[ { "question": "ከሚከተሉት መካከል ልዩ የሆነውን ቃል አውጡ፡፡", "a": "ምልሰት", "b": "ሴራ", "c": "ታሪክ", "d": "መቼት", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከሚከተሉት መካከል በውይይት ወቅት የማይፈለግ ድርጊት የቱነው?", "a": "ሃሳብ በሚሰጥበት ጊዜ ሁሉ በጭብጨባ ማድነቅ", "b": "የተለየ ሃሳብን በውይይት አስደግፎ ማቅረብ", "c": "ውይይቱን በበቂ ማስረጃ ማጠናከር ", "d": "የተወያይን ሃሳብ ማክበር ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ሾፌሩ በወያላውና በተሳፋሪው መካከል ላለው ያለመግባባት ደንታ ሳይኖረው የማሽከርከር ስራውን ተያይዞታል፡፡\nለተሰመረበት ቃል ተመሳሳይ የሚሆነው የቱ ነው?", "a": "ግድ", "b": "ግምት", "c": "ተሳትፎ", "d": "ክብር", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "አስቴር ስራ ስትቀጠር የጠለፋ ዋስ እንድታቀርብ ተጠየቀች፡፡የተሰመረበት ፈሊጥ ፍች የትኛው ነው?", "a": "ተያዥ", "b": "ጓደኛ", "c": "አለኝታ", "d": "ጠበቃ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከሚከተሉት መካከል አንዱ የልብወለድን ጽሁፍ ባህሪያት አይወክልም፡፡", "a": "ሙሉ ለሙሉ ከገሃዱ ዓለም የወጣ ነው፡፡", "b": "ማህረሰቡን ሊተች ይችላል፡፡", "c": "የሚጻፈው በጊዜና በቦታ ተወስኖ ነው፡፡", "d": "የደራሲው የምዕናብ ውጤት ነው፡፡", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "በበጋ እንዳይዘራ ጸሃይ እየፈራ ፣\nበሐምሌ እንዳይዘራ ዝናብ እየፈራ፣\nልጁ ዳቦ ቢለው በጅብ አስፈራራ ፡፡ የሚለው ቃላዊ ግጥም ምንን ይገልጻል ?", "a": "ፍቅርን", "b": "ስንፍናን", "c": "ጥላቻን", "d": "ሙገሳን", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "አንድ ጸኃፊ የአንድን ሃሳብ እውነትነት ወይም ሐሰትነት በማስረጃ በማስደገፍ ለማሳመን በመጣር የሚጽፍ ከሆነ የድርሰቱ ዓይነት ምን ይባላል?", "a": "አመዛዛኝ ድርሰት", "b": "ተራኪ ድርሰት", "c": "ስዕላዊ ድርሰት ", "d": "ገላጭ ድርሰት", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "በአንድ ተውኔት የተሳሉትን ገጸ ባህሪት በመወከል መድረክ ላይ የሚተውኑ --------------- ይባላሉ፡፡", "a": "ተዋንያን", "b": "ገጸባህሪያት", "c": "መሪተውኔት", "d": "መሪ ተዋናይ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "የልጅቷን ጥሮ ግሮ መኖር የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡ ለተሰመረበት ቃል በፍቺ የሚመሳሰለው የቱ ነው፡፡", "a": "ለፍቶ", "b": "አታሎ", "c": "ተንደላቆ", "d": "ዘንጦ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "‹‹በተንኮል ጨንብሶ›› ማለት ምን ማለት ነው ?", "a": "ውስጡን በተንኮል ሞልቶ", "b": "አይኑን አጨንቁሮ", "c": "ራሱን አሞግሶ", "d": "ራሱን ጎድቶ", "answerKey": "a", "context": "ግጥም:\n\nየሞተው ወዳጄ እኔ የማልናፍቀው፣\nያነሳኛል አሉ ሲጨንቀው ሲጠበው፣\nመቆያው ማደሪያው ከቤቴ ከደጄ\nምንድን ይሻ ይሆን ትልቁ ወዳጄ?\nታዲያ ምን ይሉታል እንዲህ ያለውን\nከመቃብር በታች ነፍስ የዘራውን፡፡\nምናልባት ሲቀበር ዐፈር አልባሾቹ፣\nኮረትና ድንጋይ አልጫኑት ከታቹ፡፡\nነፍስ እንዳለው ፍጡር እንዳልተቀበረ፣\nምነዋ ወዳጄ ብዙ ቀባጠረ?\nመኖርም መሞትም አንዴ ጥርስን ነክሶ፣\nወይ በምግባር ከብሮ ወይ በምግባር ረክሶ፣\nእንጅ እንደ ወዳጄ መች መቃብር ምሶ፣\nእንጅ እንደ ወዳጄ መች ለራስ አልቅሶ፣\nየቁም ሞትን ሙቶ በተንኮል ጨንብሶ፣\nካልሆነ በስተቀር የ‹‹ደንቆሮ››ለቅሶ፣\nመልሶ መልሶ መልሶ መላልሶ፡፡", "grade": 10, "preamble": "ቀጥሎ የቀረበውን ግጥም መሰረት አድርጋችሁ ለሚከተለው ጥያቄ ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ፡፡", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከሚከተሉት መካከል አንዱ የስነጽሁፍ ጥበባዊ ብቃት መመዘኛ አይደለም፡፡", "a": "በጽሁፍ መስፈሩ", "b": "ማራኪና ሳቢ በሆነ መንገድ መቅረቡ", "c": "በአገላለጹ አምሮ መቅረቡ", "d": "የሰውን ልጅ ሕይዎት ማሳየቱ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ማንኛውም ቋንቋ ምሉዕ ነው ሲባል ምን ማለት ነው?", "a": "የተናጋሪውን ማህበረሰብ ባህል መግለጽ ይችላል ማለት ነው፡፡", "b": "ሙሉ በሙሉ ራሱን የቻለ ነው ማለት ነው፡፡", "c": "ከሌሎች ቋንቋ ቃላት በመዋስ ጉድለቱን ይሞላል ማለት ነው፡፡", "d": "የሌላን ቋንቋ ቃል ይተረጉማል ማለት ነው፡፡", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከሚከተሉት መካከል ህቡዕ ለሚለው ቃል ሊመሳሳለወው የማይችል የትኛው ነው?", "a": "ገሃድ", "b": "ድብቅ", "c": "ስውር", "d": "ሚስጢራዊ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "… ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ተወልዶ ውስጡ ሲገባ በእሱ መኖር አለበት ፡፡ በእሱ የተባለው ምንድን ነው?", "a": "የልማድና የጽህፈት ህጉ", "b": "እያንዳንዱ ሰው", "c": "ሐይማኖቱ", "d": "ነጻነቱ", "answerKey": "a", "context": "ምንባብ:\nሰው በተፈጥሮው የረሃብና የጥም ፣የበቀልና የመሳሰለው ፍልጎቱ ሁሉ እንዲፈጸምለት ይፈልጋል፤ነገርግን ማህበሩ እያንዳንዱ ሰው የተፈጥሮ ፍላጎቱን ለመፈጸም ሲል ሌሎቹን ሰዎች እንዳይጎዳ የሚወስንበት የጽህፈትና የልማድ ሕግ ሠራ፡፡ስለዚህ የተፈጥሮ ፍልጎቱን ለመፈጸም የማህበበሩን የጽህፈትና የልማድ ሕግ የተላለፈ ነውረኛ ተብሎ ይፈረድበታል፡፡\nአንድ ሰው ከሌላው የሚያስቆጣ ነገር ቢደርስበትና ለቁጣው ምክንያት የሆነውን ሰው ለማጥፋት ቢወድ፣ በማህበሩ ህግ ቅጣት እንደሚያስከትል ስለሚያውቅ ቁጣውን ለማብረድ ፣ሌላ የሚበቀልበት አማራጭ መንገድ መመፈለግ አለበት፡፡ስለዚህ የሰው ሰውነት የነጻነትና የጭቆና ውጤት ነው ማለት ይቻላል፡፡ይህ ነጻነትና ጭቆና ማህበሩ በረጅም ዘመን ዕድሜው ከልማዱ፣ከወጉ፣ከህጉ አዋህዶና አስማምቶ የሰራው ነው፡፡ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ተወልዶ ውስጡ ሲገባ በሱ ተመርቶ መኖር አለበት፤ከማህበሩ ስርዓት አንድ ነቁጥ እንኳን አይተላለፍም፡፡\nበጠቅላላው የማህበር ትምህርት እያንዳንዱ ሰው ሲወለድ ይዟቸው የሚወለደውን ጠቃሚ ውጥኖች ነጻነት በመስጠትና በልዩልዩ መንገድ በመርዳት ጎጂዎቹነንም እንዲሁ በልዩልዩ መንገድ በመጠቆምና በማረም ሰውዬውን ማህበራዊ እንዲሆን ያደርገዋል", "grade": 10, "preamble": "ከዚህ በታች የቀረበውን ምንባብ መሰረት አድርጋችሁ ለሚከተለው ጥያቄ ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ወንድማማቾቹ በመፈቃቀር የኖሩ ቢሆኑም ፣ልሎች ካፈሩ በኋላ ግን ደመኛ ሆነዋል፡፡ የተሰመረበት ቃል ፍች ምንድን ነው?", "a": "ሀናለ", "b": "ወዳጅ", "c": "ባላንጣ", "d": "ባላንጋራ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "የቸኮለ አፍሶ ለቀመ፡፡ ለሚለው አባባል የማይመሳሳለው የቱ ነው?", "a": "ባፍ ይጠፉ በለፈለፉ፡፡", "b": "ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል፡፡", "c": "የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል፡፡", "d": "አለባብሰው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ፡፡", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "የግጥሙ መልዕክት ምንድን ነው?", "a": "ሰው በጥሩ ስራው ይታወሳል፤ በመጥፎ ስራው ይረሳል፡፡", "b": "ክፉ ስራ ከሰሩ በኋላ ጸጸት አስፈላጊ አለመሆኑን፣", "c": "ችግርን በጽናት መጋፈጥን፣", "d": "ችግርን እንደችግርነቱ መጋፈጥን፡፡", "answerKey": "a", "context": "ግጥም:\n\nየሞተው ወዳጄ እኔ የማልናፍቀው፣\nያነሳኛል አሉ ሲጨንቀው ሲጠበው፣\nመቆያው ማደሪያው ከቤቴ ከደጄ\nምንድን ይሻ ይሆን ትልቁ ወዳጄ?\nታዲያ ምን ይሉታል እንዲህ ያለውን\nከመቃብር በታች ነፍስ የዘራውን፡፡\nምናልባት ሲቀበር ዐፈር አልባሾቹ፣\nኮረትና ድንጋይ አልጫኑት ከታቹ፡፡\nነፍስ እንዳለው ፍጡር እንዳልተቀበረ፣\nምነዋ ወዳጄ ብዙ ቀባጠረ?\nመኖርም መሞትም አንዴ ጥርስን ነክሶ፣\nወይ በምግባር ከብሮ ወይ በምግባር ረክሶ፣\nእንጅ እንደ ወዳጄ መች መቃብር ምሶ፣\nእንጅ እንደ ወዳጄ መች ለራስ አልቅሶ፣\nየቁም ሞትን ሙቶ በተንኮል ጨንብሶ፣\nካልሆነ በስተቀር የ‹‹ደንቆሮ››ለቅሶ፣\nመልሶ መልሶ መልሶ መላልሶ፡፡", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "በቅኔ ውስጥ ወርቅ የምንለው -----------------------ማለት ነው?", "a": "ሚስጥሩን", "b": "በሰም የተሸፈነውን", "c": "ገበያ ሰደዷትዋና ሃሳቡን", "d": "ፈርጡን", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ፊደል ‹‹ሀ ›› ___ ሞክሼዎች አላት፡፡", "a": "ሶስት", "b": "አንድ", "c": "አስር", "d": "", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 1, "preamble": "", "category": "Grammar" }, { "question": "አንድ ሰው የበቀል እርምጃ እንዳይወስድ የሚያግደው ምንድን ነው?", "a": "የማህበሩ ስርዓት", "b": "ህሊናው", "c": "እምነቱ", "d": "ቤተሰቡ", "answerKey": "a", "context": "ምንባብ:\nሰው በተፈጥሮው የረሃብና የጥም ፣የበቀልና የመሳሰለው ፍልጎቱ ሁሉ እንዲፈጸምለት ይፈልጋል፤ነገርግን ማህበሩ እያንዳንዱ ሰው የተፈጥሮ ፍላጎቱን ለመፈጸም ሲል ሌሎቹን ሰዎች እንዳይጎዳ የሚወስንበት የጽህፈትና የልማድ ሕግ ሠራ፡፡ስለዚህ የተፈጥሮ ፍልጎቱን ለመፈጸም የማህበበሩን የጽህፈትና የልማድ ሕግ የተላለፈ ነውረኛ ተብሎ ይፈረድበታል፡፡\nአንድ ሰው ከሌላው የሚያስቆጣ ነገር ቢደርስበትና ለቁጣው ምክንያት የሆነውን ሰው ለማጥፋት ቢወድ፣ በማህበሩ ህግ ቅጣት እንደሚያስከትል ስለሚያውቅ ቁጣውን ለማብረድ ፣ሌላ የሚበቀልበት አማራጭ መንገድ መመፈለግ አለበት፡፡ስለዚህ የሰው ሰውነት የነጻነትና የጭቆና ውጤት ነው ማለት ይቻላል፡፡ይህ ነጻነትና ጭቆና ማህበሩ በረጅም ዘመን ዕድሜው ከልማዱ፣ከወጉ፣ከህጉ አዋህዶና አስማምቶ የሰራው ነው፡፡ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ተወልዶ ውስጡ ሲገባ በሱ ተመርቶ መኖር አለበት፤ከማህበሩ ስርዓት አንድ ነቁጥ እንኳን አይተላለፍም፡፡\nበጠቅላላው የማህበር ትምህርት እያንዳንዱ ሰው ሲወለድ ይዟቸው የሚወለደውን ጠቃሚ ውጥኖች ነጻነት በመስጠትና በልዩልዩ መንገድ በመርዳት ጎጂዎቹነንም እንዲሁ በልዩልዩ መንገድ በመጠቆምና በማረም ሰውዬውን ማህበራዊ እንዲሆን ያደርገዋል", "grade": 10, "preamble": "ከዚህ በታች የቀረበውን ምንባብ መሰረት አድርጋችሁ ለሚከተለው ጥያቄ ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "አንድን ግለሰብ አሁን ባለበትም ሆነ ወደፊት ለሚኖርበት ማህበረሰብ ጠቃሚ እንዲሆን ማድረጉ የማን ኃላፊነት ነው?", "a": "የማበረሰቡ", "b": "የተፈጥሮ ፍላጎቱ", "c": "የግለሰቦች", "d": "ነጻነቱ", "answerKey": "a", "context": "ምንባብ:\nሰው በተፈጥሮው የረሃብና የጥም ፣የበቀልና የመሳሰለው ፍልጎቱ ሁሉ እንዲፈጸምለት ይፈልጋል፤ነገርግን ማህበሩ እያንዳንዱ ሰው የተፈጥሮ ፍላጎቱን ለመፈጸም ሲል ሌሎቹን ሰዎች እንዳይጎዳ የሚወስንበት የጽህፈትና የልማድ ሕግ ሠራ፡፡ስለዚህ የተፈጥሮ ፍልጎቱን ለመፈጸም የማህበበሩን የጽህፈትና የልማድ ሕግ የተላለፈ ነውረኛ ተብሎ ይፈረድበታል፡፡\nአንድ ሰው ከሌላው የሚያስቆጣ ነገር ቢደርስበትና ለቁጣው ምክንያት የሆነውን ሰው ለማጥፋት ቢወድ፣ በማህበሩ ህግ ቅጣት እንደሚያስከትል ስለሚያውቅ ቁጣውን ለማብረድ ፣ሌላ የሚበቀልበት አማራጭ መንገድ መመፈለግ አለበት፡፡ስለዚህ የሰው ሰውነት የነጻነትና የጭቆና ውጤት ነው ማለት ይቻላል፡፡ይህ ነጻነትና ጭቆና ማህበሩ በረጅም ዘመን ዕድሜው ከልማዱ፣ከወጉ፣ከህጉ አዋህዶና አስማምቶ የሰራው ነው፡፡ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ተወልዶ ውስጡ ሲገባ በሱ ተመርቶ መኖር አለበት፤ከማህበሩ ስርዓት አንድ ነቁጥ እንኳን አይተላለፍም፡፡\nበጠቅላላው የማህበር ትምህርት እያንዳንዱ ሰው ሲወለድ ይዟቸው የሚወለደውን ጠቃሚ ውጥኖች ነጻነት በመስጠትና በልዩልዩ መንገድ በመርዳት ጎጂዎቹነንም እንዲሁ በልዩልዩ መንገድ በመጠቆምና በማረም ሰውዬውን ማህበራዊ እንዲሆን ያደርገዋል", "grade": 10, "preamble": "ከዚህ በታች የቀረበውን ምንባብ መሰረት አድርጋችሁ ለሚከተለው ጥያቄ ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ነጻነትና ጭቆና የ-----------------ዘመን ውጤት ናቸው፡፡", "a": "የረጅም", "b": "የአጭር", "c": "የአንድ", "d": "የመቶ", "answerKey": "a", "context": "ምንባብ:\nሰው በተፈጥሮው የረሃብና የጥም ፣የበቀልና የመሳሰለው ፍልጎቱ ሁሉ እንዲፈጸምለት ይፈልጋል፤ነገርግን ማህበሩ እያንዳንዱ ሰው የተፈጥሮ ፍላጎቱን ለመፈጸም ሲል ሌሎቹን ሰዎች እንዳይጎዳ የሚወስንበት የጽህፈትና የልማድ ሕግ ሠራ፡፡ስለዚህ የተፈጥሮ ፍልጎቱን ለመፈጸም የማህበበሩን የጽህፈትና የልማድ ሕግ የተላለፈ ነውረኛ ተብሎ ይፈረድበታል፡፡\nአንድ ሰው ከሌላው የሚያስቆጣ ነገር ቢደርስበትና ለቁጣው ምክንያት የሆነውን ሰው ለማጥፋት ቢወድ፣ በማህበሩ ህግ ቅጣት እንደሚያስከትል ስለሚያውቅ ቁጣውን ለማብረድ ፣ሌላ የሚበቀልበት አማራጭ መንገድ መመፈለግ አለበት፡፡ስለዚህ የሰው ሰውነት የነጻነትና የጭቆና ውጤት ነው ማለት ይቻላል፡፡ይህ ነጻነትና ጭቆና ማህበሩ በረጅም ዘመን ዕድሜው ከልማዱ፣ከወጉ፣ከህጉ አዋህዶና አስማምቶ የሰራው ነው፡፡ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ተወልዶ ውስጡ ሲገባ በሱ ተመርቶ መኖር አለበት፤ከማህበሩ ስርዓት አንድ ነቁጥ እንኳን አይተላለፍም፡፡\nበጠቅላላው የማህበር ትምህርት እያንዳንዱ ሰው ሲወለድ ይዟቸው የሚወለደውን ጠቃሚ ውጥኖች ነጻነት በመስጠትና በልዩልዩ መንገድ በመርዳት ጎጂዎቹነንም እንዲሁ በልዩልዩ መንገድ በመጠቆምና በማረም ሰውዬውን ማህበራዊ እንዲሆን ያደርገዋል", "grade": 10, "preamble": "ከዚህ በታች የቀረበውን ምንባብ መሰረት አድርጋችሁ ለሚከተለው ጥያቄ ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ሰዎች እቅድ አውጥተው ፣ጊዜና ቦታን በመወሰን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሐሳብ የሚለዋወጡበትና ከጋራ መግባባት ላይ የሚደርሱበት ክንውን ምንድን ነው?", "a": "ውይይት", "b": "ክርክር", "c": "ጭውውት", "d": "ትያትር", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "የሰንጎ መገን ቤት የሚባለው የግጥም ቤት በሐረግ ስንት ስንኞች ያሉት ነው፡፡", "a": "አምስት", "b": "ሶስት", "c": "ስድስት", "d": "አራት", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከሚከተሉት መካከል በውይይት አቀራረብ ጊዜ የሚከናወን ተግባር የሆነው የቱ ነው?", "a": "የርዕሱን ዓላማ ባጭሩ ማስቀመጥ", "b": "ስለ ርዕሱ ዋናዋና ሃሳቦችን መያዝ ", "c": "ርዕሱን በሚገባ መረዳት", "d": "የርዕሱን ወቅታዊነት መገምገም", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "እናንተ የአባቶቻችሁ ልጆች የአያቶቻችሁ ቅድመአያቶች ናችሁ፡፡ ተብሎ ቢገለጽ በየትኛው ዘይቤ የቀረበ ነው?", "a": "በአያዎ", "b": "በእንቶኔ", "c": "በሰውኛ", "d": "በምጸት", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "አቶ ተኮላ ስለ ወንድማቸው ድንገት በሰሙት ወሬ አዝነዋል ፡፡ ብንል የተሰመረበትን ቃል ሊተካ የሚችለው ከሚከተሉት የትኛው ነው?", "a": "ልባቸው ተነክቷል", "b": "ድርቅ ብለዋል", "c": "ቅቤ ጠጥተዋል", "d": "እፎይታ አግኝተዋል፡፡", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከሚከተሉት መካከል የስነቃል ዘርፍ ያልሆነው የቱ ነው?", "a": "የልብወለድ መጻህፍት", "b": "አፈታሪክ", "c": "ሐተታ ተፈጥሮ", "d": "ቃላዊ ግጥሞች", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ውስን መቼትና ጥቂት ገጸባህሪያት የሚታዩበት የስነጽሁፍ ዘርፍ ምን ይባላል ?", "a": "ድራማ", "b": "ተውኔት", "c": "አጭር ልብወለድ", "d": "ረጅም ልብወለድ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከክሂሎች መካከል በተፈጥሮ የምናገኛቸው ክሂሎች የትኞቹ ናቸው?", "a": "ማዳመጥና መናገር", "b": "መናገርና መጻፍ", "c": "መጻፍና ማንበብ", "d": "ማንበብናማዳመጥ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ሞክሼ ፊደላት ___ ቅርፅ አላቸው፡፡", "a": "ተመሳሳይ", "b": "የተለያየ", "c": "ሁለቱም መልስ ይሆናሉ", "d": "", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 1, "preamble": "", "category": "Grammar" }, { "question": "በዓረፍተነገሮች ውስጥ የቃላቶች ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ በሚለው ዓረፍተነገር ውስጥ ስህተት እንዲኖር ያደረገው ቃል የትኛው ነው;", "a": "ቃላቶች ", "b": "ከፍተኛ ", "c": "ሚና ", "d": "ዓረፍተነገረ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "… ከማህበሩ ስርዓት አንድ ነቁጥ እንኳን አይተላለፍም፡፡ በሚለው ሃሳብ ላይ ለተሰመረበት ቃል አቻ የሚሆነው ቃል ከሚከተሉት መካከል የትኛው ነው?", "a": "ነጥብ", "b": "ስርዓት", "c": "ትዕዛዝ", "d": "ምልክት", "answerKey": "a", "context": "ምንባብ:\nሰው በተፈጥሮው የረሃብና የጥም ፣የበቀልና የመሳሰለው ፍልጎቱ ሁሉ እንዲፈጸምለት ይፈልጋል፤ነገርግን ማህበሩ እያንዳንዱ ሰው የተፈጥሮ ፍላጎቱን ለመፈጸም ሲል ሌሎቹን ሰዎች እንዳይጎዳ የሚወስንበት የጽህፈትና የልማድ ሕግ ሠራ፡፡ስለዚህ የተፈጥሮ ፍልጎቱን ለመፈጸም የማህበበሩን የጽህፈትና የልማድ ሕግ የተላለፈ ነውረኛ ተብሎ ይፈረድበታል፡፡\nአንድ ሰው ከሌላው የሚያስቆጣ ነገር ቢደርስበትና ለቁጣው ምክንያት የሆነውን ሰው ለማጥፋት ቢወድ፣ በማህበሩ ህግ ቅጣት እንደሚያስከትል ስለሚያውቅ ቁጣውን ለማብረድ ፣ሌላ የሚበቀልበት አማራጭ መንገድ መመፈለግ አለበት፡፡ስለዚህ የሰው ሰውነት የነጻነትና የጭቆና ውጤት ነው ማለት ይቻላል፡፡ይህ ነጻነትና ጭቆና ማህበሩ በረጅም ዘመን ዕድሜው ከልማዱ፣ከወጉ፣ከህጉ አዋህዶና አስማምቶ የሰራው ነው፡፡ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ተወልዶ ውስጡ ሲገባ በሱ ተመርቶ መኖር አለበት፤ከማህበሩ ስርዓት አንድ ነቁጥ እንኳን አይተላለፍም፡፡\nበጠቅላላው የማህበር ትምህርት እያንዳንዱ ሰው ሲወለድ ይዟቸው የሚወለደውን ጠቃሚ ውጥኖች ነጻነት በመስጠትና በልዩልዩ መንገድ በመርዳት ጎጂዎቹነንም እንዲሁ በልዩልዩ መንገድ በመጠቆምና በማረም ሰውዬውን ማህበራዊ እንዲሆን ያደርገዋል", "grade": 10, "preamble": "ከዚህ በታች የቀረበውን ምንባብ መሰረት አድርጋችሁ ለሚከተለው ጥያቄ ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ሰው በተፈጥሮው ---------------------", "a": "ግላዊ ነው ፡፡", "b": "ማህበራዊ ነው", "c": "ማህበራዊነትን ይዞ ይወለዳል፡፡", "d": "በቀለኛ ነው፡፡", "answerKey": "a", "context": "ምንባብ:\nሰው በተፈጥሮው የረሃብና የጥም ፣የበቀልና የመሳሰለው ፍልጎቱ ሁሉ እንዲፈጸምለት ይፈልጋል፤ነገርግን ማህበሩ እያንዳንዱ ሰው የተፈጥሮ ፍላጎቱን ለመፈጸም ሲል ሌሎቹን ሰዎች እንዳይጎዳ የሚወስንበት የጽህፈትና የልማድ ሕግ ሠራ፡፡ስለዚህ የተፈጥሮ ፍልጎቱን ለመፈጸም የማህበበሩን የጽህፈትና የልማድ ሕግ የተላለፈ ነውረኛ ተብሎ ይፈረድበታል፡፡\nአንድ ሰው ከሌላው የሚያስቆጣ ነገር ቢደርስበትና ለቁጣው ምክንያት የሆነውን ሰው ለማጥፋት ቢወድ፣ በማህበሩ ህግ ቅጣት እንደሚያስከትል ስለሚያውቅ ቁጣውን ለማብረድ ፣ሌላ የሚበቀልበት አማራጭ መንገድ መመፈለግ አለበት፡፡ስለዚህ የሰው ሰውነት የነጻነትና የጭቆና ውጤት ነው ማለት ይቻላል፡፡ይህ ነጻነትና ጭቆና ማህበሩ በረጅም ዘመን ዕድሜው ከልማዱ፣ከወጉ፣ከህጉ አዋህዶና አስማምቶ የሰራው ነው፡፡ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ተወልዶ ውስጡ ሲገባ በሱ ተመርቶ መኖር አለበት፤ከማህበሩ ስርዓት አንድ ነቁጥ እንኳን አይተላለፍም፡፡\nበጠቅላላው የማህበር ትምህርት እያንዳንዱ ሰው ሲወለድ ይዟቸው የሚወለደውን ጠቃሚ ውጥኖች ነጻነት በመስጠትና በልዩልዩ መንገድ በመርዳት ጎጂዎቹነንም እንዲሁ በልዩልዩ መንገድ በመጠቆምና በማረም ሰውዬውን ማህበራዊ እንዲሆን ያደርገዋል", "grade": 10, "preamble": "ከዚህ በታች የቀረበውን ምንባብ መሰረት አድርጋችሁ ለሚከተለው ጥያቄ ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከሚከተሉት መካከል ‹‹ትዳር ›› የሚለው ቃል በእማሬያዊ ፍችው የገባው በየትኛው ዓረፍተነገር ነው፡፡", "a": "ትዳር ይዛለች፡፡", "b": "የሞቀ ትዳር አለኝ፡፡", "c": "ትዳሩ ፈርሷል፡፡", "d": "ትዳሩ ተናግቷል፡፡", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ሁሉአማረሽን----------------- በባዶ ቦታው ሊገባ የሚችለው አባባል ከሚከተሉት የትኛው ነው?", "a": "ገበያ አታውጧት", "b": "ገበያ ላኳት", "c": "", "d": "", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከሚከተሉት መካከል የግጥም ባህርይ ያልሆነው የትኛው ነው?", "a": "ስድጽሁፋዊነት", "b": "ምዕናባዊነት", "c": "ተጨባጭነት", "d": "ሙዚቃዊነት", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "የሶስተኛን ሰው ንግግር ለመግለጽ የሚገለግል የስርዓተነጥብ ዓይነት ምንድን ነው?", "a": "ትዕምርተ ጥቅስ", "b": "ትዕምርት ጥያቄ", "c": "ትዕምርተ አንክሮ", "d": "ትዕምርተ ስላቅ ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከሚከተሉት መካከል የስራ ደብዳቤ ውስጥ ብቻ የሚገኝ የቱ ነው?", "a": "ቁጥር", "b": "ቀን", "c": "መግቢያ", "d": "ሐተታ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከአጋም የተጠጋች ቁልቋል ዘላለም--------------------፡፡", "a": "ስታነባ ትኖራለች", "b": "ስትቀጥፍ ትኖራለች፡፡", "c": "ስታብብ ትኖራለች", "d": "አጋም አጋም ትሸታለች፡፡", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከኳስ ጨዋታ ውስጥ ጨዋታው ሲደራ፣ \nአይቀርም መድረሱ ፈጽሞ ግፍተራ፡፡ የዚህ ቅኔ ወርቅ የቱ ነው?", "a": "ግፍተራ የሚባል ቦታ መጠራቱ አይቀርም፡፡ ", "b": "መገፋፋት አይቀርም፡፡", "c": "መገፋፋት በፍጹም መኖር የለበትም፡፡", "d": "ግፍ የሰራ ሰው ተራው መድረሱ አይቀርም፡", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "መልዕክትን ለመቀበያነት የምንጠቀምባቸው የክሂል ዓይነቶች የትኞች ናቸው?", "a": "ማዳመጥናማንበብ", "b": "ማዳመጥና መናገር", "c": "መጻፍና ማንበብ", "d": "ማንበብናመጻፍ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከሚከተሉት መካከል ምዕላድ የሆነው የቱ ነው?", "a": "ሰው", "b": "ሰውነት", "c": "ሰዎች", "d": "ሰዋዊ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ልጁ እንደእስስት ባህሪው ይቀያየራል፡፡ በሚለው አገላለፅ ውስጥ ለልጁና ለእስስት የጋራ የሆነው ባህሪይ የቱ ነው?", "a": "ተቀያያሪነት", "b": "እስስትነት", "c": "ልጅነት", "d": "ተንኮለኝነት", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከሚከተሉት ዐረፍተነገሮች አንዱ ትክክለኛ ሃሳብ አልያዘም፡፡", "a": "እንስሳት ቋንቋ ስለሌላቸው በደመነፍስ አይግባቡም ፡፡", "b": "ቋንቋ ለሰው ልጆች ብቻ የተሰጠ ጸጋ ነው፡፡", "c": "ንግግር በድምጸ አልባ እንቅስቃሴ ይደገፋል፡፡", "d": "የቋንቋ ክሂሎች አራት ናቸው፡፡", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ለተሾመ ይመሰከርለታል፤ለተሻረ ይመሰከርበታል ብንል የተሰመረባቸው ቃላት ምንን ይገልጻሉ፡፡", "a": "ተሿሚው አካል ሲጠቀም ፣ከሹመት የወረደው ይጎዳል ማለት ነው፡፡", "b": "ተሿሚው አካል ተጠቃሚ ፣ከሹመት የወረደው ጥቅም ፈላጊ መሆናቸውን ይገልጻል፡፡ ", "c": "ተሿሚው አካል ተጠቃሚ ፣ከሹመት የወረደው ጠቃሚ ነው ማለት ነው፡፡", "d": "ተሿሚው አካል ጠቃሚ ፣ ከሹመት የወረደው ተጠቃሚ ነው ማለት ነው፡፡", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "የጽሁፉ ርዕስ ምን ሊሆን ይችላል፡፡", "a": "ተፈጥሯዊ ፍላጎትና ስነስርዓት", "b": "የአስተሳሰብ ለውጥ", "c": "የተፈጥሮ ስጦታ", "d": "", "answerKey": "a", "context": "ምንባብ:\nሰው በተፈጥሮው የረሃብና የጥም ፣የበቀልና የመሳሰለው ፍልጎቱ ሁሉ እንዲፈጸምለት ይፈልጋል፤ነገርግን ማህበሩ እያንዳንዱ ሰው የተፈጥሮ ፍላጎቱን ለመፈጸም ሲል ሌሎቹን ሰዎች እንዳይጎዳ የሚወስንበት የጽህፈትና የልማድ ሕግ ሠራ፡፡ስለዚህ የተፈጥሮ ፍልጎቱን ለመፈጸም የማህበበሩን የጽህፈትና የልማድ ሕግ የተላለፈ ነውረኛ ተብሎ ይፈረድበታል፡፡\nአንድ ሰው ከሌላው የሚያስቆጣ ነገር ቢደርስበትና ለቁጣው ምክንያት የሆነውን ሰው ለማጥፋት ቢወድ፣ በማህበሩ ህግ ቅጣት እንደሚያስከትል ስለሚያውቅ ቁጣውን ለማብረድ ፣ሌላ የሚበቀልበት አማራጭ መንገድ መመፈለግ አለበት፡፡ስለዚህ የሰው ሰውነት የነጻነትና የጭቆና ውጤት ነው ማለት ይቻላል፡፡ይህ ነጻነትና ጭቆና ማህበሩ በረጅም ዘመን ዕድሜው ከልማዱ፣ከወጉ፣ከህጉ አዋህዶና አስማምቶ የሰራው ነው፡፡ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ተወልዶ ውስጡ ሲገባ በሱ ተመርቶ መኖር አለበት፤ከማህበሩ ስርዓት አንድ ነቁጥ እንኳን አይተላለፍም፡፡\nበጠቅላላው የማህበር ትምህርት እያንዳንዱ ሰው ሲወለድ ይዟቸው የሚወለደውን ጠቃሚ ውጥኖች ነጻነት በመስጠትና በልዩልዩ መንገድ በመርዳት ጎጂዎቹነንም እንዲሁ በልዩልዩ መንገድ በመጠቆምና በማረም ሰውዬውን ማህበራዊ እንዲሆን ያደርገዋል", "grade": 10, "preamble": "ከዚህ በታች የቀረበውን ምንባብ መሰረት አድርጋችሁ ለሚከተለው ጥያቄ ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከሚከተሉት መካከል የምክንያትና ውጤት ትስስር የሌለው ሃሳብ የቱ ነው?", "a": "ቋንቋ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋ ተናጋሪ ሲያጣ እሱም አብሮ ይጠፋል፡፡", "b": "በርትቶ የሚያጠና ተማሪ ተገቢውን እውቀት ይቀስማል፡፡", "c": "የሰው ልጅ ቋንቋ ና የእንስሳት አንድነትም ልዩነትም አላቸው፡፡", "d": "ለስኬት ጥረት ወሳኝነት አለው፡፡", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ጭራሽ ሰነፍ የሆነን ሰው መግለፅ ብንፈልግ የትኛውን ፈሊጣዊ አነጋገር መጠቀም እንችላለን?", "a": "እጅ አደር", "b": "እጀ ሰባራ", "c": "እጅ አጠረው", "d": "አጀ አመድ አፋሽ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ጥርሱን ነከሰ ለሚለው ፈሊጥ ተመሳሳይ የሚሆነው የትኛው ነው?", "a": "ዛተ", "b": "ጥርሱን አደማ", "c": "ደፈረ", "d": "ተተናኮለ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ሞክሼ ፊደላት ___ ድምፅ አላቸው፡፡", "a": "ተመሳሳይ", "b": "የተለያየ", "c": "ሁለቱም መልስ ይሆናሉ", "d": "", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 1, "preamble": "", "category": "Grammar" }, { "question": "‹‹ልጅ የጫረው እሳት ለጎረቤት ይተርፋል›› ቢባል ምሳሌያዊ አነጋገሩ የያዘው ትርጉም ከሚከተሉት የትኛው ነው?", "a": "በልጅ የመጣ ጠብ ቶሎ አይበርድም፡፡", "b": "ልጅ ያለ ልጅ ጨመረ፡፡", "c": "የመልካም ልጅ ጎረቤት በብርድ አይጠቃም፡፡", "d": "ታታሪ ልጅ ለጎረቤቱ በረከት ነው፡፡", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ነገረ ውሽልሽል ማለት -------------- ማለት ነው፡፡", "a": "ቁምነገር የሌለበት", "b": "በደንብ የተሰራ ", "c": "ቁምነገረኛ", "d": "መናኛ ስራ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ትምህርትቤት ከገባን በኋላ የምንናገኛቸው የክሂል ዓይነቶች ከሚከተሉት የትኞቹ ናቸው?", "a": "ማንበብና መጻፍ", "b": "መናገርና መጻፍ", "c": "መጻፍና ማዳመጥ", "d": "ማዳመጥና መናገር", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "በማህበሩ ህግ መሰረት ነውረኛ የሚል ስያሜ የሚሰጠው የትኛው ክፍል ነው?", "a": "የማህበሩን ስርዓት የጣሰ ", "b": "የማህበሩን ስርዓት ያስተዳደረ ", "c": "የማህበሩን ስርዓት በእኩል ዐይን ያልተመለከተ", "d": "የማህበሩን ስርዓት ያከበረ", "answerKey": "a", "context": "ምንባብ:\nሰው በተፈጥሮው የረሃብና የጥም ፣የበቀልና የመሳሰለው ፍልጎቱ ሁሉ እንዲፈጸምለት ይፈልጋል፤ነገርግን ማህበሩ እያንዳንዱ ሰው የተፈጥሮ ፍላጎቱን ለመፈጸም ሲል ሌሎቹን ሰዎች እንዳይጎዳ የሚወስንበት የጽህፈትና የልማድ ሕግ ሠራ፡፡ስለዚህ የተፈጥሮ ፍልጎቱን ለመፈጸም የማህበበሩን የጽህፈትና የልማድ ሕግ የተላለፈ ነውረኛ ተብሎ ይፈረድበታል፡፡\nአንድ ሰው ከሌላው የሚያስቆጣ ነገር ቢደርስበትና ለቁጣው ምክንያት የሆነውን ሰው ለማጥፋት ቢወድ፣ በማህበሩ ህግ ቅጣት እንደሚያስከትል ስለሚያውቅ ቁጣውን ለማብረድ ፣ሌላ የሚበቀልበት አማራጭ መንገድ መመፈለግ አለበት፡፡ስለዚህ የሰው ሰውነት የነጻነትና የጭቆና ውጤት ነው ማለት ይቻላል፡፡ይህ ነጻነትና ጭቆና ማህበሩ በረጅም ዘመን ዕድሜው ከልማዱ፣ከወጉ፣ከህጉ አዋህዶና አስማምቶ የሰራው ነው፡፡ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ተወልዶ ውስጡ ሲገባ በሱ ተመርቶ መኖር አለበት፤ከማህበሩ ስርዓት አንድ ነቁጥ እንኳን አይተላለፍም፡፡\nበጠቅላላው የማህበር ትምህርት እያንዳንዱ ሰው ሲወለድ ይዟቸው የሚወለደውን ጠቃሚ ውጥኖች ነጻነት በመስጠትና በልዩልዩ መንገድ በመርዳት ጎጂዎቹነንም እንዲሁ በልዩልዩ መንገድ በመጠቆምና በማረም ሰውዬውን ማህበራዊ እንዲሆን ያደርገዋል", "grade": 10, "preamble": "ከዚህ በታች የቀረበውን ምንባብ መሰረት አድርጋችሁ ለሚከተለው ጥያቄ ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "መጨነቅ መጠበብ ለጠጅ ብቻ ነው፣\nለጠላ መድሐኒት ተወት ማድረግ ነው፡፡ የዚህ ቅኔ ህብረቃል ምን የሚለው ነው?", "a": "መድሐኒት", "b": "ተወት ማድረግ ነው፡፡", "c": "ለጠላ", "d": "ለጠጅ ብቻ ነው፡፡", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "‹‹ካልታረደ አይታይስባቱ ካልተናገረ አይታወቅ ብልሃቱ›› የሚለው ምሳሌያዊ አባባል ምንን ይገልጻል፡፡", "a": "የንግግርን ትልቅነት", "b": "የማዳመጥና የመስማትን", "c": "የማንበብን ትልቅነት", "d": "የመጻፍን አግባብነት", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከተከለከለው ከጨፌ እየዋለች፣\nአልታለብ ብላ ያቺስ ላም እምቢ አለች፡፡የዚህ ቅኔ ወርቅ ከሚከተሉት የትኛው ነው?", "a": "እስላሟ ሃይማኖቷን ጣለች፡፡", "b": "ላሚቱ አልታለብ አለቸ፡፡", "c": "ላሚቷ የሰው ክልል ጣሰች ፡፡", "d": "የተጠየቀችውን እስላሟ ሴት ከለከለች ፡፡", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "የስነቃልን ባለቤት በተመለከተ የትኛው ትክክል ነው?", "a": "የማህበረሰቡ የወል ሃብት ነው፡፡", "b": "ደራሲዎች በጋራ የፈጠሩት ነው፡፡ ", "c": "ታላላቅ አባቶች በስምምነት የፈጠሩት ነው፡፡", "d": "የታሪክ ምሁራን የፈጠሩት ነው፡፡", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "አቶ ደግአረገ ልበሙሉነቴ ጠቀመኝ ቢሉ፣የተሰመረበት ቃልአገባባዊ ፍችው ምንድን ነው?", "a": "ደፋርነቴ", "b": "ሚስጢር ጠባቂነቴ", "c": "ጀግንነቴ", "d": "ትዕግስተኛነቴ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "አሁን ምን ያደርጋል ነገር መለቃቀም፣\nባባቷ ያልሆነ ባያት ምን ልጠቀም፡፡የዚህ ቅኔ ህብረቃል የቱ ነው?", "a": "ባያት", "b": "ምን ልጠቀም", "c": "ባባቷ", "d": "መለቃቀም", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "በአንድ ዓረፍተነገር ውስጥ የዓረፍተነገሩ ባለቤት የሚገኝበት የሐረግ ዓይነት ምን ይባላል;", "a": "ስማዊ ሐረግ", "b": "ቅጽላዊ ሐረግ", "c": "ግሳዊ ሐረግ", "d": "ግሳዊ ሐረግ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ልብ ወለድ በሚጻፍበት ጊዜ ታሪኩ የሚያወራው ስለማን ነው ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ የትኛውን የልብወለድ አላባ ይመለከታል፡፡", "a": "ገጸባህሪያትን", "b": "መቼትን", "c": "አንጻርን", "d": "ታሪክን", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "የቋንቋ ክሂሎች በቅደምተከተል ሲቀመጡ ከሚከተሉት የትኛው ትክክል ነው?", "a": "ማዳመጥ፣መጻፍ፣መናገር፣ማንበብ ", "b": "መናገር ፣ማዳመጥ፣መጻፍ፣ማንበብ", "c": "ማዳመጥ፣መናገር፣ማንበብ፣መጻፍ", "d": "ማዳመጥ፣መጻፍ፣መናገር፣ማንበብ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "‹‹ደንቆሮ›› የሚለው ቃል በጥቅስ ምልክት የተቀመጠበት ምክንያት ምንድን ነው?", "a": "ሟቹ የአዋቂ አጥፊ ስለሆነ", "b": "የሟቹ ንግግር ስለሆነ", "c": "የተራኪው ንግግር ስለሆነ", "d": "አባባል ስለሆነ", "answerKey": "a", "context": "ግጥም:\n\nየሞተው ወዳጄ እኔ የማልናፍቀው፣\nያነሳኛል አሉ ሲጨንቀው ሲጠበው፣\nመቆያው ማደሪያው ከቤቴ ከደጄ\nምንድን ይሻ ይሆን ትልቁ ወዳጄ?\nታዲያ ምን ይሉታል እንዲህ ያለውን\nከመቃብር በታች ነፍስ የዘራውን፡፡\nምናልባት ሲቀበር ዐፈር አልባሾቹ፣\nኮረትና ድንጋይ አልጫኑት ከታቹ፡፡\nነፍስ እንዳለው ፍጡር እንዳልተቀበረ፣\nምነዋ ወዳጄ ብዙ ቀባጠረ?\nመኖርም መሞትም አንዴ ጥርስን ነክሶ፣\nወይ በምግባር ከብሮ ወይ በምግባር ረክሶ፣\nእንጅ እንደ ወዳጄ መች መቃብር ምሶ፣\nእንጅ እንደ ወዳጄ መች ለራስ አልቅሶ፣\nየቁም ሞትን ሙቶ በተንኮል ጨንብሶ፣\nካልሆነ በስተቀር የ‹‹ደንቆሮ››ለቅሶ፣\nመልሶ መልሶ መልሶ መላልሶ፡፡", "grade": 10, "preamble": "ቀጥሎ የቀረበውን ግጥም መሰረት አድርጋችሁ ለሚከተለው ጥያቄ ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ፡፡", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "በፊደል ‹‹ፀ ›› ___ የሚል ቃል ይመሰረታል፡፡", "a": "ፀሀይ", "b": "ዐይን", "c": "ወርቅ", "d": "", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 1, "preamble": "", "category": "Grammar" }, { "question": "ስሚ አንቺ እማማ ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆች የታፈርሽ ነሽ እኮ ፡፡ \n\nብንል በየትኛው የዘይቤ ዓይነት ተጻፈ፡፡", "a": "እንቶኔ", "b": "ሰውኛ", "c": "ተምሳሌት", "d": "ተለዋጭ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "በስነቃል ክዋኔ ጊዜ የተደራስያን ተግባር ያልሆነው የቱ ነው?", "a": "ስነቃሉን መምራት", "b": "ማዳመጥ", "c": "የሚከውነውን አካል ማጀብ", "d": "ምላሽ መስጠት", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ተረበኛ ለሚለው ቃል ሊመሳሳለው የሚችለው የትኛው ነው?", "a": "ቀልደኛ", "b": "ወገኛ", "c": "ጉረኛ", "d": "መተተኛ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ከሚከተሉት አማራጮች መካከል ስማዊ ሐረግ የሆነው የትኛው ነው?", "a": "ትናንት ያየኋት ቀይ መኪና", "b": "ከወንድሙ ጋር", "c": "እንደ እህቷ በጣም ቀልጣፋ", "d": "ትህትናዋ የሚማርከው አስተናጋጅ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "በተራ ቁጥር‹‹ 12›› የተጠቀሰው ስህተት ዓይነት ምንድን ነው?", "a": "የቁጥር ", "b": "የተሳቢ", "c": "የመደብ ", "d": "የቃላት ምርጫ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ቃላት መካከል ቅጽል የሆነው ቃል የትኛው ነው?", "a": "ትኩስ", "b": "እሸት", "c": "ድንገት", "d": "ዛሬ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ለጤንነት የበለጠ ጠቀሜታ ያለው አትክልት ወይስ ስጋ ? የሚለው ዓረፍተነገር ለየትኛው የድርሰት ዓይነት ምሳሌ ሊሆን ይችላል?", "a": "ለአመዛዛኝ", "b": "ለገላጭ", "c": "ለተራኪ", "d": "ለስዕላዊ", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ሰው በተፈጥሮው እንዲፈጸምለት የሚፈልጋቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?", "a": "ሁሉም", "b": "የረሃብ ፍላጎቱ", "c": "የመበቀል ፍላጎቱ", "d": "ነጻ የመሆን ፍላጎቱ", "answerKey": "a", "context": "ምንባብ:\nሰው በተፈጥሮው የረሃብና የጥም ፣የበቀልና የመሳሰለው ፍልጎቱ ሁሉ እንዲፈጸምለት ይፈልጋል፤ነገርግን ማህበሩ እያንዳንዱ ሰው የተፈጥሮ ፍላጎቱን ለመፈጸም ሲል ሌሎቹን ሰዎች እንዳይጎዳ የሚወስንበት የጽህፈትና የልማድ ሕግ ሠራ፡፡ስለዚህ የተፈጥሮ ፍልጎቱን ለመፈጸም የማህበበሩን የጽህፈትና የልማድ ሕግ የተላለፈ ነውረኛ ተብሎ ይፈረድበታል፡፡\nአንድ ሰው ከሌላው የሚያስቆጣ ነገር ቢደርስበትና ለቁጣው ምክንያት የሆነውን ሰው ለማጥፋት ቢወድ፣ በማህበሩ ህግ ቅጣት እንደሚያስከትል ስለሚያውቅ ቁጣውን ለማብረድ ፣ሌላ የሚበቀልበት አማራጭ መንገድ መመፈለግ አለበት፡፡ስለዚህ የሰው ሰውነት የነጻነትና የጭቆና ውጤት ነው ማለት ይቻላል፡፡ይህ ነጻነትና ጭቆና ማህበሩ በረጅም ዘመን ዕድሜው ከልማዱ፣ከወጉ፣ከህጉ አዋህዶና አስማምቶ የሰራው ነው፡፡ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ተወልዶ ውስጡ ሲገባ በሱ ተመርቶ መኖር አለበት፤ከማህበሩ ስርዓት አንድ ነቁጥ እንኳን አይተላለፍም፡፡\nበጠቅላላው የማህበር ትምህርት እያንዳንዱ ሰው ሲወለድ ይዟቸው የሚወለደውን ጠቃሚ ውጥኖች ነጻነት በመስጠትና በልዩልዩ መንገድ በመርዳት ጎጂዎቹነንም እንዲሁ በልዩልዩ መንገድ በመጠቆምና በማረም ሰውዬውን ማህበራዊ እንዲሆን ያደርገዋል", "grade": 10, "preamble": "ከዚህ በታች የቀረበውን ምንባብ መሰረት አድርጋችሁ ለሚከተለው ጥያቄ ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ፊደል ‹‹ሰ ›› እና ፊደል ‹‹ሠ ›› ___ ፊደላት ናቸው፡፡", "a": "ሞክሼ", "b": "መንታ", "c": "ዘመድ", "d": "", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 1, "preamble": "", "category": "Grammar" }, { "question": "የአንቀጽ ቅርጽ የሚወሰነው በምን መነሻነት ነው?", "a": "ኃይለቃሉ በሚገኝበት ስፍራ", "b": "አንቀጹ በሸፈነው ሃሳብ", "c": "በአንቀጹ መዘርዝር ዓረፍተነገሮች አማካኝነት", "d": "በዓረፍተነገሮች ብዛት", "answerKey": "a", "context": "", "grade": 10, "preamble": "", "category": "Reading comprehension" }, { "question": "ተራኪው ስለ ሟቹ ስላለው አመለካከት ምን ማለት ይቻላል?", "a": "እንደማይወደው መናገር ይቻላል፡፡", "b": "እንደሚወደው መናገር ይቻላል፡፡", "c": "እንደማያውቀው መናገር ይቻላል፡፡", "d": "እንደረሳው መናገር ይቻላል፡፡", "answerKey": "a", "context": "ግጥም:\n\nየሞተው ወዳጄ እኔ የማልናፍቀው፣\nያነሳኛል አሉ ሲጨንቀው ሲጠበው፣\nመቆያው ማደሪያው ከቤቴ ከደጄ\nምንድን ይሻ ይሆን ትልቁ ወዳጄ?\nታዲያ ምን ይሉታል እንዲህ ያለውን\nከመቃብር በታች ነፍስ የዘራውን፡፡\nምናልባት ሲቀበር ዐፈር አልባሾቹ፣\nኮረትና ድንጋይ አልጫኑት ከታቹ፡፡\nነፍስ እንዳለው ፍጡር እንዳልተቀበረ፣\nምነዋ ወዳጄ ብዙ ቀባጠረ?\nመኖርም መሞትም አንዴ ጥርስን ነክሶ፣\nወይ በምግባር ከብሮ ወይ በምግባር ረክሶ፣\nእንጅ እንደ ወዳጄ መች መቃብር ምሶ፣\nእንጅ እንደ ወዳጄ መች ለራስ አልቅሶ፣\nየቁም ሞትን ሙቶ በተንኮል ጨንብሶ፣\nካልሆነ በስተቀር የ‹‹ደንቆሮ››ለቅሶ፣\nመልሶ መልሶ መልሶ መላልሶ፡፡", "grade": 10, "preamble": "ቀጥሎ የቀረበውን ግጥም መሰረት አድርጋችሁ ለሚከተለው ጥያቄ ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ፡፡", "category": "Reading comprehension" } ]