text
stringlengths
2
383k
16ኛ አለም አቀፍ የኤችአይቪኤድስና የአባላዘር በሽታዎች በአፍሪካ 2011አይካሳ ጉባኤ ተጀመረ, ህዳር 242004ዋኢማ 16ኛው አለም አቀፍ የኤችአይቪኤድስና የአባላዘር በሽታዎች በአፍሪካ 2011አይካሳ ጉባኤ በርካታ እንግዶች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ በሚሌኒየም አዳራሽ በይፋ ተከፈተ በጉባኤው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤድስ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ሚሼል ሲዲቤ በአፍሪካ ኤችአይቪኤድስን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ተጨባጭ የሆነ እንቅስቃሴ ሴደረግ እንደነበር ቀደም ሲል የተሰሩ ስራዎችና ከውጤቶቻቸው ማየት ተችሏል ብለዋል ቀደም ባሉት አመታት በአፍሪካ ኤችአይቪኤድስን መከላከልም ሆነ መቆጣጠር እንደማይቻል ይገለፅ እንደነበር ጠቁመው አሁን እየታየ ያለው አበረታች ውጤት ቀደም ሲል ይታሰብ የነበረውን አመለካከት መለወጠቱን ተናግረዋል በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ በኤችአይቪኤድስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየቀነሰ መመጣቱንና የጸረ ኤችአይቪኤድስ መድኃኒት ተጠቃሚዎችም ቁጥር ባስገራሚ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ የስራው ውጤት ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል ቀደም ባሉት አመታት ኡጋንዳና ሴኔጋል የኤችአይቪኤድስ ስርጭትን በመቆጣጠር ረገድ ከአፍሪካ አህጉር ይጠቀሱ እንደነበር ጠቁመው በአሁኑ ወቅት ግን ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ25 በላይ የሚሆኑ ሀገራት የኤችአይቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ችለዋል መቻላቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋልበተለይም ኤችአይቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍና ህፃናት ከቫይረሱ ነፃ ሆነው እንዲወለዱ በአፍሪካ እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች ውጤት እየታየበት መሆኑን ጠቁመው በአህጉሪቱ አስገራሚ ለውጥ መገኘቱንም አመልክተዋልኤችአይቪኤድስ በአፍሪካ የበርካታ ዜጎችን ህይወት መቅጠፉን ያስታወሱት ሲዲቤ በተከናወኑት በርካታ ስራዎች የቫይረሱን ስርጭት ፍጥነትና በፀረ-ኤች አይ ቪ መድኃኒት እጦት ምክንያት የሚጠፋውን ህይወት መታደግ ተችሏል ብለዋል የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ኤችአይቪኤድስ ስርጭትን በመከላከሉና በመቆጣጠር በኩል አመርቂ ውጤት አስመዝግባለች ብለዋል ለውጤቱም በመላው ሀገሪቱ የተሰማሩት 34ሺ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በህብረተሰቡ ውስጥ መሰማራታቸውና ውጤታማ ስራ መስራታቸው ለአብነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል ኤችአይቪኤድስ ስርጭትና መከላከሉና በመቆጣጠሩ ረገድ የተጀመረው ስራ ወደፊትም በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚቀጥልም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ገልፀዋል 16ኛ አለም አቀፍ የኤችአይቪኤድስና የአባላዘር በሽታዎች በአፍሪካ 2011አይካሳ ጉባኤ በሚል መሪ ቃል ለአምስት ቀናት የሚካሄድ መሆኑን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል ዋኢማአዓ ,
በክልሉ 140 ሺህ ሰዎች ኤች አይ ቪ ኤድስ በደማቸው መኖሩ ተረጋገጠባሕር ዳር ሕዳር 222011ዓ.ም አብመድ በርካታ የወሲብ ጓደኞችን መያዝ እና በልጅነት ዕድሜ የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግም በሽታው እንዲዛመት አድርገዋል30ኛውን የዓለም የኤድስ ቀን ምክንያት በማድረግ ለኤች አይ ቪ ይበልጥ ተጋላጭ ነን እንመርመር ራሳችንን እንወቅ በሚል መሪ ሃሳብ በአማራ ክልል ጤና ቢሮ እና በባህር ዳር ጤና መምሪያ ትብብር የተዘጋጀ የፓናል ውይይት ተካሂዷልውይይቱ የተካሄደው ኤድስ በክልሉ እና በሀገሪቱ እያመጣ ያለውን ኪሳራ ለመቀነስ እና በሽታውን ለማጥፋት ነው ኤች አይቪ ኤድስ ያለበትን ደረጃ የሚጠቁም እና ምን አይነት ጉዳት እያደረሰ እንዳለ የሚያመለክት ጥናት በአማራ ክልል ጤና ቢሮ ቀርቧል በዓለም 36 ሚሊዮን ሰዎች በኤች አይቪ ኤድስ እንደተያዙ እና ከዚህ ቁጥር 70 በመቶ የሚሆነውን የአፍሪካ ሀገራት እደሚይዙ ተመላክቷልአሁን ባለው መረጃ መሰረት በአማራ ክልል 140 ሺህ ሰዎች ኤች አይቪ ኤድስ በደማቸው ይገኛልከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ደግሞ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች ናቸውከገጠር ወደ ከተማ የሚፈልሱ ሰዎች ቁጥር መብዛት ሴተኛ አዳሪነት ቁጥር ኤች አይ ቪ ኤድስ ጠፍቷል የሚል አስተሳሰብ መኖር እና ከዚህ ቀደም የነበረው የተቀናጀ ትኩረት መቀነሱ ኤች አይቪ ኤድስ በክልሉ እንዲስፋፋ ካደረጉት ምክንያቶች ተጠቃሽ እንደሆኑ ነው በቢሮው የተገለጸውየአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አበባው ገበየሁ ችግሩ በረጅም ርቀት አሽከርካሪዎችበከፍተኛ ትምረት ተቋማትበድርጅት ስራዎች እና በቀን ሰራተኞች በስፋት እንደሚከሰት ነው የተናገሩት ነው በርካታ የወሲብ ጓደኞችን መያዝ እና በልጅነት ዕድሜ የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግም በሽታው እንዲዛመት አድርገዋል ነው ያሉት ዶክተር አበባው የሃይማኖት አባቶች በየእምነት ተቋማቸው ስለ በሽታው አስከፊነት እንዲያስተምሩም ጥሪ አቅርበዋልየክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸውን ሰዎች በምርመራ በማሳወቅመድሃኒት በማስጀመርበበሽታው የተያዙ ሰዎችን በመንከባከብ እና ብቁ በማድረግ በኩል 90 በመቶ በመስራት ኤች አይቪ ኤድስን ለመቀነስ እንደሚሰራ ገልጸዋል
26ኛው የዓለም የኤች አይ ቪ ኤድስ ቀን በአገር ደረጃ በጋምቤላ ክልል ይከበራል, - ; .._2014. 0 261 197 ; 5; አዲስ አበባ ህዳር162007 ዋኢማ - 26ኛው የዓለም የኤች አይቪኤድስ ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ በጋምቤላ ክልል ይከበራል - ; የፌደራል ኤች አይቪ ኤድስ ጥምር መከላከያና መቆጣጣሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንደሻው ወልደሰንበት ለዋልታ እንደገለጹት የዓለም የኤች አይቪ ኤድስ ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ በጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በሆነችው የጋምቤላ ከተማ ከህዳር 21 ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ገልጸዋል - ; በዓሉ በሚከበርበት አንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ2ሺ ሰዎች በላይ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረት የኤች አይቪ ምርመራ እንደሚያድርጉ የገለጹት አቶ እንደሻው በተለይ ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ነብስ ጡር ሴቶች የኤች አይቪ ምርመራን በማካሄድ ላይ ትኩረት እንዲሠጡ ትምህረት ይሠጣል ብለዋል - ; እንደ አቶ እንደሻው ማብራሪያ የጋምቤላ ክልል የኤች አይቪ ኤድስን በአገር ደረጃ ለማክበር የተመረጠው በክልሉ የኤች አይቪ ኤድስ ሥርጭቱ ከፍተኛ በመሆኑ ሲሆን ኤች አይቪ ኤድስን በጋራ በመከላከል ረገድ በክልሉ መነሳሳትና ንቅናቄ ለመፍጠር ታቅዷል ብለዋል - ; የጋምቤላ ክልል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት የዘርፉ ምላሽ ሰጪ ስራ ሂደት ባለቤት አቶ ደሳለኝ ብሩ በበኩላቸው በስምንት ሰዓታት ውስጥ 5ሺ ሰዎች በፍቃደኝነት የተመሠረተ የኤች አይቪ ምርመራ ለማካሄድ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን አስታውቀዋል - ; በጋምቤላ ክልሉ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት 6ነጥብ 5 በመቶ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ደሳለኝ በተለይም በማጃንግ ዞን የስርጭቱ መጠን 13ነጥብ6 በመቶ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ተጨማሪ ሥራዎች እንደሚያስፈልጉ አመልክተዋል - ; በኢትዮጵያ 700 ሺ የሚሆኑ ሰዎች በኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ እንደሚገኝና የቫይረሱ ሥርጭት 1ነጥብ 2 በመቶ ላይ የተመዘገበ ሲሆን በአገር ደረጃ እየቀነሰ የመጣውን የኤች አይቪ ኤድስ ዳግም እንዳያንሰራራ አሁንም ህብረተሰቡ ጥንቃቄ አንዲያደርግ አቶ ደሳለኝ ጥሪ አቅርበዋል ,
የስራ ሃላፊዎች የደም ምርመራ በማድረግ አራያ ለሆኑ ይገባል ተባለ በኤች አይቪ ኤድስ ያለውን ዝምታ ለመስበር የክልሉ የስራ ሃላፊዎችና ታዋቂ ሰዎች የደም ምርመራ እንዲያደርጉ የጅጅጋ ከተማ ነዋሪዎቹ ጠየቁ በምስራቅ ሸዋ ዞን ከበሽታው ጋር የሚኖሩ 22 ሰዎች ህዝቡን ለማስተማር መዘጋጀታቸውን ገለጹ የጅጅጋ ከተማ አንዳንድ ነዋሪዎች የበሽታውን መዛመት በማስመልከት ሰሞኑን እንደገለጹት የመስተዳድር አካላት የቢሮ ሃላፊዎችና የቀበሌ አመራሮችና ታዋቂ ግለሰቦች ችምር አች አይቪ ኤድስ ምርመራ በማድረግ ለህዝቡ አራያ ሊሆኑ ይገባል የጅጅጋ ካራማራ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ሀረጉ ንጉሴ በበኩላቸው የነዋሪው ጥያቄ እውነትነት እንዳለውና በፈቃደኝነት የደም ምርመራ ለማድረግ ወደ ሆስፒታሉ ለሚመጡ ሰዎች ሆስፒታል ነጻ የኤች አይቪ ኤድስ ምርመራ ለማካሄድ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል የክልሉ የኤች አይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ሴክሬታሪያት ሃላፊ ዶክተር ከድር መሀመድ በበኩላቸው ክልሉ ከፍተኛ የንግድና እንቅስቃሴ የሚታይበት በመሆኑ ባልስልጣናትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ከምርመራው በተጓዳኝ በማስተማሩም በኩል ቢሳተፉ የተሻለ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ይችላሉ ብለዋል ይህ በእንዲህ እንዳለ በምስራቅ ሸዋ ዞን ከበሽታው ጋር የሚኖሩ 22 ሰዎች ሀብረተሰቡን ለማስተማር በአዳማ ልዩ ወረዳ አች አይቪ አድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት በፈቃደኝነት ቀርበው መመዝገባቸውን የጽህፈት ቤቱ አስተባባሪ አቶ አሚር መሀመድ ገልጸዋል ካለፈው ነሀሴ እስከ ህዳር አጋማሽ የሃኪም ማስረጃ በመያዝ በፈቃደኝነት የተመዘገቡ እነዚሁ ሰዎች ትውልድ ይዳን በእኛ ይብቃ በሚል መርህ በዞኑ የተለያዩ ከተሞች በመዘዋወር ትምህርት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ገጸዋል ጽህፈት ቤቱም ለህክምና በየወሩ ከ135- 200 ብር በመስጠት ለተነሱለት አላማ እገዛ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል አስተባባሪው አያይዘውም ከብሄራዊ ኤች አይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ሴክሬታሪያት ቢሮ ለጽህፈትቤቱ 304 ሺ ብር በጀት በመመደቡ በወረዳው 69 ቀበሌ ገበሬ ማሀበራት አስር አባላት ያላቸው የቀበሌ ጸረ- ኤድስ ኮሚቴዎች በማቋቋም ትምህርት እየሰጠ እንዳለና ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩና ወላጅ ላጡ ህጻናት እንክብካቤ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል በተመሳሳይ በጅማ ዞን መቅድም እትዮጵያ የበተሰኘ የኤቻይቪ ኤድስ መከላከያ ማሀበር የተሰባሰቡና ከበሽታው ጋር የሚኖሩ አባላት ስለኤድስ በሽታ መከላከያ ዘዴ ህዝቡን ለማስተማር መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል ህጻናትን ያለአሳዳጊ አረጋውያንን ያለጧሪ በማሰቀረት ላይ ያለውን የዚሁን በሽታ ስርጭት ለመግታት አባላቱ በገ ጠሩ ዘልቆ በመግባት ህዝቡን ለማስተማር መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል ከ20 -30 አመት እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኙባቸው እነዚሁ ወጣቶች መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የመከላከል ዘመቻ እያደረገ ባለበት ወቅት እነሱ ሳያውቁ በቫይረሱ እንደተያዙ ሁሉ ሌላው ሀብረተሰብ ከእነሱ ትምህርት እንዲወስድ አስቀድሞ ለማስተማር ቃል ገብተዋል ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ እያለ በማሀበሩ ያልተደራጁ ሌሎች ወገኖችም ራሳቸውን ከመደበቅ ይልቅ በማሀበሩ በመደራጀት ወገናቸውን ከበሽታው እንዲያድኑ ጥሪ አቅርበዋል
በስድስት ወራት ውስጥ 4 ሚሊየን ሰዎች የኤች አይ ቪ ኤድስ ምርመራ አደረጉ, - ; .._2015_16. 0 199 197 ; 5; አዲስ አበባ መጋቢት 72007 ዋኢማ - በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት 4 ሚሊየን ሰዎች በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የኤች አይ ቪ ኤድስ ምርመራ ማድረጋቸውን የፌደራል ኤች አይቪኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ - ; የጽሕፈት ቤቱ የዕቅድ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ተጠባባቂ ዳይሬክተር ዶክተር አቻምየለህ አለባቸው ለዋልታ እንደገለጹት በስድት ወራቱ ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች ውስጥ ከ1 በመቶ በታች የሚሆኑት ቫይረሱ በደማቸው ተገኝቶባቸዋል - ; ተጠባባቂ ዳይሬክተሩ አያይዘው እንደገለጹት በመላው አገሪቱ በተደረገው የተቀናጀ ጥረት የቫይረሱ ስርጭት በተለይም ባለፉት ሶስት ዓመታት ወደ 1 ነጥብ 2 በመቶ መውረዱን ገልጸዋል - ; በተያዘው በጀት ዓመት ደግሞ ስርጭቱን ወደ 0 ነጥብ 9 በመቶ ለማውረድ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል - ; የቫይረሱ ስርጭት በአገር አቀፍ ደረጃ እየቀነሰ ቢመጣም የጋምቤላ ክልልን ጨምሮ በአነስተኛ ከተሞችና በገጠር አካባቢዎች አሁንም ሥርጭቱ መኖሩን ዶክተር አቻምየለህ አመልከተዋል - ; በጋምቤላ ክልል በተለይ በማጃንግ ዞን ባለው ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ሳቢያ የበሽታው ስርጭት 13 ነጥብ 6 በመቶ መድረሱን የተናገሩት ዶክተር አቻምየለህ ስርጭቱን ለመግታት ህብረተሰቡና የመንግስት አመራሮች ጥረት እያደረጉ መሆኑን አስረድተዋል - ; እስካሁን በተደረጉትም ጥረቶች ህብረተሰቡ በቫይረሱ ላይ ያለውን ግንዛቤ እየተሻሻለ መምጣቱን አስረድተዋል - ; በመጨረሻም ህብረተሰቡ ከቫይረሱ እራሱን እንዲጠብቅና የመገናኛ ብዙሃንም በቫይረሱ ዙሪያ የህበረተሰቡን በተለይም የወጣቱን ግንዛቤ ሊያሳድጉት እንደሚገባ ተናግረዋል ,
ሴክሬታሪያት ስህፈት ቤቱ የኤች አይ ቪ አድስ ምርመራ ለማሰጠት የሚያስችል የምርመራ ጣቢያ ሊያቋቁም ነው የአማራ ክልል አች አይ ቪ ኤድስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ከዩኒሴፍ ባገኘው 140 ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ በባህርዳር ከተማ ለበጎፈቃደኞች የኤድስ ምርመራ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የምርመራ ታቢያ ለማቋቋም መዘጋጀቱን አስታወቀ የምርመራ ጣቢያውን በማቋቋም ስራ ለማስጀመር ጽህፈት ቤቱ እና በኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማሀበር የሰሜን ምእራብ ቅርንጫፍ ስህፈት ቤት ተቀናጅተው እየሰሩ መሆኑን የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ ዶክተር አለማየሁ መኮንን ለዋልታ እንፎርሜሽን ማእከል አስታውቀዋል የምርመራ ጣቢያው መቋቋም በባህርዳር ከተማ እና አካባቢዋ የሚገኙ የሀብረተሰብ ክፍሎች የኤች አይ ቪ ኤድስ ምርመራ ለማድረግ ለሚፈልጉ በጎፈቃደኞች ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ሃላፊው ተናግረዋል እንደ ዶክተር አለማየሁ ገለጻ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ጽህፈት ቤቱ ከዞን እስከ ቀበሌ ያዋቀራቸው ኮሚቴዎች ከሃይማኖት ተቋማትና ከአገር ሽማግሌዎች ጋር በመቀናጀት ለሀብረተሰቡ ትምህርት እየሰጡ ይገኛሉ አንዳንድ የባህርዳር ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት በበሽታው ወላጆቻቸውን የሚያጡ ህጻናት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሰው ስለበሽታው ግልእ ውይይት ማድረግ እና ከቫይረሱ ነጻ መሆን እና አለመሆንን ለማረጋገጥ እንዲቻል የምክር አገልግሎት ተጠናክሮ መሰጠት እንዳለበት አሳስበዋል በአገሪቱ ከሚገኙት 2 ነጥብ 4 ሚሊየን የኤድስ ተጠቂዎች 700 ሺ ያህሉ በአማራ ክልል እንደሚገኙ ይታወቃል
ኤድስየሲዲፎር በመባል የሚታውቀውን በነጭ ደም ሴል ውስጥ የሚገኘውን የሴል ቁጥር cd4 count ከ200 በታች በማድረስ የቫይረሱ መጠን በደም ውስጥ እንዲጨምር በማድረግ ለሕይወት ኣደገኛ እና ምቹ ግዝ ተባቂ በመባል የሚታውቁትን በሸታዎች ኦፓርቸንሰቲክ እንፈክሽስ Opportunistic infections OIs. በመፍጠር የኤድስ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ያደርጋል አንድ ሰው አንድ ወይም ሁለት ኢንፌክሽኖች ሲኖሩበት እና በጣም ዝቅያለ የሲዲፎር ሴል ቁጥር 350 cellsmm3 ወይም በታች ሲሆን እና የቫይረሱ ብዛት viral load ከ 1,000 copiesmL በላይ ከሆነ የኤድስ ደረጃ ላይ ደረሰ ሊባል ይችላልየበለጠ መረጃ ለማግኘት ዋና ግጽ ላይ ይመልከቱኤችአይቪኤችአይቪ ህዩመን ኢምዩኖደፊሸንሲ ቫይረስ Human Immunodeficiency Virus HIV በመባል የሚታውቅ ቫይረስ ነው ኤችአይቪ ቫይረስ የሰውነትን የበሽታ መከላከያ በተለይ የነጭ ደም ሴሎችን በማጥቃት በቀላሉ ሰውነት ለበሽታ እንዲጋለጥ የሚያረግ ቫይረስ ነው ኤችአይቪ ያለባቸው ሰዎች የበሽታው ምልክት ስይታይባቸው ለብዙ አመታት መኖር ይችላሉ ቫይረሱ በሰውነታ ውስጥ እስከ አስር ዓመት በመቆየት ምንም ሳይታውቅ እና ምንም አይነት ይህመም ምልክት ሳይታይበት በመኖር እና አለማውቅ ከአንድ ሰው ወደሌላ ሰው ሊተላለፍ የሚችል አደገኛ ቫይረስ ነውለመጀመሪያ ግዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የኤድስ ታማሚዎች መኖራችው የተረጋገጠው በ1978 ዓም ነው በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ውስጥ 1.3 ሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩ ሰዎች ከኤችአይቪ ቫይርስ ጋር አብረው ይኖራሉኤችአይቪ የሚያመለክት የደም ናሙና የተገኘው በሁለት የደም ናሙናዎችይ ላይ ብቻ ነበር እነዚህም ከታህሳስ 1976 ዓ.ም እስከ 1977 ዓ.ም ባለው ጊዜ ከተሰበሰቡ የደም ናሙና የተገኘ በመሆኑ ኤችአይቪ ኢትዬጵያ ውስጥ የተገኘው 1976 ዓ.ም ነውከአካል የሚወጡ ፈሳሾች ላይ ሁሉ ኤችአይቪን ማግኝት የሚቻል ቢሆንም መደበኛ ኤችአይቪ ምርመራ በደም ናሙና ላይ የሚደረግ የኤችአይቪ-12 አንቲ ባዲ ምርመራ ነውኤላይዛ-ዌስተርን ብሎትፈጣን የኤችአይቪ ምርመራ ማለት ለቫይረሱ የተዘጋጀ አንቲ ቦዲ በደም ውስጥ መኖሩንና አለመኖሩን የሚያመልክት የምርመራ አይነት ነው በፈጣን የምርመራ ዘዴ ውጤቱን ከ10-60 ደቂቃዎች ውስጥ ማውቅ የሚያስችል የመመርመሪያ ዘዴ ነውበኢትዮጵያ ውስጥ በአሁን ሰዓት የኤችእይቪኤድስ ትምህርት በመስፋፋቱ ጥሩ የሆነ ለውጦች በማየት ላይ እንገኛለን ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩም ሆነ ቫይረሱ እንደሌለባቸው የሚያቁም ሆን የማያቁም የቫይረሱ መስፋፋት ለመግታት የማያቋርጥ ትምህርት ያስፈልጋል ሁለተኛ ሰዎችን ከመገለልም ሆነ ከማግለል የሚመጣውን ትልቅ ጥፋት ለመታገል ይረዳል ከቫይረሱ የበለጠ ሕብረተሰባችን ጎድቶ የነበረ እና አሁንም በመጉዳት ላይ ያለው ይህ አግሎ ነው እያንዳዱ ገለሰብ ስለኤችእይቪኤድስ ያለው እውቀት ከፍተኛ ከሆነ ከመግላል እና ከመገለል የሚመጣውን መሽማቀቅ እና ጭንቀት መቆጣጠር ከቻልን ማለት ተልቅ ለውጥ እናመጣለን ማለት ነውበኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ይኸንን ዝምታ የሰበሩ ልንረሳቸው እና ሁሌ ልናስትውሳቸው የሚገቡ እራሳቸውን አውጥተው ከቫይረሱ ጋር እንድሚኖሩ ያስተማሩ እና የብዙ ወጣቶችን ሕይወት ያተረፍ የመጀመሪያው የተስፋ ጎህ ኢትዮጵያማህበር መስራቾች ናቸውኤድስ በሽታ እንደጀመረ በታማሚዎች ላይ ይታዩ የነበሩት የበሽታ ምልክቶችን በማየት የሰውነት የበሽታ መከላከያ አቅም ከመዳከም ጋር ተያያይዘው የሚመጡ ምልክቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ከመገመት በስተቀር ብዙም የሚታውቅ ነገር አልነበረ ከምን እንደመጣና በምን እንደሚተላለፍ አይታወቅም ነበር በኋላም በተለያዪ የምርምሮች ዘርፎች ተጠናክረው በመቀጠላቸው የኤድስ በሽታን የሚያመጣው ቫይረስ ለይቶ በማወቅ ተሕዋሱንም በላቦራቶሪ ለይቶ ማውጣት ተችሏል ይህ የኤድስ በሽታ መንስዔ ተዋሕሳትም በኋላ ላይ ኤችአይቪ የሚለውን ስያሜ አግኝቶዋል ሪትሮ ቫይረስ ከሚባል ተሕዋስ ምድብ ወስጥ መሆኑ ተረጋግጥዋልኤድስ ወይም Acquired Immune Deficiency Syndrome AIDS በመባል የታወቀው በሽታ የሚመጣው ህዩመን ኢምዩኖደፊሸንሲ ቫይረስ Human Immunodeficiency Virus ኤችአይቪ HIV በሚባል ጀርም ነው በሽታው የሰውነትን የበሽታ መከላከያ በተለይ ነጭ ሴሎችን በማጥፋት ለቀላል በሽታዎች ለሕይወት ኣስጊ የመሆን ዕድል በመስጠት የሚገድል ነው የሚተላለፈው ቫይረሱ ያለበት ሰው የተጠቀመበትን ያልፀዳ መርፌ በመጠቀም ወይም ኣስፈላጊዎቹ ጥንቃቄዎች ሳይደረጉ በሚፈጸሙ የተለያዩ የግብረ ሥጋ ግንኙነቶች ነው ኤድስን የሚያመጣው ሕይወት ያለው ጥገኛ ጠንቅ በኃይለኛ የማጉሊያ መሣሪያዎች ይታያል ቫይረሱ ሰውነት ውስጥ እያለ እስከ ፰ ዓመታት የማይታመሙና በሽታውን የሚያስተላልፉ ጤነኛ ሰዎች ኣሉየኤድስ በሽታ ሲጀምር ሰውነት ወይም ኣካላችን በቀላሉ የሚከላከላቸው ጀርሞች እንደፈለጋቸው በመባዛት ለሕይወት ኣደገኛ ሆነው ይገኛሉ ለምሳሌ ያህል ጤነኛ መድን በነበረን ጊዜ ከማይተናኮሉን ባክቴሪያዎች ኣንዱ ኒሞንያ ያስከትላል የቆዳ ካንሰር Kaposis Sarcoma እና የኣንጎል በሽታም ሊኖሩ ይችላሉ AIDS-related complex ARC ወይም ኣርክ የሚባሉ ምልክቶችም ሊመጡ ይችላሉ ከእነዚህም መካከል የንፍፊት ማበጥ የማይለቁ ትኩሳቶች ድካምና ተቅማጥ ክብደት መቀንስ ከ፲ በ፻ በላይ ደረቅ ሳልና ከባድ የእንቅልፍ ላብ ይገኙበታል ትረሽ Thrush እና ሽንግልስ Shingles የሚባሉ በሽታዎችም ሊኖሩ ይችላሉኤድስ ቀስ በቀስ እየተስፋፋ የመጣው ከ1970 ዓ.ም. ወዲህ ሲሆን እስከ 1985 እ.ኤ.አ. ድረስ የተበከለ ደም በመወጋትና በመሳሰሉት ብዙ ሰዎች ያለቅብጠታቸው በበሽታው ተይዘዋል ከ1988 ወዲህ ግን ኤድስ ሲይዝ ነጭ ሴል የሚሠራውን ኣንቲቦዲ Antibody በመመርመር የኤድስ ቫይረስ እንዳጋጠመን የሚጣራበት ፈጣን የምርመራ ዘዴ ስለተሠራ በተለይ የደም ማነስን ለመከላከል ሆስፒታል ከሚሰጠን ደም በመተላለፍ ሊይዝ የሚችለው ኤድስ ወደ መጣፋቱ ደርሷልኤድስ በሚከተሉት ሁኔታዎች ሊተላለፍ ይችላልከኤድስ በሽታ ለመከላከል የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይጠቅማልበተጨማሪም የሚከተሉት ታውቀዋልAZT ኤዚቲ እና የመሳሰሉት መድኃኒቶች ቫይረሱ እንዳይባዛ በመከላከል በሽታው እንዳይገድል ጊዜ ለመግዛት ይጠቅማሉ ይባላልበሽታው በመካከላችን ስላለ ባለማወቅና በጥንቃቄ ጉድለት በኤድስ ብንያዝ ጥፋቱና ፀፀቱ የራሳችን ይመስለኛል እስከ 1991 በዩናይትድ እስቴትስ ውስጥ የኤድስ ቫይረስ ከተገኘባቸው ፪፻፸ሺህ ሰዎች መካከል ፩፻ሺህ ፩00, 000 በበሽታው ሞተዋል በዓለም ላይም ፩፶፬ ኣገሮች ኣንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በኤድስ በሽታ ተይዘዋል ሕዝቡም መጠንቀቅ ካልጀመረ በቫይረሱ የሚበከለው ሰው ቍጥር በየዓመቱ እጥፍ እየሆነ ሊቀጥል እንደሚችልና ለማስታመምም ብዙ ብሊዮን ዶላርስ እንደሚያስፈልግ ተገምቷል ግብረ ሰዶም የሚያዘወትሩና ድረግ የሚወጉ ሰዎች በሽታ ነው እየተባለ ቸል ሲባል ቆይቶ ኣሁን የሁላችንም ጠር መሆኑ ስለተደሰረበት የሚፈለግብንን ብናከናውንና ከመንግሥታትም ጋር ብንተባበር በሽታውን መቆጣጠር ይቻል ይሆናል የፈንጣጣን በሽታ ከዓለም ለማጥፋት ከጠቀሙን መካከል ክትባትና የሕዝቡ ትብብር ዋናዎቹ ናቸው ስለ ግብረ ሥጋ ግንኙነት ማውራት ለማንኛውም ሕብረተሰብ ኣሳፋሪ ቢሆንም ኤድስ ያመጣብን ዱብ-ዕዳ የሕይወት ጉዳይ ስለሆነ መወያየት መጀመር ኣለብንይህ ጽሑፍ የተጻፈው የሕክምና ዕርዳታ ለመስጠት ኣይደለም በበለጠ ለመረዳት ሓኪሞቻችሁን ኣማክሩ በ1988 እ.ኤ.አ. ለእያንዳንዱ የዩናይትድ እስቴትስ ቤተሰብ Understanding AIDS የተባለ ፰ ገጽ ጽሑፍ ከU.S. Department of Health and Human Services ሲላክ ወደ አማርኛ በነፃ በዶር ኣበራ ሞላ ተተርጕሞና ተሰራጭቶ ነበር የእዚህ የ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. ጽሑፍ መነሻ ይኸው የHHS Publication No. CDC HHS 88-8404 ጽሑፍ ነው
ሴክሬታሪያቱ ለተጓዳኝ በሽታዎችና ለኤድስ መመርመሪያ መሳሪያ ግዢ 340 ሺ ዶላር መደበ ብሄራዊ ኤች አይ ቪ ኤድስ ሴክሬታሪያት በ340 ሺ ዶላር የተጓዳኝ በሽታዎች መከላከያ መድሃኒት እና የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያ ግዢ እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ የሴክሬታሪያቱ ሃላፊ ዶክተር ዳኛቸው ሃይለማርያም ዛሬ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል እንደገለጹት ለመጀመሪያ ጊዜ በጽህፈት ቤቱ አማካኝነት የሚገዙት መድሃኒቶች ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ግለሰቦች በተጓዳኝ በሽታዎች የሚደርስባቸውን ህመም ለማስታገስ ያገለግላሉ በሁሉም ክልሎች ተመጣጣኝ የተጓዳኝ በሽታዎች መከላከያ መድሃኒት በተፈለገው መጠን እንደሌለ ዶክተር ዳኛቸው ገልጸው የመጀመሪያው የመድሃኒት ግዢ አፈጻጸም ታይቶ ተከታታይ መድሃኒቶች ግዢ እንደሚከናወን ጠቁመዋል የቫይረሱ መመርመሪያ መሳሪያ ግዢም ሙሉ በሙሉ የመመርመሪያ መሳሪያ እጥረትን ባያቃልልም በተወሰነ ደረጃ እጥረቱን እንደሚያቃልል ተቁመው የመሳሪያ ግዢው ቀጣይነት እንደሚኖረው አስታውቀዋል በተመሳሳይም የእድሜ ማራዘሚያ መድሃኒት ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ በተፈቀደው መሰረት የአገዛዙን ስርጭቱንና የአጠቃቀም ስራቱ ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱን ዶክተር ዳኛቸው ተቁመዋል በተለይም የአገዛዙ ሁኔታ የኢትዮጵያውያንን አቅም ያገናዘበ እንዲሆን እንዲሁም የስርጭቱ ሂደት በማንና ከየት ይጀምር በሚለውና በአጠቃቀሙ ዙሪያ ባለሙያዎችን በማወያየት ቁጥጥርና ስራት ባለው መልኩ መድሃኒቱ የሚደርስበትን ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑን ገልጸዋል በሌላ በኩል የሴክሬታሪያቱ ሉካን በአገሪቱ ተንቀሳቅሶ በጎበኘበት ወቅት አበረታች እንቅስቃሴዎችን በሁሉም ክልሎች እንደተመለከተ የጠቆሙት ዶክተር ዳኛቸው በጸረ-ኤድስ ክበባት በመስሪያ ቤቶች በሃይማኖት ተቋማት በልዩ ልዩ ድርጅቶች እና በጎሳ መሪዎች ኤች አይቪ ኤድስ የሀብረተሰቡ አደጋ መሆኑን ካለፉት አመታት የተሻለ ግንዛቤ ተገኝቷል ብለዋል ይሁን እንጂ ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩት ግለሰቦች የሚደረገው እንክብካቤና ፍቅር ጉድለት እንዳለው የጠቆሙት ሃላፊው ሀብረተሰቡ በግልእ ስለበሽታው እየተወያየ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩትንና ወላጅ አልባ ህጻነትን ድጋፍ ሊሰጣቸው እንደሚገባ አመልክተዋል ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤቱ ሁሉንም የአገሪቱን ክፍል ለማዳረስ የሚችል የገንዘብም ሆነ የሰው ሃይል አቅም እንደሌለው ዶክተር ዳኛቸው አመልክተው ቫይረሱን ለመከላከልና ለመቆጣጠር መፍትሄውና አቅሙ ያለው ከሀብረተሰቡ ጋር በመሆኑ ሀብረተሰቡ ተቀናጅቶ እንዲንቀሳቀስ ጥሪ አቅርበዋል
በባሌ ዞን ጎሮና ጎለልቻ ወረዳዎች በፈቃደኝነት የኤች አይ ቪ ምርመራ ለማድረግ የሚፈልጉ ሰዎች በአቅራቢያቸው አገልግሎቱን ማግኘት እንዳልቻሉ ገለጹለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አስተያየት የሰጡት ነዋሪዎች እንደገለጹት ራሳቸውን ለማወቅና ጋብቻ ለመፈጸም በፈቃደኝነት ለመመርመር ቢፈልጉም አገልግሎቱን ለማግኘት አልቻሉምምርመራ ለማድረግ ወደ ሮቤና ጊኒር ረጅም መንገድ ስለሚጓዙ ለወጪና ለእንግልት መዳረጋቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋልየዞኑ ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት ባለሙያ አቶ ኡመር አናቶ ስለጉዳዩ ተጠይቀው ቀደም ሲል ችግሩ የተፈጠረው ባለሙያዎች ስራ በመልቀቃቸውና የቁሳቁስ ዕጥረት በማጋጠሙ እንደሆነ ገልጸዋልበአሁኑ ወቅት ግን ባለሙያ በመመደቡና መሳሪያዎች በመሟላታቸው አገልግሎቱ በቅርቡ እንደሚጀምር አቶ ኡመር ተናግረዋል
በአዲስ አበባ ኤድስ ምርመራ ለማካሄድ እውቅና የተሰጣቸው ክሊኒኮች 13 ብቻ ናቸው በአዲስ አበባ መስተዳድር ከሚገኙት የግል ክሊኒኮች መካከል የኤቻይቪ ኤድስ ደም ምርመራ ለማካሄድ አስፈላጊውን መመዘኛ ማሟላታቸው ተረጋገጦ እንዲሰሩ የተፈቀደላቸው ሶስት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ጨምሮ 13 ክሊኒኮች ብቻ መሆናቸው ተገለጸ በመስተዳድሩ ጤና ቢሮ የጤና አገልግሎት ስልጠና መምሪያ ተጠባባቂ ሃላፊ አቶ ኪሮስ በላቸው ሰሞኑን እንዳሉት ፈቃድ አግኝተው ምርመራውን የሚካሂዱት ክሊኒኮች ቅድመና ድህረ የምክር አገልግሎት የሚሰጡ ሙያተኞችን ጭምር ማሟላታቸው ተረጋግጦ ፈቃድ የተሰጣቸው ናቸው ፈቃድ ተሰጥቷቸው የሚሰሩት 13 ክሊኒኮችም ከመመርመሪያ መሳሪያውና የላቦራቶሪ ምርመራውን ከሚያከናውነው ባለሙያ በተጨማሪ የምክር አገልግሎት የሚሰጥ ባለሙያ ያላቸው መሆኑ ተረጋግጦ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል ከጤና ቢሮው ፈቃድ ሳያገኙ ምርመራ የሚያካሂዱትን ቢሮው የራሱን ክትትል እንደሚያደርግና ከከተማዋ ስፋት አንጻር በሁሉም አካባቢ በውስን ሰራተኞች ብቻ ውጤታማ የቁጥጥር ስራ ለማካሄድ እንደሚያስቸግር ጠቁመው ሀብረተሰብ ያለ ፈቃድ የሚሰሩ ክሊኒኮች ሲያጋጥሙት ለአቅራቢያው ጤና መምሪያ ወይም ጠና ቢሮ በመጠቆም የበኩሉን እገዛ እንዲያደርግ አሳስበዋል ያለ ፈቃድ ሲንቀሳቀሱ ተደርሶበት እርምጃ የተወሰደበት ክሊኒክ ስለመኖሩ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ኪሮስ ሲመልሱ ከአመት በፊት በዞን 5 በደረሰ ጥቆማ መሰረት አንድ ክሊኒክ መታሸጉንና ሃላፊውም በህግ አግባብ የተጠየቀ መሆኑን ዛሬ ለንባብ ለበቃው አዲስ ልሳን ጋዜጣ መናገራቸውን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል ዘግቧል
ኤችአይቪኤችአይቪ እንግሊዘኛ: Human Immunodeficiency Virus HIV ህዩመን ኢምዩኖደፊሸንሲ ቫይረስ በመባል የሚታውቅ ቫይረስ ነው ኤችአይቪ ቫይረስ የሰውነትን የበሽታ መከላከያ በተለይ የነጭ ደም ሴሎችን ህዋሳትን በማጥቃት በቀላሉ ሰውነት ለበሽታ እንዲጋለጥ የሚያረግ ቫይረስ ነው ኤችአይቪ ያለባቸው ሰዎች የበሽታው ምልክት ሳይታይባቸው ለብዙ አመታት መኖር ይችላሉ ቫይረሱ በሰውነታ ውስጥ እስከ አስር ዓመት በመቆየት ምንም ሳይታውቅ እና ምንም አይነት የሚችል አደገኛ ቫይረስ ነውኤችአይቪ የሚያጠቃው የሰውነት የነጭ የደም ሴሎችን የሰውነት የበሽታ የመከላከያ ተቁዋማትን ነው የሲዲፎር በመባል የሚታውቀውን የሰውነት የነጭ የደም ሴል ቁጥሩን cd4 count ከ 200 በታች በማድረግ የቫይረሱ መጠን በደም ውስጥ እንዲጨምር በማድረግ ለሕይወት ኣደገኛ እና ምቹ ግዝ ተባቂ በመባል የሚታውቁትን በሸታዎች ኦፓርቸንሰቲክ እንፈክሽስ Opportunistic infections OIs. በመፍጠር ኤድስ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ያደርጋል ኤችአይቪ ቀስ በቀስ እየተስፋፋ የመጣው ከ1978 ፲፱፻፸ ዓ.ም. ወዲህ ነው በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ውስጥ 1.3 ሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩ ሰዎች ከኤችአይቪ ቫይርስ ጋር አብረው ይኖራሉ በዓለም ላይም ከ 25 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በኤድስ በሚመጣ በሸታ ተይዘው ሞተዋል ለመጀመሪያ ግዜ በኢትዬጵያ ውስጥ የኤድስ ታማሚዎች መኖራችው የተረጋገጠው በ1978 ዓም ነው በ2006ዓም ወደ 2.9 ሚሊዮን የሚጠጉ ወንዶች ሴቶች እና ሕጻናትም ሕይወታቸውን አተዋል ኤችአይቪ ከተያዙት ውስጥ ከግማሸ በላይ የሚገምቱት ሲሞቱ 39.5 ሚሊዮን የሚሆኑ ከቫይርሱ ጋር በመኖር ይገኛሉ በቅርቡ በUNAIDSWHO እንደተዘገበው 4.3 ሚሊዮን የሚጠጉ አዲስ ሰዎች በኤችአይቪ እንደተያዙ ይገልጻልመከላከያ እርምጃዎች 4ቱ መ ዎችይ.የውሽት ውጤት የሚባል ዊንዶ ፔሬድ የሚባል ነገር ስላለ ከ 3-6 ወር በሃላ እርግጠኛ ለመሆን ደግመው መመርመር ይገባል ይህን ሲያረጉ ግን አሁንም ኮንዶም መጠቀሞንኤችአይቪ ቀስ በቀስ እየተስፋፋ የመጣው ከ1978 ፲፱፻፸ ዓ.ም. ወዲህ ሲሆን እስከ 1985 ድረስ የተበከለ ደም ናሙና በመወጋትና በመሳሰሉት ብዙ ሰዎች ይዚህ ሰለባ በመሆን ብዙ ሰዎች ተይዘዋል ከ1988 ወዲህ ግን ኤችአይቪ ሲኖር ደም ውስጥ ነጭ ሴል የሚሠራውን ኣንቲቦዲ Antibody በመመርመር ኤችአይቪ ቫይረስ እንዳለ እና እንደሌለ የሚጣራበት ፈጣን የምርመራ ዘዴ ስለተሠራ በሆስፒታል ከሚሰጠን ደም መተላለፉ ቀርትዋልከአካል የሚወጡ ፈሳሾች ላይ ሁሉ ኤችአይቪን ማግኝት የሚቻል ቢሆንም መደበኛ የኤችአይቪ ምርመራ በደም ናሙና ላይ የሚደረግ የኤችአይቪ-12 አንቲ ባዲ ምርመራ ነውፈጣን ምርመራዎች የሚባሉት ተመርተው በገበያላይ የቀርቡ ወደ 60 የሚቆጠሩ መመርመሪያዎች ሲኖሩ በሶስት ዋና ዋና ቴክኒኮች ላይ የተመረኮዙ ናችው አስተማማጝነታቸውም ከኤላይዛር ጋር የሚስተካከል ነውፈጣን የኤችአይቪ ምርመራ ማለት ለቫይረሱ የተዘጋጀ አንቲ ቦዲ በደም ውስጥ መኖሩንና አለመኖሩን የሚያመልክት የምርመራ አይነት ነው በፈጣን የምርመራ ዘዴ ውጤቱን ከ10-60 ደቂቃዎች ውስጥ ማውቅ የሚያስችል የመመርመሪያ ዘዴ ነው
በዲላ ከተማ በቂ የኤች አይ ቪ ኤድስ የምርመራና የምክር አገልግሎት መስጫ ባለመኖሩ ነዋሪዎች በፈቃደኝነት ምርመራ ማድረግ እንዳልቻሉ አስታወቁነዋሪዎቹ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የኤች አይ ቪ ኤድስ ምርመራ በማድረግ ራሳቸውን ለማወቅና በጥንቃቄ ለመኖር ቢያቅዱም በዲላ ሆስፒታል ከሚሰጠው አገልግሎት በስተቀር በሌላ ቦታ ባለመኖሩ ተቸግረዋልከሆስፒታሉ አገልግሎት ለማግኘት ቢሞክሩም ረጅም ሰዓት ወረፋ ለመጠበቅና ለመጉላላት በመዳረጋቸው ችግሩን ለመፍታት እንዲታሰብበት አመልክተዋልየሆስፒታሉ የኤች አይ ቪ ኤድስ የምክርና ምርመራ አገልግሎት ክፍል ሠራተኛ ሲስተር ሕይወት ዳመነ በበኩላቸው በፈቃደኝነት ለመመርመር የሚመጡ ሰዎች ብዛት ከአቅም በላይ እንደሚሆንና በቀን ለአሥር ተመርማሪዎች ብቻ አገልግሎት ስለሚሰጥ ብዙዎች እንደሚመለሱ ገልጸዋልይሁንና ችግሩን ለማቃለል በማዕከል ደረጃ የኤች አይ ቪ ኤድስ የምክርና ምርመራ መስጫ በሆስፒታሉ እየተገነባ መሆኑን አስታውቀዋልየከተማው የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት ተወካይ አቶ ብሥራት በራሶ ተጠይቀው እንዳሉት በሆስፒታሉ ብቻ ተወስኖ የሚገኘውን የምርመራና የምክር አገልግሎት በዲላና በመካነየሱስ ጤና ጣቢያዎች ለማስጀመር ጥረት በመደረግ ላይ ነው
የኢድ አል ፈጥር በአልን ምክንያት በማድረግ በሰሜን ሽዋ ዞን ደብረብርሃን ከተማ በአራት ቀናት ብቻ 294 ሰዎች የኤች አይ ቪ ምርመራ ማድረጋቸውን የከተማዋ ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅህፈት ቤት አስታወቀየፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ሰንደቆ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት በአሉን ተከትሎ በነበሩት አራት ተከታታይ ቀናት ሶስት የምርመራ ማዕከላትን በማቋቋም የኤች አይ ቪ ኤድስ ምርመራ ካደረጉት ሰዎች መካከል 28ቱ ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖሩ አውቀዋልበነዚሁ ቀናት ኢድ ሙባረክ በሚል ርዕስ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መሰጠቱን ኃላፊው ተናግረዋልየምክርና ደም ምርመራ አገልግሎቱን በነፃ የሰጡት በከተማዋ የሚገኙ ሁለት መንግስታዊና አንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የጤና ተቋማት መሆናቸውም ታውቋል
በደብረ ማርቆስ ከተማ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የደም ምርመራና የምክር አገልግሎት የሚያገኙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የደብረ ማርቆስ ሆስፒታልና የከተማዋ ጤና ጽህፈት ቤት አስታወቁ የደብረ ማርቆስ ሆስፒታል ሜዲካል ድሬክተር አቶ ጥላሁን ደምስና የከተማዋ ጤና ጽህፍት ቤት ኃላፊ ዮሐንስ አሞኘ እንደገለጹት በከተማዋ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የደም ምርመራ የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር የቻለው የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል የሚያስችል ትምህርት በተጠናከረ ሁኔታ በመሰጠቱ ነውባለሙያዎቹ በከተማዋ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የተናገሩት ቤዛ ከኤች አይ ቪኤድስ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ማህበር ሶስተኛ ዓመት የምስረታ ባህሉን ሰሞኑን በደብረ ማርቆስ ከተማ ሲያከብር ነውበኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበርበደብረ ማርቆስ ክሊነክ በደብረ ማርቆስ ጤና ጣቢያና ሆስፒታል ባለፈው ዓመት 4ሺህ 742 ሰዎች የደም ምርመራና የምክር አገልግሎት የተሰጣቸው ሲሆን ይህም ከቀዳሚው ዓመት በ1 ሺህ 867 ሰዎች ብልጫ እንዳለው ተናግረዋልበአሁኑ ወቅት በከተማዋ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ 450 ወገኖች የፀረ ኤች አይ ቪኤድስ መደሐኒት በመውሰድ ላይ መሆናቸውንም አስታወቀዋል በደብረ ማርቆስ ከተማ በነሐሴ ወር 1995 የተመሰረተው ቤዛ ከኤች አይ ቪኤድስ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ወገኖች ማህበር በአሁኑ ወቅት ከ470 ለሚበልጡ ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩ ወገኖችና በኤድስ ወላጆቻቸውን ላጡ ሕጻናት ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ላይ መሆኑን የማህበሩ የፕሮጄክት ኦፊሰር አቶ መንግስቱ እንዳለ ገልጸዋልከዚህም በተጨማሪ ማህበሩ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ 125 የሚሆኑት አባላቱ በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ስራዎች ተሰማርተው ራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ ላይ መሆኑን ኦፊሰሩ ገልጸው ከ159 ሺህ ለሚበልጡ ሰዎችም የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መስጠቱን ተናግረዋልየምስራቅ ጎጃም ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁእ አቡነ ዘካሪያስ ለማህበሩ ድጋፍ ላደረጉ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች የምስክር ወረቀት መስጠታቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧ
በጌድኦ ዞን በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች ኤች አይ ቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ የሚያደርገውን ሕክምና ጨምሮ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የምክርና የደም ምርመራ አገልገሎት መስጠት መጀመሩን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀበመምሪያው የኤች አይ ቪ ኤድስ መቆጣጠሪያ ዴስክ ሃላፊ አቶ ሃይለሚካኤል ፈጦዮ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልገሎት እንደገለጹት በወናጎበይርጋጨፌ በጨለቅለቅቱና ቡሌ ወረዳዎች በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች ኤች አይ ቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ የሚያደርገው ሕክምና በቅርቡ መስጠት ተጀምሯልበወረዳዎቹ የምክርና የደም ምርመራ አገልገሎት መስጠት በመጀመሩም የአገልገሎቱ ፈላጊዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አመልከተው ባለፈው ዓመት ምረመራ ያደረጉ 2 ሺህ 927 ሰዎች ቁጥር ከቀዳሚው ዓመት በ800 ብልጫ እንዳለው ገልጠዋልኤች አይ ቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ በሚያስችለው ሕክምና አገልገሎት ባለፈው ዓመት አንድ ሺህ 50 እናቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጠዋልበጤና ተቋማቱ በያዝነው ዓመት 30 ሺህ ለሚደርሱ ነዋሪዎች የምክርና ምርመራ አገልግሎትለስምንት ሺህ እናቶች ደግሞ ኤች አይ ቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ የሚያስችለው የሕክምና አገልገሎት ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን አስታውቀዋል
በሀዲያ ዞን በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የኤች አይ ቪ ኤድስ የደም ምርመራ የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን የዞኑ ጤና መምሪያ ገለጸየመምሪያው የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ዴስክ ኃላፊ አቶ ታምሬ ዱትሶ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በ1998 ዓም በ15 የጤና ተቋማት በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የደም ምርመራ ያደረጉ ሰዎች ቁጥር ከ3 ሺሀ 800 በላይ ደርሶአልየተመርማሪዎቹ ቁጥር በ1997 ከነበረው በ1 ሺህ ብልጫ ያሳየ መሆኑን ሀላፊው ገልጸው ከተመርማሪዎቹ መካከል 1 ሺህ 870 ያህሉ ሴቶች መሆናቸውን አስረድተዋልየምርመራና የምክር አገልግሎት መስጫዎችን በማስፋፋትና ሌሎች እገዛዎችንም በማድረግ መንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውንም ተናግረዋል በፈቃደኝነት ከተመረመሩት መካከል 286ቱ ከቫይረሱ ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖሩ መረጋገጡን ገልጸዋልበዞኑ ከ270 ሺህ ሰዎች ጋር በኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ ውይይት በመደረጉ የተመርማሪዎች ቁጥር መጨመሩን አመልክተዋል
በወላይታ ዞን በዚህ ዓመት ለ71ሺህ ሰዎች በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የኤች አይ ቪ ኤድስ የምክርና የምርመራ አገልግሎት እንደሚሰጥ የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀበመምሪያው የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ዴስክ ተወካይ አቶ ዋዱ እንዳለ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት በዞኑ 12 ወረዳዎች የምክርና የምርመራ ማዕከላትን ወደ 17 በማሳደግ ለህብረተሰቡ የተጠናከረ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓልዘንድሮ የምክርና የምርመራ አገልግሎት የሚያገኙ ሰዎች ቁጥር ከአምናው በ63 ሺህ ብልጫ እንደሚኖራቸው ተወካዩ አመልክተዋልእንዲሁም በዞኑ ለ2ሺህ 500 ሰዎች የጸረ ኤች አይ ቪ መድሃኒት እንደሚሰጥ አስታዉቀዋል
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በግሼ ወረዳ የኤች አይ ቪኤድስ የደም ምርመራና የምክር አገልግሎት መስጫ ማዕከል አለመኖሩን የወረዳው ማስታወቂያ ጽህፈት ቤት አስታወቀየጽህፈት ቤቱ ተወካይ አቶ ደምሰው መንግስቱ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በወረዳው በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የኤች አይ ቪኤድስ የደም ምርመራና የምክር አገልግሎት መስጫ ማዕከል ባለመኖሩ ነዋሪዎች አገልግሎቱን ለማግኘት ከግሼ ራቤል ወደ መህል ሜዳ ለትራንስፖርት ከፍተኛ ገንዘብ አውጥተው ለመጓዝ ተገደዋልየግሼ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ተወካይ አቶ አድማሱ አስፋው ስለጉዳዩ ተጠይቀው በወረዳው የኤች አይ ቪኤድስ የደም ምርመራና የምክር አገልግሎት መስጫ ማዕከል ለማቋቋም ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋልየዞኑ ጤና መምሪያ ተጠባባቂ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ኃይሌ በበኩላቸው ማዕከሉን ለማቋቋም መምሪያው ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ላይ ስለሆነ ችግሩ በቅርቡ ይወገዳል ብለዋል
በደቡብ ክልል ባለፈው አመት 75 ሺህ ሰዎች በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የኤች አይቪ ኤድስ ደም ምርመራ ማድረጋቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀበቢሮው የበሺታዎች መከላከልና መቆጣጠሪያ መምሪያ ሃላፊ አቶ መስቀሌ ሌራ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጡት በ1995 በክልሉ 36 ብቻ የነበሩትን የምክርና የምርመራ አገልግሎት መስጫ ማእከላት ቅጥር ወደ 200 ከፍ በማድረግ በአመቱ በአስር ወራት ውስጥ የተጠቀሰው ቁጥር ላላቸው ሰዎች አገልግሎቱን ለመስጠት ተችሏልእንዲሁም አድሎና መገለልን ለማስቀረትና ሕብረተሰቡ ስለበሺታው ያለውን ግንዛቤ እንዲያሳድግ በ1 ሺህ 850 ቀበሌዎች የማህበረሰብ ውይይት መካሄዱን ተናግረዋልየመንግስት መስሪያ ቤቶች በጀት መድበው በበሺታው ስርጭት መከላከል ዙሪያ የተጠናከረ እንቅስቃሴ እያደርጉ መሆኑንም አቶ መስቀሌ ጠቁመዋልበክልሉ የሚገኙ 200 የጤና ተቋማት ኤች አይቪ ቫይረስ ላለባቸው ወገኖች በነጻ መድሃኒት በመስጠት ላይ መሆናቸውንም አሰረድትዋል
በአሶሳ ሆስፒታል የኤች አይ ቪ ኤድስ ምርመራ ተጠናክሯል ስምንት እጮኛሞችና አስር ባለትዳሮች ከኤች አይ ቪ ነጻ ሆኑ በአሶሳ ሆስፒታል የኤች አይ ቪ ኤድስ ምርመራ መጠናከሩን የክልሉ አደጋ መከላከል ሰራተኛና ማሀበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከክልሉ አድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ስህፈት ቤት ጋ በመተባበር በተዘጋጀ አውደ ጥናት ላይ ተገለጸ በአውደ ጥናቱ ላይ የአሶሳ ሆስፒታል የምክር አገልግሎት ሰጪ ነርስ ለማ ብርሃኑ እንደገለጹት ባለፉት ስድስት ወራት በፈቃደኝነት ከጋብቻ በፊትና በኋላ የሚደረገው የኤች አይ ቪ ኤድስ ምርመራ እየጎለበተ መጥቷል በዚህ መሰረት በወራቱ 78 ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸው 13ቱ አች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተቅሰው አምስቱ ሴቶችና አንዷ የ8 አመት ታዳጊ መሆኗን አስረድተዋል እንዲሁም በ6 ወራት ውስጥ ምርመራ ያደረጉ ስምንት እጮኛሞችና አስር ባለትዳሮች ከበሽታው ነጻ ሆነው መገኘታቸውን አመልክተዋል በሌላ በኩል የቫይረሱ ተሸካሚ መሆኗን ያረጋገጠች አንዲት ሴት ራሷን ለሀብረተሰቡ ግልእ በማድረግ የበሽታው ስርጭትና መከላከል ላይ ትምህርት እየሰጠች እንደምትገኝ በአውደ ጥናቱ ላይ ተገልጿል የአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ማንኛውም ትዳር መመስረት የሚፈልግ ቴናማ ኑሮ ለመመስረት እስከፈለገ ድረስ ቅድሚያ ምርመራ ማድረግ እንደሚገባውና ግዴታም እንዲሆን የሚያስችል ደንብ እንዲወጣ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል በአውደ ጥናቱ ልዩ ልዩ ትምህርታዊ እሁፎች የቀረቡ ሲሆን 50 ያህል የሃይማኖት አባቶች የወረዳ አመራሮች የአሶሳ ተስፋና ወገን ለወገን ጸረ-ኤድስ ክበብ አባላት ተሳታፊ መሆናቸውን ዋልታ እንፎርሜሽን ማእከል ዘግቧል
በከፋ ዞን ቢጣ ወረዳ በሁለት ወራት ውስጥ አርሶ አደሮችን ጨምሮ ከ740 በላይ ሰዎች የኤች አይ ቪ ኤድስ ምርመራ ማድረጋቸውንና በወባማ ቀበሌዎች 1 ሺህ 700 አጎበሮች መሰራጨታቸውን የወረዳው ጤና ፅህፈት አስታወቀየፅህፈት ቤቱ ኀላፊ አቶ ገረመው ታከለ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጡት ነዋሪዎቹ በፈቃደኝነት ተነሳስተው የደም ምርመራውን ያደረጉት በወረዳው በቅርቡ በተከፈተው የምርመራ ማዕከል ውስጥ ነውበወረዳው በሚገኘው አንድ ጤና ጣቢያ በተቋቋመው በዚሁ ማዕከል ምርመራውን ያደረጉት ለጋብቻና ራሳቸውን ለማወቅ የፈለጉ ሰዎች መሆናቸውን የተናገሩት ኀላፊው ከመካከላቸው 90 በመቶ የሚሆኑት አርሶአደሮች መሆናቸውንም አስታውቀዋልበሌላ በኩል የክረምቱን ዝናብ ተከትሎ የሚከሰተውን የወባ በሽታ ለመከላከል ወባማ በሆኑ ቀበሌዎች 1ሺህ 700 የአልጋ አጎበሮች መሰራጨታቸውንና ከ1 ሺህ በሚበልጡ ቤቶች ላይ የወባ ትንኝ መከላከያ ኬሚካል ርጭት መከናወኑን አቶ ገረመው ጨምረው ገልጠዋል
የምክር ቤቱ አባላት በፈቃደኛነት የኤድስ ምርመራ እንዲያደርጉ ተጠየቀ የሀረሪ ክልል የኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ምክር ቤት አባላት በበጎ ፈቃደኝነት የደም ምርመራ በማድረግ ለሀብረተሰቡ አራያ እንዲሆኑ የተስፋህ ጎህ ኢትዮጵያ ማሀበር ጠየቀ ትናንት በሀረር ከተማ በተካሄደው የምክር ቤቱ ተቅላላ ጉበኤ ላይ በማሀበሩ የሀረር ቅርንጫፍ የተላለፈ መልእክት የኤድስን ስርጭት ለመግታትና የባህሪ ለውጥ ለማምጣት ለሚደረገው ሂደት ባለስልጣናትና የምክር ቤቱ አባላት በቅድሚያ ራሳቸው መመርመር ይኖርባቸዋል ብሏል በአካባቢው የጤና ባለሙያዎች ጭምር በፍቃደኝነት የደም ምርመራ የማድረግ ተነሳሽነቱ አይታይም ያለው መልእክቱ ይህ አካሄድ በኤድስ ላይ ያለውን ዝምታ የማይሰብር በመሆኑ የምክር ቤቱ አባላት ተመርምረው በአራያነት መንገዱን እንዲያሳዩ ጠይቋል በሃኪሞች ጥርጣሬ የደም ምርመራ የሚደረግላቸው ህሙማን ቫይረሱ ሲገኝባቸው ከመንገር ይልቅ በሚስጥር ስለሚያዙ ህሙማን ትንቃቄ ሳያደርጉ በሽታውን ለጤነኛው ሰው እያስተላለፉ መሆኑንም ገልጾ ከዚህ አኳያ ለህሙማኑ በቂ የስነ- ልቦናና የምክር አገልግሎት ተሰጥቷቸው በግልእ ቫይረሱ እንዳለባቸው ሊነገራቸው ይገባል ብሏል የምክር ቤቱ ሴክሬታሪያት ዶክተር መሃዲ ዘካሪያስ ባቀረቡት ሪፖርት በክልል 36 የገጠርና ከተማ ቀበሌዎች የኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ኮሚቴ እንዲሁም በሰባት ቢሮዎች ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል ከአለም ባንክና ከዩኒሴፍ በ199394 ለኤድስ መከላከያ ፕሮግራም ከተለቀቀው 1ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ውስጥ 776 ሺ 600 ብር ለ16 የከተማ ቀበሌዎች ለሰባት ቢሮዎች ክበባት መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ለክትትልና አቅምግንባታ ወጪ መደረጉን አስተባባሪው ተናግረዋል የክልሉ ርእሰ-መስተዳድር አቶ ፎአድ እብራሂም በበሽታውን ለመከላከል በክልሉ የቅንጅት ጉድለት መኖሩን ጠቁመው በቀጣይ የተጠናከረ ስራ እንደሚጠብቃቸው ለምክር ቤቱ አባላት ማሳሰባቸውን ዋልታ እንፎርሜሽን ማእከል ዘግቧል
1 ንጉሥ ዳዊት አረጀ ዕድሜውም እየገፋ ሄደ ልብስ ቢደራርቡለትም እንኳ ሊሞቀው አልቻለም2 በመሆኑም አገልጋዮቹ ለጌታዬ ለንጉሡ አንዲት ልጃገረድ ትፈለግለት እሷም ንጉሡን እንደ ሞግዚት ሆና ትንከባከበው ጌታዬ ንጉሡ እንዲሞቀው በእቅፉ ትተኛለች አሉት3 ስለዚህ በመላው የእስራኤል ግዛት በመዘዋወር ቆንጆ ልጃገረድ ፈለጉ ሹነማዊቷን አቢሻግንም አገኙ ወደ ንጉሡም አመጧት4 እሷም እጅግ ውብ ነበረች የንጉሡም ሞግዚት ሆነች ትንከባከበውም ጀመር ሆኖም ንጉሡ ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት አልፈጸመም5 በዚህ ጊዜ የሃጊት ልጅ አዶንያስ ንጉሥ እሆናለሁ! በማለት ራሱን ከፍ ከፍ ያደርግ ጀመር ለራሱም ሠረገላ ከነፈረሰኞቹ እንዲሁም ከፊት ከፊቱ የሚሮጡ 50 ሰዎች እንዲዘጋጁለት አደረገ6 አባቱ ግን አንድም ቀን ይህን ያደረግከው ለምንድን ነው? በማለት ተቃውሞት አያውቅም ነበር በተጨማሪም አዶንያስ እጅግ መልከ መልካም ነበር እናቱ እሱን የወለደችው ከአቢሴሎም በኋላ ነበር7 እሱም ከጽሩያ ልጅ ከኢዮዓብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር ተመካከረ እነሱም እርዳታና ድጋፍ አደረጉለት8 ሆኖም ካህኑ ሳዶቅ የዮዳሄ ልጅ በናያህ ነቢዩ ናታን ሺምአይ ረአይና የዳዊት ኃያላን ተዋጊዎች አዶንያስን አልደገፉትም9 በኋላም አዶንያስ በኤንሮጌል አቅራቢያ በሚገኘው በጾሃለት ድንጋይ አጠገብ በጎችን ከብቶችንና የሰቡ እንስሳትን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ የንጉሡ ልጆች የሆኑትን ወንድሞቹን በሙሉ እንዲሁም የንጉሡ አገልጋዮች የሆኑትን የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ጠራ10 ይሁን እንጂ ነቢዩ ናታንን በናያህን የዳዊትን ኃያላን ተዋጊዎች ወይም ወንድሙን ሰለሞንን አልጠራም11 ከዚያም ናታን የሰለሞንን እናት ቤርሳቤህን እንዲህ አላት የሃጊት ልጅ አዶንያስ ንጉሥ እንደሆነና ጌታችን ዳዊት ደግሞ ስለ ጉዳዩ ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ አልሰማሽም?12 ስለዚህ አሁን ነይ የራስሽንም ሆነ የልጅሽን የሰለሞንን ሕይወት ማዳን እንድትችይ አንድ ነገር ልምከርሽ13 ወደ ንጉሥ ዳዊት ገብተሽ እንዲህ በዪው ልጅሽ ሰለሞን ከእኔ በኋላ ንጉሥ ይሆናል በዙፋኔም ላይ የሚቀመጠው እሱ ነው በማለት ለአገልጋይህ የማልክላት አንተ ንጉሡ ጌታዬ አልነበርክም? ታዲያ አዶንያስ ንጉሥ የሆነው ለምንድን ነው?14 አንቺም እዚያው ገና ከንጉሡ ጋር እየተነጋገርሽ ሳለ እኔ ተከትዬሽ እገባና ያልሽው ትክክል መሆኑን እናገራለሁ15 በመሆኑም ቤርሳቤህ ንጉሡ ወዳለበት ወደ ውስጠኛው ክፍል ገባች ንጉሡ በጣም አርጅቶ ነበር ሹነማዊቷ አቢሻግም ንጉሡን እየተንከባከበች ነበር16 ከዚያም ቤርሳቤህ በንጉሡ ፊት ተደፍታ ሰገደች ንጉሡም ጥያቄሽ ምንድን ነው? አላት17 እሷም እንዲህ ስትል መለሰች ጌታዬ ሆይ ልጅሽ ሰለሞን ከእኔ በኋላ ንጉሥ ይሆናል በዙፋኔም ላይ የሚቀመጠው እሱ ነው በማለት ለአገልጋይህ በአምላክህ በይሖዋ የማልክላት አንተ ነበርክ18 ይኸው አሁን ግን አዶንያስ ንጉሥ ሆኗል ጌታዬ ንጉሡም ስለዚህ ጉዳይ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም19 እሱም በጣም ብዙ በሬዎችን የሰቡ እንስሳትንና በጎችን መሥዋዕት አድርጓል የንጉሡን ልጆች በሙሉ ካህኑን አብያታርንና የሠራዊቱን አለቃ ኢዮዓብን ጠርቷል አገልጋይህን ሰለሞንን ግን አልጠራውም20 አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ እስራኤላውያን በሙሉ ከጌታዬ ከንጉሡ በኋላ በዙፋኑ ላይ የሚቀመጠው ማን እንደሆነ እንድታሳውቃቸው ዓይኖቻቸው አንተ ላይ ናቸው21 አለዚያ ግን ጌታዬ ንጉሡ ከአባቶቹ ጋር በሚያንቀላፋበት ጊዜ እኔና ልጄ ሰለሞን እንደ ከዳተኞች ተደርገን እንቆጠራለን22 እሷም ገና ከንጉሡ ጋር እየተነጋገረች ሳለ ነቢዩ ናታን ገባ23 ወዲያውም ለንጉሡ ነቢዩ ናታን መጥቷል! ብለው ነገሩት ናታንም ንጉሡ ፊት ቀርቦ በግንባሩ መሬት ላይ በመደፋት ሰገደ24 ከዚያም ናታን እንዲህ አለ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ አዶንያስ ከእኔ በኋላ ንጉሥ ይሆናል በዙፋኔ ላይ የሚቀመጠውም እሱ ነው ብለህ ተናግረሃል እንዴ?25 ይኸው ዛሬ በጣም ብዙ በሬዎችን የሰቡ እንስሳትንና በጎችን ለመሠዋት ወርዷል እንዲሁም የንጉሡን ልጆች በሙሉ የሠራዊቱን አለቆችና ካህኑን አብያታርን ጠርቷል እነሱም በዚያ ከእሱ ጋር እየበሉና እየጠጡ ንጉሥ አዶንያስ ለዘላለም ይኑር! እያሉ ነው26 ሆኖም እኔን አገልጋይህን ወይም ካህኑን ሳዶቅን አሊያም የዮዳሄን ልጅ በናያህን ወይም አገልጋይህን ሰለሞንን አልጠራም27 ጌታዬ ንጉሡ ከእሱ በኋላ በጌታዬ በንጉሡ ዙፋን ላይ የሚቀመጠው ማን እንደሆነ ለአገልጋዩ ሳይነግረው ይህ እንዲደረግ ፈቅዷል?28 በዚህ ጊዜ ንጉሥ ዳዊት ቤርሳቤህን ጥሩልኝ አለ እሷም ገብታ ንጉሡ ፊት ቆመች29 ንጉሡም እንዲህ ሲል ማለ ከመከራ ሁሉ ባዳነኝ ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ30 ልጅሽ ሰለሞን ከእኔ በኋላ ንጉሥ ይሆናል በእኔ ምትክ በዙፋኔ ላይ የሚቀመጠውም እሱ ነው! በማለት በእስራኤል አምላክ በይሖዋ በማልኩልሽ መሠረት ዛሬም ይህ እንዲፈጸም አደርጋለሁ31 ከዚያም ቤርሳቤህ በግንባሯ መሬት ላይ ተደፍታ ለንጉሡ በመስገድ ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘላለም ይኑር! አለች32 ንጉሥ ዳዊትም ወዲያውኑ በሉ አሁን ካህኑን ሳዶቅን ነቢዩን ናታንንና የዮዳሄን ልጅ በናያህን ጥሩልኝ አለ እነሱም ገብተው ንጉሡ ፊት ቀረቡ33 ንጉሡም እንዲህ አላቸው የጌታችሁን አገልጋዮች ውሰዱና ልጄን ሰለሞንን በበቅሎዬ ላይ አስቀምጣችሁ ወደ ግዮን ይዛችሁት ውረዱ34 በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርገው ይቀቡታል ከዚያም ቀንደ መለከት እየነፋችሁ ንጉሥ ሰለሞን ለዘላለም ይኑር! በሉ35 አጅባችሁትም ተመለሱ እሱም መጥቶ በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል በእኔም ምትክ ንጉሥ ይሆናል እኔም በእስራኤልና በይሁዳ ላይ መሪ አድርጌ እሾመዋለሁ36 የዮዳሄ ልጅ በናያህም ወዲያውኑ ንጉሡን እንዲህ አለው አሜን! የጌታዬ የንጉሡ አምላክ ይሖዋ ይህን ያጽናው37 ይሖዋ ከጌታዬ ከንጉሡ ጋር እንደነበረ ሁሉ ከሰለሞንም ጋር ይሁን ዙፋኑንም ከጌታዬ ከንጉሥ ዳዊት ዙፋን የበለጠ ያድርገው38 ከዚያም ካህኑ ሳዶቅ ነቢዩ ናታን የዮዳሄ ልጅ በናያህ ከሪታውያንና ጴሌታውያን ወርደው ሰለሞንን በንጉሥ ዳዊት በቅሎ ላይ አስቀመጡት ወደ ግዮንም አመጡት39 ካህኑ ሳዶቅም ከድንኳኑ ውስጥ የዘይቱን ቀንድ ወስዶ ሰለሞንን ቀባው እነሱም ቀንደ መለከት መንፋት ጀመሩ ሕዝቡም ሁሉ ንጉሥ ሰለሞን ለዘላለም ይኑር! እያለ ይጮኽ ጀመር40 ከዚያም ሕዝቡ በሙሉ ዋሽንት እየነፋና በደስታ እየፈነደቀ ተከትሎት ወጣ ከጩኸታቸውም የተነሳ ምድሪቱ ተሰነጠቀች41 አዶንያስና የጋበዛቸው ሰዎች ሁሉ በልተው ሲጨርሱ ይህን ድምፅ ሰሙ ኢዮዓብ የቀንደ መለከቱን ድምፅ ሲሰማ በከተማዋ ውስጥ የሚሰማው ይህ ሁሉ ሁካታ ምንድን ነው? አለ42 እሱም ገና እየተናገረ ሳለ የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን መጣ ከዚያም አዶንያስ መቼም አንተ ጥሩ ሰው ስለሆንክ ምሥራች ሳትይዝ አትመጣምና ግባ አለው43 ዮናታን ግን ለአዶንያስ እንዲህ ሲል መለሰለት ምሥራች ይዤስ አልመጣሁም! ጌታችን ንጉሥ ዳዊት ሰለሞንን አንግሦታል44 ንጉሡም ካህኑ ሳዶቅ ነቢዩ ናታን የዮዳሄ ልጅ በናያህ ከሪታውያንና ጴሌታውያን አብረውት እንዲሄዱ አደረገ እነሱም በንጉሡ በቅሎ ላይ አስቀመጡት45 ከዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በግዮን ንጉሥ አድርገው ቀቡት እነሱም ከዚያ እየተደሰቱ መጡ ከተማዋ በጩኸት እየተናወጠች ነው እናንተም የሰማችሁት ይህን ድምፅ ነው46 ከዚህም በላይ ሰለሞን በነገሥታቱ ዙፋን ላይ ተቀምጧል47 የንጉሡ አገልጋዮችም አምላክህ የሰለሞንን ስም ከአንተ ስም በላይ ታላቅ ያድርገው ዙፋኑንም ከአንተ ዙፋን የበለጠ ያድርገው በማለት ለጌታችን ለንጉሥ ዳዊት ደስታቸውን ለመግለጽ መጥተዋል በዚህ ጊዜ ንጉሡ አልጋው ላይ ሰገደ48 ከዚያም ንጉሡ ዛሬ በዙፋኔ ላይ የሚቀመጥ ሰው የሰጠኝና ዓይኖቼም ይህን እንዲያዩ ያደረገው የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ይወደስ! አለ49 አዶንያስ የጋበዛቸው ሰዎችም ሁሉ ተሸበሩ እያንዳንዳቸውም ተነስተው በየፊናቸው ሄዱ50 አዶንያስም ሰለሞንን ስለፈራው ተነስቶ በመሄድ የመሠዊያውን ቀንዶች ያዘ51 በኋላም ሰለሞን አዶንያስ ንጉሥ ሰለሞንን ፈርቶታል በመጀመሪያ ንጉሥ ሰለሞን አገልጋዩን በሰይፍ እንደማይገድል ይማልልኝ በማለት የመሠዊያውን ቀንዶች ይዟል ተብሎ ተነገረው52 በዚህ ጊዜ ሰለሞን ጸባዩን ካሳመረ ከራስ ፀጉሩ አንዲቷም እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም መጥፎ ነገር ከተገኘበት ግን ይሞታል አለ53 በመሆኑም ንጉሥ ሰለሞን አዶንያስን ከመሠዊያው ላይ እንዲያወርዱት ሰዎች ላከ ከዚያም አዶንያስ መጥቶ ለንጉሥ ሰለሞን ሰገደ ሰለሞንም ወደ ቤትህ ሂድ አለው
10 የሳባ ንግሥት ስለ ሰለሞን ዝና እንዲሁም ከይሖዋ ስም ጋር ስላለው ግንኙነት ሰማች በመሆኑም አስቸጋሪ በሆኑ ጥያቄዎች ልትፈትነው መጣች2 እሷም እጅግ ታላቅ አጀብ አስከትላ እንዲሁም የበለሳን ዘይት በጣም ብዙ ወርቅና የከበሩ ድንጋዮች በግመል አስጭና ኢየሩሳሌም ደረሰች ወደ ሰለሞንም ገብታ በልቧ ያለውን ሁሉ ነገረችው3 ሰለሞንም ጥያቄዎቿን ሁሉ መለሰላት ንጉሡ ሊያብራራላት ያልቻለው ምንም ነገር አልነበረም4 የሳባ ንግሥት የሰለሞንን ጥበብ ሁሉና የሠራውን ቤት ስትመለከት5 በገበታው ላይ የሚቀርበውን ምግብ የአገልጋዮቹን አቀማመጥ አስተናጋጆቹ በማዕድ ላይ የሚያስተናግዱበትን መንገድና አለባበሳቸውን መጠጥ አሳላፊዎቹን እንዲሁም በይሖዋ ቤት ዘወትር የሚያቀርባቸውን የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ስታይ በመገረም ፈዛ ቀረች6 በመሆኑም ንጉሡን እንዲህ አለችው ስላከናወንካቸው ነገሮችና ስለ ጥበብህ በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ነገር እውነት ነው7 ይሁንና እኔ ራሴ መጥቼ በገዛ ዓይኔ እስከማይ ድረስ የተነገረኝን ነገር አላመንኩም ነበር እንደዚያም ሆኖ ግማሹ እንኳ አልተነገረኝም! በጥበብም ሆነ በብልጽግና ከሰማሁት ሁሉ እጅግ የላቅክ ነህ8 አብረውህ ያሉ ሰዎች ደስተኞች ናቸው ዘወትር በፊትህ ቆመው ጥበብህን የሚሰሙት አገልጋዮችህም እጅግ ደስተኞች ናቸው!9 አንተን በእስራኤል ዙፋን ላይ በማስቀመጥ በአንተ ደስ የተሰኘው አምላክህ ይሖዋ ይወደስ ይሖዋ ለእስራኤል ካለው ዘላለማዊ ፍቅር የተነሳ ፍትሕንና ጽድቅን እንድታሰፍን ንጉሥ አድርጎ ሾሞሃል10 ከዚያም ለንጉሡ 120 ታላንት ወርቅ እንዲሁም እጅግ ብዙ የበለሳን ዘይትና የከበሩ ድንጋዮች ሰጠችው የሳባ ንግሥት ለንጉሥ ሰለሞን የሰጠችውን የሚያህል መጠን ያለው የበለሳን ዘይት ከዚያ በኋላ መጥቶ አያውቅም11 ከኦፊር ወርቅ ጭነው የመጡት የኪራም መርከቦች ከኦፊር እጅግ ብዙ የሰንደል ዛፍ ሳንቃዎችንና የከበሩ ድንጋዮችንም አምጥተው ነበር12 ንጉሡም ከሰንደል ዛፍ ሳንቃዎቹ ለይሖዋ ቤትና ለንጉሡ ቤት ድጋፎችን እንዲሁም ለዘማሪዎቹ የሚሆኑ በገናዎችንና ሌሎች ባለ አውታር መሣሪያዎችን ሠራ ይህን ያህል ብዛት ያለው የሰንደል ዛፍ ሳንቃ እስከ ዛሬ ድረስ መጥቶም ሆነ ታይቶ አያውቅም13 ንጉሥ ሰለሞንም ለሳባ ንግሥት በልግስና ተነሳስቶ ከሰጣት ሌላ የፈለገችውንና የጠየቀችውን ነገር ሁሉ ሰጣት ከዚያም ተነስታ አገልጋዮቿን በማስከተል ወደ አገሯ ተመለሰች14 ሰለሞን በየዓመቱ 666 ታላንት ወርቅ ይመጣለት ነበር15 ይህም ከነጋዴዎች ከሸቃጮች ከሚገኘው ትርፍ ከዓረብ ነገሥታት ሁሉና ከአገረ ገዢዎች የሚሰበሰበውን ሳይጨምር ነው16 ንጉሥ ሰለሞን ከቅይጥ ወርቅ 200 ትላልቅ ጋሻዎችን ሠራ እያንዳንዱ ጋሻ በ600 ሰቅል ወርቅ ተለብጦ ነበር17 እንዲሁም ከቅይጥ ወርቅ 300 ትናንሽ ጋሻዎችን ሠራ እያንዳንዱ ትንሽ ጋሻ በሦስት ምናን ወርቅ ተለብጦ ነበር ከዚያም ንጉሡ የሊባኖስ ደን በተባለው ቤት አስቀመጣቸው18 በተጨማሪም ንጉሡ ከዝሆን ጥርስ ትልቅ ዙፋን ሠርቶ በተጣራ ወርቅ ለበጠው19 ወደ ዙፋኑ የሚያስወጡ ስድስት ደረጃዎች ነበሩ ዙፋኑም ከኋላው በኩል ክብ ከለላ ነበረው መቀመጫውም በጎንና በጎኑ የእጅ መደገፊያዎች ያሉት ሲሆን ከእጅ መደገፊያዎቹም አጠገብ ሁለት አንበሶች ቆመው ነበር20 በስድስቱ ደረጃዎች ዳርና ዳር አንድ አንድ አንበሳ በአጠቃላይ 12 አንበሶች ቆመው ነበር እንዲህ ያለ ዙፋን የሠራ አንድም ሌላ መንግሥት አልነበረም21 የንጉሥ ሰለሞን የመጠጫ ዕቃዎች በሙሉ ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ የሊባኖስ ደን በተባለው ቤት የነበሩት ዕቃዎችም በሙሉ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ ከብር የተሠራ ምንም ነገር አልነበረም በሰለሞን ዘመን ብር እንደ ተራ ነገር ይቆጠር ነበር22 ንጉሡ ከኪራም መርከቦች ጋር አብረው በባሕር ላይ የሚጓዙ የተርሴስ መርከቦች ነበሩት እነዚህ የተርሴስ መርከቦች በሦስት ዓመት አንድ ጊዜ ወርቅ ብር የዝሆን ጥርስ ጦጣና ጣዎስ ጭነው ይመጡ ነበር23 በመሆኑም ንጉሥ ሰለሞን በብልጽግናና በጥበብ ምድር ላይ ካሉ ሌሎች ነገሥታት ሁሉ ይበልጥ ነበር24 የምድር ሕዝቦችም ሁሉ አምላክ በሰለሞን ልብ ውስጥ ያኖረውን ጥበብ ይሰሙ ዘንድ ከእሱ ጋር ለመገናኘት ይጓጉ ነበር25 ወደ እሱ የሚመጡትም ሰዎች በየዓመቱ የብር ዕቃዎች የወርቅ ዕቃዎች ልብሶች የጦር ትጥቆች የበለሳን ዘይት ፈረሶችና በቅሎዎች ስጦታ አድርገው ያመጡ ነበር26 ሰለሞንም ሠረገሎችንና ፈረሶችን መሰብሰቡን ቀጠለ እሱም 1,400 ሠረገሎችና 12,000 ፈረሶች ነበሩት እነሱንም በሠረገላ ከተሞችና በኢየሩሳሌም በንጉሡ አቅራቢያ አኖራቸው27 ንጉሡ በኢየሩሳሌም ያለውን ብር ከብዛቱ የተነሳ በየቦታው እንደሚገኝ ድንጋይ አደረገው አርዘ ሊባኖሱንም ከብዛቱ የተነሳ በሸፌላ እንደሚገኘው የሾላ ዛፍ አደረገው28 የሰለሞን ፈረሶች ከግብፅ ያስመጣቸው ነበሩ የንጉሡ ነጋዴዎችም የፈረሶቹን መንጋ አንዴ በተተመነው ዋጋ ይገዙ ነበር29 ከግብፅ የሚመጣው እያንዳንዱ ሠረገላ 600 የብር ሰቅል ያወጣ ነበር አንድ ፈረስ ደግሞ 150 ሰቅል ያወጣል እነሱ ደግሞ በተራቸው ለሂታውያን ነገሥታትና ለሶርያ ነገሥታት ሁሉ ሠረገሎችንና ፈረሶችን ይሸጡ ነበር
11 ይሁንና ንጉሥ ሰለሞን ከፈርዖን ልጅ ሌላ ብዙ የባዕድ አገር ሴቶችን ማለትም ሞዓባውያን አሞናውያን ኤዶማውያን ሲዶናውያንና ሂታውያን ሴቶችን አፈቀረ2 እነሱም ይሖዋ ለእስራኤላውያን ከእነሱ ጋር አትቀላቀሉ እነሱም ከእናንተ ጋር አይቀላቀሉ አለዚያ ያለምንም ጥርጥር ልባችሁ አማልክታቸውን ወደ መከተል እንዲያዘነብል ያደርጉታል ብሎ ከነገራቸው ብሔራት ወገን ነበሩ ሆኖም ሰለሞን ከእነሱ ጋር ተጣበቀ ደግሞም አፈቀራቸው3 እሱም ልዕልቶች የሆኑ 700 ሚስቶች እንዲሁም 300 ቁባቶች ነበሩት ሚስቶቹም ቀስ በቀስ ልቡ ወደ ሌላ እንዲያዘነብል አደረጉት4 ሰለሞን በሸመገለ ጊዜ ሚስቶቹ ልቡ ሌሎች አማልክትን ወደ መከተል እንዲያዘነብል አደረጉት ልቡ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ በአምላኩ በይሖዋ ዘንድ ሙሉ አልነበረም5 ሰለሞን የሲዶናውያንን እንስት አምላክ አስታሮትንና አስጸያፊ የሆነውን የአሞናውያንን አምላክ ሚልኮምን ተከተለ6 ሰለሞንም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ አባቱ ዳዊት እንዳደረገው ይሖዋን ሙሉ በሙሉ አልተከተለም7 ሰለሞን አስጸያፊ ለሆነው የሞዓብ አምላክ ለከሞሽና አስጸያፊ ለሆነው ለአሞናውያን አምላክ ለሞሎክ ኢየሩሳሌም ፊት ለፊት በሚገኘው ተራራ ላይ ከፍ ያለ የማምለኪያ ቦታ የሠራው በዚህ ጊዜ ነበር8 ለአማልክታቸው የሚጨስ መሥዋዕት ለሚያቀርቡትና ለሚሠዉት የባዕድ አገር ሚስቶቹ ሁሉ ልክ እንደዚሁ አደረገ9 ሰለሞን ሁለት ጊዜ ከተገለጠለት ከእስራኤል አምላክ ከይሖዋ ልቡ ስለሸፈተ ይሖዋ በሰለሞን ላይ ተቆጣ10 ደግሞም ሌሎች አማልክትን እንዳይከተል በማዘዝ ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ አስጠንቅቆት ነበር እሱ ግን ይሖዋ ያዘዘውን ነገር አልጠበቀም11 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሰለሞንን እንዲህ አለው ይህን ስላደረግክ እንዲሁም ባዘዝኩህ መሠረት ቃል ኪዳኔንና ደንቦቼን ስላልጠበቅክ መንግሥትህን ቀድጄ ከአንተ እወስደዋለሁ ከአገልጋዮችህም መካከል ለአንዱ እሰጠዋለሁ12 ሆኖም ስለ አባትህ ስለ ዳዊት ስል በአንተ ዘመን ይህን አላደርግም መንግሥትህን ከልጅህ እጅ ላይ እቀደዋለሁ13 ይሁንና መንግሥቱን በሙሉ ቀድጄ አልወስድም ስለ አገልጋዬ ስለ ዳዊትና ስለመረጥኳት ስለ ኢየሩሳሌም ስል ለልጅህ አንድ ነገድ እሰጠዋለሁ14 ከዚያም ይሖዋ ከኤዶም ንጉሣዊ ቤተሰብ የሆነውን ኤዶማዊውን ሃዳድን በሰለሞን ላይ ተቃዋሚ አድርጎ አስነሳው15 ዳዊት ኤዶምን ድል ባደረገበት ጊዜ የሠራዊቱ አለቃ የሆነው ኢዮዓብ የተገደሉትን ለመቅበር ወጥቶ የነበረ ሲሆን በኤዶም የሚገኘውን እያንዳንዱን ወንድ ለመግደል ሞክሮ ነበር16 ምክንያቱም ኢዮዓብ በኤዶም የሚገኘውን እያንዳንዱን ወንድ ገድሎ እስኪጨርስ ድረስ ከመላው እስራኤል ጋር በዚያ ለስድስት ወር ተቀምጦ ነበር17 ሆኖም ሃዳድ የአባቱ አገልጋዮች ከሆኑ የተወሰኑ ኤዶማውያን ጋር ሸሸ እነሱም ወደ ግብፅ ሄዱ በወቅቱ ሃዳድ ገና ትንሽ ልጅ ነበር18 እነሱም ከምድያም ተነስተው ወደ ፋራን ሄዱ ከፋራንም ሰዎች ይዘው ወደ ግብፅ ይኸውም ወደ ግብፁ ንጉሥ ወደ ፈርዖን መጡ ፈርዖንም ቤትና መሬት ሰጠው ቀለብም እንዲሰፈርለት አደረገ19 ሃዳድም በፈርዖን ፊት ሞገስ ስላገኘ ፈርዖን የገዛ ሚስቱን እህት ማለትም የንግሥት ጣፍኔስን እህት ዳረለት20 ከጊዜ በኋላ የጣፍኔስ እህት ጌኑባት የተባለ ልጅ ወለደችለት ጣፍኔስም ልጁን በፈርዖን ቤት ውስጥ አሳደገችው ጌኑባት በፈርዖን ቤት ከፈርዖን ልጆች ጋር ኖረ21 ሃዳድ በግብፅ ሳለ ዳዊት ከአባቶቹ ጋር እንዳንቀላፋ እንዲሁም የሠራዊቱ አለቃ ኢዮዓብ እንደሞተ ሰማ በመሆኑም ሃዳድ ፈርዖንን ወደ አገሬ እንድሄድ አሰናብተኝ አለው22 ፈርዖን ግን እዚህ እኔ ጋር እያለህ ምን ጎደለብህና ነው ወደ አገርህ መሄድ የፈለግከው? አለው እሱም ምንም የጎደለብኝ ነገር የለም ብቻ እንድሄድ አሰናብተኝ አለው23 በተጨማሪም አምላክ ከጌታው ከጾባህ ንጉሥ ከሃዳድኤዜር የኮበለለውን የኤሊያዳን ልጅ ረዞንን በሰለሞን ላይ ተቃዋሚ አድርጎ አስነሳው24 እሱም ዳዊት የጾባህን ሰዎች ድል ባደረገበት ጊዜ ሰዎችን አሰባስቦ የአንድ ወራሪ ቡድን አለቃ ሆነ በመሆኑም ወደ ደማስቆ ሄደው በዚያ ሰፈሩ በደማስቆም መግዛት ጀመሩ25 ሃዳድ በእስራኤል ላይ ካስከተለው ጉዳት በተጨማሪ ረዞንም በሰለሞን ዘመን ሁሉ የእስራኤል ተቃዋሚ ሆነ በሶርያ ላይ በነገሠበትም ዘመን ሁሉ ለእስራኤል ከፍተኛ ጥላቻ ነበረው26 እንዲሁም የሰለሞን አገልጋይ የሆነ ኢዮርብዓም የተባለ አንድ ኤፍሬማዊ ነበር እሱም ከጸሬዳህ ወገን ሲሆን የናባጥ ልጅ ነበር እናቱም ጽሩዓ የምትባል መበለት ነበረች እሱም በንጉሡ ላይ ማመፅ ጀመረ27 በንጉሡ ላይ ያመፀውም በዚህ የተነሳ ነው ሰለሞን ጉብታውን ሠርቶ እንዲሁም በአባቱ በዳዊት ከተማ ቅጥር ላይ የነበረውን ክፍተት ዘግቶ ነበር28 ኢዮርብዓም ከፍተኛ ችሎታ ያለው ሰው ነበር ሰለሞንም ወጣቱ ጠንካራ ሠራተኛ መሆኑን ሲያይ በዮሴፍ ቤት በሚከናወነው የግዳጅ ሥራ ሁሉ ላይ የበላይ ተመልካች አደረገው29 በዚህ ጊዜ ኢዮርብዓም ከኢየሩሳሌም ወጣ ሴሎናዊው ነቢዩ አኪያህም መንገድ ላይ አገኘው አኪያህ አዲስ ልብስ ለብሶ ነበር በሜዳውም ላይ ሁለቱ ብቻቸውን ነበሩ30 አኪያህም ለብሶት የነበረውን አዲስ ልብስ ይዞ 12 ቦታ ቀደደው31 ከዚያም ኢዮርብዓምን እንዲህ አለውአሥሩን ቁራጭ ለራስህ ውሰድ ምክንያቱም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል እንግዲህ መንግሥቱን ከሰለሞን እጅ እቀደዋለሁ ለአንተም አሥር ነገዶችን እሰጥሃለሁ32 ሆኖም ስለ አገልጋዬ ስለ ዳዊትና ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል ስለመረጥኳት ከተማ ስለ ኢየሩሳሌም ስል አንዱ ነገድ የእሱ እንደሆነ ይቀጥላል33 ይህን የማደርገው እኔን ትተው ለሲዶናውያን እንስት አምላክ ለአስታሮት ለሞዓብ አምላክ ለከሞሽና ለአሞናውያን አምላክ ለሚልኮም ስለሰገዱ ነው አባቱ ዳዊት እንዳደረገው በፊቴ ትክክል የሆነውን ነገር በማድረግ እንዲሁም ደንቦቼንና ድንጋጌዎቼን በመጠበቅ በመንገዴ አልሄዱም34 ሆኖም ትእዛዛቴንና ደንቦቼን ስለጠበቀው ስለመረጥኩት አገልጋዬ ስለ ዳዊት ስል መንግሥቱን በሙሉ ከእጁ አልወስድም ደግሞም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ አለቃ አደርገዋለሁ35 ይሁን እንጂ መንግሥቱን ይኸውም አሥሩን ነገድ ከልጁ እጅ ወስጄ ለአንተ እሰጥሃለሁ36 አገልጋዬ ዳዊት ስሜ እንዲኖርባት ለራሴ በመረጥኳት ከተማ በኢየሩሳሌም ዘወትር በፊቴ መብራት እንዲኖረው ለልጁ አንድ ነገድ እሰጠዋለሁ37 እኔም እወስድሃለሁ አንተም በተመኘኸው ሁሉ ላይ ትገዛለህ በእስራኤልም ላይ ንጉሥ ትሆናለህ38 አገልጋዬ ዳዊት እንዳደረገው ያዘዝኩህን ሁሉ ብትፈጽም እንዲሁም ደንቦቼንና ትእዛዛቴን በመጠበቅ በመንገዶቼ ብትሄድና በፊቴ ትክክል የሆነውን ነገር ብታደርግ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ ለዳዊት እንዳደረግኩለት ሁሉ ለአንተም ጸንቶ የሚኖር ቤት እሠራልሃለሁ እስራኤልንም እሰጥሃለሁ39 በዚህም የተነሳ የዳዊትን ዘር አዋርዳለሁ ይህን የማደርገው ግን ለሁልጊዜ አይደለም40 በመሆኑም ሰለሞን ኢዮርብዓምን ሊገድለው ሞከረ ሆኖም ኢዮርብዓም ተነስቶ ወደ ግብፅ ወደ ንጉሥ ሺሻቅ ሸሸ ሰለሞን እስኪሞትም ድረስ በግብፅ ተቀመጠ41 የቀረው የሰለሞን ታሪክ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉና ጥበቡ በሰለሞን የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?42 ሰለሞን በኢየሩሳሌም ሆኖ በመላው እስራኤል ላይ የገዛበት የጊዜ ርዝመት 40 ዓመት ነበር43 ከዚያም ሰለሞን ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ በአባቱ በዳዊት ከተማ ተቀበረ በእሱም ምትክ ልጁ ሮብዓም ነገሠ
12 ሮብዓም እስራኤላውያን በሙሉ ሊያነግሡት ወደ ሴኬም መጥተው ስለነበር እሱም ወደ ሴኬም ሄደ2 የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ይህን እንደሰማ ምክንያቱም ኢዮርብዓም ከንጉሥ ሰለሞን ሸሽቶ በግብፅ ይኖር ስለነበር በወቅቱ በዚያ ይገኝ ነበር3 ልከው አስጠሩት ከዚያም ኢዮርብዓምና መላው የእስራኤል ጉባኤ መጥተው ሮብዓምን እንዲህ አሉት4 አባትህ ቀንበራችንን አክብዶብን ነበር አንተ ግን አባትህ የሰጠንን አስቸጋሪ ሥራና በላያችን የጫነብንን ከባድ ቀንበር የምታቀልልን ከሆነ እናገለግልሃለን5 በዚህ ጊዜ እንግዲያው ሂዱና ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ኑ አላቸው በመሆኑም ሕዝቡ ሄደ6 ከዚያም ንጉሥ ሮብዓም አባቱ ሰለሞን በሕይወት በነበረበት ጊዜ ሲያገለግሉት የነበሩትን ሽማግሌዎች ለዚህ ሕዝብ ምን ምላሽ እንድሰጥ ትመክሩኛላችሁ? በማለት ምክር ጠየቀ7 እነሱም ዛሬ አንተ የዚህ ሕዝብ አገልጋይ ብትሆንና የጠየቁህን ብትፈጽምላቸው እንዲሁም መልካም ምላሽ ብትሰጣቸው ምንጊዜም አገልጋዮችህ ይሆናሉ በማለት መለሱለት8 ሆኖም ሮብዓም ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ትቶ አብሮ አደጎቹ ከነበሩትና አሁን የእሱ አገልጋዮች ከሆኑት ወጣቶች ጋር ተማከረ9 እሱም እንዲህ ሲል ጠየቃቸው አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቅልልልን ለሚለኝ ለዚህ ሕዝብ ምን ምላሽ እንድንሰጥ ትመክሩኛላችሁ?10 አብሮ አደጎቹ የሆኑት ወጣቶችም እንዲህ አሉት አባትህ ቀንበራችንን አክብዶብን ነበር አንተ ግን ቀንበራችንን አቅልልልን ለሚልህ ለዚህ ሕዝብ እንዲህ በለው ትንሿ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ትወፍራለች11 አባቴ ከባድ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር እኔ ግን ቀንበራችሁን የባሰ አከብደዋለሁ አባቴ በአለንጋ ገርፏችሁ ነበር እኔ ግን በእሾህ አለንጋ እገርፋችኋለሁ12 ኢዮርብዓምና መላው ሕዝብ ንጉሡ በሦስተኛው ቀን ተመልሳችሁ ኑ ባላቸው መሠረት በሦስተኛው ቀን ወደ ሮብዓም መጡ13 ንጉሡ ግን ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ትቶ ለሕዝቡ መጥፎ ምላሽ ሰጠ14 ወጣቶቹም በሰጡት ምክር መሠረት አባቴ ቀንበራችሁን አክብዶባችሁ ነበር እኔ ግን ቀንበራችሁን የባሰ አከብደዋለሁ አባቴ በአለንጋ ገርፏችሁ ነበር እኔ ግን በእሾህ አለንጋ እገርፋችኋለሁ አላቸው15 በመሆኑም ንጉሡ ሕዝቡን ሳይሰማ ቀረ ይህም የሆነው ይሖዋ በሴሎናዊው በአኪያህ አማካኝነት ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ይሖዋ እነዚህ ነገሮች በዚህ መንገድ እንዲከናወኑ ስላደረገ ነው16 እስራኤላውያን ሁሉ ንጉሡ ሊሰማቸው ፈቃደኛ አለመሆኑን ሲያዩ ንጉሡን እንዲህ አሉት ከዳዊት ምን ድርሻ አለን? ከእሴይ ልጅ ምንም ርስት የለንም እስራኤል ሆይ ወደ አማልክትህ ተመለስ ዳዊት ሆይ እንግዲህ የገዛ ቤትህን ጠብቅ! ከዚያም እስራኤላውያን ወደየቤታቸው ተመለሱ17 ይሁንና ሮብዓም በይሁዳ ከተሞች በሚኖሩት እስራኤላውያን ላይ መግዛቱን ቀጠለ18 ከዚያም ንጉሥ ሮብዓም የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ የተመለመሉት ሰዎች አለቃ የነበረውን አዶራምን ላከው ሆኖም እስራኤላውያን በሙሉ በድንጋይ ወግረው ገደሉት ንጉሥ ሮብዓም ግን እንደ ምንም ብሎ ሠረገላው ላይ በመውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሸሸ19 እስራኤላውያንም እስከዚህ ቀን ድረስ በዳዊት ቤት ላይ እንዳመፁ ናቸው20 እስራኤላውያን በሙሉ ኢዮርብዓም መመለሱን እንደሰሙ ወደ ማኅበረሰቡ ካስጠሩት በኋላ በመላው እስራኤል ላይ አነገሡት ከይሁዳ ነገድ በስተቀር ከሕዝቡ መሃል የዳዊትን ቤት የተከተለ ማንም አልነበረም21 ሮብዓም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከእስራኤል ቤት ጋር ተዋግተው ንግሥናውን ለሰለሞን ልጅ ለሮብዓም እንዲያስመልሱ ከመላው የይሁዳ ቤትና ከቢንያም ነገድ የተውጣጡ 180,000 የሠለጠኑ ተዋጊዎች ወዲያውኑ ሰበሰበ22 ከዚያም የእውነተኛው አምላክ ቃል የእውነተኛው አምላክ ሰው ወደሆነው ወደ ሸማያህ እንዲህ ሲል መጣ23 ለይሁዳ ንጉሥ ለሰለሞን ልጅ ለሮብዓም ለይሁዳ ቤት ሁሉ ለቢንያምና ለቀረው ሕዝብ እንዲህ ብለህ ተናገር24 ይሖዋ እንዲህ ይላል ከወንድሞቻችሁ ከእስራኤላውያን ጋር ለመዋጋት አትውጡ ይህ እንዲሆን ያደረግኩት እኔ ስለሆንኩ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ ስለዚህ የይሖዋን ቃል ሰሙ ይሖዋ እንደነገራቸውም ወደየቤታቸው ተመለሱ25 ከዚያም ኢዮርብዓም በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ ሴኬምን ገንብቶ በዚያ መኖር ጀመረ ከዚያ ወጥቶ በመሄድ ጰኑኤልን ገነባ26 ኢዮርብዓም በልቡ እንዲህ ሲል አሰበ እንግዲህ አሁን መንግሥቱ ወደ ዳዊት ቤት ይመለሳል27 ይህ ሕዝብ በኢየሩሳሌም በሚገኘው የይሖዋ ቤት መሥዋዕት ለማቅረብ ወደዚያ መውጣቱን ከቀጠለ የዚህ ሕዝብ ልብ ጌታው ወደሆነው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓም ይመለሳል እኔንም ይገድለኛል ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓምም ይመለሳል28 በመሆኑም ንጉሡ ከተማከረ በኋላ ሁለት የወርቅ ጥጃዎችን ሠርቶ ሕዝቡን ወደ ኢየሩሳሌም መውጣት መንገላታት ይሆንባችኋል እስራኤል ሆይ ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ይኸውልህ አለ29 ከዚያም አንደኛውን በቤቴል ሌላኛውን ደግሞ በዳን አቆመው30 ይህም ለኃጢአት ዳረጋቸው ሕዝቡም በዳን የሚገኘውን ጥጃ ለማምለክ እስከዚያ ድረስ ይሄድ ነበር31 እሱም በኮረብቶቹ ላይ የአምልኮ ቤቶችን ሠራ ከሕዝቡም መካከል ሌዋውያን ያልሆኑ ሰዎችን ካህናት አድርጎ ሾመ32 በተጨማሪም ኢዮርብዓም በስምንተኛው ወር ከወሩም በ15ኛው ቀን በይሁዳ ይከበር የነበረው ዓይነት በዓል እንዲቋቋም አደረገ ለሠራቸውም ጥጆች በቤቴል በሠራው መሠዊያ ላይ መሥዋዕት አቀረበ በቤቴል ለሠራቸው ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችም ካህናት መደበ33 በቤቴል በሠራው መሠዊያም ላይ ራሱ በመረጠው ወር ይኸውም በስምንተኛው ወር በ15ኛው ቀን መባዎችን ማቅረብ ጀመረ ለእስራኤል ሰዎችም በዓል አቋቋመ እንዲሁም መባዎችንና የሚጨሱ መሥዋዕቶችን ለማቅረብ ወደ መሠዊያው ወጣ
13 ኢዮርብዓም በመሠዊያው አጠገብ የሚጨስ መሥዋዕት ለማቅረብ ቆሞ ሳለ አንድ የአምላክ ሰው በይሖዋ ቃል በታዘዘው መሠረት ከይሁዳ ወደ ቤቴል መጣ2 ከዚያም በይሖዋ ቃል በታዘዘው መሠረት መሠዊያውን በመቃወም እንዲህ ሲል ተጣራ መሠዊያ ሆይ! መሠዊያ ሆይ! ይሖዋ እንዲህ ይላል እነሆ ኢዮስያስ የተባለ ልጅ ለዳዊት ቤት ይወለዳል! እሱም በአንተ ላይ የሚጨስ መሥዋዕት እያቀረቡ ያሉትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ካህናት በላይህ ይሠዋቸዋል በአንተም ላይ የሰዎችን አጥንት ያቃጥላል3 እሱም በዚያ ቀን እንዲህ በማለት ምልክት ሰጠ ይሖዋ የሰጠው ምልክት ይህ ነው እነሆ መሠዊያው ይሰነጠቃል በላዩም ላይ ያለው አመድ ይፈስሳል4 ንጉሡ ኢዮርብዓምም የእውነተኛው አምላክ ሰው በቤቴል የሚገኘውን መሠዊያ በመቃወም የተናገረውን ቃል ሲሰማ እጁን ከመሠዊያው ላይ አንስቶ በመዘርጋት ያዙት! አላቸው ወዲያውኑም ወደ እሱ የዘረጋው እጁ ደረቀ እጁንም ሊያጥፈው አልቻለም5 ከዚያም የእውነተኛው አምላክ ሰው በይሖዋ ቃል ታዞ በሰጠው ምልክት መሠረት መሠዊያው ተሰነጠቀ አመዱም ከመሠዊያው ላይ ፈሰሰ6 በዚህ ጊዜ ንጉሡ የእውነተኛውን አምላክ ሰው እባክህ የአምላክህን የይሖዋን ሞገስ እንዳገኝ ለምንልኝ እጄም ወደ ቦታው እንዲመለስ ጸልይልኝ አለው በዚህ ጊዜ የእውነተኛው አምላክ ሰው የይሖዋን ሞገስ እንዲያገኝ ለመነለት የንጉሡም እጅ ተመልሶ እንደቀድሞው ሆነ7 ከዚያም ንጉሡ የእውነተኛውን አምላክ ሰው አብረኸኝ ወደ ቤት ሂድና ምግብ ብላ ስጦታም ልስጥህ አለው8 ሆኖም የእውነተኛው አምላክ ሰው ንጉሡን እንዲህ አለው የቤትህን ግማሽ ብትሰጠኝ እንኳ ከአንተ ጋር አልሄድም በዚህም ቦታ ምግብ አልበላም ውኃም አልጠጣም9 ምክንያቱም የይሖዋ ቃል ምግብ እንዳትበላ ውኃም እንዳትጠጣ በሄድክበትም መንገድ እንዳትመለስ ሲል አዞኛል10 በመሆኑም በሌላ መንገድ ሄደ ወደ ቤቴል በመጣበትም መንገድ አልተመለሰም11 በዚህ ጊዜ በቤቴል የሚኖር አንድ አረጋዊ ነቢይ ነበር ልጆቹም ወደ ቤት መጥተው የእውነተኛው አምላክ ሰው በዚያ ቀን በቤቴል ያደረገውን ነገር ሁሉና ለንጉሡ የተናገረውን ቃል ነገሩት ይህን ለአባታቸው ከተረኩለት በኋላ12 አባታቸው ለመሆኑ የሄደው በየት በኩል ነው? ሲል ጠየቃቸው ልጆቹም ከይሁዳ የመጣው የእውነተኛው አምላክ ሰው የሄደበትን መንገድ አሳዩት13 እሱም ልጆቹን በሉ አህያውን ጫኑልኝ አላቸው እነሱም አህያውን ጫኑለት እሱም አህያው ላይ ተቀመጠ14 ከዚያም የእውነተኛውን አምላክ ሰው ተከተለው በአንድ ትልቅ ዛፍ ሥር ተቀምጦም አገኘው እሱም ከይሁዳ የመጣኸው የእውነተኛው አምላክ ሰው አንተ ነህ? አለው እሱም አዎ እኔ ነኝ ሲል መለሰለት15 ከዚያም አብረን ወደ ቤት እንሂድና ምግብ ብላ አለው16 እሱ ግን እንዲህ አለው ከአንተ ጋር ተመልሼ ልሄድ ወይም ያቀረብክልኝን ግብዣ ልቀበል አልችልም ደግሞም በዚህ ቦታ ከአንተ ጋር ምግብም ሆነ ውኃ አልቀምስም17 ምክንያቱም የይሖዋ ቃል እዚያ ምግብ እንዳትበላ ውኃም እንዳትጠጣ በመጣህበትም መንገድ እንዳትመለስ በማለት አዞኛል18 በዚህ ጊዜ አረጋዊው ሰው እኔም እኮ እንደ አንተው ነቢይ ነኝ አንድ መልአክ ምግብ እንዲበላና ውኃ እንዲጠጣ መልሰህ ወደ ቤትህ አምጣው በማለት የይሖዋን ቃል ነግሮኛል አለው እሱም አታለለው19 በመሆኑም እሱ ቤት ምግብ ለመብላትና ውኃ ለመጠጣት አብሮት ተመለሰ20 እነሱም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ የይሖዋ ቃል የእውነተኛውን አምላክ ሰው መልሶ ወዳመጣው ነቢይ መጣ21 ከዚያም ከይሁዳ የመጣውን የእውነተኛውን አምላክ ሰው ጠርቶ እንዲህ አለው ይሖዋ እንዲህ ይላል በይሖዋ መመሪያ ላይ ስላመፅክና አምላክህ ይሖዋ የሰጠህን ትእዛዝ ስላልጠበቅክ22 ከዚህ ይልቅ ምግብ ለመብላትና ውኃ ለመጠጣት ስትል ምግብ እንዳትበላ ውኃም እንዳትጠጣ ወደተባልክበት ቦታ ስለተመለስክ ሬሳህ በአባቶችህ የመቃብር ቦታ አይቀበርም23 የእውነተኛው አምላክ ሰውም ከበላና ከጠጣ በኋላ አረጋዊው ነቢይ ከመንገድ መልሶ ላመጣው ለዚያ ነቢይ አህያውን ጫነለት24 ከዚያም መንገዱን ቀጠለ ሆኖም አንድ አንበሳ መንገድ ላይ አግኝቶ ገደለው ሬሳውም መንገዱ ላይ ተጋድሞ አህያው ደግሞ አጠገቡ ቆሞ ነበር አንበሳውም ሬሳው አጠገብ ቆሞ ነበር25 በዚያ የሚያልፉ ሰዎችም ሬሳው መንገድ ላይ ተጋድሞ አንበሳው ደግሞ አጠገቡ ቆሞ አዩ ከዚያም መጥተው ይህን ነገር አረጋዊው ነቢይ በሚኖርበት ከተማ አወሩ26 ከመንገድ መልሶ ያመጣውም ነቢይ ይህን ሲሰማ ወዲያውኑ ይህ ሰው በይሖዋ መመሪያ ላይ ያመፀው የእውነተኛው አምላክ ሰው ነው ይሖዋ በነገረው ቃል መሠረት እንዲቦጫጭቀውና እንዲገድለው ይሖዋ ለአንበሳ አሳልፎ ሰጥቶታል አለ27 እሱም ልጆቹን በሉ አህያውን ጫኑልኝ አላቸው እነሱም ጫኑለት28 ከዚያም ሄደ ሬሳው መንገድ ላይ ተጋድሞ አህያውና አንበሳውም አጠገቡ ቆመው አገኛቸው አንበሳው ሬሳውን አልበላውም አህያውንም ቢሆን አልቦጫጨቀውም29 ነቢዩም የእውነተኛውን አምላክ ሰው ሬሳ አንስቶ አህያው ላይ ከጫነ በኋላ አልቅሶ ሊቀብረው ስላሰበ ወደሚኖርበት ከተማ ይዞት ተመለሰ30 ከዚያም ሬሳውን በራሱ የመቃብር ቦታ ቀበረው እነሱም ወይኔ ወንድሜን! እያሉ አለቀሱለት31 እሱንም ከቀበረው በኋላ ልጆቹን እንዲህ አላቸው እኔም ስሞት የእውነተኛው አምላክ ሰው በተቀበረበት የመቃብር ቦታ ቅበሩኝ አጥንቶቼንም ከአጥንቶቹ አጠገብ ቅበሯቸው32 በይሖዋ ቃል በታዘዘው መሠረት በቤቴል በሚገኘው መሠዊያና በሰማርያ ከተሞች በሚገኙት ኮረብቶች ላይ ባሉት የአምልኮ ቤቶች ሁሉ ላይ የተናገረው ቃል ያለጥርጥር ይፈጸማል33 ይህ ሁሉ ከሆነም በኋላ ቢሆን ኢዮርብዓም ከመጥፎ መንገዱ አልተመለሰም ከዚህ ይልቅ ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች ከሕዝቡ መካከል ካህናት መሾሙን ቀጠለ እንዲሁም ካህን ለመሆን የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች ካህን ይሁን በማለት ይሾመው ነበር34 ይህም ኃጢአት የኢዮርብዓም ቤት ከምድር ገጽ እንዲጠፋና እንዲደመሰስ ምክንያት ሆነ
14 በዚህ ጊዜ የኢዮርብዓም ልጅ አቢያህ ታመመ2 በመሆኑም ኢዮርብዓም ሚስቱን እንዲህ አላት እባክሽ ተነሺና የኢዮርብዓም ሚስት መሆንሽን እንዳያውቁ ራስሽን ለውጠሽ ወደ ሴሎ ሂጂ ነቢዩ አኪያህ ያለው እዚያ ነው እኔ በዚህ ሕዝብ ላይ ንጉሥ እንደምሆን የተናገረው እሱ ነው3 አሥር ዳቦና የተቀቡ ቂጣዎች እንዲሁም አንድ ገንቦ ማር ይዘሽ ወደ እሱ ሂጂ እሱም በልጁ ላይ የሚደርሰውን ነገር ይነግርሻል4 የኢዮርብዓምም ሚስት እንዳላት አደረገች ተነስታ ወደ ሴሎ በመሄድ ወደ አኪያህ ቤት መጣች አኪያህ ከማርጀቱ የተነሳ ማየት ተስኖት የነበረ ቢሆንም ዓይኖቹ ፊት ለፊት ትኩር ብለው ይመለከቱ ነበር5 ይሖዋ ግን አኪያህን እንዲህ አለው የኢዮርብዓም ሚስት ልጇ ስለታመመ ስለ እሱ ልትጠይቅህ እየመጣች ነው እኔም ምን እንደምትላት እነግርሃለሁ እሷም እዚህ ስትደርስ ማንነቷ እንዳይታወቅ ራሷን ትለውጣለች6 አኪያህም በሩ ጋ ስትደርስ የእግሯን ኮቴ ሰምቶ እንዲህ አላት የኢዮርብዓም ሚስት ግቢ ማንነትሽ እንዳይታወቅ ራስሽን የለወጥሽው ለምንድን ነው? መጥፎ ዜና እንድነግርሽ ታዝዣለሁ7 ሂጂና ኢዮርብዓምን እንዲህ በዪው የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን ከሕዝብህ መካከል አስነሳሁህ8 ከዚያም መንግሥቱን ከዳዊት ቤት ላይ ቀድጄ ለአንተ ሰጠሁህ አንተ ግን በፊቴ ትክክል የሆነውን ነገር ብቻ በማድረግ ትእዛዛቴን እንደጠበቀውና በሙሉ ልቡ እንደተከተለኝ እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት አልሆንክም9 ከዚህ ይልቅ ከአንተ በፊት ከነበሩት ሁሉ የከፋ ድርጊት ፈጸምክ እኔንም ለማስቆጣት ለራስህ ሌላ አምላክና ከብረት የተሠሩ ምስሎችን ሠራህ ጀርባህንም ሰጠኸኝ10 በዚህም የተነሳ በኢዮርብዓም ቤት ላይ ጥፋት አመጣለሁ በእስራኤል ውስጥ የሚገኘውን ምስኪኑንና ደካማውን ጨምሮ የኢዮርብዓም የሆነውን ወንድ ሁሉ ጠራርጌ አጠፋለሁ አንድ ሰው ፋንድያን ሙልጭ አድርጎ በመጥረግ እንደሚያስወግድ ሁሉ እኔም የኢዮርብዓምን ቤት ሙልጭ አድርጌ እጠርጋለሁ!11 ከኢዮርብዓም ወገን የሆነውን በከተማ ውስጥ የሚሞተውን ሁሉ ውሾች ይበሉታል በሜዳ ላይ የሚሞተውን ደግሞ የሰማይ አሞሮች ይበሉታል ይሖዋ ይህን ተናግሯልና12 እንግዲህ አሁን ተነስተሽ ወደ ቤትሽ ሂጂ እግርሽ ከተማዋን እንደረገጠ ልጁ ይሞታል13 ከኢዮርብዓም ቤተሰብ መካከል በመቃብር ቦታ የሚቀበረው እሱ ብቻ ስለሆነ እስራኤል ሁሉ አልቅሰው ይቀብሩታል ምክንያቱም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ከኢዮርብዓም ቤት ሁሉ አንድ መልካም ነገር ያገኘበት እሱን ብቻ ነው14 ይሖዋም ከዚያን ቀን ጀምሮ እንዲያውም አሁኑኑ የኢዮርብዓምን ቤት የሚያስወግድ በእስራኤል ላይ የሚነግሥ ንጉሥ ለራሱ ያስነሳል15 ይሖዋ በውኃ ውስጥ እንደሚወዛወዝ ሸምበቆ እስራኤልን ይመታል እንዲሁም እስራኤላውያንን ለአባቶቻቸው ከሰጣቸው ከዚህ መልካም ምድር ላይ ይነቅላቸዋል ከወንዙም ማዶ ይበትናቸዋል ምክንያቱም የማምለኪያ ግንዶችን ለራሳቸው በማቆም ይሖዋን አስቆጥተውታል16 እሱም ኢዮርብዓም በሠራው ኃጢአትና እስራኤላውያን እንዲሠሩ ባደረገው ኃጢአት የተነሳ እስራኤልን ይተዋል17 በዚህ ጊዜ የኢዮርብዓም ሚስት ተነስታ በመሄድ ወደ ቲርጻ መጣች ቤቱ ደጃፍ ላይ ስትደርስም ልጁ ሞተ18 ይሖዋ በአገልጋዩ በነቢዩ አኪያህ አማካኝነት በተናገረውም መሠረት ቀበሩት እስራኤልም ሁሉ አለቀሰለት19 ኢዮርብዓም ስላደረገው ውጊያና ስለ አገዛዙ የሚናገረው የቀረው ታሪኩ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፏል20 ኢዮርብዓም የገዛበት የጊዜ ርዝመት 22 ዓመት ነበር ከዚያም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ በእሱም ምትክ ልጁ ናዳብ ነገሠ21 ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰለሞን ልጅ ሮብዓም በይሁዳ ላይ ነግሦ ነበር ሮብዓም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 41 ዓመት ነበር እሱም ይሖዋ ስሙ እንዲኖርባት ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል በመረጣት ከተማ በኢየሩሳሌም ሆኖ ለ17 ዓመት ገዛ እናቱም ናዕማ የተባለች አሞናዊት ነበረች22 ይሁዳም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ እነሱም በፈጸሙት ኃጢአት የተነሳ ከአባቶቻቸው ይበልጥ አስቆጡት23 እነሱም ቢሆኑ በእያንዳንዱ ኮረብታ ላይና በእያንዳንዱ የለመለመ ዛፍ ሥር ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችን የማምለኪያ ዓምዶችንና የማምለኪያ ግንዶችን ለራሳቸው ሠሩ24 ሌላው ቀርቶ በምድሪቱ ላይ የቤተ መቅደስ ቀላጮች ነበሩ ይሖዋ ከእስራኤላውያን ፊት አባሮ ያስወጣቸው ብሔራት ይፈጽሟቸው የነበሩትን አስጸያፊ ነገሮች በሙሉ አደረጉ25 ንጉሥ ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብፁ ንጉሥ ሺሻቅ ኢየሩሳሌምን ለመውጋት መጣ26 እሱም በይሖዋ ቤት የነበሩትን ውድ ንብረቶችና በንጉሡ ቤት የነበሩትን ውድ ንብረቶች ወሰደ ሰለሞን የሠራቸውን የወርቅ ጋሻዎች ጨምሮ ሁሉንም ነገር ወሰደ27 በመሆኑም ንጉሥ ሮብዓም በእነሱ ምትክ የመዳብ ጋሻዎችን ሠርቶ የንጉሡን ቤት በር ለሚጠብቁት የዘብ አለቆች ሰጣቸው28 ዘቦቹም ንጉሡ ወደ ይሖዋ ቤት በመጣ ቁጥር ጋሻዎቹን ያነግቡ ነበር ከዚያም ወደ ዘቦቹ ክፍል ይመልሷቸው ነበር29 የቀረው የሮብዓም ታሪክና ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?30 በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከል የማያቋርጥ ጦርነት ነበር31 በመጨረሻም ሮብዓም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ በዳዊት ከተማም ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ እናቱ ናዕማ የተባለች አሞናዊት ነበረች በእሱም ምትክ ልጁ አብያም ነገሠ
15 የናባጥ ልጅ ንጉሥ ኢዮርብዓም በነገሠ በ18ኛው ዓመት አብያም በይሁዳ ላይ ነገሠ2 እሱም በኢየሩሳሌም ለሦስት ዓመት ገዛ የእናቱ ስም ማአካ ሲሆን እሷም የአቢሴሎም የልጅ ልጅ ነበረች3 እሱም አባቱ ከእሱ በፊት በሠራው ኃጢአት ሁሉ መመላለሱን ቀጠለ ልቡ እንደቀድሞ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ በአምላኩ በይሖዋ ዘንድ ሙሉ አልነበረም4 ሆኖም በዳዊት የተነሳ አምላኩ ይሖዋ ከእሱ በኋላ ልጁን በማስነሳትና ኢየሩሳሌም ጸንታ እንድትኖር በማድረግ በኢየሩሳሌም መብራት ሰጠው5 ምክንያቱም ዳዊት በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አድርጓል እንዲሁም ከሂታዊው ከኦርዮ ጋር በተያያዘ ከፈጸመው ነገር በስተቀር በሕይወት ዘመኑ ሁሉ እሱ ከሰጠው ከየትኛውም ትእዛዝ ፈቀቅ አላለም6 በሕይወት ዘመኑ ሁሉ በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከል ጦርነት ነበር7 የቀረው የአብያም ታሪክ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? በአብያምና በኢዮርብዓም መካከልም ጦርነት ነበር8 በመጨረሻም አብያም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ በዳዊት ከተማም ቀበሩት በእሱም ምትክ ልጁ አሳ ነገሠ9 የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም በነገሠ በ20ኛው ዓመት አሳ በይሁዳ ላይ መግዛት ጀመረ10 እሱም በኢየሩሳሌም ለ41 ዓመት ገዛ የአያቱም ስም ማአካ ሲሆን እሷም የአቢሴሎም የልጅ ልጅ ነበረች11 አሳ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ12 እሱም የቤተ መቅደስ ቀላጮችን ከምድሪቱ አባረረ እንዲሁም አባቶቹ የሠሯቸውን አስጸያፊ ጣዖቶች በሙሉ አስወገደ13 ሌላው ቀርቶ አያቱ ማአካ ለማምለኪያ ግንዱ አምልኮ ጸያፍ ጣዖት ሠርታ ስለነበር ከእመቤትነቷ ሻራት አሳ አያቱ የሠራችውን ጸያፍ ጣዖት ቆርጦ በቄድሮን ሸለቆ አቃጠለው14 ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች ግን አልተወገዱም ነበር ያም ሆኖ አሳ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ልቡ በይሖዋ ዘንድ ሙሉ ነበር15 እሱና አባቱ የቀደሷቸውን ነገሮች ይኸውም ብሩን ወርቁንና ልዩ ልዩ ዕቃዎችን ወደ ይሖዋ ቤት አስገባ16 በአሳና የእስራኤል ንጉሥ በሆነው በባኦስ መካከል የማያቋርጥ ጦርነት ነበር17 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በይሁዳ ላይ ዘመተ እሱም ማንም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ እንዳይገባና እንዳይወጣ ለማድረግ ራማን መገንባት ጀመረ18 በዚህ ጊዜ አሳ በይሖዋ ቤት ግምጃ ቤትና በንጉሡ ቤት ግምጃ ቤት የቀረውን ብርና ወርቅ ሁሉ አውጥቶ ለአገልጋዮቹ ሰጣቸው ከዚያም ንጉሥ አሳ እነዚህን አገልጋዮቹን በደማስቆ ወደሚገኘው የሶርያ ንጉሥ ማለትም የሄዝዮን ልጅ የታብሪሞን ልጅ ወደሆነው ወደ ቤንሃዳድ እንዲህ ሲል ላካቸው19 በእኔና በአንተ እንዲሁም በአባቴና በአባትህ መካከል ውል አለ እኔ የብርና የወርቅ ስጦታ ልኬልሃለሁ ስለዚህ ና የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ ከእኔ እንዲርቅ ከእሱ ጋር የገባኸውን ውል አፍርስ20 ቤንሃዳድ የንጉሥ አሳን ሐሳብ ተቀብሎ የጦር ሠራዊቱን አለቆች በእስራኤል ከተሞች ላይ አዘመተ እነሱም ኢዮንን ዳንን አቤልቤትማዓካን እንዲሁም ኪኔሬትን ሁሉና መላውን የንፍታሌም ምድር መቱ21 ባኦስም ይህን ሲሰማ ወዲያውኑ ራማን መገንባቱን አቁሞ በቲርጻ መኖሩን ቀጠለ22 ከዚያም ንጉሥ አሳ ማንንም ሳያስቀር የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ እነሱም ባኦስ እየገነባባቸው የነበሩትን የራማን ድንጋዮችና ሳንቃዎች አጋዙ ንጉሥ አሳም በድንጋዮቹና በሳንቃዎቹ በቢንያም የምትገኘውን ጌባንና ምጽጳን ገነባ23 የቀረው የአሳ ታሪክ ሁሉ ኃያልነቱ ሁሉ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉና የገነባቸው ከተሞች በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? ሆኖም አሳ ባረጀ ጊዜ በእግር ሕመም ይሠቃይ ነበር24 በመጨረሻም አሳ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ በአባቱ በዳዊት ከተማም ከእነሱ ጋር ተቀበረ በእሱም ምትክ ልጁ ኢዮሳፍጥ ነገሠ25 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት የኢዮርብዓም ልጅ ናዳብ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ እሱም በእስራኤል ላይ ለሁለት ዓመት ገዛ26 በይሖዋም ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ማድረጉን ገፋበት የአባቱንም መንገድ ተከተለ እንዲሁም አባቱ እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ባደረገው ኃጢአት ተመላለሰ27 ከይሳኮር ቤት የሆነው የአኪያህ ልጅ ባኦስ በእሱ ላይ አሴረ ናዳብና እስራኤል ሁሉ የፍልስጤማውያን ከተማ የሆነችውን ጊበቶንን ከበው ሳሉ ባኦስ ጊበቶን ላይ ናዳብን ገደለው28 በመሆኑም ባኦስ የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ናዳብን ገድሎ በምትኩ ነገሠ29 እሱም እንደነገሠ ወዲያውኑ የኢዮርብዓምን ቤት ሁሉ ፈጀ ከኢዮርብዓም ቤት እስትንፋስ ያለውን አንድም ሰው አላስቀረም ይሖዋ በአገልጋዩ በሴሎናዊው በአኪያህ በኩል በተናገረው መሠረት ሁሉንም ደመሰሳቸው30 ይህም የሆነው ኢዮርብዓም በፈጸመው ኃጢአትና እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ባደረገው ኃጢአት የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን ክፉኛ ስላስቆጣው ነው31 የቀረው የናዳብ ታሪክና ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?32 በአሳና የእስራኤል ንጉሥ በሆነው በባኦስ መካከል የማያቋርጥ ጦርነት ነበር33 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የአኪያህ ልጅ ባኦስ በቲርጻ ሆኖ በመላው እስራኤል ላይ ለ24 ዓመት ገዛ34 ሆኖም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ማድረጉን ገፋበት የኢዮርብዓምን መንገድ ተከተለ እንዲሁም ኢዮርብዓም እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ባደረገው ኃጢአት ተመላለሰ
16 ከዚያም በባኦስ ላይ የተነገረው የይሖዋ ቃል የሃናኒ ልጅ ወደሆነው ወደ ኢዩ እንዲህ ሲል መጣ2 ከአቧራ ላይ አንስቼ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ አደረግኩህ አንተ ግን የኢዮርብዓምን መንገድ ተከተልክ ሕዝቤ እስራኤልም ኃጢአት እንዲሠራ አደረግክ እነሱም በኃጢአታቸው አስቆጡኝ3 ስለሆነም ባኦስንና ቤቱን ሙልጭ አድርጌ እጠርጋለሁ ቤቱንም እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮርብዓም ቤት አደርገዋለሁ4 ከባኦስ ወገን የሆነውን በከተማ ውስጥ የሚሞተውን ሁሉ ውሾች ይበሉታል ከእሱ ወገን የሆነውን በሜዳ ላይ የሚሞተውን ሁሉ ደግሞ የሰማይ አሞሮች ይበሉታል5 የቀረው የባኦስ ታሪክ ያደረጋቸው ነገሮችና ኃያልነቱ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?6 በመጨረሻም ባኦስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ በቲርጻም ተቀበረ በእሱም ምትክ ልጁ ኤላህ ነገሠ7 በተጨማሪም ባኦስ ልክ እንደ ኢዮርብዓም ቤት በእጁ በሠራቸው ነገሮች ይሖዋን በማስቆጣት በፊቱ መጥፎ የሆነውን ነገር ሁሉ ስለፈጸመ እንዲሁም እሱን ስለገደለ የይሖዋ ቃል የሃናኒ ልጅ በሆነው በነቢዩ ኢዩ አማካኝነት በባኦስና በቤቱ ላይ መጣ8 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ26ኛው ዓመት የባኦስ ልጅ ኤላህ በቲርጻ ሆኖ በእስራኤል ላይ ነገሠ ለሁለት ዓመትም ገዛ9 የግማሹ የሠረገላ ሠራዊት አለቃ የሆነው አገልጋዩ ዚምሪ በእሱ ላይ አሴረ በዚህ ጊዜ ኤላህ በቲርጻ የሚገኘው የንጉሡ ቤት ኃላፊ በነበረው በአርጻ ቤት ጠጥቶ ሰክሮ ነበር10 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ27ኛው ዓመት ዚምሪ ገብቶ ኤላህን መትቶ ገደለው በእሱም ምትክ ነገሠ11 እሱም ነግሦ ገና በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጠ የባኦስን ቤት ሁሉ መታ ከዘመዶቹም ሆነ ከወዳጆቹ መካከል አንድም ወንድ አላስተረፈም12 በዚህ መንገድ ይሖዋ በነቢዩ ኢዩ አማካኝነት በባኦስ ላይ በተናገረው ቃል መሠረት ዚምሪ መላውን የባኦስን ቤት አጠፋ13 ይህም የሆነው ባኦስ እና ልጁ ኤላህ በፈጸሙት ኃጢአት እንዲሁም ከንቱ በሆኑት ጣዖቶቻቸው አማካኝነት የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን በማስቆጣት እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ባደረጉት ኃጢአት የተነሳ ነው14 የቀረው የኤላህ ታሪክ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?15 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ27ኛው ዓመት ሠራዊቱ የፍልስጤማውያን የሆነችውን ጊበቶንን ከቦ በነበረበት ወቅት ዚምሪ በቲርጻ ለሰባት ቀን ነገሠ16 በኋላም ከተማዋን ከቦ የነበረው ሠራዊት ዚምሪ ሴራ በመጠንሰስ ንጉሡን ገድሎታል የሚል ወሬ ሰማ በመሆኑም መላው እስራኤል የሠራዊቱ አለቃ የሆነውን ኦምሪን በዚያን ቀን በሰፈሩ ውስጥ በእስራኤል ላይ አነገሡት17 ኦምሪና ከእሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከጊበቶን ወጥተው ቲርጻን ከበቡ18 ዚምሪም ከተማዋ መያዟን ሲያይ በንጉሡ ቤት ወዳለው የማይደፈር ማማ ገብቶ በውስጡ እንዳለ ቤቱን በእሳት አቃጠለው በዚህም የተነሳ ሞተ19 ይህም የሆነው የኢዮርብዓምን መንገድ በመከተል በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር በመፈጸም በሠራው በገዛ ኃጢአቱና እስራኤላውያን እንዲሠሩ ባደረገው ኃጢአት የተነሳ ነው20 የቀረው የዚምሪ ታሪክና የጠነሰሰው ሴራ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ ይገኝ የለም?21 የእስራኤል ሕዝብ በሁለት አንጃ የተከፈለው በዚህ ጊዜ ነበር አንደኛው ወገን የጊናትን ልጅ ቲብኒን ለማንገሥ ስለፈለገ የእሱ ተከታይ ሆነ ሌላኛው ወገን ደግሞ ኦምሪን ተከተለ22 ሆኖም ኦምሪን የተከተለው ሕዝብ የጊናትን ልጅ ቲብኒን በተከተለው ሕዝብ ላይ አየለ በመሆኑም ቲብኒ ሞተ ኦምሪም ነገሠ23 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ31ኛው ዓመት ኦምሪ በእስራኤል ላይ ነገሠ ለ12 ዓመትም ገዛ በቲርጻም ሆኖ ለስድስት ዓመት ገዛ24 እሱም የሰማርያን ተራራ ከሼሜር ላይ በሁለት ታላንት ብር ገዛ በተራራውም ላይ ከተማ ገነባ የገነባትንም ከተማ የተራራው ጌታ በሆነው በሼሜር ስም ሰማርያ ብሎ ሰየማት25 ኦምሪም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ማድረጉን ቀጠለ ከእሱ በፊት ከነበሩት ሁሉ የከፋ ድርጊት ፈጸመ26 የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በሄደበት መንገድ ሁሉ ሄደ እንዲሁም ኢዮርብዓም እስራኤላውያን በከንቱ ጣዖቶቻቸው አማካኝነት የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን እንዲያስቆጡት በማድረግ በተከተለው የኃጢአት ጎዳና ተመላለሰ27 የቀረው የኦምሪ ታሪክ ያደረጋቸው ነገሮችና በኃያልነቱ የፈጸማቸው ጀብዱዎች በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?28 በመጨረሻም ኦምሪ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ በሰማርያም ተቀበረ በእሱም ምትክ ልጁ አክዓብ ነገሠ29 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ38ኛው ዓመት የኦምሪ ልጅ አክዓብ በእስራኤል ላይ ነገሠ የኦምሪ ልጅ አክዓብ በሰማርያ ሆኖ በእስራኤል ላይ ለ22 ዓመት ገዛ30 የኦምሪ ልጅ አክዓብ ከእሱ በፊት የነበሩት ሁሉ ከፈጸሙት የከፋ ድርጊት በይሖዋ ፊት ፈጸመ31 አክዓብ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በተከተለው የኃጢአት ጎዳና መመላለሱ ሳያንሰው የሲዶናውያን ንጉሥ የኤትባዓል ልጅ የሆነችውን ኤልዛቤልን አገባ እንዲሁም ባአልን ማገልገልና ለእሱ መስገድ ጀመረ32 እንዲሁም በሰማርያ ለባአል በሠራው ቤት ውስጥ ለባአል መሠዊያ አቆመ33 በተጨማሪም አክዓብ የማምለኪያ ግንድ ሠራ እንዲሁም ከእሱ በፊት ከነበሩት የእስራኤል ነገሥታት ሁሉ ይበልጥ የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን የሚያስቆጣ ድርጊት ፈጸመ34 በአክዓብ ዘመን የቤቴል ሰው የሆነው ሂኤል ኢያሪኮን መልሶ ገነባ ይሖዋ በነዌ ልጅ በኢያሱ አማካኝነት በተናገረው ቃል መሠረት የከተማዋን መሠረት ሲጥል የበኩር ልጁ አቤሮን ሞተ በሮቿን ሲያቆም ደግሞ የመጨረሻ ልጁ ሰጉብ ሞተ
17 በዚህ ጊዜ ከጊልያድ ነዋሪዎች አንዱ የሆነው ቲሽባዊው ኤልያስ አክዓብን በማገለግለውና ሕያው በሆነው በእስራኤል አምላክ በይሖዋ እምላለሁ በእኔ ትእዛዝ ካልሆነ በቀር በእነዚህ ዓመታት ጠል ወይም ዝናብ አይኖርም! አለው2 የይሖዋም ቃል እንዲህ ሲል ወደ እሱ መጣ3 ከዚህ ተነስተህ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ሂድ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በከሪት ሸለቆም ተደበቅ4 ከጅረቱ ትጠጣለህ ቁራዎችም እዚያ ምግብ እንዲያመጡልህ አዛለሁ5 እሱም ወዲያውኑ ሄዶ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ ሄዶም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በከሪት ሸለቆ ተቀመጠ6 ቁራዎቹም ጠዋትና ማታ ምግብና ሥጋ ያመጡለት ነበር እሱም ከጅረቱ ይጠጣ ነበር7 ሆኖም በምድሪቱ ላይ ዝናብ ስላልዘነበ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ጅረቱ ደረቀ8 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እሱ መጣ9 ተነስተህ በሲዶና ወደምትገኘው ወደ ሰራፕታ ሂድ እዚያም ተቀመጥ እኔም በዚያ አንዲት መበለት እንድትመግብህ አዛለሁ10 ኤልያስም ተነስቶ ወደ ሰራፕታ ሄደ ወደ ከተማዋ መግቢያ በደረሰም ጊዜ አንዲት መበለት ጭራሮ ስትለቅም አገኘ መበለቲቱንም ጠርቶ እባክሽ የምጠጣው ትንሽ ውኃ በዕቃ ስጪኝ አላት11 ልታመጣለት ስትሄድም ጠራትና እባክሽ ቁራሽ ዳቦም ይዘሽልኝ ነይ አላት12 በዚህ ጊዜ እንዲህ አለችው ሕያው በሆነው አምላክህ በይሖዋ እምላለሁ በማድጋው ውስጥ ካለው አንድ እፍኝ ዱቄትና በማሰሮው ውስጥ ካለው ጥቂት ዘይት በስተቀር ምንም ዳቦ የለኝም ለእኔና ለልጄ የሆነች ነገር ለማዘጋጀት ጭራሮ እየለቀምኩ ነው እኛም እሷን ቀምሰን እንሞታለን13 ከዚያም ኤልያስ እንዲህ አላት አይዞሽ ስጋት አይግባሽ ወደ ቤት ገብተሽ እንዳልሽው አድርጊ ብቻ በመጀመሪያ ከዚያችው ካለችሽ ላይ ትንሽ ቂጣ ጋግረሽ አምጪልኝ ከዚያ በኋላ ለአንቺና ለልጅሽ የሆነ ነገር ማዘጋጀት ትችያለሽ14 ምክንያቱም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል ይሖዋ በምድሪቱ ላይ ዝናብ እስከሚያዘንብበት ዕለት ድረስ ከማድጋው ዱቄት አይጠፋም ከማሰሮውም ዘይት አያልቅም15 ስለሆነም ሄዳ ኤልያስ እንዳላት አደረገች እሷም ሆነች እሱ እንዲሁም ቤተሰቧ ለብዙ ቀናት ሲመገቡ ቆዩ16 ይሖዋ በኤልያስ አማካኝነት በተናገረው ቃል መሠረት ከማድጋው ዱቄት አልጠፋም ከማሰሮውም ዘይት አላለቀም17 ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ የቤቱ ባለቤት ልጇ ታመመ ሕመሙም እጅግ ስለጠናበት እስትንፋሱ ቀጥ አለ18 በዚህ ጊዜ ሴትየዋ ኤልያስን የእውነተኛው አምላክ ሰው ሆይ ምን አደረግኩህ? የመጣኸው በደሌን ልታስታውሰኝና ልጄን ልትገድል ነው? አለችው19 እሱ ግን ልጅሽን ስጪኝ አላት ከዚያም ልጁን ከእቅፏ ወስዶ እሱ ወዳረፈበት በሰገነቱ ላይ ወዳለው ክፍል ይዞት ወጣ ልጁንም በራሱ አልጋ ላይ አስተኛው20 እሱም አምላኬ ይሖዋ ሆይ እኔን ያሳረፈችኝ የዚህች መበለት ልጅ እንዲሞት በማድረግ በእሷም ላይ መከራ ታመጣባታለህ? በማለት ወደ ይሖዋ ጮኸ21 ከዚያም ልጁ ላይ ሦስት ጊዜ ከተዘረጋበት በኋላ አምላኬ ይሖዋ ሆይ እባክህ የዚህ ልጅ ሕይወት ይመለስለት ብሎ ወደ ይሖዋ ጮኸ22 ይሖዋም የኤልያስን ልመና ሰማ የልጁም ሕይወት ተመለሰለት እሱም ሕያው ሆነ23 ከዚያም ኤልያስ ልጁን ይዞት ሰገነት ላይ ካለው ክፍል ወደ ቤት ከወረደ በኋላ ለእናቱ ሰጣት ኤልያስም ይኸው ልጅሽ ሕያው ሆኗል አላት24 በዚህ ጊዜ ሴትየዋ ኤልያስን አንተ በእርግጥ የአምላክ ሰው እንደሆንክ በአንደበትህም ያለው የይሖዋ ቃል እውነት እንደሆነ አሁን አወቅኩ አለችው
18 ከተወሰነ ጊዜ በኋላም በሦስተኛው ዓመት የይሖዋ ቃል ሂድና አክዓብ ፊት ቅረብ እኔም በምድሩ ላይ ዝናብ አዘንባለሁ ሲል ወደ ኤልያስ መጣ2 ስለሆነም ኤልያስ አክዓብ ፊት ለመቅረብ ሄደ በዚህ ወቅት ረሃቡ በሰማርያ ክፉኛ ጸንቶ ነበር3 በዚህ ጊዜ አክዓብ በቤቱ ላይ አዛዥ የነበረውን አብድዩን ጠራው አብድዩ ይሖዋን በጣም ይፈራ ነበር4 ኤልዛቤል የይሖዋን ነቢያት እያጠፋች በነበረበት ጊዜም አብድዩ 100 ነቢያትን ወስዶ 50ውን በአንድ ዋሻ 50ውን ደግሞ በሌላ ዋሻ ውስጥ ከደበቃቸው በኋላ ምግብና ውኃ ይሰጣቸው ነበር5 ከዚያም አክዓብ አብድዩን እንዲህ አለው በምድሪቱ ላይ ወደሚገኙት የውኃ ምንጮች ሁሉና ሸለቆዎች ሁሉ ሂድ እንስሶቻችን በሙሉ እንዳያልቁ ፈረሶቹንና በቅሎዎቹን በሕይወት ማቆየት የሚያስችል በቂ ሣር እናገኝ ይሆናል6 በመሆኑም አቋርጠውት የሚሄዱትን ምድር ተከፋፈሉ አክዓብ ለብቻው በአንድ በኩል አብድዩም ለብቻው በሌላ በኩል ሄደ7 አብድዩ እየተጓዘ ሳለ ኤልያስን መንገዱ ላይ አገኘው እሱም ወዲያውኑ ስላወቀው በግንባሩ ተደፋ ከዚያም ጌታዬ ኤልያስ ሆይ በእርግጥ አንተ ነህ? አለው8 ኤልያስም አዎ እኔ ነኝ ሄደህ ለጌታህ ኤልያስ እዚህ አለ ብለህ ንገረው አለው9 እሱ ግን እንዲህ አለው እኔ አገልጋይህ እንድሞት ለአክዓብ አሳልፈህ የምትሰጠኝ ምን ኃጢአት ሠርቼ ነው?10 ሕያው በሆነው አምላክህ በይሖዋ እምላለሁ ጌታዬ አንተን ፍለጋ ሰው ያልላከበት አንድም ብሔር ሆነ መንግሥት የለም እነሱም እዚህ የለም ባሉት ጊዜ ያ መንግሥትም ሆነ ብሔር አንተን አለማግኘቱን በመሐላ እንዲያረጋግጥለት ያደርግ ነበር11 አንተ ደግሞ አሁን ሄደህ ለጌታህ ኤልያስ እዚህ አለ ብለህ ንገረው ትለኛለህ12 ከአንተ ተለይቼ ስሄድ የይሖዋ መንፈስ ወደማላውቀው ቦታ ይወስድሃል ለአክዓብ ብነግረውና ሳያገኝህ ቢቀር እንደሚገድለኝ የታወቀ ነው ነገር ግን እኔ አገልጋይህ ከወጣትነቴ ጀምሮ ይሖዋን ስፈራ ኖሬአለሁ13 ኤልዛቤል የይሖዋን ነቢያት በገደለች ጊዜ ከይሖዋ ነቢያት መካከል 100ዎቹን ወስጄ ሃምሳ ሃምሳ በማድረግ ዋሻ ውስጥ እንደደበቅኳቸው እንዲሁም ምግብና ውኃ እሰጣቸው እንደነበር ጌታዬ አልሰማም?14 አሁን ግን አንተ ሄደህ ለጌታህ ኤልያስ እዚህ አለ ብለህ ንገረው ትለኛለህ እሱም በእርግጠኝነት ይገድለኛል15 ሆኖም ኤልያስ በማገለግለው ሕያው በሆነው በሠራዊት ጌታ በይሖዋ እምላለሁ ዛሬ እሱ ፊት እቀርባለሁ አለ16 ስለዚህ አብድዩ ወደ አክዓብ ሄዶ ነገረው አክዓብም ኤልያስን ለማግኘት ሄደ17 አክዓብም ልክ ኤልያስን ሲያየው በእስራኤል ላይ ከፍተኛ ችግር የምትፈጥረው አንተ ነህ? አለው18 በዚህ ጊዜ ኤልያስ እንዲህ አለው የይሖዋን ትእዛዛት በመተውና ባአልን በመከተል በእስራኤል ላይ ችግር የምትፈጥሩት አንተና የአባትህ ቤት እንጂ እኔ አይደለሁም19 ይልቅስ አሁን እስራኤላውያንን በሙሉ ከኤልዛቤል ማዕድ ከሚበሉት 450 የባአል ነቢያትና 400 የማምለኪያ ግንድ ነቢያት ጋር በቀርሜሎስ ተራራ ላይ ሰብስብልኝ20 በመሆኑም አክዓብ ወደ እስራኤል ሰዎች ሁሉ መልእክት ላከ ነቢያቱንም በቀርሜሎስ ተራራ ላይ ሰበሰበ21 ከዚያም ኤልያስ ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ በሁለት ሐሳብ የምታነክሱት እስከ መቼ ነው? እውነተኛው አምላክ ይሖዋ ከሆነ እሱን ተከተሉ ባአል ከሆነ ደግሞ እሱን ተከተሉ! አላቸው ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል አልመለሰለትም22 ከዚያም ኤልያስ እንዲህ አላቸው ከይሖዋ ነቢያት መካከል የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ የባአል ነቢያት ግን 450 ናቸው23 እንግዲህ አሁን ሁለት ወይፈኖች ይስጡን እነሱም አንድ ወይፈን መርጠው በየብልቱ እየቆራረጡ በእንጨቱ ላይ ያድርጉት ሆኖም እሳት አያንድዱበት እኔ ደግሞ ሌላኛውን ወይፈን አዘጋጅቼ በእንጨቱ ላይ አደርገዋለሁ ሆኖም እሳት አላነድበትም24 ከዚያም እናንተ የአምላካችሁን ስም ትጠራላችሁ እኔም የይሖዋን ስም እጠራለሁ እሳት በመላክ መልስ የሚሰጠው አምላክ እሱ እውነተኛው አምላክ እንደሆነ ያሳያል በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ያልከው ነገር ጥሩ ነው አሉ25 ኤልያስም የባአል ነቢያትን እናንተ ብዙ ስለሆናችሁ በቅድሚያ አንድ ወይፈን መርጣችሁ አዘጋጁ ከዚያም የአምላካችሁን ስም ጥሩ ሆኖም እሳት አታንድዱበት አላቸው26 በመሆኑም የተሰጣቸውን ወይፈን ወስደው አዘጋጁ ከጠዋት አንስቶ እስከ እኩለ ቀን ድረስም ባአል ሆይ መልስልን! እያሉ የባአልን ስም ጠሩ ሆኖም ድምፅ የለም የሚመልስም አልነበረም በሠሩትም መሠዊያ ዙሪያ እያነከሱ ዞሩ27 እኩለ ቀን ገደማም ኤልያስ እንዲህ በማለት ያፌዝባቸው ጀመር ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ እንጂ! አምላክ እኮ ነው! ምናልባት በሐሳብ ተውጦ ይሆናል ወይም ሊጸዳዳ ሄዶ ይሆናል አሊያም ደግሞ ተኝቶ ሊሆን ስለሚችል የሚቀሰቅሰው ያስፈልገው ይሆናል!28 እነሱም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጮኹ እንደ ልማዳቸውም ደም በደም እስኪሆኑ ድረስ ሰውነታቸውን በጩቤና በጦር ይተለትሉ ነበር29 እኩለ ቀን አልፎ የእህል መባ እስከሚቀርብበትም ጊዜ ድረስ እንደ እብድ ሲያደርጋቸው ቆየ ሆኖም ምንም ድምፅ የለም የሚመልስም የለም ትኩረት የሰጠም አልነበረም30 በኋላም ኤልያስ ሕዝቡን ሁሉ ወደ እኔ ቅረቡ አላቸው ሕዝቡም ሁሉ ወደ እሱ ቀረቡ ከዚያም ፈርሶ የነበረውን የይሖዋን መሠዊያ ጠገነ31 በመቀጠልም ኤልያስ ስምህ እስራኤል ይባላል የሚል የይሖዋ ቃል በመጣለት በያዕቆብ ወንዶች ልጆች ነገዶች ቁጥር ልክ 12 ድንጋዮችን ወሰደ32 በድንጋዮቹም በይሖዋ ስም መሠዊያ ሠራ በመሠዊያውም ዙሪያ ሁለት የሲህ መስፈሪያ ዘር ሊያዘራ የሚችል ስፋት ያለው ቦይ ቆፈረ33 ከዚያም እንጨቶቹን ረበረበ ወይፈኑንም በየብልቱ ቆራርጦ በእንጨቶቹ ላይ አደረገ ቀጥሎም በአራት ጋኖች ውኃ ሞልታችሁ በሚቃጠለው መባና በእንጨቱ ላይ አፍስሱ አለ34 ከዚያም አሁንም ድገሙ አለ እነሱም ደገሙ ለሦስተኛ ጊዜ ድገሙ አላቸው እነሱም ለሦስተኛ ጊዜ ደገሙ35 ውኃውም መሠዊያውን ዙሪያውን አጥለቀለቀው ቦዩንም በውኃ ሞላው36 ነቢዩ ኤልያስም የምሽቱ የእህል መባ በሚቀርብበት ጊዜ ገደማ ወደ ፊት ቀረብ ብሎ እንዲህ አለ የአብርሃም የይስሐቅና የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ አንተ በእስራኤል ውስጥ አምላክ እንደሆንክ እኔም አገልጋይህ እንደሆንኩና እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረግኩት በአንተ ቃል እንደሆነ ዛሬ ይታወቅ37 ይሖዋ ሆይ መልስልኝ! እነዚህ ሰዎች አንተ ይሖዋ እውነተኛው አምላክ እንደሆንክና ልባቸውን ወደ አንተ እየመለስክ መሆንህን እንዲያውቁ መልስልኝ38 በዚህ ጊዜ የይሖዋ እሳት ወርዶ የሚቃጠለውን መባ እንጨቱን ድንጋዮቹንና አፈሩን በላ በቦዩ ውስጥ የነበረውንም ውኃ ላሰ39 ሕዝቡ ሁሉ ይህን ሲያዩ ወዲያውኑ በግንባራቸው ተደፉ ከዚያም እውነተኛው አምላክ ይሖዋ ነው! እውነተኛው አምላክ ይሖዋ ነው! አሉ40 በዚህ ጊዜ ኤልያስ የባአልን ነቢያት ያዟቸው! አንዳቸውም እንዳያመልጡ! አላቸው እነሱም ወዲያውኑ ያዟቸው ኤልያስም ወደ ቂሾን ጅረት ይዟቸው በመውረድ በዚያ አረዳቸው41 ኤልያስም አክዓብን የከባድ ዝናብ ድምፅ እያጉረመረመ ስለሆነ ሂድ ብላ ጠጣም አለው42 በመሆኑም አክዓብ ሊበላና ሊጠጣ ሲወጣ ኤልያስ ደግሞ ወደ ቀርሜሎስ አናት ወጣ ፊቱንም በጉልበቶቹ መካከል አድርጎ ወደ መሬት አቀረቀረ43 ከዚያም አገልጋዩን እባክህ ውጣና ወደ ባሕሩ አቅጣጫ ተመልከት አለው እሱም ወጥቶ ተመለከተና ኧረ ምንም የለም አለ ኤልያስም ሰባት ጊዜ ተመልሰህ ሂድ አለው44 በሰባተኛውም ጊዜ አገልጋዩ እነሆ! የሰው እጅ የምታክል ትንሽ ደመና ከባሕሩ እየወጣች ነው አለ ኤልያስም ሄደህ አክዓብን ሠረገላህን አዘጋጅ! ዝናቡ እንዳያግድህ ወደዚያ ውረድ! በለው አለው45 በዚህ ጊዜ ሰማዩ በደመና ጠቆረ ነፋስም ነፈሰ ከባድ ዝናብም ይጥል ጀመር አክዓብም እየጋለበ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ46 ሆኖም የይሖዋ እጅ በኤልያስ ላይ መጣ እሱም ልብሱን ጠቅልሎ መቀነቱ ውስጥ በመሸጎጥ ከአክዓብ ፊት ፊት እየሮጠ እስከ ኢይዝራኤል ድረስ ሄደ
19 ከዚያም አክዓብ ኤልያስ ያደረገውን ሁሉና ነቢያቱን በሙሉ እንዴት በሰይፍ እንደገደለ ለኤልዛቤል ነገራት2 በዚህ ጊዜ ኤልዛቤል ነገ በዚህ ሰዓት ከእነሱ እንደ አንዱ ሳላደርግህ ብቀር አማልክት እንዲህ ያድርጉብኝ ከዚህ የባሰም ያምጡብኝ! ብሎ ለኤልያስ እንዲነግረው መልእክተኛ ላከችበት3 በዚህ ጊዜ ኤልያስ ፈራ በመሆኑም ሕይወቱን ለማትረፍ ሸሸ በይሁዳ ወደምትገኘው ወደ ቤርሳቤህም መጣ አገልጋዩንም እዚያ ተወው4 ከዚያም በምድረ በዳው የአንድ ቀን መንገድ ከተጓዘ በኋላ ወደ አንድ የክትክታ ዛፍ ሲደርስ ሥሩ ተቀመጠ እንዲሞትም መለመን ጀመረ እንዲህም አለ አሁንስ በቅቶኛል! ይሖዋ ሆይ እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ሕይወቴን ውሰዳት5 ከዚያም በክትክታው ዛፍ ሥር ጋደም አለ እንቅልፍም ወሰደው ሆኖም ድንገት አንድ መልአክ ነካ አደረገውና ተነስና ብላ አለው6 እሱም ቀና ብሎ ሲመለከት ራስጌው አጠገብ በጋሉ ድንጋዮች ላይ የተቀመጠ ዳቦ እንዲሁም በውኃ መያዣ ዕቃ ውስጥ ያለ ውኃ አየ እሱም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተመልሶ ተኛ7 በኋላም የይሖዋ መልአክ ለሁለተኛ ጊዜ መጥቶ ነካ አደረገውና ሩቅ መንገድ ስለምትጓዝ ተነስና ብላ አለው8 ስለሆነም ተነስቶ በላ ጠጣም ከምግቡም ባገኘው ብርታት እስከ እውነተኛው አምላክ ተራራ እስከ ኮሬብ ድረስ ለ40 ቀንና ለ40 ሌሊት ተጓዘ9 እዚያም ሲደርስ ወደ አንድ ዋሻ ገብቶ አደረ በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቃል ወደ እሱ መጥቶ ኤልያስ እዚህ ምን ታደርጋለህ? አለው10 እሱም እንዲህ አለ እኔ ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ እጅግ ቀንቻለሁ ምክንያቱም የእስራኤል ሰዎች ቃል ኪዳንህን ትተዋል መሠዊያዎችህንም አፈራርሰዋል ነቢያትህን በሰይፍ ገድለዋል እንግዲህ የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ ይኸው አሁን ደግሞ የእኔንም ሕይወት ለማጥፋት እየፈለጉ ነው11 እሱ ግን ውጣና ተራራው ላይ ይሖዋ ፊት ቁም አለው በዚህ ጊዜ ይሖዋ እያለፈ ነበር ታላቅና ኃይለኛ ነፋስም በይሖዋ ፊት ተራሮቹን ሰነጣጠቀ ዓለቶቹንም ፈረካከሰ ይሖዋ ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም ከነፋሱ ቀጥሎ ደግሞ የምድር መናወጥ ተከሰተ ይሖዋ ግን በምድር መናወጡ ውስጥ አልነበረም12 ከምድር መናወጡ በኋላም እሳት መጣ ይሖዋ ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም ከእሳቱ በኋላ ደግሞ ዝግ ያለና ለስለስ ያለ ድምፅ ተሰማ13 ኤልያስ ይህን ድምፅ ሲሰማ ወዲያውኑ በለበሰው የነቢይ ልብስ ፊቱን ሸፈነ ወጥቶም ዋሻው ደጃፍ ላይ ቆመ ከዚያም አንድ ድምፅ ኤልያስ እዚህ ምን ታደርጋለህ? ሲል ጠየቀው14 እሱም እንዲህ አለ እኔ ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ እጅግ ቀንቻለሁ ምክንያቱም የእስራኤል ሰዎች ቃል ኪዳንህን ትተዋል መሠዊያዎችህንም አፈራርሰዋል ነቢያትህን በሰይፍ ገድለዋል እንግዲህ የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ ይኸው አሁን ደግሞ የእኔንም ሕይወት ለማጥፋት እየፈለጉ ነው15 ይሖዋም እንዲህ አለው ወደ ደማስቆ ምድረ በዳ ተመልሰህ ሂድ እዚያም ስትደርስ ሃዛኤልን በሶርያ ላይ ንጉሥ አድርገህ ቀባው16 እንዲሁም የኒምሺን የልጅ ልጅ ኢዩን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርገህ ቀባው የአቤልምሆላ ሰው የሆነውን የሻፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ደግሞ በአንተ ምትክ ነቢይ አድርገህ ቀባው17 ከሃዛኤል ሰይፍ ያመለጠውን ኢዩ ይገድለዋል ከኢዩ ሰይፍ ያመለጠውን ደግሞ ኤልሳዕ ይገድለዋል18 እኔም ለባአል ያልተንበረከኩና እሱን ያልሳሙ በእስራኤል ውስጥ የቀሩ 7,000 ሰዎች አሉኝ19 ኤልያስም ከዚያ ወጥቶ ሄደ የሻፋጥንም ልጅ ኤልሳዕን ከፊቱ 12 ጥማድ በሬዎች እያረሱ እሱም በ12ኛው ጥማድ በሬ እያረሰ አገኘው ኤልያስም ወደ እሱ በመሄድ የራሱን የነቢይ ልብስ አውልቆ ላዩ ላይ ጣል አደረገበት20 በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ በሬዎቹን እዚያው በመተው ኤልያስን ተከትሎ እየሮጠ እባክህ አባቴንና እናቴን ስሜ እንድመጣ ፍቀድልኝ ከዚያ በኋላ እከተልሃለሁ አለው እሱም ሂድ ተመለስ እኔ መቼ ከለከልኩህ? አለው21 በመሆኑም ተመለሰ ከዚያም አንድ ጥማድ በሬ ወስዶ መሥዋዕት አደረገ በእርሻ መሣሪያዎቹም የበሬዎቹን ሥጋ በመቀቀል ለሕዝቡ ሰጠ እነሱም በሉ ይህን ካደረገ በኋላም ተነስቶ ኤልያስን ተከተለው እሱንም ያገለግለው ጀመር
2 ዳዊት የሚሞትበት ቀን ሲቃረብ ልጁን ሰለሞንን እንዲህ ሲል አዘዘው2 እንግዲህ እኔ የምሞትበት ጊዜ ቀርቧል ስለሆነም በርታ ወንድ ሁን3 በሙሴ ሕግ ላይ በተጻፈው መሠረት በመንገዶቹ በመሄድ እንዲሁም ደንቦቹን ትእዛዛቱን ፍርዶቹንና ማሳሰቢያዎቹን በመጠበቅ ለአምላክህ ለይሖዋ ያለብህን ግዴታ ፈጽም ይህን ካደረግክ የምታከናውነው ሁሉ ይሳካልሃል በምትሄድበትም ሁሉ ይቃናልሃል4 ይሖዋም እንዲህ በማለት የገባልኝን ቃል ይፈጽማል ልጆችህ በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው በፊቴ በታማኝነት በመመላለስ መንገዳቸውን ከጠበቁ ከዘር ሐረግህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው አይታጣም5 የጽሩያ ልጅ ኢዮዓብ በእኔ ላይ ያደረገውን ነገር ይኸውም በሁለቱ የእስራኤል ሠራዊት አለቆች ማለትም በኔር ልጅ በአበኔርና በየቴር ልጅ በአሜሳይ ላይ ያደረገውን በሚገባ ታውቃለህ ይህ ሰው እነዚህን ሰዎች በመግደል ጦርነት ሳይኖር በሰላሙ ጊዜ ደም አፍስሷል እንዲሁም በወገቡ ላይ የታጠቀው ቀበቶና በእግሩ ላይ ያደረገው ጫማ በጦርነት ጊዜ በሚፈሰው ደም እንዲበከል አድርጓል6 እንግዲህ እንደ ጥበብህ አድርግ ሽበቱ በሰላም ወደ መቃብር እንዲወርድ አታድርግ7 ሆኖም ለቤርዜሊ ልጆች ታማኝ ፍቅር አሳያቸው እነሱም ከማዕድህ ከሚበሉ ሰዎች መካከል ይሁኑ ምክንያቱም ከወንድምህ ከአቢሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ እነሱም ከጎኔ ቆመው ነበር8 በተጨማሪም ከባሁሪም የመጣው ቢንያማዊው የጌራ ልጅ ሺምአይ አብሮህ አለ ወደ ማሃናይም በሄድኩበት ዕለት ከባድ እርግማን የረገመኝ እሱ ነው ሆኖም እኔን ለማግኘት ወደ ዮርዳኖስ በወረደ ጊዜ በሰይፍ አልገድልህም ብዬ በይሖዋ ማልኩለት9 አንተ ጥበበኛ ስለሆንክና በእሱ ላይ ምን ማድረግ እንዳለብህ ስለምታውቅ ሳትቀጣ አትተወው ሽበቱ በደም ወደ መቃብር እንዲወርድ አድርግ10 ከዚያም ዳዊት ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ በዳዊት ከተማም ተቀበረ11 ዳዊት በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ የገዛው ለ40 ዓመት ነበር በኬብሮን ለ7 ዓመት በኢየሩሳሌም ደግሞ ለ33 ዓመት ነገሠ12 ከዚያም ሰለሞን በአባቱ በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀመጠ ቀስ በቀስም ንግሥናው እየጸና ሄደ13 ከጊዜ በኋላም የሃጊት ልጅ አዶንያስ ወደ ሰለሞን እናት ወደ ቤርሳቤህ መጣ እሷም የመጣኸው በሰላም ነው? አለችው እሱም አዎ በሰላም ነው አላት14 ከዚያም አንድ የምነግርሽ ጉዳይ አለኝ አላት እሷም እሺ ንገረኝ አለችው15 እሱም እንዲህ አላት ንግሥናው የእኔ ሊሆን እንደነበረና እስራኤልም ሁሉ ይነግሣል ብለው ይጠብቁ እንደነበር በሚገባ ታውቂያለሽ ይሁንና ንግሥናው የእኔ መሆኑ ቀርቶ የወንድሜ ሆነ ምክንያቱም ይሖዋ ንግሥናው የእሱ እንዲሆን ወስኖ ነበር16 ሆኖም አሁን አንድ የምጠይቅሽ ነገር አለ መቼም አታሳፍሪኝም እሷም እሺ ንገረኝ አለችው17 እሱም እባክሽ ንጉሥ ሰለሞን የጠየቅሽውን እንቢ ስለማይልሽ ሹነማዊቷን አቢሻግን እንዲድርልኝ ጠይቂው አላት18 በዚህ ጊዜ ቤርሳቤህ መልካም! ንጉሡን አነጋግርልሃለሁ አለችው19 በመሆኑም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጉዳይ ልትነግረው ወደ ንጉሥ ሰለሞን ገባች ንጉሡም ወዲያውኑ ሊቀበላት ተነሳ ሰገደላትም ከዚያም ዙፋኑ ላይ ተቀመጠ የንጉሡም እናት በቀኙ እንድትቀመጥ ዙፋን አስመጣላት20 እሷም አንዲት ትንሽ ነገር ልጠይቅህ አስቤ ነበር መቼም እንቢ አትለኝም አለችው ንጉሡም እናቴ ሆይ ንገሪኝ የጠየቅሽኝን እንቢ አልልሽም አላት21 እሷም ሹነማዊቷ አቢሻግ ለወንድምህ ለአዶንያስ ትዳርለት አለችው22 በዚህ ጊዜ ንጉሥ ሰለሞን ለእናቱ እንዲህ ሲል መለሰላት ለአዶንያስ ሹነማዊቷን አቢሻግን ብቻ ለምን ትጠይቂለታለሽ? ታላቅ ወንድሜ ስለሆነ ንግሥናም ጠይቂለት እንጂ ካህኑ አብያታርና የጽሩያ ልጅ ኢዮዓብም እየደገፉት ነው23 ከዚያም ንጉሥ ሰለሞን እንዲህ ሲል በይሖዋ ማለ አዶንያስ ይህን በመጠየቁ ሕይወቱን ሳያጣ ቢቀር አምላክ ይህን ያድርግብኝ ከዚህ የከፋም ነገር ያምጣብኝ24 አሁንም በሚገባ ባጸናኝ በአባቴ በዳዊት ዙፋን ላይ ባስቀመጠኝና በገባው ቃል መሠረት ቤት በሠራልኝ ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ አዶንያስ በዛሬዋ ዕለት ይገደላል25 ንጉሥ ሰለሞንም ወዲያውኑ የዮዳሄን ልጅ በናያህን ላከው እሱም ወጥቶ አዶንያስን መታው እሱም ሞተ26 ንጉሡም ካህኑን አብያታርን እንዲህ አለው በአናቶት ወደሚገኘው እርሻህ ሂድ! አንተ ሞት የሚገባህ ሰው ነህ ሆኖም በአባቴ በዳዊት ፊት የሉዓላዊውን ጌታ የይሖዋን ታቦት ስለተሸከምክና በአባቴ ላይ የደረሰውን መከራ ሁሉ ስለተጋራህ ዛሬ አልገድልህም27 በመሆኑም ይሖዋ በሴሎ በኤሊ ቤት ላይ እንደሚደርስ የተናገረው ነገር ይፈጸም ዘንድ ሰለሞን አብያታርን የይሖዋ ካህን ሆኖ እንዳያገለግል አባረረው28 ኢዮዓብ ቀደም ሲል ከአቢሴሎምጋር ወግኖ ያልነበረ ቢሆንም አዶንያስን ደግፎ ስለነበር ይህን ወሬ ሲሰማ ወደ ይሖዋ ድንኳን በመሸሽ የመሠዊያውን ቀንዶች ያዘ29 ከዚያም ንጉሥ ሰለሞን ኢዮዓብ ወደ ይሖዋ ድንኳን ሸሽቶ እዚያ በመሠዊያው አጠገብ ይገኛል ተብሎ ተነገረው በመሆኑም ሰለሞን የዮዳሄን ልጅ በናያህን ሂድና ግደለው! ብሎ ላከው30 ስለዚህ በናያህ ወደ ይሖዋ ድንኳን ሄዶ ኢዮዓብን ንጉሡ ና ውጣ! ብሎሃል አለው እሱ ግን እዚሁ እሞታታለሁ እንጂ በፍጹም አልወጣም! አለ በዚህ ጊዜ በናያህ ኢዮዓብ እንዲህ እንዲህ ብሏል እንዲህም ሲል መልሶልኛል በማለት ለንጉሡ ተናገረ31 ከዚያም ንጉሡ እንዲህ አለው በል ልክ እንዳለው አድርግ ግደለውና ቅበረው ኢዮዓብ አላግባብ ካፈሰሰውም ደም እኔንና የአባቴን ቤት አንጻ32 ኢዮዓብ አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ከእሱ ይልቅ ጻድቅና የተሻሉ የነበሩትን ሁለት ሰዎች ማለትም የእስራኤል ሠራዊት አለቃ የነበረውን የኔርን ልጅ አበኔርንና የይሁዳ ሠራዊት አለቃ የነበረውን የየቴርን ልጅ አሜሳይን በሰይፍ መትቶ በመግደሉ ይሖዋ ደሙን በራሱ ላይ ይመልስበታል33 ደማቸውም ለዘላለም በኢዮዓብ ራስና በዘሮቹ ራስ ላይ ይሆናል በዳዊት በዘሮቹ በቤቱና በዙፋኑ ላይ ግን የይሖዋ ሰላም ለዘላለም ይሁን34 ከዚያም የዮዳሄ ልጅ በናያህ ወጥቶ ኢዮዓብን መትቶ ገደለው እሱም በምድረ በዳ በሚገኘው በራሱ ቤት ተቀበረ35 ከዚያም ንጉሡ በኢዮዓብ ምትክ የዮዳሄን ልጅ በናያህን በሠራዊቱ ላይ ሾመው በአብያታር ቦታ ደግሞ ካህኑን ሳዶቅን ሾመው36 ንጉሡም ሺምአይን አስጠርቶ እንዲህ አለው ኢየሩሳሌም ውስጥ ቤት ሠርተህ በዚያ ኑር ከዚያም ወጥተህ ወደ ሌላ ቦታ አትሂድ37 ከዚያ ወጥተህ የቄድሮንን ሸለቆ የተሻገርክ ቀን ግን እንደምትሞት እወቅ ደምህ በራስህ ላይ ይሆናል38 ሺምአይም ንጉሡን ጥሩ ሐሳብ ነው አገልጋይህ ጌታዬ ንጉሡ እንዳለው ያደርጋል አለው ስለሆነም ሺምአይ በኢየሩሳሌም ለብዙ ጊዜ ተቀመጠ39 ሆኖም ከሦስት ዓመት በኋላ ከሺምአይ ባሪያዎች መካከል ሁለቱ የጌት ንጉሥ ወደሆነው ወደ ማአካ ልጅ ወደ አንኩስ ኮበለሉ ሺምአይም ባሪያዎችህ ያሉት ጌት ነው ተብሎ ሲነገረው40 ወዲያውኑ አህያውን ጭኖ ባሪያዎቹን ለመፈለግ በጌት ወዳለው ወደ አንኩስ አቀና ሺምአይ ባሪያዎቹን ይዞ ከጌት ሲመለስ41 ለሰለሞን ሺምአይ ከኢየሩሳሌም ወጥቶ ወደ ጌት ሄዶ ነበር አሁን ግን ተመልሷል ተብሎ ተነገረው42 በዚህ ጊዜ ንጉሡ ሺምአይን አስጠርቶ እንዲህ አለው ከዚህ ወጥተህ ወደ ሌላ ቦታ በሄድክ ቀን እንደምትሞት እወቅ ብዬ በይሖዋ አስምዬህና አስጠንቅቄህ አልነበረም? አንተስ ብትሆን ጥሩ ሐሳብ ነው እንዳልከኝ አደርጋለሁ ብለኸኝ አልነበረም?43 ታዲያ በይሖዋ ፊት የገባኸውን መሐላና የሰጠሁህን ትእዛዝ ያልጠበቅከው ለምንድን ነው?44 ከዚያም ንጉሡ ሺምአይን እንዲህ አለው በአባቴ በዳዊት ላይ ያደረግከውን ክፉ ነገር ሁሉ ልብህ ያውቀዋል ይሖዋም ያደረግከውን ክፉ ነገር በራስህ ላይ ይመልስብሃል45 ንጉሥ ሰለሞን ግን ይባረካል የዳዊትም ዙፋን በይሖዋ ፊት ለዘላለም ይጸናል46 ከዚያም ንጉሡ የዮዳሄን ልጅ በናያህን አዘዘው እሱም ወጥቶ ሺምአይን መትቶ ገደለውበዚህ መንገድ መንግሥቱ በሰለሞን እጅ ጸና
20 በዚህ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ ቤንሃዳድ ጦር ሠራዊቱን በሙሉ አሰባሰበ በተጨማሪም ሌሎች 32 ነገሥታትን ከነፈረሶቻቸውና ከነሠረገሎቻቸው አሰባሰበ ወጥቶም ሰማርያን በመክበብ ውጊያ ከፈተባት2 ከዚያም በከተማዋ ውስጥ ወደሚገኘው ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ መልእክተኞች ልኮ እንዲህ አለው ቤንሃዳድ እንዲህ ይላል3 ብርህና ወርቅህ እንዲሁም ከሚስቶችህና ከልጆችህ መካከል ምርጥ የሆኑት የእኔ ናቸው4 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ አንተ እንዳልከው እኔም ሆንኩ የእኔ የሆነው ሁሉ የአንተ ነን ሲል መለሰለት5 በኋላም መልእክተኞቹ ተመልሰው በመምጣት እንዲህ አሉት ቤንሃዳድ እንዲህ ይላል እንዲህ የሚል መልእክት ልኬብህ ነበር ብርህን ወርቅህን ሚስቶችህንና ልጆችህን ትሰጠኛለህ6 ሆኖም ነገ በዚህ ሰዓት ገደማ አገልጋዮቼን ወደ አንተ እልካለሁ እነሱም የአንተን ቤትና የአገልጋዮችህን ቤት አንድ በአንድ ይበረብራሉ ለአንተ ትልቅ ዋጋ ያለውን ነገር ሁሉ እጃቸው በማስገባት ይወስዳሉ7 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ በምድሪቱ ያሉትን ሽማግሌዎች በሙሉ ጠርቶ እንግዲህ ይህ ሰው በእኛ ላይ መከራ ለማምጣት ቆርጦ እንደተነሳ ልብ በሉ ሚስቶቼን ልጆቼን ብሬንና ወርቄን እንድሰጠው ላከብኝ እኔም አልከለከልኩትም አላቸው8 ከዚያም ሽማግሌዎቹ ሁሉና ሕዝቡ በሙሉ እሺ አትበለው በዚህ አትስማማ አሉት9 በመሆኑም የቤንሃዳድን መልእክተኞች ጌታዬ ንጉሡን እንዲህ በሉት እኔ አገልጋይህ መጀመሪያ ላይ የጠየቅከኝን ነገር ሁሉ እፈጽማለሁ ይህን ግን መፈጸም አልችልም አላቸው መልእክተኞቹም ይህን መልእክት ይዘው ወደ እሱ ሄዱ10 ቤንሃዳድም የሰማርያ አፈር ለሚከተለኝ ሕዝብ ሁሉ አንድ አንድ እፍኝ እንኳ ቢደርሰው አማልክት እንዲህ ያድርጉብኝ ከዚህ የከፋም ያምጡብኝ! የሚል መልእክት ላከበት11 የእስራኤልም ንጉሥ መልሶ ቤንሃዳድን እንዲህ በሉት ለጦርነት እየታጠቀ ያለ ሰው ጦርነቱን ድል አድርጎ ትጥቁን እንደሚፈታ ሰው መደንፋት የለበትም አለ12 ቤንሃዳድና ነገሥታቱ በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው እየጠጡ ሳለ ቤንሃዳድ ይህን ምላሽ ሲሰማ አገልጋዮቹን ጥቃት ለመሰንዘር ተዘጋጁ! አላቸው በመሆኑም በከተማዋ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ተዘጋጁ13 ሆኖም አንድ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ ቀርቦ ይሖዋ እንዲህ ይላል ይህን እጅግ ብዙ ሕዝብ ትመለከታለህ? እኔ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ አንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃለህ አለው14 አክዓብም በማን አማካኝነት? ሲል ጠየቀ እሱም መልሶ ይሖዋ እንዲህ ይላል በአውራጃዎቹ መኳንንት አገልጋዮች አማካኝነት አለው ስለሆነም አክዓብ ታዲያ ውጊያውን የሚያስጀምረው ማን ነው? አለ እሱም አንተ ነህ! አለው15 ከዚያም አክዓብ የአውራጃዎቹን መኳንንት አገልጋዮች ቆጠረ እነሱም 232 ነበሩ በመቀጠልም የእስራኤልን ወንዶች በሙሉ ቆጠረ እነሱም 7,000 ነበሩ16 እነሱም እኩለ ቀን ላይ ቤንሃዳድ ረዳቶቹ ከሆኑት 32 ነገሥታት ጋር በድንኳኖቹ ውስጥ ሆኖ ሰክሮ ሳለ ወደዚያ ሄዱ17 የአውራጃዎቹ መኳንንት አገልጋዮች ቀድመው በወጡ ጊዜ ቤንሃዳድ ወዲያውኑ መልእክተኞችን ላከ እነሱም ከሰማርያ የመጡ ሰዎች አሉ ብለው ነገሩት18 በዚህ ጊዜ ቤንሃዳድ ሰዎቹ የመጡት ለሰላም ከሆነ በሕይወት እንዳሉ ያዟቸው የመጡት ለጦርነት ከሆነም በሕይወት እንዳሉ ያዟቸው አለ19 ሆኖም እነዚህ ማለትም የአውራጃዎቹ መኳንንት አገልጋዮችና እነሱን ይከተላቸው የነበረው ሠራዊት ከከተማዋ ሲወጡ20 እያንዳንዳቸው ሊገጥማቸው የመጣውን ሰው ገደሉ ከዚያም ሶርያውያን ሸሹ እስራኤላውያንም አሳደዷቸው የሶርያ ንጉሥ ቤንሃዳድ ግን በፈረስ ላይ ሆኖ ከተወሰኑ ፈረሰኞች ጋር አመለጠ21 ሆኖም የእስራኤል ንጉሥ ወጥቶ ፈረሶቹንና ሠረገሎቹን መታ በሶርያውያንም ላይ ታላቅ ድል ተቀዳጀ22 በኋላም ነቢዩ ወደ እስራኤል ንጉሥ ቀርቦ የሶርያ ንጉሥ በሚቀጥለው ዓመት መባቻ ላይ ስለሚመጣብህ ሄደህ ራስህን አጠናክር ምን ማድረግ እንደምትችልም አስብ አለው23 በዚህ ጊዜ የሶርያን ንጉሥ አገልጋዮቹ እንዲህ አሉት አምላካቸው የተራሮች አምላክ ነው በእኛ ላይ ያየሉብንም ለዚህ ነው ሆኖም ሜዳ ላይ ብንገጥማቸው እናሸንፋቸዋለን24 በተጨማሪም እንዲህ አድርግ ነገሥታቱን በሙሉ ከቦታቸው አንስተህ በምትካቸው አስተዳዳሪዎች አስቀምጥ25 ከዚያም ከተደመሰሰብህ ሠራዊት ጋር የሚመጣጠን ሠራዊት ሰብስብ በፈረሱ ፋንታ ፈረስ በሠረገላውም ፋንታ ሠረገላ ተካ ከዚያም ሜዳ ላይ እንግጠማቸው ያለምንም ጥርጥር እናሸንፋቸዋለን ንጉሡም የሰጡትን ምክር ሰማ እንዳሉትም አደረገ26 በዓመቱ መባቻ ላይም ቤንሃዳድ ሶርያውያንን አሰባስቦ ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ወደ አፌቅ ወጣ27 የእስራኤል ሰዎችም ከተሰባሰቡና ስንቅ ከተሰጣቸው በኋላ እነሱን ለመግጠም ወጡ የእስራኤል ሰዎች ፊት ለፊታቸው ሰፍረው ሲታዩ ሁለት ትናንሽ የፍየል መንጋ ይመስሉ ነበር ሶርያውያኑ ግን መላውን ምድር አጥለቅልቀውት ነበር28 ከዚያም የእውነተኛው አምላክ ሰው ወደ እስራኤል ንጉሥ ቀርቦ ይሖዋ እንዲህ ይላል ሶርያውያን ይሖዋ የተራሮች አምላክ እንጂ የሜዳ አምላክ አይደለም ስላሉ ይህን እጅግ ብዙ ሕዝብ በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ እናንተም እኔ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ታውቃላችሁ አለው29 እነሱም ለሰባት ቀን ያህል እንደተፋጠጡ ቆዩ በሰባተኛውም ቀን ውጊያው ተጀመረ የእስራኤል ሰዎችም በአንድ ቀን 100,000 ሶርያውያን እግረኛ ወታደሮችን ገደሉ30 የተረፉትም ወደ ከተማዋ ወደ አፌቅ ሸሹ ሆኖም ከተረፉት ሰዎች መካከል በ27,000ዎቹ ላይ ቅጥሩ ተንዶ ወደቀባቸው ቤንሃዳድም ሸሽቶ ወደ ከተማዋ ገባ አንድ ክፍል ውስጥ ገብቶም ተሸሸገ31 በመሆኑም አገልጋዮቹ እንዲህ አሉት የእስራኤል ቤት ነገሥታት መሐሪዎች እንደሆኑ ሰምተናል እንግዲህ ወገባችንን በማቅ ታጥቀንና ራሳችን ላይ ገመድ አስረን ወደ እስራኤል ንጉሥ እንውጣ ምናልባት ሕይወትህን ያተርፍልህ ይሆናል32 ስለሆነም ወገባቸውን በማቅ ታጥቀውና ራሳቸው ላይ ገመድ አስረው ወደ እስራኤል ንጉሥ በመምጣት አገልጋይህ ቤንሃዳድ እባክህ ሕይወቴን አታጥፋ ይላል አሉት ንጉሡም እስካሁን በሕይወት አለ? ወንድሜ እኮ ነው አለ33 ሰዎቹ ይህን እንደ ጥሩ ገድ በመመልከትና ንጉሡ የተናገረውን በማመን አዎ ቤንሃዳድ እኮ ወንድምህ ነው አሉ ንጉሡም በሉ ሄዳችሁ አምጡት አለ ከዚያም ቤንሃዳድ ወደ እሱ መጣ እሱም ወዲያውኑ ሠረገላው ላይ እንዲወጣ አደረገው34 ቤንሃዳድም አባቴ ከአባትህ ላይ የወሰዳቸውን ከተሞች እመልሳለሁ አባቴ በሰማርያ እንዳደረገው ሁሉ አንተም በደማስቆ ለራስህ ገበያ ማቋቋም ትችላለህ አለውአክዓብም በዚህ ስምምነት መሠረት አሰናብትሃለሁ አለውበዚህም መሠረት ከእሱ ጋር ስምምነት አድርጎ አሰናበተው35 ከነቢያት ልጆች አንዱ በይሖዋ ቃል ታዞ ጓደኛውን እባክህ ምታኝ አለው ሰውየው ግን ሊመታው ፈቃደኛ አልሆነም36 ስለዚህ የይሖዋን ቃል ስላልሰማህ ከእኔ ተለይተህ እንደሄድክ አንበሳ አግኝቶ ይገድልሃል አለው ከእሱ ተለይቶም ሲሄድ አንበሳ አግኝቶ ገደለው37 ከዚያም ሌላ ሰው አግኝቶ እባክህ ምታኝ አለው በመሆኑም ሰውየው መትቶ አቆሰለው38 ከዚያም ይህ ነቢይ ሄዶ ንጉሡን መንገድ ዳር ቆሞ ጠበቀው ማንነቱም እንዳይታወቅ ዓይኖቹን በመጠምጠሚያ ሸፍኖ ነበር39 ንጉሡም በዚያ ሲያልፍ ነቢዩ ጮክ ብሎ ንጉሡን በመጣራት እንዲህ አለ እኔ አገልጋይህ ወደተፋፋመው ጦርነት ገብቼ ነበር በዚህ ጊዜ አንድ ሰው ከዚያ ወጥቶ የሆነ ሰው ወደ እኔ ይዞ መጣ እንዲህም አለኝ ይህን ሰው ጠብቀው ይህ ሰው ቢጠፋ በእሱ ሕይወት ፋንታ የአንተ ሕይወት ይተካል ወይም ደግሞ አንድ ታላንት ብር ትከፍላለህ40 ታዲያ እኔ አገልጋይህ ሥራ በዝቶብኝ ወዲያ ወዲህ ስል ሰውየው ድንገት አምልጦ ሄደ የእስራኤልም ንጉሥ እንግዲህ በራስህ ላይ ፈርደሃል አንተው ራስህ ውሳኔውን አስተላልፈሃል አለው41 ከዚያም ፈጠን ብሎ መጠምጠሚያውን ከዓይኖቹ ላይ አነሳ የእስራኤልም ንጉሥ ይህ ሰው ከነቢያት አንዱ መሆኑን አወቀ42 ነቢዩም ይሖዋ እንዲህ ይላል እኔ መጥፋት አለበት ያልኩት ሰው ከእጅህ እንዲያመልጥ ስላደረግክ በእሱ ሕይወት ፋንታ የአንተ ሕይወት ይተካል በእሱም ሕዝብ ፋንታ የአንተ ሕዝብ ይተካል አለው43 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ፊቱ ጠቁሮና አዝኖ ወደ ቤቱ ወደ ሰማርያ ሄደ
21 እነዚህ ነገሮች ከተከናወኑ በኋላ ከኢይዝራኤላዊው ከናቡቴ የወይን እርሻ ጋር በተያያዘ አንድ ሁኔታ ተከሰተ የወይን እርሻው የሚገኘው በኢይዝራኤል ውስጥ ከሰማርያው ንጉሥ ከአክዓብ ቤተ መንግሥት አጠገብ ነበር2 አክዓብ ናቡቴን እንዲህ አለው የወይን እርሻህ ከቤቴ አጠገብ ስለሚገኝ የአትክልት ቦታ እንዳደርገው ስጠኝ እኔም በምትኩ ከዚህ የተሻለ የወይን እርሻ እሰጥሃለሁ ከፈለግክ ደግሞ የቦታውን ዋጋ እሰጥሃለሁ3 ናቡቴ ግን አክዓብን የአባቶቼን ርስት ለአንተ መስጠት በይሖዋ ፊት ተገቢ ስላልሆነ ፈጽሞ የማላስበው ነገር ነው አለው4 በመሆኑም አክዓብ ኢይዝራኤላዊው ናቡቴ የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም ስላለው ፊቱ ጠቁሮና አዝኖ ወደ ቤቱ ገባ ከዚያም ፊቱን ወደ ግድግዳ አዙሮ ተኛ ምግብ ለመብላትም ፈቃደኛ አልሆነም5 ሚስቱ ኤልዛቤልም ወደ እሱ ገብታ ምግብ አልበላ እስኪልህ ድረስ እንዲህ ያዘንከው ለምንድን ነው? አለችው6 እሱም እንዲህ አላት ኢይዝራኤላዊውን ናቡቴን የወይን እርሻህን በገንዘብ ሽጥልኝ ከፈለግክ ደግሞ በምትኩ ሌላ የወይን እርሻ ልስጥህ ብዬው ነበር እሱ ግን የወይን እርሻዬን አልሰጥህም አለኝ7 ሚስቱ ኤልዛቤልም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆነህ የምትገዛው አንተ አይደለህም? በል ተነስና እህል ቅመስ ልብህም ደስ ይበለው የኢይዝራኤላዊውን የናቡቴን የወይን እርሻ እኔ እሰጥሃለሁ አለችው8 ስለሆነም በአክዓብ ስም ደብዳቤዎች ጽፋ በእሱ ማኅተም አተመቻቸው ደብዳቤዎቹንም ናቡቴ በሚኖርበት ከተማ ወደሚገኙት ሽማግሌዎችና ታላላቅ ሰዎች ላከቻቸው9 በደብዳቤዎቹም ላይ እንዲህ ስትል ጻፈች ጾም አውጁ ናቡቴንም በሕዝቡ ፊት በክብር ቦታ ላይ አስቀምጡት10 ሁለት የማይረቡ ሰዎችንም አምጥታችሁ ከፊት ለፊቱ አስቀምጡና አምላክንና ንጉሡን ተራግመሃል! በማለት እንዲመሠክሩበት አድርጉ ከዚያም አውጥታችሁ በድንጋይ በመውገር ግደሉት11 በመሆኑም የከተማዋ ሰዎች ማለትም እሱ በሚኖርበት ከተማ ያሉት ሽማግሌዎችና ታላላቅ ሰዎች ኤልዛቤል በላከችላቸው ደብዳቤዎች ላይ በተጻፈው መሠረት አደረጉ12 እነሱም ጾም አወጁ ናቡቴም በሕዝቡ ፊት በክብር ቦታ ላይ እንዲቀመጥ አደረጉ13 ከዚያም ሁለት የማይረቡ ሰዎች መጥተው ፊት ለፊቱ ተቀመጡ እነሱም በሕዝቡ ፊት ናቡቴ አምላክንና ንጉሡን ተራግሟል! እያሉ በናቡቴ ላይ ይመሠክሩበት ጀመር ከዚያም ወደ ከተማዋ ዳርቻ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት14 እነሱም ናቡቴ በድንጋይ ተወግሮ ሞቷል በማለት ወደ ኤልዛቤል መልእክት ላኩባት15 ኤልዛቤልም ናቡቴ በድንጋይ ተወግሮ መሞቱን እንደሰማች አክዓብን ኢይዝራኤላዊው ናቡቴ በገንዘብ ሊሸጥልህ ያልፈለገውን የወይን እርሻውን ተነስና ውረስ ምክንያቱም ናቡቴ በሕይወት የለም ሞቷል አለችው16 አክዓብም ናቡቴ መሞቱን እንደሰማ ተነስቶ የኢይዝራኤላዊውን የናቡቴን የወይን እርሻ ለመውረስ ወደዚያ ወረደ17 ሆኖም የይሖዋ ቃል ወደ ቲሽባዊው ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ18 በሰማርያ የሚገኘውን የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን ለማግኘት ተነስተህ ወደዚያ ውረድ እሱም የናቡቴን የወይን እርሻ ለመውረስ ሄዶ እዚያ ይገኛል19 እንዲህም በለው ይሖዋ እንዲህ ይላል ሰው ገድለህ ንብረቱን ወሰድክ አይደል? ከዚያም እንዲህ በለው ይሖዋ እንዲህ ይላል ውሾች የናቡቴን ደም በላሱበት ቦታ የአንተንም ደም ይልሱታል20 አክዓብም ኤልያስን ጠላቴ ሆይ አገኘኸኝ? አለው እሱም እንዲህ አለው አዎ አግኝቼሃለሁ እንግዲህ አንተ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ቆርጠህ ስለተነሳህ21 ጥፋት አመጣብሃለሁ እየተከታተልኩም ሙልጭ አድርጌ እጠርግሃለሁ እንዲሁም በእስራኤል ውስጥ የሚገኘውን ምስኪኑንና ደካማውን ጨምሮ የአክዓብ የሆነውን ወንድ ሁሉ አጠፋለሁ22 ቁጣዬን ስላነሳሳህና እስራኤላውያን ኃጢአት እንዲፈጽሙ ስላደረግክ ቤትህን እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮርብዓም ቤትና እንደ አኪያህ ልጅ እንደ ባኦስ ቤት አደርገዋለሁ23 ኤልዛቤልን በተመለከተም ይሖዋ እንዲህ ብሏል ውሾች በኢይዝራኤል በሚገኘው ቁራሽ መሬት ላይ ኤልዛቤልን ይበሏታል24 ከአክዓብ ወገን የሆነውን በከተማ ውስጥ የሚሞተውን ውሾች ይበሉታል በሜዳ ላይ የሚሞተውን ደግሞ የሰማይ አሞሮች ይበሉታል25 በእርግጥም በሚስቱ በኤልዛቤል ተነድቶ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ቆርጦ የተነሳ እንደ አክዓብ ያለ አንድም ሰው የለም26 ይሖዋ ከእስራኤላውያን ፊት ያሳደዳቸው አሞራውያን እንዳደረጉት ሁሉ እሱም አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶችን በመከተል እጅግ አስነዋሪ ነገር አደረገ27 አክዓብም ይህን እንደሰማ ልብሱን ቀደደ ማቅም ለበሰ ጾመ እንዲሁም ማቅ ላይ ይተኛና በሐዘን ተኮራምቶ ይሄድ ነበር28 ከዚያም የይሖዋ ቃል ወደ ቲሽባዊው ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ29 አክዓብ ስለ እሱ በተናገርኩት ነገር የተነሳ ራሱን እንዴት እንዳዋረደ ተመለከትክ? ራሱን በፊቴ ስላዋረደ ላመጣበት የነበረውን ጥፋት በእሱ ዘመን አላመጣም ከዚህ ይልቅ በእሱ ቤት ላይ ጥፋት የማመጣው በልጁ ዘመን ነው
22 በሶርያና በእስራኤል መካከል ለሦስት ዓመት ጦርነት አልነበረም2 በሦስተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወረደ3 የእስራኤልም ንጉሥ አገልጋዮቹን ራሞትጊልያድ የእኛ እንደሆነች ታውቃላችሁ አይደል? ሆኖም እሷን ከሶርያ ንጉሥ እጅ ለማስመለስ እያመነታን ነው አላቸው4 ከዚያም ኢዮሳፍጥን በራሞትጊልያድ ለመዋጋት ከእኔ ጋር አብረህ ትሄዳለህ? አለው በዚህ ጊዜ ኢዮሳፍጥ ለእስራኤል ንጉሥ እኔ ማለት እኮ አንተ ማለት ነህ ሕዝቤ ሕዝብህ ነው የእኔ ፈረሶችም የአንተ ፈረሶች ናቸው በማለት መለሰለት5 ሆኖም ኢዮሳፍጥ የእስራኤልን ንጉሥ እባክህ በመጀመሪያ ይሖዋ ምን እንደሚል ጠይቅ አለው6 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ 400 ገደማ የሚሆኑ ነቢያትን አንድ ላይ ሰብስቦ ራሞትጊልያድን ለመውጋት ልዝመት ወይስ ይቅርብኝ? አላቸው እነሱም ዝመት ይሖዋ በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል አሉት7 ከዚያም ኢዮሳፍጥ በዚህ ቦታ የይሖዋ ነቢይ የለም? ካለ በእሱም አማካኝነት እንጠይቅ አለ8 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮሳፍጥን በእሱ አማካኝነት ይሖዋን ልንጠይቅ የምንችልበት አንድ ሰው ይቀራል ሆኖም ስለ እኔ መጥፎ ነገር ብቻ እንጂ መልካም ነገር ፈጽሞ ስለማይተነብይ በጣም እጠላዋለሁ እሱም የይምላ ልጅ ሚካያህ ነው አለው ኢዮሳፍጥ ግን ንጉሡ እንዲህ ሊል አይገባም አለ9 ስለሆነም የእስራኤል ንጉሥ አንድ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣን ጠርቶ የይምላን ልጅ ሚካያህን በአስቸኳይ ይዘኸው ና አለው10 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ የንግሥና ልብሳቸውን ለብሰው በሰማርያ መግቢያ በር ላይ በሚገኘው አውድማ ላይ በየዙፋናቸው ተቀምጠው ነበር ነቢያቱም ሁሉ በፊታቸው ትንቢት ይናገሩ ነበር11 ከዚያም የኬናአና ልጅ ሴዴቅያስ የብረት ቀንዶች ሠርቶ ይሖዋ እንዲህ ይላል ሶርያውያንን እስክታጠፋቸው ድረስ በእነዚህ ትወጋቸዋለህ አለ12 ሌሎቹ ነቢያትም ሁሉ ወደ ራሞትጊልያድ ውጣ ይሳካልሃል ይሖዋም እሷን በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል በማለት ተመሳሳይ ትንቢት ይናገሩ ነበር13 ሚካያህን ለመጥራት የሄደው መልእክተኛም እነሆ ነቢያቱ ሁሉ በአንድ ድምፅ ለንጉሡ የተናገሩት ነገር ጥሩ ነው እባክህ የአንተም ቃል እንደ እነሱ ይሁን አንተም ጥሩ ነገር ተናገር አለው14 ሚካያህ ግን ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ የምናገረው ይሖዋ የሚለኝን ብቻ ነው አለ15 ከዚያም ወደ ንጉሡ ገባ ንጉሡም ሚካያህ ራሞትጊልያድን ለመውጋት እንዝመት ወይስ ይቅርብን? ሲል ጠየቀው እሱም ወዲያውኑ ውጡ ይቀናችኋል ይሖዋ በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል በማለት መለሰለት16 በዚህ ጊዜ ንጉሡ በይሖዋ ስም ከእውነት በስተቀር ሌላ አንዳች ነገር እንዳትነግረኝ የማስምልህ ስንት ጊዜ ነው? አለው17 በመሆኑም ሚካያህ እንዲህ በማለት ተናገረ እስራኤላውያን ሁሉ እረኛ እንደሌላቸው በጎች በተራሮች ላይ ተበታትነው አያለሁ ይሖዋም እነዚህ ጌታ የላቸውም እያንዳንዳቸው በሰላም ወደየቤታቸው ይመለሱ ብሏል18 ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ ኢዮሳፍጥን ስለ እኔ መጥፎ ነገር ብቻ እንጂ ጥሩ ነገር አይተነብይም ብዬህ አልነበረም? አለው19 በዚህ ጊዜ ሚካያህ እንዲህ አለ እንግዲህ የይሖዋን ቃል ስማ ይሖዋ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ የሰማያት ሠራዊትም ሁሉ በቀኙና በግራው አጠገቡ ቆመው አየሁ20 ከዚያም ይሖዋ በራሞትጊልያድ ላይ ዘምቶ እዚያው እንዲሞት አክዓብን ማን ያሞኘዋል? አለ በዚህ ጊዜ አንዱ አንድ ነገር ሌላው ደግሞ ሌላ ነገር ተናገረ21 ከዚያም አንድ መንፈስ ወደ ፊት ወጥቶ ይሖዋ ፊት በመቆም እኔ አሞኘዋለሁ አለ ይሖዋም እንዴት አድርገህ? አለው22 እኔ እወጣና በነቢያቱ ሁሉ አፍ ላይ አሳሳች መንፈስ እሆናለሁ አለ እሱም እንግዲያው ታሞኘዋለህ ደግሞም ይሳካልሃል ውጣና እንዳልከው አድርግ አለው23 ይሖዋም በእነዚህ ነቢያትህ ሁሉ አፍ ላይ አሳሳች መንፈስ አኑሯል ሆኖም ይሖዋ ጥፋት እንደሚመጣብህ ተናግሯል24 የኬናአና ልጅ ሴዴቅያስም ወደ ሚካያህ ቀርቦ በጥፊ መታውና ለመሆኑ የይሖዋ መንፈስ እኔን በየት በኩል አልፎ ነው አንተን ያናገረህ? አለው25 ሚካያህም በየት በኩል እንዳለፈማ ለመደበቅ ወደ ውስጠኛው ክፍል በምትገባበት ቀን ታውቀዋለህ አለው26 ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ እንዲህ አለ ሚካያህን ወስዳችሁ ለከተማው አለቃ ለአምዖን እና የንጉሡ ልጅ ለሆነው ለዮአስ አስረክቡት27 እንዲህም በሏቸው ንጉሡ በሰላም ተመልሼ እስክመጣ ድረስ ይህን ሰው እስር ቤት አቆዩት ጥቂት ምግብና ውኃ ብቻ ስጡት ብሏል28 ሚካያህ ግን እውነት አንተ በሰላም ከተመለስክ ይሖዋ በእኔ አልተናገረም ማለት ነው! አለ ከዚያም እናንተ ሰዎች ሁላችሁም ልብ በሉ አለ29 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ወደ ራሞትጊልያድ ወጡ30 የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሳፍጥን እኔ ማንነቴ እንዳይታወቅ ራሴን ለውጬ ወደ ውጊያው እገባለሁ አንተ ግን ንጉሣዊ ልብስህን ልበስ አለው ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ ማንነቱ እንዳይታወቅ ራሱን ለውጦ ወደ ውጊያው ገባ31 በዚህ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ 32ቱን የሠረገላ አዛዦች ከእስራኤል ንጉሥ በስተቀር ከትንሹም ሆነ ከትልቁ ከማንም ጋር እንዳትዋጉ በማለት አዟቸው ነበር32 የሠረገሎቹ አዛዦችም ኢዮሳፍጥን ባዩት ጊዜ ያለጥርጥር ይህ የእስራኤል ንጉሥ ነው ብለው አሰቡ በመሆኑም ሊወጉት ወደ እሱ ዞሩ በዚህ ጊዜ ኢዮሳፍጥ እርዳታ ለማግኘት ጮኸ33 የሠረገሎቹ አዛዦችም የእስራኤል ንጉሥ አለመሆኑን ሲያዩ ወዲያውኑ እሱን ማሳደዳቸውን ትተው ተመለሱ34 ይሁንና አንድ ሰው በነሲብ ቀስቱን ሲያስወነጭፍ የእስራኤልን ንጉሥ የጥሩሩ መጋጠሚያ ላይ ወጋው ስለሆነም ንጉሡ ሠረገላ ነጂውን ክፉኛ ስለቆሰልኩ ሠረገላውን አዙረህ ከጦርነቱ ይዘኸኝ ውጣ አለው35 ያን ቀን ሙሉ የተፋፋመ ውጊያ ተካሄደ ንጉሡንም ሠረገላው ውስጥ እንዳለ ፊቱን ወደ ሶርያውያን አዙረው ደግፈው አቆሙት ከቁስሉ የሚወጣውም ደም በጦር ሠረገላው ውስጥ ይፈስ ነበር አመሻሹም ላይ ሞተ36 ፀሐይ ልትጠልቅም ስትል በሰፈሩ መካከል እያንዳንዱ ሰው ወደ ከተማው እያንዳንዱም ሰው ወደ ምድሩ ይመለስ! የሚል ጥሪ አስተጋባ37 በዚህ መንገድ ንጉሡ ሞተ ወደ ሰማርያም ተወሰደ ንጉሡንም በሰማርያ ቀበሩት38 እነሱም የጦር ሠረገላውን በሰማርያ ኩሬ ባጠቡት ጊዜ ይሖዋ በተናገረው መሠረት ውሾች ደሙን ላሱት ዝሙት አዳሪዎችም በዚያ ገላቸውን እየታጠቡ ነበር39 ስለቀረው የአክዓብ ታሪክ ስላደረጋቸው ነገሮች ሁሉ በዝሆን ጥርስ ስለሠራው ቤትና ስለገነባቸው ከተሞች ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ ይገኝ የለም?40 በመጨረሻም አክዓብ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ በእሱም ምትክ ልጁ አካዝያስ ነገሠ41 የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ በነገሠ በአራተኛው ዓመት የአሳ ልጅ ኢዮሳፍጥ በይሁዳ ላይ ነገሠ42 ኢዮሳፍጥ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 35 ዓመት የነበረ ሲሆን በኢየሩሳሌም 25 ዓመት ገዛ እናቱ የሺልሂ ልጅ አዙባ ነበረች43 እሱም በአባቱ በአሳ መንገድ ሁሉ ሄደ ከዚያ ፈቀቅ አላለም በይሖዋም ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ ይሁን እንጂ ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች አልተወገዱም ነበር ሕዝቡም ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች ላይ መሠዋቱንና የሚጨስ መሥዋዕት ማቅረቡን አልተወም ነበር44 ኢዮሳፍጥ ከእስራኤል ንጉሥ ጋር ሰላማዊ ግንኙነት ነበረው45 የቀረው የኢዮሳፍጥ ታሪክ በኃያልነቱ የፈጸማቸው ጀብዱዎችና ያደረጋቸው ውጊያዎች በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?46 ኢዮሳፍጥ ከአባቱ ከአሳ ዘመን የተረፉትን የቤተ መቅደስ ቀላጮች ከምድሪቱ ላይ አስወግዶ ነበር47 በዚያ ዘመን በኤዶም ንጉሥ አልነበረም እንደ ንጉሥ ሆኖ የሚገዛው አስተዳዳሪው ነበር48 በተጨማሪም ኢዮሳፍጥ ወርቅ ለማምጣት ወደ ኦፊር የሚሄዱ የተርሴስ መርከቦች ሠርቶ ነበር ሆኖም መርከቦቹ በዔጽዮንጋብር ስለተሰበሩ ወደዚያ አልሄዱም49 የአክዓብ ልጅ አካዝያስ ኢዮሳፍጥን አገልጋዮቼ ከአገልጋዮችህ ጋር በመርከቦቹ ይሂዱ ያለው በዚህ ጊዜ ነበር ኢዮሳፍጥ ግን በዚህ አልተስማማም50 በመጨረሻም ኢዮሳፍጥ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ በአባቱ በዳዊት ከተማም ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ በእሱም ምትክ ልጁ ኢዮራም ነገሠ51 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ በነገሠ በ17ኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ አካዝያስ በሰማርያ ሆኖ በእስራኤል ላይ ነገሠ በእስራኤልም ላይ ሁለት ዓመት ገዛ52 እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ማድረጉን ቀጠለ በአባቱና በእናቱ መንገድ እንዲሁም እስራኤላውያን ኃጢአት እንዲፈጽሙ ባደረጋቸው በናባጥ ልጅ በኢዮርብዓም መንገድ ሄደ53 ባአልን ማገልገሉንና ለእሱ መስገዱን ቀጠለ አባቱም እንዳደረገው ሁሉ የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን አስቆጣ
3 ሰለሞን ከግብፁ ንጉሥ ከፈርዖን ጋር በጋብቻ ተዛመደ የፈርዖንን ሴት ልጅ አገባ እሷንም የራሱን ቤት የይሖዋን ቤትና በኢየሩሳሌም ዙሪያ ያለውን ቅጥር ገንብቶ እስኪጨርስ ድረስ ወደ ዳዊት ከተማ አመጣት2 ሆኖም እስከዚያን ጊዜ ድረስ ለይሖዋ ስም የተሠራ ቤት ስላልነበረ ሕዝቡ መሥዋዕት ያቀርብ የነበረው ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች ላይ ነበር3 ሰለሞን መሥዋዕቶችንና የሚቃጠሉ መባዎችን ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች ላይ ከማቅረቡ በስተቀር በአባቱ በዳዊት ደንቦች መሠረት በመሄድ ይሖዋን እንደሚወድ አሳይቷል4 ይበልጥ ታዋቂ የሆነው ከፍ ያለ የማምለኪያ ቦታ ገባኦን ስለነበር ንጉሡ መሥዋዕት ለማቅረብ ወደዚያ ሄደ ሰለሞን በዚያ መሠዊያ ላይ 1,000 የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን አቀረበ5 በገባኦንም ይሖዋ ለሰለሞን ሌሊት በሕልም ተገለጠለት አምላክም እንድሰጥህ የምትፈልገውን ጠይቅ አለው6 በዚህ ጊዜ ሰለሞን እንዲህ አለ አገልጋይህ አባቴ ዳዊት በፊትህ በታማኝነት በጽድቅና በቅን ልቦና ስለሄደ ጥልቅ የሆነ ታማኝ ፍቅር አሳይተኸዋል በዙፋኑ ላይ የሚቀመጥ ልጅ በመስጠት እስከ ዛሬም ድረስ ለእሱ ይህን ጥልቅ የሆነ ታማኝ ፍቅር አሳይተሃል7 አሁንም አምላኬ ይሖዋ ሆይ እኔ ገና አንድ ፍሬ ልጅና ተሞክሮ የሌለኝ ብሆንም አገልጋይህን በአባቴ በዳዊት ምትክ አንግሠኸዋል8 አገልጋይህ አንተ በመረጥከው ከብዛቱም የተነሳ ሊቆጠር በማይችለው ሕዝብ መካከል ይገኛል9 ስለሆነም አገልጋይህ ሕዝብህን መዳኘት እንዲሁም መልካምና ክፉ የሆነውን ነገር መለየት እንዲችል ታዛዥ ልብ ስጠው አለዚያማ ስፍር ቁጥር የሌለውን ይህን ሕዝብህን ማን ሊዳኝ ይችላል?10 ሰለሞን ይህን መጠየቁ ይሖዋን ደስ አሰኘው11 ከዚያም አምላክ እንዲህ አለው ይህን ነገር ስለጠየቅክ እንዲሁም ለራስህ ረጅም ዕድሜ ወይም ብልጽግና አሊያም የጠላቶችህን ሞት ሳይሆን የፍርድ ጉዳዮችን መዳኘት እንድትችል ማስተዋልን ስለጠየቅክ12 የጠየቅከውን አደርግልሃለሁ ከአንተ በፊት ማንም ሰው ያልነበረውን ከአንተ በኋላም ማንም ሰው የማያገኘውን ጥበበኛና አስተዋይ ልብ እሰጥሃለሁ13 በተጨማሪም በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ከነገሥታት መካከል አንተን የሚተካከል እንዳይኖር አንተ ያልጠየቅከውን ብልጽግናና ክብር እሰጥሃለሁ14 አባትህ ዳዊት እንዳደረገው ሥርዓቶቼንና ትእዛዛቴን በመጠበቅ በመንገዶቼ ከሄድክ ረጅም ዕድሜም እሰጥሃለሁ15 ሰለሞንም ከእንቅልፉ ሲነቃ ሕልም መሆኑን ተረዳ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ በይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆመ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችንና የኅብረት መባዎችን አቀረበ ለአገልጋዮቹም በሙሉ ግብዣ አዘጋጀ16 በዚህ ጊዜ ሁለት ዝሙት አዳሪዎች ወደ ንጉሡ መጥተው ፊቱ ቆሙ17 የመጀመሪያዋም ሴት እንዲህ አለች ጌታዬ ሆይ እኔና ይህች ሴት የምንኖረው አንድ ቤት ውስጥ ነው እሷም ቤት ውስጥ እያለች ልጅ ወለድኩ18 እኔ ከወለድኩ ከሦስት ቀን በኋላ ይህችም ሴት ልጅ ወለደች ሁለታችን አብረን ነበርን ከሁለታችን በስተቀር ቤቱ ውስጥ ማንም አብሮን አልነበረም19 ሌሊት ላይ ይህች ሴት ልጇ ላይ ስለተኛችበት ልጇ ሞተ20 ስለሆነም እኩለ ሌሊት ላይ ተነስታ እኔ አገልጋይህ ተኝቼ እያለሁ ልጄን ከአጠገቤ በመውሰድ በእቅፏ አስተኛችው የሞተውን ልጇን ደግሞ በእኔ እቅፍ ውስጥ አስተኛችው21 እኔም በማለዳ ልጄን ለማጥባት ስነሳ ልጁ ሞቷል ስለሆነም በማለዳ ብርሃን ልጁን ትክ ብዬ ስመለከተው እኔ የወለድኩት ልጅ አለመሆኑን ተረዳሁ22 ሆኖም ሌላኛዋ ሴት በፍጹም በሕይወት ያለው የእኔ ልጅ ነው የሞተው የአንቺ ልጅ ነው! አለች በዚህ ጊዜ የመጀመሪያዋ ሴት በጭራሽ የሞተው የአንቺ ልጅ ነው በሕይወት ያለው የእኔ ልጅ ነው አለች እነሱም እንዲህ እያሉ በንጉሡ ፊት ተጨቃጨቁ23 በመጨረሻም ንጉሡ ይህችኛዋ ይህ በሕይወት ያለው ልጅ የእኔ ነው የሞተው የአንቺ ልጅ ነው! ትላለች ያቺኛዋ ደግሞ በፍጹም የሞተው የአንቺ ልጅ ነው በሕይወት ያለው የእኔ ልጅ ነው! ትላለች አለ24 ከዚያም ንጉሡ እንግዲያውስ ሰይፍ አምጡልኝ አለ በመሆኑም ለንጉሡ ሰይፍ አመጡለት25 ንጉሡም በሉ በሕይወት ያለውን ልጅ ለሁለት ሰንጥቁትና ግማሹን ለአንደኛዋ ሴት ግማሹን ደግሞ ለሌላኛዋ ስጡ አለ26 በሕይወት ያለው ልጅ እናት ለልጇ ስለራራች ወዲያውኑ ንጉሡን እባክህ ጌታዬ! በሕይወት ያለውን ልጅ ለእሷ ስጧት! በፍጹም አትግደሉት! በማለት ተማጸነችው ሌላኛዋ ሴት ግን ልጁ የእኔም የአንቺም አይሆንም! ለሁለት ይሰንጥቁት! ትል ነበር27 ንጉሡም መልሶ በሕይወት ያለውን ልጅ ለመጀመሪያዋ ሴት ስጧት! እናቱ እሷ ስለሆነች በፍጹም አትግደሉት አለ28 እስራኤላውያንም ሁሉ ንጉሡ የሰጠውን ፍርድ ሰሙ ንጉሡ ፍትሐዊ ፍርድ መስጠት ይችል ዘንድ የአምላክን ጥበብ እንደታደለ ስለተመለከቱ ለንጉሡ አክብሮታዊ ፍርሃት አደረባቸው
4 ንጉሥ ሰለሞን መላውን እስራኤል ይገዛ ነበር2 ከፍተኛ ባለሥልጣናቱ እነዚህ ነበሩ የሳዶቅ ልጅ አዛርያስ ካህን ነበር3 የሺሻ ልጆች ኤሌሆሬፍና አኪያህ ጸሐፊዎች ነበሩ የአሂሉድ ልጅ ኢዮሳፍጥ ታሪክ ጸሐፊ ነበር4 የዮዳሄ ልጅ በናያህ የሠራዊቱ አዛዥ ነበር ሳዶቅና አብያታር ካህናት ነበሩ5 የናታን ልጅ አዛርያስ የአስተዳዳሪዎቹ ኃላፊ ነበር የናታን ልጅ ዛቡድ ካህንና የንጉሡ ወዳጅ ነበር6 አሂሻር የቤቱ አዛዥ ነበር የአብዳ ልጅ አዶኒራም የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ በተመለመሉት ላይ አዛዥ ነበር7 ሰለሞን በመላው እስራኤል ላይ የተሾሙ ለንጉሡና ለቤተሰቡ ቀለብ የሚያቀርቡ 12 አስተዳዳሪዎች ነበሩት እያንዳንዳቸውም በዓመት ውስጥ ለአንድ ወር ቀለብ የማቅረብ ኃላፊነት ተጥሎባቸው ነበር8 ስማቸውም የሚከተለው ነው በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ የሁር ልጅ9 በማቃጽ በሻአልቢም በቤትሼሜሽ እና በኤሎንቤትሃናን የዴቀር ልጅ10 በአሩቦት የሄሴድ ልጅ ሶኮህ እና የሄፌር ምድር በሙሉ በሥሩ ነበሩ11 በዶር ሸንተረር በሙሉ የአቢናዳብ ልጅ እሱም የሰለሞንን ልጅ ጣፋትን አግብቶ ነበር12 በታአናክ እና በመጊዶ እንዲሁም ከኢይዝራኤል በታች ከጸረታን አጠገብ በሚገኘው በቤትሼን በሙሉና ከቤትሼን አንስቶ በዮቅመአም እስከሚገኘው እስከ አቤልምሆላ ድረስ የአሂሉድ ልጅ ባአና13 በራሞትጊልያድ የጌቤር ልጅ በጊልያድ የሚገኙት የምናሴ ልጅ የያኢር የድንኳን ሰፈሮች በእሱ ሥር ነበሩ እንዲሁም በባሳን የሚገኘው የአርጎብ ክልል ይኸውም በቅጥር የታጠሩና የመዳብ መቀርቀሪያ ያላቸው 60 ትላልቅ ከተሞች በእሱ ሥር ነበሩ14 በማሃናይም የኢዶ ልጅ አሂናዳብ15 በንፍታሌም አኪማዓስ እሱም ሌላኛዋን የሰለሞንን ልጅ ባሴማትን አግብቶ ነበር16 በአሴርና በበዓሎት የኩሲ ልጅ ባአና17 በይሳኮር የፓሩህ ልጅ ኢዮሳፍጥ18 በቢንያም የኤላ ልጅ ሺምአይ19 እንዲሁም የአሞራውያን ንጉሥ የሲሖን እና የባሳን ንጉሥ የኦግ ምድር በሆነው በጊልያድ ምድር የዖሪ ልጅ ጌቤር በተጨማሪም በምድሪቱ አስተዳዳሪዎች ሁሉ ላይ የተሾመ አንድ አስተዳዳሪ ነበር20 ይሁዳና እስራኤል ከብዛታቸው የተነሳ እንደ ባሕር አሸዋ ነበሩ እነሱም ይበሉና ይጠጡ እንዲሁም ይደሰቱ ነበር21 ሰለሞን ከወንዙ አንስቶ እስከ ፍልስጤማውያን ምድርና እስከ ግብፅ ወሰን ድረስ ባሉት መንግሥታት ሁሉ ላይ ገዛ እነሱም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ግብር ያመጡለት እንዲሁም ያገለግሉት ነበር22 ሰለሞን በየቀኑ የሚገባለት ቀለብ ይህ ነበር 30 የቆሮስ መስፈሪያ የላመ ዱቄት 60 የቆሮስ መስፈሪያ ዱቄት23 እንዲሁም 10 ቅልብ ከብቶች ከግጦሽ የመጡ 20 ከብቶች 100 በጎችና የተወሰኑ የርኤም ዝርያዎች የሜዳ ፍየሎችና የሰቡ ወፎች24 እሱም ከወንዙ ወዲህ ያሉትን ነገሥታት ሁሉ ጨምሮ ከቲፍሳ አንስቶ እስከ ጋዛ ድረስ የሚገኙትን ከወንዙ ወዲህ ያሉትን አካባቢዎች በሙሉ ተቆጣጥሮ ነበር በዙሪያው ባለው አካባቢ ሁሉ ሰላም ሰፍኖለት ነበር25 በሰለሞን ዘመን ከዳን አንስቶ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ በይሁዳና በእስራኤል የሚገኝ እያንዳንዱ ሰው ከገዛ ወይኑና ከበለስ ዛፉ ሥር ያለስጋት ይኖር ነበር26 ሰለሞን ሠረገሎቹን ለሚጎትቱት ፈረሶች የሚሆኑ 4,000 ጋጣዎችና 12,000 ፈረሶች ነበሩት27 እነዚህ አስተዳዳሪዎች ለንጉሥ ሰለሞንና ከንጉሥ ሰለሞን ማዕድ ለሚመገቡት ሁሉ ቀለብ ያቀርቡ ነበር እያንዳንዳቸውም በተመደበላቸው ወር የሚጠበቅባቸውን ያቀርቡ የነበረ ሲሆን ምንም ነገር እንዳይጓደል ጥንቃቄ ያደርጉ ነበር28 እንዲሁም እያንዳንዳቸው በተመደበላቸው ድርሻ መሠረት ለፈረሶቹና ለሰንጋ ፈረሶቹ የሚሆነውን ገብስና ገለባ ወደተፈለገው ቦታ ያመጡ ነበር29 አምላክም ለሰለሞን እጅግ ታላቅ ጥበብና ማስተዋል እንዲሁም በባሕር ዳርቻ ላይ እንዳለ አሸዋ ሰፊ ልብ ሰጠው30 የሰለሞን ጥበብ ከምሥራቅ ሰዎች ሁሉ ጥበብና ከግብፅ ሁሉ ጥበብ የላቀ ነበር31 እሱም ከማንኛውም ሰው ይልቅ ጥበበኛ ነበር ከዛራዊው ከኤታን እንዲሁም የማሆል ልጆች ከሆኑት ከሄማን ከካልኮል እና ከዳርዳ ይልቅ ጥበበኛ ነበር ዝናውም በዙሪያው ባሉት ብሔራት ሁሉ ዘንድ ተሰማ32 እሱም 3,000 ምሳሌዎችን አቀናበረ የመዝሙሮቹም ብዛት 1,005 ነበር33 በሊባኖስ ከሚገኘው አርዘ ሊባኖስ አንስቶ በቅጥር ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ድረስ ስለ ዛፎች ተናግሯል እንዲሁም ስለ እንስሳት ስለ አእዋፍ መሬት ለመሬት ስለሚሄዱ ፍጥረታትና ስለ ዓሣዎች ተናግሯል34 ስለ እሱ ጥበብ ሲወራ የሰሙ በተለያየ የምድር ክፍል የሚገኙ ነገሥታትን ጨምሮ ከልዩ ልዩ ብሔራት ሰዎች የሰለሞንን ጥበብ ለመስማት ይመጡ ነበር
5 የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ሰለሞን በአባቱ ምትክ ንጉሥ ሆኖ እንደተቀባ ሲሰማ አገልጋዮቹን ወደ እሱ ላከ ምክንያቱም ኪራም ምንጊዜም የዳዊት ወዳጅ ነበር2 ሰለሞንም በምላሹ እንዲህ የሚል መልእክት ወደ ኪራም ላከ3 አባቴ ዳዊት ከተለያየ አቅጣጫ ጦርነት ይከፈትበት ስለነበር ይሖዋ ጠላቶቹን ከእግሩ በታች እስኪያደርግለት ድረስ ለአምላኩ ለይሖዋ ስም የሚሆን ቤት መሥራት እንዳልቻለ በሚገባ ታውቃለህ4 አሁን ግን አምላኬ ይሖዋ በዙሪያዬ ካሉ ጠላቶቼ ሁሉ እረፍት ሰጥቶኛል የሚቃወመኝም ሆነ እየተፈጸመ ያለ ምንም መጥፎ ነገር የለም5 በመሆኑም ይሖዋ ለአባቴ ለዳዊት ለስሜ ቤት የሚሠራልኝ በአንተ ምትክ በዙፋንህ ላይ የማስቀምጠው ልጅህ ነው ሲል በገባው ቃል መሠረት ለአምላኬ ለይሖዋ ስም ቤት ለመሥራት አስቤአለሁ6 ስለሆነም አገልጋዮችህ አርዘ ሊባኖስ እንዲቆርጡልኝ ትእዛዝ ስጥ አገልጋዮቼም ከአገልጋዮችህ ጋር ይሠራሉ የአገልጋዮችህንም ደሞዝ አንተ በወሰንከው መሠረት እከፍላለሁ መቼም ከመካከላችን እንደ ሲዶናውያን ዛፍ መቁረጥ የሚችል አንድም ሰው እንደሌለ ታውቃለህ7 ኪራም የሰለሞንን መልእክት ሲሰማ እጅግ በመደሰቱ ይህን ታላቅ ሕዝብ እንዲመራ ለዳዊት ጥበበኛ ልጅ ስለሰጠው ዛሬ ይሖዋ ይወደስ! አለ8 ስለዚህ ኪራም እንዲህ የሚል መልእክት ወደ ሰለሞን ላከ የላክብኝ መልእክት ደርሶኛል የአርዘ ሊባኖስና የጥድ ሳንቃዎች በማቅረብ ረገድ የፈለግከውን ሁሉ አደርጋለሁ9 አገልጋዮቼ ሳንቃዎቹን ከሊባኖስ ወደ ባሕሩ ያወርዷቸዋል እኔም በባሕር ላይ ተንሳፈው አንተ ወደምትለኝ ቦታ እንዲደርሱ አንድ ላይ አስሬ እልካቸዋለሁ እዚያም ሲደርሱ እንዲፈቱ አደርጋለሁ ከዚያ ልትወስዳቸው ትችላለህ አንተ ደግሞ በምላሹ የጠየቅኩህን ቀለብ ለቤተሰቤ ታቀርባለህ10 በመሆኑም ኪራም ሰለሞን የፈለገውን ያህል የአርዘ ሊባኖስና የጥድ ሳንቃ አቀረበለት11 ሰለሞን ደግሞ ለኪራም ቤተሰብ ቀለብ እንዲሆን 20,000 የቆሮስ መስፈሪያ ስንዴና 20 የቆሮስ መስፈሪያ ምርጥ የወይራ ዘይት ለኪራም ሰጠው ሰለሞን ለኪራም በየዓመቱ ይህን ይሰጠው ነበር12 ይሖዋም ቃል በገባለት መሠረት ለሰለሞን ጥበብ ሰጠው በኪራምና በሰለሞን መካከል ሰላም ነበር እንዲሁም የስምምነት ውል ተዋዋሉ13 ሰለሞንም ከመላው እስራኤል የግዳጅ ሥራ የሚሠሩ ሰዎችን መለመለ የተመለመሉትም ሰዎች ብዛታቸው 30,000 ነበር14 እነሱንም በየወሩ አሥር አሥር ሺህ እያደረገ በየተራ ወደ ሊባኖስ ይልካቸው ነበር እነሱም ለአንድ ወር በሊባኖስ ለሁለት ወር ደግሞ ቤታቸው ይቀመጡ ነበር የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ የተመለመሉት ሰዎች አለቃ አዶኒራም ነበር15 ሰለሞን በተራሮቹ ላይ 70,000 ተራ የጉልበት ሠራተኞችና 80,000 ድንጋይ ጠራቢዎች ነበሩት16 በተጨማሪም ከሰለሞን መኳንንት መካከል አስተዳዳሪዎች ሆነው የሚያገለግሉት 3,300 ሰዎች ሠራተኞቹን ይቆጣጠሩ ነበር17 የቤቱን መሠረት በተጠረቡ ድንጋዮች ለመጣል በንጉሡ ትእዛዝ መሠረት ውድ የሆኑ ትላልቅ ድንጋዮችን ፈልፍለው አወጡ18 ስለዚህ የሰለሞን ግንበኞች የኪራም ግንበኞችና ጌባላውያን ድንጋዮቹን ጠረቡ እንዲሁም ቤቱን ለመገንባት የሚያስፈልጉትን ሳንቃዎችና ድንጋዮች አዘጋጁ
6 እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር በወጡ በ480ኛው ዓመት ይኸውም ሰለሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ዚፍ በተባለው በሁለተኛው ወር ሰለሞን የይሖዋን ቤት መሥራት ጀመረ2 ንጉሥ ሰለሞን ለይሖዋ የሠራው ቤት ርዝመቱ 60 ክንድ ወርዱ 20 ክንድ ቁመቱ ደግሞ 30 ክንድ ነበር3 ከቅድስቱ ፊት ለፊት ያለው በረንዳ ርዝመቱ 20 ክንድ ሲሆን ይህም ከቤቱ ወርድ ጋር እኩል ነው በረንዳው ከቤቱ አሥር ክንድ ወደ ፊት ወጣ ያለ ነበር4 ለቤቱም እየጠበቡ የሚሄዱ ክፈፎች ያሏቸውን መስኮቶች ሠራ5 በተጨማሪም በቤቱ ግድግዳ ዙሪያ ተቀጥላ ቤት ሠራ ቤቱ የተሠራው በቤቱ ግድግዳ ዙሪያ ይኸውም በቤተ መቅደሱና በውስጠኛው ክፍል ግድግዳ ዙሪያ ነበር በዚህ መንገድ በዙሪያው ተቀጥላ ክፍሎችን ሠራ6 የታችኛው ተቀጥላ ክፍል ወርድ አምስት ክንድ የመካከለኛው ወርድ ስድስት ክንድ የላይኛው ወርድ ደግሞ ሰባት ክንድ ነበር ከቤቱ ግድግዳ ጋር የሚያያዝ ምንም ነገር እንዳይኖር በቤቱ ግድግዳ ዙሪያ ተሸካሚዎችን ሠርቶ ነበር7 ቤቱ የተገነባው ሁሉ ነገር ባለቀለት ተፈልፍሎ በወጣ ድንጋይ ነበር በመሆኑም ቤቱ በተገነባበት ጊዜ የመዶሻ ወይም የመጥረቢያ አሊያም የማንኛውም የብረት መሣሪያ ድምፅ ቤቱ ውስጥ አልተሰማም8 የታችኛው ተቀጥላ ክፍል መግቢያ የሚገኘው በስተ ደቡብ በኩል ባለው የቤቱ ጎን ነበር በተጨማሪም ከታችኛው ወደ መካከለኛው ደርብ እንዲሁም ከመካከለኛው ወደ ላይኛው ደርብ የሚያስወጣ ጠመዝማዛ ደረጃ ነበር9 እሱም ቤቱን ገንብቶ አጠናቀቀ ቤቱንም ከአርዘ ሊባኖስ በተሠሩ ተሸካሚዎችና ርብራቦች ከደነው10 በቤቱ ዙሪያ እያንዳንዳቸው ቁመታቸው አምስት ክንድ የሆነ ተቀጥላ ክፍሎችን ሠራ ክፍሎቹም ከቤቱ ጋር በአርዘ ሊባኖስ ሳንቃዎች ተያይዘው ነበር11 ይህ በእንዲህ እንዳለ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሰለሞን መጣ12 በደንቦቼ ብትሄድ ፍርዶቼን ብትፈጽምና በትእዛዛቴ መሠረት በመሄድ ሁሉንም ብትጠብቃቸው እኔም እየገነባህ ያለኸውን ይህን ቤት በተመለከተ ለአባትህ ለዳዊት የገባሁለትን ቃል እፈጽምልሃለሁ13 እንዲሁም በእስራኤላውያን መካከል እኖራለሁ ሕዝቤን እስራኤልንም አልተውም14 ሰለሞንም ቤቱን ገንብቶ ለማጠናቀቅ የግንባታ ሥራውን ገፋበት15 ውስጠኛውን የቤቱን ግድግዳ በአርዘ ሊባኖስ ሳንቃዎች ሠራ ቤቱንም ከወለሉ አንስቶ እስከ ኮርኒሱ ወራጆች ድረስ በሳንቃ ለበጠ የቤቱንም ወለል በጥድ ጣውላ ለበጠው16 እንዲሁም ከቤቱ በስተ ኋላ በኩል ከወለሉ አንስቶ እስከ ወራጁ ድረስ በአርዘ ሊባኖስ ሳንቃዎች የተሠራ ባለ 20 ክንድ ክፍል ገነባ በውስጡም የውስጠኛውን ክፍል ይኸውም ቅድስተ ቅዱሳኑን ሠራ17 ከፊቱ ያለው የቤቱ ክፍል ይኸውም ቤተ መቅደሱ 40 ክንድ ነበር18 በቤቱ በውስጠኛው በኩል ያለው አርዘ ሊባኖስ የቅሎችና የፈኩ አበቦች ምስል ተቀርጾበት ነበር ሙሉ በሙሉ በአርዘ ሊባኖስ የተሠራ ነበር ምንም የሚታይ ድንጋይ አልነበረም19 እሱም የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት በዚያ ለማስቀመጥ ቤቱ ውስጥ የውስጠኛውን ክፍል አዘጋጀ20 ውስጠኛው ክፍል ርዝመቱ 20 ክንድ ወርዱ 20 ክንድ እንዲሁም ቁመቱ 20 ክንድ ነበር በንጹሕ ወርቅም ለበጠው መሠዊያውንም በአርዘ ሊባኖስ ለበጠው21 ሰለሞን ቤቱን ከውስጥ በኩል በንጹሕ ወርቅ ለበጠው በወርቅ በተለበጠው በውስጠኛው ክፍል ፊት ለፊትም የወርቅ ሰንሰለት ዘረጋ22 ቤቱ ሙሉ በሙሉ እስኪለበጥ ድረስ ቤቱን በሙሉ በወርቅ ለበጠው በውስጠኛው ክፍል አጠገብ ያለውን መሠዊያም ሙሉ በሙሉ በወርቅ ለበጠው23 በውስጠኛው ክፍል ውስጥ እያንዳንዳቸው አሥር ክንድ ቁመት ያላቸውን ሁለት ኪሩቦች ከጥድ እንጨት ሠራ24 የኪሩቡ አንድ ክንፍ አምስት ክንድ ሲሆን ሌላኛውም ክንፉ አምስት ክንድ ነበር ከአንዱ ክንፍ ጫፍ እስከ ሌላው ክንፍ ጫፍ አሥር ክንድ ነበር25 ሁለተኛውም ኪሩብ አሥር ክንድ ነበር ሁለቱ ኪሩቦች ተመሳሳይ መጠንና ቅርጽ ነበራቸው26 የአንደኛው ኪሩብ ቁመት አሥር ክንድ ነበር የሌላኛውም ኪሩብ እንደዚሁ ነበር27 ከዚያም ኪሩቦቹን ውስጠኛው ክፍል ውስጥ አስቀመጣቸው የኪሩቦቹም ክንፎች ተዘርግተው ስለነበር የአንደኛው ኪሩብ ክንፍ አንደኛው ግድግዳ ጋ የሌላኛው ኪሩብ ክንፍ ደግሞ ሌላኛው ግድግዳ ጋ ይደርስ ነበር ወደ ቤቱ መሃል የተዘረጉት ክንፎቻቸው ደግሞ ይነካኩ ነበር28 ኪሩቦቹንም በወርቅ ለበጣቸው29 በቤቱ ግድግዳ ሁሉ ላይ ይኸውም በውስጠኛውና በውጨኛው ክፍሎች ዙሪያ ሁሉ የኪሩቦችን የዘንባባ ዛፎችንና የፈኩ አበቦችን ምስል ቀረጸ30 የቤቱን ወለል ይኸውም የውስጠኛውንም ሆነ የውጨኛውን ክፍሎች ወለል በወርቅ ለበጠው31 ለውስጠኛው ክፍል መግቢያ የሚሆኑ በሮችን በጎንና በጎን የሚቆሙ ዓምዶችንና መቃኖችን አንድ አምስተኛ አድርጎ ከጥድ እንጨት ሠራ32 ሁለቱ በሮች ከጥድ እንጨት የተሠሩ ነበሩ በበሮቹም ላይ የኪሩቦችን የዘንባባ ዛፎችንና የፈኩ አበቦችን ምስል ቀረጸባቸው በወርቅም ለበጣቸው ደግሞም ወርቁን በኪሩቦቹና በዘንባባ ዛፎቹ ላይ ጠፈጠፈው33 ለቤተ መቅደሱ መግቢያ የሚሆኑትንና የአንድ አራተኛው ክፍል የሆኑትን የጥድ እንጨት መቃኖች የሠራው በዚሁ መንገድ ነበር34 እሱም ከጥድ እንጨት ሁለት በሮች ሠራ ሁለት ታጣፊ ሳንቃዎች ያሉት አንዱ በር በመሽከርከሪያዎቹ ላይ ሁለት ታጣፊ ሳንቃዎች ያሉት ሌላኛውም በር በመሽከርከሪያዎቹ ላይ ተገጥሞ ነበር35 እሱም ኪሩቦችን የዘንባባ ዛፎችንና የፈኩ አበቦችን ምስል ቀረጸ ቅርጾቹንም በወርቅ ለበጣቸው36 የውስጠኛውንም ግቢ ወደ ላይ በተነባበረ ሦስት ረድፍ ጥርብ ድንጋይና በአንድ ረድፍ የአርዘ ሊባኖስ ሳንቃ ሠራው37 በ4ኛው ዓመት በዚፍ ወር የይሖዋ ቤት መሠረት ተጣለ38 በ11ኛው ዓመት በቡል ወር ማለትም በስምንተኛው ወር የቤቱ እያንዳንዱ ነገር በንድፉ መሠረት ተሠርቶ ተጠናቀቀ በመሆኑም ቤቱን ገንብቶ ለመጨረስ ሰባት ዓመት ፈጀበት
7 ሰለሞንም የራሱን ቤት ሙሉ በሙሉ ሠርቶ ለማጠናቀቅ 13 ዓመት ፈጀበት2 እሱም የሊባኖስ ደን የተባለውን ርዝመቱ 100 ክንድ ወርዱ 50 ክንድ ቁመቱ ደግሞ 30 ክንድ የሆነ ቤት በአራት ረድፍ በተደረደሩ የአርዘ ሊባኖስ ዓምዶች ገነባ በዓምዶቹም ላይ የአርዘ ሊባኖስ ወራጆች ነበሩ3 ቤቱም በዓምዶቹ ላይ ባረፉት አግዳሚዎች ላይ የተረበረቡ የአርዘ ሊባኖስ ሳንቃዎች ነበሩት ዓምዶቹም 45 ሲሆኑ በአንዱ ረድፍ ላይ 15 ነበሩ4 በሦስት ረድፍ የተሠሩ ባለ ክፈፍ መስኮቶች ነበሩ በሦስቱም ደርቦች ላይ እያንዳንዱ መስኮት ከሌላኛው መስኮት ጋር ትይዩ ነበር5 በሦስቱ ደርቦች ላይ ያሉት ትይዩ የሆኑ መስኮቶች ከፊት ለፊት ሲታዩ አራት ማዕዘን እንደሆኑ ሁሉ መግቢያዎቹና መቃኖቹም በሙሉ እንዲሁ ነበሩ6 እሱም ርዝመቱ 50 ክንድ ወርዱ ደግሞ 30 ክንድ የሆነ የዓምዶች መተላለፊያ ሠራ ከፊት ለፊቱም ዓምዶችና ታዛ ያለው በረንዳ ነበር7 በተጨማሪም ፍርድ የሚሰጥበትን የዙፋን አዳራሽ ይኸውም የፍርድ አዳራሹን ሠራ አዳራሹንም ከወለሉ አንስቶ እስከ ወራጆቹ ድረስ በአርዘ ሊባኖስ ለበጡት8 በሌላኛው ግቢ ያለው ራሱ የሚኖርበት ቤት የሚገኘው ከአዳራሹ ጀርባ ሲሆን አሠራራቸውም ተመሳሳይ ነበር በተጨማሪም ሰለሞን ላገባት ለፈርዖን ልጅ ከዚህ አዳራሽ ጋር የሚመሳሰል ቤት ሠርቶላት ነበር9 እነዚህ ሁሉ ከውጭ አንስቶ እስከ ትልቁ ግቢ ድረስ ከመሠረቱ እስከ ድምድማቱ በውስጥም በውጭም ተለክተው በተጠረቡና በድንጋይ መጋዝ በተቆረጡ ውድ ድንጋዮች የተሠሩ ነበሩ10 መሠረቱ የተጣለው ውድ በሆኑ ትላልቅ ድንጋዮች ነበር አንዳንዶቹ ድንጋዮች ባለ አሥር ክንድ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ባለ ስምንት ክንድ ነበሩ11 በእነዚህም ላይ ተለክተው የተጠረቡ ውድ ድንጋዮችና የአርዘ ሊባኖስ እንጨቶች ነበሩ12 ለይሖዋ ቤት ውስጠኛ ግቢና ለቤቱ በረንዳ እንደተደረገው ሁሉ የትልቁ ግቢ አጥር የተሠራው በሦስት ረድፍ ጥርብ ድንጋይና በአንድ ረድፍ የአርዘ ሊባኖስ ሳንቃ ነበር13 ንጉሥ ሰለሞን መልእክተኛ ልኮ ኪራምን ከጢሮስ አስመጣው14 ኪራም ከንፍታሌም ነገድ የሆነች የአንዲት መበለት ልጅ ነበር አባቱ የጢሮስ ሰው ሲሆን የመዳብ ሥራ ባለሙያ ነበር ኪራም ከማንኛውም የመዳብ ሥራ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችሎታ ማስተዋልና ልምድ ነበረው በመሆኑም ወደ ንጉሥ ሰለሞን መጥቶ ሥራዎቹን ሁሉ አከናወነለት15 እሱም ሁለቱን ዓምዶች ከቀለጠ መዳብ ሠራ እያንዳንዱም ዓምድ ቁመቱ 18 ክንድ ነበር ሁለቱ ዓምዶች እያንዳንዳቸው በመለኪያ ገመድ ሲለኩ መጠነ ዙሪያቸው 12 ክንድ ነበር16 እንዲሁም በዓምዶቹ አናት ላይ የሚሆኑ ሁለት የዓምድ ራሶችን ከመዳብ ሠራ የአንደኛው የዓምድ ራስ ቁመት አምስት ክንድ የሌላኛው የዓምድ ራስ ቁመትም አምስት ክንድ ነበር17 በእያንዳንዱ ዓምድ አናት ላይ ያለው የዓምድ ራስ በሰንሰለት ጉንጉን የተሠሩ መረቦች ነበሩት በአንደኛው የዓምድ ራስ ላይ ሰባት በሌላኛው የዓምድ ራስ ላይም ሰባት ነበሩ18 በዓምዶቹ አናት ላይ ያሉትን የዓምድ ራሶች ለማስጌጥ በአንደኛው መረብ ዙሪያ ሮማኖችን በሁለት ረድፍ ሠራ በሁለቱም የዓምድ ራሶች ላይ እንዲሁ አደረገ19 በረንዳው አጠገብ በሚገኙት ዓምዶች አናት ላይ ያሉት የዓምድ ራሶች አራት ክንድ ቁመት ያለው የአበባ ቅርጽ ነበራቸው20 የዓምድ ራሶቹ በሁለቱ ዓምዶች ላይ ልክ ከመረብ ሥራው ቀጥሎ ካለው ከሆዱ በላይ ነበሩ በእያንዳንዱ የዓምድ ራስ ዙሪያ 200 ሮማኖች በረድፍ ተደርድረው ነበር21 እሱም የቤተ መቅደሱን በረንዳ ዓምዶች አቆመ በስተ ቀኝ ያለውን ዓምድ አቁሞ ያኪን ብሎ ሰየመው ከዚያም በስተ ግራ ያለውን ዓምድ አቁሞ ቦዔዝ ብሎ ሰየመው22 የዓምዶቹም አናቶች የአበባ ቅርጽ ነበራቸው በዚህ መንገድ የዓምዶቹ ሥራ ተጠናቀቀ23 ከዚያም ባሕሩን በቀለጠ ብረት ሠራ ባሕሩ ክብ ቅርጽ የነበረው ሲሆን ከአንዱ ጠርዝ እስከ ሌላኛው ጠርዝ 10 ክንድ ከፍታው ደግሞ 5 ክንድ ነበር መጠነ ዙሪያውም በመለኪያ ገመድ ሲለካ 30 ክንድ ሆነ24 በባሕሩም ዙሪያ ከጠርዙ ዝቅ ብሎ በእያንዳንዱ ክንድ ላይ በቅል ቅርጽ የተሠሩ አሥር ጌጦች ነበሩ ቅሎቹም በሁለት ረድፍ ከባሕሩ ጋር አንድ ወጥ ሆነው ተሠርተው ነበር25 ባሕሩ 3ቱ ወደ ሰሜን 3ቱ ወደ ምዕራብ 3ቱ ወደ ደቡብ እንዲሁም 3ቱ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ፊታቸውን ባደረጉ 12 በሬዎች ላይ ተቀምጦ ነበር ባሕሩም ላያቸው ላይ ነበር የሁሉም ሽንጥ ወደ መሃል ገባ ያለ ነበር26 የውኃ ማጠራቀሚያው ውፍረት አንድ ጋት ነበር ጠርዙ የጽዋ ከንፈር ይመስል የነበረ ሲሆን በአበባ ቅርጽ የተሠራ ነበር የውኃ ማጠራቀሚያውም 2,000 የባዶስ መስፈሪያ ይይዝ ነበር27 ከዚያም አሥር የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎችን ከመዳብ ሠራ እያንዳንዱ ጋሪ ርዝመቱ አራት ክንድ ወርዱ አራት ክንድ ቁመቱ ደግሞ ሦስት ክንድ ነበር28 የጋሪዎቹ አሠራር እንዲህ ነበር ጋሪዎቹ የጎን መከለያ ነበራቸው የጎን መከለያዎቹም በፍርግርግ መካከል ነበሩ29 በፍርግርጎቹ መሃል በነበሩት የጎን መከለያዎች ላይ የአንበሶች የበሬዎችና የኪሩቦች ምስል ነበር በፍርግርጎቹም ላይ እንዲሁ ዓይነት ምስል ነበር ከአንበሶቹና ከበሬዎቹ በላይና በታች የተንጠለጠሉ የአበባ ጉንጉኖች የሚመስሉ ቅርጾች ነበሩ30 እያንዳንዱ የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪ አራት የመዳብ መንኮራኩሮችና የመዳብ ዘንጎች ነበሩት በአራቱ ማዕዘኖች ላይ ያሉት ቋሚዎች ደግሞ ድጋፍ ይሆኗቸው ነበር ድጋፎቹ ከገንዳው በታች ነበሩ እያንዳንዳቸውም በጎናቸው ወጥ ሆኖ የተሠራ የአበባ ጉንጉን የሚመስል ቅርጽ ነበራቸው31 የገንዳው አፍ ያለው በጋሪው አናት ውስጥ ሲሆን አንድ ክንድ ከፍታ ነበረው የጋሪው አፍ ክብ ነበር በአፉ ላይ ያለው ማስቀመጫ አንድ ክንድ ተኩል ከፍታ ነበረው በአፉም ላይ የተቀረጹ ምስሎች ነበሩ የጎን መከለያዎቹም አራት ማዕዘን እንጂ ክብ አልነበሩም32 አራቱ መንኮራኩሮች ከጎን መከለያዎቹ በታች ነበሩ የመንኮራኩሮቹ ድጋፎች ከጋሪው ጋር ተያይዘው ነበር የእያንዳንዱ መንኮራኩር ቁመት አንድ ክንድ ተኩል ነበር33 የመንኮራኩሮቹ አሠራር ከሠረገላ መንኮራኩር አሠራር ጋር ተመሳሳይ ነበር የመንኮራኩሮቹ ድጋፎች ክፈፎች ራጂዎችና አቃፊዎች ሁሉ ከቀለጠ ብረት የተሠሩ ነበሩ34 በእያንዳንዱ ጋሪ አራት ማዕዘኖች ላይ አራት ድጋፎች ነበሩ ድጋፎቹም የጋሪው ክፍል ሆነው የተሠሩ ነበሩ35 በጋሪው አናት ላይ ቁመቱ ግማሽ ክንድ የሆነ ክብ ክፈፍ ነበር እንዲሁም በጋሪው አናት ላይ የሚገኙት ፍርግርጎችና የጎን መከለያዎች የጋሪው ክፍል ሆነው የተሠሩ ነበሩ36 በፍርግርጎቹና በጎን መከለያዎቹም ላይ እንደ ስፋታቸው ኪሩቦችን አንበሶችንና የዘንባባ ዛፍ ምስሎችን ቀረጸባቸው ዙሪያውንም የአበባ ጉንጉን ምስል ሠራበት37 አሥሩን ጋሪዎች የሠራው በዚህ መንገድ ነበር ሁሉም አንድ ዓይነት መጠንና ቅርጽ እንዲኖራቸው ተደርገው በተመሳሳይ መንገድ ቀልጠው የተሠሩ ነበሩ38 እሱም አሥር የመዳብ ገንዳዎችን ሠራ እያንዳንዱ ገንዳ 40 የባዶስ መስፈሪያ ይይዝ ነበር እያንዳንዱ ገንዳ አራት ክንድ ነበር በአሥሩም ጋሪዎች ላይ አንድ አንድ ገንዳ ነበር39 ከዚያም አምስቱን ጋሪዎች ከቤቱ በስተ ቀኝ በኩል አምስቱን ጋሪዎች ደግሞ ከቤቱ በስተ ግራ በኩል አደረጋቸው ባሕሩንም ከቤቱ በስተ ቀኝ በኩል በስተ ደቡብ ምሥራቅ አቅጣጫ አስቀመጠው40 በተጨማሪም ኪራም ገንዳዎቹን አካፋዎቹንና ጎድጓዳ ሳህኖቹን ሠራ ኪራምም በይሖዋ ቤት ለንጉሥ ሰለሞን ያከናውን የነበረውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ የሠራቸውም ነገሮች እነዚህ ነበሩ41 ሁለቱ ዓምዶች በሁለቱ ዓምዶች አናት ላይ የነበሩት የጎድጓዳ ሳህን ቅርጽ ያላቸው የዓምድ ራሶች በዓምዶቹ አናት ላይ የነበሩትን የጎድጓዳ ሳህን ቅርጽ ያላቸውን ሁለቱን ክብ የዓምድ ራሶች የሚያስጌጡት ሁለት መረቦች42 ለሁለቱ መረቦች የተሠሩት 400 ሮማኖች ማለትም በሁለቱ ዓምዶች አናት ላይ የነበሩትን የጎድጓዳ ሳህን ቅርጽ ያላቸው የዓምድ ራሶች ለማስጌጥ የተሠሩት በእያንዳንዱ መረብ ላይ በሁለት ረድፍ የተደረደሩት ሮማኖች43 አሥሩ ጋሪዎችና በጋሪዎቹ ላይ የነበሩት አሥር የውኃ ገንዳዎች44 ባሕሩና ከሥሩ የነበሩት 12 በሬዎች45 አመድ ማጠራቀሚያዎቹ አካፋዎቹ ጎድጓዳ ሳህኖቹና ኪራም ለይሖዋ ቤት እንዲሆኑ ለንጉሥ ሰለሞን ከተወለወለ መዳብ የሠራቸው ዕቃዎች በሙሉ46 ንጉሡ እነዚህ ነገሮች በዮርዳኖስ አውራጃ በሱኮትና በጻረታን መካከል በሚገኝ ስፍራ ከሸክላ በተሠሩ ቅርጽ ማውጫዎች ውስጥ ቀልጠው እንዲሠሩ አደረገ47 ሰለሞን ዕቃዎቹ ሁሉ እንዲመዘኑ አላደረገም ምክንያቱም ዕቃዎቹ እጅግ ብዙ ነበሩ የመዳቡ ክብደት ምን ያህል እንደሆነ አልታወቀም48 ሰለሞንም ለይሖዋ ቤት መገልገያ የሚሆኑትን የሚከተሉትን ነገሮች ሠራ የወርቅ መሠዊያውን ገጸ ኅብስት የሚቀመጥበትን የወርቅ ጠረጴዛ49 በውስጠኛው ክፍል ፊት በቀኝና በግራ የሚቀመጡትን ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ አምስት አምስት መቅረዞች ከወርቅ የተሠሩትን የፈኩ አበቦች መብራቶችና መቆንጠጫዎች50 ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩትን ሳህኖች የእሳት ማጥፊያዎች ጎድጓዳ ሳህኖች ጽዋዎችና መኮስተሪያዎች እንዲሁም ከወርቅ የተሠሩትን የውስጠኛው ክፍል ማለትም የቅድስተ ቅዱሳኑ በሮችና የመቅደሱ በሮች የሚሽከረከሩባቸውን መቆሚያዎች51 በዚህ ሁኔታ ንጉሥ ሰለሞን ከይሖዋ ቤት ጋር በተያያዘ መሥራት የሚገባውን ሥራ በሙሉ አጠናቀቀ ከዚያም ሰለሞን አባቱ ዳዊት የቀደሳቸውን ነገሮች ወደዚያ አስገባ ብሩን ወርቁንና ዕቃዎቹን በይሖዋ ቤት ግምጃ ቤቶች ውስጥ አስቀመጠ
8 በዚህ ጊዜ ሰለሞን የእስራኤልን ሽማግሌዎች የነገዶቹን መሪዎች ሁሉና የእስራኤልን የአባቶች ቤት አለቆች ሰበሰበ እነሱም የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ማለትም ከጽዮን ለማምጣት በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ንጉሥ ሰለሞን መጡ2 የእስራኤል ሰዎች በሙሉ በሰባተኛው ወር ማለትም በኤታኒም ወር በሚከበረው በዓል ላይ ንጉሥ ሰለሞን ፊት ተሰበሰቡ3 የእስራኤል ሽማግሌዎችም በሙሉ መጡ ካህናቱም ታቦቱን አነሱ4 የይሖዋን ታቦት የመገናኛ ድንኳኑንና በድንኳኑ ውስጥ የነበሩትን ቅዱስ ዕቃዎች በሙሉ አመጡ እነዚህንም ያመጡት ካህናቱና ሌዋውያኑ ናቸው5 ንጉሥ ሰለሞንና ወደ እሱ እንዲመጣ የተጠራው መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ታቦቱ ፊት ነበሩ ከብዛታቸው የተነሳ ሊቆጠሩ የማይችሉ ብዙ በጎችና ከብቶች መሥዋዕት ሆነው ቀረቡ6 ከዚያም ካህናቱ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት አምጥተው ቦታው ላይ ማለትም በቤቱ ውስጠኛ ክፍል ይኸውም በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ከኪሩቦቹ ክንፎች በታች አስቀመጡት7 የኪሩቦቹ ክንፎች ታቦቱ ባለበት ቦታ ላይ ተዘርግተው ስለነበር ኪሩቦቹ ታቦቱንና መሎጊያዎቹን ከላይ ከልለዋቸው ነበር8 መሎጊያዎቹ ረጅም ስለነበሩ የመሎጊያዎቹን ጫፎች ከውስጠኛው ክፍል ፊት ለፊት ባለው በቅድስቱ ውስጥ ሆኖ ማየት ይቻል ነበር ከውጭ ግን አይታዩም ነበር እስከ ዛሬም ድረስ እዚያው ይገኛሉ9 የእስራኤል ሰዎች ከግብፅ ምድር ሲወጡ ይሖዋ ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን በገባበት ጊዜ ሙሴ በኮሬብ ታቦቱ ውስጥ ካስቀመጣቸው ከሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች በስተቀር በታቦቱ ውስጥ ምንም አልነበረም10 ካህናቱ ከቅዱሱ ስፍራ በወጡ ጊዜ ደመናው የይሖዋን ቤት ሞላው11 የይሖዋ ክብር የይሖዋን ቤት ሞልቶት ስለነበር ካህናቱ ከደመናው የተነሳ በዚያ ቆመው ማገልገል አልቻሉም12 በዚህ ጊዜ ሰለሞን እንዲህ አለ ይሖዋ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንደሚኖር ተናግሯል13 እኔም እጅግ ከፍ ያለ ቤት ለዘላለም የምትኖርበት ጸንቶ የተመሠረተ ቦታ ገንብቼልሃለሁ14 ከዚያም መላው የእስራኤል ጉባኤ ቆሞ ሳለ ንጉሡ ዞሮ የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ መባረክ ጀመረ15 እንዲህም አለ ለአባቴ ለዳዊት በገዛ አፉ እንዲህ ብሎ ቃል የገባውና ይህን በራሱ እጅ የፈጸመው የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ይወደስ16 ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ካወጣሁበት ዕለት አንስቶ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል ስሜ የሚጠራበት ቤት እንዲሠራበት አንድም ከተማ አልመረጥኩም ዳዊትን ግን በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዢ እንዲሆን መረጥኩ17 አባቴ ዳዊት ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ስም ቤት ለመሥራት ከልቡ ተመኝቶ ነበር18 ሆኖም ይሖዋ አባቴን ዳዊትን እንዲህ አለው ለስሜ ቤት ለመሥራት ከልብህ ተመኝተህ ነበር ይህን በልብህ መመኘትህም መልካም ነው19 ይሁንና ቤቱን የምትሠራው አንተ አይደለህም ሆኖም ለስሜ ቤት የሚሠራልኝ የሚወለድልህ የገዛ ልጅህ ይሆናል20 ይሖዋ የገባውን ቃል ፈጽሟል ልክ ይሖዋ ቃል በገባው መሠረት አባቴን ዳዊትን ተክቼ በእስራኤል ዙፋን ላይ ተቀምጫለሁና በተጨማሪም ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ስም ቤት ሠርቻለሁ21 እንዲሁም አባቶቻችንን ከግብፅ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ይሖዋ ከእነሱ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን የያዘው ታቦት የሚያርፍበትን ቦታ በዚያ አዘጋጅቻለሁ22 ከዚያም ሰለሞን በይሖዋ መሠዊያ ፊት በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት ለፊት ቆሞ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘረጋ23 እንዲህም አለ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ በፊቱ በሙሉ ልባቸው ለሚመላለሱ አገልጋዮቹ ቃል ኪዳኑን የሚጠብቅና ታማኝ ፍቅር የሚያሳይ እንደ አንተ ያለ አምላክ በላይ በሰማይም ሆነ በታች በምድር የለም24 ለአገልጋይህ ለአባቴ ለዳዊት የገባኸውን ቃል ጠብቀሃል በገዛ አፍህ ቃል ገባህ ዛሬ ደግሞ በራስህ እጅ ፈጸምከው25 አሁንም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ አንተ በፊቴ እንደተመላለስከው ሁሉ ልጆችህም በጥንቃቄ በፊቴ ከተመላለሱ ከዘርህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ከፊቴ ፈጽሞ አይታጣም በማለት ለአገልጋይህ ለአባቴ ለዳዊት የገባኸውን ቃል ጠብቅ26 አሁንም የእስራኤል አምላክ ሆይ እባክህ ለአገልጋይህ ለአባቴ ለዳዊት የገባኸው ቃል ይፈጸም27 በእርግጥ አምላክ በምድር ላይ ይኖራል? እነሆ ሰማያት አዎ ሰማየ ሰማያት እንኳ ሊይዙህ አይችሉም ታዲያ እኔ የሠራሁት ይህ ቤትማ ምንኛ ያንስ!28 እንግዲህ አምላኬ ይሖዋ ሆይ የአገልጋይህን ጸሎትና ሞገስ ለማግኘት የሚያቀርበውን ልመና በትኩረት ስማ አገልጋይህ እርዳታ ለማግኘት የሚያሰማውን ጩኸትና በዛሬው ዕለት በፊትህ የሚያቀርበውን ጸሎት አዳምጥ29 አገልጋይህ ወደዚህ ስፍራ የሚያቀርበውን ጸሎት ለመስማት ስሜ በዚያ ይሆናል ወዳልከው ወደዚህ ቤት ዓይኖችህ ቀንና ሌሊት ይመልከቱ30 አገልጋይህ ሞገስ ለማግኘት የሚያቀርበውን ልመናና ሕዝብህ እስራኤል ወደዚህ ስፍራ በመጸለይ የሚያቀርበውን ልመና አዳምጥ በሰማያት ባለው ማደሪያህ ሆነህ ስማ ሰምተህም ይቅር በል31 አንድ ሰው ባልንጀራውን በድሎ እንዲምል ቢደረግ በመሐላውም ተጠያቂ ቢሆን በዳዩም በዚህ መሐላ ሥር ሆኖ እዚህ ቤት ውስጥ ባለው መሠዊያህ ፊት ቢቀርብ32 አንተ በሰማያት ሆነህ ስማ ክፉውን ጥፋተኛ በማለትና እንደ ሥራው በመመለስ ጻድቁንም ንጹሕ መሆኑን በማሳወቅና እንደ ጽድቁ ወሮታውን በመክፈል እርምጃ ውሰድ አገልጋዮችህንም ዳኝ33 ሕዝብህ እስራኤላውያን አንተን ከመበደላቸው የተነሳ በጠላት ድል ቢነሱና ወደ አንተ ተመልሰው ስምህን ቢያወድሱ እንዲሁም በዚህ ቤት ወደ አንተ ቢጸልዩና ሞገስ ለማግኘት ልመና ቢያቀርቡ34 ከሰማያት ሆነህ ስማ የሕዝብህንም የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል ለአባቶቻቸው ወደሰጠኸው ምድርም መልሳቸው35 ሕዝቡ አንተን በመበደሉ የተነሳ ሰማያት ተዘግተው ዝናብ ቢጠፋ እነሱም አንተ ስላዋረድካቸው ወደዚህ ስፍራ ቢጸልዩና ስምህን ቢያወድሱ እንዲሁም ከኃጢአታቸው ቢመለሱ36 ከሰማያት ሆነህ ስማ የአገልጋዮችህን የሕዝብህን የእስራኤላውያንን ኃጢአት ይቅር በል ስለሚሄዱበት ቀና መንገድ ታስተምራቸዋለህና ለሕዝብህ ርስት አድርገህ ባወረስከው ምድርህም ላይ ዝናብ አዝንብ37 በምድሪቱ ላይ ረሃብ ወይም ቸነፈር የሚለበልብና የሚያደርቅ ነፋስ ወይም ዋግ ቢከሰት የአንበጣ መንጋ ወይም የማይጠግብ አንበጣ ቢመጣ አሊያም ጠላቶቻቸው በምድሪቱ ላይ ባለ በየትኛውም ከተማ ውስጥ ሳሉ ቢከቧቸው ወይም ደግሞ ማንኛውም ዓይነት መቅሰፍት አሊያም ማንኛውም ዓይነት በሽታ ቢከሰትና38 ማንኛውም ሰው ወይም ሕዝብህ እስራኤል በሙሉ እያንዳንዱ የልቡን ጭንቀት ያውቃልና ወደ አንተ ለመጸለይ ወይም ሞገስ እንድታሳየው ልመና ለማቅረብ እጁን ወደዚህ ቤት ቢዘረጋ39 አንተ ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት ሆነህ ስማ ደግሞም ይቅር በል እርምጃም ውሰድ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው ብድራቱን ክፈለው ምክንያቱም አንተ ልቡን ታውቃለህ የሰውን ልብ በሚገባ የምታውቀው አንተ ብቻ ነህ40 ይህም ለአባቶቻችን በሰጠኸው ምድር ላይ በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ አንተን እንዲፈሩ ነው41 በተጨማሪም ከሕዝብህ ከእስራኤል ወገን ያልሆነ የባዕድ አገር ሰው በስምህ የተነሳ ከሩቅ አገር ቢመጣ42 መቼም ስለ ታላቁ ስምህ ስለ ኃያሉ እጅህና ስለተዘረጋው ክንድህ መስማታቸው አይቀርም ወደዚህም ቤት መጥቶ ቢጸልይ43 ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት ሆነህ ስማ የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ስምህን እንዲያውቁና እንዲፈሩህ እንዲሁም ስምህ እኔ በሠራሁት በዚህ ቤት እንደሚጠራ እንዲያውቁ ያ የባዕድ አገር ሰው የጠየቀህን ሁሉ ፈጽምለት44 ሕዝብህ ጠላቶቻቸውን ለመውጋት አንተ በምትልካቸው መንገድ ለጦርነት ቢወጡና አንተ ወደመረጥከው ከተማ እንዲሁም ለስምህ ወደሠራሁት ቤት አቅጣጫ ወደ ይሖዋ ቢጸልዩ45 ከሰማያት ሆነህ ጸሎታቸውንና ሞገስ ለማግኘት የሚያቀርቡትን ልመና ስማ ፍረድላቸውም46 በአንተ ላይ ኃጢአት ቢሠሩ መቼም ኃጢአት የማይሠራ ሰው የለም አንተም በእነሱ እጅግ ተቆጥተህ ለጠላት አሳልፈህ ብትሰጣቸው ጠላቶቻቸውም ራቅ ወዳለ ወይም ቅርብ ወደሆነ የጠላት ምድር ምርኮኛ አድርገው ቢወስዷቸው47 እነሱም በምርኮ በተወሰዱበት ምድር ወደ ልቦናቸው ቢመለሱና ወደ አንተ ዞር በማለት ኃጢአት ሠርተናል አጥፍተናል ክፉ ድርጊትም ፈጽመናል በማለት በተማረኩበት ምድር ሆነው ሞገስ ለማግኘት ወደ አንተ ልመና ቢያቀርቡ48 ማርከው በወሰዷቸው ጠላቶቻቸውም ምድር ሆነው በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው ወደ አንተ ቢመለሱ እንዲሁም ለአባቶቻቸው በሰጠሃቸው ምድር አንተ በመረጥካት ከተማና ለስምህ በሠራሁት ቤት አቅጣጫ ወደ አንተ ቢጸልዩ49 ጸሎታቸውንና ሞገስ ለማግኘት ያቀረቡትን ልመና ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት ሆነህ ስማ ፍረድላቸውም50 በአንተ ላይ የፈጸሙትን በደል ሁሉ ይቅር በማለት በአንተ ላይ ኃጢአት የሠራውን ሕዝብህን ይቅር በል የማረኳቸውም ሰዎች እንዲያዝኑላቸው ታደርጋለህ እነሱም ያዝኑላቸዋል51 ምክንያቱም እነሱ እንደ ብረት ማቅለጫ ከሆነችው ከግብፅ ያወጣሃቸው ሕዝቦችህና ርስትህ ናቸው52 አገልጋይህም ሆነ ሕዝብህ እስራኤል ወደ አንተ በሚጮኹበት ጊዜ ሁሉ ስማቸው ሞገስ ለማግኘት የሚያቀርቡትንም ልመና ዓይኖችህ ይመልከቱ53 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ አባቶቻችንን ከግብፅ ባወጣሃቸው ጊዜ በአገልጋይህ በሙሴ በኩል በተናገርከው መሠረት ከምድር ሕዝቦች ሁሉ መካከል ርስትህ አድርገህ ለይተሃቸዋልና54 ሰለሞንም ይህን ሁሉ ጸሎትና ልመና ወደ ይሖዋ አቅርቦ እንደጨረሰ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ ከተንበረከከበት ከይሖዋ መሠዊያ ፊት ተነሳ55 ከዚያም ቆሞ የእስራኤልን ጉባኤ በሙሉ ጮክ ብሎ እንዲህ ሲል ባረከ56 በገባው ቃል መሠረት ለሕዝቡ ለእስራኤል የእረፍት ቦታ የሰጠው ይሖዋ ይወደስ በአገልጋዩ በሙሴ አማካኝነት ከሰጠው መልካም ተስፋ ሁሉ መካከል ሳይፈጸም የቀረ አንድም ቃል የለም57 አምላካችን ይሖዋ ከአባቶቻችን ጋር እንደነበረ ሁሉ ከእኛም ጋር ይሁን አይተወን ደግሞም አይጣለን58 በመንገዱ ሁሉ እንድንሄድ እንዲሁም አባቶቻችን እንዲጠብቁ ያዘዛቸውን ትእዛዛቱን ሥርዓቱንና ድንጋጌዎቹን እንድንጠብቅ ልባችንን ወደ እሱ ያዘንብል59 ሞገስ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ያቀረብኩት ይህ ልመና በአምላካችን በይሖዋ ፊት ቀንና ሌሊት ይታወስ ለአገልጋዩና ለሕዝቡ ለእስራኤልም በየዕለቱ የሚያስፈልገውን ፍርድ ይፍረድላቸው60 ይህም የምድር ሕዝቦች ሁሉ እውነተኛው አምላክ ይሖዋ መሆኑን እንዲያውቁ ነው ከእሱ ሌላ ማንም የለም!61 በመሆኑም እንደ ዛሬው ዕለት ሁሉ በአምላካችን በይሖዋ ሥርዓቶች በመሄድና ትእዛዛቱን በመጠበቅ ልባችሁ በእሱ ዘንድ ሙሉ ይሁን62 ከዚያም ንጉሡና ከእሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ በይሖዋ ፊት ታላቅ መሥዋዕት አቀረቡ63 ሰለሞን 22,000 ከብቶችና 120,000 በጎች ለይሖዋ የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ በዚህ መንገድ ንጉሡና እስራኤላውያን በሙሉ የይሖዋን ቤት መረቁ64 ንጉሡም በዚያ ቀን በይሖዋ ቤት ፊት የሚገኘውን የግቢውን መሃል መቀደስ አስፈልጎት ነበር ምክንያቱም የሚቃጠሉትን መሥዋዕቶች የእህል መባዎቹንና የኅብረት መሥዋዕቶቹን በዚያ ማቅረብ ነበረበት ይህም የሆነው በይሖዋ ፊት ያለው የመዳብ መሠዊያ የሚቃጠሉትን መሥዋዕቶች የእህል መባዎቹንና የኅብረት መሥዋዕቶቹን ስብ መያዝ ስላልቻለ ነው65 በዚያ ጊዜ ሰለሞን ከመላው እስራኤል ጋር ይኸውም ከሌቦሃማት አንስቶ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝ ድረስ ካለው ምድር ከመጣው ታላቅ ጉባኤ ጋር በመሆን በአምላካችን በይሖዋ ፊት ለ7 ቀን ከዚያም ለተጨማሪ 7 ቀን በአጠቃላይ ለ14 ቀን በዓሉን አከበረ66 በቀጣዩም ቀን ሕዝቡን አሰናበተ እነሱም ንጉሡን ባረኩ ይሖዋ ለአገልጋዩ ለዳዊትና ለሕዝቡ ለእስራኤል ባሳየው ጥሩነት ሁሉ እየተደሰቱና ከልባቸው እየፈነደቁ ወደየቤታቸው ሄዱ
9 ሰለሞን የይሖዋን ቤትና የንጉሡን ቤት እንዲሁም ለመሥራት የፈለገውን ነገር ሁሉ ገንብቶ እንደጨረሰ2 ይሖዋ በገባኦን እንደተገለጠለት አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ ተገለጠለት3 ይሖዋም እንዲህ አለው በፊቴ የጸለይከውን ጸሎትና ሞገስ ለማግኘት ያቀረብከውን ልመና ሰምቻለሁ የገነባኸውን ይህን ቤት ስሜ ለዘለቄታው እንዲጠራበት በማድረግ ቀድሼዋለሁ ዓይኔም ሆነ ልቤ ሁልጊዜ በዚያ ይሆናል4 አንተም አባትህ ዳዊት እንዳደረገው ያዘዝኩህን ሁሉ በመፈጸም በንጹሕ ልብና በቅንነት በፊቴ ብትሄድ እንዲሁም ሥርዓቶቼንና ፍርዴን ብትጠብቅ5 ለአባትህ ለዳዊት ከዘር ሐረግህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው አይታጣም በማለት በገባሁለት ቃል መሠረት የመንግሥትህን ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ6 ሆኖም እናንተም ሆናችሁ ልጆቻችሁ እኔን ከመከተል ዞር ብትሉ እንዲሁም በፊታችሁ ያስቀመጥኳቸውን ትእዛዛቴንና ደንቦቼን ባትጠብቁ ሄዳችሁም ሌሎች አማልክትን ብታገለግሉና ለእነሱ ብትሰግዱ7 እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ላይ አጠፋቸዋለሁ ለስሜ የቀደስኩትንም ቤት ከፊቴ አስወግደዋለሁ እስራኤላውያንም በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ መቀለጃና መሳለቂያ ይሆናሉ8 ይህም ቤት የፍርስራሽ ክምር ይሆናል በዚያም የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ በመገረም ትኩር ብለው እየተመለከቱ ይሖዋ በዚህች ምድርና በዚህ ቤት ላይ እንዲህ ያለ ነገር ያደረገው ለምንድን ነው? በማለት ያፏጫሉ9 ከዚያም እንዲህ ይላሉ ይህ የደረሰባቸው አባቶቻቸውን ከግብፅ ምድር ያወጣውን አምላካቸውን ይሖዋን ትተው ሌሎች አማልክትን ስለተከተሉና ለእነሱ ስለሰገዱ እንዲሁም እነሱን ስላገለገሉ ነው ይሖዋ ይህን ሁሉ መከራ ያመጣባቸው ለዚህ ነው10 ሰለሞን ሁለቱን ቤቶች ይኸውም የይሖዋን ቤትና የንጉሡን ቤት ገንብቶ በጨረሰበት በ20ኛው ዓመት ማብቂያ ላይ11 የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለሰለሞን የሚፈልገውን ያህል የአርዘ ሊባኖስ ሳንቃዎች የጥድ ዛፍ ሳንቃዎችና ወርቅ ሰጠው ንጉሥ ሰለሞን ደግሞ ለኪራም በገሊላ ምድር የሚገኙ 20 ከተሞችን ሰጠው12 ስለሆነም ኪራም ሰለሞን የሰጠውን ከተሞች ለማየት ከጢሮስ ወጥቶ ሄደ ሆኖም በከተሞቹ አልተደሰተም13 እሱም ወንድሜ ሆይ የሰጠኸኝ ምን ዓይነት ከተሞችን ነው? አለው ስለዚህ እነዚህ ከተሞች እስከ ዛሬ ድረስ የካቡል ምድር ተብለው ይጠራሉ14 ይህ በእንዲህ እንዳለ ኪራም ለንጉሡ 120 ታላንት ወርቅ ላከለት15 ንጉሥ ሰለሞን የይሖዋን ቤት የራሱን ቤት ጉብታውን የኢየሩሳሌምን ቅጥር ሃጾርን መጊዶንና ጌዜርን እንዲገነቡ ስለመለመላቸው የግዳጅ ሥራ የሚሠሩ ሠራተኞች የሚገልጸው ዘገባ ይህ ነው16 የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ወጥቶ ጌዜርን ያዘ በእሳትም አቃጠላት በተጨማሪም በከተማዋ ውስጥ የሚኖሩትን ከነአናውያን ገደለ ከተማዋንም የሰለሞን ሚስት ለሆነችው ለልጁ ጎጆ መውጫ አድርጎ ሰጣት17 ሰለሞንም ጌዜርንና ታችኛውን ቤትሆሮንን ሠራ18 በተጨማሪም ባዓላትን በምድሩ በሚገኘው ምድረ በዳ ውስጥ ያለችውን ትዕማርን19 እንዲሁም የሰለሞንን የእህልና የዕቃ ማከማቻ ከተሞች በሙሉ የሠረገላ ከተሞቹን የፈረሰኞቹን ከተሞች እንዲሁም ሰለሞን በኢየሩሳሌም በሊባኖስና በእሱ ግዛት ውስጥ ባለው ምድር ሁሉ መገንባት የፈለጋቸውን ነገሮች በሙሉ ሠራ20 ከእስራኤላውያን ወገን ያልሆኑትን ከአሞራውያን ከሂታውያን ከፈሪዛውያን ከሂዋውያንና ከኢያቡሳውያን የተረፉትን ሕዝቦች በሙሉ21 ይኸውም እስራኤላውያን ፈጽመው ሊያጠፏቸው ያልቻሏቸውን በምድሪቱ ላይ የቀሩትን ዘሮቻቸውን ሰለሞን እንደ ባሪያ ሆነው የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ መልምሏቸው ነበር እስከ ዛሬም ድረስ ይሠራሉ22 ሆኖም ሰለሞን ከእስራኤላውያን መካከል አንዳቸውንም ባሪያ አላደረገም ምክንያቱም እነሱ ተዋጊዎቹ አገልጋዮቹ መኳንንቱ የጦር መኮንኖቹ እንዲሁም የሠረገለኞቹና የፈረሰኞቹ አለቆች ነበሩ23 ሰለሞን የሚያሠራውን ሥራ የሚከታተሉት ይኸውም ሥራውን የሚሠሩትን ሰዎች በቅርብ የሚቆጣጠሩት የበታች ተቆጣጣሪዎቹ አለቆች 550 ነበሩ24 የፈርዖን ሴት ልጅ ግን ከዳዊት ከተማ ወጥታ ሰለሞን ወዳሠራላት ወደ ራሷ ቤት መጣች ከዚያም ጉብታውን ሠራ25 ሰለሞን በዓመት ሦስት ጊዜ ለይሖዋ በሠራው መሠዊያ ላይ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችንና የኅብረት መሥዋዕቶችን ያቀርብ ነበር በተጨማሪም በይሖዋ ፊት በነበረው መሠዊያ ላይ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርብ ነበር ቤቱንም አጠናቀቀ26 እንዲሁም ንጉሥ ሰለሞን በኤዶም ምድር በቀይ ባሕር ዳርቻ በኤሎት አጠገብ በምትገኘው በዔጽዮንጋብር መርከቦችን ሠራ27 ኪራምም ከሰለሞን አገልጋዮች ጋር አብረው እንዲሠሩ አገልጋዮቹን ይኸውም ልምድ ያላቸውን ባሕረኞች ከእነዚህ መርከቦች ጋር ላከ28 እነሱም ወደ ኦፊር በመሄድ 420 ታላንት ወርቅ አምጥተው ለንጉሥ ሰለሞን ሰጡት
1 በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ በምትገኘው በራማታይምጾፊም የሚኖር ሕልቃና የተባለ አንድ ሰው ነበር ይህ ሰው ኤፍሬማዊ ሲሆን የጹፍ ልጅ የቶሁ ልጅ የኤሊሁ ልጅ የየሮሃም ልጅ ነበር2 እሱም ሁለት ሚስቶች ነበሩት የአንደኛዋ ስም ሐና ሲሆን የሌላኛዋ ደግሞ ፍናና ነበር ፍናና ልጆች ነበሯት ሐና ግን ምንም ልጅ አልነበራትም3 ያም ሰው አምልኮ ለማቅረብና ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ መሥዋዕት ለመሠዋት በየዓመቱ ከከተማው ወደ ሴሎ ይወጣ ነበር በዚያም ሁለቱ የኤሊ ልጆች ሆፍኒ እና ፊንሃስ ለይሖዋ ካህናት ሆነው ያገለግሉ ነበር4 አንድ ቀን ሕልቃና መሥዋዕት ሲያቀርብ ለሚስቱ ለፍናና እንዲሁም ለወንዶች ልጆቿና ለሴቶች ልጆቿ በሙሉ ድርሻቸውን ሰጣቸው5 ሆኖም ሐናን ይወዳት ስለነበር ልዩ የሆነ ድርሻ ሰጣት ይሁንና ይሖዋ ለሐና ልጅ አልሰጣትም ነበር6 በተጨማሪም ይሖዋ ልጅ ስላልሰጣት ጣውንቷ እሷን ለማበሳጨት ዘወትር ትሳለቅባት ነበር7 እሷም በየዓመቱ እንዲህ ታደርግባት ነበር ሐና ወደ ይሖዋ ቤት በወጣች ቁጥር እስክታለቅስና መብላት እስኪያቅታት ድረስ ጣውንቷ ትሳለቅባት ነበር8 ባሏ ሕልቃና ግን ሐና ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትበይም? ልብሽስ ለምን ያዝናል? ከአሥር ወንዶች ልጆች እኔ አልበልጥብሽም? አላት9 ከዚያም ሐና በሴሎ ከበሉና ከጠጡ በኋላ ተነሳች በዚህ ጊዜ ካህኑ ኤሊ በይሖዋ ቤተ መቅደስ መቃን አጠገብ ወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር10 እሷም በጣም ተማርራ ነበር ስቅስቅ ብላም እያለቀሰች ወደ ይሖዋ ትጸልይ ጀመር11 እንዲህም ስትል ተሳለች የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ አገልጋይህ እየደረሰባት ያለውን መከራ ተመልክተህ ብታስበኝና አገልጋይህን ሳትረሳት ወንድ ልጅ ብትሰጣት በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለይሖዋ እሰጠዋለሁ ራሱንም ምላጭ አይነካውም12 ሐና በይሖዋ ፊት ለረጅም ሰዓት ስትጸልይ ኤሊ አፏን ይመለከት ነበር13 ሐና የምትናገረው በልቧ ነበር በመሆኑም ከንፈሯ ሲንቀጠቀጥ ቢታይም ድምፅዋ አይሰማም ነበር በመሆኑም ኤሊ የሰከረች መሰለው14 ስለዚህ ስካሩ የማይለቅሽ እስከ መቼ ነው? የወይን ጠጅሽን መጠጣት ተይ አላት15 ሐናም መልሳ እንዲህ አለች አልሰከርኩም ጌታዬ! እኔ ብዙ ጭንቀት ያለብኝ ሴት ነኝ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም ይልቅስ ነፍሴን በይሖዋ ፊት እያፈሰስኩ ነው16 እኔ እስካሁን ድረስ እየተናገርኩ ያለሁት በውስጤ ካለው ብሶትና ጭንቀት የተነሳ ስለሆነ አገልጋይህን እንደማትረባ ሴት አትቁጠራት17 ከዚያም ኤሊ በሰላም ሂጂ የእስራኤል አምላክ የለመንሽውን ነገር ይስጥሽ አላት18 እሷም አገልጋይህ በፊትህ ሞገስ ታግኝ አለችው ከዚያም ተነስታ ሄደች ምግብም በላች ዳግመኛም በፊቷ ላይ ሐዘን አልታየም19 እነሱም በማለዳ ተነስተው በይሖዋ ፊት ሰገዱ ከዚያም በራማ ወደሚገኘው ቤታቸው ተመለሱ ሕልቃናም ከሚስቱ ከሐና ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጸመ ይሖዋም አሰባት20 ከዚያም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሐና ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች እሷም ከይሖዋ የለመንኩት ነው በማለት ስሙን ሳሙኤል አለችው21 ከጊዜ በኋላም ሕልቃና ለይሖዋ ዓመታዊውን መሥዋዕት ለመሠዋትና የስእለት መባውን ለማቅረብ ቤተሰቡን ሁሉ ይዞ ወጣ22 ሐና ግን አልወጣችም ምክንያቱም ለባሏ ሕፃኑ ጡት እንደጣለ አመጣዋለሁ እሱም ይሖዋ ፊት ይቀርባል ዕድሜውንም ሙሉ በዚያ ይኖራል በማለት ነግራው ነበር23 ባሏ ሕልቃናም መልካም መስሎ የታየሽን አድርጊ ልጁን ጡት እስክታስጥዪው ድረስ ቤት ሁኚ ይሖዋም ያልሽውን ይፈጽም ብሏት ነበር በመሆኑም ሐና ቤት ተቀመጠች ልጇንም ጡት እስክታስጥለው ድረስ ተንከባከበችው24 እሷም ልክ ልጁን ጡት እንዳስጣለችው ከልጁ ጋር የሦስት ዓመት ወይፈን አንድ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄትና አንድ እንስራ የወይን ጠጅ ይዛ ወጣች ልጁንም በሴሎ ወደሚገኘው ወደ ይሖዋ ቤት ይዛው መጣች25 እነሱም ወይፈኑን ካረዱ በኋላ ልጁን ወደ ኤሊ አመጡት26 እሷም እንዲህ አለች ጌታዬ ሆይ በሕያውነትህ እምላለሁ ጌታዬ ሆይ እኔ ወደ ይሖዋ ለመጸለይ ከአንተ ጋር እዚህ ቦታ ቆሜ የነበርኩት ሴት ነኝ27 ይህን ልጅ እንዲሰጠኝ ጸልዬ ነበር ይሖዋም የለመንኩትን ሰጠኝ28 እኔ ደግሞ በበኩሌ ልጁን ለይሖዋ እሰጠዋለሁ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ለይሖዋ የተሰጠ ይሆናልእሱም በዚያ ለይሖዋ ሰገደ
10 ሳሙኤልም የዘይት ዕቃውን አንስቶ ዘይቱን በሳኦል ራስ ላይ አፈሰሰው ከዚያም ሳመውና እንዲህ አለው በርስቱ ላይ መሪ እንድትሆን ይሖዋ ቀብቶህ የለም?2 ዛሬ ከእኔ ተለይተህ ስትሄድ በቢንያም ግዛት ውስጥ በምትገኘው በጸልጻህ ባለው የራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ እነሱም እንዲህ ይሉሃል ስትፈልጋቸው የነበሩት አህዮች ተገኝተዋል አባትህ ግን ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ ስለ እናንተ እየተጨነቀ ነው ደግሞም የልጄን ነገር ምን ባደርግ ይሻላል? እያለ ነው3 አንተም ከዚያ ተነስተህ ታቦር የሚገኘው ትልቅ ዛፍ አጠገብ እስክትደርስ ድረስ ጉዞህን ቀጥል እዚያም ሦስት ሰዎች በቤቴል ወደሚገኘው ወደ እውነተኛው አምላክ ሲወጡ ታገኛለህ እነሱም አንደኛው ሦስት የፍየል ግልገል ሌላኛው ሦስት ዳቦ ሌላኛው ደግሞ በእንስራ የወይን ጠጅ ይዘዋል4 እነዚህ ሰዎች ስለ ደህንነትህ ከጠየቁህ በኋላ ሁለት ዳቦ ይሰጡሃል አንተም ዳቦዎቹን ተቀበላቸው5 ከዚህ በኋላ የፍልስጤማውያን የጦር ሰፈር ወዳለበት ወደ እውነተኛው አምላክ ኮረብታ ትመጣለህ ወደ ከተማዋም በምትደርስበት ጊዜ ትንቢት እየተናገረ ከኮረብታው የሚወርድ አንድ የነቢያት ቡድን ታገኛለህ ከፊት ከፊቱም ባለ አውታር መሣሪያ አታሞ ዋሽንትና በገና የሚጫወቱ ሰዎች ይሄዳሉ6 የይሖዋ መንፈስ ኃይል ይሰጥሃል አንተም ከእነሱ ጋር ትንቢት ትናገራለህ ተለውጠህም እንደ ሌላ ሰው ትሆናለህ7 እነዚህ ምልክቶች ሲፈጸሙ ስታይ ማድረግ የምትችለውን ሁሉ አድርግ ምክንያቱም እውነተኛው አምላክ ከአንተ ጋር ነው8 ከዚያም ከእኔ ቀድመህ ወደ ጊልጋል ውረድ እኔም የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችንና የኅብረት መሥዋዕቶችን ለማቅረብ አንተ ወዳለህበት እወርዳለሁ እኔ ወደ አንተ እስክመጣ ድረስ ሰባት ቀን መጠበቅ አለብህ ከዚያም ምን ማድረግ እንዳለብህ አሳውቅሃለሁ9 ሳኦልም ከሳሙኤል ተለይቶ ለመሄድ ፊቱን ሲያዞር አምላክ የሳኦል ልብ ወደ ሌላ ሰው ልብ እንዲለወጥ አደረገ እነዚህም ሁሉ ምልክቶች በዚያው ቀን ተፈጸሙ10 በመሆኑም ከዚያ ተነስተው ወደ ኮረብታው ሄዱ አንድ የነቢያት ቡድንም አገኘው ወዲያውም የአምላክ መንፈስ ኃይል ሰጠው እሱም አብሯቸው ትንቢት መናገር ጀመረ11 ቀደም ሲል ያውቁት የነበሩት ሁሉ ከነቢያቱ ጋር ሆኖ ትንቢት ሲናገር ሲያዩት እርስ በርሳቸው የቂስ ልጅ ምን ሆኗል? ሳኦልም ከነቢያት አንዱ ሆነ እንዴ? ተባባሉ12 ከዚያም የአካባቢው ነዋሪ የሆነ አንድ ሰው ለመሆኑ የእነሱስ አባት ማን ነው? አለ ሳኦልም ከነቢያት አንዱ ሆነ እንዴ? የሚል ምሳሌያዊ አባባል የኖረው በዚህ የተነሳ ነው13 እሱም ትንቢት ተናግሮ ሲጨርስ ወደ ኮረብታው መጣ14 በኋላም የሳኦል አባት ወንድም ሳኦልንና አገልጋዩን የት ነበራችሁ? ሲል ጠየቃቸው ሳኦልም አህዮቹን ፍለጋ ሄደን ነበር ሆኖም በዚያ ልናገኛቸው ስላልቻልን ወደ ሳሙኤል ሄድን አለው15 የሳኦልም አጎት እስቲ ንገረኝ ሳሙኤል ምን አላችሁ? አለው16 ሳኦልም መልሶ አጎቱን አህዮቹ መገኘታቸውን በትክክል ነገረን አለው ይሁን እንጂ ሳሙኤል ስለ ንግሥና የነገረውን ነገር አልነገረውም17 ከዚያም ሳሙኤል ሕዝቡን በምጽጳ በይሖዋ ፊት እንዲሰበሰብ ከጠራ በኋላ18 እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል እስራኤልን ከግብፅ ያወጣሁት እንዲሁም ከግብፅ እጅና ይጨቁኗችሁ ከነበሩት መንግሥታት ሁሉ እጅ የታደግኳችሁ እኔ ነኝ19 ዛሬ ግን እናንተ ከመከራችሁና ከጭንቀታችሁ ሁሉ ያዳናችሁን አምላካችሁን አንቀበልም በማለት አይሆንም ንጉሥ እንዲነግሥልን እንፈልጋለን አላችሁ ስለዚህ አሁን በየነገዳችሁና በየሺህ ምድባችሁ ሆናችሁ በይሖዋ ፊት ቁሙ20 ስለዚህ ሳሙኤል የእስራኤል ነገዶች በሙሉ እንዲቀርቡ አደረገ ከእነሱም መካከል የቢንያም ነገድ ተመረጠ21 ከዚያም የቢንያም ነገድ በየቤተሰቡ ሆኖ እንዲቀርብ አደረገ የማጥራውያን ቤተሰብም ተመረጠ በመጨረሻም የቂስ ልጅ ሳኦል ተመረጠ ሆኖም ፈልገው ሊያገኙት አልቻሉም22 ስለዚህ ለመሆኑ ሰውየው እዚህ መጥቷል? በማለት ይሖዋን ጠየቁ ይሖዋም ያውላችሁ ጓዙ መካከል ተደብቋል አላቸው23 በመሆኑም ሮጠው ከዚያ አመጡት እሱም በሕዝቡ መካከል በቆመ ጊዜ ከትከሻው በላይ ዘለግ ብሎ በቁመት ከሌሎቹ ሰዎች ሁሉ በልጦ ይታይ ነበር24 ሳሙኤልም ሕዝቡን ሁሉ ይሖዋ የመረጠውን ሰው አያችሁት? ከሕዝቡ ሁሉ መካከል እንደ እሱ ያለ የለም አላቸው ሕዝቡም ሁሉ ንጉሡ ለዘላለም ይኑር! በማለት መጮኽ ጀመረ25 ሳሙኤልም ለነገሥታት ምን ሊደረግላቸው እንደሚገባ ለሕዝቡ ተናገረ እንዲሁም በመጽሐፍ ጽፎ በይሖዋ ፊት አስቀመጠው ከዚያም ሳሙኤል ሕዝቡን ሁሉ ወደየቤቱ አሰናበተ26 ሳኦልም ይሖዋ ልባቸውን ባነሳሳው ተዋጊዎች ታጅቦ በጊብዓ ወዳለው ቤቱ ሄደ27 አንዳንድ የማይረቡ ሰዎች ግን ይህ ሰው እንዴት ሊያድነን ይችላል? አሉ በመሆኑም ናቁት ምንም ዓይነት ስጦታም አላመጡለትም እሱ ግን ዝም አለ
11 ከዚያም አሞናዊው ናሃሽ ወጥቶ በጊልያድ የምትገኘውን ኢያቢስን ከበባት የኢያቢስ ሰዎች በሙሉ ናሃሽን ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን ግባ እኛም እናገለግልሃለን አሉት2 አሞናዊው ናሃሽም ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን የምገባው የእያንዳንዳችሁ ቀኝ ዓይን ከወጣ ነው ይህን የማደርገውም መላውን እስራኤል ለማዋረድ ስል ነው አላቸው3 የኢያቢስ ሽማግሌዎችም ወደ መላው የእስራኤል ግዛት መልእክተኞችን እንድንልክ የሰባት ቀን ጊዜ ስጠን ከዚያም የሚያድነን ሰው ከሌለ ለአንተ እጃችንን እንሰጣለን ሲሉ መለሱለት4 መልእክተኞቹም ሳኦል ወደሚገኝበት ወደ ጊብዓ መጥተው ይህን መልእክት ለሕዝቡ ተናገሩ ሕዝቡም ሁሉ ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ5 ሳኦል ግን መንጋውን እየነዳ ከመስክ በመምጣት ላይ ነበር ሳኦልም ሕዝቡ የሚያለቅሰው ምን ሆኖ ነው? አለ እነሱም የኢያቢስ ሰዎች ያሏቸውን ነገሩት6 ሳኦልም ይህን ሲሰማ የአምላክ መንፈስ ኃይል ሰጠው ቁጣውም ነደደ7 እሱም ጥንድ በሬዎችን ወስዶ ቆራረጣቸው እነዚህንም በመልእክተኞቹ እጅ አስይዞ ሳኦልንና ሳሙኤልን የማይከተል ማንኛውም ሰው ከብቱ እንዲህ ይቆራረጣል! በማለት እንዲናገሩ ወደ መላው የእስራኤል ግዛት ላካቸው በሕዝቡም ላይ የይሖዋ ፍርሃት ስለወደቀ ሕዝቡ እንደ አንድ ሰው ሆኖ ወጣ8 ከዚያም ሳኦል ሰዎቹን ቤዜቅ ላይ ቆጠራቸው እነሱም 300,000 እስራኤላውያንና 30,000 የይሁዳ ሰዎች ነበሩ9 የመጡትንም መልእክተኞች እንዲህ አሏቸው በጊልያድ ባለችው በኢያቢስ የሚኖሩትን ሰዎች በነገው ዕለት ፀሐይዋ በምትከርበት ጊዜ መዳን ታገኛላችሁ በሏቸው ከዚያም መልእክተኞቹ መጥተው ለኢያቢስ ሰዎች ነገሯቸው እነሱም በደስታ ፈነደቁ10 ስለሆነም የኢያቢስ ሰዎች ነገ እጃችንን ለእናንተ እንሰጣለን እናንተም መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ ልታደርጉብን ትችላላችሁ አሏቸው11 በማግስቱ ሳኦል ሕዝቡን በሦስት ቡድን ከፈለው እነሱም በማለዳው ክፍለ ሌሊት ወደ አሞናውያን ሰፈር ገብተው ፀሐይዋ እስክትከር ድረስ መቷቸው የተረፉትም ቢሆኑ ሁለቱ እንኳ አንድ ላይ መሆን እስከማይችሉ ድረስ ተበታተኑ12 ከዚያም ሕዝቡ ሳሙኤልን አሁን ሳኦል በእኛ ላይ ንጉሥ ሊሆን ነው? ሲሉ የነበሩት እነማን ናቸው? እነዚህን ሰዎች ስጡንና እንግደላቸው አለው13 ሳኦል ግን ይህ ዕለት ይሖዋ እስራኤልን ያዳነበት ስለሆነ በዚህ ቀን ማንም ሰው መገደል የለበትም አለ14 በኋላም ሳሙኤል ሕዝቡን ኑ ወደ ጊልጋል እንውጣና ንግሥናውን እንደገና እናጽና አለ15 በመሆኑም ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጊልጋል ሄደ በጊልጋልም ሳኦልን በይሖዋ ፊት አነገሡት በዚያም በይሖዋ ፊት የኅብረት መሥዋዕቶችን አቀረቡ ሳኦልና የእስራኤል ሰዎች ሁሉ እጅግ ተደሰቱ
12 በመጨረሻም ሳሙኤል እስራኤላውያንን ሁሉ እንዲህ አላቸው እንግዲህ እኔ ያላችሁኝን ሁሉ አድርጌአለሁ የሚገዛችሁም ንጉሥ አንግሼላችኋለሁ2 የሚመራችሁ ንጉሥ ይኸው! እኔ ዕድሜዬ ገፍቷል ፀጉሬም ሸብቷል እነሆ ልጆቼ አብረዋችሁ ናቸው እኔ እንደሆንኩ ከልጅነቴ ጀምሮ እስከዚህ ቀን ድረስ ስመራችሁ ቆይቻለሁ3 አሁንም ያለሁት በፊታችሁ ነው እስቲ የምከሰስበት ነገር ካለ በይሖዋና እሱ በቀባው ፊት ንገሩኝ የማንን በሬ ወይም የማንን አህያ ወስጃለሁ? ወይስ ማንን አታልያለሁ? ደግሞስ በማን ላይ ግፍ ፈጽሜአለሁ? አይቼ እንዳላየሁ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀብያለሁ? እንዲህ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ4 በዚህ ጊዜ እነሱ አታለኸንም ሆነ ግፍ ፈጽመህብን ወይም ደግሞ ከማንም ሰው እጅ ምንም ነገር ተቀብለህ አታውቅም አሉት5 በመሆኑም ሳሙኤል እኔን የምትከሱበት ምንም ነገር እንዳላገኛችሁ ይሖዋም ሆነ እሱ የቀባው ዛሬ በእናንተ ላይ ምሥክሮች ናቸው አላቸው እነሱም እሱ ምሥክር ነው አሉ6 ሳሙኤልም ለሕዝቡ እንዲህ አለ ሙሴንና አሮንን የመረጠው እንዲሁም አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር ያወጣው ይሖዋ ምሥክር ነው7 እንግዲህ እናንተ ባላችሁበት ቁሙ እኔም ይሖዋ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ ባደረጋቸው የጽድቅ ሥራዎች መሠረት በይሖዋ ፊት እፋረዳችኋለሁ8 ያዕቆብ ወደ ግብፅ በገባና አባቶቻችሁም ይሖዋ እንዲረዳቸው በጮኹ ጊዜ ይሖዋ አባቶቻችሁን ከግብፅ መርተው እንዲያወጧቸውና በዚህ ስፍራ እንዲያኖሯቸው ሙሴንና አሮንን ላከ9 እነሱ ግን አምላካቸውን ይሖዋን ረሱ እሱም የሃጾር ሠራዊት አለቃ ለነበረው ለሲሳራ ለፍልስጤማውያንና ለሞዓብ ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሸጣቸው እነሱም ወጓቸው10 በዚህ ጊዜ ይሖዋ እንዲረዳቸው ጮኹ እንዲህም አሉ ባአልንና የአስታሮትን ምስሎች ለማገልገል ስንል ይሖዋን ስለተውን ኃጢአት ሠርተናል ስለሆነም እንድናገለግልህ አሁን ከጠላቶቻችን እጅ ታደገን11 ከዚያም ይሖዋ ያለስጋት መኖር እንድትችሉ የሩባአልን ቤዳንን ዮፍታሔንና ሳሙኤልን ልኮ በዙሪያችሁ ካሉት ጠላቶቻችሁ ሁሉ እጅ ታደጋችሁ12 የአሞናውያን ንጉሥ የሆነው ናሃሽ በእናንተ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እንደመጣ ስታዩ ምንም እንኳ አምላካችሁ ይሖዋ ንጉሣችሁ ቢሆንም አይሆንም ንጉሥ እንዲነግሥልን እንፈልጋለን! አላችሁኝ13 እንግዲህ የመረጣችሁትና የጠየቃችሁት ንጉሥ ይኸውላችሁ እነሆ ይሖዋ በላያችሁ ንጉሥ አንግሦአል14 ይሖዋን ብትፈሩና ብታገለግሉ ቃሉን ብትታዘዙና በይሖዋ ትእዛዝ ላይ ባታምፁ እንዲሁም እናንተም ሆናችሁ በላያችሁ የሚገዛው ንጉሥ አምላካችሁን ይሖዋን ብትከተሉ መልካም ይሆንላችኋል15 ሆኖም የይሖዋን ቃል ባትታዘዙና በይሖዋ ትእዛዝ ላይ ብታምፁ የይሖዋ እጅ በእናንተና በአባቶቻችሁ ላይ ይሆናል16 ስለሆነም አሁን ባላችሁበት ቆማችሁ ይሖዋ ዓይናችሁ እያየ የሚፈጽመውን ይህን ታላቅ ነገር ተመልከቱ17 ዛሬ የስንዴ መከር የሚታጨድበት ጊዜ አይደለም? ይሖዋን ነጎድጓድና ዝናብ እንዲልክ እጠይቀዋለሁ እናንተም ንጉሥ እንዲነግሥላችሁ በመጠየቅ በይሖዋ ፊት ምን ያህል ታላቅ በደል እንደፈጸማችሁ ታውቃላችሁ ደግሞም ታስተውላላችሁ18 ከዚያም ሳሙኤል ይሖዋን ጠየቀ ይሖዋም በዚያ ቀን ነጎድጓድና ዝናብ ላከ በመሆኑም ሕዝቡ ሁሉ ይሖዋንና ሳሙኤልን እጅግ ፈራ19 ሕዝቡም ሳሙኤልን ሌላው ኃጢአታችን ሳያንሰን ንጉሥ እንዲነግሥልን በመለመን ተጨማሪ በደል ስለፈጸምን እንዳንሞት ስለ አገልጋዮችህ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ጸልይልን አለው20 በመሆኑም ሳሙኤል ሕዝቡን እንዲህ አለ አትፍሩ እርግጥ ይህን ሁሉ ክፋት ፈጽማችኋል ብቻ ይሖዋን ከመከተል ዞር አትበሉ ይሖዋንም በሙሉ ልባችሁ አገልግሉት21 ምንም ዋጋ የሌላቸውንና ማዳን የማይችሉ ከንቱ ነገሮችን ወደ መከተል ዞር አትበሉ ምክንያቱም እነሱ ከንቱ ነገሮች ናቸው22 ይሖዋ ስለ ታላቁ ስሙ ሲል ሕዝቡን አይተውም ምክንያቱም ይሖዋ እናንተን የራሱ ሕዝብ ሊያደርጋችሁ ፈልጓል23 እኔም ብሆን ስለ እናንተ መጸለዬን በመተው በይሖዋ ላይ ኃጢአት መሥራት ፈጽሞ የማላስበው ነገር ነው እንዲሁም መልካምና ትክክለኛ የሆነውን መንገድ እናንተን ማስተማሬን እቀጥላለሁ24 ብቻ እናንተ ይሖዋን ፍሩ በሙሉ ልባችሁም በታማኝነት አገልግሉት ለእናንተ ያደረጋቸውን ታላላቅ ነገሮች አስታውሱ25 ሆኖም በግትርነት መጥፎ ነገር ማድረጋችሁን ብትቀጥሉ እናንተም ሆናችሁ ንጉሣችሁ ተጠራርጋችሁ ትጠፋላችሁ
13 ሳኦል በነገሠ ጊዜ ዕድሜው . . . ነበር እሱም በእስራኤል ላይ ሁለት ዓመት ገዛ2 ሳኦል ከእስራኤላውያን መካከል 3,000 ሰዎችን መረጠ ከእነዚህም መካከል 2,000ዎቹ በሚክማሽና በቤቴል ተራራማ አካባቢ ከሳኦል ጋር ሆኑ ሌሎቹ 1,000 ሰዎች ደግሞ በቢንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋር ሆኑ የቀሩትን ሰዎች እያንዳንዳቸውን ወደየድንኳናቸው አሰናበታቸው3 ዮናታንም በጌባ የነበረውን የፍልስጤማውያንን የጦር ሰፈር መታ ፍልስጤማውያንም ይህን ሰሙ ሳኦልም ዕብራውያን ይስሙ! በማለት በምድሩ ሁሉ ቀንደ መለከት አስነፋ4 እስራኤላውያን በሙሉ ሳኦል የፍልስጤማውያንን የጦር ሰፈር መታ እስራኤላውያንም በፍልስጤማውያን ዘንድ እንደ ግም ተቆጠሩ ሲባል ሰሙ በመሆኑም ሕዝቡ ሳኦልን ለመከተል በጊልጋል ተሰበሰበ5 ፍልስጤማውያንም 30,000 የጦር ሠረገሎች 6,000 ፈረሰኞችና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ እጅግ ብዙ የሆነ ሠራዊት ይዘው ከእስራኤላውያን ጋር ለመዋጋት ተሰባሰቡ እነሱም ወጥተው ከቤትአዌን በስተ ምሥራቅ በሚክማሽ ሰፈሩ6 የእስራኤል ሰዎችም አደጋ እንደተጋረጠባቸው ስላዩ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ገብተው ነበር በመሆኑም ሕዝቡ በየዋሻው በየጉድጓዱ በየዓለቱ በየጎሬውና በየውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓዱ ውስጥ ተደበቀ7 እንዲያውም አንዳንድ ዕብራውያን ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ጋድና ወደ ጊልያድ ምድር ሄዱ ሳኦል ግን እዚያው ጊልጋል ነበር የተከተሉት ሰዎችም ሁሉ በፍርሃት ይንቀጠቀጡ ነበር8 እሱም ሳሙኤል የቀጠረው ጊዜ እስኪደርስ ድረስ ለሰባት ቀን ጠበቀ ሳሙኤል ግን ወደ ጊልጋል አልመጣም ሕዝቡም ሳኦልን ትቶ መበታተን ጀመረ9 በመጨረሻም ሳኦል የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕቶቹን አምጡልኝ አለ ከዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ10 ሆኖም ሳኦል የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቅርቦ እንደጨረሰ ሳሙኤል መጣ በመሆኑም ሳኦል ሊቀበለውና ሊባርከው ወጣ11 ከዚያም ሳሙኤል ያደረግከው ነገር ምንድን ነው? አለው ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰ ሕዝቡ ትቶኝ መበታተን እንደጀመረና አንተም በተቀጠረው ጊዜ እንዳልመጣህ እንዲሁም ፍልስጤማውያኑ በሚክማሽ እየተሰባሰቡ መሆናቸውን አየሁ12 በመሆኑም እንግዲህ ፍልስጤማውያን ወደ ጊልጋል ወርደው ሊወጉኝ ነው እኔ ደግሞ ይሖዋ ሞገስ እንዲያሳየኝ አለመንኩም ብዬ አሰብኩ ስለሆነም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ማቅረብ ግድ ሆነብኝ13 በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው የፈጸምከው የሞኝነት ድርጊት ነው አምላክህ ይሖዋ የሰጠህን ትእዛዝ አልጠበቅክም ጠብቀህ ቢሆን ኖሮ ይሖዋ መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም ባጸናልህ ነበር14 አሁን ግን መንግሥትህ አይዘልቅም ይሖዋ እንደ ልቡ የሚሆንለት ሰው ያገኛል ይሖዋም በሕዝቡ ላይ መሪ አድርጎ ይሾመዋል ምክንያቱም አንተ የይሖዋን ትእዛዝ አልጠበቅክም15 ከዚያም ሳሙኤል ተነስቶ ከጊልጋል በቢንያም ግዛት ወደምትገኘው ወደ ጊብዓ ወጣ ሳኦልም ሕዝቡን ቆጠረ አብረውት ያሉት ሰዎች ብዛታቸው 600 ገደማ ነበር16 ሳኦልና ልጁ ዮናታን እንዲሁም አብረዋቸው የቀሩት ሰዎች በቢንያም ግዛት በምትገኘው በጌባ ሰፍረው የነበረ ሲሆን ፍልስጤማውያን ደግሞ በሚክማሽ ሰፍረው ነበር17 በሦስት ምድብ የተከፈለው የወራሪዎች ቡድን ከፍልስጤማውያን ሰፈር ይወጣል አንደኛው ቡድን ወደ ሹአል ምድር ወደ ኦፍራ ወደሚወስደው መንገድ ያቀናል18 ሌላኛው ቡድን ወደ ቤትሆሮን ወደሚወስደው መንገድ ይሄዳል ሦስተኛው ቡድን ደግሞ የጸቦይምን ሸለቆ ቁልቁል ወደሚያሳየው ወሰን ይኸውም ወደ ምድረ በዳው ወደሚወስደው መንገድ ያቀናል19 በመላው የእስራኤል ምድር አንድም ብረት ቀጥቃጭ አልነበረም ምክንያቱም ፍልስጤማውያን ዕብራውያን ሰይፍ ወይም ጦር እንዳይሠሩ ብለው ነበር20 ስለዚህ እስራኤላውያን በሙሉ ማረሻቸውን ወይም ዶማቸውን አሊያም መጥረቢያቸውን ወይም ማጭዳቸውን ለማሳል ወደ ፍልስጤማውያን ይወርዱ ነበር21 ማረሻ ዶማ መንሽና መጥረቢያ ለማሳል እንዲሁም የበሬ መውጊያ ለማሳሰር ዋጋው አንድ ፊም ነበር22 ውጊያው በተደረገበት ቀን ከሳኦልና ከዮናታን ጋር ባሉት ሰዎች እጅ አንድም ሰይፍ ወይም ጦር አልተገኘም መሣሪያ የነበራቸው ሳኦልና ልጁ ዮናታን ብቻ ነበሩ23 በዚህ ጊዜ አንደኛው የፍልስጤማውያን ጦር በሚክማሽ ወደሚገኝ ጠባብ ሸለቆ ወጥቶ ነበር
14 አንድ ቀን የሳኦል ልጅ ዮናታን ጋሻ ጃግሬውን ና በዚያ በኩል ወዳለው የፍልስጤማውያን የጦር ሰፈር እንሻገር አለው ይህን ግን ለአባቱ አልነገረውም2 ሳኦልም በጊብዓ ዳርቻ በሚግሮን በሚገኘው የሮማን ዛፍ ሥር ሰፍሮ ነበር ከእሱም ጋር 600 ሰዎች ነበሩ3 በሴሎ የይሖዋ ካህን የሆነው የኤሊ ልጅ የፊንሃስ ልጅ የኢካቦድ ወንድም የአኪጡብ ልጅ አኪያህ ኤፉድ ለብሶ ነበር ሕዝቡም ዮናታን መሄዱን አላወቀም4 ዮናታን ወደ ፍልስጤማውያን የጦር ሰፈር ለመሻገር ባሰበባቸው መተላለፊያዎች መካከል በአንደኛው በኩል እንደ ጥርስ የሾለ ዓለት በሌላኛውም በኩል እንደ ጥርስ የሾለ ዓለት ነበር የአንደኛው ስም ቦጼጽ ሲሆን የሌላኛው ስም ደግሞ ሴኔ ነበር5 አንደኛው ዓለት በሚክማሽ ትይዩ በስተ ሰሜን እንደ ዓምድ ቆሞ ነበር ሌላኛው ደግሞ በጊብዓ ትይዩ በስተ ደቡብ ቆሞ ነበር6 በመሆኑም ዮናታን ጋሻ ጃግሬውን ና ወደ እነዚህ ያልተገረዙ ሰዎች የጦር ሰፈር እንሻገር ይሖዋ በብዙም ሆነ በጥቂት ሰዎች ተጠቅሞ ከማዳን የሚያግደው ነገር ስለሌለ ምናልባት ይሖዋ ስለ እኛ ሲል እርምጃ ይወስድ ይሆናል አለው7 በዚህ ጊዜ ጋሻ ጃግሬው ልብህ ያነሳሳህን ማንኛውንም ነገር አድርግ ወደፈለግክበት ሂድ እኔም ልብህ ወዳነሳሳህ ወደየትኛውም ቦታ ተከትዬህ እሄዳለሁ አለው8 ከዚያም ዮናታን እንዲህ አለው እንግዲያውስ ወደ እነዚያ ሰዎች እንሻገርና እንታያቸው9 እነሱም ወደ እናንተ እስክንመጣ ድረስ ባላችሁበት ጠብቁን ካሉን ባለንበት ሆነን እንጠብቃቸዋለን ወደ እነሱም አንወጣም10 ይሁንና ውጡና ግጠሙን! ካሉን ወደዚያ እንወጣለን ምክንያቱም ይሖዋ እነሱን በእጃችን አሳልፎ ይሰጠናል እንግዲህ ይህ ምልክት ይሆነናል11 ከዚያም ሁለቱ ወጥተው ለፍልስጤማውያን የጦር ሰፈር ታዩ ፍልስጤማውያኑም አያችሁ ዕብራውያኑ ከተደበቁባቸው ጉድጓዶች እየወጡ ነው አሉ12 በመሆኑም በጦር ሰፈሩ የነበሩት ሰዎች ዮናታንንና ጋሻ ጃግሬውን ኑ ወደ እኛ ውጡ እናሳያችኋለን! አሏቸው ዮናታንም ወዲያውኑ ጋሻ ጃግሬውን ይሖዋ እስራኤላውያን እጅ ላይ ስለሚጥላቸው ተከተለኝ አለው13 ዮናታንም በእጁና በእግሩ እየቧጠጠ ወጣ ጋሻ ጃግሬውም ይከተለው ነበር ዮናታንም በፍልስጤማውያን ላይ ጥቃት ሰነዘረ ጋሻ ጃግሬውም ከኋላው እየተከተለ ገደላቸው14 ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው መጀመሪያ ላይ በሰነዘሩት ጥቃት አንድ ጥማድ በሚያውል የእርሻ መሬት ላይ ግማሽ ትልም በሚያህል ቦታ 20 ሰው ገደሉ15 ከዚያም በእርሻው ውስጥ በሰፈረው ሠራዊትና በጦር ሰፈሩ ውስጥ በነበረው ሕዝብ ሁሉ መካከል ሽብር ተነዛ ሌላው ቀርቶ ወራሪ ቡድኖቹ እንኳ ተሸበሩ ምድሪቱም መንቀጥቀጥ ጀመረች ከአምላክ የመጣ ሽብርም ወረደባቸው16 በቢንያም ግዛት በምትገኘው በጊብዓ የነበሩት የሳኦል ጠባቂዎችም በየአቅጣጫው ሁከት መሰራጨቱን አዩ17 ሳኦልም አብረውት የነበሩትን ሰዎች እስቲ ሕዝቡን ቁጠሩና ትቶን የሄደው ማን እንደሆነ እወቁ አላቸው እነሱም ሲቆጥሩ ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው እዚያ እንዳልነበሩ ተረዱ18 ሳኦልም አኪያህን የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ወደዚህ አምጣ! አለው በዚያ ጊዜ የእውነተኛው አምላክ ታቦት በእስራኤላውያን ዘንድ ነበር19 ሳኦል ካህኑን እያነጋገረ ሳለ በፍልስጤማውያን ሰፈር የነበረው ትርምስ ይበልጥ እየጨመረ ሄደ ከዚያም ሳኦል ካህኑን እያደረግክ ያለኸውን ነገር ተው አለው20 በመሆኑም ሳኦልና አብረውት የነበሩት ሰዎች በሙሉ ተሰባስበው ውጊያው ወደሚደረግበት ቦታ ሄዱ እዚያ ሲደርሱም ፍልስጤማውያኑ እርስ በርሳቸው በሰይፍ ሲጨፋጨፉ አገኟቸው ከፍተኛ ትርምስ ተፈጥሮ ነበር21 ቀደም ሲል ከፍልስጤማውያን ጋር ወግነው የነበሩትና አብረዋቸው ወደ ሰፈሩ የመጡት ዕብራውያንም በሳኦልና በዮናታን ሥር ከነበሩት እስራኤላውያን ጋር ተቀላቀሉ22 በተጨማሪም በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ ተደብቀው የነበሩት የእስራኤል ሰዎች በሙሉ ፍልስጤማውያን እየሸሹ መሆኑን ሰሙ እነሱም ከሌሎቹ ጋር በመተባበር ፍልስጤማውያንን ማሳደዱን ተያያዙት23 በዚህ መንገድ ይሖዋ በዚያ ቀን እስራኤልን አዳነ ውጊያውም እስከ ቤትአዌን ድረስ ዘለቀ24 ሆኖም ሳኦል ጠላቶቼን ከመበቀሌ በፊት እስከ ማታ ድረስ እህል የሚቀምስ ሰው የተረገመ ይሁን! በማለት ሕዝቡን አስምሎ ስለነበር በዚያ ዕለት የእስራኤል ሰዎች ተጨንቀው ዋሉ በመሆኑም ከሕዝቡ መካከል አንድም ሰው እህል አልቀመሰም25 ሕዝቡም ሁሉ ወደ ጫካው ገባ መሬቱም ላይ ማር ነበር26 ሕዝቡም ወደ ጫካው ሲገባ ማሩ ሲንጠባጠብ አየ ሆኖም ሁሉም መሐላውን ስለፈሩ እጁን ወደ አፉ ያነሳ አንድም ሰው አልነበረም27 ዮናታን ግን አባቱ ሕዝቡን ሲያስምል አልሰማም ነበር በመሆኑም በእጁ የነበረውን በትር ዘርግቶ ጫፉን የማር እንጀራው ውስጥ አጠቀሰ ከዚያም እጁን ወደ አፉ ሲመልስ ዓይኑ በራ28 በዚህ ጊዜ ከሕዝቡ መካከል አንዱ አባትህ እኮ በዛሬው ዕለት እህል የሚቀምስ ሰው የተረገመ ይሁን! በማለት ሕዝቡን በጥብቅ አስምሏል ሕዝቡ በጣም የተዳከመው ለዚህ ነው አለው29 ዮናታን ግን እንዲህ አለ አባቴ በምድሪቱ ላይ ከባድ ችግር አምጥቷል እኔ ይህችን ማር በመቅመሴ ዓይኖቼ እንዴት እንደበሩ እስቲ ተመልከቱ30 ሕዝቡ ከጠላቶቻቸው ከወሰዱት ምርኮ ዛሬ በነፃነት በልተው ቢሆን ኖሮ ምንኛ የተሻለ ይሆን ነበር! የተገደሉት ፍልስጤማውያንም ቁጥር ከዚህ እጅግ በበለጠ ነበር31 በዚያም ዕለት ፍልስጤማውያንን ከሚክማሽ አንስተው እስከ አይሎን ድረስ መቷቸው ሕዝቡም በጣም ተዳከመ32 ስለሆነም ሕዝቡ ምርኮውን በመስገብገብ ተሻምቶ ወሰደ በጎችን ከብቶችንና ጥጆችን ወስደው መሬት ላይ አረዷቸው ሥጋውንም ከነደሙ በሉት33 በመሆኑም ሳኦል ይኸው ሕዝቡ ሥጋውን ከነደሙ በመብላት በይሖዋ ላይ ኃጢአት እየሠራ ነው ተብሎ ተነገረው እሱም በዚህ ጊዜ እምነት እንደሌላችሁ የሚያሳይ ድርጊት ፈጽማችኋል በሉ አሁኑኑ አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባላችሁ አምጡልኝ አለ34 አክሎም እንዲህ አለ በሕዝቡ መሃል ተበታትናችሁ እንዲህ በሏቸው እያንዳንዳችሁ በሬያችሁንና በጋችሁን አምጡ በዚህም ስፍራ አርዳችሁ ብሉ ሥጋውን ከነደሙ በመብላት በይሖዋ ላይ ኃጢአት አትሥሩ በመሆኑም በዚያ ምሽት እያንዳንዱ ሰው በሬውን አምጥቶ በዚያ ስፍራ አረደው35 ሳኦልም ለይሖዋ መሠዊያ ሠራ ይህ መሠዊያ ሳኦል ለይሖዋ የሠራው የመጀመሪያ መሠዊያ ነው36 በኋላም ሳኦል በሌሊት ፍልስጤማውያንን ተከታትለን በመውረድ እስኪነጋ ድረስ እንበዝብዛቸው አንድም ሰው በሕይወት አናስተርፍም አለ በዚህ ጊዜ ሕዝቡ መልካም መስሎ የታየህን ማንኛውንም ነገር አድርግ አሉት ከዚያም ካህኑ እዚሁ ወደ እውነተኛው አምላክ እንቅረብ አለ37 ሳኦልም ፍልስጤማውያንን ተከትዬ ልውረድ? በእስራኤላውያን እጅ እንዲወድቁ ታደርጋለህ? በማለት አምላክን ጠየቀ አምላክ ግን በዚያ ዕለት አልመለሰለትም38 በመሆኑም ሳኦል እንዲህ አለ እናንተ የሕዝቡ አለቆች ሁሉ ወደዚህ ቅረቡ በዛሬው ዕለት ምን ኃጢአት እንደተፈጸመ አጣሩ39 እስራኤልን ባዳነው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ ይህን ኃጢአት የሠራው ልጄ ዮናታን ሆኖ ቢገኝ እንኳ መሞት አለበት ሆኖም ከሕዝቡ መካከል መልስ የሰጠው አንድም ሰው አልነበረም40 ከዚያም እስራኤላውያንን በሙሉ እናንተ በአንድ በኩል ትሆናላችሁ እኔና ልጄ ዮናታን ደግሞ በሌላኛው በኩል እንሆናለን አላቸው በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሳኦልን መልካም መስሎ የታየህን ማንኛውንም ነገር አድርግ አለው41 ሳኦልም ይሖዋን የእስራኤል አምላክ ሆይ በቱሚም አማካኝነት መልስ ስጠን! አለው ከዚያም ዮናታንና ሳኦል ተመረጡ ሕዝቡም ነፃ ሆነ42 በዚህ ጊዜ ሳኦል ከእኔና ከልጄ ከዮናታን ማን እንደሆነ ለመለየት ዕጣ ጣሉ አለ ዕጣውም በዮናታን ላይ ወጣ43 ሳኦልም ዮናታንን ንገረኝ ያደረግከው ነገር ምንድን ነው? አለው በመሆኑም ዮናታን በእጄ ይዤው በነበረው በትር ጫፍ ትንሽ ማር ቀምሻለሁ እንግዲህ ይኸው ለመሞት ዝግጁ ነኝ! በማለት መለሰለት44 በዚህ ጊዜ ሳኦል ዮናታን እንደው አንተ ካልሞትክ አምላክ ይፍረድብኝ የከፋም ነገር ያድርግብኝ አለ45 ሕዝቡ ግን ሳኦልን እንዲህ አለው ለእስራኤል ይህን ታላቅ ድል ያስገኘው ዮናታን መሞት ይገባዋል? ይሄማ ፈጽሞ የማይሆን ነገር ነው! ሕያው በሆነው በይሖዋ እንምላለን ከራስ ፀጉሩ አንዷ እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም ምክንያቱም በዚህ ዕለት ይህን ያደረገው ከአምላክ ጋር ሆኖ ነው በዚህ መንገድ ሕዝቡ ዮናታንን ታደገው እሱም ከሞት ዳነ46 ሳኦልም ፍልስጤማውያንን ማሳደዱን ተወ ፍልስጤማውያንም ወደ ክልላቸው ሄዱ47 ሳኦልም በእስራኤል ላይ ንግሥናውን አጸና በዙሪያው ከነበሩት ጠላቶቹ ማለትም ከሞዓባውያን ከአሞናውያን ከኤዶማውያን ከጾባህ ነገሥታትና ከፍልስጤማውያን ጋር ተዋጋ በሄደበትም ሁሉ ድል ያደርጋቸው ነበር48 እንዲሁም በጀግንነት በመዋጋት አማሌቃውያንን ድል አደረገ እስራኤላውያንንም ከዘራፊዎቻቸው እጅ አዳነ49 የሳኦል ወንዶች ልጆች ዮናታን ይሽዊ እና ሜልኪሳ ነበሩ እሱም ሁለት ሴቶች ልጆች የነበሩት ሲሆን የትልቋ ስም ሜሮብ የትንሿ ደግሞ ሜልኮል ነበር50 የሳኦል ሚስት የአኪማዓስ ልጅ አኪኖዓም ነበረች የሠራዊቱ አዛዥ ደግሞ አበኔር ሲሆን እሱም የሳኦል አጎት የኔር ልጅ ነበር51 የሳኦል አባት ቂስ ነበር የአበኔር አባት ኔር ደግሞ የአቢዔል ልጅ ነበር52 በሳኦል ዘመን ሁሉ ከፍልስጤማውያን ጋር ከባድ ውጊያ ይደረግ ነበር ሳኦልም ብርቱ ወይም ደፋር ሰው ሲያገኝ ወደ ሠራዊቱ እንዲቀላቀል ይመለምለው ነበር
15 ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው ይሖዋ በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጌ እንድቀባህ የላከው እኔን ነበር እንግዲህ አሁን ይሖዋ ምን እንደሚል ስማ2 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል እስራኤላውያን ከግብፅ በወጡ ጊዜ በመንገድ ላይ እነሱን በመቃወም ለፈጸሙት ድርጊት አማሌቃውያንን እቀጣቸዋለሁ3 በል አሁን ሂድ አማሌቃውያንን ምታቸው እነሱንም ካላቸው ነገር ሁሉ ጋር ፈጽመህ አጥፋቸው አንዳቸውንም አታስቀር ወንድም ሆነ ሴት ልጅም ሆነ ሕፃን በሬም ሆነ በግ ግመልም ሆነ አህያ ሁሉንም ግደል4 ሳኦልም ሕዝቡን በጤላይም ሰብስቦ ቆጠረ በዚያም 200,000 እግረኛ ወታደሮችና 10,000 የይሁዳ ሰዎች ነበሩ5 ከዚያም ሳኦል እስከ አማሌቃውያን ከተማ ድረስ በመጠጋት በሸለቆው ውስጥ አደፈጠ6 ሳኦልም ቄናውያንን ከአማሌቃውያን ጋር አብሬ እንዳላጠፋችሁ ሂዱ ከእነሱ መካከል ውጡ ምክንያቱም እናንተ እስራኤላውያን ከግብፅ በወጡበት ጊዜ ለሕዝቡ በሙሉ ታማኝ ፍቅር አሳይታችኋል አላቸው በመሆኑም ቄናውያን ከአማሌቃውያን መካከል ወጡ7 ከዚያም ሳኦል አማሌቃውያንን ከሃዊላ አንስቶ በግብፅ አጠገብ እስከምትገኘው እስከ ሹር ድረስ መታቸው8 እሱም የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን ከነሕይወቱ ማረከው የቀረውን ሕዝብ ሁሉ ግን በሰይፍ ፈጽሞ አጠፋ9 ሆኖም ሳኦልና ሕዝቡ አጋግን እንዲሁም ከመንጋው ከከብቱ ከደለቡት እንስሳትና ከአውራ በጎቹ መካከል ምርጥ የሆኑትንና ጥሩ ጥሩ የሆነውን ነገር ሁሉ ሳያጠፉ ተዉ እነዚህን ሊያጠፏቸው አልፈለጉም የማይረባውንና የማይፈለገውን ነገር ሁሉ ግን ፈጽመው አጠፉ10 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሳሙኤል መጣ11 ሳኦልን ንጉሥ በማድረጌ ተጸጽቻለሁ ምክንያቱም እሱ እኔን ከመከተል ዞር ብሏል ቃሌንም አልፈጸመም ሳሙኤልም በጣም ስለተረበሸ ሌሊቱን ሙሉ ወደ ይሖዋ ሲጮኽ አደረ12 ሳሙኤል ሳኦልን ለማግኘት በማለዳ ተነስቶ ሲሄድ ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ ሄዶ በዚያ ለራሱ የመታሰቢያ ሐውልት አቁሟል ከዚያም ተመልሶ ወደ ጊልጋል ወርዷል ተብሎ ተነገረው13 በመጨረሻም ሳሙኤል ወደ ሳኦል ሲመጣ ሳኦል ይሖዋ ይባርክህ የይሖዋን ቃል ፈጽሜአለሁ አለው14 ሳሙኤል ግን ታዲያ ይህ በጆሮዬ የምሰማው የበጎችና የከብቶች ድምፅ ምንድን ነው? አለው15 በዚህ ጊዜ ሳኦል ሕዝቡ ከአማሌቃውያን ላይ ወስዶ ያመጣቸው ናቸው ከመንጋውና ከከብቶቹ መካከል ምርጥ የሆኑትን ለአምላክህ ለይሖዋ መሥዋዕት እንዲሆኑ ሳያጠፉ ተዉአቸው የቀረውን ግን ሙሉ በሙሉ አጥፍተናል አለው16 ሳሙኤልም ሳኦልን ተው በቃ! ትናንት ማታ ይሖዋ ምን እንዳለኝ ልንገርህ አለው እሱም እሺ ንገረኝ! አለው17 ሳሙኤልም እንዲህ አለው በእስራኤል ነገዶች ላይ መሪ ሆነህ በተሾምክበትና ይሖዋ በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ በቀባህ ጊዜ አንተ ራስህ እዚህ ግባ የማትባል ሰው እንደሆንክ ተሰምቶህ አልነበረም?18 በኋላም ይሖዋ ሄደህ ኃጢአተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው ጨርሰህ እስክታጠፋቸውም ድረስ ከእነሱ ጋር ተዋጋ በማለት ላከህ19 ታዲያ የይሖዋን ቃል ያልታዘዝከው ለምንድን ነው? ከዚህ ይልቅ ለምርኮው በመስገብገብ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አድርገሃል!20 ሳኦል ግን ሳሙኤልን እንዲህ አለው እኔ እኮ የይሖዋን ቃል ታዝዣለሁ! ይሖዋ የሰጠኝን ተልእኮ ለመፈጸም ሄጃለሁ የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን ይዤ አምጥቻለሁ አማሌቃውያንንም ፈጽሜ አጥፍቻለሁ21 ሕዝቡ ግን በጊልጋል ለአምላክህ ለይሖዋ ለመሠዋት ከምርኮው ላይ በጎችንና ከብቶችን ይኸውም ለጥፋት ከተለየው ነገር ላይ ምርጥ የሆነውን ወሰደ22 ከዚያም ሳሙኤል እንዲህ አለ ይሖዋን ይበልጥ የሚያስደስተው የትኛው ነው? የሚቃጠሉ መባዎችንና መሥዋዕቶችን ማቅረብ ወይስ የይሖዋን ቃል መታዘዝ? እነሆ መታዘዝ ከመሥዋዕት መስማትም ከአውራ በግ ስብ ይበልጣል23 ምክንያቱም ዓመፀኝነት ሟርት ከመፈጸም አይተናነስም እብሪተኝነትም ቢሆን ከጥንቆላና ከጣዖት አምልኮ ተለይቶ አይታይም አንተ የይሖዋን ቃል ስላልተቀበልክ እሱም የአንተን ንግሥና አልተቀበለውም24 ከዚያም ሳኦል ሳሙኤልን እንዲህ አለው ኃጢአት ሠርቻለሁ ሕዝቡን በመፍራትና ቃላቸውን በመስማት የይሖዋን ትእዛዝም ሆነ የአንተን ቃል ጥሻለሁ25 አሁንም እባክህ ኃጢአቴን ይቅር በል ለይሖዋም እንድሰግድ አብረኸኝ ተመለስ26 ሳሙኤል ግን ሳኦልን አንተ የይሖዋን ቃል ስላልተቀበልክና ይሖዋም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆነህ እንድትቀጥል ስላልፈቀደ ከአንተ ጋር አልመለስም አለው27 ሳሙኤል ለመሄድ ዞር ሲል ሳኦል የሳሙኤልን ልብስ ጫፍ አፈፍ አድርጎ ያዘ ልብሱም ተቀደደ28 በዚህ ጊዜ ሳሙኤል እንዲህ አለው ይሖዋ የእስራኤልን ንጉሣዊ አገዛዝ በዛሬው ዕለት ከአንተ ቀዶታል ከአንተ ለሚሻል ባልንጀራህም አሳልፎ ይሰጠዋል29 ደግሞም የእስራኤል ክቡር አይዋሽም ወይም ሐሳቡን አይቀይርም ምክንያቱም እሱ ሐሳቡን ይቀይር ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም30 እሱም ኃጢአት ሠርቻለሁ ሆኖም እባክህ በሕዝቤ ሽማግሌዎችና በእስራኤል ፊት አክብረኝ አብረኸኝ ተመለስ እኔም ለአምላክህ ለይሖዋ እሰግዳለሁ አለው31 በመሆኑም ሳሙኤል ሳኦልን ተከትሎት ተመለሰ ሳኦልም በይሖዋ ፊት ሰገደ32 ሳሙኤልም የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ አለ አጋግም መቼም የሞትን መራራ ጽዋ የምቀምስበት ጊዜ አልፏል ብሎ ስላሰበ ፈራ ተባ እያለ ወደ እሱ ሄደ33 ሆኖም ሳሙኤል በአንተ ሰይፍ የተነሳ ልጆቻቸውን ያጡ ሴቶች እንዳዘኑ ሁሉ የአንተም እናት ከሴቶች ሁሉ ይበልጥ ታዝናለች አለው ከዚያም ሳሙኤል በጊልጋል በይሖዋ ፊት አጋግን ቆራረጠው34 ሳሙኤል ወደ ራማ ሄደ ሳኦልም በጊብዓ ወደሚገኘው ቤቱ አቀና35 ሳሙኤልም ለሳኦል እጅግ አዘነ እስከ ዕለተ ሞቱም ድረስ ሳኦልን ዳግመኛ አላየውም ይሖዋም ሳኦልን በእስራኤል ላይ ንጉሥ በማድረጉ ተጸጸተ
16 ከጊዜ በኋላ ይሖዋ ሳሙኤልን እንዲህ አለው ሳኦል በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዲሆን አልፈለግኩም ታዲያ አንተ ለእሱ የምታዝነው እስከ መቼ ነው? በል ቀንድህን ዘይት ሙላና ሂድ የቤተልሔም ሰው ወደሆነው ወደ እሴይ እልክሃለሁ ምክንያቱም ከወንዶች ልጆቹ መካከል ንጉሥ የሚሆንልኝ ሰው መርጫለሁ2 ሳሙኤል ግን እንዴት መሄድ እችላለሁ? ሳኦል ይህን ከሰማ ይገድለኛል አለ ይሖዋም እንዲህ አለው አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድ ከዚያም የመጣሁት ለይሖዋ መሥዋዕት ለማቅረብ ነው በል3 እሴይንም ወደ መሥዋዕቱ ጥራው እኔም ምን ማድረግ እንዳለብህ አሳውቅሃለሁ አንተም እኔ የምመርጥልህን ሰው ትቀባልኛለህ4 ሳሙኤልም ይሖዋ የነገረውን አደረገ ቤተልሔም እንደደረሰም የከተማዋ ሽማግሌዎች ባገኙት ጊዜ እየተንቀጠቀጡ የመጣኸው በሰላም ነው? አሉት5 እሱም አዎ በሰላም ነው የመጣሁት ለይሖዋ መሥዋዕት ለማቅረብ ነው ራሳችሁን ቀድሱ ወደ መሥዋዕቱም አብራችሁኝ ሂዱ አላቸው ከዚያም እሴይንና ልጆቹን ቀደሳቸው ወደ መሥዋዕቱ እንዲመጡም ጠራቸው6 እነሱም እዚያ በደረሱ ጊዜ ሳሙኤል ኤልያብን ሲያየው መቼም ይሖዋ የሚቀባው ሰው ይህ መሆን አለበት አለ7 ሆኖም ይሖዋ ሳሙኤልን እንዲህ አለው እኔ ስላልተቀበልኩት መልኩንና የቁመቱን ርዝማኔ አትይ አምላክ የሚያየው ሰው በሚያይበት መንገድ አይደለም ምክንያቱም ሰው የሚያየው ውጫዊ ገጽታን ነው ይሖዋ ግን የሚያየው ልብን ነው8 ከዚያም እሴይ አቢናዳብን ጠርቶ በሳሙኤል ፊት እንዲያልፍ አደረገ እሱ ግን ይሄኛውንም ይሖዋ አልመረጠውም አለ9 ቀጥሎም እሴይ ሻማህ እንዲቀርብ አደረገ እሱ ግን ይሄኛውንም ይሖዋ አልመረጠውም አለ10 በመሆኑም እሴይ ሰባቱም ወንዶች ልጆቹ በሳሙኤል ፊት እንዲያልፉ አደረገ ሳሙኤል ግን እሴይን ይሖዋ ከእነዚህ መካከል ማናቸውንም አልመረጠም አለው11 በመጨረሻም ሳሙኤል እሴይን ወንዶች ልጆችህ እነዚሁ ብቻ ናቸው? አለው እሱም ታናሽየው ገና ይቀራል በጎች እየጠበቀ ነው አለ ከዚያም ሳሙኤል እሴይን በል ልከህ አስመጣው ምክንያቱም እሱ ሳይመጣ ምግብ ለመብላት መቀመጥ አንችልም አለው12 በመሆኑም ልኮ አስመጣው እሱም የቀይ ዳማ ዓይኑ የሚያምርና መልከ መልካም ነበር ከዚያም ይሖዋ ተነስ ቀባው የመረጥኩት እሱን ነው! አለው13 ስለዚህ ሳሙኤል የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ ፊት ቀባው ከዚያም ቀን አንስቶ የይሖዋ መንፈስ ለዳዊት ኃይል ሰጠው በኋላም ሳሙኤል ተነስቶ ወደ ራማ ሄደ14 በዚህ ጊዜ የይሖዋ መንፈስ ከሳኦል ራቀ ከይሖዋ የመጣ መጥፎ መንፈስም ይረብሸው ጀመር15 የሳኦል አገልጋዮችም እንዲህ አሉት እንግዲህ ከአምላክ የመጣ መጥፎ መንፈስ እየረበሸህ ነው16 ጌታችን በፊቱ የቆሙትን አገልጋዮቹን በገና የሚደረድር ጥሩ ችሎታ ያለው ሰው እንዲፈልጉ ይዘዝ ከአምላክ የመጣው መጥፎ መንፈስ በአንተ ላይ ሲወርድ ይህ ሰው በገና ይጫወትልሃል አንተም ደህና ትሆናለህ17 ስለዚህ ሳኦል አገልጋዮቹን እንግዲያው እባካችሁ ጥሩ አድርጎ በገና የሚደረድር ሰው ፈልጋችሁ አምጡልኝ አላቸው18 ከአገልጋዮቹም አንዱ እንዲህ አለ የቤተልሔሙ ሰው የእሴይ ልጅ በገና የመደርደር ጥሩ ችሎታ እንዳለው አይቻለሁ እሱም ደፋርና ኃያል ተዋጊ ነው ደግሞም አንደበተ ርቱዕና መልከ መልካም ሲሆን ይሖዋም ከእሱ ጋር ነው19 ከዚያም ሳኦል ወደ እሴይ መልእክተኞችን ልኮ በጎች የሚጠብቀውን ልጅህን ዳዊትን ላክልኝ አለው20 በመሆኑም እሴይ ዳቦና በወይን ጠጅ የተሞላ አቁማዳ በአህያ አስጭኖ እንዲሁም የፍየል ግልገል አስይዞ ልጁን ዳዊትን ወደ ሳኦል ላከው21 በዚህ መንገድ ዳዊት ወደ ሳኦል መጣ እሱንም ያገለግለው ጀመር ሳኦልም እጅግ እየወደደው ሄደ ጋሻ ጃግሬውም ሆነ22 ሳኦልም ዳዊት በፊቴ ሞገስ ስላገኘ እባክህ እዚሁ እኔ ጋ ሆኖ እንዲያገለግለኝ ፍቀድልኝ በማለት ወደ እሴይ መልእክት ላከ23 ከአምላክ የሚመጣ መጥፎ መንፈስ በሳኦል ላይ በሚወርድበት ጊዜ ሁሉ ዳዊት በገናውን አንስቶ ይደረድር ነበር ሳኦልም ቀለል ይለውና ደህና ይሆን ነበር መጥፎው መንፈስም ከእሱ ይርቅ ነበር
17 ፍልስጤማውያን ሠራዊታቸውን ለውጊያ አሰባሰቡ እነሱም በይሁዳ በምትገኘው በሶኮህ ከተሰባሰቡ በኋላ በሶኮህ እና በአዜቃ መካከል በምትገኘው በኤፌስዳሚም ሰፈሩ2 ሳኦልና የእስራኤል ሰዎች ደግሞ ተሰባስበው በኤላህ ሸለቆ ውስጥ ሰፈሩ እነሱም ለጦርነት ተሰልፈው ፍልስጤማውያንን ለመግጠም ወጡ3 ፍልስጤማውያን በአንድ በኩል ያለውን ተራራ ያዙ እስራኤላውያን ደግሞ በሌላ በኩል ያለውን ተራራ ያዙ በመካከላቸውም ሸለቆ ነበር4 በዚህ ጊዜ አንድ ኃያል ተዋጊ ከፍልስጤማውያን ሰፈር ብቅ አለ እሱም የጌት ሰው ሲሆን ስሙ ጎልያድ ይባላል ቁመቱም ስድስት ክንድ ከአንድ ስንዝር ነበር5 እሱም ከመዳብ የተሠራ የራስ ቁር ደፍቶ ነበር እንዲሁም ከተነባበሩ ጠፍጣፋ መዳቦች የተሠራ ጥሩር ለብሶ ነበር የጥሩሩም ክብደት 5,000 ሰቅል ነበር6 ቅልጥሙ ላይ ከመዳብ የተሠራ ገምባሌ አድርጎ ነበር በትከሻውና በትከሻውም መካከል ከመዳብ የተሠራ ጦር አንግቶ ነበር7 የጭሬውም ዘንግ የሸማኔ መጠቅለያ ያህል ነበር ከብረት የተሠራው የጭሬው ጫፍ 600 ሰቅል ነበር ጋሻ ጃግሬውም ከፊት ከፊቱ ይሄድ ነበር8 ከዚያም ጎልያድ ከቆመበት ቦታ ሆኖ የተሰለፈውን የእስራኤል ሠራዊት በመጣራት እንዲህ አላቸው ለውጊያ ተሰልፋችሁ የወጣችሁት ለምንድን ነው? እኔ ፍልስጤማዊ እናንተ ደግሞ የሳኦል አገልጋዮች አይደላችሁም? እንግዲህ አንድ ሰው ምረጡና ወደ እኔ ይውረድ9 ከእኔ ጋር ተዋግቶ እኔን መግደል ከቻለ እኛ የእናንተ አገልጋዮች እንሆናለን እኔ ባሸንፈውና ብገድለው ግን እናንተ የእኛ አገልጋዮች ትሆናላችሁ እኛንም ታገለግላላችሁ10 በመቀጠልም ፍልስጤማዊው ዛሬ ለውጊያ የተሰለፈውን የእስራኤል ሠራዊት እሳለቅበታለሁ በሉ አሁን አንድ ሰው ምረጡና እንጋጠም! አለ11 ሳኦልና እስራኤላውያን በሙሉ ፍልስጤማዊው የተናገረውን ይህን ቃል ሲሰሙ ተሸበሩ እንዲሁም በጣም ፈሩ12 ዳዊት በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም የሚኖረው የኤፍራታዊው የእሴይ ልጅ ነበር እሴይ ስምንት ወንዶች ልጆች የነበሩት ሲሆን በሳኦል የንግሥና ዘመን ዕድሜው ገፍቶ ነበር13 ሦስቱ የእሴይ ትላልቅ ልጆች ሳኦልን ተከትለው ወደ ውጊያው ሄደው ነበር ወደ ውጊያው የሄዱት ሦስቱ ወንዶች ልጆቹ የበኩር ልጁ ኤልያብ ሁለተኛ ልጁ አቢናዳብና ሦስተኛ ልጁ ሻማህ ነበሩ14 ዳዊት የሁሉም ታናሽ ነበር ትላልቆቹ ሦስቱ ሳኦልን ተከትለው ሄደው ነበር15 ዳዊት ሳኦልን ያገለግል እንዲሁም ከዚያ እየተመላለሰ በቤተልሔም የአባቱን በጎች ይጠብቅ ነበር16 ይህ በእንዲህ እንዳለ ፍልስጤማዊው 40 ቀን ሙሉ ጠዋትና ማታ ወደ እነሱ በመቅረብ ፊታቸው ቆሞ ይገዳደራቸው ነበር17 ከዚያም እሴይ ልጁን ዳዊትን እንዲህ አለው እስቲ እባክህ ይህን አንድ የኢፍ መስፈሪያ ቆሎና እነዚህን አሥር ዳቦዎች ይዘህ በጦር ሰፈሩ ውስጥ ላሉት ወንድሞችህ ቶሎ አድርስላቸው18 እንዲሁም ይህን አሥር የአይብ ጥፍጥፍ ለሺህ አለቃው ውሰድለት በተጨማሪም ወንድሞችህ እንዴት እንደሆኑ አይተህ ደህንነታቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘህ ና19 የዳዊት ወንድሞች ከሳኦልና ከሌሎቹ የእስራኤል ሰዎች ጋር ሆነው በኤላህ ሸለቆ ከፍልስጤማውያን ጋር እየተዋጉ ነበር20 በመሆኑም ዳዊት በማለዳ ተነስቶ በጎቹን ለጠባቂ ሰጠ ከዚያም ዕቃዎቹን ይዞ እሴይ ባዘዘው መሠረት ሄደ እሱም ወደ ጦር ሰፈሩ ሲደርስ የጦር ሠራዊቱ እየፎከረ ወደ ጦር ግንባሩ እየወጣ ነበር21 ለጦርነት የተሰለፉት እስራኤላውያንና ፍልስጤማውያንም ፊት ለፊት ተፋጠው ነበር22 ዳዊትም ወዲያውኑ ዕቃውን ስንቅ ጠባቂው ጋ አስቀምጦ ወደ ጦር ግንባሩ እየሮጠ ሄደ እዚያም ሲደርስ የወንድሞቹን ደህንነት መጠየቅ ጀመረ23 እሱም ከእነሱ ጋር እየተነጋገረ ሳለ የጌት ሰው የሆነው ጎልያድ የተባለው ኃያል ፍልስጤማዊ ተዋጊ መጣ እሱም ለውጊያ ከተሰለፉት ፍልስጤማውያን መካከል ብቅ ብሎ እንደ በፊቱ መደንፋት ጀመረ ዳዊትም ሰማው24 የእስራኤልም ሰዎች በሙሉ ሰውየውን ሲመለከቱት እጅግ ተሸብረው ከፊቱ ሸሹ25 እነሱም እንዲህ ይሉ ነበር እየመጣ ያለውን ይህን ሰው አያችሁት? የሚመጣው እኮ በእስራኤል ላይ ለመሳለቅ ነው እሱን ለሚገድል ሰው ንጉሡ ብዙ ሀብት ይሰጠዋል ሴት ልጁንም ይድርለታል የአባቱንም ቤት በእስራኤል ውስጥ ከማንኛውም ዓይነት ግዴታ ነፃ እንዲሆን ያደርጋል26 ዳዊትም አጠገቡ ቆመው የነበሩትን ሰዎች እንዲህ አላቸው ለመሆኑ ያን ፍልስጤማዊ ገድሎ እንዲህ ያለውን ውርደት ከእስራኤል ላይ ለሚያስወግድ ሰው ምን ይደረግለታል? ደግሞስ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጤማዊ ሕያው በሆነው አምላክ ሠራዊት ላይ የሚሳለቀው ማን ስለሆነ ነው?27 ሰዎቹም ለሚገድለው ሰውማ እንዲህ እንዲህ ይደረግለታል በማለት ቀደም ሲል የተናገሩትን ነገር ደገሙለት28 ታላቅ ወንድሙ ኤልያብም ዳዊት ከሰዎቹ ጋር ሲነጋገር ሲሰማ በእሱ ላይ እጅግ ተቆጥቶ እንዲህ አለው ወደዚህ የወረድከው ለምንድን ነው? ለመሆኑ እነዚያን ጥቂት በጎች ምድረ በዳ ላይ ለማን ተውካቸው? እኔ ትዕቢትህንና የልብህን ክፉ ሐሳብ መች አጣሁት ወደዚህ የመጣኸው ለሌላ ሳይሆን ውጊያውን ለማየት ነው29 ዳዊትም መልሶ ቆይ አሁን ምን አጠፋሁ? ጥያቄ እኮ ነው የጠየቅኩት! አለ30 ከዚያም ከእሱ ዞር ብሎ ያንኑ ጥያቄ ሌላ ሰው ጠየቀ ሰዎቹም እንደቀድሞው ያንኑ መልስ ሰጡት31 ዳዊት የተናገረው ነገር ተሰማ ለሳኦልም ተነገረው ስለዚህ ሳኦል ልኮ አስጠራው32 ዳዊትም ሳኦልን በዚህ ሰው የተነሳ የማንም ሰው ልብ አይቅለጥ አገልጋይህ ሄዶ ከዚህ ፍልስጤማዊ ጋር ይዋጋል አለው33 ሳኦል ግን ዳዊትን አንተ ገና አንድ ፍሬ ልጅ ነህ እሱ ግን ከልጅነቱ ጀምሮ ጦረኛ ነው ስለዚህ ይህን ፍልስጤማዊ ልትገጥመው አትችልም አለው34 ዳዊትም ሳኦልን እንዲህ አለው አገልጋይህ የአባቱን መንጋ በሚጠብቅበት ጊዜ አንበሳ እንዲሁም ድብ ይመጣና ከመንጋው መካከል አንድ በግ ነጥቆ ይወስድ ነበር35 እኔም ተከትዬው በመሄድ እመታውና በጉን ከአፉ አስጥለው ነበር ሊያጠቃኝ በተነሳ ጊዜም ጉሮሮውን አንቄ በመምታት እገድለው ነበር36 አገልጋይህ አንበሳውንም ሆነ ድቡን ገድሏል ይህ ያልተገረዘ ፍልስጤማዊም ሕያው በሆነው አምላክ ሠራዊት ላይ ስለተሳለቀ መጨረሻው ከእነሱ እንደ አንዱ ይሆናል37 ዳዊትም በመቀጠል ከአንበሳና ከድብ ጥፍር የታደገኝ ይሖዋ አሁንም ከዚህ ፍልስጤማዊ እጅ ይታደገኛል አለ በዚህ ጊዜ ሳኦል ዳዊትን እሺ ሂድ ይሖዋ ከአንተ ጋር ይሁን አለው38 ከዚያም ሳኦል ለዳዊት የራሱን ልብሶች አለበሰው በራሱም ላይ ከመዳብ የተሠራ ቁር ደፋለት ጥሩርም አለበሰው39 በኋላም ዳዊት ሰይፉን በልብሱ ላይ ታጥቆ ለመራመድ ሞከረ ሆኖም ከዚህ በፊት እንደዚህ ዓይነት ትጥቅ ታጥቆ ስለማያውቅ መራመድ አልቻለም ዳዊትም ሳኦልን እንዲህ ያሉ ትጥቆችን ታጥቄ ስለማላውቅ እነሱን አድርጌ መራመድ አልቻልኩም አለው በመሆኑም ዳዊት ከላዩ ላይ አወለቃቸው40 ከዚያም በትሩን በእጁ ያዘ አምስት ድቡልቡል ድንጋዮችንም ከወንዝ ከመረጠ በኋላ በእረኛ ኮሮጆው ውስጥ ጨመራቸው በእጁም ወንጭፉን ይዞ ነበር ከዚያም ወደ ፍልስጤማዊው ቀረበ41 ፍልስጤማዊውም ወደ ዳዊት እየቀረበ መጣ ጋሻ ጃግሬውም ከፊት ከፊቱ ይሄድ ነበር42 ፍልስጤማዊውም ዳዊትን ትኩር ብሎ ሲያየው ዳዊት የቀይ ዳማና መልከ መልካም የሆነ አንድ ፍሬ ልጅ ስለነበር ናቀው43 በመሆኑም ፍልስጤማዊው ዳዊትን በትር ይዘህ ወደ እኔ የምትመጣው እኔ ውሻ ነኝ? አለው በአማልክቱም ስም ረገመው44 ከዚያም እስቲ ወደ እኔ ና ሥጋህን ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ አለው45 ዳዊትም መልሶ ፍልስጤማዊውን እንዲህ አለው አንተ ሰይፍ ጭሬና ጦር ይዘህ ትመጣብኛለህ እኔ ግን አንተ በተሳለቅክበት የእስራኤል ተዋጊዎች አምላክ በሆነው በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ስም እመጣብሃለሁ46 ዛሬ ይሖዋ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጥሃል እኔም አንተን ገድዬ ራስህን እቆርጠዋለሁ በዚህ ቀን የፍልስጤማውያንን ሠራዊት ሬሳ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ በመላው ምድር የሚኖሩ ሰዎችም በእስራኤል አምላክ እንዳለ ያውቃሉ47 እዚህ የተሰበሰቡትም ሁሉ ይሖዋ የሚያድነው በሰይፍ ወይም በጦር እንዳልሆነ ያውቃሉ ምክንያቱም ውጊያው የይሖዋ ነው እሱም ሁላችሁንም በእጃችን አሳልፎ ይሰጣችኋል48 ፍልስጤማዊውም ተነስቶ ዳዊትን ለመግጠም ወደ እሱ እየተራመደ መጣ ዳዊትም ፍልስጤማዊውን ለመግጠም ወደ ጦር ግንባሩ እየተንደረደረ ሄደ49 ከዚያም ዳዊት እጁን ወደ ኮሮጆው በመስደድ አንድ ድንጋይ አውጥቶ ወነጨፈው ፍልስጤማዊውንም ግንባሩ ላይ መታው ድንጋዩም ግንባሩ ውስጥ ገብቶ ተቀረቀረ ሰውየውም በአፍጢሙ መሬት ላይ ተደፋ50 በዚህ ሁኔታ ዳዊት ፍልስጤማዊውን በወንጭፍና በድንጋይ አሸነፈው ዳዊት በእጁ ሰይፍ ባይዝም ፍልስጤማዊውን መትቶ ገደለው51 ከዚያም ዳዊት እየሮጠ ሄዶ ላዩ ላይ ቆመ የፍልስጤማዊውንም ሰይፍ ከሰገባው ውስጥ በመምዘዝ አንገቱን ቆርጦ ገደለው ፍልስጤማውያንም ጀግናቸው መሞቱን ሲያዩ ሸሹ52 በዚህ ጊዜ የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ተነስተው እየጮኹ ፍልስጤማውያኑን ከሸለቆው አንስቶ እስከ ኤቅሮን በሮች ድረስ አሳደዷቸው የፍልስጤማውያኑም ሬሳ ከሻአራይም አንስቶ እስከ ጌት እና እስከ ኤቅሮን ድረስ በየመንገዱ ወድቆ ነበር53 እስራኤላውያን ፍልስጤማውያኑን ከማሳደድ ከተመለሱ በኋላ ሰፈሮቻቸውን በዘበዙ54 ዳዊትም የፍልስጤማዊውን ራስ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው የፍልስጤማዊውን የጦር መሣሪያዎች ግን በራሱ ድንኳን ውስጥ አስቀመጣቸው55 ዳዊት ፍልስጤማዊውን ለመግጠም በሚሄድበት ጊዜ ሳኦል ዳዊትን ተመልክቶ የሠራዊቱን አዛዥ አበኔርን አበኔር ለመሆኑ ይህ የማን ልጅ ነው? አለው አበኔርም መልሶ ንጉሥ ሆይ በሕያውነትህ እምላለሁ አላውቅም! አለው56 ንጉሡም ይህ ወጣት የማን ልጅ እንደሆነ አጣራ አለው57 ስለዚህ ዳዊት ፍልስጤማዊውን ገድሎ ሲመለስ አበኔር ዳዊትን ወስዶ የፍልስጤማዊውን ራስ በእጁ እንደያዘ ንጉሡ ፊት አቀረበው58 ሳኦልም አንተ ወጣት የማን ልጅ ነህ? ሲል ጠየቀው ዳዊትም መልሶ የቤተልሔም ሰው የሆነው የአገልጋይህ የእሴይ ልጅ ነኝ አለው
18 ዳዊት ከሳኦል ጋር ተነጋግሮ እንደጨረሰ ዮናታንና ዳዊት የጠበቀ ወዳጅነት መሠረቱ ዮናታንም እንደ ራሱ ወደደው2 ከዚያን ቀን ጀምሮ ሳኦል ዳዊት ከእሱ ጋር እንዲኖር አደረገ ወደ አባቱም ቤት እንዲመለስ አልፈቀደለትም3 ዮናታንም ዳዊትን እንደ ራሱ ስለወደደው ከዳዊት ጋር ቃል ኪዳን ተጋቡ4 ከዚያም ዮናታን ለብሶት የነበረውን መደረቢያ አውልቆ ለዳዊት ሰጠው እንዲሁም ልብሶቹን ሌላው ቀርቶ ሰይፉን ቀስቱንና ቀበቶውን ሰጠው5 ዳዊትም ለውጊያ ይወጣ ጀመር ሳኦል በሚልከው በማንኛውም ቦታ ተልእኮውን በተሳካ ሁኔታ ይፈጽም ነበር በመሆኑም ሳኦል በሠራዊቱ ላይ ሾመው ይህም ሕዝቡንና የሳኦልን አገልጋዮች በሙሉ አስደሰታቸው6 ዳዊትና አብረውት ያሉት ሰዎች ፍልስጤማውያንን መትተው በተመለሱ ጊዜ በመላው የእስራኤል ከተሞች የሚገኙ ሴቶች አታሞና ባለ ሦስት አውታር መሣሪያ ይዘው በደስታ እየዘፈኑና እየጨፈሩ ንጉሥ ሳኦልን ለመቀበል ወጡ7 እየጨፈሩ የነበሩት ሴቶችም እንዲህ እያሉ ዘፈኑሳኦል ሺዎችን ገደለዳዊት ደግሞ አሥር ሺዎችን ገደለ8 ሳኦልም እጅግ ተቆጣ ዘፈኑም አላስደሰተውም በመሆኑም ለዳዊት አሥር ሺህ አሉለት ለእኔ ግን ሺህ ብቻ ያልተሰጠው ነገር እኮ መንግሥት ብቻ ነው! አለ9 ከዚያች ዕለት አንስቶ ሳኦል ዳዊትን በጥርጣሬ ዓይን ይመለከተው ጀመር10 በማግስቱም ከአምላክ የመጣ መጥፎ መንፈስ ሳኦልን ያዘው ዳዊት በፊት እንደሚያደርገው ሁሉ በገና እየደረደረ ሳለ ሳኦል ቤቱ ውስጥ እንግዳ ባሕርይ ያሳይ ጀመር ሳኦልም በእጁ ጦር ይዞ ነበር11 እሱም ዳዊትን ከግድግዳው ጋር አጣብቀዋለሁ! ብሎ በማሰብ ጦሩን በኃይል ወረወረው ዳዊት ግን ሁለት ጊዜ ከእሱ አመለጠ12 ይሖዋ ከሳኦል ተለይቶ ከዳዊት ጋር ስለነበር ሳኦል ዳዊትን ፈራው13 በመሆኑም ሳኦል ከፊቱ እንዲርቅ አደረገው የሺህ አለቃ አድርጎም ሾመው ዳዊትም ሠራዊቱን እየመራ ወደ ጦርነት ይሄድ ነበር14 ዳዊት የሚያከናውነው ነገር ሁሉ ይሳካለት ነበር ይሖዋም ከእሱ ጋር ነበር15 ሳኦልም ዳዊት ስኬታማ እንደሆነ ሲያይ ፈራው16 መላው እስራኤልና ይሁዳ ግን ዳዊትን ወደዱት ምክንያቱም ወደ ጦርነት ሲወጡ የሚመራቸው እሱ ነበር17 በኋላም ሳኦል ዳዊትን እንዲህ አለው እንግዲህ ትልቋ ልጄ ሜሮብ አለች እሷን እድርልሃለሁ ሆኖም ጀግንነትህን ለእኔ ከማሳየት ወደኋላ ማለት የለብህም የይሖዋንም ጦርነቶች መዋጋት ይኖርብሃል ሳኦል ይህን ያለው እጄን በዚህ ሰው ላይ አላሳርፍም ከዚህ ይልቅ በፍልስጤማውያን እጅ ይሙት ብሎ ስላሰበ ነው18 በዚህ ጊዜ ዳዊት ሳኦልን ለንጉሡ አማች እሆን ዘንድ እኔም ሆንኩ የአባቴ ቤተሰቦች የሆኑት ዘመዶቼ በእስራኤል ውስጥ ከቶ ማን ሆነን ነው? አለው19 ሆኖም የሳኦል ልጅ ሜሮብ ለዳዊት ልትሰጥ የነበረበት ጊዜ ሲደርስ እሷ ቀድሞውኑ ለመሆላታዊው ለአድሪዔል ተድራ ነበር20 የሳኦል ልጅ ሜልኮል ዳዊትን ትወደው ነበር ይህን ለሳኦል ነገሩት እሱም ነገሩ ደስ አሰኘው21 በመሆኑም ሳኦል ወጥመድ እንድትሆነውና የፍልስጤማውያን እጅ በእሱ ላይ እንዲሆን እሷን እሰጠዋለሁ አለ ከዚያም ሳኦል ለሁለተኛ ጊዜ ዳዊትን በዛሬዋ ዕለት በዚህች በሁለተኛዋ ሴት አማካኝነት ከእኔ ጋር በጋብቻ ትዛመዳለህ አለው22 በተጨማሪም ሳኦል አገልጋዮቹን እንዲህ ሲል አዘዛቸው ለዳዊት እንዲህ ብላችሁ በሚስጥር ንገሩት ንጉሡ በአንተ ደስ ብሎታል አገልጋዮቹም በሙሉ ይወዱሃል ስለሆነም አሁን ከንጉሡ ጋር በጋብቻ ተዛመድ23 የሳኦልም አገልጋዮች ይህን በነገሩት ጊዜ ዳዊት እዚህ ግባ ለማልባል ለእንደኔ ዓይነቱ ድሃ ከንጉሡ ጋር በጋብቻ መዛመድ እንዲህ ቀላል ነገር ይመስላችኋል? አላቸው24 ከዚያም የሳኦል አገልጋዮች ዳዊት እኮ እንዲህ እንዲህ አለ ብለው ነገሩት25 በዚህ ጊዜ ሳኦል እንዲህ አለ ዳዊትን እንዲህ በሉት ንጉሡ ከአንተ የሚፈልገው ጥሎሽ ሳይሆን ጠላቶቹን መበቀል እንዲችል የ100 ፍልስጤማውያንን ሸለፈት ብቻ ነው ሳኦል ይህን ያለው ዳዊት በፍልስጤማውያን እጅ እንዲወድቅ ተንኮል አስቦ ስለነበር ነው26 በመሆኑም አገልጋዮቹ ይህንኑ ለዳዊት ነገሩት ዳዊትም ከንጉሡ ጋር በጋብቻ የመዛመዱ ጉዳይ አስደሰተው ስለሆነም የተሰጠው ጊዜ ከማብቃቱ በፊት27 ዳዊት አብረውት ከነበሩት ሰዎች ጋር በመሄድ 200 ፍልስጤማውያንን መታ ዳዊት ከንጉሡ ጋር በጋብቻ ለመዛመድ የገደላቸውን ሰዎች ሸለፈት በሙሉ አምጥቶ ለንጉሡ ሰጠው በመሆኑም ሳኦል ልጁን ሜልኮልን ዳረለት28 ሳኦል ይሖዋ ከዳዊት ጋር እንደነበርና ልጁ ሜልኮልም ዳዊትን እንደወደደችው ተረዳ29 በዚህም ምክንያት ሳኦል ዳዊትን ከበፊቱ ይልቅ ፈራው በመሆኑም ዕድሜውን ሙሉ የዳዊት ጠላት ሆነ30 የፍልስጤም መኳንንትም ለውጊያ ይወጡ ነበር ሆኖም ለውጊያ በወጡ ቁጥር ዳዊት ከሳኦል አገልጋዮች ሁሉ ይበልጥ ይሳካለት ነበር ስሙም እየገነነ መጣ
19 በኋላም ሳኦል ዳዊት እንዲገደል ማሰቡን ለልጁ ለዮናታንና ለአገልጋዮቹ በሙሉ ነገራቸው2 የሳኦል ልጅ ዮናታን ዳዊትን በጣም ይወደው ስለነበር ዳዊትን እንዲህ አለው አባቴ ሳኦል ሊገድልህ ይፈልጋል ስለዚህ እባክህ ጠዋት ላይ ተጠንቀቅ ወደ አንድ ሰዋራ ቦታም ሄደህ ተሸሽገህ ቆይ3 እኔም እወጣና አንተ ባለህበት ሜዳ ከአባቴ አጠገብ እቆማለሁ ከእሱም ጋር ስለ አንተ እነጋገራለሁ የሆነ ነገር እንዳለ ከተረዳሁ እነግርሃለሁ4 በመሆኑም ዮናታን ለአባቱ ለሳኦል ስለ ዳዊት መልካም ነገር ነገረው እንዲህም አለው ንጉሡ በአገልጋዩ በዳዊት ላይ ኃጢአት አይሥራ ምክንያቱም እሱ በአንተ ላይ የሠራው ኃጢአት የለም ያደረገልህም ነገር ቢሆን ለአንተ የሚበጅ ነው5 ሕይወቱን አደጋ ላይ ጥሎ ፍልስጤማዊውን መታ ይሖዋም ለመላው እስራኤል ታላቅ ድል አጎናጸፈ አንተም ይህን አይተህ በጣም ተደስተህ ነበር ታዲያ ያለምንም ምክንያት ዳዊትን በመግደል በንጹሕ ሰው ደም ላይ ለምን ኃጢአት ትሠራለህ?6 ሳኦልም የዮናታንን ቃል ሰማ እሱም ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ ዳዊት አይገደልም ሲል ማለ7 ከዚያም ዮናታን ዳዊትን ጠርቶ ሁሉንም ነገር ነገረው ስለዚህ ዮናታን ዳዊትን ወደ ሳኦል አመጣው እሱም እንደቀድሞው ሳኦልን ማገልገሉን ቀጠለ8 ከጊዜ በኋላ ሌላ ጦርነት ተነሳ ዳዊትም ወጥቶ ከፍልስጤማውያን ጋር ተዋጋ ክፉኛም ጨፈጨፋቸው እነሱም ከፊቱ ሸሹ9 ሳኦል ጦሩን ይዞ ቤቱ ውስጥ ተቀምጦ ሳለ ከይሖዋ የመጣ መጥፎ መንፈስ ወረደበት በዚህ ጊዜ ዳዊት በገና እየደረደረ ነበር10 ሳኦልም ዳዊትን በጦሩ ከግድግዳው ጋር ሊያጣብቀው ሞከረ ዳዊት ግን ከሳኦል ፊት ዞር በማለቱ ጦሩ ግድግዳው ላይ ተሰካ ዳዊትም በዚያ ሌሊት ሸሽቶ አመለጠ11 በኋላም ሳኦል የዳዊትን ቤት ከበው በንቃት በመጠባበቅ ጠዋት ላይ እንዲገድሉት መልእክተኞችን ላከ ሆኖም የዳዊት ሚስት ሜልኮል ዛሬ ሌሊት ካላመለጥክ ነገ ትገደላለህ አለችው12 ሜልኮልም ዳዊት ሸሽቶ እንዲያመልጥ ወዲያውኑ በመስኮት አሾልካ አወረደችው13 ከዚያም የተራፊም ቅርጹን ወስዳ አልጋው ላይ አጋደመች በራስጌውም ከፍየል ፀጉር የተሠራ እንደ መረብ ያለ ጨርቅ አደረገች በልብስም ሸፈነችው14 ሳኦልም ዳዊትን እንዲይዙት መልእክተኞችን ላከ እሷ ግን አሞታል አለቻቸው15 በመሆኑም ሳኦል ዳዊትን እንዲያዩት መልእክተኞቹን ላከ እነሱንም ዳዊትን እንድገድለው በአልጋው ላይ እንዳለ አምጡልኝ አላቸው16 መልእክተኞቹም ሲገቡ አልጋው ላይ ያገኙት የተራፊም ቅርጹን ነበር በራስጌውም ከፍየል ፀጉር የተሠራ እንደ መረብ ያለ ጨርቅ ነበር17 ሳኦልም ሜልኮልን እንዲህ ያታለልሽኝና ጠላቴ ሸሽቶ እንዲያመልጥ ያደረግሽው ለምንድን ነው? አላት ሜልኮልም እንዳመልጥ እርጂኝ አለዚያ እገድልሻለሁ! አለኝ አለችው18 ዳዊትም ሸሽቶ አመለጠ በራማ ወደሚገኘው ወደ ሳሙኤልም መጣ ሳኦል ያደረገበትንም ነገር ሁሉ ነገረው ከዚያም እሱና ሳሙኤል ሄደው በናዮት መኖር ጀመሩ19 ከጊዜ በኋላም ሳኦል ዳዊት እኮ ያለው በራማ በምትገኘው በናዮት ነው! የሚል ወሬ ደረሰው20 ሳኦልም ዳዊትን እንዲይዙት ወዲያውኑ መልእክተኞችን ላከ የሳኦል መልእክተኞችም አረጋውያን የሆኑት ነቢያት ትንቢት ሲናገሩ ሳሙኤል ደግሞ እንደ መሪያቸው ሆኖ ቆሞ ሲያዩ የአምላክ መንፈስ ወረደባቸው እነሱም እንደ ነቢያት ያደርጋቸው ጀመር21 ይህን ለሳኦል በነገሩት ጊዜ ወዲያውኑ ሌሎች መልእክተኞችን ላከ እነሱም እንደ ነቢያት ያደርጋቸው ጀመር በመሆኑም ሳኦል ለሦስተኛ ጊዜ መልእክተኞችን ላከ እነሱም እንደ ነቢያት ያደርጋቸው ጀመር22 በመጨረሻም እሱ ራሱ ወደ ራማ ሄደ በሰኩ ወደሚገኘው ትልቅ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ እንደደረሰም ለመሆኑ ሳሙኤልና ዳዊት የት ናቸው? ሲል ጠየቀ እነሱም በራማ ባለችው በናዮት ይገኛሉ ብለው መለሱለት23 ሳኦልም በራማ ወደምትገኘው ወደ ናዮት እየሄደ ሳለ የአምላክ መንፈስ በእሱም ላይ ወረደበት እሱም በራማ ወደምትገኘው ወደ ናዮት እስኪደርስ ድረስ እንደ ነቢይ አደረገው24 ልብሱንም አወለቀ በሳሙኤልም ፊት እንደ ነቢይ አደረገው ቀኑንና ሌሊቱን ሙሉ ራቁቱን ሆኖ በዚያ ተጋደመ እነሱም ሳኦልም ከነቢያቱ አንዱ ነው እንዴ? ያሉት በዚህ የተነሳ ነው
2 ከዚያም ሐና እንዲህ ስትል ጸለየችልቤ በይሖዋ ሐሴት አደረገቀንዴም በይሖዋ ከፍ ከፍ አለአፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተበማዳን ሥራዎችህ ደስ ብሎኛልና2 እንደ ይሖዋ ያለ ቅዱስ ማንም የለምያለአንተ ማንም የለምእንደ አምላካችን ያለ ዓለት የለም3 በትዕቢት መናገራችሁን ተዉየእብሪት ቃል ከአፋችሁ አይውጣይሖዋ ሁሉን የሚያውቅ አምላክ ነውናተግባርን ሁሉ በትክክል የሚመዝን እሱ ነው4 የኃያላን ቀስቶች ተሰባብረዋልየተንገዳገዱት ግን ብርታት አግኝተዋል5 ጠግበው የነበሩት ለምግብ ሲሉ ተቀጥረው ለመሥራት ተገደዱየተራቡት ግን ከእንግዲህ አይራቡምመሃን የነበረችው ሴት ሰባት ልጆች ወለደችብዙ ወንዶች ልጆች የነበሯት ግን ብቻዋን ቀረች6 ይሖዋ ይገድላል ሕይወትንም ያድናልወደ መቃብር ያወርዳል ከዚያም ያወጣል7 ይሖዋ ያደኸያል እንዲሁም ያበለጽጋልእሱ ያዋርዳል ከፍ ከፍም ያደርጋል8 ችግረኛውን ከአቧራ ላይ ያነሳልድሃውንም ከአመድ ቁልል ላይ ያነሳልከመኳንንትም ጋር ያስቀምጣቸዋልየክብር ወንበርም ይሰጣቸዋልየምድር ምሰሶዎች የይሖዋ ናቸውፍሬያማ የሆነችውን ምድር በእነሱ ላይ አስቀምጧል9 እሱ የታማኞቹን እርምጃ ይጠብቃልክፉዎች ግን በጨለማ ውስጥ ጸጥ እንዲሉ ይደረጋሉሰው የበላይ የሚሆነው በኃይሉ አይደለምና10 ይሖዋ ከእሱ ጋር የሚዋጉትን ያደቃቸዋልእሱም ከሰማይ ነጎድጓድ ይለቅባቸዋልይሖዋ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይፈርዳልለንጉሡ ኃይል ይሰጣልየእሱ ቅቡዕ የሆነውንም ቀንዱን ከፍ ከፍ ያደርጋል11 ከዚያም ሕልቃና በራማ ወደሚገኘው ቤቱ ሄደ ልጁ ግን በካህኑ በኤሊ ፊት የይሖዋ አገልጋይ ሆነ12 የኤሊ ወንዶች ልጆች ምግባረ ብልሹ ነበሩ ለይሖዋ አክብሮት አልነበራቸውም13 ከሕዝቡ ላይ የካህናቱን ድርሻ በሚቀበሉበት ጊዜ እንዲህ ያደርጉ ነበር ማንኛውም ሰው መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ ሥጋው እየተቀቀለ ሳለ የካህኑ አገልጋይ ሦስት ጣት ያለው ሹካ ይዞ ይመጣና14 ሹካውን ወደ ሰታቴው ወይም ወደ ምንቸቱ ወይም ወደ አፍላሉ ወይም ወደ ባለ አንድ ጆሮው ድስት ይከተዋል መንሹ ይዞ የሚወጣውንም ካህኑ ለራሱ ይወስድ ነበር ወደ ሴሎ በሚመጡት እስራኤላውያን ሁሉ ላይ እንዲሁ ያደርጉ ነበር15 ሌላው ቀርቶ መሥዋዕቱን የሚያቀርበው ሰው ስቡን ከማቃጠሉ በፊት የካህኑ አገልጋይ መጥቶ ለካህኑ የሚጠበስ ሥጋ ስጠው ጥሬ ሥጋ ብቻ እንጂ የተቀቀለ ሥጋ ከአንተ አይቀበልም ይለው ነበር16 ሰውየውም በመጀመሪያ ስቡን ያቃጥሉ ከዚያ በኋላ የፈለግከውን ውሰድ ይለው ነበር እሱ ግን አይሆንም አሁኑኑ ስጠኝ ካልሆነ ግን ነጥቄ እወስዳለሁ! ይለዋል17 ሰዎቹ የይሖዋን መባ ያቃልሉ ስለነበር የአገልጋዮቹ ኃጢአት በይሖዋ ፊት እጅግ ታላቅ ሆነ18 በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ገና አንድ ፍሬ ልጅ የነበረ ቢሆንም ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ ለብሶ በይሖዋ ፊት ያገለግል ነበር19 እናቱም ዓመታዊውን መሥዋዕት ለማቅረብ ከባሏ ጋር ስትወጣ እጅጌ የሌለው ትንሽ ቀሚስ እየሠራች በየዓመቱ ታመጣለት ነበር20 ኤሊም ሕልቃናንና ሚስቱን እንዲህ ሲል ባረካቸው ለይሖዋ በተሰጠው ልጅ ምትክ ይሖዋ ከዚህች ሚስትህ ልጅ ይስጥህ አለው እነሱም ወደ ቤታቸው ተመለሱ21 ይሖዋም ሐናን አሰባት እሷም ፀነሰች ሌሎች ሦስት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ልጆችም ወለደች ብላቴናው ሳሙኤልም በይሖዋ ፊት እያደገ ሄደ22 በዚህ ጊዜ ኤሊ በጣም አርጅቶ ነበር ሆኖም ወንዶች ልጆቹ በሁሉም እስራኤላውያን ላይ ምን እንደሚያደርጉ እንዲሁም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ከሚያገለግሉት ሴቶች ጋር እንደሚተኙ አንድም ሳይቀር ሰምቶ ነበር23 እሱም እንዲህ ይላቸው ነበር እንዲህ ያለ ነገር ለምን ታደርጋላችሁ? ሰዎች ሁሉ ስለ እናንተ መጥፎ ነገር ሲናገሩ እሰማለሁ24 ልጆቼ ትክክል አይደላችሁም በይሖዋ ሕዝቦች መካከል ሲናፈስ የምሰማው ወሬ ጥሩ አይደለም25 አንድ ሰው ሌላውን ቢበድል ሌላ ሰው ይሖዋን ይለምንለት ይሆናል ሆኖም አንድ ሰው ይሖዋን ቢበድል ማን ሊጸልይለት ይችላል? እነሱ ግን የአባታቸውን ቃል ለመስማት ፈቃደኞች አልሆኑም ምክንያቱም ይሖዋ ሊገድላቸው ወስኖ ነበር26 ይህ በእንዲህ እንዳለ ብላቴናው ሳሙኤል በይሖዋም ሆነ በሰዎች ፊት በአካል እያደገና ይበልጥ ሞገስ እያገኘ ሄደ27 አንድ የአምላክ ሰው ወደ ኤሊ መጥቶ እንዲህ አለው ይሖዋ እንዲህ ይላል የአባትህ ቤት በግብፅ በፈርዖን ቤት በባርነት ያገለግል በነበረበት ጊዜ ራሴን በይፋ ገልጬለት አልነበረም?28 ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ መሠዊያዬ እንዲወጣ ዕጣን እንዲያጥንና በፊቴ ኤፉድ እንዲለብስ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል ተመርጦ ነበር እኔም እስራኤላውያን በእሳት የሚያቀርቧቸውን መባዎች በሙሉ ለአባትህ ቤት ሰጠሁ29 ታዲያ እናንተ በማደሪያዬ እንዲቀርብ ያዘዝኩትን መሥዋዕቴንና መባዬን የናቃችሁት ለምንድን ነው? ሕዝቤ እስራኤል ከሚያመጣው ከእያንዳንዱ መባ ላይ ምርጡን ወስዳችሁ ራሳችሁን በማደለብ ከእኔ ይልቅ ልጆችህን ያከበርከው ለምንድን ነው?30 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የይሖዋ ቃል እንዲህ ይላል የአንተ ቤትና የአባትህ ቤት ምንጊዜም በፊቴ እንደሚሄዱ ተናግሬ ነበር አሁን ግን ይሖዋ እንዲህ ይላል ይህ ፈጽሞ የማላስበው ነገር ነው ምክንያቱም የሚያከብሩኝን አከብራለሁ የሚንቁኝ ግን ይናቃሉ31 በቤትህ እስከ ሽምግልና ድረስ በሕይወት የሚቆይ ሰው እንዳይኖር የአንተንም ሆነ የአባትህን ቤት ብርታት የምቆርጥበት ቀን ይመጣል32 ለእስራኤል በተደረገው ብዙ መልካም ነገር መካከል በማደሪያዬ ውስጥ ተቀናቃኝ ታያለህ በቤትህም ዳግመኛ አረጋዊ የሚባል አይገኝም33 በመሠዊያዬ ፊት እንዲያገለግል የምተወው የአንተ የሆነ ሰው ዓይኖችህ እንዲፈዙና ለሐዘን እንድትዳረግ ያደርጋል ከቤትህ ሰዎች መካከል ግን አብዛኞቹ በሰዎች ሰይፍ ይሞታሉ34 በሁለቱ ልጆችህ በሆፍኒ እና በፊንሃስ ላይ የሚደርሰው ነገር ምልክት ይሆንሃል ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ35 ከዚያም ለራሴ ታማኝ የሆነ ካህን አስነሳለሁ እሱም ከልቤ ፍላጎት ጋር የሚስማማ ተግባር ይፈጽማል እኔም ዘላቂ የሆነ ቤት እሠራለታለሁ እሱም እኔ በቀባሁት ፊት ሁልጊዜ ይሄዳል36 ከቤትህ የሚተርፍ ሰው ቢኖር የሚከፈለው ገንዘብና ቁራሽ ዳቦ ለማግኘት ሲል መጥቶ ይሰግድለታል ከዚያም እባክህ ቁራሽ ዳቦ እንዳገኝ በማንኛውም የክህነት ሥራ ላይ መድበኝ ይላል
20 ከዚያም ዳዊት በራማ ከምትገኘው ከናዮት ሸሸ ሆኖም ወደ ዮናታን መጥቶ ምን አደረግኩ? የፈጸምኩትስ በደል ምንድን ነው? አባትህ ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልገው በእሱ ላይ ምን ኃጢአት ሠርቼ ነው? አለው2 ዮናታንም እንዲህ አለው ይሄማ የማይታሰብ ነው! ፈጽሞ አትሞትም! አባቴ እንደሆነ ትልቅም ሆነ ትንሽ ለእኔ ሳይነግረኝ ምንም ነገር አያደርግም ታዲያ አባቴ ይህን ነገር ከእኔ የሚደብቅበት ምን ምክንያት አለው? እንዲህማ አይሆንም3 ዳዊት ግን እንደገና ማለለት እንዲህም አለው አባትህ በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን በሚገባ ስለሚያውቅ ዮናታን ሊያዝን ስለሚችል ይህን ነገር ማወቅ የለበትም ብሎ ሊሆን ይችላል ይሁን እንጂ ሕያው በሆነው በይሖዋና በሕያውነትህ እምላለሁ በእኔና በሞት መካከል ያለው አንድ እርምጃ ብቻ ነው!4 ከዚያም ዮናታን ዳዊትን የምትለውን ማንኛውንም ነገር አደርግልሃለሁ አለው5 በዚህ ጊዜ ዳዊት ዮናታንን እንዲህ አለው እነሆ ነገ አዲስ ጨረቃ የምትወጣበት ቀን ነው እኔም ከንጉሡ ጋር ለመመገብ በማዕድ መቀመጥ ይጠበቅብኛል አንተ ካሰናበትከኝ ግን እስከ ሦስተኛው ቀን ምሽት ድረስ ወደ ሜዳ ሄጄ እደበቃለሁ6 ምናልባት አባትህ አለመኖሬን አስተውሎ ከጠየቀ ዳዊት በከተማው በቤተልሔም ለመላ ቤተሰቡ የሚቀርብ ዓመታዊ መሥዋዕት ስላለ ቶሎ ወደዚያ ይሄድ ዘንድ እንድፈቅድለት ለመነኝ በለው7 እሱም ጥሩ ነው! ካለ አገልጋይህን የሚያሰጋው ነገር የለም ማለት ነው ከተቆጣ ግን በእኔ ላይ ጉዳት ለማድረስ እንደቆረጠ እወቅ8 አገልጋይህ ከአንተ ጋር በይሖዋ ፊት ቃል ኪዳን እንዲገባ ያደረግከው አንተ ስለሆንክ ለአገልጋይህ ታማኝ ፍቅር አሳየው በእኔ ላይ ጥፋት ከተገኘ ግን አንተው ራስህ ግደለኝ ለምን ለአባትህ አሳልፈህ ትሰጠኛለህ?9 በዚህ ጊዜ ዮናታን እንዲህ ብለህ ማሰብማ የለብህም! አባቴ በአንተ ላይ ጉዳት ለማድረስ መቁረጡን ባውቅ እንዴት ሳልነግርህ ዝም እላለሁ? አለው10 ከዚያም ዳዊት ዮናታንን ታዲያ አባትህ ክፉ ቃል ቢመልስልህ ማን ይነግረኛል? አለው11 ዮናታንም ዳዊትን ና ወደ ሜዳ እንውጣ አለው በመሆኑም ተያይዘው ወደ ሜዳ ወጡ12 ከዚያም ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው ነገ በዚህ ጊዜ ወይም ከነገ ወዲያ አባቴ ያለውን አመለካከት ባላጣራ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ምሥክር ይሁንብኝ እሱ ለዳዊት ጥሩ አመለካከት ካለው ወደ አንተ ልኬ የማላሳውቅህ ይመስልሃል?13 አባቴ በአንተ ላይ ጉዳት ለማድረስ አስቦ ቢሆንና እኔ ግን ይህን ሳላሳውቅህ ብቀር እንዲሁም በሰላም እንድትሄድ ባላደርግ ይሖዋ በዮናታን ላይ ይህን ያድርግበት ከዚህ የከፋም ነገር ያምጣበት ይሖዋ ከአባቴ ጋር እንደነበር ሁሉ ከአንተም ጋር ይሁን14 አንተስ ብትሆን በሕይወት ሳለሁም ሆነ ስሞት የይሖዋን ታማኝ ፍቅር አታሳየኝም?15 ይሖዋ የዳዊትን ጠላቶች በሙሉ ከምድር ገጽ ጠራርጎ በሚያጠፋበት ጊዜም ለቤተሰቤ ታማኝ ፍቅርህን ከማሳየት ፈጽሞ ወደኋላ አትበል16 ስለዚህ ዮናታን ይሖዋ የዳዊትን ጠላቶች ይፋረዳቸዋል በማለት ከዳዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን ገባ17 በመሆኑም ዮናታን ዳዊት ለእሱ ባለው ፍቅር እንደገና እንዲምልለት አደረገ ምክንያቱም ዳዊትን እንደ ራሱ ይወደው ነበር18 ዮናታንም ዳዊትን እንዲህ አለው ነገ አዲስ ጨረቃ የምትወጣበት ቀን ነው የምትቀመጥበት ቦታ ባዶ ስለሚሆን አለመኖርህ ይታወቃል19 በሦስተኛውም ቀን አለመኖርህ ይበልጥ ግልጽ ይሆናል አንተም ያን ቀን ተደብቀህበት ወደነበረው ቦታ ሂድ እዚህ ድንጋይ አጠገብም ቆይ20 እኔም ዒላማ የምመታ አስመስዬ በድንጋዩ አጠገብ ሦስት ቀስቶችን አስፈነጥራለሁ21 አገልጋዩንም ሂድ ፍላጻዎቹን አምጣቸው ብዬ እልከዋለሁ አገልጋዩን ፍላጻዎቹ ከአንተ በዚህኛው በኩል ናቸው አምጣቸው ካልኩት ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ ሁሉ ነገር ሰላም ስለሆነና ምንም የሚያሰጋህ ነገር ስለሌለ ተመልሰህ መምጣት ትችላለህ22 ሆኖም ልጁን ፍላጻዎቹ ከአንተ ወዲያ ናቸው ካልኩት ይሖዋ አሰናብቶሃልና ሂድ23 እኔና አንተ የተጋባነውን ቃል በተመለከተም ይሖዋ በእኔና በአንተ መካከል ለዘላለም ምሥክር ይሁን24 በመሆኑም ዳዊት ወደ ሜዳ ሄዶ ተደበቀ አዲስ ጨረቃ ስትወጣም ንጉሡ ለመብላት በማዕድ ተቀመጠ25 ንጉሡ እንደተለመደው በግድግዳው በኩል ባለው መቀመጫው ላይ ተቀምጦ ነበር ዮናታን ከፊት ለፊቱ አበኔር ደግሞ ከሳኦል ጎን ተቀምጠው ነበር የዳዊት ቦታ ግን ባዶ ነበር26 ሳኦል መቼም ዳዊት እንዳይነጻ የሚያደርገው የሆነ ነገር ገጥሞት መሆን ይኖርበታል አዎ ረክሶ መሆን አለበት ብሎ ስላሰበ በዚያን ቀን ምንም አልተናገረም27 አዲስ ጨረቃ በወጣችበት ቀን ማግስት ይኸውም በሁለተኛው ቀን የዳዊት ቦታ ክፍት እንደሆነ ነበር ከዚያም ሳኦል ልጁን ዮናታንን የእሴይ ልጅ ትናንትም ዛሬም ማዕድ ላይ ያልተገኘው ለምንድን ነው? አለው28 ዮናታንም ለሳኦል እንዲህ ሲል መለሰለት ዳዊት ወደ ቤተልሔም ይሄድ ዘንድ እንድፈቅድለት ለመነኝ29 እንዲህም አለኝ ቤተሰባችን በከተማዋ ውስጥ መሥዋዕት ስለሚያቀርብና ወንድሜም በዚያ እንድገኝ ስለጠራኝ እባክህ እንድሄድ ፍቀድልኝ እንግዲህ በፊትህ ሞገስ ካገኘሁ እባክህ ወንድሞቼን አይ ዘንድ ሹልክ ብዬ ልሂድ ዳዊት በንጉሡ ማዕድ ላይ ያልተገኘው ለዚህ ነው30 በዚህ ጊዜ ሳኦል በዮናታን ላይ እጅግ ተቆጣ እንዲህም አለው አንተ የዚያች ዓመፀኛ ሴት ልጅ በራስህም ሆነ በእናትህ ላይ ውርደት ለማምጣት ከእሴይ ልጅ ጋር መወገንህን የማላውቅ መሰለህ?31 የእሴይ ልጅ በምድር ላይ በሕይወት እስካለ ድረስ አንተም ሆንክ መንግሥትህ አትጸኑም እሱ መሞት ስላለበት በል አሁኑኑ ልከህ አስመጣልኝ32 ዮናታን ግን አባቱን ሳኦልን ለምን ይገደላል? ጥፋቱስ ምንድን ነው? አለው33 በዚህ ጊዜ ሳኦል እሱን ለመግደል ጦሩን ወረወረበት ስለሆነም ዮናታን አባቱ ዳዊትን ለመግደል ቆርጦ መነሳቱን አወቀ34 ዮናታንም ወዲያውኑ በታላቅ ቁጣ ከማዕዱ ላይ ተነሳ በዳዊት ምክንያት በጣም ስላዘነና የገዛ አባቱም ስላዋረደው አዲስ ጨረቃ በወጣች በሁለተኛው ቀን ምንም ምግብ አልቀመሰም35 ዮናታንም በማለዳ ተነስቶ ከዳዊት ጋር ወደተቀጣጠሩበት ቦታ ሄደ አንድ ወጣት አገልጋይም አብሮት ነበር36 እሱም አገልጋዩን ሂድ ሩጥ የምወነጭፋቸውንም ፍላጻዎች ፈልግ አለው ከዚያም አገልጋዩ ሮጠ ዮናታንም ፍላጻውን ከእሱ አሳልፎ ወነጨፈው37 አገልጋዩም ዮናታን የወነጨፈው ፍላጻ ያረፈበት ቦታ ሲደርስ ዮናታን አገልጋዩን ጠርቶ ፍላጻው ያለው ከአንተ ወዲያ አይደለም? አለው38 ዮናታንም በድጋሚ አገልጋዩን ጠርቶ ፍጠን እንጂ! ቶሎ በል! አትዘግይ! አለው የዮናታን አገልጋይም ፍላጻዎቹን አንስቶ ወደ ጌታው ተመለሰ39 አገልጋዩ ስለ ጉዳዩ የሚያውቀው ነገር አልነበረም የዚህ ትርጉም ምን እንደሆነ የሚያውቁት ዮናታንና ዳዊት ብቻ ነበሩ40 ከዚያም ዮናታን የጦር መሣሪያዎቹን ለአገልጋዩ ሰጥቶ ሂድ ወደ ከተማ ይዘሃቸው ተመለስ አለው41 አገልጋዩም ሲሄድ ዳዊት በስተ ደቡብ በኩል ከሚገኝ በአቅራቢያው ካለ ስፍራ ተነስቶ መጣ ሦስት ጊዜም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ እጅ ነሳ ከዚያም ተሳሳሙ ተላቀሱ ይበልጥ ያለቀሰው ግን ዳዊት ነበር42 ዮናታንም ዳዊትን ሁለታችንም ይሖዋ በእኔና በአንተ በዘሮቼና በዘሮችህ መካከል ለዘላለም ይሁን ብለን በይሖዋ ስም ስለተማማልን በሰላም ሂድ አለውከዚያም ዳዊት ተነስቶ ሄደ ዮናታንም ወደ ከተማዋ ተመለሰ
21 በኋላም ዳዊት ካህኑ አሂሜሌክ ወደሚገኝበት ወደ ኖብ መጣ አሂሜሌክም ዳዊትን ሲያገኘው ተንቀጠቀጠ እሱም ምነው ብቻህን? ሰው አብሮህ የለም? አለው2 ዳዊትም ለካህኑ ለአሂሜሌክ እንዲህ ሲል መለሰለት ንጉሡ አንድ ጉዳይ እንዳስፈጽም አዞኝ ነበር ሆኖም ስለሰጠሁህ ተልእኮና ስላዘዝኩህ ነገር ማንም ሰው ምንም ነገር እንዳያውቅ ብሎኛል ከሰዎቼም ጋር የሆነ ቦታ ላይ ለመገናኘት ተቀጣጥረናል3 ስለዚህ አሁን እጅህ ላይ አምስት ዳቦ ካለ ወይም የተገኘውን ማንኛውንም ነገር ስጠኝ4 ካህኑ ግን ዳዊትን እንዲህ አለው ማንኛውም ሰው የሚበላው ዓይነት ዳቦ የለኝም ሰሞኑን ሰዎቹ ራሳቸውን ከሴት ጠብቀው ከሆነ ግን የተቀደሰው ኅብስት አለ5 ስለዚህ ዳዊት ካህኑን እንዲህ አለው ከዚህ በፊት ለውጊያ እንደወጣሁባቸው ጊዜያት ሁሉ አሁንም ፈጽሞ ሴቶች ወደ እኛ አልቀረቡም ተራ በሆነ ተልእኮም እንኳ የሰዎቹ አካል ቅዱስ ከነበረ ታዲያ ዛሬማ እንዴት ይበልጥ ቅዱስ አይሆን!6 በመሆኑም ካህኑ የተቀደሰውን ኅብስት ሰጠው ምክንያቱም ትኩስ ኅብስት በሚተካበት ቀን ከይሖዋ ፊት ከተነሳው ገጸ ኅብስት በስተቀር ሌላ ዳቦ አልነበረም7 ከሳኦል አገልጋዮች አንዱ በይሖዋ ፊት እንዲቆይ በመገደዱ ያን ቀን እዚያ ነበር ዶይቅ የተባለው ይህ ኤዶማዊ የሳኦል እረኞች አለቃ ነበር8 ከዚያም ዳዊት አሂሜሌክን ንጉሡ የሰጠኝ ተልእኮ አስቸኳይ ስለነበር ሰይፌንም ሆነ የጦር መሣሪያዎቼን አልያዝኩም እዚህ አንተ ጋ ጦር ወይም ሰይፍ ይኖራል? አለው9 ካህኑም በኤላህ ሸለቆ አንተ የገደልከው የፍልስጤማዊው የጎልያድ ሰይፍ አለ ያውልህ ከኤፉዱ ኋላ በጨርቅ ተጠቅልሎ ተቀምጧል ከእሱ ሌላ እዚህ ምንም ስለሌለ ከፈለግክ እሱን ውሰደው አለው ዳዊትም ከእሱ የተሻለማ የትም አይገኝም እሱኑ ስጠኝ አለው10 በዚያም ቀን ዳዊት ተነስቶ ከሳኦል ሸሸ ከጊዜ በኋላም ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አንኩስ መጣ11 የአንኩስ አገልጋዮችም እንዲህ አሉት ይህ የምድሪቱ ንጉሥ ዳዊት አይደለም?ሳኦል ሺዎችን ገደለዳዊት ደግሞ አሥር ሺዎችን ገደለበማለት እየዘፈኑ የጨፈሩለትስ ለዚህ ሰው አይደለም?12 ዳዊትም ይህን ቃል በቁም ነገር ተመለከተው የጌትን ንጉሥ አንኩስንም እጅግ ፈራው13 በመሆኑም በፊታቸው አእምሮውን እንደሳተ ሰው ሆነ በመካከላቸውም እንደአበደ ሰው አደረገው የከተማዋን በሮች ይቦጫጭር እንዲሁም ለሃጩን በጢሙ ላይ ያዝረበርብ ጀመር14 አንኩስም አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው እስቲ ተመልከቱ ሰውየው እኮ እብድ ነው! ታዲያ ወደ እኔ ያመጣችሁት ለምንድን ነው?15 ይህን ሰው ፊቴ እንዲህ እንዲያብድ ያመጣችሁት እኔ እብድ አጥቼ ነው? ይህስ ሰው ቤቴ መግባት ይገባዋል?
22 ዳዊትም ከዚያ ተነስቶ ወደ አዱላም ዋሻ ሸሸ ወንድሞቹና መላው የአባቱ ቤት ይህን ሲሰሙ እሱ ወዳለበት ወደዚያ ወረዱ2 ችግር ያጋጠማቸው ዕዳ ያለባቸውና የተከፉ ሰዎች ሁሉ ወደ እሱ ተሰበሰቡ እሱም አለቃቸው ሆነ ከእሱም ጋር 400 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ነበሩ3 በኋላም ዳዊት ከዚያ ተነስቶ በሞዓብ ወዳለችው ወደ ምጽጳ ሄደ የሞዓብንም ንጉሥ አምላክ የሚያደርግልኝን ነገር እስካውቅ ድረስ እባክህ አባቴና እናቴ አንተ ጋ ይሁኑ አለው4 በመሆኑም የሞዓብ ንጉሥ ጋ አስቀመጣቸው እነሱም ዳዊት በተራራው ላይ ምሽግ ውስጥ በነበረበት ጊዜ ሁሉ እዚያ ተቀመጡ5 ከጊዜ በኋላም ነቢዩ ጋድ ዳዊትን እዚህ ምሽግ ውስጥ መቆየት የለብህም ሄደህ ወደ ይሁዳ ምድር ግባ አለው በመሆኑም ዳዊት ሄዶ ወደ ሄሬት ጫካ ገባ6 ሳኦልም ዳዊትና ከእሱ ጋር የነበሩት ሰዎች መገኘታቸውን ሰማ በዚህ ጊዜ ሳኦል በጊብዓ በኮረብታው ላይ ባለው የታማሪስክ ዛፍ ሥር ጦሩን ይዞ ተቀምጦ ነበር አገልጋዮቹም ሁሉ በዙሪያው ቆመው ነበር7 ከዚያም ሳኦል በዙሪያው የቆሙትን አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው እናንተ ቢንያማውያን እስቲ ስሙኝ ለመሆኑ የእሴይ ልጅ እንደ እኔ እርሻና የወይን ቦታ ለሁላችሁም ይሰጣችኋል? ሁላችሁንስ የሺህ አለቆችና የመቶ አለቆች አድርጎ ይሾማችኋል?8 እናንተ ሁላችሁ በእኔ ላይ ደባ ፈጽማችሁብኛል! የገዛ ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋር ቃል ኪዳን ሲጋባ አንድም ሰው አልነገረኝም! ይኸው አሁን እንደምታዩት የገዛ ልጄ አገልጋዬን በእኔ ላይ እንዲያደባብኝ ማነሳሳቱን አንዳችሁም ብትሆኑ ስለ እኔ ተቆርቁራችሁ አልነገራችሁኝም9 ከዚያም በሳኦል አገልጋዮች ላይ ተሹሞ የነበረው ኤዶማዊው ዶይቅ እንዲህ ሲል መለሰ የእሴይ ልጅ በኖብ ወደሚገኘው ወደ አኪጡብ ልጅ ወደ አሂሜሌክ ሲመጣ አይቻለሁ10 አሂሜሌክም ይሖዋን ጠየቀለት ስንቅም ሰጠው ሌላው ቀርቶ የፍልስጤማዊውን የጎልያድን ሰይፍ ሰጠው11 ንጉሡም ወዲያውኑ ሰዎች ልኮ የካህኑን የአኪጡብን ልጅ አሂሜሌክንና በኖብ በአባቱ ቤት የነበሩትን ካህናት በሙሉ አስጠራ በመሆኑም ሁሉም ወደ ንጉሡ መጡ12 ሳኦልም አንተ የአኪጡብ ልጅ እስቲ ስማኝ! አለው እሱም መልሶ እሺ ጌታዬ እየሰማሁ ነው አለ13 ከዚያም ሳኦል ለእሴይ ልጅ ምግብና ሰይፍ በመስጠት እንዲሁም ስለ እሱ አምላክን በመጠየቅ አንተም ሆንክ እሱ ደባ የፈጸማችሁብኝ ለምንድን ነው? ይኸው አሁን እንደሚታየው እየተቃወመኝና እያደባብኝ ነው አለው14 በዚህ ጊዜ አሂሜሌክ ንጉሡን እንዲህ አለው እንደው ለመሆኑ ከአገልጋዮችህ ሁሉ መካከል እንደ ዳዊት ያለ እምነት የሚጣልበት ማን አለ? እሱ የንጉሡ አማች የክብር ዘቦችህ አለቃና በቤትህ የተከበረ ሰው ነው15 ስለ እሱ አምላክን ስጠይቅ ዛሬ የመጀመሪያዬ ነው? የምትናገረው ነገር ፈጽሞ ያላሰብኩትን ነው! ንጉሡ አገልጋዩንም ሆነ የአባቴን ቤት በሙሉ ጥፋተኛ አያድርግ ምክንያቱም አገልጋይህ ስለዚህ ጉዳይ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም16 ንጉሡ ግን አሂሜሌክ አንተም ሆንክ የአባትህ ቤት በሙሉ በእርግጥ ትሞታላችሁ አለው17 ከዚያም ንጉሡ በዙሪያው ቆመው የነበሩትን ጠባቂዎች ከዳዊት ጋር ስላበሩ ዙሩና የይሖዋን ካህናት ግደሉ! ዳዊት መኮብለሉን እያወቁ አልነገሩኝም! አላቸው የንጉሡ አገልጋዮች ግን የይሖዋን ካህናት ለመግደል እጃቸውን ማንሳት አልፈለጉም18 ንጉሡም ዶይቅን እንግዲያውስ አንተ ዙርና ካህናቱን ግደላቸው! አለው ኤዶማዊው ዶይቅም ወዲያውኑ ሄዶ ካህናቱን ገደላቸው በዚያን ቀን ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ የለበሱ 85 ሰዎችን ገደለ19 እንዲሁም የካህናቱን ከተማ ኖብን በሰይፍ መታ ወንድም ሆነ ሴት ልጅም ሆነ ጨቅላ ሕፃን በሬም ሆነ አህያ ወይም በግ አንድም ሳያስቀር ሁሉንም በሰይፍ ገደለ20 ሆኖም ከአኪጡብ ልጅ ከአሂሜሌክ ልጆች አንዱ የሆነው አብያታር አምልጦ ዳዊትን ለመከተል እሱ ወዳለበት እየሮጠ ሄደ21 አብያታር ለዳዊት ሳኦል እኮ የይሖዋን ካህናት ገደላቸው ሲል ነገረው22 በዚህ ጊዜ ዳዊት አብያታርን እንዲህ አለው ያን ቀን ኤዶማዊው ዶይቅ እዚያ ስለነበር ይህን ለሳኦል እንደሚነግረው አውቄአለሁ በአባትህ ቤት ላሉት ሰዎች ሁሉ ሞት ተጠያቂው እኔ ራሴ ነኝ23 አሁን እኔ ጋ ቆይ የአንተን ሕይወት የሚፈልግ የእኔን ሕይወት የሚፈልግ ስለሆነ አትፍራ እኔ ከለላ እሆንሃለሁ
23 ከጊዜ በኋላም ዳዊት ፍልስጤማውያን በቀኢላ ላይ ውጊያ ከፍተው በየአውድማው ያለውን እህል እየዘረፉ ነው ተብሎ ተነገረው2 ስለሆነም ዳዊት ሄጄ እነዚህን ፍልስጤማውያን ልምታ? በማለት ይሖዋን ጠየቀ ይሖዋም ዳዊትን ሂድ ፍልስጤማውያንን ምታ ቀኢላንም አድናት አለው3 የዳዊት ሰዎች ግን እዚህ በይሁዳ እያለን እንኳ ፈርተናል የፍልስጤማውያንን ሠራዊት ለመውጋት ወደ ቀኢላ ከሄድንማ ምን ያህል እንፈራ! አሉት4 በመሆኑም ዳዊት እንደገና ይሖዋን ጠየቀ ይሖዋም ፍልስጤማውያንን በእጅህ አሳልፌ ስለምሰጥህ ተነስተህ ወደ ቀኢላ ውረድ ሲል መለሰለት5 ስለዚህ ዳዊት ከሰዎቹ ጋር በመሆን ወደ ቀኢላ ሄዶ ከፍልስጤማውያን ጋር ተዋጋ ከብቶቻቸውን እየነዳ ወሰደ ብዙ ሰውም ገደለባቸው በዚህ መንገድ ዳዊት የቀኢላን ነዋሪዎች ታደጋቸው6 የአሂሜሌክ ልጅ አብያታር በቀኢላ ወደነበረው ወደ ዳዊት በሸሸ ጊዜ ኤፉድ ይዞ ነበር7 ሳኦል ዳዊት ወደ ቀኢላ መጥቷል የሚል ወሬ ደረሰው ሳኦልም ዳዊት በሮችና መቀርቀሪያዎች ወዳሏት ከተማ በመግባት ራሱን ወጥመድ ውስጥ ከቷል ስለሆነም አምላክ እሱን በእጄ አሳልፎ ሰጥቶታል አለ8 በመሆኑም ሳኦል ወደ ቀኢላ በመውረድ ዳዊትንና ሰዎቹን ከቦ ለመያዝ ሕዝቡን ሁሉ ለጦርነት አሰባሰበ9 ዳዊትም ሳኦል ሴራ እየጠነሰሰበት መሆኑን ሲያውቅ ካህኑን አብያታርን ኤፉዱን ወደዚህ አምጣው አለው10 ከዚያም ዳዊት እንዲህ አለ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ ሳኦል ወደ ቀኢላ መጥቶ በእኔ የተነሳ ከተማዋን ለማጥፋት ማሰቡን አገልጋይህ በእርግጥ ሰምቷል11 ታዲያ የቀኢላ መሪዎች ለእሱ አሳልፈው ይሰጡኝ ይሆን? አገልጋይህ እንደሰማውስ ሳኦል ወደዚህ ይወርድ ይሆን? የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ እባክህ ለአገልጋይህ አሳውቀው በዚህ ጊዜ ይሖዋ አዎ ይወርዳል አለው12 ዳዊትም የቀኢላ መሪዎች እኔንና ሰዎቼን ለሳኦል አሳልፈው ይሰጡን ይሆን? በማለት ጠየቀ ይሖዋም አዎ አሳልፈው ይሰጧችኋል ሲል መለሰለት13 ዳዊትም 600 ገደማ ከሚሆኑት የራሱ ሰዎች ጋር ወዲያውኑ ተነሳ ከቀኢላም ወጥተው መሄድ ወደሚችሉበት ቦታ ሁሉ ሄዱ ሳኦልም ዳዊት ከቀኢላ መሸሹ ሲነገረው እሱን ለማሳደድ መውጣቱን ተወው14 ዳዊትም በምድረ በዳው ውስጥ በሚገኙ በቀላሉ በማይደረስባቸው ቦታዎች በዚፍ ምድረ በዳ ባለው ተራራማ አካባቢ ተቀመጠ ሳኦል ሁልጊዜ ይፈልገው ነበር ይሖዋ ግን በእጁ አሳልፎ አልሰጠውም15 ዳዊት በሆሬሽ በሚገኘው በዚፍ ምድረ በዳ ሳለ ሳኦል የእሱን ሕይወት ለመፈለግ መውጣቱን አውቆ ነበር16 የሳኦል ልጅ ዮናታንም በሆሬሽ ወደሚገኘው ወደ ዳዊት ሄደ እሱም በይሖዋ ላይ ያለው ትምክህት እንዲጠናከር ረዳው17 እንዲህም አለው አባቴ ሳኦል ስለማያገኝህ አትፍራ አንተ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆናለህ እኔ ደግሞ ከአንተ ቀጥዬ ሁለተኛ ሰው እሆናለሁ አባቴ ሳኦልም ቢሆን ይህን ያውቃል18 ከዚያም ሁለቱም በይሖዋ ፊት ቃል ኪዳን ተጋቡ ዳዊትም በሆሬሽ ተቀመጠ ዮናታን ደግሞ ወደ ቤቱ ተመለሰ19 በኋላም የዚፍ ሰዎች በጊብዓ ወደነበረው ወደ ሳኦል ወጥተው እንዲህ አሉት ዳዊት እዚሁ አጠገባችን ከየሺሞን በስተ ደቡብ በሃኪላ ኮረብታ ላይ በሆሬሽ በሚገኙት በቀላሉ የማይደረስባቸው ስፍራዎች ተደብቆ የለም?20 አሁንም ንጉሥ ሆይ ወደዚህ ለመውረድ በምትፈልግበት በማንኛውም ጊዜ ወደዚህ ና እኛም እሱን ለንጉሡ አሳልፈን እንሰጣለን21 በዚህ ጊዜ ሳኦል እንዲህ አላቸው ለእኔ ስለተቆረቆራችሁ ይሖዋ ይባርካችሁ22 አሁንም እባካችሁ ሂዱና ያለበትን ትክክለኛ ቦታም ሆነ በዚያ ያየውን ሰው ማንነት ለይታችሁ ለማወቅ ጥረት አድርጉ ምክንያቱም እሱ በጣም ተንኮለኛ ሰው እንደሆነ ሰምቻለሁ23 የሚደበቅባቸውን ቦታዎች በሙሉ በደንብ አጣሩ ከዚያም ተጨባጭ ማስረጃ ይዛችሁልኝ ኑ እኔም አብሬያችሁ እሄዳለሁ በዚያ አገር የሚገኝ ከሆነ ከይሁዳ ሺዎች ሁሉ መካከል የገባበት ገብቼ አወጣዋለሁ24 በመሆኑም ሰዎቹ ተነሱ ከሳኦልም ቀድመው ወደ ዚፍ ሄዱ በዚህ ጊዜ ዳዊትና ሰዎቹ ከየሺሞን በስተ ደቡብ በሚገኘው በአረባ በማኦን ምድረ በዳ ነበሩ25 ሳኦልም ዳዊትን ለመፈለግ ከሰዎቹ ጋር መጣ ዳዊትም ይህ በተነገረው ጊዜ ወዲያውኑ ወደ ዓለቱ ወርዶ በማኦን ምድረ በዳ ተቀመጠ ሳኦል ይህን ሲሰማ ዳዊትን እያሳደደ ወደ ማኦን ምድረ በዳ ሄደ26 ከዚያም ሳኦል ከተራራው በአንደኛው በኩል ሲሆን ዳዊትና ሰዎቹ ደግሞ ከተራራው በሌላኛው በኩል ሆኑ ዳዊት ከሳኦል ለማምለጥ እየተጣደፈ ነበር ይሁን እንጂ ሳኦልና አብረውት የነበሩት ሰዎች ዳዊትንና ሰዎቹን ለመያዝ ተቃርበው ነበር27 ሆኖም አንድ መልእክተኛ ወደ ሳኦል መጥቶ ፍልስጤማውያን ምድሪቱን ስለወረሯት ቶሎ ድረስ! አለው28 በዚህ ጊዜ ሳኦል ዳዊትን ማሳደዱን ትቶ ፍልስጤማውያንን ለመግጠም ሄደ ያ ቦታ የመለያያ ዓለት የተባለው በዚህ የተነሳ ነው29 ዳዊትም ከዚያ ወጥቶ በኤንገዲ በሚገኙ በቀላሉ በማይደረስባቸው ስፍራዎች ተቀመጠ
24 ሳኦል ፍልስጤማውያንን አሳዶ እንደተመለሰ ዳዊት በኤንገዲ ምድረ በዳ ይገኛል ብለው ነገሩት2 ስለዚህ ሳኦል ከመላው እስራኤል የተመረጡ 3,000 ሰዎችን ይዞ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመፈለግ የተራራ ፍየሎች ወደሚገኙበት ዓለታማ ገደላ ገደል ሄደ3 ሳኦልም በመንገዱ ዳር ወዳለ ከድንጋይ የተሠራ የበጎች ጉረኖ ደረሰ በዚያም አንድ ዋሻ ነበር በመሆኑም ሳኦል ለመጸዳዳት ወደ ዋሻው ገባ በዚህ ጊዜ ዳዊትና ሰዎቹ በዋሻው ውስጠኛ ክፍል ተቀምጠው ነበር4 ከዚያም የዳዊት ሰዎች ይሖዋ ጠላትህን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ አንተም ደስ ያለህን ታደርግበታለህ ያለህ ቀን ይህ ነው አሉት ስለሆነም ዳዊት ተነሳ የሳኦልንም ልብስ ጫፍ በቀስታ ቆርጦ ወሰደ5 በኋላ ላይ ግን ዳዊት የሳኦልን ልብስ ጫፍ በመቁረጡ ልቡ ወቀሰው6 አብረውት የነበሩትንም ሰዎች ይሖዋ በቀባው በጌታዬ ላይ እጄን በማንሳት እንዲህ ያለውን ድርጊት መፈጸም በይሖዋ ዓይን ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነው ምክንያቱም እሱ ይሖዋ የቀባው ነው አላቸው7 ስለዚህ ዳዊት ይህን በማለት ሰዎቹን ከለከላቸው በሳኦል ላይ ጉዳት እንዲያደርሱበትም አልፈቀደላቸውም ሳኦልም ተነስቶ ከዋሻው ወጥቶ ሄደ8 ከዚያም ዳዊት ከዋሻው በመውጣት ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! በማለት ሳኦልን ጠራው ሳኦልም ወደኋላው ዞር ብሎ ሲመለከት ዳዊት በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ ሰገደ9 ዳዊትም ሳኦልን እንዲህ አለው ዳዊት የአንተን ክፉ ማየት ይፈልጋል የሚሉትን ሰዎች ወሬ ለምን ትሰማለህ?10 በዛሬዋ ዕለት በዋሻው ውስጥ ይሖዋ አንተን እንዴት አድርጎ በእጄ ሰጥቶኝ እንደነበር በገዛ ዓይንህ አይተሃል አንድ ሰው እንድገድልህ ገፋፍቶኝ የነበረ ቢሆንም እኔ ግን ለአንተ በማዘን ይሖዋ የቀባው ስለሆነ በጌታዬ ላይ እጄን አላነሳም አልኩ11 አሁንም አባቴ ሆይ ተመልከት በእጄ የያዝኩትን የልብስህን ቁራጭ እይ የልብስህን ጫፍ በቆረጥኩ ጊዜ ልገድልህ እችል ነበር ግን አልገደልኩህም እንግዲህ አንተን ለመጉዳትም ሆነ በአንተ ላይ ለማመፅ ፈጽሞ እንዳላሰብኩ ከዚህ ማየትና መረዳት ትችላለህ ምንም እንኳ ሕይወቴን ለማጥፋት እያሳደድከኝ ቢሆንም እኔ በአንተ ላይ ምንም የፈጸምኩት በደል የለም12 ይሖዋ በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ ይሖዋ አንተን ይበቀልልኝ እንጂ እኔ በምንም ዓይነት እጄን በአንተ ላይ አላነሳም13 ከክፉ ሰው ክፉ ነገር ይወጣል የሚል የጥንት አባባል አለ እኔ ግን በምንም ዓይነት እጄን በአንተ ላይ አላነሳም14 ለመሆኑ የእስራኤል ንጉሥ የወጣው ማንን ፍለጋ ነው? የምታሳድደውስ ማንን ነው? አንድን የሞተ ውሻ? ወይስ አንዲትን ቁንጫ?15 አሁንም ይሖዋ ዳኛ ሆኖ በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ ጉዳዩንም ተመልክቶ ስለ እኔ ይሟገትልኝ እሱ ይፍረድልኝ ከእጅህም ያድነኝ16 ዳዊት ይህን ተናግሮ ሲጨርስ ሳኦል ልጄ ዳዊት ይህ የአንተ ድምፅ ነው? አለው ከዚያም ሳኦል ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ17 ዳዊትንም እንዲህ አለው አንተ መልካም ስታደርግልኝ እኔ ግን ክፉ መለስኩልህ ስለሆነም አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ18 አዎ ይሖዋ እኔን በእጅህ አሳልፎ ቢሰጥህም ሳትገድለኝ በመቅረት ለእኔ ያደረግከውን መልካም ነገር ይኸው ዛሬ ነገርከኝ19 ለመሆኑ ጠላቱን አግኝቶ ጉዳት ሳያደርስበት የሚለቀው ሰው ይኖራል? ዛሬ አንተ ለእኔ መልካም ስላደረግክልኝ ይሖዋም ለአንተ መልካም በማድረግ ወሮታህን ይመልስልህ20 ደግሞም አንተ በእርግጥ ንጉሥ ሆነህ እንደምትገዛ አውቃለሁ የእስራኤልም መንግሥት በእጅህ ይጸናል21 በመሆኑም አሁን ከእኔ በኋላ የሚመጡትን ዘሮቼን እንደማታጠፋና ስሜንም ከአባቴ ቤት እንደማትደመስስ በይሖዋ ማልልኝ22 ስለዚህ ዳዊት ለሳኦል ማለለት ከዚያም ሳኦል ወደ ቤቱ ሄደ ዳዊትና ሰዎቹ ግን ወደ ምሽጉ ወጡ
25 ከጊዜ በኋላም ሳሙኤል ሞተ እስራኤላውያንም በሙሉ ሊያለቅሱለትና በራማ በሚገኘው ቤቱ ሊቀብሩት ተሰበሰቡ ከዚያም ዳዊት ተነስቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ2 በማኦን የሚኖር እጅግ ባለጸጋ የሆነ አንድ ሰው ነበር ይህ ሰው የሚሠራው በቀርሜሎስ ሲሆን 3,000 በጎችና 1,000 ፍየሎች ነበሩት በዚያን ወቅት በቀርሜሎስ በጎቹን እየሸለተ ነበር3 የሰውየው ስም ናባል የሚስቱ ስም ደግሞ አቢጋኤል ነበር እሷም በጣም አስተዋይና ውብ ሴት ነበረች ከካሌብ ወገን የሆነው ባሏ ግን ኃይለኛና ምግባረ ብልሹ ሰው ነበር4 ዳዊት በምድረ በዳ ሳለ ናባል በጎቹን እየሸለተ መሆኑን ሰማ5 ስለዚህ ዳዊት አሥር ወጣቶችን ወደ እሱ ላከ ዳዊትም ወጣቶቹን እንዲህ አላቸው ወደ ቀርሜሎስ ወጥታችሁ ናባልን ስታገኙት በስሜ ስለ ደህንነቱ ጠይቁት6 ከዚያም ናባልን እንዲህ በሉት ረጅም ዕድሜና ጤና እመኝልሃለሁ ለመላ ቤተሰብህና የአንተ ለሆነው ሁሉ ሰላም ይሁን7 በጎችህን እየሸለትክ እንዳለህ ሰምቻለሁ እረኞችህም ከእኛ ጋር በነበሩበት ጊዜ ምንም ዓይነት ጉዳት አላደረስንባቸውም በቀርሜሎስ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ ምንም ነገር አልጠፋባቸውም8 ወጣቶችህን ጠይቅ ይነግሩሃል እንግዲህ የመጣነው በደስታ ቀን ስለሆነ ወጣቶቼ በፊትህ ሞገስ ያግኙ እባክህ ለአገልጋዮችህና ለልጅህ ለዳዊት የቻልከውን ያህል ስጥ9 በመሆኑም ዳዊት የላካቸው ወጣቶች ሄደው ይህን ሁሉ በዳዊት ስም ለናባል ነገሩት ተናግረው እንዳበቁም10 ናባል የዳዊትን አገልጋዮች እንዲህ አላቸው ለመሆኑ ዳዊት ማን ነው? ደግሞስ የእሴይ ልጅ ማን ነው? በአሁኑ ጊዜ እንደሆነ ከጌቶቻቸው የሚኮበልሉ አገልጋዮች ብዙ ናቸው11 ታዲያ ዳቦዬን ውኃዬንና ለሚሸልቱልኝ ሰዎች ያረድኩትን ሥጋ ከየት እንደመጡ እንኳ ለማላውቃቸው ሰዎች መስጠት ይኖርብኛል?12 ዳዊት የላካቸው ወጣቶችም ወደመጡበት ተመልሰው በመሄድ የተባሉትን ሁሉ ነገሩት13 ዳዊትም ወዲያውኑ አብረውት ላሉት ሰዎች በሉ ሁላችሁም ሰይፋችሁን ታጠቁ! አላቸው በመሆኑም ሁሉም ሰይፋቸውን ታጠቁ ዳዊትም ሰይፉን ታጠቀ ወደ 400 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ከዳዊት ጋር ሲወጡ 200ዎቹ ግን ጓዙን ለመጠበቅ እዚያው ቀሩ14 ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአገልጋዮቹ አንዱ ለናባል ሚስት ለአቢጋኤል እንዲህ አላት እነሆ ዳዊት ለጌታችን መልካም ምኞቱን ለመግለጽ መልእክተኞችን ከምድረ በዳ ልኮ ነበር እሱ ግን የስድብ ናዳ አወረደባቸው15 ሰዎቹ ለእኛ እጅግ ጥሩ ነበሩ ምንም ዓይነት ጉዳት አድርሰውብን አያውቁም በመስክ ከእነሱ ጋር አብረን በነበርንባቸው ጊዜያት ሁሉ አንድም ነገር ጠፍቶብን አያውቅም16 መንጋውን እየጠበቅን ከእነሱ ጋር በቆየንባቸው ጊዜያት ሁሉ ሌሊትም ሆነ ቀን በዙሪያችን እንደ መከላከያ ቅጥር ሆነውልን ነበር17 እንግዲህ አሁን በጌታችንና በቤቱ ሁሉ ላይ ጥፋት መምጣቱ ስለማይቀር ምን ማድረግ እንዳለብሽ ወስኚ እሱ እንደሆነ የማይረባ ሰው ስለሆነ ማንም ሊያናግረው አይችልም18 ስለሆነም አቢጋኤል ወዲያውኑ 200 ዳቦ ሁለት እንስራ የወይን ጠጅ ታርደው የተሰናዱ አምስት በጎች አምስት የሲህ መስፈሪያ ቆሎ 100 የዘቢብ ቂጣ እንዲሁም 200 የበለስ ጥፍጥፍ ወስዳ ሁሉንም በአህዮች ላይ ጫነች19 ከዚያም አገልጋዮቿን ቀድማችሁኝ ሂዱ እኔም እከተላችኋለሁ አለቻቸው ለባሏ ለናባል ግን ምንም አልነገረችውም20 አቢጋኤልም አህያ ላይ እንደተቀመጠች በተራራው ተከልላ እየወረደች ሳለ ዳዊትና ሰዎቹም ወደ እሷ እየወረዱ ነበር እሷም አገኘቻቸው21 ዳዊትም እንዲህ ብሎ ነበር በምድረ በዳ የዚህን ሰው ንብረት የጠበቅኩለት ለካስ እንዲያው በከንቱ ነበር ደግሞም ከንብረቱ መካከል አንድም ነገር አልጠፋበትም እሱ ግን ደግ በሠራሁለት ክፉ መለሰልኝ22 የእሱ ከሆኑት ወንዶች መካከል እስከ ነገ ጠዋት ድረስ አንድ ሰው እንኳ ባስቀር አምላክ በዳዊት ጠላቶች ላይ ይህን ያድርግ ከዚህ የከፋም ነገር ያምጣ23 አቢጋኤልም ዳዊትን ባየችው ጊዜ ከተቀመጠችበት አህያ ላይ በፍጥነት በመውረድ በዳዊት ፊት በግንባሯ ተደፍታ ሰገደች24 ከዚያም እግሩ ላይ ወድቃ እንዲህ አለችው ጌታዬ ሆይ ጥፋቱ በእኔ ላይ ይሁን እባክህ አገልጋይህ እንድታናግርህ ፍቀድላት የአገልጋይህንም ቃል ስማ25 እባክህ ጌታዬ ናባል የተባለውን ይህን የማይረባ ሰው ከቁብ አትቁጠረው እሱ ልክ እንደ ስሙ ነውና ስሙ ናባል ነው ደግሞም ማስተዋል የጎደለው ሰው ነው እኔ አገልጋይህ ግን ጌታዬ የላካቸውን ወጣቶች አላየሁም26 እናም አሁን ጌታዬ ሕያው በሆነው በይሖዋና በሕያውነትህ እምላለሁ በደም ዕዳ ተጠያቂ ከመሆንና በራስህ እጅ ከመበቀል የጠበቀህ ይሖዋ ነው አሁንም ጠላቶችህና ጌታዬን ሊጎዱ የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ27 ስለዚህ አገልጋይህ ለጌታዬ ያመጣችው ይህ ስጦታ ጌታዬን ለሚከተሉት ወጣቶች ይሰጥ28 ጌታዬ እየተዋጋ ያለው የይሖዋን ጦርነት ስለሆነ ይሖዋ የጌታዬን ቤት ለዘለቄታው ያጸናለታል ስለሆነም እባክህ የአገልጋይህን መተላለፍ ይቅር በል በሕይወት ዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህ29 ማንም ሰው አንተን ለማሳደድ ቢነሳና ሕይወትህን ለማጥፋት ቢፈልግ የጌታዬ ሕይወት በአምላክህ በይሖዋ ዘንድ በደንብ በታሰረ የሕይወት ከረጢት ውስጥ ትቀመጣለች የጠላቶችህን ሕይወት ግን ከወንጭፍ እንደሚወረወር ድንጋይ ይወነጭፈዋል30 ይሖዋ ቃል የገባለትን መልካም ነገር ሁሉ ለጌታዬ በሚፈጽምለትና በእስራኤል ላይ መሪ አድርጎ በሚሾመው ጊዜ31 ጌታዬ ያለምክንያት ደም በማፍሰሱና እጁን ለበቀል በማንሳቱ ልቡን የሚቆጨው ወይም የሚጸጽተው ነገር አይኖርም ይሖዋ ለጌታዬ መልካም ነገር በሚያደርግለት ጊዜ አገልጋይህን አስባት32 በዚህ ጊዜ ዳዊት አቢጋኤልን እንዲህ አላት ዛሬ እኔን እንድታገኚኝ የላከሽ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ይወደስ!33 ማስተዋልሽም የተባረከ ይሁን! በዚህ ዕለት በራሴ ላይ የደም ዕዳ እንዳላመጣና በገዛ እጄ እንዳልበቀል ስለጠበቅሽኝ አንቺም የተባረክሽ ሁኚ34 በአንቺ ላይ ጉዳት ከማድረስ በጠበቀኝ ሕያው በሆነው በእስራኤል አምላክ በይሖዋ እምላለሁ እኔን ለማግኘት ፈጥነሽ ባትመጪ ኖሮ እስከ ነገ ጠዋት ድረስ የናባል የሆነ አንድም ወንድ ባልተረፈ ነበር35 ከዚያም ዳዊት ያመጣችለትን ነገር ከእጇ ተቀብሎ ወደ ቤትሽ በሰላም ሂጂ ይኸው ቃልሽን ሰምቻለሁ የጠየቅሽኝንም እፈጽምልሻለሁ አላት36 በኋላም አቢጋኤል በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ታላቅ ግብዣ አዘጋጅቶ ወደነበረው ወደ ናባል ተመለሰች ናባልም ልቡ በሐሴት ተሞልቶ በጣም ሰክሮ ነበር እሷም እስኪነጋ ድረስ ምንም ነገር አልነገረችውም37 ጠዋት ላይ ናባል ስካሩ ሲበርድለት ሚስቱ የሆነውን ሁሉ ነገረችው ልቡም እንደ ሞተ ሰው ልብ ሆነ ሰውነቱም እንደ ድንጋይ በድን ሆነ38 ከአሥር ቀን ገደማ በኋላም ይሖዋ ናባልን ስለቀሰፈው ሞተ39 ዳዊት ናባል መሞቱን ሲሰማ እንዲህ አለ ከናባል የደረሰብኝን ነቀፋ የተሟገተልኝና አገልጋዩን መጥፎ ድርጊት ከመፈጸም የጠበቀው ይሖዋ ይወደስ ይሖዋ የናባልን ክፋት በራሱ ላይ መለሰው! ከዚያም ዳዊት አቢጋኤል ሚስት እንድትሆነው ጥያቄ ለማቅረብ መልእክት ላከ40 በመሆኑም የዳዊት አገልጋዮች በቀርሜሎስ ወዳለችው ወደ አቢጋኤል መጥተው ዳዊት ሊያገባሽ ስለፈለገ ወደ አንቺ ልኮናል አሏት41 እሷም ወዲያውኑ ተነሳች በግንባሯም ተደፍታ በመስገድ ባሪያህ እንደ አገልጋይ በመሆን የጌታዬን አገልጋዮች እግር ለማጠብ ዝግጁ ነች አለች42 ከዚያም አቢጋኤል ፈጥና ተነሳች አምስት ሴት አገልጋዮቿንም በማስከተል በአህያ ላይ ተቀምጣ ጉዞ ጀመረች ከዳዊት መልእክተኞችም ጋር አብራ ሄደች የዳዊትም ሚስት ሆነች43 በተጨማሪም ዳዊት ከኢይዝራኤል አኪኖዓምን አግብቶ ነበር ሁለቱም ሴቶች ሚስቶቹ ሆኑ44 ሳኦል ግን የዳዊት ሚስት የነበረችውን ልጁን ሜልኮልን የጋሊም ሰው ለሆነው ለላይሽ ልጅ ለፓልጢ ድሯት ነበር
26 ከጊዜ በኋላ የዚፍ ሰዎች በጊብዓ ወደሚገኘው ወደ ሳኦል መጥተው ዳዊት በየሺሞን ፊት ለፊት በሚገኘው በሃኪላ ኮረብታ ተደብቆ የለም? አሉት2 ስለሆነም ሳኦል ከእስራኤል የተመረጡ 3,000 ሰዎችን በማስከተል ዳዊትን በዚፍ ምድረ በዳ ለመፈለግ ወደዚያ ወረደ3 ሳኦልም ከየሺሞን ፊት ለፊት በሚገኘው በሃኪላ ኮረብታ ላይ መንገድ ዳር ሰፈረ በዚህ ጊዜ ዳዊት በምድረ በዳ ይኖር ነበር ዳዊትም ሳኦል እሱን ለመፈለግ ወደ ምድረ በዳ እንደመጣ ሰማ4 በመሆኑም ሳኦል በእርግጥ መጥቶ እንደሆነ ለማወቅ ሰላዮችን ላከ5 በኋላም ዳዊት ሳኦል ወደሰፈረበት ቦታ ሄደ ሳኦልና የሠራዊቱ አዛዥ የሆነው የኔር ልጅ አበኔር የተኙበትንም ቦታ አየ ሳኦል በሰፈሩ መሃል ተኝቶ ነበር ሠራዊቱም ዙሪያውን ሰፍሮ ነበር6 ከዚያም ዳዊት ሂታዊውን አሂሜሌክንና የኢዮዓብ ወንድም የሆነውን የጽሩያን ልጅ አቢሳን ሳኦል ወደሰፈረበት ቦታ አብሮኝ የሚወርድ ማን ነው? አላቸው አቢሳም እኔ አብሬህ እወርዳለሁ አለ7 ስለዚህ ዳዊትና አቢሳ በሌሊት ሠራዊቱ ወዳለበት ሄዱ ሳኦልም ጦሩን ራስጌው አጠገብ መሬት ላይ ሰክቶ በሰፈሩ መሃል ተኝቶ አገኙት አበኔርና ሠራዊቱም በዙሪያው ተኝተው ነበር8 አቢሳም ዳዊትን አምላክ ዛሬ ጠላትህን እጅህ ላይ ጥሎታል እባክህ አሁን አንድ ጊዜ ብቻ በጦር ወግቼ ከመሬት ጋር ላጣብቀው መድገም አያስፈልገኝም አለው9 ሆኖም ዳዊት አቢሳን ጉዳት እንዳታደርስበት ለመሆኑ ይሖዋ በቀባው ላይ እጁን አንስቶ ከበደል ነፃ የሚሆን ማን ነው? አለው10 ከዚያም ዳዊት እንዲህ አለው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ ይሖዋ ራሱ ይቀስፈዋል ወይም ደግሞ እንደ ማንኛውም ሰው አንድ ቀን ይሞታል አሊያም ወደ ጦርነት ወርዶ እዚያ ይገደላል11 በእኔ በኩል ይሖዋ በቀባው ላይ እጄን ማንሳት በይሖዋ ዓይን ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነው! በል አሁን ራስጌው አጠገብ ያለውን ጦርና የውኃ መያዣውን አንሳና እንሂድ12 በመሆኑም ዳዊት ጦሩንና የውኃ መያዣውን ከሳኦል ራስጌ ወሰደ ከዚያም ሄዱ ሁሉም ተኝተው ስለነበር ያያቸውም ሆነ ልብ ያላቸው ወይም ከእንቅልፉ የነቃ አንድም ሰው አልነበረም ምክንያቱም ይሖዋ ከባድ እንቅልፍ ጥሎባቸው ነበር13 ከዚያም ዳዊት ወደ ማዶ ተሻግሮ በተራራው ጫፍ ላይ ራቅ ብሎ ቆመ በመካከላቸውም ያለው ርቀት ሰፊ ነበር14 ዳዊትም ወደ ሠራዊቱና ወደ ኔር ልጅ ወደ አበኔር ተጣርቶ አበኔር የማትመልስልኝ ለምንድን ነው? አለ አበኔርም ንጉሡን የምትጣራው አንተ ማን ነህ? ሲል መለሰለት15 ዳዊትም አበኔርን እንዲህ አለው አንተ ወንድ አይደለህም? ደግሞስ በእስራኤል ውስጥ እንደ አንተ ያለ ማን አለ? ታዲያ ጌታህን ንጉሡን በንቃት ያልጠበቅከው ለምንድን ነው? ምክንያቱም ከወታደሮቹ አንዱ ንጉሡን ጌታህን ለመግደል መጥቶ ነበር16 ይህ ያደረግከው ነገር ጥሩ አይደለም ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ ይሖዋ የቀባውን ጌታችሁን በንቃት ስላልጠበቃችሁ ሞት ይገባችኋል እስቲ ዙሪያህን ተመልከት! በንጉሡ ራስጌ አጠገብ የነበረው የንጉሡ ጦርና የውኃ መያዣ የት አለ?17 ሳኦልም የዳዊት ድምፅ መሆኑን ስለለየ ልጄ ዳዊት ሆይ ይህ የአንተ ድምፅ ነው? አለው ዳዊትም መልሶ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ አዎ የእኔ ድምፅ ነው አለ18 አክሎም እንዲህ አለ ጌታዬ አገልጋዩን የሚያሳድደው ለምንድን ነው? ምን አድርጌ ነው? የተገኘብኝስ በደል ምንድን ነው?19 ጌታዬ ንጉሥ ሆይ እባክህ የአገልጋይህን ቃል ስማ በእኔ ላይ እንድትነሳ ያደረገህ ይሖዋ ከሆነ የማቀርበውን የእህል መባ ይቀበል ሆኖም እንዲህ እንድታደርግ ያነሳሱህ ሰዎች ከሆኑ በይሖዋ ፊት የተረገሙ ይሁኑ ምክንያቱም ሂድ ሌሎች አማልክትን አገልግል! ብለው በይሖዋ ርስት ውስጥ ድርሻ እንዳይኖረኝ ዛሬ አባረውኛል20 አሁንም ደሜ ከይሖዋ ፊት ርቆ መሬት ላይ እንዲፈስ አታድርግ ምክንያቱም የእስራኤል ንጉሥ በተራራ ላይ ቆቅ የሚያሳድድ ይመስል አንዲት ቁንጫ ለመፈለግ ወጥቷል21 ሳኦልም መልሶ እንዲህ አለው በእርግጥ ኃጢአት ሠርቻለሁ ልጄ ዳዊት ሆይ ከእንግዲህ ምንም ጉዳት ስለማላደርስብህ ተመለስ ምክንያቱም በዛሬው ዕለት ሕይወቴን ውድ አድርገህ ተመልክተሃታል በእርግጥም የሞኝነት ድርጊት ፈጽሜአለሁ ትልቅ ስህተት ሠርቻለሁ22 ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰለት የንጉሡ ጦር ይኸውና ከወጣቶቹ መካከል አንዱ ይምጣና ይውሰደው23 ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ጽድቁና እንደ ታማኝነቱ የሚከፍለው ይሖዋ ነው ይኸው ዛሬ ይሖዋ እጄ ላይ ጥሎህ ነበር እኔ ግን ይሖዋ በቀባው ላይ እጄን ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆንኩም24 እነሆ ዛሬ የአንተ ሕይወት በፊቴ ውድ እንደሆነች ሁሉ የእኔም ሕይወት በይሖዋ ፊት ውድ ትሁን ከመከራም ሁሉ ያድነኝ25 ሳኦልም ዳዊትን ልጄ ዳዊት ሆይ የተባረክ ሁን አንተ ታላላቅ ሥራዎችን ታከናውናለህ ድል አድራጊም ትሆናለህ አለው ከዚያም ዳዊት መንገዱን ቀጠለ ሳኦልም ወደ ስፍራው ተመለሰ
27 ሆኖም ዳዊት በልቡ እንዲህ አለ አንድ ቀን በሳኦል እጅ መጥፋቴ አይቀርም የሚያዋጣኝ ወደ ፍልስጤማውያን ምድር መሸሽ ነው ሳኦልም ተስፋ ቆርጦ በእስራኤል ግዛት ሁሉ እኔን መፈለጉን ያቆማል እኔም ከእጁ አመልጣለሁ2 በመሆኑም ዳዊት አብረውት ከነበሩት 600 ሰዎች ጋር ተነስቶ የጌት ንጉሥ ወደሆነው ወደ ማኦክ ልጅ ወደ አንኩስ ተሻገረ3 ዳዊትና ሰዎቹም እያንዳንዳቸው ከነቤተሰባቸው ጌት ውስጥ አንኩስ ዘንድ ተቀመጡ ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ማለትም ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪኖዓም እና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢጋኤል ጋር ነበር4 ሳኦልም ዳዊት ወደ ጌት መሸሹ ሲነገረው እሱን መፈለጉን ተወ5 ከዚያም ዳዊት አንኩስን በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ በገጠር ካሉ ከተሞች በአንዱ እንድኖር ቦታ እንዲሰጡኝ አድርግ አገልጋይህ ለምን በንጉሥ ከተማ ከአንተ ጋር ይኖራል? አለው6 በመሆኑም አንኩስ በዚያ ቀን ጺቅላግን ሰጠው ጺቅላግ እስካሁንም ድረስ የይሁዳ ነገሥታት ይዞታ የሆነችው በዚህ ምክንያት ነው7 ዳዊት በፍልስጤማውያን ገጠራማ አካባቢ የኖረበት ጊዜ አንድ ዓመት ከአራት ወር ነበር8 ዳዊትም ከሰዎቹ ጋር በመሆን ገሹራውያንን ጊዝራውያንን እና አማሌቃውያንን ለመውረር ይወጣ ነበር ምክንያቱም እነዚህ ሕዝቦች ከቴላም አንስቶ እስከ ሹር እና እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ባለው አካባቢ ይኖሩ ነበር9 ዳዊት በምድሪቱ ላይ ጥቃት በሚሰነዝርበት ጊዜ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አያስቀርም ነበር ሆኖም መንጎችን ከብቶችን አህዮችን ግመሎችንና ልብሶችን ወስዶ ወደ አንኩስ ይመለስ ነበር10 አንኩስም ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ? ይለው ነበር ዳዊትም በይሁዳ ደቡባዊ ክፍል ላይ ዘምተን ነበር ወይም በየራህምኤላውያን ምድር ደቡባዊ ክፍል ላይ ዘምተን ነበር አሊያም በቄናውያን ምድር ደቡባዊ ክፍል ላይ ዘምተን ነበር በማለት ይመልስለት ነበር11 ዳዊት እሱ እንዲህ አደረገ በማለት ስለ እኛ ሊነግሯቸው ይችላሉ ብሎ ስላሰበ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አስተርፎ ወደ ጌት አያመጣም ነበር ዳዊት በፍልስጤም ገጠራማ አካባቢ በኖረበት ዘመን ሁሉ እንዲህ የማድረግ ልማድ ነበረው12 ስለዚህ አንኩስ በእርግጥም ይህ ሰው በገዛ ሕዝቦቹ በእስራኤላውያን ዘንድ እንደ ጥንብ ተቆጥሯል ስለሆነም ዕድሜ ልኩን አገልጋዬ ይሆናል ብሎ ስላሰበ ዳዊትን አመነው
28 በዚያም ዘመን ፍልስጤማውያን ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ሠራዊታቸውን አሰባሰቡ በመሆኑም አንኩስ ዳዊትን መቼም አንተና ሰዎችህ አብራችሁኝ ወደ ጦርነት እንደምትወጡ ታውቃለህ አለው2 ዳዊትም አንኩስን አገልጋይህ ምን እንደሚያደርግ አንተ በእርግጥ ታውቃለህ አለው ከዚያም አንኩስ ዳዊትን እኔም በቋሚነት የግል ጠባቂዬ እንድትሆን የምሾምህ ለዚህ ነው አለው3 በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ሞቶ ነበር እስራኤላውያንም ሁሉ አልቅሰውለት በገዛ ከተማው በራማ ቀብረውት ነበር ሳኦልም መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ከምድሪቱ አስወግዶ ነበር4 ፍልስጤማውያንም ተሰብስበው በመምጣት በሹነም ሰፈሩ ሳኦል ደግሞ እስራኤላውያንን በሙሉ አሰባሰበ እነሱም በጊልቦአ ሰፈሩ5 ሳኦል የፍልስጤማውያንን ሠራዊት ባየ ጊዜ ፈራ ልቡም እጅግ ተሸበረ6 ሳኦል ይሖዋን ቢጠይቅም ይሖዋ በሕልምም ሆነ በኡሪም አሊያም በነቢያት በኩል መልስ አልሰጠውም7 በመጨረሻም ሳኦል አገልጋዮቹን መናፍስት ጠሪ ፈልጉልኝ እኔም ሄጄ ምክር እጠይቃታለሁ አላቸው አገልጋዮቹም በኤንዶር አንዲት መናፍስት ጠሪ አለች በማለት መለሱለት8 በመሆኑም ሳኦል ማንነቱን ሰውሮና ሌላ ልብስ ለብሶ ከሁለት ሰዎች ጋር በመሆን በሌሊት ወደ ሴትየዋ ሄደ እሱም እባክሽ መናፍስትን ጠርተሽ ጠንቁይልኝ የምነግርሽንም ሰው አስነሺልኝ አላት9 ሆኖም ሴትየዋ እንዲህ አለችው ሳኦል መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ከምድሪቱ በማስወገድ ምን እንዳደረገ አንተ ራስህ በሚገባ ታውቃለህ ታዲያ እኔ እንድገደል ልታጠምደኝ የምትሞክረው ለምንድን ነው?10 ከዚያም ሳኦል ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ በዚህ ጉዳይ በጥፋተኝነት አትጠየቂም! በማለት በይሖዋ ማለላት11 በዚህ ጊዜ ሴትየዋ እሺ ማንን ላስነሳልህ? አለችው እሱም ሳሙኤልን አስነሺልኝ አላት12 ሴትየዋም ሳሙኤልን ስታየው በኃይል ጮኸች ከዚያም ሳኦልን ያታለልከኝ ለምንድን ነው? አንተ ሳኦል አይደለህ! አለችው13 ንጉሡም አትፍሪ ለመሆኑ ምን እያየሽ ነው? አላት ሴትየዋም ለሳኦል አማልክትን የሚመስል ከምድር ሲወጣ አያለሁ ስትል መለሰችለት14 እሱም ወዲያውኑ ምን ይመስላል? አላት እሷም የወጣው አንድ አረጋዊ ሰው ነው እጅጌ የሌለው ቀሚስ ለብሷል አለችው በዚህ ጊዜ ሳኦል የወጣው ሳሙኤል እንደሆነ ተገነዘበ በግንባሩም መሬት ላይ ተደፍቶ ሰገደ15 ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልን እንድነሳ በማድረግ ለምን ትረብሸኛለህ? አለው ሳኦልም እንዲህ አለው ከባድ ጭንቅ ውስጥ ገብቻለሁ ፍልስጤማውያን እየወጉኝ ነው አምላክም ከእኔ ርቋል በነቢያትም ሆነ በሕልም አማካኝነት መልስ አይሰጠኝም ስለሆነም ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንድትነግረኝ ጠራሁህ16 ሳሙኤልም እንዲህ አለው ታዲያ ይሖዋ ከራቀህና ጠላት ከሆነብህ እኔን ለምን ትጠይቀኛለህ?17 ይሖዋ በእኔ በኩል አስቀድሞ የተናገረውን ይፈጽማል ይሖዋ መንግሥትን ከእጅህ ነጥቆ ከባልንጀሮችህ አንዱ ለሆነው ለዳዊት ይሰጠዋል18 የይሖዋን ቃል ስላልሰማህና በአማሌቃውያን ላይ የነደደውን ቁጣውን ስላላስፈጸምክ ይሖዋ በዚህ ቀን ይህን ያደርግብሃል19 ይሖዋ አንተንም ሆነ እስራኤላውያንን ለፍልስጤማውያን አሳልፎ ይሰጣችኋል ነገ አንተና ልጆችህ ከእኔ ጋር ትሆናላችሁ በተጨማሪም ይሖዋ የእስራኤልን ሠራዊት ለፍልስጤማውያን አሳልፎ ይሰጣል20 በዚህ ጊዜ ሳኦል በቁመቱ መሬት ላይ ተዘረረ ሳሙኤል በተናገረውም ቃል የተነሳ በከፍተኛ ፍርሃት ተዋጠ ደግሞም ሙሉ ቀንና ሙሉ ሌሊት እህል ስላልቀመሰ አቅሙ ተሟጠጠ21 ሴትየዋም ወደ ሳኦል መጥታ በጣም እንደተረበሸ ስታይ እንዲህ አለችው እንግዲህ እኔ አገልጋይህ ቃልህን ሰምቻለሁ ሕይወቴን አደጋ ላይ ጥዬም እንዳደርገው የነገርከኝን ፈጽሜአለሁ22 አሁንም እባክህ የአገልጋይህን ቃል ስማ ትንሽ ምግብ ላቅርብልህና ብላ ከዚያም ለመሄድ የሚያስችል ብርታት ታገኛለህ23 እሱ ግን አልበላም በማለት እንቢ አለ ሆኖም አገልጋዮቹና ሴትየዋ አጥብቀው ለመኑት በመጨረሻም ቃላቸውን በመስማት ከመሬት ተነስቶ አልጋ ላይ ተቀመጠ24 ሴትየዋም ቤት ውስጥ አንድ የሰባ ጥጃ ነበራት ስለዚህ ፈጠን ብላ ጥጃውን አረደችው ከዚያም ዱቄት ወስዳ ካቦካች በኋላ ቂጣ ጋገረች25 ለሳኦልና ለአገልጋዮቹም አቀረበችላቸው እነሱም በሉ ከዚያም ተነስተው በሌሊት ሄዱ
29 ፍልስጤማውያን ሠራዊታቸውን በሙሉ በአፌቅ አሰባሰቡ እስራኤላውያን ደግሞ በኢይዝራኤል በሚገኘው ምንጭ አጠገብ ሰፍረው ነበር2 የፍልስጤም ገዢዎችም በመቶዎችና በሺዎች እየሆኑ አለፉ ዳዊትና ሰዎቹም ከአንኩስ ጋር ሆነው ከኋላ ተሰልፈው ይሄዱ ነበር3 የፍልስጤም መኳንንት ግን እነዚህ ዕብራውያን እዚህ ምን ያደርጋሉ? አሉ በዚህ ጊዜ አንኩስ የፍልስጤምን መኳንንት ይህ ሰው ከእኔ ጋር ለአንድ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ አብሮኝ የኖረው የእስራኤል ንጉሥ የሳኦል አገልጋይ የሆነው ዳዊት ነው ወደ እኔ ከተጠጋበት ቀን አንስቶ እስከዚህች ዕለት ድረስ ምንም ስህተት አላገኘሁበትም አላቸው4 የፍልስጤም መኳንንት ግን በእሱ ላይ ተቆጥተው እንዲህ አሉት ይህ ሰው እንዲመለስ አድርግ ወደሰጠኸውም ስፍራ ይመለስ በውጊያው ወቅት እኛኑ ዞሮ እንዳይወጋን አብሮን ወደ ጦርነቱ እንዲሄድ ማድረግ የለብህም ደግሞስ ከጌታው ጋር ለመታረቅ የእኛን ሰዎች ራስ ቆርጦ ከመውሰድ በስተቀር ምን የተሻለ ነገር ሊያደርግ ይችላል?5 ይህ ሰውሳኦል ሺዎችን ገደለዳዊት ደግሞ አሥር ሺዎችን ገደለ በማለት እየዘፈኑ የጨፈሩለት ዳዊት አይደለም?6 በመሆኑም አንኩስ ዳዊትን ጠርቶ እንዲህ አለው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ አንተ ቅን ሰው ነህ በእኔ በኩል ከሠራዊቴ ጋር አብረህ ብትዘምት ደስ ባለኝ ምክንያቱም ወደ እኔ ከመጣህበት ቀን አንስቶ እስከዚህች ዕለት ድረስ ምንም ስህተት አላገኘሁብህም ሆኖም ገዢዎቹ አላመኑህም7 ስለዚህ በሰላም ተመለስ የፍልስጤም ገዢዎችን ቅር የሚያሰኝ ምንም ነገር አታድርግ8 ዳዊት ግን አንኩስን ምን አደረግኩ? ወደ አንተ ከመጣሁበት ጊዜ አንስቶ እስከዚህች ዕለት ድረስ በአገልጋይህ ላይ ምን ጥፋት አግኝተህበታል? ከአንተ ጋር የማልሄደውና ከንጉሡ ከጌታዬ ጠላቶች ጋር የማልዋጋው ለምንድን ነው? አለው9 አንኩስም ዳዊትን እንዲህ አለው በእኔ በኩል አንተ እንደ አምላክ መልአክ ጥሩ ሰው ነህ የፍልስጤም መኳንንት ግን ከእኛ ጋር ለጦርነት እንዲወጣ አታድርግ አሉኝ10 አሁንም አብረውህ ከመጡት የጌታህ አገልጋዮች ጋር በማለዳ ተነሱ ልክ ጎህ ሲቀድ ጉዞ ጀምሩ11 በመሆኑም ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ፍልስጤማውያን ምድር ለመመለስ በጠዋት ተነሱ ፍልስጤማውያንም ወደ ኢይዝራኤል ወጡ
3 ይህ በእንዲህ እንዳለ ብላቴናው ሳሙኤል በኤሊ ፊት ይሖዋን ያገለግል ነበር ይሁን እንጂ በዚያ ዘመን ከይሖዋ የሚመጣ ቃል ብርቅ ነበር ራእይ ማየትም ቢሆን ብዙ የተለመደ አልነበረም2 አንድ ቀን ኤሊ የተለመደው ቦታው ላይ ተኝቶ ነበር ዓይኖቹ ስለደከሙ ማየት ተስኖታል3 የአምላክም መብራት ገና አልጠፋም ሳሙኤልም የአምላክ ታቦት ባለበት የይሖዋ ቤተ መቅደስ ውስጥ ተኝቶ ነበር4 ከዚያም ይሖዋ ሳሙኤልን ጠራው እሱም አቤት አለ5 ወደ ኤሊም እየሮጠ ሄዶ አቤት ጠራኸኝ? አለው እሱ ግን አይ አልጠራሁህም ተመልሰህ ተኛ አለው በመሆኑም ሄዶ ተኛ6 ይሖዋም እንደገና ሳሙኤል! ሲል ጠራው በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ተነስቶ ወደ ኤሊ በመሄድ አቤት ጠራኸኝ? አለው እሱ ግን ኧረ አልጠራሁህም ልጄ ተመልሰህ ተኛ አለው7 ሳሙኤል ይሖዋን ገና አላወቀውም ነበር የይሖዋም ቃል ቢሆን ገና አልተገለጠለትም ነበር8 በመሆኑም ይሖዋ ለሦስተኛ ጊዜ እንደገና ሳሙኤል! ሲል ጠራው እሱም ተነስቶ ወደ ኤሊ በመሄድ አቤት ጠራኸኝ? አለውኤሊም ብላቴናውን እየጠራው ያለው ይሖዋ መሆኑን አስተዋለ9 በመሆኑም ኤሊ ሳሙኤልን እንዲህ አለው ሂድና ተኛ እንደገና ከጠራህ ይሖዋ ሆይ አገልጋይህ እየሰማ ስለሆነ ተናገር በል ሳሙኤልም ወደ ስፍራው ተመልሶ ተኛ10 ይሖዋም መጥቶ በዚያ ቆመ እንደ ሌላው ጊዜም ሳሙኤል ሳሙኤል! ሲል ጠራው ሳሙኤልም አገልጋይህ እየሰማ ስለሆነ ተናገር አለ11 ይሖዋ ሳሙኤልን እንዲህ አለው ለሰሚው ሁሉ ጆሮ የሚሰቀጥጥ ነገር በእስራኤል ውስጥ አደርጋለሁ12 በዚያ ቀን ስለ ኤሊ ቤት የተናገርኩትን ነገር ሁሉ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በእሱ ላይ እፈጽማለሁ13 እሱ በሚያውቀው ጥፋት የተነሳ በቤቱ ላይ ለዘለቄታው እንደምፈርድ ንገረው ምክንያቱም ልጆቹ አምላክን ረግመዋል እሱ ግን አልገሠጻቸውም14 በዚህም የተነሳ የኤሊ ቤት የፈጸመው ጥፋት መሥዋዕት ወይም መባ በማቅረብ ፈጽሞ እንደማይሰረይ ለኤሊ ቤት ምያለሁ15 ሳሙኤልም እስከ ንጋት ድረስ ተኛ ከዚያም የይሖዋን ቤት በሮች ከፈተ ሳሙኤል ራእዩን ለኤሊ መንገር ፈርቶ ነበር16 ኤሊ ግን ሳሙኤልን ጠርቶ ልጄ ሳሙኤል! አለው እሱም አቤት አለው17 ኤሊም እንዲህ ሲል ጠየቀው ለመሆኑ የነገረህ መልእክት ምንድን ነው? እባክህ አትደብቀኝ እሱ ከነገረህ ነገር ውስጥ አንዲት ቃል እንኳ ብትደብቀኝ አምላክ እንዲህ ያድርግብህ ከዚያም የከፋ ነገር ያምጣብህ18 በመሆኑም ሳሙኤል እሱ የነገረውን በሙሉ ምንም ሳይደብቅ ነገረው ኤሊም ይህ ከይሖዋ ነው እሱ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ አለ19 ሳሙኤል እያደገ ሄደ ይሖዋም ከእሱ ጋር ነበር የሚናገረውም ቃል ሁሉ እንዲፈጸም ያደርግ ነበር20 ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እስራኤላውያን በሙሉ ሳሙኤል ተቀባይነት ያገኘ የይሖዋ ነቢይ እንደሆነ ተገነዘቡ21 ይሖዋም በሴሎ ይገለጥ ነበር ምክንያቱም ይሖዋ በሴሎ በይሖዋ ቃል አማካኝነት ራሱን ለሳሙኤል ገልጦለት ነበር
30 በሦስተኛው ቀን ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ጺቅላግ ሲመጡ አማሌቃውያን በስተ ደቡብ ያለውን አካባቢና ጺቅላግን ወረው ነበር እነሱም በጺቅላግ ላይ ጥቃት ሰነዘሩ በእሳትም አቃጠሏት2 ሴቶችንና በዚያ የነበሩትንም ሁሉ ትንሽ ትልቅ ሳይሉ ማርከው ወሰዱ አንድም ሰው አልገደሉም ከዚህ ይልቅ ሁሉንም ይዘው ሄዱ3 ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ጺቅላግ ሲመጡ ከተማዋ በእሳት ተቃጥላ አገኟት ሚስቶቻቸውም ሆኑ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው በምርኮ ተወስደው ነበር4 በመሆኑም ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎች ለማልቀስ አቅም እስኪያጡ ድረስ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ5 ሁለቱ የዳዊት ሚስቶችም ማለትም ኢይዝራኤላዊቷ አኪኖዓም እና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቢጋኤል በምርኮ ተወስደው ነበር6 ዳዊት ሰዎቹ ሊወግሩት እየተማከሩ ስለነበር እጅግ ተጨነቀ ምክንያቱም ሰዎቹ ሁሉ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው በመወሰዳቸው ተመርረው ነበር ይሁንና ዳዊት በአምላኩ በይሖዋ ራሱን አበረታ7 ከዚያም ዳዊት የአሂሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን እባክህ ኤፉዱን አምጣልኝ አለው አብያታርም ኤፉዱን ለዳዊት አመጣለት8 ዳዊትም ይህን ወራሪ ቡድን ላሳደው? እደርስበት ይሆን? ሲል ይሖዋን ጠየቀ እሱም በእርግጥ ስለምትደርስባቸውና የወሰዱትን ሁሉ ከእጃቸው ስለምታስጥል ሂድ አሳዳቸው አለው9 ዳዊትም ወዲያውኑ አብረውት ከነበሩት 600 ሰዎች ጋር ወጣ እነሱም እስከ በሶር ሸለቆ ድረስ ሄዱ በዚያም የተወሰኑ ሰዎች ወደ ኋላ ቀሩ10 ዳዊትም ከ400 ሰዎች ጋር ሆኖ ማሳደዱን ቀጠለ በጣም ከመድከማቸው የተነሳ የበሶርን ሸለቆ መሻገር ያልቻሉት 200 ሰዎች ግን እዚያው ቀሩ11 ከዚያም ሜዳ ላይ አንድ ግብፃዊ አግኝተው ወደ ዳዊት አመጡት የሚበላው ምግብና የሚጠጣው ውኃ ሰጡት12 በተጨማሪም ቁራሽ የበለስ ጥፍጥፍና ሁለት የዘቢብ ቂጣ ሰጡት እሱም ከበላ በኋላ ብርታት አገኘ ምክንያቱም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ሙሉ እህልም ሆነ ውኃ አልቀመሰም ነበር13 ዳዊትም ለመሆኑ አንተ የማን ነህ? የመጣኸውስ ከየት ነው? አለው እሱም መልሶ እንዲህ አለው እኔ ለአንድ አማሌቃዊ ባሪያ የሆንኩ ግብፃዊ ነኝ ሆኖም ከሦስት ቀን በፊት ታምሜ ስለነበር ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ14 የከሪታውያንን ምድር ደቡባዊ ክፍል የይሁዳን ግዛትና የካሌብን ደቡባዊ ክፍል ወረርን ጺቅላግንም በእሳት አጋየናት15 በዚህ ጊዜ ዳዊት ይህ ወራሪ ቡድን ወዳለበት መርተህ ትወስደኛለህ? አለው እሱም ብቻ እንደማትገድለኝና ለጌታዬ አሳልፈህ እንደማትሰጠኝ በአምላክ ማልልኝ እንጂ ወራሪው ቡድን ወዳለበት መርቼ አደርስሃለሁ አለው16 በመሆኑም ሰዎቹ ከፍልስጤማውያን ምድርና ከይሁዳ ምድር በወሰዱት ታላቅ ምርኮ የተነሳ በየቦታው ተበታትነው ይበሉና ይጠጡ እንዲሁም ይደሰቱ ወደነበረበት ቦታ መርቶ ወሰደው17 ከዚያም ዳዊት ጎህ ሳይቀድ ጀምሮ እስከ ማግስቱ ምሽት ድረስ መታቸው ፈጽሞም አጠፋቸው በግመል ተቀምጠው ከሸሹት 400 ሰዎች በስተቀር አንድም ሰው አላመለጠም18 ዳዊትም አማሌቃውያን የወሰዱትን ሁሉ አስጣለ ሁለቱን ሚስቶቹንም አስመለሰ19 ከትንሽ እስከ ትልቅ ምንም የጎደለ ነገር አልነበረም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም ሆነ ዘርፈው የወሰዱባቸውን ንብረት ሁሉ አስመለሱ ዳዊት የወሰዱትን ሁሉ አስመለሰ20 በመሆኑም ዳዊት መንጎቹንና ከብቶቹን በሙሉ ወሰደ እነሱም ከራሳቸው ከብቶች ፊት ፊት ነዷቸው እነሱም ይህ የዳዊት ምርኮ ነው አሉ21 ከዚያም ዳዊት በጣም ከመድከማቸው የተነሳ አብረውት ሊሄዱ ወዳልቻሉትና በበሶር ሸለቆ ቀርተው ወደነበሩት 200 ሰዎች መጣ እነሱም ዳዊትንና አብረውት የነበሩትን ሰዎች ለመቀበል ወጡ ዳዊትም ወደ ሰዎቹ በቀረበ ጊዜ ስለ ደህንነታቸው ጠየቃቸው22 ሆኖም ከዳዊት ጋር አብረው ከሄዱት መካከል ክፉ የሆኑትና የማይረቡት ሰዎች እነዚህ ሰዎች አብረውን ስላልሄዱ እያንዳንዳቸው ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ይዘው ይሂዱ እንጂ ካመጣነው ምርኮ ላይ ምንም ነገር አንሰጣቸውም አሉ23 ዳዊት ግን እንዲህ አለ ወንድሞቼ ይሖዋ በሰጠን ነገርማ እንዲህ ማድረግ የለባችሁም የጠበቀንና የመጣብንን ወራሪ ቡድን በእጃችን አሳልፎ የሰጠን እሱ ነው24 ታዲያ አሁን ይህን የምትሉትን ማን ይሰማችኋል? ወደ ውጊያ የዘመተው ሰው የሚያገኘው ድርሻና ጓዝ የጠበቀው ሰው የሚያገኘው ድርሻ እኩል ነው ሁሉም ድርሻ ይኖረዋል25 ዳዊትም ከዚያ ቀን ጀምሮ እስከዚህ ዕለት ድረስ ይህን ለእስራኤል ሥርዓትና ደንብ አድርጎ አጸደቀው26 ዳዊትም ወደ ጺቅላግ በተመለሰ ጊዜ ከይሖዋ ጠላቶች ከተገኘው ምርኮ የተሰጠ ስጦታ ይኸውላችሁ በማለት ወዳጆቹ ለሆኑት የይሁዳ ሽማግሌዎች ከምርኮው ላይ የተወሰነውን ላከ27 ስጦታውንም በቤቴል በኔጌብ ራሞት በያቲር28 በአሮዔር በሲፍሞት በኤሽተሞዓ29 በራካል በየራህምኤል ከተሞች በቄናውያን ከተሞች30 በሆርማ በቦርአሻን በአታክ31 በኬብሮን እንዲሁም ዳዊትና ሰዎቹ በሚያዘወትሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለነበሩት ላከ
31 ፍልስጤማውያን ከእስራኤል ጋር እየተዋጉ ነበር የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጤማውያን ፊት ሸሹ ብዙዎቹም በጊልቦአ ተራራ ላይ ተገደሉ2 ፍልስጤማውያንም ሳኦልንና ወንዶች ልጆቹን እግር በእግር ተከታተሏቸው ፍልስጤማውያንም የሳኦልን ልጆች ዮናታንን አቢናዳብንና ሜልኪሳን መትተው ገደሏቸው3 ውጊያው በሳኦል ላይ በረታ ቀስተኞቹም አገኙት እነሱም ክፉኛ አቆሰሉት4 ከዚያም ሳኦል ጋሻ ጃግሬውን እነዚህ ያልተገረዙ ሰዎች መጥተው እንዳይወጉኝና በጭካኔ እንዳያሠቃዩኝ ሰይፍህን መዘህ ውጋኝ አለው ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለነበር ፈቃደኛ አልሆነም በመሆኑም ሳኦል ሰይፉን ወስዶ በላዩ ላይ ወድቆ ሞተ5 ጋሻ ጃግሬውም ሳኦል መሞቱን ሲያይ እሱም በራሱ ሰይፍ ላይ ወድቆ ከእሱ ጋር ሞተ6 ስለዚህ ሳኦል ሦስቱ ወንዶች ልጆቹ ጋሻ ጃግሬውና የእሱ ሰዎች በሙሉ በዚያ ቀን አብረው ሞቱ7 በሸለቆውና በዮርዳኖስ አካባቢ የነበሩት እስራኤላውያን የእስራኤል ሠራዊት መሸሹን እንዲሁም ሳኦልና ልጆቹ መሞታቸውን ባዩ ጊዜ ከተሞቹን ጥለው ሸሹ ከዚያም ፍልስጤማውያን መጥተው ከተሞቹን ያዙ8 በማግስቱ ፍልስጤማውያን የሞቱትን ሰዎች ልብስና ትጥቅ ለመግፈፍ ሲመጡ ሳኦልንና ሦስቱን ወንዶች ልጆቹን በጊልቦአ ተራራ ላይ ወድቀው አገኟቸው9 ስለሆነም የሳኦልን ራስ ከቆረጡና የጦር ትጥቁን ከገፈፉ በኋላ ወሬው በጣዖቶቻቸው ቤቶችና በሕዝቡ ሁሉ መካከል እንዲሰራጭ ለማድረግ በመላው የፍልስጤም ምድር መልእክት ላኩ10 ከዚያም የጦር ትጥቁን በአስታሮት ምስሎች ቤት አስቀመጡት አስከሬኑን ደግሞ በቤትሻን ግንብ ላይ ቸነከሩት11 የኢያቢስጊልያድ ነዋሪዎችም ፍልስጤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን ሲሰሙ12 ተዋጊዎቹ ሁሉ ተነስተው ሌሊቱን ሙሉ ሲጓዙ አደሩ ከዚያም የሳኦልንና የልጆቹን አስከሬን ከቤትሻን ግንብ ላይ አወረዱ ወደ ኢያቢስ ተመልሰውም በዚያ አቃጠሏቸው13 ከዚያም አፅማቸውን ወስደው በኢያቢስ በሚገኝ የታማሪስክ ዛፍ ሥር ቀበሩት ለሰባት ቀንም ጾሙ
4 የሳሙኤልም ቃል ለእስራኤላውያን ሁሉ ደረሰከዚያም እስራኤላውያን ከፍልስጤማውያን ጋር ለመዋጋት ወጡ ኤቤንዔዘርም አጠገብ ሰፈሩ ፍልስጤማውያን ደግሞ በአፌቅ ሰፍረው ነበር2 ፍልስጤማውያን እስራኤላውያንን ለመግጠም ተሰልፈው ወጡ ውጊያውም እየተፋፋመ ሄደ እስራኤላውያንም ውጊያው በተደረገበት ግንባር 4,000 ሰው በገደሉባቸው በፍልስጤማውያን ድል ተመቱ3 ሠራዊቱ ወደ ሰፈሩ በተመለሰ ጊዜ የእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህ አሉ ይሖዋ በዛሬው ዕለት በፍልስጤማውያን ፊት ድል እንድንመታ የፈቀደው ለምንድን ነው? አብሮን እንዲሆንና ከጠላቶቻችን እጅ እንዲያድነን የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ከሴሎ ይዘነው እንሂድ4 በመሆኑም ሕዝቡ ሰዎችን ወደ ሴሎ ላከ እነሱም ከኪሩቤል በላይ ዙፋን ላይ የተቀመጠውን የሠራዊት ጌታ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ከዚያ ተሸክመው መጡ ሁለቱ የኤሊ ልጆች ሆፍኒ እና ፊንሃስም ከእውነተኛው አምላክ የቃል ኪዳን ታቦት ጋር አብረው ነበሩ5 የይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ሰፈሩ ሲገባ እስራኤላውያን ሁሉ ምድር እስክትናወጥ ድረስ ጮኹ6 ፍልስጤማውያንም ጩኸቱን ሲሰሙ በዕብራውያን ሰፈር የሚሰማው ይህ ሁሉ ጩኸት ምንድን ነው? አሉ በመጨረሻም የይሖዋ ታቦት ወደ ሰፈሩ እንደገባ አወቁ7 ፍልስጤማውያንም አምላክ ወደ ሰፈሩ ገብቷል! በማለት በፍርሃት ተዋጡ በመሆኑም እንዲህ አሉ ወየው ጉዳችን! እንዲህ ዓይነት ነገር ሆኖ አያውቅም!8 ወየው ጉዳችን! ከዚህ ባለ ግርማ አምላክ እጅ ማን ያድነናል? ግብፃውያንን በምድረ በዳ በተለያዩ መቅሰፍቶች የመታቸው አምላክ እኮ ይህ ነው9 እናንተ ፍልስጤማውያን አይዟችሁ ወንድነታችሁን አሳዩ አለዚያ ዕብራውያን የእናንተ አገልጋዮች እንደነበሩ ሁሉ እናንተም የእነሱ አገልጋዮች ትሆናላችሁ ወንድነታችሁን አሳዩ ተዋጉ!10 በመሆኑም ፍልስጤማውያን ተዋጉ እስራኤላውያንም ድል ተመቱ እያንዳንዱም ሰው ወደየድንኳኑ ሸሸ በጣም ብዙ ሕዝብ አለቀ ከእስራኤላውያንም ወገን 30,000 እግረኛ ወታደር ሞተ11 የአምላክም ታቦት ተማረከ ሁለቱ የኤሊ ልጆች ሆፍኒ እና ፊንሃስም ሞቱ12 አንድ ቢንያማዊ ልብሱን ቀዶና በራሱ ላይ አቧራ ነስንሶ ከጦር ግንባሩ እየሮጠ በዚያው ቀን ሴሎ ደረሰ13 ሰውየውም ሲደርስ ኤሊ በእውነተኛው አምላክ ታቦት የተነሳ ልቡ ስለተረበሸ መንገድ ዳር ወንበር ላይ ተቀምጦ ይጠባበቅ ነበር ሰውየውም ወሬውን ለመንገር ወደ ከተማዋ ገባ መላ ከተማዋም በጩኸት ትናወጥ ጀመር14 ኤሊም ጩኸቱን ሲሰማ ይህ ሁሉ ጩኸት ምንድን ነው? በማለት ጠየቀ ሰውየውም በፍጥነት ወደ እሱ ሄዶ ወሬውን ነገረው15 በዚህ ወቅት ኤሊ ዕድሜው 98 ዓመት ነበር ኤሊ ማየት ተስኖት የነበረ ቢሆንም ዓይኖቹ ፊት ለፊት ትኩር ብለው ይመለከቱ ነበር16 ከዚያም ሰውየው ኤሊን ከጦር ግንባሩ የመጣሁት ሰው እኔ ነኝ! ከጦር ግንባሩ ሸሽቼ የመጣሁትም ዛሬ ነው አለው በዚህ ጊዜ ኤሊ ልጄ ለመሆኑ የተከሰተው ነገር ምንድን ነው? ሲል ጠየቀው17 ወሬውን ያመጣውም ሰው እንዲህ አለው እስራኤላውያን ከፍልስጤማውያን ፊት ሸሽተዋል ሕዝቡም ከፍተኛ ሽንፈት ደርሶበታል ሁለቱ ልጆችህ ሆፍኒ እና ፊንሃስም ሞተዋል የእውነተኛው አምላክ ታቦትም ተማርኳል18 ሰውየው ስለ እውነተኛው አምላክ ታቦት በተናገረበት ቅጽበት ኤሊ በሩ አጠገብ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ወደኋላው ወደቀ በዕድሜ የገፋ ከመሆኑም ሌላ ሰውነቱ ከባድ ስለነበር አንገቱ ተሰብሮ ሞተ እሱም ለ40 ዓመት በእስራኤል ላይ ፈራጅ ሆኖ አገልግሏል19 የኤሊ ምራት የፊንሃስ ሚስት ነፍሰ ጡር ነበረች የምትወልድበትም ጊዜ ተቃርቦ ነበር እሷም የእውነተኛው አምላክ ታቦት እንደተማረከ እንዲሁም አማቷና ባሏ እንደሞቱ ስትሰማ ሆዷን ይዛ ጎንበስ አለች ድንገትም ምጥ ያዛትና ወለደች20 እሷም ልትሞት በምታጣጥርበት ጊዜ አጠገቧ ቆመው የነበሩት ሴቶች አይዞሽ ወንድ ልጅ ወልደሻል አሏት እሷ ግን መልስ አልሰጠችም ልብም አላለችውም21 ሆኖም የእውነተኛው አምላክ ታቦት በመማረኩ እንዲሁም በአማቷና በባሏ ላይ በደረሰው ነገር የተነሳ ክብር ከእስራኤል በግዞት ተወሰደ ስትል ለልጁ ኢካቦድ የሚል ስም አወጣችለት22 የእውነተኛው አምላክ ታቦት ስለተማረከ ክብር ከእስራኤል በግዞት ተወሰደ አለች
5 ፍልስጤማውያኑ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ከማረኩ በኋላ ከኤቤንዔዘር ወደ አሽዶድ አመጡት2 እነሱም የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ወስደው ወደ ዳጎን ቤት አስገቡት ከዳጎን አጠገብም አስቀመጡት3 በማግስቱም አሽዶዳውያን በማለዳ ሲነሱ ዳጎን በይሖዋ ታቦት ፊት መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ አገኙት በመሆኑም ዳጎንን አንስተው ወደ ቦታው መለሱት4 በሚቀጥለውም ቀን ማለዳ ሲነሱ ዳጎን በይሖዋ ታቦት ፊት በግንባሩ ተደፍቶ አገኙት የዳጎን ራስና መዳፎቹም ተቆርጠው ደፉ ላይ ወድቀው ነበር ባለበት የቀረው የዓሣው ክፍል ብቻ ነበር5 እስከ ዛሬም ድረስ የዳጎን ካህናትና ወደ ዳጎን ቤት የሚገቡ ሁሉ በአሽዶድ የሚገኘውን የዳጎንን ደፍ የማይረግጡት ለዚህ ነው6 የይሖዋም እጅ በአሽዶዳውያን ላይ ከበደባቸው እሱም አሽዶድንና ግዛቶቿን በኪንታሮት በመምታት አጠፋቸው7 የአሽዶድ ሰዎች የተከሰተውን ነገር ሲያዩ የእስራኤል አምላክ ታቦት በመካከላችን እንዲቆይ አታድርጉ ምክንያቱም እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ጨክኖብናል አሉ8 በመሆኑም ሰዎችን ልከው የፍልስጤምን ገዢዎች በሙሉ በመሰብሰብ የእስራኤልን አምላክ ታቦት ምን ብናደርገው ይሻላል? ብለው ጠየቋቸው እነሱም የእስራኤል አምላክ ታቦት ወደ ጌት ይወሰድ ሲሉ መለሱላቸው ስለሆነም የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወደዚያ ወሰዱት9 ታቦቱንም ወደዚያ ከወሰዱት በኋላ የይሖዋ እጅ በከተማዋ ላይ ሆነ ታላቅ ሽብርም ለቀቀባቸው እሱም የከተማዋን ሰዎች ከትንሽ እስከ ትልቅ መታቸው ኪንታሮትም ወጣባቸው10 በመሆኑም የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ወደ ኤቅሮን ላኩት ሆኖም የእውነተኛው አምላክ ታቦት ኤቅሮን ሲደርስ ኤቅሮናውያን እኛንም ሆነ ሕዝባችንን ለማስፈጀት የእስራኤልን አምላክ ታቦት ይኸው ወደ እኛ ደግሞ አመጡብን! በማለት ይጮኹ ጀመር11 ከዚያም ሰዎችን ልከው የፍልስጤምን ገዢዎች በሙሉ በመሰብሰብ የእስራኤልን አምላክ ታቦት ከዚህ አርቁልን እኛም ሆንን ሕዝባችን እንዳናልቅ ወደ ቦታው እንዲመለስ አድርጉ አሏቸው ምክንያቱም መላ ከተማዋ በሞት ፍርሃት ተውጣ ነበር የእውነተኛውም አምላክ እጅ በዚያ በጣም ከብዶ ነበር12 ያልሞቱት ሰዎችም በኪንታሮት ተመቱ ከተማዋ እርዳታ ለማግኘት የምታሰማው ጩኸትም ወደ ሰማይ ወጣ
6 የይሖዋ ታቦት በፍልስጤማውያን ምድር ሰባት ወር ቆየ2 ፍልስጤማውያኑም ካህናትንና ሟርተኞችን ጠርተው የይሖዋን ታቦት ምን ብናደርገው ይሻላል? ወደ ስፍራው እንዴት እንደምንመልሰው አሳውቁን አሏቸው3 እነሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው የእስራኤልን አምላክ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የምትመልሱ ከሆነ ያለመባ እንዳትመልሱት ከበደል መባ ጋር አድርጋችሁ ወደ እሱ መመለስ ይኖርባችኋል የምትፈወሱት እንዲህ ካደረጋችሁ ብቻ ነው ደግሞም እጁ ከእናንተ ላይ ያልተመለሰው ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ4 ስለዚህ ወደ እሱ መላክ የሚኖርብን የበደል መባ ምንድን ነው? ሲሉ ጠየቁ እነሱም እንዲህ አሏቸው እናንተንም ሆነ ገዢዎቻችሁን ያሠቃየው መቅሰፍት ተመሳሳይ ስለሆነ በፍልስጤም ገዢዎች ቁጥር ልክ አምስት የወርቅ ኪንታሮቶችንና አምስት የወርቅ አይጦችን ላኩ5 ምድሪቱን እያጠፉ ባሉት ኪንታሮቶቻችሁና አይጦቻችሁ አምሳያ ምስሎችን ሥሩ የእስራኤልንም አምላክ አክብሩ ምናልባትም በእናንተ በአምላካችሁና በምድራችሁ ላይ የከበደውን እጁን ያቀልላችሁ ይሆናል6 ግብፅና ፈርዖን ልባቸውን እንዳደነደኑት እናንተም ለምን ልባችሁን ታደነድናላችሁ? እሱ ክፉኛ በቀጣቸው ጊዜ እስራኤላውያንን ለቀቋቸው እነሱም ሄዱ7 ስለዚህ አሁን አዲስ ሠረገላ እንዲሁም እንቦሶች ያሏቸውና ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት ላሞች አዘጋጁ ከዚያም ሠረገላውን ጥመዱባቸው እንቦሶቻቸውን ግን ከእነሱ ነጥላችሁ ወደ ቤት መልሷቸው8 የይሖዋን ታቦት ወስዳችሁ ሠረገላው ላይ አስቀምጡት እንዲሁም ለእሱ የበደል መባ አድርጋችሁ የምትልኳቸውን የወርቅ ምስሎች በሣጥን አድርጋችሁ ታቦቱ አጠገብ አስቀምጡ ከዚያም መንገዱን ይዞ እንዲሄድ ላኩት9 ልብ ብላችሁም ተመልከቱ ታቦቱ ወደ አገሩ ወደ ቤትሼሜሽ የሚወስደውን መንገድ ተከትሎ ከሄደ ይህን ታላቅ መከራ ያመጣብን እሱ ነው ማለት ነው ካልሆነ ግን የእሱ እጅ እንዳልመታን እናውቃለን ይህ የደረሰብንም እንዲያው በአጋጣሚ ነው10 ሰዎቹም እንዲሁ አደረጉ እንቦሶች ያሏቸውን ሁለት ላሞች ወስደው ሠረገላውን ጠመዱባቸው እንቦሶቹንም በረት ውስጥ ዘጉባቸው11 ከዚያም የይሖዋን ታቦት እንዲሁም የወርቅ አይጦቹንና የኪንታሮቶቻቸውን ምስል የያዘውን ሣጥን ሠረገላው ላይ ጫኑ12 ላሞቹም ወደ ቤትሼሜሽ በሚወስደው መንገድ ቀጥ ብለው ሄዱ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ሳይሉ አንዱን ጎዳና ተከትለው እምቧ እያሉ ተጓዙ በዚህ ጊዜ ሁሉ የፍልስጤም ገዢዎች እስከ ቤትሼሜሽ ድንበር ድረስ ከኋላ ከኋላቸው ይከተሏቸው ነበር13 የቤትሼሜሽ ሰዎች በሸለቋማው ሜዳ ላይ ስንዴ እያጨዱ ነበር እነሱም ቀና ብለው ታቦቱን ተመለከቱ እሱን በማየታቸውም በጣም ተደሰቱ14 ሠረገላውም ወደ ቤትሼሜሻዊው ኢያሱ ማሳ ገብቶ እዚያ በሚገኝ አንድ ትልቅ ዓለት አጠገብ ቆመ ሰዎቹም የሠረገላውን እንጨት ፈልጠው ላሞቹን ለይሖዋ የሚቃጠል መባ አድርገው አቀረቡ15 ሌዋውያኑም የይሖዋን ታቦትና አብሮት የነበረውን የወርቅ ምስሎቹን የያዘውን ሣጥን አውርደው በትልቁ ዓለት ላይ አስቀመጧቸው በዚያም ቀን የቤትሼሜሽ ሰዎች ለይሖዋ የሚቃጠሉ መባዎችን አቀረቡ መሥዋዕቶችንም ሠዉ16 አምስቱ የፍልስጤም ገዢዎችም ይህን ሲያዩ በዚያው ቀን ወደ ኤቅሮን ተመለሱ17 ፍልስጤማውያን ለይሖዋ የበደል መባ አድርገው የላኳቸው የወርቅ ኪንታሮቶች እነዚህ ናቸው ለአሽዶድ አንድ ለጋዛ አንድ ለአስቀሎን አንድ ለጌት አንድ እንዲሁም ለኤቅሮን አንድ18 የወርቅ አይጦቹ ቁጥር አምስቱ የፍልስጤም ገዢዎች በሚያስተዳድሯቸው ከተሞች ሁሉ ይኸውም በተመሸጉት ከተሞችና በሥራቸው በሚገኙ አውላላ ሜዳ ላይ ባሉ መንደሮች ቁጥር ልክ ነበርየይሖዋን ታቦት ያስቀመጡበት በቤትሼሜሻዊው ኢያሱ ማሳ ውስጥ የሚገኘው ትልቅ ዓለት እስከ ዛሬ ድረስ ምሥክር ሆኖ ያገለግላል19 ይሁንና አምላክ የይሖዋን ታቦት ስለተመለከቱ የቤትሼሜሽን ሰዎች መታቸው ከሕዝቡ መካከል 50,070 ሰዎችን መታ ሰዎቹም ይሖዋ ብዙ ሕዝብ ስለፈጀባቸው ያለቅሱ ጀመር20 በመሆኑም የቤትሼሜሽ ሰዎች ታዲያ በዚህ ቅዱስ አምላክ በይሖዋ ፊት ማን ሊቆም ይችላል? ምናለ ከእኛ ላይ ዞር ቢልና ወደ ሌሎች ቢሄድ? አሉ21 ስለዚህ ወደ ቂርያትየአሪም ነዋሪዎች መልእክተኞችን ልከው ፍልስጤማውያን የይሖዋን ታቦት መልሰዋል ወደዚህ ውረዱና ይዛችሁት ውጡ አሏቸው
7 በመሆኑም የቂርያትየአሪም ሰዎች መጥተው የይሖዋን ታቦት በኮረብታው ላይ ወደሚገኘው ወደ አቢናዳብ ቤት ወሰዱት የይሖዋን ታቦት እንዲጠብቅም ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት2 ታቦቱም ወደ ቂርያትየአሪም ከመጣ ረጅም ጊዜ ይኸውም በአጠቃላይ 20 ዓመት አለፈው የእስራኤልም ቤት ሁሉ ይሖዋን መፈለግ ጀመረ3 ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ በሙሉ ልባችሁ ወደ ይሖዋ የምትመለሱ ከሆነ ባዕዳን አማልክትንና የአስታሮትን ምስሎች ከመካከላችሁ አስወግዱ ልባችሁንም ሙሉ በሙሉ ለይሖዋ ስጡ እሱን ብቻ አገልግሉ እሱም ከፍልስጤማውያን እጅ ይታደጋችኋል አላቸው4 በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን የባአልንና የአስታሮትን ምስሎች አስወግደው ይሖዋን ብቻ አገለገሉ5 ከዚያም ሳሙኤል እስራኤልን ሁሉ በምጽጳ ሰብስቡ እኔም ስለ እናንተ ወደ ይሖዋ እጸልያለሁ አለ6 እነሱም በምጽጳ ተሰበሰቡ ከዚያም ውኃ ቀድተው በይሖዋ ፊት አፈሰሱ ያን ዕለትም ሲጾሙ ዋሉ በዚያም በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተናል አሉ ሳሙኤልም በምጽጳ በእስራኤላውያን ላይ ፈራጅ ሆኖ ማገልገል ጀመረ7 ፍልስጤማውያንም እስራኤላውያን በምጽጳ አንድ ላይ መሰብሰባቸውን በሰሙ ጊዜ የፍልስጤም ገዢዎች እስራኤልን ለመውጋት ወጡ እስራኤላውያንም ይህን ሲሰሙ ፍልስጤማውያንን ፈሩ8 ስለሆነም እስራኤላውያን ሳሙኤልን አምላካችን ይሖዋ እንዲረዳንና ከፍልስጤማውያን እጅ እንዲያድነን ወደ እሱ መጮኽህን አታቁም አሉት9 ከዚያም ሳሙኤል አንድ የሚጠባ ግልገል ወስዶ ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርጎ አቀረበው ሳሙኤልም ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዲረዳቸው ተማጸነ ይሖዋም መለሰለት10 ሳሙኤል የሚቃጠለውን መባ እያቀረበ ሳለ ፍልስጤማውያን እስራኤላውያንን ለመውጋት ቀረቡ ይሖዋም በዚያን ዕለት በፍልስጤማውያን ላይ ኃይለኛ የነጎድጓድ ድምፅ ለቀቀባቸው ግራ እንዲጋቡም አደረጋቸው እነሱም በእስራኤላውያን ፊት ድል ተመቱ11 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ሰዎች ከምጽጳ ወጥተው ፍልስጤማውያንን ማሳደዳቸውን ተያያዙት ከቤትካር በስተ ደቡብ እስከሚገኘው አካባቢም ድረስ መቷቸው12 ከዚያም ሳሙኤል አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳ እና በየሻና መካከል አስቀመጠው ስሙንም ኤቤንዔዘር አለው ይህን ያለው ይሖዋ እስካሁን ድረስ ረድቶናል ሲል ነው13 በዚህ ሁኔታ ፍልስጤማውያን ድል ተመቱ ዳግመኛም ወደ እስራኤላውያን ክልል መጥተው አያውቁም በሳሙኤል ዘመን ሁሉ የይሖዋ እጅ በፍልስጤማውያን ላይ ነበር14 በተጨማሪም ፍልስጤማውያን ከእስራኤላውያን ላይ የወሰዷቸው ከኤቅሮን እስከ ጌት ያሉት ከተሞች ለእስራኤላውያን ተመለሱላቸው እንዲሁም እስራኤላውያን በእነዚህ ከተሞች ሥር ያሉትን ክልሎች ከፍልስጤማውያን እጅ አስለቀቁበእስራኤላውያንና በአሞራውያን መካከልም ሰላም ወረደ15 ሳሙኤልም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለእስራኤላውያን ፈራጅ ሆኖ አገለገለ16 በየዓመቱም በቤቴል በጊልጋል እና በምጽጳ በመዘዋወር በእነዚህ አካባቢዎች ሁሉ ለሚገኙ እስራኤላውያን ፈራጅ ሆኖ አገለገለ17 ሆኖም ቤቱ የሚገኘው በራማ ስለነበር ወደዚያ ይመለስ ነበር በዚያም ለእስራኤላውያን ፈራጅ ሆኖ አገለገለ በዚያም ለይሖዋ መሠዊያ ሠራ
8 ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ ልጆቹን በእስራኤል ውስጥ ፈራጆች ሆነው እንዲያገለግሉ ሾማቸው2 የበኩር ልጁ ስም ኢዩኤል ሲሆን የሁለተኛው ልጁ ስም ደግሞ አቢያህ ነበር እነሱም በቤርሳቤህ ፈራጆች ነበሩ3 ይሁንና ልጆቹ የእሱን ፈለግ አልተከተሉም ከዚህ ይልቅ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይጥሩ ጉቦ ይቀበሉ እንዲሁም ፍርድ ያጣምሙ ነበር4 ከጊዜ በኋላ የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ አንድ ላይ ተሰብስበው በራማ ወደሚገኘው ወደ ሳሙኤል መጡ5 እንዲህም አሉት እንግዲህ አንተ አርጅተሃል ልጆችህ ደግሞ የአንተን ፈለግ እየተከተሉ አይደለም ስለዚህ እንደ ሌሎቹ ብሔራት ሁሉ በእኛ ላይ ፈራጅ የሚሆን ንጉሥ ሹምልን6 ይሁንና በእኛ ላይ ፈራጅ የሚሆን ንጉሥ ሹምልን ማለታቸው ሳሙኤልን አላስደሰተውም ሳሙኤልም ወደ ይሖዋ ጸለየ7 ይሖዋም ሳሙኤልን እንዲህ አለው ሕዝቡ የሚልህን ሁሉ ስማ አልቀበልም ያሉት አንተን አይደለም ይልቁንም ንጉሣቸው አድርገው መቀበል ያልፈለጉት እኔን ነው8 እየፈጸሙ ያሉት ነገር ከግብፅ ካወጣኋቸው ቀን ጀምሮ እስከዚህች ዕለት ድረስ ሲያደርጉ የነበሩትን ነው እኔን ትተው ሌሎች አማልክትን አገለገሉ በአንተም ላይ እያደረጉ ያሉት ይህንኑ ነው9 ስለዚህ የሚሉህን ስማ ይሁን እንጂ በጥብቅ አስጠንቅቃቸው በላያቸው የሚነግሠው ንጉሥ ምን እንዲደረግለት የመጠየቅ መብት እንዳለው ንገራቸው10 በመሆኑም ሳሙኤል ንጉሥ እንዲያነግሥላቸው ለጠየቁት ሰዎች የይሖዋን ቃል ሁሉ ነገራቸው11 እንዲህ አላቸው በእናንተ ላይ የሚነግሠው ንጉሥ እንዲህ እንዲደረግለት የመጠየቅ መብት አለው ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሠረገላው ውስጥ ያስቀምጣቸዋል ፈረሰኞችም ያደርጋቸዋል የተወሰኑትንም ከሠረገሎቹ ፊት ፊት እንዲሮጡ ያደርጋል12 ለራሱም የሺህ አለቆችንና የሃምሳ አለቆችን ይሾማል አንዳንዶቹም መሬቱን ያርሳሉ እህሉን ያጭዳሉ እንዲሁም የጦር መሣሪያዎቹንና ለሠረገሎቹ የሚሆኑትን ዕቃዎች ይሠራሉ13 ሴቶች ልጆቻችሁንም ወስዶ ቅባት ቀማሚዎች ምግብ አብሳዮችና ዳቦ ጋጋሪዎች ያደርጋቸዋል14 እንዲሁም ከማሳችሁ ከወይን እርሻችሁና ከወይራ ዛፎቻችሁ ምርጥ የሆነውን ይወስዳል ለአገልጋዮቹም ይሰጣቸዋል15 ከእህል ማሳችሁና ከወይን እርሻችሁ ላይ አንድ አሥረኛውን ወስዶ ለቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱና ለአገልጋዮቹ ይሰጣል16 ወንድ አገልጋዮቻችሁንና ሴት አገልጋዮቻችሁን ከከብቶቻችሁ መካከል ምርጥ የሆኑትን እንዲሁም አህዮቻችሁን ይወስዳል ለራሱ ሥራም ይጠቀምባቸዋል17 ከመንጋችሁ መካከል አንድ አሥረኛውን ይወስዳል እናንተም የእሱ አገልጋዮች ትሆናላችሁ18 ለራሳችሁ ከመረጣችሁት ንጉሥ የተነሳ የምትጮኹበት ቀን ይመጣል ሆኖም በዚያ ቀን ይሖዋ አይመልስላችሁም19 ሕዝቡ ግን ሳሙኤል የተናገረውን ለመስማት አሻፈረኝ አለ እንዲህም አለ አይሆንም ንጉሥ እንዲነግሥልን እንፈልጋለን20 ከዚያም እንደ ሌሎች ብሔራት እንሆናለን ንጉሣችንም ፈራጅ ይሆንልናል ይመራናል እንዲሁም ጦርነት ሲገጥመን ይዋጋልናል21 ሳሙኤልም ሕዝቡ ያለውን ሁሉ ከሰማ በኋላ የተናገሩትን ነገር ይሖዋ እየሰማ በድጋሚ ተናገረ22 ይሖዋም ሳሙኤልን የሚሉህን ስማ በላያቸው የሚገዛ ንጉሥም አንግሥላቸው አለው ከዚያም ሳሙኤል የእስራኤልን ሰዎች እያንዳንዳችሁ ወደ ከተማችሁ ተመለሱ አላቸው
9 የቢንያም ሰው የሆነ ቂስ የተባለ አንድ እጅግ ባለጸጋ ሰው ነበር እሱም የቢንያማዊው የአፊያ ልጅ የቤኮራት ልጅ የጸሮር ልጅ የአቢዔል ልጅ ነበር2 ይህ ሰው ሳኦል የተባለ መልከ መልካም ወጣት ልጅ ነበረው ከእስራኤላውያንም መካከል እንደ እሱ ያለ መልከ መልካም ወንድ አልነበረም እሱም ከትከሻው በላይ ዘለግ ያለ ሲሆን ቁመቱ ከሌሎቹ ሁሉ ይበልጥ ነበር3 የሳኦል አባት ቂስ አህዮቹ በጠፉበት ጊዜ ልጁን ሳኦልን እባክህ ከአገልጋዮቹ መካከል አንዱን ይዘህ ሂድና አህዮቹን ፈልጋቸው አለው4 እነሱም የኤፍሬምን ተራራማ አካባቢና የሻሊሻን ምድር አቋርጠው ሄዱ ሆኖም አህዮቹን አላገኟቸውም ከዚያም የሻአሊምን ምድር አቋርጠው ተጓዙ አህዮቹ ግን በዚያ አልነበሩም እነሱም መላውን የቢንያማውያንን ምድር አቋርጠው ሄዱ ይሁንና አህዮቹን አላገኟቸውም5 እነሱም ወደ ጹፍ ምድር መጡ ሳኦልም አብሮት የነበረውን አገልጋዩን አባቴ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ ስለ እኛ መጨነቅ እንዳይጀምር ና እንመለስ አለው6 አገልጋዩ ግን እንዲህ አለው እነሆ በዚህ ከተማ የሚኖር አንድ የተከበረ የአምላክ ሰው አለ የሚናገረው ነገር በሙሉ መሬት ጠብ አይልም ስለዚህ ወደዚያ እንሂድ ምናልባት በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን ሊነግረን ይችላል7 በዚህ ጊዜ ሳኦል አገልጋዩን እንዲህ አለው መሄዱንስ እንሂድ ግን ለሰውየው ምን ይዘንለት እንሄዳለን? በከረጢታችን ውስጥ የያዝነው ዳቦ እንደሆነ አልቋል ለእውነተኛው አምላክ ሰው ስጦታ አድርገን የምንሰጠው ምንም ነገር የለንም ታዲያ ምን ብናደርግ ይሻላል?8 አገልጋዩም መልሶ ሳኦልን እንግዲህ ሩብ ሰቅል ብር በእጄ አለ ይህን ለእውነተኛው አምላክ ሰው እሰጠዋለሁ እሱም በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን ይነግረናል አለው9 ቀደም ባሉት ጊዜያት በእስራኤል ውስጥ አንድ ሰው አምላክን ለመፈለግ ሲሄድ ኑ ወደ ባለ ራእዩ እንሂድ ይል ነበር ምክንያቱም በዛሬው ጊዜ ነቢይ የሚባለው ቀደም ባሉት ጊዜያት ባለ ራእይ ይባል ነበር10 ከዚያም ሳኦል አገልጋዩን የተናገርከው ነገር መልካም ነው በል ና እንሂድ አለው በመሆኑም የእውነተኛው አምላክ ሰው ወደሚገኝበት ከተማ ሄዱ11 እነሱም ወደ ከተማዋ የሚወስደውን አቀበት እየወጡ ሳለ ውኃ ለመቅዳት የወጡ ልጃገረዶችን አገኙ በመሆኑም ባለ ራእዩ እዚህ ነው ያለው? አሏቸው12 እነሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው አዎ እዚህ ነው እነሆ ከፊታችሁ ነው ያለው! ፈጠን ብላችሁ ሂዱ በዛሬው ዕለት ሕዝቡ ከፍ ባለው ቦታ ላይ መሥዋዕት ስለሚያቀርብ ወደ ከተማዋ መጥቷል13 ልክ ወደ ከተማዋ እንደገባችሁ ለመብላት ወደ ኮረብታው ከመውጣቱ በፊት ታገኙታላችሁ መሥዋዕቱን የሚባርከው እሱ ስለሆነ ሕዝቡ እሱ ካልመጣ መብላት አይጀምርም ከዚያ በኋላ የተጋበዙት ይበላሉ በሉ አሁኑኑ ውጡ ታገኙታላችሁ14 ስለዚህ ወደ ከተማዋ ወጡ ከተማዋ መሃል ሲደርሱም ሳሙኤል ከእነሱ ጋር ተገናኝቶ ወደ ኮረብታው ለመውጣት ወደ እነሱ እየመጣ ነበር15 ይሖዋ ሳኦል ከመምጣቱ ከአንድ ቀን በፊት ለሳሙኤል እንዲህ ብሎት ነበር16 ነገ በዚህ ጊዜ ገደማ ከቢንያም ምድር የመጣ አንድ ሰው ወደ አንተ እልካለሁ አንተም በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ አድርገህ ቀባው እሱም ሕዝቤን ከፍልስጤማውያን እጅ ያድናቸዋል ምክንያቱም የሕዝቤን መከራ አይቻለሁ ጩኸታቸውም ወደ እኔ ደርሷል17 ሳሙኤል ሳኦልን ባየው ጊዜ ይሖዋ ሕዝቤን የሚገዛው እሱ ነው ብዬ የነገርኩህ ሰው ይህ ነው አለው18 ከዚያም ሳኦል በሩ መሃል ላይ ወደነበረው ወደ ሳሙኤል ቀርቦ እባክህ የባለ ራእዩ ቤት የት እንደሆነ ትነግረኛለህ? አለው19 ሳሙኤልም ለሳኦል እንዲህ ሲል መለሰለት ባለ ራእዩ እኔ ነኝ ከእኔ ቀድመህ ወደ ኮረብታው ውጣ ዛሬ አብራችሁኝ ትበላላችሁ በማለዳም አሰናብትሃለሁ ማወቅ የምትፈልገውንም ነገር ሁሉ እነግርሃለሁ20 ከሦስት ቀን በፊት ስለጠፉብህ አህዮች አትጨነቅ ምክንያቱም ተገኝተዋል በእስራኤል ውስጥ ያለው ምርጥ ነገር ሁሉ የማን ነው? የአንተና የመላው የአባትህ ቤት አይደለም?21 በዚህ ጊዜ ሳኦል እንዲህ አለው እኔ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ አነስተኛ ከሆነው ከቢንያም ነገድ የተገኘሁ ቢንያማዊ አይደለሁም? ቤተሰቤስ ቢሆን ከቢንያም ነገድ ቤተሰቦች መካከል እዚህ ግባ የሚባል ሆኖ ነው? ታዲያ እንዲህ የምትለኝ ለምንድን ነው?22 ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልንና አገልጋዩን ወደ መመገቢያ አዳራሹ ይዟቸው ሄደ እነሱንም በተጋበዙት ሰዎች ፊት በክብር ቦታ አስቀመጣቸው ተጋባዦቹም 30 ገደማ ነበሩ23 ሳሙኤልም ምግብ የሚያበስለውን ሰው ለይተህ አስቀምጠው ብዬ የሰጠሁህን ድርሻ አምጣው አለው24 በዚህ ጊዜ ምግብ የሚያበስለው ሰው ጭኑንና ላዩ ላይ የነበረውን አንስቶ ሳኦል ፊት አስቀመጠው ሳሙኤልም እንዲህ አለው ተለይቶ ተቀምጦ የነበረው ፊትህ ቀርቦልሃል ይህ ለዚህ ጊዜ ብለው ለይተው ያስቀመጡልህ ስለሆነ ብላ ምክንያቱም እንግዶች ጋብዣለሁ ብዬ ነግሬያቸዋለሁ በመሆኑም ሳኦል በዚያ ቀን ከሳሙኤል ጋር በላ25 ከዚያም ከኮረብታው ወደ ከተማው ወረዱ ሳሙኤልም ከሳኦል ጋር በቤቱ ሰገነት ላይ ሲነጋገር ቆየ26 እነሱም በማለዳ ተነሱ ጎህ እንደቀደደም ሳሙኤል ሳኦልን ወደ ቤቱ ሰገነት ጠርቶ በል ተዘጋጅና ላሰናብትህ አለው ስለዚህ ሳኦል ተዘጋጀ ከዚያም እሱና ሳሙኤል ወደ ውጭ ወጡ27 እነሱም በከተማዋ ዳርቻ ቁልቁል እየወረዱ ሳሉ ሳሙኤል ሳኦልን አገልጋይህ ቀድሞን እንዲሄድ ንገረው አለው እሱም ቀድሞ ሄደ ሳሙኤልም አንተ ግን የአምላክን ቃል እንዳሰማህ እዚሁ ቁም አለው
1 ከጳውሎስ ከስልዋኖስና ከጢሞቴዎስ አባት ከሆነው አምላክና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድነት ላለው የተሰሎንቄ ሰዎች ጉባኤየአምላክ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን2 ሁላችሁንም በጸሎታችን በጠቀስን ቁጥር ሁልጊዜ አምላክን እናመሰግናለን3 የእምነት ሥራችሁን ከፍቅር የመነጨ ድካማችሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ተስፋ በማድረጋችሁ የተነሳ የምታሳዩትን ጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ዘወትር እናስባለን4 አምላክ የሚወዳችሁ ወንድሞች እሱ እንደመረጣችሁ እናውቃለን5 ምክንያቱም የሰበክንላችሁ ምሥራች ወደ እናንተ የመጣው በቃል ብቻ ሳይሆን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ እንዲሁም በጠንካራ እምነት ነው ደግሞም ለእናንተ ስንል በመካከላችሁ ምን ዓይነት ሰዎች ሆነን እንደኖርን ታውቃላችሁ6 ብዙ መከራ ቢደርስባችሁምቃሉን ከመንፈስ ቅዱስ በሚገኝ ደስታ ስለተቀበላችሁ የእኛንም ሆነ የጌታን አርዓያ ተከትላችኋል7 በመሆኑም በመቄዶንያና በአካይያ ለሚገኙ አማኞች ሁሉ ምሳሌ ሆናችኋል8 የይሖዋ ቃል ከእናንተ ወጥቶ የተሰማው በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ አይደለም ከዚህ ይልቅ በአምላክ ላይ ያላችሁ እምነት በሌሎች ቦታዎችም ሁሉ ተሰራጭቷል ስለዚህ እኛ ምንም መናገር አያስፈልገንም9 ምክንያቱም መጀመሪያ ከእናንተ ጋር እንዴት እንደተገናኘን እንዲሁም ሕያው የሆነውንና እውነተኛውን አምላክ ለማገልገል ጣዖቶቻችሁን በመተው እንዴት ወደ አምላክ እንደተመለሳችሁ እነሱ ራሳቸው ሁልጊዜ ይናገራሉ10 በተጨማሪም ወደ አምላክ የተመለሳችሁት ከሞት ያስነሳውንና ከሚመጣው ቁጣ የሚታደገንን የልጁን ይኸውም የኢየሱስን ከሰማይ መምጣት ለመጠባበቅ ነው
2 ወንድሞች የእኛ ወደ እናንተ መምጣት ፍሬ ቢስ ሆኖ እንዳልቀረ እናንተ ራሳችሁ እንደምትገነዘቡ ምንም ጥርጥር የለውም2 እንደምታውቁት በመጀመሪያ በፊልጵስዩስ መከራና እንግልት ደርሶብን ነበር ይሁንና ከባድ ተቃውሞ እያለም የአምላክን ምሥራች ለእናንተ ለመንገር በአምላካችን እርዳታ እንደ ምንም ብለን ድፍረት አገኘን3 የምንሰጠው ምክር ከተሳሳተ ሐሳብ ወይም ከመጥፎ ዓላማ የመነጨ ወይም ደግሞ ማታለያ ያዘለ አይደለም4 ሆኖም ምሥራቹን በአደራ ለመቀበል በአምላክ ዘንድ ብቁ ሆነን የተቆጠርን እንደመሆናችን መጠን የምንናገረው ሰዎችን ለማስደሰት ሳይሆን ልባችንን የሚመረምረውን አምላክ ለማስደሰት ብለን ነው5 እንዲያውም የሽንገላ ቃል የተናገርንበት ወይም ስግብግብነት የሚንጸባረቅበትን ፍላጎታችንን ለመሸፈን ብለን በማስመሰል የቀረብንበት ጊዜ እንደሌለ ታውቃላችሁ ለዚህም አምላክ ምሥክር ነው!6 በተጨማሪም የክርስቶስ ሐዋርያት እንደመሆናችን መጠን እናንተን ብዙ ወጪ በማስወጣት ሸክም ልንሆንባችሁ እንችል የነበረ ቢሆንም እንኳ ከእናንተም ሆነ ከሌሎች ሰዎች ክብር ለማግኘት አልሞከርንም7 ከዚህ ይልቅ የምታጠባ እናት ልጆቿን በፍቅር እንደምትንከባከብ እኛም በመካከላችሁ በነበርንበት ጊዜ በገርነት ተንከባከብናችሁ8 በመሆኑም ለእናንተ ጥልቅ ፍቅር ስላለን የአምላክን ምሥራች ለማካፈል ብቻ ሳይሆን ራሳችንን ጭምር ለእናንተ ለመስጠት ቆርጠን ነበር ምክንያቱም እናንተ በእኛ ዘንድ እጅግ የተወደዳችሁ ነበራችሁ9 ወንድሞች ድካማችንንና ልፋታችንን እንደምታስታውሱ ጥርጥር የለውም የአምላክን ምሥራች በሰበክንላችሁ ጊዜ ማናችሁንም ብዙ ወጪ በማስወጣት ሸክም እንዳንሆንባችሁ በማሰብ ሌት ተቀን እንሠራ ነበር10 አማኞች ከሆናችሁት ከእናንተ ጋር በነበረን ግንኙነት ታማኞች ጻድቃንና ነቀፋ የሌለብን ሆነን እንደተመላለስን ምሥክሮች ናችሁ አምላክም ምሥክር ነው11 አባት ለልጆቹ እንደሚያደርገው ሁሉ እያንዳንዳችሁን እንዴት እንመክራችሁ እናጽናናችሁና አጥብቀን እናሳስባችሁ እንደነበረ በሚገባ ታውቃላችሁ12 ይህን ያደረግነው ወደ መንግሥቱና ወደ ክብሩ በጠራችሁ አምላክ ፊት በአግባቡ መመላለሳችሁን እንድትቀጥሉ ነው13 በእርግጥም አምላክን ያለማቋረጥ የምናመሰግነው ለዚህ ነው ምክንያቱም የአምላክን ቃል ከእኛ በሰማችሁ ጊዜ እንደ ሰው ቃል ሳይሆን እንደ አምላክ ቃል አድርጋችሁ ተቀብላችሁታል ደግሞም የአምላክ ቃል ነው አማኞች በሆናችሁት በእናንተም ላይ በእርግጥ እየሠራ ነው14 ወንድሞች ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ያላቸውን በይሁዳ የሚገኙትን የአምላክ ጉባኤዎች ምሳሌ ተከትላችኋል ምክንያቱም እነሱ በአይሁዳውያን እጅ መከራ እየተቀበሉ እንዳሉ ሁሉ እናንተም በገዛ አገራችሁ ሰዎች እጅ ተመሳሳይ መከራ ተቀብላችኋል15 አይሁዳውያን ጌታ ኢየሱስንና ነቢያትን ሳይቀር የገደሉ ከመሆኑም በላይ በእኛ ላይ ስደት አድርሰዋል ከዚህም በተጨማሪ አምላክን እያስደሰቱ አይደለም ከዚህ ይልቅ የሰውን ሁሉ ጥቅም የሚጻረሩ ናቸው16 አሕዛብ ይድኑ ዘንድ ለእነሱ እንዳንሰብክ ሊከለክሉን ይሞክራሉ በዚህ መንገድ ሁልጊዜ ብዙ ኃጢአት ይፈጽማሉ ይሁንና ቁጣው የሚገለጽበት ጊዜ ደርሷል17 እኛ ግን ወንድሞች በልብ ሳይሆን በአካል ለአጭር ጊዜ ከእናንተ ለመለየት በተገደድንበት ወቅት እጅግ ስለናፈቅናችሁ ከእናንተ ጋር በአካል ለመገናኘት ብርቱ ጥረት አደረግን18 በመሆኑም ወደ እናንተ መምጣት ፈልገን ነበር አዎ እኔ ጳውሎስ ከአንዴም ሁለቴ ሞክሬ ነበር ሆኖም ሰይጣን መንገድ ዘጋብን19 ጌታችን ኢየሱስ በሚገኝበት ጊዜ በእሱ ፊት ተስፋችን ወይም ደስታችን ወይም የሐሴታችን አክሊል ምንድን ነው? እናንተ አይደላችሁም?20 በእርግጥም እናንተ ክብራችንና ደስታችን ናችሁ
3 ስለዚህ ከዚህ በላይ መታገሥ ስላልቻልን በአቴንስ ብቻችንን መቅረት እንደሚሻል ተሰማን2 በመሆኑም እምነታችሁ ይጠነክር ዘንድ እንዲያጸናችሁ እንዲሁም እንዲያበረታታችሁ ጢሞቴዎስን ላክንላችሁ እሱ ወንድማችንና ስለ ክርስቶስ የሚገልጸውን ምሥራች የሚያውጅ የአምላክ አገልጋይ ነው3 የላክነውም ማንም በእነዚህ መከራዎች እንዳይናወጥ ነው እንዲህ ካሉ መከራዎች ማምለጥ እንደማንችል እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁና4 አብረናችሁ በነበርንበት ጊዜ መከራ መቀበላችን እንደማይቀር አስቀድመን እንነግራችሁ ነበር ደግሞም እንደምታውቁት ይኸው ነገር ደርሷል5 ስለዚህ ከዚህ በላይ መታገሥ ባልቻልኩ ጊዜ ስለ ታማኝነታችሁ ለመስማት እሱን ላክሁት ይህን ያደረግኩት ምናልባት ፈታኙ በሆነ መንገድ ፈትኗችሁ ድካማችን ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር ስለሰጋሁ ነው6 ይሁንና ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ አሁን ወደ እኛ መጥቶ ስለ ታማኝነታችሁና ስለ ፍቅራችሁ ምሥራች አብስሮናል ደግሞም እኛን ሁልጊዜ በመልካም እንደምታስታውሱንና እኛ እናንተን ለማየት እንደምንናፍቅ ሁሉ እናንተም እኛን ለማየት እንደምትናፍቁ ነግሮናል7 ወንድሞች በችግራችንና በመከራችን ሁሉ በእናንተና ባሳያችሁት ታማኝነት የተነሳ የተጽናናነው ለዚህ ነው8 ምክንያቱም ከጌታ ጋር ባላችሁ ዝምድና ጸንታችሁ የምትቆሙ ከሆነ ሕይወታችን ይታደሳል9 በእናንተ የተነሳ በአምላካችን ፊት ለተሰማን ታላቅ ደስታ በአጸፋው ስለ እናንተ ምስጋናችንን ለአምላክ ለመግለጽ ምን ማድረግ እንችላለን?10 ፊታችሁን ማየትና ከእምነታችሁ የጎደለውን ነገር ማሟላት እንችል ዘንድ አቅማችን በሚፈቅደው መጠን ሌት ተቀን ምልጃ እናቀርባለን11 አሁንም አምላካችንና አባታችን እንዲሁም ጌታችን ኢየሱስ ወደ እናንተ እንድንመጣ መንገዳችንን ያቅኑልን12 በተጨማሪም እኛ ለእናንተ ፍቅር እንዳለን ሁሉ እርስ በርስም ሆነ ለሰዎች ሁሉ የምታሳዩትን ፍቅር ጌታ ያብዛላችሁ ብሎም ያትረፍርፍላችሁ13 ይህም ጌታችን ኢየሱስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር በሚገኝበት ጊዜ በአምላካችንና በአባታችን ፊት ልባችሁን እንዲያጸናና ያላንዳች እንከን ቅዱስ እንዲያደርግ ነው
4 በመጨረሻም ወንድሞች አምላክን ማስደሰት እንድትችሉ እንዴት መመላለስ እንዳለባችሁ አስተምረናችኋል ደግሞም በዚሁ መንገድ እየተመላለሳችሁ ነው በመሆኑም ይህንኑ ይበልጥ በተሟላ ሁኔታ ማድረጋችሁን እንድትቀጥሉ በጌታ ኢየሱስ ስም እንጠይቃችኋለን እንዲሁም እንለምናችኋለን2 በጌታ ኢየሱስ ስም የሰጠናችሁን መመሪያዎች ታውቃላችሁና3 የአምላክ ፈቃድ እንድትቀደሱና ከፆታ ብልግና እንድትርቁ ነው4 ከእናንተ እያንዳንዱ የገዛ ራሱን አካል በመቆጣጠር እንዴት በቅድስናና በክብር መያዝ እንዳለበት ሊያውቅ ይገባል5 ይህም አምላክን እንደማያውቁት አሕዛብ ስግብግብነት በሚንጸባረቅበት ልቅ የፍትወት ስሜት አይሁን6 ማንም ሰው በዚህ ጉዳይ ከገደቡ ማለፍና ወንድሙን መጠቀሚያ ማድረግ አይኖርበትም ምክንያቱም አስቀድመን እንደነገርናችሁና በጥብቅ እንዳስጠነቀቅናችሁ ይሖዋ በእነዚህ ነገሮች ሁሉ የተነሳ የቅጣት እርምጃ ይወስዳል7 አምላክ የጠራን ለቅድስና ነው እንጂ ለርኩሰት አይደለም8 እንግዲህ ለዚህ ንቀት የሚያሳይ ሰው የሚንቀው ሰውን ሳይሆን ቅዱስ መንፈሱን የሚሰጣችሁን አምላክ ነው9 ይሁን እንጂ እናንተ ራሳችሁ እርስ በርስ እንድትዋደዱ ከአምላክ ስለተማራችሁ የወንድማማች ፍቅርን በተመለከተ እንድንጽፍላችሁ አያስፈልግም10 ደግሞም በመላው መቄዶንያ ለሚገኙ ወንድሞች ሁሉ ይህን እያደረጋችሁ ነው ሆኖም ወንድሞች ይህን ይበልጥ በተሟላ ሁኔታ ማድረጋችሁን እንድትቀጥሉ እናሳስባችኋለን11 ከዚህ በፊት እንዳዘዝናችሁ በሰላም ለመኖር በሌሎች ሰዎች ጉዳይ ጣልቃ ላለመግባትና በገዛ እጃችሁ ለመሥራት ተጣጣሩ12 ይህም በውጭ ባሉት ሰዎች ፊት ሥርዓት ባለው መንገድ እንድትመላለሱና ምንም ነገር የሚጎድላችሁ እንዳትሆኑ ነው13 በተጨማሪም ወንድሞች ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎቹ ሰዎች እንዳታዝኑ በሞት አንቀላፍተው ስላሉት ሳታውቁ እንድትቀሩ አንፈልግም14 ኢየሱስ እንደሞተና ከሞት እንደተነሳ የምናምን ከሆነ ከኢየሱስ ጋር አንድነት ኖሯቸው በሞት ያንቀላፉትንም አምላክ ሕይወት ሰጥቶ ከእሱ ጋር እንዲሆኑ ያደርጋል15 የይሖዋን ቃል መሠረት አድርገን የምንነግራችሁ ይህ ነውና ጌታ እስከሚገኝበት ጊዜ ድረስ በሕይወት የምንኖር በሞት አንቀላፍተው ያሉትን በምንም መንገድ አንቀድምም16 ምክንያቱም ጌታ ራሱ በትእዛዝ ድምፅ በመላእክት አለቃ ድምፅና በአምላክ መለከት ድምፅ ከሰማይ ይወርዳል ከክርስቶስ ጋር አንድነት ኖሯቸው የሞቱትም ቀድመው ይነሳሉ17 ከዚያም በሕይወት ቆይተን የምንተርፈው እኛ በአየር ላይ ከጌታ ጋር ለመገናኘት ከእነሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን በዚህም መንገድ ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን18 ስለሆነም በእነዚህ ቃላት ሁልጊዜ እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ
5 እንግዲህ ወንድሞች ጊዜያትንና ወቅቶችን በተመለከተ ምንም ነገር እንዲጻፍላችሁ አያስፈልግም2 የይሖዋ ቀን የሚመጣው ሌባ በሌሊት በሚመጣበት መንገድ መሆኑን እናንተ ራሳችሁ በሚገባ ታውቃላችሁና3 ሰላምና ደህንነት ሆነ! ሲሉ ምጥ እርጉዝ ሴትን እንደሚይዛት ያልታሰበ ጥፋት ድንገት ይመጣባቸዋል ደግሞም በምንም ዓይነት አያመልጡም4 እናንተ ግን ወንድሞች በጨለማ ውስጥ ስላልሆናችሁ ሌሊቱ ድንገት እንደሚነጋበት ሌባ ያ ቀን ድንገት አይደርስባችሁም5 እናንተ ሁላችሁ የብርሃን ልጆችና የቀን ልጆች ናችሁና እኛ የሌሊት ወይም የጨለማ ልጆች አይደለንም6 ስለዚህ ነቅተን እንኑር እንዲሁም የማስተዋል ስሜታችንን እንጠብቅ እንጂ እንደ ሌሎቹ አናንቀላፋ7 የሚያንቀላፉ ሰዎች የሚያንቀላፉት በሌሊት ነው የሚሰክሩም ቢሆኑ የሚሰክሩት በሌሊት ነው8 የቀን ልጆች የሆንነው እኛ ግን የማስተዋል ስሜታችንን እንጠብቅ ደግሞም የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር እንልበስ የመዳንንም ተስፋ እንደ ራስ ቁር እንድፋ9 ምክንያቱም አምላክ የመረጠን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መዳን እንድናገኝ ነው እንጂ ለቁጣ አይደለም10 እሱ በሕይወት ብንኖርም ሆነ ብናንቀላፋ አብረነው እንድንኖር ለእኛ ሞቶልናል11 ስለዚህ አሁን እያደረጋችሁት እንዳለው እርስ በርስ ተበረታቱ እንዲሁም እርስ በርስ ተናነጹ12 እንግዲህ ወንድሞች በመካከላችሁ በትጋት እየሠሩና በጌታ ሥራ አመራር እየሰጧችሁ ያሉትን እንዲሁም ምክር እየለገሷችሁ ያሉትን እንድታከብሯቸው እንለምናችኋለን13 በተጨማሪም በሚያከናውኑት ሥራ የተነሳ በፍቅር ለየት ያለ አሳቢነት እንድታሳዩአቸው እንለምናችኋለን እርስ በርሳችሁ ሰላማዊ ግንኙነት ይኑራችሁ14 በሌላ በኩል ደግሞ ወንድሞች ይህን እናሳስባችኋለን በሥርዓት የማይሄዱትን አስጠንቅቋቸው የተጨነቁትን አጽናኗቸው ደካሞችን ደግፏቸው ሁሉንም በትዕግሥት ያዙ15 ማንም ሰው በማንም ላይ በክፉ ፋንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ ከዚህ ይልቅ እርስ በርሳችሁም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ሁሉ ምንጊዜም መልካም የሆነውን ነገር ለማድረግ ተጣጣሩ16 ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ17 ዘወትር ጸልዩ18 ለሁሉም ነገር አመስግኑ አምላክ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ያለው ፈቃድ ይህ ነው19 የመንፈስን እሳት አታጥፉ20 ትንቢቶችን አትናቁ21 ሁሉንም ነገር መርምሩ መልካም የሆነውን አጥብቃችሁ ያዙ22 ከማንኛውም ዓይነት ክፋት ራቁ23 የሰላም አምላክ ራሱ ሙሉ በሙሉ ይቀድሳችሁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኝበት ጊዜ መንፈሳችሁ ነፍሳችሁና አካላችሁ በማንኛውም ረገድ ጤናማ ይሁን ደግሞም ነቀፋ አይገኝበት24 የጠራችሁ ታማኝ ነው ይህን በእርግጥ ያደርገዋል25 ወንድሞች ስለ እኛ መጸለያችሁን አታቋርጡ26 ወንድሞችን ሁሉ በተቀደሰ አሳሳም ሰላም በሏቸው27 ይህ ደብዳቤ ለወንድሞች ሁሉ እንዲነበብ በጌታ አደራ እላችኋለሁ28 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን
1 በአምላክ ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ እንዲሆን ከተጠራው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከሶስቴንስ2 በቆሮንቶስ ለሚገኘው የአምላክ ጉባኤ ይኸውም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ባላችሁ አንድነት ለተቀደሳችሁ እንዲሁም የእነሱም ሆነ የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ሆነው ከሚጠሩ ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠራችሁ3 ከአባታችን ከአምላክና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን4 በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ በሰጠው ጸጋ የተነሳ አምላኬን ሁልጊዜ ስለ እናንተ አመሰግናለሁ5 ምክንያቱም በሁሉም ነገር ይኸውም በመናገር ችሎታ ሁሉና በእውቀት ሁሉ በክርስቶስ በልጽጋችኋል6 ደግሞም ስለ ክርስቶስ የተሰጠው ምሥክርነት በእናንተ መካከል በሚገባ ሥር ሰዷል7 ስለዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በጉጉት ስትጠባበቁ ማንኛውም ስጦታ ፈጽሞ አይጎድልባችሁም8 በተጨማሪም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ከማንኛውም ክስ ነፃ መሆን እንድትችሉ እስከ መጨረሻው ያጸናችኋል9 ከልጁ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ የጠራችሁ አምላክ ታማኝ ነው10 እንግዲህ ወንድሞች ሁላችሁም ንግግራችሁ አንድ እንዲሆንና በመካከላችሁ መከፋፈል እንዳይኖር ከዚህ ይልቅ በአስተሳሰብም ሆነ በዓላማ ፍጹም አንድነት እንዲኖራችሁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አጥብቄ አሳስባችኋለሁ11 ወንድሞቼ ሆይ የቀሎኤ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አንዳንዶች በመካከላችሁ አለመግባባት እንዳለ ነግረውኛል12 ይኸውም እያንዳንዳችሁ እኔ የጳውሎስ ነኝ እኔ ግን የአጵሎስ ነኝ እኔ ደግሞ የኬፋ ነኝ እኔ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ13 ታዲያ የክርስቶስ ጉባኤ ተከፋፍሏል ማለት ነው? ጳውሎስ ለእናንተ ሲል በእንጨት ላይ ተሰቅሏል እንዴ? ወይስ የተጠመቃችሁት በጳውሎስ ስም ነው?14 ከቀርስጶስና ከጋይዮስ በስተቀር ከእናንተ አንዳችሁንም ባለማጥመቄ አምላክን አመሰግናለሁ15 በመሆኑም ከእናንተ መካከል በእኔ ስም እንደተጠመቀ ሊናገር የሚችል ማንም የለም16 እርግጥ የእስጢፋናስን ቤተሰብም አጥምቄአለሁ ከእነዚህ ሌላ ግን ያጠመቅኩት ሰው መኖሩን አላስታውስም17 ክርስቶስ የላከኝ እንዳጠምቅ ሳይሆን ምሥራቹን እንዳውጅ ነው ደግሞም የክርስቶስ የመከራ እንጨት ከንቱ እንዳይሆን ምሥራቹን የማውጀው በንግግር ጥበብ አይደለም18 ስለ መከራው እንጨት የሚነገረው መልእክት ወደ ጥፋት እያመሩ ላሉት ሞኝነት ወደ መዳን በሚወስደው ጎዳና ላይ ላለነው ለእኛ ግን የአምላክ ኃይል መገለጫ ነው19 የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ የሊቃውንትንም ማስተዋል ወዲያ እጥላለሁ ተብሎ ተጽፏልና20 የዚህ ሥርዓት ጥበበኞች የት አሉ? ጸሐፍትስ የት አሉ? ተሟጋቾችስ የት አሉ? አምላክ የዓለምን ጥበብ ሞኝነት አላደረገም?21 ዓለም በራሱ ጥበብ አምላክን ሊያውቀው ስላልቻለ አምላክ በጥበቡ እንደ ሞኝነት በሚቆጠረውና እየተሰበከ ባለው መልእክት አማካኝነት የሚያምኑትን ሰዎች ለማዳን መርጧል22 አይሁዳውያን ተአምራዊ ምልክቶች ማየት ይፈልጋሉ ግሪካውያን ደግሞ ጥበብን ይሻሉ23 እኛ ግን በእንጨት ላይ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን ይህም ለአይሁዳውያን መሰናክል ለአሕዛብ ደግሞ ሞኝነት ነው24 ይሁን እንጂ ክርስቶስ ለተጠሩት ለአይሁዳውያንም ሆነ ለግሪካውያን የአምላክ ኃይልና የአምላክ ጥበብ ነው25 ምክንያቱም የአምላክ ሞኝነት እንደሆነ ተደርጎ የሚታሰበው ነገር ከሰዎች ጥበብ ይበልጣል የአምላክ ድክመት እንደሆነ ተደርጎ የሚታሰበው ነገር ደግሞ ከሰዎች ብርታት ይበልጣል26 ወንድሞች ከራሳችሁ ሁኔታ መረዳት እንደምትችሉት በሰብዓዊ አመለካከት ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች ኃያላን የሆኑ ብዙዎች እንዲሁም ከትልቅ ቤተሰብ የተወለዱ ብዙዎች አልተጠሩም27 ከዚህ ይልቅ አምላክ ጥበበኞችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ ብርቱውንም ነገር ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ28 አምላክ በሰዎች ዘንድ ትልቅ ግምት የሚሰጠውን ነገር ከንቱ ያደርግ ዘንድ በዚህ ዓለም ዝቅ ተደርጎ የሚታየውንና የተናቀውን ነገር ይኸውም ከንቱ መስሎ የሚታየውን ነገር መረጠ29 ይህን ያደረገው ማንም ሰው በአምላክ ፊት እንዳይኩራራ ነው30 ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ሊኖራችሁ የቻለው በእሱ ምክንያት ነው ክርስቶስ ደግሞ ለእኛ ከአምላክ የመጣ ጥበብ ጽድቅና ቅድስና ሆኖልናል እንዲሁም በቤዛው ነፃ አውጥቶናል31 ይህም የሚኩራራ በይሖዋ ይኩራራ ተብሎ እንደተጻፈው ነው
10 እንግዲህ ወንድሞች አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች እንደነበሩና ሁሉም በባሕር መካከል እንዳለፉ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ2 ሁሉም ከሙሴ ጋር በመተባበር በደመናውና በባሕሩ ተጠመቁ3 ደግሞም ሁሉም አንድ ዓይነት መንፈሳዊ ምግብ ተመገቡ4 በተጨማሪም ሁሉም አንድ ዓይነት መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ ይከተላቸው ከነበረው መንፈሳዊ ዓለት ይጠጡ ነበርና ይህም ዓለት ክርስቶስን ያመለክታል5 ይሁንና አምላክ በአብዛኞቹ ስላልተደሰተ በምድረ በዳ ወድቀው ቀርተዋል6 እነሱ ጎጂ የሆኑ ነገሮችን እንደተመኙ እኛም እንዳንመኝ እነዚህ ነገሮች ለእኛ ምሳሌ ሆነውልናል7 ሕዝቡ ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ ከዚያም ሊጨፍሩ ተነሱ ተብሎ እንደተጻፈው ከእነሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት ጣዖት አምላኪዎች አትሁኑ8 ከእነሱ አንዳንዶቹ የፆታ ብልግና ፈጽመው ከመካከላቸው 23,000 የሚሆኑት በአንድ ቀን እንደረገፉ እኛም የፆታ ብልግና አንፈጽም9 ከእነሱ አንዳንዶቹ ይሖዋን ተፈታትነው በእባቦች እንደጠፉ እኛም አንፈታተነው10 በተጨማሪም ከእነሱ አንዳንዶቹ በማጉረምረማቸው በአጥፊው እንደጠፉ አጉረምራሚዎች አትሁኑ11 እነዚህ ነገሮች ምሳሌ ይሆኑ ዘንድ በእነሱ ላይ ደረሱ የተጻፉትም የሥርዓቶቹ ፍጻሜ የደረሰብንን እኛን ለማስጠንቀቅ ነው12 በመሆኑም የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ13 በሰው ሁሉ ላይ ከሚደርሰው ፈተና የተለየ ፈተና አልደረሰባችሁም ይሁንና አምላክ ታማኝ ነው ልትሸከሙት ከምትችሉት በላይ ፈተና እንዲደርስባችሁ አይፈቅድም ከዚህ ይልቅ ፈተናውን በጽናት መቋቋም እንድትችሉ ፈተና ሲደርስባችሁ መውጫ መንገዱን ያዘጋጅላችኋል14 ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ከጣዖት አምልኮ ሽሹ15 ይህን የምናገረው ማስተዋል ላላቸው ሰዎች ነው የምናገረው ነገር ትክክል ይሁን አይሁን እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ16 የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም መቋደስ አይደለም? የምንቆርሰውስ ቂጣ ከክርስቶስ አካል መቋደስ አይደለም?17 ምክንያቱም እኛ ብዙ ብንሆንም ቂጣው አንድ ስለሆነ አንድ አካል ነን ሁላችንም የምንካፈለው ከዚሁ አንድ ቂጣ ነውና18 እስቲ ሥጋዊ እስራኤላውያንን ተመልከቱ መሥዋዕቱን የሚበሉት ከመሠዊያው ጋር ተቋዳሾች አይደሉም?19 እንግዲህ ምን እያልኩ ነው? ለጣዖት የተሠዋ ነገር የተለየ ፋይዳ አለው ማለቴ ነው? ወይስ ጣዖት ዋጋ አለው ማለቴ ነው?20 እንዲህ ማለቴ አይደለም ከዚህ ይልቅ አሕዛብ መሥዋዕት አድርገው የሚያቀርቧቸውን ነገሮች የሚሠዉት ለአምላክ ሳይሆን ለአጋንንት ነው ማለቴ ነው ከአጋንንት ጋር እንድትተባበሩ ደግሞ አልፈልግም21 የይሖዋን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ መጠጣት አትችሉም ከይሖዋ ማዕድ እና ከአጋንንት ማዕድ መካፈል አትችሉም22 ወይስ ይሖዋን እያስቀናነው ነው? እኛ ከእሱ ይበልጥ ብርቱዎች ነን እንዴ?23 ሁሉም ነገር ተፈቅዷል ሆኖም ሁሉም ነገር ይጠቅማል ማለት አይደለም ሁሉም ነገር ተፈቅዷል ሆኖም ሁሉም ነገር ያንጻል ማለት አይደለም24 እያንዳንዱ ሰው ምንጊዜም የራሱን ጥቅም ሳይሆን የሌላውን ሰው ጥቅም ይፈልግ25 ከሕሊናችሁ የተነሳ ምንም ጥያቄ ሳታነሱ በሥጋ ገበያ የሚሸጠውን ማንኛውንም ነገር ብሉ26 ምድርና በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ የይሖዋ ነውና27 አማኝ ያልሆነ ሰው ቢጋብዛችሁና መሄድ ብትፈልጉ ከሕሊናችሁ የተነሳ ምንም ጥያቄ ሳታነሱ የቀረበላችሁን ሁሉ ብሉ28 ይሁንና አንድ ሰው ይህ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበ ነው ቢላችሁ ይህን ለነገራችሁ ሰውና ለሕሊና ስትሉ አትብሉ29 እንዲህ ስል ስለ ራሳችሁ ሕሊና ሳይሆን ስለ ሌላው ሰው ሕሊና መናገሬ ነው ነፃነቴ በሌላው ሰው ሕሊና ለምን ይፈረድበት?30 አመስግኜ የምበላ ከሆነ ባመሰገንኩበት ነገር ለምን እነቀፋለሁ?31 ስለዚህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ ወይም ማንኛውንም ነገር ስታደርጉ ሁሉንም ነገር ለአምላክ ክብር አድርጉ32 ለአይሁዳውያንም ሆነ ለግሪካውያን እንዲሁም ለአምላክ ጉባኤ እንቅፋት አትሁኑ33 እኔ ብዙዎች እንዲድኑ የእነሱን እንጂ የራሴን ጥቅም ሳልፈልግ በማደርገው ነገር ሁሉ ሁሉንም ሰው ለማስደሰት እንደምጥር እናንተም እንዲሁ አድርጉ
11 እኔ የክርስቶስን አርዓያ እንደምከተል እናንተም የእኔን አርዓያ ተከተሉ2 በሁሉም ነገር ስለምታስቡኝና ለእናንተ ያስተላለፍኳቸውን ወጎች አጥብቃችሁ ስለያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ3 ይሁንና የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ የሴትም ራስ ወንድ የክርስቶስ ራስ ደግሞ አምላክ እንደሆነ እንድታውቁ እወዳለሁ4 ራሱን ሸፍኖ የሚጸልይ ወይም ትንቢት የሚናገር ወንድ ሁሉ የእሱን ራስ ያዋርዳል5 ራሷን ሳትሸፍን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ሁሉ ደግሞ የእሷን ራስ ታዋርዳለች እንዲህ የምታደርግ ሴት ራሷን እንደተላጨች ሴት ትቆጠራለች6 አንዲት ሴት ራሷን የማትሸፍን ከሆነ ፀጉሯን ትቆረጥ ፀጉሯን መቆረጧ ወይም መላጨቷ የሚያሳፍራት ከሆነ ግን ትሸፈን7 ወንድ የአምላክ አምሳልና ክብር ስለሆነ ራሱን መሸፈን የለበትም ሴት ግን የወንድ ክብር ናት8 ሴት ከወንድ ተገኘች እንጂ ወንድ ከሴት አልተገኘምና9 ከዚህም በተጨማሪ ሴት ለወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ ለሴት አልተፈጠረም10 ከዚህ የተነሳም ሆነ ለመላእክት ሲባል ሴት በሥልጣን ሥር መሆኗን የሚያሳይ ምልክት በራሷ ላይ ታድርግ11 ይሁንና በጌታ ተከታዮች ዘንድ ሴት ያለወንድ አትኖርም ወንድም ያለሴት አይኖርም12 ሴት ከወንድ እንደተገኘች ሁሉ ወንድም የተገኘው በሴት አማካኝነት ነውና ሆኖም ሁሉም ነገሮች የተገኙት ከአምላክ ነው13 እስቲ እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ ሴት ሳትሸፈን ወደ አምላክ ብትጸልይ ተገቢ ይሆናል?14 ወንድ ፀጉሩን ቢያስረዝም ውርደት እንደሚሆንበት ተፈጥሮ ራሱ እንኳ አያስተምራችሁም?15 ሴት ግን ፀጉሯን ብታስረዝም ለእሷ ክብር አይደለም? ፀጉሯ የተሰጣት በመሸፈኛ ምትክ ነውና16 ይሁን እንጂ ማንም ሰው ሌላ ልማድ መከተል አለብን በሚል ለመከራከር ቢፈልግ እኛም ሆን የአምላክ ጉባኤ ከዚህ የተለየ ልማድ የለንም17 ሆኖም ስብሰባችሁ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚያመዝን እነዚህን መመሪያዎች ስሰጣችሁ ላመሰግናችሁ አልፈልግም18 በመጀመሪያ ደረጃ በጉባኤ በምትሰበሰቡበት ጊዜ በመካከላችሁ ክፍፍል እንዳለ እሰማለሁ ደግሞም ይህ በተወሰነ መጠን እውነትነት እንዳለው አምናለሁ19 በዚህ ሁኔታ በእናንተ መካከል ኑፋቄዎች ብቅ ማለታቸው አይቀርም ይህም መሆኑ ከእናንተ መካከል ተቀባይነት የሚያገኙት ሰዎች ተለይተው እንዲታወቁ ያስችላል20 አንድ ላይ በምትሰበሰቡበት ጊዜ የሚኖረው ሁኔታ የጌታ ራትን በአግባቡ ለማክበር የሚያስችል አይደለም21 የጌታ ራትን በምትበሉበት ጊዜ አንዳንዶች አስቀድመው የራሳቸውን ራት ስለሚበሉ አንዱ ይራባል ሌላው ደግሞ ይሰክራል22 የምትበሉበትና የምትጠጡበት ቤት የላችሁም? ወይስ የአምላክን ጉባኤ በመናቅ ምንም የሌላቸውን ታሳፍራላችሁ? እንግዲህ ምን ልበላችሁ? ላመስግናችሁ? በዚህ ነገርስ አላመሰግናችሁም23 እኔ ከጌታ የተቀበልኩትን ለእናንተ አስተላልፌአለሁና ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት ሌሊት ቂጣ አንስቶ24 ካመሰገነ በኋላ ቆርሶ ይህ ስለ እናንተ የሚሰጠውን ሥጋዬን ያመለክታል ይህን ሁልጊዜ ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ25 በተጨማሪም ራት ከበሉ በኋላ ጽዋውን አንስቶ ልክ እንደዚሁ አደረገ እንዲህም አለ ይህ ጽዋ በደሜ አማካኝነት የሚመሠረተውን አዲሱን ቃል ኪዳን ያመለክታል ከዚህ ጽዋ በጠጣችሁ ቁጥር ይህን ሁልጊዜ ለመታሰቢያዬ አድርጉት26 ይህን ቂጣ በበላችሁና ከዚህ ጽዋ በጠጣችሁ ቁጥር ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ሞቱን ታውጃላችሁ27 እንግዲህ የማይገባው ሆኖ ሳለ ከቂጣው የሚበላ ወይም ከጌታ ጽዋ የሚጠጣ ከጌታ አካልና ደም ጋር በተያያዘ ተጠያቂ ይሆናል28 አንድ ሰው የሚገባው እንደሆነ ለማወቅ በቅድሚያ ራሱን ይመርምር ቂጣውን መብላትና ጽዋውን መጠጣት የሚችለው ይህን ካደረገ ብቻ ነው29 ምክንያቱም አካሉ ምን ትርጉም እንዳለው ሳይገነዘብ የሚበላና የሚጠጣ በራሱ ላይ ፍርድ የሚያመጣበትን ነገር መብላትና መጠጣት ይሆንበታል30 ከእናንተ መካከል ብዙዎቹ የተዳከሙትና ታማሚ የሆኑት እንዲሁም ጥቂት የማይባሉት በሞት ያንቀላፉት በዚህ ምክንያት ነው31 ሆኖም ራሳችንን መርምረን ብናውቅ ኖሮ ባልተፈረደብን ነበር32 ይሁን እንጂ በሚፈረድብን ጊዜ ከዓለም ጋር አብረን እንዳንኮነን ሲል ይሖዋ ይገሥጸናል33 ስለዚህ ወንድሞቼ ይህን ራት ለመብላት በምትሰበሰቡበት ጊዜ እርስ በርሳችሁ ተጠባበቁ34 የምትሰበሰቡት ለፍርድ እንዳይሆን የራበው ሰው ካለ እዚያው ቤቱ ይብላ የቀሩትን ጉዳዮች ግን ስመጣ አስተካክላለሁ
12 ወንድሞች አሁን ደግሞ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች በሚገባ እንድታውቁ እፈልጋለሁ2 አሕዛብ በነበራችሁበት ጊዜ ድምፅ የሌላቸው ጣዖቶች ካሳደሩባችሁ ተጽዕኖ የተነሳ ወደመሯችሁ ቦታ ሁሉ በመሄድ እነሱን ተከትላችሁ ትባዝኑ ነበር3 ስለዚህ ይህን እንድታውቁ እወዳለሁ በአምላክ መንፈስ ተመርቶ ኢየሱስ የተረገመ ነው! የሚል ማንም የለም እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ካልሆነ በቀር ማንም ኢየሱስ ጌታ ነው! ብሎ ሊናገር አይችልም4 ልዩ ልዩ ስጦታዎች አሉ ምንጩ ግን ያው መንፈስ ነው5 ልዩ ልዩ አገልግሎቶች አሉ ሁሉም አገልግሎት የሚቀርበው ግን ለአንድ ጌታ ነው6 በተጨማሪም ልዩ ልዩ ሥራዎች አሉ ሆኖም ሁሉም ሰዎች እነዚህን ሁሉ ነገሮች እንዲያከናውኑ የሚያስችለው አንድ አምላክ ብቻ ነው7 ይሁን እንጂ መንፈስ በእያንዳንዱ ሰው አማካኝነት ጠቃሚ ለሆነ ዓላማ ይገለጣል8 ለአንዱ በመንፈስ አማካኝነት በጥበብ የመናገር ችሎታ ይሰጠዋልና ለሌላው ደግሞ በዚያው መንፈስ በእውቀት የመናገር ችሎታ ይሰጠዋል9 ለሌላው በዚያው መንፈስ እምነት ይሰጠዋል ለሌላው ደግሞ በዚያው መንፈስ የመፈወስ ስጦታ ይሰጠዋል10 እንዲሁም ለሌላው ተአምራት የመሥራት ለሌላው ትንቢት የመናገር ለሌላው በመንፈስ መሪነት የተነገረን ቃል የመረዳት ለሌላው በተለያዩ ልሳኖች የመናገር ለሌላው ደግሞ ልሳኖችን የመተርጎም ችሎታ ይሰጠዋል11 ሆኖም ለእያንዳንዱ በግለሰብ ደረጃ እነዚህን ስጦታዎች እንደፈቀደ በማከፋፈል እነዚህን ሁሉ ነገሮች የሚያከናውነው ያው አንድ መንፈስ ነው12 አካል አንድ ቢሆንም ብዙ የአካል ክፍሎች እንዳሉትና የዚህ አካል ክፍሎች በሙሉ ብዙ ቢሆኑም አንድ አካል እንደሆኑ ሁሉ ክርስቶስም እንደዚሁ ነው13 አይሁዳውያንም ሆን ግሪካውያን ባሪያዎችም ሆን ነፃ ሰዎች ሁላችንም አንድ አካል ለመሆን በአንድ መንፈስ ተጠምቀናልና እንዲሁም ሁላችንም አንድ መንፈስ እንድንጠጣ ተሰጥቶናል14 አካል በአንድ ብቻ ሳይሆን በብዙ የአካል ክፍሎች የተገነባ ነውና15 እግር እኔ እጅ ስላልሆንኩ የአካል ክፍል አይደለሁም ቢል ይህን በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ አይቀርም16 እንዲሁም ጆሮ እኔ ዓይን ስላልሆንኩ የአካል ክፍል አይደለሁም ቢል ይህን በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ አይቀርም17 አካል በሙሉ ዓይን ቢሆን ኖሮ እንዴት መስማት ይቻል ነበር? አካል በሙሉ ጆሮ ቢሆን ኖሮስ እንዴት ማሽተት ይቻል ነበር?18 ሆኖም አምላክ እያንዳንዱን የአካል ክፍል እሱ በፈለገው ቦታ መድቦታል19 የአካል ክፍሎች ሁሉ አንድ ዓይነት ቢሆኑ ኖሮ ሙሉ አካል ከየት ይገኝ ነበር?20 አሁን ግን የአካል ክፍሎች ብዙ ቢሆኑም አካል ግን አንድ ነው21 ዓይን እጅን አንተ አታስፈልገኝም ሊለው አይችልም ወይም ደግሞ ራስ እግርን አንተ አታስፈልገኝም ሊለው አይችልም22 እንዲያውም ደካማ የሚመስሉት የአካል ክፍሎች በጣም አስፈላጊ ናቸው23 እምብዛም ክብር የላቸውም ብለን የምናስባቸውን የአካል ክፍሎች የበለጠ ክብር እንሰጣቸዋለን በመሆኑም የምናፍርባቸውን የአካል ክፍሎች ይበልጥ በክብር እንይዛቸዋለን24 በአንጻሩ ደግሞ የሚያምሩት የአካል ክፍሎቻችን ምንም አያስፈልጋቸውም ይሁንና አምላክ ክብር የሚጎድለውን የአካል ክፍል ታላቅ ክብር በማልበስ አካልን ገንብቷል25 ይህን ያደረገው በአካል መካከል ክፍፍል እንዳይኖር ከዚህ ይልቅ የአካል ክፍሎች በእኩል ደረጃ አንዳቸው ለሌላው አሳቢነት እንዲያሳዩ ነው26 አንድ የአካል ክፍል ቢሠቃይ ሌሎቹ የአካል ክፍሎች በሙሉ አብረውት ይሠቃያሉ ወይም አንድ የአካል ክፍል ክብር ቢያገኝ ሌሎቹ የአካል ክፍሎች በሙሉ አብረውት ይደሰታሉ27 እንግዲህ እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ እያንዳንዳችሁም በግለሰብ ደረጃ የአካሉ ክፍል ናችሁ28 አምላክ የተለያዩ የአካል ክፍሎችን ይኸውም አንደኛ ሐዋርያትን ሁለተኛ ነቢያትን ሦስተኛ አስተማሪዎችን ከዚያም ተአምር የሚፈጽሙትን ከዚያም የመፈወስ ስጦታ ያላቸውን ጠቃሚ አገልግሎት የሚያከናውኑትን የመምራት ችሎታ ያላቸውንና በተለያዩ ልሳኖች የሚናገሩትን በጉባኤ ውስጥ መድቧል29 ሁሉ ሐዋርያት ናቸው? ሁሉስ ነቢያት ናቸው? ሁሉስ አስተማሪዎች ናቸው? ሁሉስ ተአምር ይሠራሉ?30 ሁሉስ የመፈወስ ስጦታ አላቸው? ሁሉስ በልሳን ይናገራሉ? ሁሉስ ተርጓሚዎች ናቸው?31 ይሁንና ብልጫ ያላቸውን ስጦታዎች ለማግኘት ጥረት ማድረጋችሁን ቀጥሉ ደግሞም ከሁሉ የላቀውን መንገድ አሳያችኋለሁ
13 በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ በኃይል እንደሚጮኽ ደወል ወይም ሲምባል ሆኛለሁ2 የመተንበይ ስጦታ ቢኖረኝ ቅዱስ ሚስጥርን ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ እንዲሁም ተራራን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ማንቀሳቀስ የሚያስችል እምነት ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ3 ሌሎችን ለመመገብ ያለኝን ሁሉ ብሰጥ እንዲሁም እኩራራ ዘንድ ሰውነቴን አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም የማገኘው ጥቅም የለም4 ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው ፍቅር አይቀናም ጉራ አይነዛም አይታበይም5 ጨዋነት የጎደለው ምግባር አያሳይም የራሱን ፍላጎት አያስቀድምም በቀላሉ አይበሳጭም ፍቅር የበደል መዝገብ የለውም6 ፍቅር በዓመፅ አይደሰትም ከዚህ ይልቅ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል7 ሁሉን ችሎ ያልፋል ሁሉን ያምናል ሁሉን ተስፋ ያደርጋል ሁሉን ነገር በጽናት ይቋቋማል8 ፍቅር ለዘላለም ይኖራል ሆኖም የመተንበይ በልሳን የመናገርም ሆነ የእውቀት ስጦታ ይቀራል9 እውቀታችን ከፊል ነውና ትንቢት የምንናገረውም በከፊል ነው10 የተሟላው ሲመጣ ግን ከፊል የሆነው ይቀራል11 ልጅ በነበርኩበት ጊዜ እንደ ልጅ እናገር እንደ ልጅ አስብ እንዲሁም እንደ ልጅ አመዛዝን ነበር አሁን ሙሉ ሰው ከሆንኩ በኋላ ግን የልጅነትን ጠባይ ትቻለሁ12 አሁን በብረት መስተዋት ብዥ ያለ ምስል ይታየናል በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት የማየት ያህል በግልጽ ይታየናል አሁን ስለ አምላክ የማውቀው በከፊል ነው በዚያን ጊዜ ግን እሱ እኔን በትክክል የሚያውቀኝን ያህል የተሟላ እውቀት ይኖረኛል13 ይሁን እንጂ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ይቀጥላሉ ከእነዚህ መካከል የሚበልጠው ግን ፍቅር ነው
14 ፍቅርን ተከታተሉ ሆኖም መንፈሳዊ ስጦታዎችን ይልቁንም ትንቢት የመናገር ስጦታን ለማግኘት ጥረት አድርጉ2 በልሳን የሚናገር ለአምላክ እንጂ ለሰው አይናገርምና በመንፈስ አማካኝነት ቅዱስ ሚስጥሮችን ቢናገርም እንኳ ማንም አይሰማውም3 ይሁን እንጂ ትንቢት የሚናገር በንግግሩ ሰዎችን ያንጻል ያበረታታል እንዲሁም ያጽናናል4 በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል ትንቢት የሚናገር ግን ጉባኤን ያንጻል5 ሁላችሁም በልሳን ብትናገሩ እወድ ነበር ሆኖም ትንቢት ብትናገሩ እመርጣለሁ ደግሞም ትንቢት የሚናገር በልሳን ከሚናገር ይበልጣል ምክንያቱም በልሳን የሚናገር የተናገረውን ካልተረጎመው ጉባኤው ሊታነጽ አይችልም6 አሁን ግን ወንድሞች ወደ እናንተ መጥቼ ራእይን በመግለጥ ወይም በእውቀት ወይም በትንቢት ወይም በትምህርት ካልነገርኳችሁ በስተቀር በልሳን ብነግራችሁ ምን እጠቅማችኋለሁ?7 እንደ ዋሽንትና በገና ካሉ ድምፅ የሚያወጡ ግዑዝ ነገሮች ጋር በተያያዘም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው የሚያወጡት የድምፅ ቃና ግልጽ የሆነ ልዩነት ከሌለው ከዋሽንቱም ሆነ ከበገናው የሚወጣው ዜማ እንዴት ይለያል?8 ደግሞም መለከት ለመለየት የሚያስቸግር ድምፅ ቢያሰማ ለጦርነት ማን ይዘጋጃል?9 ልክ እንደዚሁም ከአንደበታችሁ የሚወጣው ቃል በቀላሉ የሚገባ ካልሆነ ስለ ምን እየተናገራችሁ እንዳለ ማን ሊያውቅ ይችላል? እንዲህ ከሆነ ለነፋስ የምትናገሩ ትሆናላችሁ10 በዓለም ላይ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎች አሉ ሆኖም ትርጉም የሌለው ቋንቋ የለም11 አንድ ሰው የሚናገረውን ቋንቋ ትርጉም ካላወቅኩ እኔ ለሚናገረው ሰው የባዕድ አገር ሰው እሆንበታለሁ እሱም ለእኔ የባዕድ አገር ሰው ይሆንብኛል12 ስለዚህ እናንተም የመንፈስን ስጦታዎች እጅግ ስለምትፈልጉ ጉባኤውን የሚያንጹ ስጦታዎች በብዛት ለማግኘት ጥረት አድርጉ13 ስለሆነም በልሳን የሚናገር ሰው የሚናገረውን መተርጎም እንዲችል ይጸልይ14 ምክንያቱም በልሳን የምጸልይ ከሆነ የሚጸልየው የተቀበልኩት የመንፈስ ስጦታ ነው አእምሮዬ ግን ምንም የሚያከናውነው ነገር የለም15 ታዲያ ምን ማድረግ ይሻላል? በመንፈስ ስጦታ እጸልያለሁ ሆኖም የምጸልየው ትርጉሙ ገብቶኝ ነው በመንፈስ ስጦታ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ ሆኖም የምዘምረው ትርጉሙ ገብቶኝ ነው16 እንዲህ ካልሆነ በመንፈስ ስጦታ ውዳሴ ብታቀርብ በመካከልህ ያለው ምንም የማያውቅ ሰው ምን እየተናገርክ እንዳለህ ስለማይገባው ላቀረብከው ምስጋና እንዴት አሜን ሊል ይችላል?17 እርግጥ አንተ ግሩም በሆነ መንገድ ምስጋና ታቀርብ ይሆናል ሌላው ሰው ግን እየታነጸበት አይደለም18 ከሁላችሁ የበለጠ በብዙ ልሳኖች ስለምናገር አምላክን አመሰግናለሁ19 ይሁንና በጉባኤ ውስጥ አሥር ሺህ ቃላት በልሳን ከምናገር ሌሎችንም ማስተማር እችል ዘንድ አምስት ቃላት በአእምሮዬ ብናገር እመርጣለሁ20 ወንድሞች በማስተዋል ችሎታችሁ እንደ ሕፃናት አትሁኑ ለክፋት ግን ሕፃናት ሁኑ በማስተዋል ችሎታችሁም የጎለመሳችሁ ሁኑ21 በሕጉ ላይ በባዕዳን አንደበትና እንግዳ በሆኑ ሰዎች ቋንቋዎች ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ እነሱ ግን በዚያን ጊዜም እንኳ አይሰሙኝም ይላል ይሖዋ ተብሎ ተጽፏል22 በመሆኑም ልሳን ለአማኞች ሳይሆን አማኝ ላልሆኑት ምልክት ነው ትንቢት ግን አማኝ ላልሆኑት ሳይሆን ለአማኞች ነው23 ስለዚህ ጉባኤው በሙሉ አንድ ላይ ተሰብስቦ ባለበት ወቅት ሁሉም በልሳኖች ቢናገሩና በዚህ መሃል ምንም የማያውቁ ሰዎች ወይም አማኞች ያልሆኑ ቢገቡ እነዚህ ሰዎች አእምሯችሁን ስታችኋል አይሏችሁም?24 ሆኖም ሁላችሁም ትንቢት እየተናገራችሁ ሳለ አማኝ ያልሆነ ወይም ምንም የማያውቅ ሰው ቢገባ ሁላችሁም የምትናገሩት ቃል እንደ ወቀሳ የሚያገለግለው ከመሆኑም በላይ ራሱን በሚገባ እንዲመረምር ያነሳሳዋል25 በዚህ ጊዜ በልቡ የተሰወረው ነገር ይገለጣል በመሆኑም አምላክ በእርግጥ በመካከላችሁ ነው እያለ በግንባሩ ተደፍቶ ለአምላክ ይሰግዳል26 እንግዲህ ወንድሞች ምን ማድረግ ይሻላል? አንድ ላይ በምትሰበሰቡበት ጊዜ አንዱ ይዘምራል ሌላው ያስተምራል ሌላው ራእይን ይገልጣል ሌላው በልሳን ይናገራል ሌላው ደግሞ ይተረጉማል ሁሉም ነገር ለማነጽ ይሁን27 በልሳን የሚናገሩ ካሉ ከሁለት ወይም ከሦስት አይብለጡ በየተራም ይናገሩ የሚናገሩትንም ሌላ ሰው ይተርጉም28 የሚተረጉም ሰው ከሌለ ግን በጉባኤ መካከል ዝም ይበሉና ለራሳቸውና ለአምላክ ይናገሩ29 ሁለት ወይም ሦስት ነቢያት ይናገሩ ሌሎቹ ደግሞ ትርጉሙን ለመረዳት ይጣሩ30 ሆኖም አንድ ሰው እዚያ ተቀምጦ ሳለ ራእይ ቢገለጥለት የመጀመሪያው ተናጋሪ ዝም ይበል31 ሁሉም እንዲማሩና ሁሉም እንዲበረታቱ ሁላችሁም በየተራ ትንቢት መናገር ትችላላችሁ32 ነቢያት የመንፈስ ስጦታዎችን በአግባቡ ሊጠቀሙባቸው ይገባል33 አምላክ የሰላም እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምናበቅዱሳን ጉባኤዎች ሁሉ እንደሚደረገው34 ሴቶች በጉባኤ ውስጥ እንዲናገሩ ስላልተፈቀደላቸው ዝም ይበሉ ከዚህ ይልቅ ሕጉም እንደሚለው ይገዙ35 ያልገባቸው ነገር ካለ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ ምክንያቱም ሴት በጉባኤ መካከል ብትናገር የሚያሳፍር ነው36 የአምላክ ቃል የመጣው ከእናንተ ነው? ወይስ የአምላክ ቃል የደረሰው ወደ እናንተ ብቻ ነው?37 ነቢይ እንደሆነ ወይም የመንፈስ ስጦታ እንዳለው የሚያስብ ሰው ካለ እነዚህ የጻፍኩላችሁ ነገሮች የጌታ ትእዛዛት መሆናቸውን አምኖ ይቀበል38 ሆኖም ይህን ችላ የሚል ካለ እሱም ችላ ይባላል39 ስለዚህ ወንድሞቼ ትንቢት ለመናገር ጥረት አድርጉ ይሁንና በልሳኖች መናገርንም አትከልክሉ40 ሆኖም ሁሉም ነገር በአግባብና በሥርዓት ይሁን
15 አሁን ደግሞ ወንድሞች የነገርኳችሁን ምሥራች ላስታውሳችሁ እወዳለሁ ይህ ምሥራች እናንተም የተቀበላችሁትና የቆማችሁለት ነው2 በተጨማሪም እኔ የነገርኳችሁን ምሥራች አጥብቃችሁ የምትይዙ ከሆነ በምሥራቹ ትድናላችሁ አለዚያ አማኝ የሆናችሁት በከንቱ ነው ማለት ነው3 እኔ የተቀበልኩትን ከሁሉ በላይ የሆነውን ነገር ለእናንተ አስተላልፌአለሁና ይኸውም ቅዱሳን መጻሕፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ4 ደግሞም ተቀበረ ቅዱሳን መጻሕፍት እንደሚሉትም በሦስተኛው ቀን ተነሳ5 ለኬፋ ከዚያም ለአሥራ ሁለቱ ታየ6 በኋላ ደግሞ በአንድ ጊዜ ከ500 ለሚበልጡ ወንድሞች የታየ ሲሆን አንዳንዶቹ በሞት ቢያንቀላፉም አብዛኞቹ ግን አሁንም ከእኛ ጋር አሉ7 ከዚያም ለያዕቆብ ታየ ቀጥሎም ለሐዋርያቱ በሙሉ ታየ8 በመጨረሻ ደግሞ እንደ ጭንጋፍ ለምቆጠር ለእኔ ተገለጠልኝ9 እኔ የአምላክን ጉባኤ አሳድድ ስለነበር ከሐዋርያት ሁሉ የማንስና ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ ነኝ10 ሆኖም አሁን የሆንኩትን ለመሆን የበቃሁት በአምላክ ጸጋ ነው አምላክ ለእኔ ያሳየው ጸጋም ከንቱ ሆኖ አልቀረም እንዲያውም ከሁሉም የበለጠ በትጋት ሠርቻለሁ ይሁንና ይህን ያደረገው ከእኔ ጋር ያለው የአምላክ ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም11 እንግዲህ እኔም ሆንኩ እነሱ የምንሰብከው በዚህ መንገድ ነው እናንተም ያመናችሁት በዚህ መንገድ ነው12 ታዲያ ክርስቶስ ከሞት እንደተነሳ እየተሰበከ ከሆነ ከእናንተ መካከል አንዳንዶቹ እንዴት የሙታን ትንሣኤ የለም ይላሉ?13 የሙታን ትንሣኤ ከሌለማ ክርስቶስም አልተነሳም ማለት ነዋ!14 ክርስቶስ ካልተነሳ ደግሞ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ከንቱ ነው15 ከዚህም በተጨማሪ ሙታን በእርግጥ የማይነሱ ከሆነ አምላክ ክርስቶስን ከሞት ስላላስነሳው ክርስቶስን አስነስቶታል ብለን ስንመሠክር ሐሰተኞች የአምላክ ምሥክሮች ሆነን ተገኝተናል ማለት ነው16 ምክንያቱም ሙታን የማይነሱ ከሆነ ክርስቶስም ከሞት አልተነሳም ማለት ይሆናል17 ክርስቶስ ካልተነሳ ደግሞ እምነታችሁ ከንቱ ነው እናንተም ከነኃጢአታችሁ ትኖራላችሁ18 የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ሆነው በሞት ያንቀላፉትም ለዘላለሙ ጠፍተዋል ማለት ነው19 በክርስቶስ ተስፋ ያደረግነው ለዚህ ሕይወት ብቻ ከሆነ ከሰው ሁሉ ይልቅ የምናሳዝን ነን20 ይሁንና ክርስቶስ በሞት ካንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሞት ተነስቷል21 ሞት የመጣው በአንድ ሰው በኩል ስለሆነ የሙታን ትንሣኤም በአንድ ሰው በኩል ነው22 ሁሉም በአዳም እንደሚሞቱ ሁሉም በክርስቶስ ሕያው ይሆናሉና23 ሆኖም እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል ክርስቶስ በኩራት ነው በመቀጠል ደግሞ ክርስቶስ በሚገኝበት ጊዜ የእሱ የሆኑት ሕያዋን ይሆናሉ24 ከዚያም ማንኛውንም መስተዳድር እንዲሁም ሥልጣንን ሁሉና ኃይልን አጥፍቶ መንግሥቱን ለአምላኩና ለአባቱ በሚያስረክብበት ጊዜ ፍጻሜ ይሆናል25 አምላክ ጠላቶችን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግለት ድረስ ንጉሥ ሆኖ ሊገዛ ይገባዋልና26 የመጨረሻው ጠላት ሞት ይደመሰሳል27 አምላክ ሁሉንም ነገር ከእግሩ በታች አስገዝቶለታልና ሆኖም ሁሉም ነገር ተገዝቷል ሲል ሁሉንም ነገር ያስገዛለትን እንደማይጨምር ግልጽ ነው28 ይሁንና ሁሉም ነገር ከተገዛለት በኋላ ወልድ ራሱ ሁሉን ነገር ላስገዛለት ራሱን ያስገዛል ይህም አምላክ ለሁሉም ሁሉንም ነገር እንዲሆን ነው29 አለዚያማ ለመሞት ብለው በመጠመቅ ምን የሚያተርፉት ነገር ይኖራል? ሙታን ፈጽሞ የማይነሱ ከሆነ እነሱም ለመሞት ብለው የሚጠመቁበት ምን ምክንያት አለ?30 እኛስ ሁልጊዜ ለአደጋ ተጋልጠን የምንኖረው ለምንድን ነው?31 እኔ በየቀኑ ሞትን እጋፈጣለሁ ወንድሞች ይህ እውነት መሆኑን የጌታችን የክርስቶስ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በሆናችሁት በእናንተ ላይ ባለኝ ትምክህት አረጋግጥላችኋለሁ32 እንደ ሌሎች ሰዎች በኤፌሶን ከአውሬዎች ጋር ከታገልኩ እንዲህ ማድረጌ ለእኔ ምን ይጠቅመኛል? ሙታን የማይነሱ ከሆነማ ነገ ስለምንሞት እንብላ እንጠጣ33 አትታለሉ መጥፎ ጓደኝነት መልካሙን አመል ያበላሻል34 ጽድቅ የሆነውን በማድረግ ወደ ልቦናችሁ ተመለሱ ኃጢአት መሥራትን ልማድ አታድርጉ አንዳንዶች ስለ አምላክ አያውቁምና ይህን የምላችሁ ላሳፍራችሁ ብዬ ነው35 ይሁንና አንድ ሰው ሙታን የሚነሱት እንዴት ነው? ከሞት የሚነሱትስ ምን ዓይነት አካል ይዘው ነው? ይል ይሆናል36 አንተ ማስተዋል የጎደለህ! የምትዘራው መጀመሪያ ካልሞተ ሕያው ሊሆን አይችልም37 ደግሞም ስንዴም ሆነ ሌላ ዓይነት እህል ስትዘራ የምትዘራው ዘሩን እንጂ በኋላ የሚያድገውን አካል አይደለም38 ሆኖም አምላክ የፈለገውን አካል ይሰጠዋል ለእያንዳንዱም ዘር የራሱን አካል ይሰጠዋል39 ሥጋ ሁሉ አንድ ዓይነት አይደለም በመሆኑም የሰው ሥጋ አለ የከብት ሥጋ አለ የወፎች ሥጋ አለ እንዲሁም የዓሣ ሥጋ አለ40 በተጨማሪም ሰማያዊ አካላት አሉ ምድራዊ አካላትም አሉ ሆኖም የሰማይ አካላት የራሳቸው ክብር አላቸው የምድር አካላት ደግሞ ሌላ ዓይነት ክብር አላቸው41 ፀሐይ የራሷ ክብር አላት ጨረቃ ደግሞ ሌላ ዓይነት ክብር አላት ከዋክብትም ሌላ ዓይነት ክብር አላቸው እንዲያውም የአንዱ ኮከብ ክብር ከሌላው ኮከብ ክብር ይለያል42 ስለዚህ የሙታን ትንሣኤም እንደዚሁ ነው የሚዘራው የሚበሰብስ ነው የሚነሳው የማይበሰብስ ነው43 የሚዘራው በውርደት ነው የሚነሳው በክብር ነው የሚዘራው በድካም ነው የሚነሳው በኃይል ነው44 የሚዘራው ሥጋዊ አካል ነው የሚነሳው መንፈሳዊ አካል ነው ሥጋዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካልም አለ45 ስለዚህ የመጀመሪያው ሰው አዳም ሕያው ሰው ሆነ ተብሎ ተጽፏል የኋለኛው አዳም ሕይወት የሚሰጥ መንፈስ ሆነ46 ይሁንና የመጀመሪያው መንፈሳዊው አይደለም የመጀመሪያው ሥጋዊው ነው የኋለኛው ደግሞ መንፈሳዊው ነው47 የመጀመሪያው ሰው ከምድር የተገኘና ከአፈር የተሠራ ነው ሁለተኛው ሰው ደግሞ ከሰማይ ነው48 ከአፈር የተሠሩት ከአፈር እንደተሠራው ናቸው ሰማያዊ የሆኑትም ከሰማይ እንደመጣው ናቸው49 ከአፈር የተሠራውን ሰው መልክ እንደመሰልን ሁሉ የሰማያዊውንም መልክ እንመስላለን50 ይሁን እንጂ ወንድሞች ይህን እነግራችኋለሁ ሥጋና ደም የአምላክን መንግሥት አይወርስም የሚበሰብሰውም የማይበሰብሰውን አይወርስም51 እነሆ አንድ ቅዱስ ሚስጥር እነግራችኋለሁ በሞት የምናንቀላፋው ሁላችንም አይደለንም ነገር ግን ሁላችንም እንለወጣለን52 የመጨረሻው መለከት በሚነፋበት ወቅት ድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን መለከት ይነፋል ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሳሉ እኛም እንለወጣለን53 ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ይገባዋልና ይህ ሟች የሆነው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋል54 ሆኖም ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሲለብስና ይህ ሟች የሆነው የማይሞተውን ሲለብስ ሞት ለዘላለም ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል55 ሞት ሆይ ድል አድራጊነትህ የት አለ? ሞት ሆይ መንደፊያህ የት አለ?56 ለሞት የሚዳርገው መንደፊያ ኃጢአት ነው ለኃጢአት ኃይል የሚሰጠው ደግሞ ሕጉ ነው57 ሆኖም አምላክ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ድል ስለሚያጎናጽፈን የተመሰገነ ይሁን!58 ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ጸንታችሁ ቁሙ አትነቃነቁ እንዲሁም ከጌታ ጋር በተያያዘ በትጋት የምታከናውኑት ሥራ ከንቱ አለመሆኑን አውቃችሁ ምንጊዜም የጌታ ሥራ የበዛላችሁ ሁኑ
16 ለቅዱሳን መዋጮ ማሰባሰብን በተመለከተ ደግሞ በገላትያ ለሚገኙ ጉባኤዎች የሰጠሁትን መመሪያ መከተል ትችላላችሁ2 መዋጮ የሚሰባሰበው እኔ በምመጣበት ጊዜ እንዳይሆን ከእናንተ እያንዳንዱ በየሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን አቅሙ በሚፈቅድለት መጠን የተወሰነ ገንዘብ ያስቀምጥ3 ስመጣም የመረጣችኋቸውንና የድጋፍ ደብዳቤ የጻፋችሁላቸውን ሰዎች የልግስና ስጦታችሁን ኢየሩሳሌም እንዲያደርሱ እልካቸዋለሁ4 ይሁን እንጂ የእኔም መሄድ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ አብረውኝ ይሄዳሉ5 ይሁንና በመቄዶንያ በኩል ማለፌ ስለማይቀር በዚያ ሳልፍ ወደ እናንተ እመጣለሁ6 ወደምሄድበትም ቦታ የተወሰነ መንገድ እንድትሸኙኝ ምናልባት እናንተ ጋ ልቆይ እችላለሁ እንዲያውም ክረምቱን ከእናንተ ጋር አሳልፍ ይሆናል7 ይሖዋ ቢፈቅድ ከእናንተ ጋር የተወሰነ ጊዜ አሳልፋለሁ ብዬ ተስፋ ስለማደርግ አሁን እግረ መንገዴን ሳልፍ ላያችሁ አልፈልግም8 ይሁንና እስከ ጴንጤቆስጤ በዓል ድረስ በኤፌሶን እቆያለሁ9 ምክንያቱም ትልቅ የሥራ በር ተከፍቶልኛል ሆኖም ብዙ ተቃዋሚዎች አሉ10 ጢሞቴዎስ ከመጣ በመካከላችሁ በሚቆይበት ጊዜ ፍርሃት እንዳይሰማው ተባበሩት እሱም እንደ እኔ የይሖዋን ሥራ የሚሠራ ነውና11 ስለዚህ ማንም አይናቀው ከወንድሞች ጋር እየጠበቅኩት ስለሆነ ወደ እኔ እንዲመጣ በሰላም ሸኙት12 ወንድማችንን አጵሎስን በተመለከተ ደግሞ ከወንድሞች ጋር ወደ እናንተ እንዲመጣ አጥብቄ ለምኜው ነበር እሱ አሁን የመምጣት ሐሳብ የለውም ሆኖም ሁኔታው ሲመቻችለት ይመጣል13 ነቅታችሁ ኑሩ በእምነት ጸንታችሁ ቁሙ ወንድ ሁኑ ብርቱዎች ሁኑ14 የምታደርጉትን ነገር ሁሉ በፍቅር አድርጉ15 እንግዲህ ወንድሞች ይህን አሳስባችኋለሁ የእስጢፋናስ ቤተሰብ በአካይያ የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት እንደሆኑና ቅዱሳንን ለማገልገል ራሳቸውን እንደሰጡ ታውቃላችሁ16 እናንተም እንደ እነሱ ላሉት እንዲሁም ከእኛ ጋር ለሚተባበሩትና በትጋት ለሚሠሩት ሁሉ ተገዙ17 እስጢፋናስ እና ፈርጡናጦስ እንዲሁም አካይቆስ እዚህ በመገኘታቸው እጅግ ተደስቻለሁ ምክንያቱም የእናንተ እዚህ አለመኖር በእነሱ ተካክሷል18 እነሱ የእኔንም ሆነ የእናንተን መንፈስ አድሰዋልና ስለዚህ እንዲህ ላሉት ሰዎች እውቅና ስጡ19 በእስያ ያሉ ጉባኤዎች ሰላምታ ያቀርቡላችኋል አቂላና ጵርስቅላ እንዲሁም በቤታቸው ያለው ጉባኤ ሞቅ ያለ ክርስቲያናዊ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል20 ወንድሞች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል እርስ በርሳችሁ በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተለዋወጡ21 እኔ ጳውሎስ በገዛ እጄ የጻፍኩላችሁ ሰላምታ ይድረሳችሁ22 ጌታን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን ጌታችን ሆይ ና!23 የጌታ ኢየሱስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን24 የክርስቶስ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የሆናችሁ ሁሉ ፍቅሬ ይድረሳችሁ
2 ስለዚህ ወንድሞች የአምላክን ቅዱስ ሚስጥር ለእናንተ ለመግለጽ በመጣሁ ጊዜ በንግግር ችሎታ ወይም በጥበብ እናንተን ለማስደመም አልሞከርኩም2 ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዜ ትኩረቴን በኢየሱስ ክርስቶስና በእሱ መሰቀል ላይ ብቻ ለማድረግ ወስኜ ነበርና3 ወደ እናንተም የመጣሁት ደካማ ሆኜ እንዲሁም በፍርሃትና እጅግ በመንቀጥቀጥ ነበር4 ንግግሬም ሆነ የሰበክሁላችሁ መልእክት የሚያባብል የጥበብ ቃል አልነበረም ከዚህ ይልቅ የአምላክን መንፈስና ኃይል የሚያሳይ ነበር5 ይኸውም እምነታችሁ በአምላክ ኃይል ላይ እንጂ በሰው ጥበብ ላይ የተመሠረተ እንዳይሆን ነው6 በመሆኑም በጎለመሱት መካከል ስለ ጥበብ እንናገራለን ሆኖም የምንናገረው የዚህን ሥርዓት ጥበብ ወይም የሚጠፉትን የዚህን ሥርዓት ገዢዎች ጥበብ አይደለም7 ከዚህ ይልቅ የምንናገረው በቅዱስ ሚስጥር የተገለጠውን የአምላክ ጥበብ ይኸውም አምላክ ለእኛ ክብር ከዘመናት በፊት አስቀድሞ የወሰነውን የተሰወረ ጥበብ ነው8 ይህን ጥበብ ከዚህ ሥርዓት ገዢዎች መካከል አንዳቸውም አላወቁትም ቢያውቁትማ ኖሮ ታላቅ ክብር ያለውን ጌታ ባልሰቀሉት ነበር9 ይሁንና አምላክ ለሚወዱት ያዘጋጃቸውን ነገሮች ዓይን አላየም ጆሮም አልሰማም የሰውም ልብ አላሰበም ተብሎ እንደተጻፈው ነው10 አምላክ እነዚህን ነገሮች በመንፈሱ አማካኝነት የገለጠው ለእኛ ነውና ምክንያቱም መንፈስ ሁሉንም ነገሮች አልፎ ተርፎም የአምላክን ጥልቅ ነገሮች ይመረምራል11 ከሰዎች መካከል በአንድ ሰው ውስጥ ያለውን ነገር በውስጡ ካለው የሰውየው መንፈስ በቀር ማን ሊያውቅ ይችላል? በተመሳሳይም በአምላክ ውስጥ ያለውን ነገር ከአምላክ መንፈስ በቀር ማንም አያውቅም12 እኛ አምላክ በደግነት የሰጠንን ነገሮች ማወቅ እንድንችል ከአምላክ የሆነውን መንፈስ ተቀበልን እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም13 ደግሞም እነዚህን ነገሮች እንናገራለን የምንናገረው ግን ከሰው ጥበብ በተማርነው ቃል አይደለም ከዚህ ይልቅ መንፈሳዊ ጉዳዮችን በመንፈሳዊ ቃል ስናብራራ ከመንፈስ በተማርነው ቃል እንናገራለን14 ዓለማዊ ሰው ግን ከአምላክ መንፈስ የሆኑትን ነገሮች አይቀበልም እንዲህ ያሉት ነገሮች ለእሱ ሞኝነት ናቸውና በመንፈስ የሚመረመሩ ስለሆኑም ሊረዳቸው አይችልም15 ይሁን እንጂ መንፈሳዊ ሰው ሁሉንም ነገር ይመረምራል እሱ ራሱ ግን በማንም ሰው አይመረመርም16 ያስተምረው ዘንድ የይሖዋን አስተሳሰብ ያወቀ ማን ነው? ተብሏልና እኛ ግን የክርስቶስ አስተሳሰብ አለን
3 በመሆኑም ወንድሞች ከክርስቶስ ጋር በተያያዘ ገና ሕፃናት እንደሆኑ እንደ ሥጋውያን ሰዎች እንጂ እንደ መንፈሳውያን ሰዎች ላነጋግራችሁ አልቻልኩም2 ጠንካራ ስላልነበራችሁ ወተት እንጂ ጠንካራ ምግብ አልመገብኳችሁም አሁንም ቢሆን ገና አልጠነከራችሁም3 ደግሞም ገና ሥጋውያን ናችሁ ቅናትና ጠብ በመካከላችሁ ስላለ ሥጋውያን መሆናችሁ ደግሞም በዓለም እንዳሉ ሰዎች መመላለሳችሁ አይደለም?4 አንዱ እኔ የጳውሎስ ነኝ ሌላው ደግሞ እኔ የአጵሎስ ነኝ ሲል እንደ ማንኛውም ሰው መሆናችሁ አይደለም?5 ለመሆኑ አጵሎስ ምንድን ነው? ጳውሎስስ ምንድን ነው? ጌታ የሰጣቸውን ሥራ የሚያከናውኑ አገልጋዮች ናቸው እናንተም አማኞች የሆናችሁት በእነሱ አማካኝነት ነው6 እኔ ተከልኩ አጵሎስ አጠጣ ያሳደገው ግን አምላክ ነው7 ስለዚህ ምስጋና የሚገባው የሚያሳድገው አምላክ እንጂ የሚተክለውም ሆነ የሚያጠጣው አይደለም8 የሚተክለውም ሆነ የሚያጠጣው በኅብረት የሚሠሩ ናቸው ሆኖም እያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን የራሱን ወሮታ ይቀበላል9 እኛ ከአምላክ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና እናንተ በመልማት ላይ ያለ የአምላክ እርሻ ናችሁ የአምላክ ሕንፃ ናችሁ10 በተሰጠኝ የአምላክ ጸጋ መሠረት በሙያው እንደተካነ ግንበኛ እኔ መሠረት ጣልኩ ሌላው ደግሞ በዚያ ላይ ይገነባል ሆኖም እያንዳንዱ በዚያ ላይ እንዴት እንደሚገነባ በጥንቃቄ ሊያስብ ይገባል11 ማንም ሰው ከተጣለው መሠረት ሌላ አዲስ መሠረት መጣል አይችልምና ይህም መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው12 ማንም በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ በብር በከበሩ ድንጋዮች በእንጨት በሣር ወይም በአገዳ ቢገነባ13 የፈተናው ቀን ሲመጣ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል እሳቱ ሁሉንም ነገር ይገልጣልና እንዲሁም እያንዳንዱ ሰው ምን ዓይነት ግንባታ እንዳከናወነ እሳቱ ራሱ ፈትኖ ያሳያል14 ማንም በመሠረቱ ላይ የገነባው ነገር ቢጸናለት ወሮታ ያገኛል15 ይሁንና ማንም ሰው የሠራው ሥራ ቢቃጠል ኪሳራ ይደርስበታል እሱ ግን ይተርፋል ሆኖም በእሳት ውስጥ አልፎ የመትረፍ ያህል ይሆናል16 እናንተ ራሳችሁ የአምላክ ቤተ መቅደስ እንደሆናችሁና የአምላክ መንፈስ በእናንተ ውስጥ እንደሚያድር አታውቁም?17 ማንም የአምላክን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ አምላክ ያፈርሰዋል የአምላክ ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና ቤተ መቅደሱም እናንተ ናችሁ18 ማንም ራሱን አያታል ከእናንተ መካከል ማንም በዚህ ሥርዓት ጥበበኛ እንደሆነ ቢያስብ ጥበበኛ መሆን ይችል ዘንድ ሞኝ ይሁን19 ምክንያቱም የዚህ ዓለም ጥበብ በአምላክ ፊት ሞኝነት ነው ጥበበኞችን በራሳቸው ተንኮል ይይዛቸዋል ተብሎ ተጽፏልና20 ደግሞም ይሖዋ የጥበበኞች ሐሳብ ከንቱ እንደሆነ ያውቃል ተብሏል21 በመሆኑም ማንም በሰዎች አይኩራራ ሁሉም ነገር የእናንተ ነውና22 ጳውሎስም ቢሆን አጵሎስም ቢሆን ኬፋም ቢሆን ዓለምም ቢሆን ሕይወትም ቢሆን ሞትም ቢሆን አሁን ያሉት ነገሮችም ቢሆኑ የሚመጡትም ነገሮች ቢሆኑ ሁሉም ነገር የእናንተ ነው23 እናንተም የክርስቶስ ናችሁ ክርስቶስ ደግሞ የአምላክ ነው
4 እንግዲህ ሰው እኛን የክርስቶስ አገልጋዮችና የአምላክ ቅዱስ ሚስጥር በአደራ የተሰጠን መጋቢዎች እንደሆን አድርጎ ሊቆጥረን ይገባል2 በዚህ ረገድ መጋቢዎች ታማኝ ሆነው መገኘት ይጠበቅባቸዋል3 በእናንተም ሆነ በሰዎች ሸንጎ ብመረመር ለእኔ ምንም ትርጉም የለውም እኔም እንኳ ራሴን አልመረምርም4 ምክንያቱም ሕሊናዬ በሁሉም ነገር ንጹሕ ነው ሆኖም ይህ ጻድቅ መሆኔን ያረጋግጣል ማለት አይደለም እኔን የሚመረምረኝ ይሖዋ ነው5 ስለዚህ ጊዜው ከመድረሱ በፊት በምንም ነገር ላይ አትፍረዱ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጠብቁ እሱ በጨለማ ውስጥ የተሰወረውን ነገር ወደ ብርሃን ያወጣዋል እንዲሁም በልብ ውስጥ ያለውን ሐሳብ ይገልጣል በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ሰው ከአምላክ ምስጋናውን ይቀበላል6 እንግዲህ ወንድሞች አንዱን ከሌላው በማስበለጥ እንዳትታበዩ ለእናንተው ጥቅም ራሴንና አጵሎስን ምሳሌ አድርጌ በማቅረብ እነዚህን ነገሮች የተናገርኩት ከተጻፈው አትለፍ የሚለውን ደንብ እንድትማሩ ነው7 ለመሆኑ አንተን ከሌላው የተለየህ እንድትሆን ያደረገህ ማን ነው? ደግሞስ ያልተቀበልከው ምን ነገር አለ? ከተቀበልክ ደግሞ እንዳልተቀበልክ ሆነህ የምትኩራራው ለምንድን ነው?8 እንግዲህ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝታችኋል ማለት ነዋ! ባለጠጎች ሆናችኋላ! ያለእኛ ነግሣችኋል ማለት ነዋ! እኛም ከእናንተ ጋር መንገሥ እንድንችል ነገሥታት ሆናችሁ መግዛት ጀምራችሁ ቢሆን ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር!9 አምላክ እኛን ሐዋርያቱን ሞት እንደተፈረደባቸው ሰዎች መጨረሻ ላይ ወደ መድረክ እንድንወጣ ያደረገን ይመስለኛል ምክንያቱም ለዓለም ለመላእክትና ለሰዎች ትርዒት ሆነናል10 እኛ በክርስቶስ የተነሳ ሞኞች ነን እናንተ ግን በክርስቶስ የተነሳ ልባሞች ናችሁ እኛ ደካሞች ነን እናንተ ግን ጠንካሮች ናችሁ እናንተ የተከበራችሁ ናችሁ እኛ ግን ተዋርደናል11 እስከዚህ ሰዓት ድረስ እየተራብንና እየተጠማን እየተራቆትን እየተደበደብንና ቤት አጥተን እየተንከራተትን እንገኛለን12 እንዲሁም በገዛ እጃችን እየሠራን እንለፋለን ሲሰድቡን እንባርካለን ስደት ሲያደርሱብን በትዕግሥት እናሳልፋለን13 ስማችንን ሲያጠፉ በለዘበ አንደበት እንመልሳለን እስካሁን ድረስ የዓለም ጉድፍና የሁሉ ነገር ጥራጊ እንደሆንን ተደርገን እንታያለን14 እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ላሳፍራችሁ ብዬ ሳይሆን እንደተወደዳችሁ ልጆቼ አድርጌ ልመክራችሁ ነው15 ምንም እንኳ በክርስቶስ 10,000 ሞግዚቶች ሊኖሯችሁ ቢችልም ብዙ አባቶች እንደሌሏችሁ ግን የተረጋገጠ ነው በምሥራቹ አማካኝነት በክርስቶስ ኢየሱስ እኔ አባታችሁ ሆኛለሁና16 ስለዚህ እኔን እንድትመስሉ እለምናችኋለሁ17 በጌታ ልጄ የሆነውን የምወደውንና ታማኝ የሆነውን ጢሞቴዎስን የምልክላችሁ ለዚህ ነው እሱም በየስፍራው በሚገኙ ጉባኤዎች ሁሉ ሳስተምር የምጠቀምባቸውን ይኸውም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር በተያያዘ አገልግሎቴን የማከናውንባቸውን ዘዴዎች ያሳስባችኋል18 አንዳንዶች እኔ ወደ እናንተ የማልመጣ መስሏቸው በኩራት ተወጥረዋል19 ይሁንና ይሖዋ ከፈቀደ በቅርቡ ወደ እናንተ እመጣለሁ በዚያን ጊዜም እነዚህ በኩራት የተወጠሩ ሰዎች የሚናገሩትን ነገር ሳይሆን የአምላክ ኃይል ይኖራቸው እንደሆነ ማወቅ እፈልጋለሁ20 የአምላክ መንግሥት የወሬ ጉዳይ ሳይሆን የኃይል ጉዳይ ነውና21 ለመሆኑ የትኛው ይሻላችኋል? ዱላ ይዤ ልምጣ ወይስ በፍቅርና በገርነት መንፈስ ልምጣ?
5 በመካከላችሁ ዝሙት እንደተፈጸመ ይወራል እንዲህ ዓይነቱ ዝሙት ደግሞ በአሕዛብ መካከል እንኳ ታይቶ አይታወቅም ከአባቱ ሚስት ጋር የሚኖር ሰው አለ ተብሏል2 ታዲያ በዚህ ትኩራራላችሁ? ይልቁንም በዚህ ማዘንና ድርጊቱን የፈጸመውን ሰው ከመካከላችሁ ማስወጣት አይገባችሁም?3 ምንም እንኳ እኔ በአካል ከእናንተ ጋር ባልሆንም በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ ደግሞም እንዲህ ያለ ድርጊት በፈጸመው ሰው ላይ አብሬያችሁ ያለሁ ያህል ሆኜ ፈርጄበታለሁ4 በጌታችን በኢየሱስ ስም አንድ ላይ በምትሰበሰቡበት ጊዜ እኔም በጌታችን በኢየሱስ ኃይል በመንፈስ ከእናንተ ጋር እንደምሆን በመገንዘብ5 እንዲህ ያለውን ሰው ለሰይጣን አሳልፋችሁ ልትሰጡት ይገባል ይህም እሱ በጉባኤው ላይ ያሳደረው መጥፎ ተጽዕኖ እንዲወገድና የጉባኤው መንፈስ በጌታ ቀን ባለበት ሁኔታ እንዲቀጥል ነው6 መመካታችሁ መልካም አይደለም ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካው አታውቁም?7 አዲስ ሊጥ እንድትሆኑ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ ምክንያቱም የፋሲካችን በግ የሆነው ክርስቶስ ስለተሠዋ ከእርሾ ነፃ ናችሁ8 ስለዚህ በዓሉን በአሮጌ እርሾ እንዲሁም በክፋትና በኃጢአት እርሾ ሳይሆን እርሾ በሌለበት በቅንነትና በእውነት ቂጣ እናክብር9 ከሴሰኞች ጋር መግጠማችሁን እንድትተዉ በደብዳቤዬ ላይ ጽፌላችሁ ነበር10 እንዲህ ስል ግን በአጠቃላይ ከዚህ ዓለም ሴሰኞች ስግብግብ ሰዎች ቀማኞች ወይም ጣዖት አምላኪዎች ጋር አትገናኙ ማለቴ አይደለም እንዲህ ቢሆንማ ኖሮ ጨርሶ ከዓለም መውጣት ያስፈልጋችሁ ነበር11 አሁን ግን የጻፍኩላችሁ ወንድም ተብሎ እየተጠራ ሴሰኛ ወይም ስግብግብ ወይም ጣዖት አምላኪ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካራም ወይም ቀማኛ ከሆነ ማንኛውም ሰው ጋር መግጠማችሁን እንድትተዉ አልፎ ተርፎም እንዲህ ካለው ሰው ጋር ምግብ እንኳ እንዳትበሉ ነው12 በውጭ ባሉ ሰዎች ላይ የምፈርደው እኔ ምን አግብቶኝ ነው? በውስጥ ባሉት ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱም?13 በውጭ ባሉት ላይ አምላክ ይፈርዳል ክፉውን ሰው ከመካከላችሁ አስወግዱት
6 ከእናንተ መካከል አንዱ ከሌላው ጋር የሚከራከርበት ጉዳይ ቢኖረው ጉዳዩን በቅዱሳን ፊት በማቅረብ ፋንታ በዓመፀኛ ሰዎች ፊት ለማቅረብ ፍርድ ቤት ለመሄድ እንዴት ይደፍራል?2 ወይስ ቅዱሳን በዓለም ላይ እንደሚፈርዱ አታውቁም? ታዲያ እናንተ በዓለም ላይ የምትፈርዱ ከሆነ በጣም ተራ የሆኑ ጉዳዮችን ለመዳኘት አትበቁም?3 በመላእክት ላይ እንኳ እንደምንፈርድ አታውቁም? ታዲያ በአሁኑ ሕይወት በሚያጋጥሙ ጉዳዮች ላይ ለምን አትፈርዱም?4 ደግሞስ በአሁኑ ሕይወት የሚያጋጥሙ ዳኝነት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ካሉ ጉባኤው የሚንቃቸው ሰዎች እንዲዳኙት ታደርጋላችሁ?5 ይህን የምለው ኀፍረት እንዲሰማችሁ ብዬ ነው ወንድሞቹን መዳኘት የሚችል አንድ እንኳ ጥበበኛ ሰው በመካከላችሁ የለም?6 አንድ ወንድም ሌላውን ወንድም ፍርድ ቤት ይወስዳል ያውም የማያምኑ ሰዎች ፊት!7 እንግዲህ እርስ በርስ ተካስሳችሁ ፍርድ ቤት መሄዳችሁ ለእናንተ ትልቅ ሽንፈት ነው ከዚህ ይልቅ እናንተ ራሳችሁ ብትበደሉ አይሻልም? ደግሞስ እናንተ ራሳችሁ ብትታለሉ አይሻልም?8 እናንተ ግን ትበድላላችሁ እንዲሁም ታታልላላችሁ ያውም የገዛ ወንድሞቻችሁን!9 ወይስ ዓመፀኞች የአምላክን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁም? አትታለሉ ሴሰኞችም ሆኑ ጣዖት አምላኪዎች ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ግብረ ሰዶማውያን10 ወይም ሌቦች ወይም ስግብግቦች ወይም ሰካራሞች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ቀማኞች የአምላክን መንግሥት አይወርሱም11 አንዳንዶቻችሁም እንደዚህ ነበራችሁ ሆኖም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በአምላካችን መንፈስ ታጥባችሁ ነጽታችኋል ተቀድሳችኋል እንዲሁም ጻድቃን ተብላችኋል12 ሁሉም ነገር ተፈቅዶልኛል ሆኖም ሁሉም ነገር ይጠቅማል ማለት አይደለም ሁሉም ነገር ተፈቅዶልኛል ሆኖም ለምንም ነገር ተገዢ መሆን አልሻም13 ምግብ ለሆድ ሆድም ለምግብ ነው አምላክ ግን ሁለቱንም ያጠፋቸዋል አካል ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም ጌታ ደግሞ ለአካል ነው14 ይሁን እንጂ አምላክ በኃይሉ አማካኝነት ጌታን እንዳስነሳው እኛንም ከሞት ያስነሳናል15 ሰውነታችሁ የክርስቶስ አካል ክፍል እንደሆነ አታውቁም? ታዲያ የክርስቶስ አካል ክፍል የሆነውን ወስጄ ከዝሙት አዳሪ ጋር ላጣምረው? በፍጹም!16 ከዝሙት አዳሪ ጋር የሚጣመር ሁሉ ከእሷ ጋር አንድ አካል እንደሚሆን አታውቁም? አምላክ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ ብሏልና17 ሆኖም ከጌታ ጋር የተቆራኘ ሁሉ በመንፈስ ከእሱ ጋር አንድ ነው18 ከዝሙት ሽሹ! አንድ ሰው የሚፈጽመው ሌላ ኃጢአት ሁሉ ከአካሉ ውጭ ነው ዝሙት የሚፈጽም ሁሉ ግን በራሱ አካል ላይ ኃጢአት እየሠራ ነው19 የእናንተ አካል ከአምላክ ለተቀበላችሁት በውስጣችሁ ላለው መንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደሆነ አታውቁም? በተጨማሪም እናንተ የራሳችሁ አይደላችሁም20 በዋጋ ተገዝታችኋልና ስለዚህ በሰውነታችሁ አምላክን አክብሩ
7 በደብዳቤያችሁ ላይ ያነሳችኋቸውን ጥያቄዎች በተመለከተ አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ባይነካ ይሻላል2 ይሁንና የፆታ ብልግና ስለተስፋፋ እያንዳንዱ ወንድ የራሱ ሚስት ትኑረው እያንዳንዷም ሴት የራሷ ባል ይኑራት3 ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት ሚስትም ብትሆን ለባሏ እንደዚሁ ታድርግለት4 ሚስት በራሷ አካል ላይ ሥልጣን የላትም ሥልጣን ያለው ባሏ ነው በተመሳሳይም ባል በራሱ አካል ላይ ሥልጣን የለውም ሥልጣን ያላት ሚስቱ ናት5 አንዳችሁ ለሌላው የሚገባውን አትከልክሉ እንዲህ ማድረግ የምትችሉት በጋራ ስምምነት የተወሰነ ጊዜ ለጸሎት ለማዋል ካሰባችሁ ብቻ ነው ደግሞም ራሳችሁን መግዛት አቅቷችሁ ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደገና አብራችሁ ሁኑ6 ይሁን እንጂ ይህን ያልኩት እንዲህ ማድረግ እንደሚቻል ለመግለጽ ነው እንጂ ለማዘዝ አይደለም7 ይሁንና ሰው ሁሉ እንደ እኔ ቢሆን ደስ ባለኝ ነበር ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ከአምላክ ያገኘው የራሱ ስጦታ አለው አንዱ አንድ ዓይነት ስጦታ ሲኖረው ሌላው ደግሞ ሌላ ዓይነት ስጦታ አለው8 ሆኖም ላላገቡና መበለት ለሆኑ እንደ እኔ ሆነው ቢኖሩ የተሻለ ነው እላለሁ9 ራሳቸውን መግዛት ካቃታቸው ግን ያግቡ በፍትወት ከመቃጠል ማግባት ይሻላልና10 ላገቡት ሰዎች ይህን መመሪያ እሰጣለሁ ይህ መመሪያ የጌታ እንጂ የእኔ አይደለም ሚስት ከባሏ አትለያይ11 ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር ወይም ከባሏ ጋር ትታረቅ ባልም ሚስቱን መተው የለበትም12 ለሌሎች ደግሞ እንዲህ እላለሁ ይህን የምለው እኔ እንጂ ጌታ አይደለም አንድ ወንድም አማኝ ያልሆነች ሚስት ካለችውና አብራው ለመኖር ከተስማማች አይተዋት13 እንዲሁም አንዲት ሴት አማኝ ያልሆነ ባል ካላትና ባሏ አብሯት ለመኖር ከተስማማ አትተወው14 አማኝ ያልሆነ ባል ከሚስቱ ጋር ባለው ዝምድና የተነሳ ተቀድሷልና አማኝ ያልሆነች ሚስትም ከወንድም ጋር ባላት ዝምድና የተነሳ ተቀድሳለች እንዲህ ባይሆን ኖሮ ልጆቻችሁ ርኩሳን በሆኑ ነበር አሁን ግን ቅዱሳን ናቸው15 ይሁንና አማኝ ያልሆነው ወገን ለመለየት ከመረጠ ይለይ እንዲህ ያለ ሁኔታ በሚፈጠርበት ጊዜ አንድ ወንድም ወይም አንዲት እህት ምንም ዓይነት ግዴታ የለባቸውም አምላክ የጠራችሁ ለሰላም ነውና16 አንቺ ሚስት ባልሽን ታድኚው እንደሆነ ምን ታውቂያለሽ? ወይስ አንተ ባል ሚስትህን ታድን እንደሆነ ምን ታውቃለህ?17 ያም ሆነ ይህ እያንዳንዱ ሰው ይሖዋ በሰጠው ድርሻና አምላክ ሲጠራው በነበረበት ሁኔታ ይመላለስ ለጉባኤዎችም ሁሉ ይህን መመሪያ እሰጣለሁ18 አንድ ሰው የተጠራው ተገርዞ እያለ ነው? እንዳልተገረዘ ሰው አይሁን አንድ ሰው የተጠራው ሳይገረዝ ነው? ከሆነ አይገረዝ19 መገረዝ ምንም ማለት አይደለም አለመገረዝም ቢሆን ምንም ማለት አይደለም ዋናው ነገር የአምላክን ትእዛዛት መጠበቅ ነው20 እያንዳንዱ ሰው በተጠራበት ጊዜ የነበረበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በዚያው ይቀጥል21 የተጠራኸው ባሪያ እያለህ ነው? ይሄ አያስጨንቅህ ሆኖም ነፃ መውጣት የምትችል ከሆነ አጋጣሚውን ተጠቀምበት22 ባሪያ እያለ የተጠራ ማንኛውም የጌታ ደቀ መዝሙር ነፃ የወጣ የጌታ ሰው ነውና በተመሳሳይም ነፃ እያለ የተጠራ ሰው የክርስቶስ ባሪያ ነው23 በዋጋ ተገዝታችኋል የሰው ባሪያ መሆናችሁ ይብቃ24 ወንድሞች እያንዳንዱ ሰው በተጠራበት ጊዜ የነበረበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በአምላክ ፊት በዚያው ሁኔታ ይቀጥል25 ድንግል የሆኑትን በተመለከተ ከጌታ የተቀበልኩት ትእዛዝ የለኝም ይሁን እንጂ ጌታ ካሳየኝ ምሕረት የተነሳ እንደ ታማኝ ሰው የራሴን ሐሳብ እሰጣለሁ26 ስለዚህ አሁን ካለው ችግር አንጻር አንድ ሰው ባለበት ሁኔታ ቢቀጥል የተሻለ ይመስለኛል27 በሚስት ታስረሃል? ከሆነ መፈታትን አትሻ ሚስት የሌለህ ነህ? ከሆነ ሚስት ለማግባት አትፈልግ28 ይሁንና ብታገባም ኃጢአት ይሆንብሃል ማለት አይደለም እንዲሁም ድንግል የሆነ ሰው ቢያገባ ኃጢአት ይሆንበታል ማለት አይደለም ይሁን እንጂ የሚያገቡ ሰዎች በሥጋቸው ላይ መከራ ይደርስባቸዋል ነገር ግን የእኔ ምኞት ከዚህ እንድትድኑ ነው29 ከዚህም በላይ ወንድሞች የቀረው ጊዜ አጭር መሆኑን ልነግራችሁ እወዳለሁ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስት ያላቸው እንደሌላቸው ይሁኑ30 የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ የሚደሰቱም እንደማይደሰቱ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው31 እንዲሁም በዓለም የሚጠቀሙ ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንደማይጠቀሙበት ይሁኑ የዚህ ዓለም ትእይንት እየተለዋወጠ ነውና32 በመሆኑም ከጭንቀት ነፃ እንድትሆኑ እፈልጋለሁ ያላገባ ሰው ጌታን እንዴት ደስ ማሰኘት እንደሚችል በማሰብ ስለ ጌታ ነገር ይጨነቃል33 ያገባ ሰው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ ማሰኘት እንደሚችል በማሰብ ስለ ዓለም ነገር ይጨነቃል34 በመሆኑም ሐሳቡ ተከፋፍሏል በተጨማሪም ያላገባች ሴትም ሆነች ድንግል በአካሏም ሆነ በመንፈሷ ቅዱስ መሆን ትችል ዘንድ ስለ ጌታ ነገር ትጨነቃለች ይሁን እንጂ ያገባች ሴት ባሏን እንዴት ደስ ማሰኘት እንደምትችል በማሰብ ስለ ዓለም ነገር ትጨነቃለች35 ይህን የምለው ግን ለእናንተው ጥቅም ብዬ ነው እንጂ ነፃነት ላሳጣችሁ ብዬ አይደለም ከዚህ ይልቅ ተስማሚ የሆነውን ነገር እንድታደርጉና ሐሳባችሁ ሳይከፋፈል ዘወትር ለጌታ ያደራችሁ እንድትሆኑ ላነሳሳችሁ ብዬ ነው36 ይሁንና አንድ ሰው ሳያገባ ቀርቶ ራሱን መቆጣጠር እንደተሳነው ከተሰማው በተለይ ደግሞ አፍላ የጉርምስና ዕድሜን ያለፈ ከሆነና ማግባቱ የሚመረጥ ከሆነ የፈለገውን ያድርግ ኃጢአት አይሆንበትም እንዲህ ያሉ ሰዎች ያግቡ37 ሆኖም አንድ ሰው ልቡ ከቆረጠና ይህን ማድረግ እንደማያስፈልገው ከተሰማው ደግሞም ራሱን መግዛት የሚችል ከሆነና ሳያገባ ለመኖር በልቡ ከወሰነ መልካም ያደርጋል38 ስለዚህ የሚያገባ ሁሉ መልካም ያደርጋል ሳያገባ የሚኖር ሁሉ ደግሞ የተሻለ ያደርጋል39 አንዲት ሚስት ባሏ በሕይወት ባለበት ዘመን ሁሉ የታሰረች ናት ባሏ በሞት ካንቀላፋ ግን በጌታ ብቻ ይሁን እንጂ ከፈለገችው ሰው ጋር ለመጋባት ነፃ ናት40 እንደ እኔ ከሆነ ግን እንዳለች ብትቀጥል ይበልጥ ደስተኛ ትሆናለች እኔ ደግሞ የአምላክ መንፈስ እንዳለኝ እርግጠኛ ነኝ
8 ለጣዖቶች የቀረበን ምግብ በተመለከተ ሁላችንም እውቀት እንዳለን እናውቃለን እውቀት ያስታብያል ፍቅር ግን ያንጻል2 አንድ ሰው ስለ አንድ ነገር አውቃለሁ ብሎ የሚያስብ ከሆነ ስለዚያ ነገር ማወቅ የሚገባውን ያህል ገና አያውቅም3 ሆኖም አንድ ሰው አምላክን የሚወድ ከሆነ በእሱ ዘንድ የታወቀ ነው4 ለጣዖቶች የቀረበ ምግብ መብላትን በተመለከተ በዓለም ላይ ጣዖት ከንቱ እንደሆነና ከአንዱ በቀር አምላክ እንደሌለ እናውቃለን5 ብዙ አማልክት እና ብዙ ጌቶች እንደመኖራቸው መጠን በሰማይም ሆነ በምድር አማልክት ተብለው የሚጠሩ ቢኖሩም እንኳ6 እኛ ግን ሁሉም ነገር ከእሱ የሆነ እኛም ለእሱ የሆን አንድ አምላክ አብ አለን እንዲሁም ሁሉም ነገር በእሱ በኩል የሆነና እኛም በእሱ በኩል የሆን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለ7 ይሁንና ይህ እውቀት ያላቸው ሁሉም ሰዎች አይደሉም አንዳንዶች ግን ቀደም ሲል ጣዖት ያመልኩ ስለነበር የሚበሉት ምግብ ለጣዖት የተሠዋ እንደሆነ አድርገው ያስባሉ ሕሊናቸው ደካማ ስለሆነም ይረክሳል8 ይሁን እንጂ ምግብ ከአምላክ ጋር አያቀራርበንም ባንበላ የሚጎድልብን ነገር የለም ብንበላም የምናተርፈው ነገር የለም9 ነገር ግን የመምረጥ መብታችሁ ደካማ የሆኑትን በሆነ መንገድ እንዳያሰናክላቸው ተጠንቀቁ10 አንተ እውቀት ያለህ በጣዖት ቤተ መቅደስ ውስጥ ስትበላ አንድ ሰው ቢያይህ ደካማ የሆነው ይህ ሰው ሕሊናው ለጣዖት የቀረበውን ምግብ እንዲበላ አያደፋፍረውም?11 እንግዲህ ክርስቶስ የሞተለት ይህ ደካማ የሆነው ወንድምህ በአንተ እውቀት ሳቢያ ጠፋ ማለት ነው12 በዚህ መንገድ ወንድሞቻችሁን ስትበድሉና ደካማ የሆነውን ሕሊናቸውን ስታቆስሉ በክርስቶስ ላይ ኃጢአት እየሠራችሁ ነው13 ስለዚህ ምግብ ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ ወንድሜን ላለማሰናከል ስል ከእንግዲህ ፈጽሞ ሥጋ አልበላም
9 እኔ ነፃ ሰው አይደለሁም? ሐዋርያስ አይደለሁም? ደግሞስ ጌታችንን ኢየሱስን አላየሁትም? እናንተ በጌታ የሥራዬ ውጤት አይደላችሁም?2 ለሌሎች ሐዋርያ ባልሆን እንኳ ለእናንተ ሐዋርያ እንደሆንኩ የተረጋገጠ ነው! እናንተ የጌታ ሐዋርያ መሆኔን የሚያረጋግጥ ማኅተም ናችሁና3 ለሚመረምሩኝ የማቀርበው የመከላከያ መልስ ይህ ነው4 እኛ የመብላትና የመጠጣት መብት የለንም እንዴ?5 እንደ ሌሎቹ ሐዋርያትና እንደ ጌታ ወንድሞች እንዲሁም እንደ ኬፋ አማኝ የሆነች ሚስት ይዘን የመዞር መብት የለንም?6 ወይስ ሰብዓዊ ሥራ የመተው መብት የሌለን እኔና በርናባስ ብቻ ነን?7 ለመሆኑ በራሱ ወጪ ወታደር ሆኖ የሚያገለግል ማን ነው? ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው? ወይስ መንጋ እየጠበቀ ከመንጋው ወተት የተወሰነ ድርሻ የማያገኝ ማን ነው?8 ይህን የምለው ከሰብዓዊ አመለካከት አንጻር ነው? ሕጉስ ቢሆን እንዲህ አይልም?9 በሙሴ ሕግ እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰር ተብሎ ተጽፏልና አምላክ ይህን የተናገረው ስለ በሬዎች ተጨንቆ ነው?10 እንዲህ ያለው ስለ እኛ በማሰብ አይደለም? እንዲህ ተብሎ የተጻፈው በእርግጥ ስለ እኛ ነው ምክንያቱም አራሹም ሆነ የሚያበራየው ሰው ሥራቸውን የሚያከናውኑት ከምርቱ ድርሻ እንደሚኖራቸው ተስፋ በማድረግ ነው11 እኛ በእናንተ መካከል መንፈሳዊ ነገሮች ከዘራን ከእናንተ ሥጋዊ ነገሮች ብናጭድ ትልቅ ነገር መሆኑ ነው?12 ሌሎች የእናንተን ድጋፍ የማግኘት መብት ካላቸው እኛ ከእነሱ የበለጠ መብት የለንም? ይሁንና እኛ በዚህ መብት አልተጠቀምንም ከዚህ ይልቅ ስለ ክርስቶስ የሚሰበከውን ምሥራች የሚያደናቅፍ ምንም ነገር ላለመፍጠር ሁሉን ችለን እንኖራለን13 ቅዱስ አገልግሎት የሚያከናውኑት ሰዎች ከቤተ መቅደስ የሚያገኙትን ምግብ እንደሚመገቡ እንዲሁም ዘወትር በመሠዊያው የሚያገለግሉ ከመሠዊያው የራሳቸውን ድርሻ እንደሚያገኙ አታውቁም?14 በተመሳሳይም ምሥራቹን የሚያውጁ ሰዎች በምሥራቹ አማካኝነት በሚያገኙት ነገር እንዲኖሩ ጌታ አዟል15 ይሁን እንጂ እኔ ከእነዚህ ዝግጅቶች በአንዱም አልተጠቀምኩም እርግጥ ይህን የጻፍኩት እንዲህ ሊደረግልኝ ይገባል ለማለት አይደለም ማንም ሰው የምኮራበትን ነገር ከሚያሳጣኝ ብሞት ይሻለኛልና!16 አሁን ምሥራቹን እየሰበክሁ ብሆንም ለመኩራራት ምክንያት አይሆነኝም እንዲህ የማድረግ ግዴታ ተጥሎብኛልና እንዲያውም ምሥራቹን ባልሰብክ ወዮልኝ!17 ይህን በፈቃደኝነት ካከናወንኩ ሽልማት አለኝ ይሁንና ሳልወድ ባደርገውም እንኳ የመጋቢነት አደራ ተጥሎብኛል18 ታዲያ ሽልማቴ ምንድን ነው? ከምሥራቹ ጋር በተያያዘ ሥልጣኔን አላግባብ እንዳልጠቀምበት ምሥራቹን በምሰብክበት ጊዜ ምሥራቹን ያለክፍያ ማቅረብ ነው19 እኔ ከሰው ሁሉ ነፃ ነኝ ሆኖም በተቻለ መጠን ብዙዎችን እማርክ ዘንድ ራሴን ለሁሉ ባሪያ አደረግኩ20 አይሁዳውያንን እማርክ ዘንድ ለአይሁዳውያን እንደ አይሁዳዊ ሆንኩ እኔ ራሴ በሕግ ሥር ባልሆንም እንኳ በሕግ ሥር ያሉትን እማርክ ዘንድ በሕግ ሥር ላሉት በሕግ ሥር እንዳለሁ ሆንኩ21 በአምላክ ፊት ከሕግ ነፃ ያልሆንኩና በክርስቶስ ፊት በሕግ ሥር ያለሁ ብሆንም እንኳ ሕግ የሌላቸውን እማርክ ዘንድ ሕግ ለሌላቸው ሕግ እንደሌለው ሰው ሆንኩ22 ደካሞችን እማርክ ዘንድ ለደካሞች ደካማ ሆንኩ በተቻለ መጠን የተወሰኑ ሰዎችን አድን ዘንድ ለሁሉም ዓይነት ሰዎች ሁሉንም ነገር ሆንኩ23 ምሥራቹን ለሌሎች አካፍል ዘንድ ለምሥራቹ ስል ሁሉን ነገር አደርጋለሁ24 በሩጫ ውድድር ሁሉም እንደሚሮጡ ሽልማቱን የሚያገኘው ግን አንዱ ብቻ እንደሆነ አታውቁም? እናንተም ሽልማቱን እንድታገኙ በዚሁ ሁኔታ ሩጡ25 በውድድር የሚሳተፍ ማንኛውም ሰው በሁሉም ነገር ራሱን ይገዛል እነሱ ይህን የሚያደርጉት የሚጠፋውን አክሊል ለማግኘት ሲሆን እኛ ግን የማይጠፋውን አክሊል ለማግኘት ነው26 ስለዚህ እኔ ያለግብ አልሮጥም ቡጢ የምሰነዝረውም አየር ለመምታት አይደለም27 ከዚህ ይልቅ ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ እኔ ራሴ በሆነ መንገድ ተቀባይነት እንዳላጣ ሰውነቴን እየጎሰምኩ እንደ ባሪያ እንዲገዛልኝ አደርገዋለሁ
5 ስለዚህ እኔም እንደ እነሱ ሽማግሌ እንዲሁም የክርስቶስ መከራ ምሥክርና ወደፊት የሚገለጠው ክብር ተካፋይ እንደመሆኔ መጠን በመካከላችሁ ያሉትን ሽማግሌዎች እንዲህ በማለት አጥብቄ እለምናለሁ2 የበላይ ተመልካቾች ሆናችሁ በማገልገል በአደራ የተሰጣችሁን የአምላክን መንጋ እንደ እረኛ ጠብቁ ሥራችሁን በግዴታ ሳይሆን በአምላክ ፊት በፈቃደኝነት ተወጡ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በመመኘት ሳይሆን ለማገልገል በመጓጓት3 የአምላክ ንብረት በሆኑት ላይ ሥልጣናችሁን በማሳየት ሳይሆን ለመንጋው ምሳሌ በመሆን ጠብቁ4 የእረኞች አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማይጠፋ የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ5 በተመሳሳይም እናንተ ወጣቶች ለሽማግሌዎች ተገዙ ይሁንና እርስ በርስ ባላችሁ ግንኙነት ሁላችሁም ትሕትናን ልበሱ ምክንያቱም አምላክ ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል6 ስለዚህ በተገቢው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው የአምላክ እጅ በታች ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ7 የሚያስጨንቃችሁንም ነገር ሁሉ በእሱ ላይ ጣሉ ምክንያቱም እሱ ስለ እናንተ ያስባል8 የማስተዋል ስሜታችሁን ጠብቁ ንቁ ሆናችሁ ኑሩ! ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይንጎራደዳል9 ሆኖም በዓለም ዙሪያ በመላው የወንድማማች ማኅበር ውስጥ ያሉት ወንድሞቻችሁ ተመሳሳይ መከራ እየደረሰባቸው እንዳለ ተገንዝባችሁ በእምነት ጸንታችሁ በመቆም ተቃወሙት10 ከክርስቶስ ጋር ባላችሁ አንድነት ወደ ዘላለማዊ ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ እሱ ራሱ ሥልጠናችሁ እንዲጠናቀቅ ያደርጋል ጽኑ እንድትሆኑ ያደርጋችኋል ደግሞም ያጠነክራችኋል አጽንቶም ያቆማችኋል11 ኃይል ለዘላለም የእሱ ይሁን አሜን12 እኔ ታማኝ ወንድም አድርጌ በምቆጥረው በስልዋኖስ አማካኝነት ይህን በአጭሩ ጽፌላችኋለሁ የጻፍኩላችሁም እናንተን ለማበረታታትና ይህ የአምላክ እውነተኛ ጸጋ እንደሆነ አጥብቄ ለመመሥከር ነው ይህን ጸጋ አጥብቃችሁ ያዙ13 እንደ እናንተ የተመረጠችው በባቢሎን የምትገኘው ሰላምታ ታቀርብላችኋለች ልጄ ማርቆስም ሰላምታ ያቀርብላችኋል14 በፍቅር እርስ በርስ በመሳሳም ሰላምታ ተለዋወጡከክርስቶስ ጋር አንድነት ያላችሁ ሁሉ ሰላም ለእናንተ ይሁን
1 የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጴጥሮስ በጳንጦስ በገላትያ በቀጰዶቅያ በእስያና በቢቲኒያ ተበትነው ለሚገኙ ጊዜያዊ ነዋሪዎች ለሆኑ የአምላክ ምርጦች2 ይኸውም አባት የሆነው አምላክ አስቀድሞ ባወቀው መሠረት ለተመረጡት ደግሞም ታዛዥ እንዲሆኑና በኢየሱስ ክርስቶስ ደም እንዲረጩ በመንፈስ ለተቀደሱትጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ3 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይወደስ እሱ በታላቅ ምሕረቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አማካኝነት ለሕያው ተስፋ እንደ አዲስ ወልዶናልና4 እንዲሁም ለማይበሰብስ ለማይረክስና ለማይጠፋ ርስት ወልዶናል ይህም በሰማይ ለእናንተ ተጠብቆላችኋል5 እናንተንም አምላክ በዘመኑ መጨረሻ ለሚገለጠው መዳን በእምነት አማካኝነት በኃይሉ እየጠበቃችሁ ነው6 አሁን ለአጭር ጊዜ በልዩ ልዩ ፈተናዎች መጨነቃችሁ የግድ ቢሆንም በእነዚህ ሁሉ ነገሮች የተነሳ እጅግ እየተደሰታችሁ ነው7 እነዚህ ፈተናዎች የሚደርሱባችሁ በእሳት የተፈተነ ቢሆንም እንኳ ሊጠፋ ከሚችለው ወርቅ እጅግ የላቀ ዋጋ ያለውና ተፈትኖ የተረጋገጠው እምነታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን ግርማንና ክብርን ያስገኝ ዘንድ ነው8 እሱን አይታችሁት ባታውቁም ትወዱታላችሁ አሁን ባታዩትም እንኳ በእሱ ላይ እምነት እያሳያችሁና በቃላት ሊገለጽ በማይችል ታላቅ ደስታ እጅግ ሐሴት እያደረጋችሁ ነው9 ምክንያቱም የእምነታችሁ ግብ ላይ እንደምትደርሱ ይኸውም ራሳችሁን እንደምታድኑ ታውቃላችሁ10 ለእናንተ ስለሚሰጠው ጸጋ የተነበዩት ነቢያት ይህን መዳን በተመለከተ ትጋት የተሞላበት ምርምርና ጥልቅ ጥናት አካሂደዋል11 በውስጣቸው ያለው መንፈስ በክርስቶስ ላይ ስለሚደርሱት መከራዎችና ከዚያ በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ ሲመሠክር ከክርስቶስ ጋር በተያያዘ ስለ የትኛው ጊዜ ወይም ወቅት እያመለከተ እንዳለ ይመረምሩ ነበር12 እነሱ ራሳቸውን እያገለገሉ እንዳልሆነ ተገልጦላቸው ነበር ከዚህ ይልቅ ከሰማይ በተላከ መንፈስ ቅዱስ ምሥራቹን ባበሰሩላችሁ ሰዎች አማካኝነት ከተነገሯችሁ ነገሮች ጋር በተያያዘ እናንተን እያገለገሉ ነበር መላእክትም እነዚህን ነገሮች ለማየት ይጓጓሉ13 በመሆኑም አእምሯችሁን ዝግጁ በማድረግ ለሥራ ታጠቁ የማስተዋል ስሜታችሁን በሚገባ ጠብቁ ተስፋችሁን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ በምታገኙት ጸጋ ላይ አድርጉ14 ታዛዥ ልጆች እንደመሆናችሁ መጠን ቀድሞ እውቀት ባልነበራችሁ ጊዜ ትከተሉት በነበረው ምኞት መሠረት መቀረጻችሁን አቁሙ15 ከዚህ ይልቅ የጠራችሁ ቅዱስ አምላክ ቅዱስ እንደሆነ ሁሉ እናንተም በምግባራችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ16 እኔ ቅዱስ ስለሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ተጽፏልና17 ደግሞም ምንም ሳያዳላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት የምትለምኑ ከሆነ ጊዜያዊ ነዋሪዎች ሆናችሁ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ አምላክን በመፍራት ኑሩ18 እናንተ ከቀድሞ አባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከንቱ አኗኗር ነፃ የወጣችሁት ሊበላሹ በሚችሉ ነገሮች ይኸውም በብር ወይም በወርቅ እንዳልሆነ ታውቃላችሁና19 ከዚህ ይልቅ ነፃ የወጣችሁት ነውርና እንከን እንደሌለበት በግ ደም ባለ ውድ ደም ይኸውም በክርስቶስ ደም ነው20 እርግጥ እሱ አስቀድሞ የታወቀው ዓለም ከመመሥረቱ በፊት ነው ሆኖም ለእናንተ ሲባል በዘመናት መጨረሻ ላይ እንዲገለጥ ተደረገ21 እናንተም እምነታችሁና ተስፋችሁ በአምላክ ላይ ይሆን ዘንድ እሱን ከሞት ባስነሳውና ክብር ባጎናጸፈው አምላክ ያመናችሁት በእሱ አማካኝነት ነው22 እንግዲህ ለእውነት በመታዘዝ ራሳችሁን ስላነጻችሁ ግብዝነት የሌለበት የወንድማማች መዋደድ አላችሁ በመሆኑም እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ከልብ ተዋደዱ23 ሕያው በሆነውና ጸንቶ በሚኖረው አምላክ ቃል አማካኝነት እንደ አዲስ የተወለዳችሁት በሚበሰብስ ሳይሆን በማይበሰብስ ዘር ነው24 ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ነውና ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል25 የይሖዋ ቃል ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል ለእናንተም የተሰበከላችሁ ምሥራች ይህ ቃል ነው
2 እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ማታለልን ግብዝነትን ቅናትንና ሐሜትን ሁሉ አስወግዱ2 ገና እንደተወለዱ ሕፃናት በአምላክ ቃል ውስጥ ለሚገኘው ያልተበረዘ ወተት ጉጉት አዳብሩ ይህም በእሱ አማካኝነት ወደ መዳን ማደግ እንድትችሉ ነው3 ጌታ ደግ መሆኑን ቀምሳችኋልና4 በሰዎች ወደተናቀው በአምላክ ግን ወደተመረጠውና በፊቱ ክቡር ወደሆነው ወደ እሱ ይኸውም ሕያው ወደሆነው ድንጋይ በመምጣት5 እናንተ ራሳችሁ ቅዱሳን ካህናት ለመሆን እንደ ሕያዋን ድንጋዮች መንፈሳዊ ቤት ለመሆን እየተገነባችሁ ነው ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መንፈሳዊ መሥዋዕት ማቅረብ ትችሉ ዘንድ ነው6 ምክንያቱም ቅዱስ መጽሐፉ እንዲህ ይላል እነሆ በጽዮን የተመረጠ ድንጋይ ይኸውም ክቡር የሆነ የማዕዘን የመሠረት ድንጋይ አኖራለሁ ደግሞም በእሱ የሚያምን ሁሉ ፈጽሞ አያፍርም7 በመሆኑም እናንተ አማኞች ስለሆናችሁ እሱ ለእናንተ ክቡር ነው የማያምኑትን በተመለከተ ግን እንዲህ ተብሎ ተጽፏል ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እሱ የማዕዘን ራስ ድንጋይ ሆነ8 እንዲሁም የሚያደናቅፍ ድንጋይና የሚያሰናክል ዓለት ሆነ እነሱ የሚሰናከሉት ለቃሉ ስለማይታዘዙ ነው እነዚህ ሰዎች የሚጠብቃቸው ነገር ይኸው ነው9 እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእሱን ድንቅ ባሕርያት በየቦታው እንድታውጁ የተመረጠ ዘር ንጉሣዊ ካህናት ቅዱስ ብሔር ልዩ ንብረት እንዲሆን የተለየ ሕዝብ ናችሁ10 እናንተ በአንድ ወቅት የአምላክ ሕዝብ አልነበራችሁም አሁን ግን የአምላክ ሕዝብ ናችሁ ቀደም ሲል ምሕረት አልተደረገላችሁም ነበር አሁን ግን ምሕረት አግኝታችኋል11 የተወደዳችሁ ወንድሞች የባዕድ አገር ሰዎችና ጊዜያዊ ነዋሪዎች እንደመሆናችሁ መጠን እናንተን ከሚዋጉት ሥጋዊ ፍላጎቶች ምንጊዜም እንድትርቁ አሳስባችኋለሁ12 ክፉ አድራጊዎች እንደሆናችሁ አድርገው ሲከሷችሁ መልካም ሥራችሁን በዓይናቸው ማየት እንዲችሉ ብሎም አምላክ ለመመርመር በሚመጣበት ቀን እሱን እንዲያከብሩ በዓለም ባሉ ሰዎች መካከል መልካም ምግባር ይኑራችሁ13 ለጌታ ብላችሁ ለሰብዓዊ ሥልጣን ሁሉ ተገዙ የበላይ ስለሆነ ለንጉሥ ተገዙ14 ደግሞም ክፉ አድራጊዎችን ለመቅጣት መልካም የሚያደርጉትን ግን ለማመስገን በእሱ የተላኩ ስለሆኑ ለገዢዎች ተገዙ15 የአምላክ ፈቃድ መልካም ነገር በማድረግ ከንቱ ንግግር የሚናገሩትን ምክንያታዊ ያልሆኑ ሰዎች አፍ ዝም እንድታሰኙ ነውና16 እንደ ነፃ ሰዎች ኑሩ ነፃነታችሁን እንደ አምላክ ባሪያዎች ሆናችሁ ተጠቀሙበት እንጂ ለክፋት መሸፈኛ አታድርጉት17 ሁሉንም ዓይነት ሰው አክብሩ ለመላው የወንድማማች ማኅበር ፍቅር ይኑራችሁ አምላክን ፍሩ ንጉሥን አክብሩ18 አገልጋዮች ጥሩና ምክንያታዊ ለሆኑት ብቻ ሳይሆን በቀላሉ ለማይደሰቱ ጌቶቻቸውም እንኳ ተገቢ ፍርሃት በማሳየት ይገዙ19 አንድ ሰው በአምላክ ፊት ንጹሕ ሕሊና እንዲኖረው ሲል መከራን ችሎ ቢያሳልፍና ግፍ ቢደርስበት ይህ ደስ የሚያሰኝ ነውና20 ኃጢአት በመሥራታችሁ የሚደርስባችሁን ዱላ ብትቋቋሙ ምን ጥቅም አለው? መልካም ነገር በማድረጋችሁ መከራ ሲደርስባችሁ ችላችሁ ብታሳልፉ ግን ይህ አምላክ ደስ የሚሰኝበት ነገር ነው21 ደግሞም የተጠራችሁት በዚህ ጎዳና እንድትሄዱ ነው ምክንያቱም ክርስቶስም እንኳ የእሱን ፈለግ በጥብቅ እንድትከተሉ አርዓያ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራ ተቀብሏል22 እሱ ምንም ኃጢአት አልሠራም በአንደበቱም የማታለያ ቃል አልተገኘም23 ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራ ሲደርስበት አልዛተም ከዚህ ይልቅ በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን በአደራ ሰጠ24 ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እሱ ራሱ በገዛ አካሉ ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ ደግሞም በእሱ ቁስል እናንተ ተፈወሳችሁ25 እናንተ እንደባዘኑ በጎች ነበራችሁና አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል
3 በተመሳሳይም እናንተ ሚስቶች ለቃሉ የማይታዘዙ ባሎች ካሉ ያለቃል በሚስቶቻቸው ምግባር እንዲማረኩ ለባሎቻችሁ ተገዙ2 ሊማረኩ የሚችሉትም ንጹሕ ምግባራችሁንና የምታሳዩትን ጥልቅ አክብሮት ሲመለከቱ ነው3 ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በማጌጥ ይኸውም ሹሩባ በመሠራት የወርቅ ጌጣጌጦች በማድረግ ወይም ያማረ ልብስ በመልበስ አይሁን4 ከዚህ ይልቅ ውበታችሁ የማይጠፋውን ጌጥ ይኸውም በአምላክ ፊት ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን የሰከነና ገር መንፈስ የተላበሰ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁን5 ተስፋቸውን በአምላክ ላይ የጣሉ በቀድሞ ጊዜ የነበሩ ቅዱሳን ሴቶች ራሳቸውን ለባሎቻቸው በማስገዛት በዚህ ዓይነት ሁኔታ ራሳቸውን ያስውቡ ነበርና6 ሣራም አብርሃምን ጌታዬ እያለች በመጥራት ትታዘዘው ነበር እናንተም መልካም ማድረጋችሁን ከቀጠላችሁና በፍርሃት ካልተሸነፋችሁ ልጆቿ ናችሁ7 በተመሳሳይም እናንተ ባሎች ከእነሱ ጋር በእውቀት አብራችሁ ኑሩ እነሱም ከእናንተ ጋር የሕይወትን ጸጋ አብረው ስለሚወርሱ ጸሎታችሁ እንዳይታገድ ከእናንተ ይበልጥ እንደ ተሰባሪ ዕቃ የሆኑትን ሴቶችን አክብሯቸው8 በመጨረሻም ሁላችሁም የአስተሳሰብ አንድነት ይኑራችሁ የሌላውን ስሜት የምትረዱ ሁኑ የወንድማማች መዋደድ ይኑራችሁ ከአንጀት የምትራሩ ሁኑ ትሑታን ሁኑ9 ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ አትመልሱ ከዚህ ይልቅ ባርኩ የተጠራችሁት ይህን ጎዳና በመከተል በረከትን እንድትወርሱ ነውና10 ስለዚህ ሕይወትን የሚወድና መልካም ቀኖችን ማየት የሚፈልግ ሰው በምላሱ ክፉ ነገር ከመናገር በከንፈሩም ከማታለል ይቆጠብ11 ክፉ ከሆነ ነገር ይራቅ መልካም የሆነውንም ያድርግ ሰላምን ይፈልግ ይከተለውም12 የይሖዋ ዓይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና ጆሮዎቹም ምልጃቸውን ይሰማሉ የይሖዋ ፊት ግን ክፉ ነገሮችን በሚያደርጉ ላይ ነው13 መልካም ነገር ለማድረግ ቀናተኞች ብትሆኑ ጉዳት የሚያደርስባችሁ ማን ነው?14 ሆኖም ለጽድቅ ስትሉ መከራ ብትቀበሉ ደስተኞች ናችሁ ይሁን እንጂ እነሱ የሚፈሩትን እናንተ አትፍሩ ደግሞም አትሸበሩ15 ነገር ግን ክርስቶስን እንደ ጌታ አድርጋችሁ በልባችሁ ቀድሱት እናንተ ስላላችሁ ተስፋ ምክንያት እንድታቀርቡ ለሚጠይቃችሁ ሰው ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር ዝግጁ ሁኑ ይህን ስታደርጉ ግን በገርነት መንፈስና በጥልቅ አክብሮት ይሁን16 ስለ እናንተ መጥፎ ነገር የሚናገሩ ሰዎች የክርስቶስ ተከታዮች እንደመሆናችሁ መጠን በምታሳዩት መልካም ምግባር የተነሳ ስለ እናንተ በሚናገሩት በማንኛውም መጥፎ ነገር እንዲያፍሩ ጥሩ ሕሊና ይኑራችሁ17 ክፉ ነገር ሠርታችሁ መከራ ከምትቀበሉ ይልቅ የአምላክ ፈቃድ ከሆነ መልካም ነገር ሠርታችሁ መከራ ብትቀበሉ ይሻላልና18 ጻድቅ የሆነው ክርስቶስ እንኳ ለዓመፀኞች ሲል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመሞት ከኃጢአት ነፃ አውጥቷቸዋልና ይህን ያደረገው እናንተን ወደ አምላክ ለመምራት ነው ሥጋ ሆኖ ተገደለ ሆኖም መንፈስ ሆኖ ሕያው ሆነ19 በዚህ ሁኔታ እያለም ሄዶ በእስር ላሉት መናፍስት ሰበከላቸው20 እነዚህ መናፍስት ቀደም ሲል ማለትም በኖኅ ዘመን ጥቂት ሰዎች ይኸውም ስምንት ነፍሳት በውኃው መካከል አልፈው የዳኑበት መርከብ እየተሠራ በነበረበት ጊዜ አምላክ በትዕግሥት እየጠበቀ ሳለ ሳይታዘዙ የቀሩ ናቸው21 አሁንም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆነው ጥምቀት በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አማካኝነት እናንተን እያዳናችሁ ነው ጥምቀት የሰውነትን እድፍ የሚያስወግድ ሳይሆን ጥሩ ሕሊና ለማግኘት ለአምላክ የሚቀርብ ልመና ነው22 ኢየሱስ ወደ ሰማይ የሄደ ሲሆን አሁን በአምላክ ቀኝ ይገኛል እንዲሁም መላእክት ሥልጣናትና ኃይላት እንዲገዙለት ተደርጓል