-19 ምክንያት ከዓመት በላይ ተራዝሞ የነበረው ምርጫ በሶማሊያ ለወራት የዘለቁ ውዝግቦች መጫሩ አይዘነጋም። የአገሪቱ የታችኛው ምክር ቤት የምርጫ ማራዘሚያ ውሳኔን በማጽደቅ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆን የሥልጣን ዘመን ለሁለት ዓመት ማራዘሙን ተከትሎ በሶማሊያ ፖለቲከኞች መካከል የተፈጠረው ስንጥቅ በመዲናዋ ሞቃዲሾ ሁከት ማስከተሉ ይታወሳል። በፌደራል መንግሥት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች መካከል በተነሳ ግጭት ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል። በተለይም በፈርማጆ እና በጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሑሴን ሮብሌ መካከል የተፈጠረው እሰጣ ገባ ተካሮ፣ ፈርማጆ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከሥልጣን እስከማገድ ደርሰዋል። የፖለቲካ ውጥንቅጡ ያሰጋቸው የአፍሪካ ኅብረት፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ አሜሪካ እና እንግሊዝ ፈርማጆ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም መወሰናቸውን ኮንነዋል። እንዲያውም አሜሪካ "በሥልጣን ማራዘሙ በተሳተፉት" ላይ ማዕቀብ እንደምትጥልም ዝታ ነበር። በሌላ በኩል ትላንት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመቶዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች እንደገና በሶማሊያ እንዲሰማሩ ፈቃድ መስጠታቸው ተገልጿል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ 700 የሚጠጉ ሶማሊያ ውስጥ ሰፍረው የነበሩ ሁሉም ወታደሮቻቸው አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ያሳለፉትን እርምጃ ባይደን ቀልብሰው፣ የአሜሪካ የልዩ ተልዕኮ ኃይል አባላት በድጋሚ እንደሚሰማሩ ተነግሯል። የ30 ዓመታት የእርስ በእርስ ጦርነት ያሽመደመዳት ሶማሊያ በበርካታ ውስጣዊና ውጫዊ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች የተወጠረች አገር ናት። በዚያ ላይ ስር የሰደደ ሙስና እንዲሁም የጎሳ ክፍፍል ይንጣታል። አክራሪው ታጣቂ ቡድን አል-ሸባብ ሶማሊያን ከጥግ ጥግ ከማናጋት አልፎ የአፍሪካ ቀንድ ስጋት ከሆነም ሰነባብቷል። የመካከለኛው ምሥራቅም ይሁን የምዕራቡ ዓለም አገራት ሶማሊያ ላይ ካላቸው ልዩ ፖለቲካዊ ፍላጎት ባሻገር፣ አሳሳቢው ድርቅ እና ምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ ሕዝቡን እየፈተነው ይገኛል። ለመሆኑ የሐሰን ሼክ ሞሐሙድ መመረጥ ለሶማሊያ፣ ለአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ምን ማለት ነው? በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነትስ ሊለወጥ ይችላል? ዳሰሳችንን ከኢትዮጵያ ጀምረን ወደ ቀጠናው ከዚያም ወደ ሶማሊያ እናደርጋለን። አዲሱ ፕሬዝዳንት እና ኢትዮጵያ በአዲሱ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ምን ሊመስል ይችላል? የሚለውን ለመገመት ከኢትዮጵያ እና ከቀድሞው ሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ግንኙነት ጋር የተያያዙ ሁለት ቁልፍ ነጥቦችን እናንሳ። አንደኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ከፈርማጆ ጋር የደረሱት ሦስትዮሽ ስምምነት ነው። ሁለተኛው ቁልፍ ነጥብ ደግሞ የሶማሊያ ወታደሮች በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ተሳትፎ ነበራቸው የሚለው ያልተረጋገጠ ክስ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ፈርማጆ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ እአአ በ2018 መባቻ ላይ የሦስትዮሽ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል። በእርግጥ ይህ ስምምነት ዝርዝር ይዘቱ ምንድን ነው? ለሚለው ግልጽና ይፋዊ መረጃ ባይወጣም፣ ስምምነቱ ሲፈረም ፈርማጆ በትዊተር ገጻቸው "በአስመራ ከተማ ስምምነት በመፈረማችን ኩራት ይሰማኛል። ስምምነቱ የምጣኔ ሀብት፣ የፖለቲካ፣ የደኅንነት፣ የባህልና የማኅበረሰብ ትብብርን የሚያጎለብት ነው" ብለው ነበር። በቀጣይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሁለቱን መሪዎች ወደ ጎንደር ከተማ ጋብዘዋቸው በአስመራ ስለተፈረመው የሦስትዮሽ ስምምነት ውይይት ማድረጋቸው ተዘግቧል። ይህንን የሦስቱ መሪዎች ስምምነት በጥርጣሬ የተመለከቱ የፖለቲካ ልሂቃን ድምጻቸውን ማሰማታቸው አይዘነጋም። ይህ የሦስትዮሽ ግንኙነት በአዲሱ ፕሬዝዳንት ሊቀጥል ይችላል? ስንል የአፍሪካና ኦሪየንታል ስተዲስ አጥኚና የምሥራቅ አፍሪካን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉት አቶ ነዓምን አሸናፊን ጠይቀናል። የሦስትዮሽ ግንኙነቱ ቀጠናዊ ትስስርን "ገሸሽ ያደረገ ነው" ተብሎ ሲተች እንደነበረ በመጥቀስ "አዲሱ ፕሬዝዳንት የሦስትዮሽ ስምምነቱን ጥለው ሊወጡ ይችላሉ" ይላሉ። በሶማሊያ ልሂቃን ዘንድ ይህ ስምምነት ሲተች እንደነበር በማንሳት፣ ምናልባትም አዲሱ ፕሬዝዳንት ስምምነቱን እንደማያስቀጥሉ ያብራራሉ። "የሦስትዮሽ ግንኙነቱ ቀርቶ ሁለቱ አገራት [ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ] አዲስ የሁለትዮሽ ግንኙነት መጀመር ይኖርባቸዋል። ግንኙነቱ አል-ሸባብ የሚፈጥረውን የፀጥታ ስጋት እንዲሁም የተከሰተውን ድርቅ ያማከለ መሆን አለበት" ሲሉም በኢትዮጵያ በኩል መወሰድ ስለሚኖርባቸው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አቅጣጫ ለውጦች ያስረዳሉ። በሌላ በኩል፣ የሶማሊያ ወታደሮች በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ተሳትፎ ነበራቸው ስለሚለውን ያልተረጋገጠ ክስ አቶ ነዓምንን ጠይቀናል። "ክሱ እውነት ከሆነ ከዚህ በኋላ [ስምሪቱ] አይኖርም። ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ እንደ ሞሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ጦርነቱ ውስጥ ጣልቃ ከመግባት ይልቅ የማደራደር፣ የማሸማገል ሚና ሊኖራቸው ይችላል" ሲሉ መልሰዋል። ለዚህ መከራከሪያ ነጥብ እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡት ሁለት ነጥቦችን ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንዲሁም የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የህወሓት ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ለአዲሱ ፕሬዝዳንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ማስተላለፋቸውን ያጣቅሳሉ። "ሁለቱም መግለጫ ማውጣታቸው [አዲሱ ፕሬዝዳትን] አንዳች ሚና በቀጠናው እንደሚኖራቸው ጠቋሚ ነው" ይላሉ አቶ ነዓምን። በሁለተኛነት የሚጠቅሱት ሶማሊያ ለአገር ውስጥ ደኅንነቷ የኢትዮጵያን ሰላም አስከባሪዎች መፈለጓን ነው። በኢትዮጵያ ጦርነት ከተፋፋመ፣ በአሚሶም ስርና ውጭም ሶማሊያ ውስጥ የተሰማሩት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች ወደ አገር ቤት ሊመለሱ የሚችሉበት ዕድል እንደሚሰፋ በመጥቀስ አዲሱ መሪ "የኢትዮጵያ ጦር እዛው ሆኖ ሶማሊያን የማረጋጋት ሥራ እንዲቀጥል የሚፈልጉ ይመስለኛል" በማለት ያስረዳሉ። የኢትዮጵያ ጦር ሶማሊያን ጥሎ እንዳይወጣ በሚል ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በኢትዮጵያ የፌደራል መንግሥትና በትግራይ ኃይሎች መካከል ሰላም እንዲወርድ የመደገፍ ሚና እንደሚኖራቸው ነው አቶ ነዓምን የሚጠብቁት። የሁለቱ አገራት ግንኙነት ምን ሊመስል ይችላል? የሚለው በጠቅላላው ሲቃኝ በአንድ በኩል አብዛኞቹ የሶማሊያ ፖለቲካ ልሂቃን አገራቸው አሁን ለገባችበት ቀውስ ኢትዮጵያን ተጠያቂ በማድረግ ጥላቻ አዘል አስተያየት ቢሰነዝሩም፣ በሌላ በኩል አዲሱ ፕሬዝዳንት ከኢትዮጵያ ጋር መልካም ግንኙነት እንደነበራቸው ያስረዳሉ። "ከኢትዮጵያ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው። አዲስ አበባ በተደጋጋሚ ይመጡ ነበር። ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር የቀረበ ግንኙነት ነበራቸው። ከዚህ ቀደም ሥልጣን ላይ ስለነበሩና አካባቢውን ስለሚያውቁትም መመረጣቸው እንደ ጸጋ ሊወሰድ ይችላል።" በተቃራኒው ግብፅና ሌሎችም የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት የሶማሊያን "እጅ መጠምዘዝ" እንደሚችሉ ጠቅሰው፣ ይህም በተለይም ከግብፅ በኩል ወደ ኢትዮጵያ አደጋ እንደሚቃጣ ያስረዳሉ። "የመካከለኛው ምሥራቅን ሚና ለማስፋት ሶማሊያን እንደ መነሻ ይጠቀሟታል። ቱርክ የሶማሊያን ምጣኔ ሀብትና ፖለቲካ ስለምትቆጣጠርም የአዲሱ ፕሬዝዳንት ምርጫ አስጊ ሊሆን ይችላል።" የአፍሪካ ቀንድና አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የአፍሪካ ቀንድ ከውስጣዊ የፖለቲካ ቀውስ አልፎ በአገራት መካከል በሚነሳ የወሰን፣ የጥቅማ ጥቅምና ሌሎችም ግጭቶች ይታመሳል። ኬንያ እና ሶማሊያ፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን እንዲሁም ሌሎችም የቀጠናው አገራት በተጠንቀቅ ይጠባበቃሉ። ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ "ሰላምን በመስበክ" እንደሚታወቁ የሚጠቅሱት አቶ ነዓምን "ለንግግር ክፍት ይመስላሉ። እንደ ፈርማጆ በሌላ አገር ጣልቃ የመግባት አዝማሚያ ሳይሆን ከጎረቤቶቻቸው ጋር ሰላም የመፍጠር አዝማሚያ ያላቸው ይመስላል" ሲሉ ያስረዳሉ። በሶማሊያ፣ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መሪዎች መካከል የተፈረመው ሦስትዮሽ ስምምነትን በተመለከተም "ምንነቱ የማይታወቅ፣ ኢጋድን የዘለለ ስምምነት ነው። ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ ወይም ምጣኔ ሀብታዊ ለማለት የሚቸገር ስምምነት መሰል ነው። [አዲሱ ፕሬዝዳንት] በዚህ በማያውቁት ስምምነት ላይ ይገባሉ ብዬ አላምንም" ሲሉ ያክላሉ። ይህ ስምምነት ከተገታ፣ በቀጣይ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያም የተሳተፉበት ቀጠናዊ ትስስር ለመፍጠር ዕድል ሊፈጥር እንደሚችል ያምናሉ። አዲሱ ፕሬዝዳንት በተለይም ከጎረቤቶቻቸው ጋር ሰላም ማውረድ እንደሚሹ በበዓለ ሲመታቸው ገልፈዋል። ስለዚህም በሶማሊያ እና በኬንያ እንዲሁም በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል የሚከሰቱ የድንበር ግጭቶች እንደሚረግቡ ተስፋ አለ። "የቀጠናውን አሰላለፍ ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ከቱርክ እና ከምዕራቡ አገራት ፍላጎት ጋር አጣጥመው ከጎረቤቶቻቸው ጋር ሰላም እንደሚያወርዱ ይታመናል" ይላሉ አቶ ነዓምን። ለሶማሊያ አዲስ ጅማሮ? ተንታኞች እንደሚሉት፣ የሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በድጋሚ መመረጥ ሶማሊያን እንደ አዲስ ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት መነሻ ተደርጎ ይቆጠራል። በሌላ በኩል የሶማሊያን ውስብስብ ፖለቲካ፣ የውስጥና የውጭ ጠንካራ ፍላጎቶችን ከግምት በማስገባት የፕሬዝዳንቱ የሥልጣን ዘመን በፈተና እንደሚሸበብ ይገመታል። አቶ ነዓምን በበኩላቸው፣ በከፍተኛ ሙስና እና የፖለቲካ ንቅዘት ሲታማ የነበረውን የፈርማጆ አስተዳደር አውርዶ የመጣ አዲስ አመራር እንደመሆኑ "ለሶማሊያ አዲስ ተስፋ ያጭራል" ሲሉ አዲሱን አስተዳደር ይገልጹታል። በፈርማጆ እና በጠቅላይ ሚኒስትራቸው መካከል ተፈጥሮ የነበው ውዝግብ ከጎሳ አባላት ባለፈ በፖለቲካ ልሂቃኖች መካከል ክፍተት ፈጥሮ እንደነበር በማስታወስ፣ አዲሱ ጅማሮ የሶማሊያን የፖለቲካ ተዋናዮች ወደ አንድ ጠረጴዛ አምጥቶ ሰላም ለማውረድ በር እንደሚከፍት ይጠብቃሉ። ፈርማጆ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም በመሞከራቸው የተነሳው ውዝግብ ሶማሊያ ካሳየችው ማንሰራራት እየተንሸራተተች ነው የሚል ስጋት እንደጫረ ጠቅሰው፣ ቀውሱን ከማርገብ አንጻር ፕሬዝዳንቱ ተስፋ እንደሚጣልባቸው ያክላሉ። የተባበሩት መንግሥታት ወደ ረሃብ ሊሸጋገር ይችላል ላለው ድርቅ መፍትሄ ከማበጀትና አል-ሸባብን ከመዋጋት አንጻር እንደ አሜሪካ ካሉ አጋር አገራት ጋር በትብብር ለመሥራት የአዲሱ ፕሬዝዳንት መመረጥ ከፍተኛ ሚና አለው። "ውስብስቡ የሶማሊያ ፖለቲካ በአንድ ምሽት፣ በአንድ ፕሬዝዳት ይፈታል ባይባልም አዲስ ጅማሮ ነው ማለት ይቻላል" ይላሉ አቶ ነዓምን። በሌላ በኩል ደግሞ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው በ329 የጎሳ ወኪሎች የተካሄደ እንጂ ሕዝቡ የተሳተፈበት አለመሆኑን በማንሳት፣ ፖለቲካዊ ተሳትፎ እንዳልተረጋገጠ ያስረዳሉ። ጥቂት ስለ ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ አዲሱ ፕሬዝዳንት በትምህርት ዘርፍ ይታወቃሉ። የምረጡኝ ቅስቀሳቸው ማጠንጠኛ ሶማሊያን ከተቀረው ዓለም ማስታረቅና የሕዝቡን አንድነት ማረጋገጥ ነው። የተወለዱት እአአ በ1955 ሂራን ግዛት ነው። በሞቃዲሾ በመካከለኛው መደብ ሰፈር አድገው ከሶማሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርስቲ በምህንድስና በ1981 ተመርቀዋል። በቅርብ የሚያውቋቸው ዝምተኛና የማይታበዩ ሰው ናቸው ይሏቸዋል። ሶማሊያ ለ30 ዓመታት በእርስ በእርስ ጦርነት ስትናጥ አገሪቱን ጥለው ካልሄዱ ጥቂት መሪዎች መካከልም አንዱ ናቸው። ሁለተኛ ዲግሪ ከመሥራታቸው በፊት በሕንድ ቦሆፓል ዩኒቨርስቲ አስተማሪ ነበሩ። ወደ ሶማሊያ ሲመለሱ በተባበሩት መንግሥታት የተዘረጋውን የመምህራን ሥልጠና ለመምራት በትምህርት ሚኒስቴር ተቀጠሩ። በ1991 ማዕከላዊው መንግሥት ሲንኮታኮት፣ በዩኒሴፍ የትምህር ኃላፊ ሆነው ተቀጠሩ። ከሦስት ዓመታት በኋላ፣ በሞቃዲሾ ጦርነቱ ከተነሳ ወዲህ ግንባር ቀደም ከሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አንዱን ከፈቱ። የሙስሊም ወንድማማችነት (Muslim Brotherhood) የሶማሊያ ቅርንጫፍ የሆነው አል-ኢላህ ጋር ግንኙነት አላቸው። የጎሳ ግጭት በተነሳበት ወቅት ለማኅበረሰቡ የትምህርት ሥርዓት በመዘርጋት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ቡድኑ ከግብፅና ሱዳን ጋር ተመሳሳይ በሆነ የእስልምና አስተምህሮት የሚተዳደር ትምህርት ቤቶች ከፍቷል። እንደ አል-ሸባብ እና አል-ቃይዳ ያሉ አክራሪዎችንም ያወግዛል። ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ "ለዘብተኛ ሙስሊም" ተብለው ይታወቃሉ። በጦርነት የደቀቀችውን ሶማሊያ ለመደገፍ በንግድ ሰዎች የተቋቋመው 'ዩኒየን ኦፍ ኢስላሚክ ኮርትስ' ከተባለው ፍርድ ቤት ጋርም ትስስር አላቸው። የአዲሱ ፕሬዝዳንት ደጋፊዎች እንደሚሉት፣ ሰላምና መረጋጋትን ለመመለስ የሚሠሩ መሪ ናቸው። በ1990ዎቹ የሲቪል ማኅበራት ውስጥ ከፍተኛ ንቅናቄ ያደርጉ ነበር። የጎሳ ግጭትን በማርገብም ይታወቃሉ። ሞቃዲሾን ለሁለት ሰንጥቆ በሁለት ተፎካካሪ ጎሳዎች እንድትመራ ያደረጋት "ግሪን ላየን" የተባለውን አካሄድ ለማፍረስ በተደረገው ድርድር ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ከፍተኛ ድርቅን ጨምሮ በበርካታ ችግሮች የተሸበበች አገር ነው ከፈርማጆ የሚረከቡት። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው፣ ድርቁ ካልተገታ ወደ ረሃብ ከፍ ሊል ይችላል። ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በረሃብ አፋፍ ላይ ሆነው አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ይጠብቃሉ። ሶማሊያን የኑሮ ውድነትና የዩክሬን ጦርነት ያባባሰው የዋጋ ግሽበትም ይፈትናታል። በፌደራል መንግሥቱና በክልሎች መካከል እየሰፋ ያለው ልዩነትም ሌላው የሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ የቤት ሥራ ይሆናል። ሙስና ሌላው የሶማሊያ ማነቆ ነው። ተንታኞች እንደሚሉት አዲሱ ፕሬዝዳንት አገራቸው ከኬንያ፣ ጂቡቲ እና ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር ያላትን ግንኙነት የማደስ ኃላፊነትም ተጥሎባቸዋል። ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ 2012 ላይ ሲመረጡ አገራቸው ከምዕራባውያን እና ከአፍሪካ አገራት ጋር መደበኛ የዲፕሎማሲ ትስስሯን እንድታድስ አስችለዋል። በሌላ በኩል በአስተዳደራቸው ስር ያለውን ሙስና ማስወገድ አልቻሉም ተብለው ይታማሉ።
https://www.bbc.com/amharic/61475445
amh
politics
በእስራኤል የተካሄደውን ምርጫ የቤንያሚን ኔታኒያሁ ጥምር ፓርቲ አሸነፈ
በእስራኤል የተካሄደውን ምርጫ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ጥምር ፓርቲ መንግሥት ለመመስረት የሚያስችለውን  ድምጽ በማግኘት አሸናፊ ሆኗል። ይህንንም ተከትሎ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እና በምርጫው ተቀናቃኛቸው የነበሩት ያሪ ላፒድ፣ ኔታኒያሁን እንኳን ደስ አልዎት ብለዋል። ላፒድ ለተፎካካሪያቸው ደውለው መልካም እድልን የተመኙላቸው ሲሆን፣ ሥርዓቱን የተከተለ የሥልጣን ሽግግር እንደሚኖር አረጋግጠውላቸዋል። ሊኩድ የተባለው የኔታኒያሁ ፓርቲ እና የቀኝ አክራሪው ሃይማኖታዊ ፓርቲ አጋሩ በጣምራ ከእስራኤል 120 የፓርላማ መቀመጫ 64ቱን እንዳሸነፈ ባለፈው ማክሰኞ ይፋ የሆነው የመጨረሻ ውጤት አሳይቷል። ውጤቱም ባልጠበቀ ሁኔታ የቀድሞን ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሥልጣን የመለሰ ሆኗል። ውጤቱም እንደ አውሮፓውያኑ በ2019 ኔታኒያሁ ላይ የተከፈቱት እና እሳቸው ግን የማይቀባሏቸውን የሙስና፣ ማጨበርበር እና እምነትን ማጉደል ክሶች እንዲያበቁ ያደርጋል። ከዋናው ውጤት በፊት የነበሩ ቅድመ ውጤቶች ኔያኒያሁ እየመሩ እንደሆነ ካመላከቱ በኋላ፣ ባደረጉት ንግግር ለፓርቲያቸው ደጋፊዎች ባደረጉት ንግግር ያለምንም ልዩነት ሁሉንም እስራኤላዊ የሚያገለግል መንግሥት አቋቁማለሁ ብለዋል። “ደኅንነታችንን መልሰን እናረጋግጣለን፣ የኑሮ ውድነትን እንቀንሳለን፣ ሰላማችንን ይበልጥ እናጠናክራለን እስኤልን በአገራት መካከል ኃያል የሚያደርጋትን ጥረት እንመልሳለን” ብለዋል። የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን በዘገቡት የመጨረሻ ውጤት መሠረት የኔታኒያሁ ሊኩድ ፓርቲ 32 መቀመጫ፣ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ላፒድ ፓርቲ ደግሞ 24 መቀመጫ ያገኙ ሲሆን የቀኝ አክራሪው ብሔርተኛ ጽዮናዊ ፓርቲ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ የአንድነት ፓርቲ ደግሞ 12 መቀመጫ አግኝቷል። የተቀረሩትን መቀመጫዎች ደግሞ የተለያዩ ፓርቲዎች ይዘዋቸዋል። ኔታኒያሁ በንግግራቸው ጥምረታቸው የሚያካትቷቸውን ፓርቲዎች ባይጠቅሱም የጽዮናዊ ፓርቲን እንደሚያካትት ይጠበቃል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c9982drv1ero
amh
politics
ዩክሬን፡ ሩሲያ ወታደሮቼን ከዩክሬን ድንበር አስወጥቻለሁ ማለቷን አሜሪካ ሐሰት ነው አለች
የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሩሲያ ከዩክሬን ድንበር ወታደሮቼን አንቀሳቅሻለሁ ማለቷ ሐሰት ነው አሉ። ባለሥልጣኑ አክለውም የሩሲያ ተጨማሪ 7 ሺህ ወታደሮች በቅርብ ቀናት ድንበር ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል። ባለሥልጣኑ ሩሲያ ዩክሬንን "በማንኛውም ሰዓት" ለመውረር " የሐሰት" ምክንያት ልትከፍት ትችላለች ብለዋል። ሞስኮ በበኩሏ ወታደሮቿ የጦር ልምምዳቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ከዩክሬን ድንበር ለቀው መውጣታቸውን ገልጻለች። ይሁን እንጂ ምዕራባውያን ባለሥልጣናት ሩሲያ ወታደሮቿን ማስወጣቷን የሚያረጋግጥ ምንም ማስረጃ የለም ብለዋል። እንደ ጀርመን ቻንስለሪይ ከሆነ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ስኮልዝ ረቡዕ ዕለት ባደረጉት የስልክ ውይይት ሩሲያ የተባባሰውን ውጥረት ለማርገብ ትክክለኛ እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለባት ተስማምተዋል። ሩሲያ ዩክሬንን የመውረር እቅድ እንደሌላት በተደጋጋሚ ብትገልጽም ከ100 ሺህ የሚበልጡ ወታደሮቿን በድንበር አካባቢ ማስፈሯ ድንገት ወረራ ልትፈፅም ትችላለች በሚል ምዕራባውያንን አስግቷል። ረቡዕ ዕለት የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ታንኮች ክሬሚያን ለቀው ሲወጡ ለማሳየት ተንቀሳቃሽ ምሥል አውጥቷል። ይሁን እንጂ እንደ ዋይት ሃውስ ከፍተኛ ባለሥልጣን ከሆነ ረቡዕ ዕለት የደረሱትን ጨምሮ በቅርብ ቀናት በሺዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ የሩሲያ ወታደሮች ድንበር ላይ ደርሰዋል። ከፍተኛ ባለሥልጣኑ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "ይህ ሩሲያ ጦሯን ከዩክሬን ጋር ከምትዋሰንበት ድንበር እያስወጣሁ ነው ማለቷን ጥርጣሬ ውስጥ ከትቷል" ብለዋል። " ሩሲያ ወታደሮቼን አስወጥቻለሁ ማለቷ ከዚህ እና ከመላው ዓለም ከፍተኛ ትኩረት እንድታገኝ አድርጓታል፤ ነገር ግን አሁን ይህ ሐሰት መሆኑን አውቀናል" ብለዋል ከፍተኛ በላሥልጣኑ። ባለሥልጣኑ ይህንን ያሉት የዩክሬን ፕሬዚደንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ " እስካሁን ወታደሮች ወጡ ሲባል ነው የሰማነው እንጂ፤ ሲወጡ አላየንም" ሲሉ ለቢቢሲ ከተናገሩ ከሰዓታት በኋላ ነው። ፕሬዚደንቱ ይህ የተናገሩት ረቡዕ ዕለት ዩክሬን "የአንድነት ቀን" በሚል በዓል ስታከብር ነው። በዕለቱ በመላ አገሪቷ ሰማያዊ እና ቢጫ ቀለም ያላቸው ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማዎች ተሰቅለዋል። ፕሬዚደንት ዜለንስኪ ዕለቱን "የአርበኝነት በዓል" ሲሉ ያወጁት የአሜሪካ ደህንነት ቢሮ በዚያን ዕለት ሩሲያ ዩክሬን ላይ ጥቃት ልትፈፅም ትችላለች በሚል ላወጣው ሪፖርት ምላሽ ነው። ረቡዕ ዕለት የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ የሩሲያ ጦር ውጥረቱን ማርገቡን የሚያሳዩ ምልክቶች እንደሌሉ ገልጸው፤ ከሩሲያ የሚሰነዘረው ማስፈራሪያ "እየተለመደ መጥቷል" ሲሉ ተናግረዋል። በቤልጂየም ብራስልስ በተካሄደው የኔቶ መከላከያ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ሚኒስትር ስቶልተንበርግ፣ ድርጅቱ አዳዲስ የውጊያ ቡድኖችን ማለትም ብቃት ያላቸውና ራሳቸውን የሚችሉ ትናንሽ ወታደራዊ ቡድኖች በመካከለኛው እና በደቡብ ምሥራቅ አውሮፓ ለማቋቋም እያሰበ ነው ብለዋል። ኔቶ ለሩሲያ ስጋት አለመሆኑን ለማርጋገጥ የሞከሩት ሚኒስትሩ፤ ይህ ሃሳብ እአአ ከ2014 ጀምሮ 270 ቢሊየን ዶላር ወጪ የተደረገበት የአውሮፓ መከላከያን ለማጠናከር እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች አካል መሆኑን አስረድተዋል። ፈረንሳይ በሮማኒያ ውስጥ አንድ የጦር ቡድን ለመምራት ሃሳብ አቅርባ እንደነበርም ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ሚኒስትር ስቶልተንበርግ በሰጡት መግለጫ ላይ ምላሽ ለመስጠት ፍላጎት እንደሌለው ገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60377983
amh